You are on page 1of 6

ጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ

ቴ/ሙ/ት/ስ ፕሮግራመ
የሙያ ብቃት ምዘና የትግበራ እቅድ

ጀማል ሰይድ ይመር

ታህሳስ 14/2016 ዓ/ም


አዲስ አበባ
መግቢያ

በጌጅ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ በቴ/ሙ/ት/ስ ፕርግራም ስር ስልጠናቸዉን አጠናቀዉ የተመረቁ


እና ስልጠናቸዉን በመከታተል ላይ ያሉ ሰልጣኞችን በሙያ ብቃት ምዘና ዉጤታማ
እንዲሆኑና የሚጠበቅባቸዉን የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ሰነድ አማልተዉ እንዲወጡ
በማሰብ በባለፋት ወራት ዘርፈ ብዙ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸዉ ይታወቃል። ሆኖም
ግን የሙያ ብቃት ምዘና ስራና የአፈፃፀሙ ዉጤት በተቋም ደረጃ ሲለካ ብዙም አመርቂ
አይደለም። ስለሆነም በነበሩት ጊዜያት የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶችን
ለማስቀጠል፣ የታዩ ክፍተቶች ለመሙላትና ያጋጠሙ ችግሮችን ከመሰረቱ ለመፍታት
እንዲቻል በማሰብ በጌ/ዩ/ኮ ደረጃ ከማኔጅመንት አባላት የተውጣጣ የሙያ ብቃት ምዘና
ቋሚ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል። በዚህም መሰረት የታሰበዉን ዓላማ
ለማሳካት የሚያስችል የሙያ ብቃት ምዘና የትግበራ እቅድ በቋሚ ኮሚቴው የተዘጋጀ
ሲሆን እቅዱም በዋናነት በሶስት አብይ ተግባራት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ዝርዝር ጉዳዮችን
የያዙ ናችው።

አላማ
ባጠቃላይ ይህ እቅድ ዋና አላማው የተቋሙ ስር በተለያዩ ፕሮግራሞች ያሉ ብርካታ
ተማሪዎች ወደ ምዘና ስርዓት እንዲገቡ የማድረግና የምዘና ስራዉን ዉጤታማ ለማድረግ
ሊሰሩ የሚገቡ አብይና ንዑስ ተግባራትን በመለየት አፈፃፀማቸዉን ለመከታተልና
ለመገምገም የሚያስችሉ ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት ማስቻል ነው።
አብይ ተግባራት
ክላይ በተገልጸው መሰረት ቀጥሎ የሚቀርበዉ በቋሚ ኮሚቴው የተዘጋጀው የሙያ ብቃት ምዘና የትግበራ እቅድ ሲሆን እቅዱም በሶስቱ አብይ
ተግባራትና በስሩ የሚከናወኑ ናዑስ ተግባራትን ተካተውበት ለማቅረብ ተሞክሯል።

አብይ ተግባር 1 በአሮጌዉ የስልጠና ስርዓት ተምረዉ በ 2015 ዓ.ም የተመረቁ ነገር ግን የሙያ
ብቃት ምዘና ያልተመዘኑና ብቁ ያልሆኑ ሰልጣኞችን የሚመለከት ነዉ።
የመጀመሪያ ዙር እንቅስቃሴ ለማስቀጠል
1.1 ከዚህ በፊት በዕቅድ ተይዞ ሲሰራባቸው የነበሩ የምዘና ስራዎችና የአፈፃፀም

ውጤቶች ብካምፓስ ደረጃ መገምገምና ክፍተቶችን ለይቶ የማስተካከያ

እርምቶቹን ማስቀምጥ

1.2 በባለፉት ጊዚያት የታየዉን ጥሩ አጀማመርንና ተነሳሽነትን በቀጣይ አጠናክሮ

በማስቀጠል በባለፈው ዕቅድ ያልተመዘኑ ቀሪ ተማሪዎች ወደ ምዘና እንዲገቡ

በማድረግ በሙያ ብቃት ምዘና ዉጤታማ ለማድረግ የትግበራ እቅድ አውጥቶ

ወደ ስራ መግባት፣ሂደቱን መከታተልና መገምገም

1.3 በ 2015 ዓ.ም ከተመራቂ ሰልጣኞችን መካከል 90% የሚሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ

የሙያ ብቃት ምዘና ተመዝነዉ የብቃት ማረጋገጫ ሰነድ እንዲያስገቡ የሚረዱ

አሰራሮችንና ተግባራትን መስራት


1.4 በተቋሙ ከሚላኩ ተመዛኞች በተጨማሪ በግል መመዘን የሚፈለጉትን ለይቶ

የሙያ ብቃት ምዘና ተመዝነዉ የብቃት ማረጋገጫ ሰነድ እንዲያስገቡ

ማበራታትና የአፈፃፀሙን ሂደት መከታተል

1.5 በአጠቃላይ ከምዘና ስራ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎችንና የመረጃ ክፍተቶችን

ለመሙላት የሚያስችሉ ተግባራትን መስራትና የአፈፃፀም ሒደቶችን

መገምገምና ለሚመለከታቸዉ አካላት በሪፖርት መልኩ ማቅረብና መገምገም።

1.6 በተለያዩ ምክንያቶች ከመስሪያ ቤታቸዉ የመመረቂያ ሰነድ እንዲያስገቡ የተጠየቁ

ነገር ግን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰነድ ማምጣት ላልቻሉት ሰልጣኞች

የሚስተናገድበትን አግባብ ወጥነት ባለዉና ከህግ ተጠያቂነት ነፃ በሚያደርግ

መልኩ ለማሰትናግድ የሚያስችሉ አማራጮችን ማስቀመጥ

አብይ ተግባር 2 በአዲሱ የስልጠና ስርዓት መሰረት ስልጠናቸዉን አጠናቀዉ በ 2015 ዓ.ም
የተመረቁ እና በተመሳሳይ በአሁኑ ሰዓት ስልጠናቸዉን በመከታተል ላይ ያሉ የ 2016 ዓ.ም
ተመራቂ ተማሪዎችን የሚመለከት

2.1 በ 2015 ዓ.ም የተመረቁ በአዲሱ የምዘና ስርዓት ሲመዘኑ የሚገቡ ተማሪዎችን

መረጃዎችንና ማስረጃዎችን የመለየትና የማደራጀት ስራ መስራት


2.2 በ 2015 ዓ.ም የተመረቁ ሰልጣኞችን በአዲሱ የምዘና ስርዓት ለማስመዘን

የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማከናወን, መከታተል

2.3 በተመሳሳይ በ 2016 ዓ.ም የሚመረቁና በአዲሱ የምዘና ስርዓት መሰረት

የሚመዘኑ ሰልጣኞችን ለማስመዘን የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን

መስራት

አብይ ተግባር 3 ከዚህ በፊት በደረጃ ተመርቀዉ ያሉ ሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ

ማስረጃ በቅድመ ምረቃ እና በድህረ ምረቃ መርሃ ግብር ትምህርታሽውን

በመከታታል ላይ ያሉትን ተማሪዎች ወደ ምዘና ስርዓት እንዲገቡና የብቃት

ማረጋገጫ ማስረጃቸውን እንዲያያይዝ ለማድረግ የሚሰሩ ስራዎች

በተመለከተ

3.1 ምንም አይነት የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ሳይኖራችው ወይም የተወሰኑ

ደረጃዎችን ብቻ በማቅረብ የመጀመሪያ / የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት በማር

ላይ ያሉ ተማሪዎችን የመለየትና መረጃዎችን የማደራጀት ስራ መሳራት


3.2 በመረጃ መሰረት ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ ተማሪዎች በተለያዩ አማራጮች በመጠቀም የጉዳዩን አሳሳቢነት አጣዳፊነት በማስረዳት

የግንዛቤ እና የቅስቀሳ ስራ በመስራት


3.3 ቢያንች ካሉት ተማሪዎች መካከል 75% የሚሆኑትን ወደ ምዘና ስርዓት እንዲገቡ ለማድረግ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት

ስራዎችን መስራት የምዘና ስራው ዉጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዙ አሰራሮችን መዘርጋት

3.4 በተቀመጡት አማራጮች ተጠቃሚ ለመሆን በማይፈለጉና ለማይሞከሩ

ተማሪዎች ደረጃ በደረጃ የማስተማሪያ እርምጃ የመዉሰድ አሰራር መዘርጋት

3.5 በሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮች የአሰራር ክፍተቶች ለመሙላት የሚያስችል

አሰራር መዘርጋትና ለዉጤታማነቱ መስራት

You might also like