You are on page 1of 4

የጽዳት አገልግሎት የሚጸዱ ቦታዎች ካሬ ሜትር

የውጭ ግድግዳ ዕጥበት


ካሬ ሜትር

(በየቀኑ ሇስራው መሰማራት ያሇበት 408 የሰው


ኃይሌ ነው)

ጠቅላላ የካሬ ሜትር ስፋት፤ 43936.53 ካሬ ሜትር


በልዩ ልዩ መመሪያዎች ላይ የተሰጡ ማብራሪያዎች፣ ማሻሻያዎችና ማስተካከያዎች
በተለያዩ ጊዜ ባካሄድናቸው የስልጠና እና የውይይት መድረኮቻችን ማብራሪያ ወይም ማስተካከያ እንዲደረግባቸው ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በተደራጀ አግባብ ፣
ምላሽ መስጠት አስፈላጊና ተገቢ መሆኑን በማመን ከታች በዝርዝር በተቀመጡ ጉዳዬች ላይ የሚከተሉት የመመሪያ ማሻሻያዎችና ማብራሪያዎች የቀረቡ ሲሆን እነዚሁ
የየመመሪያው አካል ተደርገው ተወስደው እንዲፈፀሙ እናሳስባለን ፡፡
1. በተሻሻለው የምልመላና መረጣ መመሪያ በአንቀጽ 5.1 ንዑስ አንቀጽ 5.1.2 እስከ ሁለት ደረጃ የሚቆጠር የስጋና የጋብቻ ዝምድና በሰዉ ኃይል አስተዳድር
ሠራተኛዉና በስምሪት ዉድድር የሚሳተፈዉ ግለሰብ መካከል ካለ የሰዉ ኃይል አስተዳድር ሠራተኛ መሳተፍ እንደማይኖርበት ወይም እራሱን ማግለል እንዳለበት
ተመልክቷል፡፡ ይሁን እንጂ እስከ ሁለት ደረጃ የሚለዉ ብዝታ የፈጠረ በመሆኑ እንደሚከተለዉ ተብራርቷል፡፡
 ፈፃሚዉ ሰራተኛ ወንድ በሚሆንበት ጊዜ የፈፃሚዉ ልጅ፣ እናት፣ አባት፣ እህት፣ ወንድም፣ ሚስት፣ የሚስት የግል ልጅ፣ የሚስት እህት ወይም ወንድም
 ፈፃሚዉ ሰራተኛዋ ሴት በምትሆንበት ጊዜ የፈፃሚዋ ልጅ፣ እናት፣ አባት፣ እህት፣ ወንድም፣ ባል፣ የባል የግል ልጅ፣ የባል እህት ወይም ወንድም ሲሳተፉ ፈፃሚዎች
በስምሪቱ አይሳተፉም
2. በተሻሻለው የምልመላና መረጣ መመሪያ የስራ መልቀቂያ አሰጣጥን በተመለከተ በሁለት የተለያዩ ንዑስ አንቀፆች ላይ ማለትም በአንቀፅ 2.10 ንዑስ አንቀፅ 2.10.1
እና አንቀፅ 2.12 ንዑስ አንቀፅ 2.12.1 ፊደል ተራ ለ አንድ ሠራተኛ አሠሪዉን መ/ቤት መልቀቂያ ሲጠይቅ በምን ያህ ጊዜ ዉስጥ መልቀቂያ መስጠት እንዳለበት
የተመላከተዉ አንድ ወርና ሦስት ወር በሚል የተቀመጠዉ ለትርጓሜ የተጋለጠ ሆኖ በመገኘቱ በተሸሻለዉ የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 253/2010 አንቀፅ 82
መሠረት ማለትም አንድ የመንግስት ሠራተኛ በማነኛዉም ጊዜ የአንድ ወር ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ሥራዉን ሊለቅ ይችላል፡፡ ሆኖም መ/ቤቱ ሠራተኛዉን
በቀላሉ ሊተካዉ የሚችል ከሆን የአንድ ወሩን ጊዜ ሣይጠብቅ መልቀቂያዉን ሊሰጠዉ ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ሠራተኛዉ ለስራዉ እጅግ አስፈላጊና በቀላሉ ለመተካት
የማይቻል ሆኖ ሲገኝ የሚሰራበት መ/ቤት ወደፊት ከሚቀጠርበት መ/ቤት ጋር በመስማማት የመልቀቂያዉን ጥያቄ ከሶስት ወር ለማይበልጥ ጊዜ ሊያራዝም ይችላል፡፡
ሆኖም ተቀባይ መ/ቤት የማይስማማ ከሆነ የሚለቀዉ መ/ቤት በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ መልቀቂያዉን የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ በሚል የሁለቱ አንቀፆች ልዩነት
በአዋጁ ድንጋጌ እንዲተካ ተደርጓል፡፡
3. በተሻሻለው የምልመላና መረጣ መመሪያ በአንቀጽ 2.7.2 ንዑስ አንቀጽ 2.7.2.2 የተገለፀዉ እንደተጠበቀ ሁኖ ሁለት ተወዳዳሪዎች እኩል ዉጤት ሲያስመዘግቡ
አሸናፊዉ የሚለይበት መንገድ የተቀመጠ ቢሆንም ከፍተኛ የትም/ት ደረጃ ተደርጎ የሚወሰደዉ በምዝገባ ወቅት የቀረበዉ የትም/ት ማስረጃ እንጂ ከምዝገባ በኋላ
ዘግይቶ የሚቀርብ የትም/ት ማስረጃ አሸናፊዉን ለመለየት የሚያገለግል እንደሆነ ግንዛቤ ይወሰድ፡፡ በተጨማሪም በደረጃ እድገት ዉድድር ወቅት እኩል የሚያመጡ
ተወዳዳሪዎች ሲገጥሙ አሸናፊዉ የሚለየዉ በዚሁ አንቀፅ ነዉ፡፡
4. በምልመላና መረጣ መመሪያ ላይ ንዑስ አንቀጽ 3.7.3 ላይ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው ተወዳዳሪዎች እኩል ነጥብ ካመጡ አሸናፊው በአንቀጽ 2.7.4 በተገለፀው
መሠረት ይለያል የተባለው በዚሁ መመሪያ አንቀጽ 2.7 ንዑስ አንቀጽ 2.7.2 ቁጥር 2.7.2.3 በተገለፀው መሠረት ይለያል በሚል የንዑስ አንቀጽ አጠቃቀስ ማስተካከያ
የተደረገ ሲሆን ይኸው በደረጃ እድገት ውድድር እኩል ውጤት ላስመዘገቡ ተመሣሣይ ጾታ ላላቸው ተወዳዳሪዎችም ያገለግላል፡፡
5. በተሻሻለው የምልመላና መረጣ መመሪያ ላይ የአመልካቾች የአቀባበል ስርአት በሚለው ስር የመንግስት ሰራተኛ ሆኖ ለመቀጠር ዕድሜን በተመለከተ ያልተገለፀ
መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም እድሜአቸው ከ 14 ዓመት በላይና ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ዜጐች ስለሚቀጠሩበት ሁኔታ የወጣው መመሪያ እንደተጠበቀ ሆኖ
አመልካቾች ለመቀጠር እድሜአቸው 18 ዓመትና በላይ መሆኑ እንዲታወቅ ፣
6. ሐምሌ 2 ዐዐ 8 ዓ/ም በወጣው የተፈላጊ ችሎታ አያያዝና አጠቃቀም መመሪያ ቁጥር 2/2 ዐዐ 8 ላይ ልዩ ሙያ የሚጠይቁ የሥራ መደቦች ዝርዝር የተቀመጠ ስለሆነ
በዚሁ መመሪያ ተግባራዊ እንዲደረግ ከዚህ ማብራሪያ ጋር አባሪ ተደርጐ የተላከ መሆኑን ፣
7. የማህደር ጥራትን በተመለከተ አንቀጽ 4.5 ንዑስ አንቀጽ 4.5.2 በተመለከተው ሰንጠረዥ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተባለው ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 በሚል
የተስተካከለ መሆኑ ፣
8. በተሻሻለው የምልመላና መረጣ መመሪያ በአንቀጽ 3.7 ንዑስ አንቀጽ 3.7.3 በውጭ ዝውውር ውድድር ጊዜ ለሴት አካል ጉዳተኞች 4 ነጥብ እንደሚሰጥ የተመላከተ
ቢሆንም ለደረጃ እድገትና ለውስጥ ዝውውር ስንት እንደሚሰጥ ባለመመላከቱ ብዥታ የፈጠረ ሆኖ የተገኘ ስለሆነ በሚከተለው ማብራሪያ ተፈፃሚ ይደረግ፣
 ሴት አካል ጉዳተኛ ተወዳዳሪዎች በደረጃ እድገት፣ በውስጥ ዝውውር በውጭ ዝውውር ውድድር ከኃላፊነት ቦታዎች ውጭ በሆኑ የሥራ መደቦች ሲወዳዳሩ 4 ነጥብ
የሚሰጣቸው ሲሆን ለኃላፊነት ቦታዎች 6 ነጥብ እንዲሰጣቸው ከማድረግ በስተቀር የሴትነት ለብቻው ለአካል ጉዳተኝነት ለብቻው ተደምሮ ስምሪቱ የማይፈፀም
መሆኑን፣ ከዚህ አንፃር በመመሪያችን በንዑስ አንቀጽ 3.6.13 ላይ የተገለፀው ለየብቻው እንደሚደመር የሚያሣይ በመሆኑ ይኸው ን/አንቀጽ የማይሰራበት ተደርጐ
ይወሰድ፣
9. በተሻሻለው የምልመላና መረጣ መመሪያ አንቀጽ 3.7 ንዑስ አንቀጽ 3.7.23 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የቤተሰብ ችግር ያጋጠማቸው ከፖሊስ ወይም ከፍ/ቤት
ችግር ያጋጠማቸው መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ እንዲያቀርቡ በማድረግ ያቀረቡት ማስረጃ ስራቸውን እየሰሩ ባለበት ዞን ወይም ወረዳ ወይም ከተማ አስተዳደር ዋና
አስተዳዳሪ እና በየደረጃዉ ያለዉ ሲ/ሰርቪስ መ/ቤት ኃላፊ ጋር በጋራ በመሆን ተቀባይነት ሲያገኝ ከሚሰራበት ወረዳ ወደ ሌላ ወረዳ ወይም ከሚሰራበት ከተማ ወደ
ሌላ ከተማ አስተዳድር በዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ በኩል ተመድበው እንዲሰሩ ይደረጋል፣ ከአንድ ዞን ወደ ሌላ ዞን የሚደረግ ምደባ ግን በክልሉ ሲቪል ሰርቪስ
ኮሚሽን በኩል ይፈፀማል፡፡
10. የካርየር ተጠቃሚ ሠራተኞች የእድገት መሰላል ጣሪያቸው ጥር 2009 ዓ.ም በደመወዝ ማስተካከያ ሠንጠረዡ መሠረት የሚፈፀም ወይስ በየእድገት መሰላል
አፈፃፀም መመሪያው በተቀመጠው አግባብ የሚፈፀም ስለመሆን አለመሆኑ የግልጽነት ጥያቄ ያስነሣና ለስህተት በር የከፈተ በመሆኑ ማንኛውም የእድገት መሰላል
ተጠቃሚ ሠራተኛ በየራሱ የእድገት መሠላል አፈፃፀም መመሪያ ላይ የተቀመጠው የእድገት መሰላል ጣሪያ እስካልተሻሻለ ድረስ /እስካልተስተካከለ/ በደመወዝ
ማስተካከያው ሠንጠረዥ ላይ ከጣሪያ ደረጃ በላይ የተቀመጠውን የደረጃ ከፍታን መሠረት በማድረግ ጥቅም መስጠት እንደማይቻል ግንዛቤ ተወስዶ በዚሁ አግባብ
እንዲፈፀም ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ በሚል ማስተካከያ ተደርጓል፡፡
11. የሹፌር የዝውውር ውድድር ሲካሄድ በ JEG የተመደበበት ደረጃ ተመሣሣይ እስከሆነ ድረስ የያዘውን ደመወዝ እንደያዘ እንዲዛወር ይደረጋል፡፡ ለምሣሌ አንድ
ሾፌር ደረጃ VI ደመወዝ ብር 1586.00 የሚከፈለው ወደ ሌላ ደረጃ VI ወደ ሆነ መደብ የያዘውን ደመወዝ ይዞ እንዲዛወር ይደረጋል፡፡ በተመሣሣይ አንድ በደረጃ
VI ተመድቦ 1828 የሚከፈለው ሾፌር የያዘውን ደመወዝ እንደያዘ ሊዛወር ይችላላ፡፡
12. በነጥብ የስራ ምዘና ዘዴ በተጠኑ የስራ ደረጃዎች መደበኛ ስምሪት ሲፈፀም እስከ ባለሙያ II ዲፕሎማ ያላቸው ሠራተኞች ወይም አመልካቾች እንዲወዳደሩ
ከኮሚሽኑ ባስተላለፍነው ሠርኩላር ላይ ተገልጿል፡፡ ይሁን እንጅ ዲፕሎማ ያላቸው ወይም ከዲግሪ በታች ያላቸው ተወዳዳሪዎች በሚያሸንፉበት ጊዜ ስንት
እንደሚከፈላቸው ስለማያመላክት ከዲግሪ በታች ያላቸው ተወዳዳሪዎች በሚያሸንፉበት ጊዜ በነባሩ ለዲፕሎማ ወይም ከፍተኛ ዲፕሎማ ይከፈል የነበረው መነሻ
ደመወዝ የሚከፈላቸው ይሆናል በሚል እንዲብራራ ተደርጓል፡፡
13. አንድ ሠራተኛ በ JEG የተመደበበት ደረጃ በደረጃ እድገት ከሚወዳደርበት የሥራ መደብ ጋር አኩል ደረጃ ያለው ቢሆንም በነባሩ የሥራ ደረጃ ለፕሣ/መፕ/እጥ
የደረጃ ልዩነት እስካለ ድረስ ተወዳድሮ የነባሩን የሥራ ደረጃ ለውጥ ጥቅም ማግኘት ይችላል፡፡ ለምሣሌ፡- በ JEG አንድ ሠራተኛ ባለሙያ IV ደረጃ XIII ቢመደብ
ነገር ግን በነባሩ ይዞት የነበረው የፕሣ የሥራ ደረጃ ፕሣ.7 ቢሆን የደረጃ እድገቱ የወጣው በ JEG ደረጃ XIII ተመሳሳይ ቢሆንና የነባሩ የሥራ ደረጃ ግን ፕሣ.8 ቢሆን
ለፕሣ.8 መወዳደር ይችላል በሚል ተብራርቷል፡፡
14. ካርየር የማያስጠቅም የትምህርት ዝግጅት ኖሯቸው ካርየር በሆነ የስራ መደብ ላይ ተመድበው በመስራት ላይ የሚገኙ ሠራተኞች የትምህርት ዝግጅታቸው
ወደተካተቱባቸው የሥራ መደቦች እንደሚመደቡ ከማድረግ በስተቀር የካርየር ጥቅም መስጠት እንደማይቻል ግንዛቤ ይወሰድ፣
15. በፖለቲካ ፖርቲ ጽ/ቤት ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች የገቢ ግብር ነፃ እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 46/1980 አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 2 የተደነገገ ስለሆነ በፖለቲካ
ፖርቲ ጽ/ቤት ተቀጥረው የሰሩበት የስራ ልምድ አግባብነቱ እየታየ ተግባራዊ እንዲሆን የተወሰነ ስለሆነ በዚሁ አግባብ እንዲፈፀም፡፡
16. በተሻሻለው የምልመላ መረጣ መመሪያ አንቀጽ 2.4 በንዑስ አንቀጽ 2.4.2 የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ በሚጠይቁ የሥራ መደቦች ላይ ውድድር ሲካሄድ
የተመዝጋቢዎች ቁጥር 3 ዐ በላይ ከሆነ ለአንድ የስራ መደብ 3 ዐ አመልካቾች በዕጣ መለየት እንደሚቻልና ለ 2 ተመሳሳይ የሥራ መደብ ለእያንዳዳቸው አስር አስር
በድምሩ 2 ዐ ተመዝጋቢዎችን በዕጣ መለየት እንደሚቻል የተገለፀ ቢሆንም ለአንድ የስራ መደብ 3 ዐ ተፈቅዶ ለሁለት መደቦች ቅጥሩ አነሰ የሚል አስተያየት የቀረበ
በመሆኑ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ መደብ ለእያንዳንዱ አምስት አምስት እየተጨመረ እንዲሰራ ፡፡ ለምሳሌ 3 አንድ አይነት የስም መጠሪያ ያላቸው የስራ መደቦች ቢኖሩን
ለአንዱ የስራ መደብ 3 ዐ የሚለው እንደተጠበቀ ሆኖ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ የስራ መደብ አምስት አምስት በመጨመር በእጣ በመለየት በድምሩ 4 ዐ አመልካቾች
ለፈተና እንዲቀርቡ ይደረጋል በሚል ማስተካከያ የተደረገ መሆኑን፡፡
17. ለስልጠና ውድድር ለብሄረሰብ 5 ነጥብ የሚሰጠው ሰራተኛው ሲቀጠር በህይወት ታሪኩ ፎርም ላይ በሞላው መሠረት ተፈፃሚ እንደሚደረግ ግንዛቤ ይወሰድ፡፡
18. ማንኛውም የካርየር ተጠቃሚ ባለሙያም ሆነ ቡድን መሪ ወይም ዳይሬክተር በወረዳ ጽ/ቤት ፣ በዞን መምሪያና በክልል መ/ቤቶች ላይ ባሉ የካርየር መደቦች ላይ
በየሙያ ዘርፉ የያዘውን የካርየር ደረጃና ደመወዝ እንደያዘ ተወዳድሮ መዛወር እንደሚችል ግንዛቤ ይወሰድ ፣ ለምሳሌ፡- ቀበሌ ላይ የሚሰራ አንድ የእንስሳት ጤና
ባለሙያ የያዘውን የካርየር ደረጃና ደመወዝ እንደያዘ ወረዳ እንስሳት ጽ/ቤት ባለ የካርየር የስራ መደብ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን እስካሟላ ድረስ መዛወር ይችላል፡፡
19. . ለረዥም ጊዜ ስልጠና የተላከ ሰራተኛ ለጡረታ ካልሆነ በስተቀር ት/ቤት የቆየበት ጊዜ በማንኛውም ስምሪት ላይ እንደ ስራ ልምድ አይያዝም ፡፡ ት/ቤት ባለበት
ጊዜም ከሀገራዊ ጭማሪ በስተቀር ሌሎች ጥቅማ ጥቅም መጠየቅ መብት አይኖረውም ፡፡ ሆኖም በመንግስት ድጋፍ 2 ኛ ዲግሪያቸውን ከዩኒቨርስቲ ውጭ ሆነው
ለሚመሩ ሠራተኞች የተፈቀደው የምግብና የመኝታ አገልግሎት ክፍያ እንዲሁም ለ 3 ኛ ዲግሪ ተማሪዎች የተፈቀደው ጥቅማጥቅም ግን የሚሰጥ ይሆናል፡፡
20. ከርዕሰ መምህርነት/ሱፐርቫይዘርነት/ተነስተው ወደ ሹመት የገቡ አመራሮች የሚከፈላቸው ደመወዝ የሹመቱ ደመወዝ ብቻ ይሆናል፡፡
21. የኮሌጆች ዲን፣ ም/ዲን እና የሆስፒታል ስራ አስኪያጆች ከኃላፊነት ሲወርዱ አመዳደባቸው በተሿሚዎች አመዳደብ መመሪያ ይሆናል፡፡
22. የአይሲቲ ባለሙያዎች የዕድገት መሰላል በተመለከተ በየትምህርት ደረጃና በየአስተዳደር እርከኑ ከተቀመጠው ጣሪያ በላይ ማደግ አይችሉም፡፡ ለምሣሌ በወረዳ
ከደረጃ 8 በላይ በዞን ከደረጃ 9 በላይ ማደግ አይችሉም፡፡
23. የጤና ባለሙያዎች መነሻና ማብቂያ ጣሪያቸው ባለመታወቁ በአሰራር ላይ ከፍተኛ ችግር እያጋጠመ እንደሆነ በተለያየ ጊዜ ከሚቀርቡ ጥያቄዎች ተረድተናል ፡፡
ስለዚህ
ተ/ቁ የፓናል መነሻደረጃ ጣሪያ ምርመራ
1 መፕ 3/2 መፕ 7/2
2 መፕ 4/2 መፕ 8/2
3 መፕ 6/2 መፕ 10/2
4 መፕ 7/2 መፕ 11/2
5 መፕ 8/2 መፕ 12/2
6 ፕሳ 1/1 ፕሳ 7/1
7 ፕሳ 2/1 ፕሳ 8/1
8 ፕሳ 4/1 ፕሳ 8/1
ማሳሰቢያ፡-
 እንደ ሙያ አይነታቸዉ የትምህርት ደረጃቸዉ ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ ያሻሻሉ ባለሙያዎች ዲግሪ ይዘዉ ከተቀጠሩ ጤና ባለሙያዎች ጣሪያ ጋር እኩል ይሆናል፡፡
 የፓናል መነሻ ማለት ትምህርቱን አሻሽሎ እንደመጣ የተሰጠዉ የፓናል ደረጃ ዉሳኔ መነሻ ደመወዝ ነዉ፡፡
ማሻሻያዎች
24. በተሻሻለው የምልመላና መረጣ አፈፃፀም መመሪያ በአንቀጽ 3.7 ንዑስ አንቀጽ 3.7.1 የውጭ ዝውውር ማወዳደሪያ መስፈርቶች ተደርገው የተቀመጡት በአሰራር
ላይ ችግር እያስከተሉ በመሆኑ ማስተካከያ እንዲደረግባቸው ጥያቄ ቀርቧል በዚሁ መሰረት ፣
ሀ. ክፍት የስራ መደቡ የተግባር ፈተና የሚጠይቅ ከሆነ
1. የውጤት ተኮር 4 ዐ%
2. የማህደር ጥራት 5%
3. የተግባር ፈተና 4 ዐ%
4. የጽሁፍ ፈተና 15%
ለ. ክፍት የሥራ መደቡ የተግባር ፈተና የማይጠይቅ ከሆነ
1. የውጤት ተኮር 4 ዐ%
2. የማህደር ጥራት 5%
3. የጽሁፍ ፈተና 55% ሆኖ የተስተካከለ መሆኑ
25. በተሻሻለው የምልመላና መረጣ መመሪያ አንቀጽ 2.4 በንዑስ አንቀጽ 2.4.4 የተገለፀው በአንድ የተግባር ፈተና በሚጠይቅ የሥራ መደብ ላይ በወጣ የቅጥር
ማስታወቂያ የተመዘገቡ በክብር የተመለሱ የሰራዊት አባላት ቁጥር 1 ዐ እና በላይ ከሆነ በክብር የተመለሱ የሰራዊት አባላት እርስ በርሳቸው ዕጣ እንዲያወጡ በማድረግ
5 ዕጩዎች በእጣ የሚለዩ ሲሆን ሌሎች ተመዝጋብዎች ካሉ እንደዚሁ እርስ በርሳቸው እጣ እንዲያወጡ በማድረግ 5 እጩዎች እጣ በማስወጣት በድምሩ 1 ዐ
ዕጩዎች ለፈተና እንዲቀርቡ ይደረጋል በሚል ማስተካከያ ተደርጓል ፡፡ ይኸው የተግባር ፈተና ለማይጠይቁ የሥራ መደቦችም ቅጥር ሲፈፀም ግማሹ ድርሻ /50%/
ለክብር ለተመለሱ የሰራዊት አባላት ግማሽ ድርሻ /50%/ ደግሞ ለሌሎች ተወዳዳሪዎች የሚተው ይሆናል በሚል ማሻሻያ ተደርጐበታል፡፡
26. በአንድ የቅጥር ማስታወቂያ ተወዳድሮ በተጠባባቂነት የተመዘገበ ዕጩ የተወዳደረበት የሥራ መደብ ደረጃው ቢያድግ የስራ መደቡ መጠሪያ እስካልተቀየረ ድረስ
ተጠባባቂው ያደገውን የስራ ደረጃና ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ እስኳሟላ ድረስ የተጠባባቂ ጥሪ ተደርጐ ሊቀጠር ይችላል፡፡ሆኖም ማስረጃው በውድድሩ ጊዜ የቀረበ
መሆን አለበት፡፡ ተጠባባቂው የስራ መደቡን የማያሟላ ከሆነ ጥሪ አይደረግለትም፡፡
27. በአንድ የቅጥር ማስታወቂያ ተወዳድሮ የተቀጠረ በሙከራ ላይ እያለም ሆነ ቋሚ ሰራተኛ ከሆነ በኋላ የሥራ መደብ ደረጃው ቢያድግ የስራ መደቡ መጠሪያ
እስካልተቀየረ ድረስ የሥራ ደረጃውን ተፈላጊ ችሎታ የሚያሟላ ከሆነ ያደገውን ደረጃ ጥቅም ይሰጠዋል፡፡ሆኖም ማስረጃው በውድድሩ ጊዜ የቀረበ መሆን አለበት፡፡
የተቀጠረው ባለሙያ የተሻሻለውን ደረጃ ተፈላጊ ችሎታ የማያሟላ ከሆነና በአንድ አመት ውስጥ የስራ ደረጃውን ተፈላጊ ችሎታ የሚያሟላ ከሆነ በተጠባባቂነት
ተመድቦ የስራ መደቡን ደረጃ ጥቅም ያለውድድር በሚያሟላበት ጊዜ የሚያገኘው ይሆናል ፡፡ በአንድ አመት ውስጥ የማያሟላ ከሆነ ግን በታሳቢ እንዲመደቡ ተደርጎ
የስራ ደረጃውን ጥቅም የሚያገኘው በደረጃ እድገት ከሌሎች ሰራተኞች ጋር ተወዳድሮ ሲያሸንፍ ብቻ ይሆናል፡፡
28. በተሻሻለው ምልመላና መረጣ መመሪያ የሰው ሃብት አስተዳደር ወይም የሰው ሃይል አስተዳደር ሠራተኞች በውስጥ ዝውውርና በደረጃ እድገት ሊወዳደሩ
የሚችሉበት ሁኔታ በአንቀጽ 3.6 ንዑስ አንቀጽ 3.6.9 እና በአንቀጽ 4.5 ንዑስ አንቀጽ 4.5.16 ላይ የተመላከተ ቢሆንም አነስተኛ ከተማ አስተዳደሮች ላይ የሰው ሃይል
አስተዳደር ሠራተኛ የሥራ መደብ የተፈቀደው ገንዘብ እና ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ላይ በመሆኑ ሲቪል ሰርቪስ ላይ መወዳደር እንዳይችሉ ያደረጋቸው
በመሆኑ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤቶች ላይ እንዲወዳደሩ ግንዛቤ ተይዞበት በዚሁ አግባብ እንዲፈፀም ማስተካከያ ተደርጓል፡፡
29. በተሻሻለው ምልመላና መረጣ መመሪያ በአንቀጽ 3.7 ንዑስ አንቀጽ 3.7.21 የተሿሚ የትዳር አጋር የሆነ/የሆነች ባለቤቱ/ባለቤቷ በወረዳው በሚገኙ ቀበሌዎች
የሚሰራ/የምትሠራ ከሆነ ለተሿሚ የትዳር አጋር የቅድሚያ እድል እንደማይሰጥ የተመላከተ ቢሆንም አመራሩ የተሰጠውን ተልእኮ በብቃት መወጣት እንዳይችል ያደረገ
በመሆኑ ከቀበሌ ወደ ወረዳ ተዛውረው መመደብ እንዲችሉ የተፈቀደ ሲሆን ቁጥራቸው ከአንድ በላይ በሚሆንበት ጊዜ ግን በውጭ ዝውውር መስፈርት መሠረት እርስ
በርሳቸው ተወዳድረው አሸናፊው ቅድሚያ የሚሰጠው ይሆናል፡፡ ከተሿሚ የትዳር አጋር ውጭ የሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች በጤና ችግር ምክንያት ባሉበት ቀበሌ
መስራት እንደማይችሉ በ 3 ሐኪሞች የተረጋገጠ የህክምና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉም ካሉ ከቀበሌ ወደ ወረዳ መዛወረ እንዲችሉ የተፈቀደ መሆኑ ታውቆ በዚሁ
አግባብ እንዲፈጸም ፡፡
30. በተሻሻለው ምልመላና መረጣ መመሪያ በአንቀጽ 4.5 ንዑስ አንቀጽ 4.5.12 የሜትሮፖሊታን ከተሞች፣ የዞንና የማዕከላት ሠራተኞች በክልል ደረጃ በሚገኘው
እናት መ/ቤታቸው መወዳደር እንደሚችሉ የተገለፀ ቢሆንም የወረዳ፣ የአነስተኛ ከተማና የመካከለኛ ከተማ አስተዳደር ሠራተኞች ግን ወደ ክልል እናት መ/ቤታቸው
ሳይሆን ወደ ዞን እናት መ/ቤታቸው እንደሚወዳደሩ ተገልጿል፡፡ ይሁን እንጅ የክልል እናት መ/ቤቶች የወረዳ ወይም የመካከለኛ ከተማ ወይም የአነስተኛ ከተማ
አስተዳደር ሠራተኞችን በደረጃ እድገት እንዲሳተፉላቸው የሚፈልጉ ከሆነ ፕሣ.7 እና ከዚያ በላይ በሆኑ የሥራ ደረጃዎች ላይ ማሣተፍ እንዲችሉ ማስተካከያ
ተደርጓል፡፡ ማሳተፍ ከፈለጉ ማስታወቂያው በአየር ላይ የሚውልበት ጊዜ ለ 15 የስራ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
31. በተሻሻለው የምልመላና መረጣ መመሪያ የሾፌር ቅጥር፣ የደረጃ ዕድገትና የውጭ ዝውውር ሲፈጸም አሸናፊው የሚለይበት መንገድ በአንቀጽ 2.7 ንዑስ አንቀጽ
2.7.1 ቁጥር 2.7.1.2 እና በአንቀጽ 3.7 ንዑስ አንቀጽ 3.7.1 ፊደል ተራ ሐ ላይ ተመላክቷል፡፡ ይሁን እንጅ በእነዚህ ንዑስ አንቀጾች ላይ ቀጣሪ ወይም ዝውውር
እንዲፈፀምላቸው የሚፈልጉ መ/ቤቶች በራሣቸው መንገድ ፈተና መስጠት እንደሚችሉ የተገለጸ ቢሆንም ይህ አሰራር ለአድሎአዊ አሠራር በር የሚከፍት ሆኖ የተገኘ
በመሆኑ ከመንገድና ትራንስፖርት ወይም ከቴክኒክ ሙያ ኮሌጆች በስተቀር ፈተና መስጠት አይቻልም በሚል ማስተካከያ ተደርጐበታል፡፡ ሆኖም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
በሌለባቸው ወረዳዎችና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ያለባቸው ወረዳዎች ሆነው ፈተናውን የመስጠት ፈቃድ የሌላቸው በሆኑ ወረዳዎች ውስጥ በአቅራቢያ ወደሚገኘው
የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ወይም ለዞን ሲቪል ሰርቪስ ውክልና በመስጠት ስምሪቱ ተፈጽሞ እንዲላክላቸው ማድረግ የሚቻል መሆኑ፣
32. በተሻሻለው የምልመላ መረጣ መመሪያ በትምህርት ቤትና በጤና ጣቢያ ላይ የሚሰሩ የድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች በውስጥ ዝውውር ሊወዳደሩ የሚችሉበት አግባብ
በአንቀጽ 3.6 ንዑስ አንቀጽ 3.6.5 የተመላከተ ቢሆንም ወደ እናት መ/ቤታቸው ብቻ በውስጥ ዝውውር እንዲወዳደሩ መደረጉ ከዚህ ቀደም በ 2007 ዓ.ም በነበረው
የምልመላ መረጣ መመሪያ ከጤና ጣቢያ ወደ ሌላ ጤና ጣቢያ ከት/ቤት ወደ ሌላ ት/ቤት በውስጥ ዝውውርና በደረጃ እድገት እንዲወዳደሩ የተፈቀደውን ሁኔታ ያስቀረ
በመሆኑ እነዚሁ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ከት/ቤት ወደ ሌላ ት/ቤት ፣ ከጤና ጣቢያ ወደ ሌላ ጤና ጣቢያ በውስጥ ዝውውርና በደረጃ እድገት እንዲወዳደሩ በሚል
ማሻሻያ ተደርጓል፡፡
33. በተሻሻለው ምልመላና መረጣ መመሪያ በአንቀጽ 5.1 ንዑስ አንቀጽ 5.1.4 አንድን የስራ መደብ በቅጥር፣ በዝውውርና በደረጃ እድገት በሰው ሃይል ለማሟላት
የወጡ የስምሪት ማስታወቂያዎች አየር ላይ ከዋሉ በኋላ መሰረዝ አይቻልም በሚል ተገልጿል፡፡ ይሁን እንጅ ስምሪቱ አየር ላይ ከዋለ በኋላ ከአመራርነት የተነሳና ምደባ
የሚሰጠው ፣ በተለያየ ምክንያት ሊመደቡበት የሚችሉበት ክፍት የሥራ መደብ ባለመኖሩ በጊዜያዊነት የተመደቡ ሠራተኞች፣ ትምህርቱን አጠናቆ ሊመደብ የሚገባው
ሠራተኛ ሲኖር ፣ የስምሪት ማስታወቂያ የወጣበት የሥራ ደረጃ ደረጃው ሲሻሻልና ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ የፈተና ጊዜው ከአንድ ወር በላይ የተራዘመ ከሆነ
ስምሪቱን የጠየቀው መ/ቤት ኃላፊም ይህንኑ ሲያረጋግጥ ስምሪቱ ሊሰረዝ ይችላል በሚል ማስተካከያ ተደርጐበታል፡፡
34. በተሻሻለው ምልመላና መረጣ መመሪያ በአንቀጽ 5.1 ንዑስ አንቀጽ 5.1.5 ከተገለፀዉ በተጨማሪ በነጥብ ምዘና ዘዴ በተዘጋጀው ፎርም ቁጥር 14 ላይ የትምህርት
አይነትም መጠቀም የሚቻል መሆኑ ፣
35. በሳተላይት ከተሞች ባሉ ተቋማት የሚሰሩ ባለሙያዎች ደረጃ ዕድገትና የውስጥ ዝውውር በተመለከተ ወደ ሜትሮ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር እናት መ/ቤታቸው
መወዳደር እንዲችሉ የተፈቀደ መሆኑን ፣
36. ጥበቃና አትክልተኛ የስራ መደብ ላይ ስምሪት ለመፈፀም በ JEG በተዘጋጀው ተፈላጊ ችሎታ መሰረት የውትድርና ስልጠና የወሰደ የሚል ቢሆንም የውትድርና
ስልጠና የወሰዱ ስራ ፈላጊዎች በማይገኙበት ጊዜ የውትድርና ስልጠና የሌላቸውን ተወዳዳሪዎች የሚጠየቀውን የትምህርት ደረጃ ማሟላታቸውን በማረጋገጥ አወዳድሮ
መቅጠር ይቻላል፡፡ ከቅጥር በኋላም ለሥራው የሚያስፈልገው ስልጠና እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡
37. ከአመራርነት የሚወርዱ ተሿሚዎች የስራ ልምድ ልዩ ሙያ ከሚጠይቁ የስራ መደቦች በስተቀር አግባብ ሆኖ ይያዝላቸዋል ከሚለው በተጨማሪ የሙያ መ/ቤቱን
ሲመሩ የቆዩና ሙያው የሚጠይቀው የት/ዝግጅት ካላቸው የስራ ልምዳቸው አግባብ ሆኖ ይያዝላቸዋል ፡፡ ለምሳሌ አንድ አካውንቲንግ የትምህርት ዝግጅት ያለው
ተሿሚ የፋይናንስ ተቋማትን ሲመራ ቆይቶ ከኃላፊነት ቢነሳ የት/ዝግጅቱ ለስራ መደቡ እስከተካተተ ድረስ አግባብ ሆኖ እንዲያዝ ይደረጋል በሚል ማስተካከያ
ተደርጓል፡፡
39. የምህንድስና ባለሙያዎችን በተመለከተ መጋቢት 2001 ዓ.ም በወጣው መመሪያ በአንቀጽ 5 በንዑስ አንቀጽ 5.2 በምህንድስና፣ በከተማ ፕላንና በቅየሳ ሙያ
እየሰሩ ያሉ ባለሙያዎች ስራ ላይ እያሉም ሆነ ከስራ ውጭ ሆነው የትምህርት ደረጃቸውን አሻሽለው ሲገኙ ትምህርታቸውን ከማሻሻላቸው በፊት ከያዙት የሥራ ደረጃ
በአንድ ደረጃ ከፍ ብለው እንደሚመደቡ የተገለፀ ቢሆንም ይኸው እድል ለሌሎች የእድገት መሰላል ተጠቃሚዎች ያልተሰጠ በመሆኑ በመንግስት ድጋፍ ከሥራ ውጭ
ሆነው የትምህርት ደረጃቸውን ላሻሻሉ የምህንድስና ባለሙያዎች ብቻ በአንድ ደረጃ ከፍ ብለው እንዲመደቡ ይደረጋል በሚል እንዲስተካከል ተደርጓል፡፡
39. ከመፕ.7 በታች የሆኑ ሠራተኞች በሥራ ደረጃ ማሻሻያው አንድ እርከንና በላይም ጥቅም ያገኙ ለሌላ የደረጃ እድገት፣ ስራቸውን ሳይለቁ እና በሥራ ላይ በአዲስ
ለመቀጠር የአንድ ዓመት ቆይታ ሳይጠበቅባቸው ሊወዳደሩ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም በተሻሻለው ምልመላ መረጣ መመሪያ ክፍል ሁለት አንቀጽ 2.8 ንዑስ አንቀጽ
2.8.5 ከተገለፀው በተጨማሪ በስራ ላይ እያሉም ዲግሪና በላይ ትምህርት ዝግጅታቸውን ያሻሻሉ ሲኖሩ ያሻሻሉትን የትምህርት ደረጃ መነሻ ደመወዝ ካልደረሱ
በትምህርት ደረጃቸው መነሻ በሚወጡ የቅጥር ማስታወቂያዎች አንድ ዓመት መቆየት ሳይጠበቅባቸው መወዳደር እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡
40. የገጠር ቀበሌ ስራ አስኪያጆች ማንኛውም ስምሪት እንደሌሎች ሲቪል ሰረቫንት በዞንና በወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ብቻ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
41. በተሻሻለው ምልመላና መረጣ መመሪያ ዝውውር ሲፈፀም የዝውውር ቅድሚያ እድል የሚሰጣቸውን ሠራተኞች በተመለከተ አንቀጽ 3.7 ከንዑስ አንቀጽ 3.7.6
እስከ ንዑስ አንቀጽ 3.7.10 ተመላክቷል፡፡ ይሁን እንጅ ዝውውሩ በሚፈፀምበት ጊዜ በማወዳደሪያ መስፈርቶች መሠረት ውድድር ተካሂዶ አሸናፊው እንደሚለይ
ተደርጐ የተወሰደ በመሆኑ በዚሁ ላይ ማብራሪያ መስጠት አስፈልጓል፡፡ ስለሆነም የቅድሚያ እድል የተሰጣቸው ሠራተኞች ከሌሎች የቅድሚያ እድል ካልተሰጣቸው
ሠራተኞች ጋር ለዝውውር ውድድር ሲቀርቡ ያለውድድር በቀጥታ የሚዛወሩ ይሆናል፡፡ ሆኖም የቅድሚያ እድል ተጠቃሚዎች ቁጥራቸው ከአንድ በላይ በሚሆንበት
ጊዜ እርስ በርሳቸው እንዲወዳደሩ ይደረጋል፡፡
42. የቀበሌ ልማት ጣቢያ ባለሙያዎች ወደ ጽ/ቤት ዝውውር በተመለከተ ከ JEG በፊት በነበረው የሥራ ደረጃ በተፈቀደው የመዛወሪያ አቻ ደረጃ እንዲዛወሩ
ተፈቅዷል፡፡
43. ከትምህርት ደረጃው መነሻ ደመወዝ በታች በሚያስከፍል የሲቪል ሰርቪስ ስራ መደብ ላይ የሚሰራ ባለሙያ አግባብ ያለው የትምህርት ዝግጅት ካለው የትምህርት
ደረጃውን መነሻ ደመወዝ በሚያስከፍል የካርየር ስራ መደብ ላይ በደረጃ እድገት ሊወዳደር ይችላል፡፡ በተጨማሪም ካርየር ተጠቃሚ ባልሆኑ የሥራ መደቦች ላይ
እየሰሩ ያሉ የካርየር መነሻውን ያላለፉ ከሆነ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን አሟልተው እስከተገኙ ድረስ ወደ ካርየር መነሻ በደረጃ እድገት መወዳደር ይችላሉ፡፡ ለአብነት
ተለላኪ/ዘበኛና አትክልተኛ የሆነ ሹፌር፣ አይሲቲ ወ.ዘ.ተ/ የስራ መደቦች ላይ ለመደቡ የሚጠይቀዉን ተፈላጊ ችሎታ አሟልተዉ እስከተገኙ ድረስ በነሻዉ ላይ በደረጃ
እድገት ሊወዳደሩ ይችላሉ፡፡
44. ትምህርታቸውን በግላቸው የሚያሻሽሉ የጤና ባለሙያዎች ባልተሻሻለው ወይም ቀድሞ በነበረው የትምህርት ደረጃቸው የካርየር እድገት ካገኙ በኋላ የአንድ ዓመት
ቆይታ ሣይጠበቅባቸው ያሻሻሉት የትምህርት ደረጃ የተሰጣቸውን የፖናል ደረጃ መነሻ ካልደረሱበት ወይም ካላላፉት በደረጃ እድገት መወዳደር እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡
በተጨማሪም በግላቸዉ የትም/ት ደረጃዉን ያሻሻሉ የጤና ባለሙያዎች በተሰጣቸዉ የፓናል ደረጃ መሰረት ከመንግስት ጤና ተቋማትም ሆነ መንግስታዊ ካልሆኑ ጤና
ተቋማት ሲሰሩ የነበሩ ለቀዉ በቅጥር መወዳደር ይችላሉ፡፡
45. በቀድሞ 5 በአዲሱ 4 ዓመት የተመረቁ የምህንድስና፣ የህግና የመሬት አስተዳድር ባለሙያዎች ከፕሳ-1 የስራ መደቦች በላይ ሲቀጠሩ የፕሳ-2 መነሻ ደመወዝ
የሚከፈላቸዉ ሲሆን ፕሳ-1 ላይ የተቀጠሩት የፕሳ-1 መነሻ ደመወዝ ብቻ የሚከፈላቸዉ ይሆናል፡፡
46. ከሀምሌ 1/2008 ዓ.ም በኋላ የብቃት ማረጋገጫ ያቀረቡ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የደረጃ እድገት ማግኛ ጊዜያቸዉ የሚሰላዉ የብቃት ማረጋገጫ
ማስረጃዉን ካቀረቡበት ጊዜ ጀምሮ ይሆናል፡፡
47. በእጥ-4 የስራ መደብ በመንግስት መ/ቤት የባጃጅ ሹፌር ሁነዉ ተቀጥረዉም ሆነ ተመድበዉ እየሰሩ ያሉ የመንግስት ባጃጅ አሽከርካሪዎች ከደመወዝ ማሳያ
ሰንጠረዝ ላይ በተቀመጠዉ መሰረት እንደሌሎቱ ሹፌሮች የደረጃ እድገት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተፈቀደ መሆኑን
ማስተካከያ
48. በተሻሻለው ምልመላና መረጣ መመሪያ አንቀጽ 3.7 በንዑስ አንቀጽ 3.7.7 ላይ ከላይ በንዑስ አንቀጽ 3.7.5 ተብሎ የተገለፀው 3.7.6 በሚል የተስተካከለ መሆኑን
49. በተሻሻለው ምልመላና መረጣ መመሪያ አንቀጽ 3.8 ላይ ከንዑስ አንቀጽ 3.8.2 እስከ 3.8.7 በሚል የተገለፀው ከንዑስ አንቀጽ 3.8.1 እስከ 3.8.6 በሚል
እንዲስተካከል የተደረገ መሆኑን፣
50. በተሻሻለው ምልመላና መረጣ መመሪያ በአንቀጽ 3.6 ንዑስ አንቀጽ 3.6.2 ማሰሪያ አንቀጽ የለውም ለተባለው በተመሳሳይ የሥራ ደረጃና ደመወዝ ዝውውር
መፈፀም ይቻላል በሚል የተጠቃለለ መሆኑን፡፡
51. በተሻሻለው ምልመላና መረጣ መመሪያ አንቀጽ 3.6 ንዑስ አንቀጽ 3.6.12 ላይ ከንዑስ አንቀፅ 3.7.5 እስከ 3.7.9 የተባለዉ ከንዑስ አንቀፅ 3.7.6 እስከ 3.7.10
በሚል የተስተካከለ መሆኑን
ሽመልስ የኔሰዉ ገ/ማርያም
የሰዉ ኃብት ህጎች ማሻሻያና አቅም ግንባት ዳይሬክተር
ባ/ዳር ግንቦት 14/2011

You might also like