You are on page 1of 5

የዋጋ ቁጥጥር አመራርና አስተዳደር ረብ /በሲቪል መንዲስ ዮሐንስ ብዙነህ

ከሀዋሳ-ኢትዮጲያ /ክፍል ፩

1. መግቢያ
የዋጋ ቁጥጥር አመራር /Cost Management & Control የግንባታ ተግባራትን የሚያከናውኑ ድርጅቶች፣
ኩባኒያዎች፣ ኢንተርፕራይዞች ፣የግል ተቋሯጮች ኮርፖሬሽኖች፣ወዘተ በጣም ተጨባጭ ዋጋ ያለውና
ሊተገበር የሚገባ ራሱን የቻለ የማስተዳደር ስራን ሊሰር እንደሚጠበቅባቸው የሚያስረዳ ነው፡፡

ክልሎች ያለባቸውን የኢንፍራ ስትራክቸር እጥረት ይቀርፍላቸው በሚል የግል የግንባታ ተቋሯጮች
የማይገቡበትን ቦታዎች ግንባታ ስራ ለመሸፈን ይረዳቸው ዘንድ ጭምር በማሰብ የመንግስት የሆኑ የቤቶች
ልማት ፣የጉድጓድ ቁፋሮና መጠጥ ውኃ ፣የመንገድና ድሬኔጅ ፣ወዘተ ግንባታ ኢንተርፕራይዞች ቀስ በቀስ ደግሞ
ካፒታልና አቅማቸው ያደገውን ደግሞ ኮርፖሬሽን እያለ የሚያስተዳድራቸውን ተቋማት መፍጠር እንዲችሉ
የፌደራል መንግስት ድጋፍ የሰጠ መሆኑ እሙን ነው፡፡

ሆኖም ግን እነዚህ መንግስታዊ የተለያየ ግንበታ ተቋራች የመንግስት የልማት ድርጅት ውስጥ የሚካተቱት
ተቋማት የግንባታ ፕሮጀክቶቻቸውን ኮስት አመራርና ቁጥጥር ስራ በተገቢው መልኩ ያስፈፅማሉ ተብሎ
ይታሰባል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ግን በምን መልኩ እየተገበሩት እንዳለ እውቀቱ ያላቸው እነሱ ብቻ ናቸው
የሚለውን በድርበቡ ተስማምተን በቀጣይነትም ለፕሮጀክቶቻቸው ክንውን ፍጻሜ ማማር ያለውስ ፋይዳ
ምንድነው ብለው መጠየቅም ያለባቸው እነሱ ብቻ ናቸው ብለን ሌላውን ነገር እንዳስስ፡፡

አንዳነድ ክልልላ ባሉት መሰል ተቋማት አሁን እየታየ እንዳለው በአሉታው አስተሳሰብ /Negative Energy
እያመነጩ የፕሮጀክት አፈጻጸም ስኬታቸውን ጎጂ እንዲሆን ከሚያደርግ ከውስጥ ሰራተኞቻቸው
እንደሚሰዬል ተወንጫፊ ክፉ አስተሳሰቦች ፣ከአሰሪ፣አማካሪና ባለድርሻ አካላት ዘንድ የሚንጸባረቁ ጎታች
ሁኔታዎች አንጻር ግን የተቋሟቱን መስፈንጠር በእጅጉ የሚጎዳው ይሆናል፡፡የእርስ በርስ ሽኩቻ ፣መጠላለፍ፣
መሰለቃቀጥና ብሎም ሥራን ከመስራት ይልቅ ሀሜተኛ ፣አሉባልተኛ ፣አልባሌ ቦታ ላይ የሚውሉ አንዳንድ
ሰዎችን ፈጥሮ የአንድን ድርጅት ዓላማ፣ራዕይና ተልዕኮና ከማቀዛቀዝ አልፎ እስከማንኮታኮት የሚያደርስ
ይሆናል፡፡

በእንዲህ አይነቱ ሂደት ውስጥ ሲታለፍ “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብር ዝረፍ” እንዳሆን ጥንቃቄ ከወዲሁ
ካልተበጀና የኮስት ቁጥጥር አመራርና አስተዳደር ስራን በፅኑ መስራት ካልተቻለ ወድቀታቸው ሊፋጠን
የሚችል ተቋማት እንዳይኖሩ ያሰጋል፡፡

በኮስት ቁጥጥር አመራር ስኬት ጉድለት የሚሰቃዩ የግል ሥራ ተቋሯጮች ፣የመንግስት የልማት ተቋማት የሆኑ
የግንባታ ኢንተርፕራይዞችና ኮርፖሬሽኖች ካሉ ዘለቄታቸውን ለማረጋገጥ የኮስት አመራራቸውንና የአመራሩን
ሂደት በመፈተሸ ሠራተኞቻቸውን ወደ ተገቢ ዘዴ /efficient system የሚያስገባ ሥራን መስራት ላይም ሆነ
የአመራርና አመራሮች የመለወጥ ስራን አስከመፈጸም ድረስ የሚደርስ ውሳኔን እንደትልቅ ሁኔታ ሊያዩት
ይገባል፡፡

1.1. ዓላማ
የዚህች ብጣቂ አስተሳሰብ ውጤት የሆነውን የኮስት ቁጥጥር አመራር አስፈላጊነት በመጠኑ የሚገልጽን
አሳብን የግንባታ ፕሮጀክቶች የኮስት አመራርን ሂደት ለማሳየት የሚሞክርና በአነስተኛ ሁኔታም ቢሆን በስሱ
ለመግለጽ የተሞከረ ሲሆን ፡-
 የፕሮጀክቶችን ኮስት በአግባቡ መምራትን፣

1
 የኮስት ቁጥጥርና አመራርን ስልጠት ማጉላትንና
 ተገቢ የሆኑ የአሰራርን ስልት ለኮስት ቁጥጥርና አመራር ማበጀት

ያስችላል የሚል እሳቤን በመያዝ ለዚህ ትግበራም ይረዳሉ የተባሉ አሳቦችን ለማንጸባረቅ ነው፡፡

2. የግንባታ ፕሮጀክቶችን በአግባቡ /efficiently መምራት


የትኛውንም አይነት ፕሮጀክቶችን መምራት ቀላል እንዳልሆነ ይታወቃል ፡፡ በእኛም አገር ቢሆን ለፕሮጀክት
አመራር እቅድ እንዲሁም ለግንባታ አመራርና ቴክኖሎጂ ቦታ ተሰጥቶት በመንግስትም ሆነ በግል የከፍተኛ
ትምህርት ተቋማት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥቂት የማይባሉ በዚህ መስክ የተማሩ ሙያተኛ መሀንዲሶችን
ማፍራት እየተቻለ ነው፡፡

ይሁን እንጂ የግንባታ ፕሮጀክቶች በእቅድ ላይ ተመርኩዘው በመስራት ላይ በማበከር ተቋማታቸውንም


የሚመሩት በስትራቴጂክ እቅድ ተመርኩዘው ነው ወይ? የሚለውን የሚመልሱት እነዚሁ ተቋማት ብቻ
ናቸው፡፡ በዚህም ክንውን ስልጠት ውስጥ ምን እንደጎደላቸው ፣የቱ መሻሻል እንደሚገባው፣በምን መልኩ
በአግባቡ /efficiently ሊከናወኑ /perform እንደሚገባ ሊፈትሹ ይገባል፡፡ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ፕላት ፎርም
አዘጋጅተው ወይም ኖሯቸው ምን ሊያስተላልፉና ሊተነትኑ እንደፈለጉ ፕሮግራማቸውን እንደሚገልጹት ሁሉ
የተለያዩ ፕሮጀክቶችም በአንድ ፕሮግራም ውስጥ ተካተው ሊመሩ እንደሚችሉ የታወቀ ቢሆንም እንቋን
በምን መልኩ ሊመራ እንደሚገባ ግን በሳይንሳዊ መንገድ በተደገፈ የተቀመጠ አቅጣጫ ተቋማቱ ሊኖራቸው
ይገባል፡፡

ስለሆነም አግባብ ያለው የኮስት ማኔጅመንት አስፈላጊነት ከግምት አስገብተው የፕሮጀክት ኮስትን በአግባቡ
ሊመሩ ይገባቸዋል ፡፡ የግንባታ ፕሮጀክትን በአግባቡ /efficiently ለመምራት የሚያስፈልጉ አምስቱ ደረጃዎች
/Steps ውስጥ በዚህ ክፍል አንድ ላይ ለአሁን ሁለቱን እንያቸው፡፡

2.1. የእያንዳንዱን ፕሮጀክት ዝርዝር የኮስት ቁጥጥር አመራርና አስተዳደር እቅድ


ማዘጋጀት
ይህን ማድረግ የሚረዳው የግምት ሂደቶችን /estimation procedures መርህ ያለው /standardizing
ለማድረግ ነው፡፡በዚህ ሂደት ውስጥ የሚታየውም:-
 የሁኔታዎች ግምትን /assumptions ፣ጉዳትን /risks ና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ያልተገመቱ
ሁኔታዎችን / uncertainties ነቅሶ /capture የማውጣት ሥራ የሚሰራበትን ፣
 ክስተቶችን /events ሁኔታዎች መዘመናቸውን /updated ለማረጋገጥ
 የገንዘብ ግምትን /estimates በምልክት አሳዮች ወይም አመላካቾች /milestones አማካኝነት
በማዘመን /updated በማድረግ
 መርሀ-ግብር፣
 ዋና የአይነቶች ብዛት/Major Items quantities ወይም ነጠላ ዋጋ ብዛት /unit
cost quantities ና
 ዓላማ/Scope

በትልቁ ተለውጠው /big changed እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህም አንጻር እቅዱን ማዘጋጀት ተገቢና
አስፈላጊ መሆኑን ከላይ ከተገለጸው አሳብ አንጻር መገንዘብ ስፈልጋል፡፡ እቅድም ወደ ተግባር መቀየር ስላለበት
እቅድን አስተወሎ ማቀድ ወደ ተግባር ሲቀየር ውጤታማ እንዲሆን ይረዳዋል፡፡

2
2.2. ኮስትን መበጀት /Cost Budgeting
ይህ ማለት የእያንዳንድ ተግባራት ወይንም ጥቅል ሥራዎች /individual activities or work packages
የተገመቱ ኮስቶችን /estimated costs የኮስት ሞዴል ወይም መመዘኛ /standard (cost baseline)
ለመመስረት እነዚህን ማጠናቀሪያ ወይም መቀላቀያ ነው፡፡

በእያንዳንዱ ነጠላ የተግባራት መርሀ-ግብር ወይም ጥቅል ሥራ /individual schedule activities or work
package ተመስርቶ የፕሮጀክት ክንውንን ለመለካት የሚያገለግል ኮስት ሞዴል ለማበጀት እንዲቻል ይህ
ሞዴል ወይም መመዘኛ /baseline በእጅጉ ይረዳል፡፡በጀት ማለት እቅድን ወደ ገንዘብ የሚቀይሩበት መንገድ
ስለሆነ አስፈላጊ የሆነውን ገንዘብ ለታቀደለት ተግባር ማዋልን የሚጠይቅ ነው፡፡

3. የዋጋ ቁጥጥርና አመራርን ለማሳለጥ የሚጠቅሙ ጭብጦች


በዚህ አሳብ ዙሪያ የሚጠነጠኑት ጭብጦች ኮሰት፣ቢሊንግ፣ተከፋዮች /payable ፣የሚቀበሉት /Receivable
፣በአንድ ነጠላ አካውንት ወጪዎችን/expenditures እና የተቀበሉት/ receipts የተባሉትን ሁሉ አካቶ
የፕሮጀክትን የገንዘብ ሁኔታን /cash positions የሚያሳይ ነው፡፡ለዚህ የዋጋ ቁጥጥር አመራርና አስተዳደር
ስርፀት የሚጠቅሙ አሳቦች ውስጥ አራቱ የኮስት አመራር ደረጃዎች /four steps የሚከተሉትን ይመስላሉ:-
 የፕሮጀክት ሀብት እቅድ /project process planning
 የዋጋ ግምት/cost estimation ይህ የዋጋ ግምት እንደ ውሳኔ አሳላጭ ወይም
ፈቃጅ /cost estimation as decision enabler
 ኮስትን መበጀት /cost budgeting እና
 የኮስት ቁጥጥር/cost control ናቸው:

የፕሮክት ኮስት አመራር በአንድ ፕሮጀክት ሂደት ውስጥ /life cycle of a project ወጪዎች ከጸደቁ በኃላ
የፕሮጀክት ኮስት ጭብጥ የሆኑትን /objective of project cost የፕሮጀክት ኮስትን የመገመት፣የመበጀትና
የመቆጣጠር ሂደትን ተከትሎ መምራት የሚል ፅንሰ አሳብን የያዘ ነው፡፡

የአንድን ፕሮጀክት ስኬት ለማምጣት የዋጋ አመራር፡-


 በዓላማ /scope እና አስፈላጊነት /requirements ላይ የሚያበረክተው ወይም የሚያመጣው
አበርክቶት /delivers አሉት ፣
 የአፈጻጸም ጥራቱ በከፍተኛ መመዘኛ / high standards መሰረት ነው፣
 በመርሀ-ግብሩ መሰረት እንዲፈጸም ያደርጋልና
 በበጀት እንዲከናወኑ ያደርጋል

የሚሉት መረዳት ኖሯቸው የዋጋ ቁጥጥር አስፈላጊነት የእውነተኛ ህይወት ተምሳሌት ስለሆነ በቀላሉ
የሚረዱት /understand ጉዳይ ነው፡፡

3.1. የግንባታ ፕሮጀክት የዋጋ አመራርን ሂደት ከዋጋ አዋጭነት /benefit


cost ratio or cost benefit ratio ጋር ማስተሳሰር
የዋጋ አዋጭነት ስልት በስሌት ውል ሳይገባ በፊት የሚጀምር ሂደት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ከገበያ ዋጋ ጥናት
፣የስራ መዘርዝር ፣የምርት ካታሎግና ስፔስፊኬሽንስ ዝግጅትና የግንባታ ጥራትና ቁጥጥር ሂደት ለይቶ ማየትን
የሚፈልግም ነው፡፡

3
ፕሮጀክቶች የሚሰሩበትን የሳይት ነባራዊ ሁኔታ /site condition ማወቅ፣ ባህሪውን መለየት፣ ቶፖግራፊውን
መገንዘብ ፣ተግዳሮቶቹንና ጉዳቶቹን እየነቀሱ ማውጣት ፣የአካባቢውን ማህበረሰብ የስራ ባህሪና ልምምድ
ከምርታማነት ጋር አዛምድ መተንተንና የስራ ላይ አበርክቶቱን ከተቀመጠው መለኪያ ኖርም መሰረት
ስለመሆን አለመሆኑ ወዲያውና ወቅታዊ ሪፖርትን ማዳበርን ጨምር በተፈለገው የሰራተኛ የሙያና የጉልበት
ስብጥር መሰረት ስለመሆኑና ከተበጀተው ኮስት ጋር ስለመጣጣሙ ግንዛቤው ሊኖር ይገባል፡፡

የዋጋ አዋጭነትና ትርፋማ የሆነ ስራን መስራት የሁሉም ፍላጎት ቢሆንም ይህን የተባለውን በውጤት
ተመርኩዞ ማግኘት መቻል ግን ብዙ ጥረትንና ብዙ ልፋትን የሚጠይቅ በብዙም ሰራ የሚፈልግ ነው፡፡ለዚህም
ራሳቸውን የሰጡ፣ለጥቅም የማይገዙ ፣የዋጋ አመራሩ ገብቷቸው በብቃት ሂደቱን የሚያሳልጡ ብቁና ልምድ
ያላቸውን ማግኘት የሚፈልግና በሌብነትና ስርቆት የሚገኝ ጥቅምን የሚጠየፉ ሰዎችን ወደቦታው
ማምጣትን የሚጠይቅ ነው፡፡

ስለሆነም በዘር ፖለቲካ ሳይሆን በብቃት ፣ችሎታና ለቦታው መመጠንን ማዕከል አድርጎ በሜሪት መንቀሳቀስ
የልማት ድርጅቶችን ከውድቀት የሚታደግ እንደሆነ ሊታወቅ ያስፈልጋል፡፡አብዛኛውን ጊዜ ሲታይ ግን ብቁ
ባለሙያዎች እውነታን ይዘው ሲታገሉ ገሸሽ የማደረግ ዝንባሌ የሚታይ በመሆኑ በትርፍ ለሚተዳደሩ ተቋማት
የሚሾሙና ለኃለፊነት ወንበር ታጭተው የስልጣን መንበሩን የሚቆናጠጡ ተሿሚዎች ግን በደንብ ቀድመው
ሊፈተሸ ይገባል፡፡

3.2. የግንባታ ፕሮጀክት ኮስት አመራርና አስተዳደር መሰረታዊ መርህ /construction


cost management & administration basic principle
በትልቅ ዳታ ላይ ተመርኩዞ የፕሮጀክት ኮስት ቁጥጥርና አመራርን /project cost control & management
ማካሄዱ ጥቅም ሰጪ ሲሆን በዋናነት የሚተገበረው የተለያዩ በፕሮጀክቱ ዙሪያ ያሉ መረጃዎችን የመሰብሰብ
፣የመለየትና የማጠናቀር ስራን በመስራት ነው፡፡ይህን ተመርኩዞ ከግንባታ ዲዛይን መቀያየር ጋር ያሉ
ትንተናዎችን ለማዳበር እንደ ቴክኒካል መፍትሔ /means የሚጠቅም ስለሆነ ለዳታዎች ትልቅ ትኩረት ለሰጥ
ይገባል፡፡ የፕሮጀክት ኮስት አመራርና አስተዳደር /project cost management & administration መሠረታዊ
መርህ በፕሮጀክት ኢንቬስትመንት /project investment ፣ዕድገት /progress እና ዋጋ /cost ዘንድ ለውን
ትስስርና ዝምድና ተከትሎ ለማስተዳደርና ለመምራት የሚያስችል ነው፡፡

ስለሆነም በዚህ ሂደት የምንከተለው ነገር ቢኖር የስራ መጠንና ዋጋን መለየት/ separation of quantity &
price ሲሆን ይህም የሚከናወነው ወደ አንድ የዳታ ምንጭ /data source በመዝመም በትክክለኛው
የግንባታው ደረጃ / actual construction stage ጊዜ ሁሉም ዳታዎች ቢሆን ከመረጃ ዳታ ክፍል / data group
እንዲመነጩ በማድረግ /all generate ነው፡፡

የኢንቬስትመንት ግምት ማካሄድ በኮንትራክት ሁኔታና የግንባታ ፕሮጀክት የግንባታ ዕድገት ባህርይ /contract
condition & characteristics of construction projects ሳይንሳዊና ምክንያታዊ መንገዱን ተጠቅሞ
አጠቃላይ የግንባታ ፕሮጀክቱን ወጪዎች /using scientific & reasonable method calculating the total
expenditure የማስላት ስራን መስራትን የሚፈልግ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ይህም ሶስት ገፅታዎች ወይም
ክፍሎች ያሉታና እነሱም፡

 የቴክኒካል ኢኮኖሚክስ አመላካቾች /technical & economic indicators


 የካፒታል ፍጆታ መንስዔ /factors that are capital consumptions ና
 የጫናው ደረጃና የምክንያቶች ዲግሪ /influence degree & quantity of factors ናቸው፡፡

4
እነዚህም በዝርዝር ሲታዩ የዋጋ ቁጥጥር የልኬት ማረጋገጫ ጥራት /quality assurance measure፣ የፕሮጀክት
ላይ ኮስት ቁጥጥር /on project cost control እና ዋጋን መወሰን /determine the cost የተነሳ የዋጋ ቆይታ
ጊዜውን /duration እና የፕሮጀክት የኮስት ደረጃ /cost level of construction project እና የከፍተኛና
ዝቅተኛ ዋጋ መለኪያዎችን /standards አመዳደብን ተከተሎ በመምራት /classification of high & low
prices ሊሆን ይገባል፡፡

ስለሆነም የአጠቃላይ በጀት አስተዳደር ዘዴ /comprehensive budget management system ጉልበታም


ማስተካከያን /dynamic adjustment እና የግንባታ ፕሮጀክት የአጠቃላይ የተተከለ ወጪና የጉልበት ዋጋ ተመን
ሂደት ፍሰቱ አጠቃላይ ወጪ ቆጣቢ አጠቃቀም የሆነ እንዲሆን የማድረግ እሳቤን /optimization of the total
cost expenditure & labors rate of the construction project realization የያዘ ሊሆን ይገባል፡፡

ከነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ተለዋጭ ቅድመ ቁጥጥር መንገድ /flexible pre-control method ወይም በኮታ
ነጥሎ ማውጣት /quota pricing method መንገድ ወደ ራስ ሁኔታ በማስማማት /adopt የግንባታ ፕሮጀክት
የግንባታ ማቴሪያል ምክንያታዊ በሆነና በተጠና መንገድ ሊቀርብና ሥራ ላይ ሊውል/reasonably dispatch the
materials consumption of the construction site የሚገባ ከመሆኑ ጋር ተቆራኝቶ የእግር ተግር ክትትል
፣ቁጥጥር ፣ትንተናና ተጨባጭ የሆነ በሳይንሳዊ መንገድ የተደገፈ ሂደትን አልፎ ሪፖርትም ጭምር ሊቀርብ
የሚገባ እንደሆነ ግልፅ ሊሆን ይገባል፡፡ የፕሮጀክቱን ወቅቱን የጠበቀ ግብረ-መልስ /timely feedback
ስለመገኘቱና ተዛማጅ የሆኑ ክፍሎችም ቢሆን ከሚመለከተው ክፍል በላይ ትንተናውን ማወቅ
ባይጠበቅባቸውም እንኳን የወጪዎቹንና የዋጋ ቁጥጥር ሂደቱን ሊገነዘቡ በሚችሉበት ልክ በግብረ መልስ
አሰጣጥ ውስጥ ሊካተቱ ይገባል፡፡

የፕሮጀክት ኮስት ቁጥጥር አመራርና አስተዳደር ስራ ትኩረት የሚሻና በሚገባ ሊከናውን የሚገባ ሲሆን
የግንባታ ስራ ተቋሯጮች ከግሉ ይልቅ በተለይ የመንግስት የሆኑት ጠንክረው ሊታዩ የሚገባ እንደሆነ መታወቅ
አለበት፡፡በይበልጥ የኮስት ቁጥጥር እቅድን በማቀድ ወጪ ቆጣቢ የሆነ አመራርን በማካሄድና የበላይ
አመራሮቹም ቁርጠኛ ውሳኔን እያደረጉ ተገቢ የሆነ የአፈጻጸም ግምገማን እነሱ ተገቢ ብለው በወሰኑት ጊዜ
ውስጥ እያካሄዱ ውጤቱን መፈተሸ ይገባቸዋል፡፡

ከዚህም ሂደት ምርጥ ተሞክሮን በመቀመር የተሻሻሉ አሰራሮችን በዘመነ መልኩ ማካሄድም ተግባራቸው
ሊያደርጉት ይገባል፡፡ ለወጪዎችና ለአወጣጣቸው እንዲሁም አወጣጣቸውም በታቀደውን በተገቢው መንገድና
ትንተና አልፎ ስለመሆኑ የብሬክዳውን ተዓማኒነትን ስለማረጋገጥና በተግባር በተለይም መስክ ላይ የተሰሩ
ስራዎችን ውጤቶች በመፈተሸ ረገድ ትልቅ ትኩረት አድርገው በኃይል ሊንቀሳቀሱ ይገባል፡፡ በተለይም ይህን
ስራ የሚሰሩትን የማመን ዝንባሌ ሊኖር ነገር ግን እነዚህኑ ተግባሪዎች የመቆጣጠሪያ መንገድን /cross
checking methods የረቀቀና የሰፋ እንዲሆን ማድረግ ለጥፋቶችም ልጓምን ማበጀትና ሀይ ማለት
የሚያስችል ስልትን ማበጀት የግድ ይላል፡፡

ላይ ላዩን ሲታይ ቀላል የሚመስለው ነገር ግን የትኩረት አቅጣጫን ወደሱ ማድረግን የሚጠይቀው የፕሮጀክት
ኮስት ቁጥጥር አመራርና አስተዳደር ስራ ከጭቅጭቅና ሙጉት ነፅቶ የሚሰራበትን መንገድ ቀድሞ መተለምና
ማቀድ ከእነዚህ ተቋማት የሚጠበቅ ሲሆን ይበልጥ ማዘመኑና ከብክነት፣ስርቆት፣ማጭበርበርና ሙስና እየጸዳ
እንዳለ ፓራሜትር አስቀምጠው በመለካት የግምገማቸው አካል ሊያደርጉት ይገባል የሚለው ይበልጥ
የሚያግባባ የሚመስል ግን ደግሞ ብዙ መሪዎች የማይወዱትና ላይ ላዩን እያስመሰሉ በውስጣቸው ግን
የሚገፉት ሀቅ ነው፡፡

You might also like