You are on page 1of 8

I.

መግቢያ

የኢትዮጵያ መንገድ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከሐምሌ 1 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ በሚኒስትሮች ምክር ቤት
ደንብ ቁጥር 248/2003 የተቋቋመ ሲሆን፣ ከኢመባ ተለይቶ ራሱን ችሎ ከተደራጀበት ቀን ጀምሮ በመንግስት
የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች በበለጠ ውጤት ለማከናወን እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ወቅት 10 የመንገድ ጥገናና 8 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን የሚያስተዳድር ሲሆን፣
እነዚህን ፕሮጀክቶች ለማስተዳደር በምህንድስና እንዲሁም በሌሎች የሶሻል ሳይንስ ዘርፎች ልዩ ልዩ
ኃላፊዎችና ሠራተኞችን አሰማርቶ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ከፍተኛ ዕድገት ያሳየ ሲሆን፣ በተለይ ደግሞ የመንገድ
ኮንስራትራክሽን ዘርፉ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ይገኛል፡፡ ይህን ዕድገት ተከትሎም በርካታ የኮንስትራክሽን
ድርጅቶችና አማካሪዎች የተፈጠሩና በመፈጠርም ላይ ያሉ ሲሆን፣ እነዚህ ድርጅቶች ከኮርፖሬሽኑ በእጅጉ
የላቀ ደመወዝና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን የሚሠጡ በመሆኑ በኮርፖሬሽኑ ለረጅም አመታት የሠሩ፣ በርካታ
ሥልጠናዎችን የወሰዱና ለኮርፖሬሽኑ ጠቃሚ የሆኑ የምህንድስና ባለሙያዎችን ከገበያ መሳብና ማቆየት
አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል፡፡ ከዚህ አኳያም ኮርፖሬሽኑ ራዕዩንና ተልዕኮውን እንዲያሳካ የምህንድስና
ባለሙያዎችን ለማቆየት ብሎም ከገበያ ለመሳብ የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ
ታምኖበታል፡፡

ይህ የዳሰሳ ጥናት በኮንስትራክሽን ዘርፉ የተሻለ ተሞክሮ ያለውን የሱር ኮንስትራክሽን ድርጅትን እንዲሁም
የሌሎችን መሰል መ/ቤቶች ልምድ በማጤንና የኮርፖሬሽኑን ነባራዊ ሁኔታ በመቃኘት ለማዘጋጀት ተሞክሯል፡፡

የጥናቱ ዓላማ፣ ጥናቱን ለማጥናት መነሻ የሆኑ ምክንያቶች፣ የሌሎች መ/ቤቶች ተሞክሮ፣ የኮርፖሬሽኑ ነባራዊ
ሁኔታና የውሳኔ ሃሳብ ቀጥሎ ቀርቧል፡፡

1. የጥናቱ ዓላማ

የጥናቱ ዋና ዓላማ የኮርፖሬሽኑን ተቋማዊ ሁኔታ ከቢዝነስ ሞዴል አንፃር ለመቃኘት እየተከናወነ ያለው ጥናት
የሚያስቀምጠው መፍትሔ ፀድቆ ተግባራዊ እስከሚደረግ ድረስ የምህንድስና ባለሙያዎችን በኮርፖሬሽኑ
ውስጥ ለማቆየትና ከገበያ ለመሳብ የሚያገለግል ጊዜያዊ የጥቅማ ጥቅም መነሻ ሃሳብ ማቅረብ ነው፡፡

2. የኮርፖሬሽኑ ነባራዊ ሁኔታ


1
ኮርፖሬሸኑ በአሁኑ ወቅት፣
 10 የመንገድ ጥገና ፕሮጀክቶች፣
 8 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች፣
 መጠነ ሰፊ አቅም ያለው ማዕከላዊ ጋራዥና

 በየፕሮጀክቶቹ በቡድን ደረጃ የተዋቀሩ የመሣሪያዎች ጥገና ቡድኖችን የሚያስተዳድር


ሲሆን፣ በቀጣይም ሌሎች የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ተወዳድሮ እንደሚይዝ ይጠበቃል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በመነሻ ካፒታል 2.5 ቢሊዮን ብር የተቋቋመ ሲሆን፣ በ 2004 በጀት አመትም፣
 198 ኪ.ሜ የአስፋልት መንገድ ግንባታ
 14,066 ኪ.ሜ የመንገድ ጥገና (መደበኛ፣ ተርም እና ወቅታዊ ጥገና)

በአጠቃላይ 14,264 ኪ.ሜ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎችን ለመስራት አቅዷል፡፡ በዚህ መሠረት ከመንገድ

ግንባታ ብር 1,625,217,670፣ ከመንገድና ድልድይ ጥገና ብር 1,047,087,378፣ ከልዩ ልዩ የሲቪል ስራዎችና


ከዋናው ጋራዥ አገልግሎት ብር 21,277,980 በአጠቃላይ ብር 2,693,583,028 ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዷል፡፡

የተጣራ ትርፍም ብር 54,154,417 ለማግኘት ታቅዷል፡፡ ይህንን ለማስፈፀም ብቁና ልምድ ያለው ባለሙያ
የሚያስፈልግ ሲሆን፣ አሁን ያሉትን ባለሞያዎች ለመያዝና ሌሎች ብቁ ባለሞያዎችን ለመሳብ የሚያስችል ሁኔታ
ካልተፈጠረ በስተቀር ይህን ዕቅድ ተፈፃሚ ለማድረግ አስቸጋሪ እንደሚሆን ታምኖበታል፡፡ ይህ ደግሞ ኮርፖሬሽኑ
እንዲከስርና የበርካታዎችን ሰራተኞች ህይወት አደጋ ላይ እንዲወድቅ የሚያደርግ ነው፡፡
3. የዳሰሳ ጥናቱን ለማድረግ መነሻ የሆኑ ምክንያቶች

ለዚህ የዳሰሳ ጥናት ዋነኛ መነሻ የሆነው ምክንያት የባለሞያዎች ፍልሰትና ምትክ የሰው ኃይል ከገበያ ለመሳብ አለመቻል
ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ በመአለ የሙከራ ትግበራ ራሱን ችሎ ከኢመባ ከወጣበት ከሃምሌ/2003 ጀምሮ 46 መሃንዲሶች ሥራ
የለቀቁ ሲሆን፣ በአጠቃላይ አሁን ካሉት 211 ባለሞያዎች አንጻር ቁጥሩ ከፍተኛ መሆኑን ለማየት ይቻላል፡፡ በለቀቁት
ባለሞያዎች ምትክም የሰው ኃይል ለመቅጠር ካለው የደመወዝ ዝቅተኛነት የተነሳ ምንም ልምድ ከሌላቸው ጀማሪ
መሃንዲሶች በስተቀር ልምድ ያላቸውን ከገበያ ለመሳብ አስቸጋሪ ሁኔታ መፈጠሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጀማሪ
መሃንዲሶችም የተወሰነ ልምድ እስኪያገኙና ሥራ እስኪያፈላልጉ ድረስ እንጅ ተረጋግተው ስራቸውን ለመስራት
እንዳልሆነ ካለው የባለሞያዎች ፍልሰት እንዲሁም ከባለሞያዎች ጋር በሥራ አጋጣሚ በሚደረጉ ግንኙነቶች
ከተገኙ መረጃዎች ለመረዳት ተችሏል፡፡

በኮርፖሬሽኑ ካለው የባለሞያ እጥረት የተነሳ የኮርፖሬሽኑ የቡድን መሪ ሥራዎች ቦታውን በማያሟሉና ጀማሪ በሆኑ
መሃንዲሶች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ያክል ካሉት 96 የምህንድስና ቲም ሊደር ቦታዎች መካከል 53 ያክሉ
(ሁሉም ኤክስኪዩሽን ቲም ሊደሮች ናቸው) ተመጣጣኝ ልምድ ሳያሟሉ ልምድ ያለው የሰው ኃይል ባለመኖሩ ብቻ
በታሳቢ ተመድበው የሚያገለግሉ ሲሆን፣ ይህ ዋናው ሥራ በሚሰራበት በወርክ ኤክስኪዩሽን መሆኑ ደግሞ የመንገድ
2
ግንባታና ጥገና ሥራው ልምድ በሌላቸው ጀማሪ መሃንዲሶች እንዲከናወን አስገድዷል፡፡ ይህም የመንገድ ሥራው
በተፈላጊው ጥራት፣ ጊዜና ወጭ እንዳይከናወን በማድረጉ አሁን እየተመዘገበ ላለው የፕሮጀክቶች ኪሳራ እንደ አንድ
ምክንያት የሚጠቀስና ጉዳዩ ካልተቀረፈ የኮርፖሬሽኑን ህልውና አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል ይታመናል፡፡

የባለሙያዎች ፍልሰትና ምትክ የሰው ኃይል ከገበያ ለመሳብ ያልተቻለው በዋናነት በሚከተሉት ምክንያቶች እንደሆነ
የተደረገው የዳሰሳ ጥናት ያሳያል፡፡

3.1 የኮርፖሬሽኑ ደመዎዝና ጥቅማ ጥቅም ከሌሎች መ/ቤቶች አንጻር ዝቅተኛ መሆኑ

የኮርፖሬሽኑ ክፍያ ከገበያው አንፃር ዝቅተኛ መሆኑን ለማሳየት እንዲቻል የኮርፖሬሽኑ የመነሻ ደመወዝና
ጥቅማ ጥቅም ከሱር ኮንስትራክሽን ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ጋር ተነፃፅሮ በቀጣዩ ሰንጠረዥ ቀርቧል፡፡

ሠንጠረዥ 3.1.1 የኢመኮኮ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ከሱር ጋር ሲነጻጸር (ዋና ዋናዎቹ ጥቅማ
ጥቅሞች ብቻ ተወስደው ሲታይ)
ኢመኮኮ ሱር ኮንስትራክሽን
አላማ ፈፃሚ የሥራ የመነሻ ጥቅማ ጥቅም
መደብ ጥቅማ ጥቅም ደመወዝ(በ
ደመወዝ የሙያ የፕሮጀክ የኃላፊነት የህመም
(በብር) ብር)
(በብር) አበል ት አበል አበል አበል
አላማ ፈጻሚ የሥራ 6,362 - ህክምና ብር 14,000 75% 40% 25% 100%
መደቦች(መምሪያ+ፕ 1800 (በአገር
ሮጀክት ሥራ - መኪና ከነዳጅ ውስጥ)
አስኪያጅ) ጋር

ቡድን መሪ 5,607 >> መረጃ 10%- 40% 15% 100%


አልተገኘም 20%
ከቡድን መሪ በታች 2,532- - ህክምና ብር መረጃ መረጃ 55% --- 100%
እስከ ጀማሪ መሀንዲስ 4,922 1,800 አልተገኘም አልተገኘ

ከላይ በሰንጠረዡ እንደተመለከተው በሱር ኮንስትራክሽን አንድ የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ የመነሻ ደመወዝ ብር
14,000 ሲሆን የሙያ አበል የደመወዙን 75% (ብር 10,500)፣ የፕሮጀክት አበል የደመወዙን 40% (5,600) የኃላፊነት
አበል የደመወዙን 25% (ብር 3,500) በድምሩ ብር 33,600 ያገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ውጤትን መሠረት ባደረገ
ክፍያ መርህ መሠረት አንድ የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ከታቀደው በላይ ውጤት ሲያስመዘግብ የ 10% ቦነስ ክፍያና
በአገር ውስጥ የህክምና ተቋማት ሙሉ ህክምና አለው፡፡ ይሁንና በአሁኑ ወቅት ሱር ኮንስትራክሽን ከፍተኛ ባለሙያዎችን
እየቀጠረ ያለው በመነሻ ደመወዝ ስላልሆነ ክፍያው ከዚህም በላይ እንደሆነ ይገመታል፡፡
3
በሌላ በኩል የኮርፖሬሽኑን ባለሙያዎች ክፍያ ስንመለከት የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጆች የመነሻ ደመወዝ ብር 6,362
ሲሆን፣ ይህም ከሱር መነሻ ደመወዝ በግማሽ ያክል ያነሰ መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል፡፡ በጥቅማ ጥቅማ አኳያም
ስናየው የኮርፖሬሽኑ ጥቅማ ጥቅም ከሱር ኮንስትራክሽን አንፃር ሲታይ ዝቅተኛ ወይም ምንም የሌለው ነው ለማለት
ይቻላል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ለኃላፊዎች መኪና ከነዳጅ ጋር ያቀርባል፡፡ ይህም ከኢመባ የነበረው ልምድ በመነሳት ሲሆን፣
እሳቤውም አንድ ኃላፊ የበዓላትና የዕረፍት ቀናትን ጭምር እንዲሰራና በጊዜ ስራ ቦታው ላይ ተገኝቶ ስራውን
እንዲያከናውን ለማድረግ በመሆኑ በአመዛኙ የኮርፖሬሽኑን ጥቅም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

ከሱር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአላማ ፈጻሚዎች ማለትም አብራሪዎችና
ግራውንድ ቴክኒሻኖች ከድጋፍ ሰጪው ኃላፊ/ሠራተኛ በተለየ መልኩ የደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ድጋፍ የሚያደርግ
ሲሆን፣ የጤና ጥበቃ ሚ/ር ለጤና ባለሙያዎች፣ የንግድ መርከብ ባለስልጣን ለመርከበኞች የተለየ ደመወዝና ጥቅማ
ጥቅም እንደሚሰጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህም መ/ቤቶቹ ለተሠማሩበት ሥራ ዋና ፈፃሚ የሆነውን ባለሙያ ፍልሰት
ለማስቀረትና ድርጅቶቻቸውን ከኪሳራ ለመታደግ እንደሆነ ግንዛቤ ተይዟል፡፡

ለ/ ዩኒቨርሳል የገጠር መንገዶች ተደራሽነት ፕሮግራም (URRAP)

ሌሎች የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ከሚከፍሉት አማላይ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም በተጨማሪ በመንግስት የተጀመረው
የ URRAP ፕሮግራም መሃንዲሶች እየተደራጁ የራሳቸውን ሥራ እንዲሠሩ የሚያደርግ በመሆኑ በርካታ የኮርፖሬሽኑ
መሃንዲሶች ሥልጠና የወሰዱ ሲሆን፣ ለመልቀቅም በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህም ኮርፖሬሽኑ
ያለበትን የባለሙያዎች ፍልሰት ችግር ይበልጥ ሊያባብሰው እንደሚችል ይገመታል፡፡

ሐ/ የኑሮ ውድነት
በአሁኑ ወቅት በተለይም በምግብና አልባሳት ሸቀጦች ላይ እየተከሰተ ያለውን የኑሮ ውድነት በተመለከተ መረጃ መጥቀስ
የማያሻው ሲሆን ይህም ባለሞያዎች የተሻለ ክፍያ ወደአለበት እንዲፈልሱ እያስገደደ ያለ ጉዳይ ነው፡፡ ምንም
እንኳን የኑሮ ውድነቱ በምህንድስና ባለሙያዎች ላይ ብቻ የተከሰተ ጉዳይ ባይሆንም፣ የሸቀጦች ዋጋ መናር አሁን ያለው
ደመወዝ ቀደም ሲል ይገዛ በነበረው መጠን ሳይገዛ ሲቀር በኑሮ ላይ ችግር የሚፈጥር በመሆኑ ይህንን ችግር ለመቅረፍ
አንዱ አማራጭ የተሻለ የሚከፍል መ/ቤት ማፈላለግ ይሆናል፡፡ ከዚህ አኳያም የኑሮ ውድነት ባለሞያዎችን እንዲፈልሱ
ሊያስገድድ ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ባለሙያዎች ተረጋግተው ሥራቸውን እንዳያከናውኑ የሚያደርግና እንዲለቁም
የሚገፋፋ በመሆኑ ለባለሙያዎች ፍልሰት አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑን ለመረዳት ይቻላል፡፡

4
4. የውሳኔ አስተያየት
ኮርፖሬሽኑ በመአለ ሙከራ ትግበራ ራሱን ችሎ እንዲደራጅ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ እስከአሁን ድረስ ማለትም በአንድ
አመት ጊዜ ውስጥ 46 የሚሆኑ የምህንድስና ባለሙያዎች ስራቸውን ለቀዋል፡፡ በቀጣይም ከ URRAP ጋር በተያያዘ
በርካታ ሰራተኞች በራሳቸው ተደራጅተው ለመስራት የሚያስችል ስልጠና ከኢመባ እንደወሰዱ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በኢመባ ሥር በነበረበት ወቅትም የባለሙያዎች እጥረት ስለመኖሩ በመሠል ጥናቶች የተረጋገጠ ሲሆን፣
ኮርፖሬሽኑ ቀደም ሲልም በከፍተኛ ደረጃ እጥረት ይታይበት የነበረውን የሰው ኃይል ስብጥር ይዞ የወጣ ከመሆኑ ባሻገር
በአሁኑ ወቅት ከፍ ብለው በተጠቀሱት ምክንያቶች ጭምር የምህንድስና ባለሙያ ቁጥር(ሲቪል መሃንዲስ) እየተመናመነ
ይገኛል፡፡ ይህ የሆነበት ዋነኛ ምክንያት ደግሞ በምህንድስና ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎች አጥጋቢና ከገበያው ጋር ተመጣጣኝ
የሆነ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም የሌላቸው በመሆኑ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬሽኑ በዓመት ከ 14,000 ኪ.ሜ የሚበልጥ መንገድ በመገንባትና በመጠገን ወደ 2.7 ቢሊዮን
የሚጠጋ አመታዊ ገቢና 54 ሚሊዮን በላይ አመታዊ ትርፍ ለማስመዝገብ ያሰበ ሲሆን፣ አሁን ባለው ልምድ ያላቸው
ባለሙያዎች እጥረት ይህንን ዕቅድ ለማሳካት የሚቻል እንዳልሆነ ግንዛቤ ተይዟል፡፡ አሁን ያሉት ባለሙያዎች ለጊዜው
ሥራ ፈልገው እስኪያገኙ ድረስ ኮርፖሬሽኑን እንደ መለማመጃ (የሥልጠና ማዕከል) እየተጠቀሙበት እንደሆነ ግንዛቤ
ያለ ሲሆን ከገበያው አንጻር የደመወዝና ጥቅማ ጥቅሙ አነስተኛነት ያሉትም ቢሆኑ የኮርፖሬሽኑን ዓላማ
ለማስፈፀም ተነሳሽነታቸው ዝቅተኛ እንደሆነ በየፕሮጀክቶች በተደረጉ የሥራ ጉብኝቶች ለማየት ተችሏል፡፡

በጥናቱ የውስጥ ይዘት ለመግለጽ እንደተሞከረው መሠል መ/ቤቶች ለምሳሌ ሱር ኮንስትራክሽን ተመጣጣኝ ደመወዝና
ጥቅማ ጥቅም የሚሠጥ ሲሆን፣ እንደ አየርመንገድ፣ የጤና ሚኒስቴርና የንግድ መርከብ ድርጅት የመሳሰሉት መ/ቤቶች
ለአላማ ፈፃሚ የሥራ መደቦች በአንፃራዊነት የተሻለ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም እንደሚሠጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ
የሆነበት ምክንያትም በዓላማ ፈፃሚ የሥራ መደቦች የሚታየውን ፍልሰት ለመግታት እንደሆነ ይታመናል፡፡

በሌላ በኩልም ኮርፖሬሽኑ ሊያተርፍ ካቀደው ገንዘብ አንፃር ለዓላማ ፈፃሚዎች የሚሠጠው ጥቅማ ጥቅም አነስተኛ
መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል፡፡ አጠቃላይ ዓመታዊ ጭማሪው ብር 5.2 ሚሊዮን (ስሌቱ በሰንጠረዥ ተ/ቁ 4.1
ተቀምጧል) ሲሆን ኮርፖሬሽኑ ከ 54 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ለማትረፍ አቅዷል፡፡

በአጠቃላይ ይህንን የሲቪል ምህንድስና ባለሙያዎች ፍልሰት ለመከላከል እንዲቻል የልዩ ልዩ መ/ቤት ተሞክሮ ተወስዶ
በተቋም ደረጃ በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ሲሆን፣ ይህ ተግባራዊ እስከሚደረግ ድረስ አሁን በባለሙያዎች
ዘንድ እየተስተዋለ ያለውን ሥራ ለመልቀቅ የመነሳሳት ጉዳይ ለመፍታት በጊዜያዊነት የሚያገለግል አሠራር በአስቸኳይ
መንደፍ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ የደመወዝ ማስተካከያ ማድረግ ባለሙያዎች ለመልቀቅ የተነሳሱበት ወቅት ከመሆኑ
አኳያ ተጠንቶ እስኪቀርብ ድረስ ጊዜ የሚፈልግ ከመሆኑም በላይ የኮርፖሬሽኑን አደረጃጀት ከመከለስ ጋር መያያዝ
ስላለበት በተፈለገው ፍጥነት የሚደርስ ሆኖ አልተገኘም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የትራንስፖርት፣ የቤትና የፕሮጀክት አበልና
የመሳሰሉት ክፍያዎች አብዛኛውን ሠራተኛ የሚመለከቱ በመሆኑና በሱር ኮንስትራክሽንም ከምህንድስና ባለሙያዎች
5
ውጭ ለሆኑትም ሠራተኞች የሚሰጣቸው ጥቅማ ጥቅሞች በመሆናቸው ከፍተኛ ወጪ የሚያስከትሉ ስለሆኑ አዋጪ
አይደለም፡፡ ይሁንና የሲቪል ምህንድስና ባለሙያዎች የኮርፖሬሽኑ ዋና አላማ ፈፃሚ /Core/ በመሆናቸው የሙያ አበል
ቢከፈላቸው በሌሎች ሠራተኞች ዘንድ የሚፈጥረው ቅሬታና የሚያስከትለው ወጪም አነስተኛ ሊሆን እንደሚችል
ይታመናል፡፡ በሱር ኮንስትራክሽንም ተግባራዊ የሆነ አሠራር በመሆኑም በሌላ ድርጅት ተሞክሮም የሚደገፍ ነው፡፡
ስለሆነም ለሲቪል ምህንድስና ባለሙያዎች የሙያ አበል በጊዜያዊነት መፍቀድ ችግሩ ተቋማዊ በሆነ መንገድ እስኪፈታ
ድረስ የባለሞያዎችን ፍልሰት በመጠኑም ቢሆን ለመቀነስ እንደሚያስችለው ታምኖበታል፡፡

ስለሆነም የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ለኮርፖሬሽኑ የሲቪል ምህንድስና ባለሙያዎች የሙያ አበል
አማራጮች ቀጥለው ቀርበዋል፡፡
ዝርዝር አፈፃፀሙም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ሠንጠረዥ 4.1 የሲቪል መሀንዲሶች ጊዜያዊ የሙያ አበል ፕሮፖዛል

አማራጭ አንድ

የሙያ አበል ድምር የሙያ አበል


የሙያ አበሉ መነሻ
(መነሻ ወርሃዊ
የሚመለከተ ደመወዝ ድምር ወጭ
ተ/ቁ ብዛት ደመወዝ+ አስተያየት
ው የሥራ (አሁን በ በብር ሙያ
መደብ ያለው)
አበል)
1 የመምሪያ/ 21 6,362.00 75 4,771.5 11,133.5 100,201.5 የሙያ አበል የሚሠላው
ፕሮጀክት ባለሙያው አሁን በደረሰበት
ሥራ አስኪያጅ የደመወዝ መጠን ሳይሆን
2 ቡድን መሪ 76 5,607.00 50 2,803.5 8,410.5 213,066
በመነሻ ደመወዝ ነው፡፡ ይህም
3 ሊድ መሀንዲስ 4 4,922.00 40 1968.8 6,890.8 27,563.2
የሙያ አበሉ ጊዜያዊ በመሆኑ
4 ሲኒየር 51 4,313.00 30 1,293.9 5,606.9 65,988.9
መሀንዲስ በአንድ የሥራ መደብ ላይ ያሉ
5 መሀንዲስ 41 2,893.00 20 578.6 3,417.6 23,722.6 ኃላፊዎች/ሠራተኞች
6 ጁኒየር 18 2,532.00 10 253.2 2,785.2 4,557.6 ተመሣሣይ የሙያ አበል
መሀንዲስ እንዲያገኙና በዚህ ረገድ
ድምር 211 --- --- 11,669.50 38,245 435,099.80 ሊፈጠር የሚችለው ቅሬታ
ለመቀነስ ነው፡፡ በተጨማሪም
ወጪን ለመቀነስም
ያስችላል፡፡

6
አማራጭ ሁለት

የሙያ አበል ድምር የሙያ አበል


መነሻ
የሙያ አበሉ (መነሻ ወርሃዊ
ደመወዝ ድምር ወጭ
ተ/ቁ የሚመለከተው ብዛት በ ደመወዝ+ አስተያየት
(አሁን በብር
የሥራ መደብ  ሙያ
ያለው)
አበል)
1 የመምሪያ/ 21 6,362.00 60 3,817.2 11,133.5 80,161.2 የሙያ አበል የሚሠላው
ፕሮጀክት ባለሙያው አሁን በደረሰበት
ሥራ አስኪያጅ የደመወዝ መጠን ሳይሆን
2 ቡድን መሪ 76 5,607.00 45 2223.15 8,410.5 191,759.4
በመነሻ ደመወዝ ነው፡፡ ይህም
3 ሊድ መሀንዲስ 4 4,922.00 35 1722.7 6,890.8 6890.8
የሙያ አበሉ ጊዜያዊ በመሆኑ
4 ሲኒየር 51 4,313.00 25 1078.25 5,606.9 54990.75
መሀንዲስ በአንድ የሥራ መደብ ላይ ያሉ
5 መሀንዲስ 41 2,893.00 15 433.95 3,417.6 17791.95 ኃላፊዎች/ሠራተኞች
6 ጁኒየር 18 2,532.00 10 253.2 2,785.2 4,557.6 ተመሣሣይ የሙያ አበል
መሀንዲስ እንዲያገኙና በዚህ ረገድ
ድምር 211 --- --- 9,528.45 38,245 356,151.7 ሊፈጠር የሚችለው ቅሬታ
ለመቀነስ ነው፡፡ በተጨማሪም
ወጪን ለመቀነስም ያስችላል፡፡

አማራጭ ሦስት

መነሻ የሙያ አበል ድምር የሙያ አበል


የሙያ አበሉ ወርሃዊ
ደመወዝ (መነሻ
ተ/ቁ የሚመለከተው ብዛት ድምር ወጭ አስተያየት
(አሁን በ በብር ደመወዝ+
የሥራ መደብ
ያለው) ሙያ አበል)
1 የመምሪያ/ 21 6,362.00 50 3,181 11,133.5 66,801 የሙያ አበል የሚሠላው
ፕሮጀክት ሥራ ባለሙያው አሁን በደረሰበት
አስኪያጅ
7
2 ቡድን መሪ 76 5,607.00 40 2,242.8 8,410.5 170,452.8 የደመወዝ መጠን ሳይሆን
3 ሊድ መሀንዲስ 4 4,922.00 30 1476.6 6,890.8 5906.4 በመነሻ ደመወዝ ነው፡፡ ይህም
4 ሲኒየር 51 4,313.00 20 862.6 5,606.9 43,992.6 የሙያ አበሉ ጊዜያዊ በመሆኑ
መሀንዲስ
በአንድ የሥራ መደብ ላይ ያሉ
5 መሀንዲስ 41 2,893.00 12 347.16 3,417.6 14233.56
ኃላፊዎች/ሠራተኞች
6 ጁኒየር 18 2,532.00 10 253.2 2,785.2 4,557.6
መሀንዲስ ተመሣሣይ የሙያ አበል
ድምር 211 --- --- 8110.16 38,245 305,943.96 እንዲያገኙና በዚህ ረገድ
ሊፈጠር የሚችለው ቅሬታ
ለመቀነስ ነው፡፡ በተጨማሪም
ወጪን ለመቀነስም ያስችላል፡፡

ከላይ በሲቪል ምህንድስና ከቀረቡት የሙያ አበል አማራጮች መካከል በአማራጭ አንድ የቀረበው አማራጭ ተደግፏል፡፡
የተደገፈበት ምክንያትም፡-

 ካለው የገበያ ሁኔታ አንጻር ከአማራጭ አንድ ውጭ ያሉት የባለሞያዎቹን ፍላጎት በማሟላት ችግሩን
እንደማይፈቱ የታመነበት መሆኑ፣
 ከሌሎች መ/ቤቶች ተሞክሮ አንጻር ሲታይ በሌሎች አማራጮች የተቀመጠው አነስተኛ መሆኑና የሌሎች
መ/ቤቶች ተሞክሮም ለምሳሌ ሱር ኮንስትራክሽን ለፕሮጀክት ሥራ አስኪያጆች 75% የሚሰጠው ከፍተኛ
በሆነ ደመወዝ ማለትም በብር 14,000 እና ከዚያም በላይ ደመወዝ መነሻነት ነው፡፡ ሆኖም ግን የኮርፖሬሽኑ
መነሻ ደመወዝ አነስተኛ በመሆኑ ማለትም 6,362 በመሆኑ ከሌሎች መ/ቤቶች አንጻር ሲታይ አበሉ ዝቅተኛ
በመሆኑ፣
 የሙያ አበሉ በጊዜያዊነት የሚያገለግል ሲሆን በቀጣይ ተቋማዊ በሆነ መልኩ ለመፍታት ጥናት እየተከናወነ
በመሆኑ አበሉ ተመጣጣኝ በሆነ ክፍያ የሚተካ በመሆኑ ነው፡፡

You might also like