You are on page 1of 4

የየፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒስቴር የስራ ዝርዝር መግለጫ ቅፅ

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ


I. አጠቃላይ መግለጫ
የመስሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ I
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና የቴክኒክ
አገልግሎት ዳይሬክቶሬት
በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር /ብቻ የሚሞላ
የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ VIII 11 18 01

መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ

II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት


2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-
 መረጃዎችን በመሰብሰብና ቴክኒካል ድጋፍ በማድረግ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን የሚሰራውን ሥራ ማገዝ ነው፡፡

2.2. ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት


ውጤት 1፡ አይቲ ነክ መረጃዎችን መሰብሰብ፣
 የተቋሙን የድጋፍ ዕቅድና ጥያቄዎችን በመለየት መረጃ ይሰበስባል፣
 የተቋሙን የመረጃ ስርዓት ፍላጎት ለመለየት መረጃ ይሰበስባል፡፡
 በጥናት የተለዩት የመረጃ ስርዓት ፍላጎቶች መሰረት በማድረግ የሶፍትዌር ልማት ዋና ዋና ምዕራፍ/ ተግባራትን ማለትም የቢዝነስና
የምህንድስና አሰራሮችን በመገምገም ለአሰራር ስርዓት ትንተናና ዲዛይን እና ለፕሮግራም ኮዲንግ መረጃ የመሰብሰብ ስራ ይሰራል፡፡
 የደንበኛ እርካታ ዳሰሳ ይሳተፋል ፣ በተሰጡት ግብረ-መልሶች የሶፍትዌር ልማት ስራው በቀጣይነት እንዲሻሻል መረጃ ይሰበስባል፡፡
 በሚለሙት ሶፍትዌሮች ዙሪያ የስልጠናና የአጠቃቀም መመሪያዎችን/ማኑዋሎቸን ለማዘጋጀት መረጃ ይሰበስባል፣
 የተቋሙን ዝርዝር የመረጃ ስርዓት ፍላጎት እቅድና ያዘጋጃል፤መረጃ ይሰበስባል፣
 በተቋሙ ቀልጣፍ የመረጃ ልውውጥና የተሻሻለ አሰራር እንዲኖር ለማድረግ የመረጃ አውታር አገልግሎት /Network Services Requirement
Analysis/ ፍላጎት ትንተና እንዲከናወን መረጃ ይሰበስባል፡፡
 ከፍላጎት ዳሰሳ በመነሳት ለመረጃ አውታር ዲዛይን ሰነድ ዝግጅት መረጃ ይሰበስባል፡፡

ውጤት 2፡-ለሥራ ክፍሎች ቴክኒካል ድጋፍ ማድረግ


 የተቋሙን የድጋፍ ዕቅድ በመንተራስ፣ የድጋፍ ጥያቄዎችን በመለየት ድጋፍ ይሰጣል፣ ክፍተቶችን በመለየት ክፍተቶች የሚሞሉበት መንገድ
በመቀየስ አስፈላጊውን ማስተካከያ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
 በሥራ ዘርፉ ለደንበኞች መስጠት የሚጠበቅበትን አገልግሎት በተፈለገው ጊዜና የጥራት ደረጃ መስጠት በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀውን
የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ተግባራዊ ያደርጋል፣
 በየጊዜው ያያጋጥሙ የሲስተም ችግሮችን ይፈታል፣
 ኦፕሬቲንግ ሲስተም፣ ሶፍትዌርና ፀረ ቫይረሶችን ወደ ክምፒዩተር ላይ ይጭናል፣

1
የየፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒስቴር የስራ ዝርዝር መግለጫ ቅፅ

 የተቋሙን የመረጃ ስርዓት ፍላጎት በተመለከተ በስልጠናና ማማከር አገልግሎት ይሳተፋል፡፡


 የመረጃ አውታር አስተዳደርና እንክብካቤ ስራዎችን ይሳተፋል፡፡
III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች
.1. የሥራ ውስብስብነት
 ሥራው የተቋሙን የድጋፍ ዕቅድና ጥያቄዎችን በመለየት መረጃ መሰብሰብ፣ የተቋሙን የመረጃ ስርዓት ፍላጎት ለመለየት መረጃ
መሰብሰብ፣ በሚለሙት ሶፍትዌሮች ዙሪያ የስልጠናና የአጠቃቀም መመሪያዎችን/ማኑዋሎቸን ለማዘጋጀት መረጃ መሰብሰብ፣
በየጊዜው ያያጋጥሙ የሲስተም ችግሮችን መፍታት፣ ኦፕሬቲንግ ሲስተም፣ ሶፍትዌርና ፀረ ቫይረሶችን ወደ ክምፒዩተር ላይ
መጫን ይጠይቃል፡፡
 የተሟላና ወቅታዊ መረጃ አለማግኘት፣ የሚጋጥሙ የሲስተም ችግሮች ተለዋዋጭ መሆን፣ በተለያዩ ቫይረሶች መጠቃት፣ ድንገተኛ ችግር መከሰት
በሥራ ክንውን ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮች ሲሆኑ እነዚህን ችግሮች መረጃ ለማግኘት የሚያስችሉ የተለያዩ አማራጮችን ተግባራዊ በማድረግ፣
ጽረ ቫይረሶችን በወቅቱ በመጫንና መረጃዎች ጉዳት እንዳይደርባቸው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥራዎችን በመስራት፣ ጉዳት የደረሰባቸውንም
ወደነበሩበት እንዲመለሱ/recover/ እንዲደረጉ በማድረግ፣ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመረዳት ይፈታሉ፡፡

3.2 ራስን ችሎ መስራት


3.2.1 ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 ሥራው የሥራ ክፍሉን እቅድን፣ ቴክኒካል ማንዋሎችንና ከቅርብ ኃፊው የሚሰጠውን መመሪያ መሠረት በማድረግ ይከናወናል፣
3.2.2. ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ
 ሥራው የጥራት ደረጃውን ጠብቆ ስለመከናወኑ በቅርብ ኃላፊው አልፎ አልፎ ክትትል ይደረግበታል፡፡
3.3. ተጠያቂነት
3.3.1. ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት /Responsibility for Impact/፣
 ሥራው የተቋሙን የድጋፍ ዕቅድና ጥያቄዎችን በመለየት መረጃ መሰብሰብ፣ የተቋሙን የመረጃ ስርዓት ፍላጎት ለመለየት መረጃ
መሰብሰብ፣ በሚለሙት ሶፍትዌሮች ዙሪያ የስልጠናና የአጠቃቀም መመሪያዎችን/ማኑዋሎቸን ለማዘጋጀት መረጃ መሰብሰብ፣
በየጊዜው ያያጋጥሙ የሲስተም ችግሮችን መፍታት፣ ኦፕሬቲንግ ሲስተም፣ ሶፍትዌርና ፀረ ቫይረሶችን ወደ ክምፒዩተር ላይ መጫን
የሚጠይ ሲሆን እነዚህም በአግባቡ ካልተከናወኑ ፣ የቡድኑንና የሥራ ክፍሉን ስራዎች ያስተጓጉላል፣
3.3.2. ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣
 በሶፍትዌር ልማትና የመረጃ አውታር የሚሰበሰቡ መረጃዎች ለሌላ አካል ቢሰጡ የደንበኛውን ጥቅምና ተወዳዳሪነት በከፍተኛ ሁኔታ
ይጎዳሉ፣ በመስሪያ ቤቱና በደንበኞች መካከል ቅሬታን ይፈጥራል፡፡
3.4 ፈጠራ
 ሥራው መረጃ ለማሰባሰብ በተሻለ መንገድ ለማሰባሰብ የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራሮችን መዘርጋትእና የሚያጋጥሙ ችግሮችን
ለመፍታት የሚያስችሉ አሰራሮችን ማመንጨትና ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ ማድረግ ይጠይቃል፡፡
3.5. የሥራ ግንኙነት /Work Communication/
3.5.1 የግንኙነት ደረጃ
 ሥራው በውስጥ ከቅርብ ኃላፊ፣ በቡድኑ ውስጥ ካሉ ባለሙያዎች፣ ከሌሎች የሥራ ክፍሎች ባለሙያዎች፣ ከተቋሙ ውጭ ከባለድርሻ

2
የየፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒስቴር የስራ ዝርዝር መግለጫ ቅፅ

አካላት፣ ተገልጋዮች፣ ከቴሌ ጋር ግንኙነት አለው፡፡

3.5.2 የግንኙነቱ ዓላማ


 ከውስጥ የሥራ መመሪያ ለመቀበል፣ ለመስጠት ፣ ሪፖርት ለመቀበልና ለመስጠት፣ ለመወያየት ፣ አፈጻጸም ለመገምገም፣ በጋራ
ለመሥራት፣ ለመደገፍና ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት፣ አሰራሮችን ለመፈተሽ፣ ቅንጂታዊ ሥራዎችን ለማከናወን፣ በአቅም ግንባታ
ዙሪያ ድጋፍ ለማግኘት ግንኙነት ያደርጋል፡፡
3.5.3 የግንኙነቱ ድግግሞሽ
 ግንኙነት ድግግሞሽ 40 በመቶ ይሆናል፡፡
3.6 ኃላፊነት
3.6.1 ኃላፊነት ለሰው ሀብት
3.6.1.1 በኃላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት

 የለውም፡፡

3.6.1.2 የኃላፊነት አይነትና ደረጃ

 የለውም ፡፡
3.6.2 ኃላፊነት ለገንዘብ
 የለበትም፡፡
3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት
 ሥራውን ለማከናወን የሚያገለግሉ መሣሪያዎች ማለትም ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ላፕቶፕ፣ ፕሪንተርና ሼልፍ፣ ሰርቨርና ሌሎች የኮንፈረንስ
ፋሲሊቲዎች ፣በአግባቡ የመያዝ ኃላፊነት ያለበት ሲሆን ግምቱም እስከ 80,000 ይደርሳል፣
3.7. ጥረት

3.7.1 የአዕምሮ ጥረት

 ሥራው የተቋሙን የድጋፍ ዕቅድና ጥያቄዎችን በመለየት መረጃ መሰብሰብ፣ የተቋሙን የመረጃ ስርዓት ፍላጎት ለመለየት መረጃ
መሰብሰብ፣ በሚለሙት ሶፍትዌሮች ዙሪያ የስልጠናና የአጠቃቀም መመሪያዎችን/ማኑዋሎቸን ለማዘጋጀት መረጃ መሰብሰብ፣
በየጊዜው ያያጋጥሙ የሲስተም ችግሮችን መፍታት፣ ኦፕሬቲንግ ሲስተም፣ ሶፍትዌርና ፀረ ቫይረሶችን ወደ ክምፒዩተር ላይ መጫን
የአእምሮ ጥረትን የሚጠይቅ ሲሆን ከቀን የሥራ ሰዓት 40 በመቶ ይሆናል፡፡
3.7.2.ስነ ልቦናዊ ጥረት
 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ረገድ ዙሪያ መረጃ ለመሰብሰብ በሚደረጉ ግንኑነቶች በአፈጻጸም ላይ ችግሮች ሲያጋጥሙ ጭቅጭቅና
ያለመግባባት ሁኔታዎች ስለሚከሰቱ ይህንን ተቋቁሞ ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ ትዕግሥትንና የሥነ ልቦና ዝግጁነት ይጠይቃል፡፡
3.7.3 የዕይታ ጥረት፣
 ዘመናዊና አዳዲስ ቢዝነስና የምህንድስና አሰራሮችን በጥልቀት መረዳት፣ ችግር ፈቺ የሆኑ የመፍትሄ ሀሳቦችን ማቅረብ፣ የተለያዩ
ዶክመንቶችን ማንበብ እና በኮሚፕዩተር ለረጅም ጊዜ የመጠቀም የእይታ ጥረትን ይጠይቃል ከቀን የሥራ ሰዓት 40 በመቶ ያህል

3
የየፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒስቴር የስራ ዝርዝር መግለጫ ቅፅ

ይሆናል፡፡
3.7.4 የአካል ጥረት
 ሥራው 60 በመቶ በመቀመጥ፣ 40 በመቶ በመቆም ይከናወናል፡፡
3.8. የሥራ ሁኔታ
3.8.1. ሥጋትና አደጋ
 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጥገናና ግንባታ ወቅት የሚያጋጥም የኤሌክትሪክ ንዝረት ያጋልጣል፡፡.
3.8.2. የሥራ አካባቢ ሁኔታ
 የለበትም

3.9. እውቀትና ክህሎት፣


3.9.1. ትምህርት
የትምህርት ደረጃ የትምህርት ዓይነት
የመጀመሪያ ዲግሪ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በኮምፒውተር ሳይንስ ፣ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን
ሲስተም፣

3.9.2 ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ


የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት
0 ዓመት በሶፈትዌር ልማት ወይም በመረጃ አውታር አስተዳደር ሥራ ላይ
የሠራ፣

የሥራ ትንተና ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን

You might also like