You are on page 1of 31

የትምህርት ቤቶች አጋርነትና ትብብር ሞዴል የአሰራር ማኑዋል

(የመጀመሪያ ረቂቅ)

ጥር/2014 ዓ.ም;u
ማውጫ
ክፍል አንድ.....................................................................................................................................................3
1.1. መግቢያ.....................................................................................................................................3
1.2. የአጋርነትና የትብብር ሞዴል ማስፈፀሚያ ሰነድ አላማ.....................................................................4
1.2.1. ዋና አላማ...........................................................................................................................4
1.2.2. ዝርዝር አላማዎች...............................................................................................................4
1.3. የትምህርት ቤቶች የአጋርነትና ትብብር ሞዴል ምንነት.....................................................................4
1.4. የአጋርነትና የትብብር ሞዴል አስፈላጊነት.......................................................................................6
1.5. የትምህርት ቤቶች የአጋርናትና ትብብር የሚያስገኘው ጠቀሜታ.....................................................8
1.5.1. ለተማሪዎች.......................................................................................................................8
1.5.2. ለትምህርት ቤቶች...............................................................................................................8
1.5.3. ለመምህራን........................................................................................................................9
1.5.4. ለአጋር ድርጅቶች................................................................................................................9
1.5.5. ለወላጆች.........................................................................................................................10
1.6. የአጋርነትና ትብብር ሞዴል ታሳቢ ያደረጋቸው ጉዳዮች..................................................................10
1.7. የትምህርት ቤቶች አጋርነትና ትብብር ሞዴል መርሆች...................................................................11
1.8. የትምህርት ቤቶች አጋርነትና ትብብር ሞዴል የተፈፃሚነት ወሰን.....................................................11
ክፍል ሁለት..................................................................................................................................................13
2. የትምህርት ቤቶች አጋርነትና ትብብር ሞዴል ግቦች እና የአተገባበር ስልቶች..............................................13
2.1. የትምህርት ቤቶች የአጋርነትና ትብብር ሞዴል ግቦች......................................................................13
2.2. የትምህርት ቤቶች የአጋርነት እና ትብብር ሞዴል አተገበባር ስልት....................................................13
ክፍል ሶስት...................................................................................................................................................14
የትምህርት ቤቶች የአጋርነትና የትብብር ሞዴል አደረጃጀትና አመራር.................................................................14
3.1. የአጋርነትና የትብብር ሞዴል መዋቅራዊ አደረጃጀት...............................................................................14
3.1.1. አጋር ልየታ........................................................................................................................14
3.1.2. መዋቅራዊ መስመር...........................................................................................................15
3.1.3. አመክኗዊ መስመር............................................................................................................15
3.1.4. ስሜታዊ/የተነሳሽነት መስመር.............................................................................................15
3.1.5. ቤተሰባዊ መስመር.............................................................................................................16
3.2. የትምህርት ቤት እና የአጋር አካላት የግንኙነት መንገዶች.................................................................17

1
3.3. የትምህርት ቤቶች የአጋርነትና የትብብር ሞዴል አመራር................................................................17
ክፍል አራት..................................................................................................................................................19
4. በትምህርት ቤቶች አጋርነትና ትብብር ሞዴል የትኩረት አቅጣጫዎችና ተግባራት.....................................19
4.1. የትምህርት ቤቱን አሰራር ስርዓት ማሻሻል....................................................................................19
4.2. የተማሪዎችን የመማር ውጤቶች ማሻሻል፣.................................................................................19
ክፍል አምስት...............................................................................................................................................20
በየደረጃው ያሉ የትምህርት መዋቅሮች ተግባርና እና ኃላፊነት፣ የተጠያቂነት ስርዓት..............................................20
5.1. በየደረጃው ያሉ የትምህርት መዋቅሮች ተግባር እና ኃላፊነት...........................................................20
5.1.1. ትምህርት ሚኒስቴር..........................................................................................................20
5.1.2. የክልል/ከተማ አስተዳደር/ ዞን/ክፍለ ከተማ ትምህርት ቢሮዎች................................................20
5.1.3. የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት....................................................................................................21
5.1.4. በትምህርት ቤት ደረጃ........................................................................................................21
5.2. የተጠያቂነትና የማበረታቻ ስርዓት...............................................................................................22
5.2.1. የተጠያቂነት ስርዓት...........................................................................................................22
5.2.2. የማበረታቻ ስርዓት............................................................................................................22
ክፍል ስድስት................................................................................................................................................23
ክትትል ግምግማና መማማር.........................................................................................................................23
6.1. ክትትል.....................................................................................................................................23
6.2. ግምግማ...................................................................................................................................23
6.3. መማማር.................................................................................................................................24
7. ማጠቃለያ........................................................................................................................................24
ተቀጽላ አንድ...............................................................................................................................................25
የአጋርነት/ሽርክና እና ትብብር ሞዴል የስምምነት ሰነድ......................................................................................25
ተቀጽላ ሁለት..............................................................................................................................................30
የትምህርት ቤት አጋር አካላት ግብረኃይል የስራ እንቅስቃሴ መከታተያና መገምገሚያ ቼክሊስት..............................30

2
ክፍል አንድ
የትምህርት ቤቶች የአጋርነትና የትብብር ሞዴል አጠቃላይ ገጽታ

1.1. መግቢያ

መንግስት የትምህርት የትምህርት ተደራሽነትን እና ሽፋንን ለማሳደግ፣ ፍትሃዊነትን፣ የውስጥ ብቃትን እና


ጥራትን ለሻሻል የተለያዩ ፖሊሲዎችን፣ የትምህርት ፕሮግራሞችን፣ ስትራቴጂዎችን እና መመሪዎችን
በማዘጋጀት ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህም መሰረት የትምህርት ተደራሽነትን እና ሽፋንን ከማሳደግ
አንፃር አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል። ሆኖም ግን አሁንም ከትምህርት ፍትሃዊነት፣ ጥራት እና የውስጥ
ብቃት አንፃር አሁንም የትምህርት ስርዓቱ ችግር ሆነው ቀጥለዋል። በሌላ መልኩ የትምህርት ጥራትን
ለማረጋገጥ የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ስርኣትን በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ በማድረግ ትምህርት
ቤቶች የኢንስፔክሽን አገልግሎት እንዲያገኙ እድሉን ፈጥሯል። የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ሪፖርት
የሚያመላክተው ተማሪዎች ደረጃቸውን ባልጠበቁ ትምህርት ቤቶች እየተማሩ እንደሆነ፣ ለደረጃው
የሚመጥን መምህራን እና ር/መምህራን አለመኖራቸውን ፣ በአጠቃላይ የትምህርት ግብዓት ችግር መኖሩ እና
የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ከማሻሻል አንፃር አሁንም ብዙ ችግሮች ያሉበት እንደሆነ ነው።

ይህንን መሰረት በማድረግ በ 2012 ዓ.ም በተፋጠነ መልኩ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የተፋጠነ
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻ ስትራቴጂ አንድ እና ሁለት በማዘጋጀት ተግበባራዊ ቢደረግም በሰው ሰራሽ
በተፈጥሮ ችግሮች ምክንያት የተፈለገውን ያህል ውጤት ማምጣት አልቻለም። ስለሆነም ይህንን ስትራቴጂ
በተሟላ መልኩ ተግባራዊ በማድረግ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ይህ የትምህርት ቤቶች የአጋርነትና
የትብብር ሞዴልን ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኗል።

ሞዴሉም በትምህርት ቤት ውስጥ ያለውን አቅም ከትምህርት ቤት ውጭ ካለው አቅም ጋር በማቀናጀት


የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ነው። በውስጡም ስድስት ክፍሎችን ይዟል
ክፍል አንድ መግቢያ፣ ክፍል ሁለት የትምህርት ቤቶች አጋርነትና ትብብር ሞዴል ግቦች እና የአተገባበር
ስልቶች፣ ክፍል ሶስት፣ ክፍል የትምህርት ቤቶች የአጋርነትና የትብብር ሞዴል አደረጃጀትና አመራር፣ ክፍል
አራት በትምህርት ቤቶች አጋርነትና ትብብር ሞዴል የትኩረት አቅጣጫዎችና ተግባራት፣ ክፍል አምስት

3
በየደረጃው ያሉ የትምህርት መዋቅሮች ተግባርና እና ኃላፊነት እና ክፍል ስድስር ክትትል ግምግማና
መማማር እንዲሁም ተቀጽላዎችን በውስጡ ይዟል።

1.2. የአጋርነትና የትብብር ሞዴል ማስፈፀሚያ ሰነድ አላማ


1.2.1. ዋና አላማ
 በትምህርት ቤቶች ዙረያ ያሉትን አጋሮች በመለየት የአጋርነት/ሽርክና እና የትብብር የአሰራር
ስርዓትን በመተግበር የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል ነው።

1.2.2. ዝርዝር አላማዎች

 የትምህርት ማህበረሰቡ በትምህርት ቤት ለሚካሄዱ የመማር ማስተማር ስራ አቅም እንዲሆን


የሚስችል ስርዓት ለመዘርጋት፣
 በየደረጃው ያለው የትምህርት መዋቅር የትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሻሻል በሚከናወኑ ተግባራት
ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ፣
 በየደረጃው ያለው የትምህርት አመራሮች እና የተመረጡ ባለሙያዎች አንድ አንድ ትምህርት ቤት
በሞዴልነት ይዘው ማብቃት እንዲችሉ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት፣
 የተማሪዎችን የትምህርት እና የመማር ውጤትን በተፋጠነ መልኩ ማሻሸል እንዲቻል ምቹ
መደላድል ለመፍጠር፣
 ትምህርት ቤቶች አካባቢያዊ ጸጋዎችን አሟጠው እንዲጠቀሙ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት
በመዘርጋት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል፣
 የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን የመለየት፣ የመቀመር እና የማስፋት ስትራቴጂን ተግባራዊ
ለማድረግ ነው።

1.3. የትምህርት ቤቶች የአጋርነትና ትብብር ሞዴል ምንነት

ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁና ብዙ ጊዜ የሚወስዱ ትምህርት ቤቶችን ገንብቶና ለትምህርት ቤቶች የሚያስፈልገውን


መሰረተልማት አሟልቶ የትምህርት አገልግሎት ማቅረብ በአብዛኛው የህብረተሰቡ ወይም የመንግስት ኃላፊነት
እንደሆነ ይታሰባል። ሆኖም መንግስት ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት አንፃር የትምህርትን ተደራሽነት
በማድረግ የህብረተሰቡን እና የተማሪዎችን ፍላጎት ማሟላት ላይ ተግዳሮት ሲገጥመው ይስተዋላል። በተለይ ደግሞ
የትምህርት ጥራትን እና ፍትሃዊነትን በገጠር እና በከተማ፣ በሴቶችና በወንዶች እና ልዩ የመማር ፍላጎት ያላቸው
ተማሪዎች መካከል አሁንም ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንዳሉ ጥናቶች ያሳያሉ።

4
ስለሆነም በተመሳሳይ ችግር ውስጥ ያለፉ ሀገሮች ቸግሩን ለመቅረፍ ትምህርት ቤቶችን በመገንባትና በማደስ፣
የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት (ፋሲሊቲ) በማሟላት፣ የተሻሻለ የትምህርት አገልግሎት ለተማሪዎች ለማቅረብ
እንዲችሉ ባለድርሻ አካላትን እና ህብረተሰቡን በማስተባባር አጋርነትን በመመስረት ያሉባቸውን ችግሮች ለመቅረፍ
ሲሰሩ ይታያሉ።

የአጋርነት/ሽርክናና የትብብር ሞዴል በግለሰቦች እና በድርጅቶች ደረጃ ተግባራዊ ሊደረግ ይችላል። ሆኖም ግን ወጥ የሆነ
የአሰራር ስርዓት ያስፈልገዋል። ይህ ትብብራዊ ሞዴል አጋር አካላት ያላቸውን ሰብአዊና ቁሳዊ ህብታቸውን በማቀናጀት
በተናጠል ማሳካት የማይችሉትን ዓላማ ማከናወን እንዲችሉ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ነው። በዚህም ሁለቱም
ተባባሪ አካላት በመጀመሪያ ትብብር እንዲያደርጉ ስገደዳቸውን መሰረታዊ ችግሮች የመለየት እና ችግሩን መፍታት
በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ የአጋራ ስምምነት በማድረግ እና ወጥ የሆነ የአሰራር ስርዓት በመፍጥር ችግራቸውን
እንዲፈቱ እድል ይሰጣል።

በትምህርት ቤቶችና በአጋር ድርጅቶች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ በተለይ ተቋሟት መካከል የሚደረጉ
መደጋገፎችንና መረዳዳቶች ለትምህርት ቤቶች መሻሻል በተለይ ለተማሪ ውጤትና ስነምግባር መሻሻል ከፍተኛ የሆነ
አስተዋጽኦ አለው። ትምህርት ቤቶች ጥራት ያለው የትምህርት አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያደርገው አስተዋጽኦ
ከፍተኛ ነው።

በአጠቃላይ የአጋርነትና ትብብር ሞዴል ትምህርት ቤቶች በአካባቢያቸው ያሉ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ

ተቋማት፣ ግለሰቦች፣ ወላጆች፣ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ እና የአካባቢው ማህበረሰብ በትምህርት ቤት ስራ አመራር

ዙሪያ በማሳተፍ የተማሪዎችን ውጤትና የመማር ውጤት ለማሻሻል የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ነው።

የትምህርት ቤት አመራሮች በትምህርት ቤቶች ዙሪያ ያለውን አካባቢያዊ ሀብት/ጸጋ በተለይም ከሃብት ማሰባሰብ

በተጨማሪ በክፍል ውስጥ የሚካሄደውን የመማር ማስተማር ሂደት ከመምህሩ ጎን ሆነው ድጋፍ እንዲሰጡ የሚያደርግ

ነው። ለአብነት ታዋቂ/ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተማሪዎችን የሚመክሩበትና የሚያንጹበት፣ መንግስታዊ የሆኑና

መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ባለሙያዎች እንደየሙያቸው ለተማሪዎች የተግባር ትምህርት የሚሰጡበትና

የሚያለማምዱቡት፣ ትምህርት ቤቶች ከግቢ ውጭ ያለውን ሃብት የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማሻሻል

የሚያሰባስቡበት፣ መምህራንና የትምህርት አመራሮች እርስ በርስ የሚደጋገፉበትና የሚማማሩበትን ስርዓት እና


መምህራን የየትምህርት አይነቱን የይዘት ትንተና በማድረግ የውጭ ባለሙያ እገዛ የሚፈልጉ ይዘቶችን የመለየት እና

ተማሪዎች ተጨማሪ እውቀት እንዲያገኙ የሚያደርግ ሞዴል ነው።

የአጋርነትና ትብብር ሞዴል የሚስፈልጋቸው ተግባራትን ማለትም የትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ መሰረተልማት

አቅርቦትና የትምህርት ቤቶች አግልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል በሚደረጉ ሁለገብ እንቅስቃሴዎች በትምህርት ቤቶችና

በግል ሴክተሩ ወይም የልማት ድርጅት ወይም በህብረተሰቡ መካከል የሚመሰረት የአጋርነት ስምምነት ነው። በዚህም

መሰረት አጋር ድርጅቶችና ግለሰቦች ፣ የትምህርት ቤቶችን ብቃት በማሻሻል፣ አካባቢያዊ የፈጠራ ውጤቶችን

5
በማስተዋወቅ፣ የበጀት ድጎማ በማድረግ፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በማመቻቸት በትምህርት ቤት ማሻሻል

ማዕቀፍ ውስጥ የተቀመጡትን ስታንዳርዶች ማሟላት ነው።

ይህ የትብብርና የአጋርነት ሞዴል በተፈለገው ደረጃ ተግባራዊ እንዲሆን ከአሁን በፊት ያሉ የመንግስት የአሰራር

ስርዓቶችን እና መዋቅሮችን ይጠቃማል። ሆኖም ግን እንደ አስፈላጊነቱ ከክልል ክልል የተለያዩ የአተገባባር ስልቶችን

ሊከተል ይችላል። በትምህርት ቤት ደረጃ ይሄ ሞዴል ውጤታማ እንዲሆን የአጋርነት ስምምነት የፈረሙ አጋር አካላት

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የተደራጁ አደረጃጀቶች ውስጥ በመግባት ከዕቅድ ዝግጅት እስከ ግምገማ ባሉት

ሂደቶች እንዲሳተፉ ይደረጋል። በዚህ ሞዴል የሚከናወኑ ተግባራት ከአሁን በፊት ወጥተው ስራ ላይ የዋሉ የሕግ

ማዕቀፎች፣ ደንቦች፣ ፖሊሲዎች፣ መመሪዎችን እና የጋራ የመግባቢያ ሰነዶችን የተከተለ እንዲሆን ይደረጋል።

1.4. የአጋርነትና የትብብር ሞዴል አስፈላጊነት

ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ፣ከህብረተሰቡና አጋር ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር በመመካከር የጋራ


ፍላጎቶቻቸውንና ዓላማዎቻቸውን ማከናወን ይጠበቅባቸዋል። በሂደቱም ቁልፍ የሆኑ ተግዳሮቶችን
በመለየት ችግሮችን ለመፍታት ጥረት ያደርጋሉ። መንግስት ለትምህርት ሴክተሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ
እንደሆነ ይታወቃል። ስለሆነም በተደራሽነትና በትምህርት ሽፋን ላይ ያለው መሻሻል ይበል የሚያስብል ነው።
ነገር ግን አሁንም ቢሆን የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ከማሻሻል አንጻር እና ፍትሃዊነትን በየደረጃው
ከማሻሻል አንፃር አሁን ያልተሻገርናቸው ችግሮች እንዳሉ ግልጽ ነው። በተለይ በግብዓት እና በሂደት ላይ ያሉ
ችግሮች የትምህርት ውጤት ላይ ተጽእኖ እንዳደረጉ ግልጽ ነው።

ለምሳሌ፡- የ 2013 ዓ.ም የትምህርት አመራር የመረጃ አመታዊ መጽሄት መሰረት 40% የመጀመሪያ ደረጃ
እና 66.7% የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የውሃ አገልግሎት አላቸው፣ 30% የመጀመሪያ ደረጃ እና 76%
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት አላቸው፣ 34% የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት
ቤቶች የትምህርት መስጫ ሬዲዮና 79፣ 7% ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ኮምፒውተር አላቸው፣
በተመሳሳይ 14% የመጀመሪያ ደረጃ ቴፕ ሪከርደር እና 17% የሚሆኑት ደግሞ ቪዲዮ ሪከርድ አላቸው፣
55.7% የመጀመሪያ እና 88.2% ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቤተመፃህፍት አላቸው፣ 46.7%
የመጀመሪያ እና 90% ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቤተ ሙከራ አላቸው እና 49.6% የመጀመሪያ አና
64.4% ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ማበልፀጊያ ማዕካለት አላቸው። ይህ የሚያሳየው ትምህርት ቤቶች
የመማር ማስተማር ስራውን ሊያሳልጹ የሚችሉ የትምህርት ግብዓት እንዳሏቸው ነው። ምንም እንኳን
ትምህርት ቤቶች መሰረታዊ የሚባሉ ግብዓቶች ቢኖሩም በ 2013 የትምህርት አመራር መረጃ ዓመታዊ
መጽሄት መሰረት 7.8% የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ብቻ ናቸው ለደረጃው የተቀመጠውን ዝቅተኛ መመዘኛ
የሚያማሉ ትምህርት ቤቶች ያሉት። ከዚህ መረዳት የምንችለው ግብዓት በራሱ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ

6
ለማሻሻል በቂ እንዳልሆነ ነው። ለምሳሌ የ 2013 የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን አገልግሎት ካገኙ
ትምህርት ቤቶች ውስጥ በግብዓት በሂደት እና በውጤት ተመዝነው በአጠቃላይ ውጤታቸው ደረጃ 4 ላይ
የደረሱ ትምህርት ቤቶች አምስት ትምህርት ቤቶች ብቻ ናቸው። በተመሳሳይ በዚሁ አመት የኢንስፔክን
አገልግሎት ካገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 7.8% ደረጃ 3፣ 69% ደረጃ 2 እና 23.2% የሚሆኑት ደግሞ ደረጃ
1 ላይ ናቸው። ስለሆነም የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ሂደት ላይ ያሉ አሰራሮችን ማሻሻል እና
የትምህርት ቤት አጋርነት/ሽርክና እና ትብብር ሞዴልን በትምህርት ቤት ደረጃ ተግባራዊ ማድረግ
ያስፈልጋል።

ስለሆነም ይህ የአጋርነት/ሽርክና ሞዴል አጋር አካላት በተለይ ደግሞ ወላጆች በትምህርት ዙሪያ በቂ ግንዛቤ
እንዲኖራቸው በማድረግ ለልጆቻቸው ትምህርት ተቆርቋሪና አጋዥ እንዲሆኑ በማድረግ ለትምህርት ቤቶች
መሻሻል የድርሻቸውና አጋርነታቸው እንዲወጡ ተነሳሽነታቸውን ይጨምራል፤ በተማሪዎችም ውጤት
መሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

ትምህርት ቤቶችና አጋር ድርጅቶች በተመሳሳይ መንገድ አንድ ላይ ተጋግዘው ሲሰሩ ለትምህርት ቤቶች
መሻሻል መጠነ ሰፊ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። ለአብነት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ኢንዱስትሪዎች፣ ሲቪክ
ማህበራትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ለትምህርት ቤቶች የተግባር፣ የንድፈ ሀሳብ፣ የሀብትና መሰል
ድጋፎች ሲያደርጉ ትብብራዊ አጋርነት ያጠናክራል። የተጠናከረ ትብብር ወደ ውጤት ያመራል በተለይ ደግሞ
የትምህርት ቤቶችን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ያሻሻል፣ ሀብትን በብቃት ለመጠቀምና የትምህርትን ዓላማ
ለማሳካት ያስችላል በትምህርት ቤት ዙሪያ ለሚከናወኑ ተግባራት ወጥ የሆነ የአሰራር ስርዓት ይፈጥራል።

በአጠቃላይ ይህ ሞዴል በትምህርት ቤቶች ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ የሆነበት ዋናው ምክንያት
በትምህርት ቤት ውስጥ እና ከትምህርት ቤት ውጭ ያለውን ሃብት (የሰው እና የፋይናንስ) አቀናጅቶ
በመጠቀም የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል በማስፈለጉ ነው። የትምህርት ቤቶች ደረጃ ሲሻሻል ደግሞ
የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ይሻሻል።

የትምህርት ቤት አመራሮች በትምህርት ቤቶች ዙሪያ ያለውን አካባቢያዊ ጸጋ በክፍል ውስጥ የሚካሄደውን
የመማር ማስተማር ሂደት ከመምህሩ ጎን ሆነው ድጋፍ እንዲሰጡ የሚያደርግ መርሃ ግብር ነው።

1.5. የትምህርት ቤቶች የአጋርናትና ትብብር የሚያስገኘው ጠቀሜታ


1.5.1. ለተማሪዎች
 የተማሪዎችን የመማር እድል ያሳድጋል

 የተማሪዎችን የመማር ደህንነታቸውን ያሳድግላቸዋል በተለይ ትምህርት ቤቶች ከመኖሪያ


ቤታቸው ርቀው በሚመጡ ተማሪዎች በመንገድ ላይ ሲንቀሳቀሱ ደህንነታቸው የተጠበቀ
እንዲሆን ያግዛል፣

7
 ተማሪዎች የትምህርት አቀባበላቸውን የሚያሳድጉ ነገር ግን በራሳቸው ሊያገኙ
የማይችሏቸውን ግብዓቶች እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ( ሙዚየሞችን መጎብኘት ይችላሉ፣
የብቃት ማዕከላትን መጠቀም ይችላሉ፣ ከውጩ ጋር መገናኘት ይችላሉ፣የትምህርት ድጋፍ
ማገኘት ይችላሉ)
 ተማሪዎች የራሳቸውን ፍላጎት በማበልጸግ የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ የተለያዩ ሀገራዊና
አለማቀፋዊ ተሞክሮዎችን እንዲያገኙ፣
 የተማሪዎችን ስነምግባር ለማሻሻል አወንታዊ ሚና ይጫወታል፣
 ተማሪዎች በትምህረት ቤታቸው አፈፃፀም ዙሪያ እንዲወያዩ እና የራሳቸውን ኃላፊነት
እንዲወጡ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፣

1.5.2. ለትምህርት ቤቶች


o የተማሪዎችን የትምህርት ውጤት እንድያሻሽሉ ያግዛቸዋል፣
o የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ እና በክፍል የመገኘት ምጣኔን ያሳድጋል፣
o የመምህራንን የስራ እርካትን ያሻሽላል፣
o የወላጆች ወይም አሳዳጊዎችን ተሳትፎ ያሳድጋል፣
o የትምህርት ቤትን የስራ አካባቢ ለትምህርት ቤት ማህበረሰቡ የተመቸ እንድሆን ያደርጋል፣
o የትምህርት ቤቶችን እና የአጋር አካላትን ግንኙነት ያሳድጋል፣
o የተጠያቂነት ስርዓትን ያሳድጋል፣
o የትምህርት ጊዜያትን ይጨምራል፣
o ተማሪዎች የቤት ስራቸውን በተገቢ እንዲሰሩ፣ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲያኙ እና
የክርምት ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋሉ፣
o በትምህርት ቤት አካባቢ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የቢዝነስ ተቋማት፣ የአካባቢ መስተዳድሮችን
በማገናኘት በኩል እንደ ድልድይ ሆነው ያገለግላሉ፣
o የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ያሳድጋል
o በትምህርት ቤት ውስጥ እና ውጭ ያሉ አቅሞችን አቀናጅቶ በመጠቀም የተማሪቆችን ውጤትና
ስነምግባር እንዲያሻሽሉ እድል ይሰጣቸዋል፣
o ትምህርት ቤቱ ተማሪዎችን ወደፊት የአካባቢ ማህበረሰቡን እና አጋር ድርጅቶችን እንዲያግዙ
ለቀጣይ ህይወታቸው መሰረት እንዲጥሉ በእውቀት፣ በአመለካከት እና በክህሎት እንዲታነፁ
ያደርጋሉ፣

1.5.3. ለመምህራን

8
 የመምህራን የስራ ተነሳሽነትን ያሳድጋል፣
 የመምህራን የመኖሪያ ቤት ችግር ይቀርፋል፣
 መምህራን ለመማር ማስተማር ይደቱ የተሻለ ግብአት እንድያገኙ ይረዳቸዋል፣
 ትምህርቱ ይበልጥ ተግባር ተኮር እንድሆን ያግዛል፣
 የመምህራንና የአካባቢው ህብረተሰብ የተሻለ ግንኙነት ይፈጥራል፣
 መምህራን በኃላፊነት እና በተጠያቂነት እንዲሰሩ ያግዛል፣

1.5.4. ለአጋር ድርጅቶች


 ምርት እና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ እድል ይፈጥራል.
 ብቃት ያለው የሰው ኃይል እንዲያገኙ እድል ይፈጥራል፣
 የትምህርት ቤቶችን እና የአጋሮችን ግንኙነት ያሳድጋል፣
 የትምህርት ጥራት በድርጅታቸው ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ በመለየት ድጋፋቸውን
እንዲያሻሽሉ ያደርጋል፣

1.5.5. ለወላጆች
 ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ይልካሉ፣
 የልጆቻቸው የትምህርት ውጤት ያሻሽላል፣
 ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲያግዙ ያደርጋል፣
 በትምህርት ቤት የሚያደርጉትን ተሳትፎ ያሳድጋል

1.6. የአጋርነትና ትብብር ሞዴል ታሳቢ ያደረጋቸው ጉዳዮች


 ለተማሪዎች የትምህርት ውጤት መሻሻል አስተዋጽኦ የሚያደርጉት ትምህርት ቤት ውስጥ ያሉ
ጉዳዮች ብቻ ሳይሆን ከትምህርት ቤት ውጭ ያሉ አካላትም አስተዋጾ ያላቸው መሆኑ፣
 ለትምህርት ጥራት የሚያስፈልጉትን ሁሉንም ግብዓቶች በትምህርተ ቤቶች ብቻ ማሟላት
የማይቻል ስለሆነ፣
 በትምህርት ቤት ውስጥ የሚከናወኑ አብዛኛዎቹ ተግባራት ከትምህርት ቤቱ ር/መምህር አቅም በላይ
አለመሆናቸው፣
 በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ያልተጠቀምንበት እምቅ ሃብት (ወላጆች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ መንግስታዊና

መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ ፋብሪካዎች፣ ሱቆች/ሸማቾች ማህበር እና የልዩ ልዩ


የእደ ጥበብ ባለሙያዎች) መኖሩ፣

9
ከላይ የተቀመጡትን ታሳቢዎች ወደ ተግባራ ለመለወጥ የርዕሰ መምህራን እና በየደረጃው ያለው
የትምህርት መዋቅር የክትትልና ድጋፍ ስራ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል። እንዲሁም በትምህርት ቤቶች ዙሪያ
ያለው አካባቢያዊ አቅምና ጸጋ ለተማሪዎች የትምህርት ውጤት ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው እና
የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ሁሉንም አቅም ያማከለ ስልት አዘጋጅቶ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል።

በተጨማሪም የአካባቢን ሃብት በአግባቡ ወይም በፍትሃዊነት ለመጠቀም ከክልል እስከ ትምህርት ቤት
ድረስ ያለው የትምህርት መዋቅር ከባቢያዊ የሆነ የሃብት ስርጭት የሚያሳይ ካርታ ወይም የአሰራር ስርዓት
በማዘጋጀት ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል። የመማር ማስተማር ስራንም ውጤታማ ለማድረግ ሙያዊ
እገዛ ሊያደርጉ የሚችሉ የሰው ሃይል ልየታና ስምሪት ማድረግ ያስፈልጋል። ከዚህ አንጻር ደግሞ
የትምህርት ክፍሎች (በዲፓርትመንቶች) ከፍተኛውን ሚና መጨወት አለባቸው።

1.7. የትምህርት ቤቶች አጋርነትና ትብብር ሞዴል መርሆች

ሀ. ግልጽነት:- ስለሚከናወኑ ጉዳዮች ወይም ተግባራት በግልጽ መረጃዎችን መለዋወጥ ፤በሚፈጠሩ የአጋርነት
መርሀግብሮች ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅድሚያ ዓላማውንና አተገባበሩን እንዲረዱ እንዲሁም መረጃ
እንዲደርሳቸው ማድረግ ፤

ለ. ተጠያቂነት:- አጋር አካላት ለሚያከናውኗቸው ተግባራት ወይም ውጤታቸው ተጠያቂ ይሆናሉ፤

ሐ. ሕጋዊነት: -አጋር አካላት ለሚያደርጓቸው ክንዋኔዎች ደህንነት ሕጋዊነትን ማግኘትና ሕጋዊነትን ተላብሰው መስራት
አለባቸው።

መ. ቀጥተኛነት:- በቀጥታ ተገቢ አጋርነትን ሊያሳልጡና የትምህርት ቤቶችን ፍላጎቶች ብቻ ሊያሟሉ በሚችሉ
ትብብሮች ብቻ መወሰን

ሠ. ተለማጭነት:- ተለማጭነት በሁሉም የአጋርነት ድርጊቶች አስፈላጊና በፈጣን የዕድገት ለውጦች ስለሚወሰኑ
በያንዳንዱ የተግባር ክንውን ተለማጭ ስልቶችን መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል፤

ረ. ካለፉት ተግባራት መማር:- ከየእለት ተግባራትና ገጠመኞች በመማር የአሰራር ለውጦችን ማምጣት ልምዶችን
ማካፈል፤

ሰ. ፍትሐዊነት:- ሁሉም የህብረተሰብ አካላትን ተጠቃሚ የሚያደርግ የአጋርነት ማዕቀፎችን ተግባራዊ ማድረግ ፤

ሸ. አካታችነት:- የሁሉንም ተሳትፎ ና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በአገልግሎት አቅርቦት ውሳኔ አሰጣጥ፣ የአሰራር ፖሊሲ
ዝግጅት በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን ከግምት ማስገባት፤

10
ቀ. የጋራ ኃላፊነት፡- አጋር አካላት በትብብር ለማከናወን በጋራ የተስማሙባቸውን ተግባራት በሃላፊነት መንፈስ
ማከናወን.

1.8. የትምህርት ቤቶች አጋርነትና ትብብር ሞዴል የተፈፃሚነት ወሰን

ይህ የትምህርት ቤቶች የአጋርነት እና የትብብር ሞዴል ማንዋል በዋነኛነት ለቅድመ አንደኛ፣ ለአንደኛ፣
ለመሃከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተዘጋጀ ነው። በሌላ መልኩ በዚህ የአጋርነት/ሽርክና እና
የትብብር ሞዴል ስምምነት ውስጥ የሃይማኖት ተቋማትና የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት በሽርክና ስርዓቱ
ውስጥ አይካተቱም። ሆኖም ግን የኃይማኖት አባቶች እና የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች እንደ ግለሰብ መሳተፍ
ይችላሉ።

11
ክፍል ሁለት

2. የትምህርት ቤቶች አጋርነትና ትብብር ሞዴል ግቦች እና የአተገባበር ስልቶች


2.1. የትምህርት ቤቶች የአጋርነትና ትብብር ሞዴል ግቦች

ግብ 1:- በትምህርት ቤቶች እና በትምህርት ቤት ዙሪያ ያሉ አጋር አካላት ግንኙነትና ትብብር

ማሻሻል፣
ግብ 2፡- የመማርና የስልጠና ዕድሎችን በተለይም የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማስፋትና
ማበልፀግ፣፣
ግብ 3፡- ሁሉም አጋር አካላት በሚፈቅዱት የትምህርት ፕሮግራሞች በትምህርርት ቤቱ እንዲሳተፉ
ማድረግና ሚናቸውን ማሻሻል፣
ግብ 4፡- ትምህርት ቤቶች ከአጋር አላካትና ከህብረተሰቡ የሚያገኙትን ሃብት (በገንዘብ፣ በአይነት፣
በጉልበት እና በዕውቀት) ማሳደግ
ግብ 5፡- ከእንስፔክሽን ደረጃ አሰጣጥ አንፃር የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል

2.2. የትምህርት ቤቶች የአጋርነት እና ትብብር ሞዴል አተገበባር ስልት


 በአጋርነትና ትብብር ሞዴል አሰራር ማንዋል ላይ በየደረጃው ላሉ አካላት ግንዛቤ መፍጠር
 በየደረጃው ያሉ የትምህርት መዋቅሮች የትምህርት ቤት አጋሮችን የመለየት ስራ ይሰራል፣
 የአጋርነትና የትብብር ሞዴል የአደረጃጀት እና የአመራር ስርዓት እንዲኖረው ይደረጋል፣
 የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሳደግ ያሉ አማራጮችን ሁሉ እንዲጠቀሙ ይደረጋል፣
 ከትምህርት ሚኒስቴር እስከ ትምህርት ቤት የአጋርኔና የትበብር ሞዴልን የሚከታተል ተጠሪ ባለሙያ
ይመደባል፣
 የአጋርነትና የትብበር ሞዴል ለመተግበር የስምምነት ሰነድ በማዘጋጀት እንዲፈራረሞ ይደረጋል፣
 የትምህርት መዋቅሩ በትብብር ሊሰራ የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ይዘጋጃል.

12
ክፍል ሶስት

የትምህርት ቤቶች የአጋርነትና የትብብር ሞዴል አደረጃጀትና አመራር


3.1. የአጋርነትና የትብብር ሞዴል መዋቅራዊ አደረጃጀት

የትምህርት ቤቶች የአጋርነትና የትብብር ሞዴል አወቃቀር አመስት መዋቅራዊ


መስመሮችን ይከተላል፣

3.1.1. አጋር ልየታ

 በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ያሉ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን፤ ታዋቂ ተጽዕኖ


ፈጣሪ ግለሰቦችን፤ በንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች መለየት
 የተለዩ አጋር አካላት በትምህርት ቤቱ እቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ድጋፍና አመራር ስራዎች ላይ
ማሳተፍ፤
 ከአጋር አካላት ሊገኝ የሚችለውን አስተዋጽኦ በመለየት በመማር ማስተማሩ ስራ ላይ፣
የተማሪዎች ሰብዕና ማነጽ ላይ እንዲያግዙ ማድረግ እና በጋራ በሚሰሩ ስራዎች ላይ
የስምምነት ሰነድ በማዘጋጀት መፈራረም እና ወደ ስራ መግባት

ስዓል 1፡- የትምህርት ቤት አካባቢ የሚገኙ አጋር አካላት ምሳሌ

13
3.1.2. መዋቅራዊ መስመር

 የተማሪዎች ውጤት ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ጉዳዮችን መለየት እና ከአጋር አካላት ጋር የጋር

ግብ በማስቀመጥ እቅድ ማዘጋጀት፤


 ከአጋር አካላት ጋር በጋራ የዕቅድ ዝግጅት፣ ግምገማና የግብረመልስ ስርዓት መዘርጋት እና
ተግባራዊ ማድረግ
 ምቹ ፣ጤናማ እና ለተማሪዎች ደህንነት የማያሰጋ የትምህርት ቤት አካባቢ መፍጠር
 በመምህራን እንዲሁም በትምህርት ቤቱ ማህበረሳብ ጤናማ የሆነ የአጋርና ትብብር ሞዴል
ተግባራዊ በማድረግ የውድድር ስርዓት እንዲኖር ማድረግ፣

3.1.3. አመክኗዊ መስመር

 የትምህርት ብክነት ( ማርፈድ፣ መቅረት፣ ማቋረጥ፣ በመምህራን በስራ ቦታ እና በክፍል

ውስጥ አለመገኘት) መቀነስ፣

 የትምህርተ ቤት መተዳደሪያ ደንብን ለትምህርት ጥራት አስተዋጽኦ በሚያደርግ መልኩ

ማሻሻል፣

 የመምህራንን የስራ ተነሳሽነት በመጨመር ለሴት ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ፣

በውጤታቸው ደከም ላሉ ተማሪዎች እና የባከኑ ክፍለ ጊዜያትን በመለየት የማጠናከሪያ

ትምህርት ሊሰጡ የሚችሉበትን ስርዓት መዘርጋት፣

 ሁሉም የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በተጓዳኝ ትምህርት ውስጥ እንዲሳተፉ ማድረግ፣


 መምህራን እርስ በርስ ሊደጋገፉ የሚችሉበትን ስርዓት መዘርጋት ( የመምህራን ፎረም
በትምህርት ቤት ውስጥ ያሉትንም ሆነ ከትምህርት ቤት ውጭ ያሉ መምህራንን በጋራ
እንዲሰሩ የሚያስችል ስልት መዘርጋት)
 በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ አካታችነትን ተግባራዊ ማድረግ፣

3.1.4. ስሜታዊ/የተነሳሽነት መስመር

 የመምህራንን የስራ ተነሳሽነትና ፍላጎት ማሻሻያ ስርዓት መዘርጋት

 በትብብርና በአጋርነት ውጤታማ የመሆን ስርዓትን መዘርጋት

14
3.1.5. ቤተሰባዊ መስመር
 ወላጆች/አሳዳጊዎች የልጆቻቸውን ትምህርት የሚከታተሉበት ስርዓት መዘርጋት

 ወርሃዊ የወላጆች/የአሳዳጊዎች መምህራን ህብረት ጉባኤ ማካሄድ

 የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎችች ትምህርትን ተግባራዊ ማድረግ

ስዕል 2፡- የአጋር እና የትብበር ሞዴል አደረጃጀት

በአጠቃላይ ይህ የአጋርነት/ሽርክና እና የትብብር ሞዴል ትምህርት ቤቱ ለተማሪዎች፣ ለአካባቢው ማህበረሰብ፣


ለተለያዩ አጋር አካላት እንደ መማማሪያ እና የመገናኛ ማዕክል ሆኖ ያገለግላል። የትምህርት ቤት እና
የማህበረሰቡን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር መደበኛ ያልሆነ ትምህርት መስጫ ማዕከል ሆኖ አእንዲያገለግል
እና በሰጥቶ መቀበል መርህ የትምህርት ቤቱን ደረጃ ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲሰራ ያስችላል።

3.2. የትምህርት ቤት እና የአጋር አካላት የግንኙነት መንገዶች

15
 የትምህርት ቤት የሪፖርት ካርድ፣
 የትምህርት ቤቶች የውስጥ እና የውጭ የተማሪዎች የጠቅላላ እውቀት የጥያቄና መልስ
ፕሮግራሞች፣
 በትምህርት ቤት ደረጃ የሚካሄዱ የግጥም እና የንባብ ፕሮግራሞች፣
 በተማሪዎች የሚመሩ የተለያዩ ትምህርታዊ ጉባኤዎች/መርሃ ግብሮች፣
 የተማሪዎች ስራ ማሳያ አውደ ርዕይ/ኤግዚቢሽን
 መረጃን ሰጪ የሆኑ ፕሮግራሞች ( የተማሪ ጥረቶችን ፣ የመምህራን፣ የአመራሩን)
 ወላጆችን የሚያነቁ መልዕክቶች
 ስፖርታዊ ውድድሮች
 የየሩብ አመት የአፈጻጸም ውይይት

 የወላጆች ቀን በዓላት

3.3. የትምህርት ቤቶች የአጋርነትና የትብብር ሞዴል አመራር

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል በትምህርት ቤት ውስጥ የሚከናወኑ ሁሉንም ተግባራት ር/መምህሩ
ብቻ በቂ እንዳልሆነ እስከአሁን የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻ የሄድንበት መንገድ ያመላክታል።
በተመሳሳይ መልኩ በትምህርት ቤት ውስጥ የሚከናወኑ አብዛኛዎቹ ተግባራት ከትምህርት ቤቱ
ር/መምህር አቅም በላይ እንደማይሆኑ ግልጽ ነው። ትምህርት ቤቶችን በዘላቂነት ደረጃቸውን ለማሻሻል
ትምህርት ቤት ውስጥ ያለውን እና ከትምህርት ቤት ውጭ ያሉትን አቅሞች አቀናጅቶ መጠቀም
ውጤታማ እንደሚያደርግ ጥናቶች እና የተለያዩ ሪፖርቶች ያመላክታሉ። የትምህርት ስራ ማህበራዊ
እንደመሆኑ በየትኛውም የስራ ዘርፍ የተሰማራ እና የትኛውንም የአኗኗር መንገድ የሚከተሉ የህብረተሰብ
ክፍሎችን ይመለከታል። በዘርፉ ላይ የተደረጉ ጥናቶችም እንደሚያሳዩት የአንድ ሃገርን እድገት
ከሚወስኑት እና ከሚያፋጥኑት ሁኔታዎች ውስጥ ትምህርት ግንባር ቀደሙ ነው። ስለሆነም እስከ አሁን
በተበጣጠሰ መልኩ ይሰራበት የነበረውን የትምህርት ቤት እና የአጋር አካላት ግንኙነትን ወጥ የሆነ
አደረጃጀት በመፍጠር ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ ለትምህርት ቤቶች እንዲያበረክቱ ማድረግ አስፈላጊ
ነው። ስለሆነም በቀጣይ የትምህርት ቤቶችንና የአጋር አካላትን ግንኙነት ለማጠናከር ሊኖረን የሚችለው
አደረጀጃት ከትምህርት ሚኒስቴር እስከ ወረዳ ባለው የትምህርት ዋቅር ውስጥ የትምህርት ቤት መሻሻል
ዳይሬክቶሬት አንድ ተጠሪ ባለሙያ በመመደብ ስራውን በበላይነት እንዲያስተባብር ይደረጋለ።
በትምህርት ቤት ደረጃ ደግሞ የትምህርት ቤት መሻሻል ኮሚቴ የአጋርነት/ሽርክና እና ትብብር ሞዴል
ውጤታማ እንዲሆን ያስተባብራል። ሆኖም ግን ክልሎች ይህ ሞዴሉን በተሻለ መልኩ
ማስተግበር/ማስፈፀም ያስችለኛል የሚሉትን አደረጃጀቶች ሊጠቀሙ ይችላሉ።
16
ክፍል አራት

4. በትምህርት ቤቶች አጋርነትና ትብብር ሞዴል የትኩረት አቅጣጫዎችና


ተግባራት
4.1. የትምህርት ቤቱን አሰራር ስርዓት ማሻሻል

 በትምህርት ቤት የሚከናወን ማንኛውም የትምህርት ቤት ደረጃ የሚያሻሽሉ ተግባራት


በትምህርት ቤቱ ር/መምህር አቅም ብቻ የሚሰሩ አይደሉም። በተመሳሳይ ደግሞ በትምህርት
ቤት የሚከናወኑ ሁሉም ስራዎች የአጋር አካላትን ትብብር የሚጠይቁ አይደሉም። ስለሆነም

17
ትምህርት ቤቱ በአጋር አካላት የሚሰሩ ስራዎችን በመለየት እና በዙሪያው ያለውን እምቅ
አቅም በመጠቀም የትምህርት ቤቱን ደረጃ በማሻሻል ለተማሪዎች ጥራት ያለው የትምህርት
አገልግሎት መስጠት፣
 የትምህርት ቤቱ ራዕይ፣ ተልእኮና እሴቶች ለማሳካት ሊያግዙ የሚችሉ አጋር ድርጅቶች
(የንግድ ተቋማት፣ አሰልጣኝ ተቋማት፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣
የሃይማኖት ተቋማት፣ እድሮች፣ ሙያ እና ሲቪክ ማህበራት) እና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች
አቅምን በተደራጀ መልኩ መጠቀም ፣

4.2. የተማሪዎችን የመማር ውጤቶች ማሻሻል፣

 የተማሪዎችን የማንበብ፣ የማስላት፣ መፃፍ እና መረዳት ችሎታቸውን ማሻሻል

 የተማሪዎችን የስነ ጥበብ ችሎታቸውን አውጥተው መጠቀም እንዲችሉ ማበረታታት፣

 ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ውጭ ከአለም ጋር ለማገናኘት ሳይንስ እና ሂሳብ ላይ መሰረት


ያደረጉ ፕሮግራሞች ላይ ማሳተፍ
 ተማሪዎች የአካባቢያቸው ታሪክ፣ ባህል እና ወግ እንዲያውቁ ማበረታታት፣

 የተፈጥሮ ሃብትን በመንከባከብ ተግባራት ላይ ማሳተፍ፣

 የተማሪዎችን ማህበራዊ ድህንነት ማሻሻል

 የትምህርት የውስጥ ብቃትን ማሻሻል

 ተማሪዎች በአካባቢያቸው በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እና የተለያዩ


ክህሎቶች ባለቤት እንዲሆኑ ለማድረግ፣

ክፍል አምስት

በየደረጃው ያሉ የትምህርት መዋቅሮች ተግባርና እና ኃላፊነት፣ የተጠያቂነት


ስርዓት
5.1. በየደረጃው ያሉ የትምህርት መዋቅሮች ተግባር እና ኃላፊነት
5.1.1. ትምህርት ሚኒስቴር
• የትምህርት ቤቶችን አጋር አካላት ልየታ ያካሄዳል

• የአጋርነት/ሽርክና እና ትብብር ሞዴልን ተግባራዊ ለማድረግ፣ እቅድ ያዘጋጃል፣ ያስተዋውቃል፣


ተግባራዊ ያደርጋል

18
• የትምህርት ቤቶች የአጋርነትና የትብብር ሞዴልን ለሚመለከታቸው አካላት ያስተዋውቃል፣

• የትምህርት ቤቶች አጋርነትና ትብብር የስምምነት ሰነድ ያዘጋጃል፣ ይፈራረማል፣ ወደ ክልሎች


እንዲወርድ ደርጋል፣

• በትምህርት ቤቶች መሻሻል ፕሮግራም አተገባበር ጥንካሬና ክፍተት ይለያል

• በአጋርነትና ትብብር ሞዴል የሚከናወኑ ተግባራትን ይለያል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣

• ለክልል/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤሮ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ይሰጣል.

• የተደረጃ የክትትል፣ ድጋፍ ና መማር ስርዓት ይዘረጋል

• በከፍተኛ አመራር የሚመራ የአፈጻጸም ግምገማና ግብረ መልስ ስርዓት ይዘረጋል።

5.1.2. የክልል/ከተማ አስተዳደር/ ዞን/ክፍለ ከተማ ትምህርት ቢሮዎች


• የትምህርት ቤቶች የአጋርነትና ትብብር ሞዴልን ያስተዋውቃል

• አጋር አካላት ልየታ ያካሄዳል፣

• የጥምህርት ሚኒስቴርን መነሻ በማድረግ አጋርነት መግባቢያ ሰነድ ይዘጋጃል፣ይፈራረማሉ፣


አፈፃፀሙን ይከታተላሉ

• በትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም አተገባበር ጥንካሬና ክፍተት ይለያል

• ክልላዊ የንቅናቄ ስርዓት ይዘረጋል

• ለዞን/ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ እና ትምህርት ቤት የአቅም ግንባታ ስልጠና ይሰጣል

• የክትትል፣ ድጋፍና መማር ስርዓት ይዘረጋል

• በከፍተኛ አመራር የሚመራ የአፈጻጸም ግምገማና ግብረ መልስ ስርዓት ይዘረጋል።

5.1.3. የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት


• የአጋርነትና የትብብር ሞዴል ለመተግበር የሚያስችል ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ይተገብራል

• ደረጃ የትምህርት ቤቶች የአጋርነትና ትብብር ሞዴልን ያስተዋውቃል፣

• በወረዳ ደረጃ የአጋር አካላት ልየታ ያካሄዳል፣

• የዞን/ክፍለ ከተማ መነሻ በማድረግ አጋርነትና የትብብር የአሰራር ስርዓትን ለማጠናከር የመግባቢያ
ሰነድ ያዘጋጃል፣ይፈራረማል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣

19
• በትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም አተገባበር ጥንካሬና ክፍተት ይለያል፣

• ለወረዳ እና ለትምህርት ቤቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና ይሰጣል፣

• የክትትል፣ ድጋፍና መማር ስርዓት ይዘረጋል፣

5.1.4. በትምህርት ቤት ደረጃ


• የአጋር አካላት ትብብርን ለማጠናከር ዕቅድ ያዘጋጅል፣ ያስተዋውቃል፣ ይተገብራል፣

• በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ያሉ አጋር አካላትን ይለያሉ፣

• አጋር አካላትን በትምህርት ቤት ስራ አመራር ላይ ያሳትፋል፣

• የትምህርት ቤቱን አጠቃላይ አፈጻጸም ደረጃ በግብአት፣ በሂደት እና በውጤት ይገመግማል፣

• የትምህርት ቤቱን ጥንካሬና ክፍተት ይለያል፣

• የአጋር አካላትን እና ሚናቸውን (በህብረተሰብ ተሳትፎ፣ በመማር ማስተማር፣ በክትትልና ድጋፍ)


ይለያል

• የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል ግብ ይጥላል፣ ለማሻሻል በጋራ ይሰራል

• የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻያ ስልቶች ያዘጋጃል፣

• የአጋርነት/ሽርክናና ትብብር መግባቢያ ሰነድ ያዘጋጃል፣ ይፈራረማል፣ በስምምነቱ መሰረት


ይፈጽማል፣

• የትምህርት ቤት መሻሻል ኮሚቴ ስራውን እንዲያስተባብር ያደርጋል፣

• የደራጀ የክትትል ግምገማና መማር ስርዓትን ተግባራዊ ያደርጋል፣

5.2. የተጠያቂነትና የማበረታቻ ስርዓት


5.2.1. የተጠያቂነት ስርዓት

የተጠያቂነት ስርዓትን በየደረጃው ተግባራዊ ለማድረግ ክልሎች እንደ አስፈላጊነቱ የክልሉን ነበራዊ ሁኔታ
በመዳሰስ የተጠያቂነት ስርዓት ያዘጋጃሉ።

5.2.2. የማበረታቻ ስርዓት

20
በዚህ ስምምነት ሰነድ ውስጥ በተገባው ስምምነት መሰረት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ያሻሻሉ ትምህርት
ቤቶች፣ ባለሙያዎች እና አመራሮችን ለማበረታታት የማበረታቻ ስርዓት ይዘረጋል።

ክፍል ስድስት

ክትትል ግምግማና መማማር


6.1. ክትትል

ክትትል የታቀዱ ዓላማዎች በግባትና በውጤት ዕድገታቸው የሚመዘንበት ተከታታይ ግምገማ ነው።

በመሆኑም የትብብራዊ አጋር አካላት እንቅስቃሴአቸውንና ግስጋሴቸውን በመገምገም የተቀመጡት

አላማዎች በምን ያህል ደረጃ መሳካታቸውን በማረጋገጥ ለቀጣዩ ሂደት እርምጃዎችን

የሚተልሙበትና ተከታታይ የስራ አቅጣጫዎች የሚያመለክቱበት ክትትላዊ ዘዴ ሆኖ ያገለግላቸዋል።

በትብብራዊ አጋርነት አካላቱ የክትትል ተግባራት በተቻለ ፍጥነት ትክክለኛ ወይም ሊሆኑ የሚችሉ

ስኬቶችን ወይም ውድቀቶችን በመለየት እና ወቅታዊ ሁኔታዎችን በማመቻቸት በሂደት

ማስተካከያዎች ይደረጋሉ። የክትትል ውጤት መረጃን ከመሰብሰብ ባለፈ ይልቁንም ፕሮግራሞችን እና

እንቅስቃሴዎችን በረጅም ጊዜ ለማሻሻል የታሰበ ነው። በትብብራዊ አጋርነት የክትትል ሥርዓቱ

ሁኔታዎችን ይፈትሻል፤ ውጤቱን ይረዳል፤ በመጨረሻም ሁኔታውን በማሻሻል እርምጃዎችን ይወስዳል።

21
የክትትል ውጤቶች ለታዩ ችግሮች መፍትሔ በመጠቆም ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸው። ስለሆነም
በትብብራዊ አጋርነት ትግበራ ወቅት በሂደት የተገኙ የክትትል ውጤቶች በትምህርት ቤቶች የሚደረጉ ዓመታዊ
ዕቅዶችንና ስራ ማስኬጃ በጀቶችን ከማሻሻላቸው ባሻገር በአጋራት መካከል የሚከናወኑ የጋራ ስምምነቶች
ወደተግባር መመንዘራቸውን መከታተያና ውጤቱም ለስራዎች መሻሻል ትልቅ አቅም እንዲፈጠር ይደረጋል።

6.2. ግምግማ
ግምገማ መረጃዎች በተደራጀ ሁኔታ የሚሰባሰቡበትና የሚተነተኑበት ሥርዓት ነው። በመሆኑም በትብብራዊ
አጋርነት የስራ ክንዋኔዎች የመጡት ለውጦችና የተገኙ ፋይዳዎች ይገመገማሉ፤ ይህንንም በማድረግ
የመርሀግብሩ ብቃት፣ ውጤታማነት፣ ተገቢነትና ዘለቄታዊነቱ ይዳሰሳል። የግምግማውም ሂደት በአጋር
ድርጅቶች ወይም ግለሰቦችና በትምህርት ቤቱ መካከል በተገባው ስምምነት መሰረት ይፈፀማል።

6.3. መማማር
መማማር በትግበራ ሂደት ተገኙትን ምልካም ልምዶችና ተሞክሮዎች በመቀመርና በማሰራጨት የተሻለ
ትምህርትና ቅስሞሽ ለቀጣዩ እንቅስቃሴ የምንጠቀምበት የመማማሪያ ዘዴ ነው።በተመሳሳይ ሁኔታ
በትብብራዊ አጋርነት መርሀግብር ውስጥ አፈፃፀም የተገኙ መልካም የስራ እንቅስቃሴዎችን አጉልቶ
በማውጣት ለተሻለ ትግበራ መጠቀም ያስፈልጋል።ከተቻለም ሌሎች የትብብራዊ አጋርነት አካላት በልምዱ
እንዲጠቅሙ ለማድረግ ተሞክሮዎቹን በመቀመር ማስተላለፍ ተገቢነት ይኖረዋል።

7. ማጠቃለያ

የአጋርነትና የትብብር ሞዴልን በትምህርት በቶች በትክክል ተግባራዊ በማድረግ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል
እንደሚቻል ይታመናል። ስለሆነም ሞዴሉ በትምህርት ቤት ውስጥ እና ውጭ የአሉ አቅሞችን አቀናጅቶ በመጠቀም
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል እና የትምህርት ቤቱ ማህነረሰብ ትምህርት ቤቶችን በባለቤትነት እንዲመራቸው
የሚያስችል ነው። የትምህርት ቤቱ አመራር ከትምህርት ቤት ውጭ ያሉ አካላት ከእቅድ ዝግጅት እስከ ትግበራ ድረስ
እንዲሳተፉ እና የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ማድረግ ይኖርበታል። እንዲህ ሲሆን የትምህርት ቤቶችን ደረጃ
በዘላቂነት ማሻሻል ያስችል። ይህ ሲሆን የተማሪዎች ውጤት እና ስነምግባር አብሮ እንዲሻሻል ያደርጋል። ስለሆነም
ይህንን ሞዴል ተግባራዊ ለማድረግ ከላይ እስከ ታች ያለው የትምህርት መዋቅር እጅ ለእጅ ተያይዞ ተግባራዊ ሊያደርገው
ይገባል።

22
ተቀጽላ አንድ

የአጋርነት/ሽርክና እና ትብብር ሞዴል የስምምነት ሰነድ

በ [የአጋር አካል ሙሉ ስም]


እና
[የትምህርት ቤት ሙሉ ስም]
መካከል የተደረገ የጋራ መግባቢያ ሰነድ (Momorandum of Understanding)

ይህ የመግባቢያ ሰነድ በቀን_____________በ[የአጋር አካል ሙሉ ስም] [የድርጅቱ አድራሻና ሁኔታ


ይጠቀሳል] እና [የአጋር አካል ሙሉ ስም (የት/ቤቱ ስምና እድራሻ )ይጠቀሳል] መካከል የተደረገ
የአጋርነት ትብብር ውል ነው።

I. መግቢያ
ሁለቱ አጋር አካላት [ አጋር አካል ] እና [ ትምህርት ቤት ] ይህን የመግባቢያ ሰነድ ሲፈርሙ
ዓላማቸው ያደረጉት በትምህርት ቤተ ውስጥ ያሉትን ክፍተቶች በመለየት በትምህርት ጥራት
መሻሻል ላይ በመስራት የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር በሚሻሽሉ ተግባራት ላይ በጋራ
በመሰማራት አገልግሎት መስጠት ነው። በዝግጅት ሂደቱም የትምህርት ቤት፣
የወላጆች፣የተማሪዎች፣ የማህበረ ሰብ፣ የግል ተቋማት ተወካዮች ይሳተፋሉ።.

የፕሮግራሙ ዓላማ የትምህርት ሚኒስቴር በ 2014 ዓ.ም ካወጣው ዝርዝር መመሪያ ጋር በቀጥታ
የሚዛመድ ሆኖ

 ተማሪዎች አካዳሚያዊ ክህሎትን እንዲያሳድጉ ማገዝ፣


 ተማሪዎችን በተለያዩ የተግባር ዘርፎች ማሳተፍና
 ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርት ማገዝ የሚችሉበትን አቅም ማሳደግና በመሳሰሉት
ተግባራት ዙሪያ ይሆናል።

23
[አጋር አካል] በሰነዱ የተቀመጡትን ዓላማዎች ዕውን ለማድረግ የራሱን ጥረት
ያደርጋል።በማስቀጠልም ሰነዱ በአጋር አካላት መካከል መፈጠር ያለባቸውን የስራ ግንኙነቶችና
የቅንጅት ማዕቀፍ ዘርግቷል፤በማከልም ለፕሮግራሙ ማስፈፀሚያ የሚውለውን በጀትና ከያንዳንዱ
የሚጠበቀውን ሀብትና አገልግሎት በግልጽ አስቀምጧል። .

II. ዓላማ
የስምምነቱ ዝርዝር ዓላማ ይጠቀሳል

III. በአጋር አካል እና በትምህርት ቤቱ መካከል የሚኖረው የትብብር ዓይነት ይገለፃል

ለምሳሌ:
 የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት - የትምህርት ቤቱን መምህራን፣ አመራር፣ ተማሪዎች እና ወላጆች
የሚያካትት የዕውቀት ሽግግር ሊሆን ይችላል
 የገንዘብ ድጋፍ - የትምህርት ቤቱን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ የገንዘብ ድጋፎች ሊሆኑ ይችላሉ

IV. በዚህ የመግባቢያ ሰነድ የአጋር አካሉን ኃላፈነቶች ማስቀመጥ

ለምሳሌ:
 አጋር አካሉ ከትምህርት ቤቱ ጋር በዚህ ውል መሰረት ለሁለቱም የጋራ ጥቅም የሚያከናውናቸው
ተግባራት ተለይተው ይገለፃሉ።

V. በዚህ የመግባቢያ ሰነድ የትምህርት ቤቱን ኃላፈነቶች ማስቀመጥ

24
ለምሳሌ:

 በመግባቢያው ሰነድ መሰረት የክንውን ዕቅዱ ባስቀመጠው ልክ ትምህርት ቤቱ ከአጋር አካሉ ጋር


በጥምረት የሚሰሩ በጎ ፈቃደኞችን ይመድባል።

VI. የሁለቱ አጋር አካላት የግንኙነት አድራሻዎች

1. [አጋር አካል ተቋም]:


[የአጋር አካል ተጠሪ ስም]
[ማዕረግ]
[አድራሻ]
[የስልክ ቁጥር]

2. [ትምህርት ቤት ]:
[የአጋር አካል ተጠሪ ስም]
[ማዕረግ]
[አድራሻ]
[የስልክ ቁጥር]

VII. የመግባቢያ ውሉ የሚፀናበት እና የሚሻሻልበት ጊዜ

ይህ የመግባቢያ ውል በሁለቱ አካላት ከተፈረመ በኃላ የፀና ሲሆን ውሉ [ለሁለት (2)] ዓመት ያገለግላል።
ውሉን ያለሁለት ስምምነት መሰረት ማንኛውንም ሀሳብ መጨመር መቀነስ ወይም ማሻሻል አይቻልም።
ሁለቱ አካላት በውሉ ማቢቂያ መጨረሻ ዓመት ላይ በፅሁፍ በሚያቀርቡት የጋራ ሓሳብ ለተጨማሪ ዓመታት
ውሉን ሊያድሱ ይችላሉ። እንዲሁም የመግባቢያ ውሉን ሁለት አጋር አካላት ከተስማሙ ውሉን በጽሁፍ
ማደስ ወይም መሰረዝ ይችላሉ።

25
ሆኖም ማንኛውም አጋር አካል በሆነ ምክንያት በማንኛውም ሰዓት ውሉን ከሁለት ወር በፊት በጽሁፍ
በማሳወቅ ውሉን መሰረዝና የገንዘብ ድጋፍም ሆነ እገዛውን ማቆም ይችላል።

በዚህ ውል ውስጥ አጋር አካላቱ በማናቸውም ላይ ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያዋጡ ወይም እንዲደጉሙ ጫና
አያደርግም።በተጨማሪም አጋር አካላቱ በማናቸውም መልክ የአጋርነትን ዓላማ በሚጥስ ሁኔታ የጋራ የንግድ
ሽርክና ማቋቋም አይቻልም።

VIII. አለመግባበቶችን ማስወገድ

አጋር አካላቱ በተጋባው የውል ቃል መሰረት በመሃከላቸው ምናልባት አለመግባባት ቢፈጠር በመጀመሪያ
ጉዳያቸውን በግላቸው ተወያይተው ይፈታሉ። በአጋጣሚ መግባባት ላይ በ 60 ቀናት ባይደረስ በሌላ የግልግል
አካል አለመግባባቱን ያስወግዳሉ።, ይህም ካልተሳካ አንደኛው አጋር አካል መብቱን በሕግ ሊያስከብር ይችላል።

ይህ ውል መግባባት በሁለቱ አጋር አካላት በፊርማ ካልፀደቀ በስተቀር ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም።

ለ [የአጋር አካል ስም] ለ [የትምህርት ቤት ስም]

26
[ስም] [ስም]
[ማዕረግ] [ማዕረግ]

ቀን: ቀን

ፊርማ________________________________
ፊርማ________________________________

ውሉ የሚጠናቀቅበት ጊዜ:

(አስፈላጊ ከሆነ የሚጨመር)

ፊርማ
የእማኝ ስም ቀን

ፊርማ
የእማኝ ስም ቀን

27
ተቀጽላ ሁለት

የትምህርት ቤት አጋር አካላት ግብረኃይል የስራ እንቅስቃሴ መከታተያና


መገምገሚያ ቼክሊስት

ይህ ቼክ ሊስት የትምህርት ቤት የአጋር አካላት ግብረኃይል/ኮሚቴ የግማሽ ወይም የሙሉ ዓመት የስራ ክንውን
ለመከታተልና ለመገምገም የሚያስችል መሣሪያ ነው።ቼክ ሊስቱ ክትትልና ግምገማ ከማድረግ ባሻገር እንደሁኔታው
መሣሪያውን እንደአካባቢ ሁኔታ በማዛመድ ለግለ-ግምገማ መገልገል ይቻላል። መጠይቁ በሚሞሉበት ወቅት
በተስማሙበት ስፍራ /ሳጥን ውስጥ የ “X” ምልክት በማድረግ ያሳዩ። በመጨረሻ ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽዎን
በጽሁፍ ያስፍሩ።

ክፍል አንድ :- ቅድመ ዝግጅት

ተ.ቁ የትኩረት ነጥቦች አዎ አይደለም በተወሰነ የተለየ


ሓሳብ
ደረጃ

1 የትምህርት ቤት አጋር አካላትን ለማቋቋም በቂ


ዝግጅት ተደርጓል

2 ለት/ቤት አጋር አካላት በታቀደው መሰረት ከ 5


ያላነሱ አባላት ተለይተዋል

3 የት/ቤት አጋር አካላት በተቋቋመው ግብረኃይል


/ኮሚቴ በተሟላ ሁኔታ ይሳተፋሉ

4 ፕሮግራሙን ለማገዝ/ለማስተባበር ት/ቤቱ በቂ


የሰው ሀይል መድቧል

5 ለአጋር አካላት/አባላት በቂ የትውውቅ ስልጠና


ተስጥቷል

6 ት/ቤቱ ከአጋር አካላቱ ጋር የስምምነት ሰነድ


ተፈራርሟል

7 ፕሮግራሙን ለመምራት የሚያስችል ግቦችና


ዕቅዶች ተዘርግቷል

8 የታቀዱትን ተግባራት ለማከናወን በቂ ሀብት


ተሰብስቧል

9 የአጋር አካላት ኮሚቴ/ግብረሃይል አባላት የስራ


ድርሻና ኃላፊነት ክፍፍል አድርገዋል

28
ክፍል ሁለት:- በትግበራ ወቅት

ተ.ቁ የትኩረት ነጥቦች 1 2 3 4 5

10 አጋር አካላት በትግበራ ወቅት አደረጃጀት


መስርተው በቅንጅት ስለመስራታቸው

11 በት/ቤቱና በአጋር አካላት መካከል


የተመሰረተው ፕሮግራም ባግባቡ
ስለመከናወኑ

12 በህብረቱ ከግቡ አንፃር የተመዘገቡ ውጤቶች


/ስኬቶች ደረጃ

13 በአጋር አካላት መካከል የተፈጠረው ጤናማ


ግንኙነት ደረጃ

14 በትግበራ ወቅት የአጋር አካላት ተሳትፎ


መጠን

15 በትግበራ ወቅት የአመራር ብቃት

16 የስብሰባ/ የግንኙነት ሰዓታት ባግባቡ


ስለመከበራቸው

17 አለመግባባቶች ሲከሰቱ ችግሮችን ለመቅረፍ


/ለማስወገድ የሚደረጉ ጥረቶች

18 የአባላትን አቅም ለማሳደግ የተከናወኑ


ተግባራት

19 የት/ቤቱን መሠረተ ልማት ለማሳደግ


የተከናወኑ ተግባራት/የተደረገ ድጋፍ

20 የመማር ማስተማሩን ስራ ለመደገፍና


ለማሻሻል የተሰሩ ስራዎች ስኬት

21 የት/ቤቱን ደረጃ ለማሳደግ የተደረጉ


ጥረቶችና የተገኘ ውጤት

22 ፕሮግራሙ በተያዘለት ዕቅድና መርሀግብር


ስለመከናወኑ

ክፍል ሦስት:-ማጠቃለያ

23. በሂደት ከአጋር አካላት መካከል የአጋርነቱን ስራ የቋረጡ/ያቆሙ አጋር አካላት አሉ? አሉ የሉም

29
ካሉ ያቋረጡበት ምክንያት ቢጠቀስ/ቢብራራ
______________________________________________________________________________
______________________________________________________________________________
____________________________________________________________

24. የአጋር ትብብሩ ግብረሀይል ያከናወናቸው ቁልፍ ስራዎችና የተገኘ ውጤት ቢገለጽ
______________________________________________________________________________
______________________________________________________________________________
___________________________________________________________________
25. በፕሮግራሙ የትግበራ ሂደት የታዩ ጥንካሬዎች
______________________________________________________________________________
__________________________________________________________________
26. በፕሮግራም የትግበራ ሂደት የታዩ ድክመቶች /ክፍተቶችና የተሰጡ መፍትሔዎች
______________________________________________________________________________
_______________________________________________________________________
27. ባጠቃላይ የፕሮግራሙ የስኬት ደረጃ እንዴት ይገመግሙታል/ይገልጹታል?
______________________________________________________________________________
_________________________________________________________________________

30

You might also like