Professional Documents
Culture Documents
አዲስ ወደ ኦዲት ቡድኑ የተቀላቀለ ወይም የሚቀላቀል ኦዲተር ካለ የሙያ ስነ-ምግባር የስራ
ወረቀት ሊዘጋጅለት ይገባል፡፡
2
አዲተሩን ለሙያ ስነ-ምግባር ጥሰት የሚዳርግ አግባብ ኦዲት በሚያደርገው መ/ቤት
ከተገኘ በወቅቱ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡ ይህን የማያደርግ ኦዲተር የስነ-ምግባር ጥሰት
እንደሰራ ተቆጥሮ ተጠያቂ ይሆናል፡፡
ይህ የስራ ወረቀት በስራ ስምምነት የስራ ወረቀት መሰረት በተደረገው የስራ ክፍፍል መሰረት በእያንዳንዱ
ኦዲተር ተለይቶ የሰዓት እቅድ ሊያዝ እና ስራ ላይ የዋለው ሰዓትም ሊቀመጥ ይገባል፡፡
በእያንዳንዱ ኦዲተር የተሸነሸነው ሰዓት በድምሩ በስራ ወረቀት ላይ ሊገለፅ እና ስራ ላይ ከዋለው ሰዓት ጋር
እየተነፃፀረ ልዩነቱ ሊቀመጥ እና የልዩነቱ ምክንያት ሊገለፅ ይገባል፡፡
የተተመነውን ሰዓት በትክክል በቼክ ሊስት መሙላት ያስፈልጋል፡ በስራ አመራሩ ከተተመነው ሰዓት
በላይ (በጥናት ከተቀመጠው የኦዲት ጊዜ በላይ) በተጨባጭ ምክንያት ጭማሪ ጊዜ መጠቀም
የሚያስፈልግ ሲሆን በቅደም ተከተል በኦዲት ቡድኑ፤ በኦዲት ቡድን መሪ፣ በኦዲት
ዳይሬክተር፣በምክትል ዋና ኦዲተሩና በዋና ኦዲተሩ የመጨመር ስልጣን እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የመ/ቤቱ ደረጃ የሚጨመር ጊዜ
በኦዲት ቡድኑ በኦዲት ቡድን መሪ በኦዱት በዲይሬክተር በምክትል እና ወይም
ዋና ኦዲተሩ
በጣም ከፍተኛ 6 የሥራ ቀን ከ7 - 10 የሥራ ቀን ከ11 - 14 የሥራ ቀን ከ14 ቀን በላይ
ከፍተኛ 4 የሥራ ቀን ከ 5 - 8 የሥራ ቀን ከ9 - 12 የሥራ ቀን ከ12 ቀን በላይ
መካከለኛ 2 የሥራ ቀን ከ 3 - 5 የሥራ ቀን ከ6 - 7 የሥራ ቀን ከ7 ቀን በላይ
አነስተኛ 1 የሥራ ቀን ከ 2 - 3 የሥራ ቀን ከ4 - 5 የሥራ ቀን ከ5 ቀን በላይ
በተላለፈው ሰርኩላር መሰረት የመስክ ኦዲተሩ ለስራው በተሰጠው ተጨማሪ ጊዜ ስራውን
ካላጠናቀቀ ስራው ባለበት ቆሞ እና በኦዲት ቡድን መሪው ማረጋገጫ ተወስዶበት ከሃላፊዎች
ጋር በመነጋገር ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጠው ይችላል፡፡
መ/ቤታችን የመንግስት መ/ቤቶችንና የልማት ድርጅቶችን ሂሳብ ኦዲት ማድረግ በአዋጅ የተሰጠው
ስልጣን እና ሃላፊነት ቢሆንም ይህ የስራ ወረቀት ከኦዲት ተደራጊ መ/ቤት ጋር እንደ ስራ ውል የሚታይ
በመሆኑ የተጠያቂነትን አሰራር የሚያጠናክር ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ኦዲተሮች ወደ ስራ ሲሰማሩ የስራ ስምሪት ደብዳቤው ጋር አባሪ በመሆን ለኦዲት ተደራጊ መ/ቤት የሚላክ
ሲሆን አዘገጃጀቱም አባሪ የስራ ስምምነት ደብዳቤ በሶስት ኮፒ ተዘጋጅቶ ሁለቱ ኮፒ ለኦዲት ቡድን ይሰጥ
እና ከኦዲት ተደራጊ መ/ቤት ሀላፊ ጋር ከተፈራረሙ በኋላ አንደኛው ኮፒ የኦዲት ፋይል አካል ሆኖ
የሚያዝ ሲሆን ሁለተኛው ኮፒ ለኦዲት ተደራጊ መ/ቤት የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ሶስተኛው ኮፒ ለክትትል ይረዳ
ዘንድ ዳይሬክተሩ ላይ ፊርማ ሳይኖረው ፋይል ሆኖ ይቀመጣል፡፡
የሥራ ወረቀቱ በኦዲት ቡድን መሪው የሚዘጋጅ ሆኖ በዳይሬክተሩ የሚፈረም ሲሆን የኦዲት ቡድኑ የስራ
ስምምነት ደብዳቤውን ለኦዲት ተደራጊው መ/ቤት ከመሰጠቱ በፊት በሥራ ስምምነት ደብዳቤ ላይ በቂ
ግንዛቤ ሊያዝበት ይገባል፡፡
ኦዲት ቡድኑ የኦዲት ሥራ ስምምነት ደብዳቤ የሚፈራረመው ከኃላፊች ጋር በመሆኑ ሌሎች በኦዲት
ሥራው ላይ ወሳኝ የሆኑ አካላት ስለኦዲቱ ሥራ ስምምነት መሰረታዊ ነጥቦች መረጃ ሊኖራቸው
ስለማይችል እና ስለኦዲቱ አጠቃላይ ሂደት ግንዛቤ ለማስያዝ ይህን ደብዳቤ መነሻ በማድረግ አጭር ቃለ
ጉባኤ በማዘጋጀት በኦዲት ሥራ ስምምነት ነጥቦች ዙሪያ የመግቢያ ስብሰባ ሊደረግና ኦዲት አስደራጊ
ግለሰብ ሊወከል ይገባል፡፡
ከነጠላ ፋይናንስ ድጋፍ ሰጪ ማዕከላት ጋር ኦዲት ለሚደረጉ የገቢዎች ጽ/ቤቶች በተመለከተ ገቢዎች
ጽ/ቤት ራሱን በቻለ የጽ/ቤት ኃላፊ የሚመራ ስለሆነ ለራሱ የስራ ስምምነት ደብዳቤ ከዚህ በላይ
በተገለፀው መሰረት የሚደርሰው ይሆናል፡፡ ነገር ግን የኦዲት ስራ ሰዓትን ላለመሻማት ለገቢዎች ጽ/ቤት
የመግቢያ ስብሰባው ከነጠላ ፋይናንሱ ጋር በአንድ ላይ የሚደረግ ሲሆን ቃለ-ጉበኤው የሁለቱን መ/ቤቶች
የኦዲት ስምምነት ነጥቦችን አካቶ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
4
በሥራ ስምምነት ደብዳቤ ከተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ በላይና በታች ሥራዎችን ለመፈፀም አሳማኝ የኦዲት
ሰዓት ማሻሻያ የሚያስፈልግ ከሆነ ቀደም ሲል የኦዲት ማጠናቀቂያ ሰዓትን አሰመልክቶ በወጠው መመሪያ
መሰረት ጉዳዩን ቀደም ብሎ በማሳወቅ እና በማስፈቀድ ስራውን ሊያከናውን ይችላል፡፡
5
2.3.1. የናሙና አመራረጥ ዘዴ እና መጠን /Sampling technique Sample size/
በተሻሻለው የሬጉላሪቲ ኦዲት ማኑዋል በተቀመጠው የናሞና መረጣ መሠረት መስራት ይገባል፡፡ ይህም
መከናወን ያለበት በዚህ ኦዲት ጋይድ ተራ ቁጥር 2.2.1 በተቀመጠው የአሰራር ስርዓት መሰረት ሊሆን
ይገባል፡፡
ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ያለቸውን ሰነዶችና ከመደበኛ አሰራር ወጣ ያሉትን ቫውቸሮች
በመለየት በቀሪው የገንዘብ መጠን ላይ ናሙና አውጥቶ መስራት ይገባል፡፡
ለኦዲት ከተመረጠ Component ውስጥ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን /High value items/ ብቻ
ኦዲት አድርጎ ሌላዉን ማለፍ የሚቻለው ከተመረጠው Component ጠቅላላ የገንዘብ
ድምር ቢያንስ 70% የሚሸፍን ከሆነ ብቻ ነው፡፡
ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ያላቸው Compoment ከ 70% በታች ሆነው ከተገኙ ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን
የያዙ Compoment 35% እስኪሞሉ ድረስ ናሙና ወጥቶላቸው ኦዲት መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡
ለናሙና የተመረጡ ከፍተኛ መጠን ያለው (high value items) 70% ሆኖ አንድ የወጪ
ሰነድ ብቻ ከሆነ ቀጣዩን ዋጋ ያላቸው ሌሎች ሰነዶችን በመጨመር ቢያንስ ከ10 ያላነሱ
የወጪ ቫውቸሮች ሊታዩ ይገባል፡፡
የወጪ ሰነዶች ከ 10 በታች ቫውቸሮች ያለው ኦዲት ኮምፖነንት /component/ ሙሉ በሙሉ
(100%) በዝርዝር ይሰራል ወይም ይመረመራል፤ንሞና ሲወጣ በክፍልፋይ የሚታይ ከሆነ ወደ
ቀጣዩ ቁጥር በማጠጋጋት ሊሰራ ይገባል፡፡ ለምሳሌ፡- የንሞና መጠኑ 5.04 ቢሆን በቀጥታ 6
ቫውቸሮች መወሰድ አለበት፣
የደመወዝ ሂሣብን በዝግ ናሙና ዘዴ ሥጋት ያለባቸውን ወሮች መርጦ መስራት ይገባል፡፡
የሚሰሩት ወሮች በየኢንትሪሙ ከሁለት ወር ማነስ የለባቸውም፡፡ ስጋት አለ ተብሎ ከታመነ
በኦዲተሩ ሙያዊ ብያኔ መሰረት ሰፍቶ ሊሰራ ይችላል፡፡
የተራድኦ ሂሳቦች በመጀመሪያው ኢንትሪም ኦዲት ወቅት በኦዲተሩ ሙያዊ ብያኔ
(judgmental sampling) የናሙና ዘዴ በየአካውንታቸው ራሳቸውን ችለው በኮምፖነንት
ደረጃ ሳይደራጁ በየሂሳብ ቁጥር የተፈፀሙ ወጪዎችን በጥቅል ተዘርዝረው ኦዲት
የሚደረጉ ይሆናል፡፡
የተራድኦ ሂሳቦች በሁለተኛው ኢንትሪም ኦዲት በተግባር ስራ ላይ የዋለው ወጪ ተይዞ
ከመደበኛ ሂሳብ ወጪ ጋር በየኦዲት ኮምፖነንቱ ገብተው ናሙና እየወጣላቸው ሊሰሩ
ይገባል፡፡
በተከፋይ ሂሳብ ለምሳሌ 5028 የሚላኩ እና በወጪ ፀድቀው የሂሳብ ሰነዳቸው ከኦዲት
ተደራጊው መ/ቤት የሚያዙ ሂሳቦች እና የምግብ ዋስትና ሂሳብ በመግለጫ ደረጃ ያለውን
ጉልህነት ለመወሰን መሰረት ከሚሆነው ጥቅል ወጪ ውስጥ ሳይካተቱ ራሳቸውን ችለው
6
በኦዲተሩ ሙያዊ ብያኔ ኦዲት የሚደረጉ ሆኖ በመጀመሪያውም ሆነ በሁለተኛው ኢንትሪም
ኦዲት ወቅት ራሳቸውን ችለው ተዘርዝረው የሚሰሩ ይሆናል፡፡
ራሳቸውን ችለው ኦዲት የሚደረጉ የተራድኦ እና የወጪ ባህሪ ያላቸው በተከፋይ የሚያዙ
ሂሳቦች ማግኘት ያለባቸው የኦዲት ሽፋን በገንዘብ መጠን 70% ያላነሰ እና በቫውቸር ብዛት
ደግሞ ከ 10 ያላነሰ ሊሆን ይገባል፡፡