You are on page 1of 187

የኮሮናው መብረቅ

በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ትክክለኛ መረጃ፣


ምንነት፣ የህክምና እና የመከላከያ ዘዴዎች
ለእርስዎ፣ለቤተሰብዎ እና ለሚወዷቸው ሁሉ!!

በዶ/ር አቡሽ አያሌው እና ዶ/ር ቃልኪዳን ቅጣው፣


ዮሴፍ ጥሩነህ፣ ዶ/ር ደሳለው ካሣሁን እና ዶ/ር አብርሃም ክብረት
የተዘጋጀ
የህይወት ስጦታ

ይህን መጽሐፍ ለእርስዎ በእኔ (በድርጅቴ) ስም በስጦታ መልክ ሳበረክት


ራስዎንና የሚወዷቸውን ሌሎች ከተላላፊው በሽታ እንዲጠበቁ ከልብ
በማሰብ ነው፡፡ መልካም ጤንነትና ረጅም እድሜ ለእርስዎና ለሚወዷቸው
ሁሉ ይሁን!

ስም

ፊርማ

እርሶም ኃላፊነትዎን ይወጡ!!

ይህን መጽሐፍ ካነበቡ በኋላ ሌሎችንም አስተምሩ፡፡ ስለ ኮሮና ቫይረስ


በአማርኛ ቋንቋ ለማዘጋጀት የተገደድነው ብዙ ሰው በእንግሊዝኛ
የተጻፉትን ህክምናዊ መረጃዎች አንብቦ ስለማይረዳቸው ነው፡፡ በዚህ
መጽሐፍ ውስጥ ያሉ መረጃዎች በዓለማችን ታማኝ ከተባሉ ተቋማትና
የምርምር መጽሔቶች የተገኙ በመሆናቸው ለሌሎችም መረጃውን ያጋሩ፡፡
ለሌሎች ባስተማሩ ቁጥር እርስዎም የመከላከያ መንገዶችን በቀላሉ
ለማስታወስ ያግዎታል፡፡ ገዝተው ማንበብ ለማይችሉም ሰዎ በስጦታ
መልክ ያበክቱላቸው፡፡ ወረርሽኙ የሚቆመው ሁሉም ቫይረሱን እኩል
መዋጋት ሲችል ነውና፡፡

1

የቅጂ መብት

ይህ መጽሐፍ የቅጅ መብቱ በአሣታሚው ድርጅት ማለትም በሜዲካል


ዊዝደም አፍሪካ የተመዘገበ ነው፡፡ ያለ አሳታሚው ፈቃድ መጽሐፉን
በሙሉም ሆነ በከፊል በየትኛውም ዓይነት መንገድ በወረቀት ሆነ
በዲጂታል መልክ ማባዛት በህግ ያስቀጣል፡፡

ምስጋና
ይህን መጽሐፍ በማዘጋጀት ለህዝባችን ትክክለኛ መረጃን ለመስጠት
ማህበራዊ ኃላፊነታችንን መወጣት አለብን በሚል መንፈስ፤ ጊዜያቸውን
ሰውተው ላበረከቱት ሙያዊና ማሕበራዊ ኃላፊነት የሚከተሉት የህክምና
ባለሙያዎች ማለትም፡- ዶ/ር አቡሽ አያሌው፣ ዶ/ር አብርሃም ክብረት፤
ዮሴፍ ጥሩነህ፣ ዶ/ር ቃልኪዳን ቅጣውና ዶ/ር ደሳለው ካሳሁን አሳታሚ
ድርጅቱ በአንባቢያን ስም ሊያመሰግናቸው ይወዳል፡፡ እንዲሁም በጽሁፍ
ደረጃ ወ/ሮ እድገት ክብሩና ትዝታ ክንዴ እንዲሁም በዲዛይን ደረጃ ሜሪ
ኡርጋና አሸናፊ ሰለሞን ላደረጋችሁትሁሉ እናመሰግናለን::

ማስጠንቀቂያ፡

ይህ መጽሐፍ በህክምና ተቋማት ውስጥ ሊደረጉ የሚገቡ ህክምናዊ


ውሳኔዎችን የሚተካ አይደለም፡፡ ሰዎች በመሰላቸው መንገድ
በመተርጎምና በመጠቀም ለሚከተለው ጉዳት አሳታሚ ድርጅቱ ኃላፊነት
አይወስድም፡፡

2

ማውጫ ገፅ
የመፅሐፉ መግቢያ
የመጨረሻው መጀመሪያ ይሆንን? .......................................................... 7

በዘመናት መካከል - ከህዳር በሽታ እስከ ኮሮና ............................. 12

ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ የሚነገሩ ሳይንስ


የማያውቃቸው ሃሳቦች እና የፈጠራ መላ ምቶች ........................ 21

የኮሮና ቫይረስ መፃኢ ገፅታ


ከቀላል እስከ አስደንጋጭ፣ ከጤና እስከ ፖለቲካ!! ........................ 31

የ2019 ኖቭል ኮሮና ቫይረስ መነሻ ...................................................... 44

የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች፤


የምርመራና የህክምና ዘዴዎች .............................................................. 48

አንድ ሰው በቫይረሱ ስለመያዙ እንዴት ይታወቃል?


በላብራቶሪ ምርመራ ኮሮና ቫይረስን የመለየት ፈተና ............... 56

የኮቪድ 19 የህክምና ውጤት ምን ይመስላል? ............................ 63

ኮሮና በሌሎች በሽታዎች ላይ ያለው


ተጽዕኖና አባባሽነት ....................................................................................... 67

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለማከም


እንዴት ታቅዳለህ? እንዴትስ ተግባራዊ ታደርጋለህ?................ 73

የኮሮና ቫይረስ ጥብቅ መከላከያ እና


ማስጠንቀቂያዎች!! ..................................................................................... 102

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር


የዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም ምክሮ ....................................................... 109
ማውጫ ገፅ
አለምን ከወረርሽኝ ፍርሃት ወደ ብርሃንና
ተስፋ የወሰዱ ዓለም አቀፋዊ ኹነቶች፣ ......................................... 113

ኮሮና ቫይረስ በእድሜ በገፉት ሰዎች


ላይ ለምን አደጋው ይጨምራል? ...................................................... 117

ለኮሮና አይበገሬ የሰውነት መከላከያን


ማዳበሪያ ስምንቱ ሁነኛ ስልቶች ........................................................ 119

የሰውነትን በሽታን የመከላከል አቅም


የሚጨምሩ ስምንቱ ሁነኛ ምግቦች ................................................. 126

ልዩ ጥንቃቄ ለሚያሰፈልጋቸው ልዩ መከላከያ! ........................ 132

የኮሮናቫይረስን ድርጅቶች ስርጭት ለመከላከል


ሊያደርጋቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች! ................................................ 134

ልብ የማንላቸው የቫይረሱ አስተላላፊዎች .................................... 150

የኢኮኖሚውን አደጋ ለመቀነስ ለመንግስት


የሚመከሩ መፍትሔዎች!! ......................................................................152

የኮሮና ቫይረስ ፈዋሽ መድሐኒትና ክትባት


አልባነቱ ምስጢር ምን ይሆን? .............................................................157

የማህበራዊ ሚዲያው ክፉና ደግ-ዘመነ ኮሮና


የማህበራዊ ሚዲያው ምን አጎደለብን፣ምን አተረፈል ........... 161

ኮሮናቫይረስን በባዮሎጂክ ጦር መሳሪያነት


የሚያውለው ማን ይሆን? ..................................................................... 166

ማጣቀሻ ምንጮች ........................................................................................ 170


ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የመፅሐፉ መግቢያ
የመጨረሻው መጀመሪያ ይሆንን?
‹ የፈላ ውሃ ድንችን ያለሰልሳል፤ እንቁላልን ደግሞ ጠ ንካራ
ያደርጋል፡፡ ው ጤ ቱን የሚ ወስነው አንተ የተሰራህበት ነገር እንጂ
ው ጫ ዊው ክስተት አይደለም › ኳንተም ወርልድ

በ1918 እ.ኤ.አ 500 ሚሊየን ህዝብ አጥቅቶ 50 ሚሊየን ህዝብ የፈጀው


ኢንፍሎዌንዛ በመባል የሚጠራ የመተንፈሻ አካል ህመም የነበረ ሲሆን
(በአገራችን የህዳር በሽታ ይባላል) ይህም በወቅቱ በአለም ጤና ድርጅት
በአለም አቀፍ ወረርሸኝነት የተፈረጀ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ዘግናኝ
እልቂትን ጥሎ ያለፈ ነበር፡፡ ይህ አለም አቀፍ የመተንፈሻ አካል
ወረርሽኝ ከፍተኛ እልቂትን ለማድረግ ያበቃው አንድም በወቅቱ የነበረው
ዝቅተኛ የመከላከያና የህክምና አፀፋዊ መልሱ ሲሆን ሁለትም ደግሞ
ሠዎች ለህመሙ ሠውነታቸው ብቁ የመከላከያ አቅም ስላልነበረው ነበር፡፡
‹ ‹ ፓንደሚክ ፍሉ› › በወቅቱ የተከሰተው በሰዎች ላይ ሲከሰት የነበረውና
‹ ‹ H3N8› › የተባለው ቫይረስ በወፎች ላይ በብዛት ከሚገኘው
የኢንፍሎዌንዛ ቫይረስ ጋር በብዛት ከሚኘው የኢንፍሎዌንዛ ቫይረስ ጋር
ራሱን በማዳቀል ወደ አዲስ አይነት ዝርያ ማለትም ወደ ‹ ‹ H1N1› ›
ስለተቀየረ ነበር፡፡ ለዚህ ዲቃላ ቫይረስ ሠዎች የበሽታ መከላከያ ሃይል
አላዳበሩም ፣ አለም የመፈወሻ መድሃኒትም ሆነ መከላከያ ክትባት
አልነበራትም፡፡ በእርግጥም በብዙሃኑ ዘንድ ወረርሽኙን ለመከላከል
የሚያስችል ተገቢ ግንዛቤና አፀፋዊ ምላሽ ደካማም ነበር፡፡ በወቅቱ
የነበረው የአለም ህዝብ 1.6 ቢሊየን የነበረ ሲሆን ምናልባትም የገዳይነት

3
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 7
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

መጠኑን ወደዛሬው የአለም ህዝብ ብንቀየረው ኖሮ ከ200 ሚሊየኖች


ህዝብ በላይ ይጨርስ ነበር እንደማለት ነው፡፡ ይህ በወረርሽኙ ብቻ እንጂ
በቀጣይ በሚፈጠረው የኢኮኖሚ ድቀት የሚሞተውን አይጨምርም፡፡

አገራችንም ሆነች አለማችን በተለያየ ጊዜያት በተከሰቱ ወረርሽኞች


አልፈዋል፡፡ እያንዳንዱ ወረርሽኝና ጥፋት ዛሬ ላይ አለም ለደረሰበት
ስልጣኔ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ይህ አዎንታዊ ጎናቸው ነው፡፡
በቅርቡም የተከሰቱት እንደ ሳርስና ኢቦላም ለሰው ልጆች የማስጠንቀቂያ
ደውል ሆነው አልፈዋል፡፡ በታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጥረው የነበሩ
እንደ ፈንጣጣ ፣ ኩፍኝና ፖሊዮ በክትባት ሃይል እንዲጠፉ ተደርገዋል፡፡
ይህ ክትባት እስኪገኝ ድረስ ግን ረጅም ጊዜ ፈጅተዋል ፣ ብዙ
ጥፋቶችንም አስከትለዋል፡፡ ቫይረሶች በባህሪያቸው አስቸጋሪ ናቸው፣
እንደባክቴሪያ በቀላሉ በፀረ-ባክቴሪያ መድሃኒቶች የምናክማቸው
አይደሉም፡፡ ለአብነት እንኳን በባለፉት 40 አመታት ውስጥ 40 ሚሊየን
ህዝብ የጨረሰውን ኤች.አይ.ቪ ማጤኑ በቂ ነው፡፡ ኤች.አይ.ቪ ፈውስና
ክትባት የለሽ የአለማችን ሌላኛው የቫይረስ ወረርሽኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ኮቪድ-19 በመባል የሚጠራው አዲሱ ወረርሽኝ ልክ እንደ ፍሉ-18


ከሰውና ከእንሰሳት ዝርያ የተዳቀለ በመሆኑ ከአሁን ቀደም በሰዎች ዘንድ
ሲሰራጭ የነበረው የኮሮና ቫይረስ ከእንሰሳት ኮሮና ቫይረስ ጋር በመዳቀል
የተገኘ አዲስ አይነት ዝርያ በመሆኑ የሰውነታችን የበሽታ የመከላከያ
ሃይል ፣ ለቫይረሱ እንግዳ ነው፡፡ አዲስ ዲቃላ ቫይረስ በመሆኑም
‹ ‹ ኖቭል› › (አዲስ) የሚባል ቅጥያ ተሰጥቷል፡፡ ለዚህ ብቻ በቀላሉ
ክትባትም ሆነ ፈዋሽ መድሃኒት ለማግኘት ታዲያ የሚያዳግት አይነት
ነው፡፡ ይሁን እንጂ ተገቢና አስፈላጊ የመከላከያ ስልቶችን ተግባራዊ
4
8 ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

በማድረግ ልንከላከለው እንችላለን፡፡ ትክክለኛ መከላከል በፍርሃት ላይ


የተመሠረተ መሆን የለበትም፡፡ ስለፈራን ልንከላከለው አንችልም፡፡
በትክክለኛ እውቀት ላይ በመንተራስ ግን ስልቶቹን በየደቂቃው እያስታወሱ
ማከናወን ያስፈልጋል፡፡

ይህን መፅሐፍ ለማዘጋጀት የተገደድነውም ህዝባችን ባለማወቅ እንዳይጎዳ


በሚል እሳቤ ነው፡፡ ከተለያዩ ሠዎች በየሚዲያው የሚሰጡ የተለያዩ
እንዳንዴም የሚጋጩ መረጃዎችን ሲሰራጩ እናያለን፡፡ እንዲሁም
በፍርሃት የተነሳ ለቫይረሱ መከላከል ፋይዳ የሌላቸው እርምጃዎች
ሲወሠዱም ይታያሉ፡፡ ለምሳሌ ማስክ ለብሰው እጅ ለእጅ ተያይዘው
የሚጓዙ ሠዎች ይታያሉ፡፡ እውነቱን ለመናገር ማስኩን አውልቀው
ሳይነካኩ ቢሄዱ ነበር የሚሻለው፡፡ እንዲህና ሌሎች ብዙ ድርጊቶች
ካለማወቅ ጋር ይያያዛሉ፡፡ በፍርሃት ሳይሆን ትክክለኛ መረጃን በማንበብ
ከኮሮና ቫይረስ ተፅዕኖ ራሳችንንም ሆነ ቤተሰባችንን መከላከል
ይኖርብናል፡፡ መፍራት ያለብን ፍርሃትን እንጂ ኮሮና ቫይረስን መሆን
የለበትም፡፡

‹ ‹ ኮቪድ-19› › ምናልባትም ፈጣሪ ከረዳን በአጭር ወራት ውስጥ


ልናስቆመው እንችለለን፡፡ የራሱ የቫይረሱ የአደገኝነት ለውጥ ወደደካማ
እሱነቱ ሊቀየር ይችላል፡፡ እንደዚህ ከሆነ የስርጭት ፍጥነቱም ሆነ
የገዳይነት ደረጃው ይቀንሳል፡፡ ወይም ወደ ቀላል ጉንፋንነት እየተቀየረ
ሊጠፋ ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ ሳይንቲስቶች ፍቱን መከላከያ ወይም
መድሃኒት አግኝተው የቫይረሱን ስርጭት አሊያም የገዳይነት አቅሙን
ሊያመክኑት ይችላሉ፡፡ ወይም ደግሞ ሁሉም ከቤቱ ቢቀመጥ የቫይረሱን
ስርጭት መግታት ይችላል፡፡ አልያም ደግሞ ሁሉም ሠው በቫይረሱ ተይዞ
5
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 9

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የዳኑት ሠዎች በቂ መከላከያ ስለሚያዳብሩ ቫይረሱ ወደቀላል ጉንፋንነት


ይቀየራል፡፡ ይህ የበጎ የቢሆን አስተሳሰብ ነው፤ ወይም ‹ ‹ ቤስት ኬዝ
ሴናሪዮ› › አይነት ነው፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ቫይረሱ ባህሪውን ሳይቀይር
አሁን ባለበት ደረጃ ሊቀጥል ይችላል፡፡፡ ወይም ጭራሽ እንደ ኤች.አይ.ቪ
ዝርያውን ሊቀይርና ወደ አደገኛ ደረጃ ሊቀየር ይችላል፡፡ ሳይንቲስቶችም
ፈዋሽ መድሃኒትም ሆነ መከላከያ ማግኘት ከአመት በላይ ሊፈጅባቸው
ይችላል፡፡ ኮሮና ቫይረስ የበረደ ይመስልና እንደገና እያገረሸ ሊቀጥልም
ይችላል፡፡ እንዲህ ከሆነ ብዙ ሠዎችን ይይዛል ፣ ይገድላል፡፡ የአገርና
የአለም ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ ይደቃል፡፡ የበሽታውና ኢኮኖሚው ተፅዕኖ
ድምር ውጤት ወደ ከፍተኛ ተስፋቢስነትና ድብርት ይቀየራል፡፡ ይህ
‹ ‹ የመጥፎ ቢሆን› › ወይም ‹ ‹ ዎርስት ኬዝ ሴናሪዮ› › አይነት ነው፡፡

የትኛው የቢሆን አስተሳሰብ የበለጠ ሊከሰት እንደሚችል አይታወቅም፡፡


ይሁን እንጂ ሚዛን የሚደፋው የመጥፎ ቢሆን አስተሳሰብ ነው:: ዓለም
ቢያንስ ለቀጣዩ አንድ አመት ያዝ ለቀቅ በሚያደርግ የኮሮና ወረርሽኝ
ውስጥ ታልፋለች:: ለሁለቱም ግን አንድ የጋራ የዝግጁነት አጀንዳ ሊኖረን
ይገባል፡፡ ወረርሽኙን በቀኝ እጃችን የመከላከል ኢኮኖሚውን በግራ እጃችን
የማዳን ሚናችን መቀጠል ይኖርበታል፡፡ ወረርሽኙን የምንከላ ከልባቸው
መንገዶች ኢኮኖሚውን ክፉኛ ይጎዳሉ፡፡ ይሁን እንጂ ኮኖሚውንም አብረን
ለማከም ጥረት ካላደረግን ኮሮና ቫይረስ ቢጠፋም ጥሎብን የሚሄደው
የኢኮኖሚ ድቀት መልሶ ይሰብረናል፡፡ መንግስትም ሆነ እያንዳንዳችን
ለዚህ መሠል ትግል መረባረብ ያስፈልጋል፡፡ ስራችንን እየሠራን እንዴት
ቫይረሱን እንከላከል የወቅቱ አንገብጋቢ አጀንዳ ነው፤ ይህ መፅሐፍ

6
10
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ለሁለቱም መልስ ይዟል፡፡ በዚህ መፅሃፍ ውስጥ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን


ለማንሳትና ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡

ለህዝባችን መድረሻ ያለብን ግዜ አሁን ነው በሚል በመፅሃፉ ውስጥ


ከአምስት ያላሱ የጤና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ እርስዎም ትክክለኛ
መረጃዎችን ብቻ ይከታተሉ፤ በተለይም የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር
፣ የኢትዮጵያ የማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዮት ፣ የዓለም ጤና ድርጅት ፣
የዓለም የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል እንዲሁም የሜዲካል ጋዜጣና
መፅሔት ዌብሳይትንና የፌስቡክ ገፅን ይከታተሉ፡፡ ማናቸውንም
መረጃዎች ለማግኘት 8335 ይደውሉ፡፡ ይህን መፅሐፍ በማንበብ
ስራዎንም ሆነ ሌሎችን ለማዳን ያነበቡትን በማስተማር የዜግነት
ድርሻዎን ይወጡ፡፡ የእርስዎ ከህመሙ መጠበቅ ብቻውን ዋጋ የለውም፡፡
የሌሎችም መጠበቅ ይኖርበታል፡፡ ወረርሽኙ የሚጠፋው ሁሉም ሲጠበቅ
ነውና፡፡ ለሌላው ማሠብ ራስን ከበሽታው እንደ መጠበቅ ነው፡፡ ራስን
መጠበቅም ሌሎችን እንደመጠበቅ ነው፡፡

አንበረከክም፤ ፈጣሪ ከሁላችንም ጋር ነው፤ በፍርሃት ሳይሆን በእውቀት


ላይ በተመሠረተ ትብብር ከኮሮና ነፃ የሆነች ኢትዮጵያ ፣ አፍሪካንና
ዓለምን እናያለን!! እኛ ኢትዮጵያውያን ከተባበርን የማናሸንፈው ተዓምር

አይኖርም!!

7
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 11
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

በዘመናት መካከል - ከህዳር በሽታ


እስከ ኮሮና
ኢትዮጵያ ወረርሽኝ ለመመከት ዝግጁ ናት?
"……ፈጣሪ መጀመሪያ ሃኪሞቹን ወሰደ፣ ከዚያ ህዝቡም በወረርሽኝ
አለቀ…" ይህን የፃፉት ወንጌል ለማስፋፋት ወደኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ
ሚሽነሪዎች ናቸው፤ ዘመኑ ደግሞ 1910። በወቅቱ "የህዳር በሽታ" ተብሎ
የተጠራው የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያንን
ሕይወት የቀጠፈበት ነበር። እጅግ ጥቂት የሚባሉት የጤና ባለሞያዎች
ሳይቀሩ በወረርሽኙ የሞቱበት በመኾኑ ችግሩን መቆጣጠር አልተቻለም
ነበር። "ስምንት ሃኪሞች ቢኖሩ አራቱ በወረርሽኙ ሞተዋል፣ " መባልን
በየስፍራው ሲሄዱ መስማት የተለመደ እንደነበር ፕሮፌሰር ሪቻርድ
ፓንከርስት የወቅቱን ማስታወሻ ከታቢዎች ጠቅሰው ጽፈዋል።

ከኤደን ባህረ ሰላጤ ወደኢትዮጵያ እንደገባ የሚነገረው ይህ የመተንፈሻ


አካላትን የሚያጠቃው የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ በአዲስ አበባ ብቻ ወደ
አስር ሺህ ሰዎችን ሲገድል በተቀረው የአገሪቱ ክፍል ደግሞ እስከ ሃምሳ
ሺህ ሰዎች መሞታቸውን ፓንከርስት " The History of Epidemics In
Ethiopia " በተሰኘ ሰፊ ጽሁፋቸው ጠቅሰዋል። የህዳር በሽታ ጥቃት ብዙ
የኑሮ ዘዬ መቀየርን ያስገደደ፣ የወቅቱን መሪዎች ያስጨነቀና አሁን ድረስ
የሚታወስ ቀውስ ነው። በዚህ መነሻም በየዓመቱ ህዳር 12 "ህዳር
ሲታጠን" በሚል ስያሜ ኢትዮጵያውያን ከቤታቸውና አካባቢያቸው የበሽታ
እና የወረርሽኝ ምንጭ ሊኾኑ የሚችሉ ቆሻሻዎችን እየሰበሰቡ ያቃጥላሉ ።
ይህን መሰሉ ምላሽ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን በአንዳንድ ወረርሽኞች ክፉኛ
8
12
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ያጠቋቸው በነበሩ የደቡብ አሜሪካ አካባቢዎች እንደሚዘወተሩ መረጃዎች


ያሳያሉ። ከልምዶች ባለፈ ግን አለም በየወቅቱ ከምታስተናግዳቸው
ወረርሽኞች ብዛትና ስፋት አንፃር ምን ቋሚና ሳይንስን መሰረት ያደረጉ
ቅድመ መከላከያ ዘዴና ስርዓቶች ማበጀት ተቻለ? የሚለው ጥያቄ የብዙ
ተመራማሪና ሳይንስ አዋቂዎች ጥያቄ ነው። እንደአሁኑ ያለ የኮሮና
ቫይረስ ወረርሽኝ ሲከሰትም በኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን በአለም አቀፍ ደረጃ
ከቀደሙት አለምን ያሽመደመዱ ትልልቅ ወረርሽኞች የተወሰደ
ትምህርትና መፍትሄን መለስ ብሎ መቃኘት ለአሁኑ ትግል ትንሽም
ቢኾን አቅጣጫ ይሰጣል ይላሉ ባለሞያዎቹ።

አለም ከቀደሙ ወረርሽኞች ምን ተማረ?


ከቀደሙ ወረርሽኞች አለም ተምሮ ካስቀመጣቸው መፍትሄዎች አንዱ
በወረርሽኝ ወቅት ምልክት ያለባቸው ወይም ታማሚ ሰዎችን ነጥሎ
የማስቀመጥና ማከም (ኳራንቲን) አንዱ ነው። ይህ መፍትሄ ድንበር
ጭምር የሚሻገሩ ወረርሽኞችን ለመገደብ ብዙ ያግዛል። ኳራንቲን በህዝብ
ጤና ጠቃሚ እርምጃ ኾኖ የተጀመረው በአውሮፓ አቆጣጠር በ1580
በኤዥያ ተከስቶ በነበረው የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ ወቅት ነበር። ሌላው
ከቀደሙ አለምአቀፍ ወረርሽኞች ትምህርት ኾኖ አሁን ድረስ
የሚተገበረው የመጀመሪያውን ታማሚ ፈልጎ ማግኘትና ፣ ይህ ሰው
ያገኛቸውን ሰዎች እንዲኹም ለህመሙ ተጋላጭ የኾነባቸውን ተዋህስያን
ምንጭ የመለየት ስራ ( ትሬሲንግ) ነው። ይህ የተጀመረው በህንድ፣
እንግሊዝና ራሺያ ከተከሰቱ ሰፊ አካባቢዎችን ከሸፈኑ የኮሌራ ወረርሽኞች

9
13
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

በኋላ እንደነበር በአሜሪካው ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ታሪክ አጥኚ


የኾኑት ግራኻም ሞኒ ይናገራሉ።

በአለም የህክምና ታሪክ ክፉው ወረርሽኝ የሚባለው የ1918 የስፓኒሽ ፍሉ


ደግሞ እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ መገደብን እንደ አንድ መፍትሄ
መውሰድን አለም የተማረበት መኾኑን ባለሞያዎች ያስረዳሉ። ብዙዎቹ
የተከሰቱ የጉንፋን ወረርሽኞች ያስተማሩት ሁነኛ ትምህርት ደግሞ
አገራት በደንብ የተደራጁ የበሽታ ቁጥጥር ማዕከላትን ማቋቋም እጅግ
አስፈላጊ መኾኑንና አለምአቀፍ ትብብር ወሳኝ እንደኾነ ነበር። ይህን
ተከትሎ ነበር አሜሪካ ሲዲሲ የተባለውን የበሽታዎች ቁጥጥር ማዕከል
ያቋቋመችው። የአለም ጤና ድርጅትም የተቋቋመው በዚህ እሳቤ ነበር።
ይኹንና አለም ወረርሽኞችን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጣርና እንዳይከሰቱም
ጭምር ለማድረግ የምትችልበት አቅም ላይ አልደረሰም። የክትባቶችና ጸረ
- ተዋህስያን መድሃኒቶች መፈጠር ፣ እንዲኹም የተሻለ አቅም ያላቸው
የጤና ተቋማትን በብዙ አገራት መገንባት መቻሉ ከወረርሽኞች መመከት
የተወሰዱ ትምህርቶች ተደርገው ይወሰዳሉ።

ይኹንና ወረርሽኞችን የመመከት አቅም፣ ከቀደሙ ጉዳቶች ተምሮ


ጠንካራ ግንዛቤ ያለው ማህበረሰብና የጤና ስርዓት መገንባት ለብዙ ደሃ
አገራት ፈታኝ ነው። ኢትዮጵያም ከዚህ ጎራ ትመደባለች። ከህዳር በሽታ
ወረርሽኝ ብዙ ዘመናት በኋላም ወረርሽኝ የመመከት ብቃቷ ይጠየቃል።

10
14
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ወረርሽኞችን የመመከት አቅምና ብልሃት


በኢትዮጵያ፣

ኢትዮጵያውያንን የፈተነው የቀደመ ወረርሽኝ ኢንፍሉዌንዛ ብቻ


አልነበረም። ከ 16 ኛው ክፍለዘመን አንስቶ የተከሰቱ የታይፈስ ( ንዳድ)፣
ኮሌራ፣ ፈንጣጣ ይጠቀሳሉ። እነዚህ ወረርሽኞች ከጦርነትና ድርቅ ጋር
ተደምረው የቀደሙ ዘመናት መሪዎች የስልጣን ዘመንን በብዙ ፈትነዋል።
እነዚህ ወረርሽኞችን በቅጡ ተረድተው ምላሽ ለመስጠት፣ ዳግም
እንዳይከሰቱም ብልሃት ለማበጀት የቀደሙት ነገስታትና መሪዎች
የየአቅማቸውን ቢጥሩም ፣ በዘመናቱ የነበረው የሳይንስ እውቀት አነስተኛ
መሆን፣ የባለሞያ እጥረትና የዘመናዊ መድሃኒቶች እጦት ኢትዮጵያን
ከጦርነቶች ባላነሰ ብዙ አስከፍሏታል።

አፄ ዮሃንስና ምኒሊክ በንግስናቸው ወቅት የጤና ደንብና ህጎችን


እንዲያወጡ ካስገደዷቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ የስልጣን
ዘመኖቻቸው ላይ ይከሰቱ የነበሩ ወረርሽኞች መኾናቸውን የታሪክ
ማስታወሻዎች ይናገራሉ። ለአፄ ቴዎድሮስ ኢትዮጵያን የማዘመን ስራ
ውስጥ እንቅፋት ከነበሩ ጉዳዮች መካከል ወታደሮችና ተራው ህዝብ
በተለያዩ ወረርሽኞች ደጋግሞ መጠቃቱ አንዱ እንደነበር በውጪ አገር
ተጓዥና ጎብኚዎች የተፃፉ ማስታወሻዎች ያወሳሉ። በተለይ የኮሌራ
ወረርሽኝ ተደጋግሞ መታየቱን የሪቻርድ ፓንከርስት ጽሁፍ ይናገራል።

ኢትዮጵያውያን በቀደሙት ዘመናት ለፈንጣጣ እና ኮሌራ ወረርሽኞች


ይሰጡ የነበረውን ምላሽ በተመለከተ የፃፈው ጀርመናዊው ተጓዥ እና
11
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 15
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ጸሃፊ ጆብ ሉዶልፍ እንዳለው ኢትዮጵያውያኑ በሽታዎቹና ተባዮች ብዙ


ሰዎችን ማጥቃታቸውን ሲመለከቱ ቤትና መንደራቸውን ጥለው በመሄድ
ተራሮች ላይ ይሰፍሩ ነበር ብሏል። የጦር አዛዦችና የአገር መሪዎችም
ወረርሽኞች ሲከሰቱ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መስፈርን እንደመፍትሄ
ይወስዱ ነበር። ችግሮቹን ከፈጣሪ ቁጣ ጋር በማያያዝ ሃይማኖታዊ
መፍትሄ እና ፀሎትን የሚከተሉ መሪዎችም በኢትዮጵያ ታሪክ
ተመዝግበዋል።

ከነገስታቱ ሚኒሊክና ዮሃንስ ዘመን መልስ፣


እነ አፄ ሚኒሊክ እና አፄ ዮሃንስ የጤና ህጎችን ካስተዋወቁ ብዙ ጊዜያት
በኋላ እና የሳይንስና ጤና ትምህርት ለህብረተሰቡ ከዘለቀ አስርት
ዓመታት በኋላም ግን ኢትዮጵያ እንደ ወፍ ጉንፋን ያሉ ወረርሽኞችን
ለመመከት ዝግጁ አልነበረችም። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው የህዝብ ጤና
አጠባበቅ ትምህርት ባለሞያዎች የሆኑት ያየህይራድ ቅጣው እና ሚርጊሳ
ካባ ወረርሽኞችን የመመከት ብቃታችን ምን ላይ ነው? በሚል ርዕስ
ባሳተሙት ጥናት እንደተመለከተው ለኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ ተጋላጭ
የኾነችው ኢትዮጵያ በሽታው ላይ የመደበኛ ቅኝት (ሰርቬላንስ )
የጀመረችው ከብዙ ዝግየታ በኋላ በ1997 ዓ. ም. ነበር። የኢንፍሉዌንዛ
ላቦራቶሪም በተከታዩ አመት ተቋቁሞ ስራ ጀመረ። ለረጅም ጊዜያት
የማረጋገጫ ምርመራ ለማሰራት የደቡብ አፍሪካው የብሄራዊ ጤና
ምርምር ተቋም ዘንድ ናሙናዎችን መላክ ግድ ነበር።

የኢትዮጵያ የወረርሽኝ ምላሽ በኮሮና ዘመን


መጋቢት 4 ፣ 2012 ረፋድ ላይ የኮሚውኒኬሽን ፕሮቶኮሉን የጣሰ
በሚመስል ሁኔታ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር)

12
16 ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ታማሚ መገኘቱን በትዊተር ገፃቸው


ሲያሳውቁ የትዊተር ተጠቃሚዎች ዜናውን በድንጋጤ ተቀበሉ። ይፋዊ
መግለጫውን ለመስጠት ጋዜጠኞችን የጠሩት አዲሷ የጤና ሚኒስትር
ዶክተር ሊያ ታደሰ የስልጣን ዘመናቸውን በፈተና መጀመራቸው
ከገፅታቸው ይነበብ ነበር። የኮሮና ቫይረስ በአንድ ጃፓናዋ ላይ አዲስ አበባ
ውስጥ መገኘቱን አረጋግጠው፣ ቀድሞውኑም መስሪያ ቤታቸው ዝግጅት
ማድረግ ከጀመረ መቆየቱን ተናገሩ። ህዝቡ እንዲረጋጋና ከጤና ሚኒስቴር
በሚሰጥ መግለጫ መሰረት ተገቢውን እንዲያደርግ አሳሰቡ።

የጤና ሚኒስቴር ዝግጅት አድርጌያለሁ ቢልም በርካታ የከተማዋ


ነዋሪዎች በስነልቦና እና መረጃ አልተዘጋጁም ነበር። በሽታውን ይከላከላሉ
የተባሉ መገልገያና አላቂ እቃዎችን ብቻ ሳይኾን የምግብ ምርቶችን
ጭምር በገፍ መግዛት፣ ፍርሃት ፣ ፍፁም ሳይንሳዊ ያልኾኑ መረጃዎን
በማህበራዊ ሚዲያ መለዋወጥ በርክቶ ታየ። ቀናት እየጨመሩ ሲመጡና
ተጨማሪ ህሙማንም ሲመዘገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች በጠቅላይ
ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋ ተደረጉ። ይኹንና ከመግለጫው
በቀደሙት ሁለት ቀናት የተደረጉት የሴቶች ሩጫ እንዲኹም የብልፅግና
ፓርቲ ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች
የተሳተፉባቸው እና ለቫይረሱ መተላለፍ አጋላጭ የነበሩ ሁነቶች
እንዲካሄዱ መፍቀዱ መንግስትን ክፉኛ አስተችቶታል።
የኮሮና ቫይረስ -ኮቪድ 19- የመከላከልና መቆጣጠር ስራን በዋናነት የጤና
ጥበቃ ሚኒስቴር የሚመራ ሲኾን፣ በስሩ የሚገኘው የኢትዮጵያ
ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደግሞ የላቦራቶሪ ምርመራዎችና ነጥሎ
ማከሚያ ስፍራም አለው። በኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያ ሰሞን
13
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 17
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ምርመራዎችን ወደ ደቡብ አፍሪካ ይልክ የነበረው ይህ ተቋም አሁን ላይ


እዚሁ አገር ውስጥ መመርመርና ውጤት ማውጣት መጀመሩ ትልቅ ራስ
ምታት ቀንሷል። የድንገተኛ የጤና አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከሉም
የሚገኝበት ይህ ተቋም ብዙዎቹን ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተያያዙ ስራዎች
በብቃት እየሰራ ስለመኾኑ በስፋት ቢነገርም፣ የመረጃ ማዕከሉ ስልክ
8335 ብዙ ጊዜ አይሰራም የሚሉ ቅሬታዎች መሰማታቸው አልቀረም።
የጥሪ ማዕከሉ አስተባባሪ ለዶቸቨለ ሬዲዮ ሲናገሩ "በብዙ ቋንቋዎች
መረጃዎችን እና ጥቆማዎችን እየሰጠን ነው፣ በቀን እስከ አርባ ሺህ
ጥሪዎችን እናስተናግዳለን። በሲስተም ችግር ምክንያት ትንሽ ችግር
ገጥሞን የነበረ በኾንም አሁን በሙሉ አቅም በሶስት ፈረቃ እየሰራን ነው"
ብለዋል።

ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተጨማሪ ተዘጋጅተዋል የተባሉት


ሆስፒታሎች በቂ ዝግጅት በማድረግ በኩል ክፍተት እንዳለባቸው የተለያዩ
ባለሞያዎች በማህበራዊ ሚዲያው ሲናገሩ እየተሰማ ነው። "ውሃ ፣
የፅዳት ኬሚካሎች፣ የፊት መሸፈኛዎች፣ ጓንቶችና የመፀዳጃ ቤቶች
ሁኔታ በጣም ችግር ያለበትና እንኳን በወረርሽኝ ወቅት በደህናውም ጊዜ
ብዙ ስቃይ ያለበት ነው" ይላል ለዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ሃሳቡን ያካፈለ እና
ለኮሮና ተዘጋጅተዋል ከተባሉት ጤና ተቋማት በአንዱ የሚሰራ ባለሞያ።
ችግሩ ከአዲስ አበባ ውጪ የበለጠ እንደሚያሳስብ ባለሞያው ይጠቅሳል።
ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ የምርመራ፣ ለይቶ ማቆያና ማከሚያ ማዕከላት
በብዛት እየተቋቋሙ ቢኾንም የአቅርቦቶች ማነስ እንዳለባቸው በሚዲያ
ሪፖርቶች ሲነገርም ተደምጧል።

14
18
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን መከላከልና መቆጣጠር ግን የጤና ዘርፉና


የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጉዳይ ብቻ ባለመኾኑ የተለያዩ ዘርፎችን
ዝግጁነት፣ ወደ ስራ በፍጥነት የመግባት ፈቃደኝነትና አቅም እንዲኹም
የመቀናጀት ችግሮች ሁሉ ይፋ የወጡባቸው ነበሩ። ትራንስፖርት፣
የንግድ ተቋማት፣ ሚዲያዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ መንግስታዊ
ያልኾኑ ተቋማትና ሌሎቹንም አስተባብሮ በአንድ ፍጥነት፣ የመረጃ
ብቃትና የመተግበር አቅም ማሰለፍ ላይ የነበሩት መንጠባጠቦች እንደአገር
ለወረርሽኞች ምላሽ የመስጠት አቅም ያለበትን ደረጃ እያሳየ እንደኾነ
ማየት ተችሏል።

ከተቋማቱ በበለጠ ደግሞ በሚበዛው የማህበረሰብ ክፍል ዘንድ ያለው ቀላል


የኾኑ ጤና መጠበቂያ ልምዶችና እና እውቀት ላይ ያለው ሰፊ ክፍተት
በማህበራዊ ሚዲያ ለሚሰራጩ የሃሰት መረጃዎችና፣ ሳይንሳዊ ያልኾኑ
ምክሮችን ተቀብሎ መተግበርን አስገድዷል። የጤና ሚኒስቴር በዚህ በኩል
ጥንቃቄ እንዲደረግ ቢመክርም የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት፣ ግድየለሽነትና
ለስርጭቱ ሰበብ የሚኾኑ መንገዶችና ተግባራትን መግታት ፈተና ኾኖ
ዘልቋል።

መፀለይ……..
በርካቶች እንደአገር እየተደረጉ ያሉ ቫይረሱን በሩቅ ለመያዝ እየተደረጉ
ያሉ ጥረቶችን ቢያደንቁም፣ ገፍቶ መጥቶ በብዙ አካባቢዎች ከተሰራጨ
የጤናውን ስርዓት በእጅጉ የሚፈትንና የታመመውን ኢኮኖሚ እጅጉን
የሚያጎብጥ፣ ለበርካቶችም ህመምና ሞት የሚያዳርስ ፈተና ይኾናል።
ለዚህም ይመስላል ብዙዎች በየዕምነታቸው መፀለይና ፈጣሪን መማለድ

15
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 19
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የበለጠ ስሜት የሚሰጥ መፍትሄ አድርገው ወስደዋል። ከህዳር በሽታ


አንድ ክፍለዘመን በኋላም ወረርሽኞችን በመመከት በኩል ከመልሶች ይልቅ
ጥያቄዎች መበርከታቸው ያሳስባል ። ብዙ ጥያቄ፣ ብዙ የቤት ስራ!

16
20
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ የሚነገሩ


ሳይንስ የማያውቃቸው ሃሳቦች እና
የፈጠራ መላ ምቶች
ስለእነ ፌጦ (ሎሚ)፣ የፊት ማስክ እና ‹ ‹ የገዳም
አባቶች መድሃኒት› › ሳይንስ ምን ይላል?

<<ፌጦ፣ ነጭ ሽንኩርት እና ኮረሪማ ደባልቃችሁ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት


በፊት ብትወስዱ ከኮሮና ቫይረስ ትጠበቃላችሁ፣ ትድናላችሁ ሲሉ የገዳም
አባቶች ተናግረዋል::>> የሚል መልዕክት ከቀናት በፊት በማህበራዊ
ሚዲያ ሲሰራጭ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች እውነት ይሆን ? ብለው
ድብልቁን ወስደዋል:: ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ጨምሮ በሃይማኖታዊ
ጉዳዮች ብዙ ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች ይህን ጉዳይ አውግዘው በአባቶች
መቀለዳችሁን አቁማችሁ እጃችሁን ብቻ ታጠቡ ሲሉ ምላሽ ለመስጠት
ተገድደው ነበር፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወይም ኮቪድ -19 የተሰኘውን የመተንፈሻ አካላትን


የሚያጠቃ በሽታ በተመለከተ ሲሰራጩ የቆዩ የተሳሳቱ መረጃዎች፣
ሳይንስን ፈጽሞ የማይሸቱ ከበሽታው መዳኛና መከላከያ ምክሮች፣ የበሬ
ወለደ ዘገባዎች እና ምንጩ ይህ ነው ወይም ያ ነው የሚሉ ወለፈንዴ
መላምቶች በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ኮሮና ቫይረስ
ወረርሽኝን ለመዋጋት የሚደረገውን ጥረት እያስተጓጎሉ ካሉ ጉዳዮች
መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት እንዲሁም የሚዲያ ተቋማትና

17
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 21
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ተሰሚነታቸው ከፍ ያለ ሰዎች ይህን መሰል አመለካከትና መላምቶችን


ባገኙት አጋጣሚ በመመከት ተጠምደዋል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር)


እንዲያውም ከበሽታው ባልተናነሰ ትልቅ ፈተና የሆነው የተሳሳተው መረጃ
ወረርሽኝ ነው፣ ውጊያችን ከዚህም ጋር ነው ብለው ጉዳዩን ‹ ኢንፎዴሚክ›
ሲሉ ጠርተውታል ፡፡

ለመሆኑ በብዙ የዓለማችን ክፍሎች እየተሰሙ ያሉና ምንም አይነት


የሳይንስ መሰረት የሌላቸው ስሁት መረጃዎችና መላ ምቶች የትኞቹ
ናቸው ብለን መረጃዎችን ስናሰባስብ ተከታዮቹን በዋናነት ተመልክተናል፡፡
ከነዚህ ጠንቀቅ ይበሉ፣ ብለናል፡፡

ኮሮና በአሜሪካ ወይም ቻይና የተፈበረከ ነው?

ይህ ምናልባት በወረርሽኙ ሰሞን በሰፊው ሲናፈስ የነበረና የቻይና


ባለስልጣናት ሳይቀር በገደምዳሜ ሲናገሩት የነበረ ጉዳይ ነው፡፡ በኋላ ላይ
ወረርሽኙ ክፉኛ ካጠቃቸው አገሮች አንዷ አሜሪካ ሆና ስትገኝ ብዙዎች
ከዚህ መላ ምታቸው እየተንሸራተቱ መጥተዋል፡፡ ከዚሁ መላምት እኩል
ቫይረሱ በባዮሎጂካል ጦር መሳሪያነት በራሷ በቻይና በላቦራቶሪ ውስጥ
የተፈበረከ እና በጥንቃቄ ጉድለት አምልጦ የወጣ ሊሆን ይችላል
የሚለውንም ሃሳብ ሲሰነዝሩ የነበሩ ምዕራባውያን ሚዲያዎችም
አልጠፉም ነበር፡፡ በተለይ የመጀመሪያው የወረርሽኙ ታማሚዎች
በተመዘገቡባት የቻይናዋ ዉሃን ከተማ ከፍ ያለ ጥበቃ የሚደረግለት
የቫይረስ ምርምሮች የሚካሄዱበት የቫይሮሎጂ ላቦራቶሪ ይገኛል መባሉ
ለመላምቱ እንደማጠናከሪያ ሆኖ ሲቀርብ ነበር፡፡ አገራት ድብቅ
18
22
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የባዮሎጂካል ጦር መሳሪያዎችን ያመርታሉ የሚሉ ክሶች በተለያዩ አገራት


ቢሰሙም ይህን በሃቅ ያረጋገጠ የለም፡፡ አሁን በአሜሪካም ሆነ በቻይና
ያሉ መላምቶችን በማጦዝ የተሰማሩ ሰዎች ብዙ ቢሉም ቫይረሱ
ከሁለቱም አገራት የጤናና ወታደራዊ ሰዎች አቅም በላይ ሆኖ የብዙዎች
ህመምና ህልፈት መንስኤ ከመሆን አልተገታም፡፡ ክሶቹም ሰዎችን
የሚያዘናጉ መላምቶች ከመሆን አላለፉም፡፡

በኮሮና መያዝ ይገድላል?

በብዙ ባለሞያዎች ተደጋግሞ እየተነገረ እንዳለው የኮሮና ቫይረስ - ኮቪድ


19- የመግደል ምጣኔው በአንጻራዊነት አናሳ ነው፡፡ የአለም ጤና ድርጅት
እንደሚለው በህመሙ ከሚያዙ ሰዎች የሚሞቱት ቢበዛ ከ 2-3
በመቶዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ በተጨባጭ ብዙ ህሙማን የተመዘገቡባቸው
አገራትም ዘንድ የታየው የሟቾች መጠን ከአንድ ፐርሰንት በታች ነው፡፡
በሺዎች የሚቆጠሩ ታማሚዎች የታዩባት ቻይና ሪፖርት ባደረገችው
መሰረት 81 በመቶዎቹ ታማሚዎች ሁኔታቸው ለክፉ የሚሰጥ
አልነበረም፡፡ ገራም ኢንፌክሽን በመሆኑም በቀላሉ ታክሞ ነበር፡፡ የተቀሩት
በህክምና ክትትል እንዲሁም ፣ በታማሚዎቹ የራስ በሽታን የመከላከል
አቅም ታግዘው ጊዜ ፈጅተው መሻሻልን ያሳዩ ሲሆን፣ በሞት የተለዩት
ከሁለት በመቶ አይበልጡም፡፡

19
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 23
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የፊት ማስክና የኮሮና በሽታ

አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ የአገሪቱ ስፍራዎች እየታየ ያለው አንዱ


ጉዳይ የፊት መሸፈኛ ማስክ ተሻምቶ የመግዛት ነገር ነው፡፡በመጀመሪያ
ደረጃ የፊት መሸፈኛ (ማስክ) የሚረዳው ኢንፌክሽኑ ያለባቸው ሰዎች
በሚያስሉ እና በሚያስነጥሱ ወቅት የቫይረሱ ረቂቅ ተዋህስያን
ተፈናጥረው ወደ ሌሎች ሰዎች እንዳይሄዱ እና በሽታው እንዳይጋባ
ለመከላከል ነው፡፡ ስለሆነም በቀዳሚነት የፊት መሸፈኛው የሚጠቅመው
በበሽታው ተጠቅተው ላሉ ሰዎች ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ለህሙማኑ እንክብካቤ
የሚያደርጉ የጤና ባለሞያዎች እንዲሁም ለታማሚዎች እንክብካቤ
የሚያደርጉ የቅርብ ሰዎች ናቸው፡፡ በዚህ ላይ ብዙ ጽሁፎችን ያሰፈረው
የአሜሪካው የበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ተቋም የፊት ማስክ ከኮሮና
ይጠብቃል የሚል ሳይንሳዊ መረጃ የለም ብሏል፡፡ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ
ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ወረርሽኝ ምላሽ የሚመሩት ዶ/ር ያረጋል ፉፋ
በበኩላቸው ለባለሞያዎች የሚያስፈልጉትን ማስኮች እጥረት ከመፍጠር
ያለፈ ለበሽታው ያልተጋለጡ ጤናማ ሰዎች ማስክ የሚያደርጉበት
ምክንያት የለም የሚል ምላሽን በሚዲያዎች ወጥተው ተናግረዋል፡፡
ማስኮቹን ቅድሚያ ለጤና ባለሞያዎች ተዉላቸው፣ በአካባቢያችሁ
የታመመ ሰው ከሌለ በቀር ከጌጥነት ያለፈ ስራ የለውም ይላሉ
ባለሞያዎቹ፡፡

20
24
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ነጭ ሽንኩርት እና ሎሚ ፍቱን መድሃኒት


ነው?
<<መቼም ኢትዮጵያ ውስጥ ነጭ ሽንኩርት በመድሃኒትነት
የማይጠቀስበት በሽታ የለም፡፡>> ይላሉ የኮሮና ቫይረስና ነጭ ሽንኩርትን
ዝምድና በተመለተ ሃሳብ የጠየቅናቸው ባለሞያ፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት
ነጭ ሽንኩርት እርግጥ የጸረ - ባክቴሪያ ባህርያት እንዳሉት የሚያሳዩ
ጥናቶች አሉ፡፡ ስለሆነም ባክቴሪያ ነክ ህመሞችን ሊዋጋ ይችላል፡፡ ነገር
ግን ኮሮና በተፈጥሮው ቫይረስ ነው፣ በጸረ ባክቴሪያ መድሃኒትም ሆነ ጸረ
ባክቴሪያ ባህሪ አለው በሚባለው ነጭ ሽንኩርት አይድንም፡፡ በተመሳሳይ
ገበያው ላይ ከፍተኛ እጥረት የተፈጠረበት ምርትና በመድሃኒትነት
እየቀረበ ያለው ሎሚም በቫይረስ ገዳይነት ምንም አይነት ሚና እንደሌለው
ባለሞያዎች እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ ምናልባት ሎሚ ሊረዳ የሚችለው
የቫይታሚን ሲ ክምችት ስላለው የበሽታ መከላከል አቅምን በማገዝ በኩል
መጠነኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ በቀጥታ የጸረ ቫይረስነት
አቅም የለውም፡፡ መረርና ጎምዘዝ ያለ ነገር ሁሉ በሽታን ገዳይ ነው
የሚለው የብዙ ኢትዮጵያውያን ሃሳብን ሳይንስ መደገፊያና ማስረጃን
አላገኘለትም፡፡

በሞቃት አካባቢ ስለምንኖር ቫይረሱ


አይነካንም
ይህም በብዙ የአፍሪካ አካባቢ ያሉ ሰዎች ሃሳብ ነው፡፡ ይሁንና ቫይረሱን
ከመራባትና ከመተላለፍ ያገደው ሳይኖር በበርካታ የአፍሪካ አገራት
መሰራጨቱን ቀጥሏል፡፡ እርግጥ አንዳንድ የጉንፋን ቫይረሶች የአየር ጠባዩ

21
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 25
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ቀዝቃዛ በሚሆንበት ጊዜ የበለጠ የመራባት ጠባይን ያሳያሉ፡፡ ይሁንና


ኮሮና ተመሳሳይ ጠባይ ይኖረው እንደሆነ ሳይቲስቶች ገና አላወቁም፡፡
ቫይረሱ ብዙ ያልታወቁ ጠባዮችና ተፈጥሮ ያለው በሰዎች የበሽታ
መከላከል ስርዓትም የሚታወቅ ባለመሆኑ በሙቀት ስለመዳከሙ ወይም
እንደኢትዮጵያ ባሉ ጸሃዩ ከረር ባለባቸው አካባቢዎች የመሰራጨት መጠኑ
አናሳ ስለመሆኑ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ በዚህ ምክንያት መዘናጋትም
የተገባ እንዳልሆነ የጤና ባለስልጣናቱ እያስረዱ ይገኛሉ፡፡

ኖቭል ኮሮና ቫይረስ የሚያጠቃው


አረጋውያንን ብቻ ነው
ኖቭል ኮሮና ቫይረስ በሁሉም የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሠዎችን
እንደሚያጠቃ ተረጋግጧል፣ ይሁን እንጂ እንደማንኛውም የቫይረስ
ኢንፌክሽን ሁሉ የተወሰኑ ሠዎች በሽታው ይፀናባቸዋል፣ ህፃናት ፣
አረጋውያን ፣ በሽታ የመከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሠዎች ፣ እና
የስኳር ህመም፣ የልብ ህመም የኩላሊት መድከም፣ የጉበት ህመም፣
አስም ፣ የሳንባ ህመም እና ሌሎች የመተንፈሻ አካል ችግሮች ያለባቸው
ሠዎች ቫይረሱ በቀላሉ ህመም ሊፈጥርባቸው ይችላል፡፡ ከታመሙም
በሽታው በጣም ሊፀናባቸው ይችላል፡፡ ራሳችንንና በዙሪያችን ያሉትን
ሠዎች ከቫይረሱ ለመከላከልም ትክክለኛዎችን የመከላከያ እርምጃዎች
መውሰድ አለብን፤ ዙሪያችንንም መከታተል አለብን ፡፡

22
26
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ኖቭል ኮሮና ቫይረስን በአንቲባዮቲክስ


መከላከል ወይም ማከም ይቻላል
አንቲባዮቲክስ የሚያጠፉት ባክቴሪያን ሲሆን ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ግን
ቫይረስ ነው፡፡ ስለዚህም አንቲባዮቲክስ በኮሮና ቫይረስ ኢንፌክሽን ላይ
ምንም የሚፈይዱት ነገር የለም፡፡ ሆኖም ለኖቭል ኮሮና ቫይረስ
ኢንፌክሽን ተብለው ሆስፒታል የገቡ ሠዎች በተደራቢነት የባክቴሪያ
ኢንፌክሽንም ካለባቸው አንቲባዮቲክስ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ በአንድ ጊዜ
የባክቴሪያም የቫይረስም ኢንፌክሽን ሊከሰት ይችላል፡፡

ኮሮና ቫይረስን በአገር ባህል መድሃኒቶች


መከላከል ወይም ማከም ይቻላል
(ሆሚዮፓቲ፡- ከተለመደው የህክምና ሳይንስ የተለየ ህክምና ነው)፡፡
እስከአሁን ድረስ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ወይም ለማከም
እንደሚያስችል የተረጋገጠለት መድሃኒት የለም፡፡ ቪታሚኖችን መውሰድ
የሰውነትህን በሽታ መከላከያ ሊያዳብረው ይችላል ፣ ከቫይረሱ ግን
ሊከላከልልህ አይችልም፡፡ ፈዋሽ መድሃኒቶች ገና በጥናት ላይ ሲሆኑ
በቀጣዮቹ ጊዜያትም በሰዎች ላይ የሚደረገውን ሙከራ እየጠበቁ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅትም ብቃት ያለው የኮሮና ቫይረስ መድሃኒት ለማግኘት
ተጨማሪ ጥናትና ምርመር ያስፈልጋል፡፡

23
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 27
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ሰርጂካል ማስክ በኮሮና ቫይረስ


እንዳትያዝ ከላከልልሃል
ለአንድ ጊዜ ብቻ ተደርገው የሚጣሉ ሰርጂካል ማስኮች ከጎጂ ተዋህሲያን
የሚያደርጉት ጥበቃ አነስተኛ ነው፡፡ ምክንያቱም ከፊት ጋር የሚገጥሙ
ስላልሆኑ ጀርሞቹ በቀላሉ ሊገቡ ይችላሉ፡፡ በትክክል አለመጠቀምም
ጭምር ይሄን ችግር ያስከትላል፡፡ አብዛኞቹ አንድን ማስክ በተደጋጋሚ
ለብዙ ጊዜ ይጠቀሙበታል፣ ወይም ለአጭር ጊዜ ተጠቅመው ያወልቁትና
መልሰው ያደርጉታል ወይም ማስኩን እንደለበሱ አፋቸውን ወይም
አፍንጫቸውን ይነካካሉ፡፡ ደግሞም ማስኩን ከነካካህ በኋላ እጅህን
የማትታጠብ ወይም በጀርም መግደያ የማታፀዳ ከሆነ ጎጂ ጀርሞች
እንዲዛመቱብህ ትረዳቸዋለህ ማለት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ለአንዴ ብቻ
የሚደረግ ሰርጂካል ማስክ በአግባቡ ከተደረገ ከ40 እስከ 50 ፐርሰንት
ያህል ከቫይረሱ ይከላከላል፡፡ የበለጠ መከላከያ ለማግኘት N95 ማስኮችን
ተጠቀም፡፡ እነዚህ ማስኮች ከፊት ጋር ሙሉ በሙሉ የሚገጥሙ ሲሆኑ
አፍና አፍንጫን ሙሉ በሙሉ ያሽጉታል፡፡ ሆኖም N95 ማስኮች
የምትተነፍሰው አየር ሊያሳጡህ ስለሚችሉ ረዘም ላለ ጊዜ ልታደርጋቸው
አትችልም፡፡

ኮሮና ቫይረስ የወጣላቸው ሰዎች ዕድለኛ


ናቸው
የዛሬን አያድርገውና ከ1970ዎቹ በፊት “ፈንጣጣ ውጥቶለታል ወይም
ወጥቷላታል” ይባሉ ነበር፤ በፈንጣጣ ተይዘው የተረፉ ሰዎች፡፡ ፈንጣጣ
ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ገዳይ በሸታ ሲሆን የሚመጣውም በ ቫይረስ
ነው፡፡ ነፍሱን ይማርና በአሁኑ ወቅት በክትባት አማካኝነት ከምድረ ገፅ

24
28
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ሊጠፋ ችሏል ፣ የፈንጣጣ ቫይረስ በወቅቱም የሚታመነው አንድ ሰው


በፈንጣጣ ከተያዘና ከዳነ በድጋሜ ዳግም በፈንጣጣ በሽታ አይያዝም
የሚል እምነት ነበር፡፡ ትክክል ነው፤ በወቅቱ በፈንጣጣ ላለመያዝ
አስተማማኝ ክትባቱ በፈንጣጣ ተይዞ መትረፍ ብቻ ነበር፤ ዘመናዊ
ክትባት በመድሐኒት መልክ ሳይዘጋጅለት በፊት፡፡ ይህም የሚሆንበት
ምክንያት የሰውነት የበሽታ መከላከያ አንዴ ቫይረሱን ለመጀመሪያ ጊዜ
ካወቀው ለቫይረሱ ማጥፊያ የሚሆን ፀረ- ፈንጣጣ ፕሮቲን የሚሠራ
በመሆኑ በሌላ ጊዜ የፈንጣጣ ቫይረስ ደግሞ ወደ ሰውነት የመግባት ዕድል
ቢኖረው ቀድሞ የተሰራለት ፀረ- ፈንጣጣ ፕሮቲን ያጠፋዋልና ነው፡፡
እንዲሁም ነጭ የደም ሴሎች ካሁን ቀደም ቫይረሱ በደንብ እንዲያውቁት
አጋጣሚውን ስለፈጠረላቸው ዳግም ሲገባ ጠላት መሆኑን ያስታውሱትና
ድምጥማጡን ያጠፉታል፡፡

በአሁኑ ወቅት በኮሮና ዙሪያም የሚታመነው ይሄው ነው፡፡ አንድ ሰው


አንዴ ኮሮና ከወጣለት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በበቫይሱ ዳግም አይያዝም
የሚል አመለካከት ማለት ነው፡፡ እናም በኮሮና ቫይረስ ታሞ መዳን እንደ
ኮሮና ክትባት ይቆጠራልና ዕድለኝነት ሊመስል ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ
በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ እየወጡ ያሉ ምርምሮች እንደሚጠቁሙት ከሆነ
ቫይረሱ ለሰውነት በሽታ መከላከያ ሃይል ጥቆማ የሚሠጠውን የቫይረሱን
ውጫዊ የፕሮቲን አካል በዘር ቅይርታ አማካኝነት ሊቀይረው ይችላል
የሚል ነው፡፡ እንደዚህ ከሆነ ደግሞ የሰውነት የበሽታ መከላከያ ሃይል
በድጋሜ ቫይረሱ ራሱን ቀይሮ ከመጣ የማያውቁት በመሆኑ እንደፈለገው
እንዲባዛ፣ በሽታ እንዲያስከትል ብሎም ቢቆም ከተያዘው ሰው ወደ ሌላ
ጤነኛ ሰው መተላለፍ ሊጀምር ይችላል፡፡ ይህ ማለት ታዲያ በኮሮና
ቫይረስ የተያዘ ሰው በድጋሜ ሊያዝ ይችላል፤ አሁን ላለው ኮሮና
25
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 29
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ቫይረስም እየተሰራ ያለው ክትባት ወደ ፊት ራሡን በሚቀይረው ኮሮና


ላይሠራ ይችላል እንደማለት ነው፡፡

ኮሮና ቫይረስ የዓለማችን እጅግ አስፈሪ


ወረርሽኝ ነው
እንደተባለው ኮሮና ቫይረስ የዓለም መንግስታት ልዩ ትኩረት የሠጡት
ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ዓለማችንን በቀጣይ ጊዜያት ስጋት ላይ
የሚጥላት ዓለማቀፉ የወረርሽኝ ዓይነት ኢቦላ ሳይሆን የአዕዋፍ
ኢንፉሎዌንዛ ነው፡፡ ይህ በሽታ ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኃላ በ1918
መላምቶችም አሉ፡፡ ይሁንና እስካሁን የታወቀው እና እጅግ ጠቃሚው
መረጃ የኮሮና በሽታ በቫይረስ ምክንያት የሚመጣ እና የመተንፈሻ
አካላትን በማጥቃት ለህመምና ሞት የሚዳርግ በሽታ መሆኑ ነው:: ሁነኛ
የመከላከያ መፍትሄዎቹም አዘውትሮ እጅን በውሃና ሳሙና መታጠብ፣
ከተፋፈጉ ቦታዎች አለመገኘት እና ከሚያስሉና ሚያስነጥሱ ሰዎች በቂ
ርቀት ማበጀት እንዲሁም በአጠቃላይ ንጹህ ሆኖ መገኘት ነው፡፡ ከዚህ
ውጪ ይፋዊ መግለጫዎችን ከጤና ሚኒስቴርና ተመሳሳይ ተቋማት
እንዲሁም ተዓማኒ የመረጃ ምንጮች ብቻ በመውሰድ ራስን ማስታጠቅና
መምራት ወረርሽኙን ለማሸነፍ፣ በጤናም ለመሰንበት ያግዛል፡፡ ሁሌም
ደጋግመን ጠያቂ ከሆንን መላ ምቶቹን ማክሸፍ ይቻላል፡፡

26
30
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የኮሮና ቫይረስ መፃኢ ገፅታ


ከቀላል እስከ አስደንጋጭ፣ ከጤና እስከ ፖለቲካ!!
ኮሮና ቫይረስ በአሁኑ ወቅት በአለማችን ውስጥ ባሉ ሃገሮች ውስጥ
በመዛመት ላይ ያለ ወረርሽኝ ሲሆን ወረርሽኙን አስፈሪ ያደረገው
እንደ አብዛኞቹ በቫይረስ የተነሳ የሚመጡ ህመሞች ሁሉ ፈዋሽ
መድኒት የሌለው መሆኑ ነው፡፡ በሽታው በአጭር ጊዜ እንዲሰራጭ
ያደረገው ደግሞ በቀላሉ በትንፋሽና በንክኪ የሚተላለፍ መሆኑ
አደገኛነቱ የላቀ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ከሠዎች ጋር በቅርበት
በማውራት እና በእጅ በመጨባበጥ እንዲሁም ሠዎች የነኩትን ነገር
በመንካትም በቀላሉ ሊተላለፍ ይችላል፡፡

ቫይረሱ በዋነኛነት ሳንባን ፣ ልብንና ኩላሊትን ያጠቃል፡፡ የሳንባ አየር


አስተላላፊ ህዋሳትን በማሳበጥና ሳንባ ሙሉ በሙሉ ሥራውን
እንዳይሠራ በማድረግ የመተንፈስ ስርአትን የሚያስቆም ሲሆን
ኩላሊትንም ደምን የማጣራት ተግባሩን እንዳይሠራ በመከላከል
ያዳክመዋል፡፡ በእነዚህ ባህሪያቱ የተነሳ በሽታው ገዳይ ሊሆን ችሏል፡፡

በርካታ ተላላፊና ገዳይ ቫይረሶች እንደ ስጋት የማይታዩት የመከላከያ


ክትባት ስላላቸው ነው፡፡ ወይም ደግሞ የሠውነታችን መከላከያ ሃይል
በቂ ምላሽ ይሠጣቸዋል፡፡ በወረርሽኝ መልክ ሲከሰቱም ወዲያውኑ
የመከላከያው ክትባት ለህዝብ ስለሚራጭ በአጭር ጊዜ ለመቆጣጠር
ይቻላል፡፡ ኮሮና ቫይረስ ግን እስከአሁን ድረስ ክትባት አልተገኘለትም፡፡
ቫይረሱ ነባር ቢሆንም አሁን ግን ራሱን ቀይሮ የመጣ በመሆኑ ነው፡፡

ዶ/ር አቡሽ አያሌው 31


27

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ቶሎ በምርመራ አለመታወቁ ሌላኛው

አደገኛነቱ
አብዛኛዎቹ ሠዎች የበሽታውን ምልክት ሲያዩ ነው ለመታከም ወደ
ህክምና ተቋማት የሚሄዱት፡፡ ይሁንና ቫይረሱ ምልክቶችን
እስከሚያሳይ ድረስ የቀናትን ጊዜ ያስጠብቃል፡፡ በነዚህ ቀናት ውስጥም
በሽተኛው በርካታ ሠዎችን ሊበክል ይችላል ማለት ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሱ ሁኔታዎች አንድ ላይ ሲደመሩ በሽታውን በጣም


አስጊ ሊያደርጉት ቢችሉም ይህ ስጋት በሰዎች ስነልቦና ላይ
የሚፈጥረው ፍርሃት በጣም የተጋነነ ይሆናል፡፡

እየፈጠረ ያለው የኢኮኖሚ ቀውስ

በሽታው በጤና ላይ ከሚያስከትለው ችግር ባልተናነሰ መልኩ ከፍተኛ


የኢኮኖሚ ቀውስ በሌሎች አገሮችም ሆነ በሃገራችን ላይ ያስከትላል፡፡
በአገራችን ከበሽታው በፊትም ከፍተኛ የሆነ የሥራ አጥነት ችግር
እንዳለ ይታወቃል፡፡ በወረርሽኙ የተነሳ ድርጅቶች ገቢያቸው
ስለሚቀንስ ወይም ስለሚቋረጥ ሠራተኞቻቸውን ከሥራ ያሰናብታሉ፡፡

ወረርሽኙ ሁሉንም የንግድ ድርጅቶች የሚጎዳ ቢሆንም በተለይም


አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች የገንዘብ አቅማቸው አነስተኛ ስለሆነ
ከመጎዳትም አልፈው ይከስራሉ፡፡

በርካታ ሰዎች ቤት የሚገዙት ወይም ድርጅታቸውን የሚያቁቁሙትና


የሚያስፋፉት ከባንክ በመበደር መሆኑ የተለመደ አሠራር ነው፡፡
32 ዶ/ር አቡሽ አያሌው
28

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ሆኖም ወረርሸኙ የገቢ መቀነስን ማስከተሉ እዳቸውን መክፈል


እንዳይችሉ በማድረግ በመያዣነት ያስያዙትን ንብረት እንዲያጡ
ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡

የመሠረታዊ ፍጆታ እቃዎች ዋጋ መጨመሩ የኑሮ ውድነትን በጣም


ይጨምረዋል፡፡ አሁን ካለበት 20 በመቶም በጣም ሊያሻቅብ ይችላል፡፡
ቫይረሱ በአጭር ጊዜ መፍትሄ ካልተገኘለት በስተቀር የአገሪቱን
ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳዋል፡፡ የአገሪቱ ኢኮኖሚ አሁን ላይ
ራሱ የተቀዛቀዘ ሲሆን በዚህ ላይ ወረርሽኙ ሲጨመርበት ተፅዕኖውን
በጣም የጎላ ያደርገዋል፡፡

ሠዎች ከሥራ መፈናቀላቸው ፣ የእቃዎች ዋጋ መጨመሩ ፣ በርካታ


ድርጅቶች መክሰራቸው የብዙሃኑን ገቢ የማግኘት አቅም ስለሚጎዳው
የድህነቱ ቁጥር በጣም ይጨምራል፡፡

ሠራተኞች ወደ ሥራ የማይገቡ ከሆነ የእቃ አቅራቢ ድርጅቶች


ለአምራቾችም ሆነ ለችርቻሮ ሱቆች ምርቶችን አያቀርቡም፡፡ ይህም
ከባድ የእቃዎች እጥረትን ያስከትለል፡፡ በተመሣሣይ መልኩም
ሸማቾች ከቤት የማይወጡ ከሆነ አምራች ድርጅቶችና ቸርቻሮዎች
የያዙት ምርት አይሸጥላቸውም፡፡

የችግሩ መጠን እየጨመረ በሄደ ቁጥር ሠዎች በወደፊቱ ላይ ተስፋ


ስለማይኖራቸው ገንዘባቸውን ለማውጣት አይፈልጉም፡፡ በዚህ
የተነሳም ኢንቨስትመንት ይቀንሳል፡፡ የተለያዩ ምርትና አገልግሎቶችን
እንደወትሮው አይሸምቱም፡፡

ዶ/ር አቡሽ አያሌው 33


29

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

በወረርሽኙ የተነሳ ሠዎች ከቤታቸው መውጣት ባይቻላቸውና


መሥሪያ ቤቶች ሁሉ ከተዘጉ ለአንድ ቀን እንኳን መታገስ
የማይችሉትና ይበልጥ የሚጎዱት ደግሞ በእለታዊ ገቢ ላይ
የተንተራሰ ኑሮ የሚመሩት ሠዎች ናቸው፡፡ ወይም ተቀማጭ ገንዘብ
የሌላቸው ናቸው፡፡

በወረርሽኙ የተነሳ የምርቶች እጥረት ይከሰታል፣ በዚህ የተነሳ ሠዎች


አስቀድመው በተለይም የመሠረታዊ ሸቀጣሸቀጥ እቃዎችን ገዝተው
ቤታቸው ውስጥ ማከማቸት ስለሚፈልጉና ነጋዴዎችም በአጋጣሚው
ለመጠቀም ስለሚፈልጉና ዋጋ ስለሚጨምሩ ከዚህ ጋር ተያይዞ የዋጋ
ንረት ይከሰታል፡፡

ወረርሽኙ ኩባንያዎችን ለኪሳራ እንደሚዳርጋቸው አስቀድሞ


ስለሚተነበይ በስቶክ ማርኬት ገበያው ላይ የስቶኮች ዋጋ በጣም
ይወርዳል ፣ ገዢም ላያገኙ ይችላሉ፡፡

የውጭ አገር ደንበኞቻችን በበሽታው ስለተጠቁ ወደ ውጭ አገር


የሚላኩ እቃዎች ፈላጊያቸው ይቀንሳል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከሃገር
ውስጥም ወደ ውጪ ሃገር የሚላኩ እቃዎች አቅርቦት ስለሚቀንስ
የውጪ ምንዛሬ ቀውስ ይፈጥራል፡፡

አገራችን ወደ ውጪ የምትለካቸውን ምርቶች በዋናነት የሚገዙት


የእውሮፓ አገሮች ናቸው፡፡ አውሮፓ ውስጥ ኢኮኖሚው ከተዳከመ ደግሞ
አገራችን ውስጥ ከባድ የውጪ ምንዛሬ እጥረት ይከሰታል፡፡

30
34 ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ሌሎች የገንዘብ አይነቶች ዋጋቸው በጣም የሚቀንስ ሲሆን ይህም


የዶላርን ዋጋ ከፍ ያደርገዋል፡፡ ይህ ደግሞ ጥሬ እቃ በብዛት የሚልኩ
አገሮችን ይጎዳቸዋል፡፡

አንደ ኢትዮጵያ የመሳሰሉ ከባድ እዳ ያለባቸው አገሮች የሃገር ውስጥም


ሆነ የውጪ እዳቸው የበለጠ ይከማችባቸዋል፡፡

መንግስት በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተጨማሪ በጀት መመደብ


ሊያስፈልገው ነው፡፡ የገንዘቡ መጠንም በርካታ ሚሊዮኖች ስለሚሆን
ኢኮኖሚውን በጣም ይጎዳዋል፡፡

ሠራተኞች ከሥራ እንዳይቀሩና የመግዛት አቅማቸውን በመደጎም


ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት መንግስት የገቢ ግብራቸውን ሊቀንስላቸው
ይችላል፡፡ ይህም ማድረጉም ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንዲያወጣ
ያደርገዋል፡፡

እየፈጠረ ያለው ማህበራዊ ቀውስ!!

እርስ በእርስ ተቀራርቦ ማውራትና መነካካት ወረርሽኙን ከመዛመት አንፃር


በተለይም በአብሮነት ላይ የተመሠረተውን ማህበራዊ ህይወታችንን በጣም
ይጎዳዋል፡፡

ሠዎች በሽታውን ፍራቻ ራሳቸውን ማግለላቸው ብቻ ሳይሆን


በሽታው ካለባቸው ሠዎች ሠው ጋር መቀራረረብ አለመቻላቸው የከፋ
የመገለል ችግርን ይፈጥራል፡፡

31
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 35
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

አብዛኛው ህዝብ ከገቢው አንፃር በትራስፖርት የሚጠቀመው እንደ


አውቶቡስ ፣ ባቡርና ታክሲ የመሣሠሉትን የህዝብ ማጓጓዣዎችን
ሲሆን በወረርሽኙ ሳቢያ እነዚህ ማጓጓዣዎች ከተቋረጡ ከባድ
ማህበራዊ ቀውስ ይከሰታል፡፡

አንድ የቤተሰብ አባል በበሽታው ከተያዘ በሌሎች አባላቶች ላይ


በሽታውን አስተላልፎባቸዋል ተብሎ ስለሚታሰብ ማህበራዊ መገለል
ሊደርስባቸው ይችላል፡፡

አኗኗራችን የተፋፈነ መሆኑና የንፅህና አጠባበቅ ባህላችን እጅግ በጣም


ደካማ መሆኑ ወረርሽኙን ለመከላከል በጣም አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡

በበሽታው የተያዙና የተጠረጠሩ ሠዎች ተገልለው ወይም ካምፕ


ውስጥ ሲቀመጡ አስፈላጊው እንክብካቤ ላይደረግላቸው ስለሚችል
ህይወታቸው ከእስራት ያልተለየ ሊሆን ይችላል፡፡

በወረርሽኙ የመዛመት ፍራቻ የተነሳ ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ


ሊከለከሉ ስለሚችል ይህም ብዙዎችን ለብቸኝነት ሊዳርጋቸው
ይችላል፡፡

ሥነልቦናዊ ተፅዕኖው!!

የቫይረሱ አደገኝነት፤ ተዛማችነቱና መፍትሄ አልባነቱ ሠዎችን በጣም


ስለሚረብሻቸውና ስለሚያስፈራቸው ይሄን ተከትሎ የሚመጣው
ስነልቦናዊ ቀውስ ቀላል አይደለም፡፡

36 ዶ/ር አቡሽ አያሌው

32

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ኤምሬትስ በዋናነት የገቢ ምንጯ ነዳጅ ወደ ውጪ መላክ ሲሆን የነዳጅ


ዋጋ ግን አሁን ካለበት በበርሜል 60 ዶላር ወደ 40 ዶላር ይቀንሳል
የሚል ስጋት አለ፡፡

ሌላኛዋ የነዳጅ ጥገኛ አገር ኦማንም ከነዳጅ 53 ፐርሰንት የሚሆነውን


የምትልከው ኮሮና ቫይረስ በብዛት ወዳለባቸው አገሮች ነው፡፡ በእነዚህ
አገራት ውስጥ ነዳጅ ዘይት ተፈላጊነቱ ከቀነሰ ኢኮኖሚዋ በጣም ይጎዳል፡፡

ሳውዲ አረቢያም ኢኮኖሚዋ በነዳጅ ዘይት ላይ ጥገኛ ነው፡፡ ይህች አገር


ከቱሪዝምም ጥሩ ገቢ የምታገኝ ሲሆን በየዓመቱ ከ25 ሚሊዮን ያላነሰ
ቱሪስት ይጎበኛታል፡፡ ብዙዎች ጎብኚዎች ወደ ሳውዲ የሚሄዱትም
ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ መልኩ ከቱሪስት
የምታገኘው ገቢም በላቀ ሁኔታ ሊጎዳ የሚችል ሲሆን በሚቀጥለው
ሐምሌ ላይ የሚከናወነው የሃጂ ኡምራ ጉዞም ሊቀር ይችላል፡፡

እንደ ሩሲያ፣ የሰሜን አፍሪካ አገሮች፣ ናይጄሪያ እና አንጎላንም


የመሳሰሉት አገሮችም ኢኮኖሚያቸውን በከፍተኛ ሁኔታ በነዳጅ የሚደጎሙ
ሲሆን የነዳጅ ዋጋ ማሽቆልቆል ኢኮኖሚያቸውን ያውከዋል፡፡

ይበልጥ የሚጎዱ የስራ መስኮች

ሬስቶራንቶች ሰው የሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች በመሆናቸውና ቫይረሱ


በምግብ ንኪኪ ሊተላለፍ ስለሚችል ሰዎች ወደ ሬስቶራንት ላይሄዱ
ይችላሉ፡፡

37
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 37
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ወረርሽኙ ከኢኮኖሚው አኳያ የሚያመጣው የእቃዎች እጥረትና የኑሮ


ውድነት ብዙዎችን ኑሯቸውን ጭንቀት የበዛበት እንዲሆን
ያደርገዋል፡፡

ከንግድ ሥራ መስተጓጎል ጋር ተያይዞ ሊፈጠር ይችላል ተብሎ


የሚጠበቀው ኪሳራም የብዙዎችን ነጋዴዎች ህይወት በስጋት የተሞላ
ያደርገዋል፡፡

ቫይረሱ ገዳይነቱና መፍትሄ አልባነቱ በበሽታው የተያዘውን ሠው


ለአካላዊ ችግር ብቻ ሳይሆን ለከባድ ስነልቦናዊ ጭንቀትም ጭምር
ነው የሚዳርገው፡፡

አጠቃላይ ኢኮኖሚው ላይ የሚደርሰው ቀውስ ሁሉንም የህብረተሰብ


ክፍል የሚነካ ነው፡፡ ይሄን ተከትሎም በርካቶቹን ለድብርትና ተስፋ
ቢስነት ሊዳርገው ይችላል፡፡

በጤና መሠረተ ልማት ላይ የሚያደርሰው


ጫና!!

ወረርሽኙ በጣም እየተስፋፋ ሲሄድ በበርካታ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች


በበሽታው ይያዛሉ፡፡ በተለይም ለበሽታው በጣም አጋላጭ በሆነው
በሃገራችን ኑሮ ውስጥ ቫይረሱ ቶሎ መፍትሄ ካልተገኘለት ይሄ የማይቀር
ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ወቅት በርካታ ሠዎችን ማከም አስፈላጊ ይሆናል፡፡
የሃገራችን ተጨባጭ የጤና መሠረተ ልማት ደግሞ ለዚህ የሚፈቅድ
አይደለም፡፡

33
38 ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ህሙማን ከበሽታው እንዲያገግሙ ሆስፒታሎች የተሟላ የመድሃኒት


አቅርቦት ያስፈልጋቸዋል፡፡ የበሽታው ከሠው ወደ ሠው መተላለፍን
ለመገደብም የፊት ማስክ ያስፈልጋል፡፡ ታዲያ ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ
በሚከሰተው የእቃዎች አቅርቦት እጥረት የተነሳ መድሃኒቶችና የፊት
ማስክ በከፍተኛ ሁኔታ እጥረት ሊከሰት እና ዋጋቸውም ሊወደድ
ይችላል፡፡

በተጨማሪም ከታካሚዎች ቁጥር አንፃር ሲታይ የአምቡላንሶች ቁጥር


በጣም አነስተኛ ስለሚሆንና የሠራተኞችም እጥረት ሊኖር ስለሚችል
ህክምናው በቶሎ በፍጥነት ላይገኝ ይችላል፡፡

የህክምናው ቀዳሚ ምዕራፍ ቫይረሱ ያለበትን ከሌለበት ሠው መለየቱ


ሲሆን ለዚህ ደግሞ የተቀላጠፈ ምርመራ የሚያስፈልግ ቢሆንም ከምርት
ማነስና ከፍላጎት መብዛት የተነሳ የምርመራ ኪት (መሣሪያዎች) እጥረት
ሊያጋጥም ይችላል፡፡

በሽታው ከሚታከምባቸው መሣሪያዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው


ሬስፓይሬተር (ሠው ሠራሽ ማስተንፈሻ) ሲሆን ከበሽተኛው ቁጥርና
ከአቅርቦቱ ማነስ አኳያ አጥረት ሊከሰት ይችላል፡፡

ፖለቲካዊ ተፅዕኖው
በአገራችን በአሁኑ ወቅት የኢኮኖሚው መቀዝቀዝ ፣ የሥራ አጥ
መብዛትና የኑሮ መወደድ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ቫይረሱ ስርጭቱን አሁን
ባለበት ሁኔታ ከቀጠለ እነዚህ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ከመጠን በላይ

34
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 39
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ጎልተው ስለሚወጡ ወደ ከባድ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት መልካቸውን


ይቀይራሉ፡፡

አሁንም ቢሆን ሃገራችን ውስጥ በየቦታው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እንዳለ


ይታወቃል፣ ከዚህ ላይ ወረርሽኙ የሚያስከትለው ጣጣ ሲታከልበት
አለመረጋጋቱን መንግስት ሊቆጣጠረው የማይችለው ሁኔታ ላይ ሊደርስ
ይችላል፡፡ ወረርሽኙ በርካታ ወጣቶችን ከሥራ እንደሚያፈናቅል
ይጠበቃል፡፡ ወጣቱን ወደ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴና ወደ አመጽ ከሚመሩት
ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል አንዱ ደግሞ ሥራ አጥነት በመሆኑ ይህን
መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የተለያዩ የሃገር ውስጥና የውጪ ጠላቶች
ለፖለቲካዊ አለመረጋጋት ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡

ስለ በሽታው ትክክለኛ መረጃ አለመኖር

በአሁኑ ወቅት ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም በርካታ ሰዎች የተለያዩ


መረጃዎችን ያሠራጫሉ፡፡ የኮሮና ቫይረስም አዲስና አስጊ ወረርሽኝ
ከመሆኑ አንጻር ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚወጡ መረጃዎች በቀላሉ
ተቀባይነት ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ መረጃዎቹም በባህሪያቸው የተለያዩ
መሆናቸው የትኛው ትክክል እንደሆነ ለማወቅ አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡

ቫይረሱ በወረርሽኝ መልክ ሲከሰት ያሁኑ አዲስ በመሆኑ በዙ ጥናቶችና


ምርምሮች አልተደረጉበትም፡፡ በዚህም የተነሳ ሐኪሞቹም ሆነ የመድሃኒት
ቀማሚዎች ስለ በሽታው የተሟላ መረጃ ገና የላቸውም፡፡ ይህም
የመረጃውን ችግር ይበልጥ ያባብሰዋል፡፡

35
40 ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የገጠሩ ማህበረሰብ ከጤና ማዕከላት የራቀ በመሆኑና አኗኗሩም በድህነትና


በኋላቀርነት በመሆኑ ለቫይረሱ ስርጭት ግንባር ቀደም ተጋላጭ
ያደርገዋል፡፡ በዚህ ላይ የገጠሩ ህዝብ ከሚዲያ የራቀ መሆኑ ስለ በሽታው
አስፈላጊውን መረጃ እንዳያገኝ በማድረግ የሚፈጠረውን ችግር የባሰ
ያወሳስበዋል፡፡

ጦርነት ከፈታው ወሬ የፈታው እንደሚባለው ሁሉ የቫይረሱ በቀላሉ


ተላላፊነት፣ ገዳይነትና መድሃኒት አልባ መሆኑ በሰዎች ዘንድ
የሚፈጠረው ስሜት ቫይረሱ ከሚፈጥረው ይልቅ የከፋ አደጋ ሊያመጣ
ይችላል፡፡

ይበልጥ የሚጎዱ ሃገራት

በወረርሽኙ የተነሳ ሰዎች እንቅስቃሴያቸውን ይቀንሳሉ ወይም ይገድባሉ፡፡


በዚህ ምክንያትም ትራንስፖርት የሚጠቀም ሰው ብዛት ስለሚቀንስ ከዚህ
ጋር ተያይዞ የነዳጅ ዘይት ተፈላጊነት ይቀንሳል፡፡

በነዳጅ ዘይት ዋጋ መቀነስ ይበልጥ የሚጎዱት አብዛኛው ኢኮኖሚያቸው


በነዳጅ ሽያጭ ላይ ብቻ የተመሠረቱ አገሮች ናቸው፡፡

የሰዎች ጉዞ ማቆምም ኢኮኖሚያቸው በቱሪዝም ላይ የተመሠረተ አገሮችን


ይጎዳል፡፡ ለምሳሌ ዱባይ በየዓመቱ 17 ሚሊየን ቱሪስት የሚጎበኛት ሲሆን
በሚቀጥለው ጁላይ 2020ዓ.ም. በምታዘጋጀው ኤክስፖ ላይ 25 ሚሊዮን
ሰው ይጎበኛታል ተብሎ ይጠበቅ ነበር፡፡ በቫይረሱ የተነሳም ይህ ኤክሲፖ
ሊዘጋ ይችላል፡፡

36
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 41
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ኤምሬትስ በዋናነት የገቢ ምንጯ ነዳጅ ወደ ውጪ መላክ ሲሆን የነዳጅ


ዋጋ ግን አሁን ካለበት በበርሜል 60 ዶላር ወደ 40 ዶላር ይቀንሳል
የሚል ስጋት አለ፡፡

ሌላኛዋ የነዳጅ ጥገኛ አገር ኦማንም ከነዳጅ 53 ፐርሰንት የሚሆነውን


የምትልከው ኮሮና ቫይረስ በብዛት ወዳለባቸው አገሮች ነው፡፡ በእነዚህ
አገራት ውስጥ ነዳጅ ዘይት ተፈላጊነቱ ከቀነሰ ኢኮኖሚዋ በጣም ይጎዳል፡፡

ሳውዲ አረቢያም ኢኮኖሚዋ በነዳጅ ዘይት ላይ ጥገኛ ነው፡፡ ይህች አገር


ከቱሪዝምም ጥሩ ገቢ የምታገኝ ሲሆን በየዓመቱ ከ25 ሚሊዮን ያላነሰ
ቱሪስት ይጎበኛታል፡፡ ብዙዎች ጎብኚዎች ወደ ሳውዲ የሚሄዱትም
ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ መልኩ ከቱሪስት
የምታገኘው ገቢም በላቀ ሁኔታ ሊጎዳ የሚችል ሲሆን በሚቀጥለው
ሐምሌ ላይ የሚከናወነው የሃጂ ኡምራ ጉዞም ሊቀር ይችላል፡፡

እንደ ሩሲያ፣ የሰሜን አፍሪካ አገሮች፣ ናይጄሪያ እና አንጎላንም


የመሳሰሉት አገሮችም ኢኮኖሚያቸውን በከፍተኛ ሁኔታ በነዳጅ የሚደጎሙ
ሲሆን የነዳጅ ዋጋ ማሽቆልቆል ኢኮኖሚያቸውን ያውከዋል፡፡

ይበልጥ የሚጎዱ የስራ መስኮች

ሬስቶራንቶች ሰው የሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች በመሆናቸውና ቫይረሱ


በምግብ ንኪኪ ሊተላለፍ ስለሚችል ሰዎች ወደ ሬስቶራንት ላይሄዱ
ይችላሉ፡፡

37
42
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

እንደ አውቶብስ፣ ባቡር፣ አውሮፕላን በመሳሰሉት መጓጓዣዎች ውስጥ


ቫይረሱ በቀላሉ ይዛመታል፡፡ የቫይረሱ ሥርጭት እየጨመረ ሲሄድ
በሁሉም አገሮች ውስጥ ስለሚከሰት በእነዚህ ሁለት ምክንያቶች የተነሳ
ሰዎች ጉዞዎችን ለማድረግ ስለማይፈልጉ ሰዎችን በማጓጓዝ ሥራ ላይ
የተሰማሩ ድርጅቶች በጣም ይጎዳሉ፡፡

ከጉዞዎች ጋር በተያያዘ ሁኔታ የቱሪዝም ክፍለ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ


ይቀዛቀዛል፡፡ ወረርሽኙ የመዝናኛውን ኢንዱስትሪም በጣም ይጎዳዋል፡፡
በቫይረሱ ፍራቻ የተነሳ ሰዎች ተሰብስበው እስፖርታዊ ጨዋታዎችን
ማየት አይችሉም፡፡ ካሲኖዎች፣ ፓርኮች፣ ሲኒማ ቤቶች፣ የምሽት ቤት
መዝናኛዎች፤ ቲአትር ቤቶች እና ኮንሰርቶች ሰዎች በብዛት
የሚሰበሰቡባቸው ስፍራዎች ከመሆናቸው አንጻርም በወረርሽኙ የተነሳ
እነኚህ የመዝናኛ ፕሮግራሞች ይሰረዛሉ፡፡

ትምህርት ቤቶች፣ የስልጠና ቦታዎችና ኮንፍረንሶችም ሰዎች


የሚሰበሰቡባቸው ሥፍራዎች በመሆናቸውና ለቫይረሱ ሥርጭት
አስተዋዕኦ ስለሚኖራቸው ይዘጋሉ፡፡

እንደዚህ ባሉ ወረርሽኞች ወቅት ሰዎች የሚሸምቱት ለመሠረታዊ ኑሮ


የሚሆን ምርቶችን ብቻ ነው፡፡ ሌሎች ምርቶች ፈላጊ ስለማይኖራቸው
በርካታ የተለያዩ እቃዎችን የሚያመርተው የማኑፋክቸሪንግ ክፍለ
ኢኮኖሚው በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳል፡፡

38
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 43
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የ2019 ኖቭል ኮሮና ቫይረስ መነሻ


ቻይና ውስጥ በዲሴምበር 30/2019 እ.ኤ.አ ለመጀመሪያ ጊዜ ውሃን ግዛት
ውስጥ የታየው ቫይረስ ቀድሞ እንስሶችን ብቻ ያጠቃ የነበረና ራሱን
ሠውን ወደማጥቃቱ የቀየረ ስለነበር ነው የውሃን ቫይረስ የ2019 ኖቭል
ኮሮና ቫይረስ የተባለው፡፡ ኖቭል ማለት አዲስ ማለት ነው፡፡ ይህ ስያሜው
ጊዜያዊ ብቻ ሲሆን አለማቀፉ የቫይረሶች ስያሜ ኮሚቴ በቅርቡ ቋሚ
ስያሜውን ይወሰናል፡፡

ስለቫይረሱ አጀማመር የተሰጠው መላምትም የቫይረሱ ተሸካሚዎች


ከሆኑት እንሰሳዎች (የሌሊት ወፍ ፣ ድመት ፣ ከብት ፣ ግመል ፣ ወይም
እባብ) አፈጣጠሩን በመቀየር ከእንስሳቱ ጋር ቀጥታ ንክኪ ወደነበራቸው
ሰዎች ተዛመተ የሚለው ነው፡፡
ቫይረሱ አንዴ የሠው ልጅ ህዋሳት ውስጥ ከገባም ራሱን በማባዛትና
ኢንፌክሽን በማምጣት የበሽታውን ምልክቶች ያሳያል፡፡
እስከአሁን ድረስ የወረርሽኙ ምንጭ በትክክል አልታወቀም፡፡ ቫይረሱ
የጤናና የደህንነት ደንቦችን ካላከበረ የውሃን የባህር ምግቦችና የእንስሳት
ገበያ ጋር የተገናኘ ነው የሚል እምነት አለ፡፡ ይህ የውሃን ገበያ ወዲያውኑ
ተዘግቷል፡፡

39
44
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ስርጭት
ወደ እንሰሶቹ ገበያ ያልደረሱም ሠዎች መታመም ሲጀምሩ ቫይረሱ
ከሠው ወደ ሠው እንደሚዛመት ተረጋገጠ፡፡ ልክ እንደ ጉንፋን ሁሉ
ቫይረሱ በአየር ውስጥ ባሉ ብናኞች ፣ በእቃዎች ላይ ባሉ ብናኞች እና
ከታመሙ ሠዎች ጋር በመቀራረብ ይዛመታል፡፡
ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ከሠው ወደ ሠው እንደሚተላለፍ ከተረጋገጠበት ጊዜ
አንስቶ የውሃን ግዛት ከሌሎች አካባቢዎች ጋር እንዳይገናኙ (ኳራንቲን)
ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ቫይረሱ የቻይናን ድንበሮች አልፎ ለመዛመት
ችሏል፡፡

የኮሮና ቫይረስ በሽታ እንዴት ነው


ሠውነታችንን የሚያጠቃው?

መጀመሪያ ቫይረሱ በአፍንጫ፣ በአፍ ወይም በአይን ወደ መተንፈሻ


አካላት ከገባ በኋላ በመተንፈሻ አካል ላይ ካሉ ህዋሶች ጋር ይጣበቃል፡፡
ከዛም ወደ ህዋሱ ውስጥ ክፍል በመግባት የቫይረሱ አካል የሆነውን
ፕሮቲን/viral RNA/ ተብሎ የሚጠራውን ወደ ተጠቂው ህዋስ ይለቃል፡፡
ይሄም ህዋሱ በቫይረሱ እንዲመረዝ ያደርገዋል፡፡ የተመረዘውም ህዋስ
የቫይረሱን ፕሮቲን /RNA/ ያነበዋል ፤ ይህም የሰውነታችን የመከላከያ
ስርአት ሰውነታችን በሌላ የውጪ ሀይል አካል መወረሩን እንዲያውቅ
መልእክት ይሆነዋል፡፡ የመከላከያ ስርኣቱም ከደረሰው መረጃ በመነሳት
መከላከያ የሆኑ ፕሮቲኖችንና ተከላካይ ህዋሶችን ማዘጋጀትና መከላከል
ይጀምራል፡፡ በሽታው እየቀጠለ ሲሄድና የሰውነታችን መከላከያ ሲዳከም

40
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 45
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ግን ቫይረሱ ራሱን ማራባትና ተጨማሪ ፕሮቲኖችን ማዘጋጀቱን


ይቀጥላል፡፡ አዲስ የተራቡት የቫይረሱ ህዋሶችም በመሰባሰብ ከህዋሱ
በመውጣት ወደ ሌላ የሰውነት ህዋሳት ወይም ወደሌላ ሰው ለመሄድ
ዝግጁ ይሆናሉ፡፡ ከዚያም በቫይረሱ የተያዘው ሰው በሚያስልበት ወይም
በሚያስነጥስበት ጊዜ በሚረጨው ጠብታና ብናኝ በኩል አቅራቢያ ባለ
ሰው ወይም ቁስ ላይ በማረፍ ወደ ሌላ ሰው ይተላለፋሉ ማለት ነው፡፡

የሰውነታችን መከላከያ ለቫይረሱ የሚሠጠው


ምላሽ ምን ይመስላል?

ሰውነታችን ቫይረሱን ለማጽዳት የተለያዩ መከላከያዎችን በማዘጋጀት


ጥቃት ማድረጉና መከላከሉን ይቀጥላል፡፡ በሽታው ስር እየሰደደ ሲመጣ
የመከላከያ ስርአቱም ጥቃቱን ከፍ ባለ ሁኔታ ይቀጥላል፡፡ ይህ ሁኔታም
መከላከያው ቫይረሱ ያለበትን የሰውየውን ህዋስ ጨምሮ ማጥቃት
ይጀምራል፡፡ በዚህ የተነሳም የሳንባችንን ህዋሶች ለጉዳት ያጋልጣቸዋል፡፡
ይህ ሂደትም የሳንባ መቆጣትን ወይም የሳንባ ምች/pneumonia/
ያሥከትላል፡፡ከዚህም በተጨማሪም የሳምባችን የአየር ከረጢቶች በሞቱ
ህዋሶች እና በፈሳሽ መሙላት ይጀምርና የመተንፈስ ሂደቱ መሰናክል
ይገጥመዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በቫይረሱ የተጠቃው ሰው ያተነፋፈስ
ችግር ያጋጥመዋል ፡፡ በአንዳንድ ሰዎች ላይም አጣዳፊ የሆነ የትንፋሽ
ማጠርን/acute respiratory distress syndrome(ARDS)/ ያስከትላል፡፡
ይህ ከቁጥጥር ያለፈው የመከላከያ ስርአት መመረትና ጥቃት ሳንባን
መጉዳቱ የሳንባን የንፁህ አየር የማጣራት ተግባር አስቸጋሪ ያደርገዋል ፡፡
ይህ መሆኑ ደግሞ ኦክስጅን በበቂ ሁኔታ ለሰውነታችን ክፍሎች

41
46
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

እንዳይደርስ ያደርገዋል፡፡ ሰውነታችን በቂ ኦክስጅን ካላገኘ ደግሞ ስራውን


በአግባቡ መከወን ይቸግረዋል፡፡ በዚህ ሁኔታ የኩላሊት መድከም ጉዳቶች
ይከሰታሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የመከላከያ ስርዓቱ የቫይረሱን ስርጭት
መግታት ካልቻለ በሰውነታችን ውስጥ የቫይረሱ መራባት ከፍተኛ
ይሆናል፡፡ ይህ እንግዲህ ተጨማሪ የሠውነት መቆጣት ጉዳትን
ያስከትላል፡፡ የእነዚህ ድምር ውጤቶች በቫይረሱ የተያዘውን ሰው ወደ
ሞት አንዲያመራ ሊያደርገው ይችላል፡፡

ቫይረሱ እንዴት ነው ከአንዱ ህዋስ ወደ ሌላ


ህዋስ የሚዛመተው?
አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ህዋስ ከመበታተኑና ከመሞቱ በፊት በሚሊዮን
የሚቆጠሩ በውስጡ የተራቡትን ቫይረሶች ይለቃል፡፡ የወጡት /የተለቀቁት/
ቫይረሶች ሌሎች ህዋሶችን መመረዝ ይቀጥላሉ ወይም ከሳንባ በሚወጣ
ፈሳሽ/ብናኝ/ መልክ በቫይረሱ ከተጠቃው ሰው ወደ ውጭ /አካባቢ/
ይወጣል፡፡ ቫይረሱ ከተጠቂው ሰው ከወጣ በኋላ ከሰአታት እሰክ ቀናት
ሳይሞት በግዑዛን ነገሮች ላይ በመቆየት አጋጣሚውን ሲያገኝ ወደሌላ
ሰው በመግባት መራባቱን ይቀጥላል፡፡

በቫይረሱ የሚጠቁ የሰውነት ክፍሎች የትኞቹ


ናቸው?

ቫይረሱ በዋናነት የሚያጠቃው የመተንፈሻ አካልን በተለይ ሳንባን ሲሆን


ከዚህም በተጨማሪ ልብንና ኩላሊትን እንዲሁም አልፎ አልፎ የስርዓተ
ምግብ ክፍሎችንም ያጠቃል፡፡
42
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 47
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች፤


የምርመራና የህክምና ዘዴዎች
ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ምልክቶቹን በተመለከተ የመተንፈሻ አካል ህመም
ከሚያስከትሉ ሌሎች ቫይረሶች ጋር በጣም ተመሳሳይ ነው፡፡ ህመሙም
በጣም ቀላል ከሚባለው አንስቶ በጣም ከባድ ሊሆን የሚችል ሲሆን
ሞትም ሊያስከትል ይችላል፡፡

ምልክቶች
የኖቭል ኮሮና ቫይረስ አይነተኛ ምልክቶች

• ትኩሳት
• ሳል
• የትንፋሽ እጥረት
• የጉሮሮ ቁስለት ናቸው

በአሁኑ ወቅት የሚታሰበው የበሽታው ምልክቶች የሚያታዩት ቫይረሱ


ወደ ሠውነት በገባ ከ2 እስከ 14 ቀናት ነው ተብሎ ነው፡፡ ይሁን እንጂ
ጊዜው ገና በውል አልተረጋገጠም፡፡ የቫይረስ ተሸካሚዎች ምልክቶችን
ሳያሳዩ ቫይረሱን ሊያዛምቱ ይችላል የሚል ግምት ቢኖርም ይህም
ቢሆንም ገና በውል አልተረጋገጠም፡፡

እስከአሁን ድረስ ከተረጋገጡት የቫይረሱ ህመሞች ውስጥ 20 በመቶው


በጣም ከባድ ናቸው፡፡ የቫይረሱ ኢንፌክሸን የሚያስከትላቸው ችግሮች፤
የሳንባ ምች ፣(ኒሞኒያ) ፣ ሴፕሲስ (በኢንፌክሽን ምክንያት የሚመጣና

43
48
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የሰውነት በሽታ መከላከያ ስርአት የሚፈጥረው ለህይወት አስጊ ክስተት)


፣ ሴፖቲክ ሾክ (ከፍተኛ የደም ግፊት መቀነስና የደም ህዋሳት ለውጥ) ፣
እንዲሁም በሳንባ የመተንፈሻ የአየር ከረጢቶች ውሃ መቋጠር
የሚያመጣው ከባድ የትንፋሽ እጥረት ናቸው፡፡

በህመሙ ከባድነት የተነሳ ሠውነት ከኢንፌክሽኑ ነፃ እስኪሆን ድረስ


በሽተኛው የማስተንፈሻ ማሽን እገዛ ሊያስፈልገው ይችላል፡፡ ቫይረሱ 2
በመቶ የሚሆኑትን ህሙማን ለሞት ዳርጓቸዋል፡፡

በሽታውን መለየት

ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ኢንፌክሽንን ለመለየት ለየት ያለ የላብራቶሪ


ምርመራ ያስፈልገዋል፡፡ ለምርመራ ናሙናዎች ከጉሮሮ በጥጥ ሊወስዱ
ይችላሉ ወይም ፈሳሽ ከሳንባ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ምርመራው ፒሲአር
ቴስቲንግ የሚባል ሲሆን ውጤቱን ለማግኘትም ከ24 እስከ 48 ሰአት
ይወስዳል፡፡

የፒሲአር ምርመራ የሚደረግላቸው የሚከተሉትን መመዘኛዎች ያሟሉ


ሠዎች ናቸው፤

1. ድንገት የጀመረ ትኩሳት፣ የጉሮሮ ቁስለት ፣ ሳል ወይም የትንፋሽ


እጥረት የታየባቸው ሠዎች፤
2. ምልክቶች ከመከሰታቸው ከ14 ቀናት በፊት በሚከተሉት
መንገዶች ለቫይረሱ የተጋለጡ ሠዎች

44
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 49
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

• ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ከሠው ወደ ሠው እንደሚተላለፍ


ወደተረጋገጠባቸው አገሮች የሄዱ ሠዎች (ቻይና ፣
ሆንክኮንግ ፣ ታይላንድ ፣ ጃፓን ፣ ሲንጋፖር ፣ ወዘተ)
• ከቻይና ወይም ኖቭል ኮሮና ቫይረስ በማህበረሰቡ
እንደሚተላለፍ ከተረጋገጠባቸው አካባቢዎች ቆይቶ
የተመለሰ ሠው
• ከቤት ውጪ ፣ በስራ ቦታ ወይም በቤት ውስጥ ኮሮና
ቫይረስ ካለበት ሠው ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበረው ሠው
• የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ህሙማን የነበሩበት ወይም ያሉበት
የጤና ተቋም ውስጥ ያስታምም ወይም ይሠራ የነበረ
ሠው

በቻይናዋ የሁቤይ ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ወይም በተደጋጋሚ ወደዚያው


የሚሄዱ ሠዎች ተጋላጭነታቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ ለኖቭል ኮሮና ቫይረስ
የተጋለጡ የጤና ባለሙያዎችና የጤና መኮንኖች ምንም እንኳን ተገቢውን
የመከላከያ ጥንቃቄ ቢያደርጉም በቫይረሱ የመያዝ እድላቸው ከፍ ያለ
ነው፡፡ እስካሁን ድረስም 16 የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡
የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸው የህመሙ ከሰው ሠው
የመተላለፍ ቀዳሚ ምልክቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

45
50
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የቫይረሱ ስሜቶች እና ምልክቶች


የኮቪድ - 19 ምልክቶቹ በብዛት ከጉንፋን እና ሌሎች የመተንፈሻ አካል
ኢንፌክሽኖች ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ከነዚህ የመተንፈሻ አካል ኢንፌክሽን
ምልክቶች ውስጥ በኮቪድ 19 ላይ በብዛት የሚታዩት፡

Ø ትኩሳት - 87.9 %
Ø ሳል - 67.7 %
Ø የትንፋሽ ማጠር /dyspnea 18.6 % ሲሆን ከነዚህ በተጨማሪም
Ø የራስ ምታት
Ø የጉሮሮ መከርከር
Ø የጡንቻዎች ህመም/
Ø ብርድብርድ ማለት/
Ø የአፍንጫ መታፈን
Ø አልፎ አልፎም ተቅማጥና ትውኪያ ሊታይ ይችላል፡፡

ህመሙ ብዙ ጊዜ አክታም ሆነ ንፍጥ አልባ እንደሆነ ቢታወቅም አንዳንዴ


ግን በተለይ የንፍጥ መብዛት ሊከሰት ይችላል፡፡ የጉሮሮ የመቁሰል ስሜት
እና ደም መትፋትም ሊታይ ይችላል፡፡

እነኝህ የኮቪድ 19 ምልክቶች ሰዎች ለቫይረሱ ከተጋለጡበት ጊዜ


አንስቶ ከሁለት እስከ አስራ አራት ቀናት ውስጥ ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ይህ
ማለት ግን የቫይረሱ ምልክት ለመታየት የግድ ሁለት ሳምንታትን
መጠበቅ ያስፈልጋል ማለት አይደለም፡፡ ከፊሎቹ ለኮቪድ 19 ቫይረስ
በተያዙበት ገና በሁለት ቀናቸው ጀምረው ምልክቶችን ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡
ከፊሎቹ በአስረኛው ቀናቸው ምልክት ሊታይባቸው ይችላል፡፡ ሌሎች ላይ
46
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 51
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ደግሞ እስከ 14 ቀን ሊደርስ ይችላል፡፡ ሰዎች ምልክቶችን የሚያሳዩባቸው


የቀናት ብዛት በሚከተሉት ተጽዕኖዎች ሊወሰን ይችላል፡፡

Ø የሚበክላቸው የኮቪድ 19 ቫይረስ መጠን /ብዛት /


Ø የሰዎች ዕድሜ / በእድሜ በገፉት ላይ ፈጥኖ ይታወቃል፡፡
Ø የሰዎች አጠቃላይ የጤንነት ሁኔታ/
Ø ወይም የሰዎች በሽታን የመከላከል ብቃት
Ø እና ሌሎች አካባቢያዊ ተጽዕኖዎች ናቸው፡፡

በሁሉም የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች ለህመሙ ተመሳሳይ ምላሽ


ወይም ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ፡፡ ህጻናት የተጋነነ ምላሽ ማለትም ከፍተኛ
ትኩሳት፣ ከፍትኛ የትንፋሽ ማጠር ብሎም መጨናነቅ ሊያሳዩ ሲችሉ
አዛውንቶች እና የስኳር ህሙማን ደግሞ ብዙም ምልክታቸው ሳይጋነን
ነገር ግን ውስጥ ለውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ሊጎዱ ይችላሉ፡፡ ይህም
ባላቸው በሽታን የመከላከል አቅም እና ከዚህ ጋር ተያይዞ ለኢንፌክሽን
ምላሽ የመስጠት አቅም ልዩነት የሚመጣ ነው፡፡

ኮቪድ 19 ምልክት ከጉንፋን እንዴት መለየት


እንችላለን?

ብዙ ሰዎች የዚህን ቫይረስ ምልክቶች ከጉንፋን ጋር ሲያምታቱ ይታያሉ፡፡


ነገር ግን በተለመደው የጉንፋን ህመም የሚያስለውን ወይም
የሚያነጥሰውን ሰው ሲያዩ ሰዎች መደናገጥ፣ መድሎና ማግለል ማሳየት
ተገቢ አይደለም፡፡ መጠርጠር ብልህነት ቢሆንም የበሽታውን ባህሪ ጠንቅቆ
ካለማወቅ አብዝቶ መጨነቅ እና መደናበር ብሎም ሰዎችን ማግለል የራሱ

47
52
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

አሉታዊ ተፅዕኖ አለው፡፡ ይህም ስለሆነ ሰዎች የኮቪድ 19 በሽታ ከቫይረስ


የሚለይባቸውን ዋና ዋና ምልክቶች ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ሁለቱንም
የሚያመሳስላቸውና የሚያለያያቸው ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

Ø ሳል፣
Ø የጉሮሮ ህመም
Ø አፍንጫን ማፈን
Ø ብሎም የጡንቻዎች ህመም፣

የራስ ምታት በሁለቱም ማለትም በኮቪድ 19ም ሆነ በጉንፋን ሊመጣ


የሚችል ምልክት ወይም ስሜት ነው፡፡

Ø ትኩሳት፣
Ø ቶሎቶሎ መተንፈስ/
Ø የትንፋሽ ማጠር፣
Ø ደም ማስተፋት፣
Ø ትውኪያ፣
Ø አንዳንዴም ተቅማጥ የኮቪድ 19 ብቻ ምልክቶች፣ በጉንፋን
የማይታዩ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል የጉንፋን ሳል ብዙ ጊዜ እርጥበት የበዛበት ወይም እክታ


ያለው ሲሆን የኮቪድ 19 ሳል ደግሞ ብዙ ጊዜ ደረቅ ነው፡፡

48
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 53
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ሌላው መ ለየት የሚ ያስፈልገው የኮቪድ 19 ም ልክቶችንና


በባክቴሪያ የሚ መ ጣ ው ን የሳንባ ም ች ነው ፡፡ በሁለቱም ላይ፡-

Ø ትኩሳት፣
Ø ሳል፣
Ø የራስ ምታት፣
Ø የጡንቻ ህመም፣

ወዘተ ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን በባክቴሪያ የሚመጣው የተለመደው


የሳንባ ምች ትኩሳቱ እጅግ ከፍተኛ እና የተጋነነ ነው፡፡ የሳንባ ምች ሳል
ብዙ ጊዜ እክታ ይኖረዋል፡፡ የኮቪድ 19 ሳል ግን ደረቅ ሳል ነው፡፡
የባክቴሪያ የሳንባ ምች ከፍተኛ የደረት ውጋት ሲኖረው ይህ በኮቪድ 19
ላይ የተለመደ አይደለም፡፡

49
54 ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ምልክቶች የሚቆዩበት አማካይ ጊዜ!

ሁሉም ምልክቶች አንድ ላይ ታይተው አንድ ላይ የሚጠፉ ሳይሆን


የራሳቸው መነሻ እን የሚያበቁበት ጊዜ መኖሩን ጥናቶች
ያሳያሉ፡፡ከነዚህ ውስጥ ለምሳሌ ትኩሳት ዘጊይቶ የሚከሰት ምልክት
ነው፡፡ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ህሙማን ትኩሳት ከመታየቱ
በፊት አንዳንድ የላብራቶሪ መረበሾች ሊታይባቸው ይችላል፡፡

ምልክቶቹ የሚጠፉበት ጊዜም እንዲሁ በአያሌው የሚለያይ ነው፡፡


ለምሳሌ የሚከተሉትን ማየት ይቻላል፡፡

Ø ትኩሳት ዘግይቶ ቢጀምርም በአማካይ ለ12 ቀናት ይቆያል፡፡


Ø ሳል ለረጅም ጊዜ ሊቆይ የሚችል ሲሆን ህክምናቸውን
ጨርሰው ከውጡት ውስጥ 45 በመቶ የሚሆኑት ህሙማን
ሳል አላቸው፡፡
Ø የትንፋሽ ማጠር እስከ 13 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በበሽታው
ከሞቱት ውስጥ ግን በሁሉም ላይ እስከ ዕለተ ሞታቸው
ድረስ የትንፋሽ ማጠር ታይቶባቸዋል፡፡

ዶ/ር አቡሽ አያሌው 55


50

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

አንድ ሰው በቫይረሱ ስለመያዙ


እንዴት ይታወቃል?
በላብራቶሪ ምርመራ ኮሮና ቫይረስን
የመለየት ፈተና
ከብዙ አይነት ኢንፌክሽኖች ላይ ከሚታየው በተቃራኒው ነጭ የደም
ሴሎች በኮቪድ 19 ላይ ፣ በተለይ በመጀመሪያዎቹ ቀናት ላይ ሊቀንስ
ወይም ልክ ሊሆን ይችላል፡፡ ደም የሚያረጉ የደም ሴሎች / platelets
በመጠኑ ሊቀንሱ ይችላሉ፡፡ የጉበት ኢንዛይሞች ግን ሊያሻቅቡ ይችላሉ፡፡

የሰውነት መቆጣትን የሚጠቁሙ እና የሳንባ ኦክስጅን የማጣራት ብቃትን


የሚለካ ምርመራም አስፈላጊ እና ፍንጭ የሚሰጥ ተጨማሪ ምርመራ
ነው፡፡ እነዚህ ምርመራዎች ጠቀሜታቸው ለቫይረሱ ፍንጭ ከመስጠት
የዘለለ አይደለም፡፡ በትክልል ህመሙ የኮቪድ 19 መሆኑን
አይነግሩንምነገር ግን ፍንጭ ይሰጣሉ፡፡

ሌላው እጅግ አስፈላጊ ምርመራ የደረት ሲቲ ስካን ነው፡፡ ይህ መሳሪያ


የቫይረስ ሳንባ ምችን በተሻለ ሁኔታ የሚለይ ነው፡፡ እንዲያውም
በመጀመሪያ አካባቢ ከሁሉም የምርመራ አይነቶች ፣ የቫይረሱን ዘረመል
በቀጥታ ከሚለየው real-time polymerase chain reaction (RT-
PCR)ን ጨምሮ እጅግ የተሻለ እንደሆነ ይነገርለት ነበር፡፡ በመሳሪያው
ቫይረሱ ሳንባ ላይ ያሳረፈው ጠባሳ ለማየት ተችሏል፡፡

ለኮቪድ 19 መንስኤው SARS-COV-2 የተሰኘው ቫይረስ ነው፡፡ ይህን


ቫይረስ real-time polymerase chain reaction (RT-PCR) በተሰኘው
51
56
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ምርመራ ለመለየት ይቻላል፡፡ አሁን አለም በዋናነት እየተጠቀመበት ያለው


ምርመራም ይህ ነው፡፡ ምርመራው የቫይረሱን ዘረመል በመለየት ላይ
የተመሰረተ ነው፡፡

ለዚህ ላብራቶሪ ምርመራ የሚሆን ናሙና በሚከተሉት የሰውነት ውስጥ


ፈሳሾች ላይ ሊወሰድ ይችላል፡፡

Ø ከምራቅ
Ø ከላይኛው የመተንፈሻ አካል ሙጣጭ/ ፈሳሽ፣ አክታ
Ø ከታችኛው የመተንፈሻ አካል ሙጣጭ / አክታ
Ø ከሽንት
Ø አልፍ አልፎ ከሰገራም ናሙና ሊወሰድ ይችላል፡፡
Ø ለእነኝህ ህሙማን ከኮቪድ 19 በተጨማሪ ለሌሎች የመተንፈሻ
አካል ኢንፌክሽኖችም ምርምራ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡

ለምሳሌ ኢንፍሉዌንዛ ህመም መንስኤ ለሆኑት ኢንፍሉዊንዛ ኤ፣ ቢ፣


የጉንፋን ቫይረስ / adenovirus ፣እንዲሁም የሣንባ ምች የሚያመጡ
ባክቴሪያዎች ቅድመ ምርመራ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ ምክንያቱም
የእነዚህ ኢንፌክሽኖች በተጨማሪ መኖር የህሙማንን የመታመም እና
የመሞት እድል ይወስነዋል፡፡

ሌላው ባክቴሪያን የመሳደግ ምርመራ /culture ነው፡፡ የጸረ ተህዋሲያን


መድሃኒት ከመጀመሩ በፊት ባክቴሪያን የማሳደግ ምርመራme /culture
መደረግ አለበት፡፡ ከዛ በላብራቶሪ ባክቴሪያ አድጎ ከተለየ ለዚህ የሚሆን
መድሃኒት መጀመር ይኖርበታል፡፡

52
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 57
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ለቫይረሱ ህሙማን የሚደረግ የህክምና እርዳታ

መድሃኒት፡- በተለያዩ ሀገራት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢደረግም ለቫይረሱ


እስካሁን የራሱ የሆነ የሚፈውስ መድሃኒት ሊገኝለት አልቻለም፡፡
ሙከራዎች ግን እንደቀጠሉ ናቸው፡፡

ለጊዜው ለቫይረሱ ያለው መፍትሄ መከላከል እና ተጨማሪ እግዛዎችን


መሰጠት ብቻ ነው፡፡

በመሆኑም ህክምናው መጀመር ያለበት በቸልተኝነት የራስን እገዛ ብቻ


በማስቀደም ሳይሆን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በሚያደርጉት ጥንቃቄ
ነው፡፡ በዚህም መሰረት በኮቪድ 19 ኢንፌክሽን የተያዙ ሰዎች ወዲያውኑ
ተለይተው ለብቻቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ህሙማንን ፈጥኖ ለብቻቸው
ማድረግ ሲባልም በራስ ወዳድነት ብቻ ህሙማንን ከማህበረሰብ መነጠልና
ለብቻቸው መተው ማለት እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡ መለየት ሲባል
መድሎና ማግለል ማድረስ ማለት አይደለም፡፡ ይልቅ በዚህ ሂደት ሁለቱም
ወገን ፣ ማለትም ታማሚው እና ሌላው ወገን ሁለቱም ተጠቃሚ
ይሆናሉ ማለት ነው፡፡ በቫይረሱ የተያዘው አካል ፈጥኖ እራሱን ከሌላው
ማህበረሰብ በመነጠሉ የቫይረሱን ስርጭት በአያሌው ይቀንሰዋል፡፡ ለራሱም
በተገለለበት ክፍል ውስጥ ህክምና እና ክትትል ይደረግለታል፡፡ ነገር ግን
ታማሚው ፈጽሞ መረሳት ወይም ችላ መባል የለበትም፡፡

ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ማለት፡-

በ2 ሜትር እርቀት ውስጥ ለብዙ ጊዜ አብሮ የቆየ ሰው፣ በሚያስሉበት


ወቅት በአጠገብ የነበረ ሰው፣ አካላዊ ንክኪ የነበረው ሰው ወይም
53

58 ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ተመሳሳይ እቃዎችንና አገልግሎቶችን የተጋራ ሰው ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ


መንገድ ታማሚው አገልግሎትን እስኪያገኝ ወይም ውደ ጤና ባለሙያ
እስኪደርስ ድረስ ሌሎችን ለመታደግ ወይም ቫይረሱን ላለማጋራት
የሚያደርጋቸው ጥንቃቄዎች ሲሆኑ ቀጣይ መሆን ያለበት ደግሞ ለራስ
የህክምና አገልግሎን ማግኘት ነው፡፡

ለታማሚው የሚደረግ የህክምና እርዳታምንድ


ነው?

የመጀመሪያው ነገር በባለሙያዎች የሚደረግ የታማሚዎች ልየታ


ነው፡፡ ይህ ልየታ የሚሆነው በህመሙ ጽኑነት ደረጃ ላይ ተመስርቶ
ነው፡፡ ይህ ደረጃም በዋናነት የኦክስጅን መጠንን በመለካት ፣
ቫይታል ሳይኖችን በመውሰድ እና የበሽተኛውን ሁኔታ በማየት
የሚካሄድ ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት ታካሚዎች እንደሚከተለው
ሊለዩ ይችላሉ፡፡

1. መጠነኛ ፡- የበሽታውን ምልክት የሚያሳዩ ሆነው ቫይታል


ሳይናቸው ደህና የሆነ

2. መካከለኛ፡- በደቂቃ ከ 30 በላይ የትንፋሽ መጠን ያለው እና


የኦክስጅን መጠን ከ 93በመቶ በታች የሆነ

3. ጽኑ ታማሚ ወይም ክሪቲካል፡- ትንፋሹ የደከመበት


እና ለመተንፈስ የማሽን እገዛ የሚፈልግ

54
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 59
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ከልየታ በኋላ የሚከተለው እንደየአስፈላጊነቱ በተለያዬ ደራጃ የህክምና


እገዛ መስጠት ነው፡፡ የህክምና እርዳታም እንደ ህመሙ ጽኑነት
የሚወሰን እንጂ ለሁሉም ታካሚ ተመሳሳይ አይደለም፡፡

በተለይ ህመሙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ የብዙ ባለሙያዎችን


የተቀናጀ እገዛ የሚፈልግ ይሆናል፡፡

ኮቪድ 19 እስካሁን ፈዋሽ መድሃኒት ያልተገኘለት እንደመሆኑ


አብዛኛው ህክምና የእገዛ ህክምና ነው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፡

Ø በቂ እረፍት ማድረግ
Ø ፈሳሽን በበቂው መውሰድ
Ø የስነ-ምግብ እገዛ
Ø የሰውነት ውስጥ የፈሳሽ መጠንንና ንጥረነገሮችን መከታተልና
ማስተካከል
Ø ቫይታል ሳይኖችን እና የኦክስጅን መጠንን በንቃት መከታተል
እና የመሳሰሉት ለኮቪድ 19 ታማሚዎች ከሚደረግላቸው
እርዳታዎች መካከል ናቸው፡፡
Ø ለብዙ ህሙማን እንደ ህመሙ ጽኑነት ከከፍተኛ እስከ
አነስተኛ መጠን የኦክስጅን ህክምናም ሊሰጥ ይችላል፡፡
Ø የስርአተ ትንፈሳ መድከም /respiratory failure
ለሚታይባቸው እና መጥፎ ሁኔታ ላይ ላሉ ህሙማን አስከ
በማሽን የታገዘ እስትንፋስ ያስፈልጋቸዋል፡፡
Ø በጥቂት ህሙማን ላይ የደም ግፊት መውረድ፣ አጣዳፊ
የኩላሊት መድከም / acute renal failure፣ በቫይረስ የመጣ

60 ዶ/ር አቡሽ አያሌው


55

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የልብ መጎዳት ሊከሰት ይችላል፡፡ በመሆኑም ከነኝህ ችግሮች


ጋር የሚገናኙ የላብራቶሪ ምርመራዎችን ማድረግ ብቻ
ሳይሆን ሂደታቸውን በቅርበት መከታተልme አስፈላጊነው፡፡

የጸረ- ቫይረስ ህክምና-antiviral therapy


ከእገዛ ህክምና በተጨማሪ ቻይና ውስጥ ለሁሉም የኮቪድ 19
ህሙማን የጸረ ቫይረስ ህክምና በጥቅም ላይ ውሏል፡፡ አነዚህ የጸረ
ቫይረስ መድሃኒቶች በጸረ ኤች አይ ቪ ተግባራቸው የሚታወቁ እና
ለኤች አይ ቪ ቫይረስ ህክምና የሚውሉ ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለወባ ህክምና የሚውለው ክሎሮኪን ከአዚትሮ


ማይሲን ጋር በማጣመር ቪድ 19ን በመቆጣጠሩ ረገድ የተጠና
ውጤት ተገኝቷል፡፡ መድሃኒቱ SARS-COV-2 የተሰኘውን የኮቪድ
19 አምጭ ቫይረስ እንደሚገታ ጥናቶች አሳይተዋል፡፡ በመሆኑም
ክሎሮኪን በቻይና እና በሌሎች ሀገራት ለህክምና እየዋለ ነው፡፡

የጸረ ባክቴሪያ ህክምና/ antiobiotic


treatment
በቫይረሱ የሚደርሰው ከፍተኛ የሳንባ ውድመት በላዩ ላይ ባክቴሪያ
ኢንፌክሽን እንዲፈጥር ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡ በመሆኑም የጸረ
ባክቴሪያ ህክምና አስፈላጊ መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህ የጸረ ባክቴሪያ ህክምና
የሚያስፈልገው ግን ለሁሉም የኮቪድ 19 ህሙማን ሳይሆን ይህ ህመም
እንዳለ ሆኖ በተጨማሪ የባክቴሪያ ኢንፌክሽን መኖሩ ከተረጋገጠ ብቻ
ነው፡፡

56
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 61
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

እናም የባክቴሪያ መኖሩ ከተረጋገጠ የባክቴሪያውን ዝርያ ለማወቅ


ባክቴሪያን የማሳደግ ላብራቶሪ ይላክ እና የመርፌ ጸረ ባክቴሪያ
/አንቲባዮቲክስ ህክምና ይጀመራል፡፡

የኮርቲኮስቴሮይድ ህክምና

ይህ መድሃኒት የሰውነት ውስጥ መቆጣትን /inflammation/ ለመግታት


የሚጠቅም ነው፡፡ እንደ አጠቃላይ የኮርቲኮስቴሮይድ ህክምና ለሁሉም
ለኮቪድ 19 ህሙማን አስፈላጊ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ይህ መድሃኒት
የሰውነትን በሽታን የመከላከል አቅም የሚያዳክም እንደሆነ ይታወቃል፡፡
የሰውነት በሽታን የመከላከል አቅም ከተዳከመ ደግሞ ቫይረሱ ሰውነት
ውስጥ የመቆየት እድሉ እና ወደ ባሰ ደረጃ የመሸጋገር እድሉ እየጨመረ
ይሄዳል፡፡ ከዚህ የተነሳ ለሁሉም ህሙማን ኮርቲኮስቴሮይድ ህክምና
አይመከርም፡፡

ነገር ግን ከፍተኛ የኦክስጅን መጠን መውረድ እና የትንፋሽ ማጠር


ለሚያስቸግራቸው ህሙማን የሳንባ መቆጣትን ለመግታት መድሃኒቱ
ሊታሰብ ይችላል፡፡

ከዚህ ቀጥሎ በሽታው ውጤት ወይም ታማሚው እጣ ፈንታ ምን


መሆን አለበት የሚለውን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ማንም
ቢሆን በቫይረሱ ከተያዘ በኋላ ቀጣው እጣፈንታውን ለማወቅ
ይፈልጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተጋነኑ ፍርሃቶችና ሽብሮች
የቫይረሱን ትክክለኛ የጉዳት ልክ ካለማወቅ የመነጨ ስለሚሆን ነው፡፡

57
62
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የኮቪድ 19 የህክምና ውጤት ምን


ይመስላል?
አብዛኛዎቹ ኬዞች መጠነኛ ህመም የሚያስከትሉ እና በራሳቸው የሚድኑ
ናቸው፡፡ 80 % የሚሆኑት ኬዜች ከአነስተኛ እስከ መካከለኛ ሲሆኑ
አደገኛ ደረጃ ላይ የሚደርሱት 13.8% ብቻ እንደሆኑ በቻይና ውሃን ግዛት
ውስጥ የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

ሆኖም ኮሮና ቫይረስ ገዳይ ሊባል የሚችል በሽታ ነው፡፡ ኮሮና ቫይረስ
በትኩሳት እና በሳል ይጀምራል፡፡ ይህ ማንም ሰው በተለይ በበጋ ወራት
የያጋጥመው እንደ ጉንፋን ያለ ቀላል ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ለኮሮና ቫይረስ
ሲሆን ሴሎች የተጋነነ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

ይህ የተጋነነ ምላሽ ሳንባ እና አጠቃላይ የመተንፈሻ አካል እንዲቆጣ


ያደርጋል፡፡ የኮቪድ 19 አጠቃላይ አደገኛ የህመሙ ባሕሪ የሚነሳው ከዚህ
ሁኔታው ነው፡፡ የመተንፈሻ አካላት የተጋነነ ምላሽ ወይም መቆጣት
የቫይረሱን አደገኝነት ከሌሎች ተራ ቫይረሶች ይልቅ ከፍ እንዲል
አድርጎታል፡፡

የተጋነነ ምላሽ እና መቆጣት አካላችን ስራውን እንዳይሰራ በማድረግ እሰከ


ሞት ያደርሳል፡፡ በከፍተኛ ሁኔታ የተቆጣ ሳንባ ኦክስጅንንና
ካርቦንዳይኦክሳይድን በአግባቡ ለማመላለስ አይችልም፡፡ የተቆጣ የመተንፈሻ
አካል ስለሚያብጥ ቱቦዎች ይጠባሉ፣ እስከመዘጋትም ይደርሳሉ፡፡ ከዚህ
የተነሳ ትንፋሽ አጥሮ እስከ ሞት ያደርሳል፡፡ ይህ መቆጣት ለመተንፈሻ

58

ዶ/ር አቡሽ አያሌው 63
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

አካል ብቻ የተተወ አይደለም፡፡ ኩላሊት፣ ልብ በተመሳሳይ ሊቆጣ


ይችላል፡፡

በከፍተኛ ሁኔታ የተቆጣ ኩላሊት ስራውን በአግባቡ ለማጣራት


አይችልም፡፡ ይህም አጣዳፊ የኩላሊት መድከም አስከትሎ እስከ ሞት
የሚያደርስ ችግር ያመጣል፡፡ የህጻናት ሴሎች የተጋነነ ምላሽ በመስጠት
የታወቁ ናቸው፡፡ ነገር ግን ኮቪድ 19 በህጻናት ላይ ሲበረታ አልታየም፡፡
ይህ ግራ የሚያጋባ ግኝት ነው፡፡ ሳይንቲስቶች መሆን የነበረበት ነገር
አልሆነም፣ ነገር ግን በህጻናት ላይ ስለ ቫይረሱ እስካሁን በቂ ጥናት
አላደረግንም በማለት በጥናታቸው ላይ ሪፖርት አድርገዋል፡፡ የሆነው ሆኖ
የቫይረሱ አደገኝነት የሚነሳው ሴሎች ለቫይረሱ የተጋነነ ምላሽ እንዲሰጡ
በማድረግ ነው፡፡

በአጠቃላይ የህመሙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ በእድሜ የገፉት፣


ግፊት፣ የልብ ህመም ያለባቸው፣ የኩላሊት መድከም ያለባቸው፣ የስኳር
በሽታ ያለባቸው፣ሌላ ኢንፌክሽን ያለባቸው ሰዎች በባይረሱ የመሞት
እድላቸው ከሌላው ማህበረሰብ ይልቅ የጨመረ ነው፡፡ በቻይና ውስጥ
በተደረገው ጥናት 75 በመቶ የሚሆኑት የሞት ኬዞች የተመዘገቡት
ተጨማሪ በሽታ ባላቸው ላይ ነው፡፡

በእድሜ የገፉት ሰዎች በባይረሱ የመያዝ እና ከቫይረሱ የተነሳ የመሞት


እድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ ይህ ኮቪድ 19 ስለሆነ ብቻ አይደለም፡፡ በእድሜ
የገፉት ሰዎች በየትኛውም በሽ ቢሆን በጽኑ የመታመም እና የመሞት
እድላቸው ከሌሎች ይልቅ ከፍ ያለ ነው፡፡ ይህም የሆነው በእድሜ በገፉት
ላይ በሽን የመከላከል አቅማቸው ደካማ በመሆኑ ነው፡፡

59
64
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

እናም ጥናቶች በተደጋጋሚ እንዳሳዩት እድሜ እየጨመረ በሄደ ቁጥር


በበሽታው የመሞት እድልም መጨመሩን ነው፡፡ እድሞያቸው ከ 80
በላይ በሆኑት ተጠቂዎች ላይ የመሞት እድሉ በከፍተኛ ድረጃ
የጨመረ ሲሆን እስከ 21.9 % ይደርሳል፡፡ 80 በመቶ የሚሆነውን
የሞት መጠን የያዙትም በእድሜ ከ60 በላይ የሚሆኑት አዛውንቶች
ናቸው፡፡

በጾታ ደግሞ ሲታይ የመሞት እድሉ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ላይ


የበዛ ነው፡፡ ይህም ከመቶ ሲሰላ ለወንዶች 4.7 ለሴቶች ደግሞ 2.8
ከመቶ ነው፡፡ የዚህ ልዩነት ምክንያቱ በግልጹ የሚታወቅ አይደለም፡፡

በተመሳሳይ በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት ህጻናት ላይ በቫይረሱ


የመታመምም ሆነ የመሞት እድል ከሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች
አንጸር ሲታይ የቀነሰ ሆኖ ተገኝቷ፡፡

ከሙያ አንጻር ሲታይ ጡረታ በወጡት ላይ በቫይረሱ የመሞት እድል


የጨመረ እና 8.4 በመቶ የደረሰ ነው፡፡ ይህ ግኝት ጡረታ ስለወጡ
ብቻ የተገኘ ልዩነት ሳይሆን ጡረታ የሚወጡት በእድሜ የገፉት
ሰዎች በመሆናቸው ነው፡፡

ምንም ተጨማሪ ህመም በሌላቸው ላይ የመሞት እድል እስከ 1.4


በመቶ የደረሰ ሲሆን ተጨማሪ ህመም ባላቸው ላይ ደግሞ እጅግ የበዛ
ነው፡፡ የልብ ህመም ያላቸው በቫይረሱ የመሞት እድላቸው ከሁሉም
ከፍተኛ (13.2%) ሲሆን የስኳር በሽታ 89.2 % ፣ ግፊት 8.4%፣

ዶ/ር አቡሽ አያሌው 65


60

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ስር የሰደደ የሳንባ በሽታ 8% እና ካንሰር 7.6% በቅደም ተከተል


ተቀምጠዋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የተለያየ የሞት መጠን


ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ የሚከተሉትን ማየት ይቻላል፡፡፡፡

Ø በቻይናዋ ውሃን ውስጥ የሞት መጠን 4.9 % ሆኖ ተመዝግቧል፡፡


Ø በቻይና ሁባይ ደግሞ የሞት መጠኑ 3.1% ነው፡፡
Ø በቻይና ውስጥ ከተከሰቱት ሞቶች ውስጥ 74% ሞት
የተመዘገበው በውሃን ውስጥ ብቻ ነው፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዬ የሞት መጠን የተመዘገበው ቫይረሱን


ለመከላከል ካለው ቅድመ ዝግጅት ልዩነት የተነሳ እንደሆነ ጥናቶች
ያሳያሉ፡፡

አሁንም በተመሳሳይ ሀገር ውስጥ በተደረገው ጥናት ሆስፒታል በገቡት


እና የጽኑ ህክምና ክፍል በገቡት ህሙማን ላይ የመሞት እድላቸው
ከሌሎች ይልቅ ከፍ ያለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህም ከጽኑ ታማሚዎች
15% የሞቱ ሲሆን አልጋ ከያዙት ውስጥ ደግሞ 4.3 % የደረሰ ሞት
ተመዝግቧል፡፡

አገግመው በወጡት ህሙማን አማካይ የሆስፒታል ውስጥ ቆይታቸው 10


ቀን ሲሆን ለሞቱት ደግሞ በመጀመሪያ ምልክት ከታየበት እስከ እለተ
ሞታቸው ድረስ ያለው አማካይ ጊዜ 14 ቀን ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
እድሜያቸው ከ70 በላይ ለሆኑት ግን ይህ እስከ 6 ቀናት ድረስ ሊያጥር
ይችላል፡፡

61
66
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ይህንን ያውቃሉ?
በሌሎች በሽታዎች ላይ ያለው ተጽዕኖና
አባባሽነት
የሰውነት በሽታ መከላከያ የሚያዳክሙ ህመሞች ያሉባቸው ሰዎች ላይ
ቫይረሱ ሲከሰት በሽታው በጣም ይከፋባቸዋል፡፡ በኤች አይ ቪ የተያዙ
ሰዎችም ቢሆን የሰውነታቸው በሽታ መከላከያ ስለሚዳከም በቫይረሱ
ከተያዙ በሽታው በጣም ይባባስባቸዋል ማለት ነው፡፡ በእድሜ የገፉ
ሰዎችና የስኳር ሕሙማንም እንዲሁ በሽታውን የመቋቋም ብቃታቸው
ስለሚቀንስ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ ሕመሙ ይበረታባቸዋል፡፡

አስምና የቲቢ ሕመም ያለባቸው ሰዎች አስቀድሞ ሳንባቸው የታመመ


ስለሆነና ኮሮና ቫይረስ ደግሞ ሳንባን ስለሚያጠቃ የሳንባ ሕመሙ በጣም
ይበረታል፡፡ በሽታው በዋናነት የሚያጠቃው ሌላው የሰውነት ክፍል
ኩላሊት ሲሆን የኩላሊት ህሙማን በዚህ ቫይረስ ከተጠቁ የነበረባቸው
በሽታ ይባባስባቸዋል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ሕመሞች ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ ይበልጥ


ስለሚታዩ ቫይረሱ የሚያመጣው ተጽዕኖ በወንዶች ላይ የመበርታት
ባህሪይ አለው፡፡

የደም ግፊት ሕመም ያለባቸው ሰዎችና ሲጋራ አጫሾችም ጭምር


በቫይረሱ ሲያዙ ይበልጥ እንደሚከፋባቸው ታውቋል፡፡

62
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 67
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

በሽታውን በመከላከል ረገድ ትልቁ መሣሪያ ክትባት ቢሆንም ክትባት


ሊገኝለት የመቻሉ ሁኔታ ገና ያልታወቀ መሆኑ በሽታውን በጣም አስፈሪ
አድርጎታል፡፡

ለበሽታው አዲስ መድሃኒት ለማግኘትም ሆነ ለመሥራት በርካታ ወራ


ይጠይቃል፡፡ ኮሮና ቫይረስም ቢሆን መድሃኒት እስኪገኝለት ደረስ ብዙ ጊዜ
መውሰዱ የማይቀር ነው፡፡

ቫይረሱ ለጊዜው ሥርጭቱ ቢገታ እንኳን ጠፍቷል ማለት አያስደፍርም፡፡


ምክንያቱም እንደገና እንደማይቀሰቀስ እርግጠኛ መሆን ስለማይቻል ነው፡፡

ቫይረሶች ራሳቸውን የመቀየር ባህሪይ ያላቸው ሲሆን ይህ ቫይረስም


በቀጣይነት ወደ ምን ደረጃ ራሱን እንደሚቀይር አይታወቅም፡፡

በቫይረሱ ይበልጥ የሚጎዱ ሰዎች ምን


ያድርጉ?

ተፈጥሯዊ በሽታ የመከላከል አቅማቸው የቀነሰ ሰዎች በቫይረሱ ከተጠቁ


በሽታው ይበረታባቸዋል፡፡ እድሜያቸው ከ60 ዓመት የበለጠ ሰዎች
ዝቅተኛ በሽታ የመከላል አቅም ነው ያላቸው፡፡ ቫይረሱ ካገኛቸውም
ሕመሙ ይጸናባቸዋል፡፡

በሰውነት ውስጥ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ሕመም ያለባቸው ሰዎችም


ቫይረሱ ከያዛቸው ከሌላው የበለጠ ይጎዳቸዋል፡፡ በቫይረሱ ላለመያዝ
ከፍ ያለ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው፡፡ ከቤት መውጣት የለባቸውም፡፡
ለረዥም ጊዜ ሊያቆያቸው የሚችል የምግብ እና መሠረታዊ የፍጆታ

63
68
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

እቃዎችን ገዝተው በማከማቸትም ረዘም ላለ ጊዜ ቤታቸው ውስጥ


መቆየት አለባቸው፡፡

አንድ የኮቪድ 19 ታማሚ ህክምናውን


ጨርሶ ወደ ቤተሰቡ መቀላቀል ይለበት መቼ
ነው?
አንድ ሰው ህክምናውን ጨርሶ ከመውጣቱ በፊት በምርመራ ከቫይረሱ
ነጻ መሆን መቻል አለበት፡፡ ይህ ማለት ሁሉም ምልክቶች የግድ
መጥፋት አለባቸው ማለት አይደለም፡፡ አንዳንድ ምልክቶች ታማሚው
ከቫይረሱ ነጻ ሆኖም ለጥቂት ቀናት ሊቀጥሉ ስለሚችል በዋናነት
መታየት ያለበት ከምልክት ይልቅ የቫይረሱ መጥፋት ነው፡፡

ታማሚው ሌሎች ተጨማሪ ኢንፌክሽኖች ካሉት ግን ለኮቪድ 19 ነጻ


ቢሆን እንኳን ፈጥኖ ከሆስፒታል ባይወጣ እና ሌሎችን በሽታዎች
ታክሞ አገግሞ ቢወጣ ይመከራል፡፡

ምልክቶች ካሉብህ ምን ማድረግ እንደሚገባህ!


አስቀድሞ እንደተገለፀው ምልክቶች ስላሉ ብቻ የኮሮና ቫይረስ ኢንፌክሽን
አለ ብሎ መጨነቅ በቂ አይደለም፡፡ ሆኖም ህመሙ ካለባቸው ሠዎች ጋር
ተቀራርበህ ከሆነ ወይም ህመሙ ወዳለበት አካባቢ ሄደህ እንደነበር
ጥርጣሬው ካለህ ለምርመራው ብቁ ነህ፡፡ ቢቻል በአካል ወደ ሃኪም ጋር
ከመሄድ ይልቅ ከተቻለ ለሃኪምህ ወዲያው ደውለህ ስለአሉብህ ምልክቶች
፣ በቅርቡ ስላደረካቸው ጉዞዎች እና ቫይረሱ ካለባቸው ሠዎች ጋር
ተገናኝተህ እንደነበር ያለህን ጥርጣሬ ብትነግረው የተሻለ ነው፡፡ ይህም

64
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 69
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ሌሎችን ሠዎች ለመከላከልና የቫይረሱን መዛመት ለማስወገድ ሃኪሙ


ተገቢውን የአሠራር ስርአት እንዲከተል ለማድረግ ይረዳዋል፡፡

ሃኪሙ ጋር ስትደርስ የምርመራውን መመዘኛ ታሟላ እንደሆነ ለማወቅ


የተወሰኑ ጥያቄዎችን ትጠየቃለህ፡፡ የምታሟላ ከሆነም ከአንተ ናሙና
ተወስዶ ለፒሲአር ምርመራ ይላካል፡፡ ከ24 እስከ 48 ሰአት ውስጥም
የምርመራው ውጤትህ ፖዘቲቭ ወይም ኔጌታቭ መሆኑን ይነገርሃል፡፡
በዚህ የጥበቃ ጊዜም ተለይተህ ቫይረስ ወደ ውጪ በማያስወጣ ክፍል
ውስጥ ትሆናለህ፡፡ ምርመራው ፖዘቲቭ ከሆነም አስፈላጊ ድጋፍ ሠጪ
ህክምናዎች ይደረጉልሃል፡፡ መለስተኛ ህመሞች ብዙም ልዩ ህክምና
አያስፈልጋቸውም፡፡

ኮሮና ቫይረስ ከያዘህ ቫይረሱን ወደሌሎች የማዛመትህን ሁኔታ ለመቀነስ


የሚረዱ ምክሮች የሚከተሉት ናቸው፤

• የህክምና እርዳታ ካላስፈለገህ በስተቀር ከቤትህ አትውጣ፡፡ ወደ


ሆስፒታል የግድ መሄድ ካስፈለገህ ግን ታክሲ ወይም ሌላ የህዝብ
መጓጓዣ አትጠቀም
• ህክምና ካስፈለገህ ሁሌም አስቀድመህ ስልክ ደውል
• በሰዎች አካባቢ ስትጓዝ ሁሌም የፊት ማስክ አድርግ (ቤት ውስጥ
ወይም ወደ ህክምና ስትሄድ) ለተጨማሪ ጥንቃቄም የቤተሰቦችህ
አባላት አንተ አጠገብ ከሆኑ የፊት ማስክ እንዲያደርጉ አድርግ
• ስትስል ወይም ስታስነጥስ በቲሹ ፔፕር (ሶፍት ወረቀት) ወይም
በእጅጌህ ሸፍነው፡፡ የተጠቀምክበትን ቲሹ ፔፕር ክዳን ባለው የቆሻሻ

65
70 ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ማስቀመጫ ውስጥ ጣለው፤ ከዚያም እጅህን በውሃና ሳሙና ታጠብ፡፡


በቀጥታ በእጆችህ ላይ አትሳል ወይም አታስነጥስ፡፡
• በተደጋጋሚ በመታጠብና እጆችህን በጀርም ማምከኛ ፈሳሽ (ዲስ
ኢንፌክታንት) በማሻሻት እና ፊትህን ባለመንካት ተገቢውን ንፅህና
ጠብቅ፡፡
• ከአንተ ጋር በአንድ ቤት ውስጥ ከሚኖሩ የቤተሰቦችህ አባላት ራስህን
ለይ፡፡ ከነሱ ጋር ስታወራም የ2 ሜትር ርቀት ይኑርህ፣ ከተቻለም
የተለየ መታጠቢያ ቤት ተጠቀም፡፡
• በቤትህ ውስጥ ካሉ ሠዎች ጋር እቃዎችን በጋራ አትጠቀም፡፡ ይህም
ማለት ሳህኖችን፣ የመመገቢያ እቃዎችን፣ ኩባያዎችን፣
ብርጭቆዎችን ፣ ፎጣዎችን፣ አልጋን ፣ ልብሶችን ፣ የንፅህና
መጠበቂያ እቃዎችን ፣ የምትጠቀመበትን እቃ ሁሉ በውሃና በሳሙና
እጠብ፣ ከተቻለም የፀረ-ጀርም ፈሳሽ ተጠቀም፡፡ በተጨማሪም ስልክህን
ጠብቅ፣ በተለይም ስልህን የመንካት ልማድ ያላቸው ህፃናት ካሉ፡፡
• ከቤትህ የቤት እንሰሳት ጋር ንክኪ አታድርግ፡፡ እስከአሁን ድረስ ኮሮና
ቫይረስ ድመት ወይም ውሻን ለማጥቃቱ ማስረጃ የለም፡፡ ሆኖም
እንሰሳትን የሚያጠቁ ኮሮና ቫይረሶች አሉ፡፡ ቢሆንም ግን መጠንቀቁ
አይከፋም፡፡ የሠው ልጆች ቫይረሱ ወደ ድመቶችና ውሾች
እንደማያስተላልፉ በሳይንስ እስኪረጋገጥ ድረስ በቤት እንስሳት አጠገብ
ስትሆን ወይም እነሱን መንከባከብ ካለብህ የፊት ማስክ አድርግ፡፡
• ምልክቶችህን ተከታተል፤ ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ከባድ የጤና ችግሮችን
ሊያመጣ ይችላል፡፡ ስለዚህም ሁኔታህን መከታተልና የተለየ ነገር
ከገጠመህ ማለትም ምልክቶቹ በድንገት ከተባባሱ (የአተነፋፈስ ችግሩ

66
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 71
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

መጨመር ፣ የትኩሳቱ መበርታት ፣ ወይም ያልተለመዱ ምንም


ነገር ከገጠመህ) ወዲያዉኑ ለሃኪምህ ማሳወቅ አለብህ፡፡

Ø ከተጠቀሙ በኋላ እቃዎችን በአግባቡ ማጠብ / ለሌላ ሰው


አለማጋራት
Ø ንክኪ ያለባቸውን ነገሮና እቃዎች / ስልክ ኮምፒውተር፣ በር፣
ሽንትቤት፣ እጀታ፣ ጠረጴዛ ፣ አልጋ፣ ሁሉ በየቀኑ ማጠብ
Ø ማነኛውም የሰውነት ውስጥ ፈሳሽ የነካቸውን ነገሮች በኬሚካል
ማጽዳት / በተለይ ሌላ ሰው ሊጠቀም ይችላል ተብሎ ከታሰበ
Ø የህመሙን ሂደት በጥንቃቄ መከታተል እና የባለሙያ እገዛ
ማግኘት
Ø ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች ሁሉ ለሚመለከተው ማሳወቅ፡፡

ልጅ ፣ አዛውንት ወይም የሠውነት በሽታ መከላከያው ያነሰ ሠው ኖቭል


ኮሮና ቫይረስ ከያዘው ምልክቶቹ መለስተኛ ቢሆኑ እንኳን ልዩ ህክምና
እና የሃኪም ክትትል ሊያስፈልገው ይችላል፡፡ የህፃን በሽተኛ
እየተንከባከብክ ከሆነም ከእሱ ጋር አንተም ከላይ የተዘረዘሩትን ምክሮች
በመከተል ግለሰቡ የአንተን አርአያ እንዲከተል አድርግ፡፡

67
72
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን


ለመከላከልና ለማከም እንዴት
ታቅዳለህ ? እንዴትስ ተግባራዊ
ታደርጋለህ?
የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ በአካባቢህ ከመከሰቱ
በፊቱ የምታወጣው እቅድ

የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ በአካባቢህ ማህበረሰብ ውስጥ ለረዥም ጊዜ ሊቆይ


ይችላል፡፡ ከወረርሽኙ ከባድነት አንፃር በሚመረኮዝ ሁኔታ የጤና
ባለስልጣናት የሰዎችን ጤንነት ለመጠበቅ ፣ ለኮቪድ-19 ያላቸውን
ተጋላጭነት ለመቀነስና የህመሙን ስርጭት ለማዘግየት ማህበረሰቡ
የሚወስዳቸውን ጥንቃቄዎች በተመለከተ ምክሮችን ሰጥተው ሊሆን
ይችላል፡፡ የአካባቢው የጤና ባለስልጣናትም ለአካባቢው ተመጣጣኝ የሆኑ
ምክሮችን ሰጥተው ሊሆን ይችላል፡፡ የቤተሰብ እቅድ ማውጣትም
በማህበረሰብህ ውስጥ የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ሲከሰት የራስህንና
የቤተሰብህን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳሃል፡፡ የቤተሠብህን እቅድም
የቤተሰቡ አባላት ከሚያስፈልጋቸው ጥንቃቄዎችና የዕለት ተዕለት
ተግባራት ላይ መመርኮዝ አለብህ፡፡

68
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 73
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የቤተሰብ የድርጊት እቅድ አውጣ በእቅድህ ው ስጥ

መ ካተት ካለባቸው ሠ ዎ ች ጋር ተነጋገር፡- የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ


በማህበረሰቡ ውስጥ ቢከሰት ምን ማድረግ እንደሚቻልና እያንዳንዱ
ሰውም ምን እንደሚያስፈልገው ከቤተሰብ አባላት ፣ ከሌሎች ዘመዶችና
ጓደኞች ጋር ተገናኝተህ ተወያይ፡፡

በሽታው ይበልጥ ሊጎዳቸው ለሚችላቸው


ሠዎች ምን አይነት እንክብካቤ
እንደሚያስፈልጋቸው እቅድ አውጣ፤
ኮቪድ-19 ይበልጥ ማንን ሊጎዳ እንደሚችል በተመለከተ ያለው መረጃ
ውስን ነው፡፡ በኮቪድ -19 ህሙማን ላይ ከታየው መረጃ እና ሳርስ - እና
ሜርስ ከሚባሉት ተመሳሳይ የኮሮና ቫይረሶች ከተገኘው መረጃ አንፃር
እድሜያቸው የገፉ ሠዎችና ለብዙ ጊዜ የቆየ የውስጥ ደዌ ህመም
ያለባቸው ሠዎች በሽታው ሊከፋባቸው ይችላል፡፡ እስካሁን ድረስ የተገኘው
መረጃም እድሜያቸው የገፋ ሠዎች ለከባድ የኮቪድ-19 ህመም የተጋለጡ
መሆኑን ያመለክታል፡፡ አንተ ወይም የቤተሰብህ አባላት ለከባድ የኮቪድ-
19 ህመም የተጋለጣችሁ ከሆነ የኮቪድ-19 ምልክቶችን ስለመከታተል
በተመለከተ የበለጠ መረጃ እንዲሰጥህ ሃኪምህን አማክር፡፡

69
74
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ጎረቤቶችህን እወቃቸው፡- ስለድንገተኛ ጊዜ


እቅድ ከጎረቤቶችህ ጋር ተነጋገር፡፡

በማህበረሰብህ ውስጥ ያሉትን የእርዳታ ድርጅቶች


እወቃቸው፡- መረጃ ለማግኘትና፣ የህክምና አገልግሎት እና ድጋፎችን
በምትፈልግበት ጊዜ የምትገናኛቸውን የአካባቢህ የእርዳታ ድርጅቶችን
ዝርዝር ያዝ፡፡

የድንገተኛ ጊዜ የመገናኛ ዝርዝር ይኑርህ፡- በድንገተኛ ጊዜ


ልታገኛቸው የምትችላቸውን የቤተሰብ፣ የጓደኞች ፣ የጎረቤት ፣ የጤና
ባለሙያዎች ፣ የመምህራን ፣ የሠራተኞች ፣ የአካባቢው የጤና
ኃላፊዎች እና ሌሎችም ከማህበረሰቡ የምታገኛቸው ድጋፍ ሰጪ አካላት
መገኛ አድራሻ ወይም በስልክ ቁጥር ቤተሰብህ እንዳለው አረጋግጥ፡፡

‹ ‹ ጥሩ የግል ጤንነት ልማዶችን ተግባራዊ አድርግ ፣ በቤት


ውስጥ የሚደረጉ እርምጃዎች አቅድ› ›

የዕለት ተዕለት የመከላከያ እርምጃዎችን አሁኑኑ ተግባራዊ


አድ ርግ፡- የመተንፈሻ አካላት ህመሞችን መዛመትን ለመከላከል የሚረዱ
የዕለት ተዕለት የመከላከያ እርምጃዎችን ተግባራዊ የማድረግን
ጠቀሜታዎች ለእያንዳንዱ የቤተሰብህ አባል አስታውስ፡፡

• ከታመሙ ሠዎች ጋር በቅርበት አትነካካ


• ከታመምክም ለህክምና ካልሆነ በስተቀር ከቤት አትውጣ

70
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 75
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

• ስታስልና ስታስነጥስ አፍህንና አፍንጫህን በሶፍት ወረቀት


ያዝ
• በተደጋጋሚ የሚነኩ ነገሮችን (ለምሳሌ ጠረጴዛዎች ፣
ባንኮኒዎች ፣ ማብሪያ ማጥፊያዎች ፣ የበር እጄታዎች እና
የቁምሳጥን እጄታዎችን) በየጊዜው በሳሙና አፅዳቸው፡፡
o እነዚህ ነገሮች ቆሻሻ ከሆኑ በፀረ-ጀርም
ከመፅዳታቸው በፊት በውሃና በሳሙና መታጠብ
አለባቸው፡፡
• በተለይም ከመመገብህ በፊት ፣ ከተናፈጥክ ፣ ከሳልክ
ወይም ካስነጠስክ በኋላ እና መፀዳጃ ቤት ከገባህ በኋላ
ቢያንስ ለ20 ደቂቃ እጅህን በውሃና ሳሙና ታጠብ፡፡ ውሃና
ሳሙና የማይገኝ ከሆነም ቢያንስ 60 ፕርሰንት አልኮል
ባለው ፀረ-ጀርም ፈሳሽ (ሳኒታይዘር) እጆችህን አፅዳ፡፡
እጆችህ ቆሻሻነታቸው በግልፅ የሚታይ ከሆነም ሁለቱንም
እጆችህን በሳሙናና በውሃ ታጠብ፡፡

የታመሙ የቤተሰብ አባላትን ከጤነኞች


መለየት የሚያስችል በቤትህ ውስጥ አንድ
ክፍል ምረጥ፡- ከተቻለም ለታመሙት ለብቻቸው አንድ

መታጠቢያና መፀዳጃ ክፍል ይኑራቸው፡፡ አንድ ሠው ሲታመም ይሄን


ክፍል እንደተፈለገው የምታፀዳበትን እቅድ አውጣ፡፡

71
76 ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የልጅህ ት/ቤት ወይም የህፃናት ማቆያ ሊዘጋ


ስለሚችል ተዘጋጅ

የልጅህን የት/ቤት ወይም የህፃናት ማቆያ


ድርጅት የድንገተኛ ሥራ እቅድ እወቅ ፡- በኮቪድ-

19 ወረርሽኝ ወቅት የአካባቢው የጤና ባለስልጣናት የህመሙን ስርጭት


ለመቀነስ ት/ቤቶችን ለጊዜው ሊዘጉ ይችላል፡፡ ት/ቤት በተዘጋበት ወቅት
ቀጣይነት ስላለው ትምህርት እና ስለ ማህበራዊ አገልግሎቶች (ለምሳሌ
የተማሪዎች ምገባ) ያለውን እቅድ ተገንዘብ፡፡ ልጅህ ኮሌጅ ወይም
ዩኒቨርስቲ ውስጥ የሚማር ከሆነም ስለትምህርት ቤቱ የኮቪድ-19
ወረርሽኝ እቅድ እንዲያውቅ አበረታታው፡፡

በስራ ቦታህ ሊከሰቱ ስለሚችሉ ለውጦች


እቅድ ስለ አሠራርህ የድንገተኛ ትግበራ
እቅድ እወቅ፡- ለታመሙ ወይም የታመመን ሠው ለሚንከባከቡ

ሠራተኞች ስለሚሰጠው ፈቃድ ወይም ከቤት ውስጥ የመሥራት ፈቃድ


በተመለከተ ከአሠሪህ ጋር ተነጋገር፡፡ ቢዝነስ እና አሠሪዎች ለኮቪድ-19
እንዴት እንደሚያቅዱና የሚሰጡትን ምላሽ በተመለከተ ግንዛቤው
ይኑርህ፡፡

72
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 77
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

በአካባቢህ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሲከሰት፡-


ተግብር

በአካባቢህ ወረርሽኝ ሲከሰት ራስህንና ሌሎችን እንደሚከተለው ተከላከል፤

• በኮቪድ-19 ህመም ስትታመም ከት/ቤት ፣ ከስራ ወይም


ከሌሎች እንቅስቃሴዎች ቀርተህ እቤት መዋል አለብህ፡፡
የበሽታው ምልክቶች ትኩሳት ፣ ሳል ፣ እና ለመተንፈስ
መቸገር ናቸው፡፡
• ከታመሙ ሠዎች ራስህን ማራቅ
• በተቻለ መጠን ከሌሎች ሠዎች ራስን ማራቅ (2 ሜትር ያህል)

የቤተሰብ እቅድህን ተግብር


ስለአካባቢው የኮቪድ-19 ሁኔታ በየጊዜው መረጃ ይኑርህ፡-

ስለአካባቢው የኮቪድ-19 እንቅስቃሴ ከጤና ባለስልጣኖች በየጊዜው መረጃ


ይኑርህ፡፡ በአካባቢህ ት/ቤቶች ተዘግተው መሆኑን እወቅ፣ ይህ
የቤተሰብህን እለታዊ እንቅስቃሴ ሊቀይረው ይችላል፡፡

ከታመምክ ቤት ውስጥ ተቀመጥ፡- የኮቪድ- 19 ምልክቶች


ካሉብህ ከቤት አትውጣ፡፡ አንድ የቤተሰብህ አባል ከታመመም ከት/ቤት
እና ከሥራ ቀርተህ ኮቪድ-19ን እንዳያዛምት ተከላከል፡፡

• ልጆችህ በህፃናት ማቆያ ሌሎች ሰዎች እየተንከባከቧቸው ከሆነ


የኮቪድ -19ን ምልክቶች እንዲከታተሉ አስጠንቅቃቸው፡፡

73
78
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የዕለት ተዕለት የመከላከያ እንቅስቃሴዎችን ማድረግህን


ቀጥልበት፡- ስታስልና ስታስነጥስ በሶፍት ወረቀት ተሸፈን፣ እጆችህን
ቢያንስ ለ20 ደቂቃ በውሃና በሳሙና አዘውትረህ ታጠብ፡፡ ውሃና ሳሙና
የማይገኝ ከሆነም 60 ፕርሰንት አልኮል ባለው የእጅ ሳኒታይዘር
ተጠቀም፡፡ አዘውትረው በእጅ የሚነኩ ነገሮችን በየእለቱ በፈሳሽ ሳሙና
እና በውሃ አፅዳቸው፡፡

(ከተቻለ) ለታመሙ የቤተሰብህ አባሎች ያዘጋጀኸውን የተለየ ክፍልና


መታጠቢያ ቤት ተጠቀም፡- እንደ ምግብና መጠጥ ያሉትን በጋራ
አትጠቀም፡፡ የታመሙት የቤተሰብህ አባላት ቤት ውስጥ ንፁህ የፊት
ማስክ ይጠቀሙ፡፡(ከተቻለ) ከታመመው ሠው ጋር አላስፈላጊ መነካካትን
ለማስወድ የታማሚውን ክፍልና መታጠቢያ ክፍል እንደአስፈላጊነቱ
አፅዳ፡፡

• በቀላሉ የሚነኩ ቦታዎች ቆሻሻ ከሆኑ በዲስኢንፌክታንት


ከመታከማቸው በፊት በፈሳሽ ሳሙና እና በውሃ መታጠብ
አለባቸው፡፡

ከሌሎች ሠዎች ጋር በስልክ ወይም በኢ-ሜይል ግንኙነት


አድርግ፡- ብቻህን የምትኖር ከሆነና በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት
ከታመምክ እርዳታ ሊያስፈልግህ ይችላል፡፡ ለረዥም ጊዜ የቆየ ህመም
ካለብህና ብቻህን የምትኖር ከሆነም በወረርሽኙ ወቅት እንዲጠይቁህ
ቤተሰብህን፣ ጓኞችህን እና የጤና ባለሙያዎችን ጠይቅ፡፡ ለብዙ ጊዜ የቆየ
ህመም ያለባቸውን ሠዎችንም በየጊዜው ጠይቃቸው፡፡

74
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 79

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የቤተሰብህን የስሜት (የአእምሮ) ጤንነት ጠብቅ፡-


ወረርሽኝ ለህፃናትም ሆነ ለአዋቂዎች የሚያስጨንቅ ሊሆን ይችላል፡፡
ህፃናት ለአስጨናቂ ሁኔታዎች የሚሰጡት ምላሽ ከአዋቂዎች ይለያል፡፡
ከህፃናቱ ጋር ስለወረርሽኙ ተነጋገር፣ የተረጋጋህ ሁን፣ እነሱም ደህና
እንደሆኑ በመንገር አረጋጋቸው፡፡

የተለመደውን የሥራ ፕሮግራም መቀየር ካለብህ ለሥራ


ቦታህ አስታወቅ

የሥራ ፕሮግራምህ ከቀየርክ ፈጥነህ ለሥራ ቦታህ


አስታውቅ፡- አንተ ወይም ሌላ የቤተሰብ አባላህ በኮቪድ-19 ከታመመ
ወይም ልጅህ ከት/ቤት ከቀረ እቤትህ መስራት እንድትችል ወይም
የመቅረት ፈቃድ እንዲሰጥህ ጠይቅ፡፡

በወረርሽኝ ወቅት ልጆችህን ለመከላከል የሚከተሉትን


አድርግ

ልጆችህ በኮቪድ-19 ከታመሙ የህፃናት መቆያቸውን ወይም


ለትምህርት ቤታቸው አስታውቅ፡- እቤታቸው ውስጥ ሆነው የቤት
ሥራቸውን ስለመስራት ሁኔታ ከመምህራኖቻቸው ጋር ተነጋገር፡፡

በአካባቢህ የት/ቤት መዘጋቶች ዜናዎችን ተከታተል፡- ት/ቤቶች


ለጊዜው ከተዘጉ አስፈላጊ ከሆነ አማራጭ የህፃናት ተንከባካቢዎችን
ተጠቀም፡፡

75
80 ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ትምህርት ቤት በተዘጋበት ወቅት ህፃናትና ታዳጊዎች ሠው


በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች እንዳይሰበሰቡ አድርግ፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአካባቢህ ሲያበቃ ፡- ክትትል አድርግ

አስተውል፤ የኮቪድ19 ወረርሽኝ ለረዥም ጊዜ ሊቆይ ይችላል፡፡ በግለሰቦች


፣ በቤተሰቦች ፣ በማህበረሰቦች ላይ የሚኖረው ተፅዕኖም ከፍተኛ ሊሆን
ይችላል፡፡ የጤና ባለስልጣናት በአካባቢህ ወረርሸኙ ማብቃቱን ሲያሳውቁም
የቤተሰብህን እቅድ አሻሽል፡፡ የጤና ባለስልጣናት ለኮቪድ-19 እና ለሌሎች
ህመሞችም ወረርሽኞች እቅድ ማውጣታቸውን ሲቀጥሉ አንተና
ቤተሰብህም በእቅዱ ውስጥ ትልቅ ሚና ይኖራችኋል፡፡

የቤተሰብህን የድርጊት እቅድ ብቃት ገምግም

የቀሰምካቸውን ትምህርቶች ተወያይባቸው፣ መዝግባቸውም፡-


የኮቪድ-19 ዝግጁነትህን በቤት ውስጥ ፣ በት/ቤት እና በስራ ቦታ ላይ
ውጤታማ ነበር? በእቅድህ ላይ የተከሰቱ ችግሮችን እና ውጤታማ
መፍትሄዎችን ተነጋግርባቸው፡፡ ለአንተና ለቤተሰብህ የሚያስፈልጉትን
ተጨማሪ የመከላከያ መፍትሄዎች ለይተህ እወቅ፡፡

ስለድንገተኛ ጊዜ እቅድ በማህበረሰቡ ውይይቶች ላይ


ተሳተፍ፡- ለአንተና ለቤተሰብህ ውጤታማ ስለሆነው የዝግጁነት
እርምጃዎች ሌሎችም ይወቁ፡፡ ከአካባቢህ ማህበረሰብ ጋር ግንኙነትህን
ቀጥል (ለምሳሌ በሶሻል ሚዲያ ፣ በኢሜይል)

76
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 81

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የዕለት ተዕለት የመከላከያ እንቅስቃሴዎችን ትግበራ ቀጥል፡-


ከታመምክ እቤት ተቀመጥ፤ ስትስልና ስታስነጥስ በሶፍት ወረቀት
ተሸፈን፤ እጆችህን በውሃና በሳሙና ታጠብ፤ በተደጋጋሚ የሚነኩ
ነገሮችን በየዕለቱ በተደጋጋሚ አጽዳቸው፡፡

የቤተሰብህን የስሜት ጤንነት ጠብቅ፡- ለቤተሰብህ ያለህ ጠንካራ


ስሜት ሊቀዘቅዝ እንደሚችል አትዘንጋ፡፡ ስለ ኮቪድ-19 ዜናዎችንና
ታሪኮችን ከመስማት፣ ከማየትና ከማንበብ ገታ ብለህ ከቤተሶበችህ እና
ከጓዶችህ ጋር ተገናኝ፡፡

ከወረርሽኙ በኋላ ያለውን ጊዜ ልጆችህ እንዲቋቋሙት እርዳቸው፡- ሕጻናት


ስላሳለፉት ጊዜ ወይም ያስቡት ስለነበረው የሚያወሩበትን አጋጣሚ
ስጣቸው፡፡ የሚያሳስባቸውን ነገር እንዲያወሩና ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ
አበረታታቸው፡፡ መምህራን፣ ወላጆችና ሌሎች አዋቂዎች ሕጻናትን ለየት
በሚል አንጻር ስለሚያዩዋቸው ከወረርሽኙ በኋላ እያንዳንዱ ሕጻን
ሁኔታውን እንዴት እየተቋቋመው እንደሆነ ለማወቅ በጋራ መሥራት
አለባቸው፡፡

ከታመምክ ምን ማድረግ እንዳለብህ?

ለሐኪሞች አስታውቅ፡- በኮቪድ - 19 እንደተያዝክ ካሰብክና


ትኩሳትና ሳል፣ የመተንፈሻ ችግርን የመሳሰሉ ችግሮች ካሉብህ ለሐኪምህ
አስታውቅ(ደውለህ)፤ ምክር እንዲሰጥህም አድርግ፡፡

82 77
ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

በበሽታው ከተያዝክ የኮቪድ 19 ስርጭትን


መከላከያዎች

የሚከተሉትን ደረጃ በደረጃ አድርግ፡ በኮቪድ - 19 ተይዘህ ከታመምክ


ወይም የቫይረሱ ኢንፌክሽን ተከስቶብህ ከሆነም በሽታው ወደ ቤተሰብህና
ወደ ማህበረሰቡ እንዳይሰራጭ የሚከተለውን ደረጃ በደረጃ አድርግ፡፡

ለመታከም ካልሆነ በስተቀር ቤትህ ተቀመጥ

ቤት ውስጥ ተቀመጥ፡- በኮቪድ 19 መለስተኛ ህመም ያለባቸው


ሰዎች በታመሙበት ወቅት ቤት ውስጥ በመቀመጥ ራሳቸውን ለመነጠል
ይችላሉ፡፡ ለመታከም ካልሆነ በስተቀር ከቤት ውጪ የምታደርጋቸውን
እንቅስቃሴዎች መገደብ አለብህ

ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች አትገኝ፡- ወደ ሥራ፣ ት/ቤት ወይም


ሕዝብ ወደሚሰበሰብባቸው ሥፍራዎች አትሂድ

የህዝብ ትራንስፖ ርት አት ጠ ቀም ፡- የህዝብ ትራንስፖርት ወይም


ታክሲዎችን አትጠቀም በቤትህ ውስጥ ራስህን ከሌሎች ሰዎችና እንስሳት
ለይ

ከሌሎች ሰዎች ራቅ፡- በተቻለ መጠን ቤት ውስጥ በአንድ በተወሰነ


ክፍል ውስጥ ከሌሎች ሰዎች ተነጥለህ ተቀመጥ፡፡ ከተቻለም የተለየ
መጸዳጃ ክፍል ተጠቀም፡፡

78
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 83
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ከቤት እንስሳትና ከእንስሳት ጋር አትነካካ፡- ከሌሎች ሰዎች ጋር


እንደማትነካካ ሁሉ ከቤት እንስሳትና ከእንስሳት ጋርም መነካካት
የለብህም፡፡ ምንም እንኳን የቤት እንስሳት ወይም እንስሳት በቫይረሱ
የመጠቃታቸው ሁኔታ ያልተነገረ ቢሆንም ስለቫይረሱ ተጨማሪ መረጃ
እስከሚገኝ ድረስ በኮቪድ 19 የታመሙ ሰዎች ከእንስሳት መራቅ
እንዳለባቸው ይመከራል፡፡

ከተቻለም አንተ በታመመክበት ወቅት እንድ ሌላ የቤተሰብህ አባል


ለእንስሳቱ እንክብካቤ ያድርግ፡፡ በታመመክበት ወቅት የቤት እንስሳትን
ወይም ሌሎች እንስሳትን የግድ መንከባከብ ካለበህ ከመነካካት በፊትና
በኋላ እጆችህን ታጠብ፤ የፊት ማስክም አድርግ፡፡

ለታመመ ሰው የቤተሰብ አባላትና


ተንከባካቢዎች መረጃ

ሐኪምህን ከማየትህ በፊት ደውልለት

በቅድሚያ ደውልለት፡- የህክምና ቀጠሮ ካለህ ለጤና ባለሙያው


በመደወል ኮቪድ 19 እንዳለብህ ወይም ሊኖርብህ እንደሚችል ንገረው፡፡
ይህም ሌሎች ሰዎቸ ቫይረሱ እንዳይዛመትባቸው ቅድመ ጥንቃቄ የጤና
ባለሙያዉ እንዲያደርግ ይረዳዋል፡፡

ከታመምክ የፊት ማስክ አድርግ

ከታመምክና ሌሎች ሰዎች አካባቢ ከሆንክ (ለምሳሌ አንድ ክፍል ወይም


መኪና በጋራ እየተጠቀማችሁ ከሆነ) ወይም በቤት እንስሳት አቅራቢያ
79
84
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ከሆንክ ወይም የጤና ባለሙያ ጋር ስትቀርብ የፊት ማስክ ማድረግ


አለብህ፡፡

ሌሎችን የምትንከባከብ ከሆነ ፡- የታመመው ሰው የፊት ማስክ


ማድረግ ካልቻለ (ለምሳሌ መተንፈስ ከከለከለው) አብረውት የሚኖሩ
ሰዎች በተመሳሳይ ክፍል ውስጥ መቀመጥ ያለባቸውም ወይም ወደ ክፍል
ሲገቡ የፊት ማስክ ማድረግ አለባቸው፡፡

ስትስልና ስታስነጥስ ተሸፈን

ተሸፈን፡- ስትስል ወይም ስታስነጥስ አፍና አፍንጫህን በቲቩ ወረቀት


ሸፍን

አስወግድ፡- የተጠቀምክበትን ቲሹ ወረቀት በቆሸሻ ማስቀመጫ


ውስጥ ጣል ውሃና ሳሙና ከሌለ

60 በመቶ አልኮል በያዘ ሳኒታይዘር እጆችህን አጽዳ

በየጊዜው እጆችህን ታጠብ

እጆችህን ታጠብ፡- በተለይም አፍንጫህን ከነካካህ በኋላ፣ ከሳልክ፣


ካስነጠስክ፣ መጸዳጃ ቤት ከገባህ በኋላ እና ምግብ ከተመገብክ በኋላ ወይም
ካዘጋጀህ በኋላ እጆችህን በውሃና በሳሙና ታጠብ፡፡

የእጅ ሳኒታይዘር፡- ውሃና ሳሙና የማይገኝ ከሆነ ቢያንስ 60 በመቶ


አልኮል የያዘ የእጅ ሳኒታይዘር እጅህን ሙሉ በሙሉ እና እስኪደርቅ
ድረስ በማሻሻት አጽዳ

80
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 85
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ሳሙናና ውሃ፡- እጆች ቆሻሻነታቸው በግልጽ የሚታይ ከሆነ ሳሙናና


ውሃ ተመራጭ ናቸው፡፡

አትነካካ፡- አይኖችህን፣ አፍንጫህን እና አፍህን ባልታጠበ እጅህ አትንካ

የግል ዕቃዎችን በጋራ አትጠቀም

የእጅ አስተጣጠብ
አት ጋራ ፡- ሳህኖችን፣ ብርጭቆዎችን፣ ስኒዎችን፣ የመመገቢያ እቃዎችን፣
ፎጣዎችን ወይም አልጋ ከሌሎች ሰዎች ወይም እንስሳት
አትጋራከተጠቀምክ በኋላ በጥሩ ሁኔታ እጠባቸው፡- እነዚህን እቃዎች
ከተጠቀምክባቸው በኋላ በሳሙናና በውሃ ደህና አድርገው መታጠብ
አለባቸው፡፡

በተደጋጋሚ የሚነኩ ነገሮችን በየዕለቱ


አጽዳቸው

- አጽዳቸውና ዲስ ኢንፌክት አድርጋቸው


በተደጋጋሚ የሚነኩ ነገሮችን በየጊዜው የማጽዳት ልማድ ይኑርህ፡፡
በተደጋጋሚ የሚነኩ ነገሮች ባንኮኒዎች፣ ጠረጴዛዎች፣ የበር እጄታ፣
መጸዳጃ ቤት፣ ስልኮች፣ ኪቦርድና ታብሌቶች እና ቤድሳይድ ታብሌቶች
ናቸው፡፡

የሳሙና ፈሳሽ የነካቸው ቦታዎች ዲስ ኢንፌክት አድርግ፡- ደም፣


አይነምድር ወይም የሠውነት ፈሳሽ የነካውን ነገር አጽዳ

81
86 ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የቤት ውስጥ ማ ጽጃዎ ች፡- የሚረጭ የቤት ውስጥ ማጽጃ እስፕሬይ


ወይም መጠራረጊያ ዋይፕስ ማሸጊያው ላይ ባለው ትዕዛዝ መሰረት
ተጠቀም ፣ ኬሚካሉን በምትጠቀምበት ጊዜ የምትወስዳቸውን ጥንቃቄዎች
ይዘረዝራሉ፡፡ (ለምሳሌ ጓንት ስለመጠቀም፣ በቦታው ጥሩ የአየር ዝውውር
ስለመኖር)

ምልክቶችን መከታተል
ወደ ሐኪም ጋር ሂድ፡- ሕመምህ እየተባባሰ ከሄደ (ለምሳሌ ተንፈስ
ከተቸገርክ ወደ ሐኪም ሂድ፡፡

ለሐኪም ደውል፡ ሀኪም ጋር ከመሄድህ በፊት ስልክ በመደወል ኮቪድ 19


እንዳለብህ ወይም ሊኖርብህ እንደሚችል ተናገር፡፡

ከታመምክ የፊት ማስክ አድርግ፡- ወደ ሆስፒታል ከመግባህ በፊት የፊት


ማስክ አድርግ፡፡ ይህም በቦታው ያሉ ሌሎች ሰዎች ለቫይረሱ
እንዳይጋለጡ ያደርጋል፡፡

ቤት ውስጥ ተለይቶ መቀመጥን በተመለከተ

ለመውጣት እስከምትታዘዝ ድረስ እቤት ተቀመጥ፡- ወደ


ሌሎች ሰዎች የማስተላለፍ ሁኔታ ዝቅተኛ እስከሚሆን ድረስ ኮቪድ 19
እንዳለባቸው የተረጋገጠባቸው ሰዎች በቤት ውስጥ ተለይተው መቀመጥ
አለባቸው፡፡

82
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 87
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ከሐኪም ጋር ተነጋገር፡- ቤት መቀመጥ መቼ እንደሚቋረጥ


የሚወሰነው ከሐኪሞችና ከአካባቢው የጤና ባለሙያዎች ጋር በመመካከር
ነው፡፡

የቃላት ትርጓሜ፡-

ትኩሳት በመለኪያ የተረጋገጠም ያልተረጋገጠም ሊሆን ይችላል፡፡

በሽተኛውን መቅረብ ማለት፡-

1. ከበሽተኛው በ2 ሜትር ባነሰ ቅርበት ለረዥም ጊዜ መቆየት፡-


በሽተኛውን በመቅረብ ኮቪድ 19 ሊከሰት የሚችለው
ሲያስታምሙት፣ አብረው ሲኖሩ፣ ሲጠይቁት ወይም
ሆስፒታል ውስጥ በመጠበቂያ ሥፍራ ወይም አንድ ክፍል
በመጋራት ነው፡፡
2. በበሽተኛው ሰውነት የሚወጡ ፈሳሾች በቀጥታ (ለምሳሌ
ከተሳለበት)
አንድ ሰው መከላከያ ሳይጠቀም ይህ ከተከሰተበት (ጋዋን፣ ጓንት፣ ማስክ
የአፍ መከላከያ) ግለሰቡ የቅርብ ክትትል ያስፈልገዋል፡፡
በሽተኛውን መቅረብ የሚባለውን በመረጃ ለማስደገፍ ይከብዳል፡፡ ይህ
ሁኔታ በሚገመገምበት ወቅት መታሰብ ያለባቸው የተጋለጠበት ጊዜ
እርዝማኔ (ለረዥም ጊዜ ከሆነ ስጋቱን ይጨምረዋል) እና

83
88
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ኮቪድ -19 ያለበት ሰው የሚያሳያቸውን ምልክቶች (መሳል እና በጣም


ለታማመ ሰው መጋለጥ ስጋቱን ይጨምረዋል)፡፡ በጤና ማዕከላት ውስጥ
የተጋለጡ ሰዎች ልዩ ትኩረት ያስፈልጋቸዋል፡፡

የመዘጋጃ የጥንቃቄ ዝርዝር

በኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ወቅት አንተንና ቤተሰብህን ሊከላከል የሚችል


እቅድና ውሳኔ ላይ መድረስ ትችላለህ፡፡ የራስህንና የቤተሰብህን ጤንነት
ለመጠበቅ የሚያስችል እቅድ ለማውጣት እና ትግበራዎችን ለማድረግ
ይህን የመዘጋጃ የጥንቃቄ ዝርዘር ተጠቀም፡፡

አቅድና ተዘጋጅ

- ከጤና ባለስልጣናት ስለ አካባቢው የኮቪድ 19 ሁኔታ በየጊዜው


መረጃ አግኝ
- ለቤተሰብህም የትግበራ እቅድ አውጣ

- በእድሜያቸው የገፉ ሰዎችና በሽታ ያለባቸው የመሳሰሉትን


ለሕመሙ ይበልጥ የተጋለጡ የቤተሰቡ አባላትን ታሳቢ አድርግ
- ምን እቅድ እንዳላቸው ጎረቤቶችህን ጠይቅ

- የጤና ማዕከላትን አገልግሎት፣ ድጋፍና ሌሎች ነገሮችን


ብትፈልግ እንኳን ልታገኛቸው የምትችላቸውን የአካባቢ ድርጅቶች
ዝርዝር ያዝ፡፡

- በድንተኛ ጊዜ የሚያስፈልጉህን የቤተሰብ፣ የጓደኞች፣ የጎረቤቶች፣


የጤና ፕሮግራም ሠራተኞች፣ የአከባቢው የጤና ቢሮ እና ሌሎች

84
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 89
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

መፍትሄ አቅራቢ ድርጅቶችን የምታገኝበትን መገናኛ ሁኔታ


በዝርዝር ያዝ፡፡

የዕለት ተዕለት የመከላከል ትግበራዎችን


አድርግ

- እጆችህን በተደጋጋሚ ታጠብ


- አይኖችህን፣ አፍንጫህንና አፍህን አትንካ

- ከታመምክ እቤትህ ውስጥ ተቀመጥ


- ስትስልና ስታስነጥስ በሶፍት ወረቀት ተሸፈን፣ ከዚያም ወረቀቱን
በቆሻሻ ማስቀመጫ አስቀምጠው
- በተደጋጋሚ የሚነኩ ነገሮችን አጽድተህ ዲስኢንፌክት
አድርጋቸው፡፡ ት/ቤት ወይም የሕጻናት ማቆያዎች ከተዘጉ የሥራ
ጊዜህን ለመቀየር ተዘጋጅ፡፡

ተግብር፡-

በአካባቢህ ወረርሽኝ ከተከሰተ ራስህንና ሌሎችን ከበሽታው ተከላከል

ትኩሳት፣ ሳል ወይም የትንፋሽ እጥረት ከተከሰተብህ እቤትህ ተቀመጥ፣


ሐኪምህንም በስልክ አናግር

የድንገተኛ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ከተከሰቱብህ በፍጥነት ሐኪም ጋር


ሂድ፡፡ ምልክቶቹም

- የትንፋሽ እጥረት

85
90
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

- የደረት የማያቋርጥ ህመም ወይም መወጣጠር


- መምታታት ወይም ለመንቃት አለመቻል

- የከንፈሮች ወይም የፊት ሰማያዊ መሆን


- ሌሎች ተጨማሪ ምልክቶችን ለማወቅ ሐኪሞችን አማክር
- በተቻለ መጠን ከታመሙ ሠዎች ራስህን አርቅ (ቢያንስ 2
ሜትር)

የቤተሰብ እቅድህን ተግብር

- የዕለት ተዕለት ትግበራዎችን መተግበርህን ቀጥልበት


- ከቤተሰብ አባላት አንዱ ከታመመ በተዘጋጀው ክፍል ውስጥ
ለይተህ አስቀምጠው
- የቤተሰብ አባል የምታስታምም ከሆነም የጥንቃቄ ምክሮችን
ተከተል፤ የራስህን ጤንነትም ተከታተል
- አዘውትረው የሚነኩ ነገሮችን ዲስ ኢንፌክት አድርግ
- የግል እቃዎችን በጋራ አትጠቀም

- ከታመምክ ከሌላ ሰዎች ጋር በስልክና በኢሜይል መገናኘትህን


ቀጥል
- በአካባቢው ስላለው የወረርሽኝ ሁኔታ በየጊዜው መረጃ ይኑረህ
- የሥራ ፕሮግራምህ ለውጥ ካስፈለገው ለአሰሪህ አስታውቅ
- የቤተሰቦችህን የስሜት(አአምሮ) ጤንነት፣ የአንተንም ጭምር
ተንከባከብ

86
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 91
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ይበልጥ ሥጋት ላለባቸው ሰዎች በተለይም እድሜያቸው ለገፋና ሥር


የሰደደ ሕመም ላለባቸው ሰዎች ተጨማሪ ጥንቃቄዎችን አድርግ

- አንተ ወይም አንድ የቤተሰብህ አባል በእድሜ የገፋ ወይም የቆየ


ሕመም ካለበት ከህዝብ ርቆ ቤት ውስጥ መቀመጥ አለበት፡፡
- ቤት ውስጥ መቀመጥ ካለብህ የበርካታ ሳምንታት መድሃኒት
እንዳለህ አረጋግጥ
- ሰው ወደተሰበሰበበት ስትወጣ ከታመሙ ሰዎች ራስህን አርቅ፣
ሌሎችም አትቅረብ

አቅድና ተዘጋጅ

- ጥሩ የእጅ ንጽህና ተግብር

በወረርሽኝ ወቅት ልጆችህን ከበሽታው ለመከላከል የሚከተሉትን ደረጃ


በደረጃ አድርግ፡-

- ልጅህ በኮቪድ - 19 ከተያዘ ለት/ቤቱ አስታውቅ

- በአካባቢህ ት/ቤቶች መዘጋታቸውን ተከታተል


- ህጻናትና ታዳጊዎች ህዝብ በሚሰበሰብበት ቦታ እንዳይሰበሰቡ
አስጠንቅቃቸው
-

87
92
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ትክክለኛው የእጅ አስተጣጠብ


የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ
አድሃናም አማካኝነት የእጅ መታጠብ ዘመቻን ሲያስጀምሩ የአስተጣጠብ
ሂደቶችን በሚከተለው መልኩ አሳይተዋልና እርስዎም ይከተሉት፤

እጅን በአግገባቡ ለማፅዳት ለ20 ሠኮንዶች


ያህል ልንከተል የሚገቡን ሂደቶች፡-

1. እጅን በውሀ ማራስና መዳፎቻችንን በሳሙና ማሸት


2. ሳሙናውን በማስቀመጥ የሳሙናውን አረፋ በመዳፍና ጣቶቻችን
እንዲሁም በጀርባ እጃችን ላይ ማዳረስ
3. በመዳፍ በኩል የእጅ ጣቶችን በማቆላለፍ በደንብ ማሸት
4. በመቀጠልም የእጃችንን የቀኝ ጀርባ በግራ መዳፋችን ማሸት ፤
የግራ እጃችንንም እንዲሁ እያቀያየርን ማሸት
5. ከዛም የእጃችንን ጣቶች ከጀርባ የሌላኛውን ጫፍ በማቆላለፍ
ማሸት
6. አውራ ጣትን ዙሪያውን እያሽከረከርን በደንብ ማሸት/ሁለቱንም/
7. የአንድኛውን እጃችንን መዳፍ በሌላኛው እጃችን ጣቶች ማሸት
(ይህንንም ማቀያየር)
8. ሙሉ እጅን እስከ ሰአት ማሰሪያ ደረስ ማሸት
9. ከዛም በንፁህ ውሀ ሳሙናውን ማጥራት
10. በመጨረሻም በንፁህ ፎጣ እጅን ማድረቅ ወይም በራሱ
እንዲደርቅ ማደረግ
88
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 93
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

11. እጃችንን ያደረቅነው በሶፍት ከሆነ በሶፍቱ ቧንቧውን መዝጋትና


ሶፍቱን በቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ
መጣል (እጃችንን ያፀዳነው በፎጣ ከሆነ ግን ቧንቧውን በክርናችን
መዝጋት)

በቤት ውስጥ ሳኒታይዘር (ማፅጃን) እንዴት


ማዘጋጀትና መጠቀም እንችላለን

የሚያስፈልጉን ነገሮችና መጠናቸው -

• 99 በመቶ አልኮል የያዘ ማፅጃ - የብርጭቆ 3/4 (ከግማሽ


በላይና ከሙሉ አነስ ያለ) ያህል
• ወይራ ዘይት - የብርጭቆ 1/4(ሩብ) ያህል
• የሎሚ ጭማቂ - 10 ጠብታ

እንዴት ማዘጋጀትና መጠቀም እንችላለን?

• ከመጀመራችን በፊት እጃቸንን በውሀና ሳሙና በደንብ መታጠብ


• ከዛም ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች በሳህን በአንድ ላይ አንድ በአንድ
መቀላቀል
• በንፁህ ማንኪያ በደንብ መቀላቀልና ማዋሀድ
• የተቀላቀለውን ውህድ ንፁህና ክዳን ባለው እንዲሁም ለአጠቃቀም
ምቹ ወደሆነ እቃ ላይ መገልበጥ
• መከደኑን እርግጠኛ መሆን
• ለአጠቃቀም ምቹ በሆነ ቦታ ላይ ማሰቀመጥ

89
94
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

እንዴት እንጠቀም?

• ያዘጋጀነውን ማፅጃ አንደኛው መዳፋችን ላይ መንፋት ወይም


ጠብ ማድረግ
• የእጃችንን ሁሉንም ክፍል ባዳረሰ መልኩ(ከላይ በውሃና ሳሙና
ስንታጠብ በተከተልነው ሂደት መሰረት) በደንብ ማሸት
• ማሸቱን ከ30—40ሰከንድ መቀጠል
• እስኪደርቅ መጠበቅ

አልኮልን እንዴት ለማፅጃነት እንጠቀምበት?

አንዳንዶች ካለማወቅ በአልኮል ይታጠባሉ፤ ይህ ትክክለኛ አይደለም፡፡


በቤት ውስጥ አልኮልን በመጠቀም እንዴት ማዘጋጀትና መጠቀም
እንደምንችል የሚከተለውን እንመልከት፡፡

1. የሚያስፈልጉ ነገሮች -
• ጥጥ ወይም የተቆራረጡ ሶፍቶች ወይም ንፁህ ጨርቆ
• 70 በመቶ(ንክኪ ላላቸው እቃዎች) ወይም 90 በመቶ አልኮል
2. እንዴት ማዘጋጀት እንችላለን---- በቅድሚያ እጅን በአግባቡ
መታጠብ
• ጥጡን ወይም ጨርቁን መቆራረጥና ማድቦልቦል
• ጥጡን ወይም ጨርቁን በንፁህና ላጠቃቀም አመቺ በሆና
ክዳን ባለው እቃ ላይ ማድረግ

90
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 95
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

• ጥጡ ወይም ጨርቁ ላይ አልኮሉን ማፍሰስ ወይም


ስንጠቀም ማፍሰስ
• እቃ ላይ ያደረግነውን መክደን (ምክንያቱም አልኮሉ ስለሚተን)

እንዴት እንጠቀም

1. እጅን በአልኮል ብቻ ለማፅዳት


• መዳፋችን ላይ አልኮሉን ጠብ ማድረግ
• የእጃችንን ሁሉንም ክፍል ባዳረሰ መልኩ(ከላይ በውሀ
ስንታጠብ በተከተልነው ሂደት መሰረት) በደንብ ማሸት
• ማሸቱን ከ20 ሰከንድ መቀጠል
• ማድረቅ

ወይም

2. በጥጥ ብቻ ማፅዳት
• ከላይ ከጥጥ ጋር ያዋሃድነውን አልኮል በተመሳሳይ መንገድ
መጠቀም እንችላለን፡፡
• አንድ አልኮል የፈሰሰበትን ትንሽ ቁራጭ ጥጥ ከላይ ካለው
እቃ ማውጣት
• የመዳፍ ፣ የጣቶችና የጀርባ እጆቻችንን ማዳረስና ማሸት
• ማሸቱን ለ20 ሰኮንድ መቀጠል
• ማድረቅ

96 91
ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

• ሌላው በቤት ውስጥ የምንጠቀምባቸውን እቃዎች ባዘጋጀነው


አልኮልና ጥጥ ወይም አልኮልና ጨርቅ ከእያንዳንዱ ንክኪ
ቀጥለን ማፅዳት ይኖርብናል፡፡

እጅ መታጠብ መቼ?

Ø ሁሉም የተጋላጭ የቤተሰብ አባላት እጅ ቶሎ ቶሎ የመታጠብ

ልማድ እንዲያዳብሩ ማድረግ

Ø እጅን ለ20 ደቂቃ መታተብ ያስፈልጋል

Ø እጅ ሲታጠቡ ቀዶ ጥገና ሲገገቡ ባለሙያዎች የሚከተሉትን

የመታጠብ ቅደም ተከተል ጠብቀው ቢሆን ይመረጣል

Ø ካስነጠሱ ፣ ካሳሉ እና ከተናፈጡ በኋላ መታጠብን

አለመርሳት

Ø ሽንት ቤት ከተጠቀሙ በኋላ መታጠብ

Ø ከመመገብ በፊት መታጠብ

Ø እንስሳትን በነኩ ቁጥር መታጠብ

Ø ህመም ያለባቸውን ሰዎች ከማገዝ እና ካገዙ በኋላ መታጠብ

Ø ጤነኛ ሰውም ቢሆን ሰላምታ ከጨበጡ በኋላ መታጠብ

Ø ትራንስፖርት፣ ገበያ እና ሌሎች አገልግሎቶችን ከተጠቀሙ

በኋላ መታጠብ አስፈላጊ ነው

ዶ/ር አቡሽ አያሌው 97


92

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

በገጠር ለሚኖሩ ዜጎች


• ምንም እንኳን በገጠር ውስጥ የሳሙና እጥረት ቢያጋጥም
እጅን ወትሮ ለልብስ ማጽጃነት የምንጠቀመው እንዶድ
በአማራጭነት መጠቀም ይኖርብናል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ
በተገለጸው መሠረት እንዶድ በመጠቀም እጆቻችንን ደጋግመን
መታጠብ ይኖርብናል፡፡ በእርግጥ በዋናነት የሚመከረው
ሳሙና መሆኑን ግን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡

• እንዲሁም በከተማ ውስጥ የሚሸጡና አልኮልና ሳኒታዘር
የመሰሉ የእጅ ማጽጃ ፈሳሽ ኬሚካሎች እጥረት ሊያጋጥም
ከቻለ በገጠሩ ክፍል ተዘውትሮ የሚጠጣው የአበሻ አረቄ
በአልኮል ምትክ በእጅ ማጽጃነት እንደ አማራጭ ልንጠቀመው
እንችላለን፡፡ አጠቃቀሙም በዚህ መጽሐፍ ውስጥ አልኮልን
ለማጽጃነት በምናዘጋጅበትና በምንጠቀምበት መልኩ ሊሆን
ይገባል፡፡ እዚህ ጋ ልብ ሊባል የሚገባው ግን ጠላ፣ ቢራ
ወይም ጠጅ የአልኮል መጠናቸው ዝቅተኛ በመሆኑ
አይጠቅሙንም፡፡

93
98
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

በቤታችን ውስጥ እንዴት የሎሚ ውሀ


ማዘጋጀት እንችላለን?

ትክክለኛውን የሎሚ ውሃ ለማዘጋጀት እንዲህ


ያድርጉ፡-

የኮሮና ቫይረስን ከመከላከል አንፃር የሞቀ የሎሚ ውሃ አዘውትሮ


መጠጣት የሚመከር ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንዶች ካለማወቅ ሎሚውን
ከውሃው ጋር በማፍላት የሚፈለገውን ቫይታሚን ሲ ያጡታል፡፡

የሚያስፈልጉ ነገሮች፡-

§ ሎሚ
§ ንፁህ የፈላ ውሀ

እንዴት እናዘጋጅ? - ከመጀመራችን በፊት እጅን መታጠብ

ü ሎሚውን ማጠብና መቆራረጥ


ü ንፁህ ሳህን ወይም ጆግ ላይ ሎሚውን መጭመቅ
ü የተጨመቀውን የሎሚ ቅሪትና ልጣጩን ሳይቀር
በጆጉ ውስጥ መጨመር
ü ከዛም ለአንድ ሙሉ ሎሚ ስምንት የፈላ ብርጭቆ
ያህል ውሀ መጨመር
ü በንፁህ ማንኪያ ማዋሀድ

94
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 99
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ü ከዚያም መክደን
ü ከደቂቃዎች በኋላ መጠቀም

ምን ያደርጋሉ?

የቤተሰብ አባል የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ቢታይበት ወይም


ምልክት ከታየበት ሰው ጋር ንክኪ ቢገጥመው ምን ማድረግ
አለብን?

ü በነፃ የስልክ መስመር 8335 ላይ በአስቸኳይ በመደወል


ማሳወቅና የህክም ና እርዳታ መጠየቅ፤
ü የህክምና ሰጪ ቡድኑ እስኪደርስ ግለሰቡን በመለየት በአንድ
ክፍል ውስጥ ለብቻ ማቆየት፤
ü የለየነውን ክፍል በር መዝጋት/መክፈት፤ (ነገር ግን አየር በደንብ
የሚዘዋወርበት መሆኑን እርግጠኛ መሆን ወይም መስኮት
መክፈት) ፤
ü ንክኪዎችን ማስቀረት፤
ü ራስን መጠበቂያ(መከላከያዎችን) ማለትም የፊት ጭንብል
እንዲሁም ጓንት መጠቀም፤
ü ከተጠርጣሪው ክፍል የሚወጡ ቆሻሻዎችን ከቤቱ ቆሻሻዎች ጋር
ከመቀላቀላችን በፊት ለይተን ቢያንስ ለ72 ሰአታት ማቆየት
ይኖርብናል ፤
ü ግለሰቡ የተጠቀመበትን ሶፍት ወይም መሀረብ ክዳን ባለው
የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ ማስወገድ፤

95
100
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ü የተጠቀንምንባቸውንና የነካካናቸውን እቃዎች በሳሙናና ውሀ


ማፅዳት
ü የተቀረው የቤተሰብ አካል እጆቹን በውሃና ሳሙና (በአልኮል
ማጽጃ) ቶሎ ቶሎ እንዲታጠብ ማድረግ፤
ü ከግለሰቡ የተለየ ማብሰያ እንዲሁም መፀዳጃ ቤት መጠቀም፤

ዶ/ር አቡሽ አያሌው 101 96



ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የኮሮና ቫይረስ ጥብቅ መከላከያ እና


ማስጠንቀቂያዎች!!
1. አፍን እና ጉሮሮውን ከመድረቅ መጠብቅ፣ በየ 15 ደቂቃ ለብ ያለ
ውሃ መጎንጨት የሚመከር ነው ፡፡ ምክንያቱም ቫይረሱ ወደ አፍ
ቢደርስ እንኳን ውሃው ቫይረሱን አጥቦት ወደ ጨጓራ
ይወስደዋል፡፡ ቫይረሱ እዚህ ላይ ከደረሰ የጨጓራ አሲድ ቫይረሱን
ያጠፋዋል፡፡ በቂ ውሃ ካልተጠጣ ግን ቫይረሱ ወደ ጨጓራ
በመሄድ ፈንታ ወደ መተንፈሻ አካላት ፣ ወደ ሳንባ የመዛመት
እድል አለው፡፡
2. ይህ አዲሱ ቫይረስ ሙቀትን መቋቋም የሚችል አይደለም፡፡ ከ26-
27 ዲግሪ ሙቀት ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡ ጸሀይንም አይቋቋምም፡፡
ስለሆነም አካባቢን ከቅዝቃዜ መጠበቅ ይመከራል፡፡
3. አንድን ሰው ካስነጠሰው ከ20 ጫማ በላይ ቫይረሱ እርቆ
አይሄድም፡፡ ቫይረሱ አየር ወለድ በሽታ ጀምሮ አይደለም፡፡ ነገር
ግን በዚህ ቅርበት ላይ በተደጋጋሚ የሚያስነጥስ ወይም
የሚያስለው ከሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በተለይ የችግሩ
ባለቤት የሆነው ሰው የፊት ማስክ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
4. ቫይረሱ ብረት ነገር ላይ ካረፈ እስከ 12 ሰዓታት ሊቆይ ይችላል፡፡
በመሆኑም ነገሮችን ከጨበጥን በኋላ ፈጥነን እጃችንን በሳሙና
እና ውሃ ብንታጠብ፣ ይህ ከሌለን ደግሞ እጃችንን በኬሚካል
ብናጸዳ ቫይረሱን እናጠፋዋለን፡፡
5. ቫይረሱ በትንፋሽ የሚተላለፍ በመሆኑ የእርስ በእርስ መራራቅን
97

102 ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

በሁለት እርምጃ ልክ ወይም በሁለት ሜትር ርቀት በመተባበር


ይነጋገሩ ወይም ይሰለፉ
6. በፕላስቲክ ነገሮች ላይ ቫይረሱ ከ 6- 12 ሰኣታት ሊቆይ ይችላል፡፡
በመሆኑም መሰል እቃዎችን ነክተን ስንገባ አሁንም የተለመደው
ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

7. ቫይረሱ የላውንደሪ ዲተርጀንቶችን አይቋቋምም፡፡ በዲተርጀንት


እቃዎችን፣ ነገሮችንና እጃችንን ማጽዳት የሚያስፈልገው ለዚህ
ነው፡፡

8. ትኩስ ውሀ መጠጣት ለኮቪድ 19 ብቻ ሳይሆን ለብዙ ቫይረሶች


ፍቱን ነው፡፡ ፈሳሾችን በበረዶ ላለመጠጣት መሞከር መልካም
ነው፡፡ ይህ ለቫይረሱ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

9. ቫይረሱ እጃችን ላይ ሊቆይ የሚችለው ከ5- 10 ደቂቃ ነው፡፡ በዚህ


ደቂቃ ውስጥ ግን ብዙ ነገር ሊገጥመን ይችላል፡፡ አፍ እና
እፍንጫ ሊነካ ይችላል፡፡ ስለሆነም በተደጋጋሚ እጅ በሳሙና
መታጠብ አስፈላጊ ነው፡፡

10. በጨው ለብ ባለ ውሃ አፍን መጉመጥመጥ ሌላው ጠቃሚ ነገር


ነው፡፡ በዚህ ጊዜ
Ø አንደኛ ቫይረሱ ትኩስ ውሃ መቋቋም ስለማይችል ይሞታል
Ø ሁለተኛ ዉሃው ቫይረሱን ያጥበዋል
11. ማህበራዊ መገለልን ይተግብሩ
98
103
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

Ø እጅግ ተጋላጭ የሆኑ ትምህርት ቤቶችን መዝጋት፣


Ø የስራም ሆነ የተለያዩ ማህበራዊ ግንኙነቶችን እና ስብስቦችን
መቀነስ፣
Ø ህዝባዊ እና ሀይማኖታዊ ባዕላትን አደባባይ ላይ አለማክበር
Ø ብዙ ህዝብ የሚያስተናግዱ ስፖርቶችን መቀነስ
Ø እጅግ አስፈላጊ ያልሆኑ ትራንሰፖርቶችን መቀነስ
12. ጉዞ እጅግ አንገብጋቢ ካልሆነ በቀር የቫይረሱ ስርጭት ወደ ባሰባቸው
ሀገራት ሆነ ከሌሎች ጉዞ አያድርጉ

የጓንት አጠቃቀም
አንድ ጊዜ ተጠቅመን የምናስወግድ ጓንት ማድረግ
Ø ጓንቶች ጥቅም ላይ ከዋሉ በኋላ በጥንቃቄ ማስወገድ
Ø ኮቪድ 19 ለማጽዳት የተጠቀምንበትን ጓንት ለሌላ ነገር
አለመጠቀም
Ø ጓንት ባጠለቅንበት እጃችን ፊታችንን ፈጽሞ አለመንካት
Ø ያወለቅነውን ጓንት ክዳን ባለው ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ
ማስገባት
Ø ጓንቱን ካወለቅን በኋላ እጃችንን በውሃና በሳሙና መታጠብ
ወይም በአልኮል መወልወል

99
104 ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የማስክ አጠቃቀም፡-
ማስክ ማድረግ የሚያስፈልገው መቼ ነው፣ ማነው?
የቫይረሱ መጠን በአንጻሩ ትልቅ የሚባል ስለሆነ ማነኛውም ማስክ
ቫይረሱን እንደሚከላከል በተለይ ቻይና ላይ ተተደረጉ ጥናቶች
ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ሰው ማስክ ማድረግ አይጠበቅበትም፡፡

ሁልጊዜ ማሰከ መጠቀም ጠቃሚ ካለመሆም በተጨማሪ የአተነፋፈስ


ስርዓትን በማጨናነቅ ተገቢው የትንፋሽ ዝውውር እንዳይኖር
ስለሚያደርግ ይህ ልማድ አይመከርም፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ማስክ ማዘውተር አላስፈላጊ የማስክ እጥረት


ስለሚያስከትል ማስኩ ለሚያስፈልገው አካል እንዳይደረስ ያደትጋል፡፡
ለሚያስፈልገው አካል ካልደረሰ ደግሞ ከዚህ የተነሳ የበሽታው
ስርጭት ሊጨምር ይችላል፡፡

እናም ማስክ ለሚከተሉት አካላት ብቻ ተለይቶ ጥቅም ላይ ቢውል


ይመረጣል፡፡

ትኩሳት ፣ ሳል እና ማስነጠስ ካለ ወይም በተደጋጋሚ ይህ ምልክት


ካለባቸው ሰዎች ጋር የሚቀርቡ ከሆነ ማስክ ማድረግ ይመከራል፡፡

በመሆኑም
1. የኮቪድ 19 ታካሚዎችን የሚንከባከቡ ባለሙያዎች ወይም
ቤተሰቦች
በቫይረሱ የተያዙ ወይም የተጠረጠሩ

100
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 105
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ማስክ ለሁሉም ሰው ቅድመ - መከላከያ


አይሆንም የሚባለው በሚከተሉት ምክንያቶች
ነው፡፡

በርግጥ ከቫይረሱ ማስክን የማለፍ እድል አለመኖሩ ጋር ተያይዞ ሀሳቡ


የሚጋጭ ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን መልዕክቱ ይህ ነው፡፡ ኮቪድ
19 አይር ወለድ በሽታ አይደለም፡፡ አይር ላይ ተንሳፎ የሚቆይ
አይደለም፡፡ ከተያዘው ሰው በተለያዬ መልኩ ሲወጣ በቀጥታ ወደ
መሬት ወይም ወደ እቃዎች ይወድቃል፡፡

ከሁለት ሜትር በላይ እርቆ መሄድ አይችልም፡፡ ማስኩን ህመሙ


ያለባቸው ሰዎች ቢጠቀሙት የሚወጣውን ቫይረስ ይዞ እዛው
ያስቀረዋል፡፡ በመሆኑም ቫይረሱ ነገሮች ላይ እንዳይወድቅ ወይም
አጠገቡ ካለው ሰው ላይ እንዳያርፉ ያደርጋል፡፡ በዚህም ቫይረሱን
ስርጭት መግታት ይቻላል፡፡

አንድ ሰው ምንም በሌለበት ሁኔታ ማስክ ቢጠቀሙ ግን አላስፈላጊ


እጥረት ከመፍጠር ውጭ የሚገኝ ትርፍ የለውም፡፡

ይህ እንዳለ ሆኖ ማስክ መጠቀም ብቻውን ቫይረሱን ለመከላከል


ዋስትና አይሆንም፡፡ የማስኩን አጠቃቀም በሚገባ ማወቅም
ያስፈልጋል፡፡ ይህም ማስኩ እንዳለ ሆኖ የእጅ እና የአፍ፣ የአፍንጫ፣
የአይን ንክኪ የሚኖር ከሆነ ቫይረሱ በዚህ ንክክ ማስኩን አልፎ
ሊተላለፍ ይእላል፡፡ በየ ጊዜው ማስክን ማጽዳት ወይም መቀየር
ሌላው የሚመከር ነገር ነው፡፡
106 ዶ/ር አቡሽ 101
አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

እነዚህ እርምጃዎች ሁሉ አንድ የኮቪድ 19 ታማሚ ሆስፒታል


ከመድረሱ በፊት ሊወስዳቸው የሚገቡ ናቸው፡፡

የተለዩ የማህበረሰብ ክፍሎች

እነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች ለኮቪድ - 19 በተለዬ ሁኔታ ተጋላጭ


የሆኑት ሲሆኑ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡፡

1. በጤና ተቋምም ሆነ በሌላ ቦታ የኮቪድ 19 ታካሚዎችን


የሚያግዙ ባለሙያዎች ወይም
2. የቫይረሱን ታማሚ የሚንከባከቡ የታማሚ ቤተሰቦች
3. በእድሜ የገፉ ሰዎች
4. ተጨማሪ በሽታ ያለባቸው ሰዎች
5. በተለያየ ምክንያት የሰውነትን በሽታን የመከላከል አቅም
የሚያዳክሙ መድሃኒቶችን የሚወስዱ ሰዎች
እነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡
በመሆኑም ከሌላው ማህበረሰብ በበለጠ መከላከሉ ላይ ትኩረት ማድረግ
ይኖርባቸዋል፡፡ ለምሳሌ ተጨማሪ በሽታ ያለባቸውና በእድሜ የገፉ ሰዎች
ከሌሎች ይልቅ ለቫይረሱ የሚያጋልጡ ትራንስፖርቶችንና ሌሎች
መተላለፊያ መንገዶችን መቀነስ ወይም ማስወገድ ይኖርባቸዋል፡፡
ይህ ብቻ ሳይሆን እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ማነኛውም አይነት
መከላከያ መሳሪያ ከሌላው ማህበረሰብ ይልቅ ቅድሚ ማግኘት እና
መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡

102
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 107
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ለምሳሌ ህሙማንን የሚያግዙ ባለሙያዎች እና ሌሎች የተሟላ መከላከያ


መሳሪያ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚህ መከላከያ መሳሪያዎችም
የሚከተሉት ናቸው፡፡

Ø ጋወን
Ø የፊት ማስክ
Ø ጓንት
Ø መከላከያ መነጽር

መሳሪያዎቹ የሚያግዙት ባለሙያው እራስን እንዲከላከል ብቻ ሳይሆን


ቫይረሱን ከአንዱ ወደ ሌላ እንዳያስተላልፍ ጭምር ነው፡፡

103
108
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር


የዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም ምክሮ
መንግስታት በፍጥነት እና በቁርጠኝነት አቅማቸውን እንዲተገብሩ
ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ ብዙ ሀገራት ላይ ኬዞችን እያየን ቢሆንም
ከፍተኛ ትኩረታችንን ያደረግነው ቁጥራቸው እየጨመረ በመሄድ ላይ
ያሉትን እና የመከላከል አቅማቸው የተዳከመባቸው ሰዎች ጭምር
ሪፖርት የተደረጉባቸውን ሀገራት ነው ::

ይህ አይነት ስርጭት ለሁሉም ሀገራት፣ ደሀም ሆኑ ሀብታም ለሁሉም


እስጊ ነው፡፡ የበለጸጉ ሀገራትም አስደንጋጭ ሁኔታን መጠበቅ
ይኖርባቸዋል፡፡

አንዳንድ ሀገራት ይህን ችግር አሳሳቢ አድርገው አላዩትም ወይም ምንም


የሚያደርት ነገር እንደሌለ እራሳቸውን አሳምነው ተቀምጠዋል፡፡

በአንዳንድ ሀገራት ላይ የሚታየው የፖለቲካ ቁርጠኝነት መጠን እና


ትግበራ መሬት ላይ ካለው የችግሩ አሳሳቢነት ጋር አለመመጣጠኑ
ያሳስበናል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ተስፋ የምንቆርጥበት ጊዜ አይደለም

ይህ ለችግሩ ይቅርታ የምናደርግበት ጊዜ አይደለም

ይህ ማቆሚያ ገመዶችን ሁሉ የምንስብበት ጊዜ ነው፡፡

104
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 109
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ሁሉም ነገር በእጃችን ላይ ነው

ማህበረሰቡን አስተምሩ፣ ምልክቶች ምን እንደ ሚመስሉ እና እንዴት


እራሳቸውን እና ሌሎችን ሰዎች መከላከል እንደሚችሉ መረጃ ስጧቸው፡፡

• የምርመራ አቅማችሁን አሳድጉ፤


• ሆስፒታሎቻችሁን ዝግጁ አድርጉ፤
• አስፈላጊ ግብዓቶች ሁሉ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጡ፤
• ኬዞችን መለየት እንዲችሉ፣ታማሚዎችን ማከም
እንዲችሉ፣እራሳቸውን እንዴት መከላከል እንደሚችሉ የጤና
ባለሙያዎቻችሁን አሰልጥኑ፤
• ሀገራት ኬዞችን በትክክል መለየት ከቻሉ፣ ህሙማንን ከሌላው
መነጠል እና ማከም ከቻሉ፤
• ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ተከታትለው መመርመር ከቻሉ የቫይረሱን
አካሄድ መቀየር ይቻላል፡፡
• ምንም ማድረግ የምችለው ነገር የለም ብለን ዝም ካልን
እራሳችንን ነው የምንገድለው፡፡

ከመፍራት በእውቀት ላይ ተመስርቶ መጠንቀ

ሰዎች እንደፈሩ እናውቃለን፡፡ ይህ ትክክል እና መሆን ያለበት ነው፡፡


ፍርሃቱ ግን በትክክለኛ መረጃ መታገዝ አለበት፡፡

105

110 ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ፍርሃት በጣም ካስቸገራችሁ በዙሪያችሁ ወዳሉት ነገሮች ተመልከቱ፡፡


የማህበረሰቡ የድንገተኛ ምላሽ ምን እንደሆነ እወቁ፣ እገዛም አግኙ፡፡ ብዙ
የማናውቀው ነገር አለ፡፡ ነገር ግን በየቀኑ አዳዲስ ነገሮችን እየተማርን
ነው፡፡ የእውቀታችንን ክፍተት ለመሙላት በየሰአቱ እየሰራን ነው፡፡ የዚህ
ቫይረስ ገዳይነት የሚመሰረተው በራሱ በቫይረስ አይደለም፡፡ እኛ ለቫይረሱ
በምንሰጠው ምላሽ ነው፡፡ ይህ በሽታ አደገኛ ነው፡፡ ለብዙ ሰዎች ገዳይ
አይደለም፤ ቢሆንም ግን መግደልም ይችላል፡፡ ሁላችንም ለቫይረሱ
የመያዝ እድላችንን ለመቀነስ ሀላፊነት አለብን:: ከተያዝን ደግሞ
ለሌሎች ላለማጋራት ሀላፊነት አለብን፡፡

የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሁላችንም ማድረግ የምንችለው ነገር


አለን፡፡ ይህ አደጋ የተደቀነው ለአንድ ሀገር ወይም ለአንድ ሰው ብቻ
አይደለም፡፡ ሁላችንም የዚህ ችግር ሰለባ ነን፡፡ ህይወትን የምንታደገውም
በጋራ ስንተባበብር ብቻ ነው፡፡

በድፍረት ሁሉም ሀገራት ቫይረሱን ስርጭት


ይቀለብሳሉ ብለን ለመናገር እንደፍርም

ቫይረሱን በትክክል መመርመር፣ መከላከል፣ ማከም እና ሰዎችን መለየት


የቻሉት ሀገራት ግነ ሊቀለብሱት ይችላሉ

በርካታ ሀገራት ቫይረሱ እንዲቀንስ እና በቁጥትር ስር እንዲሆን


ለማድረግ ችለዋል::

የተወሰኑት ሀገራት ደግሞ ቫይረሱን ለመቆጣጠር አቅም አጥተዋል፡፡

106
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 111
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ልንጠቀምባቸው የሚገቡ ወሳኝ መፍትሔዎች

• በቅድሚያ ዝግጁ እንሁን፤


• በማስቀጠል ቫይረሱን እንለየው፣ እንከላከለው፣ እናክመው፤
• ሶስተኛ የቫይረሱን ስርጭት እንቀንሰው፤
• አራተኛ ምርምር እና ትምህርት እንውሰድ፤
• ሁሉም ሀገራት የድንገተኛ ምላሽ መስጫ ተቋማትን እንዲያዘጋጁ
ለማስታወስ እፈልጋለሁ፡፡
• ከህዝቦቻችሁ ጋር ስለ አጋላጭ መንገዶች እና መከላከያ ዘዴዎች
እንድትመክሩ አሳስባለሁ::

• ቫይረሱን አግኙት፣ ለዩት፣ አክሙት፣ ንክኪ ያላቸውን ሰዎች


ለዩ፡፡

107
112
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

አለምን ከወረርሽኝ ፍርሃት ወደ


ብርሃንና ተስፋ የወሰዱ ዓለም
አቀፋዊ ኹነቶች፣
ከኢትዮጵያ እስከ ቻይና፣ ከጣልያን እስከ ብራዚል፣ ኮሮና ቫይረስ
በተገኘባቸው አገራት ያሉ በዕድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች ከዛሬ ነገ በቫይረሱ
እንያዝ ይኾን ወይ በሚለው ስጋት በተወጠሩበት ሰሞን ነበር ከቻይናዋ
ዉሃን ግዛት ለየት ያለ ዜና የተሰማው። የአንድ መቶ ሶስት አመት
ዕድሜዋ ወይዘሮ ዛኅግ ጉዋንፌን ከኮሮና ኢንፌክሽን አገግመው
ከሆስፒታል ሲወጡ የሚያሳየው ፎቶና ቪዲዮ በቲቪና በማህበራዊ ሚዲያ
ገፆች ሲታይ ተስፋ ተበሰረ። የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመ
ስለሚኾን ቫይረሱ በዕድሜ የገፉት ሰዎች ላይ ይበረታል የሚለውን
የሃኪሞች መግለጫ ገሸሽ ያደረገ የመሰለው የ103 አመቷ አዛውንት ጤና
መመለስ ብዙ የህመም ፣ ሞት እና ጭንቀት ዜናዎች መካከል የፈነጠቀ
ብርሃን ተደርጎ በብዙ የዜና ማሰራጫዎች ተስተጋብቷል። ሃሳብና ሃዘን
ጫን ባለው የኮሮና ሰሞን የተሰሙ ብርሃን የሚሰጡ ሌሎች ወሬዎችና
ልብ የሚያሞቁ የሳይንሱ ዓለም ግኝቶችም ፣ በተለይ ከኮሮና ክትባት ጋር
የተያያዙት ዘገባዎች ጥቂት አይደሉም።

የኮሮና ህመምና ሞት የቀነሰባቸው አገራት

የወረርሽኙ ጅማሬ በታየባት ቻይና ለቀናት አዲስ ታማሚዎች


አልተመዘገቡም። ይህን ከፍተኛ ውጤት ያሳካችው ቻይና ለኮሮና ብላ
የገነባቻቸውን ሆስፒታሎች የዘጋች ሲኾን፣ ሰዎች ወደመደበኛ እንቅስቃሴ
108
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 113
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የሚመለሱባቸውን የተወሰኑ የስራ ዘርፎችም እየከፈተች እንደኾነ


አለምአቀፍ ዜና ማሰራጫዎች ዘገባዎችን ሰርተዋል። ብዙ ታማሚዎች
ስትመዘግብ በነበረችው ደቡብ ኮሪያ ከህመሙ የሚያገግሙት ሰዎች ቁጥር
ከአዳዲስ ታማሚዎች በብዙ ቁጥር እየጨመረ መኾኑም ደስታ ፈጥሯል።

የክትባትና መድሃኒት ተስፋዎች

በበርካታ አገራት እየተሞከሩ ያሉ የክትባት ሙከራዎች ተስፋ ሰጪ


ውጤት እያሳዩ መኾኑ በታማሚዎች ላይ ብቻ ሳይኾን ለወዳጅ ዘመዶችም
የተስፋ ዜና ኾነው ታይተዋል። በካናዳ ሳይንቲስቶች የኮሮና ቫይረስ ኮፒን
መስራት ችለዋል። ይህ አንዱ ክትባት የመስራት ሂደትን የሚረዳ
መልካም ዜና ነው ተብሎ ተዘግቧል።ቻይና ከዚህ አልፋ አምስት የክትባት
አይነቶችን እየሞከረች ሲኾን እስራኤልም በተመሳሳይ ክትባት የማግኘት
ሙከራዋን ተያይዛለች። በአሜሪካ የካይሰር ኢንስቲትዩት ደግሞ ሙከራ
ተጀምሯል ሲል ኒዎዮርክ ታይምስ ፅፏል።

አውስትራሊያ ውስጥ ደግሞ የኮሮና ቫይረስን እንደሚያድኑ ተስፋ


የተጣለባቸው ሁለት መድሃኒቶች በሙከራ ሂደትላይ መሆናቸው
ተሰምቷል። ሜትሮ ሄልዝ የተባለ በአሜሪካ የሚገኝ የላቦራቶሪ
መመርመሪያ ቅመም አምራች ኩባንያ ደግሞ ለኮቪድ -19 መመርመሪያ
የሚያገለግል ፈጣን ኪት ማምረቱ ሲዘገብ ነበር። ይህ መመርመሪያም
ውጤት የሚወጣበትን ሰዓት ወደ ሁለት ሰዓት ያሳጥራል ሲል ላይቭ
ሳይንስ ገፅ ፅፏል። ይህ በሆነ ጥቂት ቀናት ልዩነት ደግሞ የኦክስፎርድ
ዩኒቨርሲቲ ባለሞያዎች የኮሮና ቫይረስ ውጤትን በሰላሳ ደቂቃ
የሚያሳውቅ መመርመሪያን አግኝተናል ብለዋል። ፋቪፒራቪር የተሰኘ

109
114
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ጠንከር ላለ ጉንፋን የሚታዘዘው መድሃኒት ኮሮና ቫይረስን በማከም


ውጤት ማሳየቱም ከጃፓን ተሰምቷል።

ጥበብ በጭንቅ ወቅት…

የወሰርሽኙ ከፍተኛ ጫና ከአቅሟ በላይ የሆነባት ጣልያን የሰዎችን


እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ መገደብ ግዴታ ሆኖባት ፣ ጣልያናውያን
በየቤታቸው መዋል ከጀመሩ ሰንብተዋል። ይህ የኑሮ መልክ ከፍ ያለ
ድብታ ውስጥ የከተታቸው የጣልያን ሙዚቀኞች የሙዚቃ መሳሪያዎችን
ይዘው በየመስኮቶቻቸው ብቅ እያለ መጫወትና ሌሎችን ማዝናናቱን
ተያይዘው ታይተዋል። የሳክስፎን ጨዋታዎቹን የተመለከቱ የማህበራዊ
ሚዲያ ተጠቃሚዎች የተቀረፁ ቪዲዮዎችን ሲቀባበሉ ሰንብተዋል።
በሌሎች የአለም ክፍሎችን የሙዚቃና ሌሎች የጥበብ ስራዎችን በተከለሉ
አካባቢዎች በርቀት ኾነው ሲያቀርቡም ታይተዋል። እነዚህ ስራዎችም
በማህበራዊ ሚዲያው እየተጋሩ ብለበርካቶች የብርታትና ስነልቦና ድጋፍ
ምንጭ ኾነዋል።

ለሰዎች መድረስና ትብብር

የኮሮና ቫይረስ በተከሰተ ሰሞን ጉዳዮን አቅልለው ያዩና ቸል ያሉ አገራት


አለምአቀፍ ትብብርን እየፈለጉ እና አብረን ካልሰራን ይህን ቀውስ
አንፈታውም የሚሉ መልዕክቶችን ለተለያዩ አገራት፣ የንግድ ኩባንያዎችና
ለተቀረው የህብረተሰብ ክፍል ማቅረባቸው ሲዘገብ ሰንብቷል።
በስግብግብነት በዚህ ሰሞን ትርፍ ፍለጋ የተለያዩ ምርቶች ዋጋ ላይ
ከፍተኛ ጭማሪ ካደረጉ ጥቂት የንግድ ሰዎች በተቃራኒው አስፈላጊ

110
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 115
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የበሽታ መከላከያ አቅርቦቶችናና ምግቦችን ጭምር ከየቤታቸው መውጣት


ለማይችሉ የሚሰጡ፣ ሌሎችን ሲደግፉ የሰነበቱ ግለሰብና ድርጅቶችን
ማየት ከፍ ያለ የስነልቦና ድጋፍ ሆኖ ተመዝግቧል። በተለይ በአሜሪካ
ብዙ አካባቢዎች ይህ የመተሳሰብ ድርጊት መታየቱ ተዘግቧል። የእንግሊዝ
ቀይ መስቀል ደግሞ ለኮሮና ምላሽ የመስጠት ስራውን ለማገዝ ከ10, 000
በላይ ሰዎች በበጎ ፈቃድ ሰራተኝነት መመዝገባቸውን ተናግሯል።

የመዝናኛው ኢንዱስትሪ ድጋፍ

የእንግሊዙ የእግር ኳስ ክለብ ቼልሲ በስታምፈርድ ብሪጅ የሚገኘውን


ሆቴሉን ለኮሮና ቫይረስ ምላሽ ለመስጠት ለሚለፉት የአገሪቱ የብሄራዊ
ጤና ኢንስቲትዩት ሰራተኞች ማረፊያ እንዲኾን ፈቅዶ መስጠቱን
ቴሌግራፍ ጋዜጣ ዘግቧል። ዘፋኝና ተዋናዩ ጀስቲን ቲምበርሌክ
በሚኖርበት አካባቢ አቅም ለሌላቸው ምግብ የሚያቀርበውን የምግብ ባንክ
በገንዘብ አግዟል። ጀስቲን ቢበር ደግሞ ድጋፉን የወረርሽኙ ዋና ጥቃት
ለደረሰባት ቻይና ልኳል። ከገንዘብ ድጋፍ ባለፈ መንፈስን የሚያበረቱ
የፈጠራ ሰዎች ጋር በትብብር ስራ በመስራት ሰዎችን የማረጋጋትና መረጃ
የመስጠት ስራ የሚሰሩ የመዝናኛው ኢንደስትሪ ሰዎችም ታይተዋል።
አሜሪካዊቷ ተዋናይት ጄኒፈር ጋርነር በዚህ መሰሉ ስራ ከተሳተፉት
መካከል ትጠቀሳለች።

111
116
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ይህን ያውቃሉ?

ኮሮና ቫይረስ በእድሜ በገፉት ሰዎች


ላይ ለምን አደጋው ይጨምራል?
ስናረጅ በሽታ የመከላከል አቅማችን ይወርዳል፡፡ ይህ ደግሞ በቀላሉ
ለተለያዩ ህመሞች በቀላሉ እጅ እንድንሰጥ ያደርገናል፡፡ በተለይ
የመተንፈሻ አካላት ህመሞች፣ ኢንፍሎዌንዛ እንዲሁም የሳንባ ምች
በእድሜ በገፉ ሰዎች ላይ የተለመዱ ህመሞች ናቸው፡፡ ኮሮና ቫይረስ
ደግሞ የሳንባ ምች ሊያመጣ የሚችል አንፍሎዌንዛ መሰል የመተንፈሻ
አካል ህመም አምጪ ጀርም በመሆኑ በተለይ እድሜያቸው በገፉ ሰዎች
ላይ አደጋው የበለጠ ይጨምራል፡፡

እንደ ሳይንቲስቶች ጥናት ቫይረሱ ወደ አደገኛ ደረጃ በዚህ እድሜ


የሚሸጋገርባቸው ሦስት ዋና ዋና ምክንያቶች የሚባሉት የመጀመሪያዎቹ
ቫይረሶችን በዋና ተከላካይነት የሚታወቀው ‹ ቲ-ሴል› በመባል የሚጠሩት
የሰውነት ልዩ ኮማንዶዎች እድሜ ሲገፋ ቁጥራቸው ስለሚቀንስ ነው፡፡
‹ ‹ ታይመስ› › በመባል የሚጠራው የቲ-ሴል አምራች እጢ እድሜ በገፋ
ቁጥር እየሟሟ አቅሙ በመዳከሙ የተነሳ ነው፡፡ እንዲሁም የተለያዩ
የነጭ የደም ህዋሳት በማምረት ትልቅ ሚና የሚጫወተውም የአጥንታችን
መቅኒ እድሜ በገፋ ቁጥር በሚፈለገው ደረጃ የማምረት ብቃቱ እየቀነሰ
የሚሄድ በመሆኑ ነው፡፡

112
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 117
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

በተጨማሪም አንድን ህመም ለመቋቋም ውስጣዊ የሰውነት ክፍሎች


አቅም ብቃት ወሳኝ ነው፡፡ እድሜ ሲገፋ ግን ብዙ የሰውነት ክፍሎቻችን
አብረው ስለሚያረጁ እንደ ኮሮና ቫይረስ ሀመምን ተቋቁሞ ለመቆየት
ይቸገራሉ፡፡ ለዚያም ነው ብዙውን ጊዜ እርጅና ሲመጣ ልዩ ልዩ ህመሞች
ተያይዘው የሚመጡት፡፡

113
118
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ለኮሮና አይበገሬ የሰውነት


መከላከያን ማዳበሪያ ስምንቱ ሁነኛ
ስልቶች
የጤና ባለሞያዎች በሚመክሩት መሰረት እጅዎን አዘውትረው በውሃና
በሳሙና እየታጠቡ ነው? የተፋፈጉ ቦታዎች መገኘትንስ ቀንሰዋል? ይህ
ጥሩ የኮሮና ቫይረስ በሽታን -ኮቪድ 19 - መከላከያ ዜዴ ነውና ደግ
አድርገዋል ። ሌሎች የበሽታ መከላከል አቅምዎን የሚገነቡ ሳይንሳዊ
መንገድና ስትራተጂዎችስ ይኖሩ ይኾን? የተለያዩ ባለሞያዎችን ምክሮችና
ጽሁፎች ተመልክቶ ዮሴፍ ጥሩነህ ተከታዮቹን ዘዴዎች ቢተገብሯቸው
ያለበትን ሃተታ እነሆ።

የእንቅስቃሴ በረከት
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሰው ልጅ ኑሮን ለማሸነፍ ጥረት ከጀመረበት
ጊዜ አንስቶ ልምድ ያደረገው፣ ግን ደግሞ በጊዜ ብዛትና እንቅስቃሴን
ገዳቢ የስራ መስኮች በመበራከታቸው እየገታው የመጣ የሕይወት ዘዬ
ነው። ዛሬ ላይ ግን በመንቀሳቀሻ ማሽኖች እና በሃኪም ምክር ታጅቦ
በጥቂቶች ብቻ የሚደረግ ዘመነኛ ጉዳይ ሆኗል። ሳይንሳዊ ጥናቶችም
እንደኮሮና ያሉ ጉንፋን መሰል በሽታዎችን ለመዋጋት እንቅስቃሴ ወሳኝ
ነው እያሉ ነው። በብሪቲሽ ጆርናል ኦፍ ስፖርት ሜዲስን የጥናት
መፅሄት በቅርቡ የወጣውና አንድ ሺህ ሰዎች የተሳተፉበት ጥናት ይህንኑ
አሳይቷል። በጥናቱ የተሳተፉትና በሳምንት አምስት ቀናት እንቅስቃሴ
የሚያደርጉ ሰዎች ብዙ ሰዓት በሚያስቀምጥ የኑሮ ዘዬ ካላቸው ጋር
ሲነፃፀር በቫይረስ ነክ ጉንፋኖች የመጠቃት አጋጣሚያቸው 50 በመቶው

114
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 119
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ቀንሶ ታይቷል። ለዚህ ባለሞያዎቹ የሚሰጡት ምክንያት ሰዎች


እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በሽታ ተከላካዮቹ የነጭ የደም ህዋሳትና ጸረ
ተዋህሶቹ አንቲቦዲዎች በደም ስርዓት ውስጥ እንደልብ የመንሸራሸር እና
በሽታን የመዋጋት አቅማቸው የሚያድግ መሆኑን ነው። መንቀሳቀስ
የውጥረት ሆርሞኖችም በሰውነት እንዳይመነጩ በማገዝ ህመምና
ጭንቀትን ይቀንሳል።

እንቅስቃሴው የእግር ጉዞን ሊያካትት ይችላል። በተለይ ለኮሮና ቫይረስ


አጋላጭ ከኾኑ ምክንያቶች አንዱ የኾነው በተፋፈገ ሁኔታ ውስጥ
መቆየትን ለማስወገድ ከአውቶብሶች፣ ባቡርና ታክሲ ይልቅ እየተጫወቱ
በእግር መጓዝ በእጅጉ ይመከራል።ታዲያ እንቅስቃሴ እንደየዕድሜና የጤና
ሁኔታ የተመጠነ መኾን አለበት። አለዚያ ጉዳቶችን ሊያስከትል ይችላል።
በአማካይ በሳምንት ከ 3 - 5 ቀን ለ 30 ደቂቃ የሚደረግ እንቅስቃሴ
ተመካሪ ነው።

ምግብዎ - ዋስትናዎ!
የሰውነትን የበሽታ መከላከል አቅም ከሚወስኑ ጉዳዮች መካከል
የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው አመጋገብ መኾኑን በሃርቫርድ ሄልዝ
ሪቪው መፅሄት ሃሳባቸውን ያጋሩት ዶ/ር ዩፋንግ ሊን ያስረዳሉ። በቂ
ምግብ ማግኘት ፈተና ለሆነባትና መቀንጨር እስከ 35 በመቶ የሚደርሱ
ህፃናቷ ችግር ለሆነባት ኢትዮጵያ ይህ የበሽታ መከላከል አቅም መገንቢያ
አማራጭ ፈታኝ ይመስላል። ይኹንና የምግብ መጠኑ ብቻ ሳይኾን
ይዘትና ቅንብሩ ከብዙ አገሮች የተሻለ እና ተፈጥሯዊ ይዘቶችን ያማከለ
መኾኑ እንደጥንካሬ ይታያል።

120 115
ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የበሽታ መከላከልን የሚያጠናክሩትና ፀረ ባክቴሪያ ጠባይ ያላቸው እነ ነጭ


ሽንኩርት፣ ባለብዙ ማዕድኑ ጤፍ እና ሌሎችም ኢትዮጵያዊ ምግቦች
ውስጥ የሚታወቁ ግብዓቶች አስተዋፅዖዋቸው ቀላል አይደለም። ዋናው
ጉዳይ ሚዛን ከመጠበቁ ላይ እንደኾነ ባለሞያዎች ያስረዳሉ። ቫይታሚን
ሲ፣ ዚንክ ማዕድን እንዲሁም አንቲኦክሲዳንት የሚባሉ የሰውነት
መቆጣትን የሚያስከትሉ ኬሚካሎችን ከሰውነት ሰባብረው የሚያስወጡ
ይዘቶች ያላቸው አትክልትና ፍራፍሬ የበዛቸው ምግቦች ላይ ትኩረት
ማድረግም ሰውነትን ያበረታል፣ ኮሮናንም ወግድ ለሚለት ይረዳል።

በእንቅልፍዎ አይደራደሩ
እንቅልፍ የሰውነት የስራ እና እረፍት ሚዛን የሚሰራበት፣ ተፈጥሯዊ
የአእምሮ እና አካል ሚዛን መጠበቂያ ክኒን እንደኾነ በጉዳዩ ላይ የተሰሩ
ጥናቶች ያስረዳሉ። እርግጥ ነው ወረርሽኞች ሲከሰቱና የሞትና ጉዳት
ዜናዎች እዚህም እዚያም ሲሰሙ መጨነቅና እንቅልፍ ማጣት ይኖራል።
ይኹንና ይህ ከልክ ያለፈ ጭንቀት እና እንቅልፍ ማጣት የሰውነትን
ሚዛን በማዛባት ለቫይረሱ መግባትና መራባት ምቹ ሁኔታን ስለሚፈጥር
ጥንቃቄ ማድረግን፣ በእንቅልፍዎም አለመደራደርን ባለሞያዎች
ይመክራሉ። በአማካይ ከሰባት እስከ ስምንት ሰዓት እንዲተኙና ጥሩ
እንቅልፍ እንዲያገኙ ይጠበቃል።

በሚለውጡት ጉዳይ ብቻ ይጨነቁ፣


እንቅልፍ ሁናቴዎን በትኩረት ከመከታተልና ማሻሻል ጎን፣ የእንቅልፍ ፀር
የኾነውን ጭንቀት ወይም ውጥረት እንዲቆጣጠሩ በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ
ተላላፊ በሽታዎች ስፔሻሊስቷ ሞርጋን ካትዝ ለዎል ስትሪት ጆርናል
116
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 121

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ባካፈሉት ምክር ያሳስባሉ። እርስዎ መቆጣጠር የሚችሉት ጉዳይ ላይ ብቻ


ያተኩሩና ሰውነትዎን ያበርቱ ሲሉ መክረዋል።

ሲጋራ ያቁሙ፣ መጠጥ በልክ


የመተንፈሻ አካላት ህመም ያለባቸውና ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች በኮሮና
ቫይረስ የመጠቃት እድላቸውና ውስብስብ ውጤቶች ላይ የመድረስ
አጋጣሚያቸው ከፍ ያለ መኾኑን ከሰሞኑ የወጡት የባለሞያ ምልከታዎች
እያሳዩ ይገኛሉ። የኮሮና ቫይረስ አንዱ መዳረሻ ሳንባ እንደመሆኑ ሳንባ
ላይ ጫና የሚያደርጉ ማናቸውንም ነገሮች ማስተናገድ በራስ ላይ አደጋ
መጋበዝ ነው ይላሉ ዶ/ር ካትዝ። ከዚህ በተጨማሪ አልኮል መጠጦችን
ማዘውተርም ለሰውነት የጤና ሚዛን መዛባትና የበሽታ መከላከል መዳከም
ሚናው የሚናቅ ባለመኾኑ መሸታ ቤቶቹን በዚህ የኮሮና ዘመን
አያዘውትሯቸው የሚል ምክርን ባለሞያዎቹ ሰጥተዋል።

የሠውነት ፈሳሽ ምጣኔ


የሠውነታችን የፈሳሽ ክምችት ጥሩ መሆን የበሽታ መከላከል አቅማንን
በእጅጉ ያሳድገዋል፡፡ በቀን ውስጥ በዛ ያለ ውሃ መጠጣት በተለይም
የሎሚ ውሃ እዚህ ጋር ይመከራል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ የሠውነት ፈሳሽን
የሚቀንሱ እንደ አልኮል ቡና የመሠሉ መጠጦችን መቀነስ ያስፈልጋል፡፡
ፈሳሽ የሚሠጡ ፍራፍሬዎችንም በተለይ እንደ ኩከምበርና
ወተርሚሎን(ሃብሃብ) የተባሉትን ማዘውተር ይመከራል፡፡

117
122
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ከውጥረት የፀዳ አእምሮ

ውጥረት በበዛ ቁጥር የሠውነት የበሽታ መከላከል አቅም ይዳከማል፡፡


ውጥረት ሲባል የሥራ ብዛት ብቻ አይደለም፡፡ መጨነቅ ፣ ስጋት ፣
መነጫነጭ ፣ ቁጠኝነትን መቀነስ ያስፈልጋል፡፡ ራስን ማረጋጋትና
ጠዋትና ማታ መፀለይ እንዲሁም ዮጋና ሜዲቴሽን መስራት ውጥረትን
ይቀንሳል፡፡

ከቅዝቃዜ ይልቅ ሙቀት

ብርድና ቅዝቃዜ የሠውነት የበሽታ መከላከያ ሃይል ያዳክማል፡፡ ለዚያም


ነው ጉንፋንና ኢንፍሎዌንዛ በክረምት ወራት የሚበዛው፡፡ በተለይም
ቀዝቃዛ በሆነ አካባቢ የሚኖሩ ከሆነ ወይም እለቱ የሚበርድ ከሆነ
ተደራቢ ልብስ ይልበሱ፣ ሙቀት ያላቸውን ፈሳሾች ያዘውትሩ ፣
ሰውነትዎ ይሙቅ፤ ኮሮና ደግሞ በባህሪው ሙቀት አይወድም፡፡

118
123
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት


የተመሰከረላቸው 3ቱ ቫይታሚኖች
ለኮሮና ቫይረስ ላለመጋለጥ ጥረት ማድረጋችን እንደተጠበቀ ሆኖ
ብንጋለጥና ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን ቢገባ ግን መድህን ሊሆነን
የሚችለው የበሽታ መከላከያ ሃይላችን ነው፡፡ አንድ አገር በጠላት ቢወረር
የሚተማመነው በጠንካራ መከላከያ ሃይሉ ነው፡፡ በመሆኑም የመከላያ
ሃይሎቻችን ከኮሮና ጋር ለሚያደርጉት የፊት ለፊት የጨበጣ ውጊያ
ጥንካሬን ያገኙ ዘንድ የሚከተሉት ቫይታሚኖችና ማዕድኖች በእጅጉ
ይመከራሉ፡፡

1. ቫይታሚን ሲ ፡- ይህ የበሽታ ተከላካይ ሃይላችንን በእጅጉ


ከሚያጎለብቱ ቫይታሚኖች ውስጥ ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ በእርግጥም
የቫይታሚን ሲ እጥረት በራሱ የበሽታ መከላከያ ሃይላችንን ያዳክምና
ለተለያያዩ ህመሞች ተጋላጭ ያደርገናል፡፡ ቫይታሚን ሲ በተለይ
ተፈጥሯዊ ከሆኑ ምንጮች የተገኘ ከሆነ ብቃቱ ከፍ ያለ ሲሆን
አንዳንዴ ግን ሰዎች በበሽታ ሲጠቁ በሰውነታቸው ውስጥ ያለውን
ቫይታሚን ሲ ለመተካት ሲሉ በሐኪም የሚታዘዙ የቫይታሚን ሲ
እንክብል ይሰጣቸዋል፡፡ ከእንክብሎቹ ይልቅ ግን በተፈጥሮ የሚገኙት
የተሻሉ ናቸው፡፡ ከእዚህም ብርቱካን፣ ሎሚ ፓፓያ፣ እንጆሪ ፣ ካሊ፣
ስፒናች፣ ዝንጅብል፣ ነጭ ሽንኩርት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

2. ቫይታሚን ቢ6፡- ይህም ሌላኛው የሰውነት የበሽታ መከላከል

አቅምን በእጅገ የሚያሳድግ ሲሆን በተለይ ከዶሮ፣ ከሳልሞንና ከቱና


119
124
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ይገኛል፡፡ እንዲሁም ከአረንጓዴ ቅጠላ ቅጠሎች ፣ ነጭ ሽንብራ(ዱቤ)


ይገኛል፡፡ እንዲሁም በእንክብል መልክ ከሚወሠዱ ኪኒኖች (በሐኪም
ሲታዘዙ የሚገኙ ናቸው)፡፡

3. ቫይታሚን ኢ፡- የሰውነት የበሽታ መከላከል ሃይል ከኮሮና ጋር


በሚያደርገው ግብ ግብ በሰውነታችን ውስጥ አላስፈላጊ ጎጂ
ኬሚካሎች ይመነጫሉ፡፡ ቫይታሚን ኢ - እነዚህን ጎጂ ኬሚካሎች
በማምከን (አንቲኦክሲዳንት) ነው ስራውን የሚሠራው፡፡ የቫይታሚን
ኢ ዋነኛ መገኛውን ውስጥ ስፒናችና ኦቾሎኒ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

120
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 125
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የሰውነትን በሽታን የመከላከል አቅም


የሚጨምሩ ስምንቱ ሁነኛ ምግቦች
1/ የሲትሪክ አሲድ ምግቦች /ቫይታሚን ሲ

ብዙ ሰዎች ጉንፋን ሲያማቸው እነዚህን ምግቦች መውሰድን


ያዘወትራሉ: : ይህን የሚያደርጉት ሰውነታቸው በሽታን የመከላከል
አቅማቸውን ስለሚጨምርላቸው ነው: : የሲትሪክ ምግቦች ነጭ የደም
ህዋሳት መጠን ይጨምራሉ: : ይህ በሽታን ከመከላከል እረገድ ቁልፍ
መንገድ ነው::

ከነዚህ ምግቦች ውስጥ ሎሚ እና ብርቱካን በቀላሉ የምናገኛቸው ናቸው;;


እናም መውሰድ የሚያሰፈልገው ዘወትር ነው ምክንያቱም ሰውነታችን
አያመርታቸውም ወይም አያከማቻቸውም

2 / በርበሬ (Red bell peppers)

121

126 ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ሲትሪክ አሲድ ምግቦች ከፍተኛውን ቫይታሚን ሲ ይዘዋል ከተባለ ስህተት


ነው:: በርበሬ /ቃሪያ (Red bell peppers) ኩሉም የሲትሪክ አሲድ
ምግቦች ከሁለት እጥፍ በላይ ቫይታሚን ሲ ይዝዋል:: ከዚህ

በተጨማሪ ቤታ ካሮቲን ይዘዋል:: ይህ ንጥረ ነገር የሰውነታችንን


መራዦች የማስወገድ ተግባር ያለው ነው:: አይናችን እና ቆዳችንም
ጥራት እንዲኖረው ያግዛል::

3. ብሮክሊ /Broccoli

አበባ ጎመን በከፍተኛ ቫይታሚኖች እና ማዕድኖች የበለጸገ ነው::


ከቫይታሚኖች ውስጥ ቫይታሚን ኤ፣ ሲ እና ኢ አለው:: በተጨማሪም
መራዦችን የሚያስወግዱትን ሽና ፋይበሮችን ይዟል:: እነዚህን
ቫይታሚኖች እና ማዕድኖችን ለማግኘት የአበባ ጎመንን እጅግ በመጠኑ
ብቻ መቀቀል አስፈላጊ ነው፡፡

4 ነጭ ሽኩርት

122
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 127
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ነጭ ሽኩርት በሁሉም የአለማችን ክፍል የሚገኝ ምግብ ሲሆን ለጤና


እጅግ አስፈላጊ ከመሆኑ የተነሳ ሁልጊዜም ከገበታ እንዳይጠፋ የሚመከር
ነው:: ለነጭ ሽኩርት በሽታ ተከላካይነት እውቅና የተሰጠው በጥንታዊ

ስልጣኔ ነው:: ከዚህም በተጨማሪ ነጭ ሽንኩርት የደም ግፊትን


ለመቀነስ እና የደም ስርን ለማለሳለስ እጅግ ጠቃሚ ነው::የነጭ
ሽኩርት በሽታን የመከላከል ሚስጥር ያለው ምግቡ ከሚይዘው ሰልፈር ነክ
ውህድ ላይ ነው::

5 ዝንጅብል

ጅንጅብል ብዙ ሰዎች ህመም ሲሰመማቸው አስቀድመው የሚወስዱት


ምግብ ነው:: ዝንጅብል የሰውነት መቆጣት / ኢንፍላሜሽን እና
ትውኪያ ይቀንሳል::በተጨማሪም የሰውነት ውስጥ የኮሌስትሮል
ተካከል ሚና አለው::
መጠንን የማስተካከል

6. ስፒናች

123
128
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ስፒናች እጅግ ተፈላጊ የሚያደርገው በሽታን የመከላከል አቅሙ ብቻ


አይደለም:: የያዘው ንጥረ ነገር መርዛማ የሰውነት ውስጥ ኬሚካሎችን
የማስወገድ አቅም ስላለው ጭምር ነው:: በመሆኑም በውስጡ የያዘውን
ንጥረ ነገር ላለመጉዳት በትንሹ ብቻ መቀቀል ይኖርበታል::

7. እርጎ/ Yogurt

እርጎ በሽታን ይከላከላል: በተጨማሪም የቫይታሚን ዲ ምንጭ ነው::


በመሆኑም ለጥርስ እና አጥንት ጥንካሬ አስፈላጊ ነው::

ከምንም ስኳር ነክ ከሆኑ ነገሮች ነጻ የሆነ፣ ያልተቀነባበረ እርጎ መጠቀም


ያስፈልጋል::

8. እርድ

እርድ ለጥርስ መቦርቦር ፣ለሽርይ፣ እና ለሌሎች የሠውነት መቆጣቶች


(ኢንፍላሜሽ) ሁነኛ ፈውስ ነው፡፡

124
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 129
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ኮሮና ቫይረስና ቁጥሮቹ


● ከ 2.5% … በቫይረሱ ከተያዙ 200 ሰዎች ውስጥ በትንሹ 5ቱ
ይሞታሉ፡፡

● 0 ……….. እስካሁን በሽታውን የሚፈውስ መድሐኒት ወይም


ሊከላከል የሚችል ክትባት ምንም የለም!!

• 142………. የኮሮና ቫይረስ በሰውነት ውስጥ ከገባ በኋላ ምልክት


እስከሚያሳይ ድረስ የሚወስድበት ቀን፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንዴ
በሁለት ቀናት ውስጥ ሊታይ የሚችል ሲሆን ብዙውን ጊዜ በ12
ቀናት ውስጥ ሊገለጥ ይችላል፡፡

● 14000…… እስከ መጋቢት ወር መጀመሪያ /2012 ዓም


በበሽታው ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር!

● 142………… በበሽታው በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ሊሆኑ


የሚችሉ ሰዎች አምስት ዓይነት ናቸው (የጤና ባለሙያዎች፣
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንኪኪ ያላቸው የቤተሰብ አባላት፣
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንኪኪ ያለው ማንኛውም ሰው፣
በቀብር ወቅት በበሽታው ከሞተ ሬሳ ጋር ንኪኪ የሚኖራቸው፣
በበሸታው ከተያዙ እንሠሳት ጋር ንኪኪ ያላቸው ሰዎች፤
እድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆናቸው፤

የአስም ህሙማን፣ የል ህመምተኞች ፣ የደም ግፊት ህሙማን፣


የካንሰር ህሙማን፣ ሲጋራ አጫሾች፤ ወንዶች::

● 160…............. በሽታው የተሠራጨባቸው አገራት (በማርች


20/2020)
125
130
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

● 2019 …….. እኤአ ቫይረሡ ለመጀመሪያ ጊዜ የታወቀበት ወቅት


ሲሆን ቦታውም በቻይና በተለይም ውሃ ተብሎ በሚጠራው ከተማ
ነበር፡፡ ‹ ኮቪድ -19 በሚለው ስም ውስጥ ‹ 19› የተባለው ቁጥር
ያገኘውም ከዚህ ዓመተ ምህረት በኋላ ነው፡፡

● 99.9% ….. በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድ ሰው በኦስትሪያ የመዳን


ዕድሉ!

ዶ/ር አቡሽ አያሌው


126
131

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ይህንን ያውቃሉ?
ልዩ ጥንቃቄ ለሚያሰፈልጋቸው ልዩመከላከያ!

“ልዩ ጥንቃቄ” የሚያስፈልጋቸው የሚባሉት እነዚህ ናቸው፤ እነሱም


በዋናነት በበሽታው ከተያዙ ወይም ከሞቱ ሰዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት
ያላቸው ሲሆኑ እነሡም የጤና ባለሙያዎች፣ አስታማሚዎች፣ የቀብር
ስነስርዓት ፈፃሚ ሰዎችና የመዘጋጃ ቤት ሠራተኞች እንዲሁም
የአምቡላንስ ሹፌሮች ናቸው፡፡ ለእንዲህ መሠል ሰዎች የሚመከረው
ተጨማሪ መከላከያ በስዕሉ ላይ የተመለከተው ነው፡፡ በጭንቅላት
የሚደረግ ሠርጅካል ኮፍያ፣ የእጅ ጓንት፣ የዓይን መከላከያ ጐግል፣
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ፣ የሰውነት መከላከያ ቱታ እና የእግር
ቡትስ ጫማ ናቸው፡፡

127
132
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

አለማወቅ የሚያስከፍለው አሳዛኝ ታሪክ


ሴራሊዮን ውስጥ በኬሳዙን ከተማ የኢቦላ ወረርሽኝ በተቀሰቀሰበት ጊዜ
አንድ የህክምና ቡድን ከከተማ ውጪ ባሉ መንገደሮች አምርቱ ነበር፡፡
ህብረተሰቡ ኢቦላ የተባለ በሽታ ስለ መከሠቱ የሚያውቁት ነገር የለም፡፡
ከዚህ ቀደምም ጥንቃቄ በጐደለው መንገድ በኢቦላ የሞተን ሰው ሲቀብሩ
ነበር፡፡ በተለመደው የቀብር ባህል መሠረት አንድ ሰው ሲሞት ልብሱ
ይወልቃል፤ ገላው እስኪፀዳ ይታጠባል፤ እንደገና ይለብሳል፡፡ ከዚያም
ገላው ተስሞ ይቀበራል፡፡ ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ያለምንም መከላከያ
ነበር፡፡ በወቅቱም በተወሰኑት ላይ የምራቅ ናሙና በመውሰድ ባደረግነው
የኢቦላ ምርመራ 2 ሰዎች ከፍተኛ የቫይረስ ክምችት እንዳለባቸው
አረጋገጥን፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከዚያ መንደር በየቀኑ 30 ሰዎች በኢቦላ
እየተያዙ ወደ ማዕከላችን ይመጣሉ፡፡ ሁሉም ጥንቃቄ በሌለው መንገድ
የቀብር ስነ ስርዓቱን የፈፀሙ ነበሩ፡፡ በጣም ያሳዝናል፡፡ ምክንያቱም ብዙ
ሰዎች በኢቦላ ሊያዙና ሊሞቱ ችለው ነበርና፡፡

እነዚህ መንደሮች ሙሉ በሙሉ የተገለሉ በመሆናቸው መረጃ


የሚያገኙበት መንገድ አልነበረም፡፡ ኢንተርኔት አይደርሳቸውም፤ የሞባይል
ኔትወርክ እንኳን የማይደርስባቸው ክልሎች ናቸው፡፡ የጤና ባለሙያዎች
ወደ እነሱ ሲሄዱ የሚናገሩት ነገር እውነት አይመስላቸውም፡፡ ከዚህ
ይልቅ ማድረግ የተጀመረው ነገር ከኢቦላ የተረፉ ሰዎች ወደ እነዚህ
መንደሮች በመሄድ እውነታውን እንዲያሳውቋቸው ነበር፡፡ ከዚህ
የምንማረው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሞቱ ሠዎችን ከንኪኪ በፀዳ
ጥንቃቄ መቅበር እንደሚገባ ነው፡፡

128
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 133
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የኮሮናቫይረስን ድርጅቶች ስርጭት


ለመከላከል ሊያደርጋቸው የሚገቡ
ጥንቃቄዎች!
ኮሮና ቫይረስ በየቀኑ በፍጥነት እየተዛመተ ባለበት ሁኔታ በተለይ
ድርጅቶች በሠራተኞች መካከል የእርስ በእርስ መተላለፍ እንዳይሰከት
ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው፡፡ ድርጅቶች በአንድ በኩል ሥራዎች እንዲሰሩ
ይፈልጋሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በቢሮ ውስጥ ቫይረሱ እንዳይሰራጭ
ወይም ሠራተኞች ተይዘው እንዳይታመሙ የሚያስችል ሥርዓትንና
መከላከልን ያቀናጀ ስልቶች መከተል ይኖርባቸዋል፡፡

1. በዚህ ረገድ የድርጅቶች የሰው ሃይል አስተዳደሮች ኮሮና ተኮር


የአሰራር መርህን መከተል ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተለይ ስራን
ከማከናወን አንጻር አመራሮችና ሰራተኞች ሁሉንም ዓይነት
የግንኙነት መርህ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተለይ
በግድግዳ ላይ በሚለጠፉ ፖስተሮች ፣ በኢሜይሎች፣
በቴሌግራም፣ በዋትስአፕ፤ በስካይፒ ግንኙነት ማዘውተር
ያስፈልጋቸዋል፡፡ የመረጃ ልውውጡ በአንድ በኩል ስራን በሌላ
በኩል ደግሞ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከልና አዳዲስ ክስተቶችን
ለማሳወቅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ኮሮናን በተመለከተ መረጃዎች
ከትክክለኛ ምንጭ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

2. ተቀያሪ የአሰራር እቅድን መተግበር፡- ከአሁን


ቀደም ከፍተኛ የቫይረሱ ስርጭት ያለባቸው አገራት እንዳደረጉት
ሰራተኞች ከቤታቸው ሆነው የሚሠሩበትን አሰራር ተግባራዊ
129
134
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ በቢሮ ውስጥ ሊኖር


የሚችልን መነካካትና ከሰው ወደ ሰው የሚደረግን ስርጭት
ለማስቀረት ያግዛል፡፡ በእርግጥ ድርጅቱ በቢሮ ውስጥ ብቻ የሚገታ
አይደለም፤ ሠራተኞች ከቤታቸው ወደ ቢሮ በሚመጡ ጊዜ በተፋፈገ
ትራንስፖርት ውስጥ ሲጓጓዙ ሊያዙም ስለሚችሉና ይህንንም
ስርጭት ወደ ቢሮ ይዘው የመምጣታቸው ጉዳይ ነው፡፡ አሁን
ያለንበት ዘመን ቢዝነስን እንደ ወትሯችን ለመስራት የሚያስችሉ
የቴክኖሎጂዎች ውጤቶች ያሉበት በመሆኑ ይህን አሰራር
ልንከተለው እንችላለን፡፡
3. በአካል መገኘት የግድ ሲሆን፡- የአንዳንድ ድርጅቶች ስራ
የግድ ቢሮ መገኘት የግድ የሚል ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ
የተወሰነው ዲፓርትመንት ከቤት ሆኖ ላይሰራ ይችላል፡፡ ለምሳሌ
በባንክ ውስጥ ገንዘብን ከደንበኞች የሚቀበልና የሚከፍል የባንክ
ባለሙያ በባንክ የግድ መገኘት አለበት፡፡ እንዲሁም የሆቴልና
የሱፐር ማርኬት ሰራተኞች የስራው ዓይነት ቦታው መገኘት
የግድ ይላቸዋል፡፡ በአንዲህ መሰል ሁኔታ ውስጥ የቢሮና
የሠራተኛ ጽዳትን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግና ለዚህም
የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ማሟላት አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ይህ
የሚጠቅመው ሠራተኛውን ብቻ ሳይሆን ከሠራተኛው ጋር
በቀጥታ የሚገናኙ ደንበኞችንም ጭምር ነው፡፡ በመሆኑም የፊት
ማስክ፣ የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘርና ሳሙና እንዲሁም
የቢሮ ጽዳት እቅድ ተግባራዊ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ የበላይ
አመራሮች በተለይ ከብዙ ሰራተኞች ጋር የሚገናኙ በመሆናቸው

ዶ/ር አቡሽ አያሌው 135


130

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ተገቢ በሆኑባቸው ቦታዎች ሁሉ ማስክ ማድረጉን ማስታወስ


ይኖርባቸዋል፡፡
4. በቢሮ ውስጥ የሙቀት መለኪያ ፡- በቢሮ ውስጥ
የሠራተኞችን ሙቀት መለካት እንደ አንድ መልካም ዘዴ ተደርጎ
ይወሰዳል፡፡ ይህም ለሁሉም ሠራተኛ የእርስ በእርስ መተማመት
ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ ቴርሞሜትርን በብብት ውስጥ ለ5
ደቂቃ ያህል በመያዝ የሠውነት ሙቀት ከ380C በላይ ወይም
ከ990F በላይ መሆኑን ማጤን ከተቻለ ትኩሳቱ እንዳለማጠን
ይቻላል፡፡ ቴርሞሜትሩን በአልኮል በተነከረ ጥጥ መወልወል
ያስፈልጋል፡፡
5. ቴክኖሎጂ መር ስብሰባዎች፡- በአንድ ድርጅት ውስጥ ያሉ
ቡድኖች ወይም የዲፓርትመንት ሠራተኞች ስብሰባቸውን
በቴክኖሎጂ ቢያደርጉት ይጠቅማል፡፡ መሰብሰቡ ራሱን የቻለ
የንኪኪና የትንፋሽ ስርጭትን ያስከትላል፡፡ በመሆኑም በቴክኖሎጂ
የታገዙ ስብሰባዎች ለማድረግ የሚያስችሉ እንደ ስካይፒ፣ ጉግል፣
ሐንጋውትስ ወይም ዙም መጠቀም ይችላሉ፡፡
6. የእረፍት መርህን ማየት፡- ሠራተኞች የሚከፈልበት
የእረፍት ጊዜ ሊኖራቸው ወይም ላይኖራቸው ይችላል፡፡ በተለይ
ደግሞ ከሌላቸውና ከታመሙ የግድ ከስራ ገበታቸው ላለመባረር
ሲሉ ባይሻላቸውም ወደ መ/ቤቱ ሊመጡ ይችላሉ፡፡ ይህ እነሱንም
የበለጠ ውጥረት ውስጥ የሚከት ከመሆኑም ባሻገር ሳይሻላቸው
ወደ መ/ቤቱ በመምጣታቸው በመንገዳቸውም ላይ ሆነ በመ/ቤቱ
ውስጥ በሚነካቸው ነገሮች ሁሉ ቫይረሱን ወደ ሌሎች
ሊያሠራጩ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ምንም ዓይነት የትኩሳት
136 131
ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ማስታገሻ ወይም የሳል መድሃኒት ሳይወስዱ የትኩሳትና የሳል


ምልክት ለባለፉት 24 ሰአታት ካልታየባቸው ብቻ መመለስ
ይችላሉ፡፡

በመሆኑም አንድ ድርጅት ውጤት ተኮር አሰራር እስካለው ድረስ


የትም ቢሰራ የሚፈለገው ስራውና ውጤቱ እስከመጣ ድረስ
ቴክኖሎጂን በመጠቀም በቤታቸው ሆነው የሚሰሩበትን መዘየድ
ብልህነት ይሆናል፡፡

7. የተጠረጠሩ ሰራተኞችን በተመለከተ፡- አንዳንድ ሰራተኞች


በየዕለት ስራቸው ውስጥ እንዳሉ መታመማቸው ሊጠረጠር
ይችላል፡፡ ወይም እነሱ የበሽታውን ምልክቶች ሳልና ትኩሳት
ማየት ይጀምራሉ፡፡ በዚህ ወቅት ጤና ባለሙያን መጥራትና
ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ወቅት በአፋጣኝ ከሌሎች አንዲለዩና
ወደ ቤታቸው እንዲሄዱና እንዳያርፉ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ምልክቱ የታየባቸው ሠራተኞችም በሚስሉበትና በሚያስነጥሱበት
ወቅት በጨርቅና በሶፍት ወይም በክርናቸው አለያም በትከሻቸው
መሸፈን ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተከታታይነት ያለው ጽዳት፡- በየጊዜው ሊነኩ የሚችሉ
ቦታዎችን ለምሳሌ፡- የሰራተኞች
የሠዓት ወይም የአሻራ መቆጣጠሪያ ማሽን፣ የቢሮ በሮች፣ የቢሮ
መፀዳጃና ቤቶች፣ ጠረንጴዛዎች፣ የሊፍት(አሳንሰር) ማዘዣ
ቁልፎች በተከታታይ በአልኮል ወይም ሳኒታይዘር ወይም በውሃና
ሳሙና በተነከረ መወልወያ ጨርቅ ማጽዳት ያስፈልጋል፡፡
እንዲሁም እያንዳንዱ ሠራተኛ ከመጠቀሙ በፊት የበር መያዣ፣
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 137
132

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የኮምፒውተር ኪቦርድ፣ ማውዝና ጠረጴዛ በአልኮል ወይም


በሳሙናና ውሃ የተነከረ ጨርቅ መወልወለ ያስፈልጋል፡፡
9. ሠራተኞችን ማስገንዘብና ማሳሰብ፡- ለሠራተኞች በሚታይ
ቦታ ላይ በፖስተሮች መለጠፍ፡፡ በተለይ የህመም ምልክት
ሲኖርባቸው በቤታቸው መቅረት እንዳለባቸው ፣ሲስሉና
ሲያስነጥሱ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንዲሁም የእጅ ንጽህና
አጠባበቅ ምን እንደሚመስል የሚገልጹ መረጃዎችን ያካተቱ
ፖስተሮች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
10. ለሠራተኞች የንጽህና ግብአቶችን (በተለይ አልኮል
የተነከረ ጥጥ) ማቅረብና በየቦታው እንዲገኙ
ማድረግ፡- የሠራተኞችን ንጽህና አጠባበቅ ያበረታታል፡፡
ሠራተኞች እጆቻቸውን በአልኮል በተነከሩ መወልወያ ጥጦች
በየጊዜው እንዲያጸዱ መመሪያ መስጠት፡፡ ከዚህ አንጻር የአልኮል
መጠኑ ከ60-95% የሚደርስ ምጣኔ ያለው ቢሆን ጥሩ ነው፡፡
ወይም ደግሞ እጆቻቸውን በሳሙናና በውሃ ለ20 ሰከንዶች ያህል
መታጠብን መምከር፡፡ በተለይ እጆች በሚታይ ደረጃ የቆሸሹ ከሆነ
ከአልኮል ይልቅ ሳሙናና ውሃ የበለጠ ይመከራሉ፡፡
11. ቤተሰቦቻቸው ለታመሙ ሠራተኞች ፡- እነሱ ጤናማ
ቢሆኑም ለአለቆቻቸው ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡- ይህ ሠራተኞችም
በቫይረሱ የተያዙ ስለመሆኑም ቀጣይ ምርመራ ሊደረግላቸው
ይገባል፡፡
12. አንድ ሠራተኛ በቫይረሱ መያዙ ከተረጋገጠ አሰሪዎች የዚህን
ግለሰብ ማንነት ምስጢር በመጠበቅ ነገር ግን ባልደረቦቻቸው

138 133
ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ለቫይረሱ የተጋለጡ መሆኑን ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ከታመመው


ግለሰብ ጋር ቅርርብ የነበራቸው ባልደረቦች በቫይረሱ የተያዙ
ስለመሆናቸው ቀጣይ ክትትል ያስፈልጋቸዋል፡፡
13. ጉዞ ያለባቸው ሠራተኞችን መምከር፡- አንዳንድ ድርጅቶች
ከሰራቸው ባህሪ አንጻር በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ
ጉዞዎች የሚያደርጉ ሠራተኞች ይኖሯቸዋል፡፡ በመሆኑም
ሠራተኞች ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ራሳቸው ምንም ዓይነት
የመተንፈሻ አካል ህመም ምልክቶች እንደሌሉባቸው ማጤን
ያስፈልጋል፡፡ ይህም ግለሰቡ በሌላ ሃገር እንዳይንገላታ
ስለሚጠቅመውና በጉዞም ወቅት ሌሎችንም እንዳያሲዝ በሚል
ነው፡፡ ግለሰቡም በቶሎ እዚህ አገር ህክምና በማግኘት እንዲድን
ይሆናል፡፡ እንዲሁም ከፍተኛ የቫይረሱ ስጋት ካሉባቸው ሃገራት
የመጡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው መረዳት
ያስፈልጋል፡፡ ለአለቃቸው በመንገር በቤቱ መቆየት ይኖርበታል፡፡

በጉዞ ላይ እያሉ ከታመሙ ደግሞ ለአለቃቸው ደውለው ማሳወቅና


ለአየር መንገዱ ሠራተኞች በማሳወቅ ምርመራ እንዲደረግላቸው
ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ እዲሁም ጉዞው ያን ያህል አንገብጋቢ ካልሆነ
ማራዘም ወይም መሰረዝ ጥሩ መፍትሄ ነው፡፡ ምክንያቱም በሌላ ሃገር
ውስጥ ሆነው ቢታመሙ ያሉበት አገር የጉዞ ማእቀብ የሚያደርግ
ከሆነ ወደ አገራቸው ለመመለስ ይቸገራሉ፡፡

14. ቀድሞ መዘጋጀት፡- ድርጅቶች ብዙ ሠራተኞቻቸው


ቢቀሩባቸው እንዴት የቢዝነሶቻቸውን ሥራ ማስቀጠል
እንደሚችሉ ቀድመው ማቀድና መዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ዶ/ር አቡሽ አያሌው


134
139

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ሠራተኞች ሊታመሙ ይችላሉ፤ የታመመ የቤተሰብ አካል


ሊያስታምሙ ይችላሉ፡፡ ልጆቻቸው ከት/ቤት በመቅረታቸው
እነሱን መንከባከ የግድ ሊላቸው ይችላል፤ እንዲሁም በህዝብ
መጓጓዣ የሚመጡ ከሆነ በሽታውን በመፍራት ወደ መ/ቤት
ላይመጡ ይችላሉ፡፡ በዚህ መሰል ሁኔታ ውስጥ እንዴት
መስራትና ቢዝነሱን ማስቀጠል እንደሚቻል እንዲሁም ብዙ
ሠራተኞች ቢቀሩ እነዚህን ሁሉ እንዴት በቤታቸው ሆነው
እንዲሰሩ ማድረግ እንደሚቻል የቴክኖሎጂውን ሥርዓት ከወዲሁ
መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡
15. በሥራ ቦታ ንኪኪን መ ቀነስ፡- በስራ ውስጥ ሠራተኞች
እርስ በእርስ እንዳይነካከሉ፤ ቢቻል ተራርቀው እንዲሰሩ፤ ለምሳሌ
ወደ ሬስቶራንቶች ከመሄድ ይልቅ በመ/ቤት ውስጥ ምግብ
እንዲዘጋጅላቸው ማድረግ፤ የራሳቸውን ብቻ መመገቢያና መጠጫ
እንዲጠቀሙ፤ ከጋራ ይልቅ ለብቻቸው እንዲመገቡ፤ የጠጡበትንና
የበሉበትን ዕቃ በሚገባ በሳሙናና ውሃ እንዲያጸዱ ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡
16. የተጋላጭነት እድል መወሰን፡- በኮሮና ቫይረስ ሁሉም

እኩል የተጋላጭነት እድል የለውም፡፡ አንዳንዴ ደግሞ መካከለኛ


ተጋላጭነት እድል ይኖረዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ የተጋላጭነት
እድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ ሰዎች በቀጣይ ሊወስዷቸው የሚገቡ
እርምጃዎች እንደተጋላጭነት እድላቸው የሚወሰን ነው
የሚሆነው፡፡ ይህ እንዴት እንደሚከናወን በቀጣይ እንመልከት፡፡

140 135
ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ወደተጋላጭነት እድል ከመግባታችን በፊት


ዜጎች የሚከተሉትን መርሆዎች ሊያውቋቸው
ይገባል፡-

1. የኮሮና ምልክቶች፡- ግለሰቡ የታዘባቸው ወይም በምርምራ


የተረጋገጡ ሣል ፤ ትኩሳት፤ ወይም ደግሞ ለመተንፈስ መቸገር
የሚሉት ናቸው፡፡
2. ራስን መከታተል፡- ይህም ማለት ግለሰቦች ከላይ የተጠቀሱ
ምልክቶች በራሳቸው ላይ ስለመከሰታቸው ለምሳሌ ትኩሳት፣
ሳልና ለመተንፈስ መቸገር የተሰኙት ምልክቶች ከታዩባቸው
በቀጣይ 14 ቀናት የራሳቸውን ለውጥ ሊከታተሉ ይችላሉ፡፡ በዚህ
ጊዜም ሙቀት ከተሰማቸውና ሳል ካጤኑ ወይም መተንፈስ
ከተቸገሩ ራሳቸውን ከሌሎች መነጠልና ግኙነቶችን መገደብ
ይጠበቅባቸዋል፡፡ እንዲሁም ወደ ሃኪም በመደወል ምክር ማግኘት
ይጠበቅባቸዋል፡፡
3. ቀጥተኛ ክትትል፡- ይህ እንግዲህ በመንግስት ጤና ተቋም
ወይም በአየር መንገዶች በኩል የሚደረግ እለታዊ ክትትል ነው፡፡
ትኩሳት፤ ሳል ወይም መተንፈስ የመቸገር ምልክቶች
ስለመከሰታቸው በሚመለከተው የጤና ተቋም በኩል በስልክ
ወይም በኢ-ሜይል ክትትል ማድረግን ይመለከታል፡፡ ይህ በቀን
ቢያንስ አንድ ጊዜ ይተገበራል፡፡
4. የቅርብ ንኪኪ፡- አንድ ሰው የቅርብ ንኪኪ አድርጓል ለማለት
የኮሮና ህመም ካለበት ሰው ጋር ቢያንስ በሁለት ሜትር ርቀት
136
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 141
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ውስጥ መቀራረብ፤ በበሽታው የተያዘን ሰው ከተንከባከበ፤


በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር አብሮ ከኖረ ወይም በህክምና መስጫ
ተቋም ውስጥ ተመሳሳይ ክፍልን (ቦታን) ከተጋራ ነው፡፡
እንዲሁም ደግሞ አንድ በበሽታው ከተያዘ ሰው በማስነጠስ ወይም
በሳል አማካኝነት ፈሳሽ ሰውነቱ ላይ ካረፈ ነው፡፡
በመሆኑም አንድ ሰው እንደ የቫይረሱ ተረጋላጭነት ደረጃው
የሚወሠዱት ቀጣይ እርምጃዎች የሚለያዩ ይሆናል፡፡

1. ከፍተኛ የስጋት እድል ፡- አንድ ሰው ከፍተኛ የስጋት


እድል አለበት ለማለት በቫይረሱ መያዙ ከተረጋገጠ ሰው ጋር
አብሮ ከኖረ ፣ የትዳር አጋር ከሆነ፤ ወይም አስፈላጊ ጥንቃቄ
ሳያደርግ ለታማሚው ግለሰብ እንክብካቤ የሰጠ ከሆነ ነው፡፡
እንዲሁም አንድ ሰው ሁቤይ ወይም ውሃን ከተባለ የቻይና
አካባቢ የመጣ ከሆነ ከፍተኛ የስጋት እድል ያለበት ተደርጎ
ይወሰዳል፡፡
2. መካከለኛ የስጋት እድል፡- በቫይረሱ መያዙ ከተጠረጠረ
ሰው ጋር የቅርብ ንኪኪ ካለ፤ በአውሮፕላን ውስጥ በሁለት
ሜትር ክልል ውሰጥ መቀራረብ ካለ፤ አስፈላጊውን ጥንቃቄ
በማድረግ በቫይረሱ የተያዘን ሰው በቤት ውስጥ የተንከባከበ
ወይም አብሮ የኖረ እንዲሁም ከቻይና ሁቤይ(ውሃን) ውጭ
ከየትኛውም የቻይና አገር የመጣ፤ ከኢራን ፣ ከጣልያንና
ከደቡብ ኮሪያ የመጣ፤ እንዲሁም ከሮና በከፍተኛ ደረጃ
ከባሰባቸው አገራት የመጣ በዚህ በመካለኛ የስጋት ደረጃ
ውስጥ ይመደባል፡፡
142 137
ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

3. ዝቅተኛ ስጋት እድል፡- ከላይ ያሉትን የንኪኪ


መስፈርቶች የማያሟላና ቫይረሱ ከላይ ከተጠቀሱት አገራት
ውጭ የመጣ ከሆነ በዚህ መደብ ውስጥ ይካተታል፡፡

የስጋት ደረጃ መፍትሔዎች፡- ሰዎች እንደየስጋት ደረጃቸው

የሚደረግላቸውና እነሱም የሚያደርጉት ይለያያል፡፡ ምልክት እንዳሳዩበትና


እንዳላሳዩበት ቀጣይ እርምጃዎች ይለያያሉ፡፡ ይህም ማለት እያንዳንዳቸው
የስጋት ደረጃዎች ምልክት ያሳዩና ምልክት ያላሳዩ በሚል በሁለት
ይከፈላሉና ነው ቀጣይ የመፍትሄ እርምጃዎች ና ጥንቃቄዎች
የሚወሠዱት፡፡

ሰዎች እንደ ስጋት እድላቸው የሚከተሉት ትግባራዎች ሊከናወኑ ይገባል፡፡


ይህ በመ/ቤትም ሆነ በአየር ትራንስፖርት ጣቢዎች እንዲሁም በህክምና
መስጫ ተቋማት ውስጥም ሊሆን ይችላል፡፡ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡

1. በከፍተኛ ስጋት ውስጥ የተመደቡ፡


1.1 ምልክት ላላሳዩ፡- ማቆያ ክፍል ውስጥ ማስቀመጥ ፣
ምንም ዓይነት ማህበረሰባዊ ተግባር እንዳይኖራቸው
ማድረግ ፣ በየቀኑ የነቃ ክትትል ማድረግ ፣ (ምልክቶቹን
በተንተራሰ መልኩ) እንዲሁም የሚጓዙ ከሆነ ጥብቅ
ቁጥጥር (ክትትል) ባለበት ሁኔታ መጓዛቸውን ማረጋገጥ
ያስፈልጋል፡፡
1.2 ምልክት ላሳዩ፡- በፍጥነት ለይቶ ማቆያ ቦታ
መውሰድ ፣ የህክምና ምርመራ ማድረግ ፣ የህክምና
ምርመራ ከመደረጉ በፊት የምርመራ ባለሙያዎችን
138
143
ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ቀድሞ ስለ ህመሙ ማሳወቅ (እንዲጠነቀቁ) ፣ ሰዎቹ


በአየር መጓጓዝ ካለባቸው በህክምና መስጫ አውሮፕላን
እንዲሆን ፣ የአገር ውስጥ ጉዞ ደግሞ በአምቡላንስ
አልያም በግል መኪና ከሆነ ምልክቱን ያሳየ ሰው የፊት
ማስክ ሊጠቀም ይገባል፡፡

2 መካከለኛ የስጋት ደረጃ ለሚመደቡ


- በቤታቸው እንዲቆዩ ይመከራሉ

- ራሳቸውን ከሌሎች ሰዎች ማራቅ ይኖርባቸዋል፡፡


- ራሳቸውን ትኩሳት ሳልና የመተንፈስ መቸገር ምልክቶች
እንዳለባቸውና ሙቀታቸውን በቴርሞ ሜትር በየቀኑ ይለካሉ፡፡
- ቀጣይ የጉዞ እቅዶችን ማራዘም ይኖርባቸዋል፡፡

3 ዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ያለባቸው፡- በዚህ ደረጃ ውስጥ

የተመደቡ ሰዎች በየትኛውም ቦታ የመንቀሳቀስ ገደብ የሌለባቸው


ሲሆን ነገር ግን ራሳቸውን ለበሽታው ምልክቶች ተጋላጭ
ስለመሆናቸው መከታተል ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም እራሳቸው የኮሮና
መከላከያ ስልቶችን በመጠቀም መከላከል ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን አንድ
የበሽታው ምልክቶች ከታዩባቸው ራሳቸውን እንዲለዩና ከየትኛውም
ማህበራዊ ግንኙነቶች እንዲርቁ ይመከራሉ፡፡ የህክምና ምከር
በመጠየቅም ቀጣይ ምርመራ እንደሚያስፈልጋቸውና እንደማያስፈ
ልጋቸው መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡ ምልክቱ እስኪጠፋ ድረስ በህዝብ
ወይም በንግድ ትራንስፖርቶች መሄድን ማቆም ይኖርባቸል፡፡

139
144
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የኮቪድ 19 ምልክቶች ከታዩ እና በቫይረሱ


ተይዘናል ብለው ካሰቡ ምን ማድረግ
ይኖርብዎታል?

የመጀመሪያው ነገር አለመረበሽና አለመደናገጥ ነው፡፡ በቫይረሡ ተያዙ


ማለት የሞት ፍርድ ማለት አይደለምና ምንም እንዳልሆነ አውቆ በጥበብ
የባለሙያ እገዛ መሻት እና ወደሌሎች መፍትሄዎች ማነጣጠር ነው፡፡
የሚከተሉትን ያድርጉ፤

ü ሌሎች ሰዎችን ለቫይረሱ ላለማጋለጥ መጠንቀቅ፣ መተላለፊያ


መንገዶችን በማስተዋል ጥንቃቄ ማድረግ
ü ህዝባዊ ቦታዎችንና ህዝባዊ ትራንስፖርቶችን አለመጠቀም
ü ሌሎች ሰዎች ወይም እንስሳት በአቅራቢያዎ ከሆኑ ማስክን
በአግባቡ መጠቀም
ü ሲያስነጥሱ ወይም ሲያስሉ ፊትዎን በአግባቡ መሸፈን
ü የተጠቀሙትን ማስክም ሆነ ሶፍት ሰው ወይም እንስሳት
በማይደርሱበት ቦታ በአግባቡ ማስወገድ
ü ከቤተሰብ እራስን መለየት
ü ለራስ ብቻ የተለዩ አገልግሎቶችን መጠቀም
ü ከእንስሳት ጋርም ቢሆን ንኪኪ መቀነስ
ü ወደ እርዳታ ወይም ጤና አገልግሎት መደወል እና ከመሄድዎ
በፊት አስቀድሞ ማሳወቅ
ü ማንኛውንም የቤት ውስጥ እቃዎችን ለሌላ ሰው አለማጋራት
ü ከተጠቀሙ በኋላ እቃዎችን በአግባቡ ማጠብ
140
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 145

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ü ንኪኪ ያለባቸውን ነገሮን እቃዎች እና ነገሮች፣ ስልክ


ኮምፒውተር፣ በር፣ ሽንትቤት፣ እጄታ፣ ጠረጴዛ ፣ አልጋ፣ ሁሉ
በየቀኑ ማጠብ
ü ማንኛውም የሰውነት ውስጥ ፈሳሽ የነካቸውን ነገሮች በኬሚካል
ማጽዳት
ü ማስክን በአግባቡ መጠቀም
ü የህመሙን ሂደት በጥንቃቄ መከታተል እና የባለሙያ እገዛ
ማግኘት
ü ለሚመለከተው አካል ወይም ጤና ተቋም መደወል
ü በቀጥታ ከመሄድ በፊት ምልክቶችን በመንገር ስጋትን ማጋራት
እና እገዛ ማግኘት
ü ንኪኪ የነበራቸውን ሰዎች ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ፡፡

ንኪኪ የነበራቸው ሲባል ምን ማለት ነው?

ü ንኪኪ የነበራቸው ሰዎች በ2 ሜትር እርቀት ውስጥ ለብዙ ጊዜ


አብሮ የቆየ ሰው፣
ü በሚያስሉበት ወቅት አጠገብ የነበረ ሰው፣
ü አካላዊ ንክኪ የነበረው
ü ወይም ተመሳሳይ እቃዎችንና አገልግሎቶችን የተጋራ ሰው ሊሆን
ይችላል፡፡
ü ንኪኪ ያላቸውን ሰዎች ማሳወቅ አንድም ቫይረሱ ወደማህበረሰቡ
እንዳይሰራጭ ያግዛል፣ ሁለትም ሰዎቹ ህመሙ ሳይጠናባቸው
የባለሙያ እገዛ እንዲያገኙ ያግዛል፡፡

146 141
ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የዳሸን ባንክ ምርጥ ተሞክሮ

ኮሮና ቫይረስን በመካከሉ ረገድ ውጤታማ ተሞክሮ ካላቸው ድርጅቶች


ውስጥ ዳሸን ባንክ ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ እስከ አስር ሺህ ሠራተኞችን
በስሩ የሚያስተዳድረውና በአገር አቀፍ ደረጃ ከ418 በላይ ቅርንጫፎች
ያሉት፤ በአገራችን በአትራፊነቱ ከግንባር ቀደሞቹ ኩባንያዎች ውስጥ
የሚሰለፈው፤ በተለያዩ የቴክኖሎጂ ብልጽግናው ሁልጊዜም አንድ እርምጃ
ቀዳሚ የሚል መርህን የሚከተለው ዳሸን ባንክ ኮሮና ቫይረስን በብቃት
ከመከላከል አንጻር በቦታው ሄደን የታዘብነውን ጉዳይ እዚህ ጋር ማካፈሉ
ለሌሎች ድርጅቶች ትልቅ ምሳሌ ይሆናል፡፡

ዳሸን ባንክ በመጀመሪያ ያደረገው ነገር ቢኖር በዋና ሥራ አስፈጻሚው


አቶ አስፋው ዓለሙ የሚመራ ኮሚቴ ማቋቋም ነበር፡፡ ይህ ኮሚቴ
የመጀመሪያ ሥራውን በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ አስፈላጊውን ግንዛቤ መር
እቅድ ከነደፈ በኋላ ለሁሉም ሠራተኞች የዕለታዊ የመረጃ ልውወጥ
በማድረግ ሁሉም ሠራተኛ በመከላከሉ መርሃ ግብር ግንዛቤ
እንዲጨብጥ፣ ንቁና ዝግጁ በመሆን የራሱንም ሆነ የስራ ባልደረቦቹን
ጤንነት እንዲሁም የደንበኛቸውን ደህንነት እንዲጠብቁ ማድረግ ነበር፡፡

ባንኩ ለተለያዩ የስራ ክንውኖች የሚደረጉ ማናቸውም ስብሰባዎች


እንዳይደረጉ ያገደ ሲሆን ለሠራተኞቹም ሆነ አመራሮች ይሰጡ የነበሩ
ስልጠናዎችም ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፉ አድርጓል፡፡ ይህንንም ያደረገበት
በሠራተኞች ዘንድ ሊኖር የሚችልን ታሳቢ ተጋላጭነት ለማስወገድ
በሚል ነው፡፡

142
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 147
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ከዚህ ጋር በተያያዘ የግድ ቢሮ በአካል በመምጣት መሥራት


የማይጠበቅባቸውን ሠራተኞች ቢሮ ሳይመጡ በቤታቸው እንዲሰሩ
አድርጓል፡፡ በተለይም ቴክኖሎጂን በመጠቀም ባንኩን የሚያግዙ
ሠራተኞች ይህን መስመር ተከትለዋል፡፡ ባንኩ ወትሮም ልዩ ልዩ ዘመናዊ
የቴከኖሎጂ ሲስተሞችን የሚጠቀም በመሆኑ ይህን ለማድረግ
አልተቸገረም፡፡ እንዲሁም ምንም እንኳን በአካል መገኘትን የግድ የሚሉ
ስብሰባዎች ቢኖሩም ሠራተኞችና አመራሮች በቢሯቸውና በቤታቸው
በመሆን በአስፈላጊ ጉዳይ ላይ መወያየት የሚያስችላቸውን ልዩ የቪዲዮ
ኮንፈረንስ ቴክኖሎጂ ይጠቀማል፡፡

አንዲሁም ባንኩ ለቫይረሱ ተጋላጭነት እድል አለባቸው በሚባሉ


ሠራተኞች የተለየ የበሽታው ምልክቶች የሚያሳዩ ሠራተኞች ደሞዝ
ታሳቢ የሚደረግለትን የእረፍት ቀን እንዲጠቀሙ አድርጓል፡፡ ይህም
መሆኑ ሠራተኞች አንዳቸ አጠራጣሪ ምልክት በራሳቸው ላይ ቢታዘቡ
እንኳን የደመዎዝ ጉዳይ አሳስቧቸው ወደ ቢሮ የመምጣት የአጋላጭነት
እድል እንዳይኖራቸው ያስችላቸዋል፡፡

ዳሸን ባንክ የእጅ ማጽጃዎች ማለት በልዩ የመርጫ ፕላስቲክ በመጠቀም


በእያንዳንዳቸው የሠራተኞች በቢሮ ተሞልቶላቸው የሚቀመጥ ሲሆን
በየባንኩ በረንዳዎችና የኤቲኤም ማሽኖች አካበቢም በመኖራቸው ደንበኞች
ሳይቀሩ እጃቸውን እንዲያጸዱ እድሉ እንዲኖራቸው አስችሏል፡፡

ባንኩ በራሱ የማህበረሰብ ሚዲያ በመጠቀም በየእለቱ በመላው አገር


የሚገኙ ሠራተኞች አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ

143
148 ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

እንዲደርሳቸው ያደርጋል፡፡ ይህም በግልጽነትና በግንዛቤ ላይ የተንተራሰ


ወቅታዊና ዕለታዊ መረጃ የሠራተኞችን በራስ መተማመን ከፍ ያደርጋል፡፡

ከዚህም በላፈ የባንኩ ደንበኞች ወረርሽኙ በሚያስከትለው የኢኮኖሚ መር


የተነሳ የተበደሩትን መክፈል በማይችሉና የብድር ማራዘም የሚጠይቁ
ቀድሞ ሲያስከፍል የነበረው የኮሚሽን ክፍያ እንዲቀር አድርጓል፡፡

እንዲሁም ሰዎች ባንክ ሳይመጡ ገንዘብ ማውጣት እንዲችሉና የንኪኪ


ደረጃቸውን እንዲቀንሱ ለማድረግ እንዲሁም ከብር ይልቅ በኤቲኤም ላይ
የተንተራሰ ግብይትን ይከናወኑ ዘንድ ወትሮ ሲያስክፍል የነበረውን
የኤቲኤም ኮሚሽን ክፍያ አስቀርቷል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በዓለማቀፉ
ወረርሽኝ ሳቢያ ነጋዴ ደንበኞቹ ከውጪ ወደ አገር ውስጥ እቃ
አስመጥተው ነገር ጊዜው ቢዘገይባቸውና ማራዘም ሲፈልጉ ወትሮ
ለማራዘሚያ ያስከፍል የነበረውንና በዓመት እስከ 200 ሚሊዮን ብር ገቢ
ያገኝበት የነበረውን የኮሚሽን ክፍያ አስቀርቷል፡፡

በአጠቃላይ የኮሮና ቫይረስን ለመከላል ሁሉን አቀፍ ስራ ከመስራት ባለፈ


በሽታው በኢኮኖሚ ላይ እያደረሰ ያለውን ተጽዕኖ በመቀነስ ደግሞ ከባንኩ
ጋር ለሚሠሩ ክቡር ደንበኞች የልዩ ልዩ የኮሚሽን ክፍያዎች እፎይታን
ለመስጠት በመቻሉ ባንኩን አገራዊና ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት
ረገድ በእጅጉ እንድናመሰግነውና እንድናከብረው ያደርገናል፡፡ ይህንንም
ተሞክሮ ሁላችንም በመጋራት የበኩላችንን ትንንሽ አስተዋጽኦ ብንጫወት
በአገር ደረጃ የሚመጣው ድምር ውጤት እጅግ ከፍተኛ ይሆናል፡፡

144
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 149
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ይህን ያውቁ ኖሯል?


ልብ የማንላቸው የቫይረሱ አስተላላፊዎች
ቫይረሱ የመተንፈሻ አካል ህመምን የሚያጠቃ በመሆኑ እንደ ጉንፋንና
ቲቢ ሁሉ በትንፋሽ ይተላለፋል፡፡ ትንፋሽ ሲባልም ሳልንና ማስነጠስን
ይጨምራል፡፡ በመሆኑም የትኛውም ሰው ተመርምሮ ኔጌቲቭ እስካልተባለ
ድረስ የሚያዋጣው የኮሮና ቫይረስ ሊኖርበት ይችላል በሚል መጠርጠሩ
ነው፡፡ እርስዎም ጨምር፡፡ በመሆኑም ሲያወሩም ሆነ ሲበሉ አይቀራረቡ፡፡
ድንገት ማን እንደሚስልም ሆነ እንደሚያስነጥስ አይታወቅምና የሁለት
ሜትር ርቀት ይኑርዎ፡፡

ከገንዘብ ወረቀቶችና ሳንቲሞች ይልቅ ኤሌክትሮኒክስ የአከፋፈል


ስርዓቶችን ይጠቀሙ፡፡ በወረርቀትና በሳንቲም ገንዘቦች ላይ ለሠዓታት
ይቆያል፤ በእነሱም በኩል ይተላለፋል፡፡ ገንዘብ ሲከፍሉም ሆነ ሲቀበሉ
እጆችዎን በሳሙናና በውሃ ይታጠቡ፡፡ በሱፐር ማርኬቶች በኩል
የኤቲኤም ካርድዎን ይጠቀሙ፡፡ ወይም ደግሞ የአሞሌ ደንበኛ ይሁኑ፡፡
ገንዘቦትን በሞባይል ባንኪንግ በኩል ያስተላልፉ፡፡ በተቻለ መጠን የገንዘብ
ንኪኪ ይቀንሱ፡፡

እስኪርቢቶና ሞባይል ለሰው አያውሱ፡፡ ቫይረሱ በእነዚህ በኩል


ይተላለፋል፡፡ የራስዎን ብዕር በሄዱበት ቦታ ሁሉ ይጠቀሙ፡፡ የሌላ ሰው
ብዕር ከተጠቀሙም ወዲያውኑ እጆችዎን በሳሙናና ውሃ ይታጠቡ ወይም
በአልኮል ይወልውሉ፡፡

145
150
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

እንዲሁም የሚከተሉት ነገሮች ሰዎች በጋራ የሚጠቀሙባቸው በመሆኑ


የንኪኪ መጠንን ልብ ብለው ይቀንሱ፡፡

- የሊፍት የቁጥር ቁልፍ ወይም አሳንሰር ባይጠቀሙ ይመከራል፡፡


- የመ/ቤት የሠዓት መቆጣጠሪያዎች፣ ማብሪያና ማጥፊያዎች፣

- በቢሮ ውስጥ የወረቀት ልውውጦች፣ በቢሮም ሆነ በሬስቶራንት


ውስጥ የበር እጀታዎች፣
- በቢሮም ሆነ በሬስቶራንቶች ውስጥ ያሉ መጸዳጃ ቤቶች እና
የቧንቧ መክፈቻና መዝጊያዎች፣ የቢሮ ጠረጴዛዎች ይጠቀሳሉ፡፡

ለዚያም ነው በጋራ የምንነካቸው ነገሮች ስለሚበዙ እጅን ደጋግሞ


መታጠብ የሚመከረው፡፡ በጋራ የምንነካቸውን ነገሮችም በተደጋጋሚ
ማጽዳትና መወልወል ያስፈልጋል፡፡

146
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 151

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የኢኮኖሚውን አደጋ ለመቀነስ


ለመንግስት የሚመከሩ
መፍትሔዎች!!
የመንግሥት ትልቅ ሚናው መሆን ያለበት የማህበረሰቡን ደህንነት
ማስጠበቅ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ እንዳሁኑ ዓይነት ወረርሽኝ በተከሰተ ጊዜ
የመንግስት ሚና በትልቁ ጎልቶ መታየት ይኖርበታል፡፡ ሕይወት በማዳን
ረገድ ማለትም ያልተያዙ ሰዎች በቫይረሱ እንዳይያዙ፤ የተያዙትም ደግሞ
በቫይረሱ እንዳይሞቱ አስፈላጊ የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ አፋጣኝ
ስልቶችና መፍትሄዎችን ተግባራዊ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

የቫይረሱ ስርጭት ፈጣን ከመሆኑ አንጻር የኢትዮጵያ መንግስት ካለበት


የበጀት ውስንነት ለቫይረሱ የሚደረገውን አጸፋዊ ምላሽ ውስን እንዲሆን
ያደርገዋል፡፡ ይህ ደግሞ ብዙ ህዝብ እንዲጠቃና የተጠቃውም በቀላሉ
እንዲሞት ሊያስገድድ ይችላል፤ ሁሉንም የሚያስተናግድ የጤና መሠረተ
ልማትና በጀት ዝቅተኛ በመሆኑ፡፡

በመሆኑም መንግሥት ከሌሎች በጀቶችም ቢሆን በመቀነስ ለጤናው ዘርፍ


ፈጣን ምላሽ በመስጠት ለተቀናጀ የመከላከል ሥራ ዝግጁ መሆን አለበት፡፡
ወደፊት የሚመጣውም አደገኛ የኢኮኖሚ ቀውስ መከላከል የምንችለው
ዛሬ ላይ በምናወጣው የመከላከልና የማከሚያ የገንዘብ ወጪ ላይ ነው፡፡
ከአሁን ቀደም ተከሰቶ የነበረውን የኢቦላ ወረርሽኝ በማቆም ረገድ በጤና
ላይ የሚደረግ የገንዘብ ፈሰስ ዓይነተኛ ሚና እንደነበረው መረጃዎች
ያመለክታሉ፡፡ ተጨማሪ የጤና በጀት ብዙ ህይወት ያድናል፡፡

147
152
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

መንግስት ሁለቱንም ጉዳዮች ማለትም ጤናንም ሆነ ኢኮኖሚን በትይዩነት


ሊሰራባቸው ይገባል፡፡ አሁን አንገብጋቢው ጉዳይ ጤና ቢሆንም ጤናው
የሚያስከትለውን የኢኮኖሚ መዛባት በማከም ጭምር አዳዲስ
መመሪያዎችን መቅረፅ ይጠበቅበታል፡፡ በቫይረሱ ስርጭት ሳቢያ በባሰ
ሁኔታ የኢኮኖሚ ተጎጂ የሚሆኑት የንግድ ማህበረሰብ ክፍል ህልውና
ለከፋ አደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ በቱሪዝም ላይ ጥገኛ የሆነና
በቤተሰብ የሚተዳደር ሆቴል ወደ ኪሳራ በመግባት የቤተሰብን አባላት
አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል፡፡ እንዲሁም በአንድ ፋብሪካ ሰራተኛ ላይ
ቫይረሱ ቢገኝ እንዳለ የፋብሪካው ሰራተኞች ወደ ማግለያ ጣቢያ
ስለሚወሰዱ ፋብሪካው ስራ ሊያቆም ይችላል፡፡

አንደምሳሌ የተነሱት የፋብሪካው ባለቤቶችና ሰራተኞችም ሆኑ የሆቴሉ


ባለቤቶች ወደ ኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ የገቡት በራሳቸው ምክንያት
አይደለም፡፡ እርግጥ ነው ቫይረሱ በሚፈጥረው ፍርሃት መገብየት
የሚያቆሙ ደንበኞች ሳቢያ ብዙ ንግዶች ከስራ ውጪ መሆናቸው
አይቀርም፡፡

በመሆኑም መንግስታት ችግሩን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚከተሉትን


መፍትሄዎች በሚችለው አቅም ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባዋል፡፡
የዓለማችን የኢኮኖሚ ምሁራን፡-

1. ገንዘብ ለማውጣት መዘጋጀት፡- ይህም በሽታውን

ለመመርመር፤ ለመከላከል፤ ለማከምና በቀጣይም ለመግታት የሚወሰዱ


እርምጃዎችን ለማጠን ይጠቅማል፡፡ ይህ ወጪ እንዲገለሉ ለታመነባቸው
የህብረተሰብ ክፍሎች አስፈላጊውን አገልግሎት ለማቅረብም ጭምር

148
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 153
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የሚያግዝ ነው፡፡ እንዲሁም በቫይረሱ ስርጭት የተነሳ ቢዝነሳቸው


የተጎዳባቸውንም ለመደገፍ ጭምር ነው፡፡

2. የኢኮኖሚ ኪሳራ ለደረሰባቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች


የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ፡- ይህ ድጋፍ ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ
ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባም ቫይረሱን ለመከላከል ሲባል ሠራተኞች
በቤታቸው እንዲቀመጡ፤ አንዳንድ ድርጅቶች እንዲዘጉ ሊገደዱ ይችላሉ፡፡
ማካካሻ የሚሆን ገንዘብ በግለሰቦችም ሆነ ቀጥተኛ የጉዳት ሰለባ ለሆኑ
ድርጅቶች ማድረግ ከሰብአዊነትም ባለፈ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል
ያግዛል፡፡ በዚህ ረገድ ፈረንሳይና ጃፓን ጥሩ ምሳሌ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
በቤታቸው እንዲቀመጡ ለሚደረጉ ሰዎች የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
እንዲሁም ፈረንሳይ በቫይረሱ የተነሳ በቤታቸው መቀመጥ ላለባቸው
ሰዎች የሐኪም የእረፍት ፈቃድ እንዲሰጣቸው አድርጋለች፡፡
(የሚከፈልበት እረፍት መሆኑ ነው)፡፡

3. ከፍተኛ የኢኮኖሚ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ልዩ እገዛ


ማድረግ፡- ይህም ማለት ኑሯቸውን በዕለት ጉርስ ላይ ላደረጉ

የማህበረሰብ ክፍሎች በኢኮኖሚ መዛባት የተነሳ ሰርተው መዋል


አይችሉም፡፡ እንዲሁም በቤት ውስጥ የመገታት እድል ከገጠማቸው
ተቀማጭ ገንዘብ ወይም ምግብ ከሌላቸው ለከፍተኛ ስቃይ ይጋለጣሉ፡፡
ከዚህ አንጻር ቻይና ያደረገቸው ስራ አጥ ለሆኑ ዜጎች የገንዘብ እርዳታ
የሚያገኙበት ወይም በዓይነት የማቆያ ድጋፍ የሚያገኙበትን መንገድ
የማመቻቸት ስራን ሰርታለች፡፡ በተለይ ከአሁን ቀደም በመንግስት ደረጃ

149
154
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ሲተገበሩ የነበሩት ጸረ ድህነት ስልቶችና የሴፍቲኔት ፕሮግራሞች አሁን


ፊታቸውን ወደዚህ ማዞር ይጠበቅባቸዋል፡፡

በዚህ ረገድ የብልጽግና ፓርቲ እንደ ሳሙና ላሉ የንጽህና ግብዓቶች


መግዛት ለማይችሉ 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ መስጠቱ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡

4. መክፈል ለማይችሉ ዜጎች የግብር እፎይታን መስጠት፡-


በኢኮኖሚው መቀዛቀዝ ሳቢያ ግለሰቦችም ሆኑ የንግድ ድርጅቶች በተለይ
ቀጥተኛ ተጎጂ የሆኑ እንደ ትራንስፖርት ዘርፍ፣ ቱሪዝም፤ ሆቴሎች ፣
አምራች ድርጅቶች ላሉ ዘርፎች ቻይና የግብር እፎይታን አድርጋለች፡፡
ኮሪያ ደግሞ የገቢ ግብርንና የቫየት ክፍያን አራዝማለች፡፡ ቻይናና
ቬትናምም ይህንኑ የማራዘሚያ አከፋፈል ተግባራዊ አደርገዋል፡፡ ኢራን
ደግሞ ለድርጅቶች በአጠቃላይ የግብር ቅነሳ መመሪያን ይፋ አድርጋለች፡፡
በተጨማሪም ቻይና ድርጅቶችን የማህበራዊ ደህነት ክፍያን እንዳይከፍሉ
ለጊዜው እፎይታ ሰጥታለች፡፡

5. የንግድ ስራ ቀጣይነትን ማረጋገጥ፡ ወረርሽኙ እየተስፋፋ


ሲመጣ ሰራተኞች በፍርሃት ሳቢያ በቤታቸው ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ በዚህን
ጊዜ የመንግስት ዋና ዋና መ/ቤቶች ከሰራ ውጪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
የግብርና የጉምሩክ ሰራተኞች ለግብር ከፋዮችና ለሸቀጥ አስመጨዎች
አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ እንዲሁም እንደ ቴሌና
መብራት ሃይልን ጨምሮ ከፍተኛ ወረርሽኝ ቢከሰት አገልግሎታቸውን
እንዴት ከቤታቸው ሆነው መስጠት እንደሚችሉ የቅድመ ዝግጅት እቅድ
ሊኖራቸው ይገባል፡፡

150
ዶ/ር አቡሽ አያሌው

155
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

6. መንግስት ከአበዳሪ አካላት ገንዘብ ማሰባሰብ፡ የኢትየጵያ


መንግስት በቅርቡ ከቻይናው የአሊባባ ግሩፕ የፊት ማስክና የህክምና
መጽሐፍ አቅርቦትን በተመለከተ ኢትዮጵያ እንድታተገዝ የደረሰው
ስምምነት ጥሩ አብነት ሲሆን፤ እንደ አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም አለም
ባንክ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ 50 ቢሊዮን ዶላር የመደበ በመሆኑ ያለ
ወለድ መበደር ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም ከዓለም ባንክና ሌሎች አበዳሪና
ለጋሽ ተቋማት የጥሬ ገንዘብ ማምጣትና ወረርሽኙን ለመከላከልም ሆነ
ኢኮኖሚውን ለመደገፍ ሊያውለው ይገባል፡፡

151
156 ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የኮሮና ቫይረስ ፈዋሽ መድሐኒትና


ክትባት አልባነቱ ምስጢር ምን
ይሆን?
በሽታውን አስፈሪ ካደረጉት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ይህ ነው የሚባል ፈዋሽ
መድሐኒትም ሆነ ለመከላከል የሚያስችል ክትባት የሌለው መሆኑ ነው፡፡
ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ፈዋሽ መድሐኒትም ሆነ ክትባት ለማግኘት ረጅም
ዓመታት የሚወስድ በመሆኑና ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ ጭምር መሆኑ
ነው፡፡ በመድሐኒትነት ምርምር ላይ የሚሠሩ ኩባንያዎች ይህን ያህል
ዓመታትንና ገንዘብን አውጥተው ሲሠሩ መድሐኒቱ በስፋት ጥቅም ላይ
የማይውል ከሆነ ለኪሳራ ሊዳርጋቸው ስለሚችሉም ጭምር ነው፡፡
እንደሚታወቀው ኮሮና ቫይረስ እስካሁን በታሪኩ በውስን አገራት ላይ ብቻ
ያዝ ለቀቅ እያለ ሲከሰት የነበረ እንጂ እንዲህ እንዳሁኑ ራሱን አዳቅሎ
ሠፊ አደጋንና ስጋትን ያስከተለ ባለመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው አለመቻሉ
አንዱ ምክንያትም ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ፈዋሽ መድሐኒትና
ክትባት ለማግኘት ከፍተኛ ርብርብ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በተለይም
አሸባሪዎች ኮሮና ቫይረስን ለጥቃት ዒላማ ሊጠቀሙት ይችላሉ የሚለው
ስጋት በተለይም በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ በኩል ከፍተኛ ስጋት እየፈጠረ
በመሆኑ መድሐኒቱን በፍጥነት ለማድረስ እንደ አንድ አስጨናቂ
ምክንያት ይጠቀሳል፡፡

ለኮቪድ 19 አስተማማኝ ክትባት እስካሁን ባይገኝለትም ክትባቱን


ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራዎች በመደረግ ላይ ናቸው፡፡ ለዚህ የቫይረስ
ቤተሰቦች ማለትም ሳርስ ኮሮና ቫይረስ እና መርስ ኮሮና ቫይረስ ለተባሉት

152
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው 157
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ቫይረሶች ለእንሳስት እና አእዋፍት ክትቫት የተገኘ ቢሆንም ይህ በሰዎች


ላይ ሊሰራ አልቻለም፡፡ ለኮቪድ 19ም ቢሆን እጅግ የበዙ ድርጆቶች እና
ሀገሮች ብዙ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም እስካሁን ክትባቱ ግን አልተገኘም፡፡

የአሜሪካ የጤና እና የሰው ሃብት ዲፓርትመንት በበኩሉ ከጃንሰን እና


ከሳኖፊ ከምፓኒዎች ጋር እጅ እና ጓንት ሆኖ በመስራት በሚቀጥሉት
ጥቂት ወራት ውስጥ ወደ ክትባቱ ግኝት እንደሚያመራ ተስፋ አለው፡፡

የቡልጋሪያው ባዮቴክኖሎጂ ካምፓኒ በበኩሉ ለባለፉት አራት አመታት


ለኮቪድ 19 ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ለኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች ክትባት
በመፈለግ ላይ ቆይቷል፡፡ አሁን ደግሞ እስከ 2020 አጋማሽ የኮቪድ 19
መንስኤ ለሆነው SARS- CoV-2 ክትባት እንደሚያገኝ አስታውቋል፡፡

የአሜሪካው ብሔራዊ የአለርጂ እና የተላላፊ በሽታዎች ማዕከል


እንዳስታወቀው ደግሞ ለኮቪድ 19 ክትባትን ለማግኘት በትንሹ ከአመት
እስከ 18 ወራት ድረስ ሊፈጅ ይችላል፡፡

አንድ ለምርምር ማዕከላት ለጥናት የሚሆኑ ኮምፒውተሮችን በማቅረብ


የሚታወቀው የበጎ አድራጎት ድርጅት በፌብራውሪ 27 እንዳስታወቀው
ደግሞ ክትቫቱ እየተዘጋጀ ነው ነገር ግን የቫይረሱን ፕሮቲን ቅርጽ
ለማውጣት የኮምፒውተር ስራ እየተሰራለት ይገኛል፡፡

የህንድ ጤና ሚኒስቴር እንዳሳወቀው ደግሞ ኢንስቲቲዩታቸው 11 አይነት


የቫይረስ ዝርያዎችን ለይቶ ማውጣት እንደቻለ እና ክትባቱን ለመስራት
በትንሹ ከ 18 ወራት እስከ 2 አመታትት ድረስ ሊፈጅ እንደሚችል
ገልጽዋል፡፡

153
158 ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ይህም ይባል ያ ግን እስካሁን በተጨባጭ የተገኘ የኮቪድ 19


ክትባትም ሆነ መድሃኒት የለም፡፡ ከ18 ወራት በፊት ለቫይረሱ ክትባት
ይገኛል ብሎ እንደማያምን የአለም ጤና ድርጅትም አሳውቋል፡፡ ነገር ግን
በቅርቡ ቢያንስ ክትባት ሊገኝለት እንደሚችል በአለም ዙሪያ የሚደረጉ
ሳይንሳዊ ሽቅድድሞች ፍንጭ ይሰጣሉ፡፡

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ በብዙ መገናኛ ብዙሃን ለኮቪድ 19 የታወቀ


ክትቫት ያለ ነገር ግን ሆን ተብሎ እንደተደበቀ ተደርጎ የሚናፈሰው
ከአሉባልታ የዘለለ አይደለም፡፡

154
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 159

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ማንበብ ብቻ ሳይሆን እውቀቱን


ያስታውሱት፤ ወደ ልማድም ይቀይሩ

የኮሮና ቫይረስ መተላለፊያ መንገዶች ማለትም ንኪኪዎች ብዙ ናቸው፡፡


ለመከላከል የሚያስችሉ ልዩ ልዩ መንገዶች ደግሞበዚህ መፅሃፍ ውስጥ
ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡ ይሁን እንጂ ከመጽሐፉ ያገኙትን እውቀት ወደ
ዕለት ተዕለት ትግበራ መቀየር ቀላል አይደለም፡፡ በቀላል ምሳሌ እንኳን
ፊታችንን፣ ዓይናችንን፣ አፋችንን፣ አፍንጫችንን በእጃችን መንካት
እንደሌለበን እያወቅን በቀን ውስጥ ሳናውቅ ደጋግመን እንደነካን ራሳችንን
ሳንታዘበው አልቀረንም፡፡ በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና ታጠቡ፣
አትጨባበጡ እየተባልን ይህን ለማክበር የቀድሞው ልማዳችን
ያስቸግረናል፡፡

በመሆኑም ሁላችንም የልማድ ውጤት በመሆናችን ስለ ኮሮና ቫይረስ


መተላለፊያ መንገዶችና መከላከያ ስልቶች በየቀኑ ደጋገመን ማንበብ
ትውስታችንን በማሳደግ አዲስ ልማድ እንድናዳበር ያደርገናል፡፡ እንዲሁም
ከቤተሰብ አባላት ጋር እያነበብን በተወያየን መጠን ትውስታችንና
ልማዳችን ይዳብራል፡፡

በመሆኑም መጽሐፉን በቀጣይ አምስት ቀናት ጧትና ማታ ደጋግመው


ያንብቡት፤ ከሌሎች ጋር ይወያዩበት፤ ሌሎችንም ያስተምሩ፤ በየዕለቱ
ማታ ማታ ከመጽሐፉ መረጃዎች አንጻር ምን ምን ጉዳዮች ላይ ስህተት
እንደሰሩና ጥሩ እንደሰሩ ራስዎን በመገምገም ልማድዎን ያሻሽሉ፡፡

155
160
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የማህበራዊ ሚዲያው ክፉና ደግ-


ዘመነ ኮሮና
የማህበራዊ ሚዲያው ምን አጎደለብን፣ምን
አተረፈልን?
ቻይናዊቷ ዶኮተር አይ ፌን በውሃን ከተማ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል
የድንገተኛ ክፍልን ትመራለች። ከታህሳስ መጨረሻ ዕለታት በአንዱ
የአንድ ታካሚ የምርመራ ካርድ እና ታሪክ ትኩረቷን ሳበው። ይህ የሳንባ
ምች መሰል በሽታ የያዘው ሰው የህክምና ታሪክ ከአስራ ሰባት ዓመታት
በፊት ቻይናን ያሸበረው የሳርስ ወረርሽኝን የሚመስል ቫይረስን ያሳይ
ነበር። ሁኔታውንም ዶኮተር ፌን ለባልደረባዎቿ አሳወቀች። ይህን ካወቁ
ሃኪሞች አንዱ የነበረው ሊ ዋኒላንግ እና ሌሎች ሰባት ሃኪሞች ይህን
መረጃ ለሌሎች በማካፈላቸው በህዝብ መካከል "ጥርጣሬና ሃሜት
በማሰራጨት" ክስ በፖሊስ ተይዘው ነበር። በኋላ ላይ በዚህ ያልታወቀ
ቫይረስ የሚታመሙ ሰዎች ሲበረክቱ ወደ ህክምና ስራቸው እንዲመለሱ
ተደርጎ ነበር። ዶ/ር ሊ ግን ከቻይና ፖሊስ በባሰ ባለስልጣን ተያዘ። በኮሮና
ቫይረስ ተጋልጦ ነበርና በቫይረሱ ተጠቅቶ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።
በቻይና ባለስልጣናት ዘንድ ለህዝብ መረጃውን በማህበራዊ ሚዲያ
አውጥተሃል ተብሎ ውግዘት የደረሰበት ሃኪም ህይወቱ ቢያልፍም
መረጃው በሰፊው መዳረሱ ቻይና የተፈጠረውን ችግር አምና ማብራሪያ
እንድትሰጥና ፣ ምንነቱን በይፋ ያላወቀችው ቫይረስ በርካቶችን ህመም
ላይ እንደጣለ ይፋዊ መግለጫን እንድታወጣ አስገድዷት ነበር። በርካታ
ቻይናውያን ዊ-ቻት እና ዊቦ በተሰኙትና የትዊተር አቻ በኾኑት

156
አቡሽ አያሌው
ዶ/ር 161
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻቸው መንግስታቸውን ሲያወግዙ፣ በዚህ


የቴክኖሎጂና ማህበራዊ ሚዲያ ዘመን እንዴት ወረርሽኝ ይደበቃል? ሲሉ
ቁጣቸውን ገልጠዋል።

ማህበራዊ ሚዲያና ወረርሽኞች


አለምአቀፍ ወረርሽኞች ለአለማችን ብርቅ አይደሉም። በተለይም ማህበራዊ
ሚዲያ ከተስፋፋ ወዲህ የመጡት እንደ ኢቦላና፣ ዚካ በአንፃራዊነት የተሻለ
ቁጥጥር የተደረገባቸውና ማህበራዊ ሚዲያም አስተዋፅዖ ያደረገበት ነበር
። ግን እንዳሁን አልነበረም። በዘመነ ኮሮና ቫይረስ ማህበራዊ ሚዲያ
ፈፅሞ ቸል የማይባል ትልቅ መሳሪያ መኾኑ በእርግጥ ታይቷል።
ማህበራዊ ሚዲያው በእርግጥም የተደበቀውን ይፋ ማውጣት ብቻ ሳይኾን
የኮሮና ቫይረስን የተመለከቱ ብዙ ጥሩም ኾነ የተፋለሱ የውሸት መረጃዎች
መንሸራሸሪያ ቦታ ኾኖ ታይቷል። በክፉም በደግም ተፅዕኖውም በስፋት
እየተነሳም ይገኛል።
ከበጎ ተፅዕኖው መካከል ዋነኛው ባለፉት ሳምንታት ሰዎች በማህበራዊ
ሚዲያ ስለኮሮና ቫይረስ - ኮቪድ 19 - ከአለም ጤና ድርጅት፣ ከየአገራት
ጤና ሚኒስትሮችና ስም ያላቸው ሚዲያ ተቋማት ሁነኛ መረጃ
ያገኙባቸውና እርስ በእርስ የተጠያየቁባቸው፣ እንዲሁም ስነልቦናዊ ድጋፍ
የጠየቁባቸው፣ በአቅም ለደከሙት ደግሞ ገንዘብ የማሰባሰብ እና ለተጎዱት
መድረስ የተሰራበት ሆኗል።

157
162 ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ


ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ ሰዎች መረጃ የሚፈልጉት ከዋነኞቹ ሚዲያ
ተቋማት ይልቅ ከማህበራዊ ሚዲያው መኾኑን ብዙዎቹ አረጋግጠዋል።
ለወትሮው የማህበራዊ ሚዲያ እጅግም የማይስባቸው ሰዎች ሳይቀር ወደ
ማህበራዊ ሚዲያ መምጣታቸውም ተስተውሏል። ይህ ምናልባትም
ወረርሽኙ በየሰዓቱ ስፋትና ጥቃቱ እየጨመረ ከመምጣቱና መረጃዎችም
በፍጥነት እያደጉና እየተቀያየሩ ከመምጣታቸው ጋር የተያያዘ እንደኾነ
ፖለቲኮ ለተሰኘው ድረ ገፅ የቴክኖሎጂ ጉዳዮችን የሚተነትኑት ማርክ
ስኮት ፅፈዋል።

ማህበራዊ ሚዲያ - በኮሮና "ቁም እስር" ወቅት


የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሲባል እንቅስቃሴዎች በጠቅላላው
ታግደው በነበሩባቸው የቻይና ከተሞች ከ 50 ሚሊዮን የሚልቁ ሰዎች
ከቤታቸው መውጣት አይችሉም ነበር። በጣሊያንና ሌሎች የወረርሽኙ
ወላፈን ክፋኛ የገረፋቸው አገራት ዜጎች ከቤታቸው መቆለፍ ግዴታቸው
ሆኗል። ለእነዚህ ሚሊዮኖች ከተቀረው ዓለም መገናኛ ሁነኛው አማራጭ
ማህበራዊ ሚዲያ ኾኖ ቆይቷል። መርከቦችን ጨምሮ በብዙ ስፍራዎች
ተነጥለው የተቀመጡ ሰዎች ስቃይና ከራሞታቸውን አጫጭር ቪዲዮዎ
እየቀረፁ ለወዳጅና ዘመዶቻቸው እንዲኹም ለሚዲያ ተቋማት ሲያጋሩ
ታይተዋል። ይህን ተከትሎም በርካቶች አይዟችሁ የሚሉ መልዕክቶችን
በመላክ ሲያፅናኗቸው እና ስነልቦናዊ ድጋፍ ሲሰጧቸው ተስተውሏል።

158
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 163

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

የውሸት መረጃ አምባ


ከዚህ በተቃራኒው የሃሰት መረጃዎች፣ ከኮሮና እንፈውሳለን ባዮች ሰዎችን
ያጭበረበሩባቸውንና ያልተገባ ትርፍ ያገኙባቸው መድረኮችም ኾነው
ቀጥለዋል ። በተለይ የማህበራዊ ሚዲያ መረዳት ሚዲያ ሊትሬሲ
አቅማቸው ዝቅተኛ በኾኑ አገራት ማህበራዊ ሚዲያውን ማረቅ ለጤና
ባለስልጣናቱ ትልቅ ፈተና ሆኗል።

ወግድ የማይሉትን የማረቅ ጥረቶች


የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በማህበራዊው ሚዲያ የሚሰራጩ የኮሮና
መረጃዎችን ለመቆጣጠርና ለማጥለል ብዙ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።
የቻይናው ማህበራዊ ገፅ ዊ ቻት፣ ፌስቡክ እና ትዊተር የገፆቻቸውን
ሃሰተኛ መረጃ መለያ ዘዴዎች ወይም አልጎሪዝም በማሰልጠን ብዙ እየሰሩ
ይገኛሉ። ጉግል ለምሳሌ የኮሮና ቫይረስን ወረርሽኝ የተመለከተ መረጃ
ለሚጠይቁ ሰዎች በቀዳሚነት በፍለጋው ውጤት የሚያሳየው እንደአለም
ጤና ድርጅት ያሉ ተዓማኒ ገፆችን ነው። እርግጥ ጥረቱ ገና ብዙ
የሚቀረው እንደኾነ የጉግል ስራ ሃላፊዎች ተናግረዋል።

የሁሉም ባለሞያዎች ምክር ማህበራዊ ሚዲያ ይቅርባችሁ የሚል


አይደለም። ምክንያቱም አወንታዊ ተፅዕኖውን መካድ አይቻልምና።
ፌስቡክ እና ጎግል ባወጡት መግለጫ እንዳሳሰቡት ብዙ ተከታይ
ያሏቸውን ሰዎች በቁጥር ሚዛን ብቻ በመከተል የተጣራ የኮሮናን መረጃ
ማግኘት ስለማይቻል ከማህበራዊ ሚዲያ ተቋማት እውቅና ያገኙ ሰዎችና
ተቋማትን (ቬሪፋይድ አካውንቶች) ብቻ በመከተል፣ አንድን አጠራጣሪ

164 159
ዶ/ር አቡሽ አያሌው

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

መረጃ ከተጨማሪ ምንጮች በመፈለግና በማየት የራስን ማጣሪያ


ማበጀትና መረጃውን መውሰድን መክረዋል። ይፋዊ የጤና ሚኒስቴር
መስሪያ ቤቶችና የነርሱ ተቋማት፣ እንዲኹም የሚዲያ ተቋማትን
የትዊተርና ፌስቡክ ገፆች መከተልም ይመከራል።

160
ዶ/ር አቡሽ አያሌው 165

ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ይህንን ያውቃሉ?
ኮሮናቫይረስን በባዮሎጂክ ጦር
መሳሪያነት የሚያውለው ማን
ይሆን?
አሁኑ ወቅት ዓለማችንን ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ እያመሰ ያለው ወሬ
አንድ ቡድን ወይም አንድ አገር ሌላውን አገር በኮሮና ወረርሽኝ የማጥቃት
ዓላማ ሊኖረው ይችላል የሚለው ነው፡፡ ይህን መሠሉ ተላላፊ በሽታን
እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም የመረበሽ ወይም የማስፈራራት አካሄድ
ባዮቴሮሪዝም በመባል ይጠራል፡፡ ለምሳሌ አንድ በአሸባሪነት የተፈረጀ
ቡድን ይህን ስልት ሊጠቀመው ይችላል፡፡

ኮሮና ቫይረስን ለባዮቴሮሪዝም


ባዮቴሮሪዝም ማለት ባዮሎጂካዊ የሆኑ ህይወት ያላቸው በሽታ አምጪና
በቀላሉ ተዛማጅ የሆኑ ቫይረሶችን ሆን ብሎ በአንድ አገር ህዝብ ላይ
በማዛመት የአንድን አገር ህዝብና መንግስት ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ
የመክተት ተልዕኮ ነው፡፡ ህዝብ በከፍተኛ ደረጃ ያልቃል፤ በእጅጉም
ይረበሻል፣ የአገሪቱ ደህንነት አደጋ ላይ ይወድቃል፣ የዚያች አገር
ኢኮኖሚም ክፉኛ ይጐዳል ማለት ነው፡፡ ባዮቴረሪዝም ራሱን የቻለ
የባዮሎጂክ የጦር መሳሪያ ሲሆን የሚያደርሰው አደጋም ከኑክሌር ቦምብ
የሚተናነስ ላይሆን ይችላል።

ለመሆኑ የኮሮና ቫይረስን ለዚህ መሠል አገልግሎት ጥቅም ላይ ያዋሉ


አገሮች አሉ?
161
166
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

በእርግጥ በጥቅም ላይ ያዋሉ የሉም፡፡ ይሁን እንጂ ከአሁን ቀደም


የቀድሞዋ ሶቪዬት የአሁኗ ሩሲያ ኢቦላን ለባዮሎጂ የጦር መሳሪያነት
ለመጠቀም ሙከራ ያደረገች የመጀመሪያዋ አገር ነች፡፡ ሶቪዬት ሪፐብሊክ
በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ምርምር በማድረግ ጠላት በምትላቸው አገራት
ላይ ለመጠቀም ትኩረት አድርጋ የሠራችባቸው ጀርሞች እነዚህ ነበሩ፡፡
ፈንጣጣ አምጪው ቫይረስ (Small pox)፣ የአባ ሠንጋ በሽታ (anthrax)፣
የነርቭ በሽታ የሚያስከተለው ጀርም (ቦቱሊዝም) እንዲሁም ኢቦላ ዋና
ዋና ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት የፈንጣጣ ቫይረስን በላብራቶሪ ደረጃ
ከያዙ አገራት ውስጥ አንዷ ሩሲያ ናት፡፡ ይህ በሽታ በውጤታማ የክትባት
ዘመቻ ከምድረ ገፅ ቢጠፋም ቫይረሱ በአጋጣሚ አምልጦ ቢወጣ ወይም
ሆን ተብሎ ቢለቀቅ እጅግ ተላላፊ በመሆኑ ብዙዎችን የመጨረስ አቅም
አለው፡፡

ለመሆኑ አንድ በአሸባሪነት የተፈረጀ ቡድን በአንድ አገር ላይ ይህን በሽታ


እንዴት ሊያዛምተው ይችላል?

ይህ እንግዲህ በተለያየ መልኩ ሊተገበር ይችላል፡፡ በዋናነት ይህ ቫይረስ


በአሁኑ ወቅት ክፉኛ እየተዛመተ የሚገኝና መላውን የዓለም ህዝብ
በማሸበር የሚገኝ በሽታ ነው፡፡ ይህ በሽታ ወደዚህ ደረጃ ሊያድግ የቻለው
በቅድሚያ ከእንስሳት የተዛመተው ቫይረስ አንድን ቻይናዊ ግለሰብ
ከማጥቃት በመጀመር ነው፡፡ ይህም የመጀመሪያ ግለሰብ በህክምናው
አጠራር “patient zero” በጊዜ ሂደት ውስጥ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች
መለከፍና ህልፈት አስተዋፅኦ ሊያደርግ ችሏል፡፡ እውነታው ይህ ከሆነ
ታዲያ በሽታውን ሆን ብለው የሚያዛምቱ ጥቂት ሰዎች ወደ አተገባበሩ
ከመጡ ብዙ ሰዎችን የመጨረስ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ ማለት

162
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው
167
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ይሆናል።ይህን መሠል ጥፋት ለማድረስ ታዲያ በቀላሉ አራት መንገዶችን


መጠቀም ይችላሉ፡፡ የመጀመሪያው መንገድ የኮሮና ቫይረስን በተቀጣጣይ
ፈንጆች ውስጥ በማድረግና ህዝብ በተሠሳሰበባቸው ቦታዎች ላይ
እንዲፈነዳ በማድረግ ነው፡፡ አንዴ ቦምቡም ሲፈነዳ እስከ 30 ጫማ ርቀት
ክልል ውስጥ ባሉ ሰዎች ሰውነት ላይ ፍንጥርጣሪው የማረፍ ዕድል
ይኖረዋል፡፡ ይህም ፍንጥርጣሪ ቫይረሱን ተሸክሞ በሰዎች ሰውነት ላይ
ያርፋል ማለት ነው፡፡ እነዚህም ሰዎች እያንዳንዳቸው በሂደት ሌሎች
ሰዎችን ቢያስይዙ እንዲህ እንዲህ እያለ በአጭር ሳምንታት ውስጥ
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ይያዛሉ ማለት ነው፡፡ በሽታው ተዛማች
በመሆኑ፡፡

ሁለተኛው መንገድ ተብሎ የተቀመጠው ደግሞ በኢቦላ ላይ የተመሰረተ


አብረን እንጥፋ ተልዕኮ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም ማለት ጥቂት ሰዎች
ቫይረሱ ወዳሉባቸው አገራት በመሄድ ከተያዙ ሰዎች ምልክቱ
ሳይታይባቸው ያንን አገር በመልቀቅና በአውሮፕላን በመሳፈር ጥቃቱን
ወደሚፈፅሙበት አገር መዝመት ይሆናል፡፡ በዚያም አገር ሰው
በተሰበሰበበት አካባቢ ሠላም በማለት ፣ በማስነጠስና በማሳል ማዛመት
አንዱ መንገድ ሊሆን ይችላል፡፡ በመጨረሻ በበሽታው ራሳቸው እስኪሞቱ
ድረስ፡፡

በአራተኛ ደረጃ የተቀመጠው ደግሞ ራሳቸውን በበሽታው ሆን ብለው


በማስያዝና ቦምብ በመታጠቅ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦምቡን በማፈንዳት
የሰውነታቸውን ፍንጥርጣሪ በሰዎች ላይ እንዲበተን የማድረግ ተልዕኮ
ሊሆንም ይችላል የሚለው ነው፡፡ በአምስተኛ ደረጃ ደግሞ በኮሮና ከተያዘ

163
168
ዶ/ር አቡሽ አያሌው
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ሰው ፈሳሽ በመውሰድ በልዩ መርጫ መሳሪያ ውስጥ በማስገባት ሰዎች


በጋራ በሚጠቀሙባቸው ነገሮች ላይ መርጨት የሚል ይገኝበታል፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህን ሁሉ መንገዶች በእሳቤ ደረጃ ሊጠቀሙ ይችላሉ


የሚለው ግምት በትግበራ ደረጃ ከባድና ውስብስብ በመሆኑ የሚሳካ
እንደማይሆንም ተመራማሪዎች እየገለፁ ይገኛሉ፡፡

164
ዶ/ር
አቡሽ አያሌው
169
ይህንያውቁ ኖሯል
በሽታው ለሚያስከትለው
የሳል ህመም የሳል መድሐኒት
መውሰድ፣ ለትኩሳቱ ደግሞ
ፓራሲታሞል መውሰድ የሚመከር
ሲሆን አይቡፕሮፌን የተባለውን
የትኩሳትና የህመም ማስታገሻ
መውሰድ ግን ህመሙን ያባብሰዋል
እና ይጠንቀቁ፡፡
ኮሮና ቫይረስ / Corona Virus

ማጣቀሻ ምንጮች
1. ብሪቲሽ ሜዲካል ጆርናል (ሳምንታዊ ጥንቅር ፣ ከጥር እስከ
መጋቢት 2012)
2. ዘላንሴት ጆርናል ፤ሣምንታዊ ጥንቅር (ከጥር እስከ መጋቢት
(2012)
3. ዘኒው ኢንግላንድ ጆርናል ኦቭ ሜድስን (ሳምንታዊ ጥንቅር
ከጥር እስከ መጋቢት(2012)
4. ኒው ሳይንቲሰተስ መጽሄት (ሳምንታዊ ጥንቅር ከጥር እስከ
መጋቢት(2012)
5. ሳይንቲፊክ አሜሪካ (ሳምንታዊ ጥንቅር ከጥር እስከ
መጋቢት(2012)
6. የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚ/ር ዌብሳይት (ከጥር እስከ
መጋቢት(2012)
7. የኢትዮጵያ የማህበረሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዌብሳይት (ሳምንታዊ
ጥንቅር ከጥር እስከ መጋቢት(2012)
8. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዌብሳይት
9. የዓለም የበሽታዎች መከላከያ ማዕከል ዌብሳይት (እለታዊ ጥንቅር
ከጥር እስከ መጋቢት(2012)
10. የዓለም ጤና ድርጅት ዌብሳይት (ዕለታዊ ጥንቅር ከጥር
እስከ መጋቢት(2012)
11. በቻይና ውሃንና ሁቤይ ግዛቶች የተደረጉ ልዩ ልዩ ምርምሮች

170 165
ዶ/ር አቡሽ አያሌው

በልዩ ልዩ ጤና ጉዳዮችና
በኮሮና ዙሪያ ሳይንሳዊ
ትንታኔዎችና ዜናዎችን
ለመከታተል ተወዳጇ
ሜዲካል ጋዜጣ
“ Medical Newspaper”
የሚለውን የፌስቡክ ገፅ
“Like” በማድረግ
ትክክለኛ መረጃ ያግኙ!!
የዶ/ር አቡሽን ተከታታይ
ትምህርቶችና የማነቃቂያ
ንግግሮች በዩቲዩብ
ይከታተሉ፤
“Dr Abush Ayalew”
የሚለውን የዩቲዩብ ቻናል
በየሳምንቱ መረጃዎች
እንዲደርሶት
“Subscribe” ያድርጉ!!

You might also like