Professional Documents
Culture Documents
ንብረት አስተዳደር
አዲስ አበባ
ሐምሌ/2009
1. ክፍል አንድ
1.1 ጠቅላላ
0
1.1.1 አውጪው ባለስልጣን
የኮርፖሬሽኑ ቦርድ በደንብ ቁጥር 83/2009 የተደነገጉትን ለማስፈፀም ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡
ይህ መመሪያ የኮርፖሬሽኑ ንብረት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር /2009 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
1.1.3 ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ ያሉ ቃላትና ሐረጎች
የሚከተሉት ትርጉም ይይዛል፡፡
1. “ቋሚ ንብረት” ማለት ዋጋቸው ከብር 1000.00 /አንድ ሺህ/ እና ከዚያ በላይ የሆኑ ንብረቶች እና
ከአንድ ዓመት በላይ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ናቸው፡፡
2. “አላቂ እቃ” ማለት የተናጠል ዋጋው ከብር 1000.00 /አንድ ሺህ/ በታች የሆነ ወይም የአገልግሎት
ዘመናቸው ከአንድ አመት በታች የሆነ ንብረት ነው፡፡
3. “ተሽከርካሪ” ማለት በመንገድ ላይ በሞተር ኃይል የሚንቀሳቀስ ወይም የሚጐተት ለሰው እና/ወይም
ለዕቃ ማጓጓዣ የሚውል ማንኛውም ተሽከርካሪ ነው፣
4. “የእርጅና ቅናሽ” ማለት ንብረቱ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ይሰጣል ተብሎ በሚገመትበት ዕድሜ ስርዓት
ባለው አኳኋን የንብረቱን ዋጋ እንደወጪ እያሰቡ መቀነስ ማለት ነው፡፡
5. “ስቶክ” ማለት በኮርፖሬሽኑ የተመረቱ ወይም የተገዙ በእርዳታ የተገኙ ንብረቶች ሆነው በመደበኛ
የስራ እንቅስቃሴ ውስጥ አገልግሎት ላይ እስከሚውሉ ድረስ በመጋዘን የተቀመጡ ቋሚ ዕቃዎች፣
መሣሪያዎችና አላቂ እቃዎች ማለት ነው፡፡ ሆኖም አገልግሎት ላይ ውለው የሚመለሱ ዕቃዎችን
አይመለከትም፡፡
6. “ኤጀንሲ” ማለት የከተማ አስተዳሩ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ነው፡፡
1
ዘመናዊ፣ ቆጣቢ፤ ለሀብት በቂ ጥበቃ የሚያደርግና ውጤታማ የንብረት አስተዳደር ስርዓት በማስፈን፣
ኮርፖሬሽኑ በእጁ ያለውን ንብረት በጥንቃቄ የመያዝ፣ የመጠቀም፣በሂሳብ መዛግብት የመመዝገብ፤
የመቆጣጠር እና አገልግሎት ሲያበቃ ወይም አገልግሎት ላይ በማይውሉበት ጊዜ በወቅቱና በተገቢው መንገድ
እንዲያስወግድ ማስቻል ነው፡፡
ክፍል ሁለት
ሀ. ለንብረት ሥራ የሚመደቡ ሠራተኞች ቢቻል በሙያው ወይም ተዛማጅነት ባለው የትምህርት ዘርፍ
የሠለጠኑ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣
ሐ. የኮርፖሬሽኑ ንብረት ኢኮኖሚያዊና ውጤታማ አገልግሎት እንዲሰጥ ከስራ ክፍሉ ጋር በመሆን የጥገና
ሥርዓት መዘርጋት፣
መ. ኮርፖሬሽኑ ንብረት ላይ ጉድለት መታየቱ በኦዲተሮች ወይም በሌላ አካል ሲረጋገጥ ንብረቱ በምርመራው
መሠረት በአይነት ወይም በገንዘብ እንዲተካ ማድረግ፣
ሠ. ዓመታዊ እና እንደአስፈላጊነቱ ድንገተኛ የንብረት ቆጠራ እና የስቶክ ምርመራ እንደ ንብረቱ አይነት የጊዜ
ገደብ በማስቀመጥ እንዲካሄድና ሪፖርት እንዲቀርብ ማድረግ፣
ለ. ኮርፖሬሽኑ የንብረት አስተዳደር ተግባርን የሚያከናውን የሥራ ክፍል የተጠናቀረ መረጃ የያዘ የቋሚ ንብረት
መመዝገቢያ ካርድና መዝገብ መያዙን የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት መወጣቱን ማረጋገጥ አለበት፡፡
2
ሐ. በኮርፖሬሽኑ የንብረቱ ተጠቃሚ ሰዎችን የንብረት ምዝገባ ካርድ መያዝ ማረጋገጥ አለበት፡፡
መ. ኮርፖሬሽኑ ለእያንዳንዱ ቋሚ ንብረት የራሱ የሆነ መለያ ቁጥር መስጠት ያለበት ሲሆን፣ ይህ ቁጥር በቋሚ
ንብረቱ ላይ መለጠፍ ወይም መጻፍ ማከታተል አለበት፡፡
ሠ. የንብረት አስተዳደር ተግባርን የሚያከናውነው የሥራ ክፍል የቋሚ ንብረት ካርዶችና የቋሚ ንብረት
መዝገቦች ወቅታዊ መደረጋቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡
ረ. ኮርፖሬሽኑ በየዓመቱ የቋሚ ንብረቶች ቆጠራ ማካሄድ አለበት፡፡ ቋሚ ንብረቶቹ ያሉበት አቋም ወይም
የሚገኙበት ቦታ ላይ ማናቸውም ለውጥ ቢኖር ይኸው በቋሚ ንብረት ካርዱ፣ በቋሚ ንብረቱ መዝገብ
እና በጠባቂዎች የንብረት ወይም የመጋዘን ኃላፊ ዝርዝር ውስጥ እንዲመላከት መደረጉን መከታተል
አለበት፡፡
ሰ. በኮርፖሬሽኑ የማናቸውም ንብረት መጥፋት ወይም መኖሩ የማይታወቅ ሆኖ ሲገኝ ጉዳዩ ለዋና ስራ
አስኪያጁ ሪፖርት ተደርጎ ወዲያውኑ ምርመራ መካሄዱን ማረጋገጥ አለበት፡፡
ሸ. የንብረት ቆጠራ ሲደረግ ያልተገኙ ወይም መኖራቸው ያልታወቁ ቋሚ ንብረቶች ሲያጋጥሙ ለኮርፖሬሽኑ
ዋና ስራ አስኪያጅ ሪፖርት ያቀርባል፡፡ በምርመራውም ሪፖርት ጉዳይ የወንጀል ድርጊት ያለው መሆኑ
በማስረጃ ሲደገፍ ለኮርፖሬሽኑ የሕግ ተግባርን ለሚከታተል የሥራ ክፍል ሪፖርት ያደረጋል፡፡
ቀ. ዋጋቸው ከብር 1000.00 /አንድ ሺህ/ በታች ሆነው የአገልግሎት ዘመናቸው ከአንድ አመት በላይ የሆኑ
ንብረቶች ለብክነት ሊዳርጉ ስለሚችሉ ለብቻ ተመዝግበው በመያዝ የወጪና ገቢ እንቅስቃሴያቸው
ቁጥጥር እንዲኖር ያደረጋል፡፡
በ. ቋሚ ንብረት ለአንድ የሥራ ክፍል ወይም ሠራተኛ ወጪ ሆኖ ከተሰጠ በኋላ ወደ መጋዘን ሣይመለስ
በዚያው ወደ ሌላ ሠራተኛ ወይም የሥራ ክፍል በርክክብ እንዲተላለፍ ያዛል የንብረት እንቅስቃሴና
አጠቃቀምን ይወስናል የቋሚ ንብረቱ መዝገብና ካርድ ከዚህ አኳያ መስተካከሉን ማረጋገጥ አለበት፡፡
ሀ. ይህንን መመሪያ እንዲሁም የንብረት አስተዳዳር ማንዋሎችን መሠረት በማድረግ ሙያው በሚጠይቀው
ክህሎት የኮርፖሬሽኑን ንብረት ያስተዳድራል፣
3
በዚህ መመሪያ መሠረት የሚቋቋመው የንብረት አስወጋጅ/ሽያጭ ኮሚቴ፡-
ሠ. የኮሚቴው የአገልግሎት ዘመን ሁለት አመት ይሆናል፡፡ ሆኖም የኮርፖሬሽኑ የበላይ ኃላፊ አስፈላጊ
ሆኖ ሲያገኘው የኮሚቴውን የአገልግሎት ዘመን ለሁለተኛ ጊዜ ማራዘም ይችላል፡፡
የንብረት ሽያጭ አጽዳዊ ኮማቴ በኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስኪያጅ የሚቋቋም አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ ሲሆን
የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡
4
ክፍል ሦስት
ሐ. ከላይ በተራ ቁጥር ሀ ወይም ለ የተጠቀሱት ሁኔታዎች ተሟልተው ካልተገኙ ዋጋው በግምት ተተምኖ
ይሰራል፡፡
3.1.2. ግንባታዎች፣
ኮርፖሬሽኑ ያከናወኑዋቸውን ወይም የተረከባቸውን የግንባታ ሥራዎች እንደ ቋሚ ንብረቶች በተለየ መዝገብ
መመዝገብ አለበት፡፡
5
ሀ. ኮርፖሬሽኑ ህንጻዎችን ለመስራት የተደረገን የቅድመ ግንባታ ቀጥተኛ ያልሆኑ ወጪዎች እና
የአስተዳደር ምክር አገልግሎት እና የመሣሰሉትን ቀጥተኛ ያልሆኑ ወጪዎችን በቋሚ ንብረት ካርድ
መመዝገብ አለበት፡፡
ሐ. ለሕንፃው የእርጅና ቅናሽ የሚታሰበው ሕንጻውን ለመሥራት ወይም ለመግዛት የተደረገውን ጠቅላላ
ወጪ በመነሻነት በመውሰድ ከዚሁ ሂሣብ ላይ በየዓመቱ አምስት በመቶ በመቀነስ ይሆናል፡፡
ሕንጻውን ለመሥራት ወይም ለመግዛት የተደረገው ጠቅላላ ወጪ የማይታወቅ ከሆነ የሕንጻው
ወቅታዊ የመተኪያ ዋጋ እንደመነሻ ይወስዳል፡፡
I. የግልጽ ገበያ አተማመን ዘዴ፡- ሕንጸው በግልጽ ጨረታ ቢሸጥ የሚኖረውን የገበያ ዋጋ
መሠረት በማድረግ የሕንጻ ዋጋ ላይ መድረስ፡
II. የወቅቱ የመተኪያ ዋጋ ዘዴ፡- የሕንጻው ትክክለኛ ዋጋ የማይታወቅ ከሆነ በአሁኑ ጊዜ
ዋጋ ማውጣት ይቻላል፡፡
ሀ. የተሽከርካሪዎች ዋጋ የሚተመነው አዲስ የመተኪያ ዋጋን መነሻ በማድረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ትብብር
ሚኒስቴር ያዘጋጀውንና በየዓመቱ አስር በመቶ የዋጋ ቅናሽ በማድረግ የማስላት ዘዴን በመጠቀም
ይሆናል፡፡
ለ. የቢሮ ዕቃዎች ዋጋ የሚተመነው ዕቃዎቹ ያሉበትን አቋም መሠረት ባደረገ መስፈርት ይሆናል፡፡
6
ሐ. የቢሮ መሣሪያዎች ዋጋ የሚተመነው የመሣሪያዎቹን የአገልግሎት ዘመን በመስፈርትነት በመውሰድ ሲሆን
ስሌቱ በየዓመቱ መሣሪያዎቹን አስር በመቶ የዋጋ ቅናሽ በማድረግ የሚሰላ ይሆናል፡፡
መ. የማይንቀሳቀሱ ወይም ሙሉ በሙሉ የተበላሹ ቋሚ ንብረቶች በመዝገብ ዋጋቸው (Book value) አስር
ብር ሆኖ ይመዘገባሉ፡፡
በኮርፖሬሽኑ ቋሚ ንብረት ላይ የእርጅና ቅናሽ ማስላት ያስፈለገው በሀገሪቱ የገቢ ግብር ህግ እንደ
ልማት ድርጅት የሚጠበቅበትን የታስና ግብር ግዴታ ለመወጣት ሆኖ የንብረቱን ትክክለኛ ዋጋ
ለመወሰን ሣይሆን አግባብነት ካለውና ሚዛናዊ ከሆነ የሀብት ሚዛን /ዋጋ/ ላይ ለመድረስም
ጭምር ነው፡፡ የቋሚ ንብረቱ ትክከለኛ ዋጋ የሚታወቀው ሲሸጥ በሚገኝ የገበያ ዋጋ ብቻ
ይሆናል፡፡ ስለሆነም፡-
ሐ. የእርጅና ቅናሽ የሚሰራው በሀገሪቱ የታክስና ግብር ህግ መሰረት ሆኖ ቀጥተኛ የእርጅና ቅናሽ
ዘዴን በመጠቀም ይሆናል፡፡ ሆኖም ከዚህ የተለየ ዘዴ መጠቀም ካስፈለገ ለቦርዱ ቀርቦ በሚሰጥ
መመሪያ መሠረት ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
7
መ. የቋሚ ንብረት የእርጅና ቅናሽን የማስላትና በመዝገብ ላይ የመመዝገብ ኃላፊነት
የኮርፖሬሽኑ ጠቅላላ ሒሣብ እና የንብረት አስተዳደር ተግባርን የሚያከናውን የሥራ ክፍል
ይሆናል፣
ሠ. ለቋሚ ንብረቶች የእርጅና ቅናሽ የሚሰላው ንብረቱ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ዕለት
አንስቶ ይሆናል፡፡
ሰ. በቋሚ ንብረቱ የመጨረሻ የእርጅና ቅናሽ ዘመን ከዓመቱ የእርጅና ቅናሽ ላይ ብር 10 /አስር/
ተቀንሶ የንብረቱ የመዝገብ ዋጋ እንዲሆን ይደረጋል፡፡
ቀ. ዋጋውን በእርጅና ቅናሽ የጨረሰ ንብረት የጥገና ወጪ የዚያ ዓመት ወጪ እንጂ የንብረቱ ዋጋ
ተደርጎ አይወሰድም፡፡
8
ክፍል አራት
4. የስቶክ አስተዳደር ሥርዓት
4.1.1. የስቶክ ቁጥጥር ሥርዓት በኮርፖሬሽኑ መዘርጋት ያለበት ሲሆን በስቶክ የሚቀመጡ ዕቃዎች ለጤና
አደገኞች ወይም ባላቸው ዋጋና በቀላሉ የመንቀሳቀስ ባህርይ ምክንያት ለሥርቆት የሚጋለጡ ናቸው
ተብሎ ሲታመን ልዩ ቁጥጥር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
4.1.2. በኮርፖሬሽኑ የሚደረገው የስቶክ ቁጥጥር ሥርዓት የሚከተሉትን የስቶክ ቁጥጥር ሥርዓት መሠረታዊ
ኮርፖሬሽኑ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ሁለት የሥራ መደቦች ላይ በሚገኙ ሠራተኞች መካከል በቂ የኃላፊነት
መነጣጠል መደረጉን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
9
ለ. በተመሳሳይ ስቶክ የመያዝ፣ የመረከብ፣ ክፍያን የመፍቀድና ግዥን የማከናወን ኃላፊነቶች
መለያየት አለባቸው፡፡
4.3. መሠረታዊ የስቶክ መዛግብቶች
1. የኮርፖሬሽኑ ንብረት አስተዳደር ሥራ ክፍል በተዘጋጁት ቅጾች መሠረት የስቶክ መረጃዎችን
መያዝ አለባቸው፣
2. የኮርፖሬሽኑ ንብረት አስተዳደር ሥራ ክፍል የዚህን መመሪያ ድንጋጌዎች በማይጻረር መንገድ
በሚዘጋጅ የኤሌክትሮኒክስ ዘዴ የስቶክ መረጃን መያዝና ማስተዳደር ይችላሉ፣
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የንብረት አስተዳደር ክፍል
የስቶክ መረጃቸውን በተለየ ሁኔታ ለመያዝ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኙት ለኮርፖሬሽኑ
ማኔጅመንት ጥያቄ በማቅረብ ሲፈቀድ መረጃውን በተለየ ፎርም መዝግበው መያዝ
ይችላሉ፡፡
4.4. ስቶክ ስለመቀበል
ኮርፖሬሽኑ አዲስ ስቶክ ሲቀበል በሚከተሉት ላይ ተገቢውን ማጣራት ማድረግ ይኖርበታል፡፡
ሀ. የዕቃ ግምጃ ቤት ኃላፊው ዕቃውን ለመረከብ የሚያስችል ከሚመለከተው የሥራ ክፍል
የተሰጠ ትዕዛዝ መኖሩን፣
ለ. የዕቃ ግምጃ ቤት ኃላፊው የዕቃውን ትክክለኛነት ከተሰጠው ትዕዛዝ የዕቃ ዝርዝር
(Specification) ጋር በማመሳከር ወይም ባለሙያ የሚፈልግ ከሆነም በባለሙያ
ስለትክክለኛነቱ ማረጋገጫ ማግኘት፣
ሐ. ስቶኩ የተገኘው ከኮርፖሬሽኑ ውስጥ ከሚገኙ ሌሎች የሥራ ክፍሎች ወይም ስቶኩን
ከሚመልሱ የኮርፖሬሽኑ አባላት ሲሆን የተገኘው ስቶክ ወጪ ከተደረገበት በሌላ
የኮርፖሬሽኑ የሥራ ክፍል ከተዘጋጀው የንብረት ወጪ ማድረጊያ ሰነድ ጋር ማመሳከር፣
መ. የስቶክ አስተዳደር ተግባርን የሚያከናውን የሥራ ክፍል ኃላፊ ከማናቸውም ምንጭ
ንብረት ሲገኝ የስቶኩን መዝገብ ንብረቱን በተቀበለበት ዕለት የማስተካከል፣
10
ሀ. የስቶክ አስተዳደር ተግባራትን የሚያከናውን የሥራ ክፍል ኃላፊ ስቶክ ከመጋዘን ሲወጣ
በዋናው የስቶክ መዝገብ ላይ ተገቢውን ማቀናነሻ መደረጉን ለእያንዳንዱ ሠራተኛ
የስቶክ ዝርዝር ተመዝግቦ መያዙን ማረጋገጥ አለበት፡፡
ለ. የስቶክ ወጪ መጠየቂያ ተጠቃማ የሥራ ክፍሎች ወይም ሠራተኞች ለስራ
የሚያስፈልጋቸውን ንብረት በሚፈልጉበት ወቅት የዕቃ መጠየቂያ ቅጽ በተገቢው ሁኔታ
በመሙላትና በሚመለከተው ኃላፊ በማስፈረም የስቶክ አስተዳደር ተግባርን
ለሚያከናውን የሥራ ክፍል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ሐ. የስቶክ ወጪ ጥያቄን በማረጋገጥ የስቶክ ንብረት የሚያስተዳድረው የሥራ ክፍል
የተጠየቁት ዕቃዎች በመጋዘን ውስጥ ያሉ መሆናቸውን በማጣራት ለኃላፊው በማቅረብ
ያስወስናል፡፡
መ. የተጠየቀ የስቶክ ዕቃን ወይም ንብረትን ለመረከብ/ወጪ ለማድረግ የተጠየቀው ዕቃ ወይም
ንብረት በንብረት መረከቢያ ቅጽ ላይ በተገቢው ሁኔታ ተሞልቶ በተረካቢው ተረጋግጦ ወጪ
መደረግ አለበት፡፡
ሠ. ንብረት ከመጋዘን ወጥቶ ከኮርፖሬሽኑ ውጪ ሲሰራጭ ወይም ሲወገድ ወይም ሲሸጥ
የንብረት አስተዳደር ተግባርን በሚያከናውን የሥራ ክፍል ኃላፊ በተረጋገጠ የዕቃ ማውጫ
ቅጽ መሠረት ወይም የኤሌክትሮኒክስ የመረጃ ሥርዓት በመጠቀም በተረጋገጠው መሠረት
መሆን አለበት፡፡
12
ክፍል አምስት
5. የኮርፖሬሽኑ ንብረት አወጋገድ
ኮርፖሬሽኑ በዚህ መመሪያና በሌሎች ሕጎች መሠረት ቋሚ ንብረቶችን የማስወገድ ሥልጣን አለው፡፡
13
ኮርፖሬሽኑ ንብረቶችን ለማስወገድ የሚከተለውን ሂደት መከተል ይኖርበታል፣
ሀ. የኮርፖሬሽኑ ንብረቶችን በባለበትነት የመከታተል ኃላፊነት የተሰጠው የሥራ ክፍል የሚወገዱ ንብረት ዝርዝርን
በቅፅ ሞልቶ ኮርፖሬሽኑ በወቅቱ ማቅረብ ይኖርበታል፣
ሐ. የኮርፖሬሽኑ ንብረቶች አስወጋጅ ኮሚቴ የተመራለትን መጠየቂያ ቅፅ መርምሮ በዚህ መመሪያ መሰረት
አስፈላጊውን ይፈፅማል፡፡
መ. የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስኪያጅ የሚሰይመው ንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ ያፀድቃል፡፡
እንዲወገዱም ውሳኔ የተሰጠባቸውን የኮርፖሬሽኑ ንብረቶች በወቅቱ እንዲወገዱ ያደርጋል፡፡
1. ንብረትን ለሕዝብ በሐራጅ ወይም በጨረታ መሸጥ የሚያስከትለው ወጪ ከፍተኛ ሆኖ የሚታወቅ በመሆን
ኮርፖሬሽኑ ለማስወገድ የፈለገውን ንብረት ወደ ሌላ የመንግስት መስሪያ ቤት ለማዛወር ይቻል እንደሆነ
በቅድሚያ ጥረት ማድረግ አለበት፡፡
2. በመንግስት መስሪያ ቤቶች ወይም በልማት ድርጅት መካከል የሚደረገው የንብረት ዝውውር የሚፈፀመው
የወቅቱን የንብረቱን ዋጋ ግምት በመመዝገብ መሆን አለበት፡፡
15
iii. ከላይ በተራ ቁጥር i በተጠቀሰው መንገድ ሽያጩ ካልተወሰነ የንብረት አስወጋጅ/ሽያጭ
ኮሚቴ ንብረቱ የሚወገድበትን ሌላ አማራጭ ዘዴ ለዋና ስራ አስኪያጅ በማቅረብ ሲወሰን
ንብረቱ እንዲወገድ ያደርጋል፡፡
5.7.2. በጨረታ ስለሚደረግ ሽያጭ
ሀ. ኮርፖሬሽኑ የሚያወጡት የጨረታ ማስታወቂያ ኤጀንሲው ባዘጋጀው ቅፅ የተገለፁትን
ማካተት አለበት፡፡
ለ. ተጫራቾች እንዲጫረቱ በሚሰጠው ቀን ከ 15 እስከ 30 ቀናት ሆኖ በኮርፖሬሽኑ ንብረቶች
አስወጋጅ ኮሚቴ የሚወሰን ይሆናል፡፡
ሐ. ኮርፖሬሽኑ በጨረታ ማስታወቂያው እስከተመለከተው ጊዜ ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ የተለየ
የጨረታ ሳጥን ማዘጋጀት አለበት፡፡ አስወጋጅ ኮሚቴውም ጊዜው ሲደርስ ጨረታ ሳጥኑን
ማሸግ አለበት፡፡ ማናቸውም ለጨረታው ማቅረቢያ የተሰጠው ጊዜ ካለፈ በኋላ የሚቀርቡ
የጨረታ ሰነዶች ሳይከፈቱ ለተጫራቾች መመለስ አለባቸው፡፡ በጨረታ ሽያጭ በቂ ተወዳዳሪ
ካልቀረበ ወይም የቀረበው ዋጋ ተቀባይነት ካላገኘ መስሪያ ቤቱ የጨረታውን ማስታወቂያ
በድጋሚ የማውጣት ወይም ጨረታውን በመሰረዝ ሌላ የማስወገጃ አማራጭ የመጠቀም
መብት አለው፡፡
መ. ኮርፖሬሽኑ ተጫራቾች የጨረታ ማስከሪበያ እንዲያስይዙ መጠየቅ ያለበት ሲሆን፣
ለእያንዳንዱ በጨረታ መከናወን ላለበት ሽያጭ የጨረታ ማስከበሪያ ሊኖር እንደሚገባ
መወሰን አለበት፡፡ የሽያጭ ኮሚቴውም ለእያንዳንዱ ሽያጭ የሚያዘውን የጨረታ
ማስከበሪያ በጨረታው ያሸነፈው ተጫራች እንደተመረጠ ወዲያውኑ ጨረታውን ላላሸነፋ
መመለስ አለበት፡፡
ሠ. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው እና የሽያጭ ኮሚቴ አባላት ባሉበት ለሕዝብ ግልፅ
ሆኖ መከፈት አለበት፡፡ የተጫራቾች ስምና የመጫረቻው ጊዜ በሽያጭ ኮሚቴ አስተባባሪ
መነበብ አለበት፣ የሽያጭ ኮሚቴ ፀሐፊም ይህንኑ መዝግቦ መያዝ አለበት፡፡
ረ. ኮሚቴው የትኛውን የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳብ መቀበል እንዳለበት ይወስናል፡፡ ከፍተኛው
ጨረታ በመነሻነት በተያዘው ዋጋ ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ ኮሚቴው ከፍተኛውን የጨረታ
ዋጋ ሊቀበል ይችላል፡፡
ሰ. የንብረት አስወጋጅ/የሽያጭ ኮሚቴው በጨረታው የደረሰበትን የአፈፃፀም ሂደት
እንዲያፀድቀው ለመስሪያቤቱ የበላይ ኃላፊ ማቅረብ አለበት፡፡
5.7.3. በሀራጅ ስለሚደረግ ሽያጭ
ሀ. ኮርፖሬሽኑ የሚያወጣው የሐራጅ ማስታወቂያ ኤጀንሲዉ ባዘጋጀው ቅጽ መሠረት ተሞልቶ
መቅረብ አለበት፡፡
ለ የሐራጁ መሪ ሐራጁ ከመጀመሩ በፊት የመነሻውን ዋጋ መግለጽ አለበት፡፡ በሐራጁ የመነሻው ዋጋ
ወይም ከዚህ በላይ ንብረቱን የሚገዛ ካልተገኘ የንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ የተሻለ ነው
የሚለውን የማስወገጃ ዘዴ መምረጥ አለበት፡፡
16
5.7.4. የተሽከርካሪዎችና መሣሪያዎች ማስወገጃ መመዘኛዎች
17
ሐ. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 7/ለ ላይ የተመለከቱት ዋና ዋና አካላቱ የተሟሉ ባይሆንም
የተሽከርካሪው ወይም የመሣሪያው ቀሪ አካል በገበያ ላይ ተፈላጊ መሆኑ ከተረጋገጠ፣
19
1. ሻጭ ኮርፖሬሽኑ የሸጠበትን ገንዘብ ተቀብሎ የሸጣቸውን ተሽከርካሪዎች፣ መሣሪያዎችና ሌሎችም
የስም ዝውውር የሚያስፈልጋቸው ንብረቶች በገዥው ስም ተመዝግቦ የባለቤትነት መታወቂያ
እንዲሰጠው ስልጣን የተሰጠውን አካል በደብዳቤ በመጠየቅ ማስፈፀም ይኖርበታል፣
2. ኮርፖሬሽኑ በሚሰጠው ደብዳቤ ላይ የሽያጡን ቃለ ጉባኤ፣ የገዥውን ስም፣ በጨረታ የተሸጠበትን ገንዘብ
ልክ፣ የተሸጠውን ንብረት መለያ ቁጥር፣ አይነትና ሞዴል፣ ተሽከርካሪዎችን የሻንሲና የሞተር ቁጥር
እንዲሁም የሌሎች ንብረቶችን ሌሎች መለያዎች በመዘርዘርና የጉምሩክ ቀረጥ የተከፈለበትን ሰነድ
በማያያዝ የማይከፈልበትም ከሆነ ይህንኑ በመግለጽ ማስተላለፍ አለበት፡፡
ሐ. የቀረበው አቤቱታ በኤጀንሲው ወይም በሌሎች ባለሙያዎች ዝርዝር ምርመራ ተደርጎበት ሪፖርት
እንዲቀርብለት የማድረግ፣
መ. ምስክሮችን የመጥራት፣ ምስክሮችና የንብረት ሽያጩ የሚመለከታቸው ወገኖች ቃላቸውን በመሃላ
እንዲሰጡ የማድረግ፣
ሠ. አቤቱቃ የቀረበበት የመንግስት መስሪያ ቤት ቀጣይ የአፈጻጸም እርምጃ እንዳይወስድ የማገድ፣
ረ. የመንግስት መስሪያ ቤቱ በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር አዋጅ በተደነገገው መሰረት ስራውን
እንዲያከናውን ትዕዛዝ የማስተላለጽ፣
ሰ. የመንግስት መስሪያ ቤቱ ከህግ ውጭ ያከናውነው ተግባር ወይም የሰጠው ውሳኔ በሙሉ ወይም በከፊል ቀሪ
እንዲሆን የማድረግ፣
ሸ. ተገቢ ሆኖ ካላገኘው የንብረት ገዢውን አቤቱቃ ውድቅ የማድረግ፣ ናቸው፡፡
20
1. የንብረት ገዢ አቤቱታ የማቅረብ መብት
ጨርታውን ያወጣው ኮርፖሬሽኑ በዚህ መመሪያ የተመለከተውን በአግባቡ አልፈፀሙም በሚል ቅር
የተሰኘ ተጫራች/ገዢ ጨረታው እንደገና እንዲታይለት ወይም ሂደቱ እንዲጣራለት እንደ ጉዳዩ ሁኔታ
ለኮርፖሬሽኑ የበላይ ኃላፊ ወይም ለቦርድ ጽህፈት ቤት አቤቱታ ማቅረብ ይችላል፡፡
2. አቤቱታ ማቅረብ የማይቻልባቸው ሁኔታዎች
ሀ. ኮርፖሬሽኑ በመረጠው የንብረት ማስወገድ ዘዴ ላይ፣
ለ. በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው የሽያጭ መነሻ ዋጋ ላይ፣
ሐ. በሚከተሉት ምክንያቶች ጨረታውን ውድቅ ለማድረግ በተሰጠ ውሳኔ፣
I. በሽያጭ አካሄዱ ላይ ውጤቱን ሊያዛባ የሚችል ስህተት መፈፀሙ ከተረጋገጠ፣
II. የኮርፖሬሽኑን ፍላጐት ለማሟላት ሌላ የተሻለ የማስወገጃ አማራጭ መገኘቱ በኮርፖሬሽኑ
ከታመነ፣
III. የቀረበው ከፍተኛ ዋጋ ኮርፖሬሽኑ ካስቀመጠው የመሸጫ መነሻ ዋጋ ያነሰ ከሆነ፣
IV. በዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም በሽያጭ ኮሚቴ አባላት ጨረታውን ለማዛባት የመመሳጠር ተግባር
መፈፀሙ ከተረጋገጠ፣
V. አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ተጫራቾች በመቅረባቸው ምክንያት በቂ ውድድር ባለመደረጉ
ተስማሚ የሽያጭ ዋጋ ባለመገኘቱ፡፡
21
4.12.1 ለቦርድ ጽህፈት ቤት አቤቱታ የሚቀርብበትና የሚጣራበት ስርዓት
1. የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቤቱታው ከቀረበበት ቀን አንስቶ በሚቆጠር አስር ቀናት ውስጥ
ለአቤቱታው ውሳኔ ካልተሰጠ ወይም ውሳኔ ተሰጥቶ አቤቱታ አቅራቢው በተሰጠው ውሳኔ ያልረካ
እንደሆነ ኮርፖሬሽኑ ውሳኔ ከተገለፀበት ወይም ውሳኔ ካልሰጠ ውሳኔውን መስጠት ከነበረበት ቀን ገደብ
ማብቂያ ጀምሮ በሚቆጠር 5 /አምስት/ የስራ ቀን ጊዜ ውስጥ አቤቱታውን ለቦርድ ጽህፈት ቤት ማቅረብ
ይችላል፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላ በቦርድ ጽህፈት ቤት የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
2. ንብረት ገዢው አቤቱታውን ለቦርድ ጽህፈት ቤት ሲያቀርብ ለኮርፖሬሽኑ ያቀረበውን አቤቱታ የሚያሳይ
ደብዳቤ ኮርፖሬሽኑ ለአቤቱታው ውሳኔ ተሰጥቶ ከሆነ የውሳኔውን ቅጂ፣ የአቤቱታውን ጭብጥና፣
ተያያዥ ማስረጃዎችን በአባሪነት ማያያዝ ይኖርበታል፡፡
3. ቦርዱ አቤቱታው እንዲቀርብለት ወዲያውኑ አቤቱታ የቀረበ መሆኑን በቀረበበት አቤቱታ ላይ ያለውን
ማስረጃና መግለጫ ማስታወቂያው በደረሰው በአምስት የስራ ቀን ውስጥ እንዲያቀርብ እንዲሁም ውሳኔ
እስከሚሰጥ ድረስ ቀጣይ እንቅስቃሴ እንዲያቆም የሚገልጽ ማሰታወቂያ ለኮርፖሬሽኑ ይልካል፡፡
4. አቤቱታው የቀረበበት ኮርፖሬሽን አቤቱታውን ለማጣራት የሚያስፈልጉትን ንብረት ሽያጭ
የተፈፀመባቸው ሰነዶችና መግለጫ እንዲቀርቡለት ከቦርድ ጽህፈት ቤት ጥያቄ በቀረበለት 5 /አምስት/
የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይኖርበታል
5. ቦርዱ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4 የተጠየቁት ሰነዶች ከኮርፖሬሽኑ ሲቀርብለት ጉዳዩን ከአዋጅና ከዚህ
መመሪያ አኳያ በመመርመር ውሳኔውን በ 15 /አሰራ አምስት/ የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ በጽሁፍ መስጠት
አለበት፡፡ በጽሁፍ የተሰጠው ውሳኔ የውሳኔውን ምንነትና የሚወሰደውን እርምጃ የሚያሳይ መሆን
ይኖርበታል፡፡
6. ቦርዱ የሰጠው ውሳኔ ግልባጭ ውሳኔው በተሰጠ በ 5 /አምስት/ የስራ ቀናት ውስጥ አቤቱታውን ላቀረበው
ንብረት ገዢ አና ለመስሪያ ቤቱ እንዲደርስ ማድረግ አለበት፡፡
ክፍል አምስት
5. ልዩ ድንጋጌ
22
5.1 መመሪያ ስለማሻሻል
በዚህ የንብረት አስተዳደር አፈፃፀም መመሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ
ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን ስራ አመራር ቦርድ ሲታመንበት መሻሻል ይችላል፡፡
5.1 መመሪያ የሚፀናበት ጊዜ
ይህ መመሪያ ከ ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡
አባተ ስጣታው
የኮርፖሬሽኑ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ
አባሪ ሰነዶች
የገቢ ዕቃ ደረሰኝ
Goods Receiving Note
የጽ/ቤት ስም____________
የእቃው ኮድ__________ ቀን _____________ የግዥ መጠየቂያ ቁጥር_________
የአቅራቢው ስም:_________________ Purchase requisition No._________
23
Supplier Name የግዥ ማዘዣ ቁጥር:_______ L/C ቁጥር ___________
Purchase Order No._____
ድምር /Total
ያዘጋጀው ___________ አስረካቢ:_______ ተረካቢ:_________________
Prepared Delivered by Received by
ፊርማ/Signature_______ፊርማ/Signature_________ ፊርማ/Signature_________
ቀን/Date_________ ቀን/Date____________ ቀን/Date___________
የቅጂ ስርጭት
ንብረት ማሰራጫ ቅጽ
24
ቀን/Date__________________________
የገቢ ሰነድ ቁጥር (GRN No.)_______________________
የተላካለት ጽ/ቤት __________________________________ የተረካቢ/የአሽከርካሪው ስም
Dispatched to Driver's Name
መለያ ቁጥር_____________________________________ የመታወቂያ ቁጥር
Address I.D. Number
ስልክ ሰሌዳ ቁጥር
Tel. Plate No.
የተሳቢ ሰሎዳ
Trailer
በዚህ ሰነድ የላክነው ንብረት በመልካም ሁኔታ መድረሱን እባኮ በገቢ ሰነድ ያለጋግጡልን
Please acknowledge the receipt of the following good's or items in confirmation of receiving inproper condition and send us your
የንብረት ወጪ ደረሰኝ
25
ወሳጅ /issued________________________________ ቀን /Date
የእስቶር መጠየቂያ ቁጥር/ Store Requisition No_______________________ ወጪ የሚመዘገብበት ክፍል/ስራ /cost
center_______________
የአንዱ
ዋጋ
የንብረቱ መለያ የእቃው ዓይነት
ወጪ የሚሆነው total
Code No. Description
ተቁ.S መለኪያ ብዛት Qty unit ጠቅላላ ዋጋ
/No. Unit issued price unit price መግለጫ Remark
26
የስራ ክፍል ______________________________________________ SR NO._______________
ምክንያት/Purpose Of Request/_________________________________________
ቀን/Date_____________________
ንብረት ማስተላለፊያ ቅጽ
Property Transfer Form
27
ከ___________________________________ ለ_____________________________
From_____________________________________________________________________________________________________________
የአስረካቢ ስራ ክፍል የተረካቢ ስራ ክፍል
የአንዱ ጠቅላላ
ገቢ የሆነው ብዛት Qty. ዋጋ ዋጋ
የንብረቱ ዓይነት Item Received Unit Total
ተ.ቀ. Description መለኪያ Unit Price Price መግለጫ Remark
Yadanoo_____________________________________________________________________________________________________________________________________________
________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
Document
Destribution 2.ቢጫ-ለተረካቢ 4. አረንጎዴ- ንብረት ቁጥጥርና ምዝገባ
Yellow-Receivers Green Record& Control
29
30
የቁሚ ንረት መዝገብ (Fixed Asset Registration Book )
ጽ/ቤት/ፕሮጅቸት__________________________________
ገጽ_____________
የንብረቱ ጠቅላላ መረጃ መግለጫ (General Information of Equipment)
ንብረቱ የአገልግሎ የሚዘኝ
ተ.ቁ. የንብረቱ ሰሌዳ የንብረቱ ኮድ የተገዛበት ወቅታዊ በስጦታ ት ዘመን መት ቦታ ተጨማሪ
(Ite ዓይነት ሞድል ቁጥር የኮርፖሬሽኑ ዘመን የተገዛበት ዋጋው የተገኘበት (Expecte (Current መረጃዎች ስለ
m (Item (Model (Plate ( corporation (Purchased ዋጋ(Purchas (Current ቀን/ገቢ d life Location (Additional ሞተሩ
No.) Discription ) ) No.) code NO.) Year) ed Value) Value) የሆነበት time) ) Information) (Engine)
የሻንሲ
የአምራቹ ቁጥር የተመረተ የሞተሩ ንብረቱ
መለያ (Transm በት ቁጥር የሞተር አምራች የሚገኝበት
የንብረቱ ቁጥር ission (Country ቁጥር መለያ ሁኔታ
ቀለም (Serial Serial of (Horse (Serial ሞድል( (Status of
(colour) Number) No.) Origin) Power) No.) Model) the Item)
1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17
31
ክፍል አራት
ረ/ የተሽከርካሪው ዋጋ እና
4.1.2 በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሱት መረጃዎች በበቂ ምክንያት ተሟልተው
እና ቅባት ፍጆታ መጠን፣ የጥገና ወጪ፣ የተጓዘው ኪ.ሜ መጠን፣ በእነማን ይዞታ ስር
4.1.4 የተሽከርካሪው የህይወት ታሪክ መዝገብ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ እየተፈተሸ ወቀታዊ
መደረግ ይኖርበታል፡፡
32
4.2.1 የዋና ስራ አስኪያጅ የኮርፖሬሽኑ ተሽርካሪዎች በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውሉ
4.2.1 የዋና ስራ አስኪያጅ ለጋራ አገልግሎት፣ በልዩ የሥራ ባህሪያቸው ተሽርካሪ ለሚያስፈልጋቸው
4.2.3 ለበላይ ኃላፊዎችና ኃላፊዎች ከተመደቡት በዋና ስራ አስኪያጁ ወይም ከወከለው አካል ልዩ
መደረግ ይኖርበታል፡፡
የሞተር ዘይት መጠን፣ የፍሬን ሁኔታ …ወዘተ አስቀድሞ በጥንቃቄ በማየት ተሽከርካሪው
4.3.3 ማንኛውም ለጋራ አልግሎት የተመደበ ተሽከርካሪ በልዩ ሁኔታ ካልተፈቀደ በስተቀር
እንዲያድር አይፈቀድም፡፡
4.3.4 በበላይ ኃላፊዎችና ከሚሽከረከሩ ወይም በኮርፖሬሽኑ በተፈቀደው መሠረት በተለየ ሰሌዳ
4.3.7 በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3.6 አፈፃፀም በመስክ ሥራው የተሰማሩ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች
ክፍል አምስት
ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
34
5.3 ለበላይ ኃላፊዎች አና ለኃላፊዎች ከሚመደቡ ተሽከርካሪዎች በስተቀር እያንዳንዱ ተሽከርካሪ
የፈጀው የነዳጅ መጠን ከሸፈነው የኪ.ሜትር መጠን ጋር እየተመዘገበ ተገቢው ሪፖርት በየወሩ
መቅረብ ይኖርበታል፡፡
5.4 የኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎች አገልግሎት ተሽከርካሪዎች የሚውለው ነዳጅ፣ ቅባትና ዘይት የመሳሰሉት
ግምገማ ያካሂዳል፡፡
6.2 ማንኛውም አሽከርካሪ ወይም በራሱ እንዲያሽከረክር የተፈቀደለት ኃላፊ ያረጃ ጎማና ቸርኬን
6.3 በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 5.1 መሠረት ወደ ዕቃ ግምጃ ቤት ተመላሽ የሚደረገው የመለዋወጫ
ዕቃ መለያ ቁጥር (Serial Number) ከዕቃ ግምጃ ቤት በሚላከው መረጃ መሰረት ቀደም ሲል
ይደረጋል፡፡ የመለዋወጫ ዕቃው መለያ ቁጥርም በተሽከርካሪው የግል ማህደር ውስጥ ተመዝግቦ
6.5 ኮርፖሬሽኑ የራሱ ጋራዥ ስለሌለው የጥገና አገልግሎት ከሚሰጠው ከተመረጠው ጋራዥ ጋር
የመለዋወጫ ዕቃ አቅርቦትንም ሲያገኝ ከሆነ የተለወጠው የመኪና ዕቃ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
ክፍል ሁለት
7 የኮርፖሬሽኑ ኃላፊነት
35
7.2 የኮርፖሬሽኑ ተሽከርሪዎች የህይወት ታሪክ፣ የተሽከርካሪዎችን የስምሪት ሪፖርት፣ የተሽከርካሪዎች
ክትትል ያካሂዳል፡፡
ባለው አካል የተሰጠና አግባብነት ያለው የታደሰ የማሽከርከር ፈቃድ ያላቸው መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
7.5 በተሽከርካሪዎቹ የግል ማህደር ውስጥ ከሚመዘገበው ሬከርድ በመነሳት ተሽከርካሪዎች ወቅታቸው
7.7 ተሽከርካሪዎች ተገቢውን የእሳት አደጋ መከላከያ፣ ክሪክ፣ መፍቻዎችና የመሳሰሉት እንዲኖሩዋቸው
ያደርጋል፡፡
7.8 በኃላፊነቱ ስር ያሉትን ተሽከርሪዎች ብዛት፣ ዓይነት፣ የሚገኙበትን ሁኔታ… መዘተ የመሳሰሉትን
8 የኮርፖሬሽኑአሽከርካሪዎች ኃላፊነት
8.2 የትራፊክ ደህንነት ደንብና መመሪያን አክብሮ ማሽከርከርና ተሽከርካሪውን ለተመደበለት ዓላማ
ብቻ ማዋል፡፡
8.4 ተሽከርካሪው ለእንቅስቃሴ ዝግጁ መሆኑን ከማረጋገጥ አንፃር የሞተር ዘይት፣ የፍሬን ዘይት፣ የጎማ
በየጊዜው መፈተሽ፣
36
8.5 በማያሽከረክረው ተሽከርካሪ ላይ ብልሽት፣ ስርቆት ወይም አደጋ ከደረሰ በአካባቢው ለሚገኝ
ፖሊስና ለመ/ቤቱ ለሚመለከተው የሥራ ክፍል ወዲያውኑ ዝርዝር ሪፖርት በስልክ ወይም በጽሁፍ
ማቅረብ፣
8.9 የትራንስፖርት ሕግና ደንብ በመተላለፍ በተሽከርካሪው ላይ ለሚደርስ ጉዳት ኃላፊና ተጠያቂ
ክፍል አምሰት
ልዩ ልዩ
9.2 በመንግሥት ንብረት አሰተዳደር መመሪያ ቁጥር 9/2003 ላይ ስለመንግሥት ንብረት አስተዳደርና
አወጋገድ የሚደነግጉ አንቀፆች፣ በሥሪ ላይ ያሉት የመንግሥት የቋሚ ንብረት አስተዳደር እና የስቶክ
37
አስተዳደር ማንዋሎች እንደአግባብነታቸው ለመንግስት ተሽከርካሪዎች አስተዳደርም ተፈፃሚነት
ይኖራቸዋል፡፡
9.3 የመንግስት መ/ቤቶች ከዚህ መመሪያ ጋር አባሪ የሆኑትን ቅፆች መጠቀም አለባቸው፡፡
10 የተሻሩ መመሪያዎች
ሊሰራባቸው ይችላል፡፡
11 መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ
ይህ መመሪያ ከ ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡
አባተ ስጣታው
የኮርፖሬሽኑ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ
38
አባሪዎች
ቅጽ 01
1. የመንግስት መስሪያ ቤቱ ስም
2. የተሽርካሪው፣
የተጠቀሰውን ተሽከርካሪ ስረከብ ከላይ የተዘረዘሩትን መፍቻዎችና ዕቃዎች እንዲሁም የተሽከርካሪውን ሁኔታ
የተረካቢው ስም ፊርማ ቀን
የአስረካቢው ስም ፊርማ ቀን
የአረካካቢው ስም ፊርማ ቀን
40
ቅጽ 02
የመንግስት ተሽከርካሪ ዕለታዊ የነጃጅ፣ የዘይትና የኪ.ሜ መመዝገቢያ
የመስሪያ ቤቱ ስም የወር ዓ.ም
ነዳጅ በኩፖን
የሞተር ዘይት
የፍሬን ዘይት
የጥራስ ጥርስ
ዘይት
ግሬስ
የሞተር ዘይት
የፍሬን ዘይት
የጥራስ ጥርስ
ዘይት
ግሬስ
የመዝጋቢው ሥም ፊሪማ ቀን
ማሳሰቢያ፡- ይህ ቅጽ የነዳጅ ማደያ ዲፖ ላላቸው የመንግስት መ/ቤቶች እንዲሁም በተለያዩ ማደያዎች ነደጅ ለሚቀዱ በካርድ ፎርም ታትሞ የየዕለቱ ፍጆታ የሚመዘገብበት ካርድ ነው፡፡
ቅጽ 03
41
የመንግስት ተሽከርካሪ ወርሀዊ የነዳጅ፣ የዘይትና የጥገና ወጪ ማጠቃለያ
የመ/ቤቱ ሥም
ያዘጋጀው ስም ፊርማ ቀን
ያፀደቀው ስም ፊርማ ቀን
ማሳሰቢያ ይህ ቅጽ በሦስት ተሠርቶ፣ የመጀመሪያ ቅጅ ለመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ ይቀርባል፣ ሁለተኛው ቅጅ ለመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ይላካል፣ ሦስተኛው ቅጅ
በትራንስፖርት ስምሪት ይቀመጣል፡፡
42
ቀጽ 04
1. የመንግስት መስሪያ ቤቱ ስም
2. የተሽከርካሪው
43
ማሳሰቢያ፡- ይህ ቅጽ በአንድ ኮፒ ተሠርቶ ከተሽከርካሪው የሕይወት ታሪክ ማህደር ጋር ተያይዞ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡ በየወሩ መጨረሻ ከቅጽ 03 ጋር በማወራረስ ወርሀዊ ሪፖርት መራት
አለበት፡፡
44
ቅጽ 05
የህ ቅጽ የሚሞላው አዲስ የተገዛን ወይንም ነባር ተሽከርካሪን ከአንድ የሥራ ሂደት ወደ ሌላ አዛውሮ መመደብ
ሲያስፈልግ ነው
1. የመንግስት መስሪያ ቤቱ ስም
2. የተሽርካሪው
3.2 የፕሮጀክት
የመሥሪያ ቤቱ ኃላፊ
ውሳኔ
ስም ፊርማ ቀን
ማሳሰቢያ፡- 1 ይህ ቀጽ የሚሞላው አዲስ የተገዛ ተሽከርካሪ ለተጠቃሚ ሲመደብ ወይም ነባር ተሽከርካሪ ከአንድ የስራ
ለተጠሟ ይሰጣል፡፡
ቅጽ 06
2. የተጓዡ ሥም ሀ. ለ.
ሐ. መ.
3. የሚሄዱበት ሥፍራ
4. ምክንያት
የሾፌሩ ስም ፊርማ ቀን
ማሳሰቢያ
46
ቅጽ 07
ልዩ መታወቂ
ስማቸው፣ ፎቶግራፋቸው እና ፊርማቸው በዚህ መታወቂያ ካርድ ላየ የሚታየው የስራ ኃላፊ ንብረትነቱ የ
………………………………….. መስሪያ ቤት የሆነውን ተሽከርካሪ እንዲያሽከረክሩ ተፈቅዶላቸዋል፡፡
ፊርማ…………………………
እናመሰግናለን
47
ቅጽ 08
ቀን
ከ ዳይሬክቶሬት
የተጠየቀበት ምክንያት
ነዳጅ ናፍጣ
የሞተር ዘይት
የፍሬን ዘይት
የጥርሳ ጥርስ ዘይት
ግሬስ
የእጥበት አገልግሎት
የጠያቂው ስም ፊርማ ቀን
የፈቃጁ ስም ፊርማ ቀን
48
ማሳሰቢያ፡- ይህ ቅጽ በሁለት ቅጅ ከተሠራ በኋላ፣ የመጀመሪያው ቅጅ በተሽከርካሪ ስራ ክፍል ይቀመጣል፡፡ ሁለተኛው ቅጅ
በጠያቂው/በተጠቀሚው ስራ ክፍል ይያዛል፡፡
ቅጽ 09
የመሥሪያ ቤቱ ሥም ቀን
ለ
የሠሌዳ ቁጥር የተሽከርካሪው ዓይነት
ተሽከርካሪው የሚከተሉት ብልሽቶች ስላሉት ተመርምሮ እንዲጠገንልን እንጠይቃለን፡፡
የብልሽቱ ዓይነት
ሥም ፊርማ ቀን
እነድንጋይ ኳሱ
49
ቅጽ 10
ድምር ድምር
50
ማሳሰቢያ፡- ይህ ቅጽ ጋራዥ ላላቸው የመንግስት መ/ቤቶች ወይንም ድርጅቶች የጥገና የሥራ ትዕዛዝ
የሚሞላበት ሲሆን ቅፁ በሁለት ቅጅ ተዘጋጅቶ የመጀመሪያው ቅጅ ለጥገና ክፍል ሁለተኛው ቅጅ ለጥገና
ትዕዛዝ ለሞላው ክፍል ይሰጣል፡፡
51