You are on page 1of 22

በአብክመ ትምህርት ቢሮ በሰ/ጎ/ዞ ትም/መምሪያ

በመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የመምህራንና የትምህርት

ተቋማት አመራሮች የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት

ዋና የስራ ሂደት

የ 2010 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እቅድ

ገንዳ ውሃ
2010 ዓ.ም

1. መግቢያ
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት

በኢትዮዽያ ዘመናዊ ትምህርት ከተጀመረ ከአንድ ምዕተ አመት በላይ ቢሆነውም ባለፉት አመታት
የጥራት፣ የተገቢነት፣ የፍትሃዊነት እና የዴሞክራሲያዊነት ችግሮች ሲፈታተኑት ቆይተዋል፡፡ በ 1986
በፀደቀው የአገራችን የትምህርት እና ስልጠና ፖሊሲ ላይ እነዚህ ምዕት አመት ተሻግረው የዘለቁ
ችግሮችን ለመፍታት እና የትምህርትን ማህበራዊ አና ዴሞክራሲያዊ ጠቀሜታ በማዳበር የሀገሪቱ ዜጎች
እውቀትን የሚሹ፣ ምክንያታዊ የሆኑ፣ ችግር ፈች፣ ስራ ፈጣሪ እና ሃብትን በአግባቡ የሚጠቀሙ እና
ለአካባቢ ተስማሚ ቴክኖሎችን የሚፈጥሩ ሆነው ማደግ እንዳለባቸው በአጠቃላይ አላማው ላይ
ያትታል፡፡ የትምህርት ሥራ ዴሞክራሲን ለመገንባት፤ የተፋጠነ ማህበራዊ ለውጥ ለማምጣት እና
የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ውጤታማ ለማድረግ ቁልፍ ድርሻ እንዳለውም መንግስት ቁርጠኛ
አቋም አለው፡፡ በዚህ ሂደትም አሁን ከደረስንበት ደረጃ አንፃር በተቀመጠው የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት
እየሰራን መሆኑን በየት/ቤቶቻችን የሚሰጠውን የትምህርት ጥራት የመከታተልና የመደገፍ አስፈላጊነት
ወሳኝ እየሆነ መጥቷል:: በተጨማሪ በመማር ማስተማሩ ሂደት ቁልፍ ባለቤቶች የሆኑት መምህራንና
የት/ቤት አመራሮችን የማልማትና ሀገራዊ ግቡን ተረድተው ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ የማድረግ ሥራን
አጠናክሮ በመቀጠልና በውጤት ተኮር ምዘና ውጤታቸውን በማረጋገጥ የመማር ማስተማሩ ሂደት
ለዜጐች ተገቢ አገልግሎት የሚሰጥበት እንዲሆን ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ወደ ትምህርት ሙያ የሚሰማሩና
የተሰማሩት ሁሉ ሙያው የሚጠይቀውን የብቃት ደረጃ ማሟላታቸውን ማረጋገጥ የሚያስችል ስርዓት
ተዘርግቶ እንቅስቃሴው ተጀምሯል፡፡ ይህ ሂደት በተማሪዎቻችን ውጤት መሻሻል ላይ ጉልህ ድርሻ
እንደሚኖረው ይታመናል፡፡

ስለሆነም በ 2005 ዓ.ም በትም/ጽ/ቤታችን ስር ላሉ መምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች በሙያ


ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ምንነት፣ ፋይዳና የወደፊት አቅጣጫ ላይ መነሻ ሰነድ በትምህርት ሚኒስቴር
ተዘጋጅቶ በተለያየ ጊዚያት ለመምህራን፣ ለርዕሳነ መምህርን፣ ለሱፐርቫይዘሮች እና ለባለድርሻ አካላት
ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል፡፡ ከወቅቱ የሃገራችን የቴክኖሎጂና የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር የተጣጣሙ
የሙያ ብቃት ደረጃዎች (Standards) ለመምህራን፣ ለርዕሳነ መምህራንና ለሱፐርቫይዘሮች ተዘጋጅተው
ትምህርት ቤት ደርሰዋል፡፡

የ 2009 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ተገምግሞ የሁኔታ ትንተናዎች የ 2 ዐ 10 ዓ.ም ዕቅድ መነሻ ተደረጓል፡፡ ይህ
እቅድ ከትም/ጽ/ቤት ጀምሮ ባለው አመራርና ባለሙያ የሚስተዋሉ ችግሮችንና የመፍትሄ አቅጣጫዎች
ተካተውበታል፡፡ በመሆኑም የመምህራንና የትም/ተቋማት አመራሮች የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና
የሥራ ሂደት የሚጠበቅበትን ውጤት ለማምጣት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድንና የውጤት ተኮር
እቅድን በማስተሳሰር ከትም/ጽ/ቤት ጀምሮ እስከ ትምህርት ተቋማት ድረስ የተናበበ እቅድ በማቀድ፣
በማስተዋወቅ፣ ግምገማና የሪፖርት ግንኙነት ሥርዓት በመዘርጋት በተቀናጀ መልኩ መፈፀም እንዲቻል
ይህ የ 2010 ዓ.ም እቅድ ተዘጋጅቷል፡፡

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት 2010 ዓ.ም እቅድ Page 2
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት

2. የእቅዱ መነሻዎች
2.1 የበላይ አካላትን እቅድ እንደመነሻ
የመምህራን እና የትምህርት ተቋማት አመራሮች የሙያ ፈቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ዋና የስራ ሂደት
የ 2010 ዓ.ም እቅድን ሲያዘጋጅ የትምህርት ቢሮን እቅድ እንደመነሻ ተጠቅሟል፡፡ ይህ የሆነበት
ምክንያት በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ያሉት ከትምህርት ቢሮ በሚነሱ መነሻዎች በመሆኑ እና
አንዳንዶቹም በሁለትዮሽ ትብብር እየሰራናቸው ያሉ ተግባራት በመሆናቸው ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ
በትም/ጽ/ቤት ደረጃ በአጠቃላይ በእቅድ አመቱ ሊተገበሩ የሚገባቸው ዋና ዋና የርብርብ ማዕከላት
ለይቶ በማስቀመጥ የስራ ሂደቱ ከነዚህ ተግባራት በዘርፉ የሚመለከተውን በመምረጥ እንደመነሻ
ተጠቅመንባቸዋል፡፡

2.2 . የ 2009 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም እንደመነሻ

2.2.1 የመምህራንና የትምህርት ተቋማት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ተግባር ያለበት ሁኔታ፡
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ተግባር ሶስት መሠረታዊና እርስ በዕርስ የተሳሰሩ ደረጃዎችን ይይዛል፡፡
እነዚህ ደረጃዎች ግንዛቤ የመፍጠር፣ የስልጠናና የትግበራ ደረጃዎች ናቸው፡፡ በእነዚህ ደረጃዎች በ 2009
ዓ.ም የነበረንን አፈጻጸም በዝርዘር እንመልከት፡፡

2.2.1.1 የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ ያለበት ሁኔታ

በትምሀርት ሥራ ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች በሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ምንነት፣


ፋይዳና የወደፊት አቅጣጫ ላይ መነሻ ሰነድ ከትምህርት ቢሮ ተዘጋጅቶ በተላከው መሰረት በትምህርት
ንቅናቄ ሳምንትና በሌሎች መድረኮች ለሁሉም ባላድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ተሰርቷል፡፡
በሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ምንነትና ፋይዳ ላይ ሁሉም ተሳታፊ በጋራ በመግባባቱ አብዛኛው የሚነሳ
ጉዳይ ይህን ስራ ተግባራዊ የማድረጉ ሂደት ለምን ይህን ያህል ይዘገያል እና በአፈፃፀም ወቅት ሊደርሱ
ይችላሉ ተብለው በሚታሰቡ ስጋቶችና ጉዳዬች ላይ ያተኮሩ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡

የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ሥርዓቱን ባለድርሻ አካላት የበለጠ እንዲረዱት እና አጋዥ እንዲሆኑ
ለማድረግ በየደረጃው ካሉ የመምህራን ማህበራት ጋር በርካታ ሥራዎች ተሰርተዋል፤ በቀጣይም
ተከታታይ ስራዎች በህዝብ ክንፍ፣ በመንግስት ክንፍና በድርጅት ክንፍ በስፋት መሰራት ይኖርበታል፡፡
በግንዛቤ መፍጠር ሂደትም መልካም የሚባል ውጤት ቢገኝም ሁሉም መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን፣
ሱፐርቫይዘሮች እና የትምህርት ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት እኩል ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከማድረግ
አንፃር የተለያየ ደረጃ ላይ ናቸው፡፡ የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ሥርዓት በትምህርት ቤት ማህበረሰብ
ተቀባይነት እንዲኖረው እና ሁሉም ይጠቅመናል በሚል አስተሳሰብ እንዲቀበለው ለማድረግ ከመምህራን

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት 2010 ዓ.ም እቅድ Page 3
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት

በተጨማሪ በወላጆችና ተማሪዎች ዘንድ የባለቤትነት ስሜት ለመፍጠር አደረጃጀቶችን ተጠቅሞ


መስራት ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ለፖለቲካ አመራሩ የግንዛቤ የማስጨበጥ ስራው ተጠናክሮ መቀጠል
አለበት፡፡

2.2.1.2 የሥልጠና ሥራችን ያለበት ደረጃ

ሀገራችን አሁን ከደረሰችበት ዕድገት ጋር የተጣጣሙ የሙያ ብቃት ደረጃዎች (Standards)


ተዘጋጅተዋል፡፡ የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ሥራውን ለማስፈፀም የሚረዱ መመሪያዎችና
ማስፈፀሚያ ማንዋሎች በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅተው እንድናውቃቸው ተደርጓል፡፡ እነዚህ ሰነዶች
መምህራን እና የትምህርት ተቋማት አመራሮች የሙያ ፈቃድ የሚያገኙበትና የሚያድሱበትን አሰራር
የሚያሳዩና እንደመነሻ የሚሆኑ ናቸው፡፡ ለብቃት ምዘና ሥራዎች ሙያ ፈቃድ አሰጣጥ ሥራ በሁሉም
ደረጃ በመመሪያና በስታንዳርዶች ዙሪያ በርካታ የሆነ አጫጭር ስልጠና በማዘጋጀት እንዲታወቁና
እንዲሠራባቸው ተደርጓል፡፡ በ 2009 ዓ.ም ከሠራዊት ግንባታ አንፃር መተግበር ያለብን የላቀ ፈፃሚነቱን
ያረጋገጠ የመንግስት ክንፍ ከመፍጠር አንፃር ያለው ተግባር በሙያ ፈቃድና እድሣት ተግባራት አምኖ እና
በድርሻው ሊወጣው የሚገባውን ሀላፊነት እንዲወጣ የሚያስችል ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ ለመሥራት
የተመደበውን የሰው ኃይል ወደ ስራ ለማስገባት በተመረጡ ርዕሶች የስራ ሂደት ጥናቱ ላይ፣ በሙያ ፈቃድ
አሰጣጥ እና እድሳት መመሪያ እና ማንዋል እና በስታንዳርዶች ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በክልል
ደረጃ ለመርሱ በተሰጠዉ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መሰረት ሰልጥነው ከተመለሱ በኋላ ለመመህራበን፣
ለርዕሳነ መምህራን እና ለሱፐርቫይዘሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ የሙያ
ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ሥራ ዘላቂነቱን አስተማማኝ መሠረት ላይ ለመጣል በየደረጃው የመርሱዎችን
አቅም በመገንባት ረገድ ብዙ መሥራት ይጠበቃል፡፡ የመርሱዎችን ክፍተቶች በመለየት በየጉድኝቶች
የተጠናከረ ሥልጠና መስጠት ያስፈልጋል፡፡

የሙያ ፈቃድ አተገባበር ያለበት ሁኔታ

 አደረጃጀቱ ያለበት ሁኔታ

የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት አደረጃጀት ከወረዳ ትም/ጽ/ቤት ጀምሮ እስከ ትም/ቤቶች ድረስ
ለማደራጀት ተሞክሯል፡፡

ይህ ሥራ በትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ተግባራችን ካለው ፋይዳ አንፃር አደረጃጀታችን ከወረዳ


ትም/ጽ/ቤት ጀምሮ በተከታታይ እየጨመረ የሚመጣውን ሥራ የመሸከም አቅም ሊኖረው ይገባል፡፡
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት የተደራጀ ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ የመረጃ ሰንሰለት በመፍጠር ረገድ
በጥንካሬ መሥራት ይጠበቅበታል፡፡ በአመለካከት የተለወጠ፣ ከኪራይ ሰብሳቢነት የፀዳ አሠራርና

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት 2010 ዓ.ም እቅድ Page 4
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት

አደረጃጀት መፈጠር እና መጠናከር አለበት፡፡ የመምህራን እና የት/ቤት አመራሮችን የተመለከተ


የምዝገባና የምዘና ውጤት የሚያዝበትም ሆነ የሚገለፅበት የመረጃ ስርዓት ሊኖር ይገባል፡፡ ብቃታቸው
ለተረጋገጡ መምህራን እና የትምህርት ተቋማት አመራሮች መረጃ የመስጠትና የማደስ፣ ቅሬታ
የማስተናገድና የመፍታት አቅማችን ከምናስተናግደው ደንበኛ ጋር የሚመጣጠን እና የሚጣጣም መሆን
ይኖርበታል፡፡

 የሙያ ብቃት ምዘና አፈፃፀም ያለበት ደረጃ

በ 2007 ዓ.ም የፅሁፍ ምዘና ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆኑ መምህራን ውስጥ ወንድ 21 ሴት 10 ድምር
31 ርዕሰ መምህር ወንድ 3 ሴት 0 ድምር 3 ለሆኑ መርሱዎች የፅሁፍ ምዘና ተሰጥቷል፡፡
የችግሮቹ መንስኤና ትንተና
 በወረዳችን አመራር የሚታዩ ችግሮች

በጽ/ቤታችን ባለው አመራራችን የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ተግባራችንን ተገቢውን


አደረጃጃት ፈጥሮ እያደገ የሚመጣውን ተግባር ለመሸከም የሚችል እንዲሆን ለማድረግ
የሚያስችል በቂ ግንዛቤ በመፈጠሩ በአንዳንድ ወቅት እየተሰሩ ይስተዋላሉ፡፡ በየደረጃው ባለው
ባለሙያ የጠራ ግንዛቤና አመለካከት ፈጥሮ ስራውን በባለቤትነት ከመምራት አንጻር አንዳንድ
ክፍተቶች ይስተዋላሉ፡፡ በተለይ ሂደቱን ፈጥኖ በማደራጀት እና በቂ የመስሪያ ምቹ ሁኔታ
በመፍጠር በኩል ብዙ መሰራት ይኖርበታል፡፡ ሂደቱ ላይ የተመደቡ ባለሙያዎች ቁጥራቸው 2
በመሆኑ ከመጠን በላይ በሆነ ጫና ስራ እየሰሩ በመሆኑ ስራቸውን ከዚህ በበለጠ በጥራት
ለመስራት በ 2010 ዓ.ም መስተካከል ይኖርበታል፡፡

ስለሆነም ይህ በአመራር የሚስተዋለውን ችግር ከመነሻው በአግባቡ ገምግሞ ለቀጣይ ስራ ማነቆ


አለመሆኑን በማረጋገጥ የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ተግባራችን ወሳኝ ተግባር መሆኑን
በመረዳት በሠራዊት አቅም ለሙሉ ትገበራው ዝግጁ መሆን ይኖርብናል፡፡

 በጽ/ቤት ባለሙያዎች የሚስተዋሉ ችግሮች

የሙያ ብቃት ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ላይ የተሟላ ግንዛቤ በመያዝ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሙያ
አጋሮቹም ሆነ ለባለድርሻ አካላት ለማስጨበጥ የሚደረገው ጥረት አናሳ መሆን ለበርካታ
የአመለካከት ችግሮች በር ከፍቷል፡፡ በስልጠና ወቅት ስራው በተጨባጭ በትምህርት ጥራት
መሻሻል ላይ ያለውን ድርሻ ለመረዳትና በእምነት ይዞ በመጓዝ የተዘጋጁትን ስታንዳርዶች፣
መመሪያዎች ወዘተ ከማስጨበጥ አንጻር ብዙ ይቀረናል፡፡

በአጠቃላይ በፈጻሚዎች ዘንድ የሚስተዋሉትን ችግሮች በመሠረታዊነት ቀይሮ ወደ ተሻለ ደረጃ


በማምጣት ውጤታማ በሆነ መንገድ ዕቅዱን ቆጥሮ ተቀብሎና ቆጥሮ የመፈጸም ብቃት ያለው
ሠራዊት መሆን ይኖርብናል፡፡

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት 2010 ዓ.ም እቅድ Page 5
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት

 በመምህራንና በትምህርት ተቋማት አመራሮች የሚታዩ ችግሮች

የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ተግባር ከተጀመረ ወዲህ በተደረጉ በርካታ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኮች
የነበሩ የተዛቡ አመለካከቶች እንዲጠፉ የተደረገ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ በመምህራን አካባቢ ተቀርፏል ማለት ግን
አይደለም፡፡ በአብዛኛው መምህራን ዘንድ በሥርዓቱ መተግበር በጎ አዝማማሚያ ቢስተዋልም ከሙያ ብቃት
ምዘና ጋር ተያይዞ አበል ይከፈለን የሚሉት ችግሮች ነበሩ፡፡ ይህ አስተሳሰብ መኖሩ ደግሞ ተመዛኞች
ለምዘናው በቂ ትኩረት ሰጥተው ባለመመዘናቸው እየተመዘገበ ባለው የተማሪዎች ውጤት ላይ
አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳለው ያመለክታል፡፡

የትምህርት ተቋማት አመራሮችም የጠራ ግንዛቤ በመያዝ ለስራው መሳካት በየተቋማቸው ግንዛቤ በመፍጠርና ለምዘና
የሚረዱ መረጃዎችን ከማደራጀት አኳያና ለመምህራንና ለር/መምህራን በወቅቱ መረጃዎችን ከማድረስና በትክክል
አስፈጽሞ ከማምጣት ረገድ ክፍትቶች ተስተውለዋል፡፡

የመምህራንም ሆነ የትምህርት ተቋማት አመራሮች የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ተግባር ዋና አላማ ተማሪዎች
ብቃታቸው በተረጋገጠ መምህራን እንዲማሩ፣ ተቋማቱም ብቃታቸው በተረጋገጠ አመራሮች እንዲመሩ በማስቻል
የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል ነው፡፡ በመሆኑም ሂደቱ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተዘረጋ ሥርአት መሆኑን
በማመን እና በመቀበል ለሙሉ ትግበራው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

2.1.3 ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉን ጉዳዮች

ከላይ ለመዘርዘር እንደተሞከረው የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ትግበራ የመጀመሪያ ከመሆኑ
አንጻር ችግሮቹ መፈጠራቸው የሚጠበቅ ቢሆንም ከችግሮቻችን በመማር ቀጣይ ተግባሮቻችንን
የተሳኩና ውጤታማ ለማድረግ ትምህርት መውሰድ እና እንዳይደገሙ መጠንቀቅ ትልቅ ፋይዳ
ይኖረዋል፡፡ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሥርዓቱ መዘርጋት በትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ተግባራችን
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮችን ብቃት መዝኖ እውቅና መስጠት ወሳኝ ተግባር አድርጎ
ከመውሰድ አኳያ ያለበትን የአመላካትና ክህሎት ችግር መፍታት ይኖርብናል፡፡ ተግባራችንን
ከለውጥ መሳሪያዎች ጋር አስተሳስሮ በተደራጀ የሠራዊት አቅም እና ከባለድርሻ አካላት ጋር
በተቀናጀ መንገድ መፈጸም ትርጉም ያለው መሻሻል ለማምጣት ያስችለናል፡፡

 አጋሮችን ለይቶ መስራት

የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ሥርዓትን ተጠቃሚውን የህብረተሰብ ክፍል ከዕቅድ ዝግጀት
እሰከ አተገባበር በማሳተፍ የሚገኘው ውጤት ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን የአተገባበሩም አካል
ማድረግ በሁሉም ደረጃ ይጠበቃል፡፡ በየደረጃው ያለው አደረጃጀት ይህን ህብረተሰብ መለየት
መቻል ይኖርበታል፡፡ ትርጉም ባለው መንገድ መሳተፍ እንዲችል ተገቢውን መዋቅር በመዘርጋት
ከትምህርት ቤት ጀምሮ አደረጃጀት እንዲፈጠር መስራት ይኖርብናል፡፡ ስራን በጋራ ማቀድ፣
መከታተልና መገምገም እንዲሁም ከስታንዳርድ ስረጭት እስከ ምዘና ውጤት አገላለጽ ድረስ
የተጠያቂነትና ግልፀኝነት አሰራር መስፈኑ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ በተለይም በስምምነት ቻርተሩ

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት 2010 ዓ.ም እቅድ Page 6
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት

ከተፈራረምናቸው የህዝብ ክንፍ አደረጃጀቶች ጋር በጥብቅ ዲሲፕሊን ስራችንን አስተሳስረን


መፈጸም ይኖርብናል፡፡

 የመረጃ ጥራት ችግራችንን መፍታት

የተደራጀ፣ ግልጽ የሆነና ተአማኒነት ያለው የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት የመረጃ ስርአት
ማደራጀት ይኖርብናል፡፡ በዚህ መረጃ መሠረት የትኛው ደረጃ ላይ ያለ መምህር ወይም
የትምህርት ተቋማት አመራር እንደሚመዘን መርሃግብር ተነድፎ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ ይህንን
በማጠናከር ለቀጣይ ሥራ የመጠቀም ባህላችንን የማጎልበት፣ አፈጻጸማችንን በተጨባጭና በወቅቱ
የማረጋገጥ ሥራ መሥራት ይገባናል፡፡ በቢሯችን ባለው የመረጃ ስርዓት ችግር የእኛ ሂደትም
ተጋላጭ ስለሚሆን ከመርሱ ልማት ዋና የስራ ሂደት እና ከእቅድና መረጃ ደጋፊ የስራ ሂደት ጋር
በኢንተርፌስ የሚኖረንን ግንኙነት በማጎልበት ችግሩን መሻገር ይኖርብናል፡፡ ሂደቱ በመሰረታዊ
የስራ ሂደት ለውጥ ጥናቱ በተጠናው መሰረት ባለሙያ እንዲሟላ በማድረግ በተለይ የመረጃ
ስራው በውጤታማነት እንዲሰራ መደረግ ይኖርበታል፡፡

3. የ 2010 ዓ.ም እቅድ


3.1 የዕቅዱ ዓላማ

የዓመቱን የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ከነበሩበት ችግሮች በማላቀቅ በበቂ ቅድመ ዝግጅትና
ንቅናቄ በመምራት ብቃት ባላቸው መምህራንና የትምህርት ተቋማት አመራሮች ሙያው እንዲሸፈን
በማድረግ የትምህርት ጥራትን ማሻሻል ነው፡፡
3.2 .የእቅዳችን የርብርብ ማዕከላት፣
 የተደራጀ የልማት ሰራዊት መገንባት፣
 ውጤታማ የምዘና ስርዓትን በማስፈን የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ፣
 የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት፣
 ውጤታማ የመረጃ ስርዓት መዘርጋት፣

3. የእቅዱ ቁልፍ ተግባር

የ 2010 ዓ.ም ቁልፍ ተግባራችን የትምህርት ልማት ሰራዊት በሁሉም ደረጃዎች በመገንባት የትምህርት
ጥራትን ማረጋገጥ ነው፡፡ ለዚህ ቁልፍ ተግባር እውን መሆን የሚከተሉት ዋና ዋና ግቦች ተለይተዋል፡፡
የተደራጀ የልማት ሰራዊት መገንባት፣
ግብ 1፡- ለውጡን የሚመራ ግንባር ቀደም የሂደት አመራር መፍጠር፣
ተግባር አንድ፣ በየደረጃው የሚገኙትን የሂደቱን የልማት ቡድን አመራሮች የተሟላ የግንባር ቀደም መሪነት
ቁመና እንዲይዙ ማድረግ፣

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት 2010 ዓ.ም እቅድ Page 7
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት

ተግባር ሁለት፣ የልማት ቡድን መሪዎች አመራሮችን አፈጻጸም መገምገም፣ በቂ ዝግጅት በማድረግ ወደ ሥራ
ማሠማራት፣
ተግባር ሦስት፣ ግንባር ቀደሞች ሚናቸውን እንዲጫወቱ የጠራ መድረክ ማመቻቸት፣ 
የሚጠበቅ ውጤት፣
- የልማት ቡድኖችን ሊመሩ የሚችሉ ግንባር ቀደሞችን ለአመራርነት ማብቃት፣
- በትራንስፎርሜሽን ፎረም እየሰፋ የመጣ የግንባር ቀደሞች ሚና፣
ግብ 2. የላቀ ፈጻሚነቱን ያረጋገጠ የመንግሥት ክንፍ መፍጠር፣
ተግባር አንድ፣ ከወረዳ እስከ ት/ቤት ባለው የሂደቱ የልማት ቡድኑ የትምሀርት አመራሩንና የፈጻሚውን የእቅድ
አፈጻጸምን በጋራ በመገምገም የአመለካከትና ክህሎት ክፍተት በመለየት ያለማቋረጥ
መገንባት ፣
ተግባር ሁለት፣ የትምህርት አመራሩና ፈጻሚው በቂ ዝግጅት አድርጐ በተቀመጠው የሠራዊት ግንባታ
አደረጃጀትና አሠራር ሥርዓት በልማት ቡድን የተጀመረውን ስራ ማስቀጠል፣
ተግባር ሦስት፣ የልማት ቡድኖቻችን የተሻለ የአገልግሎት አሰጣጥ ቁመና እንዲኖራቸው ማድረግ፣
ተግባር አራት፣ የሂደቱን ባለሙያዎች በዝግጅትና በትግበራ ምእራፍ በበቂ ሁኔታ በማዘጋጀት የሠራዊት አቅም
ሆነው እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ፣
የሚጠበቅ ውጤት፣
o በልማት ቡድኑ በተግባር የተገነባ የልማት ሠራዊት፣
o በተገነባው የልማት ሠራዊት የተሻሻለ የአገልግሎት አሰጣጥ፣

ግብ 3. የህዝብ ክንፍን የሠራዊቱ አካል አድርጎ በማደራጀት ሚናውን እንዲወጣ ማድረግ፣

ተግባር አንድ፣ በስምምነት ቻርተሩ ከተለዩት የሕዝብ ክንፍ አካላት ጋር (መምህራን ማህበር) ፣ መርሱ የስራ
ሂደት በእቅድ ላይ የተመሠረተ የግንኙነትና የተጠያቂነት ሥርዓት በመዘርጋት የሙያ
ፈቃድ አሰጣጥና እድሳቱን ተግባር መምራት፣
የሚጠበቅ ውጤት፣
o በፈቃድ አሰጣጥና እድሳት የተፈጠረ የባለቤትነት ስሜት፣
o በፈቃድ አሰጣጥና እድሳት የላቀ ተሣትፎ

ግብ 4፡- ውጤታማነቱ የተረጋገጠ የሦስቱን አቅሞች ትስስር መፍጠር፣


ተግባር አንድ፣ የውጤት ተኮር ሥርዓቱን አጠናክሮ በመቀጠል የአገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል፣
ተግባር ሁለት፣ ቸክሊስቶችን በየወሩ በሙሉ በመላክ የሂደቱን የመረጃ ስርአት ቀልጣፋ ማድረግና ማጠናከር፣
ተግባር ሶስት፣ ለሂደቱ የተመደበውን በጀት በአግባቡ መጠቀም፣
የሚጠበቅ ውጤት፣
o የተሻሻለ አገልግሎት አሰጣጥ፣
ግብ 5፡- ኪራይ ሰብሳቢነትን በመዋጋት ልማታዊ አመለካከት ማጎልበት፣

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት 2010 ዓ.ም እቅድ Page 8
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት

ተግባር አንድ፣ የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮችን መለየት ክለሳ ማድረግ፣


ተግባር ሁለት፣ ልማታዊ አመለካከትን ማጎልበት፣
የሚጠበቅ ውጤት፣
o የተፈጠረ ልማታዊ አስተሳሰብ፣

ግብ 6. በሚሰጠው አገልግሎት ተገልጋይን ማርካት፣

ተግባር አንድ፣ የተገልጋዮችን እርካታ የአገልግሎት ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ


ተግባር ሁለት፣ ብሮሸሮችን በማዘጋጀት (የሥነ ምግባር መርሆዎችን ሁሉም እንዲያውቀው ማድረግ፣ የሂደቱን
ፈጻሚ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ በመለጠፍ እንዲያውቁት ማድረግ)፣ የተቋሙን
ራእይ፣ ተልእኮ፣ እሴቶች፣ የስራ ሂደቱን ዋና ዋና ተግባራት ሁሉም እንዲያውቀው
ማድረግ፣
ተግባር ሶስት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እስታንዳርድንና የዜጎች ቻርተር ያማከለ ፈጣን ምላሽ አገልግሎትን
በእቅድ የመፈጸም አቅምን ማጎልበት
የሚጠበቅ ውጤት፣
o በስራ ሂደቱ አገልግሎት አሰጣጥ የረካ ተገልጋይ፣

ግብ 7፣ በአህዝቦት ሥራ የለውጡን ተቀባይነት ማጎልበት፣

ተግባር አንድ፣ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ማዘጋጀት፣


ተግባር ሁለት፣ በእቅዱ መሠረት የኮሙኒኬሽን ሥራዎችን ማካሄድ፣
ተግባር ሶስት፣ በየወሩ ግንባር ቀደሞችን በመለየት ሁሉም ት/ቤቶች እንዲያውቁ ማድረግ ለሚመለከተውም
ማሳወቅ፣
ተግባር አራት፣ የለውጥ ኘሮግራሞችን በመተግበር የተሻለ አፈጻጸሞችን በመቀመር ሌሎች እንዲተገብሩት
ማስፋት፣
ተግባር አምስት፣ የልማት ቡዱኑ የለውጡን እንቅስቃሴ በማደራጀት የተቋሙ ማህበረሰብና ተጠቃሚው
እንዲያውቀው የማድረግ ሥራ መሥራት፣
የሚጠበቅ ውጤት፣
o በሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ላይ የጠራ ግንዛቤ፣
ግብ 8 ፡- የክትትል፣ ግምገማና ድጋፍ ሥርዓትን በተጠናከረ መልኩ መዘርጋት፣

ተግባር አንድ፣ የሰራዊቱ ግንባታ ክትትልና የድጋፍ፣ የግምገማና የግብረ-መልስ ሥርአትን መሠረት በጥብቅ
ዲሲፒሊን ተግባራዊ ማድረግ፣
ተግባር ሁለት፣ የፈጻሚዎችንና የትም/አመራሩ የእቅድ አፈጻጸም በመገምገም መልካም አፈጻጸም ያላቸውን
ማበረታታትና ዝቅተኛ አፈጻጸም ያላቸውን እየለዩ መደገፍ፣
ተግባር ሦስት፣ እያንዳንዱ ግለሰብ የራስ ግምገማ እንዲያካሂድ ማድረግ፣
የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት 2010 ዓ.ም እቅድ Page 9
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት

ተግባር አራት፣ ሚዛናዊ የአሠራር ሥርዓት ትግበራ ላይ የታዩ ምርጥ ተሞክሮዎችንና የሌሎችን ልምድ
መቀመርና ማስፋፋት
የሚጠበቅ ውጤት
 የተሰጡ ክትትሎች፣ ድጋፎችና የተሰጡ ግብረ-መልሶች፣
 በሚዛናዊ የውጤት ተኮር አሰራር ተቀምረው የተስፋፉ መልካም ተሞክሮዎች፣
4. ውጤታማ የምዘና ስርዓት በመዘርጋት የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ፣
ግብ 9፣ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ በመለስተኛ እና በመምህር ደራጃ ያሉ 30% መምህራንን እና ሌሎችን መመዘን፡፡
ተግባር አንድ፣ በሁሉም ደረጃ ያሉ በመለስተኛ ደረጃ እና በመምህር ደራጃ የሚገኙ መምህራንን፣ ተመራቂና ፒጅዲቲ
መምህራንን 
መምህራንን  መለየት፣
ተግባር ሁለት፣ ለተለዩት የተመዛኝ መጠን የሚበቃ የምዘና መሳሪያዎችን እና የበጀት ዝግጅት
ማከናዎን፣
ተግባር ሦስት፣ የምዘና ማስተዳደር እና ውጤት ገላጻ ተግባራትን ማከናወን፣
ተግባር አራት፣ በስታንዳርዱ መሰረት ምዘናውን ላለፉ መምህራን የሙያ ፈቃድ መስጠት፣
የሚጠበቅ ውጤት፣
o ተማሪዎች ብቃታቸው በተረጋገጠ መምህራን ይማራሉ፣
o መምህራ ለስራቸው ይተጋሉ ለሙያቸው ክብር ይሰጣሉ፣

ግብ 10፣ የይዘት እና የፔዳጎጂ ምዘና ለወሰዱ ጀማሪ መምህራን የተግባር ምዘና እንዲሰጥ ማድረግ፣
ተግባር አንድ፣ የይዘት እና የተግባ ምዘና የተመዘኑ መምህራንን የስምሪት መረጃ ማደራጀት፣
ተግባር ሁለት፣ ለተመዛኞች በቂ ሊሆን የሚችል መዛኝ እንዲመቻች ማድረግ፣
ተግባር ሶስት፣ ለተመዛኞች የተዘጋጀውን ሩብሪክስ ለተመዛኞች ቀድሞ እንዲደርስ ማድርግ፣
ተግባር አራት፣ የመዛኝ ስምሪት እና የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን ማከናወን፣
ተግባር አምስት፣ የተመዛኞችን ውጤት ከመዛኞች መቀበል እና የማጠናቀር ስራ መስራት፣
ተግባር ስድስት፣ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ውጤት ላመጡ መምህራን የሙያ ፈቃድ
እናዲያገኙ ማድርግ፣
የሚጠበቅ ውጤት፣
o ተማሪዎች ብቃታቸው በተረጋገጠ መምህራን ይማራሉ፣
o መምህራ ለስራቸው ይተጋሉ ለሙያቸው ክብር ይሰጣሉ፣
5. የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት፣
ግብ 11፣ በየደረጃው ያለው በመምህራን እና በትምህርት ተቋማት የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት                ሊከሰት
የሚችል የመልካም አስተዳደር ችግር ተቀርፏል፣
ተግባር አንድ፣ በሁሉም ደረጃ ግልጽ የአሰራር ሂደት በመከተል መምህራን እና አመራሩ መረጃ
እንዲያገኙ ማድረግ፣
ተግባር ሁለት፣ ከመምህራን ማህበር እና ከህዝብ ክንፍ አደረጃጀቶች ጋር በመስራት በሁሉም ባለድርሻ ዘንድ ባለቤትነት
መፍጠር፣

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት 2010 ዓ.ም እቅድ Page 10
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት
ተግባር ሶስት፣ መምህራን እና አመራሩ ለፈጻሚው አካል የሚያቀርቡት መረጃ ሁሉ በመተማመኛ                          ፊርማ
የተረጋገጠ እንዲሆን ማስቻል፣
ተግባር አራት፣ አገልግሎት አሰጣጣችንን በማሳለጥ መጉላላትን ማስወገድ፣

የሚጠበቅ ውጤት፣
o በመተማመን እና በመከባበር ላይ የተመሰረተ ፈጣን እና ውጤታማ አገልግሎት፣
6. ውጤታማ የመረጃ ስርዓት መዘርጋት፣
ግብ 12፣ ታዓማኒ፣ ወቅታዊ፣ በቂ እና ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ የመረጃ ሰርአት መዘርጋት፣
ተግባር አንድ፣ በሁሉም ደረጃ ያሉ መምህራን እና የትምህርት ተቋማት አመራሮችን መረጃ
መለየት፣
ተግባር ሁለት፣ በየደረጃው የተለየውን መረጃ የማደራጀት እና ለአጠቃቀም እንዲመች የማድረግ ስራ
መስራት፣
ተግባር ሶሰት፣ በየጊዜው ከሚኖረው ለውጥ ጋር መራጃውን ውቅታዊ የማደረግ ስራ መስራት፣
ተግባር አራት፣ ለመራጃ ማደራጀት፣ መተንተን እና ወቅታዊ የማድርግ ስራ ምቹ የሆኑ ሶፍትዌሮችን
መፈለግና በእነሱ መጠቀም፣
ተግባር አምስት፣ መረጃ ለሚፈልግ አካል ሁሉ ታዓማኒና ወቅታዊ መረጃ መመገብ፣
                               የሚጠበቅ ውጤት፣
o ቀልጣፋ የተግባር አፈጻጸም፣
o ውጤታማ የውሳኔ አሰጣጥ፣
8. የ 2010 ዓ.ም የመምህራንና የትምህርት ተቋማት የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት የሚዛናዊ
ውጤት ተኮር እቅድ፣

I. የተገልጋይ ዕይታ 36%

ግብ
የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ 4%
ዋና ዋና ተግባራት
1. የደንበኞቻችን ፍላጎት ያለማቋረጥ መለየት፣ መተንተን የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል፣
2. የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነትን ለመለካት 2 የዳሰሳ ጥናት ማካሄድ፣

የሚጠበቅ ውጤት: በተሰጠው አገልግሎት የተፈጠረ የደንበኞች እርካታ

ግብ
የትምህርት ውጤታማነትን ማሻሻል፣ 32%

 በሁሉም ደረጃ ያሉ በመለስተኛ ደረጃ እና በመምህር ደራጃ የሚገኙ መምህራንን መለየት፣


 ለተለዩት መምህራን የሚመጥን መዛኝ እንዲሟላ መጠየቅ፣
 ለተለዩት የተመዛኝ መጠን የሚበቃ የምዘና መሳሪያዎችን እና የበጀት ዝግጅት ማከናዎን፣

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት 2010 ዓ.ም እቅድ Page 11
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት

 የምዘና ማስተዳደር እና ውጤት ገላጻ ተግባራትን ማከናወን፣


 በስታንዳርዱ መሰረት ምዘናውን ላለፉ መምህራን ከፌደራል የሚላክልንን የሙያ ፈቃድ ተቀብሎ
መስጠት፣
 የይዘት እና የተግባር ምዘና የተመዘኑ መምህራንን የስምሪት መረጃ ማደራጀት፣
 ለተመዛኞች በቂ ሊሆን የሚችል መዛኝ አንዲሟላ ማድረግ፣
 ለተመዛኞች የተዘጋጀውን ሩብሪክስ ለተመዛኞች ቀድሞ እንዲደርስ ማድርግ፣
 የመዛኝ ስምሪት እና የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን ማከናወን፣
 የተመዛኞችን ውጤት ከመዛኞች መቀበል እና የማጠናቀር ስራ መስራት፣
 በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ውጤት ላመጡ መምህራን የሙያ ፈቃድ እንዲያገኙ ማድርግ፣
 በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ ስታንዳርዶችን በሙሉ ለሚመለከታቸው የማስተዋወቅ ስራ መስራት፣
 የሙያ ብቃት ስታንዳርዶች፣ የአፈፃፀም መመሪያ ቅጅዎችና የማስተግበሪያ ማኑዋሎች ከዞኑ የስራ ሂደት ተቀብሎ
ማሰራጨት፣
 የትምህርት ይዘትና ፔዳጎጂክ ስታንዳርዶችን ማሰራጨት ፣ (የአፈፃፀም መመሪያ፣ የማስተግበሪያ ማኑዋሎች፣
የይዘትና ፔዳጎጂክ ስታንዳርዶቹን፣ የሙያ ብቃት ስታንዳርዶች፣ በሁሉም ተቋማችን ማሰራጨት)
 የትምህርት አይነቶች የሙያ ብቃት ምዘና መሣሪያዎችን ከዞኑ የሥራ ሂደት መቀበል እና በወረዳ ደረጃ የተሰጠንን
ምዘና እንዲሰጥ ማድረግ፡፡
 የየትምህርት አይነቶች ዝርዝር የምዘና ትንተና /Item analysis/ ማካሄድ ፣
II. ፋይናንስ ዕይታ 10%

ግብ
የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነትን ማሻሻል 10%
1. ለሂደቱ የተመደበውን በጀት በቅልጥፍናና በውጤታማነት /ለታቀደለት ተግባር/ ጥቅም ላይ ማዋል፣

ለግንዛቤ መፍጠር አና ለስልጠና የተያዘ በጀትን በውጤታማነት መጠቀም፣

የሚጠበቁ ውጤቶች

 የተመደበውን በጀት ጥቅም ላይ ማዋል

III. የውስጥ አሠራር ዕይታ 24%

ግብ
የአገልግሎት አሰጣጥን ቅልጥፍናና ውጤታማነት ማሻሻል 6%

1. ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ብቃት ያለው የውስጥ የአሠራር ሥርዓት ማጎልበት፣

 ሁሉንም የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ሰነዶች ተገልጋይ በቀላሉ እንዲያገኛቸው ማስቻል፣
 በየወሩ የስራ ሂደቱን ዕቅድና ሪፖርት ሰነዶች፣ የክትትልና ግምገማ ግብረመልሶችን ማደራጀት፣
የተለያዩ የመልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴዎችን በመጠቀም በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት 2010 ዓ.ም እቅድ Page 12
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት

ማቅረብ፣
 የተቋማትና የመምህራን መረጃዎችን በዝግጅት ምዕራፍ ማሰባሰብ፣ ማደራጀትና አገልግሎት ላይ
ማዋል፣
 የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳትን አስመልክቶ ከባለድርሻዎች የሚሰጠውን ግብረመልስ በሙሉ
እንደ ግበዓት በመጠቀም የአገልግሎት ቅልጥፍናን ማሻሻል፣
 ሁሉም ተመዛኞች ውጤታቸውን ምዘናውን ከወሰዱ ወር ባልሞላ ጊዜ መግለጽ፣
የሚጠበቅ ውጤት፤

o ከወጭ፣ ከግዜ፣ ከመጠንና ከጥራት አኳያ የተሰጠ ቀልጣፋና                                        ውጤታማ


አገልግሎት፣

ግብ
የሥራ ግንኙነትን ማሻሻል 6%

1. የስራ ሂደቱን እቅድ በፈጻሚዎች ሙሉ ተሳትፎ ማዘጋጅት፣


ሁሉም ባለሙያ በውጤት ተኮር እቅድ ዝግጅት ዑደት በባለቤትነት መሳተፍ፣
የግል እቅድ በ 15 ቀንና በዕለት ሸንሽኖ ማዘጋጅትና መተግበር፣
በየ 15 ቀን በሚደረግ ግምገማ መስተጋብሩ ዲሞክራሲያዊ መሆኑን መፈተሽ፣
2. በስራ ሂደቱ እና በሌሎች የስራ ሂደቶች እንዲሁም ከባለድርሻዎች ጋር ውጤታማ የሥራ ግንኙነት መፍጠር፣
 ከመርሱ የስራ ሂደት፣ ከ ICT፣ ከእቅድና መረጃ የስራ ሂደቶች በጋራ እቅድ የተመሰረተ የምክክር
ስብሰባዎችን ማድረግ፣
 አጋሮችንና የተሳትፎ መስካቸውን መለየትና መተንተን (መምህራን ማህበር፣ ተማሪዎችና ወላጆች)፣
በየወሩ ወቅታዊ የመረጃ ልውውጥ ከት/ቤቶች ጋር ማድረግ፣
3. የአህዝቦት ሥራዎችን መሥራት፣
በስራ ሂደቱ በሚዘጋጀው ብሮሸሮች ላይ መረጃዎችን እና የግንዛቤ መፍጠሪያ ጹህፎችን እንዲወጡ
ማድርግ፣
ከባለድርሻዎች ጋር /በዋናነት ከመምህራን ማህበር ጋር/ ውይይቶችን ማካሄድ፣

የሚጠበቅ ውጤት፤
የፈጻሚዎችን የሥራ ባለቤትነትን ስሜት ማሳደግ፣
በትምሀርት ተቋማት መካከል የተጠናከረ የእርስ በእርስ ግንኙነት፣
ከባለድርሻዎች ጋር ጤናማ የሥራ ግንኙነት በመፍጠርና የአህዝቦት ሥራዎችን በመሥራት
ዕቅዶች በተገቢው ጥራት፣ ጊዜና ወጪ እንዲከናወኑ ማስቻል፣
ግብ
የክትትል ግምገማና ድጋፍ አሠራርን ማጎልበት 12%፣

1. የስራ ሂደቱን ዕቅዶች በተገቢው ጥራት፣ ጊዜና ወጪ እንዲከናወኑ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
በእየለቱ ተግባራትን በአንድ ለአምስት እየገመገሙ መፈጸም፣

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት 2010 ዓ.ም እቅድ Page 13
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት
በየሳምንቱ የእያንዳንዱን ፈፃሚ የዕቅድ አፈጻጸም በቡድን መገምገም፣
በግምገማ በተለዩ እጥረቶች (አመለካከት፣ ክህሎት፣ ግብዓት) ላይ ድጋፍ በመስጠት ፈፃሚውን ማብቃት፣
የስራ ሂደቱን የ 15 ቀን፣ ወራሃዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመትና የዓመት የዕቅድ ክንውኖችን በስራ ሂደት ደረጃ
በጋራ መገምገም፣
የ 15 ቀን፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመትና የዓመት የዕቅድ ክንውን ሪፖርቶችን በጥራት አዘጋጅቶ
ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በወቅቱ ማቅረብ፣
በሚሰጡ ግብረ መልሶች መሠረት ዕቅዶቻችንን የመከለስና ሪፖርቶቻችንን የማስተካከል ሥራ መሥራት፣
2. በሁሉም ተቋማት መመሪያዎች፣ ስታንዳርዶች፣ የሙያ ብቃት ምዘና ትንተናዎች እና የተገኙ ውጤቶች ተግባር ላይ
መዋላቸውን ማረጋገጥ፣
በሁሉም ተቋማት በተመረጡ የምዘና ማዕከላት በመገኘት ከቅድመ ዝግጅት እስከ የምዘና መረጃ አሰባሰብ
ያለውን የአፈፃፀም ሂደት መከታተል፣ የሙያ ድጋፍ ማድረግ፣ መገምገምና ግብረ መልስ መስጠት፣
ሁሉንም ባለድርሻዎች የሚያሳትፍ የስድስትና የዘጠኝ ወር የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ (Annual
Review meeting) በማዘጋጀት የዕቅድ አፈፃፀምን በጋራ መገምገምና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ መግባባት፣
ከህዝብ ክንፎች ጋር የጋራ አንድ የእቅድ አፈጻጸም መድረክ መፍጠር፣

የሚጠበቅ ውጤት ፡

በሁሉም ተቋማት ወጥና ቀጣይነት ያለው አፈጻጸም እንዲኖር ማስቻል፣

መማማርና እድገት 30%


ግብ 
ተቋማዊ የትምህርትና ሥልጠና ልማት ሠራዊት አቅም ማሳደግ፣12%

1. በአመለካከት፣ በክህሎትና በዕውቀት የተገነባ ጠንካራ የለውጥ ኃይል ማፍራት

የለውጥ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ እቅድ ማዘጋጀት


በሁሉም ፈፃሚ ሰራተኞች መካከል የሚታየውን የአመለካከትና የክህሎት ክፍተት መለየት

ከፈጻሚ ሠራተኞች መካከል በአመለካከትና ተጨባጭ ውጤት በማስመዝገብ ሁሉንም የለውጥ ሀይል
እንዲሆኑ ማበረታታት፣
ተጨባጭ ውጤት ማምጣት ያልቻሉት የአመለካከት ለውጥ እንዲያመጡ በተግባራዊ እንቅስቃሴ
በመደገፍ ማብቃት፣
የለውጥ ፍላጎቱ ኖሯቸው የአቅም ችግር ያለባቸውን ተጨማሪ ስልጠና በመስጠት አቅማቸውን
ገንብቶ ማሰማራት፣
በየሳምንቱ ሂደታዊ ክትትልና ግምገማ በማካሄድ የትም/አመራሩን ብቃት ማሻሻል፣

የሚጠበቅ ውጤት ፣

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት 2010 ዓ.ም እቅድ Page 14
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት
o በአመለካከት፣ በክህሎትና በዕውቀት የተገነባ ጠንካራ የለውጥ ኃይል መፍጠር።
o ደረጃውን የጠበቀ ዕቅድ የማቀድ አቅም መፍጠር
o በተቀመረ ምርጥ ተሞክሮ ድጋፍ መስጠት
2. ግንዛቤ መፍጠሪያ ስልጠና በማዘጋጀት የትም/ተቋማት አመራሮችን ማብቃት፣
ለ 20 የትም/ተቋማት አመራሮችን ሥልጠና መስጠት፣

ትምህርት ቢሮው በሚያዘጋጃቸው ስልጠናዎች በአግባቡ በመሳተፍ የራስን አቅም ገንብቶ ለሌሎች
አቅም መሆን፣

3. ምርጥ ተሞክሮ ቀምሮ ማስፋት፣

የሚጠበቅ ውጤት ፤

o በሥራ ላይ ሥልጠና የመፈፀም አቅማቸው የተገነቡ ባለሙያዎች፣

ግብ
የስራ ሂደቱን የአሠራር ሥርዓት ማሻሻል 18%፣

1. በወረዳ ደረጃ የመምህራንና የትምህርት ተቋማት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ስቲሪንግ ኮሚቴ
እንዲቋቋም ማድረግ፣
o ስቲሪሚንግ ኮሚቴ በየደረጃው ማቋቋም
o ለተቋቋመው ስትሪሚንግ ኮሚቴ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መስራት፣

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት 2010 ዓ.ም እቅድ Page 15
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት
I. የ 2010 ዓ.ም የመምህራንና የትምህርት ተቋማት የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት የስራ ሂደት የሚዛናዊ ውጤት ተኮር እቅድ ስኮር ካርድ፣

ዕይታዎች ግቦችና ተግባራት ለግቡና የግብና የተግባር መለኪያ የአፈፃ የ 2010 የአፈፃፀም የሚፈፀምበት ሩብ ዓመት ፈጻሚ በጀት
ና ለተግባሩ ውጤት ፀም ኢላማ ደረጃዎች አካል
ክብደታቸ የተሰጠ መነሻ
ው ክብደት

መካከለኛ
ዝቅተኛ

ከፍተኛ

የላቀ

1ኛ

2ኛ

3ኛ

4ኛ
ተገልጋይ እይታ 36%
ግብ: የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ 4% በተሰጠ አገልግሎት የደንበኛ 89% 100%

80-94

95-100
50-59

60-79
የተፈጠረ የደነበኞች እርካታ
እርካታ በመቶ
ኛ፣
ተግባር 1 የደንበኞቻችን ፍላጎት በመለየትና 4% የተዘጋጀ የፍላጎት % 0 100 x x x x x
በመተንተን የአገልግሎት አሰጣጥን ትንተና ሰነድ
ማሻሻል፣
ተግባር 2 የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነትን 4% የጥናት ሰነድ % 0 100 x x
በዳሰሳ ጥናት መለካት

ግብ: የትምህርት ውጤታማነትን ማሻሻል፣ 32% የሙያ ፈቃድ ያገኙ ቁጥር        


መምህራንና
የት/ተቋማት
አመራር
ተግባር 1 በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ 6% ትውውቁን ያገኙ ቁጥር 1 x x x x
ስታንዳርዶችን በሙሉ ለሚመለከታቸው ፈጻሚዎች ብዛት
የማስተዋወቅ ስራ መስራት፣

ተግባር 2 የሙያ ብቃት ስታንዳርዶች፣ የአፈፃፀም መመሪያ 4% የተሰራጩ ሰነዶች ቁጥር 0     X   X X X


ቅጅዎችና የማስተግበሪያ ማኑዋሎች ከትምህርት
ሚኒስቴር ተቀብሎ ማሰራጨት፣

ተግባር 3 የትምህርት ይዘትና ፔዳጎጂክ ስታንዳርዶችን 5% የተሰራጩ ቁጥር 0 X X X X


ማሰራጨት ፣ ስታንዳርዶች ብዛት
(የአፈፃፀም መመሪያ፣ የማስተግበሪያ
ማኑዋሎች፣ የይዘትና ፔዳጎጂክ
ስታንዳርዶቹን፣ የሙያ ብቃት ስታንዳርዶች፣
በሁሉም ተቋማት ማሰራጨት
ተግባር 4 የትምህርት አይነቶች የሙያ ብቃት ምዘና 3% የተመዘኑ መምህራን ቁጥር 31 X X X X
መሣሪያዎችን ከትምህርት ሚኒስቴር መቀበል ብዛት
እና በወረዳ ደረጃ የተሰጠንን ምዘና
መመዘን፡፡

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት የ 2010 ዓ.ም እቅድ Page 16
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት
ተግባር 5 የየትምህርት አይነቶች ዝርዝር የምዘና ትንተና 4% ትንተና ቁጥር 0 X X X X X
/Item analysis/ ማካሄድ ፣ የተሰራባቸው 5
የትምህር አይነት
ተግባር 6 በትንተናው ውጤት ላይ የተመሠረቱ 6% የተካሄዱ መድረኮች በቁጥር 0 2 X X X X
አውደጥናቶችና የምክክር መድረኮች ብዛት
ማካሄድ

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት የ 2010 ዓ.ም እቅድ Page 17
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት
የፋይናንስ እይታ 10%        
  የተመደበውን ሀብት በመቶኛ                  
ግብ: የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነትን 10% ለታቀደለት ዓለማ
ማሻሻል ጥቅም ላይ ማዋል
ተግባር 1 ለሂደቱ የተመደበውን በጀት በቅልጥፍናና 10% የተመደበውን ሀብት በመቶኛ 0 100      X X X X X
በውጤታማነት /ለታቀደለት ተግባር/ ለታቀደለት ዓለማ
ጥቅም ላይ ማዋል፣ ጥቅም ላይ ማዋል

የውስጥ አሠራር 24%


ግብ : የአገልግሎት አሰጣጥን ቅልጥፍናና 6% የተሰጠ ቀልጣፋና
ውጤታማነት ማሻሻል ውጤታማ
አገልግሎት

ተግባር ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት 6% የተሰጠ ቀልጣፋና % 80 90 X X X X X


1 ለመስጠት የሚያስችል ብቃት ያለው ውጤታማ
የውስጥ የአሠራር ሥርዓት ማጎልበት፣ አገልገሎት

  ግብ: የሥራ ግንኙነትን ማሻሻል 6% ዕቅዶች በተገቢው                      


ጥራት፣ ጊዜና ወጪ
ክንውን
ተግባር የስራ ሂደቱን እቅድ በፈጻሚዎች ሙሉ 3% እቅድ አፈጻጸም % 100 100 X X
1 ተሳትፎ ማዘጋጅት፣ በመቶኛ
ተግባር በስራ ሂደቱ እና በሌሎች የስራ ሂደቶች 3% የተሰሩ የአህዝቦት % 70 95 X X X X X
2 እንዲሁም ከባለድርሻዎች ጋር ውጤታማ ሥራዎች
የሥራ ግንኙነት መፍጠር፣
  ግብ : የክትትል ግምጋማና ድጋፍ አሠራርን 12% የተከናወነ ክትትል፣ በዙር                
ማጎልበት ድጋፍ፣ ግምገማና
ግብረ መልስ
ተግባር ዕቅዶች በተገቢው ጥራት፣ ጊዜና ወጪ 6% የግምገማ በቁጥር 0 X X X X X
1 እንዲከናወኑ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣ መድረኮች፣
ሪፖርቶች፣
ግብረመልሶች 4
ተግባር የመምህራንና የትምህርት ተቋማት 6% የተደረገ ክትትልና በዙር 0 X X X X
2 አመራር መመሪያ፣ስታንዳርዶች ፣ የሙያ ግምገማ
ብቃት ምዘና ትንተናዎች እና የተገኙ
ውጤቶች ተግባር ላይ መዋላቸውን
ማረጋገጥ፣ 2
መማማርና እድገት 30%
ግብ: ተቋማዊ የትምህርትና ሥልጠና 12% በአመለካከት፣              

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት የ 2010 ዓ.ም እቅድ Page 18
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት
ልማት ሠራዊት አቅም ማሳደግ፣ በክህሎትና
በዕውቀት የተገነባ
ጠንካራ የለውጥ
ኃይል መፍጠር።
ተግባር በአመለካከት፣ በክህሎትና በዕውቀት 6% በአመለካከት፣ X X X X X
1 የተገነባ ጠንካራ የለውጥ ኃይል ማፍራት በክህሎትና
በዕውቀት የተገነባ
ጠንካራ የለውጥ
ኃይል በመቶኛ 70 90
ተግባር ግንዛቤ መፍጠሪያ ስልጠና በማዘጋጀት 6% የተሰጠ ሠልጠና X X X X X
2 የትም/ተቋማት አመራሮችን ማብቃት፣
በቁጥር 18 20
  ግብ: የስራ ሂደቱን የአሠራር ሥርዓት 18% በሁሉም ደረጃ                      
ማሻሻል የመ/ትም/አመራር
የሙያ ፈቃድ
አሰጣጥና እድሳት
ተግባራትና
ኃላፊነቶችን
መሸከምና ውጤት
ማስመዝገብ የሚችል
አደረጃጀት
ተፈጥሯል፡፡
ተግባር በወረዳ እና በት/ቤት ደረጃ የመምህራንና 18% የተፈጠረ ቁጥር X X
1 የትምህርት ተቋማት አመራር የሙያ አደረጃጀት
ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ስቲሪንግ ኮሚቴ
እንዲቋቋም ማድረግ፣
30 89

የ 2010 ዓ.ም የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት ዕቅድ ማስፈጸሚያ የድርጊት መርሃ ግብር፣

የርብር የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መነሻ ኢላማ የመፈጸሚያ ጊዜ በሩብ አመት ምርመራ



ማዕከል 1ኛ 2ኛ 3ኛ 4ኛ
የ ግብ 1፡- ለውጡን የሚመራ ግንባር ቀደም የሂደት አመራር መፍጠር፣


ተግባር አንድ፣ የልማት ቡድን አመራሮች የተሟላ የግንባር ቀደም መሪነት ቁመና እንዲይዙ ማድረግ፣ 75 100 X X X X
ራ ተግባር ሁለት፣ የልማት ቡድን መሪዎች አመራሮችን አፈጻጸም መገምገም፣ በቂ ዝግጅት በማድረግ ወደ ሥራ ማሠማራት፣ 82 100 X X X X


ተግባር ሦስት፣ ግንባር ቀደሞች ሚናቸውን እንዲጫወቱ የጠራ መድረክ ማመቻቸት፣  34 100 X X X X
ል ግብ 2. የላቀ ፈጻሚነቱን ያረጋገጠ የመንግሥት ክንፍ በመፍጠር፣

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት የ 2010 ዓ.ም እቅድ Page 19
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት
የርብር የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መነሻ ኢላማ የመፈጸሚያ ጊዜ በሩብ አመት ምርመራ

ማዕከል 1ኛ 2ኛ 3ኛ 4ኛ
ማ ተግባር አንድ፣ በልማት ቡድኑ አመራሩንና የፈጻሚውን የእቅድ አፈጻጸምን በጋራ በመገምገም የአመለካከትና ክህሎት ክፍተት 67 100 X X X X
ት በመለየት ያለማቋረጥ መገንባት ፣

ራ ተግባር ሁለት፣ አመራሩና ፈጻሚው በቂ ዝግጅት አድርጐ በተቀመጠው የሠራዊት ግንባታ አደረጃጀትና አሠራር ሥርዓት በልማት 87 100 X X X X
ዊ ቡድን የተጀመረውን ስራ ማቀጣጠል፣
ት ተግባር ሦስት፣ የልማት ቡድኖቻችን የተሻለ የአገልግሎት አሰጣጥ ቁመና እንዲኖራቸው ማድረግ፣ 70 100 X X X X


ተግባር አራት፣ የሂደቱን ባለሙያዎች በዝግጅትና በትግበራ ምእራፍ በበቂ ሁኔታ በማዘጋጀት የሠራዊት አቅም ሆነው 89 100 X X X X
እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ፣
ን ግብ 3. የህዝብ ክንፍን የሠራዊቱ አካል አድርጎ በማደራጀት ሚናውን እንዲወጣ ማድረግ፣

ት፣ ተግባር አንድ፣ ከተለዩት የሕዝብ ክንፍ አካላት ጋር በእቅድ ላይ የተመሠረተ የግንኙነትና የተጠያቂነት ሥርዓት በመዘርጋት የሙያ 60 100 X X X X
ፈቃድ አሰጣጥና እድሳቱን ተግባር መምራት፣
ግብ 4፡- ውጤታማነቱ የተረጋገጠ የሦስቱን አቅሞችትስስር መፍጠር፣
ተግባር አንድ፣ የውጤት ተኮር ሥርአቱን አጠናክሮ በመቀጠል የአገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል፣ 93 100 X X X X
ተግባር ሁለት፣ ቸክሊስቶችን በየወሩ በመላክ የሂደቱን የመረጃ ስርአት ማጠናከር፣ 100 100 X X X X
ተግባር ሶስት፣ ለሂደቱ የተመደበውን በጀት በአግባቡ መጠቀም፣ 0 100 X X X X
ግብ 5፡- ኪራይ ሰብሳቢነትን በመዋጋት ልማታዊ አመለካከት ማጎልበት፣
ተግባር አንድ፣ የኪራይሰብሳቢነት ምንጮችን መለየት ክለሳ ማድረግ፣ 70 100 X X X X
ተግባር ሁለት፣ ልማታዊ አመለካከትን ማጎልበት፣ 70 100 X X X X
ግብ 6. በሚሰጠው አገልግሎት ተገልጋይን ማርካት፣
ተግባር አንድ፣ የተገልጋዮችን እርካታ የአገልግሎት ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ 80 100 X X
ተግባር ሁለት፣ ኩዊክ ዊንን ሥርአት ማድረግ (የሥነ ምግባር መርሆዎችን ሁሉም እንዲያውቀው ማድረግ፣ የሂደቱን ፈጻዎሚዎች 69 100 X X X X
የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ በመለጠፍ እንዲያውቁት ማድረግ)፣የተቋሙን ራእይ፣ ተልእኮ፣ እሴቶች፣ የስራ ሂደቱን ዋና ዋና
ተግባራት ሁሉም እንዲያውቀው ማድረግ፣
ተግባር ሶስት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እስታንዳርድንና የዜጎች ቻርተር ያማከለ ፈጣን ምላሽ አገልግሎትን በእቅድ የመፈጸም 80 90 X X X X
አቅምን ማጎልበት
ግብ 7፣ በአህዝቦት ሥራ የለውጡን ተቀባይነት ማጎልበት፣
ተግባር አንድ፣ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ማዘጋጀት፣ 0 100 X X X
ተግባር ሁለት፣ በእቅዱ መሠረት የኮሙኒኬሽን ሥራዎችን ማካሄድ፣ 0 100 X X X X
ተግባር ሶስት፣ በየወሩ ግንባር ቀደሞችን በመለየት ሁሉም ሠራተኛ እንዲያውቅ ማድረግ ለሚመለከታችው ማሳወቅ፣ 0 100 X X X X
ተግባር አራት፣ የለውጥ ኘሮግራሞችን በመተግበር የተሻለ አፈጻጸሞችን በመቀመር ሌሎች እንዲተገብሩት ማስፋት፣ 0 100 X X X X
ተግባር አምስት፣ የልማት ቡዱኑ የለውጡን እንቅስቃሴ በማደራጀት የተቋሙ ማህበረሰብና ተጠቃሚው እንዲያውቀው የማድረግ 7 100 X X X X
ሥራ መሥራት፣
ግብ 8 ፡- የክትትል፣ ግምገማና ድጋፍ ሥርዓትን በተጠናከረ መልኩ መዘርጋት፣
ተግባር አንድ፣ የሰራዊቱ ግንባታ ክትትልና የድጋፍ፣ የግምገማና የግብረ-መልስ ሥርአትን መሠረት በጥብቅ ዲሲፒሊን ተግባራዊ 70 100 X X X X
ማድረግ፣
የ ተግባር ሁለት፣ የፈጻሚዎችንና አመራሩ የእቅድ አፈጻጸም በመገምገም መልካም አፈጻጸም ያላቸውን ማበረታታትና ዝቅተኛ 0 100 X X
ት አፈጻጸም ያላቸውን እየለዩ መደገፍ፣
ም ተግባር ሦስት፣ እያንዳንዱ ግለሰብ የራስ ግምገማ እንዲያካሂድ ማድረግ፣ 75 100 X X X X

ተግባር አራት፣ ሚዛናዊ የአሠራር ሥርዓት ትግበራ ላይ የታዩ ምርጥ ተሞክሮዎችንና የሌሎችን ልምድ መቀመርና ማስፋፋት 65 100 X X X X

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት የ 2010 ዓ.ም እቅድ Page 20
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት
የርብር የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መነሻ ኢላማ የመፈጸሚያ ጊዜ በሩብ አመት ምርመራ

ማዕከል 1ኛ 2ኛ 3ኛ 4ኛ
ር ግብ 9. በሁሉም ደረጃ የሚገኙ በመለስተኛ እና በመምህር ደራጃ ያሉ መምህራንን፣ የ 2007 ዲፕሎማ ተመራቂ እና ፒጅዲቲ
ት መምህራንን መመዘን፣
ን ተግባር አንድ፣ በሁሉም ደረጃ ያሉ በመለስተኛ ደረጃ እና በመምህር ደራጃ የሚገኙ መምህራንን፣ ዲፕሎማ ተመራቂ እና ፒጅዲቲ 90 100 X X X
ው መምህራንን መለየት፣
ጤ ተግባር ሁለት፣ ለተለዩት መምህራን የሚመጥን መዛኝ መለየትና ለስልጠና መላክ፣ 0 100 X X

ተግባር ሶስት፣ ለተለዩት የተመዛኝ መጠን የሚበቃ የምዘና መሳሪያዎችን እና የበጀት ዝግጅት ማከናዎን፣ 0 100 X X

ነ ተግባር አራት፣ የምዘና ማስተዳደር እና ውጤት ገላጻ ተግባራትን ማከናወን፣ 75 100 X X
ት ተግባር አምስት፣ በስታንዳርዱ መሰረት ምዘናውን ላለፉ መምህራን የሙያ ፈቃድ መስጠት፣ 0 100 X

ሳ ግብ 10፣ የይዘት እና የፔዳጎጂ ምዘና ለወሰዱ ጀማሪ መምህራን የተግባር ምዘና መስጠት፣
ደ ተግባር አንድ፣ የይዘት እና የተግባር ምዘና የተመዘኑ መምህራንን የስምሪት መረጃ ማደራጀት፣ 0 100 X X

ተግባር ሁለት፣ ለተመዛኞች በቂ ሊሆን የሚችል መዛኝ መለየት እና ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ፣ 0 100 X X
ተግባር ሶስት፣ ለተመዛኞች የተዘጋጀውን ሩብሪክስ ለተመዛኞች ቀድሞ እንዲደርስ ማድርግ፣ 20 100 X X X X
ተግባር አራት፣ የመዛኝ ስምሪት እና የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን ማከናወን፣ 0 100 X X X X
ተግባር አምስት፣ የተመዛኞችን ውጤት ከመዛኞች መቀበል እና የማጠናቀር ስራ መስራት፣ 0 100 X X
የመልካ ግብ 11፣ በየደረጃው ያለው በመምህራን እና በትምህርት ተቋማት የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ሊከሰት የሚችል የመልካም
ም አስተዳደር ችግር ተቀርፏል፣
አስተዳ ተግባር አንድ፣ በሁሉም ደረጃ ግልጽ የአሰራር ሂደት በመከተል መምህራን እና አመራሩ መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ፣ 90 100 X X X X
ደር
ተግባር ሁለት፣ ከመምህራን ማህበር እና ከህዝብ ክንፍ አደረጃጀቶች ጋር በመስራት በሁሉም ባለድርሻ ዘንድ ባለቤትነት መፍጠር፣ 70 100 X X
ችግርን
መፍታ ተግባር ሶስት፣ መምህራን እና አመራሩ ለፈጻሚው አካል የሚያቀርቡት መረጃ ሁሉ በመተማመኛ ፊርማ የተረጋገጠ እንዲሆን 100 100 X X X X
ት ማስቻል፣
ተግባር አራት፣ አገልግሎት አሰጣጣችንን በማሳለጥ መጉላላትን ማስወገድ፣ 95 100 X X X X
ውጤ ግብ 12፣ ታማኒ፣ ወቅታዊ፣ በቂ እና ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ የመረጃ ሰርአት መዘርጋት፣
ታማ ተግባር አንድ፣ በሁሉም ደረጃ ያሉ መምህራን እና የትምህርት ተቋማት አመራሮችን መረጃ መለየት፣ 95 100 X X X X
የመረ
ጃ ተግባር ሁለት፣ በየደረጃው የተለየውን መረጃ የማደራጀት እና ለአጠቃቀም እንዲመች የማድረግ ስራ መስራት፣ 95 100 X X X X
ስርአት ተግባር ሶሰት፣ በየጊዜው ከሚኖረው ለውጥ ጋር መራጃውን ወቅታዊ የማደረግ ስራ መስራት፣ 95 100 X X X X
መዘርጋ
ት ተግባር አራት፣ ለመረጃ ማደራጀት፣ መተንተን እና ወቅታዊ የማድርግ ስራ ምቹ የሆኑ ሶፍትዌሮችን መፈለግና በእነሱ መጠቀም፣ 55 100 X X X X
ተግባር አምስት፣ መረጃ ለሚፈልግ አካል ሁሉ ታማኒና ወቅታዊ መረጃ መመገብ፣ 90 100 X X X X

                             

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት የ 2010 ዓ.ም እቅድ Page 21
የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዋና የስራ ሂደት

የመተማ ወረዳ የሙያ ፈቃድና እድሳት ዋና የሥራ ሂደት የ 2010 ዓ.ም እቅድ Page 22

You might also like