You are on page 1of 26

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር

የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ

ልማት ጽ/ቤት

የ 2013 ዓ.ም በጀት ዓመት

መሪ ዕቅድ፡፡

ሰኔ 2012 ዓ.ም

1
መግቢያ

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት የሀገሪቱን የከተማ አስተዳደሩን
ፖሊሲና ስትራቴጂ እንዲፈፅሙ ከተቋቋሙት ጽ/ቤቶች አንዱ እንደመሆኑ መጠን በክ/ከተማችን
የተጀመረውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግና የህ/ሰቡን ተጠቃሚነት
ለማረጋገጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል፡፡የክ/ከተማችን ነዋሪም በልማት መስክ ተጠቃሚነቱን
ለማረጋገጥ በተለያዩ የስራ ዕድሎች በተደራጀ መንገድ ተሳታፊነቱን በተግባር በማረጋገጥ በርካታ የልማት
ሥራዎችን እያከናውነ መጥቷል፡፡ የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ጽ /ቤት በስሩ በተዋቀሩት ሁለት ቡድኖች
መካከል ማለትም የአካባቢ ብክለትና የአየር ንብረት ለውጥ ፤እንዲሁም የአረንጓዴ ቦታዎች አያያዝና
አጠቃቀም ክትትል ቁጥጥር ቡድን ናቸው፡፡ ስለዚህ ከላይ የጠቀስናቸው ሁለት ብድኖች ውጤታማ ሊሆኑ
የሚችሉት ተቋሙ በተደራጀ አግባብ መምራት ሲችልና ርብርብ ሲያደርግ ነው፡፡ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ
በክ/ከተማችን ደረጃ ቁልፍ አጀንዳ እየሆነ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ጽ/ቤቱም ስለአካባቢ ጉዳይ ልዩ ትኩረት
በመስጠት መላ ህ/ሰቡ ከብክለት የፀዳ አካባቢ የመኖር መብቱ እንዲጠበቅ ሚዛናዊ የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም
እንዲሰፍን ከአካባቢ ጋር የተጣጣመ ዘላቂ ልማት እንዲኖር ከፍተኛ ጥረት እያተደረገ ቆይቷል፡፡ ህዝብን
ተደራሽ ለማድረግ በተዘረጋው አሰራር እስከ ወረዳ ድረስ በማጠናከር የሚሰጡ አገልግሎቶችን የደንበኛ እርካታ
የሚያረጋግጡ ፣የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁና ፍትሃዊ እንዲሆኑ በተቀመጠው የዜጎች ቻርተር መለኪያ
ስታንዳርድ ተገልጋዮች መብታቸውን ተጠቅመው አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ
ሁኔታዎች የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ሥርዓት በመዘርጋት የተሻለ አፈፃፀም ለማምጣት ጥረት ተደርጓል፡፡
የተጀመረውን የልማት ሠራዊት ግንባታ የተሟላ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር በፀረ -
ኪ/ሰብሳቢነት ላይ የተጀመረውን የሰላ ትግልአጠናክሮ በመቀጠል ልማታዊ ፖለቲካዊ ለውጥ ለማረጋገጥ
የ 2013 በጀት ዓመት ግልጽ አቅጣጫ በመያዝ ወደ ተሟላና ወደ ተሟሟቀ ሥራ የምንገባበት የበጀት ሲሆን
የበጀት አመቱ መነሻ እቅድ እንደሚከተለው ማቅረብ ተችሏል ፡፡

የዕቅዱ መነሻ ሁኔታ፡-

2
- የ 2012 በጀት ዓመት የስራ አፈፃጸማችን ገምግመን የነበሩብንን ጠንካራና ደካማ ጎኖቻችንን ለይተን የአሰራር
አቅጣጫ አስቀምጠን ለቀጣይ ሥራችን መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ ዓበይት ጉዳዮች በመለየት ለ 2013 በጀት

ዓመትቅድመ ዝግጅት ተደርጓል፡፡


- በ 2012 ተግባር አፈፃፀም የቁልፍ ተግባርና የዓበይት ተግባራት አፈፃፀም በባለፈው በጀት ዓመት ዕቅድ

አፈፃፀም የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ሪፖርት በማዘጋጀት ዕ/ቤቱና የወረዳ ሞያተኞች እንዲመዘኑ ተደርጓል ፡፡

የ 2012 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም በፅ/ቤትገ ምግመን ለቀጣዩ ለ 2012 ዓ.ም ለስራችን መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ

ዓበይት ጉዳዮች ለመለየት ተችሏል፡፡ ስለሆነም አደረጃጀትን አሰራርን እስከ ታችኛው እርከን በማጠናከር

የሚሰጡ አገልግሎቶችን ግልፅነትና ተጠያቂነት ያላቸው የህ/ሰቡን እርካታ የሚያረጋግጡ የጥራት ደረጃቸውን

የጠበቁ አሰራሮችን መዘርጋትያስፈልጋል፡፡


- ስለሆነም ጽ/ቤቱ የአካባቢ ብክለትና የአየር ንብረት ለውጥ የአረንጓዴ ቦታዎች አያያዝና አጠቃቀም ክትትል

ቁጥጥር ቡድን በድምሩ ሲታይ የተራቆቱ ቦታዎች መለየት፤የተለያዩ ችግኞች መትከል እና መንከባከብ

፤የድምጽ፣ የአየር፤ የውሃ፤ የአፈር፣ የኬሚካል፣ የደረቅ ቅሻሻዎች ብክለት አወጋገድና የተጀመሩትን የልማትና

የመልካም አስተዳደር ተግባር ቀጣይነት እንዲኖረው ያቀድነውን በመተግበር የመላ ህ/ሰቡ ተጠቃሚነትና

ተሳታፊነት ከመቼውም ጊዜ በተሻለ መልኩ በማጎልበት የባለድርሻ አካላት የሆኑትን አደረጃጀቶች የህ/ሰቡ

ጥንካሬ ለስራችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖረው መነሻ ሁኔታዎቹ የያሉበትን ደረጃ የ 2012 አፈፃፀም

በጥንካሬም በክፍተትም እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርቦ ማየት የሚያስፈልግ ይሆናል በዚህ መሰረት

የክ/ከተማችን ነባራዊ ሁኔታን የገናዘበ መሆን ስላለበት የክፍለ ከተማችንን ሁኔታ ስንመለከት ፡፡
- ክ/ከተማችን ከመሬት አቀማመጧ ጋር ተያይዞ ወጣ ገባነት የበዛበት በሱማሌ ተራ፤ አምባሳደር፤ ቀጨኔ፤ ቀበና፤

ግንፍሌ፤ ራስ መኰንን ድልድይ፤ ባሻ ወልዴ ቁጥር አንድና ሁለት፤ አሮጌ ቄራ በትላልቅ ወንዞች የተከበበች ናት፡፡

እንዲሁም የአብዛኛው የህ/ሰብ ክፍል የሚጠቀምበት መፀዳጃ ቤት ባህላዊና ዘመናዊነት ያልተከተለ ፍሳሽ ወደ

ወንዝ የሚለቀቅበት የጋራዦች፤ የፋብሪካዎች፤የመኪና እጥበት የሆቴሎች ተረፈ ምርቶች አደገኛ ቆሻሻ ወደ

ወንዝ የሚለቀቅበት ክ/ከተማ በመሆንዋ ወንዞቻችን ከመነሻ እስከ መድረሻ እየተበከሉ ይገኛሉ፡፡ ይህ

ችግርየተፈጥሮ ሃብት መመናመንን እንደሚያስከትል ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም ከድምፅ ብክለት፤ከአየር፤ ከውሃ

ብከለት፣ከደረቅ ቆሻሻ፣ ጋር ተያይዞምውስብስብ ችግሮች ያሉባት ክ/ከተማ ናት ፡፡ ይህንንም ሴክተር ጽ/ቤቱ

ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ይህንን የአካባቢ ችግር ለመታደግ በርካታ ተግባራት እያከናወነ የመጣ ቢሆንም

ችግሩ አሁንም ገና ቀጣይ ርብርብ የሚያስፈልገው ይሆናል፡፡

የክ/ከተማው አመራር ሁኔታ፡- የክ/ከተማው አመራር ሲባል በፅ/ቤቱ ያለ ዋናው አመራርና የብድን

አመራሮችን ሲሆን አጠቃላይ ሁኔታወቻቸውን ስንመለከት እንደሚከተው ለማቅረብ ተችሏል

3
 ከአመለካከት አንፃር፡-ቁልፍ የሆነውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ግቦችን ለማሳካትየህ/ሰቡን ተጠቃሚነት

ለማረጋገጥ በፀረ-ኪ/ሰብሳቢነት ትግል የሚያደርጋቸው ጥረቶች በጥሩ ጎኑ የሚጠቀሰውን አመራሩ ከጊዜ ወደ

ጊዜ ልምድ እያደገና እየተሻሻለ የመጣበትና የሥራ ተነሳሽነቱ እየጎለበት መጥቷል ተግባር እንደቁልፍ ተግባር

በመውሰድ ተግባራትን በሰራዊት አቅም ለመምራትና ሰራዊት ለመፍጠር የተደረጉ እንቅስቃሴወች፡፡

 በድክመት፡ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ እየገመገሙ ያሉትን ጠንካራና ደካማ ጎኖችን እየለየ ተከታታይ ውይይት

በማድረግ ላይ ውስንነቶች ታይቷል በተወሰኑ ወረዳወች ለችግኝ ማጓጓዝያ መኪና የማመቻቸት ችግር መኖር

አለአግባብ በመውደቃቸው ምክኒያት ቤት ሊያፈርሱ የተዘጋጁ ዛፎችን ጉዳይ አስተባብሮ መፍትሄ ያለመስጠት

ችግር፣ ፡፡

 ከክህሎት አንፃር፡- ከላይ የሚወርዱ ተግባራትን ወደ ታች አውርዶ እንዲፈጸሙ የሚያደርጓቸው

የክትትል አግባቦች

- የፅሕፈትቤቱ ተግባራት ኣፈፃፀም በየግዜው እየገመገሙ በመሄድ ያልተተገበሩ ስራዎችን በማስጀመርና

በተሻለመልኩ የተከናወኑትን እውቅና በመስጠትፈፃሚን በማብቃት በኩል መሻሻሎች ታይቷል፡፡ ሙሉ ጊዜውን

ለስራ መስዋዕት ማድረግ፤ተግባራትን በየጊዜው እየገመገሙ ለመሄድ የተደረገው ጥረት፣አሰራሮችን

አስቀምጦ እስከ ወረዳ ድረስ የተደረገው የድጋፍና ክትትል አግባብ በማስቀመጥ በስራቸው የሚገኙ

ባለሞያዎች ለማብቃት የተለያዩ ስልጠናወች አዘጋጅተው የሰጡበት ሁኔታ፤ተግባራትን እያከፋፈሉ

መስጠትና ቆጥሮ መቀበል ለባለሞያ አቅም ሆኖ መሄድ የተሸለ ነበር ማለት ይቻላል

 ክፍተት፡-በፅ/ቤቱ እለ አካባቢ ብክለት የግንዛቤ ለመፍጠር ብዙ ጥረት ተደርጎ መሻሻሎች ቢኖሩም አሁንም

ያልተሻገርናቸው ችግሮች መኖራቸው፡፡

 ከግብዓትአኳያ፡-ለስራ አስፈላጊ የሆኑ የሰው ሃይልና የማቴሪያል እጥረቶች ለማስተካከል ተሞክሯል፡፡

- በፅ/ቤቱ የነበረው የባለሞያ ለማሟላት የተደረገው ጥረት በጥንካሬ የሚወሰድ መሆኑ ፡

- ለስራ አስፈላጊ የሆኑ የሰው ሀይልና የማትሪያል እጥረቶች ለማስተካከል ተሞክሯል

- በፅ/ቤቱ የነበሩ የቢሮና የቁሳቁስ ችግሮች ለመፍታት የተሄደበት ጥረት

- ብዙ ጊዜ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ የቆየው የሰራተኞች የሴፍቲንግ ማትሪያል መግዛት የተጀመረበት

ሁኔታ በጥንካሬ መውሰድ ያስፈልጋል


- በድክመት፣ፅ/ቤቱ ተሸከርካሪ የሌለው በመሆኑ ስራ በአግባቡ ለመስራት እንቅፋት ስለሆነ በትግል ጽ/ቤቱ ላይ

መኪና እንዲመደብ ያለማድረግ

4
- በፅ/ቤቱ የማተሪያል እጥረቶች ለማስተካከል የተካሄደው ጥረት ጥሩ ቢሆንም አብዝሀኛው ማተሪያሎች

በሁለተኛው መንፈቅ የተገዙ ከመሆናቸው አንፃር የ 1 ኛ መንፈቅ አመት ስራችን ላይ ተፅእኖ ነበራቸው ቀጣይ

ማስተካከል የሚገባን መሆኑ

የወረዳ አመራር ሁኔታ


- የወረዳው አመራር ስለአካባቢ በቂ የሆነ ግንዛቤ በአካባቢ እየደረሰ ያለውን ችግር ትኩረት እየሰጡ አለመሄድ

የክህሎትና የአመለካከት ክፍተት እንዳለ በግልጽ ያመለክታል ስለዚህ በ 2013 ዓ.ም ለአጠቃላይ አመራር

ስለአካባቢ ጉዳይ ግንዛቤ መፍጠር የግድ ይላል፡፡


- ከሶስቱ የልማት ክንፎች አንዱ የመንግስት ክንፍ የምንለው ዋናውና የልማት ተዋንያን የመንግስት ሠራተኛ

እንደመሆኑ መጠን በሠራተኛው የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የሰው ሃይል ልማት ልዩ ትኩረት የሚሰጠው

ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህም ተከታታይነት ባለው መልኩ በአስተሳሰብና በክህሎት አቅምን የመገንባት እንዲሁም

ፍትሃዊ የሆነ የሰው ሃይል አስተዳደር ሥርዓት ለመዘርጋት ጥረትማድረግ ዋናው ነው፡፡ ሠራተኛው በመንግስት

ፖሊሲ ስትራቴጂ በለውጥ ሥራዎች ተከታታይ ግንዛቤና የማብቃት ሥራ መስራት፡፡ ስለዚህ ፈፃሚ

ኪ/ሰብሳቢነትን ከመጠየፍ አደጋውን ተረድቶ ራሱን ለውጦ ሌሎችን በመታገል የሚደረገውን እንቅስቃሴ

ያለበት ሁኔታ መልካም ነው፡፡ አሁንም ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት የተቀናጀ ትግልና ርብርብ ይጠይቃል፡፡

ከክህሎት አንፃር፡-ፈፃሚው አደረጃጀቶችን፤ አሰራሮችን፤ መመሪያዎችን፤ ደንቦችን በአግባቡ ተገንዝቦ በጥራትና በጊዜ

በመፈጸም፣ዕቅድ አዘጋጅቶ እንዲፈፅም በየደረጃው የተደረገው የድጋፍና ክትትል አግባብ የተሸለ ነው፡፡

ቢሆንም የተስተካከለና የተሟላ ዕቅድ ከማቀድና ተግባራትን በተያዘላቸው መርሀ ግብር መሰረት ሁሉንም

እቅዶች ከመፈጸም አንፃር እጥረቶች የተስተዋሉ ችግሮች ለይተው ግብረ መልስ እየሰጡ መሄድ ላይ

ችግሮች ታይተዋል፡፡

ከአመለካከት አንፃር፡-የአካባቢ ጥበቃ ተግባራት በአግባቡ ይዞ በስራቸው ያሉ ባለሞያወች ወደ ተግባር ከማሰማራት

ይልቅ በአንዳንድ ወረዳወች ባለሞያወችን ወደ ሌላ ጽ/ቤት በማዘዋወር እንዲሰሩ የማድረግ ሁኔታወች ታይቷል፡፡
የክፈለ ከተማው ባለሞያ ሁኔታ
ከአመለካከት አንፃር፡-ስንመለከት የተሰጣቸውን በሃላፊነት መንፈስ ለመፈፀም የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ከጊዜ

ወደጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱ፤የእርሰበርሱ ትግል እየተጠናከረ መምጣቱ፤ቁለፍ ተግባሮችንና አበይ ተግባሮችን

ለይቶ ውጤት ለማምጣት ርብረብ ማድረጉ በጥሩ ሁኔታ የሚያዝ ሲሆን ሞርኒግ ብሪፊንግ እየገመገሙ

ከመስራት አንፃር መሰተካከል የሚገባው መሆኑ ታይቷል፤በተጨማሪም ሰ ዓት መሸራረፍ የሚታይ ሲሆን

ቀጣይ መስተካከል ይኖርበታል

5
ከክህሎት አንፃር፡- ቁልፍና አበይት ተግባራትን አቅዶ ወደስራ መገባቱና ርብርብ መደረጉ በጥንካሬ የታ

ቢሆንም የእቅድ ጥራትን በተመለከተ በሚቀጥለው የሚስተካከል መሆኑን ተረድተናል

የወረዳ ባለሞያ ሁኔታ


በአመለካካት፡- በወረዳ ደረጃ የተወሰኑ ሞያተኞች በተደራጀ አግባብ ከሚመለከታቸው ጋር ቁልፍ ና
አበይት ተግባራትን በባለቤትነት እየገመገሙ መስራት መሞከራቸው እነደ ጥንካሬ የታየ ቢሆንም
አብዝሀኛወቹ በሚያስብል ደረጃ ተከታታይነት ባለው መልኩ ተግባሮቹን እየገመገሙ የለመስራት
ችግሮች የታዩ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት የሚሰተው ነው።በተጨማሪም ከፍተኛ የሆነ የጠባቂነት
ስሜት ይታይባቸዋል
ከክህሎት አንፃር፡-የተወሰኑ ሞያተኞች ቁልፍ ና አበይት ተግባራትን አቅደው ወደ ስራ የመግባት ሙከራ ቢኖርም
አብዝሀኛወቹ ቁልፍና አበይት ተግባራትን በጥራት አቅዶ በጥራትና በወቅቱ በጥራት ሪፖርት የለማድረግ ችግር

ታይቷል

በተደራጀ ሁኔታ አካባቢውን የማልማትና አቅም ያለው ህዝብ


- የክ/ከተማችን የህዝበ አደረጃጀቶች የተለያዩ የህ/ሰብ ክፍሎች በልማትና በመልካም አስተዳደር ሥራዎች ላይ
አዎንታዊ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
- የወጣቶችና የሴቶች አደረጃጀት ከፍተኛ የሆነ የልማትና የመልካም አስተዳደር ማለትም በ፤ በችግኝ ተከላ፤
በብክለት ቁጥጥር፤ ክትትል፤ የማይናቁ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ በተለይ በሴቶች ህፃናትና ወጣቶች፤ በንግድ
ተቋማት በድምፅ ብክለት በመከታተል በማጋለጥ የት/ቤት ክበባት በሰንደቅ ዓላማ ሰልፍ ስለአካባቢ ጉድለት
ትምህርት በመስጠት በሚኒሚዲያ ፕሮግራም በመወያየትአብዛኛው የህ/ሰብ ክፍል በተፈጠረው የዜጎች
የስምምነት ቻርተር መብትን በማወቅ ለመብት በመታገል አንድ እርምጃ ወደፊት መራመድን ያመለክታል፤
- ት/ቤቶች በአካባቢያቸው ችግኝ በመትከል የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው ያሳዩ ቢሆንም ሁሉም ት/ቤቶች በእኩል
ደረጃ ችግኞችን ወስዶ በፍጥነትያለመትከል ክፍተቶች ነበሩ፡

በጉድለት፡-በሚፈጠሩመድረኮች በስፋት አለመገኘት፤ ሁሉም ነገር መንግስት እንዲፈታው መጠበቅ፤መብትና ግዴታን

ሁለቱን አስተሳስሮ አለመሄድ፤ ግዴታን በተመለከተ በተለያዩ መድረኮች መንግስትና ህዝብ በጋራ መስራት አለብን የሚል

ከቃል ንግግር በዘለለ በተግባር አለመተርጎም

የህዝብ አደረጃጀት፡- የክ/ከተማችን ህዝብ አደረጃጀቶች ቀላል የማይባል የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት

እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ችግኝ መትከል ፣የችግኝ ጉድጓድ በመቆፈር አካባቢን የሚያቆሽሹ የሚበክሉ በመምከርና ጥቆማ

በመስጠት በርካታ የህዝብ ኃላፊነት ተግባራት አከናውነዋል፡፡

6
የባለድርሻ ጽ/ቤቶች ሁኔታ፡- በድምፅ ብክለት ከንግድና ኢንዱስትሪ፤ከደንብ ማስከበር፣ ከኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት፣ከምግብ

መድሀኒት ቁጥጥር ጽ/ቤትየተጀመሩትን ተግባራት በጋራ የተሰሩ መልካም ተግባራት ናቸው፤በተጨማሪምያለአግባብ

በወንዝ ዳርቻ የሚደፉ አፈር ቆሻሻዎች በጋራ ተቀናጅቶ ያለመስራት ከመሬት ልማት ማኔጅመንት አብሮ በመስራት

የተጀመሩ ነገሮች ቢኖሩም የወንዝ ዳርቻ ተለይቶ የወሰን ማስከበሩ በውል አለመቀመጡ በአረንጓዴ ልማት ላይ ሌላ

ግንባታ ሲሰራ እርምጃ አለመውሰድ፤በጉድለት የሚወሰድ ይሆናል፡፡

የ BPR የ BSC ተግባራት ያለበት ሁኔታ

- የ BPR የ BSC የአውቶሜሸን ስራ ጥሩ የሚባልና የአካባቢ ብክለትና የአየር ንብረት ለውጥ የአረንጓዴ
ቦታዎች አያያዝና አጠቃቀም ክትትል ቁጥጥር ቡድን እየተተገበረ መሆኑና ውጤቱም እስከ ፕርንት አውት
መደረጉ እንደ ጠንካራ የሚያዝ ነው፡፡

- ስኮር ካርድ እስከ ግለሰብ ካስኬድ እየተተገበረ መሄዱየ የሩብ አመቱና የአመቱ ሪፖርት መውጣቱ በጠንካራ

የሚወሰድ ተገባር ነው፡፡

የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በተመለከተ፡- ተቋሙ መጠቀም ያለበት ቴክኖሎጂ ውጤት ለመጠቀም ጥረት ያደረገ ቢሆንም

ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ የህ/ሰቡን እርካታ ማረጋገጥ ላይ በርካታ ተግባራት ይቀራሉ፤በኮምፒውተር በመታገዝ ተግባራትን

በስታንዳርዱ በስኮር ካርድ አውቶሜሽን በመስራት ተግባራትንበመለካት ያለ ጅማሮመልካም ነው፤

የባለድርሻ ተቋማት ትስስርና ያለበ ሁኔታ፡-ከንግድ ተቋማት፤ ከሆቴሎች፤ ከጭፈራ ቤቶች፤ ከት/ቤቶች ክበባት፤

ከማህበራት፤ ከፎረሞች ጅምር ስራው ጥሩ ቢሆንም እያበቁ ሞዴሎችን እየፈጠሩ መሄድ ላይ ክፍተት አለ፡፡በአጠቃላይ

ከሰራዊት ግንባታ አንፃር ጽ/ቤቱ ምቹ ሁኔታ ላይ ያለ ቢሆንም በሚቀጥለው ጀማሪ ሰራዊት ለመገንባት ሁሉ

አቅማችን አሟጠን መጠቀም ያስፈልገናል፡፡

ከመልካም አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥና ፍትሃዊነት፡- የምንሰጣቸውአገልግሎቶች በሁለት ብድን ሲሆን 15 ስታንዳርድ

የወጣላቸው ተግባራት ሲኖሩ ተግባራቱን ለማስፈጸም የአፈጻጸም የብክለት መመሪያ ባለመኖሩ ችግር ያለባቸውን

ተቋማት እርምጃ ለመውሰድ ችግር የገጠመን ሲሆን ለሚመለከተው ማለት ለኮሚሽን መሰሪ ቤቱ ያሳወቅን ሲሆን

በክ/ከተማችን የሚነሳውን የድምጽ በዘላቂነት ለመፍታት በ 2013 ዓ.ም በኮሚሽኑ የወጣውን የድምጽ መመሪያ

ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅብናል ፡፡

የፀረ- ኪ/ሰብ ትግል ማጎልበትና የኪ/ሰብሳቢነት ምንጭ መለየትና የማክሰሚያ ስትራቴጂ በተመለከተ፡-የኪ/ሰብሳቢነት

ምንጮችና የማክሰሚያ ስትራቴጂ በማዘጋጀት በተለይ በማርፈድና ቀድሞ በመውጣትብዙያልተሰራበት ቢሆንም

ተግባሩን በመተግበር ያለው ሁኔታ ጥሩ ነው ብለን ብንወስድም አሁንም ሞርኒግ ብሪፊንገ በለውጥ ቡድንና በፅ/ቤት

7
ደረጃ በግዜው እየገመገምን ምንጮችን ለይተን ህዝቡ በአግባቡ አሳትፈን እያጋለጥንና እያከሰምን

መሄድያስፈልጋል፡፡
ክፍል ሁለት

የ 2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ቁልፍ ተግባር የቁልፍ ተግባሩ አጠቃላይ ዓላማና ግቦች ዋና ዋና
ተግባራትና የአፈፃፀም አቅጣጫዎች፡፡

የ 2013 በጀት ዓመት የሴክተሩ ቁልፍ ተግባር


- የአካባቢ ብክለትና የአየር ንብረት ለውጥ የአረንጓዴ ቦታዎች አያያዝና አጠቃቀም ክትትል ቁጥጥር ቡድን

የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን በተደራጀ አግባብ በላቀ ደረጃ መፈጸም፤


- የኪ/ሰብሳቢነት ምንጮችን በመለየት በዚሁ ልክ የማክሰሚያ ስትራቴጂ በማዘጋጀት የኪ/ሰብሳቢነት
አመለካከትና ተግባር በማያቋርጥ ሁኔታ ማቆም
የቁልፍ ተግባሩ አጠቃላይ ዓላማዎች
- የኪ/ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ አመለካከትና ተግባር በማያዳግም ሁኔታ በማኮላሸት ከብክለትና ከተፈጥሮ

ሀብት መራቆት የፀዳች ክ/ከተማ በመፍጠር


- የልማት አጠናክሮ በመቀጠል የተፈጠረውን ልማታዊ መነቃቃት ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር የልማትና

የመልካም አስተዳደር ተግባሮቻችን አመርቂ በሆነ መንገድ ማስቀጠል ፤


- በክ/ከተማችን እየደረሰ ያለውን የብክለት ዓይነት መነሻና መድረሻ ፣ መንስኤና መፍትሔማስቀመጥ፤

- ብክለት የሚያደርሱ ተቋማትና አካላት ትምህርታዊ ግንዛቤ በማስጨበጥ በተደጋጋሚ የሚያጠፉትን


ደግሞ ስርዓቱን የጠበቀ ሕጋዊ እርምጃ በመውሰድ የአካባቢ ብክለት እንዲቀንሰ ማድረግ፡፡
- ሁሉም የንግድ ተቋማት እንዲሁም የህንጻ ግንባታዎች ህጋዊ በሆነው በአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ
ሥርዓት እንዲያልፉ የአሰራር ስርዓት በማመቻቸት ልማት እድገትና አካባቢ ተጣጥመው እንዲሄዱ
ማድረግ፤

- ትክክለኛ ጥናት መሠረት ያደረገ የአካባቢ የአረንጓዴ ልማት ስራ መስራት፤

- የክ/ከተማው ነዋሪ የሃይል ቆጣቢ ቴክኖሎጂንና አማራጭ ሃይል ምንጮችን እንዲጠቀሙ በማድረግ
መግዛት ለማይችሉና አቅመ ደካሞች በመስጠት የሃይል እጥረትን በመከላከል የህ/ሰቡ ኢኮኖሚያዊ
ማህበራዊና ከባቢያዊ ሁኔታ ማሻሻል፤

8
- ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት በማስፋፋት የአገልግሎት ፍትሃዊነትን ተደራሽ በማድረግ በበጀት
ዓመቱ የተያዙ ግቦችንበቁርጠኝነት ማሳካት፤

- የምንሰጣቸው አገልግሎቶችን በስታንዳርዱ መሠረት በመለካት የህ/ሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ


ጊዜ የለኝም በሚል መንፈስና ወኔ በመላበስ እንዲሁም የተገባሮቻችን ዋና መሣሪያ የሆኑትንየሪፎርም
ስራዎችን አቀናጅቶ በመምራት በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ቅልጥፍና ማረጋገጥ፤

የቁልፍ ተግባሩ አጠቃላይ ዓላማ


- አዳዲስ የዕድገትና የለውጥ አስተሳሰቦች በማፍለቅ የኪ/ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ አመለካከትና
ተግባር በትግል በመስበር ሶስቱን የልማትክንፎች አቀናጅቶ ወደ ሙሉ ተግባር በማስገባት ከብከለት
የፀዳችና የአረንጓዴ የልማት ኢኮኖሚ ገፅታ የተላበሰች አራዳን በመፍጠርና ልማታዊ ፖለቲካል
ኢኮኖሚ የበላይነቱን እንዲጎናፀፍ ማድረግ፤
የቁልፍ ተግባሩ አጠቃላይ ግብ

- የኪ/ሰብሳቢነትአስተሳሰብና ተግባር በመናድ በማጥራት ሁለተኛውን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን


ዕቅድ የሚያሳካ ልማታዊ አስተሳሰብን የተላበሰና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቁርጠኛ አቋም
ያለው ሠራዊት ተፈጥሯል፤

የሴክተሩ ቁልፍ ተግባር

የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶቻችንን በተደራጀ የልማት ሰራዊት ቁመና በላቀ ደረጃ
መፈፀም ነው፡፡ በዚህ ሂደት በክ/ከተማ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር በማያቋርጥ
የተደራጀ ትግል በመናድ በምትኩ የልማታዊ ዲሞክራሲ አመለካከትና ተግባር ማስፋትና
ማዳበር ይሆናል፡፡

የቁልፍ ተግባሩ ዓላማ


የመ/ቤቱ የመልካም አስተዳደር፣ የአገልግሎት አሰጣጥና የለውጥ ስራዎችን በተቀናጀ ሁኔታበመፈፀም
በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ላይ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣትና በኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ላይ
ከምንጊዜውም በተለየ ቀጣይነት ያለው የተደራጀ ትግል በማካሄድ ልማታዊ አመለካከትን ማስፋትና የኪራይ
ሰብሳቢነትን አመለካከትና ተግባርን ማዳከም፡፡
የቁልፍ ተግባሩ ዋና ዋና ግቦችና ተግባራት
የዝግጅት ምዕራፍ

9
የተገልጋይ ዕርካታ ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር፣የአመራር ሥርዓታችንን በቀጣይነት በመፈተሸና በማስተካከል ለተልዕኮ
ዝግጁ ማድረግ፣ልማታዊ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ እንዲገነባ በሪፎርምና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ግምገማ ነክ
ስልጠናዎችን ማካሄድ፣የለውጥ መሣሪያዎችን አሟጦ ተግበራዊ ማድረግ፣የመንግስት ክንፍ፣ የህዝብ ክንፍንና የግንባር
ቀደሞችን ትስስር በሁሉም የዕቅድ ምዕራፎች ላይ በማጠናከር የለውጥ ሠራዊት መገንባት፣ከ 4 ቱም የሕዝብ ክንፍ
ከተውጣቱ አባላትና ከት/ቤት አባላት ጋር በየሩብ ዓመቱ የጋራ የውይይት መድረክ ማካሄድ የሪፎርምና
የትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች ማካሻሻ ስራዎችን መሥራት፣ተከታታይ የሆኑ የሕዝብ ክንፍ መድረኮችን የእርካታ ደረጃ
እየለኩ በቀጣይነት ማሳደግ፡፡
 ምላሽ ያገኙ የህዝብ ክንፍ ጥያቄዎች/ ችግሮችና በዚህም የተገኘ እርካታ
 የሕዝብ ክንፍን በብክለት ቁጥጥር ላይ በተለያዩ መንገዶች በማሳተፍ ድርሻን መለየትና ባለቤትነትን
ማረጋገጥ ፣

 ማንኛውም በክ/ከተማ ደረጃ ለሚቀርቡ የማለድርሻ አካባቢን በተመለከተ ስልጠና በክ/ከተማው

ባለሙያዎች መስጠት መቻል፡

ሪፎርምና መልካም አስተዳዳር


መልካም አስተዳደር ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችና መንስኤዎቻቸውን መለየት፣ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ማስቀመጥና
መተግበር፤በፈጣን ምላሽ የሚፈቱትንና የአሠራር ግልጸኝነት በመፍጠር የሪፎርምና መልካም አስተዳዳር ችግሮችን
ምላሽ በመስጠት የሠራተኛውን እርካታ ማሳደግ፤የኪራይ ሰብሳቢነት መገለጫዎችን በመለየት ማክሰሚያ ስልት
ተግባራዊ ማድረግ፤ቀልጣፋና ውጤታማ የቅሬታ አቀራረብ ሥርዓት መዘርጋት፤
የኪራይ ሰብሳቢነት መገለጫዎች በመለየት ማክሰሚያ ስልት ተግባራዊ ማድረግ

 በብቃት ለማስፈፀም የሚያስችል የተዘረጋ አደረጃጀት መፍጠር፣

 የአሰራር ማኑዋሎችን ወጥ አድርጎ በማዘጋጀት ሁሉም ፈፃሚ እንዲያውቀው ማድረግና

የአገልግሎት አሰጣጥን ቅልጥፍናና ውጤታማነት ማረጋገጥ፣


 ሥራዎች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድና መስፈርት መሰረት ስለመሠራታቸው ክትትልና

ግምገማ ማድረግ፣
 ቀልጣፋና ውጤታማ የቅሬታ አቀራረብ ሥርዓት መዘርጋት፣

 በቅሬታ አቀራረብ ያሉ ችግሮችን በሠራተኛውና በሕዝብ ክንፍ ተሳትፎ መለየት፣

 የተገኘውን ግብዓት በመውሰድ ተቋማዊ የቅሬታ አቀራረብ እና አፈታት ሥርዓት


መዘርጋት፣
 በተቋሙ ግልፅ ሆነው በሚታዩ ቦታዎች ላይ የሃሳብ መስጫ ሳጥኖች ማስቀመጥ፣
 በሃሳብ መስጫ ሳጥኖች የሚሰጡ አስተያየቶች በየጊዜው መፈተሸና ለቀጣይ ማሻሻያ
እንዲውሉ ማድረግ፣

10
 የቅሬታ ማቅረቢያ ቅፆችን በማዘጋጀት በሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣

በእቅድ አፈጻጸም ሂደት የሚጠበቁ መልካም እድሎችና ስጋቶች


5.1 መልካም እድሎች
 የአካባቢ ጉዳይ አለም አቀፍ ትኩረት ማግኘቱ
 በሀገር አቀፍ ደረጃ የአየርንብረት ለውጥን የሚቋቋም አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ተግባር ላይ መዋሉ
 ህብረተሱ በአካባቢ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ግንዛቤ ፣እንቅስቃሴ መኖሩ
 ስለአካባቢ ጉዳይ ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን መኖሩ
 እያንዳንዱ የሴክተር መስሪያ ቤቶች የአካባቢን ጉዳይ የስራቸው አካል አድርገው ወስደው እንዲሰሩ አቅጣጫ
መያዙ
 የባለድርሻ አካላት የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ

5.2 ስጋቶች
 ህጎች መመሪያዎች ደንቦች በተፈለገው ጊዜ አለመጽደቅ
 የባለሙያ ፍልሰትና የግብአት ችግር
 አንዳንድ ተቋማት ተቀናጅቶ ለመሰራት አለመቻላቸው
 አመራሮች ለአካባቢ የሚሰጡት ትኩረት አነስተኛ መሆን
6. የክትትልና ድጋፍ ስርዓት
6.1. የሪፖርት ስርዓት
 በየሳምንቱ ፣በወር፣በሩብ ዓመት እና ዓመታዊ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲቀርብ ክትትል ማድረግ
 በሚቀርበው ሪፖርት እና በመስክ በሚደረግ ቅኝት የመደበኛ ስራዎችን በመከታተል ጥሩ የሰሩትን
እንዲቀጥሉበት ደከም ያሉትን የሚደገፉበትን ስልት በመነደፍ ተግባራዊ ማድረግ
 ለወረዳዎች በፕሮግራም የተሸከርካሪ እና የቴክኒክ ድጋፍ ማድረግ
 በአፈፃፀም ዝቅተኛ ደረጃ ያላቸውን ሰራተኞች ስልጠና በመስጠት የአፈፃፀም አቅማቸውን ማሳደ

6.2. የሱፐርቪዥንና ግብረ መልስ አሠራር


 በየሳምንቱ፣ በየወሩ፣ በሩብ ዓመትና በዓመታዊ ሪፖርቶች ላይ በመመስረት እያንዳንዱ የስራ ክፍል ምን ያህል
እንዳከናወነ ይገመገማል
 በሪፖርቶቹ ላይ በመንተራስ በአፈፃፀም የታዩ ጉድለቶች የእርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ግብረመልስ
ይሰጥባቸዋል
 በተለያዩ መድረኮች ስራዎች ይገመገማሉ የማስተካከያ አቅጣጫም ይወሰዳል፡፡

6.3 የግምገማ አሠራር

11
በለውጥ ስራዎች ትግበራ ሂደት በተቀመጠው የመከታተያ ቼክ ሊስት መሠረት ከአመራር ጀምሮ እስከ ፈፃሚው ድረስ
የተግባራት አፈፃፀም ያጋጠሙ ችግሮችና ቀጣይ አቅጣጫዎች በየደረጃው እየተገመገመ ሪፖርት የመረጃ ቅብብሎሽ
ስርዓቱን ጠብቆ እንዲላክ ይደረጋል፡፡

7. ማጠቃለያ
በአካባቢ ላይ መጠነ ሰፊ ግንዛቤ የሚፈጥሩና የሚያስጨብጡ ስራዎችን በመስራት የህብረተሰቡንና የባለድርሻ አካላትን
ያሳተፈ የአካባቢ ልማትና እንክብካቤ ስራዎችን መስራት፣ የአካባቢ ሕጎች፣ ደንቦችና የአፈፃፀም መመሪያ እንዲተገበሩ
በማድረግ የክትትልና ግምገማ ስራዎችን መስራት፤ በአካባቢ ላይ እየሰሩ ተጨባጭ ለውጥ ላመጡ ግለሰቦች፣ ድርጅቶች
እና ተቋማት ሽልማትና እውቅና መስጠት፤ አሁን እየተሰራባቸው ያሉትን የትስስር ሰነዶች አጠናክሮ ማስቀጠልና
አዳዲስ የትስስር ሰነዶችን በመፈራረም እንዲተገበሩ በማድረግ የ 2013 ዓ.ም እንዲሳካ ይደረጋል ፡፡

አካባቢ ብክለት የአየር ንብረት ለውጥ ቡድን የሚከናወኑ አበይት ተግባራት

ዓለማ 1፡ በክ/ከተማው የሚደርሰውን የአካባቢ ብክለትን በመከላከልና በመቆጣጠር ለነዋሪዎቿ ንጹህና ጤናማ አካባቢ

መፍጠር፡፡
ግብ 1፡ በክ/ከተማው ልማትና አካባቢ ተጣጥመው እንዲሄዱ 12 የተለያየ ደረጃ ያላቸው አዳዲስ አገልግሎት ሰጭና
ማምረቻ ተቋማት/ፕሮጀክቶች ከአካባቢ አንጻር እንዲገመገሙ ማድረግ ፡፡
1.1. ይሁንታ እንዲሰጣቸው የሚፈልጉ ተቋማትን ጥያቄ መቀበል
1.2. የመስክ መረጃ መሰብሰብ ፤ሙያዊ ትንታኔ ማድርግና ምላሽ መስጠት
1.3. በአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ያለፉ ፕሮጀክቶችን አተገባበር መከታተልና መቆጣጠር
1.4. የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ አሰራርን ከወረዳዎች ጋር እየተገናኙ መገምገምና ድጋፍ ማድረግ

12
1.5. ከሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር ትስስር መፍጠርና ነባር ትስስሩን ማጠናከር
1.6. በአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ዘርፍ የባለሙያውንና የባለድርሻ አካላትን አቅም ማሳደግ
ግብ 2፡ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራርን በመዘርጋት በ 300 አገልግሎት ሰጭና
ማምረቻ ተቋማት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ፡፡
2.1. መረሀ-ግብር ማዘጋጀት
2.2. የተቋሙን ማኔጅመንት ማናገር፤ ስለስራው ማሳወቅና የተቋሙን የአካባቢ ሁኔታ መገምገም
2.3. የግምገማውን ውጤት መተንተን ማሳወቅና የመፍትሄ እርምጃ ማመላከት
2.4. የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የሚረዱ ስልቶችን ነድፎ በተቋማት መካከል የውድድር መንፈስ
መፍጠር
ግብ 3፡ በወረዳ ሊፈቱ ያልቻሉ የብክለት ይወገድልኝ አቤቱታዎችን ማስተናገድ
ግብ 3.1 ፡ 20 የድምጽ ብክለት ይወገድልኝ አቤቱታዎችን መቀበል፣ ማስተናገድና ምላሽ የመስጠት ስራ መስራት ፡፡
3.1.1 ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን መቀበል
3.1.2 የመስክ መረጃ ማሰባሰብ፤ ሙያዊ ትንታኔ ማዘጋጀትና ምላሽ መስጠት
3.1.3 የማስተካካያ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግና መከታተል
ግብ 3.2፡ 15 የፍሳሽ ውኃ ብክለት ይወገድልኝ አቤቱታዎችን መቀበል፣ ማስተናገድና ምላሽ የመስጠት ስራ መስራት ፡፡
3.2.2 ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን መቀበል
3.2.3 የመስክ መረጃ ማሰባሰብ፤ ሙያዊ ትንታኔ ማዘጋጀትና ምላሽ መስጠት
3.2.4 የማስተካካያ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግና መከታተል
ግብ 3.3፡ 6 የአየር ብክለት (የብናኝ፣ የሽታ፣ የጭስ፣ ወዘተ) ይወገድልኝ አቤቱታዎችን መቀበል፣ ማስተናገድና ምላሽ
የመስጠት ስራ መስራት ፡፡
3.3.1 ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን መቀበል
3.3.2 የመስክ መረጃ ማሰባሰብ፤ ሙያዊ ትንታኔ ማዘጋጀትና ምላሽ መስጠት
3.3.3 የማስተካካያ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግና መከታተል
ግብ 4፡ ብክለት ባደረሱ 20 ተቋማትና ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ በመወሰድ እና ህጋዊ ጉዳዮች ላይ
ክትትል በማድረግ የአካባቢ ደረጃን የማስከበር ስራ መስራት ፡፡
4.1 የአካባቢ ብክለትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ስርአትን መዘርጋት
4.2 ከህጉ ውጭ ብክለትን በሚያደርሱ ተቋማት ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ መውሰድ
4.3 የተወሰደውን እርምጃ አፈጻጸም መከታተል
ግብ 5. የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ይሁንታ ያገኙ 12 ፕሮጀክቶችን አተገባበር መከታተልና መቆጣጠር

ተግባር 1. የፕሮጀክቱን ተጽእኖ ግምገማ ዶክመንቱና የአሉታዊ ተፅዕኖ የአካባቢ አያያዝ ዕቅድ በማነጻጸር ለግምገማ የሚሆን
ቼክሊሰት ማዘጋጀት፣ መስክ በመሄድ ለ 200 ዶክመንቶች በተሰጠቸው ይሁንታ መሠረት እየተሰራ ያለውን ስራ በቼክሊስቱ
መሰረት መገምገም

13
ተግባር 2. ግብረመልስ ለሚመለከተው አካል/ለተቋማቱ ማቅረብ፣ የጎላ ግድፈት በታየባቸው ፕሮጀክቶች እንዲያስተካክሉ
አስተደደራዊ እርምጃ መውሰድ
ግብ 6፡በ 4 መድረኮች በአካባቢ ብክለት ችግሮችና መፍትሄዎች ላይ ለ 300 ለተለያዩ የክፍለከተማው የህብረተሰብ
ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበቻ ስራ መስራት ፡፡
5.1 በአካባቢ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ላይ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ አውዴጥናቶችንና
ስልጠናዎችን መስጠት
5.2 ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚደርሱና በተለያየ አካባቢ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ 400 ብሮሸሮችን
በማዘጋጀት ማሰራጨት
5.3 የተለያዩ የኤልክትሮኒክስ ህትመቶችንና ሚዲያዎችን በመጠቀም በአካባቢ ጉዳይ ላይ መረጃዎችን
ማስተላለፍ
5.4 በአካባቢ ጉዳይ ላይ ጉልህ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት እውቅና መስጠትና የማበረታች
ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት
ግብ 7፡ 1 ምርጥ ተሞክሮዎችን የመቀመርና የማስፋት ስራ መስራት ፡፡
6.1 ለልምድ ልውውጥ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ማመሟላት
6.2 ምርጥ ተሞክሮ የሚቀሰምባቸውን ተቋማት መለየት
6.3 ተሞክሮዎችን መቅሰምና በክፍለ ከተማችን ላይ ተግባራዊ ማድረግ
ግብ 8፡ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር በመቀነስ ህብረተሰባዊና ተቋማዊ ለውጥ መስራት ፡፡
7.1 የመንግስት ንብረትን ለግል ጉዳይ አለመጠቀም
7.2 የመንግስት የስራ ሰዓት ማክበር
7.3 የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ በመመሪያው መሰረት ይሁንታ ለሚገባቸው ድርጅቶች መስጠት

ግብ 9፡- ሰባት ለሚሆኑ ፈጻሚዎችና የጽ/ቤቱ ሰራተኞች የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ

(ICT) ስልጠና የሚያገኙበት መንገድ ማመቻቸት ፡፡

8.1 GIS ስልጠና በማዘገጀት የፈጻሚውን አቅም ማጎልበት

8.2 እቅድን ወደ automation ማስገባትና ሪፖረት ለሚመለከተው አካል ለመላክ የሚያስችል ስልጠና መስጠት

፡፡

14
የአረንጓዴ አካባቢዎች አያያዝ፣አጠቃቀም፣ክትትልና ቁጥጥር ቡድን

ግቦች እና ተግባራት

ግብ 1. በ 10 ወረዳዎች በቋሚ ማስታወቂያ ቦርዶች ላይ 10 የግንዛቤ መስጫ ጽሁፎችን መለጠፍ ፡፡


ተግባር 1. አጀንዳ መምረጥና ማስገምገም

ተግባር 2.ቋሚ ማስታወቂያ ቦርዶችን መዘጋጀት እና ማቆም

ተግባር 3.ግብረ መልስ መሰብሰብ

ግብ 2. በ 10 ወረዳዎች በ 10 ትምህርት ቤቶች ለ 1 ሺህ ተማሪዎች በ 5 መድረክ ስለ አረንጓዴ ልማት ስልጠና

መስጠት ፡፡

ተግባር 1. ተሳታፊዎችን መለየትና ጥሪ ማድረግ፡፡


ተግባር 2. ሎጀስቲክ ማሟላት፡፡
ተግባር 3. ውይይቱን ማድረግ፤ግብዓት መሰብስብና ማካተተ፡፡
ግብ 3. 100% በጊዜያዊ ውል በግለሰቦች፤ በአጥቢያ ነዋሪዎች፤ በተለያዩ አደረጃጀቶች፤በቢዝነስ እና
በሃይማኖት ተቋማት፤ጥበቃ እና ልማት ስር የነበሩ 10 አረንጓዴ ስፋራዎችን የአካል ግምገማ እና
ውልማደስ ስራዎችን ማከናወን ፡፡
ተግባር 1. የነባራዊ ሁኔታ ሪፖርት ማዘጋጀት

15
ተግባር 2 .ውል ማደስ/ውል መሰረዝ/
ግብ 4. ለአዳዲስ ግለሰቦች፤ የአጥቢያ ነዋሪዎች፤ የተለያዩ አደረጃጀቶች፤የቢዝነስ እና የሃይማኖት ተቋማት፤በተፈጥሮ ሃብት
ጥበቃ፤ልማት ጥያቄ የተሰጠ 100 %ምላሽ እና 4 ድጋፍና ክትትል ስራ ማከናወን፡፡
ተግባር 1. የቦታዎች ልየታ ማከናወን

ተግባር 2. ማመልከቻዎችና ፕሮፖዛሎችን መገምገም

ተግባር 3. በመመሪያው መሰረት ውሳኔ መስጠት

ተግባር 4. የትግበራ ምእራፉን ክትትል ማድረግ

ግብ 5. የተፋሰስ እና አረንጓዴ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር የተሰጠውን ተልእኮ አንዲፈጽም 4 ጊዜ ድጋፍ፤ክትትል እና ቁጥጥር
ማድረግ፡፡
ተግባር 1. ወቅታዊ እቅዶች እና ሪፖርቶች የጋራ ግምገማ ማድረግ፤
ተግባር 2. የድጋፍ ፍላጎትን መለየት፤
ተግባር 3. የክትትል ቼክ ሊስት ማዘጋጀት፤
ተግበር 4. በቼክ ሊስቱ አማካይነት ከትትል ማድረግ፤
ተግባር 5. ሪፖርት ማዘጋጀት ፤ ግብረ መልስ መስጠት፤
ተግባር 6. የግብረ- መልሱን አፈጻጸም መከታተል፤
ግብ.6.ወረዳዎች የተሰጣቸውን ተልእኮ አንዲፈጽሙ 4 ጊዜ ድጋፍ ፤ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፡፡
ተግባር 1. ወቅታዊ እቅዶች እና ሪፖርቶች የጋራ ግምገማ ማድረግ፤
ተግባር 2. የድጋፍ ፍላጎትን መለየት፤
ተግባር 3. የክትትል ቼክ ሊስት ማዘጋጀት፤
ተግበር 4. በቼክ ሊስቱ አማካይነት ከትትል ማድረግ፤
ተግባር 5. ሪፖርት ማዘጋጀት ፤ ግብረ መልስ መስጠት፤
ተግባር 6. የግብረ- መልሱን አፈጻጸም መከታተል፤
ተግባር 7. አካል ግምገም ማድረግ ውሳኔ ማሳወቅ፤
ተግባር 8. በተሰጠው ውሳኔ መሰረት መፈጸሙ ክትትል ማድረግ
ግብ 7. በተጠሪ መስሪያ ቤቶች እና በተባባሪ አካላት አማካይነት የችግኞች የጸድቀት መጠን ከ

86 ወደ 88 ፐርሰንት እንዲሻሻል ድጋፍ የማድረግ ስራ መስራት

ተግባር 1. ስራውን ለመከታተል የሚረዳ ቼክ ሊስት ማዘጋጀት፤

16
ተግባር 2. የችግኞች ቁጥር ፤ ስፍራ፤ ተካይ ተቋም፤ ተተከለበት ጊዜን ጨምሮ መረጃ አንዲያዝ ድጋፍ ማድረግ

ተግባር 3. የጽደቀት ሁኔታ ሪፖርት በዓመት 2 ጊዜ ማዘጋጀት፤ ግብረ መልስ መላክ፤

ግብ 8. በግል ይዞታ ላይ ደን ለመቁረጥ ፍቃድ ለሚጠይቁ 10 ግለሰቦች(ድረጅቶች) 100 % ምላሽ መስጠት፡፡


ተግባር 1፣ጥያቄ ማቅረቢያና መመዘኛ መስፈርት ማዘጋጀት

ተግባር 2. የፈቃድ ጥያቄ መቀበልና የቀረቡትን ሰነዶች ማጣራት

ተግባር 3. የመስክ ምልከታና መረጃ መሰብሰብ ሪፖርት ማዘጋጀትና ውሳኔ መስጠት

ተግባር 4.መረጃ መሟላቱን ማረጋገጥና ውል ማዘጋጀት

ተግባር 5. የዛፍ ይዘት ማስላት


ተግባር 6.የልማትክፍያ(ሮያሊቲ)ማስከፈል
ግብ 9. የአረንጓዴ እና የተፋሰስ አካባቢዎች ልማት እንዲያደግ እና የዕጽዋት ሽፋን እንዲጨምር
ክትትል ማድረግ
ተግባር 1.የተተከሉ ችግኞችን ከባለድርሻ ጋር እንክብካቤ እንዲደረግ ማድረግ

ተግባር 2. የፅድቀት መመዘኛ በትክክል እንዲሰራ ማድረግ

ተግባር 3.የተደራጀና የተነፃፀረ መረጃ ማደራጀት

ግብ.10 5 የተፋሰስና አረንጓዴ ቦታዎችን የማልማት ፈቃድና የብቃት ማረጋገጫ መስጠት


ተግባር 1.ጥያቄ ማቅረቢያና መመዘኛ መሽፈርት ማዘጋጀት

ተግባር 2.የፈቃድ ጥያቄ መቀበል የቀረቡት ሰነዶች ማጣራት ፣ጥያቄውን መመዝገብ

ተግባር 3. የመስክ ምልከታና መረጃ መሰብሰብ

ተግባር 4.ጂፒኤስ ንባብ መውሰድ ካርታ ማዘጋጀት

17
18
ሂደት ዝርዝር መርሀ-ግብር
የክንውን ጊዜ
ዓላማዎች
ግቦችና ዝርዘዝር ተግባራት ምርመራ
(goals)
(objectives and

4
መለኪያ የ 2013

3
activities) ኢላማ

ኛ ሩብ ዓመት
ኛ ሩብ ዓመት

ኛ ሩብ ዓመት

ኛ ሩብ ዓመት
ግብ 1፡ በክ/ከተማው ልማትና አካባቢ በቁጥር 12 3 3 3 3
ዓለማ 1፡ ተጣጥመው እንዲሄዱ 12 የተለያየ ይረጃ
በክ/ከተማው ያላቸው አዳዲስ አገልግሎት ሰጭና
የሚደርሰውን ማምረቻ ተቋማት/ፕሮጀክቶች ከአካባቢ
የአካባቢ ብክለትን አንጻር እንዲገመገሙ ማድረግ ፡፡
1.1 ይሁንታ እንዲሰጣቸው የሚፈልጉ    
በመከላከልና
በመቆጣጠር ተቋማትን ጥያቄ መቀበል
1.2 የመስክ መረጃ መሰብሰብ ፤ሙያዊ    
ለነዋሪዎቿ
ትንታኔ ማድርግና ምላሽ መስጠት
ንጹህና ጤናማ
1.3 በአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ያለፉ    
አካባቢ መፍጠር፡፡
ፕሮጀክቶችን አተገባበር
መከታተልና መቆጣጠር
1.4 የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ አሰራርን    
ከወረዳዎች ጋር እየተገናኙ
መገምገምና ድጋፍ ማድረግ
1.5 ከሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ 
ቤቶች ጋር ትስስር መፍጠርና ነባር
ትስስሩን ማጠናከር
1.6 በአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ዘርፍ 
የባለሙያውንና የባለድርሻ አካላትን
አቅም ማሳደግ
ግብ 2፡ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከልና በቁጥር 200 50 50 50 50
ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራርን
በመዘርጋት በ 200 አገልግሎት ሰጭና
ማምረቻ ተቋማት ላይ ክትትልና
ቁጥጥር ማድረግ ፡፡
2.1 መረሀ-ግብር ማዘጋጀት

2.2 የተቋሙን ማኔጅመንት ማናገር፤  


ስለስራው ማሳወቅና የተቋሙን የአካባቢ
ሁኔታ መገምገም
2.3 የግምገማውን ውጤት መተንተን  
ማሳወቅና የመፍትሄ እርምጃ
ማመላከት የአካባቢ ብክለትን
ለመከላከል የሚረዱ ስልቶችን
ነድፎ በተቋማት መካከል የውድድር
መንፈስ መፍጠር

19
ግብ 3፡ በወረዳ ሊፈቱ ያልቻሉ የብክለት በቁጥር 100% 100% 100% 100% 100%
ይወገድልኝ አቤቱታዎችን ማስተናገድ
ግብ 3.1፡- 20 የድምጽ ብክለት በቁጥር 20 6 4 4 6
ይወገድልኝ አቤቱታዎችን መቀበል፣
ማስተናገድና ምላሽ የመስጠት ስራ
መስራት ፡፡
3.1.1 ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን    
መቀበል
3.1.2 የመስክ መረጃ ማሰባሰብ፤   
ሙያዊ ትንታኔ ማዘጋጀትና
ምላሽ መስጠት
3.1.3 የማስተካካያ እርምጃ
እንዲወሰድ ማድረግና
መከታተል
ግብ 3.2፡ 15 የፍሳሽ ውኃ ብክለት በቁጥር 15 7 3 3 2
ይወገድልኝ አቤቱታዎችን መቀበል፣
ማስተናገድና ምላሽ የመስጠት ስራ
መስራት ፡፡
3.2.1 ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን   
መቀበል
3.2.2 የመስክ መረጃ ማሰባሰብ፤  
ሙያዊ ትንታኔ ማዘጋጀትና
ምላሽ መስጠት
3.2.3 የማስተካካያ እርምጃ
እንዲወሰድ ማድረግና መከታተል
ግብ 3.3 ፡ 6 የአየር ብክለት (የብናኝ፣ በቁጥር 6 2 2 2 2
የሽታ፣ የጭስ፣ ወዘተ) ይወገድልኝ
አቤቱታዎችን መቀበል፣ ማስተናገድና
ምላሽ የመስጠት ስራ መስራት ፡፡
3.3.1 ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን    
መቀበል

3.3.2 የመስክ መረጃ ማሰባሰብ፤  


ሙያዊ ትንታኔ ማዘጋጀትና
ምላሽ መስጠት
3.3.3 የማስተካካያ እርምጃ
እንዲወሰድ ማድረግና
መከታተል

ግብ 4፡ ብክለት ባደረሱ 20 ተቋማትና በቁጥር 20 5 5 5 5


ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊና ሕጋዊ
እርምጃ በመወሰድ እና ህጋዊ ጉዳዮች
ላይ ክትትል በማድረግ የአካባቢ ደረጃን

20
የማስከበር ስራ መስራት፡፡
4.1 የአካባቢ ብክለትን ለመቆጣጠር 
የሚያስችል ስርአትን መዘርጋት
4.2 ከህጉ ውጭ ብክለትን በሚያደርሱ    
ተቋማት ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ
እርምጃ መውሰድ
4.3 የተወሰደውን እርምጃ አፈጻጸም
መከታተል

ግብ 5፡በ 4 መድረኮች በአካባቢ ብክለት በቁጥር 300 100 100 50 50


ችግሮችና መፍትሄዎች ላይ ለ 300
ለተለያዩ የክፍለከተማው የህብረተሰብ
ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበቻ ስራ
መስራት ፡፡
5.1 በአካባቢ ችግሮችና    
መፍትሄዎቻቸው ላይ ለባለድርሻ
አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ
አውዴጥናቶችንና ስልጠናዎችን
መስጠት
5.2 ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች    
የሚደርሱና በተለያየ አካባቢ
ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ 500
ብሮሸሮችን፤

5.3 የተለያዩ የኤልክትሮኒክስ    


ህትመቶችንና ሚዲያዎችን
በመጠቀም በአካባቢ ጉዳይ ላይ
መረጃዎችን ማስተላለፍ
5.4 በአካባቢ ጉዳይ ላይ ጉልህ አስተዋጽዖ
ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት እውቅና
መስጠትና የማበረታች ፕሮግራሞችን
ማዘጋጀ
ግብ 6፡ 1 ምርጥ ተሞክሮዎችን የመቀመርና በቁጥር 1 1
የማስፋት ተሰርቷል ፡፡
6.1 ለልምድ ልውውጥ የሚያስፈልጉ 
ግብአቶችን ማመሟላት

6.2 ምርጥ ተሞክሮ የሚቀሰምባቸውን 


ተቋማት መለየት

6.3 ተሞክሮዎችን መቅሰምና በክፍለ 


ከተማችን ላይ ተግባራዊ ማድረግ

21
ግብ 7፡የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና በ% 100% 100% 100% 100% 100%
ተግባር በመቀነስ ህብረተሰባዊና ተቋማዊ
ለውጥ መጥቷል ፡፡
7.1 የመንግስት ንብረትን ለግል ጉዳይ    
አለመጠቀም
7.2 የመንግስት የስራ ሰዓት ማክበር    

7.3 የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ በመመሪያው


መሰረት ይሁንታ ለሚገባቸው ድርጅቶች
መስጠት
ግብ 8፡- 5 ለሚሆኑ ፈጻሚዎችና በቁጥር 7 3 4
የጽ/ቤቱ ሰራተኞች የቴክኖሎጂ
ተጠቃሚ እንዲሆኑ የኢንፎርሜሽን
ቴክኖሎጂ (ICT) ስልጠና የሚያገኙበት
መንገድ ተመቻችቷል ፡፡

8.1 GIS ስልጠና በማዘገጀት  


የፈጻሚውን አቅም ማጎልበት

8.2 እቅድን ወደ automation 

ማስገባትና ሪፖረት ለሚመለከተው አካል

ለመላክ የሚያስችል ስልጠና መስጠት

ዓላማ ግቦችና ዝርዝር ተግባራት መለኪያ የ 2013 1 ኛ ሩብ 2 ኛ ሩብ 3 ኛ ሩብ 4 ኛሩብ


እቅድ
(ብዛት)

መ ጥ ህ ታ ጥር የካ መጋ ሚ ግ ሰ
ሀምሌ

ነሀሴ

ግብ 1.በ 10 ወረዳወች በቋሚ ቁ 10 1 1 1 2 1 1 2 1


ማስታወቂያ ቦርዶች ላይ 10 የግንዛቤ
መስጫ ጽሁፎችን መለጠፍ፡፡

ተግባር 1. አጀንዳ መምረጥና / / / / / / / /

ማሰገምግም

22
ተግባር 2.ቋሚ ማስታወቂያ ቦርዶችን / / / / / / / /

መዘጋጀት እና ማቆም

ተግባር 3.ግብረ መልስ መሰብሰብ / / / /

ግብ 2.በ 10 ወረዳወች በ 10 ትምህር ቁ 1000 200 200 200 200 200

ቤቶች ለ 1 ሺህ
ተማሪዎች በ5
መድረክስለ አረንጓዴ
ልማት የሚሰጥ ግንዛቤ ፡
ተግባር 1.ተሳታፊዎችን መለየትና ጥሪ / / / / / /

ማድረግ፡፡
ተግባር 2. ሎጀስቲክ ማሟላት፡፡ / / / / / /
ተግባር 3. ውይይቱን ማድረግ፤ግብዓት / / / / /
መሰብስብና ማካተተ፡
ግብ 3.100%በጊዜያዊውልበግለሰቦች፤ ቁ 10 2 2 2 2 2

በአጥቢያ ነዋሪዎች፤
በተለያዩ
አደረጃጀቶች፤በቢዝነስ
እና በሃይማኖት
ተቋማት፤ጥበቃ እና
ልማት ስር የነበሩ
አረንጓዴ ስፋራዎች
የተደረገ የአካል ግምገማ
እና ውል ማደስ፡
ተግባር 1. የነባራዊ ሁኔታ ሪፖርት / / / / /

ማዘጋጀት
ተግባር 2.ውል ማደስ/ውል መሰረዝ/ / / / / /
ግብ 4. ለአዳዲስ ግለሰቦች፤ የአጥቢያ ቁ 4 1 1 1 1

ነዋሪዎች፤ የተለያዩ
አደረጃጀቶች፤የቢዝነስ እና የሃይማኖት
ተቋማት፤በተፈጥሮ ሃብት
ጥበቃ፤ልማት ጥያቄ የተሰጠ 100

%ምላሽ እናየተደረገ ድጋፍና


ክትትል፡፡
ተግባር 1. የቦታዎች ልየታ ማከናወን / / / / /
ተግባር 2 ማመልከቻዎችና / / / /

ፕሮፖዛሎችን መገምገም
ተግባር 3.በመመሪያው መሰረት ውሳኔ / / / /

መስጠት
ተግባር 4.የትግበራ ምእራፉን ክትትል / / / / / /

23
ማድረግ
ግብ 5. የተፋሰስ እና አረንጓዴ ቦታዎች ቁ 4 1 1 1 1
ልማትና አስተዳደር የተሰጠውን
ተልእኮ አንዲፈጽም የተደረገ ወርሃዊ
ድጋፍ፤ክትትል እና ቁጥጥር
ተግባር 1 ወቅታዊ እቅዶች እና / / / / / / / / / / /
ሪፖርቶች የጋራ ግምገማ
ማድረግ፤
ተግባር 2 የድጋፍ ፍላጎትን / / / / / / / / / / / /
መለየት፤
ተግባር 3 የክትትል ቼክ ሊስት / / / / / / / / / / / /
ማዘጋጀት፤
ተግባር 4 በቼክ ሊስቱ አማካይነት / / / / / / / / / / / /
ከትትል ማድረግ፤
ተግባር 5 ሪፖርት ማዘጋጀት ፤ / / / / / / / / / / / /
ግብረ መልስ መስጠት፤
ተግባር 6 የግብረ- መልሱን / / / / / / / / / / / /
አፈጻጸም መከታተል፤
ግብ 6.በክፍለ ከተማ ቁ 4 1 1 1 1
ወረዳዎችየተሰጣቸውን ተልእኮ
አንዲፈጽሙ የተደረገ ድጋፍ
፤ክትትልና ቁጥጥር
ተግባር 1 ወቅታዊ እቅዶች እና / / / /
ሪፖርቶች የጋራ ግምገማ ማድረግ
ተግባር 2 የድጋፍ ፍላጎትን / / / /
መለየት፤
ተግባር 3 የክትትል ቼክ ሊስት / / / /
ማዘጋጀት፤

ተግባር 4. በቼክ ሊስቱ አማካይነት / / / /


ከትትል ማድረግ፤
ተግባር 5 ሪፖርት ማዘጋጀት ፤ / / / /
ግብረ መልስ መስጠት፤
ተግባር 6 የግብረ- መልሱን / / / /
አፈጻጸም መከታተል፤
ግብ 7.በተጠሪ መስሪያቤቶች እና % 86% 88 88

በተባባሪ አካላት አማካይነት የችግኞች


የጸድቀት መጠን እንዲሻሻል ድጋፍ
ማድረግ፡፡
ተግባር 1.ስራውን ለመከታተል / / / /

የሚረዳ ቼክ ሊስት ማዘጋጀት፤

ተግባር 2. የችግኞች ቁጥር ፤ ስፍራ፤ / / / / / / / / / / /

ተካይ ተቋም፤ ተተከለበት ጊዜን


ጨምሮ መረጃ አንዲያዝ ድጋፍ
ማድረግ

ተግባር 3.የጽደቀት ሁኔታ ሪፖርት / /

24
በዓመት 2 ጊዜ ማዘጋጀት፤ ግብረ
መልስ መላክ፤

ግብ 8 በግል ይዞታ ላይ ደን ለመቁረጥ ቁጥር 10 1 1 1 1 1 1 1 1 1 1

ፍቃድ ለሚጠይቁ 10

ግለሰቦች(ድርጅቶች) 100 %ምላሽ

መሥጠት፡፡
ተግባር 1፣ጥያቄ ማቅረቢያና / / / / / / / / / / / /
መመዘኛ መስፈርት ማዘጋጀት
ተግባር 2. የፈቃድ ጥያቄ መቀበልና / / / / / / / / / / / /
የቀረቡትን ሰነዶች ማጣራት
ተግባር 3.የመስክ ምልከታና መረጃ / / / / / / / / / / / /
መሰብሰብ ሪፖርት ማዘጋጀትና ውሳኔ
መስጠት
ተግባር 4.መረጃ መሟላቱን ማረጋገጥና / / / / / / / / / / / /
ውል ማዘጋጀት
ተግባር 5.የዛፍ ይዘት ማስላት / / / / / / / / / / / /
ተግባር 6.የልማት ክፍያ(ሮያሊቲ) / / / / / / / / / / /
ማስከፈል
ግብ 9.የአረንጓዴእና የተፋሰስ % 86% 88 88%
%
አካባቢዎች ልማት እንዲያደግ እና
የዕጽዋት ሽፋን እንዲጨምር
ጌዜክትትል ማድረግ
ተግባር 1.የተተከሉ ችግኞችን / / / / / / / / / / / / /
ከባለድርሻ ጋር እንክብካቤ
እንዲደረግ ማድረግ
ተግባር 2. የፅድቀት መመዘኛ በትክክል / /
እንዲሰራ ማድረግ
ተግባር 3.የተደራጀና የተነፃፀረ መረጃ / / / /
ማደራጀት
ግብ 10 የተፋሰስና አረንጓዴ ቁ 5 1 1 1 1 1

ቦታዎችን የማልማት
ፈቃድና የብቃት
ማረጋገጫ መስጠት
ተግባር 1.ጥያቄ ማቅረቢያና መመዘኛ / / / / / / /
መሽፈርት ማዘጋጀት
ተግባር 2.የፈቃድ ጥያቄ መቀበል / / / / / / /
፣የቀረቡት ሰነዶች ማጣራት
፣ጥያቄውን መመዝገብ
ተግባር 3. የመስክ ምልከታና መረጃ / / / / / / /
መሰብሰብ
ተግባር 4.ጂፒኤስ ንባብ መውሰድ / / / / / /
ካርታ ማዘጋጀት

25
ተግባር 5.በመስክ የተገኙ መረጃወች
በኮምፒዩተር ማስገባትና ለአልሚወች
በተለያዩ ቦታወችናመሬት አጠቃቀም
መገናዘ

ተግባር 6.የሚመለከተውን አካል / / / / / / / /


ይሁንታ መጠየቅ

ተግባር 7.ያቀረቡትን ፐሮፖዛል ጥናት / / / / / / / /

መገምገም፣መረጃ መሟላቱን አረጋግጦ


ውል አዘጋጅቶ ፈቃድ መስጠት

በአራዳ ክ/ከ የአረንጓዴ አካባቢወች አያያዝ፣አጠቃቀም፣ክት/ቁ/ቡድን 2013 የድርጊት-

መርሀግብር

26

You might also like