You are on page 1of 316

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ.

ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማእከል


የከተማ ልማት ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ዘርፍ
የተጠና ጥናት

የከተማ መልሶ ማልማት በኢትዮጵያ፡ስኬቶች፣


ተግዳሮቶች እና የወደፊት አቅጣጫዎች

(የተጠናቀቀ የጥናት ሰነድ)

አዲስ አበባ

ጥር, 2009 ዓ/ም

i
ምስጋና

ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማእከል፤ የከተማ ልማት ጥናትና ምርምር ዘርፍ ጋር በመሆን ይህ
“የከተሞች መልሶ ማልማት: ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች” የሚመለከት ጥናት ያጠኑትን
የጥናት ቡድኑ አባላት፤ አቶ አበበ ዘልኡል፣ አቶ አያሌው አባይ፣ አቶ ደመቀ ሃይሌ፣ አቶ አሸናፊ መሓሪ እና
ወ/ት ብሌን ገብረስላሴ ላበረከቱት ያልተቆጠበ ሞያዊ አስተዋጽኦ ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ
የኢትዮጵያ ስቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ እና የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ጥናቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ
ድረስ ከማእከላችን ጋር በትብብር በመስራት ላደረጉት በጎ እገዛ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ በመጨረሻ
ለዚህ ጥናት በናሙናነት የተመረጡት የአዲስ አበባ፣ መቀሌ፣ ድሬዳዋ፣ ሃዋሳ፣ ደሴ-ኮምቦልቻ እና ጅማ
ከተሞች የስራ ሃላፊዎች እና ባለሞያዎች፤ እንዲሁም መጠይቆችን በመሙላት፣ በቃለ-መጠይቅ፣ በትኩረት-
ቡድን ውይይት እና በባለሞያ ውይይት ላይ በመሳተፍ እውቀታችሁንና ልምዳችሁን ላካፈላችሁን የሕ/ሰብ
ክፍሎች ላደረጋችሁት የላቀ አስተዋጽኦ ምስጋናችንን ማቅረብ እንወዳለን፡፡

ii
ማውጫ

አርእስት ገፅ
የጥናቱ ግኝት ማጠቃለያ .............................................................................................................................................

ክፍል አንድ፡ መግቢያ ............................................................................................................................................. 1

1.1. የጥናቱ መነሻ .................................................................................................................................................... 1

1.2. የጥናቱ ዓላማና ግቦች ......................................................................................................................................... 5

1.2.1. ዋና ዓላማ ................................................................................................................................................. 5

1.2.2.ዝርዝር ግቦች ............................................................................................................................................. 6

1.3. የጥናቱ ወሰን /Scope of the Study/ .................................................................................................................... 6

1.4. የጥናቱ ዘዴ ..................................................................................................................................................... 7

1.4.1. የተከተለው መርህ ....................................................................................................................................... 7

1.4.2. የትንተና ዘዴና ስልት/Analytical Tools/ ......................................................................................................... 7

ክፍል ሁለት፡ የንድፈ ሃሳብና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ዳሰሳ ........................................................................................... 11

2.1. የንድፈ ሃሳብ ዳሰሳ .......................................................................................................................................... 11

2.1.1. የከተማ ምንነት እና የመልሶ ማልማት አስፈላጊነት.............................................................................................. 11

2.1.2. የከተማ መልሶ ልማት ታሪካዊ አጀማመርና ሂደት.............................................................................................. 13

2.1.3. በከተማ መልሶ ልማት የመንግስት ሚና አስፈላጊነት........................................................................................... 16

2.1.4. በመልሶ ማልማት ቀዳሚ ትኩረት የሚሹ የልማት አጀንዳዎች .............................................................................. 19

2.1.5. በከተማ መልሶ ልማት ዙርያ የዘመኑ መነጋገርያ አጀንዳዎች.................................................................................. 26

2.2. የተመረጡ ሀገራት የከተማ መልሶ ማደስ ተሞክሮ ቅኝት ........................................................................................... 28

2.2.1. ከተማ መልሶ ማልማት የቻይናና ኮሪያ ተሞክሮ ................................................................................................ 28

2.2.2.የቱርክ ከተማ ማደስ ተሞክሮ ....................................................................................................................... 31

2.2.3. የቬትናም ከተሞች መልሶ ማደስ ቅኝት .......................................................................................................... 36

2.3. የንድፈሃሳብና የዓለም አቀፍ ተሞክሮ ቅኝቱ ማጠቃለያ ............................................................................................. 40

2.3.1. የተወሰነ የከተማ ክፍልን ተፈላጊነት መውደቅ ትርጉም ....................................................................................... 40

2.3.2. አከባቢው ያልተሟላበትና የሚወድቀበት ምክንያት ........................................................................................... 40

i
2.3.3. አንድ ቦታ መልሶ መልማት የሚያስፈልግበት ጊዜ ............................................................................................. 41

2.3.4. መልሶ ማልማት የተመራበት ዓላማ ተሞክሮዎች .............................................................................................. 41

2.3.5. በከተሞች መልሶ ማልማት የመንግስት ወሳኝ ሚና ............................................................................................ 41

2.3.6. መልሶ ማልማት ከታሪክ ዕይታ የሚነሱ አቋሞች .............................................................................................. 42

2.3.7. የከተማ መልሶ ማልማት ስኬታማነት መገለጫዎች............................................................................................ 42

ክፍል ሶስት፡ የከተሞች የመልሶ ማልማት ቅኝት............................................................................................................ 44

3.1. የአጠቃላይ ማዕቀፍ ቅኝት ................................................................................................................................. 44

3.1.1. የከተማ መልሶ ማልማት አጀንዳ ወሳኝነትና ወቅታዊነት በኢትዮጵያ ........................................................................ 44

3.1.2. ሀገራዊ የህግ ማዕቀፍ ቅኝት ......................................................................................................................... 45

3.1.3. ሀገራዊ የመልሶ ማልማት አስቻይ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶች ................................................................................... 53

3.1.4. አጠቃላይ ማዕቀፍ እንደምታ ....................................................................................................................... 54

3.2. የናሙና ከተሞች ቅኝት .................................................................................................................................... 60

3.2.1. የከተሞቹ ነባራዊ ሁኔታ ............................................................................................................................. 60

3.2.2. መልሶ ልማት አጀማመር ........................................................................................................................... 69

3.2.3. ቦታ መረጣ መስፈርትና ሂደቱ ..................................................................................................................... 80

3.2.4. መልሶ ልማት የተመራበት ዓላማ ................................................................................................................. 93

3.2.5. ተቋማዊ አደረጃጀት ................................................................................................................................. 99

3.2.6. መልሶ ልማት የሚጠይቅ የቦታ ስፋት ......................................................................................................... 105

3.2.7. የዕቅድ ስፋት ከፍላጎት አንፃር ሲመዘን ........................................................................................................ 123

3.2.8. ፕሮጀክት ትግበራና ዕቅድ አፈፃፀም ............................................................................................................ 142

3.2.9. የመልሶ ልማት ፋይዳዎች ........................................................................................................................ 177

3.2.10. መልሶ ልማቱ በቀጣይ የሚኖረው የመስፋት ዕድል ........................................................................................ 203

3.2.10.1. መልሶ ልማት በነዋሪዎች ዕይታ............................................................................................................ 203


3.2.10.2. የልማት ተነሺዎች አያያዝ .................................................................................................................. 230
3.2.10.3. አካታችነት እና ፍትሓዊ የልማት ተጠቃሚነት ......................................................................................... 241
3.2.10.4. የልማቱ ጂኦግራፊያዊ ስርጭት............................................................................................................ 244

ii
3.3. ማጠቃለያ .................................................................................................................................................. 247

ክፍል አራት፡ በቀጣይ የከተማ መልሶ ማልማት ልንከተለው የሚገባ አቅጣጫ ..................................................................... 249

4.1. የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ ................................................................................................................................. 249

4.1.1. ለከተማ መልሶ ማልማት እራሱን የቻለ የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ የመኖር አስፈላጊነት ............................................. 249
4.1.2. የፖሊሲና የህግ ማዕቀፉ ሀገራዊ የመሆን አስፈላጊነት .................................................................................... 250
4.1.3. የፖሊሲ ምላሽ የሚሹ መሰረታዊ ጉዳዮች .................................................................................................. 251
4.2. የማስፈጸም አቅምና አመለካከት አጀንዳዎች ........................................................................................................ 268

4.3. የትግበራና ቴክኒካዊ ጉዳዮች ........................................................................................................................... 270

ማጣቀሻ ................................................................................................................................................................

አባሪዎች ................................................................................................................................................................

iii
የጥናቱ ግኝት ማጠቃለያ
ከተሞች ህይወት ያላቸው የሰው ልጆች መኖሪያ፣ መዝናኛና የሥራ ቦታ እንደ መሆናቸው መጠን ቅርፃቸውም
ሆነ ውስጣዊ ይዞታቸው የቆረቆራቸውና የኖረባቸው ማህበረሰብ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት
ነፀብራቅ ነው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ከተሞች ኡደታቸውን ጠብቀው ይወለዳሉ/ይቆረቆራሉ/፣ ያድጋሉ፣
ያረጃሉ፣ ይሞታሉ፣ በሥርዓት ከተመሩ ራሳቸውን ያድሳሉ አልያም ሞተው እስከ መጨረሻው ይጠፋሉ፡፡
የምዕራባውያን ከተሞች ያለፉበትን የዕድገት ፈለግ መሠረት አድርገው ሰፊ የምርምር ሥራ ያከናወኑ ፕሮፌሰር
ሊዮን በርግ የተባሉ ምሁር ድምዳሜ ይህን እውነታ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ እንደምሁሩ ግኝትና ድምዳሜ
ከተሞች በሚከተሉት አራት የዕድገት ኡደቶች ውስጥ /Urbanization processes/ ያልፋሉ፡፡

የመጀመርያው ኡደት ከተሞቹ ከተቆረቆሩበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ እስኪደርሱ ድረስ
የሚያልፉበትን ሂደት/urbanization process/ የሚመለከት ሲሆን ሁለተኛው የትራንስፖርት አገልግሎት
መሻሻልን ተከትሎ የከተሞች ዕድገት ከመሃል ወደ ሳተላይት ከተሞች የሚያደርጉትን መስፋፋት /sub-
urbanization/ ይመለከታል፡፡ ሦስተኛው ኡደት የኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም አቅም
ያላቸው ነዋሪዎች ወደ ከተማ ዳርቻ መሰደዳቸውን ተከትሎ የሚከሰተውን የዋናው ከተማ መውደቅ /dis-
urbanization/ የሚመለከት ሲሆን የመሃል ከተማውን ውድቀት ለመታደግ ሲባል በሚወሰድ የከተማ ማደስ
እርምጃ አማካይነት የሚፈጠረው የዋናው ከተማ ማንሰራራት /re-urbanization/ የመጨረሻው የከተሞች
ዕድገት ኡደት ነው (በርግ፣ 1987)፡፡

ከዚህ መረዳት የሚቻለው ከተሞች ምንጊዜም በማይቋረጥ የለውጥ ሂደት ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን እና
የነባር ከተሞች ድቀትና እርጅና /Urban Degeneration/ በየትኛውም የዕድገት ደረጃ ላይ በሚገኙ አገሮች
የሚስተዋል ክስተትና የሁሉም ከተሞች የጋራ ባህሪይ መሆኑን ነው፡፡ በዚህ ክስተት ዙሪያ ከከተማ ከተማ
/ከአገር አገር/ ልዩነት አለ ከተባለም በድቀቱ መንስኤዎች፣ ጥልቀትና ስፋት እንዲሁም ችግሩን ለመቅረፍ
በሚወሰዱ እርምጃዎች ዓይነትና ስኬት የሚታይ ልዩነት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

እንደተባበሩት መንግሥታት መረጃ በዓለም ላይ ለመኖሪያና ለሥራ ምቹ ባልሆኑ አካባቢዎች (Slum areas)
የሚኖሩ የከተማ ነዋሪዎች ድርሻ 31.6% ነው፡፡ ይህ አሃዝ በበለፀጉ ሀገራት 6% በታዳጊ ሀገራት 43% ሲሆን
ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ደግሞ 71.9% ነው (UN - Habitat, 2003)፡፡ የኢትዮጵያ የከተሞች
እርጅና የሚገኝበት ደረጃ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ካለው ሁኔታ የከፋ እንደሆነ ከተለያዩ
ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ለምሳሌ እ.ኤ.አ በ2010 በአገሪቱ ከነበረው የከተማ ነዋሪ ውስጥ
80% የሚሆነው ደረጃውን ባልጠበቀ የመኖሪያ አካባቢ ይኖር እንደነበር ከተባበሩት መንግሥታት የተገኘ
መረጃ ያመለክታል (UN-Habitat, 2010)፡፡ እዚህ ላይ ትኩረት የሚገባው ጉዳይ ቢኖር ይህ አሃዝ በጥልቅ
እርጅና በተጠቁ አካባቢዎች የሚኖሩትን ብቻ ሳይሆን መሠረታዊ አገልግሎት ባልተሟላላቸው የከተማ

iv
አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችን ጭምር የሚያካትት መሆኑ ነው፡፡ የአብዛኞቹ ከተሞቻችን በፕላን ያልተቃኘ
ዕድገትና አደረጃጀት ግምት ውስጥ ከገባ ይህ አሃዝ ከእውነታው የራቀ ነው ማለት አይቻልም፡፡

በሀገራችን የከተማ እርጅና ለዘመናት ሲከማች የኖረ ችግር ነው፤ ችግሩ በሁሉም ከተሞቻችን ተንሰራፍቶ
እንዲገኝ ያደረገው ዋናው መንስኤ ከከተሞቻችን አመሠራረት ይጀምራል፤ የአብዛኞቹ ከተሞቻችን አቆራቆርም
ሆነ ዕድገት በተሟላ የከተማ ፕላን የተመራ ሳይሆን ከገጠር ሠፈራ ባልተለየ መልኩ በዘፈቀደ እየተስፋፋ የመጣ
ነው፡፡ ጥቂት የማይባሉት ከተሞችም ከወታደር ካምፕነት ወደ ከተማነት የተሸጋገሩ ናቸው፡፡

የከተሞቻችን አብዛኛው ክፍል ከደረጃ በታች በሆኑ የግንባታ ቁሳቁሶች የተገነባ ከመሆኑም በላይ አስፈላጊው
የመሰረተ ልማት አውታር የሌላቸው ሲሆኑ የተፋፈጉ ሠፈሮች ቁጥርም ብዙ ነው፡፡ በዚህ ላይ ከተሞቻችን
ከጊዜው ጋር እራሳቸውን እያደሱና እያስተካከሉ የመጡ አይደሉም፡፡ በተለይ የተወረሱ የመንግሥት (ቀበሌ)
ቤቶች በስፋት የሚገኙባቸው ሠፈሮች ባለፉት አርባ ዓመታት የነባር ከተማ ማሻሻያ ፕሮግራም ያልጎበኛቸው
አካባቢዎች ናቸው፡፡ በዚህም የተነሣ አብዛኛው ክፍል ጥልቅ በሆነ የከተማ እርጅና (Urban Decay) የተጠቃ
ነው፡፡ በመሆኑም እላይ የተጠቀሰው ከተባበሩት መንግሥታት የተገኘው መረጃ መሬት ላይ ያለውን እውነታ
የሚያንፀባርቅ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡

የከተማ ማደስ ልማት አጀንዳ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በአገራችን የመንግሥትን ትኩረት እያገኘ መምጣቱ
ይታወቃል፡፡ በተለይ በትልልቅ ከተሞች ተቋማዊ ምላሽም ማግኘት ጀምሯል፤ በዚህ በኩል አዲስ አበባ
በቀዳሚነት ትጠቀሳለች፡፡ በሌሎች አንጋፋ ከተሞችም በተወሰነ ደረጃ ጅምሮች ይታያሉ፡፡ እነዚህ ጅምሮች
እንደተጠበቁ ሆነው የነባር ከተማ ማደስ ፕሮግራም በሀገራችን በተሟላ አደረጃጀት፣ ዘላቂ በሆነ አቅጣጫና
ወጥ በሆነ ፖሊሲ እየተመራ ነው ለማለት አያስደፍርም፡፡

የነባር ከተማ ማደስ ልማት ዘርፈ ብዙ እንድምታዎች ያሉት በአግባቡ ከተመራ በርካታ ኢኮኖሚያዊና
ማህበራዊ ችግሮችን የሚፈታ፣ በአግባቡ ካልተመራ ግን ሰፊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዋጋ የሚያስከፍል
የልማት አጀንዳ ነው፡፡ ልማቱ በርካታ አካላትን (Urban Actors) የሚነካ እንደ መሆኑ መጠን ሂደቱ
ውስብስብ ነው፤ በልማቱ የሚነኩ ባለድርሻ አካላትን ፍላጎት የሚያሟላ የከተማ ማደስ ስራ ለመስራት ወጥ
የሆነ የፖሊሲ ማዕቀፍ፣ ጠንካራ ተቋምና ግዙፍ የፋይናንስ ሀብት ይጠይቃል፡፡ እነዚህ ግብዓቶች
ባልተሟሉበት ሁኔታ የሚካሄድ የከተማ ማደስ ፕሮግራም አንድም የሚፈለገውን ዓላማ ሳያሣካ ተንገራግጮ
ሊቆም ይችላል፤ በግፊት እንዲቀጥል ከተደረገም የሚያስከፍለው ማህበራዊ ዋጋ ቀላል አይሆንም፡፡

የከተማ መልሶ ልማት ተነሽዎችን አያያዝና መልሶ ማቋቋም በተመለከተ የአገሪቱ ሕጎች የበላይ በሆነው
በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት የተቀመጠው አጠቃላይ አቅጣጫ በተሟላ ዝርዝር ሕግ ቢደገፍ ኖሮ ብዙ ርቀት
መጓዝ ያስችል ነበር፡፡ ነገር ግን በሕገ መንግሥቱ የተቀመጠውን አቅጣጫ መሠረት አድርጎ የተቀረፀ የተሟላ
(comprehensive) ሀገራዊ የከተሞች መልሶ ማልማት ፖሊሲ ማዕቀፍ ካለመኖሩም በላይ ሕገ - መንግሥቱን

v
ተከትለው የወጡ ቦታ ነክ ሕጎችና መመሪያዎች ከሕገ መንግሥቱ የፖሊሲ አቅጣጫ ጋር የማይጣጣሙ
ድንጋጌዎችን ይዘው በመውጣታቸው የተነሣ የሕገ መንግሥቱን ድንጋጌ ወደ ተግባር መመንዘር አልተቻለም፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ የከተማ መልሶ ልማት ፕሮግራምን ግድ የሚሉ በርካታ ነባራዊ ሁኔታዎች በአገራችን አሉ፤
ከከተማ እርጅና ባሻገር አገሪቱ እያስተናገደች ያለው ፈጣን የከተማ ዕድገት በመልሶ ማልማት ነባር አካባቢዎችን
እንደገና ማደስን አጥብቆ ይጠይቃል፡፡ አገራችን በዝቅተኛ የክተማ ዕድገት ላይ የምትገኝ አገር መሆኗ
ይታወቃል፡፡ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች እንደሚጠቁመት የአገሪቱ የክተማ ዕድገት ደረጃ (level of urbanization)
ከ20% በላይ የዘለለ አይደለም፡፡ ይህ አሃዝ ከአፍሪካ አማካይ የክተማ ዕድገት (40%) በግማሽ የሚያንስ ነው፡፡
በዚህ መሠረት ከዚህ ዝቅተኛ የከተማ ዕድገት ለመውጣትም ሆነ በ2017 አገሪቱን መካከለኛ ገቢ ካላቸው
አገሮች ተርታ ለማሰለፍ በመጭዎቹ አስር ዓመታት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የከተማ ዕድገት ማስተናገድ የግድ
ይላታል፡፡ አሁን እያስመዘገበችው ያለው 5% ዓመታዊ የከተማ ዕድገት የሚያሳየው ነገር ቢኖር ይህንኑ ነው፡፡

በአገራችን ፈጣን የከተማ ዕድገት ከሁለት ግፊቶች የሚመነጭ ነው፤ ይኸውም በአንድ በኩል የገጠሩ ኢኮኖሚ
የመሸከም አቅም ዝቅተኛ ከመሆኑ የተነሳ ወደ ከተማ የሚፈልሰው ሕዝብ በከተማው ላይ በሚያሳርፈው ጫና
በሌላ በኩል የአገሪቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ ተከትሎ ከሚመጣ ዕድገት በሚመነጭ ግፊት
የአገሪቱ ቀጣይ የከተማ ዕድገት እስካሁን ከታየው እጅግ የላቀ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይህን ግዙፍ የከተማ እድገት ለማስተናገድ ከተሞቻችን ያለባቸው ኃላፊነት ቀላል አይደለም፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ
በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣውን የሕዝብ ቁጥር እድገት ለማስተናገድ በነባሩ የአስተዳደር ክልላቸው ውስጥ
(within municipal boundary) በቂ የመስፋፊያ አካባቢ የሌላቸው ከተሞች እስካሁን በዙሪያቸው
ወደሚገኘው የገበሬ ይዞታ በመስፋፋት ጫናውን ለማስተንፈስ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ከአሁን በኋላ ግን
በዚህ መንገድ ብዙ ርቀት መጓዝ ይቻላል ተብሎ አይገመትም፡፡ ይህ አማራጭ እየጠበበ መሄዱ ስለማይቀር
ከተሞቻችን በነባር የይዞታ ክልላቸውን አሟጠው በመጠቀም ተጨማሪ ነዋሪና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ
ለማስተናገድ ራሳቸውን ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፤ በዚህ ረገድ የነባር አካባቢ መልሶ ማልማት አማራጭ
የሌለው እርምጃ ነው፡፡ በመሆኑም የከተማ መልሶ ማልማት ፕሮግራም ወደ ፊት የአገራችን ቁልፍ የከተማ
ልማት አጀንዳ መሆኑ አጠያያቂ አይሆንም፡፡ የመልሶ ማልማት ወደፊት በአገራችን ወሳኝ የልማት አጀንዳ
የሚሆነው በእርጅና የተጠቁ የከተማ አካባቢዎችን ለማደስ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ አገሪቱ የምትጠብቀውን
ፈጣን የከተማ ዕድገት ለማስተናገድም ጭምር ነው፡፡

በአገራችን ከተሞች የተካሄዱ የመልሶ ልማት ጥረቶች መሬት ላይ ካለው ፍላጎትና ከችግሩ ስፋት አንፃር
እሰካሁን የተጓዙት ርቀት አመርቂ ባይሆንም የከተሞችን ገጽታ በማሻሻል ረገድ የሚታየው ጅምር አወንታዊ
ነው፡፡ በነባር አካባቢዎች ለኑሮና ለስራ ምቹ ያልነበሩ ሠፈሮች የየከተሞቹ ፕላን ባስቀመጠው አቅጣጫ
እየተለወጡ መሆኑን የሚያመላክቱ ተስፋ ሰጪ ምልክቶች መታየት ጀምረዋል፡፡ በመሃል ከተሞች የትራፊክ
እንቅስቃሴ ፍሰትን ማቀላጠፍ፣ ከደረጃ በታች በሆነ አገልግሎት ተይዘው የነበሩ ቦታዎች ለተሻለ አገልግሎት

vi
ማዋል፣ የግል ኢንቨስትመንት መስፋፋት፣ የመሳሰሉ መሻሻሎች የመልሶ ማልማት እንቅስቃሴዎችን ተከትለው
የመጡ አወንታዊ ውጤቶች ናቸው፡፡ እነዚህ አወንታዊ ውጤቶችና ተስፋዎች እንደተጠበቁ ሆነው ከከተሞች
መልሶ ማልማት እንቅስቃሴ ጋር ተያይዘው የሚስተዋሉ በርካታ ክፍተቶች አሉ፤ በናሙናነት በተወሰዱ ከተሞች
ልምድና ተሞክሮ ዙሪያ የተደረገው ዳሰሳ ጥናት ግኝት እንደሚያመለክተው ችግሮቹ በከፊል ከፖሊሲ ክፍተት
በከፊል ደግሞ ከአፈፃፀም ጉድለት የሚመነጩ ናቸው፡፡

በአብዛኞቹ የአገራችን ከተሞች በሙከራ ደረጃ ላይ የሚገኘው የመልሶ ማልማት እንቅስቃሴ ገና ከጅምሩ ችግር
እየገጠመው ያለው ልማቱ ወጥና ግልጽ በሆነ የፖሊሲ ማዕቀፍ (Federal Policy Framework) የሚመራ
እንዳልሆነ ብዙዎች ያምናሉ፡፡ በዚህ ጥናት አስተያየታቸውን ከተጠየቁ የከተማ አስተዳደር ኃላፊዎችና
ባለሙያዎች መካከል አብዛኞቹ ይህን እምነት ይጋራሉ፡፡ የካሳ ክፍያና ምትክ ቤት/ቦታ አሠጣጥን አስመልክቶ
ከወጣው የሕግ ድንጋጌ ውጭ ለልማት ተነሽዎች የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ የሚሠጥበትን አግባብ የሚመለከት
የተሟላ ሕግ ወይም የፖሊሲ ማዕቀፍ በአገሪቱ የለም፡፡ የከተማ አስተዳደሮች በመልሶ ልማት ተነሽዎች ላይ
እየደረሰ ያለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መጎሳቆል ከፍተኛ መሆኑን ቢያምኑም ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል
ሀገራዊ የፖሊሲ ማዕቀፍ በሌለበት ሁኔታ ምንም ማድረግ እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡ በልማት ተነሽዎች አያያዝና
መልሶ ማቋቋም ዙሪያ የሚስተዋለው ክፍተት ከመልሶ ልማቱ የማይተናነስ አሳሳቢና ትኩረት የሚሻ ጉዳይ
መሆኑን እንደሚረዱ በናሙና ጥናቱ የተካተቱ የከተማ አስተዳደር ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ያለ ልዩነት
ይገልጹታል፡፡

በከተሞች መልሶ ማልማት ፕሮግራም ትግበራ ዙሪያ ከሚስተዋሉ ክፍተቶች አንዱ ልማቱን በባለቤትነት
የሚያስፈፅም ራሱን የቻለ ብቃት ያለው ተቋም በከተሞቹ አስተዳደር ሥር አለመደራጀቱ ነው፡፡ በዚህ ረገድ
የተሻለ ሙከራ ያለው በአዲስ አበባ ከተማ ነው፤ በሌሎቹ ከተሞች በአብዛኞቹ ምንም ዓይነት ተቋም የሌለ
ሲሆን በተወሰኑት በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ሥር በንዑስ ሥራ ሂደት ደረጃ በተዋቀረ የሥራ ክፍል
ልማቱን ለማስፈፀም ጥረት እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የመልሶ ማልማት ፕሮግራም የሚከታተል የሥራ
ክፍል በንዑስ የሥራ ሂደት ደረጃ በተዋቀረባቸው ከተሞችም ቢሆን የሥራ ክፍሉ በበቂ ባለሙያ
እንዳልተደራጀ በዚህ የዳሰሳ ጥናት ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በተቋም ደረጃ ባለቤት በተዋቀረለት በአዲስ አበባ
ከተማም ሆነ በንዑስ ሥራ ሂደት ልማቱን ለመምራት ጥረት በሚያደርጉ ከተሞች የሥራ ክፍሎቹ ተልዕኮና
እንቅስቃሴ ለኢንቨስትመንት የሚሆን የከተማ ቦታ ከነባር ተጠቃሚዎች ነፃ በማድረግ ላይ እንደሚያተኩር
በዚህ ዳሰሳ ጥናት ላይ መገንዘብ ተችሏል፡፡

በተቋማዊ ማዕቀፍ ረገድ የዓለምአቀፍ ተሞክሮ የሚያሳየው ልምድ በአገራችን ካለው ጋር የተለየ ነው፤ ብዙ
አገሮች ለከተሞቻቸው መልሶ ማልማት ተቋም የሚያደራጁት በኮርፖሬሽን ደረጃ ነው፡፡ ሂደቱም ቅርብ
የፖለቲካ አመራር አይለየውም፡፡ በዚህ ጥናት የተዳሰሱ ሀገራት ልምድና ተሞክሮ የሚያረጋግጠው መልሶ
ማልማት ጠንካራ የፖሊቲካ አመራር የሚጠይቅ ልማት መሆኑን ነው፡፡ ለምሳሌ በደቡብ ኮሪያ በማእከላዊ

vii
መንግስት ደረጃ ሚኒስትሮችንና የግሉን ዘርፍ ተወካዮች በአባልነት ያካተተ በጠቅላይ ሚኒስቴር የሚመራ ልዩ
የከተማ መልሶ ማልማት ኮሚቴ አደራጅተው ልማቱን ይመሩታል፡፡ ከሀገራዊው የመልሶ ልማት ኮሚቴ
በተጨማሪ በመሬት፣ በመሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውስጥ የከተማ ማደስ ፕላን
ቡድን በማደራጀት ሂደቱን በወጥነት በሙያ ታግዞ እንዲከናወን ይደረጋል፡፡

በከተሞቻችን የመልሶ ማልማት እንቅስቃሴ የሚስተዋለው ሌላው ፈታኝ ተግዳሮት ለልማቱ የሚጠይቀው
በጀት አነስተኛ መሆን ነው፡፡ የከተማ አስተዳደሮች ከደረጃ በታች በሆነ ግንባታ የተያዙ የከተማ አካባቢዎችን
መልሶ የማልማት ግብ ከፌደራልና ከክልል መንግሥታት ይሠጣቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ይህን ተልዕኮ ለማሳካት
የሚያስችል የፋይናንስ ድጋፍ ከፌደራልም ሆነ ከክልል መንግሥታት ሲመደብ አይታይም፡፡ ለምሳሌ
በሁለተኛው የአምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ከደረጃ በታች የሆኑ የከተማ
አካባቢዎችን (Slum Areas) 50% የመቀነስ ሀገራዊ ግብ ተጥሏል፡፡ ይህም ሀገራዊ ግብ እውን መሆን
የሚችለው በከተማ አስተዳደሮች አማካይነት መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ሀገራዊ ግቡ ሲቀመጥ
ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልገው የገንዘብ ምንጭ ከየት እንደሆነ አልተጠቀሰም፡፡

ከዚህ መገመት የሚቻለው ሀገራዊ ግቡን የመፈፀም ሙሉ ኃላፊነት ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች የተተወ
መሆኑን ነው፡፡ በሌላ በኩል ሁሉም ከተሞች ይህን ግብ እውን ለማድረግ የሚያስችል የፋይናንስ አቅም
የላቸውም፤ በክልሎች ዓመታዊ በጀት አመዳደብም የከተሞች መልሶ ማልማት ፕሮግራም ትኩረት ሲሰጠው
አይታይም፡፡ በክልሎች ዓመታዊ የሥራ ዕቅድ ጎልቶ የሚታየው ከተሞች ለኢንቨስትመንት መስፋፋትና ለሥራ
ዕድል ፈጠራ በቂ መሬት ማዘጋጀት የሚጠበቅባቸው መሆኑ ነው፡፡ ከተሞች ለኢንቨስትመንት ቦታ ማዘጋጀት
ካለባቸው የሚኖራቸው ምርጫ አንድም በመስፋፊያ አካባቢ በአርሶ/ አርብቶ አደር እጅ የሚገኘውን ያልለማ
መሬት ማስለቀቅ ነው፤ አለበለዚያ በመሃል ከተማ በመልሶ ማልማት ፕሮግራም አማካይነት ቦታን ከነባር
ባለይዞታ ነፃ ማድረግ ነው፡፡ በሁለቱም አማራጮች ቦታን ከነባር ተጠቃሚ ነፃ አድርጎ ለአዲስ ኢንቨስትመንት
ማዘጋጀት የሚጠይቀው ፋይናንስ ቀላል አይደለም፡፡

የከተሞች መልሶ ማልማት የሚጠይቀው ግዙፍ የፋይናንስ ሃብት በከተማ አስተዳደሮች አቅም ብቻ የሚሸፈን
አይደለም፡፡ በሌላ በኩል የመልሶ ማልማት በሚካሄድባቸው የከተማ አካባቢዎች ከሚነሣው ነዋሪ አብዛኛው
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፤ በመሆኑም ልማቱ በይዘቱም ሆነ በውጤቱ ከድህነት ቅነሣ ጋር
በጥብቅ የተሣሠረ ነው፡፡ የድህነት ቅነሳ አጀንዳ ደግሞ ከአንድ ከተማ አስተዳደር ወይም ክልል ኃላፊነት በላይ
ነው፡፡ ስለሆነም በፌደራል መንግሥት ደረጃ ለዚህ ልማት ማስፈፀሚያ የሚሆን ፋይናንስ (Federal Fund)
ማቋቋም አስፈላጊነት ከፍ ያደርገዋል፡፡ የዓለም አቀፍ ተሞክሮ እንደሚያሣየው ለመልሶ ልማት ማስፈፀሚያ
የሚሆን ሀገራዊ ፈንድ ማቋቋም የተለመደ ነው፡፡ በዚህ የልማት ዘርፍ ሠፊ ተሞክሮ ባላቸው ሀገራት
(እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ኮሪያ፣ ቻይና፣ ቱርክና ቬትናም) ስኬት እንደ ዋና የስኬት ምሰሶ የሚጠቀሰው እርምጃ
ለልማቱ ማስፈፀሚያ የሚሆን አስተማማኝና ዘላቂ የፋይናንስ ሥርዓት መዘርጋታቸው ነው፡፡

viii
በአገራችን ከተሞች መልሶ ማልማት እንቅስቃሴ የሚስተዋለው ሌላው መሰረታዊ ክፍተት መልሶ ማልማት
ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች ለሚፈናቀሉ ወገኖች በቂ የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ የማይደረግላቸው መሆኑ ነው፡፡
በመልሶ ማልማቱ ምክንያት ከመኖሪያቸውና ከሥራቸው የሚፈናቀሉ ዜጎችን ቁጥር ለመቀነስ የሚደረገው
ጥረትም አናሣ ነው፡፡ በመልሶ ማልማት አማካይነት በነባር የከተማ አካባቢዎች የሚመጣው የኢኮኖሚ ለውጥ
በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን የሚያሳትፍ አይደለም፡፡ መልሶ ማልማት በባህሪው ጥቃቅንና
አነስተኛ ተቋማትን ከመሃል ከተማ የሚገፋ በምትካቸው ትልልቅና ዘመናዊ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ተቋማትን
ወደ መሃል ከተማ የሚስብ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ነባሩ ከተማ በከፍተኛ የኢኮኖሚ መዋቅር (Higher Order
Goods) እየተያዘ በሄደ ቁጥር በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘው ህብረተሰብ የኢኮኖሚ መሠረት
እየተመናመነ መሄዱ አይቀሬ ነው፡፡

ስለሆነም በመልሶ ማልማት ሳቢያ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘው ህብረተሰብ ሕይወት የሚናጋው በሥራ
ዕድል መጣበብ ብቻ ሳይሆን በመጠለያ እጦትም ጭምር ነው፡፡ ይኸውም የመልሶ ልማቱን ተከትሎ በመሃል
ከተማ የሚገነቡ (በተለይ በሪል ስቴት የሚቀርቡ) የመኖሪያ ህንፃዎች ዋጋ/ኪራይ/ ለአብዛኛው የከተማ ነዋሪ
የሚቀመስ አይደለም፡፡ በመሆኑም አሁን በተያዘው አካሄድ የነባር አካባቢዎች መልሶ ልማት እንቅስቃሴ
በአብዛኛው የከተማ ነዋሪ ኑሮ ላይ እያሳረፈ ያለው አሉታዊ ተጽእኖ ከፍተኛ ነው፡፡

እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ ማንኛውም ልማት የተወሰነ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዋጋ ማስከፈሉ
አይቀሬ ነው፤ አንድን አገር ወይም ከተማ ለዘመናት ተዘፍቆ ከኖረበት ኋላ ቀርነትና ችግር ለማውጣት
በግለሰብ፣ በማህበረሰብና በሀገር ደረጃ የተወሰነ ዋጋ መከፈል አለበት፡፡ በማንኛውም የልማት መስክ ዋጋ
መክፈል (Trade- Off) ያለ ነው፤ ነገር ግን የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ
የሚጋሩበት አግባብ ከሌለ ልማቱ ቀጣይና ዘላቂ (Sustainable) ሊሆን አይችልም፡፡ በተለያዩ የሕብረተሰብ
ክፍሎች መካከል ፍትሃዊ የሆነ ልማት ለማምጣት ወጥ የሆነ አገር አቀፍ ፖሊሲና ቅርብ የፖለቲካ አመራር
መኖር ወሳኝ ነው፡፡ በቴክኖክራት የሚመራ ልማት ለፍትሃዊነት ቅድሚያ ትኩረት ይሠጣል ተብሎ
አይጠበቅም፡፡ የከተማ መልሶ ማልማት ስራ በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎችን የሚነካ የልማት ፕሮግራም
እንደመሆኑ መጠን ልማቱ ቅርብ የፖለቲካ አመራር ይፈልጋል፡፡

ሚዛናዊ የልማት ስርጭትን ማረጋገጥ ሌላው በመልሶ ማልማት ፕሮግራም ትግበራ ትኩረት የሚሻው ጉዳይ
ነው፡፡ ድሃና ሃብታም፣ ዘመናዊና ባህላዊ አኗኗር፣ አነስተኛና ከፍተኛ ተቋማት ጎን ለጎን ተሰባጥረውና
ተስማምተው ለዘመናት መኖራቸው የኢትዮጵያ ከተሞች ከሚታወቁባቸውና ከሚደነቁባቸው እሴቶች መካከል
አንዱና ቁልፉ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በአገራችን ከተሞች የመልሶ ማልማት እንቅስቃሴ ይህን
መልካም እሴት ለማስቀጠል በቂ ጥንቃቄና ጥረት ሲደረግ አይስተዋልም፡፡ መልሶ ማልማት በተካሄደባቸው
ነባር የከተማ አካባቢዎች እየተመዘገበ ያለውን ለውጥ ለሚያስተውል መልሶ ማልማት ተመሳሳይ ለሆኑ
ተቋማት/የሕብረተሰብ ክፍሎች ወደ አንድ አካባቢ መሰባሰብ (Segregation) ምክንያት እየሆነ መሆኑ ግልጽ

ix
ነው፡፡ በመልሶ ማልማት የሚፈናቀሉ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ወደ ከተሞች ዳርቻ
ሲገፉ መሃል ከተማው ጠንካራ የኢኮኖሚ አቅም ባላቸው ወገኖች እየተያዘ ነው፡፡ ይህ ክስተት ነባሩን
ማህበራዊ ስብጥር እንዲዛባ ከማድረግም ባሻገር የዜጎችን ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት የሚሸረሽር ነው፡፡
ለምሳሌ በመሃል አዲስ አበባ መልሶ ማልማት በተካሄደባቸው ሠፈሮች ጥቃቅንና አነስተኛ ሥራዎች በትላልቅና
ዘመናዊ የኢኮኖሚ ተቋማት እየተተኩ ነው፣ ይህን ተከትሎ የመሃል ከተማው ማህበራዊ መዋቅር እየተቀየረ
ነው፡፡

ከተሞቻችን የሚያካሂዱትን መልሶ ማልማት ተከትሎ የነባር አካባቢዎች የኢኮኖሚ መዋቅር መቀየር የማይቀር
ብቻ ሳይሆን የሚፈለግም ነው፡፡ ሆኖም ለውጡ በአንድ ጊዜ ነባሩን ጠርጎ በማስወጣት በምትኩ ፍፁም አዲስ
በሆነ የኢኮኖሚ መዋቅር የሚተካ ሳይሆን ነባሩን የኢኮኖሚ መዋቅርም ይዞ የሚጓዝ፤ ሂደታዊ በሆነ መንገድ
ደግሞ ደረጃ በደረጃ ትራንስፎርም እያደረገ የሚሄድ ልማት መሆን ይኖርበታል፡፡

ነባሩን ኢኮኖሚና ነዋሪ ከአዲሱ የከተማ መዋቅር ጋር አዋህዶ ጎን ለጎን እየተለወጠ እንዲሄድ ማድረግ
ከተሞቻችን የሚታወቁበትን የተሰባጠረ (non-segrageted) አኗኗር የሚያስቀጥል ከመሆኑም በላይ
የሚከፈለውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዋጋ ለመቀነስ ያስችላል፤ በልማቱም አብዛኛውን የከተማ ነዋሪ
ተጠቃሚ ለማድረግ የተሻለ ዕድል ይሠጣል፡፡ በመሆኑም የመልሶ ማልማት ስራዎቻችን የመሃል ከተሞቻችንን
ገጽታና የኢኮኖሚ መዋቅር ከማሻሻል ባሻገር ለነባሩ ነዋሪ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ሕይወት መለወጥና ለአስተኛና
ጥቃቅን የኢኮኖሚ ተቋማት ሂደታዊ ለውጥ በቂ ትኩረት መስጠት ይኖርበታል፡፡

በመልሶ ማልማት አማካይነት ከተሞችን የማሻሻልና ወደ ዘመናዊ የኢኮኖሚ መዋቅር የማሸጋገር እርምጃ
አስፈላጊነት ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ጉዳይ አይደለም፤ ይልቁንም ለዓመታት የዘገየ፣ የከተሞቻችን የወደፊት ቁልፍ
የልማት አጀንዳ ነው፡፡ ጥያቄውም መልሶ ማልማት ዜጎችን እያፈናቀለ ስለሆነ መገታት አለበት? ወይስ
የለበትም? የሚል አይደለም፡፡ ልማቱንም መግታት የሚታሰብ አይሆንም፤ ይልቁንም እርምጃው ይበልጥ
መስፋፋትና መፍጠን አለበት፡፡ ከመልሶ ማልማት ጋር ተያይዞ የሚነሣው ጥያቄ በልማቱ ምክንያት የሚነኩ
ዜጎችና ተቋማት መልሶ ማቋቋም ዙሪያ ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡

በከተሞች መልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች ምክንያት ከቤት ንብረታቸው እየተፈናቀሉ ያሉ ዜጎች ቁጥር ቀላል
አይደለም፤ በተለይ እንደ አዲስ አበባ ባሉ ትልልቅ ከተሞች በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች በመልሶ ልማት
ምክንያት ከኢኮኖሚና ማህበራዊ ሕይወታቸው እየተፈናቀሉ ይገኛሉ፡፡ በሌሎች ከተሞችም በሚፈለገው ደረጃ
ወደልማቱ ስላልተገባ ካልሆነ በስተቀር መልሶ ልማት ከሚፈልገው የከተማ ክፍል ግዝፈት አኳያ ሲታይ
በአገሪቱ ከተሞች የተሟላ የመልሶ ማልማት እንቅስቃሴ ማድረግ ሲጀመር ልማቱ የሚነካው የሕብረተሰብ
ክፍል ቀላል አይሆንም፡፡

x
በዚህ መሠረት ልማቱ ለሚያፈናቅላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቀደም ሲል የነበራቸውን ሕይወት የሚያስቀጥል
የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ እስካልተደረገላቸው ድረስ በየዓመቱ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ሕይወት ወደ ባሰ
ድህነት ሊገፋ ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ከመልሶ ማልማት ፕሮግራም መሠረታዊ ዓላማ ጋር የሚጋጭ፣ አገሪቱ
የተያያዘችውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እርምጃ የሚሸረሽር፣ ለዜጎች እኩል ተጠቃሚነት ቅድሚያ ትኩረት
ከሚሠጠው የልማታዊ መንግሥት መርህ ጋር አብሮ የማይሄድ ነው፡፡

የከተሞች መልሶ ማልማት የነባር አካባቢዎችን ገጽታ ለመቀየር ብቻ የሚከናወን ልማት ሳይሆን በኢኮኖሚና
ማሕበራዊ፣ በአካባቢ ደህንነት፣ በታሪክና ቅርስ ጥበቃ ዙሪያ ተጨማሪ እሴት ለመፍጠር ጭምር የሚካሄድ
ዘርፈ ብዙ የልማት ፕሮግራም ነው፡፡ ይሁን እንጂ በመልሶ ማልማት አማካይነት እየተፈጠሩ ያሉት ተጨማሪ
እሴቶች ተደማሪነታቸው በመልሶ ማስፈሪያ ቦታዎችና በልማት ተነሺዎች ህይወት ዙሪያ በሚከሰተው ክፍተት
ሳቢያ ድምር ውጤቱ ተጨማሪ ዓቅም ከመፍጠር አንፃር የተሟላ አይደለም፡፡ ምክንያቱም መስፈሪያ ቦታዎች
የከተማው አካል ሆነው ጎን ለጎን እንዲለሙ እየተደረጉ ባለመሆኑ ነው፡፡

በዚህ ጥናት በናሙናነት የተወሰዱ ከተሞች ተሞክሮ እንደሚያሳየው በመልሶ ማልማቱ ዘላቂነት ዙሪያ በርካታ
ችግሮች ይስተዋላሉ፤ የመልሶ ማልማት ፕሮጀክት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ይኖሩ/ይሰሩ የነበሩ ዜጎች
አያያዝ በውዝግብ የተሞላ ነው፣ ሂደቱም የተጓተተና ነባሩን የሕብረተሰብ ክፍል የልማቱ ተቋዳሽ የሚያደርግ
ሳይሆን የሚገፋ የመሆን አዝማምያ ይታይበታል፡፡ ለተነሺዎች መልሶ መስፈሪያ ተብለው የሚገነቡ ቤቶች
(ለምሳሌ ደሴ እና ጅማ) በነባሩ አካባቢ ከፈረሱት ቤቶች የማይሻሉና ከወዲሁ ሌላ መልሶ ማልማት የሚጠይቁ
ናቸው፡፡ መልሶ በሚለማው አካባቢ የሚሰሩ ግንባታዎችም የአጭር ጊዜ ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር ከቦታ
አጠቃቀምም ሆነ ከዲዛይን አንጻር ሲታይ ነገን ተሸጋሪ አይደሉም፡፡

የመልሶ ልማት በሚካሄድባቸው አከባቢዎች በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሊከሰት የሚችል የፍላጎት ለውጥን ታሳቢ
ያላደረገ እርምጃም ይስተዋላል፡፡ ለዚህ የድሬዳዋ ከተማ ጥሩ ማሳያ ይሆናል፤ በድሬዳዋ የከተማው ማዕከል
ሳቢያን እየተባለ ወደሚጠራው አከባቢ እየተሳበ ባለበት ሁኔታ ነባሩ የንግድ ማዕከል (CBD) አሁንም
በከተማው ማዕከልነት ሚናው እንዲቀጥል የመፈለግ ዝንባሌ ይታያል፡፡ ሆኖም ፍላጎቱ የነባሩን የከተማ ክፍል
የንግድ ማዕከል ሚና በሚያጠናክር ተጨባጭ እርምጃ የታጀበ ባለመሆኑ ከምኞት የሚያልፍ ሆኖ አልተገኘም፡፡

በልማት ተነሽዎች መስፈሪያ አካባቢ ምርጫ ላይም ቢሆን ነገን የማይሻገር እርምጃ በስፋት ይስተዋላል፡፡ ለሌላ
ልማት በሚፈለጉ ወይም የመሰረተ ልማት መስመር በሚያርፍባቸው ቦታዎች ላይ የልማት ተነሽዎችን በማስፈር
ለድጋሜ መፈናቀል ማጋለጥ፣ ለመኖሪያ ምቹ ያልሆኑ ገደላማ ቦታዎችን ለልማት ተነሽዎች በምትክ ቦታነት
መስጠት፣ የመኖሪያ ቤት መስፈርት የማያሟሉ ምትክ ቤቶችን መገንባት በብዙ ከተሞቻችን የሚስተዋል ችግር
ነው፡፡ እነዚህን የመሳሰሉ እርምጃዎች የመልሶ ማልማት ሂደቱን በውጥረትና በውዝግብ የተሞላ እያደረጉት
ይገኛሉ፤ የልማት ሃብት (ፋይናንስ፣ መሬት፣ የባለሙያ ጊዜ፣ ወዘተ) መፍሰሱ እስካልቀረ ድረስ ልማቱ አዋጭና
ዘላቂ መሆኑን በቅድሚያ ማረጋገጥ ተገቢ ይሆናል፡፡

xi
ውድና ውስን የሆነውን የከተማ መሬት በቁጠባ በመጠቀም ረገድም ቢሆን የሚታየው ክፍተት ሰፊ ነው፤
በመልሶ ማልማት ከተለቀቀው ቦታ የሰፋ ምትክ ቦታ መስጠት ይስተዋላል፡፡ ለምሳሌ ደሴ ከ26 ሜትር ካሬ
በታች ከሆነ ቦታ ለተነሱ የቀበሌ ቤት ተከራዮች 171 ሜትር ካሬ ቦታ መስጠት፣ በአዲስ አበባ በ2 ካሬ ሜትር
ላይ ይነግድ ለነበረ ተነሺ 25 ሜትር ካሬ ቦታ መስጠት ብዙ ርቀት የሚያስኬድ እርምጃ አይደለም፡፡ በዚህ
አካሄድ መርካቶ አካባቢ ለልማት ከፈረሰው ቦታ በላይ ምትክ ቦታ የጠየቁ ሂደቶች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በደሴ ከተማ የተስተዋለውና የመልሶ ማልማቱ ስራ እየሰፋ ሲሄድ ብዙ ርቀት ሊያስጉዝ የማይችል ለተወሰኑ
የንግዱ ማሕበረሰብ አባላት ኮንቴነር የመስጠት እርምጃ እንደ አማራጭ ተወስዷል፡፡

በአጠቃላይ ያረጁ አካባቢዎችን በመልሶ ማልማት ለማደስ የሚከናወን ልማት በመስፈሪያ አካባቢዎች
ተጨማሪ እሴት መፍጠር አልቻለም፡፡ የልማቱ ቁልፍ ዓላማ ዜጎችን የልማት ተጠቃሚ ማድረግ ሆኖ ሳለ
ከዜጎች ይልቅ ለቦታና ግንባታ መለወጥ ቅድሚያ ትኩረት እየተሰጠ እንደሆነ ማየት ተችለዋል፡፡ በዚህ ዓይነት
ቅኝት የሚካሄድ የከተማ መልሶ ልማት ስራ ስርነቀልና ዙርያ መለስ (Transformational) ውጤት ያመጣል
ተብሎ አይጠበቅም፡፡

xii
ክፍል አንድ፡ መግቢያ
1.1. የጥናቱ መነሻ
ከተሞች ህይወት ያላቸው የሰው ልጆች መኖሪያ፤ መዝናኛና የሥራ ቦታ እንደ መሆናቸው መጠን
በቅርጻቸውም ሆነ በይዘታቸው የመሠረቷቸው እና የኖሩባቸው ማህበረሰብ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ
ዕድገት ነፀብራቅ ናቸው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ከተሞች እንደ ማንኛውም ሕይወት ያለው ፍጡር
የሚያልፉዋቸው የጉዞ ሂደቶች ማለትም ይመሰረታሉ (ይወለዳሉ)፣ ያድጋሉ፣ ያረጃሉ፣ ይሞታሉ፡፡ ነገር ግን
ህይወት ካላቸው የሚለዩበት ባህሪ አላቸው፡፡ የከተሞች ዕድገት በሥርዓት ከተመራ እድገታቸው ሙሉ በሙሉ
ወደ እርጅና ሳይለወጥ እራሳቸውን እያደሱ ሁሌ እንዲያድጉ ዕድል አላቸው፡፡ ዕድገታቸው በስርዓት ካልተመራ
ደግሞ ሞተው እስከመጨረሻው ይጠፋሉ፡፡

የምዕራባውያን ከተሞች ያለፉበትን የዕድገት ፈለግ መሠረት አድርገው ሰፊ የምርምር ሥራ ያከናወኑት


ፕሮፌሰር ሊዮን በርግ የተባሉ ምሁር የደረሱበት ድምዳሜም ይህን እውነታ የሚያረጋግጥ ነው፤ እንደምሁሩ
ግኝትና ድምዳሜ ከተሞች በሚከተሉት አራት የዕድገት ኡደቶች ውስጥ (Urbanization processes) ያልፋሉ፡፡

የመጀመርያው ኡደት ከተሞቹ ከተቆረቆሩበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ እስኪደርሱ ድረስ
የሚያልፉበትን የክተማ ምዕራፍ (urbanization stage) የሚመለከት ሲሆን ሁለተኛው የትራንስፖርት
አገልግሎት መሻሻልን ተከትሎ የከተሞች ዕድገት ከዋናው ከተማ መሃል እየወጡ ከዋናው ከተማ በተወሰነ
ርቀት ወደሚገኙ አነስተኛ ከተሞች (Satellite towns) የሚያደርጉትን መስፋፋት (sub-urbanization)
ይመለከታል፡፡ ሦስተኛው የዑደቱ ምዕራፍ በመሃል ከተማው መጨናነቅ፣ ለኑሮና ሥራ ምቹ አለመሆን የተነሣ
የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች መሃል ከተማውን እየለቀቁ ወደ ሳተላይት ከተሞች መሰደዳቸውን
ተከትሎ የሚከሰተውን የዋና ከተማው ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊ፣ አካባቢያዊ፣ ወይም የሁሉንም ተፈላጊነት
መውደቅ (dis-urbanization) የሚመለከት ሲሆን የመሃል ከተማውን ተፈላጊነት መውደቅ ለመታደግ ሲባል
በሚወሰድ የከተማ ማደስ እርምጃ አማካይነት የሚፈጠረው የዋና ከተማ ማንሰራራት (re-urbanization)
አራተኛውና የመጨረሻው የከተሞች ዕድገት ዑደት ነው (በርግ፣ 1987)፡፡

ከዚህ መረዳት የሚቻለው ከተሞች ምንጊዜም በማይቋረጥ የለውጥ ሂደት ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን እና
የነባር ከተሞች ድቀትና እርጅና (Urban Degeneration) በየትኛውም የዕድገት ደረጃ ላይ በሚገኙ አገሮች
የሚስተዋል የሁሉም ከተሞች የጋራ ባህሪይ መሆኑን ነው፡፡ በዚህ ክስተት ዙሪያ ከከተማ-ከተማ /ከአገር-አገር/
ልዩነት ካለም በድቀቱ መንስኤዎች፣ ጥልቀትና ስፋት እንዲሁም ችግሩን ለመቅረፍ በሚወሰዱ እርምጃዎች
ዓይነትና ውጤታማነት ነው፡፡

አብዛኛው የከተማ እርጅናና ድቀት (Urban Degeneration) በስፋት የሚስተዋለው በመሃል ከተማ (Inner
City) ነው፤ ለዚህ ደግሞ መሠረታዊ ምክንያቱ፡-

1
 መሃል ከተማ /inner City/ መጀመሪያ ከተሞች የሚቆረቆሩበት አካባቢ እንደ መሆኑ መጠን ረጅም
ዕድሜ ያስቆጠሩ ግንባታዎች በስፋትና በብዛት የሚገኙበት መሆኑ፣
 መሃል ከተማ ከተሞቹ ሲቆረቆሩ በነበረው የኢኮኖሚ መዋቅር፣ ዕውቀት፣ የአኗኗር ባህልና ቴክኖሎጂ
ላይ ተመስርቶ የሚገነባ እንደ መሆኑ መጠን ከዘመኑ የዕድገት ፍላጎት ጋር አብረው የማይሄዱ
ግንባታዎች በስፋት የሚገኙበት መሆኑ፣
 የትራንስፖርት አገልግሎት መሻሻልን ተከትሎ አቅም ያላቸው ነዋሪዎችና ተቋማት በመሃል ከተማ
የሚስተዋለውን ከፍተኛ መጨናነቅና ብክለት ምክንያት መሃል ከተማውን ጥለው ወደ ከተማ ዳርቻ
/satellite cities/ መሸሻቸውን ተከትሎ የመሃል ከተማው ኢኮኖሚ የሚዳከም መሆኑ ናቸው፡፡

መሃል ከተማው ለሥራና ለኑሮ ምቹ አይደለም በሚል ሰበብ አቅም ያላቸው ተቋማትና ነዋሪዎች መሀል
ከተማውን ትቶ ወደ ከተማ ዳርቻ የመሸሽ ክስተት በአብዛኛው የሚስተዋለው በበለፀጉት የምዕራባውያን
አገሮች ሲሆን በኤሽያና አፍሪካ የመሃል ከተሞች ትልቁ ፈተና ከአቅም በላይ በሆነ ነዋሪ እንዲሁም
በኢኮኖሚና ማህበራዊ ተቋማት እንቅስቃሴ መጨናነቅ ነው፡፡

የመሃል ከተማ መውደቅ (Urban Degeneration) መንስኤ በበለፀገው የምዕራቡ ዓለምና በታዳጊ አገሮች
መካከል ለሚታየው ልዩነት ዋናው ምክንያት የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎታቸው የሚገኝበት የዕድገት ደረጃ
ነው፡፡ በምዕራቡ ዓለም ፈጣን የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስፋፋት በመሃል ከተማና በከተማ ዳርቻ
መካከል ያለውን የቦታ ርቀት ስላጠበበው ነዋሪዎችም ሆኑ ተቋማት ከመሃል ከተማው የተጨናነቀ ሕይወት
ራሳቸው ነፃ ለማድረግ ያላቸው አማራጭና ዕድል ሰፊ ነው፡፡

እላይ በተጠቀሰው የፕሮፌሰር ሊዮን በርግ ጥናት ግኝት መሰረት አብዛኞቹ የበለጸጉ ሀገራት ተከታታይ በሆኑ
የከተማ ዕድገት ዑደቶች ውስጥ አልፈው ዛሬ ከተሞቻቸውን ጤናማ ወደሆነ ሕይወት ማሸጋገር ስለቻሉ
የከተማ መውደቅ ብዙ አያሳስባቸውም፤ ችግሩ ፈታኝና ጊዜ የማይሰጥ የልማት አጀንዳ ሆኖ የሚገኘው በታዳጊ
ሀገራት ነው፡፡

ከተሞች በለውጥ ፍላጎት መጠን የተወሰነ ክፍላቸው ማርጀት የማይታለፍ ነው፡፡ በመሆኑም ያረጀውን አካባቢ
መልሶ መልማት የማይታለፍ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የሚነሳው ጥያቄ ቢኖር ያረጀውን (ተፈላጊነቱ የወደቀውን)
አካባቢ ለማደስ የመንግስት ጥረት ለምን ያስፈልገዋል? ለምንስ እራሱን አያድስም ወይም መልሶ አይለማም?
ለሚለው ጥያቄ ምላሹ እንደየ ሀገራቱ ሁኔታ የሚለያይ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በብዙዎቹ የሚታዩት ወሳኝ
ኩነቶች በእድሜ፣ በቴክኖሎጅ፣ በግንዛቤ፣ በአቅምና ፍላጎት ለውጥ፣ ሀገራትና ከተሞች የተገበሩት የፖሊሲ
ውጤት፣ ተስፈኝነት (speculation)፣ መሃል ከተማ በሚኖረው ስበት ከፍተኛነት የተነሣ የሚመጣ
መጨናነቅ፣ በፍላጎቶች ግጭት /አንዱ ሊያለማ ሲፈልግ ሌላው በመቃወሙ/ ሂደቱ የሚገታ ስለሚሆን (ክሪስ፣
1990)፣ እና እርስ በእርስ መጠባበቅና መቆራኘት (prisoner’s dilemma) ተሳስሮ ባለበት ይቆማል፡፡

2
ይህ ክስተት በበለጸጉት ሀገራት በስፋት የነበረና አሁን በተወሰነ ደረጃ የተሻገሩት ሲሆን፣ አሁንም አልፎ አልፎ
ባህሪያዊ በሆነ መልኩ ሲከሰት ሳይሰፋ መቅረፍ የሚችሉበት ደረጃ ስለደረሱ ትልቅ አጀንዳ ላይሆን ይችላል፡፡
በተወሰነ ስፋት የሚስተዋለው በግሎባላይዜሽን ምክንያት እየተከሰተ ካለው የካፒታልና የጉልበት ዝውውር
ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ከተሞች ያለውን ሁኔታ ስንመለከት ደግሞ ባለንበት ዘመን
ከተከሰተው ፈጣን የክተመት ሂደት (Rapid Urbanization) እና ከአቅም ውሱንነት ጋር በተያያዘ ችግሩ
እየገዘፈና እየተንሰራፋ በመሄድ ላይ ያለ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

የከተማ ውድቀትን ለመቅረፍ ከተሞቹ ያላቸው የመቋቋም አቅም ውሱን ስለሆነ ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ፣ የደቀቁና
የተፋፈጉ መኖርያዎች ግዝፈት እየሰፋ ያለበት ፍጥነት አስደንጋጭ ነው፡፡ እንደተባበሩት መንግሥታት መረጃ
በዓለም ላይ ለመኖሪያና ለሥራ ምቹ ባልሆኑ አካባቢዎች (Slum areas) የሚኖሩ የከተማ ነዋሪዎች ድርሻ
31.6% ነው፤ ይህ አሃዝ በበለፀጉ ሀገራት 6% በታዳጊ ሀገራት 43% ሲሆን ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ
ሀገራት ደግሞ 71.9% ነው (UN - Habitat, 2003)፡፡

በኢትዮጵያ የከተሞች እርጅና የሚገኝበት ደረጃ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ካለው ሁኔታ የከፋ
እንደሆነ ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፤ ለምሳሌ እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር በ2010
በአገሪቱ ከነበረው የከተማ ነዋሪ ውስጥ 80% የሚሆነው ደረጃቸውን ባልጠበቁ የመኖሪያ አካባቢዎች ይኖር
እንደነበር ከተባበሩት መንግሥታት የተገኘ መረጃ ያመለክታል (UN - Habitat, 2010)፡፡

በሀገሪቱ የከተማ እርጅና ለዘመናት ሲከማችና ሲንሰራፋ የኖረ ችግር ነው፤ ችግሩ በሁሉም ከተሞቻችን
እንዲንሰራፋ ያደረገው ዋናው ምክንያት ከከተሞቻችን አቆራቆርና አመሠራረት ይጀምራል፤ የአብዛኞቹ
ከተሞቻችን አቆራቆርም ሆነ ዕድገት በተሟላ የከተማ ፕላን የተመራ ሳይሆን ከገጠር ሠፈራ ባልተለየ መንገድ
በዘፈቀደ እየተስፋፋ የመጣ ነው፡፡ ጥቂት የማይባሉትም ከወታደር ካምፕነት ወደ ከተማነት የተሸጋገሩ ናቸው፡፡

ከተሞቹ አብዛኛውን ክፍላቸው ከደረጃ በታች በሆኑ የግንባታ ቁሳቁሶች የተገነባ ከመሆኑም በላይ አስፈላጊው
የመሰረተ ልማት አውታር ያልተዘረጋላቸው የተፋፈጉ ሠፈሮች ቁጥርም ቀላል አይደለም፡፡ በዚህ ላይ
ከተሞቻችን ከጊዜው ጋር እራሳቸውን እያደሱና እያስተካከሉ የመጡ አይደሉም፡፡ በተለይ የተወረሱ
የመንግሥት (ቀበሌ) ቤቶች በስፋት የሚገኙባቸው ሠፈሮች ባለፉት አርባ ዓመታት የነባር ከተማ ማሻሻያ
ፕሮግራም ያልጎበኛቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡ በዚህም የተነሣ አብዛኛው ክፍል ጥልቅ በሆነ የከተማ እርጅና
(Urban Decay) የተጠቃ ነው፡፡ በዚህ መሠረት እላይ የተጠቀሰው የተባበሩት መንግሥታት መረጃ መሬት
ላይ ካለው እውነታ ብዙ ይርቃል ተብሎ አይገመትም፡፡

ቀደም ባለው ዘመን ያረጀ፣ ልማት ያቆመና ተፈላጊነቱ የወደቀ የከተማ ክፍል መልሶ እንዲያንሰራራ የማድረጉ
ሂደት ነባር ግንባታን ጠርጎ በማፅዳት ላይ ያተኮረ፣ ሰፊ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት የሰፈነበት እንደነበር
በስፋት ተዘግቦ ይገኛል (ክሪስ 1990፣ ካርሞን 1999፣ ቨርማ 1990፣ ኤለን ዜይትዝ 1979፣ ጀምስ ዊልሰን

3
1966፣ ፒተር ሮበርት 2000)፡፡ ሆኖም በሂደት ይህ አካሄድ በሚያስከትለው ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ
ኪሳራ ሳቢያ በበርካታ ከተሞች ከፍተኛ ተቋውሞ የገጠመው ሲሆን በምትኩ የበርካታ አካላትን ተሳትፎና
ድርሻ የሚጋብዝ፣ የሚወሰደው እርምጃም እንደየቦታው ተጨባጭ ሁኔታ የሚለያይ፣ ግንባታን መለወጥ
ሳይሆን ዙርያ መለስ (ፊሲካላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ወዘተ) እይታ ያለው እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ይዘቱም
ከጠርጎ እድሳት (Urban Renewal) ወደ መልሶ ማልማት (Urban Regeneration) ተሸጋግሯል ፡፡

በአገራችን የከተማ ማደስ ልማት አጀንዳ የመንግሥትን ትኩረት እየሣበ የመጣው ከጥቂት ዓመታት ወዲህ
ነው፡፡ በተለይ በትልልቅ ከተሞች ተቋማዊ ምላሽም ማግኘት ጀምሯል፤ በዚህ በኩል አዲስ አበባ በቀዳሚነት
ተጠቃሽ ናት፡፡ በሌሎች አንጋፋ ከተሞችም በተወሰነ ደረጃ ጅምሮች ይታያሉ፡፡ እነዚህ ጅምሮች እንደተጠበቁ
ሆነው በሀገራችን የነባር ከተማ ማደስ ፕሮግራም በተሟላ አደረጃጀት፣ ዘላቂ በሆነ አቅጣጫና ወጥ በሆነ
ፖሊሲ እየተመራ ነው ማለት ግን ያስቸግራል፡፡

በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች፣ ሲካሄድ የቆየውና አሁንም የሚካሄደው መልሶ ልማት ተጠንቶ ተገቢውን
ትምህርት ተወስዶ የሚተገበር አይደለም፡፡ በተለይም ቀጥለው የተጠቀሱት ጉዳዮች በዝርዝር ተጠንተው
የተሟላ ግንዛቤ ባልተጨበጠበት ሁኔታ የተገባበት ልማት ነው፡፡
 መልሶ ልማት ማካሄድ ያስፈለገበት ምክንያትና እንዲሳካ የሚፈለግ ዓላማ
 የመልሶ ልማት አማራጭ አግባቦች ጥንካሬዎችና ድክመቶች
 ተጠቃሚውና ተጎጂው የትኛው የሕ/ሰብ ክፍል መሆኑ እንዲሁም የነዋሪው ተጠቃሚነትና ጉዳት ደረጃ
 ከተሞች መልሶ ልማት በመምራት ያላቸው ዓቅም እና አጠቃላይ የአመራር ስርዓቱ
 መልሶ ልማት ከከተማው የረጅም ጊዜ የልማት ራዕይ ጋር ያለው ትስስር ወዘተ

በእነዚህና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ የተቀመረ ዕውቀት እምብዛም አይደለም፡፡ መልሶ ልማት የተወሰነ
ወቅትና የተወሰኑ ከተሞች አጀንዳ ሳይሆን የከተሞች ተፈጥሮአዊ ሂደት ውጤት በመሆኑ ከተሞች እስካሉ
ድረስ የሚኖር ነው፡፡ ስለዚህ መልሶ ልማት ከተሞችን ተደማሪ ሁለንተናዊ አወንታዊ ለውጥ
እንዲያስገኝላቸው በእውቀት ታግዞ መመራት ይኖርበታል፡፡

የነባር ከተማ መልሶ ልማት ዘርፈ ብዙ እንድምታዎች ያሉት በአግባቡ ከተመራ በርካታ ኢኮኖሚያዊና
ማህበራዊ ችግሮችን የሚፈታ፣ በአግባቡ ካልተመራ ግን ሰፊ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ ዋጋ
የሚያስከፍል የልማት አጀንዳ ነው፡፡ ልማቱ በርካታ አካላትን (Urban Actors) የሚነካ በመሆኑ ሂደቱ
ውስብስብ ነው፤ በልማቱ የሚነኩ ባለድርሻ አካላትን ፍላጎት የሚያሟላ የከተማ መልሶ ማልማት ወጥ የሆነ
የፖሊሲ ማዕቀፍ፣ ጠንካራ ተቋምና ግዙፍ የፋይናንስ ሀብት ይጠይቃል፡፡ እነዚህ ግብዓቶች ባልተሟሉበት
ሁኔታ የሚካሄድ የከተማ ማደስ ፕሮግራም አንድም የሚፈለገውን ዓላማ ሳያሣካ ተንገራግጮ ሊቆም ይችላል፤
በግፊት እንዲቀጥል ከተደረገም የሚያስከፍለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዋጋ ቀላል አይሆንም፡፡

4
የዚህ ጥናት አስፈላጊነትም መሬትን በስርዓት ከመምራት፤ ሀብትን ከማከፋፈል፤ መልካም አስተዳደርን
ከማስፈን እንዲሁም የግል ባለሀብቱን ወደ ልማት ከማስገባት አንጻር ትልቅ ፋይዳ ያለውን የከተሞች መልሶ
ማልማት ሂደት ነባራዊ ችግሮች ስፋትና ይዘት ለመገምገም፤ በከተሞች የተካሄዱና በመካሄድ ላይ የሚገኙ
የመልሶ ልማት ጥረቶች ነባራዊ ሁኔታ በመተንተን አወንታዊ ተሞክሮዎቹ የሚያጎለብትና የነዋሪውና የከተማው
ተደማሪ ፋይዳ የሚያኮላሹ የአፈጻፀም ክፍተቶች የሚያስተካክል የጥናት ሰነድ ማዘጋጀትና የመፍትሔ ምክረ-
ሓሳብ ማቅረብ ነው፡፡

በመሆኑም በአንዳንድ ከተሞች በተወሰነ ዳሰሳ እንደተለየው ትልቁ ትኩረት ከተማን ወደጎን መለጥጥ ላይ
እንደነበር፤ የከተማው ነባር ክፍል በአግባቡ እንዳልለማ፤ መልሶ ማልማት የተገባበት ሲታይም ሂደቱ ከፍላጎት
አንጻር የማይመጣጠን፤ ወጥነት የጎደለውና በባለድርሻዎች ዘንድ ያለው የአካሄድ ተቀባይነት ዝቅተኛነት
ከወዲሁ በጥናት የተደገፈ ዘላቂና ባለድርሻን ማእከል ያደረገ ፖሊሲና የአሰራር ማእቀፍ ማበጀት ተገቢነት
ታምኖበት ይህ ፕሮጀክት በኢፌዴሪ ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል የከተማ ልማት ፖሊሲ ጥናትና ምርምር
ዘርፍ ተነድፏል፡፡

ጥናቱ የተካሄደውና ሪፖርትም የተዘጋጀው ማእከሉ ባዘጋጀው የስራ ቢጋር መሰረት ሲሆን ስራውን ለማከናወን
በጥናት ቡድኑ አንድ አስተባባሪና አራት ባለሙያዎች ተሳታፊ ነበሩ፤ ለጥናቱ በናሙናነት ከተመረጡ ስድስት
ከተሞች ደግሞ ከእያንዳንዱ ከተማ ሶስት ባለሙያዎች በተባባሪነትና በአመቻችነት ታሳትፎ አድርገዋል፡፡

የጥናት ሪፖርቱ በመጀመሪያ ይህንን መግቢያ ይዟል፡፡ በመቀጠል ከስራው የሚጠበቅ ፋይዳ በጥቅል ዓላማ
መልክና በሂደት መቅረብ ያለበትን ውጤት በዝርዝር ግብ መልክ ያመላክታል፡፡ የጥናቱን ወሰንና ውስንነቶች
ካሳየ በኋላ ጥናቱ የተከተለውን የአጠናን ዘዴ ይገልጻል፤ የተከናወነውን የንድፈሃሳብና የመልካም ልምድ ዳሰሳ
በማሳየት በኢትዮጵያ በናሙና በተመረጡ ከተሞች የተከናወነውን የነባራዊ ሁኔታ ቅኝት በማመላከት የጥናቱን
ግኝት ያሳያል፡፡ በመጨረሻም በትግበራ ላይ ልንከተለው የሚገባ አቅጣጫ በማመላከት ይደመድማል፡፡
በአባሪነት ደግሞ የመረጃ መሰብሰብያ መሳሪያዎችና የተወሰኑ ዝርዝር ገላጭ ደጋፊ ሰነዶች ተያይዘዋል፡፡

1.2. የጥናቱ ዓላማና ግቦች


1.2.1. ዋና ዓላማ
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ ከተሞች ወጥና ባለድርሻዎችን ማእከል ያደረገ ዘላቂና ተቀባይነት ያለው
የከተማ መልሶ ማልማትን በማረጋገጥ በከተሞች ደረጃውን የጠበቀ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንዲመዘገብ
የሚያስችል፤ ለዜጎች የኑሮ ሁኔታ መሻሻል የበኩሉን ድርሻ የሚጫወት፤ በከተሞች እይታና ከባቢያዊ ሁኔታ
መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያግዝ የፖሊሲ ማእቀፍና ዝርዝር የአሰራር ስርአት እንዲዘረጋ ማድረግ ነው፡፡

5
1.2.2.ዝርዝር ግቦች
በዚህ ጥናት ሂደትና መጨረሻ ላይ በውጤትነት የሚጠበቁ ግቦች
1. በከተማ መልሶ ማልማት ዙሪያ ለፖሊሲ ግብአት፣ ለህግ ማእቀፍ፣ ለአደረጃጀት፣ ለትግበራ ስትራቴጅ
ቀረጻና ዝርዝር ጋይድ ላይን ለማዘጋጀት የሚረዳ የሀገራችንና የሌሎች ከተሞችን ተሞክሮ የዳሰሰ
ዝርዝር ጥናት ማካሄድና ሪፖርት ማቅረብ
2. በጥናቱ ግኝትና በሚደረስበት አቅጣጫ መሰረት በከተማ መልሶ ማልማት የፖሊሲ፣ የህግ ማእቀፍ
ግብአት፣ የትግበራ የአደረጃጀት አቅጣጫ ማቅረብ፣
3. በሂደቱ ስራውንና አፈጻጸሙን የተገነዘበና የተቀበለ ባለድርሻ መፍጠር የሚሉ ናቸው፡፡

1.3. የጥናቱ ወሰን /Scope of the Study/


በስራው ቢጋር እንደተመላከተው ጥናቱ በሁለት መልኩ የሚታይ ሲሆን በመጀመሪያ በሀገራችን ውስጥ ያለው
የመልሶ ማልማት ተሞክሮ ሲመለከት ቀጣዩ የዳበረ ልምድና መልካም ተሞክሮ ያለባቸውን ሀገራት አሰራር
መቀመር ይመለከታል፡፡ በሀገራችን የከተማ የመልሶ ማልማት ፕሮጀክት የተካሄደባቸው ከተሞች በርካታ
ቢሆኑም በዋናነት በዚህ ጥናት ለማካተት የተሞከረው አዲስ አበባ (ልደታ)፤ ጅማ (መርካቶና ዙሪያው)፣ ደሴ
እና መቀሌ፣ ሃዋሳና ድሬዳዋ ከተሞች ላይ የተከናወኑ ተሞክሮዎችን መቀመር ላይ ነው፡፡ ወደ ውጭ ስናይ
ደግሞ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች የእነ ቻይና (ሀንጁ/ሸንዘን)፣ ደቡብ ኮሪያ (ሶል)፣ የቱርክና ቬትናም
ተሞክሮዎችን መቀመርና ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ የሚጠቅሙትን ለይቶ ማስቀመጥ ላይ
ያተኩራል፡፡ በመቀጠል የሚነደፈውን የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ ለመሞከር ደግሞ የናሙና ዳሰሳ ጥናት
በማካሄድ በቀደምት ከተማነታቸው ያረጁና የደቀቁ ሰፈሮች የበዙባቸው ከተሞች (ደሴ፣ ጅማ፣ መቀሌ፣ ሃዋሳ፣
ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ) የከተማ አቀፍ ትንታኔ በማካሄድ የከተማ ማደስ የሚያስፈልጋቸው አካባቢዎችን
በመለየት ፕሮጀክት ለመንደፍ የሚረዳ ሰነድ ማዘጋጀት ላይ የተወሰነ ነው፡፡ በእነዚህ ከተሞች በናሙናነት
የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች መሪ፤ ፈጻሚና ባለድርሻን ለማዘጋጀት ማገዝ ወደፊት የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በጥናቱ ወቅት መረጃ በተፈለገው ጊዜና ሁኔታ አለመገኘት፣ ለተሞክሮ ማጋራት የተመረጡ ከተሞችና ሀገራት
በተፈገለው ጊዜ በተፈለገው አግባብ ለማስተናገድ አለመቻል ችግሮች ያጋጠሙ ሲሆን መረጃ በተፈለገው
ጊዜና ሁኔታ አለማግኘትን ለመቅረፍ በመጀመሪያ ደረጃ ባለድርሻዎች ግንዛቤ የማስጨበጫ ውይይት
በማድረግ ሙሉ ባለቤትና ተሳታፊ እንዲሆኑ የማድረግ፤ በተረፈ ቀድሞንም ችግሩ በተወሰነ እንደሚገጥም
በማሰብ በተገኘው መረጃ ጥልቅ ትንተናና የመስራት ስልት ለመከተል ተችሏል፡፡ ለተሞክሮ ማጋራት
የተመረጡ ከተሞችና ሀገራት በተፈገለው ጊዜ በተፈለገው አግባብ ለማስተናገድ አለመቻልን ለመቅረፍ
ፍላጎትን ቀድሞ በግልጽ ማስቀመጥና ቀደም አድርጎ በማሳወቅ ለመፍታት ጥረት ቢደረግም ሊሳካ ባለመቻሉ
የውጭ ተሞክሮ ቅመራ ስራ አልተከናወነም፡፡ ይህን ክፍተት ለመድፈን ከአሁን በፊት በሌሎች አካላት
የተደረጉ የተሞክሮ ጉዞዎች የተቀመሩ ጽሁፎችና ሌሎች አማራጮች ለመሸፈን ተሞክረዋል፡፡

6
1.4. የጥናቱ ዘዴ
1.4.1. የተከተለው መርህ
i. አሳታፊነት፡ ጥናቱ ከጅምር አንስቶ ባለድርሻዎችን ያሳተፈ ነበር፡፡
ii. ፈጻሚዎችን ባለቤት የማድረግ ስልት፤ በተለይ በናሙናነት በተመረጡ ከተሞች ያሉ አመራሮች
ሂደቱን በባለቤትነት ይዘው እንዲጓዙ የተደራጀ ተሳታፎ እንዲኖራቸው ለማድረግ ተሞክሯል፡፡
iii. የተቀናጀ አካሄድ፡ ይህ ከተማ መልሶ የማልማት ጥናት ጎን ለጎን ከሚከናወኑ በቀጥታና በተዘዋዋሪ
የሚቆራኙ የከተማ ጥግግት እና የከተሞች መስፋፋት ጥናቶች አንዱ ሌላኛውን መመገብ በሚችልበት
አግባብ ተቀናጅቶ የተከናወነ ነበር፡፡
iv. ዘላቂ ልማትን ማእከል ያደረገና የባለድርሻ አካላት ፍላጎትና ተጠቃሚነት ግምት ውስጥ ያስገባ
እንዲሆን ጥረት ተደርገዋል፡፡

1.4.2. የትንተና ዘዴና ስልት/Analytical Tools/


በስራው መጀመርና ግንዛቤ ምእራፍ ወቅት ከፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማእከል የዘርፉ አስተባባሪ ሚኒስቴርና
የጥናት ክፍሉ ቡድን በጋራ ውይይት በማካሄድ ስለ ስራው አድማስና አካሄድ የጋራ ግንዛቤ መጨበጥ፡፡
በመስኩ ቅድመ ዳሰሳ በማካሄድ ዝርዝር የስራ መርሃ ግብርና ተፈላጊ አደረጃጀትና ግብአት ማመላከት ስራዎች
ተከናውነዋል፡፡ የዚህ ምዕራፍ ተግባር የተደመደመው የግንዛቤ ሪፖርት በማቅረብ ነው፡፡ የዚህ አካል የሆነው
ሌላው ስራ የመረጃ ማሰባሰቢያ መጠይቆችና ቃለመጠይቆች መቅረጽ፤ የጥናቱን አመላካች ማውጫ
ማዘጋጀትና ለስራው ሙሉ አደረጃጀት መፍጠርን የያዙ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

የአጠናኑ ዘዴም የዳሰሳ ጥናት (Survey) እና ምርመራ ዓይነት (Case Study) የሚያካትት ሆኖ አግባብነት
ያላቸው የፖሊሲ እና የስትራቴጂ ሰነዶች ተለይተው በጥልቀት በመገምገም፣ ጥናቱን ለማዳበር የሚረዱ
መረጃዎች የመሰብሰብ፣ በዘርፉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች ዙሪያ የተጠኑ ጥናቶችን በመከለስ የሰነድ ትንተና
(Document Analysis) ማድረግና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት (በሞያው ላይ በቂ እውቀት ያላቸው
ባለሙያዎች) ጋር ቃለ መጠይቅ ማድረግና ከተመረጡ የባለሙያ ቡድኖች ጋር የርዕሰ ጉዳይ ውይይት መድረክ
(Thematic panel) በማዘጋጀት በመልሶ ማልማት ዙሪያ ስፋትና ጥልቀት ያለው ውይይት ማካሄድ፣ በመልሶ
ማልማት ምክንያት ከመኖሪያና ከመስሪያ ቦታቸው ከተፈናቀሉ ነዋሪዎች፣ በመልሶ ማልማቱ ዙሪያ ካሉ
ወገኖች፣ በቀጣይ ለመልሶ ማልማት በተመረጡ አካባቢዎች ካሉ የሕ/ሰብ ክፍሎች ስለነባሩ የመልሶ ማልማት
ሂደት እና ስለ ቀጣይ አቅጣጫ መጠይቅ በማዘጋጀት መረጃ ተለቅሞ የማደራጀትና የመተንተን ስራ
ተከናውኗል፡፡ በመስክ በአካል በመገኘትም ምልከታና የመረጃ ለቀማ ተካሂዷል፡፡

የሀገራዊ ተሞክሮና ነባራዊ ሁኔታ ጥናት ምእራፍ ወቅት የሰነድ ማሰባሰብ/ በከተማ መልሶ ማልማት ዙሪያ
በሀገራችን የተጠኑ ጥናቶች፤ የቀረቡ እቅዶችና ሪፖርቶች፣ ስራው በተከናወነበትና በማሳያነት እንዲቀመር

7
በተመረጡ ከተሞችና በቀጣይ በናሙናነት ሊተገበርባቸው የተመረጡን በመስክ በአካል በመገኘት ምልከታ
ማድረግና በቦታው ስላለው ለውጥ በምስል የተደገፈ መረጃ ማሰባሰብ እውነታውን ማረጋገጥ፤ በተመረጡት
ከተሞች በመልሶ ማልማት ዙሪያ በባለድርሻነት ከሚታዩ አካላት ጋር ስለ ሁኔታው ያላቸውን ግምገማና
ግንዛቤ እንዲሁም የመፍትሄ አማራጭ ለመረዳት ውይይት ማድረግ፤ በመልሶ ማልማት ተሞክሮ ቅመራ
በተመረጡት ከተሞች/ፕሮጀክቶች በቦታው የነበሩ አካላት ከ100 እስከ 150 ሰው፣ እንዲሁም በአካባቢው
ሂደቱን ከሚያውቁ ከ100-120፣ በቀጣይ በመልሶ መልማት ከሚታቀፉ እንዲሁ ከ100-120 ሰዎችን ስለመልሶ
ማልማት ሂደት እንዲሁም ስላስከተለው በጎና መጥፎ ውጤት በቀጣይ ሂደቱን በተሻለ ለመምራት መፍትሄ
ስለሚሉት ሃሳብ በመጠይቅ መረጃ መሰብሰብና ማደራጀት፣ የመረጃ ትንተና፣ ነባራዊ ሁኔታና የተሞክሮ
ሪፖርት ዝግጅት፣ ለቴክኒክና አብይ ኮሚቴ ውይይት ማቅረብ፣ ሰነዱን በግብአት አዳብሮ ማጠናቀቅ ስራ
ተከናውኗል፡፡

በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር በተመሳሳይ በጥናትና ምርምር ተቋማት በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ የተዘጋጁ ፅሁፎችና
ዶክመንቶችን ዳሰሳ (Literature Review) ተደርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የውጭ ተሞክሮዎችን በመውሰድ
ንፅፅራዊ ትንተና (Comparative Analysis) ማድረግና በከተማ መልሶ ማደስ ስኬታማ ከሆነ የውጭ ሀገር
ተሞክሮ ቤንችማርክ (Benchmark) ማድረግ ስራም የጥናቱ አካል ነበር፡፡ በዚህም ከላይ በጥናቱ ወሰን
እንደተጠቀሰው፣

 በሀገራችን ከተሞች በአዲስ አበባ (ልደታ) እንዲሁም በደሴ፣ በጅማ እና በመቀሌ ከተማ የመልሶ
ማደስ ፕሮጀክት የተከናወነባቸውን ተሞክሮ መቀመርና መልካሞችን አንጥሮ ማውጣት፤
 በሌሎች አገሮች እየተሰራባቸው ያሉ የከተሞች ማደስ መልካም ተሞክሮዎችን መምረጥና ከሀገር
ውስጥ ልምድ ጋር ያላቸውን ልዩነትና ተዛምዶ ማመላከት፤
 በማደግ ላይ ያሉ አገሮች የእነ ቻይና (ሀንጁ)፣ ደቡብ ኮሪያ (ሶል) ቱርክና ቬትናም ተሞክሮዎችን
መቀመርና ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ የሚጠቅሙትን ለይቶ ለማስቀመጥ፤
ተሞክሯል፡፡

በንድፈሃሳብ ዳሰሳና የሌሎች ሀገራት የተሞክሮ ቅመራ ጊዜ ደግሞ ከርእስ ጉዳዩ ጋር አግባብነት ያላቸው
ንድፈ-ሃሳብና ተሞክሮ ሰነዶች ማሰባሰብ፤ ዳሰሳ ማካሄድ፤ በርእሱ ዙሪያ ከዚህ በፊት በተለያዩ አካላት
በተደረጉ ትምህርታዊ ጉብኝቶች ተጠናክረው የቀረቡ ሃሳቦችን መቀመር ቀዳሚ ነበር፡፡ በርእሱ ዙሪያ ከዚህ
በፊት በተለያዩ አካላት በተደረጉ ትምህርታዊ ጉብኝቶች ተጠናክረው የቀረቡ ሃሳቦችን ባልሸፈኑት ሃሳብ ላይ
ትኩረት በማድረግ ለልምድ መቅሰም ለተመረጡ ሀገራትና ከተሞች ፍላጎታችን አውቀው በመዘጋጀት
ልምዳቸውን እንዲያጋሩን ለማስቻል የፍላጎት መግለጫ በማዘጋጀት፤ ከሚመለከታቸው ጋር መገናኘትና
ፕሮግራም ለማዘጋጀት፤ የተሞከረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያች ባለመሳካቱ የተሞክሮ ቅመራው በተገኙ ሰነዶች
ላይ ብቻ የታጠረ እንዲሆን ተገዷል፡፡

8
ስእል 1.1፡ የከተማ መልሶ ማልማት ጥናት ማዕቀፍ
ሂደት የምርመራ ነጥብ
 የኑሮ/ህይወት ለውጥ መምጣት የግድ የሆነ
 መሰረተ ልማትን፤ ከአቅም በታች መጠቀም
የቦታ መርጣ/የመልሶ ማልማቱ መነሻ
ዓላማ  ጥቅሙ ወደ ሌላ የመስፋት እድሉ
 ለትግበራ ያለው ቅለት/ያልተወሳሰበ
 በቦታው ያሉ ወገኖች ፍላጎት መኖር
 በፕላን የተለየ መሆን

 ዙሪያ መለስ/ፊሲካላዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የ


ፕላንና ፕሮግራም ዝግጅት ሁኔታ ያየ/ዘርፈ ብዙ ዓለማ ባ
 ተገቢውን የመልሶ ማልማት ስልት የለየ ለ
 የተቀናጀ/ከመዋቅራዊ ፕላኑ፤ ከዙሪያው እርስ ድ
በራሱ ር
 ሊተገበር መቻል/በአቅምና ተቀባይነት አንጻር ሻ
 የቦታ አጠቃቀም ቅይጥነት ዎ
 ፕላኒንጉ በግልጽ ስትራቴጅና ፕሮግራም የተመራ ች
ማደረጀት ሂደት ተ
የክትትልና ግምገማ ስርአት

 ለተግባሩ የሚመጥን/በቂ ሀብት ነጻነትና ሳ


ቅንጅት ያለው ት
 ለባለድርሻዎች ያለው ተደራሽነት ፎ


 የተሰጠው ጊዜ/ለማንሳት፤ ለማልማት
ትግበራ አመራር የ
 ተለማጭነት/በእውነታ ያለው ምልሰት

 የባለድርሾች ተቀባይነት/በካሳ በማዛወር ለ
 ፕላንን የተከተለ መሆን ቤ
 ለፍላጎት ያለው ምልሰት ት


 የተመዘገበ ውጤት ከእቅድ
ውጤት በማነጻጸር/በመጠን በጊዜ ደ
 የወጣ ወጭ ውጤት ከእቅድ በማነጻጸር ረ
 በባለድርሻዎች ያገኘው ተቀባይነት ጃ

 ያስገኘው ጠቀሜታ ካስከተለው ጉዳት


ፋይዳ o ከባቢያዊና ፊዚካላዊ
o ኢኮኖሚያዊ
o ማህበራዊ /ትስስር፤ ስራ፤ ገቢና
ወጭ ሁኔታ

9
ስእል 1.2: አደረጃጀት

1.5. የነበሩ ተግዳሮቶችና የተፈቱበት አግባብ


• በቃለ መጠይቅና ውይይቶች የተገኘው መረጃ ሂደቱን በማሳወቅ መልኩ ጠቀሜታ አለው፤ ዕውነታን
ብቻ ከማስጨበጥ የራስ አመለካከትም ማንጸባረቅን የሚታየው ውሱን ክስተት በውይይት፣ በማጥሪያ
ጥያቄዎች፣ በሌሎች መረጃዎች፣ በምልከታ በተገኘ ግብአት ለማስተካከል ተሞክሯል፡፡
• ከአስተዳደሩ ከሚጠበቅ የሁለተኛ ደረጃ መረጃ ምንጭ በበቂ ያልተገኘው የመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች
መነሻ ሰነድ፤ አፈጻጸም የተገመገመበት ወጭና ገቢ መረጃ ጉድለት በውይይቶች፣ በመስክና ጎጉል ማፕ
በመጠቀም ለማካካስ ተሞክርዋል፡፡
• የውጭ ልምድ ተሞክሮ ተጽፈው የተገኙት ሪፖርቶች የተወሰነ ብቻ ሲሆኑ እነሱም በአመዛኙ ርዕሰ
ጉዳዩን በቀጥታ የሚመለከቱ ስላልሆኑ ብቁነት ይጎድላቸዋል፤ ሁለተኛ ምንጭ ከዌብ ሳይትም የተገኘው
ከሚፈለገው አንጻር የተቃኘና ብቁ ያለመሆን ስለታየ ቀጥታ ተሞክሮው በጥናት ቡድኑ ለማምጣት
የሚረዳ ሰነድ ተዘጋጅቶ ጉድለቱን ለመሙላት የተሞክረ ቢሆንም ፕሮግራሙ ባለመሳካቱ ቅመራው
በሰነድ ላይ ብቻ ያተኮረ ሆኗል፡፡

10
ክፍል ሁለት፡ የንድፈ ሃሳብና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ዳሰሳ

2.1. የንድፈ ሃሳብ ዳሰሳ


2.1.1. የከተማ ምንነት እና የመልሶ ማልማት አስፈላጊነት
ወደ ከተማ ማደስ መሠረተ ሃሳብ ዝርዝር ትንተና ከመግባታችን በፊት፣ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ከተማ የሚለው
ቃል የሚወክለው የሕይወት ዘርፍ ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ ማየት ተገቢ ነው፡፡ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ
ከተማ የሚለው ቃል የሚወክለው ለመልሶ ልማት በተከለለ አካባቢ የሚገኝን ሁለንተናዊ የሕይወት ዘርፍ
(Urban Fabrics) ማለትም ፊዚካላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የሕይወት ዘርፎችንና አካባቢውን ነው፡፡

ከተማ በአጠቃላይ በርካታ ህዝብ እንዲሁም የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴ በአንድ የተወሰነ አካባቢ
የሚስተናገድበት፣ ከገጠር በተለየ ሁኔታ የኑሮ መሰረቱ ከግብርና ውጭ የሆነ ህዝብ በብዛት የሚኖርበት፤
ከተሜነት፤ ዘመናዊነት፤ የኑሮ ዘይቤያቸው ከገጠር በተለየ ሰዎች በተወሰኑ የስራ መስኮች የየራሳቸው ልዩ
ስምሪት (Specialization) የሚታይበት፤ የሚያመረተውና የሚጠቀመው የተለያየ፤ የሚያመርተው በተነጻጻሪ
ገቢ አስገኝነቱ ከደስታና እርካታ ምንጭነቱ ባለፈ በቀጥታ ከሚጠቀመው ጋር ያልተቆራኘ፤ መሰረተ ልማት እና
ተፈላጊ አገልግሎቶች ተቀራርበው የሚያገኙበት፤ እንቅስቃሴ የጦፈበት ወዘተ በማለት እንደ ሙያ ዲስፒሊኑ
አተያይ በአንድ ወገን የሚያተኩር የሚለያይ ትርጉም ወይንም ሁሉን ለማርካት የሚሞክር ትርጉም ሊሰጥ
ይችላል፡፡

በዋናነት ግን ከተማ ሰውና ልዩ ልዩ ተቋማት በብዛትና በጥግግት የሚኖሩበት፣ ለተለያዩ አገልግሎቶች የዋሉ
ቦታዎችን ነዋሪው በጋራ የሚጠቀምበት ክልል (Geographic area) ነው፡፡ የሰው ልጅ እንደማንኛውም
ፍጡር ሁሉ ተፈጥራዊ ሂደት ውስጥ ያልፋል፣ ይወለዳል፣ ያድጋል፣ ይሰራል፣ ያረጃል፣ ይሞታል፡፡ በመሆኑም
ሰው የሰራው ነገር ሁሉ ዘላለማዊ አይደለም፤ ይሰራል/ይገነባል፣ አገልግሎት ይሰጣል፣ ያረጃል፣ ካልታደሰ
ከነጭራሹ ይጠፋል፡፡ በሌላ በኩል የሰው ልጅ ፍላጎት ገደብ የለውም፤ ሁል ጊዜ ለውጥ ፈላጊና ለለውጥ
የሚጥር በመሆኑ ከሌሎች እንስሳት ይለያል፡፡

የሰው ልጅ በማይቋረጥ ፍላጎቱና ጥረቱ ዓለምን ይለውጣል፤ ከተሞች የሰው ልጅ የስራ ውጤቶች፣ የፈጠራ
ግኝቶችና የእድገት መገለጫዎች ናቸው፡፡ ከተሞች ሁልጊዜ በለውጥ ውስጥ መሆናቸው ባይካድም ከሰው ልጅ
ፍላጎትና ቴክኖሎጂ ዕድገት ፍጥነትና መጠን ጋር አብረው እየተለወጡ መሄድ የመቻልና ያለመቻላቸው ጉዳይ
ወሳኝ የእድገታቸው አጀንዳ ነው፡፡ የከተሞች የተወሰነ ክፍል ከአጠቃላይ የለውጥ ፍላጎት ጋር አብሮ
የማይሄድበት (የሚያረጅበት) ምክንያት እንደየ ሀገሩ ተጨባጭ ሁኔታ የሚለያይ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ
የሚከተሉት ወሳኝ ኩነቶች በብዙ ከተሞች የሚስተዋሉ የጋራ ባህርያት ናቸዉ፡፡

11
ረጅም ጊዜ ኣገልግሎት መስጠት፡

ረዥም ዕድሜ ያስቆጠሩ ግንባታዎች ማርጀታቸው ተፈጥሮአዊ ነው፣ በእድሜ ምክንያት ማርጀትም ያለ ነው፤

የቴክኖሎጅ ለውጥ፡

ምንጊዜም ቴክኖሎጂ በማያቋርጥ የለውጥ ሂደት ውስጥ ነው የሚገኘው፤ በዚህ መሠረት ከተሞች ሲቆረቆሩ
የነበሩ ቴክኖሎጂዎችን ታሳቢ አድርገው የተገነቡ የመሰረተ ልማት አውታሮች በየጊዜው ከሚፈጠሩ
ቴክኖሎጂዎች ጋር አብሮ መሄድ ሲያቅታቸው አካላዊ እርጅና ባይታይባቸውም የቴክኒካል እርጅና
(Technical obselesence) ሰለባ ይሆናሉ፡፡ የተገነቡበት ቁስም ሆነ ቴክኖሎጂ ኋላ ቀር መሆን (እድሜ
የማይሽራቸውና እንደተወደዱ የሚዘልቁ ያሉትን ያህል የሚሰለች ጥቅም የማይሰጥ ማደሻ ስልት የሌለው
ቴክኖሎጂም አለ)፡፡

ለቴክኖሎጂ አመጣሽ እርጅና በቀላሉ ተጋላጭ ከሚሆኑ የኢኮኖሚ መሠረተ ልማት አውታሮች መካከል
የተሽከርካሪዎች መንገድ፣ የባቡር መስመርና ኢንዱስትሪ በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል
ብዙ ከተሞች ከገጠር በፈለሱና የገጠርን የአኗኗር ዘይቤ ይዘው በመጡ ነዋሪዎች ያለ ፕላን የሚቆረቆሩ
እንደመሆናቸው መጠን ከተሞቹ መጀመርያ የተቆረቆሩበት ማእከላዊ የከተማ ክልል (inner city) የሚገኘው
ግንባታ ብዙም ከገጠሩ ያልተለየ፤ የገጠር ቤቶች ሲገነቡ በነበረው ቁስና የአገነባብ ዘዴ የተገነቡና ለከተማው
የማይመጥን ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ በቴክኖሎጂ ለውጥ ፍጥነት ምክንያት ከእድሜው በፊትም ቢሆን ነባሩ
ከአዲሱ ጋር ሲታይ የወደቀ ሊሆን ይችላል፡፡ ከመሀል ከተማው ወጣ ስንል ደግሞ መደበኛ በሆነ -ምክንያት
የደቀቁ አካባቢዎች ይፈጠራሉ፡፡ ይህ ክስተት በማደግ ላይ ባሉ አገሮች የከፋ ነው፡፡

የፍላጎት ለውጥ፡

ገቢ ሲያድግ የተሻለ ኑሮ መፈለግ/ሰፊና ጥራት ያለው ቤት መሻት፣ የከተማ እንቅስቃሴ ዘመናዊ የትራንስፖርት
ሥርዓት ሲሸጋገር አዲሱን የትራንስፖርት ስርዓት የሚያስተናግድ መሰረተ ልማት ማስፈለጉ፤ ለአነስተኛና
ጥቃቅን ተቋማት ሥራ እንቅስቃሴ ያገለግል የነበረ ቦታ (Urban Space) ከፍተኛ የኢኮኖሚ መዋቅር
እንቅስቃሴን መሸከም ባለመቻሉ የተነሣ ሌላ ቅርጽና ስፋት ያለው ቦታ ስለሚያስፈልግ፣ ነባሩ የከተማ ክልል
እየጨመረ የሚሄደውን ነዋሪ ማስተናገድ ሲያቅተው መጀመሪያ ማካፈል (Sub-division) ችግሩ በዚህ
እርምጃ ካልተቀረፈ በመልሶ መገንባት ጥግግትን ወደ ማሳደግ እርምጃ መሸጋገር፤ ግንዛቤ ሲያድግ በፊት
ትኩረት የማይሰጣቸው ጉዳዮች ትኩረት ማግኘትና የሁኔታዎች መለወጥ/ ለምሳሌ ለንጽህና መጠበቂያ
ያገለግሉ የነበሩ ወንዞች ሲበክሉ ወይም ከተማው ሲሰፋ የተለመደው አገልግሎት ሊሰጡ አለመቻል፣ ክፍትና
መዝናኛ ቦታ እንደ ቅንጦት ይታይ የነበረ መሰረታዊ ፍላጎት ሆኖ መምጣት፤ በእግር ሁሉንም ቦታ መድረስ
በሚቻልበት ወቅት የማያስፈልገው መሰረተ ልማት ከተማ ሲሰፋ ለመሰረተ ልማት መሬት ማስለቀቅ ግድ
ማለት፡፡

12
የከተማ ሕይወት እጅግ ውስብስብና ተለዋዋጭ በሆኑ የአኗኗር ሥርዓቶች የተሞላ ነው፡፡ እነኝሁ ሥርዓቶች
ፊዚካላዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ሽግግሮች የሚመሯቸው በርካታ ሂደቶች ከማንፀባረቃቸውም
ባሻገር ለብዙ ለውጦችም እንደ ግንባር ቀደም መንስኤዎች ተደርገው የሚወሰዱ ክስተቶች ናቸው፡፡ በዚህ
መሠረት በየትኛውም የዕድገት ደረጃ ላይ የሚገኝ ከተማ ከየወቅቱ ሁኔታ ጋር ተጣጥሞ እንዲራመድ
ከሚገፋፉት የውጭ ተጽእኖዎች እንዲሁም እድገትም ሆነ ዝቅጠት ከሚያስከትሉ ውስጣዊ ግፊቶች ራሱን ነፃ
ለማድረግ ያለው እድል በጣም አናሳ ነው፡፡

ይህ ክስተት በአሁኑ ጊዜ በበለጸጉ ሀገራት በስፋት አይስተዋልም፡፡ በምዕራቡ ዓለም በቅርቡ የታየውና ሰፊ ስራ
ተሰራ የሚባለው ምእራብ እና ምስራቅ ጀርመን ሲዋሃዱ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ የነበረው ፍልሰት
የፈጠረውን የከተማ መጎሳቆል ለማስተካከል የተወሰዱ እርምጃዎች ናቸው፡፡ ከዚህ ባሻገር በግሎባላይዜሽን
ምክንያት እየተከሰተ ካለው የካፒታልና የጉልበት ዝውውር ጋር የተያያዙ ክስተቶች የሚያሳርፉት ተጽዕኖ
አልፎ አልፎ ለምዕራቡ ዓለም ከተሞች መውደቅና መነሣት መንስኤ ሲሆኑ ይስተዋላል፡፡ በማደግ ላይ ባሉ
ሀገራት ከተሞች ግን ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ፣ የደቀቁና የተፋፈጉ መኖርያዎች ግዝፈት እያደገ ያለበት ፍጥነት ምን
ያህል አስደንጋጭ እንደሆነ ቀደም ሲል ተገልጿል፡፡ የተባበሩት መንግስታትም የሁኔታውን አሳሳቢነት በማየት
ነው በ2020 በትንሹ ከ100 ሚሊዮን በላይ የደቀቁ አካባቢ ኗሪዎችን ሁኔታ ማሻሻልንና በቀጣይ ክስተቱን
መግታትን እንደ አንድ መሠረታዊ ግብ ያስቀመጠው (the 7th goal of UN MDG)፡፡

ከተማን መልሶ መገንባት፣ መልሶ ማስነሳት፣ ማደስ፣ መልሶ ማልማት ወይም መፍጠር የብዙ ተጽእኖዎች
ድምር ውጤቶች ወይም ምላሾች እንደሆኑ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ ከተከታታይ የፖሊሲ አፈጻጸም ሂደቶች
ለማየት እንደሚቻለው በከተሞች የሚከሰቱ ፈርጀ ብዙ ለውጦች እንደ ግል ውሣኔ ነጠላና ድምር ውጤቶች
(Individual and collective decision) ይታያሉ፡፡ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከግሎባላይዜሽን መስፋፋት
ጋር በተያያዘ በከተሞች አካባቢ ውሣኔዎችን ከሚያስከትሏቸው ውጤቶች ለይቶ የመመልከት አዝማሚያ
በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መጥቷል (ኩራን እና ብላክበርን 1994 እ.ኤ.አ) ፡፡

2.1.2. የከተማ መልሶ ልማት ታሪካዊ አጀማመርና ሂደት


ከተማን መልሶ የማልማት እና የማዘመን እንቅስቃሴ እንደ አንድ የከተማ ልማት አጀንዳ ተይዞ ራሱን የቻለ
ፕሮግራም ተቀርጾለት መተግበር ከጀመረበት ከ193ዐ (እ.ኤ.አ) መጀመሪያ አንስቶ በተለያየ ቅርጽ፣ ይዘትና
የትኩረት መስክ የከተማ ማደስ ሥራ በተለያዩ አገራት ሲተገበር ቆይቷል፡፡ ከተማን መልሶ የማልማት እርምጃ
በተለያዩ ሀገራት/ከተሞች/ የተለያየ ስያሜ ሲሰጠው መቆየቱ እንደተጠበቀ ሆኖ እስከ 1970ዎቹ የተተገበሩ
የመልሶ ልማት ፕሮግራሞች በሚከተሉት ሦስት አበይት ምዕራፎች /Generations/ ተለይተው ይታወቃሉ
/ካርሞን 1999) እነሱም፤

 አሮጌ ግንባታን ጠርጎ ማንሳት (Urban Renewal - the Era of Bulldozing ከ1930 - 40ዎቹ)

13
 የነባር ከተማ መልሶ ማንሠራሪያ ፕሮግራም (The Era of Neighborhood Rehabilitation በ1960ዎቹ)
 የነባር ከተማ ልማትን የማነሳሳት ፕሮግራም (Revitalization በ1970ዎቹ) ናቸው፡፡

በቅርብ ዘመናት የተተገበሩ የነባር ከተማ ልማት ፕሮግራሞችም እንዲሁ መልሶ መገንባት (Reconstruction)፣
የወደቀ ከተማ ልማትን መመለስ (Regeneration) እና መልሶ ማልማት (Redevelopment) በሚል ስያሜ
ይጠቀሳሉ (ስቶር፣1989፣ ሊችፌልድ፣ 1992 እ.ኤ.አ.)፡፡

እስከ 1950ዎቹ መጨረሻ ነባር ግንባታን ጠርጎ በማንሳት ላይ ያተኩር የነበረው የመልሶ ልማት ፕሮግራም
ያስከፈለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዋጋ ከፍተኛ ነበር፡፡ የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ በመሃል ከተማ የነበረውን
ያረጀና የወደቀ ግንባታ በአዳዲስና ዘመናዊ ግንባታዎች መተካት ስለነበር ከመሃል ከተማ ለሚነሱ ነዋሪዎች
ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ አልነበረም፡፡ በዚህም የተነሣ ፕሮግራሙ ከፍተኛ ተቃውሞ
ገጥሞት ነበር፡፡

ራሱን የቻለ የከተማ ማደስ ፕሮግራም ቀርጾ ተግባራዊ በማድረግ በኩል እንግሊዝ በፋና ወጊነት ትጠቀሳለች
(ፒተር ሮበርተስ 2000)፡፡ እንግሊዝ በማዕከላዊ መንግስት የፖሊሲ ማዕቀፍ እና የፋይናንስ ድጋፍ
(Earmarked Fund) አማካይነት በ1930ዎቹ በርካታ ነባር ከተሞቿን ማደስ ችላለች፡፡ ከእንግሊዝ ቀጥሎ ሰፊ
የከተማ ማደስ ተሞክሮ እንዳላት የምትጠቀሰው አሜሪካ ናት (ጀምስ ዊልሰን 1966)፡፡ በአሜሪካ በ1940ዎቹ
አሮጌ ግንባታን ጠርጎ በማንሳት በምትካቸው ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ የመገንባት ሰፊ ዘመቻ ተካሂዷል፤ የዚህ
ዘመቻ ዋና ዓላማ ጥቁሮችን ከመሃል ከተማ ማስወጣት ነው የሚል እምነት በብዙዎች ይስተዋላል ፡፡

እስከ 1950ዎቹ መጨረሻ በብዙ ምዕራባውያን ከተሞች የተካሄዱ ነባር ግንባታን ጠርጎ በአዲስ ግንባታ
የመተካት እርምጃ ከፍተኛ ተቃውሞ አስተናግደዋል፤ እስከዚህ ጊዜ ድረስ የተነሺዎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ
ሕይወት የከተማ ማደስ ፕሮግራም ቁልፍ አጀንዳ አልነበረም፡፡ በዚህም የተነሣ የተነሺዎች አያያዝና መልሶ
ማቋቋም ሰፊ ችግር የሚስተዋልበት ነበር፡፡

በአጠቃላይ በተለያዩ ዘመናት ሥራ ላይ የዋሉ የከተማ ማደስ ፕሮግራሞች ሥራ ላይ ባዋሏቸው ስልቶች


(approaches and strategies)፣ ባሰለፏቸው ተዋንያን (stakeholders)፣ በተተገበሩበት ጂኦግራፊያዊ ክልል
ደረጃ (Spatial level)፣ በኢኮኖሚ ግባቸው (Economic Focus)፣ በማህበራዊ ውጤታቸው (Social
Impact) እንዲሁም በአካባቢ ደህንነት ጥበቃ አግባባቸው (Environmental Approach) የራሳቸው መለያ
ባህሪያት ነበሯቸው (ፒተር ሮበርትስ እና ሂዩ ሳይክስ፣ 2ዐዐዐ)፡፡

በዚህ ሂደት ከተስተዋሉ የአጀማመርና የአፈጻጸም ክፍተቶች እንዲሁም ካስከተሏቸው ውጤቶች በተወሰዱ
ትምህርቶች ሳቢያ ባሁኑ ወቅት በመጣመርና በመመጋገብ በሥራ ላይ እየዋሉ የሚገኙት የከተማ ልማት
ስትራቴጂዎች በዋነኝነት ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም የነባር ከተማ መሻሻያ (upgrading) የከተማ ማደስ
(Urban Renewal) እና መልሶ ማልማት (Regeneration) ናቸው፡፡
14
ከተማ ማሻሻል ትኩረቱ በአካባቢው የጎደለን ከማሟላትና መጠነኛ ጥገናዊ ለውጥ ከማድረግ ጋር የሚያያዝ
በአመዛኙ መደበኛ ባልሆኑና የዝቅተኛ ህብረተሰብ መኖሪያዎች ላይ የሚደረግ የልማት እንቅስቃሴ ሲሆን
ይዘቱ የኗሪዎቹን የአኗኗር ሁኔታ መቀየር ላይ የሚያነጣጥር፤ አካባቢያዊ ለውጥ ሂደታዊ እንደሚሆን የሚያስብ
ነው፡፡ እንደ አንደርሰን (1964 እ.ኤ.አ) አመለካከት “ከተማ ማደስ” ማለት “የተጐሣቆሉና ያረጁ ግንባታዎችን
በመጠነ - ሰፊ የማፍረስ እንቅስቃሴ ጠርጎ የማንሳት ሂደት ነው፡፡” እንደ ጊር (1965 እ.ኤ.አ) አስተያየት ደግሞ
የከተሞችን ማዕከላዊ ሥፍራዎች መልሶ በመገንባት የተጐሣቆሉ ግንባታዎችን ከመሃል ከተማ ማጥፋት ነው፡፡
ሪቻርድሰን የተባለ የዘርፉ ተመራማሪ እንደሚያስረዳው የከተማ ማደስ ጽንሰ ሀሳብ የሚከተሉትን ሦስት
ትርጉሞች ያቅፋል፤
 መልሶ ማልማት (Redevelopment) ማለት አንድን አጠቃላይ አካባቢ ማፍረስ፣ ማጽዳትና መልሶ
መገንባት ነው፡፡
 መልሶ ማቋቋም (Rehabilitation) ማለትም የደከሙ ግንባታዎችን ወደ ተቀመጠ ዘመናዊ
ስታንዳርድ/ደረጃ ማምጣት ነው፡፡
 መንከባከብ (Conservation) ማለትም የአንድ አካባቢ ፊዚካል ገጽታ ጠብቆ ለማሻሻል ሲፈለግ
የሚካሄድ ከፊል የማጽዳትና ተገቢ መልሶ ግንባታ ማከናወን ነው (ከባልዊን፣ ዴቪድ እና ዌን
የተወሰደ፣ 2ዐዐዐ፡278-279)

ባልዊንና ጓደኞቹ ከሪቻርድሰን ትርጓሜ በመነሳት ለመልሶ ማልማትና ለመልሶ ማቋቋም የበኩላቸውን ትርጉም
ለመስጠት ሞክረዋል፡፡ እንደ እነርሱ አተያይ፤

 መልሶ ማቋቋም ጥገናን፣ እድሳትንና ጠንካራ ከወቅቱ የአገልግሎት ፍላጐት ጋር የተጣጣሙ


ሕንፃዎችን የሚያጠቃልል የከተማ ልማት እስትራቴጂ (ገጽ 279) ሲሆን፣
 መልሶ ማልማት ደግሞ ነባር ሕንፃዎችን ሙሉ በሙሉ መተካትን የሚመለከት ስልት ነው፡፡ በሌላ
አነጋገር ይህ መልሶ ማልማት የመሬት አጠቃቀምን፣ የይዞታ ሽፋንን፣ እንዲሁም አዳዲስ የሕንፃ
ግንባታ ቴክኒኮችን፣ ስታንዳርዶችን፣ ስፔሲፊኬሽኖችን፣ ንድፎችን እና አቀማመጦችን ማስተዋወቅ
ማለት ነው (ገጽ 279)፡፡

ሮበርትስ (2ዐዐዐ፡17) የተባለው የዘርፉ ባለሞያ በበኩሉ መልሶ ማልማት/ማነቃቃት የሚለውን ጽንሰ ሀሳብ
እንደሚከተለው ይተረጉመዋል፡፡ መልሶ ማልማት/ማነቃቃት ማለት ወደ ከተማ ነክ ችግሮች መፍትሔ
የሚያመራና ለኤኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፊዚካላዊና አካባቢያዊ ሁኔታዎች ዘላቂ መሻሻል ለማምጣት
የሚቀመር አጠቃላይና ውሁድ ራዕይና እርምጃ ማለት ነው ፡፡ ይህንኑ ትርጓሜ በማስፋት ይኸው ባለሞያ
የከተማ መልሶ ማልማት/ማነቃቃትን ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘረው መልኩ ያጠቃልለዋል፡፡ በዚህም መሠረት
መልሶ ማልማት/ማነቃቃት (Regeneration) ማለት ለከተማ ልማት ስኬት ሲባል፣
 የሚካሄድ ጣልቃ የመግባት እንቅስቃሴ
15
 የሕዝብን፣ የግሉንና የማህበረሰብ ሴክተሮች በመሻገር የሚፈጸም ተግባር
 በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በፖለቲካ ሁኔታዎች ለውጥ ሳቢያ ተገቢውን ተቋማዊና መዋቅራዊ
ምላሽ ለመስጠት የሚከናወን እንቅስቃሴ
 የጋራ ጥረትን በማሰባሰብ በሥራ ላይ የሚያውል የልማት መሣሪያ
 የተጎሳቆሉ የከተማ አካባቢዎችን ለማሻሻል የሚያበቁ ፖሊሲዎችና እርምጃዎችን ለማመልከትና
ለመወሰን የሚያስችል መሣሪያ ማለት ነው (ገጽ፡ 22)፡፡

ከላይ ከተመለከቱት የከተማ-ነክ ፖሊሲዎች ማስፈጸሚያ ስልቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለዋዋጭነት በሥራ
ላይ እየዋሉ ያሉት ሦስቱ ማለትም የከተማ ማደስ፣ መልሶ ማልማትና መልሶ ማነቃቃት ሲሆኑ እንደ ስተኸር
እና ሌችፊልድ አመለካከት የእነኝህ እስትራቴጂዎች ዓይነት፣ ቁልፍ ተዋንያንና ያገባናል ባዬች፣ ስልቱ
የሚተገበርበት ሕዋዊ እርከን፣ የኤኮኖሚ ትኩረት፣ ማህበራዊ ይዘት፣ የፊዚካል ትኩረትና የአካባቢ ደህንነት
አግባብ ደግሞ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱት ናቸው፡፡

ቀደም ሲል እንደተገለፀው የከተሞችን መጎሳቆል ሁኔታ ለመቀየር የተወሰዱ እርምጃዎች፤ ለችግር ምንጭነትና
መፍትሄ ሀገራት በነበራቸው ምልከታ ምክንያት በየሀገራቱና በተለያዬ ጊዜያት የተለያዩ ቢሆንም ጠቅለል ብሎ
ሲታይ በሶስት መልክ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡
 የመጀመርያው የደቀቀ አካባቢ የማይፈለግ የከተማ ክፍልና በህግ አግባብ ባልተፈቀደላቸው ወገኖች
የተፈጠረና ቢፈርስ ሊጠፋ እንደሚችል በመገመት የተካሄደ የማፍረስ ተግባር /the era of
bulldozing in 1930s in Britain and in 1940s in USA/ ነዉ፡፡
 ሁለተኛው ክስተቱ የከተሞች አንድ ገጽታ ነው፤ ቢፈርስ ይተካል፤ የሚፈርስባቸው ወገኖች መድረሻ
የላቸውም፣ ይጎዳሉ፣ ስለሆነም መከናወን ያለበት አካባቢን የማሻሻል ሥራ ነው የተባለበት ዘመን/ the
era of neighborhood rehabilitation in 1960s/ ሲሆን፣
 ሶስተኛው ለአካባቢው መውደቅ መንስኤውን መፈለግና ያን በማከም አካባቢው በራሱ እንዲቀየር
በር መክፈት እንጂ ማፍረስ ችግሩን አይፈታውም፤ ወጭውም ብዙ ነው፤ በማሻሻልም የሚገኘው
ለውጥ መጠነኛና ቁሳዊ ብቻ ነው፤ አካባቢው በዘላቂነት ላይቀየር ይችላል፤ ስለዚህ የሚያስፈልገው
አካባቢን መልሶ እንዲያንሰራራ የሚያደርግ ተግባር ነው የተባለበት ዘመን /the era of urban
revitalization starting from the 1970/ ተብሎ ሊታይ ይችላል (ካርመን፣ 2001)፡፡

2.1.3. በከተማ መልሶ ልማት የመንግስት ሚና አስፈላጊነት


አንድን አካባቢ ሲያረጅ ለምን በገበያ ኃይል መስተጋብር መልሶ ራሱ አይለማም? ለሚለው ጥያቄ ምላሹ የገበያ
ጉድለት /Due to market failure/ የሚል ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ምላሽ ስህተት ባይሆንም ‘ኮች’ ከዚህ ያለፈ
ዝርዝር ምክንያት ይሠጣል፤ እንደ ኮች አተያይ የከተማ ማደስ ለገበያ የማይተውባቸው ምክንያቶች፤

16
 ከተማ ማደስ በገበያ ኃይል የማይመለሱ ማህበራዊ ግቦች ስላሉት፤
 ከተማ ማደስ በትርፍ መርህ ለሚመራ የግል ኢንቨስትመንት አዋጪ ስለማይሆን፤
 በገበያ ኃይል በሚመራ ወጥነት የሌለው (Spontanuous/ ከተማ ማደስ የሚፈልገውን ለውጥ
ማምጣት ስለማይቻል፤
 በከተሞች የሚስተዋለው ውስብስብና ፈጣን ማህበራዊና ቴክኖሎጂካዊ ለውጥ የመንግሥትን ጣልቃ
ገብነት ግድ የሚል መሆኑ ነው፡፡

በአጠቃላይ ከተማ ማደስ ማህበራዊ ፋይዳው ሰፊ የሆነ የልማት ፕሮግራም /Public Good/ ነው፤ ማህበራዊ
ፋይዳው ሰፊ የሆነ ልማት ለገበያ ኃይል አይተውም፡፡ በዚህም የተነሣ በዓለም ላይ የከተማ ማደስ ፕሮግራም
መሪ ተዋናይ መንግሥት ነው፤ መንግሥት የፖሊሲ ማዕቀፎችን ከመቅረጽ ጀምሮ ፕሮግራሙን የሚያስፈጽም
ተቋም በማደራጀትና አስፈላጊውን የፋይናንስ ሃብት በመመደብ በከተማ ማደስ ፕሮግራም ትግበራ ቀዳሚ
ሚና ይጫወታል፡፡ በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የከተማ ማደስ ፕሮግራሞች ለመንግሥት ቀዳሚ ሚና
መነሻዎች ናቸው ተብለው በሚጠቀሱ መርሆች መካከል መለስተኛ ልዩነት ቢኖርም መሠረታዊ ምክንያቱ
የልማቱ ማህበራዊ ፋይዳና እንድምታ ነው፡፡ ለከተማ መውደቅ ምክንያት ከሆኑና የመንግሥትን ጣልቃ
መግባት ግድ ከሚሉ ምክንያቶች መካከል የሚጠቀሱት ዓበይት ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፤

ሀ) ሀገራት የሚከተሉት ማህበራዊ ፖሊሲ


ማህበራዊ - ተኮር የመንግስት መርህ (welfare states) በሚያራምዱ ሀገራት የማዕከላዊ ቦታ ፍላጎት
በሚጨምርበት ሁኔታ ነባሩ ግንባታ ቢያረጅም እንደመጠለያ ያሉ መሠረታዊ ፍላጎቶችን /Basic needs/
በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደር ህብረተሰብ ተደራሽ ለማድረግ ሲባል መንሥት በሚያስቀምጠው የኪራይ ጣርያ
ሳቢያ ባለሀብቱ ወደ አዲስ ኢንቨስትመንት እንዳይገባ ይገድባል ፡፡ በዚህ ላይ በመሃል ከተማ የቤት ፍላጎት
እየጨመረ ስለሚመጣ ባለሃብቱ ያለውን ቤት እየሸነሸነ ወደ ማከራየት ይሽጋገራል፤ ይህም ለአካባቢው
መጨናነቅ ተጨማሪ ምክንያት ይሆናል፡፡ ይህን ተከትሎ የሚከሰተው የመሃል ከተማ ውድቀት የመንግሥትን
ጣልቃገብነት ግድ ይላል፡፡ ሌላው የፖሊሲ ውጤት የፕላን ክልከላ ነው፡፡ ለማህበራዊና ታሪካዊ እሴቶች
ጥበቃ ሲባል የተወሰነ የከተማ ክልል ባለበት ሁኔታ እንዲቀጥል የሚደነግግ የፕላን ክልከላ ለዚህ ዓላማ
የተከለለው ክፍል አንዳይቀየር ይገድባል (ሴርኒያ፣ 1998)፡፡

ለ) ሳያለሙ የመጠቀም አባዜ የተጠናወታቸው ተስፈኞች /Speculators/


የከተማ መሬት ለተስፈኝነት /speculation/ በከፍተኛ ደረጃ የተጋለጠ ውስን ሀብት ነው፡፡ ከተማ ሲያድግ
የመሬት ፍላጎትም አብሮ ስለሚያድግ መሬት የያዙ ነገ የተሻለ ዋጋ ያወጣል በሚል እሳቤ ሶስተኛ አካል
በሚያወጣው ወጪ የሚፈጠር እሴትን መጠበቅ፤ የመሬት ዋጋ ነገ ይጨምራል በሚል ተስፋ ይዘው መጠበቅ
የተወሰኑ የከተማ ክፍሎች እንዳይለወጡ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ በይዞታቸው ዙሪያ

17
ያለው መሰረተ ልማት ሲያድግና አካባቢው ሲለማ ይዞታቸውን ሸጠው ባለፉበት ለመጠቀም የሚቋምጡ
የተስፈኝነት አባዜ በብዙ ሀገራት የታየና ከተሞች ራሳቸውን እንዳያድሱ የሚገታ የልማት እንቅፋት ነው፡፡
በመሆኑም ይህን ማነቆ ለመስበር መንግሥት ሥራ ላይ የሚያውላቸው በአግባቡ ባልለሙ ይዞታዎች ላይ
የሚጣል ግብርና የከተማ ፕላን ያሉ የፖሊሲ መሣሪያዎች መኖራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በእነዚህ የፖሊሲ
መሣሪያዎች አማካይነት ሊመጣ ያልቻለውን ልማት ለማምጣት የመንግሥት ቀጥታ ጣልቃ ገብነት አስፈላጊ
የሆኑባቸው አጋጣሚዎች በርካታ ናቸው፡፡

ሐ) የመሃል ከተሞች መጨናነቅ ውጤት


ጥግግት ልኩን እስካላለፈ ድረስ ለተጨማሪ ስበትና ለአካባቢ ተፈላጊነት መጉላት ወሳኝ ሚና የሚጫወት
መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ መጠኑን ሲያልፍ ግን ልማት ገፊ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ፈጣን የከተማ ዕድገት
በመሃል ከተማ ላይ የሚያሳርፈውን ጫና ለመቀነስ በብዙ አገራት በተለይ በምዕራቡ ዓለም የተወሰደው
እርምጃ በዋና ከተሞች ዙሪያ የሚገኙ ከተሞችን (Satellite Cities) ከመሃል ከተማው ጋር በፈጣን የህዝብ
ትራንስፖርት አገልግሎት ማስተሳሰር ነው፡፡ ይህ በመንግሥት እንጂ በገበያ ኃይል ሊመጣ አይችልም፤ ይህን
እርምጃ በሚፈለገው ደረጃ የወሰዱ አገራት የወደቁ ከተሞቻቸውን በተሳካ መንገድ ማደስ ችለዋል፡፡ ፈጣን
የሕዝብ ትራንስፖርት ባልተስፋፋባቸው ከተሞች መሃል ከተማው በትራፊክ መጨናነቅ የተነሣ በቀላሉ
ተደራሽ ስለማይሆን በአልሚ የሚኖረው ተፈላጊነት ይቀንሳል፤ የመታደስ እድሉም አብሮ ይሞታል፡፡

መ) የፍላጎቶች ግጭት
በተለይ በታዳጊ አገራት መሃል ከተሞች የብዙ አካላት ፍላጎት የስበት ማዕከል ናቸው፤ ሀብታሞች/ተቋማት/
መሃል ከተማውን ለስራ ሲፈልጉት ድሃው ጉልበቱን ሽጦ በቀላሉ የዕለት ጉርሱን ለማግኘት ከመሃል ከተማው
መራቅ አይፈልግም፣ የመንግሥት አካላት ነዋሪውን በቅርብ ሆነው ለማገልገል ቢሯቸውን በመሃል ከተማ
መክፈት ይመርጣሉ፡፡ በአጠቃላይ መሃል ከተሞች የብዙ ፍላጎቶች የስበት ማዕከል /Battle field of many
interests/ ናቸው፡፡ የተለያዩ አካላት ማዕከላዊ ቦታዎችን በእጃቸው ለማስገባት የሚያደርጉትን ሩጫ ተከትሎ
በሚከሰት የፍላጎቶች ግጭት የአንዱ የልማት እርምጃ ሌላው በሚፈጥረው እንቅፋት የሚገታበት አጋጣሚ
በርካታ ነው (ክሪስ፣ 1990)፡፡ በመሆኑም በተለያዩ በልማት ተዋንያን መካከል የሚከሰተውን የፍላጎት ግጭት
ፈትቶ መሀል ከተማውን ከገባበት ውድቀት ለማውጣት የመንግሥት እርምጃ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል፡፡

ሠ) የልማት ኃይሎች መቆላለፍ ውጤት


የከተማ ውድቀት /Degeneration/ በአንድ የከተማ ሕይወት ዘርፍ ብቻ የሚወሰን አይደለም፤ ውድቀቱ
በቁሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ወይም በአካባቢ ደህንነት ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡ ሁሉም በአንድ ጊዜ
ሊወድቁም ላይወድቁም ይችላሉ፤ ሁሉም በአንድ ጊዜ የማይወድቁበት አጋጣሚ ቢኖርም ቀድሞ የሚወድቀው
የሌላውን ውድቀት ስለሚያፋጥነው ቦታው ራሱን መልሶ ማልማት የሚችልበት ዕድል ጠባብ ይሆናል (ቨርማ፣

18
1990)፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአጎራባቾች መካከል በሚኖር አንዱ ሌላው አድፍጦ የመጠበቅ አባዜ /the
prisoner’s dilemma/ ሳቢያ የገበያ ኃይሎች የከተማ ውድቀትን ሳይታደጉ የሚቀሩበት አጋጣሚ ሰፊ ነው፡፡
በመሆኑም ይህን ማነቆ /Deadlock/ ሰብሮ የተለያዩ የልማት ተዋንያንን ወደ መልሶ ልማት እንቅስቃሴ ውስጥ
ለማስገባት የመንግሥት ሚና ወሳኝ ነው፡፡

እንደ ክላውዲዮ (1999) አተያይ የመልሶ ማልማት የፖሊሲ ማዕቀፍን በመቅረጽ፣ የሌሎችን ተሳትፎ
የሚያነሣሣ ማበረታቻ በማቅረብና ሂደቱን ህጋዊ ይዘት በማላበስ በኩል ከመንግሥት ሚና ውጭ ሌላ ሊታሰብ
አይችልም፤ የአውሮፓና ላቲን አሜሪካ ሀገራት ተሞክሮ የሚያረጋግጠው ይህንኑ ነው፡፡ በእነዚህ አህጉራት
ከተሞች በመልሶ ማልማት ፕላን ዝግጅት ወቅት ለቅይጥ ቦታ አጠቃቀም በቂ ትኩረት መስጠት የቻሉት፤
ተገቢውን ተቋማዊ አደረጃጀት የፈጠሩት፤ እና አስፈላጊውን የፖሊሲ ማዕቀፍና ተቋማዊ ቅንጅት ማስፈን
የቻሉት በመንግስት ግንባር ቀደም ሚና እንደሆነ ምሁሩ በጥናታቸው ማረጋገጣቸውን ያስረዳሉ፡፡

የግል ሀብትና መብት ገዥ ነው በሚባልበት አሜሪካ እንኳን ሳይቀር ድሃና ጥቁር ቀለም ያላቸውን ከመሃል
ከተማ የማባረር ሂደት ተብሎ የተፈረጀውን የ1950ዎቹን መልሶ ማደስ አካሄድ ትተን እ.ኤ.አ በ2ዐዐ5 የአሜሪካን
ጠቅላይ ፍ/ቤት/ ጐስቋላ የመኖሪያ አካባቢዎችን ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ለኢኮኖሚ ልማት ለማዋል የግል
ይዞታን ለመንግሥት ማስረከብ ሕገ መንግሥቱ ላይ የተቀመጠውን የግል ንብረት ዋስትና ሕግ አንቀጽን
አይፃረርም ሲል ኣምስት ለኣራት በሆነ ድምፅ በይኗል /ኤግል፣ 2ዐ1ዐ እ.ኤ.አ፤ ስታሌይ፣ 2ዐ1ዐ እ.ኤ.አ.፣27/
አተገባበሩ በየስቴቱ ቢለያይም ጉዳዩ ከውሳኔ አልፎ ወደ ትግበራ ገብቷል፡፡ በዚህ መሠረት በመልሶ ማልማት
የመንግስት መሪነት በአንድ ሀገር ወይም የኢኮኖሚ ሥርዓት ብቻ ሳይሆን በሁሉም ሀገራት ያለ ነው ብሎ
መውሰድ ይቻላል ፡፡

የከተማ መልሶ ማልማት የመንግስትን ሚና ግድ እንደሚል ከዓለም አቀፍ ልምዱ መማር ይቻላል፡፡ በመልሶ
ማልማት የመንግስታት ሚና ሕግና ሥርዓትን ከማስፈን (Regulatory) ባሻገር በልማቱ ላይ በሚደረግ ቀጥታ
ተሳትፎ ላይ የሚያዘነብል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በሌላ በኩል በሁሉም ሀገራት በሚባል ደረጃ ልማቱን ለመምራት
ጥቅም ላይ የዋሉት ተቋማዊ ማዕቀፍ መደበኛ የመንግስት መዋቅርን (Bureaucracy) ሳይሆን ወጪን በራስ
መንገድ በመሸፈን መርህ የሚሰራ የመንግሥት ልማት ድርጅትን (Urban Development Corporation)
በማደራጀት ነው፡፡ የልማት ድርጅቱን ወደ ሥራ የሚያስገባ ልዩ ፈንድ ማቋቋም ከአሜሪካ ከተሞች መልሶ
ማልማት ጀምሮ በበርካታ ሀገራት በስፋት የተተገበረ ስልት ነው፡፡

2.1.4. በመልሶ ማልማት ቀዳሚ ትኩረት የሚሹ የልማት አጀንዳዎች


በአንድ ከተማ ዘላቂና የተሣካ መልሶ ልማት መካሄዱን ለማረጋገጥ ለአራት አንኳር የልማት አጀንዳዎች
ተገቢው ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ የዘርፉ ምሁራን ይመክራሉ፡፡ ትኩረት የሚሹት የልማት
አጀንዳዎቹም የኤኮኖሚ ሽግግርና የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ማህበራዊና ማህበረሰባዊ አጀንዳዎች፣ የግንባታ

19
እርጅናና የመሬት ፍላጎት፣ የአካባቢ ደህንነት ናቸው (ኩክሊኒስኪ 199ዐ) ፡፡ በእነዚህ አጀንዳዎች ዙሪያ
ትኩረት ማድረግ የሚያስፈልግበት ምክንያቶች ደግሞ ከዚህ ቀጥሎ ቀርበዋል፤

ሀ) የኢኮኖሚ ለውጥና የሥራ እድል ፈጠራ


በዓለም ላይ በሚስተዋለው ፈጣን የገጠር-ከተማ ሽግግር (Rural-Urban Shift) እና የሥራ ክፍፍል (Spatial
Division of Labour) ሳቢያ በርካታ ሠራተኞች አዲስ እየተፈጠሩ ባሉ የኢኮኖሚ ዕድሎች ተጠቃሚ መሆን
አልቻሉም (ደዘርጊል እና ጉደጂን 1982 ፣ ማሴ 1984 እ.ኤ.አ)፡፡ በአንዳንድ ምሁራን አስተያየት ይህ ሊሆን
የቻለው አዲሱ ኢኮኖሚ የሚጠይቀው የሙያና የክህሎት ፍላጐት ተሟልቶ ባለመገኘቱ ነው (ማክግሬገርና
ማክኮናአቺ፣ 1995 እ.እ.አ)፡፡ እንግዲህ ይህን መሠረታዊ ችግር ለመቅረፍ ሲባል ነው የከተማ መልሶ ማልማት
/ማደስን፣ ማነሳሳትና ማነቃቃትን ባካተተ መልኩ መፈፀም እንዳለበት እየተሰመረበት የመጣው፡፡

ለ) ማህበራዊና ማህበረሰባዊ አጀንዳዎች


ምንም እንኳ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንደ ክስተት ሁለገብ ወሳኝነቱ ባያከራክርም የከተሞችን መዋቅርና የዕድገት
አቅጣጫ በመወሰኑ ረገድ ብቸኛ ጉዳይ ተደርጎ አይወሰድም፡፡ በተለይ በአሁኑ ጊዜ ሌሎች በከተሞች
አጠቃላይ ሕይወትና ዕድገት ላይ ከፍተኛ አወንታዊና አሉታዊ ተጽእኖዎች የሚያሳርፉ መሠረታዊ ጉዳዮች
ብቅ እያሉ ነው፡፡ ከእነዚህ መሠረታዊ ጉዳዮች መካከል አንዱ በማህበረ - ሕዝብ ዘርፍ የሚስተዋለው ለውጥ
(Socio-Demographic Trends) እና ይህን ተከትሎ የሚከሰተው የባህላዊ ቤተሰብና ማህበረሰባዊ መዋቅር
መፈራረስ (adjustment and breakdown of traditional family and community structures) እንደሆነ
የዘርፉ ምሁራን ያስረዳሉ፡፡

የማህበረ-ሕዝብ እድገት ለውጥን ተከትሎ በርካታ ነዋሪዎች ከነባር መኖሪያቸው በዋናነት ከማዕከላዊ የመኖሪያ
አካባቢዎች ወደ ከተማ ዳርቻ ይገፋሉ፡፡ ይህ የሕዝብ እንቅስቃሴ የሚከሰተው በእቅድ ላይ ተመስርቶ
በሚወሰድ እርምጃ ወይም ያለ ምንም እቅድ ሊሆን ይችላል (ሎውለስ፣ 1989 እ.ኤ.አ)፡፡ ለመሰል
እንቅስቃሴዎች መንስኤ ከሚሆኑ ውስብስብ ምክንያቶች መካከል አብዛኞቹ በከተሞች የለውጥ ሂደት
የሚከሰቱ አግላይ ልዩነቶች ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛሉ (ሂሌይና ጓደኖቹ፣ 1995 እ.ኤ.አ)፡፡

በከተሞች የለውጥ ሂደት ከሚከሰቱ ያልተጠበቁ አሉታዊ ውጤቶች መካከል አንዱና ዋነኛው የባህላዊ
ቤተሰቦችና ማህበረሰቦች አወቃቀር መፈራረስ ነው፡፡ በዚህ ለውጥ ሳቢያ ባህላዊ የሥራ እድሎች ይጠፋሉ፣
ማህበራዊ አገልግሎቶች ይዳከማሉ፤ የአካባቢ ደህንነት ማሽቆልቆል ይከሰታል፡፡ ይህን ሂደት ተከትሎ
የማህበራዊ ደህንነት መዋቅሮች እየተዳከሙ ይሄዳሉ፣ ከተሞችም የሚፈልጉትን ገጽታ መላበስና ተነፃፃሪ
ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ አይችሉም፡፡

20
ሐ) የግንባታዎች እርጅናና አዳዲስ የመሬት አጠቃቀም ፍላጐት
በበርካታ ታዳጊ አገሮች ከተሞች ላይ ከሚስተዋሉ መሠረታዊ ችግሮች መካከል ከደረጃ በታች የሆኑ
አካባቢዎች መስፋፋት አንዱ ነው፡፡ የከተሞች እርጅና ከሚከሰትባቸው መንገዶች መካከል ዘመን ያለፈባቸው
ግንባታዎችና የመሠረተ ልማት አውታሮችና አገልግሎቶች ከወቅቱ ፍላጎት ጋር አብሮ መሄድ አለመቻልና
የተጐሣቆሉ አካባቢዎች መበራከት በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው፡፡

ከተሞች የሚገኙበትን ፈጣን የቴክኖሎጂ ለውጥ ተከትሎ የሚከሰተው የከተሞች ፊዚካል እርጅና ሰፊ ነው፡፡
በየጊዜው በሚከሰቱ የለውጥ ሂደቶች የተነሣ የነባር ግንባታዎች አንጻራዊ ጠቀሜታ ይቀንሳል፤ ይህን ተከትሎ
የአዳዲስና የተጨማሪ መሥሪያ ቦታ፣ የመሠረተ ልማትና የተጓዳኝ አገልግሎቶች ፍላጐት ይከሰታል፡፡
በሚያስገርም ሁኔታ በአንዳንድ ከተሞች ነባር አካባቢዎች ከፍተኛ የአገልግሎት ወይንም የሴክተር ለውጥ
አስፈላጊነትን በስፋት ይጋብዛሉ፡፡ እነዚህ ነባር አካባቢዎች (Inner Cities) የከተሞች ቁልፍ የመኖሪያ፣
የመሥሪያና የመዝናኛ ማእከላት በመሆን ሰፊ የሀብትና ጥሪት ምንጭ ወደ መሆን ይሸጋገራሉ፡፡ ከዚህ
ተጨባጭ እውነታ በመነሳት ነው ታዋቂዋ የከተማ-ነክ ጉዳዮች ተመራማሪ ፌንስቴን (1994 እ.ኤ.አ) ለሰብአዊ
እንቅስቃሴ በተገነባው ከባቢ አጠቃቀምና በገበያ ማዕከላት ሚና መካከል ያለውን ልዩነት በአጠቃቀምና
በልውውጥ (Use and exchange) እሴቶች መካከል ያለ ልዩነት ነው ስትል ያጠቃለለችው፡፡

እንግዲህ ይህ ልዩነት ነው በከተማ የሰብአዊ እንቅስቃሴ መናሃሪያነትና በጥሪት (asset) ማመንጫነቱ መካከል
ለሚፈጠረው ተቃርኖ እንደ ነፀብራቅ የሚወሰደው፡፡ ይኸው ሁኔታም ነው ለብዙዎቹ የከተማ ችግሮች እንደ
አንኳር ርዕሰ ጉዳይ የሚታየው፡፡ በከተማነት አፈጣጠርና የእድገት ሂደት ታሪክ ላይ በውል እንደተመለከተው
ከተሞች በጊዜ ሂደት ይለወጣሉ፤ በጥቅሉ ሲታይ ይህ ሂደት አይቀሬና እንደ ጥሩ ክስተት መወሰድ የሚገባው
ነው፡፡ ምንጊዜም ቢሆን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች አዳዲስ ፍላጐቶችንና የእድገት
እድሎችን አንግበው ብቅ ይላሉ፡፡ በእርግጥ በጥቅሞቹ ላይ ከፍተኛ የአመለካከት ልዩነቶች አሉ፣ ይኖራሉም፡፡
እንደ መምፎርድ (1940 እ.እ.አ) አመለካከት በከተማ ውስጥ የተራራቁ ኃይሎችና ተጽእኖዎች ከአካባቢ
ሁኔታዎች ተቀላቅለው ይታያሉ፡፡ ግጭቶችም ከስምምነታቸው/ከመጣጣማቸው ያላነሱ ክስተቶች ናቸው፡፡
እንግዲህ ለነኝህ መሣይ ቅራኔዎች ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ሲባል ነው ፖለቲከኞች፣ አልሚዎች፣ ኘላነሮችና
ዜጐች በየወቅቱ ከሂደቱ ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽ ለመቀመር በስፋት ሲንቀሳቀሱ
የሚታዩት፡፡

በከተሞች ለሚከሰቱ አዳዲስ ፍላጎቶችና ፈተናዎች (Challenges) የሚሰጠው ምላሽ ከተሞቹ እንደሚገኙበት
ተጨባጭ ሁኔታ ይለያያል፡፡ በዚህ ረገድ ከሚወሰዱት እርምጃዎች መካከል የከተማ አስተዳደር ድንበሮችን
ማስፋት፣ የመሬት አጠቃቀም ስብጥርን ከወቅቱ ፍላጎት ጋር ማጣጣምና ከነባር ሥፍራዎች ጋር ማናበብ፣
ተጨማሪ የመኖሪያ፣ የፋብሪካ፣ የቢሮና የንግድ ማዕከላትን መገንባት የመሳሰሉ እርምጃዎች ከፊሎቹ ናቸው፡፡
በከተማ መልሶ ማልማት ዘርፍ ቀደም ሲል እንደተገለፀው በተለያዩ ዘመናት የተወሰዱ እርምጃዎች በዘመኑ
21
እንደነበረው ፍላጎት የሚለያዩ ናቸው፤ ይኸውም እ.ኤ.አ. ከ195ዐዎቹ ቀደም ሲል የከተማ ማደስ (Renewal)፣
በ1960ዎቹና 7ዐዎቹ የመልሶ ማነሳሳት (Revitalization)፣ ከ198ዐዎቹ ወዲህ ደግሞ የመልሶ ማልማት
(Redevelopment/Regeneration) ቁልፍ የመልሶ ማልማት ስትራቴጂ ነበሩ፡፡

መ) የአካባቢያዊ ጥናትና ዘላቂ ልማት፡


ተደጋግሞ እንደታየው የከተማ አካባቢዎች የታሰቡና ያልታሰቡ ከፍተኛ ድንገተኛ ወጪዎችን በማስከተል
ይታወቃሉ፡፡ ከእነኝህ ወጪዎች መካከል ከመጠን በላይ የናረ የኢነርጂ ፍጆታ፣ ያልተሳለጠ የጥሬ እቃ
አጠቃቀም፣ የክፍት ቦታዎች ትኩረት ማጣት፣ የመሬት የውሃና የአከባቢ አየር ብክለት በቀዳሚነት ተጠቃሽ
ናቸው፡፡ በቀደምት ዘመናት የከተሞች ትኩረት ወደ ኢኮኖሚ ብልጽግና ማምራት ላይ ያተኩር የነበረ ሲሆን
ባሁኑ ወቅት በሕብረተሰብ የአመለካከት ለውጥ ሳቢያ የከተሞች ስኬት የሚለካው በአካባቢ ገጽታና አፈጻጸም
ላይ እየሆነ መጥቷል፡፡ ይህም በመሆኑ ወደ ፊት ከተሞች የተሳካ ልማት ያመጡባቸዋል ተብለው ከሚገመቱት
ግብአቶች ውስጥ መሬትና ጉልበት በስፋት በማቅረብ ብቻ የሚታጠሩ አይሆንም፡፡ ከዚያ በመዝለቅ ለአካባቢ
ደህንነት ሰፊ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ በሚችሉ እንቅስቃሴዎች ማለትም እንደ ዘመናዊ የሕዝብ ትራንስፖርት
አውታር ዝርጋታ፣ የተመጠነ የሕዝብ ብዛት የሚይዙ ከተሞች ምሥረታ፣ ብቃት ያለው የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ
አወጋገድ ሥርዓት መዘርጋት የሚያስችል የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በመፍጠር እንዲሁም መሠረተ ልማትና
አገልግሎት የተሟላለት መሬት በነባር የከተማ ክልሎች ማዘጋጀትና ለመልሶ ማልማት ሥራ ማዋል
በመሳሰሉት እንቅስቃሴዎች ላይ መሣተፍን የሚጋብዝ እየሆነ መጥቷል፡፡

እነኝህ አማራጮችና ተመጋጋቢ ስትራቴጂዎች አብይ ግባቸው ለከተማ-ነክ ለውጦችና ተግዳሮቶች ዘላቂ
መፍትሔ መስጠት በመሆኑ ለሂደታቸውም ሆነ ለስኬታቸው በርካታ ገዢ መርሆች (principles)
እንዳሏቸውም የዘርፉ ባለሞያዎች ያረጋግጣሉ፡፡ እንደ ሮበርትስና ስካይስ (2ዐዐዐ እ.ኤ.አ) አተያይ የከተሞች
ዕድገት ስትራቴጂዎች ወደ ሚፈለገው ስኬት ያደርሳሉ ተብለው የሚገመቱት ቀጥሎ በተጠቀሰው አቅጣጫ
ሲቃኙ ነው፡፡

 በከተሞች አካባቢ ባሉ ሁኔታዎች ላይ ዝርዝር ትንታኔዎች ሲከናወኑ ፤


 በከተሞች አካባቢ ለተከሰቱ ፊዚካል ነዶዎች (Fabrics)፣ ማህበራዊ መዋቅሮች፣ ለኢኮኖሚያዊ
መሠረቶች እና ለአካባቢ ደህንነት ሁኔታዎች ጋር ሲጣጣሙ፤
 ለፊዚካል ነዶዎች፣ ማህበራዊ መዋቅሮች፣ ኢኮኖሚያዊ መሠረቶች እና ለአካባቢ ደህንነት ምቹ
ለመሆን በሚደረጉ ጥረቶችና ተግባር ላይ የሚውሉ ስልቶች እንደ አጠቃላይ ውሁድ ስትራቴጂ
ሲነደፉ፤
 የሚዘጋጁ ስትራተጂዎችም ሆኑ ኘሮግራሞች ከዘላቂ ልማት ዓላማዎች ጋር ከተናበቡ፤
 በአሀዝ ሊገለጹ የሚችሉ የትግበራ ግቦች ማስቀመጥ ሲቻል፤

22
 በተቻለ መጠን የሁሉንም ያገባኛል ባዮች ስምምነት ማግኘት ሲቻል፤ የአካባቢውን የተፈጥሮ፣
የኤኮኖሚ፣ የሰብአዊ፣ የመሬትና የከተማው ነባር የሀብት ምንጮች በከፍተኛ ደረጃ መጠቀም ሲቻል፤
 የስትራቴጂውንና የትግበራውን ሂደት መከታተልና መገምገም የሚያስችል ስልት ከተበጀለት፤
 በየጊዜው ከሚከሰቱ ለውጦች አንዱ የማሻሻልን አስፈላጊነት የሚቀበል ሲሆን ፤
 ለተለያዩ ግቦች የተለያዩ ፍጥነቶች እንደሚሹ ግንዛቤውን የወሰዱ ከሆነ፤

በሌላ በኩል በከተማ መልሶ ማልማት ኘሮግራሞችና ኘሮጀክቶች ላይ የሚነሳው መሠረታዊ ጥያቄ ለምን?
ከሚለው መነሻ ይልቅ እንዴት? በሚለው ነጥብ ላይ የሚያጠነጥን እየሆነ መጥቷል (ዓለም ባንክ፣ 2ዐዐ4
እ.ኤ.አ)፡፡ በዚህ ረገድ እስከ ቅርብ ጊዜ የተመዘገቡ ተሞክሮዎች የፖሊሲና የአሠራር ርዕሰ ጉዳዩች ውስጥ
መካተት የሚገባቸውን ርዕሰ ጉዳዬች ማለትም የመልሶ ማልማት የፖሊሲ ወሰኖች፣ የመልሶ ማስፈር አግባቦች፣
የተጠያቂነት መመዘኛዎች፣ የካሣ ስሌቶች ወዘተ እና የመልሶ ማልማት ኘሮግራሞችና ኘሮጀክቶች በከተማ
መልሶ ማልማት ፕሮግራሞች እንደ ስትራቴጂክ መነሻ የሚያገለግሉ መሆናቸውን የሚያስረግጡ አልነበሩም፡፡
በዚህም የተነሣ ብዙዎቹ የከተማ ፖሊሲዎች በዚህ ረገድ ስትራቴጂክ ራዕይ ወይንም የረዥም ጊዜ አመለካከት
የሚጐድላቸው ነበሩ፡፡ ይህም ሊሆን የቻለበት ምክንያት የመልሶ ማልማት ሥራዎች በስፋት ሳይሆን በጥቂት
አካባቢዎች የሚከናወኑ ዓይነት ሆነው መቆየታቸው እንደነበር አንዳንድ የዘርፉ ምርምሮች ያመለክታሉ (ቱሮክ
እና ሸት፣ 1994 እ.ኤ.አ)፡፡ በዚህም ምክንያት ለርዕሰ ጉዳይ ስትራቴጂካዊ አመለካከት ለመቅረጽ የተደረገው
ጥረት እጅግ አናሳ ነው፡፡ እ.ኤ.አ. በ198ዐዎቹ የተከናወኑ እንቅስቃሴዎች በይዘታቸው ጊዜያዊ ኘሮጀክቶች
እንጂ የረዥም ጊዜ እና ክልላዊ እይታ ኖሯቸው የተተገበሩ አልነበሩም፡፡ በዚህም ምክንያት በሂደት
የሚያጋጥሙ ችግሮች ቢኖሩ መፍትሄ ለመስጠት ሲሞከር የቆየው በቁጥ ቁጥ እንጂ ከመልሶ ማልማት ጋር
ለተሳሰሩ ርዕሰ ጉዳዩች ትኩረት በመስጠት ላይ በማነጣጠር አልነበረም፡፡ ይህ ዓይነት ጥረትና የኤኮኖሚ
እንቅስቃሴ (Economic Activity) ደግሞ አንድን ሥራ ደጋግሞ ማከናወንን አስከትሏል፡፡

ይህን የተመለከተው ሂሊ (1997 እ.ኤ.አ) የተባለ የዘርፉ ባለሙያ ከተማን ለማዘመን የሚካሄድ የመልሶ
ማልማት ኘሮጀክት በተናጠል የሚታቀድና የሚተገበር ሥራ መሆን የለበትም ሲል ይደመድማል፡፡ በዚህ ረገድ
ለሚከሰት ክፍተት መፍትሔው ለመልሶ ማልማት ስኬት ወሳኝ ለሆኑ ኤኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ከባቢያዊ
ርዕሰ ጉዳዬች ትኩረት መስጠት ነው ሲል ካርተር (2ዐዐዐ እ.ኤ.አ) የተባለ ሌላ የዘርፉ ተመራማሪ ይመክራል፡፡

በተለያየ የከተማ እርከን ለሚካሄዱ የመልሶ ማልማት ፕሮግራሞች ስኬት በቅድሚያ ወጥ የሆነ ከተማ - አቀፍ
ስትራቴጂካዊ ማዕቀፍ (Strategic Framework) መቅረጽና ሥራ ላይ ማዋል ወሳኝ ነው፡፡ ይህን መሣይ
ማዕቀፍ መቅረጽ የመልሶ ማልማት የትግበራ አድማስን ለመወሰን ከማስቻሉም በላይ ኘሮግራሙ/ኘሮጀክቱ
ከሚያስገኘው ኤኮኖሚ ግብ ባሻገር ከማህበራዊ እና ከባቢያዊ የረዥም ጊዜ አላማዎች ጋር የተጣጣመ
ስለመሆኑ በትክክል ለመለካት ሰፊ እድል ይሰጣል፡፡ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ባሁኑ ወቅት በፖሊሲ ውሣኔ ሰጪዎች

23
መካከል በመልሶ ማልማት ስትራቴጂካዊ አግባብ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ፖርኪንሰን (1996 እ.ኤ.አ)
እንደሚያስረዳው የአውሮፓ ኮሚሽን እ.ኤ.አ. በ1988 መዋቅራዊ ለውጥ ሲያካይድ አራት የመልሶ ማልማት
መርህዎችን ለይቶ አስቀምጧል፡፡ መርህዎቹም፤
 ኘሮግራሞቹ/ኘሮጀክቶቹ ተጨማሪ እሴት የሚፈጥሩ መሆን አለባቸው፣
 በተለያዩ ያገባናል ባዬች መካከል የሽርክናን አሠራር ለማስፈን የሚያግዙ መሆን አለባቸው፣
 የፕሮግራሞቹ ግቦች በግልጽ የተቀመጡ መሆን አለባቸው፣
 ከተለያዩ የፖሊሲ መሳሪያዎችና አግባቦች ጋር የሚናበቡ መሆን አለባቸው፤ የሚሉ ናቸው፡፡

ማክሬገርና ጓደኞቹ (1992 እኤ.አ) በበኩላቸው ስትራቴጂክ ማዕቀፍ ሊያካትታቸው የሚገቡትን መርህዎች
በተመለከተ ሲጽፉ የሰነዘሩት ሙያዊ ምክር የመልሶ ማልማት ኘሮጀክት ማዕቀፍ ማተኮር ያለበት ለኘሮጀክቱ
ትግበራ የሚውሉ የሀብት ምንጮች ዘላቂ ውጤት የሚያመጡ መሆናቸውን ማስረገጥ እንዳለበት ነው ፡፡
በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሰፊ ምርምር ያደረገው ፓርኪንሰን የተባለው ባለሞያ በበኩሉ ስለ መልሶ ማልማት
ስትራቴጂክ ማዕቀፍ ይዘቶች ሲጽፍ እንዲህ ይላል፡፡ ማዕቀፉ የተሟላ እንዲሆን፤
 በግልጽ የሰፈረ ራዕይና ስትራቴጂ ሊኖረው እንደሚገባ፤
 የተመረጡት የትግበራ ስልቶችና የተደለደሉት/የተመደቡት የሀብት ምንጮች የረዥም ጊዜውን ራዕይ
በማሳካት በኩል የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማመልከት ተገቢ እንደሆነ፤
 የመልሶ ማልማቱን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ከባቢያዊ ትኩረቶች ማዋሀድ እንደሚያስፈልግ፤
 ለመልሶ ማልማቱ የኘሮጀክት ስኬት የመንግሥትና የግሉ የማህበረሰብ የሀብት (በገንዘብ ወይም
በዓይነት) ድርሻ የማመላከት አግባብነት፤
 የያገባናል ባዬች ሚናና አስተዋጽኦ ለይቶ ማስቀመጥ አስፈላጊነት፤
 ለመልሶ ማልማት የሚውሉ ፖሊሲዎች፣ ተግባራትና የሀብት ምንጮች ከነ ምንጮቻቸው ማዋሀድም
ወሳኝነት፣
 ፖሊሲዎችን ከልዩ ልዩ የልማት ኘሮግራሞች ማለትም የቤት ልማት፣ ትምህርት፣ ትራንስፖርት፣
ጤና፣ ፋይናንስ ማስተሳሰር አለበት፤
 የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረዥም ጊዜ ዓላማዎች ተዛምዶ ለይቶ ማመልከት አለበት፣
 ከልማቱ በፊት የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ እና የፊዚካል ሁኔታ መነሻ ግምገማ ማካሄድ ይኖርበታል፤
 የየወቅቱ አፈጻጸም ለማመላከት የክንውን የማዕዘን ድንጋይ (milestone) ማስቀመጥ አለበት፤
 ውጤቱን መከታተልና መገምገም እንዲሁም ፋይዳውን ማመላከት አለበት /ካርተር 2ዐዐ5 ገጽ 43/

ለማጠቃለል በየጊዜው እያደገ ለሚመጣው ሕዝብ ፍላጐት እርካታ የሚወሰን የኤኮኖሚ ልማት በአዳዲስ
የፊዚካል መሠረተ ልማት ግንባታዎች ላይ ተመርኩዞ የሚከናወን እንቅስቃሴ ነው፡፡ ይህ እንቅስቃሴ ምንጊዜም

24
ቢሆን መሬትንና በላዩ ላይ ያረፉ ጥሪቶችን ወደ መልሶ ልማት ማስገባት አይቀሬ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ
እርምጃ በተቃራኒው መሬትና ጥሪት የተወሰደባቸውን ዜጐች ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ደህንነት በአሉታዊ መልኩ
ይፈተናል፡፡ በእርግጥ በመልሶ ማስፈር ዙሪያ የሚያሳርፈውን መሰል ተጽእኖ፣ ውጤትና አንድምታ
በኢኮኖሚያዊ መስፈርት ብቻ ሙሉ በሙሉ መለካት አይቻልም፡፡ ይሁን እንጂ በደንብ ታቅዶ ተግበራዊ
በሆነው የመልሶ ማልማት ኘሮጀክት/ ወይም ኘሮግራም አማካኝነት መልሶ ማስፈርን ወደ ልማታዊ እድሎች
ማሸጋገር ይቻላል፡፡ እዚህ ላይ ትልቁ ተግዳሮት መልሶ ማስፈርን እንደ ውጫዊ ጉዳይ ማየት ሳይሆን የመልሶ
ማልማት ሂደቱ አንዱ አካል መሆኑን በተመለከተ በቂ ግንዛቤ ከማስጨበጥ ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ ይኸውም
በመልሶ ማልማት የሚነሱ ወገኖች የልማቱ ተጠቃሚ እንጂ ተጠቂ እንዳልሆኑ በተጨባጭ ማሳየት መቻል
የብዙዎች ፈተና ነው፡፡ የመልሶ ማልማት ኘሮግራም ሊሳካ የሚችለውም በዚህ ረገድ ውጤታማ ሥራ
ማከናወን ሲቻል ነው፡፡

በተሞክሮ እንደተረጋገጠው የመልሶ ማስፈር ችግሮች የሚመነጩት ከአላማቸው ሳይሆን ከአተገባበራቸው


ነው፡፡ በበርካታ ሀገራት የመልሶ ማስፈር አብይ መፈክር “መልሶ ማስፈር ከልማት ጋር” (Resettlement –
with Development) የሚል እየሆነ መጥቷል፡፡ የመንግሥታት ጥያቄም መልሶ ማስፈር ለምን (why for)
የሚል ሳይሆን እንዴት (How) እንሂድበት የሚል ነው (ኢያን ጆንሰን፣2ዐዐ4) ፡፡

በፌደራል የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት የከተማ ማሻሻልና መልሶ ማልማት ማንዋል ላይ እንደተጠቃለለው
ከዓለም አቀፍ ልምድ በቁልፍነት መውሰድ የሚቻለው ተሞክሮ የሚከተሉት ናቸው፡፡

 የባለድርሻዎች ሙሉ ተሳትፎ ወሳኝነት አለዉ፤ በመሆኑም የባለድርሻዎች ፍላጎትና እንዲሆን


የሚመኙትን ጉዳይ እንደ ወሳኝ ግብ መያዝ ለውጤቱ ማማር አስፈላጊ ነዉ፤
 እንድንሰራ የምንፈልገው ነገር በባለድርሻዎች አቅም የሚቻል መሆን አለበት፤ ለዚህ ደግሞ ከፕላን
ስራው ጀምሮ የባለድርሻዎችን አቅም ማወቅ ተገቢ ነዉ፤
 ድሆች እንዳይጎዱ የሚያደርግ ድጎማ አስፈላጊ እንደሆነና ለዚህም ከፕሮጀክቱ ጥቅም የሚያገኝ ወገን
መሸፈን እንደሚገባው ያትታል፤
 ከፕሮጀክቱ ጅምር እስከ ፍጻሜው ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ይፈልጋል፤
 ፕሮጀክቶች በሙሉ በተቀናጀ መልኩ ቁሳዊ፣ ማህበራዊና የአካባቢ ጥበቃን ባካተተ መልኩ መቀረጽና
ድህነትን ለመቀነስ ያተኮሩ መሆን ይገባቸዋል፤
 ስራውን በስፋትና በጥራት ለማከናወን ተገቢ ተቋማዊ አደረጃጀትና የህግ ድጋፍ ሊኖር ይገባል፤
 ዓላማው ማልማት እንጂ ሰውን ለማፈናቀል ካለመሆኑ ጋር በተያያዘ በተቻለ መጠን ተነሺዎችን
ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስራቸው እንዳይቋረጥ በአንድነት በአካባቢው የሚሰፍሩበትን ሁኔታ
ማመቻቸት ሊታይ ይገባል፤ የሚሉ ናቸው (ብ.ከ.ፕ.ኢ፣ 2006)፡፡

25
2.1.5. በከተማ መልሶ ልማት ዙርያ የዘመኑ መነጋገርያ አጀንዳዎች
ከማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች እይታ አኳያ

መልሶ ማልማት ሲከናወን ማህበራዊ ትስስር እንዳይጠፋ ምን ይደረግ? የደቀቀ አካባቢ ኗሪዎች እንዴት ይነሱ?
የትና እንዴት ይስፈሩ? ምን ድጋፍ ይደረግ? በሚሉት ዙርያ በርካታ ሃሳቦች ይንጸባረቃሉ፡፡ ለዚህም እንደ
መፍትሄ የሚያቀርቡት መሬት በማካፈል ኗሪዎችን በዚያው በቦታው ማስፈር፤ ቦታውን ማካፈል ካልተቻለ
በቅርብ እርቀት ማህበራዊ ትስስራቸው ሳይቋረጥ ለመቀጠል የሚያስችል ሰፈራ ይከናወን፤ ይህ የማይቻል
ከሆነ ደግም ማህበረሰቡን በአንድ ላይ ሳይለያዩ ማስፈር፣ የሚሉ ናቸው፡፡

ከኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች እይታ አንፃር

ነባሩ ኢኮኖሚ ወይስ አዲስ ቅይጥ? የኢኮኖሚ ተጠቃሚዎች እነማን ይሁኑ? መልሶ ማልማት ሲከናወን
በተነሺዎች ላይ የስራና ገቢ ማጣት ወይም መቀነስ እንዳይከሰት ምን ይደረግ? የትኛው ማህበረሰብና ስራ
ይጎዳል? እንዴት ይነሱ? የትና እንዴት ይስፈሩ? ምን ድጋፍ ይደረግ? በሚሉት ዙርያ በርካታ ሃሳቦች
ይንጸባረቃሉ፡፡ ለዚህም እንደ መፍትሄ የሚያቀርቡት በሰፈራው ምክንያት ከነበሩበት የኑሮ ሁኔታ መውረድ
የለባቸውም፤ ለሚደርስ ጉዳት ሁሉ የጥቅሙ ዋነኛ ባለድርሻ ይካስ፤ በሂደቱ ሊጎዱ የሚችሉት ዝቅተኛ
የህብረተሰብ ክፍሎች ስለሚሆኑ ከስራና የገቢ ምንጫቸው ሳይርቁ ይስፈሩ፤ በሚሰፍሩበት ቦታና ቤት ነባሩን
ስራ ለማከነወን የሚችሉበት ሁኔታ ይታይ፤ አማራጭ የስራና ኢኮኖሚ መስክ ማመቻቸት ይገባል፤ የመልሶ
ማቋቋም ድጋፍ ማድረግ ይገባል፤ የሚሉ ናቸው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በአለም ባንክ የፖሊሲ ሰነዱ ላይ
የሰፈረው ሃሳብም የልማት ተነሺዉ በፊት ከነበረበት የኑሮ ሁኔታ ቢቻል መሻሻል አለዚያ ግን ሊወርድ
አይገባም፤ በልማቱ ተጠቃሚው የተጎጅን ጉዳት መሸፍን አለበት ይላል (የዓለም ባንክ፣ 1990)፡፡ የተነሸዎች
መልሶ ማስፈሪያ ቦታም ከነባር መኖሪያቸው 500 ሜትር ራዲየስ ውጪ መሆን የለበትም የሚል መርህ
ያስቀምጣል፡፡

ከታሪክና የቅርስ ባለሙያዎች እይታ አንፃር

በመልሶ ማልማት ስለ ቅርስ መጥፋት ሁሉም የነበረው አሰፋፈር ታሪካችንና ቅርሳችን ነው፣ ባለበት ይጠበቅ፤
ድሮ እንዴት እንደ ነበር የሚናገረው ፎቶ እና አንድ ሁለት ቤት ብቻ ሳይሆን እንዳለ ሁሉም ሲጠበቅ ነው፤
ከሚለው ጫፍ የወጣ እይታ ጀምሮ ለታሪክ እይታ ትርጉም ያላቸውን መገለጫዎች ለይተን እንጠብቅ፣ እናጉላ
ወዘተ፤ እንዲሁም አይሆንም፣ ድህነት ታሪካችን ነው ብለን ልንጠብቅ አይገባም፣ ሁሉም መታደስና ማደግ
አለበት፤ የሚሉ አመለካከቶች ይንጸባረቃሉ፡፡

26
ከፖለቲካና ከፕላን እይታ

የእድሳት ቅድሚያ ያለው ማእከላዊ ቦታ ሲለማ ለምን ግልጋሎትና ለየትኛው ወገን ይገበዋል የሚል አጀንዳም
አለ፡፡ አካባቢው ሁል ጊዜ የሞቀ እንዲሆን አገልግሎቱና የህብረተሰብ አሰፋፈሩ ቅይጥ ይሁን የሚሉና፤
የክሪስታለር መርህ የሚያራምዱ የከተማ ማእከላት ደረጃ ይገባል የሚል አስተያየት ሲሰነዝሩ ይደመጣል፡፡
በክሪስታለር እምነት የከተሞች ማእከላዊ ሥፍራዎች ለከፍተኛ አገልግሎቶች (Higher order services/
መዋል አለበት ከማዕከላዊ ሥፍራዎች ውጪ ያሉ አካባቢዎች እንደተዋረዳቸው ለሚመጥኑት አገልግሎት
መመደብ አለባቸው፡፡ ይህ አተያይ አቅም ያለው ያሸንፍ አቅም የሌለው ወደ ከተማ ዳርቻ ይገፋ የሚል
እንድምታ አለው፡፡

ስእል 2.1፡ በገበያ ብቻ ከተመራና ዳርቻ አካባቢን ካልለማ፣ ትራንስፖርት ተደራሽና ቀልጣፋ ካልሆነ የሚከሰት
የቦታ አጠቃቀም ተዋረድ

መሃል ከተማ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ሸቀጥ


? ?? ?
ከመሃል ከተማ ቀጥሎ ያለ መኖርያ ሰፈር ማደራጃ

የከተማ ዳርቻ ኢንዱስትሪና ልዩ ማእከል አገልግሎት


? ?? ?
ከከተማ ወጣ ያለ የግብርና ስራ ማደራጃ

27
2.2. የተመረጡ ሀገራት የከተማ መልሶ ማደስ ተሞክሮ ቅኝት
2.2.1. ከተማ መልሶ ማልማት የቻይናና ኮሪያ ተሞክሮ
የሀገራቱ ነባራዊ ሁኔታ/Context

ከተማ በሂደት የሚገነባ እንደመሆኑ ቀድሞ በነበረ አቅምና ቴክኖሎጂ የተሰራ ግንባታ በሂደት በአቅም፣
በፍላጐትና ቴክኖሎጂ ለውጥ እንዲሁም በእድሜ እርጅና ምክንያት መቀየር ይኖርበታል፡፡ አለዚያ አዲስ
ግንባታ ወደ ውጭ እየወጣ ነባሩ ባለበት ከቀጠለ ከተማው የሚሞት ይሆናል፡፡ ከተማ ማደስ ቀጣይ ሂደት
ነው፡፡ በተለይ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ከተሞች ነባር ግንባታ ደረጃው በእጅጉ የወረደና ለኑሮ ምቹ ያልሆነ፤
በአመዛኙም ያለ ፕላን በራሱ ሂደት የተገነባ እንደ መሆኑ መጠን ማደስ የግድ ይላል፡፡

ቻይና ከ35 ዓመት በፊት እንዲሁም ኮሪያ ከ50 አመት በፊት በነበሩበት አስከፊ ድህነት ምክንያት በዚያን ጊዜ
የነበሩት ነባር የከተማ ክልሎች ከዚያም በእድገታቸው የመጀመሪያ ምእራፍ የተገነቡ መለስተኛ ግንባታዎች
እድገታቸው በፈቀደ መጠን መቀየራቸው የግድ ነበር፡፡ ቻይና ከ1998 በፊት ከእዝ ኢኮኖሚ ፍልስፍና ጋር
በተያያዘ በመንግስት የተገነቡት መጠለያዎች በሙሉ ለኑሮ ምቹ ባለመሆናቸው ብቻ ሳይሆን የህዝቡ ኢኮኖሚ
አቅም ሲያድግ ፍላጎቱ ስለተቀየረ በነዚህ መጠለያዎች የመኖር ፍላጎቱ በመቀነሱ መቀየራቸው ግድ ነበር፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን የከተማ ያለቅጥ ወደ ጎን መስፋፋት ለመገደብና የገጠር እርሻ መሬት ወደ ግንባታ በፍጥነት
መቀየርን ለመቀነስ፤ የደቀቁ አካባቢዎችን መቀየር/ማሻሻል እንደሚገባ በማመን መንግስት ወደ ተግባር
ገብቷል፡፡ የደቀቁ የከተሞች ክፍልን ሁኔታ ለመቀየርና ማራኪ ገጽታ እንዲላበሱ፣ ኢኮኖሚያቸው እንዲነቃቃ፤
የህዝቡ ኑሮ እንዲሻሻል፣ የመሬት አጠቃቀም ውጤታማነት እንዲረጋገጥ፤ ማድረግ ችለዋል፡፡

ኮሪያ የመልሶ ማልማት ጅምር የታየው በ1960ዎቹ ነው፤ በ1960ዎቹ የከተማ እድሳት ሲጀመር ህግ አልነበረም፡፡
በወቅቱ የከተማ ማደሱ ትኩረቱ በቤትና አካባቢ ለውጥ ፊዚካል ለውጥ ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር፡፡ ለማህበረሰብ
መፈናቀል፤ ለአከባቢው በኢኮኖሚ ማደግና መቀየር ትኩረት አልነበረውም፡፡ ሂደቱ ከተገመገመ በኃላ የህግ
ማእቀፍ እንዲኖረው ለማድረግ ለማህበራዊ ልማት፤ ለባህልና ቅርስ ጥበቃ፤ ለኢኮኖሚ እድገት በቂ ትኩረት
ለመስጠት፤ ከግለሰብ ፍላጎት ተነስቶ ከሚከናወን እድሳት በማህበረሰብ ለውጥ ግፊትና ህዝብን ማእከል
አድርጎ ወደ ሚከናወን ልማት፤ ለመሬት አጠቃቀም ውጤታማነት፤ አሰራሩን ወጥ ለማድረግ፤ ሙስናን
ለመዋጋት፣ ድሃው በሂደቱ እንዳይጎዳ ለመከላከል የሚሉ ዓላማዎችን ያካተተ የህግ ማእቀፍ አውጥተው
መርተውታል፡፡ ውጤቱም ከተማ ለማደስ የህግ ማእቀፍ መኖር አስፈላጊነትን አሳይተዋል፡፡

ህጉ አንዴ ወጥቶ የቀረ ሳይሆን ለበርካታ ጊዜያት ማሻሻያ እየተደረገበት አማራጭን በማስፋት ከተማ የማደሱ
ስራ ከሙሉ አፍርሶ መገንባት በተጨማሪ ሌሎች ስልቶችን በማካተት የተከናወነ ነው፡፡ ለምሳሌም መሰረተ-
ልማት ጥሩ በሆነበት አከባቢ የብሎክ ልማት የሚል አሰራርን በመፍቀድ ከአንድ ሄክታር በታች ያሉ ቦታዎች
እንዲለሙ፤ የቤትና አካባቢ መሻሻል ስልት በሚል ደግሞ መንግስት መሰረተ ልማቱን ሲቀይር የቤት ባለቤቶች

28
ማህበራት ቤቱን አፍረሰው አሻሽለው ተጨማሪ መኖሪያ አካተው እንዲገነቡና መንግስት በተወሰነ ደረጃ
ለድሃው ተደራሽ የሆነ ቤት በመገንባት፤ የኢንዱስትሪ አከባቢ መሻሻል ስልትን በማካተት ልማቱን ለማስፋትና
ለማፋጠን ችለዋል፡፡ የመልሶ ማልማት አማራጭን ማስፋት ለልማቱ መፍጠንና የሁሉን አቅም አሟጦ
በመጠቀም ረገድ ጠቀሜታውን ያስመሰከረ ሂደት ነበራቸው፡፡ በመልሶ ማልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ
በማሳደግም እንዲሁ ውጤታማ ነበሩ፡፡ ለምሳሌ የመሬት መጋራት፣ የመሬት ማስተካከል ስልትን በመከተል
የማስነሻ ወጭ ሳይንር፣ ውዝግብ ሳያስከተል ተሳታፊዎች ጠቀሜታውን እንዲገነዘቡ በማድረግ መልሶ
ማልማቱን ማፍጠን ችለዋል፡፡ ህጉን ከአስር ጊዜ በላይ በማሻሻል ውጤታማነቱንና አማራጭ የማሳተፍ ሂደትን
የሰመረ እንዲሆን አድርገዋል፡፡ ህጉ መጀመርያ የወጣው በ1962 ሲሆን እስከ 2012 ዘጠኝ ጊዜ እንዲሻሻል
ተደርጓል (በ1971፣ 1973፣ 1976፣ 1984፣ 1987፣ 1989፣ 1999፣ 2002፣ 2012)፡፡

ማእከላዊ መንግስት መልሶ ማልማትን የተመለከተ ሀገር አቀፍ መርህ (Guideline) ያወጣ ሲሆን የዚህ ሁሉን
አቀፍ መርህ መኖር በሀገሪቱ ወጥ አሰራር እንዲሰፍንና ቅሬታ ቀንሶ ልማት እንዲፋጠን ምቹ ሁኔታ የፈጠረ
ነው፡፡ ይህንን መሰረት በማድረግ ከተሞች እና ክፍለ ከተሞች የመልሶ ማልማት ቦታዎችን የለየ መሰረታዊ
ስትራቴጅክ ፕላን እንዲሁም የእድገት መርሃ ግብር በመስራት መልሶ ማልማቱን በተሟላ እቅድ መርተዋል፡፡

ከህግና እቅድ በተጨማሪ መልሶ ማልማቱን በወጥነትና በትኩረት የሚመራ አደረጃጀት ፈጥረው
እንዳከናወኑት ለመረዳት ተችሏል፡፡ በማእከላዊ መንግስት ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስቴር የሚመራ ሚኒስትሮችና
የግል ዘርፉን ተወካዮች በአባልነት ያካተተ ልዩ የከተማ መልሶ ማልማት ኮሚቴ አደራጅተዋል፤ ከዚያም
በመሬት መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውስጥ የከተማ ማደስ ፕላን ቡድን
በማደራጀት ሂደቱን በወጥነት በሙያ ታግዞ እንዲከናወን አድርገዋል፡፡ በሜትሮፖሊታንና ከተማ ደረጃ ደግሞ
የመልሶ ማልማት ኮሚቴ እና እራሱን የቻለ መልሶ ማልማቱን የሚመራ የመንግስት ተቋም በመፍጠር ለህዝብ
ልማት ድጋፍ/ በህዝብ ለሚከናወን መልሶ ማልማት ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚሰጥ/ የከተማ መልሶ ማልማት
ማእከል በማደራጀት ሂደቱን ከታች እስከ ላይ በህግ፤ በፕላን፤ በሙያ ግብአትና ወጥነት መስራት ችለዋል፡፡

መልሶ ማልማቱ ወጥ ሂደት የሚከተል ሲሆን የሚከናወኑ ተግባራትም የሚከተሉትን ጉዳዮች ያካትታል

 በተለያየ ደረጃ አስፈላጊው የመልሶ ማልማት ፕላን ይዘጋጃል


 መሰረታዊ ፕላኑ በከተማ ደረጃ ላለው የከተማ ማደስ ኮሚቴ ቀርቦ ይፀድቃል
 ልማቱን ወደ ተግባር ለማሸጋገር ከኗሪው ጋር ስምምነት ላይ ይደረሳል፤ ይኸውም የጋራ ግብ
ከተቀመጠ በኋላ ሂደቱ ወደ ተግባር እንዲገባ ከኗሪው 70% ሊቀበለው ይገባል፡፡ በዚህ ሂደት ህዝቡ
የተሟላ መረጃ እንዲኖረው ይደረጋል፤ ለዚህ ሲባል ፕላኑ ቢያንስ ለ14 ቀን ለህዝብ ክፍት ይደረጋል፡፡
 መልሶ ልማቱን የሚያከናውን አካል መረጣ፤ ማጸደቅና ማስተዋወቅ ሌላው ተግባር ነው
 ማፍረስና መገንባት የመልሶ ልማቱ የመጨረሻው ሂደት ነው፡፡

29
እነዚህ ሁኔታዎችና ሂደቶች በመጀመሪያዎቹ ዘመናት በተካሄዱ የመልሶ ማልማት ፕሮግራሞች ብዙም ትኩረት
አይሠጣቸውም ነበር፡፡ ከ1990 በኋላ ግን አንድ ፕሮጀክት ከመተግበሩ በፊት ከላይ በተገለፁት ሂደቶች
ማለፋቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ፕሮጀክቱ ለመጽደቅ ቀጥሎ ከተጠቀሱት መስፈርቶች አኳያ መገምገም
ይኖርበታል፡፡
 ፕሮጀክቱ በተቻለ መጠን ኗሪውን ከቦታው ላለማፈናቀል የሚያስችል አካታች ፕላን ያካተተ መሆኑ፤
 ፕሮጀክቱ ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውን የመሰረተ ልማት አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮግራም
ያካተተ መሆኑ
 ፕሮጀክቱ የአከባቢ ኢኮኖሚ መነቃቂያ፣ የገቢና ስራ ማስገኛ ሃሳብ የያዘ መሆኑ የሚሉት ወሳኝ ናቸው

በህዝብ አቅም የሚከናወኑ ሥራዎች በተሟላ ፕላን እንዲመሩ የሚያግዝ ትምህርትና ስልጠና በመንግስት
ይሰጣል፡፡ ፕላኑን መንግስት የሚሰራው ከሆነ ደግሞ የህዝቡ ፍላጎትና ሃሳብ በፕላኑ መካተቱ ይረጋገጣል፤
ለትግበራ የሚረዳ የፖሊሲ ድጋፍ እንዲሁም የሥራ ተቋራጭ ጨረታ ትግበራና ጥራት ቁጥጥር ድጋፍ
ያደርጋል፡፡ በህዝብ የሚሰራው ልማት ከህዝቡ ገቢ ማደግና ከግንዛቤ መጎልበት ጋር ተያይዞ በአይነትና
በጥልቀትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሠፋና ትኩረት እያገኘ ያለ መስክ ነው፡፡

የኮሪያ አጠቃላይ የተለያዩ መልሶ ማልማት ውጤትን ለማመላከት ያክል እስከ 2011 ባለው ጊዜ ውስጥ 641
ዞን እና 828 ሄክታር ሙሉ በሙሉ በመልሶ ግንባታ፣ 1,175 ዞን እና 446,300 ቤት በመኖርያ አካባቢ ልማት፣
1,187 ዞን እና 7,452 ሄክታር ቦታ 878,737 ቤት በማፍረስ 1,078,719 ቤት መገንባት /በቤት መልሶ ግንባታ
ስልት/ ሸፍነዋል፡፡ መልሶ ልማቱ የተመራበት ትኩረት ከጅምሩ ወጥ ሳይሆን በልማት እንደተደረሰበት ደረጃና
ግንዛቤ መስፋት ጋር በተያያዘ በየዘመኑ የተለያየ ትኩረት ነበረው፡፡ በ1960ዎቹ ጀምሮ የተመራው የከተማውን
ግንባታ መቀየር ቆየት ሲል ደግሞ የኗሪውን ህይወት መቀየር ያማከለ ነበር፡፡ በ1990ዎቹ ደግሞ የከተሞችንና
የአካባቢን ልዩ ገጽታ መጠበቅ፣ ማፈናቀልን ማስወገድ፣ ፈጠራ ለተሞላበት አካሄድ ማበረታታት፣ ለዘላቂ
ልማት ማሰብ የሚሉትን ቅኝቶች የያዘ ነው፡፡ ከተማን መልሶ ለማልማት አንድ ዘዴ ብቻ ችግሩን ስለማይፈታ
የተለያዩ ስልቶች መጠቀም ተገቢ እንደሆነ ህዝብን ማሳተፍ ተገቢነት እንዳለውም ግንዛቤ አግኝቷል፡፡

ከሁለቱ ሀገራት መማር የሚቻለው ተሞክሮ


1) የከተማ እድሳት ቀጣይ ስራና ከቤት አቅርቦት በላይ የከባቢውን ሁኔታ በመቀየር፣ የኗሪዎችን የኑሮ ደረጃ
በማሻሻል፣ በገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ሚና እንዳለው
2) የከተማ ማደስ ትኩረት ፊዚካላዊ ለውጥ ብቻ ሳይሆን ሁሉን አቀፍ መሆን እንደሚገባውና ለከተማ
ማደስ የህግ ማእቀፍ መኖር አስፈላጊነትን፣ ህጉም በየወቅቱ ካለ ችግርና ፍላጎት አንጻር በየጊዜው
መሻሻል እንደሚገባው አሳይተዋል፡፡

30
3) መልሶ ማልማቱም አማራጭ ስልት እንዲኖረው ማድረግ ለልማቱ መፍጠን፣ የህዝብ ተቀባይነት
ማግኘትና ወጭ ቆጣቢነት ተገቢ እንደሆነ
4) በማእከላዊ መንግስት በኩል መልሶ ማልማትን የተመለከተ ሀገር አቀፍ መርህ መኖር በሀገሪቱ ወጥ
አሰራር እንዲሰፍንና ቅሬታ ቀንሶ ልማት እንዲፈጥን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር
5) ከህግና እቅድ በተጨማሪ መልሶ ማልማቱን በወጥነትና በትኩረት የሚመራ ተዋረድ ያለው አደረጃጀት
መኖር እንዳለበት
6) ልማቱን ለማከናወን ከኗሪው ጋር መተማመንና ዝቅተኛ ግብ ማስቀመጥ ጠቀሜታ እንዳለው
7) የመልሶ ልማት ትኩረት ከጅምሩ ወጥ ሳይሆን በልማት እንደተደረሰበት ደረጃና ግንዛቤ መስፋት ጋር
በተያያዘ በየዘመኑ መለያየት እንዳለበት፡፡ በትምህርትነት የታዩ ግኝቶች ናቸው፡፡

2.2.2.የቱርክ ከተማ ማደስ ተሞክሮ


የሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ
ቱርክ በከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ የምትጠቃ ስትሆን እ.ኤ.አ. በ 2ዐ11 ዓ.ም የደረሱባት ሁለት ተከታታይ
አደጋዎች የግንባታ ሂደቷን መለስ ብላ እንድትመረምር አስገድዷታል፡፡ በዚህም የቱርክ ማዕከላዊ መንግስት
ባለፈው አስር ዓመት ውስጥ በተለይም ሀገሪቱ በ2ዐ11 በደረሳት ርዕደ-መሬት ተከትሎ ህግ አውጥቷል፡፡ እ.ኤ.አ
በግንቦት 2ዐ12 “በአደጋ ስጋት ውስጥ የሚገኙ አካባቢዎችን ማደስ” በሚል ባወጣው እና ስራ ላይ በዋለው
ህግ መሰረት መንግስት በአስጊ አካባቢዎች የሚገኙ ህንጻዎችን፡፡ ህገወጥ ግንባታዎችን እና ያረጁ ቤቶችን
ለማደስ ጥብቅ እርምጃ ወስዷል፡፡ ኢንስታቡልን ጨምሮ በመላው የሀገሪቱ ከተሞች ከፍተኛ የከተማ መልሶ
ማልማት ኘሮጀክቶች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡

ከመሬት መንቀጥቀጡ ሌላ ቱርክ በአለም ከፍተኛ የከተሜነት ደረጃ ካላቸው አገሮች አንዷ በመሆኗ ከፍተኛ
የህዝብ ዕድገት በመጨመሩ ምክንያት በሀገሪቱ በከተሞች ላይ ጫና ፈጥሯል፡፡ ፈጣን የህዝብ ዕድገቱ
ከኢንዳስትሪው ዕድገት ጋር ተዳምሮ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው የህዝብ ፍልሰት በመባባሱ የቱርክን
የከተሜነት ፍጥነት እየጨመረ እ.ኤ.አ. ከ2ዐ12 ወዲህ የከተሜነት ደረጃው 77% ደርሷል፡፡ በዚህም ምክንያት
የቤት ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ከመምጣቱም ሌላ ያረጁ አካባቢዎችን የመልሶ ማልማት
አስፈላጊነትም በተመሳሳይ እያደገ መጥቷል፡፡

በሚቀጥሉት 2ዐ ዓመታት ጊዜ ውስጥም ከ6 እስከ 7 ሚሊዮን የሚጠጉ ቤቶች ፈርሰው በአዲስ መልክ
እንደሚገነቡ ተገምቷል፡፡ ይህም በአመት በአማካኝ የ334,ዐዐዐ ቤቶች እድሳት የሚጠይቅ ሲሆን ለዚህ
ተግባራዊነትም 23 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጭ እንደሚያስፈልግ ተገምቷል፡፡

31
በቱርክ የከተማ መልሶ ማልማትን አስፈላጊነት ግድ ያሉ ምክንያቶች ሲጠቃለሉ፡

 በኢንዳስትሪው ዕድገት ምክንያት ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው የህዝብ ፍልሰት በመባባሱ የቱርክን
የከተሜነት ፍጥነት እንዲጨምር ማድረጉ፣ ከህዝብ ዕድገቱ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት
መከሰቱ፣

 የቤቶች እርጅናና ጥራት መውረድ እና የመሬት መንቀጥቀጥ ስጋት፣

 ፈጣን የከተሜነት ሁኔታ በከተሞች ስርዓትና ቅርፅ (form)፣ በትራንስፓርቴሽን እና በመሰረተ ልማት
ስርዓት ላይ ያለው አሉታዊ ተጽዕኖ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የከተማ መልሶ ማልማት ደንብ፡ ዋና ዋና አካባቢዎች እና ተግዳሮቶች


በቱርክ የከተማ መልሶ ማልማት /ሪጄኔሬሽን/ ሂደት በአደጋ (ስጋት) ላይ ያሉ አካባቢዎችን ለማደስ በወጣው
ህግ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ህጉ በተለይ የሚያተኩረውም የህይወትና የንብረት ጥፋትና/ውድመት ሰጋት
አለባቸው ተብለው በተለዩ አካባቢዎች ላይ ነው፡፡

በተጠቀሰው ህግ መሰረት በአደጋ ስጋት ውስጥ ያሉ ግንባታዎች ማለት “በስጋት አካባቢ ወይም ከዚያ ውጭ
ያሉ ግንባታዎች ሆነው የኢኮኖሚ እድሜያቸውን የጨረሱ ወይም በሳይንሳዊና ቴክኒካዊ መንገድ በመፍረስ
ሂደት ወይም በከፍተኛ የጉዳት ስጋት ውስጥ መሆናቸው የተረጋገጡ ግንባታዎች” ናቸው፡፡ የስጋት አካባቢዎች
የሚለዩትና የሚወሰኑትም በአካባቢና ከተማ ልማት ሚ/ር፣ በቤቶች ልማት አስተዳደር ወይም ማዘጋጃ ቤቶች
ሲሆን በተለዩት የስጋት አካባቢዎች ላይ የአደጋና ድንገተኛ ጉዳዮች ማኔጅመንት ኘሬዚደንሲ አስተያየት
ከታከለበት በኋላ በሚኒስትሮች ም/ቤት የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጠዋል፡፡

የአካባቢና ከተማ ልማት ሚ/ር እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በከተማ መልሶ ማልማት ጽንሰ ሃሳብ መሰረት በመላው
ቱርክ 1ዐዐ የስጋት አካባቢዎችን የለየ ሲሆን በቅድሚያም 165,ዐዐዐ የሚጠጉ ግንባታዎች እድሳት በ35
ከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ አቅዷል፡፡ በመላው ሃገሪቱ 6.7 ማሊዮን የሚጠጉ ቤቶች እንዲታደሱ
መታቀዱም እ.ኤ.አ. ከ2ዐዐ1 በፊት የተገነቡ ቤቶች ሁሉ ስለመሬት መንቀጥቀጥ በወጣው የዲዛይን ሴፍቲ ኮድ
መሰረት ያልተገነቡ መሆናቸው በመታመኑ ነው፡፡

በየአመቱ የመልሶ ማልማት ከሚካሄድባቸው ብዛታቸው 334,000 ከሆኑ ቤቶች መካከል ‘ቶኪ’ (የቱርክ
የቤቶች ልማት አስተዳደር) የሚገነባው በአመት 5ዐ,ዐዐዐ ያህል ብቻ በመሆኑ ከግሉ ዘርፍ ጋር ተባብሮ
የመሰራቱ አስፈላጊነት አያጠያይቅም፡፡ እንደዚሁም የቤት ባለንብረቶችም የራሳቸውን ቤት እንዲያፈርሱ
ለማበረታታት መንግሥት እንደ ’ዞኒንግ ቦነስ’ እና የልማት መብትን ማስተላለፍ የመሳሰሉ ማበረታቻዎችን
ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡

32
የመልሶ ልማት ኘሮጀክት ዓላማና ትኩረት
የከተማ መልሶ ማልማት ዋና ዓላማ ለታሪካዊ ሰፈሮች ለጤና ተስማሚ መኖሪያ ቤቶችን እና የመሰረተ ልማት
አገልግሎቶችን በማሟላት ከከተማ የስነ ህንጻ ቅርስ እና ከታሪካዊው አቀማመጥ ጋር በተጣጣመ መልኩ
ለማደስ ሲሆን በፕሮጀክቶቹ ትኩረት የሚደረግባቸው ዝርዝር ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፡

 ባህላዊ ቅርሶችን ማስጠበቅ፣


 ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መኖሪያ አካባቢ በመፍጠር በነዋሪው ዘንድ የእኔነት ስሜት እንዲኖር
ማድረግ፣
 ከፍተኛ ወንጀል እና ህገወጥ ተግባራት የተሞሉ ማህበራዊ ሳንካዎችን ማስወገድ፣
 የአካባቢ እርጅናና መበስበስን መከላከል፣
 መስህብነት ያላቸውን የከተማ ቦታዎች በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ልማትን ማምጣት፣
 የስጋት ዞን ሆነው የተለዩ የመኖሪያም ሆነ የሥራ አካባቢዎችን ከተቀረው የከተማ ክፍል ጋር
በማህበራዊ እና በባህላዊ እንቅስቃሴ ማስተሳሰር፣ እንዲሁም
 በመልሶ ማልማቱ የህዝብ አሳታፊ ሂደትን መፍጠር፡፡

የከተማ መልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች አጠቃላይ ሂደትና የሚከተሉት ስልት


በመንግሥት የመሬት ይዞታ ላይ የተገነቡ የተጎሳቆሉ አካባቢዎች የመኖራቸውን ያህል በተቃራኒው ደግሞ የግል
የመሬት ባለንብረትነትም በስፋት የሚታዩበት ሁኔታ አለ፡፡ የከተማ መልሶ ማልማት ሳይቶች በቅድሚያ
በፕላን ተለይተው ይታወቃሉ፤ የተለዩት የከተማ መልሶ ማልማት አካባቢዎች እንደሆኑ ይታወጃሉ፣ አዋጁን
ተከትሎም ከተማ መልሶ ማልማት ኘሮጀክቶች በከተማ መልሶ ማልማት እና ጥበቃ ቦርድ እንዲሁም በማዘጋጃ
ቤት እንዲፀድቁ ይደረጋል፡፡

ወደ ትግበራ ሲገባ የከተማ ማዘጋጃ ቤቶች ብቻ ሳይሆኑ የግል አልሚዎችም በክልሉ የከተማ መልሶ ማልማት
ኘሮጀክቶችን ያካሄዳሉ፡፡ የተለያዩ የግል አልሚ ካምፓኒዎችም በሚታደሰው ቦታ ላይ የመኖሪያ፣ የቢሮ፣ የገበያ
ማዕከሎችን እና የመሳሰሉትን አካተው የያዙ ቅይጥ አገልግሎት መስጫ ኘሮጀክቶች ላይ ያተኮሩ የከተማ
መልሶ ልማት ሥራዎች ያከናውናሉ፡፡

ማዘጋጃ ቤቶች የግል አልሚዎችንና ኮንትራክተሮችን በመወከል ስለሚገኘው የመሬት መጠንና የቤት ብዛት
ከቤትና መሬት ባለንብረቶች ጋር የሚደራደር የከተማ መልሶ ማልማቱን የሚደግፍ ጎፓስ /GOPAS/ የተሰኘ
አንድ ልዩ አጋዥ ክፍል አላቸው፡፡

በከተማ መልሶ ማልማት ሂደት በፕሮጀክቱ የከተሞችን ታሪካዊ ገጽታ ከመጠበቅ ጎን ለጎን የጥንታዊዎቹ
የኦቶማን ቤቶችን ዲዛይን በአፓርታማዎቹ ዲዛይን ላይ ለማካተት ትኩረት ይሰጣል፣ የከተማ ነባር ባህል
ለማስጠበቅ እና ለማስቀጠል የሚረዱ ተቋማት ህንጻዎችም ይገነባሉ፡፡
33
የከተማ መልሶ ማልማት የሚካሄደው በተዘጋጀ የከተማ ፕላን ላይ ተመስርቶ ሲሆን ኘላኑ በራሱ ከፍተኛ
ፎቆች እና ከፍተኛ የህዝብ ጥግግት ላይ የተመሰረተ መሆኑ የከተማውን የለውጥ ሂደት ቀላል እንዲሆን
አድርጎታል፣ ይህ ሁኔታ የአካባቢውን መሬት ዋጋ ከፍተኛ እንዲሆን እያደረገው ነው፡፡ ኘላኑ ይፋ ከተደረገ
በኋላም ኮንትራክተሮቹ ወደ አካባቢው መጥተው የጎስቋላዎቹ ቤቶች ባለንብረቶች የተሻለ ዋጋና ጥራት
ባላቸው አዳዲሰ አፓርትመንት ቤቶች እንዲቀየርላቸው ሀሳብ የሚያቀርቡበት ሁኔታ አለ፡፡

እየተካሄደ ባለው ለውጥ ምክንያት አንድ ፎቅ ያላቸው ነባር ደሳሳ ቤቶች እና ሰማይ ጠቀስ ዘመናዊ ህንጻዎች
አብረው ሆነው ይታያሉ፣ ይሁን እንጂ በአጭር ጊዜያት ውስጥ አንድም ተመሳሳይ ጎስቋላ ባለ አንድ ፎቅ
ህንጻዎች እንደማይታዩ ይጠበቃል፣

የከተማ ማደሱ ፖሊሲዎች ተግባራዊ ሲደረጉ ለተነሺዎች የሚደረጉ የድጋፍ እቅዶች፡


ለነባር የቤት ባለንብረቶች ከወቅቱ የቤታቸው ዋጋ ጋር ያለውን ልዩነት ከከፈሉ ከአዲሶቹ አፓርታማዎች
መካከል ይሸጥላቸዋል፣ በግንባታው ወቅትም ቶኪ (የቱርክ የቤቶች ልማት አስተዳደር) ተከራዮች ለሆኑት
መቆያ እንዲያገኙ ሁለት አማራጮችን አቅርቧል እነሱም፡

 በግንባታ ወቅት በየወሩ የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል ዋስትና እንዲሰጣቸው፣


 በከተማ ማደስ አካባቢዎች ከተጠናቀቀው ኘሮጀክት አፓርታማ እና በተጨማሪም በየወሩ የተወሰነ
ገንዘብ ለመክፈል ሁለተኛ አማራጭ ሀሳብ አቀረበላቸው፣

ከሁለተኛው አማራጭ ጋር በማያያዝም እስከ ከተማው መሃል ድረስ የሚያመላልስ የነጻ አውቶብስ
ትራንስፖርት አገልግሎት አቀረበላቸው፣ ይሁን እንጂ፣ ቦታው ከከተማው ማእከላዊ ስፍራ እራቅ ያለ በመሆኑ፣
የግለሰቦቹ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ማለትም ዝቅተኛ ወርሀዊ ገቢ ያላቸው መሆኑ፣ ምንም ሥራ ያልነበራቸው
በመኖራቸው፣ በአብዛኞቹ ባለንብረቶች ወደዚያ አልሄዱም፡፡

ሌላው ጉዳይ የታሪካዊዎቹ ህንጻዎች ባለንብረቶች ባለባቸው የፋይናንስ እጥረት መንደራቸውን እንዲለቁ
መገደዳቸው ነው፤ ምክንያቱም እነዚህን ህንጻዎች ለመጠገንና ለማደስ የሚጠይቀው ወጭ ከፍተኛ በመሆኑ፡፡

ትኩረት የሚሹና በክፍተትነት የሚታዩ ጉዳዮች

 የከተማ ማደስ ፋይናንስን በተመለከተ የግል ካምፓኒዎች የራሳቸውን ጥሪት ለግንባታ እየተጠቀሙ
መሆኑ፣
 አጠቃላይ ሂደቱን የሚያስተባብር አንድ አካል ባለመሆኑ ፕላን የማጽደቅ ሂደት በተለያዩ ተቋማት
የሚፈጸምና በጣም ጊዜ የሚወስድ መሆኑ፡፡
 የከተማ ማደሱ ኘሮጀክት ከማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሃድሶ አቅጣጫ ባለው ክፍተት የሚተች
ሲሆን፣

34
 ከአጠቃላይ የከተማ ዲዛይን ጋር በተያያዘ ያለው ክፍተትም ሌላው የከተማ ማደሱ ኘሮጀክት ላይ
ትችት እያሰነዘረበት ያለ ጉዳይ መሆኑ ናቸው፣

ከቱርክ የከተማ ማደስ የምንማረው


የቱርክ ከተማ የሚያስተምረው ጉዳይ ቢኖር ከስኬት ጀርባ የነበሩን ወስዶ ለማዋሃድ ከውድቀት ደግሞ
ምክንያቶችን አውቆ እነሱ እንደወደቁ ላለመውደቅ/ላለመድገም ስለመሆን በመጀመሪያ ከስኬታቸው ስንነሳ

 የከተማው ማዘጋጃ ቤት ብቻ ሳይሆን የግል አልሚዎችም በክልሉ የከተማ ማደስ ኘሮጀክቶችን


መሳተፋቸው፣
 በግሉ አልሚዎች እና በተነሽ ባለንብረቶች መካከል የማደራደር ስራ የሚያከናውን ልዩ የማዘጋጃቤት
አጋዥ ክፍል መኖሩ፣
 የተጠቀሰው አጋዥ ክፍል ውጤታማ የሆነ የድርድር ሂደት እንዲኖር መድረኮችን የሚያመቻች ሲሆን
በዚህም የግል ካምፓኒዎች ከቤትና መሬት ባለንብረቶች ጋር በቀጥታ እንዳይገናኙና ለተራዘመ እና
ውጣውረድ ለበዛበት የድርድር ሂደት እንዳይጋለጡ መርዳቱ፣
 ምናልባት ለኛ ከተሞች እምብዛም አዲስ ባይሆን መስህብነት ያላቸውን የከተማ ቦታዎች በመፍጠር
ኢኮኖሚያዊ ልማትን ማምጣት የከተማ ማደሱ አካል መደረጉ፣
 በፕሮጀክቱ ታሪካዊ ገጽታ ከመጠበቅ ጎን ለጎን የጥንታዊዎቹን ታሪካዊ ቤቶች ዲዛይን በአፓርታማዎቹ
ዲዛይን ላይ ማካተት፣
 ከነዚህ በተጨማሪ ጥንታዊ ባህልን ለማስጠበቅ እና ለማስቀጠል የሚረዱ ተቋማት እንዲገነቡ
መደረጉ/መታቀዱ፣
 የከተማ ማደስ አካባቢዎች ከተለዩ በኋላ ይኸው በአዋጅ መደንገጉ፣
 አዋጁን ተከትሎም በሚመለከተው የከተማው ቦርድ እና በሚመለከተው ከተማ ማዘጋጃ ቤት
መጽደቁ፣

ለተነሺዎች የሚደረገውን ድጋፍ አስመልክቶም፣ በመልሶ ግንባታው ወቅት የቱርክ የቤቶች ልማት አስተዳደር
ተከራዮች ለሆኑት ማቆያ እንዲያገኙ ካቀረባቸው አማራጮች መካከል፡ ከተጠናቀቁ ኘሮጀክቶች አፓርታማ እና
በየወሩ የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል ካቀረበው አማራጭ በተጨማሪ እራቅ ወዳለ አካባቢ ሲሰፍሩም እስከ
ከተማው መሃል ድረስ የሚያመላልስ የነጻ አውቶብስ ትራንስፖርት አገልግሎት ማቅረቡ፣

ከነበሩባቸው ክፍተታቸው ልንማር የምንችልባቸው ጉዳዮች በተመለከተ ደግሞ፡-

 አጠቃላይ የከተማ ማደሱን ሂደት የሚያስተባብር እንደ ኮሪያው “የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን” ዓይነት
አንድ አካል መኖሩ አስፈላጊ መሆኑ፣

35
 የከተማ ማደሱ ኘሮጀክት ከማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሃድሶ አቅጣጫ ባለው ክፍተት የሚተች
መሆኑ በእኛም ለናሙና ከተመረጡ ከተሞች የዳሰሳ ጥናት የተገነዘብነው ይህ መሆኑ ትኩረት
ሊደረግበት እንደሚገባ፣
 የከተማ ማደስ ፕሮጀክቶችን ከአጠቃላይ የከተማ ዲዛይን ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባ፣ እና
 የልማት ተነሺዎች በጊዜያዊ ማቆያነትም ሆነ በቋሚ መኖሪያነት በአዲስ አካባቢ በምናሰፍርበት ጊዜ
የግለሰቦቹን ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ወይም የገቢያቸውን ሁኔታ ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፍልጋል
የሚሉት ዋናዎቹ ናቸው፡፡

2.2.3. የቬትናም ከተሞች መልሶ ማደስ ቅኝት


የሰፈሮች መልሶ ልማት መነሻ ምክንያት

በዓለማችን የከተሞች ዑደት ታሪክ በርካታ የመልሶ ማልማት ገፅታዎች ታይቷል፡፡ የጥናት ድርሳናት
እንደሚያሳዩት የተወሰነ የከተሞች ክፍል መልሶ ለማደስ የተለያዩ መነሻ ምክንያቶች ነበሩዋቸው፡፡ የከተማ
ማደስ /መልሶ ማልማት/ ዓላማዎችም እንዲሁ ይለያያሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ1987 የእዝ ኢኮኖሚ አስተሳሰብ መክሰም
ተከትሎ በዚህ መርህ ሲመሩ የቆዩት በርካታ ሀገራት የኢከኖሚ መርህ ለውጥ አድርገዋል፡፡ ይህ የኢኮኖሚ
መርህ ለውጥ መሳሪያ በማድረግ የከተሞቻቸው ገፅታ ለመለወጥ ከተንቀሳቀሱ ሀገራት አንዷ ቬትናም ናት፡፡

መሬት የህዝብና የመንግስት ይዞታ የሆነባት ቬትናም እ.ኤ.አ እስከ 1980 መጨረሻዎቹ አካባቢ የእዝ ኢኮኖሚ
ስርዓት ስትከተል የቆየች ስትሆን የከተማ መልሶ ማደስ የጀመረችው እ.ኤ.አ ከ2000 በኃላ ነው (ሪዚሊያንት
ኢኒሸቲቭ፣ 2015)፡፡ የከተማ መልሶ ማደስ ስራው የተጀመረው በሀገሪቱ ውስጣዊ ፍላጎት ሳይሆን ከኢኮኖሚ
መርህ ለውጥ ጋር የተያያዘ መሆኑ በሀገሪቱ በርካታ ጥናት ያደረጉት የማሕበራዊ ባህል ዕድገት (Social
Anthropologists)፣ የከተማ ገፅታ (Urban Geographers) እና የከተማ ልማት ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡

በሀገሪቱ የተካሄዱ የመልሶ ማደስ ፕሮጀክቶች መነሻቸው የካፒታሊዝም የምጣኔ ሃብት ስርአት መገንባት እና
የሶሻል ስርዓት መገለጫዎች (በእዝ ኢኮኖሚ ስርዓቱ በተግባር ላይ የዋሉ የስነ-ህንፃ እና የዲዛይን ጥበብ፣
ሀውልቶች፣ ቅርሶች፣ በዘመኑ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች እና የንግድ ቤቶች እንዲሁም ሌሎች ህንፃዎች ወዘተ)
ለመለወጥ ነበር፡፡ ፕሮጀክቱም መንግስትና የካፒታል ስርዓት የሚያራምዱ እንደ የተባበሩት መንግስታት
የህዝብ አሰፋፈር ጥናት ማእከል (UN-habitat) የመሰሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት በጋራ ነበር፡፡ እነዚያ ዓለም
አቀፍ ተቋማትና መንግስት በሰፊ የመገናኛ ብዙሓን ሽፋን ተደግፈው የመልሶ ማደስ ስራው ለኑሮ የተመቹ
በፕላን ተመርተው የሚያድጉና የተዋቡ ዘመናዊ ከተሞች እንዲገነቡ እንዲሁም በአመለካከትና በዕውቀት ያደገ
(Civil) ማሕበረሰብ ለመገንባት የካፒታል ስርዓት ተከትሎ መከወን እንዳለበት አቋም ወስደዋል፡፡ ስለዚህ
በሶሻል ስርዓቱ ጊዜ የተገነቡ በመንግስት እጅ የነበሩ በርካታ መኖሪያ ቤቶች ወደ ግል እንዲዛወሩ እንዲሁም
የመልሶ ማደስ ስራው በግል ይዞታነት እንዲከናወን በስፋት ተሰርቶበታል፡፡

36
በመልሶ ማደስ እንቅስቃሴው መንግስትና የካፒታል ስርዓቱ እግር ለማስተከል የሚሯሯጡ አለም አቀፍ
ተቋማት በእዝ ኢኮኖሚ ስርዓቱ ጊዜ የነበሩ መገለጫዎች የካፒታል ስርዓቱ ይፈጥረዋል ተብሎ ለታሰበው
ዘመናዊ ውብ ከተሞችና ሲቪል ማሕበረሰብ ዕንቅፋት መሆናቸው ቢገመገሙም የሕብረተሰቡ ግምገማ
በተቃራኒው አቅጣጫ ነበር፡፡ በመሆኑም መንግስት ለቅርስ ጥበቃ የነበረው የተዛባ አመለካከት
እንዲያስተካክል ዕድል ሰጥቶታል፡፡ በምስራቅ አውሮፓ የታየ ሙሉ የማጥፋት እርምጃ በቬትናም እንዳይደገም
አድርጎታል፡፡ በቪንህ ከተማ "ኳንግ ትራንግ" በመባል በሚታወቅ አከባቢ የተካሄደ መልሶ ማደስ ፕሮጀክት
ገበያዎች እና የህዝብ ማስታወሻዎች እንዲጠበቁ፣ እንዲጠገኑ ካልሆነም እንደ አዲስ እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡
በተለይ በሃኖይ ከተማ የመልሶ ማደስ ፕሮጀክቶች ለቅርስ ጥበቃ የተሻለ ትኩረት ተሰጥተዋል፡፡ ከተማዋ ለ20
ዓመታት እንዲያገለግል እ.እ.አ በ1984 ዓ.ም. የፀደቀው ማስተር ፕላን በከተማዋ መሃል የሚገኙ የቀድሞ ገፅታ
የሚያሳዩ የስነ ህንፃ ውጤቶች በቅርስነት እንዲጠበቁ እውቅና ሰጥቶአል፡፡ ፋይዳ ያላቸው አከባቢያዊ፣
ተፈጥሮአዊ እና ባህላዊ ገፅታዎችም እንዲጠበቁ የከተማ መልሶ ማደስ ስራው በዞን ልማት ቁጥጥር
እንዲደረግና (Zoning Control) ይህንን የሚያስፈፅም ለከተማው ምክር ቤት በቀጥታ ተጠሪ የሆነ
አደረጃጀት ተፈጥሮ ተመርቷል፡፡

በመልሶ ልማት የመንግስት ሚና፣ የመልሶ ልማት አግባቦች፣ እና አካታችነት ውጤቶች

የተባበሩት መንግስታት የህዝብ አሰፋፈር የጥናት ማእከልና ሌሎች ሊበራል የኢኮኖሚ አስተሳሰብ የሚያራምዱ
አለም-አቀፍ ተቋማት በመንግስት አስተባባሪነት የሚካሄድ የመልሶ ማልማት ፕሮጀክት ሰፊ ብክነት እና
የመልካም አስተዳደር ችግር እንደሚገጥመው ከፍተኛ ዘመቻ ስለከፈቱበት በቬንህ ከተማ የተጀመረውና በኋላ
በዋና ከተማዋ በሀኖይ እና ሌሎች ከተሞች የተስፋፋው የመልሶ ማደስ ስራ በግል የሪል እስቴት አልሚዎች
እንዲከናወን አስገድዶታል፡፡

ህዝቡ በፈጠረው ግፊት ምክንያት መንግስት ለቅርስ ጥበቃ ቦታ ቢሰጥም በገበያ ህግጋት የሚነጉድ የግል
አልሚ ያካሄደው የመልሶ ማደስ እንቅስቃሴ ግን አብዛኛው ሕበረተሰብ ተጠቃሚ አላደረገም፡፡ የግል ሪል
እስቴት አልሚዎች ረጃጅም ኮንደሚኒየም ቤቶች ሲገነቡ ዋጋቸው የማይቀመስ ነበር፡፡ በቬንህ ከተማ የተገነቡ
ኮንደሚኒዬም ቤቶች ዋጋቸው ለአብዛኛው የሀገሬው ዜጎች ተደራሽ ስላልሆነ (እ.ኤ.አ በ2006 ዓ.ም በአማካይ
38,000 የአሜሪካን ዶላር) ከተሰሩት ቤቶች ገዥ ያገኙት 60% ብቻ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ
መርህ መቀየሩ ለውጭ ዜጎች የንብረት ባለቤትነት የመሆን መብት ስለተፈቀደላቸው በሂደት የቋሚ ንብረት
ገበያው እየተሻሻለ እ.ኤ.አ በ2010 ዓ/ም የቤቶቹ ዋጋ በዕጥፍ ቢጨምርም ሙሉ በሙሉ ተሽጠዋል፡፡ ገበያ
የመራው የመልሶ ማደስ ተግባሩ ሃያ ዓመት ዕድሜ ያላስቆጠሩ በርካታ አፓርትመንት ቤቶች ከማፍረሱ እና
ነዋሪዎቹ ከማፈናቀሉ ባሻገር የተፈናቀሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ አላደረጋቸውም፡፡

ለመልሶ ማደስ ከታቀደው ቦታ የሚነሱ ነዋሪዎች አያያዝ ላይ የቬትናም መንግስት በጥንካሬ የሚታይ
አይደለም፡፡ በተለይ በቬንህ ከተማ "ኳንግ-ትራንግ" ይኖሩ የነበሩ ከስራቸው በጥሮታ የተገለሉ፣ በጦርነቱ ጊዜ

37
የተጎዱ ወዘተ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሲሆኑ በመንግስት ቤቶች ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶአቸው ዝቅተኛ ኪራይ
እየከፈሉ የሚኖሩ ነበሩ፡፡ 56% የሀኖይ ከተማ ነዋሪዎችም ከመንግስት ኪራይ ቤት ውጭ ለመክፈል ዓቅም
ያልነበራቸው ናቸው፡፡

ይሁንና የመልሶ ማደስ ተግባሩ ለፊዚካላዊ ገፅታ ለውጥ ብቻ ታሳቢ ያደረገ፤ ፍትሓዊ የልማት ተጠቃሚነት፣
ማህበራዊ እሴት፣ የነዋሪው ገቢ ላይ ትኩረት የማይሰጥ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ከቦታው ለሚፈናቀሉ ነዋሪዎች
የሚከፈላቸው ካሳ ከመፈናቀላቸው በፊት ይዘውት የነበረ የቤት ስፋት 30% ተጨምሮ በአዲሶቹ ቤቶች ቦታ
እንዲኖራቸው ታሳቢ ይደረግ ነበር፡፡ ነገር ግን የአዲሶቹ ቤቶች ስፋት ከነባሮቹ በመብለጡ ምክንያት በአዲሶቹ
ቤቶች የተጨማሪ ስፋቱ አማካይ ዋጋ 19,000 የአሜሪካን ዶላር ስለነበር ተፈናቃዮች መክፈል አልቻሉም፡፡
ለተወሰኑ የተሻለ ዓቅም የነበራቸው በአዲሱ ኮንዶሚኒየም ቤት ከመግዛት ይልቅ በሌላ አከባቢ መሬት ገዝተው
የግል ቤት መገንባት የተሻለ አማራጭ ሆኖ ታይቷል፡፡

ከሁለቱ አማራጭ በአንዱ መስተናገድ ለማይችሉ የሕብረተሰብ ክፍል የሚያስተናግድ አሰራር አልነበረም፡፡
በተለይ በቬኒህ ከተማ የሚፈናቀሉ ነዋሪዎች ምን መሆን እንዳለባቸውና የት መልሰው መስፈር እንዳለባቸው
ሳይታቀድ የመልሶ ማደስ ተግባሩ እንዲከናወን ተደርጓል፡፡ አጠቃላይ የመልሶ ልማት ስራው መካከለኛ ገቢ
ላላቸው የሕብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ሲያደርጋቸው ድሀው ዋጋ እንዲከፍል አስገድዶታል፡፡

በቬትናም ከተሞች የተካሄዱ የመልሶ ልማት አግባቦች መልሶ ማደስና አከባቢው ማሻሻል (Upgrading)
ገፅታዎች ነበሩት፡፡ ሁለቱም አማራጮች ጎን ለጎን መተግበራቸው በቅርስና የከተሞች ኢኮኖሚያዊ ዕድገት
(Local Economic Development) የተለያየ ውጤት አስከትለዋል፡፡

በሀኖይ ከተማ 36 ሰፈሮች መሰረተ ልማት ተሟልቶላቸው ቀድሞ ሲከወኑ የነበሩት የቢዝነስ ዓይነቶች
እንዲቀጥሉ መደረጉ ለቅርስ ጥበቃው ከፍተኛ ሚና ከመጫወቱ በተጨማሪ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የሕብረተሰብ
ክፍል የሚተዳደርበት ስራም እንዳይነፈግ አድርጎታል፡፡ በአንፃሩ የመልሶ ማደስ በተካሄደባቸው አከባቢዎች
በአንድ በኩል የመልሶ ማደስ ልማቱ የተከናወነው በግል ሪል እስቴት አልሚዎች በመሆኑ ነባር ስራዎች
በአዳዲስ ዘመናዊ የቢዝነስ ዓይነቶች ስለተቀየሩ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደር የሕብረተሰብ ክፍል የገቢ ምንጩ
አሳጥቶታል፡፡ አከባቢዎቹ ባለ ኮከብ ደረጃ ሆቴሎች፣ ቢሮዎች፣ ፕላዛዎች፣ ረጃጅም የኮንዶሚኒየም ቤቶች
ወዘተ ስለተገነቡበት እነኝህ እንቅስቃሴዎች መካከለኛ ገቢ ላለው የሕብረተሰብ ክፍል የተመቻቸ የኢኮኖሚ
ምንጮች ሁነዋል፡፡ በሌላ መልኩ በመልሶ ማደስ ምክንያት የቱሪስት ፍሰት በከፍተኛ መጠን ስለጨመረ
ሳይታደሱ መሰረተ ልማት እንዲሻሻልላቸው በተደረጉ አከባቢዎች ሲከወኑ የነበሩ ስራዎች ከቱሪስት
መስተንግዶ ጋር የተያያዙ የንግድና አገልግሎት ዓይነቶች ተለውጠዋል፡፡

በአጠቃላይ በቬትናም ከተሞች የተካሄዱ የመልሶ ልማት ስራዎች ሰፊ አካባቢዎች በፍጥነት በማደስ
የሚታወቅ ቢሆንም ከውጤት አኳያ ሲታይ አካባቢው ገፅታ በመቀየርና የከተሞቹ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ

38
መዋቅራዊ ለውጥ በማምጣት በበጎ ገፅታው የሚወሳ ሲሆን በነዋሪዎቹ የልማት ተጠቃሚነት ሲመዘን ግን
መካከለኛና ከፍተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የተመቸ፣ ለውጭ ሀገራት ዜጎች የንብረት ባለቤትነት
በመፍቀድ ከሀገሪቱ ዜጎች ይልቅ የውጭ ሀገራት ዜጎች ተጠቃሚ ያደረገ፣ ከመነሻውም መልሶ ልማቱ በውጭ
ሃይል ጫና የተተገበረ መሆኑ በአሉታዊ መልኩ የሚወሱ ናቸው፡፡ ሀገሪቱ እ.ኤ.አ በ1987 ዓ/ም ነፃ የኢኮኖሚ
ስርዓት ይፋ ማድረግዋ እንዲሁም የመልሶ ማደስ ስራው የውጭ ባለሀብቶችም እንዲሳተፉ መደረጉ የከተሞቹ
የንግድ እንቅስቃሴ ከፍ ቢያደርገውም (ለምሳሌ እ.ኤ.አ በ2000 ዓ.ም በሀኖይ ከተማ ጠቅላላ የተመዘገበ
የንግድ ፈቃድ 4,691 ብቻ የነበረ ሲሆን ከአራት ዓመታት በኃላ 15,068 መድረሱ) ተጠቃሚዎቹ ግን የሀገሩ
ዜጎች አልነበሩም፡፡ ይልቁንም በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ደገሞ ይባስ ተጎጂ ነበሩ፡፡

39
2.3. የንድፈሃሳብና የዓለም አቀፍ ተሞክሮ ቅኝቱ ማጠቃለያ
ከላይ የተብራራውን የንድፈ ሃሳብና የተሞክሮ ቅኝት ጠቅለል ባለ መልኩ ከእኛ ሁኔታ ጋር ለማዛመድ በሚረዳ
ሁኔታ እደሚከተለው ቀርቧል፡፡

2.3.1. የተወሰነ የከተማ ክፍልን ተፈላጊነት መውደቅ ትርጉም


የአንድን ከተማ የተወሰነ ክፍሉ ወይም ሙሉውን ከተማ ተፈላጊነቱ ወድቋል ተብሎ የሚባልበት እና ይህንን
መውደቅ የሚገለፁበት የተለያዩ መለኪያዎች አሉት፡፡ ከቴክኒክ እይታ አንጻር ከአራቱ የከተማ መገለጫዎች
ማለትም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፊዚካላዊና አካባቢያዊ ደህንነት አንደኛው ሲታመም፣ ሳይሟላ ሲቀር፣
ከጅምሩም ያልነበረው ሲሆን ወይም በሂደት ያረጀና የወደቀ ሲሆን ነው፡፡ ይህ ማለት አከባቢው አሁን
በተደረሰበት ፍላጎት ደረጃ የማይመጥን (ለኑሮ ለስራ ተስማሚ ያልሆነ) በትልቅ መስፈርትነት መያዝ አለበት፡፡
ነገር ግን አካባቢው ለኑሮም ሆነ ለስራ የማይመጥንና የማይመች መሆኑ መወሰን/መፈረጅ/ ያለበት ባለሙያ
ሳይሆን ከፖለቲካዊ ትክክለኛነት አንጻር በባለድርሻዎች እይታ መሆን ይገበዋል፡፡

በአከባቢው ግልጽ ችግር መኖሩ እየታየም ኗሪዎቹ መጪው ምን ሊሆን ይችላል በማለት የለውጥ ስጋት፣ ተጎጅ
የመሆን ስጋት፣ በተለይ የሥራና ገቢ ማጣት ስጋት፣ የመፈናቀል ስጋት ወዘተ መነሻ ተመችቷቸው እየኖሩ
እንደሆነ ራሳቸውን በማሳመን እንዲነካ ያለመፈለግ፤ ከችግሩም ጋር መለማመድ ወዘተ እንደሚያጋጥም
የታወቀ ነው፡፡ ያም ቢሆን ለመተማመን ጊዜ ሰጥቶ ከመሄድ በተለየ እኔ አውቃለሁ ቦታው ለኑሮና ስራ ምቹ
አይደለም ተብሎ በባለሙያ ወይንም በአመራር ብቻ ታምኖበት ከተገባ ከጅምሩ የአፈጻጸም ችግር
እንደሚገጥመው በንድፈሃሳብ ሳይሆን በተግባር ተሞክሮ የተረጋገጠ ነው፡፡

2.3.2. አከባቢው ያልተሟላበትና የሚወድቀበት ምክንያት


አንድን አከባቢ ተፈላጊነቱ ወድቋል ብሎ ለመፈረጅ እንደ መስፈርት የሚወሰዱት በሁሉም ሀገራት ተመሳሳይ
ናቸው፡፡ ለውድቀቱ መነሻ ተደርገው የሚወሰዱ ምክንያቶች ግን ከሀገር ሀረር እንዲሁም ከከተማ ከተማ
ይለያያሉ፡፡ በኤሲያና ላቲን አሜሪካ ከተሞች ለመውደቅ ያበቁት ዋና ምክንያቶች የህዝብ እድገት መጨመርና
ከፍተኛ የገጠር ከተማ ፍልሰት ኢኮኖሚው መሸከም ባለመቻሉ ሕገወጥ ሰፈራ እና በእነዚህ ሕገወጥ ሰፈራዎች
የሚስፋፋ ፕላን ያልተከተለ አሰፋፈርና ከደረጃ በታች ግንባታዎች ናቸው፡፡

በአፍሪካ የመውደቁ ምክንያት ቅኝ ግዛት የፈጠረው ጠባሳ ነው፡፡ በብዙ የአፍሪካ ሀገራት የቅኝ ግዛት ውጤት
ድሃው ተገፍቶ ተነጥሎ ከከተማ ዳርቻዎች፣ በማዕድን ማውጫ አከባቢዎች በሚገኙ ብዙም ለሰፈራ ባልተመቹ
ቦታዎች የተገነቡ ሰፈሮች ከጅምሩ ብዙ ጉድለት ያለባቸው፤ በሂደትም ከይዞታ አለመረጋገጥና መተፋፈግ ጋር
በተያያዘ አለመታደስ አሁንም ቢሆን ከተሞቹ ሰፊው ክፍላቸው የከተማ እርጅና እንዳጠቃው ይገኛል፡፡
የአውሮፓ ከተሞች እርጅና ሲታይ ደግሞ የቴክኖሎጅ ለውጥ፤ የሴክቶራል ትራንስፎርሜሽን ውጤት፤

40
(መሰረተ ልማት ለማስፋትና የተለየ መረብ ለመዘርጋት፤ ከኢንዱስትሪ ወደ አገልግሎት እና የአይ.ቲ ዘመን መቀየር)
ውጤት አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡

2.3.3. አንድ ቦታ መልሶ መልማት የሚያስፈልግበት ጊዜ


ከተለያዩ ምክንያቶች በመነሳት ወደቀ ተብሎ የሚፈረጀው አካባቢ መልሶ ለማልማት ሁለት ዓይነት አግባቦች
ተግባር ላይ ውለዋል፡፡ አንደኛው እስካሁን ያልታመመውን ክፍል/ገጽታ ላለመንካት፣ በጥሩ ሁኔታ ያለውን
እስከመጨረሻው አሟጦ ለመጠቀም፣ ተቃውሞ ለማለዘብ እንዲሁም አቅም አነስተኛ በሚሆንበት ጊዜ
ወቅታዊ ወጭን ከመቀነስ አንጻር ሁሉም እስኪጓደል የመጠበቅ ሲሆን፤ ሁለተኛው መልክ ደግሞ ከወጭና
ቶሎ መልሶ ለማልማት የመቻል እድልን ከመጠቀም አንጻር አንዱ/ሁለቱ ሲወድቅ ሌላው የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ
በስተቀር መውደቁ ስለማይቀር የቦታው ሙሉ ተፈላጊነት ሳይጠፋ የታመመውን ማከም የሚል ነው፡፡

2.3.4. መልሶ ማልማት የተመራበት ዓላማ ተሞክሮዎች


መልሶ ማልማት ያስከተሉ ምክንያቶች በየሀገሩና በየከተማው የተለያዩ የመሆናቸው ያህል በየሀገሩ የተከናወኑ
የመልሶ ማልማቱ ስራ ለመምራት ሀገራቱ/ከተሞቹ የተለያዩ ዓላማዎች ነድፈው ነበር፡፡ ለመጥቀስ ያህል፡-
 በእንግሊዝ ሀገር መልሶ ማልማት የተጀመረው በ1930ዎቹ ሲሆን መነሻውና ግቡ በኢንዱስትሪው
አብዮት ምክንያት የተቀጣጠለው የከተማ አብዩት መቀዛቀዝን ለመታደግ በሚል መሆኑ፤
 በአሜሪካ በ1950ዎቹ በመሀል ከተማ የታየውን ስርአት አልበኝነት/ወንጀል መበራከት ለማስወገድ
ወይንም ከከተማ መሀል ለማውጣት ሲባል የተከናወነ መሆኑ፡
 በፈረንሳይና በጀርመን ከተማን ለማዘመን ከመፈለግ የሚመነጭ የመልሶ ማልማት ስራ የነበረ መሆኑ፤
 በቱርክ በስፋት የተገባው ከመሬት መንቀጥቀጥ ጋር ተያይዞ በደረሰ አደጋ መነሻነት መሰል ስጋት ያዘሉ
ህንጻዎችን መልሶ መገንባት በሚል በ2012 ሀገር አቀፍ አዲስ ህግ በማውጣት እየተከናወነ ያለ ነው፡፡

2.3.5. በከተሞች መልሶ ማልማት የመንግስት ወሳኝ ሚና


የወደቀውን የከተማ ክፍል መልሶ የማልማት ሓላፊነት የመንግስት መሆን አለበት ወይስ በገበያው ሓይል
እራሱን መለወጥ አለበት የሚለውን የፍልስፍና ክርክር ሲደረግበት ይታያል፡፡ ነገር ግን እስካሁን በየትኛውም
ሀገር የታየው ተሞክሮ ገበያው መልሶ ማልማትን ዳር እንዳልደረሰ፤ ይልቁንስ የመንግስት ሚና እጅግ ወሳኝ
መሆኑ ነው፡፡ ምክንያቶቹም፡
 በብዙ ሀገራት የኪራይ ጣሪያና የፕላን ክልከላዎች፤ አልሚዎችን ስለማያበረታታቸው፣
 ተስፈኝነትና ዋዣቂነት፤ እነሱ ሳያለሙ ሌሎች እንዲያለሙና የያዙት ቦታ ዋጋው ጨምሮ ተጠቃሚ
ለመሆን መፈለግ (ሳይለፉ ሌሎች በለፉት ለመጠቀም ማድፈጥ ስለሚታይ)፣

41
 የፍላጎቶች ግጭት ጡዘት ምንጭነቱ /አንዱ ማልማት ሲፈልግ ሌላው ፍላጎቴን ይጎዳል በሚል መከላከል/
ስለሚኖር፣
 ሰፊ የመልሶ ማልማት ስራ በየትም ሀገር ያለመንግስት ጣልቃ ገብነት የገበያው ጉድለት በራሱ ተፈቶ
አልሄደም፡፡ የመንግስት ሚና ሙሉ በሙሉ ቦታውን ከማልማት ጀምሮ ፖሊሲና ህግ ማመቻቸትና
የተወሰነ ድጋፍ እስከማድረግ ውሱን ድርሻ ሊወስድ ይችላል፡፡

2.3.6. መልሶ ማልማት ከታሪክ ዕይታ የሚነሱ አቋሞች


የከተሞችን ነባር አካባቢ መልሶ ሲለማ ከቅርስና ታሪክ ጥበቃ ጋር ተያይዞ አከራካሪ ጉዳዮችን ያስተናግዳል፡፡
በአንድ በኩል በአካባቢው የሚገኝ ሁሉም ነገር ቅርስ እንደሆነ አቋም በመውሰድ አከባቢውን እንዳይነካ
የመከላከል ሲሆን ሁለተኛው የአመለካከት ጫፍ ደግሞ መልሶ እንዲለማ የተፈለገ ቦታ የድህነት መገለጫ
አድርጎ በማየት ሁሉን እንዲለወጥ አቋም የሚይዝ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ጫፎች ለማስታረቅና ሁለቱም
ያላቸው በጎ ጎን ጥቅም ላይ ለማዋል አዲሱ ልማትም ቅርስ መጠበቅ አለበት የሚል አማራጭ ተፈጥሯል፡፡ ይህ
አማራጭ በመርህ ደረጃ የሚያስማማ ቢሆንም ሚዛኑ ወዴት? በምን መስፈርት? የቱ ቅርስና ስንት መቶኛ
ቅርስ ተብሎ ይያዝ? የቱ በምን ደረጃ ይቀየር? ወዘተ የሚሉትን የሚዛን ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ስራ መስራት
የሚጠይቅ ነው፡፡

መልሶ ማልማት ምን ላይ ያተኩር በሚለው ደግሞ የታመመ/የጎደለውን ማከም ብቻ የሚል አንዱ አመለካከት
ሲሆን ሌላው ጫፍ ሁሉም አዲስ እስኪሆን አብሮ መለወጥ የሚል ጽንፍ ይታያል፡፡ ለምሳሌ ፊዚካልና
ኢንቫሮመንታል ህመም/ጉድለት ካለ ፊዚካል/አካባቢያዊ ገፅታ ለውጥ ብቻ አድርጎ ነባሩ ማህበረሰብና
ኢኮኖሚን ማስቀጠል፡፡ የማህበራዊ ችግር ከሆነ እሱን ቀርፎ ሌላውን በመተው የአፕግሬዲንግ ስራ መስራት
የሚለውን ጫፍ ሲወስድ ሌላኛው ፊዚካልና ኢንቫሮመንታል ካደስን መሬቱ የሚጠብቀው ከፍተኛ ጠቀሜታ
ያለው ልማት መምጣት አለበት፤ ኢኮኖሚው ከፍ ካለ ደግሞ ሌላ የማህበረሰብ ገጽታ ስለሚይዝ ነባሩ ነዋሪ
ሌላ ቦታ መሄድ አለበት(displacing the endigenious people and all Previous activities) የሚል ነው፡፡
በመሃል ደግሞ የአካታችነት አማራጭ የሚያቀርብ ሲሆን በዚህ ደረጃ ልዩነት የሚታየው የሚዛን ጉዳይ ብቻ ነው፡፡

2.3.7. የከተማ መልሶ ማልማት ስኬታማነት መገለጫዎች


ተፈላጊነቱን የቀነሰ/የወደቀ ነባር የከተሞች ክፍል መልሶ ማልማት ለአካባቢውና በአጠቃላይ ለከተማው
ተደማሪ የልማት ውጤት ሊያስገኝ ይገባል፡፡ በመሆኑም መልሶ ማልማት ለመከወን እንደ መርህ መከተል
በሚገባው ጉዳዮች ላይ የተለያዩ የምሁራን አስተያየቶች ያሉ ሲሆን በተግባር ከተከናወኑ ፕሮጀክቶች በመነሳት
የተለያዩ የዘርፉ ተመራማሪዎችና ተቋማት መልሶ ማልማት ለውጤት የሚያበቁት መስፈርቶች በመለየት ወደ
ፖሊሲዎችና ስትራተጂዎች እንዲካተቱና ሀገራት እንዲተገብሩዋቸው አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡ ከዚህ አንፃር
ስኬታማ የሚባል የመልሶ ማልማት ፕሮጀክት መገለጫ ተደርገው ከሚወሰዱ ዋናዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡

42
 የታቀደና ከፍላጎት አንጻር የሚመጥን/ያልሰፋ ያልጠበበ
 አላማውን አብዛኛው ባለድርሻ የደገፈው፤
 በሂደቱ ሁሉም ባለድርሻ የተሳተፈበትና ደስተኛ የሆኑበት (በቦታው የነበሩ መስተንግዶ/አያያዝ)፤
 በሂደቱና ውጤቱ ተጎጅ የሌለ (ሁሉን ተጠቃሚ ያደረገ)፤
 አካባቢው ሁለንተናዊ ይዘቱ ወድቆ መልሶ የማልማት እድሉ ጠቦ ፈተናው ሳይሰፋ በወቅቱ የተተገበረ፤
 ችግሩን አሟልቶ (ፊዚካል ኢንቫሮመንታል፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ/ የፈታ) አዲስ ችግር ያልፈጠረ፤
 ያለውን መሰረተ ልማት በላቀ ሁኔታ መጠቀም ያስቻለ (ጫና ያልፈጠረ/ከአቅም በታች ያልተጠቀመ)፤
 ከመሬቱ መገኘት የሚገባውን እሴት ያሰገኘ (ለመሬቱ ዋጋ የሚመጥን ልማት)፤
 ለከባቢው በጎ ትሩፋት የቸረ (ከባቢውን የጎዳ ሳይሆን ያነቃቃና ተጠቃሚ ያደረገ)፤
 አካታች ነባሩና አዲሱን ያዋሃደ፤ ነባሩን ቢዝነስ አዳብሮ ያስቀጠለ፤ አዲስ ለውጥ ያካተተ፤ ለድሃና
ለሃብታም በፍትሃዊነት ተደራሽ፤
 መሰረታዊ ለውጥ ያመጣ (ትራንስፎርሜሽን የታየበት)
 የቦታ አጠቃቀሙ ውጤታማ የሆነ፤ ቦታ ቆጣቢ፤ የመሬት አቅርቦትን ችግር የፈታ
 የቀጥታ ፋይናንስም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ከወጭው የላቀ
 ታሪክና ባህልን የጠበቀ (ያላፈረሰ፣የላንኳሰሰ/ያበለጸገ)
 የከተማዋን አሰፋፈር ሚዛን ያላዛባ (ተፈላጊውን የአሰፋፈርና ሞቢሊቲ ሚዛን የጠበቀ)፤
 ሞቢሊቲን አከባቢያዊ ያደረገ ቅይጥና ሁሉ አቀፍ፤
 ልማትን አንድ ቦታ ብቻ ሳይሆን ሚዛን ጠብቆ በማእከልና ንዑስ ማዕከላት እንዲከናወን ያስቻለ፤
 ዘላቂነት ያለው፤ መደገምና መስፋት የሚችል፤ ነገ መልሶ ማፈረስን የማይጋብዝ፤
 ግንባታ በተናጠል ከመፍቀድ ባለፈ በቦታው የታሰበው ልማት በቀጣይ በቦታው የሚኖረው እንድምታ፤
 ተጠቃሚው ተጎጅውን የካሰበት፤ ተጠቃሚው ጥቅሙን የሚያገኝበትና ተጎጅው ድጋፍ በሚሻበት ጊዜ
ልዩነት መፍቻ ስልት ያለው/የፈታ፤
 ማህበራዊ ትስስርን የጠበቀ/ያጎላ፤
 ለስኬታማነቱ ራሱ የቻለ የተሟላ የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ ያለው፤
 መንግስት ተገቢውን የልማት አደረጃጀት ፈጥሮ ባህሪው ያገናዘበ የፋይናንስ ሰርአት ተበጅቶለት የተመራ፤
 በረጅም፤ መካከለኛና አጭር ጊዜ የተሟላ እቅድ ያለውና በታቀደለት ጊዜ የተጠናቀቀ
 አስቻይ ሁኔታን በአግባቡ የተጠቀመ፤ ገች/ፈታኝ ተግዳሮቶችና ችግሮች በአግባቡ ያስተናገደ

43
ክፍል ሶስት፡ የከተሞች የመልሶ ማልማት ቅኝት

3.1. የአጠቃላይ ማዕቀፍ ቅኝት


በኢትዮጵያ ከተሞች ሲካሄድ የቆየውና አሁንም በመካሄድ ላይ የሚገኘው የመልሶ ማልማት ስራ ምን ዓይነት
ባህሪ እንዳለውና ውጤቱ ምን እንደሚመስል ለማየት መጀመሪያ አጠቃላይ የከተሞቹ ሁኔታ እና የመልሶ
ማልማት አጠቃላይ ሀገራዊ ማዕቀፍ ምን እንደሚመስል ምልከታ ማድረግ ይጠቅማል፡፡ ስለሆነም መልሶ
ማልማት በሀገሪቱ ወቅታዊ መሆኑ አለመሆኑ፤ የሀገሪቱ ፖሊሲዎች፣ ስትራተጂዎችና የሕግ ማዕቀፎች መልሶ
ልማትን ምን ያህል ዕውቅና እንደሰጡት እና የሚከተሉት አቅጣጫ፤ አጀንዳው ወቅታዊ ከሆነ ልማቱ
ለመከወን አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸውና አለመኖራቸው እንዲሁም ጥንካሬያቸው ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል፡፡

3.1.1. የከተማ መልሶ ማልማት አጀንዳ ወሳኝነትና ወቅታዊነት በኢትዮጵያ


ኢትዩጵያ እንደ ሀገር ገና በመልማት ላይ ያለች በመሆኗ ያላት የክትመት ደረጃ ዝቅተኛ ነው፡፡ የማዕከላዊ
ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ትንበያ በ2014 የኢትዩጵያ የከተሜነት ደረጃ አስራ 9% እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡ ሌሎች
ጥናቶችም ቢሆን - ለምሳሌ ሀገራዊ እስፓሻል ጥናት በ2015/16 የኢትዩጵያ የከተሜነት ደረጃ ከ20% ያልበለጠ
እደሆነ ያሳያሉ፡፡ በአንጻሩ የክትመት ፍጥነቱ ሲታይ ደግሞ ከ4% በዓመት እንደሚበልጥና ይህም በዓለም
ፈጣን ከሚባሉት ውስጥ እንደሆነ ያሳያል፡፡ እንደ ከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር (2007) መረጃ ከሆነ
ደግሞ ከሃያ ሺ ህዝብ በላይ ያላቸው ከተሞች ከ112 አይበልጡም፤ አብዛኞቹ ከ1,500 በላይ ከተሞች ገና
በአነስተኛ ደረጃ ያሉ ናቸው፡፡

ከሀገሪቱ የከተሜነት ደረጃ አንፃር ከታየ ከተሜነቱ ጅምር በመሆኑ ከተማ መልሶ ማልማትን ገና ሊመስል
ይችላል፡፡ በዚህ ዝቅተኛ የከተሜነት ደረጃ እና ጅምር ከተሜነት ሂደት ውስጥ ተሁኖ ስለመልሶ ማልማት
ማሰብ የሚያስፈልግበት በቂ ምክንያቶች ግን አሉ፡፡ ከተማ ተብለው የሚፈረጁት መንደሮች ከተማ ለመባል
ብዙ የሚቀራቸው፤ አገነባባቸው በአመዛኙ ያለፕላን፤ በነበረው ኋላ ቀርነት የተነሳ የግንባታ ዘርፉ ባለመዳበሩ
የግንባታ ደረጃው የወረደ፤ ኢኮኖሚውና የግንባታ ቁሱ ደካማ ስለሆነ በከተሞች ያለው አብዛኛው ግንባታ
ደረጃውን ያልጠበቀና ፈርሶ መሰራት ያለበት ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2007 የተባበሩት መንግስታት የህዝብ አሰፋፈር ጥናት መሰረት አብዛኛው የኢትዩጵያ ከተሞች ቤት
በደካማ የግንባታ ቁስ የተሰሩ፤ ከፍተኛ የጥራት ችግር ያለባቸውና እንደ አዲስ መገንባት ያለባቸው መሆናቸው
ያመላክታል፡፡ ይሄው ጥናት የ1994 የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ መረጃን ጠቅሶ እንዳሰፈረው በሀገሪቱ
ያሉት 80% ቤቶች በጭቃና እንጨት እንደተሰሩ፤ 73% ወለላቸው አፈር እንደሆነ፤ 98% የሚጠጉት ፎቅ
እንዳልሆኑ ከዚህ ውስጥ 54% በመደዳ ተያይዘው የተሰሩ እንደሆኑ፤ ቤቶቹ ያላቸው ክፍል ሲታይም 41.8%
ባለ አንድ ክፍል 30.54 ደግሞ ባለሁለት ክፍል መጠለያዎች መሆናቸውን፤ 42.3% የሚሆኑት ቤቶች ንጽህና

44
መጠበቂያ ቤት እንደሌላቸው፤ 39.2% ደግሞ ማድቤት የሚባል እዳልገነቡ፤ እና 27% የቧንቧ ውሃ
እንደሌላቸው ያስነብባል፡፡

ስለሆነም የከተማ መልሶ ማልማት ስራ በኢትዮጵያ የወቅቱ ወሳኝ አጀንዳ መሆኑ ይታያል፡፡ ከተሞችን መልሶ
ማልማት ወሳኝ የሚያደረገው ሌላው ጉዳይ ከተሞቻችን ነባሩ ክፍል በአግባቡ ሳይጠቀሙበት፤ ያለውን ውሱን
መሰረተ ልማት በሚጠበቀው ደረጃ ሳይገለገሉበት ወደ ውጭ እየተለጠጡ እንዳሉና ከወጭም ሆነ
ከአስተዳደር ዘላቂነት አንጻር ወደ ውጭ ከማማተር ቀድሞ ወደ ውስጥ መመልከት እንደሚገባ አዲስ አበባን
በምሳሌ በማስቀመጥ በቅርቡ በዓለም ባንክ የተከናወነው የከተሜነት ሁኔታ ዳሰሳ (Urbanization Review)
ጥናት ያመላክታል፡፡

3.1.2. ሀገራዊ የህግ ማዕቀፍ ቅኝት


የመልሶ ማልማት ጉዳይ ወሳኝ አጀንዳ መሆኑ ካየን ወደ ቀጣዪ ስለ ከተማ መልሶ ማልማት አፈጻጸማችን
በተመረጡ ከተሞች ዳሰሳ ከመግባታችን በፊት በጉዳዩ ዙሪያ ምን አጠቃላይ ማዕቀፍ አለ የሚለውን
እንደሚከተለው እናያለን፡፡ በመጀመሪያ መናገር የሚቻለው ከተማ ማደስን የተመለከተ ራሱን የቻለ የፖሊስም
ሆነ የህግ ማዕቀፍ የሌለ ሲሆን ጉዳዩን በአንድም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተመለከቱ የህግ ማዕቀፎችን ይዘት
ስናይ የድሮውን ትተን አሁን በስራ ላይ ያለውና የህጎች የበላይና ቀዳሚው በ1967 የወጣው አዋጅ ቁጥር
47/67 ሲሆን ቀጣዩ የ1987 ህገ መንግስት እናገኛለን፡፡

አዋጅ ቁጥር 47/67 ውስጥ ከተማ መልሶ ማልማት ጋር እንድምታ ያላቸውን ድንጋጌዎች ለማየት ያክል
አዋጁ የከተማ ቦታና ትርፍ ቤት እንዲወረስ ያደረገ ሲሆን በአንድ ግቢ ውስጥ ያለን ቤት ዋናውን ወይንም
ሰርቪሶቹን በመውረስ ይዞታ በግቢ ደረጃ እንዲቀላቀል ያደረገ፣ ከዚያም ግቢ ቢለያይም በአንድ አካባቢ ያለው
መንደር ይዞታ ቅልቅል በመፍጠሩ የኢኮኖሚ ስርዓቱ ገበያ መር ሲሆን ይዞታው በገበያው ሀይል ፍላጎት
እንዳይለማ እንቅፋት ሆኗል፡፡ አብዛኞቹ ቤቶቹ ሲወረሱ የተገነቡበት ቁስ ለረጅም ጊዜ ውበቱን ጠብቆ
የማይቆይ እንጨትና ጭቃ ከመሆኑም በላይ በወቅቱ ከነበረው የኪራይ ዋጋ በግማሽ ቀንሶ እስከ አሁንም
ባለበት ስለቀጠለ የኪራይ ገቢው ቤቶቹን ለማደስ ቀርቶ ለመጠገን እንኳን የማያስችል በመሆኑ ቤቶቹ
ሳይጠገኑ ቆይቷል፡፡

የቤቶቹን ኪራይ በቤቱ ያሉ ወገኖች መጥተው ሲከፍሉ ከመሰብሰብ ያለፈ በአደረጃጀትም ሆነ በአሰራር አቅም
ያለው መዋቅር ስላልነበር ከብዙ ቤቶች ከተገኘው ገቢም አንድና ሁለት ቤት እንኳን የመጠገን ስራ
አልተሰራም፡፡ ይባስ ብሎ ቤቶቹን የሚከታተል አካል ባለመኖሩ በቤቱ ያሉ ወገኖች በነበሩ ክፍት ቦታዎች ላይ
የሰርቪስ ቅጥያ እየሰሩ በመጠቀምና በማከራየት ጭምር ሰፈሮች በሙሉ መተንፈሻ የሌላቸውና ለኑሮ
የማይመቹ ሆነዋል፡፡ ለመልሶ ልማት ስራ ቤት ወደ ማፍረስ ሲገባ ይህ የተከራይ አከራይ ስፋት የራሱ
ውስብስብ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡ በእርግጥ ግንባታው ከመነሻውም ቢሆን ዝቅተኛ ዋጋ ባለው ቁሱ የተሰራና

45
ሳይጠገን የቆየ ከመሆኑም በላይ ካሳ በቀጥታ የማይከፈልበት መሆኑ አሁን ለሚካሄደው መልሶ ማልማት
ቀጥታ ወጭ መቀነስ የራሱ በጎ አስተዋጽኦ እንዳለው እሙን ነው፡፡

አዋጁ ቤት ከመውረስ ሌላ በወቅቱ በአንድ ከተማ ወይም ሰፈር ያልተወረሰ ቤት ያለው ሰው ከተማ ወይም
ሰፈር ሲቀይር ቤቱን አከራይቶ ሌላ መከራየት ስለማይፈቅድ የነበረው ምርጫ ቤቱን ለመንግስት አስረክቦ
በምትኩ በሚፈልግበት ከተማና ቦታ በማካካሻነት መንግስት ከተወረሱ ቤቶች የሚፈቅደበትና የቤቶቹ ግምት
ልዩነት የኪራይ ማካካሻ በሚል የሚከፈልበት አካሄድ ነበር፡፡ ስለሆነም በስራ ምክንያት አከባቢያቸውን ለቀው
ቤታቸው በሌላ ከተማ (ኤርትራ ጭምር) ያለና የሚኖሩት በተወረሰ የቀበሌ ቤት የሆኑ ወገኖች ቦታው ለመልሶ
ማልማት ሲፈለግ የሚስተናገዱበት አግባብ የተወሳሰበ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በዚህ ምክንያት የመልሶ
ማልማት ስራው እንዲጓተት የነዚህ ወገኖች መስተንግዶም የመልካም አስተዳደር ችግር እንዲሆን አድርጓል፡፡

ከዚህ ሌላ ቤት በአዋጁ አፈጻጸም መሰረት ከተወረሰ በኋላ በተለያየ ምክንያት በተለይ በ1974 በወጣ መመሪያ
የአንድ ቤት መስፈርት ሳያሟሉ የተወረሱ ክፍሎች ለግለሰቦቹ የተመለሱ ሲሆን እነዚህ ቤቶች ኪራይ
ሲከፈልባቸው ስለነበር ኪራይ ቀመስ ናቸው ተብሎ ስለሚታሰብ ለአፈፃፀም ማነቆ ሆኗል፡፡ ከዚህም
በተጨማሪ ባዶ ቦታ ላይ ግለሰቦች ቤት እየሠሩ ለመንግስት ኪራይ እንዲከፍሉ ይደረግ ስለነበረና በኋላ ኪራይ
የመክፈል ሂደቱ ስለተቋረጠ ግለሰቦቹ የቤቱ ባለቤት እንደሆኑ የባለቤትነት መብት እንዲረጋገጥላቸው
ስለሚጠይቁ መልሶ ልማት እንዲጓተት ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንድ ሆኗል፤ ሌላው ኪራይ ቀመስ ቤት
በሚል መሰተንግዶ መስጠት የማይቻልበት በተሰወነ ደግሞ ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች የሰሩትና ግለሰቦች
የሚኖሩበት ቤት እንዲሁ የኗሪዎቹ መብት የተከራይ ነው ወይስ የባለቤትነት በሚል ውዝግብ መልሶ
ማልማቱን እየጎተተ ያለ ጉዳይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ህገ መንግስት

ከህገ መንግስቱ ውስጥ ከጉዳዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን አንቀጾች ለመጥቀስ ያክል

 አንቀጽ 44/1 - ሁሉም ሰዎች ንጹህና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት እንዳላቸው፣
 አንቀጽ 43/4 - የልማት እንቅስቃሴ ዋና ዓላማ የዜጎችን የዕድገትና መሰረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት
እንደሆነ፣
 አንቀጽ 44/2 - መንግስት በሚያካሂዳቸው ፕሮግራሞች ምክንያት የተፈናቀሉ ወይንም ኑሮዋቸው
የተነካባቸው ሰዎች ሁሉ በመንግስት በቂ ዕርዳታ ወደ ሌላ አካባቢ መዛወርን ጨምሮ ተመጣጣኝ
የሆነ የገንዘብ ወይም ሌላ አማራጭ ማካካሻ የማግኘት መብት እንዳላቸው፣
 አንቀጽ 40/2 - ንብረት ማለት በጉልበቱ፤ በፈጠራ ችሎታው ወይም በካፒታሉ ያፈራው ተጨባጭና
ተጨባጭ ያልሆነ ዋጋ ያለው ውጤት መሆኑ፣

46
 አንቀጽ 40/8 - የንብረት ባለመብትን ንብረት ለህዝብ ጥቅም ከተፈለገ መንግስት በቅድሚያ
ተመጣጣኝ ካሳ በመክፈል ሊወሰድ እንደሚችል፣
 አንቀጽ 40/3 - መሬትና የተፈጥሮ ሀብት የባለቤትነት መብት የመንግስትና የህዝብ ብቻ እንደሆነ፣
የዚህን ሀብት አጠቃቀምና አጠባበቅ ህግ የማውጣት ስልጣን የፌደራል መንግስት (አንቀፅ 51/5)
ሲሆን የማስተዳደሩ መብት ደግሞ የክልሎች (አንቀጽ 52/2) ነው፡፡

ከዚህ ማየት የሚቻለው ህገ-መንግስቱ ለመልሶ ማልማት በቂ ትኩረትና ድንጋጌ እንደሰጠ ነው፡፡ ለዜጎች
ንጹህና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት ሲሰጥ የወደቁ የከተማ ክፍሎች መታደስ እንዳለባቸው አስገዳጅ
ነው፡፡ ህገመንግስቱ የዜጋ መብት ነው ያለውን ጉዳይ እንዲከበር ሁኔታዎችን መፍጠር ያለበት መንግስት
መሆኑ የግድ ነው፡፡ በልማት ምክንያት ለሚነካ ላፈራው ንብረት ካሳ እና የመልሶ መቋቋም ድጋፍ ሊደረግለት
እንደሚገባም ያስረዳል፡፡ ንብረት የሚለውን ሃሳብ ሲተረጎም ግንባታን ብቻ አይወስድም፤ ተጨባጭ ያልሆነ
ሀብትንም ያካተተ ነው፡፡ የልማት ዓላማም የግንባታ ለውጥ ማምጣት ሳይሆን የዜጎች ተጠቃሚነት እንደሆነ
በማያሻማ ሁኔታ ያስቀመጠ ነው፡፡ ስለሆነም ህገመንግስቱ ከዚህ አንጻር ምሉእ እንደሆነ አሳማኝ ነው፡፡

በህገመንግስት ደረጃ መሬት የህዝብና የመንግስት መደረጉ ለልማት ትልቅ እድል ነው፡፡ በሌሎች ሀገራት
ከተማን መልሶ ለማልማት መሬትን ለማሰባሰብና በቦታው ያለን ወገን ለማንሳት ሲታሰብ ካሳው የመሬት
ወጭን ለመጨመር እጅግ ከፍተኛና አቅም የሚፈትን ነው፡፡ ለህዝብ ጥቅም ሲባል ማስነሳት መቻል
በህገመንግስት እውቅና ማግኘቱም ሌላ ለመልሶ ማልማት ጥሩ አስቻይ ሁኔታ ነው፡፡

ከተማን መልሶ ማልማት የመሬት አስተዳደር ጉዳይም ስለሆነ ከህገመንግስቱ ድንጋጌ ስንነሳ መሰረታዊ ጉዳይ
ወሳኝ ህግ የማውጣት ስልጣን የፌደራል መንግስት ሲሆን ማስተዳደሩ ደግሞ የክልሎች/ከተሞች እንደሆነ
ነው፡፡ ይሁን እንጅ እስከ አሁን ድረስ መልሶ ማልማትን የሚመለከት ራሱን የቻለ ህግ ላለመውጣቱ መወቀስ
ካለበት ተወቃሹ የፌደራል መንግስት ነው፡፡

ይህም ለጉዳዩ የተሰጠውን ትኩረትና ያለንን ግንዛቤ አነስተኛነት ሲያሳይ እዚህ ላይ የጉዳዩን አንደኛው ገጽታ
ማለትም ስለ ካሳ ክፍያ ብቻ የሚደነግገውን አዋጅ ቁጥር 455/1997 እንኳን ብንጠቅስ አዋጁ የወጣው በ1997
መሆኑ ከዚያ በፊት ሂደቱ ይመራ የነበረው ሰፊ ክፍተት እንደነበረው ያሳየናል፡፡ በእርግጥ ከዚያ በፊት የወጡት
የሊዝ ህጎች ከዚያም ቀደም የፍትሃብሄር ህጉ ለህዘብ ጥቅም ሲባል ቦታን ማስለቀቅ እንደሚቻል ለሚነሱ
አካላት ደግሞ የንብረት ካሳ መክፈል እንዳለበት ድንጋጌዎች የያዙ ስለነበር ከማስነሳትና ካሳ መክፈል ጋር
በተያያዘ የህግ መነሻ ነበር ቢባልም የህገመንግስቱን ይዘት የሚተረጉምና በመርህም መልሶ ማልማት መቼ፣
እንዴት፣ በማን ሊከናወን እንደሚገባ የሚያመላክት፣ የመንግስትና የሌሎች ባለድርሻዎችን ሚና ያሳየ
ስላልነበር ጉድለቱ ሰፊ ነበር፡፡

47
ለህዝብ ጥቅም ሲባል መሬት ለማስለቀቅና ካሳ አከፋፈል ለመወሰን የተደነገገ አዋጅ ቁጥር 455/1997

 አንቀጽ 2(1) ላይ ካሳ ማለት የመሬት ይዞታውን እንዲለቅ ለሚወሰንበት ባለይዞታ በመሬቱ ላይ


ላሰፈረው ንብረት በአይነት ወይም በገንዘብ ወይም በሁለቱም የሚከፈል ክፍያ መሆኑ ሲደነግግ
አንቀጽ 7 ተራ ቁጥር 1 ላይ በመሬቱ ላደረገው ቋሚ ማሻሻያም ካሳ እንደሚከፈል ይገልጻል፡፡
 አንቀጽ 2(2) ደግሞ የሚከፈለው ካሳ ንብረቱን ባለበት ሁኔታ ለመተካት የሚያስችል ይሆናል ይላል፡፡
 ክፍያው ለከተማ ኗሪ ሲሆን ዝቅተኛው ካሳ የሚመለከተው ክልል ባወጣው ስታንዳርድ መሰረት
አንድ ክፍል የቁጠባ ቤት ሊያሰራ ከሚችል ያነሰ መሆን እንደሌለበት ይደነግጋል፡፡ ማዛወር የሚቻል
ንብረት ከሆነ ካሳው ነቅሎ ለሌላ ቦታ ለመትከል የሚፈልገው ወጭ ብቻ እንዲከፈል ይደነግጋል፡፡
 መፈናቀያ ካሳ በተመለከተ ደግሞ በከተማው መጠኑ የሚወሰን ምትክ ቤት መስሪያ ቦታ፤ እና የአንድ
ዓመት የቤት ኪራይ/ነጻ ቤት እንደሆነ ደንግጓል፡፡

ይህ አዋጅ ወጥ ያልነበረውን የካሳ አሰራር ወጥ ለማድረግ መሞከሩ እና ዝቅተኛው የካሳ መጠን በስታንዳርድ
መልኩ ወለል ማስቀመጡ፣ ለተነሽ ምትክ ቦታ መስጠትን በአስገዳጅነት መጥቀሱ፣ በበጎ ጎኑ የሚታይ
ቢሆንም ከመነሻው የራሱ የሆነ መሪ የበላይ ፖሊሲና ስትራቴጅ ሳይኖረው በቀጥታ ወደ ህግ የወረደ፣ ከዚያም
የህገ መንግስቱን አጠቃላይ መንፈስ ያልያዘ እንደሆነ መረዳት የሚቻል ነው፡፡ ይህንን ለመገንዘብ በመጀመሪያ
መልሶ ማልማትን ለማረጋገጥ በቦታው ያሉ አካላትን ከቦታው ከማስለቀቅ ባሻገር አማራጮችንም ማየት ሲገባ
አላየም፡፡

በእርግጥ የህጉ ይዘት በማስነሳት ወቅት ለሚከፈል ካሳ በመሆኑ ሌሎች አማራጮችን ባለማሳየቱ ብዙ ማለት
ባይቻልም፡ ህገመንግስቱ ንብረትን ሲተረጉም ከግንባታ ያለፈ ሲያደርገው በዚህ ህግ ግን ንብረት ማለት
ግንባታና የመሬት ቋሚ ማሻሻያ ብቻ እንደሆነ ከመገደቡም በላይ የሚከፈለው ካሳ ንብረቱን ባለበት ሁኔታ
ስለመተካት እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ቤቱ ባለበት ሁኔታ እንዲተካ የተባለበት መነሻ አዲስና አግልግሎት የሰጠ
አሮጌ ቤት፣ መጠነኛ ጉዳት ያለው፣ የፈራረሰ ወዘተ እኩል አዲስ እንዲገነቡ የሚያስችል ካሳ መስጠት አዲስ
ቤት ባላቸው ዘንድ ቅሬታ ሊፈጥር እንዳይችልና ለሰራው ግንባታ ረጅም ጊዜ በፍሬው የተገለገለ ወገን
ካልተገለገለው ጋር እኩል ሲካስ ከፍትሃዊነት አንጻር እንደ ጉድለት ሊነሳ ስለሚችል ነው፡፡ ነገር ግን አሮጌ ቤት
አሮጌ ሆኖ እንዲተካ ስለሚያስብ ካሳው ግንባታውን በአዲስ መመለስ አያስችልም፡፡

በህጉ አግባብ ግንባታው ለመተካት ሲታሰብ አዲስ ቁስ ሳይሆን አሮጌ ስለመፈለግ፣ ቤት/የስራ ቦታ ከሀብትነት
ሌላ አገልግሎት ስለሆነ ቤቱን/የስራ ቦታውን ባለበት ስፋትና አደረጃጀት መተካት ስለማያስችል ቤቱ ድሮ
ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት ሊሰጥ በሚችል ደረጃ መተካት አያስችልም፡፡ ለምሳሌ 60ሜትር ካሬ ያለው
ባለሁለት ክፍል ሆኖ ከፍተኛ ጉዳት ያለው ነገር ግን አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ቤት በካሳው ማነስ የሚሰራው
ቤት በስፋትና አደረጃጀት ከነባሩ ሲያንስ የነባሩን ቤት ግልጋሎት መስጠት አይችልም፡፡

48
ስለሆነም ቤቱ አዲስ ሆኖ ካሳውን አዲስ ለመተካት የሚያስችለው ከሆነው ወገን ውጭ በልማት ምክንያት
ከነበረበት ሁኔታ ወደ ከፋ የሚገፋበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ንብረት የሚባለው ከግንባታ
ባለፈ የተገነባ መልካም ስም/ቁሳዊነት የሌለውም/ እንደሆነ ህገ መንግስቱ ከሚለው አንጻር የጎደለ፣ አንድ አካል
ከነበረበት ቦታ ሲነሳ ለሚደርስበት የንብረት ጉዳት ሁሉ ካሳ የማግኘት መብት አዋጁ እውቅና አልሰጠውም፡፡

ከንብረት ጉዳት ሌላም ቦታውን ሳይለቅ ጭምር ሊከሰት የሚችል (ለምሳሌ ልማቱ ሲከናወን በይዞታውና ነባሩ
ግንባታው ወጥ አገልግሎት ለመስጠት የማይችል) እንዲዘጋ የሚገደድ፣ ገቢው የሚቀንስ፣ ወጭው የሚበዛ፣
በኋላም ነባሩ ስራውን መቀጠል የማይችል፣ ወጭና የባንክ እዳ ግን መክፈል የሚገደድ /የኢኮኖሚና ማህበራዊ
ጉዳት/ ገቢ መቀነስ ወጭ መጨመር /በህገመንግስቱ ይዘት ማለት ልማት ለህዝብ ተጠቃሚነት እንጅ ለግንባታ
ለውጥ አይደለም የሚለውና ተጎጅ ካለ ለደረሰበት ጉዳት ሁሉ መካስና መልሶ የመቋቋም ድጋፍ ሊደረግለት
እንደሚገባ የተደነገገው ሃሳብ አዋጁ ተገቢውን ትርጉም አልሰጠውም፡፡

በመርህ ደረጃ ልማት ቢቻል ሁሉን ከፍተኛ ተጠቃሚ ማድረግ ሲጠበቅበት፤ ካልተቻለ የተጠቃሚነት ልዩነት
እንዳላቸው ተሳትፎና የመጠቀም አቅም የሚለያይ የመጨረሻው ግን በልማት ተጎጅና ከነበረበት ሁኔታ ወደ
ከፋ ደረጃ የሚያወርድ መሆን የለበትም፡፡ በልማቱ የሚነካ ወገን ከነበረበት እንዳይወርድ የልማቱ ቀጥተኛና
የላቀ ተጠቃሚ በሌላው ወገን ኪሳራ መሆን ስሌለበት የተጎጅውን ወገን ጉዳት መሸፈን ይኖርበታል፡፡ ይህ
መርህ በአዋጁ ላይ አልተንጸባረቀም፡፡

ሌላው ጉዳይ ለመሬት ካሳ አንከፍልም የሚለው ጭብጥ እንዳለ ሆኖ ለዚያ ቦታ እሴት መጨመር የግል
ግንባታዎቹና እንቅስቃሴዎቹ ድርሻ ማን ሊወስደው ይገባል የሚለው መመለስ አለበት፡፡ ይህ ጉዳይ ጎላ ብሎ
የሚወጣው ደግሞ ለምሳሌ አንድ መንገድ ሲሰፋ ፊት ለፊት የነበረው ይዞታ ሲነሳ እሱና መሰሎቹ በጋራ
ለቦታው የፈጠሩት እሴት ተጋሪ/ተጠቃሚ ሳይሆኑ ከጀርባ የነበሩና ለቦታው እሴት ምንም ድርሻ ያልነበራቸው
ወገኖች ወደ ግንባር መጥተው ባልፈጠሩት እሴት መንግስት በሰራው መሰረተ ልማት ጭምር የተገኘውን እሴት
በሙሉ ተጠቃሚና ሲሸጡ ንግድ ቤት ከሆነ ብቻ ከሚከፈል 15% ካፒታል ዋጋ እድገት መጋራት ውጭ
ከፍተኛ ተጠቃሚ ሲሆኑ እሴት መውሰድ ያለበት እሴቱን የፈጠረው መሆን አለበት የሚለውን መርህ እንኳን
ብንተወው አንድን መንገድ ስናለማ ከፍትሃዊነት አንጻር አንዱን ባላፈራው እሴት ከፍተኛ ተጠቃሚ አድርገን
ሌላውን በቦታው የፈጠረውን የዕሴት ድርሻ እንኳን ሳይጋራ ተጎጅ ማድረግ ከአንድ ልማታዊ መንግስት
የሚጠበቅ አይደለም፡፡ ይህ ሃሳብም በህጉ አልተንጸባረቀም፡፡

ለገጠር መሬት ተነሺዎች በመሬት ላይ ላከናወኑት ቋሚ ማሻሻያ በካሳ ሊታሰብላቸው መብት ሲሰጥ በከተማ
ከግንባታ ውጭ ለተከናወነ የመሬት ማሻሻያ (ለምሳሌ የጎርፍ መከላከል ወዘተ) የካሳ እውቅና አይሰጥም፡፡
አርሶ አደሮች እርሻቸው ሲወሰድ ለጊዜው የሚከሰትን ገቢ ማጣትን ለተወሰነ ጊዜ ለመደገፍ በሚል የ10 ዓመት
ምርት የገበያ ዋጋ ሂሳብ የመፈናቀያ ካሳ ሲፈቅድ በከተማ ለሚከናወን የከተማ ግብርና ለምሳሌ የወተት ላም፤
ዶሮ እርባታ ወዘተ ስራና ገቢ መቋረጥ ህጉ እውቅና አይሰጥም፡፡

49
በልማቱ ምክንያት ለሚከሰት የከተማ ቢዝነስ መቋረጥና ገቢ መቀነስ፣ ለአርሶ-አደሩ እንደተጠበቀው ማለትም
አርሶ-አደሩ ከተሜ ሁኖ (ለከተማ ስራ ራሱን አዘጋጅቶ የከተማ ስራ ፈጥሮ) ተቀጥሮ እርሻው በመወሰዱ
የሚያጣውን ገቢ ማግኘት እስኪጀምር በራሱ ላይ ለውጡን ለማከናወን የሚወስድበትን ጊዜ ግምት ውስጥ
በማስገባት በዚህ የዝግጅት ጊዜ ገቢው በመቋረጡ ጉዳት እንዳያገኘው 10 ዓመት የዕርሻውን ውጤት
እንዲያገኝ የተደነገገው ይበቃል/አይበቃም፣ ምን አይነት አርሶ-አደር ነው በዚህ መልኩ በተቀመጠው የጊዜ
ማዕቀፍ ውስጥ ተለውጦ የከተማ ስራና ገቢ መፍጠር የሚችለው የሚለውን በጥናት መለያየትና የድጋፍ
ልዩነት መደንገጉ አስፈላጊ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ከተማም መለወጥ ያለበት ድሃው ነው፤ ለድሃ መኖሪያ
ቤቱ ሁሉ ነገሩ ነው፤ ገቢው፣ የስራው ቦታ፣ መዝናኛው ነው፡፡

ከቦታው ሲነሳ ገቢው ሊቀንስ/ወጭው ሊበዛ እንደሚችል በተለይ ከባቢያዊ ጥገኝነት ያላቸው አገልግሎት
መስጫዎች፣ መደበኛ ባልሆነ ቢዝነስና ጥቃቅን ስራ የተሰማሩና ጉልበታቸውን በሚሸጡ ወገኖች ዘንድ
የሚከሰት እንደመሆኑ መጠን እስከመቸ በምን መልክ ቢደገፍ ገቢያቸው ሊቀጥል እንደሚችል ተጠንቶ መሰል
የድጋፍ ድንጋጌ ማካተት ሲገባው ያየው ነገር የለም፡፡

የከተማ ኗሪ የሆነ ወገን ከቦታው ሲነሳ ስለሚደርስበት ጉዳት ያለው እሳቤ በመጠለያ ማጣት ብቻ የታጠረ
ነው፡፡ ድጋፍ ሲልም ቤት እስኪሰሩ አመት ቢወስድባቸው ቤት እንዲከራዩ በሚለው የተወሰነ ነው፡፡ ቤት
በአንድ አመት ሊጠናቀቅ ይችላል አይችልም በመርህ ክርክር መግባት ብዙም የሚጠቅም ባይሆንም
ከተጨባጭ ሁኔታው ግን ባለን የኮንስትራክሽን ዘርፍ አሰራር፣ በመልሶ መስፈሪያዎች በምናቀርበው የመሰረተ
ልማት ፍጥነትና የፋይናንስ አቅርቦት ሲመዘን እውን እየሆነ ያለ አደለም፡፡

ከታች የምንጠቅሰው የሊዝ ህግ እንኳን የመኖሪያ ግንባታ መጀመሪያን /ለዲዛይን ስራና ማስፈቀድ/ 6ወር
ሲሰጥ የግንበታ ማጠናቀቅያ የሚያስቀምጠው ገደብ 24 ወር ነው፡፡ የቤት ኪራይ በመክፈል ማስነሳት ለልማቱ
መፍጠን ድርሻ ቢኖረውም ተነሺዎችን ሁለት ጊዜ እንዲፈናቀሉ የሚያደርግና የነሱን ችግር ያላገናዘበ መሆኑ
አሁንም የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡

ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው መሪ ሃሳቦች ካካተቱት ሌሎች ማዕቀፎች ውስጥ የከተማ ልማትና የከተማ መሬት
ልማትና ማኔጅመንት ፖሊሲዎች እናገኛለን፡፡

የከተማ ልማት ፖሊሲ

የፖሊሲው ክፍል 2.4/4 የከተማ ልማት ስራ ማዕከሉ ድህነትን መቀነስ እንደሆነ በማያሻማ መንገድ
አስቀምጦታል፡፡ ክፍል 4.3.3 ላይ ደግሞ በከተማ አስተዳደርና በማህበራት የሚከናወኑ የቁጠባ ቤቶች ግንባታ
ያረጁ ቤቶችና መንደሮችን እየተካ የሚያድስና ከተማውን የሚያሻሽል መሆን እንዳለበት፣ ግንባታው በዋናነት
በከተማው ውስጥ ባሉ ክፍት ቦታዎችና ያረጁ ሰፈሮች በማፍረስ የሚሰራ እንደሚሆን፡፡

የፖሊሲ ሰነዱ ህጋዊ ቤት ለፈረሰባቸው በካሳ ህጉ መሰረት መካስ፤ ምትክ መሬት ወይንም የቁጠባ ቤት ግዥ
ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚገባም ይገልጻል፡፡ የማይፈርሱና ደረጃቸውን ያልጠበቁ ቤቶች አካባቢያቸውን
50
የሚያሻሽል መሰረተ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት በመዘርጋት ባለቤቶች ቤታቸውን እንዲያሻሽሉ
ማበረታታት፤ ይህ ካልተቻለ ደግሞ በሂደት በቁጠባ ቤት መተካት እንደሚገባም ያስቀምጣል፡፡

የከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ፖሊሲ

የፖሊሲ ሰነዱ ክፍል 2.1.2.6 በከተሞች ያረጀውና የደቀቀው ክፍል 60% በላይ እንደሆነ፣ በነዚህ ቤቶች
ከሚኖረው 70% ደግሞ ከድህነት ወለል በታች የሚኖር በመሆኑ መልሶ ማልማቱ በመሰረታዊነት ድህነትን
ለማስወገድ የሚረዳ እንቅስቃሴ አንዱ አካል እንደ መሆኑ መጠን የነዋሪውን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፣
የከተሞችን ፊዚካል ገጽታ በመቀየር ነዋሪው የከተሞች የመኖሪያ አካባቢ እንዲኖረው በማድረግና የመሬት
አቅርቦት አቅማቸውን በማጠናከር ረገድ ሰፊ ድርሻ ይኖረዋል ይላል፡፡ የሰነዱ ክፍል 6.1.2.6 የከተማ ማደሱ
ዓላማ ያረጁ የደቀቁና ከአገልግሎት በታች የሆኑ በከተሞች መሃል የሚገኙ አካባቢዎችን መልሶ በማልማት
ገጽታቸውን በመቀየር፣ በተቻለ መጠን የነዋሪውን ትስስርና ተጠቃሚነት ያረጋገጠ፣ የተመቻቸ እና ጤናማ
የመኖሪያና የስራ አካባቢ ለመፍጠር የሚከናወን መሆኑ አፅንኦት ሰጥቶታል፡፡

በፖሊሲው ላይ ደግሞ መልሶ ማደሱ

 ነዋሪውን ያሳተፈ፣ በተቻለ መጠን ትስስሩን የጠበቀ ተጠቃሚነታቸውን ያረጋገጠ


 ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀትና ግልጽ የአሰራር ስርአት የተበጀለት
 ፕሮጀክቶች በምክር ቤት እንዲጸድቁ ህዝቡ እንዲያውቅና በባለቤትነት እንዲሳተፍ
 የፋይናንስና የግሉ ሴክተር ተሳትፎ አማራጭ ስትራቴጅ ተቀይሶ እንዲተገበር ያመላክታል፡፡

እነዚህ ሰነዶች ከካሳ ህጉ ይልቅ ስለ መልሶ ማልማት ሰፋ ያለ ሃሳብ የያዙ ናቸው፡፡ በመነሻም ጥሩ እይታ
ያስቀመጡ እንደሆነ ለመረዳት ይቻላል፡፡ የደቀቁ አካባቢዎች መልሰው መልማት እንዳለባቸው የህገመንግስቱን
ሃሳብ ይጋራሉ፡፡ በነዚህ በደቀቁ ሰፈሮች የሚኖረው ድሃው ማህበረሰብ እንደሆነ እውቅና ይሰጣሉ፡፡ በመልሶ
ልማት ወቅት በቦታው ያሉ ወገኖች በሂደቱ ተሳታፊ እንዲሆኑም መርህ አስቀምጠዋል፡፡

ይሁን እንጅ እነዚህ ፖሊሲዎችም ቢሆኑ በመፈናቀል ስለሚደርስ የኢኮኖሚ ጉዳት ካሳ ያነሱት ነገር የለም፡፡
የከተማ ልማት ሂደት ያረጀና የደቀቀ የከተማውን ክፍል የሚያሻሽል መሆን እንዳለበት በአስገዳጅነት
ሲያስቀምጥ ለመልሶ ማልማት በሚወሰኑ ቦታዎች ላይ ያሉት ወገኖች ድሆች እንደሆኑና መልሶ ማልማቱ
የማህበረሰቡን ህይወት በመቀየር ሰፊ ሚና እንደሚኖረው ሲያመላክት ሁኔታው አስገዳጅ አለማድረጉ የኗሪው
ህይወት ለውጥ እንደ ልማቱ አይቀሬ ውጤት መመልከቱ የልማቱ ቅኝት በግድ ይዞት ካልሰራበት የሕይወት
ለውጡ እውን እንደማይሆን ከዚያ በባሰም በተቃራኒው ድሃውን ወደ ባሰ ድህነት ሊገፋው እንደሚችል
ያልተገነዘበ አተያይ መሆኑ መረዳት ይቻላል፡፡

በእርግጥ ልማት ይምጣ እንጅ በተዘዋዋሪ በተራዘመ ሂደት በሚንጠባጠብ (trickle down) መልኩ ተጎጅውም
ሊጠቀም እንደሚችል የሚከራከሩ፤ የተወሰኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች በማበልፀግ ለሌሎች ይተርፋል የሚል የሊብራል

51
አስተሳሰብ አቀንቃኞች ሳይቀር በልማት የሚነሳ ወገንን በተሻለ ደረጃ ተጠቃሚ ማድረግ ባይቻል ከነበረበት ሁኔታ
መውረድ የለበትም የሚለውን ልማታዊ መርህ ይቀበላሉ፡፡ መቀበል ብቻም ሳይሆን እንደመርህ በሁሉም ሀገር በመሰል
ሁኔታ በስራ ላይ እንዲውል በዓለም ባንክ ፖሊሲ ሰነድ ጭምር ያካተቱት ጉዳይ ነው፡፡

ሊብራል አራማጆች እንኳን የተቀበሉት ይህ መርህ በልማታዊ መንግስት ሲመዘን በከተማው 60% ቦታ ላይ ያለን 70%
ዝቅተኛ ኑሮ ያለውን ማህበረሰብ ወደ ከፋ ሁኔታ የሚገፋ ልማት ከሆነ ልማቱ ለማን የወገነ ነው? አካሄዱ ከመንግስት
ባህሪ ጋር የሚሄድ ነወይ? በሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ለህዝብ ጥቅም ሲባል ቦታን ማስለቀቅ እንደሚቻል የሚጠቅሰው
የህዝብ ተጠቃሚነት ማንን የሚመለከት ነው የሚለው ህገመንግስቱን ያገናዘበና የመንግስትን ባህሪ የሚገልጽ ፖሊስና
የህግ ማዕቀፍ መኖር እንዳለበት ያስገነዝባል፡፡

ስለኢኮኖሚ ጉዳት ካሳ፣ በቦታ ላይ ስለተፈጠረ እሴት መጋራትና ስለ መልሶ ማቋቋም በሚመለከት እነዚህ
ፖሊሲዎችም ህገመንግስቱንና መርህን ያገናዘበ አቅጣጫ በማስቀመጥ ረገድ እጥረት አለባቸው፡፡ ከተማ መልሶ
ማልማቱም የት ቦታ እና መቼ መከናወን እንዳለበት እንዲሁም በምን አማራጭ ስልት እንደሚመራ ማመላከት
ላይ ጉድለት ይታይባቸዋል፡፡ በእርግጥ የመሬት ፖሊሲው ስለተቋማዊ አደረጃጀት፣ ስለአሰራር ስርአት፣
ስለፋይናንስና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ጉዳይ አቅጣጫ በማስቀመጡ የስራውን ልዩ ባህሪና ክብደት እውቅና
እንደሰጠ ቢያመላክትም ይህንን እውን ለማድረግ ከፖሊሲው ቀጥሎ በወጣ የሊዝ ህግ ማዕቀፍ ወይንም በሌላ
ህግ ባለመሸፈኑ እየተተገበረ አይደለም፡፡

የከተማ መሬት በሊዝ ለማስተዳደር የተደነገገው አዋጅ ቁጥር 721/2004

በመጨረሻ ከጉዳዩ ጋር ተዛምዶ ያለው ሌላው የህግ ማዕቀፍ የሊዝ ህግ ሲሆን አዋጅ ቁጥር 721/2004 ከተማ
መልሶ ማልማትን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን አካቷል፡፡

 ስታንዳርድ ወጥቶ ሽንሻኖ ሲስተካከል ለተጨማሪ መሬት ሊዝ ይከለል ሲል የአዋጁ አንቀጽ 6/2/ለ
እና 6/6 ያለው ነባርና ሊዝ ሲቀላቀል ሁሉም ወደ ሊዝ ይገባል የሚለው አተረጓጎም ስለ መልሶ
ማልማት እንድምታ አላቸው፡፡
 አንቀፅ 12/3 የልማት ተነሺው ተከራይ ከሆነ ምትክ ቤት መስጠት ካልተቻለ በሊዝ መነሻ ዋጋ
የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ የማግኘት መብት ይኖረዋል፤ አዲስ አበባ ሲሆን የጋራ ቤት ቅድሚያ ግዥ
መብት ይፈቅዳል፡፡ ተነሺው የመንግስት ንግድ ቤት ተከራይ ከሆነ ክልሉ/ከተማው በሚወስነው
መሰረት ይስተናገዳል ይላል፡፡
 አንቀጽ 23 ላይ ግንባታ ማጠናቀቅያ እንደ ፕሮጀክቱ ግዝፈት ከ24 ወር እስከ 48 ወራት ገደብ
ያስቀምጣል፡፡
 የሊዝ ገቢውም 90% ለመሰረተ ልማትና ቤት ስራ እንዲውል ደንግጓል፡፡

ይህ አዋጅ ከከተማ መልሶ ማልማት አንጻር ከነባሮቹ የሊዝ አዋጆች ጋር ሲነጻጸር ለተነሺዎች መልሶ መስፈሪያ
ቦታና ቤት አሰጣጥ ዘርዘር ያለ ሃሳብ በመያዙ የተሻለ ነው፡፡ በተለይ የመንግስት ቤት በመከራየት በንግድ ስራ
52
የተሰማሩ ወገኖች በካሳ ህጉ ያልነበረ ተከራዮቹ የልማቱ አካል እንዲሆኑ መሬት በሊዝ መነሻ የማግኘት መብት
መፍቀዱ በጥሩ ርቀት መሄዱ የሚደነቅ ነው፡፡

ነገር ግን ለልማት የቦታ ማቅረብያው ዘዴ በወሳኝነት ጨረታ እንዲሆንና ቦታው ለጨረታ ሲቀርብም የለማና
ከይገባኛል የጸዳ መሆን እንዳለበት የደነገገው ሃሳብ አልሚዎች ፈጥነው ወደ ግንባታ እንዲገቡ የሚያስችል እና
ከተሞች መሬት በማስተላለፍ ማግኘት ያለባቸውን እንዲያገኙ የሚረዳ ቢሆንም መልሶ ከማልማት አንጻር
ሲታይ ግን ግንባታ ያለበት ቦታን በሊዝ ድርድር ለአልሚ ስለመስጠትና አልሚዎች በቦታው ያሉ ወገኖችን
እንዲክሱ፣ መልሶ መስፈሪያ ቤት እንዲሰሩ፣ በልማቱ እንዲያካትቷቸው ወዘተ የማድረግ እድልን ያጠበበ
ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ነባር ወይንም ቀድመው በሊዝ የወሰዱትን ቦታቸውን ለማልማት፤ ወይንም ቢዝነሳቸውን
ለማስፋት የተወሰነ ቦታ የሚፈልጉ ወገኖች ከቦታቸው ኩታ ገጠም ያለን ቦታ በቀጥታ በድርድር በሊዝ
ሊወስዱ የሚችሉበት በር የዘጋ በመሆኑ ለመልሶ ማልማቱ ፍጥነትና ጥራት የራሱ አሉታዊ ጎን አለው፡፡
በእርግጥ ሽንሻኖ ተስተካክሎ የተወሰነ መሬት ቢጨመር ለተጨማሪው ሊዝ እንዲከፈል የሚደነግግ አንቀጽ
ቢኖረውም ወረድ ብሎ ደግሞ ሊዝና ነባር ሲቀላቀል የፕሮፖርሽን አሰራር ሳይሆን ሁሉም ሊዝ መግባት
እንዳለበት ስለሚያስገድድ የሚተገበር ድንጋጌ አይደለም፡፡

አዋጁ በአልሚዎች ላይ ስለግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቅያ መደንገጉ ቦታ ለአልሚ ከተላለፈ በኋላ እንዲለማ
የሚገፋ መሆኑ በበጎ ጎን መጥቀሱ እንደተጠበቀ ሆኖ ቦታ ከነባር ግንባታ መጽዳት ተጀምሮ የሚጠናቀቅበት
እና ነጻ ከሆነ በኋላ እስከ ምን ጊዜ ድረስ ለአልሚ መተላለፍ እንዳለበት ገደብ ባለማስቀመጡ ከተሞች
የተጓተተና የተበጣጠሰ ቦታ ነጻ ማድረግ ስራ እንዲያከናውኑ፣ ቦታ አፍርሰው ለአልሚ ሳያስተላልፉ ጭምር
ሲቆዩ፣ ለአልሚ ከተላለፈ በኋላም አልሚውን በወቅቱ እንዲገነባ ባያደርጉ ምን ሊከተል እንደሚችል ግልጽ
የተጠያቂነት ግዴታ በከተሞች ላይ ባለመጣሉ የተጓተተና የተበጣጠሰ የቦታ ማጽዳት ስራና የጸዱ ቦታዎች
ያለልማት መቆየት በሌሎች ቦታዎች መልሶ ማልማት ስራ ሲታሰብ የፈረሰው ሳይገባ ለምን የሚል የብሶትና
ተገቢነት ያለው ጥያቄ እንዲነሳ እያደረገ ይገኛል፡፡

3.1.3. ሀገራዊ የመልሶ ማልማት አስቻይ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶች


ከህግ ማዕቀፍ ወጣ ብለን ሌሎች የመልሶ ማልማት ሀገራዊ ነባራዊ አስቻይ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶችን
ስንመለከት ከላይ እንደተጠቀሰው ነባሩ ግንባታ በደከመ ቁስ የተሰራ፣ የማፍረስ ወጭው አነስተኛ የሆነ፣ በዚህ
ላይ ቀጥታ ካሳ ክፍያ ማከናወን ውስጥ ሳይገባ መፍረስ የሚችለው የቀበሌ ቤት ስፋት በነባሩ የከተማ ክፍል
ከፍተኛ መሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከሀገሪቱ ኢኮኖሚ ማደግ ጋር በተያያዘ እየተፈጠረ ያለው የኢኮኖሚ አቅምና
መነቃቃት፣ የይቻላል መንፈስ፣ ከድህነት ጋር ተላምዶ ከመኖር ለመፋታት የመወሰንና የተፈጠረው የመልማት
ጉጉት፣ በቦታዎቹ ያለው ማህበራዊ ሁኔታ ባለመውደቁ ምክንያት ማዕከላዊው ቦታ ፍላጎት ከፍተኛ የሆነ፣

53
በአንጻራዊነትም ነባሩ የከተማ ክፍል በዙሪያው የተሻለ መሰረተ ልማት ስላለው የቦታዎቹ ተፈላጊነት ስላልቀነሰ
መልሶ ለማልማት እንደ ከፍተኛ እድል የሚወሰዱ ናቸው፡፡
በሌላ መልኩ ደግሞ ለውጥ ቢኖርም ከተሞችም ሆነ ኗሪዎቹ አሁንም በከፋ የኢኮኖሚ ድህነት ውስጥ የሚገኙ
በመሆኑ፣ የፋይናንስ አቅም ውስንነት፣ የፋይናንስ/የካፒታል ገበያው ለመሰል የረጅም ጊዜ ልማት ፋይናንስ አማራጭ
የሰፋ አለመሆን ልማቱን ይፈትናል፡፡ በከተሞች ያለው የመፈጸም አቅም ውሱንነት፣ በመሬት ህጎቻችን ላይ ግንባታ
ያረፈበት ነባር ይዞታም ሆነ ሊዝ በገበያ መግባት እንደሚችል በዚህም ማልማት ያቃተው መብቱን አዛውሮ አቅም
ያለው ሊያለማ የሚችልበት እድል ባይዘጋም ለልማት በከተማ መሀል ያለው የግል ይዞታ በቀበሌ ቤት መታጠር አንድ
ግቢ ሳይቀር የሚጋራና መልማት የማይችልበት/ቢችል እንኳን ተጠቃሚነቱ የተገደበ በመሆኑ የማይበረታታበት፣ እንደ
አጠቃላይ በከተማ ይባስ ደግሞ በመሬት ዘርፍ ውስጥ የአመራር አለመረጋጋት፣ የመወሰን ብቃት ጉድለት ደግሞ
ከአጠቃላይ የከተሞች የማስፈፀም ዓቅም አኳያ ልማቱን እንዳይፈጥን ያደርጉታል፡፡ ከሁሉም በላይ በመልሶ ማልማት
በተወሰኑ ቦታዎች ያሉ ወገኖች አያያዝ ወጥነት መጓደል፣ ከላይ በህግ ማዕቀፉ እንደተጠቀሰው ሁለንተናዊ ጉዳታቸውን
ያገናዘበ ካሳና መልሶ ማቋቋም ድጋፍ አለመደረጉ ልማቱን ለማስፋት ትልቅ ተግዳሮቶች ናቸው፡፡

3.1.4. አጠቃላይ ማዕቀፍ እንደምታ


በኢትዮጵያ የከተሞች ጠቅላላ ወይንም የተወሰነ ክፍል ውድቀት የተከሰተበት ምክንያት
የኢትዩጵያ የከተሜነት ደረጃ ከ20% ያልበለጠ እደሆነ ስናይ ስለ ከተማ መልሶ ማልማት ማሰብ ወቅቱን
ያልጠበቀ አጀንዳ ሆኖ ሊታይ የሚችልበት መነሻ ያለ ቢመስልም፤ ከተማ ተብለው የሚፈረጁት መንደሮች
ከተማ ለመባል ብዙ የሚቀራቸው፤ ከተማ የሚባለውን መስፈርት ለማሟላት ያላቸው ግንባታና መሰረተ
ልማት ሲመዘን በእጅጉ ወደ ኋላ የቀሩ በመሆናቸው ሁሉም በሚባል ደረጃ እንደ አዲስ መገንባት ያለባቸው
እንደሆኑ ሲታይ የመልሶ ማልማቱ ስራ ወቅታዊ ያደርገዋል፡፡

ከ80% በላይ ቤቶች በጭቃና እንጨት የተሰሩ፤ የመሰረተ ልማት አቅርቦታቸው ከግማሽ በታች የሆኑ እንደሆነ
ስለሚያሳይ የከተሞቹ አገነባብ በአመዛኙ ያለ ፕላን፣ በነበረው ኋላ ቀርነት የተነሳ የግንባታ ዘርፉ ባለመዳበሩ
የግንባታ ደረጃው የወረደ፣ ኢኮኖሚውና የግንባታ ቁሱ ደካማ የሆነ፤ በከተሞች ያለው አብዛኛው ግንባታ
ደረጃውን ያልጠበቀና ፈርሶ መሰራት ያለበት በመሆኑ ነው፡፡ ከተሞች ነባሩ ክፍል በአግባቡ ሳይጠቀሙበት፣
ያለውን ውሱን መሰረተ ልማት በሚጠበቀው ደረጃ ሳይገለገሉበት ወደ ውጭ እየተለጠጡ እንዳሉና ከወጭም
ሆኖ ከአስተዳደር ዘላቂነት አንጻር ከተማ መልሶ ማልማት ጉዳይ የከተሞች ወሳኝ ወቅታዊ አጀንዳ መሆኑን
ያረጋግጣል፡፡

ለከተሞች የተወሰነ ክፍል መውደቅና አለመታደስ በእኛ ሁኔታ እንደ አውሮፓ ከኢኮኖሚ ለውጥና እንደ
አብዛኛው የአፍሪካ ክፍል ከቅኝ ግዛት መከፋፈል በተለየ የራሳቸው መልክ ያላቸውና በተወሰነ ከኤሲያ ጋር
የሚመሳሰል ከገጠር ወደ ከተማ ፍልሰት መነሻን የሚጠቁሙ ናቸው፡፡ ሀገር በቀል /ከተሞቹ ለጦር ካምፕነት
ሲመሰረቱ ንጉሱ ለጦር አዛዦችና መሪዎች በሰፈር ቦታ ሲመሩ እነሱ ደግሞ ቀጥለው በዙሪያቸው ለጠባቂና
ለሰራተኞቻቸው ቦታ የተወሰነ የኪራይ ቤት በመስራት የሰፈር ስብስብ ሆኖ ወደ ከተማ ያደጉ ናቸው፡፡

54
እንደ ባህሩ ዘውዴ ጥናት ከሆነ ደግሞ በጣልያን ወረራ ወቅት ግንባታ ታግዶ የነበረ ሲሆን ጣልያን ሲወጣ
ከገጠር ወደ ከተማ ከነበረው ከፍተኛ ፍልሰት ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ የሆነ የቤት እጥረት በመከሰቱ ያንን ችግር
እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ የመሬት ከበርቴዎች በዝቀተኛ ቁስ ገቢያቸውን የሚያሳድግላቸው የኪራይ
ቤት በስፋት ገንብተው እንዳቀረቡ ያስረዳል፡፡

ያለ ፕላን ወደ ከተማነት ማደግ፣ እንደየ ኑሮ ደረጃ የአሰፋፈር መለያየት (Segregation)፣ የተሰሩበት ቁሥ


የወረደ መሆን / በደርግ ጊዜ ደግሞ ቀበሌ መራሽ ሰፈራ በተወሰነም የፖለቲካ ትኩሳት እያየ በህገ ወጥ ሰፈራና
ከገጠር ወደ ከተማ መካተት፣ ያለ ፕላን የተከናወነ የወረደ ሰፈራና በሂደት ያለ ጥገና/የተወረሱ ቤቶች ኪራይ
ማነስ የሚጠግን አካል አለመኖር፤ በመሀል ያሉ የግል ይዞታዎች በፕሎት ደረጃ ከቀበሌ ቤት ጋር የተዳበሉ
መሆንና አዲስ ለመገንባት ቀርቶ ለማደስ የማይቻልበት አስተዳደር ደብተር የመስጠት አካሄድ፣ ይዞታዎች
ስፋትና ቅርጽ በፕላን የተቀመጠውን የልማት ደረጃ ማሰራት አለመቻል፣ ዙሪያው በተወረሱ ቤቶች ስለታሰረ
ባለይዞታዎች ቢያድሱም ተጠቃሚ እንማይሆኑ መታየቱ፣ የግል ይዞታ ያለው ወገንም የካፒታል አቅም ገደብ
ምክንያት ለመገንባት አለመቻል ነበሩ፡፡ ከከተሞች አስተዳዳር የገቢ አቅም ውሱንነት ጋር በተያያዘ መሰረተ
ልማት ለማስፋፋትና ባለይዞታዎች እንዲገነቡ ማበረታታት አለመቻል ከመውደቅ ጋር የተያያዘ ነው፡፡

የመልሶ ማልማት ፍላጎቱ በገበያ ብቻ የማይሳካ ስለመሆኑ


በብዙ ሀገራት እንደሚስተዋለው ገበያው ተፈላጊነቱ የወደቀውን የከተማ ክፍል መልሶ ማደስ የማይችልበት
ምክንያት ሲታይ የኪራይ ጣሪያና የፕላን ክልከላዎች አልሚዎችን አያበረታታም፡፡ ተስፈኝነትና የፍላጎት
ወዣቂነት፣ ሳያለሙ ሌሎች እንዲያለሙና የያዙት ቦታ ዋጋው ጨምሮ ተጠቃሚ ለመሆን መፈለግ ማለትም
ሳይለፉ ሌሎች በለፉት ለመጠቀም ማድፈጥ፣ የፍላጎቶች ግጭት ጡዘት፣ አንዱ ማልማት ሲፈልግ ሌላው
ፍላጎቴ ይጎዳል በሚል የመከላከል ክፍተቶች በመኖራቸው እነዚህ ሁኔታዎች ገበያ የሚፈታቸው አይደሉም፡፡

በእኛ ሁኔታ ምንጩ እንደ ሌሎች ሀገራት ተስፈኝነትና መዋዠቅ ሲስተዋሉ ለየት ባለ ሁኔታ ደግሞ የይዞታ
መቀላቀል ለምሳሌ የቀበሌና የግል ቤት ግቢ መጋራት፣ የይዞታዎች ስፋትና ቅርጽ ለልማት ምቹ አለመሆን (ያለ
ፕላን መሰራቱ ይዞታው ቅርጽና ስፋት ከፍተኛ ግንባታ ለማሳረፍ የማይመችና የማይበቃ መሆን) ናቸው፡፡
በሌሎች ሀገራት ያለው የመንግስት ጣልቃ ገብነት መነሻ የገበያው ጉድለትና ፍትሃዊነት ሲሆን በእኛ ሀገር
ከቴክኒካዊ ጉዳዮቹ ይበልጥ የልማት ፍልስፍና ፖሊሲው የመንግስት ሰፊና ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዲኖር
ያስገድዳል፡፡

ከመንግስት ባህሪ አንጻር ፍትሃዊ የልማት ክፍፍል ለማረጋገጥ ሲባል መንግስት በዚህ ዘርፍ መግባቱ የግድ
ነው፡፡ ሌላው መልክ መንግስት ዘርፈ ብዙ ባለድርሻ ስለሆነ ይህም በመሬት ባለቤትነት፣ በተወረሱ ቤቶች
አስተዳዳሪነትና የገበያ ጉድለት አቃኝነቱ ሲታይ በእኛ ሁኔታ ለመልሶ ማልማቱ የመንግስት ሚና ከፍተኛ
ነው፡፡ መንግስት ሁሉን መሸከም አለበት ወይንስ የተወሰነ የህግና የትግበራ ድጋፍ ሰጥቶ ሌሎች ባለድርሻዎችን
ለማሳተፍ መግፋት አለበት የሚለውን በተገቢው ታይቶ አቋም ሊወሰድበት የሚገባ ነው፡፡

55
ስለ ከተማ ዕድሳት የፖሊሲና የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ
ቀደም ብሎ እንደታየው በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ መልሶ ልማት ወሳኝ የመሆኑን ያክል ራሱን የቻለ
የፖሊሲም ሆነ የህግ ማዕቀፍ የለውም፡፡ ቢሆንም የ1987 ህገ መንግሰት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት እንደሰጠ
መወሰድ የሚቻል ነው፡፡
 ለዜጎች ንጹህና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት ሲሰጥ የወደቁ የከተማ ክፍሎች መታደስ
እንዳለባቸው አስገዳጅ ነው፡፡
 በሂደቱ ለሚነካ ሰው ለንብረት ካሳ እና የመልሶ መቋቋም ድጋፍ ሊደረግለት እንደሚገባም ያስረዳል፡፡
 የልማት ዓላማም የግንባታ ለውጥ ማምጣት ሳይሆን የዜጎች ተጠቃሚነት እንደሆነ በማይሻማ ሁኔታ
ያስቀመጠ ነው፡፡
 መሬትን የህዝብና የመንግስት ማድረጉም ለልማት ትልቅ እድል ነው፡፡ ከተማን መልሶ ማልማት
የመሬት አስተዳደር ጉዳይም ስለሆነ በጉዳዩ ህግ የማውጣት ድርሻ የፌደራል መንግሰት ስለሆነ እስከ
አሁንም ድረስ ስለጉዳዩ ወጥና ራሱን የቻለ ህግ ላለመውጣቱ ተወቃሹ የፊደራል መንግስት ነው፡፡

ከጉዳዩ ጋር ቀረቤታ ያለው ቀዳሚ ህግ አዋጅ ቁጥር 455/1997 ሲሆን አዋጁ በቦታ ማስለቀቅ እና ካሳ ላይ
ያተኮረ በመሆኑ መልሶ ማልማት በጥቅል አለመያዙ እንደተበቀ ሆኖ ዘግይቶ በ1997 መውጣቱ ለጉዳዩ
የተሰጠውን ትኩረትና የነበረንን ግንዛቤ አነስተኛነት ሲያሳይ፡
₋ ወጥነት ያልነበረውን የካሳ አሰራር ወጥ ለማድረግ መሞከሩ እና ዝቅተኛው ካሳ መጠን በስታንዳርድ
መልኩ ወለል ማስቀመጡ፤ ለተነሽ ምትክ ቦታ መስጠትን በአስገዳጅነት መጥቀሱ፤ በበጎ የሚታይ ነው፡፡
₋ ከመነሻው የራሱ የሆነ መሪ የበላይ ፖሊሲና ስትራቴጅ ሳይኖረው በቀጥታ ወደ ህግ የወረደ፤ ከዚያም ስለ
ልማት ዓላማ፤ ሰለ ንብረት፤ አንድ ሰው በልማት ሲነካ ሊከፈለው ስለሚገባ የጉዳት ካሳ፣ ስለ መልሶ
ማቋቋምና በሙሉ የህገመንግስቱን አጠቃላይ መንፈስ ያልያዘ እንደሆነ መረዳት የሚቻል ነው፡፡
₋ ትኩረቱ የማህበረሰብ ልማት ይዘት ሳይሆን መሬት ማስተዳደር፤ ልማት ግንባታ እንደሆነ የሚያይ ነው፡፡
ንብረት ማለት ግንባታና የመሬት ቋሚ ማሻሻያ ብቻ እንደሆነ ከመገደቡም በላይ የሚከፈለው ካሳ
ንብረቱን ባለበት ሁኔታ ለመተካት እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ አንድ አካል ከነበረበት ቦታ ሲነሳ ለሚደርስበት
ጉዳት ካሳ የማግኘት መብት በህጉ አልተሸፈነም፡፡
₋ ለመሬት ካሳ አንከፍልም የሚለው ጭብጥ እንዳለ ሆኖ ለዚያ ቦታ እሴት መጨመር የግል ግንባታዎቹና
እንቅስቃሴዎቹ ድርሻን ማን ሊወስደው ይገባል የሚለውን አልመለሰም በመሆኑም ለቦታው የፈጠሩት
እሴት ተጋሪ/ተጠቃሚ ሳይሆኑ ሲነሱ ለቦታው እሴት ምንም ድርሻ ያልነበራቸው ወገኖች ተጠቃሚ
የሚያደርግ ከፍትሃዊነት አንጻር ሲታይ ከአንድ ልማታዊ መንግስት የሚጠበቅ አይደለም፡፡
₋ አርሶ አደሮች እርሻቸው ሲወሰድ ለጊዜው የሚከሰት የገቢ ማጣት ለተወሰነ ጊዜ ለመደገፍ በሚል የ10
ዓመት ሰብል ሂሳብ ሲፈቅድ በከተማ ለሚከናወን የከተማ ግብርና ቢዝነስ መቋረጥና ገቢ መቀነስና ወጭ

56
መጨመር ያየው ነገር የለም፡፡ የከተማ ኗሪ የሆነ ወገን ከቦታው ሲነሳ ስለሚደርስበት ጉዳት ያለው እሳቤ
በመጠለያ ማጣት ብቻ የታጠረ ነው፡፡ ድጋፍ ሲልም ቤት እስኪሰሩ አመት ቢወስድባቸው ቤት
እንዲከራዩ በሚለው የተወሰነ ነው፡፡ ቤት በአንድ አመት ሊጠናቀቅ ይችላል አይችልም በመርህ ክርክር
መግባት ባያስፈልግም ከተጨባጭ ሁኔታው በመነሳት ባለን የኮንስትራክሽን ዘርፍ አሰራር፤ በመልሶ
መስፈሪያዎች በምናቀርበው የመሰረተ ልማት ፍጥነትና የፋይናንስ አቅርቦት ሲመዘን እውን
የሚሆን/እየሆነ ያለ አደለም፡፡ ከታች የምንጠቅሰው የሊዝ ህግ እንኳን የመኖሪያ ግንባታ መጀመሪያን
6ወር ሲሰጥ/ለዲዛን ስራና ማስፈቀድ/ የግንባታ ማጠናቀቅያ የሚያስቀምጠው ገደብ 24 ወር ነው፡፡
የቤት ኪራይ በመክፈል ማስነሳት ለልማቱ መፍጠን ድርሻ ቢኖረውም ተነሺዎችን ሁለት ጊዜ
እንዲፈናቀሉ የሚያደርግና የነሱን ችግር ያላገናዘበ መሆኑ አሁንም የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡

ስለጉዳዩ ሰፋ ያለ ሽፋን የሰጡት ሌሎች ማዕቀፎች ውስጥ የከተማ ልማት፤ የከተማ መሬት ልማትና
ማኔጅመንት ፖሊሲዎች ይገኛሉ፡፡ ፖሊሲዎቹ ከካሳ ህጉ ይልቅ ስለ መልሶ ማልማት ሰፋ ያለ ሃሳብ የያዙ
ናቸው፡፡

₋ የደቀቁ አካባቢዎች መልሰው መልማት እንዳለባቸው የህገመንግስቱን ሃሳብ ይጋራሉ፡፡


₋ በነዚህ በደቀቁ ሰፈሮች የሚኖረው ድሃው ማህረሰብ እንደሆነ እውቅና ይሰጣሉ፡፡
₋ በመልሶ ልማት ወቅት በቦታው ያሉ ወገኖች በሂደቱ ተሳታፊ እንዲሆንም መርህ አስቀምጠዋል፡፡
₋ ስለ ኢኮኖሚ ጉዳት ካሳ፤ በቦታ ላይ ስለተፈጠረ እሴት መጋራትና ስለ መልሶ ማቋቋም ረገድ እነዚህ
ፖሊሲዎችም ህገመንግስቱንና መርህን ያገናዘበ አቅጣጫ በማስቀመጥ ረገድ እጥረት አለባቸው፡፡ የኗሪው
ህይወት ለውጥ እንደ ልማቱ አይቀሬ ውጤት መመልከቱ ልማት ትሪክል ዳውን (trickle down)
ያደርጋል የሚሉ የሊብራል መረህ አቀንቃኞች ሳይቀር በልማት የሚነሳ ወገንን ከነበረበት ሁኔታ መውረድ
የለበትም የሚለውን ሲቀበሉ በልማታዊ መንግስት ሲመዘን በከተማው 60% ቦታ ላይ ያለን 70%
ዝቅተኛ ኑሮ ያለውን ማህበረሰብ ወደ ከፋ ሁኔታ የሚገፋ ልማት እንዳይሆን ለህዝብ ጥቅም ቦታን
ማስለቀቅ ሲባል የየቱ ህዝብ ተጠቃሚነት እንደሆነ መልስ አልሰጡም፡፡
₋ የመሬት ፖሊሲው ስለተቋማዊ አደረጃጀት፤ ስለ አሰራር ስርአት፤ ስለ ፋይናንስና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ
ጉዳይ አቅጣጫ በማስቀመጡ የስራውን ልዩ ባህሪ እውቅና እንደሰጠ ቢያመላክትም ይህንን እውን
ለማድረግ ከፖሊሲው ቀጥሎ በወጣ የሊዝ ህግ ማዕቀፍ ወይንም በሌላ ህግ ባለመሸፈኑ የተተገበረ
አይደለም፡፡

ሌላው በዚህ ዘርፍ ተጠቃሽ ህግ የሊዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 ነው፡፡

₋ አዋጁ ከከተማ መልሶ ማልማት አንጻር ከነባሮቹ የሊዝ አዋጆች ጋር ሲነጻጸር ለተነሺዎች መልሶ
መስፈሪያ ቦታና ቤት አሰጣጥ ዘርዘር ያለ ሃሳብ በመያዙ የተሻለ ነው፡፡ በተለይ የመንግስት ቤት

57
በመከራየት በንግድ ስራ የተሰማሩ ወገኖች በካሳ ህጉ ያልነበሩ ተከራዮቹ የልማቱ አካል እንዲሆኑ መሬት
በሊዝ መነሻ የማግኘት መብት መፍቀዱ በጥሩ ርቀት መሄዱ የሚደነቅ ነው፡፡
₋ ነገር ግን ለልማት የቦታ ማቅረብያ ዘዴው በወሳኝነት ጨረታ እንዲሆንና ቦታው ለጨረታ ሲቀርብም
የለማና ከይገባኛል ባይ የጸዳ መሆን እንዳለበት የደነገገው ሃሳብ ከመልሶ ማልማት አንጻር ሲታይ ግንባታ
ያለበት ቦታን በሊዝ ድርድር ለአልሚ ስለመስጠትና አልሚዎችን በቦታው ያሉ ወገኖችን እንዲክሱ፤
መልሶ መስፈሪያ ቤት እንዲሰሩ/ በልማቱ እንዲያካትቷቸው ወዘተ የማድረግ እድልን ያጠበበ ነው፡፡
በመልሶ ማልማቱ ቀጥተኛ ተጠቃሚው በሂደቱ ጉዳት የሚደርስባቸውን ወገኖች ጉዳት መካስ
በተመለከተ ጅማ እና አዲስ አበባ (ሸራተን፤ ደንበል ሲቲ ሴንተር) ላይ ጅምር ቢኖርም አልሰፋም፡፡
ከዚህ አንጻር ሰው ያለበትን ቦታ በድርድር ማስተላለፍ በሊዝ አዋጅ መከልከል ይጠቀሳል፡፡
₋ ነባር ቦታቸውን ለማልማት፤ ወይንም ቢዝነሳቸውን ለማስፋት የተወሰነ ቦታ የሚፈልጉ ወገኖች
ከቦታቸው ኩታ ገጠም ያለን ቦታ በቀጥታ በድርድር በሊዝ ሊወስዱ የሚችሉበት በር የዘጋ በመሆኑ
ለመልሶ ማልማቱ ፍጥነትና ጥራት የራሱ አሉታዊ ጎን አለው፡፡
₋ አንድን ቦታ ከነባር ግንባታ ለማጽዳት ተጀምሮ የሚጠናቀቅበት እና ነጻ ከሆነ በኋላ እስከምን ጊዜ ድረስ
ለአልሚ መተላለፍ እንዳለበት ገደብ ባለማስቀመጡ ከተሞች የተጓተተና የተበጣጠሰ ቦታ የማጽዳት ስራ
እንዲያከናውኑ፤ ቦታ አፍርሰው ያለ ግንባታ ለአልሚ ሳያስተላልፉ ጭምር ሲቆዩ፤ ለአልሚ ከተላለፉ
በኋላም አልሚውን በወቅቱ እንዲገነባ ባያደርጉ ምን ሊከተል እንደሚችል ግልጽ የተጠያቂነት ግዴታ
በከተሞች ላይ ባለመጣሉ የተጓተተና የተበጣጠሰ የቦታ ማጽዳት ስራና የጸዱ ቦታዎች ያለልማት መቆየት
በሌሎች ቦታዎች መልሶ ማልማትን ለማካሄድ የፈረሰው ሳይገነባ ለምን የሚል የብሶትና ተገቢነት ያለው
ጥያቄ እንዲነሳ እያደረገ ያለ ሂደት ነው፡፡

የመልሶ ማልማት ሀገራዊ ነባራዊ አስቻይ ሁኔታዎች


₋ ነባሩ ግንባታ በደከመ ቁስ የተሰራ፤ የማፍረስ ወጭው አነስተኛ መሆን፤ በዚህ ላይ ቀጥታ ካሳ ክፍያ
ማከናወን ውስጥ ሳይገባ መፍረስ የሚችለው የቀበሌ ቤት ስፋት በነባሩ የከተማ ክፍል ከፍተኛ መሆን፤
₋ በአሁኑ ወቅት ከሀገሪቱ ኢኮኖሚ ማደግ ጋር በተያያዘ እየተፈጠረ ያለው የኢኮኖሚ አቅምና መነቃቃት፤
የይቻላል መንፈስ፤ ከድህነት ጋር ተላምዶ ከመኖር ለመፋታት የመወሰንና የተፈጠረው የመልማት ጉጉት፤
₋ ወደ ስራው በስልት ገና ያልገባን በአንጻሩ ደግሞ በርካታ ሀገራት ያለፉበት መንገድ ስላለ መቀመርና ወደ
ራስ የማምጣት፤ የዘግይዎች ከሌሎች የመማር ዕድል በስፋት መኖር፤
₋ ነባሩ እና አሁንም በአመዛኙ የኢኮኖሚው መሰረት አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ደረጃ የሚታይ ከዚህ ጋር
በተያያዘና በቦታዎቹ ያለው ማህበራዊ ሁኔታ ባለመውደቁ ማዕከላዊው ቦታ ፍላጎት ከፍተኛ የሆነ፤
በአንጻራዊነትም ነባሩ የከተማ ክፍል በዙሪያው የተሻለ መሰረተ ልማት ስላለው የቦታዎቹ ተፈላጊነት
ስላልቀነሰ መልሶ ለማልማት እንደ ከፍተኛ እድል የሚወሰዱ ናቸው፡፡

58
የመልሶ ማልማት ሀገራዊ ነባራዊ ተግዳሮቶችን
₋ ለውጥ ቢኖርም ከተሞችም ሆነ ኗሪዎቹ በከፋ የኢኮኖሚ ድህንት ውስጥ መሆን፤ የፋይናንስ ውስንነት፤
₋ የፋይናንስ/የካፒታል ገበያው ማለትም ለመልሶ ልማት ተፈላጊ የሆነውን የረጅም ጊዜ ልማት ፋይናንስ
አማራጭ ማቅረብ ላይ ገና ያልተፈጠረና ያልሰፋ መሆኑ፤
₋ በመሬት ህጎቻችን ላይ ግንባታ ያረፈበት ነባር ይዞታም ሆነ ሊዝ በገበያ መግባት እንደሚችል በዚህም
ማልማት ያቃተው መብቱን አዛውሮ አቅም ያለው ሊያለማ የሚችልበት እድል ባይዘጋም ለልማት
በከተማ መሀል ያለው የግል ይዞታ በቀበሌ ቤት መታጠር አንድ ግቢ ሳይቀር የሚጋራና መልማት
የማይችልበት/ቢችል እንኳን ተጠቃሚነቱ የተገደበ የታሰረ በመሆኑ የማይበረታታበት፤
₋ በከተማ ይብስ ደግሞ በመሬት ዘርፍ ውስጥ የአመራር አለመረጋጋት፤ የመወሰን ብቃት ጉድለት፤
₋ ከሁሉም በላይ ለመልሶ ማልማት በተወሱ ቦታዎች ላይ ያሉ ወገኖች አያያዝ ወጥነት መጓደል፤
ሁለንተናዊ ጉዳታቸውን ያገናዘበ ካሳና መልሶ ማቋቋም ድጋፍ አለመደረግ ልማቱን ለማስፋት ትልቅ
ተግዳሮቶች ናቸው፡፡

59
3.2. የናሙና ከተሞች ቅኝት
3.2.1. የከተሞቹ ነባራዊ ሁኔታ
መልሶ ማልማት የወቅቱ የሀገራችን ከተሞች አጀንዳ መሆኑ ከላይ ተጠቅሷል፡፡ መልሶ ማልማት የማይታለፍ
የወቅቱ አጀንዳ መሆኑ እስከታወቀ ድረስ ከተሞቻችን ለአጀንዳው ያላቸው ቅርበት ምን እንደሚመስል ለጥናቱ
የተመረጡ የናሙና ከተሞቹ ተጨባጭ ሁኔታ በጥልቀት መመርመር ያስፈልጋል፡፡ ለጥናቱ የተመረጡ
ከተሞችም አጀንዳውን በተገቢ ደረጃ የሚወክሉ ናቸው፡፡

ከጉዳዩ ስፋትና ጥልቀት አንፃር ግንባር ቀደም ከተማ አዲስ አበባ ናት፡፡ ከ129 ዓመት በፊት የተመሠረተችው
አዲስ አበባ አሁን በምትገኝበት ሥፍራ ላይ አጼ ምኒሊክ ቤተ መንግሥታቸውን ስለሰሩ ነበር የተፈጠረችው፡፡
ንጉሱ ቤተ መንግስታቸውን መገንባታቸውን ተከትሎ በዙሪያቸው ለመኳንንቱና ለጦር መሪዎቻቸው መሬት
ከፋፍለው በመስጠት ቤት እንዲገነቡ ሲፈቅዱ መኳንንቱና የጦር መሪዎች በበኩላቸው ተከታዮቻቸውን
በዙሪያቸው በማስፈር በዘልማዳዊ የገጠር ቤት ይዞታ አሰፋፈር የተከተለ የየራሳቸውን ሰፈር እንዳደራጁ
በተለያዩ የታሪክ ሰነዶች በስፋት ተዘግቦ ይገኛል፡፡

ስእል 3.1፡ አዲስ አበባ ስትመሠረት የነበራት ገጽታ በከፊል

ምንጭ፡ የአዲስ አበባ 125ኛ ዓመት ሲከበር የተዘጋጀ ሰነድ


በዚህ መሠረት የአዲስ አበባ አመሠራረት የጦር ሠፈር አደረጃጀትን (Garrison City) የተከተለ ሲሆን ቀጣይ
የከተማዋ ዕድገትም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የተነጣጠሉ ሠፈሮችን እያካተተ (By addition and accretion)
ዕቅድ የለሽ በሆነ መንገድ ሲስፋፋ የነበረ ነው፡፡
ስእል 3.2፡ የአዲስ አበባ ነባር አካባቢ ነባራዊ ገጽታው በከፊል

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ


60
ከዚህም ባሻገር በአዲስ አበባ የግንባታ ፈቃድ ሳይኖራቸው የሚገነቡ ቤቶችን እንደ ኢ-መደበኛ ግንባታ
/Informal houses/ የሚፈረጅ አሠራር ለበርካታ ዓመታት አልነበረም፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ የግንባታ ፈቃድ
ማውጣት ለቤት ሠሪዎች ብዙም የሚያሳስብ ጉዳይ አልነበረም፡፡ የከተማው ማዘጋጃ ቤትም በግለሰቦች ይዞታ
ውስጥ የሚካሄድ ግንባታን ለመቆጣጠር የሚያስችል ተቋማዊ አቅምም ሆነ ሥልጣን አልነበረውም፡፡ በዚህም
የተነሳ በከተማው ነባር አከባቢ በቅድመ አብዮት ዘመን ከተካሄዱ ግንባታዎች መካከል አብዛኞቹ ያለ ግንባታ
ፈቃድ የተገነቡ ነበሩ፡፡

የከተማ ቦታና ትርፍ ቤትን ወደ መንግሥት ንብረትነት ያዛወረው አዋጅ 47/67 ከታወጀ በኋላም አዋጁ
የከተማ ቦታን ጠባቂ አልባ ማድረጉ፣ በግለሰብም ሆነ በድርጅት ቤት ሰርቶ መሸጥና ማከራየት መከልከሉ፣
የግሉን ዘርፍ ሚና ይተካል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው መንግሥት በከተሞች በቂ መኖሪያ ቤት ገንብቶ ማቅረብ
አለመቻሉ በኢትዮጵያ ከተሞች ሰፍኖ የነበረው ሁኔታ የኢ-መደበኛ ግንባታን የሚያስፋፋ እንጂ የሚገታ
አልነበረም፡፡ አዲስ አበባ ከተማም የዚህ ችግር ግንባር ቀደም ሰለባ ለመሆን አብቅቷታል፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ
በከተማው ከነበሩት በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰነድ አልባ ግንባታዎችን እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙት ሕገ
ወጥ ሰፈራዎችን ማየት ሁኔታውን ለመረዳት በቂ መረጃ ነው፡፡

ስእል 3.3፡ በአዲስ አበባ ከተማ በስፋት የሚገኙ ኢመደበኛ ስፈራዎች ገጽታ

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ


ከ1967 ወዲህ የመሬት ስሪቱ ከግል ባለቤትነት ወደ ህዝብና የመንግስት ባለቤትነት ቢዞርም ስርዓቱ ከፍተኛ
አስተዳደራዊ ማነቆና ችግሮች የነበሩበት ነበር፡፡ በመደበኛ መንገድ ሄደው የቤት መስሪያ ቦታ አግኝተው ቤት
ለመገንባት ያልቻሉ ነዋሪዎች መደበኛ ያልሆነውን (Informal) አማራጭ ለመከተል ተገደዋል፡፡ በዚህም
ምክንያት ብዙ ጨረቃ ቤቶች እየተስፋፉ መጥተዋል፡፡

ከተወሰኑ አከባቢዎች ውጭ በከተማዋ መካከል የሚገኙ በርካታ ቦታዎች ዕድሜ ልካቸውን የከተማ ማሻሻያ
ስላልተደረገላቸው አብዛኛው መሃል አዲስ አበባ ጥልቅ በሆነ የከተማ እርጅና (Urban Degeneration)
ሊጠቃ ችሏል፡፡ በአጠቃላይ አብዛኞቹ የአዲስ አበባ ነባር አከባቢዎች ከደረጃ በታች በሆነ ግንባታ የተያዙ፣
ቁልፍ የመሠረተ ልማት ያልተዘረጋላቸው፣ መሠረታዊ የከተማ አደረጃጀት መሥፈርትን የማያሟሉ፣ ዘመናዊ
የከተማ ሕይወትን ማስተናገድ የማይችሉ፣ ለመዲናዋ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሚና የማይመጥኑ ናቸው፡፡
61
ከዚህ የተደነጋገረ የከተማ ምስል (Urban blight) ጎን ለጎን አዲስ አበባ ባለፉት አስር ዓመታት በታሪኳ
አይታው የማታውቀው ፈጣን ዕድገትና ስር ነቀል የሆነ ለውጥ ያስመዘገበች ከተማ ናት፡፡ በመኖሪያ ቤት፣
በመንገድ፣ በባቡር መሠረተ ልማት፣ በሆቴሎችና ሌሎች ሁለ-ገብ ሕንፃዎች ግንባታ የተመዘገበው ውጤት
መዲናዋን ዘመናዊነት እያላበሳት በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ከተማዋን በዘመናዊ ፕላን እንደገና ለማደራጀት ከዛሬ
15 ዓመት በፊት በተጀመረው ጥረት የተመዘገበው ስኬትም ቀላል አይደለም፡፡ ዛሬ የአዲስ አበባ ዓለም አቀፋዊ
ገጽታዋ ተቀይሯል፡፡ መዲናዋ የጎብኝዎችን፣ የባለሃብቶች እና የዓለም አቀፍ ጉባኤተኞችን ቀልብ ከሚስቡ
ጥቂት ዓለም አቀፍ ከተሞች ተርታ መሰለፍ እየቻለች ነው፡፡

ይሁንና ከላይ እንደተገለፀው የተወሰነ ክፍሏ የከተማዋ አጠቃላይ ተወዳዳሪነት ፈተና ውስጥ የሚከቱ በርካታ
ችግሮች ያሉበት በመሆኑ ከተማዋ ማየት የጀመረችው ብሩህ ተስፋና የለውጥ ጉዞ ሙሉ እንዳይሆን
ያደርገዋል፡፡ እንዳውም የከተማዋን ነባር አከባቢ ጉስቁልና እና ጉራማይሌነት እንደ ማስረጃ በመጥቀስ
በዲፕሎማቲክ ኮሙኒቲው አከባቢ የአዲስ አበባን የአፍሪካ መዲናነት ጥያቄ ውስጥ ለማስገባት ይደረግ
የነበረው ቅስቀሳ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ አሁንም በመሃል አዲስ አበባ የተንሰራፋው እርጅናና ጉስቁልና
ፈጥኖ ካልተፈታ ይህ ጥያቄ እንደገና ተመልሶ አይነሳም ብሎ መደምደም አይቻልም፡፡ ስለዚህ ከተማው እጅግ
ሰፊ መልሶ ማልማት ዘመቻ የሚጠይቅ ሁኔታ ላይ ነው የምትገኘው፡፡

የከተማው አጠቃላይ ዕድገት ሲታይ ደግሞ ይህንን ያህል ያረጀ፣ እንደ መንገድ፣ ውሃ፣ ተፋሰስ እና ፍሳሽ ቆሻሻ
ማስወገጃ የልማት አስቻይ መሰረተ ልማቶች ያለመኖራቸው እጅግ ውድ የሆነ የከተማው መሬት እንዲታሰርና
ልማቱን የሚመጥን እሴት እንዳይፈጥር ምክንያት ሆነዋል፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን ከ70% ያህል በዝቅተኛ ገቢ
የሚተዳደር የከተማዋ ነዋሪ የሚገኘው በእነዚህ ሰፈሮች በመሆኑ በከተማው ሰፊና ዙሪያ መለስ የልማት
ለውጥ የሚያመጣ መልሶ ልማት ማካሄድ ማለት ድህነትን ትርጉም ባለው ደረጃ መናድ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡

የአዲስ አበባ የአስተዳደራዊ ክልል ሙሉ በሙሉ ግንባታ ያረፈበት ማለትም ለምቷል በሚያስብል ደረጃ
መድረሱ ከተማው ወደ ጎን የመስፋት ዕድሉ ጠባብ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከተማዋ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ
ዕድገት የስህበት ማእከል በመሆኑዋ ምክንያት የህዝብ ዕድገቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ
ይገኛል፡፡ የኢኮኖሚው ዕድገት እና ኢንቨስትመንት ፍሰት የወለደው ስራ ፍለጋ ተስፋ የህዝብ እድገቱ
እንዲቀጥል ያደርገዋል፡፡ ከተማዋ በአለም አቀፍ ደረጃ ካላት የፖለቲካ ሚና ጋር ተያይዞ የሚመጣ ዕድገትም
ሳይቆራረጥ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያድግም ገሀድ ነው፡፡

ይህንን ሁሉ የህዝብ ዕድገት እና የኢኮኖሚ እድገት የምታስተናግደው አሁን ባላት የመሬት ስፋት ብቻ መሆኑ
እሙን ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ አጠቃላይ የከተማዋ የቆዳ ስፋት እና ከተማዋ የምታስተናግደው የህዝብ ብዛት
እና የኢኮኖሚ መጠን ጥምርታ ከሌሎች ታዳጊ ሀገራት ከተሞች ሲነፃፀር ሰፊ ልዩነት አለበት፡፡ የከተማዋ የቆዳ
ስፋት ገና ብዙ ተጨማሪ ነዋሪ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ማስተናገድ ይችላል ብቻ ሳይሆን የሚጨምረው
መጠን አሁን ካለው በላይ እንደሚሆን የሌሎች ታዳጊ ሀገራት ከተሞች ተሞክሮ ይጠቁመናል፡፡ ይህንን እውን

62
የሚሆነው ግን አሁን ያለው የመሬት አጠቃቀም ከመሰረቱ መለወጥ እና በማነጣጠርያነት ያቀረብናቸው
ከተሞች የደረሱበት የመሰረተ ልማት ዓቅም መገንባት እንዲሁም የግንባታ ልማት ደረጃ መድረስ ይጠይቃል፡፡
እንዲህ ዓይነት ሁኔታ የሚፈጥረው ብቸኛ መንገድ ደግሞ መልሶ ልማት ነው፡፡

ደረጃው ቢለያይም የአዲስ አበባ ገፅታ በሌሎች ቀደምት ከተሞቻችንም ተመሳሳይ ነው፡፡ በመሆኑም ድሬዳዋ
ከተማም ከዚሁ ችግር አላመለጠችም፡፡ የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር መስመር ዝርጋታ የወለዳት ድሬዳዋ የከተማዋ
አብዛኛውን ነባር አከባቢዎች ከአንድ መቶ ዓመት በላይ ዕድሜ ባስቆጠሩ ግንባታዎች የተሞላ ሆኖ
እናገኘዋለን፡፡

የድሬዳዋ ከተማ ዕድገት እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከምስረታዋ ጀምሮ ከኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር እንቅስቃሴ ጋር
በጥብቅ የተሣሠረ ስለነበር በኢንዱስትሪ ማዕከልነት በአገሪቱ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ከተሞች
መካከል አንዷ እንደነበረች የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ከባቡሩና ከኮንትሮ ባንድ ንግድ ጋር በተያያዘም ቀደም
ሲል የድሬዳዋ ንግድ እንቅስቃሴ ሞቅ ያለ ነበር፡፡ የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ድርጅት ሥራ ማቆም በድሬዳዋ ከተማ
ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ምን ያህል ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳሳረፈ ለመረዳት በአሁኑ ጊዜ ከተማዋን
ተዘዋውሮ መመልከት ብቻ ይበቃል፡፡

በዚህ ሂደት ክፉኛ የተጎዱት ባቡር ጣቢያው የሚገኝበት ከዚራ እና በዙሪያው የሚገኙ ነባር አከባቢዎች ሲሆኑ
በአሁኑ ጊዜም የከተማው ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መሃል ከተማውን እየለቀቀ ወደ ሰሜን ምስራቅ የከተማዋ
መስፋፊያ አከባቢ በመሸሽ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ የተነሣ የድሬዳዋ ነባር አከባቢ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ከጊዜ
ወደ ጊዜ እየተዳከመ በመሄድ ላይ ነው፤ ግንባታዎች ጥልቅ በሆነ እርጅና ተጠቅተዋል፤ በአካባቢው የንግድና
አገልግሎት እንቅስቃሴ ተቀዛቅዟል፤ በብዙ አገሮችና ከተሞች እንደሚስተዋለው የመሃል ከተማውን የኢኮኖሚ
እንቅስቃሴ መዳከምና በእርጅና መጠቃት ተከትሎ አቅም ያላቸው ነዋሪዎች ነባሩን አካባቢ እየለቀቁ
በመስፋፊያ አካባቢ ወደ ተመሰረቱ አዲስ ሰፈሮች በመስፈር ላይ ናቸው፡፡ ይህም ሂደት የመሀል ከተማውን
መውደቅ (Urban Degeneration) ይበልጥ እያባባሰው እንደሆነ መሬት ላይ ያለው እውነታ ያመለክታል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ የነባር አካባቢዎች እርጅና ከአዲስ አበባ በጣም የተለየ ነው፡፡ የአዲስ አበባ በርካታዎቹ
ስፍራዎች ያለፕላን የተፈጠሩ እና ቤቶቹም ረጅም ጊዜ በማይቆዩ የግንባታ ግብአቶች ከመገንባታቸው
የተፈጠረ እርጅና ሲሆን የአካባቢው የመሬት ተፈላጊነት ግን ከፍተኛ ነው፡፡ የድሬዳዋ ከዚህ በተቃራኒ መልኩ
ይገኛል፡፡ ምንም እንኳ የከተማው ነባር አካባቢ ዕድሜ ጠገብ የሆኑ ግንባታዎች በስፋት የሚታዩበት አከባቢ
ቢሆንም የከተማዋ አደረጃጀትና ዕድገት ፕላን የተከተለ እንደነበር የሚያመላክቱ አሻራዎች እስካሁን
አልጠፉም፡፡ አዲስ አበባ ላይ የሚታየው የመሬት ተፈላጊነት ግን ድሬዳዋ ላይ አይገኝም፡፡

የደሴ ከተማ ዕድገት ታሪክ ስንመለከት ደግሞ ከወታሀደራዊ ማእከልነት ጋር የሚገናኝ በመሆኑ በርካታ
ሰፈሮች አግባብ ባለው የከተማ ፕላን በስርዓት ተሟልተው የተደራጁ አይደሉም፡፡ በመሆኑም ሰፊው

63
የከተማው ሰፈሮችና ቤቶች ለኑሮና ለስራ የተመቹ እንዳልሆኑ የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ 93.2% ያህሉ ቤቶች
ከጭቃና እንጨት እንዲሁም ከጭቃ ብሎኬት የተገነቡ መሆናቸው ቤቶቹ ቁመናው ሳይዳከም ለረጅም ጊዜ
እንዲቆይ የሚያስችሉ አይደሉም፡፡ እጅግ ሰፊው የከተማው ክፍል እንደ ኩሽና፣ ሽንት ቤት፣ መታጠቢያ ቤት
የመሳሰሉት በቤት ደረጃ ሊኖሩ የሚገባቸው መሰረተ ልማቶች (site level facilities) የተሟላለት አይደለም፡፡
በከተማው ከሚገኙ የቀበሌ ቤት ይዞታዎች ካጠቃላይ ቤቶች 35% በላይ የሚሸፍኑ ሲሆኑ እነዚህ ይዞታዎች
በአያያዝና አስተዳደር በሚገጥማቸው ችግር ከግል ይዞታዎች በባሰ ከላይ በተጠቀሱ ችግሮች የተጎዱ ናቸው፡፡
በከተማው የሚገኙ የአብዛኞቹ ቤቶቹ አሰራር በጣም የተጨናነቀ ነው፡፡ በአንድ ብሎክ የሚገኙ ቤቶች
የተያያዙ በመደዳ የተገነቡ መሆናቸው ለእሳትና ሌሎች አደጋዎች በቀላሉ ተጋላጭ ጭምር ናቸው፡፡

ስእል 3.4፡ በደሴ ከተማ የሰፈርና ቤቶ እርጅና ገፅታ በከፊል

ምንጭ፡ የደሴ ከተማ አስተዳደር፣ 2002 ዓ/ም

የከተማው ችግር የቤቶችና ሰፈሮች እርጅና ብቻ ሳይሆን እጅግ የተጨናነቀ አሰፋፈር መኖሩ ጭምር ነው፡፡
በ1999 ዓ/ም የከተማው አስተዳደር ያጠናው ጥናት የሚያሳየው በአንድ ክፍል ቤት አምስት እና ከአምስት
በላይ ሰው የሚኖር የከተማው ነዋሪ 55.97% ያህል መሆኑ ከፍተኛ ነው፡፡

የቤቶች ቁመና፣ በግል ይዞታ መሟላት የሚገባው መሰረተ ልማት፣ እንዲሁም የቤቶችና ሰፈሮች እርጅና
በመውሰድ ሲመዘን በከተማው ከሚገኙ ቤቶች 75% ያላነሱ ዝቅተኛ መስፈርት/ደረጃ የማያሟሉ ናቸው፡፡
በ2002 ዓ/ም የተጠናው የከተማው መዋቅራዊ ፕላን እንደሚያሳየው አብዛኛውን የከተማው ክፍል (ሰኞ ገበያ፣
ሳላይሽ፣ ቢለን፣ ሙጋድ፣ መድሃኒአለም፣ አውቶቡስ መናሃሪያ፣ አይጠየፍ ቤተ መንግስት፣ ጦሳ ተራራ ስር)
በድምሩ ከ4,000 በላይ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች (ከ4ዐዐ ሄክታር ያላነሰ) የእርጅና ደረጃቸው እና ለመሰረተ
ልማት ተደራሽነት ካላቸው ችግር አንጻር ሲመዘኑ ባሉበት ከማሻሻል ይልቅ ሙሉውን አፍርሶ መገንባት
የሚያስፈልጋቸው እንደሆኑ አስቀምጠዋል፡፡

64
አሁን ያለው ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ቀጣይም ከተማው ፈተናዎች እንደሚደቀኑበት ማየት ተገቢ ነው፡፡ የደሴ
ከተማ ብቻው እንደቆመ ከተማ ከማየት ይልቅ ከኮምቦልቻ ከተማ እንደ አንድ ተመጋጋቢ ማእከል ተደርጎ
ማየት ሁኔታውን ይበልጥ ለመረዳት ይጠቅማል፡፡ የኮምቦልቻ ከተማ በሀገሪቱ ለኢንዱስትሪ ማእከልነት
ከተመረጡ፣ ቀድሞም ቢሆን ከሌሎች ማእከላት ቀድማ የኢንዱስትሪ ማእከል ሆና እያገለገለች የምትገኝ
በመሆንዋ ከተማዋ ከፍተኛ የህዝብ እድገት እያስተናገደች መሆኑ ይታያል፡፡ ለምሳሌ አሁን በስራ ላይ የሚገኝ
የከተማ መዋቅራዊ ፕላን ከታሰበለት ጊዜ አራት ዓመታት ቀድሞ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል፡፡ ኮምቦልቻ ከተማ
እንዲህ እየተጣበበ ሲሄድ ጫናው ወደ ደሴ ከተማ መፍሰሱ አይቀርም፡፡

ሁለቱም ከተሞች በ25 ኪሎ ሜትር ቅርበት መገኘታቸው ኮምቦልቻ ላይ በሚፈጠር ሰፊ የስራ ዕድል
አማካኝነት የሚቀጠር ኃይል መኖሪያው ደሴ ማድረጉ አይቀሬ ነው፡፡ ኢንዱስትሪውን በንግድና አገልግሎት
ዘርፍ የሚፈጥረው ተጨማሪ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ (Multiplier Effect) በንግድና አገልግሎት ዘርፎች
የተመሰረተው የደሴ ከተማ ይበልጥ እንደሚጠናከር ይጠበቃል፡፡ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የሚፈጥረው ተጨማሪ
የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴም ቀላል አይሆንም፡፡ ስለዚህ የደሴ ከተማ ዕድገት ባለበት
የሚገታ ሳይሆን ፈጣን እንደሚሆን መጠበቅ ተገቢ ይሆናል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከተማው የመኖሪያ ቤት እና የስራ ቦታ ሰፊ እጥረት ከሚታይባቸው የሀገሪቱ ከተሞች


አንዷ ነች፡፡ ከሌሎች ከተሞች በተለየ የደሴ ከተማ በአስቸጋሪ የመሬት አቀማመጥ የምትገኝ በመሆኑዋ
ዕድገትዋን ተከትሎ ለሚፈጠረው የመኖሪያ እና የስራ ቦታ ፍላጎት ተጨማሪ መሬት ከማስፋፊያ ቦታ
ለማግኘት የምትቸገር ከተማም ነች፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ ከተማዋ በውስጧ የሚገኘው መሬት በአግባቡ
ጥቅም ላይ ውለዋል የሚባል አይደለም፡፡ መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ፎቅ ያልሆኑ ናቸው፡፡ የንግድ
ህንጻዎችም ቢሆን ከ1996 በኃላ በመካሄድ ላይ የሚገኝ መልሶ ልማት እንቅስቃሴዎች ዋና መንገድ ተከትሎ
የሚገኙ ይዞታዎች ወደ ፎቅ እየተቀየሩ ሲሆን ከስፋቱ አንፃር አልተነካም ማለት ይቻላል፡፡ ቀጣይ የሀገሪቱ
የኢኮኖሚ ዕድገት በዋናነት በከተሞች የሚወሰን በመሆኑ የከተማው የነዋሪዎች የገቢ ደረጃ ስለሚሻሻል አሁን
ያሉት የመኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ፈርሰው እንደ አዲስ መገንባታቸው የማይቀር ነው፡፡ የከተማው
የኢኮኖሚ ባህሪን የሚመጥን እና የሚስማማ የስራ ቦታ መፍጠርም ትኩረቱ አሁን የደቀቀውን የከተማው
ቦታዎች ላይ መሆኑ አይቀርም፡፡

የከተማው ነባራዊ ሁኔታ እና መጪው ሁኔታዋ እጅግ ሰፊ መልሶ ማልማት የሚጠይቅ ቢሆንም በከተማው
የሚካሄደው መልሶ ማልማት ሌሎች ከተሞች ላይ ከሚካሄደው የተለየ ነው የሚሆው፡፡ በከተማው
የሚከናወነው የመልሶ ማልማት ጥረት አስቸጋሪውን የመሬት አቀማመጥ ተጋፍጦ ለመጠቀም የሚያስችል
ከፍተኛ የከተማ ዲዛይን ጥበብ ጭምር የሚጠይቅ ስለሚሆን የሚጠይቀው ዕውቀት፣ ክህሎት እና ሀብት
ከፍተኛ ይሆናል፡፡

65
የቀደምት ሰፈሮች የአሰፋፈር ችግር እና የቤቶች እርጅና እንዲሁም ለመሰረተ ልማት ያላቸው ተደራሽነት
ዝቀተኛ መሆን አዲስ አበባና ደሴ ከተሞች ላይ የሚታየው ችግር የጅማ ከተማም ግግሩ ይታያል፡፡ በአሁን ጊዜ
የከተማዋ መካከለኛ ስፍራዎች እጅግ አርጅቷል፡፡ የከተማው ዋነኛ የቢዝነስ ማእከል መርካቶ እና የብሺሼን
ገበያን ጨምሮ የከተማው መካከል ቀበሌዎች ላይ የሚገኙ ይዞታዎች ከ50% በላይ የተወረሱ የቀበሌ ቤቶች
ሲሆኑ እነዚህ አከባቢዎች እና ቤቶች ለረጅም ጊዜ ምንም ዓይነት መሻሻል ሳይደረግላቸው ስለቆዩ ለከፋ
የእርጅና ደረጃ ተጋልጠዋል፡፡ ሂርማታ፣ ሂርማታ-መንቲና፣ ሂርማታ-መርካቶ፣ መንቲና፣ አዊቱ መንደራ
ቀበሌዎች የሚገኙ ይዞታዎች ችግራቸው የቤቶች እርጅና ብቻ ሳይሆን የቤቶችና ብሎኮች አደረጃጀታቸው
የተሟላ ፕላን የተከተለ አለመሆኑ ጭምር ነው፡፡ የውኃ፣ መንገድ፣ ተፋሰስ፣ መሰረተ ልማቶች በአከባቢው
የሚኖረውን ህዝብ የሚሸከም እንዳልሆነም ከከተማው ባለሙያዎችና አመራሮች ጋር ከተደረገው ውይይት
ለመረዳት ተችሏል፡፡

የሀገሪቱ ከተሞች ችግር ከምስረታ እና ቀደምት ዕድገት የሚመነጭ እርጅና፣ የአሰፋፈር ስርዓት ያለመጠበቅ፣
የመሰረተ ልማት ሽፋንና ጥራት ብቻ ሳይሆን በቅርብ ጊዜ የለሙ አከባቢዎችም ጭምር ተመሳሳይ ችግር
ያለባቸው መሆኑ የጅማ ከተማ ነባራዊ ምስል ለምስክርነት ቆሟል፡፡

ስእል 3.5፡ በቅርብ ጊዜ የለሙ የጅማ ከተማ ቦታዎች ላይ የሚታየው የመሬት አጠቃቀም ችግር ማሳያ

ምንጭ፡ ከጎግል ኤርዝ የተወሰደ

ከላይ በፎቶው እንደሚታየው በጅማ ከተማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለልማት የዋሉ ቦታዎች በፕላን የተመሩ
ቢሆኑም የመካከል ሰፈሮች የሚታይባቸው ችግሮች ተጋሪ ናቸው፡፡ ቤቶቹ የሚገነቡት ከእንጨትና ጭቃ
ስለሆኑ ትውልድ ተሸጋሪ አይሆኑም፡፡ ከመካከል ቦታዎች በራቁ ቁጥር የመንገድ፣ ውኃ፣ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ
ማስወገጃ፣ የተፋሰስ መሰረተ ልማቶች ተደራሽነት እየቀነሰ አንዳንድ ቦታዎች ላይም ጭራሽ አልተዳረሰም፡፡
በግለሰብ ይዞታ የሚገነቡ ክፍሎችም አንዱ በሌላኛው ላይ እየቀጠሉ የሚገነቡ የግቢውን አደረጃጀት ጥሩ
ዕይታ እንዳይኖረው የሚያደርጉ ናቸው፡፡ በእንዲህ ዓይነት የሚገነቡ ቤቶች ለዕይታ የማይማርኩ በመሆናቸው
ሰፈሮቹን ፕላን የሌላቸው አስመስሎዋቸዋል፡፡ የመሰረተ ልማት ውስንነት ዓቅም ሲፈጠር በሂደት እየተሟላ
ሊሄድ የሚችል ሲሆን የእነዚያ ቦታዎች አሳሳቢ ችግር መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ እየዋለ አለመሆኑ ነው፡፡

66
ባጠቃላይ ሰፋፊ ይዞታዎች ላይ የተገነቡ ትናንሽ ቤቶች ከመሬቱ ዋጋ ጋር ፍፁም የሚጣጣሙ ባለመሆናቸው
የመሬቱ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዲቀንስ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ጅማ ከተማ ላይ የሚካሄድ መልሶ ማልማት
በእንዲህ ዓይነት አከባቢዎች ሊከተለው የሚገባ የተለየ ስልት ማሰብ ተገቢ ይሆናል፡፡ ምናልባት እነዚህ
አከባቢዎች እንደ አዲስ ማስፋፊያ በማሰብ መልሶ እንደ አዲስ ማደራጀት ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

ቀደም ሲል የከተማዋ ዋነኛ የኢኮኖሚ መሰረት ከንግድና ከግብርና ምርቶች ጋር የተያያዙ መለስተኛ
አገልግሎቶች ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን የከተማው መሰረት ንግድ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት የከተማው የንግድ
እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ እንደተቀዛቀዘ የንግዱ ማሕበረሰብና ነዋሪዎች ይገልፃሉ፡፡ የንግዱ ማሕበረሰብ
እንደሚሉት የንግዱ መቀዛቀዝን ተከትሎ ወደ ከተማው የሚፈሰው የኢንቨስትመንት መጠን እጅጉ ቀንሷል፡፡
ይባስ ደግሞ በከተማው የነበሩ የተሻለ አቅም የነበራቸው ባለሀብቶች ከተማውን ለቀው ወደ አዲስ አበባና
ሌሎች ከተሞች እየፈለሱ በመሆኑ የከተማው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እና ጥንካሬ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸረሸረ
እንደሆነ ለከተማ ዕድገት ስጋት ሆኗል፡፡ በዚህ ሣቢያ በ2000 ዓ/ም በተከናወነ የልማት ንቅናቄ ምክንያት
የተጀመረው መልሶ ማልማት መርካቶ ላይ ጥሩ ማሳያ የሚሆን ቦታ ማልማት የተቻለ እንዲሁም አወንታዊ
ተፅዕኖው ወደ አውቶብስ መናሀሪያ፣ ስቴዲየም፣ አራት አንበሳ አደባባይ አካባቢ፣ ዳውሮ በር እና መርካቶ
ዙሪያ በነጠላ ይዞታ ደረጃ የተሸጋገረ ቢሆንም አሁን አሁን የልማቱ ፍጥነት እጅጉን ቀዝቅዟል፡፡

ከላይ የተጠቀሱ የችግሮች ስፋትና የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ከተማዋን በልማት ለማነቃቃት የመልሶ ማልማት
ኢንቨስትመንት አዋጭ ላይሆን ይችላል የሚል ስጋት ሊቀርፍ የሚችል ዕድልም አለ፡፡ በሀገሪቱ የከተሞች ሚና
ፍረጃ ጅማ ከተማ የግብርና ምርምር ማእከል እንድትሆን መፈረጇ፣ የአከባቢውን እምቅ የግብርና ዓቅም
መልማት በሚችልበት ደረጃ ከለማ፣ እንዲሁም የግብርና ምርቶች የሚያቀነባብር የኢንዱትሪ ፓርክ በከተማዋ
እንዲገነባ መንግስት ማቀዱ የከተማዋ ኢኮኖሚ ማንሰራራት ብቻ ሳይሆን ባንድ ጊዜ ወደ ከፍተኛ ደረጃ
ስለሚያሸጋግረው የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት አዋጭ ያደርገዋል፡፡ ስለሆነም መልሶ ማልማት ከፊቱ ያለው
ሁኔታ ብሩህ እንጂ ጨለማ አይደለም፡፡

ከነባር አካባቢዎች ጥቅል የከተማ እርጅና ስፋት አንፃር መቐለ እና ሀዋሳ ከተሞች ከሌሎቹ የተለየ ምስል
ያላቸው ሲሆን በመካከላቸው ደግሞ የከተሞቹ ፊዚካል ሁኔታ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ምስላቸው
ይበልጥ ተቀራራቢነት ይታይባቸዋል፡፡

የለማውን የመቐለ ከተማ ፊዚካል ምስሉ ሲታይ ከተማዋ የተመሰረተችበት ቀበሌ 14 ከስድስት ብሎኮች
የማይበልጥ፣ እንዲሁም ቀበሌ 03 ውሱን ቦታ ከደረጃ በታች ይዞታዎች የሚገኙበት ሲሆን እርጅናም ጭምር
ይታይባቸዋል፡፡ በ1998 ዓ/ም የተዘጋጀው የከተማው መዋቅራዊ ፕላን ወደ ከተማው ያካተታቸው የገጠር
መንደሮችና ትናንሽ ከተሞች (ኲሓ ነባሩ ሰፈርና አይናለም በሙሉ) ደግሞ ሰፎሮቹ በፕላን የተደራጁ
አይደሉም፡፡ እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች አልፎ አልፎ ከከተማው ከደረጃ በታች የሆኑ ግንባታዎች አሉ፡፡
መዋቅራዊ ፕላኑ ያስከተለው የመሬት አጠቃቀም ለውጥ ተከትሎም የመሬት አጠቃቀሙ መለወጥ የሚጠይቅ

67
ቦታዎች ከመኖራቸው ባለፈ ከተማው ባጠቃላይ ሲገመገም የእርጅና እና መተፋፈግ ችግሩ የጎላ ነው የሚባል
አይደለም፡፡ ሰፋ ያለ የመልሶ ማልማት የሚጠይቀው የአይናለም አከባቢ ሲሆን መልሶ ማልማቱ
የሚያስፈልግበት ምክንያትም በእርጅና ምክንያት ሳይሆን የአከባቢ የልማት ፕላኑ ሲተገበር በርካቶቹ ቤቶች
እንዲፈርሱ እና ይዞታዎች እንዲስተከካሉ ስለሚጠይቅ ነው፡፡

የሀዋሳ ከተማም ቢሆን ዕድገቷ የቅርብ ጊዜ ውጤት በመሆኑ የሰፈሮች እርጅና እና የፕላን ችግር የጎላ
አይደለም፡፡ ይህ ከተማም መቐለ ላይ እንደሚታየው ሁሉ አልፎ አልፎ እርጅና የሚታይባቸውና የመሰረተ
ልማት ተደራሽነት ችግር ያለባቸው ሰፈሮች አሉ፡፡ በነጠላ ፕሎት ላይ ተበታትነው የሚታዩ ከደረጃ በታች
ቤቶችም አሉ፡፡ አልፎ አልፎም የተወሰኑ ሰፈሮች ጥቅል የከተማ እርጅና የሚታይባቸው አሉ፡፡ የችግሩ ስፋት
በድምር ሲታይም አሳሳቢ አይደለም ብሎ መደምደም ይቻላል፡፡

ሁለቱም ከተሞች በሀገሪቱ በፈጣን ዕድገታቸው የሚታወቁ ከተሞች ናቸው፡፡ የከተሞቹ ዋነኛ የኢኮኖሚ
መሰረት ንግድና አገልግሎት ዘርፍ ሲሆን የኢንዱትሪ ዘርፍ የሁለተኝነት ሚና አለው፡፡ ከተሞቹ የየክልሉ
የፖለቲካ ማእከላት የመሆናቸው ያህል ከፍተኛ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅሰቃሴ የሚታይባቸው ናቸው፡፡
ጅማ እና ድሬዳዋ ከተሞች የተጋረጠባቸው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መቀዛቀዝ በእነዚህ ከተሞች አይታይም፡፡
በተለይ ሀዋሳ ከተማ የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ጥንካሬው እንደቀጠለ ይታያል፡፡ በተለይ ለቱሪዝም
መስህብነት ያላት ዕምቅ ዓቅም ደግሞ የኢንቨስትመንት ፍሰቱም ሆነ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ጠንካራ ሆኖ
እንዲቀጥል ተጨማሪ ዋስትና እየሰጠው ነው፡፡ የሁለቱም ከተሞች የዕድገት ስርጭት ሲታይ ደግሞ በአንድ
ማእከል የተወሰኑ ሳይሆኑ የየከተማው ዕድገት ከቦታ አንፃር የሚኖረው ስርጭት የተመጣጠነ እንዲሆን
የሚያግዙ በርካታ ማእከላት ያላቸው ናቸው፡፡

ከተሞቹ የየክልሉ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ የስህበት ማእከላት ሆነው መቀጠላቸው እና ትላልቅ የኢንዱስትሪ
ማእከላትም የሚገነቡባቸው (የሀዋሳ ወደ ስራ ገብቷል) የከተሞቹ ዙሪያ መለስ ዕድገት ሳይስተጓጎል
እንደሚቀጥል የሚያስችል መልካም ዕድል አላቸው፡፡ ነገር ግን እስካሁን በነበራቸው ሂደት ከተሞቹ ያለ ቅጥ
ወደ ጎን እየተለጠጡ በመሄዳቸው የመሬት ሃብታቸው አጠቃቀም ቆጣቢ አልነበረም፡፡ ስለሆነም ለወደፊቱ
የልማት እና እድገት ጉዞው ላይ ስጋት እንደሚፈጥር ጥርጥር የለውም፡፡ እስካሁን የለማው የከተሞቹ ክፍል
ስፋት እጅግ የተለጠጠ ነው፡፡

በተለይ ሀዋሳ ለመኖሪያ ቤት የሚሰጥ የሽንሻኖ (plot) ስፋት እስከ 400 ሜትር ካሬ በመሆኑ የመሬት
አጠቃቀሙ ውጤታማ ነው የሚያስብል አይደለም፡፡ የሁለቱም ከተሞች የመካከል ስፍራዎች ላይ የሚታየው
የአሰፋፈር ጥግግት ደረጃ ከአዲስ አበባ፣ ጅማ እና ደሴ ከተሞች ተመሳሳይ ቦታዎች ጋር ሲወዳደር እጅግ
ዝቅተኛ (ለምሳሌ መቐለ - ቐዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ 56 ሰው በሄክታር) ነው፡፡ የከተሞቹ እድገት ተከትሎ
የመሬት የመጠቀሚያ መብት ዋጋም በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ሶሥት መሰረታዊ
ሁኔታዎች የከተሞቹን ዕድገት ዘላቂነት አስተማማኝ ሆኖ እንዲቀጥል የከተማ ልማት ትኩረታቸው ወደ ውስጥ
68
እንዲሆን መታሰብ እንዳለበት አከራካሪ አይደለም፡፡ ወደ ጎን የሚደረገውን የተለጠጠ ማስፋፋት በማቀብ
በዋናነት በመልሶ ማልማት ላይ ትኩረት ማድረግ አማራጭ የሌለው ይሆናል፡፡

ድምር ሀገራዊ ምስሉ ሲታይ ከተሞቹ ያሉባቸውን ችግሮች እና ቀጣይ ዕጣ ፈንታቸው መልሶ ማልማት ላይ
የተመሰረተ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ መልሶ ማልማት ያረጁ ቤቶች በአዲስ ቤቶች ወይም ግንባታዎች መቀየር
ብቻ አይደለም፡፡ መሰረታዊ ጉዳዩ እነዚህ ያረጁ እና የተፋፈጉ ቤቶችና ሰፈሮች ለኑሮ እና ለስራ የሚመቹ
እንዲሆኑ፣ ደሳሳ ግንባታዎች አስረው የያዙት የመሬት ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ለከተማው ከፍተኛ ጥቅም
እንዲውል ማስቻል፣ በእነዚያ ደሳሳ አከባቢዎችና ቤቶች የሚኖሩ ዜጎች የመኖሪያ ቤት ችግር መቅረፍ
እንዲሁም የኢኮኖሚያቸው መሰረት መቀየር ወይም ገቢያቸው ማሻሻል፣ ማህበራዊ ችግሮቻቸውን መፍታት፣
በአከባቢው የጎደሉት የፕላን ይዘቶች መጨመር ወዘተ ዘርፈ ብዙ እንድምታዎች ያሉት ልማት መተግበር
ነው፡፡ በመሆኑም የከተማ መልሶ ማልማት ስራ በአግባቡ ከተመራ በርካታ ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊና
አካባቢያዊ ጠቀሜታዎች የሚገኙበትና የከተሞቹ ሁለንተናዊ ዕድገት የሚያፋጥን ተደማሪ የልማት ዓቅም
የሚፈጥር ሲሆን በአግባቡ ካልተመራ ደግሞ ሰፊ አሉታዊ ውጤት የሚያስከትል የልማት አጀንዳ ነው፡፡

ልማቱ በርካታ አካላትን (Urban Actors) የሚነካ እንደመሆኑ መጠን ሂደቱ ውስብስብ ነው፤ በልማቱ
የሚነኩ ባለድርሻ አካላትን ፍላጎት የሚያሟላ ከተማ ማደስ ወጥ የሆነ የፖሊሲ ማዕቀፍ፣ ጠንካራ ተቋምና
ግዙፍ የፋይናንስ ሀብት ይጠይቃል፡፡ እነዚህ ግብዓቶች ሳይሟሉ የሚካሄድ የከተማ ማደስ ፕሮግራም አንድም
ዓላማውን ሳያሳካ ተንገራግጮ ሊቆም የሚችል፤ በግፊት እንዲቀጥል ከተደረገም የሚያስከፍለው ኢኮኖሚያዊና
ማህበራዊ ዋጋ ከባድ ይሆናል፡፡

3.2.2. መልሶ ልማት አጀማመር


መልሶ ልማት የሚጠይቅ ሁኔታ የተፈጠረበት ምክንያት ከከተማ ከተማ ይለያያል፡፡ በርካቶቹ ከተሞች
ከአመሰራረታቸውና ቀደምት ዕድገታቸው ታሪክ በቀጥታ የተያያዘ ሲሆን እንደ መቐለ እና ሀዋሳ ባሉ ከተሞች
ደግሞ የነባር ሰፈሮችና ቤቶች እርጅና የወለደው ሳይሆን በዋናነት የከተሞቹ አጠቃላይ ዕድገት የወለደውን
የመሬት ኢኮኖሚያዊ ዓቅም ወደ ከፍተኛ ፋይዳ ለማዋል ሲባል ነው፡፡

በየከተማው በመካሄድ ላይ የሚገኙ የመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች ትግበራ አጀማመሩም እንደየከተሞቹ


ነባራዊ ሁኔታ የተለያየ ነው፡፡ የመልሶ ማልማት ቀደም ብላ የጀመረችውና ከሌሎች ሰፋ ያለ ቦታ ማልማት
የቻለችው አዲስ አበባ ከተማ የልማቱ አጀማመር ስንመለከት በመጀመሪያዎቹ 60 አመታት የመከተም ሂደት
ስለነበር እድሳት የሚባል አጀንዳ አልነበረም፡፡ ነገር ግን ከዚያ በኃላ ስፋቱና የአፈጻጸም ስልቱ ይለያይ እንጂ
የከተማ ማደስ ስራ ለአዲስ አበባ ባዕድ አልነበረም፡፡ በተወሰነ ደረጃ ከጣልያን ወረራ በፊትና በኃላም
በመንገድ መክፈትና ማሻሻል እንዲሁም ዘመናዊነት ሲመጣ በአንድና ሁለት ይዞታዎች ላይ የሚደረግ አፍረሶ
መገንባት ነበር፡፡ በአዲስ አበባ ነባር አከባቢዎችን አፍርሶ ለአዲስ ግንባታ ማዋል ከጣሊያን ወረራ በፊት

69
ብዙም የሚታወቅ አልነበረም፡፡ በአምስት አመቱ የወረራ ዘመን የራስ መኮነን ሰፈር ተብሎ ይጠራ ከነበረው
(አሁን ካዛንቺስ ተብሎ በሚጠራው 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ አከባቢ) በርካታ የሀገሬውን ተወላጆች ያፈናቀለ
እርምጃ እንደተወሰደ የታሪክ ተመራማሪዎች ያስረዳሉ (ሪቻርድ ፓንክረስት 1986)፡፡

እላይ በተጠቀሰው አከባቢ ለጣሊያን ሹማምንቶች መኖሪያ ቤት ግንባታ ሲባል እ.ኤ.ኤ ከ1937 - 1940
በነበረው ጊዜ 5,409 አባወራዎች ከአካባቢው ተነስተው ለሀገሬው ተወላጅ መኖሪያ እንዲሆን ወደ ተዘጋጀው
ሥፍራ (በአሁኑ ጊዜ አዲስ ከተማ) እንዲሠፍሩ ተደርጓል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሀገሬውን ተወላጅ
ከጣሊያኖች መኖሪያ አከባቢ ለማራቅ ሲባል ከተቀየሰው የአከባቢ ጤና ማሻሻያ ፕሮግራም ጋር በተያያዘ
ከ1937 - 1938 በነበረው የሁለት ዓመት ጊዜ 30,000 የሚሆኑ የሀገሬው ተወላጆች ከተለያዩ አካባቢዎች
ተነስተው ወደ አዲስ ከተማ እንዲዛወሩ መደረጉን እላይ በተጠቀሱት የታሪክ ተመራማሪዎች ተገልጿል፡፡

ይህም እርምጃ በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያው በሰፈር ደረጃ የተካሄደ የመልሶ ማስፈር ፕሮግራም ተደርጎ
ሊወሰድ ይችላል፤ ከዚያ በፊት እዚህም እዚያም ለመንግሥት መስሪያ ቤት የቢሮ ሕንፃ እና ለመንገድ ግንባታ
አገልግሎት የሚውል ቦታ ሲፈለግ ነባር ግንባታዎች ይፈርሱ እንደነበር የሚታወቅ ቢሆንም ከ1937 ዓ.ም በፊት
ይካሄድ የነበረው ቦታ የማስለቀቅ እርምጃ ከአንድ ይዞታ (Single plot) የሚዘል አልነበረም፡፡

ከ1940ዎቹ-60ዎቹ ከተማዋን ዘመናዊነት ለማላበስ እንዲሁም የመንገድና ሌሎች የመሠረተ ልማት አውታሮችን
ለመዘርጋት በተደረጉ እንቅስቃሴዎች ደግሞ በመሃል ከተማ በርካታ ግንባታዎች ሲፈርሱ የመሰረተ ልማት
ዝርጋታው በከተማውን ነዋሪ ዘንድ እንደ ልማት ሳይሆን እንደ ጥፋት ትኩረት የሳበ ቁልፍ የሕዝብ አጀንዳ
ነበር፡፡ በዚህ ዕይታም ከተባሉት የወቅቱ ሥነ-ቃል አንዱ፡
ጣልያንም መጣ ሄደ ተመለሰ
እንግሊዝም መጣ ሄደ ተመለሰ
ሙሴ ሚናስ ቀረ ቤት እያፈረሰ
ተብሎ ተገጥሞለት ነበር፡፡ ሙሴ ሚናስ በወቅቱ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ይሠራ የነበረ መሃንዲስ ሲሆን
በመሃል አዲስ አበባ የመንገድ አውታር ባልተዘረጋባቸው አከባቢዎች መዳረሻ መንገድ ለመክፈት ሲባል
የተካሄዱ ግንባታ የማፍረስ እንቅስቃሴዎችን በበላይነት ይመራ የነበረ ባለሙያ ነው፡፡

ከዚህ ባሻገር በጥልቅ እርጅና ውስጥ ወድቆ የነበረውን የተ/ሃይማኖት አከባቢ ለማሻሻል ከ1960ዎቹ ጀምሮ
የተለያዩ የነባር ከተማ ማሻሻያ /urban upgrading/ ፕሮግራሞች ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ
ሲካሄዱ ቆይቷል፡፡ ይህ እንቅስቃሴ በነባር አከባቢ ማሻሻያ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያው
የተሟላ እርምጃ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ከመጀመሪያው ዙር የተክለሃይማኖት ነባር አከባቢ ማሻሻያ ፕሮግራም ትግበራ ጋር በተያያዘ 91 አባወራዎች


ከአከባቢው ተነስተው ኮልፌ አከባቢ የከተማው ማዘጋጃ ቤት ወደ አሠራቸው ቁጠባ ቤቶች ተዛውረዋል፡፡
በቀደምት ጊዚያት ሰፋ ያለ መልክ የነበራቸው የመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶችን በ1974 ለሚኒስትሮች ምክር
70
ቤት ቢሮና ለብሄራዊ ሸንጎ አዳራሽ ግንባታ ታስቦ እንዲፈርስ የተደረገው አሁን ለሸራተን የተሰጠው ቦታ (3-4
ሄክታር) በከፊል የመጀመርያው ነው፡፡ ከቦታው የተነሱት 500 አከባቢ አባዎራዎች በወቅቱ ብርጭቆ ፋብሪካ
አከባቢ መንግስት ባስገነባው ቤት ሰፍረዋል፡፡ ከዚያ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዲሱ አዳራሽ የተሰራበት
(3-4 ሄክታር) ቦታ ይጠቀሳል፡፡ በመቀጠል የደንበል ህንጻ የተሰራበት (3-4 ሄክታር) ወዘተ፡፡

ከዚያም ሰፋ ባለ ሁኔታ የተሰራው የሸራተን ሆቴል መገንቢያ ቦታ (5-7 ሄክታር) እና የቀለበት መንገድ ስራ
ፕሮጀክቶችን ማንሳት ይቻላል፡፡ ለቢሮ ታስቦ ኃላ ለሸራተን ከተመደበው እንዲሁም ከቀለበት መንገድና
የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ግንባታ ውጭ በወቅቱ መልሶ ማልማቱ በአብዛኛው የተከናወነው በግል
ባለሀብት ፍላጎትና ማኔጅመንት ነበር፡፡ በነዚህ አከባቢዎች የነበረው ቤት ይዞታ በአብዛኛው የመንግስት
ስለሆነ የግል ባለሀብቱ ቦታዉን ለማልማት ሲፈልግ ከግል ባለይዞታዎች ጋር የሚያገናኘው ጉዳይ አልነበረም፤
በመሆኑም ፍላጎት ያለው ባለሀብት የማልማት ፍላጎቱን ለመንግስት በማቅረብና በማሰፈቀድ የተከናወነ መልሶ
ማልማት ሂደት ነበር፡፡

የተክለሃይማኖት ነባር አከባቢ ማሻሻያ ፕሮግራም ቀጣይ ምዕራፍ (ዘጠኝ ቀበሌዎች የሚሸፍን) በ1980ዎቹ
መጀመርያ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተደረገ፡፡ የፕሮግራሙ ይዘት የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ፣ የንፁህ ውሃ
አቅርቦትና የጽዳት አገልግሎት ማሻሻያ ሥራዎችን በሚቀርፍ መልኩ የተቀረጸ ነበር፡፡ ሆኖም የፕሮጀክቱ
ድኅረ-ትግበራ ግምገማ ውጤት እንደሚያመለክተው የታለመለትን ዓላማ አላሳካም፡፡ መንገዶቹ በሚገነቡበት
መስመር ላይ የነበሩ ቤቶች እንዳይፈርሱ ከነዋሪው ተቃውሞ በመነሣቱ ምክንያት የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን
በሁሉም አከባቢ ማዳረስ አልተቻለም፡፡ በመጠጥ ውሃ አቅርቦት በኩልም የቦኖ ውሃ-ነዋሪ ጥምርታን ከ1፡600
ወደ 1፡100 ዝቅ ለማድረግ ታቅዶ ማሳካት የተቻለው ጥምርታውን ወደ 1፡254 ብቻ ነበር፡፡ አብዛኛው ነዋሪ
የቀበሌ ቤት ተከራይ በሆነበት አከባቢ የቤቶቹ ባለቤት ባለመሆኑ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር የህዝብ መፀዳጃ
ቤቶች ለመገንባት የራሱ ንብረት ላልሆነ ቤት ለሚሠራ መፀዳጃ ቤት ብድር ለመውሰድ ፍቃደኛ ሆኖ
ስላልተገኘ ፕሮግራሙን በታሰበው ደረጃ መተግበር አልተቻለም፡፡

በዓለም ባንክ ድጋፍ ከተካሄደው የነባር አከባቢ ማሻሻያ ፕሮግራም በተጨማሪ በተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ
ድርጅቶች አማካይነት ተመሳሳይ የነባር አከባቢ ማሻሻያ ሥራዎች ሲከናወን ነበር፡፡ በከተማው በዚህ ሥራ ላይ
በስፋት ከተሳተፉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (መያዶች) መካከል፡
 ሬድ ባርና
 ኮንሰርን
 የተቀናጀ ከተማ ልማት ፕሮግራም (በሲስተር ጀምበር ይመራ የነበረ)
 አገር በቀል መያድ/
 ኬር ኢትዮጵያ
 የማህበራዊ ተሃድሶ ልማት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ተቋም
በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
71
ሬድ ባርና በጥልቅ እርጅና የተጎዱ ቤቶችን በባለ አንድ ፎቅ ቁጠባ ቤቶች በመተካት እንዲሁም ፕሮጀክቱ
በሚያቅፋቸው አከባቢዎች የሚኖሩ ቤተሰቦችን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች የሚቀርፉ እንደ ብድርና
የሥራ ዕድል ፈጠራ ያሉ ድጋፎችን አቀናጅቶ በማቅረብ በይዘት ወደ ከተማ ማደስ የሚቀርብ ጥረት
አድርጓል፡፡ በዚህ የመልሶ ልማት ፕሮግራም በከተማው የተለያዩ አከባቢዎች 540 የሚሆኑ ባለአንድ ፎቅ
ቁጠባ ቤቶች ተሠርተው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች እንዲከፋፈሉ ተደርጓል፡፡

የሬድ ባርና ነባር አካባቢ ማሻሻያ ፕሮግራም ዓላማ የቁጠባ ቤቶችን ለድሃው የሕብረተሰብ ክፍል ከማቅረብ
ባሻገር ገቢያቸው ዝቅተኛ የሆኑ ቤተሰቦችንና ልጆቻቸውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ አከባቢያዊ ሁኔታ
ማሻሻልን ያካትት ነበር፤ በልማት ሂደቱ በተለይ ለሴቶችና ለወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ልዩ ትኩረት ይሰጥ
እንደነበርም የፕሮጀክት ሰነዶች ይጠቁማሉ፡፡ የተጠቃሚዎችን የራስ መተማመን መንፈስ በማሳደግ፣
ህብረተሰቡ የራሱን ፍላጎትና ችሎታ እንዲገነዘብ በማድረግ፣ የጋራ ችግርን በጋራ የመፍታት ጥቅምን
ህብረተሰቡ እንዲረዳ በማድረግና በማበረታታት፣ ለገቢ ማስገኛ ዘዴዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት የፕሮጀክቱን
ዓላማ ዘላቂነት ለማረጋገጥ በዚህ ፕሮጀክት ሰፊ ጥረት ተደርጓል፡፡

በዚህ መሠረት ከሬድ ባርና የከተማ ማሻሻያ ፕሮጀክት ብዙ መማር ይቻላል፤ ህብረተሰቡ የራሱን ችግር በራሱ
እንዲለይ እና የመፍትሄውም አካል እንዲሆን በቂ እድል መስጠት በነባር ከተማ መልሶ ልማት ሂደት ትልቅ
እርምጃ ነው፡፡ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ሕይወት (ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ አከባቢያዊ) የሚያሻሽሉ
እርምጃዎች በፕሮጀክቱ እንዲታቀፉ መደረጉ ሌላው ከዚህ ፕሮጀክት የምንማረው ትልቅ ትምህርት ነው፡፡

ይሁን እንጅ በዚህ ፕሮጀክት የተሰሩ ቤቶች አሁን ባለበት ሁኔታ ኗሪዎቹ 20 ዓመት የሚጠበቀውን ከፍለው
ጨርሰው ከ1996 ጀምሮ የጣሪያ ግብር እና የአፈር ኪራይ ለከተማው እየከፈሉ ነው፡፡ ነገር ግን የይዞታ
ማስረጃ ጥያቄ ለከተማው አቅርበው ምላሽ እንዳላገኙ ይገልጻሉ፡፡ በመሰል ሁኔታ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተሰሩ
ቤቶች ኗሪዎች በተለየ መልኩ የቤቱ ኪራይ ለቀበሌ ስለሚከፍሉ 55% ወጪውን የከፈሉት ለራሳቸው ማህበር
ሲሆን 45% ድጎማ ነው፡፡ የቤቱ ባለቤት በሚመለከት ግን መልስ ሳያገኝ ተንጠልጥሎ ይገኛል፡፡

የሌሎቹ መያድዎች ተሳትፎ በነባር ከተማ ማሻሻያ ፕሮግራም (urban upgrading) ላይ የሚያተኩር ሆኖ
በሲስተር ጀምበር ይመራ ከነበረው የተቀናጀ የከተማ ልማት ፕሮግራም በስተቀር የሌሎቹ እንቅስቃሴ በአንድ
ወይም በሁለት ሥራዎች የተወሰነ ነበር፡፡ ለምሳሌ የኬር እንቅስቃሴ በአብዛኛው በውስጥ ለውስጥ የድንጋይ
ንጣፍ መንገድ ግንባታ የተወሰነ ሲሆን የማህበራዊ ተሃድሶ ልማት ፕሮግራም በአመዛኙ በማህበራዊ
አገልግሎት ማሻሻያ ሥራዎች ላይ የሚያተኩር ነበር፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የነባር ከተማ ማሻሻያ ፕሮግራም በተሻለ አደረጃጀትና ዝግጅት ተግባራዊ መደረግ
የጀመረው ከ1983 በኋላ ነው፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በተደራጀ መንገድ በመዲናዋ የተንሰራፋውን የከተማ
እርጅና (severe urban decay) ችግር ለመቅረፍ ተንቀሳቅሷል፡፡ የከተማ መሬት ሊዝ አስተዳደር አዋጅ

72
መውጣትን ተከትሎ በከተማው ነባር አከባቢ ከደረጃ በታች የሆኑ ግንባታዎችን አንስተው አዲስ
ኢንቨስትመንት እንዲያካሂዱ ከከተማ አስተዳደሩ ለግል አልሚዎች በተላለፈ ጥሪ መሠረት በርካታ ባለሃብቶች
የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና ፕሮጀክቱን ለማካሄድ የመረጧቸውን አከባቢዎች በመጠቆም
በድርድር መሬት ወስደው ለማልማት ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡ በወቅቱ ይህን አሰራር ተከትለው ሥራ
ላይ የዋሉት ፕሮጀክቶች ቁጥር ጥቂት አልነበረም፤ በዚህ መንገድ ከተተገበሩ ፕሮጀክቶች መካከል የመርካቶ
መልሶ ልማት፣ የኮልፌና የጨርቆስ ገበያ ልማት፣ የደንበልና ሸራተን ሆቴል ፕሮጀክትን በምሳሌነት መጥቀስ
ይቻላል፡፡

ከዚህ እውነታና ከወቅቱ የከተማው ዕድገት ፍላጎት በመነሣት የከተማ አስተዳደሩ መሃል አዲስ አበባን መልሶ
የልማት ፕሮግራም እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ለምሳሌ በ8 ዓመት ጊዜ (ከ2001 - 2008) በመሃል አዲስ
አበባ 392 ሄክታር ስፋት ያለው መሬት ለመልሶ ልማት ፕሮግራም የዋለ ሲሆን 25,101 አባወራዎች ከነባር
መኖሪያቸው እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ 23,151 ግንባታዎች በመልሶ ልማት ፕሮግራም ፈርሰው
በአዳዲስ ልማቶች በመለወጥ ላይ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን እስካሁን የተከናወነው ስራ ከችግሩ ስፋት አኳያ ሲታይ
እዚህ ግባ የማይባል ነው፡፡

በድምሩ ሲታይ የአዲስ አበባ ከተማ መልሶ ማልማት ታሪክ የሚያሳየው ቀድመውም ቢሆን በአጋጣሚ
የተጀመረ ሳይሆን (ዓላማው የተለያየ ምክንያት ቢኖረውም) በታቀደ አኳኃን ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በተለይ
ላለፉት ስምንት ዓመታት የተካሄዱ የመልሶ ማልማት ስራዎች በዕቅድም በስፋትም የተሻሉ ናቸው፡፡ ከተማዋ
መልሶ ለማልማት የከተማ አስተዳደሩ የሚወስዳቸው እርምጃዎች ዘርፈ ብዙ ናቸው፡፡ ነባሩን የከተማ ክፍል
በማደስ በኩል የበሰበሱ ሰፈሮችን አፍርሶ እንደ አዲስ እንዲገነቡ ማድረግ ከዚህ ጋር ተያይዞም ደረጃቸውን
የጠበቁ ቤቶች በመገንባት በከተማው ተንሰራፍቶ የቆየውን የመኖሪያ ቤቶች እጥረት መፍታት፣ መዳረሻ
መንገድ ለሌላቸው አከባቢዎች አዲስ መንገድ መክፈት፣ የነባር መንገዶችን ደረጃ ማሻሻል፣ የፍሳሽና ጎርፍ
ማስወገጃ መስመሮችን መዘርጋት፣ የማህበራዊ አገልግሎት አቅርቦትን ማሻሻል፣ የዋና ዋና ጎዳናዎችና
አደባባዮች ዳርቻ (Business corridor) ማልማት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ካጠቃላይ ይዘት እና ስፋት አኳያ ሲታይ የከተማው ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ ያልተመሰረተ ቢሆንም የደሴ
ከተማ መልሶ ማልማት አጀማመርም በአንድ ወይም በሌላ መልክ በዕቅድ ነበር ብሎ ማስቀመጥ ያስደፍራል፡፡
በከተማው መልሶ ማልማት የተጀመረው የአማራ ክልል መልሶ ልማትንም የሚመለከት ምንም ዓይነት የህግ
ድጋፍ ሳያወጣ ነበር፡፡ ከተማዋ ቀደም ብላ የራሷ የከተማ አቀፍ መሬት ነክ ፖሊሲ በማውጣት ነበር መልሶ
ማልማቱን የጀመረችው፡፡ መልሶ ልማት ማካሄድ ያስፈለገበት ምክንያትም ከተማዋ ማስፋፍያ ክፍት ቦታ
እጥረት ስላጋጠማት የመሬት አቅርቦት ፍላጎቱ ለመመለስ ሲባል እንደሆነ ፖሊሲው በግልፅ ሰፍሮ ይገኛል፡፡

በፖሊሲው ውስጥ መልሶ ልማቱ በስኬት ለማስኬድ የተቀመጡ አቅጣጫዎች ሲታይ የሚያፈናቅላቸው
ነዋሪዎች በተቻለ መጠን ውስን እንዲሆን ይህም ለተነሺዎች የሚከፈል የካሳ ወጪ ለመቀነስና ለአስተዳደራዊ

73
ቅለት ታሳቢ ስላደረገ ነበር፡፡ የፖሊሲ ሰነዱ የሚያመላክተው ሌላ የትኩረት አቅጣጫ መልሶ ማልማቱ የቀበሌ
ቤቶች ባሉበት አካባቢ እንዲሆን ነበር፡፡ በመልሶ ልማት ምክንያት ከሚኖሩበት የቀበሌ ቤት ለሚፈናቀሉ
ምትክ የቀበሌ ቤት እንዲሰጣቸው ካልሆነ ደግሞ የከተማው አስተዳደር መጠለያ ሰርቶ እንዲያቀርብ፣
ከተማው የንግድ ቦታ መልሶ ማልማት ሲፈለግ ደግሞ በቦታው ለሚነግዱ ወገኖች በሊዝ መነሻ ዋጋ ቅድሚያ
የማልማት ዕድል መስጠት እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ በተቻለ መጠን የልማት ተነሺዎች ፍትሓዊ አያያዝ
እንዲደረግላቸው የታሰቡ አቅጣጫዎች ነበሩ፡፡ አልሚዎች በመልሶ ልማት ኢንቨስትመንት ለማበረታታት
ሲባል የመሬት የሊዝ ማስተላለፍያ ዋጋው በጨረታ ከሚሆን በመነሻ ዋጋው እንዲሆን የተነደፉ ስልቶች ነበሩ፡፡

ከፖሊሲ ማውጣትና ቦታ መረጣ በኋላ ማህበረሰቡን ለማወያየት ጥረት ሲደረግ ነበር፡፡ የመነሻ ሃሳቡ
ለውይይት ሲቀርብ የንግዱ ማህበረሰብ ባሉበት ሁኔታ አትራፊና ምቹነት ይሰማቸው ነበር፡፡ በመጀመርያ
መልሶ እንዲለማ በተፈለገ ቦታ አዳዲስ ግንባታዎች ቢገነቡ ከነበራቸው ገቢ የተሻለ ገቢ ሊያገኙ እንደሚችሉ
ስላልታያቸው ቦታ ለማደስ ሰፊ ተቃውሞ ሲያሰሙ ነበር፡፡ በሂደት ግን ከተማው አካሄዱን በመለወጥ ሌሎች
ከተሞች ሲለሙ ደሴ “ሰው እንደሌላት ወደ ኋላ ቀረች” የሚል አቀራረብ ሲይዝና የቀበሌ ቤትን ማፈረስ
መብቱ እንደሆነ ስለገፋበት የተወሰኑ ባለሀብቶች በመነሃሪያ አካባቢ ሂደቱን ደግፈው ወደ ስራ ገቡ፡፡

እነዚህ ባለሀብቶች ህንጻቸው ተገንብቶ ሳያልቅ ተጨማሪ ገቢ የማግኘት፣ ተገልጋዩ ንጽህና ያለውን ህንጻ
መርጦ የመጠቀም ሂደት ሲያሳይና በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድም (እንዴት እሱ ከኔ በላይ ከፍ ብሎ ያየኛል
የሚል ጭምር) ከቢዝነስ ወጣ ያለ የውድድር መንፈስ መፈጠር መጀመሩ ወደ መልሶ ማልማት ገብተዋል፡፡
በዚህም ከ1989 ዓ/ም መጨረሻ ጀምሮ እስከ 1998 ባለው ጊዜ ብቻ 168 ባለሀብቶች ቦታ በሊዝ በመውሰድ
43 ግንባታ ጨርሰው ወደ አገልግሎት መስጠት ደረጃ ሲደርሱ 41 ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ እንደነበሩ በወቅቱ
በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ በአካባቢ ልማት ዙሪያ በሚሰጥ ስልጠና ሰነድ ዝግጅት አካል የተደረገ ጥናት ያሳያል፡፡
በዚሁ ሰነድ እንደተጠቀሰው በሂደቱና በአፈጻጸሙ የተለያዩ ችግሮች እንደነበሩም ተጠቅሰዋል፡፡ ከተጠቀሱት
ዋና ዋና ችግሮች ለመጥቀስ ያህል፡-
 ለመልሶ ማልማት ቦታ መምረጫ መስፈርት የተጎዳ ማህበረሰብ ያለበትና ህይወቱ በቀዳሚነት መቀየር
ያለበት ወገን የሰፈረበትን ቦታ አፍርሶ መለወጥ የሚል አካሄድና ሰውን ማዕከል ያላደረገና ሰውን
መለወጥ የሚል መርህ ያለመከተሉ፤
 የወቅቱ የከተማው ፖሊሲ የግል ባለይዞታዎችና የክራይ ቤቶች ድርጅት ተከራዮችን በተመለከተ
በዝምታ ያለፈ በመሆኑ የቀበሌ ቤቶች ፈርሰው ሲሰሩ እነዚህ ይዞታዎች በአነስተኛ መጠን ጭምር
ተለጥፈው ተቆርጠው መቅረትና የታለመው ውበት መኩሰስ፣ መሬት አጠቃቀሙ መዛባት እና የገነቡ
ባለሀብቶች ካለሙት ልማት ሊያገኙት ይገባ የነበረ የላቀ ተጠቃሚነታቸው እንደቀነሰባቸው፤
 ከተማው ባለሀብቱን እንዲገነባ ሲያደፋፍር እራሱ መስራት ያለበትን አብሮ የሚሄድ መሰረተ ልማት
አለመስራቱ (ለምሳሌ ፍሳሽ ማስወገጃ) ልማቱ የተሻለ ጥራት እንዳይኖረው ያደረገ ነበር፤

74
 ልማቱ በተሟላ የአካባቢ ልማት ፕላን የታገዘ ባለመሆኑ ግንባታው ፊቱን ወደ ዋናው መንገድ ብቻ
የዞረና የኋላውን እንዲለማ ሳይሆን እንዲሸፈን በማድረጉ ልማቱ አከባቢውን ማነቃቃት አለመቻሉ፤
 ግንባታው እየሰፋ ሲሄድ ሁሉም ግንባታውን የላቀ ጥቅም በሚሰጠው ንግድ ብቻ እንዲውል በማሰብ
መገንባት ጎን ለጎን የተፈጠረው ተጨማሪ የስራ ቦታ በማስተዋወቅ ረገድ ከተማው የሰራው ነገር
ስላልነበር ከመጀመሪያዎቹ ግንባታዎች ውጭ ከሁለተኛው ፎቅ በላይ ክፍት መሆን በዚህም
ባለመበረታታት ያልተጠናቀቁ ጅምር ህንጻዎች መበራከት የሚሉ ይገኙበታል፡፡

የጅማ ከተማ መልሶ ማልማት አጀመማር ምክንያት ከሌሎች ከተሞች ለየት ያለ ነው፡፡ ልማቱ እንዲጀመር
ካስቻሉት ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ የከተማው እምብርት እና ዋነኛው የከተማው የቢዝነስ ስፍራ በሆነው
መርካቶ እጅግ የተጨናነቀ ከመሆኑም በላይ የነዋሪውና የንግዱ እንቅስቃሴዎች ማስተናገድ የሚችል የመንገድ
መሰረተ ልማት አለመኖሩ ነው፡፡ መንገዶቹ ጠባብና በስርዓት ያልተደራጁ ነበሩ፡፡ በዝናብ ወቅት እግረኛም
ሆነ ተሽከርካሪ የማይንቀሳቀስባቸው እንደነበሩ ነዋሪዎች ያወሳሉ፡፡ ከዚህ ችግር በመነሳት አካባቢው ስርዓቱና
ደረጃው የጠበቀ የመንገድ መሰረተ ልማት እንዲገነባለት ነዋሪው ለዘመናት ሲጠይቅ ነበር፡፡ ይህንን ችግር
ለመፍታት የልማት ፎረም በማቋቋም እንቅስቃሴ ሲደረግ የቆየ ሲሆን በወቅቱ በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ
ፕሮግራም (ቴሎቶን) ቃል ከተገባው ብር 106,000,000 ብር 36,000,000 ተሰብስቦ 20-25 ሜትር ስፋት
ያለው አስፋልት መንገድ በመገንባት ነበር ልማቱ የተጀመረው፡፡

ሁለተኛው ምክንያት የኢትዮጵያ ሚለኒየም በሀገር አቀፍ ደረጃ የፈጠረው የልማት መንፈስ መነሳሳት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሁለተኛው ሚሌኒየም ለአንድ ዓመት ያህል በልማት እንቅስቃሴ መከበሩ ለከተሞች ገፅታ ለውጥ
መልካም ዕድል ፈጥሮ ነበር፡፡ የጅማ ከተማም በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንቅሰቃሴው አንድ
ማእከል ሆና በልማት ንቅናቄው ትኩረት ተሰጥቷት እንደነበር በውይይት ጊዜ ተገልፀዋል፡፡ የከተሞች ገፅታ
ለመለወጥና ዕድገታቸው በኢንቨስትመንት ለማፋጠን እንቅስቃሴ ሲጀመር የክልሉ መንግስትና የከተማው
አስተዳደር የአከባቢው ባለሀብቶች በከተማው በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሳተፉ ጥሪ ሲያቀርቡ
ከሀገር ውጭና በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ባለሃብቶች እንዲሁም የከተማው ነዋሪዎች በአክሲዮኖች በመደራጀት
በግንባታ ኢንቨስትመንት ተሰማርተዋል፡፡

በውል ባልታቀደ የተጀመረው የጅማ ከተማ መልሶ የማልማት ጥረት የሊዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 መደንገግን
ተከትሎ ከ2005 ዓ/ም ወዲህ መልሶ ልማት በአካባቢ የልማት ዕቅድ ማዕቀፍ እንዲመራ የሚያስችል
የአቅጣጫ ለውጥ ለመቀየስ ተደርሷል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ መልሶ ማልማት አጀማመርም የራሱ የሆኑ ሶስት መሰረታዊ ምክንያቶች ያሉት እንደሆነ
ከአስተዳደሩ አተያይ ለመገንዘብ ይቻላል፡፡ አንደኛው ቁልፍ ምክንያት እንደሌሎቹ ከተሞች ከተማዋ ረጅም
ዕድሜ ያስቆጠረች ከተማ እንደመሆኗ መጠን የደቀቁ እና የወደቁ አካባቢዎች በስፋት ይታዩባታል፡፡ ጥልቅ

75
የከተማ እርጅና (Urban Degeneration) ከሚስተዋልባቸው ነባር አካባቢዎች መካከል ከዚራ፣ መጋላ፣
ለጋሃሬ፣ ገንደ ቆሬ፣ ታይዋን/ፖሊስ መሬት/፣ ነምበር ዋን እና ጎሮ ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛሉ፡፡

ስእል 3.6፡ በድሬዳዋ የሚስተዋለው የግንባታ እርጅና ገጽታ

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ


በድሬዳዋ ነባር ሰፈሮች የሚገኙ ግንባታዎች እድሜ ጠገብ መሆናቸው ባያከራክርም አብዛኞቹ ግድግዳቸው
ከድንጋይ፣ ሸክላና ብሎኬት የተገነባ በመሆኑ በቀላሉ ታድሰው የሚሻሻሉ ናቸው፡፡ በድሬዳዋ ነባር አካባቢ
በግንባታው ላይ ከሚስተዋለው የከተማ እርጅና ይልቅ የኢኮኖሚ ድቀቱ የከፋ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

ስእል 3.7፡ የድሬዳዋ ነባር አካባቢ ገጽታ

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ


ከከተማው ምሥረታ ጀምሮ የድሬዳዋ ኢኮኖሚ ከኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መስመር እንቅስቃሴ ጋር በጥብቅ
የተቆራኘ ስለነበር የዚህ ኩባንያ እንቅስቃሴ መቆም የድሬዳዋ እንቅስቃሴ እጅግ እንደጎዳው በርካታ አስተያየት
ሰጪዎች ይገልፃሉ፡፡ የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ኩባንያ እንቅስቃሴ በመቋረጡ የተነሣ ከድሬዳዋ በላይ ሰለባ የሆነ
ሌላ ከተማ ይኖራል የሚል ግምት እንደሌላቸው እነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች ያሰምሩበታል፡፡ የጥናቱ ቡድኑም
በመስክ ምልከታው ያስተዋለው እውነታ ይህን ግምት የሚያጠናክር እንጂ የሚያፈርስ አይደለም፡፡

ቀደም ሲል ከፍተኛ የንግድና የሕዝብ እንቅስቃሴ መናሃሪያ እንደነበሩ የሚነገርላቸው እንደ ከዚራ፣ ለጋሃሬ፣
መጋላና ቀፊራ ባሉ የከተማዋ ነባር አካባቢዎች በአሁኑ ጊዜ የሚስተዋለው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የተዳከመ

76
ነው፡፡ ጎዳናዎቹ ሰው አልባ፣ የንግድ እንቅስቃሴያቸው ቀዝቃዛ፣ አጠቃላይ ድባባቸው ጎብኝንም ሆነ ሸማችን
የሚስብ አይደለም፡፡ በዚህ መሠረት የከተማ እርጅና ለድሬዳዋ መልሶ ልማት አጀንዳ እንደ አንድ መሠረታዊ
መነሻ ተገቢ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡

በድሬዳዋ የከተማ መልሶ ልማት (Urban Regeneration) ፕሮግራምን ቁልፍ የልማት አጀንዳ የሚያደርገው
ሁለተኛው መነሻ በከተማው የተቀናጀ ዕድገት ፕላን (IDP) የተቀመጠው ራዕይ እንደሆነ የአስተዳደሩ
ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ያለ ልዩነት ይገልፃሉ፡፡ የትግበራ ዘመኑ በ1998 የተጀመረው የከተማው የተቀናጀ
ዕድገት ፕላን ያረጁ አካባቢዎችን በ50% የመቀነስ ግብ ጥሎ እንደነበር ሰነዶች ያመለክታሉ፡፡

በከተማዋ ዳርቻ ከሚስተዋለው ሕገ ወጥ ግንባታ በስተቀር የድሬዳዋ ከተማ አመሠራረት፣ አደረጃጀትና


ዕድገት ፕላን የተከተለ መሆኑን በምስሉ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

ስእል 3.8: ከአየር ላይ እይታ (Areal Photo)

ምንጭ፡ ድሬዳዋ ከተማ መሬት ልማትና ማነጅመንት


በዚህ መሠረት የድሬዳዋ የተቀናጀ ልማት ፕላን ይህን ታሪካዊ እሴት ይበልጥ በማጠናከር
“በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነች፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ ለኑሮና ለሥራ ምቹ የሆነች፣
የንግድ፣ አገልግሎት እና ኢንዱስትሪ ማዕከል የሆነች ድሬዳዋን”

የማየት ራዕይ የሰነቀ ነው፤ ይህን ራዕይ እውን ለማድረግም ነባሩን የከተማ ክፍል በመልሶ ልማት እንደገና
ማደስ አስፈላጊና ቁልፍ ጉዳይ መሆኑ በፕላኑ በግልጽ ተሰምሮበት ይገኛል፡፡

እላይ ከቀረበው የአየር ካርታ መመልከት እንደሚቻለው የድሬዳዋ አመሠራረትም ሆነ ዕድገት በዘመናዊ
የከተማ ፕላን የተቃኘ ነው፡፡ የከተማዋን ነባር ሰፈሮች ተዘዋውሮ ለተመለከተም ሠፈሮቹ ከምሥረታቸው
ጀምሮ ታስቦበት (By Design) የተወሰነ ሚና የተሰጣቸው መሆኑን ለመገመት አያዳግተውም፤ ከዚራ፣ ለገሃሬ፣
ግሪክ ሠፈርና ነምበር ዋን አካባቢዎች በዋናነት የመኖሪያ ሠፈሮች እንደነበሩ የሚያመላክቱ አሻራዎች እስካሁን
አልጠፉም፡፡ መጋላ፣ ታይዋን እና ቀፊራ በዋናነት የንግድ ማዕከላት ሲሆኑ ኢንዱስትሪዎች የባቡር መስመሩን
ተከትለው የተደራጁ ናቸው፡፡ በከተማው የተቀናጀ ልማት ፕላንም ሆነ እሱን ተከትለው በተዘጋጁ የአካባቢ

77
ልማት ፕላኖች የተቀመጠው አጠቃላይ የዕድገት አቅጣጫም በድሬዳዋ ነባር አካባቢዎች ተሃድሶ
(renaissance) ታሪካዊ ሚናቸውን በመመለስና ከወቅቱ የከተማው ዕድገት ፍላጎት ጋር በማጣጣም ቀደም
ሲል የነበራትን ታሪካዊ ሥፍራ መልሳ እንዲትቀዳጅ ማድረግ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በመጪዎቹ አስር ዓመታት ራሷን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ የሰነቀችውን
ራዕይ እውን ለማድረግ የነደፈችውን የኢንዱስትሪ ልማት እንዲያስተናግዱ በአገር አቀፍ ደረጃ ከተመረጡ
ከተሞች መካከል ድሬዳዋ አንዷ ናት፡፡ ይህን ሀገራዊ ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት በአሁኑ ጊዜ ከተማዋ ሰፊ
ዝግጅት በማድረግ ላይ ትገኛለች፤ ለኢንዱስትሪ ልማት የሚውል ሰፊ መሬት ከማዘጋጀት ጀምሮ፣ አዲሱን
አገር አቀፍ የባቡር ትራንስፖርት የሚያስተናግድ ዘመናዊ ጣቢያ በመገንባት ላይ ትገኛለች፡፡ እነዚህን ግዙፍ
የልማት ሥራዎች ተከትሎም የድሬዳዋ ነዋሪ ብዛት ከ650,000–700,000 እንደሚደርስ የልዩ ዞኑ ጥናት
ሰነዶች ያመለክታሉ፡፡

በአስተዳደሩ የበላይ ኃላፊዎች እንደሚታመነው በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው
ኢንዱስትሪዎች በድሬዳዋ ከተማ ይገነባሉ፤ ይህን ተከትሎ ከተማዋ በብዙ ሺ የሚቆጠር ተጨማሪ ነዋሪ
ትቀበላለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም ይህን ከፍተኛ ሀገራዊ ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት በሚደረገው
ጥረት በከተማው መስፋፊያ አካባቢ ከሚካሄደው የልማት እንቅስቃሴ ጎን ለጎን ነባሩ የከተማው ክፍል
ተጨማሪ ነዋሪ እና ኢንቨስትመንት ማስተናገድ በሚችልበት መንገድ እንደገና መልሶ መልማት አለበት የሚል
ጽኑ እምነት አስተዳደሩ እንዳለው ኃላፊዎቹ ይገልፃሉ፡፡

የነባር ከተማ መልሶ ልማት ፕሮግራም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚነካቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም ቢሆኑ
ድሬዳዋ የኢንዱስትሪ ማዕከል ሆና መመረጥም ሆነ ነባሩ የከተማ ክልል በመልሶ ማልማት ፕሮግራም
መታደሱ እነሱንም ሆኑ ድሬዳዋን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸው መሆኑን እንደሚረዱ በልማቱ ዙሪያ
ከሚሰጡት አስተያየት መገንዘብ ይቻላል፡፡

መቐለ እና ሀዋሳ ከተሞች ላይ ከሌሎቹ ከተሞች ሲነፃፀር መልሶ ማልማት ቀለል ባሉ አጀንዳዎች አማካኝነት
እንደተጀመረ ነው የሚታየው፡፡ ሀዋሳ ላይ የከተማዋ ተወዳዳሪነት እና ዕድገት ለማጠናከር ሲባል ደረጃቸውን
የጠበቁ የከተማ ውስጥ መንገዶች እና የተፋሰስ መሰረተ ልማቶች ለመገንባት የተደረገ እንቅስቃሴ ነበር፡፡ ያረጁ
ሰፈሮች በአዲስ ልማት ለመለወጥ መልሶ ማልማቱ በስፋት የተከሄደበት ባይሆንም ከላይ የተጠቀሱ መሰረተ
ልማቶች በመዘርጋታቸው ምክንያት በፕሎት የተናጠል ልማትን እንዲጀመርና በተበታተነም ቢሆን ከተማ
ለመለወጥ ተስፋ የሚሰጥ ልማት እንዲጀመር አድርጓል፡፡

የመቐለ ከተማ መነሻዎችም በአንድ በኩል 1998 የተዘጋጀውን መዋቅራዊ ፕላን ለመተግበር ሲባል በከተማው
ነባር ሰፈሮች (ቀበሌ 14፣ 13፣ 07፣ 08፣ እንዳስላሰ፣ እንዳየሱስ፣ እንዳማርያም ወዘተ) ፕላን ጠብቆ
ያለመመስረቱ ለእንቅስቃሴ የማይመቹ ከመሆናቸው በተጨማሪ አልፎ አልፎ እርጅናና የመተፋፈግ ክስተት

78
የሚታይባቸው በመሆናቸው አካባቢዎቹ ባሉበት እንዲሻሻሉ (Upgrading)፣ ሙሉ በሙሉ አፍርሶ የማልማት
(Renewal)፣ እንዲሁም አካባቢዎቹ በፕላን ማደራጀት አስፈላጊ ነበር፡፡ በሌላ በኩል መዋቅራዊ ፕላኑ ወደ
ከተማው ያካተታቸው አይናለም፣ ፈለግ ዳዕሮ፣ ላጪ፣ ዓዲሓ፣ ሰራዋት ወዘተ የገጠር መንደሮች አሰፋፈራቸው
ስርዓት የጠበቀ የከተማ ባህሪ ስላልነበራቸው በፕላን ስርዓት ለማስያዝ የአካባቢ የልማት ፕላን ማዘጋጀት
የግድ ብለዋል፡፡ ከገጠር ወደ ከተማ የተካለሉ ሰፈሮች የሚገኙ ባለይዞታዎ ይዞታቸው ሕጋዊ ለማድረግ
እንዲሁም የአሰፋፈር ገፅታቸው የከተማ ፕላኑ ያልተከተሉ በፕላኑ ለማስተካካል ደግሞ ሁለተኛው ምክንያት
ነው፡፡ በመሆኑም ብር 3,000,000 በጀት በመመደብ 12 የአካባቢ የልማት ዕቅዶች (Local Development
Plans) በአማካሪ ተጠንተዋል፡፡ ሰነድ አልባ ነባር ይዞታዎች ሕጋዊ መብት መፍጠር (ማረጋገጥ) የአካባቢ
ልማት ዕቅዶቹ አንድ አካል ተደርጎ በመወሰዱ ብር 600,000 በጀት በመመደብ ይህንን የሚያስፈፅም የሰነድ
አልባና ነባር ይዞታዎች ማስተናገጃ (Regularization) ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ተቋቁሞ ይዞታዎች
ሕጋዊነታቸው እንዲረጋገጥ በቅንጅት እንዲሰራ ነበር የታቀደው፡፡

ባጠቃላይ እንደ ሀገር ድምር ምስሉ ሲታይ በየከተማው ሲካሄዱ የቆዩ መልሶ ልማቶች ድምር ባህሪያቸው
በሁለት መክፈል ይቻላል፡፡ ቀደም ባሉት ጊዚያት ሲከናወን የነበረው የከተማ መልሶ ማልማት ሂደት ሀገር
አቀፍም ሆነ ከተማ አቀፍ ማዕቀፍ ባይኖረውም በባህሪው የአልሚዎችን ፍላጎት ለመመለስ የተደረገ
የተቆራረጠ ይዘት ያለው፣ መሪ ሳይሆን ተከታይ ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተከሄዱ የሚገኙ መልሶ
ማልማት መነሻው የምዕተ ዓመቱ የከተማ ዘርፍ የልማት ግብ፣ የከተማ መሬት በሊዝ ለማስተዳደር የወጣው
አዋጅ 272/1994 እና 1998 ዓ/ም የተዘጋጀው የከተማ ልማት ፓኬጅ ናቸው፡፡ በምዕተ ዓመቱ የልማት ግብ
በ2007 ዓ/ም በከተሞች የደቀቁ አካባቢዎች በግማሽ የመቀነስ ተልዕኮ የነበረው ነው፡፡ የመሰረተ ልማት
ተደራሽነት ማሻሻልም የከተማው ዘርፍ ሌላኛው ትኩረት ነበር፡፡ የሊዝ አዋጅ 272/1994 መልሶ እንዲለማ
የተፈለገው ቦታ ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች የሚስተናገዱበት ስርዓት እንዲሁም የግሉ ዘርፍ በመልሶ ልማት
ኢንቨስትመንት ተሳትፎ ይደነግጋል፡፡ የከተማ ልማት ፓኬጁ በመልሶ ልማት ሊመለሱ የሚገቡ ይዘቶችና
ዝርዝር ግቦች አስቀምጧል፡፡ ስለዚህ እንደ ሀገር ሕጋዊ መነሻ ነበር/አሁንም አለ፡፡ በየከተሞቹ የሚካሄዱ
የመልሶ ልማት ጥረቶች ሲታይ ግን የተለያዩ መነሻ ገፅታዎች አሉዋቸው፡፡

መልሶ ልማት በመቐለ ከተማ በ1998 ዓ/ም የተዘጋጀ መዋቅራዊ የልማት ዕቅድ ለመተግበር ሲባል እንጂ
በከተማው መልሶ ልማት የሚያስፈልገው ቦታ በመኖሩ ምክንያት ታስቦበት የተተገበረ አይደለም፡፡ የተሟላ
ሕጋዊ ሰነድ ያልነበራቸው ይዞታዎች ሕጋዊ የይዞታ ሰነድ ለመስጠት ከደረጃ በታች የሆኑ ነገር ግን እርጅናም
ያላቸው ይዞታዎችና ሰፈሮች በፕላን ለማደራጀት ሲባል እንዲሁም ነዋሪው ቤቱን ለማሻሻል የግንባታ ፈቃድ
ሲጠይቅ የአካባቢው የፕላን መስፈርቶችና የመሬት አጠቃቀም ያሟላ ግንባታ እንዲያከናውን ስለሚደረግ
በእግረ መንገዱ የታሰበ ነበር፡፡ ደሴ ከሌሎች ከተሞች በተለየ መልኩ ሂደቱን ያስጀመረችው የራሷ የሆነ
የከተማ አቀፍ መሬት ነክ ፖሊሲ በማውጣት ነበር፡፡ የደሴ ከተማ መልሶ ልማት አብዛኛው የከተማው ክፍል
ማርጀትና ለኑሮም ሆነ ለስራ አመቺ አለመሆን መነሻ አላደረገም፡፡ ዋና ምክንያቱ የማስፋፊያ ቦታ ዕጥረቱ

79
ለመፍታት ያለመ ነበር፡፡ ጅማ ከተማ ላይ የነዋሪው የቆየ የመሰረተ ልማት ጥያቄ እና የሁለተኛው ሚሌኒየም
የፈጠረው የልማት መነቃቃት የግል ባለሀብት የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች መነሻ ምክንያቶቹ ናቸው፡፡

ከጥናቱ ለመረዳት የተቻለው ከአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ውጭ መልሶ ማልማት ሲጀመር በመርህ
ላይ ተመስርቶ የከተሞቹ የረጅም ጊዜ የልማት ራዕይና ዓላማ ለማሳካት የታሰበ አልነበረም፡፡ የአዲስ አበባና
ድሬዳዋ መነሻ ምክንያት አጠቃላይ ሀገራዊ መነሻዎቹ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ አንደኛው የከተሞቹ ሀገራዊ
ተልዕኮ ሲሆን ሁለተኛው የደቀቁ አካባቢዎች 50% ለመቀነስ የምዕተ ዓመቱ የልማት ግብ ነው፡፡ በሌሎቹ
ከተሞች አንድም የአጭር ጊዜ ችግር ለመፍታት ሲባል የሚሰራ ካልሆነም በእግረ መንገዱ የሚከናወን ተደርጎ
ሲታይ ቆይቷል፡፡

3.2.3. ቦታ መረጣ መስፈርትና ሂደቱ


መልሶ ልማት ማከናወን ያስፈለገበት ምክንያትና ልማቱ እንዲያሳካው የሚፈለገው ዓላማ እንዲሁም የልማቱ
ይዘት ምን መሆን እንዳለበት ከታወቀ በኃላ ቀጣዩ ተግባር ፕሮጀክቱ የሚተገበርባቸው ቦታዎች መምረጥ
እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር እያንዳንዱ ከተማ መልሶ ማልማት የሚተገበርባቸው ቦታዎች ለምረጥ
የተከተላቸው መርሆችና ዝርዝር መስፈርቶች ምን ይመስሉ እንደነበሩ ከዚህ በታች በየከተማው በዝርዝር
ቀርቧል፡፡

በአዲስ አበባ የከተማ ማደስ ፕሮግራም የሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚለዩበት መንገድ እንደ ፕሮጀክቶቹ
ዓይነትና እንደ አስፈፃሚዎቹ ማንነት ይለያያል፡፡ ነባር አካባቢዎችን የተሻለ የመኖሪያና የሥራ አካባቢ
ለማድረግ የሚካሄዱ የልማት ሥራዎች በርካታ ናቸው፤ ከእነዚህ መካከል፡-
- የዋና መንገዶችን ደረጃ የማሳደግ፣
- የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የማሻሻል፣
- የጎርፍና ፍሳሽ ማስወገጃ መስመር የመዘርጋት፣
- በእርጅና የተጠቁ አካባቢዎችን አፍርሶ እንደገና መገንባት፣ በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

እላይ እንደተገለፀው እነዚህ የልማት ሥራዎች የሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚለዩበት መንገድ እንደ
ፕሮጀክቱ ዓይነት ይለያያል፤ ለምሳሌ የዋና መንገዶች ደረጃና ጥራት መሻሻያ ፕሮጀክት የሚካሄድበት አካባቢ
በዋናነት የሚለየው የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን መሠረት አድርጎ ነው፡፡ ደረጃቸው የሚሻሻል ዋና ዋና
መንገዶች በከተማው መዋቅራዊ ፕላን ቀድመው የተለዩ ናቸው፡፡ በመዋቅራዊ ፕላን ለተለዩት ለእነዚህ
መንገዶች የትግበራ ቅደም ተከተል አውጥቶ፣ የማሻሻያ ዲዛይን አዘጋጅቶ ወደ ተግባር የማሸጋገር ኃላፊነት
የሥራው ባለቤት የሆነው የመንገዶች ባለሥልጣን መሆኑ ይታወቃል፡፡

በሌላ በኩል የውስጥ ለውስጥ መንገድ ማሻሻያ ሥራዎች እንዲሁም እንደ ጎርፍና ፍሳሽ ማስወገጃ መስመር
ያሉ የመሠረተ ልማት አውታሮች የሚዘረጋባቸው አካባቢዎች ምርጫ በዋናነት ከነዋሪው በሚቀርብ ጥያቄና

80
ግፊት የሚወሰን ነው፡፡ ለእነዚህ ፕሮጀክቶች ትግበራ የነዋሪው ተሳትፎ ወሳኝ ስለሆነ የሚጠበቅባቸውን
አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ የሆኑ ነዋሪዎች የሚገኙበት አካባቢ ቀድሞ የመመረጥ ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡

በእርጅና የተጠቁና ከደረጃ በታች በሆነ ግንባታ የተያዙ አካባቢዎችን አፍርሶ የመገንባት ሥራ የሚካሄድባቸው
አካባቢዎች አስቀድመው በመዋቅራዊ ፕላንና በአካባቢ ልማት ፕላን የሚለዩ ሲሆን በፕላን ከተለዩት
አካባቢዎች መካከል ቀድሞ የሚለማውን አካባቢ የመለየቱ ኃላፊነት የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ
ነው፡፡ በዚህ ውስጥ የአልሚ ግለሰቦች ፍላጎት በስፋት ሂደቱን ይመሩ እንደነበርም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ከ2001 ዓ.ም በፊት የተካሄዱ የመልሶ ልማት ፕሮጀክቶች ያለፉበትን ሂደት ለመቃኘት ከ1990-2001 ዓ/ም
ከተተገበሩ ፕሮጀክቶች የተወሰኑትን በምሳሌነት ወስደን ስንመለከት የመልሶ ልማት ፕሮጀክቶች የሚያግዝና
ወጥነት እንዲኖረው የሚረዳ መመርያ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን ከግል ባለሀብቱ ግፊትና ተነሳሽነት
ጎን ለጎን በመንግስት ደረጃም ሰፋ ያለ የመልሶ ማልማት እንቅስቃሴ የታየበት ጊዜ ነበር፡፡

የካዛንችስ መልሶ ማልማት ስራ ከመጀመሩ በፊት ራሱን የቻለ የፕሮጀክት ጥናት እንደተከናወነ ሰነዶች
ያመለክታሉ፡፡ በፕሮጀክቱ ሰነድ ላይ የተመለከተውን ጠቅሶ አበበ (2001) እንዳስቀመጠው ካዛንችስ ለመልሶ
ማልማት የተመረጠበት መነሻዎች፡-
 የአካባቢው ፕላን በሚፈልገው ደረጃ አካባቢውን ለማልማት፣
 የአካባቢውን ገጽታ በዓለም አቀፍ ከተማ ደረጃ ለመቀየር፣
 በአካባቢው የግንባታ ፕሮጀክት ለማካሄድ ይታይ የነበረውን ሰፊ የእንቨስትመንት ፍላጎት ለመመለስ፣
 ከሌሎች አካባቢዎች አንጻር ሲመዘን ለትግበራ ያለው ቅለት፣
 ከደረጃ በታች የነበረውን የመሬት አጠቃቀም ውጤታማ በሆነ አገልግሎት ለመተካት፣
 በዙርያው ያለውን የመሰረተ ልማት አውታር በተሻለ ደረጃ ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ፣
 በተፋፈገና ለአደጋ ተጋላጭ በሆነ ሰፈራ ምክንያት አደጋ ላይ ያለውን የኗሪዎች የጤንነትና
የአገልግሎት አቅርቦት ሁኔታ ለማቃለል፣ እና
 የከተማዋን ውበትና እይታ ለማሻሻል፣ የሚሉ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል በባለሃብቱ ግንባር ቀደም ተሳትፎ መልሶ ልማት የተካሄደባቸው ቦታዎች የተመረጡበትን ሂደት
ስንመለከት በአንድ ወቅት (በ1980ዎቹ መጨረሻ አካባቢ) የከተማ አስተዳደሩ ከደረጃ በታች በሆነ ግንባታ
የተያያዙ አካባቢዎች ወደ ልማት የሚገቡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ሲል ባለሃብቶች በይዞታቸው ሥር
(በካርታም ሆነ በኪራይ) በሚገኝ ቦታ ላይ ማስተር ፕላኑ የሚፈቅደውን ግንባታ የማካሄድ ፍላጎት ካላቸው
ፕሮጀክት ቀርጸው እንዲያቀርቡ ባደረገው ጥሪ በርካታ ባለሀብቶች ይዞታቸውን የማልማት ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡

81
ከ1990-1994 ዓ/ም አምስት ዓመታት የነበረው አሠራር በባለሃብቱ ቦታ ምርጫ ላይ የተመሰረቱ ፕሮጀክቶች
ሲቀርቡ አስተዳደሩ የሚያደርገው የተጠቆሙት ቦታዎች ለታሰበው አገልግሎት ለመዋል በማስተር ፕላኑ
የሚፈቅድ መሆኑና አለመሆኑ፣ ቦታው ለሌላ የህዝብ አገልግሎት የሚፈለግ መሆኑና አለመሆኑ በማረጋገጥ ሌላ
መስፈርት ሳይታይ ይሰጥ ነበር፡፡ በዚህ በኩል ቦታውን ለታቀደው ፕሮጀክት ለማዋል የሚከለክል ምክንያት
አለመኖሩ እንደተረጋገጠ ሂደቱ ከሊዝ ክፍያ እና ግንባታ ማንሳት ጋር ወደ ተያያዙ ድርድሮች ይሸጋገራል፡፡
ድርድሩ በስኬት ሲቋጭም የቦታ ጥያቄው አወንታዊ ምላሽ ያገኛል፡፡

ከ2006 ጀምሮ ወደ መልሶ ማልማት የሚገቡ ቦታዎች የሚለዩበት መስፈርቶች ከቀደምቶቹ መስፈርቶች
ይበልጥ የተዘረዘሩና የተሻለ ምክንያታዊ የሚያደርጋቸው ባህሪያት የተላበሱ ናቸው፡፡ መስፈርቶቹም ሰንጠረዥ
3.1 ላይ ቀርበዋል፡፡

ለከተማ ማደስ ፕሮጀክት የሚውሉ ቦታዎች እላይ ከተጠቀሱት መስፈርቶች አንፃር በዝርዝር ተመዝነው
የሚመረጡ ከሆነ ቀድሞ መልማት የሚገባው አካባቢ ቅድሚያ የሚያገኝበት አሰራር የፈጠረ ሲሆን መፍረስ
የሌለበት አካባቢ ቀድሞ እንዳይፈርስም ለመከላከል ያስችላል፡፡

ሆኖም መሬት ላይ በተግባር የሚሠራው ሥራ የመልሶ ልማት ፕሮጀክት የሚካሄድባቸው አካባቢዎች ግልጽ
በሆነ መስፈርት የሚመረጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ አይደለም፡፡ በዚህ በኩል በአንፃራዊነት የተሻለ አፈፃፀም
የሚታየው በመንገድ ልማት በኩል ነው፡፡ የዋና መንገድ ደረጃ ማሻሻያ የሚካሄድበት ወይም አዲስ መንገድ
የሚከፈትበት አካባቢ የሚመረጥበትን መስፈርት ሕዝብ በግልጽ ባያውቀውም በዚህ ዘርፍ የጎላ የቅደም
ተከተል ችግር አይስተዋልም፡፡ ለዚህ ደግሞ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ከከተማው መዋቅራዊ ፕላን ጋር
ለማስተሳሰር በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በኩል የሚደረገው ጥረት አስተዋጽኦ ሳያደርግ አይቀርም፡፡

82
ሰንጠረዥ 3.1፡ በአዲስ አበባ ለመልሶ ልማት የሚውል አካባቢ የሚመረጥባቸው መስፈርቶች
ቁ የልማት ቅደም ተከተል መምረጫ መስፈርት ክብደት
ቦታው/አካባቢው በመዋቅራዊ ፕላን ኢንተርቬንሽን ማፕ ላይ በከተማ መልሶ ማደስ (Urban
1 15
Renewal) የተመለከተ ሲሆን
2 አካባቢውን ለማልማት የመንግሥት ፕሮግራም/አቅጣጫ ሲኖር 5
በአካባቢው ያለው ችግር ስፋት (Problem Pressure):-
 የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የፊዚካል ችግር የጎላ ሆኖ ሲታይ
3 12
 ከአካባቢው ኅብረተሰብ የቅድሚያ ይልማልን ጥያቄ ሲቀርብ
 የቤቶች ሁኔታና ተጓዳኝ ፋሲሊቲዎች ለኑሮ ምቹ ካልሆኑ
በአካባቢው የተፈጠረ የልማት እንቅስቃሴ (Development Pressure):-
 ተደጋጋሚ የአልሚዎች ጥያቄ የሚቀርብበት
4 12
 በአካባቢው ከተጀመሩና እየተሰሩ ካሉ የመልሶ ማደስ ሥራዎች ጋር ያለው ቀጣይነት/ተያያዥነት
 የከተማውን ገቢ ሊደጉምና የከተማዋን ገጽታ ሊቀይር የሚችል የልማት ጥያቄ ሲቀርብ
5 የማኅበራዊ እና የፊዚካል መሠረተ ልማቶች ከፍተኛ ዕጥረት ሲኖር 10
ምቹ አካባቢ (Conducive Environment)፡-
 ቶሎ ለመልማት ያለው ዕድል (Investment Potential and Ease of Implementation)
6  የመሠረተ ልማት ያለበት ሁኔታ (Availability Of Infrastructure) 12
 የኅብረተሰቡ/የነዋሪው ድጋፍ (Community Support)
 አመቺ የመሬት አቀማመጥ (Topography) መኖር
አካባቢው መልሶ በመልማቱ የሚያስገኘው ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ አስተዳደራዊ፣
7 8
ፊዚካላዊ እና የአካባቢ ጽዳትና የአረንጓዴ ቦታዎች ጠቀሜታ
ተቋማዊ አቅም (Institutional Capacity)፡-
 ለልማት የሚመረጠው አካባቢ የልማት ሥራ ስፋት መጠን ሥራውን ከሚያከናውነው ባለሙያ
8 ጋር ያለው ምጣኔ 6
 በልማት ለሚነሳው ንብረት ካሣ የሚከፈለው በጀት አቅም ምጣኔ
 በልማት ምክንያት የሚነሱ ነዋሪዎችና በምትክ የሚሰጡ ቦታና ቤቶች አቅርቦት ምጣኔ
የመልሶ ማልማት አካባቢው ሲከለል የተፈጥሮ መልክዓ ምድርን፣ የክፍለ ከተማና ወረዳ ክልልን፣
9 10
እንዲሁም የአካባቢ ልማት ፕላን ወሰንን መከተል
በካሣ፣ ምትክ እና በልማት ሥራው ላይ የሚፈጠረውን ተጽዕኖ ለመቀነስ፡-
10  በቁጥር አነስተኛ የግል ይዞታ ሰፍሮ የሚገኝበት አካባቢ 10
 በተነጻጻሪ አነስተኛ ነዋሪ ሰፍሮ የሚገኝበት አካባቢ
ምንጭ፡ የአዲስ አበባ መሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ

በህዝብ ተሳትፎ ላይ በሚመሠረቱ የአካባቢ ማሻሻያ ፕሮጀክቶች በኩል የነዋሪዎች ዝግጁነት እና ግፊት በቦታ
መረጣ ከፍተኛ ቦታ ሲኖረው የሕዝብ ተሳትፎን የማስተባበር ኃላፊነት ያላቸው አካላት ጥንካሬና ጥረትም
የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ በቦታ መረጣ በኩል ሰፊ ክፍተት የሚስተዋለው ነባር ግንባታዎችን አንስቶ
በአዲስ ግንባታ በሚተካው የከተማ ማደስ የልማት ዘርፍ ነው፡፡ ቀደም ሲል እንደተገለፀው በዚህ ዘርፍ ሰፊ
ሥራ የተሠራው ባለፉት ስምንት ዓመታት ነው፤ ከስምንት ዓመት በፊት አካባቢዎችን በመደዳ የማፍረስ
እርምጃ በተወሰኑ አካባቢዎች/ፕሮጀክቶች የሚስተዋል ክስተት ነበር፡፡

በደሴ ከተማ ሳይቶች መልሶ ለማልማት የሚመርጡባቸው መለኪያዎች በየወቅቱ የተለያዩ ሶስት ዓይነት
አቀራረብ ተከትለው ነበር፡፡ መልሶ ማልማቱ መሬት ለማቅረብ ዋነኛ መሳሪያ ተደርጎ በተወሰደበት በ1990ዎቹ

83
ልማቱ የሚካሄድባቸው ቦታዎች ለመለየት የተጠቀሙባቸው መለኪያዎች በሰነድ የሰፈረ ነገር ባይኖርም
በውይይት በተገኘው መረጃ መረዳት የተቻለው፡-
 የከተማዋ እይታ/ውበት/፣
 መሰረተ ልማት ከደረጃ በታች መጠቀም፣
 ለትግበራ ያለው ቅለት/ከካሳ ወጭና ማስፈረስ መብት አንጻር የቀበሌ ቤት ትኩረት ማድረግ፣
 የቦታው በንግዱ ማሕበረሰብ የሚኖረው ተፈላጊነት፣ የሚሉት መሆናቸው ነው፡፡

በእንዲህ መልክ የተጀመረ መልሶ ማልማት እንቅስቃሴ ልማቱ ፕላን ተዘጋጅቶለት መከናወን እንዳለበት
ግንዛቤ እንዲወሰድ ትምህርት ሰጥቷል፡፡ ስለሆነም የአማራ ክልል ፕላን ኢንስቲትዩት ለደሴ ከተማ መዋቅራዊ
ፕላን እንዲሰራላት አነሳስቷል፡፡ ፕላኑ ሲዘጋጅ የፕላን ኢንስቲትዩቱ ከደቡብ ወሎ ዞን ሥራና ከተማ ልማት
ፅሕፈት ቤት እና ከከተማው የአገልግሎት ፅሕፈት ቤት ጋር በመሆን ቀድሞ የነበሩ መስፈርቶች ተሻሽለው
እንዲዘጋጁ ተደርጎ ነበር፡፡ መስፈርቶች ደግሞ፡-
 የቦታው ኢኮኖሚያዊ ፊዚካላዊ የመልማት ዕምቅ ዓቅም
 ማዕከላዊነት ወይም ለመሀል ከተማው ያለው ቅርበት
 የህንፃዎችና የመሰረተ ልማት አውታሮች የእርጅና ደረጃ
 የተጠቃሚውና የተጎዳው ህዝብ ብዛት
 አካባቢያዊ ሁኔታ የሚሉት ነበሩ፡፡
ከተማዋ እራሷን በተከተለችው አቅጣጫ እና በኃላም በክልሉ የፕላን ኢንቲትዩት ድጋፍ አማካኝነት በተለዩት
መስፈርቶች ላይ ተመስርታ ስታደርግ የነበረውን መልሶ ልማት ከ2006 ዓ/ም በኋላ ሕጋዊ ሽፋን እንዲያገኝ
ተደረጓል፡፡ በ2006 ዓ/ም የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ መልሶ-ልማት ለመምራት የሚያስችል
ስርዓት ለመዘርጋት ተዘጋጅቶ በትግበራ ላይ እንዲውል የተደረገው መመሪያ መልሶ ልማት ሲከናወን የከተማ
ልማት ራዕይ ለማሳካት ከተሞች የረጅም፣ መካከለኛና አጭር ጊዜ የልማት ዕቅድ በማዘጋጀት እንዲመራ
በማለም የተቀረፀ ሲሆን የሚከተሉት መርሆች አስቀምጧል፤

i. የከተማ ልማት ራዕዩ ለማሳካት፡-የከተማ መልሶ-ልማትና መልሶ ማደስ የሚከናወነው ከተሞች ምቹ


የስራና የመኖሪያ፣ ባጠቃላይ የልማትና የዕድገት ማእከላት እንዲሆኑ ለማድረግ፣
ii. የደቀቁ የከተሞች አካባቢዎች በግማሽ የመቀነስ የምዕተ ዓመቱ ግብ ለማሳካት፣
iii. በከተሞች በብዙ መልኩ የሚገለፀውን ድህነት በመቀነስ ለሀገራችን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ጉዞ
ከፍተኛ ሚና ማበርከት ታሳቢ እንዲደረግ፣
ይህ መመሪያ መልሶ የሚለማ ቦታ ለመለየት የሚያስችሉ መስፈርቶች ከመለየት በፊት የደቀቁ አካባቢዎችን
መልሶ ለማልማት ተግባር ላይ ሊውሉ የሚገባ አግባቦች "መልሶ ማደስ" እና "መልሶ ማልማት" በሚል ለይቶ
በድንጋጌው አስፍሯል፡፡

84
ሰንጠረዥ 3.2፡ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተሞች መልሶ የሚለማ ቦታ መምረጫ መስፈርት
መስፈርት ከተማ ማደስ ከተማ መልሶ ልማት
 5-10 ሄክታር  ከ10 ሄክታር በላይ ከሆነ በመልሶ
 ከ5 ሄክታር በታች የዋና መንገድ ልማት ቀጠና የሚለማ ይሆናል
አጠቃላይ የቦታው ስፋት ዳርቻዎችና አደባባዮች በኪስ  ከ10 ሄክታር በታች ከሆነ
ቦታዎች ልማት አግባብ ይለማል በብሎክ ደረጃ ይለማል
ከተከለለው የቦታ ስፋት የሚጠበቀውን ከ50% የማይበልጥ ታሳቢ አያደርግም
የፕላን መስፈርት የማያሟላ
የህንፃ ሕጉ መስፈርት (standard) ከ50% የማይበልጥ ከ60% በላይ
የማያሟሉ ግንባታዎች
ዝቅተኛውን የሽንሻኖ መጠን ከ50% የማይበልጥ ከ50% በላይ
(standard) የማያሟሉ ይዞታዎች
ውኃ፣ መንገድ፣ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ምቹ የስራ አካባቢ ማድረግ ብቻ ነዋሪዎች በትፍፍግና ለኑሮ
ማስወገጃ ችግር ያለበት የሚጠይቅ ከሆነ በማይመች ሁኔታ የሚኖሩበት ከሆነ
ለአጠቃላይ የከተማው ልማት ባለው በመልሶ ማደስ አስፈላጊነት በከተማው ም/ቤት በኩል ውሳኔ
ፋይዳ የከተማው ካቢኔ ከወሰነ ሲሰጥበት፣
1
የግንባታዎች ማርጀትና መድቀቅ ታሳቢ አያደርግም ከ50% በላይ
አጠቃላይ የይዘቱ እንደምታ አካባቢን ማሻሻል ይመለከታል ወደ መልሶ ልማት ይጠጋል
ምንጭ፡ ከአማራ ከተማ ልማትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ መመሪያ ቁጥር 6/2006 ገፅ 1-7 የተቀመረ
መልሶ ማደስ እንዲያሳካው የሚፈለግ ዓላማ ያልተሟሉ መሰረተ ልማቶች በማሟላት፣ የቤቶች ደረጃ
በማሻሻል፣ የአከባቢውን ኢኮኖሚያዊና የአሰፋፈር አግባብ በማስተካከል የዕይታ ገፅታን ማሻሻል ሲሆኑ
የአካባቢ ልማት ፕላን ማዘጋጀት አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ አይደለም፡፡ መልሶ ማልማት ደግሞ የደቀቁ
አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል አፍርሶ መገንባት ያካተተ ሰፋ ያለ የልማት አግባብ እንደሚመለከት
ተደንግጓል፡፡ መልሶ ልማት ለማከናወን የአካባቢ የልማት ዕቅድ ማዘጋጀት የግድ ነው፡፡

በመመሪያው የተወሰኑት መስፈርቶች ቴክኒካዊ ይዞታቸው ኮሪያዎች ከሚጠቀሙዋቸው የሚመሳሰሉ ሲሆኑ


አግባብነታቸውም ለጥያቄ የሚዳረግ አይደልም፡፡ መስፈርቶቹ መልሶ ልማት የሚያስፈልገው አካባቢ መለካት
በሚቻል ደረጃ ለማጥናት ያስችላሉ፡፡ በተለያዩ ተዋናዮች በቀላሉ መግባባት ላይ ለመድረስ የሚያስችሉ ግልፅ
ቋንቋ ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡ የትኛው አካባቢ ቀድሞ መልማት እንደሚገባ ከግምታዊ አሰራር በፀዳ
አኳኃን ለመተግበር ያስችላሉ፡፡

የዜጎች ኢኮኖሚያዊ ለውጥ የትንተናው ማእከል ሳይደረግ ከታየ በመመሪያው የተቀመጡ መስፈርቶች በደሴ
ከተማ በቀጥታ ሊተገበሩ የሚችሉ መሆናቸው የከተማው ነባራዊ ሁኔታ ያሳያል፡፡ በመስፈርቶቹ መለካት
ሳያስፈልግ እንኳ አብዛኛውን የደሴ ከተማ ክፍል መልሶ ልማት የሚጠይቅ መሆኑ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡
በከፊል ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ አፍርሶ መገንባት የሚጠይቅ ቦታ ብቻ እንኳ ከተወሰደ በጣም ሰፊ ነው፡፡
ከላይ የተጠቀሱት አካባቢዎች በእያንዳንዳቸው የተጎሳቆሉ ቦታዎች ላይ ሰፋፊና ኩታ ገጠም መሆናቸው ሰፋ
ያለ ቦታ ለማልማት የተሻለ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ (Scale of Economics) ሊያስገኝ ይችላል፡፡

1
በከተማ አስተዳደር ክልል ውስጥ የሚገኝ የደቀቁ እና ያረጁ ግንባታዎች እና ከደረጃ በታች የሆነ አሰፋፈር የሚገኝበት ለኑሮ እና ለስራ
አመቺ የሆኑ አቅርቦቶች በመሰረታዊነት የተጓደሉበት የከተማ ክፍል ነው (መመሪያ ቁጥር 6/2006 አንቀፅ 2 ቁጥር 6)፡፡

85
መስፈርቶቹ ከይዘት አኳያ ሲፈተሹ የሚታየው ውስንነት ቴክኒካዊ ቅኝት የተላበሱ ፊዚካላዊ ጉዳዮችን ከማየት
አልፎ በኢኮኖሚያዊ ዕይታዎች ጠለቅ ያለ አይደለም፡፡ መልሶ ልማት ለማካሄድ የግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንት
በግንባታ እያደረገ ያለው ወይም በቅርብ ጊዜ ሊመጣ የሚችል ተሳትፎና ፍላጎት ወሳኝ ነው፡፡ ካልሆነም መልሶ
ልማቱ (በተለይ አፍርሶ መገንባት የሚጠይቅ) በባለይዞታው ዓቅም የሚሰራ መሆኑና አለመሆኑ ማጥናት
ይጠይቃል፡፡ በሌላ አባባል የነዋሪው ኢኮኖሚያዊ አቅም እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ ሌላው ከግምት መግባት
የሚገባው ጉዳይ ለዚህ ተብሎ የተዘጋጀ የፋይናንስ ምንጭ መኖር ይጠበቃል፡፡ ካልሆነ ቴክኒካዊ መስፈርት
ስለተዘጋጀ ብቻ ልማቱ ይከናወናል ብሎ ማሰብ ውጤታማ እንደማይሆን የተግባር ተሞክሮው ያሳያል፡፡

የአማራ ክልል በከተሞች መልሶ ልማት ለመምራት ያወጣው መመሪያ መልሶ ልማት የሚከናወንበት ቦታ
ለመምረጥ ከተሞች ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ መስፈርቶች በዝርዝር ወስኖ ማስቀመጡ ቦታ መረጣው በከተማ
ልማት ባለሙያዎች እንዲከናወን የሚያደርግ ሲሆን የከተሞቹ የፖለቲካ አመራሩም ይሁን የከተማው ነዋሪ
ቦታውን በመምረጥ በኩል ሚና የላቸውም ማለት ይቻላል፡፡ መመሪያው ያለቀላቸው መለኪያዎቹ መደንገጉ
በቦታ መረጣ ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል የጥቅም ግጭትና መጓተት የሚያስቀር ቢሆንም መልሶ ልማት ከፍተኛ
የፖለቲካ እና የልማት ጉዳይ ሳይሆን ቴክኒካዊ ስራ ተደርጎ እንዲታይ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ ፖለቲካዊ
አመራሩም ሆነ የከተማው ነዋሪ በተወካዮቹ አመካኝነት በሚያደርገው ውሳኔ ሰጭነት ስለማይኖር የልማቱ
ባለቤትነት ስሜቱ ዝቅተኛ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ መልሶ የሚለማ መሬት ለመምረጥ የሚከተለው ስርዓት የሚያሳየው ደግሞ የአማራ ክልል
መመሪያ ቁጥር 6/2006 ከሚለው በተቃራኒ መልኩ ነው፡፡ በድሬዳዋ ከተማ ቦታውን መርጦ የሚያቀርበውን
አካል የመሬት ልማትና ማነጅመንት ቢሮ ነው (የአስተዳደሩ የካሣ ክፍያና ምትክ ቤትና ቦታ ምደባ አፈፃፀም
መመሪያ አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 1)፡፡ መመሪያው “የመሬት ልማት ቢሮ የራሱን ዕቅድና የሌሎች አስፈፃሚ
መ/ቤቶች የመሬት ፍላጎት መነሻ በማድረግ የከተማ ቦታ ለሕዝብ ጥቅም እንዲውል ቅደም ተከተል
በማውጣት ከሚተገበርበት በጀት ዓመት ከአንድ ዓመት በፊት አጥንቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለካቢኔ ያቀርባል፤
ሲወሰንም እንዲፈፅም ይደነግጋል፡፡

በዚህ መሰረት የመሬት ፍላጎቱ ለመመለስ መልሰው መልማት ያለባቸው ቦታዎች ወደ ማጥናት ገብተዋል፡፡
የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት ለመልሶ ልማት የሚውሉ
ቦታዎች የሚመረጡት በቢሮው ማኔጅመንት አባላት የጋራ ስብሰባ ነው፡፡ በድሬዳዋ አንድ ቦታ ለመልሶ ልማት
ፕሮጀክት እንዲውል ከሚመረጥባቸው መስፈርቶች አንዱ ለቦታው የአካባቢ ልማት ፕላን የተዘጋጀ መሆኑ
ነው፡፡ አስተዳደሩ የአካባቢ ልማት ፕላን ባልተዘጋጀለት አካባቢ በነባር ግንባታ የተያዘ ቦታን ለመልሶ ልማት
ፕሮጀክት እንደማይመድብ ባለሙያዎቹ ይገልፃሉ፡፡

በሌላ በኩል ለመልሶ ልማት እንዲውል የሚመረጠው ቦታ ከደረጃ በታች በሆነ አገልግሎት የተያዘ መሆኑ
አያጠያይቅም፣ አብዛኞቹ ቦታዎች በመሃል ከተማ የሚገኙ እንደመሆናቸው መጠን በቂ የመሠረተ ልማት

86
አውታር የተዘረጋባቸው፣ ለትግበራ ቀላልና በአልሚዎች የሚፈለጉ መሆናቸውም ጥያቄ ውስጥ የሚገባ
አይደለም፡፡ የመመሪያው አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 2 ደግሞ እላይ የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ ሌሎች
አስፈፃሚ መ/ቤቶችም ለሥራቸው የሚፈልጉትን መሬትና መሬቱ የሚገኝበትን ሥፍራ የሚያሣይ መረጃ
ቢያንስ ሥራው ከመጀመሩ ከአንድ ዓመት በፊት ለመሬት ልማት ቢሮ የመላክና የማስፈቀድ ኃላፊነት
እንዳለባቸው ተደንግጓል፡፡ የቦታዎቹ ዝርዝር በቢሮው ሥር በተዋቀረው የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ንዑስ
የሥራ ሂደት ተዘጋጅቶ ለቢሮው ማኔጅመንት ኮሚቴ የሚቀርብ ሲሆን በማኔጅመንት ኮሚቴው ተቀባይነት
ያገኘው የቦታ ዝርዝር በአስተዳደሩ ካቢኔ ቀርቦ እንዲፀድቅ ይደረጋል፡፡ በዚህ መሠረት በአስተዳደሩ ካቢኔ
እስኪፀድቅ ድረስ የሚካሄደው የቦታ ምርጫ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሚፈፀም ሲሆን ቦታው ለመልሶ
ልማት እንዲውል የካቢኔ ውሳኔ ካገኘ በኋላ ተጠቃሚዎች/ነዋሪዎች እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡

መመሪያው መልሶ ልማት የሚተገበርበት ቦታ የማጥናት ሂደቱ ከታች ጀምሮ በከተማው ካቢኔ ይሁንታ
እንዲጠናቀቅ ማድረጉ ፖለቲካዊ አመራሩ የልማቱ ባለቤት የሚያደርግ ነው፡፡ ቦታው ላይ የሚገኙ
ተጠቃሚዎች/ነዋሪዎች ግን ይህንን የባለቤትነት ስሜታቸው ጠንካራ እንዳይሆን ያደርገዋል፡፡

መቐለ ከተማ ተግባር ላይ የዋሉ መስፈርቶች ሲታይ ደግሞ የልማቱ ዓይነት የሚያንፀባርቁ ናቸው፡፡
መስፈርቶቹ የአዲስ አበባ እና የአማራ ክልል ከሚጠቀሙባቸው መስፈርቶች የሚለዩበት ባህሪ ፊዚካል
ገፅታዎች በአሃዛዊ መለኪያዎች ከማመላከት ይልቅ የነዋሪን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ ሕጋዊ
ጉዳዮችንና የጎደለውን አገልግሎት ለመሙላት የሚያስችሉ ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡ የመስፈርቶቹ መነሻም
መልሶ ልማት የሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ከመለየት የሚጀምር ሳይሆን የአካባቢ የልማት ዕቅዶች ነበሩ፡፡
የአካባቢ የልማት ዕቅዶች ሲዘጋጁ ደግሞ መሰረታዊ የሆኑ የህዝቡ የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ ምን ዓይነት
የልማት አማራጭ (Planning Intervention) ለየትኛው አከባቢ እንደሚስማማ ማጤን ላይ ያተኮሩ ነበሩ፡፡
ባጭሩ ከየአካባቢ የልማት ዕቅዱ የተለዩ መስፈርቶች የሚከተሉት ነበሩ፡
 በከተማው ፕላን በአግባቡ ያልተደራጁ
 መሰረተ ልማት ያልተዳረሰባቸው
 ነዋሪው ያነሳቸው የልማት ጥያቄዎች
 ከመሬት አጠቃቀም፣ ግንባታ ደረጃና ከፍታ፣ የግንባታ ግብአት ዓይነት እንዲሁም የይዞታ ስፋት
መስፈርት አኳያ በወቅቱ ከነበረ የከተማዋ መዋቅራዊ ፕላን ጋር የሚጣረሱ
 የቤቶች ውጫዊ እርጅና
 መልሶ የሚለሙ ቦታዎች ሊያስገኙት የሚችሉ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ
 የዕቅዱ ዓይነት ለመተግበር የከተማው ዓቅም
 የባለሀብት የልማት ጥያቄ የቀረበባቸው ቦታዎች

87
መልሶ የሚለሙ ቦታዎች (Sites) ለመለየት ያገለገሉ መስፈርቶች በመርህ የተቀመጡ ነበሩ፡፡ ሙሉ በሙሉ
ፈርሰው እንደ አዲስ እንዲገነቡ የታሰቡ ቀበሌ 14 እና ቀበሌ 04 መስጊድ አካባቢዎች የሚገኙ ጥቂት ብሎኮች
ውጫዊ ገፅታቸው ማርጀትና ከሚፈቀድ የይዞታ ስፋት ከደረጃ በታች መሆናቸው ከመግለፅ ባለፈ ተቆጥረው
የሚለኩ መስፈርቶች አልተቀመጡም፡፡ ይህንን እሳቤ ከተወሰደ ተመሳሳይ፣ ካልሆነም የባሰ የእርጅናም ሆነ
ከደረጃ በታች ገፅታ ያላቸው ቦታዎችና ይዞታዎች እንዳየሱስ፣ እንዳስላሴና ኲሓ አከባቢዎች ቢኖሩም እነዚህ
ቦታዎች ፈርሰው እንዲገነቡ የሚል ፕሮፖዛል አልቀረበባቸውም፡፡

የአካባቢ የልማት እቅዶች ሲጠኑ ቦታዎቹ ለመምረጥ ያገለገሉ መስፈርቶቹ በአጠቃላይ መስፈርትነት ችግር
ባይሆንም መለካት በሚቻልበት አግባብ ከማመላከት ይልቅ በግምገማ ላይ በመመርኮዝ የተዘጋጁ መሆናቸው
የትኛውን ሰፈር መቅደም እንዳለበት ለመረዳት የሚያስችሉ አይደሉም፡፡ መስፈርቶቹ የሕግ ሽፋንም
የላቸውም፡፡ ከዚህ አንፃር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በከተሞች መልሶ ልማት ለማካሄድ አካባቢዎቹ
ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች (መምሪያ 6/2006) መለካት በሚቻልበት ደረጃ ማለትም የግንባታና
የይዞታ ስታንዳርድ ካለሟሟላት፣ ከመሬት አጠቃቀም ተስማሚነት፣ ከቤቶችና አካባቢዎች እርጅና ደረጃና
ስፋት ወዘተ በአሃዛዊ ልኬት በዝርዝር ከማስቀመጡም በላይ መስፈርቶቹ ሕጋዊ እውቅና እንዲኖራቸው
ማድረጉ በመልካም ተሞክሮነቱ የሚታይ ነው፡፡

መስፈርቶቹ የአካባቢ የልማት ዕቅዶቹ ያዘጋጀውን አማካሪ የለያቸው ሲሆን መነሻውም የከተማው የወቅቱ
መዋቅራዊ ፕላን ላይ የተቀመጡ ፕሮፖዛሎች ነበሩ፡፡ መስፈርቶቹ የአካባቢ ልማት ዕቅዶች ላይ በውስጠ
ታዋቂነት የተቀመጡ ስለነበሩ የልማት ዕቅዶቹ ከህዝብ ጋር ውይይት ሲደረግ ነዋሪዎችና ተወካዮቻቸውን
እንዲሁም የልማት ዕቅዶቹ የማፅደቅ ስልጣን የተሰጠው የከተማው ምክር ቤት እውቅና እንደሰጣቸው
ለመረዳት ይቻላል፡፡ የአካባቢ የልማት ዕቅዶቹ ረቂቅ ከነዋሪዎች ጋር በሚካሄድ ውይይት ዳብሮ የከተማው
ካቢኔና የነዋሪዎቹ ተወካዮች ካፀደቁት በኃላ የከተማው ምክር ቤት ይሁንታ ተችሮት ወደ ትግበራ እንዲገባ
ተደርገዋል፡፡ ነገር ግን የፖለቲካ አመራሩና የከተማው ምክር ቤት በአማካሪ ድርጅቱ ተዘጋጅቶ የቀረበለት
ዕቅድ ከማፅደቅ በዘለለ መልሰው እንዲለሙ/እንዲሻሻሉ የሚፈለጉ ቦታዎች የሚመረጡበት አግባብ አመራር
ከመስጠት አኳያ ሲመዘን ጠንካራ ነበር ለማለት አይቻልም፡፡

የሀዋሳ ከተማ ሰፋ ያለ መሬት የሚሸፍን (Area Based) ትርጉም ያለው የመልሶ ማልማት ፕሮጀክት እስካሁን
ያልተተገበረ ቢሆንም በከተማው መካከል ይተገበራሉ ተብለው በተዘጋጁ የአካባቢ የልማት ዕቅዶች መልሶ
ልማት የሚያካትቱ ናቸው፡፡ ነገር ግን ልማቱ እንዲካሄድባቸው የታሰቡ ቦታዎች የተመረጡበት መንገድ
በግልፅ የሚያሳይ የጠራ መረጃ አልተገኘም፡፡ ሁኔታው መረዳት የሚቻለው የአካባቢ የልማት ፕላኖች ሲዘጋጁ
ለትንተና ግብአት የዋሉ ጉዳዮችን በጥልቀት በመመርመር ነው፡፡ በከተማው መካከል አካባቢዎች እንዲተገበሩ
የተዘጋጁ የአካባቢ የልማት ፕላኖቹ መልሶ ማልማት የፕላኑ አንድ አካል አድርገውታል፡፡ መልሶ ማልማት
የሚያስፈልግበት ምክንያት ደግሞ የግንባታዎች ጥንካሬ እና ዓይነት፣ የግንባታ ግብአት ዓይነት እና የወሳኝ

88
መሰረተ ልማቶች ሽፋንና ጥራት ላይ ያተኮረ ትንተና ተካሂደዋል፡፡ ሆኖም ግን ትንተናው የቀረበው መልሶ
ማልማቱ ፕሮጀክት የሚተገበርበት ቦታ የቱ መሆኑ በሚያሳይ መልኩ በንፅፅር ሳይሆን የአካባቢ ልማት ዕቅዶቹ
ተግባራዊ የሚሆኑበት ቦታ ላይ የሚገኙ ገፅታዎች በድምር ነው፡፡

ስእል 3.9፡ በሃዋሳ መሀል ከተማ የመልሶ ማልማት ከሚካሄድባቸው ቦታዎች በከፊል

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰዱ


ይኸው አንዱ ድክመት ሲሆን በሀዋሳ ከተማ የመልሶ ማልማት ኘሮጀክት በተበታተነ ሁኔታ ለኢንቨስትመንት
ጥያቄ የቀረበባቸውን ተፈላጊ ቦታዎች እየተከተሉ የሚደረግ መሆኑም ሌላኛው መገለጫ ባህሪው ነው፡፡ አሁን
በውስን ደረጃ የመልሶ ማልማት እየተካሄደባቸውና ለወደፊትም ለዚሁ ተግባር የተያዙት ቦታዎች በከተማው
መሪ ኘላን መሰረት ለንግድና ለኢንቨስትመንት እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች መስጫ ህንጻ መስሪያ
የተመደቡ የመሃል አካባቢ ቦታዎች በመሆናቸው ዋነኛው መለያ መስፈርቱ የቦታው ተፈላጊነት መሆኑ
ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

ከላይ እንደተጠቀሰው የጅማ ከተማ መልሶ ልማት የተጀመረው መልሶ ማልማቱ ከከተማው የልማት ፍላጎት
አንፃር ታስቦበት የረጅም እና የመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ ተዘጋጅቶለት አልነበረም፡፡ ስለዚህ መስፈርቱ የነዋሪዎች
የመሰረተ ልማት ጥያቄ እና በኃላም የባለሀብት የኢንቨስትመንት የመሬት አቅርቦት ፍላጎት ለመመለስ ሲባል
ነበር፡፡ ከሙያ አኳያ መልሶ ማልማት የተካሄደባቸው እና አሁንም በእቅድ ደረጃ የሚገኙ ቦታዎች ለመምረጥ
ከተማው የተጠቀማቸው መስፈርቶች በፅሑፍ ለማግኘት ስላልተቻለ ጉዳዩ ለማጤን የተመረጠው አካሄድ
ከሚመለከታቸው ባለሙያዎችና የስራ ሓላፊዎች ጋር በመወያየት ነበር፡፡ ከውይይቱ ለመረዳት የተቻለው
መልሶ ልማቱ ትኩረት ያደረገባቸው መስፈርቶች፡-
 መጋቢና መዳረሻ የመንገድ መሰረተ ልማት የሌላቸው፣
 ያረጁና የተጨናነቁ ሰፈሮች፣
 በብዛት የቀበሌ ቤቶች የሚገኙበት፣
መሆናቸው በውይይቱ የተሳተፉ ባለሙያዎች ቢያብራሩም ዝርዝር የመልሶ ልማት ፕሮግራም አለያም
የመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ ባለመኖሩ ምክንያት የተጠቀሱት መስፈርቶች ከመነሻው በውል ታስቦበት የተቀመሩ
መሆናቸው እንዲሁም ጥልቀታቸው ምን እንደሚመስል ለማጤን ያስቸግራል፡፡ ይህንን ክፍተት ሰፊ የመስክ

89
ምልከታ በማድረግና ከበርካታ ነዋሪዎች በመወያየት ለመሙላትና ሁኔታው ለመረዳት ተሞክረዋል፡፡ መልሶ
ልማት በተካሄደበት የመርካቶ አካባቢ የሚገኙ ሰፈሮች ገፅታቸው በአካል ምልከታ ሲመረመር፡-

 ቤቶቹ ውጫዊ ገፅታቸው በጣም ያረጁ


 ቤቶቹ በተናጠል ለማልማትና ለማሻሻል ዕድል የማይሰጡ በመደዳ የተያያዙ፣
 የቀበሌ ይሁን የግል ቤቶች ጥበት፣ በቤተሰብ ደረጃም ቢሆን በቂ የማይባሉ መሆናቸው
 በርካቶቹ ይዞታዎች ደረጃውን የጠበቀ ሽንት ቤት የሌላቸው፣
 መንገዶቹ በስርዓቱ ያልተደራጁና ለነዋሪ እንቅስቃሴ የማይመቹ፣ የትራፊክ ፍሰቱ የማያስተናግዱ፣
አጠቃላይ የአካባቢው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የማይሸከሙ መሆናቸው፣
 በሰፈርና በብሎክ ደረጃ ሲታይ የጋራ ክፍት ቦታዎች የሌላቸው ፣ ናቸው፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት ወደ ልማት እንዲገቡ ከተጠኑት ሁለት ብሎኮች (ጋሊሞሌና መርካቶ) ለመረዳት
የተቻለውም ካሁን በፊት የለሙ ከላይ የተገለፁ ምስሎች የሚያሟሉ እንደነበር መደምደም ይቻላል፡፡

መልሰው የለሙና ቀጣይም እንዲለሙ የተጠኑ አካባቢዎች የተመረጡበት መስፈርቶች አግባብነታቸው ትክክል
እንደሆነ ነዋሪዎችም በተሰጣቸው መጠይቆች አረጋግጠዋል፡፡ ከተሰበሰበው 205 መጠይቆች 80% ያህሉ
ነዋሪዎች ቦታው እንዲለማ መደረጉ አግባብ እንደሆነ ሲገልፁ 9.7% ብቻ ናቸው ድጋፍ ያልሰጡ፡፡ በተመሳሳይ
93.3% ነዋሪዎች በልማቱ ምክንያት የተነሱ ቦታዎቹ የተመረጡበት ዕይታ ትክክል መሆኑ ያምናሉ (አባሪ
ይመልከቱ)፡፡ በቅርቡ በመልሶ ልማት ምክንያት ከሚነሱት 20% ያህሉ ይቃወማሉ (ኣባሪ ይመልከቱ)፡፡
በመጠይቅ የተሰበሰበው መረጃ ያስገኘው ግኝት ትክክል መሆኑ ከነዋሪዎች ጋር በተካሄዱ ቃለ መጠይቆችና
ውይይቶች ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ከመርካቶ እስከ አውቶብስ መናሀሪያ፣ ከስታዲየም እስከ መናሃሪያ እንዲሁም ከመናሃያ እሰከ ዳውሮ በር
አደባባይ ዋና መንገዶችን ተከትሎ በነጠላ ይዞታ ደረጃ የተካሄዱና በመካሄድ ላይ የሚገኙ መልሶ የልማት
አካባቢዎቹ እንደ መርካቶ እጅግ በተጎሳቆሉ ቤቶች ላይ ያነጣጠረ ሳይሆን ከመሬት ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ
የሚገናኝ ነው፡፡ ማለትም በእንዲህ ዓይነት ቦታዎች የሚካሄዱ መልሶ ማልማቶች መስፈርቱ የከተማው
መዋቅራዊ የልማት ፕላን የግንባታ ስታንዳርድ እና የመሬት አጠቃቀም ዓይነት ነው የሚሆነው፡፡

ባልተቀናጀ መልኩ 2000 ዓ/ም የተጀመረው መልሶ ልማት 2005 ዓ/ም የአካባቢ የልማት ዕቅድ እየተዘጋጀ
እንዲፈፀም መሰረታዊ ለውጥ መደረጉ ከቴክኒካዊ መለኪያዎች በተጨማሪ ዕይታዎች እየተካተቱ ነው፡፡
በመሆኑም መልሶ ልማት የሚጠይቅ አካባቢ ለከተማው ገቢ እና የንግድ እንቅስቃሴ የጎላ ሚና የሚያበረክት
መሆን እንዳለበት ታሳቢ ተደርጓል፡፡ የሊዝ አዋጅ 721/2004 መደንገግን ተከትሎ መሬት በድርድር ማቅረብ
መቆሙ በመልሶ ልማት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ቦታዎች ለከተማው የተሻለ ገቢ የሚያስገኙ መሆን
ይገባቸዋል፡፡ ከዚህ አኳያ ሲታይ መልሶ ልማቱ ለንግድ አገልግሎት በሚውሉ ቦታዎች ላይ ያነጣጠረ ሆኖ
90
ቀጥሏል፡፡ በጅማ ከተማ መልሶ ልማት የተጀመረበት ሁኔታ ከላይ የተጠቀሱ አጠቃላይ መስፈርቶች ታሳቢ
ያደረገ እንደነበር ባለሙያዎች በውይይት ወቅት ቢገልፁም ታሳቢዎቹ በሚለኩ መስፈርቶች የተደገፉ
አልነበሩም፡፡

ድምር ምስሉ ሲታይ በየከተሞቹ መልሶ ማልማት የሚጠይቅ ቦታ ሰፊ በመሆኑ ቦታዎቹ መምረጥ የቅደም
ተከተል እና የዓቅም ጉዳይ እንጂ ገና ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ አካባቢያዊ ደህንነት ሁኔታዎችን ላይ
በመመስረት ገና ፋይዳቸው ተሟጦ ያላለቁ እና ያሉበት ሁኔታ ህይወት ያለው የኢኮኖሚ እና ማሕበራዊ
እንቅስቃሴ የማይታይባቸው በሚል ለማወዳደር ያህል መስፈርት አይደለም የምናየው፡፡

ባጠቃላይ በሀገራችን ከተሞች የሚካሄዱ የመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች አግባብነት ከሶስት ዋና ዋና መርሆች
መገምገም ያስፈልጋል፡፡ አንደኛው እና የመጀመሪያው መርህ መልሶ ማልማት ያስፈለገበት ምክንያት ሊኖር
ይገባል፡፡ አንድን አካባቢ ካሁን ቀደም ሲሰጠው የነበረ አገልግሎት ዓይነት ከከተማው ወይም የተለያዩ ሙያዊ
ማወዳደሪያ መስፈርት በታች እጅጉን ከወረደ፤ አብዛኛውን/ሌላውን የከተማው አካባቢ እጅግ እያደገ ባለበት
ሂደት ይህ አካባቢ ዕድገቱ የተገታ ሆኖ እያደገ ከሚገኘው ሰፊውን ክፍል ከኃላ ከርቀት ሲቀር ወይም ይህ
አካባቢ መስጠት የሚችለው ዙሪያ መለስ ኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ ጥቅም እያስገኘ ካልሆነ ነው፡፡ ይኼ
ማለት አካባቢው በልማት ያለው ፋይዳ ላሽቋል የሚባልበት ደረጃ ሲደርስ ነው ማለት ነው፡፡

ከዚህ አንፃር በእኛ ሁኔታ እንደታየው በናሙና በተመረጡት ከተሞች ዳሰሳ የተደረሰበት ድምዳሜ ቦታ/አካባቢ
ወደቀ የሚባለው ከቴክኒክ እይታ አንጻር ከአራቱ የከተማ መገለጫዎች/ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ገፅታ እና
ኣካቢያዊ ደህንነት/ ሁለቱ ማለትም ገፅታዊና ኣካባቢያዊ ደህንነት ሁኔታ ደረጃውን ያልጠበቀ መሆን እና
ማርጀትን ሲመለከት በተወሰነ ከድሬድዋና ከጅማ በቀር የቦታዎቹ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ያልወረደ
እንዲያውም ከሌላው የከተማው ክፍል የሞቀ በመሆኑ ተፈላጊነቱ እንደማሳያ ማቅረብ የሚቻል ነው፡፡

በሰነድ የሰፈረው የተወሰነ ቢሆንም ሳይጻፍ መልሶ የሚለማ ቦታ በናሙና በታዩት የከተሞች የተመረጠበት
መስፈርት ይመሳሰላሉ፡፡ መልሶ ልማት የተካሄደባቸው ቦታዎች የከተማው መሀል፣ የደቀቁ ግንባታዎች
የበዙበት ቦታ፣ የመሰረተ ልማት ተደራሽነት ችግር ያለባቸው፣ ግንባታዎቹ በአካባቢው የሚገኝ መሰረተ ልማት
ዓቅም አሟጦ ለመጠቀም የማያስችሉ፣ በፕላን ያልተደራጁ አሰፋፈር የሚሉ ፊዚካላዊ መስፈርቶች ናቸው፡፡

ከሌሎች ክልሎች በተለየ የአማራ ክልል መስፈርቶቹ በሚለኩ መልኩ እንዲዘጋጁ ከማድረግ ባሻገር የሕግ
ድጋፍ/ሽፋን/ እንዲኖራቸውም አድርጓል፡፡ መቐለ (ከይዞታ ስፋት ውጭ)፣ ጅማ፣ ድሬ ዳዋ፣ ሐዋሳ አመላካች
መስፈርቶች በግምገማ ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ መልሶ ልማት የሚጠይቁ ቦታዎች ለመምረጥ ሁሉንም
ከተሞች የተጠቀሙዋቸው ፊዚካል መስፈርቶቹ አግባብነት ያላቸው ናቸው፡፡

ሁለተኛው መሰረታዊ መርህ አንድን አካባቢ መልሶ መልማት አለበት የሚባል ከሆነ አካባቢው የሚሰጠው
የልማት ፋይዳ ከሌላው ሲነፃፀር በምን ያህል ሲወርድ ወይም የአካባቢው አካል ከሆኑ የልማት አጀንዳዎች

91
ስንቶቹ ሳይኖሩ ሲቀሩ መሆኑ መልስ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ይህንን መርህ ሁለት የተለያዩ አመለካከቶች
በስፋት ይንሸራሸሩበታል፡፡ በአንድ በኩል የአካባቢው የልማት አካል ከሆኑት አንዱን ሲጎድል ሌሎቹ
ፋይዳቸው ተሟጦ እስካላለቀ ድረስ መልሶ ከመልማት ይልቅ የጎደለውን ማሟላት ተገቢነት የሚደግፍ ነው፡፡
ይህንን ሁኔታ ዓቅም በማይኖርበት/በሚያንስበት ጊዜ ተመራጭ መፍትሔ ነው፡፡

በእኛ ሀገር ሁኔታም የአቅም ውሱኑነቱ በነበረ ጊዜና አሁንም በተወሰነ መልኩ ያለ አካሄድ ነው፡፡ ከኬር
ኢትዩጵያ ባዞላ ንጣፍ መንገድ፣ የጋራ ንጽህናቤት እና ቦኖ ውሃ ግንባታ ጀምሮ የአካባቢ ልማት ፕሮጀክት ሰፊ
ስራ ተከናውኗል አሁንም ሰፈርን ለመቀየር የኮብል ስቶን ግንባታ በሁሉም ከተሞች በስፋት የታያ ነው፡፡ እንደ
አዋሳ በዋናነት የተተገበረውም የጎደለውን ዋና መሰረተ ልማት በማምጣት መልሶ ማልማትን ለማስፋት
የተኬደበት ርቀት ከከተማዋ ነባራዊ ይዞታ አደረጃጀትና ባለይዞታ አሰላለፍ በጥሩ ጎኑ የሚታይ ነው፡፡

ሁለተኛው ዕይታ ደግሞ አንዱን አካል ከጎደለ አጠቃላይ መልሶ ልማት መካሄድ እንዳለበት የሚደግፍ ዕይታ
ነው፡፡ ከወጭና ቶሎ መልሶ ለማልማት የመቻል እድልን ከመጠቀም አንጻር አንዱ/ሁለቱ ሲወድቅ ሌላው
የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ስለሚወድቅ የቦታው ሙሉ ተፈላጊነት ሳይጠፋ የሞተን ከማስነሳት ያልተለየውን
ሁሉ ከወደቀና ከተበላሸ በኋላ ከሚደረግ መልሶ ልማት ፈተና የታመመን ማከም ስለሚሆን/ ከባቢያዊ
ማፈረስና መልሶ መገንባት የተከናወነባቸው የእኛ ሀገር ከተሞች በአመዛኙ ይህንን መርህ መከተላቸውን
ያረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ ከላይ የከተሞቹ ገፅታዊ እና ኣካባቢያዊ ይዞታቸው ወደቀ እንጂ ማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ ይዞታቸው ስላልወደቀ የመልማት እድላቸው ከፍተኛ እያለ ማለትም ሳይሟጠጥ ወደ መልሶ
መልማት እንደገባ ያሳያል፡፡

ሶስተኛው ጉዳይ ቦታው የሚመርጠው አካልና አመራረጥ ሂደቱን ይመለከታል፡፡ በሀገራችን ከተሞች
እየተካሄዱ የሚገኙ መልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች የቦታ መረጣ ውሳኔው በአመዛኙ በመሬት ተቋማት ባሉ
ባለሙያዎችና በፕላን ሂደት በቴክኒካል ሰዎች እንደሚወሰን የፖለቲካ ክፍሉ እራሱ ትግበራው ላይ ካልሆነ
በቦታ መረጣው በንቃት እንደማይሳተፍ ፤ ከሁሉም በላይ ግን በተወሰነ የአዲስ አበባ ልደታ ተሞክሮ በቀር
በቦታ መረጣና በልማት አማራጮች ላይ ማህበረሰቡ እንደማይሳተፍ በግለጽ የታየ ነው፡፡

ማወያየት የሚባለው እንደ ሃሳብ ራሱ የሚጀምረው በተወሰነ ፕላን ሲሰራ ከሁሉም በላይ ግን ቦታው ተመርጦ
መልሶ እንደሚለማ ተወስኖ በአፈጻጸም ጉዳይ ያተኮረ ነው፡፡ በአካባቢው ግልጽ ችግር መኖሩ እየታየም
ኗሪዎቹ መጪው ምን ሊሆን ይችላል በማለት የለውጥ ስጋት፤ ተጎጅ የመሆን ስጋት፤ በተለይ የሥራና ገቢ
ማጣት ስጋት የመፈናቀል ስጋት ወዘተ መነሻ ተመችቷቸው እየኖሩ እንደሆነ ራሳቸውን በማሳመን እንዲነኩ
ያለመፈለግ፤ ከችግሩም መለማመድ ወዘተ እንደሚያጋጥም በሌሎች ሀገራት ልምድና በንደፈሃሳብ የታወቀ
ቢሆንም የእኛ ከተማ አስተዳደሮች አለማወያየታቸው እንጅ ህዝቡ ከ90% በላይ የመልሶ ማልማትን ዓላማ
እንደሚደገፈው በናሙና ጥናቱ ማረጋገጥ ተችለዋል፡፡

92
3.2.4. መልሶ ልማት የተመራበት ዓላማ
ዓለም አቀፍ ተሞክሮ የሚያሳየው መልሶ ማልማት የሚከናወንበት ዓላማ ላይ የተለያዩ ክርክሮች ይነሳሉ፡፡
ዋናው መከራከሪያ ነጥብ ደግሞ የመልሶ ማልማት ዓላማ አካባቢን መለወጥ ወይስ የዜጎችን ዙሪያ መለስ
ኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ ለውጥን ነው የሚል ነው፡፡

በእርግጥ መልሶ ማልማት የተካሄደባቸው አካባቢዎች ውጫዊ ገፅታቸውና ኢኮኖሚያዊ ዓቅማቸው ከመሰረቱ
እንደሚለወጥ በቬትናም ከተሞች በቅርብ ጊዜ የተካሄዱ መልሶ ልማቶች ምስክር ናቸው፡፡ ነገር ግን በቦታው
የነበሩ ዜጎች ለመለወጥ የተካሄደ አልነበረም፡፡ ከልማቱ ተጠቃሚ የሆኑ አልሚዎቹ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡
ይኸው ውጤት ልማቱ ያነገበው የዜጎችን ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ዓላማ አላሳካም፡፡

በእኛ ሀገር የተካሄዱ መልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች ያነገቡት ዓላማ ምን ያህል ስፋት እንዳለው፣ ይዘቱ በምን
ላይ እንደሚያተኩር፣ ዓላማው በራሱ በውል ተቀምጦ ነው ወይ የሚካሄደው የሚሉት ጉዳዮችን መሰረት
ተደርጎ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

በአዲስ አበባ የመልሶ ማልማት እንዲያሳካቸው የሚፈለጉ መሠረታዊ የልማት ግቦች

 በመሃል አዲስ አበባ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን የከተማ እርጅና በመቅረፍ የመዲናዋን ዓለም አቀፋዊ
ገጽታና ተወዳዳሪነት ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር፣
 ለኑሮ ምቹ ባልሆኑና ለአደጋ በተጋለጡ የበሰበሱ መኖሪያ አካባቢዎች ውስጥ የሚገኘው የከተማ ነዋሪ
ወደ ተሻለ መኖሪያ አካባቢ በማዛወር የሕዝቡን ሕይወት ማሻሻል፣
 በመሃል ከተማ ከደረጃ በታች በሆነ ግንባታ የተያዘውን የከተማ ቦታ ለተሻለና በከተማው መሪ ፕላን
ለተጠበቀው የመሬት አጠቃቀም እንዲውል በማድረግ ውስን የሆነው የከተማ ቦታ የተሻለ ጥቅም
እንዲሠጥ ማድረግ፣
የሚሉት እንደሆኑ ከከተማ ማደስ ልማት ጋር ተያያዥነት ባላቸው ልዩ ልዩ ሰነዶች ላይ በአንድ ወይም
በሌላ መንገድ ተጠቅሶ እናገኘዋለን፡፡

እነዚህ ዓላማዎች በጥልቀት ሲመረመሩ ጥልቅና ዙሪያ መለስ ልማትን ታሳቢ ያደረጉ አይደሉም፡፡ አንደኛው
ጉዳይ በከተማው መሃል አከባቢዎች የተንሰራፋው የቤቶችና ሰፈሮች እርጅና በአዲስ ግንባታ ብቻ በመለወጥ
ከተማይቱ ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ከፍ ለማድረግ ዋስትና አይደለም፡፡ የከተማዋ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት
ከፍ ማድረግ የሚቻለው መልሶ ልማቱ ሰፋ ባለ የልማት ግብ ሲመራ መሆኑ ግንዛቤው ጠንካራ ነው የሚባል
አይደለም፡፡ ዓላማው የአካባቢውን ኢኮኖሚ እንዲያንሰራራ ወይም ከመሰረቱ እንዲለወጥ የሚያስችል ዕይታ
እንዲይዝ አልተደረገም፤ በዚሁ ልክም ሊለኩ የሚችሉ ግቦች እንዲኖሩት አልተደረገም፡፡

93
ሁለተኛው የአካባቢዎቹ ለውጥ ዜጎች የተሻለ የመኖሪያ ቤትና አካባቢ እንዲያገኙ በማድረግ የዜጎች የኑሮ ደረጃ
በማሻሻል በኩል የማይካድ ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚያስገኝ ቢሆንም መልሶ ማልማቱ መደበኛ ባልሆነ የኢኮኖሚ
ዘርፍ ተሰማርቶ የሚተዳደር ህዝብ ስራውና ገቢውን ከመሰረቱ እንዲለወጥ ወይም እንዲሻሻል፣ ካልሆነ ቢያንስ
እንዳያጣ የሚያስችሉ ዓላማዎች አይደሉም፡፡ ስለዚህ የዓላማዎቹ ድምር ትርጓሜ ሰውን ሳይሆን አካባቢን
በልማት መለወጥ ሲሆን መልሶ ማልማቱ ከመሬት የመጠቀሚያ መብት እና ሪል እስቴት ልማት ኢኮኖሚያዊ
ዓቅም ለከተማይቱ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ቢሆንም ተጠቃሚ ተጎጂውን የሚክስበት አግባብ የለም፡፡

በድሬዳዋ ከተማ የተከናወኑት መልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች የተመሩበት ዓላማም ቢሆን ከአዲስ አበባው ጋር
ይመሳሰላል፡፡ ቀደም ሲል አስተዳደሩ ለተለያዩ አካባቢዎች ያዘጋጃቸው የአካባቢ ልማት ፕላን (LDP) ሰነዶች
የነባር አካባቢ ልማት ዓላማ በመሀል ድሬዳዋ የሚስተዋለውን የኢኮኖሚ ድቀት መቅረፍ፣ የመሃል ከተማውን
የተጎሳቆለ ገጽታ መቀየር፣ ከደረጃ በታች በሆነ ግንባታ የተያዘውን የከተማ ክፍል ደረጃውን ለጠበቀ/በከተማው
መዋቅራዊ ፕላን ለታለመለት/ አገልግሎት ማዋል፣ ድሬዳዋን ተወዳዳሪና ሳቢ ማድረግ እንደቁልፍ ዓላማ
ይጠቀሳሉ፡፡ የአስተዳደሩ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች አስተያየትም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡

የአካባቢ ልማት ፕላን ሰነዶች እላይ የተጠቀሱትን ግቦች እንደ ቁልፍ ዓላማ ቢያስቀምጡም በድሬዳዋ የነባር
ከተማ እና የመስፋፊያ አካባቢዎች ልማት የሚገዛበት የሕግ ማዕቀፍ እነዚህ ዓላማዎች በቂ ትኩረት የሰጠ
አይመስልም፡፡ በድሬዳዋ ነባርና መስፋፊያ አካባቢዎች የሚካሄደው ልማት የሚገዛበት የሕግ ማዕቀፍ
“ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ እንዲለቀቅ ሲደረግ ለባለይዞታው ካሳ የሚከፈልበትና ምትክ ቤትና
ቦታ የሚሰጥበት የአፈፃፀም መመሪያ ” ነው፡፡ የጥናት ቡድኑ ከነዚህ ሰነዶች ውጭ የድሬዳዋን መልሶ ልማት
ዓላማ የሚያብራራ ሌላ የህግ ማዕቀፍ ወይም የፕሮጀክት ሰነድ አላገኘም፡፡

ከላይ የተጠቀሰው የአስተዳደሩ መመሪያ ቁልፍ አጀንዳ የልማት ተነሺዎች ካሳ ክፍያና ምትክ ቤት/ቦታ
አሠጣጥ ሲሆን ባለይዞታዎች ከነባር አካባቢያቸው እንዲነሱ የሚደረገው ደግሞ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል
ቦታውን ከግንባታ ወይም ከነባር ይዞታ ነፃ ለማድረግ እንደሆነ በግልጽ ተደንግጓል፡፡ ከዚህ ድንጋጌ መረዳት
የሚቻለው በድሬዳዋ ነዋሪዎችም ሆኑ ተቋማት ከነባር አካባቢ የሚነሱት በተነሽዎቹ የተያዘውን መሬት ለአዲስ
ኢንቨስትመንት እንዲውል ለማድረግ ነው፡፡ በዚህ መሠረት በድሬዳዋ የከተማ ማደስ ፕሮግራም ቁልፍ ዓላማ
ለኢንቨስትመንት ወይም ለማህበራዊ ተቋማት ግንባታ የሚውል ቦታ ማዘጋጀት ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡

እዚህ ላይ ትልቁ ጥያቄ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል መሬትን ማስለቀቅ በሚለው መሠረተ ሃሳብ ዙሪያ ነው፤
በድሬዳዋ የሚካሄደው የነባር ከተማ መልሶ ልማት ፕሮግራም መነሻ እንደሆኑ ቀደም ሲል የተጠቀሱት ሦስት
ጉዳዮች ማለትም የከተማ እርጅናን መቀነስ፣ ከተማዋን በፕላን እንደገና መልሶ ማደራጀት እንዲሁም ከፌደራል
መንግሥት ለድሬዳዋ የተሰጣትን ሀገራዊ ተልዕኮ መወጣት በአጠቃላይ ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት
ሥራዎች መሆናቸው አያከራክርም፡፡ ይኸውም የከተማ እርጅናን ለመቀነስ የሚወሰድ እርምጃ ዋና ዓላማ
የከተማዋን የተጎሳቆለ ገጽታ መቀየር ሲሆን ከደረጃ በታች በሆነ አገልግሎት የተያዘ ቦታን ለተሻለ መሬት

94
አጠቃቀም ማዋል የከተማ ፕላን ቁልፍ አጀንዳ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሚደረገው የሕዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ
ሲባል እንደሆነ የአስተዳደሩ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በአጽንኦት ይገልፃሉ፡፡

ከተጀመረ ሁለት ዐመት ገደማ የሆነው የሀዋሳ ከተማ መልሶ ማልማት እንቅስቃሴ በእስካሁን ሂደቱ
ለኢንቨስትመንት የሚያስፈልገውን ቦታ ለማዘጋጀት ሲባል ነዋሪውን እያስለቀቁ ለሚያለሙ ባለሃብቶች
በጨረታ ቦታ ለመሸጥ ሲሆን እንደ ዋና ዓላማም የከተማዋን ያረጀ ክፍል በማደስ (regenerate) ገጽታዋን
ለመለወጥ፣ ያለውን የመሬት አቅርቦት እጥረትን ለመቅረፍ፣ የተጠጋጋ ልማትን በማምጣት ወደ ጎን መለጠጥን
ለመከላከል፣ የከተማውን የመሰረተ ልማት ችግር ለመቅረፍና ብሎም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን
በመፍታት መሻሻል እና እድገትን ለማምጣት የሚል ነው፡፡

የልማት ተነሽዎች ሕይወት ከነበረበት እንዳይወርድ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግሥት ድንጋጌ ጥበቃ የተደረገለት
የልማት አጀንዳ ነው፡፡ ነገር ግን በየከተሞቹ የሚታዩ የመልሶ ማልማት ዓላማውና ግቦቹ በመልሶ ልማት ሂደቱ
በቦታው ላይ የነበሩ ነባር ባለይዞታዎችን ኑሮ ለማሻሻል ወይም ከነበረበት እንዳይወርድ ለማድረግ የሚደረገው
ጥረት፣ እንዲሁም የመልሶ ማልማት የዓላማው ፓኬጅ በርካታውን በድህነት የሚኖር ዜጋ የመለወጥ አቅጣጫ
መከተሉን በሚመለከት አጠያያቂ ያደርገዋል፡፡ ይኸው ሁኔታ በሌሎች ሀገራት ዜጎችን የመለወጥ ባህሪ
ባልነበራቸው መልሶ ማልማት ስራ ያስከተሉት ውጤት ተመሳሳይ ባህሪ እያሳየ ነው፡፡

በነባር ከተማ መልሶ ልማት ዙሪያ ምርምር ያደረጉ ምሁራን ምክርም ሆነ የተሳካ መልሶ ልማት ያካሄዱ ሀገራት
ልምድና ተሞክሮ የሚያሳየው የነባር ባለይዞታዎችን/ተጠቃሚዎችን ሕይወት የማያሻሽል መልሶ ልማት ዘላቂ
አይደለም የሚለውን ድምዳሜ በእኛ ሀገርም እውነታውን እየታየ ነው፡፡ መነሻውም የልማት ዓላማ ምን ያህል
እውነተኛ ዜጎችን መለወጥ ነው የሚለውን እንዲጠየቅ ያደርገዋል፡፡

በደሴ ከተማ ሲካሄድ የቆየ መልሶ ልማት ተልእኮ ከጅምሩ መሬት አቅርቦት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን
የተሻለ ዓቅም ላላቸው የመሬት ፍላጎት ለመመለስ የሚኬድ ነው፡፡ ያም ሆኖ ግቡ ምን ያህል የመሬት አቅርቦት
ችግር መፍታት እንዳለበት በሚለካ አግባብ አልተቀመጠም፡፡ ሰፈሮች በፕላን ለማደራጀት፣ በተወሰነ መልኩም
ማስተንፈሻ ክፍት ቦታዎች ለመጨመር የሚደረግ እንቅስቃሴም ቢሆን የመሬት ፍላጎቱ ለመመለስ በሚደረግ
ጥረት በእግረ መንገዱ የሚከናወኑ ናቸው ብሎ መውሰድ ይቀላል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ያወጣውና በስራ ላይ የሚገኘው መመሪያ ቁ.6/2006
በከተሞች የሚከናወን መልሶ ልማት ዜጋ ከድህነት እንዲላቀቅ እና ከተሞች የኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ
ልማት ማእከላት እንዲሆኑ ለማድረግ መሆኑ መርህ ቢያስቀምጥም የደሴ ከተማ የአካባቢ የልማት ዕቅዶች
ሲዘጋጁ መርሁ በአግባቡ ሲተረጉሙት አይታይም፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ወደ መልሶ ልማት ሲገባ በድህነት
የሚኖር ዜጋ ካለበት ድህነት የሚወጣበት የልማት ይዘት ከማቀድ ይልቅ ይባስ ድህነቱ እንዲጨምር
የሚያደርጉ አካሄዶች ይታያሉ፡፡

95
የመቐለ ከተማ መልሶ ማልማት ዋናው ይዘት አፍርሶ መገንባት ሳይሆን አካባቢን ማሻሻል ላይ ያተኮረ በመሆኑ
መልሶ ማልማቱ የተከተላቸው ዓላማዎች ሌሎቹ ከተሞች ላይ ከሚታዩ ለየት ያለ ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን
የይዞታዎች ሕጋዊነት የማረጋገጥ ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከዚህ አንፃር መልሶ ማልማቱ ያነገባቸው ዓላማዎች፡

 ፕላን ያልጠበቁ ሰፈሮች የከተማ ስርዓት እንዲኖራቸው ለማድረግ


 ከ30% የማያንሱ ሰነድ አልባ ይዞታዎች ህጋዊ ማረጋገጫ ለመስጠት
 መሰረተ ልማት ያልተዳረሰባቸው አካባቢዎችና ሰፈሮች መሰረተ ልማት ለማሟላት፣
 ቋሚ ንብረቱ በካፒታል ገበያው ተገቢውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲያስገኝ ለማስቻል፣ የሚሉ
መሆናቸው በየአካባቢ የልማት ዕቅዶቹ ሰፍረው ይገኛሉ፡፡

መቀሌ ከተማ (ቀበሌ 14) ላይ በዕቅድ የቀረው አፍርሶ የመገንባት አማራጭ ዓላማው ውጫዊ ገፅታ ከመቀየር
በዘለለ የተሟላ የከተማ ልማት ዓላማዎች ያካተተ (Comprehensive) ሆኖ አይታይም፡፡ መልሶ ልማት
ከሚፈለግባቸው መሰረታዊ ምክንያቶች አንዱ መሬት በአግባቡ ለመጠቀም ነው፡፡ ፈርሰው እንደገና ቢገነቡ
ይበልጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚሰጡ ቦታዎች (ቀበሌ 14፣ ዐ4 መስጊድ አካባቢ፣ ማይሊሓም ወዘተ) ከአጭር
ጊዜ የከተማው የፋይናንስ እጥረት ብቻ በማየት ቀበሌ 14 ከአጼ ዮሐንስ ሆቴል በስተጀርባ ያሉት ጥቂት
ብሎኮች ብቻ እንዲሁም መስጊድ ዐ4 አካባቢ አንድ ብሎክ ብቻ ሙሉ በሙሉ ፈርሰው እንደ አዲስ እንዲሰሩ
ሲታቀድ በአካባቢዎቹ ሰፋ ያለ ቦታ ፈርሶ እንደ አዲስ ቢገነባ በዙሪያው የሚያሳርፈው የተፅዕኖ ስፋትና
ጥንካሬ ከግምት ያስገባ ኘላን አልተከተለም፡፡

ለቅርስነት ልዩ ጥበቃ የሚደረግለት የተከለለ አካባቢ እንደተጠበቀ ሆኖ ቀበሌ 14 ቀስ በቀስ እራሱን እየለወጠ
እንዲሄድ መፈቀዱ አካባቢው ካለው ዕምቅ ኢኮኖሚ ዓቅም ጋር አብሮ የሚሄድ ውሳኔ አይደለም፡፡ በሌላ
በኩል በርካቶቹ ይዞታዎች ጠባብ በመሆናቸው ባለይዞታዎች በጋራ እንዲያለሙ ካልሆነ ሽጠው እንዲለቁ
ለማድረግ ከተቀየሱ ስልቶች ጋር የሚጣጣም አይሆንም፡፡

ሌላው የመልሶ ማልማት መሰረታዊ ዓላማ ተጨማሪ ቦታ መፍጠርና ጥግግት ማሻሻል ነው፡፡ ይህንን ዓላማም
ቢሆን እየተሰራበት ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለም፡፡ ከተዘጋጁት 17 የአካባቢ ልማት ኘላኖች ምን ያህል ጥግግት
(density) መደረስ እንዳለበት ታሳቢ አላደረጉም፡፡

በፕሮጀክት ደረጃ የሚታዩ ከፍ ሲል የተገለፁ ውስንነቶች ቢኖሩም መልሶ ማልማቱ ካጠቃላይ የከተማው
የእድገት ፍላጎት እና ዕምቅ ኢኮኖሚያዊ ዓቅም ጋር እንዲቀናጅ በማድረግ በኩል ከሌሎቹ ከተሞች የተሻለ
ነው፡፡ ቀበሌ 14 እና እንዳየሱስ አካባቢ የልማት ዕቅዶች እንደ ምሳሌ ብንመለከት የልማቱ ይዘት ከመሬት እና
ግንባታ አልፎ ከቱሪዝም እና ተያያዥ ኢኮኖሚያዊ ዕምቅ ዓቅሞች ጋር እንዲተሳሰር ተደርጎ ተዘጋጅተዋል፡፡

ዓለም አቀፍ ተሞክሮ የሚያሳየው የመልሶ ማልማት ዓላማ የሚወሰነው ከልማቱ ይዘት መነሻነት እንደሆነ
ነው፡፡ ከይዘቱ አኳያ የተለያዩ ሙያዊ ክርክሮችም ሆነ የተለያዩ ሀገራት የፖሊሲ አማራጮች መልሶ ማልማቱ

96
ምን ላይ ያተኩር በሚለው በአንድ ጫፍ የጎደለውን መሙላት ብቻ በቂ እንደሆነ ለምሳሌ ውጫዊ ገፅታና
አካባቢያዊ ጉድለት ካለ እነሱን ብቻ በመለወጥ/በማሟላት ነባሩ ማህበረሰብና ኢኮኖሚን ማስቀጠል፤ ጉድለቱ
የማህበራዊ ችግር ከሆነ እሱን ቀርፎ ሌላውን መተው የሚለው ሲሆን የሚከተለው የልማት አማራጭም
አካባቢን ማሻሻል የሚለውን ጫፍ እንደሆነ ከፍ ሲል ተብራርቷል፡፡

ሌላው ጫፍ ደግሞ ሁሉም አዲስ እስኪሆን አብሮ መለወጥ የሚል ቅኝት ይታያል፡፡ ለምሳሌ ፊዚካልና
አካባቢያዊ ሁኔታውን ከታደሰ ከመሬቱ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲገኝ ይጠበቃል፤ ኢኮኖሚው ከፍ
ካለ ደግሞ የአዲሱ ማህበረሰብ ገጽታ ስለሚይዝ በአካባቢው የነበረውን ነባር እንቅስቃሴ ሌላ ቦታ መሄድ
(Displacement) አለበት የሚል ዕሳቤ ስለሚነሳ ከሙያዊ አስተሳሰብነታቸው ባሸጋር የፖሊሲ አማራጮች
ጭምር ሆነው ሲተገበሩ ይታያሉ፡፡

ወደ የኢትዮጵያ መልሶ ማልማት ሁኔታ ስንመለስ መልሶ ማልማት ህገ መንግስቱን ተከትሎ የሰውን ሂወት
መቀየር መሆኑን ከግምት ማስገባቱ የሚያሳይ አንዳች መረጃ የለም፡፡ ሂደቱ በአመዛኙ ግልጽ አላማ በጽሁፍ
ያላስቀመጠ፤ ከቦታ ቦታ የተለያየና ወጥ መርህ ያልተከተለ መሬት ለማግኘት የሚመስል፣ በአመዛኙ ፊዚካላዊ
ሁኔታን ለመለወጥ ያለመ ግን በገቢ ሲለካ ከመሬቱ መገኘት የሚገባው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ መገኘቱ
አጠያያቂ ነው፡፡

መልሶ ማልማቱ የግንባታውንና መሰረተ ልማት ደረጃ መለወጥ ቢችልም በፕላን አለመኖር፣ የጎደለው የህዝብ
ክፍትና መናፈሻ ቦታ ምላሽ እያገኘ አይደለም፤ በአንፃሩ ችግር የሌለበትን ማህባራዊ ይዘቱን በስፋት ነክቷል፤
ነባሩን ኢኮኖሚና ማህበራዊ እሴት በቦታው መጠበቅ ያልቻለ በአመዛኙ መቀየር የሚለውን የሚከተል ነው፡፡
መልሶ ማልማቱ ትኩረት የእይታና ግንባታ ለውጥ ላይ ያነጣጠረ ነው ሲባል፤

₋ ቦታ ሲመረጥ ጀምሮ ቦታው የተጎሳቆለ መሆኑ እንጅ ማህረሰቡ የህይወት ለውጥ በማወዳደር ቅድሚያ
መስጠት እንደማይታይ፡
₋ ፊዚካል ለውጥ ሲታሰብም ለምሳሌ ደሴ ነባሩ አሰፋፈር ቅርጽ እንደያዘ ልማቱ፤ የመሬት ዋጋን
ከማሳደግ ቢዝነስ ከማስፋት፤ ማህበራዊ ትስስር ከማሳደግ ይልቅ እንዲዳከም ያደረገ ውጤት ታይቷል፡
₋ አዲሱ ከነባሩ ግንባታና እርስ በዕርስ አለመዋሃድ /አዲስ አበባ የቀድሞ ማዛገጃ ቤት ህንፃ፣ መቐለ
ቀዳማይ ወያነ ገበያ/
₋ ልማቱ አከባቢውን ለማነቃቃት አለመቃኘት /ደሴ የህንፃዎች ዲዛይንና መንገዶች የመሬት አቀማመጡ
ተከትለው ያለመገንባት፣ መቐለ የቐዳማይ ወያነ የገበያ ማእከል በነባሮቹ ህንፃዎች መታሰሩ/

አካታችነትን በተመለከተ ከመኖሪያ ቤት በተለየ የንግድ ቦታዎች ላይ በቦታው ያሉ/የነበሩ እንዲያለሙ


የተፈቀደበት ሂደትም በስፋት ነበር፤ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ከተሞች ይህ ስልት ተተግብሯል፡፡ በአመዛኙ
በዚህ መንገድ መገንባት ሲፈቀድም ቦታው ከለማ በኋላ ነባሩን ቢዝነስ ሳይሆን ሌላ ስራ መግባት የሚጠይቅ

97
የግንባታና የፕላን ጥሰት ይከሰታል፡፡ ለምሳሌ የደሴ ጦሳ ማህበር ወደ ሆቴል ስራ ነው የተገፋፉት፡፡ አዲስ
አበባ ላይ የቂርቆስ ገበያ ከዕህል ንግድ በህንጻ ውስጥ ወደ ሚከናወን ሌላ ባህሪ ያለው አገልግሎትና ንግድ ነው
የተለወጠው፡፡ በዚያ ቦታ ከነበሩ ከ50% ያላነሱት ሸጠው እንደወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በመሆኑም በእርግጥ
ነባሮቹ በቦታው አሁንም እየሰሩ ተለውጧል ወይ የሚለው በደንብ መፈተሽ ያለበት ነው፡፡

የአካባቢ መሻሻል ይዘት ያለው መልሶ ማልማት (ማለትም ግንባታ ከማፍረስ በመለስ ለከባቢው ወሳኝ
መሰረተ ልማት የማሟላት ይዘት ያለው) ስራም በስፋት እንደሚከናወን የታየ ጉዳይ ነው፡፡ አከባቢን ከነባር
ግንባታ ጠርጎ ማደስ በቅድሚያ ከፍተኛ መሰረተ ልማትን በመዘርጋት ከባቢው እንዲቀየር የማድረግ የከተማ
መልሶ ማልማትን እንደ ዋነኛ አማራጭ የተገበረችው አዋሳ ስትሆን በማሻሻል (Upgrading) በሁሉም ከተማ
ያለ ሲሆን በዚህ መልክ ስፋት ያለው ስራ የተከናወነው ደግሞ በአዲስ አበባ ነው፡፡ በአዲስ አበባ በስፋት ኬር
የሚባል ድርጅት የአካባቢ ልማት ፕሮጀክት በሚል አሁን ደግሞ የማህበረሰብ ልማት ኤጀንሲ ስር በማዋቀር
ሰፊ ስራ ተከናውኗል፡፡

ከዚህ አካሄድ በበጎ የሚታየው ጉዳይ አብዛኛውን ሰፈር የቀየረ እና በሂደቱም በቦታው ያሉ አካላትን ተጠቃሚ
ያደረገ መሆኑ ነው፡፡ በጉድለት የሚነሳበት ደግሞ በመጀመሪያ በሀብት አመዳደቡ ፍትሃዊነት ላይ ነው፡ ሀብት
የሚመደበው ህዝቡ ባወጣው መጠን 35% ማጣመሪያ ስለሆነ ዝቅተኛ ገቢ ማህበረሰብ ያለበትና ዝቅተኛ
መሰረተ ልማት ያለበት ሰፈር ባለበት ሲቀር ጠቀም ያለ ማዋጣት የሚችለው ወገን ያለበት መንደር ደግሞ
በፍጥነት እንዲለወጥ በማድረግ ከፍትሃዊነትና ሚዛን መጠበቅ አንጻር ክፍተቱ ሰፊ ነው፡፡ ሁለተኛ ጉዳይ ፈርሶ
በሚለማ ቦታ ሀብት ማባከን፣ ከዚህ ሌላ ደግሞ ህገወጥ ሰፈራዎች እንደ ህጋዊነት ማግኛ መሳሪያ ለመገልገል
የሚደረግ የማምታታት ሂደት ሰለባም ሆኗል፡፡ ሀብት አመራሩም በፊት ኮሚቴ የሚዘርፍበት፤ አሁን ደግሞ
ሂሳቡ ወደ አስተዳደሩ አካውንት ገቢ ሆኖ ሲመራ ከማህበረሰቡ ነጻነት ይልቅ በአስተዳደሩ የሚታሰርበትን
ሁኔታ መኖሩ ሌላኛው ደካማ ጎኑ ነው፡፡

አከባቢን እንዳለ አፍርሶ ከመገንባት ጎን ለጎን ቀደም ሲል የተጀመረውና አሁንም በሁሉም ከተሞች በተለይ
ደግሞ በአዋሳና መቀሌ በስፋት ያለው አዲስ አበባም ቸርችል ጎዳና፣ ቦሌ መንገድ እና ሀይሌ ገብረስላሴ ጎዳና
የታየው አካሄድ አንድና ሁለት ይዞታ ላይ የሚከናወን መልሶ ማልማት ነው፡፡ ይህ አካሄድ በአመዛኙ በገበያ
በራሱ የሚመራ፣ በቦታው የነበሩ/ያሉ አካላትን ተጠቃሚ ያደረገ፣ በአስተዳደሩ ላይ የካሳ ጫና ያልፈጠረ፣
አከባቢዎችን በሚዛናዊነት ለማነቃቃትና ቅይጥ ይዘት እንዲኖራቸው ረድቷል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ዙሪያው
አብሮ ስለማይለማ የገነባ ወገን ተጠቃሚነት የተገደበበት፣ አንዳንድ ሰፈሮች ላይ ደግሞ አላስፈላጊ የትራፊክ
መጨናነቅ የፈጠረበት፣ በህንጻ ከፍታ ልዩነቱም የአጎራባች ነጻነት የተጣሰበት፣ ሁለት ሶስት እንጨት ለየብቻ
እንደሚነድበት እሳት ሁሉ ከተማውን የማሞቅና የማነቃቃት ብቃቱ የተገደበ መሆን፣ ከተሞቹ ዋና
ማዕከላቸውና ዳራቸው የማይለይበትና የተረበሸ ሁኔታ መፈጠሩ በችግር የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

98
ከአንድና ሁለት ይዞታ ሰፋ ያለ በቦታው ያሉ አካላት ቅድሚያ በመስጠት መልሶ እንዲለማ የተሄደበት ስልት
በአዲስ አበባ መርካቶ፣ ኮልፌ፣ ቂርቆስ ገበያን፣ በመቀሌ የቐዳማይ ወያነ ገበያ፣ እና ጅማ መርካቶ፣ በደሴ ጦሳ
ማህበር የተሰራው ልማት በውጤት የሚጠቀሱ ሲሆኑ በሂደቱ በቦታው ያሉ አካላትን በቦታው የፈጠሩትን
እሴት በመልሶ ማልማቱም እንዲጠቀሙ እንዳይፈናቀሉ እንደረዳ ሲታመን አብሮ የመስራት ባህሉ
ባለመዳበሩና እርስ በእርስ መተማመን ባለመፈጠሩ ልማቱ እንደታሰበው በከተሞች ፈርሶ ከሚለማው የፈጠነ
ሳይሆን የተጓተተና በእርስ በእርስ ውዝግብ የተሞላ ነበር፡፡

መሰረተ ልማት መር የሆነው ከተማ መልሶ ማልማት ደግሞ በተለይ የመንገድ ስራው ለከተሞች መለወጥ
ትልቅ ድርሻ ያበረከተ ሲሆን ይህ ስኬት በሁሉም ከተማ በሚባል ደረጃ የታየ ሲሆን ጉድለት የተንጸባረቀው
በአዲስ አበባና በደሴ ነው፡፡ ጉድለቱም በአመዛኙ ዓላማው የትራፊክ ፍሰት ፍጥነትና ከአደጋ መጠበቅ
በመሆኑና ኢኮኖሚውን ማሳደግ፤ ማህበራዊ ትስስርን ማጎልበት የመሬት ዋጋን መሻሻል በአግባብ ይዞ
ባለመሄዱ በዲዛይንና በግንባታ ከተማን ለሁለት የከፈለ የትስስርና መቀራረብ ጥቅም (Agglomeration)
ያጠፋ፤ ማህበራዊ ትስስርን ያቋረጠ፤ ለምሳሌ የአዲስ አበባ ቀለበት መንገድና የቀላል ባቡር መስመር፤ የደሴ
የሰኞ ገበያ መንገድ/መጥቀስ በቂ ነው፡፡

ተፈላጊ የልማት ዓይነትን ወስኖ ከመምራት አልሚው የፈለገውን እንዲሰራ ማስተናገድ ሌላ ጉድለት ነበር፡፡
ካሳንችስ ላይ እንደታየው አካባቢው የሆቴል መነሃርያ ሆኖ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ እንዲፈጠር የሆነው
በቦታው ስንት ሆቴል ሊኖር እንደሚገባና ሌሎች አገልግሎቶች ሊኖራቸው የሚችለው ምጣኔ በፕላን
ባለመመራቱ የተከሰተ ነው፡፡

3.2.5. ተቋማዊ አደረጃጀት


መልሶ ማልማት የሚመራ ተቋም ምን ዓይነት አደረጃጀት ሊኖረው እንደሚገባ ለማጤን መጀመሪያ መታየት
ያለበት "መልሶ ልማት መንግስታዊ አገልግሎት ነው ወይስ ልማት?" የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ ከላይ በተዛማጅ
ጥናቶች ዳሰሳው እንደታየው መልሶ ማልማት ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ የሚፈስበት ኢንቨስትመንት እንጂ
የማዘገጃቤታዊ ወይም መንግስታዊ አገልግሎት አይደለም፡፡ ልማቱ የመንግስት መዋእለ ንዋይ የሚፈስበት
ብቻም ሳይሆን ከፍተኛ የግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንትም የሚንቀሳቀስበት ነው፡፡

በእኛ ሀገርም ቢሆን መንግስት በከተሞች የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ለመገንባት ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ ሲያፈስ
የግሉ ኢንቨስትመንት በህንፃ ግንባታ (መኖሪያ ቤት፣ የንግድ ቤት) ዘርፉ እየተሳተፈ መሆኑ በናሙና ከተሞቹ
የተደረገውን ቅኝት ያሳያል፡፡ ስለዚህ መልሶ ማልማት የልማት አጀንዳ በመሆኑ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት
የሚኖራቸው ተሳትፎ አገልግሎት በመስጠት በኩል ከሚያበረክቱት አስተዋፅኦ በተለየ መልኩ የጥቅም ግጭት
ጭምር የሚታይበት ግንኙነት እንደሚኖራቸው ግልፅ ነው፡፡ ይህንን ታሳቢ በማድረግ በሀገራችን ከተሞች

99
የሚካሄደውን መልሶ ማልማት የሚመራ ተቋም ከላይ የተጠቀሰውን ባህሪ ያለው ልማት ለመምራት
በሚያስችል መልኩ የተደራጀ አይደለም፡፡

የመቐለ፣ ጅማ እና ሀዋሳ ከተሞች መልሶ ማልማት የሚመራ የተለየ ተቋም አላደራጁም፡፡ በየከተማው ሲካሄዱ
የቆዩ የአካባቢ ማሸሻል እና በሓሳብ ተገድቦ የቀረም ቢሆን እንዲሰሩ የታሰቡት አፍርሶ መገንባትን ያካተተ
መልሶ ማልማት በተለየ ተቋም ሳይሆን የመሬት ልማትና ማነጅመንት ከዚህ ካለፈም የከተማ ፕላን የስራ
ሂደቶች ቴክኒካዊ የስራ ድርሻ ተደርጎ የተወሰደ ነው፡፡ ምክንያቱም መልሶ ልማት የከተሞቹ እና አካባቢዎች
ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ለመለወጥ ወይም ለማሻሻል የሚከናወን ኢንቨስትመንት ሳይሆን የመሬት አቅርቦት ተግባር
ተደርጎ ስለሚወሰድ ነው፤ ከዚሁ ካለፈ የአካባቢ ውበት፣ ፅዳት ደህንነት ለማሻሻል የሚከናወን ተደርጎ
ይወሰዳል፡፡

የከተሞቹ ፕላን ዝግጅትና ትግበራ የስራ ሂደት (ጅማ ከተማ ጭራሽም ፕላን የሚመለከት የተሟላ የስራ ሂደት
መዋቅር የለውም) የተሰጠው ተግባርና ሓላፊነት በአማካሪዎች ተጠንቶ የቀረበውን የከተማው ፕላን ጥራት
እንዲሁ ትግበራው ከመከታተል በመለስ ስለ ከተሞቹ ጠለቅ ያለ የልማት ፕሮግራም አያጠናም፡፡

የየከተሞች የመሬት ልማትና ማነጅመንት የስራ ሂደቶች ደግሞ በፀደቀው ፕላን መሰረት ለማልማት ጥያቄ
ያቀረበ አካል ላይ ተመስርቶ የተጠየቀውን ቦታ ከይገባኛል ጥያቄ አፅድቶ ለአልሚው መስጠት፣ ካልሆነም
መሬቱ በጨረታ ከማስተላለፍ በዘለለ የልማት ጥናት እያጠኑ እንዲተገበር የሚመሩ አይደሉም፡፡ አካባቢው
መልሶ እንዲለማ ተጨማሪ ጥናቶች በማካሄድ ፕሮጀክት እያዘጋጀ ለከተማው ምክርቤት በማቅረብ በጀት
እያስፈቀደ እንዲለማ የማድረግ ሓላፊነት አልተሰጠውም፤ በራሳቸው ተነሳሽነትም የሚያደርጉት ጥረት
አይታይም፡፡ በአካባቢው ሲኖሩ ለነበሩ ነገር ግን አካባቢው ሊያስገኘው የሚገባ የልማት ዓቅም እያስገኘ
ባለመሆኑ በአካባቢው ሊከናወን የሚችል ልማት አሟጦ ለመጠቀም (Optimization) ሲባል ከቦታው
በሚነሱ ነዋሪዎች ላይ የሚያሳድረው ያልተፈለገ ተፅዕኖ ተገቢው ትንተና ተሰርቶለት ከግምት ስለማይገባ
በልማቱ የሚፈናቀሉ ዜጎች ኑሮአቸው እንዳይናጋ የሚያደርግ ስራ መስራት የመልሶ-ልማቱ ፕሮጀክት አካል
ተደርጐ እየተወሰደ አይደለም፡፡

በሌላ በኩል በከተሞች የሚካሄደውን መልሶ ልማት የተወሰነ ጊዜ ወይም የአንድ ወቅት ተግባር ተደርጎ
ይወሰዳል፡፡ በከተማው ክልል ውስጥ፣ በክልል ደረጃና በሀገር ደረጃ የሚከናወኑ የተለያዩ የልማት
ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች እንዲሁም የኢኮኖሚ ዕድገት ለውጥ ምክንያት በከተማው ፕላን ላይ ቀጣይ
ለውጦች ማስከተሉ ስለማይቀር መልሶ ልማት የተወሰነ ጊዜ አጀንዳ ብቻ ሊሆን እንደማይችል ግንዛቤው
አልተወሰደም፡፡

በየከተሞቹ መልሶ ልማት መምራት የሚችል ብቁ ተቋም ያለመደራጀት በከተሞቹ የሚወሰን ሳይሆን ክልሎች
ለመልሶ ልማት ያላቸው ዕይታ የሚያመላክት ነው፡፡ በኦሮሚያ፣ ትግራይና ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና

100
ህዝቦች ክልሎች በከተሞች የሚካሄደውን መልሶ ልማት ለመምራት የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍም የላቸውም፡፡
ከባለሙያዎች ጋር በተደረጉ ውይይቶች ለመረዳት የተቻለው መልሶ-ልማት በትርጉም ደረጃም ቢሆን ጥልቀት
ያለው አይደለም፡፡ መልሶ-ልማት የአንድ አካባቢ ሁለንተናዊ (ፊዚካላዊ፣ አካባቢያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣
ማሕበራዊ፣ ውጫዊ ገፅታው፣ አካባቢያዊ ውበትና ውህደት) አቀናጅቶ በመለወጥ በኩል ሳይሆን ከቤቶችና
ሰፈሮች የዕይታ ለውጥ (Physical change)፣ ከዚህ ካለፈም የመሬት አቅርቦት ተግባር ተደርጐ ይወሰዳል፡፡

እላይ ከተጠቀሱ ክልሎች በተለየ መልሶ ማልማት በሕግ እንዲደገፍ ያደረገው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስት ብቻ ነው፡፡ የሕጉ ድንጋጌዎች ይዘትም ሲታይ መልሶ ልማት የሰፈሮችና ቤቶች ገፅታ ማደስ ብቻ
ሳይሆን የከተማ ልማት ትርጉም በሰፊው የተገነዘበ መሆኑም ያመላክታል፡፡ መልሶ ማልማት/መልሶ ማደስ
የከተማ ልማት ኘሮግራሞች ማስፈፀሚያ መሆን እንደሚገባቸው በግልፅ የመደንገጉ ያህል በከተሞች የመልሶ
ማልማት ኘሮግራም ትግበራ ለመምራት በክልልና በከተሞች የተለያዩ አደረጃጀት እንዲኖርም ይፈቅዳል፡፡
በክልል ደረጃ በከተማ ልማት ቢሮ ሐላፊ የሚመራ ከተሞችን የሚደግፍ የቴክኒክ ኮሚቴ እንዲደራጅ የተደነገገ
ሲሆን በከተማ ደረጃ ደግሞ፡

i. ከንቲባ የሚመራው ባለድርሻ አካላት (5-7 አባላት) ያካተተ ዓብይ ኮሚቴ፣


ii. እራሱን የቻለ የበጀትና የግብአት ግዥ ቡድን (እንደ አስፈላጊነቱ) ሊደራጅ እንደሚችል፣
iii. መልሶ ልማት የኘሮጀክት ፅሕፈት ቤት (እንደ ከተሞቹ ዓቅምና ፍላጐት)፣
iv. በቴክኒክ ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ የሚመራ (የከተማው መልሶ ማልማት ባለሙያዎችና የከተማ
ኘላን ባለሙያዎች ያካተተ) የቴክኒክ ቡድን፣ እንዲደራጁ ተደንግጓል፡፡

የአማራ ክልል ከሌሎቹ ክልሎች በተለየ የከተሞቹ መልሶ ልማት ለመምራት የተሻለ አደረጃጀት እንዲኖረው
የሚያስችል ቢሆንም የደሴ ከተማ ተጨባጭ ሁኔታ ሲታይ ግን አደረጃጀቱ ተፈጥሯል ለማለት የሚቻል
አይደለም፡፡ የዓብይ ኮሚቴውና የቴክኒክ ኮሚቴው አደረጃጀት በግልፅ የሚታይ አይደለም፡፡ የተደራጀ
እንቅስቃሴ በማድረግም እንዲሁ አይታይም፡፡ የእያንዳንዱ ኮሚቴና የአባላት (ባለድርሻዎችን ጨምሮ) የስራ
ድርሻ አልተለየም፡፡ ቴክኒክ ኮሚቴው የሚያከናውነው ዝርዝር ሓላፊነት ግልፅ ሆኖ አልተቀመጠም፤
ባለሙያዎቹ በፅሕፈት ቤቱ ስላሉ ካልሆነ በስተቀር ስራውን የሚሰራ ቡድን በውል አልተደራጀም፡፡
የፕሮጀክት ፅሕፈት ቤቱም ሆነ የግዥ ቡድን አልተቋቋሙም፡፡ ባጠቃላይ መመሪያው እውቅና በሰጠው ልክ
አደረጃጀቱ መፈጠሩ የሚያሳይ መረጃ አልተገኘም፡፡

የአማራ ክልል በከተሞች መልሶ ማልማት የሚመራ አደረጃጀት እንዲኖር ቢፈቅድም የደሴ ከተማ አደረጃጀቱ
ፈጥሮ ልማቱ እስካልመራ ድረስ ከመቐለ፣ ጅማ እና ሀዋሳ ከተሞች የተለየ ነው የሚያስብል ምክንያት
የለውም፡፡ ይህም በመልሶ ልማት ትግበራ የሚታዩ መልሶ የሚለማ ቦታ መረጣ ጥናት፣ የነዋሪዎች እና የልማት
ተነሺዎች የልማቱ አካል እና ባለቤት ማድረግ፣ የፕሮጀክት ትግበራ መጓተት፣ ወዘተ ተግዳሮች ተመሳሳይ
ሆነው ተገኝተዋል፡፡

101
የመንግስት/ማዛገጃቤታዊ/ አገልግሎት እንደሚሰጡ ቢሮክራሲያዊ አደረጃጀቶች የተፈጠሩም ቢሆን የድሬዳዋ
እና አዲስ አበባ ከተሞች ከሌሎች ከተሞች/ክልሎች/ መልሶ ልማት ባለቤት እንዲኖረው በማድረግ በኩል
የተሻሉ ናቸው፡፡ በድሬዳዋ ከተማ የነባር አካባቢ መልሶ ልማት የአስተዳደሩን ትኩረት እየሳበ የመጣ የልማት
አጀንዳ መሆኑን የሚያረጋግጡ እርምጃዎች መወሰድ የጀመረው ከ2006 ዓ.ም ወዲህ ነው፡፡ ሥራውን በቅርብ
ለመከታተል የሚያስችለውን አሠራር የዘረጋ መሆኑም የጥናት ቡድኑ ባካሄደው የሰነድ ፍተሻና ጉዳዩ
ከሚመለከታቸው ፈፃሚዎች ጋር ባካሄደው ውይይት ለመረዳት ችሏል፡፡ የከተማ አስተዳደሩን የቅርብ ክትትል
ለማረጋገጥ ከተዘረጉ አሰራሮች መካከል የካሣ ግምት ኮሚቴ አንዱ ነው፡፡ የከተማ አስተዳደሩ መመሪያ ቁጥር
9/2006 የካሣ ገማች ኮሚቴ ተጠሪነት ቀጥታ ለአስተዳደሩ ከንቲባ እንዲሆን፣ የኮሚቴ አባላቱም አግባብ
ካላቸው ባለድርሻ አካላት የተወከሉ ባለሙያዎች እንዲሆኑ ተደንግጓል፡፡

በድሬዳዋ የከተማ መልሶ ልማት ሂደት የሚጀምረው ለሕዝብ ጥቅም በሚውል ቦታ መረጣና ምደባ ነው፡፡
ለህዝብ ጥቅም የሚውል ቦታ ምደባ መነሻዎች የተለያዩ ናቸው፤ ከእነዚህ መነሻዎች መካከል ቀዳሚውን
ሥፍራ የሚይዘው ለተለያዬ አገልግሎት/ኢንቨስትመንት የሚውል ቦታ ጥያቄ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በቀጥታ
የሚቀርበው ለመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ሲሆን ቢሮው ከተለያዩ አካላት ጥያቄው ሲቀርብለት በሥሩ
በተዋቀሩት ንዑስ የሥራ ሂደቶች ማለትም፡-

 በከተማ ፕላን ንዑስ የሥራ ሂደት ቦታው በፕላን ፎርማት ላይ ሰፍሮ ከፕላን አስተያየት ጋር
እንዲቀርብ፤
 በመሬት ባንክና ከተማ ማደስ ንዑስ የሥራ ሂደት በኩል ደግሞ ስለቦታው ዝርዝር መረጃ እንዲቀርብ
አመራር ይሠጣል፡፡ ከንዑስ ሥራ ሂደቶቹ የሚጠበቀው መረጃ ተሟልቶ እንደቀረበ በቢሮው
ማኔጅመንት ስብሰባ ላይ ጥያቄው በጋራ ከታየ በኋላ የውሳኔ ሃሳብ ለአስተዳደሩ ካቢኔ እንዲቀርብ
ይደረጋል፡፡

የቦታ ምደባው/የመልሶ ልማት ውሳኔ ሃሳቡ/ የካቢኔውን ይሁንታ እንዳገኘ ለቀጣይ ሥራዎች ተመልሶ ወደ
ቢሮው እና ወደ ካሳ ክፍያ ገማች ኮሚቴ ይመራል፡፡ ቢሮው ቦታውን ከነባር አገልግሎት ነፃ ወደ ማድረግ፣
የካሳ ኮሚቴው ደግሞ ወደ ካሳ ግምት ሥራ ይገባሉ፡፡ ሁለቱም አካላት በቀጥታ ለአስተዳደሩ ካቢኔ ተጠሪ
እንደመሆናቸው መጠን በሥራቸው ላይ የካቢኔው ቅርብ ክትትልና ድጋፍ አይለያቸውም፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ የቆዩ እና አሁንም ተጠናክረው እየተተገበሩ የሚገኙ የመልሶ ልማት ተቋማዊ
አመራር በጊዜ ሂደት ከልማቱ ይዘት ጥልቀት እና ስፋት በሚመጥን ደረጃ ባይሆንም እየተጠናከረ መጥቷል
ማለት ይቻላል፡፡ ከ2001 ዓ.ም በፊት የመልሶ ልማት ሥራው ከሌሎች ተግባራት ጋር በተደራቢነት በተለያዩ
ተቋማት ያዝ ለቀቅ ሲደረግ የቆየ የልማት ሥራ ነበር፡፡ ራሱን የቻለ ተቋም ተደራጅቶለት በተሻለ ተቋማዊ
ዝግጅት ተግባራዊ መደረግ የጀመረው ከ2001 ዓ.ም ወዲህ ነው፡፡ በከተማው የተንሰራፋውን የከተማ እርጅና

102
በተደራጀ መንገድ ለመቅረፍ አስተዳደሩ በወሰደው እርምጃ ይህን ተልዕኮ እንዲያስፈፅሙ ኃላፊነት
ተሰጥቷቸው የተደራጁ ተቋማት፡
 የአካባቢ ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት
 የኢኮ-ሲቲ ጽ/ቤት
 የኮብል ስቶን ልማት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ከመንገድ ባለስልጣን ጋር በመተባበር)
 የተቀናጀ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት
 የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ፕሮጀክት ጽ/ቤት
 የማህረሰብ ተሳትፎ ልማት ኤጀንሲ በቀዳሚነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
እላይ ከተዘረዘሩት ተቋማት መካከል የአካባቢ ልማት፣ የኢኮ - ሲቲ፣ እና የኮብል እስቶን ልማት ማስተባበሪያ
ጽ/ቤቶች እና የማህረሰብ ተሳትፎ ልማት ኤጀንሲ ተልዕኮ በአብዛኛው በመለስተኛ የነባር ከተማ ማሻሻያ
/Upgrading/ ፕሮግራም ላይ የሚያተኩር ሲሆን የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ፕሮጀክት/ፅሕፈት ቤት/
ስያሜው እንደሚያመለክተው በቀጥታ የነባር ከተማ ማደስ ተልዕኮን ያነገበ ተቋም ነው፡፡

የአካባቢ ልማት ፕሮግራም ሥራ ላይ በቆየባቸው ዓመታት በመላው አዲስ አበባ እስከ ቀበሌ ድረስ የሚወርድ
አደረጃጀት ተዘርግቶ፣ ወጪ መጋራትን ጨምሮ ነዋሪውን በስፋትና በብዛት በልማቱ በማሳተፍ በከተማው
ነባር አካባቢ ከፍተኛ ችግር ይታይባቸው የነበሩ እንደ ፍሳሽ ማስወገጃ መስመር፣ የጠጠር መንገዶች፣ የደረቅ
ቆሻሻ ማከማቻ ጣቢያዎች ያሉ የመሠረተ ልማት አውታሮችን በመገንባት ሰፊ ስራ አከናውነዋል፡፡

በኮብል ስቶን ልማት በኩልም በመላው አዲስ አበባ የሚገኘውን የውስጥ ለውስጥ መንገድ /Local Street/
ከጥርጊያ አፈር መንገድ ወደ ተሻለ የመንገድ ደረጃ ያሸጋገረ ሲሆን ቀደም ሲል ተሽከርካሪ የማይደርስባቸውን
ሠፈሮች ጭምር በተሽከርካሪ ተደራሽ እንዲሆኑ ያስቻለ የልማት ሥራ ተከናውነዋል፡፡

የተቀናጀ የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ተልእኮ በከተማው የሚታየውን የመኖሪያ ቤት እጥረት መቅረፍ ሲሆን
ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ በመሃል አዲስ አበባ በገነባቸው በርካታ የኮንዶሚኒየም ቤቶች አማካይነት የተጎሳቆለውን
ነባር የከተማ አካባቢ ገጽታ በመቀየር በኩልም ከፍተኛ መሻሻል እንዲመዘገብ አስችሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው የሚካሄዱ የተለያዩ የመልሶ ልማት ስራዎች ለመምራት የተሟላ
ሊባል የሚችል መዋቅር በማደራጀት ለስራው ባለቤት በመፍጠር በኩል ከሌሎች ክልሎች በጥንካሬው
የሚጠቀስ ነው፡፡ ይሁንና አሁንም ቢሆን የተፈጠረውን መዋቅር በተሰጠው ተግባርና ሓላፊነት ጠንካራ ነው
የሚያስብል አይደለም፡፡ በአንድ በኩል የከተማ ማደስና የመሬት ልማት ሥራዎችን በአንድ ተቋም ኃላፊነት
ሥር የማደራጀት አዝማሚያ ይስተዋላል፡፡

ቀደም ባለው ጊዜ የከተማ ማደስ ሥራን በተደራቢነት ይከታተል የነበረው ተቋም ዋና ተልዕኮ መሬት ልማት
ስለነበር ስያሜውም የመሬት ልማት ኤጀንሲ የሚባል ነበር፡፡ ዋናው ውስንነት ደግሞ መልሶ ልማት
የኢንቨስትመንት ማለትም የልማት አመራር አጀንዳ ሳይሆን ቋሚ የመንግስት አገልግሎት ተደርጎ ስለታየ
103
ተቋማዊ መዋቅሩ ቢሮክራሲያዊ አገልግሎት የሚሰጥ ዓይነት ባህሪ ያለው ሆኖ ነበር የተደራጀው፡፡ ይህንን
ሞዴል አደረጃጀት ልማቱን በተገቢው መንገድ ለመምራት የማያስችል መሆኑ እንዲለሙ በተወሰነባቸው
ቦታዎች በጊዜው ያለማስነሳት፣ የታቀዱ ፕሮጀክቶች ለዓመታት ወደ ትግበራ ሳይሸጋገሩ መኖር፣ የመሰረተ
ልማት ግንባታው መጓተት ሁነኛ ምስክሮች ናቸው፡፡

በድምሩ ከተጠኑት ናሙና ከተሞች መረዳት የተቻለው መልሶ ልማቱ ሊመራ የሚችል የተጠናከረ መዋቅር
እየተፈጠረ አለመሆኑ ነው፡፡ አገልግሎት የሚሰጡት የመንግሰታዊ መዋቅሮች ዓይነት አደረጃጀት
(Bureaucratic) ባህሪ ተከትለው የተደራጁ የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተሞችም ቢሆኑ ቅኝታቸው ልማት
ለመምራት የሚያስችል ሳይሆን ኮሚቴአዊ አደረጃጀት የተከተለ የአማራ ክልል ደግሞ የልማት አመራሩ
ባለቤት በግልፅ ሳይታወቅ ተልዕኮውን ለማስፈፀም ተግዳሮት መሆኑ ታይተዋል፡፡ ከዚህ በባሰ ሌሎች ክልሎች
መልሶ ማልማት የተለየ አመራር እንደሚያስፈልገው ተገቢውን ግንዛቤ ያላቸው ሆነው አልተገኙም፡፡

ልማቱን የሚመራ ሕጋዊ እውቅና ያለው፣ የተጠናከረ፣ መደበኛ አገልግሎት ከሚሰጡ የመንግስት መዋቅሮች
የተለየ ዓይነት አደረጃጀት ያለው ቋሚ አደረጃጀት የማይፈጠርበት ምክንያት መልሶ-ልማት ብዙውን ጊዜ
በልማት ይዘቱ ሳይሆን መሬት ለማቅረብ ሲባል የሚከናወን ተደርጎ ስለሚወሰድ ነው፡፡ በልማት መለወጥ
የሚገባው ነባር አካባቢ መልሶ እንዲለማ ሲደረግ መነሻው ቀድሞ ከነበረው የተሻለ ፋይዳ ለማስገኘት መሆኑ
እንዲሁም መልሶ እንዲለማ በተፈለገው አካባቢ እንዲመጣ የሚፈለገውን የልማት ፋይዳ ለማጣጣም ሲባል
ከቦታው የሚነሱ ነዋሪዎች ተጠቃሚነት ምን መሆን እንዳለበት እንዲሁም በልማቱ እንዴት መሳተፍ
እንዳለባቸው የሚደነግግ ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ የለም፡፡ ይህንን በሃገሪቱ የሕግ ማዕቀፎች (ከህገ መንግስቱ
በስተቀር) በአግባቡ እውቅና ስላልተሰጣቸው ያን ያህል የልማት ተልእኮ ሊሸከም የሚችል አደረጃጀት
እንዳይታሰብ ምክንያት ሆኖዋል ማለት ይቻላል፡፡

የበርካታ ሀገራት ተሞክሮ የሚያሳየው መልሶ-ልማት ከተለመደው ቢሮክራሲያዊ አሰራር ይልቅ


በኢንቨስትመንት መልኩ መተግበር ለውጤታማነቱ የተሻለ ያደረገዋል፡፡ መልሶ ልማቱ የግሉ ኢንቨስትመንት
በህንፃ ግንባታ ብቻ የተገደበ ሳይሆን መሬት ልማትም በግል ኩባንያዎች ይካሄዳል፡፡ ልማትና ማዛገጃቤታዊ
አገልግሎት የተለያዩ ስራዎች በመሆናቸው ልማቱን የሚመራ የተለየ መንግስታዊ ተቋም (ለምሳሌ በህንድና
ፓኪስታን - የከተማ ልማት ኮርፖሬሽን፣ ኮሪያ - የመሬት ልማትና ቤት ኮርፖሬሽን) በማቋቋም ከመደበኛው
የቢሮክራሲ አሰራር ተነጥሎ ይከናወናል፡፡ የተለየ የሕግ ማዕቀፍ እንደሚያስፈልግም ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

ባለፉት ጥቂት አመታት በብዛት በግል ዘርፉ በገበያ ፍላጎት የተበጣጠሰ መልሶ ግንባታና በተወሰኑ ከተሞች
እንደ አዲስ አበባና ድሬድዋ መንግስት በቀጥታ በመግባት የተወሰኑ የመልሶ ማልማት ጅምሮች ቢኖሩም
አሁንም ሰፊ ስራ ይቀራል፡፡ አብዛኛው የነባር ከተሞቹ ነባር መሀል ስፍራዎች እጅግ የወደቀና ለኑሮ ምቹ
ያልሆነ ነው፡፡ መሬት አጠቃቀም ሲታይ በመሬት መተፋፈግ እንጂ ወደ ላይ ያልተነሳ መተንፈሻ የሌለው
ውጤታማ ያልሆነ ነው፡፡ የተጎሳቆሉ መንደሮች መቀየር ጉዳይ ሰፊ ስራ የሚጠይቅ ነው፡፡

104
ነገር ግን በእኛ ሁኔታ መንግስት ስራው ለመምራት እየሞከረ ያለው በአመዛኙ የተለየ አደረጃጀት ሳይፈጥር
በአዲስ አበባና ድሬድዋ የራሱ ተቋም መፍጠር የተሞከረ ቢሆንም የስራውን ባህሪ በተረዳ ልማትን የሚመራ
ኮርፖሬት ባህሪ ሳይዝ በመደበኛ ቢሮክራሲ ለዚያም ለስራው ስፋት የማይመጥን አደረጃጃት እንደሆነ፡
ሰለፋይናንስ ሲነሳም የስራውን ልዩነት በተገነዘበ መልኩ ያልተቃኘ እንደሆነ ይታያል፡፡

በቢሮክራሲያዊ መልኩ የተቋቋሙም ቢሆን አሁን እየተከሄደበት ባለው ሁኔታ ስራውን ለመምራት የሚያስችል
ቁመና አንደሌላቸው ይታመናል፡፡ በተለይ የሰው ኃይል ብዛትና ሙያዊ ጥንቅር እንደማያሰራ በባለቤቶቹ
እየተተቸ ነው፡፡ ኦሮሚያ፣ ትግራይና የደቡብ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ክልሎች መልሶ ልማት የሚመራ ምንም
ዓይነት የተለየ አደረጃጀት አልተፈጠረም፡፡ ከመሬት ልማትና ማነጅመንት ጋር ተደርቦ ይሰራል፡፡ የአማራ
ክልል በኮሚቴዎችና ፕሮጀክት ፅሕፈት ቤት እንዲመራ በሕግ ቢደነግግም ስራውን በልማት ቅኝት ለመምራት
የሚያስችል ግን አልሆነም፡፡

የመልሶ ማልማት ስራ የተለያዩ አካላትንና ተቋማትን ተሳትፎ የሚጠይቅ ከመሆኑ አንጻር ሁሉም ባለድርሻ
በመልሶ ማልማቱ ስራ ላይ ድርሻቸዉን እንዲወጡ የሚያስችል ዘላቂነት ያለው አደረጃጀትና አሰራር የለም፡፡
በዚህም የተነሳ በመልሶ ግንባታው ተሳታፊ የሆኑት የግል አልሚዎች፤ መልሶ ሰፋሪዎችና መሰረተ ልማት
አቅራቢዎች፤ ከአስተዳደሩ ግንባታና እቅድ ጋር እኩል መራመድ አልቻሉም፡፡ በዚህም የተነሳ ቀድመው
ያለሙትን ተጎጅ ማድረጉ ተስተውሏል፡፡

3.2.6. መልሶ ልማት የሚጠይቅ የቦታ ስፋት


የሀገራችን ቀደምት ከተሞች አመሰራረታቸው ከወታሀደራዊ እና መስፍናዊ ስርዓት ንግስና ጋር በተያያዘ (አዲስ
አበባ፣ ደሴ፣ ጅማ) እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከተሞቹን ያለ ፕላን ከመቆርቆራቸው በተጨማሪ ዕድገታቸው
ለመምራት የሚያስችሉ የከተማ ፕላን መዘጋጀት ከተጀመረም ቢሆን ጥቂት ለማይባል ዘመናት ፕላኑ በአግባቡ
ሳይተገበር እየተጣሰ በሕገወጥ መንገድ እየሰፉ ተጉዘዋል፡፡ በዚህም የተነሳ አብዛኞቹ ግንባታዎች በግንባታ
ግብአትም ሆነ ሌሎች መስፈርቶች ከጅምሩ ከደረጃ በታች ሆነው እንዲገነቡ ምክንያት ሆኗል፡፡ በፕላን
በአግባቡ ያልተመራ እና በሕገ ወጥ የተስፋፋ ይዞታ የከተሞቹ እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ የመንገድ መሰረተ
ልማት እንዳይኖር አድርጎታል፡፡

መሬት የህዝብና የመንግስት ያደረገው አዋጅ 47/1967 መደንገግን ተከትሎ ደግሞ ወደ መንግስት ይዞታነት
የተዛወሩ ቤቶች ይባስ እንዲጎሳቆሉ አድርጓቸዋል፡፡ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት 70% ያህል የእነዚህ
ከተሞች ነዋሪ በእንዲህ ዓይነት የተጎሳቆሉ ሰፈሮች እና ቤቶች ይኖራል፡፡ ይህ ማለት የሰፈሮቹ እና ቤቶቹ ችግር
አካላዊ ድቀት ብቻ ሳይሆን ድህነትም ጭምር መሆኑ ነው፡፡

ኢህአዴግ ሀገሪቱን ማስተዳደር ከጀመረ በኃላም የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ተከትሎ የከተሞቹ ዕድገትና
ስፋት በእጅጉ እየተለወጠ ቢመጣም የመሰረተ ልማት ችግራቸው ተማልቶ አልተፈታም፡፡ ቀድሞ

105
የተፈጠረውን የፕላን ችግር ገና ረጅም ርቀት መጓዝ የሚጠይቅ ነው፡፡ በርካቶቹ አካባቢዎች ለኑሮ እና ለስራ
የተመቹ ለማድረግም እጅግ ሰፊ ጥረት ይጠይቃል፡፡

በሌላ በኩል እንደ መቐለ እና ሃዋሳ ደግሞ ዕድገታቸውና ስፋታቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመጣ ከመሆኑ ጋር
በተያያዘ መሰረታዊ ችግራቸው ያረጁና የተጎሳቆሉ ሰፈሮች ብዛት ሳይሆን በመሬት ላይ ያረፈውን ግንባታ
መሬቱ ሊሰጠው ከሚችል ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በታች የሆኑ አካባቢዎች መኖራቸው ነው፡፡ የከተሞቹ
እድገት የሚመጣጠን የመሰረተ ልማት ዝርጋታም ሌላኛው ችግራቸው ነው፡፡ ይህ ማለት ግን የኮሰሱ
አካባቢዎች የላቸውም ማለት አይደለም፡፡ ይህ መነሻ በማድረግ በየከተማው መልሶ ማልማትን የሚጠይቅ
የቦታ ሽፋን ምን ያህል መሆኑ ከዚህ በታች ቀርቧል፡፡

የአዲስ አበባ አጠቃላይ የከተማ ልማት ገፅታ ከአመሰራረቷ እና ዕድገት ሂደቷ በቀጥታ የተገናኘ ነው፡፡ ከተማዋ
የተቆረቆረችባቸው ሠፈሮች በቤት አሠራራቸውም ሆነ በአደረጃጀታቸው ከገጠር መንደር የሚሻሉ እንዳልነበሩ
በታሪክ ድርሳናት በስፋት ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ድርሳናቱ እንዳሰፈሩት የቤቶቹ ግድግዳ ከእንጨትና ጭቃ የተሠራ፣
ጣራቸው ሳር፣ ወለላቸው አፈር ሲሆን በሰፈሮቹ መካከልም ከእግረኛና እንስሳት መተላለፍያ ውጭ ሌላ
የመንገድ አውታር አልነበረም፡፡ በአዲስ አበባ የባህላዊ ቤት አሠራር ሥርዓት እስከ 1928ቱ የጣሊያን ወረራ
ድረስ ተጠናክሮ ዘልቋል፡፡ ለምሳሌ ከ1900-1913 ድረስ በከተማዋ ከተሠሩት ቤቶች መካከል 14ሺ የሚሆኑት
በባህላዊ መንገድ የተሰሩ የሳር ጎጆዎች ሲሆኑ በወቅቱ ሹማምንት /elites/ በዘመናዊ አሠራር የተገነቡ ቤቶች
ቁጥር ከ100 አይበልጡም ነበር፡፡

የከተማ ፕላንና የግንባታ ደረጃ በጊዜ ሂደት እየተሻሻለ እንደሚሄድ የሚጠበቅ ቢሆንም በከተማው እየተባባሰ
የሄደውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ስርዓቱ ላልጠበቀ አሰፋፈርና ከደረጃ በታች ግንባታ መስፋፋት ምክንያት ሆኖ
ቆይቷል፡፡ ለምሳሌ በ1911 ዓ.ም ከከተማዋ ነዋሪ ውስጥ ከ1 ሺ እስከ 2 ሺ የሚሆነው በድንኳን ውስጥ የሚኖር
ነበር፡፡ ይህ የመኖሪያ ቤት ችግር የጣሊያን ወረራን ተከትሎ ይበልጥ በመዲናዋ እየተባባሰ እንደመጣ የተለያዩ
የታሪክ ምሁራን ይገልፃሉ፡፡

በከተማው የተከሰተውን ይህን ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት እጥረት የተመለከቱ የመሬት ባለቤቶች በይዞታቸው
ሥር የነበረውን መሬት እየሸነሸኑ ለራሳቸው መኖሪያም ሆነ የኪራይ ቤት ለሚገነቡ ግለሰቦች መሸጡን
ተያያዙት፤ የገንዘብ አቅም የነበራቸው ግለሰቦችም ከነዋሪው የኢኮኖሚ አቅም ጋር ተመጣጣኝ የሆኑ በርካሽ
የሚከራዩ አነስተኛ ቤቶችን በመገንባት ሥራ ላይ በስፋት ተሰማሩ፡፡ ከዚህ ባሻገር ነዋሪው አነስተኛ ቤቶችን
ግቢው ውስጥ ከዋናው ቤት እየቀጠለ ለኪራይ ማቅረቡን በስፋት ተያያዘው፡፡ በዚህም የተነሣ ነባሩ የከተማው
ክልል በግንባታ ተጨናነቀ፡፡ በወቅቱ የኪራይ ቤት ፈላጊ ከነበረው የከተማ ነዋሪ መካከል አብዛኛው በዝቅተኛ
የኑሮ ደረጃ ላይ መገኘት የቤት ሠሪዎችን እንቅስቃሴ ከደረጃ በታች በሆኑ አነስተኛ ቤቶች ግንባታ ላይ
እንዲያተኩር አስገድዷል፡፡ በዚህም 1940ዎቹ - 60ዎቹ የተገነቡ አብዛኞቹ የከተማዋ ነባር አካባቢዎች ከደረጃ
በታች በሆኑ ግንባታዎች እየተሞሉ መጡ፡፡

106
የከተማ ቦታ በግል ይዞታ ሥር በነበረበት ቅድመ - አብዮት ዘመን የቦታ ምሪት በአብዛኛው በመሬት ባለቤቶች
ውሳኔና ፍቃድ ላይ የተመሠረተ ስለነበር በዚህ ዘመን ይካሄድ የነበረውን ግንባታ በመቆጣጠሩ ረገድ
የከተማው ማዘጋጃ ቤት ሚና ውስን ነበር፡፡ ምንም እንኳ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለከተማ ቦታ የግል
ይዞታ ሕጋዊ እውቅና የተሠጠው እ.ኤ.አ በ1907 በታወጀው የአዲስ አበባ ከተማ የቦታ አስተዳደር አዋጅ
መሆኑ ቢታወቅም ሕጉ ከትልልቆቹ ባለይዞታዎች አልፎ ከእነሱ ቦታ ገዝተው ግንባታ ላካሄዱ ነዋሪዎች ይዞታ
እውቅና ሳይሰጥ ረዥም ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡

የከተማ ቦታና ትርፍ ቤትን ወደ መንግሥት ንብረትነት ያዛወረው አዋጅ 47/67 ከታወጀ በኋላም በኢትዮጵያ
ከተሞች ሰፍኖ የነበረው ሁኔታ የኢ-መደበኛ ግንባታን የሚያስፋፋ እንጂ የሚገታ አልነበረም፡፡ ይኸውም
አገሪቱ በዕዝ ኢኮኖሚ ሥርዓት በቆየችባቸው 17 ዓመታት ከፍተኛ እቀባ ተጥሎባቸው ከነበሩ የኢኮኖሚ
ዘርፎች መካከል የመኖሪያ ቤት ግንባታ /Housing sector/ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው፤ ዘርፉ በፍፁም ዕቀባ
ውስጥ በነበረባቸው በእነዚህ ዓመታት በሚከተሉት ተመጋጋቢ ምክንያቶች የተነሣ ኢ-መደበኛ ግንባታ
በከተሞች በስፋት ሊስፋፋ ችሏል፡፡

አዋጅ 47/67 መሬትና ትርፍ ቤት የመንግስት ንብረት በማድረግ የከተማ ነዋሪውን ተጠቃሚ ለማድረግ
በሚል የታወጀ ቢሆንም ውጤቱ ግን ተቃራኒ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ የከተማ ቦታን ጠባቂ አልባ በማድረጉ፣
በግለሰብም ሆነ በድርጅት ቤት ሰርቶ መሸጥና ማከራየት ማገዱና የግሉን ዘርፍ ሚና ይተካል ተብሎ ይጠበቅ
የነበረው መንግሥት በከተሞች በቂ መኖሪያ ቤት ገንብቶ ማቅረብ ሳይችል በመቅረቱ ለሕገወጥ የመሬት
ወረራና ሕገወጥ ቤቶች እንዲስፋፉ ምክንያት ከሆኑት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው፡፡

ከ1967 ወዲህ የመሬት ስሪቱ ከግል ባለቤትነት ወደ ህዝብና የመንግስት ባለቤትነት ቢዞርም ስርዓቱ ከፍተኛ
አስተዳደራዊ ማነቆና ችግሮች የነበሩበት ነበር፡፡ ቤት ለመገንባት የሚፈልጉ ነዋሪዎች የመገንቢያ ቦታ ለማግኘት
ከፍተኛ የሆነ የቢሮክራሲ ውጣ ውረድ ማለፍን ይጠይቃል፤ ከዚያም ባለፈ ለከተማው የመሬት አስተዳደርና
የግንባታ ፈቃድ ሀላፊዎች አግባብ ያልሆነ ክፍያ መክፈልንም የሚጠይቅ ሁኔታ ነበር፡፡ በመደበኛ መንገድ
ሄደው ቦታ አግኝተው ቤት ለመገንባት ያልቻሉት ነዋሪዎች የነበራቸው አማራጭ መደበኛ ያልሆነውን
(Informal) አካሄድ መምረጥ ነው፡፡ አብዛኛው ሰው መደበኛ (Formal) የሚባለውን ቤት ለመስራት
ኢኮኖሚያዊ አቅሙ ስለሚያንሰው፣ የከተማ ቦታ በህጋዊ መንገድ ለማግኘትም ሁኔታው ስለሚከብደው፣
መደበኛ ወዳልሆነ (Informal) የቤት አሰራር ለመሄድ ተገዷል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ጨረቃ ቤቶች
ሊስፋፉ ችለዋል፡፡

የእዝ ኢኮኖሚ ሥርዓት ከተወገደበት ከ1983ቱ የሥርዓት ለውጥ በኋላም የመሬት ወረራ እና ሕገ ወጥ ግንባታ
እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ አልቆመም፡፡ እንዳውም መጀመሪያ ላይ በቤት ግንባታና ሽያጭ ላይ ተጥሎ
የነበረው እገዳ መነሣትን ተከትሎ የከተማ ቦታን ላልተገባ ጥቅም ለማዋል በሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች
/Speculators/ አማካይነት የመሬት ወረራው ተባብሶ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን ሕገ ወጥ የመሬት ግብይትና

107
ግንባታ ተጨባጭ የከተማዋ መሰረታዊ ችግር መሆኑ በዘርፉ ጥናት ያካሄዱት እንደ ይርጋለም ማህተሜ (2001
ዓ.ም) ያመላክታሉ፡፡

ይህ ዓይነት የመሬት ግብይትና ሕገ ወጥ ግንባታ ከደላላ፣ ደንብ አስከባሪዎች፣ መሬት አስተዳደር፣ ከተማ
ፕላን፣ ፖሊስ ተቋማት ባለው ሕገወጥ ሰንሰለት የሚፈፀም ሲሆን በከተማው ዙሪያም ሆነ በከተማው መሃል
ስፍራዎች የሚገኙ ክፍት ቦታዎች ለሕገ ወጥ ግንባታ እንዲውል እንደሚደረግ ታይቷል፡፡ ስለዚህ ቀደምት
ጊዚያት የፈጠሩት መጠነ ሰፊ ፕላን ያልጠበቀ አሰፋፈርና ለኑሮ አስጊ ግንባታዎች በአሁን ሰዓት ከተማዋ
ያጥለቀለቃት ሆኖ እጅግ ሰፊ የፕላን ማስተካከልና መልሶ ልማት የሚጠይቅ ቦታ ፈተና ቀጣይም ተመሳሳይ
ችግር የሚያጋጥም መሆኑ የሚያሳዩ ሁኔታዎች በስፋት አሉ፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ከፕላን ስርዓት፣ ሰፈሮችና ቤቶች ለኑሮ እና ለስራ ካላቸው አመቺነት፣ የመሰረተ ልማት
ተደራሽነትና ከአጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያለው ውህደት፣ መሬት ሊሰጠው ከሚገባ ጥቅም፣ መሬት
ውጤታማ በሆነ መንገድ ከመጠቀም አንፃር ሲታይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰፊው ክፍል መልሶ ልማት
የሚጠይቅ ነው፡፡

የተለያዩ ጥናቶችና መረጃዎች ይህንን እውነታ አሃዛዊ በሆነ መልኩ አመላክተውታል፡፡ የዩኤን ዲፒ እና ሌሎች
የዩኤን ጥናቶች 85% የከተማ ይዞታዎች ኢ-መደበኛ ከመሆናቸው ባሻገር ከደረጃ በታች ግንባታዎች
ያረፉባቸው መሆኑ ይጠቅሳሉ፡፡ አንድ የዩኤን ሀቢታት ጥናት እንደሚያሳየው የከተማዋ ግንባታ መውደቅ ስር
የሰደደ መሆኑን ለማሳየት እ.ኤ.ኣ ከ1969 እስከ 1972 ከተሰሩት ቤቶች የግንባታ ፈቃድ ወስደው የሰሩት
12.62% ብቻ ናቸው (ሀቢታት፣ 2003፡ገፅ 9)፡፡ በ1986 የተካሄደው የቤቶችና ሕዝብ ቆጠራ ውጤት
እንደሚያመለክተውም ከተማው ውስጥ በወቅቱ ከነበረው ቤት 82% የሚሆነው ግድግዳው ከእንጨትና ጭቃ
የተሠሩ እንደነበሩ ነው፡፡

ከመሃል ከተማው ክፍል ለማሳያ ያክል የልደታ ሰንጋ ተራ የነበረውን ሁኔታ ብንመለከት የከተማ ኘላንና መረጃ
ኢንስቲትዩት ባደረገው ቅድመ ጥናት እንዲሁም በኋላ ክፍለ ከተማው ባሰባሰበው ዝርዝር መረጃ መሠረት
በ26 ሄክታር የቆዳ ስፋት ውስጥ 1,343 አባወራዎች ወይም ከ5,ዐዐዐ በላይ ነዋሪዎች የሚኖሩበት ከዓቅም
በላይ የተጨናነቁ ሰፈሮች ነበሩ፡፡ አብዛኛዎቹ መኖሪያ ቤቶች ከ4ዐ ዓመት በላይ በማገልገላቸው ያረጁ ነበሩ፡፡

በዚህ የመልሶ ማልማት ኘሮጀክት ክልል ውስጥ ከነበሩት 1,454 ቤቶች መካከል 36ዐ የግል፣ 55 የመንግሥት
ቤቶች ኤጀንሲ እንዲሁም 1,ዐ39 የቀበሌ ቤቶች ነበሩ፡፡ አካባቢዉም በውስጡ ለኑሮ ምቹ ያልሆነና ሰፊ
የመሠረተ ልማት ችግሮች የነበሩበት፣ ያረጁ ቤቶች በብዛት የሚገኙበት፣ የመፀዳጃና የምግብ ማብሰያ ቤቶች
የሌላቸው፣ በአንድ ክፍል ውስጥ ቆጥ በቆጥ ላይ እየተሰራ ከ5-8 ቤተሰብ የሚኖርበት፣ የጽዳት ችግር ያለበት፣
የፍሳሽ ማስወገጃ ያልነበራቸው፣ የኤሌክትሪክ ዝርጋታዉ ሥርዓት የሌለዉ፣ በቤቶች መካከል የውስጥ ለውስጥ
መንገድ የሌላቸውና በጣም ጠባብና የተፋፈጉ በመሆኑ መኪና የማያስገባ ከመሆኑም ባሻገር እሳት አደጋ ቢነሳ

108
ለማጥፋት የማይቻልበት ለአደጋ የተጋለጠ አካባቢ ነበር፡፡ ይህንን በማሳያነት የቀረበ የልደታ ሁኔታ
የአብዛኛው የከተማውን ማእከል ክፍል የሚወክል ነው፡፡
 በዓለም አቀፍ ክስተቱ እንደታየው የእድሜ እርጅና፤
 በፕላን ካለመገንባት፤ ሽንሻኖው ቅርጽ ስፋት የይዞታ ቅልቅል/መልማት የማይችል የሚለማውን ያሰረ፤
ዙርያው በደቀቁ ቤቶች የታጠረ፤
 በነበረው ኃላቀር የግንባታ ቴክኖሎጅ፤ ቶሎ በሚወድቅ የግንባታ ቁስ ጭቃና እንጨት የተገነባ፤
 በነበረውና ባልተፈታው የኢኮኖሚ ድህነት ምክንያት ሲገነባም በደካማ ቁስ ከመሆኑም በላይ
ለማሻሻል አለመቻል፤
 ከ1967 በፊት በነበረው መሬት ስሪት ፖሊሲና መዋቅር የመቆጣጠር አቅም ማነስ፤ ፍላጎት ሲያድግ
የተደረገ ቅጥልጥል ግንባታ ምክንያት መጨናነቁ፤
 ከ1967 በኃላ ደግሞ አብዛኛው ቅጥያ ቤት በመወረሱ/ከ60% በላይ ቤቱ የመንግስት መሆን/
ያለመንግስት ሙሉና ቀጥተኛ ተሳትፎ መልማት የማይችልበት ሁኔታ መፈጠሩ፤ ይህ ሁኔታ መንግስት
የወረሰው ቤት መልማት ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ሁኔታ ከታየው በከፋ መልኩ/አንድ ግቢ የይዞታ
ቅልቅል ለመልሶ ማልማት ይቅርና ለእድሳት እንኳ የማይፈቅድ መሆኑ/ አካባቢው ካልለማ ሊለማ
የሚችል ይዞታ ያለው ግለሰብም የእስረኛ ዋዣቂ ፍላጎት እንደሚሉት የተሰራበት ሁኔታ መፈጠሩ፡፡
ይህ ክስተት እዚያው ሳለም ተስፈኝነትን ማስፋቱ/ይዞታውን ሳይለማ የቦታ ዋጋ ጭማሪን መጠበቅ/፤
 በሌላ በኩል ከ1967 በኃላ የነበረው የካፒታል ገደብም የግል በለሀብትና ልማትን ያሰረ መሆን፤
 የጨረቃ ቤት በመባል የሚታወቀው መደበኛ ያልሆነ የቤት አይነት በከተማይቱ ካሉት ቤቶች 35%
የይዞታ ዋስትና ስለሌለው መቀየር አለመቻል፤
 የከተማ ኘላን ዝግጅትና ትግበራ; ኘላኖች የሚያስቀምጧቸው መስፈርቶችና የቤት ደረጃዎች
የከተማው ነዋሪ ህዝብ የኢኮኖሚ አቅም አለማገናዘባቸው ለውድቀቱ ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው፡፡
በከተማው መዋቅራዊ ፕላን ጥናት መሰረት በመሰል ሁኔታ የሚታየው እና ሙሉ በሙሉ አፍርሶ መገንባት
የሚጠይቅ የከተማው ክፍል ከሁለት ሺ ሄክታር በላይ ሲሆን ከዚህ ሁኔታ በመለስተኛ ደረጃ የሚሻል፣ ነገር
ግን በከተማ የጥራት ደረጃ የማይታየውና መልሶ ማደስ ባይቻል እንኳን መሻሻል እንዳለበት በመዋቅራዊ ፕላኑ
የተመለከተው የከተማው ክፍል ደግሞ ሰላሳ አራት ሺ ሄክታር /የከተማው 63%/ አካባቢ ነው፡፡ ይህ ሲታይ
አቅም ቢፈቅድ ከተማዋ ከሞላ ጎደል እንደ አዲስ መገንባት ያለባት እንደሆነ ያመላክታል፡፡ በሕገ ወጥ መንገድ
የተገነቡ ይዞታዎች እንኳ ሲታይ (ጨረቃ ቤት በመባል የሚታወቀው መደበኛ ያልሆነ የቤት አይነት)
በከተማይቱ ካሉት ቤቶች 35% ወይም በቁጥር 90ሺ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡ በእነዚህ የጨረቃ ቤቶች
የሚኖረውም የህዝብ ቁጥር 450ሺ እንደሚሆን ይገመታል፡፡

109
እነዚህ አሀዞች ከተማው ምን ያህል የመልሶ ልማት ፍላጎት እንዳለ የሚያሳዩ ሲሆኑ ከዓቅም አንፃር ሲታይ
ደግሞ መልሶ የማልማት ስራው ስርዓት ያልጠበቁ ቤቶች በፕላን ማደራጀት ብቻ ሳይሆን ለኑሮና ለስራ
የማይመቹ ብሎም ለነዋሪዎች ደህንነት ስጋት የሆኑ ቤቶች አፍርሶ መገንባት፣ ሰፈሮችና ቤቶች ተገቢውን
የከተማ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችሉ እጅግ ሰፊ የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ ከተማዋ ያላት ሃገራዊ፣
አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ቦታ ተወዳዳሪነትዋ ለማጎልበት የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶች ግንባታ
ስለሚያካትት ፈተናው ቀላል አይደለም፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የሰፈሮች አደረጃጀት፣ የመንገድ ስርጭት እና ፕላን፣ የሰፈሮች እርጅና፣ የቤቶች ዓይነትና
ደረጃ ወዘተ ችግሮች ምስል በደሴ እና በጅማ ከተሞችም በስፋት ይታያል፡፡ የደሴ ከተማ ሰፈሮች እና ቤቶች
እርጅና መነሻው አዲስ አበባ ከተማ ላይ እንደታየው ከጅምሩ አሰፋፈሩ በፕላን ካለመደራጀት እና አግባብ
ያለው የግንባታ ደረጃ ካለመተግበር ነው፡፡ በርካታ ነባር ሰፈሮች አግባብ ባለው የከተማ ፕላን በስርዓት
ተሟልተው የተደራጁ አይደሉም፡፡ በመሆኑም ሰፊው የከተማው ሰፈሮችና ቤቶች ለኑሮና ለስራ የተመቹ
እንዳልሆኑ የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በከተማው የሚገኙ የአብዛኞቹ ቤቶቹ አሰራር በጣም የተጠጋጋና
የተጨናነቀ ነው፡፡ በአንድ ብሎክ የሚገኙ ቤቶች የተያያዙ በመደዳ የተገነቡ ከመሆናቸው በላይ 51.9% ቤቶች
ባለ አንድ ወይም ሁለት ክፍል ናቸው፡፡ 93.2% ያህሉ ቤቶች ከጭቃና እንጨት እንዲሁም ከጭቃ ብሎኬት
የተገነቡ መሆናቸው ቤቶቹ ቁመናው ሳይዳከም ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ የሚያስችሉ አይደሉም፡፡

እጅግ ሰፊው የከተማው ክፍል በቤት ደረጃ ሊኖሩ የሚገባቸው መሰረተ ልማቶች (site level facilities)
የተሟላለት አይደለም፡፡ 60.6% ቤቶች የግል ባህላዊ ኩሽና ሲኖራቸው 20% ከሌሎች ይጋራሉ፡፡ የግል ሽንት
ቤት ያለው 52.7% ብቻ ናቸው፡፡ 32.9% ከሌሎች ተጋርተው ይጠቀማሉ፡፡ ያም ሆኖ የዘመናዊ ሽንት ቤት
ድርሻ 2.5% ብቻ ነው፡፡ 10.6% ምንም ዓይነት ሽንት ቤት የላቸውም፡፡ በተመሳሳይ ከ80% በላይ ቤቶች
ሻወር የላቸውም፡፡ የግል ቧንቧ ውኃ ሽፋን 47.5% ብቻ ነው፡፡ የቤቶችና ሰፈሮች ጥራትና ደህንነት ሲታይ
ተመሳሳይ ችግር አለባቸው፡፡ ፍሳሽ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ያላቸው ቤቶች 1% አካባቢ ሲሆኑ 15% ቤቶች
የሚኖር ህዝብ ንፅህናውን ባልተጠበቀ ሽንት ቤት ይጠቀማሉ፡፡ በከተማው ከሚገኙ የቀበሌ ቤት ይዞታዎች
ካጠቃላይ ቤቶች 35% በላይ የሚሸፍኑ ሲሆኑ እነዚህ ይዞታዎች በአያያዝና አስተዳደር ችግር የተነሳ ከግል
ይዞታዎች በባሰ ደረጃ በእርጅና የተጎዱ ናቸው፡፡

በ1999 ዓ/ም ከተማው ያጠናው ጥናት በአንድ ክፍል ቤት አምስትና ከዛ በላይ ሰው የሚኖር የከተማው ነዋሪ
55.97% መሆኑ ታይቷል፡፡ ስለዚህ የከተማው ችግር የቤቶችና ሰፈሮች እርጅና ብቻ ሳይሆን እጅግ የተጨናነቀ
አሰፋፈር መኖሩ ጭምር ነው፡፡

የቤት ቁመና፣ በግል ይዞታ መሟላት የሚገባው መሰረተ ልማት፣ እንዲሁም የቤቶችና ሰፈሮች እርጅና
በመውሰድ ሲመዘን በከተማው ከሚገኙ ቤቶች 75% ያላነሱ በደህና ደረጃ የማይገኙ መሆናቸው

110
ተፈርጀዋል፡፡ እነዚህ መስፈርቶች የሰፈሮችና ቤቶች ውጫዊ የእርጅና ገፅታ ሁኔታ ብቻ የሚገልፁ
በመሆናቸው የነዋሪዎች የተጨናነቀ አሰፋፈር እንደ መስፈርት ከተወሰደ የችግሩ ስፋት ከዚህ በላይ ነው፡፡

ስእል 3.10፡ እንዲለማ በታቀደው ቦታ የሚገኙ ቤቶች ማሳያ /አራዳ/

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ፣ ጥር 2008 ዓ/ም

ከላይ የተጠቀሱ የሰፈሮችና ቤቶች ተጨባጭ ሁኔታዎች በከተማው ምን ያህል የመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ ሰፈሮች
በፕላን ማደራጀት፣ ቤቶች ማሻሻል ወይም ሙሉ በሙሉ አፍርሶ እንደ አዲስ መገንባት እንደሚያስፈልግ
የከተማውን ችግር አጉልተው የሚያሳዩ አስረጂ ምስሎች ናቸው፡፡ በ2002 ዓ/ም የተጠናው የከተማው መዋቅራዊ
ፕላን እንደሚያሳየው አብዛኛውን የከተማው ክፍል (ሰኞ ገበያ፣ ሳላይሽ፣ ቢለን፣ ሙጋድ፣ መድሃኒአለም፣ አውቶስ
መናሃሪያ፣ አይጠየፍ ቤተ መንግስት፣ ጦሳ ተራራ ስር) የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች የእርጅናና መጨናነቅ ደረጃ
ከአከባቢ መሻሻል ይልቅ ሙሉውን አፍርሶ መገንባት እንደሚያስፈልጋቸው አመላክቷል፡፡ በጥናት ሰነዱ
(የከተማው ዋና የንግድ ማእከል የሆነውን አራዳን ጨምሮ) በድምሩ ከ4,000 በላይ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች
(ከ4ዐዐ ሄክታር ያላነሰ) እጅግ ያረጁና ለስራም ሆነ ለኑሮ አመቺ እንዳልሆኑ ተለይቷል፡፡

ከከተማው አመሰራረትና ዕድገት ታሪክና ገፀ መሬት በተያያዘ የመሰረተ ልማት ተደራሽነት ችግር ቀላል አይደለም፡፡
80% ያህል የከተማው የትራፊክ ፍሰት 2 መንገዶች ብቻ ያስተናግዱታል፡፡ በከተማው የአገር አቋራጭ መንገዶች
የሚያቋርጡበት 28.8 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ሲኖር በከተማው 100 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ
ይገኛል፡፡ 59 ኪ.ሜ የተለያዩ ደረጃና ጥራት ያላቸው መዳረሻ መንገዶች ይገኛሉ፡፡ ይህ መረጃ የሚያሳየው
የመንገድና የከተማ ትራንስፖርት ተደራሽነት ሽፋኑ ጠባብ መሆኑ ነው፡፡ ጎልተው ከሚታዩ ችግሮች የመዳረሻ
መንገድ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው፡፡ ከዋና መስመር ውጭ የሚገኙ ቦታዎች ለከተማ ውስጥ ትራንስፖርት
ያላቸው ተደራሽነት ውሱን ነው፡፡ ተፈጥሮአዊ የመሬቱ አቀማመጥ አስቸጋሪነት በርካታ ሰፈሮች በፕላን
ያልተስተካከሉ ከመሆናቸው ጋር ተዳምረው መንገዶችና ትራንስፖርት ተደራሽነቱ ውስን እንዲሆን አድርገውታል፡፡
ተፈጥሮአዊ የመሬት አቀማመጡ ከተማው በከፍተኛ ደረጃ ለጎርፍ አደጋ የተጋለጠ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

111
የመልሶ ልማት አጀንዳ ለተወሰነ ወቅትና ለተወሰኑ ከተሞች ብቻ ሳይሆን የከተሞች ተፈጥሮአዊ ሂደት ውጤት
በመሆኑ ከተሞች እስካሉ ድረስ የሚኖር ነው፡፡ ስለዚህ መልሶ ልማት ከተሞችን ተደማሪ ሁለንተናዊ አወንታዊ
ለውጥ እንዲያስገኝላቸው በእውቀት ታግዞ መመራት ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን በከተማው ሲካሄድ የቆየ መልሶ
ልማት አጠቃላይ ሂደቱ ትክክለኛነት እና በከተማው አጠቃላይ ልማት እና የነዋሪው ኑሮ ከመለወጥ አኳያ
ያስገኘው ፋይዳ አስመልክቶ የተቀመረ እውቀት እምብዛም አይደለም፡፡

በደሴ ከተማ መልሶ የሚለማ ቦታ ለመምረጥ ቀደም ሲል በክልሉ ከተማ ፕላን ኢንስቲትዩት የተለዩት
መስፈርቶች የአማራ ክልል መመሪያ ቁጥር 6/2006 እውቅና ሰጥቶአቸዋል፡፡ ስለዚህ ቀደም ብለው የተዘጋጁ
ሰባት የአካባቢ የልማት ፕላኖች መልሰው እንዲለሙ ያካተቱዋቸው ዕቅዶች አሁንም መልሶ ልማት
እንደሚያስፈልጋቸው እውን ነው፡፡2 ከነዚያ የአካባቢ ልማት ዕቅዶች ሰፋ ያለ የመልሶ ልማት (አፍርሶ
መገንባትን ጨምሮ) ስራ የሚፈልጉ የአራዳ (ጠቅላላ ስፋት 38 ሄክታር)፣ ፒያሳ (ጠቅላላ ስፋት 25.12
ሄክተር) እና የሰኞ ገበያ - ሸዋ በር (ጠቅላላ ስፋት 75 ሄክታር) ናቸው፡፡

አፍርሶ መገንባት ጭምር ያካተተ መልሶ ልማት የሚጠይቅ ቦታ አብዛኛውን የከተማው ክፍል ከመሆኑ ባሻገር
በአስቻይ ሁኔታዎች የታጀበ ጭምር ነው፡፡ የመዋቅራዊ ጥናት ሰነዱ እንደሚያሳየው በከተማው ከሚገኙ 19,334
ይዞታዎች 6,779 (35.ዐ6%) የቀበሌ እና 36ዐ (1.86%) የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ በድምሩ 36.92% ያህሉ
በመንግስት እጅ የሚገኙ ናቸው፡፡

እነኝህ ይዞታዎች የሚያስከትሉት የባለቤትነትና ተያያዥ ክርክሮች እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡ ለቤቶቹ የሚከፈለው የካሳ
ወጪም አይኖርም፡፡ 92% ያህሉ ቤቶት የተገነቡበት ግብአት እንጨትና ጭቃ በመሆኑ ለግል ባለይዞታዎች
የሚከፈለው የካሳ መጠን እንደ መቀሌ በመሰሉ ከተሞች ለንብረት ከሚከፈለው ካሳ በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ በቋሚ
ንብረት ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት አዋጭነት መጨመርም ሌላኛው መልካም ዕድል ነው፡፡ ከፒያሳ /ደሴ-ህንፃ/
እስከ አሮጌ ፖስታ ቤት እንዲሁም ፒያሳ ዙሪያ በሚገኙ ህንፃዎች 16-2ዐ ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ሱቆች ብር
4,000 እስከ ብር 7,ዐዐዐ በወር ይከራያሉ፡፡ በተለይ ምድር ቤት የሚገኙ ሱቆች ከፍተኛ ተፈላጊነት አላቸው፡፡
አራዳ አካባቢ (ዕድገት፣ ሚሊኒየም፣ ሰላምና አባይ የገበያ ማዕከላት) ምድር ቤት የሚገኙ ሱቆች እስከ 4ዐዐዐ ብር
ይከራያሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በመካከለኛው የከተማው አካባቢ (በተለይ አዲስ አበባ - መቀሌ ዋና መስመር)
መንገድ ዳር የሚገኙ ቦታዎች የሊዝ የጨረታ ዋጋ እያደገ መሆኑ የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ፡፡ በካሬ ሜትር ብር
7,ዐዐዐ የተላለፈ ቦታ አለ፡፡ የመልሶ ማልማት አማራጩ በኘሎትና በብሎክ ደረጃ መፈቀዱ በግል አልሚዎች
በተናጠል ሰፊ ቦታ የመልማት ዕድል ይፈጥራል፡፡ በተግባር እስካሁን የተሰራውም በዚሁ መልክ ነው፡፡

ፈርሰው እንደገና መገንባት ያካተተ መልሶ ልማት በሚጠይቁ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ልማቱን
ይደግፉታል፡፡ አካባቢው ገፅታው እንዲቀይር፣ መሰረተ ልማት እንዲሟላለት ብሎም አጠቃላይ የተሟላ
የከተማ አገልግሎት እንዲሰጥ እንደሚፈልጉ በተደረጉ ቃለመጠይቆችና ውይይቶች ተገልጿል፡፡ ቀደም ሲል

2
የአካባቢ ልማት ዕቅዶቹ የጥናት ሪፖርት ሰነድነና ፕሮጀክቶች አልተገኘም፡፡ የተገኘው ግራፊክሱ ብቻ ነው፡፡

112
በተመሳሳይ ሁኔታ የተነሱ ነዋሪዎች አካባቢዎቹ መልሰው መልማታቸው አግባብ መሆኑ ያምናሉ፡፡ በርካቶቹ
የሚያነሱት ጥያቄ በለመዱት አካባቢ ለመኖር ካላቸው ፍላጎት ይልቅ ከነበሩበት የመኖሪያ አካባቢ የተሻለ
ሁኔታ እንዲፈጠርላቸውና በቀድሞ መኖሪያቸው ሲያገኙት የነበረው ገቢ ማግኘት የሚችሉበት ሁኔታ
እንዲፈጠርላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ የልማት ተነሺዎች ማሕበራዊ ትስስራቸው ሳይፈርስ የከተማው
ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ የተሻለ የመኖሪያ አካባቢ ካገኙና ቢያንስ በቀድሞ መኖሪያቸውና የስራ ቦታቸው
ሲያገኙት የነበረ ገቢ ካላጡ መልሶ ልማቱን ለመግታት አይሰለፉም፡፡

ለመኖሪያ የሚውል መሬት የሊዝ መነሻ ዋጋ በሜትር ካሬ ከብር 3ዐዐ በላይ ስላይደለ የልማት ተነሺዎች
መሬት ከቀረበላቸው ቤት ለመገንባት የሊዝ መነሻ ዋጋው እጅግ ፈታኝ አይሆንባቸውም፡፡ በከተማው ለቤት
ግንባታ የሚውል ግብአት ዋጋ ከመቀሌ፣ ሀዋሳና አዲስ አበባ ከተሞች ሲነፃፀር የተሻለ በመሆኑ ምትክ መሬት
ማዘጋጀት ከተቻለና የብድር ድጋፍ ከተመቻቸ ሙሉ በሙሉ የመንግስት ጥገኛ የሚሆኑበት ዕድል ጠባብ ነው፡፡
በስራ ላይ የሚገኘው የጅማ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን እንደሚያሳየው በከተማው መካከል የሚገኙ ይዞታዎች
አብዛኞቹ የተወረሱ የቀበሌ ቤቶች ናቸው፡፡ ይህም በርካታ ነገር ግን በእርጅና እጅግ የተጎዱ የቀበሌ ቤቶች
ከሚገኙባቸው በተለያዩ ጥናት ፊት ከሚጠቀሱ የሀገሪቱ ትላልቅ ከተሞች የጅማ ከተማ አንዷ ነች፡፡

ሰንጠረዥ 3.3፡ የጅማ ከተማ የይዞታ ብዛት በዓይነት


ይዞታ ዓይነት በመንግስት
የቀበሌ ስም የቀበሌ የግል የኪራይ ቤቶች የማሕበራትና ሕጋዊ ድምር ይዞታነት
ይዞታ ኤጀንሲ ድርጅቶች ያልሆኑ የሚታወቅ
ሂማታ 983 346 78 - 415 1822 58.28
ሂርማታ መንቲና 786 595 22 - 1403 57.57
ሂርማታ መርካቶ 906 381 213 85 14 1599 70.2
ቦሳ ኪቶ 843 897 127 512 2379 40.78
ቦሳ አዲስ ከተማ 320 850 - - - 1170 27.35
መንቲና 550 650 5 1205 40.04
አወይቱ መንደራ 390 870 - 120 220 1600 31.88
ጊንጆ ጉድሩ 340 556 - - 30 926 36.72
ጊንጆ *** *** *** *** *** 1200 ??
ቤቾ ቦሬ *** *** *** *** 3000 11000 ??
ሰጦ ሰመሮ 80 1466 - 82 1066 2694 27.0
ጂረን *** *** *** *** *** 489 ??
ድምር 29487 ??
?? መረጃ ያልተገኘበት

ምንጭ፡ የጅማ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን፣ 2002 ዓ/ም


የቀበሌ ቤቶች ይዞታ በሂርማታ መርካቶ 56.7፣ ሂርማታ መንቲና 56፣ ሂርማታ 54፣ መንቲና 45.6፣ ጊንጆ
ጉድሩ 36.72፣ ሰጦ ሰመሮ 27% ድርሻ ይሸፍናል፡፡ በ2005 ዓ/ም የተዘጋጀው የቤቾ ቦሬ የአከባቢ ልማት
ዕቅድ እንደሚያሳየው በናሙና ከተወሰዱ 245 ቤቶች 27% በቀበሌ ይዞታ የሚገኙ ናቸው፡፡ በተመሳሳይ
የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ የሚያስተዳድራቸው ቤቶች በሄርማታ መርካቶ 13.32፣ አዌቱ መንደራ 7.5፣ ቦሳ ኪቶ
5.34፣ ሂርማታ ሜንቲና 1.57% ናቸው፡፡

113
የግንባታ ግብአት ዓይነት፣ የቤቶቹ የእርጅና ደረጃ፣ ቤቶቹ መጠገን አዋጭነት እንዲሁም የሰፈሮች ውጫዊ
ገፅታ መስፈርቶችን በመውሰድ የተጠና 35.8 ሄክታር የቤቾ ቦሬ የአከባቢ ልማት ዕቅድ እንደሚያሳየው
70.08% ያህሉ ቤቶች (25.09 ሄክታር) እጅግ ያረጁና የተጎዱ ብሎም በቀላል ጥገና ሊሻሻሉ የማይችሉ
መሆናቸው ተፈርጀዋል፡፡ 4.86% (1.74 ሄክታር) በደህና ደረጃ እንዳሉና በጥሩ 13.68 (4.9 ሄክታር) ሁኔታ
እንደሚገኙ ጥናቱ ያሳያል፡፡ ይህ መረጃ 70.08% (25.09 ሄክታር) መልሶ ልማት የሚጠይቅ መሆኑ የችግሩ
ስፋት ያሳያል፡፡ 40 ሄክታር በሚሸፍነው የጅማ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ የልማት ጥናት 58% ያህሉ ቤቶች
ለመኖርም ሆነ ለስራ በማይመቹ ደረጃ እንደሚገኙ በአንፃሩ 18% ብቻ በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙ ያሳያል፡፡
በተመሳሳይ 62 ሄክታር የመርካቶ አካባቢ ልማት ጥናት የሚያሳየው በመልሶ ልማት ከተለወጡ የተወሰኑ
ቦታዎች ውጭ ያለ ቦታ በሙሉ ፈርሶ እንደ አዲስ መገንባት እንዳለበት ነው፡፡
ስእል 3.11፡ በጅማ ከተማ የሰፈሮችና ቤቶች የእርጅና ደረጃ ማሳያ

ምንጭ፡ ከጎግል ማፕ የተወሰደ


ከላይ የተቀመጡ ቴክኒካዊ መስፈርቶች ብቻ እንኳ ቢወሰድ አብዛኛውን የከተማው ክፍል አፍርሶ መገንባትን
ያካተተ በስፋት መልሶ ልማት እንደሚጠይቅ መደምደም ይቻላል፡፡ የመርካቶ፣ ቦቼ ቦሬ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣
መርካቶ፣ በጊቤ አዳራሽ እና ማሪያም ቤተ ክርስትያን መካከል እንዲሁም ከፈንጅ አራዳ እስከ ግብርና ኮሌጅ
የሚገኙ ቦታዎች መልሶ ልማትን ይጠይቃሉ፡፡

በአጠቃላይ የከተማው ዋና ማእከል (ከፈረንጅ አራዳ፣ መርካቶና ጊቤ አዳራሽ እስከ ሄርማታ መንቲና) 150
ሄክታር የሚገኝበት እንደ ከተማ በድምሩ 200 ሄክታር አፍርሶ መገንባት የሚፈልግ መሆኑ የመዋቅራዊ ፕላኑ
ጥናት ያሳያል፡፡ በተመሳሳይ ባለበት የይዞታ ማስተካከል፣ ለእግረኛ እና ትራፊክ እንቅስቃሴ የሚያሳልጡ
መንገዶች መዘርጋትና ማስተካካል፣ ሌሎች አስቻይ መሰረተ ልማቶች ማለትም ውኃ፣ ኤሌክትሪክ ሲቲ፣
ተፋሰስ ማስወገጃ፣ ክፍት እና አረንጓዴ ማስተንፈሻ ቦታዎች በማሟላት የአከባቢ ማሻሻልን የሚጠይቅ 200
ሄክታር መኖሩ መዋቅራዊ ፕላኑ አስቀምጧል፡፡

114
ስእል 3.12፡ በጅማ ከተማ መልሶ ልማት ዓቅም

ምንጭ፡ ከጎግል ማፕ 2016 የተወሰደ

የጅማ ከተማ ከደሴ የሚለየው በየጊዜው የሚመሰረቱ አዳዲስ ሰፈሮች ጭምር ከመነሻው ደረጃቸው የጠበቁ
ቤቶች የማይገነቡበት መሆኑ ነው፡፡ አብዛኞቹ ይዞታዎች ከያዙት የመሬት ስፋት የማይመጣጠን ግንባታ
ያረፈባቸው፣ የቤቶቹ ቁመና አንድ ትውልድ የማይሻገር፣ ሰፈሮቹ መሰረተ ልማት ያልተሟላላቸው ወዘተ
ናቸው፡፡ በመሆኑም በከተማው የሚካሄድ መልሶ ልማት የተለመደ እሳቤ ላይ ብቻ የተመሰረተ አይሆንም፡፡
መሬትን አቀናጅቶ ከመጠቀም አኳያ በቅርብ ጊዜ የተመሰረቱ ሰፈሮች ሳይቀር መልሶ ልማት የሚጠይቁ ናቸው፡፡

በድሬዳዋ ነባር አካባቢዎች የሰፈሮች እና ቤቶች እርጅና የተንሰራፋ ችግር ነው፡፡ እስካሁን በድሬዳዋ ከ21
በላይ የሚሆኑ አካባቢዎች የአካባቢ ልማት ፕላን የተዘጋጁ ሲሆን በከተማው መካከል ስፍራዎች ላይ የተዘጋጁ
አስር የአካባቢ የልማት ፕላኖች የሚያሳዩት አካባቢውን ባንድ ወይም በሌላ መልኩ መልሶ ልማት የሚጠይቅ
942.5 ሄክታር ቦታ ማለትም ከከተማ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት 32% የሚሸፍን ነው፡፡

115
ሰንጠረዥ 3.4፡ የአከባቢ ልማት ፕላን የተጠናላቸው የድሬዳዋ ከተማ መካከል ቦታዎች
ተ/ቁ የአካባቢዎቹ መጠሪያ የሚሸፍኑት ክልል ስፋት (በሄ/ር)
1 ከዚራ 65.7
2 መጋላ 61.5
3 ለጋሃሬ 80.4
4 ገንደ ቆሪ/ግሪክ ካምፕ 81.7
5 ታይዋን/ፖሊስ መሬት 103
6 ነምበር ዋን 120.4
7 ሳቢያን 155
8 ዲፖ ማርያም 51.2
9 ጎሮ 163.4
10 ጂቲዜድ - ገንደ ተስፋ 60.2
ድምር 942.5
ምንጭ፡ ከአካባቢ ልማት ፕላን (LDP) ሰነዶች ተወስዶ የተቀመረ
የሀዋሳ ከተማ ዕድገት የቅርብ ጊዜ ቢሆንም በከተማዋ የመሃል አከባቢዎች አለፍ አለፍ ብሎ ከደረጃ በታች
የሆኑ ሰፈሮች እና ቤቶች አሉ፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን የተመቻቸ ስብጥር ያላቸው ልማትን የሚያፋጥኑ የመንገድ
አውታሮች መገንባት የመሬትን ዋጋ ከፍ እንዲል አድርገውታል፤ ስለሆነም በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ
ግንባታዎች መሬት ሊያስገኘው የሚገባ የኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አሟጦ ለመጠቀም የሚያስችሉ ባለመሆናቸው
መልሶ ልማት መታሰቡ የሚቀር አይደለም፡፡

ከላይ የተገለፁት ሁለት ምክንያቶች ላይ ማእከል በማድረግ በ5 ቦታዎች መልሶ እንዲለማ የተጠናው እና
የታቀደው አጠቃላይ የቦታ ስፋት 54 ሄ/ር ሲሆን በጠቅላላው 2,349 ቤቶች ወይም 3,042 አባወራዎች
በመልሶ ማልማቱ ዕቅድ ውስጥ ይካተታሉ፡፡ ከነዚህ 2,349 ቤቶች መካከልም 1,280 ያህሉ የቀበሌ ቤቶች
ሲሆኑ 930 ያህሉ ደግሞ የግል ቤቶች እንደሆኑ የከተማው አስተዳደር ለይቷል፡፡

116
ስእል 3.13፡ በሀዋሳ ከተማ የመልሶ ማልማት የሚካሄድባቸው የአካባቢ ልማት ዕቅድ ሳይቶችን የሚያሳይ ካርታ

ምንጭ፡ የሃዋሳ ማስተር ፕላን ሰነድ

እስካሁን የተከናወነውና በቀጣይም የታቀደው የመልሶ ማልማቱ ተግባር በከተማዋ ማዕከላዊ ስፍራ በሚገኙት
እና የከተማዋ የአከባቢ ልማት ኘላን በሚተገበርባቸው ሶስት ዋና ዋና ክፍለ ከተሞች ውስጥ ባሉት አምስት
ቀበሌዎች ሲሆኑ እነሱም፡-
 ከባህል አዳራሽ ክፍለ ከተማ፡- አዳሬ እና አንድነት ቀበሌዎች
 ከሀይቅ ክፍለ ከተማ፡- ገበያ ዳር ቀበሌ
 ከመሀል ክፍለ ከተማ ደግሞ፡- ለኩ እና ንጋት ኮከብ ቀበሌዎች ናቸው

የአካባቢ ልማት ፕላን የተዘጋጀው በከተማዋ ማእከላዊ እና ቀድሞ የለማው አከባቢ በሀዋሳ ሀይቅ ዳር ነው፡፡
አከባቢው ሜዳማ በመሆኑ ለጎርፍ የተጋለጠም ነው፡፡ አጠቃላይ አምስቱ የአከባቢ ልማት ፕላን 292 ሄክታር
ቦታ የሚሸፍን ሲሆን ከዚሁ በ5 ዓመቱ መልሶ እንዲለማ የታቀደው የቦታ ሽፋን 54 ሄክታር ነው፡፡

117
ስእል 3.14፡ ለአካባቢ ልማት ፕላን የተመረጡ አምስት ሳይቶችን የሚያሳይ ካርታ

ምንጭ፡ ኮምፓስ ኮንሰልታንት፣2006


የከተማ ማደሱ ሂደት በአንዳንድ የሀገሪቱ ትላልቅ ከተሞች እንደሚደረገው ሰፋፊ ብሎኮችን በሸፈነ ሁኔታ
ሳይሆን አለፍ አለፍ እያሉ በአንድ ወይም በሁለት ይዞታዎች ላይ ነው እየተካሄደ ያለው፡፡ ቅድሚያ ትኩረት
የተሰጠው በተዘጋጀው የአካባቢ ልማት ፕላን ጥናት መሰረት ለመሰረተ ልማት ዝርጋታ በመሆኑ የግንባታ
ልማቱ ለወደፊት በስፋት ሊተገበር በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

የመቐለ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ለመተግበር ከተዘጋጁ የአከባቢ ልማት ዕቅዶች በአራቱ (እንዳ ማሪያም-ጋብር፣
ቀበሌ 14፣ ዓዲ ሓቂ፣ ማይዱባ) በድምሩ 23 ሄክታር ያህል መሬት ስርዓት ያለው አሰፋፈር ባለመሆኑ፣
የይዞታዎች ጥበት ከደረጃ በታች መሆናቸው መሬት ሊያስገኘው የሚችል ጥቅም እንዳያስገኝ የሚያደርግ
በመሆኑ፣ የግንባታ እርጅና ደረጃ፣ ዝቅተኛ ተደራሽነት እንደ መስፈርት በመውሰድ እንደ አዲስ ፈርሶ መገንባት
እንደሚያስፈልገው ተለይቷል፡፡ የኲሓ አዲሱ ሰፈርና የማይ ሊሓም አከባቢ ልማት ዕቅዶችም በተመሳሳይ
መልሶ ልማት የሚያስፈልጋቸው ውሱን ቦታዎች እንዳሉ ተጠቁመዋል፡፡

አፍርሶ እንደ አዲስ መገንባት ያስፈልጋቸዋል ብሎ ለመወሰን ብዙውን ጊዜ የሚወሰደው መስፈርት የቤቶች
ወይም የአንድን ሰፈር አጠቃላይ የፊዚካላዊ እርጅና ደረጃና የመሰረተ ልማት ተደራሽ ያለመሆን ናቸው፡፡
የቤቶች ወይም ሙሉ ሰፈር እርጅና እንደ መስፈርት ከተወሰደ ከቀበሌ 14ና የኲሓ ነባሩ ሰፈር በስተቀር መልሶ
ልማት በከተማው አጀንዳ እንደማይሆን በክለሳ ላይ የሚገኝ የከተማው መዋቅራዊ ፕላን የጥናት ሰነድ ያሳያል፡፡

118
ሰንጠረዥ 3.5፡ የቤቶች የግንባታ ግብአት ዓይነት በመቐለ ከተማ
መረጃው የተጠናበት ጠቅላላ የግንባታ ግብአት ዓይነት
ጊዜ ቤቶች ድንጋይ ብሎኬት ጡብ እንጨትና ጭቃ ጭቃ ብሎኬት ሌላ
1999 (ሙሉ ቆጠራ) 54,710 67.3% 14.3% 0.1% 17.15% (9,387) 0.1% (31) 1%
(36,825) (7,832) (68) (567)
2006/7 (ናሙና) 7622 48.56% 31.74% 0.46% 4.59% (350) 1.6% (122) 0.01
(3,701) (2,419) (35) (8)
ምንጭ፡ የመቐለ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ክለሳ ጥናት፣ 2006/7 ዓ/ም

በከተማው ከ81.7% ቤቶች ረጅም ጊዜ መኖር ከሚችል ግንባታ ግብአት (ድንጋይና ብሎኬት) የተገነቡ
መሆናቸው በ1999 ዓ/ም የተካሄደው የቤትና ህዝብ ቆጠራ መረጃ በመጥቀስ መዋቅራዊ ፕላኑ ሰነድ
ያስነብባል፡፡ በጥናቱ ጊዜ በናሙናነት የተወሰዱ ቤቶችም ተቀራራቢ ውጤት አስገኝተዋል (80.76%)፡፡
በ1999 ዓ/ም ከእንጨትና ጭቃ የተሰሩ ቤቶች 17.15% ነበር፡፡

በአሁኑ ጊዜ ምጣኔው ወደ 4.59% እንደቀነሰ ናሙናው ያሳያል፡፡ በከተማው ነባር ሰፈሮች የሚባሉት ቀበሌ
14፣ እንዳማሪያም ደቡባዊ አቅጣጫ እንዲሁም እንዳ ኪዳነምህረት ቤተ ክርስትያን አከባቢዎች ከጭቃና
እንጨት የተገነቡ ቤቶች አይታዩም፡፡ እንዲህ ከመሰሉ የግንባታ ግብአት የተገነቡ ቤቶች በብዛት ኲሓ የድሮ
ሰፈር የሚታዩ ሲሆን አይናለም፣ እንዳስላሴ፣ ማይዱባ በጥቂቱ ይታያሉ፡፡ ስለዚህ የቤቶች እርጅና አፍረሶ
ለመገንባት እንደ ዋነኛ ምክንያት የሚወሰድበት ምክንያት አይኖርም፡፡ በእርግጥ ቀበሌ 14 የሚገኙ ቤቶች
ከሞላ ጎደል ከድንጋይ የተገነቡ ቢሆንም ለመፍረስ የተቃረቡ ጥቂት ቤቶች ይገኛሉ፡፡

የቤቶችና ሰፈሮች እርጅና የሚገለፅበት ሁለተኛው መስፈርት የቤት (ኩሽና፣ ሽንት ቤት ሻወር) እና የአከባቢ
መሰረታዊ አገልግሎቶች (ውኃ፣ ኤሌክትሪክ ሲቲ፣ መንገድ) ተደራሽነትና ጥራት ናቸው፡፡ እነዚህ አመላካቾች
በመውሰድ ቤቶችና አከባቢዎቹ ሲቃኙም ከደሴ እና ጅማ ከተሞች እጅጉን የተሻሉ ናቸው፡፡

ሰንጠረዥ 3.6፡ የቤትና ሰፈር አገልግሎት መሰረተ ልማቶች


መጠጥ ውኃ ሽንት ቤት ሻወር ኩሽና
የግል ቧንቧ 81% በውኃ የሚሰራ 57% የግል 29.11% ዘመናዊ 38.84%
የህዝብ ማደያ 11% ደረቅ 29% የጋራ 23.83% ባህላዊ 53.36%
ባህላዊና 6.8%
ድምር 92 ድምር 86 ድምር 52.94 ድምር
ዘመናዊ 92.2
ምንጭ፡ የመቐለ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ክለሳ ጥናት፣ 2006/7

81% ባለይዞታዎች በየቤታቸው የግላቸው የውኃ ቆጣሪ አላቸው፡፡ 11% ያህሉ ደግሞ በአከባቢያቸው ከሚገኙ
የህዝብ ማደያዎች የመጠጥ ውሃ ያገኛሉ፡፡ 57% በውኃ አገልግሎት የሚሰጥ ዘመናዊ ሽንት ቤት ሲኖራቸው

119
29% ደረቅ ሽንት ቤት አላቸው፡፡ 45.6% ዘመናዊ እና 60.16% ባህላዊ ኩሽና ሲኖራቸው ኩሽና የሌለው ቤት
ከቁጥር የማይገባ ነው፡፡

በከተማው ከፍተኛ የህዝብ ጥግግት ያለው ነባሩ ሰፈር ቀበሌ 14 ያካተተ የቐዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ነው፡፡
በዚህ ክፍለ ከተማ በአንድ ሄክታር መሬት 56 ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ሓወልቲ 49፣ ዓዲ ሓቂ 35 ሰው በሄክታር
ሁለተኛና ሶተኛ ደረጃ ይዘዋል፡፡ የኲሓ ክፍለ ከተማ ዝቅተኛ ጥግግት (6 ሰዎች በሄክታር) ነው፡፡ በአጠቃላይ
እንደ ከተማ ሲመዘን 61% ያህል ነዋሪ በኪራይ ቤት እየኖረ አጠቃላይ የጥግግት ደረጃው 14 ሰው በሄክታር
የሚኖር መሆኑ የመጨናነቅ ጉዳይ በከተማው አጀንዳ ሊሆን አይችልም፡፡

ሰንጠረዥ 3.7፡ የመኖሪያ ቤት መጨናነቅ ደረጃ


በአንድ ይዞታ የሚገኙ የክፍል ብዛት አጠቃላይ ጥግግት
አንድ 2-3 ከ3 በላይ አማካይ ሰው በአንድ ሰው በኪራይ
በክፍል በሄክታር ተደርቦ
የሚኖር
1999 2006/7 1999 2006/7 1999 2006/7 1999 2006/7 1999 2006/7 2006/7 1999
60.39% 19% 26.12% 43.22% 13.46% 37.61% 1.5% 3.3% 2.0%3
1.6% 6 እስከ 61%
56
ምንጭ፡ የመቐለ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ክለሳ ጥናት፣ 2006/7 አማካይ
14
ውጫዊ ዕይታ እርጅና፣ ይዞታ ስታንዳርድ፣ የግንባታ ደረጃና ግብአቶች፣ መጨናነቅና መተፋፈግ፣ የመንገድና
ተያያዥ መሰረተ ልማቶች ተደራሽነት መለኪያዎች በመጠቀም ከተመዘነ በከተማው መልሶ ልማት ይጠቃሉ
ተብለው የተፈረጁ አከባቢዎች ቤቶቹ የተገነቡበት የግብአት ዓይነት ለረጅም ጊዜ የሚቆይ (ግራናይት ዓይነት
ግርፍ ድንጋይ) በመሆኑ በእርጅና የሚታሙ አይደሉም፡፡ የአከባቢዎቹ መሰረታዊ ችግር በፕላን
ያለመደራጀትና በርከት ያሉ ግንባታዎት ትናንሽ መሆናቸው ናቸው፡፡ ከላይ የተጠቀሱ መስፈርቶች የሚያሟላ
አከባቢ ቢኖር የኲሓ ምስራቃዊ ጫፍ /ነባሩ ሰፈር/ እና በተወሰነ ቀበሌ 14፣ 04 ይሆናሉ፡፡

3
1999 ዓ/ም በተካሄደው የህዝብና ቤቶች ቆጠራ የከተማው የህዝብ ብዛት 215,914 ነበር፡፡ ይህ አሃዝ እስከ 2005 ዓ/ም 286,624 እንዳደገ
ተተንቢየዋል፡፡ የከተማው ትንበያ በአንፃሩ በተመሳሳይ ወቅት የከተማው የህዝብ ብዛት 313,332 ያደርሰዋል፡፡ ስለዚህ የከተማው ህዝብ
በስድስት ዓመት ውስጥ 70,710-97,418 ዕድገት አሳይቷል፡፡ ከ1998 እስከ 2006 ዓ/ም በከተማው ለመኖሪያ አገልግሎት የቀረበ የይዞታ
ሽንሻኖ ብዛት (Plots) 11,500 አካቢ በመሆኑ በአንድ ክፍል የሚኖር አማካይ የሰው ብዛት ቢጨምር እንጂ ይቀንሳል ተብሎ አይጠበቅም፡፡
በመሆኑም ቁጥሩ ቀንሶ የሚታየው ከናሙና አወሳሰድ ስርጭት ጋር ተያይዞ እንደመጣ ማየቱ ተገቢ ነው፡፡

120
ስእል 3.15፡ ቀበሌ 14 አከባቢ ልማት ፕላንና መልሶ ልማት ዕቅድ ሽፋን

ስእል 3.16፡ እንዳ ማሪያም ጋብር አከባቢ ልማት ፕላንና መልሶ ልማት የሚጠይቅ መሬት ስፋት

የመቐለ ባህሪ ከሌሎች ከተሞች ለየት ብሎ ይታያል፡፡ በሌሎቹ ናሙና ከተሞች የታዩ መለኪያዎች እና በከተማ
ልማት ዙሪያ ተቋማዊ ሙያና ልምድ ያላቸው ድርጅቶች የሚጠቀሙት መስፈርት በመውሰድ መቐለ ከተማ
ላይ አፍርሶ መገንባት የሚጠይቅ ሰፊ አከባቢ የለም፡፡ በከተማው መልሶ ልማት ሲታሰብ ዓላማው ግልፅ
መሆን ይኖርበታል፡፡ ከዚህ አንፃር መቐለ ከተማ የሚካሄደው የመልሶ ልማት የዓላማ ዋና ማጠንጠኛ
ከሰፈሮችና ቤቶች እርጅና በተነሳ ምክንያት የአከባቢዎች ውጫዊ ገፅታ ማሻሻልና መቀየር (Physical
Change) ሳይሆን መሬት ሊያስገኘው ከሚችለው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አንፃር ተደርጎ የሚወሰድ ይሆናል፡፡

መሬት ሊያስገኘው የሚችል ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አንፃር ከታየ በከተማው መልሶ ልማት የሚጠይቅ ቦታ ሰፋ
ያለ መሆኑ በ2000 ዓ/ም የተጠኑ የአከባቢ የልማት ዕቅዶቹ ጠቁመዋል፡፡ ከነባሩ መናሃሪያ እስከ ሂል ቶፕ
ሆቴል በሚወስደው አስፋልት መንገድ በስተደቡብ የሚገኘው 11 ሄክታር ቦታ ለአገልግሎት ተፈላጊነት

121
ይኖረዋል፡፡ እንዳስላሴ አከባቢ 12 ሄክታር መሬት ማቀናጀት ይፈልጋል፡፡ ከ ዘስላሰ አደባባይ ወደ ደጀን
በሚወስደው አስፋልት መንገድና በሰሜን እንዳማሪያም መካከል የሚገኝ ከ7 ሄክታር አገልግሎቱ የመቀየር
ሂደት እየታየበት ነው፡፡ በመሆኑም ከቐዳማይ ወያነ ገበያ፣ ሓውዜን አደባባይ፣ ዘስላሴ አደባባይ፣ ወደ ደጀን
ከሚወስደው አስፋልት መንገድ ተናቦ መለወጥ ያስፈልጋል፡፡

መሬት ለግል ባለሀብት አጓጊ ባይሆንም የሰፈሮቹ አደረጃጀት አለመመቸትና የቤቶች እርጅና ደረጃ መስፈርቶች
ሲመዘን ኲሓ በስተምስራቅ አከባቢ /ደስታ አረቄ ፋብሪካ መንገድ/ እጅግ ያረጀ፣ በፕላን ያልተደራጀ፣
የመዳረሻ መንገድ የሌለው የመኖሪያ ሰፈር ይገኛል፡፡ ይህ ሰፈር መልሶ ልማት ሊካሄድበት የሚገባ ሁነኛ ምሳሌ
ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡ ይህ የሚያመላክተው መልሶ ልማት በከተማ መሀል ስፍራዎች ብቻ ሳይሆን
በከተማ ዳርቻ የሚገኙ ሰፈሮችም መልሶ ልማት ሊጠይቁ እንደሚችሉ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የመልሶ-ልማት ስራ
የሚካሄደው በከተማ መካከል ብቻ ተደርጎ እየተወሰደ መሆኑ ይታያል፡፡

በከተሞች ዳርቻ የሚታይ እርጅናና መተፋፈግ እንደ ከተማው መካከል በሂደት የመጣ ተደርጎ የሚወሰድበት
ዕድል ጠባብ ሁኖ ይታያል፡፡ እንዲህ ዓይነት እርጅናና መተፋፈግ ከሕገወጥ አመሰራረትና መስፋፋት የመነጨ
ተደርጎ ስለሚወሰድ አከባቢዎቹ የከተማው ስታንዳርድ እንድያሟሉ ከማድረግ ይልቅ ማፍረስና ነዋሪዎቹ
ማፈናቀል የተለመደ ክስተት በመሆኑ በሀገራችንም ለሁኔታው ተገቢውን ትንተና እንዳይሰጥ ተፅዕኖውን
ያሳደረ ይመስላል፡፡ ከላይ እንደተገለፀው ከከተማው ዳርቻዎች ከምንም በላይ የተጎዱ ሰፈሮች እያሉ ለመልሶ
ልማት የሚታጩት በከተማው መካከል የሚገኙት ቦታዎች ብቻ ነው፡፡

በድምር ሲታይ መሬት ከፍተኛ ፋይዳ ወዳለው አጠቃቀም መለወጥ ወይም ያለውን የአገልግሎት ዓይነት
ሳይለወጥ ከፍተኛ የመሬት አጠቃቀም (Intensity of use) ለማምጣት በከተማው ሰፋ ያለ ቦታ መልሶ ልማት
እንደሚጠይቅ ተጨባጭ ምስል ቢኖርም ለኑሮ አመቺ ያልሆኑ ያረጁ ቦታዎችና ሰፈሮች ለመቀየር የሚደረግ
መልሶ ልማት የሚጠይቅ ቦታ ውሱን ነው፡፡ ምናልባትም ከቀበሌ 14፣ ቀበሌ 03 እና ኲሓ ምስራቃዊ ጫፍ
ዉሱን ብሎኮች የሚበልጥ አይሆንም፡፡

የናሙና ከተሞቹን ሁኔታ በድምር ስናይ የከተማ ፕላን ያለማሟላት፣ የሰፈሮችና የቤቶች ውጫዊ እርጅና እና
የቤት አካባቢ አገልግሎቶች፣ የወሳኝ መሰረተ ልማቶች (መንገድ፣ ውኃ፣ ተፋሰስ፣ ወዘተ) ተደራሽነት፣
በአጠቃላይ ከከተሞቹ አጠቃላይ መዋቅር (Urban Fabric) ሲታይ ከመቐለና ሃዋሳ በስተቀር በሌሎቹ
ከተሞች መልሶ ልማት የሚጠይቅ ቦታ እጅግ ሰፊ ነው፡፡

ደሴ ከ92% በላይ ቤቶች ከእንጨትና ጭቃ የተገነቡ ናቸው፡፡ 35.06% ያህሉ ቤቶች የቀበሌ ናቸው፤ እነዚህ
ቤቶች እጅግ ያረጁና የደቀቁ ናቸው፡፡ በከተማው በድምር 4000 ቤቶች (400 ሄክታር) ጊዜ የማይሰጥ እንደ
አዲስ ፈርሶ መገንባት የሚገባው ነው፡፡ በከተማው ከሚገኙ ቤቶች 75% በላይ በጥሩ ሁኔታ አይገኙም፡፡
በአጠቃላይ አብዛኛውን የከተማው ክፍል ሰፊ መልሶ ልማት ይጠይቃል፡፡ በድሬ ዳዋ የመሀል ቦታዎች (12

122
ሄክታር ስፋት ያለውን የኢት-ጂቡቲ የባቡር ጣቢያ ግቢ ሳይጨምር) ከ700 ሄክታር በላይ መልሶ ልማት
ይጠይቃል፡፡ ጅማ ከተማ ላይ በከተማው መሀል ቦታዎች 58-70% ቤቶች ያረጁ ለመኖርም ሆነ ለስራ
የማይመቹ ናቸው፡፡ ከ50% በላይ ያረጁ የቀበሌ ቤቶች ናቸው፡፡ በከተማው 200 ሄክታር አፍርሶ መገንባት
እንዲሁም 200 ሄክታር ማሻሻል ይጠይቃል፡፡

የግንባታ ማርጀትና ተፈላጊ አገልግሎት ባልጎደለበት ሁኔታም ቢሆን ከከተማው ዕድገት በተያያዘ መሬት
ሊሰጠው ከሚገባው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ተገቢውን እየሰጠ ያልሆነው የከተማው ክፍል መቀየሩ የግድና
አዋጭ አካሄድ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር መቐለ ከተማ ሰፊ (በድምሩ 23 ሄክታር ያህል መሬት) መልሶ ልማት
ይጠይቃል፡፡ በጅማ ከተማ ከዋናው የከተማው መሀል ቦታዎች ውጭ ሰፊ ቦታ መሬትን ለማቀናጀት ሲባል
መልሶ ልማት ይጠይቃል፡፡

3.2.7. የዕቅድ ስፋት ከፍላጎት አንፃር ሲመዘን


በናሙናነት የተዳሰሱት ከተሞች በአንድ በኩል ከአመሰራረትና ዕድገት ሂደት ታሪካቸው የሚመነጭ የሰፈሮች
እና ቤቶች የማርጀት፣ የበርካታ ሰፈሮች አደረጃጀቱ ፕላን ያልተከተለ በመሆኑ ለእግረኛ ትራፊክ እንቅስቃሴ
የማይመች ከመሆኑ በተጨማሪ ለጤና ጠንቅ መሆን፣ አጠቃላይ ሁኔታው ጤናማ የሚባል የከተማ ባህሪ
ያላሟላ በርካታ አገልግሎቶችና ይዘቶች የጎደሉት መሆኑ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የሰፈሮች/ቤቶች እርጅና ባይኖም
አካባቢዎቹ የከተማውን ዙሪያ መለስ ልማት ለመፍጠን የሚያግዛቸው መሰረተ ልማቶች በጥራት ያልተዳረሰው
የከተሞች ክፍል ቀላል አይደለም፡፡

ይህ ብቻም ሳይሆን የተለያዩ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች እና ልዩ ኢንቨስትመንቶች ተከትሎ የሚፈጠር


የልማት ዓቅም ለመጠቀም በቦታው የቆዩ ግንባታዎች/ይዞታዎች የማይመጥኑ መሆናቸው በዕንቅፋትነት
ይታያሉ፡፡ ከዚህ የሚመነጭ የመልሶ ማልማት ፍላጎት በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች የነበሩበት አጠቃላይ ሁኔታ
እንዲታወክ ስለሚያደርገው ሌላ የልማት ፍላጎት ያስከትላል፡፡ ይህንን እውነታ መነሻ በማድረግ በናሙናነት
የተዳሰሱት ከተሞች የመልሶ ማልማት ጉዳይ የማይታለፍ መሆኑ በመገንዘብ የልማት ፍላጎቱ ለመመለስ ምን
ያህል አቅደው እየሰሩ መሆኑ፣ የመልሶ ማልማቱ ዕቅዱ ይዘት፣ የዕቅድ ዝግጅት ሂደቱ ምን እንደሚመስል
ከዚህ ቀጥሎ በየከተማው በዝርዝር ቀርቧል፡፡

በአዲስ አበባ የነባር ከተማ ማደስ ፕላን ዝግጅት የሚጀምረው በከተማው መሪ ፕላን ዝግጅት ሂደት ነው፡፡
ቀደም ሲል ለአዲስ አበባ ከተማ ከተዘጋጁት መሪ ፕላኖች መካከል ለነባር ከተማ መልሶ ግንባታ ሰፊ ትኩረት
የሰጡት የመጨረሻዎቹ ሁለት መሪ ፕላኖች ናቸው (በጣሊያኖች የተዘጋጀው የ1979ኙ ማስተር ፕላንና
ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተዘጋጀው የ1994ቱ መዋቅራዊ ፕላን)፡፡

123
እንደሚታወሰው የ1979 ማስተር ፕላን ወደ ተግባር ሳይሸጋገር ሸልፍ ላይ የቀረ ፕላን ከመሆኑም በላይ
ባለሙያዎች በር ዘግተው ያዘጋጁት ሰነድ (Blue Print) ስለነበር ከተማዋን መልሶ በማደራጀቱ በኩል ጥሎት
ያለፈው አሻራ የጎላ አይደለም፡፡

ከዝግጅት ሂደቱ ጀምሮ የተሻለ የህዝብ ተሳትፎ የታየበትና የከተማዋን መሠረታዊ ችግሮች በዝርዝር ለይቶ
ችግሮቹ የሚፈቱበትን አቅጣጫ ያስቀመጠው እንዲሁም በአንፃራዊነት ቀደም ሲል ከተዘጋጁት ፕላኖች በተሻለ
ደረጃ ፕላኑን ወደ መሬት ለማውረድ በሚያስችሉ ማስፈፀሚያ መሣሪያዎች (ተቋማዊ፣ ሕጋዊና ፋይናንሻል)
የተደገፈው የ1994 መዋቅራዊ ፕላን ነው፡፡

የ1994 የአዲስ አበባ መዋቅራዊ ፕላን በአገራችን የከተማ ፕላን ዘርፍ መሠረታዊ ለውጥ (Paradigm shift)
ያመጣ መሆኑን እንዲሁም ባለፉት 10 ዓመታት በአገራችን ለተካሄዱ የከተማ ልማት ስራ አመራር ማሻሻያዎች
(Urban Reforms) ፈር ቀዳጅ መሆኑን ለማስረገጥ በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የአካባቢ ልማት ፕላን
አስገዳጅ የከተማ ፕላን አካል (Compulsory urban planning component) እንዲሆን የተደረገው በዚህ
ፕላን ዝግጅት ወቅት መሆኑን መጥቀስ ይበቃል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚከናወን ማንኛውም ግንባታ የመዲናዋን መሪ ፕላን ጠብቆ መከናወኑን ለማረጋገጥ
የሚያስችሉ ሥርዓቶችን በመዘርጋቱ በኩልም ባለፉት አስር ዓመታት የተሻለ ሥራ ተሠርቷል ማለት ይቻላል፡፡
ለመሪ ፕላኑ ማስፈፀሚያ ሥርዓት ከመዘርጋት ባሻገር የልማት ፕሮጀክቶች ትግበራ ለመሪ ፕላኑ ተገዥ
እንዲሆኑ በማድረጉ በኩል ባለፉት 10 ዓመታት የተሻለ ፖለቲካዊ ፍላጎትና ቁርጠኝነት የታየበት ጊዜ ነበር
ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡

በተመሣሣይ የከተማ ማደስ ፕሮጀክቶችን በከተማው መዋቅራዊ ፕላን እና እሱን ተከትሎ በሚዘጋጁ የአካባቢ
ልማት ፕላኖች ማዕቀፍ ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፤ በዚህ መሠረት በአዲስ አበባ የከተማ
ማደስ ፕላን ዝግጅት የመጀመሪያ ምዕራፍ የሚጠናቀቀው በከተማው መዋቅራዊ ፕላን እና በአካባቢ ልማት
ፕላኖች ዝግጅት ወቅት ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ በዚህ መሰረት ባለፉት ስምንት ዓመታት በአራት ክፍለ
ከተሞች 24 የአካባቢ የልማት ዕቅዶች በማዘጋጀት በድምሩ 391.7 ሄክታር መሬት በዋናነት አፍርሶ እንደ
አዲስ ለመገንባት ተንቀሳቅሷል፡፡

124
ሰንጠረዥ 3.8፡ ባለፉት ስምንት ዓመታት መልሰው እንዲለሙ የታቀዱ ፕሮጀክቶች
ከፍለ የቦታው የተጀመረበት የይዞታው አይነት
የፕሮጀክቱ ስም የልማት ተነሺ ብዛት
ከተማ ስፋት ዓ.ም የግል የቀበሌ ኪራይ ቤት ኤጀንሲ
ልደታ ሰንጋ ተራ (ፍርድ ቤት) 26 2001 1442 373 1018 7
ሰንጋ ተራ ቁጥር 2 17 2003 619 78 496 25
ሸበሌ ጀርባ 10.4 2006 428 53 284 91
ተክለሃይማኖት 33 2007 2733 536 2100 97
ቂርቆስ ሸራተን ማስፋፊያ 25 2002 1944 473 1471
ኢሰ.ኤ ማስፋፊያ 2 2002 321 81 174
አፍሪካ ህብረት ቁጥር 1 23 2002 145 33 109 3
አፍረካ ህብረት ቁጥር 2. 12 2003 639 141 476 22
ወሎ ሰፈር 9.8 2001 537 180 346 1
መስቀል መግቢያ 3.2 2001 223 26 198
ካዛንቺስ ቁጥር 2 26 2005 687 145 474 68
ካዛንቺስ ቁጥር 3 23 2006 2793 524 1833 100
ፈለገ-ዮርዳኖስ 17.1 2007 909 163 849 17
ባሻ ወልዴ ቁጥር 1 27 2002 1640 262 1027 53
ባሻ ወልዴ ቁጥር 2 14 2002 1319 270 713 12
አሮጌ ቄራ ቁጥር 1 9 2004 1874 168 935 3
አራዳ አሮጌ ቄራ ቁጥር 2 45 2006 1246 224 841 181
ሸራተን ማስፋፊያ 17 2002 1342 389 985 4
ፓርላማ ማስፋፊያ 4 2002 319 70 259 5
ደጃች ውቤ 11.6 2007 762 121 568 70
ሰንጋ ተራ(ፍርድ ቤት) 26 2001 1442 373 1018 7
አሜሪካ ግቢ ቁ.2 6.7 2007 218 33 172 13
ገዳም ሰፈር 13.9 2007 1012 147 685 93
አዲስ
አሜሪካ ግቢ ቁጥር 1 16 2007 1949 256 1345 182
ከተማ
ድምር 391.7 25,101 4746 17358 1047
ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና ማነጅመንት ፅሕፈት ቤት

ይሁንና የከተማው አብዛኛውን ክፍል የመልሶ ልማት ስራ እንደሚፈልግ መለየት እና የአካባቢ የልማት ዕቅዶች
ማዘጋጀት በቂ ፕላን ሊሆን አይችልም፡፡ መዋቅራዊ ፕላኑ ለ10 ዓመታት እንዲተገበር የሚዘጋጅ ሲሆን መልሶ
ልማት የሚፈልግ ስፋት ግን በአስር ዓመት የሚያልቅ አይሆንም፡፡ ስለዚህ አጠቃላይ የመልሶ ልማት
ፕሮግራም ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን የአካባቢ ልማት ዕቅድ ሲዘጋጅ ምን ያህል ቦታ ለማልማት
መሆኑ ከመዋቅራዊ ፕላኑ ያለመናበብ ክፍተት እንዳለው ማየት ተገቢ ነው፡፡ በከተማው ከ2000 ሄክታር
በላይ ሙሉ በሙሉ አፍርሶ መገንባት እንዲሁም ከ34,000 ሄክታር የከተማው ክፍል በላይ ደግሞ የተለዩ
የአካባቢ ማሻሻል የሚጠይቅ መሆኑ ቢያመላክትም ባለፉት ስምንት ዓመታት መልሶ ማልማት የሚሰራበት
የታቀደ የቦታ ስፋት ሲታይ ግን 391.7 ሄክታር ብቻ ነው፡፡ ይህ ማለት በዓመት 49 ሄክታር ለማልማት
የታቀደ ነው ማለት ሲሆን በዚህ ሂደት ከተሰራ 2000 ሄክታሩ ለማልማት 40 ዓመት ገደማ ያስፈልጋል ማለት
ይሆናል፡፡

125
የመልሶ ማልማት ፕላኑ ይዘት ስንመለከት አራት ዋና ዋና ተግባራት ያካተተ ነው፡፡ እነሱም፡
 በፕሮጀክት ክልሉ ውስጥ የሚገኘውን ነባር ግንባታ በማፍረስ ለልማት ዝግጁ ማድረግ፣
 መሬታቸው በልማት ለተወሰደባቸው ባለይዞታዎች ምትክ ቦታ መስጠት፣
 ከቦታው ለተነሱ ነዋሪዎች ምትክ ቤት መስጠት፣
 ለፈረሱ ንብረቶች ካሣ መክፈል፣
ሲሆኑ እነዚህ ተግባራት በዋናነት የመሬት ዝግጅት ሥራዎች ናቸው፡፡ በዚህ መሠረት ከከተማ ማደስ ፅንሰ -
ሃሳብ አኳያ ሲታይ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ እየተወጣ ያለው የመሬት ልማት ተልዕኮውን ነው፤
እነዚህን ተግባራት ብቻ በማከናወኑ የከተማ ማደስ ኃላፊነቱን ተወጥቷል ብሎ መደምደም ያስቸግራል፡፡
እርግጥ ነው እነዚህ እርምጃዎች የከተማ ማደስ ፕሮጀክት የሚካሄድባቸውን አካባቢዎች ኢኮኖሚ ያሻሽላሉ፣
የአካባቢውንም ሆነ የከተማውን ገጽታ ይቀይራሉ፣ ከደረጃ በታች በሆነ አገልግሎት የተያዘውን ውድ የከተማ
መሬት ደረጃውን ለጠበቀ አገልግሎት ማዋል ያስችላሉ፡፡

ነገር ግን መሬት በከተማው/አካባቢውን ሊገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ጥቅም እንዲያስገኝ ማቀድ ዋናው የልማት
እቅድ ሊሆን አይችልም፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ሳይቶች ለማልማት ሲባል በፕሮጀክቶቹ ከ25 ሺ በላይ አባወራ
ተፈናቅለዋል፡፡ ይህ ማለት 90,000 (ዝቅተኛ አማካይ የቤተሰብ ቁጥር 3.6 ከሆነ) እስከ 100,000 (ከፍተኛ
አማካይ የቤተሰብ ቁጥር 4 ከሆነ) የማያንስ ህዝብ ማፈናቀል የግድ ብሏል፡፡ በአጠቃላይ ከተነሺዎች መካከል
የአብዛኞቹ ኑሮ በመኖሪያ አካባቢ በሚከናወን ኢ-መደበኛ ሥራ (Home based activity) ላይ የተመሰረተ
ነው፡፡ ከእነዚህ መካከል ተማሪዎች፣ በቤት ውስጥ ሥራ ህይወታቸውን የሚገፉ እናቶች፣ በጎዳና ሥራ
ቤተሰባቸውን የሚደግፉ ወጣቶች ይገኙባቸዋል፡፡ ለምሳሌ እላይ በተጠቀሱት ፕሮጀክቶች ከተነሱ ተፈናቃዮች
መካከል በናሙናነት ተወስደው የከተማ አስተዳደሩ እያካሄደ ባለው የከተማ ማደስ ልማት ዙሪያ አስተያየት
እንዲሰጡ በዚህ ጥናት ከተጠየቁ አባውራዎች መካከል 51% የሚሆኑት ኢ-መደበኛ በሆነ ጥቃቅን የንግድ ሥራ
ላይ የተሰማሩ ሲሆኑ 13% ሥራ አጥ፣ 21% የሚሆኑት ደግሞ መደበኛ በሆነ የግል ሥራ የሚተዳደሩ ናቸው፡፡
በሌላ በኩል በመጠይቁ ከተሳተፉ ተነሽዎች መካከል የመንግሥት/የግል ተቋም ተቀጣሪ የሆኑት ከ6.4%
አይበልጡም፡፡

የልማት ዕቅዱ በመልሶ ልማት ከስራቸውና ከሚኖሩበት አካባቢ ሲነሱ ለሚያጡት ጥቅም በሚሰጣቸው
ምትክ ቤት፣ ምትክ መሬት እና ሌሎች የመፈናቀያ ካሳዎች የሚካካስ መሆኑ በውስጠ ታዋቂነት ያለፋቸው ሆኖ
ነው የሚታየው፡፡ ነገር ግን በልማት ሳቢያ የሚያጡት ጥቅም ከሞላ ጎደል በዚህ መንገድ ሊተካላቸው የሚችሉ
የመንግሥት/የግል ተቋም ተቀጣሪ ከሆኑ ብቻ ነው፡፡ በተቀጣሪነት የሚተዳደሩ ዜጎች ምንም እንኳን ከነባር
መኖሪያቸው ርቀው እንዲሠፍሩ መደረጋቸው ለተጨማሪ የትራንስፖርት ወጪ የሚዳርጋቸው ቢሆንም ቋሚ
ሥራ ያላቸው ተነሽዎች የትም ሆነው ሥራቸውን መቀጠል ይችላሉ፡፡

126
ይሁን እንጂ በናሙና ጥናቱ ማረጋገጥ እንደሚቻለው ከመሃል አዲስ አበባ በልማት ከሚፈናቀሉት መካከል
ቋሚ ሥራ ያላቸው ተነሺዎች ድርሻ ውስን ነው፤ እላይ ከቀረበው መረጃ ማየት እንደሚቻለው አብዛኞቹ
ተነሺዎች ከእጅ ወደ አፍ በሆነ የዕለት ሥራ ህይወታቸውን የሚገፉ ናቸው፡፡ አጠቃላይ የመልሶ ማልማት
ዕቅዶቹ ስለአጠቃላይ የነዋሪዎች በተለይ ደግሞ በልማቱ ምክንያት የሚነሱ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ዜጎች
ዙሪያ መለስ ለውጥ ካልሆነም ይኖሩት ከነበረ በታች እንዳይሆኑ የሚያስችል ይዘት አይታይበትም፡፡ እላይ
ከቀረበው ሪፖርት እንደምናየው በመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ የሚሠራው የመልሶ ማቋቋም ሥራ
ምትክ ቤትና ቦታ መሥጠት ለፈረሠ ንብረት ካሣ መክፈል ብቻ ነው፡፡

የመልሶ ማልማት ፕላን ዝግጅት ላይ አዲስ አበባ ከተማ ላይ የሚታዩ ባህሪያት በሌሎች ከተሞች በተለይ
ደሴና ጅማ ከተሞች በስፋት ተንፀባርቀዋል፡፡ በደሴ ከተማ ከላይ ከፍ ሲል የተገለጹ ችግሮች እና የልማት
ፍላጎቶች መልስ ለመስጠት መልሶ ልማት የተጀመረው ከ1996 ዓ/ም ወዲህ ነው፡፡ በተናጠል በፕሎትና
በብሎክ ደረጃ ሲካሄድ የቆየው የመልሶ ልማት ጥረት በአሁኑ ሰዓት አንድን የተሳሰረ አካባቢ በሙሉ ማልማት
የሚቻልበት የአስተሳሰብ ደረጀ ተደርሷል፡፡ እቅዶች ተዘጋጅተው ለመተግበርም ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

በስራ ላይ የሚገኘው የደሴ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን የተዘጋጀው በ2002 ዓ/ም ሲሆን መዋቅራዊ ፕላኑ
ለመተግበር ሰባት የአካባቢ ልማት ፕላኖች በተመሳሳይ ጊዜ ተዘጋጅተዋል4፡፡ ከነዚያ የአካባቢ ልማት ዕቅዶች
ሙሉ በሙሉ አፍርሶ መገንባትን ያካተተ ሰፋ ያለ የመልሶ ልማት የሚጠይቅ ቦታ እንዳለ የሚንፀባረቅባቸው
የአራዳ (38 ሄክታር)፣ ፒያሳ (25.12 ሄክተር) እና የሰኞ ገበያ - ሸዋ በር (75 ሄክታር) ናቸው፡፡

ስእል 3.17፡ ሰፋፊ መልሶ ልማት ያካተቱ የአከባቢ ልማት ዕቅዶች

ሰሜን ፕያሳ

አራዳ

ሰኞ ገበያ - ሸዋ በር

ምንጭ፡ የደሴ ከተማ አስተዳደር፣ 2002 ዓ/ም


4
የአካባቢ ልማት ዕቅዶቹ የጥናት ሪፖርት ሰነድነና ፕሮጀክቶች አልተገኘም፡፡ የተገኘው ካርታዎቹ ብቻ ናቸው፡፡

127
የፒያሳ አካባቢ ልማት ዕቅድ የሚሸፍነው ቦታ የመሬት አጠቃቀሙ በአብዛኛው በንግድና አስተዳደር የተያዘ
ነባር የይዞታዎች ምስል ሲታይ 65% የመንግስት ቤቶች 70% የሚሆኑት ለመኖሪያነት የዋሉ ሲሆን
ግድግዳቸው ከጭቃና እንጨት የተገነቡ ናቸው፡፡

አዲሱ የአካባቢ የልማት ዕቅድ ከበደ አበጋዝ ሆቴል ፊት ለፊት የነበሩ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ፈርሰው
ለንግድና አገልግሎት በሚውሉ ህንፃዎች እንዲተኩ አድርጓል፡፡ ክፍትና አረንጓዴ ቦታዎችም ተካተዋል፡፡ በዚህ
አካባቢ ከሚኖር ማህበረሰብ 42% የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ሴቶች ናቸው:: ቦታውን ለልማት ማዘጋጀት፣
ሰውን ማስነሳት፣ መሰረተ ልማት ለመዘርጋት፣ መልሶ ማስፈርና አስተዳዳራዊ ወጪዎች በከተማ አስተዳደሩ
በሊዝና በኪራይ ከመሬት ከሚያገኘው ገቢ የካፒታል በጀት በመመደብ እንደሚሸፈን ታሳቢ ሲደረግ አጠቃላዩ
ልማት በጥቅሉ ብር 500,000 በሄክታር ሂሳብ ሲሰላ 8 ሚሊዮን ብር በአስር አመት እንደሚሆን ይገመታል
(ዴቨሎፕመንት ፓርትነርስ፤ ሰኔ 2002 ዓ.ም)

ስእል 3.18፡ የፒያሳ አራዳ አካባቢ ልማት ፕላን

ምንጭ፡ የደሴ ከተማ አስተዳደር፣ 2002 ዓ/ም

የሰኞ ገበያ - ሳላይሽ አካባቢ የልማት ዕቅድ ትኩረት ያደረገው ሰኞ ገበያን ከሸዋ በር እስከ ገራዶ መውጪያ
ጫፍ የከተማው ነባር ሰፈሮች ላይ የሚገኙ በእርጅና የተጎሳቆሉ ቤቶችን መለወጥ ነው፡፡ አካባቢው
የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያገኘው ወደ ምዕራብ ወረዳዎች እየተገነባ ባለው አስፋልት መንገድ እንጂ ሌላ
መዳረሻ መንገድ ስለሌለው የከተማ ውስጥ ትራንስፖርት አገልግሎትም እንደልብ አይደርስበትም፡፡
128
ስእል 3.19፡ የሰኞ ገበያ አካባቢ ልማት ፕላን

ምንጭ፡ የደሴ ከተማ አስተዳደር፣ 2002 ዓ/ም


ነባሩ የመሬት አጠቃቀም መኖሪያና የገበያ ስፍራ ነበር፡፡ የተዘጋጀለት አዲስ የአካባቢ የልማት ዕቅድም
ተመሳሳይ ነው፡፡ የመሬት አጠቃቀም ምጣኔው ከአራዳና ፒያሳ በተሻለ ለመኖሪያ የተመደበው ቦታ ምጣኔ ሰፋ
ያለ ነው፡፡ በአጠቃላይ የታቀደው የመሬት አጠቃቀም ምጣኔ ሚዛናዊ ነው ማለት ይቻላል፡፡ የአካባቢ የልማት
ዕቅዱ መልሶ መገንባት እንደሚያካትት ያሳያል፡፡ የንግድ ህንፃዎቹ ከ2-5 ፎቅ ሆነው እንዲገነቡ ተፈልጓል፡፡

ሰኞ ገበያ በመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ ብቻ ደባሎችን ጨምሮ 229 ቤተሰቦችን (በጠቅላላዉ 1441 ነዋሪዎች)
የሚያፈናቅል ሲሆን (16ቱ ቤተሰቦች በ8 ቤቶች ውስጥ በደባልነት የሚኖሩ የቤተሰብ መሪዎች ናቸው)፡፡
እንዲሁም ሁለት የመንግስት ንብረት የሆኑ ቢሮዎችን (የኢትዮ ቴሌኮም እና የደሴ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር)
ጨምሮ በኘሮጀክቱ ምክንያት የሚፈርሱ እንደሆነ፡፡ በኘሮጀክቱ ምክንያት የሚወድመው ንብረት አጠቃላይ
የገንዘብ ግምት የግለሰብ ቤቶችና ተያያዥ ነገሮች ግምት ብር 11,078,896.45 ሲሆን የቴሌኮሙኒኬሽን እና
ኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች 377,970.10 ተገምቷል፡፡ ነዋሪዎቹን በጊዜያዊ ለ3 ወራት በኪራይ ቤት ለማቆየት
ብር 452,000.00 (74 አዳዲስ የቀበሌ ቤቶችን ለመገንባትና ሌሎች የመልሶ ማስፈር ወጭዎች ጭምር) ወጪ
ይጠይቅ ነበር፡፡ በአጠቃላይ የመልሶ ማስፈር የድርጊት ኘላኑን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልገው የወጭ
ግምት ብር 13,016,937.90 እንደሆነ ያሳያል፡፡

የከተማው የንግድ ማእከል የሆነውን አራዳ ዋናው የመልሶ ልማት ማእከል ተደርጎ ተወስዷል፡፡ አዲስ አበባ -
መቐለ ዋና መንገድ በስተግራ በኩል ቀድሞም ቢሆን የከተማው ዋነኛ የንግድ ማእከል የነበረ በመሆኑ
የተዘጋጀው የአካባቢ የልማት ዕቅድ የቦታው ሚና ይበልጥ የሚያጠናክር ነው፡፡ የነበሩ መደዳና ፎቅ ያልሆኑ
ቤቶች በፎቆች ለመተካት የሚያስችል ሽንሻኖ ተሰረቶለታል፡፡ ከፕያሳ ጫፍ ወደ ሰኞ ገበያ በሚወስደው
መንገድ እና በስተጀርባ በኩል ለቅይጥ አገልግሎት ተፈቅደዋል፡፡ የመዝናኛና የታክሲ ስምሪት ቦታዎች
129
ተካተውበታል፡፡ ከመንገድ በላይ የፊት ብሎኮች የንግድ አገልግሎት እየሰጡ የቆዩ ሲሆን በፕላኑ ለቅይጥ
አገልግሎት እንዲውሉ ተወስኗል፡፡ ግማሽ ያህሉ ለክፍት ቦታዎችና መዝናኛ ፓርኮች ታስቧል፡፡ ለተለያዩ ቅይጥ
አገልግሎት ልማት የተፈቀደላቸው ቦታዎችም አሉ፡፡ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ማምረቻ የሚውል
ቦታ ተካቶበታል፡፡ የአካባቢው የልማት ዕቅድ ከመንገድ በታች የሚገኝ ቦታ የንግድ ማእከልነቱ ሳይለቅ
በይበልጥ ለማጠናከር ነገር ግን ግንባታዎች በአዳዲስ እንዲቀየሩ የሚያደርግ ሲሆን ከመንገድ በላይ የመሬት
አጠቃቀሙ ሙሉ ለሙሉ የሚቀይር ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የአራዳ የመልሶ ልማት ዕቅድ አፍርሶ መገንባት
የማይታለፍ ነው፡፡

ስእል 3.20፡ አራዳ አካባቢ ልማት ፕላን


ንግድ
ቅይጥ
አረንጓዴ ቦታ
ማሕበራዊ አገልግሎቶች
ትራንስፖርት
ጥቃቅንና አናስተኛ ማምረቻ

ምንጭ፡ የደሴ ከተማ አስተዳደር፣ 2002 ዓ/ም

ባጠቃላይ ሲታይ አብዛኛው የደሴ ከተማ ቤቶች እርጅና ያጎሳቆላቸው ናቸው፡፡ ቤቶቹ ተሳስረው በመደዳ
የተሰሩ በመሆናቸው የቤቶቹ አካላዊ እርጅና ለእሳት አደጋ ያላቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
በርካታ ሰፈሮች በፕላን ያልተደራጁ በመሆናቸው ከመሬቱ ተፈጥሮኣዊ አቀማመጥ ጋር ተዳምሮ የመንገድና
ትራንስፖርት ተደራሸነታቸው ዝቅተኛ ነው፡፡

የከተማው አጠቃላይ የአሰፋፈር፣ መሰረተ ልማት ዝርጋታና ተደራሽነት፣ የሰፈሮች አደረጃጀትና ፕላን፣ የቤቶች
ቁመናና አቀማመጥ ፕላን እንደ መስፈርት ተወስዶ ሲታይ አብዛኛውን የከተማው ክፍል አፍርሶ መገንባትን
ጨምሮ የተለያዩ ፕላን የማስተካከል ስራዎች የሚጠይቅ ቢሆንም ይህንን ለመምራት የሚያስችል የተሟላ
ዝርዝር ጥናት፣ የመልሶ ማልማት ፕሮግራም እና የማስፈፀሚያ መርሃ ግብር የለም፡፡

130
ስለዚህ ምን ያህሉ የከተማው ስፋትና ይዞታዎች በየትኛው ዓይነት የልማት አማራጭ፣ እንዲሁም በከተማው
መልሶ ልማት የሚጠይቅ ቦታ መቼ እንደሚያልቅ፣ የልማቱ ፋይናንስ ጉዳይ የሚመለከት ጥናት አለ ለማለት
አይቻልም፡፡ የትኛው አካባቢ ቀድሞ መልማት እንደሚገባው የሚያሳይ ምክንያታዊ ጥናት ላይ የተመሰረተ
የማስፈፀሚያ መርሃ ግብርም የለም፡፡ ክፍተቱ የጀምረው ከመዋቅራዊ ፕላኑ ዝግጅት ነው፡፡ የከተማው
መዋቅራዊ እቅድ ሲዘጋጅ አፍርሶ መገንባት የሚጠይቁ ሰፈሮችና ቤቶች ስፋት እንዳላቸው በማሳየት መልሶ
ልማት ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ አጀንዳ መሆኑ ድምዳሜ ደርሷል፡፡ ነገር ግን የ10 ዓመቱ የልማት
ፕሮግራሞች ሲለዩ የመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ብቻ በማትኮር አጠቃላይ ሰፈሮቹ ለመቀየር የሚያስችል
የተሟላ የመልሶ ልማት ፕሮጀክት አልታቀደም፡፡

ሌላው መሰረታዊ ውስንነት መልሶ ልማት ሲታሰብ ዓላማው የከተማው /ሰፈሩ/ ችግሮች ከመፍታት አኳያ
በሚገባ የተቃኘ አልነበረም፡፡ በነባር ቦታዎች ላይ የሚዘጋጁ የአካባቢ የልማት ዕቅዶች በከተማው የሚታየውና
በቀጣይም ፈተና ሆኖ መቀጠሉ የማይቀር የመኖሪያ ቤት አቅርቦቱ ለመፍታት የሚያስችሉ አይደሉም፡፡
የልማት ዕቅዶቹ ሰፊውን ይዞታ ከመኖሪያ ወደ ንግድና ሌሎች አገልግሎቶች እንዲለወጥ ስለሚያደርጉት
የሚታየው የመኖሪያ ቤቶች ችግር ለመፍታት በማስፋፊያ አካባቢዎች አርሶ አደሩን በመካስ ተጨማሪ መሬት
እንዲቀርብ እንደ አማራጭ ተወስዷል፡፡ ከመሬት አጠቃቀም ለውጥ ጋር ተያይዞ ቤታቸው ለሚፈርስባቸው
ነዋሪዎች ጭምር በማስፋፊያ አካባቢዎች መሬት ይሰጣቸዋል፡፡ በእንዲህ ቅኝት የሚታቀድ ዕቅድ የሚለሙ
አካባቢዎች የተመጣጠነ የአሰፋፈር ስርጭትና ተፈላጊውን ጥግግት ደረጃ ለማምጣት አያስችልም፡፡ የመሬት
አቅርቦት ችግሩ አይፈታም፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን የለሙ መሰረተ ልማቶች ሊሰጡት የሚችሉት አገልግሎት
አሟጦ ለመጠቀም አያስችልም፡፡

በእቅድ ዝግጅት የሚታየው ሌላው መሰረታዊ ውስንነት ስለልማት ተነሺዎች ስራና ገቢ በዝምታ የሚያልፍ
መሆኑ ነው፡፡ የዚህ ድክመት መነሻው የከተማው መዋቅራዊ ፕላን ድክመት ነው፡፡ መልሶ ልማት
የሚያስፈልጋቸው ቦታዎች መደበኛም ሆነ መደበኛ ያልሆነ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ማእከላት በመሆናቸው
የበርካታ ነዋሪ ህልውና መሆናቸው ታሳቢ አላደረገም፡፡ እነዚህ አካባቢዎች ፈርሰው እንደ አዲስ ሲገነቡ
በተለይ መደበኛ ባልሆነ ስራ የሚተዳደር በርካታ ሕብረተሰብ ገቢውና ስራውን እንዳይቋረጥ የታቀደ ነገር
የለም፡፡ መዋቅራዊ ዕቅዱ ላይ የታቀደ የስራ ዕድል ፈጠራ ወጣቱ ላይ ብቻ ያተኮሩ ናቸው፡፡ የአካባቢ የልማት
ዕቅዶች ይዘትና አቅጣጫም ከመዋቅራዊ የልማት ዕቅዱ የተለዩ አይደሉም፡፡

በቀበሌ ቤት ይኖሩ የነበሩ ተነሺዎች የመኖሪያ ፍላጎታቸው ለመመለስ የኮንዶሚንየም ቤት በግዥ ቅድሚያ
እንዲያገኙ፣ ምትክ የቀበሌ ቤት እንዲሰጣቸው፣ ካልሆነም መሬት ተሰጥቶአቸው በግላቸው ቤት እንዲገነቡ
አማራጭ ይቀርብላቸዋል፡፡ በተግባር የኮንደሚንየም ቤት ግንባታ ስለቆመ ዓቅም ያለውም ቢሆን የመግዛት
ዕድል የላቸውም፡፡ የቀበሌ ቤቶችም ግማሾቹ በመልሶ ማልማቱ ምክንያት እየፈረሱ ናቸው፡፡ የልማት
ተነሺዎች ለማስተናገድ ያሉት አማራጮች በከተማው የሽንሻኖ ስፋት ደረጃ የቤት መስሪያ ቦታ መስጠት

131
ካልሆነም ምትክ የቀበሌ ቤት ገንብቶ ማቅረብ ናቸው፡፡ ይሁንና በልማቱ ምክንያት ከቦታቸው የሚለቁ
ነዋሪዎች በነበሩበት መልሰው የማይሰፍሩ ከሆነ እነሱን በቋሚነት የሚሰፍሩበት ቦታ ቀድሞ ማቀድና ማዘጋጀት
ከተማ አስተዳደሩ ሊወጣው የሚገባ ግዴታ ቢሆንም መልሶ ማስፈሪያ አካባቢዎች የመልሶ ልማቱ አካል
ተደርገው ቀድመው አይታቀዱም፡፡

በሁሉም የአዳዲስ ማስፈሪያ ቦታዎች መሰረተ ልማት የሚዳረሰው ከዓመታት በኋላ ነው፡፡ ከጋሪ ተራ፣ አርባ
ቁጠባ፣ አራዳ አካባቢዎች ተነስተው ቀጋ በሚባለው አካባቢ መሬት ተሰጥቶአቸው ቤት ሰርተው የሰፈሩ
ኤሌክትሪክ ከሶስት ዓመት በኋላ፣ ውሃ ከስድስት ዓመት (2005 ዓ.ም) በኋላ ነው ማግኘት የቻሉት፡፡ ያም
ሆኖ ተፈናቃዮቹ ኤሌክትሪክ መስመር ለማስገባት እያንዳንዱ ቤተሰብ ብር 300 እና በላይ፣ የውሃ መስመር
ለማስገባትም እስከ ብር 400 በማዋጣት ከከተማው አስተዳደር በሽርክና በተደረገው ጥረት ነው ለማግኘት
የቻሉት፡፡ የመዳረሻ መንገድ ለማሰራት እያንዳንዱ ቤተሰብ ከብር 300 በላይ እያዋጣ ባጠቃላይ ብር 14,500
እንዳሰባሰቡ የአሰሪው ኮሚቴ አባላት ለጥናት ቡድኑ አባላት ገልፀዋል፡፡ ከዚህ በባሰ በ2004 ዓ.ም ከአይጠየፍ
አካባቢ ተነስተው ሰንሰል ሰፈር በሚባል አካባቢ የሰፈሩ የተወሰኑ ነዋሪዎች ደግሞ እስካሁን የውሃና
የኤሌክትሪክ አገልግሎት አላገኙም፡፡

በተነሺዎች አያያዝ ላይ ቀድሞ በመዘጋጀት በዕቅድ ከመምራት ይልቅ ለሚፈጠረው ችግር መልስ ለመስጠት
ነው የሚሞከረው፡፡ ያም ሆኖ ጥያቄዎቹ መልስ የሚያገኙት ከዓመታት በኋላ ነው፡፡ በከተማው የተሻለ
ተሞክሮ የታየው በአንድ ሳይት ብቻ ነው፡፡ ሰኔ 2005 ዓ.ም ከሰኞ ገበያ ተፈናቅለው በግ ተራ የሰፈሩ
ከአካባቢው ተወላጆች በተሰበሰበው የድጋፍ ገንዘብ (ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ከብር 30,000 በላይ) በስድስት
ወር ጊዜ ውስጥ መብራትና ውሃ አግኝተዋል፡፡

የልማት ተነሺዎች መልሶ ለማስፈርና ለማቋቋም በዕቅድ የማይመራና የተሟላ ቅድመ ዝግጅት የማይደረግበት
መሰረታዊ ምክንያት የልማት ተነሺዎች ለንብረታቸው ከሚከፈል ካሳ ውጭ የሚኖራቸው ሕጋዊና ሰብአዊ
መብቶች የመኖሪያ ቤት ጉዳይ ብቻ ተደርጎ ስለሚወሰድ መልስ መስጠት የሚሞከረውም በዚህ ልክ ነው፡፡

ቀደም ሲል እንደተገለፀው መቐለ ከተማ ላይ ከሰፈሮች እና አካባቢዎች እርጅና በተያያዘ መልሶ ልማት
አንገብጋቢ አጀንዳ አይደለም፡፡ ከዚህ እሳቤ አፍርሶ መገንባት የሚገባቸው አካባቢዎች ከሌሎች ከተሞች እና
ከቦታዎቹ ስፋት አንጻር ጉዳዩ ሲመዘን አሳሳቢ አይደለም፡፡ ስለሆነም የከተማው የልማት ትኩረት በ1998
ዓ/ም የተዘጋጀው መዋቅራዊ ፕላን ወደ ከተማው ክልል ያስገባቸው የገጠር መንደሮች በፕላን ማደራጀት፣
በከተማው ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ያልተሰጣቸው ይዞታዎች ሕጋዊ ሰነድ ማሟላት፣ የመሰረተ ልማት
አደረጃጀት ችግር ያለባቸው ማስተካከል እና ያልተዳረሰባቸው ማዳረስ ሲሆን አፍርሶ መገንባት ያካተተ መልሶ
ልማት ጥቂት ቦታዎች አካቷል፡፡

132
በዚህ ጥናት ከተዳሰሱት ከተሞች የአካባቢ መልሶ ልማት ወይም ሌላ ዓይነት ልማት ጥረት የሚፈልግ ስፋት
በማጥናት ልማቱ በሚጠይቀው ልክ ከማቀድ አንፃር የመቐለ ከተማ ያህል የተጓዘ የለም፡፡ 17 የአካባቢ የልማት
ዕቅዶቹ የከተማው ሙሉውን ክፍል የሸፈኑ ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡

ሰንጠረዥ 3.9፡ የአካባቢ የልማት ስፋትና ወጪ ዕቅድ


የአካባቢ ልማት ፕላን ስፋት በሄክታር የወጪ ግምት ብር
አይናለም 163.23 58,406,000
ዓዲ ሽምዱሕን 219.80 4,420,000
ላጪ 358.14 15,943,000
እንዳማሪያም ጋብር 147.00 3,544,190
ዓዲ ወለል - ዓዲ ከንፈሮ 149.50 7,111,490
ማይ ሊሓም 112.2 1,332,850
ዓዲሓ 560.00 12,961,453
ማይ ዱባ 617.20 9,666,700
ኲሓ ነባር - እምባ ፈቓዱ 828.00 7,131,000
ዓዲ ሓቂ 58.45 28,631,500
እንዳ ስላሴ 170.00 5,334,100
ሰራዋት 683.00 7,994,000
ኲሓ አዲሱ ሰፈር 850.00 17,154,500
ቀበሌ 14 34.17 3,506,950
ደጀን - 03 212.00 4,914,200
እንዳየሱስ 190.30 7,165,800
ፈለግ ዳዕሮ 168.00 መረጃ አልተገኘም
ድምር 5,520.90 195,217,733 (+)
ምንጭ፡ የመቐለ ከተማ አካባቢ ልማት ጥናቶች፡ 2000 ዓ/ም

ከነዚህ የአካባቢ የልማት ዕቅዶች የቀበሌ 14 እንደ አዲስ አፍርሶ መገንባት ያካተተ የአካባቢ ማሻሻል፣
አይናለም ሰፊ ፕላን ማደራጀት የሚጠይቅ በመሆኑ አዲሱ ሽንሻኖ የመሬት አጠቃቀም ለውጥ አስከትሏል
ከማስከተሉ በላይ በጣም በርካታ ይዞታዎች እንዲስተካከሉና ቤቶች እንዲፈርሱ አድርጓል፡፡ ይህ ብቻም
ሳይሆን በአዲሱ የፕላን ሽንሻኖ መሰረት የከተማው ፕላን (የግንባታ ደረጃ) መስፈርት የሚያሟላ ግንባታ
ማከናወን ስለሚጠይቅ አብዛኛውን ቦታ ፈርሶ እንዲገነባ የግድ ይላል፡፡ እንዳ ማሪያም-ጋብር እና ኲሓ አዲሱ
ሰፈር ደግሞ የተወሰነ ፈርሶ የሚገነባና ሰፊ የአካባቢ ማሻሻል እንደሚጠይቅ የታቀደ ሲሆን ሌሎቹ በዋናነት
አካባቢዎቹ ባሉበት ማሻሻል እና መሰረተ ልማት እንዲሟላላቸው የታቀዱ ናቸው፡፡

የአካባቢ የልማት ዕቅዶች ሲዘጋጁ የሰፈሮችና አካባቢያዊ ውጫዊ ገፅታዎች እንዲሁም መሰረተ ልማት
ማሟላት ላይ ብቻ ያተኮሩ አልነበሩም፡፡ ከደሴና ጅማ በተለየ የአካባቢ ልማት ዕቅዶቹ የእያንዳንዱ አካባቢ
የኢኮኖሚ ዕምቅ ዓቅም ተመላክተዋል፡፡ በዋና ዋና መንገዶች ሁለት መደዳ ብሎኮች ከፍተኛ የግንባታ ደረጃ
(Height function) እንዲኖራቸው እና በዋናነት ለንግድና አገልግሎት (Business) ቢዝነስ እንዲውል
ታቅደዋል፡፡ እያንዳንዱ አካባቢ የሚኖረው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳና በተጨባጭ ሊከናወን የሚችል የኢኮኖሚ

5
ከአየር ፎቶ የተወሰደ መረጃ

133
እንቅስቃሴም ተለይቷል፡፡ ለምሳሌ ቀበሌ 14 ማእከሉ ንግድ ሆኖ ከቅርስና ታሪክ ጥበቃ ተያይዞ የቱሪዝም
ማእከል እንዲሆን የታቀደ ሲሆን የእንዳየሱስ አካባቢም በዋናነት ለመዝናኛና ለቱሪዝም ማእከልነት የሚኖረው
ዓቅም ከፍተኛ እንደሆነ ተለይቷል፡፡ በታሪካዊነትና ቅርስነት መጠበቅ የሚገባቸው ቦታዎችና ህንፃዎች
ተለይቷል፡፡ ቀበሌ 14 የከተማው ታሪካዊ ገፅታ (Morphology) የሚያንፀባርቅ በመሆኑ ህንፃዎቹ ማሻሻልና
መልሶ መገንባት ሲያስፈልግ ገፅታው በማይቀይር መልኩ እንዲሆን ለማድረግ የህንፃ ከፍታ፣ የኮንስትራክሽን
ግብአት ዓይነት፣ የህንፃ ጥበብ ስልት ወዘተ ዝርዝር መስፈርት ተበጅቶለታል፡፡ የልማት ተነሺዎች
ሊያጋጥማቸው የሚችል የኢኮኖሚ ተግዳሮት ለመፍታት ብሎም ኑሮአቸው ለማሻሻል የሚያስችሉ
ፕሮፖዛሎችም ተዘጋጅተው ነበር፡፡

በጅማ ከተማ የመልሶ ማልማት እንቅስቃሴ የተጀመረው የተሟላ ዕቅድ ሳይዘጋጅለት የከተማው ነዋሪ
ካነሳቸው የመንገድና ተፋሰስ መሰረተ ልማት ጥያቄና የኢትየጵያ ሚሌኒየም በፈጠረው የልማት ንቅናቄ
አጋጣሚዎች በመጠቀም በ2000 ዓ/ም ነበር፡፡ በወቅቱ ሲሰራበት የነበረ የከተማው መዋቅራዊ ፕላን
የከተማው መሃል ቦታዎች ላይ መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጡ ፕሮጀክቶች አልነበሩትም፡፡ ስለሆነም በወቅቱ
መልሶ ልማት ለማሰብ ዕድልም አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡

ከላይ የተጠቀሱ አጋጣሚዎች የመንገድ መሰረተ ልማት አቅርቦት/መሻሻል/ በሂደት በዕቅድ እንዲካተት ዕድል
ፈጥረዋል፡፡ በቦታው የሚካሄድ የግንባታ ኢንቨስትመንት የዕቅዱ መሰረት የባለሀብቱ ጥያቄ ነበር፡፡ እስከ
2005 ዓ/ም መልሶ ልማቱ የሚመራበት ግልፅ ዕቅድ መኖሩ የሚያሳይ መረጃ የለም፡፡

በነጠላ ሽንሻኖ ሲካሄድ የቆየ መልሶ ልማት የሊዝ አዋጅ 721/2004 መደንገግን ተከትሎ በአካባቢ የልማት
ዕቅድ እንዲመራ ዕድል ፈጥሯል፡፡ የአካባቢ የልማት ዕቅዶቹ መነሻቸው ደግሞ 2002 ዓ/ም የተዘጋጀው
የከተማው መዋቅራዊ የልማት ዕቅድ ነው፡፡ በመቐለና ደሴ ከተሞች መዋቅራዊ ፕላን ያልታየ የጅማ መዋቅራዊ
ፕላን የትኞቹ አካባቢዎች መልሰው መልማት እንዳለባቸው በግልፅ አመላክቷል፡፡

በ2005 ዓ/ም ከተዘጋጁ አምስት የአካባቢ የልማት ዕቅዶች የሶስቱ ዕቅዶች ትኩረት መልሶ ልማት ላይ ነው፡፡
መርካቶ 62 ሄክታር፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ 40 ሄክታር፣ ቦቼ ቦሬ 35.8 ሄክታር በድምሩ 137.8 ሄክታር
የሚሸፍን ቦታ መልሶ እንዲለማ ታቅዷል፡፡ በተለይ መርካቶ ሙሉ በሙሉ ፈርሶ እንደ አዲስ እንደሚገነባ
በመዋቅራዊ ፕላኑ ተጠቅሷል፡፡ ከችግሩ ስፋትና ካለው የመልሶ ልማት ዓቅም ጋር ሲነፃፀር ሶስቱም የአካባቢ
የልማት ዕቅዶች ከታቀደው የትግበራ ጊዜ ብቻ ከታየ በቂ መልስ የሚሰጡ ናቸው፡፡

134
ስእል3.21፡ ጅማ ከተማ የመርካቶ አካባቢ ልማት ፕላን

ምንጭ፡ ከጅማ ከተማ መሬት ልማትና ማነጅመንት ኤጀንሲ 2000 ዓ/ም የተወሰደ

ስእል 3.22፡ ጅማ ከተማ የቦቾ ቦሬ የአካባቢ ልማት ፕላን ሽፋን

ምንጭ፡ ከጅማ ከተማ መሬት ልማትና ማነጅመነት ኤጀንሲ 2000 ዓ/ም የተወሰደ
ይሁን እንጂ ዓመታዊ የትግበራ ዕቅዶቹ በአካባቢ የልማት ዕቅዶቹ የተቀመጠ ግብ የሚያሳኩ አይደሉም፡፡

ማሳያዎቹ ፡

i. በ2005 ዓ/ም የተዘጋጁት የአካባቢ የልማት ዕቅዶች ለዚህ ጥናት ግብአት የሚውል መረጃ
እስከተሰበሰበት /መጋቢት 2008 ዓ/ም/ በሚታይ መልኩ ወደ ትግበራ አልገቡም፤
ii. ለ2008 በጀት ዓመት ቦቼ ቦሬና መርካቶ የተያዘ የመልሶ ልማት ዕቅድ 1.55 ሄክታር ብቻ ነው፤ ይህ
ደግሞ የአካባቢ የልማት ዕቅዶቹ ሲዘጋጁ በከተማው ፍላጎትና ዓቅም ያልተመሰረቱ መሆናቸው
ካልሆነም የከተማው አስተዳደር በዕቅዶቹ ዕውቅና እንዳልነበረው ያመላክታሉ፡፡

135
iii. ክልሉ የሚሰጠው ግብም የአካባቢ የልማት ዕቅዶቹ ላይ የተቀመጠው ግብ የሚያሳካ አይደለም፡፡
ለምሳሌ በበጀት ዓመቱ 10 ሄክታር ያህል መልሶ እንዲለማ ለከተማው ግብ ተጥሏል፡፡ ያም ሆኖ ግን
ከተማው ከዓቅሙ በላይ መሆኑ እየገለፀ ነው፡፡

የችግሩ ስፋት የአካባቢ የልማት ዕቅዶች በማዘጋጀት ብቻ የሚፈታም አይደለም፡፡ መዋቅራዊ ፕላኑ ላይ
የተመላከቱ ችግሮች ሰፊ በመሆናቸው መልሶ የሚለማው ቦታ ዝርዝር ጥናትና የፕሮግራም ሰነድ ይጠይቃል፡፡

የዕቅዱ ይዘት በስፋትና በጥልቀት ሲመዘን የከተማው ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል አይደለም፡፡
በመልሶ ልማት ምክንያት የሚነሱ ነዋሪዎች ገቢያቸውና ኑሮአቸው ምን ላይ እንደተመሰረተና ቢያንስ በምን
መልኩ ማስቀጠል እንደሚቻል፣ ከተቻለም እንደሚሻሻል ጠለቅ ያለ ጥናት እየተካሄደበት አይደለም፡፡ በሃሳብ
ደረጃም መኖሩ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ የልማት ተነሺዎቹ ጥያቄ የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ብቻ ተደርጎ
እየተወሰደ ነው፡፡ በከተማው መካከል በመልሶ ልማቱ ምክንያት መሰረተ ልማቶች ሲሟሉ የልማት ተነሺዎች
ለዓመታት የውኃ፣ መንገድ፣ ኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችና የትራንስፖርት አገልግሎት ተነፍገው ይኖራሉ፡፡

ስእል 3.23፡ የጅማ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ልማት ፕላን

ምንጭ፡ ከጅማ ከተማ መሬት ልማትና ማነጅመነት ኤጀንሲ 2000 ዓ/ም የተወሰደ
የልማት እቅዶቹ በርካታ ነዋሪ ከመኖሪያውና ከስራው እንዲፈናቀል አድርገውታል፡፡ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ
በርካታ ነዋሪዎች በተለያዩ የልማት ፍላጎቶች ምክንያት ከሚኖሩበትና ከሚሰሩበት አካባቢ ተፈናቅለዋል፡፡
ነዋሪዎች ከሚሰሩበትና ከሚኖሩበት አካባቢ እንዲፈናቀል የሚያደርጉት ምክንያቶች በአራት ተከፍለው
የሚታዩ ናቸው፡፡

136
አንዱ ምክንያት የመንግስት ኢንቨስትመንት የሚያስከትለው መፈናቀል ነው፡፡ በ2000 ዓ/ም የጅማ አየር
ማረፊያ ሲገነባ በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርቶ የነበረ 93 ቤተሰቦች ተፈናቅለዋል፡፡ በተመሳሳይ ዓመት
የወጣቶች ማእከል ለመገንባት ሲባል 9 ቤተሰብ ከአራት አንበሳ አደባባይ አካባቢ ተፈናቅለዋል፡፡ የከተማው
የመሬት ልማትና ማነጅመንት መስሪያ ቤት ለመገንባት 45 በቀበሌ ቤት ተከራይተው የሚኖሩ ቤተሰቦች
ለማስነሳት የከተማው ማዛገጃ ቤት መጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡ በከተማው ሲካሄድ የቆየ የመንገድ
ተደራሽነትና ደረጃ የማሻሻል ፕሮግራም ሌላው መፈናቀል ያስከተለ ልማት ነው፡፡ በከተማው የከተሞች
ልማትና ዓቅም ግንባታ ፕሮግራም (Urban Local Governments Capacity Building Program) የውስጥ
ለውስጥ መንገዶች በድንጋይ ንጣፍ ሲሰራ ድንበር ለማስከበር 5 ቤተሰቦች ተፈናቅለዋል፡፡ በዝቅተኛ ስፍራ
የሚገኙ የተወሰኑ አካባቢዎች የውኃ ሙላት ያስቸግራቸዋል፡፡ ይህንን መሰል የአደጋ ተጋላጭነት ለማስወገድ
ሲባል በ2000 ዓ/ም ከለግሃር 26 ቤተሰዎች ተነስተዋል፡፡ በከተማው ያረጁ ቦታዎች ለማደስ ከ1999 ዓ/ም
እስከ 2004 ዓ/ም ከመርካቶ ከ200 በላይ ቤተሰቦች አፈናቅሏል፡፡

ሰንጠረዥ 3.10፡ 1999-2008 በተለያዩ ምክንያቶች የተነሱ ናሙና መረጃዎች


ከግል ከቀበሌ የተነሺዎች ምርጫ የተግባር አፈፃፀም
ተ. ነዋሪዎች ነዋሪዎቹ ይዞታው ኪራይ ቤት ምትክ ተለዋጭ ምትክ
ቁ የተነሱባቸው የተነሱበት ምክንያት የተነሱ የተነሱ ቤት መሬት ቤት መሬት
አካባቢዎች ዓመት ቤተሰብ ቤተሰብ
1  ሂርማታ መርካቶ የጠራ መረጃ ባይገኝም
 ሄርማታ መንቲና ከ 200 በላይ በርካቶቹ ምትክ ቤት
 ሄርማታ 2000 - መልሶ-ልማት የግል ባለይዞታዎች ተገንብቶላቸዋል፡፡ አዋጁ
 ለገሀር 2003 ጥቂት እንደነበሩ ይህንን ይደግፍ ስለነበር -
 አዊቱ መንደራ ተገልጿል
2 ለገሃር
ጊንጆ ጉድሩ 2001 አደጋ - 20 - - 20 -
ተጋላጭነት
3 አራት አንበሳ 2008 መልሶ-ልማት 3 39 1 31 1 31
4 አየር ማሪፊያ 2001 ኢንቨስትመንት 47 - - 47 - 47
5 ዩኒቨርሲቲ 2001 ኢንቨስትመንት 37 - - 37 - 37
ማስፋፊያ
6 በቾ ቦሬ 1998 የጋራ መኖሪያ 63 - - 63 - 63
ኮንደሚንየም ቤት ግንባታ
ምንጭ፡ ጅማ ከተማ መሬት ልማትና ማነጅመንት ኤጀንሲ፣ ጅማ ከተማ የኢንቨስትመንት ኤጀንሲና ከመስክ

ለግል ኢንቨስትመንትና ለመንግስት ተቋማት መሬት ለማቅረብ ሲባል በሚቀጥሉት ሁለትና ሶስት ዓመታት
በርካታ ነዋሪዎች በተመሳሳይ ከቀበሌ ቤት ይነሳሉ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሚያሰራው ፅሕፈት ቤትና
አገልግሎት መስጫ ማእከል የሚውል 5,500 ሜትር ካሬ መሬት ለማቅረብ ጋሊ-ሞሌ አካባቢ በቀበሌ ቤት
የሚኖሩ 45 ቤተሰቦች ካሉበት ይለቃሉ፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክና ኢትዮ ተሌኮም ተመሳሳይ ጥያቄ እያቀረበ
እንደሆነ የከተማው የመሬት ልማትና ማነጅመንት ባለሙያዎች ገልፀዋል፡፡ ሄርማታ መርካቶ ውስጥ ለግል
ኢንቨስትመንት የሚውል አንድ ሄክታር መሬት ለማዘጋጀት 96 ነዋሪዎች ይፈናቀላሉ፡፡

137
ሰንጠረዥ 3.11፡ ቀጣይ የመልሶ ማልማት ዕቅድና የሚፈናቀለው ነዋሪ
የታቀደ የመልሶ ማስፈር
ተ. በልማቱ የሚነሱ የቤተሰብ ብዛት አማራጭ
ቁ ለልማት የግል ባለ የግለ ሰብ የቀበሌ ቤት ምትክ አልሚ
የተጠና ይዞታዎች ቤት ተከራዮች ተከራዮች ቤት መሬት ሌላ
አካባቢ
1 ሄርማታ 18 አልተጠናም 78 - 96 - ለግል
መርካቶ ባለሃብቶች
2 በቾቦሬ 7 አልተጠናም 38 45 - - የኢትዮጵያ
/ጋሊሞሊ/ ንግድባንክ
ድምር 25 - 116 45 96 -
(17.73%) (82.27%) (31.91%) (68.09%)
ምንጭ፡ የጅማ ከተማ መሬት ልማትና ማነጅመንት ኤጀንሲና ከመስክ ዳሰሳ የተወሰደ
በከተማው በተካሄዱና በመካሄድ ላይ ያሉ እንዲሁም ለወደፊቱ እንዲከናወኑ በታሰቡ የተለያዩ የልማት
ዕቅዶች የተፈናቀሉና የሚፈናቀሉ ነዋሪዎች አብዛኞቹ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ናቸው፡፡ በርካቶቹ በጥቃቅን
የንግድና አገልግሎት፣ መደበኛ ባልሆነ በግል ተቀጥረው የሚሰሩ፣ በቀን ስራ፣ በመንግስት ስራ፣ በጡረታ
አበል፣ የሸክላ ስራ ውጤቶች ማምረት፣ የሚተዳደሩ ናቸው፡፡ ቀጣይ ከሄርማታ መርካቶና ጋሊሞሊ
የሚነሱትም ተመሳሳይ የስራ ስምሪት ምስል አላቸው፡፡

የጅማ ከተማ የመልሶ ማልማት ተሞክሮ በአረዳድና የዕቅድ ይዘት ሲመዘን ከሌሎች ከተሞች የተለየ
አይደለም፡፡ የመልሶ ልማቱ ተግባር ሲከናወን የቆየው ያለ ፕሮግራም ነው፡፡ የመልሶ ማልማቱ ዓላማ፣
የማስፈፀሚያ ጊዜ ሰሌዳ፣ የፋይናንስ ምንጭና መጠን በዝርዝር የተዘጋጀ ዕቅድ የለም፡፡

የሀዋሳ ከተማ መልሶ ማልማት ማእከል በዋናነት የመንገድ እና ተፋሰስ መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ያተኮረ
ሲሆን ቀጣይ የመልሶ ማልማቱ ትኩረት በከተማው መካከል የመሬት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ
እንዳይሰጥ እንቅፋት የሆኑት የያዙት ከደረጃ በታች ግንባታዎች ላይ አድርጓል፡፡

የመልሶ ማልማቱ ፕሮጀክት ለኣምስት የተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች በተጠናው የአካባቢ ልማት ፕላን
በተጠናላቸው የመሃል አካባቢ ቦታዎች ላይ ብቻ የሚካሄድ ሲሆን የአካባቢ የልማት ፕላን ጥናቱም ከከተማዋ
መዋቅራዊ ፕላን ላይ ተመርኩዞ የተዘጋጀ ነው፡፡ በመሆኑም የመልሶ ማልማቱ ፕሮጀክት በከተማው ፕላን
የቦታ አገልግሎት ምደባ መሰረት ነው እየተካሄደ ያለው፡፡

የከተማው የመልሶ ማልማት ፕሮጀክት ከኘላን ዝግጅቱ ጀምሮ የተመሰረተው በግምባር ቀደምትነት በከተማዋ
ማዕከላዊ አካባቢዎች በርካታ ያረጁ ቤቶች በሚገኙበት ሰፈር ሲሆን ቅድሚያ ትኩረት የተሰጠውም ከግል
ንብረት ይልቅ የቀበሌ ቤቶች ያሉበትን ሰፈር መልሶ ለማልማት ነው፡፡

138
ስእል 3.24፡ የከተማ ማደስ የሚተገበርባቸው አምስት ማእከላዊ ቀበሌዎች አጉልቶ የሚያሳይ ካርታ

ምንጭ፡ ኮምፓስ ኮንሰልታንት፣2006

የመልሶ ማልማቱ አንዱና ዋናው ክፍል የሆነው የመንገድ ልማት በአካባቢ ልማት ፕላኑ መሰረት የማስፋፋት
እና ጥራቱንም የማሳደግ ሥራ ሲሰራ የግል ቤቶችና አጥሮች የሚሸረፉበት አልፎ አልፎም ሙሉ ለሙሉ
የሚፈርሱበት ሁኔታ አለ፡፡

የመሰረተ ልማት ግንባታው ያረጁ የመንግስት ቤቶች የሰፈሩበትን ቦታ በሊዝ ጨረታ ለአልሚ ባለሀብቶች
በማስተላለፍ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው የንግድ፣ የተለያዩ የቢዝነስና የቢሮ ህንጻዎች እንዲሰሩ አስችሏል፡፡ ይህም
የአካባቢ ልማት ፕላን ጥናቱን ከሊዝ ደንቡ ጋር በማቀናጀት ከተማዋን የማደሱ ሥራ ለመጀመር የተደረገው
እንደ ጥሩ ዝግጅት ሊታይ ይችላል፡፡

በከተማዋ እስካሁን በሰፋፊ ቦታ እና ወደ ጎን ሲካሄድ የነበረው ልማት ከተማዋን ያለ ቅጥ እንድትለጠጥ እና


የመሬት እጥረት እንዲፈጠር ከማድረጉ ባሻገር የመሀሉን ከተማ መሰረተ ልማት አውታሮች ከአቅም በታች
ጥቅም ላይ እንዲውሉ አድርጓል፡፡ የከተማው አስተዳደር በማስፋፊያ አካባቢዎች ለመሰረተ ልማት ዝርጋታ
የሚያውለውን እጅግ ከፍተኛ ወጭ በሌላ የከተማውን ኢኮኖሚያዊ ልማትና እድገት በሚያፋጥን የልማት
ተግባር ላይ እንዳይውል ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

የመልሶ ልማት ዕቅድ ሲዘጋጅ እነዚህ ክፍተቶች ላይ ተገቢውን እሳቤ ተደርጎባቸዋል፡፡ ፕላኑ ወጪ ቆጣቢ
እንዲሆን የመልሶ ማልማቱ በአነስተኛ መጠን እንዲጀመር፣ ለነባር ወይም አዳዲስ ለሚገነቡ መሰረተ ልማት
የቀረቡ በከተማው ማዕከላዊ ቦታዎች እንዲጀመር፣ የግል ቤቶች ይልቅ በአብዛኛው የመንግስት ቤቶች
በሚበዙበት ቅድሚያ መስጠት፣ እንደዚሁም መልሶ ማልማቱ በተዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላኖች መሰረት

139
የመሰረተ ልማት ግንባታ ቅድሚያ እንዲከናወን የሚሉት ስልቶች ተከትለዋል፡፡ የሚወጣው ወጪም
ከከተማው አጠቃላይ ዕድገት ጋር በሚጣጣም መልኩ ተከናውኗል፡፡

ስእል 3.25፡ የከተማ ማደስ የሚካሄድባቸው በመሃል ከተማ የሚገኙ የቀበሌ ቤቶች በከፊል ገጽታ

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ

የመንግስት ቤቶች የነበሩበት ቦታ በአንድ ሜትር ካሬ ብር 15,000.00 /በአስራ አምስት ሺህ ብር/ እና ከዚህ
በላይ በሊዝ ጨረታ እየተላለፈ በመሆኑ መልሶ ማልማቱ ለማዘጋጃ ቤቱ እንደ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ሊሆን
የሚችልበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡

በእቅድ ደረጃ ሲታይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርም በከተማው ነባር አካባቢዎች ተንሰራፍቶ የሚገኘውን
የከተማ እርጅና ለመቅረፍ 924.5 ሄክታር ቦታ ማለትም ካጠቃላይ የከተማው የቆዳ ስፋት 32% ያህል ዕቅድ
ተይዞ ነበር፡፡ እስካሁን አስተዳደሩ ከወሰዳቸው እርምጃዎች መካከል አንዱ አካባቢዎቹ መልሰው
የሚለሙበትን አማራጭ በዝርዝር የሚያመለክት የአካባቢ ልማት ፕላን (LDP) ማዘጋጀት ነው፡፡ እስካሁን
በድሬዳዋ ከተማ ከተዘጋጁ 21 የአካባቢ ልማት ፕላን በከተማው መካከል የሚገኙት ነባር አካባቢዎች የተዘጋጁ
10 የአካባቢ ልማት ፕላኖች በአንድ ወይም በሌላ መንገድ መልሶ ማልማትን ያካተቱ ናቸው፡፡
ሰንጠረዥ 3.12፡ የአካባቢ ልማት ፕላን የተጠናላቸው አካባቢዎች
ተ/ቁ የአካባቢዎቹ መጠሪያ የሚሸፍኑት ክልል ስፋት (በሄክታር)
1 ከዚራ 65.7
2 መጋላ 61.5
3 ለጋሃሬ 80.4
4 ገንደ ቆሪ/ግሪክ ካምፕ 81.7
5 ታይዋን/ፖሊስ መሬት 103
6 ነምበር ዋን 120.4
7 ሳቢያን 155
8 ዲፖ ማርያም 51.2
9 ጎሮ 163.4
10 ጂቲዜድ - ገንደ ተስፋ 60.2
ድምር 942.5
ምንጭ፡ ከአካባቢ ልማት ፕላን (LDP) ሰነዶች ተወስዶ የተቀመረ

140
የእነዚህ አካባቢዎች የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅት እንደተጠናቀቀ ጥናቶቹ ባስቀመጡት አቅጣጫ የትግበራ
መርሃ - ግብር ተቀርጾ፣ በጀትና ፈፃሚ አካል ተመድቦ፣ በተሟላ ዝግጀት ወደ ትግበራ ይገባል ተብሎ ይጠበቅ
የነበረ ቢሆንም እስካሁን በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ የከተማ ማደስ ልማት ሥራዎች ውስን ናቸው፡፡

ከናሙና ከተሞቹ መረዳት የተቻለው የአብዛኞቹ ከተሞቸ የችግሩ ስፋት ቀላል አይደለም፡፡ በችግር ምክንያት
መልሶ ልማት የሚጠይቁ ብቻ ሳይሆን መሬት መስጠት ከሚገባው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ሲመዘንም መልሶ
ልማት የሚጠይቅ ዓቅም ከፍተኛ ነው፡፡ በመሆኑም ሁሉንም ከተሞች መልሶ ልማት የሚጠይቅ ቦታ
በመዋቅራዊ ዕቅዶቻቸው በማመላከት ችግር የለባቸውም፡፡

በጥቅል የተመላከቱ ዕቅዶች ወደ ተግባር ዕቅድ በመለወጥ ግን ሰፊ ልዩነት አለ፡፡ የደሴ ከተማ ሰፊ አፍርሶ
መገንባት ያካተተ ከ113 ሄክታር በላይ (2002-2007 የሚከናወን የአካባቢ የልማት ዕቅዶች)፣ ጅማ ከተማ
138.7 ሄክታር (2005 ዓ/ም የተዘጋጁ አካባቢ ልማት ፕላኖች)፣ ሐዋሳ ከተማ 2,349 ቤቶች የሚገኙበት 54
ሄክታር (2006 ዓ/ም የተዘጋጀው አልፕ)፣ ድሬዳዋ ከተማ በአብዛኛው መልሶ ልማት የሚጠይቅ 942.5
ሄክታር የአካባቢ የልማት ዕቅዶች ተዘጋጅተዋል፣ አዲስ አበባ 228 ሄክታር የተጠጋ መሬት (ካሳንችስ ቁጥር 1.
መገናኛ፤ ልደታ፤ በሻ ወልዴ ቁጥር1፣ መስቀል አደባባይ መግብያ፤ ወሎ ሰፈር፤ ሰንጋተራ) ከሞላ ጎደል መልሶ
የለማና በመልማት ሂደት ሲሆን ሌላ ሁለት መቶ አስራ ሁለት ሄክታር ገዳማ (ለሸራተን ማስፋፋያ ሙሉ
በሙሉ የጸደው 42 ሄክታ፤ በሻ ወልዴ ቁጥር2፤ አሜሪካ ግቢ ካሳንችስ ቁጥር2 እና 3 ወዘተ) ደግሞ ነባር
ግንባታ በአብዛኛው በጽዳት ይገኛል፡፡ ከዚህ ሌላ በ2008 ዓ/ም በዕቅድ የተያዘው ተጨማሪ 360 ሄ/ር ሲሆን
በአጠቃላይ የተሰራውና የታቀደው 760 ሄ/ር አካቷል፡፡

ከተሞቹ በመዋቅራዊ ፕላንና አካባቢ ልማት ፕላን የታቀዱት ዕቅድ ወደ ተጨባጭ የትግብራ ዕቅድ
እየለወጡት ግን አይደለም፡፡ የጅማ ከተማ ለ2008 በጀት ዐመት በክልሉ የተሰጠው 10 ሄክታር ግብ ከዓቅም
በላይ እንደሆነ እየተቃወመ ነው፤ የደሴ ከተማ ትርጉም ያለው የተግባር ዕቅድ ሳያዘጋጅ 5 ዓመታት
አስቆጥሯል፡፡ የድሬዳዋ ከተማ 2.35 ሄክተር ብቻ የተግባር ዕቅድ አዘጋጅቷል፡፡ መቐለ ከተማ አፍርሶ መገንባት
የሚጠይቁ ቦታዎች ለመለወጥ ወደ ተግባር አላሸጋገረም፡፡ እርጅና የሌለባቸው ነገር ግን መሬት ለከፍተኛ
ጠቀሜታ ለማዋል የሚያስችሉ ዕቅዶች የሐሳብ ዕቅዶች ብቻ ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ በነባሩ መዋቅራዊ ፕላን
መልሶ እንዲለማ ካስቀመጠው 2000 ሄክታር በ10 ዓመት ለመተግበር የተሞከረው 270 ሄክታር ሲሆን የአሁኑ
ፕላን ደግሞ 4000 ሄክታር ከታቀደው ሲመዘን ባለፉት ጊዚያት የተሰራው እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡

በድምር ሲታይ በሁሉም ከተሞች የመልሶ ልማት የተግባር ዕቅድ ለችግሩና ፍላጎቱ የማይመጥኑ እዚህ ግባ
የማይባሉ ናቸው፡፡ በመዋቅራዊ የልማት ዕቅድና የአካባቢ የልማት ፕላን የሚታቀዱ የተግባር ዕቅዶች
አይደሉም፡፡ ያለ ልዩነት በሁሉም ከተሞች መዋቅራዊ ፕላንና የአካባቢ የልማት ዕቅዶች ማዘጋጀት በቂ
እንደሆነና በከተማው እንዲካሄድ የሚፈለገው የመልሶ ልማት ዝርዝር ፕሮግራም ጥናት የማይካሄድ መሆኑ
እንዲሁም የማስፈፀሚያ መርሀ ግብር ያለማዘጋጀት ሌላኛው ችግር ነው፡፡ መልሶ ማልማት ከሚያሰፈልገው

141
መጠን አንጻር እየተሰራ ያለው ስራ በጣም ዝቅተኛ ነው/በተለይ አዲስ አበባ፤ ጅማና ደሴ/ጥቅምና ጉዳት
ሳይመዘን ግንባታ ስሌለለው ብቻ ወደ ውጭ መለጠጥ/፡፡ በክልልም ሆነ በከተሞች ደረጃ የመልሶ ማልማት
የት ተጀምሮ የትና መቸ እንደሚከናወን የሚመራ ፕሮግራም የለም፡፡

3.2.8. ፕሮጀክት ትግበራና ዕቅድ አፈፃፀም


በየከተማው የተዘጋጁ መዋቅራዊ ፕላኖች በጥልቀት ሲመረመሩ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ልማቶች በጥልቀት
ባያካትቱም ከተሞች ከሰፈሮች/ቤቶች እርጅና፣ የፕላን አደረጃጀት ችግር፣ የመሰረተ ልማት እና አገልግሎቶች
ተደራሽነት፣ የተጓደሉ እንደ ክፍት ቦታዎች እና አረንጓዴ ማስተንፈሻ ቦታዎች ችግር ለመመለስ የሚያስችሉ
ፕሮፖዛሎች ያስቀምጣሉ፡፡ የመካከለኛ ጊዜ የኣካባቢ የልማት ዕቅዶች ሲዘጋጁ መዋቅራዊ ፕላኑ ያስቀመጠውን
ችግር እንዳለ እውቅና የሚሰጡ ናቸው፡፡ ዋናው ክፍተት የሚፈጠረው ወደ ተግባር እቅድ ሲለወጥ መሆኑ
ከላይ ታይቷል፡፡ ከተሞቹ ላይ የሚታየው ችግር የተግባር ዕቅዱ የልማት ፍላጎቱ ስፋት የሚመጥን አለመሆኑ
ብቻ ሳይሆን ከዚህ በከፋ መልኩ የተዘጋጀውን የተግባር ዕቅድ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ያለማጠናቀቅ ችግር
መኖሩ ነው፡፡ እያንዳንዱ ከተማ ያለው ተጨባጭ ምስል ደግሞ ቀጥሎ በዝርዝር ቀርቧል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ላይ መልሶ ማልማት የተጀመረው በ1980ዎቹ ነበር፡፡ በወቅቱ የተለያዩ የአካባቢ መሻሻል
ስራዎች በተለያዩ አካላት ድጋፍ ሰፊ ስራ ተሰርቷል፡፡ ባለሀብቱ በስፋት የሚሳተፍበት አፍርሶ እንደ አዲስ
መገንባት እንደ ስትራተጂ ተግባር ላይ መዋል የተጀመረው ግን በዋናነት ከ1990ዎቹ መጀመሪያ ነው፡፡ በተለይ
የሊዝ አዋጅ 272/1994 አልሚ ባለሀብቶች መሬት በድርድር የሚያገኙበት አሰራር መፍቀዱን ተከትሎ የከተማ
አስተዳደሩ በመመሪያዎች አስደግፎ ባለሀብቶች የመረጡት ቦታ እንዲያለሙ የመሬት አጠቃቀሙ የሚፈቅድ
መሆኑ ሲረጋገጥ ከጨረታ ውጭ በድርድር ይሰጣቸው ነበር፡፡

ከ1990-1994 በነበረው የአምስት ዓመት ጊዜ ብቻ ይህን ጥሪ ተከትሎ 306 ሄክታር ስፋት ያለው መሬት
ለማልማት 822 ፕሮጀክቶች ቀርበው እንደ ነበር ጥናቶች ያመለክታሉ (አያሌው፣ አ.ኤ.አ. 2001)፡፡ ከእነዚህ
ፕሮጀክቶች መካከልም 415 የሚሆኑት በከተማ አስተዳደሩ ተቀባይነት ያገኙ ሲሆን ትግበራቸው በተለያየ
ምክንያት ቢጓተትም ወደ ትግበራ የተሸጋገሩ ፕሮጀክቶች ቁጥርም ቀላል አልነበረም፡፡ በባለሃብቱ ተነሳሽነት
ሰፊ የመልሶ ልማት ከተካሄደባቸው አካባቢዎች መካከል መርካቶና ኮልፌ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው፤
በመርካቶ ብቻ ከ80 የማያንሱ ፕሮጀክቶች ለከተማ አስተዳደሩ ቀርበው ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ በመሃል አዲስ
አበባ ከሚካሄዱ ግንባታዎች አብዛኞቹ በዚህ ጊዜ ለባለሃብቱ የተፈቀዱ ቦታዎች ናቸው፡፡

በዚህ አካሄድ የነበረው ፈተና ባለሃብቱ የሊዝ ክፍያ ከከፈለና ካርታ ከወሰደ በኋላ ቦታውን ከግንባታ ነፃ
አድርጎ ለፕሮጀክቱ አገልግሎት እንዲውል በማድረግ በኩል ነበር፡፡ በቦታው ላይ የግል ይዞታ ካላቸው
ተነሽዎች መካከል የተወሰኑት ቤታችን አይፈርስም የሚል የፍ/ቤት እግድ ስለሚያቀርቡ እንዲሁም ሌሎች
የሚያከናውኑትን የግንባታ ፕሮጀክት በቦታው ላይ ለማከናወን ቅድሚያ ሊሰጠን ይገባል የሚል ተቃውሞ

142
ስለሚያቀርቡ የፕሮጀክት ትግበራ የሚጓተትበት አጋጣሚ በርካታ ነበር፡፡ የግለሰብ ተቃውሞ በሌለበት
አካባቢም ደግሞ ነባር ተጠቃሚዎችን ፈጥኖ በማንሳቱ በኩል አስተዳደሩ በነበረበት ችግር ሳቢያ የግል
ባለሃብቶች ተስፋ ቆርጠው ፕሮጀክታቸውን የሚያቋርጡበት አጋጣሚ ሰፊ ነበር፡፡

በአጠቃላይ በ1980ዎቹ መጨረሻ እና በ1990ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የግል ባለሃብቱ በመልሶ ማልማት ፕሮጀክት
ለመሳተፍ ያሳየው ከፍተኛ ተነሳሽነት ቦታን ከነባር ተጠቃሚ ነፃ አድርጎ በማስረከቡ ረገድ በነበረ ችግር እንደ
ጅምሩ መቀጠል አልቻለም፡፡ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ዳር ለማድረስ በነበረው ውጣ ውረድም በከተማ
አስተዳደሩና በባለሃብቶች መካከል የነበረው ግንኙነት በውጥረት የተሞላ ነበር፡፡

በጊዜው የነበረ እሳቤ የማስነሳት ችግር የሚያጋጥመው በቦታው ላሉ የማልማት ዕድል ከተሰጣቸው የማስነሳት
ሂደቱ የመዘግየት ዕድሉ ጠባብ ይሆናል የሚል ነበር፡፡ በአንፃሩ ቦታው እንዲያለማ የሚፈቀድለት እዛው
ያልነበረ ከሆነ በቦታው የነበሩ ተቃውሞ ስለሚያስነሱ ያለመግባባቱ ለመፍታት የጊዜ መጓተት እንደሚያጋጥም
ነበር የታሰበው፡፡ ከዚህ በመነሳት ባለሀብቶች ያሉበትን ቦታ እንዲያለሙ ለመወሰን የተሄደበት መነሻ፤
 አሁን እየሰሩበት ላለው ቦታ ተፈላጊነት ማደግ በቦታው እየሰሩ ያሉ አካላት ድርሻ ስላላቸው በልማቱ
ተጠቃሚ እንዲሆኑ፤
 በቦታው እየሰሩ ያሉ አካላት አቅሙ ስላላቸው በቦታው ያፈሩትን እሴት ቦታው ለማልማት
እንዲያዉሉት፤
 በመፈናቀል ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እንዳይሰፋ፤
 ቦታ አጽድቶ የማልማት ስልትን ለመተግበር ተነሳ/አትነሳ ስለሚኖር ልማት ይጓተታል በአንጻሩ ግን
በቦታው ያለ አልማ ሲባል ልማቱ እንዲፈጥን ይሆናል፤ የሚሉ ነበሩ፡፡
ከዚህ ሌላ ለልማቱ ፍጥነት ማነቆ ሊሆን የሚችለው ቦታው ለማልማት ፈርሶ እስኪገነባ ድረስ የስራና ገቢ
መቋረጥ ስለሆነ ለዚህ ሂደት መቃናት አጋዥ እንዲሆንና በልማት ወቅት የንግድ ስራቸው እንዳይገታ ጊዚያዊ
መነገጃ ቦታ አሰጣጥ አብሮ የተካተተ አካሄድ ነበር፡፡ በአጠቃላይ በባለሃብቶች ተነሳሽነት ይካሄድ ከነበረው
የመልሶ ማልማት እንቅስቃሴ ደካማና ጠንካራ ጎኖች መካከል የሚከተሉት በቀዳሚነት መጥቀስ ይቻላል፡፡

ይህ አካሄድ መከተል በተቀመጠው መነሻ የተጓዙ የተወሰኑ አልሚዎችን ጠቅሟል፡፡ የልማቱ ፍጥነት ከጊዜ
አንፃር የተጓተተ ቢሆንም አካባቢዎቹ እንዲለወጡ አስችሏል (ቂርቆስ፣ ኮልፌ፣ መርካቶ)፡፡ እነዚህ አወንታዊ
ውጤቶች እንዳሉ ሆነው ሂደቱ በርካታ እክሎችን አጋጥመውታል፡፡ ከታዩ ደካማ ጎኖች ዋና ዋናዎቹ
የሚከተሉት ነበሩ፤

 የልማቱ ፍጥነት እንደታሰበው አልነበረም፡፡ ፍጥነቱ አስነስቶ ከማልማት የበለጠ አድካሚና የዘገየ
እንደሆነ ታይቷል፡፡ በተለይ በመርካቶ መጀመርያ በህንጻ ከፍታ ሰበብ፤ ከዚያ በባለሀብቱ ዘንድ አብሮ

143
የመስራት ባህልና መተማመን ችግር፤ በጥቅም ግጭት (አንካተት/አትካተትም ንትርክ) እስካሁን ከ10
ዓመት በላይ ሳይለሙ የቆሙ ቦታዎች አሉ፡፡
 ሂደቱም ግልጽነትን እየጎዳ አስተዳዳሩም ከቦታው ሊያገኝ የሚገባውን ጥቅም እያጣ እንዲሄድ
አድርጓል፡፡ ቦታው በድርድር ሲሰጥ የሚገኘው ዋጋ በጨረታ ቢሰጥ ሊገኝ ከሚችለው ያነሰ ነው፡፡
 እኔ ቀዳሚ ነኝ፤ እኔም መብት አለኝ በሚል የሚነሳ ክርክርን በመዳኘት ሰበብ አላስፈላጊ ጊዜና
መሳሳብ ተከስቷል፡፡
 በገንቢዎች የግንዛቤ ችግር እንዲሁም አስተዳደሩ በነበረው ፕላን የማስጠበቅ አቅምና ቁርጠኝነት
ድክመት የተነሳ ፕላኑ በተሟላ መልኩ አልተተገበረም /ለምሳሌ በመርካቶ መልሶ ማልማት ሂደት
ፕላኑ ባስቀመጠው አቅጣጫ ታሪካዊ ይዘቷን ማስጠበቅ አልተቻለም፡፡

አዋጅ ቁጥር 721/2004 ተከትሎ ቦታ በድርድር የሚሠጥበት አሠራር ሲቆም ለመልሶ ልማት የሚውሉ
አካባቢዎችን ከነባር ግንባታና ተጠቃሚ ነፃ አድርጎ ለአዲስ ግንባታ ዝግጁ የማድረግ ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ
በከተማ አስተዳደሩ ጫንቃ ላይ ሲወድቅ፡ የመልሶ ማልማት ይዘትና ጥልቀትም ይበልጥ ፈታኝ እየሆነ
መጥቷል፡፡ መሬት በድርድር መስጠት የከተማ አስተዳደሩ ከመሬት ማግኘት የነበረበት ገቢ እንዳያገኝ
ከማድረጉ በላይ የልማቱ ሂደት ፍጥነት ለጥያቄ የሚዳርግ ስለሆነ የመሬት አሰጣጥ ሂደቱ ወደ ጨረታ ስርዓቱ
እንዲገባ ተደርጓል፡፡ በድምር ሲታይ ግን ቅድመ አዋጅ 721/2004 ወደ መልሶ ልማት የገቡት ቦታዎችም ሆነ
አዋጁ ከመደንገጉ በኃላ ወደ ትግበራ የገቡ ቦታዎች የፕሮጀክት አፈፃፀም ምስላቸው ሲታይ ፍጥነት
የላቸውም፡፡

144
ሰንጠረዥ 3.13፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ በመልሶ ማልማት
ላይ የተሰሩ ስራዎችን የሚያሳይ መረጃ
ምትክ ቤት የወሰዱ ምትክ ያለበት ደረጃ
ከፍለ የቦታው የተጀመረበት የልማት የተከፈለ ካሳ
የፕሮጀክቱ ስም ቦታ
ከተማ ስፋት ዓ.ም ተነሺ ብዛት መጠን
ኮንዶ ቀበሌ ቤት የወሰዱ

ሰንጋ ተራ (ፍርድ ቤት) 26 2001 1442 949 160 261 119,768,578 የተጠናቀቀ
ልደታ ሰንጋ ተራ ቁጥር 2 17 2003 619 427 59 55 35,105,097 የተጠናቀቀ
ሸበሌ ጀርባ 10.4 2006 428 175 36 24 11,989,660 የተጠናቀቀ
ተክለሃይማኖት 33 2007 2733 1190 219 132 102,615,857 በመፍረስ ላይ
ሸራተን ማስፋፊያ 25 2002 1944 934 421 179,383,770 የተጠናቀቀ
ኢሰ.ኤ ማስፋፊያ 2 2002 321 140 245 11,195,308 የተጠናቀቀ
አፍሪካ ህብረት ቁጥር 1 23 2002 145 49 22,999,839 የተጠናቀቀ
ቂርቆስ አፍረካ ህብረት ቁጥር 2. 12 2003 639 352 70 40,626,531 ብዙውየተጠናቀቀ
ወሎ ሰፈር 9.8 2001 537 133 9 168 42,462,879 የተጠናቀቀ
መስቀል መግቢያ 3.2 2001 223 162 16 75 12,900,000 ???
ካዛንቺስ ቁጥር 2 26 2005 687 241 1 43,335,437 ???
ካዛንቺስ ቁጥር 3 23 2006 2793 1337 111 280 21,075,237 ???
ፈለገ-ዮርዳኖስ 17.1 2007 909 1,935,177 ???
ባሻ ወልዴ ቁጥር 1 27 2002 1640 962 194 204 37,933,158 የተጠናቀቀ
ባሻ ወልዴ ቁጥር 2 14 2002 1319 853 2 62 42,514,47116 ብዙውየተጠናቀ
አሮጌ ቄራ ቁጥር 1 9 2004 1874 326 77 20,678,822 ???
አሮጌ ቄራ ቁጥር 2 45 2006 1246 789 110 168 49758375 ???
ሸራተን ማስፋፊያ 17 2002 1342 873 318 286 39,814,114 የተጠናቀቀ
ፓርላማ ማስፋፊያ 4 2002 319 191 69 48 3.591.052 ???
አራዳ ደጃች ውቤ 11.6 2007 762 373 149 11,084,116 ???
ሰንጋ ተራ(ፍርድ ቤት) 26 2001 1442 949 160 261 119,768,579 የተጠናቀቀ
አሜሪካ ግቢ ቁ.2 6.7 2007 218 ??? ??? ??? 27,842 ???
ገዳም ሰፈር 13.9 2007 1012 ??? ??? ??? 31,633,116 ???
አዲስ ከተማ አሜሪካ ግቢ ቁጥር 1 16 2007 1949 1542 ??? 204 55,180,776 ???
ድምር 391.7 25,101 11998 1523 2710 934,018,161 ???

ምንጭ፡ ከአዲስ አበባ መሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ የተገኘ፣ 2008 ዓ/ም
እላይ ባለው ሠንጠረዥ ማየት እንደሚቻለው ባለፉት ስምንት ዓመታት በአራት ክፍለ ከተሞች (ልደታ፣
ቂርቆስ፣ አራዳና አዲስ ከተማ) ለሚገኙ 24 አካባቢዎች የከተማ ማደስ ፕሮጀክት ተቀርጾ ወደ ተግባር የተገባ
ሲሆን በአሁኑ ጊዜም ፕሮጀክቶቹ በተለያየ የትግበራ ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከ2001-2007 በጀት ዓመታት
እንዲለማ ከታቀደው ጠቅላላ 391.7 ሄክታር መሬት ውስጥ 209.2 ሄክታር (53.4%) ሙሉ በሙሉ
ልማታቸው የተጠናቀቁና ወደ መጠናቀቅ የቀረቡ ሲሆኑ 33 ሄክታሩ (8.4%) ደግሞ ገና ግንባታዎቹ በመፍረስ
ላይ ይገኛሉ፡፡ የተቀረው 149.5 ሄክታር (38.2%) ያህሉ የአፈፃፀም ደረጃቸው በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ
የሚያሳይ መረጃ አልተገኘም፡፡

ከዛሬ ስምንት ዓመት በፊት የተጀመሩ የመልሶ ልማት ፕሮጀክቶች እስካሁን ድረስ መጠናቀቅ አልቻሉም፡፡
በመሬት ልማትና ከተማ ማደስ እምነት ተጠናቀዋል ተብለው በተጠቀሱት ፕሮጀክቶችም ቢሆን እስካሁን
የተጠናቀቁት ሥራዎች ግንባታ ማፍረስ፣ ነባር ባለይዞታዎችን/ተከራዮችን ከቦታው ማንሳትና የካሳ ክፍያ

145
መክፈል ብቻ ናቸው፡፡ የከተማ ማደስ ተግባር ደግሞ በእነዚህ ሥራዎች ብቻ የሚወሰን አይደለም፤
የተለቀቀው ቦታ ለአዲስ ግንባታ እስኪውል ድረስ ፕሮጀክቱ ተጠናቀቀ ብሎ መውሰድ አይቻልም፡፡ እስካሁን
የታሰበው ልማት ከሞላ ጎደል ተጠናቋል ተብሎ ሊወሰድ የሚችለው የልደታ መልሶ ልማት ፕሮጀክት ነው፡፡

ባለፉት 8 ዓመታት ወደ ትግበራ ከገቡ የመልሶ ልማት ፕሮጀክቶች መካከል ግንባታ በአግባቡ ፀድቶ ቦታው
ለአዲስ ግንባታ ዝግጁ የሆነው የሸራተን ማስፋፊያ ፕሮጀክት ብቻ ሲሆን ቀሪዎቹ ፕሮጀክቶች በአብዛኞቹ
ቦታው ገና ከነባር ግንባታ ሙሉ በሙሉ አልፀዳም፡፡ የሸበሌ ጀርባ ከተማ ማደስ ፕሮጀክት እላይ
ተጠናቅቀዋል ተብለው ከተጠቀሱት ፕሮጀክቶች አንዱ ነው፤ ነገር ግን ቀጥሎ የቀረበው ፎቶ የሚያሣየው
ቦታውን የማፅዳት ሥራ ገና እንዳልተጠናቀቀ ነው፡፡

ስእል 3.26: የሸራተን ማስፋፊያ መልሶ ልማት ፕሮጀክት

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ


ስእል 3.27: ከዋቢ ሸበሌ ጀርባ ግንባታቸው በከፊል የፈረሱ አካባቢዎች

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ


እላይ ከቀረበው ፎቶ ማየት እንደሚቻለው ሙሉ በሙሉ ያልፈረሱ ቤቶች በቦታው የሚገኙ ሲሆን ቦታው ላይ
ሕገ ወጥ ሠፈራ የሚጋብዙ የተዝረከረኩ ግንባታዎች ይገኛሉ፡፡ ቦታውን ተዘዋውረን እንዳየነውም በከፊል
የፈረሱ ግንባታዎችን በመጠለያነት የሚገለገሉ ነዋሪዎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ከዛሬ ስድስት ዓመት በፊት
የተጀመረው ባሻ ወልዴ ችሎት የመልሶ ልማት ፕሮጀክት አሁን የሚገኝበትን ደረጃ ስንመለከት ከሸበሌ ጀርባ
ፕሮጀክት የተለየ አይደለም፡፡

146
ስእል 3.28: የባሻ ወልዴ መልሶ ልማት ፕሮጀክት
ግንባታ በከፊል የተነሳበት አካባቢ ግንባታ በሙሉ ተነስቶ በከፊል ለልማት የዋለ አካባቢ

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ


ስእል 3.29፡ የካዛንችስ መልሶ ልማት

ቁጥር 2 ፕሮጀክት ቁጥር 3 ፕሮጀክት


ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ
ገና በሂደት ላይ ባሉ የመልሶ ልማት ፕሮጀክቶች ያለው ግንባታ የማፍረስ አያያዝ ሲታይ ቦታውን አፅድቶ
ቦታውን ለአዲስ ግንባታ ዝግጁ ማድረግ አይመስልም፡፡
ስእል 3.30: በአሜሪካን ግቢ የከተማ ማደስ ፕሮጀክት ግንባታ የፈረሰበት አካባቢ

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ

147
አካባቢው ሙሉ በሙሉ ፀድተው ወደ ልማት ባልገቡ ቦታዎች ላይ ሕገ-ወጥ መጠለያዎች ቦታውን
ወረውታል፡፡ በዚህ ሁኔታ ለዓመታት ወደ ግንባታ ያልገቡ በርካታ ቦታዎች በሰንጋ ተራ፣ ካዛንችስና ባሻ ወልዴ
ከተማ ማደስ ፕሮጀክት (Sites) በስፋት ይታያል፡፡

ይህ አካሄድ ለምን እንደማይቀረፍ ግንባታዎቹ ልክ እንደ ሸራተን መስፋፊያ ጽድት ብለው እንደማይነሱ
ለቀረበው ጥያቄ የአስፈፃሚ አካላት ምላሽ ቤታችን አይፈርስብንም የሚል ተቋውሞ የሚያነሱ ባለይዞታዎች
የሚያመጡትን የፍ/ቤት ዕግድ እና ቦታው የተላለፈላቸው አልሚዎች ፈጥነው ወደ ግንባታ አለመግባታቸውን
እንደ ዋና ምክንያት ይጠቅሳሉ፡፡ ነገር ግን ብዙ አካባቢዎች እንደሚስተዋለው ግንባታው ሙሉ በሙሉ
ባልተነሣበትና በህገ ወጥ ግንባታ በተወረረበት ሁኔታ የወሰን ድንጋይ ተተክሎ ቦታው ለአልሚዎች ተላልፏል
ብሎ ለማመን ያስቸግራል፡፡ ከዚህ አኳያ በደንብ ሊስተዋልበት የሚገባው ቢኖር አንነሳም ሲሉ አንድ እነዚህ
ሰዎች ከመጀመሪያውኑ ለልማቱ እንደ አጋር አካል ያለመወሰዳቸው ነው፡፡ ማንሳት ሲፈለግ ብቻ ተነሱ ሲባሉ
የማይቃወሙበት ምክንያት አይኖርም፡፡ በልማት ምክንያት ከቦታቸው ለሚንሱ ሰዎች ልማቱ ገና ሲታሰብ
ተሳታፊነታቸው መረጋገጥ እንዳለበት ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ይህ ሲሆን የባለቤትነት ሰሜት ይሰማቸዋል
በሚካሄደው ውይይትም ሆነ ዉሳኔ እስካመኑበት ድረስ ልማቱ በትክክል ለታለመለት ነገር ይውላል፡፡

ወደ ትግበራ የተሸጋገሩት የከተማ ማደስ ፕሮጀክቶች ምን ያህል የአካባቢውን ልማት ፕላን ጠብቀው
ተግባራዊ ይሆናሉ የሚለው ጥያቄ ሌላው የሚያነጋግር ጉዳይ ነው፤ እስካሁን በተሟላ ደረጃ ከተተገበሩ
የከተማ ማደስ ፕሮጀክቶች በቦታ ስፋትም ሆነ በልማት ደረጃ ካዛንቺስ አንድና ልደታ ከተማ ማደስ በግንባር
ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ልደታ መልሶ ልማት ፕሮጀክት በከተማ አስተዳደሩ በሞዴልነት ተወስዶ የቅርብ
ክትትል የተደረገበት በመሆኑ የአካባቢ ልማት ፕላኑን ጠብቆ የተተገበረ ፕሮጀክት ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡

በካዛንቺስ ቁጥር አንድ መልሶ ልማት ፕሮጀክት ፕላን ጠብቆ በመፈፀም በኩል ሰፊ ክፍተት ይታያል፤ ለዚህ
የከተማ አመራሩም፣ ባለሙያውም፣ አልሚዎችም የየበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዳደረጉ ሂደቱን በቅርበት
የተከታተሉ ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡

ስእል 3.31: የካዛንቺስ ቁጥር 1 መልሶ ልማት ፕሮጀክት

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ

148
በመጀመርያ ደረጃ ካሳንችስ የሆቴሎች ግንባታ በጣም ብዙ ነው፡፡ ነገር ግን በምልከታ እንደተስተዋለው እና
በስእሉ እንደሚታየው ቦታው ከፍታ ባላቸው ህንፃዎች የታጠረ ነው፡ መንገዶቹ በጣም ጠባብና ለትራፊክ
መጨናነቅ ዋነኛ ምክንያት ናቸው፡፡ ሌላ ደግሞ የመኪና ማረፍያ እጥረት አለ፡፡ ለአረንጓዴ ቦታ የተባለው
እስከ አሁን አለመሰራቱ፡፡ ይህ ሁሉ ተደምሮ የዚህ ቦታ ልማት ዘላቂነት በጥያቄ ውስጥ ነው፡፡

እላይ እንደተገለፀው ባለፉት ስምንት ዓመታት ተግባራዊ በሆኑ 24 የከተማ ማደስ ፕሮጀክቶች ሳቢያ
ከመኖሪያና ሥራ ቦታቸው የተፈናቀሉ አባውራዎች ብዛት ከ25 ሺ በላይ ነው፤ ከእነዚህ የልማት ተነሽዎች
መካከል 11,998 ለሚሆኑት የኮንዶሚኒየም ቤት፣ 1,523 ለሚሆኑት ደግሞ ምትክ የቀበሌ ቤት የተሰጠ ሲሆን
ምትክ ቦታ የተመደበላቸው ተነሺዎች ቁጥር ደግሞ 2,710 ነው፡፡ ከዚህ አሃዛዊ መረጃ መገንዘብ የሚቻለው
የከተማ አስተዳደሩ የተቀናጀ ቤቶች ልማት ፕሮግራም ለከተማ ማደስ ልማት ቀጣይነት ምን ያህል ጠንካራ
መሠረት የጣለ መሆኑን ነው፡፡

ሙሉ በሙሉ ጠርጎ ማልማት ስልት የሚከተል የአዲስ አበባ መልሶ ማልማት ያቀደበት ያህል እንዳልተጓዘ
በቀላሉ ከተዘጋጁ የአካባቢ ልማት ዕቅዶች እና የተግባር አፈፃፀም በማነፃፀር በቂ ዕይታ ማግኘት ይቻላል፡፡
ልማቱ በርካታ ምክንያታዊ ተግዳሮቾችና የአፈጸፀም ዓቅም ውስንነት ችግሮች እንዳይፈጥን አድርገውታል፡፡

በመሃል አዲስ አበባ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የመንገድ መሠረተ ልማት ማሻሻያ እና በተናጠል ቦታዎች
(Single Plots) ላይ የሚካሄዱ ግንባታዎች የከተማ አስተዳደሩ የከተማ መልሶ ልማት እንቅስቃሴ አካል
በመሆናቸው በአፈፃፀም የሚስተዋሉ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን መዳሰስ ጠቃሚ ነው፡፡

ነባሩ የአዲስ አበባ ክፍል በቂ የመንገድ አውታር ባልተዘረጋበት ሁኔታ የተገነባ እንደመሆኑ መጠን መሃል
ከተማው የሚጠይቀው ተጨማሪ የመንገድ መሰረተ ልማት የመስፋፊያ አካባቢዎች ከሚጠይቁት የሚተናነስ
አይደለም፡፡ ከዚህ መሠረታዊ እውነታ በመነሣት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ባለፉት አስር ዓመታት
በመሃል ከተማው ገጽታ መሠረታዊ ለውጥ ያመጡ በርካታ መንገዶችንና አደባባዮችን ገንብቷል፡፡ በመሃል
አዲስ አበባ የሚካሄዱ የመንገድ ፕሮጀክቶች መነሻ፡-
 በመሃል ከተማው የሚታየው የትራፊክ መጨናነቅ፣
 በነባር ከተማው የሚታየው መዳረሻና የአማራጭ መንገድ እጥረት፣
 የህዝብ ጥያቄና ውትወታ እንደሆኑ፣ ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በከተማው ማስተር ፕላን የተለዩ የመንገድ አቅርቦት ክፍተቶች (missing links) ለመሙላት የባለሥልጣን
መ/ቤቱ ቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ የሚሠራ ሲሆን የመንገድ ፕሮጀክቶችን በራስ ኃይልና በሥራ ተቋራጭ
ተሳትፎ ትግበራዊ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በለማው የከተማው ክልል የሚካሄድ የመንገድ ግንባታ በማስፋፊያ አካባቢዎች እንደሚካሄደው ቀላል
አይደለም፤ ከወሰን ማስከበር ጀምሮ መንገዱ በሚያልፍበት ክልል የተዘረጉ የመሠረተ ልማት ነባር መስመሮችን

149
ማንሳት ፈታኝ ሥራዎች እንደሆኑ የባለሥልጣን መ/ቤቱ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡ ባለሥልጣን
መ/ቤቱ ነባር ግንባታዎችን ለማስነሣት ከመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ፣ የመሠረተ ልማት
መስመሮችን ለማስነሣት ከመሠረተ ልማት ተቋማት ጋር፣ ነዋሪዎችን ከቦታው ለማስነሣት ከክ/ከተሞች ጋር
አብሮ መሥራት ይጠበቅበታል፡፡

በመሆኑም የመንገድ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ስኬትና ስልጠት የሚወሰነው በባለሥልጣን መ/ቤቱ ጥረት ብቻ
ሳይሆን እላይ በተጠቀሱት ተቋማት እርብርብ ጭምር ነው፡፡ በሥራው ሂደት ላይ ባለሥልጣን መ/ቤት
ከሚያጋጥሙት ችግሮች መካከል የሚከተሉት በቀዳሚነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
 በወሰን ማስከበር ስራዎች ላይ በክ/ከተሞች በኩል የተሟላና አጥጋቢ ምላሽ ያለማግኘት ሁኔታ ስራን
የሚያንጓትት መሆኑ፣
 ከመሰረተ ልማት ዘርጊ ተቋማት ጋር በጋራ በሚሰራ የወሰን ማስከበር ስራ የኤሌክትሪክ፣ የቴሌፎን
እና የውሃ መስመሮች በተፈለገው ጊዜ አለመነሣት፣
 ባለድርሻ አካላት የወሰን ማስከበር ስራን እንደ ተጨማሪ እንጂ እንደ ዋና ስራ አቅደው የማይፈፅሙ
መሆናቸው፣
 የሚነሳው ቤት ወይም አጥር የመንግስት ተቋም ንብረት ከሆነ ለማስነሳት ከግለሰብ በበለጠ ከፍተኛ
ትግል የሚጠይቅ መሆኑ፣

ሀ/ ተግዳሮቶች
1) ኮንዶሚኒየም ቤት አቅርቦት
የኮንዶሚኒየም ቤት አቅርቦት ባልነበረበት ቀደም ባለው ጊዜ ከነባር አካባቢ ነዋሪዎችን በልማት ማንሳት ፈተና
የነበረው ለተነሺዎቹ መልሶ ማስፈሪያ በቂ ቤት ማግኘት ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ የነባር ከተማ መልሶ ልማት
ያዝ ለቀቅ ይደረግ የነበረ የልማት አጀንዳ ከመሆኑም በላይ ፕሮጀክቶች ለረዥም ጊዜ ሲጓተቱ ማየት በስፋት
ይታይ ነበር፡፡ ለከተማ ማደሱ ስራ ፍጥነት መጓደል በዋና ምክንያትነት የሚቀርበው ከምትክ ቤት ምደባ ጋር
የተያያዘ ሲሆን ለማሳያ ያክል በኤጀንሲው በ2003 መጨረሻ በቀረበ ሪፖርት እንደተጠቀሰው ከ2002 ጀምሮ
በመልሶ ማልማት ከታቀፉት የሸራተን ማስፋፍያ፤ ባሻ ወልዴ ችሎት ቁጥር 1 እና ሌሎችም ምትክ
የኮንዶሚኒየም ቤት ከመረጡ 2,997 ቤቶች 1,093 ያህሉን ማፍረስ ያልተቻለበት ምክንያቶች ብለው
ያቀረቡዋቸው፣
 በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ጽ/ቤት በኩል የካራአሎ የሳይት ስራ አለመጠናቀቁ፤ ገላን 6 ብሎክ
ግንባታው ባለመጠናቀቁ፡ የካ ክፍለ ከተማ የቁልፍና የመስታወት እጥረት ለመፍታት ያስቀመጠው
አቅጣጫ መናበብ ችግር ፣
 በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ በኩል የካ-አያትና ካራአሎ ሳይት ውሃ ባለማስገባቱ ፣

150
 በኢትዮጵያ መብራት ሃይል ባለስልጣን በኩል፡ ቦሌ-አያት የኤሌክትሪክ ምሰሶ ከመጣል ያለፈ ስራ
አለመከናወኑ፡ መስመር ዝርጋታ ቢከናወንም በገላን በካራአሎ፤ የካ-አያት ከቤቶቹ የማገናኘት ስራ
አለመከናወኑ፤ ጀሞ ብዙ ስራ ቢሰራም ተቆራርጠው የተዘለሉ ብሎኮች መኖር፣
 ምትክ የቀበሌ ቤት ከመረጡ 958 ቤቶች መካከል ለ452 ያህሉ ምትክ ቤት አለመስጠቱ፣
 ካሳ ለሚገባቸው ተነሺዎች የሚገባቸውን ካሳ መወሰን ላይ መጓተት መኖሩ፣
 ማፍረሱን መግፋት ላይ እንዲሁ ሰፊ ክፍተት መታየቱ፣
 በማእከል ያለው የአደረጃጀትና የአቅም ውሱንነት፣
 የመመርያዉ ክፍተት ለማሻሻል የቀረበው ሰነድ ቶሎ ሳይወሰን መዘግየቱ፣
 የልማት ተነሺዎች በፍላጎታቸው የሚፈልጉት የቤት ዓይነት አለማግኘት ለምሳሌ ባለ ሶስት መኝታ
ተጠይቆ ባለ አንድ እንዲወስዱ ማስገደድ፣
 ለልማት ተነሺዎች ብቻ ተብሎ ኮንዶሚኒየም ቤት በእቅድ አለመገንባት፣
 አቅም ለሌላቸው የቀበሌ ቤት ተከራይ ኮንዶሚኒየም መክፈል የማይችሉ የልማት ተነሺ ሲያጋጥም
በአማራጭ ዝቅተኛ ክፍያ ያላቸው የቁጠባ ቤቶች ገንብቶ ለልማት ተነሺው አለመስጠት የሚሉ
ናቸው፡፡

ይህ ችግር በመሰል ሁኔታ አሁንም እንደቀጠለ ታይቷል፡፡ ለዚህም ማሳያ ከ2004 ጀምሮ በፕሮጀክት የተያዙ
መልሶ ማልማት ቦታዎች በከፊል የፈረሱ ሲሆን አሁንም በሙሉ አልጸዳም፤ በአንዱም ሳይት ላይ ግንባታ
አልተጀመረም፡፡

ባጠቃላይ የቀበሌ የመንግስት ቤት ተከራይ የሆኑ እንዲሁም የግል የልማት ተነሺ ምትክ ኮንደሚኒየም
ከመረጡ በመመሪያ ቁጥር 19/2006 በሚፈቅድላቸው መሰረት ምትክ ኮንደሚኒየም በወቅቱ መስጠትና
ማስነሳት ሲገባ የሚፈለገው ቤት አለማግኘት መልሰው እንዲለሙ የሚፈለጉ ቦታዎች በጊዜው ማፅዳት
አልተቻለም፡፡ ቤቶቹ ተገንብተው ሲያበቁም መሰረተ ልማት ግንባታው ከቤቶቹ ግንባታ ጎን ለጎን እኩል
ስለማይጠቃለል ተጠቃሚዎቹ ለማንሳት ዕንቅፋት እየሆነ ይገኛል፡፡ በተለይም ውሃ በወቅቱ አለመግባት
ለአብነት ቦሌ ቡልቡላ ከ1600 በላይ የልማት ተነሺዎች መነሳት ከነበረባቸው ወቅት በወራት ዘግይተው የነበረ
መሆኑ፡፡ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ መጓተት በኮንደሚንየም ሳይቶች ብቻ ሳይሆን ለልማት ተነሺዎች የሚሰጥ
ምትክ መሬት ላይም ተመሳሳይ ችግር እየፈጠረ ነው፡፡

አጠቃላይ የቤት ግብይቱ በድለላ ሰንሰለት የተያዘ ያህል የኮንደሚንየም ቤት አቅርቦቱ ላይም የልማት
ተነሺዎች ከመክፈል ዓቅማቸው በላይ የቤት ዓይነት እንዲጠይቁ በማድረግ በፍላጎት በኩል (Demand Side)
ከፍተኛ አሉታዊ ጫና እንዲፈጠር እያደረገ ነው፡፡ አብዛኛውን በኪራይ ቤት የሚኖር ደግሞ መደበኛ ባልሆነ
የኢኮኖሚ ዘርፍ የሚተዳደር እና ዝቅተኛ ገቢ ያለው መሆኑ የሚታመን ሲሆን የኮንደሚንየም ቤት ፍላጎቱ

151
ሲያስመዘግብ ግን ሊከፍለው ከሚችል ዓቅም በላይ የሆኑ ዓይነት ቤቶች ይመርጣል፡፡ ይህም የደላላው
መስመር እነኝህ የልማት ተነሺዎች ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ቤቶች እንዲመዘገቡ በማድረግ በአንድ በኩል ቤቶቹ
ዕጣ ሲወጡ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደር ዜጋ ቅድሚያ ክፊያቸውም ሆነ በየወሩ የሚከፈለውን መክፈል
ስለማይችል ከዜጎቹ ከሕጋዊ ግብይቱ ውጭ በሆነ ግብይት በመግዛት መንግስት በከፍተኛ ድጎማ የሚገነባቸው
ቤቶች የመንግስት ድጎማውና በሚሸጡበት ጊዜ የሚያስገኝላቸው ከፍተኛ ትርፍን ጨምረው ከበርቴ
የሚሆኑበት ሁኔታ ተፈጥረዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ያለ ዓቅሙ የተመዘገበ ባይሸጠውም ክፊያውን መክፈል
ስለማይችል በነበረበት ቦታ ይቅርና መልሶ ልማቱ እንዲስተጓጎል እያደረገው መሆኑ ከተለያዩ የስራ ሓላፊዎች
እና ባለሙያዎች በተደረጉ ውይይቶች ለመረዳት ተችሏል፡፡

2) የቀበሌ ቤት እጥረት
የቀበሌ የመንግስት ቤት ተከራይ የሆኑ በልማት ሲነሱ በመመሪያ ቁጥር 19/2006 መሰረት ምትክ ቤት አቅም
ከሌላቸው ምትክ የቀበሌ ቤት ማግኘት እንደሚችሉ የተደነገገ ቢሆንም ከልማት ተነሺዎቹ በአቅም ማነስ
ምክንያት የኮንደሚኒየም ቤት ቅድሚያ ክፍያ መክፈል ስለሚከብዳቸው ምትክ የቀበሌ ቤት እንዲሰጣቸው
የሚፈልጉ ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ በመሆኑም ፍላጎቱ የሚመልስ የቀበሌ ቤት ማቅረብ አልተቻለም፡፡
ስለዚህ ነዋሪዎቹ በጊዜ ማስነሳት ማነቆ ሆኗል፡፡ በ193 ሄ/ር መልሶ ማልማት ላይ ብቻ ያጋጠመ የቀበሌ ቤት
እጥረት ለአብነት ሲታይ፤
 ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የ45 ግለሰቦች የቀበሌ ቤት ምትክ ባለመገኘቱ ማስነሳት ባለመቻሉ ምክንያት 26
ሄክታር የታነቀ
 ልደታ ክፍለ ከተማ 360 ግለሰቦች የቀበሌ ቤት ምትክ ባለመገኘቱ ማስነሳት ባለመቻሉ ምክንያት 44
ሄክታር የታነቀ
 አራዳ ክፍለ ከተማ 350 ግለሰቦች የቀበሌ ቤት ምትክ ባለመገኘቱ ማስነሳት ባለመቻሉ ምክንያት 16
ሄክታር ወደ ልማት ማስገባት ኣልተቻለም፤ ሌሎች 260 ግለሰቦች ማስነሳት አለመቻሉ፡፡

3) በመካካሻ የተያዙ ቦታዎች ምላሽ ማጣት


 ከክልል ከተሞችና ከአዲስ አበባ ቤት አስረክበው የማካካሻ ቤት የያዙ ተነሺ በሚሆኑበት ወቅት ምላሽ
ለመስጠት እስኪጣራ በማለት በደብዳቤ መፃፃፎች ምክንያት መጓተት መፍጠሩ፡፡

4) በፍ/ቤት እግድ ምክንያት ሥራ መጓተት


 ፍርድ ቤቶች በመመሪያ ስልጣን ባልተሰጣቸው፣ ውሳኔ ባገኙ እና መልስ በተሰጣቸው ጉዳዮች ላይ
እግድ ከአመት በላይ መስጠታቸው፤ ለአብነት የቀበሌ ቤት ተከራይ ንግድ ቤት እንዳይፈርስ ማሣገድ
እንዲሁም 1997 አየር ካርታ ላይ የማይታይ ግንባታ እንዳይፈርስ እግድ መጣል፡፡

152
5) የይዞታ ቅልቅል
 አዋጅ 47/1967 አንድ ይዞታ ላይ የነበሩ ቤቶች የተወሰኑ ክፍሎች የባለቤቱ ሲያደርግ ትርፍ የተባሉ
ቦታዎችና ክፍል ቤቶች ደግሞ በመንግስት ባለቤትነት ስር እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ ይህ ዓይነት የይዞታ
ቅልቅል የአንዳንዱ ድርሻ በካርታ ተለይተው እንዲሰሩና የግል ይዞታው መብት ለማስከበር
በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ መጓተትን ያስከትላሉ፡፡
6) በበላይ አመራር የተያዙ ጉዳዮች በወቅቱ አለመቋጨት
 የካሣ አዋጅና መመሪያ የሚያስተናግዳቸውን የልማት ተነሺዎች በመልካም አስተዳደር ስም ለመፍታት
/በበላይ አመራር/ መፈለጉ ነገር ግን መፍትሄ የማይሰጥ በመሆኑ የማፍረስ ሥራ ማጓተቱ ለአብነት
ከ1997 ዓ.ም ወዲህ በህገ ወጥ መንገድ ገንብተው የሚገኙ የከተማ ነዋሪዎች ጥያቄያቸውን ተቀብሎ
በወቅቱ ምላሽ አለመስጠት ወዘተ

 ብዙውን ጊዜ የአደረጃጀት ለውጥ ጥያቄ ቢቀርብም ለተወሰነ ግዜ ባለው ቀጥሉ መባሉ፡፡


7) በልማቱ ላይ ህብረተሰቡን በበቂ ሁኔታ አለማሳተፍ

 በመልሶ ማልማቱ ተጠቃሚነት በእምነት እንዲይዝ በበቂ ሁኔታ የልማት ተነሺውን አለማሳተፍ
ተጠቃሚነቱን አለማጎልበት፡፡
8) ስራና የሰው ኃይል ያለመመጣጠን የሠራተኛ ፍልሰት
 በተቋሙ የሚገኙ ሙያተኞች የተሻለ ክፍያ ባለማግኘታቸው የተሻለ ክፍያና ጥቅማጥቅም ፍለጋ
የሠራተኛ ፍልሰት ይታያል፡፡

 አንድ ጽ/ቤት/ክፍለ ከተማ/ ከ8 በላይ ፕሮጀክቶችን በአንድ ግዜ እንዲሠራ መደረጉና ፕሮጀክት ቤዝድ
አደረጃጀት ባለመኖሩ ሥራ ተጀምሮ ለማጠናቀቅ ችግር መሆኑ፡፡

 የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ሲደራጅ በመሐል ከተማ 200ሄ/ር መልሶ ማልማት እንዲሰራ
ቢሆንም በየዓመቱ እንዲከናወን በተያዘው እቅድ መሰረት ባለመከናወኑ ባክሎግ ተደምሮ አዲስ
ከተያዘው እቅድ ጋር እንዲከናወን ጥረት ሲደረግ ሠራተኛው መሸከም ከሚችለው በላይ እንዲሰራ
ማድረግ ድምር የስራ ውጤት ላይ ውድቀት ማስከተሉ፡፡
9) ለስራ አጋዥ ስራ ማስኬጃ በጀት አለመመደብ

 በፕሮጀክት ተይዘው የሚከናወኑ ሥራዎች ለስራው አጋዥ የሚሆን ራኒንግ ኮስት በጀት አለመያዝ እና
ሠራተኛው ጥቅማጥቅምና የማትጊያ ሥርዓት የሌለ መሆኑ፡፡
10) የቅንጅት መጓደል
በፕሮጀክት ተይዘው የሚከናወኑ ስራዎች ቦታ ከማጽዳት ጀምሮ እስከመልሶ ግንባታ ድረስ በርካታ
ባለድርሻዎች የሚያሳተፉበት ሲሆን የነዚህ አካላት ቅንጅት መጓደል ለልማቱ መጎተት ትልቅ ምክንያት ነበር፡፡

153
በተወሰነ ደረጃ እንደ ልደታ መልሶ ማልማት ጊዚያዊ ኮሚቴና ግብረ-ሃይል በመፍጠር በባለድርሻዎች ዘንድ
ቅንጅትን ለማምጣት ጥረት የተደረገና ከሌሎች አንጻር ውጤቱ በጥሩ ቢታይም እንደ አጠቀላይ ግን ይህ
የቅንጅት ጉድለት መልሶ ማልማቱን ከመጎተቱ ሌላ ላላስፈላጊ ወጭና ብክነት የዳረገ፤ ለቅሬታና ለመልካም
አስተዳደር ችግር ምክንያት የሆነ ነበር፡፡
ለ/ ተቋማዊ የማስፈፀም ውስንነት
i. ጠንካራ የክትትልና ድጋፍ ስርዓት ያለመዘርጋት
ባለፉት ስምንት ዓመታት (2001-2008) በአራዳና ቂርቆስ ክ/ከተሞች ሰፊ የመልሶ ማልማት ሥራ (19 የመልሶ
ልማት ፕሮጀክቶች) ወደ ትግበራ የገቡ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ በአዲስ አበባ ለመልሶ ልማት ከተከለለው
ጠቅላላ የከተማ መሬት ስፋት 80% የሚሆነው በእነዚህ ፕሮጀክቶች የተሸፈነ ነበር፤ በልማት ተነሺዎች
በኩልም በ8 ዓመት ከሥራና መኖሪያ አካባቢዎች በልማት ከተነሱ አባውራዎች ውስጥ 77% የሚሆኑት
ከአራዳና ቂርቆስ ክ/ከተሞች የተነሱ ናቸው፡፡

በመሆኑም በእነዚህ ክ/ከተሞች መልሶ ማልማት ፕሮጀክት አፈፃፀም የታዩ ክፍተቶችን በዝርዝር መፈተሽ
በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ስላለው አጠቃላይ እንቅስቃሴ በቂ ስዕል ይሰጣል ተብሎ ይታመናል፡፡ ከዚህ
መሠረታዊ እምነት በመነሳት የከተማ አስተዳደሩ በ2005 ዓ/ም ግብረ ሃይል በማዋቀር የተወሰኑ የመልሶ
ማልማት ፕሮጀክቶች ቴክኒካል አፈፃፀም በዝርዝር ለመመርመር ተሞክሮ ነበር፡፡

በወቅቱ በተከናወነው ምርመራ የተገኘው ግኝት መልሶ ማልማት ሂደታችን በምን ያህል የተወሳሰበ ችግር
ውስጥ እደሚያልፍ አመላካች ነው፡፡ የችግሩን ግዝፈት ለማመላከት ሲባል በወቅቱ በምርመራው የተደረሰበትን
ዋና ዋና ጭብቶች ብቻ ቀጥሎ ከቀረበው ሠንጠረዠ መመልከት ይቻላል፡፡

154
ሰንጠረዥ 3.14፡ የምርመራው ዋና ግኝቶች በአጭሩ
በአራዳ ክ/ከተማ በቂርቆስ ክ/ከተማ
 በባሻ ወልዴ ከ26 ሄክታር ከሚነሱ 758 የመንግስት  በሸራተን ማስፋፊያ ፕሮጀክት ከ1,203 የመንግስት
ይዞታዎች 118 ያህሉ /15.56%/ እና ከ327 የግል ይዞታዎች ይዞታዎች 40/3.33%/ና ከ583 የግል ይዞታዎች 501
መካከል 242 ያህሉ /74.00%/ ችግር እንዳለባቸው /85.9%/ ያህሉ ችግር እንዳለባቸው
 በሸራተን ማስፋፊያ ከሚነሱ 512 የመንግስት ይዞታዎች 57  በመስቀል መግቢያና ኢሲኤ ጀርባ መልሶ ማልማት
ያህሉ /11.13%/ እና ከ329 የግል ይዞታዎች 269 ያህሉ ከሚነሱ 342 የመንግስት ይዞታዎች 56 /16.37%/ እና
/81.76%/ ችግር እንዳለባቸው ከ141 የግል ይዞታዎች 84 /59.57%/ ያህሉ ችግር
እንዳለባቸው
 በወሎ ሰፈር ከሚነሱ 228 የመንግስት ይዞታዎች 20
/8.77%/ እና ከ296 የግል ይዞታዎች 110 /37.16%/
ያህሉ ችግር እንዳለባቸው
 3,070 ካ/ሜ ስፋት ያላቸው ቦታዎች ለ85 ሰዎች በእላፊ  30 ያህል ግለሰቦች 8,314,258.61 ብር በአንድ ቤት
ተሳትፏል፤ ለአብነት 200 ካ/ሜ ሲገባቸው 450 ተደጋጋሚ ክፍያ ሊከፈላቸው በዝግጅት ላይ የነበሩ
የተሰጣቸው፣ 325 ካ/ሜ መሰጠት ሲገባቸው 450 ካ/ሜ  7,875 ካ/ሜ ስፋት ያላቸው ቦታዎች ለ162 ሰዎች
ተሰጣቸው ተሰጥተዋል፡፡ ለአብነት 90 ካ/ሜ ሲገባቸው 105
 ለ7 ሰው መሰጠት ከሚገባው በታች ተሰቷል፣ለአብነተ 105 የተሰጣቸው፣ 175 ካ/ሜ መሰጠት ሲገባቸው 450
ካ.ሜ መሰጠት ስገባቸው 90 ካ.ሜ ተሰቷል ካ/ሜ የተሰጣቸው ይገኙበታል፣
 31 ግለሰቦች 17 የኮንዶሚኒየም እና 14 የቀበሌ ቤቶችን  ለ5 ሰዎች መስጠት ከሚገባው በታች ተሰቷል፣ለአብነተ
በድምሩ 31 ቤቶችን በትርፍነት ወስደዋል፡፡ ማለትም 90 ካ/ሜ መሰጠት ስገባቸው 75 ካ/ሜ ተሰቷል፣
በአንድ የቤት ቁጥር መውሰድ ከሚገባቸው 1 ቤት ውጭ  35 ግለሰቦች 24 የኮንዶሚኒየም እና 11 የቀበሌ ቤቶችን
በተጨማሪነት እያንዳንዳቸው 1 ቤት ያለአግባብ ወስደዋል፡ በድምሩ 35 ቤቶችን በትርፍነት ወስደዋል፡፡ ማለትም
 32 ግለሰቦች 20 የኮንዶሚኒየም እና 12 የቀበሌ ቤት በአንድ የቤት ቁጥር መውሰድ ከሚገባቸው 1 ቤት
የወሰዱ ሲሆን፣ እንዲሁም ቤት ለመውሰድ በሂደት ላይ ውጭ በተጨማሪነት እያንዳንዳቸው 1 ቤት ያለአግባብ
የነበሩ 15 ግለሰቦች ተለይተዋል፡፡ ወስደዋል፡፡
 41 ሰዎች 8 የኮንዶሚኒየም እና 33 የቀበሌ ቤት፣  12 ግለሰቦች 21 የኮንዶሚኒየም ቤት እንዲወስዱ
 39 ሰዎች 732,869.30 ብር የግል ባለይዞታ ሆነው ምትክ ተደርጓል፡፡ ማለትም መውሰድ ከሚገባቸው 12 ቤት
የኮንዶሚንየም ቤት ወስደው እያለ ከመመሪያ ውጭ ውጭ በተጨማሪነት እያንዳንዳቸው አንድ ሰው 3 እና
የመፈናቀያ ክፍያ የተከፈላቸውን 4 ቤት ያለአግባብ በመውሰዳቸው ቁጥሩን ከፍ
 183 የግል ባለይዞታ ማግኝት ከሚገባቸው በላይ ካሳና ልያደርገው ችሏል፡፡
የመፈናቀያ ክፍያ የተከፈላቸው፡-
 የካሳ ክፍያ 4,417,632.52 ብር፣
 የመፈናቀያ ብር 1,382,005.90፣
 187 የግል ባለይዞታ ማግኝት ከሚገባቸው በታች
1,805,388.23 ብር፣ የመፈናቀያ ክፍያ የተከፈላቸው
ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

155
ሰንጠረዥ 3.15፡ የምርመራው ግኝት ማጠቃለያ
የችግሩ መጠን
ተ. የግኝት ዓይነት በክ/ከተማ
ቁ አራዳ ቂርቆስ
1 በአንድ ቤት ተደጋጋሚ ክፍያ ሊከፈላቸው በዝግጅት ላይ የነበሩ - 101
2 የተለያዩ የቦታ ስፋት ሲያጋጥም በዝቅተኛው መጠን ይሰጣል የሚለውን መመሪያ በመጣስ 85 162
የተሰጡ ቦታዎች
3 በአንድ የቤት ቁጥር በተመሳሳይና በተለያየ ስም ከአንድ በላይ ቤት የወሰዱ 32 47
4 የመልሶ ማልማቱ ፕሮግራም ከመጀመሩ በፊት የቀበሌ ቤት ውል ሳይዋዋሉ ምትክ ቤት የወሰዱ 32 20
5 የቀበሌ ወይንም የመ/ቤ/ኤ ቤት ተከራይ ውል የሚያሳየውና ምትክ ቤት የወሰዱ ሰዎች ስም 41 5
የማይመሳሰል
6 የግል ባለይዞታ ሆነው ምትክ የኮንዶሚንየም ቤት ወስደው እያለ ከመመሪያ ውጭ የመፈናቀያ 39 10
ክፍያ የተከፈላቸው፣
7 የግል ባለይዞታ ሆነው ከጂአይኤስ አንጻር ከቢል ታፕ ኤሪያ በላይ /ሌላ ደጋፊ ማስረጃ ሳይኖር/ 182 140
ከመመሪያ ውጭ ማግኝት ከሚገባቸው በላይ የመፈናቀያ ክፍያ የተከፈላቸው፣
8 ክፍያው አጠራጣሪ ሆኖ በመገኘቱ በድጋሜ የመረጃ ልኬት ሲወሰድ በመቀንሱ ያለአግባብ 28 73
ተከፍሎ የተገኘው ካሳ መጠን
9 ስለ ይዞታው ካርታ፣ ደብተር፣ ሌላ ማስረጃ ሰነድና ንግድ ፍቃድ ሳይኖራቸው ድርጅት ተብለው - 3
ምትክ ቦታ የወሰዱ
10 የግል ቤት ስለመሆኑ በመረጃ ሳይረጋገጥና የጂ.አይ.ኤስና የሲ.አይ.ኤስ መረጃ ሳይኖራቸው 8 56
ምትክ ቦታ የወሰዱ
11 የቀበሌ ቤት ሆነው በጂ.አይ.ኤስና በቅጽ 008 ላይ የሌሉ ምትክ ቤት የወሰዱ 32 13
12 ቤቱ የቀበሌ ቤት ሆኖ ሳለ ካሳና ምትክ ቦታ የወሰዱ፣ 7 9
13 የግል ቤት ሆኖ ስም ዝውውር ሳይደረግ የተስተናገዱ፣ 269 45
14 ምንም ሰነድ የሌላቸው ካሳና መፈናቀያ ክፍያ የወሰዱ 6 4
15 በዕጣ ኮንዶሚኒየም ደርሷቸው በድጋሚ ምትክ ቤት የወሰዱ 73 8
16 የኪራይ ውል ድርጅት ሆኖ ሳለ መኖሪያ በምትክ የወሰዱ 14 2
17 በመልሶ ማልማቱ ክልል ሳይኖሩ በግል ይዞታ ስም የኮንዶሚኒየም ቤት የተሰጣቸው፣ 1 -
18 የተነሽዎች ዝርዝር ውስጥ ሳይኖሩ በግል ይዞታ ስም የኮንዶሚኒየም ቤት የተሰጣቸው 60 -
19 በስማቸው የተመዘገበ ቤት እያላቸው አሁን ደግሞ የምትክ ቤት የተሰጣቸው፣ 10 -
20 ማግኘት ከሚገባቸው በታች የካሳና መፈናቀያ ክፍያ እንዲሁም ምትክ ቦታ የተሰጣቸው 187 106
21 የቤተሰብ ዝውውር ቅጽ ላይ የሌሉና ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት የቤተሰብ አካል ሳይሆኑ 3 -
እንደ የቀበሌ ቤት ነዋሪ ሆነው ምትክ ቤት የተሰጣቸው
22 የካሳ ስሌት ሲሰራ በ40 ፐርሰንት መባዛት የሚገባውን በ60 ፐርሰንት በማብዛት ያለአግባብ - 3
የተፈፀመ ክፍያ
23 በመመሪያ መሰረት የተወሰነላቸውን የምትክ ቦታ ስፋት ዕጣ በሚያወጡበት ወቅት ለውጠው - 4
የተሰጠ ቦታ ስፋት
ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

156
ii. የከተማ አመራር ዓቅም
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መዋቅር በደረጃው ከሚገኝ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሩ እስከ ፈፃሚው ባለሙያ
የከተማው ፕላን ለመተግበር የሚያስችል ከፍተኛ የዓቅም ውስንነት እንዳለው አዲሱ የከተማው መዋቅራዊ
ፕላን አስመልክቶ የተጠና ጥናት ያመለክታል፡፡

አንዱ የዓቅም ፈተና የከተማው ከፍተኛ አመራር ተረጋግቶ ለረጅም ጊዜ ስለማይቆይ ሁሌ አዲስ የተሾመ
አመራር ስራውን እስኪለምደው ጊዜ ይወስድበታል፡፡ ስራውን ለመልመድ ሲቃረብ ደግሞ ሴክተር ይቀይራል
ወይም ከነበረበት ሓላፊነት ስለሚለቅ ፖለቲካዊና ተቋማዊ ጥንካሬ እንዳይኖር እያደረገ ነው፡፡ ይህንን
በከተማ፣ ክፍለ ከተማ እና ወረዳዎችም ካቢኔ ተመሳሳይ ችግር ይስተዋላል፡፡

እንደ ከተማ ከፍተኛ አመራር ተብሎ የሚፈረጅም የትምህርት ዝግጅቱ ከፍተኛ ቢመስልም ከተማን ለመምራት
የሚያስችል የከተማ ስራ አመራር እውቀቱ ዝቀተኛ መሆኑ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ ጥናቱ የሙያ መስመርና ያላቸው
የስራ ልምድ ከሚመሩት ተቋም አኳያ ሲቃኝ በጣም ሰፊ ክፍተት ያለበት ሲሆን 50% ያህሉ ብቻ ተገቢ የሙያ
መስመርና ልምድ አላቸው፡፡ ሌሎች ከሚመሩት ባለሙያ ጋር እንኳን ሲነጻጸር የማይመጣጠን ልምድና
እውቀት/በሙያ መስመርና የስራ ልምድ/በመኖሩ እስቸጋሪነቱን ያጎላዋል፡፡ በእውቀት የመምራት ክፍተት
በስፋት እንዲታይ ያደርጋል፡፡

በክፍለ ከተማ ደረጃ ሆነ በወረዳዎች የሚገኝ አመራር ደግሞ በአብዛኛው በወጣትነት ዕድሜ የሚገኝ ሲሆን
ከልምድ አንፃር በበቂ ደረጃ የበሰለ አለመሆኑ ፈታኝ የከተማ ልማት ስራ ለመምራት እንደሚቸገር
ተጠቁሞዋል፡፡ በዚህ እርከን የሚገኙ በእድሜ የበሰሉ አይደሉም፡፡ ነባር የበሰለ አመራር በተቋሙ መኖር
ወጣቶቹን ለመደገፍ እና ለማሳየት ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ቢታመንም የትምህርት ዝግጅቱ ዝቅተኛ
ስለሚሆን የማሰፈፀም ዓቅሙ ውስን ነው፡፡

ከዓቅም ውስንነት በባሰ በፕላን የተያዙ ስራዎች ሳይፈፀሙ የሚቀሩበት ምክንያት አስመልክቶ አመራሩ
ሲጠየቅ 35% ምክንያቱ እንደማያውቁ፣ 22% የማስፈጸም አቅም ውስንነት የወለደው መሆኑ፣ 16% ደግሞ
የአደረጃጀት ችግር ስላለ መሆኑ ዕይታቸው አስቀምጠዋል፡፡ ምክንያቱን የማያውቀው አመራር 35% ሲሆን ይህ
ቁጥር የሚያሳየው በርካታ አመራር ስለ ረጅም ጊዜ እቅዶችና አፈጻጸም፣ ተደማሪ ውጤቶችን፣ የተቀመጠ
ዒላማን፣ የተሳካ ያልተሳካ ግብ ለይቶ ምክንያቱን ከማወቅ አኳያ ሰፊ ክፍተት ያለበት መሆኑም ታይቷል፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ አመራሩ ስለተቋሙ ድክመትና ጥንካሬ እንዲሁም ያለውን ክፍተት ጠንቅቆ ያለማወቅንና በአመራሩ
ላይ ያለውን ክፍተት የሚያሳይ ነው፡፡ በድምሩ ከተገኘው መረጃ መገንዘብ የሚቻለው አመራሩ ሌላ ይቅርና
የውድቀቱ ምክንያት ያለማወቅ ከተማው የመመራት ሓላፊነቱ ለመወጣት ያለው ተነሳሽነት በዝቅተኛ ደረጃ
የሚገኝ መሆኑ ነው፡፡ የክህሎትና ሙያዊ ዕውቀት ባይኖረው እንኳ የውድቀቱ ምክንያት ጠንቅቆ ማወቅ
ይጠበቅበት ነበር፡፡

157
የከተማ ፕላኑ ከማስፈፀም አንፃር ተቋማት የተጣለባቸውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችል
አመራር መኖሩ የሚያምነው 59% ብቻ ናቸው፡፡ 41% ኃላፊነቱን ሊወጣ የሚችል አመራር እንደሌለ ያላቸው
እምነት የሚያመላክተው በከፍተኛ የማስፈፀም ሓላፊነት እየተመደበ ያለው አመራር ከከተማው ተልእኮ
የሚመጣጠን ካልሆነ ልማትን የመምራትና የማስተግባር ዕድሉ በመልሶ ልማት እየታየ እንዳለ ሁሉ
የተንጠባጠበ እንደሚሆን ግልፅ ነው፡፡ የአመራሩን የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት መደረግ ያለበት ብለው
ያመላከቱት መፍትሄ ከፍተኛውን ቦታ ማለትም 83.7% የያዘው ሀሳብ አመራሩ ጠንካራ የአቅም ግንባታ ስራ
እንደሚጠይቅ ማመናቸው ከላይ ከፍ ብሎ የተገለፀውን ድክመት መኖሩ የሚመሰክር ነው፡፡

ለተቋሙ የተሰጡትን ተልእኮዎች ለመወጣት የሚያስችል የአመራር የማስፈፀም አቅም፣ አደረጃጀትና ዝግጁነት
አለመኖሩም አመራሩ እራሱ የሚያምነው ጉዳይ ሆነዋል፡፡ በጥናቱ ከተሳተፈው አመራር 65% የሚሆነው
የከተማ ተልዕኮውን ለማስፈፀም የሚያስችል የአመራር አቅም፣ አደረጃጀትና ዝግጁነት እንደ ሌለ ያምናሉ፡፡
የመምራት ዓቅምና ሙያዊ ክህሎትም ሆነ እውቀት ያለ መኖር እንደተጠበቀ ሆኖ አመራሩ የመንፈስ ዝግጁነት
እንደሌለው ማመላከቱ ተልእኮውን ለመወጣት ያለው ትርጉም ከፍተኛ ትኩረት የሚያስፈልገው ነው፡፡
በአብዛኛው ማለትም 46% የያዙት ዝርዝር እውቀት የሌላቸው ሲሆኑ ከተገኘው መረጃ መገንዘብ
እንደሚቻለው በአብዛኛው አመራሮች ስለ ቀድሞ መሪ ፕላን ምንም ግንዛቤና እውቀት እንደሌላቸው ማወቅ
ይቻላል፡፡ ይህ የሚያመለክተው እነዚህ አመራሮች አዳዲሶች መሆናቸውና በመስሪያ ቤቶቹ ያለው የሀላፊዎች
መለዋወጥ ምን ያህል ተከታታይነት ያለው መሆኑን እና በስራዎች ላይ የሚያመጣውን ክፍተት ነው፡፡

iii. የከተማ ፈፃሚ ባለሙያ ሁኔታ


በተለያዩ ፈፃሚ መስሪያ ቤቶች ከሚገኙ ባለሙያዎች የተሰበሰበ መረጃ ያሳየውም ባለሙያው ያለው ሙያዊ
ዕውቀትና ክህሎት፣ የስራ ተነሳሽነት እና ልማታዊ አስተሳሰብ የከተማው ተልዕኮ ከሚጠይቀው ደረጃ ጋር
የማይመጣጠን መሆኑ ያሳያል፡፡ የመጀመሪያው ቀላል አመለካከት በተለያዩ እርከኖች በሓላፊነት ደረጃ የሚገኝ
አመራር በፈፃሚ ባለሙያው ላይ ያለው እምነት ነው፡፡ በመጠይቅ የተሰበሰበ መረጃ የሚያሳየው 54% ያህል
አመራር የፈጻሚውን አቅም ዝቅተኛ ወይም በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ ፈርጆታል፡፡ ይሁን እንጂ ከግማሽ በላይ
አመራር የከተማ ልማት ስራን ለመምራት የሚያስችለው የሙያ መስመር ተከትሎ ያልመጣ በመሆኑ እንዲሁም
አጠቃላይ የአመራሩ ቁመና በጥንካሬ የማይገለፅ ሆኖ ሲያበቃ ፈፃሚውን በትክክል ለመገምገም ይችል
እንደሆነ ጥያቄ የሚያስነሳ ሊሆን ይችላል፡፡ አመራሩ ፈፃሚውን በደካማነት ሲፈርጅ በፈጻሚው ላይ
የሚስተዋል የስነ ምግባርና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር እንደ ማሳያ ወስዷል፡፡ አመራሩ ራሱ ብቃት
ስለሚጎድለው ፈፃሚውን ማብቃት ያለመቻሉ፣ የተሻለ ክህሎትና ልምድ ያለው ፈጻሚ የመልቀቅና ልምድ
ያለውና የነባር ባለሙያ እጥረት እንደሆነም በምክንያትነት እየታዩ ነው፡፡

ከፈፃሚው የተሰበሰበው መረጃ የሚያሳየው መረጃም ቢሆን ግን የፈፃሚው ድክመት የሚሸፍን አይደለም፡፡
ሥራዎች ታቅደው በአግባቡ የማይተገበሩበት ምክንያት በፈፃሚው በኩል ያሉ ድክመቶች ሲታይ የመፈጸም

158
አቅም፣ ክህሎትና እውቀት ማነስ (49.3%)፣ ግንዛቤ ማጣትና የአመራር ማነስ (12.7%) ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ይሁን እንጂ 69.8% ያህሉ ባለሙያዎች ፕላኑን ከማስፈጸም አንፃር የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ
ለመወጣት የሚያስችሉ ፈፃሚዎች አሉ ብለው ማመናቸው የትምህርት ዝግጅታቸውና የሙያ መስመራቸው
ከሚያሳየው ጥንካሬ ጋር የሚጣረስ ነው፡፡ ለተቋሙ የተሰጡትን ተልእኮዎች ለመወጣት የሚያስችል
የፈፃሚዎች የመፈፀም አቅም፣ አደረጃጀትና ዝግጁነት መኖሩን በተመለከተ 71.8% የለም የሚል አቋም ያላቸው
እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን ቀሪዎቹ 28.1% ብቻ በንጽጽር አቅም አለ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ይህ ውጤት
የሚያሳየው ራሱ ፈፃሚው ከግንዛቤ እጥረትም ይሁን ከክህሎት ማጣት የተነሳ ተልእኮውን በቀላሉ ለመፈጸም
ብቃትና ዝግጁነት እንደሌለው ያመላከተና ተቋማቱ የተፈለገውን ተልእኮ መፈጸም እንዲችሉ ተጨማሪ ስራ
መሰራት ያለበት መሆኑን የሚጠቁም ነው፡፡ የፈፃሚውን የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት መደረግ ያለበትን
አስመልክቶ ከፍተኛውን ቦታ ማለትም 77% ለፈፃሚው ሰፊ የአቅም ማጎልበትና ስልጠና እንደሚያስፈልገውና
ትክክለኛ ባለሞያዎችን በቦታው መመደብ እንዳለበት ይገልጻል፡፡

በአመራሩ የሚታየው አጠቃላይ የማስፈፀም ዓቅም ውስንነት በቢሮክራሲያዊ መዋቅሩም በተመሳሳይ ሁኔታ
ይታያል፡፡ ዋነኛ መገለጫው የስራ መደቦች አግባብነት ባላቸው የሙያ መስኮች የተመረቀ ሰው
አይመደብላቸውም፡፡ በሲቪል ሰርቪስ ለእያናንዱ የስራ መደብ ተገቢ ነው ተብሎ የሚፀድቀው የሙያ መስክ
ሲታይ ለአንድ ስራ መደብ ጭራሽ የማይዛመዱ ከስድስት በላይ የሙያ መስመሮች እንደሚመጥን ተደርጎ
ስለሚወሰድ የስራ መደቦች ብቃት ባለው ባለ ሙያ እንዳይመሩ እያደረገ መሆኑ እየተጠቀሰ ነው፡፡ የመንግስት
ስራ የሚያስፈፅም በቢሮክራሲው መዋቅር የሚገኝ ሰራተኛም አጠቃላይ የማስፈፀም ዓቅሙ ለመገምገም
የሚያስችል ዳሰሳ የተደረገለት ሆኖ ውጤቱ የሚያሳየው ፈፃሚውም እንደ አመራሩ ሁሉ የከተማው የልማት
ፕላን ለመፈፀም የሚያስችል ሙያዊ ዕውቀትና ክህሎት እንዲሁም አደረጃጀት ደካማ መሆኑ ነው፡፡

የታቀደውን ያህል ያለመፈፀም ችግር የሚታየው አዲስ አበባ ከተማ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ
ነው፡፡ በደሴ ከተማ ሲካሄድ የቆየ መልሶ ልማት በዋናነት አዲስ አበባ - መቐለ ዋና መንገድ እንዲሁም አዲስ
አበባ-ተንታ መንግዶች በፈጠሩት መልካም ዕድል ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ከአራዳ ደቡባዊ ጫፍ (ወደ አዲስ
አበባ መውጪያ) እሰከ አሮጌው ፖስታ ቤት መንገድ ዳር አዲስ አበባ - መቐለ አስፋልት መንገድ ስለሚገኝ
አካባቢው በሂደትም ቢሆን ቀስ በቀስ ሰፋ ያለ ቦታ እንዲለወጥ አድርጓል፡፡ ከአሮጌ ፖስታ ቤት እስከ ወሎ
ዩኒቨርሲቲ አስፋልት መንገድም በተመሳሳይ መንገድ ዳር የሚገኙ ቦታዎች አልፎ አልፎ አዳዲስ ግንባታዎች
ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል፡፡ በከተማው የተካሄደ መልሶ ልማት ውጤት ዝርዝሩ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

በከተማው መልሶ ልማት የተጀመረው በ1996 ዓ/ም ነበር፡፡ የሊዝ አዋጅ ቁጥር 272/1994 መደንገጉ አራዳ
በንግድ ተሰማርተው ከነበሩ 230 በማሕበራት ተደራጅተው አራት የንግድ ህንፃዎች ገንብተዋል፡፡ በሸዋ በር፣
ፒያሳና አራዳ መካከል ባለሀብቶች የንግድ ህንፃዎች ገንብተዋል፡፡ በግንባታ ላይ የሚገኙም አሉ፡፡ በድምሩ

159
በዚህ አካባቢ እስካሁን 5 ሄክታር ያህል መሬት ለምቷል፡፡ በብሎክ ደረጃ የተካሄዱ መልሶ የማልማት ስራ ጎላ
ያለ ቦታ ለመለወጥ አስችሏል፡፡

ስእል3.32፡ ደሴ ከተማ በመልሶ ልማትና መልሶ ማደስ የተለወጡ አካባቢዎች ስፋት

የአራዳ አካባቢ ልማት ፕላን ሽፋን

በመልሶ ልማት የተለወጠ አካባቢ

ምንጭ፡ የጥናት ቡድኑ

ከሸዋ በር እስከ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ የግራ መስመር እንዲሁም ከፒያሳ እስከ ፖስታ ቤት ዋና መንገድ
በሁለቱም ዳር የነበሩ ቤቶች በፕሎት ደረጃ በተናጠል እየለሙ በአዳዲስ የንግድ ህንፃዎች ተለውጧል፡፡
ከፕያሳ ወደ ወሎ ዩኒቨርሲቲ በሚወስዱት አስፋልት መንገዶች ሁለቱም ጎን እየተነቃቃ ይገኛል፡፡

በተናጠል በፕሎት ደረጃ እና በማሕበራት /አክሲዮን/ በብሎክ ደረጃ ሲካሄዱ የቆዩ የተናጠል ልማቶች ተያያዥ
በሆኑ ቦታዎች ተናበው በመሰራታቸው ሰፋ ያለ የዕይታ ውበት ፈጥረዋል፤ ኢንቨስትመንቱ እንዲነቃቃ ዕድል
ፈጥረዋል፡፡ ይሁን እንጂ እስካሁን የተሰራው ሲታይ ከፍላጎት ይቅርና ከዕቅድ ጋር ሲመዘን እዚህ ግባ የሚባል
አይደለም፡፡ እንደ ከተማ ስፋት ያለው መልሶ ልማት (Area Based Redevelopment) ተግባራዊ አልሆነም፡፡

በሀገሪቱ የኢኮኖሚ መርህ እና ከተሞች ካላቸው ፋይናንሳዊ ዓቅም ውስንነት ምክንያት በመልሶ ልማት
ያላቸው ሚና የሚለማ ቦታ በማጥናት ለግሉ ባለሃብት ማስተላለፍና መሰረተ ልማት በማቅረብ በኩል የተገደበ
መሆኑ ስህተት ባይሆንም የደሴ ከተማ አስተዳደር መልሰው እንዲለሙ ባቀዳቸው ቦታዎች ያደረገው
ኢንቨስትመንት ጎልቶ የሚታይ አይደለም፡፡

160
ነባር አካባቢዎች መልሰው እንዲለሙ ሲደረግ እንደ ቦታው ስፋት አለያም ካጐራባች ቦታዎች ታሳቢ
በማድረግ ካሁን በፊት ያልነበሩ የመሬት አጠቃቀም ለውጥ ይከሰታል፡፡ በከተማው ከተከሰተ ለውጥ አንዱ
ክፍት ቦታዎችና ፖርኮች ተካተዋል፡፡ ነገር ግን በዕቅድ ከተያዙ በርካታ ክፍት ቦታዎችና የህዝብ ፓርኮች
ታስቦበት በዕቅድ የተሰራ 0.41 ሄክታር መሬት የሚሸፍን የፒያሳ ፓርክ ብቻ ነው፡፡ ፓርኩ አማካሪ ተቀጥሮ
ስራው ወደ ማለቁ ደርሷል፡፡ ይህ ፓርክ ብቻውን የቆመ ሳይሆን አራዳ ከመንገድ በላይ በዕቅድ ፀድቆ ገና
ያልለማ ሰፊ ፓርክ አካል ነው፡፡

ስእል 3.33፡ በመልሶ ማልማት ምክንያት የተፈጠረ አረንጓዴ መናፈሻ /ፓርክ/

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ፣ ጥር 2008 ዓ/ም


አራዳ ከመንገድ በታች በንግድ ህንፃዎቹ ለመኪና ማቆሚያና አረንጓዴ ቦታ በፕላን የፀደቀው ቦታ በጥቃቅንና
አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ ክፍት የገበያ ቦታ እንዲሆኑ መደረጉ ለታለመለት ዓላማ አልዋለም፡፡ በሰኞ
ገበያና ፕያሳ አካባቢ ልማት ዕቅዶች ላይ ለአረንጓዴ ፓርኮች የተመደቡ ቦታዎች ገና አልለሙም፡፡

161
ስእል 3.34፡ ለመኪና ማቆሚያ የታቀደ ክፍት ቦታ በገበያነት እያገለገለ የሚገኝ

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ፣ ጥር 2008 ዓ/ም


በከተማው ሲተገበሩ የቆዩ የአካባቢ ልማት ዕቅዶች ዝርዝር ጥናትና የፕሮጀክት ወጪ ግምት ሰነድ የሌላቸው
በመሆኑ መዋቅራዊ ፕላኑ ላይ የታቀዱ ወጪዎች ላይ በመመስረት የቀረበ ግምት ማስቀመጥ የግድ ሆኗል፡፡
በዚህ መሰረት የከተማ አስተዳደሩ የውስጥ ለውስጥ መዳረሻ መንገዶች ለመገንባት ብር 164,500,000.00፣
የተፋሰስ መሰረተ ልማቶች ለመስራት ብር 3,110,000.00፣ ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መሰረተ ልማቶች ለማሟላት
ብር 12,000,000.00 እንዲሁም የመሬት መንሸራተት ለመከላከል ብር 11,600,000.00 እንደሚጠብቀው
ታቅዶ ነበር፡፡ የሰሜን ፕያሳ አካባቢ ልማት ፕላን ለማከናወን ብር 8,000,000.00 እንዲሁም የሰኞ ገበያ
አካባቢ ልማት ፕላን ለማስፈፀም ብር 13,016,937.90 እንደሚያስፈልግ ተገምቶ ነበር፡፡ እነዚህ ወጪዎች
ከመልሶ ልማት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተያያዙ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የወጣውን ወጪ የሚያሳይ
የፋይናንስም ሆነ የግምገማ ሰነድ አልተገኘም፡፡ በመሆኑም መልሶ ልማት ከፋይናንሳዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ
አዋጭነት ለመተንተን አስቸጋሪ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

መቐለ ከተማ ላይ እንደታየው በደሴ ከተማም የልማት ዕቅዶች ወደ ትግበራ የገቡት ከዓመታት በኃላ ነው፡፡
የተዘጋጁት ሰባት የአካባቢ የልማት ዕቅዶች ሁሉንም ለስድስት ዓመታት ያህል በትግበራ ላይ ናቸው፡፡ በተለይ
ሰፊ አፍርሶ መገንባት የሚጠይቁ ሶስት የአካባቢ የልማት ዕቅዶች (አራዳ፣ ሰኞ ገበያ፣ ሸዋ በር እና ፕያሳ)
የአካባቢ ዕቅዶች ገና አልተነኩም ማለት ይቀላል፡፡ መልሶ ልማቱ የሚመራበት ስትራተጂክ ዕቅድ ስለሌለው
የልማት ዕቅዱ በጊዜው ማለቁና አለማለቁ ለመገምገም የተሟላ መረጃ ባይገኝም የአካባቢ የልማት ዕቅዶች
ተዘጋጅተው ወደ ስራ የገቡበት ጊዜ የሚያሳየው ግን አፈፃፀሙ በታቀደለት ጊዜ መጠናቀቅ ይቅርና የአካባቢ
ልማት ዕቅዶቹ ይጠናቀቃሉ ተብለው በሚታሰበው ጊዜ ነው ወደ ትግበራ የገቡት፡፡

162
የከተማው መሀል ስፍራዎች ተፈላጊነት እያደገ መሆኑ ከመሬት ሊዝ ማስተላለፊያ ዋጋ ዕድገት እና እየተካሄዱ
ካሉ ግንባታዎች መረዳት ይቻላል፡፡ ሰፋ ያለ ቦታ እንደ አዲስ እንዲገነባ ፕሮፖዛል የተካተተባቸው የአራዳ እና
የፒያሳ የአካባቢ የልማት ፕላኖችም በከተማው ከፍተኛ የመሬት ፍላጎት በሚታይባቸው ቦታዎች ያካተቱ
ናቸው፡፡ በዚሁ ምክንያት መልሶ ልማቱ ትግበራ በፍጥነት ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቅ ቢሆንም በተግባር
ሲታይ ግን ምትክ ቤት እና መሬት አቅርቦት እጥረት እንዲሁም የመሰረተ ልማት ግንባታ ከግሉ ባለሃብት
ልማት ጎን ለጎን ኣብሮ አለመገንባት አፈፃፀሙ ዝቅተኛ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

ሀ/ ምትክ ቤት አቅርቦት

በከተማው የሚካሄድ መልሶ ልማት ትኩረት የቀበሌ ቤቶች ላይ አነጣጥሯል፡፡ እስካሁን በልማቱ ከሚነሱ
70% ያህሉ ነዋሪዎች የሚኖሩት ደግሞ በቀበሌ ቤቶችን ነው፡፡ በአንድ በኩል ነባሮቹ የቀበሌ ቤቶች በመልሶ
ልማት ምክንያት እየፈረሱ ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መሆኑ እውን ነው፡፡ በሌላ በኩል የከተማ
አስተዳደሩ ምትክ የቀበሌ ቤት ገንብቶ የማቅረብ ስልጣን ቢኖረውም የሚፈናቀለው ነዋሪ በርካታ በመሆኑ
ምትክ ቤት ገንብቶ ለማስተናገድ ዓቅም እንደማይኖረው ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው፡፡ እንኳንስ የአንድን
ቀበሌ ያህል ቤት መተካት ይቅርና እስካሁን በትናንሽ ቦታዎች ለሚካሄዱ ልማቶች ሲባል ነባር ቤቶች
ለማፍረስ የሚከፈል በጀት እጥረት ስለሚያጋጥመው የከተማ አስተዳደሩ ከነዋሪዎች በመወያየት የመተማመኛ
ደብዳቤ በመስጠት ቤታቸው በፈቃደኝነት እንዲያፈርሱ እንዲሁም ለተወሰነ ጊዜ ካሳው ሳይከፈላቸው
እንዲቆዩ መፍትሔ ለማስቀመጥ ጭምር ጥረት የሚያደርግበት ሁኔታ መኖሩ በውይይት ወቅት ተገልጿል፡፡

ለ/ ለመኖሪያ ቤት የሚሆን መሬት አቅርቦት

ምትክ የቀበሌ ቤትም ሆነ የኮንደሚንየም ቤት አቅርቦት ባለመኖሩ ምክንያት ተፈናቃዮች ቤት እንዲገነቡ


መሬት መስጠት የተሻለ አማራጭ ሆኖ ተወስዷል፡፡ ነገር ግን በከፍተኛ ጥግግት በትናንሽ ይዞታዎች ይሰራና
ይኖር የነበረ ነዋሪ ሲፈናቀል በከተማው ሽንሻኖ ደረጃ ቤት መስሪያ ቦታ ስለሚሰጠው የመሬት አቅርቦቱ ፈታኝ
አድርጎታል፡፡ በከተማው ክልል ውስጥ የሚገኝ የማይታረስ መሬት አቀማመጡ ለግንባታ የማይመች በመሆኑ
አማራጩ ገራዶ፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ጢጣ፣ ሃቢታት አካባቢ በአሁኑ ለግብርና አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ
መሬት ላይ ጥገኛ መሆን የማይታለፍ ነው፡፡ ይህንን መሬት ወደ ከተማ አገልግሎት ለማስገባት ደግሞ አርሶ
አደር የመፈናቀያ ካሳ ለመክፈል የበጀት ዓቅም ውስንነት ፈታኝ ነው፡፡ በተለይ ከ90% በላይ የልማት
ተነሺዎች ምርጫቸው ምትክ ቤት ሳይሆን ለመኖሪያ ቤት የሚውል መሬት ማግኘት መሆኑ ቀጣይ ፈተና
መሆኑ አይቀርም፡፡

ሐ/ የመሰረተ ልማት ግንባታ ቀድሞ ወይም ከግሉ ኢንቨስትመንት ጎን ለጎን አለመስራት

በከተማው እስካሁን የተከናወኑ መልሶ ልማት ፕሮጀክቶች ሰፋ ያለ አካባቢ የሚሸፍኑ ሳይሆኑ በብሎክ እና
በነጠላ ይዞታ ደረጃ ናቸው፡፡ እነዚህም በዋናነት አራዳ፣ ሸዋ በር፣ ፕያሳ እና መናሀሪያ አካባቢዎች ዋና

163
መንገዶች ተከትለው የተከናወኑ ናቸው፡፡ የዋና መንገዶች ዳር ተከትለው የተከናወኑ ለውጦች ከበስተጀርባቸው
የሚገኙ ቦታዎች እንኳ እምብዛም ሲነቃቃ አይታይም፡፡ ምክንያቱም ለውጡ ሊገፋ የሚችል የመንገድ መሰረተ
ልማት ያለመገንባት ነው፡፡ ቢያንስ ከዋና መንገዶች ቀጥለው የሚገኙ ሁለተኛ መደዳ ብሎኮች ለልማት
እንዲነቃቁ ደረጃቸው የጠበቁ መንገዶች አልተገነቡም፡፡

ከጊዜ መጓተት በስተቀር የተጠኑ የአካባቢ የልማት ዕቅዶች ወደ ተግባር በመለወጥ የመቐለ ከተማም ቢሆን
ለትግበራ ቀላል በሆኑ ስራዎች ላይ ነው ትኩረት አድርጎ ሲሰራ የሚታየው፡፡ በ1998 ዓ/ም የተዘጋጀው
መዋቅራዊ ፕላን ለመተግበር ከ5500 ሄክታር ያህል ቦታ የአካባቢ የልማት ፕላኖች ተዘጋጅተውለት ሲተገበሩ
ቆይቷል፡፡ በከተማው ሰፊ ስራ የተከናወነው ስራ ቢኖር ሰፈሮች በፕላን የማደራጀትና የመንገድ መሰረተ ልማት
በማሟላት በኩል ነው፡፡ ከአይናለምና የከተማው ዳር ቦታዎች በስተቀር ሌሎች አካባቢዎች የመዳረሻ
መንገዶች ጌጠኛ ድንጋይ (Cobble Stone) ተነጥፎላቸዋል፡፡ የአካባቢ የልማት ዕቅዶች ሲዘጋጁ የጠጠርና
የአፈር መንገዶች እንዲሰሩ ታቅደው የነበሩ ጭምር በድንጋይ ንጣፍ (Cobble Stone) ተሰርተዋል፡፡ ከመስፍን
ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ በዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ሓወልቲ ክፍለ ከተማ የሚደርስ፣ ከሰማእታት
መታሰቢያ ሐወልት እስከ ደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ፅሕፈት ቤት የሚወስድ ባለ ሁለት አቅጣጫ
ትራፊክ አስፋልት መንገዶች ተገንብተዋል፡፡ ከከተማ አስተዳደሩ ፅሕፈት ቤት እስከ አብርሃ-ወ-አፅብሃ ወደ
ዓዲ ሓቂ የሚወስደውን መንገድ የሚያገናኝ ባለ 25 ሜትር ስፋት የአስፋልት መንገድም በመገንባት ላይ
ይገኛል፡፡ በፕላን ያልተደራጁ ሰፈሮች (እንዳ አቡነ አረጋዊ፣ ቀበሌ 14፣ አይናለም፣ በርካቶቹ ከገጠር ወደ
ከተማ የተካለሉ) ተስተካክለዋል፡፡

ከመሰረተ ልማት በመለስ የታቀዱት ስራዎች አፈፃፀም ሲታይ ግን እጅግ አመርቂ ነው የሚባል አይደለም፡፡
ቀበሌ 14 ያለው ከፍተኛ ዕምቅ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዲያስገኝ የቀረበ ፕሮፖዛል ለማስፈፀም የተቀመጡ
ስትራተጂዎች የከተማው አስተዳደር የሕግ ማዕቀፍ አስደግፎ ወደ ተግባር አላሸጋገረውም፡፡ ከከተማው ሽንሻኖ
በላይና በታች የሆኑ ይዞታዎች እንደ አዲስ ሽንሻኖ ተሰርቶላቸው መሬቱ እንዲቀናጅ ከመደረጉም በላይ
ከሽንሻኖ ደረጃ በታች ይዞታ ያላቸው ነዋሪዎች በጋራ እንዲያለሙ፣ በአካባቢው የፕላን ደረጃ መገንባት
የማይችሉ ከሆነ ይዞታቸው ሽጠው እንዲለቁ የተቀመጡ ማበረታቻዎችና አስገዳጅ ሁኔታዎች ወደ ተግባር
አልተለወጡም፡፡ የከተማውና የነዋሪው ዓቅም፣ የባለይዞታዎች ኢኮኖሚያዊ ዓቅም፣ ባለይዞታዎች ተቃውሞ
እንዳያነሱ በስጋት ስለታየ በርካታ ቦታዎች አፍርሶ ከመገንባት ቀስ በቀስ እራሳቸው በሂደት እንዲለወጡ
አማራጭ መወሰዱ አካባቢዎች በፍጥነት እንዳይለወጡ ካደረጉት ሁለተኛው ምክንያት ነው፡፡ ከመሬት
አጠቃቀም ለውጥ ጋር በተያያዘ ቀበሌ 14 ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚገኝበት ቦታ፣ ማይ ዱባ አካባቢና ሌሎች
ለአረንጓዴና ፓርክ የታቀዱ ቦታዎች ሲሆኑ አንዱንም ተግባራዊ አልሆነም፡፡ ምክንያቱም በቦታው የሚገኙ
ይዞታዎች ለማስነሳት የሚጠይቀውን ወጪ ከግምት በማስገባት ሲሆን አረንጓዴ ስፍራ እንዲሆኑ የታቀዱት
ቦታዎች ግን ተገቢውን ትኩረት ካለመስጠትም ጭምር የመነጨ ነው፡፡

164
ሌላው ምክንያት ከዓቅም በላይ ማቀድ የወለደው ነው፡፡ በአንድ ጊዜ ከ5,500 ሄክታር በላይ ለመሸፈን
መታሰቡ መልሶ ልማት የሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ለማልማት የፋይናስ ዓቅም ፈተና መሆኑ አልቀረም፡፡
የዚህ ውጤት በርካቶቹ ዕቅዶች በቅጡ በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ እንዳይጠናቀቁ ምክንያት ሆኖባቸዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ በመሰረተ ልማት ዝርጋታና አካባቢዎች በፕላን ማደራጀት በሰራው ስራ ምክንያት በከተማ
መሃል ስፍራዎች የግሉ ኢንቨስትመንት እንዲፋጠን አድርጎታል፡፡ ቀበሌ 14 ላይ የነበሩ በጣም ጠባብ
መንገዶች የተወሰነ ስፋት ጨምረዋል፤ ጌጠኛ ጥርብ ድንጋይ ተነጥፎላቸዋል፡፡ በቦታው የነበረ አገልግሎት
እየተወጣ መምጣቱ ምክንያት የቦታው ተፈላጊነት ጨምሯል፡፡ ስለሆነም በነጠላ ፕሎት ደረጃ በርካታ
ግንባታዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡ ከሓውዜን አደባባይ ወደ ደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ የሚወስደው አስፋልት
መንገድ ሰሜን አቅጣጫ እና እንዳ ማሪያም መካከል የሚገኝ አካባቢ መንገዶቹ መስፋትና ደረጃቸው መሻሻል
በአካባቢው የግንባታ ለውጥ መታየት ጀምረዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ያደረገው አካባቢን የማሻሻል ስራን
ተከትሎ ቀበሌ 16 የነበረውን የቦታ አጠቃቀም ለውጥ አስከትሏል የቦታው አገልግሎት ለውጥ ደግሞ
ባለሃብቶች በስፋት ወደ ግንባታ ልማት እንዲገቡ አስችሏል፡፡

ከተማው አስተዳደር ባካሄዳቸው የተለያዩ የልማት ጥረቶች ውጤት ሌላኛው የቐዳማይ ወያነ የገበያ ማእከል
ነው፡፡ ይህ ባለአራት ፎቅ የገበያ ህንጻ የተገነባው ድሮ ከቀላል ግብኣት የተሰሩ የንግድ ሱቆች በነበሩበት
የከተማው ዋነኛ የገበያ ስፍራ (business area) ነው፡፡

ስእል 3.35፡ቀደማይ ወያነ የገበያ ማእከል አካባቢ

ምንጭ፡ የጥናት ቡድኑ

የዚህ ህንፃ መገንባት የመሬት አጠቃቀሙ ከፍተኛ ዋጋ እንዲኖረው ከማድረግ በተጨማሪ ከ600 በላይ
የተለያዩ የንግድ ሱቆች፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና የፋይናንስ ተቋማት የስራ ቦታ እንዲያገኙ አስችሏል፡፡
ነገር ግን የገበያ ማእከሉ 130 ያህሉ የድሮ ህንፃዎች ስለከበቡት ሌሎች ቦታዎች እንደሚታየው በአካባቢው

165
ተጨማሪ መነቃቃት መፍጠር አልቻለም፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን የገበያ ማእከሉ ከዋና መንገዶች በቀላሉ ተደራሽ
አይደለም፡፡

መሬት ሊያስገኘው ከሚችል ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አንፃር ሲመዘን ማይሊሓም፣ ቀበሌ 14፣ 16፣ 10፣ 11፣ 03
(እንዳማሪም ቡግሳ)፣ አካባቢዎች በከተማው ዋና የንግድ ማእከል በኩታ ገጠም የሚገኙ ቦታዎች በመሆናቸው
በነጠላ ሽንሻኖ /ፕሎት/ ደረጃ ከሚደረግ የግንባታ ኢንቨስትመንት ይልቅ መሬቱ በማቀናጀት አንድ ላይ
ተጠቃልሎ ቢለማ ለከተማው ሁለንተናዊ ለውጥ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡

በከተማው እንዲተገበሩ የተጠኑ 17 የአካባቢ ልማት ዕቅዶች ለመፈፀም ብር 200 ሚሊዮን በጀት
እንደሚያስፈልግ ተገምቶ ነበር፡፡ ምጣኔው 0.4% ይዞታ ለማረጋገጥ ለሚሰሩ ቴክኒካዊ ስራዎች፣ 6.8%
ለማሕበረ-ኢኮኖሚያዊ ልማት ስራዎች፣ 19% ለሚፈርስ ንብረት ካሳ እንደሚውል የተሰላ ሲሆን የአንበሳው
ድርሻ (73.8 %) መጋቢ እና መዳረሻ መንገዶች ለመገንባት የታቀደ ነበር፡፡

ሰንጠረዥ 3.16፡ የአካባቢ ፕላን ለመተግበር የቀረበ የወጪ ግምት


ስፋት የወጪ ግምት በብር
የአካባቢ በሄክታር ይዞታ የመንገድ ልማት ለንብረት ካሳ ለማሕበረ-
ልማት ማረጋገጥ ኢኮኖሚያዊ ድምር
ፕላን ስም ብር % ብር % ብር % ብር %
አይናለም 163.23 0 0 47900000 82 8415000 14.4 2091000 3.6 58406000
ዓዲ ሽምዱሕን 219.80 0 0 2562000 58 1370000 31 488000 11 4420000
ላጪ 358.14 0 0 12210000 76.6 1642000 10.3 2091000 13.1 15943000
እንዳማሪያም- 147.00 0 0 2536940 71.6 685750 19.3 321500 9.1 3544190
ጋብር
ዓዲ ወለል - 149.50 0 0 3531990 49.7 3091500 43.5 488000 6.9 7111490
ዓዲ ከንፈሮ
ማይ ሊሓም 112.2 0 0 710850 53.3 489000 36.7 133000 10 1332850
ዓዲሓ 560.00 0 0 4500000 34.7 8035453.2 62 426000 3.3 12961453.2
ማይ ዱባ 617.20 0 0 6950000 72 2475000 25.6 241700 2.5 9666700
ኲሓ እምባ 828.00 0 0 4400000 61.7 0 0 2731000 38.3 7131000
ፈቓዱ
ዓዲ ሓቂ 0 0 25935000 90.6 2607000 9.1 89500 0.3 28631500
እንዳ ስላሴ 170.00 658200 0 3202625 60 985275 18.5 488000 9.1 5334100
ሰራዋት 683.00 0 0 5250000 65.7 1800000 22.5 944000 11.8 7994000
ኲሓ አዲሱ 850.00 75000 0 16598000 96.8 150000 0.1 331500 1.9 17154500
ሰፈር
ቀበሌ 14 34.17 0 0 1359200 38.8 1826250 52.1 321500 9.2 3506950
ደጀን - 03 212.00 0 0 3900000 79.4 772500 15.7 241700 4.9 4914200
እንዳየሱስ 190.30 0 0 2520000 35.2 2730000 38.1 1915800 26.7 7165800
ፈለግ ዳዕሮ 168.00 ?? ?? ?? ?? ?? ?? ?? ?? ??
ድምር 5463+ 733200 0.4 144066605 73.8 37074728.2 19 13343200 0.7 195217733.2
ምንጭ፡ ከ17 የአካባቢ ልማት ዕቅዶች የተቀመረ፣ 2008 ዓ/ም

166
በ2000 ዓ/ም የተጠኑ የአካባቢ የልማት ዕቅዶች በጊዜው ባለመከናወኑ ምክንያት የታቀደው ብር 200
ሚሊዮን በጀት መጠን ወጪው ከአንድ ቢልዮን ብር በላይ እንደደረሰ ከከተማው ባለሙያዎች በተደረገው
ውይይት ለመረዳት ተችሏል፡፡

ስእል 3.36፡ የአካባቢ ልማት ፕላን ሽፋን እና ወጪ ግንኙነት በመቐለ ከተማ

ምንጭ፡ ከመቐለ ከተማ የ17 አካባቢ የልማት ፕላኖችን የተቀመረ


አንድን የተጠና የአካባቢ ልማት ፕላን ትግበራው በአምስት ዓመታት ውስጥ መጠናቀቅ ተገቢ ቢሆንም
በርካቶቹ የአካባቢ ልማት ፕላኖች እስካሁን በትግበራ ላይ ይገኛሉ፡፡ የአይናለም አካባቢ ልማት ፕላን ወደ
ትግበራ የተሸጋገረው ባለፈው በጀት ዓመት መገባደጃ አካባቢ መሆኑ የከፋ ያደርገዋል፡፡ የእንዳ ማሪያም- እንዳ
ጋብር አካባቢ ልማት ፕላንም በትግበራ ላይ ይገኛል፡፡

በተለይ አፍርሶ እንደ አዲስ መገንባት የሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ልማቱ የሚመራ የተለየ አደረጃጀት
ባለመፈጠሩ ምክንያት የፀደቀውን ዕቅድም ቢሆን ወደ ትግበራ አልተሸጋገረም፡፡ የተንዛዛ የትግበራ ጊዜ
በባለይዞታዎች ላይ ቀላል የማይባል ኢኮኖሚያዊና ስነ ልቦናዊ ጫና እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ቀበሌ 14 ፈርሶ እንደ
አዲስ ለመገንባት በታቀደ አካባቢ የሚኖሩ 70 ያህሉ ባለይዞታዎች የግንባታ ፈቃድ በመከልከላቸው
ቤታቸውን እንዳያሻሽሉ ዕንቅፋት እንደሆነባቸው ገልፀዋል፡፡ ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ግንባታ የማይፈቀድላቸው
ከሆነ ካሳና ምትክ ቦታ ተሰጥቶአቸው እንዲለቁ የሚያመለክቱ ሰዎች ያሉ ቢሆንም መልስ አላገኙም፡፡

ለዘመናት አካባቢው ይፈርሳል ተብሎ ይታሰብ ስለነበረ በርካታ ነዋሪዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ (Site
Plan) አልተሰጣቸውም፡፡ ሰነድ አልባና ነባር ይዞታዎች ሕጋዊነት ለማላበስ ተቋቁሞ የነበረ ፕሮጀክት ፅሕፈት
ቤት ለነዚህ ነዋሪዎች መፍትሔ ኣላስገኘላቸውም፡፡ ባለይዞታዎቹ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲሰጣቸው
በየጊዜው ለከተማው ስራ አስኪያጅ ፅሕፈት ቤት ጥያቄ ቢያቀርቡም መልስ እንዳላገኙ ይናገራሉ፡፡ ሓላፊ
በተቀየረ ቁጥር ጥያቄው እንደ አዲስ ይጀምራሉ፣ ውሳኔ ሳይሰጣቸው ሓላፊ ይቀየራል፡፡ ከዚህ የባሰው ደግሞ
ሃሰተኛ ምስክርነት አማካኝነት ይዞታቸው የሚያጡ እንዳሉም ባለጉዳዮች አግኝተናል፡፡ የዚህ ሁሉ መነሻ
የአካባቢ የልማት ዕቅድ በጊዜው ሙሉ በሙሉ ያለመፈፀሙ ነው፡፡

167
የሀዋሳ ከተማን የመልሶ ማልማት ትግበራ ውጤት ከዕቅድ ክንውን አንጻር ሲነጻጸር በከተማው መሀል
አካባቢዎች በ3 ክፍለ ከተሞች እና በ5 ቀበሌዎች ውስጥ የአካባቢ ማሻሻያ አከባቢ ኘላን ተዘጋጅቶ በ5 ዓመት/
ከ2ዐዐ6 እስከ 2ዐ1ዐ ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በ54 ሄክታር (3,042 አባወራዎች የሚኖሩባቸውን 1,280 የቀበሌ
እና 930 የግል ቤቶች) ቦታ ላይ የከተማ ማደስ ለማከናወን ታቅዶ ነበር፡፡

የመልሶ ልማቱ ክንውን ጎልቶ የሚታይ በመሰረተ ልማት ግንባታ እና በነጠላ ይዞታ በግል አልሚዎች
የሚካሄድ የተበታተነ ልማት ነው፡፡ የመልሶ ማልማቱ ሂደት በተለይ የዋና ዋና አስፋልት መንገድ እና የውስጥ
ለውስጥ ‘ኮብል ስቶን’ ንጣፍ በስፋት ያካተተው የመንገድ ግንባታው በከተማ ውስጥ በባለድርሻዎች ዘንድ
የልማት መነቃቃት የፈጠረ ቢሆንም ሰፊ አካባቢን የሚሸፍን (Area based) መልሶ ልማት ገና
አልተጀመረም፡፡ አልፎ አልፎ ከተሰሩት ደረጃቸውን የጠበቁ ባለ3 እና ከዚያ በላይ ባለፎቅ የአገልግሎት
መስጫ ህንጻዎች ከፈጠሩት ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ጥቅም ባለፈ በከተማዋ ሰፊ ውጤት የታየበት የመልሶ
ማልማት ተግባር አልተከናወነም፡፡

ስእል 3.37: በከተማ ማደሱ በመሃል ከተማ አካባቢዎች እየተገነቡ ከሚገኙ ህንጻዎች ከፊሎቹ

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ

ሰፋ ያለ መልሶ ልማት ለመተግበር በጅምር ደረጃ የሚገኘው ለማሪዮት ሆቴል በሀዋሳ ሀይቅ አጠገብ 3
ሄክታር ቦታ የተከለለ ብቻ ነው፡፡ ቢያንስ በብሎክ ደረጃ መልሶ ልማት የሚጠይቁ የደቀቁ ቦታዎች እያሉ
የተዘጋጀውን የአካበቢ ዕቅድ ወደ ተግባር ያለማስገባት የደቀቁ አካባቢዎች በግማሽ ለመቀነስ በምእተ ዓመቱ
እንዲከናወን የተያዘ ግብ ለማሳካት ያስቸግራል፡፡

በከተማው እስካሁን በተግባር የተሰራ ነገር ቢኖሩ የመንገድ ግንባታና በተለያዩ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች
ምክንያት ለሚነሱ ነዋሪዎች የሚሆን ምትክ ቤቶች ግንባታ ነው፡፡ በዕቅድ ዘመኑ በመሀል ከተማ መልሶ
168
ማልማት ፕሮጀክት ምክንያት ለተነሱት ዜጎች 380 ገደማ ምትክ ቤቶች የተሰሩት ሲሆኑ ከነዚህም 315 ገና
ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ ያሉ በመሆኑ ተነሺዎች አልገቡባቸውም፡፡ በድምሩ ከከተማ መሀል ስፍራዎች
ለሚነሱ እና ከከተማው መስፋፊያ አካባቢዎች ለኢንዱስትሪ ዞን ከተከለሉ ቦታዎች የተነሱ አርሶ አደሮች
የተከናወነው የምትክ ቤት ግንባታ ያለፉት 4 ዓመታት ዕቅድ ክንውን መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ሰንጠረዥ 3.17፡ የምትክ ቤት ግንባታ መጠን መረጃ


ተ.ቁ ዓ.ም ዕቅድ ክንዉን % መግለጫ
1 2004 25 11 44.00 ለኢንቨስትመንት ለውሃ መስመር ዝርጋታ
2 2005 70 73 104.29 እና ለኢንዳስትሪ ፓርክ ልማት የተነሱ
3 2006 70 71 101.43 ነዋሪዎች የተሰሩ ሲሆን በግል ባለሀብቶች
4 2007 120 312 260.00 የተሰሩ ምትክ ቤቶችንም ያካትታል፡፡
ድምር 285 467 163.86
ምንጭ፡ የመስክ መረጃ
በሰንጠረዡ የተመለከተው የ4 ዓመት የምትክ ቤት ግንባታ ዕቅድ አፈጻጸም ስንመለከት የመጀመሪያው የ2ዐዐ4
ክንውን ዝቅተኛ (ከግማሽ በታች) የነበረ ሲሆን ከዚያ ወዲህ ባሉት 3 ዓመታት በተከታታይ ዕቅዱ ሙሉ
በሙሉ የተፈጸመ እና በ2007 እንዲያውም ከእጥፍ በላይ መከናወኑን ያሳያል፡፡ አጠቃላይ አማካይ የዕቅድ
አፈጻጸም ሲታይ ደግሞ ከዕቅድ በላይ 63% ብልጫ እንደተከናወነ ማየት ይቻላል፡፡ ከተገነቡት ምትክ 30%
የሚጠጉ ቤቶች ለውሀ መስመር ዝርጋታ እና ለኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ከከተማው የማስፋፊያ አካባቢዎች
ለተነሱ ነዋሪዎች የተሰሩ ናቸው፡፡ ከአጠቃላዩ 7ዐ% የሚጠጉት ብቻ ናቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት ከመሃል
ከተማ መልሶ ማልማት ለተነሱና ገና በመነሳት ሂደት ላይ ላሉ የተሰሩት፡፡ ይህም ሆኖ የግንባታ ሂደቱ
ባብዛኛው በመጠናቀቅ ላይ ያለ በመሆኑ ከጥቂቶቹ በስተቀር ተነሺዎች ገና አልገቡባቸውም፡፡ የጋራ
መጠቀሚያ የቦኖ ውሀ መስመሮች የተዘረጉላቸው ሲሆን 300 የሚሆኑት የቁጠባ ቤቶች ግን የመብራት
አገልግሎት ገና አላገኙም፡፡ ይህ ቀድሞ መሰረተ ልማት ለማሟላት የተሞከረው ጥረት ከደሴና ጅማ የተሻለ
ተሞክሮ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡

ስእል 3.38፡ ለተነሺዎች ዶሮ እርባታ ሰፈር የተሰሩ ባለ1 መኝታ ክፍል የጭቃ እና ብሎኬት ቤቶች በከፊል

ምንጭ፡ የመስክ መረጃ


169
ሀዋሳ ከተማ ለልማት ተነሺዎች የሚሰሩ ምትክ ቤቶች በፕላን ስርዓቱ ጠብቆ በተደራጀ ሰፈር የሚገነቡ ሲሆኑ
በጊዚያዊነት ታስበው የሚሰሩ ሳይሆን ቋሚ መኖሪያ ቤቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰፈሮች ቋሚ መኖሪያ ሰፈሮች
በመሆናቸው መሰረተ ልማት አብሮ እንዲሰራ እየተደረገ ነው፡፡ ስለዚህ ደሴ እና ጅማ ከተሞች ላይ
እንደታየው መልሶ ልማቱ ከግንባታ አኳያ የዘላቂነት ችግር አልፈጠረም፡፡ ቀደም ሲል በጭቃና እንጨት (ስዕል
7 ይመልከቱ) ይሰሩ የነበረ ሲሆን አሁን በብሎኬት ነው እየተሰራ ያለው፡፡ እሰካሁን ያለው የቤቶቹ አሰራርም
በመደዳ ነው፡፡ ለወደፊቱ ግን ወደ ላይ እስከ G+2፣ እና G+3 ለመገንባት ነው የታቀደው፡፡ ያም ሆኖ ለልማት
ተነሺዎች የሚሰሩት ምትክ ቤቶች ወጭ የከተማውን አስተዳደር ካዝና የማይጎዱ ወጪ ቆጣቢ አይነት
ናቸው፡፡ በቅርብ እየተሰሩ ያሉት ባብዛኛው ስቱዲዮና ባለ አንድ የመኝታ ክፍል ያላቸው ናቸው፡፡ አነስተኛ
እቃ ቤት እና የጋራ መጸዳጃ ቤትም ተሰርቶላቸዋል፡፡ በዚህም በጥራትና አገልግሎት ከማሟላት አንፃር
ከጅማና ደሴ እጅጉን የተሻሉ እንደሆነ ማየት የሚቻል ነው፡፡

ስእል 3.39፡ ለተነሺዎች የተሰሩ ባለ1 መኝታ ክፍል ምትክ የመኖሪያና መጸዳጃ ቤቶች በከፊል

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ


ሀዋሳ ከተማ ላይ የሚታየው ጅምር ተሞክሮ የልማት ተነሺዎች ከነባር ቦታቸው ሲነሱ የሚገነባላቸው ምትክ
ቤት ቢያንስ ዝቅተኛ የሚባል ደረጃ የሚያሟላ መሆኑ ከደሴ እና ጅማ ከተሞች የተለየ መሆኑ ብቻ ሳይሆን
ካሁን በፊት የነበራቸው ገቢ እንዲያገኙ የሚያስችሉ የስራ መስኮች አብረው እንዲኖሩ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡
ይህ ተሞክሮ ሌሎች ከተሞች ሊማሩበት የሚችል አዳጊ ተሞክሮ ነው፡፡

በድምር የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር መልሶ እንዲያለማው ያቀደው ዕቅድ ወደ ተግባር በመለወጥ በኩል አመርቂ
ርቀት አልሄደም፡፡ ከዚህ ሌላ ከአመራሩና ከተለያዩ ወገኖች መረጃ በተሰበሰበበት ወቅት የተሰመረበት ጉዳይ
ከአመራር እስከ ባለሙያ ድረስ አወያይቶና መክሮበት ጠንካራ ቅንጅት ፈጥሮ መግባት ላይ ክፍተት መኖሩ
ነው፡፡ ይህ ለመሆኑም የመልሶ ማልማት ሂደቱ በበቂ ዕቅድና ዝግጅት በቂ በጀትና አስፈላጊው ሀብትም
ተይዞለት እና መዋቅራዊ አደረጃጀት ተፈጥሮለት የሚተገበር ባለመሆኑ፣ እዚያም እዚህም የተበታተነ የተለመደ
የማዘጋጃ ቤት የቦታ ምሪት ወይም ነጠላ ኘሎት በማዘጋጀት ላይ የተመሰረተ እንጂ ሰፊ ከሆነው ከመሰረተ
ልማቱ ግንባታ እና ማሻሻል ስራ ውጭ ሰፊ የመልሶ ማልማት ተግባርም ሆነ አመራር አልተጀመረም፡፡

170
የጅማ ከተማ መልሶ ማልማት አፈፃፀም ልዩ መለያ በዕቅድ ተይዞ ከተሰራው ይልቅ በውል ሳይታቀድ ነገር ግን
የልማት ንቅናቄ ብቻ በመፍጠር የተሰራው ስራ አመርቂ ውጤት ያስመዘገበ ሲሆን መልሶ ልማቱ መልሶ ልማት
እውን የከተሞች የልማት አጀንዳ መሆኑ እውቅና ባገኘበት ትግበራውን ሊደግፉ የሚችሉ መዋቅራዊ ፕላንና
የአካባቢ የልማት ዕቅዶች በተዘጋጁበት የተሰራ ስራ ግን ምንም የለም ብሎ መደምደም ይቻላል፡፡

ባልተቀናጀም ይሁን በተወሰነ የፕላን ማዕቀፍ በጅማ ከተማ ለ10 ዓመታት ሲሰራ የቆየው መልሶ ልማት
ከልማቱ ፍላጎት ይቅርና ከተዘጋጁ የአካባቢ የልማት ዕቅዶች አንፃር ሲነፃፀር አመርቂ አይደለም፡፡ በመርካቶና
ተያያዥ ቦታዎች እስካሁን 5 ሄክታር የሚሸፍን ቦታ ለማልማት ከታሰበው አብዛኛው ህንፃዎች ግንባታቸው
ተጠናቋል፤ የተወሰኑትም በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡ መርካቶ ውስጥ 23-25 ያህሉ የባለሀብቶች አክሲዮን
ማሕበራት ባለ አራት ፎቅ የንግድ ህንፃዎች ገንብተዋል፡፡ ከስድስት ያላነሱትም በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡
በአክሲዮን ሳይደራጁ እያለሙ የሚገኙም አሉ፡፡ በአካባቢው ሲካሄድ የቆየና በመካሄድ ላይ የሚገኝ መልሶ
ልማት ኩታ-ገጠም ብሎኮች በጋራ እንዲለወጡ ያደረገ በመሆኑ አካባቢው ላይ ያሳረፈው አወንታዊ የገፅታ
ለውጥ ቀላል አይደለም፡፡

ስእል 3.40፡ ጅማ ከተማ መርካቶ አካባቢ በመልሶ ማልማት የተለወጠ

ስፋት 77 ሄክታር ስፋት 5 ሄክታር


ምንጭ፡ ከጎግል ኤርዝ 2016 ምስል ተወስዶ በጥናት ቡድኑ የተቀናጀ
የመርካቶ ተፅዕኖ ወደ መናሃሪያ አካባቢ ተሻግሯል፡፡ ከመርካቶ-መናሃሪያ፣ ከስታዲየም-መናሃሪያ እንዲሁም
ከመናሃሪያ-ዳውሮ በር አደባባይ መንገዶች ተከትሎ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ከሁለት-አራት ፎቅ
ያላቸው ህንፃዎች በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት አንድ ሄክታር መሬት መርካቶ ውስጥ እንዲሁም ጋሊ-ሞሌ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ህንፃ ግንባታ 0.55 ሄክታር መሬት እንዲለማ ተጠንቷል፡፡ እነኝህ ሳይቶች ካሁን በፊት በለሙ ሳይቶች ጎን
ስለሚገኙ መልሰው እንዲለሙ የተደረጉ አካባቢዎች ይበልጥ ሰፊ ተፅዕኖ እንዲኖራቸው ያደርገዋል፡፡

171
በ2005 ዓ/ም የተዘጋጁ የመርካቶ፣ በቾ ቦሬ እና የጅማ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ አካባቢ የልማት ዕቅዶች ሰፊ
የመሬት አጠቃቀም ለውጥ እንደሚያስከትሉ ያሳያሉ፡፡ የመርካቶ አካባቢ የልማት ፕላን ለንግድ አገልግሎት
በዋለው ብቻ ሳይሆን ሰፊ የመኖሪያ ሰፈሮች አካቷል፡፡ የቢሺሼ ገበያ አካባቢ ሁለት እስከ አራት ፎቅ ያላቸው
ህንፃዎች ይገነባሉ፡፡ የቤቾ ቦሬ አካባቢ የልማት ዕቅድ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል የመሬት ስፋት ከ39%
ወደ 10.64% ያወርዷል፡፡ በአንፃሩ 23.9% የነበረው የንግድ ቦታ ስፋት ከዕጥፍ በላይ እንዲያድግ ታቅደዋል፡፡
እንዲሁም የጅማ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ አካባቢ ልማት ፕላን ከ50% በላይ የነበረ መኖሪያ ሙሉ በሙሉ
ለቅይጥ አገልግሎት እንዲውል ታስበዋል፡፡ እነዚህ ለውጦች ከመልሶ ልማት ውጪ የሚከናወኑ አይደሉም፡፡
እስካሁን መልሶ የለማው የመሬት ስፋት ሲታይ ግን እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡

በከተማው ዕቅድ ወደ ተግባር ያለመቀየር ድክመት የሚመነጨው ከሁለት መሰረታዊ ምክንያቶች ነው፡፡
አንደኛው የከተማው ፖለቲካ አመራር ለከተማው የሚዘጋጁ የልማት ፕላኖች ባለቤት ካለመሆን የሚመነጭ
ነው፡፡ የክልሉ ከተማ ፕላን ኢንስቲትዩት አማካሪ ቀጥሮ ያሰራቸው መዋቅራዊ ፕላኑም ሆነ የአካባቢ የልማት
ፕላኖች በቀጥታ ወደ ተግባር የሚገቡ ሳይሆን በከተማው አመራርና ፈፃሚ ባለሙያዎች ውይይት በልፅገው
በከተማው ምክር ቤት ፀድቀው መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ የከተማው በጀት ተከፍሎበት የተዘጋጀ
ፕላን ትርጉም ያለው ስራ ሳይሰራበት ባክኖ እየቀረ ነው፡፡ የፖለቲካ አመራሩ የከተማ ፕላኑ ባለቤት ስላልሆነ
ከክልሉ የሚሰጠው የመልሶ ማልማት ግብ እንኳ ቢኖር ከከተማው ዓቅም በላይ እንደሆነ እየገለፀ ነው፡፡
ለምሳሌ 2008 በጀት ዓመት 10 ሄክታር መልሶ እንዲያለማ ከክልሉ የተሰጠው ግብ አልችል ብሎ አንድ
ሄክታር ብቻ ለማልማት አቅዷል፡፡ ሁለተኛው ምክንያት የከተማው የበጀት ዓቅም ውስንነት መኖሩ ነው፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር መልሶ ልማት የሚመራ ባለቤት አደረጃጀት ቢያበጅም አፈፃፀሙ ሲታይ ግን
አደረጃጀቱ ለይተው ካልፈጠሩ ከተሞች እጅጉን ያነሰ ነው፡፡ በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ
ትግበራ ዘመን በድሬዳዋ ከተማ የተከናወነውን የነባር አካባቢ ልማት አስመልክቶ የመሬት ልማትና
ማኔጅመንት ቢሮ ያቀረበው ሪፖርት እንደሚያመለክተው በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ በተካሄደው የከተማ
ማደስ ልማት የተሸፈነው ነባር አካባቢ ከ3.56 ሄክታር አይበልጥም፡፡ ይህም ነባር ግንባታ ተነስቶ
ያልተጠናቀቀበትን የሳቢያ 2.13 ሄክታር ቦታ አካቶ ነው፡፡ በዚህ መሠረት እስካሁን በድሬዳዋ ከተማ ለአዲስ
ግንባታ የዋለው ነባር አካባቢ ከ1.43 ሄክታር አይበልጥም ማለት ይቻላል፡፡

የአካባቢ ልማት ፕላኖቹም ባለፉት አምስት ዓመታት የተዘጋጁ እንደመሆናቸው መጠን ጥናቶቹ
የተመሠረቱባቸው መረጃዎችም ሆኑ ታሳቢዎች መሬት ላይ ካለው እውነታ ብዙ ይርቃሉ ተብሎ
አይገመትም፡፡ በመሆኑም ለመልሶ ልማት የሚውሉ ቦታዎችን በአልፕ ላይ ተመስርቶ መለየት ብዙ ችግር
ይኖረዋል ተብሎ የሚወሰድ አይደለም፡፡

ቀደም ሲል እንደተገለፀው በድሬዳዋ ነባር አካባቢ ለመልሶ ልማት የሚውሉ ቦታዎችን ለመለየት የመሬት
ባንክና ማስተላለፍ ሥራ ሂደት እንደመነሻ የሚጠቀምበት ብቸኛ ሰነድ የአካባቢ ልማት ፕላን ነው፡፡ ሥራውን

172
የሚመሩትና የሚተገብሩት ፈፃሚዎች የከተማ መልሶ ልማት በጥናት ላይ ተመስርቶ የሚካሄድ መሆኑን
ለማስረዳት የሚያቀርቡት መከራከሪያ ልማቱ የአካባቢ ልማት ፕላን በተዘጋጀላቸው አካባቢዎች የሚካሄድ
መሆኑን ነው፡፡ ፕላኖቹም ሁሉን አቀፍ /Comprehensive/ ከመሆናቸውም በላይ ከቅርብ ጊዜ በፊት የተዘጋጁ
እንደመሆናቸው መጠን ልማቱን ለመምራት በቂ ናቸው፣ ከዚህ በላይ ተጨማሪ የፕሮጀክት ሰነድ ማዘጋጀት
አስፈላጊ አይደለም የሚል እምነት በአስተዳደሩ ባለሙያዎች አካባቢ እንዳለ ለመረዳት ተችሏል፡፡

እዚህ ላይ ግንዛቤ ሊያገኝ የሚገባው ጉዳይ ቢኖር መልሶ ልማት የሚካሄድበትን አካባቢ የመሬት አጠቃቀምና
ዞኒንግ እንዲሁም የመሠረተ ልማት አውታር ዝርጋታ በአዲስ መልክ ለማደራጀት አልፕ በቂ መነሻ ሊሆን
ይችላል፤ ነገር ግን በፕላኑ ላይ የተቀመጠውን የልማት ሃሳብ /Proposal/ በተሟላ መልኩ ወደ ተግባር
ለማሸጋገር አስፈላጊ የሆነውን ዝግጅት (የተቋም፣ የፋይናንስ፣ የድርጊት መርሃ - ግብር፣ ወዘተ) በዝርዝር
የሚገልጽ የመልሶ ልማት ፕሮጀክት ሰነድ ባልተዘጋጀበት ሁኔታ የተሳካ የመልሶ ልማት ፕሮግራም ማካሄድ
ይቻላል ተብሎ አይጠበቅም፡፡

በነባር አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው ልማት ቀደም ሲል ለየአካባቢዎቹ በተዘጋጁት የአካባቢ ልማት ፕላኖች
የተቀመጠውን የልማት ሃሳብ /Proposal/ በተሟላ መልኩ ወደ መሬት የወረደ መሆኑን በመስክ ምልከታ
ማረጋገጥ አልተቻለም፤ በመጀመሪያ ደረጃ እስካሁን በድሬዳዋ አካባቢ-አቀፍ /Area wise/ የሆነ የከተማ
ማደስ መካሄዱን ለማስረገጥ በማስረጃነት የሚጠቀስ ፕሮጀክት የለም፡፡

እላይ እንደተገለፀው ሰፋ ያለ አካባቢን (2.35 ሄክታር) የሚሸፍን የመልሶ ማልማት ሙከራ የተደረገው ሳቢያን
በተባለ አካባቢ ነው፤ በዚህ አካባቢም ቢሆን ነባር ተጠቃሚዎችን ከአካባቢው ከማንሳት ያለፈ ገና የከተማ
ማደስ ሥራ አልተሠራም፡፡ በሌሎቹ አካባቢዎች የተካሄዱ የነባር ከተማ መልሶ ማልማት ሥራዎች ከአንድ እና
ሁለት ቦታዎች (Plots) የሚያልፉ አይደሉም፡፡ እነሱም ቢሆኑ ኩታ ገጠም ሳይሆኑ በተለያዩ አካባቢዎች
የተበታተኑ ናቸው፡፡ የዚህ ዓይነት መልሶ ማልማት በአካባቢ ልማት ፕላን ከተቀመጠው የልማት ራዕይና
ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣም አይደለም፡፡

ለምሳሌ በከዚራ አካባቢ ተዳክሞ የሚገኘውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት በአሁኑ ጊዜ በክልሉ
ያለአገልግሎት ተዘግተው በሚገኙ ሰፋፊ መጋዘኖች እና እርጅና በተጫጫናቸው ግንባታዎች የተያዙ ቦታዎችን
ለአዲስ ልማት ማዋል እንዲሁም አካባቢውን እንደገና በአዲስ መልክ ማደራጀት አስፈላጊ እንደሆነ የከዚራ
አካባቢ ልማት ፕላን /አልፕ/ ምክረ - ሃሳብ /Proposal/ በአጽንኦት ይገልፃል፡፡

ይህን ምክረ - ሃሳብ ወደ መሬት ለማውረድም በአካባቢው ያለውን የመንገድ አውታርና መሬት አጠቃቀም
እንደገና ስር ነቀል በሆነ መንገድ ማደራጀት እንደሚያስፈልግ ፕላኑ አበክሮ ይመክራል፤ ከዚራ የሰውን
እንቅስቃሴ የማይስቡ፣ ሰፋፊ ግቢዎች እና ህንፃዎች ጀርባቸውን የሰጧቸው ጎዳናዎች በስፋት የሚገኙበት
አካባቢ ነው፡፡

173
ስእል 3.41፡ ድሬዳዋ ከተማ ከዚራ አካባቢ ከሚገኙ ሕይወት አልባ ጎዳናዎች አንዱ

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ

በመሆኑም በዚህ አካባቢ የከተማ ህይወትን የሚዘሩና አካባቢውን የሚያነቃቁ ህዝብ ሳቢ የሆኑ ተቋማትን
ማምጣት ወሳኝ እንደሆነ በክልሉ አልፕ ተሰምሮበታል፡፡ ከዚህ መሠረተ ሃሳብ በመነሳት በአሁኑ ጊዜ ተዘግቶ
በሚገኘው የኢትዮ - ጂቡቲ ባቡር ጣቢያ እና በዙሪያው ከአገልግሎት በታች በሆኑ ግንባታዎች ለተያዙ
አካባቢዎች አዲስ የመሬት አጠቃቀምን ጨምሮ አዳዲስ የመዳረሻ መንገዶች፣ ሰፋፊ የህዝብ መናፈሻ ፕላዛዎች
የሚደራጁበት ምክረ - ሃሳብ በፕላኑ ተካቷል፡፡

ስእል 3.42፡የከዚራ መልሶ ልማት አልፕ እና የልማቱ ራእይ

ምንጭ፡ ድሬዳዋ ከተማ መሬት ልማትና ማነጅመንት

ነገር ግን እስካሁን በፕላኑ የተቀመጡ ምክረ - ሃሳቦችን ወደ ተግባር በማሸጋገሩ ረገድ ተጨባጭ እርምጃ
በአካባቢው የተወሰደ መሆኑን ወይም በአካባቢው መሠረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ልማት ለማካሄድ ዝግጅት
መኖሩን በመስክ ምልከታ ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ ቀደም ሲል በአካባቢው የተካሄዱ የልማት ሥራዎችን
ስንመለከትም በክልሉ አልፕ የተቀመጠውን የልማት አቅጣጫ በተሟላ መልኩ አያንፀባርቁም፡፡ ለምሳሌ
በከዚራ አካባቢ ከቅርብ ጊዜ በፊት ከተካሄዱ አዳዲስ ግንባታዎች መካከል አብዛኞቹ የመንግሥት ተቋማት
ህንፃዎች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡

174
ስእል 3.43፡ ድሬዳዋ ከተማ በመልሶ ማልማት ከተገነቡ ህንፃዎች ማሳያ

የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ህንፃ የፖስታ ቤት ህንፃ


ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ
የእነዚህ ተቋማት ወደ አካባቢው መምጣት የአካባቢውን ገጽታ በማሻሻሉ በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ
እንደሚኖራቸው ባያጠያይቅም የክልሉን ልማት እንዲመራ የተዘጋጀው አልፕ በተሟላ ደረጃ ባልተተገበረበት
ሁኔታ የመሰል ህንፃዎች አልፎ አልፎ መገንባት የአካባቢውን መሠረታዊ ችግር ይፈታል ተብሎ አይጠበቅም፡፡

ቀደም ሲል እንደተገለፀው በድሬዳዋ ነባር አካባቢ የሚታየው የኢኮኖሚ መዳከም በክልሉ ከተንሰራፋው
የግንባታ እርጅና የሚተናነስ አይደለም፡፡ የከተማዋ ኢኮኖሚ ምሰሶ የነበረው የኢትዮ - ጂቡቲ ባቡር ድርጅት
መዘጋት የድሬዳዋን ኢኮኖሚ በአጠቃላይ የመሃል ከተማውን እንቅስቃሴ በተለይ በከፍተኛ ደረጃ ጎድቶታል፡፡
በመሆኑም የድሬዳዋ ወቅታዊ የልማት ፍላጎት ይህን እውነታ ትርጉም ባለው ደረጃ መቀየር የሚችል የመልሶ
ልማት ማካሄድ ነው፤ የዚህ ዓይነት ልማት አካባቢ-አቀፍ ከሆነ የተቀናጀ የመልሶ ልማት ፕሮግራም ውጭ
ሊታሰብ አይችልም፡፡ ነገር ግን ቀደም ሲል አስተዳደሩ በከተማው ነባር አካባቢ የተወሰዱ እርምጃዎች የዚህ
ዓይነት ግንዛቤ መኖሩን እና የአስተዳደሩ ዝግጅትም በዚህ አቅጣጫ የተቃኘ መሆኑን አያመለክትም፡፡

ከከተማ አስተዳደሩ በተገኘ መረጃ መሠረት ለመልሶ ልማት የሚመደቡ ቦታዎች የሚመረጡት ለተለያየ
ግንባታ የሚውል ቦታ የማቅረብ ኃላፊነት በተሰጠው የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊዎች የጋራ
ስብሰባ ነው፡፡ የዚህ ቢሮ ተልዕኮ በዋናነት ለኢንቨስትመንትና ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውል ቦታ ከግንባታ
ነፃ አድርጎ ማቅረብ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ አሠራር በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ውስጥ ለማይወድቁ
የመልሶ ልማት አጀንዳዎች በቂ ትኩረት ይሰጣል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ለመልሶ ማልማት የሚውሉ
አካባቢዎች ምርጫም ከመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ በላይ ኃላፊነትና ተልዕኮ ባላቸው አካላት እጅ
ባለመያዙ የተነሣ በቅድሚያ መልማት የሚገባቸው አካባቢዎች በቂ ትኩረት ላያገኙ ይችላሉ፡፡

በመልሶ ልማት ፕሮግራም ሌላው ልዩ ትኩረት ይሻል ተብሎ በአካባቢ ልማት ፕላኖች የተጠቀሰው ጉዳይ
የድሬዳዋ መንገድ ዳርቻ ዛፎች እጣ ፈንታ ነው፤ በሞቃታማው የአየር ፀባይ አስገዳጅነትም ሆነ ከተማዋን
ውበት ለማላበስ ሲባል የተተከሉት የጎዳና ዛፎች የድሬዳዋ ልዩ መለያ ናቸው፡፡

175
ስእል 3.44፡ የድሬዳዋ ከተማ ጎዳናዎች ነባራዊ አረንጋዴ ሁኔታውና ቀጣይ ፕላን

ከዚራ አካባቢ ከሚገኙ ጎዳናዎች አንዱ የጎዳና አረንጓዴ ልማት ፕላን በከዚራ አልፕ
ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ

በመልሶ ልማት ሂደት እነዚህ የጎዳና ዛፎች እንዳይጎዱ /እንዳይጠፉ/ ጥንቃቄ እንዲደረግ በከተማዋ የተቀናጀ
ልማት ፕላን እንዲሁም ይህን መሠረት አድርገው በተዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላኖች ተሰምሮበታል፡፡

ነገር ግን በከተማዋ ነባር አካባቢ በሚካሄዱ የመልሶ ልማት እንቅስቃሴዎች ይህ ጉዳይ በቂ ትኩረት ያገኘ
አይመስልም፡፡ ለምሳሌ መጋላ አካባቢ የሚገኝ ለመልሶ ልማት የተመረጠን አንድ አካባቢ ቅድመ - ማፍረስና
ድህረ - ማፍረስ እይታ ስንመለከት ለጎዳና ዳር ዛፎች የሚጠበቀውን ያህል ጥንቃቄ ይደረጋል ብሎ መውሰድ
ይከብዳል፡፡ መሬት ላይ ያለውን እውነታ ቀጥሎ ከቀረበው ፎቶ ማየት ይቻላል፡፡

ስእል 3.45፡ መልሶ ማልማት በከተማው ዛፎች የሚያደርሰው ጉዳት

የቅድመ - ማፍረስ እይታ የድኅረ - ጠረጋ ገጽታ


ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ

በድሬዳዋ የአካባቢ ልማት ፕላኖች ሌላው ትኩረት ያሻዋል ተብሎ የተጠቀሰ መሠረታዊ ጉዳይ የታሪካዊ
ቅርሶች ጥበቃና እንክብካቤ ነው፡፡ ከድሬዳዋ የቅርስ ጥበቃ ሥራ ሂደት ባገኘነው መረጃ መሠረት በፌደራል
ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን የተመዘገቡ 60 ያህል ቅርሶች ድሬዳዋ ውስጥ ይገኛሉ፤ በቅርስነት ከተመዘገቡት
ህንፃዎች መካከል አብዛኞቹ የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ንብረት በመሆናቸው በህንፃዎቹ ላይ በሚወሰድ
ማንኛውም እርምጃ ውስጥ የሥራ ሂደቱ ጣልቃ ለመግባት እንደሚቸገር ኃላፊዎቹ ይገልፃሉ፡፡ ለምሳሌ በ1926

176
ዓ.ም እንደተገነባ የሚነገርለትና በፌደራል ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን በቅርስነት የተመዘገበው የግሪክ ት/ቤት
መንገድ ለማስፋት ተብሎ ሲፈርስ ማስቆም እንዳልቻሉ የሥራ ሂደቱ ኃላፊዎች ያስረዳሉ፡፡

በድሬዳዋ መልሶ ልማት ሂደት የታሪካዊ ህንፃዎች ጥበቃን መሠረታዊ ጉዳይ የሚያደርገው ከእነዚህ ህንፃዎች
መካከል አብዛኞቹ ለመልሶ ልማት በተከለሉ አካባቢዎች የሚገኙ መሆናቸው ነው፤ ለምሳሌ እላይ ከተጠቀሱት
60 ቅርሶች መካከል 35 የሚሆኑት ለመልሶ ልማት በተከለለው የከዚራ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡

የናሙና ከተሞቹ የመልሶ ማልማት አፈፃፀም በድምር የሚያመላክተው እየተከናወነ ያለውን የመልሶ ማልማት
ስራ እንኳንስ ነባራዊ የችግሩ ስፋት ለመፍታት የታቀደው ያህል እንኳ እየተፈፀመ አይደለም፡፡ በሁሉም
ከተሞች አካባቢን ማእከል ካደረገ የተሟላ መልሶ ልማት ይልቅ በተናጠል በፕሎት ደረጃ የሚካሄድ ልማት
የተሻለ ሁኖ ይታያል፡፡ መቐለ ከተማ አካባቢ ማእከል ያደረገ መልሶ ልማት ተግባራዊ አልተደረገም፡፡ ይልቁን
ቀበሌ 14፣ 11፣ 16፣ 13 የአካባቢ መሰረተ ልማት መሻሻል ተከትሎ የግንባታ ልማት በተናጠል በስፋት ሲካሄድ
ይታያል፡፡ ደሴ (የአራዳ እና የዋና መንገዶች ዳር አካባቢዎች) እና ጅማ (መርካቶ እና አጎራባች የዋና መንገዶች
ዳር) የሚታየው ለውጥ የአካባቢ የልማት ፕላኖች ሳይዘጋጁ ነበር፡፡ ጅማ መዋቅራዊ እና የአካባቢ የልማት
ዕቅዶች የተግባር ዕቅድ ያለማድረግ ችግር እንደተጠበቀ ሁኖ የታቀደው ያህል ያለመፈፀም ድክመት የባሰ
ነው፡፡ ድሬዳዋ ሳቢያን 1.43 ሄክታር ተጠናቆ 2.13 ሄክታር ፈርሶ ግንባታ ያልተካሄደ፣ ከዚህ ውጭ በተናጠል
የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ናቸው፡፡ በሐዋሳ ከተማም ትግበራው የተናጠል የተበታተነ ምስል አለው፡፡

አካባቢን መሰረት ያደረገ መልሶ ልማት (Area Based Development) አፈፃፀሙ አመርቂ አይደለም፡፡
በሁሉም ከተሞች የተሻለ አፈፃፀም የሚታየው የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ናቸው፡፡ ዋና እና መጋቢ
መንገዶች ግንባታና እድሳት፣ የመዳረሻ መንገዶች ግንባታና የድንጋይ ንጣፍ ስራዎች በመልካም አፈፃፀም
የሚታዩ ናቸው፡፡ ለዝቅተኛ አፈፃፀም ምክንያት ከሆኑ ቁልፍ ጉዳዮች ደግሞ፡-
₋ መዋቅራዊ ፕላንና የአካባቢ የልማት ዕቅዶች ሲዘጋጁ የተቀመጡ ማበረታቻዎችና አስገዳጅ ስልቶች
በሕግ ማዕቀፍ አስደግፎ ወደ ተግባር ያለማስገባት (መቐለ)
₋ የልማት ተነሺዎች ለማስነሳት ምትክ የቀበሌ ቤት ያለመኖር እና የኮንደሚኒየም ቤቶች በጊዜው
ተጠናቀው ያለመገኘት (አዲስ አበባ፣ ሐዋሳ)
₋ በሁሉንም ክልሎች የልማት ፋይናንስ ችግር
₋ የተሞከሩ የመልሶ ማልማት ስራዎች ከልደታና መሰል በቀር በውዝግብ የተሞሉ የተጓተቱና ተነሽዉን
የልማቱ ተቋዳሽ ያደረጉ ሳይሆን የገፉ ናቸው በሚል ሰፊ ትችት የሚቀርብባቸው ናቸው፡፡

3.2.9. የመልሶ ልማት ፋይዳዎች


በከተሞች ሲካሄዱ የቆዩ የተለያየ ይዘት ያላቸው የመልሶ ማልማት ስራዎች ፋይዳቸው ማጤን የተነሱበት
ዓላማ ምን ያህል አግባብነት ነበረው ለሚለው መሰረታዊ ጥያቄ እንድንመልስ ያግዘናል፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን

177
ገና በጅምር ላይ ላለ ነገር ግን የከተሞቹ እና ሀገራዊ የልማት አጀንዳዎቹ መልሶ ማልማትን በስፋት ማስኬድ
የግድ የሚል በመሆኑ የእስካሁን ሂደት ያስገኘው ፋይዳ ምልከታ ማድረግ ክፍተቱ ከወዲሁ ለማረም አስፈላጊ
ነው፡፡

በመሆኑም የልማቱ ፋይዳ ለመመልከት መጀመሪያ ልማቱ ሲታሰብ ከተሞቹ አንግበውት የተነሱ የገፅታ ለውጥ
ስፋት እና ለኢንቨስትመንት የሚሆን መሬት አቅርቦት ዓላማ፣ እንዲሁም የእያንዳንዱ ከተማ ቁልፍ ችግር
በመለየት መልሶ ማልማቱ የከተማውን ችግር ለመፍታት ምን ያህል እንዳስቻለ (ቀድሞ ያልነበሩ መልሶ ልማቱ
ያስገኛቸው) እንዲሟሉ ያደረጋቸው የተጓደሉ የጋራ መገልገያ የከተማ ፕላን ይዘቶች (ክፍት ቦታዎች፣ አረንጓዴ
መናፈሻዎች፤ የመኖሪያ ቤት እጥረት መፍታት እንዲሁም ስራ እና ገቢ መሻሻል፤ የመሬት ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ
ወዘተ) የሚሉትን ቅርበት ያላቸው አመላካቾች በመጠቀም በአጠቃላይ ልማቱ ምን ያህል ችግር እንደፈታ
ወይም ሳይፈታቸው የቀጠሉ ችግሮች እንዲሁም በልማቱ አማካኝነት የተከሰቱ አዳዲስ ችግሮች ለማመላከት
ጥረት ተደርጓል፡፡
i. የከተሞቹ ኢኮኖሚያዊ መነቃቃት
የከተሞች ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ከሃገሪቱ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ተያይዞ የሚታይ መሆኑ ለማንም
ግልፅ ነው፡፡ በዚህ ጥናት ናሙና ተወስደው የተጠኑት ከተሞች ውጤት የሚየሳየው ደግሞ በየከተማው
የተከናወኑና በመከናወን የሚገኙ የመልሶ ልማት ፕሮጀክቶች የከተሞቹ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ/ዓቅም
በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር እንዳደረገው ነው፡፡

ይህንን በተጨባጭ ማስረጃ አስደገፎ ማየት ተገቢ ነው፡፡ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ላለፉት በተከታታይ ማደጉ
በከተሞች ይታይ የነበረ የግንባታ ልማት በዋናነት በመኖሪያ ቤት ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ በመሆኑም ልማቱ
በከተሞ ማስፋፊያ ኣካቢዎች እንጂ በከተሞች መካከል ቦታዎች ላይ እምብዛም ጎልቶ የሚታይ አልነበረም፡፡
ይኸው ብቻ ሳይሆን የከተሞቹ የኢኮኖሚ ስብጥርም ሰፊ አልነበረም ማለት ይቻላል፤ የከተሞች እምብርት
ቦታዎች በአብዛኛው እጅግ ጥቃቅን ንግድ የሚከናወንባቸው ማእከላት ነበሩ፡፡ እነዚህ ማእከላትና በዋናዋና
የትራንስፖርት መስመር የሚገኙ ቦታዎች ሳይቀር የመሬት የመጠቀሚያ መብት ዋጋቸው ዝቅተኛ እንደነበረ
ግልፅ ነው፡፡

መልሶ ልማቱ ሲጀመር በአብዛኛው የከተሞቹ ሁለንታዊ ገፅታ እንደቀየር አድርጎታል፡፡ በመንግስት ሰፊ
የመሰረተ ልማት ግንባ መካሄድ የግሉ ዘርፍ ወደ ግንባታ ልማት በስፋት እንደሳብ ዋስትና ስለሰጠው የመሬት
የመጠቀም መብት ዋጋም በከፍተኛ ደረጃ እንዲያድግ ምክንያት ሆኖታል፡፡ በከተሞቹ በርከታ ሰፈሮች በአዲስ
መልክ የተገነቡት መልሶ ልማትን ተከትለው ነው፤ በተናጠልም ቢሆን በጣም በርካ የግባታ ኢንቨስትመንቶች
የታዩት በተመሳሳይ ምክንያት ነው፡፡ አዲስ አበባ ከተማ እነደ አዲስ መገንባት የጀመረችው ከ1996 በኃላ
መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ የደሴ ከተማ አራዳና ፕያሳ ኣካባቢዎች እንደ አዲስ መገንባት የተጀመረውም በ1996፤

178
የጅማ ከተማ የመርካቶ ኣካባቢ ከ2000 ጀምሮ፤ የመቐለ ከተማ የመሃል ቦታዎች ከ2002 በኃላ፣ የሀዋሳ ከተማ
ከቅርብ ጊዘወ ወደሂ ነው በርከታ ሰፈሮች እየለወጡ የመጡት በመልሶ ልማት ምክንያት ነው፡፡

የመልሶ ልማት ፕሮጀክቶች የልማት ፋይዳ በፕሮጀክት ሳይቱ የታጠረ አይደለም፡፡ መልሰው የለሙ
አካባቢዎች በዙሪያቸው በሚገኙ አካባቢዎች ላይ የሚፈጥሩት የልማት መነቃቃት ሰፊ ነው፡፡ በዙሪያቸው
ላለው አካባቢ ይዘውት የሚመጡት የልማት ዕድል የፕሮጀክቶቹ ትግበራ እስኪጠናቀቅ የሚጠብቅ
ኣይደለም፡፡ አሁን የተያዘው አካሄድ አንድ አካባቢ በመልሶ ልማት ከተከለለ ቀጥሎ ያለው ሰፈር በተመሳሳይ
ፕሮጀክት የሚታቀፍ መሆኑን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ መልሶ ልማት ሰፊ
ከመሆኑ እና ይዘቱ በየጊዜው እንዲያድግ መደረጉ በከተማይቱ የፈጠረው የኢኮኖሚ መነቃቃት ትልቅ ነው፡፡
ከ2001 ዓ/ም ወዲህ አስተዳደሩ እንደ አዲስ ከተዋቀረ በኃላ ለመልሶ ማልማቱ የተሻለ አደረጃጀት በመፍጠር፤
ከነበሩት ችግሮች በመማር መልሶ ማልማቱ የሚመራበት መመርያ በማጽደቅ፤ ህዝቡ በከተማዋ አዲስ ልማት
እየመጣ መሆኑን በማየት ለልማትና ለለውጥ ያለው መንፈስ ተነሳስቷል፡፡ ለዚህም የልደታ፣ በርበሬ ተራና
ቂርቆስ አካባቢ ህዝብ ተፈራርሞ “አካባቢያችን በመልሶ ማልማት ይታቀፍ” የሚል ጥያቄ ማቅረብ መጀመሩን
እንደ ማሳያ መውሰድ ይቻላል፡፡

ii. መሬት ሊያስገኘው የሚችል ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ


መልሶ ልማት በተካሄደባቸውና በቅርቡ እንዲተገበር በታቀዱ ቦታዎች የመሬት የመጠቀሚያ ዋጋ እና የቋሚ
ንብረት ዋጋ ከድሬዳዋ በስተቀር በሌሎች ከተሞች በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መጥቷል፡፡

መቐለ ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ እና አጎራባች ቦታዎች ከሌሎች አካባቢዎች ሲነፃፀር የመሬት የመጠቀሚያ
የሊዝ ዋጋ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ በመሆኑም በዚህ አካባቢ በተናጠል በፕሎት ደረጃ የሚካሄድ መልሶ ማልማት
ተጧጥፎ ቀጥሏል፡፡

በየከተማው የመሀል ቦታዎች የተካሄዱ ልማቶች ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በመሬት አጠቃቀም ለውጥና የመሬት
የመጠቀም መብት ዋጋ መጨመር ጎልተው ይታያሉ፡፡ ለምሳሌ መቐለ ከተማ ላይ ቀበሌ 14 በተለያዩ
አቅጣጫዎች ከቀለበት መንገዱና ሌሎች መጋቢ መንገዶች ጋር መገናኘቱና የውስጥ መዳረሻ መንገዶች በፕላን
መደራጀታቸው ከባህላዊ መጠጥ ማምረቻነቱ እንዲላቀቅ አስችሎታል፡፡ አካባቢው ቀድሞ ከነበረው
የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች የተሻሉ /higher order/ ማለትም ካፊቴሪያዎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የችርቻሮ ሱቆች
ወዘተ ማእከል እየሆነ ይገኛል፡፡ የግንባታ ገደብ ባልተጣለባቸው ቦታዎች ደግሞ ባለ ሁለትና በላይ ፎቅ
ዘመናዊ ህንፃዎች ተገንብቷል፤ በመገንባትም ይገኛሉ፡፡ በጥናቱ የተዳሰሱ ነዋሪዎች ደግሞ የግንባታ ገደቡ
ከተነሳላቸው በራሳቸው ዓቅም የተሻለ ግንባታ ለማካሄድ ዝግጁ የሆኑ ነዋሪዎች በርካታ መሆናቸው ግንዛቤ
ተወስዷል፡፡

179
በአካባቢው የመሬትና የቤት ዋጋም በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡ በከተማው የመሬት ልማትና ማነጅመንት
ረጅም ጊዜ የሰሩ ባለሙያዎች እንደሚሉት የአካባቢ ልማት ፕላን ከመተግበሩ በፊት የመሬት ዋጋ ከ40 እስከ
60ሺ ብር ነበር፡፡ አካባቢው ወደመልሶ ማሻሻል መግባቱን ተከትሎ በትናንሽ ይዞታዎች ላይ ያረፉ ጎስቋላ
ቤቶቹ ጭምር በሚልዩን ብር እየተሸጡ መሆኑ ይናገራሉ፡፡ የባለሙያዎቹ እምነትና ግምገማ እንደተጠበቀ ሆኖ
በአካባቢው እየታየ ያለው የመሬት የሊዝ ጨረታ ዋጋ በከተማው ተፈላጊ ከሚባሉ ቦታዎት ጋር ሲነፃፀር
በአማካይ ተመሳሳይ መሆኑ ለውጡ ለመሬት የመጠቀምያ መብት ዋጋ መሻሻል ያበረከተው ፋይዳ ምን ያህል
መሆኑ የሚያሳይ ነው፡፡

መቐለ ከተማ ላይ ያልተጠበቀ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ፋይዳ ለውጥ ከታየባቸው አካባቢዎች ቀበሌ 16 ተጠቃሽ
ነው፡፡ ከሮማናት አደባባይ በአጼ ዮሃንስ ት/ቤት፣ ፎቶ ደስታ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቀለ ቅርንጫፍ ዋና
መንገዶች፣ እንዲሁም በመካከል ቦታዎች የተወሰኑ የሕግ ጠበቆች ቢሮዎችና መኝታ ቤቶች ካልሆነ በስተቀር
አካባቢው የመኖሪያ ሰፈር ነበር፡፡ ሰፈሩ በሕጋዊ መንገድ /በፕላን/ የመሬት አጠቃቀሙ ዓይነት ባይቀየርም
የውስጥ ለውስጥ መንገዶቹ በጥርብ ድንጋይ መነጠፋቸው ሰፈሩ ሙሉ በሙሉ በራሱ ውስጣዊ ኢኮኖሚያዊ
ሂደት ወደ ንግድ ማእከልነት ተለውጧል፡፡ የመንገዶቹ ዳር ሙሉ በሙሉ ቀን ቡና ሲያስተናግዱ ይውላሉ፤
አመሻሹ ከ12፡00 እስከ ሌሊቱ 6፡00 ቤቶቹ የሞቁ ባር ሆነው የሚያድሩ የሞቀ የንግድ ሰፈር ሆኗል፡፡ ሰፈሩ
በርካታ ባህላዊና ዘመናዊ ሬስቶራንቶች ተቀላቅለውታል፡፡ ከቀበሌ 14 በበለጠ ይህንን በርካታ ከፍተኛ
ግንባታዎች /ሆቴሎች፣ መኝታ ቤቶች…./ እየተገነቡበት ይገኛል፡፡

ከዘስላሰ አደባባይ እስከ ሮማናት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በስተቀኝ በኩል የሚገኘው ቦታ የአካባቢ
ልማት ፕላን መተግበር የተጀመረው በቅርብ ጊዜ በመሆኑ የቀበሌ 14 እና ቀበሌ 16 ያህል የጐላ ለውጥ
ባይታይበትም ሂደቱ ግን ተመሳሳይ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል የሚጠቁሙ ምልክቶቹ ጐልተው
መታየት ጀምረዋል፡፡ አካባቢው ባህላዊ መጠጥና ትናንሽ ምግብ ቤቶች የበዙበት አካባቢ የነበረ ሲሆን አሁን
እየተቀየረ ይገኛል፡፡ ግንባታዎችም መቀየር ጀምሯል፡፡

ይህንን በመቐለ ከተማ የታየው ለውጥ በሌሎች ከተሞችም /ጅማ መርካቶ፣ ፕያሳ-መናሃሪያ/፣ ደሴ /አራዳ፣
ፕያሳ/ በስፋት ይታያል፡፡ በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ ከሁሉም በላይ የጎላ ነው፡፡ ጅማ መርካቶ፣ ቦቼ ቦሬ፣
የጅማ ዩኒቨርስቲ ዋና ግቢ አካባቢ የመቐለ ያህል ባይሆንም የግሉ ዘርፍ እንቅስቃሴ መኖሩ ይታያል፡፡ ደሴ
ከተማ መንገድ ዳር ለንግድና ቅይጥ አገልግሎት የሚውል መሬት የሊዝ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡
ጅማ ከተማ ላይ የተከናወነ የመልሶ ማልማት መነሳሳት ጥረት የግሉ ዘርፍ በግንባታ ልማት በኢንቨስትመንት
እንዲሳብ አድርጓል፡፡ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትም የከተማውና የግሉ ኢንቨስትመንት ለማበረታታት
በመሰረተ ልማት ላይ ተጨማሪ መዋእለ ንዋይ አፍስሷል፤ የመርካቶና አካባቢው መንገዶች 20-25 ሜትር
ስፋት ያላቸው የአስፋልት መንገዶች ተሰርቷል፡፡

180
ሀዋሳ ከተማ በስፋት የተሰራው የከተማዋ አጠቃለይ ዕድገት የሚያፈጥኑ የመንገድና ተፋሰስ መሰረተ ልማቶች
ግንባታዎች ነው፡፡ እነዚህ መሰረተ ልማቶች ሲገነቡ በተለያዩ ቦታዎች የባለሃብቱ የልማት ፍላጎት አነሳስቷል፡፡
የከተማው ዕድገት የተመጣጠነ ስርጭት ለማስጠበቅ የሚያግዙ 11 የአስፋልት መንገዶች (ከታደሰ እንጆሪ እስከ
ክልል ፋይናንስ ቢሮ"፣ ከሩዶልፍ ሆቴል እስከ ሀዋሳ እርሻ ልማት ድረስ፣ ከኬራውድ ሆቴል በመነሳት በወሊሶ
ሆቴል አልፎ የሚሄደው ትልቅ መንገድ፣ ከኮሪ መስጊድ እስከ ሀዋሳ እርሻ ልማት ድርጅት) መገንባታቸው
ቀድሞ ደካማ የነበሩትን የከተማዋን ማዕከላዊ ሰፈሮች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴአቸው እንዲሞቅ
አድርጎታል፡፡ እነዚህ መንገዶች መገንባት በተናጠልም ቢሆን በርካታ ይዞታዎች እራሳቸውን እንዲያሻሽሉ በር
ከፍቶላቸዋል፡፡ አልፎ አልፎ ነጠላ ይዞታ ላይ ያተኮሩ መልሶ ማልማት በተካሄደባቸው ቦታዎች አከባቢ
የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው በዓይነትና በመጠን እየሰፋና እየተነቃቃ የመጣ ሲሆን የአከባቢው የመሬት
የመጠቀሚያ መብት ዋጋ በመጨመሩ በዚያ የቀሩት ነዋሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ህብረተሰቡም ለልማት
ያለውን ተነሳሽነት አጠናክሮታል፡፡ በአነስተኛ መጠን የተጀመረ በመሆኑም ያረጁ ቤቶች የተነሱበትን ቦታ
ለሜ/ካሬ እስከ ብር 15000.00/አስራ አምስት ሺ/ እና ከዚያ በላይ ለአልሚዎች መተላለፉ ፕሮጀክቱ
እንዲያውም የከተማው አስተዳደር/ማዘጋጃ ቤት ለልማት ጠቀም ያለ ገቢ የሚያገኝበት ሁኔታ ፈጥረዋል፡፡

መልሶ ማልማት የመሬት ኢኮኖሚያዊ ዓቅም በመፍጠር በኩል ሊያስገኘው ከሚገባው ሌላው ገዳይ የመሬትን
አጠቃቀም ምርታማነት ማሳደግ ነው፡፡ ነገር ግን መልሶ ልማቱ የካፒታልና መሬት ጥምርታው መሬት
ለመቆጠብ ያስቻለ አይደለም፡፡ መልሶ ልማቱ ቢያንስ በቦታው ከነበረ ኢኮኖሚያ እና ነዋሪ በላይ ለመሸከም
የሚያስችል ዓቅም መፍጠር ሲገባው በቦታው የነበረ ለማስተናገድም እየቻለ አይደለም፡፡ ይህንን አዲስ አበባ፣
ጅማ እና ደሴ ከተሞች በጉልህ ይታያል፡፡

ለምሳሌ የበደሴ ከተማ ተጨባጭ ምስል እንመልከት፡፡ የመልሶ ልማት ከተካሄደባቸው አካባቢዎች መካከል 10
ቦታዎች በናሙናነት ተወስደው የተካሄደው የግምገማ ውጤት በመልሶ ማልማት ተጨማሪ ኢኮኖሚ ወይም
ነዋሪ የሚያስተናግድ ቦታ ማትረፍ አልተቻለም፡፡ ይኸውም ከእነዚህ 10 ቦታዎች 560 ቤተሰቦች (181
ባለይዞታዎችና 379 የቀበሌ ቤት ተከራዮች) በመልሶ ልማት የተነሱ ሲሆን እነዚህን ቤተሰቦች መልሶ
ለማስፈር ለመኖሪያ ቤት ብቻ 9.58 ሄክታር መሬት አስፈልጓል፡፡ በዚህ ላይ የሚሰፍሩበት ቦታ አዲስ ሰፈር
በመሆኑ ለመሰረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታ ተጨማሪ 13.7 ሂክታር ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ ነዋሪዎች ይዘውት
የነበረው ቦታ ግን ከዚህ እጅግ በጣም ያነሰ ነው፡፡

iii. የተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን


ለከተማ መልሶ ማደስ ከከተማይቱ መሪ ኘላን ጋር የተጣጣመ የአካባቢ ልማት ኘላን አስፈላጊ ነው፡፡ የአንድን
አካባቢ ልማት እውን ለማድረግና ወደ መሬት ለማውረድ ዝርዝር የአካባቢ ልማት ኘላን ሲዘጋጅ እንደሆነ
ይታወቃል፡፡ ይህ በጐ ጅምር ያሉትን ጉድለቶች አሻሽሎ ሊቀጥል ይገባል፡፡

181
መልሶ ማልማቱ አንድን አካባቢ የተሟላ የከተማ አገልግሎት መስጠት እንዲችል የጎደሉት የጋራ መገልገያ
መሰረተ ልማቶች (ክፍትና አረንጓዴ ቦታዎች) እንዲካተቱ ዕድል እየፈጠረ ነው፡፡ በተሟላ መንገድ ባይሆንም
30፡30፡40 የመሬት አጠቃቀም ፖሊሲ ለመተግበር መልካም ዕድል ፈጥሯል፡፡ በተለይ የደሴ ከተማ
አስተዳደር ከሌሎቹ ከተሞች በተለየ በዕቅድ ደረጃ ለአረንጓዴ ቦታዎች የሰጠው ትኩረት በምሳሌነቱ ሊታይ
የሚገባው ነው፡፡

በድሬዳዋና ሃዋሳ ከተሞች በነባር ሰፈሮቹ ላይ የሚገኙ ይዞታዎች በአንጻራዊነት ሰፋፊ አደረጃጀት ያላቸው
ስለሆነ ነባር ግንባታን ጠርጎ ልማትን ግድ የሚሉ አይደሉም፤ መልሶ ማልማቱ በተናጠል ይዞታ ለማከናወን
የሚያስችል ሁኔታ መኖር በበጎ የሚታይ ነው፡፡ በአንድና ሁለት ይዞታ ተበታትኖ የሚመጣ ልማት ወጥ
አይደለም፤ የተሰባሰበ ትልቅ ልማት ዓቅም (Agglomeration) በቶሎ መፍጠር ባለመቻሉ ቢተችም አከባቢን
በተመጣጠነ ሁኔታ በቅይጥነት ባለብዙ ማዕከል አድርጎ ለማልማት ጠቀሜታው ሰለሚያመዝን በጎ ጎኑ በስፋት
መጠቀም የሚሻ ነው፡፡

መልሶ ልማቱ በፕላን እንዲመራና ወደ መልሶ ልማት የሚገባውን አካባቢ የተጓደሉትን ይዘቶች በመሟላት
በኩል ልምዱ እየተሻሻለ መሆኑ በተለያዩ ጊዚያት የተዘጋጁ የአካባቢ የልማት ዕቅዶች በማየት መረዳት
ይቻላል፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን መስተካከል የሚገባቸው መሰረታዊ ስህተቶች አሉ፡፡

አንደኛው ጉዳይ በቂ ይዘት ያለው የአካባቢ የልማት ፕላን ያለማዘጋጀት ነው፡፡ አንዳንዶቹ የከተማ ማደስ
ኘሮጀክቶች ያለ በቂ የአካባቢ ልማት ኘላን ዝግጅት ይከናወናሉ፡፡ ሌላኛው ጉዳይ ከዝርዝር አካባቢ ልማት
ጥናቱ በተጨማሪ የአካባቢዉን የተለየ ባህሪ መሰረት ያደረገ የአርባን ዲዛይን ስራ አለመከናወኑና አርባን
ዲዛይን ያላቸውንም ቢሆን ለአካባቢዉ የሚፈጥረዉን የገጽታ ለዉጥ በተለያዩ ሞዴሎች በማዘጋጀት ለህዝቡ
ተጨባጭ ስዕል የሚፈጥር በቂ የሚባል የማስተዋወቅ ስራ ሲሰራ አይታይም፡፡ ሶስተኛው ውስንነት ደግሞ
በአንፃራዊነት በቂ የአካባቢ ልማት ኘላን አላቸው የሚባሉትም (ለምሳሌ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ካዛንቺስ፣
መርካቶ፣ ፒያሳ) ቢሆን የአፈፃፀም ሂደታቸዉ ኘላኑን የተከተለ አይደለም፡፡ ቀደም ሲል በተለመደው የመሬት
ሸንሻኖና የተሸነሸነውን መሬት ለቅልቅልና የንግድ አገልግሎት መመደብ መገንባት እንጂ የሚሸነሸነው መሬት
እላዩ ላይ ከሚገነባው ህንፃ ምንነትና አገልግሎት እንዲሁም ከአጎራባች ህንፃዎች ጋር ያለው ግንኙነት በበቂ
የከተማ ዲዛይን (Urban Design) ሳይቃኝ የሚተገበር ነው፡፡ አልሚው ደግሞ የመሬቱን አጠቃቀም ከፍ
ለማድረግ ሲል የተገልገዮች መኪና ማቆሚያ ማሰብ ይቅርና የሚገነባው ህንፃ ደህንነት ለመጠበቅ እንኳ
ከመንገዱ ዳር ሁለትና ሶስት ሜትር ገባ ብሎ መገንባት አይታይም፡፡ በዚህ ሂደት ዘመናዊና የከፍተኛ ህንፃዎች
የተጐሳቆለ ሰፈር (Slums) እየፈጠርን ነው፡፡

በመቐለ ከተማ እየተከናወነ የሚገኝ መልሶ ልማት ከፕላን አንፃር ሌላ ትምህርት ሊወሰድ የሚገባ ሆኖ
እናገኘዋለን፡፡ ቀበሌ 14፣ 03 እና 04 ከተወሰኑ ብሎከች ውጭ አካባቢው በሂደት እራሱ እንዲለወጥ መፍቀዱ
የልማት አማራጩ ችግር ባይኖረውም አብዛኛው የይዞታ ሽንሻኖው ከደረጃ በታች በመሆኑ በነጠላ ይዞታዎች

182
ከሶስት እስከ ስድስት ፎቅ (G+3 - G+6) ከፍታ ያላቸው ህንፃዎች እንዲገነቡ መደረጉ የህንፃ የከፍታ ፕላኑ
ከህንፃ ሕግ አለመጣጣሙ ያሳያል፡፡ ዮታዎቹ ሙሉ በሙሉ ግንባታ የሚያርፍባቸው ከመሆኑም በላይ
በአካባቢው የጋራ መገልገያ /ለመኪና ማቆሚያ ቦታና አረንጓዴ ሥፍራ/ በአካባቢያቸው ስለማይኖር ሰፈሩን
በከፍተኛ ደረጃ ያጨናንቁታል፡፡ በቂ የመዳረሻ መንገድም ስለማይኖር የትራፊክ መጨናነቅ ተመሳሳይ ግንባታ
ለተካሄደባቸው አካባቢዎች ትልቅ ፈተና እየሆነ መጥቷል፡፡

ስእል 3.46፡ ቀበሌ 14 የታቀደው የመንገድ መረብ (መቀሌ)

PA አውራ መንገድ/30ሜተር/
-2
CS መዳረሻና ሰብሳቢ መንገድ
(12 እስከ 15 ሜትር)

ምንጭ፡ የቀበሌ 14 አካባቢ ልማት ፕላን፡ 2000 ዓ/ም

በዚህ መንገድ የተናጠል መልሶ ልማት የሚካሄድበት አካባቢ እየተጨናነቀ የሚሄድ ከሆነ ልማቱ ለአካባቢው
ሊያስገኘው የሚችለውን ሁለንተናዊ ተደማሪ ጥቅም /Economies of Scale/ እያዳከመው ይሄዳል፡፡ የከተማ
አስተዳደሩ የከተማ ፕላንና መሬት ልማት ባለሙያዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ያላቸው ድምዳሜ ተመሳሳይ ነው፡፡

ከመሬት አጠቃቀም ፕላን ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ሌላው ጉዳይ የአገልግሎት ምድብ ለውጥ ነው፡፡ የአካባቢ
የልማት ዕቅዶ መዛኑ የጠበቀ ልማት ከማሰብ ሰፊ ክፍተት ይታይበታል፡፡ ለምሳሌ መቐለ ከተማ ላይ በነባሩ
የከተማው ዋና ማእከል ቐዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ እና አጎራባች ቦታዎች የታቀዱ የመሬት አጠቃቀም
ለውጦች እንዲሁ የአካባቢው የንግድ ማእከልነት ቀጣይነትን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ነገር ግን በከተማው አዳዲስ
ሚዛን የሚደፉ የንግድ ማእከላት እየተፈጠሩ ነው፤ ለምሳሌ ወደ ዓዲ ሓውሲ በርካታ የገንዘብ ተቋማትና
ሌሎች አገልግሎት ሰጭ ተቋማት እየተሰባሰቡ ነው፣ ከቐዳማይ ወያነ ዋና ማእከል ጋር በአብርሃ ካስትል በኩል
የሚያገናኘው መስመርም ወደ ንግድ ማእከልነት እየተለወጠ ነው፣ በተመሳሳይ ዓዲ ሽምደሑን ወደ ንግድ
ማእከልነት ተለውጧል፡፡ በመሆኑም በነባሩ ዋና ማእከል የሚደረግ የመሬት አጠቃቀም እነዚህን ለውጦች
ታሳቢ ያደረገ መሆኑን መለስ ብሎ ማየት ያስፈልጋል፡፡

አዳዲሶቹ ማእከላት እየጎለበቱ በሄዱ ቁጥር የነባሩ ማእከል ሚና እየቀነሰ ስለሚሄድ በቦታው የተገነቡ የንግድ
ህንፃዎች ተፈላጊነትና ኢኮኖሚያዊ ምርታማነት እንዳይቀንስ ከወዲሁ ተገቢው ጥንቃቄ የሚሻ ነው፡፡ አሁን

183
እየታየ ባለው ለውጥ የከተማው አጠቃላይ ዕድገት ወደ ደቡብ፣ ምዕራብና ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫዎች
እየተሳበ በመሆኑ ነባሩ ዋና ማእከል የነበረውን ጥንካሬ ጠብቆ እንዲቀጥል ማድረግ ፈታኝ ሊሆን ይችላል፡፡

በሌላ መልኩ የከተማው ዋና ማእከል የሆነው የቐዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ዝቅተኛ የነዋሪ ጥግግት /56 ሰው
በሄክታር/ እንዳለው እየታወቀ በመሃል ከተማው የሚስተዋለውን ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት እጥረት የሚቀርፍ
የመሬት አጠቃቀም መተግበር አለመቻል ትልቅ ክፍተት ነው፡፡ ስለዚህ የቅይጥ መሬት አጠቃቀም መሰረተ
ሃሳብ አግባብነት እንደተጠበቀ ሆኖ የመኖሪያ ቤት ድርሻ ምጣኔው ግን ልዩ ትኩረት ይሻል፡፡

መኖሪያ ከመሀል ስፍራዎች ጠርጎ ወደ ዳር እየተገፉ መሄዳቸው መሃሉ ቀን ብቻ የሚሰራ ሌሊት ደግሞ የሞተ
የሚያደርግ ሲሆን ዳሩ የዚሁ ተፃራሪ ባህሪ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ የዚህ ውጤት የመሬት ምርታማነት
የሚያጠፋ አካሄድ ነው፡፡ ይኸው ብቻም አይደለም፤ ከተሞች ከአዲስ አበባ መማር ሲገባቸው መዋቅራዊ
ፕላኖቻቸውም ሆነ የአካባቢ ልማት ፕላኖቻቸው የትራፊክ ፍሰቱ ጧተ ወደ መሃል ፣ ማታ ወደ መኖሪያ/ጫፍ/
እንዲጎርፍ የሚደርጉ ናቸው፡፡ የእሂህ ውጤት ደግሞ የጊዜ ብክነት፣ የእያንዳንዱ ዜጋ ምርታማነት ብክነት፣
አከባቢያዊ ብክለት ወዘተ መሆናቸው ከአዲስ አበባ ከተማ መማር ይቻላል፡፡

የመሬት አጠቃቀም ለውጥ የመቀየጥ አቅጣጫ በኢንቨስትመንት በኩልም ሌላ እንደምታ አለው፡፡ በከተማው
የተገነቡና በመገንባት ላይ የሚገኙ ህንፃዎች ንግድና መሰል አገልግሎቶች ታስበው የተሰሩ ቢሆኑም ሙሉውን
ዓቅማቸው አገልግሎት እየሰጡ አይደሉም፡፡ ለምሳሌ ደሴ ከተማ አራዳ አካባቢ ከተገነቡ የገበያ ማእከላት
መካከል አራቱ ናሙና ይህንኑ እውነታ ያሳያሉ፡፡

ሰንጠረዥ 3.18፡ ከንግድ ህንፃዎች ጥቅም ላይ የዋለ አቅም (ደሴ)


የአክሲዮን የማሕበሩ አባላት በሙሉ አቅማቸው የሚሠሩ/በኪራይ ወይም በባለቤቱ እጅ/ ሱቆች
ማሕበሩ ስም ብዛት ምድር ቤት 1ኛ ፎቅ 2ኛ ፎቅ 3ኛ ፎቅ
ዕድገት 44 44 1ዐ (23) 1 (23) 1 (23)
ሚሊንየም 33 33 29 (33) 4 3 (33)
ሰላም 35 35 19 (35) ግንባታ ላይ ግንባታ ላይ
አባይ 118 118 ግንባታ ላይ ግንባታ
አላለቀምላይ ግንባታ ላይ
ምንጭ፡ መስክ ዳሰሳ አላለቀም አላለቀም

ከሠንጠረዡ ማየት እንደሚቻለው ሁሉም ምድር ቤት (ground) ላይ የሚገኙ ሱቆች ቢከራዩም አንደኛ ፎቅ
ላይ ግማሽ ያህሉ ብቻ ተከራይቷል፡፡ የተቀሩት ለመጋዘንነት አገልግሎት እየዋሉ ይገኛሉ፡፡ ባለቤቶችም ሆኑ
ተከራዮች የሚመርጡት ምድር ላይ የሚገኙ ሱቆችን ነው፤ ወደ ላይ በተወጣ ቁጥር ገበያው ቀዝቃዛ ስለሆነ
ሱቆቹን የሚፈልጋቸው የለም፡፡ ህንፃዎቹ የተገነቡት የባለ ቤቶቻቸው የስራ ቦታ ፍላጎት ብቻ ለማሟላት
ሳይሆን ለበርካታ የንግዱ ማሕበረሰብ የስራ ቦታ ለመፍጠር ቢሆንም ከፍተኛ የኢንቨስተመንት ሀብት
ፈሶባቸው የተገነቡ ህንፃዎች ውስጥ ሱቆች ተከራይ አጥተው ይታያሉ፡፡ የአከባቢው ልማት ፕላን መኖሪያ
መቀየጥ ባለመፍቀዱ ምክንያት በህናዎቹ ላይ የፈሰሰ ሃብት ለብክነት ዳርጎታል፡፡

184
ስእል 3.47፡ ለዓመታት ሳይከራዩ የሚገኙ ሱቆች (ደሴ)

ምንጭ፣ ከመስክ የተወሰደ፣ ጥር 2008 ዓ/ም


iv. የመሰረተ ልማት አቅም አሟጦ መጠቀም
በየከተሞቹ የተዘረጉ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ሊሰጡት የሚችሉ ጥቅም ለማስገኘት የሚያስችል የግንባታ
ልማት እየተካሄደ ነው፡፡ የመሰረተ ልማት ዝርጋታው የፈጠረው የመሬት የመጠቀሚያ ዋጋ የሚመጥን
የግንባታ ኢንቨስትመንት ለማካሄድ ምክንያት ሆነዋል፡፡ ሐዋሳ ከተማ ላይ የህንጻዎቹ አሰራር ባብዛኛው በፎቅ
ወደ ላይ የተሰሩ እና የመንገድ ግንባር ስፋታቸው ጠበብ ያለ ሆኖ በመሰራታቸው መሰረተ ልማቱን የሚመጥን
ግንባታ ከማከናወን በሻገር የመንግድ መሰረተ ልማቱ በቁጠባ ለመጠቀም የሚያስችል ተሞክሮ ነው፡፡ ይህንን
መለት ደግሞ የመሬቱ/የአካባቢው ምርታማነት ከፍ የሚደርግ መልካም የፕላን ተሞክሮ ሆኖ ታይቷል፡፡

በአንጻሩ በተለያዩ ከተሞች የተለያዩ ውስንነቶች አሉ፤

 በደሴ ከተማ የመንገዶች ዲዛይን ልዩነት ፈጣሪ ሆነዋል፡፡ የመንገዶች ዲዛይን ከመሬት ገፅታ
ስለማይስማማ መንገድ ዳር የሚገኙ በርካታ ይዞታዎችና በላያቸው ላይ ያረፈ ግንባታ እንዲቀበር ወይም
ከላይ እንዲንጠለጠል ስላደረጉት የቋሚ ንብረቱ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ይባስ እንዲጠፋ አድርጎታል፡፡
ከሸዋ በር እስከ ገራዶ መውጪያ መንገድ በሁለቱም ዳር የሚገኙ ቦታዎች የዚህ ችግር ሰለባ ናቸው፡፡
 መቐለ ከተማ ቀበሌ 14 መልሶ ልማት የሚጠይቁ ቦታዎች ባለመልማታቸው ምክንያት ከፍተኛ የመሬት
የመጠቀሚያ ዋጋ ባለው መሬት ላይ ባረጁ ትናንሽ ቤቶች እንዲታሰር ምክንያት ሆነዋል፡፡
 በጅማ ከተማ የሚታይ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከሌሎቹ የመቀዝቀዝ ባህሪ አለው፡፡ በመሆኑም
ከስቴዲየም በሰጦ ቀበሌ እስከ ጅማ የኒቨርሲቲ ዋና ግቢ አካባቢ፣ ከዳውሮ በር እስከ ቶታል
ኮንደሚኒየም፣ ከዳውሮ በር እስከ ቦሬ መስመር፣ እንዲሁም በአጋሮ መስመር ከደጊቱ ሆቴል እስከ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ግቢ ደቡብ ጫፍ የተዘረጉ ዋና የአስፋልት መንገዶችን ተከትሎ የሚካሄድ

185
የግንባታ ልማት እምብዛም በለመሆኑ መሰረተ ልማቱ አሟጦ ለመጠቀም የሚያስችል ዕድል
አልተፈጠረም፡፡

v. አካባቢያዊ ውበትና ደህንነት /Environmental/


መልሶ ልማት የፕላን ህግ እንዲከበር አስችሏል፡፡ አዳዲስ ግንባታዎች የአካባቢ የልማት ፕላን እና የንፃ ግንባታ
መመሪያ ተከትለው ስለሚገነቡ የህንፃዎቹ የከፍታ ዕይታ ውህደት (Pattern) የአካባቢው የዕይታ ውበት
የተዘበራረቀ እንዳይሆን ጠብቆታል፡፡ የግንባታ ልማቱ በአካባቢው ከሚሰሩ የመንገድ መሰረተ ልማት
መመጣጠናቸው በሁለቱም መካከል የተቀናጀ ውበት መፍጠር ችለዋል፡፡ በመልሶ ማልማቱ ሂደት የተገነቡ
ህንፃዎችና በእነዚህ መልሰው የለሙ ሰፈሮች የሚከናወን የኢኮኖሚ ባህሪና የከተሞቹን ተወዳዳሪነት ከፍ
የሚያደርጉ ናቸው፤ ለምሳሌ አዲስ አበባ ለአፍሪካ ህብረት መቀመጫ አትመጥንም፣ ደረጃቸው የጠበቁ
ሆቴሎች ቁጥር ከከተማው አለምአቀፍ ሚና ሲሰላ ከዚህ ግባ የማይባሉ ናቸው፣ ወዘተ የሚሉ ግምገማዎች
በመልሶ ማልማቱ መልስ እየሰጠ ያለ በጎ ሂደት ነው፡፡

መቐለ ከተማ ላይ እንዳ ማሪያም፣ ቀበሌ 14 የተወሰኑ ቦታዎች እና ሌሎች ደረቅ ቆሻሻ በየመንገዱ ዳር
የመድፋት ክስተት አልፎ አልፎ የሚሰተዋል የነበረ ሲሆን አካባቢዎቹ በፕላን እንዲደራጁ መደረጉና የውስጥ
ለውስጥ መንገዶች በጌጠኛ ድንጋይ መነጠፋቸው ኣካባቢው ከቆሻሻ መድፊያነት ታድጎታል፡፡ ቀበሌ 14 እና
እንዳ ማሪያም ባህላዊ መጠጦች በስፋት ይሰራባቸው ስለነበረ በየቦታው መሽናት፣ ቆሻሻ ውሃ መንገድ ላይ
መድፋት የተለመደ ክስተት ነበር፡፡ ባለፉት ዓመታት ሁኔታው በከፍተኛ ደረጃ ተለውጧል፡፡ ያልነበሩ የከተማ
አረጓዴ ቦታዎች እንዲፈጠሩ ካስቻሉ የመልሶ ልማት ጥረቶች የደሴ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ የልደታ
ፕሮጀክት ተጠቃሽ አብነቶች ናቸው፡፡

ሀዋሳ ከተማ ላይ መልሶ ልማቱ ባረጁና ለጤና ተስማሚነት በጎደለው ሁኔታ የውስጥ ለውስጥ መተላለፊያ
እንደልብ በሌላቸው የመሃል ሰፈሮች የተጀመረ ፕሮጀክት በመሆኑ መልሶ ማልማቱ በነዋሪዎች የሚደገፍ
አድርጎታል፡፡ መልሶ ማልማት በተካሄደባቸው ቦታዎች የአከባቢ ንፅህናው እየተሻሻለ በመሆኑ ለእይታም ሆነ
ለጤና ተስማሚ መሆኑ ሌላው የመልሶ ማልማቱ ጅምር እንቅስቃሴ ፋይዳ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡

በሌላ በኩል ውበት እንደተመልካቹ የሚለያይና በወጥነት ለመናገር አዳጋች ይዘት ቢኖረውም በደሴ ከተማ
የአካባ የልማት ዕቅዶች፣ የመንገድ መሰረተ ልማት ዕቅዶች ሲዘጋጁ ከመሬቱ አቀማመጥ ተቀናጅቶ ተጨማሪ
ውበት በሚያስገኝ ስልት ባለመከተላቸው በመልሶ ማልማት የውበት ውህደት እየተፈጠረ አይደለም፡፡
የተገነቡት ህንፃዎች በአብዛኛው የአርባን ዲዛይን ወጥቶ የሚመሩ ባለመሆኑ አንዱ ከአንዱ አይናበብም፤
ከመንገዱና ከክፍት ቦታው ያላቸው መስተጋባር ሳቢነት ይጎለዋል፡፡ በአዲስ አበባ የተገነባው የቀላል ባቡር
መስመርም ተጨማሪ የውበት መፍጠር ይቅርና መንገዱ መስመሩ ከመገንባቱ በፊት የነበረ የውበት ውህደት
እንዲጠፋ ምክንያቶ መሆኑ ብዙዎች የሚተቹት ነው፡፡

186
መልሶ ልማት የተከናወነባቸው አካባቢዎች ከፅዳት ጉድለት ከሚመነጭ አካባቢያዊ ደህንነት ሙሉ በሙሉ
ተላቀዋል የሚባልም አይደለም፤ ገና ያልተፈቱ ችግሮች አሉ፡፡ መቐለ ከተማ ላይ ከሌሎች ከተሞች ይበልጥ
ረጅም መንገድ የተጓዘ ቢሆንም መንገድ ዳር አትክልትና ፍራፍሬ የሚነገድባቸው አካባቢዎች አሉ፡፡ ዕዳጋ ሰኒ
በርከት ያሉ መጋዝኖችና የንግድ ማእከላት በመኖራቸው ምክንያት ጭነት ታሽጐባቸው የሚመጡ የተለያዩ
/የወረቀት፣ ፕላስቲክ፣ ጆኒያ ወዘተ/ ቁሳቁሶች አካባቢውን ሲያቆሽሹት ይታያል፡፡

vi. ማሕበራዊ ደህንነት


በአዲስ አበባ፣ ጅማ እና መቐለ ከተሞች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴአቸው ዓይነት የተለወጡ አካባቢዎች
በመለወጡ ምክንያት ማሕበራዊ ስጋቶች አብረው እንደቀነሱ ነዋሪዎች ይገልፃሉ፡፡ ሁሉንም ዓይነት ወንጀል
/ስርቆት፣ ዝርፊያ፣ አደንዛዥ ዕፆች መጠቀም ወዘተ/ በከፍተኛ ደረጃ እንደቀነሰ ነዋሪዎች ይመሰክራሉ፡፡ መቐለ
ከተማ ላይ ቀበሌ 14፣ እንዳ ማሪያም (ሐውዜን አደባባይ - ደደቢት ማ/ፋይናንስ ዋና መንገድ በስተቀኝ
በኩልና ንግስተ ሳባ ሆቴል በስተጀርባ) እንዳየሱስ (ነባሩ አውቶብስ መናሃሪያ በስተጀርባ) እንደስላሴ
(ሐውዜን ሆቴል- አይናለም ዋና መንገድ በስተደቡብ) አካባቢዎች ሁነኛ ማሰያዎች ናቸው፡፡

vii. ማህበራዊ ውህደት


በኢትዮያ ከተሞች ገቢን ማእከል ያደረገ የማሕበረሰብ የአሰፋፈር ልዩነት መገለጫው አልነበረም መላት
ይቻላል፡፡ ምናልባት አለከተባለም በተወሰኑ የአዲስ አበባ ሰፈሮች እንደሚሆን ግልፅ ነው፡፡ አሁን መልሶ
ልማቱ ማሕበራዊ ልዩነት ጎልቶ እንዲወጣ የሚያስችል ዕድል እየፈጠረ መሆኑ መታየት ጀምሯል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የመልሶ ልማት ፕሮጀክት የተካሄደባቸውን አካባቢዎች ተዘዋውረን ስንመለከት አካባቢው
ሙሉ በሙሉ ተቀይረዋል ማለት ይቻላል፡፡ የመኖሪያ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ንግድ ማዕከልነት
ተለውጠዋል፡፡ ከመልሶ ልማቱ በፊት ዘመናዊና ነባር የኢኮሚ መስኮች፣ ድሃና ሃብታም፣ መኖሪያና ንግድ
ተዋህደው የነበረ ከተማ አዲስ መልክና ቅርጽ (Urban character) እንዲይዝ ያደረጉ የመልሶ ልማት
ፕሮጀክቶች ጥቂት አይደሉም፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ከሚሆኑት የሚሆነው የካዛንችስ ቁጥር አንድ መልሶ ልማት
ፕሮጀክት ነው፡፡ ከመልሶ ልማት በፊት አካባቢውን ያውቅ የነበረ ሰው አሁን ተመልሶ ወደ ካዛንቺስ ቢመጣ
አካባቢውን ቀደም ሲል ያውቀው የነበረውን ነጥብ ለመለየት የሚያስችለው ምልክት በአሁኑ ጊዜ ማግኘት
አይችልም፡፡

ከዛሬ 10 ዓመት በፊት በልደታ መልሶ ልማት ፕሮጀክት ክልል ውስጥ ይኖር የነበረ ግለሰብ፣ ቤተሰብ፣ የንግድ
ተቋም ዛሬ በአካባቢው የማግኘት ዕድሉ እጅግ ጠባብ ነው፡፡ መልሶ ልማት ነባሩን ጠርጎ የሚያስወግድና
ሙሉ በሙሉ አዲስ የመተካት አካሄድ ይጎላል፡፡ ይህ አካሄድ ከቀጠለ ከተማዋ ወደ ማታውቀው
የማሕበረሰባዊ ልዩነት ወደሰፋበት አደረጃጀት (Segregation) እንዳይወስዳት ያሰጋል፡፡ ይህ ኢ-አካታች የሆነ
አካሄድ ታሪክን በመጫን፣ ቅርሶችን በማጥፋትና የከተማዋን እሴት በመሸርሸር ይወቀሳል፡፡

187
viii. የትራፊክ ፍሰት ሰለጤን
መልሶ ልማት አሮጌ ግንባታ በአዲስ ግንባታ ለመተካት የሚከናወን ሳይሆን ሁለንተናዊ የከተማ ፕላን ጤንነት
ለማረጋገጥ የሚከናወን በመሆኑ የአካባቢ የልማት ዕቅዶቹ ከፈቱዋቸው መሰረታዊ ጉዳዮች የትራፊክ
እንቅስቃሴ መሆኑ አስረገጦ መናገር ይቻላል፡፡ በመሆኑም ፕላን ሳይዘጋጅ በተናጠል የተከናወኑትና በአግባቡ
ባለመመራቱ ምክንያት ፕላን የጠሰው የካሳንችስ ቁጥር አንድ ከተፈጠረው የትራፊክ መጨናነቅ ውጭ
መንገዶች ስፋታቸው፣ ደረጃቸውና አደረጃጀታቸው ተሻሽሏል፤ በአንድ አቅጣጫ ብቻ ሲያስኬዱ የነበሩ
መንገዶች በሁለት አቅጣጫ የሚያስኬዱ ሆነዋል፤ የትራፊክ ፍሰቱ የተሳለጠ እንዲሆንም እያስቻለ ይገኛል፡፡

የታክሲ ስምሪትና ማቆምያ ቦታዎች ባለመኖራቸው የትራፊክ ፍሰቱ የተሳለጠ እንዳይሆን ከፍተኛ ተግዳሮት
በሆኑበት አካባቢዎች የመሬት አጠቃቀም ለውጥ ተደርጎ ግንባታዎች በማፍረስ ያልነበሩ የታክሲ የስምሪት ቦታ
እንዲኖና የትራፊክ ፈሰቱ የተሳለጠ በማድረግ የመቐለ ከተማ ተጠቃሽ መልካም ተሞክሮ ነው፡፡ አዲስ አበባ
ከተማ ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተካሄዱና በመካሄድ ላይ የሚገኙ መልሶ ልማቶች ሁሉን አቀፍ ይዘት
እንዲኖራቸው ሆነው የመታቀዳቸው ያህል የትራፊክ ፍሰት የሚያሻሽሉ የመንገዶ ማስፋትና ደረጃቸውን
ማሳደግ እንዲሁም የህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች የስመሪትና ማቆሚያ ቦታዎች በቁጥርም ሆነ
በማስተናገድ ዓቅም እንዲሻሻል አድርጓል፡፡ በሌሎች ከተሞችም ቢሆን ተመሳሳይ ቦታዎች እንደሚኖሩ በፕላን
ደረጃ ተለይተው ተቀምጧል፡፡

ለምሳሌ መቐለ ከተማ ላይ በዋናነት ቀበሌ 14 እና እንዳ ስእል 3.48፡ መቐለ ቀበሌ 14 ላይ የተሰራ አዲስ
ማሪያም፣ ሌሎች ነባር ሰፈሮች ደግሞ ባጠቃላይ በስርዓቱ አደባባይና የሰፋ መንገድ

ያልተደራጁ፣ እጅግ ጠባብና ለትራፊክ ፍሰት የማይመቹ


ነበሩ፡፡ መልሶ ልማቱ የመንገዶቹ አጠቃላይ አደረጃጀት
የትራፊክ ፍሰቱ የተሳለጠ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በተለይ
ቀበሌ 14 የተሰራ በአርአያነት የሚጠቀስ ነው፡፡ አካባቢው
ከነባሩ አውቶብስ መናሀሪያ፣ ከጎዳና ሰላም በሁለት
አቅጣጫዎች፣ ከሚላኖ ሆቴል ቀለበት መንገድ
የሚያገናኙ ሰፋፊ መንገዶች በመከፈታቸው ተደራሽነቱ
ከሮማናትና ዘስላሰ አደባባዮች፣ ከቀለበት መንገድ
ተሻሽለዋል፡፡ የውስጥ ለውስጥ መዳረሻ መንገዶችም
እንዲሁ፡፡ ቀበሌ 14ና እንዳ ማሪያም (ንግስተ ሳባ ሆቴል -
ደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ዋና መንገድ በስተቀኝ በኩል)
አካባቢዎች የሚገኙ የመዳረሻ መንገዶች በሁለት
ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ ታሕሳስ 2008
አቅጣጫ ትራፊክ የማስተናገድ ዓቅም ፈጥረዋል፡፡ ለእግር ዓ/ም

188
መዳረሻነት ብቻ ሲያገለግሉ የነበሩ መንገዶች ቢያንስ በአንድ አቅጣጫ ተሸከርካሪ እንዲያስኬዱ ሆነው
ሰፍቷል፡፡

ባጠቃላይ ሁሉንም ከተሞች ላይ በፕላን ሳይደራጁ ለዘመናት የኖሩትን ሰፈሮች ፕላን ጠብቀው እንዲስተካከሉ
መደረጉ የመንገዶች አደረጃጀት እና ቅርፅ ተስተካክሏል፡፡ የትራፊክ ፍሰቱ ዕይታ ጨምሯል፡፡

ix. ታሪክና ቅርስ ጥበቃ/ History Preservation/


ታሪክና ቅርስ ጋር በተያያዘ ሁሉም ቅርስ ነው አይነካ ከሚለው ጫፍ ተነስቶ ይህ አመለካከት ድህነትም ታሪክ
ነውና ይጠበቅ እንደ ማለት ነው ብሎ በማየት ሁሉን መጥፋት እንዳለበት የሚሰብክ ሁለት ጫፍ የነካ አተያይ
በኢትዮጵያ ከተሞችም የተንጸባረቀና የተሞከረ ጉዳይ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ጫፎች የሚያስማማ ልማትም
ቅርስ መጠበቅም ሊታሰብ ይገባል በሚል ደግሞ ሚዛኑ ወዴት በምን መስፈርት የቱ ቅርስና ስንት መቶኛ ቅርስ
ተብሎ ይያዝ የቱ በምን ደረጃ ይቀየር ወዘተ በሚል በስፋት የሚኬድበት ስልት ነው፡፡ በዚህ ስልት ራሱ
ሚዛኑ ወዴት እንደሚያመዝን ብዙ ማንሳት ይቻላል፡፡

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ስለ ታሪካዊ ቦታና ግንባታ አጠባበቅ አሁንም ወጥ አቋም አልተወሰደም በሙሉ
ይፍረስና እንደ አዲስ ይልማ ከሚለው ጀምሮ አይነካ የሚል ጫፍም የተሞከረበት ነው፡፡ ለምሳሌ በመቀሌ
ቀበሌ 14 ሳይነካ ይቆይ የሚል የፕላን ሃሳብ ተይዞ ልማት ለረጅም ጊዜ ተገድቦ ነበር፡ በሌላ መልኩ በደሴ ይህ
ነው የሚባል የሚጠበቅ ቤት አልተስተዋለም፡፡ የማቀላቀል ሃሳብና ሙከራም አለ፤ ለምሳሌ የመቀሌ ገበያ
መልሶ ልማት በዙሪያው ነባሩ ግንባታ ተጠብቆ ማሀሉ መልሶ መገንባት በአዲስ አበባም የተወሰኑ ህንጻዎች
ለይቶ መጠበቅ አለ፡፡ ወጥ መስፈርትና አቋም የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡ በታሪካዊነቱ የተለየ ህንጻን ማለፍ
ጅምር ቢታይም /ትኩረት አለመስጠት፤ ልማቱ ነባሩን ታሪካዊ ህንጻ በሚያኮስስ ለምሳሌ አዲስ አበባ
የቀድሞው ማዘጋጃ፤ ወጥ አቋም አልተወሰደም በሙሉ ይፍረስ በሚል በደሴ በአዲስ አበባም በአመዛኙ
መፍረስ ላይ ማዘንበል፤ በስፋት ታይቷል፡፡

በታሪክና ቅርስ ልየታና አጠባበቅ ወጥነት ባይታይም የመቐለ ከተማ ተሞክሮ በአስተማሪነቱ ሊታይ የሚችል
ነው፡፡ የቀበሌ 14 እና እንዳየሱስ አካባቢ ልማት ፕላኖች ሲዘጋጁ ለቅርስና ታሪክ ጥበቃ ተገቢውን ትኩረት
የሰጡ ነበሩ፤ መነሻውም 1998 ዓ/ም የተዘጋጀው የከተማው መዋቅራዊ ፕላን መነሻ ማዐቀፍ በመስጠቱ ነው፡፡
በተለይ ቀበሌ 14 ከተማው የተመሰረተበት አካባቢ በመሆኑ የቤቶቹ ገፅታና የግንባታ ግብአት በዘመኑ የነበረ
የስነ-ህንፃ ጥበብ ማሳያዎች በመሆናቸው አካባቢው በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ፈርሶ እንዲገነባ ሲወሰንና
መዳረሻ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ሲዘረጉ በቅርስነት መጠበቅ ያለባቸው ህንፃዎች ተለይቷል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ቀበሌ 14 በሙሉ በቅርስነት እንዲጠበቅ ለማድረግ አካባቢው በሂደት ሲሻሻልም


ከባለሁለት ፎቅ በላይ ህንፃዎች እንዳይገነቡ የህንፃ ቁጥጥር እንዲደረግበት በአካባቢ ልማት ዕቅዱ ማስፈፀሚያ
ስትራተጂ ተቀምጠዋል፡፡ ለግንባታ የሚውሉ ግብአቶች ቢያንስ 50% ያህሉ ከአካባቢው የሚገኝ ዓይነት

189
እንዲሆን፣ “የህድሞነት” ገፅታው እንደጠበቀ የቤቱ ክዳን ቆርቆሮ ወደ ውጭ እንዳይታይ የሚሉት የግንባታ
መስፈርቶች ተቀምጠውለታል፡፡ ነገር ግን ታሪክና ቅርስ ለመጠበቅ በእቅድ ደረጃ የተቀመጡ ስልቶች በጥብቅ
ዲሲፕሊን እየተፈፀመ እንዳልሆነ አመላካቾች አሉ፡፡ እየተገነቡ ያሉ ህንፃዎች በልማት ዕቅዱ ላይ የተቀመጡ
ገደቦች የተከተሉ አይደሉም፡፡

በሌሎች ከተሞች የሚካሄዱት የመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች በከተሞቹ የሚገኙትን ቅርሶች በአግባቡ
ከመለየትና ከመጠበቅ አኳያ ተገቢ ጥንቃቄ እየተወሰደ ኣይደለም፡፡ መልሶ ልማቱ አጠገቡ የሚገኙ በቅርስነት
ሊገለፁ የሚችሉ ይዞታዎች ከማጎልበት ይልቅ የማኮስስ ባህሪ ይስተዋላል፡፡ የከተማው ልዩ መገለጫ ለይቶ
በመጠበቅም እንዲሁ ውስንነት አለ፡፡ በድሬዳዋ ከተማ የአካባቢ የልማት ዕቅዶች ሲዘጋጁ ለቅርስ ጥበቃ
ተገቢውን ትኩረት አልተሰጠም፡፡ በከተማ ደረጃ የከተማው መገለጫ ተብለው የሚታሰቡ ይቅርና እንደ ሀገር
በቅርስነት የተመዘገቡትንም ጭምር በመልሶ ልማት ምክንያት እየፈረሱ ነው፡፡

የደሴና የጅማ ከተሞች መዋቅራዊ ፕላን ሰፊ መልሶ ልማት እንደ ሚኖር ታሳቢ ሲያደርጉ ለቅርስና ታሪክ
ጥበቃ የሰጡት ትኩረት ስለመኖሩ መረጃ አልተገኘም፡፡

በቅርስና ታሪክ ጥበቃ ሊወሰድ የሚገባው ትምህርት ከቅርስና ታሪክ ጥበቃ እና ማጎልበት በመርህ ደረጃ
ያልተፈታ መሆኑ፤ በበቂ የሕግ ማዕቀፍ ድጋፍም ያልተሸፈነ መሆኑ አንድም በቅርስነት ምክንያት ልማትን
የሚገድብበት፣ በአንፃሩ ደግሞ የከተሞቹ ልዩ መገለጫዎች እንዲሁም በአገር ደረጀም ጭምር በቅርስነት
የተመዘገቡ የሚወድሙበት ሁኔታ እየታየ ነው፡፡ ስለሆነም በፌደራል የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን የሚመዘገቡ
ቦታዎችና ህንፃዎች እንደተጠበቁ ከዚህ ውጭ ከተሞች መገለጫቸው የሆኑ ቦታዎችና ግንባታዎች በቅርስነት
ለመያዝና ለመጠበቅ የሚያስችል አሰራር የለም፡፡ ምን ዓይነት መስፈርት የሚያሟሉ ቦታዎችና ግንባታዎች፣
ምን ያህል ስፋት፣ ታሪካዊ ቦታዎችና ህንፃዎች የመለየት ስልጣን ወዘተ በሕግ አግባብ መወሰንም ይጠይቃል፡፡

x. የሚገነቡ ቤቶች ከዘላቂነት አንፃር፡ ነገን ታሳቢ ያላደረገ ግንባታ


በደሴ ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ የሚገኘው የመልሶ ማልማት እንቅስቃሴ በተሰሩበት ጊዜ መልሶ ማልማት
የሚያስፈልጋቸው መንደሮች እየተፈጠሩ ይገኛሉ፡፡ አዲስ በሚገነቡ ምትክ የቀበሌ ቤቶች ጠባብ (16 እስከ 24
ካሬ ሜትር) ሲሆኑ ቤተሰቡ የማስተናገድ ዓቅም የላቸውም፡፡ የቤቶቹ አሰራር ከነባሮቹ በባሰ የተፋፈጉና
የተጨናነቁ ናቸው፡፡ ለግንባታቸው ግብአት የዋለው እንጨትና ቆርቆሮ ከድሮ የቀበሌ ቤቶች የፈረሰ ነው፡፡
መልሶ ማልማት ለከተማው ተጨማሪ የልማት ዓቅም ከመፍጠር መሰረታዊ ስህተቶች እየተከሰቱበት ነው፡፡
የደሴ ከተማ መልሶ ማልማት መሰረታዊ ከሚባሉ ጉድለቶች መካከል የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡

190
xi. የመኖሪያ ቤት ፍላጎት መልስ ከመስጠት አኳያ
ከከተማ መልሶ ማልማት ፕሮግራም ቁልፍ ዓላማዎች መካከል ያረጁ አካባቢዎችን መልሶ በማደስ
የአካባቢውን ገጽታ ማሻሻል፣ ከደረጃ በታች በሆነ አገልግሎት የተያዘ የከተማ ቦታን ለተሻለ አገልግሎት
ማዋል፣ የመሰረተ ልማት አውታሮችን ማሻሻል፣ አካባቢዎቹ ለኑሮና ለሥራ የተመቸ ጤናማ ማድረግ የሚሉት
ሲሆኑ የእነዚህ ዓላማዎች የመጨረሻ ግብ የነዋሪዎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍታት መሆኑ
የሚያከራክር አይደለም፡፡ ይኸውም መልሶ ልማት በከተመው የሚታይ ቁልፍ ችግርን መፍታት
ይጠበቅበታል፡፡ ስለዚህ መልሶ ልማት ቁልፍ ችግሮችን ከመፍታት አኳያ በሁለት መስፈርቶ ተዳሷል፤
የመኖሪያ ቤት እጥረት በመቅረፍ እና የልማት ተነሺዎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት፡፡

በከተሞች የመኖሪያ ቤት እጥረት ዘለመናት የተከማቸ መሆኑ የተለያዩ አካላት በተለያዩ ጊዚያት የተከናወኑ
ጥናቶች ያለመክታሉ፡፡ በከተሞ ሰፊ መልሶ ልማት እንዲከናወን ካደረጉት ቁልፍ ምክንያቶችም የመኖሪያ ቤት
ፍላጎቱ በየወቅቱ ስላልተመለሰ ከተሞቹ በአብዛኛው በሕገወጥነት፣ ሕጋዊም ቢሆን ያለ ፕላን የተመራ ስለነበር
ከጅምሩ ጎስቋላ ሰፈሮች መስፋታቸው ነው፡፡ ስለዚህ መልሶ ልማት ለዘመናት የተከማቸ ይህንን ቁልፍ ችግር
መፍታት ከቀዳሚ ግቦቹ ኣንዱ መሆኑ ግንዛቤ ተወስዷል፡፡

በከተሞቹ እየተካሄደ የቆየው መልሶ ልማት የመኖሪያ ቤት ችግሩ ከመፍታት በአወንታም በአሉታም የሚገለፁ
ውጤቶችን ይታዩበታል፡፡ አወንታዊ ጎኑ በመልሶ ልማት ምክንያት የሚፈርሱ ቤቶች በጋራ የመኖሪያ ቤቶች፣
እንዲሁም /ተከራዮችም ሳይቀር/ የልማት ተነሺዎቹ በከተማው የሽንሻኖ ደረጃ ቤት እንዲገነቡ በማድረግ
ለመተካት ይሰራል፡፡

ይሁን እንጂ አጠቃላይ የቤት አቅርቦቱ በየጊዜው የሚፈጠረው ፍላጎት መመለስ ይቅርና በመልሶ ልማቱ
ምክንያት ለሚፈርሱ የሚተካ ኣይደለም፡፡ የዚህ ምክንያትም በሁለት አቅጣጫ የሚታይ ነው፡፡ አንዱ
ምክንያት በመልሶ ልማት የሚከናወን የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ መጓተት ነው፡፡ ለምሳሌ ባለፉት ስምንት
ዓመታት አዲስ አበባ ላይ የተከናወኑት 24 የመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች ከመኖሪያና ሥራ ቦታቸው 25ሺ
በላይ አባወራዎች እነዲፈናቀሉ ሲያደርጉ ከነዚህ የልማት ተነሺዎች የኮንዶሚኒየም ቤት ያገኙት 11,998 ብቻ
ናቸው፡፡ ይኸው ብቻም ሳይሆን በከተማይቱ በተለያዩ የቤት ልማት ኣማራጮች የተመዘገበው የቤት ፈላጊ
ከ800 በላይ ሆኖ ላለፉት አስር ዓመታት የተገነቡት የጋራ የመኖሪያ ቤቶች በዛት ግን ከ350 በላይ ኣይደለም፡፡

ሁለተኛው/ምናልባትም ዋነው ጉዳይ ደግሞ ከመሬት አጠቃቀም ፕላን ለውጥ ተያይዞ የሚከሰት ነው፡፡
በሁሉም ከተሞች ሲከናወኑ የቆዩ የመልሶ ልማት ፕሮጀክቶች መኖሪያ ሰፈሮች ወደ ንግድ አገልግሎት የቀየሩ
ናቸው፡፡ ይህንን ችግር በሁሉም ከተሞች በተመሳሳይ ደረጃ የሚታይ ቢሆንም ተጨባጭ ምስሉ የተሟላ
መረጃ ከተገኘባቸው የደሴና መቐለ ከተሞች በማሳያነት ወስዶ መረዳት ይቻላል፡፡

191
በደሴ ከተማ ሰፊ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ከፍተኛ ነው፡፡ የከተማው የህዝብ ብዛት 1999 ዓ/ም ከነበረበት
151,904 (30,218 ቤተሰብ) በ2012 ዓ/ም 280,874 (50,323 – 56,175 ቤተ ሰብ) ይደርሳል ተብሎ
ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪ የቤተ ሰብ ምስረታ ዕድገት ፍጥነት (rate) ከጠቅላላ ህዝብ ዕድገት ፍጥነት በላይ
ይሆናል ተብሎ ስለሚጠበቅ በየዓመቱ የሚፈጠር አዲስ የቤተሰብ ቁጥር ሲጨምር የቤት ፍላጎቱ አብሮ
ያድጋል፡፡ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለማስላት የተለያዩ ምክንያታዊ ታሳቢዎች ከግምት ገብተዋል፡፡
i. እስከ 1995 ዓ/ም ድረስ የተንከባለለ 3,600 የቤት ፍላጎት እንዳልተመለሰ የሚታወቅ መሆኑ፣
ii. 1996 ዓ/ም እስከ 2001 ዓ/ም በድምሩ 12,163 ቤት መስሪያ ሽንሻኖዎች በየዓመቱ የነበረ የቤት ፍላጎት
እንደመለሰ በማሰብ፣
iii. 4,000 ያረጁ ቤቶች መፍረስ እንደሚገባቸው በመዋቅራዊ ፕላን ጥናቱ የተጠቆሙ እንደሚፈርሱና
መተካት እንደሚያስፈልጋቸው በመቀበል፣
iv. በአንድ ቤተሰብ ውስጥ በአማካይ 5 ሰው እንደሚቀጥል ታሳቢ በማድረግ፣
v. ለአንድ ቤተ ሰብ አንድ ቤት መስሪያ ፕሎት እንደሚያስፈልግና ዕድሜአቸው 18 ዓመት የሞሉ በትዳር
ውስጥ እንደሚኖሩ ግምት በመውሰድ፤
ከ1999 ዓ/ም እስከ 2012 ዓ/ም 20,105 እስከ 25,957 አዲዳስ ቤተሰቦች ይመሰረታሉ (2.5 ዝቅተኛ የህዝብ
ዕድገት እና 3.75 ከፍተኛ የህዝብ ዕድገት በቅደም ተከተል)፡፡ ስለዚህ አጠቃላይ የቤት ፍላጎቱ 27,705 -
33,557 ይሆናል፡፡ የከተማው ዝቅተኛ የመኖሪያ ቤት ሽንሻኖ ስፋት 171 ካሬ ሜትር በመውሰድ የመኖሪያ ቤቱ
ፍላጎት ለመመለስ 473.76 እስከ 573.83 ሄክታር መሬት ያስፈልጋል፡፡ የከተማ ፕላን ስትራተጂ መተግበር
የማይታለፍ በመሆኑ ካጠቃላይ የሚለማው ግንባታ የሚያርፍበት ስፋት 40% ነው፡፡ ስለዚህ የቤት ፍላጎቱ
ለማሟላት 1,184.4 እስከ 1,434.56 ሄክታር ተጨማሪ መሬት ከማስፋፊያ ቦታ መገኘት ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን
ይህን ያህል ማስፋፊያ በደሴ ከተማ ማግኘት እጅግ ከባድ ነው፡፡ በአንድ በኩል ይህንን ያህል ሰፊ መሬት ካሳ
ለመክፈል የከተማ አስተዳደሩ ዓቅም ላይፈቅድ ይችላል፡፡ በሌለ በኩል የከተማውና ዙሪያው የመሬት
አቀማመጥ ከተማውን ወደጎን ለማስፋት የሚመች አይደለም፡፡

ይህ ሁሉ በድምሩ ሲታይ መልሶ ማልማት በደሴ ከተማ ሲታቀድ የከተማው ተጨማሪ የመኖሪያ ቤት
ፍላጎትም ሆነ መልሶ ማስፈር መስተናገድ የሚችለው በመሃል ከተማ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ መሆን
ነበረበት፡፡ በአንፃሩ በመሃል ከተማ የመኖሪያ አካባቢዎች እየፈረሱ ከመኖሪያ ውጭ ለሆኑ አገልግሎቶች
እንዲውል እየተደረገ ነው፡፡ በደሴ ከተማ አራዳ ከመንገድ በላይ የነበረ የመኖሪያ አካባቢ ሙሉ በሙሉ ወደ
ንግድና፣ አረንጓዴ ቦታዎች፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ማምረቻነት ተለውጧል፡፡ በተመሳሳይ ከሸዋ በር እስከ ገራዶ
ጫፍ መንገድ ዳር የሚገኙ ብሎኮች ለግንድና አገልግሎት ታቅደዋል፡፡ ፒያሳ ከበደ አበጋዝ ሆቴል ፊት ለፊት
የነበሩ መኖሪያ ቤቶች ፈርሰው ቦታው ለኢትዮ ቴሌኮም ሕንፃ ተመድቧል፡፡

192
ስእል 3.49፡ የደሴ ከተማ የህዝብ ብዛትና ዕድገት 1976-2012

ምንጭ፡ ከደሴ መዋቅራዊ ፕላን የቤት ጥናት መረጃ ገፅ 28-32 የተቀመረ

መቐለ ለመልሶ ልማት የተጠኑ የአካባቢ የልማት ዕቅዶ የመኖሪያ አካባቢዎችን ሙሉ በሙሉ ወደ ንግድ
ማዕከልነት ቀይረውታል፡፡ ቀበሌ 14፣ በእንዳማሪያም እና ከሓውዜን አደባባይ ወደ ደጀን በሚወስደው መንገድ
መካከል የሚገኘውን አካባቢ፣ በኲሓ ዋና መንገዱ ሁለቱም ዳርቻዎች ለሚገኙ አካባቢዎች የተዘጋጀው
የመሬት አጠቃቀም ሙሉ በሙሉ ለንግድና አገልግሎት እንዲውል ተወስኗል፡፡

ምንም እንኳ የተወሰኑ ቦታዎች /መንገድ ዳር፣ በንግድ ማእከላት አጠገብ የሚገኙ/ ለንግድ አገልግሎት መከለል
በከተማ ፕላን የተለመደ ቢሆንም መልሶ ልማት የከተማው ቁልፍ ችግር የሆነውን የመኖሪያ ቤት እጥረት
ግምት ውስጥ አስገብቶ በሂደት እጥረቱን ካልቀረፈ ችግር ፈቺነቱ የተሟላ አይሆንም፡፡ የከተማውን መዋቅራዊ
ፕላን የመሬት አጠቃቀም መሠረት አድርጎ ተግባራዊ የሚደረግ የመልሶ ልማት ነዋሪዎችን ከመሃል ከተማ
ጠርጎ የሚያስወጣ ሆኗል፡፡ ለቀበሌ 14 የተዘጋጀውን የአካባቢ ልማት ፕላን መሬት አጠቃቀም አሁን መሬት
ላይ ካለው የመሬት አጠቃቀም በማነፃፀር የዚህን ክስተት አይቀሬነት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

ስእል 3.50፡ የቀበሌ 14 ነባር የመሬት አጠቃቀም

የመኪና ማቆምያ
የንግድ ኣካባቢ
ማህበራዊ ግልጋሎት
መኖሪያ
ቅይጥ አገልግሎት

193
ስእል 3.51፡ በቀበሌ 14 የአካባቢ ልማት ፕላን መሠረት አዲሱ የመሬት አጠቃቀም


ንግድ


  ቅይጥ አገልግሎት
Selam Street   
  
ማሕበራዊ አገልግሎት
 

  

 


ፓርክና አረንጓዴ ቦታ
 

 ታሪካዊ ቦታ



Hakfen Street



ምንጭ፡ የቀበሌ 14 የአካባቢ ልማት ፕላን (መቀሌ)

በነባሩ የመሬት አጠቃቀም ካርታ እንደተመለከተው ከቀበሌ 14 ክልል ከ50% በላይ የሚሆነው በመኖሪያ
የተያዘ ነበር፡፡ አዲሱ ቅይጥ መሬት አጠቃቀም ውስጥ የሚካተት እስካልሆነ ድረስ የመኖሪያ አቅርቦት
የሚያበረታታ ዕድል ጠባብ ነው፡፡ በመሆኑም ቀበሌው ሙሉ በሙሉ የቢዝነስ ማዕከል መሆኑ አይቀርም፡፡
ከቦታው ማዕከላዊነትና ከመሬት የሊዝ ዋጋ ከፍተኝነት አኳያ ባለሃብት ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው
የህ/ሰብ ክፍሎች መኖሪያ ቤት በቀበሌ 14 ያቀርባል ተብሎ አይጠበቅም፡፡

ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው የከተማውን ነዋሪዎች ከመሃል ከተማ ጠርጎ የማስወጣት እርምጃ የሚጀምረው
በፕላን ዝግጅት ወቅት መሆኑን ነው፤ ብዙ ጊዜ የከተሞችን ፕላን ከተማን ከማዘመን ፍላጎት አኳያ የሚቃኝ
በመሆኑ የተለያዩ የማህብረሰብ ክፍሎችን ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ ረገድ ክፍተቶች የሚታዩበት መሆኑን
የቀበሌ 14 ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ ነገር ግን ሚዛኑን ያልጠበቀ፣ ነባራዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ ያላደረገ ፕላንም ሆነ
መልሶ ማልማት የመሃል ከተማው ውጤታማ ለሆነ አገልግሎት ስለመዋሉን አያረጋግጥም፡፡

እላይ በቀረበው የአካባቢ ፕላን መሬት አጠቃቀም መልሶ ልማቱ ተግባራዊ ሲደረግ ቀበሌ 14 ቀን የሞቀ
እንቅስቃሴ የሚታይበት፣ ሌሊት ጭር የሚል ሙት ከተማ ወደመሆን መሸጋገሩ አይቀሬ ነው፤ የአዲስ አበባው
መርካቶ ዓይነት የከተማ ሕይወት ማለት ነው፡፡

በከተማው ማዕከላዊ ክፍል ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት ፍላጎት


የሚያስተናግድ በቂ ቦታ በፕላን እስካልተከለለ ድረስ በመልሶ ልማቱ ሂደት የኑሮ መሠረታቸው ከመሃል

194
ከተማ ጋር የተሳሰረ ቤተሰቦች የሚኖራቸው ዕጣ ፋንታ ለዘመናት ከኖሩበት አካባቢ መፈናቀል ብቻ ነው፡፡
ይህ እርምጃ የሚያፈናቅላቸው ከመኖሪያቸው ብቻ አይደለም፤ ከስራና ገቢያቸው ጭምር እንጂ፡፡ የመሃል
ከተማውን የሞቁ የንግድ ማእከል የሚያደርጋቸው በመልሶ ማልማት ትልልቅ የንግድ ተቋማት ወደዚህ አካባቢ
የሚሰባሰቡበት ሁኔታ ስለሚፈጠር ብቻ ሳይሆን በቦታ በቂ ነዋሪ መኖር ሲችል ጭምር ነው፤ አሁን እየሆነ
ያለው ግን ነዋሪውን ከመሃል ከተማው እያወጡ የንግድ ተቋማትን ወደ መሃል ከተማ ማምጣት ነው፡፡

በመቀሌ ከተማ 18 ዓመት የሞላቸውን ልጆች ሳይጨምር ከ2,970 ቤተሰቦች በላይ በመልሶ ማልማት ከቤት
ንብረታቸው ተነስተዋል፤ በመስክ ጉብኝት ማረጋገጥ እንደተቻለው የልማት ተነሺዎች ምትክ ቦታ የተሰጣቸው
በመሃል ከተማና በመስፋፊያ አካባቢዎች ነው፡፡ እንደ አቡነ-አረጋዊ ባሉ አካባቢዎች በነበሩበት አካባቢ
መልሰው እንዲሰፍሩ (ቦታ እንዲያገኙ) የተደረጉ የልማት ተነሽዎች ከሞላ ጐደል ሁሉም በተሰጣቸው ቦታ ላይ
ቤት ገንብተው መኖር ጀምረዋል፡፡ በተለይ ቅድመ- ታሪካቸው አርሶ አደር የሆኑ በነበሩበት አካባቢ መሬት
ሲሰጣቸው እዛው ቤት የመስራትና የመኖር ዕድላቸው ሰፊ እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በሌላ በኩል ከኖሩበት አካባቢ ርቀው በከተማው ዳርቻ ተለዋጭ መሬት ከተሰጣቸው እጅግ የሚበዙት
በቦታው ላይ የሉም፡፡ ለምሳሌ በሰውሔ ንጉስ ምትክ ቦታ የተሰጣቸው የልማት ተነሽዎች በምን ደረጃ ላይ
እንደሚገኙ ብናይ ጥሩ ማሳያ ሊሆነን ይችላል፡፡ በሰውሔ ንጉስ አካባቢ በ2ዐዐ5 ዓ/ም ምትክ ቦታ
ከተሰጣቸው የልማት ተነሺዎች አንዱም ቤት ሰርቶ አልገባም፤ ለዚህ ጥናት መረጃ ለማሰባሰብ የመስክ ጉብኝት
በተካሄደበት ጊዜ በአካባቢው ለልማት ተነሺዎች በተመደቡ አራት ብሎኮች ውስጥ ሦስት ቤቶች ብቻ
ተጠናቀው ሰው የገባባቸው ሲሆን ሌሎች 5 ቤቶች ግንባታ ላይ ነበሩ፤ ከዚህ ውጭ አካባቢው ምንም ዓይነት
እንቅስቃሴ አይታይበትም፡፡ በሌላ በኩል በአሁኑ ጊዜ በሰውሔ ንጉስ አካባቢ ቤት ሰርተው መኖር
የጀመሩትም ሆኑ ግንባታ በማካሄድ ላይ የሚገኙት ሁሉም ከልማት ተነሽዎች መሬት ገዝተው የገቡ
መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ የሚያሳየው ከመሃል ከተማ ተነስተው በመስፋፊያ አካባቢ ምትክ ቦታ
ከሚሰጣቸው የልማት ተነሽዎች መካከል አብዛኞቹ በተሰጣቸው ቦታ ላይ ቤት ሰርተው እንደማይኖሩ ነው፡፡
ምንም እንኳ በዚህ ጥናት ሰዎቹን አግኝቶ ምክንያታቸውን ማወቅ ባይቻልም አንድም ከኖሩበት መሃል ከተማ
ርቀው መሄድ አልፈለጉም አለበለዚያ የሚሠጣቸው ገንዘብ ቤት ሰርቶ ለመግባት ስለማይበቃቸው ቦታውን
ለሶስተኛ ወገን አስታልፈው ጊዝያዊ ችግራቸው ለመፍታት አውለውታል ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ክስተት
የመልሶ ልማት ፕሮግራሞችን ችግር ፈችነት ጥያቄ ውስጥ የሚጥለው ነው፡፡

የልማት ተነሺዎች ኢኮኖሚያዊ ህልውና

በከተሞች ተንሰራፍቶ የቆየውን የሰፈሮችና ቤቶች እርጅና በመቅረፍ በኩል የመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች
ያስገኙት ውጤት ቀላል አይደለም፡፡ በተለይ አዲስ አበባ ከተማ ዓለምአቀፍ ገፅታወ ለመለወጥ እያስቻላት
መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ በልደታ፣ በካዛንቺስ፣ በቸርቸር ጎዳና፣ በኃይሌ ገ/ሥላሴ ጎዳና እና በመገናኛ

195
አደባባይ ዙሪያ የተካሄዱ የመልሶ ማልማት ፕሮግራሞች የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታን በመቀየሩ ረገድ ከፍተኛ
አስተዋጽኦ ማድረጋቸው አያጠያይቅም፡፡ ደሴና ጅማ ከተሞችም ተመሳሳይ ነው፡፡

በየከተማው የተካሄዱና በመካሄድ ላይ የሚገኙ የመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶቸ የከተሞቹ ገጽታ ከመቀየር አልፎ
የከተሞቹ ኢኮኖሚ እንዲጎለብትም እያደረገ ይገኛል፡፡ ይሁን መልሶ ልማት በድምር ለከተሞቹ ያስገኘውን
ጥቅም ያህል ለልማት ተሸዎች አስገኝቷል ለማለት አያስደፍርም፡፡ መልሶ ልማቱ ከፍተኛ ማህበራዊና የልማት
ከልማት ተነሺዎች በኩል ኢኮኖሚያዊ ዋጋ እያስከፈለም ነው፡፡

መልሶ ልማት ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች በስፋት የሚፈናቀሉት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች
ናቸው፤ ይኸውም የመልሶ ማልማት የሚካሄድባቸው አካባቢዎች በአብዛኛው የሚመደቡት ለከፍተኛ የልማት
ፕሮጀክቶች እንደመሆኑ መጠን በእነዚህ ፕሮጀክቶች የሚከናወኑ ግንባታዎች ለድሃው የህብረተሰብ ክፍል
የኑሮ መሠረት ለሚሆኑ የኢኮኖሚ ተቋማት የሚውሉ አይደሉም፡፡ በመሆኑም የመልሶ ማልማቱን ተከትሎ
በሚመጣው የኢኮኖሚ መዋቅር የማይታቀፈው የሕብረተሰብ ክፍል አካባቢውን ለቆ ለመውጣት ይገደዳል፡፡
በተግባር የሆነውም ይኸው ነው፤ ለምሳሌ የካዛንቺስ ቁጥር አንድ ፕሮጀክት በተካሄደበት ክልል ይኖር የነበረ
ማህበረሰብ የተለየ ሥልጠናና ልዩ የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ ካልተደረገለት አሁን በቦታው ላይ በመጣው
የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አካል መሆን የሚችልበት ዕድል ይኖራል ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡

ዋነኛው የደሴ ከተማ የኢኮኖሚ መሰረት የንግድና አገልግሎት ዘርፎች ናቸው፡፡ ሰፊው ነዋሪ የሚሸከመው
በመደበኛው ኢኮኖሚ ያልተመዘገበ ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ ለመደጎም በሚያስችል ስራ የሚፈረጅ የንግድና
አገልግሎት ዘርፎች ላይ ነው፡፡ ዕድሜአቸው 10 ዓመትና በላይ ከሆኑ ዜጎች በመደበኛ ኢኮኖሚው
ያልተመዘገቡ (Informal) ንግድና አገልግሎት ዘርፎች 38.8% ያህሉ (ወንዶች 37.6%፣ ሴቶች40.3%)
ነዋሪዎች ተሸክሟል፡፡ ይህ አሃዝ ከሀገራዊ አማካይ (26.7%) ምጣኔው በላይ ነው፡፡ 14.7% የቤተሰብ
አስተዳዳሪዎች በጡረታ አበል ይተዳደራሉ፡፡ እነዚህ አሃዞች የሚያሳዩት አብዛኛውን የሕብረተሰብ ክፍል
በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደር መሆኑ ነው፡፡ በድምሩ 30% (ሴቶች 42.2፣ ወንዶች 18.2) ዕድሜአቸው 10
ዓመትና በላይ ከሆኑ ነዋሪዎች ስራ አጥ ናቸው፡፡ ከዚህ አንፃር ሲታይ የልማት ተነሺዎች የገቢ ምንጭ ጥያቄ
መሰረታዊና ከመኖሪያ ቤት ተነጥሎ የሚታይ አይደለም፡፡ ይልቁንም ስራ ከቤት በላይ አንገብጋቢ መሆኑ
የሚያከራክር አይሆንም፡፡ ከነዋሪዎች በመጠይቅ፣ ቃለ መጠይቅ እና ውይይት የተሰበሰበው መረጃም
ተመሳሳይ ግኝት ያሳያል፡፡

ከሰኞ ገበያ መንገድ፣ ሸዋበር፣ ቡና ተራ፣ አራዳ አካባቢዎች የተነሱት እና አሁንም ከአራዳ የሚነሱ ነዋሪዎች
ከመነሳታቸው በፊት ይኖሩት በነበሩ ቦታዎች የንግድ አካባቢዎች በመሆናቸው ከህፃን እስከ አዛውንት
በጥቃቅን የንግድና የቀን ስራ ላይ ተሰማርተው ኑሮአቸው ለመደጐም እምብዛም የማይቸገሩ እንደነበሩ፤
በአንፃሩ አዲስ በሰፈሩበት አካባቢ የነበራቸው ገቢ ማግኘት እንዳልቻሉ ይገልፃሉ፡፡ በተለይ በዕድሜ የገፉ
ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ በቤተሰብ ጥገኛ እንዳደረጋቸው ያወሳሉ፡፡ ሴቶችም በተመሳሳይ የችግሩ ተጠቂዎች

196
ናቸው፡፡ ከቀጋ፣ አውራ ጐዳና፣ ሰንሰል ሰፈር ወዘተ እየተመላለሱ ይሰሩት የነበረ ስራ ለመስራት ጊዜና ወጪ
ያባክንባቸዋል፡፡ ነባር መኖሪያዎቹ እጅግ ያረጁና የተጐዱ ቢሆኑም ነዋሪዎች እራሳቸው ለመጦር ይችሉ ነበር፡፡
በየቤታቸው ደጃፍና የመንገድ ዳር ተጠቅመው በተለያዩ ጥቃቅን ንግድ እና አገልግሎት በመሰማራት ያገኙት
የነበረ ገቢ ከአዲሱ ሰፈር ተመላልሰውም ቢሆን ማግኘት አይችሉም፡፡ ዋናው ምክንያት አዳዲስ መስፈሪያ
አካባቢዎች ነባር አካባቢዎቹን ይሰጡት የነበረ ኢኮኖሚያዊ ጠቀመሜታ እያስገኙ አይደሉም፡፡

የከተማው የንግድ ማእከል የተጠናከረ እንዲሆን ያደረጉት አሁን በመልሶ ልማት ምክንያት እየተፈናቀሉ
የሚገኙ ነዋሪዎች ሲሆኑ እነዚህ ነዋሪዎች ከስራቸው ሲፈናቀሉ በተነሺዎቹና በአጠቃላይ በከተማው ድህነትና
ስራ አጥነት እየጨመረ መሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ነዋሪዎቹ እንደሚሉት በድሮ ሰፈሮቻቸው ከልጅ እስከ
አዛውንት እንደየ አቅሙ ሰርቶ ለመኖር እምብዛም የማይቸግራቸውና ለቤተሰብ ጥገኝነት ኣይዳረጉም ነበር፡፡
አዲሱ ሰፈራቸው ከከተማው የንግድ እንቅስቃሴ የራቀ በመሆኑ አቅመ ደካሞች ሙሉ በሙሉ በሌላ የቤተሰብ
አባል ጥገኛ መሆን አማራጭ የሌለው ሆኖባቸዋል፡፡ ጉልበት ያለው ወጣቱ ሃይል ከሰፈር ተመላልሶ ለመስራት
የትራንስፖርት ወጪ ፈተና ይሆንበታል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የመሀል ስፍራዎች ሰፊ ስራ የሚገኘው በነባር ሰፈሮቹ ሆኖ ሳለ በአደሱ የመስፈሪያ
አካባቢዎች ተመሳሳይ ሁኔታ እንዲኖር፣ ነዋሪው መሰል አነስተኛ ስራዎችን ሰርቶ ኑሮውን የሚደጉምበት ዕድል
እንዲፈጠር ለማስቻል የሚደረግ ጥረት ዝቅተኛ ነው፡፡ አዲሶቹ ሰፈሮች እንዲነቃቁ የሚያደርግ ኢንቨስትመንት
አይታይም፡፡ አካባቢዎቹ ለመሰረተ ልማት ተደራሽ ባለመሆናቸው የንግድ እንቅስቃሴ የማይታይባቸው ወጥ
የመኖሪያ ሰፈሮች ብቻ እተፈጠሩ ይገኛሉ፡፡

የነባር ከተማ መልሶ ልማት ፕሮግራም የልማት ተነሺዎችን ችግር በሚፈታበት አቅጣጫ የተቃኘ አይደለም፡፡
በዚህም የተነሣ ሂደቱ በውጥረት የተሞላ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ነዋሪዎች የመሃል አዲስ አበባን መቀየር
እየደገፉ ልማቱ የእነሱን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ባለመፍታቱ የተነሣ በሚፈልጉት ልማት በተቃርኖ
እንዲቆሙ ይገደዳሉ፤ በዚህም የተነሣ አካባቢውን ለልማት ላለመልቀቅ ያንገራግራሉ፡፡ ልማቱ ከሚነካቸው
ዜጎች ቁጥር ግዝፈት አኳያ ለተነሺዎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፍላጎት/ሕይወት በቂ ትኩረት የሚሠጥበት
ሁኔታ ካልተፈጠረ የልማቱ ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ይሆናል፡፡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ
ዜጎች የእለት ኑሮአቸውን የሚገፉት ከሚኖሩበት አካባ በጥብቅ የተቆራኘ በመሆኑ ሰፈራቸው ሲለቁ ኑሯቸውን
ለመቀጠል በማይችሉበት አካባቢ እንዲሰፍሩ የማድረጉ እርምጃ የሚቀጥል ከሆነ ልማቱ ተንገራግጮ ሊቆም
ይችላል፡፡

በጅማ ከተማ መርካቶ ማእከል አድርጎ የተከናወነ ልማት ሽፋኑ ጠባብ ቢሆንም በተሰራው ስራ በኩል የሚታዩ
ተጨባጭ አወንታዊ ፋይዳዎች አስገኝቷል፡፡ የመርካቶ፣ በጅምር ደረጃ ደግሞ ግንጆ-ጉድሩ እና ፒያሳ አካባቢ
የተካሄዱ መልሶ ማልማት እንቅስቃሴዎች የአካባቢው ምቹነት በማሻሻል እና በግንባታ ልማት የግሉ ዘርፍ
ኢንቨስትመንት በመሳብ ለአካባቢው ልማት በጎ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ቢሆኑም በልማቱ ምክንያት የተነሱት

197
በርካታ ነዋሪዎች ግን ከልማቱ ጋር አብረው እንዲለወጡ አድርጓል የሚያስብል አይደለም፡፡ ከቦታዎቹ የተነሱ
ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ በተለያየ የንግድ ስራዎች ይተዳደሩ እንደነበሩ መንደራ ቆጪ
ጤና ኬላ፣ ሰጦ-ሰመሮ ቀይ መስቀል አካባቢ፣ ሸነን ጊቤ ሆስፒታል ጀርባ፣ ወልዳ በናሙና ከተጎበኙ ቤተሰቦች
ለመረዳት ተችለዋል፡፡ በልማቱ ምክንያት የፈረሱ ቤቶች ለመኖሪያነት እና ለንግድ ስራ የሚያገለግሉ ስለነበር
እነሱ ሲፈርሱ ከቦታው የተነሱ ከ200 በላይ ነዋሪዎች ሙሉ ገቢያቸውና ስራቸው እንዲያጡ አድርጓቸዋል፡፡
ከቦታው ለተነሱ ነዋሪዎች በከተማው አስተዳደርም ሆነ በአልሚ ባለሃብቶች (ከጥቂቶቹ በስተቀር) የተገነቡ
ቤቶች ከፈረሱ ቤቶች የማይሻሉ ደሳሳ ናቸው፡፡

ይህ ማለት በከተማው የተካሄደ መልሶ ማልማት ኢኮኖሚያቸው የደከሙ፣ ግንባታቸው ያረጁና የተጐዱ፣
መሰረተ ልማቶቹ ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ፣ የአሰፋፈር ሁኔታቸው ስርዓት የሌላቸው ባጠቃላይ ለከተማው
ነዋሪዎች ሊሰጧቸው ከሚታሰቡ አገልግሎቶች በታች አገልግሎት የሚሰጡ ካልሆነም ሙሉ በሙሉ መስጠት
ያቋረጡት አካባቢዎች ነዋሪው የሚፈልገውን አገልግሎት እንዲሰጡ እንዲሁም የተዳከመውን ኢኮኖሚ
እንዲያንሰራራ ለማድረግ የተከናወነ አይደለም፡፡ መሃል ከተማው ላይ የነበሩ ችግሮች ወደ ሌሎች አካባቢዎች
እንዲዛወሩ በማድረግ ችግሮቹ የሚገኙበት ቦታ እንዲቀየር ከማድረግ ውጭ የልማቱ ውጤት ተደማሪ ዓቅም
የፈጠረ ነው የሚያስብል አይደለም፡፡

የሀዋሳ ከተማ መልሶ ልማት ውጤትም እላይ ከተጠቀሰው የተለየ ኣይደለም፡፡ በቦታው የነበሩ ነዋሪዎች
ኢኮኖሚያዊ ዓቅምም አብሮ እንዲለወጥ ያደረገ አይደለም፤ ኑሮአቸው የሚመሩበት ስራም እንዲጠፋ
አድርጓል፡፡ ለምሳሌ ቀደም ሲል ተነስተው ወደ አዲሱ ሰፈር ከተዛወሩት 30 ነዋሪዎች በነባሩ ሰፈራቸውና
ቤታቸው ያካሄዱ የነበረውን ስራ በቀጥታ መስራት አላስቻላቸውም፡፡ አዲሱ ሰፈራቸው የወደፊቱ ባይታወቅም
አሁን የመኖርያ አገልግሎት ብቻ የሚያገኙበት ነው፡፡ ይህም ኢኮኖሚአቸው እንደተናጋ አመላካች ነው፡፡
በተለይ ግምባር ላይ የነበሩት ለንግድ ድርጅቶች አከራይተው ያገኙ የነበረው ገቢ በአዲሱ ሰፈር
ቀርቶባቸዋል፡፡ ይህንን ሁኔታ በከተማዋ ማእከላዊ ሰፈሮች ከሚገኙ ነዋሪዎች መካከል 59.3% የሚሆኑት
በነበሩበት አካባቢ ተመልሰው እንዲሰፍሩ ይፈልጋሉ (ኮምፓስ የግል አማካሪ 2013 እኤአ)፡፡

በድሬዳዋ ከተማ እዚህም እዚያም የሚታየው የመልሶ ማልማት እንቅስቃሴ የአካባቢውን ሁለንተናዊ ገጽታ
(ፊዚካላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ወዘተ) መቀየር በሚችል አቅጣጫ የተቃኘ እንዳልሆነ የጥናት ቡድኑ
በአካባቢው ባደረገው የመስክ ምልከታ ለመገንዘብ ችሏል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ቀደም ሲል እንደተገለፀው
በእነዚህ አካባቢዎች እስካሁን የመልሶ ማልማት የተካሄደበት ቦታ ስፋት ከ1.43 ሄክታር አይበልጥም፡፡
እስካሁን የተከናወነው የመልሶ ማልማት ሥራ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ
ማደስ ልማት ዙሪያ የተያዘው ግንዛቤ ከደረጃ በታች የሆኑ ግንባታዎችን በአዲስ ግንባታ ከመተካት የሚያልፍ
አይደለም፡፡ ከተማ ማደስ ማለት የወደቀውን ሁለንተናዊ የከተማ ሕይወት ማደስ እንደሆነ የተሟላ ግንዛቤ ያለ
መሆኑን የሚያረጋግጥ ተግባር መሬት ላይ አይታይም፡፡ በመሆኑም የከተማ ማደስ ልማት አሁን በተያዘው

198
አቅጣጫ የሚቀጥል ከሆነ ከሚያስገኘው አወንታዊ ፋይዳ ይልቅ የሚያስከፍለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዋጋ
ያመዘነ ይሆናል፡፡

በአስተሳሰብ ደረጃ ሲታይ መልሶ-ማልማት የቤቶች ወይም ሰፈሮች ውጫዊ ገፅታ ለውጥ ተደርጎ የሚወሰድ
መሆኑ በተግባር ከተከናወኑ ስራዎች መረዳት ይቻላል፡፡ እስከነ ክፍተቱም ቢሆን የልማት ተነሺዎች ተለዋጭ
ቤት፣ ካልሆነም ቤት ለመገንባት ቦታ እንዲያኙ የሚደረግ በበጎ ጎን የሚታይ ሲሆን ነዋሪዎቹ ቋሚ የገቢ
ምንጭ እንዲኖራቸው ሲታሰብበት ኣይታይም፡፡

ነባር መኖሪያና የስራ አካባቢዎች መልሰው እንዲለሙ የሚደረግበት ምክንያት ያላቸው የመሰረተ ልማት ዓቅም
የከተማ አገልግሎት ለመስጠት የማያስችል መሆኑ አንዱ ነው፡፡ አዳዲስ መስፈሪያ ቦታዎች መጨናነቅ፣
መተፋፈግና እርጅና ችግሮችን ለመፍታት ቢያስችልም ለመሰረተ ልማት ያላቸው ቅርበትና ሽፋን ግን ለረጅም
ጊዜ ሳይፈታላቸው ይቆያሉ፡፡ በተለይ በማስፋፊያ ቦታዎች የሰፈሩ የመንገድና መጓጓዣ ከፍተኛ ችግር
አለባቸው፡፡ እጅግ አስጊ የተፋሰስ አደጋ የተጋረጠባቸው የመስፈሪያ አካባቢዎችም አሉ፡፡

በድምሩ አዳዲስ የማስፈሪያ አካባቢዎች ተነሺዎች ከመነሳታቸው በፊት ከረጅም ጊዜ ታስቦበት መሰረተ ልማት
ሟሟላት ሲገባው የልማት ተነሺዎቹ ከአሮጌ (የተጐዳ) ነገር ግን ለመሰረተ ልማት የተሻለ ቅርበት ካለበት
(Accessible) አካባቢ በማስነሳት ለዓመታት ለኑሮና ለስራ ወሳኝ የሚባሉት መሰረተ ልማትና አገልግሎቶች
እንዲነፈጉ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህ የሚያመለክተው የተጐዱ አካባቢዎች መልሶ የማልማት ተግባርና የልማት
ተነሺዎች የሚሰፍሩባቸው አካባቢዎች የተሟሉ የከተማ አገልግሎት እንዲሰጡ አስቀድሞ ማዘጋጀት
የኘሮግራሙ ሁለት ዘርፎች (ኘሮጀክቶች) መሆናቸው ካለመገንዘብ የሚመነጭ ነው፡፡

ከፍ ሲል በዝዝርዝ የተቀመጠው በየከተማው መልማት ምክንያት መነሳትን ተከትሎ የልማት ተነሺዎቹ


የሚያጋጥማቸው የስራ እና ገቢ ማጣት እንደተጠበቀ ሆኖ የመቐለ ከተማ ሌላ መልክም አለው፡፡ በስመ
ቅርስነት አብዛኞቹ የቀበሌ 14 ባለይዞታዎች በአካባቢው የተፈጠረውን የመሬት መጠቀም መብትና ቋሚ
ንብረት ከፍተኛ የዋጋ ዕድገት ወደ ጥቅም እንዳያውሉት ገድቧቸዋል፡፡ ሰፊ አካባቢ በታሪካዊ ቅርስነት መከለሉ
በዚህ ክልል ውስጥ ከባለ ሁለት ፎቅ በላይ ግንባታ እንዳይካሄድና ከባህላዊ የግንባታ ቁሳቁስ (Local
material) ውጭ ሌላ ግብዓት ጥቅም ላይ እንዳይውል የፕላን ገደብ ተጥሏል፡፡ በታሪካዊ ቅርስነት በተከለለው
ክልል የሚገኙ የግል ባለይዞታዎች ንብረታቸው ከአካባቢው ተፈላጊነት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ጥቅም እየሰጠን
አይደለም የሚል ቅሬታ እንዲያስነሱ አድርጓቸዋል፡፡ ይህን ያህል ስፋት ያለው አካባቢ ከልማት ውጭ መሆን
የግል ባለይዞታዎችን ብቻ ሳይሆን ከተማውንም ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል፡፡

እርግጥ ነው ቱሪዝም በአካባቢው ኢኮኖሚ ቁልፍ ሚና የሚጫወትበት ሁኔታ ከተፈጠረ ይህን አሉታዊ
ውጤት መቀልበስ ይቻላል፡፡ አካባቢው ለታሪክና ቅርስ ጥበቃ ሲባል በቱሪዝም ዘርፍ ኢኮኖሚ እንዲለማ
ቢደረግም ከአጭርም ሆነ ከረጅም ጊዜ አኳያ በግል ባለይዞታዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ማስወገድ

199
ያዳግታል፡፡ በመሆኑም አካባቢው በቅርስነት እስከተከለለ ድረስ የሕንፃ አገልግሎትና ይዞታ ለውጥ ማድረግ
ግድ ነው፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ቀዳማይ ወያነ ገበያ ላይ የሚታየው ችግር የተለየና የዚህ ተቃራኒ ነው፡፡ የቀዳማይ ወያነ
ነጋዴዎች ሕ/ስ/ማሕበር ባስገነባው ባለ አራት ፎቅ ዘመናዊ የገበያ ማአከል ለ65ዐ ነጋዴዎች የስራ ቦታ
ከመፍጠሩም በላይ በዙሪያው አነስተኛ ንግድ ለሚነግዱ ዜጎች የስራ ቦታ ፈጥሮላቸዋል፡፡ በህንፃው ዙሪያ
የሚገኙ በተለምዶ "ድፍኦ" እየተባሉ የሚጠሩ የአጼ ኃይለስላሴ መንግስት ያደረሰውን ጅምላ ጭፍጨፋ
የሚያስታውሱ በመቃብር ቅርፅ በተገነቡ ህንፃዎች የሚገኙ ሱቆች ቁጥር ከ119 አይበልጥም፡፡ ከቦታ ስፋት
አኳያ በ"ድፍኦ" ሱቆች የተያዘው ቦታ የቀዳማይ ወያነ ነጋዴዎች ሕ/ስ/ማሕበር ገበያ አዳራሽ ካረፈበት ቦታ
የሰፋ ነው፤ ነገር ግን ቦታው የሚያስተናግደው ነጋዴ ቁጥር እላይ እንደተገለፀው አነስተኛ ነው፡፡

በ"ድፍኦ" ሕንፃዎች የተያዘው ቦታ የሚሰጠው አገልግሎት ከደረጃ በታች መሆኑ ይታወቃል፤ ሆኖም አካባቢው
በቅርስነት የተከለለ በመሆኑ ህንፃዎቹን አፍርሶ አዲስና ዘመናዊ ህንፃ ለመግንባት አይቻልም፡፡ ባለይዞታዎቹም
ህንፃዎቹ ፈርሰው በአዲስ እንዲተኩ አይፈልጉም፤ ምክንያታቸው አሁን የምንሠራውን የንግድ ሥራ አዲስ
በሚገነቡ ሕንፃዎች ውስጥ መቀጠል እንችል ይሆናል ከሚል ስጋት የሚመነጭ ነው፡፡ ስለሆነም ለታሪክና
ቅርስነት ጥበቃ ሲባል የአካባቢው ልማት እንዲገታ በመደረጉ መሬቱ ሊሰጠው የሚገባውን ጥቅም እንዳይሰጥ
አድርጎታል፡፡

በመልሶ ማልማት ሂደት ለታሪካዊ ሕንፃዎች ጥንቃቄና ጥበቃ ማድረግ ተገቢ ነው፤ ሆኖም በታሪካዊ ቅርስነት
የተከለለው አካባቢ ሰፊ ሲሆን የአካባቢውን ኢኮኖሚ የሚያነቃቃ ስትራቴጂ ተቀርፆ ተግባራዊ ካልተደረገ
የቅርስ ጥበቃው የሚያስከፍለው ኢኮኖሚያዊ ዋጋ ከፍተኛ ይሆናል፡፡

ሌላው መሰረታዊ ችግር መልሶ ልማቱ የሚያፈናቅላቸው ዜጎች ለዘላቂ ኑሮአቸው ዋስትና የሚሰጥ ቋሚ
ንብረት እንዲፈራ በማድረግ በኩል የሚሰራ ስራ በከተሞቹ በስፋት ይሰተዋላል፡፡ የልማት ተነሺዎች ኢኮኖሚ
ዓቅማቸው ሳይታሰብ በጅምላ መልሰው ወደ ቀበሌ ቤት እንደዛወሩ ማድረግ ዜጎች በኢንቨስትመንት
እንዲሰማሩና ሃብት እንዲያፈሩ አያበረየታታም፡፡ ከሀገሪቱ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ልማት አቅጣጫ አንፃር
ሲታይ ዜጐች የንብረት ባለቤት የመሆን ዕድላቸው ያጠባል፡፡ ዜጐች ድህነታቸው የሚቀረፈው ንብረት
ሲያፈሩ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በተለይ በከተሞች ዜጐች የቋሚ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ማድረግ አማራጭ
የለውም፡፡ ይህ ዕድል ከተፈጠረ ዜጉች የቁጠባ ባህላቸውና ዓቅማቸው ያጐለብታል፡፡

በተለይ በከተማው ለግንባታ የሚውል ግብአት በተነፃፃሪ በቀላል ዋጋ የሚገኝ በመሆኑ በርካታ ዜጎች የቤት
ባለቤት የመሆን ዕድላቸው ሰፊ መሆኑ ዓቅም እንደሌላቸው የተፈረጁ ዜጐችም ጭምር ቤት መገንባት
እንደሚችሉ ለማረጋገጥ ይቻላል፡፡ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደር የሕብረተሰብ ክፍል ቤት መገንባት
እንደማይችል የሚቀርብ ክርክርም ደሴ ከተማ ላይ ማረጋገጫ አልተገኘም፡፡ በኣንፃሩ በዝቅተኛ ገቢ

200
የሚተዳደር የሕብረተሰብ ክፍል ጊዜ ከተሰጠው ቀስ በቀስ ቤት መስራት እንደሚችል ተጨባጭ መረጃ አለ፡፡
ስለዚህ የቀበሌ ቤቶች እየገነቡ ማቅረብ ነዋሪዎች ሃብት እንዳያፈሩ የሚገታ መሆኑ ግንዛቤ ሊወሰድበት
ይገባል፡፡ በተለይ ቤት መስራት ለሚፈልጉት የልማት ተነሺዎች በቀበሌ ቤት ማስፈር ተቀዳሚ አማራጭ
ሊሆን አይገባም፡፡

መልሶ የለማው በቦታው የፈጠረው በጎ ተፅዕኖ ስፋት

 ትላልቅ አዳዲስ መንገዶች መከፈትና ነባሮች ደረጃቸው ማሻሻል የግሉ ኢንቨስትመንት እንዲፋጠን የጎላ
ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡ በተለይ መቐለ የመዳረሻ እና መጋቢ መንገዶች ሳይቀር በግንባታው መስክ
ተፅዕኖ መፍጠር ችለዋል፡፡
 አዲስ አበባ አካባቢን ማእከል ያደረገ ሁለንተናዊ ልማት ካልሆነ በስተቀር ከዋና ዋና መንገዶች ዳር
በአብዛኛው በፕሎት ደረጃ በተናጠል የሚደረግ ኢንቨስትመንት ወደ ውስጥ ዘልቆ በመግባት የጎላ
ተፅዕኖ የሚፈጥር ሆኖ አልታየም፡፡ ደሴ ከተማ ወደ ምዕራብ ወረዳዎች የሚወስደው መንገድ መገንባት
አካባቢውን በፍጥነት ለውጥ እንዲያሳይ አላስቻለም፡፡
 በተወሰኑ ቦታዎች የተካሄዱ መልሶ ልማቶች ለመስፋትና ላለመስፋት የከተማው አጠቃላይ ዕድገት
ይወስነዋል፡፡ ጅማ መርካቶ የተካሄደው አካባቢን ማእከል ያደረገ ልማት ከመርካቶ-አገር አቋራጭ
አውቶብስ መናሀሪያ መስመር በተናጠል ልማት እንዲለማ መነቃቃት ፈጥሯል፡፡ ነገር ግን ሰፊ ቦታ ላይ
ተፅዕኖ ማሳረፍ አልቻለም፡፡ መቐለ ቀበሌ 14 የተጀመረው የልማት ጥረት ከአካባቢው አልፎ ቀበሌ 16፣
13፣ 11 ሰፊ ቦታ እንዲነቃቃ አድርጎታል፡፡
 መልሶ የሚለማው ቦታ በአካባቢው የሚያሳርፈው የማነቃቃት ደረጃ በሚዘጋጀው የአካባቢ የልማት
ዕቅድ ይዘትም ይወሰናል፡፡ ደሴ የመንገድ መሰረተ ልማቱ ከመሬቱ ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ
ባለመጣጣሙ በግንባታ ልማት የፈጠረው አወንታዊ ተፅዕኖ ጠባብ ነው፡፡ የመቐለ የቐደማይ ወያነ
የገበያ ማእከል ከአካባቢው ጋራ አብሮ ባለመታቀዱ ለራሱም ጭምር ተደራሽ እንዳይሆን አድርጎታል፡፡

መልሶ ልማቱ ያልፈታቸው ችግሮች፡


ከላይ የተጠቀሱ ስኬቶች በተሰራው ያህል የተመዘኑ እንጂ የተሟላ ስኬት ማሳያዎች አይደሉም፡፡ በየከተማው
የተካሄዱ የመልሶ ልማት ጥረቶች ከፍላጎቱ አንፃር ሲመዘኑ አመርቂ አይደሉም፡፡ ስለዚህ መልሶ ልማት
ለመከወን ያስገደዱ ችግሮች ከስፋት አንፃር በቂ መልስ አላገኙም፡፡ ቢሆንም የተሰራው ያህል ከግምት
በማስገባት ሲገመገምም ያልተፈቱ ችግሮች አሉ፤
 በአብዛኛው ውድቀት የታየባቸው ክፍትና አረንጓዴ ቦታዎች ልማት አንድ ነው፡፡ መንገዶች ለማስፋት
የሚደረገው ጥረት ያህል ለአረንጓዴ ቦታዎች አልተሰጣቸውም፡፡ በተለይ የመቐለ ከተማ በከተማው
መካከል ክፍትና አረንጓዴ መናፈሻዎች የሌለው እያለ በመልሶ ልማት ዕቅድ ከተያዙ አረንጓዴ ልማት
አንዱንም አልለማም፡፡ የተወሰነ ጥረት የሚደረገው በተወሰኑ የመንገድ አካፋዮች ላይ ነው፡፡
201
 መልሶ ልማት የመሬት አቅርቦት ችግር ለማቃለል እያስቻለ አይደለም፡፡ ልማቱ በተካሄደባቸው
አካባቢዎች ተገቢውን ጥግግት እንዲመጣ ማድረግ ላይም የተሳካ አይደለም (ከአዲስ አበባ ውጭ)፡፡
ጅማ፣ መቐለ፣ ድሬዳዋ እና ደሴ ከተሞች የልማት ተነሺዎች ከያዙት ጠባብ ቦታ በማንሳት ሰፊ መሬት
በምትክነት ሰጥቷል፡፡ ይህ ዓይነት ሂደት ምን ያህል ዘላቂ እንደሚሆን አጠያያቂ ነው፡፡
 የከተሞች የስራ አጥነትና ድህነት ለመቅረፍ እያስቻለ አይደለም፡፡ በአንፃሩ ስራ አጥነትና ድህነት
እንዲስፋፋ ምክንያት እየሆነ ነው፡፡ የልማት ተነሺዎች በቋሚነት የተሰማሩባቸው የስራ መስኮች
እንዲያጡ እያደረገ ይገኛል፡፡ ግንባታና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ የሚፈጥሩዋቸው የስራ ዕድል ስፋት
እጅግ ጠባብ ከመሆናቸው በላይ ጊዚያዊ ናቸው፡፡ ስለዚህ የልማት ተነሺዎች ያጡት ስራና ገቢ በእነዚህ
ዘርፎች ስለማይካካስ በከተማ ደረጃ ድህነትና ስራ አጥነት የማስፋፋት ዝንባሌው ያመዝናል፡፡
 መቐለ ከተማ እንዳለ ሳይሆን ቀበሌ 14 እና እንዳየሱስ የቱሪዝም የኢኮኖሚ ማእከል ለማድረግ
የታቀደው በተገቢው መንገድ ወደ ተግባር አልተለወጠም፡፡
 መልሶ ማልማቱ በአመዛኙ ከተወሰነ የአዲስ አበባ ተጠቃሽ ተሞክሮ (ልደታ፤ ሰንጋ ተራና ባሻ ወልዴ)
በስተቀር የሚገነቡ ህንጻዎች ንግድና አገልግሎትን ለማስተናገድ ብቻ ያለሙ በመሆናቸው የነበረውን
ቅይጥ አሰፋፈር እያጠፋ ነው፡፡ መልሶ መስፈሪያ ቤትና ቦታ አሰጣጡም የነበረውን ድሃና ሀብታም
አብሮ የመኖር እሴት እየቀየረ በገቢ ላይ የተመሰረተ ማሕበራዊ ልዩነት እያስከተለ መጥቷል፡፡

መልሶ ልማቱ ያገኛቸው ጠቀሜታዎች እና ለፕሮጀክቶቹ ትግበራ የወጣውን ሃብት ሚዛን

መልሶ ልማት ሲታቀድ የፕሮጀክቱ ወጪ የመንግስት ፋይናንስ ብቻ ነው በዕቅድ የሚታየው፡፡ የግሉ ዘርፍ
ኢንቨስትመንት በዕቅድ አይካተትም፡፡ ያም ሆኖ መንግስት በመሰረተ ልማት፣ ፕላን ዝግጅት ወዘተ ያወጣቸው
ወጪዎች እና አፈፃፀማቸው በግልፅ የሚያሳይ ሰነድ ማግኘት አልተቻለም፡፡ ልማቱን ለማከናወን የታቀደውና
የወጪ አፈጸጸም ልማቱ ካስገኘው ጥቅም በማነጻጸር በፕሮጀክት ደረጃ የተሟላ የገንዘብ/ሃብት ትንተና
እየተደረገ አይደለም፡፡ የተወሰነ ሙኮራ የሚታየው አዲስ አበባ ከተማ ላይ ብቻ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር በተወሰኑ ፕሮጀክቶች ኦዲት አስደርጓል፡፡ ኦዲቱ የሚያሳየው በተለያዩ ምክንያቶች የሚገለፅ የሃብት
ብክነት ይከሰታል፡፡ በድምር ሲታይ ግን የተከናወነ መልሶ ልማት ያስገኛቸው ጠቀሜታዎች የፋይዳ ግምገማ
እየተደረገ ባለመሆኑ ፕሮጀክቶች ምን ያህል አዋጭ መሆናቸው/አለመሆናቸው ተጨባጭ ድምዳሜ ለመድረስ
አይቻልም፡፡ ይህም ቀጣይ ሂደቶች በጠራ መንገድ እንዳይመሩና የፕሮጀክቶቹ ውጤታማነት እንዳይሻሻል
ያደርገዋል፡፡

202
3.2.10. መልሶ ልማቱ በቀጣይ የሚኖረው የመስፋት ዕድል
3.2.10.1. መልሶ ልማት በነዋሪዎች ዕይታ

ሀ. ነዋሪዎች ለመልሶ ልማት ዓላማ ያላቸው ድጋፍ

የማንኛውም ልማት ጠቀሜታ የሚገመገመው ካስገኛቸው ፋይዳዎች በመነሳት ሳይንሳዊ አግባብ ቢሆንም
የልማቱ ሂደትም ይሁን ፋይዳ በተጠቃሚው ማሕበረሰብ ይሁንታ ካልታከለበት ዋስትና ሊኖረው አይችልም፤
ቀጣይነቱም በማያፈናፍን ተግዳሮት እንዲገታ ያደርገዋል፡፡ ከዚህ መርህ በመነሳት በልማቱ ምክንያት
የተፈናቀሉ፣ ያልተፈናቀሉ፣ ቀጣይ የሚፈናቀሉት በልማቱ ዓላማ፣ ሂደትና ውጤት ያላቸው ዕይታ ከዚህ በታች
በዝርዝር ቀርቧል፡፡

ቀድሞ መታየት የሚገባው ነዋሪው በልማቱ ዓላማ ዙሪያ ያለው ዕውቀትና የድጋፍ ደረጃ ማወቅ ነበር፡፡ የዳሰሳ
ጥናቱ በልማቱ ምክንያት ከመኖሪያቸውና ከስራ ቦታቸው የተነሱት ሳይቀር 96.9% የአዲስ አበባ ከተማ
ነዋሪዎች የልማቱ ዓላማ እንደሚደግፉት ታይቷል፡፡

ሰንጠረዥ 3.20፡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለመልሶ ልማት ዓላማ ያላቸው የድጋፍ ደረጃ
አስተያየት ሰጪዎች የድጋፍ ደረጃ ድምር
ጠንካራ መካከለኛ ተቃውሞ መልስ ያልሰጡ
በልማት ምክንያት የተነሱ 86 38 1 3 128
ይዞታቸውን እንዲያለሙ የተፈቀደላቸው 147 43 7 3 200
ድምር 233 81 8 6 328
መቶኛ 71% 25% 2% 1.8% 100%

የመረጃ ምንጭ፡ የመስክ ዳሰሳ

ዓላማውን ለመደገፋቸው የጠቀሷቸው ምክንያቶች የከተማዋን ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ከማሳደግ፣


የወደቀውን መሰረተ ልማትና አካባቢ ከመለወጥ፣ የሕዝቡን ኑሮ ከማሻሻል፣ በፕላን የተደራጀ አሰፋፈርና
ዕድገት እውን ከማድረግ፣ የከተማውን ውበትና ገጽታ ከማሻሻል ከሚያስገኛቸው ፋይዳዎች የተቃኙ ናቸው፡፡

በቦታው እንዲያለሙ ከተፈቀዳለው 95% ዓላማውን የሚደግፉ ሲሆን ምክንያት ሲጠየቁ የወደቀውን መሰረተ
ልማትና አካባቢ ያስነሳል (92.9%)፣ የከተማው ውበት ያስጠብቃል ያሉት (92.2%)፣ የህዝቡን ኑሮ ያሻሽላል
(81.9%)፣ ፕላን የጠበቀ እድገት ያመጣል (66.1%) የሚሉት ናቸው፡፡ ይህ መረጃ የሚያሳየው የተለያዩ
የሕብረተሰብ ክፍሎች የልማቱን ዓላማ የሚደግፉት ለከተማው የሚኖረውን ድምር ፋይዳ ግምት ውስጥ
በማስገባት ሲሆን የግል ወይም የቤተሰብ ተጠቃሚነትን ከቤት አቅርቦት አኳያ ብቻ እንደሚቃኙት ይታያል፡፡

የመልሶ ማልማቱ ዓላማ በዚህ ደረጃ በሕዝብ ተቀባይነት ማግኘቱ ለሂደቱ መፋጠንና ስኬት ትልቅ ዕድል
ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህ ሁኔታ በብዙ ሀገራት የመልሶ ማልማት ተሞክሮ ያልተለመደ ነው፡፡

203
በመሆኑም እላይ የተጠቀሰው የተነሽዎች አስተያየት የሚያረጋግጠው መዲናዋ የምትገኝበት አስከፊና ገፊ ሁኔታ
ህዝቡን ምን ያህል እንዳስመረረውና ከዚህ አስከፊ ሁኔታም ለመውጣት ምን ያህል በልማቱ ላይ ተስፋና
አመኔታ እንደጣለ ነው፡፡

ትህንን እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ በመሰል ሁኔታ ለአዲስ አበባ 125ኛ ዓመት ክብረ በዓል ጥናት በተከናወነበት
ጊዜ የነበረው ከፍተኛ ድጋፍና ልደታን ተከትሎ ይቀርብ የነበረው "ቦታችን ይልማልን" ጥያቄ በነበረው/ባለው
የተነሺዎች አያያዝ ጉድለትና ቦታው ከጸዳ በኋላ ቶሎ ካለመልማት ጋር በተያያዘ ምከንያት ድጋፉ
እየቀነሰ/እየተሸረሸረ እንዳለ የሚያሳይ አዝማምያ በኖሩን በአያያዝ ለውጥ ካልመጣና በዚህ መልክ ከቀጠለ
ለልማቱ እንቅፋት እንደሚሆን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ነዋሪዎች የልማቱ ዓላማ የሚደግፉትን ያህል በልማቱ ውጤት የልማት ተነሺዎቹ ሁለንተናዊ
ተጠቃሚነት አሟልቶ ስለማይገኝ ከቅሬታ ነፃ ነው ለማለት ግን አይቻልም፡፡ ቀደም ሲል በዝርዝር
እንደተገለፀው የመልሶ ልማት ፕሮግራሙ የልማት ተነሺዎችን ችግር በሚፈታበት አቅጣጫ ከመቃኘት በጉልህ
የሚለይ ክፍተት አለው፤ ልማቱ የተነሺዎቹን ተጠቃሚነት በእውን የተሻለ የሚያደርግ ከሆነ እነርሱም ጭምር
አካባቢያቸው ወደ መልሶ ልማት እንዲገባ ተነሳሽነት ወስደው እንደሚጠይቁ የልደታ ተሞክሮ እና እሱን
ተከትለው የታዩ ፍላጎቶች ማየት በቂ ማስረጃዎች ናቸው፡፡

በደሴ ከተማ የልማት ተነሺዎች ላይ የተካሄደው ዳሰሳ ያስገኘው ውጤት እንደሚያመለክተው ተነሺዎች
ለልማቱ ጠንካራ ድጋፍ አላቸው፡፡ በልማት ምክንያት ከተፈናቀሉት 150 ነዋሪዎች፣ በቅርቡ እንደሚነሱ
በዝግጅት ላይ የሚገኙ 100 ቤተሰቦች እንዲሁም መልሶ ልማት በሚካሄድበት አካባቢ የሚኖሩ 151 በመልሶ
ልማት ዓላማ የሰጡት አስተያየት ቀጥሎ የተመለከተውን ይመስላል፡፡

ስእል 3.52፡ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ለመልሶ ልማት ዓላማ ድጋፍ ላይ ያላቸው የድጋፍ ሽፋን

ምንጭ፡ መስክ ዳሰሳ፣ ጥር 2008 ዓ/ም

204
ከነዋሪዎች የተሰበሰበው መረጃ የሚያሳየው ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ለመልሶ ልማት ዓላማ ያላቸው
ዕይታ ተመሳሳይ ነው፡፡ ልማቱ ካፈናቀላቸው 92.7%፣ በቀጣይ ከሚነሱ 95% እንዲሁም ልማቱ በተካሄደበት
አካባቢ ከሚኖሩ 94.7% የመልሶ ልማት ዓላማን ይደግፋሉ፡፡

ስእል 3.53፡ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ለመልሶ ልማት ዓላማ ለመደገፍ ምክንያቶች

ምንጭ፡ መስክ ዳሰሳ፣ ጥር 2008 ዓ/ም

የመልሶ ልማቱን ዓላማ የሚደግፉበትን ምክንያት ስንመለከት በአጠቃላይ በነዋሪው ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ
ሕይወት አወንታዊ ውጤት ይኖረዋል ከሚል እምነት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ከተፈናቀሉት 19.3%፣
ቀጣይ ከሚፈናቀሉት 37%፣ ካልተፈናቀሉት 34.4% መልሶ ልማት የሚደግፉበት ምክንያት ከተማው የተሻለ
ውበት ያጎናፅፋል ከሚል ግምገማ ነው፡፡ የከተማዋን ተወዳዳሪነት ማስጠበቅ ሁለተኛ የነዋሪዎች ድጋፍ የተሰጠው
ምክንያት ሆኗል፡፡ ከዚህ አንፃር ዓላማውን የሚደግፉት ከተፈናቀሉት 82%፣ ቀጣይ ከሚነሱት 42%፣ ካልተነሱት
16.6% ናቸው፡፡

የመልሶ ልማት ዓላማ በመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ዘንድ ያለውን ተቀባይነት ስንመለከት እላይ በአዲስ አበባና
በደሴ ነዋሪዎች ከተንፀባረቀው የተለየ አይደለም፡፡ በልማቱ ምክንያት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ከተፈናቀሉት
71.2% የልማቱ ዓላማ ተገቢ መሆኑ ደግፈውታል፡፡ በአንፃሩ ሳይነሱ የቀሩና እዛው የሚኖሩ በተነፃፃሪ አነስ ያለ
(67.6%) ድጋፍ አላቸው፡፡

205
ሰንጠረዥ 3.21፡ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ለመልሶ ልማት ዓላማ ያላቸው ድጋፍ ደረጃ
ለዓላማ ድጋፍ የሰጡት ግምገማ ደረጃ የተፈናቀሉ ያልተፈናቀሉ
አሃዝ % አሃዝ %
ጠንካራ 106 39.1 83 39.5
መካከለኛ 87 32.1 59 28.1
እውቀት የሌላቸው 7 2.6 6 2.9
የሚቃወሙ 62 22.9 58 27.6
መልስ ያልሰጡ 9 3.3 4 1.9
ድምር 271 100 210 100
ምንጭ፡ መስክ ዳሰሳ፣ ታሕሳስ 2008 ዓ/ም

ነዋሪዎቹ የሚሰጡት ግምገማ ሚዛናዊ መሆኑና አለመሆኑ ለመገምገም ነዋሪዎቹ በመልሶ ልማት ዓላማ
ያለቸው አመለካከት ቀድሞ መታየት የሚገባው ጉዳይ ይሆናል፡፡ የልማት ተነሺዎችና ልማቱ በተከናወነባቸው
አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች በልማቱ ዓላማ ላይ ተመሳሳይ የድጋፍ ሚዛን አላቸው፡፡ አንፃራዊ አሃዙ ሲታይ
በልማቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ይበልጥ ድጋፍ አላቸው፡፡ በተለይ የልማት ተነሺዎች በልማቱ ዓላማዎች ዙሪያ
የሚንፀባርቁት ተቃውሞ 23% በታች መሆኑ ነዋሪዎቹ በልማቱ ውጤት ላይ የሚሰጡት ግምገማ ሚዛናዊ
እንደሆነ እራሱ የቻለ ማረጋገጫ ነው፡፡

ሰንጠረዥ 3.22፡ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች መልሶ ልማትን የሚደግፉበት/የሚቃወሙበት ምክንያት


የመልሶ ልማት ዓላማ ለመደገፍ ምክንያቶች የመልሶ ልማት ዓላማ ለመቃወም ምክንያት የሆኑ
ምክንያት የተፈናቀሉ ያልተፈናቀሉ ምክንያት የተፈናቀሉ ያልተፈናቀሉ
ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር %
ምክንያት ያልገለፁ 75 27.7 121 57.2 ምንም ፋይዳ 7 11.3 6 10.34
ስለሌለው
ከተማው ተወዳደሪ ለማድረግ 63 23.2 17 8.1 የተወሰኑ ብቻ 21 33.9 4 6.9
ይጠቀማሉ
የመ/ልማትና አካባቢ ያስነሳል 117 43.2 57 27.1 ህዝቡን ይጎዳል 0 0.0 0 0.0
የከተማው ውበት ያስጠብቃል 51 18.8 33 15.7 ተነሺዎች ይጎዳል 62 100 45 77.6
የህዝቡን ኑሮ ያሻሽላል 41 15.1 19 9.1 መልሶ በለማው 19 30.7 12 20.7
አካባቢ መዳከምና
ፕላን የጠበቀ ዕድገት ይኖራል 47 17.3 10 ስጋት መፍጠር
4.8 መስፈሪያ አካባቢ 14 22.6 6 10.34
ያዳክማል
ተነሺዎች የተሻለ መኖሪያ ቤትና 4 1.5 4 1.9 ሌላ ምክንያት 1 1.6 0 0.0
አካባቢ እንዲኖራቸው
መልሶ የለማው አካባቢ ያነቃቃል 1 0.4 3 1.4
መልሶ ማስፈሪያ አካባቢ ያነቃቃል 1 0.4 1 0.5
ሌላ ምክንያት 0 0.0 0 0.0
ድምር 271 100 210 100 ድምር 62 100 58 100
ምንጭ፡ መስክ ዳሰሳ፣ ታሕሳስ 2008 ዓ/ም

በመቀሌ ከተማ የልማት ተነሽዎች የመልሶ ልማቱን ዓላማ የሚደግፉበትንና የሚቃወሙበትን ምክንያት
ስንመለከት ከተነሺዎች 43.2% ያህሉ የወደቀውን መሰረተ ልማትና አካባቢ ያሻሽላል ከሚል እሳቤ ሲሆን

206
23.2% የከተማውን ሁለንተናዊ ተወዳዳሪነት ያስጠብቃል በሚል እምነት፣ 18.8% የሚሆኑት የከተማውን
ውበት ማስጠበቅን፣ 17.3% የሚሆኑት ፕላን የተከተለ ዕድገት እንዲኖር በሚል ምክንያት እንደሚደግፉት
ታይቷል፡፡

ልማቱ በተከናወነባቸው አካባቢዎች ከሚገኙት በርካቶቹ (57.2%) የልማት ዓላማውን የሚደግፉበት


ምክንያት በውል የሚያውቁ አይደሉም፣ 17.1% ለድጋፋቸው ያስቀመጡት ምክንያት የወደቀውን መሰረተ
ልማትና አካባቢ ለማስነሳት፣ 15.7% የከተማው ተወዳዳሪነት ስለሚያስጠብቅ መሆኑ ታይቷል፡፡

መልሶ ልማቱን የሚቃወሙ ወገኖች በሁለቱም በኩል የሚሰጧቸው ምክንያቶች በመልሶ ልማቱ ምክንያት
ለሚፈናቀሉትም ሆነ ልማቱ በተከናወነበት ዙሪያ የሚኖሩና የሚሰሩ መልሶ ልማቱ ሊያስገኘው የሚገባ
ሁለንተናዊና ዘላቂ ለውጥ (Transformational) አመለካከት የሚያንፀባርቁ አይደሉም፡፡ በአንፃሩ በሰፈሮቹና
በቤቶች ውጫዊ ሁኔታ ለውጥ ያነጣጠሩ መሆናቸው ልማቱን ለመቃወም ከቀረቡ ምክንያቶች በማየት
ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ በልማት ምክንያት የተነሱት በሙሉ መልሶ ልማት ተነሺዎችን ተጎጂ እንደሚያደርግ
ሲቃወሙት 33.9% በመልሶ ልማት ተጠቃሚ የሚሆኑ የተወሰኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ብቻ እንደሆኑ፣
30.7% መልሶ በሚለማው አካባቢ መዳከምና ስጋት እንደሚፈጥር፣ 22.6% መስፈሪያ አካባቢዎች
እንደሚያዳክም ያምናሉ፡፡ በልማቱ ካልተፈናቀሉና የመልሶ ልማት ዓላማውን ከሚቃወሙ 58 ሰዎች 77.6%፣
6.9%፣ 20.7%፣ 10.34% በቅደም ተከተላቸው ተመሳሳይ ምክንያት አቅርበዋል፡፡ መልሶ ልማት ምንም ፋይዳ
እንደሌለው የሚያምኑም በሁለቱም ወገን ተመጣጣኝ ናቸው፡፡

በጅማ ከተማ በዳሰሳ ጥናቱ ከተሸፈኑ 205 የልማት ተነሽዎች መካከል 72.3%፣ በቅርቡ ከሚነሱ ነዋሪዎች 91.7%
የመልሶ ልማቱን ዓላማ ይደግፋሉ፡፡

ሰንጠረዥ 3.23፡ በጅማ ከተማ በቅርቡ የሚነሱ ለመልሶ ልማት ዓላማ የሰጡት ግምገማና ምክንያቶች
መልስ ቁጥር መቶኛ ለድጋፋቸው ምክንያት ቁጥር መቶኛ
ጠንካራ ድጋፍ ያላቸው 42 70.0 የከተማው ተወዳደሪነት ማስጠበቅ 19 32.8
መካከለኛ ድጋፍ ያላቸው 13 21.7 የወደቀውን መሰተ ልማትና አካባቢ ስለሚያነሳ 34 58.6
የማይደግፉ 1 1.7 የከተማው ውበት ማስጠበቅ 1 1.7
ተነሺዎች የተሻለ ቤት እና መኖሪያ አካባቢ 1 1.7
ዕውቀቱ የሌላቸው 3 5.0
እንዲኖራቸው ያደርጋል
መልስ ያልሰጡ 1 1.7 ለድጋፋቸው ምክንያት ያልገለፁ 3 5.2

ድምር 60 100.0 ድምር 58 100.0


ምንጭ፡ መስክ ዳሰሳ
የልማት ተነሽዎች የልማት ዓለማውን ለመደገፍ ምክንያት ይሆናሉ ተብለው ከቀረቡላቸው አማራጮች
58.6% የሚሆኑት ያረጀውንና የተጎሳቆለውን አካባቢ መሰረተ ልማት ለማደስ/ለማንሳት/ስለሚያስችል የሚል
መልስ ሲሰጡ 32.8% የሚሆኑት ደግሞ ከተማዋን ተወዳዳሪ እንዲትሆን ስለሚያስችል የሚል ምክንያት
ሰጥተዋል፡፡

207
ሰንጠረዥ 3.24፡ ጅማ በልማት ምክንያት የተነሱት ለመልሶ ልማት ዓላማ የሰጡት ግምገማና ምክንያቶች
መልስ ቁጥር መቶኛ ለተቃውሞአቸው ምክንያት ቁጥር መቶኛ
ጠንካራ ድጋፍ ያቸው 14 23.3 የተወሰኑ ቡድኖች ብቻ ስለሚጠቀሙ 1 1.7
መካከለኛ ድጋፍ ያላቸው 4 6.7 ነዋሪዎችን ስለሚጎዳ 1 1.7
የማይደግፉ 37 61.7 ተነሺዎች ስለሚጎዳ 21 35.0
ዕውቀት የለንም ያሉ 1 1.7 መልሶ ማልማት በሚካሄድባት አካባቢ ስጋት ይፈጥራል 11 18.3
መልስ ያልሰጡ 4 6.7 ምንም ዓይነት አወንታዊ ለውጥ ስለማያመጣ 21 35.0
ድምር 60 100.0 ድምር 60 100
ምንጭ፡ መስክ ዳሰሳ

በመልሶ-ልማት ምክንያት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በመልሶ ልማት ዓላማ ላይ ያላቸው ግምገማ እጅጉን የተለየ
ነው፡፡ ይኸውም የመልሶ ልማቱን ዓላማ የሚደግፉ 30% ብቻ ሲሆኑ 61.7% ዓላማውን አይደግፉትም፡፡
ተነሺዎቹ የመልሶ ልማቱን ዓላማ ለመቃወም ምክንያታቸውን ስናይ 35% የሚሆኑት መልሶ ልማት
የሚያስገኘው አወንታዊ ፋይዳ የለውም፣ 35% መልሶ ልማት ተነሺዎችን በቀጥታ ይጎዳል፣ 18.3% መልሶ
ልማት በሚካሄድበት አካባቢ ተረጋግቶ ለመስራትና ለመኖር ዕንቅፋት ይፈጥራል የሚል ምክንያት ሰጥተዋል፡፡

ለምሳሌ መርካቶ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የመልሶ ልማት እንቅስቃሴ ሲጀመር ወሰን ለማስከበር ነዋሪዎች
ያለ ማንም ቀስቃሽ በራሳቸው ፈቃድ ቤቶቻቸው በማፍረስ ከፍተኛ ተነሳሽነት ማሳየታቸውና በጉልበት
የሚከናወኑ ስራዎች ያለ ምንም ክፍያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸው በውይይት ጊዜ በመልካም ገፅታው
ቀርቧል፡፡ ነገር ግን ከላይ በሰንጠረዡ እንደተመለከተው በልማቱ ምክንያት የተነሱ ነዋሪዎች ከጊዜ በኃላ
መልሶ ልማቱ ትክክል እንዳልነበረ ፀፅቷቸዋል፡፡ ከነዋሪዎች በተደረጉ የፊት ለፊት ውይይቶችና ቃለ-መጠይቆች
አካባቢዎቹ መልማታቸው አግባብ መሆኑ አሁንም ድረስ የሚደግፉ ቢሆኑም የተቃውሞአቸው መነሻ
ከራሳቸው ተጎጂነት በኩል የሚንፀባረቅ እንጂ ልማቱን ከመቃወም የሚመነጭ አይደለም፡፡ ከዚህ መረዳት
የሚቻለው በአፈፃፀም ጉድለት ነዋሪውን ወደ ልማት ተቃዋሚነት እየገተገፋፋ መሄዱ የማይቀር መሆኑ ነው፡፡

የድሬዳዋ ነዋሪዎች የከተማዋ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ/በተለይ ንግድ መቀዛቀዙ በተለያየ መንገድ ቁጭቱን
ሲገልፅ ይደመጣል፡፡ በመሃል ከተማው እየተካሄደ ያለውን የመልሶ ልማት እንቅስቃሴ በተመለከተ በዚህ
ጥናት አስተያየታቸውን ከተጠየቁ ነዋሪዎች ምላሽ ማወቅ እንደተቻለው ሕዝቡ የድሬዳዋን መቀየር አጥብቆ
ይሻል፡፡

ለዘመናት ከኖሩበት የሥራና መኖሪያ አካባቢ መነሳታቸው ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዋጋ


እንደሚያስከፍላቸው የሚረዱት የልማት ተነሽዎች ጭምር ድሬዳዋ አሁን ካለችበት ሁኔታ መላቀቅ ከቻለች
ከአካባቢያቸው መነሳታቸው ቅር እንደማይላቸው ይገልፃሉ፡፡ ከዚህ መረዳት የሚቻለው ሕዝቡ ከግል ችግሩ
ይልቅ የከተማውን መለወጥ የማስቀደም ዝንባሌ ለተጀመረው የመልሶ ልማት እንቅስቃሴ ትልቅ አስቻይ
ሁኔታ ነው፡፡ ይህን የሕዝብ ድጋፍና ቁጭት ወደ ልማት ኃይልነት መቀየር ከተቻለ ለድሬዳዋ መልሶ ልማት
ትልቅ አቅም ነው የሚሆነው፡፡

208
ለ. ነዋሪዎች በመልሶ ልማት ሂደት አፈፃፀም ዙሪያ ያላቸው ግምገማ
የመልሶ ልማት ሂደት ልማቱ የሚካሄድበትን አካባቢ ከመከለል የሚጀምር መሆኑ ይታወቃል፤ ከዚህ ሂደት
ጀምሮ እስከመጨረሻው ድረስ ያለውን አፈፃፀም አስመልክቶ የተነሽዎች እይታ ምን እንደሚመስል ለመዳሰስ
ተሞክሯል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የአዲስ አበባ የልማት ተነሽዎችን አስተያየት አፈፃፀሙ ሰፊ ክፍተት እንዳለበት የሚያመላክት
ነው፡፡ ይኸውም በአሁን ጊዜ ሥራ ላይ ባለው አሠራርም ሆነ ቀደም ሲል በነበረው የድርድር ሥርዓት
ተነሽዎች በአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅት ወቅት ከሚሰጡት አስተያየት ውጭ የሚኖሩበት አካባቢ ለመልሶ
ማልማት ሲከለል አካባቢው ስለሚለማበት መንገድ የበኩላቸውን አማራጭ የሚያቀርቡበት ዕድል ጠባብ
እንደሆነ ተነሽዎች ይገልፃሉ፡፡ በአጠቃላይ ከመልሶ ማልማት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች አስተያየት እንዲሰጡ
የተጠየቁ ተነሽዎች ምላሽ ቀጥሎ ቀርቧል፡፡

ሰንጠረዥ 3.25፡ በአዲስ አበባ ከተማ የልማት ተነሺዎች በመልሶ ልማት አፈጻጸም ያላቸው እይታ
የግምገማ ደረጃ
የከተማ መልሶ ማልማት ተግባር መለክያ እ.በ.ጥሩ ጥሩ መካከለኛ ዝቅተኛ በ.ዝቀተኛ መልስ ያልሰጡ
የቦታ አመራረጥ ጥራት ብዛት 20 73 22 7 7 0
መቶኛ 16 57 17 6 6 0
የተነሺዎች ተሳትፎ ብዛት 18 62 33 9 6 0
መቶኛ 14 48 26 7 5 0
ምትክ ቦታ አመዳዳብ ብዛት 15 55 19 5 4 30
መቶኛ 12 43 15 4 3 23
ምትክ ቤት አመዳዳብ ብዛት 22 65 24 12 4 1
መቶኛ 17 51 19 9 3 0.8
የካሳ መጠን ብዛት 0 1 2 28 14 83
መቶኛ 0 1 1.6 22 11 65
ለመነሳት የሚሰጠው ጊዜ ብዛት 2 19 55 68 36 17
መቶኛ 2 15 43 30 21 1
ለተነሺ የሚደረግ እገዛ ብዛት 1 7 35 56 27 2
መቶኛ 1 6 27 44 27 2
ብዛት 20 21 27 34 26
የብድር አሰጣጥ ድጋፍ
መቶኛ 16 61 21 27 20
ብዛት 3 27 59 22 17
የአገልግሎት መስተንግዶ መቶኛ 2 21 46 17 13
ብዛት 27 46 37 17 1
መልሶ ልማት ፍጥነትና ጥራት
መቶኛ 21 40 29 13 1

በመልሶ ማልማቱ ተግባራት ዙሪያ የተነሺዎች ግምገማ እንደየ ርዕሰ ጉዳዩ ቢለያይም ለመነሳት የሚሰጠው
የዝግጅት ጊዜ ማነስና የዘመቻ ባህሪ መያዝ፣ የብድር ድጋፍ፣ ለተነሺዎች የሚደረግ እገዛና መስተንግዶ እንዲሁም
የመልሶ ልማቱ ፍጥነትና ጥራት ዝቅተኛ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ በካሳ ክፍያ አብዛኞቹ ተጠያቂዎች መልስ
ያልሠጡት የመንግሥት ተከራይ በመሆናቸው ሲሆን የብዙዎቹ ቅሬታ ከመልሶ ማቋቋም ጋር ነው፡፡

209
የግል ይዞታ የነበራቸው ተነሺዎች የከተማ መልሶ ማልማት ችግሮች ናቸው ብለው የጠቀሷቸው ደግሞ ካሳው
ቤት መተካት እንደማያስችል፣ የባለይዞታ ጥቅም ሳይታይ የባለሀብት መብት ማስቀደም፣ የቅንጅት ችግር
መኖሩ፣ ህዝቡ በሚኖርበት አካባቢ እንዲሰፍር አለመደረጉ፣ ወደ ገጠር ማስፈሩ፣ ከፈረሰ በኋላ ቶሎ
አለመልማት፣ ለተነሺዎች ቅድመ ሁኔታ አለመመቻቸት፤ ህዝብ አለማሳመን፣ ለአርንጓዴ ቦታና የስፖርት
ማዘውተርያ ትኩረት አለማድረግ፣ የወጣቱን ፍላጎት ግምት ውስጥ አለማስገባት፣ የግሉን ዘርፍ በስፋት
አለማሳተፍ የሚሉ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ በአሁኑ ጊዜ በከተማው በስፋት የሚስተዋለው አካባቢዎችን በመደዳ የማፍረስ እርምጃ በተሟላ
ጥናት ላይ ያልተመሠረተ፣ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቂ ምክክር ያልተደረገበት፣ የነባር
ተጠቃሚዎችን ፍላጎት ማዕከል ያላደረገ፣ የልማት ስርጭትን አካባቢያዊ ሚዛን ያልጠበቀ ነው የሚል
አስተያየት ከተነሽዎች በስፋት ይሰነዘራል፡፡

እዚህ ላይ በመሃል አዲስ አበባ ሁሉም አካባቢ ተመሳሳይ ችግር ይኖረዋል ተብሎ አይገመትም፤ መፍትሄውም
ተመሳሳይ ሊሆን አይችልም፡፡ ነገር ግን በተግባር እየታየ ባለው እንቅስቃሴ አካባቢዎችን አፍርሶ እንደገና
ከመገንባት ውጭ ሌላ የነባር ከተማ ማሻሻያ ልማት በአማራጭነት የሚታይ መሆኑን ማረጋገጥ አይቻልም፡፡

በደሴ ከተማ መልሶ እንዲለማ የሚፈለግ ቦታው የሚመረጥበት አግባብ ላይ ተፈናቃዮች አወንታዊ ዕይታ
እንዳላቸው የዳሰሳ ጥናቱ ያመለክታል፡፡

ሰንጠረዥ 3.26፡ በደሴ ከተማ የልማት ተነሺዎች በመልሶ ልማት ትግበራ ሂደት ላይ የሰጡት ግምገማ
ዝርዝር አማላካች /ርእሰ በጣም ጥሩ ጥሩ መካከለኛ ዝቅተኛ በጣም መልስ
ጉዳዮች/ ዝቅተኛ ያልሰጡ
አሀዝ % አሀዝ % አሀዝ % አሀዝ % አሀዝ % አሀዝ %
መልሶ የሚለማ ቦታ መረጣ 12.7 18.7 32.7 16.0 28 18.7 2 1.3
19 28 49 24
ትክክለኛነት
የተነሺዎች ተሳትፎ 12 8.0 54 36.0 44 29.3 14 9.3 25 16.7 1 0.7
ምትክ ቦታ አመዳደብ 9 6.0 45 30.0 35 23.3 22 14.7 29 19.3 10 6.8
ምትክ ቤት አመዳደብ 3 2.0 13 8.7 16 10.7 17 11.3 20 13.3 81 54.0
የካሳ መጠን 2 1.3 5 3.3 17 11.3 34 22.7 59 39.3 33 22.0
ለተፈናቃዮች የተሰጠ 22.0 20.0 20.7 20.7 24 16.0 1 0.7
33 30 31 31
የዝግጅት ጊዜ
ለተነሺዎች የሚደረግ ድጋፍ 14 9.3 22 14.7 42 28.0 31 20.7 37 24.7 4 2.7
ተነሺዎች ብድር እንዲያገኙ 0.7 5.3 4.0 16.7 49 32.7 61 40.7
1 8 6 25
የሚደረግ ድጋፍ
የአገልግሎት መስተንግዶ 30 20.0 41 27.3 39 26.0 21 14.0 15 10.0 4 2.7
መልሶ ልማት ፍጥነትና 7 4.7 4 2.7 19 12.7 52 34.7 44 29.3 24 16.0
ጥራት ድምር 130 8.7 250 16.7 298 19.9 271 18.1 330 22.0 221 14.7
ምንጭ፡ የመስክ ዳሰሳ ጥር 2008 ዓ/ም

210
እላይ ከቀረበው ሠንጠረዥ ማየት እንደሚቻለው ለዳሰሳ ጥናቱ ምላሽ ከሰጡት መካከል 31.4% የሚሆኑት
ቦታዎቹ የሚመረጡበት አግባብ ጥሩ/በጣም ጥሩ ያሉ ሲሆን 32.7% የሚሆኑት ደግሞ በመስፈርቱ መካከለኛ
ስፍራ ላይ ናቸው፡፡ በአንፃሩ 32.7% ትክክል እንዳልሆነ ቢያምኑም ከከተማው ተጨባጭ ሁኔታ የተመረጡ
አካባቢዎች መልሶ ልማት የሚጠይቁ መሆናቸው አያከራክርም የሚል አስተያየት አላቸው፡፡ ነዋሪዎቹ የቦታ
አመራረጡን ትክክል አይደለም ብለው የሚነቅፉበት ምክንያት ለእነርሱ በሚደረግ የአያያዝ ጉድለት የተነሣ
ነው፡፡

በደሴ ከተማ የመልሶ ልማት የተነሽዎችን ተሳትፎ አስመልክቶ በተሰጠ አስተያየት በዳሰሳ ጥናቱ ከተሳተፉ
ተነሽዎች መካከል 40% የሚሆኑት በልማት ሂደቱ የነበራቸው ተሳትፎ ጥሩ/በጣም ጥሩ ነው በሚሉ
የስምምነት ደረጃዎች ላይ የሚያርፍ ሲሆን 29.3% የሚሆኑት ምላሽ ተሳትፎአቸው መካከለኛ ነው የሚል
ነው፡፡ ነገር ግን ፊት ለፊት ከተደረጉ ቃለ መጠይቆችና ውይይቶች ለመረዳት የተቻለው የተሳትፎ ባህሪው
ነዋሪው እንዲያውቀው ከማድረግ በዘለለ ነዋሪው ሓሳቡን የሚደመጥበትና አማራጭ የሚያቀርብበት ዕድል
ጠባብ መሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ተነሺዎች "ተሳትፎ" የሚለውን ትርጓሜ ምን ማለት እንደሆነ እንዳልተገነዘቡት
ያሳያል፡፡ በአገልግሎት መስተንግዶ በኩል የተሰጠው መልስም በተመሳሳይ ነዋሪዎች በአግባቡ ያለመረዳት
ችግር የፈጠረው ነው፡፡

ምትክ ቦታ አመዳደብ በሚመለከት ነዋሪዎች የሰጡት መልስ ሁለት የተለያዩ ጉዳዮችን ለይቶ ያሳያል፡፡
በእርካታ በኩል ሲታይ (6% በጣም ጥሩ፣ 30% ጥሩ፣ 23.3% መካከለኛ) ከተፈናቀሉት 68% (የ 10 ሳይቶች
ናሙና) በቀበሌ ቤት ይኖሩ የነበሩ በመሆናቸው ሲፈናቀሉ መሬት ተሰጥቶአቸው የግላቸው ቤት ለመስራት
ዕድል ማግኘታቸው የሰጡት ሚዛን ከፍተኛ መሆኑ ያሳያል፡፡ እርካታ በማጣት (34%) በኩል ሲታይ አንድም
የተሰጣቸው ቦታ አመቺ ባልሆኑ እሩቅ አካባቢዎች በመሆኑ ምክንያት ሲሆን ሁለተኛውና ዋናው ምክንያት
ደግሞ ሁሉንም የልማት ተነሺዎች እኩል ካለማስተናገድ የሚመነጭ የፍትሓዊነት ጥያቄ ያሳያል፡፡

ለዝግጅት የተሰጣቸው ጊዜ በቂ መሆኑ የሚያምኑ ተነሺዎች 42% ናቸው፤ 20.7% በመካከለኛነት


ፈርጀውታል፡፡ እንዲህ ዓይነት መልስ የሰጡ ነዋሪዎች መነሻቸው ከሚመለከተው አካል ይፋዊ መረጃ
ስለሚሰጣቸው ሳይሆን መረጃው በይፋ ከመነገሩ በፊት ቀደም ብሎ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ስለሚደርሳቸው
ነው፡፡ መልሰው የሚለሙ ቦታዎች የከተማ አስተዳደሩ በይፋ ባላወጀባቸው ነገር ግን በዕቅድ በተያዙ
አካባቢዎች የሚኖሩ ጭምር መረጃው ይኖራቸዋል፡፡ ነገር ግን ቀደም ብሎ (ከአራት ዓመታት በፊት) መረጃው
ሳይኖራቸው በድንገት የተነሱም በርካታ ናቸው፡፡ ስለዚህ 36.7% ለዝግጅት የሚሰጠው ጊዜ በቂ አለመሆኑ
የሰጡት መልስ አግባብነት አለው፡፡ 45.7% ለተነሺዎች በሚደረግ ድጋፍ፣ 49.4% ተነሺዎች የብድር
አገልግሎት እንዲያገኙ በሚደረግ ድጋፍና ትብብር፣ እንዲሁም 64% መልሶ ልማት በእቅዱ የጊዜ ገደብ
ያለመፈፀምና የልማቱ ጥራት ላይ መልካም አፈፃፀም እንደሌለ የሰጡት መልስ አግባነቱ መሬት ላይ
በተጨባጭ ይታያል (ዝርዝር ሁኔታው በውጤትና ፋይዳ ዳሰሳ ላይ ተቀምጧል)፡፡ ተነሺዎች በካሳ መጠን

211
ለሰጡት ግምገማ ለማረጋገጥ የተሟላ መረጃ ባይገኝም የካሳ ሕጉ ይዘት በማየት ሁኔታው የተገመገመ ሲሆን
ከዚህ በታች እራሱን በቻለ አርእስት ቀርቧል፡፡

በአጠቃላይ የልማት ተነሺዎች በመልሶ ልማት ትግበራ ሂደት ግምገማ የሰጡት መልስ 8.7% በጣም ጥሩ፣
16.7% ጥሩ የሚሉት የስምምነት ደረጃዎች በድምር 25.4% ብቻ እንደረኩ የተሰበሰበው መረጃ ያመለክታል፡፡
በግምገማው መካከለኛ እርካታ የሚሰማቸው 19.9% ናቸው፡፡ በአንፃሩ 18.1% ሂደቱ በዝቅተኝነት ሲፈርጁት
22% በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ሰጥተውታል፡፡ በድምሩ ሲታይ የትግበራ ሂደት ግምገማው በልማት ተነሺዎች
ጠንካራ አወንታዊ ምስል አልፈጠረም፡፡

ሰንጠረዥ 3.27፡ በደሴ ከተማ በልማት በቅርቡ የሚነሱ ነዋሪዎች የመልሶ ልማት ትግበራ ላይ የሰጡት
ግምገማ አስተያየት
ዝርዝር አማላካች /ርእሰ ጉዳዮች/
በጣም ጥሩ መካከለኛ ዝቅተኛ በጣም ዝቅተኛ መልስ
ጥሩ ያልሰጡ
አሀዝ % አሀዝ % አሀዝ % አሀዝ % አሀዝ % አሀዝ %
መልሶ የሚለማ ቦታ መረጣ 2 2 44 44 15 15 23 23 16 16 - -
ትክክለኛነት
የተነሺዎች ተሳትፎ - - 27 27 54 54 13 13 5 5 1 1
ምትክ ቦታ አመዳደብ - - 32 32 23 23 26 26 17 17 2 2
ምትክ ቤት አመዳደብ 1 1 24 24 27 27 29 29 17 17 - -
የካሳ መጠን - - 16 16 22 22 36 36 24 24 2 2
ለተፈናቃዮች የተሰጠ የዝግጅት 1 4 26 58 6 6 5 5
1 4 26 58
ጊዜ
ለተነሺዎች የሚደረግ ድጋፍ - - - - 11 11 52 52 31 31 6 6
ተነሺዎች ብድር እንዲያገኙ - - 3 51 41 41 5 5
- - 3 51
የሚደረግ ድጋፍ
የአገልግሎት መስተንግዶ 1 1 31 31 37 37 19 19 7 7 5 5
መልሶ ልማት ፍጥነትና ጥራት - - 4 4 24 24 54 54 13 13 5 5
ድምር 5 0.5 182 18.2 242 24.2 361 36.2 177 17.7 31 3.1
ምንጭ፡ የመስክ ዳሰሳ ጥር 2008 ዓ/ም

በቅርቡ በተመሳሳይ ምክንያት እንደሚነሱ የሚጠበቁ ነዋሪዎች የሚለማ ቦታ መረጣ ትክክለኛነት፣ የተነሺዎች
ተሳትፎ፣ ምትክ ቦታ አመዳደብና የተነሺዎች መስተንግዶ ላይ ያላቸው የስምምነት ደረጃ ካአሁን ቀደም
የተፈናቀሉት ከሰጡት መልስ ተመሳሳይ ነው፡፡ በሌሎች አመላካቾች ቀጣይ ተነሺዎች ግምገማቸው አሉታዊ
ገፅታው ያመዝናል፡፡ ምትክ ቦታ አመዳደብ 43%፣ ምትክ ቤት አመዳደብ 46%፣ የካሳ መጠን 60%፣
ለዝግጅት የሚሰጥ ጊዜ 64%፣ ለተነሺዎች የሚደረግ ድጋፍና እገዛ 83%፣ የልማት ተነሺዎች ብድር እንዲያገኙ
የማመቻቸት ድጋፍ 92%፣ መልሶ ልማት ፍጥነትና ጥናት 67% ዝቅትኛ/እጅግ ዝቅተኛ እንደሚሆን
ይጠብቃሉ፡፡

መልሶ ልማት በተካሄደባቸው አካባዎች ከሚኖሩ 44.4% መልሶ የለማው ቦታ እንዲለማ የመምረጥ
ትክክልኛነት ጥሩ/በጣም ጥሩ እንደሆነ ፣ 36.4% ደግሞ መካከለኛ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ ልማቱ በተካሄደበት
አካባቢ የሚኖሩ የልማቱ ቀጥተኛ ተጠቃሚዎች እንደሆኑ የሚጠበቅ ቢሆንም ግምገማቸው የተፈናቀሉትና

212
በቅርቡ የሚፈናቀሉት ከሰጡት ይባስ አሉታዊ ገፅታው ያመዝናል፡፡ ምክንያቱም በመልሶ ልማት ትግበራ
ፍጥነትና ጥራት ላይ ያሳዩት የእርካታ ደረጃ ሌሎቹ ካሳዩት በታች ነው፡፡

ሰንጠረዥ 3.28፡ ደሴ ከተማ በልማቱ ምክንያት ያልተፈናቀሉ በመልሶ ልማት ትግበራ ላይ የሰጡት ግምገማ
ዝርዝር አማላካች በጣም ጥሩ ጥሩ መካከለኛ ዝቅተኛ በጣም መልስ
/ርእሰ ጉዳዮች/ ዝቅተኛ ያልሰጡ
አሀዝ % አሀ % አሀዝ % አሀ % አሀዝ % አሀዝ %
ዝ ዝ
መልሶ የሚለማ ቦታ መረጣ 16 10.6 51 33.8 55 36.4 21 13.9 8 5.3 - -
ትክክለኛነት
የተነሺዎች ተሳትፎ 8 5.8 45 29.8 70 46.4 22 14.6 6 4.0 - -
ምትክ ቦታ አመዳደብ 5 3.3 30 19.9 47 31.1 50 33.1 18 11.9 1 0.7
ምትክ ቤት አመዳደብ 3 2.0 28 18.5 52 34.4 46 30.5 18 11.9 4 2.6
የካሳ መጠን 3 2.0 13 8.6 36 23.8 70 46.4 23 15.2 6 4.0
ለተፈናቃዮች የተሰጠ 27 17.9 63 41.7 29 19.2 14 9.3 13 8.6 5 3.3
የዝግጅት ጊዜ
ለተነሺዎች የሚደረግ ድጋፍ 4 2.6 31 20.5 58 38.4 41 27.2 14 9.3 3 2.0
ተነሺዎች ብድር እንዲያገኙ 8 5.3 62 41.1 24 15.9 27 17.9 13 8.6 17 11.3
የሚደረግ ድጋፍ
የአገልግሎት መስተንግዶ 10 6.6 36 23.8 58 38.4 28 18.5 17 11.3 2 1.3
መልሶ ልማት ፍጥነትና ጥራት 3 2.0 17 11.3 20 13.2 80 53.0 30 19.9 1 0.7
ድምር 87 5.76 376 24.9 449 29.74 399 26.4 160 10.6 39 2.58
የመረጃ ምንጭ፡ የመስክ ዳሰሳ ጥር 2008 ዓ/ም

ስለ ተነሺዎች ተሳትፎ፣ ምትክ ቤት/መሬት አመዳደብ፣ ለፈረሰ ቤት የሚከፈል ካሳ እንዲሁም መልሶ ልማት
አፈፃፀም ፍጥነትና ጥራት በሚመለከት የተፈናቀሉትና በቅርቡ የሚፈናቀሉት የሰጡት መልስ ተመሳሳይ ነው፡፡

በድምሩ ሲታይ በልማቱ ምክንያት የተፈናቀሉት ከፍተኛ እርካታ ማጣት ያሳዩት ለቤታቸው በተከፈላቸው
የካሳ መጠን በቂ ያለመሆን፣ የብድር ድጋፍ ስለማይደረግላቸው፣ የሚደረግላቸው አስተዳደራዊ ድጋፎች በቂ
ያለመሆን፣ ለዝግጅት የሚሰጣቸው ጊዜ በቂ ያለመሆን እንደየ ቅደም ተከተሉ ተቀምጠዋል፡፡

213
ስእል 3.54፡ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች መልሶ ልማት ትግበራ ሂደት ላይ ያላቸው ግምገማ ንፅፅር

ምንጭ፡ መስክ ዳሰሳ፣ ጥር 2008 ዓ/ም

በቅርቡ የሚነሱት ደግሞ ብድር እንዲያገኙ የሚደረግላቸው ድጋፍ፣ አስተዳደራዊ ድጋፎች፣ ለዝግጅት
የሚሰጣቸው ጊዜ፣ ለንብረታቸው በሚከፈላቸው ካሳ ላይ ቅድመ ግምታቸው ከተፈናቀሉት በላይ ከፍተኛ
ስጋት አንፀባርቀዋል፡፡ ለስጋታቸው መነሻ ምክንያት ከአሁን ቀደም የተፈናቀሉት ያጋጠሙዋቸው ችግሮች
የተግባር ተመክሮዎች ላይ የተመሰረቱ መሆናቸው ከቃለ መጠይቆችና ውይይቶች መረጋገጥ ተችሏል፡፡

ስእል 3.55፡ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች መልሶ ልማት ትግበራ ሂደት ላይ ያላቸው ግምገማ ንፅፅር

ምንጭ፡ የመስክ ዳሰሳ፣ ጥር 2008 ዓ/ም

214
መልሶ እንዲለማ የታቀደው ቦታ በጊዜው ባለመልማቱና የስራው አጠቃላይ ጥራት ላይ ሶስቱም የሕብረተሰብ
ምድቦች እኩል በድክመት ገምግመውታል፡፡

መልሶ ልማት ትግበራ ሂደት እንዲሳካ ወይም እንዳይሳካ ሊያደርጉት ይችላሉ ተብለው ከሚታመንባቸው
ምክንያቶች በዋናነት ከአስፈፃሚ አካላት የማስፈፀም ዓቅምና ከሕግ ማዕቀፍ አንፃር የሚገለፁ መሆኑ
በመጠይቅ የተሰበሰበው መረጃ ያሳያል፡፡ ለዝግጅት የሚሰጠው ጊዜ በቂ ያለመሆን (22.9%)፣ ለተነሺዎች
የሚደረግ እገዛ (28.7%)፣ የተነሺዎች አያያዝና መስተንግዶ (31.7%) ከአስፈፃሚ አካላት ስነ ምግባር ጋር
አያይዘውታል፡፡

በመቀሌ ከተማ የመልሶ ልማት የሚነካቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች አስተያየት ስንመለክት መልሶ ልማት
በተካሄደበት አካባቢ የሚኖሩ በአብዛኛው የልማቱ ቀጥተኛ ተጠቃሚዎች እንጂ የችግሮቹ ገፈት ቀማሾች
ባለመሆናቸው በእርካታ በኩል ከተጠቀሱ አሀዞች ይልቅ እርካታ በማጣት በኩል ያሉ አሃዞች ሲታይ ትርጉም
አላቸው፡፡

ሰንጠረዥ 3.29፡ በቐለ ከተማ መልሶ ልማት ያላፈናቀላቸው በልማቱ ሂደት ላይ ያላቸው ግምገማ
በጣም ጥሩ ጥሩ መካከለኛ ዝቅተኛ በጣም ዝቅተኛ መልስ
ዝርዝር አማላካች ያልሰጡ
አሀዝ % አሀዝ % አሀዝ % አሀዝ % አሀዝ % አሀዝ %
የቦታ መረጣ ትክክለኛነት 4 1.9 86 41.0 32 15.2 9 4.3 70 33.3 9 4.3
የተነሺዎች ተሳትፎ 52 24.8 54 25.7 40 19.0 43 20.5 12 5.7 9 4.3
ምትክ ቦታ አመዳደብ 1 0.5 41 19.5 62 29.5 36 17.1 40 19 30 14.
የካሳ መጠን 81 38.6 17 8.1 21 10.0 27 12.9 0 0 64 30.
3
ለዝግጅት የሚሰጥ ጊዜ 2 1.0 115 54.8 47 22.4 16 7.6 18 8.6 5
12 5.7
ለተነሺዎች የሚደረግ 0 0 4 1.9 26 20.4 84 40.0 93 44.3 3 1.4
ድጋፍ አሰጣጥ ድጋፍ
የብድር 10 4.8 40 19.0 78 37.1 26 12.4 12 5.7 44 21.
የአገልግሎት መስተንግዶ 10 4.8 41 19.5 108 54.1 36 17.1 11 5.2 4 0
1.9
መልሶ ልማት ፍጥነትና 11.4 17.6 23.3 17.6 57 27.1 6 2.9
24 37 49 37
ጥራት
ድምር 229 10.9 448 21.4 517 24.6 335 16.0 313 14.9 256 12.2
ምንጭ፡ መስክ ዳሰሳ፣ ታሕሳስ 2008 ዓ/ም
ለትግበራ አፈፃፀም የተሰጠው ግምገማ እንደተጠበቀ ሆኖ ነዋሪዎቹ ለእያንዳንዱ አመላካች መስፈርት ጥንካሬ
ወይም ድክመት ዋነኛ ምክንያቶች እንዲለዩ ቢጠየቅም አብዛኞቹ ነዋሪዎቹ ለእያንዳንዱ መስፈርት ምክንያት
ለማስቀመጥ ዕውቀት ያላቸው ሆነው አልተገኙም፤ በመሆኑም 53.2-65.3% (በአማካይ 62.2%) ምክንያቶቹ
ለመለየት ተቸግረዋል፡፡ እውቀቱና መረጃው ካላቸው ነዋሪዎች የሰጡት መልስ ሲታይ ደግሞ የአስፈፃሚ
አካላት ዓቅም ውስንነትና ከሕግ ማዕቀፍ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች በቅደም ተከተል ከፊት የሚጠቀሱ ምክንያቶች
ናቸው፡፡

215
ሰንጠረዥ 3.30፡ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ለትግበራ ሂደት ውስንነት የተሰጡ ምክንያቶች
መለኪያ /አመላካች/ የአስፈፃሚ የገንዘብ የአስፈፃሚው የሕግ ያልተገለፀ የተነሺው ሌላ
ስነምግባር ችግር ዓቅም ማዕቀፍ የራሱ ምክንያት
ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥ % ቁጥ % ቁጥ % ቁጥ %
የቦታ አመራረጥ 2 0.4 - - 99 20.6 95 19.8 271 56.3 3 0.6 11 2.3
የተነሺዎች ተሳትፎ 12 2.5 58 12.1 62 12.9 26 5.4 259 53.8 60 12.5 4 0.8
ምትክ ቦታ አመዳደብ 18 3.7 - - 107 22.2 40 8.3 308 64.0 - - 8 1.7
የንብረት ካሳ 20 4.2 27 5.6 86 17.9 65 13.5 275 57.2 1 0.2 7 1.5
ልዝግጅት የሚሰጥ ጊዜ 20 4.2 2 0.4 40 8.3 63 13.1 352 73.2 - - 2 0.4
ለተነሺዎች የሚደረግ 3.3 1.7 31 6.4 256 53.2 - - - -
16 8 162 33.7
እገዛ
የብድር አሰጣጥ 17 3.5 - - 115 23.9 30 6.2 314 65.3 2 0.4 3 0.6
የተገልጋይ መስተንግዶ 33 6.9 - - 125 26.0 18 3.7 294 61.1 8 1.7 3 0.6
መልሶ ልማት ፍጥነትና 7.1 9.8 12.1 49 10.2 288 59.9 1 0.2 4 0.8
34 47 58
ጥራት
ድምር 188 3.9 144 3.0 930 19.4 432 9.0 2988 62.2 75 1.6 45 0.9
ምንጭ፡ መስክ ዳሰሳ 2008 ዓ/ም
የመልሶ ልማቱ አተገባበር ሂደት ለመገምገም ከነዋሪው በመጠይቅ የተሰበሰቡ መረጃ ትግበራው በድምር
ከቦታው የተነሱትም ሆነ ልማቱ በተካሄደበት የሚገኙ ነዋሪዎች በቂ እርካታ እንዳልፈጠረ ያመለክታል፡፡
በመሆኑም በተለይ ከቦታቸው የተነሱ ነዋሪዎች እርካታ የሚያጡባቸው መስኮች በንብረት ካሳ፣ ምትክ መሬት፣
የዝግጅት ጊዜ እና የተፈናቀሉ ነዋሪዎች አያያዝ የሚመለከቱ ሲሆኑ በርእሰ ጉዳዩ ተለይተው ከዚህ ቀጥሎ
ቀርበዋል፡፡

ሰንጠረዥ 3.31. መቐለ ከተማ ላይ የልማት ተነሺዎች በመልሶ ልማት አፈፃፀም ያላቸው ግምገማ
አማላካች አጀንዳዎች በጣም ጥሩ ጥሩ መካከለኛ ዝቅተኛ በ/ ዝቅተኛ መልስ ያልሰጡ
ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር %
የቦታ መረጣ 5 1.8 68 25.1 62 22.9 37 13.7 99 36.5 0 0
ትክክለኛነት
የተነሺዎች ተሳትፎ 2 0.7 48 17.7 55 20.3 39 14.4 123 45.4 4 1.5
ምትክ ቦታ አመዳደብ 2 0.7 34 12.5 54 19.9 55 20.3 103 38.0 23 8.5
የካሳ መጠን 0 0 4 1.5 32 11.8 30 11.1 169 62.4 36 13.3
ለዝግጅት የተሰጠ ጊዜ 2 0.7 92 33.9 58 21.4 64 23.6 43 15.9 12 4.4
ለተነሺዎች የሚደረግ 0.7 2.2 8.1 26.9 156 57.6 12 4.4
2 6 22 73
ድጋፍ
የብድር ማመቻቸት 15 5.5 24 8.9 53 19.6 53 19.6 85 31.4 41 15.1
ድጋፍ
የአገልግሎት 5 1.8 22 8.1 51 18.8 51 18.8 127 46.9 15 5.5
መስተንግዶ
መልሶ ልማት 29 10.7 32 11.8 37 13.7 31 11.4 133 49.1 9 3.3
ፍጥነትና ጥራት
ድምር 62 2.3 338 12.5 451 16.6 441 16.3 1124 41.5 294 10.9
ምንጭ፡ መስክ ዳሰሳ፣ ታሕሳስ 2008 ዓ/ም

ለልማት በተመረጡ ቦታዎች ትክክለኛነትና በልማቱ ምክንያት ከቦታቸው ለሚለቁ ነዋሪዎች ለመነሳት
በተሰጣቸው የዝግጅት ጊዜ ላይ እጅግ ሰፊ ቅሬታ እንዳላቸው የሚያሳይ አይደለም፡፡ በቦታ መረጣ 26.9%

216
እንደረኩ ሲገልፁ 23% ደግሞ አልተከፉም፡፡ ለመነሳት ዝግጅት በተሰጣቸው ጊዜ 34.6% ጊዜው በቂ
እንደሆነ እርካታቸው ሲገልፁ 21.4% ያህሉ አልተከፉም፡፡ በሌሎቹ የትግበራ መመዘኛዎች ከቦታቸው የተነሱ
እርካታ የላቸውም ማለት ይቻላል፡፡ አጠቃላይ በመጠይቁ ከተዳሰሱ 84.5% ለተነሺዎች በሚደረግ እገዛ፣
73.5% በተከፈላቸው የካሳ መጠን፣ 65.7% በድህረ መፈናቀል አያያዝና መስተንግዶ፣ 60.5% በመልሶ ልማቱ
ትግበራ ጥራትና ፍጥነት፣ 59.8% በተነሺዎች ተሳትፎ፣ 58.3% በምትክ ቦታ አመዳደብ እርካታቸው ዝቅተኛ
ነው፡፡

በልማቱ ምክንያት ያልተፈናቀሉ ነዋሪዎች ለተነሺዎች የሚደረግ ድጋፍ አርኪ እንዳልሆነ የተፈናቀሉት ከሰጡት
መልስ የተለየ አይደለም (84.3%)፡፡ በሌሎቹ አመላካቾች ሲታይ ያልተፈናቀሉ የተሻለ አወንታዊ አመለካከት
አላቸው፡፡ ለዝግጅት በሚሰጥ ጊዜ (55.8%)፣ የተነሺዎች ተሳትፎ (50.5%)፣ ለንብረት በሚከፈል ካሳ
(46.7%)፣ በቦታ አመራረጥ ትክክለኛነት (42.9%) መርካታቸው ገልፀዋል፡፡ እነዚህ አሃዞች የተፈናቀሉ
ከሰጡት ግምገማ በአንፃራዊነት የተሻለ አወንታዊ ዝንባሌ የሚያመላክቱ እንጂ ልማቱ ያላፈናቀላቸው ጠንካራ
ድጋፍ እንዳላቸው የሚያመለክት ድምዳሜ ላይ የሚያደርሱ አይደሉም፡፡

በሀዋሳ የመልሶ ልማት ስንመለከት እስካሁን በከተማው በስፋት የተካሄደው መልሶ ልማት በመሠረተ ልማት
አውታር ዝርጋታ ላይ ያተኮረ ስለነበር መሠረተ ልማት በሚዘረጋበት አካባቢ ነዋሪው አጥራቸውን
በፍቃደኝነት እስከማፍረስ ድረስ ተሳትፎ እንደነበራቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ ማለት ግን በሌሎች የመልሶ
ልማት ፕሮጀክቶች የነዋሪው ተሳትፎ ተመሳሳይ ነው ማለት አይደለም፡፡ ይህንም ቀጥሎ ከቀረበው ስዕላዊ
መግለጫ ማየት ይቻላል፡፡

ስእል 3.56፡ በሀዋሳ ከተማ የመልሶ ማልማት የተነሽዎች ተሳትፎ ግምገማ

ምንጭ፡ ከመስክ ከተሰበሰበው መረጃ

በሌላ አገላለጽ ያረጁ አካባቢዎችን የማደሱ ስራ እንደ ውሃ እና መብራት የመሳሰሉት መሰረታዊ የመኖሪያ
አገልግሎቶች በቅድሚያ ባልተሟሉበት ሁኔታ እና ህብረተሰቡንም ከዕቅዱ አንስቶ በምትክ ቦታ መረጣው፣
በምትክ ቤቶች ዲዛይን እስከ ግንባታው ድረስ ባሉት ሂደቶች በበቂ ሁኔታ አለማሳተፉ የህብረተሰቡ ቅሬታ
ስላልፈታ ከተማው የተከተለው የመልሶ ማልማት ዕቅድና ዝግጅት በቂ ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡

217
ከላይ እንደተመለከተው በዳሰሳ ጥናቱ ከተሳተፉ ነዋሪዎች አብዛኞቹ (37%) ተሳትፎው ዝቅተኛ ነው የሚል
ምላሽ የሰጡ ሲሆን 19% ደግሞ በጣም ዝቅተኛ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ይህም በድምር 56% የሚሆነው
ድርሻ ይይዛል፡፡

በሀዋሳ የመልሶ ማልማቱ እርምጃው የባለሃብቶችን የልማት ቦታ ጥያቄ ከመመለስ ባሻገር ለነዋሪዎች ሕይወት
መለወጥ በቂ ትኩረት እንደማይሰጥ ነው የተነሽዎች አስተያየት የሚያመለክተው፤ በዚህም የተነሣ በእስካሁኑ
አካሄድ አብዛኞቹ ተነሽዎች ቅሬታ አላቸው፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ የምትክ ቤት አሰጣጡ የቤተሰብን ብዛትና
አጠቃላይ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚአዊ ሁኔታቸውን ያገናዘበ ባለመሆኑ ተደራሽነቱ አጥጋቢ አይደለም የሚል
ነው፡፡ በከተማ ዳርቻ አከባቢዎች ተነሽዎችን መልሶ ለማስፈር የሚገነቡ ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁ አይደለም
የሚል ቅሬታ በተነሽዎች ይንፀባረቃል፡፡

ስእል 3.57፡ ሀዋሳ ከተማ ላይ በፕሮጀክቱ ከመሃል ከተማ ለሚነሱ የተገነቡ ወጭ ቆጣቢ ቤቶች

ምንጭ፡ ከመስክ ላይ በአጥኚው ቡድን የተወሰደ

በተለይ ዳያስፖራ እና ሞኖፓል ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች የተሰሩት ቤቶች ስፋት ስቱዲዮና ባለ ጠባብ
አንድ መኝታ ክፍሎች ብቻ በመሆናቸው ያን ያህል እርቀት ከመሀል ከተማ በወጣ ቦታ ላይ እንደዚያ ዓይነት
መሠራቱ ለተነሽዎች ሕይወት መሻሻል ምንም ትኩረት አለመስጠት ነው የሚል አመለካከት በተነሽው
እንዲሰፍን ምክንያት ሆኗል፡፡ በተለይ ከሁለት ዐመት ወዲህ በመሀል ከተማ እየተካሄደ ያለው መልሶ ማልማት
በተነሺዎች ላይ ያለው ተቀባይነት አናሳ እየሆነ መጥቷል፡፡

በአዲሶቹ የሰፈራ አካባቢዎች የውሃ እና የመንገድ አገልግሎት የሚያቀርቡት በከተማው ማዘጋጃ ቤት ስር ያሉ


የሥራ ክፍሎች ሲሆኑ መብራት ግን አቅራቢው ከከተማው አስተዳደር መዋቅር ውጭ ያለ በመሆኑ
በተፈለገው ጊዜ አገልግሎቱን ያለማግኘት ከፍተኛ ችግር አለ፡፡ በዚህም ምክንያት ለተነሺዎች የተሰሩት ከ300
በላይ ወጭ ቆጣቢ ቤቶች የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ስራ ቢጠናቀቅም ትራንስፎርመር ባለመቅረቡ ሰዎቹ
ከነበሩበት ቦታ መነሳት አልቻሉም፤ የመልሶ ማልማቱ ፕሮጀክትም እንደታቀደው ሊጠናቀቅ አልቻለም፡፡

ለከተማ መልሶ ማልማት በተመረጡት ቦታዎች ላይ የሚኖሩት ወገኖች ለልማት ሲባል ቢነሱና ወደ ሌላ
አካባቢ ቢዛወሩ ቅሬታ እንደሌላቸው ይስማማሉ፡፡ ሆኖም ግን ባግባቡ የሚያነጋግራቸው አካልና በአዲሱ ቦታ

218
በቂ ክፍል ያለው ቤት እንዲሁም ውሃና መብራት፣ መጸዳጃ ቤት የትምህርት፣ የጤና፣ የትራንስፖርት እና
የገበያ አገልገሎት የተሟላለት አካባቢ እንዲሆን፤ በቂ ካሳም እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ሁሉ ከተሟላ
እና በሂደቱ እስከተሳተፉ ድረስ ከነባሩ ቤትና ሰፈራቸው በመፈናቀላቸው ለከተማው ልማት በመሆኑ
እምብዛም እንደማይከፉ ይናገራሉ፡፡

በጅማ የልማት ተነሽዎች አስተያየት በከተማው የመልሶ ልማት ፕሮግራም አፈፃፀም እርካታቸው ዝቅተኛ
እንደሆነ ያሳያል፡፡ በተለያዩ የልማት ስራዎች ከመኖሪያቸውና ከስራ ቦታቸው የተፈናቀሉ አካባቢያቸው
ለመልሶ ልማት እንዲከለል ሲወሰንም ሆነ የምትክ ቦታ አካባቢ ሲመረጥ በሂደቱ የመሳተፍ እድል
እንዳልተሰጣቸው ነው የሚገልፁት፡፡ ይኸውም በዳሰሳ ጥናቱ ከተሳተፉ ተነሽዎች መካከል 56.7% የሚሆኑት
አግባብነት ያለው ተሳትፎ ያለማድረጋቸው፣ 88.4% ለመነሳት የተሰጣቸው የዝግጅት ጊዜ አነስተኛ መሆኑን፣
96.7% ለተነሺዎቸ የሚደረግ እገዛ አለመኖሩን፣ 76.7% ለሚያቀርቡት ጥያቄና ቅሬታ ተገቢውን መልስ
ያለማግኘታቸው፣ እንዲሁም 93.3% መልሶ ልማቱ በጥራትና በፍጥነት የማይተገበር መሆኑን ይገልፃሉ፡፡

በመልሶ ልማት ለሚነሱ የቀበሌ ቤት ተከራዮች መልሶ ማስፈሪያ ተለዋጭ ቤት ባለሃብቶች እንዲገነቡ የከተማ
አስተዳደሩ መሬት የሚያቀርብላቸው ሲሆን ቦታው የተሰጠው ባለሀብት ምትክ ቤቶቹን ገንብቶ ለማዛገጃ ቤቱ
ያስረክባል፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ሁሉ ሂደት የልማት ተነሺዎቹ በሂደቱ ምንም ዓይነት ተሳተፎ የላቸውም፡፡
ነዋሪዎቹ መቼ እንደሚነሱ ሳያውቁ በድንገት ወደ ተገነባላቸው ቤት እንዲገቡ ሲደረግ መቆየቱንም ይገልፃሉ፡፡
ከዚህ በባሰ ከአየር ማሪፊያ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የተነሱት 47 ቤተሰቦች ምትክ ቤትም ይሁን መሬት
ሳይዘጋጅላቸው በድንገት መኖሪያቸውን እንዲለቁ በመደረጉ ከአንድ ዓመት በላይ በግለሰብ ግቢ መጠለያነት
ለመኖር ተገደዋል፡፡

ስእል 3.58፡ በጅማ ከተማ ተነሺዎች በመልሶ ልማት ትግበራ ላይ የሰጡት ግምገማ

ምንጭ፡ መስክ ዳሰሳ፣ መጋቢት 2008

219
በቅርቡ እንደሚነሱ የተነገራቸው ነዋሪዎችም በመልሶ ልማት ትግበራ ሂደት በሰጡት አስተያየት ባለሙያዎችና
የአመራር አካላት የልማት ተነሺዎችን የማወያየት ልምድ እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቅሰው ቀደም ሲል የነበረው
አካሄድ ብዙ ክፍተት እንደነበረው ይገልፃሉ፡፡ በዳሰሳ ጥናቱ ከተሳተፉ ነዋሪዎች 45% የሚሆኑት ብቻ ናቸው
ተሳትፎው አርኪ ነው የሚል ምላሽ የሰጡት፡፡

ስእል 3.59፡ ጅማ ከተማ ላይ ቀጣይ ተነሺዎች በመልሶ ልማት ትግበራ ላይ የሰጡት ግምገማ

ምንጭ፡ መስክ ዳሰሳ

ድሬዳዋ ከተማ ላይ ምንም እንኳ በመልሶ ልማት እስካሁን የተደረጉ እንቅስቃሴዎች በተሟላ ዕቅድና ዝግጅት
የተከናወኑ ባይሆንም በተለይ ከካሣ ክፍያና ምትክ ቤት/ቦታ ምደባ ጋር በተያያዘ ከተነሺዎች ጋር በቂ
ውይይትና ምክክር እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ስእል 3.60፡ በድሬዳዋ በከተማ ካሣ ክፍያና ምትክ ቤት/ቦታ አሠጣጥ ዙሪያ ከተነሺዎች ጋር ከተካሄዱ
ውይይቶች አንዱ

ምንጭ፡ ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር


220
በድሬዳዋ በመልሶ ልማቱ ዙሪያ ምክክርና ውይይት የሚካሄድ መሆኑ በተነሽዎቹ በኩል ባይካድም መድረኩ
የእነሱ ፍላጎትና ችግር የሚደመጥበት ሳይሆን የአስተዳደሩን ውሳኔ እንዲቀበሉ ግፊት የሚደረግበት የአንድ
ወገን ፍላጎት ማስፈፀሚያ ነው የሚል ስሜት በተነሽዎቹ ይንፀባረቃል፡፡

በዳሰሳ ጥናቱ ከተሳተፉ ተነሽዎች መካከል ለተሳትፎ 10% በጣም ጥሩ የሚል ግምገማ የሰጡት ሲሆኑ 52%
የሚሆኑት ጥሩ፣ 35% የሚሆኑት ከመካከለኛ በታች ነው የሚል አስተያየት ነው ያላቸው (ሰንጠረዥ 32)፡፡

በሌላ በኩል አስተዳደሩ ተነሽዎችን ማነጋገር የሚጀምረው ቦታው ለአዲስ ግንባታ/መልሶ ልማት እንዲውል
የካቢኔ ውሳኔ ካረፈበት በኋላ እንደሆነና የውይይቱ ዋና አጀንዳም አካባቢው ለመልሶ ልማት የተከለለ መሆኑን
ለነዋሪው ማሳወቅ እና ነዋሪዎቹ ከቦታው በሚነሱት አግባብ ዙሪያ መነጋገር እንደሆነ የስብሰባውን ሂደት
ከሚያሳይ ዶክሜንተሪ ፊልም ይዘት መረዳት ተችሏል፡፡

221
ሠንጠረዥ 3፡32፡ የልማት ተነሺዎች በመልሶ ልማት አፈፃፀም ላይ ያላቸው ግምገማ (ድሬዳዋ)
የግምገማ ደረጃ ለውጤቱ ዝቅተኛነት/ከፍተኛነት ዋናው ምክንያት
ዝርዝር አማላካች በጣም ጥሩ ጥሩ መካከለኛ ዝቅተኛ በጣም ዝቅተኛ መልስ ያልሰጡ የህግና መመሪያ የአስፈፃሚ አቅም የአስፈፃ ስነ ምግባር ተነሺው ራሱ የገንዘብ እጥረት
ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር %
የቦታ መረጣ ትክክለኛነት 11 7 66 45 24 16 12 8 28 19 7 5 56 38 76 52 4 3 11 10 1 1
የተነሺዎች ተሳትፎ 15 10 76 52 21 14 18 12 13 9 5 3 12 8 22 15 16 11 86 58 3 2
የምትክ ቦታ/ቤት አመዳደብ 8 5 54 37 22 15 25 17 25 17 14 5 27 18 100 68 4 3 - - - -
የካሳ መጠን - - 9 6 11 7 50 34 71 48 7 5 17 12 85 57 6 4 1 1 - -
ለዝግጅት የተሰጠ ጊዜ 1 1 10 7 14 10 50 34 70 47 3 2 7 5 116 78 19 13 - - - -
ለተነሺዎች የሚደረግ ድጋፍ - - 2 1 12 8 59 40 72 49 3 2 9 6 107 72 23 16 - - - -
የብድር አሰጣጥ ድጋፍ - - 3 2 12 8 55 37 71 48 7 5 12 8 111 75 15 10 - - - -
የአገልግሎት መስተንግዶ 2 1 7 5 15 10 48 32 71 48 5 3 4 3 56 38 77 52 11 7 - -
መልሶ ልማት ፍጥነትና ጥራት 1 1 13 9 33 22 54 37 44 30 3 2 9 6 120 81 11 7 1 1 - -
ምንጭ፡- በልማት ተነሽዎች ከተሞላ ቃለ መጠይቅ የተቀመረ

222
ሐ. በልማቱ ውጤት ላይ የተነሺዎች ግምገማ

ከላይ በመልሶ ልማት ዓላማ እና የልማቱ ሂደት የነዋሪዎች ግምገማ በየከተማው የተደረገ የዳሰሳ ጥናት ውጤት
በዝርዝር ቀርቧል፡፡ የልማቱ ዓላማ የልማት ተነሺዎችን ጨምሮ በነዋሪው ሰፊ ተቀባይነት መኖሩ የዳሰሳ ጥናቱ
የአሳይቷል፡፡ ነገር ግን የልማቱ አተገባበር ሂደት ሰፊ ጉድለት የሚታይበት በመሆኑ ሕብረተሰቡ ለልማቱ ዓላማ
የሰጠው ይሁንታ ሊቀንስ፣ ብሎም ለቋረጥ ይችላል፡፡ ለዓላማ የተሰጠ ድጋፍና በትግበራ ሂደት ላይ እየተፈጠረ
ያለው ቅሬታ ሚዛን የሚገለፀው ደግሞ በልማቱ ውጤት በመሆኑ ነዋሪዎች በመልሶ ልማት ውጤት ያላቸው
ዕይታም መዳሰስ ተገቢ ነው፤ የተደረገው የዳሰሳ ውጤትም ከዚህ ቀጥሎ በዝርዝር ቀርቧል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የመልሶ ልማት የሚነካቸው ነዋሪዎች በልማቱ ውጤት ዙሪያ ያላቸውን አስተያየት
በተመለከት የተካሄደ ዳሰሳ ጥናት ውጤት ቀጥሎ በቀረበው ምስል የተመለከተውን ይመስላል፡፡

ስእል 3.61፡ የአዲስ አበባ የልማት ተነሺ በመል ሶልማት ውጤት የሰጡት ግምገማ

ምንጭ፡ መስክ መረጃ፣ ግንቦት 2008 ዓ.ም

223
እላይ ከቀረበው መረጃ ማየት እንደሚቻለው ተነሽዎች በልማቱ ውጤት ዙሪያ በመልካም ጎንነት
የሚያነሱዋቸው ጉዳዮች የተሻለ ምትክ ቤት የሚሰጥ መሆኑ (74.3%)፣ ከነዋሪዎች ጋር መግባባት ሳይደረስ
ወደ ማፍረስ መግባት መቆሙ (54.7%)፣ ሙሉውን አፍርሶ መገንባት እንደብቸኛ አማረጭ የማይወሰድ
መሆኑ (45.3%) ናቸው፡፡ በሌላ በኩል በመልሶ መስፈሪያ አካባቢዎች የመሠረተ ልማትና ማሕባራዊ
አገልግሎቶች አለመገንባታቸው በተነሽዎች ከፍተኛ ቅሬታ (85%) አሳድሯል፤ በመልሶ ማስፈርያ የመንገድ፣
ውሀ፣ እና ኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች በፍጥነት ያለማድረስ (86.7%)፣ የምትክ ቤት ዋጋ በዝቅተኛ ገቢ
ለሚተዳደር የህብረተሰብ ክፍል ያማከለ አለመሆኑ (71.9%)፣ አረንጓዴ እና ክፍት ቦታዎች ትኩረት ያላገኙ
መሆናቸው (73.5%)፣ የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባርና አመለካከት መኖሩ (62.5%)፣ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ
ተነሽዎች ተገቢውን ድጋፍ ያለመስጠት (61.7%)፣ የፈረሰ ቦታ ቶሎ ያለመልማት (58.6%)፣ በተዋናዮች
መካከል ቅንጅታዊ አሰራር የሌለ መሆኑ (58.6%) እንዲሁም በታቀደው ልክ የማይሰራ መሆኑ (48.4%)
በነዋሪዎች እርካታ እንዳይፈጠር ካደረጉት ዋና ምክንያቶች በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ስእል 3.62፡ አዲስ አበባ በቦታቸው ላይ እንዲያለሙ የተፈቀደላቸው በመ/ልማቱ ውጤት ያላቸው ግምገማ

ምንጭ፡ መስክ መረጃ፣ ግንቦት 2008 ዓ.ም

224
በቦታቸው እንዲያለሙ የተፈቀደላቸው ነዋሪዎች የመልሶ ልማቱ ውጤት ግምገማ ተነሺዎቹ ከሰጡት ግምገማ
የተለየ ይሆናል ተብሎ ቢገመትም ልዩነት አልታየበትም፡፡ ስለዚህ ውጤቱ የነዋሪዎች እርካታ እጅጉን
የሚቀንሱ ምክንያት ትኩረት ተሰጥቶአቸው ማስተካከል ካልተደረገ ነዋሪው ለልማቱ እየሰጠው ያለ ድጋፍ
ሊቀለበስ ይችላል፡፡ ነዋሪው እርካታ እያጣባቸው የሚገኙ ልማቱ በአካባቢው ያመጣል ተብሎ የሚገመት
ተጨማሪ የከተማ እሴት እና የልማት ተነሺዎቹ የጋራ እና የግል ተጠቃሚነት ሚዛን ከመጠበቅ አኳያ ጉድለት
እንዳለበት እየታየ ነው፡፡

በደሴ ከተማ የመልሶ ማልማት ፕሮግራም እያስገኘ ያለውን ውጤት ልማቱ የሚነካቸው ወገኖች እይታ ቀጥሎ
በቀረበው ምስል የተገለፀውን ይመስላል፡፡

ስእል 3.63፡ ደሴ ከተማ የልማት ተነሺዎች በልማቱ ውጤት ላይ ያላቸው ግምገማ

ምንጭ፡ የመስክ ዳሰሳ ጥር 2008 ዓ/ም


በልማት ምክንያት ከተፈናቀሉት ነዋሪዎች በተገኘው መረጃ መሠረት ንብረት ሳይወጣ እና መግባባት ሳይደረስ
ቤቶቹ ለማፍረስ የሚደረግ ሙኮራ ያን ያህል አስከፊ እንዳልሆነ ነው የሚያመለክተው፡፡ እንዲህ ዓይነት

225
ሙኮራዎች የተከሰተው ቀደም ብሎ በለሙ ቦታዎች ላይ በመሆኑ በመጠይቁ የተገኘው መረጃ ትክክለኛነቱ
አያጠራጥርም፡፡ ለንግድ አገልግሎት እንዲውል በፕላን በፀደቀ ቦታ ላይ የሚኖሩ አካባቢው ለመልሶ ልማት
ሲውል ዓቅማቸው ከፈቀደ በጋራ ህንፃ እንዲገነቡ ስለሚፈቀድላቸው በመጠይቅ የተሰበሰበው መረጃም ይህንን
እውነታ የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ መልሶ ልማት ሲካሄድ በአስፈፃሚዎች ኪራይ ሰብሳቢነት ተግባርና አስተሳሰብ
ከባድ ችግር አይደለም የሚል እምነትም አላቸው፡፡

ከእነዚህ ውጭ በሌሎቹ የመልሶ ልማት ስኬት አመላካቾች ላይ ያላቸው አተያይ አሉታዊ ምስሉ ይጎላል፡፡
የሚሰፍሩበት ቦታ ይኖሩበት ከነበረው ቦታ መራቁና ከከተማው ዳር ቦታዎች ከመሆናቸው ጋር በተያያዘ
ከፍተኛ የትራንስፖርት ወጪ የሚያስወጣቸው በመሆኑ፣ ገቢያቸው እንደቀነሰ፣ መስፈሪያ ቦታዎች አስቀድሞ
መሰረተ ልማት ያለማሟላት የከፉ ችግሮች መሆናቸው አስቀምጠዋል፡፡ በስእላዊ መግለጫው እንደታየ
በሌሎቹ አመላካቾችም ቢሆን መልሶ ልማቱ ውጤት ላይ እርካታቸው ዝቅተኛ ነው፡፡

መልሶ ልማት በቅርቡ ከሚያነሳቸው ነዋሪዎች የተሰበሰበው መረጃም ቢሆን በትርጉም ደረጃ የተፈናቀሉት
ከሰጡት የተለየ አይደለም፡፡ ልዩነት የሚታየው ቀጣይ የሚፈናቀሉት የግምገማቸው አሉታዊ ሚዛን
ከተፈናቀሉት በላይ መሆኑ ነው፡፡

ስእል 3.64፡ ደሴ ከተማ ላይ በቅርቡ የሚፈናቀሉ በመልሶ ልማት ውጤት ላይ ያላቸው ግምገማ

ምንጭ፡ የመስክ ዳሰሳ ጥር 2008 ዓ/ም

226
ከምንም በላይ እነዚህ ነዋሪዎች ትኩረታቸውን የሳበው መልሶ ልማት በአካባቢው ስጋትና ያለመረጋጋት
ይፈጥራል የሚል እምነት ነው፡፡ ለመልሶ ማልማት በተከለሉ አካባቢዎች ላይ የቋሚ ንብረት ዋጋና/ኪራይ/
የቦታው ተፈላጊነት ለጊዜው ይቀንሳል፣ የንግድ እንቅስቃሴው ይቀዛቀዛል፣ አካባቢው ፈርሶ ሲገነባ በዙሪያው
የሚገኙ የንግድ እንቅስቃሴዎች ይስተጓጎላሉ የሚል እምነት አላቸው፡፡

መልሶ ልማት በተካሄደባው ቦታዎች የሚኖሩ የህ/ሰብ ክፍሎች ዕይታ በልማቱ ከተነሱ እጅጉን የሚቀራረብ
ሆኖ ተገኝቷል፤ የፈረሰ ቦታ ቶሎ የማይለማ መሆኑ፣ እንዲሁም ክፍትና አረንጓዴ ቦታዎች የሚሰጠው ትኩረት
ማነስ ትኩረታቸው ይበልጥ ስቦታል፡፡

ስእል 3.65፡ ደሴ ከተማ ላይ በመልሶ ልማት ያልተፈናቀሉ አካላት በመልሶ ልማት ውጤት ግምገማ

ምንጭ፡ የመስክ ዳሰሳ ጥር 2008 ዓ/ም

227
በመቀሌ ከተማ በመልሶ ልማት የተነሱ ነዋሪዎች ልማቱ ያመጣውን ውጤት በተመለከተ የሰጡት አስተያየት
ደግሞ ቀጥሎ በቀረበው ምስል የተመለከተውን ይመስላል፡፡

ስእል 3.66፡ መቐለ ከተማ ላይ በመልሶ ልማት የተፈናቀሉ በልማቱ ውጤት ላይ ያላቸው ግምገማ

ምንጭ፡ መስክ ዳሰሳ፣ ታሕሳስ 2008 ዓ/ም

በመልሶ ልማት ሂደት የሚከሰቱ ችግሮችን በተመለከተ በዳሰሳ ጥናቱ የተሰበሰው የልማት ተነሺዎች አስተያየት
ሲጠቃለል አረንጓዴና ክፍት ቦታዎችን ያለመካተት (76.7%)፣ የፈረሰ ቦታ ቶሎ ያለመልማት (66.1%)፣
የሚከፈላቸው ካሳ ቤት ለመተካት ያለማስቻል (65.3%)፣ መስፈሪያ አካባቢዎች ማሕበራዊ አገልግሎት
ያለሟሟላት (64.2%)፣ የተፈናቃዮች ገቢ መቀነስ (61.9%)፣ የትራንስፖርት ወጪ መጨመር (60.6%) ሆኖ
ተገኝቷል፡፡ በመልሶ ማስፈሪያ አካባቢዎች መሰረተ ልማት ያለማሟላት፣ በቦታው የሚኖሩ ቅድሚያ የማልማት
ዕድል ያለማግኘት፣ በታቀደው ልክ ያለመስራት፣ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር፣ መግባባት

228
ሳይደረስ ማፍረስ የሚሉትን ችግሮች ከፍተኛ ክብደት የሰጧቸው አስተያየት ሰጪዎች ለዳሰሳ ጥናቱ መልስ
ከሰጡት ከ50% በላይ ድርሻ አላቸው፡፡
ስእል 3.67፡ መቐለ ከተማ ላይ በመልሶ ልማት ያልተፈናቀሉ በልማቱ ውጤት ላይ የሰጡት

ምንጭ፡ መስክ ዳሰሳ፣ ታሕሳስ 2008 ዓ/ም

በልማቱ ያልተነሱም ቢሆን ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ግምገማ አላቸው፡፡ እጅግ ዝቅተኛ እርካታ ያሳዩባቸው ልዩ
ድጋፍ ለሚሹ ተገቢውን ድጋፍ ያለማድረግ (60.5%)፣ ተፈናቃዮች ገቢያቸው መቀነስ (60.0%)፣ መስፈሪያ
ኣካባቢዎች ቶሎ መሰረተ ልማት ያለማሟላት (54.3%)፣ አረንጓዴና ክፍት ቦታዎች ያለመካተት (55.2%)፣
ቅድሚያ የማልማት ዕድል ያለማግኘት (51.0%) ናቸው፡፡ ነገር ግን የችግሮቹ ቀጥተኛ ሰለባ ስላልሆኑ የካሳ
መጠን፣ ማሕበራዊ አገልግሎቶች ያለማሟላት፣ ሩቅ ቦታ ማስፈር፣ ለተጨማሪ ትራንስፖርት ወጪ መዳረግ
ለሚሉት መስፈርቶች በልማቱ የተነሱት ከሰጡት የክብደት ደረጃ ግምገማ በተወሰነ ደረጀ ረገብ ያለ ነው፡፡

229
ይሁንና ለእያንዳንዱ አማላካች በከፍተኛ ችግር ከ40% በላይ መሆናቸው የልማት ተነሺዎች የሰጡት ደረጃ
ክብደት የተጋነነ መሆኑን አያሳይም፡፡

በመልሶ ልማት ዓላማ፣ ትግበራ ሂደት እና ውጤት ዙሪያ የተነሺዎችን እይታ አስመልክቶ በስድስቱ ናሙና
ከተሞች የተካሄደው የዳሰሳ ጥናት ውጤት ሲጠቃለል፤
₋ በመልሶ ልማት ተጠቃሚዎች እንዳሉ ሁሉ ተጎጂዎችም ይኖራሉ፤ ነገር ግን ነዋሪዎች በልማቱ ተጠቃሚ
ሆኑም አልሆኑም ከተማቸው እንዲለወጥ ባላቸው ጽኑ ፍላጎት ሁሉም ዓላማውን ይደግፉታል፡፡
ተነሺዎች ልማቱ ሲደግፉ ከልማቱ ቀጥታ ተጠቃሚ በመሆናቸው ሳይሆን ልማቱ ለከተማው
የሚያስገኘውን ድምር ውጤት ግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ በልማቱ ቀጥተኛ ተጎጂ መሆናቸውን
እያወቁ ዜጎች ልማቱን የሚደግፉት ለልማቱ ሲባል ይዞታቸውን መልቀቅ የሚጠበቅባቸው ሕጋዊ ግዴታ
እንደሆነ በማመናቸው ነው፡፡ በአጠቃላይ መልሶ ልማቱ ሲሰራ ይህ ይደረግ፣ ያ ይሟላ ከማለት ባለፈ
የወደቁ ከተሞቻችን ባሉበት ይቀጥሉ የሚለው ወገን በጣም ውስንና እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡
₋ የተነሺዎች እርካታ ብዙ ጊዜ የሚጓደለው በመልሶ ልማት ፕሮጀክቶች ትግበራ ሂደት በሚከሰቱ
የአፈፃፀም ክፍተቶች/ችግሮች ዙሪያ ነው፡፡ በዚህ ረገድ በዳሰሳ ጥናቱ ተደጋግሞ የተጠቀሰው ችግር
በልማት አማራጭ፣ በመልሶ ማቋቋምና በካሳ ክፍያ ዙሪያ የተነሽዎች ድምጽ የሚሰማበት ዕድል ጠባብ
መሆኑ ነው፡፡ የልማት ተነሺዎች ተሳትፎ የይስሙላ ያህል እንጂ ሕጋዊ መብቶቻቸውንና ጥቅሞቻቸውን
ማስከበር የሚችሉበት መድረክ እያገኙ አይደለም፡፡ በመልካም ምሳሌነት የሚጠቀሰውን የአዲስ
አበባውን የልደታ መልሶ ልማት ተሞክሮ በሌሎች ከተሞችና ፕሮጀክቶች መድገም አልተቻለም፡፡
₋ የስድስቱ ናሙና ከተሞች የእስካሁን ተሞክሮ እንሚያሳየው የመልሶ ልማት እርምጃዎቻችን ውጤቶች
በአወንታም በአሉታ የሚፈረጁ ናቸው፡፡ አወንታዊ ውጤቶቹ በከተሞች ገጽታ መሻሻል፣ በነዋሪዎች
መኖሪያና ሥራ አካባቢ መሻሻል ሲገለፁ በአፈጻፀም ጉድለት የተነሣ የልማት ተነሽዎች የሚከፍሉት
ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዋጋ በአሉታዊ ጎን የሚጠቀስ ነው፡፡

3.2.10.2. የልማት ተነሺዎች አያያዝ


በአገሪቱ ከተሞች የመልሶ ልማት እንቅስቃሴ የልማት ተነሺዎችን አያያዝና መስተንግዶ ክስተቱ ወጥነት
የጎደለውና ሰፊ ክፍተት የሚስተዋልበት ነው፡፡ በናሙናነት ከተወሰዱት ከተሞች አንዱ አዲስ አበባ በቅድመ
1983 ከአንድ አካባቢ ብዛት ያለው ነዋሪን ከመሃል ከተማ ወደ ዳርቻ ያፈናቀለ እርምጃ የተወሰደው በፖስታ
ቤት አካባቢ ለጎርፍ አደጋ የተጋለጡ ቦታዎች ላይ ሰፍሮ የነበረውን ነዋሪ ወረዳ 24 ብሔረ ጽጌ ተብሎ
ወደሚታወቅ አካባቢ ያዛወረው የከተማ አስተዳደሩ እርምጃ ነበር፡፡ ሂደቱ በተቻለ መጠን ተነሽዎችን በአንድ
ላይ የማንሳትና በአንድ አካባቢ የማስፈር ጥረት የተደረገበት በመሆኑ በማህበራዊ ትስስር ላይ ያሳረፈው ጫና
ውሱን ነበር፡፡

230
ከ1983 ወዲህ ከተካሄዱና በአንድ ጊዜ ብዙ ነዋሪ ካስነሱ የመልሶ ልማት ፕሮጀክቶች መካከል የሸራተን አዲስና
የደንበል ገበያ ማዕከል ፕሮጀክቶች በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

እነዚህ ፕሮጀክቶች የሚታወቁት በርካታ ነዋሪዎችን በማስነሳት ብቻ ሳይሆን ተነሽዎችን መልሶ በማስፈር ሂደት
የግል አልሚዎችን በማሣተፋቸው በበጎ ጎናቸው ጭምር ነው፡፡ በተቻለ መጠን ተከራዮችንና የግል
ባለይዞታዎችን በአንድ አካባቢ እንዲሰፍሩ ለማድረግ የተደረገው ጥረት በፕሮጀክቶቹ የታየው ሌላው መልካም
ተሞክሮ ነው፡፡ ይህ ሂደት የተነሺዎች ማህበራዊ ትስስር በተወሰነ ደረጃ ሳይበጣጠስ እንዲቀጥል ያስቻለ
ነበር፡፡

በአዲስ አበባ የቀለበት መንገድ ተነሺዎች መስተንግዶ ከዚህ በተለየ ሁኔታ ነበር የተከናወነው፡፡ በወቅቱ ወጥ
የሆነ የአፈጻጸም መመርያ ስላለነበረ ለተነሺዎች ምትክ ቤት የተሰጠበት አግባብ አልነበረም፡፡ በዚህ ፕሮጀክት
የተደረገው ለግል ባለይዞታዎች ካሳና ምትክ ቦታ፣ ለተከራዮች ደግሞ የ12 ወር ቤት ኪራይ ብር 1,200 ብቻ
መስጠት ነው፡፡

በወቅቱ ተነሽዎች ከመኖሪያና ከሥራ ቦታቸው በመፈናቀላቸው ምክንያት የደረሰባቸውን የገቢና ስራ ማጣት
ችግር የሚያካክስ የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ ያልነበረ መሆኑ ሁሉም ፕሮጀክቶች አንድ ያደርጋቸዋል፡፡ የተወሰነ
ሙከራ ተደርጓል ከተባለ ለሸራተን ተነሺዎች ከአዲሱ ሰፈር ወደ መሃል ከተማ ተፈናቃዮችን የሚያመላልስ
የትራንስፖርት አገልግሎት ለተወሰነ ጊዜ መመቻቸቱ ነው፡፡ ይህም ለረዥም ጊዜ አልዘለቀም፤ ጥረቱ ግን በበጎ
ትምህርት የሚጠቀስ ነው (አበበ፣ 2001)፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ከተሞች የልማት ተነሽዎች አያያዝና መስተንግንዶ የሚገዛው ለህዝብ
ጥቅም ሲባል በሚለቀቅ መሬት ላይ ለሰፈረ ንብረት የሚከፈል ካሳንና ምትክ ቦታ/ቤት አሰጣጥን በተመለከተ
በኢፌዲሪ መንግሥት እና በከተማ አስተዳደሮቹ በወጡ አዋጆችና ደንቦች ድንጋጌ መሠረት ነው፡፡ እንደ አገር
ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትና ለንብረት ካሳ የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን በኢፌዲሪ
መንግሥት የወጣው አዋጅ ቁጥር 455/1997 እና ይህንን አዋጅ ለማስፈፀም የወጣው የሚኒስትሮች ም/ቤት
ደንብ ቁጥር 135/1999 ገዢ ናቸው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በዚህ ረገድ ቀጥታ በአሁኑ ጊዜ በስራ ላይ የሚገኝ አግባብነት ያለው የሕግ ማዕቀፍ
ለሕዝብ ጥቅም ሲባል በሚለቀቅ መሬት ላይ ለሰፈረ ንብረት ስለሚከፈል ካሳና ምትክ ቦታ አሰጣጥ የአፈፃፀም
መመሪያ ቁጥር 19/2006 ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ሥራውን ሲያከናውን በዋናነት የሚመራው
በእነዚህ የሕግ ሰነዶች ነው፤ ከዚህ በተጨማሪ ለከተማ ማደስ ፕሮጀክት የሚከለሉ ቦታዎችን ለመለየት
የከተማውን መዋቅራዊ ፕላንና የአካባቢ ልማት ፕላኖችን እንደመነሻ ይወስዳል፡፡ በእነዚህ ሰነዶች ላይ

231
ተመስርቶ የፕሮጀክት ክልልን ከወሰነ በኋላ ቀጥሎ በፕሮጀክት ክልሉ የሰፈሩትን ነዋሪዎች እና ተቋማት
ማንነትና በቦታው ያላቸውን ሕጋዊ መብት ወደ ማጣራቱ ይሸጋገራል፡፡

በዚህ መሠረት ኤጀንሲው በከተማ ማደስ ፕሮጀክት ክልል ውስጥ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ንግግር የሚጀምረው
ቦታው ለከተማ ማደስ ፕሮጀክት ከተከለለና ነዋሪዎቹ ከአካባቢው እንዲነሱ ከተወሰነ በኋላ ነው፡፡ በዚህ
መሠረት ከዚህ በኋላ በተነሺዎችና በከተማ አስተዳደሩ መካከል የሚካሄደው ምክክርና ውይይት ዋና አጀንዳ
በምትክ ቦታ/ቤት አሠጣጥ፣ በካሣ ክፍያ ግምት፣ ቦታውን ለቀው ከአካባቢው በሚነሱበት ጊዜ ሰሌዳ ላይ
ይሆናል ማለት ነው፡፡

እርግጥ ነው የከተማው መሪ ፕላን ባስቀመጠው የመሬት አጠቃቀምና የልማት ደረጃ የማልማት አቅምና
ፍላጎት ያላቸው ነዋሪዎች በመልሶ ማልማቱ የመሳተፍ ዕድል እንደ አማራጭ ይሰጣቸዋል፡፡ ነገር ከተነሽዎች
መካከል አብዛኞቹ አቅም ስለሌላቸው የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን አይችሉም፡፡

በዚህ መሠረት የልማት ተነሽዎች አያያዝና መስተንግዶ ከምትክ ቦታ/ቤት አሠጣጥ፣ እንዲሁም ከካሣ ክፍያ
እና ከግንባታ ማፍረስ ሂደት ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ በከተማ አስተዳደሩ መመሪያ ቁጥር 19/2006 ድንጋጌ
መሠረት አስተዳደሩ በከተማ ማደስ ፕሮጀክቱ ዓላማና ፋይዳ ዙሪያ ከልማት ተነሽዎች ጋር መወያየትና የጋራ
መግባባት ላይ መድረስ ይጠበቅበታል፡፡ ተነሸዎችም በተወካዮቻቸው ወይም በቀጥታ እላይ በተጠቀሱት
ጉዳዮች ዙሪያ ከአስተዳደሩ ጋር የሚወያዩበት መድረክ መመቻቸት እንዳለበት መመሪያው ይደነግጋል፡፡

ከተነሽዎች ¾ እና ከዚያ በላይ የሆኑ ነዋሪዎች በሚሳተፉበት መድረክ ላይ ከሚመረጡ የነዋሪ ተወካይ ጋር
አስተዳደሩ የጋራ መግባቢያ ሰነድ መፈራረም እንዳለበት እላይ የተጠቀሰው መመሪያ ይደነግጋል፡፡ በመልሶ
ልማት ዙሪያ በተለያየ ደረጃ የሚሳተፉ አስፈፃሚዎች እንደሚያስረዱት ይህ አካሄድ በተሟላ ደረጃ ተግባራዊ
የተደረገው በልደታ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ላይ ነው፤ በሌሎቹ ፕሮጀክቶች መመሪያውን በመተግበሩ ረገድ
ክፍተቶች እንደሚታዩ ሂደቱን በቅርበት የሚከታተሉ አካላት ያትታሉ፡፡

የልማት ተነሽዎች በተሳትፎ ዙሪያ ያላቸውን እርካታ በተመለከተ በዚህ ጥናት ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት
መልስ የተሟላ ተሳትፎ እንደማያደርጉ የሚጠቁም ነው፤ በተሳትፎው ከፍተኛ እርካታ ያላቸው ጥቂቶች ናቸው
/14%/፡፡ በቦታው ላይ የማልማት ዕድል የተሰጣቸው ባለሃብቶች በተሳትፎ ዙሪያ ያላቸው አስተያየት ከልማት
ተነሽዎች የተለየ አይደለም /8% ከፍተኛ እርካታ/፡፡

በቦታ መረጣ በኩልም ባለው አካሄድ ተነሽዎችም ሆኑ አልሚዎች ደስተኛ እንዳልሆኑ የሰጡት አስተያየት
ይጠቁማል፤ በዚህ ጉዳይ ከፍተኛ እርክታ ያላቸው አልሚዎችና ተነሽዎች እንደ ቅደም ተከተላቸው 16% እና
8.5% ናቸው፡፡

232
ቀደም ሲል እንደተገለፀው በአዲስ አበባ በተነሺዎች አያያዝና ተሳትፎ በኩል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሚታየው
አካሄድ ቀደም ሲል በተተገበሩ ፕሮጀክቶች የተሻለ ተሞክሮ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ለምሳሌ በ1980ዎቹ
አጋማሽ ሸራተን አዲስ በተሰራበት ቦታ ላይ የነበሩ ነዋሪዎች የተነሱበትን ሂደት ስንፈትሽ አሁን ካለው የተሻለ
አካሄድ እንደነበር ለመገንዘብ እንችላለን፡፡ በዚህ ፕሮጀክት ቦታ ላይ የነበሩ ነዋሪዎች በሚሰፍሩበት አካባቢ
ምርጫ፣ በሚሠጣቸው ምትክ ቤት ዓይነትና በድኅረ - መነሳት ስለሚደረግላቸው ድጋፍ ከአልሚው ጋር ሰፊ
ድርድርና ምክክር ማድረጋቸውን ተነሽዎች ያስረዳሉ፡፡

ተነሺዎቹ የሰፈሩበት የአልታድ መንደር የተመረጠው የተነሺ ተወካዮች በተካተቱበት ቡድን ሲሆን ቡድኑ
በአማራጭ ቦታዎች ምልከታ ካደረገ በኋላ ነው፡፡ ነዋሪዎቹ ከመነሳታቸው በፊት ለ10 ያህል ጊዜ ውይይት
የተደረገ ሲሆን ውይይቱ የተነሺዎቹ ተወካይ፣ ባለሀብቱ፣ የከተማው ከንቲባ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸው
የመንግስት ኃላፊዎች የተሳተፉበት ነበር፡፡ በአልታድ መንደር ቤቶቹ ሲሰሩም የተነሺዎቹ 10 ተወካዮች
የግንባታውን ሂደት የተከታተሉ ሲሆን ተወካዮቹም በግንባታው ጥራቱ ላይ አስተያየትና ሀሳብ የሚሰጡበት
ዕድል ተመቻችቶላቸው ነበር፡፡

ግንባታው እንደተጠናቀቀም ህዝቡ ለመነሣት ዝግጁ የሚሆንበትን ጊዜ እንዲገልጽ እድል የተሰጠው ሲሆን
ባለሀብቱም የተነሽዎችን ጊዜ ሰሌዳ ተቀብለው የማስነሣት ሂደቱ በዚያው አግባብ እንዲፈፀም ተደርጓል፡፡
በመሆኑም የልማት ተነሽዎችን ለረዥም ጊዜ ከኖሩበት አካባቢ ለማንሳት በሚወሰደው እርምጃ
የሚስተዋለውን ውጥረት ለማስወገድ ከሸራተን ፕሮጀክት ተሞክሮ ትልቅ ትምህርት መውሰድ ይቻላል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከተካሄዱ የመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች መካከል ሌላው በመልካም ተሞክሮ
የሚጠቀሰው የልደታ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ነው፡፡ በዚህ ፕሮጀክት አፈፃፀም አግባብ ያላቸው የከተማ
አስተዳደሩ አካላት የቅርብ ክትትል ያደረጉበት፣ ነዋሪውም ፍላጎቱን እንዲገልፅ የሚያስችል መድረክ
እንደነበረው በሂደቱን በቅርብ የተከታተሉ ኃላፊዎች ያወሳሉ፡፡ የልደታ መልሶ ልማት ፕሮጀክት ነዋሪዎችን
በማሳተፍ የተሻለ ሥራ የተሠራበት መሆኑን ከአካባቢው የተነሱ ነዋሪዎች ጭምር ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፤
አካባቢውን ለመልሶ ልማት ከተከለለበት ጊዜ ጀምሮ ነዋሪዎች ተነስተው ወደ መልሶ መስፈሪያ ቦታ
እስከተዛወሩበት ጊዜ ድረስ ከ11 በላይ የጋራ ውይይት መድረክ እንደተዘጋጀ ፕሮጀክቱን በበላይነት የመሩት
የአስተዳደሩ ኃላፊዎች ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ውይይት ላይ ከንቲባውን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ የበላይ
ኃላፊዎች ከነዋሪው ጋር ለውይይት የተቀመጡባቸው አጋጣሚዎች እንደነበሩ ይታወቃል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በአሁኑ ጊዜ ለመልሶ ልማት በተከለሉ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች በሌላ አካባቢ የታዩ
ችግሮች እነሱም እንዳይገጥሟቸው ስጋታቸውን ይገልፃሉ፡፡ ለምሳሌ በተክለሃይማኖት መልሶ ልማት ፕሮጀክት
ክልል የሚገኙ ነዋሪዎች አስተያየት እንዲሰጡ በዚህ ጥናት ለቀረበላቸው ጥያቄ ሁሉም ማለት ይቻላል ልማቱን
የማይቃወሙ፣ የተሻለ ነገር እንዲሰራም የሚፈልጉ፣ አካባቢው ያረጀ የተጨናነቀ፣ ለእይታ፣ ለመኖርያም ሆነ

233
ለሥራ አመቺ እንዳልሆነ የሚገነዘቡ፣ አካባቢው በአሁኑ ጊዜ በመሃል አዲስ አበባ እየመጣ ካለው ለውጥ ጋር
አብሮ የማይሄድ በመሆኑ መታደሱ እንደማይቀርለት መሆኑ የሚያምኑ፣ ቢሆኑም
 የግል ባለይዞታዎች ምትክ ቦታ የሚሰጣቸው በከተማ ዳርቻ በመሆኑ ለልጆቻቸው ት/ቤት ማግኘት
ችግር ይገጥመናል የሚል ስጋት አላቸው
 ማህበራዊ ትስስራቸውም እንዳይፈርስ ትልቅ ስጋት እንደሆነባቸው ይናገራሉ፡፡ ከ40 ዓመት በላይ
ያሳለፉት ማህበራዊ ግንኙነት (መረዳዳቱ፣ ሲጣሉ መታረቁ፣ እቃ መዋዋሱ፣ መበዳደሩ፣ ሲታመሙ
መጠያየቁ፣ ሲሞቱ መቀባበሩ) ይቋረጣል የሚል ስጋት አላቸው፡፡
 ሰፈራቸው ከመርካቶ በቅርብ እርቀት የሚገኝ እንደ መሆኑ መጠን የሥራ አካባቢ ነው፤ በመሆኑም
ከዚህ አካባቢ ሲነሱ ሥራቸውን ለመቀጠል እንደሚቸገሩ ይገልፃሉ፤ ለምሳሌ ከዚህ ቀደም ለገጣፎ
አካባቢ የኮንዶሚኒየም ዕጣ የደረሳቸው አዲሱን ቤታቸውን ትተው እየተመለሱ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

ከዚህ በመነሣት መነሳታችን ካልቀረ ለምን በአካባቢያችን ኮንዲሚኒየም ቤት ተሰርቶ እንድንዛወር አይደረግም
የሚል ጥያቄ በነዋሪዎች ይነሣል፤ ከመኖሪያ አካባቢያችን ስንርቅ ከስራና ማህበራዊ ኑሮአችን ጭምር
እንፈናቀላለን ይላሉ፡፡ በአነስተኛ የንግድ ስራ የሚተዳደረው ማህበረሰብ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ስለሚወድቅ
መንግሥት ሊያስብበት ይገባል የሚል አስተያየትም ይሰጣሉ፡፡

በድምሩ ሲታይ በልማት ተነሺዎች አያያዝ ከአዲስ አበባ ከተማ የመልሶ ልማት ተሞክሮ ሊወሰዱ ከሚችሉ በጎ
ተስፋዎችና መጎልበት ካለባቸው በጎ ጎኖች መካከል የሚከተሉት አበይት ናቸው፤
 በልማቱ አስፈላጊነትና ዓላማ ዙሪያ በባለድርሻ አካላት ዘንድ መግባባትና የጋራ እምነት መያዝ፣
 የልማት ተነሺዎች ወደ ኮንዶሚኒየም ቤት የሚገቡበትን ሁኔታ ማመቻቸት የመዲናዋን ነዋሪዎች
ከቤት ተከራይነት ወደ ቤት ባለቤትነት የሚያሸጋገረው መሆኑ፣ ለፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል፤ ለስራ
ትጋትና ለቁጠባ የሚያነሣሣ መሆኑ፣
 አቅም ያላቸው የልማት ተነሺዎችን አካታች የሆነ የመልሶ ማልማት /ለምሳሌ የመርካቶ፣ ኮልፌ፣
ጨርቆስ መልሶ ማልማት/
 ከአነስተኛ ይዞታና ቤት ለሚነሱ ወገኖች ቤት አልባ እንዳይሆኑና ደረጃውን የጠበቀ ቤት
እንዲኖራቸው የሚደረገው ድጋፍ

በልማት ተነሺዎች አያያዝና መስተንግዶ በደሴ ከተማ ያለው ተሞክሮ በሌሎች ከተሞች ከሚታየው ብዙም
የተለየ አይደለም፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ስራ አስፈፃሚ ከነዋሪው ጋር የሚያደርገው ውይይት አጀንዳ የልማት
ተነሽዎችን ይዞታቸው ለመልሶ ልማት ፕሮጀክት እንዲለቁ ከማሳመን የሚያልፍ አይደለም፡፡ በልማት ተነሽዎች
አያያዝ ደሴን ከሌሎች ከተሞች የተለየ የሚያደርገው ለመልሶ መስፈሪያ በሚመርጣቸው ቦታዎች ነው፤ ብዙ

234
ጊዜ የከተማ አስተዳደሩ ለልማት ተነሺዎች የሚመድባቸው ቦታዎች ገደላማ፣ ለኑሮ የማይመቹና ለጎርና
የመሬት ናዳ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ናቸው፡፡

በሚዘጋጁ የሕዝብ መድረኮች ላይ ለተነሺዎች የሚገለፅላቸው ነገር ቢኖር በደፈናው አካባቢው ለልማት
ስለሚፈለግ ቤታቸው እንዲፈርስ መወሰኑና ለሚፈርስባቸው ቤት ካሳ፣ ምትክ ቦታና ቤት የሚሰጣቸው መሆኑ
ነው፡፡ ውይይቶቹ የሚያካሂዱት በዋናነት በቀበሌ (ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ከከተማ ልማት ፅሕፈት ቤት
ባለሙያዎች) በመሆኑ የልማት ተነሺው ጥያቄዎችና የትኩረት አጀንዳዎች (Concerns) በተገቢው የመለየትና
የመረዳት ክፍተት እንዳለ ተነሺዎቹ ከሚያሰሙት እሮሮ በላይ በተግባር እያጋጠማቸው ካለው ተጨባጭ
ሁኔታ የበለጠ መረዳት ይቻላል፡፡

የልማት ተነሺዎች ከመነሳታቸው በፊትም ሆነ ከተነሱ በኋላ ለሚያነሱዋቸው የመብትና ፍትሓዊ አያያዝ
ጥያቄዎች ተገቢውን መልስ ከመስጠት ይልቅ እንዲህ አይነት ጥያቄ የሚያነሱትን ልማትን እንደሚፃረሩ
ተደርገው እንዲፈረጁ፣ ከህዝብ እንዲነጠሉ፣ ጥያቄው የበርካታ ተነሺዎች ሲሆን ደግሞ በአድመኝነት እየፈረጁ
ማሳቀቅ በደሴ የተለመደ አካሄድ እንደሆነ የልማት ተነሺዎች በስፋት አውስቷል፡፡

ለልማት የተከለሉ አካባቢዎችን እንዲለቁ የሚሰጣቸውን የዝግጅት ጊዜ በተመለከተ የደሴ ከተማ ተሞክሮ ሰፊ
ክፈተት ታይቶበታል፤ ለምሳሌ በ2000 ዓ.ም መናፈሻ አካባቢ በቀበሌ ቤት ይኖሩ የነበሩ ተነሽዎች
አካባቢያቸው ለልማት እንደሚፈለግ በተነገራቸው ማግሥት ቤታቸው በዶዘር መፍረሱን ያወሳሉ፡፡ ይህ
አካሄድ የተመረጠው ነዋሪዎች ሳያንገራግሩ ፈጥነው ንብረታቸውን እንዲያሸሹና አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ
ለማድርግ እንደነበር ነዋሪዎቹ ገልፀዋል፡፡ በዚህ መንገድ ግፊት የተደረገባቸው 65 ቤተሰቦች በአንድ ሳምንት
ውስጥ አካባቢውን ለቀው እንደሄዱ አውስቷል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሁኔታው የተወሰነ መሻሻል እየታየበት የመጣ መሆኑን በቅርብ ጊዜ የተነሱና በቀጣይ
እንዲለማ በተከለለ ቦታ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች ከሰጡት አስተያየት ለመረዳት ተችሏል፡፡ ለልማት በሚፈለጉ
አካባቢዎች የሚኖሩ ቦታው እንደሚፈርስ መደበኛ ባልሆነ መንገድ መረጃው ቀደም ብሎ እንደሚደርሳቸው
አራዳ ከሚኖሩና ከተለያዩ ቦታዎች ተነስተው በግ ተራ እና ሰንሰል ሰፈር ከሰፈሩ ነዋሪዎች ጋር ከተደረጉ
ውይይቶች ለማወቅ ተችሏል፡፡ ቀደም ሲል መደበኛ ባልሆነ መንገድ መረጃ ይደርሰው ለነበረ ሕብረተሰብ
አሁን አሁን ስርዓቱን ጠብቆ መረጃ የሚሰጥበት አካሄድ እየተለመደ መጥቷል፡፡ ለምሳሌ ከሰኞ ገበያ እና
አይጠየፍ አዳራሽ አካባቢዎች የተነሱት ነዋሪዎች ከመነሳታቸው በፊት በርካታ ጊዜ ውይይት እንዳካሄዱ
ገልፀዋል፡፡ ነገር ግን የሚመለከተው አካል ተነሺዎቹን በይፉ ካወያያቸው በኋላ የሚኖራቸው ጊዜ አጭርና
አጣዳፊ እንደሆነ ነዋሪዎቹ ይገልፃሉ፡፡ የዝግጅት ጊዜው ከአንድ ሳምንት እንደማይበልጥ አውስቷል፡፡

በተለይ በቀበሌ ቤቶች ይኖሩ የነበሩ የልማት ተነሺዎች የተሰጣቸው የዝግጅት ጊዜ አጭር በመሆኑ እጅግ
ፈታኝ ጊዜ እንዳሳለፉ ገልፀዋል፡፡ ምትክ ቤት ሳይሰጣቸው መኖሪያ ቤታቸው ፈርሷል፤ ምትክ የቀበሌ ቤት

235
ለመገንባት በተዘጋጀው ቦታ ላይ የእንጨት ግድግዳ ካቆሙ በኋላ ሌሊት በማዳበሪያ/ሸራ/ ጋርደው እያደሩ ቀን
ጭቃ እየመረጉ ቤቶቹን እንደሰሯቸው ያስታውሳሉ፡፡

በደሴ የዝግጅት ጊዜ ከይዞታ ዓይነት የተለያየ ጭምር ነው፡፡ የግል ባለይዞታዎች ይኖሩበት የነበረ ሰፈር
ለልማት ሲባል እንደሚፈለግ በይፋ ከተነገራቸው በኋላ ቢያንስ 6 ወር ያህል ቤታቸው ሳይፈርስ ይቆያል፡፡
የግል ባለይዞታዎች ከቀበሌ ቤት ተከራዮች ቀድሞ መረጃ ይደርሳቸዋል፡፡ የቀበሌ ቤት ተከራዮች መኖሪያቸው
እንደሚፈርስ የሚነገራቸው በድንገት ነው፤ ለዚህም ነው የቀበሌ ቤት ተከራዮች በፌደራል የካሳ ክፍያ አዋጅና
በክልሉ መመሪያ (መመሪያ ቁጥር 6/2ዐዐ6) የተደነገገው የሶስት ወር መዘጋጃ ጊዜ አለአግባብ ተሸሮ ነዋሪዎች
በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ የሚገደዱት፡፡ እንደ ነዋሪዎቹ መረጃ ከሆኑ
ደሴ ላይ ቤት ለመገንባት ቢያንስ 6 ወር ይጠይቃል፡፡ ይህንን ኣልተከበረም፤ የከተማ አስተዳደሩ አቅም
የለውም በሚል ሰበብ አዋጁ ያስቀመጠው የአንድ ዓመት የቤት ኪራይ ወጪ ያለመክፈልም በደሴ ከተማ
የተለመደ ነው፡፡

ተነሺዎች መንግሥት ወደ ሚያሠራው የኮንዶሚንየም የጋራ ቤቶች የሚገቡ ከሆነ የቤቱን ዋጋ ግምት ከ3ዐ-
35%፣ በግላቸው ቤት የሚገነቡ ከሆነ ደግሞ 2ዐ% በዝግ የባንክ ሒሳብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል (መመሪያ
ቁ6/2ዐዐ6)፡፡ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኝ ቤተሰብ ይህን ያህል ገንዘብ በዝግ የባንክ ሂሳብ ማስቀመጥ
ትልቅ ፈተና ነው፤ ለግንባታ መዋል የሚገባው ገንዘብ ከመነሻውም በዝግ ሒሳብ እንዲታሰር መደረጉ የልማት
ተነሺዎችን ዓቅም የሚያዳክም እንጂ የሚያጎለብት ኣይደለም፡፡

ሌላው ከተነሺዎች አያያዥ የሚነሳው መሰረታዊ ጉዳይ ለፈረሰ ቤት የሚከፈል የካሳ ግምት ጉዳይ ነው፡፡ የካሰ
ግምት ያንሳል፣ የነበረውን ቤት በአዲስ መልክ ለመገንባት አያስችልም ከሚሉት በሁሉም ከተሞች ከሚሰጡ
አስተያየቶች በደሴ ከተማ የተለየ ተጨማሪ ኣሳማኝ ምክንያትም አለ፡፡ በደሴ ከተማ ለልማት ተነሽዎች
የሚሰጠው ካሳ ቤት ለመስራት በቂ የማይሆንባቸው የከተማው ልዩ የሆኑ ምክንያቶች፡
 ለልማት ተነሽዎች ምትክ ቦታ የሚሰጥበት አካባቢ ብዙ ጊዜ ገደላማ ነው፤ በመሆኑም የሚሰጠው ካሳ
መሬቱን ለመደልደልና ደጋፊ ግንብ ለመገንባት እንኳ አይበቃም፡፡ የካሳ ስሌቱም ይህንን ወጪ ታሳቢ
አያደርግም፡፡
 የልማት ተነሺዎች የሚገነቡት ቤት በከተማው መሪ ፕላን የተቀመጠውን መስፈርት ማሟላት
ይጠበቅበታል፡፡ የሚከፈለው ካሣ መጠን የሚወሰነው ደግሞ በሚፈርሰው ቤት ላይ ተመስርቶ ነው፤
በዚህ የተነሣ በካሣ ክፍያውና ለምትክ ቤት ግንባታ የሚፈለገው ገንዘብ መጠን የሚጣጣም አይደለም፡፡
 የልማት ተነሺዎች ቀደም ሲል ከነበራቸው የተሻለ ቤት መሥራት ይገባቸዋል፣ በስፋት በግንባታ
ቁሳቁስ፣ እንደ መታጠቢያና ወጥ ቤት ያሉ መገልገያዎችን ያሟላ ቤት ለመስራት የሚከፈላቸው ካሳ በቂ
አይሆንም፡፡

236
በምትክ ቦታ አሰጣጥ በደሴ ከተማ የሚስተዋለው ሌላው ለየት ያለ አሠራር መኖሪያ ቤት ወይም የንግድ
ድርጅት በልማት ምክንያት የፈረሰበት ባለይዞታ ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጥ ቤት ወይም ቦታ በስሙ
ወይም በትዳር አጋሩ የተመዘገበ በከተማው ካለው ለፈረሰበት ቤቱ ተለዋጭ ቤት ወይም ምትክ ቦታ ማግኘት
አይፈቀድለትም፡፡ ይህ አሠራር በፌደራልም ሆነ በክልሉ መንግሥት ጉዳዩን አስመልክቶ ከወጡ የሕግ
ድንጋጌዎች ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም፡፡

ቀደም ባለው ጊዜ በደሴ ከተማ የቀበሌ ቤት ተነሺዎች ምትክ ቤት መስሪያ መሬት ይሰጥ የነበረ ሲሆን ከ2004
ዓ.ም ወዲህ ቦታ መስጠት ስለቆመ ምትክ ቤት ተሰርቶ የሚሰጠው በከተማ አስተዳደሩ ነው፡፡ ነገር ግን
የከተማ አስተዳደሩ የሚገነባቸው ምትክ ቤቶች ለመኖሪያ ብቁ አይደሉም፤ ለዚህ እውነታ ከአይጠየፍ አዳራሽ
አካባቢ ለተፈናቀሉ ተነሺዎች የተገነቡት ቤቶች ጥሩ ማሳያ ናቸው፡፡

ስእል 3.68፡ ከአይጠየፍ አካባቢ ለተነሱ ተፈናቃዮች የተገነቡ ቤቶች

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ፣ ጥር 2008 ዓ/ም

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተሞችን መልሶ ማልማት ፕሮግራም ለመምራት ያወጣው መመሪያ
ቁጥር 6/2006 አንቀፅ 8.1(ለ) ፈርሰው እንዲለሙ በሚፈለጉ አካባቢዎች ወደ ትግበራ ከመግባቱ በፊት ሰነድ
አልባ ይዞታዎች ህጋዊ ባለቤትነታቸው ማንነት ተጣርቶ ህጋዊ መብት እንዲፈጠርላቸው ይደነግጋል፤ የካሳ
መመሪያውም (አንቀፅ 4) ተመሳሳይ ይዘት አለው፡፡ ይህ የሕግ ድንጋጌ ቢኖርም በተግባር ድንጋጌውን የሚጥስ
እርምጃ እንደሚወሰድ በመስክ ጉብኝት ወቅት ከልማት ተነሺዎች በተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይኸውም የሰነድ አልባ ይዞታዎች ህጋዊ ባለቤቶች ማንነት ተሟልቶ ሳይጣራ ወደ ማፍረስ የተገባበት አጋጣሚ
በርካታ ነው፡፡ የዚህ ዓይነት እርምጃ መገለጫ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል ከወላጆቻቸው በውርስና ስጦታ ቤት
የተሰጣቸው ተነሽዎች እንዲሁም ያለሰነድ በዘልማድ ቤት የገዙ ተነሺዎች ውርሱ/ሥጦታው ወይም የቤት
ግዥው በሰነድ ባለመደገፉ ብቻ የንብረት ካሣም ሆነ ምትክ ቦታ/ቤት ሳይሰጣቸው ቀርቷል፡፡ የዚህ ዓይነት
ሰነድ አልባ ይዞታ የነበራቸው ተነሺዎች ካሳና ምትክ መሬት እንደሚሰጣቸው በአካባቢው አስተዳደር

237
የተገባላቸውን ቃል አምነው ቤታቸውን ካፈረሱ በኃላ የንብረት ካሳም ሆነ ምትክ መሬት እንደተከለከሉ
ለማወቅ ተችሏል፡፡ የእነዚህ የልማት ተነሽዎች የመጨረሻ እጣ ፋንታ ቀበሌ ባሰራው 4ሜትር በ4ሜ በሆነ
መጠለያ ኪራይ እየከፈሉ መኖር ሆኗል፡፡

በልማት ተነሽዎች አያያዝና መስተንግዶ በኩል በመቀሌ ከተማ ያለው አሠራር በአንፃራዊነት በደሴ ከተማ
ከታየው የተሻለ ቢሆንም በንብረት ካሣ ግምት የሚታየው ኢ-ፍትሃዊ አሠራር ግን በተነሽዎች ሰፊ ቅሬታ
የሚቀርብበት ነው፡፡ ለምሳሌ ቀጥሎ በቀረበው ምስል ላይ የሚታዩ ሦስት ቤቶች በተገነቡበት ቁሳቁስ፣
በስፋታቸውና በዕድሜያቸው ብዙ የማይለያዩ ሆነው ሳለ የሦስቱ የካሳ ዋጋ ግምት ግን በጣም የተራራቀ ሆኖ
ነው፡፡

ስእል 3.69፡ ለንብረት /ቤት/ የሚከፈለው ካሳ የፍትሓዊነት ችግር መሆኑ የነዋሪዎች ያቀረቡዋቸው
ማሳያዎች

ሙሉውን ቤት ብር 65000 የተካሰ ሙሉውን ቤት ብር 80000

የፊት ግድግዳው ብቻ ለፈረሰ ብር 140000

ምንጭ፣ ከመስክ የተወሰደ፡ ታሕሳስ 2008 ዓ/ም

በካሣ ክፍያና ምትክ ቦታ አሠጣጥ ከመቀሌ ከተማ ሊወሰድ የሚችል ለየት ያለ ተሞክሮ ቤት የፈረሰባቸው
የልማት ተነሽዎች የፈረሰባቸውን ቤት በገንዘብ ሳይሆን በመሬት ለመካስ ፈቃደኛ ከሆኑ 250 ካሬ ሜትር ቦታ
እንዲሠጣቸው የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት መሬት በካሣ መልክ ለተነሽዎች
የሚሠጥበት አሠራር ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ ከ250 ካሬ ሜትሩ 140 ካሬው ለተወሰደባቸው ቦታ በምትክነት
የሚታሰብ ሲሆን የተቀረው 110 ሜትር ካሬ ለፈረሰ ቤት መከፈል የነበረበት የገንዘብ ካሳ ማካካሻ ተሳቢ
ይደረጋል፡፡

238
ይህ አሰራር የፋይናንስ እጥረት የልማት ማነቆ የሆነባቸው ከተሞች እንደ አማራጭ ሊያዩት የሚችሉት አሠራር
ነው፤ ነገር ግን የከተማ መሬት እራሱን የቻለ ውስን የጋራ ሃብት በመሆኑ ይህንን መፍትሔ ቀጣይ አይሆንም፤
በሂደት በሚያጋጥም የቦታ እጥረት የተነሣ ዘላቂነቱ አጠያያቂ ነው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ ይህንን አማራጭ
በገንዘብ ቢሰላ የተለያየ የካሳ መጠን የሚጠይቁ እኩል እንዲከፈሉ የሚያደርግ በመሆኑ በሂደት የፍትሓዊነት
ጥያቄም ያስነሳል፡፡

በልማት ተነሽዎች አያያዝና መስተንግዶ ረገድ በጂማ ከተማ የሚስተዋለው ችግር ስፋት በደሴ ከተማ ከታየው
ተመሳሳይ ስፋት ያለው ሲሆን በግል ባለይዞታዎች የሚደርሰው እንግልት ግን የባሰ ነው፡፡ የግል ባለይዞታዎች
የሚከፈላቸው ካሣ በቂ ካለመሆኑም በላይ ክፍያውን ለማግኘት የሚደርስባቸው ውጣ ውረድና እንግልት
ከፍተኛ ነው፡፡ ለምሳሌ ከአየር ማረፊያ አካባቢ የተነሱና ወልዳ አካበቢ የሰፈሩ ነዋሪዎች የሚገባቸውን የካሳ
ክፍያ ማግኘት የቻሉት በአራት ዙር ተቆራርጦ ከአራት ዓመት በኃላ ነው፡፡

በጂማ ከተማ ለልማት ተነሽዎች የሚገነቡ ምትክ ቤቶች በልማቱ ምክንያት ከፈረሱት ቤቶች ቢያንስ በ75%
የተሻሉ ሆነው እንዲገነቡ የከተማ አስተዳደሩ በመርህ ደረጃ ወስኖ እየሰራ መቆየቱ በውይይቱ ወቅት ቢገለፅም
በተግባር እየሆነ ያለው በተቃራኒው መሆኑ ተጨባጭ ስራው ይመሰክራል፡፡ ቀጥሎ ባለው ፎቶ ግራፍ ላይ
የሚታዩ ቤቶች ለልማት ተነሽዎች ማስፈሪያ ታስበው የተገነቡ ናቸው፤ እነዚህ ቤቶች የተሠሩበት አካባቢም
ሆነ የቤቶቹ አቋም የመኖሪያ መስፈርትን የሚያሟሉ አይደሉም፡፡ ቤቶቹ ከወዲሁ ለመፍረስ የተቃረቡ
ከመሆናቸውም በላይ ስፋታቸው በልማቱ ከፈረሱ ቤቶች አይሻልም፡፡ ከነባር ቤቶች ስፋት በታች የተገነቡ
እንዳሉም ተነሺዎች ገልፀዋል፡፡

ስእል 3.70፡ በባለሀብቶች የተሰሩ ምትክ የቀበሌ ቤቶች


በከተማ አስተዳደሩ ለ10 ቤተሰቦች መልሶ
ማስፈሪያ የተገነቡ ምትክ የቀበሌ ቤቶች
እንደመታጠቢያና ወጥ ቤት ያሉ መሠረታዊ
መገልገያዎች ያልተሟላላቸው እንደነበሩ
በተነሺዎች የሚገለጽ ሲሆን መንደራ ቆጪ
ጤና ጣቢያ አካባቢ ለ14 ቤተሰብ የተገነቡ
ሽንት ቤቶች በየዓመቱ የሚሰምጡና በስብሶ
ለአደጋ እየተጋለጡ በመሆናቸው ለነዋሪዎቹ
አገልግሎት እየሠጡ አይደለም፡፡ አራት ህፃናት
የዚህ አደጋ ሰለባ መሆናቸው ነዋሪዎች
ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ፣ መጋቢት 2008 ዓ/ም ገልፀዋል፤ አንዷ የዚህ ሰላባ ህፃን በመስክ
ጉብኝት በአካል አጋጥሟል፡፡

239
በተነሺዎች መስተንግዶ የሚስተዋለው ሌላ ለየት ያለ ጉዳይ የልማት ተነሽዎች የሚሰፍሩባቸው አካባቢዎች
ለመልሶ መፈናቀል የተጋለጡ መሆናቸው ነው፡፡ አመኑ አካባቢ ከሰፈሩ 46 ቤተሰቦች 15 ያህሉ በአዲስ
መንገድ ግንባታ ዳግም የመፈናቀል አደጋ የሚያንዣብባቸው ሲሆኑ ሸነን ጊቤ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኙ
ነዋሪዎች የጅማ ዩኒቨርሲቲ በአካባቢው ባዮጋዝ ማምረቻ ፕሮጀክት ስለሚገነባ ድጋሜ የመፈናቀሉ ናቸው፡፡
ወልዳ አካባቢ የሰፈሩ እንዲሁ አካባቢው ለአረንጓዴ ሥፍራና ለፓርክ ስለሚፈለግ ድጋሜ መፈናቀላቸው
አይቀሬ ነው፡፡

በድሬዳዋ መልሶ ልማት የሚፈናቀሉ ነዋሪዎች አያያዝ ከሌሎች ከተሞች የተሻለ እንደሆነ ከልማት ተነሺዎቹ
ከመረዳት በላይ መመሪያዊችና የተግባር ስራዎቹም ይመሰክራሉ፡፡ በምትክ ቦታና ቤት አሰጣጥ በኩል
አስተዳደሩ የሚከተለውን አሰራር ስንመለከት የኮንዶሚኒየም ቤት ለማግኘት ማሟላት የሚጠበቅባቸውን
መስፈርቶች ለሚያሟሉ ተነሸዎች በከተማው ዳርቻ አስተዳደሩ ካሠራው የኮንዶሚኒየም ቤት አቅማቸውን
የሚመጥን ቤት የሚሠጣቸው ሲሆን በምትክ ቦታ በኩል ከ160 ካሬ ሜትር ጀምሮ ተመጣጣኝ ቦታ
እንዲሠጣቸው ይደረጋል፡፡ በዚህ በኩል ተነሽዎች የሚገጥማቸው መሠረታዊ ችግር ምትክ ቦታ
በሚመደብላቸው አካባቢ አስፈላጊ የሆኑ የመሠረተ ልማት አውታሮች ቶሎ አለመዘርጋት ነው፡፡

ስእል 3.71፡ በድሬዳዋ ከተማ መሰረተ ልማት ባልደረሰበት ኣካባቢ ቦታ የተመሩት የልማት ተነሺዎች ለግንባታ
ከሌላ አካባቢ አጓጉዘው ያጠራቀሙት ውሃ

ምንጭ፡ ከመስክ የተወሰደ

የውሃ መስመር ባልተዘረጋበት አካባቢ ምትክ ቦታ የተመደበላቸው ተነሺዎች ለግንባታ ሥራ


የሚያስፈልጋቸውን ውሃ ከሩቅ ቦታ በአህያና ተሸከርካሪ በማስመጣት በታንከርና ፕላስቲክ ላይ አጠራቅመው
ለመጠቀም ይገደዳሉ፡፡ ድሬዳዋ ውስጥ ውሃ ቅርብ ቦታ ስለማይገኝ የውሃ ግዥ የሚጠይቀው ገንዘብ ቀላል
እንዳልሆነ ተነሽዎቹ ይገልፃሉ፡፡ ከአስተዳደሩ በካሣ ክፍያ ስም የሚሠጠን ገንዘብ ለዚህ ሁሉ ወጪ የሚውል
በመሆኑ የጀመርነው ቤት መጠለያ መሆን በሚችልበት ደረጃ ላይ ሳይደርስ ገንዘቡ ያልቃል የሚል እሮሮ
ከተነሽዎች በስፋት ይደመጣል፡፡

240
3.2.10.3. አካታችነት እና ፍትሓዊ የልማት ተጠቃሚነት
በዚህ ጥናት በከተሞ የሚካሄደው መልሶ ማልማት አካታችነቱን ምንያህል እንደሆነ ለማመላከት ጥቅም ላይ
የዋሉ የቀረቡ መለኪያዎች (Proxy indicators)፡
 ነባር ነዋሪዎችን/ተቋማትን የልማቱ ተጠቃሚ/ተሳታፊ ማድረግ
 ነባር የከተማ አገልግሎቶችን ከአዲሱ ልማት ጋር አዋህዶ ማስቀጠል
 ድሃና ሀብታም፣ ዘመናዊና ባህላዊ የከተማ ሕይወት፣ ከፍተኛና ዝቅተኛ እርከን የከተማ አገልግሎት
ተጣጥመው ጎን ለጎን አብረው የሚኖሩበትን ሁኔታ የሚመለከቱ ናቸው፡፡

በዚህ ጥናት በናሙናነት ከተወሰዱ ከተሞች አንዱ በሆነው በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄዱ ባሉ የመልሶ
ልማት ፕሮጀክቶች ተዘዋውረን ስንመለከት አካባቢው ሙሉ በሙሉ ተቀይሮ ነው የምናገኘው፤ እንዳውም
ልማቱ ታሪካዊ ቅርሶችን ጭምር የሚያጠፋ ነው የሚል ትችት ይሰነዘርበታል፡፡ የመኖሪያ አካባቢዎች ሙሉ
በሙሉ ወደ ንግድ ማዕከልነት የተቀየሩበት፣ ዘመናዊና ባህላዊ ኢኮኖሚ፣ ድሃና ሃብታም፣ መኖሪያና ቢዝነስ
ተዋህደው የኖሩባትን አዲስ አበባ ወደ አዲስ መልክና ቅርጽ የቀየሩ የመልሶ ልማት ፕሮጀክቶች ጥቂት
አይደለም፡፡

ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የካዛንችስ ቁጥር አንድ መልሶ ልማት ፕሮጀክት ነው፤ ከመልሶ ልማት በፊት
አካባቢውን ያውቅ የነበረ ሰው አሁን ተመልሶ ወደ ካዛንቺስ ቢመጣ አካባቢውን ቀደም ሲል ያውቀው
የነበረውን ነጥብ ለመለየት የሚያስችለው ምልክት በአሁኑ ጊዜ ማግኘት አይችልም፡፡

ልማቱ የማያካትተው ነባር ነዋሪዎችን ጭምር ነው፤ ከዛሬ 10 ዓመት በፊት በልደታ መልሶ ልማት ፕሮጀክት
ክልል ይኖር የነበረ ግለሰብ፣ ቤተሰብ፣ የንግድ ተቋም ዛሬ በአካባቢው ማግኘት የሚቻል አይሆንም፡፡ በአዲስ
አበባ በሚካሄደው መልሶ ልማት ነባሩን ጠርጎ የሚያስወግድና ሙሉ በሙሉ በአዲስ የመተካት አካሄድ
ይጎላል፡፡ ይህ አካሄድ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ አዲስ አበባን ወደ ማታውቀው ኢ-አካታች ወደ ሆነ አደረጃጀት
(Segregation) እንዳይወስዳት ያሰጋል፡፡

በደሴ ከተማ የሚካሄደው የመልሶ ማልማት እንቅስቃሴ ምን ያህል አካታች ነው የሚለው ጥያቄ ምላሽ
ከሌሎች ከተሞች የተለየ አይደለም፡፡ መልሶ እንዲለማ የሚፈለገው ቦታ ዋጋ ተፈላጊነቱ ስለሚጨምር የቦታው
ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አሟጦ ለመጠቀም የሚያስችሉ ህንፃዎች መገንባት አግባብ ነው፡፡ የመሬት የመጠቀም
መብት ዋጋ በገበያ ስለሚወሰን በዚህ ቦታ ማልማት የሚችል በፀደቀው ፕላን መሰረት ለመገንባት የሚችል
ዓቅም ያለው መሆኑ የግድ ነው፡፡ ስለዚህ ዓቅሙ የማይፈቅድለት ነዋሪ ከአካባቢው ስለሚለቅ ከተፈጠረው
የልማት ዕድል ተጠቃሚ አይደለም፡፡ የግሉ ዘርፍ በልማቱ ያፈሰሰው የኢንቨስትመንት ወጪ ለመመለስ
በአካባቢው የሚንቀሳቀስ ንግድና የሚሰጥ አገልግሎት የላቀ ዋጋ ያለቸው ዓይነት (Higher order goods)
ይሆናሉ፡፡ ለበርካታ ዜጎች የስራ መስክ የነበሩ የተለመዱ ስራዎች ከአካባቢው ይጠፋሉ ካልሆነም ይቀንሳሉ፡፡

241
ልማቱን ተከትሎ የሚፈጠር አዲሱ የስራ መስክ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደር የሕብረተሰብ ክፍል እና የስራ
መስኮች እያካተተ አይደለም፡፡

እንደ አዲስ እየለሙ ባሉ ቦታዎች የነበሩ መኖሪያና የንግድ ቤቶች የወቅቱ የፕላን ደረጃ ባያሟሉም ሰፈሩ
ሲቆረቆር ለነበረ ፕላን የሚመጥኑ ነበሩ፡፡ የግሉ ኢንቨስትመንት ዓይን እየሳቡ የሚገኙት ቦታዎች መጀመሪያ
ወደ ንግድ ማእከልነት እንዲለወጡ ያደረጋቸው በቦታው ሲኖሩና ሲሰሩ በቆዩ ነዋሪዎች ነው፡፡ ከከተማው
የዕድገት ፍላጎት በመነጨ መሬት ሊያስገኘው የሚገባ ፋይዳ እንዲያስገኝ መሬትና የግንባታ ልማት ማጣጣም
(Opimization between Land and Improvemen) ሲባል በቦታው የነበሩ ዓቅም የማይፈቅድላቸው
ነዋሪዎች ማፈናቀል የማይቀር ቢሆንም ተጠቃሚዎች ተጎጂዎቹን የሚክሱበት መርህ የለም፡፡ በሌሎች ከተሞች
እንደታየው ሁሉ ደሴ ላይ እየተካሄዱ የሚገኙ የመልሶ ልማት እንቅስቃሴዎች ነዋሪው የልማቱ አካልና
ተጠቃሚ ማድረግ ይቅርና ጥቂቶች የሚጠቀሙበትና ብዙሓኑ የሚጎዱበት ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡
ተጠቃሚው ተጎጂውን አይክስም፤ በርካታ ነዋሪ ለድህነት ተላልፎ የሚሰጥበት ክስተት ይስተዋላል፡፡

የልማት ተነሺዎች ለዘመናት ከኖሩበት አካባቢ ሲነሱ ለዓመታት የገነቧቸውን የገቢ ማስገኛ መንገዶች
እንዲሁም ማሕበራዊ ትስስራቸውን የሚያጡ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ የከተማ መልሶ ማልማት
የሚካሄድባቸው አካባቢዎች በአብዛኛው የሚገኙት በከተሞች ማዕከላዊ ክፍል እንደ መሆኑ መጠን የልማት
ተነሽዎች ከዚህ አካባቢ በመነሳታቸው የሚያጡትን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሕይወት በከተማ ዳርቻ በቀላሉ
ማግኘት አይችሉም፡፡

በአገሪቱ ከተሞች የኢኮኖሚ መዋቅርና አደረጃጀት መሃል ከተሞች በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ የሚገኙ ቤተሰቦች
የሚሰማሩባቸው ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት በስፋት የሚገኙባቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌ በመቀሌ ከተማ ቀበሌ
14 እና እንዳ ማርያም አካባቢዎች በርካታ ቤተሰቦች ባህላዊ መጠጦች፣ አነስተኛ ምግብ ቤቶችና ሻሂ ቤቶች፣
ከከሰል እስከ አትክልት ችርቻሮ ንግድ ላይ ተሰማርተው ኑሮአቸውን ሲገፉ የቆዩባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡
እነዚህ አካባቢዎች በመልሶ ማልማት ፕሮግራም ሥር ሲታቀፉ አካባቢዎቹ ካላቸው ከፍተኛ የመልማት ዓቅም
አኳያ ነባራዊ ሁኔታውን የሚለውጥ የኢኮኖሚ መዋቅር መምጣቱ አይቀሬ በመሆኑ ነባር የስራ ዘርፎች ከፍ
ያለ ደረጃ ባላቸው የስራ መስኮች (Higher order economic activities) ይተካሉ፤ በዚህ ሂደት በዝቅተኛ
ገቢ የሚተዳደሩ ቤተሰቦች የኑሮ መሠረት ከአካባቢዎቹ ይጠፋል፤ ካልሆነ ተገፍቶ ወደ ከተማው ይበታተናል፡፡

እላይ ከተጠቀሱት አካባቢዎች የሚፈናቀሉ የልማት ተነሺዎችን እንደ ሰውሔ ንጉስ ባሉ ዳርቻ አካባቢዎች
ምትክ ቦታ ሰጥቶ እንዲሰፍሩ ማድረግ የተነሽዎችን ኢኮኖሚያዊ ሕይወት በነበረበት ሁኔታ ማስቀጠል
አያስችልም፡፡ ምክንያቱም በዚህ አካባቢ ከመሃል ከተማ ለመጡ የልማት ተነሺዎች የሕይወት መሠረት
የሚሆን የኢኮኖሚ መዋቅር የለም፡፡ በመሆኑም እላይ እንደተጠቀሱት ካሉ አካባቢዎች የሚፈናቀሉ ነዋሪዎች
የሚጠይቁት ምትክ ቦታና ካሳ ብቻ ሳይሆን የተቋረጠውን የኑሮ ዋስትናቸውን ማስቀጠል የሚችል የመልሶ
ማቋቋም ድጋፍ ጭምር ነው፡፡

242
አሁን እንደሚታየው በመቀሌ ከተማ ያለው መልሶ ማስፈር በራሱ የተሟላ አይደለም፡፡ ከመሃል ከተማው
ለሚነሱ የልማት ተፈናቃዮች የሚሰጣቸው ተለዋጭ መሬት በከተማው ዳርቻ ባሉ አካባቢዎች (የሰውሒ
ንጉስ፣ ዲያስፖራ፣ ኩሓ ደስታ አረቄ ፋብሪካ አጠገብ ወዘተ) ነው፡፡ እነዚህ አካባቢዎች የመንገድና
የትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽነት አይደሉም፤ የውሃና ኤሌክትሪክ መስመር የተሟላላቸው አይደሉም፡፡
እነዚህ የልማት ተነሽዎች ጥለውት የመጡት አካባቢ በከተማ እርጅና የተጠቃ ቢሆንም ከነዋሪዎቹ የዕለት
ተዕለት ሕይወት ጋር ትስስር ካላቸው የኢኮኖሚና ማህበራዊ ማዕከላት ያለው ቅርበት ከአዲሱ የሠፈራ አካባቢ
እጅግ በጣም የተሻለ ነው፡፡

በከተሞች የሚካሄዱ የመልሶ ማልማት ፕሮግራሞች አንዱ መሠረታዊ ዓላማ የከተሞችን እምቅ የኢኮኖሚ
አቅም አሟጦ መጠቀም (Optimization) ነው፡፡ ከደረጃ በታች በሆነ አገልግሎት የተያዙ የከተማ ቦታዎች
በመልሶ ማልማት ለላቀ አገልግሎት እንዲውሉ በማድረግ በከተሞች የተሻለ የኢኮኖሚ ስልጠት /Efficiency/
ማምጣት የሚቻል መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ይህ ልማት የተሟላ ሊሆን የሚችለው በመልሶ ማስፈር አካባቢዎች
ብቃት ያለው የመሬት አጠቃቀም እንዲኖር ማድረግ ከተቻለ ነው፡፡ በተግባር የሚታየው አካሄድ ግን ይህን
አያረጋግጥም፤ ይኸውም ከፍተኛ ዋጋ ባለው መሬት ላይ ዋጋው የማይመጥን ደሳሳ ጎጆ መስራት ወይም
ለሽንሻኖው ስፋት የሚመጥን ቤት አለመገንባት ከመሬት ሊገኝ የሚገባውን ጥቅም እያሳጣን ይገኛል፡፡

ሰዎች ከነባር ይዞታቸውና ከሥራ ቦታቸው እንዲነሱ የሚደረግበት አንዱ ምክንያት ልማትን ለማመጣጠን
ሲባል ነው፤ ሆኖም በከተሞቻችን ብዙ ጊዜ ይህ ጉዳይ ከግምት ሲገባ አይታይም፡፡ ባለሃብቶች ከደረጃ በታች
የሆኑ አካባቢዎችን አልምተው ሃብት የሚያፈሩበትን ዕድል መፍጠር የሚበረታታ እርምጃ ነው፤ ነገር ግን
ከልማት አካባቢዎች የሚነሱ ዜጎች የልማቱ ተቋዳሽ የሚሆኑበት አግባብ ጎን ለጎን እስካልተጠረ ድረስ
የተመጣጣነ ልማት ሊመጣ አይችልም፡፡ ከዓለምአቀፍ ተሞክሮዎች ላይ በመመስረት የመስኩ ባለሙያዎች
የሚሠጡት ምክረ ሃሳብ የልማት ተነሽዎችን በተቻለ መጠን ቀደም ሲል ከነበራቸው ኑሮ እንዲሻሻል ካልሆነ
ቢያንስ ከመፈናቀላቸው በፊት ከነበራቸው ሕይወት ያላነሰ ኑሮ እነዲኖሩ የማያደርግ መልሶ ልማት ዘላቂ
(Sustainable) አይደለም፡፡

በአጠቃላይ መልሶ ልማት የከተሞቹ የህዝብ ማሕበራዊ ስብጥር ከነበረበት ምስል ሌላ አዲስ መልክ እንዲይዝ
እያደረገ ይገኛል፡፡ መልሶ ልማቱ የሚያፈናቅላቸው በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች
የሚሰፍሩበት የከተሞቹ ዳር አካባቢዎች በመሆናቸው የድሀውና ሌላኛው ክፍል ሰፈሮች ከወዲሁ ተለይተው
ስብጥሩ እንዲዛባ እየተደረገ ነው፡፡ በስራ ቦታም ተመሳሳይ ምስል እየያዘ ይገኛል፡፡ አብዛኛውን ነዋሪ
የሚደግፉ የስራ መስኮች መልሰው ከለሙ አካባቢዎች ተጠርገው እየጠፉ ናቸው፡፡ ስለዚህ ማሕበራዊ ስብጥሩ
ይበልጥ የተዛነፈ ይሆናል፡፡

የከተሞቹ መሃል ክፍል መልሶ ማልማት አካባቢው ለማደስ የሚከናወን ሳይሆን በኢኮኖሚ፣ ማሕበራዊ፣
አካባቢያዊ ውህደትና ውበት፣ የአካባቢና የነዋሪው ደህንነት፣ የከተማው ታረክና ልዩ መገለጫዎች ልማት

243
ተጨማሪ እሴት መፍጠር ነው፡፡ በመልሶ ልማት ምክንያት የሚፈጠሩ ተጨማሪ እሴቶች ተደማሪነታቸው
በመልሶ ማስፈሪያ ቦታዎችና በልማት ተነሺዎች በኩል (በተለይ በኢኮኖሚው) እየጎደለ ድምር ውጤቱ
ተጨማሪ ዓቅም ከመፍጠር አንፃር የተሟላ አይደለም፡፡ ምክንያቱም መስፈሪያ ቦታዎች የከተማው አካል
ሆነው ጎን ለጎን እንዲለሙ እየተደረጉ አይደሉም፡፡

በቦታው የነበሩ አካላት አያያዝ፤ ከልደታና ሌሎች ውሱን መሰል አከባቢዎች በቀር በውዝግብ የተሞሉ
የተጓተቱና ተነሽዉን የልማቱ ተቋዳሽ ያደረጉ ሳይሆን የገፉ መሆናቸው፤ ለተነሺዎች መልሶ መሰፈሪያ
ተብለው የሚገነቡ ቤቶች (ለምሳሌ ደሴ) ችግርን ከመፍታት ይልቅ ከነባሩ ወደሌላ ማዛወር ነው ውጤተቱ፡፡
ለመልሶ ማስፈሪያ የተገነቡ ቤቶች ከፈረሱት የባሱ መሆን፤ መልሶ በሚለማው ቦታ የሚሰሩ ግባታዎችም
ለተፈላጊ ጉዳያቸው በቂ ቦታ ሰጥተው በዲዛይንም ነገን ተሸጋሪ ያለማድረግ፤ አዋጭነትና የፍላጎት ዝንባሌ
አለማገናዘብ (ለምሳሌ በድሬ ድዋ) ነባሩ የከተማ ክፍል ማዕካለዊነት እየጠቀየረ ወደ ሳቢያን እየተሳበ መሆኑ
በግልጽ እየታየ አሁንም ነባሩን ማዕከል በነባር ሚናው መጠን አንዲለማ መፈለግ ይህ አውነታውን ያየ ቢሆን
ማዕከሉን ማዕከል ሆኖ ይቀጥላል ከማለት በፊት በምን ስልት ማስቀጠል እንደሚቻል አቅዶ አለመስራት፤ ነገ
የማይቀጥል ነባሩ ቦታ ሰፊ ምትክ ቦታ መስጠት (ለምሳሌ በደሴ) 50 ሜ.ካና በታች ቦታ ላይ ለነበሩ የቀበሌ
ቤት ተከራዮች 171 ሜትር ካሬ መስጠት፤ በአዲስ አበባ በሁለት ሜትር ካሬ ይነግድ ለነበረ 25 ሜትር ካሬ
መስጠት በዚህ አካሄድ መርካቶ አካባቢ ለልማት ከፈረሰው በላይ ቦታ የጠየቁ ሂደቶች አንደሉ ታይቷል፡፡
ስራው ሲሰፋ መተግበር የማይቻል ለተወሰኑ ህብረተሰቦች ኮንቴነር መስጠት /በደሴ/ የታየ ነው፡፡

በድምር ያረጁ አካባቢዎች ለማንሳት የሚከናወን ልማት በማስፈሪያ አካባቢዎች ተጨማሪ እሴት መፍጠር
አልቻለም፡፡ የዓላማው ማእከልም ከዜጎች ይልቅ ለቦታ ትኩረት የሚሰጥ ነው፡፡ በእንዲህ ዓይነት ቅኝት
የሚካሄድ ልማት ያስከተለው የለውጥ ዓይነት እውነተኛ (Transformational) ለውጥ ሊሆን አይችልም፡፡

3.2.10.4. የልማቱ ጂኦግራፊያዊ ስርጭት


የመልሶ ማልማት ፕሮግራም በኢኮኖሚና ማህበራዊ ተቋማት እንዲሁም በመኖሪያ ሠፈሮች አካባቢያዊ
ስርጭት ላይ የሚኖረው ውጤት ፕሮግራሙ እንደሚሸፍነው ክልል ስፋት ይለያያል፤ በልማቱ የሚሸፈነው
ክልል በሰፋ ቁጥር በተቋማቱ አካባቢያዊ ስርጭት ላይ የሚያሳርፈው ተጽእኖ እየሰፋ ይሄዳል፡፡ ከዚህ
መሠረታዊ ጉዳይ አኳያ የከተሞቹ ተሞክሮ ምን እንደሚመስል ቀጥለን እንደመልከት፡፡

ከመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች ስፋት አኳያ የአዲስ አበባ ተሞክሮ ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል፤ በዚህ መሠረት
የመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች በኢኮኖሚና ማህበራዊ ተቋማት ጂኦግራፊያዊ ስርጭት ላይ ያላቸውን ውጤት
ለማየት የመዲናዋን ተሞክሮ በቅድሚያ መመልከት ይጠቅማል፡፡ ቀደም ሲል እንደተገለጸው በአዲስ አበባ
የመልሶ ማልማት እንቅስቃሴ ረዥም ታሪክ አለው፤ ቀደም ባለው ጊዜ በመዲናዋ የነበረው እንቅስቃሴ በነባር
ከተማ ማሻሻያ (urban upgrading) ፕሮጀክቶች ላይ ያተኩር ስለነበር መልሶ ማልማቱ በከተማዋ አወቃቀር
ላይ ያሳርፍ የነበረው ለውጥ የጎላ አልነበረም፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን የመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች

244
በስፋትም በብዛት እየጨመሩ ከመምጣታቸው ጋር ተያይዞ በከተማዋ አጠቃላይ አወቃቀር ያላቸው እንድምታ
እየሰፋ መጥቷል፡፡

አሁን አሁን ነባር ሰፈሮችን በመደዳ ጠርጎ የማንሳት እርምጃ እየተጠናከረ መጥቷል፤ በዚህም የተነሣ የልማቱ
ጂኦግራፊያዊ ስርጭት በተወሰኑ አካባቢዎች የመሰባሰብ (Concerntration) አዝማሚያ እየታየ ነው፡፡ የመልሶ
ማልማቱ እንቅስቃሴው በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ማትኮር ብቻ ሳይሆን ነዋሪዎችን ከመሃል ከተማ እያስወጣ
በምትኩ መሃል ከተማው በአብዛኛው ወደ ንግድ ማዕከልነት እየቀየረው መጥቷል፡፡

ይህ አካሄድ ልማቱ ከሚነካቸው ዜጎች ቁጥር ግዝፈት አኳያ ሲታይ የሚያዋጣ አይመስልም፤ በመጀመሪያ
ደረጃ በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለው ሰፈሮችን በመደዳ እያፈረሱ ነዋሪውን ከመሃል ከተማ
ጠርጎ የማስወጣት እርምጃ በልማቱ ዘላቂነት ላይ አሉታዊ ውጤት ይኖረዋል፡፡

ጂኦግራፊያዊ ስርጭቱ ሚዛኑን ያልጠበቀና በተወሰነ አካባቢ የታጠረ እንዲሁም መኖሪያና የሥራ ቦታን
የሚያራርቅ መልሶ ማልማት ዘላቂ አይሆንም፡፡ መልሶ ማልማቱ ከሚካቸው ዜጎችና አካባቢዎች ስፋት አኳያ
ሲታይ ኢ-ፍትሃዊ የሆነ የልማት ፕሮጀክቶች አካባቢያዊ ስርጭት አሳሳቢ ነው፡፡ አሁን በአዲስ አበባ በተያዘው
አቅጣጫ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተሯሩጠው የእለት ጉርሳቸውን ከሚያሟሉበት አካባቢ በጥድፊያ እየተነሱ
በመዲናዋ ዳርቻ እንዲሰፍሩ የማድረጉ እርምጃ የሚቀጥል ከሆነ ልማቱ ተንገራግጮ የሚቆምበት ጊዜ ሩቅ
አይሆንም፡፡

መልሶ ማልማቱ በተመወሰነ አካባቢ ላይ እንዲያተኩር ማድረግ የከተማውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ


ወዳልተፈለገ ውስብስብ ችግር ሊመራው ይችላል፤ ልማቱ በተወሰነ ማዕከል በተሰባሰበ ቁጥር የትራፊክ
ፍሰቱን ከተለያዩ የከተማው ማዕዘናት ወደዚህ ማዕከል እንዲሳብ ስለሚያስገድደው የትራፊክ እንቅስቃሴው
እየተጨናነቀ መሄዱ አይቀሬ ነው፡፡ የመኖሪያ ሰፈሮች ወደ ከተማዋ ዳርቻ እየተገፉ የሥራ ቦታዎችና
የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በተቃራኒው በመሃል ከተማ በተሰባሰቡ ቁጥር በነዋሪው የዕለት ተዕለት
እንቅስቃሴ የሚሸፈነው ጎዞ እርቀት እየጨመረ ይሄዳል፡፡ በነዋሪው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚሸፈነው
እርቀት በረዘመ ቁጥር ተሸከርካሪን በጉዞ አማራጭነት የመጠቀም ፍላጎትም እየጨመረ ነው የሚሄደው፡፡
አሁን በአዲስ አበባ በግልጽ ይታያል፡፡ አሁን በተያዘው አቅጣጫ በተወሰነ አካባቢ ብቻ ነባሩን የከተማ ክፍል
እያፈረሱ የመኖሪያ ሰፈሮችን ወደ ከተማዋ ዳርቻ የማስወጣት እርምጃ የሚስተካከልበትን ዕድል ቆም ተብሎ
ካልታሰበ በተለይ የአዲስ አበባ የወደፊት የትራፊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መውደቁ የሚያጠያይቅ
አይሆንም፡፡

በአብዛኞቹ ከተሞች የሚካሄድ መልሶ ልማት የተለያዩ የከተማው ክፍሎች ዕድገት ለማመጣጠን የሚያስችል
መርህ የተከተለ አይደለም፡፡ አንድ ቦታ ላይ የተጀመረው ልማት በኩታ ገጠም የሚገኝ ቦታ ለማልማት እንጂ
በተለያዩ የከተማው ክፍሎች የመልማት ዕድል በመፍጠር ሚዛኑ የጠበቀ ዕድገት/ለውጥ/ እንዲኖር የሚያደርግ

245
አይደለም፡፡ ይህ አካሄድ የከተማው ዋና ማእከል እየጎለበተ ለሌሎች ማእከላት እንዲቀጭጩ በር የሚከፍት
ይከፍታል፡፡ ጅማ ከዋና ማእከሉ /መርካቶና ቦቼ/ በተጨማሪ ጊንጆ በሁለተኛ ማእከልነት ታስቦ መልሶ ልማት
መታቀዱ የከተማው ሚዛን ለመጠበቅ የሚያስችል ዕድል በመፍጠር ከሌሎቹ ከተሞች መልካም ተሞክሮ
የሚታይበት ነው፡፡

በተወሰነ ቦታ ተከታታይ መልሶ ልማት ማካሄድ የሚያስከትለው ችግር ልማት ባለማመጣጠን ብቻ የሚቆም
ሳይሆን በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደር የሕብረተሰብ ክፍል ከመሀል እየወጣ ዳር አካባቢዎች የድሀ ማከማቻ
እንዲሆኑም ያደርጋቸዋል፡፡

በሁሉም ከተሞች ነባር የንግድ ማእክል ተብለው የሚታወቁ ቦታዎች ከንግድ ሚናቸው ባልተናነሰ የመኖሪያ
አካባቢዎችም ናቸው፡፡ ከመኖሪያ አካባቢዎች በተሻለ ደረጃ የህዝብ ጥግግት አላቸው፡፡ በእነዚህ ማእከላት
የሚካዴድ መልሶ ልማት የመሬት አጠቃቀሙ መኖሪያ ሙሉ በሙሉ እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ ይህ በመሆኑ
ሶስት ወሳኝ ችግሮች ያስካትላል፡፡
₋ በአካባቢው የነበሩ መኖሪያ ቤቶች ስለሚፈርሱ የከተሞች ዋነኛ ፈተና የሆነውን የቤት ፍላጎት ማሟላት
ወደ ከፋ ፈተና ያስገበዋል፡፡ በከተሞች የሚታየው ያልተመለሰ የቤት ፍላጎት ለመመለስ ከፍተኛ
የመሬት አቅርቦት ለማስተናገድ እየተቸገሩ ተጨማሪ ፍላጎት እንዲፈጠር እየተደረገ ነው፡፡ በአጠቃላይ
መልሶ ልማት መሬት ከመቆጠብ ይልቅ የመሬት ፍላጎት እንዲጨምር አድርጓል፡፡
₋ መልሶ እንዲለማ በሚፈለግ ቦታ የሚገነባ ግንባታ በዋናነት ለንግድ አገልግሎት የሚሰጡ በመሆናቸው
ህንፃዎቹ ሙሉ ዓቅማቸው ስለማይሰሩ በዘርፉ የሚደረግ ቀጣይ ኢንቨስትመት ፈተና ይጋረጥበታል፡፡
₋ ከላይ በተገለፀው መልኩ በእያንዳንዱ ከተማ የተመጣጠነ ልማት እንዳይኖር ምክንያት እየሆነ ነው፡፡

246
3.3. ማጠቃለያ

እስካሁን በአገሪቱ ከተሞች በተካሄዱ የመልሶ ማልማት እንቅስቃሴ የተመዘገቡ ውጤቶች ከፍላጎትና ከችግሩ
ስፋት አንፃር አመርቂ ናቸው ባይባልም የተሰራውን ያህል አወንታዊ ለውጦች መታየት ጀምረዋል፡፡ ለኑሮና
ለስራ የማይመቹ አካባቢዎችን በፕላን መልሶ ከማደራጀት፣ ለኑሮ መሻሻልና ለስራ ዕድል ፈጠራ እገዛ
የሚያደርጉ የመሰረተ ልማት አውታሮችን ከማሟላት፣ የትራፊክ ፍሰትና እንቅስቃሴን ቀልጣፋ በማድረግ፣
የተሻለ የመሬት አጠቃቀም ከማስፈን፣ የግል ኢንቨስትመንትን በግንባታው ዘርፍ ከማስፋፋት እንዲሁም
ከአካባቢ ጥበቃና ደህንነት አኳያ መሰረታዊ ለውጦች እየተመዘገቡ ይገኛሉ፡፡

መልሶ ማልማቱ ያስገኛቸው አወንታዊ ወጤቶች እንደተጠበቁ ሆነው ከአፈፃፀም ክፍተት ጋር በተያያዘ
የሚስተዋሉ ችግሮች በርከታ ናቸው፡፡ ልማቱ በሚካሄደባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ከልማቱ ጋር
አብረው አለመለወጣቸው ቅድምያ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡ በመልሶ ማልማት የሚነሱ ነዋሪዎች በሂደቱ
ለመጠለያና የሥራ ዋስትና ማጣት፣ መሰረተ ልማት ባልተሟላባቸው አካባቢዎች መስፈር፣ ቀደም ሲል
ያፈሩትን ሃብት ማጣትና ለከፍተኛ ውጣ ውረድ መጋለጥ እጅግ ሰፊ ነው፡፡ በመልሶ ማልማት የሚፈጠረው
የኢኮኖሚ ጥቅም ስርጭት መሠረቱ ጠባብ በመሆኑ በልማቱ ከሚጠቀመው ማህበረሰብ ይልቅ ተጎጂው
በቁጥር ይበዛል በዚህም የተነሣ ከልማቱ አወንታዊ ጎን አሉታዊ ጎኑ ያመዝናል፡፡

የነዋሪው አሠፋፈር ማሕበራዊ ስብጥር የመልሶ ማልማት ሂደቱን ተከትሎ ከጊዜ ወደ ጊዜ አዲስ ምስል እየያዘ
መጥቷል፡፡ መልሶ ማልማቱ ከመሃል ከተማ ከሚያፈናቅላቸው ነዋሪዎች አብዛኞቹ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ
የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች ስለሆኑ ድሃው ወደ ከተሞቹ ዳርቻ እየተገፋ በምትኩ የተሻለ የኢኮኖሚ አቅም
ያለው ወደ መሃል ከተማ ስለሚሰባሰብ ድሃና ሃብታም በአንድ አካባቢ ተሰባጥሮ የመስፈር ዕድሉ እየጠበበ
በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በማህበራዊ ስብጥር በኩል የሚስተዋለው መዛባት በመኖሪያ ሰፈር ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ በኢኮኖሚና
ማህበራዊ ተቋማት ስርጭትም ተመሳሳይ ክስተቶች ይስተዋላሉ፡፡ ለአብዛኛው የከተማ ነዋሪ የኑሮ መሠረት
የሆኑ አነስተኛና የንግድና አገልግሎት የኢኮኖሚ ዘርፎች ከመሃል ከተማ ተጠራርገው መውጣት ለማሕበራዊ
ስብጥሩ ይበልጥ መዛነፍ የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የከተሞች መልሶ ማልማት መሠረታዊ ዓላማ የመሃል ከተማውን የኢኮኖሚ መዋቅር መቀየር ሳይሆን በነዋሪው
ኢኮኖሚና ማሕበራዊ ህይወት፣ በአካባቢ ደህንነት፣ በቅርስና ታሪካዊ ቦታዎች ልማት ተጨማሪ እሴት
መፍጠር መሆን ሲገባው በተግባር የሚስተዋለው በልማት ተነሺዎች ኑሮና በመልሶ መስፈሪያ አካባቢዎች
የሚደርሰው ጉደለት በመሃል ከተማ የሚፈጠረውን እሴት ተደማሪነት የሚቀንስ ነው፡፡ በዚህም የተነሣ
የመልሶ ማልማቱ አጠቃላይ ውጤትና ፋይዳ ይሸረሸራል፡፡

247
በአጠቃላይ የከተሞቻችንን መልሶ ማልማት እንቅስቃሴ ዘላቂነት የሚፈታተኑ በርካታ ችግሮች ይስተዋላሉ፡፡
የልማት ተነሽዎች አያያዝና መስተንግዶ (ከልደታ መልሶ ማልማት በስተቀር) በውዝግብ የተሞላ፣ የተጓተተና
ተነሽዉን የልማቱ ተቋዳሽ የሚያደርግ ሳይሆን የሚገፋ፣ በኣብዘኛው ከተሞች ለተነሺዎች መልሶ መስፈሪያ
ተብለው የሚገነቡ ቤቶች ችግርን ከነባሩ አካባቢ ወደ ሌላ ከማዛወር የተለየ ባህሪ የሌላቸው፣ ነገን ተሻጋሪ
ያልሆኑ ግንባታዎችን በመልሶ ማልማት አካባቢዎች ማካሄድ ፣ የአዋጭነትና ፍላጎት አለማገናዘብ፣ ለመልሶ
ልማት ከተለቀቀው ቦታ የሰፋ ቦታ የሚጠይቅ የምትክ ቦታ አሠጣጥ መከተል በከተሞች መልሶ ማልማት
እንቅስቃሴ የሚስተዋሉ ክፍተቶች ናቸው፡፡

ያረጁ አካባቢዎችን ለማደስ የሚወሰዱ እርምጃዎች ልማቱ የሚያመጣውን ተጨማሪ እሴት ተደማሪነት
በሚቀንሱ ክስተቶች የተከበቡ ናቸው፡፡ የልማቱ ቁልፍ ዓላማ የዜጎችን ሕይወት መለወጥ መሆን ሲገባው
ለአዲስ ኢንቨስትመንት የሚሆን ቦታን ከነባር ባለይዞታ/ግንባታ ነፃ ማድረግ ላይ ማትኮሩ የልማቱን ዘላቂነት
ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል፡፡ በዚህ ዓይነት ቅኝት በሚካሄድ ልማት መሠረታዊ ለውጥ
(Transformational) ማምጣት አይቻልም፡፡

248
ክፍል አራት፡ በቀጣይ የከተማ መልሶ ማልማት ልንከተለው የሚገባ አቅጣጫ

4.1. የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ


4.1.1. ለከተማ መልሶ ማልማት እራሱን የቻለ የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ የመኖር አስፈላጊነት
ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ከደረሱ አገሮች ተርታ የማሰለፍ ራዕይ የሀገሪቱን ከተሞች በአለም አቀፍ ደረጃ
ተወዳዳሪ፣ ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ሳቢ፣ ለሥራና ኑሮ ምቹ ማደረግ ግድ ይላል፡፡ አሁን ከተሞቹ ባሉበት
ሁኔታ ይህ የሚታሰብ አይደለም፡፡

የሁሉም ከተሞች ከ60% በላይ የሆነው ክፍላቸው መልሶ ማደስ ይጠይቃል፡፡ አስፈላጊ የከተማ መስፈርትን
የማያሟላና ከደረጃ በታች በሆኑ ሠፈሮች (Slums) የተሞላ ነው፡፡ በዚህ ደረጃ የሚፈረጁ የከተማ አካባቢዎች
ለሥራና ኑሮ ተፈላጊውን ሁኔታ የማያሟሉ፣ በእርጅና የተጠቁ፣ አስፈላጊው መሰረተ ልማት ተሟልቶላቸዋል
የሚባሉትም ቢሆኑ ከወቅቱ የከተማ ዕድገት ፍላጎት አኳያ መሬት ሊሰጠው ከሚገባው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ
በታች የሆነ ጥቅም እየሰጠ የሚገኝባቸው ናቸው፡፡ ከዚህ አንፃር የሀገሪቱ ከተሞችን 60% የሚሆነው
ክፍላቸው በአንድ ወይም በሌላ መንገድ መቀየር ለከተሞቹ ሁለንተናዊ የልማት ዕድገት አስፈላጊና አዋጪ
እርምጃ ነው፡፡

የሀገሪቱ ከተሞች ለሥራና ለኑሮ ምቹ ለማድረግም ሆነ ዓለምአቀፋዊ ተወዳዳሪ ለማድረግ በርካቶቹ ከተሞች
መልሶ መደራጀት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ከተሞችን መልሶ ማደራጀት ከሚቻልባቸው ግንባር ቀደም ተጠቃሽ
መንገድ ደግሞ መልሶ ማልማት ነው፡፡ በዚህ መሠረት የከተማ መልሶ ማልማት አጀንዳ ለኢትዮጵያ ወቅታዊና
ሁሉንም ከተሞቻችንን የሚመለከት ነው፡፡

የከተማ መልሶ ማልማት በባህሪው ውስብስብና በርካታ የሕብረተሰብ ክፍልንና የከተማ ሕይወትን ይነካል፡፡
መልሶ ማልማት የነበረ ግንባታን፣ ማህበራዊ ትስስርን፣ የኢኮኖሚ መሠረትን፣ ባህልና ቅርስን፣ የመኖሪያ
ሰፈርን፣ የመሠረተ ልማት አውታርን፣ ይነካል፡፡ በሂደቱም በርካታ ባለድርሻ አካላትን የሚያሳትፍ የልማት
አጀንዳ ነው፡፡ ስለሆነም የከተማ መልሶ ማልማት ግልጽ በሆነ አቅጣጫ ከተመራ ሀገራዊ ፋይዳው ልማቱ
ከሚካሄድበት ከተማ ወይም ክልል የሚያልፍ፣ ከተማንም ሆነ አገርን ወደ ከፍተኛ የዕድገት እርከን
የሚያሸጋግር (Transformational)፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንድምታው ዘርፍ ብዙ፣ በርካታ ዜጎችን
ከድህነት አረንቋ የሚያወጣ ወሳኝ ልማት ነው፡፡ ሂደቱ በትክክል ካልተመራ ደግሞ አሉታዊ ውጤቱ ዘርፈ
ብዙ፣ ከተሞችን ወዳልተፈለገ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ውስብስብ ችግር ውስጥ ስቦ የሚያስገባ፣
ዜጎችንም ለባሰ ድህነትና መጎሳቆል እንደሚዳግ ከዳሰሳ ጥናቱም ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

የከተማ መልሶ ማልማት በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎችን የሚነካ ልማት እንደመሆኑ መጠን ሂደቱ የተለያዩ
የፍላጎቶች ግጭት የሚንፀባርቅበት፣ የዜጎችን መብትና ጥቅም በአወንታዊ ወይም በአሉታዊ መንገድ የሚነካ፣

249
የሀገር ዕድገትን የሚወስን እንዲሁም ከፍተኛ የፋይናንስ ሃብትና ጠንካራ አስፈፃሚ አካል የሚጠይቅ ነው፡፡
ባጭሩ የከተማ መልሶ ልማት ግልጽ በሆነ የፖሊሲ አቅጣጫ ካልተመራ ከጥቅሙ ይልቅ የሚያስከትለው
ጉዳት እንደሚያመዝን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ የሌሎች ሃገራት ተሞክሮዎች የሚያሳዩትም ይህንኑ ነውና፡፡
በኢትዮጵያ ከተሞች የሚከናወነው የከተማ መልሶ ማልማትም በኢፌዲሪ ህገ-መንግስት የተቀመጠውን መርህ
መሠረት ያደረገ የራሱ ፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ ሊኖረው ይገባል ፡፡

4.1.2. የፖሊሲና የህግ ማዕቀፉ ሀገራዊ የመሆን አስፈላጊነት


የከተማ መልሶ ማልት ከመሬት ሀብት አስተዳደርና የመጠቀም መብት ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ነው፤ ይህ ማለት
መልሶ ማልማት የዜጎች የልማት ተጠቃሚነትና የንብረት ባለቤትነት መብቶች የሚመለከት ትልቅ ህገ-
መንግስታዊ አጀንዳ በመሆኑ እራሱን የቻለ ሀገራዊ ፖሊሲ እና የሕግ ማዕቀፍ ያስፈልገዋል፡፡

በሀገሪቱ ሕገ መንግስት ድንጋጌና መርህ መሠረት የመሬት ሀብት አጠቃቀም የሚመራበትን ፖሊሲና ሕግ
የማውጣት ስልጣንና ሓላፊነት የፌደራል መንግሥት ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር በዚህ ጥናትና ድምዳሜ ላይ
እንደታየው እና በፌደራል የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ፖሊሲ ሰነድ እንደሰፈረው ከደረጃ በታች በሆኑ
የደቀቁ የከተማ አካባቢዎች ከሚኖረው ህዝብ ውስጥ 70% የሚሆነው ዝቅተኛ ገቢ ያለውና ከእጅ ወደአፍ
የሆነ ኑሮ የሚገፋ ነው፡፡ ይህ ማለት ከደረጃ በታች የሆኑ የከተማ አካባቢዎች ማደስ የሚመለከተው እነዚህን
የሕብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ ከአገሪቱ ከተሞች 60% በሆነው አከባቢ የሚኖረውን የከተማ ነዋሪና የኢኮኖሚ
እንቅስቃሴ የሚመለከት የልማት አጀንዳ ግልጽና ወጥ የሆነ ሀገራዊ ፖሊሲ ይፈልጋል፡፡ ልማቱ የሚነካው
የሕብረተሰብ ክፍልም በተናጠል በፕሮጀክት ደረጃ ሲታይ ትንሽ ሊመስል ቢችልም በከተማና በሀገር ደረጃ
ሲታይ በተለይ እንደ ደሴ፣ ጅማና አዲስ አበባ ባሉ ዕድሜ ጠገብ ከተሞች በልማቱ የሚነካው የሕ/ሰብ ክፍል
በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ለምሳሌ አዲስ በተዘጋጀው የአዲስ አበባ መሪ ፕላን በቀጣይ የመልሶ ማልማት
ፕሮግራም ይካሄድበታል ተብሎ የተለየውን 4,000 ሄክታር ክልል ብንወስድ በቀጣይ አስር ዓመት 220,000
አባወራ ወይም 1.1 ሚሊዮን የሚሆን የመዲናዋ ነዋሪ ሕይወት በአንድ ወይም በሌላ መንገድ በመልሶ ማልማት
ፕሮግራም ይነካል ማለት ነው፡፡

የመልሶ ማልማቱ የሚጠይቀው የፖሊሲ ማዕቀፍ ሰፊ የሕብረተሰብ ክፍልን ሕይወት የሚመለከት፤ ከዚህም
የሕብረተሰብ ክፍል አብዛኛው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኝ እንደመሆኑ መጠን የመልሶ ማልማት አጀንዳ
ክልላዊና ከተማ አቀፍ ብቻ ሳይሆን ሀገራዊ የድህነት ቅነሳ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ሽግግር እንዲሁም የዜጎችን
ፍትሓዊ የልማት ተጠቃሚነት የማረጋገጥ አጀንዳ ነው፤ በመሆኑም የሚፈልገው ፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ
ሀገራዊ መሆኑ ግድ ነው፡፡

250
4.1.3. የፖሊሲ ምላሽ የሚሹ መሰረታዊ ጉዳዮች
ሀ/ የመልሶ ማልማቱን ቁልፍ ዓላማ በተመለከተ
የመልሶ ማልማቱ ዓላማ አሁን እየታየ እንዳለ የመሬት ፍላጎት ለመመለስ ወይም አካባቢያዊ ዕይታን ለማሻሻል
ሲባል የሚከናወን ሳይሆን ሰፊና ዙሪያ መለስ ዕይታ ሊኖረው ይገባል፡፡ በኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት በግልጽ
እንደተደነገገው የመልሶ ማልማቱ ዋና ትኩረት ህዝብን ተጠቃሚ ያደረገ ልማት ማምጣት መሆን አለበት፡፡
የልማቱ ዋና ዓላማ በግንባታ ለውጥና በከተሞች ገጽታ መሻሻል ላይ ብቻ መታጠር የለበትም፤ ከዚህ ባለፈ
የህዘብን ህይወት መቀየር አለበት፡፡ ፖሊሲው የልማት ተነሽዎችን ህይወት የማያሻሻል ወይም የሚጎዳ መልሶ
ልማት በከተሞች መካሄድ እንደሌለበት በግልጽ አቅጣጫ ማስቀመጥ አለበት፡፡

የልማቱ ፋይዳ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ወደ ሰፊው ሕዝብ ቀስ በቀስ መፍሰሱ (Trickle down) አይቀሬ
ነው ብለው የሚያምኑት የሊብራል መርህ አቀንቃኞች ሳይቀሩ በልማት የሚነሳ ዜጋ የኑሮ ደረጃ ቀደም ሲል
ከነበረበት መውረድ የለበትም የሚለውን መርህ ሲቀበሉ ለፍትሃዊ ልማት በቆመ ልማታዊ መንግስት በሚመራ
አገር እና 70% በዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች የሚኖሩበትን 60% በላይ የሀገሪቱን የከተማ ክልል
የሚመለከት ልማት የበርካቶቹ ዜጎችን ተጠቃሚነት ካላስቀደመ ዘላቂ መሆን አይችልም፡፡

አንድን አካባቢ ለመልሶ ማልማት የሚከለልበት ዋና መሥፈርት አከባቢው ለሥራና ለመኖሪያ ምቹ


አለመሆኑና ነዋሪውም በከፋ ድህነት ውስጥ መገኘቱ መሆን አለበት፡፡ የመልሶ ማልማት ፕሮግራሙ ይዘትም
በቦታው የሚገኙ ነዋሪዎችን ካሉበት የከፋ ድህነት ማውጣት፣ ከደረጃ በታች የሆኑ ግንባታዎችን በአዲስ
ግንባታ መተካት እንዲሁም የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ማሳለጥ መሆን እንዳለበት
በፓሊሲው ሊሰመርበት ይገባል፡፡

አንድ አካባቢ ለመልሶ - ማልማት የሚከለልበት መሠረታዊ መነሻ ለህዝብ ጥቅም መሆን አለበት፡፡ የህዝብ
ጥቅምም በሊዝ ህጉ ከተደነገገው የህዝብ መገልገያ መሰረተ ልማት ከማሟላት ባለፈ ሰፋ ብሎ መተርጎም
ያስፈልጋል፡፡ በከተማ መልሶ ማልማት ላይ ውሳኔ መስጠት ያለበት በፕላን ተመስርቶ በተዋረዱ ባሉ የህዝብ
ተወካይ ምክርቤቶች መሆን አለበት፡፡ ቦታ ሲመረጥ ጀምሮ ግንባታው ከደረጃ በታች መሆኑና ለስራና ለኑሮ
ምቹ አለመሆኑ እንዲሁም ቦታው ሊሰጥ ከሚችለው አገልሎት በታች ጥቅም ላይ መዋሉ ቀድሞ መምጣት
ያለበት በቦታው ያሉ አካላት በከፋ ድህነት ውስጥ መሆናቸውና የነሱን ህይወት መቀየር የቅድሚያ ቅድሚያ
የሚሰጠው መሆኑ እና የመልሶ ማልመቱ ዓላማም የሰው/ የዝቅተኛውን ማህበረሰብ ክፍል ህይወት ለውጥና
ድህነት ቅነሳ መሆን አለበት፡፡

መልሶ ማልማቱ የአንድ አካባቢን ውጫዊ ገጽታ መለወጥን እንደ ቁልፍ ዓላማ ይዞ የተነሣ ከሆነ በተለይ
ፕሮጀክቱ አካባቢ አቀፍ ሲሆን የለማ መሬት በማስገኘት በኩል ቢያንስ ወጪውን የሚመልስ፣ ቀደም ሲል
አካባቢው በፕላን ባለመገንባቱ የተነሣ የጎደለውን የመሠረተ ልማትና የሌሎች መገልገያዎችን ክፍተት የሚሞላ

251
መሆን ይኖርበታል፡፡ በአገር አቀፍ የከተማ ፕላን ስትራቴጅ ሰነድ ላይ የተቀመጠውን የ30፡30፡40 የመሬት
አጠቃቀም ስብጥር ምጣኔን ማሳካት ይጠበቅበታል፡፡

በመልሶ ማልማቱ ሂደት ያልተበላሸን/ያልታመመውን ክፍል/ ማህበራዊ ትስስሩን ለመጠበቅ በቅድሚያ


በቦታው ያሉ ወገኖች በዚያው ቦታ ልማት ውስጥ እንዲካተቱ፤ የማያሥችል ሁኔታ ካለ በሁለተኛ ደረጃ
አማራጭነት ነባራዊ ትስስራቸውን በቅርብ ርቀት ለመቀጠል በሚችሉበት መልኩ ከነበሩበት ቦታ በአምስት
ኪሎ ሜትር ዙሪያ እንዲሰፍሩ፤ ሁለቱ አማራጮችን መተግበር የማያስችል ተጨባጭ እውነታ ከሌለ አብረው
የነበሩ ማህበረሰቦች አብረውና ነባራዊውን ሁኔታቸው እንደጠበቁ የመሰረተ ልማት፣ የአገልግሎትና ስራ ሁኔታ
ያለበት ቦታ ማስፈርን ያስፈልጋል፡፡

ፊዚካላዊ ለውጥ ሲታሰብ ልማቱ የመሬት ዋጋን ከማሳደግ፤ ቢዝነስ ከማስፋት፤ ማህበራዊ ትስስር
ከማስቀጠል፤ አዲሱና ነባሩ ግንባታ እርስ በእርስ ስለማዋሃድ እና እንደ አጠቃላይ ልማቱን አከባቢውን
ስለማነቃቃት ብቃቱ በዓላማ መያዝ አለበት፡፡

መልሶ ማልማቱ የኢኮኖሚ ለውጥን ማዕከል ያደረገ ከሆነ ልማቱ እንደቦታው የለውጥ ፍላጎት የሚለያይ
መሆኑ እደንተጠበቀ ሆኖ ወደ አካባቢው ከፍተኛ የኢኮኖሚ መዋቅር (Higher order goods) እንዲመጡ
የሚጠበቅና የሚታሰብ ከሆነ ነባሩን የኢኮኖሚ መዋቅር ጠርጎ ከአካባቢው ላለማስወጣት ጥንቃቄ ሊደረግበት
ይገባል፡፡ ለቦታው የተመደበው የፕላን ድርሻ ፍጹም ልዩና ሌሎች መስኮችን ለማካተት እንደማይችል በግድ
ካልተወሰነ በቀር በተቻለ መጠን በመስኩ የነበሩ አካላት በቢዝነስ የኖሩና ለመለወጥ የሚችሉ መሆናቸው
ስለሚጠበቅ በተሟላ የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ አብረው እንዲካተቱ መታቀድ አለበት፡፡

ከአቅምና ከቦታው ተፈላጊነት አኳያ ሲመዘን መልሶ ማልማቱ አካባቢውን አፍርሶ መልሶ መግንባትን ግድ
የማይል ከሆነ አዋጪ የሚሆነው እርምጃ የአካባቢ ማሻሻያ ልማት (urban upgrading) ይሆናል፡፡ በዚህ
አማራጭ ትኩረት የሚደረግባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች አካባቢው የሚፈልጋቸውን ቁልፍ የመሰረተ ልማት
አውታሮችን ማሟላት፣ አካባቢውን ለመኖሪያና ለሥራ ምቹ ማድረግ፣ በቦታው ላይ ያሉ አካላትን ይበልጥ
ተጠቃሚ የሚያደርግ በተቻለ መጠንም በሂደት በቦታው ያሉ አካላት በሚያገኙት ለውጥ መጠን የመኖሪያና
የስራ ቦታቸውን መለወጥን የሚፈቅድና ከመሰረታዊ መሰረተ ልማትና አገልግሎት ባለፈ አጠቃላይ አከባቢያዊ
መሻሻል እንዲመጣ አስቻይ ሁኔታ መቃኘት ያስፈልጋል፡፡

በቦታው የሚካሄደው የመልሶ ማልማት ስራ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ከሆነ፣ በተለይ ነባር ግንባታውን ጠርጎ
አካባቢው ከማደስ አስቀድሞ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት አውታርን በመዘርጋት አካባቢውን እንዲቀየር
የሚደረግ ከሆነ እርምጃው ሁለት አካባቢን እንደ መንገድ ባሉ የመሰረተ ልማት አውታሮች በማገናኘት
ፈጣንና አደጋን የሚቀንስ የትራፊክ ፍሰትን ማሳለጥ ላይ ብቻ መወሰን የለበትም፡፡ የሚዘረጋው መሰረተ

252
ልማት የሚያልፍበትን ማህበረሰብ ህይወት የሚለውጥ፤ ማሕበራዊ ትስስሩን ከተቀረው የከተማው ክፍል
የሚያስቀጥል፤ አከባቢያዊ ኢኮኖሚውን የማነቃቃት ዓላማን በጥምር የያዘ ሆኖ መሰራት አለበት፡፡

ለ) በመልሶ ማልማቱ የመንግስት ሚና


ሂደቱ በከፍተኛ ደረጃ በመንግስት መመራት አለበት፡፡ በሌሎች ሀገራት በዚህ ስራ ላይ መንግስት የሚገባበት
መነሻ ምክንያት የገበያው ጉድለትና ፍጥነት ሲሆን በእኛ ሀገር የኢኮኖሚ እና ማሕበራዊ ልማት መርህ አንጻር
ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልን ለማረጋገጥም ሲባል መንግስት በዚህ ዘርፍ መግባቱ የግድ ይላል፡፡

ከልማቱ ምክንያታዊ መርህ በመነጨ መንግስት ዘርፈ ብዙ ባለድርሻ ስለሆነ /በመሬት ባለቤትነት፤ በተወረሱ
ቤቶች አስተዳዳሪነትና የገበያ ጉድለት አቃኝነት አንጻር/ በከተማ መልሶ ማልማት የመንግስት ሚና ከፍተኛ
ነው፡፡ ስለሆነም መንግሰት ሂደቱን መምራቱ አንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉን ከመሸከም በተወሰነ ደረጃ የህግና
የትግበራ ድጋፍ በማድረግ ሌሎች ባለድርሻዎችንም ለማሳተፍ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ይገባል፡፡

ሰፊ መልሶ ማልማት ስራ በየትም ሀገር ያለመንግስት መሪነት የገበያው ጉድለት በራሱ ፈትቶ አልሄደም፡፡
የመንግስት ሚና ሙሉ በሙሉ ቦታውን ተረክቦ ከማልማት ጀምሮ የፖሊስና የህግ ማቀፍ ማመቻቸትና
የተወሰነ ድጋፍ እስከማድረግ ውሱን ድርሻ ሊወስድ ይችላል፡፡ ስራው በይዘት ድህነት ማስወገድና ሁለንተናዊ
የእድገት ለውጥ ማስመዝገብያ አንድ አጀንዳ እንደመሆኑ መጠን በሁሉም ደረጃ ያለው የመንግስት መዋቅር
ማለትም ፌደራል፤ ክልልና ከተሞች ሙሉ ባለቤቶች ሆነው መንቀሳቀስ አለባቸው፡፡

ሐ) የማህበረሰብና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ


ተፈላጊነታቸው ለወደቁ አካባቢዎች መልሶ በማልማት በኩል አሁን ያለውን ጠንካራ የህዝብ ድጋፍ ተጠናክሮ
እንዲቀጥል ከተፈለገ ህዝብ የሚያነሳቸው የሂደቱ ጉድለቶች መፈታት አለበቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ ከመልሶ
ማልማት ዕቅድ ዝግጅት ጀምሮ ህዝብን ማማከር፣ በመልሶ ማልማት ዙሪያ የሕዝቡን አማራጭና ድምጽ
ማዳመጥ፣ ከሕዝቡ ጋር ስፋትና ጥልቀት ያለው ውይይት አካሂዶ መነሳት የግድ ይላል፡፡ በእርግጥ በተሟላ
የሕዝብ ተሳትፎ ላይ የሚመሠረት ልማት እንደጎታች እና ጊዜ አባካኝ ተደርጎ ሊታይ ይችላል፡፡ ሆኖም ዋናው
ጉዳይ ልማቱን መጀመር ሳይሆን የሚጀመረውን ልማት ጫፍ ማድረስ ነው፤ ከመጀመርያው ሕዝቡን አሳምኖ
ወደ ልማቱ ከተገባ አምኖ የተሰለፈ ሃይል ለአፈጻጸም ፍጥነትና ለሂደቱ ሳይንገራገጭ ጫፍ መድረስ ወሳኝ
ስለሆነ ሊተኮርበት ይገባል፡፡

በህዝብ ቀጥታ ተሳትፎ እና ወሳኝነት ላይ ጠንካራ እምነት ባለው ልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መስመር በሚከተል
መንግሰት ቀርቶ በሊብራል አስተሳሰብ በሚመሩ ሃገራትም የከተማ መልሶ ማልማት ያለ ማህበረሰቡ ቀጥተኛ
ተሳትፎ መካሄድ እንደሌለበት በዓለም አቀፍ ደረጃ ጉዳዮን በሚያቀነቅኑት እንደ ዓለም ባንክ ባሉ ተቋማት
ሰነዶች ላይ በግልጽ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ሰለሆነም እንደ አጠቃላይ የትኛው የከተማው ክፍል በምን ስልት መልሶ
መልማት አለበት ከሚለው ከተማ አቀፍ ፕላን ዝግጅት ጀምሮ የሂደቱ መሪ የረጅምና መካከለኛ ፕሮግራም

253
ሲቀረጽ ከዚያም የሰፈር ልማት ፕላን ሲዘጋጅና የአፈጻጸም መርሃ ግብር ሲቀረጽ ማህረሰቡ በየደረጃው በሙሉ
ባለቤትነት ስሜት በተደራጀ አግባብ በሰፊው ማሳተፍ ይኖርበታል፡፡

መሳተፍ የሚገባው ወገን መልሶ ማልማት በሚካሄድበት አከባቢ የሚገኘው ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን በሂደቱ
የሚሳተፉ አካላት ጭምር መሆን አለበት፡፡ በመልሶ ማልማቱ ስራ ተሳታፊ የሚሆኑት የግል አልሚዎች፣
በቦታው ላይ ያሉ ወገኖች፣ መሰረተ ልማት ዘርጊዎች ከአስተዳደሩ ግንባታና እቅድ ጋር እኩል መራመድ
እንዲችሉ፣ ቀድመው የገቡት የሚጎዱበትና የዘገዩት ሳይደክሙ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ኢ-ፍትሃዊ አካሄድ
ለማስወገድ፣ በአጠቃላይ የአካባቢው ለውጥ ወጥ ባለመሆኑ የተነሣ የከተማው ተጠቃሚነት እንዳይቀንስ፣
እንዲሁም የመልሶ ማልማቱ እርምጃ የተለያዩ አካላትንና ተቋማትን ተሳትፎ የሚጠይቅ ከመሆኑ አንጻር
ሁሉም ባለድርሻ አካላት በመልሶ ማልማቱ ስራ ላይ ድርሻቸዉን እንዲወጡ የሚያስችል ዘላቂነት ያለው
አደረጃጃትና አሰራር መዘርጋት አለበት፡፡

መ) አካታችነትና ፍትሓዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ መልሶ ማልማት


ለመልሶ ማልማት በተከለለ ቦታ ላይ ያሉ አካላት ከልማቱ ጋር ህይወታቸው አብሮ ወደ ተሻለ ደረጃ መሸጋገር
አለበት፤ በተቻለ መጠን መልሶ ማልማት ሲታሰብ ሰፊ የሥራ ዕድልና ሁሉንም የኢኮኖሚ መስኮች በአግባቡ
የሚያቅፍ መደላድል በመፍጠር ቀደም ሲል አብዛኛው ነዋሪ ተሰማርቶባቸው የነበሩ የሥራ መስኮች
እንዲሻሻሉና አንዲስፋፉ ማድረግ እንጅ እንዲከስሙ የሚያደርግ መሆን የለበትም፡፡ በእንዲህ ዓይነቱ ሂደት
በመልሶ ልማቱ ተጠቃሚ የሚሆነው አካል ተነሺዎቹን የሚክስበት አሰራር መፈጠር ያስፈልጋል፣ በዚህ
መሠረት ልማቱ ነባሩንና አዲሱን ያዋሃደ፤ ነባሩን ቢዝነስ አዳብሮ ያስቀጠለ፤ አዳዲስ ለውጦችንም ያካተተ፤
ለድሃውም ለሃብታሙም ተደራሽ የሆነና ሚዛኑን የጠበቀ መሆን አለበት፡፡ አካታችነት ሲነሳ በምን መልኩ
የሚለው ጉዳይ አብሮ መታየት አለበት፤ ሁሉ ባለበት የነበረውን ስራ በአዲስ ግንባታ ማከናወን ነው ተብሎ
ከተተረጎመ ድህነት ባለበት የሚያስቀጥል አዋጭ ያልሆነ የቢዝነስ ሃሳብ የመሆኑን ያህል አንድ ልማት አካታች
መሆኑ የሚመዘነው ደግሞ ነባሩ ኗሪና የቢዝነስ ባለቤት ህይወቱ ተቀይሮ የልማቱ አካል ማድረግ ሲችል መሆኑ
በግልጽ መቀመጥ አለበት፡፡

የከተማ መልሶ ማልማቱ ስራ መሰረታዊ ለውጥ (Transformation) ያመጣ፤ የልማቱ ይዘት ከግንባታ
ለውጥና ከገጽታ መቀየር ባለፈ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ መቃኘት ያስፈልጋል፡፡
ከዚህ አኳያ ሲታይ በቦታው የነበረው ሰው ስራውን ቀይሮ በአዲሱ ቢዝነስ መሰማራት የሚያስችለው ድጋፍ
እና አቅጣጫ ያስፈልጋል፡፡ ድጋፉም ከገንዘብ ያለፈ መሆን ይኖርበታል፡፡ ገንዘብ ሰውን መለወጥ የሚችለው
ሰውየው ያለበት ሁኔታ፤ ዕድሜ፤ የትምህርት ዝግጅት፤ ልምድ፤ ፍላጎት፤ አዋጭ የገንዘብ አጠቃቀም ክህሎት
እንዲሁም ሁኔታው ለለውጥ አስቻይና ሳቢ መሆን ሲችል ነው፡፡ አልበለዚያ ደግሞ ስልጠና፤ የስራ ቦታ
ማመቻቸት፤ ገበያ የማለማመድ ድጋፍ፤ የካፒታል ብድር ወዘተ ያካተተ ፓኬጅ ተቀርጾ መተግበርን
ይጠይቃል፡፡

254
ነባር ባለይዞታ በቦታው ላይ አንዲያለማ መፍቀድና መደገፍ ትክክለኛ ስልት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ መልሶ
ማልማት ማለት ታስሮ የነበረውን ባለይዞታ ነጻ የሚያወጣ፣ ተጨማሪ መሰረተ ልማት የሚገነባ፣ ዙሪያው
በመልማቱ እሴት የሚፈጥር ስለሆነ ለዚህ ሁኔታ መከሰት ድርሻ ያላቸው ወገኖች አንደ ድርሻቸው ወጭና
ጥቅምን መጋራት አለባቸው፡፡ ቦታው እንዳለ በመቀየሩ የግል ባለይዞታው በቦታ ዋጋም ሆነ በሚያከናውነው
ስራ ተጨማሪ ጠቀሜታ እንዲያገኙ ማስቻል ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለሚያገኘው ተጨማሪ እሴት ድርሻውን
እንዲወጣ የተወሰነ ክፍያ የሚፈጽምበት ወይንም መሬቱን/ይዞታውን የማጋራት (Land Sharing) መርህ
መተግበር አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ባለይዞታው በመልሶ ማልማቱ ምክንያት የተፈጠረ እሴት ከፍተኛ ተጠቃሚ
እንዲሆን የሚያደርግ በተወሰነ መልኩም ስፔኩሌሽንና ሽያጭን የሚያበረታታ አካሄድ ከመሆኑም በተጨማሪ
የከተማ አስተዳደሮች ልማቱን ዘላቂ ከማድረግ አንጻር ቦታው መልሶ እንዲለማ ያወጡትን ወጭ
ሊያካክስላቸው የሚችል እድል የሚያጠብ ነው፡፡ ይህ ቦታን ሳይቀላቀል ባለበት መልኩ በባለይዞታው
እንዲለማ የሚፈቅድ ስልት ልማቱ በተበጣጠሰ ይዞታ እንዲቀጥል የሚያደርግ፣ ትልልቅ ኢንቨስትመንቶችን
የሚያደናቅፍ፣ ለዕይታም ሳቢ ያልሆነ እና ቦታ አባካኝ ልማት የሚያስከትል ስለሚሆን በተወሰነ ቦታና ሁኔታ
መገደብ አለበት፡፡ መሰል የግል ይዞታ በተናጠል ማልማት መፈቀድ ያለበት ቦታው ከብሎክ ባነሰ መልማት
አንደሚችል በፕላን ከተመላከተ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ በብሎክ የሚለማ ከሆነ ደግሞ በብሎኩ ያሉ ሰዎች
አቅሙና ፍላጎቱ ኖሯቸው ሲደራጁ መሆን አለበት፡፡ ችግሩ የፋይናንስ በሚሆንበት ወቅት በፋይናንስ አቅርቦት
የሚደገፉበት ካልሆነ ደግሞ 51% እና ከዛ በላይ ያለውን ቦታ የያዙት ተስማምተው ቀሪዎቹ ካልፈለጉ
መብታቸው ተጠብቆ ቦታውን የሚለቁበት ሁኔታ መመቻቸት አለበት፡፡

ሠ) የመልሶ ማልማት ዕቅድ ይዘትና ሂደት


የመልሶ ማልማት ሂደቱ መከናወን ያለበት በከተማ አቀፍ መዋቅራዊ ፕላን ተካቶ፤ ከዚያም አከባቢያዊ
ፕሮጀክት ከመንደፉ በፊት የረጅምና መካከለኛ ጊዜ ልማት እንዲሁም የማስፈፀሚያ መርህ ግብር
ተዘጋጅቶለት ሊሆን ይገባል፡፡ መቸ፤ የቱ ቦታ፤ በምን ስልት፤ በምን ፋይናንስ መከናወን እንዳለበት በከተማ
አቀፍ የመልሶ ማልማት ፕሮግራም ሰነዱ ላይ መወሰን አለበት፡፡ ፕላኑ በመልሶ ማልማቱ ዓላማ መመራትና
የዓላማ ማስፈጸሚያ መሳሪያ መሆን አለበት፡፡

ከጠቀሜታም ሆነ ከአቅም አንጻር መልሶ ማልማት ሲባል በሁሉም ከተማና ቦታ ተመሳሳይ ይዘት ኖሮት
ሊከናወን አይችልም፡፡ ስለሆነም የከተማ ፕላን ጥናት ሲከናወን የመሬት አጠቃቀም ውሳኔ ከማሳለፍ በዘለለ
የቱ ቦታ በምን ስልት፤ ምን ይዘት ኖሮት ሊሠራ እንደሚገባ፤ መቼ መልማት እንዳለበት ማዕቀፍ መስጠት
አለበት፡፡ ጥናቱ እንደ የቦታው ሁኔታ መልሶ ማልማቱ ምን ላይ ያተኩር በሚለው ደግሞ የታመመ
/የጎደለውን/ ክፍል ብቻ ማከም፤ ከሚለው ጀምሮ ሁሉንም አዲስ እስኪሆን አብሮ መለወጥ የሚል ቅኝት
ማመላከት አለበት፡፡

255
በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉን የከተማው ክፍል እንዳለ ፈርሶ መገንባት እንዳለበት መታሰብ የለበትም፡፡ ከጅምሩ
ሙሉና ሁለንተናዊ ለውጥ መታሰብ ያለበት በከተሞች ዋና ማዕከላት፤ ንዑስ ማዕከላት እና የትራንስፖርት
ኮሪደሮች ላይ መሆን አለበት፡፡ ከመሰል ቦታዎች ራቅ ያሉ ውጫዊ የዕይታ ገፅታ እና አካባቦያዊ ደህንነት
ጉድለት ላለባቸው ቦታዎች ፕላኑ ይህንኑ ለውጥ ብቻ አድርጎ ነባሩ ማህበረሰብና ኢኮኖሚን ማስቀጠል
እንደሚገባ ማመላከት አለበት፡፡ አንዱ ይዘቱ ሲለወጥ ሌላው የመለወጥ ፍላጎት ማሳየቱና በሂደት መለወጡ
አይቀሬ እንደሆነ ማለትም ውጫዊ ገፅታ መደራጀትና አካባቢያዊ ደህንነት ጉድለት ከታደሰ/ከተሻሻለ መሬቱ
የሚጠብቀው ከፍተኛ ጠቀሜታ ዋጋ ያለው ልማት/ከፍ ያለ ኢኮኖሚ መምጣቱ፤ ኢኮኖሚው ከፍ ካለ ደግሞ
ሌላ የማህበረሰብ ገጽታ ለመያዝ ግፊት ማሳደሩ ስለማይቀር በፕላን ዝግጅቱ ላይ ይህ ክስተት የሚያስተናግድ
ሁኔታ መታሰብ ተገቢ ነው፡፡

መልሶ ማልማት ለገበያው ብቻ ከተተወ በባህሪው የሚከሰተው ነገር አገልግሎቶች በተወሰነ ቦታ መሰባሰብ፤
ተመሳሳይ ገቢ ያለው ማህረሰብ እንዲሁ ከሌላው የመነጠል አዝማሚያ ያጠናክራል፤ ይህ ክስተት በነባሩ
ከተማ ተጠብቆ የቆየውና ከተሞች ቀንም ሆነ ማታ ህይወት እንዲኖራቸው የሚያስችለው ሁኔታና ድሃና
ሀብታም አብሮና ተደጋግፎ የኖረበትን ሰላማዊና በበጎ ዓይን የመተያየት መንፈስን እንዳያጠፋ በፕላን ደረጃ
በአግልግሎትም ሆነ በገቢ መለያየትና መነጣጠል እንዳይከሰት ገዥ ድንጋጌ ማካተት አለበት፡፡ ይህ ማለት
የንግድ ህንጻ ሲገነባ መኖሪያ፤ መኖሪያ ሲገነባ አገልግሎትና ንግድ፤ ለሀብታሙ የሚሆን ሞዴል ሲታሰብ ድሃም
የሚኖርበት ሁኔታ ጎን ለጎን መካተት አለበት፡፡ በመልሶ ማልማት ቦታ ያሉ ወገኖችን ማስነሳት የግድ ከሆነ
መልሶ መሰፈሪያ በመረጠው ቦታ የመኖርና በፕላን ደረጃ የነበረውን ድሃና ሀብታም አብሮ የመኖር ሁኔታ
ቀይሮ በገቢ ላይ የተመሰረተ ማሐበራዊ ልዩነት እዳያስከትል መጠንቀቅና መምራት ያስፈልጋል፡፡

በመልሶ ማልማት ሂደት ሁሉም ነገር ቅርስና ታሪክ ነው፣ አይነካ ወይንም አሁን ያለው ግንባታ በሙሉ ድሃ
ሳለን የተገነባ ድህነትም ታሪክ ነውና ይጠበቅ/አይወገድ እንደማለት ነው ከሚሉ ጫፍ የወጡ እይታዎች የራቀ
የፕላን ዝግጅት መኖር አለበት፡፡ ፕላኑ ሲዘጋጅ በግልጽ መስፈርት ማህበረሰቡ ቅርስ፤ ታሪክና ባህል ዘካሪ ነው
ሊጠበቅ ይገባል የሚለው ሀብት በሙሉ መለየት አለበት፡፡ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር/ቢሮ ሊጠበቅ
የሚገባው ቅርስና ባህል በመለየት ለህዝቡና ፕላን ለሚሰራው አካል አቅርቦ ከማሰመዘገብ በዘለለ እራሱ ፈራጅ
መዝጋቢና በፈለገው ጊዜ ሰራዥ ከሆነ ሂደቱ ለኪራይ ሰብሳቢነት የተጋለጠ ይሆናል፡፡ ሁሉም የተለየ ቅርስ
ይዘት ያለው ሁኔታ ባለበት መልኩ መጠበቅ ብቻ የግድ ላይሆንና የማይቻልም ይሆናል፡፡ ይህ ቅርስ ባለበት
ሊጠበቅ የሚችለው የግንባታ ቁሱ መቆየት የሚችል፤ የቦታ ብከነት የሌለውና ሌሎችን ልማቶች የማያደናቀፍ
ከሆነ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ይህ የተለየ ቅርስና ታሪክ በምን መልክ ሊንጸባረቅ፣ ሊጠበቅና ሊጎለብት እንደሚገባ
በፕላኑ በግለጽ ምላሽ መሰጠት ይኖርበታል፡፡

256
ረ) የቦታ መረጣ መስፈርትና አመራረጥ ሂደት
በከተማ አቀፍ ደረጃ በፕላን በተመላከተው የመልሶ ማልማት ስልትና መርሃግብር መሰረት አንድ ቦታ ለመልሶ
ማልማት ትግበራ ሲመረጥ ቀዳሚው መስፈርት በቦታው ያለው ማህረሰብ ያለበት የኑሮ ሁኔታ መሆን
ይገባዋል፡፡ መልሶ ማልማት የሰውን ህይወት ለመለወጥ በተለይ በቦታው ላይ ያሉ ማህበረሰቦች ቅድሚያ
ዕድል መስጠት ድህነትን በግንባር መፋለም ተደርጎ ከተተገበረ ልማቱ ለኔ ቅድሚያ ይምጣ የሚል ፉክክር
ለልማት መጓጓት ምክንያት የሚሆንበት እንጅ እስካሁን እንደነበረው ልማቱ መጣብን የሚባል ስለማይሆን
መርሁ በጥብቅ ሊከበር የሚገባ ነው፡፡

በመቀጠል ከተማውን የማነቃቃትና የመለወጥ አቅሙ፣ ከተማው በዕኩል ሚዛን እንዲለማ ማዕከልና ንዑስ
ማዕከላት ጎን ለጎን ካልተሰራ የተጀመረውን ልማት በኩታ ገጠም የሚገኝ ቦታ ለማልማት በሚል አንድ አካባቢ
ብቻ ማተኮር ያ አካባቢ ብቻውን እየጎለበተ ሌሎች ማእከላት እንዲቀጭጩ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ
በሂደት ሁሉም ነገር ወደዚህ ማዕከል ለመሳብ ተደራሽነቱ ፈተና ይገጥመዋል፤ በአካባቢው የትራፊክ ፍሰቱ
ስለሚጦዝ በራሱ ጊዜ ወደ ውድቀት የሚያመራ ይሆናል፡፡ ቦታ መረጣው ከከተማ አቀፍ ሚናው ሌላ
የአከባቢው ፊዚካላዊና ኢንቫሮመንታል ጉድለት ደረጃውና ህመሙ ወዳልታመመው ክፍሉ የመዛመት
አዝማሚያ፣ ለትግበራ ቅለቱ /ውስብስብና ወጭ የሚያበዛ አለመሆኑ/፣ የሚያሰገኘው ጠቀሜታ ከፍተኛነት
ወዘተ በመስፈርትነት ሊካተቱ ይገባል፡፡

ቦታ መረጣው ከላይ የተጠቀሰውን መርህ ቢከተል እንኳ ቦታው ላይ ያሉ አካላትን ተጠቃሚ ለማድረግ ታስቦ
የኪራይ ዕደላ ባህሪ ኖሮት መመራት ቀርቶ እንደ በፊቱ በተመረጠው ቦታ ያሉ ወገኖች ላይ ጉዳት
የሚያስከትል ወይም ጉዳትም ጥቅምም የሌለው ቢሆን ይዘቱ ፖለቲካዊ እንጅ ቴክኒካዊ አይደለም፡፡ ስለሆነም
ቦታ መረጣው ከቴክኒክ እይታ አንጻር በግልጽ መስፈርት መከናወን ያለበት ቢሆንም ውሳኔው በፖለቲካ ክፍሉ
መሪነት በህዝብ ሙሉ ተሳትፎና ባለቤትነት መከናወን አለበት፡፡ ቦታ የሚመረጠው ለህዝብ ጥቅም መሆኑና
የህዝብ ጥቅም ማለትም በሊዝ ህጉ እንደተደነገገው የህዝብ መገልገያ መሰረተ ልማት ከሚለው በሰፋ በፕላን
ልማትን መረጋገጥን ማካተቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህ ውሳኔ መስጠት ያለበት በፕላን ተመላክቶ በተወረዱ ባሉ
ምክርቤቶች መሆን አለበት፡፡

በዚህ ሂደት በአካባቢው ግልጽ ችግር መኖሩ እየታየም ነዋሪዎቹ መጪው ምን ሊሆን ይችላል በማለት
ከለውጥ ስጋት፣ ተጎጅ ከመሆን ስጋት፣ በተለይ ሥራና ገቢ ከማጣት፣ ከመፈናቀል ወዘተ መነሻ ተመችቷቸው
እየኖሩ እንደሆነ ራሳቸውን በማሳመን እንዲነኩ ያለመፈለግ፤ ገፋ ሲልም ከችግሩ ጋር መለማመድ ወዘተ
እንደሚጋጥም በሌሎች ሀገራት ልምድና በንደፈሃሳብ የታወቀ ስለሆነ ግዜ ሰጥቶ የመተማመን ስራ መከናወን
አለበት፡፡

257
ሰ) ቦታ ከተመረጠ በኋላ ዝርዝር የሰፈር ልማት ፕላን /LDP/ የማዘጋጀት አስፈላጊነት፡
ለሁሉም የከተማው ክፍል የሰፈር ልማት ፕላን ማዘጋጃት አይቻልም፤ ቢዘጋጅም ሁሉም አንድ ጊዜ ተግባራዊ
ስለማይሆን ጠቀሜታ አይኖረውም፡፡ ነገር ግን በአካባቢ ደረጃ መልሶ ማልማት በሚሰራበት ሰፈርና በዋና
የመሰረተ ልማት ዝርጋታና የትራንስፖርት መረብ ልማት በተጓዳኝ ስለሚከናወን መልሶ ማልማት የራሱ የሆነ
ዝርዝር የሰፈር ፕላን ሊዘጋጅለት ይገባል፡፡ የሰፈር ፕላን ዋና ዓላማ በከተማ ደረጃ የተቀመጠውን ፕላን
ከወቅታዊና አከባቢያዊ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማዛመድ የላቀ ጥቅም በሚያመጣ መልኩ እንዲለማ ማስቻል
ነው፡፡ ስለሆነም ፕላኑ እውነታውን የሚያንጸባርቅና እንዳለ ሊተገበር የሚችል መሆን አለበት፡፡ በዝግጅት
ሂደቱ የአከባቢውን ማህበረሰብ ሙሉ ተሳትፎ ይዞ አካባቢው በምን ራዕይ እንዲለማ እንደሚመኙ፣ ሊፈታው
የተፈለገ ችግር እና በምን ስልት ሊፈታ እንሚገባ የተመከረበት መሆን ይኖርበታል፡፡

አከባቢ ተኮር የሰፈር ልማት ፕላን እንደ ቦታው ሁኔታ/ታሪካዊ ቅርስና ባህል የሚንጸባረቅበት፣ መጠበቅና
መጉላት የሚሻ፤ ለከተማው መገለጫ ልዩ ባህሪ የሚታይበት ከሆነ/ የአካባቢ ልማት ፕላኑ ሲሰራ እስከ አርባን
ዲዛይን ድረስ መውረድ ይኖርበታል፡፡

መልሶ ልማት ሲታቀድ የፕሮጀክቱ ወጪ የመንግስት ፋይናንስ ብቻ ሳይሆን የግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንት
በዕቅድ ውስጥ መመላከት አለበት፡፡ ለልማቱ የሚወጣው ወጪ ከሚገኘው ገቢና ጥቅም ጋር አዋጭነቱ በፕላን
ዝግጅቱ ወቅት መፈተሽና አዋጭ እንዲሆን ሰልት መንደፍ ያስፈልጋል፡፡

ሸ) አማራጭ ስልት መኖርና ውሳኔ አሰጣጥ፤


በሁሉም ከተሞችና በሁሉም የከተማው ክፍል ወጥና አንድ ዓይነት ስልት መተግበር ከአቅምም ሆነ ከፋይዳ
አንጻር የሚደገፍ አይሆንም፡፡ ስለሆነም የስልቱ መወሰኛ ግልጽ መስፈርትና ሂደት መደንገግ አለበት፡፡ ስልቱ
የሚወሰነው በፖለቲካ አመራሩ መሪነት በማህበረሰቡ ሙሉ ባለቤትነት መሆን ይኖርበታል፡፡

እንደ አጠቃላይ የቦታው ተፈላጊነት ከፍተኛ በሆነው የከተማ ክፍል ይህንን እድል ተጠቅሞ እውነተኛ ለውጥ
(transformation) ለማምጣት ማቀድና መተግበር የሚገባ ሲሆን ይህ ሁኔታ ካልተፈጠረ ደግሞ በጥናት
ተደግፎ አዋጭና መተግበር የሚቻለው የመሻሻል፣ የሰፈራው ይዘት ከመሬቱ ተፈጥሮዊ አቀማመጥ ጋር
የሚጣጣምና የሚያስችል ሲሆን በይዞታ ደረጃ፣ መሰረተ ልማት መር ስልት በመከተል፣ በከተማ
ጣብያ/ብሎክ/ደረጃ በደረጃ በገበያው በራሱ ጭምር መልሶ ማልማቱ እንዲመጣ አስቻይ ሁኔታ መኖር
አለበት፤

ቀ) ገበያው በተወሰነ ደረጃ መልሶ ማልማትን እንዲያመጣ አስቻይ ሁኔታ መፍጠር፡


ከላይ እንደተጠቀሰው በአንድ ስልት ብቻ የመልሶ ማልማቱን ስራ ማስፋት ስኬታማ አያደርግም፡፡ ስለሆነም
በየደረጃው በገበያ ኃይል ጭምር መልሶ ማልማቱ እንዲመጣ እና በቀጣይም ራሱን እየቀየረ መሄድ እንዲችል
የፖሊሲና የከተማ አቀፍ ፕላኖች መምራት አለባቸው፡፡ አፈጻጸሙ በየጊዜው እየተፈተሸ ዘላቂነት፣ ከመርህ

258
ውጭ የሚከናወን፣ ጎታች፣ አበረታች ያልሆኑ ይዘት ያላቸውን በመለየት የማሻሻል ስራ በቋሚነት መሰራት
አለበት፡፡

በሌሎች ሀገራት ያለው የተስፈኝነት (Speculation) እንቅፋትና በእኛ ሀገር ልዩ ሁኔታ ያለው የይዞታ ቅልቅል/
የቀበሌና የግል/ እና የይዞታዎች ስፋትና ቅርጽ ለልማት ምቹ አለመሆን/ያለፕላን ከመሰራቱ በተያያዘ የይዞታው
ቅርጽና ስፋት ከፍተኛ ግንባታ ለማሳረፍ የማይመችና የማይበቃ መሆን/ ያለውን ችግር ለመፍታት በአንድ
ይዞታና ብሎክ መልማት ያለባቸውን ይዞታዎች በፕላን ደረጃ መወሰን ቀዳሚው ተግባር ሊሆን ይገባል፡፡ እንደ
አንድ ይዞታ/ብሎክ መልማት ባለበት ቦታ ላይ ያሉ ባለይዞታዎች ይዞታን እንደ ድርሻቸው ወደ አንድ
መጠቅለል የሚቻልበት፣ ተጋሪዎቹ ግለሰቦች ከሆኑ ደግሞ በጋራ ወደ ልማት ፈጥነው ሲገቡ ወይንም ለአልሚ
አስተላልፈው ልማቱ ሲመጣ የሚበረታቱበት፣ በይዞታና በብሎክ ልማት ደረጃ አብዛኞቹ ባለይዞታዎች
በመልሶ ማልማቱ ተስማምተው የተወሰኑት በተስፈኝነትና ሌሎች ልማታዊ ባልሆኑ አደናቃፊ ምክንያቶች
ልማቱን እንዳያደናቅፉ ሌሎች የተስማሙ ወገኖች ያገኙት ጥቅምና ሁኔታ ተጠብቆላቸው ለልማቱ
የሚገደዱበት ስልት ቀይሶ መተግበር ያስፈልጋል፡፡

ከዚህ አንጻር የሊዝ አዋጅ የመንግስት ቤት በመከራየት በንግድ ስራ የተሰማሩ ወገኖች የልማቱ አካል እንዲሆኑ
ተደራጅተው በነፍስ ወከፍ አስከ 25 ሜትር ካሬ መሬት በሊዝ የመነሻ ዋጋ ቅድሚያ የማልማት መብት
መፍቀዱ እንዳለ ሆኖ ይህ ስልት የሚተገበረው መንግስት ቦታውን በመልሶ ልማት እቅድ ይዞ በሚገባበት ጊዜ
ብቻ ሳይሆን እነዚህ ወገኖች መንግስት በቦታው ዕቅድ ይዞ ከመግባቱ ቀድመው በራሳቸው ማልማት
ሲፈለጉም ጭምር ሊፈቀድላቸው የሚችልበት የድንጋጌ ማሻሻያ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ከዚህ ሌላ ለልማት የቦታ ማቅረብያው ዘዴ በወሳኝነት ጨረታ እንዲሆንና ቦታው ለጨረታ ሲቀርብም የለማና
ከይገባኛል ጥያቄ የጸዳ መሆን እንዳለበት በሊዝ አዋጁ የተደነገገው ሃሳብ ከመልሶ ማልማት አንጻር ሲታይ
ግንባታ ያለበት ቦታን በሊዝ ድርድር ለአልሚ ለመስጠትና አልሚዎች በቦታው ያሉ ወገኖችን እንዲክሱ፤
መልሶ መስፈሪያ ቤት እንዲሰሩ/ በልማቱ እንዲያካትቱዋቸው ወዘተ የማድረግ እድልን ያጠበበና ቀደም ሲል
ሥራ ላይ በነበረው የሊዝ አዋጅ ቁጥር 272/1994 በስፋት ሲሰራበት የነበረውን የከተማ መልሶ ማልማት ስራ
ያስቆመ ሆኗል፡፡ የሊዝ አዋጅ ቁጥር 272/1994 መተግበር ከተጀመረበት ማግስት ጀምሮ ሀገራዊ የልማት
ለውጡ በከተሞችም በስፋት እንዲከናወን የጎላ ድርሻ የነበረው መሆኑ ይታወቃል፡፡

አዲሱ የሊዝ አዋጅ (721/2004) ለልማት የሚፈለግ መሬት በድርድር ማስተላለፍ በማስቀረት ወደ ጨረታ
መቀየሩ ኪራይ ሰብሳቢነትን ከመታገል አንጻር የሚደገፍ ቢሆንም የልማቱ መጓተት/አለመስፋት በራሱ ኪራይ
ሰብሳቢነት እንዲከስም የማያደርግ ስለሆነ መቀየስ ያለበት ስልት ችግሩን እየታገሉ/ ልማቱን ማፋጠን መሆን
ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም መልሶ ልማቱ እንዲሰፋ ለማድረግ ካለው ፋይዳ አንጻር ግንባታ ያለበት ቦታ በግልጽ
መስፈርትና በቦታው ያሉ ወገኖችን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ በድርድር ማስተላለፍ የሚቻልበት ስልት
የሊዝ አዋጁ መፍቀድ ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም መልሶ ማልማቱን እንዲሰፋ ለማድረግ ግንባታ ያለበት ቦታ

259
በግልጽ መስፈርት የሚከናወን እንደዚሁም በቦታው ያሉ ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመሬት የሊዝ
ዋጋውን ሳይሆን ኩታ-ገጠም መሬትን በድርድር ማጠቃለል የሚቻልበት ስልት እንዲኖር የሊዝ አዋጁ መሻሻል
ይኖርበታል፡፡

የመልሶ ማልማትን ሂደት አማራጭ ከማስፋትና ከማፋጠን አንጻር ከዚህ ቀደም በህጋዊ መንገድ በነባር
ስሪት/በሊዝ የተያዙ ቦታቸውን ለማልማት፤ ወይም ቢዝነሳቸውን በማስፋት በመልሶ ማልማት ለመሳተፍ
የተወሰነ በአጎራባች ያለውን ቦታ ማጠቃለል የሚፈልጉ ወገኖች ልማት አሳማኝና በቦታው ያሉ ወገኖችን
ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ከሆነ ከቦታቸው ኩታ ገጠም ያለውን ቦታ በቀጥታ በድርድር በሊዝ ሊወስዱ
የሚችሉበት ሁኔታ መፈቀድ አለበት፡፡ ይህ ማለት በመሬት የሊዝ ዋጋ ላይ ድርድር ይኖራል ማለት ሳይሆን
ቦታው አጠቃልለው ማልማት የሚችሉበትን ሁኔታ መፍጠር ያስፈልጋል ማለት መሆኑ በግልጽና በማያሻማ
መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡

በ) የካሳ ክፍያ መርህና አተገባበር


ካሳ ችሮታ ሳይሆን ህገመንግስታዊ መብት ነው፡፡ ከሳ መከፈል ያለበት አንድ ሰው በጉልበቱ፣ በአእምሮው እና
በሀብቱ ላፈራውና በልማት ምክንያት ለሚያጣው ንብረት ሁሉ መሆን አለበት፡፡ የህገ-መንግስቱ ትርጓሜ
ንብረት ማለት ግንባታና የመሬት ቋሚ ማሻሻያ ብቻ አይደለም፡፡ የልማት ተነሺዎች ለፈረሰ ቤታቸው
የሚከፈላቸው የካሳ መጠን የነበረ ቤታቸውን በነበረበት ደረጃ ለመተካት የሚያስችል ሳይሆን በቂ የሚባልና
ቤቱን በአዲስ መልክ ለመገንባት የሚያስችል መሆን ይገበዋል፡፡ ለቤት የሚከፈለው ዝቅተኛ የካሳ መጠን
በከተማው የሚፈቀድ ዝቅተኛውን የቤት ደረጃ ያሟላ ቤት ለመገንባት የሚያስችል መሆን አለበት በሚል
ከዚህ ቀደም የተደነገገው ሃሳብ መቀጠል አለበት፡፡ ከዚህ ሌላ ቤት በገንዘብ የሚለካ ሀብት ከመሆኑ
በተጨማሪ የመጠለያ አገልግሎት (function) ነው፡፡ ስለሆነም በልማት የሚነሳ ወገን በቤቱ ሲያገኝ የነበረው
የመጠለያ አገልግሎት ደረጃ ሊቀንስበት አይገባም፤ የሚከፈለው ካሳ ከነበረበት ስፋትና አደረጃጀት ያነሰ
አገልግሎት የሚሰጥ ቤት የሚያስገነባ መሆን የለበትም፡፡

ለመሬት ካሳ የማይከፈል ቢሆንም ለተሸለ ልማት ለተፈለገው ቦታ እሴት መጨመር የግል ግንባታዎች እና
እንቅስቃሴዎእ የነበራቸውን ድርሻ፣ በጉልበታቸው በአእምሯቸውና በንብረታቸው ተባብረው የፈጠሩት ስለሆነ
ከህገ-መንግስቱ አንጻር ሲታይ የራሳቸው ሀብት ነው፤ ስለሆነም ተፈጥሮ የቆየውን እሴት ለፈጠሩት ወገኖች
ሊሆን ይገባል፡፡ እነዚህ ወገኖች ለቦታው የፈጠሩት እሴት ተጋሪ ሳይሆኑ ሲነሱ ለቦታው እሴት መጨመር
ምንም ድርሻ ያልነበራቸው ወገኖች ተጠቃሚ የሚያደርግ አካሄድ ከፍትሃዊነት አንጻር ሲታይ የሚደገፍ
አይሆንም፡፡ እሴት ለፈጠረው እሴቱን መጋራት የሚያስችል፤ እሴቱን ሳይፈጥር ተጠቃሚ ለሆነው ደግሞ
የመንግስት እሴት ድርሻ መጋርያ ስልት ሊነደፍና ሊተገበር ይገባል፡፡ ከዚህ ሌላ በጋራ የገነቡትን መሰረተ
ልማትና መገልገያ (መንገድ፣ ድልድይ፣ ንጽህና ቤት ወዘተ) የሚፈርስ ከሆነ ወይም ሊገለገሉበት በማይችሉበት

260
ቦታ እንዲሰፍሩ ከተደረገ የልማቱ ግምት ተሰልቶ ማህረሰቡ በሚሰፍርበት አከባቢ የመረጠው የጋራ ልማት
በማቀረብ ሊካካስለት ይገባል፡፡

በመልሶ ልማት ምክንያት በቦታው የነበሩ ወገኖች ላይ የሚደርሰው ቋሚ የገቢ መቋረጥ ለማካካስ
የሚከናወነው ዘላቂ የመልሶ ማቋቋም ሊታሰብበት ይገባል፡፡

ከአዋጅ ቁጥር 47/67 አፈጻፀም ጋር በተያያዘ የተፈጠረው የማካካሻና ኪራይ ቀመስ የሚባሉ ቤቶች ጉዳይ
በቤቱ ያሉ ወገኖች መብት አጠባበቅና ካሳ ክፍያ አሰራር የመልሶ ማልማት ስራውንና የቋሚ ንብረት ምዝገባ
ሂደቱን እያደናቀፈ በመሆኑ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

በመልሶ ማልማት ስራ ምክንያት የሚፈናቀሉ ዜጎች ካሳ መከፈል ያለበት ነባሩ ግንባታ ከመፍረሱ ቀደም ብሎ
ቢቻል ዳግም መፈናቀልን የሚያስቀር እና በአዲስ መልክ መልሰው የሚሰሩትን ግንባታ ማጠናቀቅያ ጊዜን
ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት፡፡ በልማቱ ልዩ ባህሪ ምክንያት በህግ ከተፈቀደው የግንባታ ማጠናቀቅያ
ጊዜ ቀድሞ ማስነሳት የግድ ሲሆን በግንባታ ማጠናቀቅያ ጊዜ ውስጥ ሌላ ቤት/ቦታ ተከራይተው እንዲቆዩ
የኪራይ ወጭና በሽግግር ጊዜ የሚከሰቱ ሌሎች ወጪዎች/የትምህርት ቤት፣ የስራ ቦታ መመላለሻ/ ክፍያ
ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ያም ቢሆን የኪራይ ቤት የሚፈልጉበት ጊዜ ከ6 ወር ማነስ የለበትም፡፡ ይህ ዓይነቱ ክፍያ
መልሶ ማቋቋሚያ ሳይሆን በልማት ምክንያት ለደረሰ ጉዳት ካሳ ሆኖ መያዝ ይኖርበታል፡፡ በአጠቃላይ የመልሶ
ማልማቱ ስራ በቂ ቅደመ ዝግጅት ሊደረግበት ይገባል፡፡ የዘመቻ ስራ መሆን የለበትም፡፡

ተ) መልሶ ማቋቋም ድጋፍ ይዘት


መልሶ ማቋቋም ሲመች የሚሰራ፣ ሳይመች የሚቀር/የሚዘለል፣ አስተዳደሩ እችላሎህ ብሎ ባመነውና
በተቀበለው መጠን የሚወሰን የከተማ አስተዳደሮች መብት ሳይሆን የመንግስት/ የከተማ አስተዳደሮች ግዴታና
የዜጎች ህገ-መንግስታዊ መብት መሆኑ በግልጽ መቀመጥ አለበት፡፡

በተወሰነ ፕሮጀክት ልኬት ብቻ በመመዘን ለህዝብ ጥቅም በቦታው ያሉ ወገኖች በተወሰነ መልኩ ቢጎዳም
ለልማቱ የሚከፈል መስዋዕትነት እንደሆነ ተደርጎ የሚወሰድ ቢሆንም የተወሰነ የሕ/ሰብ ክፍልም ቢሆን
በልማት ምክንያት ተጎጂ መሆን የለበትም ከሚለው አጠቃላይ መርህና ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌ አንጻር
ሲመዘን ተገቢነት የለውም፡፡ የልማታዊ መንግስት ይወግንለታል የሚባለውን ዝቀተኛ ኑሮ የሚገፋ
ማህበረሰብን የሚመለከት በመሆኑ ይህ ክፍል ተጎድቶ ሌላ ህዝብ የሚባል ተጠቃሚ እንደሌለ መታወቅ
አለበት፡፡

የከተማ አስተዳደሮች አቅም የለንም በሚል መነሻ ለልማት ተነሺዎች በቂ ድጋፍ አለማድረግ ተቀባይነት
የለውም፡፡ ቦታው ተፈላጊ ሆኖ አከባቢያዊ መልሶ ማልማትን የሚሻ ከሆነ በአከባቢው ለነበሩና ለአከባቢው
መፈለግ ሚና የነበራቸውን አካላት መደገፍ ቀርቶ ለከተማዋ አጠቃላይ የመሰረተ ልማትና የቤት ግንባታ ገቢ

261
እንደሚገኝበት የሚጠበቅ ቦታ እንደመሆኑ መጠን ወጭው በመሬቱ ገቢ ሊሸፍን የሚችል እንጅ የከተሞችን
ሌላ አቅም የሚሻማ አይደለም፡፡ በእርግጥ የመሬቱ ገቢ የሚገኝበትና ወጭው የሚጠበቅበት ጊዜ ልዮነት
ስላለው ይህን የሚያስታርቅ የፋይናንስ ስርአት መገንባት ያሰፈልጋል፡፡ ዝርዝር የፋይናንስ ስርአት ግንባታ
ሃሳቡ ፋይናንስን በሚመለከተው ርዕስ ተመላክቷል፡፡

ከንብረት ካሳ በተጨማሪ ንብረት ያላፈሩ ነገር ግን ቦታውን ሲለቁም ሆነ ሳይለቁ በመልሶ ማልማቱ ስራ
ምክንያት ያጡትን ጥቅም በነበረበት ሁኔታ ማስቀጠል የሚያስችል ድጋፍ በተገቢው መለየት አለበት፡፡
በልማቱ ምክንያት የሚከሰት የስራና የገቢ መቋረጥ፣ የስራ ቦታ ማጣት፣ የስራ መስክ ለመቀየር ስልጠናና
ድጋፍ ወጭ መዳረግ፤ የመጠለያ ማጣት/አገልግሎት መቀነስ፣ የማህበራዊ ትስስር መቋረጥ፤ ወጭ መጨመር
ወዘተ በሙሉ በመልሶ ማቋቋሙ ፓኬጅ ውስጥ ተገቢ ግምት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

የመልሶ ማቋቋሙ ይዘት ሁሉን አቀፍ ፓኬጅ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የሚደረገው ድጋፍ ለሁሉም አካላት
አንድና ወጥ ሊሆን አይችልም፡፡ እንደ ቦታው፣ እንደ ስራው አይነት፣ እንደ ዜጎቹ ዕድሜ፣ አካላዊ ሁኔታ፣
የትምህርትና የስራ ልምድ፣ እንደ አከባቢው የስራ ምቹነት ሁኔታ የተለያየ መሆን አለበት፡፡ የሁኔታዎቹ
ግምገማ በጥናት ከተከናወነ በኋላ መለወጥ ለሚችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚደረገው ድጋፍ ለመለወጥ
የሚያበቃቸውን ፓኬጅ በጊዜ ገደብ ተወስኖ ለውጣቸው ተመዝኖ የሚሰጥና የሚቋረጥ በመርህ በለውጥ
ምክንያት የተፈጠረ የህይወት መናጋት ለመቋቋምና (shock absorption) ለውጥን የራስ ለማድረግ እንደገና
በተረጋጋ ሁኔታ ህይወትን ለመምራት የሚያስችል ድጋፍ መሆን ሲገባው፤ በእድሜ፣ አካላዊ ሁኔታ ወዘተ
ምክንያት ለውጥን ማስተናገድ፤ መለወጥ ለማይችሉ ደግሞ ድጋፉ ኑሮአቸውን በዘላቂነት መደጎምና ማህበራዊ
ዋስትና ማዕቀፍ ውስጥ ማካተት ይጠይቃል፡፡

በመልሶ ማልማት ምክንያት ሊከሰት የሚችል መጠለያ አልባነትን ለማስቀረት የሚደረገው የመልሶ ማቋቋም
ድጋፍ የልማት ተነሺዎችን ከተከራይነት ወደ ቤት ባለቤትነት የሚያሸጋግረው የተጀመረው ቤት እየገነቡ በግዥ
የማስተላለፍ አካሄድ ለሀብት ክፍፍል፣ ለስራ ትጋትና የቁጠባ ባህል ለማሳደግ ከፍተኛ ድርሻ ያለው በመሆኑ፣
መቀጠል ያለበት ነው፡፡ በዚህ ሂደት የታየው የቅድሚያ ክፍያ ለመፈፀም ባለመቻል እየተከሰተ ያለውን ፈተና
ለመፍታት ልዩ የብድር ሁኔታ ማየት ተገቢ ይሆናል፡፡ በዚህ ሁኔታ የቤት ባለቤት ለመሆን የሚያስችል
የኢኮኖሚ መሰረት የሌላቸው በቀጣይም ተለውጠው ገቢ ማሳደግ ለማይችሉ የልማት ተነሺዎች በአነስተኛ
ኪራይ እና በድጎማ መጠለያ ሊቀርብ የሚችልበት ሁኔታ ማመቻቸት በዚህ ደረጃ የሚፈረጁትን ደግሞ ግልጽ
መስፈርትና ስልት ቀይሶ መለየትና ማስተናገድ ይጠይቃል፡፡

በመልሶ ልማት ክልል ውስጥ ያሉ የቀበሌ ቤት ተከረዮች ሁሉንም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ናቸው ብሎ
ማጠቃለል አይቻልም፡፡ የቀበሌ ቤት ተከራዮች፤ የገቢ አቅማቸው እየታየ ሳይሆን የቀበሌ ቤት ተከራዮች
በመሆናቸው ብቻ ያለ ምንም ልዩነት ሁሉንም ምትክ የቀበሌ ቤት ወይም በከፍተኛ የመንግስት ድጎማ የሚሰሩ

262
የጋራ መኖራያ ቤቶች ቅድሚያ የመግዛት ዕድል መስጠት መደጎም የሌለባቸውም ጭምር እንዲዶጎሙ
እያደረጋቸው ይገኛል፡፡

ስለሆነም በመርህ ደረጃ በቀጣይ የመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች የድጎማ ተጠቃሚዎች ሊሆኑ የሚገባቸው
የቀበሌ ቤት ተከራይ እና የግል ቤት ተከራይ በሚል ግርድፍ መመዘኛ ሳይሆን በጠራ የገቢ አቅም መረጃ ላይ
የተመሰረተ እና መደጎም የሚገባውን ብቻ የሚደጉም መሆን ይገባዋል፡፡ ይሁንና ምንም እንኳን ከመርህ እና
ከፍትሃዊነት አንጻር ሲታይ የቀበሌ ቤት ተከራዮችንም ሆነ የግል ቤት ተከራዮች የገቢ አቅማቸው እየታየ
እኩል መስተናገድ የሚገባቸው ቢሆንም አሁን ካለው ተጨባጭ የከተማ እስተዳድሮች አቅም አኳያ ሲታይ
ሁሉንም የቀበሌ እና የግል ቤት ተከራዮችን ማስተናገድ ስለማይችሉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የግል ተከራዮች
የማስተናገዱ ጉዳይ ደረጃ በደረጃ እና አቅም በፈቀደ መጠን ተግባራዊ እየተደረገ ሊሄድ ይገባል፡፡ ይህ እንዳለ
ሆኖ አብዛኛው የቀበሌም ሆነ የግል ቤት ተከራይ የመኖሪያ ቤት ችግር የሚፈታው በመልሶ ማልማት
አማካኝነት በሚከናወን ድጎማ ሳይሆን አጠቃላይ የቤት አቅርቦት ስርአቱን በማሻሻል በቤት ፍላጎትና በቤት
አቅርቦት መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት ማቀራረብ ሲቻል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

ህጋዊ ለሆኑት አካላት የምትክ ቤት እና መሬት አቅርቦት ስርዓቱ ዜጎች እንደ አቅማቸውና ፍላጎታቸው
እንዲሁም የአስተዳደሩ አቅምና ዝግጁነት ያገናዘበ በፍትሃዊነት የሚመራ መሆን አለበት፡፡ ህጋዊ ሰነድ
አሟልተው የማይገኙ፣ ኢመደበኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች በሂደቱ ከፍተኛ
ጉዳት ሊደርስባቸው የሚችሉ ሲሆን በአንጻሩ ከድጋፉ ፈታኝነት ይልቅ መረጃው ቀድሞ ያልተደራጀና ልየታው
ለኪራይ ሰብሳቢነት ሊጋለጥ የሚችል መሆኑን በመገንዘብ ግልጽና አሳታፊ የልየታ ስልት ተቀይሶ መተግባር
ይኖርበታል፡፡ በቦታው ያሉ ቤቶች ወቅታዊና የተደራጀ መረጃ ለመያዝ የከተማ አቀፍ የአየር በረራ/ሳተላይት
መረጃ ተይዞ ቢቻል በከተማ ደረጃ ካልሆነ ደግሞ በአንድ አከባቢ የመልሶ ማልማት እቅድ ተይዞ ወደ ተግባር
ከመገባቱ በፊት በመዋቅራዊ ፕላን ደራጃ ለመልሶ ማልማት በተወሰኑ ቦታዎች ያሉ አካላት መረጃ ለቀማና
የማደራጀት ስራ መከናወን አለበት፡፡ መረጃው እንደተደራጀ ለማህበረሰቡ ይፋ ሆኖ ስህተቶችን ማስተካከል
ከተቻለ በተጠቃሚ ልየታ ወቅት የሚከሰተውን የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋ ለመቀነስ የሚረዳ ይሆናል፡፡ ያም
ቢሆን በየሂደቱ ማህበረሰቡ እንዲተችበት እና ኦዲት እየተደረገ እርማት እየተወሰደ በትግል ሊመራ ይገባል፡፡

ሁሉንም ተነሽ አንድ ዓይነት አድርጎ የማየት ዝንባሌ ማለትም ሁሉም ቤት ይስራ በሚል ቦታ ማደል
አለበለዚያም ቤት አይሰራም በሚል የቀበሌ ቤት መስጠት፤ ከዚያም ኮንዶሚንየም ምትክ ሲታሰብ አቅም
ላለው ክፍል በራሱ መስራት ሲችል ድጎማ ለማይገባው የማደል አሰራር ውስጥ ስለሚያስገባ ስልቱ ሁሉንም
አማራጮች ክፍት ቢያደርግም ለማን የቱ ምርጫ ሊከበርለት እንደሚገባ ግልጽ መስፈርትና አሰራር መቀየስና
መተግባር ይጠይቃል፡፡ ምትክ ቤት ሲሰጥም መሀል ከተማ ላይ የተገነባ እና የከተማው ዳር ላይ የተሰራ
ኮንዶሚንየም ለሁሉም እኩል ዕድል /ለተነሽና ለቤት አልባ/ በሚል እሳቤ በዕጣ የማከፋፈል አሰራር ማህበራዊ

263
ተስስርን ከማፍረስ በዘለለ በፍትሃዊነቱ ላይም ሰፊ ችግር ስላለው ተነሺዎችን ቅድሚያ በመስጠት በአንድ
ከባቢ ማስፈር ያስፈልጋል፡፡

በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደር የሕብረተሰብ ክፍል ቤት መስራት አይችልም የሚል አባባልም በከተሞቻችን ነባራዊ
ሁኔታና የመረዳዳት ማህበራዊ ካፒታላችን ያገናዘበ ስላልሆነ ይህ የሕብረተሰብ ክፍል ቤት ለመስራትና
ላለመስራት ወሳኝ የሆነው የብድር አቅርቦት፣ የሚሰጠው ጊዜ እና ለቦታ የሚጠየቅ ቅድሚያ ማስያዥያ ብር
አሰራር እንደሆነ ስለታየ፤ ይህ የሕብረተሰብ ክፍል ዓቅም የለውም በሚል ጥቅል ድምዳሜ ቋሚ ሃብት
እንዳያፈራና የቁጠባ ባህሉን እንዳያሳድግ፣ በሀብት ክፍፍል ተጠቃሚ እንዳይሆን የሚገደብ ስለሆነ ዕድሉ
መከፈት አለበት፡፡ በዚህ ሂደት በራሱና በማህበራዊ ካፒታሉ ታግዞ ቤት መገንባት በማይችለው ማህበረሰብ
ጀርባ ኪራይ ሰብሳቢ ደላላ ሀይል እንደይሰለፍ አሰራርና ክትትሉ ጥብቅ መሆን ይኖርበታል፤ ይዞታው
በአጭርና መካከለኛ ጊዜ ውስጥ ተላልፎ ከተገኘ የተላለፈለት ወገን እንደ ቀረጥ ነጻ መብት ሁሉ ለማይገባው
እንዳይተላለፍ የሚደረግበት ስልት ማለትም ይህ መብት ሲተላላፍ ተቀባዩ ወገን የመሬቱን የሊዝ ከፍተኛ
የጨረታ ዋጋና ቅጣት የሚከፍልበትና በዚህ መልኩ ያለን ይዞታ ለመቀራመት የሚደረግ ሩጫን የሚገታ ስልት
መተግበር ይኖርበታል፡፡

የከተማውን የፕላን መስፈርት ደረጃ የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚፈቀደው የጊዜ ገደብ የሀገሪቱን የግንባታ
ዘርፍና አቅርቦት አቅምና ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ የታየው የሊዝ ህጉ የ2 ዓመት ድንጋጌ በዚህ ወቅትም
ተፈጻሚ መሆን አለበት፡፡

በልማት ምክንያት አንድ ኗሪ ከነበረበት ቦታ ከ5 ኪ.ሜ. በራቀ ቦታ እንዲሰፍር ከተደረገ የነበረውን ማህበራዊ
ትስሰር ለማሰቀጠል ባይችል እንኳን አዲስ ለመመስረት ማለትም አዲስ እድር ለመመዝገብና መሰል ሁኔታ
ለሚጠይቀው ማህበራዊ መልሶ መቋቋም፣ ተማሪ ልጁን ወደ ቅርብ ት/ቤት ለማዛወር የሚጠይቀው
ማስመዘገብያ ወጭ፣ ወደ ነባሩ ማህበራዊ መገልገያና ስራ ቦታ ለመድረስ ለሽግግር ጊዜ የሚያስፈልግ
የትራንስፖርት ወጭን ያገናዘበ ድጋፍ መደረግ አለበት፡፡

በመልሶ ማልማት ቦታ ክልል ኖረው በልማቱ ለሚሳተፉ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት፤ ቦታ መመደቡ ተገቢነት
እንደለ ሆኖ ቦታ ምደባው በወጥነት 25 ሜትር ካሬ መሆን የለበትም፡፡ በቦታው የሚጠበቀው የስራ ባህሪና
በቦታው ያለው ወገን ይሰራው የነበረው ቢዝነስ የተቀራረበ ከሆነ አስከ 25ሜትር ካሬ ታሳቢ ተደርጎ በማህበር
ቦታው ሊሰጥ ይችላል፡፡ አልሚው ያከናውነው የነበረው ስራ እንደ ሆቴል፣ ጋራዥ፣ ኢንዱስትሪና መጋዘን
ባህሪ ኖሮት በ25 ሜትር ካሬ ነባሩን ቢዝነስ ማከነወን የማይችል ከሆነ በመነሻ ዋጋ ቦታ የማግኘት
የሚችልበትና ለስራው የሚመጥን ቦታ በፕላን በሚፈቀድ ቦታ በወቅቱ የአከባቢው የጨረታ ዋጋ በቅድሚያ
ቦታ የሚሰጥበት ስልት መታየት አለበት፡ ይህ ማድረግ ካልተቻለ ቢዝነስ እንዲቀይር የሚረዳው ድጋፍ
ሊደረግልት ይገባል፡፡ መብቱ የተጠበቀለት ወገን ለልማት ሙሉ ትብብር ማደረግ አለበት፤ ካልሆነ መብቱ
አስተከበረ ድረስ ልማት እንደያደናቅፍና አንዳያጓትት በህግ ሊገደድ ይገባል፡፡

264
ቸ) አደረጃጀትና አሰራር
የመሬት ፖሊሲው ስለ ተቋማዊ አደረጃጀት፣ ስለ አሰራር ስርአት፣ ስለ ፋይናንስና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ጉዳይ
አቅጣጫ በማስቀመጡ የስራውን ልዩ ባህሪና ክብደት እውቅና እንደሰጠ ሁሉ ይህ ሃሳብ ወደ ተግባር
እንዲቀየር በህግ ማዕቀፍ መደገፍ አለበት፡

የልማታዊ መንግስት በምትከተለው ኮርያ እንደታየው የስራው ውስብስብነትና የአመራር ጉድለት መንግስትና
ህዝብን ሊያለያይ የሚችል ባህሪ ያለው መሆኑን በመገንዘብ፣ እንደዚሁም ስራው ከሚፈልገው የቅንጅት
ደረጃና ለአጠቃላይ ሀገራዊ እድገት ካለው ፋይዳ አንጻር መልሶ ልማቱ የሚመራው በጠቅላይ ሚኒስቴር ደረጃ
በሚመራ ምክርቤት ነው፡፡ በእኛ ሃገርም ቢሆን በተመሳሳይ ደረጃ ሂደቱን የሚከታተል የበላይ አመራር
ምክርቤት ያስፈልገዋል፡፡ ጉዳዩ የሚለማው ሰፈርና ከተማ ጉዳይ ብቻ ተደርጎ ከተተወና በአግባቡ ካልተመራ
የሚያሰከፍለው ዋጋ ከፍተኛ ስለሆነ በተዋረዱ ስትራቴጅክ አመራር ሊሰጠው ይገባል፡፡ ይህ አደረጃጀት
የሂደቱን ፍትሃዊነት ከመፈተሸ ባሻገር ለቅንጅትም ስምረት ተገቢ ነው፡፡ የአልሚዎች ቅንጅት ወሳኝ ነው፡፡ ይህ
ስራ በጊዚያዊ ኮሚቴ መልክ ሊመጣ አይችልም፤ አልሚዎች በሙሉ የፕላን፤ የዲዛይንና የግንባታ ጊዜ መርሃ
ግብር አቅርበው ተቀናጀቶ የሚሰጥ ህጋዊ ፈቃድ መሰረት ብቻ ሊሰሩ ይገባል፡፡

የፖለቲካ ክፍሉ የተቋሙ ስትራቴጅክ አመራር በመስጠትና ሚዛን በመጠበቅ የተቋሙን ጤንነት የሚፈትሽ፣
የሚደግፍ፣ የሚቆጣጠር፣ ተቋሙ ህዝብና ልማትን የሚጎዳ ተግባር እንዳይፈጽም የሚከታተል፣ ህዝቡም
ከመብቱ በላይ በመጠየቅ ልማቱን እንዳያደናቅፍ የሚያደርግ ሚዛናዊ ብይን በሚሰጥበትና የማግባባት ስራ
ማከናወን በሚችልበት ቅርጽ ማደራጀትና መቃኘት አለበት፡፡

የመልሶ ማልማት ስራው ይዘት ሲፈተሽ ስራ ተቆጣጣሪ (regulatory) ከመሆን ይልቅ ኢንቨስትመንት ተደርጎ
ሊወሰድ የሚገባው በመሆኑ ፈጻሚው የታችኛው መዋቅር በበርካታ ሀገራት እንደታየው (በኮርያ የመሬትና
ቤት ልማት ኮርፖሬሽን፤ በፈርንሳይ፣ በጀርመንና በኔዘርላንድ ወዘተ ደግሞ የከተማ ልማት ካምፓኒዎች)
በወጭ ማስመለስ መርህ የሚሰራ እና በኮርፖሬት መልክ የሚደራጅ መሆን አለበት፡፡ ሰፊ ስራ ባላቸው እንደ
አዲስ አበባ፣ ጅማ፣ ደሴና መሰል ከተሞች አደረጃጀቱ በከተማ ደረጃ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ሌሎቹ በተናጠል
በከተማ ደረጃ መዋቅሩን መፍጠር አዋጭ በማይሆንባቸው አነስተኛ ከተሞች ደግሞ ልማቱን የሚሰራ የጋራ
አደረጃጀት በሽርክና ሊያደራጁት ይችላሉ፡፡ የልማት ቴክኒካዊ ስራው በዚህ መልክ ቢደራጅም ስትራቴጅክ
አመራሩና ቁጥጥሩ ግን እንኳንስ በእኛ ሃገር ሁኔታ ለልማት ፍጥነትና ለፍትሃዊ ተጠቃሚነት መሬትን የህዝብና
የመንግሰት በሆነበት ሃገር በሌሎችም ሃገራት በፖለቲካ የበላይ አመራሩ ስር መሆኑ የግድ ነው፡፡

በተቻለ መጠን ስራን ጎን ለጎን ለማስኬድ እንዲቻል ለተነሺዎች ምትክ ቤት ገንቢው፣ ቦታን ለልማት
አስለቃቂውና መሬት አቅራቢው ተቋም እንደ ኮርያ አንድ ተቋም እንዲሆን ማድረግ አዋጭ ያደርገዋል፡፡
ከስራው ስፋት አንፃርም የመሬት ልማትና አቅርቦትም ሆነ የቤት ልማት በተቀናጀ መንገድ ከመምራት አኳያ

265
ገና ጀማሪዎች በመሆናችን ሁለት ተቋማት ከማቋቋም ይልቅ በአንድ ተቋም ተጀምሮ በሂደት የስራው ስፋት
እየታየ የሚወሰን ቢሆን አዋጭ ያደርገዋል፡፡ ከወዲሁ ሁለቱም ተቋማት ለየብቻቸው ማቋቋም ከወጪ አንፃር
እና አሁን የሚታየው ዝቅተኛ የማስፈፀም ዓቅም አንዱ ለሌላው ተቋም ዕንቅፋት መሆኑ አይቀርም፡፡
ለአመራር ቅለት አንድ ተቋም በአንድ የሙያ መስክ እንዲያተኩር በሚል እሳቤ ስራውን ወደ አንድ ለማምጣት
ካልተመረጠ ግን ስራዎቹ እርስ በእርስ የሚፈላለጉና ተደጋጋፊ እንደመሆናቸው መጠን ቅንጅትን ለማምጣት
ቋሚ አገናኝ አደረጃጀትና አሰራር መፈጠር አለበት፡፡ እዚህ ዋናው ጉዳይ የመሬትና የቤት ልማት ኮርፖሬሽኖቹ
በአንድ ተቋም ስር ይደራጁ ወይስ ራሳቸውን የቻሉ ሁለት ተቋማት ሆነው ይቋቋሙ የሚለው ሳይሆን
ተቋማቱ በኢንቨስትመንት ሞዴል እና በወጪ መመለስ መርህ መደራጀት ያለባቸው መሆኑ ነው፡፡

ግንባታ ላይ የሚሳተፉ አልሚዎች በየፊናቸውና በፈለጉ ጊዜ እየገቡ ልማት እንዳይጓተትና አንዱ አንዱን
እንዳይጎዳ የተመረጠው መልሶ ልማት ቦታ ሙሉ በሙሉ በተቋሙ ስር ሆኖ ሌሎቹ ከስር በኮንትራክተርነት
በሰብሊዝ የሚገቡበትና የተሰራውን ፕላን ጊዜውን ጠብቀው አብረው እየገመገሙ የሚሰሩበት ከዚያ ውጭ
ሲሆኑ የሚጠየቁበት፣ ከባሰም ከሂደቱ በተጠያቂነት የሚወጡበት ስርአት መኖር አለበት፡፡

ቦታን ከነባር ግንባታ ማጽዳት ተጀምሮ የሚጠናቀቅበት፣ ቦታው ከነባር ግንበታ ነጻ ከሆነ በኋላ ለምን ያህል
ጊዜ ድረስ ለአልሚ መተላለፍ እንዳለበት በህግ ደረጃ ገደብ መቀመጥ አለበት፡፡ ከተሞች የተጓተተና
የተበጣጠሰ ቦታ የማጽዳት ስራ ሲያከናውኑ፣ ቦታ አፍርሰው ለአልሚ ሳያስተላልፉ ሲቆዩ፣ ለአልሚ ከተላለፈ
በኋላም ህጉን ተከትለው ካላስፈጸሙ ግልጽ ተጠያቂነት ድንጋጌ ሊኖር ይገባል፡፡ በሊዝ ህጉ የተገለጸው
ለአልሚዎች የሚሰጠው የማልማት ጊዜ ገደብም መከበር አለበት፡፡

የአካባቢ መሻሻል ስልትን የተከተለ የመልሶ ማልማት ስራ ሲከናወን ማህበረሰቡ የልማቱ ቀጣይ ባለቤትና
ተንከባካቢ እንዲሆን በልማቱ ሂደትም አቅም በማሰባሰብ የማልማት ደረጃን ለማጎልበት እንዲረዳ በገንዘብ፤
በአይነትና በጉልበት አስተዋጾ እንዲያደርግ የሚያስችልበት አሰራር ማጠናከረ ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን
በመንግስት የሚሰጠው የማጣመሪያ ሀብት አመዳደቡ ፍተሃዊነትና የተመጣጠነ ልማትን የሚያረጋግጥ መሆን
ይኖርበታል፡፡ ዝቅተኛ ገቢ ያለው ማህበረሰብ ለሚኖርበት ሰፈር የሚታቀደው ማጣመሪያ መቶኛ
መካከለኛውና ከፍተኛ ገቢ ያለው ማህበረሰብ ከሚኖርበት ሰፈር የተለየ መሆን አለበት፡፡ የሀብት ምደባ
ምጣኔውም በልማት ወደ ኋላ ለቀረውና ዝቅተኛ ገቢ ያለው ማ/ረሰብ ላለበት ያደላ ቀመር ተዘጋጅቶ
በከተሞች ምክርቤት ተወስኖ ሰፈሮች በሚኖርባቸው ማህበረሰብ የገቢ ሁኔታና የመሰረተ ልማት ደረጃ
ተፈርጀው መከናወን ይኖርበታል፡፡

የአካባቢ ማሻሻል ልማት መከናወን ያለበት ቦታው ቢያንስ በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ ለበለጠ ከፍተኛ መልሶ
ልማት ያልተያዘ፣ ሁኔታው ያን ያህል ጊዜ የማይሰጥና ቅጽበታዊ መሻሻልን የግድ ካለ የላቀው ልማት ሲመጣ
ፈራሽ የማይሆን ተደማሪ ይዘት ያለው ልማት መከናወን አለበት፡፡ ይህ ካልተቻለም የአገልግሎት ጊዜው
አነስተኛ ወይንም ተነስቶ ሌላ ቦታ ላይ አግልግሎት ሊሰጥ በሚችል ቁስ መሰራት አለበት፡፡

266
የአካባቢ ማሻሻል ልማት የሃብት አመራሩ ማህበረሰቡ በመረጠውና አስተዳደሮች የሚቆጣጠሩት ነገር ግን
ለማህበረሰቡ ሪፖርት እያቀረቡ ማህበረሰቡ ያወጣውም ሆነ መንግስት የመደበው ገንዘብ በአግባቡ
ለታለመለት ስራ መዋሉን የሚያይበትና ማህብረሰቡ አመኔታ የሚሰጠው አንዱ ሌላኛውን የሚቆጣጠሩበት
(check and balance) የአሰራር ስርዐት መፍጠር ይጠይቃል፡፡ ለማህበረሰቡ የቀረበ ፖለቲካ መዋቅሩ
አመራር በስራ ውል፣ ክፍያና መሰል ሁኔታ ዝርዝር ትግበራ ውስጥ ሳይገባ ሂደቱን በስትራቴጅክ አመራር
ሰጭነት በተቆጣጣሪነት የህዝቡ ወኪልነቱን በጠበቀ መልኩ የሚሰራ መሆን ይኖርበታል፡፡

የካሳ ንብረት ግመታ ስራ አስነሺ ተቋም/ቦታውን የሚፈልግ ወገን የሚያከናውነው ሲሆን የፈለገውን ያክል
እውነታን ለማነጸባረቅ ቢጥር እንኳን ገለልተኛ ባለመሆኑ በተነሺዎች ዘንድ ያመዘነው ለአስነሺው
እንደሚወግን ሊሰማቸው ስለሚችል የተለየ አደረጃጃትና በገበያ በአማራጭነት ሊቀርብ በሚችልበት ሁኔታ
መደራጀት አለበት፡፡ ለንብረት ግመታው የገበያ ቀራቢነት ደግሞ የገበያው ግልጽነት መዳርና የመረጃ
መጠናከር የግድ ስለሆነ ስርአቱ ሊገነባ ይገባል፡፡

ሁሉም ሂደት በቦታው ያሉ አካላትን በመደገፍ መንፈስ ቢሰራም ከስራው ባህሪ አንጻር ቅሬታ የሚኖራቸው
ወገኖች ስለማይታጡ ይህ መብት መከበርና በስርአት መስተናገድ አለበት፡፡ ቅሬታው በአግባቡና በፍጥነት
ካልተስተናገደ የልማት አደናቃፊነት ይዘት እንደሚኖረው ስለሚታመን በመጀመሪያ ደረጃ ከማህበረሰቡ ጋር
በጋራ በሚደራጅ የልማት አመራር ኮሚቴ ደረጃ ለመፍታት የሚያስችል አሰራር መፈጠር አለበት፡፡ ከዚያ
ሲያልፍ በሊዝ ህጉ በተቀመጠው አግባብ እንደ ከተሞቹ የመልሶ ማልማት ስፋት የራሱ የቦታ ማስለቀቅ
ይግባኝ ሰሚ አደረጃጀት ከመፍጠር ጀምሮ እንደ አቤቱታው ስፋትና ይዘት ቶሎ ለመጨረስ የሚያስችል ጉዳዩ
የሚታይበት ልዩ ችሎት መሰየምና ቀን ወስኖ ማስተናገድ ይገባል፡፡

ኀ) የማክሮ ኢኮኖሚና ፋይናንስ


የግሉ ዘርፍ ማእከል ያደረገ የመልሶ ማልማት ስራ ከተማው ለኢንቨስትመንት ባለው ተፈላጊነት የሚወሰን
መሆኑ የከተሞቹ ተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታ ያሳያል፡፡ ስለሆነም ስለከተማ መልሶ ማልማት ከመታቀዱ በፊት
ከተሞችን ለልማት ሳቢ የሚያደርግ ሁኔታ መፍጠር የግድ ነው፡፡ የከተማ መልሶ ማልማት ለማከናወን በከተማ
ደረጃ የተቀዛቀዘ ኢንቨስትመንት ሁኔታ ካለ ማነቃቃት እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ ከሁሉ በፊት ደግሞ በከተሞቹ
ኢንቨስትመንትን ለማነቃቃት ያላስቻሉ ሁኔታዎችን አጥንቶ መፍታት ተገቢ ይሆናል፡፡

በሀገሪቱ ብሎም በከተሞቹ የኢኮኖሚ ዕድገትና ለውጥ እየቀጠለ ቢሆንም ከተሞችም ሆነ ኗሪዎቹ አሁንም
ከከፋ የኢኮኖሚ ድህነት ያለመላቀቃቸው እንዲሁም አጠቃላይ የፋይናንስ አቅሙ ውሱን መሆኑ ስለሚታወቅ
የሚታቀደው መልሶ ማልማት ስራ አቅምን ታሳቢ ማድረግ የግድ ይለዋል፡፡ እዚያው ሳለ ግን አቅም የለንም
በሚል ታሳቢ ዛሬ የሚሰራው ልማት በአጭር ጊዜ ፈራሽና ዘመን የማይሻገር መሆን የለበትም፡፡ አቅም

267
አላላውስ ብሎ ከፍተኛ ጥራት ያለው ልማት ዛሬ መምጣት ቢያቅት ዛሬ የምሰራው ስራ ነገ ተደማሪ ሆኖ ወደ
ምንፈልገው ጥራት ደረጃ የሚያድግ መሆን ይኖርበታል፡፡

የፋይናንስ /የካፒታል ገበያው ለመልሶ ልማት ተፈላጊ የሆነውን የረጅም ጊዜ ልማት ፋይናንስ ማቅረብ ላይ
ክፍተት እንዳለው በመገንዘብ በመንግስት ደረጃ ለዚህ ስራ ፈንድ መቋቋም አለበት፡፡ ለፈንዱ መነሻ ካፒታል
ከውጭም ሆነ ከሀገር ውስጥ መመደብ ያለበት ሲሆን በሂደት ከመሬትና ከመልሶ ማልማት ገቢ ራሱን በራሱ
እያሳደገ የሚሄድ መሆን ይኖርበታል፡፡ በዚህም ከተሞች መልሶ ማልማትን ለማምጣት በመነሻ ላይ
ያለባቸውን የፋይናንስን እጥረት በመቅረፍ ልማቱ እንዲፈጥን ማገዝ ተገቢ ነው፡፡ ፈንዱ ለከተሞቹ መነሻ
ልማት ፋይናንስ የሚደርስ ብቻ ሳይሆን በአንድ ቦታ መልሶ ማልማት የሚሰሩ የግል አልሚዎች በቦታው
የሚሰሩት ግንባታ እንዲከናወን በሚጠበቅበት ወቅት እንዲሰራና እንዲጠናቀቅ በሚያግዝ መልኩ ተደራሽ
መሆን አለበት፡፡

4.2. የማስፈጸም አቅምና አመለካከት አጀንዳዎች


አንድ ሰነድ በህዝብና ባለ-ድርሻ አካላት ሙሉ ተሳትፎ መዘጋጀቱ ለትግራው ያለው ድርሻ ከፍተኛነት
አንደተጠበቀ ሆኖ ሰነዱ በባለድርሻ አካላቱ ዘንድ ሙሉ እውቅና እንዲተገበር ካስፈለገ ተከታታይ
የማስተዋወቅና ግንዛቤ የማስፋት ስራ መስራት ይጠይቃል፡፡ በነበሩት ህጎች ደረጃ እንኳን ልማትን ማፋጠንና
ጥራትን ማስጠበቅ ያልተቻለው በባለድርሻዎች ዘንድ በሰነዶቹ ላይ ያለው ግንዛቤ አነስተኛነት መሆኑ ሲታይ
በከተማ መልሶ ማልማት ዙሪያ የወጡ ፖሊሲዎች፣ ህጎች፣ መመሪያዎች፣ የፕላን ሰነዶች … በሙሉ
ተከታታይነት ባለው መልኩ ለባድርሻዎች/ማህበረሰቡ የማስጨበጥ ስራ መከናወን አለበት፡፡

ማህበረሰቡ ከህልውናው ጋር የተቆራኘው የከተማ መልሶ ማልማት ጉዳይ ይቅርና በተዘዋዋሪ በሚታይ
ሁኔታም ቢሆን አሳታፊ ልማት አመራር ለቀጣይ ልማት ስኬትና ዘላቂነት፣ ለመንግስትና ህዝብ መቀራረብና
መተማመን አስፈላጊ ጠቀሜታውም ከፍተኛ ነው፡፡ በሂደት ነዋሪው እንዳለው መብትና ፍላጎት ልዩነት በየራሱ
የተናጠል መድረክ ሊፈጠርለት ቢቻልም በመነሻ በመልሶ ማልማት ፕሮጀክት ደረጃ ለውይይት የሚጋበዘው
በቦታው የሚኖር እና የሚሰራ በሙሉ መሆን አለበት፡፡

የውይይቶች ይዘት መልሶ እንዲለማ የተፈለገው አካባቢ ላይ እንዲመጣ የተፈለገው ልማት ላይ በመመስረት
ነዋሪዎች የአማራጩ ስልት ባለቤትና ደጋፊዎች መሆናቸው፣ ካልሆነም አማራጭ የሚሉትን ሃሳብ የሚሰጡበት
ሁኔታ የሚፈጥር መሆን ይኖርበታል፡፡ የልማት ተነሺዎች ግዴታቸውና መብታቸውን ማሳወቅና
የሚስተናገዱበት አማራጭ /መሬት አቅርቦት ወይም ምትክ ቤት መሆኑ/ ማስመረጥ ሂደት መከናወን ያለበት
በልማቱ መተማመን ከተደረሰ በኅላ መሆን አለበት፡፡

በመልሶ ማልማቱ ሂደት ውስጥ ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመዋጋትና የተጠያቂነት ስርአት ለመፍጠር የአፈጻጸም
ሂደቱ በየምዕራፉ ኦዲት መደረግ አለበት፡፡ ለዚህ የኦዲቲንግ ስራ የራሱ አደረጃጀትና አሰራር መገንባት

268
አለበት፡፡ የኦዲት ግኝቱ ለቀጣይ መሰል ስራዎች ትምህርት የሚወሰድበትና የህግ ማዕቀፎች አሰራሮች
ተፈትሸው የሚስተካከሉበት፣ ያጠፋ ወገኖች እንደጥፋታቸው ስፋትና መነሻ ተጠያቂ የሚሆኑበት፣ ጥሩ የሰሩ
ደግሞ ለውጤቱ የሚመሰገኑበት ስርአትና አፈጻጸሙን መሪ የፖሊታካ አደረጃጀትም ሊፈጠርለት ይገባል፡፡

የመልሶ ልማት አስፈጻሚው ተቋም የከተማና የሰፈር ፕላኑን ቀድሞ የሚጥስ ሲጣስ በዝምታ የሚያልፍ
ሳይሆን ፕላን አክባሪና አሰከባሪ መሆን አለበት፡፡

እንደ አጠቃላይ በከተማ ይብስ ደግሞ በመሬት ዘርፍ ውስጥ የአመራር አለመረጋጋት፣ የማሰፈጸም አቅም
ማነስ፣ የመወሰን ብቃት ጉድለት ወዘተ ሰፊ ስለሆነ ስራው በተገቢው እንዲከናወን ከተፈለገ ከፖሊሲና ህግ
ማዕቀፍ ማሟላትና መዋቀር ማስተካከል በበለጠ ባለው ህግና መዋቀር እንኳን የተወሰነ መፈጸም የሚችል
አቅም የመፍጠር ጉዳይ ከሁሉ መቅደም ያለበት ወሳኝ አጀንዳ ነው፡፡ ስለሆነም ሰፊ የአቅም ግንባታና
የአመለካከትና ቅኝት ማስተካከል፣ ቁርጠኝነትና ተነሳሽነት ማጎልበት ስራ የራሱ ፕሮግራም ተቀርጾለት በሰፊው
መሰራት አለበት፡፡

የልማት ተነሺዎች ህዝቡ ሲጠቀም ይጠቀማሉ የሚል የተዛባ አመለካከት ለህዝብ ጥቅም ሲባል የተወሰነ ሰው
ጉዳት ቢደርሰው ነገ በተዘዋዋሪ ሃገሪቱ ስትለማ ተጠቃሚ ነው፣ ተከራዮች ከመንግስት ጋር ያላቸው ተዛምዶ
ኮንትራታዊ እንደሆነ፣ መንግሰት ቤቱን ሲፈልግ ከማስለቀቅ ያለፈ ድጋፍ እንዲያዳደርግ የሚያስገድድ ነገር
ያለመኖር፣ ከዚህ በላይ ምን ሊደረግ ይችላል፣ ከተማው አቅም ስለሌለው ከዚህ በላይ ማድረግ ቢፈልግም
አይችልም እና በቦታው የነበረ የቀበሌ ቤት ተከራይ በዝቅተኛ ቤት ኪራይ ተጠቃሚ የነበረ ስለሆነ ሌላው ቤት
አልባና ከፍተኛ ጉዳት ከነበረበት ጋር ሲነጻጸር ቅድሚያ ሊታይ የሚገባው አይደለም ወዘተ የሚሉትን
አመለካከቶች መሰረታዊ የመርህ ለውጥ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህን የማስተካካል ስራ መሰራት ያለበት ከከፍተኛ
አመራሩ ጀምሮ መሆን ይኖርበታል፡፡

በዚህ ዘርፍ በፈጻሚውና አመራሩ ላይ የሚታየው የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር እንዲሁ ሰፊና
ተከታታይ ትግል የሚጠይቅ ነው፡፡

በልማት ተነሺዎች ውስጥም አጋጣሚውን በመጠቀም ባልተገባ መንገድ ከፍተኛ ተጠቃሚ ለመሆን ወይን
ከመነሳት ጋር ያልተያያዘውን ችግር ለሁሉም መፍቻነት ለመጠቀም የማሰብና የመንቀሳቀስ ዝንባሌ ደግሞ
ጥገኞችን ሁሉ ራሳቸውን እንዲችሉ፤ እሱ የሚገባው ተደርጎለት ሌላ ሰው በቤቱ አስቀምጦ እንዲጠቀም
የመፈለግ ወዘተ/ በአሰራርም ሆነ በትግል በተከታታይነት መስተካከል የሚኖርበት ነው፡፡

በከተማ አሰተዳደሮች የታየው ማፍረስን እንደ ዋና ግብ በመውሰድ የመልሶ ግንባታውን ጉዳይ ትኩረት
አለመስጠትና ተገቢውን ክትትል ያለማድረግ፣ ተነሺው ከቦታው እስኪነሳ የማባበል እና የማይፈጸም ቃል
የመግባት ከተነሳ በኋላ ቃል የገቡትን ያለመፈጸም አካሄድ መታረም አለበት፡፡

269
መሰል ተከታታይና ዘላቂ ልማትን የሚመራ ተቋም በየጊዜው ፈርሶ የሚገነባ፤ በግለሰብ አመራር ላይ
የሚንጠለጠል ሳይሆን የሚማር ተቋም መሆን አለበት (የተረጋጋ፣ አሰራርን ግለሰባዊ ሳይሆን ተቋማዊ
የሚያደርግ፣ አመራርና ባለሙያ ሲቀየር አሰራሩና ሂደቱ የማይናወጥ፣ ተግባራትን በፊት ካከናወነበት
በተደማሪንት እያደገ የሚሄድ፣ መረጃና ልምድ በተቋሙ ውስጥ የሚያቀርብና የሚያሰርጽ፣ የማስተላለፍ
ብቃቱ የተገነባ፣ ከትላንት ዛሬ የተሻለ፣ ከዛሬ ደግሞ ነገ የሚሻል፣ ለለውጥ የሚተጋ፣ ተገልጋዩ ከሚጠብቀው
ልቆ የሚገኝ፣ የማይዋዥቅ መሆን አለበት፡፡ የዚህ ሰራ ፈተናው ከባድና ለኪራይ ሰብሳቢነት የተጋለጠ ከመሆኑ
ጋር በተያያዘ በተቋሙ የሚፈለገው ባለሙያና አመራር ብቃቱ የላቀ፣ ስብዕናው የተገነባ፣ በቀላሉ የማይሸረሸር
ለማድረግ ከሚሰራው የአቅምና አመለካከት ግንባታ ጎን ለጎን በኑሮ ጫና እንዳይንሸራተትና ሳቢ ነገር ግን
ተገቢ የክፍያና ማበረታቻ ስርአት ሊበጅለት ይገባል፡፡ ይህ ሁሉ ተደርጎ መስመሩን ከሳተ ቶሎ መደገፍ፤ አውቆ
የሚገባና የማይድን ከሆነ የሚቆረጥበት፤ ሙሉ ተጠያቂነት ያለበት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ስራው ሁልጊዜ
በምርምር ታግዞ ጥራቱ ተጠብቆ በተደማሪነት የሚያድግና የማይዋዥቅ በተገልጋዩ ዘንድ አመኔታ የሚሰጠውና
ተገማች ባህሪ ያለው መሆን አለበት፡፡

4.3. የትግበራና ቴክኒካዊ ጉዳዮች

 በመልሶ ማልማት ፕላን ዝግጅት ወቅት መታየት ያለበት ሌላው ጉዳይ በመልሶ ማልማት የሚታሰበው
የመሬት አጠቃቀም ጥልቀትና ውጤታማነት የሚመጥን፣ ስበቱ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያመጣ
የመዳረሻ መንገዶች ስፋት ደረጃም መፈተሽና መስተካከል አለበት፡፡ የመኪና ማቆሚያ ቦታ፣ የህዝብ
ማመላለሻዎች ተሳፋሪ መውረጃና መጫኛ ማግለያ ቦታ፤ ትራፊክ ሳቢ ህንጻዎችና አገልግሎቶች መግብያ
መውጫ ከዋናው መስምር የተለየ መሆን እንደሚገባው ማንጸባረቅ ይኖርበታል፡፡
 በአንድና ሁለት ይዞታ በተበተነ ሁኔታ የሚመጣ ልማት ወጥና ትልቅ ልማት እንደሚፈጠረው ስብስብ
መጠን በቶሎ ማምጣት ባለመቻሉ ቢተችም አከባቢን በተመጣጠነ ሁኔታ፣ በቅይጥነት፣ በባለብዙ
ማዕክል አድርጎ ለማልማት ጠቀሜታው የሚያመዝን ነው፡፡ ስለሆነም በፕላን የተገነቡ በአንጻራዊነት
ሰፋ ያለ የይዞታ አደረጃጀት ያላቸው ከተሞች ሰፊ ነባር ግንባታን ጠርጎ ልማትን ግድ የማይልና ይዞታን
ያማከለ መልሶ ማልማት አስቻይና በበጎ የሚታይ ስለሆነ ከማዕከላትና ንዑስ ማእከላት አካባቢ ወጣ
ባሉ ቦታዎች መበረታታት ያለበት ነው፡፡
 በፕላን ደረጃ መንገድ ሲወሰንና የትራንስፖርት መረብ ሃሳብ ሲመላከት የመሬት አጠቃቀሙ ጥልቀትና
ውጤታማነትም ግምት ውስጥ መግባት አለበት፡፡ የሚዘረጋው መሰረተ ልማት አዋጭና ልማት
አፋጣኝ፤ አከባቢውን የሚያነቃቃ እንዲሆን ፈቃጅና መሪ ፕላን መሆን አለበት፡፡ የመሰረተ ልማቶች
ዲዛይን ሲሰራ በአከባቢው ካለው መሬት ገፅታ የሚስማማና በመሰረተ ልማቱ ዳር የሚገኙ ይዞታዎችና
በላያቸው ላይ ያረፈ ግንባታ እንዲቀበር ወይም ከላይ እንዲንጠለጠልና ተገቢውን ፋይዳ እንዳያገኙ
ማድረግ የለበትም

270
 የትልልቅ ልማቶች /ከፍተኛ የግንባታ ቦታ የሚፈልጉ ግዙፍ የማልማት ዓቅም ያላቸው ፕሮጀክቶች/
ለምሳሌ ዩኒቨርሲቲዎች እና ሌሎች መስሪያቤቶች፣ ትልልቅ ሆቴሎች፣ የመንግሰት መስሪያቤቶች፣
ማህራበራዊ ተቋማት ወዘተ/ ያረጁና የደቀቁ እንዲሁም ኢኮኖሚያቸው የደከሙ አካባቢዎች
ለማነቃቃት ፋይዳ እንዲኖራቸው ወደ ውስጥ መሳብ አለባቸው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ዲዛይንና ግንባታቸው
አከባቢን ገዳይ እንዳይሆን፣ ልማቱ አከባቢውን እንዲያነቃቃ በዙሪያቸው ዘጊ አጥር ከማስፈር ሳቢ
ልማት እንዲያከናውኑ አስገዳጅ የዝርዝር ፕላን ሃሳብ መኖር አለበት፡፡
 በፕላን ደረጃ የሚመለከተው የጥግግት ምጣኔ መልሶ ልማት የመሬት አቅርቦት ችግር ማቃለል ስልት
ሆኖ እንዲያገለግል ማገዝ አለበት፡፡
 ውበት እንደ ተመልካቹ የሚለያይና በወጥነት መናገር አዳጋች ይዘት ቢኖረውም በመልሶ ማልማቱ
ሂደት የሚገነቡና የሚቀርቡ አገልግሎቶች የከተሞቹን ተወዳዳሪነት እንዲዳብሩ፣ በፕላን ደረጃ
የህንጻዎቹ እርስ በዕርስ ውህደት ያላቸው፣ ግንባታው ከመሬቱ አቀማመጥ ተቀናጅቶ ተጨማሪ ውበት
የሚያስገኝ፣ ከመንገዱና ከሌሎች መሰረተ ልማቶችና ክፍት ቦታዎች ጋር ያላቸው መስተጋብር ሳቢነት
እንዲኖረው መታሰብ አለበት፡፡ መልሶ ልማቱ ሲጠናቀቅ በከባቢው የሚፈጥረዉን የገጽታ ለዉጥ
በተለያዩ ሞዴሎች በማዘጋጀት ለህዝቡ ተጨባጭ ስዕል የሚፈጥር የፕሮሞሽን ስራ መስራት፡፡
 የመልሶ ማልማቱ ጊዜ የፈጠነ እንዲሆንና ውበቱና ምቹነቱ ከወዲሁ እንዲታይ በወሳኝ ቦታዎች አርባን
ዲዛይን ስራው የሚከናወነው በአንድ ባለሙያ ከሚሆን የባለሙያዎች አማራጭ ዲዛይን ውድድር
ተካሂዶ ማህበረሰቡ በሚመርጠው መልክ እንዲገነባ፤ ከዚያም ገንቢው አካል በቀጣይ የጸደቀውን
አርክቴክቸር ተጠብቆ ወደ ዝርዝር ዲዛይን በቀላሉ መወሰድ የሚችለውና የዝርዝር ዲዛይን ጊዜ
አጥሮለት ወደ ተግባር እንዲገባ በሚረዳ መልኩ መመራት አለበት፡፡
 በመልሶ ልማት ቦታዎች አዲስ አበባ ካሳንችስ ላይ እንደታየው አልሚው የፈለገውን እንዲሰራ መፍቀድ፣
ከመሰረተ ልማቱ አቅምና አደረጃጃት ጋር አለመጣጣምን ስለሚያስከትል በአካባቢው ሊመጡ
የሚገባቸው አገልግሎቶች አይነትና ሊኖራቸው የሚችለው ምጣኔ በፕላን መመራት አለበት፡፡
 በዝርዝር የሰፈር ፕላን ደረጃም ቢሆን የመኪና ማቆሚያ፣ ክፍትና የአረንጓዴ ቦታ ልዩ ትኩረት መስጠት
 የግል ባለሀብቱ የመሬቱን አጠቃቀም ከፍ ለማድረግ ሲል ሙሉ በሙሉ መገንባትን (100% BAR)
ምርጫ ውስጥ እንዳይገባ ተሸንሸነው ለልማት የሚሰጡ ቦታዎች በበቂ የከተማ ዲዛይን መመሪያ
(Urban Design brief) መመራት ይኖርበታል፡፡
 ፖሊሲ አንድ ጊዜ ወጥቶ ለዘላለም የሚቆይ ሳይሆን ዑደቱን ጠብቆ መፈተሸና መከለስ አለበት፡፡
ሰለሆነም ሰለከተማ መልሶ ማልማት የሚወጣው ፖሊሲም ወደ ትግበራ እንዲገባ በመጀመሪያው ሁለት
ዓመትና በመቀጠል ቢያንስ በየሶስት ዓመቱ በጥናት ተደግፎ እየተገመገመና እየዳበረ ለውጥን
እያስተናጋደ ህይወት ኖሮት ሊቀጥል ይገባል፡፡

271
 ፕላኖች ከትግበራ በኋላ ሊገመገሙ ይገባል፡፡ ፕላኖች ሲተገበሩ ያለ ጉድለት የተተገበሩ፤ ከታቀደው
የወጡ፤ ለአፈጻጸሙ ምክንያቶቹ፤ ስራው ምን ፋይዳ አስገኘ፤ ከተቀመጠለት ዓላማ አንጻር ያስገኘው
ፋይዳ፤ ጥቅምና ጉዳት መመዘንና ለቀጠይ ፕላን ስራና ትግበራ ትምህርት ሊወሰድበት ይገባል፡፡
የተከናወኑ መልሶ ልማት ስራዎች ያስገኛቸው ጠቀሜታዎችና የፋይዳዎች ግምገማ ፕሮጀክቶች ምን
ያህል አዋጭ ሆነው መፈጸማቸውን ለመገምገም የሚያስችል የጠራና ተደራሽ የመረጃ ስርአት መገንባት
ተገቢ ነው፡፡
 መፍረስ የሚገባው እንደሚገነባ እርግጠኛ በተሆነበት መጠን መሆን አለበት፡፡ ያነሰም ሆነ የበዛ
የማፍረስ ሰራ ማቀድ ተገቢ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የተሟላ መረጃ ላይ በመመስረት የባለሀብቱና የከተማ
አስተዳደሩን የማልማት አቅም መገመት መቻል ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡
 ሰዎችን ከነበሩበት ቦታ የማስነሳት ስራ ጊዜ ተሰጥቶት መከናወን እንዳለበት እደተጠበቀ ሆኖ ወራቱ
ተማሪዎችን ማስመዝገብ የሚቻልበትንና የህዝቡን በዓላትና እምነት ማገናዘብ አለበት
 አካባቢን መሰረት ያደረገ መልሶ ልማት (Area Based Development) አፈፃፀሙ አመርቂ እንዲሆን
ለዝቅተኛ አፈፃፀም ምክንያት የሆኑትና ከላይ በሌሎች ርዕሶች ከታዩት በተጨማሪ-ፕላኖች ተለማጭ
(flexible) መሆን፣ ለእውነታ መቅረብ፣ መዋቅራዊ ፕላንና የአካባቢ የልማት ዕቅዶች ሲዘጋጁ
የተቀመጡ ማበረታቻዎችና አስገዳጅ ስልቶች በሕግ ማዕቀፍ ማስደገፍና ወደ ተግባር ማስገባት
ያስፈልጋል፡፡
 ቦታ ከጸዳ በኋላ ቢያንስ ወጭውን የሚሸፍን ዋጋ እንዲያስገኝ በሊዝ ሽያጭ መተላለፍ ያለበትን ቦታ
ምጣኔ መወሰን፣ ቦታው ከመተላለፉ በፊት መሰረተ ልማት በሟሟላት ቦታው ሳቢ እንዲሆን
ተደራሽነቱን ማጎልበት ወደ ቦታው የሚያደርስ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት መዘርጋት፣
ኢንቨስትመንት የሚጠራ ልማት ቀድሞ መስራት ያስፈልጋል፡፡
 አንድ ቦታ ለመልሶ ልማት ሲፈለግ ለቦታው ተፈላጊነት እሴት የጨመሩ የእሴት ጭማሪ ድርሻን
ለማስላት፡ ከሊዝ ጨረታ ዋጋ በመነሳት፤ የተለያዩ ቦታዎች ማለትም መሰረተ ልማት የሌለው ባዶ
ቦታ/ሙሉ፣ የግንባታ ከፍታው የተወሰነ/ያልተወሰነ ቦታ፣ ቀድሞ ሳቢ እንቅስቃሴ የሌለበት/የነበረበት
ወዘተ ልዩነት ትንታኔ በመስራት ለእሴት ጭማሪው የእያንዳንዱን እሴት ፈጣሪ ግብአት ድርሻ በመለየት
መስራት ይቻላል፡፡
 በመልሶ ማልማት ምክንያት አንድ ተቋም ቦታው ሲዛወር ከፍተኛ ጉዳት የሚደርስበት፣ አገልግሎት
መስጫና አነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ሲሆን ምርትና ጅምላ ማከፋፈል መጋዘንና መሰል ደረጃ የሚታይ
መካከለኛና ግዙፍ ተቋማት የሚደርስ ጉዳት ጊዚያዊና አዲሱን ቦታ ለደንበኛ ማስተዋወቅያን
የሚመለከት ነው፡፡ ጉዳቱ የሚከፋባቸው አነሰተኛና ጥቃቅን ተቋማት በመሆናቸው በልማት የሚነሳ
ወገን ወይም በልማት የገቢ ማጣትና መቀነስ የሚከሰትበት ወገን ከቦታው ከመነሳቱ በፊት ያገኝ
የነበረውን ገቢ ለማወቅ ደግሞ ለመደበኛ ቢዝነስ በዝቅተኛ ግብር ሲገብርበት የነበረው ዓመታዊ ገቢ

272
ከባለፉት አምስት አመታት የተሻለውን መውሰድ፤ መደበኛ ቢዝነስ ካልሆነ ቢያንስ በዝቅተኛ ዓመታዊ
ግብር የሚጠየቅበት ገቢ/7000/ እንደ ዓመታዊ ገቢ መውሰድ ይቻላል፡፡
 በመልሶ ልማት ምክንያት የሚነሱ ተቋማት ለሚደረግ ድጋፍ ማጥራት ሂደቱን ግልጽነት ለማላበስ
የሚሰሩትን ስራ አይነት መለያው በንግድ መዝገብ ያስመዘገቡት ሲሆን ጥቃቅንና አነስተኛ ለመሆናቸው
ማሳያው ደግሞ ያስመዘገቡት ካፒታልና በአመታዊ ሽያጭነት ያሳወቁት ገቢ መሆን አለበት፡፡ በመልሶ
ማልማት ምክንያት ገቢያቸው የሚቋረጥ ወይንም የሚቀንስ ወገኖች የሚሰጠው ድጋፍ እንደ ተነሺዎቹ
እና መልሶ መስፈሪያ አስቻይ ሁኔታ የሚለያይ ሆኖ በይዘቱ ግን
ሀ/. ነባሩን ስራ መቀጠል ለማይችሉ በሌላ የስራ መስክ መሰማራት የሚያስችላቸው የሙያ ሰልጠና
ለ/ ነባሩን ስራ መቀጠል ለማይችሉ ከስልጠና በተጨማሪ የቴክኒክ ድጋፍ
ሐ/ የስራ ቦታ/በራሳቸው መገንባት ለሚችሉ የሊዝ ህጉ በሚፈቅደው አግባብ በማህበር ተደራጅተው የስራ
ቦታ የሚገነቡበት መሬትና የብድር አቅርቦት ማመቻቸት፤ ወደ ግንባታ ለመግባት አቅም ከሌላቸው
የሚከራይ ንግድ ቤት ካለ ንግድ ቤት በራሳቸው ወደ ስራ ከመግባት የመቀጠር ሁኔታን የሚመርጡ
ከሆነ ለቅጥር ዝግጁ የሚያደርጋቸው ስልጠናና ቦታውን ወስደው የሚያለሙ አካላት በቅድሚያ የቅጥር
እድል እንዲሰጣቸው ማድረግ፤ በምንም መልኩ ወደ ስራ መግባት የሚችሉበት ሁኔታ ከሌለ የማህበራዊ
ዋስትና ድጋፍ ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሰራር መኖር አለበት፡፡
መ/ ነባሩን ስራቸው ለማስፋት ወይም አዲስ ስራ ለመጀመር የሚያሰፈልጋቸውን ካፒታል በብድር
የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ያሰፈልጋል፡፡
 እዚህ ላይ ጥንቃቄ የሚሻ ጉዳይ ስራው የኪራይ እደላ ባህሪ ስላለው ላላስፈላጊ ኪራይ ሰብሳቢነት
ታጋላጭ በመሆኑ ግልጽ አሰራር በየምዕራፉ ሂደቱን በጥብቅ መከታተል እና ኦዲት ማድረግን
ይጠይቃል፡፡ ከዚህ ሌላ የመለወጥ ፍላጎትና ዝግጁነት የሌለው ወገን በድጋፍ ብቻ መለወጥ
አይቻልም፡፡ ስለሆነም ቀደሞ መሰራት ያለበት ስራ ፍላጎትና ዝግጅነቱን መፍጠር፣ ክህሎት አዳብረውም
ቢሆን አዲሱን ስራ አንደሚያሳኩት በሚተማመኑበት ስራ መስክ መደገፍ እንደሚገባ ነው፡፡
 በመልሶ ማልማት አካባቢ የግል ቤት ኖሮአቸው ለመልሶ መስፈሪያ ቦታ ምትክ መሬት የመረጡ ነገር
ግን ግንባታውን ለማከናወን በእድሜና አካላዊ እክል ምክንያት የማይችሉ ወገኖች ካሉና ከማህበረሰቡ
በጋራ መለየትና መተማመን ከተደረሰ ለነዚህ ወገኖች መልሶ ማልማቱን የሚመራው ተቋም ቤታቸውን
በካሳቸው መገንባት አለበት፡፡
 አንድ የመልሶ ማልማት አካባቢ የላቀ ሚና እንደኖረው ለማስቻል የመሰረተ ልማት ስራው በቦታው
ብቻ የታጠረ ሳይሆን የቦታው ተደራሽነት ለማስፋትም መሆን አለበት፡፡ አብረውና ተቀናጅተው
መሰራት ያለባቸው ልማቱን የሚደግፉና ልማቱ የሚፈልጋቸው ሌሎች ስራዎች ሁሉ ጎን ለጎን መሰራት
ይኖርባቸዋል፡፡

273
ማጣቀሻ

AAHDPO (2012), “a paper (Amharic version) presented for discussion related to Addis
Ababa’s 125th anniversary Addis Ababa
Abebe Zeluel and Getachew Birhanu October, 2007 Tenure and Institutional Options for
Intervolve Awassa Urban Renewal project
Abebe Zeluel, (2001), Urban Renewal in Addis Ababa, a case study of Sheraton Addis and
Kasanchis projects, Addis Ababa
Acioly Ji. Claudio, (1999), Institutional and Urban Management Instruments for Inner City
Revitalization/ IHS working paper/
Addis Ababa City Government Finance & Economic Development Bureau (2002): Urban
Development Indicators, Addis Ababa
Ayalew Abey, (2001), Urban Renewal in Addis Ababa Prospects and Constrints for Private
investment, Rotterdam
Bahru Zewde (1991), “A History of Modern Ethiopia Addis Ababa”: Addis Ababa
University Press and Publications Office, 1991).
Berg, Leo van den (1987), Urban Systems in a Dynamic Society, Aldershot: Ashgate
Burgess, R. Carmon, M., and Kolstee, T.(1997), The Challenge of Sustainable Cities,
London
C Schwenkel, (2012), Civilizing the City: Socialist Ruins and Urban Renewal in Central Vietnam
, available at https://anthropology.ucr.edu/people/faculty/.../ Civilizing_the_City.pdf
C Schwenkel, (2013), Ruination and Reconstruction of the Nation in Urban Vietnam, available at
https://anthropology.ucr.edu/people/faculty/.../Schwenkel _CA_2013.pdf
Cernea, M. Michel (1998), Directions in Development, the Economies of Involuntary
Resettlement Qustions and Chllenges, Washington, D.C.
Coch, Chris, (1990), Urban Renewal Theory and Practice, London
Compas consultant (2013): Hawasa City administration, Final LDP and Urban Design Report
Compass AEPED Consultancy Plc: Mudi Aneno LDP & Urban Design Report; October,
2013, Dire Dawa
Compass AEPED Consultancy Plc: Taiwan Police Meret LDP & Urban Design Project;
October, 2013, Dire Dawa
Cushman & Wakefield (2014), Research brief Urban Regeneration turkey, Istanbul.
Available from፡ < https://www.cushmanwakefield.com/knowledge > [2 June 2014]

274
Davidson, Forbes, and Others, (1993) Relocation and Resetelement, a Gouid to Managing
and Planning, Relocation, Rotterdam
Desssie City Administration (2014), Resettlment Action Plan for Segno Gebeya- Salaysh
gravel road sub project. Consultant: Amhara Design and Supervision Works Enterprise
(ADSWE) January 23, 2014January 17, Dessie, Ethiopia
Development Partners: Local Development Plan of Goro; July, 2012 Dire Dawa
Dominique Couret, and Daniel Solomon (2003), “Elements for analyzing Addis-Ababa’s
current urban transformation”: Research Report Ethio-French research program “Addis-
Ababa's urban dynamics environmental approach" ECSC – IRD – EPB. Addis-Ababa, the
1st of April 2003
Elias Yitbarek, Yonas Alemayehu et al (2011) “Performance Evaluation Development Plan
of Addis Ababa 2003 – 2010, Housing Component”
Esayas Ayele (2001) “Policy Impacts on Housing Sector” The Case of Addis Ababa
Ezana Haddis Weldeghebrael, (2011), Factors Influencing Affected Group Participation in
Urban Redevelopment in Addis Ababa: The Case of Senga Tera-Fird Bet I Project,
Urban Management and Development, MSc Thesis
Federal Urban Planning Institute, (2006), Urban Upgrading And Renewal Manual, Addis
Ababa
Google (2016), Map of Hawasa City
Mekonen Wube E. (Year unspecified) “Addis Ababa Integrated Housing Development
Program: A strategy for Urban Poverty Reduction and Sustainable Socio-Economic
Transformation”, a power point presentation
Michael Waibel, (2004), 'The Ancient Quarter of Hanoi – A Reflection of Urban Transition
Processes' Asien Journal, Vol., 92, PP., 30-48, available at www.michael-
waibel.de/Asien92-Beitrag-Hanoi-Waibel-2004.pdf
NUPI: Integrated Development Plan (IDP) of Dire Dawa Administration (2006/7 -
2010/2011); July 2006, Dire Dawa
Ozgur Kormaz (2013), Urban renewal process in turkey-General overview, economic and
social analysis, masters thesis No231. Department of Real Estate and Construction
Management Stockholm. Available from: <https://www.google.com/search?
client=opera&q=•+ Ozgur+Kormaz+ 2013&sourceid=opera&ie=UTF-8&oe=UTF-8> [23
August 2013]
Prime Consult Plc: Legehare Local Development Plan; April 2010 Dire Dawa
Tadesse G.Giorgis (2000) “The Urban Housing Situation in Ethiopia: Problems and
Prospects”: A Paper Discussed at Symposium on "Reviewing Ethiopia's Socioeconomic

275
Performance 1991-99", Organized by Inter Africa Group, 26 – 29, April 2000, Addis
Ababa
Tesfaye Beza, Berhanu Mekonen & Tekle Tilahun (1987) “Historical Development of Addis
Ababa”, revised issue
The World Bank Group, Upgrading Urban Community A Resource Framework, 1999-2001F
UNDP (1999), PPPUE working paper series vol I, NY: World Business Council for
Sustainable Development.
UN-HABITAT (1996), “Global Report on Human Settlements” released in March 1996,
cited in the un-published course handout of Housing development by Demeke Haile,
2008, to Urban planning, Urban Engineering and Urban Management Departments,
IUDS, ECSU, Addis Ababa, Ethiopia.
UN-HABITAT (2011) “Condominium Housing in Ethiopia, the Integrated Housing
Development Programme”
United Nations Human Settlements Programme (UN-HABITAT), Nairobi, 2007 Situation
Analysis of Informal Settlements in Addis Ababa Addis Ababa Slum Upgrading
Programme, Verma, (1990).
Wikipedia encyclopedia (2016)፣ Hawasa city profile

Wondimu Consult: Boren Local Development Plan; April 2010 Dire Dawa
Wondimu Consult: Kezira Local Development Plan, December 2008 Dire Dawa
Wondimu Consult: Megala Local Development Plan; April 2010 Dire Dawa
Wondimu Consult: Sabian Local Development Plan; April 2010 Dire Dawa
World Bank (1990), Operational Directive 4.30 Involuntory Resettlement Overview,
Washington, D.C.
Yewoineshet Meazah H. (2007), “integrated housing development programs for urban
poverty alleviation and sustainable urbanization (the case of Addis Ababa): a paper
presented at international conference 25-28 June 2007, Rotterdam
ORAAMP (Nov - 2002), Addis Ababa Structure Plan Sort Summery, Addis Ababa.
መቐለ ከተማ አስተዳደር (200? ዓ/ም)፣ የዓዲሓ አካቢ ልማት ፕላን ሪፖርት፣ መቐለ ከተማ አገልግሎት
ፅሕፈት ቤት፡፡
መቐለ ከተማ አስተዳደር (2000 ዓ/ም)፣ የላጪ አካባቢ ልማት ፕላን ማጠቃለያ ሪፖርት፣ በማቴዎች አማካሪ
ድርጅት የተጠና፡፡
መቐለ ከተማ አስተዳደር (2000 ዓ/ም)፣ የማይ ሊሓም አካባቢ ልማት ፕላን ሪፖርት፣ በማቴዎች አማካሪ
ድርጅት የተሻሻለ፡፡

276
መቐለ ከተማ አስተዳደር (2000 ዓ/ም)፣ የማይ ዱባ አካቢ ልማት ፕላን ሪፖርት፣ በማቴዎች አማካሪ ድርጅት
የተሻሻለ፡፡
መቐለ ከተማ አስተዳደር (2000 ዓ/ም)፣ የሰራዋት አካባቢ ልማት ፕላን ሪፖርት፣በማቴዎች አማካሪ ድርጅት
የተጠና፡፡
መቐለ ከተማ አስተዳደር (2000 ዓ/ም)፣ የቀበሌ 14 የአካባቢ ልማት ፕላን ሪፖርት፣ በማቴዎች አማካሪ
ድርጅት የተጠና፡፡
መቐለ ከተማ አስተዳደር (2000 ዓ/ም)፣ የአይናለም አካባቢ ልማት ማጠቃለያ ሪፖርት፣ በማቴዎች አማካሪ
ድርጅት የተጠና፡፡
መቐለ ከተማ አስተዳደር (2000 ዓ/ም)፣ የዓዲ ሓቂ አካባ ልማት ፕላን ሪፖርት፣ በማቴዎች አማካሪ ድርጅት
የተጠና፡፡
መቐለ ከተማ አስተዳደር (2000 ዓ/ም)፣ የዓዲ ወለልና ዓዲ ከንፈሮ አካባ ልማት ፕላን ሪፖርት፣ በማቴዎች
አማካሪ ድርጅት የተጠና፡፡
መቐለ ከተማ አስተዳደር (2000 ዓ/ም)፣ የዓዲ ዳዕሮ-ዓዲ ሽምዱሑን አካባቢ ልማት ፕላን ሪፖርት፣
በማቴዎች አማካሪ ድርጅት የተጠና፡፡
መቐለ ከተማ አስተዳደር (2000 ዓ/ም)፣ የእንዳ ማሪያም-ጋብር አካባ ልማት ፕላን ሪፖርት፣ በማቴዎች
አማካሪ ድርጅት የተሻሻለ፡፡
መቐለ ከተማ አስተዳደር (2000 ዓ/ም)፣ የእንዳ ስላሴ አካባቢ ልማት ፕላን ሪፖርት፣ በማቴዎች አማካሪ
ድርጅት የተጠና፡፡
መቐለ ከተማ አስተዳደር (2000 ዓ/ም)፣ የእንዳየሱስ አካባቢ ልማት ፕላን ሪፖርት፣ በማቴዎች አማካሪ
ድርጅት የተሻሻለ፡፡
መቐለ ከተማ አስተዳደር (2000 ዓ/ም)፣ የኲሓ አዲሱ ሰፈር አካባቢ ልማት ፕላን ሪፖርት፣ በማቴዎች
አማካሪ ድርጅት የተጠና፡፡
መቐለ ከተማ አስተዳደር (2000 ዓ/ም)፣ የደጀን 03 አካባቢ ልማት ፕላን ሪፖርት፣ በማቴዎች አማካሪ
ድርጅት የተጠና፡፡
መቐለ ከተማ አስተዳደር (2001 ዓ/ም)፣ የኲሓ ነባሩና የእምባ ፈቓዱ አካቢ ልማት ፕላን ሪፖርት፣ በማቴዎች
አማካሪ ድርጅት የተጠና፡፡
መቐለ ከተማ አስተዳደር (2006 ዓ/ም)፣ የመቐለ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ክለሳ ረቂቅ የጥናት ሰነድ፣ መቐለ
ዩኒቨርሲቲ፡፡
የደሴ ከተማ አስተዳደር (ሰኔ 2002.ዓ.ም) በደሴ ከተማ ካፒያስ በስተሰሜን በኩል የሚገኙ አካባቢዎች ልማት
ፕላን
የኢትዮጵያ ፈደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ የከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ፖሊሲ
የኢትዮጵያ ፈደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ የከተማ ልማት ፖሊሲ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር (2011) የከተማ መልሶ ማልማት ያለበት ደረጃ፤ ያሉ ችግሮች እና ቦታዎችን
ወደመልሶ ግንባታ ለመስገባት የተነደፈ መነሻ እቅድ የያዘ እጭር ሪፖርት ነው።

277
ኢፌዲሪ፡ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትና ለንብረት ካሳ የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን
የወጣው አዋጅ ቁጥር 455/1997
የሀዋሳ ከተማአስተዳደር ኮንስትራክሽን መምሪያ፣ የወጭ ቆጣቢ ቤቶች ዲዛይኖች በ2005፣2006፣2007
የተዘጋጁ
የመሬት ልማት፤ ባንክና ከተማ ማደስ ፕሮጀክት(ጥቅምት 2004)፣ የከተማ ማደስና መሬት ባንክ ስራ
ለተሞክሮ ልውውጥ የተዘጋጀ ሰነድ፣ አዲስ አበባ
የቤት ልማትና የከተማ ማደስ በአዲስ አበባ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር; 2003, የመሬት ልማት፤ ባንክና
ከተማ ማደስ ስራ አመራር እቅጣጫ መሪ ሰነድ(Road map ) (ረቂቅ)
የትግራይ ክክል ስራ አስፈፃሚ ምክርቤት (2003 ዓ/ም)፣ የነባርና ሰነድ አልባ ይዞታዎች ሕጋዊነት ማረጋገጥ
መመሪያ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ስተዳደር 2005, Ykasana meteke bota/byte msetnegedo mmriya 14/2003
የኢትዮጵያ ፈደራላዊ ሪፖብሊክ መንግስትየሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ 1999፣ ደን ቁጥር 135/1999 ለህዝብ
ጥቅም ሲባል በሚለቀቅ መሬት ለሰፈረ ንብረትስለሚከፈል ካሳ የወጣ ደንብ
የኢትዮጵያ ፈደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ መንግስት 1987፣ አዋጅ ቁጥር 1/1987 የኢትዮጵያ ፊደራላዊ
ዲሞክራሲያ ሪፖብሊክ ህገ መንግሰት በስራ ላይ መዋሉን ለማሳወቅ የወጣ አዋጅ
የኢትዮጵያ ፈደራላዊ ዲሞክራሲያዊሪፖብሊክ መንግስትየህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ 1997፣ አዋጅ ቁጥር
455/1997 ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬትይዞታ የሚለቀቅበትንና ለንብረት ካሳ የሚከፈልበትን ሁኔታ
ለመወሰን የወጣ አዋጅ
የኢትዮጵያ ፈደራላዊ ዲሞክራሲያዊሪፖብሊክ መንግስትየህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ 2004 አዋጅ ቁጥር
721/2004 የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት ነጋሪት ጋዜጣ፣የተሻሻለው የደቡብ
ብሔሮች፤ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግስት የከተማ መሬት ሊዝ ደንብ ቁጥር123/2007
የድሬዳዋ አስተዳደር፡ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ እንዲለቀቅ ሲደረግ ለባለይዞታው ካሣ
የሚከፈልበትንና የምትክ ቤትና መሬት አሰጣጥ የአፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 9/2006፣ መጋቢት 2006
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር፡ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ የአፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2005፣ ታህሳስ
2005 ዓ.ም ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር፡ የይዞታ አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 6/2005፣ 2005 ድሬዳዋ

278
አባሪዎች

1፡ በመልሶ ልማት አፈፃፀም ዙሪያ የልማት ተነሺዎች የሰጡት ግምገማ ማጠቃለያ


ዝርዝር አማላካች በጣም ጥሩ ጥሩ መካከለኛ ዝቅተኛ በጣም ዝቅተኛ መልስ ያልሰጡ
ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር %
የቦታ መረጣ ትክክለኛነት 20 15.6 73 57.0 22 17.2 7 5.5 6 4.7 0 0.0
የተነሺዎች ተሳትፎ 18 14.1 62 48.4 33 25.8 9 7.0 6 4.7 0 0.0
ምትክ ቦታ አመዳደብ 15 11.723. 55 43.0 19 14.8 5 3.9 4 3.1 30 23.4
ምትክ ቤት አመዳደብ 22 4
17.2 65 50.8 24 18.8 12 9.4 4 3.1 1 0.8
የካሳ መጠን 1 0.8 2 1.6 28 21.9 14 10.9 83 64.8
ለዝግጅት የተሰጠ ጊዜ 2 1.6 19 14.8 55 43.0 30 23.4 21 16.4 1 0.8
ለተነሺዎች የሚደረግ 1 0.8 7 5.5 35 27.3 56 43.8 27 27.1 2 1.6
ድጋፍ
የብድር አሰጣጥ ድጋፍ 20 15.6 21 16.4 27 21.1 34 26.6 26 20.3

የአገልግሎት መስተንግዶ 3 2.3 27 21.1 59 46.1 22 17.2 17 13.3


መልሶ ልማት ፍጥነትና 27 21.1 46 35.9 37 28.9 17 13.3 1 0.8
ጥራት
2፡ በቦታው እንዲያለሙ እድል የተሰጣቸው ባለሃብቶች በመልሶ ልማት አፈፃፀም ዙሪያ የሰጡት ግምገማ
ዝርዝር አማላካች በጣም ጥሩ ጥሩ መካከለኛ ዝቅተኛ በጣም መልስ ያልሰጡ
ዝቅተኛ
ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር %
የቦታ መረጣ ትክክለኛነት 16 8.0 89 44.5 40 20.0 37 18.5 14 7.0 4 2.0
የተነሺዎች ተሳትፎ 17 8.5 45 22.5 48 22.0 62 31.0 24 12.0 4 2.0
ምትክ ቦታ አመዳደብ 1 0.5 47 23.5 40 20.0 55 27.5 53 26.5 4 2.0
ምትክ ቤት አመዳደብ 8 4.0 47 23.5 42 21.0 47 23.5 48 24.0 8 4.0
የካሳ መጠን 14 7.0 27 13.5 61 30.5 74 37.0 24 12.0
ለዝግጅት የተሰጠ ጊዜ 11 5.5 64 32.0 44 22.0 47 23.5 33 16.5 1 0.5
ለተነሺዎች የሚደረግ 1.5 21.5 23.0 55 27.5 48 24.0 2.5
3 43 46 5
ድጋፍ
የብድር አሰጣጥ ድጋፍ 11 5.5 42 21.0 40 20.0 51 25.5 33 16.5 23 11.5

የአገልግሎት መስተንግዶ 3 1.5 32 16.0 53 26.5 53 26.5 54 27.0 5 2.5


መልሶ ልማት ፍጥነትና 8 4.0 25 12.5 47 23.5 57 28.5 62 31.0 1 0.5
ጥራት
ድምር

279
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

3፡ የመልሶ ልማት ፕሮጅክት አፈፃፀም ዙሪያ የተነሺዎች ግምገማ ማጠቃለያ


የግምገማ ደረጃ ለውጤቱ ዝቅተኛነት/ከፍተኛነት ዋናው ምክንያት
ዝርዝር አማላካች በጣም ጥሩ መካከለኛ ዝቅተኛ በጣም መልስ የህግና የአስፈፃሚ የአስፈፃ ስነ ተነሺው የገንዘብ
ጥሩ ዝቅተኛ ያልሰጡ መመሪያ አቅም ምግባር ራሱ እጥረት
ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር %
የቦታ መረጣ ትክክለኛነት 11 7 66 45 24 16 12 8 28 19 7 5 56 38 76 52 4 3 11 10 1 1
የተነሺዎች ተሳትፎ 15 10 76 52 21 14 18 12 13 9 5 3 12 8 22 15 16 11 86 58 3 2
የምትክ ቦታ/ቤት 8 5 54 37 22 15 25 17 25 17 14 5 27 18 100 68 4 3 - - - -
የካሳ መጠን
አመዳደብ - - 9 6 11 7 50 34 71 48 7 5 17 12 85 57 6 4 1 1 - -
ለዝግጅት የተሰጠ ጊዜ 1 1 10 7 14 10 50 34 70 47 3 2 7 5 116 78 19 13 - - - -
ለተነሺዎች የሚደረግ - - 2 1 12 8 59 40 72 49 3 2 9 6 107 72 23 16 - - - -
ድጋፍ
የብድር አሰጣጥ ድጋፍ - - 3 2 12 8 55 37 71 48 7 5 12 8 111 75 15 10 - - - -
የአገልግሎት መስተንግዶ 2 1 7 5 15 10 48 32 71 48 5 3 4 3 56 38 77 52 11 7 - -
መልሶ ልማት ፍጥነትና 1 1 13 9 33 22 54 37 44 30 3 2 9 6 120 81 11 7 1 1 - -
ጥራት

280
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

4: በጥናቱ የተዳሰሱ ሰዎች መግለጫ /መቐለ/


የመፈናቀል ሁኔታ ዕድሜ በዓመት ፆታ የትምህርት ደረጃ የትዳር ሁኔታ የቤተሰብ ብዛት
መግለጫ በአሃዝ መቶኛ ዝርዝር አሀዝ መቶኛ ዝርዝር አሀዝ መቶኛ ዝርዝር አሀዝ መቶኛ መግለጫ አሀዝ መቶኛ ዝርዝር አሀዝ መቶኛ
የተነሱ 150 37.4 22 - 25 23 5.7 ወንድ 222 55.4 መሃይምነት ያጠፉ 31 7.7 የፈቱ 5 1.2 1-2 34 8.5
በቅርቡ 26 - 30 ሴት 174 43.4 1-8 ክፍል 87 21.7 31.9
100 24.9 34 8.5 ባለትዳር 322 80.5 3-4 128
የሚነሱ
ሳይፈናቀሉ 31 - 40 ያልተገለፀ 5 1.2 9-12 ክፍል 125 31.2 38.4
151 37.7 81 20.2 ያላገቡ 60 15.0 5-6 154
የቀሩ
ድምር 401 100.0 41 - 50 75 18.7 ሰርቲፊኬት 11 2.7 በሞት የተለዩ 8 2.0 7-8 53 13.2
51 - 60 113 28.2 ዲፕሎማ 53 13.2 ያልተገለፀ 5 1.5 9-14 25 6.2
61 - 70 45 11.2 1ኛ ዲግሪና በላይ 18 4.5 ያልተገለፀ 7 1.7
71 - 80 19 4.7
81-90 4 1.0
ያልተገለፀ 7 1.7 ያልተገለፀ 76 20
ድምር ድምር 401 100 ድምር 401 100 ድምር 401 100 ድምር 401 100 ድምር 401 100

281
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

5: ነዋሪዎች ለመልሶ ልማት ዓላማ ያላቸው የድጋፍ ደረጃ /መቐለ/

መልሶ ልማት ዓላማ ድጋፍ ግምገማ የመልሶ ልማት ዓላማ የሚደግፉበት ምክንያት የመልሶ ልማት ዓላማ የሚቃወሙበት ምክንያት
ቀጣይ ያልተነሱ የተፈናቀሉ ቀጣይ ያልተፈናቀሉ የተፈናቀሉ ቀጣይ ያልተፈናቀሉ
የተፈናቀሉ
ተነሺዎች ተነሺዎች ተነሺዎች
ደረጃ አሃዝ % አሃዝ % አሀዝ % ምክንያት አሃዝ % አሃዝ % አሃዝ % ምክንያት አሃዝ % አሃዝ % አሃዝ %
ጠንካራ 103 68.7 81 81.0 109 72.2 ምክንያት ያልገለፁ 13 8.7 5 5.0 7 ምክንያት ያልገለፁ 135 97 97.0 142 94.0
34 22.5 ከተማው ተወዳደሪነት 42 28.0 42 42 25 ምንም ፋይዳ - - - - 0 0.0
መካከለኛ 36 24.0 14 14.0
ስለሌለው
የወደቀው መ/ልማትና 31 20.6 15 15 9 የተወሰኑ ብቻ 2 1.3 1 1.0 5 3.3
እውቀት 1 0.7 አካባቢ ያስነሳል
3 2.0 0 0.0 ተጠቃሚ
የሌላቸው
ስለሚያደርግ
የሚቃወ 5 3.3 የከተማው ውበት 29 19.3 37 37 52 ህዝቡን ይጎዳል 7 4.7 0 0.0 1 0.7
4 2.7 3 0.0
ሙ ያስጠብቃል
መልስ የህዝቡን ኑሮ ያሻሽላል 34 22.7 22 22 10 ተነሺዎች ይጎዳል 0 0.0 0 0.0 2 1.3
4 2.7 2 2 2 1.3
ያልሰጡ
ፕላን የጠበቀ ዕድገት 40 26.7 9 9 20 መልሶ በሚለማ 3 2.0 1 1.0 0 0.0
እንዲኖር አካባቢ ያደክማል
ተነሺዎች የተሻለ 27 18.0 11 11 28 በተነሺዎች መስፈሪያ - - 0 0.0 0 0.0
መኖሪያ ቤትና አካባቢ መዳከምና ስጋት
እንዲኖራቸው የደርጋል ይፈጥራል
መልሶ የለማው አካባቢ 16 10.7 11 11 1 ሌላ ምክንያት 3 2.0 1 1.0 2 1.3
ያነቃቃል
ሌላ ምክንያት 14 9.3 7 7 0 0.0
ድምር 150 100 100 100 151 100 ድምር 150 100 100 100 151 100 ድምር 150 100 100 100 151 100

282
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

6፡ ለችግሮች የተሰጠ የደረጃ ግምገማ /ደሴ ከተማ በመልሶ ልማት ምክንያት የተነሱ/
ለችግሮቹ የተሰጣቸው የግምገማ ክብደት
ምክንያቶች 1 2 3 4 5 ያልተጠቀሰ
ቁጥር % ቁጥር % ቁጥ % ቁጥ % ቁጥ % ቁጥር %
ለአረንጓዴና ክፍት ቦታዎች ትኩረት አለመስጠት 30 20.0 1 ር
0.7 13 ር ር
8.7 29 19.3 75 50.0 2 1.3
ሙሉ ከማፍረስ ውጭ ሌላ አማራጭ አለመኖር 33 22.0 10 6.7 28 18.7 20 13.3 56 37.3 3 2.0
የካሳ መጠን ቤት ለመተካት የማይበቃ መሆኑ 16 10.7 3 2.0 13 8.7 31 20.7 75 50.0 12 8.0
የልማት ተነሺዎች በቦታው እንዲያለሙ ቅድሚያ ዕድል ያለማግኘት 32 21.3 11 7.3 20 13.3 20 13.3 63 42.0 4 2.7
መግባባት ሳይደረስ ማፍረስ 19 12.7 14 9.3 48 32.0 24 16.0 45 30.0 - -
ለመነሳት በቂ የማይሰጥ መሆኑ 42 28.0 14 9.3 20 13.3 32 21.3 38 25.3 4 2.7
ወጥነት የሌለው አፈራረስ 23 15.3 9 6.0 33 22.0 38 25.3 47 31.3 - -
ኪራይ ሰብሳቢት ተግባርና አስተሳሰብ 33 22.0 46 30.7 19 12.7 19 12.7 31 20.7 2 1.3
መልሶ መስፈሪያ ከመጀመሪያ ቦታ መራቅ 17 11.3 3 2.0 24 16.0 26 17.3 80 53.3 - -
ንብረት ሳይወጣ ማፍረስ 91 60.7 16 10.7 8 5.3 8 5.3 25 16.7 2 1.3
መልሶ መስፈሪያ ጫፍ አካባቢ መሆን 30 20.0 9 6.0 25 16.7 20 13.3 65 43.3 1 0.7
ተፈናቃዮች ገቢያቸው ይቀንሳል 31 20.7 - - 8 5.3 33 22.0 74 49.3 4 2.7
ምትክ ቤት በጊዘው አለመሰጠት 33 22.0 20 13.3 37 24.7 25 16.7 32 21.3 3 2.0
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ድጋፍ ያለማድረግ 44 29.3 6 4.0 11 7.3 30 20.0 55 36.7 4 2.7
በመስፈሪያ አካባቢዎች ማሕባራዊ አገልግሎቶች ያለመገንባት 37 24.7 1 0.7 13 8.7 42 28.0 57 38.0 - -
ለመልሶ ማስፈሪያ በፍጥነት መ/ልማት ያለማደረስ 25 16.7 2 1.3 9 6.0 37 24.7 74 49.3 2 1.3
ምትክ ቤት ዋጋ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ግምት ያለማስገባት 15 10.0 2 1.3 10 6.7 32 21.3 61 40.7 30 20.0
ምትክ ቤት በቂ አለመሆን 19 12.7 7 4.7 19 12.7 18 12.0 37 24.7 50 33.3
ቅድሚያ የማልማት ዕድል ያለማግኘት 64 42.7 15 10.0 22 14.7 18 12.0 23 15.3 8 5.3
የፈረሰ ቦታ ተሎ ያለመልማት 31 20.7 1 0.7 9 6.0 31 20.7 77 51.3 1 0.7
ለተጨማሪ ትራንስፖርት ወጪ መጋለጥ 24 16.0 2 1.3 3 4.0 31 20.7 89 59.3 - -
መልሶ በሚለማው አካባቢ ስጋት መፍጠር 30 20.0 17 11.3 30 20.0 12 8.0 60 40.0 1 0.7
በታቀደው ልክ ያለመሰራት 7 4.7 6 4.0 34 22.7 36 24.0 58 38.7 9 6.0
በተዋናዮች መካከል ቅንጅት ያለመኖር 21 14.0 5 3.3 18 12.0 44 29.3 48 32.0 14 9.3
ድምር 747 20.7 220 6.10 474 13.2 656 18.2 1345 37.4 156 4.3

283
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

7፡ለችግሮች የተሰጠ የደረጃ ግምገማ /ደሴ ከተማ በመልሶ ልማት ምክንያት በቅርቡ የሚነሱ
ለችግሮቹ የተሰጣቸው የግምገማ ክብደት
ምክንያቶች 1 2 3 4 5 ያልተጠቀሰ
ቁጥር % ቁጥር % ቁጥ % ቁጥ % ቁጥ % ቁጥር %
ለአረንጓዴና ክፍት ቦታዎች ትኩረት አለመስጠት 1 1 1 1 ር
17 17 ር
26 26 ር
53 53 2 2
ሙሉ ከማፍረስ ውጭ ሌላ አማራጭ አለመኖር 2 2 4 4 5 5 30 30 58 58 1 1
የካሳ መጠን ቤት ለመተካት የማይበቃ መሆኑ 1 1 4 4 24 24 29 29 39 39 3 3
የልማት ተነሺዎች በቦታው እንዲያለሙ ቅድሚያ ዕድል ያለማግኘት 5 5 8 8 7 7 15 15 64 64 1 1
መግባባት ሳይደረስ ማፍረስ 7 7 22 22 26 26 33 33 11 11 1 1
ለመነሳት በቂ የማይሰጥ መሆኑ 3 3 4 4 40 40 33 33 19 19 1 1
ወጥነት የሌለው አፈራረስ 1 1 7 7 34 34 32 32 25 25 1 1
ኪራይ ሰብሳቢት ተግባርና አስተሳሰብ 1 1 4 4 24 24 45 45 25 25 1 1
መልሶ መስፈሪያ ከመጀመሪያ ቦታ መራቅ 4 4 3 3 6 6 11 11 75 75 1 1
ንብረት ሳይወጣ ማፍረስ 13 13 35 35 35 35 5 5 11 11 1 1
መልሶ መስፈሪያ ጫፍ አካባቢ መሆን 4 4 2 2 7 7 8 8 78 78 1 1
ተፈናቃዮች ገቢያቸው ይቀንሳል - - 3 3 6 6 4 4 84 84 3 3
ምትክ ቤት በጊዘው አለመሰጠት 3 3 5 5 24 24 24 24 42 42 2 2
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ድጋፍ ያለማድረግ - - - - 2 2 9 9 87 87 2 2
በመስፈሪያ አካባቢዎች ማሕባራዊ አገልግሎቶች ያለመገንባት 1 1 6 6 7 7 8 8 77 77 1 1
ለመልሶ ማስፈሪያ በፍጥነት መ/ልማት ያለማደረስ 1 1 2 2 5 5 10 10 81 81 1 1
ምትክ ቤት ዋጋ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ግምት ያለማስገባት 1 1 2 2 7 7 20 20 68 68 2 2
ምትክ ቤት በቂ አለመሆን - - 20 20 36 36 14 14 29 29 1 1
ቅድሚያ የማልማት ዕድል ያለማግኘት - - 1 1 23 23 28 28 47 47 1 1
የፈረሰ ቦታ ተሎ ያለመልማት 1 1 4 4 20 20 25 25 49 49 1 1
ለተጨማሪ ትራንስፖርት ወጪ መጋለጥ 3 3 2 2 8 8 8 8 78 78 1 1
መልሶ በሚለማው አካባቢ ስጋት መፍጠር - - 1 1 5 5 13 13 80 80 1 1
በታቀደው ልክ ያለመሰራት - - 6 6 29 29 37 37 27 27 1 1
በተዋናዮች መካከል ቅንጅት ያለመኖር - - 2 2 22 22 36 36 39 39 1 1
ድምር 52 2.2 148 6.3 419 17.5 503 21 1246 51.9 32 1.3

284
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

8፡ ለችግሮች የተሰጠ የደረጃ ግምገማ/ያልተነሱ


ለችግሮቹ የተሰጣቸው የግምገማ ክብደት
ምክንያቶች 1 2 3 4 5 ያልተጠቀሰ
ቁጥር % ቁጥር % ቁጥ % ቁጥ % ቁጥ % ቁጥር %
ለአረንጓዴና ክፍት ቦታዎች ትኩረት አለመስጠት 5 3.3 4 2.6 ር
9 6.0 ር
9 ር 81.3
6.0 122 2 1.3
ሙሉ ከማፍረስ ውጭ ሌላ አማራጭ አለመኖር 13 8.6 12 7.9 12 7.9 27 18.0 76 50.7 1 0.7
የካሳ መጠን ቤት ለመተካት የማይበቃ መሆኑ 3 2.0 8 5.3 10 6.6 15 10.0 112 74.7 3 2.0
የልማት ተነሺዎች በቦታው እንዲያለሙ ቅድሚያ ዕድል 8 5.3 15 9.9 13 8.7 48 32.0
61 40.4 6 4.0
ያለማግኘት
መግባባት ሳይደረስ ማፍረስ 65 43.0 5 3.3 23 15.2 12 7.9 45 30.0 1 0.7
ለመነሳት በቂ የማይሰጥ መሆኑ 81 53.6 15 9.9 16 10.6 9 6.0 29 19.3 1 0.7
ወጥነት የሌለው አፈራረስ 71 47.0 5 3.3 10 6.6 17 11.3 47 31.3 1 0.7
ኪራይ ሰብሳቢት ተግባርና አስተሳሰብ 33 21.9 24 16.0 34 22.5 11 7.3 47 31.3 2 1.3
መልሶ መስፈሪያ ከመጀመሪያ ቦታ መራቅ 7 4.6 4 2.6 10 6.6 15 10.0 114 76.0 1 0.7
ንብረት ሳይወጣ ማፍረስ 104 68.9 12 7.9 6 4.0 7 4.6 21 14.0 1 0.7
መልሶ መስፈሪያ ጫፍ አካባቢ መሆን 7 4.6 5 3.3 12 7.9 19 12.7 105 70. 3 2.0
ተፈናቃዮች ገቢያቸው ይቀንሳል 13 8.6 5 3.3 12 7.9 14 9.3 102 68.0 5 3.3
ምትክ ቤት በጊዘው አለመሰጠት 17 11.3 32 21.3 33 21.9 23 15.3 43 28.7 3 2.0
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ድጋፍ ያለማድረግ 4 2.6 6 4.0 8 5.3 20 13.3 111 74.0 2 1.3
በመስፈሪያ አካባቢዎች ማሕባራዊ አገልግሎቶች ያለመገንባት 9 6.0 15 9.9 10 6.6 26 17.3 90 60.0 1 0.7
ለመልሶ ማስፈሪያ በፍጥነት መ/ልማት ያለማደረስ 5 3.3 1 0.7 8 5.3 22 14.7 114 76.0 1 0.7
ምትክ ቤት ዋጋ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ግምት ያለማስገባት 11 7.3 5 3.3 10 6.6 21 14.0 103 68.7 1 0.7
ምትክ ቤት በቂ አለመሆን 16 11 7 4.6 28 18.5 14 9.3 77 51.3 9 6.0
ምትክ ቤት ሲሰጥ ያላውና የሌለው ያለመለየት /ቅደም ተከተል/ 78 51.7 5 3.3 9 6.0 17 11.3 41 27.3 1 0.7
የፈረሰ ቦታ ተሎ ያለመልማት 8 5.3 3 2.0 7 4.6 13 8.7 119 79.3 1 0.7
ለተጨማሪ ትራንስፖርት ወጪ መጋለጥ 1 0.7 7 4.6 8 5.3 17 11.3 116 77.3 2 1.3
መልሶ በሚለማው አካባቢ ስጋት መፍጠር 6 4.0 6 4.0 12 7.9 20 13.2 106 70.2 1 0.7
በታቀደው ልክ ያለመሰራት 9 6.0 10 6.6 38 25.2 17 11.3 73 48.7 4 2.6
በተዋናዮች መካከል ቅንጅት ያለመኖር 7 4.6 10 6.6 24 15.9 35 23.2 74 49.0 1 0.7
ድምር 634 17.5 214 5.9 364 10.01 413 11.4 1935 53.5 54 1.5

285
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

9፡ በጥናቱ የተዳሰሱ ሰዎች መግለጫ /መቐለ/

የመፈናቀል ሁኔታ ዕድሜ በዓመት ፆታ የትምህርት ደረጃ የትዳር ሁኔታ የቤተሰብ ብዛት
መግለጫ በአሃዝ መቶኛ ዝርዝር አሀዝ መቶኛ ዝርዝር አሀዝ መቶኛ ዝርዝር አሀዝ መቶኛ መግለጫ አሀዝ መቶኛ ዝርዝር አሀዝ መቶኛ
የተፈናቀሉ 271 56.3 22 - 25 13 2.71 ያልተገለፀ 3 0.6 ያልተገለፀ 173 35.97 የፈቱ 4 .8 1-2 36 7.48
ያልተነሱ 210 43.7 26 - 30 64 13.33 ሴት 200 41.6 ያልተማሩ 24 4.99 ባለትዳር 395 82.1 3-4 130 27.03
31 - 40 103 21.46 ወንድ 278 57.8 1-8 ክፍል 151 31.39 ያላገቡ 74 15.4 5-6 154 32.02
41 - 50 111 23.13 9-12 ክፍል 84 17.46 ያልተገለፀ 8 1.5 7-8 101 21.00
51 - 60 76 15.83 ዲፕሎማ 28 5.80 9-12 42 8.73

61 - 70 77 16.04 1 ዲግሪና በላይ 21 4.37 ያልተገለፀ 18 3.74
71 - 80 36 7.50
ድምር 481 100.0 ድምር 481 100.0 ድምር 481 100 ድምር 481 100 ድምር 481 100 ድምር 481 100

286
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

10፡ ለችግሮች የተሰጠ የደረጃ ግምገማ /መቐለ/


ሀ/ በልማት የተነሱ የሰጡት ግምገማ
ለ ችግሮቹ የተሰጣቸው የግምገማ ክብደት
ምክንያቶች 1 2 3 4 5 ያልተጠቀሰ
ቁጥር % ቁጥር % ቁጥ % ቁጥ % ቁጥ % ቁጥር %
ለአረንጓዴና ክፍት ቦታዎች ትኩረት አለመስጠት 2 0.7 20 7.4 26 9.6 ር ር
9 ር
3.3 199 73.4 15 5.5
የካሳ መጠን ቤት ለመተካት የማይበቃ መሆኑ 10 3.7 17 6.3 24 8.9 14 6.3 160 59.0 45 16.5
የልማት ተነሺዎች በቦታው እንዲያለሙ ቅድሚያ ዕድል ያለማግኘት 29 10.7 35 12.9 46 17.0 10 3.7 132 48.7 19 7.0
መግባባት ሳይደረስ ማፍረስ 36 13.3 46 17.0 48 17.7 53 19.6 84 31.0 4 1.5
ለመነሳት በቂ የማይሰጥ መሆኑ 38 14.0 76 28.0 72 36.6 41 15.1 33 12.2 11 4.1
ወጥነት የሌለው አፈራረስ 43 15.9 42 15.5 45 16.6 22 8.1 112 41.3 7 2.6
ኪራይ ሰብሳቢት ተግባርና አስተሳሰብ 54 19.9 13 4.8 16 5.9 9 3.9 130 48.0 49 18.1
መልሶ መስፈሪያ ከመጀመሪያ ቦታ መራቅ 71 26.2 27 10.0 22 8.1 8 3.0 127 46.9 16 5.9
ንብረት ሳይወጣ ማፍረስ 68 25.1 86 31.7 67 24.7 16 5.9 28 10.3 6 2.2
መልሶ መስፈሪያ ጫፍ አካባቢ መሆን 76 28.0 24 8.9 63 23.2 12 4.4 74 27.3 22 8.1
ተፈናቃዮች ገቢያቸው ይቀንሳል 24 8.9 38 14.0 21 7.7 21 7.7 147 54.2 19 7.0
ምትክ ቤት በጊዘው አለመሰጠት 74 27.3 30 11.1 21 7.7 5 1.8 122 45.0 19 7.0
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ድጋፍ ያለማድረግ 11 4.1 24 8.9 10 3.7 2 0.7 172 63.5 52 19.2
በመስፈሪያ አካባቢዎች ማሕባራዊ አገልግሎቶች ያለመገንባት 22 8.1 39 14.4 40 14.8 16 5.9 136 50.2 18 6.6
ለመልሶ ማስፈሪያ በፍጥነት መ/ልማት ያለማደረስ 6 2.2 22 8.1 47 17.3 11 4.1 168 62.0 17 6.3
የፈረሰ ቦታ ተሎ ያለመልማት 32 11.8 39 14.4 26 9.6 24 8.9 140 51.7 10 3.7
ለተጨማሪ ትራንስፖርት ወጪ መጋለጥ 41 15.1 38 14.0 26 9.6 4 1.5 143 52.8 19 70
መልሶ በሚለማው አካባቢ ስጋት መፍጠር 30 111 46 17.0 42 15.5 5 1.8 137 50.6 11 4.1
በታቀደው ልክ ያለመሰራት 31 11.4 21 7.7 7 2.6 5 1.8 128 47.2 79 29.2
በተዋናዮች መካከል ቅንጅት ያለመኖር 33 12.2 36 13.3 36 13.3 12 4.4 124 45.8 30 11.1
ድምር 731 13.5 719 13.3 705 13.0 299 5.5 2496 46.1 466 8.6

287
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

ለ/ ለችግሮች የተሰጠ የደረጃ ግምገማ


ለችግሮቹ የተሰጣቸው የግምገማ ክብደት
1 2 3 4 5 ያልተጠቀሰ
ምክንያቶች
ቁጥር % ቁጥር % ቁጥ % ቁጥ % ቁጥ % ቁጥር %
ለአረንጓዴና ክፍት ቦታዎች ትኩረት አለመስጠት 1 ር ር ር
0.5 50 23.8 35 16.7 20 9.5 96 45.7 8 3.8
የካሳ መጠን ቤት ለመተካት የማይበቃ መሆኑ 3 1.4 11 5.2 31 14.8 27 12.9 77 36.7 61 29.0
የልማት ተነሺዎች በቦታው እንዲያለሙ ቅድሚያ ዕድል ያለማግኘት 23 11.0 25 11.9 47 22.4 34 16.2 73 34.8 8 3.8
መግባባት ሳይደረስ ማፍረስ 17 8.1 38 18.1 19 9.0 47 22.4 88 41.9 1 0.5
ለመነሳት በቂ የማይሰጥ መሆኑ 56 26.7 32 15.2 48 22.9 51 24.3 19 9.0 4 1.9
ወጥነት የሌለው አፈራረስ 36 17.1 47 22.4 36 17.1 71 33.8 18 8.6 2 1.0
ኪራይ ሰብሳቢት ተግባርና አስተሳሰብ 70 33.3 33 15.7 20 9.5 19 9.0 41 19.5 27 12.9
መልሶ መስፈሪያ ከመጀመሪያ ቦታ መራቅ 38 18.1 31 14.8 22 10.5 22 10.5 73 34.8 24 11.4
ንብረት ሳይወጣ ማፍረስ 72 34.3 56 26.7 56 26.7 9 4.3 10 4.8 7 3.3
መልሶ መስፈሪያ ጫፍ አካባቢ መሆን 57 27.1 26 12.4 20 9.5 17 8.1 60 28.6 30 14.3
ተፈናቃዮች ገቢያቸው ይቀንሳል 5 2.4 45 21.4 20 9.5 30 14.3 96 45.7 14 6.7
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ድጋፍ ያለማድረግ 2 1.0 27 12.9 26 12.4 59 28.1 68 32.4 28 13.3
በመስፈሪያ አካባቢዎች ማሕባራዊ አገልግሎቶች ያለመገንባት 12 5.7 44 21.0 38 18.1 27 12.9 69 32.9 20 9.5
ለመልሶ ማስፈሪያ በፍጥነት መ/ልማት ያለማደረስ 8 3.8 36 17.1 43 20.5 62 29.5 52 24.8 9 4.3
የፈረሰ ቦታ ተሎ ያለመልማት 26 12.4 53 25.2 25 11.9 34 16.2 62 29.5 10 4.8
ለተጨማሪ ትራንስፖርት ወጪ መጋለጥ 36 17.1 36 17.1 26 12.4 20 9.5 72 34.3 20 9.5
መልሶ በሚለማው አካባቢ ስጋት መፍጠር 26 12.4 46 21.9 46 21.9 52 24.8 35 16.7 5 2.4
በታቀደው ልክ ያለመሰራት 32 15.2 48 22.9 21 10.0 37 17.6 34 16.2 38 18.1
በተዋናዮች መካከል ቅንጅት ያለመኖር 37 17.6 53 25.2 26 12.4 24 11.4 55 26.2 15 7.1
ድምር 557 14 737 18.5 605 15.2 662 16.6 1098 27.5 331 8.3

288
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

11፡ የመጠይቅ ተሳታፊዎች አጠቃላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎች /ሀዋሳ/


መግለጫ ዝርዝር ብዛት ፐርሰንት
የእድሜ ሁኔታ በ 20 እና 30 መካከል 159 46.9
በ 40 እና 55 መካከል 141 41.59
በ 56 እና 70 መካከል 38 11.21
በ 71 እና 80 መካከል 1 2.95
የት/ት ደረጃ ያልተማሩ 38 11.34
1ኛ ደረጃ 117 34.93
2ኛ ደረጃ 97 28.96
ዲፕሎማ 62 18.51
ዲግሪ ያላቻው 21 6.12
መልስ ያልሰጡ 8 2.33
የተጠያቂዎች የመንግስት 66 19.24
የስራ ሁኔታ የግል ስራ 103 30%
ንግድ 67 20%
የቀን ስራ 6 2%
ጡረተኛ 8 2%
ስራ አጥ 87 25%
መልስ ያልሰጡ 6 2%
የጋብቻ ሁኔታ ያገቡ 292 85.13
ያላገቡ 35 10%
መበለት 2 1%
ፈት 2 1%
መልስ ያልሰጡ 12 3%
የቤተሰብ ብዛት ከ 1 እስከ 5 አባላት ያሉበት 133 38.77
ከ 5 እስከ 10 አባላት ያሉበት 175 51.02
ከ 10 የቤተሰብ አባላት በላይ ያሉት 9 2.62
መልስ ያልሰጡ 26 7.58

289
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

12፡ ከመላሾች መካከል የከተማ ማደሱን ዓላማ በተመለከተ ተጠይቀው የሰጡት ግምገማ ማጠቃለያ /ሀዋሳ/

አጠቃላይ አስተያየት
የግምገማ ዓይነት ብዛት ፐርሰንት
ሀ የከተማ ማደሱ ዓላማ በጣም የሚያበረታታ ነው ያሉ 190 55.39
ለ የከተማ ማደሱ ዓላማ የሚያበረታታ ነው ያሉ 116 33.82
ሐ የከተማ ማደሱ ዓላማ የሚደገፍ አይደለም ያሉ 18 5.25
መ ስለከተማ ማደሱ ዓላማ አላውቅም ያሉ 5 1.46
ሠ መልስ ያልሰጡ 14 4.08
ድምር 343

የከተማ ማደሱን ዓላማ የሚደግፉ የሰጡት ምክንያት ማጠቃለያ


የግምገማ ዓይነት ብዛት ፐርሰንት
ሀ የከተማ ማደሱ የከተማዋን ተወዳዳሪነት ስለሚያስጠብቅ ያሉ 194 56.55
ለ የከተማ ማደሱ የወደቀውን መሰረተልማትና ኣካባቢውን 160 46.65
ስለሚያስጠብቅ
ሐ የከተማ ማደሱ ለከተማው ውበት ስለሚያጎናጽፍ 152 44.32
መ የከተማ ማደሱ ለኅዝቡ ኑሮ መሻሻል ስለሚረዳ 156 45.48
ሠ በፕላን ያልተሰራውን ፕላን ስለሚያስጠብቅ 129 37.61
ረ ለተነሺዎች ከነበሩበት የተሸለ ቤጽና ቦታ ስለሚያስገኝ 91 26.53
ሰ በመልሶ ማልማቱ ያካባቢ መነቃቃትና የተሻለ ኑሮ ተስፋ 79 23.03
ስለሚያመጣ
ሸ በተነሺዎች መስፈሪያ አካባቢዎች መነቃቃትና ተስፋ ስለሚያመጣ 19 5.54
ድምር 343

የከተማ ማደሱን ዓላማ የማይደግፉ የሰጡት ምክንያት ማጠቃለያ


የግምገማ ዓይነት ብዛት

ሀ የከተማ ማደሱ ምንም ለውጥ ስለማያመጣ 2

ለ የከተማ ማደሱ የተወሰነ ክፍልን ብቻ ተጠቃሚ ስለሚያደርግ 4

ሐ የከተማ ማደሱ ህዝቡን ስለሚጎዳ 1

መ የከተማ ማደሱ ተነሺዎችን ስለሚጎዳ 7

ሠ የከተማ ማደሱ በመልሶ ማልማቱ ዙሪያ አካባቢዎች መዳከምና ስጋት 2


ስለሚያመጣ
ረ በተነሺዎች አካባቢዎች መዳከምና ስጋት ስለሚያመጣ 7

ድምር

290
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

13፡ የመልሶ ማልማቱ ሂደት ግምገማ /ሀዋሳ/


የመልሶ ማልማት ቦታ መረጣ ግምገማ
ግምገማ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
በጣም ጥሩ ነው 42 12.28
ጥሩ ነው 138 40.35 52.63 ፐርሰንት
መካከለኛ ነው 60 17.54
አርኪ አይደለም 2 0.58 29.82 ፐርሰንት
ዝቅተኛ ነው 53 15.50
በጣም ዝቅተኛ 47 13.74
ድምር 342

የመልሶ ማልማት የተነሽዎች ተሳትፎ ግምገማ


ግምገማ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
በጣም ጥሩ ነው 9 2.62 18.36 ፐርሰንት
ጥሩ ነው 54 15.74
መካከለኛ ነው 82 23.91 25.08 ፐርሰንት
አርኪ አይደለም 4 1.17
ዝቅተኛ ነው 128 37.32 56.56 ፐርሰንት
በጣም ዝቅተኛ 66 19.24
ድምር 343

የምትክ ቦታ አሰጣጥ ግምገማ


ግምገማ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
በጣም ጥሩ ነው 7 2.04 14.58 ፐርሰንት
ጥሩ ነው 43 12.54
መካከለኛ ነው 2 0.58 44.89 ፐርሰንት
አርኪ አይደለም 152 44.31
ዝቅተኛ ነው 69 20.12 40.53 ፐርሰንት
በጣም ዝቅተኛ 70 20.41
ድምር 343

የምትክ ቤት አሰጣጥ ግምገማ


ግምገማ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
በጣም ጥሩ ነው 5 1.46 17.49 ፐርሰንት
ጥሩ ነው 55 16.03
መካከለኛ ነው 131 38.19 38.77 ፐርሰንት
አርኪ አይደለም 2 0.58
ዝቅተኛ ነው 73 21.28 43.73 ፐርሰንት
በጣም ዝቅተኛ 77 22.45
ድምር

291
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

ለተነሺዎች የካሳ መጠን ግምገማ


ግምገማ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
በጣም ጥሩ ነው 0 0 0.87 ፐርሰንት
ጥሩ ነው 3 0.87
መካከለኛ ነው 15 4.37 56.27 ፐርሰንት
አርኪ አይደለም 178 51.90
ዝቅተኛ ነው 75 21.87 42.86 ፐርሰንት
በጣም ዝቅተኛ 72 20.99
ድምር 343

ለተነሺዎች የሚሰጥ የመነሻ ጊዜ ግምገማ


ግምገማ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
በጣም ጥሩ ነው 64 18.66 30.90 ፐርሰንት
ጥሩ ነው 42 12.24
መካከለኛ ነው 86 25.07 25.94 ፐርሰንት
አርኪ አይደለም 3 0.87
ዝቅተኛ ነው 98 28.57 43.15 ፐርሰንት
በጣም ዝቅተኛ 50 14.58
ድምር 343

ለተነሺዎች የሚሰጥ ድጋፍ ግምገማ


ግምገማ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
በጣም ጥሩ ነው 8 2.33 21.57 ፐርሰንት
ጥሩ ነው 66 19.24
መካከለኛ ነው 110 32.07 34.40 ፐርሰንት
አርኪ አይደለም 8 2.33
ዝቅተኛ ነው 79 23.03 44.02 ፐርሰንት
በጣም ዝቅተኛ 72 20.99
ድምር 343

ለተነሺዎች የሚሰጥ የጊዜ ብድር ድጋፍ ግምገማ


ግምገማ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
በጣም ጥሩ ነው 1 0.29 14.58 ፐርሰንት
ጥሩ ነው 49 14.29
መካከለኛ ነው 39 11.37 15.74 ፐርሰንት
አርኪ አይደለም 15 4.37
ዝቅተኛ ነው 136 39.65 69.68 ፐርሰንት
በጣም ዝቅተኛ 103 30.03
ድምር 343

292
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

የቅሬታ አቀባበል ግምገማ


ግምገማ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
በጣም ጥሩ ነው 8 2.33 33.23 ፐርሰንት
ጥሩ ነው 106 30.90
መካከለኛ ነው 138 39.94 41.69 ፐርሰንት
አርኪ አይደለም 6 1.75
ዝቅተኛ ነው 48 13.99 24.78 ፐርሰንት
በጣም ዝቅተኛ 37 10.79
ድምር 343

የመልሶ ግንባታው ፍጥነትና ጥራት ግምገማ


ግምገማ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
በጣም ጥሩ ነው 6 1.75 17.20 ፐርሰንት
ጥሩ ነው 53 15.45
መካከለኛ ነው 101 29.45 31.20 ፐርሰንት
አርኪ አይደለም 6 1.75
ዝቅተኛ ነው 67 19.53 51.60 ፐርሰንት
በጣም ዝቅተኛ 110 32.07
ድምር 343

ለአረንጓዴና የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ ትኩረት አለማድረግ


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 114 33.53
4 43 12.65 46.18 ፐርሰንት
3 107 31.48
2 68 20.00
1 8 2.35
ድምር 340

ከሙሉ ማፍረስ ውጭ ሌላ አማራጭ አለመከተል


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 11 3.23
4 24 7.04 10.27 ፐርሰንት
3 116 34.02
2 126 36.95
1 63 18.48 55.43 ፐርሰንት
ድምር 341

293
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

ለተነሺዎች የማልማት ቅድሚያ አለመስጠት


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 51 15
4 51 15 30 ፐርሰንት
3 140 41.18
2 70 20.59
1 28 8.24 28.83 ፐርሰንት
ድምር 340

ህዝብን ሳያሳምኑ ወደ ማፍረስ መግባት


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 18 5.28
4 43 12.61 17.89 ፐርሰንት
3 59 17.30
2 64 18.77 64.81 ፐርሰንት
1 157 46.04
ድምር 341

አፈራረሱ ወጥ አለመሆን
ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 22 6.51
4 56 16.57 23.08 ፐርሰንት
3 77 22.78
2 87 25.74
1 96 28.40 54.14 ፐርሰንት
ድምር 338

በመልሶ ማልማት የሙስና መኖር


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 51 15.00
4 50 14.71 29.71 ፐርሰንት
3 88 25.88
2 79 23.24
1 72 21.18 44.42 ፐርሰንት
ድምር 340

ህዝቡን ከሚኖርበት ሰፈር አርቆ ማስፈር


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 98 28.82
4 71 20.88 49.7 ፐርሰንት
3 94 27.65
2 49 14.41
1 27 7.94
ድምር 340

294
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

ንብረት ሳይወጣ ማፍረስ


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 121 35.69
4 31 9.14
3 27 7.96
2 79 23.30
1 181 53.39
ድምር 339

የተሺዎች ገቢ ማጣት ወይም መቀነስ


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 116 34.12
4 78 22.94 57.06 ፐርሰንት
3 111 32.65
2 37 10.88
1 1 0.29
ድምር 340

ምትክ ቤትና ቦታ ቶሎ አለማስረከብ


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 31 9.20
4 75 22.26
3 101 29.97
2 77 22.85
1 53 15.73
ድምር 377

ለአቅመ ደካሞች ሲነሱ ልዩ ድጋፍ አለማድረግ


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 108 31.76
4 42 12.35
3 124 36.47
2 39 11.47
1 26 7.65
ድምር 340

በመስፈሪያ ቦታ ማህበራዊ ተቋማት አብረው አለመገንባት


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 128 37.65
4 145 42.65 80.3 ፐርሰንት
3 49 14.41
2 12 3.53
1 6 1.76
ድምር 340

295
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

በመስፈሪያ ቦታ የመሰረተ ልማት በቶሎ አለማሟላት


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 164 48.24
4 103 30.29 78.53 ፐርሰንት !!!
3 54 15.88
2 13 3.82
1 6 1.76
ድምር 340

የምትክ ቤቱ ዋጋ የዝቅተኛውን ህ/ሰብ አቅም ያገዘበ አለመሆን


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 64 18.93
57.39 ፐርሰንት
4 130 38.46
3 69 20.41
2 19 5.62
1 56 16.57
ድምር 338

የምትክ ቤቶች ጥበት


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 128 37.65
4 65 19.12 56.77 ፐርሰንት
3 75 22.06
2 52 15.29
1 20 5.88
ድምር 340

ለተነሺዎች ምትክ ቤት ሲሰጥ ቤት ያለውንና የሌለውን አለመለየት


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 54 15.88
4 70 20.59 36.47 ፐርሰንት
3 123 36.18
2 74 21.76
1 19 5.59
ድምር 340

ከፈረሰ በኋላ ቶሎ አለማልማት


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 58 17.06
4 108 31.76 48.82 ፐርሰንት
3 115 33.82
2 35 10.29
1 24 7.06
ድምር 340

296
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

ለተሺዎች የትራንስፖርት ወጭ መጨመር (በአዲሱ ሰፈር)


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 140 41.18
4 37 10.88 53.06 ፐርሰንት
3 67 19.71
2 75 22.06
1 21 6.18
ድምር 340

በመልሶ ማልማቱ ዙሪያ ስጋት መፍጠር


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 76 22.35
4 76 22.35 44.7 ፐርሰንት
3 122 35.88
2 52 15.29 55.3 ፐርሰንት
1 13 3.82
ድምር 340

በታቀደው መጠን አለመሰራት


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 93 27.60
4 78 23.15 50.75 ፐርሰንት
3 125 37.09
2 24 7.12
1 17 5.94
ድምር 337

የመልሶ ማልማቱ የቅንጅት ችግር ያለበት መሆን


ለችግሩ የተሰጠ የክብደት ነጥብ ብዛት ፐርሰንት የክብደት ማጠቃለያ
5 174 51.63
4 71 21.07 72.70 ፐርሰንት!!
3 71 21.07
2 10 2.97
1 11 3.26
ድምር 337

297
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

14፡ ነዋሪዎች ለመልሶ ልማት ዓላማ ያላቸው ድጋፍ /ጅማ ከተማ/


የሚደግፉበት ምክንያት የተቃውሞ ምክንያት
መልስ ቁጥር % ምክንያት ቁጥር % ምክንያት ቁጥር %
መልስ ያልሰጡ 10 4.9 ያልገለፁ 28 13.7 ለውጥ ስለማያመጣ 2 4.7
የከተማዋ ተወዳደሪነት 34 16.6 የተወሰኑ ቡድኖች ብቻ 1 2.3
ጠንካራ ድጋፍ ያላቸው 117 57.1
ስለሚያስጠብቅ ስለሚጠቀሙ
የወደቀውን መሰረተ ልማትና 54 26.3 ነዋሪዎችን ስለሚጎዳ 2 4.7
መካከለኛ ድጋፍ ያላቸው 33 16.1
አካባቢ ስለሚያሻሽል
የማይደግፉ 40 19.5 ከተማው ውበት ያስጠብቃል 31 15.1 ተነሺዎች ስለሚጎዳ 22 51.2
የነዋሪዎች ኑሮ ስለሚያሻሽል 9 4.4 መልሶ ማልማት በሚካሄድባት 11 25.6
ዕውቀት የለንም ያሉ 5 2.4
አካባቢ ስጋት ይፈጥራል
በፕላን የሚመራ ዕድገት እንዲኖር 1 0.5 መልሶ ማስፈሪያ አካባቢ 5 11.6
ያደርጋል ስለሚያዳክም
ተነሺዎች የተሻሉ ቤትና አካባቢ 5 2.4
እንዲኖራቸው ያደርጋል
አካባቢዎች የሞቀ ኢኖኖሚያዊ 1 0.5
እንቅስቃሴ ይኖራቸዋል
ድምር 205 100.0 ድምር 163 100 ድምር 43 100

15፡ በልማት ምክንያት የተነሱት ለመልሶ ልማት ትግበራ የሰጡት ግምገማ /ጅማ ከተማ/
የግምገማ ደረጃ
መገምገሚያ አጀንዳዎች ያልተገለፀ በጣም ጥሩ ጥሩ መካከለኛ ዝቅተኛ እጅግ ዝቅተኛ
ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር %
የቦታ አመራረጥ ትክክለኛነት 2 2.3 39 65.0 14 23.3 3 5.0 - - 2 3.3
የተነሺዎች ተሳትፎ 2 3.3 4 6.7 13 21.7 7 11.7 22 36.7 12 20.0
ምትክ ቦታ አመዳደብ 2 3.3 5 8.3 39 65.0 11 18.3 - - 3 5.0
ምትክ ቤት አመዳደብ 4 6.7 25 41.7 11 18.3 9 15.0 1 1.7 10 16.7
የካሳ መጠን በቂ ስለ መሆኑ 12 20.0 - - 2 3.3 1 1.7 2 3.3 43 71.7
ለመነሳት ዝግጅት የሚሰጥ ጊዜ 2 3.3 - - 1 1.7 4 6.7 10 16.7 43 71.7
ለተነሺዎች የሚደረግ እግዛ 2 3.3 - - - - - - 3 5.0 55 91.7
ለየልማት ተነሺዎች የብድር አሰጣጥ 1 1.7 - - - - 3 5.0 2 3.3 54 90.0
አገልግሎት አሰጣጥ 2 3.3 - - - - 6 10.0 7 11.7 45 75.0
የመልሶ ልማት ጥራትና ፍጥነት 2 3.3 - - 1 1.7 1 1.7 8 13.3 48 80.0

298
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

16፡ በቅርቡ የሚነሱ ለመልሶ ልማት ትግበራ የሰጡት ግምገማ /ጅማ ከተማ/
ግምገማ ደረጃ
ያልተገለፀ በጣም ጥሩ ጥሩ መካከለኛ ዝቅተኛ እጅግ ዝቅተኛ
መገምገሚያ አጀንዳዎች ቁ. % ቁ. % ቁ. % ቁ. % ቁ. % ቁ. %
የቦታ መረጣ ትክክለኛነት 19 31.7 10 16.7 7 11.7 12 20.0 2 3.3 10 16.7
የተነሺዎች ተሳትፎ 13 21.7 15 25.0 12 20.0 6 10.0 10 16.7 4 6.7
ምትክ ቦታ አመዳደብ 36 60.0 2 3.3 10 16.7 6 10.0 1 1.7 5 8.3
ምትክ ቤት አመዳደብ 37 61.7 - - 10 16.7 5 83 3 5.0 3 5.0
የካሳ መጠን 42 70.0 3 5.0 2 3.3 2 3.3 5 8.3 6 10.0
ለመነሳት ዝግጅት የሚሰጥ ጊዜ 39 65.0 - - 6 10.0 4 6.7 3 5.0 8 13.3
ለተነሺዎች የሚደረግ እግዛ 37 61.7 6 10.0 9 15.0 2 3.3 2 3.3 4 6.7
የብድር አሰጣጥ 43 71.7 4 6.7 6 10.0 1 1.7 2 3.3 4 6.7
የአገልግሎት አሰጣጥ 36 60.0 5 8.3 8 13.3 5 8.3 1 1.7 5 8.3
የመልሶ ማልማት ጥራትና 61.7 10 16.7 3 5.0 2 3.3 3 5.0
5 8.3 37
ፍጥነት

299
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

17፡ ነዋሪዎች ለመልሶ ልማት ትግበራ የሰጡት ግምገማና ምክንያቶች /አዲስ አበባ ከተማ/
ግምገማ ደረጃ ምክንያቶች
መገምገሚያ አጀንዳዎች ያልተገለፀ በጣም ጥሩ ጥሩ መካከለኛ ዝቅተኛ እጅግ ያልተገለፀ የመመሪ የአስፈፃ የአስፈፃሚ የተነሺው የገንዘብ ሌላ
ዝቅተኛ ያ ደንብ ሚ ዓቅም ስነ ምግባር የራስ ችግር እጥረት
ቁ. %
ቁ. % ቁ. % ቁ. % ቁ. % ቁ. % ቁ. % ቁ. % ቁ. % ቁ. % ቁ. % ቁ. % ቁ. %
ቦታ መረጣ ትክክለኛነት 21 10.2
89 43.4 41 20.0 34 16.6 6 2.9 14 6.8 46 22.4 98 47.8 43 21.0 11 5.4 3 1.5 4 2.0 - -
የተነሺዎች ተሳትፎ 15 7.3
23 11.2 50 24.4 32 15.6 59 28.8 26 12.7 45 22 51 24.9 47 22.9 44 21.5 14 6.8 2 1.0 2 1.0
ምትክ ቦታ አመዳደብ 55 26.5
16 7.8 62 30.2 35 17.1 19 9.3 18 8.8 70 34.1 66 32.2 29 14.1 25 12.2 13 6.3 2 1.0 - -
ምትክ ቤት አመዳደብ 61 29.8
31 15.1 36 17.6 31 15.1 21 10.2 25 12.2 75 36.6 63 30.7 27 13.2 23 11.2 9 4.4 8 3.9 - -
የካሳ መጠን በቂ መሆኑ 112 54.6
4 2.0 8 3.9 8 3.9 18 8.8 55 26.8 121 59.0 9 4.4 18 8.8 17 8.3 6 2.9 33 16.1 1 0.5
ለመነሳት ዝግጅት የሚሰጥ 8.8 27 13.2 26 12.7 31 15.1 62 30.2 68 33.2 26 12.7 36 17.6 52 25.4 13 6.3 10 4.9 - -
41 20.0 18
ጊዜ
ለተነሺዎች የሚደረግ እግዛ 50 24.4 10 4.9 24 11.7 16 7.8 29 14.1 76 37.1 65 31.7 27 13.2 35 17.1 61 29.8 8 3.9 9 44 - -
የብድር አሰጣጥ 47 22.9 10 4.9 14 6.8 30 14.6 24 11.7 80 39.0 70 34.1 16 7.8 25 12.2 34 16.6 10 4.9 50 24.4 - -
አገልግሎት አሰጣጥ 45 22.0 7 3.4 29 14.1 28 13.7 31 15.1 65 31.7 76 37.1 24 11.7 27 13.2 64 31.2 6 2.9 8 3.9 - -
የመልሶ ማልማት ጥራትና 25.4 46 22.4 15 7.3 17 8.3 68 33.2 32 15.6 54 26.3 27 13.2 64 31.2 - - 28 13.7 - -
7 3.4 52
ፍጥነት
ድምር 454 260 337 255 255 489 668 434 314 395 82 154 3
16.4 12.4 12.4 23. 48. 31.4 22. 28. 5.9 11.1 0.2
% 22.1 12.7
9 3 7 6

300
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

18፡ ለችግሮች ደረጃ የተሰጠ ግምገማ /አዲስ አበባ ከተማ/


ለችግሮቹ የተሰጣቸው የግምገማ ክብደት
ምክንያቶች ያልተጠቀሰ 1 2 3 4 5
ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር ቁጥር % ቁጥር % ቁጥር %
ለአረንጓዴና ክፍት ቦታዎች ትኩረት አለመስጠት 3 15 12 5.9 8 3.9 33 16.1 15 7.3 134 65.4
ሙሉ ከማፍረስ ውጭ ሌላ አማራጭ ያለመከተል 2 1 23 11.2 10 4.9 18 8.8 12 5.9 140 68.3
የካሳ መጠን ቤት ለመተካት የማይበቃ መሆኑ 16 7.8 11 5.4 20 9.8 17 8.3 19 9.3 122 59.5
የልማት ተነሺዎች በቦታው እንዲያለሙ ቅድሚያ 21 10.2 23 11.2 35 17.1 96 46.8
2 1 28 13.7
ዕድል ያለማግኘት
መግባባት ሳይደረስ ማፍረስ 1 0.5 29 14.1 19 9.3 18 8.8 20 9.8 118 57.6
ለመነሳት በቂ የማይሰጥ መሆኑ 2 1 8 3.9 18 8.8 30 14.6 26 12.7 121 59.0
ወጥነት የሌለው አፈራረስ 2 1 38 18.5 14 6.8 30 14.6 26 12.7 95 46.3
ኪራይ ሰብሳቢት ተግባርና አስተሳሰብ 2 1 48 23.4 17 8.3 15 7.3 33 16.1 90 43.99
መልሶ መስፈሪያ ከመጀመሪያ ቦታ መራቅ 3 1.5 24 11.7 18 8.8 16 7.8 24 11.7 120 58.8
ንብረት ሳይወጣ ማፍረስ 3 1.5 57 27.8 17 8.3 14 6.8 15 7.3 99 48.3
መልሶ መስፈሪያ ጫፍ አካባቢ መሆን 3 1.5 26 12.7 14 6.8 16 7.8 28 13.7 118 57.6
ተፈናቃዮች ገቢያቸው ይቀንሳል 2 1 24 11.7 8 3.9 16 7.8 19 9.3 136 66.3
ምትክ ቤት በጊዘው አለመሰጠት 4 2 21 10.2 27 13.2 19 9.3 47 22.9 87 42.4
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ድጋፍ ያለማድረግ 2 1 11 5.4 19 9.3 14 6.8 9 4.4 150 73.2
በመስፈሪያ አካባቢዎች ማሕባራዊ አገልግሎቶች 12 5.9 24 11.7 25 12.2 114 55.6
5 2.4 25 12.2
ያለመገንባት
ለመልሶ ማስፈሪያ በፍጥነት መ/ልማት ያለማደረስ 3 1.5 33 16.1 13 6.3 13 6.3 18 8.8 125 61.0
ምትክ ቤት ወጪ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ 22 10.7 23 11.2 22 10.7 75 36.6
63 30.7 - -
ከግምት ያለማስገባት
ምትክ ቤቶቹ በቂ ያለመሆን 63 30.7 27 13.2 9 4.4 25 12.2 22 10.7 59 28.8
ምትክ ቤት ቅድሚያ ቤት ለሌላቸው አለመሰጠት 63 30.7 45 22.0 14 6.8 17 8.3 13 6.3 53 25.9
የፈረሰ ቦታ ተሎ ያለመልማት 2 1 39 19.0 39 19.0 15 7.3 19 9.3 91 44.4
ለተጨማሪ ትራንስፖርት ወጪ መጋለጥ 4 2 43 21.0 20 9.8 23 11.2 30 14.6 85 41.5
መልሶ በሚለማው አካባቢ ስጋት መፍጠር 2 1 16 7.8 17 8.3 18 8.8 18 8.8 134 65.4
በታቀደው ልክ ያለመሰራት 10 4.9 37 18.0 12 5.9 23 11.2 33 16.1 90 43.9
በተዋናዮች መካከል ቅንጅት ያለመኖር 2 1.0 22 10.7 14 6.8 14 6.8 25 12.2 128 62.44

301
የከተማ መልሶ ልማት በኢትዮጵያ፡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች

19፡ በቃለ - መጠይቅ የተሣተፉ ተነሺዎች ዝርዝር ሁኔታ /ድሬዳዋ/


የዕድሜ ስብጥር የፆታ ስብጥር የጋብቻ ሁኔታ የትምህርት ደረጃ የቤተሰብ ሁኔታ ሥራ
የዕድሜ ብዛት % ዝርዝር ብዛት % ዝርዝር ብዛት % ዝርዝር ብዛት % የቤተሰብ አባላት ብዛት % ዝርዝር ብዛት %
ክልል ብዛት
25 - 34 28 19 ወንድ 74 50 የፈቱ 10 7 ያልተማሩ 40 27 ከ1-3 35 24 የመንግ.ሠራተኛ 23 16
35 - 44 39 26 ሴት 73 49 ያገባ 121 81 ከ1 – 8 ክፍል 49 33 ከ4-6 75 51 የግል ሥራ 66 44
45 - 54 35 24 ያልተገለፀ 1 1 ያላገቡ 16 11 ከ9 – 12 ክፍል 37 25 ከ7 - 9 27 18 ጡረታ 10 15
55 - 64 28 19 ያልተገለፀ 1 1 ድፕሎማ 18 12 10 እና ከዚያ በላይ 6 4 የቤት እመቤት 7 5
Over 64 17 11 1ኛ ዲግሪና ከዚያ 4 3 ያልተገለፀ 5 3 ሥራ አጥ 5 3
በላይ
ያልተገለፀ 1 1 ያልተገለፀ 25 17
ድምር 148 100 148 100 148 100 148 100 148 100 148 100

20፡ በመልሶ ማልማቱ ዓላማ ዙሪያ የተነሽዎች አስተያየት ማጠቃለያ ሠንጠረዥ /ድሬዳዋ/
የከተማ ማደስ ዓላማ ዓላማውን የሚደግፉ ከሆነ ምክንያቱ ዓላማውን የማይደግፉ ከሆነ ምክንያቱ
አሀዝ % አሀዝ % አሀዝ %
በጣም 111 76 የከተማዋን ተወዳዳሪነት ስለሚያሳድግ - ምንም ለውጥ ስለማያመጣ -
የሚያበረታታ
ነው ነው
ደህና 31 21 የወደቀውን መ/ልማትና አካባቢ ስለሚለውጥ 31 22 የተወሰነ ክፍል ብቻ ስለሚጠቅም 1 25
የሚደገፍ 3 2 ለከተማው ውበት ስለሚያጎናጽፍ 44 31 ሕዝቡን ስለሚጎዳ 1 25
አላውቀውም
አይደለም 1 1 ለሕዝቡ ኑሮ መሻሻል ስለሚረዳ 37 27 ተነሽዎችን ስለሚጎዳ 1 25
የከተማ ፕላን ስለሚያስጠብቅ 17 12 በመልሶ ልማቱ ዙሪያ መዳከምና ስጋት ስለሚያስከትል 1 25
ለተነሽዎች የተሻለ ቤትና መኖሪያ አካባቢ 11 8 ተነሽዎች በሚሰፍሩበት አካባቢ መዳከምና ስጋት , -
ስለሚያሰገኝ ስለሚያስከትል
ለዙሪያው መነቃቃትና ተስፋ ስለሚዘራ - -

302

You might also like