You are on page 1of 13

በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር

ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ አሰራር ማሻሻያ ቢሮ

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ሕግ ማዕቀፎች ዝግጅት


ዳይሬክቶሬት

የኮንስትራክሽን አማካሪዎች አሰራር መመሪያ


(የመጀመሪያ ረቂቅ)

ታህሳስ/ 2013 ዓ.ም

ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴ


የኮንስትራክሽን አማካሪዎች አሰራር ቁጥር---- /2013

የኮንስትራክሽን ሥራዎች ጥራትና ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲሰሩ ለማድረግ እንዲቻል በሴክተሩ ተዋናይ የሆኑ
ፈጻሚና አስፈጻሚ አካላት መኖራቸው የሚታወቅ ነው፡፡ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ በሚካሄዱ የተለያዩ የግንባታ
ፕሮጀክቶች ላይ ከቅድመ ግንባታ ጀምሮ እስከ የግንባታ ውል አስተተዳደር ድረስ ባለው ሂደት ተዋናይ ከሆኑ
የሙያ አካላት ውስጥ አማካሪዎች በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት አንዱ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

በመሆኑም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ጤናማ እድገቶች የሚጎዱ መልካም ያልሆኑ ገፅታዎችን፣ ሙስናንና
ብልሹ አሰራር ለመከላከል፣ ሙያዊ ሥነ ምግባርን እንዲከበር ማድረግ እና የስራ ዲሲፕሊን በማስፈን በዘርፉ
የሚሳተፉ አካላት የሚመሩበት የድጋፍ፣ ክትትል፣ ቁጥጥርና የተጠያቂነት ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ
በመገኘቱ ፣

በዚህ መሰረት የሀገራችንን፣ የሴክተሮችን የኢንደስትሪውን ፖሊሲና ስትራቴጂ አጣጥመው እንዲዘጋጁ፣


ለኢንደስትሪው ልማት ምርታማነትና ሁለንተናዊ ትራንስፎርሜሽን ቀጣይነት ያለው እድገት እንዲመጣ
ዲዛይኖች ከ ጥራት፣አስተማማኝነት፣ ወቅታዊ ዋጋ፣ ምቹ፣እና ከሙስና የጸዳ ከመሆን አኳያ እንዲከናወኑ
ለማስቻል፣የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና በጀት እንዲሁም የሚፈለገውን የጥራት ደረጃ
ጠብቀው እንዲጠናቀቁ የአማካሪ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ስራቸውን በኃላፊነትና ተጠያቂነት ስሜት ተገቢውን
ትኩረት እንዲሰጡ ለማድረግ ፣ እንዲሁም ሀላፊነታቸውን በትክክል በማይወጡት በመንግስትና ህዝብ ላይ
ለሚያደርሱት ጉዳትና ኪሳራ ተጠያቂ በማድረግ የሚያርሙና ለሌሎች ማስተማሪያ የሚሆኑ ተገቢና
ተመጣጣኝ ቅጣቶች የሚደነግግ የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት በማስፈለጉ፣የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር
መ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 1097/2011 ዓ.ም አንቀጽ 22/አ 1183/2012 አንቀጽ 4(1) በህግ በተሰጠው የውክልና
ስልጣን መሰረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

ክፍል አንድ

ጠቅላላ ድንጋጌ

1. አጭር ርዕስ

1
ይህ መመሪያ “የኮንስትራክሽን አማካሪዎች አሰራር መመሪያ ቁጥር --------/2013 ” ተብሎ ሊጠቀስ
ይችላል፡፡

2. ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ ፡-
1) “ኮንስትራክሽን ማለት“ ከመሬት በታችና በላይ የሚከናወኑ ህንጻን እና ሌሎች የምህንድስና መሠረተ
ልማትን ጨምሮ በቋሚ ንብረቶች ላይ የዕቃዎች እና አገልግሎቶች ጥምር የሆነ የልማት፣
የማስፋፋት፣ የመገጣጠም፣ የጥገና፣ የዕድሳት፣ የማሻሻል፣ የቁፋሮ፣ የማወላለቅ እና የማፍረስ
ሥራዎችን የሚያካትት ተግባር ነው ፡፡
2) የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት” ማለት በመንግስት፣ በግሉ ዘርፍ እና በመንግስትና በግሉ ዘርፍ ጥምረት
የሚከናወኑ ማናቸውም የምህንድስና ጥናት፣ እቅድ፣ ዲዛይንና የኮንስትክሽን ሥራዎችን
ያጠቃልላል፡፡
3) “አማካሪ” ማለት ሕጋዊ ሥልጣን በተሰጠው አካል ተመዝግቦ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ
የአማካሪነት የምዝገባ/ብቃት ምስክር ወረቀት ፈቃድ የተሰጠው እና የንግድ ፈቃድ ያለው ድርጅት
ነው፡፡
4) “የሥራ ተቋራጭ” ማለት ሕጋዊ ሥልጣን በተሰጠው አካል ተመዝግቦ የኮንስትራክሽን ሥራዎች
የሥራ ተቋራጭነት የምዝገባ/ብቃት ምስክር ወረቀት ፈቃድ የተሰጠው እና የንግድ ፈቃድ ያለው
ድርጅት ነው፡፡
5) “የዲዛይን ባለሙያ” ማለት ሕጋዊ ሥልጣን በተሰጠው አካል ተመዝግቦ የኮንስትራክሽን ዲዛይን
ለመስራት የምዝገባ ምስክር ወረቀት የተሰጠው ሰው ነው፡፡
6) “አሰሪ“ ማለት ማንኛውንም የግንባታ ፕሮጀክት አፈጻጸም የሚከታተልና የሚያስፈጽም ከአማካሪ
ድርጅት ወይም ከሥራ ተቋራጭ ጋር ውል ገብቶ የሚያሰራ አካል ነው፣
7) “ብክነት” ማለት ዲዛይን ሲዘጋጅ ተገቢውን ግብዓት ተጠቅሞ መስራት እየተቻለ ለፕሮጀክቱ
ከተቀመጠው በጀት፣ ጥራትና ጊዜ በላይም ሆነ በታች በመጠቀሙ የሚፈጠር ብክነት ወይም ኪሳራ
ማለት ነው፡፡
8) “ቅድመ ዲዛይን” ማለት ዲዛይን ከመሰራቱ በፊት የፕሮጀክት የመስክ ምልከታን፣ አዋጪነት
ጥናትንና የቅየሳ ሥራን ያካትታል፡፡
9) “ዲዛይን” ማለት የአንድን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት መጠን፣ ዓይነትና ስፋት እንዲሁም
የሚሠራበትን ቁሳቁስና የአገነባብ ዘዴን የሚያሳይ ንድፍ ወይም ሞዴል ሲሆን የአርክቴክቸር፣
የስትራክቸር፣ የሳኒተሪ፣ የኤሌክትሪካል፣ የሜካኒካል፣ የእሳት አደጋ መከላከልና የሌሎች ሥራዎችን
ንድፍ ሊያካትት ይችላል፤
10) “ሚኒስቴር” ማለት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ነው፡፡

2
11) “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ወይም በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው ማንኛውም አካል ነው፡፡
12) በዚህ መመሪያ ውስጥ በወንድ ጾታ የተገለጸው ሁሉ በሴት ጾታ ላይም ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

3. የተፈጻሚነት ወሰን
1. ይህ መመሪያ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡-

ሀ. በማንኛውም የግልም ሆነ የመንግስት የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ላይ በአማካሪነት ሥራ ላይ


በሚሰማሩ አማካሪዎች

ለ. መመሪያው ከመውጣቱ በፊት ተጀምረው ዲዛይናቸው ባልተጠናቀቀ ፕሮጀክቶች ላይ

2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው ቢኖርም በሚከተሉት ተፈጻሚ አይሆንም፡-

ሀ. መመሪያው በሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ዲዛይናቸው በጸደቀ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች፣

ለ. የሃገር ደሕንነት በተመለከተ በሚዘጋጁ ዲዛይኖች፣

ሐ. መመሪያው ተፈጻሚ እንዳይሆን በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወሰንባቸው የኮንስትራክሽን


ፕሮጀክቶች፣

4. መርሆዎች
ማንኛውም በኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ላይ የሚሳተፍ አማካሪ ሊከተላቸው የሚገቡ መርሆዎች

1. የኢትዮጵያን የኮንስትራክሽን ህጎች እንዲሁም አገር አቀፍና ዓለምአቀፍ የኮንስትራክሽን ኮዶችና


ስታንዳርዶች ተከትሎ ስራውን መፈፀም፣

2. በኮንስትራክሽን ሕጎች እና በገባው ውል መሰረት የተቀበላቸውን ኃላፊነቶች ሙያዊ ዕውቀቱን


ተጠቅሞ የአሰሪውን ፍላጎት ማስጠበቅ፣

3. አማካሪዎች ለሚያዘጋጇቸው ዲዛይኖች ተጠያቂነት በማረጋገጥ ሀላፊነታቸውን በትክክል

በማይወጡት በሕዝብ፣ በመንግስት እና በአሰሪው ላይ ለሚያደርሱት ጉዳትና ኪሳራ ተጠያቂ


በማድረግ የሚያርሙና ለሌሎች ማስተማሪያ የሚሆኑ ተገቢና ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲቀጡ
ማድረግ፣
4. አማካሪዎች ለሚያዘጋጇቸው ዲዛይኖች ከጥራት፣ ከአስተማማኝነት፣ ከወቅታዊ ዋጋ፣ ከምቹነት እና ከሙስና
የጸዱ ተደርገው እንዲከናወኑ ለማስቻል፣

5. የተመዘገቡ ባለሙያዎችን ስለመቅጠር

3
1. ማንኛውም የኮንስትራክሽን ዲዛይን አማካሪ የኮንስትራክሽን ዲዛይን ሲሰራ ለሥራው በሚመጥን የዲዛይን ባለሙያ
ቀጥሮ ማሠራት አለበት፣
2. የሚቀጠሩ የዲዛይን ባለሙያዎች የዲዛይን ሥራ ለማከናወን የተመዘገቡና ለበጀት ዓመቱ የታደሰ የባለሙያ ምስክር
ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት
ክፍል ሁለት
የዲዛይንና ተጓዳኝ ሥራዎች
6. ስለቅድመ ዲዛይን ሥራ
1. በቅድመ ዲዛይን አማካሪ የሚያዘጋጀው የፕሮጀክት አዋጭነት ጥናት የቅየሳ ሥራ በውሉ
ባይገለጽም የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ በትክክልና በዝርዝር የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡

7. የአፈር ምርመራ

1. የአፈር ምርመራ እንዲያካሂድ የተቀጠረ አማካሪ ስራውን ሲሰራ ሳይንሳዊ የሆኑ አገር አቀፍ እና
አለም አቀፍ ስታንዳርዶችንና ኮዶችን መሠረት አድርጎ ፕሮጀክቱ የሚያርፍበትና የአካባቢውን
ወካይ(ገላጭ) ናሙና መውሰድ አለበት፤
2. አማካሪው የዲዛይን ስራ የሚሰራ ከሆነ ወደዚያ ሰራ ከመግባቱ አንድ ወር በፊት የአፈር ምርመራ
ውጤቱንና ዝርዝር መረጃዎችን ለአሰሪው ማሳወቅ አለበት፤
3. አማካሪው ያገኘውን የአፈር ምርመራ ውጤት መሰረት አድርጎ በፕሮጀክት ቦታ ለሚዘጋጅ
ዲዛይን ወይም ለሚካሄድ ግንባታ ተገቢነት ያለው ሳይንሳዊና ሙያዊ አስተያየት መስጠት አለበት፡፡
8. የዲዛይን ዝግጅት
ማንኛውም ዲዛይን እንዲያዘጋጅ የተቀጠረ አማካሪ ፡-
1. የሕንጻ፣ የመንገድ፣ የከተማ፣ የአረንጓዴ ስፍራ ማስዋብ፣ የድልድይ፣ የመሰረተ-ልማት እና
ሌሎች ተያያዥ ዲዛይኖችን ማናበብና ማጣጣም ይኖርበታል፤

2. በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት ያላቸውን የአገር አቀፍና አለም አቀፍ ህጎች፣ ኮዶችና
ስታንዳርዶች እንዲሁም የአካባቢው ፕላን ያስቀመጣቸውን ህግጋት መከተል ይኖርበታል፤

3. በአሰሪው ፍላጎት መሰረት ደህንነትን፣ ጥራትንና አገልግሎትን ሳያጓድል ግንባታው በተመጣጣኝ


ወጪ(Cost Efficient) ሆኖ እንዲካሄድ የሚያስችል ዲዛይን ማዘጋጀት ይኖርበታል፤

4. ዲዛይኑ በተመጣጣኝ ወጪ የተሰራ መሆኑን ከሚኖሩ ሌሎች አማራጮች በማነፃፀር የዋጋ


ልዩነት በሚያሳይ መልኩ በማቅረብ የዋጋ ትንተና ሪፖርት ማዘጋጀት ይኖርበታል፤

4
5. አስፈላጊ የሆነ የግንባታ ፕሮጀክት የዲዛይኑ የቆረጣ ምልከታ (section) ተወስዶ ዝርዝር
ዲዛይኖችን (Design details)፣ መለኪያዎችን እና የግብዓት ዝርዝርን (materials) በግልጽ
ማስቀመጥ ይኖርበታል፤

9 የሥራ ዝርዝር (Specification)


1. የሥራ ዝርዝር ሰነዱ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ የቴክኒካል የሥራ ዝርዝር (Specification) ሕጎችን፣
መስፈርቶችን (Standards) እና የይዘት መስፈርያዎችን (Measurment) መሰረት ያደረገና ያሟላ መሆን
አለበት፤
2. ከዲዛይኑ በመነሳት ሊሰራ ለታሰበው ሥራ በማያሻማ ሁኔታ አስፈላጊውን የግብዓት ዓይነት
(Materials)፣ ይዘት፣ መጠንና ጥራት በመግለጽ መዘርዘር አለበት፤
3. በዲዛይኑ የሚያካትታቸው የግንባታ ግብዓቶች በሃገር ውስጥ ገበያ ላይ ሊገኙ የሚችሉ እና አገር አቀፍና
አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው፤
10 የሥራ መጠን ትንተና እና ነጠላ ዋጋ ግመታ (take off and cost break down)
1. አማካሪ ያዘጋጀው የሥራ መጠን ትንተና ከዲዛይኑ ጋር በመጠንም ሆነ በይዘት መለያየት የለበትም፤
2. አማካሪው የሥራ መጠን ትንተና ሲያዘጋጅ የሥራ ዝርዝሩንና መለኪያውን እና የክፍያ መጠን
በትክክል መግለጽ አለበት፤
3. በሀገሪቱ ተቀባይነት ባለው የአሰራር ሥርዓት (መመሪያ) መሠረት፡-
ሀ. ለአንድ ሥራ የሚያስፈልግ የግንባታ ቁሳቁስ መጠን (material requirement)፣
ለ. በግንባታው የሚሰማራው የሰው ሃይል እንደየሙያውና ድርሻው በስራው የሚቆይበት ግዜ (man
power and utility factor) እና ሌሎች የሚያስፈልጉ ማሽኖችና የእጅ መሳሪዎችን (machinery
and tools)፣
ሐ. ለያንዳንዱ የሥራ ዓይነት የሚያስፈልገው ቡድን በሰአት የሚሰራውን ሥራ (out put)
በመጠቀም የዋጋ ግምት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
4. የግንባታ እቃ ዋጋ (material cost)፣ የሰው ሃይል (man power cost) እና የሚያስፈልጉ ማሽኖችና
የእጅ መሳሪዎችን (machinery cost) ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ከማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ
በተሰበሰበውና ጸድቆ በወጣው ዋጋዎችን ተከትሎ የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡
11. ስለ የግንባታ ውል ማዘጋጀት
ማንኛውም አማካሪ አግባብነት ያላቸውን የኮንስትራክሽንና የግዢ ሕጎች፣ ደረጃዎች እና የፕሮጀክቱን
አጠቃላይ ሁኔታ ያገናዘበ እንዲሁም ፕሮጀክቱ በሚጠበቅበት ጥራት፣ ጊዜና የታሰበለትን አገልግሎት
በሚያሳካ አገባብ ለማጠናቀቅ የሚያስችል የግንባታ ስራ ውል ማዘጋጀት አለበት፡፡

ክፍል ሶስት

5
የግንባታ ቁጥጥር አማካሪ

12. የግንባታ ቁጥጥር እንዲያካሄድ የተቀጠረ አማካሪ:-


1) በተሰጠው የፀደቀ ዲዛይን፣ የስራ ዝርዝር እና የውል ሰነድ መሠረት ሥራ ተቋራጩ ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜና ዋጋ
እንዲሁም በተቀመጠው የጥራት ደረጃ እየገነባ ስለመሆኑ ይቆጣጠራል፤ ይከታተላል፤ ከስራ ተቋራጩ የተቀበለውን የክፍያ
ጥያቄ አረጋግጦ ለአሰሪው ያቀርባል፤

2) የግንባታ ቁጥጥሩን /ሱፐርቪዝን/ ሲያከናውን አጠቃላይ ስራውን በአግባቡ ለመቆጣጠር በሚያስችለው አስቀድሞ የተዘጋጀ
ቸክ ሊስት መሠረት መሆን አለበት፣

3) የሥራ ተቋራጩን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በአካል ይቆጣጠራል፤ ያረጋግጣል፤

4) የጥራት መቆጣጠሪያ ቼክሊስቶችን ያዘጋጃል፤


5) እያንዳንዱን ስራ የሚቆጣጠርበትና በፊርማው የሚያረጋግጥበት የየዕለት ክንውን መቆጣጠሪያ ቅጽ ያዘጋጃል፤ በአሰሪው
ያፀድቃል፤
6) በሳይት ቡክ ያዘዛቸውን ስራዎች ዝርዘርና አጠቃላይ መረጃ እንዲሁም የየዕለቱን የስራ አፈጻጸም የተጠቃለለ ሪፖርት
በሳምንቱ መጨረሻ እንዲሁም የየሳምንቱን ሪፖርት አጠቃሎ በወሩ መጨረሻ ለአሰሪው ሪፖርት ያቀርባል፤
7) በዚህ አንቀፅ በንኡስ አንቀጽ 6 መሰረት የሚቀርብ ወርሃዊ ሪፖርት ቢያንስ በተግባር የተከናወኑ ስራዎች፣ የተላለፉ
ትዕዛዞች፣ ያጋጠሙ ችግሮች፣ የተወሰዱ መፍትሄዎች፣ የፕሮጀክቱን የፊዚካልና ፋይናንሺያል አፈጻጸም፣ በፕሮጀክቱ
የተሰማራ የሰው ኃይል መጠንና ማህደር፣ በሳይት ላይ ያሉ የግንባታ ግብዓቶችና መሳሪያዎችን ዝርዝር ሁኔታ አካቶ
መቅረብ አለበት፤
8) እያንዳንዱ የስራ ምዕራፍ ሲጠናቀቅ ሥራ ተቋራጩ የሚያቀርበውን የሥራው መጠን ዝርዝር አማካሪው በማረጋገጥ
ፈርሞ አሰሪው እንዲያውቀው ግልባጩን መላክ አለበት፡፡

ክፍል አራት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
15 ስለ ቅጣት
አማካሪው በዚህ መመሪያ የተገለፁት ግዴታዎቹን በመጣስ በአሰሪው ወይም ሌሎች ስራው የሚነካቸው
አካላት ለሚያደርሰው ጉዳት የሚኖረው የወንጀል፣ ፍትሀ ብሄር እና አስተዳደራዊ ሀላፊነት በተመለከተ ሌሎች
አግባብነት ያላቸው ሕጎች የሚደነጉግት ቅጣት እንደተጠበቁ ሆኖው፤

6
15.1 በዚህ መመሪያ ከአንቀፅ 6-11 የተደነገጉት ግዴታዎች በመጣስ አማካሪዎች በቅድመ ግንባታ
ስራዎች የሚፈፀሙት ጥፋት
15.2 ከቅየሳ ጋር የተያያዙ ጥፋቶች
ሀ. አማካሪው ያቀረበው የአካባቢ ነባራዊ ሁኔታ በግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ የቅየሳ ስራ ሰርቶ ሲገኝ ጥፋቱ
የመጀመሪያው ሆኖ በፕሮጀክቱ ያደረሰው ጉዳት የሌለ እንደሆነ ፤ አማካሪው በራሱ ወጪ ጥፋቱን
እስከሚያርም ሊደርስ ለሚችል ማንኛውም ብክነት ወይም ጉዳት ከአሰሪው ጋር በገባው ውል
የሚኖረው ሀላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ ዳግም ተመሳሳይ ጥፋት አንዳይፈፅም የፅሑፍ ማስጠንቀቅያ
ተሰጥቶት በስራው ሊቀጥል ይችላል፡፡
ለ. አማካሪው ሰርቶ ባቀረበው የቅየሳ ስራ ውጤት የፈፀመው ጥፋት በፕሮጀክቱ ላይ ጉዳት ያደረሰ ከሆነ
፤ቀጣሪው ችግሩን ለማስተካከል ያወጣውን ሙሉ ወጪ ሸፍኖ የስራ ውሉ መቋረጡና ሌሎች
በገባው ውል መሰረት ለአሰሪው ወይም ቀጣሪው የሚኖረው ሀላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ የሙያ
ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱ ለ 2 (ሁለት) ዓመት ይታገዳል እንዲሁም በገባው የመድን ዋስትና መሰረት
የተጠቀሰውን ካሳ ይከፍላል፡፡
ሐ. አማካሪው የፈፀመው ጥፋት ሆን ብሎ፤ ለራሱ ወይም ለሌሎች ሕጋዊ ያልሆነ ጥቅም ለማስገኘት
ወይም በአሰሪው ሆነ በተቋራጩ ላይ ጉዳት ለማደረስ ከሆነ ወይም ጥፋቱ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ
እንደሆነ፤ አግባብነት ባለው የወንጀል ሕግ መጠየቁ፣ ውሉ መቋረጡ፣ በገባው ዋስትና መሰረት
የሚከፍለው ካሳ ወይም በገባው ውል መሰረት የሚኖሩት ሌሎች ሀላፊነቶች እንደተጠበቁ ሆኖው፤
እንደ ጥፋቱ ክብደት ከ 3 (ሶስት) አስከ 5 (አምስት) ዓመት ለሚደርስ ጊዜ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ
ፈቃዱ ይታገዳል፡፡

15.3 ከአፈር ምርመራ ጋር የተያያዙ ጥፋቶች


ሀ. አማካሪው በዚህ መመሪያ አንቀጠጽ 6.1 አፈር ምርመራ ናሙና ሳይወስድ አፈር ምርመራ ውጤት
ሪፖርት ካቀረበ ያቀረበው ሪፖርት የውሽት መሆኑ ከተረጋገጠ የስራ ውሉ እንዲቋረጥ ተደርጎ ለዚየ
ስራ የተከፈለውን የገንዘብ መጠን አምስት እጥፍ እንዲቀጣ ይጣልበታል ወይም ለተከታታይ 4 አመት
ፍቃዱ ይታገድበታል
ለ. አማካሪው በዚህ መመሪያ አንቀፅ 6.2. መሰረት አፈር ምርመራ ውጤቱን ሳያሳውቅ ወደ ቀጣይ ስራ
የገባ እንደሆን የጹሁፍ ማስተንቀቂያ እና 25,000(የሀያ አምስት ሺ) ብር ቅጣት ይጣልበታል፡፡
15.4 ከዲዛይን ዝግጅት ጋር የተያያዙ ጥፋቶች

7
ሀ. አማካሪው በዚህ መመሪያ 7.1 ተዘረዘሩት ዲዛይኖች ሳያናብብ ካቀረበ በራሱ ወጭ ያስተካክላል
ስህተቱን ለማስተካከል ለሚፈጀው የጊዜ ብክነት ለስራው ሊከፈለው የተዋዋለውን ገንዘብ መጠን
10%ቅጣት ይጣልበታል፡፡
ለ. አማካሪው በአንቀጽ 8.2 የጠጠቀሱትን ህጎች ኮዶች እና ስታንዳርዶች ያልጠበቀ ዲዛይን ሰርተው
ካቀረቡ ፍቃዳቸው ለተከታታይ 3 አመት ታግዶ ለዲዛይ ዝግጅት ተከፈለውን ገንዘብ መጠን 50%
እንዲቀጣ ይጣልበታል፡፤
ሐ. አማካሪው ባዘ ጋጀው ዲዛይን ምክኒያት ያላግባብ ብክነት የፈጠረ እንደሆን ብክነቱን 25%ቅጣት
ይጣልበታል እንዲሁም ፈቃዱ ለ 2 ተከታታይ አመት ይታገድበታል፡፡
መ. አማካሪው በዚህ መመሪያ አንቀጽ 7.4 የተዘረዘሩትን ይዘቶች የማያሟላ ዲዛይን ሰርቶ ካቀረበ ፈቃዱ
ለ 2 ተከታታይ አመት ይታገድበታል፡፡
ሠ. አማካሪው ያዘጋጀው ዲዛይን ዚህ መመሪያ አንቀጽ 7.4 የተዘረዘሩትን ይዘቶች የማያሟላ ዲዛይን
ሰርቶ ካቀረበ እና ዲዛይኑ ሊያሰራ የማችል መሆኑ ከተረጋገጠ በራሱ ወጭ እንዲያስተካክል
እና ለማስተካከል ሲባል ለተፈጠረው የጊዜ ብክነት በቀጣሪው ላይ የደረሰውን ኪሳራ
25%ቅጣት ይጣልበታል እንዲሁም ፈቃዱ ለ 2 ተከታታይ አመት ይታገድበታል፡፡
15.5 ከስራ ዝርዝር ጋር የተያያዙ ጥፋቶች
ሀ. በአማካሪው የተዘጋጀ ማንኛውም የስራ ዝርዝር (specification) ከዲዛይኑ ጋር ልዩነት ካለው በራሱ
ወጭ እንዲያስተካክል እና በቀታሪው ላይ ደረሰውን ኪሳራ ተሰልቶ 25-50% እንዲከፍል
ይደረጋል፤
ለ. በአማካሪው የተዘጋጀው የስራ ዝርዝር የሚሰራውን ስራ በበቂ ሁኔታ ያልገለጸ፣ አስፈላጊውን ይዘት
ላሟላ ዌም ሊከተለው የሚገባውን አቀራረብ ስክት ያልተከተለ እንደሆን ሰነዱን በራሱ ወጭ
እንዲያስተካክል ይደረጋል እንዲሁም በቀጣሪው ላይ የደረሰው ኪሳራ 50% እንዲከፍል
ይደረጋል፤
ሐ. አማካሪው በብቃት ማነስ ምክኒያት ሚሰራውን ስራ በበቂ ሁኔታ ያልገለጸ እንደሆን የስራ ውሉ
እንዲቅረጥ ይደረጋል እንዲሁም የስራ ፈቃዱ ለተከታታይ 2 ዓመት ይታገዳል፡
15.6. ከስራ መጠን መክፈያ ሰነድ/BOQ ጋር የተያያዙ ጥፋቶች
ሀ. አማካሪ ያዘጋጀው የሥራ መጠን መክፈያ በተቻለ መጠን ከዲዛይኑ ጋር በመተንም ሆነ በይዘት
መለያየት የለበትም
ለ. አማካሪው ስራ መጠን ሲያዘጋጅ የስራ ዝርዝሩንና መለኪያውን እንዲሁም የክፍያ መጠን በትክክል
መግለጽ አለበት፡፡
15.7 የስራ መጠን መክፈያ BOQ ጋር የተያያዘ ጥፋት

8
ሀ. አማካሪው ሆን ብሎ ያለአግባብ ጥቅም ለማግኘት ወይም የሌሎችን ጥቅም ለማስገነት የስራ
መጠን መክፈያ ሰነድ ሲያዘጋጅ ከዲዛይኑ ጋር በመተን ወይም በይዘት ወይም በሁለቱም ላይ ልዩነት
ከፈጠረ ሰነዱን ከንደገና አስተካክሎ በራሱ ወጭ የሚያዘጋጅ ሆኖ ክፍያው 10% እንዲቀጣ ይደረጋል::
ለ. አማካሪው ያዘጋጀው የስራ መጠን መክፈያ ሰነድ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 10 የተገለጹትን ማያሟላ
ከሆነ ሰነዱን በራሱ ወጭ እንዲያስተካክል ተደርጎ የአንድ ወር ክፍያ ሙሉውን እንዲቀጣ ይደረጋል፡፡
15.8 ከግንባታ ውል ማዘጋጀት ጋር የተያያዘ ጥፋት
ሀ. ማንኛውም የግንባታ ውል የሚያዘጋጅ አማካሪ አግባብነት ያላቸውን የኮንስትራክሽንና የግዢ ሕጎች፣
እና የፕሮጀክቱን አጠቃላይ ሁኔታ ያገናዘበ እንዲሁም የግዢ ህጉን በመተው ፈቃዱ ለ 4 ተከታታይ አመት
ይታገዳለል፤
ለ. ማንኛውም አማካሪ በውል ጊዜ መከተል ያለበትን የግዚ ህግ ተከትሎ ያልተዘጀ ሰነድ በራሱ ወጭ እና
ጊዜ እንዲያስተካክል ይደረጋል፡
ሐ. ማንኛውም አማካሪ የግዢ ህጉን በመተው የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅም ሆነ ለሌሎች ጥቅም
ለማስገኘት ሲባል ውል ያዘጋጀ እንደሆን ከማንኛውም ስራ የሚታገድ ይሆናል፡፡

15.9. ከግንባታ ቁጥጥር ጋር የተያያዙ ጥፋቶች


1) ማንኛውም አማካሪ ሆን ብሎ የግል ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሶስተኛ ወገን ለማስገኘት
ከስፔሲፊኬሽን ውጪ ስራ እንዲሰራ ከፈቀደ የስራ ውሉ የሚቋረጥ ሆኖ በቀጣሪው ላይ የደረሰውን ኪሳራ
25 በመቶ እንደቅጣት ይጣልበታል፤ወይም የስራ ፈቃዱ ከአምስት አመት ላልበለጠ ጊዜ ይታገዳል፤
2) ማንኛውም አማካሪ በቸልተኝነት ከስፔሲፊኬሽን ውጪ ስራ እንዲሰራ ከፈቀደ የስራ ውሉ የሚቋረጥ
ሆኖ በዚህ ምክንያት ቀጣሪው ላይ የሚደርሰውን ኪሳራ 15 በመቶ እንደ ቅጣት ይጣልበታል፤ ወይም
ከማኝኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ፕሮጀክት ከሶስት አመት ላልበለጠ ጊዜ ይታገዳል፤
3) አማካሪው በፕሮጀክቱ ላይ የተሰማራው የስራ ተቋራጩ የሰው ሀይል ሙያ ጉድለት ምክንያት በቀጣሪው
ላይ የሚደርሰውን ኪሳራ 25 በመቶ እንደ ቅጣት ይጣልበታል፤ ወይም ከማኝኛውም የመንግስትም ሆነ የግል
ፕሮጀክት ከሶስት አመት ላልበለተ ጊዜ ይታገዳል፤
4) አማካሪው በሀገር አቀፍ እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ ስታንዳርዶችን ያልጠበቀ የግንባታ
ግብአት ካጸደቀ ለመጀመሪያ ጊዜ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የአንድ ወር ክፍያው እንደ ቅጣት
ይጣልበታል፤ከአንድ ጊዜ በላይ ጥፋቱን ከደገመ ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያየስራ ውሉ ይቋረጣል
፤ውሉ በመቋረጡ ምክንያት በቀጣሪው ላይ ሚደርሰውን ኪሳራ 50 በመቶ እንደቅጣት ይጣልበታል፤
5) ከላይ በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 4 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አማካሪው በሀገር አቀፍ እንዲሁም
በአለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ ስታንዳርዶችን ያልጠበቀ የግንባታ ግብአት አጽድቆ ወደ ስራ እንዲገባ
ካደረገ፡-

9
ሀ. የግንባታ ግብአቱ ከግንባታው ከስትራክቸራል ጋር ተያያዥነት ካለው ለአራት አመት የስራ ፈቃዱ
ይታገዳል፤በቀጣሪው ላይ ያደረሰውን ኪሳራ የመክፈል አቅሙ ታይቶ እንደ ኪሳራው መጠን ከ 5 እስከ 15
በመቶ እንደቅጣት ይጣልበታል፤
ለ. የግንባታ ግብአቱ ከግንባታው ስትራክቸራል ጋር ተያያዥነት የሌለው ከሆነ የስራ ፈቃዱ ለሁለት አመት
ይታገዳል፤በቀጣሪው ላይ ያደርሰውን ኪሳራ 25 በመቶ እንደቅጣት ይጣልበታል፤
6) አማካሪው በሚመለከተው የመንግስት አካል ናሙና ሊያስጸድቅ ሲገባው ሳያጸድቅ ወደ ስራ እንዲገባ
ካደረገ የአንድ ወር ክፍያው እንደ ቅጣት ይጣልበታል፤ናሙናውንም እንዲያጸድቅ ይደረጋል፤
7) ከላይ በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 6 መሰረት ናሙናው ጸድቆ ሲመጣ ከስታንዳርድ በታች መሆኑ
ከተረጋገጠ በአንቀጽ 13.5.ሀ እና 13.5.ለ ላይ የተደነገጉት ተፈጻሚ ይሆናሉ፤
8) አማካሪው በሚመለከተው አካል ከጸደቀ ናሙና የተለየ የግንባታ ግብአት ወደ ስራ እንዲገባ ካደረገ
ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የስራ ውሉ የሚቋረጥ ሆኖ የስራ ፈቃዱ ከሶስት አመት ላልበለጠ ጊዜ
ይታገዳል፤ወይም ስራው በመሰራቱ በቀጣሪው ላይ የደርሰውን ኪሳራ 25 በመቶ እንደቅጣት ይጣልበታል፤
9) አማካሪው ያጸደቃቸውን የግንባታ ግብአቶች ዝርዝር የሙከራ ውጤት/ Test result በተቀመጠው የጊዜ
ገደብመሰረት ለቀጣሪው ካላሳወቀ ለመጀመሪያ ጊዜ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከአንድ ጊዜ በላይ ከደገመና
የአንድ ወር ክፍያው እንደ ቅጣት ይጣልበታል፤
10) በአንቀጽ 13.9 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አማካሪው እነዚህን ግብአቶች ለቀጣሪው ሳያሳውቅ ወደ
ስራ ካስገባ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የሶስት ወራት፤ ክፍያው እንደ ቅጣት ይጣልበታል፤
11) አማካሪው ለቀጣሪው ሊያቀርብ የሚገባውንሳምንታዊና ወርሀዊ ሪፖርት ሳያቀርብ ከቀረ እና
የመጀመሪያው ከሆነ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል ነገር ግን ጥፋቱ የተደጋገመ እንደሆን እንደሳምንቶቹ
ብዛት ከ 1/4 ኛ እስከ ሙሉ ወርሀዊ ክፊያው ድረስ ቅጣት ይጣልበታል፤
12) በዚህ መመሪያ አንቀጽ 12.7 መሰረት የተቀመጡትን ተፈላጊ አነስተኛ ይዘት ያላሟላ ሪፖርት ካቀረበ
ለመጀመሪያ ጊዜ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከአንድ ጊዜ በላይ ከደገመ የአንድ ወር 1/2 ኛ ክፍያው እንደ ቅጣት
ይጣልበታል፤
13) አማካሪው ውሸት ሪፖርት ካቀረበ ለመጀመሪያ ጊዜ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከአንድ ጊዜ በላይ ካጠፋ
ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምክንያቱ ተጠቅሶ የስራ ውሉ የሚቋረጥ ሆኖ ጥፋቱ እንደሚያስከትለው
ጉዳት ክብደት የስራ ፈቃዱ እና ከአንድ እስከ ሁለት አመት ይታገዳል፤
14) የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና እና የስራ አፈጻጸም ዋስትና ጊዜው ያለፈ ተቋራጭ ዋስትናውን ሳያድስ
እንዲሰራ ያደረገ አማካሪ የሙያ ፈቃዱ ለተከታታይ 4 አመት የሚታገድ ይሆናል፤
15) የተጨማሪ ስራ መጠኑ በውሉ ከተቀመጠው በላይ ሆኖ በቅድሚያ ለባለቤቱ ሳያሳውቅ ስራው
እንዲቀጥል ያደረገ አማካሪ ለአራት ተከታታይ አመት ፈቃዱ የሚታገድ ሆኖ የልዩነቱን 30 በመቶ እንዲቀጣ
ይደረጋል ፡፡

10
15.10 .ከበጀትና ለውጥ ስራ ጋር የተያያዙ ጥፋቶች
1) አማካሪው ላልተሰራ ስራ የስራ ተቋራጩን የክፍያ ጥያቄ አጽድቆ ለቀጣሪው ክፍያ እንዲፈጸም ጥያቄ
ካቀረበ ውሉ የሚቋረጥ ሆኖ ለዛ ስራ ተጠየቀውን የክፍያ መጠን እንደ ቅጣት ይጣልበታል፤
2) አማካሪው የክፍያ ጥያቄ ቀርቦለት ከ 14 ቀናት በላይ ለቀጣሪው ሳያስተላልፍ ካዘገየ በዘገዩት ቀናት ልክ
የወቅቱ የባንክ የወለድ መጠን ተሰልቶ ሁለት እጥፍ እንደ ቅጣት ይጣልበታል፤
3) አማካሪው ለቀጣሪው ሳያሳውቅ የለውጥ ስራ ካዘዘ ለተከታታይ ሁለት አመት ፈቃዱ የሚታገድ ሆኖ
የሁለት ወር ክፍያው እንደ ቅጣት ይጣልበታል፤
4) አንቀጽ 14.3 እንደተጠበቀ ሆኖ አማካሪው ያዘዘው የለውጥ ስራ አስፈለጊ መሆኑን ቀጣሪው ካመነበት
ለለውጥ ስራው የወጣው ወጪ ከገበያ ዋጋ ጋር ተነጻጽሮብልጫ ካለው ልዩነቱ እንደ ቅጣት ይጣልበታል፤
5) አማካሪው እንደባለሙያ አይቶና መዝኖ የለውጥ ስራ አስፈለጊ መሆኑን ለቀጣሪው ማሳወቅ ሲገባ
ሳያሳውቅ የለውጥ ስራው ሳይሰራ ከታለፈ ችግሩን ለማስተካከልየሚወጣውን ወጪ 50 በመቶ እንደ ቅጣት
ይጣልበታል፤ በዚሁአንቀጽ መሰረት የሚጣልበት ቅጣት በምንም ዓይነት ከ 25000 ብር ማነስ የለበትም፡፡

16 የማማከር ሥራ ከተቋረጠ ወይም ከተጠናቀቀ በኋላ የሚታወቁ ጥፋቶች


ማንኛውም አማካሪ የማማከር ሥራውን ካቆመበት ወይም ካጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 10 (አስር)
አመት ድረስ ከሰራቸው የዲዛይንና የማማከር ሥራዎች ጋር ተያይዞ በፕሮጀክቱ ላይ የሚከሰቱ ችግሮች
በግንባታ ወቅት እንደተከሰቱ ተቆጥረው እንደ ጥፋቱ ዓይነትና ክብደት በዚህ አንቀፅ ከላይ በንኡስ አንቀፅ
2 እና 3 የተቀመጡት ተያያዥ ቅጣቶች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
17. የሌሎች ህጎች ተፈጻሚነት
የዚህ መመሪያ ስራ ላይ መዋል የወንጀል እና ፍትሀ ብሄር ህግ ድንጋጌዎች እንዲሁም የሌሎች
አማካሪዎችን የሚመለከቱ የሃገሪቱ ህጎች ተፈጻሚነት ሊያስቀር አይችልም፡፡

18. የቅሬታ አቀራረብ ስርዓት


በዚህ መመሪያ አንቀፅ 13 መሰረት ቅጣት የተጣለበት አማካሪ፤ በሌሎች ሕጎች የተከበሩለት የቅ ሬታና
ይግባኝ አቀራረብ መንገዶች እንደተጠበቁ ሆኖው፤ በሙያ ብቃት ፈቃዱ የተጣለውን እግድ እንዲሻሻልለት
ወይም እንዲነሳለት፤ እግዱን ያስተላለፈው በዘርፉ የሚመለከተው የስራ ክፍል በቀጥታ ተጠሪ ወደ ሆነበት
የመንግስት አካል መታገዱን ባወቀ በአንድ ወር ውስጥ አስተዳደራዊ አቤቱታውን ማቅረብ ይችላል፡፡
19. ቅሬታ ስለማስተናገድ

11
ቅጣት የተጣለበት እና ቅሬታውን እንዲስተናገድ ይግባኝ ያቀረበ አማካሪ በሙያ ብቃት ፈቃዱ ላይ እግድ
ወይም ስረዛ የተጣለበትን ምክኒያት ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ የዘርፉ የሚመለከተው የስራ ክፍል በቀጥታ
ተጠሪ የሆነው የመንግስት አካል ለደንበኛው ማሰወቅ ግዴታ አለበት አለበት፡፡
20. የኮንስትራክሽን ዲዛይን አማካሪ ተግባርና ኃላፊነት
1. ማንኛውም የተመዘገበ የዲዛይን አማካሪ ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት ለሰራው ዲዛይን፣ ፕላንና የሥራ ዝርዝር
ወይንም ሶስቱንም አገልግሎት በጣምራ ሲያከናውን ሊደርሱ ለሚችሉ ጉዳቶች እና ግድፈቶች ለዲዛይን ሥራ
በወጡ ሕጎች መሰረት ከታወቀ የመድህን ድርጅት የጉዳት ማካካሻ ዋስትና ማቅረብ አለበት፣

2. የመተባበር ግዴታ
ማንኛውም ሰው ይህንን መመሪያ ከማስፈጸም አኳያ የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡

21.መሪያውን ስለማሻሻል
ይህ መመሪያ ማሻሻል ሲያስፈልግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሊያሻሽለው ይችላል፡፡

22 መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ
ይህ መመሪያ በጠቅላይ ዓቃቢ ቁጥር ተሰጥቶ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

------ቀን፣ 2013 ዓ/ም

አይሻ መሐመድ (ኢ|ር)


የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር

12

You might also like