You are on page 1of 83

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። በአካል በአካል ሥም በአካል ግብር በአካል ግብር ሥም በከዊን

በከዊን ሥም ሦስት፣ በባሕርይ በባሕርይ ግብር ሥም በህልውና በአገዛዝ አንድ በሆነው በእግዚአብሔር ሥም የግእዝ
ትምህርትን እንጀምራለን።

ልሳነ ግእዝ ክፍል ፩

እግዚአብሔር ቋንቋን የሰጠን እርሱን አመስግነንበት፣ እኛ ተግባብተንበት በደስታ እንድንኖር ነው። አዳም በቋንቋው
ለእንስሳቱ ለአዕዋፋቱ ስም አውጥቷል። ዘፍ. ፪፣፳ "አዳምም ለእንስሳት ሁሉ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ ለምድር
አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው" ተብሎ ተነግሯል። እስከ ናምሩድ መነሳት ድረስ የዓለም ቋንቋ አንድ ነበረ። ዘፍ.
፲፩፣፩ "የዓለም ሁሉ ቋንቋ አንድ ነበረ፣ ንግግሩም አንድ ነበረ" እንዲል። ከዚህ በኋላ ግን የሰው ልጅ ቢበድል ቋንቋም
በምድር በዝቷል ማለት ነው። ምንም ይሁን ምን ግን ሰው በሚያውቀው ቋንቋ እግዚአብሔርን ማመስገን ይገባዋል።

እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምእመን ግእዝ ቋንቋን መማር ግዴታ ነው። ምክንያቱም
ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን የሚፈጸሙት፣ ሰማያዊ የሆነው ሥርዓተ ቅዳሴ የሚከናወነው፣ ማኅሌት የሚቆመው፣
መጻሕፍቱ የሚነበቡት፣ ወዘተ በግእዝ ቋንቋ ነው። ግእዝ ቋንቋን የማያውቅ ሰው ምን እየተባለ እንደሆነ ሰለማያውቅ
ሐሳቡ ሌላ ቦታ ይሆናል። ትዳር ስንይዝ በቁርባን ስንጋባ፣ በተክሊል ስንጋባ ሥርዓቱ የሚከናወነው በግእዝ ቋንቋ ነው።
ስንወለድ ክርስትናው ሥርዓተ ጥምቀቱ፣ ስንሞት ፍትሐቱ የሚፈጸመው በግእዝ ቋንቋ ነው። ቃሉን ብትሰሙት ደግሞ
ምሥጢሩ ልዩ ነው። አስተውሎ ለሰማው ሰው አእምሮን ወደ ሰማይ ያመጥቃል። የቅዳሴው ምሥጢር የማኅሌቱ
ጣዕም የቅኔው የትርጓሜው ነገር ሲሰሙት ይመስጣል። ስለዚህ በትክክል ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ለማወቅ እኛም
የበረከቱ ተካፋይ ለመሆን ሃይማኖታችንን በደንብ ለመረዳት ግእዝ ቋንቋ ወሳኝነት አለው።

የግእዝ ቋንቋ የራሱ የሆነ ፊደል፣ የራሱ የሆነ ቁጥር፣ የራሱ የሆነ ሥርዓተ ንባብ አለው። ይህንንም በጥልቀት እያንዳንዱን
እንማማራለን ማለት ነው። በደንብ ልናስተውለው የሚገባን ነገር ግን ቋንቋ የእኛ መግባቢያ፣ እግዚአብሔርን ማመስገኛ
እንጂ መሰዳደቢያ አይደለም። ለመሰዳደቢያ ቢሆን ኖሮስ እግዚአብሔር ቋንቋን ባልሰጠን ነበር። እርሱ ለመልካምነት
የሰጠንን ቋንቋ እኛ ለመሰዳደቢያ እንዳናውለው እንጠንቀቅ።

ልሳነ ግእዝ ክፍል ፪

የግእዝ ፊደላት ፴ ናቸው። እነዚህም፣


ሀ፣ሐ፣ኀ፣ለ፣መ፣ሠ፣ሰ፣ረ፣ቀ፣በ፣ተ፣ነ፣አ፣ዐ፣ከ፣ወ፣ዘ፣የ፣ደ፣ገ፣ጠ፣ጰ፣ጸ፣ፀ፣ፈ፣ፐ፣ቈ፣ኈ፣ኰ፣ጐ ናቸው። ከእነዚህም
ቈ፣ኈ፣ኰ፣ጐ ካዕብ እና ሳብዕ የላቸውም። ሌሎቹ ግን ከግእዝ እስከ ሳብዕ አላቸው። ለምሳሌ ሀ፣ሁ፣ሂ፣ሃ፣ሄ፣ህ፣ሆ ብንል

ሀ___ግእዝ

ሁ___ ካዕብ

ሂ___ ሣልስ
ሃ____ ራብዕ

ሄ____ኀምስ

ህ____ሳድስ

ሆ____ሳብዕ

ይባላሉ። እኒህን ማወቅ ወደፊት ለምንማረው ትምህርት ወሳኝነት አላቸው። ለምሳሌ የ"መ" ራብዕ ማን ነው ብትባሉ
"ማ" ብላችሁ መመለስ አለባችሁ ማለት ነው። በግእዝ ሏ፣ሟ፣ሷ፣ ወዘተ የሚባሉ ፊደሎች የሉም። በግእዝ በእንደነዚህ
ዓይነት ያሏቸው አራት ፊደላት ብቻ ናቸው። እነዚህም ኳ፣ ኋ፣ ቋ፣ ጓ ናቸው። "ሐ" እና "ሓ" የአነባበብ አንድነት
ቢኖራቸውም የተለያዩ ፊደላት መሆናቸውን ማወቅ ይገባል። ለምሳሌ መርሐ ሲል መራ ማለት ነው። መርሓ ሲል ግን
ሴቶች መሩ ተብሎ ይተረጎማል። ስለዚህ በተለይም ሣልሷን 'ዪ' እና ሳድሷን 'ይ'፣ ካዕቡን 'ዉ' እና ሳድሱን 'ው'፣ ግእዙን
'አ' እና ራብዑን 'ኣ' መለየት ያስፈልጋል። እኒህን ካፋለስን የትርጉም ለውጥም ስለሚያመጣ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

ሌላው ልናስተውለው የሚገባን ሐመሩን "ሐ" ከሀሌታው "ሀ" እንዲሁም ከብዙኃኑ "ኀ" መለየት ያስፈልጋል። ዓይኑ "ዐ"ን
ከአልፋው " አ" መለየት ያስፈልጋል። ጸሎቱ "ጸ" ን ከፀሐዩ "ፀ" መለየት ያስፈልጋል። እሳቱ "ሰ"ን ከንጉሡ "ሠ" መለየት
ያስፈልጋል። ከዚህ ቀጥሎ ልዩነታቸውን በምሳሌ እንመልከት።

ሠረቀ_ወጣ

ሰረቀ_ሰረቀ

ሠዐለ_ሳለ (ሥዕል ሳለ)

ሰአለ_ለመነ

ይላል።በሌሎችም እንዲህ ዓይነት ልዩነት ስለሚያመጣ ፊደላትን ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል። በዚህ ዙሪያ የኪዳነ ወልድ
ክፍሌ መዝገበ ቃላት ስለሚጠነቅቅ ያንን ማየት መልካም ነው።

ኰኲኳኴኵ

ቈቊቋቌ_ቍ

ኈኊኋኌ_ኍ

ጐጒጓጔጕ

ይላል። እነዚህን አነባበባቸውን በቴሌግራም እለቃቸዋለሁ። ከዚያ ገብታችሁ ስሙ። አስተውል ኰ ግእዝ፣ ኲ ሣልስ፣ ኳ
ራብዕ፣ ኴ ኀምስ፣ ኵ ሳድስ ናቸው። ለእነዚህ ፊደላት ካዕብና ሳብዕ የላቸውም። "ጐ" የሚባል ፊደል የለም። ስልኬ
ፊደሉ ስለሌላት ነው ያለውን የጻፍኩት እንጂ። የግእዝ ፊደላት ያይደሉ የአማርኛ ፊደላት የሆኑ አሉ። እነዚህም
"ጨ፣ቨ፣ሸ፣ኘ፣ዠ፣ቸ፣ኸ" ናቸው።
#ልሳነ #ግእዝ #ክፍል #ሦስት

አኀዝ/ቁጥር

ግእዝ ቋንቋ የራሱ የሆኑ ቁጥሮች አሉት። መሥራች ቁጥሮች የሚባሉትም የሚከተሉት ናቸው።

፩=አሐዱ=አንድ

፪=ክልዔቱ=ሁለት

፫=ሠለስቱ=ሦስት

፬=አርባዕቱ=አራት

፭=ኀምስቱ=አምስት

፮=ስድስቱ=ስድስት

፯=ሰብዓቱ=ሰባት

፰=ሰመንቱ=ስምንት

፱=ተስዓቱ=ዘጠኝ

፲=አሠርቱ=አስር

፳=ዕሥራ=ሃያ

፴=ሠላሳ=ሠላሳ

፵=አርብዓ=አርባ

፶=ኀምሳ=አምሳ

፷=ስድሳ/ስሳ=ስልሳ

፸=ሰብዓ=ሰባ

፹=ሰማንያ=ሰማንያ

፺=ተስዓ=ዘጠና

፻=ምእት=መቶ

፼=እልፍ=አስር ሺ
፻፼=አእላፋት=ሚልዮን

፼፼=ትእልፊታት=መቶ ሚልዮን

፻፼፼=ምእልፊታት=አስር ቢልዮን

ናቸው። እነዚህ መስራች ቁጥሮች ናቸው። ለዛሬ እስከ ቁጥር ፲፻ (አንድ ሺ) ያሉትን እንመልከት። አስር ካልን በኋላ
አስራ አንድ ለማለት አሠርቱ ወአሐዱ ማለት ነው። ሲጻፍም ፲፩ ይሆናል። 46 ቁጥርን በግእዝ ጻፍ ብትባል ፵፮
ታደርገዋለህ። ሲነበብ ደግሞ አርብዓ ወስድስቱ ይላል።

ከመቶ እስከ አንድ ሺ ያሉ ቁጥሮች ወደ ግእዝ ሲለወጡ ደግሞ እንደሚከተለው ነው። ለምሳሌ 200 ወደ ግእዝ ሲለወጥ
፪፻ ይሆናል። ሲነበብም ክልዔቱ ምእት ይሆናል። 204 ወደ ግእዝ ሲለወጥ ደግሞ ፪፻፬ ይሆናል ሲነበብ ደግሞ ክልዔቱ
ምእት ወአርባዕቱ ይሆናል። 253 ወደ ግእዝ ሲለወጥ ፪፻፶፫ ይሆናል ሲነበብም ክልዔቱ ምእት ኀምሳ ወሠለስቱ ይሆናል።
በዚህ መልኩ እስከ አንድ ሺ ያሉ ቁጥሮችን መስራት ይቻላል። ለምሳሌ 444 ን በግእዝ ለመጻፍ ፬፻፵፬ ይሆናል ሲነበብም
አርባዕቱ ምእት አርብዓ ወአርባዕቱ ይላል ማለት ነው። እንዲህ እያለ አንድ ሺ ላይ ሲደርስ አሠርቱ ምእት ይላል። አስር
መቶ እንደማለት ያለ ነው። ከአንድ ሺ እስከ አስር ሺ በቀጣይ ክፍል እንመለከታለን።

የዕለቱ ጥያቄዎች

የሚከተሉትን ቁጥሮች ግእዝ ለውጡ። እንዴት እንደሚነበቡም ግለጽ።

፩) 996

፪) 84

፫) 340

፬) 702

፭) 175

የጥያቄዎች መልስ

፩) ፱፻፺፮ ተስዓቱ ምእት ተስዓ ወስድስቱ።

፪) ፹፬ ሰማንያ ወአርባዕቱ።

፫) ፫፻፵ ሠለስቱ ምእት ወአርብዓ።

፬) ፯፻፪ ሰብዓቱ ምእት ወክልኤቱ።

፭) ፩፻፸፭ ምእት ወሰብዓ ወኀምስቱ ።


#ልሳነ #ግእዝ #ክፍል #አራት

ከ 1000 እስከ 10000 ያሉ ቁጥሮች

፲፻_አሠርቱ ምእት 1 ሺ

፳፻_ዕሥራ ምእት_2 ሺ

፴፻_ሠላሳ ምእት_3 ሺ

፵፻_አርብዓ ምእት 4 ሺ

፶፻_ኀምሳ ምእት_5 ሺ

፷፻_ስሳ ምእት__6 ሺ

፸፻_ሰብዓ ምእት_7 ሺ

፹፻ሰማንያ ምእት 8 ሺ

፺፻_ተስዓ ምእት_9 ሺ

፼እልፍ__10 ሺ

ነው። በዚህ መካከል ያሉ ቁጥሮችን ለመጻፍ ለምሳሌ 1008 ን በግእዝ ለመጻፍ ፲፻፰ ይሆናል ሲነበብም አሠርቱ ምእት
ወሰመንቱ ይሆናል። 1018 ን በግእዝ ለመጻፍ ፲፻፲፰ ይሆናል ሲነበብም አሠርቱ ምእት አሠርቱ ወሰመንቱ ይሆናል።
1118 ን በግእዝ ለመጻፍ ፲፻፩፻፲፰ ወይም ፲፩፻፲፰ ይሆናል። ሲነበብም የመጀመሪያው አሠርቱ ምእት ወአሐዱ ምእት
አሠርቱ ወሰመንቱ ይላል። ሁለተኛው ደግሞ አሠርቱ ወሰመንቱ ምእት አሠርቱ ወሰመንቱ ይላል። በብዛት መጻሕፍት
ላይ የምናገኘው ሁለተኛውን ነው። 2016 በግእዝ ለመጻፍ ፳፻፲፮ ይላል። ሲነበብም እሥር ምእት አሠርቱ ወስድስቱ
ይላል። 7683 በግእዝ ሲጻፍ ፸፻፮፻፹፫ ይሆናል። ሲነበብም ሰብዓ ምእት ወስድስቱ ምእት ሰማንያ ወሠለስቱ ይላል።
እንዲህ እያልን አስር ሺ ላይ ስንደርስ እልፍ እንላለን ማለት ነው።

የዕለቱ ጥያቄዎች

የሚከተሉትን ቁጥሮች ወደ ግእዝ ለውጥ። ንባባቸውንም በግእዝ ጻፍ።

፩) 3251

፪) 8888

፫) 7004

፬) 5500

፭) 4690
የጥያቄዎች መልስ

፩) ፴፻፪፻፶፩ ሠላሳ ምእት ወክልኤቱ ምእት ኃምሳ ወአሐዱ።

፪) ፹፻፰፻፹፰ ሰማንያ ምእት ወሰመንቱ ምእት ሰማንያ ወሰመንቱ።

፫) ፸፻፬ ሰብዓ ምእት ወአርባዕቱ።

፬) ፶፻፭፻ ኃምሳ ምእት ወኀምስቱ ምእት።

፭) ፵፻፮፻፺ አርብዓ ምእት ወስድስቱ ምእት ወተስዓ።

#ልሳነ #ግእዝ #ክፍል #አምስት

ከ 10000 እስከ ሚልዮን ያሉ ቁጥሮች

፼_እልፍ_10 ሺ

፪፼ክልዔቱ እልፍ 20 ሺ

፫፼ሠለስቱ እልፍ 30 ሺ

፬፼አርባዕቱ እልፍ 40 ሺ

፭፼ኀምስቱ እልፍ 50 ሺ

፮፼ስድስቱ እልፍ 60 ሺ

፯፼ሰብዓቱ እልፍ 70 ሺ

፰፼ሰመንቱ እልፍ 80 ሺ

፱፼ተስዓቱ እልፍ_90 ሺ

፲፼አሠርቱ እልፍ_100 ሺ

አንድ መቶ ሺ አሠርቱ እልፍ ነው። በሌላ አገላለጽ አእላፍ እየተባለም ይጠራል። ከዚያ ቀጥሎ ያሉ ቁጥሮች ደግሞ
እንደሚከተለው ቀርበዋል።

፳፼_ዕሥራ እልፍ_200 ሺ

፴፼ሠላሳ እልፍ 300 ሺ

፵፼አርብዓ እልፍ 400 ሺ

፶፼ኀምሳ እልፍ 500 ሺ


፷፼ስድሳ እልፍ 600 ሺ

፸፼ሰብዓ እልፍ 700 ሺ

፹፼ሰማንያ እልፍ 800 ሺ

፺፼ተስዓ እልፍ 900 ሺ

፻፼አእላፋት_1 ሚልየን

ናቸው። በምሳሌ ለመመልከት ያህል 20004 በግእዝ ሲጻፍ ፪፼፬ ይሆናል ሲነበብ ክልዔቱ እልፍ ወአርባዕቱ ይላል።
20690 በግእዝ ሲጻፍ ፪፼፮፻፺ ይሆናል። ሲነበብ ክልዔቱ እልፍ ስድስቱ ምእት ወተስዓ ይላል። 48749 በግእዝ ስንጽፈው
፬፼፹፻፯፻፵፱ ይላል ሲነበብም አርባዕቱ እልፍ ወሰማንያ ምእት ወሰብዓቱ ምእት አርብዓ ወተስዓቱ ይላል። 144000
በግእዝ ሲጻፍ ፲፼፬፼፵፻ ይላል ሲነበብም አሠርቱ እልፍ ወአርባዕቱ እልፍ ወአርብዓ ምእት ይላል። በመጨረሻም
777777 በግእዝ ሲጻፍ ፸፼፯፼፸፻፯፻፸፯ ይላል ሲነበብም ሰብዓ እልፍ ወሰብዓቱ እልፍ ወሰብዓ ምእት ሰብዓ
ወሰብዓቱ ይላል ማለት ነው።

የዕለቱ ጥያቄዎች

የሚከተሉትን ቁጥሮች ወደ ግእዝ ለውጥ ንባባቸውንም አስቀምጥ።

፩) 50045

፪) 238029

፫) 612340

፬) 708257

፭) 983216

የጥያቄዎች መልስ

፩) ፭፼፵፭ ኀምስቱ እልፍ አርብዓ ወኀምስቱ።

፪) ፳፼፫፼፹፻፳፱ ዕሥራ እልፍ ወሠለስቱ እልፍ ወሰማንያ ምእት ዕሥራ ወተስዓቱ። በሌላ አገላለጽ ፳፫፼፹፻፳፱
ዕሥራ ወሠለስቱ እልፍ ወሰማንያ ምእት እስራ ወተስዓቱ ይላል።

፫) ፷፼፩፼፳፻፫፻፵ ስሳ እልፍ ወአሐዱ እልፍ ወዕሥራ ምእት ወሠለስቱ ምእት ወአርብዓ ይላል። በሌላ አገላለጽም
፷፩፼፳፫፻፵ ስሳ ወአሐዱ እልፍ ዕሥራ ወሠለስቱ ምእት ወአርብዓ ይላል።

፬) ፸፼፹፻፪፻፶፯ ሰብዓ እልፍ ወሰማንያ ምእት ወክልኤቱ ምእት ኃምሳ ወሰብዓቱ ይላል። በሌላ አገላለጽ
፸፼፹፪፻፶፯ ሰብዓ እልፍ ሰማንያ ወክልኤቱ ምእት ኃምሳ ወሰብዓቱ ይላል።
፭) ፺፼፰፼፴፻፪፻፲፮ ተስዓ እልፍ ወሰመንቱ እልፍ ሠላሳ ምእት ወክልዔቱ ምእት አሠርቱ ወስድስቱ ይላል። በሌላ
አገላለጽ ፺፰፼፴፪፻፲፮ ተስዓ ወሰመንቱ እልፍ ሠላሳ ወክልኤቱ ምእት አሠርቱ ወስድስቱ ይላል።

#ልሳነ #ግእዝ #ክፍል #ስድስት

ከሚልዮን በላይ ያሉ ቁጥሮች

፻፼አእላፋት 1 ሚልዮን

፪፻፼ክልዔቱ አእላፋት 2 ሚልዮን

፫፻፼ሠለስቱ አእላፋት 3 ሚልዮን

፬፻፼አርባዕቱ አእላፋት 4 ሚልዮን

፭፻፼ኀምስቱ አእላፋት 5 ሚልዮን

፮፻፼ስድስቱ አእላፋት 6 ሚልዮን

፯፻፼ሰብዓቱ አእላፋት 7 ሚልዮን

፰፻፼ሰመንቱ አእላፋት 8 ሚልዮን

፱፻፼ተስዓቱ አእላፋት 9 ሚልዮን

፲፻፼አሠርቱ አእላፋት 10 ሚልዮን

ይላል ማለት ነው። አሠርቱ አእላፋት በሌላ አገላለጽ ትእልፊት እየተባለም ይጠራል። ከዚህ በኋላ ዕሥራ አእላፋት
(፳፻፼) ሠላሳ አእላፋት (፴፻፼) እያለ እስከ ትእልፊታት (፼፼) ይዘልቃል። ትእልፊታት ደግሞ ክልኤቱ ትእልፊታት
(፪፼፼) ሠለስቱ ትእልፊታት እያለ እስከ ምእልፊታት ይዘልቃል (፻፼፼)። በመካከል ፲፼፼ (አሠርቱ ትእልፊታት) በሌላ
አገላለጽ ምእልፊት ይባላል።አንድ ቢልዮን የሚባለው በግእዝ ምእልፊት ነው። በግእዝ ቋንቋም እስከ ፈለገን ድረስ
መቁጠር እንችላለን። አንድ ምሳሌ እንመልከት ለምሳሌ 2763892623 ውደ ግእዝ ሲለወጥ
፳፼፼፯፻፼፻፷፻፼፫፼፻፹፼፱፼፳፻፮፻፳፫ ይሆናል።ሲነበብም ዕሥራ ትእልፊታት ወሰብዓቱ ትእልፊታት ስድሳ
አእላፋት ወሠለስቱ አእላፋት ሰማንያ እልፍ ወተስዓቱ እልፍ ዕሥራ ምእት ወስድስቱ ምእት ዕሥራ ወሠለስቱ ይላል
ማለት ነው።

የዕለቱ ጥያቄዎች

የሚከተሉትን ቁጥሮች ወደ ግእዝ ለውጥ ንባባቸውንም ጻፍ

፩) 3456987247

፪) 234789289
የጥያቄዎች መልስ

፩) ፴፼፼፬፼፼፶፼፻፮፼፻፺፼፰፼፸፻፪፻፵፯ ሠላሳ ትእልፊታት ወአርባዕቱ ትእልፊታት ወኀምሳ አእላፋት ወስድስቱ


አእላፋት ወተስዓ እልፍ ወሰመንቱ እልፍ ወሰብዓ ምእት ወክልኤቱ ምእት አርብዓ ወሰብዓቱ ይላል። ወይም በሌላ
አገላለጽ ፴፬፼፼፶፮፼፻፺፰፼፸፪፻፵፯ ሠላሳ ወአርባዕቱ ትእልፊታት ኃምሳ ወስድስቱ አእላፋት ተስዓ ወሰመንቱ
እልፍ ሰብዓ ወክልዔቱ ምእት አርብዓ ወሰብዓቱ ይላል።

፪) ፪፼፼፴፼፻፬፼፻፸፼፰፼፺፻፪፻፹፱ ክልኤቱ ትእልፊታት ወሠላሳ አእላፋት ወአርባዕቱ አእላፋት ወሰብዓ እልፍ


ወሰመንቱ እልፍ ወተስዓ ምእት ወክልኤቱ ምእት ሰማንያ ወተስዓቱ ይላል። ወይም በሌላ አገላለጽ
፪፼፼፴፬፼፻፸፰፼፺፪፻፹፱ ክልኤቱ ትእልፊታት ሠላሳ ወአርባዕቱ አእላፋት ሰብዓ ወሰመንቱ እልፍ ተስዓ ወክልኤቱ
ምእት ሰማንያ ወተስዓቱ ይላል።

መልሶቻችሁን በዚህ መገምገም ትችላላችሁ። ስለ አኃዝ ከዚህም በላይ ሰፋ አድርጌ ለመጻፍ አስቤ ነበር ነገር ግን
አብዛኛው ሰው ከበደን ስላለ ቢያንስ እስከዚህ ያለውን ካወቀ ከፍ ያለውን ደግሞ ሌላውን ከተማርን በኋላ ወይ መጨረሻ
ላይ እንማማረዋለን።

❤️ግእዝ ❤️ክፍል ❤️ሰባት

የኢትዮጵያ ሊቃውንት ለእያንዳንዱ ፊደል ነገረ ሃይማኖትን የሚገልጥ ትርጉም ሰጥተዋል።

ሀ ብሂል ሀልወቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም የአብ መኖር ከዓለም በፊት ነው ማለት ነው።

ሁ ብሂል ኪያሁ ተወከሉ።በእርሱ (በእግዚአብሔር) ታመኑ።

ሂ ብሂል አስተይዎ ብሂዐ አይሁድ ጌታን ሖምጣጤ አጠጡት ማለት ነው።

ሃ ብሂል ሃሌ ሉያ።ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ማለት ነው።

ሄ ብሂል በኲለሄ ሀሎ። እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ እና ጊዜ አለ ማለት ነው።

ህ ብሂል ህልው እግዚአብሔር። እግዚአብሔር አለ ማለት ነው።

ሆ ብሂል ኦሆ ይቤ ወመጽአ። እሺ ብሎ መጣ ማለት ነው።አዳምን ለማዳን እግዚአብሔር በፈቃዱ ሥጋን መዋሐዱን


ያመለክታል።

ለ ብሂል ለብሰ ሥጋ ዚኣነ።እግዚአብሔር የእኛን ሥጋ ተዋሐደ ማለት ነው።

ሉ ብሂል ሣህሉ ለእግዚአብሔር። የእግዚአብሔር ይቅር ባይነት ማለት ነው።

ሊ ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው ማለት ነው።

ላ ብሂል ላሜድ ልዑል እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ልዑል ነው ማለት ነው።


ሌ ብሂል መቅለሌ ዕጹብ። ጭንቀትን (ጭንቅን) የሚያቀል እግዚአብሔር ማለት ነው።

ል ብሂል መስቀል ዘወልደ አብ። የአብ ልጅ መስቀል ማለት ነው።

ሎ ብሂል ዘሀሎ እምቅድም። ቅድመ ዓለም የነበረ እግዚአብሔር ማለት ነው።

ሐ ብሂል ሐመ ወሞተ በእንቲአነ። ክርስቶስ ስለእኛ መከራን ተቀበለ ሞተ ማለት ነው።

ሑ ብሂል ሰብሑ ለስመ እግዚአብሔር። የእግዚአብሔርን ሥም አመስግኑ ማለት ነው።

ሒ ብሂል መንጽሒ። ከበደል የሚያነጻ እግዚአብሔር ማለት ነው።

ሓ ብሂል መፍቀሬ ንሥሓ። ንሥሓን የሚወድ እግዚአብሔር ማለት ነው።

ሔ ብሂል ሔት ሕያው እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ሕያው ነው ማለት ነው።

ሕ ብሂል ሕያው እግዚአብሔር

ሖ ብሂል ንሴብሖ ለእግዚአብሔር። እግዚአብሔርን እናመስግነው ማለት ነው።

መ ብሂል መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር። የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው ማለት ነው።

ሙ ብሂል ሙጻአ ሕግ

ሚ ብሂል ዓለመ ኀታሚ።ዓለምን የፈጠረ፣ ዓለምን የሚያኖር ዓለምን የሚያጠፋ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው።

ማ ብሂል ፌማ መንፈስ ቅዱስ። መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው።

ሜ ብሂል ሜም ምዑዝ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ምዑዝ ነው ማለት ነው።

ም ብሂል አምላከ ሰላም። የሰላም አምላክ እግዚአብሔር ማለት ነው።

ሞ ብሂል ሞተ በሥጋ። በሥጋ ሞተ ማለት ነው።

ሠ ብሂል ሠረቀ በሥጋ እምድንግል። ቃል ከድንግል ማርያም በሥጋ ተወለደ ማለት ነው።

ሡ ብሂል መንበረ ንግሡ።

ሢ ብሂል ሢመተ መላእክት። የመላእክት ሹመት ማለት ነው።

ሣ ብሂል ሣህል ወርትዕ። ይቅርታና ቅንነት ማለት ነው።

ሤ ብሂል ሤሞሙ ለካህናት። እግዚአብሔር ካህናትን ሾመ ማለት ነው።

ሥ ብሂል ንጉሥ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ንጉሥ ነው ማለት ነው።

ሦ ብሂል አንገሦ ለአዳም። እግዚአብሔር አዳምን አነገሠው ማለት ነው።


ረ ብሂል ረግዐ ሰማይ ወምድር በጥበቡ። በእግዚአብሔር ጥበብ ሰማይና ምድር ረጋ ማለት ነው።

ሩ ብሂል በኲሩ ለአብ። ወልድ የአብ አንድያ ልጁ ማለት ነው።

ሪ ብሂል ዘይሰሪ አበሳ። በደልን ይቅር የሚል እግዚአብሔር ማለት ነው።

ራ ብሂል ጌራ መድኃኒት።

ሬ ብሂል ሬስ ርኡስ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር አለቃ ነው ማለት ነው።

ር ብሂል ርግብ መንፈስ ቅዱስ። መንፈስ ቅዱስ ርግብ ማለት ነው።

ሮ ብሂል ፈጠሮ ለዓለም። እግዚአብሔር ዓለምን ፈጠረው ማለት ነው።

ሰ ብሂል ሰብአ ኮነ ከማነ። እግዚአብሔር ወልድ እንደኛ ሰው ሆነ ማለት ነው።

ሱ ብሂል ፋሲልያሱ።

ሲ ብሂል ዘይሤሲ ለኩሉ ዘሥጋ። ደማዊ ፍጥረታትን ሁሉ የሚመግብ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው።

ሳ ብሂል ሳምኬት ስቡሕ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ምስጉን ነው ማለት ነው።

ሴ ብሂል ለባሴ ሥጋ። ሥጋን የተዋሐደ እግዚአብሔር ቃል ማለት ነው።

ስ ብሂል ለብስ ለዕሩቃን። ለታረዙት ልብስ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው።

ሶ ብሂል መርሶ ለአሕማር።

ቀ ብሂል ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ በመጀመሪያ ቃል ነበር ማለት ነው።

ቁ ብሂል ጽድቁ ለኃጥእ።

ቂ ብሂል ፈራቂሁ ለዓለም።ዓለምን የፈጠረ እግዚአብሔር ማለት ነው።

ቃ ብሂል ቃልየ አጽምዕ። አቤቱ ቃሌን ስማ ማለት ነው።

ቄ ብሂል ሰዋቄ ኃጥኣን።

ቅ ብሂል ጻድቅ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር እውነተኛ ነው።

ቆ ብሂል ቆፍ ቅሩብ እግዚአብሔ። እግዚአብሔር ቅርብ ነው ማለት ነው።

❤️ግእዝ ❤️ክፍል ❤️ስምንት

በ ብሂል በትሕትናሁ ወረደ ለቤዛ ኲሉ ዓለም። ዓለምን ሁሉ ለማዳን በትሕትናው ሰው ሆነ።

ቡ ብሂል ጥበቡ ለአብ። የአብ ጥበቡ ማለት ነው።


ቢ ብሂል ረቢ ነአምን ብከ። መምህር ክርስቶስ ሆይ እናምንሀለን ማለት ነው።

ባ ብሂል ባዕድ እም አማልክተ ሐሰት። ከሐሰት አማልክት የተለየ እግዚአብሔር ማለት ነው።

ቤ ብሂል ቤት ባዕል እግዚአብሔር እግዚአብሔር ባዕለጸጋ ነው ማለት ነው።

ብ ብሂል ብርሃነ ቅዱሳን። የቅዱሳን ብርሃን ማለት ነው።

ቦ ብሂል አልቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌሁ። ከእግዚአብሔር በስተቀር ሌላ አምላክ የለም ማለት ነው።

ተ ብሂል ተሰብአ ወተሠገወ እማርያም እምቅድስት ድንግል። ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ ማለት ነው።

ቱ ብሂል መዝራእቱ ለአብ።የአብ ክንዱ ማለት ነው።

ቲ ብሂል ተአኳቲ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ተመስጋኝ ነው ማለት ነው።

ታ ብሂል ታው ትጉህ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ትጉህ ነው ማለት ነው።

ቴ ብሂል ከሣቴ ብርሃን። ብርሃንን የሚገልጥ ማለት ነው።

ት ብሂል ትፍሥሕት ወሐሴት። ፍጹም ደስታ ማለት ነው።

ቶ ብሂል ነአምን ልደቶ ለክርስቶስ። የክርስቶስን መወለድ እናምናለን ማለት ነው።

ነ ብሂል ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ። ክርስቶስ ደዌያችንን ነሣ መከራችንንም ተሸከመ ማለት ነው።

ኑ ብሂል ዛኅኑ ለባሕር።

ኒ ብሂል ኮናኒ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ገዢ ነው ማለት ነው።

ና ብሂል መና እስራኤል።

ኔ ብሂል መድኃኔ ዓለም። የዓለም መድኃኒት ክርስቶስ ማለት ነው።

ን ብሂል መኮንን እግዚአብሔር። እግዚአብሔር መኮንን ነው ማለት ነው።

ኖ ብሂል ኖላዊ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ጠባቂ ነው ማለት ነው።

ኀ ብሂል ኀብአ ርእሶ።

ኁ ብሂል እኁዝ አቅርንቲሁ።

ኂ ብሂል ዘልማዱ ኂሩት። በጎነት ልማዱ የሆነ እግዚአብሔር ማለት ነው።

ኃ ብሂል ኃያል በኃይሉ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ኃያል ነው ማለት ነው።

ኄ ብሂል ኄር እግዚአብሔር ቸር ነው ማለት ነው።


ኅ ብሂል ኅብስት ለርኁባን። ለተራቡት ኅብስት እግዚአብሔር ነው ማለት ነው።

ኆ ብሂል ኆኅተ ገነት ወልድ። የገነት ቁልፍ ወልድ ነው ማለት ነው።

አ ብሂል አአኲቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር። እግዚአብሔርን ፈጽሞ አመሰግነዋለሁ።

ኡ ብሂል ሙጻኡ ለቃል።

ኢ ብሂል ለሊሁ ተንሣኢ ወለሊሁ አንሣኢ።ክርስቶስ ራሱ ተነሺ ራሱ አንሺ ማለት ነው።

ኣ ብሂል ኣሌፍ ፈጣሬ ኩሉ ዓለም ቀዳማይ ወደኃራዊ።

ኤ ብሂል አምጻኤ ዓለማት እግዚአብሔር። ዓለማትን ከአለመኖር ያመጣ የፈጠረ እግዚአብሔር ማለት ነው።

እ ብሂል እግዚአብሔር እግዚእ። እግዚአብሔር ጌታ ነው ማለት ነው።

ኦ ብሂል እግዚኦ። አቤቱ ጌታ ሆይ ማለት ነው።

ከ ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው ማለት ነው።

ኩ ብሂል ዐርኩ ለመርዓዊ። የሙሽራው ሚዜ ማለት ነው።

ኪ ብሂል ኪያሁ ንሰብል። እርሱን ጌታን እናስተምራለን። አንድም ስለእርሱ እንሰብካለን።

ካ ብሂል ካፍ ከሃሊ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው ማለት ነው።

ኬ ብሂል ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማእከለ አኃው።

ክ ብሂል ክብሮሙ ለመላእክት። የመላእክት ክብራቸው ማለት ነው።

ኮ ብሂል ዘረዳእኮ ለአብርሃም። አብርሃምን የረዳሀው እግዚአብሔር ማለት ነው።

ወ ብሂል ወረደ እምሰማያት። ከሰማያት ወረደ ማለት ነው።

ዉ ብሂል ጼው ለምድር። የምድር ጨው ማለት ነው።

ዊ ብሂል ናዝራዊ። ኢየሱስ ናዝራዊ ነው ማለት ነው።

ዋ ብሂል ዋው ዋሕድ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር።አንድ ነው ማለት ነው።

ዌ ብሂል ዜናዌ ትፍሥሕት። ደስታን የሚናገር ማለት ነው።

ው ብሂል ሥግው ቃል። ሰው የሆነ አምላክ ማለት ነው።

ዎ ብሂል ቤዘዎ ለዓለም። ዓለምን አዳነው።

❤️ግእዝ ❤️ክፍል ❤️ዘጠኝ


ዐ ብሂል ዐቢይ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ታላቅ ነው ማለት ነው።

ዑ ብሂል በግዑ ለእግዚአብሔር። የእግዚአብሔር በግ ማለት ነው።

ዒ ብሂል ለሊሁ ሠዋኢ ወለሊሁ ተሠዋኢ።ኢየሱስ ራሱ መሥዋእት አቅራቢ ራሱ መሥዋእት ነው ማለት ነው።

ዓ ብሂል ዓይነ ኲሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ። ጌታ ሆይ የሰው ሁሉ ሰውነት አንተን ተስፋ ያደርጋል ማለት ነው።

ዔ ብሂል ዔ ዐቢይ እግዚአብሔር።

ዕ ብሂል ብፁዕ እግዚአብሔር።እግዚአብሔር ብፁዕ ነው ማለት ነው።

ዖ ብሂል ሞዖ ለሞት ወተንሥአ። ክርስቶስ ሞትን አሸንፎ ተነሳ ማለት ነው።

ዘ ብሂል ዘኲሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር። ሁሉን የያዘ እግዚአብሔር ማለት ነው።

ዙ ብሂል ምርጒዙ ለሐንካስ

ዚ ብሂል ናዛዚ። የሚያረጋጋ እግዚአብሔር ማለት ነው።

ዛ ብሂል ዛይ ዝኲር እግዚአብሔር።

ዜ ብሂል አኃዜ ዓለም በእራኁ። ዓለምን በመሐል እጁ የያዘ እግዚአብሔር ማለት ነው።

ዝ ብሂል ሐዋዝ ሕገ እግዚአብሔር። የእግዚአብሔር ሕግ መልካም ነው ማለት ነው።

ዞ ብሂል አግአዞ ለአዳም። አዳምን ነጻ አወጣው ማለት ነው።

የ ብሂል የማነ እግዚአብሔር። የእግዚአብሔር ቀኝ ማለት ነው።

ዩ ብሂል ዕበዩ ለእግዚአብሔር። የእግዚአብሔር ታላቅነት ማለት ነው።

ዪ ብሂል መስተስርዪ። ኃጢኣትን የሚያስተሰርይ ማለት ነው።

ያ ብሂል አንተ ኬንያሁ።

ዬ ብሂል ዐሣዬ ሕይወት። ሕይወትን የሚያድል ማለት ነው።

ይ ብሂል ሲሳይ ለርኁባን።

ዮ ብሂል ዮድ የማነ እግዚአብሔር።

ደ ብሂል ደመረ መለኮቶ ምስለ ሥጋነ ወሥጋነ ምስለ መለኮቱ። እግዚአብሔር ወልድ ቃሉን ከሥጋችን ሥጋችንን ከቃሉ
አዋሐደ ማለት ነው።

ዱ ብሂል ፈዋሴ ዱያን። ሕመምተኛን የሚፈውስ እግዚአብሔር ማለት ነው።


ዲ ብሂል ቃለ ዓዋዲ።

ዳ ብሂል ዳሌጥ ድልው እግዚአብሔር።

ዴ ብሂል ዐማዴ ሰማይ ወምድር።

ድ ብሂል ወልድ ዋሕድ።

ዶ ፈነወ ዋሕዶ ወተሰብአ።

ገ ብሂል ገባሬ ሰማያት ወምድር። ሰማይና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔር ማለት ነው።

ጉ ብሂል ለአስካለ ሕይወት ሐረጉ።

ጊ ብሂል ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር።

ጋ ብሂል ጋሜል ግሩም እግዚአብሔር።

ጌ ብሂል ጽጌ ቅዱሳን።

ግ ብሂል ሐጋጌ ሕግ።

ጎ ብሂል ሰርጎሙ ለሐዋርያት።

ጠ ብሂል ጠቢብ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ጠቢብ ነው ማለት ነው።

ጡ ብሂል ውስጡ ለሰብእ እግዚአብሔር።

ጢ ብሂል መያጢሆሙ ለኃጥኣን።

ጣ ብሂል የውጣ እንተ አሐቲ ሕርመታ።

ጤ ብሂል ጤት ጠቢብ እግዚአብሔር።

ጥ ብሂል ስሉጥ ወርኡስ እግዚአብሔር።

ጦ ብሂል ሦጦ ለመንፈስ ቅዱስ ላእሌነ።

ጰ ብሂል ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ።

ጱ ብሂል ኮጱ መዓዛ ሰብእ።

ጲ ብሂል ሠራጲሁ ለዓለም። ዓለምን የሚቀድስ እግዚአብሔር ማለት ነው።

ጳ ብሂል ጳጳሰ ወንጌል።

ጴ ብሂል አክራጴ ኃጢኣት። ከኃጢኣት የሚያነጻ እግዚአብሔር ማለት ነው።


ጵ ብሂል ጵርስፎራ። ሥጋ ወደሙ ማለት ነው።

ጶ ብሂል ጶሊስ።

ጸ ብሂል ጸጋ ወጽድቅ እግዚአብሔር።

ጹ ብሂል ገጹ ለአብ።

ጺ ብሂል ሐዋጺ ነፍሰ ትሑታን። የትሑታንን ሰውነት የሚጎበኝ እግዚአብሔር ማለት ነው።

ጻ ብሂል ጻዴ ጻድቅ እግዚአብሔር።

ጼ ብሂል አእቃጼ ሰኮና።

ጽ ብሂል ጽንሑ ተስፋሁ ለአብ።

ጾ ጾም ትፌውስ ቁስለ ነፍስ። ጾም የነፍስን ቁስል ታድናለች።

ፀ ብሂል ፀሐየ ጽድቅ እግዚአብሔር። የእውነት ፀሐይ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው።

ፁ ብሂል ዮም ሠረፁ ጽጌ በረከት።

ፂ ብሂል መላፂ ዘክልኤ አፉሁ።

ፃ ብሂል ፋፃ መንፈስ ቅዱስ።

ፄ ብሂል ሕፄሁ ለዳዊት

ፅ ብሂል ዕፅ አብርሃም ዘሠፀረ ለምሥዋዕ።

ፆ ብሂል ማዕፆ አፉሆሙ ለጻድቃን።

ፈ ብሂል ፈጠረ ዓለመ በጥበቡ። ዓለምን በጥበቡ ፈጠረ ማለት ነው።

ፉ ብሂል ምዕራፉ ለዓለም፣

ፊ ብሂል ፊደለ ወንጌል።

ፋ ብሂል አልፋ ወኦ

ፌ ብሂል ኀዳፌ ነፍሳት።

ፍ ብሂል ፍኖት ለኀበ አቡሁ።

ፎ ብሂል ፎራ ኅብስተ ቁርባን።

ፐ ብሂል ፓፓኤል ሥሙ ለእግዚአብሔር።


ፑ ብሂል ኖፑ አስካለ ወንጌል።

ፒ ብሂል ፒላሳሁ።

ፓ ብሂል ፓንዋማንጦን።

ፔ ብሂል እግዚአብሔር።

ፕ ብሂል ሮፕ ጽኑዕ እግዚአብሔር።

ፖ ብሂል በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ። በመጀመርያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ ማለት ነው።

❤️ግእዝ ክፍል አስር❤️


ኈ ብሂል ኈለቈ አዕፅምትየ። አጥንቶቼን ቆጠረ ማለት ነው።

ኊ ብሂል በኍባኊ ሥጋ አዳም። የአዳም ሥጋ የተፈጠረ ነው ማለት ነው።

ኋ ብሂል ሰንኋቲ ሥጋ ሰብእ። የሰው ሥጋ የሚበጣ ነው ማለት ነው።

ኌ ብሂል ይኌልቍ አሥዕርተ። ሣሮችን ይቆጥራል ማለት ነው።

ኍ ብሂል ዑጽፍት ወኅብርት። የለበሰች የተሸለመች ማለት ነው።

ቈ ብሂል ተኈለቈ ምስለ ጊጉያን። ከበደለኞች ጋር ተቆጠረ ማለት ነው።

ቊ ብሂል ቍየጺሁ አዕማደ ባላቅ። ጭኖቹ እንደ ምሰሶዎች ናቸው ማለት ነው።

ቋ ብሂል እንቋዕ እንቋዕ። እሰይ እሰይ ማለት ነው።

ቌ ብሂል ቀነተ ሐቌሁ ለኀጺበ እግረ አርዳኢሁ። የደቀመዛሙርቱን እግር ለማጠብ ወገቡን ታጠቀ ማለት ነው።

ቍ ብሂል ቍርባነ ወንጌል። የወንጌል ቁርባን ማለት ነው።

ጎ(ጐ) ብሂል ጎሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ። ልቤ መልካም ነገርን አወጣ ማለት ነው።

ጒ ብሂል ሰንጓጒ እምኃጢአት። ከኃጢአት የሚያጠራ ማለት ነው።

ጓ ብሂል ዕጓለ እመሕያው። ሰው ማለት ነው።

ጔ ብሂል ዝንጓጔ መስቀል።

ጕ ብሂል ጕንደ ሐረገ ወይን። የወይን ሐረግ ግንድ ማለት ነው።

ኰ ብሂል ኰናኔ ዓለም። ዓለምን የሚገዛ ማለት ነው።


ኲ ብሂል ኲናተ ጌዴዎን ዘቈልቈለ ላዕለ ስድሳ ምእት ሐራ በምዕር። በአንድ ጊዜ በስድስት ሺ ወታደሮች ላይ የተሰበቀ
የጌዴዎን ጦር ማለት ነው።

ኳ ብሂል ኳሄላ አይሁድ ወልድ። የአይሁድ ጥንግ ወልድ ማለት ነው። እንደ ጥንግ ያገኘው ሁሉ መትቶታልና።

ኴ ብሂል ወይኴንን እም ባሕር እስከ ባሕር። ከጫፍ እስከ ጫፍ ይገዛል ማለት ነው።

ኵ ብሂል ኵርጓኔ ቅዱሳን። የቅዱሳን ስብስብ ማለት ነው።

❤️ግእዝ ክፍል አስራ አንድ❤️


ሥርዓተ ንባብ_

የግእዝ ቋንቋ የራሱ የሆነ ሥርዓተ ንባብ አለው ብለን ነበር። አራት ዓይነት ንባቦች አሉ። እነዚህም።

፩) ተነሽ

፪) ተጣይ

፫) ወዳቂ

፬) ሰያፍ

ናቸው። አንድን ቃል ለምሳሌ "አእመራ" የሚለውን ቃል ብናይ አንስተን ካነበብነው "ሴቶች አወቁ" የሚል ትርጉም
ይኖረዋል። አእመራ የሚለውን በወዳቂ ንባብ ስናነበው ደግሞ "አወቃት" የሚል ትርጉም ይኖረዋል። ስለዚህ አንድን ቃል
ከነሥርዓተ ንባቡ ማወቅ አለብን። የአንድን ቃል ሥርዓተ ንባብ ለመለየት የሚያገለግሉ መለያዎች አሉ። እነዚህም:-

፩) መድረሻ ፊደሉ

፪) ቃሉ ግሥ ነው ወይስ አይደለም የሚለው

ናቸው። እነዚህን መነሻ አድርገን አራቱን ንባባት ከዚህ ቀጥየ አቀርባለሁ።

#ተነሽ #ንባባት

መድረሻ ፊደላቸው ከሳድስ እና ከኃምስ ውጭ በግእዝ፣ በካእብ፣ በሣልስ፣ በራብዕ እና በሳብዕ ሊጨርሱ ይችላሉ። ብዙ
ጊዜ ተነሽ ንባባት ግሦች ናቸው። በግእዝ ቀደሰ፣ በካእብ ቀደሱ፣ በሣልስ ቀድሲ፣ በራብዕ ቀደሳ፣ በሳብዕ ይቀድሶ ይላል።
አስተውል ተነሽ ንባብ በሳድስ እና በኃምስ አይጨርሱም።

#ወዳቂ #ንባባት

መድረሻ ፊደላቸውን በግእዝ፣ በካእብ፣ በሣልስ፣ በራብዕ፣ በኃምስ፣ በሳብዕ ይጨርሳሉ። በሳድስ ግን "ዝ" የሚለው ቃል
ብቻ ነው። "ዝ" ከሚለው ውጭ በሳድስ የሚጨርስ ወዳቂ ንባብ የለም። ብዙ ጊዜ ከግሥ ውጭ ያሉ ቃላት ሥርዓተ
ንባባቸው ወዳቂ ነው። ምሳሌ ህየንተ፣ ክልኤቱ፣ ቀዳሲ፣ ራማ፣ ቅዳሴ፣ ከበሮ ይላል።
#ተጣይ #ንባባት

መድረሻ ፊደላቸው ሁልጊዜም ሳድስ ብቻ ነው። ብዙ ጊዜ ተጥለው የሚነበቡ ቃላት ከግሥ ውጭ ያሉ ቃላት ናቸው።
ለምሳሌ ሕይወት፣ ማርያም፣ ቃል ወዘተ ተጣይ ንባባት ናቸው።

#ሰያፍ #ንባባት

መድረሻ ፊደላቸው እንደ ተጣይ ሁሉ ሁልጊዜም ሳድስ ነው። ግሦችም ስሞችም ተሰይፈው ሊነበቡ ይችላሉ። ምሳሌ
አእመረት፣ ኢሳይያስ፣ ዳንኤል ይላል።

የእለቱ ጥያቄዎች

የሚከተሉትን ቃላት ሥርዓተ ንባባቸውን ግለጽ

፩) መንግሥት

፪) አንፈርአፁ (በደስታ ዘለሉ)

፫) አአምን (አምናለሁ)

፬) ምናሴ

፭) ኅብስት

❤️ግእዝ ክፍል አስራ ሁለት❤️


የንባብ ዓይነቶች

ሦስት ዓይነት የንባብ ዓይነቶች አሉ። አሁን ያሉ የኢትዮጵያ ጳጳሳት፣ ፓትርያርኩ፣ ቀሳውስት፣ ታላላቅ መምህራን ሁሉ
ካሉበት ደረጃ የደረሱት ከፊደል ጀምሮ ቀጥለው ያሉትን የንባብ ዓይነቶች ተምረው ነው። የንባብ ዓይነቶች ሦስት
ናቸው። እነዚህም:-

፩) ግእዝ ንባብ

፪) ቁም ንባብ

፫) ውርድ ንባብ

ናቸው።እያንዳንዳቸውን በዝርዝር ቀጥለን እንመልከት።

#ግእዝ #ንባብ

እያንዳንዱን ቃል እየለዩ አጠር ባለ ዜማ የሚነበብ ነው። እንዴት እንደሚነበብ በቴሌግራም ግሩፑ ማታ ሦስት ሰዓት
ጀምረን እንማማራለን።
#ውርድ #ንባብ

በማኅዘኒ ድምፅ የሚነበብ ሲሆን ይህም ከግእዝ ንባቡ ከፍ ያለ ዜማ ነገር ያለው ነው።ተነሽ ንባብ ብዙ ጊዜ በውርድ ንባብ
ጊዜ ቅድመ መድረሻውን ያዝ አድርጎ መድረሻ ፊደሉን ረገጥ አድርጎ ይነበባል።ነገር ግን ቅድመ መድረሻው ሳድስ ከሆነ
ቅድመ ቅድመ መድረሻውን ያዝ አድርጎ መድረሻ ፊደሉን ረገጥ አድርጎ ይነበባል።ወዳቂ ቃል በውርድ ንባብ ጊዜ መድረሻ
ፊደሉን ረገጥ ያዝ አድርጎ ድምጽን ሳብ በማድረግ ይነበባል። ተጣይ ቃል በውርድ ንባብ ጊዜ ቅድመ መድረሻውን ያዝ
አድርጎ መድረሻ ፊደሉን ረገጥ ሳያደርግ ይነበባል።ሰያፍ ቃል በውርድ ንባብ ጊዜ ቅድመ ቅድመ መድረሻውን ያዝ አድርጎ
መድረሻውን ረገጥ ሳያደርግ ይነበባል። ብዙ ጊዜ የስቅለት ጊዜ ይነበባል። ግፍዖሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍዑኒ የሚለው ንባብ
ነው።

#ቁም #ንባብ

ይህ ተነሹን በተነሽ ወዳቂውን በወዳቂ ሰያፉን በሰያፍ ተጣዩን በተጣይ በፍጥነት እና ቀጥ ባለ ድምፅ እየለየን የምናነበው
ንባብ ነው። በቅዳሴ ሰዓት ወንጌሉ መልእክቱ ሲነበብ በዚህ የንባብ ስልት ነው። የሦስቱንም አነባበብ በቴሌግራም ግሩፑ
ማታ ሦስት ሰዓት ስለምለቀው በዚያ ይከታተሉ።

በሌላ መልኩ ደግሞ ሁለት ዓይነት የንባብ ዓይነቶች አሉ። እነዚህም:-

፩) ጠብቆ የሚነበብ

፪) ላልቶ የሚነበብ

ናቸው። አንድን ቃል ፊደሉን አጥብቀን ስናነበውና አላልተን ስናነበው የተለያየ ትርጉም ሊያመጣ ይችላል። ለምሳሌ
"ሰብሐ" የሚለውን ቃል 'ብ'ን አጥብቀን ስናነበው አመሰገነ የሚል ትርጉም ይኖረዋል። 'ብ'ን አላልተን ስናነበው ግን ሰባ
የሚል ትርጉም ይኖረዋል። ይህን የመሰሉ ሲጠብቁና ሲላሉ የተለያየ ትርጉም ያላቸው ቃላት ብዙ ናቸው። ተጨማሪ
ምሳሌ ፈጸመ፣ጸብሐ ይገኛሉ።

#የፊደላት #ተጽእኖ

በሥርዓተ ንባብ ጊዜ ተነሹን ሰያፉን ተጣዩን ወዳቂ፣ ወዳቂውን ደግሞ ተነሽ የሚያደርጉ ፊደላት አሉ። ከእነዚህም
"ሰ፣ሂ፣ኒ፣መ" ይጠቀሳሉ። ለምሳሌ አኮኑ ወዳቂ ነው። ነገር ግን "መ" ፊደል ሲጨመርበት አኮኑመ ብሎ ተነስቶ ይነበባል።
ይእዜ ወዳቂ ነው። ነገር ግን "ሰ" ሲጨመርበት ይእዜሰ ብሎ ተነስቶ ይነበባል። ስለዚህ "ሰ" እና "መ" ወዳቂውን ተነሽ
ያደርጉታል። "ሰ" ተጣዩን፣ ሰያፉንና ተነሹን ወዳቂ ያደርገዋል። "ሂ" እና "ኒ" አራቱንም ንባባት በወዳቂ ንባብ እንዲነበቡ
ያደርጋሉ። አምላክነሰ፣ አንትሙሰ፣ አምላክነሂ፣ ይእዜኒ የሚሉት የፊደላት ተጽእኖ ያለባቸው ናቸው። በቅዱሳት
መጻሕፍት ብዙ እናገኛለን። "ሰ" በተለየ በአነ ላይ ሲወድቅ ግን ተነስቶ እንዲነበብ ያደርገዋል። አንሰ እፄ ወአኮ ሰብእ
እንዲል።

#የእለቱ #ጥያቄዎች
የሚከተሉትን ቃላት ሥርዓተ ንባባቸውን (ተነሽ፣ ወዳቂ፣ ሰያፍ፣ ተጣይ ለይተህ) ጻፍ።

፩) አንተሂ

፪) ማርያምሰ

፫) እፎኑመ

፬) ወዘእንበሌሁሰ

፭) ኢሳይያስኒ

የጥያቄዎች መልስ

፩) ወዳቂ

፪) ወዳቂ

፫) ተነሽ

፬) ተነሽ

፭) ወዳቂ

#የግሥ #ጥናት #ክፍል #አንድ

ግእዝ=አማርኛ

፩) ሃልሀ=ወደረ (የከብት)

፪) ለሕሐ=ቀዳ (የውሃ የመጽሐፍ)

፫) ላሕልሐ=ራሰ

፬) ለስሐ=አልጫ ሆነ (የወጥ)

፭) ለቅሐ=አበደረ

፮) ለብሐ=ሠራ (የሸክላ ብቻ)

፯) ለትሐ=ተጎነጨ (የመጠጥ)

፰) ሎሐ=ጻፈ

፱) ለጥሐ=ገበረ

፲) ማሕምሐ=አፈረሰ
፲፩) መልኀ=መዘዘ

፲፪) መልሐ=አጣፈጠ

፲፫) መስሐ=ምሳ አደረገ

፲፬) መርሐ=መራ

፲፭) ሞርቅሐ=ላጠ

፲፮) ሞቅሐ=አሰረ (የሰው ብቻ)

፲፯) መትሀ=ሣሣ፣ቀጠነ (የመርቀቅ)

፲፰) መንዝሐ=ተደላደለ

፲፱) መድሐ=ፈጨ

፳) ሞጥሐ=ለበሰ

፳፩) ሰርሐ=ሠራ

፳፪) ሠርሐ=አቅናና፣አከናወነ

፳፫) ሣርኀ=አበራ

፳፬) ሰብሐ=አመሰገነ

፳፭) ሠብሐ=ስብ ሆነ (የከብት)

፳፮) ሰንሐ=በራ ሆነ

፳፯) ሰይሐ=ታመመ

፳፰) ሴሐ=ወገጠ

፳፱) ሰጥሐ=አሰጣ፣ ዘረጋ

፴) ሰፍሐ=ሰፋ (ሰፊ ሆነ)

፴፩) ረምሐ=ወጋ (የጦር)

፴፪) ረስሐ=ጎሰቆለ

፴፫) ረቅሐ=ጋረጠ (የጋሬጣ)

፴፬) ረብሐ=ረባ
፴፭) ረውሐ=ቀደደ

፴፮) ሮሐ=ወለወለ፣አራገበ፣አናፈሰ

፴፯) ቀሕቅሐ=ተንቆራቆሰ፣አሰምቶ ተናገረ

፴፰) ቈልሐ=ፍሬ ያዘ

፴፱) ቀምሐ=አፈራ

፵) ቀርሐ=ጨለጠ

፵፩) ቃርሐ=ተኰሰ

፵፪) ቄሐ=ቀላ (የመቅላት)

፵፫) ቀድሐ=ቀዳ (የመጽሐፍ የውሃ)

፵፬) በኅብኀ=ከረፋ፣ቀረና

፵፭) በኍበኈ=ሸተተ፣ በሰበሰ

፵፮) በልኀ=ተሳለ፣ስለት ሆነ

፵፯) ባልሐ=አዳነ

፵፰) በርሀ=ብርሃን ሆነ

፵፱) በርሐ=በራ ሆነ

፶) በዝኀ=በዛ

፶፩) በጥሐ=በጣ

፶፪) በጽሐ=ደረሰ

፶፫) ታሕትሐ=ፈላ

፶፬) ተመክሐ=ተመካ

፶፭) ቶስሐ=ጨመረ

፶፮) ተራኅርኀ=ቸር ሆነ፣ራራ

፶፯) ተቃድሐ=ተደነባበረ (የድንበር)

፶፰) ተበውሐ=ሠለጠነ፣ፈቃድ ተቀበለ


፶፱) ተንሀ=አገመ

፷) ተወፅሐ=ተፈጨ፣ተቆላ (የመከራ)

፷፩) ተዋህውሀ=ተመላለሰ

፷፪) ተየውሃ=የዋህ ሆነ፣ ተሞኘ፣ ገራም ሆነ

፷፫) ቴሀ=ቀላወጠ

፷፬) ተጋህግሀ=ክፍት ክፍት አለ

፷፭) ተጋውሐ=ጎረቤት ሆነ

፷፮) ተግሀ=ተጋ

፷፯) ተጻብሐ=እንዴት አድርህ ተባባለ

፷፰) ተፈሥሐ=ደስ ተሰኘ

፷፱) ናሕንሐ=ትርፍርፍ አለ

፸) ነስሐ=ተጸጸተ

፸፩) ነስኀ=ሸተተ፣ከረፋ

፸፪) ነቅሀ=ነቃ

፸፫) ነብሐ=ጮኽ (የውሻ፣የሰው፣የንብ)

፸፬) ኖኀ=ረዘመ

፸፭) ነዝሀ=ረጨ

፸፮) ነድሐ=ነዳ

፸፯) ነግሀ=ነጋ

፸፰) ነጽሐ=ንጹሕ ሆነ፣ነጻ

፸፱) ነፍኀ=ነፋ፣ቀበተተ

፹) አምኀ=እጅ ነሣ

፹፩) አመልትሐ=አመሳቀለ

፹፪) አመርግሐ=አንከባለለ
፹፫) አመድቅሐ=ሠራ (የቤት)

፹፬) አመብኵሐ=አናፋ (የእሳት የትንፋሽ)

፹፭) አስተማዝሐ=አቀበጠ አቀማጠለ

፹፮) አርሳሕስሐ=አረሳሳ፣አስነወረ

፹፯) አቅያሕይሐ=አቅላላ

፹፰) አብሐ=አሰናበተ

፹፱) አንሳሕስሐ=አነሳሳ ተነሳሳ

፺) አንቆቅሐ=ቋቋ (የእንቁላል)

፺፩) አንባሕብሐ=ዱብ ዱብ አደረገ

፺፪) አንካሕክሐ=ፈተፈተ

፺፫) አንግሀ=ማለደ

፺፬) አውጽሐ=አቀረበ ቀዳ

፺፭) ኤኀ=ጠፋ

፺፮) አጸንሕሐ=አሻተተ

፺፯) አጽናሕንሐ=ወዘወዘ (የጽና)

፺፰) ከልሐ=ጮኽ (የሰው የከብት)

፺፱) ከልትሐ=አሰረ (የነዶ)

፻) ኰስሐ=ተናጻ

፻፩) ኰርሀ=ግድ አለ

፻፪) ወክሐ=ደነፋ፣ ፎከረ

፻፫) ወጥሐ=ከመረ፣ ደረደረ

፻፬) ዛሕዝሐ=ትርፍርፍ አለ

፻፭) ዘልሐ=ጠመቀ (የጠላ)

፻፮) ዘብሐ=አረደ
፻፯) ዘግሐ=ዘጋ

፻፰) የውሀ=አታለለ

፻፱) ደኅኀ=ጸና

፻፲) ደምሐ=ጠለቀ

፻፲፩) ደርግሐ=ደረተ፣ሰፋ

፻፲፪) ደቅሐ=ደቃ፣ቀጠቀጠ

፻፲፫) ገህሀ=አበራ

፻፲፬) ጋህግሀ=ክፍት ክፍት አደረገ (የመስኮት)

፻፲፭) ገምሀ=ነጨ፣አለፋ፣መለጠ (የቆርበት)

፻፲፮) ገርሀ=ገራ፣ግር ሆነ (የጠባይ የእርሻ)

፻፲፯) ጎርሐ=ተተነኳኮለ

፻፲፰) ገንሐ=ተቆጣ

፻፲፱) ጎሐ=ጠባ፣ነጋ

፻፳) ጠብሐ=አረደ

፻፳፩) ጠፋልሐ=መዘነ

፻፳፪) ጠፍሐ=አጨበጨበ

፻፳፫) ጻሕጽሐ=አጎረፈ

፻፳፬) ጸርሐ=ጮኸ

፻፳፭) ጸብሐ=ጠባ

፻፳፮) ጸብሐ=ገበረ

፻፳፯) ጸንሐ=ቆየ

፻፳፰) ጼሐ=ጠረገ

፻፳፱) ጸፍሐ=ገለበጠ፣ለመጠ

፻፴) ፈልሐ=ፈላ
፻፴፩) ፈርሀ=ፈራ

፻፴፪) ፈትሐ=ፈታ፣ፈረደ

፻፴፫) ፎሐ=ገመሰ

፻፴፬) ፈጽሐ=ገመሰ፣ሰነጠቀ፣ፈነቀለ

#የግሥ #ጥናት #ክፍል #ሁለት

ግእዝ=አማርኛ

፩) ሐለለ=አረረ፣በራ፣ተቃጠለ

፪) ሐመለ=ለቀመ፣ቀነጠሰ

፫) ሐሰለ=ለበበ (የልጓም)

፬) ሐቀለ=ቀማ

፭) ኀበለ=ተደፋፈረ

፮) ሐበለ=ታታ

፯) ሐብለ=ዋሸ

፰) ሐንበለ=ጫነ (የኰረቻ)

፱) ሖለ=ቀላቀለ፣አደባለቀ

፲) ሐዘለ=አዘለ

፲፩) ኀየለ=በረታ

፲፪) ኄለ=መነጨ

፲፫) ሀጕለ=ጠፋ

፲፬) ሐፈለ=ቁንጥር ቁንጥር አለ (የስካር)

፲፭) መሐለ=ማለ

፲፮) መለለ=ላገ፣ጠረበ፣አለሰለሰ (የእንጨት)

፲፯) መምዔለ=ወነጀለ

፲፰) መሰለ=መሰለ
፲፱) መሰለ=ጣዖት ሠራ

፳) መበለ=ብልጭ አለ

፳፩) መዐለ=ወነጀለ

፳፪) መከለ=ቆረጠ

፳፫) ሞጽበለ=ሞረደ

፳፬) ሰሐለ=ሳለ (የብረት)

፳፭) ሳሕለለ=ደረቀ

፳፮) ሰመለ=አለዘበ (የጠባይ የእንጨት)

፳፯) ሰሰለ=ወገደ

፳፰) ሰቀለ=ሰቀለ

፳፱) ሰብለ=ዘረዘረ

፴) ሰንሰለ=አያያዘ፣አቆራኘ

፴፩) ሰአለ=ለመነ

፴፪) ሰከለ=አፈራ

፴፫) ሶለ=ሸተ፣ጮረቃ

፴፬) ሰደለ=መዘነ

፴፭) ሰገለ=ጠነቆለ

፴፮) ሰፈለ=መታ፣ቀጠቀጠ (የዱቄት የብረት)

፴፯) ረመለ=ጠነቆለ

፴፰) ሮለ=በሳ፣ቀደደ

፴፱) ረገለ=ቀዘፈ

፵) ቀለ=ቀለለ

፵፩) ቈልቈለ=ዘቀዘቀ

፵፪) ቈስለ=ቆሰለ
፵፫) ቀበለ=ሸኘ

፵፬) ቀብለ=ጎደለ፣አነሰ

፵፭) ቀተለ=ገደለ

፵፮) ቀፈለ=ለበጠ፣ሸለመ

፵፯) ብህለ=አለ

፵፰) በልበለ=አረጀ፣አለቀ (የልብስ)

፵፱) በሰለ=በሰለ

፶) በቈለ=በቀለ

፶፩) ብዕለ=ባዕለጸጋ ሆነ

፶፪) ቤዐለ=ወደደ

፶፫) በአለ=እንቢ አለ

፶፬) ቤወለ=ወደደ

፶፭) በጠለ=ጠፋ

፶፮) በጸለ=ቦጨቀ

፶፯) ትሕለ=ቀላወጠ

፶፰) ተልዕለ=ከፍ ከፍ አለ

፶፱) ተማሕለለ=ምሕላ ያዘ

፷) ተመዝጎለ=ተከራከረ

፷፩) ተሠሀለ=ይቅር አለ

፷፪) ተሰአለ=ተጠያየቀ፣ጠየቀ

፷፫) ተሰነአለ=ተስማማ

፷፬) ተቀበለ=ተቀበለ

፷፭) ተቀጸለ=ተቀዳጀ

፷፮) ተበቀለ=ቂም ያዘ፣ተበቀለ


፷፯) ተንበለ=ለመነ

፷፰) ተአንተለ=ቸል ቸል አለ

፷፱) ተዐገለ=ቀማ

፸) ተከለ=ተከለ

፸፩) ተኬወለ=ወደኋላ አላ

፸፪) ተወከለ=ታመነ

፸፫) ተድሕለ=ኮበለለ

፸፬) ተደንገለ=ተጠበቀ፣ድንግል ሆነ

፸፭) ተዳወለ=ተዳካ፣ተዋሰነ

፸፮) ተጋደለ=ተጋደለ

፸፯) ተፋወለ=አሟረተ

፸፰) ንኅለ=ፈረሰ

፸፱) ነቀለ=ነቀለ

፹) ነዐለ=ተጫማ

፹፩) ነደለ=በሳ

፹፪) ነጸለ=ለየ፣ነጠለ

፹፫) አሕመልመለ=ለመለመ፣አለመለመ

፹፬) ዐለለ=ጎለተ፣ርስት ጉልት አደረገ

፹፭) አመስቀለ=አመሳቀለ

፹፮) አማዕቀለ=ጥልቅ አደረገ

፹፯) አማዕበለ=ማዕበል አደረገ

፹፰) አማእከለ=መካከል አደረገ

፹፱) አመድበለ=አከማቸ

፺) አስተሰነአለ=አስማማ፣ተስማማ፣ ተሰነባበተ
፺፩) አቍጸለ=ለመለመ፣አለመለመ

፺፪) አብዐለ=አከበረ

፺፫) ዐበለ=አሰኘ

፺፬) አንሳሕለለ/አንዛሕለለ=አለ ዘለል አለ (ሥራ የመፍታት)

፺፭) አንቀልቀለ=ተነዋወጠ፣አነዋወጠ

፺፮) አንበልበለ=ነበልባል አደረገ

፺፯) አንኮለለ=ዱብ ዱብ አደረገ

፺፰) አንጦለለ=ለየ

፺፱) አከለ=በቃ፣ልክ ሆነ

፻) ዐዘለ=በረታ

፻፩) ዔለ=ዞረ፣ተንከረተተ

፻፪) ዐገለ=አቆመ፣በገረ፣አስበገረ፣ ደረደረ

፻፫) አገንጰለ=ጻፈ፣ገለበጠ

፻፬) አጰንገለ=ተረጎመ፣ጻፈ

፻፭) አጽለለ=አረፈ፣አሳረፈ

፻፮) አጽደልደለ=አበራ

፻፯) ክህለ=ቻለ

፻፰) ኵሕለ=ኳለ

፻፱) ከለለ=ጋረደ

፻፲) ከፈለ=ከፈለ

፻፲፩) ወዐለ=ዋለ

፻፲፪) ዝሕለ=ዛገ፣አደፈ፣ሻገተ (የወርቅ የብረት)

፻፲፫) ዘለለ=ጠመቀ፣ዘለለ (የጠላ)

፻፲፬) ዘበለ=ተናጻ
፻፲፭) ዘወለ=አቀለመ፣አጠቆረ

፻፲፮) ደለለ=ከፈከፈ፣ደለለ (የቤት የሰው)

፻፲፯) ደበለ=ሰበሰበ፣አከማቸ

፻፲፰) ገልገለ=ገላገለ

፻፲፱) ገንጰለ=ገለበጠ

፻፳) ገደለ=ጣለ (የጥንብ)

፻፳፩) ጥሕለ=አተለ (የሚያትል ሁሉ)

፻፳፪) ጠለ=ለመለመ

፻፳፫) ጠቀለ=በነገር ነካ

፻፳፬) ጤቀለ=ጻፈ

፻፳፭) ጠብለለ=ጠቀለለ

፻፳፮) ጸሐለ=ሠራ (የብረት)

፻፳፯) ጸለለ=ጋረደ

፻፳፰) ጸለለ=ተንኳፈፈ

፻፳፱) ጸበለ=ትቢያ ሆነ

፻፴) ጸንጸለ=መታ

፻፴፩) ጸዐለ=ሰደበ

፻፴፪) ጽእለ=ቆሰለ

፻፴፫) ጸደለ=በራ

፻፴፬) ፈሐለ=ቁንጥር ቁንጥር አለ

፻፴፭) ፈልፈለ=መነጨ

፻፴፮) ፈተለ=ፈተለ

፻፴፯) ፈደለ=ጻፈ

#የግሥ #ጥናት #ክፍል #ሦስት


ግእዝ=አማርኛ

፩) ሐለመ=አለመ (የሕልም)

፪) ሐመ=ታመመ

፫) ሐመመ=ተመቀኘ

፬) ሐሠመ=ከፋ

፭) ሐረመ=ተወ

፮) ሐርተመ=ጎሰቆለ

፯) ኀተመ=አተመ

፰) ሐከመ=አከመ

፱) ሀደመ=አንቀላፋ

፲) ሐደመ=አወጋ፣ተረተ

፲፩) ልሕመ=ላመ

፲፪) ለምለመ=ለመለመ

፲፫) ለተመ=አሸ፣ፈተገ፣ወገጠ፣ ልጦ ጉርድ አወጣ

፲፬) ለጎመ=ለጎመ፣ገታ

፲፭) ሰለመ=ፈታ

፲፮) ሠረመ=አጠለቀ፣አሰጠመ

፲፯) ሶርየመ/ሶርዔመ=ለምድ አወጣ

፲፰) ሰቀመ=ማረከ

፲፱) ሰተመ=ደረሰ

፳) ሰዐመ=ሳመ

፳፩) ሰከመ=ተሸከመ

፳፪) ሤመ=ሾመ

፳፫) ሰገመ=አሰረ
፳፬) ረመ=ራመመ (የብራና)

፳፭) ረመመ=ጻፈ

፳፮) ረቀመ=ረጨ (የቀለም)

፳፯) ረዐመ=ጮኽ

፳፰) ሬመ=ከፍ ከፍ አለ፣ወጣ (የሰማይ የደርብ)

፳፱) ረገመ=ረገመ

፴) ቀለመ=ጻፈ

፴፩) ቀሠመ=ለቀመ

፴፪) ቀሰመ=አጣፈጠ

፴፫) ቀረመ=ለቀመ

፴፬) ቆመ=ቆመ

፴፭) ቀደመ=ቀደመ

፴፮) ብህመ=ዲዳ ሆነ

፴፯) በለመ=ጻፈ

፴፰) ተለመ=ተለመ (የእርሻ)

፴፱) ተሳለመ=ተፈቃቀረ

፵) ተሰዐመ=ተስማማ

፵፩) ተሰጥመ=ተሰጠመ

፵፪) ተርጎመ=ተረጎመ

፵፫) ተቃወመ=ተከራከረ

፵፬) ተቀየመ=ቂም ያዘ

፵፭) ተነወመ=አለመ

፵፮) ተደመ=ተደነቀ

፵፯) ተጽመመ=ቸል ቸል አለ
፵፰) ተፍእመ=ጎረሰ

፵፱) ንእመ=አክ አለ

፶) ኖመ=ተኛ

፶፩) ዐለመ=ፈጠረ

፶፪) አስተሐመመ=አስተጋ፣ተጋ

፶፫) አስተቃሰመ=አሟረተ

፶፬) አርመመ=ዝም አለ

፶፭) አልኰመ=አስነካ (የነገር፣የመንካ፣የከንፈር)

፶፮) ዐቀመ=ለካ

፶፯) ዐቀመ=ቆረጠ (የነገር)

፶፰) ዐተመ=ተቆጣ

፶፱) አነመ=ሠራ (የልብስ)

፷) ዔመ=መሰገ፣ሰበሰበ

፷፩) አደመ=አማረ

፷፪) አግደምደመ=አግደመደመ (የእግር)

፷፫) ከመመ=ቆረጠ፣አስተካከለ

፷፬) ከረመ=የወይን ጠጅ አደረገ

፷፭) ከርመ=ከረመ

፷፮) ከተመ=ጫፍ ሆነ

፷፯) ወስከመ=ሰነገ፣አሰረ፣ጠለፈ (የማነቂያ)

፷፰) ዝሕመ=ሞቀ

፷፱) ዘመመ=አሰረ፣ ለጎመ፣ አፈነ፣ ዘመመ፣ ለበበ

፸) ዘንመ=ዘነበ

፸፩) ዳሕመመ=አፈረሰ፣ናደ
፸፪) ደምደመ=አጎተነ፣አጎፈረ (የጸጉር)

፸፫) ደክተመ=ድኻ አደግ ሆነ

፸፬) ደክመ=ደከመ

፸፭) ደገመ=ደገመ

፸፮) ገረመ=ተፈራ፣አስፈራ

፸፯) ጎርየመ/ጎርዔመ=አገመ

፸፰) ገዘመ=ቆረጠ

፸፱) ገደመ=አገደመ፣ገደመ (የነገር የመንገድ የገዳም)

፹) ጠለመ=ከዳ፣ሸፈተ

፹፩) ጠመ=ጠመመ

፹፪) ጠቀመ=ሠራ፣አደሰ (የግንብ)

፹፫) ጥዕመ=ቀመሰ

፹፬) ጦመ=ጠቀለለ፣ጠመጠመ፣አጠፈ

፹፭) ጽሕመ=በቀለ

፹፮) ጸልመ=ጠቆረ

፹፯) ጸመ=ደነቆረ

፹፰) ፀመ=ደረቀ

፹፱) ጸምጸመ=ሠራ፣ጨመጨመ (የቤት)

፺) ጸተመ=ደረሰ

፺፩) ጾትኤመ/ጾትየመ/ጾተመ=የወይን ጠጅ አደረገ

፺፪) ጾመ=ጾመ

፺፫) ፀገመ=ጠመመ

፺፬) ፍሕመ=ፋመ፣ሞገደ

፺፭) ፈለመ=ጀመረ
፺፮) ፈፀመ=ነጨ (የፊት)

፺፯) ፈጸመ=ጨረሰ

የግሥ ጥናት ክፍል አራት

ግእዝ=አማርኛ

፩) ኀመሰ=አምስት አደረገ

፪) ኀሠሠ=ፈለገ

፫) ኈሠሠ=ጠረገ

፬) ሐረሰ=አረሰ

፭) ኀበሰ=ጋገረ

፮) ሐንከሰ=አነከሰ

፯) ሖሰ=ቀላቀለ

፰) ሖሰ=ነቀነቀ፣አንቀሳቀሰ

፱) ኄሰ=ተሻለ

፲) ሔሰ=ነቀፈ፣ሰደበ

፲፩) ሐደሰ=አዲስ አደረገ

፲፪) ሐፈሠ=ዘገነ

፲፫) ላቀሰ=አለቀሰ

፲፬) ለብሰ=ለበሰ

፲፭) ለንጰሰ=ሠራ (የልብስ)፣ ተንቦገቦገ (የብርሃን)

፲፮) ሎሰ=ለወሰ

፲፯) መሐሰ=ቆፈረ

፲፰) መለሰ=መለሰ

፲፱) መረሰ=ነከረ፣ዘፈቀ

፳) መርሰሰ=ዳሰሰ፣ነካ
፳፩) መቈሰ=አጠፋ

፳፪) መንኰሰ=መነኮሰ

፳፫) ሜሰ=አደለ፣አሳለፈ

፳፬) ሠለሰ=ሦስት አደረገ

፳፭) ሰንኰረሰ=አስተማረ

፳፮) ሰኰሰ=ጠረገ

፳፯) ሰደሰ=ስድስት አደረገ

፳፰) ርሕሰ=ራሰ፣ረጠበ

፳፱) ረምሰ=ጋለ

፴) ረመሰ=ዘፈቀ፣ነከረ፣ዘፈዘፈ

፴፩) ርእሰ=አለቃ ሆነ

፴፪) ረኵሰ=ረከሰ

፴፫) ሮሰ=ወለደ

፴፬) ቆመሰ=ቆሞስ ሆነ

፴፭) ቀሰ=አገለገለ

፴፮) ቀደሰ=አመሰገነ

፴፯) በስበሰ=አረጀ፣በሰበሰ

፴፰) ብእሰ=ባሰ፣ከፋ

፴፱) ተሞገሰ=ባለሟል ሆነ፣ተወደደ

፵) ተቃለሰ=ታገለ

፵፩) ተበአሰ=ተጣላ

፵፪) ተተረአሰ=ተንተራሰ

፵፫) ተአንሰሰ=እንስሳ ሆነ፣ተሞኘ

፵፬) ተዐገሠ=ቻለ፣ታገሠ
፵፭) ተከነሰ=አንድ ሆነ፣ተቀላቀለ

፵፮) ተከውሰ=ተነቃነቀ

፵፯) ተኬሰ=መታ፣ጠመጠመ፣ መነጨ

፵፰) ተውሕሰ=ዋስ ሆነ፣ተዋሰ

፵፱) ተግሕሠ=ወገደ፣ሸሸ

፶) ተጰጰሰ=ጳጳስ ሆነ

፶፩) ተጸነሰ=ተቸገረ

፶፪) ተፈርነሰ=ተደሰተ፣ተፈረነሰ

፶፫) ተፋሰሰ=እጣ ተጣጣለ

፶፬) ነሐሰ=ሠራ (የቤት፣የመዳብ)

፶፭) ነስነሰ=ጎዘጎዘ፣ነሰነሰ

፶፮) ንእሰ=አነሰ

፶፯) ነግሠ=ነገሠ

፶፰) ነፍሰ=ነፈሰ

፶፱) አልኈሰሰ=ሹክ ሹክ አለ

፷) አመርሰሰ=ጸጥ አደረገ

፷፩) አስተንፈሰ=አሻተተ

፷፪) አርመስመሰ=አጥመሰመሰ፣ አንኮሻኮሸ፣ አርመሰመሰ

፷፫) አበሰ=በደለ

፷፬) አነሰ=አነሰ፣ሰው ሆነ

፷፭) አንበስበሰ=ተገለባበጠ፣ አገለባበጠ

፷፮) አክሞሰሰ=ፍግግ ፍግግ አለ

፷፯) አኮሰ=አቅባባ፣አዋሐደ፣ አገናኘ፣ አማሰለ

፷፰) ዔሰ=ዞረ፣ዛበረ
፷፱) ዐጠሰ=አነጠሰ

፸) አጽሐሰ=አሸበሸበ

፸፩) አፅበሰ=ልምሾ አደረገ

፸፪) ኵሕሰ=ተናጻ

፸፫) ከልሰሰ= አሰረ (የነዶ)

፸፬) ኰስኰሰ=ተዝጎረጎረ

፸፭) ከበሰ=ጠመጠመ

፸፮) ወረሰ=ወረሰ

፸፯) ወቀሠ=ወቀሠ

፸፰) ወደሰ=አመሰገነ

፸፱) ወጠሰ=አቃጠለ፣ተቃጠለ

፹) ዘልገሰ=ታመመ፣ቆሰለ፣አበጠ

፹፩) የብሰ=ደረቀ

፹፪) ደሐሰ=ሠራ (የዳስ)

፹፫) ደመሰ=ጨለመ

፹፬) ደምሰሰ=አጠፋ፣ደመሰሰ

፹፭) ደረሰ=ደረሰ (የድርሰት)

፹፮) ደቀሰ=ተኛ፣አንቀላፋ

፹፯) ደነሰ=ኃጢአት ሠራ

፹፰) ደጎሰ=ደጎሰ

፹፱) ግሕሰ=ወገደ

፺) ገመሰ=ገመሰ

፺፩) ገሰሰ=ዳሰሰ

፺፪) ገረሠ=ሠራ (የወርቅ)


፺፫) ገብሰሰ=አረጀ

፺፬) ጌሠ=ገሠገሠ

፺፭) ጠረሰ=አፋጨ

፺፮) ጠበሰ=ጠበሰ

፺፯) ጤሰ=ጤሰ

፺፰) ፀረሰ=በለዘ

፺፱) ፀበሰ=ልምሾ ሆነ

፻) ፀንሰ=ፀነሰ

፻፩) ፀወሰ=ሰለለ (የሕማም)

፻፪) ፈሐሰ=ፈተለ (የፈትል)፣ አበበ (የአበባ)

፻፫) ፈለሰ=ተሰደደ

፻፬) ፈወሰ=አዳነ

፻፭) ፈደሰ=ቆራ (የሳዱላ)

የግሥ ጥናት ክፍል አምስት

ግእዝ=አማርኛ

፩) ኀስረ=ጎሰቆለ

፪) ሐረረ=አረረ፣ተኮሰ፣ሞቀ

፫) ሐብረ=አንድ ሆነ፣ተባበረ

፬) ኆበረ=ሸለመ

፭) ሐንገረ=እሽኮኮ አለ

፮) ሖረ=ሔደ

፯) ኀደረ=አደረ

፰) ሐጸረ=አጠረ

፱) ኀጽረ=አጭር ሆነ፣አጠረ (የቁመት፣ የጊዜ)


፲) ኀፈረ=ወደደ

፲፩) ኀፍረ=አፈረ

፲፪) ሎረ=በሳ

፲፫) ለጠረ=መዘነ

፲፬) መሀረ=አስተማረ

፲፭) መረ=መረረ

፲፮) መተረ=ቆረጠ

፲፯) መከረ=መከረ

፲፰) መከረ=ጠበሰ

፲፱) መዘረ=ጠመቀ፣ዘለለ (የጠላ)

፳) መዝበረ=ፈረሰ፣ተናደ፣ተበተነ

፳፩) መደረ=ጸና

፳፪) መጸረ=አመሰኳ

፳፫) መቈረ=አጣፈጠ

፳፬) ሠምረ=ወደደ

፳፭) ሰረረ=ወጣ

፳፮) ሣረረ=ሠራ (የቤት)

፳፯) ሰቈረ=በሳ

፳፰) ሰበረ=ሰበረ

፳፱) ሰተረ=ቀደደ

፴) ሰዐረ=ሻረ

፴፩) ሥዕረ=ለመለመ

፴፪) ሰክረ=ሰከረ

፴፫) ሰወረ=ሸሸገ
፴፬) ሰዘረ=ሰነዘረ

፴፭) ሠገረ=ተራመደ

፴፮) ሠጸረ=ሰነጠቀ፣ፈለጠ

፴፯) ሰፈረ=ለካ፣ሰፈረ

፴፰) ቀሐረ=ተኰሰ (የሕማም)

፴፱) ቀመረ=ቆጠረ

፵) ቈረ=ቀዘቀዘ

፵፩) ቀበረ=ቀበረ

፵፪) ቆበረ=ጭጋግ ሆነ

፵፫) ቀተረ=ሳበ

፵፬) ቀትረ=ቀትር ሆነ

፵፭) ቈጰረ=ቆረጠመ

፵፮) ቀጸረ=ከበበ፣ቀጠረ፣አጠረ (የአጥር)

፵፯) ቈጸረ=ቋጠረ

፵፰) ቀፈረ=ለካ፣ሳበ፣ገተረ (የጦር የደጋን)

፵፱) ባሕረረ=ብርር ብርር አለ፣ባከነ፣ ደነገጠ፣ሰፋ (የመብረር)

፶) በረ=በረረ፣ሮጠ

፶፩) በርበረ=በረበረ፣ዘረፈ፣በዘበዘ

፶፪) በኰረ=ታጎለ

፶፫) በደረ=ቀደመ

፶፬) ተበኵረ=አለቃ ሆነ፣በኵር ሆነ

፶፭) ተዐወረ=ቸል ቸል አለ

፶፮) ተዐዝረ=ጭልጥ ብሎ ሄደ

፶፯) ተዐየረ=ተመጻደቀ፣ተሳደበ
፶፰) ተከወረ=ነዳ፣ቀዘፈ

፶፱) ተወዐረ=አደነቀ

፷) ተዘከረ=አሰበ

፷፩) ተዝኅረ=ኰራ፣ታጀረ፣ተጀነነ (የአካሄድ የአለባበስ)

፷፪) ተድኅረ=ወደኋላ ሆነ

፷፫) ተደረ=በላ፣ተመገበ (የራት)

፷፬) ተደብተረ=ሰፋ (የድንኳን)

፷፭) ተገበረ=አረሰ

፷፮) ተገረ=ተክለ (የካስማ የድንኳን)

፷፯) ተጋወረ=ጎረቤት ሆነ፣ተጎራበተ

፷፰) ተገየረ=መጻተኛ ሆነ

፷፱) ተጠየረ=አሟረተ፣ጠነቆለ

፸) ተፃመረ=አንድ ሆነ

፸፩) ተፃረረ=ተጣላ

፸፪) ተጽዕረ=ተጨነቀ

፸፫) ንኅረ=አኮረፈ (የሰው የውሃ)

፸፬) ነሰረ=በረረ፣ዱብ ዱብ አለ (የደም የአሞራ)

፸፭) ነቈረ=አንድ ዓይና ሆነ

፸፮) ነበረ=ተቀመጠ

፸፯) ነከረ=ለየ

፸፰) ነዘረ=ወጋ፣ነከሰ (የአውሬ)

፸፱) ነገረ=ነገረ

፹) ነጠረ=ብልጭ አለ (የብልጭታ)

፹፩) ነጸረ=አየ
፹፪) ነፀረ=ለየ፣ሰነጠቀ፣ከፈለ

፹፫) ነጽረረ=ከበደ

፹፬) አኀረ=አንድ አደረገ

፹፭) አኅሰርሰረ=አቅባባ፣ቀባ (የውርደት ስም)

፹፮) አመረ=አመለከተ፣ተመለከተ

፹፯) አማኅበረ=ማኅበር አደረገ፣ ሰበሰበ፣ ሸነጓ

፹፰) አመስጠረ=አራቀቀ፣ አመሰጠረ

፹፱) አምረረ=አሳዘነ

፺) አመንዘረ=አመነዘረ

፺፩) አመዐርዐረ=አጣፈጠ

፺፪) አመዝበረ=አፈረሰ፣ናደ

፺፫) አማዕረረ=ማረረ

፺፬) አማዕዘረ=አበራ፣አፍለቀለቀ፣ አንጽባረቀ

፺፭) አምዘረ=ጠመቀ (የጠላ ብቻ)

፺፮) አምደረ=አጸና

፺፯) አሥመረ=አገለገለ

፺፰) አሰረ=አሰረ

፺፱) ዐሠረ=ዐሥር አደረገ

፻) አስቈረረ=ተጸየፈ፣አጸየፈ

፻፩) አስተሐቀረ=አቃለለ

፻፪) አስተመሐረ=አማለደ፣ማለደ

፻፫) አስተናበረ=አዘጋጀ

፻፬) አስተደኀረ=ወደኋላ አለ፣ አከታተለ

፻፭) አስተፃመረ=አንድ አደረገ


፻፮) አስተፃረረ=አጣላ

፻፯) አሥገረ=አጠመደ

፻፰) አረረ=ለቀመ (የአዝመራ)

፻፱) ዐቈረ=ቋጠረ

፻፲) ዐበረ=ድርቅ ሆነ፣ደረቀ

፻፲፩) አብሠረ=ነገረ (የምሥራች)

፻፲፪) አብደረ=መረጠ

፻፲፫) አንከረ=አደነቀ

፻፲፬) አንኰርኰረ=ተገለባበጠ፣ አገለባበጠ

፻፲፭) አንወረ=አነወረ፣ነቀፈ፣ሰደበ

፻፲፮) አንዘረ=መታ (የዘፈን የአዝማሪ)

፻፲፯) አንዶረረ(አንጾረረ)=ጩርቅ ጩርቅ አለ፣ተጨነቀ

፻፲፰) አንገርገረ=ጣለ፣አፍገመገመ፣ ተፍገመገመ (የጋኔን)

፻፲፱) አንጎርጎረ=አጉረመረመ፣ አንጎራጎረ፣ ተጉረመረመ (የመክፋት)

፻፳) አንጸረ=ተመላከተ፣ አመለከተ፣ አሳየ

፻፳፩) አእመረ=አወቀ

፻፳፪) ዖረ=ታወረ

፻፳፫) አውተረ=አዘወተረ

፻፳፬) ዐየረ=አሳልፎ ሰጠ

፻፳፭) አገረ=ወታደር ሆነ፣ተራመደ

፻፳፮) አግመረ=ቻለ

፻፳፯) አግረረ=ገዛ፣አስገዛ

፻፳፰) አገበረ=ግድ አለ

፻፳፱) አጥሀረ=ጠመቀ፣አጠመቀ፣ አጠራ፣ አነጻ (የጠላ፣ የሰው)


፻፴) ዐጸረ=ጠመቀ (የጠላ)

፻፴፩) አፅረረ=ሸፈተ

፻፴፪) አጽበረ=ጭቃ አደረገ

፻፴፫) አፍቀረ=ወደደ

፻፴፬) ኰስተረ=ጠረገ

፻፴፭) ከብረ=ከበረ

፻፴፮) ከተረ=ከበበ፣ጋረደ

፻፴፯) ከፈረ=ለካ (የስፍር)

፻፴፰) ወሠረ=ገዘገዘ፣ሰነጠቀ

፻፴፱) ወቀረ=ወቀረ፣አለዘበ

፻፵) ወተረ=ሳበ፣ገተረ፣ዘረጋ (የደጋን)

፻፵፩) ወዘረ=ሸለመ፣ለበጠ፣አስጌጠ (የሕንጻ)

፻፵፪) ወገረ=ወገረ፣መታ፣ደበደበ

፻፵፫) ወፈረ=ተሰማራ

፻፵፬) ዘመረ=አመሰገነ

፻፵፭) ዘርዘረ=በተነ

፻፵፮) ዘከረ=ስም ጠራ

፻፵፯) ዞረ=ዞረ፣ከበበ

፻፵፰) ዘፈረ=ጫፍ ሆነ (የልብስ)

፻፵፱) ደኀረ=አጨ

፻፶) ደመረ=ጨመረ

፻፶፩) ደበረ=ደበረ፣ገዳም አደረገ

፻፶፪) ደጎረ=በሳ፣ቀደደ

፻፶፫) ደፈረ=ደፈረ
፻፶፬) ገብረ=አደረገ

፻፶፭) ገረረ=ተገዛ

፻፶፮) ገዐረ=ጮኽ፣ተጨነቀ

፻፶፯) ገዘረ=ገረዘ

፻፶፰) ገየረ=ቀባ፣ለሰነ፣ለቀለቀ

፻፶፱) ጎጽፈረ=አከከ

፻፷) ጥህረ=ጮኽ

፻፸) ጦመረ=ጻፈ

፻፸፩) ጠፈረ=ታታ

፻፸፪) ፀመረ=አንድ አደረገ

፻፸፫) ጸበረ=ጭቃ አደረገ

፻፸፬) ጽዕረ=ተጨነቀ

፻፸፭) ጾረ=ተሸከመ

፻፸፮) ጸጎረ=ጨጎራም ሆነ

፻፸፯) ፀፈረ=ታታ፣ጠለፈ (የባጥ)

፻፸፰) ፈኀረ=አጨ

፻፸፱) ፈርፈረ=ቆረሰ (የመቆራረስ)

፻፹) ፈከረ=ተረጎመ

፻፹፩) ፈጠረ=ፈጠረ

የግሥ ጥናት ክፍል ስድስት

ግእዝ=አማርኛ

፩) ኀልቀ=አለቀ

፪) ኈለቈ=ቆጠረ

፫) ሐመቀ=ብላሽ ሆነ
፬) ሐብቀቀ=አረከሰ፣አበላሸ

፭) ሐብቈቈ=ሣሣ

፮) ሐነቀ=አነቀ

፯) ሐንቀቀ=ተድላ ደስታ አደረገ

፰) ልህቀ=አደገ

፱) ሌቀ=አለቃ ሆነ

፲) ለጸቀ=አንድ ሆነ፣ ተጣበቀ

፲፩) ለፈቀ=አጥብቆ ያዘ

፲፪) መቀቀ=አንጣጣ

፲፫) መተቀ=ጣፈጠ፣ማር ማር አለ

፲፬) ሞቀ=ሞቀ

፲፭) መጠቀ=ረዘመ

፲፮) ሠሀቀ=ሳቀ

፲፯) ሰረቀ=ሰረቀ

፲፰) ሠቅሠቀ=ከፈለ፣ለየ

፲፱) ሰበቀ=ሰበቀ፣መታ (የማርስ)

፳) ሠነቀ=ስንቅ ያዘ

፳፩) ሶቀ=ደገፈ (የሚያዝ ነገር ሁሉ)

፳፪) ሰደቀ=ዘረጋ (የሰዴቃ)

፳፫) ሠጠቀ=ሰነጠቀ፣ፈለጠ፣ተረተረ

፳፬) ርሕቀ=ራቀ

፳፭) ረቀ=ረቀቀ

፳፮) ረቀቀ=ጻፈ

፳፯) ረፈቀ=ተቀመጠ
፳፰) በረቀ=ብልጭ አለ

፳፱) ቤደቀ=ሠራ (የቤት)

፴) ተላጸቀ=አንድ ሆነ

፴፩) ተስቈቈ=ሣሣ፣ነፈገ

፴፪) ተሣለቀ=ተዘባበተ፣ተሣለቀ

፴፫) ተዐረቀ=ተራረቀ፣ታረቀ

፴፬) ተዐርቀ=ተራቆተ

፴፭) ተዳደቀ=ተጣላ

፴፮) ተጠውቀ=ተከፋ፣አስከፋ

፴፯) ተጽዕቀ=ተጨነቀ

፴፰) ተጸደቀ=ተመጻደቀ

፴፱) ነሰቀ=ሰደረ፣ደረደረ (የደንጊያ)

፵) ነደቀ=ሠራ (የቤት)

፵፩) ነፈቀ=ከፈለ

፵፪) ናፈቀ=ተጠራጠረ

፵፫) አልጸቀ=ደረሰ

፵፬) ዐመቀ=ጥልቅ ሆነ፣ጎደጎደ

፵፭) ዐሰቀ=አሸበ ሠራ (በልብስ ላይ ወርቅ የማፍሰስ)

፵፮) ዐረቀ=አስታረቀ

፵፯) ዐርቀ=ተራቆተ

፵፰) አበቀ=ታመመ

፵፱) ዐነቀ=አሰረ (የአንገት)

፶) አንጸብረቀ=አንጸባረቀ፣አብረቀረቀ

፶፩) ዖቀ=አወቀ
፶፪) አድለቅለቀ=ተነዋወጠ፣ አነዋወጠ

፶፫) ዐጠቀ=ታጠቀ

፶፬) አጥመቀ=አጠመቀ

፶፭) አጥዐቀ=አጣበቀ

፶፮) ወሰቀ=ሳበ፣ገተረ (የቀስት)

፶፯) ወረቀ=ተፋ

፶፰) ወድቀ=ወደቀ

፶፱) ዘሐቀ=ገፈፈ (የቆዳ)

፷) ዘረቀ=አቧለተ (የዋዛ)

፷፩) ዜርዜቀ=ነፋ (የወንፊት)

፷፪) ደመቀ=ወጋ

፷፫) ደቀ=ልጅ ሆነ

፷፬) ደደቀ=ተጣላ

፷፭) ጕሕቈ=ጎበጠ፣አጎበጠ፣ አጎነበሰ

፷፮) ጠለቀ=አደፈ፣ረከሰ

፷፯) ጠበቀ=ያዘ

፷፰) ጠነቀቀ=ጻፈ

፷፱) ጠንቀቀ=ጠነቀቀ

፸) ጠየቀ=ተረዳ

፸፩) ጽሕቀ=ተጋ

፸፪) ጸረቀ=ጋገረ

፸፫) ጸንቀቀ=ነከረ፣ዘፈቀ፣ለወሰ

፸፬) ጸድቀ=እውነተኛ ሆነ

፸፭) ጸፈቀ=ጀጎለ (የአጥር)


፸፮) ፈሐቀ=ፋቀ

፸፯) ፈረቀ=ከፈለ

#የግሥ #ጥናት #ክፍል #ሰባት

ግእዝ=አማርኛ

፩) ሐለበ=አለበ

፪) ሐሰበ=አሰበ

፫) ሐበበ=ሀብ ሀብ አለ፣ ከዚያም ከዚያም ረገጠ፣ ወዳጅ ሆነ

፬) ሐብሐበ=ማለ

፭) ሐንበበ=አፈራ

፮) ሐንከበ=አሰፈረ

፯) ሐዘበ=ጠረጠረ

፰) ሔበ=ቀዳ፣ጠለቀ (የውሃ)

፱) ሐጠበ=ለቀመ (የእንጨት)

፲) ኀፀበ=አጠበ፣አጠራ፣አነጻ

፲፩) ልህበ=ወዛ፣ላበ፣ሞቀ፣ተኮሰ

፲፪) ለበበ=ሸበበ

፲፫) ለገበ=ሰፋ (የአቅማዳ)

፲፬) መረበ=ጣለ (የዓሣ)

፲፭) ማዕሰበ=ገለሞተ

፲፮) መገበ=ሾመ (የሹመት)

፲፯) ሰሐበ=ጎተተ፣ሳበ

፲፰) ሣህበበ=ሻገተ፣ተበላሸ

፲፱) ሰለበ=ሰለበ

፳) ሠረበ=ማገ፣መጠጠ፣ጠጣ
፳፩) ሰበ=ዞረ፣ከበበ፣ገጠመ (የሠራዊት)

፳፪) ሠብሠበ=ሕግ ሠራ

፳፫) ሠአበ=ተከተለ

፳፬) ሥእበ=ተዳደፈ፣ረከሰ

፳፭) ሰከበ=ተኛ

፳፮) ሤበ=ሸበተ (የሰው ብቻ)

፳፯) ርኅበ=ተራበ

፳፰) ረበ=ረበበ (የመልአክ የደመና ክንፍ ያለው ነገር ሁሉ)

፳፱) ረበበ=ዘረጋ

፴) ረከበ=አገኘ

፴፩) ረጥበ=ረጠበ

፴፪) ቀለበ=ዋጠ

፴፫) ቀረበ=ቆረበ

፴፬) ቄረበ=ቆረበ

፴፭) ቈረበ=ቆረበ

፴፮) ቀርበ=ቀረበ

፴፯) ቀቀበ=ሰፋ (የሰይፍ ማኅደር)

፴፰) ቀጸበ=ጠቀሰ (የጥቅሻ)

፴፱) ተሐዘበ=ታዘበ

፵) ተመንደበ=ተቸገረ፣ተጨነቀ፣ ተጠበበ

፵፩) ተማዕሰበ=ገለሞተ

፵፪) ተመገበ=በላ

፵፫) ተዐፅበ=ተጨነቀ፣ተደነቀ

፵፬) ተጥበበ=ብልሃተኛ ሆነ
፵፭) ነሀበ=ሠራ፣አነበ (የብረታ ብረት የንብ)

፵፮) ነቀበ=ለየ

፵፯) ነበበ=ተናገረ፣ነገረ

፵፰) ነጥበ=ነጠበ

፵፱) አመክዐበ=እጥፍ ድርብ አደረገ

፶) አማዕሰበ=ቤተ ፈት ሆነ (የሚስት)

፶፩) አማዕቀበ=አደራ አለ

፶፪) አማዕተበ=አመሳቀለ፣ አማተበ

፶፫) አስተርከበ=አስተዋለ

፶፬) አስተአዘበ=ሸና፣አፈሰሰ

፶፭) አስተዐፀበ=አደነቀ፣አስጨነቀ

፶፮) ዐሰበ=ሰጠ (የደመዎዝ)

፶፯) ዓሰበ=ፈታ፣ለቀቀ፣ተወ (የሚስት)

፶፰) ዐርበ=ገባ (የፀሐይ)

፶፱) ዐቀበ=ጠበቀ

፷) ዐተበ=ባረከ

፷፩) ዐንሰበ=አሟረተ

፷፪) አንበበ=አነበበ

፷፫) አንጠብጠበ=አንጠበጠበ፣ ተንጠበጠበ

፷፬) አውሰበ=አገባ

፷፭) አውገበ=አኮረፈ (የእንቅልፍ)

፷፮) አውጸበ=ሠራ (የቀለበት)

፷፯) ዐዘበ=ቆነነ፣ሠራ (የጭራ)

፷፰) አጠበ=ለቀመ (የእንጨት)


፷፱) ዐጸበ=አስጨነቀ

፸) አጽሐበ=ዘበዘበ፣ነዘነዘ፣ ጨቀጨቀ፣ ነገር አበዛ፣ አደከመ

፸፩) ከሰበ=ገረዘ፣ቆረጠ

፸፪) ከረበ=ለቀመ፣ሰበሰበ (የወይን)

፸፫) ኬረበ= አራት ዓይነት አድርጎ ጠረበ

፸፬) ኰረበ=ሰቀለ (የባጥ እንደ ዳስ ያለ ሁሉ)

፸፭) ከበበ=ከበበ (የማጀብ)

፸፮) ከብከበ=ሰርግ አደረገ

፸፯) ከተበ=ጻፈ

፸፰) ከዐበ=ሰደረ፣ካበ፣ደረደረ

፸፱) ወሀበ=ሰጠ

፹) ወከበ=ቸኰለ

፹፩) ወጸበ=ሠራ (የቀለበት)

፹፪) ዘረበ=መታ፣ቀጠቀጠ (የመዶሻ)

፹፫) ዘገበ=ሰበሰበ፣አከማቸ (የገንዘብ)

፹፬) የበበ=እልል እልል አለ፣ አመሰገነ፣ ዘመረ፣ ዘፈነ

፹፭) ደበበ=ዘረጋ (የጥላ የዝንቦ)

፹፮) ደብደበ=ነፋ (የሆድ)

፹፯) ደየበ=ወጣ፣አረገ

፹፰) ገለበ=ሸሸ፣ጋለበ፣ነዳ፣ አጠመደ

፹፱) ገልበበ=ሸፈነ፣ከደነ፣አለበሰ፣ አከናነበ

፺) ጠቀበ=ሰፋ፣ጠቀመ (የልብስ)

፺፩) ጠበ= ብልሃተኛ ሆነ

፺፪) ጠበጠበ=ጻፈ
፺፫) ጠብጠበ=ገረፈ

፺፬) ጤበ=ኮላ ኳለ፣ቀባ

፺፭) ጸለበ=ሰቀለ

፺፮) ጸረበ=ጠረበ

፺፯) ጸበ=ጠበበ

፺፰) ጾበ=ጨለጠ፣ጠጣ

፺፱) ጸግበ=ጠገበ

ለማስታዎስ ያህል

_ ስም____ትርጉም

1 ፊላታዎስ፦የአምላክ ወዳጅ

2 ሮብዓም፦ሕዝብ ይብዛ

3 ቴዎድሮስ፦የእግዚአብሔር ስጦታ

4 ሮቤል፦እነሆ ወንድ ልጅ

5 ማራናታ፦ጌታ ሆይ ና

6 ቤቴል፦የእግዚአብሔር ቤት

7 ቄርሎስ፦የተመረጠ ምርጥ

8 እስጢፋኖስ፦አክሊል

9 ሳውል/ሳኦል፦ከእግዚአብሔር የተለመነ

10 ሴዴቅያስ፦የእግዚአብሔር ጽድቅ

11 ፊቅጦር፦ኀዘኔን አራቀልኝ

12 ንፍታሌም፦ታጋይ የሚታገል

13 ዮርዳኖስ፦ወራጅ

14 ዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል

15 ገነት፦የአትክልት ስፍራ
16 ፊልድልፍያ፦የወንድማማች ፍቅር

17 ዲና፦ፈረደ

18 ማኑሄ፦እረፍት

19 መልሕቅ፦ከብረት የተሠራ የመርከብ ማቆሚያ

20 ራማ፦ከፍታ

21 ኤርምያስ፦እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል

22 ሐና፦ ስጦታ

23 ሕርያቆስ፦ኅሩይ

24 ፊልጶስ፦ወንድም ወዳጅ

25 ቶማስ፦ፀሐይ

26 ጎርጎርዮስ:-ንቁሕ የተጠበቀ

27 ማትያስ፦ፀሐይ

28 ቀሌምንጦስ፦ግንብ

29 አቤል፦በግ ወይም ደመና

30 ኖኅ፦ደስታ

31 ሴም፦ተሾመ

32 ይሥሐቅ፦ደስታ አንድም

33 ሙሴ፦የውሃ ልጅ

34 አሮን፦የእግዚአብሔር ተራራ

35 ጌዴዎን፦እግዚአብሔር ኃያል ነው

36 እሴይ፦ዋጋየ

37 አሚናዳብ፦መንፈስቅዱስ

38 ዳዊት፦የተወደደ ልበ አምላክ

39 ዕንባቆም፦ጠቢብ አዋቂ አስተዋይ


40 ሄኤሜን፦ምኞቴን አገኘሁ

41 አሞጽ፦እግዚአብሔር ጽኑ ነው

42 ዮናስ፦ርግብ

43 ሐጌ፦የእግዚአብሔር መልእክተኛ

44 ራኄል፦በግዕት

45 ዕዝራ፦ረዳቴ

46 ሔርሜላ፦ከክብር ዘመድ የተገኘች

47 መርቆሬዎስ፦የአባት ወዳጅ

48 ኤጲፋንዮስ፦ምስጢር ገላጭ

49 ሜሮን፦የተባረከ ሽቱ

50 ሱላማጢስ፦ሰላማዊት

51 ሶምሶን፦ፀሐይ

52 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ

53 ማርታ፦እመቤት

54 ሊዲያ፦ፈራሂተ እግዚአብሔር

55 ኤፍሬም፦ፍሬያማ ፍሬው

56 ኤፍራታ፦ክብርት የተከበረች

57 ታዴዎስ፦ተወዳጅ

58 ኢየሩሳሌም፦የሰላም ሀገር

59 ሄኖስ፦ሰው

60 ሰሎሜ፦ሰላም

61 ሩሐማ፦ምሕረት

62 ዮዳሔ፦እግዚአብሔር ያውቃል

63 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ
64 ኑኃሚን፦ደስታየ

65 ናትናኤል፦የእግዚአብሔር ስጦታ

66 አዛሄል፦እግዚአብሔር ያያል

67 ኢዮስያስ፦እግዚአብሔር ይደግፋል

68 ኢዩኤል፦እግዚአብሔር አምላክ ነው

69 በርናባስ፦የመጽናናት ልጅ

70 ሶፎንያስ፦እግዚአብሔር ሰውሯል/ጠብቋል

71 ሕዝቅኤል፦እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል

72 ኬልቅያስ፦እድል ፈንታየ እግዚአብሔር

73 ሳሙኤል፦እግዚአብሔር ሰማኝ

74 ሚኪያስ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!

75 ሆሴዕ፦እግዚአብሔር ያድናል

76 ሔዋን፦የሕያዋን ሁሉ እናት

77 ሕዝቅያስ፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው

78 መልከጼዴቅ፦የሰላም ንጉሥ

79 ሚልኪያስ፦መልእክተኛየ

80 ሣራ፦ልዕልት

81 ስምዖን፦ሰማ

82 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ

83 ናሆም፦መጽናናት ማለት ነው።

84 ናታን፦ እግዚአብሔር ሰጥቷል

85 አልዓዛር፦ትርጉሙ እግዚአብሔር ረድቷል

86 አስቴር፦ኮከብ

87 አቤሜሌክ፦የንጉሥ አገልጋይ
88 አቤሴሎም፦አባቴ ሰላም ነው

89 አብድዩ፦የእግዚአብሔር አገልጋይ

90 አብራም፦ታላቅ አባት

91 አብርሃም፦የብዙዎች አባት

92 አኪያ፦እግዚአብሔር ወንድሜ ነው

93 አክዐብ፦የአባት ወንድም

94 ባሮክ፦ቡሩክ

95 አዳም፦መልካሙ

96 ኢሳይያስ፦ እግዚአብሔር ደኅንነት ነው

97 ባርቅ፦መብረቅ

98 ኢያሱ፦እግዚአብሔር አዳኝ ነው

99 ኢዮሳፍጥ፦እግዚአብሔር ፈርዷል

100 ኢዮራም፦እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ

101 ኢዮርብዓም፦ሕዝቡ እየበዛ ይሄዳል

102 ቤተልሔም፦የእንጀራ ቤት

103 ኢዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል

104 ኢዮአቄም፦እግዚአብሔር አቆመ

105 ኢዮአብ፦እግዚአብሔር አባት ነው

106 ኢዮአታም፦እግዚአብሔር ፍጹም ነው

107 ኢዮአካዝ፦እግዚአብሔር ይዟል

108 ኤልሳዕ፦እግዚአብሔር ደኅንነት ነው

109 ኤልያስ፦እግዚአብሔር አምላክ ነው

110 ኤልያቄም፦እግዚአብሔር ያስነሳል

111 ኤዶም፦ቀይ/የገነት ሌላ ስም ነው
112 እስራኤል፦ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፍማል

113 ኤልሳቤጥ፦እግዚአብሔር መሐላየ ነው

114 ኤልሻዳይ፦ሁሉን ቻይ አምላክ

115 ሀሌሉያ፦እግዚአብሔርን አመስግኑ

116 ሰሎሞን፦ሰላማዊ

117 ኬብሮን፦ኅብረት

118 አዛርያስ፦እግዚአብሔር ረድቷል

119 ኤደን፦ደስታ

120 ዖዝያን፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው

121 ዘካርያስ፦እግዚአብሔር ያስታውሳል

122 ይሳኮር፦ ዋጋዬ

123 ይዲድያ፦በእግዚአብሔር የተወደደ

124 ዮሐናን፦እግዚአብሔር ጸጋ ሰጪ ነው

125 ዮሐንስ፦እግዚአብሔር ጸጋ ነው

126 ዮሴፍ፦ይጨምር

127 ዮናስ፦ርግብ

128 ዮናታን፦እግዚአብሔር ሰጥቷል

129 ዮአኪን፦እግዚአብሔር ያቆማል

130 ዮካብድ፦እግዚአብሔር ክብር ነው

131 ምናሴ፦ማስረሻ

132 ዮፍታሔ፦እግዚአብሔር ይከፍታል

133 ዲቦራ፦ንብ

134 ዳንኤል፦እግዚአብሔር ፈራጅ ነው

135 ጎዶልያስ፦እግዚአብሔር ታላቅ ነው


136 ጽዮን፦አምባ

137 ጳውሎስ፦ብርሃን ማለት ነው።

138 ሴት፦ምትክ ማለት ነው።

139 ጴጥሮስ፦አለት ማለት ነው።

140 ሄኖክ፦ታደሰ ማለት ነው።

_ #የግእዝ #ጥያቄዎች_

ምርጫ

፩) ስለ ግእዝ ቋንቋ ትክክል የሆነው የቱ ነው?

ሀ) የራሱ የሆነ ቁጥር አለው

ለ) የራሱ የሆነ ሥርዓተ ንባብ አለው

ሐ) የራሱ የሆነ ፊደል አለው

መ) ሁሉም

፪) 7777 በግእዝ ቁጥር ሲጻፍ___ይሆናል?

ሀ) ፸፻፯፻፸፯

ለ) ፯፯፯፯

ሐ) ፸፯፸፯

መ) ፸፼፯፻፸

፫) "ውእቱኬ፣ ውእቱ፣ ዕንባቆም፣ ሕይወት" የሚሉት ቃላት ሥርዓተ ንባባቸው በቅደም ተከተል ምንድን ነው?

ሀ) ተነሽ፣ ወዳቂ፣ ሰያፍ፣ ተጣይ

ለ) ተነሽ፣ ወዳቂ፣ ተጣይ፣ ሰያፍ

ሐ) ወዳቂ፣ ተነሽ፣ ሰያፍ፣ ተጣይ

መ) ወዳቂ፣ ተነሽ፣ ተጣይ፣ ሰያፍ

፬) መካከለኛ ፊደሉ ጠብቆ የሚነበበው ቃል የቱ ነው?

ሀ) ሰብሐ-ሰባ
ለ) ፈጸመ-ጨረሰ

ሐ) ጸብሐ-ነጋ

መ) መሐረ-ይቅር አለ

፭) ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ) ሠረቀ-ወጣ

ለ) ሠዐለ-ለመነ

ሐ) መሀረ-አስተማረ

መ) ጸለየ-ለመነ

#እውነቱን "ጽድቅ" ውሸቱን "ሐሰት" በማለት መልሱ

፮) "መ" በወዳቂ ቃል ላይ ሲወድቅ ተነስቶ እንዲነበብ ያደርገዋል።

፯) "ዝ" የሚለው ቃል ሥርዓተ ንባቡ ወዳቂ ነው።

፰) አንድ ሺ ቁጥር በግእዝ ቋንቋ እልፍ ነው

፱) ስምንት ቁጥር በግእዝ ስምንቱ ይባላል።

፲) "ሂ፣ ኒ፣ ሰ" በተጣይ፣ በሰያፍና በተነሽ ቃል ላይ ሲወድቁ ብዙ ጊዜ በወዳቂ ንባብ እንዲነበቡ ያደርጋቸዋል።

#አዛምድ

ሀ. ለ.

፲፩) ሠምረ ሀ) ፈለገ

፲፪) ኀሠሠ ለ) ተናገረ

፲፫) ኖመ ሐ) ተኛ

፲፬) አጽደልደለ መ) ወደደ

፲፭) ነበበ ሠ) አበራ

#የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ


፲፮) የ"ወ"ን ካእብ፣ የ"የ"ን ሣልስ እንዲሁም የ "ሐ" እና የ "አ" ን ራብዕ ጻፍ።

፲፯) በአማርኛ የምንጠቀምባቸው በግእዝ ቋንቋ የሌሉ ስምንት ፊደላትን ጥቀስ።

፲፰) 379124 በግእዝ ሲጻፍ እንዴት ይሆናል?

፲፱) ተነሽ ንባብ የማይጨርስባቸው ሆሄያት ማን እና ማን ናቸው?

፳) የስቅለት ቀን ግፍዖሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍዑኒ የሚለው የመዝሙረ ዳዊት ክፍል የሚነበበው በምን የንባብ ዓይነት ነው

ሠናይ መክፈልት

(መልካም እድል)

አዘጋጅ:-መ/ር በትረማርያም

የጥያቄዎች መልስ

የጥያቄዎች መልስ

፩) መ

፪) ሀ

፫) ሐ

፬) ለ

፭) ለ

፮) ጽድቅ

፯) ጽድቅ

፰) ሐሰት

፱) ሐሰት

፲) ጽድቅ

፲፩) መ

፲፪) ሀ

፲፫) ሐ

፲፬) ሠ
፲፭) ለ

፲፮) ዉ፣ ዪ፣ ሓ፣ ኣ

፲፯) ዠ፣ ቸ፣ ሸ፣ ቨ፣ ጨ፣ ኘ፣ ኽ፣ ጀ

፲፰) ፴፼፯፼፺፻፩፻፳፬ ወይም ፴፯፼፺፩፻፳፬ ይላል።

፲፱) ሳድስና ኃምስ

፳) ውርድ ንባብ

#ግእዝ #ክፍል ፳፩

መራሕያን

መራሕያን ማለት መሪዎች ማለት ነው። አንድና ብዙን፣ ሴትና ወንድም ሩቅና ቅርብን የሚያሳውቁን ናቸው። መራሕያን
10 ናቸው። እነዚህም:-

ግእዝ_አማርኛ English

፩) ውእቱ_እርሱ___He

፪) ውእቶሙ_እነርሱ They

፫) ይእቲእርሷ__She

፬) ውእቶን__እነርሱ_They

፭) አንተ__አንተ_you

፮) አንትሙ__እናንተ_you

፯) አንትን_እናንተ___you

፰) አንቲአንቺ__you

፱) አነእኔ__I

፲) ንሕነ_እኛ___We

ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ "ውእቶን" እና "አንትን" ሥርዓተ ንባባቸው ተጣይ ነው። ሌሎቹ ሁሉም ተነስተው ይነበባሉ።
ውእቶሙ በሌላ አገላለጽ እሙንቱ ይባላል። ውእቶን ደግሞ እማንቱ ይባላል። ትርጉማቸው ተመሳሳይ ነው። ሁሉም
እነርሱ ማለት ነው። እሙንቱ እና እማንቱ ሥርዓተ ንባባቸው ወዳቂ ነው። እንግዲህ እነዚህ አስሩ መራሕያን በጾታ ሴትና
ወንድ ተብለው ይከፈላሉ። የሴት የሚባሉት:-
አንቲ

ይእቲ

ውእቶን/እማንቱ

አንትን

ናቸው። የወንድ የሚባሉት ደግሞ:-

አንተ

ውእቱ

አንትሙ

ውእቶሙ/እሙንቱ

ናቸው። አነ እና ንሕነ ግን ጾታ አይለዩም ለሴትም ለወንድም ይሆናል። ሴቷም እኔ ለማለት "አነ" ትላለች። ወንዱም እኔ
ለማለት "አነ" ይላል ልዩነት የለውም።

በሌላ አከፋፈል ደግሞ መራሕያን አንደኛ መደብ፣ ሁለተኛ መደብ እና ሦስተኛ መደብ ተብለው ይከፋላሉ። አንደኛ
መደብ የሚባሉትን አነ እና ንሕነ ናቸው። ሁለተኛ መደብ የሚባሉት አንተ፣ አንቲ፣ አንትሙ፣ አንትን ናቸው። ሦስተኛ
መደብ የሚባሉት ውእቱ፣ ውእቶሙ/እሙንቱ፣ ይእቲ፣ ውእቶን/እማንቱ ናቸው። በቅኔ ቤት አገላለጽ ደግሞ ቅርብ እና
ሩቅ ተብለው ይከፈላሉ። ቅርብ የሚባሉት አነ፣ ንሕነ፣ አንተ፣ አንትሙ፣ አንቲ እና አንትን ናቸው። ሩቅ የሚባሉት
ከተናጋሪው የራቁት ውእቱ፣ ውእቶሙ/እሙንቱ፣ ይእቲ፣ ውእቶን/እማንቱ ናቸው።

በሌላ አከፋፈል መራሕያን አንድና ብዙ ተብለው ይከፈላሉ። አንድ/ነጠላ የሚባሉት ውእቱ፣ አነ፣ ይእቲ፣ አንተ እና አንቲ
ናቸው። ብዙ የሚባሉት ደግሞ ውእቶሙ/እሙንቱ፣ ውእቶን/እማንቱ፣ አንትሙ፣ አንትን እና ንሕነ ናቸው።

የዕለቱ ጥያቄዎች

፩) አንደኛ መደብ ብዙ መራሒ ማን ነው?

፪) ሦስተኛ መደብ ብዙ፣ ሴት የሆነች መራሒ ማን ናት?

፫) ሁለተኛ መደብ ወንድ፣ ብዙ የሆነ መራሒ ማን ነው?

♥️ግእዝ ቋንቋ ክፍል ፳፪♥️

#የመራሕያን #አገልግሎት

መራሕያን በዓረፍተ ነገር ውስጥ ሲገኙ ሦስት ዓይነት አገልግሎት አላቸው። እነዚህም:-

፩) የስም ምትክ
፪) አመልካች ቅጽል

፫) ነባር አንቀፅ

ናቸው። ትርጉማቸውም እንደየአገልግሎታቸው ሊለያይ ይችላል። በክፍል ፳፩ ባየነው የሚተረጎሙት የስም ምትክ
ሆነው ሲያገለግሉ ነው። መራሕያን የስም ምትክ ሆነው ሲያገለግሉ ደግሞ ብዙ ጊዜ ግሥ በፊት ይመጣሉ። ለምሳሌ
ድንግል ማርያምን "ይእቲ ተዐቢ እምኪሩቤል" ይላታል። ይእቲ የሚለው መራሒ እርሷ ተብሎ ይተረጎማል። ስለዚህ
እርሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች ተብሎ ይተረጎማል። ይእቲ "ተዐቢ" ከሚለው ግሥ (verb) ፊት እንደመጣ አስተውል።
መራሕያን የስም ምትክ ሆነው ሲያገለግሉ የሚኖራቸውን ትርጉም ክፍል ፳፩ ላይ ስለጻፍኩ ከዚያ ይመልከቱ።

#አመልካች #ቅጽል

መራሕያን አመልካች ቅጽል ሆነው ሲያገለግሉ የሚኖራቸው ትርጉም የሚከተለው ነው።

፩) ውእቱ__ያ

፪) ውእቶሙ___እነዚያ

፫) ይእቲ__እርሷ

፬) ውእቶን_እነዚያ (ሴ)

፭) አንተ_አንተ

፮) አንትሙ___እናንተ

፯) አንቲ_አንቺ

፰) አንትን____እናንተ (ሴ)

፱) አነ__እኔ

፲) ንሕነ_እኛ

ይላል። መራሕያን በአመልካች ቅጽል አተረጓጎም የማተረጎሙት ከስም (noun) በፊት ከመጡ ነው። ለምሳሌ "ውእቱ
ቃል ሥጋ ኮነ" የሚለውን ብንመለከት ውእቱ የሚለው መራሒ "ቃል" ከሚለው ስም(noun) በፊት ስለመጣ የሚኖረው
ትርጉም "ያ" የሚል ይሆናል ማለት ነው። ሙሉው "ያ ቃል ሥጋ ሆነ" ይላል። ይእቲ ማርያም እምነ ቢል። ይእቲ
የምትለው መራሒ ማርያም ከሚለው ስም በፊት ስለሆነች ይህቺ ማርያም እናታችን ናት ተብሎ ይተረጎማል።

#ነባር #አንቀጽ

መራሕያን እንደ ነባር አንቀጽ (as auxiliary verb) ሆነው ሲያገለግሉ የሚኖራቸው ትርጉም ነን፣ነበርን፣አለን

፩) ውእቱ__ነው፣ነበረ፣አለ
፪) ውእቶሙ__ናቸው፣ነበሩ፣አሉ

፫) ይእቲ_ናት፣ነበረች፣አለች

፬) ውእቶን___ናቸው፣ነበሩ፣አሉ

፭) አንተ___ነህ፣ነበርክ፣አለህ

፮) አንትሙ__ናችሁ፣ነበራችሁ፣ አላችሁ

፯) አንቲ____ነሽ፣ነበርሽ፣አለሽ

፰) አንትን__ናችሁ፣ነበራችሁ፣ አላችሁ

፱) አነ____ነኝ፣ነበርኩ፣አለሁ

፲) ንሕነ___ነን፣ነበርን፣አለን

ተብለው ይተረጎማሉ። መራሕያን እንደነባር አንቀጽ የሚያገለግሉት ከስም (noun) በኋላ ሲመጡ ነው። ለምሳሌ
ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ሲል ብናገኘው "ውእቱ" የሚለው መራሒ "ቃል" ከሚለው ስም በኋላ ስለመጣ የሚተረጎመው
ነበር ተብሎ ነው። ስለዚህ "በመጀመሪያ ቃል ነበር" ተብሎ ይተረጎማል።ስለዚህ መራሕያንን በዓረፍተ ነገር ውስጥ
ስናገኛቸው በየትኛው እንደሚተረጎሙ መገንዘብ ያስፈልጋል። "ውእቱ" በነባር አንቀፅነቱ ከዘጠኙም መራሕያን በኋላ
እየመጣ በዘጠኙም አፈታት ያስተረጉማል። ለምሳሌ አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም ሲል ብናገኘው "ውእቱ" አንቲ
ከሚለው መራሒ በኋላ መጥቷል። ሲተረጎም የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ ይላል። ውእቱ ነሽ ተብሎ እንደተተረጎመ
አስተውል። በእንደዚህ ዓይነት ጊዜ መጀመሪያ ያለው መራሒ በስም ምትክ ይተረጎማል። ቀጥሎ ያለው በነባር አንቀፅ
ይተረጎማል።

የዕለቱ ጥያቄዎች

ከሚከተሉት ዓረፍተ ነገሮች የመራሕያኑን አገልግሎት ለይ

፩) አነ ውእቱ ብርሃኑ ለዓለም

፪) ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም

፫) አንትሙ ሐዋርያት ትትፈቀሩ በኀበ ኩሉ

♥️ግእዝ ክፍል ፳፫♥️

#ድርብ #መራሕያንና #ተሳቢ #መራሕያን

ድርብ መራሕያን (Reflexive Pronouns) የሚባሉት በመራሕያን ላይ እየተደረቡ የሚመጡ አጽንዖት መስጫ ቃላት
ናቸው።እነዚህም ፲ ናቸው።

፩) ለሊሁ____ እርሱ ራሱ
፪) ለሊሆሙ_እነርሱ ራሳቸው

፫) ለሊሃ_እርሷ ራሷ

፬) ለሊሆን__እነርሱ ራሳቸው

፭) ለሊከ____አንተ ራስህ

፮) ለሊክሙ__እናንተ ራሳችሁ

፯) ለሊኪ____አንቺ ራስሽ

፰) ለሊክን___እናንተ ራሳችሁ

፱) ለልየ_እኔ ራሴ

፲) ለሊነ_እኛ ራሳችን

የሚሉት ናቸው። ለምሳሌ አነ ለልየ ሰማዕቱ ለዝንቱ ቢል። እኔ ራሴ ለዚህ ምስክር ነኝ ተብሎ ይተረጎማል። ለሊነ ነአምር
ኵሎ ዘኮነ ቢል የሆነውን ሁሉ እኛ ራሳችን እናውቃለን ተብሎ ይተረጎማል።

#ተሳቢ #መራሕያን

ተሳቢ መራሕያን የሚባሉት ደግሞ በተሳቢነት የሚያገለግሉ ናቸው። እነዚህም ቁጥራቸው ፲ ናቸው።

፩) ኪያሁ___እርሱን

፪) ኪያሆሙ__እነርሱን

፫) ኪያሃ____እርሷን

፬) ኪያሆን___እነርሱን

፭) ኪያከ____አንተን

፮) ኪያክሙ___እናንተን

፯) ኪያኪ____አንችን

፰) ኪያክን____እናንተን

፱) ኪያየ____እኔን

፲) ኪያነ_እኛን

የሚል ትርጉም ይኖራቸዋል። ለምሳሌ በቅዳሴ ጊዜ ኪያከ እግዚኦ ንሴብሐከ እንላለን።ትርጉሙ አቤቱ አንተን
እናመሰግንሃለን ማለት ነው።
የዕለቱ ጥያቄዎች

የሚከተሉትን ዓረፍተ ነገሮች ተርጉሙ።

፩) ኪያሃ አፍቀረ

፪) ኪያክሙ ሠምረ

፫) ኪያየ ወደሰ

♥️ግእዝ ቋንቋ ክፍል ፳፬♥️

አመላካቾች

፩) ዝንቱ፣ዝ___ይህ

፪) ዛቲ፣ዛ_ይህች

፫) ዝኵ፣ዝስኵ፣ዝክቱ____ያ

፬) እንታክቲ፣ እንትኵ____ያች

፭) እሉ፣ እሎንቱ___እነዚህ

፮) እላ፣እሎን፣ እላንቱ፣__እነዚህ (ሴ)

፯) እልኰን፣ እልክቶን___እነዚያ(ሴ)

፰) እልኵ፣ እልክቱ____እነዚያ

በዓረፍተ ነገር ባለቤት ሆነው ሲያገለግሉ ለምሳሌ ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም።ትርጉሙ ለዘለዓለም ማረፊያየ ይች ናት
ማለት ነው። ቅጽል ሆነው ሲያገለግሉ ዳህንኑ ዝስኵ አቡክሙ ይላል። ትርጉሙ ያ አባታችሁ ደህና ነውን ማለት ነው።
ተሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ። አፍቅር ዛተ ቢል ያችን ውደዳት ማለት ነው።

የ"ዘ፣እለ፣እንተ" አስሩ ዝርዝርም ተናበው አመላካች የሚሆኑበት ጊዜ አለ። ትርጉማቸውም እንደሚከተለው ነው።

፩) ዚኣሁ/እንቲኣሁ___የእርሱ

፪) ዚኣሆሙ/እንቲኣሆሙ__የእነርሱ

፫) ዚኣሃ/እንቲኣሃ___የእርሷ

፬) ዚኣሆን/እንቲኣሆን__የእነርሱ

፭) ዚኣከ/እንቲኣከ___የአንተ
፮) ዚኣክሙ/እንቲኣክሙ__የእናንተ

፯) ዚኣኪ/እንቲኣኪ___የአንቺ

፰) ዚኣክን/እንቲኣክን___የእናንተ

፱) ዚኣየ/እንቲኣየ____የእኔ

፲) ዚኣነ/እንቲኣነ_የእኛ

ሲናበቡ አመልካች ቅጽል ይሆናሉ። ለምሳሌ ሀገረ ዚኣነ ቢል ትርጉሙ የእኛ ሀገር ማለት ነው። ሕይወተ ዚአኪ ሲል
የአንቺ ሕይወት ተብሎ ይተረጎማል። የእኔ ሀገር ለማለት ዚኣየ ሀገር አይባልም። ከዚያ ይልቅ ሀገረ ዚኣየ ይላል እንጂ።
እንተ ለሴት ሲሆን፣ ዘ ደግሞ ለሴት ለወንድ ለአንድ ለብዙ ይሆናል። እለ ለብዙ ይሆናል።ሲዘረዘርም እንደሚከተለው
ነው።

፩) እሊኣሁ___የእርሱ

፪) እሊኣሆሙ__የእነርሱ

፫) እሊኣሃ____የእርሷ

፬) እሊኣሆን___የእነርሱ

፭) እሊኣከ____የአንተ

፮) እሊኣክሙ___የእናንተ

፯) እሊኣኪ____የአንቺ

፰) እሊኣክን___የእናንተ

፱) እሊኣየ____የእኔ

፲) እሊኣነ____የእኛ

ይላል። ለምሳሌ እልመክኑን ወረደ ውስተ ዓለም ወእሊኣሁ ሰቀልዎ ሲል ትርጉሙ ጌታ ወደ ዓለም ወረደ የእርሱ
ወገኖችም ሰቀሉት ተብሎ ይተረጎማል።

የዕለቱ ጥያቄዎች

የሚከተሉትን የአማርኛ ሐርጎች ወደ ግእዝ ተርጉም።

፩) የአንቺ ሰላም

፪) የእኔ ትምህርት
፫) እነዚያ ሰማዮች

♥️ግእዝ ቋንቋ ክፍል ፳፭♥️

የስም ዝርዝር በመራሕያን

አንድ ስም በአስሩ መራሕያን በተለያየ መልኩ ይነገራል። ይህም የራሱ የሆነ ሕግ አለው። ሕጎችን ቀጥለን
እንመለከታለን:-

#በሳድስ #የሚጨርሱ #ስሞች

፩) በውእቱ ጊዜ መድረሻ ፊደሉን ወደ ካእብ መቀየር ነው።

፪) በውእቶሙ ጊዜ መድረሻ ፊደሉን ወደ ሳብዕ ቀይሮ "ሙ" ፊደልን መጨመር ነው።

፫) በይእቲ ጊዜ መድረሻ ፊደሉን ወደ ራብዕ መቀየር ነው።

፬) በውእቶን ጊዜ መድረሻ ፊደሉን ወደ ሳብዕ ቀይሮ "ን" ፊደልን መጨመር ነው።

፭) በአንተ ጊዜ "ከ"ን መጨመር ነው።

፮) በአንትሙ ጊዜ "ክሙ"ን መጨመር ነው።

፯) በአንቲ ጊዜ "ኪ"ን መጨመር ነው።

፰) በአንትን ጊዜ "ክን"ን መጨመር ነው።

፱) በአነ ጊዜ "የ"ን መጨመር ነው።

፲) በንሕነ ጊዜ "ነ"ን መጨመር ነው። ለምሳሌ "ፍቅር" የሚለውን ቀጥለን እንመልከት።

መራሒ__ግእዝ_አማርኛ

፩) ውእቱ_ፍቅሩ___ፍቅሩ

፪) ውእቶሙፍቅሮሙፍቅራቸው

፫) ይእቲ_ፍቅራ___ፍቅሯ

፬) ውእቶን_ፍቅሮን_ፍቅራቸው

፭) አንተ_ፍቅርከ___ፍቅርህ

፮) አንትሙፍቅርክሙፍቅራችሁ

፯) አንቲ_ፍቅርኪ_ፍቅርሽ
፰) አንትን_ፍቅርክን_ፍቅራችሁ

፱) አነ_ፍቅርየ__ፍቅሬ

፲) ንሕነ__ፍቅርነ___ፍቅራችን

የውእቱ ዝርዝር እና የይእቲ ዝርዝር ሥርዓተ ንባባቸው ወዳቂ ነው። ፍቅሩ፣ ፍቅራ ወዳቂ ናቸው ማለት ነው። የአንትን
ዝርዝርና የወእቶን ዝርዝር ደግሞ ሥርዓተ ንባባቸው ተጣይ ነው። እኒህም ፍቅሮን፣ ፍቅርክን ናቸው። ሌሎቹ ግን
ሁሉም ተነሽ ናቸው።

የዕለቱ ጥያቄዎች

የሚከተሉትን ስሞች በአስሩ መራሕያን አርባ

፩) ሀገር

፪) ቤት

፫) እም (ትርጉሙ እናት ማለት ነው)

♥️ግእዝ ቋንቋ ክፍል ፳፮♥️


____ከባለፈው የቀጠለ

ከሳድስ ውጭ የሚጨርሱ ስሞች በአስሩ መራሕያን ሲዘረዘሩ በሦስተኛ መደቦች ከባለፈው ይለያሉ። በሁለተኛና
በአንደኛ መደቦች ግን ክፍል ፳፭ ላይ እንዳየነው ነው አይለወጡም። በሦስተኛ መደቦች ግን ከባለፈው ስለሚለዩ ቀጥለን
እሱን እንይ:-

፩) በውእቱ ጊዜ "ሁ" ፊደልን መጨመር ነው።

፪) በውእቶሙ ጊዜ "ሆሙ" የሚለውን መጨመር ነው።

፫) በይእቲ ጊዜ "ሃ" ፊደልን መጨመር ነው።

፬) በውእቶን ጊዜ "ሆን" የሚለውን መጨመር ነው።

በአንተ "ከ"ን፣ በአንትሙ "ክሙ"ን፣ በአንቲ "ኪ"ን፣ በአንትን "ክን"ን፣ በአነ "የ"ን፣ በንሕነ "ነ"ን መጨመር ነው። "ሥጋ"
በሚለው ቃል አስሩንም ቀጥለን እንመልከት።

መራሒ_ግእዝ_አማርኛ

፩) ውእቱሥጋሁሥጋው
፪) ውእቶሙ__ሥጋሆሙ_ሥጋቸው

፫) ይእቲ_ሥጋሃ_ሥጋዋ

፬) ውእቶንሥጋሆንሥጋቸው

፭) አንተ_ሥጋከ_ሥጋህ

፮) አንትሙሥጋክሙሥጋችሁ

፯) አንቲ_ሥጋኪ_ሥጋሽ

፰) አንትን__ሥጋክንሥጋችሁ

፱) አነ__ሥጋየ__ሥጋየ

፲) ንሕነ_ሥጋነ_ሥጋችን

ይላል። በሳድስ ከሚጨርሱ ስሞችም በአፈንጋጭነት በተለየ "አብ_አባት" የሚለውን የመሰሉት ይህንን መስለው
ይረባሉ።አብ መድረሻውን ካእብ አድርጎ ተዘርዝሯል። አቡሁ፣ አቡሆሙ፣ አቡሃ፣ አቡሆን፣ አቡከ፣ አቡክሙ፣ አቡኪ፣
አቡነ፣ አቡየ፣ አቡክን ይላል።

ብዛትነት ያላቸው ስሞችም ምንም እንኳ በሳድስ ቢጨርሱ የሚረቡት ግን ከላይ ባለው መልኩ ነው። በተጨማሪ ግን
ቅድመ መድረሻቸውን ወደ ሣልስ ቀይረው ይዘረዘራሉ። ለምሳሌ ሊቃውንት የሚለውን ብንመለከት እንደሚከተለው
ነው።

መራሒ_ግእዝ_አማርኛ

፩) ውእቱ_ሊቃውንቲሁ_ሊቃውንቶቹ

፪) ውእቶሙ_ሊቃውንቲሆሙ_ሊቃውንቶቻቸው

፫) ይእቲ_ሊቃውንቲሃ_ሊቃውንቶቿ

፬) ውእቶን_ሊቃውንቲሆን_ሊቃውንቶቻቸው

፭) አንተ_ሊቃውንቲከ_ሊቃውንቶችህ

፮) አንትሙ_ሊቃውንቲክሙ_ሊቃውንቶቻችሁ

፯) አንቲ_ሊቃውንቲኪ_ሊቃውንቶችሽ
፰) አንትን_ሊቃውንቲክን_ሊቃውንቶቻችሁ

፱) አነ_ሊቃንውቲየ__ሊቃውንቶቼ

፲) ንሕነ_ሊቃውንቲነ_ሊቃውንቶቻችን

ይላል። እነዚህ ተሳቢያቸውም ተመሳሳይ ነው። ይህን የመሰሉ ቃላት በሳድሱ መንገድም ይሄዳሉ። ይሄም ሊቃውንቱ፣
ሊቃውንቶሙ፣ ሊቃውንታ፣ ሊቃውንቶን፣ ሊቃውንትከ፣ ሊቃውንትክሙ፣ ሊቃውንትኪ፣ ሊቃውንትክን፣ ሊቃውንትየ፣
ሊቃውንትነ ይላል። በዚህ ጊዜ ተሳቢያቸው ሊቃውንተከ፣ ሊቃውንተክሙ፣ ሊቃውንተኪ፣ ሊቃውንተኪ፣ ሊቃውንተነ
ይላል። ሦስተኛ መደቦችና ከአንደኛ መደብ አነ ግን አይለውጡም። ከሦስተኛ መደቦች ውእቱ ሊቃውንቶ ይላል።

የዕለቱ ጥያቄዎች

የሚከተሉትን ቃላት በአስሩ መራሕያን ዘርዝር

፩) አዝማድ

፪) አዕይንት

፫) መሰንቆ

♥️ግእዝ ቋንቋ ክፍል ፳፯♥️

ተናባቢ ቃላት

ሁለት የተለያዩ ቃላት በአንድ ድምፅ ሲነበቡ ተናባቢ ቃላት ይባላሉ። ቃላት ሲናበቡ የራሳቸው የሆነ ሕግ አላቸው።
እርሱን ቀጥለን እንመልከት:-

በሳድስ የሚጨርሱ ቃላት ከሌሎች ጋር ሲናበቡ መድረሻቸው ፊደላቸውን ወደ ግእዝ ይለውጣሉ። በሣልስ የሚጨርሱ
ቃላት ከሌሎች ጋር ሲናበቡ መድረሻ ፊደላቸውን ወደ ኃምስ ይቀይራሉ። ቀጥለን በምሳሌ እንመልከት:-

ቃል፩ቃል፪_ሲናበቡ

፩) ቃል_ሕይወት_ቃለ ሕይወት

፪) መጋቢሐዲስመጋቤ ሐዲስ

፫) ሊቅ__ሊቃውንት_ሊቀ ሊቃውንት

፬) በላኢመጻሕፍትበላኤ መጻሕፍት

ይላል።በራብዕ፣ በኃምስ እና በሳብዕ የሚጨርሱ ቃላት ግን ከሌሎች ጋር ሲናበቡ የሚያመጡት ለውጥ የለም። በምሳሌ
እንመልከት:-

ቃል፩_ቃል፪___ተናባቢ
፩) ውዳሴማርያምውዳሴ ማርያም

፪) መሰንቆዳዊትመሰንቆ ዳዊት

፫) እንዚራስብሐት__እንዚራ ስብሐት

ይላል ማለት ነው። መጋቤ ሐዲስ ከሚለው ቃል። ሐዲስ የሚለው የመጋቢ ዘርፍ ይባላል። "ቤተ መንግሥት" ከሚለው
ቃል መንግሥት የቤት ዘርፍ ነው። በሌላ መልኩ የሚናበቡትን ቃላት በ "ዘ" እና በ "ለ" ማያያዝ ማናበብ ይቻላል።
ለምሳሌ ቤተ መንግሥት የሚለውን በ"ዘ" ሲገለጽ ቤት ዘመንግሥት ማለት ይቻላል። ወይም ዘመንግሥት ቤት ማለት
ይቻላል። የሦስቱም ትርጉም ተመሳሳይ ነው። የመንግሥት ቤት ማለት ነው። ቤት ዘመንግሥት በሚልበት ጊዜ "ዘ" ዘርፍ
አያያዥ ይባላል። ዘመንግሥት ቤት ሲል ደግሞ "ዘ" ዘርፍ ደፊ ይባላል። በ"ለ" ሲያያዝም ለምሳሌ ቤተ ያዕቆብ የሚለው
ቤቱ ለያዕቆብ ወይም ለያዕቆብ ቤቱ ይላል። ትርጉሙ የሦስቱም የያዕቆብ ቤት ማለት ነው። ቤቱ ለያዕቆብ ሲል "ለ"
ዘርፍ አያያዥ ይባላል። ለያዕቆብ ቤቱ ሲል ደግሞ "ለ" ዘርፍ ደፊ ይባላል። ሌላ ደግሞ ዘርፍ ጠምዛዥ የሚባል አለ።
ይኽውም ለምሳሌ ኅብስተ ዘኅሬ ሕይወት ቢል "ዘ" ዘርፍ ጠምዛዥ ይባላል። በምልዐት ኅብስተ ሕይወተ ኅሬ እንዲል
ያደርገዋል።

የዕለቱ ጥያቄዎች

የሚከተሉትን ቃላት ተናባቢ አድርጉ

፩) ማኅሌት እና ጽጌ

፪) ጽጌ እና ማኅሌት

፫) መጋቢ እና አእላፍ

የሚከተሉትን ቃላት በ"ለ" እና በ"ዘ" አያይዙ። ትርጉማቸውንም ተናገሩ

፬) ሀገር እና ያሬድ

፭) ወልድ እና አብ

የጥያቄዎች መልስ

፩) ማኅሌተ ጽጌ

፪) ጽጌ ማኅሌት

፫) መጋቤ አእላፍ

፬) ሀገር ዘያሬድ

ሀጉሩ ለያሬድ

ዘያሬድ ሀገር
ለያሬድ ሀገሩ

፭) ወልዱ ለአብ

ወልድ ዘአብ

ዘአብ ወልድ

ለአብ ወልዱ

♥️ግእዝ ቋንቋ ክፍል ፳፰♥️


ባለቤትና ተሳቢ

አንድ የግእዝ ቃል ባለቤት ሲሆንና ተሳቢ ሲሆን የተለያየ ቅርጽ ይኖረዋል። ለምሳሌ ዳቦ በግእዝ ኅብስት ነው። ዳቦ ይበላል
የሚል ዓረፍተ ነገር ቢኖረን ከዚህ ዳቦ የዓረፍተ ነገሩ ባለቤት ነው። ያዕቆብ ዳቦ በላ ብንል ግን የዓረፍተ ነገሩ ባለቤት
ያዕቆብ ሲሆን ዳቦ የሚለውን ግን ተሳቢ ይሆናል። በአማርኛው ባለቤትም ሲሆን ተሳቢም ሲሆን ምንም ዓይነት የቅርጽ
ልዩነት አላመጣም። በግእዝ ግን ኅብስት ይትበላእ ሲል ባለቤት ይሆናል። ያዕቆብ በልዐ ኅብስተ ሲል ደግሞ ተሳቢ
ይሆናል። ባለቤት ሲሆን ኅብስት ይል የነበረው ተሳቢ ሲሆን ኅብስተ እንዳለ አስተውል።

በሳድስ የሚጨርስ ቃል ተሳቢ ሲሆን መድረሻ ፊደሉን ወደ ግእዝ ይለውጣል። በካእብ የሚጨርስ ቃል ተሳቢ ሲሆን
መድረሻ ፊደሉን ሳብዕ ያደርጋል። በሣልስ የሚጨርስ ቃል ተሳቢ ሲሆን መድረሻ ፊደሉን ወደ ኃምስ ይቀይራል። በምሳሌ
እንመልከታቸው:-

ባለቤት___ተሳቢ

፩) ሕይወት__ሕይወተ

፪) ቤቱ__ቤቶ

፫) አእማሪ___አእማሬ

ይላል። በኃምስ፣ በሳድስ እና በሳብዕ የሚጨርሱ ቃላት ግን ተሳቢ ሲሆኑም አይለውጡም። ከባለቤታቸው ጋር ተመሳሳይ
ናቸው።ምሳሌ:-

ባለቤት__ተሳቢ

፩) እንዚራ___እንዚራ

፪) ውዳሴ___ውዳሴ

፫) መሰንቆ__መሰንቆ

ይላል።በስም ዝርዝር ጊዜ ተሳቢው የማይለወጥ የውእቶሙ፣ የይእቲ፣ የውእቶን፣ እና የአነ ዝርዝሮች ናቸው። በምሳሌ
ለማየት:-
ባለቤት__ተሳቢ

፩) ኅብስቶሙ____ኅብስቶሙ

፪) ኅብስቶን_ኅብስቶስን

፫) ኅብስታ__ኅብስታ

፬) ኅብስትየ_ኅብስትየ

ይላል። ሌሎቹ ዝርዝሮች ግን ተሳቢያቸውን ይለውጣሉ። በምሳሌ እንደሚከተለው እንመልከት:-

ባለቤት__ተሳቢ

፩) ኅብስቱ__ኅብስቶ

፪) ኅብስትከ____ኅብስተከ

፫) ኅብስትኪ___ኅብስተኪ

፬) ኅብስትክሙ___ኅብስተክሙ

፭) ኅብስትክን____ኅብስተክን

፮) ኅብስትነ__ኅብስተነ

ይላል ማለት ነው።ዘርፍነት የሌለው የሰው ስም ተሳቢ ሲሆን "ሀ" ን ይጨምራል። ለምሳሌ ያዕቆብ የሚለው ተሳቢ
ሲሆን ያዕቆብሀ ይላል። ፍጹም ሳድስ ያልሆኑ የሀገር ስሞች ባለቤታቸውም ተሳቢያቸውም ተመሳሳይ ነው። ምሳሌ:-

ባለቤት___ተሳቢ

፩) ኢየሩሳሌም____ኢየሩሳሌም

፪) ዮርዳኖስ__ዮርዳኖስ

፫) ባቢሎን___ባቢሎን

ይላል።ፍጹም ሳድስ የሆኑ ግብፅ፣ ምስር፣ ጽርዕን የመሰሉ ግን ተሳቢያቸው ግብፀ፣ ምስረ፣ ጽርዐ እያለ ይሄዳል።

የሚከተሉትን ቃላት ተሳቢያቸውን ጻፍ

፩) መንበሩ

፪) ኢትዮጵያ

፫) ሀገርከ
፬) ማርያም

፭) ቅዱስ

♥️ግእዝ ቋንቋ ክፍል ፳፱♥️


የግሥ ዝርዝር በመራሕያን

አንድ ግሥ በአስሩ መራሕያን ይዘረዘራል። እንዴት እንደሚዘረዘርም ቀጥለን እንመልከት።

፩) በውእቱ ጊዜ የሚጨመርም ሆነ የሚለወጥ ፊደል የለም ራሱ ግሡ ነው።

፪) በውእቶሙ ጊዜ መድረሻ ፊደሉን ወደ ካእብ መለወጥ ነው።

፫) በይእቲ ጊዜ "ት" ፊደልን መጨመር ነው።

፬) በውእቶን ጊዜ መድረሻ ፊደሉን ወደ ራብእ መለወጥ ነው።

፭) በአንተ ጊዜ መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ "ከ" ፊደልን መጨመር ነው።

፮) በአንትሙ ጊዜ መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ "ክሙ" የሚለውን መጨመር ነው።

፯) በአንቲ ጊዜ መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ "ኪ" ፊደልን መጨመር ነው።

፰) በአንትን ጊዜ መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ "ክን" የሚለውን መጨመር ነው።

፱) በአነ ጊዜ መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ "ኩ" ፊደልን መጨመር ነው።

፲) በንሕነ ጊዜ መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ "ነ" ፊደልን መጨመር ነው።

በአንደኛና በሁለተኛ መደቦች መጀመሪያ ቅድመ መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ እንደሚዘረዘር አስተውል። በምሳሌ
እንመልከት:-

መራሒ_ግእዝ____አማርኛ

፩) ውእቱ_ዘገበ_ሰበሰበ

፪) ውእቶሙ_ዘገቡ__ሰበሰቡ

፫) ይእቲ__ዘገበት__ሰበሰበች

፬) ውእቶን_ዘገባ___ሰበሰቡ

፭) አንተ_ዘገብከ___ሰበሰብክ

፮) አንትሙ_ዘገብክሙ_ሰበሰባችሁ
፯) አንቲ__ዘገብኪ_ሰበሰብሽ

፰) አንትንዘገብክንሰበሰባችሁ

፱) አነ__ዘገብኩ_ሰበሰብኩ

፲) ንሕነ_ዘገብነ__ሰበሰብን

የአንትን ዝርዝር ሥርዓተ ንባቡ ተጣይ ነው። ዘገብክን የሚለው ንባቡ ተጣይ ነው ማለት ነው። የይእቲ ዝርዝር ሥርዐተ
ንባቡ ሰያፍ ነው። ዘገበት የሚለው ተሰይፎ ይነበባል ማለት ነው።

በ"ነ" የሚጨርሱ ፊደላት ሲዘረዘሩ በንሕነ ዝርዝር ጊዜ "ነ" ራሱን ይውጥና ጠብቆ እንዲነበብ ያደርጋሉ። ሌላው
እንደላይኛው ነው። ቀጣዩን ምሳሌ ይመልከቱ:-

መራሒ__ግእዝ__አማርኛ

፩) ውእቱ_ወጠነ____ጀመረ

፪) ውእቶሙ_ወጠኑ_ጀመሩ

፫) ይእቲ_ወጠነት___ጀመረች

፬) ውእቶን__ወጠና__ጀመሩ

፭) አንተ_ወጠንከ___ጀመርክ

፮) አንትሙ_ወጠንክሙ_ጀመራችሁ

፯) አንቲ_ወጠንኪ__ጀመርሽ

፰) አንትን_ወጠንክንጀመራችሁ

፱) አነ_ወጠንኩ____ጀመርኩ

፲) ንሕነ__ወጠነ___ጀመርን

በደንብ አስተውል በጽሑፍ "ውእቱ ወጠነ" የሚለውና "ንሕነ ወጠነ" የሚለው ይመሳሰላል። በንባብ ግን ንሕነ ወጠነ ሲል
"ነ" ይጠብቅልን ውእቱ ወጠነ ሲል ግን "ነ" ላልቶ ይነበባል።

የዕለቱ ጥያቄዎች

የሚከተሉትን ቃላት በአስሩ መራሕያን ዘርዝር

፩) ቀደሰ___አመሰገነ

፪) ረበነ___አስተማረ
፫) መሐረ__ይቅር አለ

♥️ግእዝ ቋንቋ ክፍል ፴♥️

____ከባለፈው የቀጠለ

ሦስትና ከዚያ በላይ ሆሄያት ያላቸው ቃላት ሆነው በ"ሀ" እና በ"አ" የሚጨርሱ ግሦች ሲዘረዘሩ በአንደኛና በሁለተኛ
መደቦች ቅድመ መድረሻቸውን ወደ ራብዕ ቀይረው ይዘረዘራሉ። በምሳሌ እንመልከት:-

መራሒ__ግእዝ__አማርኛ

፩) ውእቱ_መርሐ__መራ

፪) ውእቶሙመርሑ_መሩ

፫) ይእቲ__መርሐት_መራች

፬) ውእቶን_መርሓ__መሩ

፭) አንተ__መራሕከ_መራህ

፮) አንትሙ__መራሕክሙ_መራችሁ

፯) አንቲ_መራሕኪ__መራሽ

፰) አንትን_መራሕክንመራችሁ

፱) አነ__መራሕኩ__መራሁ

፲) ንሕነ_መራሕነ__መራን

ይላል።የ"አ"ም ከዚሁ ጋር ተመሳሳይ ነው። መጽአ፣ መጽኡ፣ መጽአት፣ መጽኣ፣ መጻእከ፣ መጻእክሙ፣ መጻእኪ፣
መጻእክን፣ መጻእኩ፣ መጻእነ ይላል። ነገር ግን ሁለት ፊደል ሆኖ በ"ሀ" እና በ"አ" የሚጨርሱ ሕጎች ክፍል ፳፱ ላይ ባየነው
ሕግ መሰረት ይረባሉ። ለምሳሌ ቦአ_ገባ የሚለው በአስሩ ሲዘረዘር ቦአ፣ ቦኡ፣ ቦአት፣ ቦኣ፣ ቦእከ፣ ቦእክሙ፣ ቦእኪ፣ ቦእክን፣
ቦእኩ፣ ቦእነ ይላል።

የክህለ ቤት ሆኖ በ"የ" የሚጨርስ ግሥ ሲዘረዘር በአንደኛና በሁለተኛ መደቦች ቅድመ መድረሻውን ሣልስ አድርጎ "የ"ን
ጎርዶ ይነበባል። በምሳሌ እንመልከተው:-

መራሒ_ግእዝ___አማርኛ

፩) ውእቱ_ጥዕየ____ዳነ

፪) ውእቶሙ_ጥዕዩ__ዳኑ

፫) ይእቲ_ጥዕየት____ዳነች
፬) ውእቶን__ጥዕያ__ዳኑ

፭) አንተ_ጥዒከ____ዳንክ

፮) አንትሙ_ጥዒክሙዳናችሁ

፯) አንቲ_ጥዒኪ___ዳንሽ

፰) አንትን_ጥዒክን__ዳናችሁ

፱) አነ_ጥዒኩ_ዳንኩ

፲) ንሕነ__ጥዒነ___ዳንን

ይላል ማለት ነው። የክህለ ቤት የሚባሉት መጀመሪያ ፊደላቸውና ቀጥሎ ያለው ፊደል ሳድስ ሆኖ መጨረሻ ፊደላቸው
ግእዝ የሆኑ ግሦችን ነው።

የዕለቱ ጥያቄዎች

የሚከተሉትን ግሦች በአስሩ መራሕያን ዘርዝሩ

፩) ርእየ___አየ

፪) ተፈሥሐ___ተደሰተ

፫) ኖኀ___ረዘመ

፬) ዘርዐ___ዘራ

You might also like