You are on page 1of 4

የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ


I. አጠቃላይ መግለጫ
የመስሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
የሒሳብ ሠራተኛ III

የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ


IX 02 02 03

መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ

II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት


2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-
 የመ/ቤቱን ለውስጥም ሆነ ለውጭ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ባግባቡና በተቀላጠፈ ሁኔታ ተመቻችተው
እንዲፈጸሙና የተቀላጠፈ የክፍያ ሥርዓት እንዲኖር ለማድረግ ድጋፍ በመስጠት የሥራ ክፍሉን ዓላማ ማሳካት ነው፡፡
2.2.ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
ውጤት 1፡ የሒሳብ መረጃዎችን መዝግቦ መያዝ
 በጥሬ ገንዘብ የተከፈለባቸውን ሠነዶች በመረከበ የሳጥን ሂሳብ እንዲተካ ያደርጋል
 የመደበኛና ዕርዳታ ሒሳቦችን ለይቶ በማጣራት ክፍያዎችን በየወጭ ርዕሳቸው ለይቶ ወደ መረጃ ቋት ያስገባል
 የዕርዳታ ሂሳቦችን በተለየ አካውንት ይመዘግባል፣ እንደየዕርዳታ ሰጭዎች ፍላጎትም ሪፖርት አዘጋጅቶ ያስተላልፋል፣
 ለጡረታ መብት ማስከበር የሚያስችል ዝርዘር መረጃ ያዘጋጃል፣ ለሰው ሀብት ልማት የሥራ ሂደት ያስተላልፋል፣
ውጤት 2፡ የክፍያ ማዘዣ ሠነድ ማዘጋጀት
 በጥሬ ገንዘብ ለሚፈፀሙ ወጭዎች፣ የውሎ አበሎችና ሌሎች የክፍያ ጥያቄዎች ሠነዱን በማጣራት የቅድመ-ክፍያ
/SPV/ ያዘጋጃል፣ ክፍያ ለተፈፀመባቸው አስፈላጊውን የወጭ አርዕስት በመስጠት የክፍያ ማመሰካሪያ ያዘጋጃል፣
 የመብራት፣ የውኃ፣ የሥልክና የኢንተርኔት እና ሌሎች ክፍያ ጥያቄዎችን አጣርቶ የክፍያ ማዘዣ ያዘጋጃል
 ከተለያዩ አገልግሎቶች ለሚሰበሰቡ ገቢዎች የገቢ ደረሰኝ ያዘጋጃል፣ ለሚመለከተው ያስተላልፋል፣
 ስለሚሰበሰቡና በእንጥልጥል ላይ ስለሚገኙ የተለያዩ ክፍያዎች ዝርዝር ያዘጋጃል፣
 ልዩ ልዩ የፈሰስ ሂሳቦችን ለሚመለከተው አካል ገቢ እንዲሆን ያደርጋል፣
 ያልተወራረዱ ልዩ ልዩ ተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦችን በአመተ ምህረት ለይቶ በማጠናቀር እንዲወራረዱ ሪፖርት
ያደርጋል ፣
 ለልዩ ልዩ ገቢዎች፣ ከወጪ ተመላሽ ፣ለአደራ ሂሣቦች የገቢ ደረሰኝ ያዘጋጃል፣
 የተመዘገቡትን የሂሣብ ሠነዶች በመለየት በቅደም ተከተል እንዲደራጅ ድጋፍ ያደርጋል፣ በስራ ላይ ያሉ ደረሰኞችን ማመዛዘኛ
ያዘጋጃል፣
ውጤት 3፡ የተመዘገበን ሂሳብ ማስታረቅ፣ ማስተካከያ መስራትና ሪፖርት ማዘጋጀት
 ተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦችን ያጣራል፣ ልዩነት ካለው በማስታረቅ ማስተካከያ /Adjustment/ ይሠራል

1
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

 የተመዘገበውን ሒሳብ ከሠነዱ ጋር በማናበብ ዕርማት ካለው ምዝገባውን ያስተካክላል፡፡


 የወሩን የባንክ ሂሳብ ከባንክ መግለጫ ጋር ያስታርቃል፣ ያልተሰበሰቡ የባንክ አድቫይሶች እንዲሰበሰቡ ዝርዝሩን
ያሰታውቃል፡፡
 የተከፈለ ቼክ ተመላሽ ሲሆን ማስተካከያ ይሠራል፡፡
 የኮንፈርሜሽን ደብዳቤ ባንክ ያደርሳል፣ የባንክ አድቫይሶችንና ስቴትሜንቶችን ከባንክ ያመጣል፣ ለሚመለከተው
ያስተላልፋል
 ቼክ ከማለቁ በፊት የሚመለከተውን ኃላፊ አስፈርሞ ከባንክ ያወጣል፣
 ሂሳቦችን በጋራ ይዘጋል፣ ለቀጣዩ የበጀት ዓመት መነሻ ሂሳብ ያዘጋጃል፡
 የሂሳብ ሰነዶችንና መዛግብቶች ለውስጥና ለውጭ ኦዲተሮች ለምርመራ ያቀርባል፣
III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች
3.1 የሥራ ውስብስብነት
 ስራው ተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦችን ማጣራት፣ የወሩን የባንክ ሂሳብ ከባንክ መግለጫ ጋር ማስታረቅ፣ የተከፈለ ቼክ
ተመላሽ ሲሆን ማስተካከያ መስራት፣ክፍያዎችን በየወጭ ርዕሳቸው ለይቶ ወደ መረጃ ቋት ማስገባት፣ ለጡረታ መብት
ማስከበር የሚያስችል ዝርዘር መረጃ ማዘጋጀት፣ የክፍያ ማዘዣ ሠነድ ማዘጋጀት ነው፡፡የተመዘገበ መረጃ መፋለስ፣
ወቅታዊ መረጃ አለመገኘት የሚያጋጥም ችግር ሲሆን ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች መረጃዎችን በመጠቀምና
በማመሰካር ማከናወንን ይጠቃይል፡፡
3.2 ራስን ችሎ መስራት
3.2.1 ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 ሥራው በደንብና መመሪያ መሠረት የሚከናወን ነው፡፡
3.2.2 ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ
 በተሰጠ መመሪያ መሰረት የጥራት ደረጃውን ጠብቆ ስለመከናወኑ በቅርብ ኃላፊ ክትትል ይደረግበታል፣
3.3 ተጠያቂነት
3.3.1 ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት /Responsibility for Impact/፣
 ሥራው በተገቢው መንገድ ባይከናወን የተገልጋይ/ ደንበኞችን መጉላላት ያስከትላል፣ በመሥሪያቤቱ የሥራ ክፍሎችን
ሥራ ያስተጓጉላል፡፡
3.3.2 ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣
 ምስጢራዊ መረጃ የለውም
3.4 ፈጠራ
 ከተገልጋዩ ፍላጎት አኳያ በተቀላጠፈ አግልግሎት አሰጣጥ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ የክፍያ እና የገቢ ማሰባሰቢያ
ፎርማት እንዲሻሻሉ አዳዲስ ሀሳቦችን ማቅረብን ይጠይቃል
3.5. የሥራ ግንኙነት /Work Communication/
3.5.1 የግንኙነት ደረጃ

2
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

 ከውጭ፡- ከባንኮች፣ ከተገልጋይ


 ከውስጥ፡- ከቅርብ የስራ ኃላፊ፣ ከውስጥ ሠራተኞችና ከተለያዩ የስራ ክፍሎች
3.5.2 የግንኙነቱ ዓላማ
 ከውጭ፡- ከባንክ ለኮንፎርሜሽን፣ ለአድቫይስ እና ስቴትሜንት ለማምጣትና ለመስጠት፣ ለቼክ ግዥ፣ባላንስ
ለመጠየቅ፣ ከውጭ ተገልጋይ ክፍያ ሠነድ ለማዘጋጀት፣
 ከውስጥ የተለያዩ ክፍያ ሠነዶችንና ለሥራ ሚረዱ መረጃዎችን ለመለዋወጥ
3.5.3 የግንኙነቱ ድግግሞሽ
 ከውጭ ወቅታዊ
 ከውስጥ በየዕለቱ፣ እንዳስፈላጊነቱ ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች በጊዜው መረጃ ሲፈለግ 50 ከመቶ ያህል ይሆናል
3.6 ኃላፊነት
3.6.1 ኃላፊነት ለሰው ሀብት
3.6.1.1 በኃላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት
 የለበትም፡፡

3.6.1.2 የኃላፊነት አይነትና ደረጃ


 የለበትም፡፡
3.6.2 ኃላፊነት ለንዋይ
 የለበትም፡፡
3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት
 ኮምፕዩትር፣ ጠረጴዛ፣ ሸልፍ፣ የሂሳብ ማሽን፣ በድምሩ 50000 የሚደርስ ንብረት ኃላፊነት አለበት፡፡
3.7. ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት
 የተለያዩ የሂሳብ ሰሌቶችን መሥራት፣ የስሌት ስሕተቶችን ማጥራት፣ የተቀናናሽ ሂሳቦችን መስራት የሚጠይቅ ሲሆን
ከሥራ ጊዜው 55% ያህል ይሆናል፡፡
3.7.2.ስነ-ልቦናዊ ጥረት
 ሥራው ከተገልጋይ ፍላጎት ጋር ቀጥታ የሚገናኝ በመሆኑ በተለያዩ አስተዳደራዊና ቴክኒካዊ ችግሮችንና የክፍያ ሠነድ
ዝግጅት ሲጓተት ከተገልጋይ የሚደርሱ የሥነ-ልቦና ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ መሥራትን ይጠይቃል፡፡፡
3.7.3 የዕይታ ጥረት፣
 የክፍያ ሠነዶችን ለረጅም ሠዓት መናበብ፣የክፍያ መረጃዎችን ለቅሞ ወደ መረጃ ቋት ማስገባት 40% ያህል

ይሆናል
3.7.4 የአካል ጥረት
 ሥራው መቀመጥ ከ 90% በመቶ በላይ በመቀመጥ የሚከናወን ነው፡፡
3.8. የሥራ ሁኔታ

3
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

3.8.1. ሥጋትና አደጋ


 ሥራው ስጋትና አደጋ የለበትም፡፡
3.8.2. የሥራ አካባቢ ሁኔታ
 ሥራው በምቹ የሥራ አካባቢ የሚከናወን ነው፡፡
3.9. እውቀትና ክህሎት፣
3.9.1. ትምህርት
የትምህርት ደረጃ የትምህርት ዓይነት
ዲፕሎማ የሂሳብ መዝገብ አያያዘ

3.9.2 ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ


የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት

4 ዓመት በተያያዥ ሙያ

የሥራ ትንተና ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን

You might also like