Professional Documents
Culture Documents
2014 2nd Half EPE Guideline
2014 2nd Half EPE Guideline
3. አንድ ሰራተኛ ሶስት ወር እና ከዚያ በላይ ሌላ ክፍል ሰርቶ በግምገማ ወቅት ሌላ ክፍል ቢገኝ አሁን
ላይ ያለው የቅርብ አለቃው ምንም መሙላት ሳይጀምር Change Main Appraiser የሚለውን
በመጫን ግምገማውን ወደ ሚመለከተው ገምጋሚ ማስተላለፍ አለበት፡፡
1
ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም
Planned የሚል ከሆነ ለመገምገም ዝግጁ ስለሆነ የእስራስ ምልክቱን በመጫን ግምገማውን
መጀመር ይቻላል፡፡
Pending Approver ካለ የግምገማ ሂደቱ ወደ አጽዳቂው ተልኳል ማለት ነው፡፡
Transferred to Appraisee የሚል ከሆነ የግምገማ ሂደቱ ተገምጋሚው ጋር ስለሆነ
የግዴታ ተገምጋሚው የግምገማ ሂደቱን መመለስ ይኖርበታል ማለት ነው፡፡
Ongoing with Main Appraiser ከሆነ ግምገማ ሂደቱ በዋናው ገምጋሚ መጀመሩን
ያሳያል በመሆኑም update በማድረግ የሂደቱን ወደ ሚመለከተው መላክ ይኖርበታል፡፡
2
ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም
3
ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም
11. ገምጋሚዎች የግምገማ ውጤቱን ወደ ተገምጋሚው ከመላኩ በፊት ሁሉንም ነጥቦች በትክክል
መሞላቱን ማረጋገጥ አለበት፡፡ እንዲሁም ተገምጋሚዎችም ውጤቱ በሚላክበት ወቅት
አጠቃላይ ውጤቱን ከማየት ባሻገር እያንዳንዱ ነጥቦች በትክክል መሞላታቸውን ማረጋገጥ
አለባቸው፡፡
12. እያንዳንዱ የስራ መሪ በግምገማ ወቅት በስሩ ያሉት የሰራተኞች የግል BSc ከዲቪዝን ወይም
ከዞን እና ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሪክተር BSc ውጤት የሚቃረን መሆን የለበትም፡፡
4
ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም
1. ለማኔጅመንት የሥራ መደብ የግለሰብ ውጤት ተኮር (Individual BSc) እይታዎች ለእያንዳንዱ
እይታ እንደየዲፖርትመንቱ የተለያየ ክብደት ሲኖረው አጠቃላይ ውጤቱ ከ55% ይሆናል፡፡
በተጨማሪም የካምፖኒ እሴቶች እና የንኪኪ ነጥቦች /touch points/ 30% ውጤቱን ሲይዙ
ቀሪው 15% የዲቪዥን ወይም የዞን እና የሪጅን ውጤትን የሚወስዱ ይሆናል፡፡
2. ለሠራተኛ የሥራ መደብ የግለሰብ ውጤት ተኮር (Individual BSc) እይታዎች በተመሳሳይ እንደ
ማኔጅመንት የሥራ መደብ እንደየዲፖርትመንቱ የተለያየ ክብደት ሲኖራቸው አጠቃላይ ድምር
ውጤቱ ከ70% ሲሆን የካምፖኒ እሴቶች እና የንኪኪ ነጥቦች /touch points/ 15% ውጤቱን
ሲይዙ ቀሪው 15% የዲቪዥን ወይም የዞን እና የሪጅን ውጤትን የሚወስዱ ይሆናል፡፡
3. በግምገማ ወቅት የሚታዩ የውጤት አሰጥጥ ስህተቶች፤
በግምገማ ሂደት ጊዜ የሚታዩት የተለመዱ የምዘና ውጤት አሰጣጥ ስህተቶች ከዚህ በታች
ተዘርዝረዋል፤
3.1 መካከለኛ የስራ አፈፃፀም የመስጠት ስህተት፣
• ሠራተኞች አፈፃፀማቸው ከፍተኛ ወይም ዝቅተኛ ቢሆንም ጽንፎችን ለማስወገድ በመሞከር እና
ተጠያቂነትን ለመሸሽ ሁሉንም ሠራተኞች በመካከለኛ የአፈፃፀም መደብ ውስጥ መሰብሰብ
ሲሆን ይህ አሰራር ጥረት የሚያደርጉ ሠራተኞችን የስራ ተነሳሽነት ሊቀንስ ይችላል፤
3.2 በመለሳለስ የሚፈጠር ስህተት፣
• ሠራተኞች በሰሩት ሥራ ከመገምገም ይልቅ ላለመጋጨት ወይም በሠራተኞች ለመወደድ
ሲባል ለሁሉም ከፍተኛ የሥራ አፈፃፀም መስጠት፤
3.3 በጥሩ ስራ ብቻ የመመዘን ተጽዕኖ፣
• በግምገማ ስርዓቱ ውስጥ ከተለመዱ ስህተቶች አንዱ ሲሆን ሠራተኛን አንድ ጊዜ በተሰራ ጥሩ
ስራ ወይም በአንድ ነገር ላይ የተደረገ ጥሩ ነገርን መነሻ ብቻ በማድረግ ሁሉንም ሥራዎች
መመዘን፤
3.4 በመጥፎ ስራ ብቻ የመመዘን ተጽዕኖ፣
5
ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም
• ሰራተኛን በተሠራ አንድ መጥፎ ስራ ወይም መጥፎ ፀባይ ብቻ ሁሉንም ሥራዎች የመመዘን
ችግር፤
3.5 ባለፈ ሥራ የመገምገም ስህተት፣
• ሠራተኞችን አሁን እየሰሩ ባሉት ስራ ሳይሆን በፊት በሰሩት መጥፎም ይሁን ጥሩ ስራን
መሠረት በማድረግ መገምገም፤
3.6 በአድሎዓዊነት የሚደረግ የግምገማ ስህተት፣
• ሠራተኞችን በሰሩት ስራ ከመገምገም ይልቅ በዘር፣ በብሔር፣ በጾታ፣በሃይማኖት፣ በዕድሜ፣
ወዘተ ባሉ አመለካከቶች የሚደረግ ግምገማ፤
3.7 ቅርብ ጊዜ በተሠራ ሥራ ብቻ የመገምገም ስህተት፤
• ዓመቱን ሙሉ የተሰሩ ሥራዎችን በመተው ሠራተኛን በቅርብ ጊዜ በተሰራ ጥሩም ይሁን
መጥፎ ሥራ ብቻ መገምገም ነው፡፡ ይህ የሚሆነው ገምጋሚው በመጨረሻዎቹ ጥቂት የስራ
ሳምንታት ላይ ያላቸውን አፈፃፀም ላይ ሲመሰርት ነው፡፡
በግምገማ ወቅት በውጤት አሰጣጥ ላይ የሚከሰቱ ስህተቶች የምዘና ውጤቱን የተሳሳተ ቁመና
እንዲኖረው እና ትክክለኛውን ውጤት እንዳይታይ ካምፓኒው ክፍተቶችን አይቶ ማስተካከያ
እንዳያደርግ የሚያደረጉ ምክንያቶች ናቸው። ስለሆነም "ገምጋሚዎች ከአዎንታዊ ሆነ አሉታዊ
ሁኔታዎች እና እውነታውን ከሚያዛባ ከማንኛውም ነገር መጠንቀቅ አለባቸው። ከላይ የተዘረዘሩትን
የሰራተኛ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መርሆዎች እና የምዘና ስህተቶችን ከግንዛቤ በማስገባት
በተቀመጠው ቀነ ገደብ የሥራ አፈጻጸም ግምገማውን እንድታጠናቅቁ እናሳስባለን፡፡
6
ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም
ማሳሰቢያ
ማንኛውን ተገምጋሚም ሆነ ገምጋሚም እንዲሁም አጽዳቂ የሲስተም መጨናነቅ እንዳይከሰት ከላይ
በተቀመጠው መረኃ ግብር መሠረት ብቻ የግምገማ ሂደቱን ማከናወን አለበት፡፡ ከተሰጠው ጊዜ ሰሌዳ ውጭ
የሚከናወን የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ሲስተሙ የማይቀበል ሲሆን እንደ ከዚህ በፊቱም በማኑዋል የማንቀበል
በመሆኑ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ለሚፈጠረው ማንኛውም ክፍተት ገምጋሚውና ተገምጋሚው ኃላፊነት የሚወስዱ
ይሆናል፡፡