You are on page 1of 37

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት አዋጅ

(የመጀመሪያ ረቂቅ)
መግቢያ

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሰረተ ልማቶችን በመገንባት፣ ሰፊ የሥራ ዕድሎችን


በመፍጠር እና ድህነትን በመቀነስ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ የማይናቅ ሚና የሚጫወት በመሆኑ፣
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በመንግስት ከፍተኛ በጀት የሚመደብለት እና ሰፊ የግል ዘርፍ መዋዕለ ንዋይ
የሚፈስበት በመሆኑ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ጥራትና ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲሰሩ ለማድረግ፣
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው አለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ በተረጋጋ እና እድገትን በሚያበረታታ
አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ማድረግ አሰፈላጊ በመሆኑ፣
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 55 (1) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

ክፍል አንድ
ጠቅላላ ድንጋጌ
አንቀጽ 1፡ አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ ”የኮንስትራክሽን ኢንዱሰትሪ ልማት አዋጅ ቁጥር……/2014” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
አንቀፅ 2. ትርጓሜ
በዚህ አዋጅ ውስጥ፡-
1) “ሚኒስቴር” ወይም “ሚኒስትር” ማለት እንደቅደም ተከተሉ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ወይም
ሚኒስትር ነው፡
2) “ኮንስትራክሽን” ማለት ከመሬት በታች እና በላይ የሚከናወኑ የህንጻን እና ሌሎች የምህንድስና የመሰረተ
ልማት ሥራዎችን ጨምሮ በቋሚ ንብረቶች ላይ የዕቃዎች እና አገልግሎቶች ጥምር የሆነ የልማት፣
የማስፋፈት፣ የመገጣጠም፣ የጥገና፣ የዕድሳት፣ የማሻሻል፣ የቁፋሮ፣ የማወላለቅ እና የማፍረስ ተግባር
ነው፡፡
3) ”የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ" ማለት የተለያዩ ተፈጥሯዊና የተመረቱ ግብዓትንና ሀብቶችን ለማህበራዊ
እና ኢኮኖሚያዊ ልማት አስፈላጊ ወደ ሆኑ የግንባታ ውጤቶች የሚለውጥ፣ ቋሚ ንብረቶችን በመፍጠር
እና በመንከባከብ ላይ እሴት የሚጨምሩ ኢንዱስትሪዎች እና ዘርፎች ሰፊ ስብስብ ነው፣
4) "ኢንዱስትሪ" ማለት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ነው፣
5) “ተዛማጅ የኮንስትራክሽን ሥራ” ማለት ለኮንስትራክሽን ሥራ ተዛማጅ የሆኑ የአገልግሎት ወይም
የአቅረቦት ሥራዎች ላይ በተሰማሩ ሰዎች፣ የኮንስትራክሽን ግብአቶች፣ መሳሪያዎችና መገልገያዎች
አቅራቢ፣ አስመጪ፣ ላኪ፣ አከራይ በመሳሰሉት ሰዎችና ድርጅቶች የሚከናወን ተግባር ነው፡፡
6) "አሠሪ" ማለት የኮንስትራክሽን ወይም የምክር አገልግሎት ወይም የአቅርቦት ሥራ እንዲሰራለት
የሚፈልግ ሰው ወይም ድርጅት ነው፣
7) "ሥራ ተቋራጭ" ማለት ሕጋዊ ሥልጣን በተሰጠው አካል ተመዝግቦ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሥራ
ተቋራጭነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት የተሰጠው እና በንግድ ሥራ ሂደት ወይም እድገት ውስጥ
የኮንስትራክሽን ሥራዎችን የሚያከናውን፣ የሚመራ ወይም የሚቆጣጠር ነው፣
8) “ ንኡስ ተቋራጭ” ማለት በግንባታ ውል ውስጥ የሚሠራው ሥራ በኮንትራክተሩ ወይም በሌላ ንዑስ

ተቋራጭ የተገዛለት ሰው ነው፤


9) "አማካሪ ድርጅት" ማለት ሕጋዊ ሥልጣን በተሰጠው አካል ተመዝግቦ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የአማካሪነት
የምዝገባ የምስክር ወረቀት የተሰጠው እና የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው ድርጅት ነው፣
10) "ባለሙያ" ማለት ሕጋዊ ሥልጣን በተሰጠው አካል ተመዝግቦ በዲዛይን ወይም በኮንስትራክሽን
ባለሙያነት የምስክር ወረቀት የተሰጠው ባለሙያ ነው፣
11) “ድርጅት” ማለት በኮንስትራክሽን እና ተዛማጅ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ላይ የተሰማራ የግል ንግድ
ወይም የንግድ ማህበር የሆነ የንግድ ተቋም ነው፡፡
12) “አመልካች” ማለት ኮንስትራክሽን ወይም ተዛማጅ የኮንስትራክሽን ሥራ ላይ ለመሰማራት ፈልጎ
የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለማግኘት ማመልከቻ ያቀረበ ሙያተኛ ወይም ድርጅት ነው፡፡
13) “የምስክር ወረቀት” ማለት አግባብ ባለው ሕግ መሠረት የሚጠየቁ መስፈርቶችን በማሟላት ለተመዘገበ
ሰው የሚሰጥ የምዝገባ ማረጋገጫ ነው፡፡
14) “የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት” ማለት አግባብ ባለው ሕግ መሠረት የሚጠየቁ መስፈርቶችን
ላሟላ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ሲሆን፡- የክፍያ፣የብቃት፣ የርክክብ፣የእውቅና፣የመልካም ስራ አፈጻጸም፣
የዋስትና/warranty, የብልሸት/defect እና ሌሎችንም የሚያጠቃልል ነው፡፡
15) “ፕሮጀክት” ማለት የህንጻና ሌሎች መሠረተ ልማቶች ወይም ከኮንስትራክሽን ሥራዎች ጋር ተያያዥ
የሆኑ ሌሎች ከኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ናቸው፤
16) "ፈቃድ" ማለት በኢንዱስትሪው ተለያዩ ስራዎች ፣አገልግሎቶች ላይ ለመሰማራትም ሆነ በየደረጃው
ያሉ ስራዎችን እና አገልግሎቶችን ለማለከናወነወ በሚመለከተው አካል የሚሰጥ ፈቃድ ሲሆን፡- የሥራ
ፈቃድ፣ የግንባታ ማስጀመሪያ ፈቃድ፣ የመጠቀሚያ ፈቃድ፣ የግንባታ ፈቃድ እና ሌሎችንም
የሚያጠቃልል ነው፡፡
17) ”ፌደራል” ማለት
18) ”የኮንስትራክሽን ደረጃዎች” ማለት
19) ”የኮንስትራክሽን አይነቶች” ማለት
20) “ሙያተኛ” ማለት በምህንድስና፣ በስነ ህንጻ እና ሌሎች የኮንስትራክሽን ሙያዎች የሰለጠነ ሰው ነው፡፡
21) “መዝገብ” ማለት የሙያተኛ፣ የድርጅት፣ የፕሮጄክት እና የተዛማጅ የኮንስትራክሽን ሥራዎች የተደራጀ
መረጃ የሚያዝበት መዝገብ ነው፡፡
22) “የተመዘገበ ሙያተኛ” ማለት በዚህ አዋጅ በተገለፀው መሰረት ያሉትን ልዩ ልዩ መስፈርቶች አሟልቶ
የተመዘገበ ሙያተኛ ነው፡፡
23) “ምዝገባ” ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት ስም እና ሌሎች ዝርዝሮችን የያዘ የኮንስትራክሽን ሙያተኞች፣
ባለሙያዎች፣ ተዛማጅ የኮንስትራክሽን ሥራ የሚሰሩና የሥራ ተቋራጮች፣ የኮንስትራክሽን አማካሪዎችና
የፕሮጀክቶች ምዝገባ ነው፡፡
24) "ተዋናይ" ማለት በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ በኮንስትራክሽን ሥራ፣ በምርት ወይም
በአገልግሎት ወይም በአቅርቦት ቀጥተኛ ተሳትፎ ያለው ግለሰብ ወይም ድርጅት ነው፣
25) "ባለድርሻ አካል" ማለት በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የሚመለከተውና ያገባኛል የሚል አካል ነው፣
26) "ቀጥተኛ ባለድርሻ አካል" ማለት በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ በኮንስትራክሽን ሥራ፣ በምርት
ወይም በአገልግሎት ወይም በአቅርቦት ቀጥተኛ ተሳትፎ ያለው ግለሰብ ወይም ድርጅት ነው፣
27) "ቀጥጠኛ ያልሆነ ባለድርሻ አካል" ማለት በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ ማንኛውም
ይመለከተኛል ወይም ያገባኛል የሚል ግለሰብ ወይም ድርጅት ነው፣
28) “ክልል ማለት በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 47 መሠረት የተቋቋመ አካል ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ እና
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን ይጨምራል፣
29) “የከተማ አስተዳደር” ማለት በሕግ ወይም በሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ውክልና የከተማ አስተዳደር
ሥልጣን የተሰጠው አካል ነው፣
30) "የግንባታ ደረጃ እቅድ" ማለት የጤና እና የደህንነት ዝግጅቶችን, የቦታ ደንቦችን እና ለግንባታ ስራ ልዩ

እርምጃዎችን የሚመዘግብ ሰነድ;

31) “የቅድመ-ግንባታ ደረጃ” ማለት ለአንድ ፕሮጀክት የሚከናወን ፣ በግንባታው ደረጃ ሊቀጥል የሚችል የንድፍ ወይም

የዝግጅት ስራ የሚከናወንበት ጊዜ ነው።

1) “የቅድመ-ኮንስትራክሽን ፍተሻ” plan-in-hand inspection ማለት ሊገነባ የታሰበው ፕሮጀክት በተመለከተ


የተዘጋጀውን የመጀመሪያ ዲዛይን በመያዝ በዲዛይነሩ፣ በአማካሪው ወይም በአስገንቢው ተወካይ አማካኝነት
ፕሮጀክቱ በሚሰራበት መስክ በመገኘት በፕሮጀክቱ አግባብነት relevancy፣ ተተግባሪነቱ constructability፣

የፕሮጀክቱ እቅድ እና ስፔስፊኬሽን specifications የተሟላ መሆኑን የሚረጋገጥበት የንድፍ ወይም የዝግጅት

ስራ የሚከናወንበት ጊዜ ነው።፡

32) "የግንባታ ቦታ"ማለት የግንባታ ሥራ በሚካሄድበት ወይም ሠራተኞቹ የሚደርሱበት ቦታን ያጠቃልላል, ነገር ግን

በቦታው ውስጥ ከግንባታ ሥራ ውጭ ለሆኑ ዓላማዎች የተመደበውን የሥራ ቦታ አያካትትም;

33) “የግንባታ ምዕራፍ” ማለት በማንኛውም ፕሮጀክት ግንባታ የሚጀመርበትና የዚያ ፕሮጀክት ግንባታ ሥራ

ሲጠናቀቅ የሚያልቅበት ጊዜ ነው።

34) “ፕሮጀክት ባለቤት ” ማለት ፕሮጀክት የሚካሄድለት ማንኛውም ሰው ነው፤


36) “ንድፍ” ስዕሎችን፣ ለአንድ መዋቅር ጋር የሚዛመዱ እና ለ የአንድ ንድፍ ዓላማ ሚዘጋጅ የንድፍ ዝርዝሮችን፣

ዝርዝሮችን እና የመጠን ሂሳቦችንና የዕቃ ዝርዝር ስፔሰፊኬሽን ያካትታል

37) “ዋና ሥራ ተቋራጭ” ማለት በአንቀፅ 5(1)(ለ) ከአንቀፅ 12 እስከ 14 የተዘረዘሩትን ተግባራት እንዲያከናውን

የተሾመ ኮንትራክተር ነው።

38)“የሥራ ቦታ” ማለት ለግንባታ ሥራ ዓላማ ወይም ከግንባታ ሥራ ጋር በተሚገናኘ ለሚነሱ የማናቸውም አይነት

ተግባራት ዓላማዎች ወይም ለግንባታ ሥራ የሚውል ማንኛውም ቦታ ነው፤

39) "ዋና ዲዛይነር" ማለት በአዋጁ አንቀፅ 5(1)(ሀ) መሰረት በአንቀፅ 11 እና 12 የተመለከተውን ተግባር እንዲፈጽም

የተሾመ ዲዛይነር ነው፡

40) “ፕሮጀክት” ማለት የኮንስትራክሽን ሥራን የሚያካትት ወይም ለማካተት የታሰበ እና ሁሉንም የዕቅድ፣ የንድፍ፣

እስከ የኮንስትራክሽን መጨረሻ ምዕራፍ የአስተዳደር ወይም ሌሎች ሥራዎችን ድረስ የሚያካትት የፕሮጀክት

ትግበራ ሂደት ነው፤

አንቀጽ 3፡ ዓላማ
ይህ ዓዋጅ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡-
1) ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ያለው ሀገር በቀል የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ እንዲፈጠር በማድረግ
ፍትሃዊነት፣ ተጠያቂነት እና ግልፀኝነት የሰፈነበት እንዲሁም የኢንዱስትሪውን ጤናማ እድገቶች
የሚጎዱ መልካም ያልሆኑ ገፅታዎችን እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እና ሙያዊ ሥነ ምግባር እንዲከበር
ማድረግ፣
2) ፍታሀዊነት የሰፈነበት በውድድር በሚመራ ገበያ ውስጥ ኢንዱስትሪው ለሚከፈለው ዋጋ ተመጣጣኝ
እሴት ማቅረቡን ማረጋገጥ፣
3) የባለድርሻ አካላት ሚናና ተሳትፎ እና የሰው ሃይል ልማትን ያማከለ የኢንዱስትሪው አቅም በተደማሪነት
እና በዘላቂነት መገንባቱን ማረጋገጥ፣
4) የኮንስትራክሽን ስራ ብቃታቸው በተመዘነ እና በተረጋገጠ ሙያተኞች፣ ባለሙያዎች እና ድርጅቶች ብቻ
እንዲፈፀም የሚያስችል አገር አቀፍ የተሳለጠ የሙያተኛ፣ የባለሙያ፣ የድርጅትና የፕሮጀክት የምዝገባ
እና የፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት መዘርጋት፣
5) ኢንዱስትሪው የማህበረሰቡን ጤንነትና ደህንነት ባስጠበቀና ፣ በጊዜ፣ በጥራት እንዲሁም ወጪ ቆጣቢ
ሆኖ እንዲከናወን እና በውድድር በሚመራ ገበያ ውስጥ ኢንዱስትሪው ለሚከፈለው ዋጋ ተመጣጣኝ
እሴት ማቅረቡን ማረጋገጥ፣
6) የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ግዥና የውል አስተዳደር ውጤታማነት ማሳደግ፣
አንቀጽ 4፡ የተፈፃሚነት ወሰን
ይህ አዋጅ፡-
1) በኮንስትራክሽን እና ተዛማጅ የኮንስትራክሽን ሥራ ዘርፍ ላይ በተሰማሩ ሙያተኞች፣ ባለሙያዎች,
ድርጅቶች እና ፕሮጀክቶች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
2) በሁሉም ክልሎች በማንኛውም የኮንስትራክሽን ሥራ ላይ በተሰማራ ሰው ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ክፍል ሁለት

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት መርሆች አይነቶች ህጎች እና ደረጃዎች

አንቀጽ 5፡ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት መሰረታዊ መርሆዎች፣

በኮንስትራክሽን ተግባራት የተሰማሩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የሚከተሉትን መሰረታዊ መርሆዎች መጠበቅ


ይኖርባቸዋል፡፡

1) በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ልማታዊ አቅም እንዲፈጥር በማድረግ ሌብነትና ብልሹ አሠራር የሚጸየፍና
የሚከላከል ኃይል መፍጠር፤
2) ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሚሆን ፕሮፌሽናል ባለሙያ ማብቃበት
3) በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ ቅልጥፍና እና ወጤታማነትን የሚያረጋግጥ እና ጠንካራ
የገበያ ውድድር የሚያሰፍን አሠራር መዘርጋት፣
4) የፕሮጀክቶች ሥራ አመራር እና የቴክኖሎጂ ዕድገት ሽግግሩን በማቀላጠፍ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን
ማዘመን፤
5) አስተማማኝ የኮንስትራክሽን ግብዓት አቅርቦት ሠንሠለት እንዲዘረጋና ሥርዓትም እንዲገነባለት ማድረግ
6) ዘመናዊና ለኮንስትራክሽን ልማት የተመቻቸ የፋይናንስና የመሣሪያዎች አቅርቦት ድጋፍ የሚሰጥበት ሥርዓት
መፍጠር
7) የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዋና ዋና ባለሚናዎች ለዘርፉ የተፋጠነ ዕድገት በጋራ የሚሰሩበትን አቅጣጫ መከተል
8) የኮንስትራክሽነ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥርና መጠቀሚያ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ማጠናከር
9) በሃገራችን ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሰራተኛውን ጤንነትና ደህንነት የሚጠብቁ ዘላቂ የኮንስትራክሽን ልምዶች
እንዲስፋፉ በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ በህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ሁኔታዎች አስቀድሞ
መከላከል፣
10) የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የልማት አቅጣጫ ለአካባቢ ጥበቃ ሚዛናዊ ትኩረት የሰጠ እንዲሆን ማድረግ
11) የስራ ዕድል ፈጠራን በማሳደግ ድህነትን መዋጋት
12) የኮንስትራክሽን ሕግጋት፣ ኮዶችና ስታንዳርዶች አክብሮ በመስራት የተጠናቀቀው ፐረሮጅክት የመጨረሻ
(ተተቃሚውን)ተገልጋዩን ፍላጎት ያሟላ መሆኑን ማረጋገጥ
13) የህንፃና መሰረተ ልማት ግንባታ ሂደትና ዲዛይን ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ፣
14) የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በሥርዓት እንዲመራ፣ ሥርዓቶችን በአግባቡ መተግበር እንዲበቃ በማድረግ ላይ
የተመሠረተና ኢንዱስትሪው ፈጣን ዕድገት ለማምጣት የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መፍጠር ነው፡፡
15) በማንኛውም የኮንስትራክሽን ሥራ የሚሳተፍ ድርጅትም ሆነ ባለሙያ የሚጠበቅበትን ሙያዊ ስነ-ምግባር አክብሮ
መስራቱን ማረጋገጥ፤
16) የሚፈለገው የስነ-ምግባር ደረጃ የህይወትና የንብረት ደህንነትን፣ ኢኮኖሚያዊ ስልጠትን፣ ብሄራዊ ደህንነትን፣
ህጋዊና ባህላዊ ተገቢነትን ማገናዘብ፡፡

አንቀጽ 6፡ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፕሮጀክት አይነቶች


1) በዚህ አዋጅ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት የህንጻ መሰረተ-ልማት፣ የመንገድና የትራንስፖርት መሰረተ-

ልማት፣ የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ መሰረተ-ልማት እና የኮሚዩኒኬሽን መሰረተ-ልማት ፕሮጀክቶችን የሚያካትት

ይሆናል፤

2) በዚህ አዋጅ የግንባታ ውልን የሚመለከቱት ከግንባታ ሥራዎች ጋር በተገናኘ ሥራ ለመሥራት ወይም

ለግንባታው ውል ረዳት የሆኑ አገልግሎቶችን ለመስጠት ስምምነትን ያካትታል፡-

ሀ) የስነ-ህንፃ ፣ የንድፍ ፣ የአርኪኦሎጂ ወይም የቅየሳ ሥራ ፣

(ለ) የምህንድስና ወይም የፕሮጀክት አስተዳደር አገልግሎቶች፣ ወይም

(ሐ) በግንባታ፣ በምህንድስና፣ በውስጥ ወይም በውጪ ማስጌጥ ወይም በመልክዓ ምድር አቀማመጥ ላይ ማማከር

ሥራ፤

3) በዚህ አዋጅ ንኡስ አንቀጽ (1 እና 2) የተደነገገው እንደተጠበቁ ሆነው የኮንስትራክሽን ስራ የሚከተሉትን

አይጨምርም፤

(ሀ) የግንባታ ወይም የምህንድስና አካላት ወይም መሳሪያዎች የማምረት ወይም ወደ ግንባታ አካባቢ የማድረስ፤

(ለ) ለኮንስትራክሽን ስራውን ለማሳለጥ የሚያስፈልጉ የመስሪያ መሳሪያ፣ ተክል ወይም ማሽነሪ፣ ወይም ለማሞቂያ ፣

ለመብራት ፣ የአየር ማቀዝቀዣ ፣ የአየር ማናፈሻ ፣ የኃይል አቅርቦት ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ፣ የንፅህና አጠባበቅ ፣

የውሃ አቅርቦት ወይም የእሳት አደጋ መከላከያ ወይም ለደህንነት ወይም የግንኙነት ስርዓቶች መዘርጋት፤

ሐ) የድፍድፍ ነዳጅ፣ የተፈጥሮ ጋዝና ሌሎች የማዕድን ሀብቶችን የማፈላለግ ወይም የማጣራት ስራ በሚካሄድበት

ቦታ የሚደረጉ የመቦርቦር ወይም የማውጣትን ወይም የዝግጅት ስራዎችን እና

መ) የድፍድፍ ነዳጅ፣ የተፈጥሮ ጋዝና ሌሎች የማዕድን ሀብቶችን ለማውጣትና ለማጣራት ጥቅም ላይ የሚውሉ

የመስሪያ መሳሪያዎችን የማምረት ወይም የመገጣጠም ስራ እንዲሁም


ሠ) በሌላ ህግ የኮንስትራክሽን ስራ ዘርፍ የማይካተቱ ናቸው፤

5) ለዚህ አዋጅ ዓላማ የኮንስትክሽን ሥራ ጋር የተያያዙ ሙያዊ አገልግሎቶች የሚባሉት የሒሳብ, የገንዘብ, ወይም

ህጋዊ, አገልግሎቶችን ሳያካትት ከኮንስትራክሽን ሥራ ጋር በቀጥታ የተገናኙ ወይም አዋጭነቱን ለመገምገም

የሚከናወኑ የቅየሳ፣ እቅድ ማውጣት፣ የወጪ ጥናት፣ የቤተ-ሙከራ፣ አርክቴክቸር፣ ዲዛይን፣ ንድፍ ስራ፣

የምህንድስና፣ ኳንቲቲ ሰርቬይንግ፣ እና የፕሮጀክት አስተዳደር፣ አገልግሎቶች ናቸው፤

6) ለዚህ አዋጅ አተገባበር በሌላ ህግ የተደነገጉ ከኮንስትራክሽን ሥራ ጋር የተያያዙ ሙያዊ አገልግሎቶች የሚሰጡ

ፕሮፌሽናል አገልግሎቶችን ያካትታል፤

አንቀፅ 7፡ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ማስፈጸሚያ ህግ


ማንናውም በዚህ ዘርፍ ውስጥ የሚሳተፍ ድርጅትም ሆነ የመንግስት አካል እንዲሁም ግለሰብ በኮንስትራክሽን
ኢንዱስትሪው ውስጥ የተዘረጉ የአሠራር ሥርዓቶች አዋጆችን፣ ደንቦችን፣ ስታንዳርዶች፣ ኮዶች፣
መመሪያዎችን አክብሮ መስራት የሚጠበቅበት ሲሆን የሚከተሉትን የማስፈጸሚያ ስርዓት ያካትታል፤
1) የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት በቅድመ ዲዛይን ምዕራፍ፣ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ትግበራ
በሚካተቱ የዲዛይን ዝግጅት አገልግሎትና የኮንስትራክሽን የፕሮጀክት ክንውን ምዕራፍ፣ በፕሮጀክት
ዲዛይን ግምገማ፣ የጥራት ቁጥጥር ወይም የጥራት ማረጋገጥ እና የውል አስተዳደር እንዲሁም
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ትግበራ ስራ ከማጠናቀቅና ከድህረ- መጠናቀቅ በኋላ ውጤታማነተን
ለመገምገም የተደነገጉ የተያያዙ ህግጋት፤
2) የኮንስትራክሽን መሰረተ ልማትና ተያያዥ ህግጋት፡- የከተማ ፕላን፣ መሬት፣ ህንፃ፣ ውሃ እና
የኢንቨስትመንት ተያያዝ ህግጋት
3) የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት የጤና እና ደህንነት፣ የጥራት፣ የአካባቢያዊ እና የእሳት ጋር የተያያዥነት
ያላቸው ህግጋት
4) ከኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ግዥና የውል አስተዳደር ጋር ተያያዥነት ያላቸው ህግጋት
5) የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት የባለሙያ፣ የኩባንያ እና ማሽነሪ ምዝገባ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ህግጋት
6) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ አመራር የአሠራር ኮድ/Code of practice እና ሌሎች ናቸው፡፡

አንቀፅ 8. በኮንትራክሽን ሥራ መሰማራት


1. ማንኛውም የኮንስትራክሽን ሥራ በዚህ አዋጅ እንዲሁም አግባብነት ባላቸው ሌሎች ህጎች የተቀመጡ
ግዴታዎችን እና ክልከላዎችን በማክበር መከናወን አለበት፤
2. ማንኛውም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ዲዛይን የፕሮጀክቱ አይነትና ውስብስብነት የሚጠየቀውን

መስፈርት አሟልቶ በተመዘገበና የምዝገባ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ባለው የኮንስትራክሽን አማካሪ

ድርጅት መሠራት አለበት፡፡

3. ማንኛውም አሰሪ ለሚያሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት ዲዛይን እንዲዘጋጅለት ወይም በአማካሪነት

ለመቅጠር የሚመርጠው ሰው በዚህ አዋጅ በተደነገገው መሰረት በዲዛይን ዝግጅት ወይም የአማካሪነት

ስራውን በተገቢሁ ሁኔታ ለማከናወን የሚያስችለውን ብቃት ያለው እና በቂ ሀብት የመደበ ወይም በቂ

ሃብት የሚመድብ መሆኑ አሳማኝ በሆነ ዘዴ ማወቁን ካላረጋገጠ በስተቀር በአማካሪነት ወይም በዲዛይን

አዘጋጅነት ለመሾም ወይም ለመቅጠር ስምምነት ማድረግ የለበትም፤

4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የኮንስትራክሽን ዲዛይኑን ቴክኒካል ሥራ

የሚያስተባብረው የዲዛይን የባለሙያ በሚመለከተው አካል ተመዝግቦ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው

ወይም አርክቴክቱ ነው፡፡ ዝርዝሩ ይህን አዋጅ ለማስፈፀም በሚወጣው ደንብ ይወሰናል፡፡

5. የኮንስትራክሽን ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ የኮንስትራክሽን አማካሪ ድርጅት የሥራ ተቋራጩን

የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችንም ይቆጣጠራል፡፡ የኮንስትራክሽን ሥራው ሲጠናቀቅ በዚህ አንቀፅ ንዑስ

አንቀፅ /1/ ላይ የተጠቀሰው አማካሪ ድርጅት የፈረመበትና መጠናቀቁን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት

ለተቋሙ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

6. ማንኛውም የኮንስትራክሽን ሥራ ለማከናወን ውል የሚወስድ የዲዛይን አማካሪ ድርጅት በዲዛይን የተነሳ

ሊደርሱ ለሚችሉ ጉዳቶች ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡ ለፕሮጀክቱ የሚያዘው የዋስትና መጠንና አቀራረብ

፣የዋስትና ሰጪ አካላት ሀላፊነት ይህን አዋጅ ለማስፈፀም በሚወጣው ደንብ ይወሰናል፡፡

7. የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ለማሰራት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ለፕሮጀክቱ በሚመጥን የኮንስትራክሽን

ሥራ ተቋራጭ፣ የኮንስትራክሽን አማካሪ ወይም ዲዛይነር ማሰራት አለበት፡፡ ዝርዝሩ ይህን አዋጅ

ለማስፈፀም በሚወጣው ደንብ ይወሰናል፡፡

8. የኮንስትራክሽን ስራው እንደሚጀመር እርግጠኛ በሆነበት ሁኔታ አሰሪው አማካሪ መሾም ወይም መቅጠር

አለበት፣

9. ማንኛውም አሰሪ ለሚያሰራው የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ሥራ ተቋራጩ የኮንስትራክሽን ስራውን

ለማከናወን ወይም እንደነገሩ ሁኔታ ለማስተዳደር የሚያስችለው ብቃት ያለው፣ በቂ ሀብት የመደበ ወይም
በቂ ሃብት የሚመድብ መሆኑ አሳማኝ በሆነ ምክንያት ካላረጋገጠ በስተቀር ሥራ ተቋራጩ ጋር ስምምነት

ማድረግ የለበትም፤

10. በዚህ አዋጅ የተቀመጠውን ግዴታ መስፈርት እስካሟላ ድረስ የንዑስ አንቀፅ 7 ድንጋጌ አሰሪው አንድን

አማካሪ እና ዋና ስራ ተቋራጭ በተመሳሳይ ጊዜ ከመሾም አያግደውም፤ ወይም አሰሪው የአዋጁን ግዴታ

እስካሟላ ድረስ አሰሪው አማካሪ ወይም ስራ ተቋራጭ ወየይም ሁለቱንም በተመሳሳይ ስራ ላይ በመሾም

ማሰራት አይከለከልም፤

አንቀፅ 9፡ ስለ ኮንስትራክሽን ምዝገባ

1) ማንኛውም የኮንስትራክሽን ባለሙያ፣ ሙያተኛና ድርጅት ዋጋ ባላቸው የኮንስትራክሽን ሥራዎችን ላይ


ለመሰማራት፣ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ጨረታ ለመወዳደር እና በከፊል ወይም በሙሉ ውድድር በማሸነፍና
ለማከናወን በቅድሚያ ለምዝገባ የሚያበቃውን መስፈርት በማሟላት በባለስልጣኑ መመዝገብና የምዝገባ ማረጋገጫ
የምስክር ወረቀት ማግኘት አለበት፡፡
2) ለምዝገባና ለበቃት ማረጋገጫ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎችን አሟልቶ የተገኘ አመልካች በመስፈርት ማሟያነት
ያቀረባቸው ማስረጃዎች ላይ ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ ለምስክር ወረቀት ሰጪው አካል የማሳወቅ ግዴታ ያለበት
ሲሆን ምስክር ወረቀት ሰጪው አካልም የቀረበውን ማሻሻያ መርምሮ ለተመዘገበበት ወይም የብቃት ማረጋገጫ
ላወጣበት ደረጃ የሚመጥን መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡
3) ማንኛውም የምዝገባ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የተሰጠው ድርጅት ቋሚ አድራሻውን ሲቀይር ለመዝጋቢው አካል
በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ማሳወቅ አለበት፡፡
4) በማንኛውም ደረጃ የባለሙያ ብቃት ማረጋገጫ ወይም ምዝገባ ምስክር ወረቀት ለማግኘት የሚጠይቁ አመልካቾች
መስፈርቶችን በተናጠል እስካሟሉ ድረስ ከአንድ በላይ በሆኑ የሙያ መስኮች ምስክር ወረቀት ማግኘት ይችላሉ፡፡
5) ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው የኮንስትራክሽን ድርጅት የምሰክር ወረቀት የሚሰጠውና የሚመዘገበው
በደረጃ አንድ ብቻ ነው፡፡
6) ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው የኮንስትራክሽን ድርጅት በፓርትነርሽፕ ወይም በጣምራ (በጆይንት ቬንቸር)
ከሀገር ውስጥ የኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር ሲሰራ የሚሰራውን የስራ አይነት፣ መጠን እና የሀገር ውስጥ
የኮንስትራክሽን ድርጅትን መረጃ ለምስክር ወረቀት ሰጪው አካል የማስመዝገብ ሃላፊነት አለበት፡፡
7) የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው ባለሙያ የባለሙያ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማውጣት ከፈለገ በሚመለከተው አካል
የተረጋገጠ የትምህርት ማስረጃና አቻ ግመታ እንዲሁም አግባብነት ያለው የስራ ልምድ፣ ህጋዊ እውቅና ካለው አካል
አግባብነት ባለው ቋንቋ የተተረጎመ እንዲሁም በሚመለከተው አካል የተረጋገጠ የስራና የመኖሪያ ፍቃድ ማቅረብ
ይኖርበታል፡፡
8) የብቃት ማረጋገጫና የምዝገባ ምስክር ወረቀት የሚሰጠዉ አካል ከሚጠቀምባቸዉ ቋንቋዎች ውጪ የተዘጋጀ
የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃ ህጋዊ የትርጉም ፈቃድ ባለው ድርጅት የብቃት ማረጋገጫና የመዝገባ ምስክር
ወረቀት የሚሰጠዉ አካል ወደ ሚጠቀምባቸዉ ቋንቋ ተተርጉሞ መቅረብ አለበት፡፡
አንቀፅ 10. ስለ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ምዝገባ
1) ማናቸውም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በዚህ አዋጅ መሠረት መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
2) ማንኛውም ስራ ተቋራጭ እና አማካሪ የሚሰራቸውን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ማስመዝገብ ይኖርበታል፡፡
3) ማንኛውም በፌደራል በጀት የሚገነቡ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችን በተመለከተ አሰሪው አካል በየበጀት ዓመቱ
መጀመሪያ ስራዎቹን ለባለስልጣን መ/ቤቱ በቅድሚያ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

4) ማንኛውም በፌደራል መንግስት በጀት የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን አሰሪው አካል በቅድሚያ ከዲዛይን ጀምሮ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ
እየተገመገመና ይሁንታን እያገኘ እንዲያልፍ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
5) ማንኛውም በፌደራል መንግስት በጀት የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ከዚህ በታች የተገለጹትን አጠቃላይ የአፈጻጸም መረጃዎች
አሰሪው አካል በየስድስት ወሩ ለባለስልጣኑ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

አንቀፅ 11. ስለ ግልፅነት


ማንኛውም የኮንስትራክሽን ሥራ ፈቃድ የሚሰጥ አካል የሚከተሉት ሃላፊነቶች ይኖሩበታል፡-
1) ለኮንስትራክሽን ፈቃድ አሰጣጥ የወጡ ደንቦችንና ሌሎች የአሠራር ሥርዓቶችን ሕዝቡ በግልጽ ሊያየው
በሚችል ቦታ መለጠፍ ይኖርበታል፣
2) ለማንኛውም የግንባታ ፈቃድ ለቀረበ ጥያቄ ከ 10 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ፈቃድ መስጠት
ይኖርበታል፣ ፈቃድ ለመስጠት የማያስችሉ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ምክንያቶቹን ዘርዝሮ በጽሁፍ
በተቀመጠው ጊዜ ገደብ መሰረት ለጠያቂው መስጠት አለበት፣
3) በተሰጠው የኮንስትራክሽን ፈቃድ መሠረት የኮንስትራክሽን ሥራው እየተከናወነ መሆኑን መከታተልና
መቆጣጠር ይኖርበታል፣
4) በኮንስትራክሽን ፈቃድ አሠጣጥ የተሰማሩ ሠራተኞችና ባለሙያዎች ሥራቸውን በተቀመጠው
የአሠራር ሥርዓት መሠረት ማከናወናቸውንና የሕዝብ ጥያቄ በአግባቡ መመለሱን መከታተልና
መቆጣጠር ይኖርበታል፣

አንቀፅ 12. የፕሮጀክት መረጃ አያያዝ እና አስተዳደር

1. የኮንስትራክሽን ተዋናኞች መረጃ ለዚሁ ተብሎ በሚዘጋጅ ዳታቤዝ መመዝገብና መደራጀት አለበት፤
2. ማንኛውም ፕሮጀክት አስፈፃሚ አካል የሚከታተለውን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ከፅንሰሀሳብ
/ከቅድመ-ዲዛይን ጀምሮ እስከ ትግበራ ድረስ ያለውን መረጃ በመደበኛነት ደህንነቱ በተረጋገጠ የመረጃ
ቋት የመያዝ ሀላፊነት አለበት፡፡
3. ዋና ዋና የፕሮጀክቶች መረጃዎች ተደራሽ በሆኑ የመገናኛ አግባቦች ድህረ ገጾችን ጨምሮ
ወቅታዊነታቸውን ጠብቀው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ያደርጋል፤

አንቀፅ 13፡ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አመራር ዑደቶች


1) ማንኛውም በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት የቅድመ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ዲዛይን አገልግሎት፣ የዲዛይን
አገልግሎት፣ የትግበራ፣ ዲዛይን ክለሳ እና/ወይም የጥራት ቁጥጥር ወይም የጥራት ማረጋገጥ እና የውል
አስተዳደር አገልግሎት ምዕራፍ፣ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ እና የድህረ-መጠናቀቅ አገልግሎት ዑደቶች
ይኖሩታል፡፡
2) በሀገር ውስጥ እና በውጭ ብድር በፌደራል መንግስት ዋስትና የሚከናወኑ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች
በዚህ አዋጅ የተደነገጉትን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አመራር ዑደቶች ጠብቀው መዘጋጀታቸውን
ተግባራዊ መደረጋቸውን መረጋገጥ አለበት፤

አንቀፅ 14፡ የቅድመ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ዑደቶች መሰረታዊ መርሆዎች


3) ማንኛውም ፕሮጀክት አስፈፃሚ አካል ላመነጨው የፕሮጀክት ሀሳብ የፕሮጀክቱ አላማ ግልፅና
የፕሮጀክት ዕቅድ ለማዘጋጀት በሚያስችል መልኩ የፕሮጀክት ፅንሰ-ሀሳብ ማዘጋጀት አለበት፤
4) የፕሮጀክት ቅድመ አዋጭነት እና አዋጭነት ጥናት መከናወን ያለበት እንደየፕሮጀክቱን አይነት
የዳበረ ሙያዊ ልምድና እውቀት ሰፊ ስብጥርን ባቀፈ የባለሙያ ስብስብ መሆን አለበት፤
5) የአዋጭነት ጥናት ለአሰሪው የኢኮኖሚ አማራጭ ማሳየት፣ የቴክኒክ ፍላጎት፣ የካፒታል ወጪ
የፋይናንስ ሁኔታውን የከባቢያዊ ሁኔታ በግልፅ ማመላከትና አለበት
6) በሁሉም ፕሮጀክቶች ላይ የቅድመ ግንባታ ኮንፈረንስ በማድረግ የግንባታውን እቅድ እና የሁሉም
አካላት የሚጠበቁ እና ኃላፊነቶች ግልጽ ግንዛቤን መፍጠር አለበት
7) በሌላ ህግ የተሰጣቸው ሥልጣንና ተግባር እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት
አስፈፃሚ አካል፡-
8) የአዋጭነት ጥናት የተደረገበትን ፕሮጀክት በራሱ አቅም የአዋጭነት ግምገማ በማካሄድ ጥራቱን
ማረጋገጥ አለበት፤
9) ማንኛውም ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት ስልጣን በተሰጠው አካል ገለልተኛ
የቅድመ-አዋጭነትወይም የአዋጭነት ግምገማ ተደርጎ ተቀባይነት ያለው መሆን ይኖርበታል፤
አንቀፅ 15. የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ዲዛይን አገልግሎት ምዕራፍ መሰረታዊ መርሆዎች

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ዲዛይን አገልግሎት የሚከተሉትን መሰረታዊ መርሆዎች በመከተል መዘጋጀት


አለበት፡
1) ማንኛውም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ዲዛይን ዝግጅት አካባቢያዊ፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ
ህጎችን፣ ስታንዳርዶችንና ቅደም ተከተሎችን ዘላቂ መሰረተልማት በሚያመጣ ባማከለ መልኩ
መዘጋጀት አለበት፤
2) ማንኛውም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ዲዛይን ዝግጅት ለአሰራር ቀላል፣ በአካባቢ በቀላሉ የሚገኝ፣
ጠንካራና ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጥ፣ ዝቅተኛ ብክለትና ለጤና ስጋት እንዲሁም መልሶ ለመጠቀም
የሚያስችል የግብዓት መመረጥ አለበት፤
3) ማንኛውም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ዲዛይን ዝግጅት ኢኮኖሚካል ታሳቢ ያደረገ ሆኑ የወጭና
ጥቅም ትንታኔ፣ ሊፍ ሳይክል ትንታኔ፣ አዋጭነት እና በባንክ ስራ የሚካተት
4) የተጠቃሚው ማህበረሰብ ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ የህዝብ ተሳተሰፊነት፣ የባለቡን አሳታፊ፣ ተደራሽ
የሆነ፣ የሰራተኞችንና የተጠቃሚውን ጤና እና ደህንነት የሚያረጋግጥ፣ የህብረተሰቡ ቅቡልነት፣
የባህል የሚጠብቅ፣ የመሬት አጠቃቀም፣ ለታሪካዊ ቦታዎች እና አርኪዎሎጂካል ቦታዎችን
እንክብካቤ ታሳቢ ያደረገ፣ የጉዳት ትንታኔ እና ተፈጥሮአዊ ክስተት ጉዳት የሚቀንስ፣ ፣
5) የፖሊሲና ህግ ሁኔታ የቁጥጥር ህጋዊ ቅድመሁኔታዎችን በዘላቂነት ታሳቢ ያደረገ፣ ዘላቂ አጠቃቀም
መርህን ያካተተ
6) የዲዛይንና የፕሮጀክት ስራ አመራር ስርዓት ስር የሥራ ተቋራጩ አሳታፊ የሆነ፣ የአቅራቢዎች
አሳታፊ የሆነ፣ ተስማሚ ውል አመራረጥ/ ተስማሚ ውል ማስረከብ አይነት፣ አግባብ ባለው የጥራት
ቁጥጥር ሂደት የሚመራ
7) የከባቢያዊ ሁኔታ በተመለከተ ለአየር ንብረት ለውጥና የተፈጥሮ አደጋ የሚቋቋም፣ ለአየር ንብረት
ለውጥና ጉዳት ተጋላጭነት የሚቀንስ፣ በግንባታም ሆነ በአጠቃቀም ውጤታማ ሀይል ቆጣቢ የሆነ፣
ሚዛናዊ ተፈጥሮ ሃብትን አጠቃቀም፣ ሚዛናዊ የመስሪያ ቦታ አጠቃቀም፣ ብክነትን የሚቀንስ
መልኩ መዘጋጀት አለበት፤
8) የቴክኒክ ጉዳዮች በተመለከተ የተሟላ ሳይት ሰርቬይና የመሬት ምርመራ፣ የመፍትሄ ፕሮፖሳል
ከመቅረቡ አስቀድሞ አማራጮችን ያካተተ፣ ከአዋጭነት ጥናት ጀምሮ የተቀናጀ ሰፊ የሙያ ሰብጥር
ባለው የዲዛይን ቲም ተሳትፎ፣ ለሚፈለገው አላማ የሚሆን እና ለተጠቃሚ ምቾተት ያሚሰጥ፣
ለጥገና ምቹ በሆነ ቁስ፣ የተሟላ እና ለአጠቃቀም ግልፅ የሆነ ሰነድ፣ እሴት በሚጨምር እና
ከአካባቢው የአየር ሁኔታ ጋር የተስማማ፤
9) የዲዛይን ባለሙያዎችና የዲዛይን ዝግጅት ሂደት በተመለከተ ዘላቂነትን አስመልክቶ የአሰሪው፣
የዲዛነሩ የእውቀት ሁኔታ፣ የዲዛይነሩ እውቀትና ልምድ፣ የጥበብ፣ ለዝግጅት የሚመደበው በቂ ጊዜ፣
በዲዛይን ስህተት ለሚከሰት አሳማኝ ካሳ ክፍያ ፣ በባለሙያ ዲዛይነሮች መካከል የተዋቃጣለት
አስተባባሪ፣ ዘላቂነት ያለው ዲዛይን የማዘጋጀት መርህን ተጠቅሞ ለማዘጋጀት ያለ የዲዛይነሩ
ፍላጎት ከግምት ውስጥ ማስገባት አለበት፤
አንቀፅ 16. የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ዲዛይን ዝግጅት ቅድመ ሁኔታዎች
1) ዲዛይን አውጭው እና ሌሎች በዲዛይን ዝግጅት ሚሳተፍ ቲም ስራን ለማከናወን የአሰሪውን ምንነት
መረዳት እና ፍላጎቱን ጠንቅቆ ማወቅ አለበት
2) የአዋጭነት ጥናትን መሰረት በማድረግ ዲዛይን እንዲዘጋጅለት ውሳኔ የተሰጠበት የኮንስትራክሽን
ፕሮጀክት የፕሮጀክት ትግበራ እቅድ እና የዲዛይን ዝግጅት ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላቱ መረጋገጥ
አለበት፤
3) ማንኛውም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ተገቢነት ያላቸው የዲዛይን ዝግጅት ህግጋት፣ ስታንዳርዶች እና
ሌሎች መስፈርቶች መሰረት መዘጋጀት አለበት፣
4) እንደየ ፕሮጀክቱ አይነት ለዲዛይን ዝግጅት መሟላት የሚጠበቅበትን ዝቅተኛ መስፈርት ባላከበረ
ሁኔታ በተዘጋጀ ዲዛይን የኮንስትራክሽን ሥራ ማከናወን የተከለከለ ነው፣
5) ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጥ ማንኛውም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ለሕፃናት፣ አረጋውያን እና የአካል
ጉዳተኞችን ልዩ ፍላጎት ባካተተ መልኩ መዘጋጀት አለበት፡፡
6) ለትግበራ ዝግጁ የሆነ ማንኛውም የኮንስትራክሽን ዲዛይን ወደ ፕሮጀክት ትግበራ ከመሸጋገሩ
አስቀድሞ የተዘጋጀውን የመጀመሪያ ዲዛይን በፕሮጀክቱ አግባብነት relevancy፣ ተተግባሪነቱ
constructability፣ የፕሮጀክቱ እቅድ እና ስፔስፊኬሽን specifications የተሟላ ስለመሆኑ በቅድመ-
ኮንስትራክሽን ፍተሻ መረጋገጥ አለበት፣
አንቀፅ 17፡ የኮንስትራክሽን ሥራ ፈቃድ ማግኘት ግዴታ ስለመሆኑ
1) በኮንስትራክሽን ሥራ ዘርፍ ለመሳተፍ ፍላጎት ያለው ማንኛውም ሰው በቅድሚያ ከሚመለከተው አካል
ተገቢውን የኮንስትራክሽን ሥራ ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል፡፡
2) በየደረጃው የሚገነባ ማንኛውም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት የሚዘጋጀው ዲዛይን ለፕሮጀክቱ በሚመጥኑ
የተመዘገቡ ባለሙያዎች ወይም ድርጅት መሆን አለበት፣
3) በየደረጃው የሚከናወን ማንኛውም የኮንስትራክሽን ሥራ ደረጃውን በጠበቀና በተመዘገበ የሥራ ተቋራጭና
ባለሙያዎች መሰራት አለበት፣

አንቀፅ 18. የኮንስትራክሽን ሥራ ፈቃድ ለማግኘት መሟላት ስለሚገባቸው ሁኔታዎች


1) ማንኛውም ሰው የኮንስትራክሽን ፈቃድ ለማግኘት በቅድሚያ የታቀደው የኮንስትራክሽን ሥራ
ከአካባቢው የመሬት አጠቃቀም ፕላን ጋር የተገናዘበ ስለመሆኑ ከሚመለከተው አካል የመሬት አጠቃቀም
ፕላን ስምምነት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
2) በከተማ ክልል ውስጥ የሚገነቡ የመሠረተ ልማት አውታሮች ከከተማው አስተዳደር የኮንስትራክሽን ፈቃድ
ማግኘት ይኖርባቸዋል፣
3) ከከተማ ክልል ውጪ የሚገነቡ የመሠረተ ልማት አውታሮች ግንባታው ከሚካሄድባቸው ክልል
የኮንስትራክሽን ተቋማት የኮንስትራክሽን ፈቃድ ማግኘት ይኖርባቸዋል፣
4) የመሬት አጠቃቀም ፕላን ባልተዘጋጀለት አካባቢ ለሚከናወን የኮንስትራክሽን ሥራ የአካባቢው አስተዳደር
በሚያወጣው የአሰራር ዕርዓት መሠረት ከአገር አቀፍ የከተሞች የልማት ዕቅድ ጋር በተናበበ ሁኔታ
የተዘጋጀ የፕላን ስምምነት መቅረብ አለበት፡፡
5) ተቋሙ የቀረበለትን የመሬት አጠቃቀም ፕላን ስምምነት መሠረት በማድረግ አመልካቹ የኮንስትራክሽን
ሥራ ፈቃድ ማመልከቻ እንዲያቀርብ በጽሁፍ ያሳውቀዋል፡፡
6) በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 5 መሰረት የኮንስትራክሽን ፈቃድ ማመልከቻ እንዲያቀርብ በፅሁፍ የተነገረው
ሰው ማመልከቻ እንዲያስገባ በተፈቀደለት ጊዜ ውስጥ ማመልከቻውን ማቅረብ አለበት፡፡ የማመልከቻው
ዝርዝር ይዘት ይህን አዋጅ ለማስፈፀም በሚወጣ ደንብ እና መመሪያ ላይ ይወሰናል፡፡
7) የኮንስትራክሽን ሥራ ፈቃድ ለማግኘት የሚፈልግ ሰው የኮንስትራክሽን ዲዛይን ማቅረብና ማስፀደቅ
አለበት፡፡
አንቀፅ 19. ስለ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ዲዛይን መገምገም እና ስለ ማስፀደቅ
1) ተቋሙ አንቀጽ 8 (6) እና (7) መሰረት የቀረበለትን ዲዛይን ለማፅደቅ ከዚህ አዋጅ፣ ይህን አዋጅ ለማስፈፀም
ከሚወጡት ደንብ፣ መመሪያ እንዲሁም ሌሎች ተቀባይነት ያላቸው የኮንስትራክሽን ዲዛይን ስታንዳርዶች ጋር
የተጣጣመ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡
2) ተቋሙ የቀረበለትን የኮንስትራክሽን ዲዛይን ይህን አዋጅ ለማስፈፀም በሚወጣው ደንብ በሚወሰነው የጊዜ
ገደብ ውስጥ መገምገም እና ማጽደቅ አለበት፡፡
3) በዚህ አዋጅ ወይም ይህን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣ ደንብ ወይም መመሪያዎች ያልተካተቱ መመዘኛዎችን
ምክንያት በማድረግ ዲዛይን እንዳይፀድቅ ማድረግ አይችልም፡፡
4) የቀረበው ዲዛይን መሰረታዊ ግድፈት የሌለበት ከሆነ እና ተፈላጊው ማስተካከያ በኮንስትራክሽን ሂደት በቀላሉ
መስተካከል እንደሚችል በታመነበት ጊዜ ተቋሙ አስተያየቱን በማስፈር ዲዛይኑን ሊያፀድቀው ይችላል፡፡
በዲዛይን ዝግጅት የመሰረታዊ ግድፈት መመዘኛዎችን በተመለከተ በደንብ እና መመሪያ ይወሰናል፡፡
5) የፀደቀ ዲዛይን በላዩ ላይ “ፀድቋል” የሚል ማህተም የተደረገበት፣ የምዝገባ ቁጥርና የፀደቀበትን ቀን የያዘና
የሚመለከተው ባለሙያ እና የስራ ኃላፊ ፊርማ እንዲሁም የተቋሙ ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል፡፡
6) ይዞታው ለሌላ አካል ሲዛወር የፀደቀውን ዲዛይን ለውጥ ከሌለው ፀደቁ በተዛወረው ዲዛይን በላዩ ላይ “ከ--
ወደ---ተዛውሯል” የሚል ማህተም የተደረገበት፣ የምዝገባ ቁጥርና የተዛወረበትን ቀን የያዘና የሚመለከተው
ባለሙያ እና የስራ ኃላፊ ፊርማ እንዲሁም የተቋሙ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት፡፡
7) ከፀደቀው ዲዛይን ጋር አብረው የቀረቡት የማመልከቻ ቅፆች በቅፆች ውስጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ክፍት
ቦታ ላይ “ፀድቋል” የሚል ምልክት ተደርጐባቸው የምዝገባ ቁጥርና የፀደቀበት ቀን ይሠፍርባቸዋል፡፡ አስተያየት
ካለ ለዚሁ በተዘጋጀው ክፍት ቦታ ላይ ሰፍሮ በተቋሙ የስራ ኃላፊ ይፈረምበታል፡፡
8) ማህተምና ፊርማ ያረፈበት የማመልከቻ ቅፅ እና በአባሪነት የተያያዘው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /3/
መሠረት የፀደቀ ዲዛይን ሁለት ቅጅ ለአሰሪው መሰጠት ያለበት ሲሆን፤ ሌላው አንድ ቅጅ ደግሞ በተቋሙ ዘንድ
ይቀመጣል፡፡
አንቀፅ 20. የኮንስትራክሽን ዲዛይን ውድቅ ስለማድረግ
1) ከዚህ አዋጅና ይህን አዋጅ ለማስፈጸም ከሚወጣ ደንብ ወይም መመሪያዎች ጋር የማይጣጣም ዲዛይን ውድቅ
ይደረጋል፡፡
2) ዲዛይን ውድቅ የሚሆን ከሆነ ተቋሙ ውድቅ የተደረገበትን ምክንያት በጽሑፍ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
3) ውድቅ የተደረገ ማመልከቻና ዲዛይን በእያንዳንዱ ቅጂ ላይ “ውድቅ ተደርጓል” የሚል ምልክትና ቀን
እንዲሁም የሚመለከተው ባለሙያ ወይም ኃላፊ ፊርማ ይሠፍርበታል፡፡
4) በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 እና 3 ውድቅ የተደረገ ዲዛይን አንድ ቅጂ በተቋሙ ዘንድ የሚቀመጥ ሲሆን
ቀሪው ለአሰሪው የሚመለስ ይሆናል፡
አንቀፅ 21. የኮንስትራክሽን ፈቃድ ፀንቶ ስለሚቆይበት ጊዜ
የኮንስትራክሽን ፈቃድ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ እንደ ኮንስትራክሽን ሥራው አይነትና ውስብስብነት እየታየ ይህን አዋጅ
ለማስፈጸም በሚወጣ ደንብ ወይም መመሪያ መሠረት ይሆናል፡፡

አንቀፅ 22. የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ትግበራ ምዕራፍ መሰረታዊ መርሆዎች


1) ይህ የትግበራ ምዕራፍ በውል ሰነድ መሰረት የዲዛይን ስራው ወደ ውጤት የሚቀየርበት ሂደት
በተያዘለት ጊዜ፣ ወጭ እና የፕሮጀክቱ ዝርዝር ውል የጠበቀ ሁኔታ የአሰሪውን ፍላጎትና ለታቀደለትን
አላማ አገልግሎት መስጠት መቻል አለበት
2) ማንኛውም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ሥራ የሚከተሉትን ውጤት ማስገኘት መቻሉ መረጋገጥ
አለበት
3) አሰሪው የስራውን ስፋትና ጥልቀት፣ የጊዜ ሰሌዳ፣ የጥራት ስራ አመራር፣ የጤንነትና ደህንነት እና
የበጀት ሁኔታ መገንዘብ አለበት
4) ማንኛውም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ዋና የፕሮጀክት ስራ አመራር ሂደቶችን በማለፍ በወጭ፣
በጊዜ፣ በጥራት እና በደህንነት አንፃር አስቀድሞ የታቀደለትን ዒላማ ከግብ ማድረስ አለበት፤
5) ሥራ ተቋራጩ የአቅርቦት ሰንሰለት ስራ የመምራት የውል ግዴታ አለበት
6) ፕሮጀክቱ ሠራ አስኪያጅ በበኩሉ ይህንን አቅርቦት በውጤታማነት መምራት እና ሊከሰት የሚችል
መዘግየት፣ አላስፈላጊ የወጭ ጭማሪ ዌም ሌላ በፕሮጀክቱ ላይ ጉዳት የሚያስከትል ሁኔታ ማስወገድ
መቻል አለበት፤
አንቀፅ 23. የፕሮጀክት ትግበራ ሥራ ከመጀመሩ በፊት መወሰድ ያለባቸው አጠቃላይ የጥንቃቄ
እርምጃዎች፡-
1) በነባር ህንጻዎች እና መሠረተ ልማቶች ደህንነት እና አገልግሎቶች ላይ ተፅዕኖ መፍጠር የለበትም;
2) የህብረተሰቡን ጤና እና በአቅራቢያ በሚገኙ ንብረቶችን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን
ማስወግድ አለበት;
3) በአካባቢው ያለውን የትራፊክ ፍሰት የሚያደናቅፍ ማንኛውንም እንቅፋት ማስወግድ አለበት;
4) የግንባታ ሥራ በምሽት የሚከናወን ከሆነ በሕዝብ ላይ መረበሽ እንዳይፈጠር እና በአስተማማኝ እና
ምቹ በሆነ ሁኔታ እንዲከናወን ከሚመለከተው አካል የምሽት ግንባታ ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል፤
5) ኮንትራክተሩ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ዲዛይን እና ዝርዝር ሥራዎችን በጽሁፍ በማቅረብ
ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ማግኘት አለበት;
6) አጎራባች የቴክኒክ እውቀት ካላቸው ወይም በተወካዩ ቴክኒካል ባለሞያዎች በግንባታው ወቅት
በንብረት ላይ አደጋን ለመከላከል እና ክትትልን ለመከላከል በህንፃው ባለቤት የሚወሰዱ የደህንነት
እርምጃዎች አጥጋቢ መሆናቸውን የማወቅ እና የማረጋገጥ ምክክር ማድረግ መብት አለበት;

አንቀፅ 24. የትግበራ ቅድመ ሁኔታዎች


1) ዲዛይን ተዘጋጅቶለት ለአዋጭነት ግምገማ የሚቀርብ እና ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ የተሰጠበት
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ከመተግበሩ በፊት የትግበራ ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላቱ መረጋገጥ አለበት፤
2) ማንኛውም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ትግበራ ሂደት አካባቢያዊ፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ህጎችን፣
ስታንዳርዶችንና ቅደም ተከተሎችን ባማከለ መልኩ መከናወን አለበት፤
3) በማንኛውም የግንባታ ሥራ ወቅት ማንኛውንም አደጋ እንዳይከሰት ለመከላከል ሥራ ተቋራጩ
የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ አለበት:
ሀ. የግንባታ ቦታውን ተቀባይነት ባለው ቁሳቁስ መሸፈን፤
ለ. በመሬት ቁፋሮ ወቅት የመሰረተልማት አውታሮችን እንዳይጎዱ ማድረግ;
ሐ. በግንባታ ጣቢያው ዙሪያ የትራፊክ ፍሰት ደህንነትን ማረጋገጥ;
መ. ተቀጣጣይ የግንባታ እቃዎች ለእሳት አደጋ እንዳይጋለጡ ማድረግ፤
ሠ. ለጣቢያ ሰራተኞች እና ጎብኝዎች የደህንነት ልብሶችን ማቅረብ፣
ረ. ለግንባታ ዓላማ የኬሚካል ምርቶችን አላግባብ በመጠቀማቸው ምክንያት በሰው ልጅ ሕይወት እና
በንብረት ላይ ሊከሰት የሚችል አደጋን ለማስወገድ የመከላከያ እርምጃዎችን መውሰድ አለበት፤
ሰ. አቧራን፣ ጭስን፣ ጨረሮችን እና ሌሎችን ተመሳሳይ ንጥረ ነገሮች በአካባቢው ላይ የድምፅ ብክለት
እንዳይፈጠር የሚከላከሉ ተስማሚ ዘዴዎችን መጠቀም አለበት፤
አንቀፅ 25. የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት የአተገባበር ዲዛይን ክለሳ እና/ወይም የጥራት ቁጥጥር ወይም የጥራት
ማረጋገጥ እና የውል አስተዳደር አገልግሎት ምዕራፍ መሰረታዊ መርሆዎች
1) ማንኛውም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ስራ አስፈላጊውን ጥራት ቁጥጥር እና የጥራት ማረጋገጥ
መስፈረት ያሟላ ስለመሆኑ ከመሰረት እስከ ማጠቃለያ ስራ የአፈፈጻጸም ክትትል መደረግ አለበት
2) የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ የአሰሪውን ጥቅም በሚያስጠብቅ ሁናቴ ሁሉም አስፈላጊ የቁጥጥርና
የክትል ስርዓት በአግባቡ ተዘርግቶ ትግበራ ላይ ስለመሆኑ ማረጋገጥ አለበት፡
3) ከፕሮጀክት መደበኛ ክትትል በተጨማሪ ፕሮጀክቱ ከደረሰበት አፈፃፀም ደረጃ አኳያ በዋናነት
የፕሮጀክቱ አፈፃፀም 50 በመቶ ወይም በመካከለኛ ዘመን እንዲሁም ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ርክክብ
በሚካሄድበት ወቅት መገምገም ይኖርበታል፤
4) እንደ ፕሮጀክት ውስብስብነት እና የትግበራ መርኃ ግብር ርዝመት የመካከለኛ ዘመን ግምገማ ይዘት
ያለው ተጨማሪ ግምገማ በፕሮጀክት ትግበራ ዘመን ሊከናወን ይችላል፤
5) የፕሮጀክቱ ወሰን የተቀየረ ከሆነ፣ በፕሮጀክቱ ላይ ከቁጥጥር ውጭ በሆኑ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ
ክስተቶች ምክንያት ፕሮጀክቱን መከለስ የሚያስገድድ ሁኔታ ከተፈጠረ የፕሮጀክት ክለሳ ሊፈቀድ
ይችላል፡፡
6) አንድ ፕሮጀክት በግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር ፮፻፵፱/፪ሺ፩ መሰረት ክለሳ ማድረግ
ከተፈቀደው መጠን በላይ የዋጋ ጭማሪ የሚያስፈልገው ከሆነ ፕሮጀክቱ ተዘጋጅቶ በድጋሚ
የአዋጭነት ግምገማ ተደርጎበት መከለስ ይኖርበታል፤
7) በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (4) መሰረት የክለሳ ጥያቄ ቀርቦበት በድጋሚ በሚደረግ የአዋጭነት ግምገማ
መሰረት ተቀባይነት ያገኘ ፕሮጀክት ለውሳኔ ሰጭ አካላት ቀርቦ መፅደቅ አለበት፡፡

አንቀፅ 26. ስለ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ጥራት

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በጥራት እንዲከናወን መሟላት ስለሚገባቸው መሰረታዊ ግዴታዎች፤

1) ፕሮጀክቱ በተጠየቀው ወይም ውል በገባው የጥራት ደረጃ መጠናቀቅ አለበት

2) ከአቅም በላይ በሆኑ ምክኒያቶች እስካልሆነ በቀር ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ መጠናቀቅ አለበት

3) ፕሮጀክቱ ተጠቃሚውን ወይም ባለቤቱን ማርካት አለበት

4) የሰራተኞች ተነሳሽነት እና ማበረታቻ ስርዓት

5) ፕሮጀክቱ በተቻለ አቅም ግጭትን ለማስቀረት የቻለ መሆን አለበት

6) በዓላማ ላይ የተመሰረተ አፈፃፀም


አንቀፅ 27. የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት የአተገባበር ዲዛይን ክለሳ

1. ማንኛውም የፕሮጀክት ዲዛይን ክለሳ ጥያቄ በሳይት ማናጀሩ ወይም ፕሮጀክት መሃንዲሱ ሊቀርብ
ይችላል፤
2. ማንኛውም የፕሮጀክት ዲዛይን ክለሳ ወደ ትግበራ ሂደት የሚሸጋገር የክለሳ ጥያቄውን በአሰሪው
ሲታመንበትና ተለዋጭ ስራውን አንድ በአንድ በመዘርዘር ፈቃደኛነቱን በፅሁፍ ሲገልጥ ነው
3. የተለዋጭ ሥራ ትዕዛዝ ማረጋገጫ የተደረገበት ፕሮጀክት የእያንዳነንዱን አይተም ማብራሪያና
የሚከለስበትን ማሃንዲሳዊ ምክንያት በመግለፅ አለበት የማይለወጥ አይተም በጉልህ በሚለይ ሁኔታ
በመገለፅ አፅዳቂው አካል ስም፣ ፊርማ እና ማረጋገጫ የተሰጠበት ቀን ይፃፍበታል፤
4. ማብራሪያው ትርጉም ክፍት ያልሆነ፣ ያልተንዛዛ እና ሌላ ማብራሪያ የምይጠይቅና በቀላሉ መረዳት
እንዲቻል ሆኖ መዘጋጀት አለበት፣
5. የተለዋጭ ስራ ጥያቄ ይሁንታና ማረጋገጫ ካላገኘ ጥያቄው እንደገና ተዘጋጅቶ ሊቀርብ ወይም ውድቅ
ሊደረግ ይችላል
6. ውድቅ የተደረገ የተለዋጭ ስራ ጥያቄ ወዲያውኑ ለሚመለከተው የበላይ ተቆጣጣሪ በፅሁፍ ወይም በስልክ
በቃል ጥያቅው ውድቅ መደረጉን ማሳወቅ አለበት
7. በድጋሜ የቀረበ የተለዋጭ ስራ ጥያቄ በድጋሜ የቀረበ መሆኑን በሚገልፅ መልኩ መቅረብ አለበት

አንቀፅ 28. የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማጠቃለያ ምዕራፍ መሰረታዊ መርሆዎች

1) የፕሮጀክት ርክብብ ሂደት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የኮንትራት ውል መሰረት መከናወናቸውን


በሚያረጋግጥ መልኩ መከናወን አለበት፡፡
2) ተጠናቆ ርክክብ የተደረገበት ፕሮጀክት ወደ ስራ ለማስገባት እና ለማስቀጠል የቅድመ ዝግጅት
ስራዎች በታቀደ መልክ መከናወን አለባቸው፡፡
3) መንግስት አንድን ፕሮጀክት ወደ ምርት ወይም አገልግሎት ማስገባት የሚያስችል በጀት በወቅቱ
የመመደብ ኃላፊነት አለበት፡፡
4) ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ የማጠናቀቂያ ሪፖርት በማዘጋጀት አለበት፡፡

አንቀፅ 29. የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት የድህረ-ማጠቃለያ አገልግሎት ምዕራፍ መሰረታዊ መርሆዎች

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማጠቃለያ ምእራፍ ሂደት የሚከተሉት ንዑስ ዑደቶች ይኖረዋል፡-


ለ) የፕሮጀክት ርክክብ ፣ የማጠቃለያ ግምገማ እና ሀብት ምዝገባ፤
ሐ) ፕሮጀክትን ወደ ምርት ወይም አገልግሎት ወደ መስጠት ማስገባት፣ እና ማስቀጠል፤
….
…….
አንቀፅ 30. የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት የድህረ-ማጠቃለያ አገልግሎት ምዕራፍ

1) በአንቀፅ 15 ንዑስ አንቀፅ (2) እና (3) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ ፕሮጀክት የፕሮጀክት ኡደቶችን
ሳይጠብቅ ወደ ትግበራ እንዲገባ ሊደረግ ይችላል፤ዝርዝሩ በደንብ ይወሰናል፡፡
2) የዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ ቢኖርም የአንድ ኮንስትራክሽን ፕሮጀከት የቅድመ አዋጭነት፣
የአዋጭነት ጥናት እና ዲዛይን ተዘጋጅቶ ተገምግሞ ተቀባይነት ካላገኘ ወደ ቀጣይ ሂደት ሊሸጋገር
አይችልም፡፡
3) በተመረጡ ፕሮጀክቶች ላይ የፕሮጀክቶች ድህረ ትግበራ ግምገማ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ ስራ ከገቡ
ቢያንስ ከ 2 ዓመት ቢበዛ በ 10 ዓመት በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ መከናወን አለበት፡፡
4) ማንኛውም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አስፈጻሚ አንድን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት በተገባለት ውል መሰረት
የታለመለትን አላማና ውጤት በሚያሳካ መንገድ መጠናቀቁን አረጋግጦ መረከብ እንዲሁም ፕሮጀክቱ ወደ
ምርት ወይም አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ማረጋገጥ አለበት፤
5) ተግባራዊ የተደረጉ ከፍተኛ እና መካከለኛ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ እንደ አስፈላጊነቱ የድህረ ትግበራ
ግምገማ ያከናውናል፣ በድህረ ትግበራ ግምገማ የተገኙ ግብዓቶችን በቀጣይ ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ዝግጅት
ጥቅም ላይ መዋዋላቸውን ያረጋግጣል፤

አንቀፅ 31፡ ስለ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አፈጻጸም ምዘና


1) የኢንዱስትሪው ተዋናዮች የፕሮጀክት አፈጻጸም ምዘና እንዲያደርግ የሚያስችል አስገዳጅ ስርዓት
በመዘርጋት በምዘና መተግበር አለበት
2) ማናኛውም የኮንስትራክሽን ተዋናኞች የፕሮጀክት አፈጻጸም በየምዕራፉ እየተገመገመ ውጤቱ ይፋ
መደረግ ይኖርበታል፤

አንቀፅ 32. የኮንትራክሽን ፕሮጀክት ግዥ


1. የዚህን አዋጅ ዓላማ ለማሳካት ማንኛውም የመንግስት የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ግዢ ሂደት
ለኮንስትራክሽን ግዢ እና ውል አስተዳደር የወጡ የማስፈፀሚያ ህጎችን እና የአሰራር ስርአቶችን
የተከተለ ስለመሆኑ ማረጋገጥ አለበት፤
2. የመንግስት የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ግዢ የፕሮጀክት አተገባበር ብቃትን መሰረት በማድረግ
የሚከናወን መሆን አለበት ለዚህም ቁልፍ የአፈጻጸም መለኪያ በማዘጋጀት የአፈጻጸም ምዘና ስርአት
በመዘርጋት ጥቅም ላይ እንዲውል መደረግ አለበት፣

አንቀፅ 33. ስለ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል/ግብዓት እና ቴክኖሎጂ አግባብነት መርህ/Standard of materials


1) ማንኛውም የሥራ ተቋራጭ የሚጠቀመው የኮንስትራክሽን ግብዓት በውል ሰነድ በተካተተው አይነትና ደረጃ

ልክ የኮንስትራክሽን ግብዓት መጠቀምና ስራውን በተገቢው ጥራት ማከናወን ይኖርበታል

2) ለግንባታ የሚቀርበው ግብዓት ደረጃ በውል በግልፅ ባልተቀመጠ ጊዜ ስራ ተቋራጩ የኮንስትራክሽን ስራውን

ከጉድለት ነፃ በሆነና እንደፕሮጀክቱ አይነት ተገቢነት ባለው ግብዓት ማከናወን ይጠበቅበታል፤

3) ይሁን እንጂ የጥራት ጉደለት ያለበትን የግንባታ ግብዓት እንዲጠቀም በአሰሪው ትዕዛዝ ግዴታ የተደረገበት

የሥራ ተቋራጭ ጉድለት ባለበት ግብዓት ለሰራው ስራ ተጠያቂ አይሆንም፤

4) በተዋዋዮች መካከል ስለ ፕሮጀክቱ ትግበራ ሂደት ስለሚያሰማራው የባለሙያ ስራንዳርድ በውል በግልፅ

ባልተካተተ ጊዜ ሥራ ተቋራጩ ለስራው ተገቢነት ባለው ባለሙያ ማሳተፍ እና ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ

ስራውን የማከናወን ግዴታ አለበት

5) ማንኛወም የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጭ የግንባታ ግብዓት በማቅረብ ለማከናወን ከተዋዋለ እና ለፕሮጀክቱ

አላማ ተገቢነት ያለው (fit for the purpose) የግንባታ ግብዓት በመጠቀም የመገንባት ግዴታ አለበት፤

6) ሥራ ተቋራጩ ሆነ ንዑስ ስራ ተቋራጩ አሳማኝ ባልሆነ ሙያዊ አሰራር ላከናወነው ስራ ተጠያቂ ነው፡፡

አንቀፅ 34. የፕሮጀክቱ አሰሪ ወይም ባለቤት ግዴታ

1) ማንኛውም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አሰሪ ወይም የፕሮጀክት ባለቤት ሥራ ተቋራጩ ሥራውን

ለማከናወን በሚያደረገው ጥረት ስራውን እንዳያከናውን ከሚያግድ ማንናውም አይነት ድርጊት በመራቅ

ለሥራው ስኬት ሥራ ተቋራጩን በንቃት የመተባበር ግዴታ አለበት፤

2) አሰሪው ሳይዘገይ የሥራ ቦታ/ሳይት ማስረከብ፣ አርክቴክት መሰየም፣ ንዑስ ስራ ተቋራጭ እና

የኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢ መሰየም፣ አስፈላጊ የሆኑ ትዕዛዛትን፣ መረጃዎችን፣ ዕቅዶችን እና የንድፍ

ስራዎችን ማቅረብ

3) በማንኛውም ሰው ወይም ተወካይ ለሥራ ተቋራጩ በሚቀርብ አስፈላጊ የኮንስትራክሽን እቃ አቅርቦት

ላይ ጣልቃ በመግባት ወይም ውሉን እንዲያስተዳድር ስልጣን በተሰጠው ነፃ አካል አሰራር ላይ ጣልቃ

መግባት የለበትም፤

4) አማካሪው ለሚያከናውነው ማንኛውም ፕሮጀክት አሰሪው በተቻለ ፍጥነት (ነገር ግን የመረጃው ጋር


ተዛምዶ ባለው ጉዳይ ላይ የኮንስትራክሽን ምዕራፍ ከመጀመሩ አስቀድሞ) አስፈላጊው መረጃ ሁሉ

ለአማካሪው የደረሰው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፤

5) በንዑስ አንቀፅ 4 መሰረት እንዲሟላ የሚፈለገው መረጃ በዚህ አዋጅ በተደነገገው መሰረት ከአማካሪው

ግዴታ ጋር ተገቢነተት ያላቸው መረጃዎች እና በአሰሪው ይዞታ ወይም በሌላ ሰው ይዞታ ሲሆን አሳማኝ

በሆነ ዘዴ በመጠቀም መረጃውን ማረጋገጥ የሚቻልባቸው መሆን አለባቸው፤

አንቀፅ 35. የሥራ ተቋራጩ ግዴታ/Contractor’s obligations

1) የኮንስትራክሽን ስራ ለማከናወን የሚሰማራ ማንኛውም ሥራ ተቋራጭ ግዴታ በገባበት ስምምነት

መሰረት ግዴታውን አክብሮ በመስራት ፕሮጀክቱ የታለመለትን አገልግሎት መስጠት (the completed

works will be fit for their purpose) በሚያስችል ሁኔታ የማከናወን ኃላፊነት አለበት፣

2) ማንኛወም የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጭ ለማከናወን ውል በወሰደበት የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት

የፕሮጀክቱን ማጠናቀቂያ ጊዜ በውል ቢቀመጥም ባይቀመጥም ሥራውን በትጋት በመስራት

ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ማጠናቀቅ አለበት፣

3) የኮንስትራክሽን ሥራ ለማከናወን ውለታ የሚወስድ ማንኛውም ሥራ ተቋራጭ በትግበራ ላይ

በፕሮጀክት ጥራትና በጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት ሊደርስ ለሚችል ጉዳት ማካካስ የሚረዳ ዋስትና

ማቅረብ አለበት፡፡ ዝርዝሩ ይህንን አዋጅ ለማስፈፀም በሚወጣው ደንብ ይወሰናል፡፡

አንቀፅ 36 የንድፍ አውጭው/ዲዛይነር ግዴታ Architects Obligation

1) በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ዲዛይን ለማዘጋጀት ፈቃድ ያለው ባለሙያ ወይም ድርጅት ዲዛይን

የሚዘጋጅለት ፕሮጀክት ለታለመለት አላማ ወይም አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል ሁኔታ ተገቢነት

ያለው ጥንቃቄ እና ሙያዊ ግዴታን በመተግበር መዘጋጀቱን የማረጋገጥ ግዴታ አለበት፤

2) በማንኛውም ሁኔታ በኮንስትራክሽን ዲዛይን የጥራት ጉድለት ለሚከሰት የዲዛይን ስህተት ወይም

በዲዛይን የጥራት ጉድለት ምክንያት ለሚደርሰው ጉዳት ዲዛይኑን ያዘጋጀው አርክቴክት ወይም ድርጅት

ተጠያቂ ነው፤ ሆኖም ግን እንደ ፕሮጀክቱ አይነት ዲዛይን የማዘጋጀትና የኮንስትራክሽን ስራው በአንድ

ሥራ ተቋራጭ በሚከናወንበት ውል በዲዛይን ስህተት ለመጣው ጉድለት ሥራ ተቋራጩ ተጠያቂ ይሆናል

3) በአሰሪው ይሁንታ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ንዑስ ንድፍ አውጭ በውክልና በተሳተፈበት የዲዛይን ዝግጅት

ለሚከሰት ማንኛውም የዲዛይን ስህተት ለሚደርስ ጉዳት ዋና አርክቴክቱ ወይም ዋና ንድፍ አውጭው
ሃላፊ ነው፤

4) ዋና ንድፍ አውጭው አርክቴክት አሰሪው ለሚያሰራው ፕሮጀክት ንኡስ ዲዛይነር እንዲቀጠር አስፈላጊ

መሆኑን ባወቀ ጊዜ ተገቢ ጥንቃቄ እና ሙያዊ ክህሎት ተግባራዊ በማድረግ ለአሰሪው ሃሳብ ማቅረብ

አለበት፣ በቸልተኝነት ያቀረበው ንኡስ ዲዛይነር ለአሪው ጉዳት ዋና ንድፍ አውጭው አርክቴክት ተጠያቂ

ይሆናል፤

5) ዲዛነሩ የኮንስትራክሽን ሥራ ግብዓት ዝርዝር ስፔሲፊኬሽን ዝግጅት ተገቢውን ጥንቃቄና ሙያዊ ክህሎት

ተግባራዊ በማድረግ የሚመረጠው ግብዓት ለታለመለት አላማ እንዲውል የሚያስችል መሆኑን በማረጋገጥ

ማዘጋጀት አለበት፣

6) ማንኛውም የኮንስትራክሽን ዲዛይን አግባብነት ያላቸውን ህግጋት መስፈርት ያሟላ መሆን አለበት፣

7) የኮንሰትራክሽን ዲዛይን በኮንሰትራክሽን ሥራ ተቋራጩ በሚከናወንበት የኮንሰትራክሽን ፕሮጀክት ውል

ለተከሰተው የንድፍ ስህተት ሥራ ተቋራጩ በራሱ ሃላፊነት አለበት

8) በአርክቴክቱ ይሁንታ ሥራ ተቋራጩ፣ ንዑስ ሥራ ተቋራጩ ወይም ሌላ አቅራቢ የንድፍ ስራውን

እንዲያቀርብ በተደረገ ጊዜ ዋና አርክቴክቱ እና ዲዛይኑ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ ሃላፊነት የወሰደው ሰው

በጋራ ተጠያቂ ይሆናሉ፤

አንቀፅ 37. የውል አስተዳዳሪው/አማካሪ ሃላፊነት

1) በውሉ ማሻሻል ወይም መለወጥ በሚለው ስር በግልጽ ካልተካተተ በስተቀር ማንኛውም አማካሪ በዋናው

ውል ስምምነት ይዘት የማሻሻል ወይም የመለወጥ፣ አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ስራን የማስተላለፍ

ትዕዛዝ የመስጠት ስልጣን የለውም፤

2) በውል የተሰጠውን ስልጣን በመተላለፍ በሶስተኛ ወገን ላይ ጉዳት እንዲከሰት ምክንያት የሆነ አማካሪ

ድርጅት ለሚደርሰው ጉዳት በግል ተጠያቂ ነው፤

3) አማካሪው ስራውን በሚሰራበት ሁኔታ አሳማኝ ጥንቃቄ እና ክህሎት የአሰሪውን ጥቅም በሚያስከብር

ሁኔታ ምክር መስጠት እንዲሁም ማንኛውንም የትግበራ ሂደት ክትትል በማድረግ ስራውን ማከናወን

አለበት፤

አንቀፅ 38. ስለ ክትትልና ቁጥጥር


1) ሕጋዊ የኮንስትራክሽን ሥራ ፈቃድ አግኝቶ ሥራው በተጀመረ ማንኛውም ኮንስትራክሽን ሥራ ላይ ለኮንስትራክሽን ሥራው
የሚውሉ ግብዓቶች የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ እና በሚመለከተው አካል የተረጋገጡ ስለመሆናቸው እና የኮንስትራክሽን
ሥራው የሚካሄድበት ቦታ ደህንነትና ጤንነት አስተማማኝ ለመሆኑ በተቋሙ ክትትልና ቁጥጥር ይደረግበታል፤ ዝርዝሩ ይህንን

አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣው ደንብና መመሪያ ይወሰናል፡፡ (አንቀጽ 3 እና 4 ተካተዋል)

2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በየእርከኑ ክትትል ሊደረግባቸው የሚገቡ የኮንስትራክሽን
ስራዎች ሲከናወኑ ክትትልና ቁጥጥር በሚያደርገው አካል ሳይፈቀድ ሥራው ወደፊት መቀጠል አይችልም፡፡
3) በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኝ ማንኛውም ፕሮጀክት ግንባታው እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ ለሥራው በሚመደቡ የግንባታ
ተቆጣጣሪዎች ክትትልና ቁጥጥር ይደረግበታል፣
4) በዚህ አዋጅ የተቀመጠው የቁጥጥር ሥርዓት እንደተጠበቀ ሆኖ በሌሎች ዘርፎች ለሚከናወኑ የኮንስትራክሽን ሥራዎች
የቁጥጥር ዓይነትና አሠራር እንዲሁም የተቆጣጣሪዎች ሥልጣንና ሃላፊነት በህግ ይወሰናል፣
5) ምስክር ወረቀት ሰጪው አካል በመመሪያው መሠረት የሰጣቸውን የብቃት ማረጋገጫ ወይም የምዝገባ ምስክር ወረቀት
ባለሙያው፣ ሙያተኛው ወይም ድርጀቱ ስራውን በህጉ መሠረት መስራቱንና ፈቃዱ ይሰራበታል ተብሎ ለታቀደለት አላማ

መዋሉን ሚ/ር ም/ቤቱ ይቆጣጠራል፡፡

6) በዚህ መመሪያ መሠረት ምሰክር ወረቅት ያልያዘ የኮንስትራክሽን ባለሙያ፣ ሙያተኛ፣ ስራ ተቋራጭና አማካሪ ድርጅት

ምሰክር ወረቅት በመያዝ በግንባታ ስራ ላይ እንዲሰማራ በቀባለስልጣን መ/ቤቱ ሚ/ር መ/ቤቱ ቁጥጥርና ድጋፍ ያደረጋል፡፡

7) ማንኛውም ስራ ተቋራጭ እና አማካሪ ድርጅት ለመስፈርት ማሟያነት ባቀረባቸው ባለሙያዎችና ሌሎች በመስፈርቱ ላይ
የተገለጹ ሁኔታዎችን አሟልቶ እየሰራ መሆኑን ለማረጋገጥ ቁጥጥር ያካሂዳል፡፡
8) ማንኛውም የኮንስትራክሽን ባለሙያ ወይም ድርጅት በተሰማራበት የሙያ መስክ ምስክር ወረቀት ደረጃ መስፈርት ያልጠበቀ

ሆኖ ከተገኘ ሚ/ር መ/ቤቱ በሚወስነው የጊዜ ገደብ ውስጥ ጉድለቶቹን እንዲያስተካክል የጽሑፍ ትዕዛዝ ይሰጠዋል፡፡

9) በዚህ አንቀጽ መሠረት የሚደረገው ቁጥጥር በቀባለስልጣን መ/ቤቱ ሚ/ር መ/ቤቱ አመቺ ነው ብሎ ባመነበት ጊዜ ሊያካሂድ
ይችላል፡፡
10) በዚህ አንቀጽ መሰረት ሚ/ር መ/ቤቱ የሚመድባቸው ተቆጣጣሪዎች ለሚያቀርቡለት ጥያቄ ድርጅቱ ወይም ባለሙያው
ተገቢውን መረጃ የመስጠት እና የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
ሚ/ር መ/ቤቱ የሚመድባቸው ተቆጣጣሪዎች የመታወቂያ ወረቀት እና የሚ/ር መ/ቤቱን ደብዳቤ ቁጥጥሩን
ለሚያካሄድበት ድርጅት ባለቤት ወይም ለህጋዊ ወኪሉ ማሳየት አለባቸው።
አንቀፅ 39. የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ሥራ አመራር
በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጀመንት ስራ ላይ የተሰማራ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት እንዲሁም የመንግስት አካል በዘርፉ

(በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጀመንት ኢንስቲቲዩት የተዘጋጁ 18 ማንዋሎችን ስራ ላይ አውሎ መስራት የሚችል ሲሆን
የሚመለከተው አካል የተዘጋጁ ማንዋሎችን ለማስፈጸም አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ተደራሽ የማድረግ ግዴታ አለበት፣

አንቀፅ 40. የኮንስትራክሽን ሥራ ቦታ/ሳይት ርክክብ

1) ሌላ የውል ቃል ከሌለ በስተቀር አሰሪው ወይም የፕሮጀክቱ ባለቤት ውሉ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በሁለት

ወራት ውስጥ ለስራ ተቋራጩ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት የሚከናወንበትን ቦታ ርክክብ ማከናወን አለበት

2) በውል በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት የሚከናወንበትን ቦታ ርክክብ ያላከናወን


ማንኛውም አሰሪ ውል ባላከበረበት ልክ ለጉዳት ሃላፊ ነው፤ ፕሮጀክቱ በመዘግየቱ ለተከሰተው ኪሳራም

ስራ ተቋራጩን መጠየቅ አይችልም፤

3) እንዳለ ሆኖ ስራ ተቋራጩ ርክክቡ እንዳይፈጻም የተከለከለው ከአሰሪው አቅም በላይ በሆነ ከሆነ በሶስተኛ

ወገን ጣልቃ ገብነት ወይም ሌላ ህገወጥ ድርጊት ከሆነ አሰሪው ዋስትና እንዲሰጥ አይገደድም ሃላፊም

አይሆንም፤

4) ለሥራው ቅልጥፍኛ ሲባል ማንኛውም የሥራ ተቋራጭ የተለመደና ተገቢ ትጋት በማድረግ የፕሮጀክቱ

በተገቢ ፍጥነት በቂ የዕድገት ደረጃ ማሳደግ አለበት ፤

5) አንድ ፕሮጀክት ስራ በተግባር ተጠናቀቀ የሚባለው ሁሉም ኮንስትራክሽን ስራ ሲጠናቀቅ ወይም

ለተፈለገው አላማ በሚሆን ደረጃ ለአሰሪው ይዞታ ስር መሆን የሚስችል

6) እንዳለ ሆኖ በግልጽ ሚታይ ጉድለት እስካልሆነ ድረስ የተተወ ስራ ወይም ጥቃቅን መናኛ ጉድለት ቢኖርም

ተቆጣጣሪው የፕሮጀክት ትግበራው ማለቁን ማረጋገጫ ሊሰጠው ይችላል፤

አንቀፅ 41. የፕሮጀክት መጠናቀቅ የሚያስከትለው ውጤት

1) በተዋዋይ ወገኖች መካከል የተደረሰው የውሉ ስምምነት እንደተጠበቀ ሆኖ ውሉን የሚቆጣጠረው አካል

የፕሮጀክቱን መጠናቀቅ ማረጋገጫ የሚሰጥ ሆኑ የፕሮጀክት መጠናቀቅ የሚከተሉት የተለመደ ውጤት

ያስከትላል

2) የፕሮጀክቱ ባለመብትነት እና ባለይዞታነት ለአሰሪው በስሩ እንዲሆን ይገደዳል

ሥራ ተቋራጩ ስራው መጠናቀቁን ማረጋገጥ ሃላፊነት አለበት

3) በመዘግየት ምክንያት ለሚደርስ ጉዳት ስራ ተቋራጩ ካሳ ከመክፈል ያድነዋል፣ ተጠናቅቆ ርክክብ

የተደረገበት ፕሮጀክት ጉድለት የነበረው መሆኑ ዘግይቶ የታወቀ ቢሆንም እንኳን ስራ ተቋራጩ

አስቀድሞ የተሰጠውን የማጠናቀቅ ማረጋገቻ ሰርተፊኬት ሊሽረው አይችልም፤

4) ሥራ ተቋራጩ በመያዣነት ያለ ያልተከፈለ ቀሪውን ግምሽ ገንዘብ ይከፈለዋል

5) በጉድለት ስለመኖሩ ምክንያት ሃላፊነት የሚጀምርበት ጊዜ ጀምራል፤

አንቀፅ 42. ተቀባይነት ያለው የጊዜ ማራዘሚያ

1) የፕሮጀክት ማጠናቀቂያ ጊዜ ሚራዘመው ውሉ ከፈቀደ እና በውሉ ድንጋጌ መሰረት ነው ይሁን እንጂ ሥራ

ተቋራጩም ሆነ አሰሪው ተቀባነት ያለው የጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄ የሚከተሉት ናቸው


2) ያልታሰበ ክስተት ውሉን በከፊል ዌም በሙሉ ለማከናወን ፍፁም የማይቻል ሁኔታ ሲያጋጥም

3) ከተለመደው የተለየ የአየር ንብረት መለዋጥ ሁኔታ ሲያጋጥም እና ክስተቱ ለትግበራው መዘግየት ጉልህ

አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያስከትል ከሆነ

4) ሰደድ እሳት፣ መብረቅ፣ ፍንዳታ፣ ሞገድ፣ ጎርፍ፣ ገደብ ያለፈ የውሃ ታንከር፣ፍሰት ወዘተ ምክንያት

በሚከሰት በአደገኛ ክስተት ለሚፈጠር ጉዳት

5) የሥራ ማቆም አድማ ወዘተ

አንቀፅ 43. ስለ የውል ግዴታዎች ልዩነቶች/ለውጥ/Varietion of contractual obligations

1) በኮንስትራክሽን ውል ውስጥ ስለ ሥራ ተቋራጩ ግዴታዎች ልዩነቶች/ለውጥን በሚመለከት የጽሁፍ ድንጋጌ

ባይኖርም ልዩነቶችን በሚመለከቱ ድንጋጌዎች በውል እንደተካተቱ ይቆጠራሉ፣

2) በዚህ ሁኔታ የልዩነቱ/ለውጥ ስፋትና መጠን እና አሰሪው ለሥራ ተቋራጩ የሚከፍለው መጠን ወይም

መጠኑን ለማስላት የሚያስችል ዘዴ ላይ ኮንትራክተሩ እና አሰሪው ካልተስማሙ በስተቀር ማንኛውንም ስራ

ተቋራጭ በልዩነት ምክንያት ግዴታዎች ለመፈጸም አይገደድም፣

አንቀፅ 44. የሥራ ተቋራጩ ክፍያዎችን የመጠየቅ መብት

1. ማንኛውም ሥራ ተቋራጭ ለሚያከናውናቸው ግዴታዎች በቂ ክፍያ የመከፈል መብት ያለው ሲሆን ሙሉ

በሙሉ ግዴታውን አከናውኖ ባያጠናቅቅም ግዴታውን በፈጻመበት መጠን ምክንያታዊ ክፍያ ይከፈለዋል፣

2. በስራው መጠን መጨመር እየታየ የሚከናወን ክፍያን በተመለከተ በአሰሪው ያልተከፈለ ውዝፍ ክፍያን

ጨምሮ ኮንትራክተሩ ካከናወናቸው ግዴታዎች ጋር በተያያዘ አንድ ወይም ብዙ የክፍያ ጥያቄዎችን

ለማቅረብ መብት አለው፣

3. የሥራ ተቋራጩ የሂደት ክፍያ ጥያቄ ተቋራጩ ማንኛውንም ግዴታውን ከፈጸመ በኋላ በማንኛውም ጊዜ

ሊደረግ ይችላል፣

4. የሥራ ተቋራጩ የሂደት ክፍያ ጥያቄ መጠየቅ ሥራ ተቋራጩ በዚህ ውል መሠረት ወይም ከዚህ ጋር

በተያያዘ ለሚከፈለው ገንዘብ ማንኛውንም ሌላ ጥያቄ ከመጠየቅ አያግደውም።

አንቀፅ 45፡ የክፍያ ጥያቄዎች


የክፍያ ጥያቄዎች ማለት፡-

1. ሥራ ተቋራጩ በውል ውስጥ ያሉትን ግዴታዎች አፈጻጸምን በሚመለከት መጠን ገንዘብ እንዲፈለው

ለአሰሪው የሚያቀርበው የይገባኛል ጥያቄ ወይም

2. አሰሪው በውል ውስጥ ያሉትን ግዴታዎች በመፈፀም ወይም አለመፈጸምን በሚመለከት ከስራ ተቋራጩ

የሚጠይቀው የገንዘዘብ ጥያቄ ነው፣

አንቀፅ 46. ለክፍያ ጥያቄ / ክርክር ማስታወቂያ ምላሽ መስጠት.

1. የክፍያ ጥያቄ የተቀበለው ተዋዋይ ወገን ጥያቄው ውድቅ መደረግ አለበት ብሎ የሚያምን ከሆነ

ጥያቄው በውል መሠረት ስላልቀረበ፤ ወይም የይገባኛል ጥያቄውን በሙሉ ወይም በከፊል

የሚያከራክር ልዩነት ያለበት ሲሆን ጥያቄው የቀረበለት ወገን የይገባኛል ጥያቄውን ከተቀበለ በኋላ በ

14 ቀናት ውስጥ ለጠያቂው የክርክር ማስታወቂያ መስጠት አለበት ።

2. የክርክር ማስታወቂያ፤

(ሀ) በጽሑፍ መሆን አለበት; እና

(ለ) ለጠያቂው መቅረብ አለበት;; እና

(ሐ) ማስታወቂያውን የሰጠውን ወገን ስም እና

(መ) የማስታወቂያውን ቀን እና

(ሠ) ማስታወቂያው የቀረበበት የይገባኛል ጥያቄ መለየት; እና

(ረ) የይገባኛል ጥያቄው በንኡስ አንቀጽ (1) (ሀ) ውድቅ ከተደረገ - በውሉ መሠረት የክፍያ ጥያቄው

እንዳልቀረበ ያስደረገውን ምክንያቶች መግለፅ; እና

(ሰ) የይገባኛል ጥያቄው በንኡስ አንቀጽ (1) (ለ) መሠረት አከራከሪ ከሆነ - እያንዳንዱን የይገባኛል

ጥያቄውን እና ከእያንዳንዳቸው ጋር በተዛመደ የክርክር ምክንያቶችን መግለፅ እና

(ሸ) ማስታወቂያውን በሚሰጠው አካል መፈረም አለበት


3. ተዋዋይ ወገኖች የክፍያ ጥያቄ ከተቀበለ በኋላ በ 28 ቀናት ውስጥ የይገባኛል ጥያቄው ውድቅ ከተደረገ

ወይም ሙሉ በሙሉ በንኡስ አንቀጽ (1) መሠረት ካልተከራከረ በስተቀር ፓርቲው ከሚከተሉት

ውስጥ አንዱን ማድረግ አለበት -

(ሀ) ክርክር የሌለበትን የይገባኛል ጥያቄ መጠን ክፍል መክፈል;


(ለ) የይገባኛል ጥያቄውን ሙሉ በሙሉ መክፈል.

4. (በዚህ ውል መሠረት አሰሪው ለሥራ ተቋራጩ የሚከፍለውን ማንኛውንም የገንዘብ መጠን ከፊሉን

ለመያዝ መብት ያለው እንደሆነ፡-

(ሀ) ንኡስ አንቀጽ (3) መብቱን አይጎዳውም; እና

(ለ) አሰሪው በመብቱ ውስጥ የያዘውን ማንኛውንም ገንዘብ ለኮንትራክተሩ በጽሑፍ (በክርክር

ማስታወቂያ ወይም በተናጠል) ማሳወቅ አለበት።

አንቀፅ 47፡ ውዝፍ ክፍያዎች ላይ ስለሚከፈል ወለድ

በኮንስትራክሽን ውል ውስጥ በውል በተቀመጠው ጊዜ ያልተከፈለ ማንኛውም ክፍያን በተመለከተ ወለድ ስለ

መክፈል የጽሁፍ ድንጋጌ ከሌለው;

1. በውል መሠረት በተወሰነው ቀን ወይም ከዚያ በፊት ለሌላ ተዋዋይ ወገን ተከፋይ መደረግ የተበረበት

ነገር ግን ከዚያ ቀን በኋላ ላልተከፈለ ገንዘብ መጠን ወለድ ታስቦበት ተከፋይ መሆን አለበት፣

2. ወለድ የሚከፈልበት ቀን የሚጀምረው ክፍያ መፈፀም ከነበረበት ቀን ማግስት ጀምሮ እና የሚያበቃው

ደግሞ ክፍያ የተፈጻመበት ቀን ጨምሮ ላለው ጊዜ ነው።

3. በማንኛውም ጊዜ የሚከፈለው የወለድ መጠን በብሔራዊ ባንክ የወለድ ልውውጥ መሠረት ለዚያ ጊዜ
ከሚወሰነው ልክ ነው።

አንቀፅ 48፡ ስለ ፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ/ ስለ ክርክር/ሙግት


ክፍል ሶስት
ጤና እና ደህንነት ተግባራት እና ሚናዎች
አንቀፅ 49. አጠቃላይ ተግባራት
1) በኮንስትራክሽን በፕሮጀክት ላይ የሚሰማራ ማንኛውም ሰው በፕሮጀክት ትግበራ ሂደት የጤና እና የደህንነትን

የጥንቃቄ መስፈርቶችን ሚና ለመወጣት የሚያስችለውን ክህሎቶች, ዕውቀት እና ልምድ ያለው መሆን አለበት፤

2) በኮንስትራክሽን በፕሮጀክት ላይ የሚሰማራ ማንኛውም አርክቴክት ወይም ሥራ ተቋራጭ በንዑስ አንቀጽ (1)

የተመለከቱትን ሁኔታዎች ካላሟል በቀር ለአንድ ፕሮጀክት ስራ ለመስራት አይችልም።

3) የግንባታ ስራ ለማሰራት የሚፈልግ ማንኛውም አሰሪ ወይም ባለቤት ለስራዉ የሚቀጥራቸው አርክቴክት ወይም

ሥራ ተቋራጭ በንዑስ አንቀጽ (1) ውስጥ ያሉ ሁኔታዎች ያሟላ ባለሙያ ወይም ድርጅት መሆናቸው ማረጋገጥ

ይኖርበታል፤

4) በዚህ አዋጅ መሰረት ግዴታ ያለበት ማንኛውም ሰው ከፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ግዴታ ወይም ተግባር ያለበትን ሰው

ግዴታውን ለመወጣት በሚያስችል መጠን የመተባበር አለበት።

5) በሌላ ሰው ቁጥጥር ሥር ሆኖ በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ላይ የሚሠራ ማንኛውም ሰው በራሱ ጤንነት ወይም

ደኅንነት ወይም ሌሎችን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል መረጃ ካወቀ የሚያውቀውን መረጃ ለሚቆጣጠረው ሰው

ማሳወቅ አለበት፤

6) በዚህ አዋጅ መሰረት መረጃ የመስጠት ወይም ሪፖርት የማድረግ ሀላፊነት ያለበት ማንኛውም ሰው በስራ ሂደት

የሚያጋጥመውን የተሟላ መረጃ በተቻለ ፍጥነት ሪፖርት ማድረግ አለበት።

አንቀፅ 50. የአርክቴክት ግዴታ


1) የፕሮከክት ባለቤት በዚህ አዋጅ መሠረት የሚጠበቅበትን ግዴታዎች የሚያውቅ መሆኑን እስካላረጋገጠ ድረስ

ከፕሮጀክት ጋር በተያያዘ አርክቴክቱ የንድፍ ሥራ መጀመር የለበትም፣


2) ንድፍ አውጪው ንድፍ ሲያዘጋጅ ወይም ሲቀይር አጠቃላይ የጥንቃቄ መርሆዎችን ግምት ውስጥ ማስገባት እና
ማንኛውንም ቅድመ-ግንባታ መረጃን በመጠቀም በተቻለ መጠን በማንኛውም ሰው ጤና እና ደህንነት ላይ
ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን ለማስወገድ በሚያስችል መልኩ ማከናወን ይኖርበታል፤
3) አደጋዎችን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት የማይቻል ከሆነ ንድፍ አውጪው ጉዳት ለመቀነስ ወይም ይህ ካልተቻለ
ደግሞ በሚቀጥለው በቀጣይ የንድፍ ሂደት ውስጥ አደጋዎችን ለመቆጣጠር በሚያስል መልኩ ዲዛይን ማድረግ፣
ስለ አደጋዎች መረጃ ማሳወቅ እና መረጃ በጤና እና ደህንነት መዝገብ ውስጥ መመዝገቡን ማረጋገጥ አለበት፤
4) ንድፍ አውጪው ስለሰራው የንድፍ ስራ ጋር ጋር በተያያዘ ለደንበኛው ስለ ንድፉ፣ ግንባታው ሂደት በበቂ ሁኔታ
እንዲረዳው በቂ መረጃ መስጠት እንዲሁም ሌሎች ዲዛይነሮች እና ኮንትራክተሮች በእዚህ አዋጅ መሰረት
ግዴታቸውን እንዲወጡ ድጋፍ መረጃ ለመስጠት ጥረት ማድረግ አለበት።
አንቀፅ 51. በቅድመ-ኮንስትራክሽን ሂደት ላይ ከጤና እና ከደህንነት ጋር በተገናኘ የዋና የአርክቴክት ሀላፊነት
1) ዋናው ዲዛይነር ከግንባታው በፊት ያለውን ሂደት ማቀድ፣ ማስተዳደር እና መከታተል፣ ከጤና እና ከደህንነት ጋር

የተያያዙ ጉዳዮችን ማስተባበር፣ በተቻለ መጠን ፕሮጀክቱ በጤና እና ደህንነት ላይ አደጋ ሳያስከትል

እንዲተከናወን በቂ ጥንቃቄ ማድግ አለበት፡፡

2) ንድፍ አውጪው በአንቀጽ (1) ላይ ያለውን ግዴታ በመወጣት ላይ እና በተለይም ደግሞ በአንድ ጊዜ ወይም

በቅደም ተከተል የሚከናወኑትን የንድፍ ስራ፣ ቴክኒካዊ እና ድርጅታዊ ገጽታዎች፣ ሥራውን ወይም የሥራ

ደረጃዎች ለማጠናቀቅ የሚፈጀውን ጊዜ በመገመት አጠቃላይ የጥንቃቄ መርሆችን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም

የሁሉንም የግንባታ ደረጃዎች እቅድ ይዘት እና ማንኛውም የጤና እና የደህንነት መረጃዎችን ከግምት ውስጥ

ባስገባ መልኩ ማከናወን አለበት፤

3) በአንቀጽ (1) የተመለከቱትን ሥራዎች ሲፈጽም ንድፍ አውጪው የኮንስትራክሽን ሥራ በማከናወን ላይ ባለ

ወይም ጉዳት ሊደርስበት የሚችል በማንኛውም ሰው ሰው ጤና ወይም ደህንነት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን

ለመለየትና ለማስወገድ ወይም ለመቆጣጠር ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት፤

4) ዋናው ዲዛይነር ዋና ዲዛይነር በተሾመበት ጊዜ ከዋናው ሥራ ተቋራጭ ጋር በመገናኘት የግንባታውን ደረጃ

እቅድ, አስተዳደር እና ክትትል እና በግንባታው ደረጃ ላይ የጤና እና የደህንነት ጉዳዮችን ማስተባበርን

የሚመለከቱ መረጃዎችን ከዋናው ተቋራጭ ጋር ማካፈል አለበት. .

አንቀፅ 52. በግንባታ ደረጃ ላይ ከጤና እና ከደህንነት ጋር በተገናኘ የዋና ተቋራጭ ተግባራት
1) ዋናው ሥራ ተቋራጩ የኮንስትራክሽን ምዕራፍ ማቀድ፣ ማስተዳደርና መከታተል እና በግንባታው ምዕራፍ

ውስጥ ከጤናና ከደህንነት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በማስተባበር ለጤናና ለደህንነት አደጋ ሳይጋለጥ የግንባታ

ሥራ መከናወኑን ማረጋገጥ አለበት።

2) ሥራ ተቋራጩ በአንቀጽ (1) ላይ ያለውን ግዴታ በመወጣት ላይ እና በተለይም ደግሞ በአንድ ጊዜ ወይም

በቅደም ተከተል የሚከናወኑትን ቴክኒካዊ እና ድርጅታዊ ገጽታዎች፣ ሥራውን ወይም የሥራ ደረጃዎች

ለማጠናቀቅ የሚፈጀውን ጊዜ በመገመት አጠቃላይ የጥንቃቄ መርሆችን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም የሁሉንም

የግንባታ ደረጃዎች እቅድ ይዘት እና ማንኛውም የጤና እና የደህንነት መረጃዎችን ከግምት ውስጥ ባስገባ

መልኩ ማከናወን አለበት፤

3) ዋናው ሥራ ተቋራጩ በተመሳሳይየግንባታ ቦታ ላይ የሚሳተፉ ተከታታይ ተቋራጮችን ጨምሮ

በኮንትራክተሮችን ያስተባብራል፣ በህግ የተደነገጉ የጤና እና የደህንነት መስፈርቶች እንዲተገበሩ


የኮንትራክተሮች አፈፃፀምን ይከታተላል፤ አሠሪዎች እና ለሠራተኞች ደህንነት አስፈላጊ አጠቃላይ የመከላከያ

መርሆችን እንዲተገበሩ ክትትል ማድረግ ይኖርበታል፤

4) ዋናው ሥራ ተቋራጭ ለኮንስትራክሽን ስራው ተስማሚ ጣቢያ መዘጋጀቱን፣ የልተፈቀዱ ሰዎች ወደ ግንባታው

ቦታ እንዳይደርሱ ለመከላከል የሚያስችል አስፈላጊ እርምጃዎች መከናወናቸው እና በሁሉም የግንባታ ምዕራፍ

አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች የጥንቃቄ መገልገያዎች መሟላታቸውን ማረጋገጥ አለበት፤

5) ዋና ሥራ ተቋራጩ ዋና ዲዛይነር በተሾመበት ጊዜ ከዋናው ዲዛይነር ጋር በመገናኘት በቅድመ-ግንባታ ምዕራፍ

ማስተባበርን እንዲሁም የጤና እና የደህንነት ጉዳዮችን የሚመለከቱ የቅድመ-ግንባታው ሂደት እቅድ፣

አስተዳደር እና ክትትል መረጃዎችን ከዋናው ዲዛይነር ጋር መለዋወጥ አለበት።

አንቀፅ 53. የአሰሪው የጤና እና ደህንነት ፋይል የማደራጀት ግዴታ ለቁጥጥር

1) ማንኛውም አሰሪ ለሚያሰራው ፕሮጀክት ስለ ጤና እና ደህንነት የቀረበለትን መረጃ ፋይል በህጉ

መሰረት የተቀመጡ መስፈርቶች እና ክልከላዎች እየተከበሩ ስለመሆኑ መረጃ በማየት ቁጥጥር

ለማድረግ ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ለቁጥጥር ስራ በሚያመች ሁኔታ መደራጀቱን ለማረጋገጥ

የሚያስችል በቂ ትጋት ማድረግ አለበት፤

2) በግንባታ ንብረት ላይ ያለውን ሀላፊነት የጤና እና የደህንነት ማህደር ሙሉ በሙሉ ያስተላለፈ አሰሪ

የጤና ማህደሩ ለተላለፈለት ሰው የደህንነት ማህደሩን ምንነት እና አላማ እንደሚያውቅ ካረጋገጠ

በንዑስ አንቀጽ (1) ያለበትን ግዴታ እንዳከበረ ይቆጠራል፤

አንቀፅ 54 - የኮንስትራክሽን ምዕራፍ እቅድ እና የጤና እና የደህንነት ፋይል


1) በቅድመ የኮንስትራክሽን ምዕራፍና የኮንስትራክሽን ቦታ ከማዘጋጀቱ በፊት ሥራ ተቋራጩ የኮንስትራክሽን

ምዕራፍ እቅድ ያወጣል ወይም የኮንስትራክሽን ምዕራፍ ዕቅድ ለማዘጋጀት የሚያስችል ዝግጅት ያደርጋል።

2) የኮንስትራክሽን ምዕራፍ ዕቅድ ዝግጅት የጤና እና የደህንነት ጥንቃቅ ሁኔታዎችን እና የግንባታ ቦታ መርሆችን

አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በግንባታው ቦታ ላይ የሚከናወኑ የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴዎችን ከግምት ውስጥ

በማስገባት መዘጋጀት አለበት፤

3) ንድፍ አውጭው ከፕሮጀክቱ ባለቤት የተገኘ የቅድመ-ግንባታ መረጃ እንዲሁም ከኮንስትራክሽን እቅድ ጋር

ተያያዥነት ያለው ከሌላ አካል የተገኘ ማንኛውምመረጃ ለሥራ ተቋራጭ መስጠት እና የሥራ ተቋራጩን

የኮንስትራክሽን ምዕራፍ ዕቅድ ዝግጅት ስኬታማ እንዲሆን በማድረግ ሂደት የመተባበር ግዴታ አለበት።
4) ሥራ ተቋራጭ በፕሮጀክቱ ትግበራ ሂደት ጊዜ የግንባታው ምዕራፍ ዕቅዱ በትክክል እንዲተገበር፣

እንደአስፈላጊነቱም በየጊዜው መሻሻሉን እና መከለሱን ማረጋገጥ፣ የግንባታው ስራ በተቻለ መጠን በሰዎች

ጤና እና ደህንነት ላይ አደጋ ሳያስከትል እንዲከናወን በሚያስችል መልኩ መከናወኑን ማረጋገጥ አለበት።

5) አርክቴክቱ በቅድመ-ግንባታው ምዕራፍ በቀጣይ ለሚከናወኑ ሌሎች ፕሮጀክቶች ትግበራ የሚያስፈልጉ

ከፕሮጀክቱ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ጨምሮ እንደየ ፕሮጀክቱ ባህሪያት አስፈላጊ የሆነ የጤና እና የደህንነት

ማህደር በማዘጋጀት የማንኛውንም ሰው ጤና እና ደህንነት ማረጋገጥ በሚያስችል ሁኔታ በማከናወን አለበት፤

6) ዋናው ዲዛይነር ሥራው እና በስራ ሂደት የተደረጉ ለውጦችን ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ የጤና እና የደህንነት

ማህደሩ በተገቢው ሁኔታ መተግበሩን፣ እንደጊዜው መሻሻሉን እና መከለሱን ማረጋገጥ ማረጋገጥ ይኖርበታል።

7) ሥራ ተቋራጩ በፕሮጀክቱ ትግበራ ጊዜ የሚያወቀውን ማናቸውንም ከደህንነት ፋይሉ ጋር ተዛማጅነት ያለው

መረጃ በጤና እና ደህንነት ፋይል ውስጥ ለማካተት በሚያስችል መልኩ ለዲዛይነር መስጠት አለበት ።

8) የዲዛይነሩ የሥራ ጊዜ ፕሮጀክቱ ከማለቁ በፊት የተጠናቀቀ እንደ ሆነ ዋናው ዲዛይነር የጤና እና የደህንነት

ማህደሩን ለዋናው ሥራ ተቋራጭ ማስተላለፍ አለበት።

9) የጤና እና ደህንነት ማህደሩ በአንቀጽ (8) ለዋናው ተቋራጭ የተላለፈ እንደሆነ ዋናው ስራ ተቋራጩ የጤና እና

የደህንነት ማህደሩን በተገቢው ሁኔታ መተግበሩን፣ ከስራው ሂደት ጋር የተከሰቱ ለውጦች.ማሻሻሉን እና

ማናቸውንም ጉዳዮች ከጊዜ ወደ ጊዜ መከለሱን ማረጋገጥ አለበት።

10) በፕሮጀክቱ መጨረሻ ላይ ዋናው ዲዛይነር ወይም ዋና ዲዛይነር በሌለበት ዋናው ሥራ ተቋራጭ, የጤና እና

የደህንነት ማህደሩን ለደንበኛው/ለባለቤቱ ማስተላለፍ አለበት፡፡

ክፍል አራት

ለሁሉም የኮንስትራክሽን ሳይቶች አጠቃላይ መስፈርቶች

አንቀፅ 55፡ የኮንስትራክሽን የሥራ ቦታ ደህንነትን ስለማረጋገጥ


1) ይህ ክፍል የሚመለከተው በኮንስትራክሽን ሳይት ላይ ብቻ ነው።
2) የኮንስትራክሽን ሥራውን የሚያከናውን አንድ ሥራ ተቋራጭ ወይም በሥራ ተቋራጩ ቁጥጥር ሥር ያለ
ማንኛውንም ሠራተኛ የሚመለከቱ ወይም በተቋራጩ ቁጥጥር ውስጥ ባሉ ጉዳዮች ላይ በዚህ ክፍል
የተመለከተውን መስፈርት ማክበር አለበት።
3) የኮንስትራክሽን ሠራተኞችና የሥራ አካባቢ ጤንነትና ደህንነት በዓለም አቀፍ ስታንዳርድ መሠረት የተሟላ
መሆን አለበት፣
4) ማንኛውም ሥራ ተቋራጭ በግንባታ ሳይቶች ሥራ ላይ የሚውል የደህንነት ፖሊሲ አዘጋጅቶ በሥራ ላይ
የማዋል ግዴታ አለበት፣ ፖሊሲው በግንባታ ግዢ አንዱ የመወዳደሪያ መስፈርት ይሆናል፣
5) በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች አስገዳጅ የሥራ ላይ ደህንነት ማረጋገጫ
ሥርዓት ተዘርግቶ በሥራ ላይ መዋል አለበት፣
6) በኮንስትራክሽን የሥራ አካባቢ በሰዎች ጤናና ደህንነት ላይ አደጋ የማያደርሱ የመሣሪያዎች እንቅስቃሴ እና
የሥራ አካባቢ እንዲኖር መደረግ አለበት፣
7) በኢንዱስትሪው የሚሰማራው የሰው ሃይል መብት፣ ግዴታና ጥቅም ለመጠበቅና ለማስጠበቅ የሚያስችል
የአሠራር ሥርዓት ተዘርግቶ በሥራ ላይ መዋል አለበት፣
8) ማንኛውም የሥራ ተቋራጭ በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ የሚሰማሩ ሠራተኞችን ከአደጋ መከላከል
የሚያስችል የደህንነት መጠበቂያ አልባሳትና መሣሪያዎች የማቅረብ ግዴታ አለበት፣

አንቀፅ 56. የኮንስትራክሽን ስራ አስተማማኝ የደህንነት ቦታዎች


1) የኮንስትራክሽን የስራ ቦታ ሚዛናዊ በሆነ አተያይ ለስራው ተስማሚ እና በቂ የሆነ ደህንነቱ የተጠበቀ
መዳረሻና መውጫ ያለው እና እያንዳንዱ የኮንስትራክሽን ቦታ በሥራ ላይ እያለ በአቅራቢያው ለሚደረግ
የማንኛው ሌላ ሰው እንቅስቃሴ የማይገድብ መሆን አለበት፤
2) የኮንስትራክሽን የስራ ቦታ በሰራተኞች ጤና ምንም አይነት አደጋ በማይፈጥር እና ደህንነቱ አስተማማኝ
ነው በሚያስብል ደረጃ የተዘጋጀ መሆን አለበት።
3) በተቻለ መጠን በቁጥር 1 ወይም 2 የተመለከቱትን መስፈርቶች ማሟላቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ማንም ሰው
ወደ ኮንስትራክሽን ቦታ እንዳይገባ ወይም እንዳይወጣ ለማድረግ የሚያስችል የጥንቃቄ ዕርምጃ ሊወሰድ
ይገባል።
4) የኮንስትራክሽን የስራ ቦታው ሚዛናዊ በሆነ አተያይ ማናቸውንም አስፈላጊ የሥራ መሣሪያዎችን ጥቅም
ላይ ለማዋል የሚያስችል በቂ እና የተስተካከለ የሥራ ቦታ ያለው እንዲሁም በትግበራ ላይ ላሉ ሰራተኞች
ወይም በቀጣይ በስራው ለሚሳተፉ ማንኛውም ሰው ምቹ መሆኑን ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት።
አንቀፅ 57. ስለ አቀማመጥ እና የጣቢያ ደህንነት
1) የኮንስትራክሽን ሥራ የሚካሄድባቸው እያንዳንዱ ክፍሎች በተቻለ መጠን ስራን ከሚያደናቅፉ ነገሮች የፀዱ
እና ንጽህናቸው የተጠበቀ መሆን አለባቸው።
2) ለጤናና ደህንነት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የኮንስትራክሽን ጣቢያ በስራ ሂደት ሊያስከትል የሚችለውን የአደጋ
ስጋት ደረጃ መሠረት ያደረገ መጠኑንና ስፋቱን በቀላሉ መለየት የሚያስችል በዙሪያው ተገቢ ምልክት
ማስቀመጥ ወይም በአጥር መከለል አለበት፤
3) ለማንኛውም ሰው የአደጋ ምንጭ እንደሚሆን የሚገመት እንጨት ወይም ምስማር ወይም ተመሳሳይ ሹል
ነገር በማንኛውም የኮንስትራክሽን ሳይት ውስጥ ጥቅም ላይ ማዋል ወይም ያለ በቂ ጥንቃቄ በዘፈቀደ
ማስቀመጥ የተከለከለ ነው፤
አንቀፅ 58. ስለ ማዋቀሪያ/መደገፊያ አካል / ስካፎሆልዲንግ ደህንነት ጠንካራ
1) የግንባታ ሥራውን ሂደት ላይ ባለ አዲስ ወይም ነባር ማዋቀሪያ በማንም ሰው ላይ አደጋን እንዳያስከትል
ለማድረግ የሚያስችል አስፈላጊ የጥንቃቄ እርምጃዎች መደረግ አለበት።
2) ማንኛውም መደገፊያ, ጊዜያዊ ድጋፍ ወይም ጊዜያዊ መዋቅር ሊጫኑበት የሚችሉትን ማንኛውንም
ተገማች ሸክሞችን ክብደት ለመቋቋም በሚየስችል ዓይነት ለታቀደው፣ ለተገጠመለት እና ለተያዘለት
ዓላማ ብቻ ጥቅም ላይ መዋል አለበት።
3) መደገፊያ ውቅር ለማንም ሰው ደህንነት አደጋን በሚፈጥር ደረጃ ከተፈቀደው አቅም በላይ መጫን
የለበትም።

አንቀፅ 59. ማፍረስ ወይም መነቃቀል


1) ማንኛውም መደገፊያ ውቅር የማፍረስ ወይም የመነቃቀል ተግባር የሚፈጸመው በታቀደና አደጋ
በማይፈጥር መልኩ የሚከናወን መሆን ይኖርበታል ወይም ሙሉ በሙሉ መከላከል የማይቻል በሆነ ጊዜ
በተቻለ መጠን አደጋውን በሚቀንስ ሁኔታ መከናወን አለበት።
2) መደገፊያ ውቅር የማፍረስ ወይም የማወላለቅ ሥራ ከመጀመሩ በፊት የዝግጅት ሂደቱ በጽሑፍ መመዝገብ
እና በተደራጀ መልኩ መከናወን አለበት።
56. ቁፋሮዎች
1) ማንኛውም በኮንስትራክሽን ስራ የተሰማራ በማናቸውም አይነት ቁፋሮ ወይም የቁፋሮው ክፍል
እንዳይፈርስ፣ ከግድግዳው ወይም ከጣሪያው ወይም ከአጠገቡ ምንም ዓይነት ቁፋሮ እንዳይናድ ወይም
እንዳይወድቅ እና ማንም ሰው በቁፋሮ ውስጥ እንዳይቀበር በቂ የደህንነት ጥንቃቄ እርምጃዎች በመወሰድና
አደጋን መከላከል አለበት፣
2) ማንኛውም ሰው፣ የሥራ መሣሪያ ወይም የቁስ ክምችት በማናቸውም ቁፋሮ ውስጥ እንዳይወድቅ
ለመከላከል ምቹና በቂ የሆነ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፣
3) አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከተቆፈረው ጉድጓድ አጠገብ ያለውመሬት ወይም የመሬት ክፍል መሸከም ከሚችለው
ክብደት በላይ የሥራ መሣሪያ ወይም ዕቃ እንዳይጫነው ለመከላከል ተስማሚ እና በቂ የሆነ የጥንቃቄ
እርምጃ መወሰድ አለበት።
4) በንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት በተደነገገው መሰረት ካልሆነ በቀር ማናቸውንም ድጋፎች ወይም ስታፋ
በተገጠመለት ቁፋሮ ውስጥ የኮንስትራክሽን ሥራ የሚከናወነው ቁፋሮው እና ማንኛቸውም የሥራ
መሣሪያዎች እና ቁሳቁሶች በደህንነት ላይ ጉዳት የማያስከትሉ መሆኑ፣ ሥራው በሚካሄድበት ፈረቃ
መጀመሪያ ላይ በመሬት ቁፋሮው ላይ ያለውን ጥንካሬ ወይም መረጋጋት ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር የሚችል
ማንኛውም ክስተት መኖር ወይም አለመኖሩ እና ማንኛውም ያልተገመተ የወደቀ ወይም የተናደ ቁሳቁስ
መኖር አለመኖሩ ብቃት ባለው ሰው ምርመራና ፍተሸ ተደርጎበት የኮንስትራክሽን ሥራውን ያለጉዳት
ማከናወን እንደሚቻል ያረጋገጠ ከሆነ ነው፤
5) የቁጥጥር ሥራ የሚያካሂደው ሰው ቁጥጥሩን በመወከል ለሚመለከተው ሰው በማናቸውም ጉዳዮች ላይ
(በዚህ አዋጅ ቁጥር … በተደነገገው መሰረት ያልረኩበት መሆኑን ካሳወቀ ጉዳዩ በአጥጋቢ ሁኔታ
እስኪስተካከል ድረስ በቁፋሮው ውስጥ የኮንስትራክሽን ሥራ መከናወን የለበትም

አንቀፅ 60. ከፈርዳምስ እና ካሲሰን Coffer dams እና caissons


1) ከፈርዳምስ እና ካሲሰን ተስማሚ ዲዛይን እና ግንባታ የተደረገለት; ውኃ ወይም ቁሳቁስ ከገባ ሠራተኞቹ መጠለያ

እንዲያገኙ ወይም ከጉዳት እንዲያመልጡ በሚገባ የለበሱ እና ደህንነቱ በማያሰጋ መልኩ በአግባቡ የተያዘ.መሆን

አለባቸው፡-

2) ኮፈርዳም ወይም ካሲሰን እና ማንኛውም የሥራ መሣሪያዎች እና ቁሶች በኮንስትራክሽን ሥራ ለመሥራት ጥቅም

ላይ ሊውሉ የሚችሉ ሥራው በሚካሄድበት ፈረቃ መጀመሪያ ላይ ብቃት ባለው ሰው ምርመራ ተደርጎበት

ኮፈርዳም ወይም በካይሰን ጥንካሬ ወይም መረጋጋት ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር የሚችል ክስተት መኖር ወይም

አለመኖሩ ምርመራውን ባካሄደው ሰው ተፈትሾ የኮንስትራክሽን ሥራው በአስተማማኝ ሁኔታ ሊከናወን

እንደሚችል የተረጋገጠ ከሆነ ነው፡

3) ምርመራውን የሚያካሂደው ሰው ምርመራውን በመወከል ለሚመለከተው ለሚመለከተው ሰው በማናቸውም

ጉዳዮች ላይ (አንቀፅ ቁጥር … በተደነገገው መሰረት ያልረኩበት መሆኑን ካሳወቀ ጉዳዩ በአጥጋቢ ሁኔታ

እስኪስተካከል ድረስ በቁፋሮው ውስጥ የኮንስትራክሽን ሥራ መከናወን የለበትም፤

አንቀፅ 61. የፍተሻ ሪፖርቶች


1) በአንቀፅ 21 እና 22 ላይ ምርመራ ያካሄደ ሰው በተመረመረበት ቦታ የኮንስትራክሽን ሥራ በአስተማማኝ ሁኔታ

መከናወኑን የማይችል መሆኑን የተረዳው እንደሆነ በማንኛዉም ሰው ደኅንነት ላይ አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉትን

ጉዳዮች ፍተሻው ከማለቁ በፊት የተሟላ የምርመራ ሪፖርት በማዘጋጀት ሪፖርቱን ወይም ግልባጩን ምርመራው

ለተደረገለት ሰው ማሳወቅ አለበት፤

2) ምርመራውን የሚያካሂደው ሰው በሌላው ሰው ቁጥጥር ሥር ሆኖ የሠራ እንደሆነ (ተቀጣሪ

3) ሰራተኛ ወይም በሌላ አኳኋን) ቀጣሪው ወይም አሰሪው ሰው ፍተሻውን ያከናወነው ሰው በንዑስ አንቀጽ (1)

መስፈርቶችን ያከበረ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት


4) ምርመራው የተደረገለት ሰው የግንባታ ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ምርመራው በተደረገበት ቦታ ሪፖርቱን ወይም

ቅጂውን ለአስፈፃሚው ተቆጣጣሪ አካል ማቅረብ አለበት፣

አንቀፅ 62- የኃይል ማከፋፈያ ጭነቶች


1) አደጋን ለመከላከል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በኮንስትራክሽን ስራ የሚተከሉ የኃይል ማከፋፈያዎች በተገቢው ቦታ

መቀመጥ፣ በየጊዜው ፍተሸ ማድረግ እና ግልጽ በሆነ ቦታ መመላከት አለባቸው፤

2) ለኮንስትራክሽን ስራ አደጋ የሚፈጥር ከኤሌክትሪክ ሃይል ኬብሎች የሚመነጭ አደጋ የሚከሰት ከሆነ ከአደጋው

አካባቢ እንዲርቁ ወይም ኃይሉ የተነጠለ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ መሬት ላይ እንዲቀበር መደረግ አለበት.

3) በንዑስ አንቀጽ 2 የተደነገገውን ለመተግበር ባልተቻለ ጊዜ የማያስፈልጉትን እንቅፋት የሆኑ የሥራ

መሣሪያዎችን ማስወገድ ወይም ተመጣጣኝ የደህንነት ደረጃን የሚሰጡ ተስማሚ የማስጠንቀቂያ

ማሳወቂያዎች መኖር አለባቸው፡-

4) በተቻለ መጠን አደጋውን ለመከላከል ተስማሚና በቂ የጥንቃቄ ዕርምጃዎች ካልተከናወኑ በቀር (በዚህ አዋጅ

የሚፈለጉትን ማንኛውንም ዕርምጃዎች ጨምሮ) በጤና ወይም በደኅንነት ላይ አደጋ ወይም ጉዳት

የሚያስከትል ከመሬት በታች የሚከናወን የኮንስትራክሽን ሥራ መከናወን የለበትም።

አንቀፅ 63 - ስለ መስጠም መከላከል


1) የኮንስትራክሽን ሥራው በውኃ ውስጥ ወይም በሌላ ፈሳሽ ውስጥ የመውደቅ እና የመስጠም አደጋ ለመከላከል

የሚያስችል ተስማሚ እና በቂ እርምጃዎች መወሰድ አለበት፤

2) ከውሃ ወደ ሥራ ቦታ በመጓጓዝ ለሚሰራ ማንኛዉም ሰው ማጓጓዣው ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ለማድረግ

ተስማሚ እና በቂ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው

3) ሰው በውኃ ወደ ሥራ ቦታ ለማድረስ የሚውለው ማንኛውንም ጀልባ መጨናነቅ ወይም ከመሸከም አቅም

በላይ የሆነ ክብደት መጫን የለበትም።

ክፍል አምስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
አንቀጽ 64፡ የመተባበር ግዴታ
1. ይህንን አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ ማንኛውም ሰው የመተባበር ግዴታ አለበት፣
2. ማንኛውም ሙያተኛ እና ድርጅት ይህንን አዋጅ እና ተከትሎ የሚወጡ ደንብ እና መመሪያ
ለማስፈጸም አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን የመስጠት ግዴታ አለበት፣
3. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ግለሰብ እና ድርጅት እንዲሁም የመንግስት አካል በዘርፉ የወጡ ህጎችን
ማለትም አዋጅመ ደንብ፣ መመሪያ፣ እስታንዳርዶች ፣ማንዋሎች ቼክ ሊስቶች አክብሮ የመተግበር
ግዴታ አለበት
አንቀጽ 65፡ ደንብ የማውጣትሥልጣን
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ደንቦችን ሊያወጣ ይችላል፡፡

አንቀጽ 66፡ መመሪያ የማውጣትሥልጣን


ሚኒስቴሩ ይህንን አዋጅ እና በዚህ ዓዋጅ መሰረት የሚወጡ ደንቦችን ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ
መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል፡፡
አንቀጽ 67፡ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ
ሁሉም ሙያተኛ፣ ባለሙያ እና ድርጅት ይህ አዋጅ በጸደቀ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በዚህ አዋጅ ላይ እና
በዚህ አዋጅ መሰረት በሚወጡ ደንቦችን እና መመሪያዎች ላይ የተመለከቱትን መስፈርቶች አሟልቶ
መመዝገብ፣ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማውጣት እና ሌሎች ምዝገባዎችን መፈፀም አለባቸው፡፡

አንቀጽ 68፡ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ


ይህ አዋጅ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ …………. ቀን 2014


ሳህለወርቅ ዘውዴ

You might also like