Professional Documents
Culture Documents
የውል ስምምነት
ስልክ ቁጥር፡+251115584766/+251947377025
እና
ዉል ተቀባይ፡_____________________
አድራሻ፡________________________
ስልክ ቁጥር፡______________________
ይህ ዉል በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኝን 9.6 ሜ በ 5.30 ሜ የሆነ ባለሁለት ክፍል ከጭቃ የተሰራ መኖሪያ ቤት አፍርሶ
በዲዛይንና ስፔስፊኬሽን በተመለከተዉ መሰረት መገንባት ሲሆን ይህም “ስራዉ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ በመሆኑም ዉል
ተቀባይ በብር፡ _________________________________________________________________
የእጅ ዋጋ ይህ “የዉል ዋጋ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ዉል ተቀባይ ስራዉን ርክክብ ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ በሰላሳ (30)
ቀናት ዉስጥ ግንባታዉን አጠናቆ ለዉል ሰጭ ማስረከብ አለበት፡፡
(ሀ) ግዥ ፈፃሚው አካል የተወሰኑ የግንባታ ሥራዎች መካከል፡በጥንቃቄ የጭቃ ቤቱን የማፍረስ ስራ፤ የቁፋሮ ስራ፤
የግንብ ስራ፤የአርማታ ስራ፤ የብሎኬት ግድግዳ ስራ፤የማሳመር/የአጨራረስ ስራ፤የልስን ስራ፤ የታይሊንግ ስራ፤
የቀለም ቅብ ስራ፤ የጣሪያ ና ቆርቆሮ ማልበስ ስራ፤ የበርና መስኮት ስራ፤ የመስተዋት ገጠማ ስራ፤የቧንቧ መስመር
ገጠማ ስራ፤ የመብራት መስመር ስራ
(ከዚህ በኋላ “የግንባታ ሥራዎች” እየተባሉ የሚጠሩ) ሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራዎቹን ለማከናወን ያቀረበውን ጠቅላላ
የእጅ የውል ዋጋ ብር በፊደል____________________________ በአሀዝ:____________________________
(ከዚህ በታች “የውል ዋጋ” እየተባለ የሚጠራ) ሰለተቀበለ፣
(ለ) ሥራ ተቋራጩ የግዥ ፈፃሚ አካሉን በመወከል ተፈላጊውን የሙያ ችሎታ፣ ሠራተኞችና የቴክኒክ ዕውቀት
በመጠቀም የተጠየቁት የግንባታ ሥራዎች በዚህ የውል ሁኔታዎች መሠረት ለመፈፀም ስለተስማማ፣
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ
የምርታማነት ማሻሻያ እና የልህቀት ማዕከል
ሁለቱ ወገኖች እንደሚከተለው ተዋውለዋል፡፡
1. ስምምነት
1.1 በዚህ ውል ውስጥ ቃላቶችና አገላለፆች በተጠቀሰው ውል ሁኔታዎች ውስጥ በቅደም ተከተል የተሰጣቸውን
ተመሳሳይ ትርጉሞች ይኖራቸዋል።
1.2 ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሰነዶች በግዥ ፈፃሚው አካልና በሥራ ተቋራጩ መካከል በተደረገው ስምምነት
ውስጥ የተካተቱና የውሉ አካል ሆነው የሚነበቡ/የሚቆጠሩ ናቸው።
1. ይህ የውል ስምምነት ከአባሪዎች ጋር
2. በግዥ ፈፃሚ አካል ለሥራ ተቋራጩ የተፃፈ የአሸናፊነት ድብዳቤ
3. ልዩ የውል ሁኔታዎች
4. አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች
5. የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥና አባሪዎቹ
6. የቴክኒክ መወዳደሪያ ሀሳብ ከግንባታ ስራዎች ዝርዝር
7. የንድፍ ሰነዶች (Drawings)
(ለ) ለጥቅል ዋጋ ውሎች: የጥቅል ዋጋው ዝርዝር ((የስሌት ስህተቶች ከታረሙ በኋላ)
1.3 ይህ ውል በሁሉም ሰነዶች ላይ የበላይነት ይኖረዋል፡፡ በውሉ ሰነዶች ላይ ልዩነት ወይም ያለመጣጣም
በሚኖርበት ጊዜ ከላይ በተዘረዘሩት ቅደም ተከተል መሠረት የበላይነት ይኖራቸዋል፡፡
1.4 ግዥ ፈፃሚው አካል ለሥራ ተቋራጩ የሚፈጽመውን ክፍያ ግምት ውስጥ በማስገባት በዚህ ውል ውስጥ
እንደተመለከተው ሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራዎቹን ለማከናወንና በውሉ ድንጋጌዎች መሠረት ግድፈቶችን
ለማረም ከግዥ ፈፃሚው አካል ጋር ግዴታ ይገባል፡፡
1.5 ግዥ ፈፃሚው አካል ሥራ ተቋራጩ ለሚተገብራቸው የግንባታ ሥራዎች፣ እንዲሁም ግድፈቶች ለማረም
ለገባው ግዴታ የውሉን ዋጋ ወይም በውሉ ድንጋጌዎች መሠረት ተከፋይ የሚሆነውን መጠን በተባለው ጊዜና
ሁኔታ ለመክፈል ግዴታ ይገባል፡፡
2.1.2.1.የቅድሚያ ክፍያ ለዉሉ ጉዳይ ብቻ አገልግሎት ላይ የሚዉል ከጠቅላላ ዋጋ እሰከ 20% የማግኘት መብት አለዉ፡፡
2.1.2.2.የግንባታ ስራዉ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ጊዜያዊ ርክክብ እሰከ ሚደረግበት ጊዜ ባለዉ ዉስጥ ለስራዉ የተመደበዉን
የዉሉን ገንዘብ ቅድሚያ ክፍያን ሳይጨምር በ 4 ዙር እንዲከፈለዉ የመጠየቅ መብት አለዉ፡፡
2.2.1.የዉል ሰጪ ግዴታዎች
2.2.1.1 ቅድሚያ ክፍያና ሌሎች ለተሰሩ ስራዎች ተከታታይ ክፍያዎች እንዲከፈለዉ በዉል ተቀባይ ሲጠየቅ እና በዉል ሰጪ
አማካሪ ወይም አግባብ ባለዉ ተቆጣጣሪ መሃንዲስ ተረጋግጦ ሲቀርብ ስለ ትክክለኛነቱ መርምሮ በማጽደቅ ክፍያ የመፈጸም
ግዴታ ይኖርበታል፡፡
2.2.1.2 ግንባታዉ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ በ አምስት(5)ቀናት ዉስጥ ጊዚያዊ ርክክብ ይፈጽማል፡፡
2.2.1.3. የግንባታዉን ስራ የሚያደናቅፍ እና በዉል ሰጪዉ ጥረት ወይም ጣልቃ ገብነት ሊወገዱ የሚገባቸዉን እክሎች
ስለማጋጠማቸዉ ዉል ተቀባይ በጽሁፍ አድርጎ ለዉል ሰጪ ተቌም ገቢ በማድረግ ሲገለጽለት እክሉ በዉል ሰጪ የሚወገዱ
ከሆነ ተገቢዉን ህጋዊ እገዛ ያደርጋል፡፡
2.2.1.4 ዉል ሰጪ ለግንባታዉ አስፈላጊ የሆኑ የግንባታ ጥሬ ዕቃዎችን በወቅቱ ለዉል ተቀባይ ያቀርባል፡፡
2.2.2.የዉል ሰጪ መብቶች
2.2.2.1. በዚህ ዉል ጉዳይ የዉል ሰነዶች በተለይም የስራ ስፔስፊኬሽን በተመለከተዉ ዓይነት፤ ጥራት ና በተወሰነዉ ጊዜ
የግንባታዉ ስራ ተጠናቆ የመረከብ መብት አለዉ፡፡
2.2.2.2. ለዉል ተቀባይ በዚህ ዉል የሰጠዉን የግንባታ ስራ በሚመድበዉ ተቆጣጣሪ መሀንዲስ እና እንደአስፈላጊነቱ
በሚያሰማራዉ አማካሪ አማካኝነት ይቆጣጠራል፡፡
2.2.2.3. ለዉል ተቀባይ በዚህ የግንባታ ዉል የቅድሚያ ክፍያ የሚፈጸምለት ከሆነ ይኸዉም የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ
ለግንባታዉ ስራ ከሚከፈለዉ ተከታታይ ክፍያዎች በመቶኛ እየተሰላ ተቀናሽ በማድረግ የማስመለስ መብት አለዉ፡፡
2.2.2.4. ተቌራጭ ግዴታ የገባበትን የግንባታ ስራ በዉሉ አግባብ በተቀመጠዉ ዓይነትና በተወሰነዉ ጊዜ ማጠናቀቅ ሳይችል
ሲቀር ስራዉን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በሌላ ተቌራጭ የማስጨረስ ሙሉ ስልጣን አለዉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ
የምርታማነት ማሻሻያ እና የልህቀት ማዕከል
3. ስለ ክፍያ አፈፃጸም
3.1.ዉል ሰጪ ለግንባታ ስራዉ የተስማማበትን የእጅ ዋጋ ብር፡
__________________________________________________________________
ብቻ ስራዉ ተጠናቆ ጊዜያዊ ርክክብ ሲፈጽም ለዉል ተቀባይ ይከፍላል፡፡
3.2.ከላይ በተራ ቁጥር 3.1 የተገለጸዉ ገንዘብ መጠን በ አራት(4) ተከታታይ የክፍያ ጊዜ የሚፈጸም ሆኖ የመጀመሪያዉ ዙር
ከጠቅላላ የፊዚካል ስራዉ 25% ሲከናወን፤ሁለተኛዉ ዙር ከጠቅላላ የፊዚካል ስራዉ 50% ሲከናወን፤ሶስተኛዉ ዙር ከጠቅላላ
የፊዚካል ስራዉ 75% ሲከናወን፤አራተኛዉ ዙር ከጠቅላላ የፊዚካል ስራዉ 100% ተጠናቆ ጊዚያዊ ርክክብ ሲፈጸም
የሚከፈል ይሆናል፡፡
2. የቁፋሮ ስራ(Excavation)
3. የግንብ ስራ(Masonry)
ጠቅላላ የእጅ ዋጋ
ምስክሮች
ምርታማነት ማሻሻያና የልህቀት ማዕከል ስም፡-_______________________
ፊርማ፡- __________________ ፊርማ ፡- __________________
ስም ፡- __________________ ስም ___________________
ኃላፊነት፡- _________________ ኃላፊነት፡- ______________
ቀን፡- _____________________ ቀን፡- ____________________