Professional Documents
Culture Documents
መግቢያ፡-
የሀገራችንን ህዳሴ ለማረጋገጥ መንግስት የ 5 ዓመት የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በመንድፍ በርካታ ተግባራት
በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የልማት ፣ የመልካም አስተዳደርና የመ /ስ/ግንባታ ተግባራትን በቀጣይነትና በዘላቂነት
ለመተግበር የተደራጀ የልማት ሰራዊት ፈጥሮ መገንባት አማራጭ የሌለዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ በመሆኑም የጥራት ያለው
ትምህርት አለመስጥ፣ በት/ቤቶች ስታንዳርዱን የጠበቀ ክፍል፣ወንበርና ሌሎች የትምህርት መሳሪያዎች አለመኖር
ከስር መሰረቱ ለመፍታት ትምህርት ሙያተኛውና የመረሱ የልማት ሰራዊት አደረጃጀት በማዋቀር ተግባራትን
መፈጸም ከተጀመረ ዉሎ አድሯል ፡፡
በመሆኑም ከማኔጅመንት ኮሚቴ እስከ 1 ለ 5 አደረጃጀት በማደራጀትና ወደ ስራ በማስገባት ባለፈዉ ዓመት የተሻለ
ጅምር ስራ ተሰርቷል ፡፡ በዚህ በጀት ዓመትም ሁሉን የጽ/ቤት ተግባራት በኃላፊነት ለመፈፀም ያመች ዘንድ ይህን
የማኔጅመንት ኮሚቴ እቅድ ተዘጋጅቷል ፡፡
የዕቅዱ ዋና ዓላማ
የእቅዱ አስፈላጊነት
ግንባታ ማዕከል ያደረገ ሳምንታዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ በማድረግ ጠንካራ ጎኖቻችንን ማጎልበትና ከደክመቶቻችን
ፈጥነን እንድንወጣ የሚያስችል የማስተካከያ ስራ በመስራት ደረጃ በመለየት እዉቅና በመፍጠር ማኔጅመንቱን የስራዊት
ቁመና በማላበስ ትምህርት ሙያተኛውና የመረሱ የልማት ሰራዊት ለመፍጠርና ለመገንባት ነው፡፡
ግብ 1
የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚን አምሮው የሚፀየፍ የልማታዊ ፖለቲካል ኢኮኖሚ በመስሪያ ቤታችን እንዲገነባ
አልሞ የሚሰራ የለዉጥ ሀዋሪያ የሆነ ሰራተኛ መፍጠር
የሚከናወኑት ተግባራት
ሁሉን የስራ ሂደት አስተባባሪዎች እና ባለሙያዎች ከእቅድ ዝግጅት እስከ ማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ ተግባራትን በበላይነት
እንዲፈፅሙና የሀላፊነት መንፈስ እንዲላበሱ ማድረግ
ሳምንታዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ በተከታታይ ለማድረግ ሰራተኛዉን ደረጃ መለየት
የእለት ግምገማ በማድረግ በየቀኑ ሞዴል ሰራተኛ መፍጠር
በየሳምንቱ በየወሩ ኮከብ ሰራተኞችን መለየትና ማበረታታት
አጫጭር ስልጠናዎች በማዘጋጀት በጽ/ቤቱ ያሉ የአመለካከት፣ የክህሎት፣የአስ /አደረጃጀት ችግሮችን በየጊዜዉ መፍታት
፡፡
የጽ/ቤታችን የሚከሰቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለቅሞ በመለየት ራሱን የቻለ ዕቅድ በማዘጋጀት ችግሮች
መፍታትና መላዉ ሰራተኛ አገልግሎት አሰጣጡን በከፍተኛ ደረጃ ማሻሻል ፡፡
ምርጥ ተሞከክሮችዎችን መቀመርና ማስፋፋት
ግብ 2
ለተቋማችን የጋራ አስተሳሰብ /Hegemony/ እና የቡድን መንፈስ/Team sprit/ በመግንባት በሁሉም ሙያተኞች
የተቀራረበ የአመለካከት አንድነት መፍጠር
የሚከናወኑ ተግባራት
`በስድስቱም ሂደት ተግባርን ማዕከል ያደረገ የአስተሳሰብ አንድነት እንዲፈጠር ማድረግ
ስራን በመደባዊ ትግል በመምራት ፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት አቋም ያለዉ ሙያተኛ መፍጠር
ግብ 3
በተግባራቸዉ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸዉ ሞዴል ሰራተኞችን በመለየትና በማፍራት የመሪነት ሚና እንዲያስቀጥሉ
ማድረግ
በየጊዜዉ በሚካሄዱ ግምገማዎች የሞዴል ሰራተኞች ልየታ ተግባርን ማዕከል ያደረገ እንዲሆን ማስቻል
በየወሩ ጠንካራ አፈፃፀም ያላቸዉን የስራ ሂደቶች መለየትና እወቅና መስጠት
ልዩ ልዩ ስልጠና ነክ የግምገማ መድረኮችን ማዘጋጀት
በሁሉም የስራ ሂደት ባሉ ባለሙያዎች በመማማር ዕድገት ፕሮግራም የተቀራረበ እዉቀት በመፍጠር
የሰራተኛዉን አቅም ማመጣጠን መቻል ፡፡
ግብ 4 በስድስቱም የስራ ሂደቶች ያሉትን አደረጃጀቶች በጥብቅ በመፈተሸና አቅም በመገንባት የልማት ሰራዊት
ማፍሪያ ማዕከል ማድረግ ፡፡
የ 1 ለ 5 ዕለታዊ ዉይይት በዕቅዱ መሰረት እየገመገሙ አፈፃፀሙን ለዉጤት በሚበቃ ሁኔታ መምራት
የስራ ቡድን አደረጃጀት በሳምንቱ የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ
በስራ ሂደቱ ባሉ ባለሙያዎች ተቀራራቢ እውቀትና ክህሎት ለመማማርና እድገት ፕሮግራም ወደ ተቀራረበ
አፈጻጸም እንዲኖራቸው ማድረግ
በሁሉም የስራ ሂደቶች ተግባራትን በልማት ሰራዊት ግንባታ ስራዎች እንዲፈጸሙ ማድረግ