You are on page 1of 32

ነገረ ማርያም

በሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ

(የ፬ቱ ጉባኤያት መ/ር)

ምዕራፍ አንድ
ትርጉም ፡ የወንጌል መግቢያ የነገረ ድኅነት መጀመሪያ ማለት ነውና እግረ መንገዳችንንም
የሰው ልጆችን የመዳን ታሪክ የምናይበት ትምህርት ነዉ፡፡

- ወንጌለ ማቴዎስ እና ወንጌል ሉቃስ ሲጽፉ ነገረ ማርያምን ዜና አድርገው ነው


የጀመሩት፡፡
- ነገረ ክርስቶስን ለማምጣት ነገረ ማርያም ስለሚቀድም ነው፡፡ ይላል፡፡

የእመቤታችን ድንግል ማርያም የስሟ ትርጓሜ

የእመቤታችን የስሟ ትርጓሜ በሁለት መንገድ ከፍለን ማየት እንችላለን

 በትርጉም እና
 በትርጓሜ

ትርጉም ፡-ማለት ቃሉ ማርያም የሚለው ከምንም ነገር ጋር ሳይያያዝ ቀጥተኛ ትርጉሙ ማለት
ነው፡፡

ትርጓሜ፡- ማለት ደግሞ ዝርዝር ጉዳይ የያዘ ነው ከተሠጣት ቃልኪዳን ክብር ከመሳሰሉት ጋር
ተገናዝቦ የሚተረጎም ነው፡፡

 ምሣሌ ማየት ይቻላል

ነቅዐ ጥበብ የሚለው ስም በትርጉም ደረጃ ሲታይ የእውቀት ምንጭ ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ስሙ
ከምንም ጋር ሳይያያዝ ማለት ነው፡፡ ቀጥተኛ ትርጉሙ ማለት ነው፡፡ ይህ የሚሆነው ነቅዓ ጥበብ ማለት
ምን ማለት ነው ለሚለው ጥያቄ ነው፡፡

 በትርጉም አንቀጽ ካየነው ግን ነቅዐ ጥበብ ማነው የሚል ይሆናል ፡፡


ለዚህ መልሱ ደግሞ አጭር ከሆነ አጭር ጥቁር ከሆነ ጥቁር ቀይ ከሆነ ቀይ እየተባለ ሊመለስ
ይችላል……

በዚህ መሠረት ማርያም የሚለውን በትርጉም ደረጃ የምናየው ከሆነ ቃሉ በእብራይስጥ ማርያም
ተብሎ ይጠራል፡፡
ማር የሚል እና ያም የሚል ሁለት ቃላት ተገጣጥመው የሚነበብ ነው፡፡
ማር ማለት መራራ ፣ጎምዛዛ፣ሀሞት፣ እሬት ማለት ይሆናል፡፡
ያም ማለት ዮም ከሚል ግእዝ ቃል የተገነ ሲሆን
ትርጉሙ ዘመን ፣እለት፣መዋእል ማለት ይሆናል፡፡
ሁለቱ በአንድነት ሲጠሩ
ዘመነ መራራ
ዘመነ እሬት
ዘመነ ቆምጣጣ
ዘመነ መራራ የሆነባት ሴት ማለት ይሆናል፡፡ ይህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ያለው ነው፡፡
- በመጀመርያ ማርያም ተብላ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠራችው የሙሴ እህት ማርያም ናት ፡፡
- ታድያ ለምን ማርያም ብለው ጠሯት ሲባል
- በእርሷ ዘመን እስራኤል በመከራ ስደት ይኖሩ ነበርና እንዲሁ በእርሷ ዘመን የእስራኤል
ወንዶች እየታገቱ ይገደሉ ነበርና በዚህ የተነሳ ዘመንሽ መራራ ጎምዛዛ ነው ሲሉ ስሟን ማርያም
ጠርተዋታል፡፡
- ብሉይት ማርያም ለአዲስ ኪዳኗ ማርያም ምሣሌ መርገፍ ሆና የተጠቀሰች ናት ፡፡
- በአዲስ ኪዳንም ማርያም ጊዜ ልጇን ይዛ ተሰዳለችና በእርሷም ጊዜ ሔሮድስ ወንድ ህጻናትን
አስፈጅቷልና ስሟን ዘመንሽ መራራ፣ ቆምጣጣ፣ ጎምዛዛ ነው ሲሉ ማርያም ብለው
ጠርተዋታል፡፡
 ማርያም ማለት ኮከብ ባህር ማለት ነው፡፡

እግዚአብሔር ለእስራኤል ባህር በከፈለ ጊዜ ጠላቶቻቸውን በገደለ ጊዜ የሙሴ እህት ማርያም ከበሮዋን
ነጥቃ በባህር ወስጥ አንደኮከብ ቦግ ቦግ እያለች ንሴብሆ እያለች አመስግናለችና ፡፡

ሌላው ራእይ ዮሐንስ 8፣10 ላይ ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ በውሃም ምንጮች ሢሶ ላይ ወደቀ የኮከቡም
ስም ዕጉስታር (ሬቶ) ይባላል፡፡

ይህ ሲተረጎም

 ባህር ማለት ዘመን ማለት ነው (ባህረ ሀሳብ እንዲሉ)


 ኮከቡ ደግሞ ዕጉስታር (ሬቶ) ይባላል ሁለቱ በአንድ ላይ ሲገጥም
 ዘመነ መራራ
 ዘመነ ሬት
 ዘመነ ጎምዛዛ የሆነባት ሴት ማለት ይሆናል፡፡

 እመቤታችን የምንላት የንጉስ እናት ንግስት በመሆኗ ነው፡፡

ከእመቤታችን በስተቀር በመፅሐፍቅዱስ እመቤታችን ተብላ የተጠራች አንድም ሴት የለችም፡፡

እመቤታችን የወለደችው የዓለሙን (የሁላችንንም) ንጉስ ጭምር ነው፡፡

እመቤታችን የንጉስ እናት ንግስት ብቻ አይደለችም የንጉስ መናገሻ ቤተ መንግስትም ናት


እንጂ፡፡

በማዕፀን ውስጥ ንጉስ ሆኖ የተወለደ እርሷ ከወለደችው ክርስቶስ በስተቀር ማንም የለም፡፡

ማቴ 2-1 ‹‹የተወለደው የአይሁድ ንጉስ ወዴት ነው››

ቅ/ዮሐንስ በመልዕክቱ ለአንዲት ሴት ‹‹እመቤት እርስ በእርሳችን እንዋደድ ዘንድ ብሎ


ተናግሯል፡፡ምክንያቱም የሴትን እመቤትነት ለጥቂት ሠዎች እንጂ ለአለሙ ሁሉ የለዉም
እመቤታችን ግን የአለሙ ንጉስ የሆነ መድኃኔዓለምን ስለወለደችው ዓለሙ ሁሉ ባንድ ላይ
‹‹እመቤታችን›› ብሎ የጠራት እርሷን ነው፡፡

መዝ 44 ላይ ንግስቲቱ ብሎ ዳዊት የጠራትም ለዚሁ ነው፡፡

ማርያም ማለት ምን ማለት ነው

 ማርያም የተፀውኦ ስሟ ነው፡፡

ማርያም ማለት ምን ማለት ነው

፩. መርህ ለመንግስት ሰማያት ማለት ነው፡፡

- ወደ መንግስት ሰማያት መርታ የምታስገባ ማለት ነው

 ይህ አባባል ስለ ሦስት ነገር ነው የተነገረው

ሀ) መንግስት ስማያት ክርስቶስ ነውና አምላክ ሰው የሆነባት ሰውም አምላክ የሆነበት እርሷ
ስለሆነች ነው፡፡

- መንግስተ ሰማያት መርታ የምታስገባ ያልናት ሰለዚህ ነው፡፡


- ጌታ መንግስት ሰማያት ከሆነ ወደ ጌታ የምታቀርብ ደግሞ እርሷናት እናቱ ነች፡፡
- ከክርስቶስ ጋር ታገናኛለች ማለታችን ነው፡፡

የቤ/ክ ራስ የሆነው ክርስቶስ የተገኘው ከእርሷ ስለሆነ ነው፡፡ ኤፌ 5-1

- እመ አምላክ ወደ መንግስተ ሰማያት መርታ ታስገባለች፡፡


- አመቤታችንን ወላዲተ መንግሰተ ሠማያት ብለን ልንጠራት እንችላለን፡፡
- መንግስተ ሠማየት ማለት ክርስቶስ ለመሆኑ ማሳያ ፈያታዊ ዘየማንን ‹‹ዛሬ ከእኔ ጋር
በገነት ትኖራለህ›› ብሎታል ይህ የሚያሳየው ገነት በራሷ ከእግዚአብሔር ጋር ካልሆነ
የምትሰጠን ገነት አትሆንም፡፡እንዲያማ ባይሆን ኑሮ ‹‹ዛሬ በገነት ትኖራለህ›› ባለው
ነበር ስለዚህ ገነት ክርስቶስ ከሆነ መንግስት ሠማያትም ክርስቶስ ነው፡፡

ለ) የቅዱስ ቁርባን መገኛ ስለሆነች ነው፡፡ መርህ ለመንግስት ሠማያት ያልናት፡፡

- እመቤታችን የቅዱስ ቁርባን መገኛ ሰለሆነች ‹‹ሙዳይ ቅዱስ ቁርባን›› ትሰኛለች፡፡


- ምክንያቱም ክርስቶስ ከእርሷ ተገኝቶ መለኮትን ተዋህዶ የቀረበ ቁርባን ሰለሆነ ነው፡፡
- ቁርባን ማለት አመሃ ፣ሥጦታ፣ እጅመንሻ ማለት ስለሆነ ፡፡ እጅ መንሻነቱ ደግሞ
ለመንግስተ ሠማያት መግቢያነት ነው፡፡ ይህን እጅ መንሻ ቁርባን ክርስቶስን ያስገኘች
ደግሞ እመቤታችን ናት፡፡
- ስለዚህ እርሷን ወደ መንግስት ሠማያት መርታ የምታስገባ ብንላት ስህተት አይደለም፡፡

ሥጋውና ደሙ የመንግስተ ሠማያት መያዣ ነው፡፡

- መንግስተ ሰማያት ለመግባታችን ማረገጋጫው ሥጋውና ደሙ ነው፡፡


- የገዛ ሥጋውና ደሙን ሳይነፍግ የሰጠን መንግስቱንማ እንዴት ይከለክለናል ብለን
እንድናምን እንገዳደልን፡፡

ሐ) ቀዳሚት ሔዋን ወደዚህ ዓላም እንደንመጣ ምክንያታችን (መሪያችን) ነበረች፡፡

- እመቤታችን ደግሞ በመጀመሪያ ለሐዲስ ኪዳን (ለወንጌል) በመቀጠል (በሁለተኛደረጃ


)ደግሞ ለመንግስተ ሠማያት መሪያችን ሆናለች፡፡
- አንዲት ሴት ከመንግሰተ ሠማያት ያስወጣችውን ትውልድ፡፡ አንዲት ሴት መልሣ
ይዛው የምትገባ ስለሆነ ነው፡፡
- ቀዳማዊቷ ሔዋን ሞትን ለዓለም ያስተዋወቀው ቃየንን ስትወለድ ፣ ዳግሚት ሔዋን
እመቤታችን ደግሞ ሕይወትን ለዓለም የሰጠው ክርስቶስ ወለደችልን፡፡
- የእመቤታችን የሚደንቀው ከርሷ ልጅ የተነሣ ‹‹ወንሴፎ ትንሳኤ ሙታን›› ብለን
መንግስተ ሠማያትን ተስፋ እንድናደርግ መድኃኒያለም ወለደችልን፡፡
-
- መንግስተ ሠማያት ማለት ትልቁ ደስታ ነው፡፡
- ጌታ ሲወለድም የነበረዉ ደስታ ታላቅ ነው፡፡ ሉቃ 2÷8
 በዚህ መሠረት የታላቁ ደስታ አስገኚ እመቤታችን ናት፡፡
- ‹‹በዛቲ ዕለት ተፈፀመ ደስታ ለቤተክርስቲያን ›› ታላቁ ሊቅ በሃይማኖተ አበው
የተናገረው ነው፡፡
- ዜና መንግስተ ሠማያት በእመቤታችን ማህፀን የተጀመረ ነው፡፡
- የመንግስተ ሠማያትን ዜና ቀድማ ሰምታ ያሠማችን እርሷ ስለሆነች መርህ ለመንግስተ
ሠማያት እንላታለን
- የመረገሙን ዜና ደግሞ ቀድመን የሠማነው በቀዳሚት ሔዋን ማዕፀን ነው፡፡
-

፪. እመ ብዙሀን (የብዙዎች እናት )ማለት ነው፡፡

- አዳምና ሔዋን መንታ መንታ ቢወልዱም ምድርን እስከ አሁን አልሞሉትም ፡፡


- እመቤታችን ግን አንድ ሆና ተወልዳ ፣ አንድ ወልዳ ምድሩንና ሠማዩን ሞልታዋለች ፡፡

ማርያም የሚለውን ቃል ስንተረጉመው ሦስት ልዩ ልዩ ትርጉም ይሰጠናል ፡፡ በፊደል ደረጃ

ሀ) ወላዲተ አምላክነቷን ያሳያል

ለ) ደግነቷን (አዛኝነቷን) ያሳይል

ሐ) ተስፋ ምእመናን መሆንዋንም ያሳየናል

ማ ፡-ማህደረ መለኮት ስለሆነ

ወላዲተ አምላክነቷን ያሳያል

ር፡- ርግብየ መደምደምያዬ ማለት ስለሆነ

ደግነቷን (አዛኝነቷን) ያሳየናል

ያ፡- ያንቃዐዱ ሃቤኪ ኩሉ ፍጥረት

ተስፋ ያደርጉሻል ፍጥረት ሁሉ ወዳንቺ ቀና ብለው ይመለከታሉ ፡፡ወዳንቺ የንጋጥጣሉ

ም፡- ምሳል ወምሥጋድ


ቤተ ፀሎት ቤተ ሥግደት ማለት ነው፡፡

ያው በፀሎት በቤተ መቅድስ ተማፅነው ተስፋ ያረጉናል ማለት ነው፡፡

ያንቃዐዶ ከሚለው ጋር ተመሣሣይ ነው፡፡

- ማርያም የሚለውን ሥም የያዙ ሁሉ ለእመቤታችን የተሰጠው ትርጉም ሁሉ


ይሰጣቸዋል ማለት አይደለም

የእመቤታችን የዘር ሐረግ

- የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ቴክታ እና በጥሪቃ ይባላሉ፡፡


- ቴክታ እና በጥሪቃ ሰባት ልጆችን ወልደዋል እመቤታችን ሰባተኛው ትውልድ ነች፡፡
- ቴክታ እና በጥሪቃ መካኖች ነበሩ ፡፡ ከብዙ ቆይታ በኃላ ነው ልጅ የታቀፉት፡፡
- የመጀመሪያ ልጃቸውም ሄኤሜን ትባላለች

የዘር ሐረጓን በዚህ መልኩ ስናስቀምጥ

ቴክታ + በጥሪቃ =ሄኤሜን ዳርዲ ቶናህ ሲካር ሄርሜላ ሀና

(የእመቤታችን የዘር ሐረግ ይህን ይመስላል፡፡)

- በኦሪቱ ከ22ቱ አርስተ አበው 7ኛው ትውልድ የነበረው ሄኖክ ተስፋ ትንሳኤን እንዳሳየን ሁሉ
በሐዲስ ኪዳን በወንጌል አንደተገለፀው ጌታ እኔ ትንሳኤ እና ህይወት ነኝ ማለቱ ይታወቃል
ይህን ትንሳኤና ሕይወት የሆነ ጌታንም የወለደች እመቤታችን በ7ኛውትውልድ የተገኘች ነች፡፡

- ጌታም ከፈጠራቸው ቀናት መሀከል 7ኛውን ቀን


በልዩ ሁኔታ ባረከው አከበረው ብሎም ከሥራው
ሁሉ በዚህ ዕለት አረፈ፡፡

- እመቤታችንንም ከሰው ሁሉ ለይቶ ቀደሳት አከበራት ቅድስተ ቅዱሳንም ተስኝታ እንድትጠራ


አደረጋት አልፎም ተርፎ ወደ ዓለም ለመጣ ባሠበም ጊዜ መረፍያዉ ሆነችው፡፡

- መዝ 131 ‹‹ይህች ለዘላለም ማረፊያዮ ናት››ም አለ፡፡

- ሰባት ቁጥር ፍፁም እንደሆነ ሁሉ በ7ኛው ትውልድ የተገኘች እመቤታችንም የማይጠራጠሩት


ድንግልና የማይከራከሩበት ቅዱስና እና ፍፁም ንፅህና ያላት ሆና ተገኘች፡፡
- ከርሷ በኃላ የተገኘው ክርስቶስ ደግሞ 8ኛው ትውልድ ሆኖ መሥጋ ተገለጠ፡፡

ክርስቶስ ለምን በስምንተኛው ሺህ ትውልድ ተመሰለ 

- ስምንቱ ብሔር ኦሪት ምግብናቸውን ሲጨርሱ የሚወለድ መሆኑን ይጠይቃል፡፡

 ፍጻሜው ግን 8000 ዘመን (ዓመት) ሲፈጸም ጌታ ወደእኛ መጥቶ እኛም ወደእርሱ


ሄደን የመኖራችን ምሳሌ ነው፡፡
 አዳም የወደቀው ስምንተኛ መዓረግ ላይ ሳለ ሲሆን ጌታም በስምንተኛው ትውልድ
መገኘት ወደቀደመ ክብራችን ሊመልሰን ማሰቡን እንረዳለን፡፡
ምዕራፍ ሁለት
እመቤታችን ከሥነ ፍጥረት በፊት
ምዕራፍ ሦስት

እመቤታችን በሥነ ፍጥረት


እመቤታችን በ22ቱም ሥነ ፍጥረት እየተመሰለች ይነገርላታል፤ ምክንያቱም 22ቱም አርእስተ
አበው አባቶቿ ናቸውና፡፡

የእመቤታችን ምሳሌዎች

፩. በሰባቱ ሠማያት እንመስላታለን

 ሰባት መሆናቸው የፍጹም ክብሯ ምሳሌ ነው፡፡


 ሠማያቱ ሦስት ክፍል ነው ያላቸው፡፡
 እመቤታችንም ሦስት ድንግልና ነው ያላት፡-
o የሥጋ ድንግልና
o የነፍስ ድንግልና
o የህሊና ድንግልና

ሀ) የመጀመሪያው ክፍል መቅደሰ እግዚአብሔር የሚባለው

o ፅርሃ አርያም
o መንበረ ስብሐት
o ሠማይ ውዱድ
ከላይ የተጠቀሱት መቅደሶች ፍጡራን የማይገቡባቸው
የእግዚአብሔር ብቻ ከተሞች ናቸው፡፡

- እግዚአብሔር ለፍጡራን ልገለፅ ባለ ጊዜ በእነዚህ ስፍራዎች ነው የሚገለፀው፡፡


እመቤታችንም ፍጡራን የማያድሩባት የእግዚአብሔር ብቻ ቤተመቅደስ ነች፡፡
- ይህ ማለት ፍጡር ያልተፀነሰበት ማዐፀን የላት ማህደረ እግዚአብሔር ናት፡፡

ለ) ሁለተኛው ክፍል የሰው ልጅች ያሉበት መንግስተ ሠማያት ነው፡፡

የሠው ልጅ ያለአንዳች ሐዘንና መከፋት የሚኖሩባት የደስታ ከተማ ናት፡፡

እመቤታችንንም በመንግሰተ ሠማያት ስንመስላት ለፍጥረት ሁሉ ደስታ የሆነ ጌታን ይዛ


ስለተገኘች ነው፡፡

የሰው ማደሪያ መንግስት ሠማያት ነው፡፡ ሌላም ተስፋ የለውም፡፡


ሰው የተገኘባት የሰው ማደርያ እመቤታችን ድንግል ማርያም ነች፡፡

ሐ) ሦስተኛው ክፍል ዓለመ መላእክት ነው፡፡

አስር ከተማ ያለው የብዙ ሠሪዊት መኖርያ እና ሦስት ክፍል ያለው ዓለም ነው፡፡

እመቤታችንም በአስሩ የስሜት ሕዋሳቶች ሦስቱን ድንግልናዎቿን ጠብቃ በመኖሯ የብዙ


ምእመናን መመኪያ መሆኗን ለማጠየቅ ነው፡፡

፪) እመቤታችንን በምድር እንመስላታለን

ምድር ብለን የመሠልናት እንደ አምላክነቱ ባርያው መሆኗን ለመግለጥ ነው ሠማይ ስንል ግን
ባለሟልነቷን ለመግለፅ ነው፡፡

እመቤትነትን ከገረድነት ጋር፣ ገረድነትን ከእመቤትነት ጋር ፣እናትነትን ከድንግልና ፣


ድግልናን ከእናትነት ጋር አስተባብራ የያዘች እመቤታችን ብቻ ናት፡፡ከ እመቤታችን በስተቀር
ይህ የሚደርግለት ማንም የለም፡፡

 እመቤታችን በሠማይም በምድርም ትመሰላለች፡፡

 አንድም ሠማያውያን መላእክት ወደ ምድር እንደመጡ ሰውም ወደ ሰማይ እንዲወጣ


ምክንያት የሆነች እመቤታችን ስለሆነች ነው፡፡

 አንድም በተፈጥሮዋ ከምድራውያን ሰዎች በንፅህናዋ ግን ከመላእክት የምትተካከል


በመሆኗ ሠማይን ምድርንም በእመቤታችን እንመስላለን፡፡
 አንድም ምድር ብችዋን አዳምን እንዳስገኘችው ሁሉ እመቤታችንም ብቻዋን ያለ
ዘርአ ብእሲ ጌታን የወለደች መሆኗን ለመጠየቅ ነው፡፡
 አንድም የሚበላውንና የሚጠጣውን ለእኛ ያዘጋጀች ምድር ስትሆን የመንፈስ ምግብ
የሆነ ክርስቶስን ያስገኘች ደግሞ እመቤታችን ናት፡፡
 ተፈስሂ ኦ ቤቴልሔም ብለን የምናመሰግናት የእንጀራ ቤታችንም ስለሆነች ነው፡፡

፫ እመቤታችን በ ፬ቱ ባሕርያት ትመሠላለች፡፡

እነዚህ አራት ባህርያት ለመሬታዊ ፍጥረት ሥር እና መሠረት ናቸው፡፡ ከእመቤታችን


ለፍጥረት ሁሉ ሥር የሆነው ክርስቶስ ስለተገኘ ነው ይለዋል፡፡
፬ እመቤታችን በዕለተ እሁድም ትመሠላለች፡፡

ዕለተ እሁድ ይህ ዓለም አዲስ ሆኖ የተጀመረባት ዕለት በኃላም አዲሱ ዓለም መንግሰተ ሠማይ
የሚከፍትባት ዕለት ናት፡፡ እመቤታችንም የፍጥረት ሁሉ መጀመርያ አዳም የታደሰባት በኩር
ሆኖ የተጠራባት ክርስቶስም የተገኘባት ስለሆነች ነው በዕለተ እሁድ የምንመስላት፡፡

፭ እመቤታችን በዕለተ ሠኑይ ትመሰላለች

 የእመቤታችን ውዳሴ ሰኞ ተጀምሮ እሁድ ነዉ የሚያበቃው


 ሰኞ ለቀናት ሁለተኛ በመሆኑ እመቤታችንም ሁለተኛዋ ሴት ነች፡
 እሁድ በሐዲስ ኪዳን የመጨረሻ ቀን ነው ለዚህ ነው ቅዱስ ኤፍሬምም ውዳሴዋን
በእሁድ የጨረሰው
 ውዳሴዋም የሚያልቀው በዕድሜዋ ልክ በ64 ክፍል ነው

የዚህ ዓላም መፈፀምያው እሁድ ስለሆነ የእመቤታችንም ውዳሴዋ በዕለተ እሁድ ያልቃል፡፡

በሰኞ የመሰለችበት ምክንያትም ያልተዘጋጀችው ዓለም የተዘጋጀችው በዕለተ ሠኑይ ስለሆነ


ነው፡፡ ጌታም ከእመቤታችን ከተወለደ በኃላ ነው ሃጢያት ያፈረሰውን ዓለም በድጋሜ በደሙ
የሠራው፡፡

ሐዋ 15-17 ‹‹እንደገና እሰራታለሁ›› ብሏል

ዩሐ 14-2 ‹‹በአባቴ ቤት ብዙ መኖርያ አለ… ማረፍያ አዘጋጅላችኃለው….

 በዕለቱ ሰኑይ ምድር ክዳን ያገኘችበት ዕለት ነው፡፡

እንደ ወዝ ከንባይ አድርጎ በላይዋ ላይ ከደነባት እስከዚህ ዕለት ምድር ክዳን አልነበራትም

እመቤታችንም ራቁቱን ከገነት ለተሠደደ አዳም ልብስ ክርስቶስን አስገኘችለት‹‹ በክርስቶስ


የተጠመቃችሁ ሁላችሁ ክርስቶስን ለብሳችሁታል ›› ገላ 3÷27

በዐለተ ሠኑይ ምድር የነበረባትን ሸክም ሁሉ ያራገፈችበት ዕለት ዕለት ነበር፡፡ በዚህ ዕለትም
አንድ ግዜ ሸክሟ ረግፎላት ተገኘ፡፡

ምድር የተባለ የሰው ልጅም የዕዳ፰ ደብዳቤው ተነስቶለት የሃጢያት ሸክሙ ቀሎለት
በእግዚአብሔር ፊት መታየት የጀመረው እመቤታችን ጌታን ካስገኘች በኃላ ነው፡፡

ጉም ከምድር ትወጣ ነበር ምድርንም ታጠጣ ነበር ዘፍ2÷1ለምድር ለራሷ መዳንን


የሚያስገኝላት ተስፋዋ ከራሷ ከምድር የሚወጣ መሆኑን ያሳያል፡፡ይህም በእመቤታችን በኩል
ነው የሆነው፡፡ ጌታም መሬታዊ የሆነው በእመቤታችን በኩል ነው፡፡
፮ እመቤታችን በዕለተ ሠሉስ ትመሰላለች

ለሥጋውያን ምግብ የሆኑ ነገሮች የተገኙት በዕለተ ሠሉስ ነው፡፡ ከእመቤታችንም


የመንፈሳዊያን ሁሉ ምግብ ክርስቶስ ተገኝቷልና ፡፡

በዕለተ ሠሉስ የተገኙት ገበሬ ያልደከመባቸው ዘር ያልቀደማቸው እጽዋት ናቸው የተገኙት ፡፡


ከእመቤታችንም ዘር ያልቀደመው በሦስት ወገን ምግብ የሆነን (በትምህረቱ በተዓምራቱ እና
በመስዋእቱ )የምንመገበው ምግብ ክርስቶስ ስለተገኘ ነው፡፡ በዕለተ ሠሉስም ዘር ፣አታክልት እና
እጽዋት እነዚህ ሦስቱ

 በጎ መዓዛ ያላቸው እጽዋት የተገኙት በዕለተ ሠሉስ ነው፡፡ እመቤታችን መዓዛዋ


ያማረላት የተወደደላት ጽጌ አንቺ ነሽ ብሎ ያመሰገናት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫም ለዚህ
ነው፡፡
 ዳግመኛም የገነትን መዓዛ ያሸተትንና የሕይወት መዓዛ አለን ብለን የተመካነው
በእመቤታችን ነው፡፡
 ስለዚህ እመቤታችንን እለተ ሠሉስ ብለን እንመስላታለን፡፡
 አንድም በዚህ እለት የተገኙ አዝርእት በሁለት መንገድ ይባዛሉ በዘርና እንበለ ዘር

ከእመቤታችን የተወለደው ክርስቶስ ያስገኛቸው ምዕመናንም በሁለት መንገድ ሲበዙ


ይኖራሉ፡፡

 በዘርና
 በግብር

በዕለተ ሠሉስ የተፈጠረውን ምግብ እስካሁን ድረስ እየበላን እና እየለበስን የምንገኘው


ከእመቤታችንም አንድ ጊዜ ተገኝቶ አንድ ጊዜ ተሰዋው ክርስቶስ የዘለዓለም ምግባችን ሆኖ
ይኖራል ፡፡

፯ እመቤታችን በዕለተ ረቡዕ ትመሰላለች

ዕለተ ረቡዕ ሦስቱም ብርሃናት የተፈጠሩበት ዕለት ነው፡፡

ዕለተ ረቡዕ ከእሁድ ጀምሮ ለቆጠረም አራኛ ዕለት ነው፡፡

እመቤታችንም ከአራተኛው ትውልድ ከአይሁድ ነውና የተወለደችው በዚህ እለት ትመሰላለች፡፡

ዕለተ ረቡዕ ከኋላውም ላሉት ከፊትም ላሉት ሦስት ሦሰት ቀናት የብርሃን ምንጭ ሆኗል፡፡
መጀመርያ የተፈጠረላቸው ብርሃንና ጨለማ ሲፈራረቅባቸው በዕለተ ረቡዕ በተሰጠው ብርሃን
መጠቀም ጀምረዋል፡፡ በዛኛው ብርሃን አይጠቀሙም ነበር

እመቤታችንም ከእርሷ በፊት ለነበረው ለብሉይ ኪዳን ሕዝብና ከእርሷ በኋላ ለሚነሳው የሐዲስ
ኪዳን ሕዝብ ብርሃን ክርስቶስን ይዛ ስለተገኘች ነው የተመሰለችው፡፡

ከፊትም ከኋላም ያሉት ቀናት ዕድሜያቸው የሚሰላው በዕለተ ረቡዕ በተፈጠሩት በፀሐይ
፣ጨረቃ እና ከዋክብት ነው፡፡

እመቤታችንም ላለፈውም ለሚመጣውም ትውልድ የዘመን መቁጠሪያ የሆነውን ክረስቶስን ይዛ


ስለተገነች በዕለተ ረቡዕ እንመስላታለን፡፡

ቅዱሳን ዕድሜያቸውን የሚያሰሉት በክርስቶስ (ፀሐይ)ብርሃን ነው፡፡

ራዕይ 12፡1 ‹‹ ፀሐይን የተጎናፀፈች ጨረቃን የተጫማች 12 ክዋክብት በራስዋ ላይ ያሉ….››

ፀሐይ የተጎናፀፈች፡- ክርስቶስን የወለደች

ጨረቃን የተጫማች ፡- ክብሯ ከምዕመናን በላይ የሆነ

12ቱ ከዋክብት በራሷ ላይ ያሉ፡- 12ቱ ሐዋርያት ጌጥ የሆኑላት የሚሰብኳት አንድም 12


ዓመት ያገለገሏት ማለታችን ነው፡፡

፰ እመቤታችን በዕለተ ሐሙስ ትመሰላለች

በዕለተ ሐሙስ የተፈጠሩ ፍጥረታት በልብ የሚሳቡ በእግር የሚሽከረከሩና በክንፍ የሚበሩ
ናቸው፡፡ምሣሌዎቻቸውም በቅደም ተከተሉ መሠረት የሃጥያን ፣የፃድቃንና ፣የመላእክት ነው፡፡

 እመቤታችንም የኃጢያን ተስፋቸው ፣ የጻድቃን ፀጋቸው የመላእክትም እህታቸው


ስለሆነች ነው፡፡

በገነት ወስጥ ያሉ ጻድቃን በአንቺ የደሰታሉ በደይን( በመከራ) ያሉ አንቺን ተስፋ ያደርጋሉ
(አባ ጽጌ ድንግል)

 አንድም በልብ የመሳቡት በዚህ ዓለም የሚኖሩት ምእመናን


 በእግር የሚሽከረከሩት በገዳም የሚኖሩ የመነኮሳት ባህታውያንን በክንፍ የሚበሩት
ደግሞ የሰማዕታት ምሣሌ ዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ሹመትን ያገኙት ጌታ
ከእመቤታችን በመወለዱ ምክንያት ነውና፡፡
 መላእክት እነሆ እህታችን ይላሉ በፀጋ ስለምትመስላቸው አብረው በማደግም እህታቸው
ናትና፡፡(..15›)

፱ እመቤታችን በዕለተ ዓርብ ትመሰላለች

ዕለተ ዓርብ አራት ፍጥረታትን ያስገኘች ዕለት ናት

በዕለቱ የሚበሉም የማይበሉም እንስሳት ተፈጥረዋል

የሚበሉት በእስራኤል የማይበሉት ደግሞ በአህዛብ ተመስለዋል

ከእመቤታችን የተወለደው ጌታ ግን የእስራኤልም የአህዛብም አምላክ ነው፡፡

በዕለተ ዓርብ የፈጠራቸውን የሚበሉም የማይበሉም እንስሳትና አራዊትን በእኩል በረከት ነው


የባረካቸው፡፡
ምዕራፍ አራት
እመቤታችን በሠው ተፈጥሮ

ሀ/ የመጀመርያው ሰው አዳም ከታተመች ከአዲስ ምድር ነው የተገኘው፡፡ ሁለተኛው ሰው


ክርስቶስም ከታተመች ምድር ከእመቤታችን ለመገኘቱ ማሳያ ነው፡፡

ለ/ በስምንተኛው ቀን ከጎኑ ሔዋንን አስገኝቷል ይህም ስምንቱ ብሔረ ኦሪት ሲፈፀሙ ከባህሪው
እመቤታችን ለመገኘቷ ምሳሌ ነበር፡፡

ሐ/ አማናዊቷ ሄዋን እመቤታችን ስለሆነች ነው

ቀድሞዋ ሄዋን ትውልድ እንዲበዛ የተፈጠረች ነበረች የአሁኗ አማናዊቷ ሔዋን ድንግል
ማርያም ግን ትውልድ እንዲባረክ የተፈጠረች ነች፡፡

 እመቤታችንን ለምንድነው አማናዊት ሔዋን የምንላት

ሀ/ ከግብሯ የተነሣ ሔዋን የሚለው ለመጀመርያይቱ ሴት ስለማይነገር፡፡

ምክንያቱም ሔዋን ማለት የህያዋን እናት ማለት ሲሆን እሷ ግን የቃኤል እናት ስለሆነች
በዚያም ላይ ሞትን የተማርነው ከእርሷ ቃል የተነሣ ስለሆነ ነው፡፡

 ሃ/አበው ዘ ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹ የሔዋን ቃል እፀበለስ አሳየን በዚያም እንጨት


ምክንያት ሞት ወደ ዓለም ገባ›› ብሏል፡፡
 እመቤታችን ግን አማናዊት ሔዋን ያልናት የሕይወት ክርስቶስ እናት ስለሆነች ነው፡፡
በዚያም ላይ ከርሷ የተገኘው የአብ ቃል የዘላለም ሕይወትን የሰበልን ስለሆነ ነው፡፡ዮሐ
8፣1
 በእመቤታችን ቃል እጸመስቀል ተገለጠ ፡፡ በዚያም እፀ መስቀል የዘላለም ሕይወት
ተሰበከ፡፡
 ከእመቤታችን የተገኘው ዘር ለሞት የማይመች ዘር ነው፡፡

ለ/ ሔዋን የተገኘችው ከተኛው ካንቀላፋው አዳም ነው፡፡

ኦ.ዘፍ 2÷21 ‹‹ እግዚአብሔርም ከአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ አመጣበት…›

በከባድ እንቅልፍ ውስጥ ከነበረው አዳም ሔዋንን አስገኘ

አስገኚው አዳም በእንቅልፍ ውስጥ ሳለ ሴቲቱ ግን አላንቀላንፋችም ነበር፡፡


አዳም በሞት ጥላ ሥር ሆኖ ሳለ እመቤታችን ከአብራኩ ተገኘች ነገር ግን የነቃች ሔዋን
ከተኛው አዳም ተገኝታለች ፡፡ ይህም በእመቤታችን ለሞት የሚያበቃው አዳማው በደል ፡፡
(ጥንተ አብሶ) ያልተላለፈላት መሆኑን ያስረዳል፡፡(ስላይድ 17 ድረስ)

ሃ/አበው ዘ ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 27ን በተረጎመበት አንቀፁ እንዲህ
ብሏል፡፡

እመቤታችን የተወለደችበት ዘመን የመንቃት የትንሳኤ ዘመን ስለነበር …እርሷ ግን ክርስቶስን


ስታስገኝ ያለማንቀላፋት ነበር ብሏል፡፡

የሔዋን ዕዳ ከፋይ

የሔዋን ዕዳ ምን ነበር?

ወንዱ ያለሴት ሴትን አስገኝቶ ነበርና ሴቲቱ ያለ ወንድ ወንድን ሳታስገኝ 5500 ዘመን ቆይታ
ነበርና እመቤታችን ያለ ወንድ ወንድን በማስገኘት ዕዳዋን ከፈለችላት፡፡

በቀደመው ዘመን ወንዶች በሴቶች ላይ ከእኛ ነው የተገኛችሁት እያሉ ይመኩ ነበር፡፡ በሐዲስ
ኪዳን ግን እመቤታችንም ያለ ወንድ ዘር ወንድን በመውለዷ የደናግል መመኪያ ተሰኝታለች፡፡

ድንግልናዋን በማስመለስ የቀዳሚት ሔዋንን ዕዳ የከፈለች እመቤታችን ነች፡፡

ሔዋን ለመጀመርያ ጊዜ የዓለምን ድንግልና በዲያብሎስ አማካኝነት ያስወሰደች እናት ነበረች፡፡


ድንግል ማርያም ግን በብዙ ነገር ድንግል ሆና ነው የተገኘችው፡፡

በዚህም ምክንያት ነው በ ሉቃ 1፡25 ላይ አንዲት ድንግል ተብላ የተጠራችው ምክንያቱም


ድንግልና በሌለ ዓለም ውስጥ የተገኘች ብቸኛዋ ድንግል እርሷ ስለሆነች ነው፡፡

ቀዳማዊት ሔዋን ድንግልናዋን አጥታ ሞትን ስታስገኝ ዳግሚት ሔዋን ድንግል ማርያም ግን
ድንግልናዋን በመጠበቅ ሕይወትን ለዓለሙ ሁሉ አስገኝታለች፡፡

ድንግልና የሚጀምው ከህሊና ነው፡፡ ከዚያም በነፍስና በሥጋ ድንግል መሆን ይመጣል ማለት
ነው፡፡

በዚህም ምክንያት እመቤታችን ድንግል ማርያም የቀዳሚት ሔዋን ዕዳ ከፋይ ሆናለች፡፡ በዚህም
የተነሳ ሴት ተብላ ተጠርታለች፡፡
እመቤታችን ለምን ሴት ተባለች?

ሴት ማለት ምትክ ማለት ነው፡፡

አዳም በተሰጠው የነቢይነት ጸጋ እርሱን የምትተካ በመሆኗ ነው ሴት ብሎ የሰየማት፡፡

ዳሩ ግን ሴት የሚለው የምትክነት ስም ለቀዳሚት ሔዋን የተገባት አይመስልም ነበር፡፡


ምክንያቱም ሔዋን ከማሕፀን ጀምሮ ሞታቸውን ተሸክመውና ሞታቸውን አረጋግጠው
የሚወለዱ ልጆች ነውና የነበሩዋት፡፡

በዚህ መሰረት ሔዋን ለአዳም ምትክ መሆን አልቻለችም፡፡

እመቤታችን ግን ለአዳም ምትክ በመሆን በትክክልም ሴት ለመባል በቅታለች፡፡ ያለ ወንድ


ወንድን ያስገኘች ብቸኛ ሴት እርሷ ነችና፡፡ በዚህም ምክንያት የቀደመው ፍጥረት ከአዳም
የሚጀምር ሲሆን አዲሱ ፍጥረት ግን ከእመቤታችን ይጀምራል፡፡ ምክንያቱም አዲሱ አዲሱ
ሰው ክርስቶስ የተገኘው ከእመቤታችን ነውና፡፡ ሃ/አበው ምዕራፍ 66፡28-29

ዘፍ 3 ‹‹ በአንተና በሴቲቱ መካከል በዘርህና በዘሯ መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ›› ብሎት


ነበር፡፡

ሴቲቱ ተብላ የተጠራችው እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፡፡ ምክንያቱም በዘሯና በርሷ
መካከል ከዲያብሎስ ጋር ጠላትነት የተደረገ ስለሆነ ነው፡፡

ራዕይ 12፡1-6 ‹‹ ከዘሯ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፡፡›› ይህ ጠላትነት የተደረገው በእመቤታችን ዘመን
ነው እንጂ በሔዋን ዘመን አልነበረም፡፡

መዝ 73፡12 ‹‹የእባቡን እራስ አንተ ቀጠቀጥኸው››

ቆላ 2፡1 ‹‹ በመስቀል የእባቡን እራስ ቀጠቀጥኸው››

እባብም በአይሁድ አደረና የክርስቶስ ሰኮናውን በምስማር በመስቀል ላይ አስቸነከረው፡፡ በዚህም


የተነሳ በርሷ ዘር በሆነው በክርስቶስና በዲያብሎስ መሀከል ጠላትነቱ እንደቀጠለ ነው፡፡

የሔዋን ዘርማ ከዲያብሎስ ጋር ምንም ጠላትንት አልነበረውም፡፡ እንዲያውም እርሷ


የወለደችው በዲያብሎስ ተግባር ተሣታፊ የሆነ ቃኤልን ነበር፡፡
የመጀመሪያው ትውልድ ሞትን የተማረበት ፊደል ሔዋን ነበረች፡፡ አማናዊቷ ፊደል
እመቤታችን ግን ወንጌል ክርስቶስ የተጻፈባት ፊደል ነች፡፡

 ‹‹ፊደል ትመስያለሽ ወንጌልንም ትወልጃለሽ›› አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንደገለጸው፡፡


 እመቤታችን ወንጌል የተጻፈባት የሕይወት ፊደል ናትና ወንጌል በተሰበከበት ቦታ ሁሉ
ስሟን እንጠራለን፡፡
ምዕራፍ አምስት

እመቤታችን በቅዱስ ወንጌል


እመቤታችን በቅዱስ ወንጌል በተለያየ ቦታ ብትገለጽም ራሱን የቻለ በስሟ የተጻፈ ወንጌል ግን
የለም፡፡

 በእመቤታችን የሚጀምር ምዕራፍ በወንጌል ለምን አልኖረም?

ሀ) በወቅቱ እንደ አርጤምስ ያሉ ታላላቅ የሴት አማልክት ስለነበሩና ትላልቅ ቤተ መቅደስ


ተገንብቶ ይመለኩ ስለነበር። ከነዚያ ጣኦት ጋር አገናኝቶ እንዳያመልኩ ሕዝቡም በዚህ
እንዳይሰናከሉ ነበር።

ለ) የክርስቶስ የባሕሪ አምላክነት ከአይሁድ ጀምሮ እስከ አህዛብ ድረስ ሕዝቡ ያልተቀበለበት
ጊዜ ስለነበር ነው።

በቅዱስ ወንጌል ሐዋርያት እመቤታችንን ማን ብለዋታል?

1. የንጉስ እናት ብለዋታል።

 ማቴ 2፥2 “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት አለ”


 ይህን ማለታቸው ልጇን ንጉሥ ሲሉ እርሷን ደግሞ የንጉሥ እናት ማለታቸው ነው።
 ት.ሚክ 5፥2 “ከአንቺ ንጉስ ይወጣል ወገኔ እስራኤልን የሚጠብቃቸው”….ተብሎ
ተጽፏል…..

2. የነቢያት የትንቢታቸው ፍጻሜ ብለዋታል።

 በማቴዎስ ወንጌል ብቻ ከ40 በላይ ትንቢቶች ተፅፈው እናገኛለን።


 ጌታ ከእመቤታችን በመወለዱ ምክንያት ነው የነብያት ትንቢታችው ፍፃሜ ያገኘው።

3. በነገረ ድኅነት ላይ ከፍጡራን ሁሉ ተለይታ ተሳትፎ ያላት ናት ብለዋታል።

 ዮሐ 2፥1-11 “በዶኪማስ ሠርግ ቤት የነበረው ታሪክ ለዚህ ማሳያ ይሆናል”


 በዚያ ሠርግ ቤት ከእመቤታችን በቀር የተናገረ ማንም የለም። ሐዋርያትም ፣ የሠርጉ
ቤተሠብም የወይን ጠጁ እንዳለቀ እያወቁ ዝም ነበር ያሉት።
 የወይን ጠጁ እንዳለቀ ለእመቤታችን የነገራት እንኳን እንዳች የለም። እርሷ ግን ወደ
ልጇ ቀርባ የወይን ጠጅ የላቸውም አለችው። እርሱም ሲመልስላት “ጊዜዬ ገና
አልደረሰም” አላት። ፈቃዴ ገና ነው ሲላት ነው። ነገረ ድኅነቱን የሚፈጽምበት።
 ሠርገኞቹ የወይን ጠጁ ማለቁን ለእርሷ እንኳ ያለመንገራቸው። አምላክን ውለጅልን
ብለው እመቤታችንን የተማጸናት እንደሌለ ለማጠየቅ ነው።
 የሠርጉ ቤት የዚህ አለም ምሳሌ ነበር።
 6ቱ የድንጋይ ጋኖች ጌታ ሠው የሆነበት የስድስተኛው ሺህ ክ/ዘመን ምሣሌ ነው።
 ጋኖቹ የድንጋይ የሆኑት፡ ሰው ሁሉ እንደ ድንጋይ ፈዞ የነበረበት ዘመን ስለነበር ነው።
እነዚህ የድንጋይ ሦስት ጋኖች ሦስት ሦስት ሁለቱ ጋኖች ድግሞ ሁለት ሁለት
መስፈርያ ይችሉ ነበር።
3*2=6
3*3=9
6+9=15
 በ10 ቃላት እየተመሩ 5ቱ የመስዋዕት እይነቶች ሲያቅርቡ መኖራቸውን ለማስረዳት
ነው።
 2 እና 3 በጋራ 5 ናቸው። የ5500 ዘመን ምሣሌ
 በሠርግ ቤት የነበሩ ታዳሚዎች ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የነበረው የሕዝብ ምሳሌዎች
ናቸው።
 ያለቀው የወይን ጠጅ የዓመተ ፍዳ የዓመተ ኩነኔ ምሣሌ ነው።
 ያለቀውን የወይን ጠጅ ያዘጋጁት ሠዎች እንደነበሩ ሁሉ ዘመኑንም ዓመተ ፍዳ ዓመተ
ኩነኔ ያሰኘው የሠዉ ሥራ ነው።
 ውሃ የቀዱ አገልጋዮች የነቢያት ምሳሌ ነበሩ። “የሚላችሁን አድርጉ”
 ውሃው የትንቢታቸው ምሣሌ ነው።
 አዲሱ የወይን ጠጅ የዓመተ ምህረት ምሳሌ ነው።
 ይህ የወይን ጠጅ በአምላክ እንጂ በሰው እጅ እንዳልተሠራ ዘመኑንም ዓመተ ምህረት
ያሰኘው የአምላክ ሰው መሆን እንጂ የሰው ሥራ አይደለም።
 ዓመተ ምህረትም የነቢያት የትንቢታቸው ውጤት ነው።
 ክርስቶስም ሳይቀር የነቢያት የትንቢታቸው ውጤት ነው። “አምላክ ይወርዳል ይወለዳል፣
ከድንግል ይወለዳል አሉት፣ በቤተልሔም ይወለዳል አሉት፣ ይሞታል ይደማል አሉት”
ጌታም ሁሉንም ፈጸመላቸው።
 ነቢያት ለዘመናት የማይጣፍጠውን ውሃ ሲቀዱ ነበር ጌታ ግን በሠርጉ ቤት ተገኝቶ
ውሃቸውን አጣፈጠው።
 ጊዜዬ ገና አልደረሰም፡ ያለበት በጋኑ ውስጥ ትንሽ ጭላጭ ነበርና ያ ጭላጭ
እስኪሟጠጥ ነው። ምክንያቱም እንደ ኤልያስ የነበረውን ባረከ እንዳይሉት።
 ጭላጭ የተባለው የዓመተ ፍዳ ሊያበቃ የቀረው 15 ዓመት ብቻ ስለነበር ነው።
 እመቤታችን እናት በመሆን (ለተሠቀለውና ለሞተው (ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ
ለተወለደው ስለኛ ለተሰቀለው በስጋ ለሞተው በሶስተኛውም ቀን ከሙታንም ለተነሳው
ላረገው.. ክርስቶስ እናት (መገኛ) በመሆን በነገረ ድኅነት ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ/ድርሻ
አላት።
4. የመድኃኒት እናት ብለዋታል

 ማቴ 1፥21 “ልጅም ትወልዳለች ሕዝቡንም ከኃጥያታቸው ያድናቸዋል”

መድኃኒት የተባለው “ከኃጥያታቸው ያድናቸዋል” የሚለው ቃል ነው።

ለዚህ ነው ትውልዱ በሙሉ እመቤታችንን “ቤዛዊተ ኩሉ “ ብለን የምንጠራት “ቤዛዊተ ዓለም


ብለናታል።

5. የዕርቅ ሰነድ ብለዋታል

 ማቴ. 1፥23 “እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል


ትለዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው።”
 ለ5500 ዘመን ሰውና እግዚአብሔር የተለያዩበት ጥል በዘፍ. 6፥3 ላይ በተነገረው ቃል
ነበር የተጀመረው።
 እርሷ ግን አማኑኤል ክርስቶስን ወልዳ አስታረቀችን።
 ማቴ 3፥13 በጥል ምክንያት ከሰው ርቆ የነበረው የእግዚአብሔር መንፈስ ዳግመኛ
በእመቤታችን አማካኝነት በርግብ አምሳል የእግዚአብሔር መንፈስ ተመለሰ።
 እመቤታችን ሰውና እግዚአብሔር የታረቁባት እንዲሁም የእርቅ ሠነድ የተፈራረሙባት
የዕርቅ ሠነድ ነች።
 ዕርቁ በዚህ አላቆመም
 ሉቃ 2፥8 “መላእክትና ሰው በጋራ የተወለደውን ማመስገን ጀመሩ።” ዕርቁም ያኔ ዓለም
አቀፋዊ ሆነ።
 እረኞቹን መላእክት መዝሙር አስጠንተዋቸው በጋራ ወደ ጌታ ሄደው “ስብሐት
ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰበዕ”ብለው አመሰገኑት ታድያ
መላእክት ይህን መዝሙር ለእረኞቹ ባያስጠኑ ኑሮ እነዛ እረኞች እንዴት ይሄን
መዝሙር ያውቁ ነበር ?
 ይህም የሚያሳየው ሠማይና ምድር በጌታ ልደት መታረቃቸውን ነው።
 ማቴ. 2፥2 ሰብዓ ሰገል መምጣታቸው በጌታ ልደት ህዝብና አህዛብ እንኳ ሳይቀር
መታረቃቸውን የሚያስረዳ ነው። ምክንያቱም ሰብዓ ሰገል ከአሕዛብ መሳፍንት ወገን
ነበሩና።
 እመቤታችን የዕርቅ ሠነድ ሆና በመቅረብ አስቀድሞ ምንም ዋጋ ያወጣ ያልነበረ የሰው
ልጅ ወላዲተ አምላክ ባስገኘችው ፍሬ ግን የሠው ልጅ ከበረ። ምንም እንኳ ዓላማው
መልካም ባይሆንም የሠው ልጅ ዋጋ ማውጣት የጀመረው ጌታ በ30 ብር ከተሸጠ በኋላ
ነው።

እመቤታችን በሉቃስ ወንጌል

 የሉቃስ ወንጌል አጀማመሩ በራሱ የሚያስገርም ነው። በመካኒቱ ቤት ታሪክ ይጀምርና


በድንግሊቱ ሴት ታሪክ ይጨርሰዋል።
 የመካኒቱ ሴት ምሳሌ ዓለም እስከ ክርስቶስ ልጅነት ድረስ የዘንዶውን ራስ
የሚቀጠቅጡበት ወንድ ልጅ አጥታ መቆየቷን ለማጠየቅ ነው።
 ሉቃ. 1፥25 መካኒቱ ሴት በመምከኗ ምክንያት አምስት ወር ያህል ራሷን ሸፈነች። ይህ
የሚያሳየው ለ5500 ዘመን ያህል እግዚአብሔር ያልጎበኛት ዓለም መሆንዋን የሚያሳይ
ነው።
 ከዚህ በኋላ ግን በስድስተኛው ወር የጌታ መላዓክ ወደ ሴቲቱ መጣ። ይህም ማለት
በስድስተኛው ሺህ የዓለማችን የመጎብኘት ዘመን መምጣቱን ያሳያል።
 የሉቃ 1፥26 ሲተረጎም
1. ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ
 ቀድሞ ወደሰው የተላከው መልዕክተኛ ከሰይጣን ነበር።
 አሁን ወደ ሠው ልጅ የመጣው ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ ነው።
2. ወደ ናዝሬት ወደ ገሊላ
 ይህ ከተማ የተናቀ የማይጠበቅ ከተማ ነበር።
 ሃገሪቱ ደግ ሰው ይወጣባታል ተብሎ የማይጠበቅባት የወንበዴዎች ከተማ
ነበረች።
 ዮሐ 1 “በውኑ ከናዝሬት መልካም ሰው ይወጣልን?”
 ናዝሬት የወንበዴዎች የቀጥቃጮች ከተማ ነበረች።
 ሌሎች የተሻሉ ከተሞች እያሉ እነ እየሩሳሌም እያሉ
 ኃጥያት ከበዛበት ከተማ ነበር ጌታ ሊወለድ የሻተው
 የጌታ ነገር የሚደንቀው በወንበዴዎች ከተማ ተወለደ ሲሞትም በወንበዴዎች
መካከል ተሰቅሎ ሞተ
 እርሱ ከወንበዴዎች መካከል ተቆጥሮ እኛን ከቅዱሳን መላእክት መካከል
እንድንቆጠር አደረገን ከ99ኙ ነገድ
 ብዙዎችም ራሳቸውን እየነቀነቁ ወንበዴ ነበር ለካ አሉ።
3. ወደ አንዲት ድንግል
 አሁን የዓለም ታሪክ ከመካንነት ወደ ድንግል ተቀየረ
 በመካኒቱ ዓለም የነበረች ብቸኛ ድንግል ስለነበረች ነው። “አሃቲ ድንግል” ብሎ
የገለፃት።
 ዓለም በሔዋን በኩል የተነጠቀችውን ድንግልና በእመቤታችን በኩል አስመለሰች።
 የሔዋን ድንግልና በህሊናዋ (በክፉ ምኞቷ) ጠፋ። የህሊና ድንግልና ደግሞ
የነፍስ ድንግልናን ያስከትላል።
 እመቤታችን ግን በህሊናም በነፍስም በሥጋም ድንግል ሆና ስለተገኘች ከርሷም
በቀር ሌላ ድንግል አይገኝምና አንዲት ድንግል አላት።
4. እናት ትሆኛለሽ አላት
 እናት ሆና ድንግል፣ ድንግል ሆና እናት ለእርሷ ብቻ የተሰጠ ፀጋ ነው።
 ሐ/አበው ዘቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ “የሃይማኖታችን መሪ” ብሏታል።
 እርሷ እናትነትን ከድንግልና አስተባብራ እንደያዘች ሁሉ የሃይማኖታችን መሪ
ልጇም አምላክነትን ከሰው አስተባብሮ የያዘ መሆኑን ሲያጠይቅ ነው።
 ለዘላለም ድንግል ሆኖ መኖር ከርሷ በስተቀር ከቶስ ለማን ይቻላል?
 የ431 ዓ.ም ጉባኤ “እግዝትነ ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ” ተብላ
እንድትጠራ በኤፌሶን በቅ/ቄርሎስ መሪነት የተመራው የቤ/ክ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ
ወስኗል።
 አንጢዲቆማርጦሳውያን የተሰኙ መናፍቃን እመቤታችን ከጌታ በኋላ ሌሎች
ልጆች ወልዳለች ብለው ያስተምራሉ። እንጂ ይህ አስተምህሮ የማርቲን ሉተር
አደለም።
 አንጢዲቆማርጦስ ማለት ፀረማርያም ማለት ነው (በመዝገበ ቃል)
5. ለዮሴፍ ወደ ታጨች
 እመቤታችን ለዮሴፍ መታጨቷ ለሞተችው ለእናታቸው ፈንታ ሆና ለዮሴፍ
እንድትሰጥ የጌታ ፍቃድ ስለነበረ ነው።
 ያኔ የ ዮሴፍ ልጆች ያለእናት የነበሩበት ጊዜ ነበርና ምክንያቱም አረጋዊው ዮሴፍ
ሚስቱ ሞታ ነበርና
 እመቤታችንም እናትነትን የጀመረችው በዮሴፍ ቤት ነበር።
 እናቱ ሔዋንን በሞት ላጣው ዓለም እናት ሆና እስክትሰጥ ድረስ እናትነቷ
በዮሴፍ ቤት ይጀምራል።
 ዮሐ 19፥27 “እንኋት እናትህ” ብሎ እስኪሰጥ ድረስ በዮሴፍ ቤት ነበረች።
 እናታቸውን በሞት የወሰደባቸው እግዚአብሔር ለዮሴፍ ልጆች ከቤተ መቅደስ
እናት ሰጣቸው። ይህችም እናት ለሌላው አለም በእግዚአብሔር ቅድስና ውስጥ
ተጠብቃ የምትኖር ቅድስት እናት ያዘጋጀለት መሆኑን ለመግለጥ ነበር።
ስለዚህም ከቤተ መቅደስ ወጣች።
 መታጨቷ የሠው ልጆች ባሕሪ ተዋሕዶ የሚታጭበት ጊዜ መድረሱን የሚናገር
ምሥጢር ነው።
 መታጨት በቅ/ወንጌል የተፃፈላት ሴት እመቤታችን ብቻ ናት። እግዚአብሔር
ቤተ መቅደስን የሚያጭበት ጊዜ እንደደረሰ ተናገረ። 1ቆሮ 11
 የጥታጨችው ከዳዊት ወገን ለሆነ ሰው ነው። ይህም ክርስቶስ ከዳዊት ወገን ሆኖ
ተወልዶ ቤ/ክንን ማጨቱን ለማሳየት ነው።
6. መልዓኩም ወደ እርሷ ገባ
 በትህትና እርሷን መስሎ መቅረቡን ለማጠየቅ ነው።
 ወደ ዘካርያስ ሲመጣ መልዐኩም ወደ እርሱ ገባ አይልም። በመሰዊያው ቀኝ
ቆሞ ታየው ተብሎ ተፃፈ እንጂ።
 መልዐክ ወደ እርሷ ገባ ተብሎ የተነገረውና የሚነገረው ለእመቤታችን ብቻ
ነው።
 ደስ እያለው ስለነበር መልዐኩ የመጣው ገና ከሩቅ ሲመጣ ክንፉን እያማታ
በሚያስደነግጥ ግርማ ነበር። እመቤታችንን ያስደነገጣት ግን ግርማው ሳይሆን
ፈፅሞ ያልጠበቀችው ቃሉ ነው።
7. ደስ ይበልሽ አላት
 ይህ ቃል የወንጌል የመጀመርያው ቃል ነው። ሉቃ 1፥23
 የመጀመርያው ለሴቲቱ የደረሳት አስጨናቂ ቃል በፀነሽ ጊዜ ጭንቀትሽን
አበዛዋለሁ አላት ለሔዋን። ዘፍ 3፥6
 ዓመተ ፍዳ የተጀመረው ሔዋን ይህን ቃል ስጸማ ነው፣
 ዓመተ ምህረት የተጀመረው ደግሞ እመቤታችን ደስ ይበልሽ የሚለውን ቃል
ስትሰማ ነው
 የመላእክት ሐዋርያ የተባለ ቅዱስ ገብርኤል ለመጀመርያ ጊዜ መላእክትን ሁሉ
ወክሎ ይህን የምስራች ወንጌል ለእመቤታችን እና ለዓለም ሰበከ።
 ሔዋንም በብሉይ ኪዳን የነበሩትን ሁሉ ወክላ የመጀመርያውን የሞትና
የጭንቀት ቃል ሰማች።
 እመቤታችን ደግሞ ቤ/ክንን ሁሉ ወክላ ይህን የምስራች ቃለ ወንጌልን ሰማች።
8. ፀጋን የተመላሽ ሆይ (ኦ ምልዕተ ፀጋ)
 ፀጋ ለሰው ልጆች የሚሰጥበት ጊዜ መድረሱን ያጠየቀ ነበር አነጋገሩ።
 ፀጋ ያለብሽ ሳይሆን ያላት ፀጋ የሞላብሽ ሆይ ነው ያላት።
 ሠው ሁሉ አንዳንድ ፀጋ ያለው ነው። እርሷን ግን ፀጋ የሞላብሽ ነው ያላት።
 በቅዳሴያችን “ተውቦ ምህረት ለሚካኤል ወብስራት ለገብርኤል፣ ወሀብተ
ሰማያት ለማርያም ድንግል።” የመባሉ ምሥጢር ለሚካኤልና ለገብርኤል
የተሰጣቸውን አንዳንድ ፀጋና ሀብት እንዳለ ያሳያል ወሀብተ ሰማያት ለማርያም
ድንግል ሲል ግን በምን ፀጋ እንወስንሽ ሲሉ የአንቺ ፀጋ (ሀብት) ሠማያዊ
ነው እንላታለን።
9. እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው
 ከጥንትም ጀምሮ እግዚአብሔር ያልተለያትና ያልተቀየማት ንፁህ ዘር መሆኗን
ሲያጠይቅ ነው
 በእርግጥ እንዲህ የተባሉ በመጽሀፍ ነበሩ የእርሷ የሚለይ ነው
10. በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻል
 እመቤታችን ከሰው ተለይቶ የተሰጣት ሦስት ሀብታት አሏት እነርሱም
ሀ) ባለሟልነት ፦ በሥላሴ ዘንድ
ለ) መወደድ፦ በሠው ልጅና በመላእክት
ሐ) መፈራት፦ በአይሁድና በአጋንንት
 አዳም ከኮበለለ በኋላ የመጀመርያይቱ ባለሟል መሆኗ የተነገረላት እመቤታችን
ድንግል ማርያም ነች።
11. አትፍሪ
 ለጊዜው መልዐክ ፍርሃትን አርቆ መናገር ልማዱ ስለሆነ ነው። ዘካርያስንም
ዳንኤልንም አትፍሩ ብሏቸውል።
 ፍፃሜው ግን የሞት ፍርሃት ከሰው ልጆች የሚርቅበት ጊዜ መድረሱን ለመግለፅ
ነው።
12. ይህ እንዴት ያለ ሠላምታ ነው ብላ አሰበች
 እንድትደነግጥ ያደረጋት ሰላምታው ነው።
 ከሔዋን ልዩ ያደረጋት ውዳሴ ከንቱን አለመሻቷ ነው።
 ከሴቶች ሁሉ ልዩ የተባለችውም ለዚሁ ነው።
 የተሽጎደጎደውን ሰላምታ ያለመፈለጓ ምስጢርም ቅድስናዋን ነው የሚያሳየው።
13. ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ
 የእባቡን (የዘንዶውን) ራስ የሚቀጠቅጥ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ ሲል ነው።
 በግብፅ ፈርኦን ቤት ከእስራኤል የተወለደ ወንድ ልጅ ይገደል ብሎ ዲያብሎስ
አሳወጀ ምክንያቱም አንድ ቀን ያ ወንድ ልጅ ተወልዶ ራስ ራሱን
እንደሚቀጠቅጠው ያስብ ነበርና።
 ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ “ ወንድ ልጅ የበጎ ነገር ተምሣሌት ነው።” ይለዋል። (ኦ.ዘፀ
ምዕ 3) በተረጎመበት

እመቤታችን ጥንተ አብሶ አለባትን

 ጥንተ አብሦ ፦ ቀጥታ ትርጉሙ የበደል መነሻ ማለት ነው።


 ጥንተ በደል ተብሎም ሊተረጎም ይችላል።
 ጥንተ አብሦ አዳምና ሔዋን በለስን በልተው ለሰሩት በደል ብቻ የተሰጠ ስያሜ ነው።
የጥንተ አብሦ በደል ለሌሎች በደሎች ሁሉ መሰረት ሆኗል።
 እግዚአብሔር ሠው እንዲሆን ምክንያት የነበሩት የበደል አይነቶች ሁለት ናቸው።
እነርሱም፦
1. ጥንተ አብሶ
2. ምልዓተ ኃጥያት
 ምልዐተ ኃጥያት ፦ ይህ ኃጥያት ከጥንት የሰው ፍጥረት ከአዳም ጀምሮ የተነሣው
ትውልድ በሙሉ እየተቀባበለ የሰራው ኃጥያት ነው።
 ምልዐተ ኃጥያት፡- ኃጥያትን ወደ ፍጹምነት ያደረሰ ኃጥያት ነው።
 በጥንተ አብሦ ያገኘነው ፍሬ ሞት ነው። ሮሜ 8
 በበደል (በአዳም በኩል በሆነ በደል) ምክንያት ሞት ወደ ዓለም መጥቷል። በጽድቅ
(በክርስቶስ በኩል በሆነ ጽድቅ) ምክንያት ደግሞ ሕይወት ወደ ዓለም መጥቷል። (ሮሜ
5) በዚህም ምክንያት ዓለሙ ሁሉ በአንዱ የክርስቶስ ጽድቅ ድኗል ለ5500 ዘመን የነበረ
ባርነት ተወግዷል።

የጥንተ አብሶ ባሕሪ ምንድነው


 ከማህፀን ጀምሮ በደም በኩል የሚተላለፍ የኃጥያት ውርስ ነው ።
 ይህ የጥንተ አብሦ ባህሪ ከአዳም ጀምሮ የነበረ ሲሆን ነገርግን በዚያ ሁሉ ጊዜ ውስጥ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያለጥንተ አብሶ የኖረች ቅድስት ናት። ት.ኢሳ 1፥9
“.... ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ...”እንዲል
 ወርቅን በጭቃ ላይ ብንጥለው ከጭቃው ላይ ምንም አንድነት ተሳትፎ የሌለው ሆኖ
እናገኘዋለን። እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ንፅህተ ንፁሃን ወላዲተ አምላክ ድንግል
ማርያምም ከሠው በአዳም ባሕሪ ውስጥ ብትኖርም በመንፈስ ቅዱስ ተጠብቃ የኖረች
ናት።
እመቤታችን ያለ ጥንተ አብሶ እንዴት ኖረች
1. በመንፈስ ቅዱስ ጥበቃ!

ይህ እንዴት ሆነ ቢሉ?

እግዚአብሔር ገነትን በቅዱሳን መላእክት ማስጠበቁ ይታወቃል (ዘፍ. 3፥4)

ገነት የተጠበቀችው ለምን ነው? ቢሉ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገነት መውጣቱ ይታወቃል።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ አዳም በገነት ቆይቶ ቢሆን ኖሮ ዕፀ ሕይወትን በልቶ ባልሞተና ከክብሩ
ባልተለየ ነበር። ነገርግን አዳም በድሏልና ቅጣትም እንዲገባው እግዚአብሔር ብሏልና ።
ወደገነት ተመልሶ ዕፀ ሕይወትን እንዳይበላ ገነት በምትገለባበጥ ሰይፍ መታጠርና መጠበቅ
ለዚህ ነው ይላል።

ዕፀ ሕይወት ምንድነው ?

በገነት ውስጥ ሦስት አይነት ምግቦች(ተክሎች) ነበሩ።

ሀ) ዕፀ በለስ:- መልካሙን እና ክፉውን የምታሳውቅ

ለ) ዕፀ ምግብ:- አዳምና ሔዋን እንዲበሉ የተፈቀደላቸው

ሐ) ዕፀ ሕይወት:- አዲስን ሕይወት የምታሰጥ አዳም ሳይበድል በገነት ቆይቶ ቢሆን ኖሮ 1000
(አንድ ሺ) ያህል ዓመት ከቆየ በኋላ ዕፀ ሕይወትን በልቶ ዳግመኛ ልጅ ሆኖ የኖረበት የነበረ
ምግብ ነው።

 ለዚህም ነው ዕፀ ሕይወት (ዕፀ ምግብ ) የተባለችው አዲስ የሆነ ሕይወትን የምታሰጥ


ስለሆነች በዕፀ ሕይወት ሞት የሚባል ነገር የለም። ስለዚህም ነዉ አዳም ከዚህች ዕፀ
ሕይወት በልቶ እንዲኖር እግዚአብሔር የከለከለውና ገነትንም ያስጠበቃት።
 እንግዲያውስ ገነት መጠበቋ እና መታጠሯ የዕፀ ሕይወት መገኛ ስለሆነች ነው። በገነት
የተመሠለች እምቤታችን በመንፈስ ቅዱስ ጥበቃ ብትጠበቅ ምን ያስደንቃል?
ምክንያቱም በገነት የነበረ ዕፀ ሕይወት ሕይወትን እንደሚሰጥ ሁሉ ከእመቤታችን
የተወለደው ዕፀ ሕይወት የሆነ ክርስቶስም የዘላለም ሕይወትን የሠጠ ነው።
 እውነተኛዋ የሕይወት ዛፍ ክርስቶስ የተገኘባት እመቤታችንማ እንዴት ከገነት አብልጦ
አይጠብቃትም ። አዳም ከይቅርታ በኋላ የሕይወት ዛፍን ያገኘው በማህፀነ ማርያም
ነው። ይህ የሚያስረዳው አዳም ከበደለበት ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር እመቤታችንን
ማስጠበቁ ነው።
 እግዚአብሔር ገነትን ለምንድነው ያላጠፋት? አዳም ሲበድል ገነትንም ለምን አብሮ
አላጠፋትም? እንኪያስ ገነት የሕይወት ዛፍ መብቀያ ስፍራ በመሆኗ ተጠብቃ
እንድትኖር እንጂ እንድትጠፋ እግዚአብሔር ፈቃዱ አይደለም (አልነበረም)። በደለኞቹ
አዳምና ሔዋንን አስወጣቸው እንጂ። የምትገለባበጥ ሰይፍ የተባለውም የመንፈስ
ቅዱስን ሥልጣን ለማሳየት ሲሆን መንፈስ ቅዱስ በጥበቃው እመቤታችንን አጥሯትና
ከልሏት መኖሩን ለማጠየቅ ነው።

2. ምሣሌ አበው ይፈፀም ዘንድ

 "ወደዚህ አትቅረብ አንተ የቆምህባት ሥፍራ የተቀደሰች መሬት ናት።" (ኦ.ዘፀ 3፥5)
 ለሙሴ የተገለጠችው ይህች ምድር (መሬት) የእመቤታችን ምሣሌ ናት ይህች ምድርም
በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠች ምድር ናት።
 ከተረገመች ምድር መሀከል ሙሴ ጫማህን ከእግርህ አውልቅ የተባለላት ቅድስት ቦታ
(ምድር) መገኘት ከቻለች። ዕፀ በለስን በልታ ሞትንና ኃጢያትን ለማስተዋወቅ
ከተረገመችው ሔዋንም (ቀዳሚት ሔዋን) የተቀደሰችዋና የሔዋን ርግማን ወይም ጥንተ
አብሶ የማያውቃት ንጽህት ዘር እመቤታችን (ዳግሚት ሔዋን) መገኘቷ ለተቀደሰችው
ምድር ምሣሌ ናት።
 ይህች ቅድስትና ንጽህት ምድር እመቤታችንም የልቦናችንን የኃጥያት ጫማ አውልቀን
ወደ እርሷ ብንቀርብና አማልጂን ልንላት የምትገባ እናት ሆና በቀራንዮ በእግረ መስቀሉ
ሥር በፀጋ የተሰጠችን እመቤት ናት።
 ቅዱስ ቄርሎስ:- ሐመልማሉ ከነበልባሉ ሳይለወጥ ...
 ሐመልማሉና ነበልባሉ :- የመለኮትና የሰው ምሣሌ ነው።
 ቅድስት ምድር:- ደግሞ የእመቤታችን ምሣሌ ናት ፣ አማናዊ ሙሴ እየሱስ ክርስቶስም
የነገረ ድህነት አገልግሎቱን የጀመረው ገና በማዕዘነ ማርያም ሣለ ነው።
3. እግዚአብሔር በመልዓኩ አድሮ ባናገራት ቃል

ሀ) ከሴቶች ይልቅ አንቺ ብሩክት ነሽ የማህፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።

አብርሃም እንኳ "እባርክሃለሁ" አለው እንጂ አንተ የተባረክህ ነህ አላለውም። ነገርግን የመባረክ
ተስፋ ግን አሳይቶታል። አልፎ ተርፎም "በዘርህ አህዛብ ሁሉ ይባረካሉ" በብሎታል።
እመቤታችንን ግን ከፍጥረት ሁሉ ለይቶ እንደመረጣት የምንረዳው "አንቺ የተባረክሽ ነሽ" ነው
ያላት። አብርሃምን ስለመባረኩ ኦ.ዘ.ፍ 12፥2 እመቤታችን ብሩክ ስለመሆኗ ሉቃ 1፥26-40
መንፈስ ቅዱስ ገና ወደ እመቤታችን ሳይመጣ እርሷ የተባረከች ናት።

ለ) ፀጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ።

እመቤታችን ጌታችንን ሳትፀንስም ከፀጋው አልጎደለችም። የሚገርመው ነገር ፀጋ "የሞላብሽ


ሆይ" ነው የተባለችው ይህም የሚያሳየው እመቤታችን አስቀድማም በእግዚአብሔር ሕሊና
ትታሰብ የነበረች መሆኗን ነው። ድንግል ሆና ፀንሣ መገኘቷ ለዚህ ማረጋገጫው ነው።

…..ይቆየን….

You might also like