You are on page 1of 29

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት

ደቡብ ነጋሪት ጋዜጣ


DEBUB NEGARIT GAZETA
OF THE SOUTHERN NATIONS, NATIONALITIES AND PEOPLES REGIONAL
STATE
25¾ ›mT q$_R 15 Year No. 25 No 15
ሀ êú HÄR 17 qN 2011 ›.M Hawassa November 26/2018
bdb#B B/@éC½ B/@rsïCÂ ?ZïC
KL ል E መንግሥት M ክር b@T ጠባቂነት
የወጣ

መግቢያ

አዲስ የተቋቋሙና ለሚቋቋሙ ዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች ከነባር የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች
የተወሰኑ ወረዳዎችንና ቀበሌዎችን እንደገና በማደራጀት የተቋቋሙ በመሆናቸው በነባሩ ዞንና ወረዳ
አስተዳደር እርከን የሚገኘውን በጀት፣ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር መረጃዎችና ንብረት እንዲሁም የሰው
ኃይል ሥምሪትና ምደባን ፍትሀዊ በሆነ መንገድ መደልደልና መከፋፈል የሚያስችል የአሰራር ሥነ-ስርዓት
በማስፈለጉ፤

የክልሉ ምክር ቤት በ 5 ኛ ዙር 4 ኛ ዓመት 8 ኛ መደበኛ ጉባኤ በውሳኔ ቁጥር 12/2011 ባሳለፈው ውሳኔ
መሰረት ወደ ተግባር አፈፃፀም መግባት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የመስተዳድር ምክር ቤት በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት አዲስ የዞን አስተዳደር
እና የወረዳ አስተዳደር እርከኖችን ለማቋቋም በተሰጠ ውሳኔ ቁጥር 12/2 ዐ 11 ዓ/ም አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ
1 እና አንቀጽ 15 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡

ክፍል አንድ
ጠቅላላ

1
1) አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት አዲስ ለተቋቋሙና ለሚቋቋሙ የዞንና የወረዳ አስተዳደሮች የሰዉ ኃይል እና
የሀብት ድልድልና ክፍፍል አሰራር ደንብ ቁጥር 169/2011 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2) ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ ያሉ ቃላትና ሐረጎች ከዚህ
በታች የተመለከቱትን ትርጉም ይሰጣል፣
1) "ቢሮ" ማለት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የፋይናንስና ኢኮኖሚ
ልማት እና የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ኃብት ልማት ቢሮ ነው፡፡
2) "መምሪያ" ማለት የዞንና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት እና የፐብሊክ
ሰርቪስ የሰው ኃይል መምሪያ ነው፡፡
3) "ጽ/ቤት" ማለት የልዩ ወረዳ፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት እና
የፐብሊክ ሰርቪስ ሰው ኃይል ጽ/ቤት ነው፡፡
4) "የዞን እርከን" ማለት የዞንና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት አስተዳደር እርከን ነው፡፡
5) "የወረዳ እርከን" ማለት የልዩ ወረዳ፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር የመንግሥት አስተዳደር
እርከን ነው፡፡
6) "የመንግሥት መሥሪያ ቤት" ማለት ማንኛውም በከፊል ወይም በሙሉ በክልሉ መንግሥት በጀት
የሚተዳደር መሥሪያ ቤት ነው፡፡
7) "ህትመት" ማለት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የገንዘብ፣ የንብረት እና የሂሳብ እንቅስቃሴዎችን
ህጋዊ እውቅና እንዲሰጥ ታስቦ በቢሮ ታትሞ የሚቀርብ ተከታታይ ንምራ ቁጥር ያለው ሆኖ
የገንዘብ ገቢ እና የወጪ ደረሰኞች፣ የንብረት ገቢና ወጪ ደረሰኞች፣ የሂሳብ ምዝገበ ማዘዣ እና
ሌሎች የሂሳብና የንብረት መዛግብትና ቅጻ ቅጾችን የሚያጠቃልል ነው፡፡
8) "የገቢ ደረሰኝ" ማለት መሂ 7/ሀ፣ 7/ለ፣7/ሐ፣ መሂ 7/መ የሚያጠቃልል ሆኖ የመንግሥት መ/ቤቶች
ከተለያዩ ምንጮች የሚሰበሰቡትን የገቢ ዓይነትና መጠን እውቅና ለመስጠት የሚያገለግሉ ህጋዊ
ሰነድ ነው፡፡
9) "የወጪ ደረሰኝ" ማለት እያንዳንዱ የመንግስት መሥሪያ ቤት ለዓመታዊ ሥራ ማስፈጸሚያ
የተፈቀደለትን የወጪ በጀት ለክፍያ የሚያስፈልገዉ የገንዘብ መጠን በክፍያ ዓይነት፣ በወጪ ሂሳብ
መደብ እና በጊዜ ተለይቶ የሚቀርብበት የገንዘብ እንቅስቃሴ ማረጋገጫ ደረሰኝ ነዉ፡፡
10) "የሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ" ማለት የመንግሥት ሂሳብ እንቅስቃሴ ዉስጥ ለሂሳብ ማስተካከያና
ገንዘብ ነክ ያልሆኑ ሂሳብ ምዝገባ ለማካሄድ የሚያገለግል ቫዉቸር ወይም የሂሳብ ሰነድ ነዉ፡፡

2
11) "የንብረት ገቢ ሞዴል 19" ማለት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በግዥና በሥጦታ በዓይነት
የሚያገኙቸዉን ቋሚና አላቂ ንብረቶች መረከቢያ ሰነድ ነዉ፡፡
12) "የንብረት ወጪ ሞዴል 22" ማለት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በግዥና በሥጦታ በዓይነት
የሚያገኙቸዉን ቋሚና አላቂ ንብረቶች ለመንግሥት ሥራ እንዲዉል ኃላፊነት በተሰጠዉ አካል
ሲፈቀድ ወጪዉ ህጋዊ እዉቅና የሚያገኝበት ደረሰኝ ነዉ፡፡
13) "ንብረት" ማለት ለመ/ቤቱ ኢኮኖሚያዊ ጠቃሜታ ያለዉ በግዥ ወይም በእርዳታ የተገኘ ቋሚና
አላቂ ንብረት ሆኖ ህትመትንም ያጠቃልላል፡፡
14) "ገቢ" ማለት እያንዳንዱ የመንግሥት መ/ቤት በበጀት ዓመቱ ዉስጥ በሕግ በተደነገገዉ መሠረት
የታክስ፣ የቀረጥ እና ታክስ ካልሆኑ የገቢ ምንጮችና ለህብረተሰቡ ከሚሰጡት አገልግሎት እና
ከሚያቀርቡት እቃ የሚሰበስቡት በሕግ ካልተፈቀደ በስተቀር ሰብሳቢዉ መ/ቤት ሊጠቀምበት
የማይችል ገንዘብ በምንጭ እና በሂሳብ መደብ ተለይቶ የሚሰበሰብ ጥሬ ገንዘብ ነዉ፡፡
15) የገቢ በጀት ማለት በአንድ በጀት ዓመት መንግሥት ከታክስ፣ ታክስ ካልሆኑ፣ ከካፒታል ገቢና
ከዉጭ በሚገኝ ብድርና እርዳታ የሚሰበሰብ ሃብት ነዉ፡፡
16) "የወጪ በጀት" ማለት መንግሥት በአንድ የበጀት ዓመት ዉስጥ ለሚሳጣቸዉ አገልግሎቶችና
የልማት ሥራዎች እንዲሁም ዉል ወይም ግዴታ ለተገባባቸዉ ጉዳዮች የሚደለደል ሃብት ነዉ፡፡
17) "የፀደቀ በጀት" ማለት በክልል ምክር ቤት ተቀባይነት አግኝቶ የፀደቀና የተፈቀደ በጀት ማለት
ነዉ፡፡
18) "የበጀት ዝውውር" ማለት በመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 128/2002 አንቀጽ 23
የተሰጠዉ ትርጉም እንደተጠበቀ ሆኖ ከአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ወደ ሌላ የመንግሥት
መሥሪያ ቤት በአርዕስት፣ በንዑስ አርዕስት፣ በሂሳብ መደብ ወይም ከአንድ ፕሮጅክት ወደ ሌላ
ፕሮጅክት የሚደረግ የተፈቀደ የበጀት ዝዉዉርን ይጨምራል፡፡
19) "ተሰብሳቢ" ማለት አንድ የመንግሥት መ/ቤት ለሌሎች መ/ቤቶች /ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች
ለሰጠው አገልግሎት ወይም ለሸጠው እቃ/አገልግሎት ያልተሰበሰበ ሂሳብ ወይም በቅድሚያ
ተከፍሎ ገንዘቡ በሥራ ላይ መዋሉ ማስረጃ ያልቀረበለት ወይም በጥሬ ገንዘብ ተመላሽ ያልተደረገ
ሂሳብ ሲሆን ግብር፣ መቀጫ፣ የዋስትና ገንዘብ፣ ብድር እና የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ሂሳብ ወይም ሌላ
ማንኛውም ለመንግስት ገቢ መደረግ ያለበት ገንዘብ ነው፡፡
20) "ተከፋይ ሂሳብ" ማለት በአጭር እና በረዥም ጊዜ ውስጥ መከፈል ያለበት ዕዳ ነው፡፡
21) "ጥሬ ገንዘብ (Cash)" ማለት የወረቀት ገንዘብ፣ ሣንቲም እንደ ጥሬ ገንዘብ የሚቆጠሩ ሰነዶች፣
በባንክ የተረጋገጠ ቼክን የሚያጠቃልል ነው፡፡

3
22) "የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር" ማለት የተሰበሰበውን የመንግሥትን ገቢ በተፋጠነ መንገድ ወደ ባንክ
ገቢ የሚሆንበት ክፍያ በጥሬ ገንዘብ ዕቅድ ላይ የሚመሰረትበትና ለአጭር ጊዜ ወጪ መሸፈኛ
ከባንክ በሚወሰደው ገንዘብ ላይ የሚከፈለውን የወለድ መጠን ለመቀነስ የሚያስችል አሰራር
ነው፡፡
23) "ሠራተኛ" ማለት በመንግሥት መሥሪያ ቤት በገንዘብ ሰብሳቢነትና ያዥነት፣ በሂሳብ
ሠራተኛነት፣ በግዥና በክፍያ፣ በንብረት ያዥነት ወይም በመንግሥት መ/ቤት በሌሎች የሥራ
መደብ ላይ የተሰማራ ተቀጣሪ ሰው ነው፡፡
24) "የተጣራ ሀብት" ማለት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የመደበኛ፣ የካፒታል እና የፕሮግራሞች
አመታዊ ሂሳብ ሲጠቃለል የሚገኝ የሀብትና የዕዳ ልዩነት ነው፡፡
25) «ተንቀሳቃሽ ንብረት´ ማለት በራሱ ወይም በሰው ጉልበት ጉዳት ሳይደርስበት ወይም ተፈጥሯዊ
ባህሪውን ሳይቀይር ሊጓዝ ወይም ሊጓጓዝ የሚችል ግዙፋዊ ህልውና ያለው ንብረት ማለት ነው፡፡
26) «የማይንቀሳቀስ ንብረት´ ማለት ተፈጥሯዊ ባህሪውን ሳይቀይር ሊጓዝ ወይም ሊጓጓዝ
የማይችል ግዙፋዊ ህልውና ያለው ንብረት ማለት ነው ፡፡
27) «ቋሚ ዕቃ´ ግዙፋዊ አቋም ያለው፣ ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ የጠቀሜታ እሴት
የሚኖረው፣አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝና የተናጠል ዋጋዉ 1,000.00 /አንድ ሺህ/ እና ከዚያ
በላይ የሆነ ንብረት ነዉ::
28) «አላቂ ዕቃ´ ማለት ከቋሚ ዕቃ ውጪ የሆነ ማናቸውም  የመንግሥት ንብረት ሲሆን ጥቅም ላይ መዋል
ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አንድ ዓመት አገልግሎት ሊሰጥ የሚችልና የተናጠል ዋጋዉ ከብር 1,000.00
/አንድ ሺህ/ እና ከዚያ በታች የሆነ ንብረት ነዉ:::
29) «የመዝገብ ዋጋ´ ማለት ቋሚ ዕቃ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በቀጥታ የዕርጅና
ቅናሽ ዘዴ መሠረት አገልግሎት የሰጣባቸው አመታት የዕርጅና ቅናሽ ተቀንሶ የሚኖረው የንብረቱ
ዋጋ ማለት ነው፡፡
30) የእርጅና ቅናሽ ማለት ንብረቱ ኢኮኖሚያዊ ጠቃሜታ ይሰጣል ተብሎ በሚገመትበት ዕድሜ
ሥርዓት ባለዉ አግባብ የንብረቱን ዋጋ እንደወጪ እያሰቡ መቀነስ ማለት ነዉ፡፡
3) የደንቡ አስፈላጊነት
በነባሩ ዞን/ወረዳ እስከ አሁን የሚገኘውን የመንግሥትን ሀብት እና የሰው ኃይል አዲስ ለተቋቋሙና
ለሚቋቋሙ ዞንና ለወረዳ አስተዳደር እርከኖች ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በመደልደልና በማከፋፈል አዲሱ
ዞኖችና ወረዳዎች የተቋቋሙበትን ዓለማ እንዲያሳኩ ለማድረግ ነው፡፡
4) የተፈፃሚነት ወሰን

4
ይህ ደንብ በክልሉ ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት ለተቋቋሙና ለሚቋቋሙ የዞንና የወረዳ አስተዳደር
እርከኖች ሀብትን እና የሰው ኃይል ለመደልደልና ለመከፋፈል ብቻ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
5) የደንቡ ዓላማ
በ 2011 በጀት ዓመት በክልሉ ምክር ቤት በተላለፈዉ ዉሳኔ መሠረት አዲስ የተቋቋሙ የዞንና የወረዳ
አስተዳደር እርከኖች በነባሩ ዞንና ወረዳ እስከ አሁን የሚገኘውን የመንግሥትን ሀብት እና የሰው ኃይል
ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለመደልደልና ለመከፋፈል ሲሆን ዝርዝር ዓላማዎች እንደሚከተለው ተለይተዋል፡፡
1) በ 2011 በጀት ዓመት መጀመሪያ በነበሩት የወረዳና የዞን አስተዳደር እርከኖች የፀደቀዉን ጥቅል
በጀት በፍትሃዊነት ለመደልደል ዝርዝር መስፈርቶችን ለማስቀመጥ፡
2) በነባሩ የዞንና የወረዳ እንዲሁም በልዩ ወረዳ አስተዳደር እርከኖች እስከአሁን ድረስ የሚገኘዉን
አዲስ ለተቋቋሙትና ለሚቋቋሙ የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች የመንግሥትን ፋይናንስ
አስተዳደር መረጃዎች ማለትም ተሰብሳቢ ሂሳቦች፣ ዕዳዎች፣ ጥሬ ገንዘብ እና የተጣራ ሀብት
ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ለማከፋፈል፡፡
3) በመንግሥት መ/ቤቶች የሚገኘውን ቋሚና አላቂ የመንግሥት ንብረት ፍትሀዊ በሆነ መንገድ
ለማከፋፈል፡፡
4) የሀብት ክፍፍልና ድልድል በሚደረግበት ጊዜ የሚፈጠሩ ብዥታዎችን ለማስወገድ፡፡
5) በሀብት ድልድልና ክፍፍል ወቅት የፋ/ኢ/ል/ቢሮ፣ መምሪያ እና ጽ/ቤቶች ተግባርና ኃላፊነት ለይቶ
በዝርዝር ለማስቀመጥ፡፡
6) የሰው ኃይል ሥምሪትና ምደባ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለመደልደል ያለሙ ናቸው፡፡

6) በደንቡ ውስጥ የተካተቱት ዋና ዋና ጉዳዮች


1) የሰው ኃይል ሥምሪት ምደባ፣ እና ዝውውር ሥርዓት፣
2) የበጀት ድልድልና ክፍፍል አሰራር ሥርዓት፣
3) የመንግሥት ሂሳብ መረጃ አያያዝ፣ አጠባበቅ አስተዳደርና ክፍፍል አሰራር ሥርዓት፣
4) የመንግሥት ንብረት አያያዝ፣ አስተዳደር እና ክፍፍል አሰራር ሥርዓት፣
5) የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የደረሰኞችና የሌሎች ህትመቶች አያያዝ፣ አስተዳደር፣ አጠቃቀም
እና ክፍፍል አሰራር ሥርዓት፣
6) አዲስ የተቋቋሙና የሚቋቋሙ የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች የሂሳብ መረጃ አያያዝና
ሪፖርት አቀራረብ፣
7) በየአስተዳደር እርከን የሚገኙ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያና
የፋ/ኢ/ል/ቢሮ/መምሪያ እና ጽ/ቤቶች በሰው ኃይል እና በሀብት ድልድልና ክፍፍል ወቅት ሊኖሩ
የሚገባቸው ተግባርና ኃላፊነት፣

5
8) በሰው ኃይልና በሀብት ድልድልና ክፍፍል ወቅት የሚፈጠሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚቻልበት
የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀትና አፈታት ሥርዓት ናቸው፡፡

6
ክፍል ሁለት

አዳዲስ ለተደራጁ ዞንና ወረዳ የሰው ኃይል ዝውውር አፈጻጸም አቅጣጫ

7. ከነባር ዞን፣ ልዩ ወረዳና ወረዳ ወደ አዲስ ዞንና ወረዳ የባለሙያዎች ስራ ስምሪት /ዝውውርና ምደባ /
ሁኔታ፣

1) አዲስ ለተቋቋመ ዞንና ወረዳ አስፈላጊው የሰው ኃይል እንዲሟላ የሚደረገው ወደፊት የበጀት
አቅምና ሌሎች የስራ ሁኔታዎች ተጠንቶ እስክሟላ ድረስ ስራ ለማስጀመር የሚያስችል የሰው ኃይል
ከነባር ዞንና ወረዳ በዝውውር/በምደባ እንዲሟላ ይደረጋል፡፡
2) ከነባር ዞንና ወረዳ ወደ አዲስ ወደ ተቋቋመ ዞንና ወረዳ የሠራተኛ ስምሪት/ዝውውርና ምደባ
የሚፈጸመው ሠራተኛው በነባሩ ዞን ወይም ወረዳ በያዘው የስራ መደብ፣ የስራ ደረጃና ደመወዝ ብቻ
ነው፡፡ ይህ ማለት ከነባሩ የዞን ወይም የወረዳ መስሪያ ቤት የሚዛወር /የሚመደብ/ ሠራተኛ ከነባሩ
መስሪያ ቤት የሜሪት ስርዓትን ተከትሎ የያዘው ስራ መደብ፣ የስራ ደረጃና ደመወዝ የሚጠበቅለት
ሲሆን በዚህ ምደባ/ዝውውር ምክንያት ከፍ ያለ የስራ ደረጃና ደመወዝ አይፈቀድለትም ማለት ነው፡፡
3) ከነባር ዞንና ወረዳ ወደ አዲሱ ዞንና ወረዳ የሚመደቡ/የሚዛወሩ ባለሙያዎች በነባሩ ዞንና ወረዳ
ተመድበው ሲሰሩበት በነበረው የትምህርት ሙያ መስመር እና ተመሳሳይ የሥራ መደብ ደረጃና
አግባብነት ባለው መልኩ የሚፈጸም ይሆናል፡፡ ምሳሌ፡-በነባሩ ዞን ወይም ወረዳ የሰብል ልማት ባለሙያ
ሆኖ ሲሰራ የነበረ ባለሙያ በአዲሱ ዞንና ወረዳ በተመሳሳይ ሙያና ስራ መደብ ላይ ተመድቦ እንዲሰራ
ይደረጋል፡፡
4) ከነባሩ ዞንና ወረዳ ወደ አዲሱ ዞንና ወረዳ ባለሙያዎች/ሰራተኞች/ የሚደለደሉት፡-
ሀ) በአጎራባች ከሚገኙ ዞንና ወረዳ በሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለሰራተኛው ፍላጎት ቅድሚያ
በመስጠት ማስታወቂያ በማውጣት በተመሳሳይ የሥራ ደረጃና ደመወዝ እንዲመደቡ
ይደረጋል፡፡ ሆኖም ወደ አዲሱ ዞንና ወረዳ ለመመደብ የሚፈልጉ ባለሙያዎች ብዛት
ከሚፈለገው የሰው ሃይል በላይ ከሆነ ምደባው በደልዳይ ኮሚቴ አማካኝነት በግልጽ ውድድር
የሚፈጸም ይሆናል፡፡

ለ) ከላይ በተራ ቁጥር ‹‹ሀ›› በተገለጸው አግባብ ከነባር ዞንና ወረዳ ወደ አዲስ ዞንና ወረዳ የሚደለደሉ
ሰራተኞች የሰው ሀይል እጥረት በሚያጋጥም ጊዜ ለአንድ ዓመት ለማይበልጥ ጊዜ ሰራተኞችን
በትውስት አዛውሮ ማሰራት ይቻላል፡፡

ሐ) በተራ ቁጥር ‹‹ሀ›› እና ‹‹ለ›› የተቀመጡትን አማራጮች ለመፈጸም አስቸጋሪ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ


ከነባር ዞንና ወረዳና መስሪያ ቤቶች የሚፈለገውን የሰው ሀይል በነባሩ ዞንና ወረዳ ካሉት
ባለሙያዎች ውስጥ በዕጣ በመለየት ወደ አዲስ ዞንና ወረዳ በዝውውር እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡

7
5) አዲስ ለተደራጁ ዞንና ወረዳ የድጋፍ ሰጪ የስራ መደቦች በተመለከተ፤-
1) በአዲስ መልክ የተደራጁ ዞንና ወረዳ የድጋፍ ሰጪ የስራ መደቦች መዋቅር/የሰው ሀይል/
አጠቃቀምን በፑል አስተዳደር የሚመሩ/ ይሆናል፡፡
2) የሰው ሀብት አስተዳርና ልማት እና የሰው ሀብት ስራ አመራር መረጃ ስታቲክስ በአዲሱ
ዞንና ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት በፑል የሚመራ ይሆናል፡፡
3) የልማት እቅድና በጀት ዝግጅት ደጋፊ የስራ ሂደት አዲስ በተደራጀው ዞንና ወረዳ
በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ /ጽ/ቤት/ በኩል በፑል የሚመራ ይሆናል፡፡
ክፍል ሦስት
የሀብት ድልድልና ክፍፍል አሰራር ሥርዓት
ምዕራፍ አንድ
የበጀት አስተዳደር
8) የዞንና ወረዳ አዲስ አወቃቀር እና የበጀት ክፍፍል ሁኔታ
1) ልዩ ወረዳ ወደ ዞን አስተዳደር ከፍ ባለ ደረጃ ሲዋቀር
ሀ) ቀደም ሲል በበጀት ዓመቱ ለልዩ ወረዳው የተመደበው በጀት ሙሉ በሙሉ የአዲሱ ዞን በጀት ይሆናል፡፡
ከጥቅል የዞኑ በጀት እስከ 12 በመቶ ለዞን ማዕከል መዋቅር የመደበኛ በጀት/ደመወዝን ጨምሮ/ እና
ለካፒታል በጀት ሊመደብ ይገባል፡፡ እንዲሁም እስከ 1 በመቶ ለዞኑ መጠባበቂያ በጀት ሊመደብ
ይገባል፡፡
ለ) በአዲሱ ዞን አስተዳደር ስር ለሚገኘው የከተማ አስተዳደር ለመሠረተ ልማት ግንባታዎችና ለሌሎች
ማህበራዊና ለአስተዳደራዊ ጉዳዮች የሚያስፈልገውን ጥቅል የበጀት ፍላጎት እና ከተማ አስተዳደሩ
ሊሰበስብ የሚችለውን ገቢ ታሳቢ በማድረግ ከዞኑ ጥቅል የድጎማ በጀት ሊመደብለት ይገባል፡፡
ሐ) በአዲሱ ዞን አስተዳደር ስር ለተዋቀሩ አዳዲስ ወረዳዎች ከዚህ በላይ በንኡስ አንቀፅ ሀ እና ለ የበጀት
መጠን ከዞኑ ጥቅል በጀት በመቀነስ የሚቀረውን በጀት በአዲሶቹ የወረዳዎች ህዝብ ቁጥር ድርሻ
መጠን በጀት በፍትሐዊነት ሊመደብላቸው ይገባል፡፡
2) አንድ ነባር ዞን አስተዳደር ወደ ሁለትና ከዚያ በላይ አዳዲስ ዞኖች በመከፋፈል ሲዋቀር
ሀ) በነባሩ ዞን ተመድቦ የነበረው የነባር ወረዳዎች በጀት በአዲስ በታወቀሩበት ዞን ስር ይዘው
የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡
ለ) የነባሩና የአዲሱ የዞን አስተዳደሮች በጀት በዞኑ ስር የተዋቀሩትን ወረዳዎች በጀት እና የዞን ማዕከል
በጀትን በማካተት የሚመደብ ይሆናል፡፡ የነባሩና የአዲሱ ዞን አስተዳደሮች የዞን ማዕከል በጀት
ቀደም ሲል ሁለቱ ዞኖች በአንድ ላይ በተዋቀሩበት ወቅት የነበረውን የነባሩን ዞንና የዞን ማዕከል
በጀት/መጠባበቂያን ጨምሮ/ዞኖች ባላቸው የህዝብ ቁጥር መጠን ድርሻ በመቶኛ በማከፋፈል
የሚመደብ ይሆናል፡፡

8
ሐ) በነባሩም ሆነ በአዲሱ የዞን አስተዳደር ስር አዳዲስ ወረዳዎች የሚዋቀሩበት ሁኔታ ሲፈጠር
አዲሶቹ ወረዳዎች ከነባሩ ወረዳዎች ይዘው በመጡት የህዝብ ቁጥር በመቶኛ መጠን ከነባሩ ወረዳ
በመቀነስና ለነዚሁ አዳዲስ ወረዳዎች በጀት በፍትሐዊነት ሊመደብ ይገባል፡፡

3) ከነባሩ ዞን ወረዳ ወጥቶ በዞን ደረጃ ለብቻ የሚዋቀርበት ሁኔታ ሲፈጠር


ሀ) የአዲሱ ዞን በጀት በነባሩ ዞን በወረዳ ደረጃ የነበረው በጀት እና የነባሩ ዞን ለዞን ማዕከል ከነበረው
በጀት አዲሱ ዞን ያለውን የህዝብ ቁጥር በመቶኛ መሠረት በማድረግ የሚደርሰውን በጀት
በማካተት የሚመደብ ይሆናል፡፡
ለ) አዲሱ ዞን ከጥቅል የዞኑ በጀት እስከ 12 በመቶ ለዞን ማዕከል መዋቅር የመደበኛ በጀት/ደመወዝን
ጨምሮ/ እና ለካፒታል በጀት ሊመደብ ይገባል፡፡ እንዲሁም እስከ 1 በመቶ ለዞኑ መጠባበቂያ በጀት
ሊመደብ ይገባል፡፡
ሐ) በአዲሱ ዞን አስተዳደር ስር ለሚገኝ የከተማ አስተዳደር ለመሠረተ ልማት ግንባታዎችና ለሌሎች
ማህበራዊና ለአስተዳደራዊ ጉዳዮች የሚያስፈልገውን ጥቅል የበጀት ፍላጎት እና ከተማ
አስተዳደሩ ሊሰበስብ የሚችለውን ገቢ ታሳቢ በማድረግ ከዞኑ ጥቅል የድጎማ በጀት ሊመደብለት
ይገባል፡፡
መ) በአዲሱ ዞን አስተዳደር ስር የሚቋቋሙ አዳዲስ ወረዳዎች ባላቸው የህዝብ ቁጥር በመቶኛ ድርሻ
መጠን በጀት ሊመደብላቸው ይገባል፡፡ እንዲሁም አዲስ የሚቋቋም ወረዳ ከሌሎች ነባር ዞኖችና
ወረዳ ቀበሌዎችን አካቶ የሚቋቋም ከሆነ የቀበሌዎች የህዝብ ቁጥር በመቶኛ መጠን ለአዲሱ
ወረዳ በጀት ሊመደብለት ይገባል፡፡
ሠ) ከነባሩ ዞን ወጥቶ በአዲስ ዞን/ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የቀድሞ ወረዳዎችን በማካተት/ ወይም
በአዲስ ልዩ ወረዳ/ በነባሩ ዞን ወረዳ የነበሩ/ ሲዋቀሩ በነባሩ ዞን ለወረዳዎቹ የተመደበው በጀት እና
ከነባሩ ዞን ለዞን ማዕከል ከተመደበው በጀት አዲሱ ዞን/ልዩ ወረዳ/ ባለው የህዝብ ቁጥር በመቶኛ
መጠንን በማካተት ለአዲሱ ዞን ወይም ልዩ ወረዳ በጀት ሊመደብ ይገባል፡፡
4) በነባር ዞኖች ስር አዳዲስ ተጨማሪ ወረዳዎች የሚዋቀሩበት ሁኔታ ሲፈጠር
በነባሩ ዞን ስር ለሚዋቀሩ አዳዲስ ወረዳዎች ከነባር ወረዳዎች ተለይተው በአዲስ ወረዳ ውስጥ
እንዲካተቱ የተወሰኑትን ቀበሌዎች ህዝብ ቁጥር በመቶኛ ድርሻ መጠን ከነባሩ ወረዳ የቀድሞ ጥቅል
በጀት ላይ በመቀነስ ለአዲሱ ወረዳ በጀት በፍትሐዊነት ሊመደብ ይገባል፡፡
9) ከዚህ በላይ የተገለጹ እንደተጠበቁ ሆኖ ለበጀት ክፍፍል ብቻ /የንብረትንና የፋይናንስ አስተዳደር መረጃዎች
ክፍፍልን ሳያካትት/ ቀደም ሲል በዞን አስተዳደር ምክር ቤቶች የፀደቀዉ የበጀት ክፍፍል አዳዲስ የወረዳ
አስተዳደር እርከኖችን ያካተተ ከሆነ በነባሩና በአዲሱ የወረዳ አስተዳደር መካከል ሌላ የበጀት ክፍፍል
ሳይሰፈልግ በዞን ምክር ቤት ባፀደቀዉ መሠረት ተፈፃሚ የሚደረግ ይሆናል፡፡

9) የተመደበዉን የበጀት ጣሪያ ስለማሳወቅ

9
አዲስ የተቋቋሙና የሚቋቋሙ የዞን፣የልዩ ወረዳ አስተዳደር እርከኖች ከነባሩ ዞንና ልዩ ወረዳ አስተዳደሮች የተመደበዉን
የበጀት ጣሪያ በክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በኩል በደብዳቤ እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡ እንዲሁም
አዲስ የተቋቋሙና የሚቋቋሙ የወረዳ አስተዳደር እርከኖች ከነባሩ ወረዳ አስተዳደር እርከኖች የተመደበዉን የበጀት
ጣሪያ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በኩል በደብዳቤ እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡
11) በአዲስ የአስተዳደር እርከኖች የሚደራጁ ሴክተር መ/ቤቶች የሚደረግ የበጀት ክፍፍል ዝግጅት

በየአስተዳደር እርከን በዋናነት በጀት የሚመደበው የተሰጠውን የወጪ ኃላፊነት መሠረት በማድረግ ይሆናል፡፡
በመሆኑም፣
1) በጀትን ለሴክተር ለማከፋፈል የወቅቱን የመንግስት ፖሊሲ ስትራቴጂና የትኩረት አቅጣጫ በመከተል
ድህነት ቀናሽ ለሆኑ የልማት ሴክተሮች ማለትም ትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና፣ ውሃና መንገድ ቅድሚያ
የሚሰጣቸው ሲሆን የጥቃቅን ንግድ አነስተኛ ኢንዱስትሪም ትኩረት ከተሰጣቸው ሴክተሮች አንዱ
በመሆኑ ለሴክተሩ ዕድገት አስፈላጊ የሆነውን በጀት በመመደብ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

2) በበጀት ዝግጅት ወቅት የሴክተሮችን ኘሮግራሞችና ኘሮጀክቶች ቅድሚያ የበጀት ድልድል ለማካሄድ
እንዲረዳ በየሴክተሩ የሚቀርቡ ዕቅዶችና ኘሮግራሞች እንዲሁም የወጪ ጥያቄዎች ከፖሊሲ ትኩረትና
ከሀብት መኖር አንጻር መመደብ ይጠበቅበታል፡፡

3) ዓመታዊ የአፈጻጸም ቅደም ተከተል ከግምት ውስጥ በማስገባት የመደበኛና የካፒታል ወጪዎች ድርሻም
ተለይቶ መገመት ይኖርበታል፡፡

12) የበጀት ዝግጅትና አደረጃጀት

የመደበኛና የካፒታል በጀት አደረጃጀት በዞን በወረዳ ባሉ ማንኛውም የመንግስት መ/ቤት በጀት የሚደራጀው
በየአስተዳደር እርከኖች ወጥ በሆነ መልኩ በተዘጋጀው የመንግስት መ/ቤት ስምና መለያ ቁጥር፣ የኘሮግራም
ስምና መለያ ቁጥር፣ የሥራ ክፍል ስምና መለያ ቁጥር፣ የኘሮጀክት ስምና መለያ ቁጥር በማካተት ይሆናል፡፡

1) ለመደበኛ በጀት ዝግጅት የሚደረጉ የበጀት ዝግጅት ሥራዎች፣

ሀ. ለመንግስት ሰራተኞች የ 12 ወር ደመወዝ በበጀት መደገፍ እና የጡረታ መዋጮ የመንግስት


ድርሻ ለእያንዳንዱ የመንግስት ሠራተኛ የደመወዙን 11% እንዲሁም የፖሊስ አባላት
የጡረታ መዋጮ የመንግስት ድርሻ ከደመወዛቸው 25% በበጀት መደገፍ ይገባል፡፡
ለ. በዞን ወይም በወረዳ ውስጥ የተዋቀሩ መ/ቤቶች የሰው ኃይል ፍላጐት ማሟያ የሚሆን የበጀት ጥያቄ
ሲያቀርቡ ከአቅም ጋር የተጣጣመ፣ ከሰው ኃይልና ከፋይናንስ አቅርቦት ጋር የተገናዘበ መሆን
ይኖርበታል&

10
ሐ. ለመምህራንና ለጤና ባለሙያዎች ለኬርየር ስትራክቸርና ልዩ ልዩ የሙያ አበል ለተለያዩ
ባለሙያዎችና ኃላፊዎች ከሲቪል ሰርቪስ ስምምነት የተሰጠ የመዘዋወሪያ አበል ክፍያዎች በበጀት
ውስጥ መካተት ይኖርበታል፡፡
መ. ለሰውና ለእንሰሳት የሚያስፈልገው የመድሃኒት ግዥ በዞኑ/በወረዳው የበጀት ጣሪያ ሥር ተመድቦ
መታየት አለበት፡፡
ሠ. ቀደም ሲል ግንባታቸዉ ለተጠናቀቁ ካፒታል ፕሮጅክቶች ወደ ሥራ ማስገቢያ መደበኛ በጀት
ሊያዝላቸው ይገባል፡፡

2) የካፒታል በጀት ዝግጅት ወቅት ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮች፣

ሀ) ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ የመንግሥት ሃብት ወጥቶባቸዉ የተገነቡ ኘሮጀክቶች ሥራ ላይ ሊውሉ


የሚችሉበትን ሁኔታ በልዩ ትኩረት ቅድሚያ በመስጠት በጀት መመደብ አለበት፡፡

ለ) በመካሄድ ላይ ያሉ ኘሮጀክቶችና ኘሮግራሞች እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ሊከናወኑ የሚችሉ


ሥራዎችንና ሊከፈል የሚገባዉን በጀት በትክክል በመለየት የሚቀሩ ሥራዎችን ቅድሚያ በመስጠት
በጀት መመደብ አለበት፡፡

ሐ) ባለፉት ዓመታት የተጠናቀቁ ኘሮጀክቶች የመያዣ ክፍያ ቀደም ሲል የነበረውን ኘሮጀክት ስምና መለያ
ኮድ ሣይቀየር በበጀት መደገፍ አለበት፡፡

መ) አዳዲስ ኘሮጀክቶች በካፒታል በጀት እንዲያዙ ሲቀርብ የዞን/ወረዳዉ የማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ


ችግሮች ለማቃለል በድህነት ቅነሣ ላይ የሚኖራቸው ጉልህ አስተዋጽኦ ከግምት ውስጥ ያስገባ እና
ኘሮጀክቶቹ በጥናት ላይ የተመሠረተ ግልጽ አላማና ግብ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡

ሠ) የሴክተሩ ኘሮግራም ስምና መለያ ቁጥር እንዲሁም ኘሮግራሙን የሚያስፈጽመው የሥራ ክፍል ስምና
መለያ ቁጥር የሚዘጋጀው በክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በኩል ይሆናል፤

ረ) ቀደም ስል የነበሩ የብድርና እርዳታ በጀት በበጀት ዓመቱ በተፈቀደበት በነባሩ ወረዳ አስፈጻሚ መሥሪያ
ቤት ላይ የሚመደብ ይሆናል፡፡

13 የበጀት ዝዉዉር አፈጻጸም

1) የበጀት ዝውውር ቀደም ብሎ የፀደቀው የበጀት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 25/2008 እንደተጠበቀ
በነባርና በአዲስ የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች የሚደረገዉ የበጀት ዝውውር የሚፈፀምበት የጊዜ
ገደብ አዲስ የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች ከተቋቋሙት ጊዜ እስከ ጥር 3 ዐ ቀን 2011 ዓ/ም ብቻ
ማዘዋወር ይችላል፡፡

11
2) የአዲስ ወረዳ አስተዳደር በጀት በወረዳዉ የፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ጠያቂነት አጽዳቂ በነባሩ ወረዳ
ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ኃላፊ ይሆናል፡፡

3) የበጀት ዝውውር የሚፈፀመው በቅጽ በማ 1/ ብቻ መሆን አለበት፡፡

4) አዲስ የተቋቋሙት የዞን ሆነ የወረዳ አስተዳደር እርከኖች በጀታቸውን የሚያዘዋውሩት አዲስ


በሚቋቋመው ሴክተር እና የበጀት መዋቅር መለያ ቁጥር ይሆናል፡፡

5) አዲስ የተዋቀሩ የዞንና ወረዳ አስተዳደር በጀት የሚመዘገበው በበጀት ማደራጃ ሥርዓት (በ IBEX
ሲስተም) ይሆናል፡፡

6) አዲስ ለተዋቀሩ ዞንና ወረዳ የበጀት እስትራክቸር ኮድ /የዞን፣የወረዳ /መለያ ቁጥር ከክልሉ ፋይናንስ
ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ተዘጋጅቶ የሚላክ ይሆናል፡፡ በዚህ መሠረት አዲስ የዞንና የወረዳ አስተዳደር
እርከን የበጀት መረጃዉን በበ IBEX ሲስተም መመዝገብ አለበት፡፡

ምዕራፍ ሁለት
የመንግሥት ፋይናንስ መረጃዎች
14. የመንግሥት ፋይናንስ መረጃዎች አያያዝ፣አስተዳደርና ክፍፍልን በተመለከተ፣
አንድ ዞን ወደ ሁለት ዞኖች ሲከፈል፣ በነባሩና በአዲሱ ዞኖች ሥር ካሉት ከተለያዩ ወረዳዎች ሥር የተለያዩ
ቀበሌዎች ወጥተዉ አዲስ ወረዳዎች ሲደራጁ እንዲሁም አንድ ወረዳ ወይም ልዩ ወረዳ የተለያዩ አዳዲስ
ወረዳዎችን በሥሩ ይዞ ነባሩ ወረዳ/ልዩ ወረዳ በዞን ደረጃ ሲደራጅ በነባር ዞኖች፣ ልዩ ወረዳ እና ወረዳዎች
ሲተዳደርና ሲመራ የነበረዉ የ 2011 በጀት ዓመት በጀት፣ እስከ አሁን ድረስ የሚገኙ የመንግሥት ፋይናንስ
መረጃዎች፣ የመንግሥት ንብረቶች እና ሌሎችም የመንግሥት ሀብት አዲስ ለተቋቋሙ፣ ለሚቋቋሙ እና
ለነበሮቹ አስተዳደር እርከኖች ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ድልድልና ክፍፍል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይህንን ፍትሃዊ
ድልድልና ክፍፍል ለማድረግ ነባሮቹ ዞኖች፣ልዩ ወረዳ እና ወረዳዎች ከዚህ በላይ የተጠቀሱ የመንግሥት
ሀብቶችን መረጃ በአግባቡ አደራጅቶ በመያዝ ፍትሃዊ በሆነ ሀብት ድልድልና ክፍፍል ላይ ከፍተኛ ሚና
መጫወት አለባቸዉ፡፡

1) ለነበረው ወረዳ/ዞን/ልዩ ወረዳ ተመድቦ ከነበረው በጀት በሌሎች ዞኖች/ወረዳዎች/ልዩ ወረዳ


ዓመታዊ በጀት በሚከፋፈሉበት አሰራር ሥርዓት (በተቀመጠው መስፈሪት) መሠረት የአዲሱን
ዞን/ወረዳ ድርሻ በጀት በማስቀረት ለተቋቋሙ ወረዳዎችና ዞኖች ቀሪው በጀት ከመደልደሉ
በፊት በነባሩ ወረዳ/ዞን እስከ መስከረም 30/2011 ዓ/ም ድረስ (አዲሶቹ ወረዳዎች/ዞኖች)
እስከሚቋቋሙ ድረስ የሚገኘውን ማንኛውም የዕዳና የተጣራ ሀብት ታሳቢ መደረግ አለበት፡፡

12
2) ከአንድ ነበር ዞንና ወረዳ ወጥተዉ በአዲስ ዞንና ወረዳ አስተዳደር እርከን ሲደራጁ በ 2011
በጀት ዓመት ለነበሩ ዞን ማዕከል/ወረዳ ዞኖቹና ወረዳዎች በአንድ ላይ በነበሩበት ጊዜ
ተመድበዉ የነበረዉን በጀትና ሌሎች የመንግሥት ፋይናንስ መረጃዎችን ከነባሩ ዞን/ወረዳ
በወጡት ዞን/ወረዳ/ቀበሌ ብዘት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የሀብት ድልድልና ክፍፍል መደረግ
አለበት፡፡ ሀብት ክፍፍል ከመደረጉም በፊት አስፈላጊው መረጃ በሙሉ በአግባቡ ተደራጅቶ
መያዝና መቀመጥ አለበት፡፡ ስለሆነም የመንግሥት ፋይናንስ መረጃዎች ክፍፍል ከዚህ በታች
በዝርዝር በሚቀርበው ሁኔታ ሊከናወን ይገባል፡፡
15) የተሰብሳቢ ሂሳቦች መረጃ አያያዝ፣ አስተዳደር እና ክፍፍልን በተመለከተ፡-
በቀድሞ በነባሩ /ዞን/ወረዳ አስተዳደር የነባሩ የተሰብሳቢ ሂሳቦች ዝርዝር መረጃ በአግባቡ
በግለሰቦች፣ በድርጅቶች እና በመንግሥት መ/ቤቶች ስም ተለይቶና ተደራጅቶ በአግባቡ በመያዝ፡
1) በነባሩ ዞን/ወረዳ አስተዳደር እርከን አስፈላጊው ማስረጃ ቀርቦ ሊወዳደቁ የሚገባቸው ተሰብሳቢ
ሂሳቦች ከሀብት ክፍፍል በፊት እንዲወዳደቁ በማድረግ ሂሳቡ በወጪ መመዝገብ አለበት፡፡
ማስረጃ ቀርቦ ሊወዳደቁ የማይገቡ ግን በጥሬ ገንዘብ መተካት ያለበትን ተሰብሳቢ ሂሳቦች
በጥሬ ገንዘብ እንዲተካ በማድረግ ገንዘቡ ባንክ ገቢ መደረግ አለበት፣
2) ከካፒታል ፕሮጀክቶች ጋር ተያይዞ የተከፈለ ቅድመ ክፍያ፣ የተከፈሉ ክፍያዎችና ሲቀናነሱ የቀሩ
ተሰብሳቢ ሂሳቦች የካፒታል ፕሮጀክት ወደ ሚሰራበት አዲስ ወረዳ አስተዳደር ከሆነ ተሰብሳቢ
ሂሳቦቹን በትክክለኛ ቦታ እንዲያዝ ማድረግ ስለሚያስፈልግ፤
ሀ) በነባሩ ዞን/ወረዳ አስተዳደር እርከን የነበረው የካፒታል ፕሮጀክት ተሰብሳቢ ሂሳብ ወደ አዲሱ
ዞን/ወረዳ አስተዳደር እርከን እንዲተላለፍ ሲደረግ ማከናወን የሚገባው የሂሳብ አያያዝ
ሥርዓት በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ ላይ (Journa Voucher) ላይ፡- ዴቢት 5601 (የተጣራ
ሀብት) እና ክሬዲት 4253 (ተሰብሳቢ ሂሳብ) በማድረግ ምዝገባውም በነበሩ ዞን/ወረዳ
አስተዳደር IBEX ውስጥ እንዲመዘገብ ይደረጋል፡፡ የተሰብሳቢና የተጣራ ሀብት ሚዛንም
በነባሩ ዞን/ወረዳ አስተዳደር እንዲቀነስ መደረግ ያለበት ሲሆን፡-
ለ) አዲስ የተቋቋመ ዞን/ወረዳ አስተዳደር ከነባሩ ዞን/ወረዳው አስተዳደር በመሸኛ ደብዳቤ
የሚላክለትን ለሂሳብ ምዝገባ መነሻ የሚሆኑ የካፒታል ፕሮጅክቶችን ከመጀመሪያ ጀምሮ
በትክክል የሚያስረዳ ከዋና ሰነዶች ጋር የተገናዘቡ ማስረጃዎችና ደጋፊ የሂሳብ ሰነዶችን
መነሻ በማድረግ ቀጣይነት ላለው ካፒታል ፕሮጀክቶች በቅድሚያ ተከፍሎ ሳይወዳደቅ
ወደፊት የፕሮጀክቶች ቀሪ ሥራዎች ተጠናቆ የክፍያ ሰርተፍኬት ቀርቦ የተሰብሳቢ ሂሳብ
እየተቀናነሰ መረጃውን ለመያዝ በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ መመዝገብ ያለበት ሂሳብ ዴቢት
ተሰብሳቢ (4253) እና ክሬዲት የተጣራ ሀብት (5601) ተደርጎ መመዝገብ አለበት፡፡

13
ይህ የሂሳብ መረጃ በአዲሱ ወረዳ/ዞን አስተዳደር በመንግሥት ሂሳብ አያያዝ ሥርዓት
መሠረት በ IBEX መመዝገብ እና ማወራረስ ያለበት ሲሆን የተጠራ ሀብትና የተሰብሳቢ
ሂሳብ ሚዛኑ የሚጨምር ይሆናል፡፡
ሐ) ከነባሩ ወረዳ/ዞን ወደ አዲሱ ወረዳ/ዞን በሚዛወሩ ሠራተኞች (ባለሙያዎች) ስም የሚገኝ
ያልተወዳደቀ ማለትም ከ 2011 በጀት ዓመት በፊት የነበሩ ተሰብሳቢ ሂሳቦች፡-
1) ቢቻል በነባሩ ዞን/ወረዳ አስተዳደር እርከን ተወዳድቆ ሂሳቡ በወጪ ሂሳብ ተመዝግቦ
እንዲያዝ መደረግ አለበት፡፡
2) ሊወዳደቁ የማይችሉ ከሆኑ በነባሩ ዞን/ወረዳ አስተዳደር የሚገኘውን ተሰብሳቢ ሂሳቦች
በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ (Journal Voucher) ላይ ዴቢት የተጣራ ሀብት (5601) እና
ክሬዲት ተሰብሳቢ ሂሳብ አድርጎ በመመዝገብ መረጃውን አዲስ የተቋቋመው ዞን/ወረዳ
አስተዳደር ተቀብሎ የተላከውን መረጃ መነሻ በማድረግ ዴቢት ተሰብሳቢ ሂሳብ
(4211) እና ክሬዲት የተጣራ ሀብት (5601) ሆኖ ሂሳቡ በመንግሥት ሂሳብ አያያዝ
ሥርዓት መሠረት መመዝገብና ማወራረስ አለበት፡፡
3) ከነባር ዞን/ወረዳ ወደ አዲሱ ዞን/ወረዳ አስተዳደር የሚላከው ተሰብሳቢ ሂሳብ የ 2011
በጀት ዓመት ተሰብሳቢ ሂሳብ ከሆነ አዲስ ለተቋቋመው ዞን/ወረዳ አስተዳደር
የሚሰጠው የበጀት አካል እንዲሆን መደረግ አለበት፡፡ ነባሩ የዞንና የወረዳ አስተዳደሮች
የ 2011 በጀት ዓመት በጀት አካል የሆነዉን ተሰብሳቢ ሂሳብ አዲስ ለተቋቋሙት ዞንና
ወረዳ አስተዳደር ሲተላለፍ የነበሩ ዞን/ወረዳ የሂሳብ ምዝገባ ዴቢት 1621/1622 እና
ክሬዲት ተሰብሳቢ ሂሳብ ይሆናል፡፡ የአዲሱ ዞንና ወረዳ የሂሳብ ምዝገባ ዴቢት
ተሰብሳቢ ሂሳብ እና ክሬዲት 1621/1622 ይሆናል ማለት ነዉ፡፡
4) ከ 2011 በጀት ዓመት በፊት ከነበሩት በጀት አመታት ተያይዞ የመጡ ተሰብሳቢ ሂሳቦች
ከዚህ በላይ በተራ ቁጥር 3 በዝርዝር በቀረበው መሰረት ለአዲሱ ዞን/ወረዳ አስተዳደር
የሚተላለፉ ተሰብሳቢ ሂሳቦች የ 2011 በጀት ዓመት በጀት ለአዲሱ ዞን/ወረዳ
አስተዳደር ሲደለደል ታሳቢ የሚደረጉ አይደሉም፡፡
16. የግብዓት ተሰብሳቢ ሂሳቦችን በተመለከተ፡-
የግብርና ግብዓቶች በየቀበሌ ለማን፣ ምን ያህልና መቼ እንደተሰጠ የዞን/ወረዳ አስተዳደር እርሻና
ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ/ጽ/ቤት የተሟላ መረጃ እንደሚኖራቸው ይታወቃል፡፡ ከነዚህ መሥሪያ
ቤቶች የተሟላ የግብዕት ዕዳ መረጃ በዝርዝር ለነባሩ ዞን/ወረዳ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ/ጽ/ቤት መስጠት
አለበት፡፡ ነባሩ ዞን/ወረዳ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ/ጽ/ቤት ከእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ሴክተር በየ ቀበሌ
የሚገኘውን መረጃ ከወሰደ በኋላ (መረጃው ከተገኘ በኋላ)፡-

14
1) በአዲሱ ወረዳ አስተዳደር ሥር የሚገኙ የቀበሌዎች የግብዕት ዕዳ በአዲሱ ወረዳ አስተዳደር
እንዲመዘገብ ዝርዝር መረጃው ሲተላልፍ በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ (Journal Voucher) ላይ፡-
ዴቢት የተጣራ ሀብት(5601) እና ክሬዲት የግብዕት ተሰብሳቢ ሂሳብ (4273) አድርጎ ሂሳቡን
በመመዝገብ መረጃውን ለአዲሱ ወረዳ/ዞን ማተላለፍ አለበት፡፡
2) አዲሱም ወረዳ አስተዳደር ከነባሩ ወረዳ አስተዳደር የተቀበለው ዝርዝር የግብዕት ዕዳ (ተሰብሳቢ ሂሳቦችን)
የሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ (Journal Voucher) ኮፒዎች በማያያዝ፡- ዴቢት በእያንዳንዱ ሰው ተሰብሳቢ
ሂሳቦች (4273) እና ክሬዲት የተጣራ ሀብት (5601) አድርጎ መመዝገብ አለበት፡፡ በአዲስ ወረዳ
አስተዳደር መረጃውን አደራጅቶ በማስቀመጥ ከግብዕት የሚሰበሰበው ገንዘብ አጠቃቀምን በተመለከተ
ከዚህ በፊት ከቢሮ የተላለፈውን ሰርኩላር መነሻ በማድረግ ይሆናል፡፡
17. ባለቤት የሌላቸዉ ተሰብሳቢ ሂሳቦችን በተመለከተ፣
በነባሩ ዞን/ወረዳ አስተዳደር ሳይወዳደቁ ለዘመናት እየተንከባለሉ የቆዩና ባለቤታቸው የማይታወቁ
ተሰብሳቢ ሂሳቦች ወደ አዲሱ ዞን/ወረዳ አስተዳደር ማስተላለፍ ሳያስፈልግ በመጀመሪያ በነበሩበት
ነባር የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች ተመዝግቦ እንዲያዙ በማድረግ ለወደፊቱ መረጃውን
በአግባቡ በማደራጀት በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሂሳብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 6/2004
በሚደነግገው መሠረት ሊሰበሰቡ የማይችሉትን ሂሳቦች ከመዝገብ እንዲሰረዝ (Write-Off)
የተቀመጠውን የአሰራር ሥርዓት ተከትሎ የማስተካከያ እርምጃ መወሰድ አለበት፡፡

15
18. የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ተሰብሳቢ ሂሳብን በተመለከተ፡-
የጥሬ ገንዘብ ጉድለት በውስጥ ወይም በውጭ ኦዲተሮች ማረጋገጥ አለበት፡፡ የጥሬ ገንዘብ ጉድለት
ከግለሰቦች ተመላሽ መደረግ ያለበት ገንዘብ በመሆኑ የጥሬ ገንዘብ ጉድለት የታየበት የሥራ ቦታዎች
መለየት አለባቸው (ለምሳሌ የአንድ ትምህርት ቤት፣ የአንድ ጤና ጣቢያ ቢሆን ገንዘቡ ተመላሽ ሲደረግ
ትምህረት ቤቱ ወይም ጤና ጣቢያ በሚገኝበት በአዲሱ ወረዳ አስተዳደር ተመዝግበው በመያዝ ለወደፊት
ገንዘቡ ተመላሽ ሲደረግ አሳውጆ መጠቀም ስለሚቻል የሂሳብ ምዝገባው እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
1) የነባሩ ወረዳው አስተዳደር የሂሳብ ምዝገባ ዴቢት የተጣራ ሀብት (5601) እና ክሬዲት የጥሬ
ገንዘብ ጉድለት ተሰብሳቢ (4202) ሆኖ መመዝገብ አለበት፡፡
2) የአዲሱ ወረዳ/ዞን አስተዳደር የሂሳብ ምዝገባም ዴቢት የጥሬ ገንዘብ ጉድለት የተሰብሳቢ ሂሳብ
(4202) እና ክሬዲት የተጣራ ሀብት (5601) አድርጎ ሂሳቡ በአግባቡ ተመዝግቦ መያዝ አለበት፡፡
3) የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ያለበት ባለሙያ/ገንዘብ ያዥ በአዲሱ ወረዳ አስተዳደር በዝዉዉር የሚመደብ
ከሆነ ጉድለቱ ያጎደለ ገንዘብ ያዥ/ባለሙያ በሚገኝበት ወረዳ አስተዳደር ሂሳቡን መዝግቦ በመያዝ
የጎደለዉ ጥሬ ገንዘብ ሲሰበሰብ በአዲሱ ወረዳ አማካይነት ለሚመለከታቸዉ አካላት ማተላለፍ
አለበት ወይም የአሰራር ሥርዓትን ተከትሎ አሳውጆ በሥራ ላይ መዋል አለበት፡፡

ምዕራፍ ሦስት
ተከፋይ ሂሳቦች
19. ስለ ተከፋይ ሂሳቦች መረጃ አያያዝ፣ አስተዳደር እና ክፍፍል በተመለከተ፤
1) የተከፋይ ሂሳቦች መረጃ በግለሰብ፣ በድርጅት እና በመሥሪያ ቤቶች ስም በአግባቡ ተለይቶ በዝርዝር
ተደራጅቶ መቅረብ አለበት፡፡
2) ተለይቶ በዝርዝር የተያዘውን የተከፋይ ሂሳብ መረጃዎች መነሻ በማድረግ ለሚመለከታቸዉ አካላት
በነባሩ ዞን/ወረዳ አስተዳደር መከፈል አለበት፡፡
3) ነባሩ ወረዳ አስተዳደር እርከን ለሦስተኛ ወገን መክፈል የነበረበት የተከፋይ ሂሳቦች በወቅቱ
በመክፈል ከዕዳ ነፃ መሆን የነበረበት ቢሆንም በወቅቱ የውስጥ ገቢን በመሰብሰብ በተፈቀደው
በጀት መሠረት ጥሬ ገንዘብ መጠቀም ሲገባው በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት መተላለፍ
የነበረበት የተከፋይ ሂሳብ ጥሬ ገንዘብ በሥራ ላይ በማዋሉ ምክንያት ውዝፍ ተከፋይ ሂሳብ ካለ
በ 2011 በጀት ዓመት በጀት ላይ ዕዳውን በጋራ በነባሩ ወረዳ/ዞን አስተዳደር አማካይነት ክፍያ
በመፈፀም የቀሪውን በጀት ድልድል መደረግ አለበት፡፡ የተከፋይ ሂሳቦችም የወጪ መጋራት፣
የጡረታ መዋጮ የ 2%፣ ሌሎች ከፔይሮሉ ተቀናናሽ … ወዘተ ናቸዉ፡፡
20) የግለሰብ ተከፋይ ሂሳቦች ተጣርቶ ጥሬ ገንዘብ መኖሩን በማጣራት በነባሩ ወረዳ/ዞን ክፍያው ለግለሰቦቹ
ተፈፅሞ ሚዛኑ ዜሮ መሆን አለበት፡፡

16
21) ከ 2011 በጀት ዓመት በጀት ተቀንሶ የሚተካ የጥሬ ገንዘብ ብድር በ 2010 በጀት ዓመት ተወስዶ አዲሱ
ወረዳ/ዞን አስተዳደር እርከን እስኪቋቋም ድረስ ያልተከፈለ ተከፋይ ሂሳብ ለአዲሱ ወረዳ/ዞን አስተዳደር
እርከን በሚደርሳቸው በጀት ድርሻ መጠን በ 2011 በጀት ዓመት መተካት ያለበት በመሆኑ፡
1) ነባሩ ወረዳ/ዞን የሂሳብ ምዝገባ በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ ላይ ዴቢት ተከፋይ ሂሳብ (5024/5027)
ክሬዲት የተጣራ ሀብት (5601) በማድረግ ምዝገባ በማከናወን የተሟላ ዝርዝር መረጃ ለአዲሱ
ወረዳ/ዞን አስተዳደር መላክ አለበት፡፡
2) አዲሱ ወረዳ/ዞን አስተዳር ከነባር ወረዳ/ዞን አስተዳደር የተላከውን የጥሬ ገንዘብ ብድር መረጃ መነሻ
በማድረግ ሂሳቡን በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ (Journal Voucher) ላይ ዴቢት የተጣራ ሀብት (5601)
እና ክሬዲት የጥሬ ገንዘብ ብድር ተከፋይ (5024/5027) አድርጎ መረጃውን በመንግሥት ሂሳብ
አያያዝ ሥርዓት መሠረት መመዝገብና ማወራረስ አለበት፡፡
22) ከካፒታል ፕሮጀክቶች ግንባታ ሥራዎች ጋር በተያያዘ የሚኖር ተከፋይ (ሪቴንሽን) ሲኖር ሂሳቡ
ተመዝግቦ መያዝ ያለበት የካፒታል ፕሮጀክቶች በሚገኙበት ወረዳ መሆን አለበት፡፡ በመሆኑም ተከፋይ
ሂሳቡ ተመዝግቦ መያዝ ያለበት፡፡
1) በአዲሱ ወረዳ/ዞን አስተዳደር እርከን ከሆነ የነበሩ ወረዳ ሂሳብ በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ (Journal
Voucher) ላይ ዴቢት የተከፋይ ሂሳብ (5061) እና ክሬዲት የተጣራ ሀብት (5601) ሆኖ በነባሩ
ወረዳ/ዞን አስተዳደር ሂሳቡ መመዝገብ አለበት፡፡
2) የአዲሱ ወረዳ/ዞን አስተዳደር የሂሳብ ምዝገባ ዴቢት የተጣራ ሀብት (5601) እና ክሬዲት 5061 ተደርጎ
በአዲሱ ዞን/ወረዳ አስተዳደር ሂሳቡ መመዝገብ አለበት፡፡
3) ይህ ተከፋይ ሂሳብ ወደ አዲሱ ወረዳ/ዞን አስተዳደር እንዲተላለፍ ሲደረግ ክፍያዎች በሚፈፀሙበት
ጊዜ በባንክ የተቀመጠ የሪቴንሽን ጥሬ ገንዘብ ወደ አዲስ ወረዳ/ዞን አስተዳደር ባንክ አካውንት ገቢ
መደረግ አለበት፡፡ በዚህ ሁኔታ የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ሲፈፀም ማከናወን ያለበት የሂሳብ ምዝገባ ዴቢት
ተከፋይ ሂሳብ(5061) እና ክሬዲት የባንክ ሂሳብ (4103/4105) ተደርጎ የሚመዘገብ ይሆናል፡፡
4) የአዲሱ ወረዳ/ዞን አስተዳደር የሂሳብ ምዝገባ ከነባሩ ወረዳ/ዞን አስተዳደር የተላከውን የጥሬ ገንዘብ
ዝውውር የባንክ ደብዳቤና ባንክ ገቢ የተደረገበት የክሬዲት አድቫይስ መነሻ በማድረግ ዴቢት ባንክ ያለ
ገንዘብ (4103/4105) እና ክሬዲት የተከፋይ ሂሳብ 5061 ተደርጎ መመዝገብ አለበት፡፡
5) ከካፒታል ፕሮጅክቶች ተቀንሶ የቆየዉ ሪቴንሽን ገንዘብ በ 2011 በጀት ዓመት ክፍያዉ አዲስ
በተቋቋሙ ዞኖችና ወረዳ አስተዳደር የሚፈፀም ከሆነ ለክፍያዉ የሚያስፈልግ ጥሬ ገንዘብ የ 2011
በጀት ዓመት በጀት ድልድል ሲደረግ ታሳቢ መደረግ አለበት፡፡
6) እስከአሁን ድረስ ከ 2011 በጀት ዓመት በፊት ለዘመናት እየተንከባለሉ ረዥም ዘመናትን ያስቆጠሩና
ባለቤት የሌላቸዉ የተከፋይ ሂሳቦች በነባሩ የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች ባሉበት ተደራጅት
እዲቀመጡ በማድረግና መረጃዉን በአግባቡ በማጣራት የማስተካከያ እርምጃ ሊወሰድባቸዉ ይገባል፡፡

17
ምዕራፍ አራት
የጥሬ ገንዘብና የተጣራ ሀብት
23. የጥሬ ገንዘብ አያያዝ አስተዳደርና ክፍፍል በተመለከተ፤
1) ከ 2011 በጀት ዓመት በፊት የተጠራቀመ የተጣራ ሀብት በነባሩ ወረዳ/ዞን አስተዳደር ሲኖር
ወደፊት እንደሚታወጅ ታሳቢ በማድረግ በ 2011 በጀት ዓመት የነበረዉን የአሰራር ሥርዓትን
ተከትሎ ታዉጆ በሥራ ላይ እንዲዉል ለማድረግ ለአዲሶቹ ወረዳዎች በሚደርሰው በጀት ድርሻ
መጠን በማከፋፈል ፍትሀዊ በሆነ መንገድ እንዲጠቀሙ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዚሁ
ሁኔታ ከነበረው የተጣራ ሀብት ለአዲሱ ወረዳ/ዞን አስተዳደር የጥሬ ገንዘብ ሲተላለፍ የነባሩ
ወረዳ/ዞን አስተዳደር የሂሳብ ምዝገባ የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ደብዳቤና የባንክ ዴቢት አድቫይስ
መነሻ በማድረግ ዴቢት የተጣራ ሀብት (5601) እና ክሬዲት ባንክ ያለ ገንዘብ (4103/4105) ተደርጎ
መመዝገብ አለበት፡፡
2) አዲሱ ወረዳ/ዞን ከነባሩ ወረዳ/ዞን የተላከውን የጥሬ ገንዘብ ዝውውር የባንክ ደብዳቤ እና ባንክ ገቢ
የተደረገበት የባንክ ክሬዲት አድቫይስ መነሻ በማድረግ ዴቢት ባንክ ያለዉ ገንዘብ(4105/4103)እና
ክሬዲት የተጠራ ሀብት በማድረግ መመዝገብ አለበት፡፡ በዚሁ ሁኔታ ከነባሩ ዞን/ወረዳ አስተዳደር
ወደ አዲሱ ዞን/ወረዳ አስተዳደር የተላከዉን ገንዘብ በነባሩ ወረዳ አስተዳደር ስም የ 2010 በጀት
ዓመት የነባሩ ዞን/ወረዳ አስተዳደር ሂሳብ ሲዘጋ የሚኖረው የተጣራ ሀብት ሚዛን በቢሮ ሲረጋገጥ
አሳውጆ መጠቀም የሚቻል ይሆናል፡፡

24) አዲስ የተቋቋሙ የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች በ 2011 በጀት ዓመት የተፈቀደዉን በጀት መነሻ
በማድረግ የጥሬ ገንዘብ ገቢና ወጪ ዕቅድ በማዘጋጀት መጠቀም አለባቸዉ፡፡ በነባሩ የዞንና የወረዳ
አስተዳደር እርከኖች እስከአሁን ተጠራቅሞ የሚገኝ የተጣራ ሀብት (ጥሬ ገንዘብ) የማዘጋጃ ቤት
እንዲሁም የጤና ተቋማት እና የትምህርት ተቋማት ከሆነ ያለ አንድ ቅድመ ሁኔታ ጥሬ ገንዘቡ አሁን
ማዘጋጀ ቤትና የጤናና የትምህርት ተቋማት በሚገኙበት ወረዳ የአሰራር ሥርዓትን ተከትሎ ታዉጆ
በሥራ ላይ መዋል አለበት፡፡

ምዕራፍ አምስት
የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ አያያዝና አጠባበቅ
25). በነባሩ የዞንና የወረዳ አስተዳደር የመረጃ አያያዝና አጠባበቅ፣
1) በ 2011 በጀት ዓመት በክልሉ ምክር ቤት ዉሳኔ መሠረት አዲስ የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች
ሲቋቋሙ በነባሩ የዞንና የወረዳ አስተዳደር ፋይናንስና እኮኖሚ ልማት መምሪያ/ጽ/ቤት የሚገኙ
የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር መረጃዎች በአመቺ ቦታ በአግባቡ መያዝና መጠበቅ አለበት፡፡

18
2) አዲሶቹና ነባሮቹ የአስተዳደር እርከኖች አዲስ የተቋቋሙና የሚቋቋሙ የዞንና ወረዳ አስተዳደር
እርከኖች በሀብት ድልድልና ክፍፍል አሰራር መመሪያ መሠረት የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር
መረጃዎችን ክፍፍል ከተደረገ በኃላ በነባሮቹ የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከን በዉስጥ ወይም
በዉጭ ኦዲተሮች ኦዲት ተደርጎ አዲስ የተቋቋሙት የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች
የሚመለከታቸዉ የተከፋይና የተሰብሳቢ ሂሳቦች ቢገኙ በተደረገዉ በሀብት ድልድልና ክፍፍል
አሰራር መመሪያ መሠረት አዲሶቹ የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች የሚደርሳቸዉን ዕዳ
የሚከፍሉ ወይም የሚቀበሉ ይሆናሉ፡፡
26) የመንግሥት የሂሳብ መረጃ አያያዝና የሪፖርት ዝግጅትና አቀራረብ፣
1) አዲስ የተቋቋሙ የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች ከነበሩ ዞንና ወረዳ የተገኘዉን የመንግሥት
ፋይናንስ መረጃዎችን መነሻ በማድረግ ሂሳባቸዉን የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚጠቀሙትን
በጥሬ ገንዘብ ላይ የተመሰረተዉን የተሻሻለዉን የሂሳብ አያያዝ ሥርዓትን በመጠቀም መመዝገብ
አለባቸዉ፡፡ ሥራቸዉንም ከጀመሩበት ከጥር 1 ቀን 2011 ዓ/ም ጊዜ አንስቶ በመንግሥት
መሥሪያ ቤቶች የሂሳብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 6/2004 መሠረት የተሟላ የሂሳብ ሪፖርታቸዉን
አዘጋጅቶ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
2) አዲስ የተቋቋሙ የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች የ 2011 በጀት ዓመት የበጀት ድርሻቸዉን፣
የሂሳብ መረጃዎችና እና ንብረት አግኝቶ ሥራቸዉን በአግባቡ ከመጀመራቸዉ በፊት እስከ ታህሳስ
30 ቀን ድረስ ያለዉን የሂሳብ ሪፖርቶችን በመንግሥት መ/ቤት ሂሳብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር
6/2004 መሠረት ነባሮቹ የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች በአንድ ላይ የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡

ምዕራፍ ስድስት
ህትመቶችና ሌሎች የሂሳብ ሰነዶች
27) የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የደረሠኞችና የሌሎች የህትመት አያያዝ፣ አስተዳደርና ክፍፍል፤
የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የመንግሥት ገንዘብና ንብረት የሚያንቀሳቅሱበት የተለያዩ ደረሰኞችና ሌሎች
ህትመቶች አያያዝና የአጠቃቀም ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ግልጸኝነት
በመፍጠር አግባብነት ያለውን ጥበቅና ጠንካራ የቁጥጥርና የክትትል ሥርዓት በመዘርጋት ለሚፈጠሩ የጥፋትና
የማጭበርበር ተግባር የተጠያቂነት አሰራር ሥርዓት በሥራ ላይ ለማዋል እንዲቻል በክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ
ልማት ቢሮ እውቅና በመስጠት ለታተሙት የገቢ ደረሰኞች፣ የክፍያ ሰነዶች እና የሌሎች የህትመት አያያዝ፣
አጠባበቅ እና አስተዳደር በተመለከተ መመሪያ ቁጥር 27/2010 ወጥተው በሥራ ላይ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም
የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የደረሰኞችና የሌሎች የህትመት አያያዝ፣ አጠባበቅ፣ አስተዳደር በወጣው
በመመሪያ ቁጥር 27/2010 የሚፈፀም ሆኖ አዲስ ለተቋቋሙ ዞኖችና ወረዳዎች የሚደረገውን የገቢና የወጪ
ደረሰኞች እና የሂሳብ ምዝገባ ማዛዣ አያያዝ፣ አስተዳደር እና ክፍፍልን በተመለከተ፡-
1) ገቢ ደረሰኞችን በተመለከተ፣

19
1) ነባሩ የዞንና የወረዳ አስተዳደሮች ከክልሉ ፋ/ኢ/ል/ቢሮ በህጋዊ መንገድ ወጪ አድርጎ በመውሰድ
በወረዳው ንብረት ክፍል ገቢ የተደረጉ የገቢ ደረሰኞች በዓይነትና በንምራ ቁጥር በዝርዝር
በመመዝገብ መረጃውን አደራጅቶ መያዝ አለበት፡፡
2) በነባር ወረዳ ንብረት ክፍል በሞ/19 ገቢ ከተደረጉት የገቢ ደረሰኞች ውስጥ ወጪ ባደረጉት
በሠራተኞችና መሥሪያ ቤቶች ስም በደረሰኞቹ ዓይነትና በንምራ ቁጥር መረጃውን ለይተው
በመመዝገብ አደራጅቶ መያዝ አለበት፡፡
3) ወጪ ያደረጉት ሠራተኞች በነባሩ ወረዳ/ዞን ሥር በሚገኙት መንግሥት መ/ቤቶች (ጤና
ጣቢያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች …. ወዘተ) የሚገኙ ከሆኑ የወሰዱት የገቢ
ደረሠኞች ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገባቸው በነበሩበት ሁኔታ በመንግሥት መ/ቤቶች
የደረሰኞና የሌሎች የህትመት አያያዝና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 27/2010 መሠረት በሥራ
ላይ እንዲውሉ ይደረጋሉ፡፡
4) የገቢ ደረሰኞች የወሰዱ ሠራተኞች አዲስ ወደተቋቋሙ ዞን/ወረዳ በዝውውር የሚሄዱ ከሆኑ
የገቢ ደረሰኙን ከወሰደበት ጊዜ ጀምሮ የሰበሰቡት ገንዘብ በአግባቡ ወደሚመለከታቸው
አካላት/ባንክ አካውንት/ ገቢ መደረጉንና ገቢ ስለማድረጋቸው ህጋዊ ሰነድ መኖሩን በውስጥ
ኦዲተሮች ተረጋግጦ በተደረሰበት ገቢ ደረሰኝ ገጽ ጀርባ ላይ በውስጥ ኦዲተሮች ምልክት ተደርጎ
ወጪ ሆኖ ወደ ተሰጠበት ንብረት ክፍል ተመላሽ መደረግ አለበት፡፡ ገቢ ያልተደረገ ገንዘብ ካለም
ወደ ነባሩ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት መደበኛ ባንክ አካውንት ገቢ መደረግ አለበት፡፡
28) የገቢ ደረሰኝ ከነበሩ ወረዳ/ዞን የወሰዱ ሠራተኞች አዲስ በተቋቋመው ወረዳ/ዞን ሥር በሚገኙ ጤና
ጣቢያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች እና ሌሎችም ተቋማት ውስጥ ተመድበው የሚገኙ
ከሆኑ በወሰዷቸው በገቢ ደረሰኝ ዓይነትና ንምራ ቁጥር በዝርዝር መረጃ ተይዞ፡-
1) ገቢ ተሰብስቦበት የተጠናቀቁ የገቢ ደረሠኞችና የተሰበሰበው ገንዘብ በሙሉ በአግባቡ በህጋዊ
መንገድ በነባሩ ወረዳ/ዞን ባንክ አካውንት ገቢ ተደርጎ ህጋዊ ሰነድ መኖሩን በማረጋገጥ
የተሰራባቸው ደረሰኞች ወደ ነባሩ ወረዳ/ዞን ንብረት ክፍል ተመላሽ ማድረግ አለበት፡፡ ወደ
ንብረት ተመላሽ በሚደረግበት ጊዜ በውስጥ ኦዲተሮች ተረጋግጦ ምልክት መደረግ
አለባቸው፡፡
2) ያልተጠናቀቁ የገቢ ደረሰኞች ካሉ ገቢ የተሰበሰበባቸው የገቢ ደረሰኝ ቅጠሎች (ገጾች) ተቆጥሮ
የተሰበሰበው ገቢ ወደ ነባር ወረዳ/ዞን ባንክ ገቢ መደረጉን በውስጥ ኦዲተሮች ተረጋግጦ
ደረሰኞች አዲስ ወረዳ/ዞን በተቋቋሙት ወረዳ/ዞን ሥር በሚገኙ መንግሥት ተቋማት ባሉበት
እንዲቀጥሉ ነባሩና አዲሱ ወረዳ/ዞን የነባሩ ወረዳ/ዞን የውስጥ ኦዲተሮችና ሌሎች
የሚመለከታቸው አባላት ማለትም (አስረካቢ፣ ተረካቢ እና አረካካቢዎች) በተገኙበት ርክክብ
መፈፀም አለበት፡፡

20
29) ገቢ ያልተሰበሰበባቸው የገቢ ደረሰኞች በሚገኙበት መንግሥት መ/ቤት ስም ለወደፊቱ በሥራ ላይ
እንዲውሉ ነባሩና አዲሱ ዞን/ወረዳ አማካይነት አስረካቢ፣ ተረካቢ እና አረካካቢ በተገኙበት
በማፈራረም የገቢ ደረሰኞችን በንምራ ቁጥር በመመዝገብና የሚገኙበት የመንግሥት ተቋማት
በመጥቀስ በሥራ ላይ እንዲውሉ መደረግ አለበት፡፡

30) የክፍያ ሰነዶችንና የሂሳብ ምዝገባ ማዘዣን በተመለከተ

1) ነባሩ ወረዳ/ዞን ከክልል ፋ/ኢ/ል/ቢሮ በህጋዊ መንገድ በሞ/22 ፈርሞ የወሰዳቸውን የክፍያ ሰነዶችና
የሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ መረጃውን በዓይነትና በንምራ ቁጥር በዝርዝር መዝግቦ መያዝ አለበት፡፡
2) በነባሩ ወረዳ/ዞን ንብረት ክፍል በሞ/19 በዓይነትና በንምራ ቁጥር ገቢ ከተደረጉት የክፍያ ሰነድና
የሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ ውስጥ አዲስ በተቋቋሙ ወረዳ/ዞን ሥር በሚገኙ ተቋማት ሥር (ጤና
ጣቢያ፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች እና ሌሎችም) እጅ የሚገኙትን (የተሰራባቸው፣
የተጠናቀቁ እና ያልተሰራባቸው) በሙሉ ባለበት ሁኔታ እንዲቀጥሉ የነበሩና የአዲሱ ዞን/ወረዳ
የሚመለከታቸው አካላት (አስረካቢ ተረካቢ እና አረካካቢዎች) በሚገኙበት ርክክብ መፈፀም
አለበት፡፡ ነባሩና አዲሱ ዞን/ወረዳ ለክትትልና ቁጥጥር መረጃው አደራጅቶ በአግባቡ መያዝ
አለባቸው፡፡

ምዕራፍ ሰባት
የመንግሥት ንብረት
31) የመንግስት ንብረት አያያዝ ፣አስተዳደር እና ክፍፍል አሰራር ሥርዓትን በተመለከተ

1. በየደረጃው ያለው የአስተዳደር እርከኖች ወደ ንብረት ክፍፍሉ ዝርዝር አስራር ከመገባቱ በፊት በነባሩ
ዞን/ልዩ ወረዳ ወይም ወረዳ አስተዳደር ሥር በተደራጀ እያንዳንዱ አስፈፃሚ መ/ቤት፡-

1) ንብረት ክፍል ውስጥ የሚገኙትን አላቂ ንብረቶች በዝርዝር ቆጥሮ መዝግቦ መያዝ ማለትም
የንብረቶቹን ዓይነት፣ ብዛት፣ ያንዱን ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ማወቅ፣
2) ንብረት ክፍል ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቋሚ ንብረቶች ወደፊትም አገልግሎት የሚሰጡትን
አገልግሎት ከማይሰጡት በመለየት በዝርዝር ቆጥሮ መዝግቦ መያዝ ማለትም የቋሚ ንብረቱን
ዓይነት፣የተገዛበትን ጊዜ፣ የተገዛበትን ዋጋ፣ የተጠራቀመ የዕርጅና ቅናሽ ተቀንሶ ያለው የመዝገብ
ዋጋ፣ ንብረቱ የሚገኝበት ደረጃ መዝግቦ መረጃ መያዝ፣
3) ውስጥ በሚገኙ ሠራተኞች ለመ/ቤቱ ሥራ አገልግሎት በስማቸው ወጪ ተደርገው በሠራተኞቹ
እጅ የሚገኙትን ቋሚ ንብረቶች በንብረት ክፍል ውስጥ ከሚገኘው በሠራተኛው ሥም ወጪ
የተደረጉ ቋሚ ንብረቶችን መመዝገቢያና መቆጣጠሪያ ካርድ /UC/ ላይ መረጃ በመውሰድ

21
እያንዳንዱ ሠራተኛ በእጁ የሚገኙትን ቋሚ ንብረቶች መ/ቤቱ ድረስ በአካል ይዞ እንዲቀርብ
በማድረግ በዝርዝር ቆጥሮ መዝግቦ መያዝ ማለትም የቋሚ ንብረቱን ዓይነት፣ ሞዴል፣
የተገዛበትን ጊዜ፣ የተገዛበትን ዋጋ፣ የተጠራቀመ የዕርጅና ቅናሽ ተቀንሶ ያለው የመዝገብ ዋጋ፣
ንብረቱ የሚገ"በት ደረጃን መዝግቦ መረጃ መያዝ፣
4) ውስጥ የሚገኙ ሙሉ በሙሉ በአላቂም ሆነ በቋሚ ንብረት ትርጉም ውስጥ የማይካተቱትን
ንብረቶች በዝርዝር ቆጥሮ መዝግቦ መያዝ ማለትም የንብረቱን ዓይነት፣የተገዛበትን ጊዜ፣
የተገዛበትን ዋጋ፣ ንብረቱ የሚገኝበት ደረጃን መዝግቦ መረጃ መያዝ፣
5) ንብረት ክፍል ውስጥም ይሁን ከንብረት ክፍል ውጪ በሠራተኛ እጅ ሆነው አገልግሎት የማይሰጡና
ሊወገዱ የሚገባቸውን ንብረቶች አገልግሎት ከሚሰጡት ለይቶ ለብቻ በዝርዝር ቆጥሮ መዝግቦ
መያዝ ማለትም የንብረቶቹን ዓይነት፣ የሚወገድበትን ምክንያት፣ የሚገኝበት ደረጃን መዝግቦ
መረጃ መያዝ፣
6) ወደ ንብረት ክፍፍሉ ከመገባቱ በፊት በነባሩ ዞን/ልዩ ወረዳ ወይም ወረዳ አስተዳደር ሥር በተደራጀ
እያንዳንዱ አስፈፃሚ መ/ቤት ይዞታ ሥር ያሉ ሊወገዱ የሚገባቸው ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ
አግባብ በሆነው ንብረት ማስወገጃ መንገድ ንብረቶቹን ማስወገድ፣ በሽያጭ የተወገደ ከሆነ
የተሰበሰበውን ገቢ ለነባሩ አስተዳደር የፋይናንስ ፑል ገቢ ማድረግ፣
2. በነባር ዞን/ልዩ ወረዳ ወይም ወረዳ አስተዳደር ሥር በተደራጁ አስፈፃሚ መ/ቤቶች ይዞታ ሥር የነበሩ
ንብረቶችን መረጃ ከዚህ በላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 በተዘረዘሩት ሁኔታ በዝርዝር ለይቶ ከተያዘ በኋላ ፡-

1) ከነባር ዞን አስተዳደር በመውጣት አዲስ ዞን አስተዳደር ሆኖ ለተደራጀ መዋቅር የሚደረገው የንብረት

ክፍፍል በነባሩ ዞን ሥር የተደራጁ አስፈፃሚ መ/ቤቶች ይዞታ ሥር ተገኝተው ከላይ ከተራ ቁጥር

31.1 እስከ 31.6 ባሉት አግባቦች የተቆጠሩትን ንብረቶች ከየዓይነቱ ቀደም ሲል በነበረው የዞን

አስተዳደር ሥር በነበሩ ወረዳዎች ልክ ፍትሀዊ በሆነ ሁኔታ በአዲሱ ዞን ሥር ለሚደራጁት አስፈፃሚ

መ/ቤቶች መደልደል፣

2) በነባር ዞን አስተዳደር ሥር በወረዳ አስተዳደር ደረጃ የነበረና ከነባሩ ዞን በመውጣት አዲስ ዞን

አስተዳደር ሆኖ ለተደራጀ መዋቅር የሚደረገው የንብረት ክፍፍል በነባሩ ዞን ሥር የተደራጁ

አስፈፃሚ መ/ቤቶች ይዞታ ሥር ተገኝተው ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 ባሉት አግባቦች

የተቆጠሩትን ንብረቶች ከየዓይነቱ ቀደም ሲል በነበረው የዞን አስተዳደር ሥር ለነበሩ ወረዳዎች

ፍትሀዊ በሆነ ሁኔታ ከሚደለደለው የድርሻውን በአዲሱ ዞን ሥር ለሚደራጁት አስፈፃሚ መ/ቤቶች

መደልደል፣

22
3) ከነባር ወረዳ አስተዳደር በመውጣት ሁለት ወይም ሦስት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ አዲስ ወረዳ

አስተዳደር ሆኖ ለተደራጀ መዋቅር የሚደረገው የንብረት ክፍፍል በነባሩ ወረዳ ሥር የተደራጁ

አስፈፃሚ መ/ቤቶች ይዞታ ሥር ተገኝተው ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 ባሉት አግባቦች

የተቆጠሩትን ንብረቶች ከየዓይነቱ ቀደም ሲል ለነበረውና አዲስ ለተዋቀሩት የወረዳ አስተዳደር ሥር

ለሚዋቀሩት አስፈፃሚ መ/ቤቶች ፍትሀዊ በሆነ ሁኔታ መደልደል፣


4) በነባሩ የዞን/የልዩ ወረዳ ወይም የወረዳ አስተዳደር ይዞታ ሥር የነበሩ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች
እስከአሁን ያለው የተጠራቀመ የዕርጅና ቅናሽ ተቀንሶ የሚቀረው የመዝገብ ዋጋ ለአዳዲሶቹ የዞን
ወይም የወረዳ አስተዳደሮች በሚደርሳቸው ልክ በገንዘብ ወይም በአይነት መካፈል ይኖርበታል፡፡
የዚህም አፈጻጸም አዲስ የተቋቋሙ፣ እና ነባሮቹ የአስተዳደር እርከኖች መካከል በሚደረግ ስምምነት
የሚፈፀም ይሆናል፡፡
5) በነባሩ የዞን/የልዩ ወረዳ ወይም የወረዳ አስተዳደር ቀደም ሲል በግብረ ሰናይ ድርጅቶች ለተወሰኑ
አካባቢዎች ህብረተሰብ አገልግሎት እንዲሰጡ ታስቦ ለህብረተሰቡ በስጦታ የተሠጡ ንብረቶች
አካባቢው ለተካለለበት የዞን ወይም የወረዳ አስተዳደሮች መደልደል ይኖርበታል፡፡
3. ነባሮቹ የዞን/የልዩ ወረዳ ወይም የወረዳ አስተዳደሮች ለአዲሶቹ የዞን ወይም የወረዳ አስተዳደሮች ተደልድሎ
የደረሳቸውን ንብረቶች በሞዴል 22 ወጪ አድርገው ከነሙሉ የንብረቶቹ መረጃ ጋር ለአዲሶች ማስረከብ
አለባቸው፡፡
4. አዲሶቹም የዞን ወይም የወረዳ አስተዳደሮች በፋይናንስ ፑሎቻቸው ውስጥ በየአስፈፃሚ መ/ቤቶቹ ስም
የንብረት ገቢ መቀበያ ደረሰኝ፣ የንብረት ወጪ ማድረጊያ ደረሰኝ፣ ቢን ካርድ፣ ስቶክ ካርድ፣ በሠራተኛ ስም
ወጪ የሚደረግ ቋሚ ንብረት መመዝገቢያ ካርድ /UC/ እና አጠቃላይ የቋሚ ንብረት መመዝገቢያ ካርድ
/FAR/ አቋቁመው ምዝገባ መጀመር አለባቸው፡፡

ምዕራፍ ሥምንት

ተግባርና ኃላፊነት

32) አዲስ በተቋቋሙ ዞኖችና ወረዳዎች ሀብት ድልድልና ክፍፍል ላይ የፋ/ኢ/ል/ቢሮ፣ መምሪያዎች እና
ጽ/ቤቶች ተግባርና ኃላፊነት
1. የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ተግባርና ኃላፊነት፡-
1) የሀብት ድልድልና ክፍፍል አሰራር መምሪያ ያዘጋጀል፤ ያሰራጫል አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡
2) የሀብት ድልድልና ክፍፍል ሥራዎች በሚተገበሩበት ጊዜ የድጋፍና ክትትል ሥራዎች ያከናውናል፡፡

23
3) የሀብት ድልድልና ክፍፍል በሚደረግበት ወቅት ቅሬታዎች ቢኖሩ ጉዳዩን በአግባቡ በማጣራት
የመጨረሻ ዉሳኔ ይሰጣል፡፡
4) በሀብት ድልድልና ክፍፍል አሰራር መመሪያ ላይ ለሚመለከታቸው ለሴክተሩ ኃላፊዎችና
ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ይሰጣል፡፡
5) አዲስ ለተቋቋሙ ዞኖችና ወረዳዎች አዲስ የበጀት ስትራክቸር አዘጋጅቶ ይሰጣል፡፡
2. የዞን/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ተግባርና ኃላፊነት፡-
1) በቢሮ ተዘጋጅቶ በተላከው በሀብት ድልድልና ክፍፍል አሰራር መምሪያ መሠረት የ 2011 በጀት ዓመት
በዞን ለዞን ማዕከልና ለወረዳዎች የፀደቀውን በጀት በዓይነትና በፋይናንስ ምንጭ እና በየመሥሪያ ቤቶች
የተመደበውን የተሟላ በጀት መረጃ በማዘጋጀትና እንዲዘጋጅም በማድረግ መረጃዉን አደራጅቶ
ማስቀመጥ፤
2) እስከ ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ/ም ድረስ ሳይወዳደቅ በግለሰብ፣ በድርጅቶች እና በመንግሥት መ/ቤቶች ስም
የሚገኘውን የተሰብሳቢ ሂሳቦች በዕድሜ ዘመን መረጃውን በዝርዝር አደራጅቶ መያዝ፣
3) የሀብት ድልድልና ክፍፍል ከመደረጉ በፊት ከሐምሌ 1 ቀን 2010 ዓ/ም ጀምሮ ያለው የ 2011 በጀት
ዓመት ተሰብሳቢ ሂሳቦችን ማስረጃ ቀርቦ እንዲወዳደቁ በማድረግ ያልተወዳደቁ ተሰብሳቢ ሂሳቦችን
በዕድሜ ዘመን በዝርዝር መረጃውን አደራጅቶ መያዝ፣
4) ያልተከፈሉ የተከፋይ ሂሳቦች ካሉ ለሚመለከታቸው አካላት ክፍያ መፈፀም፣
5) ያልተከፈሉ ተከፋይ ሂሳቦች በዕድሜ ዘመን መረጃውን በዝርዝር መዝግቦ መያዝ፣
6) ሳይታወጅ እስከ አሁን ያለ ገንዘቦች ካሉ የተጠራቀመዉን የገንዘብ ምንጭ ሊያሳይ በሚችል ሁኔታ
መረጃውን አደራጅቶ መያዝ፣
7) የገቢ ደረሰኞች፣ የክፍያ ደረሰኞች፣ የሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ በንብረት ክፍል ወጪ አድርጎ የወሰዱ መስሪያ
ቤቶች /ተቋማት/፣ ወረዳዎች እና ሠራተኞች በንምራ ቁጥር ላይቶ በመመዝገብ መረጃውን አደራጅቶ
መያዝ፡፡
8) በአንድ ዞን ሥር አዲሱ ወረዳ ሲቋቋም ከሌሎች ወረዳዎች ተገንጥሎ የወጡ ቀበሌዎች ከየትኞቹ ነባር
ወረዳዎች እንደመጡና የቀበሌው የህዝብ ብዛት የሚያሳይ መረጃ መዝግቦ መያዝ፡፡
9) አዲሱ ዞን/ወረዳ እስከተቋቋሙበት ቀን ድረስ ከ 2011 በጀት ዓመት በጋራ የተከፈሉ ክፍያዎች በመለየት
መዝግቦ መረጃውን አደራጅቶ መያዝ፤
10) በ 2011 በጀት ዓመት ከልዩ ልዩ ገቢ የተሰበሰበ የገንዘብ መጠን በተቋማት በመለየትና ከቢሮ የተላለፈው
የድጎማ ገንዘብ መጠን መረጃው አደረጅቶ መያዝ፤
11) በ 2011 በጀት ዓመት ሊሰበሰብ የታቀደው የገቢ ዕቅድ (ከውስጥ ገቢ፣ ከማዘጋጃ፣ ከትምህርት እና ከጤና
ተቋማት) መረጃውን አደራጅቶ መያዝ፤
12) በየመሥሪያ ቤቱ የሚገኘውን ቋሚ ንብረት በአግባቡ መዝግቦ መረጃውን አደራጅቶ መያዝ፤

24
13) የዞን ማዕከል ባለሙያዎች አዲስ የተቋቋሙ ወረዳዎች ሥራዎችን በአግባቡ እስኪጀምሩ ጠንካራ
የድጋፍና የክትትል ስራዎችን ማከናወንና አፈጻጸሙን መከታተል፡፡
14) የመስከረም 30 ቀን 2011 ዓ/ም የተጠቃለለ የሂሳብ ሪፖርት የነባር ዞን/ወረዳ በሃርድ ኮፒና በሶፍት ኮፒ
የሂሳብ ሪፖርቶች ተዘጋጅቶ መረጃውን አደራጅቶ መያዝ፤
15) በአዲስ የተቋቋሙ የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች ስራዎቻቸዉን በአግባቡ እስከሚጀምሩበት ጊዜ
ድረስ ያለዉን የመንግሥት ፋይናንስ መረጃዎችን መነሻ በማድረግ ነባሩ የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከን
የተሟላ የሂሳብ ሪፖርታቸዉን ያቀርባሉ፡፡
3. የወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤቶች ተግባርና ኃላፊነት፡-
1) በቢሮ ተዘጋጅቶ በተላከው በሀብት ድልድልና ክፍፍል አሰራር መምሪያ መሠረት የ 2011 በጀት ዓመት ለነበሩ
ወረዳ የፀደቀውን በጀት በዓይነትና በፋይናንስ ምንጭ እና በየመሥሪያ ቤቶች የተመደበውን የተሟላ በጀት
መረጃ በማዘጋጀት አደራጅቶ ማስቀመጥ፤
2) እስከ ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ/ም ድረስ ሳይወዳደቅ በግለሰብ፣ በድርጅቶች እና በመንግሥት መ/ቤቶች ስም
የሚገኘውን የተሰብሳቢ ሂሳቦች በዕድሜ ዘመን መረጃውን በዝርዝር አደራጅቶ መያዝ፣
3) ከሐምሌ 1 ቀን 2010 ዓ/ም ጀምሮ ያለው የ 2011 በጀት ዓመት ተሰብሳቢ ሂሳቦችን ማስረጃ ቀርቦ
እንዲወዳደቁ በማድረግ ያልተወዳደቁ ተሰብሳቢ ሂሳቦችን በዕድሜ ዘመን በዝርዝር መረጃውን አደራጅቶ
መያዝ፣
4) ያልተከፈሉ የተከፋይ ሂሳቦች ካሉ ለሚመለከታቸው አካላት ክፍያ መፈፀም፣
5) ያልተከፈሉ ተከፋይ ሂሳቦች በዕድሜ ዘመን መረጃውን በዝርዝር መዝግቦ መያዝ፣
6) ሳይታወጅ እስከ አሁን ያለ ከገቢ ዕቅድ በላይ የተሰብሳበ ገቢ እና ሌሎች ገንዘቦች ካሉ የተጠራቀመዉ የገንዘብ
ምንጭ ሊያሳይ በሚችል ሁኔታ መረጃውን አደራጅቶ መያዝ፣
7) የገቢ ደረሰኞች፣ የክፍያ ደረሰኞች፣ የሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ በንብረት ክፍል ወጪ አድርጎ የወሰዱ መስሪያ
ቤቶች /ተቋማት/ እና ሠራተኞች በንምራ ቁጥር ላይቶ በመመዝገብ መረጃውን አደራጅቶ መያዝ፡፡
8) አዲሱ ወረዳ ሲቋቋም የሚገኙ ቀበሌዎች ከየትኞቹ ነባር ወረዳዎች ተገንጥሎ እንደመጡና የቀበሌው
የህዝብ ብዛት የሚያሳይ መረጃ መዘጋጀትና አደረጅቶ መያዝ፣
9) አዲሱ ወረዳ እስከተቋቋሙበት ቀን ድረስ ከ 2011 በጀት ዓመት የተከፈሉ ክፍያዎች በመለየት መረጃውን
አደራጅቶ መያዝ፤
10) በ 2011 በጀት ዓመት ከውስጥ ገቢ የተሰበሰበ የገንዘብ መጠን በተቋማት በመለየትና ከቢሮ የተላለፈው
የድጎማ ገንዘብ መጠን መረጃው መዝግቦ መያዝ፤
11) በ 2011 በጀት ዓመት ሊሰበሰብ የታቀደው የገቢ ዕቅድ (ከውስጥ ገቢ፣ ከማዘጋጃ፣ ከትምህርት እና ከጤና
ተቋማት) መረጃውን አደራጅቶ መያዝ፤
12) በየመሥሪያ ቤቱ የሚገኘውን ቋሚ ንብረት በአግባቡ መዝግቦ መረጃውን አደራጅቶ መያዝ፤

25
13) የመስከረም 30 ቀን 2011 ዓ/ም የተጠቃለለ የሂሳብ ሪፖርት የነባር ወረዳ በሃርድ ኮፒና በሶፍት ኮፒ
ተዘጋጅቶ ሪፖርቱን ለዞንና ለክልል ፋ/ኢ/ል/መምሪያ/ቢሮ በመላክ ሪፖርቱን አደራጅቶ መያዝ፣
33) የሰው ኃይል ክፍፍል/ዝውውር/ ኮሚቴ መቋቋም፣ሥልጣንና ተግባር
1. ከነባር ዞንና ወረዳ ወደ አዲሱ ዞንና ወረዳ የሚደረግ የሰው ኃይል ክፍፍል/ዝውውር/ የሚያከናውን የሰው
ኃይል ክፍፍል/ዝውውር/ የሚከተሉት 5 /አምስት/አባላት ይኖሩታል፡፡

1) የአዲስ ዞን/ወረዳ ም/ል አስተዳደር ሰብሳቢ

2) የነባር ዞን/ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ/ጽ/ቤት------ፀሐፊ

3) ከነባሩ ወረዳዎች/ቀበሌዎች ወደ አዲሱ ዞን/ወረዳ የተቀላቀሉ አዲስ መዋቅር የግብርና ጽ/ቤት


ኃላፊ-----------አባል፡፡

4) ከነባሩ ዞን/ወረዳ የተወከለ የፋይናንስና ኢኮ/ ልማት ጽ/ቤት ም/ል ኃላፊ-------አባል

5) አዲሱ ዞን/ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት የሰው ሀብት አስተ/ና ልማት ባለሙያ-- አባል

2. የኮሚቴው ሥልጣንና ተግባር

1) የሰው ኃይል ምደባ እና ሥምሪት ሥርዓቱን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ መደልደል

2) የተደለደሉትን የሰው ኃይል በግልጽ ማስታወቂያ በነባሩና በአዲሱ አስተዳደር እርከኖች


እንዲታወቅ ማድረግ፣

3) በየደረጃው ያለውን የሰው ኃይል ምደባ የተከናወኑትንና ምደባ እስካሁን ያልተፈጸመባቸውን


መደቦች በሚገባ መዝግቦ መያዝ፣

4) የተዛወሩትንም ሆነ በነባር ዞን የሚቀሩትን ሠራተኞች ፋይል በአግባቡ ማደራጀት፣

5) ለሥራው አስፈላጊ የሆኑትን ሕጋዊ ተግባራትን ማከናወን ናቸው፣

3. በሰው ኃይል ዝውውር/ምደባ ስርዓት ላይ ቅሬታ ያለው አካል በየደረጃው ለተቋቋመው ቅሬታ ሰሚ
ኮሚቴ ቅሬታውን ሊያቀርብ ይችላል፡፡

ምዕራፍ ዘጠኝ
የቅሬታ አቀራረብና ውሳኔ አሰጣጥ ሁኔታ
34) በ 2011 በጀት ዓመት በክልሉ ምክር ቤት ወሳኔ መሠረት አዲስ የተቋቋሙ፣ የሚቋቋሙ እና በነባሩ
የዞን፣የልዩ ወረዳ እና ወረዳ አስተዳደሮች የሀብት ድልድልና ክፍፍል ፍትሃዊ ባለመሆኑ ምክንያት

26
ቅሬታዎች ሲፈጠሩ በአግባቡ መርምሮ ዉሳኔ መስጠት ይገባል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች በተመለከተዉ
ሁኔታ ለሚፈጠሩ ቅሬታዎች ዉሳኔ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
1) በክልሉ ምክር ቤት ዉሳኔ የተቋቋሙና የሚቋቋሙ አዳዲስ የዞን፣ የልዩ ወረዳ እና የወረዳ
አስተዳደሮች የሀብት ድልድልና ክፍፍል በዚህ አሰራር መመሪያ መሠረት የሚፈፀም ይሆናል፡፡
2) በሀብት ድልድልና ክፍፍል ላይ የሚነሱ ቅሬታዎች በየደረጃዉ በተቋቋሙት የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ
እየተወሰነ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
3) በየደረጀዉ የሚቋቋመዉ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አደረጃጀት በሚከተለዉ አኳኃን ይሆናል፡፡
1. በክልል ደረጃ የሚቋቋመዉ የቅሬታ ሰሚ አካላት፣
ሀ) የፋ/ኢ/ል/ቢሮ ኃላፊ
ለ) የፋ/ኢ/ል/ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊና የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደርና ቁጥጥር ዘርፍ ኃላፊ፣
ሐ) የፋ/ኢ/ል/ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊና የልማት ዕቅድና ኢኮኖሚ አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ እና
መ) የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንስ ዋና ዳይሬክተር ናቸዉ፡፡
2. በዞን ደረጃ የሚቋቋመዉ የቅሬታ ሰሚ አካላት፣
ሀ) የዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ኃላፊ፣
ለ) የዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ኃላፊ፣
ሐ) የዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ የልማት ዕቅድና ኢኮኖሚ አስተዳደር ኃላፊ እና
መ) የዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል ኃላፊ ናቸዉ፡፡
3. በወረዳ ደረጃ የሚቋቋመዉ የቅሬታ ሰሚ አካላት፣
ሀ) የወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ኃላፊ፣
ለ) የወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ኃላፊ፣
ሐ) የወረዳ የልማት ዕቅድና ኢኮኖሚ አስተዳደር ኃላፊ እና
መ) የወረዳ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል ኃላፊ ናቸዉ፡፡
4) በወረዳ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በተሰጠዉ ወሳኔ ላይ ለዞን ቅሬታ ሰሚ ይግባኝ የማቅረብ መብት
ይኖራል፡፡ የዞን ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በሚሰጠዉ ወሳኔ የማይረካ ከሆነ የክልሉ ቅሬታ ሰሚ
ኮሚቴ የሰጠዉ ወሳኔ የመጨረሻ ዉሳኔ ይሆናል፡፡
5) በዞን ደረጃ በተደረገዉ ሀብት ድልድልና ክፍፍል ላይ ቅሬታ ቢኖር የዞን ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ
በተሰጠዉ ዉሳኔ የማይረካ ከሆነ ለክልሉ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ይግባኝ የማቅረብ መብት
ይኖራል፡፡ የክልሉ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ የሰጠዉ ዉሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡

27
6) በየደረጃ ለሚገኙ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች ቅሬታ ሲቀርብ ፍትሃዊ የሆነ ምላሽ ለመስጠት
ጉዳዩን አጣርቶ ሪፖርት የሚያቀርቡ ቴክኒክ ኮሚቴዎች በየደረጃ ይደራጀሉ፡፡ የቴክኒክ ኮሚቴ
አባላት ተግባርና ኃላፊነት በክልሉ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ይወሰናል፡፡
7) በሰው ኃይል ዝውውር/ምደባ ስርዓት ላይ ቅሬታ ያለው አካል በየደረጃው ለተቋቋመው ቅሬታ
ሰሚ ኮሚቴ ቅሬታውን ሊያቀርብ ይችላል፡፡

ክፍል ሦስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

36. መብትና ግዴታዎችን ስለማስተላለፍ፣


1) አዲስ የተቋቋሙ የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች የሰው ሀብት እና የሀብት ድልድልና ክፍፍል አሰራር
ደንብ መሠረት በነባሩ የዞንና፣ የልዩ ወረዳ እና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች የሚገኙ የሰው ኃይል፣
የ 2011 በጀት ዓመት በጀት፣ የመንግሥት ፋይናንስ መረጃዎች እና የንብረት መረጃዎች በአግባቡ
መዝግቦና አደራጅቶ በመያዝ ለሰው ኃይልና ለሀብት ድልድልና ክፍፍል ኮሚቴ የማቅረብ ግዴታ
አለባቸዉ፡፡
2) አዲስ የተቋቋሙ የዞንና የወረዳ አስተዳደር እርከኖች የሰው ሀብት እና በሀብት ድልድልና ክፍፍል አሰራር
ደንብ መሠረት የሚደርሳቸዉን የሰው ኃይል እና ሀብት መነሻ በማድረግ ከጥር 1 ቀን 2011 ዓ/ም
ጀምሮ ሥራዎቻቸዉን የመጀመር ግዴታ አለባቸዉ፡፡
3) የነባሩ የዞን፣ ልየ ወረዳ እና ወረዳ አስተዳደር እርከኖች አዲስ የተቋቋሙ የዞንና የወረዳ አስተዳደር
እርከኖች ስራዎቻቸዉን እስከጀመሩበት ጊዜ እስከ ታህሳስ 30 ቀን ድረስ ያለዉን የፋይናንሻልና
የፊዝካል ሪፖርቶችን በጋራ የማቅረብ ግዴታ አለባቸዉ፡፡
4) የነባሩ የዞንና የወረዳ አስተዳደሮች የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር መረጃዎችን በአግባቡ አደረጅቶ
አመቺ በሆነ ቦታ የመስቀመጥ ግዴታ አለባቸዉ፡፡
5) ከሀብት ድልድልና ክፍፍል በኃላ በነባሩ የዞንና የወረዳ አስተዳደሮች በዉስጥም ሆነ በዉጭ ኦዲተሮች
ኦዲት ተደርጎ ዕዳ ቢገኝ ወይም ተሰብሳቢ ሂሳብ ቢኖር አዳዲስ የዞንና የወረዳ አስተዳደሮች
የሚደርስባቸዉ ዕዳ የመክፈልና ተሰብሳቢዉን ሂሳብ ወስደዉ የማወዳደቅ ግዴታ አለባቸዉ፡፡

36) ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ፣


በ 2011 በጀት ዓመት በክልሉ ምክር ቤት በተወሰነዉ ዉሳኔ መሠረት አዳዲስ የዞን፣ የልዩ ወረዳ እና የወረዳ
አስተዳደሮች ከተቋቋሙበት ጊዜ ህዳር 17 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

28
ሚሊዮን ማቲዎስ
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግሥት
ርዕሰ መስተዳደር

29

You might also like