Professional Documents
Culture Documents
ከግንባታ ማቴሪያሎች አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በሰዎች ጤና ላይ የሚደርስ የጤና ጉዳት
ከግንባታ ማቴሪያሎች አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በሰዎች ጤና ላይ የሚደርስ የጤና ጉዳት
ክፍል አንድ
በዓለምም ይሁን በአገራችን በአጠቃላይ በብዙ ቦታዎች ላይ የግንባታ ስራዎች በብዛት እንደሚሰራ ይታወቃል፡፡
በተጨማሪም እነዚህን የግንባተ ስራዎችን ለመስራት ከሚያገለግሉት ኢኪውፕመንትስ ተብለው ከሚጠሩ
ጀምሮ በተጨማሪነት የሰው ኃይልም በተለያየ የስራ ሁኔታና የሙያ ዓይነት በደረጃና በቁጥር ተለክቶና
ተመጥኖ በእነዚሁ የግንባታ ስራዎች ላይ ይውላል፡፡
ይሁን እንጂ በግንባታ ስራ ላይ ተቀጥሮ መስራት በብቻው እንደገንዘብ ማስገኛ የገቢ ምንጭነት፣የስራ በር
ዕድል መክፈትና ራስን እንደማስቻያ መንገድ የሚቆጠር ቢሆንም አብረው እየዋሉ የግንባታውን ስራ
ስለሚያናወኑባቸው የግንባታ ማቴሪያሎች በጤና ላይ ስለሚያሳድሩት አሉታዊ የሆነ የጎንዮሽ ጠንቅ ግን
የሚወራበትም ሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ የሚሰራበት ሁኔታን ግን በአገራችን ላይ ማየት ግን አልተቻለም፡፡
ይህ ልብ እየተባለ ያይደለና የትኩረት አቅጣጫንም ያላገኘ ጭብጥ (issue) መነሳትና መፈተሽ ያለበት
ይመስለኛል፡፡
ይህም ጉዳይ እውቅናን ሊያገኝ የሚገባ በመሆኑ ምክንያት የተነሳ በብዙዎች ተመራማሪዎች የምርምር
ፅሁፋቸው ላይ ሲገለፅ የቆየና ለውጡ ያደጉት አገራት አዲስ ጉዳይ ባለመሆኑ ትኩተር ሰጥተው እየሰሩ
ቢሆንም በእነሱም ዘንድ ቢሆን አሁንም ጉድለትና ክፍተት እንዳለ ራሳቸው ከሚያወጧቸው መረጃዎች ላይ
ማየት ይቻላል፡፡
አንዲት ሀገር ሀብታምም ትሁን ድሀ ብቻ ያላት የሰው ሀይል ቁጥር ብዛት ሀብት የሚሆናትና ይህንንም የሰው
ሀይል አምራች እንዲሆን በማድረጉም ረገድ ቢሆን ምርቷ እንዲበለፅግ የሚያደርግ ስለመሆኑ በማመን
መርግም ሳይሆን በረከቷ አድርጋ ልትቆጥረው እንደሚገባ ግልፅ ነው፡፡ በሰላም እጦትና በዘር ክፍፍል
የአመለካከት፣ የታሪክ መዛባትና የውሸት ትርክት መናኘት የተነሳ እርስ በእርስ መተላለቅና ፍጅት በምትሰቃይ
የኛ አይነት ኢኮኖሚዋ እንደሚወራው ሳይሆን ድቀት ባለበት ላይ የሰውን ልጅ ከብሔሩና ማንነቱ የተነሳ
በህይወት መኖር ብርቅ በሆነበትና የጅምላ ግድያ የአሁኑን ወይም የጊዜውን የፖለቲካ አመራርን በያዘ ፓርቲ
ውስጥ ሆነው እየመሩ ባሉ አመራሮች ተሳታፊነት ጭምር ጭዳ በሚደረግበት ሁኔታ አይደለም በቆይታ
ሰብዕናን አቃውሶ በየቦታው እንደፈንግል ያለ የዶሮ በሽታ ይሉ አይነት የሰው ነፍስ በሚጠፋባት አገር ውስጥ
እየኖሩ የግንባታ ማቴሪያልን ጉዳትና ጠንቅ ማውራት የቅንጦት ሊመስል ይችላል፡፡
ከዚህም ባለፈ አይደለም መሪዎቻችን ከቀድሞ ጀምሮ ሶስቴ ሊያበሉን ካለላቸውም መክሰስን ጨምሮ አራቴ
እናበላችኋለን ሲሉንና ሆዳችን በጉጉት እያማረው ቀኑን ናፍቆ ሲጨህ ኖረን በባዶ እዚህ ደርሰናል፡፡ አሁን ያሉን
መሪዎች ደግሞ መልክ ከሆድ ይወጣልና በሌማት እህል እናቀርብላችኋለን እያሉን በተስፋ እየጠገብን በረሀብ
ለምንሰቃይ ህዝቦች ደግሞ በእያንዳንዱ የደቂቃ ሽርፍራፊና የሴኮንድ ብልጭታ አንገት በሚያስደፋና ታሪክ
በሚያጎድፍ ብሎም ለትውልድ የሚተርፍ ለመረጃና ማስረጃ በቪዲዮና ኦዲዮ ተደግፎ ግድያ አሸን በሆነባት
አገር ላይ እየያዝን ካለው አንገት አስደፊ የታሪክ ጠባሳ ምዝገባ ላይ በሰፊው እንደ ጀብድና ገድል ለየዕለት
1
የሞት አድማቂነት እየተጣደፍን ባለንበት ይህን ርዕስ ይዞ መፃፍ ለጆሮ የማይጥም ቢመስልም መግለጡ ግን
የሚከፋ አይሆንም፡፡
ጥንቃቄና የስራ ላይ የጤናን ደህንነት ጉዳይ ለአገራችን የግንባታ እንዱስትሪ ጠቃሚ ስለሆነ ቦታ የሚሰጠው
መነጋገሪያ ርዕስ ቢሆን ምንም አይነት ክፋትም ሆነ ጉዳት አይኖረውም፡፡ በቀደመው የ 19 ነኛው ክ/ዘመን
የኢንዱስትሪ አብዮት የህንፃ ግንባታ ማቴሪያሎችን በተለያየ ዓይነት፣መጠን ፣ቅርፅ፣ የማቴሪያል ውህድና ይዘት
ያላቸውን የህንፃ ግንባታ ማቴሪያሎችን መፈብረክ ማስቻሉ የኢኮኖሚ ዕድገትና የሰራተኛ ቅጥርን መሻሻል
ባለበት መልኩ ብዙ የህንፃ ግንባታ ተግባራትን መፍጠር አስችሏል፡፡
በ 2013 እ.ኤ.አ ‹‹ሌሰን ለርንድ ፍሮም ኤክስፖዠር ቱ ቢውልዲንግ ማቴሪያልስ›› በሚል ርዕስ በታተመው
የምርምር ፅሁፋቸው ላይ ዛሪን ኢስኒን፣ሳባሪና ሼህ አህመድ እና ዛህራ ያያ የሰው ሰራሽ ውጤት ከሆኑት
አብዛኛው የግንባታ ማቴሪያሎች ውስጥ የተወሰኑት በሰዎች ጤና ላይ የጎንዮሽ ጠንቅን (adverse effects to
human health) የሚያስከትሉ ናቸው በማለት ፓችኮ ቶርጋል እና ጃላሊ የተወሰነ መርዛማነት ፎርም የያዙትን
ብዙ ቁጥር ያላቸውን ለህንፃ ግንባታ መተግበሪያነት አገልግሎት የሚውሉ ማቴሪያሎችን ዘርዝረው በ 2013
እ፣ኤ አ በጸፉት የምርምር ፅሁፋቸውን በዋቢነት ጠቅሰው አስፍረዋቸዋል፡፡
በኢትዮጵያ የግንባታ ኢንዱስትሪ ውስጥ የጤናና የደህንነት (health & safety) ጉዳይ በጣም ከሚያሳስባቸውና
ከሚያንገበግባቸው አንጋፋና እንቁ ባለሙያዎቻችን ውስጥ አንቱ ከተባሉት ጉምቱ የሆኑት ፕሮፌሰር አበበ
ድንቁ በብዙው ስለ ኸልዝና ሴፍቲ መታገላቸውን በተጨባጭ አውቃለሁ፡፡ ሆኖም ግን በተለያየ ምክንያት
ተግባራዊነቱ መውተርተር ልጀምር በማይልባት አገራችን ትንሽ ፈቅ የማይል ከዳር የማይደርስና መንግስትም
ትኩረት የማይሰጠው ጉዳይ ከመሆኑ ጋር ተዳምሮ ህግ ብቻ በማውጣት የተጠመደ እንጂ ለተግባራዊነቱ
መሳካት ቁብ የሚሰጠው በሌለበት የሚመለከተው ሴክተር ባለስልጣናት የበለጠ ግዴለሽነት፣ የክልሎች በዚህ
ጭብጥ ላይ ቆራጥ እርምጃ መውሰድ አለመቻል፣እንደ ሲቪል ኢንጂነርስ አሶሴሽን አይነቶቹ የሙያ ማህበራት
ለጥናት ፣ምርምርም ሆነ መንግሰትን ከመገፋፋት አንጻር ገፍተው መሄድ ያልቻሉበትና መንግሰት እንደ ግዙፍ
ችግር በመውሰድ ችግሮችን ነቅሶ እያወጡ ለመቅረፍ አለመቻልም ሆነ የክልሎች በዚህ ጉዳይና በጭብጡ ላይ
ተንተርሰው የራሳቸውን እርምጃ ወስዶ ለመተግበር ያለ የተነሳሽነት ደካማ መሆን ጋር ተዳምሮ በጥናት
የተደገፈ የጉዳቱን ልክና መጠን ለማሳየት የተቻለ በማይመስል ሁኔታ ላይ እንደለ የሚገባው ሁሉ ይገባዋል፡፡
ሌላው ቀርቶ በተገነቡ ህንፃዎች ውስጥ የምንኖር ኗሪዎችም ከእነዚህ በጥናት የተለዩ አንዳንድ መርዛማ የህንፃ
ግንባታ ማቴሪያሎች (toxic building materials) የተነሳ የሚደርስብንን የጤና ችግር ወይም እክልን አጢነነው
የምናውቅና መረዳቱ (awareness) ያላንሰ ስለመሆኑ ትዝ የሚለንስ ስንቶቻችን እንደሆንን ማወቅ
አይቻልም፡፡
በቤት ውስጥ የአየር ብክለት ተጋላጭነት ጋር በተያያዘ በመተንፈሻ አካላችን ላይ በርካታ የሆኑ ጉዳቶች
ሊስተናገዱ (ሊታዩ) የሚችሉ ሲሆን እነዚህን ጨምሮ ፑሊመናሪ ፋንክሽን አኪውትና ስር የሰደደ (chronic)
ለውጦች ወይም የመተንፈሻ ሲምፕተም ኢንሲደንስና ፕሪቫለንስ መጨመርን አስመልክቶ ከተካሄደው ጥናት
ላይ መገንዘብ የተቻለው ነገር ቢኖር፡-
2
ከሻጋታና እርጥበት መካከል ባለ ለኑሮ አመቺ ባልሆነ መኖሪያ ቤት ውስጥ ባለ
ኢንቫይሮመንት ያልተቋረጠ ትስስር ምክንያት የተነሳ የመተንፈሻ ሲስተምና አስም
ጉዳት ይደርሳል
ለኑሮ ምቹ ባልሆነ ህንፃ ውስጥ ከሚኖሩ 40 እጅ አካባቢ የሚሆኑ ሰዎች በአብዛኛው
በአስም (Asthma) ይሰቃያሉ፡፡
የትኛውም ዓይነት አሉታዊ ሁኔታዎች የመረበሽ ውጤት (disturbing effects) እና የቦታዎች አጠቃቀም
ጉድለት (failure of the usage of the space) ለጤና ጠንቅ የሚሆኑ ነገሮች መከሰት ምክንያት ይሆናል
ሲሉ ኪራን ኤ ፓላቶጉሉ ከቢና ቢልጂስ ጊሪስ ጋር በጥምር ሆነው የምርምር ፅሁፋቸው ላይ
ባስነበቡበት 3 ኛ እትም ባሲም ያይን መርከዚ ኦሲታንቡል 49-65(2010) ላይ በሚገባ ገልፀውታል፡፡
ካንሰር
አስም (asthma)
የአለርጅክ ምልክቶችን የሚያሳዩ (allergic reactions) እና
ከዚያም በላይ የሆኑትን የሰው ልጅ ጤና የሚያስተናግድ በመሆኑ ጤናው መቃወስ ውስጥ እንደሚገባ
አስገንዝበዋል፡፡
እንደ ግንባታ ማቴሪያሎች በህንፃ ግንባታው ላይ የሚያሳርፉት ጉልህ አሻራና ውጤት ማርካት መኖር
አንፃር ሲታይ በዚሁ ልክ አንዳንድ የህንፃ ግንባት ማቴሪያሎች ኢኮሎጂካልና ዘላቂ የአካባቢ ጤናን
በመፍጠሩ ረገድ የማይካድ ታላቅ ሚናን መጫወት መቻላቸው ያለ ሀቅ እንደመሆኑ መጠን ቀድመው
የምህንድስናውን ዲዛይንና ስፔስፊኬሽንን የሚያዘጋጁ ባለሙያዎች ይህንን ሚና ሊወጡ የሚችሉትን
የህንፃ ግንባታ ማቴሪያሎችንም በትክክል መርጦ ለግንባታ ስራ ጥቅም ላይ የማዋል እውቀትና ግንዛቤን
መኖር የሚጠይቁም እንደሆነ ሊዘነጋ አይገባም ሲሉ ይመክራሉ፡፡
የህንፃ ግንባታ ማቴሪያሎች የቤት ውስጥ የአየር ጥራትን በተለያየ ምክንያት የተነሳ የሚበክሉ እንደሆነ
ይታመናል፡፡ እነዚህ ምክንያቶች የሚነሱት ምናልባትም ከስትራክቸሩ ይዞታና ከማቴሪያሎቹ
አመራርጥም ሆነ አጠቃቀም የተነሳ ነው የሚል እሳቤም አለ፡፡የተለያዩ የሰዎች ስብሰባ (group)
ማለትም እንደ ዲዛይነር፣አምራቾችና፣ተቆጣጣሪዎች (supervisors) ያሉት ከአንድ ህንፃ ጥንስስ ጀምሮ
እስከ ግንባታውና ፍፃሜው ድረስ የራሳቸው የሆነ ክፍል (ድርሻ) ያለቸው እንደሆነም የታመነ ጉዳይ
ነው፡፡
እንግዲህ ባደጉት አገር ሰዎች በመኖሪያ ቤት ውስጥ ከሚጠቀሟቸው ባዮሎጂካል ኬሚካሎች የተነሳ
በሰዎች ጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከላይ በተገለፀው ሁኔታ የተመለከተና የተብራራ ቢሆንም
4
የአገራችንን ሁኔታ ስናይ ደግሞ ጤና ጥበቃ ከግንባታው ኢንዱስትሪ ጋር እየተቀናጀ በዚህ ረገድ ምን
ያህል የጥናትና ምርምር ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ስለሚለው ለጊዜው መረጃና ማስረጃው የሌለኝ
ከመሆኑ አንፃር ከዚህ በላይ በብዕሬ ላስውበው አልቻልኩም፡፡
በጁኔድ አህመድ ማሊክ ኢኮሎጂካል ኤንድ ኸልዝ አፌክትስ ኦፍ ቢውልዲንግ ማቴሪያልስ በሚል ርዕስ
በሻሪም ማራዝ አርታኢነት በኒውዘርላንድ በ 2022 እ.ኤ.አ ከታተመው የምርምር ፅሁፍ ላይ
እንደሚነበበው የህንጻ ውቅራት (structures) የመሬት ሀብትን(resources) በዓለም ላይ ከየትኛውም
የሰዎች ተግባራት ይበልጥና ይበልጥ የሚጠቀሙ እንደሆነ ግልፅ ነው ይላል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ብዙ
ሚሊዮን ቶን የግሪን ሀውስ ጋዞችና መርዛማ የሆኑ ኢሚሽኖችን ፣የውሃ በካዮችን እና ጥጥር
ቆሻሻዎችን ወይም ተወጋጆችን ከግንባታ ጋር በተያያዘ ተግባራት መከናወን የተነሳ ይፈጥራሉ፡፡ ይህም
በአካባቢ ሁኔታ ላይ ታላቅ ተፅዕኖን አሳድሮ በሰዎችና በአካባቢ ሁኔታ ላይ ታላቅ ተፅዕኖን ፈጥሮ
በሰዎችና እንስሳት ጤና (Health issue) ጉዳይ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫናን ያሳድራሉ፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ
ላይ ኢኮሎጂካልና የጤና ሪኳየርመንት ማውጣት የሚችል ከአካባቢ ጋር ተዛማጅ(eco-friendly) የሆኑ
የግንባታ ማቴሪያሎችን በመጠቀም ምቹ የግንባታ ኢንቫይሮመንት ለመፍጠር ከፍተኛ እርብርብ በዓለም
ላይ እየተደረገ ያለበት ሁኔታ እንዲኖር የሚያስችል ጉዳይ ተፈጥሯል ሲል ይህ ፅሁፍ ያብራራል፡፡
የዓለም ጤና ጥበቃ (WHO) በቅርቡ ካሰፈረው ወይም ከገለፀው መረጃ ላይ መረዳት እንደሚቻለው
ከሆነ ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ወደ 40 እጅ የሚጠጉ በግንባታው ሴክተር ውስጥ ጥቅም ላይ
የሚውሉ ማቴሪያሎች በተፈጥሮ በኃይለኛው ቁጡ (aggressive) መሆን የተነሳ በኢንዱስትሪ
በበለፀገው የውጩ ዓለም ማህበረሰብ ውስጥ ኗሪዎችን እየጎዱ ያሉ ችግሮች እንዲፈጠሩ ምክንያት
እየሆኑ ያሉት ሲል ይህ ከላይ የተጠቀሰው የምርምር ፅሁፍ በመግቢያው ላይ ይፋ አውጥቶት የታየው፡፡
የግንባታ ማቴሪያሎች ተፅዕኖ ቀላል ያልሆነ በቤት ውስጥ በሰዎች ጤና ላይ በሚያደርሱት ጉዳት ልክ
ብቻ ያልተገደበ ስለመሆኑ ብዙ የምርምር ፅሁፎችን ዋቢ እያደረጉ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ህንፃዎች ወይም
ቤቶች ለሰው ልጆች መጠለያነት (መኖሪያነት) የሚያገለግሉ እንደመሆናቸው መጠን ሲገነቡም ሆነ
ከተገነቡ በኋላ በአካባቢ፣በሰዎችና በእንስሳት ጤና ላይ የሚያደርሱት አሉታዊ ተፅእኖ የጎንዮሽ ጠንቅ
ተግዳሮት መኖር ጋርና ከጤናም ጋር ተያይዞ በሚከሰት ሁኔታ ብዙ ጉዳቶች እንዲስተናገድ ምክንያት
እየሆነ ቆይቷል፡፡
ከላይ በተገለፀው የእነ ኒል ኮኩሉ የሁለቱ እንስት ተመራማሪዎች የምርምር ፅሁፍ ላይ በምሳሌነት
ከተጠቀሱት የግንባታ ማቴሪያሎች ውስጥ በደረጃና ወይም ደግሞ በወለል ላይ የምንጠቀምቸው
አንዳንድ የግራናይት አይነቶች የግንባታ ማቴሪያሎች ከሚለቋቸው ራዶን (radon) ምክንያት የተነሳ
የሳምባ ካንሰር ጉዳትን የሚያባብስ ሁኔታ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል በማለት ተጠቅሷል፡፡በቁጥር
ከ 70 በላይ የሚሆኑ የግንባታ ማቴሪያሎች ከጤና አንፃር የሚያመጡትን የጎንዮሽ ጠንቅን በተመለከተ
በርካታ በዚህ ጉዳይ ላይ ምርምር ያካሄዱ ተመራማሪዎች በምሁር ብዕራቸው በሚገባና በተገቢው
ሁኔታ አብራርተውታል፡፡
5
ከአለርጂ የተነሳ የህክምና ትሪትመንት እንዲሰጣቸው በሚል ሀኪሞቻቸውን ለመጎብኘት የሚገደዱ
ስለመሆኑም እንዲሁ በዚህ የምርምር ፅሁፍ ላይ ተብራርቷል፡፡
ሰዎች ራሳቸው ባመረቷቸው (በፈጠሯቸው) ብሎም ዲዛይን አድርገው ውብ በሆነ ሁኔታ ከገነቧቸው
ህንፃዎች ላይ ከሚውሉ አንዳንድ የግንባታ ማቴሪያሎች የተነሳ በሰዎች ጤና ላይ የሚፈጠሩ አሉታዊ
ተፅእኖዎችም ቢሆኑ ቀላል ግምት የሚሰጧቸውና ቦታ የማያገኙም ሊሆኑ አይገባም፡፡ሂል ብሪፊንግ
በሚባለው በቤልጂየም ብራስልስ በሚገኘውና በኸልዝ ኤንድ ኢንቫይሮመንት ተባባሪዎች (Aliance) ሂል
(HEAL) የተሰኘው ተቋም ኸልዚ ቢውልዲንግ፤ ሄልዚየር ፒውፕል በሚል ከሚታተመው መጣጥፍ ላይ
መረዳት እንደሚቻለው እስከ 2017 እ.ኤ.አ. ድረስ ከተደረጉ የምርምር ፅሁፎች ላይ የተገኙ ውጤቶችን
ሰድሮ በመያዝ ቀጥሎ በተዘረዘረው ሁኔታ ያብራራቸዋል፡፡ ለመኖሪያ ምቹ ያልሆኑ ህንፃዎች የካንሰር
ጉዳትን በመጨመር ለካርዲዮ ቫስኩላር ጤና ቀውስ እንዲጋለጥ (jeopardize) ያደርጉታል፡፡
6
የቀዝቃዛ ቤቶችን የተርማል ጥራት (thermac quality) ማሻሻል ደግሞ በጣም ጉልህ በሆነ
ሁኔታ የደም ግፊትን (blood pressure) ህመምን መቀንስም ሆነ ሆስፒታል ታሞ
ከመተኛትም (hospital admission) ሆነ መድኃኒቶችን መጠቀምንም ተጋላጭነት (use
medication) ይቀንሳል፡፡
እንደ አውሮፓ ህብረት (European union) ማሳሰቢያ ከሆነ ደግሞ ወደ 56 ሚሊዮን
ከሚጠጋ ህዝብ 54 እጅ ያህል የሚሆኑ ከ 250 ሺህ ኗሪዎች በላይ የሚኖሩባቸው ቦታዎች
(living area) ኤል ዲ ኢ ኤን (LDEN) ለ 55 ዴሲብል የመንገድ ትራፊክ ድምፅ ብክለት
ተጋላጭ በመሆናቸው የተነሳ ጤናቸው አደጋ ውስጥ ነው ያለው (risky to health)
ተብሎ ይታሰባል ሲል ይገልጻል፡፡