Professional Documents
Culture Documents
ውዳሴ-ማርያም-በአማርኛ
ውዳሴ-ማርያም-በአማርኛ
ይዌድስዋ መላእክት............................................................. 15
የዘወትር ጸሎት
፩፤ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ንጹሕ ልዩ ክቡር ጽሩይ በሆኑ
በሦስትነት ወይም በሥላሴ እያመንኩና እየተማፀንኩ ጠላቴ ሰይጣንን እክድሃለው፣ በዚች በእናቴ
በቤተ ክርስቲያን ፊት ቁሜ እክድሃለው ለዚህም ምስክሬ ማርያም ናት በዚህም ዓለም
በወዲያኛውም ዓለም እሷን አምባ መጠጊያ አድርጌ እክድሃለሁ።
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ማቴ 26፥41 2020
፬፤ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ፤ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም
እልሻለሁ በሃሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም ድንግል ነሽ። የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ፤ ላንቺ
ሰላምታ ይገባል። ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽና የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።
ፀጋን የተመላሽ ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጅሽ
ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን ለምኝልን ኃጢአታችንን
ያስተሰርይልን ዘንድ አሜን።
የሃይማኖት ጸሎት
፭፤ ሁሉን የፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ሰማይንና ምድርን
የፈጠረ የሚታየውንና የማይታየውን ዓለም ሳይፈጠር ከርሱ ጋር በነበረ አንድ የአብ ልጅ በሚሆን
በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን ፥ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ
እውነተኛ አምላክ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ በባሕርዩ ከአብ ጋር የሚተካከል ሁሉ በእርሱ የሆነ
በሰማይም ካለው በምድርም ካለው ያለርሱ ምንም ምን የሆነ የለም ስለኛ ስለሰዎች እኛን
ለማዳን ከሰማይ ወረደ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ፣ ደግሞ
ስለኛ ተሰቀለ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን እርሱ መከራን ተቀበለ ሞተ ተቀበረ በሦስተኛውም
ቀን ከሙታን ተለይቶ ተሰሣ፣ በቅዱሳን መጻሕፍት እንደተጻፈ በክብር በምስጋና ወደሰማይ ዐረገ።
በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ፣ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ በምስጋና ይመጣል
ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም። በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ
ከአብ የሠረፀ ከአብ ከወልድ ጋራ በአንድነት እንሰግድለታለን እናመሰግነዋለን እርሱም በነቢያት
አድሮ የተናገረ ነው። ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሠሯት በአንዲት ክብርት ቤተ
ክርስቲያን እናምናለን። ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀትም እናምናለን የሙታንንም
መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ።
፯፤ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንዲት ስግደት እሰግዳለው /3 ጊዜ በል/። አንድ ሲሆን ሦስት
ሦስት ሲሆኑ አንድ በአካል ሦስት ሲሆኑ በመለኮት አንድ ለሚሆኑ እሰግዳለው አምላክን ለወለደች
ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም እሰግዳለው፣ ዓለምን ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ
ለተሰቀለበት መስቀልም እስገዳለሁ። መስቀል ኃይላችን ነው ኃይላችን መስቀል ነው የሚያፀናን
2
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ማቴ 26፥41 2020
መስቀል ነው፣ መስቀል ቤዛችን ነው፣ መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው፣ አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን
እናምነዋለን ያመነውም እኛም በመስቀሉ እንድናለን፣ ድነናለም።
፰፤ ለአብ ምስጋና ይገባል፣ ለወልድም ምስጋና ይገባል፣ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል። /3
ጊዜ በል/ አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ምስጋና ይገባል። ለኢየሱስ
ክርስቶስ መስቀልም ምስጋና ይገባል። ክርስቶስ በቸርነቱ ያስበን ዘንድ፣ ዳግመኛም በመጣ ጊዜ
እንዳያሳፍረን፣ ስሙን ለማመስገን ያነቃን ዘንድ፣ እርሱንም በማምለክ ያጸናን ዘንድ፣ እመቤታችን
ጸሎታችንን አሳርጊልን፣ ኃጢአታችንንም አስተሥርዩልን በጌታችን መንበር ፊት ጸሎታችንን
አሳርጊልን፣ ይህንን ኅብስት ላበላን ይህንንም ጽዋ ላጠጣን፣ ምግባችንንና ልብሳችንንም
ላዘጋጀልን፣ ኃጢአታችንንም ሁሉ ለታገሠልን፣ ክቡር ደሙን ቅዱስ ሥጋውን ለሰጠን፣ እስከዚችም
ሰዓት ላደረሰን ለእሱ ለልዑል እግዚአብሔር ፍፁም ምስጋና ይገባል፣ ለወለደችው ለድንግም
ምስጋና ይገባል፣ ለክቡር መስቀሉም ምስጋና ይገባል። የእግዚአብሔር ስሙ
ፈጽሞ ይመሰገን ዘንድ ዘወትር በየጊዜያቱና በየሰዓቱ ምስጋና ይገባል።
፬፤ ሰው የሆነና በኛ ያደረ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ክብሩንም ለአባቱ አንደ እንደመሆኑ ክብር
አየን። ይቅር ይለን ዘንድ ወደደ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
3
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ማቴ 26፥41 2020
፲፤ በዚህ ዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምታበራ እውነትኛ ብርሃን ስለሰው ፍቅር ወደ ዓለም
የመጣህ ፍጥረት ሁሉ በመምጣትህ ደስ አለው አዳምን ከስህተት አድነኸዋልና ሔዋንንም ከሞት
ጻዕረኝነት ነፃ አድርገኻታልና የምንወለድበትን መንፈስ (ረቂቁን ልደት) ሰጠኸን ከመላእክት ጋርም
አመስገንህ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
4
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ማቴ 26፥41 2020
5
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ማቴ 26፥41 2020
6
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ማቴ 26፥41 2020
፱፤ ኆኅትም ደጅም መድኃኒታችንን የወለደች ድንግል ናት። እርሱን ከወለደች በኋላ እንደ
ቀድሞ በድንግልና ኖራለችና። መጥቶ ምሕረት ከሌለው ጠላት እጅ ያዳነን ጌታን የወለጅሽ ሆይ
የማኅፅንሽ ፍሬ የተባረከ ነው፥ አንቺ ፍጽምትና የተባረክሽ ነሽ የእውነት አምላክ በሆነ በክብር
ባለቤት ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና በምድር ላይ ከሚኖር ሁሉ ይልቅ ገናንነትና ክብር ለአንቺ
ይገባል። የአብ ቃል መጥቶ በአንቺ ሰው ሆነ። ከሰው ጋርም ተመላለሰ። መሓሪ ይቅር ባይ ሰውን
ወዳጅ ነውና በልዩ አመጣጡ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
፩፤ ርኵሰት የሌለባት ድንግል ማርያም ሙሴ በበረሃ በነደ እሳት ጫፎቿ ሳይቃጠሉ ያያት ዕፅን
ትመስላለች፤ የአብ ቃል በርስዋ ሰው ሆኗልና፣ እሳተ መለኮቱ (የመለኮቱ ባሕርይ) አላቃጠላትምና
ከወለደችውም በኋላ ድንግልናዋ አልተለወጠምና ሰውም ቢሆን መለኮቱ አልተለወጠም በዕውነት
አምላክ ነውና በዕውነት አምላክ የሆነ እርሱ መጥቶ አዳነን። ቅድስት ሆይ ልምኝልን።
፫፤ ሔዋን እንጨት በልታ ባደረገችው ዓመፅ በባሕርያችን ያደረ የቀድሞው እርግማን በእርስዋ
የጠፋልን አምላክን የወለደች ድንግል ማርያም የሁላችን መመኪያ ናት። ስለ ሔዋን የገነት ደጅ
ተዘጋ ዳግመኛም ስለ ድንግል ማርያም ተከፈተልን። ከዕፀ ሕይወት እንበላ ዘንድ አደለን። ይኸውም
እኛን ስለመውደድ መጥቶ ያዳነን የክርስቶስ ክብር ሥጋው ክብር ደሙ ነው። ስለ እርሷ ድንቅ ሆኖ
የሚነገረውን ይህን ምሥጢር ማወቅ የሚቻለው ምን ልቡና ነው? መናገር የሚቻለው ምን
አንደበት ነው? መስማት የሚቻለው ምን ጆሮ ነው? ሰውን የሚወድ እግዚአብሔር አንድ ብቻ
የሆነ አምላክነቱ ሳይለወጥ ከዓለም በፊት የነበረ የአብ ቃል ከአብ ዘንድ መጥቶ ልዩ ከሆነች እናቱ
ሰው ሆነ። ከወለደችውም በኋላ ድንግልናዋ አልተለወጠም። ስለዚህ አምላክን የወለደች
እንደሆነች ታወቀች። የእግዚአብሔር የጥበቡ ስፋት ምን ይጠልቅ? በጻእር በምጥ በልብ ጋር
ትወልድ ዘንድ የፈረደባት ማኅፀን የሕይወት መገኛ ሆነች ከባሕርያችን እርግማንን የሚያጠፋልንን
ያለ ወንድ ዘር ወለደችልን። ስለዚህም ሰውን የምትወድ ሆይ ክብር ላንተ ይገባል፤ ቸርና
የሰውነታችን መድኃኒትም ነህ እያልን እናመስግነው። ቅድስት ሆይ ልምኝልን።
አምላክ እንደሆነ በተረዳ ነገር አውቀነዋልና። ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ
ምን ይደንቅ ቃልን ወሰነችው። ልደቱንም ዘር አልቀደመውም። በመወልዱም ንግልናዋን
አልለወጠውም። ቃል ከአብ ያለ ድካም ወጣ። ከድንግልም ያለ ሕማም ተወለደ። ሰብአ ስገል
ሰገዱለትም አምላክ ነውና ዕጣን አመጡለት ንጉሰም ነውና ወርቅ አመጡለት ስለእኛ በፈቃዱ
ለተቀበለው መዳኛችን ለሆነ ሞቱም ከርቤ አመጡለት። ቸር ሰውን
ወዳጅ የሆነ አንድ እርሱ ብቻ ነው ። ቅድስት ሆይ ልምኝልን።
፭፤ ከአዳም ጎን አንዲት ዐፅም ማንሣት ምን ይደንቅ? ከእርሱ ሴትን ፈጠረ የሰው ፍጥረትንም
ሁሉ ፈጠረ። ጌታ የአብ ቃል ተሰጠ። ከልዩ ድንግልም ሰው ሆነና አማኑኤል ተባለ ስለዚህ ሁል ጊዜ
እርስዋን እንለምን፣ ከተወደደ ልጅዋ ታማልደን ዘንድ። በቅዱሳንና በሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ ቸር ናት
ደጅ የሚጠኑትን ወልዳላቸዋልችና ለነቢትም ትንቢት የተናገሩለትን ወልዳላቸዋለችና
ለሐዋርያትም እስከ ዓለም ዳርቻ በስሙ ያስተማሩለትን ወልዳላቸዋለችና ሰማዕታትና
ምዕመናንም የተጋደሉለትን የጥበቡ ጸጋ ብዛት የማይታወቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርስዋ
ተወልዷልና የይቅርታውን ብዛት መርምረን እንወቅ (እንገፈልግ) መጥቶ አድኖናልና። ቅድስት ሆይ
ልምኝልን።
፰፤ ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ መዋረዳችንን አይቶ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ባሕርዩን ዝቅ
አደረገና መጥቶ በድንግል ማኅፀን አደረ። ከብቻዋ ከኃጢአት በቀርም አንደኛ ሰው ሆነ፤ ነቢያት
ትንቢት እንደተናገሩለት በቤተልሔም ተወለደ። ፈጽሞ አዳነን ወገኖቹም አደረገን። ቅድስት ሆይ
ልምኝልን።
8
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ማቴ 26፥41 2020
፩፤ ንጽሕት ነሽ ብርህትም ነሽ። ጌታን በመኻል እጅሽ የያዝሽው ሆይ በሁሉ የተቀደሽ ነሽ።
ፍጥረት ሁሉ ቅድስት ሆይ ለምኝልም ብለው እየጮኹ ካንቺ ጋር ደስ ይላቸዋል። ቅድስት ሆይ
ለምኝልን።
፯፤ ከተለዩ የተለየች የተባልሽ የኪዳን ጽላት ያለብሽ የተሰወረ መና ያለበት የወርቅ መሶብ
ያለብሽ ደብተራ ድንኳን አንቺ ነሽ። ይኸውም መና የተባለው መጥቶ በድንግል ማርያም ማኅፀን
ያደረው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። የአብ ቃል በርስዋ ሰው ሆነ መጥቶ ያዳነን የባሕርይ ንጉሥን
በዓለም ውስጥ የወደችው የሚናገር በግ የክርስቶስ እናቱ ገነት ደስ ይላታል ለዘለዓለም የሚኖር
የአብ ልጅ እርሱ መጥቶ ከኃጢአት አድኖናልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
፰፤ የንጉስ ክርስቶስ እናቱን ተባልሽ እርሱን ከወለድሽ በኋላም በድንግልና ኖርሽ። ድንቅ
በሆነ ምሥጢርም (ተዋህዶ) አማኑኤልን ወለድሽው ስለዚህም ባለመለወጥ አጸናሽ። ቅድስት
ሆይ ለምኝልን።
10
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ማቴ 26፥41 2020
ይኸውም ካንቺ ሰው የሆነና ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያሳረገ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
፰፤ የእግዚአብሔርን ቃል የወለድሽልን መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ ደሽ ይበልሽ። ከዕሴይ
ሥር የወጣሽ መዐዛሽ ያማረ አበባ አንቺ ነሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
፱፤ ሳይተክሏትና ውሃ ሳያጠጧት የለመለመች የአሮን በትር ነበረች ያለ ዘር ሰው ሆኖ ያዳነን
እውነተኛ አምላክችንን ክርስቶስን የወለድሽልን ሆይ አንቺ እንደርሷ ነሽ። ቅድስት ሆይ
ለምኝልን።
፲፤ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ትለምኝልን ዘንድ ላንቺ ይገባል። አንቺ ከሊቃነ
ጳጳሳት ትበልጫለሽ ከነቢያትም ከመምህራንም ትበልጫለሽ። ከሱራፌልና ከኪሩቤል ግርማ
የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ። በእውነቱ የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ። ለሰውነታችንም
ሕይወትን የምትለምኝ ነሽ። ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምኝልን ፤ እርሱን
በማመን በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ ይቅርታውንና ምሕረቱን ይሰጠን ዘንድ በቸርነቱ ብዛት
ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
፲፩፤ ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት ከልጇ ከወዳጇ ከ _______________ እንዲሁም
ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋራ ለዘለዓለሙ ይኑር፤ አሜን።
ይዌድስዋ መላእክት
፩፤ መላእክት ማርያምን በመንጦላዕት ውስጥ ያመሰግኗታል፤ ሐዳስ ጣዕዋ ላንቺ ምስጋና ይገባሻል
እያሉ። መልአክ ማርያምን ቃልን ተቀበይው አላት ካንቺ ዘንድ ይመጣልና በማኅፀንሽም ያድራል።
እንዴት ከድሀ ቤት አደረ እንደ ምስኪን ከሰማያት ወርዶ የርስዋን ባሕርይ ባሕርይ አድርጎ ተወለደ?
፪፤ በ፮ኛው ወር ገብርኤል መልአክ ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ ተላክ ካንዲት አገር ናዝሬት ገሊላ
ከምትባል ለዮሴፍ እጮኛ ከሆነች ከድንግል ዘንድ። የዚች የድንግል ስሟ ማርያም ነው መልአኩ ወደ
እርስዋ ገብቶ እንዲህ አላት ደስታ ይገባሻል እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ካንቺ
ሰው ሆኗልና ከሴቶች ይልቅ አንቺ ቡርክት ነሽ። ከቃሉ አነጋገር አይታ ደነገጠች እንዲህም አለች
እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ መንሻ ይደረግልኛል ? መልአክ እንዲህ አላት ማርያም ሆይ አትፍሪ
ከእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና እነሆ ትፀንሻለሽ ትወልጃልሽ ስሙንም ኢየሱስ
ትይዋለሽ እርሱም ታላቅ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል እግዚአብሔር አምላክም የዳዊት ያባቱን
ዙፋን ይሰጠዋል እርሱም በያዕቆብ ወገን ለዘላለሙ ይነግሣል መንግሥቱም አያልፍም፤ ማርያምም
መልአኩን እንዲህ አለችው ይህ ነገር እንደምን ይሆንልኛል እንዘ ኢየአምር ብእሴ መልአኩም
እንዲህ አላት፤ መንፈስ ቅዱስ ይጠብቅሻል የልዑል ኃይልም ያድርብሻል ይህ የሚወለደው ከሦስቱ
ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ነው እነሆ ኤልሣቤጥ ካንቺ ወገን የምትሆን ከሸመገለች ካረጀች በኋላ ፀነሰች
ልጅም አገኘች እነሆ ይህ ስድስት ወር ሆነ መካን ሲሏት ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።
ማርያምም መልአኩን እንደ ቃልህ ይደረግልኝ እኔ ለእግዚአብሔር ባሪያው ነኝ አለቸው።
፫፤ መልአኩ ገብርኤል ማርያም ድንግል ላንቺ ክብር ምስጋና ይገባሻል አላት።ክብር ምስጋና
ይድረስሽ ወላዲተ አምላክ ክብር ምስጋና ይገባሻል፣
ቅድስት ነሽና ክብር ምስጋና ይገባሻል፣ የመለኮት ማደሪያ ነሽና ክብር ምስጋና
ክብር ምስጋና ይጋባሻል፣ የሁሉ ሰላም ማርያም ክብር ምስጋና ይገባሻል፣ ልዑል
12
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ማቴ 26፥41 2020
ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ለምኝልን ያድነን ዘንድ ከአባቱ ምስጋና
ከቅዱሳን መላእክቶቹ ጋር በመጣ ጊዜ ጻድቅንን በቀኙ ኃጥአንን በግራው ባቆመ ጊዜ እኛን
ከሰማዕት እንጢፋኖስ ከመጥምቁ ዮሐንስ እና ከሁሉ ቅዱሳን ከሰማዕታትም ጋር ያቆመን ዘንድ
ለምኝልን ለዓለመ ዓለም አሜን፤ ለዘለዓለሙ ይቅር ይበለን።
13
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ማቴ 26፥41 2020
14