You are on page 1of 47

የህዳሴ ጉዞአችን የሚገኝበት ሁኔታ፡-

ስኬቶችና ተግዳሮቶች

ለክረምት ስልጠና ለአወያዮች ማጣቀሻ/ደጋፊ ፅሁፍ

ሐምሌ 2006

0
የህዳሴ ጉዞአችን የሚገኝበት ሁኔታ

መግቢያ

በሀገራችን ለዘመናት ተንሰራፍተው የነበሩ ዓፋኝና ጨቋኝ ስርዓቶች በህዝቦች መራራ


ትግል በማስወገድ በአዲስ ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ መንገድ መጓዝ በመቻላችን ቀጣይነት
ያለው ዕድገት እያረጋገጥን እንገኛለን። ለዘመናት በላያችን ላይ ተጭኖ የአለም ጭራ ሆነን
እንድንታይ ያደረገን ድህነት ለማስወገድ የጀመርነው የፀረ-ድህነት ትግል በማቀጣጠልም
በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን የድህነትና የኋላቀርነት ተምሳሌት የመሆናችን ታሪክ ከጊዜ ወደ
ጊዜ እየደበዘዘ በአንጻሩ በዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ዘንድ የፈጣን ዕድገት እና የብሩህ
ተስፋ ተምሳሌት በመሆን ላይ እንገኛለን። ይህም የሚያሳየው በአንድ ወቅት በአለም
ስልጣኔ ማማ ላይ የነበረች ለረጂም ጊዜ በማሽቆልቆል ጉዞ ተጉዛ ልትበታተን የተቃረበች
ሀገር ከማሽቆልቆል ጉዞ ወጥታ ወደ ነበረችበት የስልጣኔ ቦታዋ ለመመለስ ወደላይ
የመውጣት የህዳሴ ጉዞ የጀመረች መሆኑ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የህዳሴ ጉዞ በጽኑ ህዝባዊ
መሰረት የተጀመረና በትውልዶች ቅብብሎሽ የሚጠናቀቅ የረጅም ጊዜ ግብ የሰነቀ
የሁሉንም ኢትዮጵያዊያን ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑ ተሰምሮበት ያደረ ነው፡፡

የህዳሴ ጉዟችን አሁን ላይ ሆነን ስናየው በስኬቶች ታጅቦ እየቀጠለ ይገኛል፡፡የሀገራችን


ህዳሴ ዋነኛ መሰረቱ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ፈቅደውና አምነው
ያጸደቁት ዴሞክራሲያዊ ህገ መንግስታችን ነው፡፡ ህገ መንግስቱን መሰረት አድርገው
ከሀገራችን ተጨባጭ የልማት፣ የሰላም እና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች የመነጩ ሀገር በቀል
ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች ተቀርጸው ተግባራዊ መደረጋቸው ደግሞ የስኬቶቻችን
ምንጮች ናቸው፡፡ ገጠርና ግብርናን መር የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴያችን ግንባር
ቀደም ተጠቃሽ ነው። የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲዎቻችን ፀጋዎቻችን አሟጠን
መጠቀም በሚያስችለን መልኩ የተቀረፀ በመሆኑ ዕድገታችን ፈጣን፣ ቀጣይነት ያለው እና
ፍትሐዊ ሆኖ ሁሉም የሀገራችን ህዝቦች የሚያሳትፍ እና በተሳትፎአቸው ልክ ተጠቃሚ
እያደረገ ይገኛል። የበለፀገችና የዳበረ ኢኮኖሚ የገነባች አዲሲቷ ኢትዮጵያ የመገንባት
ራዕያችን እውን ማድረግት እንችል ዘንድ ኢኮኖያዊ መዋቅሩ ከግብርና መር ወደ
ኢንዱስትሪ መር የልማት አቅጣጫ መሸጋገር እንዳለብን በመገንዘብ በአምስት ዓመቱ
የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችን ግልፅ አቅጣጫ አስቀምጠን ቀጣይነት ያለው

1
ርብርብ እያደረግን እንገኛለን። የኢንዱስትሪ ልማታችን በቀጣይነት በመገንባት የሀገራችን
ህዳሴ እውን ማድረግ የሚያስችሉን አበራታች ስኬቶች በማስመዝገብ ላይ ስንሆን በዘርፉ
ያሉት ማነቆዎችን ለመፍታት አቅጣጫዎች ተቀምጠው ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ።

በመሰረተ ልማት ረገድም ባለፉት 23 ዓመታት በሀገራችን የተከናወኑ የልማት ስራዎች


ውጤታማ ነበሩ ማለት ይቻላል። በመሰረተ ልማት ዘርፍ የተከናወኑ ሰራዎች አንድ
የኢኮኖሚ ማሕበረሰብ ለመገንባት ያስቀመጥነው ሕገ መንግስታዊ ዓላማ ዳር ለማድረስ
እጅግ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ። ስለሆነም በሀገራችን ለዘመናት ተከማችቶ
ከነበረው ችግራችን አንፃር አሁንም ብዙ የሚቀረንና ብዙም መስራት የሚጠበቅብን
ቢሆንም በመንገድና ትራንስፖርት፣ በቴሌኮም ማስፋፋትና ተደራሽነት፣ በኃይል
አቅርቦትና ተደራሽነት እንዲሁም መሰል ዘርፎች የተከናወኑ ስራዎች ስኬታማ ናቸው ብሎ
መውሰድ ይቻላል።

በማሕበራዊ ልማት ዘርፍም እንዲሁ ወደ ፊት እየገሰገስን እንገኛለን። የሰለጠነና ጤንነቱ


የተጠበቀ አምራች ዜጋ በመፍጠር ረገድ ሀገራችን ስኬታማ ተግባር እያከናወኑ ከሚገኙ
ሀገራት መካከል ማሰለፍ ችለናል። ሀገራችን የተያያዘችው የተሃድሶ ጉዞ በሚፈለገው ደረጃ
ለማሳካት በዕውቀት የዳበረ፣ በቂ ክህሎት ያለው እና የተስተካከለ አመለካከት ያለው ዜጋ
ማፍራት ላይ ትኩረት ሰጥተን በመስራታችንም ተጨባጭ ውጤቶችን በማስመዝገብ ላይ
እንገኛለን። በጤና ረገድም መከላከልን ማዕከል ያደረገው ፖሊሲያችን ሀገራችን የምዕተ
ዓመቱን የጤና ግቦች ከሚያሳኩ ጥቂት ሀገሮች መካከል ማሰለፍ አስችሏታል።

በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደትም ሀገራችን ከአንድ የስኬት ምዕራፍ ወደ ቀጣዩ


የስኬት ምዕራፍ በመሸጋገር ላይ ነች። ሀገራችን የየራሳቸው የአኗኗር ዘይቤ፣ ታሪክ፣
ሃይማኖትና እምነት፣ ቋንቋ፣ ባህልና ወግ ያላቸው በርካታ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች
የሚኖሩባት የብዙሃን ሀገር እንደመሆኗ መጠን ብዝሃነታችን በአግባቡ በማስተናገድ
አንድነታችን ጠብቀን በመቀጠል የፌዴራል ስርዓቱ ሀገር ይበታትናል በሚል የጥፋት
ትንበያ ላይ ለተሰማሩ የውጭም ሆኑ የውስጥ ሃይሎች በተግባር ያከሸፈ ዴሞክራሲያዊ
የፌዴራል ስርዓት መገንባት አስችሎናል። ለዚህም የሀገራችን የፌዴራል ስርዓት በሌሎች
ሀገሮችና ህዝቦቻቸው እንደ ስኬታማ ማሳያ እየሆነ በመምጣቱ ከሀገራችን ልምድና ተሞክሮ
የሚወስዱበት ሁኔታ እየተጠናከረ መጥቷል።

2
በሁሉም ዘርፎች ያስመዘገብናቸው ዘርፈ ብዙ ስኬቶች የሀገራችን ህዳሴ እውን ለማድረግ
እውነታኛ ማሳያዎቸ ቢሆኑም በየዘርፉ ያሉብን ተግዳሮቶች በቀጣይነት እየፈተሹ ወቅታዊ
ምላሽ የመስጠቱ ጉዳይም እንዲሁ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ነው። በመሆኑም እዚህም
እዚያም የሚያጋጥሙን ተግዳሮቾት አንዳንዶቹ ፈጣኑ ልማታችን የወለዳቸው የልማት
ውጤቶች ስለሆኑ መፍትሔውም ልማታችን ማፋጠን ሲሆን ሌሎች ከኪራይ ሰብሳቢነት
አስተሳሰብ እና አመለካከት የሚመነጩት ደግሞ ልማታዊ ፖለቲካል ኢኮኖሚ በመገንባት
አቅጣጫ ለመፍታት ያለሰለሰ ጥረት ማድረግ ይኖርብናል።

በዚህ ጽሁፍ የሃገራችን የህዳሴ ጉዞ ያለበትን ሁኔታ በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር


በመረጃ ተደግፎ ለመተንተን ተሞክሯል፡፡ በመሰረታዊ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ
ጉዳዮች በማተኮር ያሉን ስኬቶች፣ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን እና የመፍትሄ
አቅጣጫዎችን በማመላከት ቀርቧል፡፡

1. የግብርናና ገጠር ልማት ትራንስፎርሜሽንና ህዳሴያችን

በቅድመ 1983ዓ.ም የነበሩ የሀገራችን ገዥ መደቦች የሀገሪቱ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት


ለሆነው የግብርና ዘርፍ ሲሰጡት የነበረው ትኩረት እጅግ አናሳ ከመሆኑም በላይ
ግብርናውን የሚፈልጉት የህዝቡ ኑሮ ለማሻሻል ሳይሆን ለገዥ መደቦችና ተከታዮቻቸው
መጠቀሚያ ነበር። ስርዓቶቹ ለግብርናው ዘርፍ ተገቢ ትኩረት ካለመስጠታቸው
በተጨማሪ የሀገራችን አርሶ አደር ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ በመጣው ኋላቀር
የግብርና ዘይቤ ተጠቅሞ ያመረተውን ምርት በነፃነት እንዳይጠቀም የተለያዩ ስልቶችን
እየቀየሱ አርሶ አደሩ እያመረተ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚረከቡበት ሁኔታ ነበር።
በመሆኑም አርሶ አደሩ በአንድ በኩል ከዘመናዊ የግብርና አሰራር እንዲተዋወቅ
ባለመደረጉ በሌላ በኩል ደግሞ በልምድ ያመረተውም ቢሆን የገዥ መደቡ መጠቀሚያ
በመሆኑ ለዘመናት ሁለት ስለት ባለው ቢላ እየተቀረጠፈ አስከፊ ህይወት ለመግፋት
ሲገደድ ነበር።

የዓፈናና የጭቆና ስርዓቱ በህዝቦች መራራ ትግል ከተገረሰሰ ወዲህ ግን ግብርና መር


የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ በማዘጋጀት የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ በበቂ ሳይንሳዊ
ዕውቀት መምራት የሚያስችል ስልት ተቀይሶ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል፡፡ እነሆ አሁን

3
ግብርናችን በከፍተኛ ፍጥነት ማደጉን ተያይዞታል። ለዘመናት ምርቱን ወደ ገበያ ማቅረብ
ቀርቶ ቤተሰቡን እንኳን በአግባቡ መመገብ ባለመቻሉ አብዛኛው ህዝባችን በአስከፊ
ድህነት ውስጥ ይማቅቅ የነበረበት የትላንት ታሪካችን በመሰረቱ እየተቀየረ መጥቶ በአሁኑ
ሰዓት በሚልዮኖች የሚቆጠር ሃብት መቋጠር የጀመሩ በርካታ አርሶና አርብቶ አደሮች
ማፍራት ችለናል። የግብርና ልማታችን ለህዳሴ ጉዟችን እያበረከተው ያለው አስተዋፆና
ያለበት ሁኔታ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

1.1 በአርሶ አደሩ አነስተኛ ማሳ የሚካሄድ ግብርናና ትራንስፎርሜሽን ለህዳሴያችን

በሀገራችን የተቀየሰው የግብርና መር የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ አማካኝነት


ለግብርናው ዘርፉ በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት መሰረት ሀገር አቀፍ ምርትና ምርታማነት
በቀጣይነት በማደግ ላይ ይገኛል። ኢትዮጵያን እጅግ ፈጣን ዕድገት ከሚያስመዘግቡ ጥቂት
የዓለም ሀገራት መካከል ማሰለፍ የተቻለውም የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ዋነኛው
የዕድገታችን ምንጭ አድርገን በመረባረባችን ነው። በ5 ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን
እቅድ በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ የሚካሄደው ልማት ዋነኛው የግብርና ዕድገት ምንጭ ሆኖ
እንዲሚቀጥል አቅጣጫ ተቀምጦ ተግባራዊ በመሆን ላይ ይገኛል።

አርሶ አደሩ በአነስተኛ ማሳ ላይ እያካሄደ ያለው ልማት ምርትና ምርታማነቱ በቀጣይነት


እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የሀገር በቀል ፖሊሲያችን ትክክለኛነት በተግባር
በማረጋገጥ የገበያ አክራሪዎችንና የተላላኪዎቻቸውን በተበጣጠሰ የአርሶ አደር ማሳ ላይ
የተመሰረተ ግብርና የትም መድረስ አይቻልም የሚለውን አቋም በተግባር ያከሸፈ ሆኗል።

በአርሶ አደሩ ማሳ በመመስረት የግብርናውን ምርትና ምርታማነት በመጨመር የሀገራችን


ኢኮኖሚ በቀጣይነት መገንባት እንደሚቻል በተግባር አረጋግጠናል። የዕድገቱን ቀጣይነት
ለማጠናከርም አርሶ አደሩ ዘመናዊ የግብርና አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎችን ተጠቃሚ
እንዲሆን በርከታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል። ከእነዚህ ስራዎች መካከል በአርሶ አደሩ
ማሳ ላይ እየተገኙ ቀጣይነት ያለው ሙያዊ ድጋፍ የሚሰጡ የግብርና ልማት ሰራተኞች
በየቀበሌው መመደብ ይገኝበታል። ባለሙያዎች የሚሰጡት ድጋፍ ውጤታማ ይሆን
ዘንድም 25 የግብርና ልማት ጣቢያ ሠራተኞችን የሚያሰለጥኑ የግብርና ቴክኒክና ሙያ
ማሰልጠኛ ኮሌጆችና ከ1ዐ ሺህ በላይ የሚሆኑ የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ማዕከላት
ተገንብተው አርሶ አደሩን በቅርበት እየደገፉ ይገኛሉ። ከ70 ሺህ በላይ የግብርና

4
ሙያተኞችን በማሰልጠንም በየገጠር ቀበሌው በእንስሳት ሃብት ልማት፤ በሰብል ልማትና
በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና ልማት ዘርፎች ሶስት ሙያተኞችን፣ መስኖ ባለበት አካባቢ
ደግሞ የመስኖ ልማት ሙያተኛ በመጨመር አርሶ አደሩን በተደራጀ ሁኔታ
የኤክስቴንሽን አገልግሎት ተጠቃሚ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው፡፡

የግብርና ልማት ስራችን ትኩረት የሰብል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በሀገራችን


ዘላቂነትና ቀጣይነት ያለው የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ለግብርና
ልማት በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት መሰረት በ1983 ዓ.ም በዋና ዋና ሰብሎች የነበረውን
52 ሚሊዮን ኩንታል የምርት መጠን በ2005 ዓ.ም ወደ 251.5 ሚሊዮን ኩንታል ማሳደግ
ተችሏል። ይህም በሀገር ደረጃ በምግብ ሰብል እራሳችን እንድንችል አድርጎናል፡፡ በግብርና
ልማት እየመጣ ላለው እድገት የተከተልነው የልማት ሰራዊት ግንባታና የማስፋት
ስትራቴጂ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በየደረጃው የተገኙትን ምርጥ ተሞክሮዎችና
ልምዶችን በመለየትና በመቀመርና ወደ ሌሎች አርሶና አርብቶ አደሮች አካባቢዎች
የማስፋት ስትራቴጂ ተከትለናል፡፡
በአርሶ አደሩ አነስተኛ ማሳ ላይ የሚካሄድ ግብርና ለህዳሴያችን ወሳኝ ነው የምንለው 83
በመቶ ለሚሆነው ሕዝባችን የኑሮ መሠረትና አብዛኛው የልማት ኃይላችን ያቀፈ ዘርፍ
በመሆኑ ጭምር ነው። ስለሆነም አሁን ባለንበት ሁኔታ የዚህን ሰፊ የልማት ሃይል
ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት በማሳደግ ከራሱ ህይወት አልፎ ለተቀረው የከተማ ነዋሪ
የሚተርፍበት የግብርና አማራጭ ከመከተልና በጥብቅ ዲሲፕሊን ከመፈፀም የተሻለ
አማራጭ የለንም።

በአጠቃላይ በአርሶ አደሩ አነስተኛ ማሳ ላይ እየተካሄደ ያለው የግብርና ልማት በቀጣይነት


እያደገ በመምጣቱ በየደረጃው ያለው አርሶ አደር በልማቱ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
በዋነኛነትም የአርሶና አርብቶ አደር ገቢ እንዲጨምርና ኑሮውም በቀጣይነት እንዲሻሻል
አድርጓል፡፡ እጅግ በርካታ አርሶ አደሮች የድህነት ሰንሰለትን በጥሰው በመቶ ሺህዎችና
በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት ባለቤቶች መሆን የቻሉትም ለአርሶ አደሩ ማሳ በተሰጠው
ከፍተኛ ትኩረት አማካኝነት ነው፡፡
በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ የሚካሄደው የግብርና ልማት ስራ ይበልጥ ውጤታማ ይሆን ዘንድ
በዘርፉ የሚታዩ ማነቆዎች በቀጣይነት እየፈተሹ ማስተካከል ይጠይቃል። በተለይ በአርሶ
አደሩ የሚታዩ የግብርና ቴክኖሎጂ በስፋት ያለመጠቀም ሁኔታ፣ አሁን ያለው የስራ ባህል

5
ዝቅተኛ መሆንና ታካችነት እንዲሁም በአርሶ አደሩ የሚታይ የጠባቂነት ሁኔታ ለመቅረፍ
ቀጣይ ርብርብ የሚጠይቅ ይሆናል። የባለሙያዎች ድጋፍ በተመለከተም እንዲሁ ከጊዜ
ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም የአርሶ አደሩ ምርትና ምታማነት በቀጣይነት
ለማሳደግ የሚደረግ ደጋፍ በብዙ መልኩ መሻሻል ይገባዋል።

1.2 በግል ባለሃብቱ የሚካሄድ ዘመናዊ ግብርና

የግል ባለሃብቱ ለዘመናዊ ግብርና ዕድገትና ቀጣይነት ከአርሶ አደሩ ቀጥሎ የሚሰለፍ
ኃይል ነው። መንግስት የግል ባለሃብቱን ለመደገፍ ሁሉን አቀፍ ርብርብ እያደረገ ሲሆን
ባለሃብቱም የተፈጠረለትን ምቹ ሁኔታ ተጠቅሞ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምሯል።
በመንግስት በኩል በግብርና ኢንቨስትመንት መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች ሁለት
መሰረታዊ አማራጮች ተቀምጠዋል። አንደኛው አማራጭ የግል ባለሃብቱ በደጋማና
በከተሞች አካባቢ በአነስተኛ መሬት ላይ ሰፊ ጉልበት፣ ካፒታል እና ቴክኖሎጂ ተጠቅመው
የአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን በማምረት የተሻለ ገቢ ማግኘት ማስቻል ሲሆን
ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ ሕዝብ ባልሰፈረባቸው በሀገሪቱ ቆላማ አካባቢዎች በሚገኙ
ሰፋፊ መሬቶች ዘመናዊ የማምረቻ መሳሪያዎችን እና አነስተኛ ጉልበትን በመጠቀም
ለኢንዱስትሪ ጥሬ እቃነት እና ለምግብነት የሚውሉ የሰብል ምርቶችን በስፋት ማምረት
ነው፡፡

ይህን አቅጣጫ ተከትሎ የግብርና ኢንቨስትመንቱን ለማጠናከር በተደረገው እንቅስቃሴ


በዘርፉ መሰማራት የጀመሩት ባለሀብቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እያደገ መጥቷል።
ከተከተልነው ግልፅና አሳታፊ የግብርና ኢንቨስትመንት ስትራቴጂ በተጨማሪ በሀገራችን
የሰፈነው ሰላምና መረጋጋትም ለዘርፉ ዕድገት ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።
በሀገሪቱ እየተመዘገበ ያለው ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ዕድገት
እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ የነበረን ጥሩ ያልሆነ ገፅታ እየተቀየረና ተሰሚነታችንም
በዛው ልክ እያደገ በመምጣቱም እንዲሁ በዘርፉ የሚሰማሩት የውጭ ባለሀብቶች ቁጥር
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል።

የግብርናው ኢንቨስትመንት የስራ ዕድል ከመፍጠር አኳያም ፋይዳው የጎላ ሲሆን በ2003
ዓ.ም ላይ ዘርፉ 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል። በ1992

6
ከነበረው 400ሺህ ጋር ሲነፃፀር የለውጡን ከፍተኛነት መገንዘብ ይቻላል። ይህ ዘርፍ
በየዓመቱ 4 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለውጭና ለሃገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ
ላይ ነው፡፡ ለገበያ ከሚቀርቡት ምርቶች መካከል ጥጥ፣ ሰሊጥ፣ ቡና፣ አኩሪ አተር፣
ፍራፍሬና ባዮ ፊዩል ይገኙበታል፡፡

የባለሃብቱን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በቀጣይነት ማሳደግ ይቻል ዘንድ በዕድገትና


ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የመጨረሻ ዓመት (2007 ዓ.ም) 5ሚሊዮን 700ሺህ ሄክታር
መሬት ለማቅረብ እየተሰራ ነው፡፡ የተሰጣቸውን መሬት በአግባቡ አልምተው ለጨረሱ
ባለሃብቶች ተጨማሪ መሬት በመስጠትና አዳዲስ የውጭና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችን
በመሳብ በሆርቲካልቸር፤ በኢንዱስትሪ ጥሬ እቃና በሌሎች የሰብል ልማቶች ላይ
እንዲሰማሩ በማድረግ ዘርፉን በተቻለ ፍጥነት ለማስፋፋትና ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ
በመሰራት ላይ ነው። ለእርሻ የሚሆን መሬት ለኢንቨስተሮቹ ከማስተላለፍ ጎን ለጎን ወሳኝ
የሆኑ የመሰረተ ልማት አገልግሎቶችን ለሁሉም አካባቢዎች ደረጃ በደረጃ ለማዳረስ ጥረት
እየተደረገ ነው። በዚህ ረገድ መንገድ፤ የኤሌክትሪክና የስልክ አገልግሎት በሁሉም
አካባቢዎች ለማዳረስ የተደረገው ጥረት በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው።

በአጠቃላይ እስካሁን ወደ ልማት ያልገቡ ሰፋፊ መሬቶች በማልማትና በእነዚህ መሬቶች


ላይ በጥራቱ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ የሆነ ምርት በማምረት የሀገራችን ተወዳዳሪነት
በማሳደግና የውጭ ምንዛሬ ዓቅም በቀጣይነት በማጎልበት ዘርፉ የሚጫወተው ሚና እጅግ
ከፍተኛ ነው። ዘርፉ ያሉበትን ማነቆዎችን በቀጣይነት እየተከታተሉ በማስተካከል
የሚጠበቅበትን ከፍተኛ ድርሻ እንዲያበረክት የሚሰጠው ልዩ ትኩረት ተጠናክሮ የሚቀጥል
ይሆናል።

የግብርናው ዘርፍ እያደገ ቢሆንም ከውጭም ሆነ ከውስጥ በርካታ ተግዳሮቶች ያሉት ነው።
በተለይ ሰፋፊ የሆኑ የግብርና ኢንቬስትመንት በሚካሄዱባቸው አካባቢዎች ነዋሪዎች
እየተፈናቀሉ ነው፣ ሰፋፊ መሬቶች ለውጭ ባለሃብቶች በመስጠት መንግስት በርካሽ ዋጋ
መሬት እየሸጠ ነው፣ የመሬት ወረራ እየተካሄደ ነው፤ … ወዘተ የሚሉ ከኒዮልበራል ኃይሉ
የሚሰዘነሩ መሰረተ ቢስና የተዛቡ ውንጀላዎች ይስተዋላሉ። የኒዮልበራል ሃይሉን
ውንጀላዎች በማራገብ ላይ ያተኮሩት የሀገር ውስጥ ፀረ ልማት ሃይሎችና ግለሰቦችም
ተመሳሳይ የሆኑ አፍራሽ አሉባልታዎችን በማሰራጨት በእነዚህ አካባቢዎች እየተካሄደ

7
ያለውን ልማት ለማደናቀፍ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። በመሆኑም የዚህ የተዛባ
አመለካከት መሰረተ ቢስነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ግንዛቤ እየተያዘበት ቢሆንም ህዝባችን የተሟላ
መረጃና ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖረው መስራት ይኖርብናል፡፡

የባለሃብቶች ተሳትፎም ቢሆን በሚፈለገው ደረጃ ላይ የደረሰ አይደለም። በሌላም በኩል


መሬት ወስደው ባቀረቡት ፕሮጀክት መሰረት ቶሎ ወደ ልማት ከመግባት አንፃር በርካታ
ውስንነቶች ይታያሉ፡፡ በቀጣይ በገቡት ቃል መሰረት ወደ ተጨባጭ ልማት የገቡትን
የማበረታት፣ በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ መሰረት ወደ ልማት ለማይገቡ ባለሃብቶች
ምክርና ድጋፍ በመስጠት ቶሎ ብለው ወደ ልማት እንዲገቡ የማድረግ እንዲሁም ድጋፍና
ምክር ተደርጎላቸው ማልማት የማይችሉት ደግሞ ሕጋዊ እርምጃ የመውሰድ አሰራር
አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል።

1.3 አግሮ ፕሮሰሲንግ አጠናክሮ የማስቀጠል ፋይዳ

ሀገራችን በኢንዱስትሪው ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ የምትችለው በአንፃራዊነት


ከፍተኛ የሆነ የማደግ ዕድል (Comparative Advantage) ባላቸው ዘርፎች ላይ በመረባረብ
ነው። በመሆኑም የኢኮኖሚያችን የጀርባ አጥንት የሆነው የግብርና ልማታችንን ታሳቢ
ባደረጉ ኢንዱስትሪዎች ላይ ማተኮር በአንድ በኩል የግብርና ምርትና ምርታማነት
የሚያነቃቃ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ኢንዱስትሪዎቹ አስተማማኝ የምርት ግብአት
በማግኘት የዕድገታቸው ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሚያስችላቸው ይሆናል። ይህ ደግሞ የአርሶ
አደሩናና የአርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት በቀጣይነት የሚያረጋግጥ ሲሆን እዛው ሳለም
የሀገራችንን የኢንዱስትሪ ዕድገት በአስተማማኝ መሰረተ ላይ እንዲገነባ የሚያሰችል
ይሆናል። እነዚህ ኢንዱስትሪዎች የገጠር ልማቱንና የከተማውን ዕድገት በማስተሳሰር
ረገድም ተኪ የላቸውም።

ሀገራችን ባለፉት 10 ዓመታት ያስመዘገበችው ፈጣን፣ ቀጣይነት ያለውና ፍትሐዊ


ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ማበብ ብሩህ ተስፋ እየፈነጠቀ
ይገኛል። እነዚህ ኢንዱስትሪዎች የግብርና ምርቶችን በግብአትነት የሚጠቀሙ
በመሆናቸው ግብርናው ከፍጆታ በላይ ባሉ የተሻለ ዋጋ ያላቸው ምርቶች ላይ እንዲያተኩር
በማድረግ በኩል ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ናቸውና በእርግጥም ሀገር በቀሉ ግብርና መር

8
የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂያችን ያለንነ ሃብት በአግባቡ ተጠቅመን ቀጣይ ዕድገታችን
ለማረጋገጥ የሚያስችል ትክክለኛ አቅጣጫ መሆኑን በማስመስከር ላይ ነው።

የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ዕድገታችን በአጠቃላይ የዕድገት ፍጥነታችንና በግብርናው


ዕድገት ላይ የተመሰረተ እንደመሆኑ መጠን ዕድገቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ
ይገኛል። በተለይ ደግሞ አትክልትና ፍራፍሬን ወደ ጭማቂ የመቀየር፣ ወተትና የወተት
ተዋፅኦን ፓስትራይዝድ የማድረግ፣ የስጋ ምርትን ኤክስፖርት የማድረግ፣ ስኳርና የተጓዳኝ
ምርቶች የማቅረብ፣ ማርን የማቀነባበር ወዘተ የመሳሰሉ ስራዎች የሚፈለገው ደረጃ ላይ
ባይደርሱም የተሻለ ጅምር ይታይባቸዋል።

በአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፎችም ምርቱን በቀጣይነት ማሳደግ የሚያስችሉ በርካታ


ተግባራት እየተከናወኑ ሲሆን አርሶ አደሩ ከፋብሪካዎች ጋር በአውትግሮዎርነት
በማስተሳሰር ተስፋ ሰጭ ስራዎች ተጀማምረዋል፡፡ በተለይ ደግሞ አዳዲስ
ኢንቨስትመንትን በመሳብ የሀገራችንን ኢኮኖሚ ለሚያሳድጉ እንደ የሻይ ልማት፣ የቡና
ልማት፣ ጥጥ፣ የቅባት እህሎች፣ የዓሳ እርባታ፣ የአትክልትና ፍራፍሬና የአበባ ምርቶች
ትኩረት ተጥተን በመስራት ላይ እንገኛለን።

የአግሮ ፕሮሰሲንግና አጠቃላይ የኢንዱስትሪ ዘርፍን በላቀ ደረጃ እንደሚያሳድግ


የሚጠበቀው የ13 ዓመት የኢንዱስትሪ ፍኖተ ካርታም ተዘጋጅቶ ስራ ላይ ለማዋል
ዝግጅት እየተጠናቀቀ ሲሆን ይህም ሀገራችን በዘርፉ ያላትን እምቅ ሀብት በአግባቡ
ለማልማት የሚያስችላት ይሆናል። በተመሳሳይ ሁኔታ ዘርፉን ለማሳደግ 5 የዘርፉ
የኢንዱስትሪ ኮሪደሮች ተለይተው ኢንዱስትሪዎቹን በክላስተር ማልማት የሚያስችል
አቅጣጫ ዘርግተን ወደ ተግባር ለመግባት እየተንቀሳቀስን ነው፡፡ ይህ በአንድ ማዕከል
ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ለመፍጠር የሚያስችለን ይሆናል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ እምብዛም ያልተነካ እምቅ ሀብት ቢኖራትም
አብዛኞቹ የግብርና ምርቶች ኤክስፖርት የሚደረጉት ፕሮሰስ ሳይደረጉ በመሆኑ ከዘርፉ
ማግኘት የሚገባንን ጥቅም እንድናገኝ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት ያለበት ነው።
ለምሳሌ ሀገራችን በእንስሳት ሃብት ብዛት በተለይ ደግሞ በቀንድ ከብት ብዛት ከአፍሪካ
ቀዳሚ ብትሆንም ከእንስሳት ሃብቷ እያገኘት ያለችው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ግን መሻሻል
እያሳየ ቢሆንም ብዙ የሚቀረው ነው። በየአካባቢው ማቆጥቆጥ የጀማመሩ የአግሮ

9
ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪዎች የቀጣይ ሀገራዊ ዕድገታችን ተስፋ ቢሆኑም በዘርፉ ያለን
እምቅ ሃብት ከመጠቀም አንፃር አሁንም ብዙ ርቀት መጓዝ ይጠይቃል።

ውጤታማ የሆኑ የህብረት ስራ ማሕበራትን መፍጠር ያለመቻል፣ የሃገር ውስጥም ሆነ


የውጭ ኢንቨስትመንት በሚፈለገው ደረጃ ያለማደግ እንዲሁም የአግሮ ፕሮሰሲንግ
ተቋሞቻችን ቴክኖሎጂ የመጠቀም ችግር ያለባቸውና ተወዳዳሪ ለመሆን የሚቸገሩ
መሆናቸውና ይህንን ለማስተካከል የሚሰጠው ድጋፍ በአጥጋቢ ደረጃ ውጤታማ ያለመሆን
በዘርፉ ከሚታዩት ተግዳሮቶች ተጠቃሾች ናቸው። በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች
በክላስተር በማደራጀት የአግሮ ፐሮሰሲንግ ኮሪደሮችን ለማልማት የተያዘውን ዕቅድ ወደ
ተግባር ከመቀየር አንፃር እዚህ ግባ የሚባል ስራ ስላልተሰራ በቀጣይ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ
ይሆናል። የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የተሰራው ስራም ዝቅተኛ ነው ማለት
ይቻላል። ስለሆነም ዘርፉን በማጠናከር ያለን ያልተነካ እምቅ ሀብት ለሀገራዊ ዕድገታችን
የማዋል ስራው በቀጣይ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራበት ይሆናል።

1.4 ዘመናዊ የመስኖ አውታሮች ለግብርና ትራንስፎርሜሽን፣

ከዝናብ ጥገኝነት የተላቀቀ ግብርና ለመፍጠር እየተደረገ ባለው ሁሉን አቀፍ ርብርብ
የመስኖ ልማት ስራው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ በዓመት አንድ ጊዜ ያውም
ዝናብ ጠብቆ ይካሄድ የነበረው የግብርና ስራ በዓመት ሁለትና ከዛ በላይ ማምረት
በሚቻልበት የመስኖ ልማት እየተተካ ይገኛል። የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ
እንዲቻል ባህላዊና ዘመናዊ የመስኖ ልማት ስራው አጠናክረን መቀጠል እንዳለብን በፅኑ
በማመን በሁለቱም አቅጣጫዎች ስኬታማ ተግባራት በማከናወን እንገኛለን።

የሀገራችን የግብርና ልማት ስራ ለዘመናት በሳይንሳዊ ዕውቀትና ዘመናዊ አሰራር ሳይደገፍ


በመቆየቱ ያለአገልግሎት ሲፈሱ የነበሩ ወንዞቻችን በአሁኑ ሰዓት የልማታችን አቀጣጣይ
ኃይሎች ወደመሆን ተሸጋግረዋል። በተለይ ደግሞ የተበታተነ ህዝብ የሚኖሩባቸው የታላላቅ
ወንዞቻችን ተፋሰሶች የሰፋፊ የመስኖ ልማት ስራዎች መዳረሻ እየሆኑ ነው። በተለይ
በመንግስት እየተከናወኑ ያሉ ግዙፍ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ለሀገራችን ዘመናዊ
ግብርና መስፋፋት በር ከፋች ሆነዋል። በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችን የተያዙ
ታላላቅ የስኳር ልማት ፕርጀክቶችና ሌሎች ዘመናዊ የመስኖ ልማት ስራዎች በተያዘላቸው
አቅጣጫ መሰረት በመከናወን ላይ ይገኛሉ። ለአብነት የከሰምና ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ

10
በመጀመሪያው ምዕራፍ እንደየቅደም ተከተላቸው 77.2 በመቶ እና 84 በመቶ፣ የርብ
መስኖ ፕሮጀክት 59.45 በመቶ፣ የቆቦ ጊራና ፕሮጀክት 67 በመቶ እንዲሁም ራያ 94
በመቶ ደርሰዋል።

በሌላ በኩል ለባህላዊ መስኖ በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት መሰረት ሁሉም አርሶ አደር
አማራጭ የውሃ ምንጮችን እንዲጠቀም ለማድረግ በተሰራው ሰፊ ስራ አበረታች ውጤት
እያስመዘገብን እንገኛለን። አርሶ አደሩ በየትኛውም ወቅት የተገኘችውን የዝናብ ጠብታ
በአግባቡ በማጠራቀም በምርትና ምርታማነት ላይ መጫወት የሚችለውን አስተዋፅኦ
በሙሉ ለማበርከት በመረባረቡ የተረጂዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲቀንስ ምክንያት
ሆኗል። በዚህ መሰረትም በ2006ዓ.ም ብቻ ከ3ነጥብ 1 ሚልዮን ሄክታር በላይ መሬት
በመስኖ ለማልማት ዕቅድ ተይዞ ስኬታማ በሆነ ሁኔታ ተፈጽሟል። ያም ሆኖ አሁንም
ሀገራችን ከመስኖ ልማት መጠቀም ከሚገባት ደረጃ ላይ አልደረስንም፡፡ አሁንም የመስኖ
ልማትን እንደ ወሳኝ የግብርና ልማት ዘርፍ አድርጎ ያለማየት ችግር ይስተዋላል፡፡ ሁሉም
አርሶ አደር የውሃ አማራጭ እንዲኖረው የማድረግ ግባችን ለማሳካት ቀጣይ ርብርብ
ይጠይቃል፡፡

2. የኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ትራንስፎርሜሽን

የሀገራችንን የኢንዱስትሪ ልማት በቀጣይነት ማሳደግ ይቻል ዘንድ የኢንዱስትሪው


አንቀሳቃሽ ሞተር የግል ባለ ሃብቱ እንዲሆን፣ ዘርፉ ግብርና መር አቅጣጫውን ተከትሎ
ማደግ እንዳለበት፣ የኢንዱስትሪ ዋና ትኩረት ኤክስፖርት እንዲሆን፣ ጉልበት በስፋት
መጠቀም እንዳለበት፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶችን ማቀናጀት እንደሚገባ፣ መንግስት
በዘርፉ ጠንካራ የአመራር ሚና መጫወት እንዳለበት እንዲሁም መላው ህብረተሰብ
በኢንዱስትሪ ልማት ላይ በጋራ የሚሰለፍበትን አቅጣጫ መከተል እንደሚገባ በኢንዱስትሪ
ልማት ስትራቴጂያችን ላይ በግልፅ በማስቀመጥ ወደ ተጨባጭ ስራ ተገብቷል።

በ5 ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችን ላይም ዘርፉን በቀጣይነት ማሳደግ


በሚችሉ ዋና ዋና ዘርፎች ላይ አተኩረን መስራት እንዳለብን አስቀምጠናል። በዚህም
በኢንዱስትሪ መስክ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት በማረጋገጥ ዘረፉ ደረጃ በደረጃ
ቀጣይ የሀገሪቱ ልማት መሰረት የሚሆንበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ

11
ሲሆን በተለይ ደግሞ ዋነኛ የስራ ዕድል መፍጠሪያ ለሆነው የአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት
ልማት ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ላይ ነው። የሀገራችንን
የኢንዱስትሪ ዕድገት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ለመካከለኛና ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ዘርፍም
እንዲሁ ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል።

2.1 የአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች እድገትና ፋይዳቸው

የአነስተኛና ጥቃቅን ተቋሞች መስፋፋትና መጠናከር ከፍተኛ የስራ ዕድልን በመፍጠር


የከተማን ህዝብ ኑሮ ለማሻሻል በሂደቱም የከተሞችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶች
ለማፋጠን የማይተካ ሚና እንዳላቸው በዝርዝር በመፈተሽ ፖሊሲና ስትራቴጂ ተቀርጾ
ተግባራዊ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ ተቋማቱ ሰፊ የስራ እድልንና ቀጣይነት ያለው
አስተማማኝ ገቢ የሚፈጥሩ ናቸው፡፡ አሁን እየተቀረፈ የመጣ አስተሳሰብ ቢሆንም ዘርፉን
የኋላ ቀርነት መለኪያ አድርጎ የመውሰድ የተሳሳተ አመለካከት ይታያል፡፡ የአለም ተሞክሮ
የሚያሳየው ግን የበለጸጉት አገሮች በእነዚህ ተቋማት በስፋት እየተጠቀሙ መሆኑን ነው፡፡
ከአነስተኛና ጥቃቅን ዘርፍ አንፃር በእኛና በበለፀጉ ሃገራት መካከል ያለው ልዩነት
የአቅጣጫ ሳይሆን ተቋማቱ የሚጠቀሙት ቴክኖሎጂ፣ ምርታማነትና የምርት ጥራት ነው
ማለት ይቻላል፡፡ በጃፓን እነዚህ ተቋማት ለትላልቅ ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት የሚውሉ
ጥራት ያላቸው ግብዓቶችን በማምረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ናቸው፡፡
በቻይናም የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ዋነኛ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የቴክኖሎጂ
መፈልፈያ ሆነው ለአገሪቱ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ ይገኛሉ፡፡
በሀገራችንም እነዚህ ተቋማት አሁን ከሚፈጥሩት የስራ እድል ባሻገር ወደፊትም የማምረቻ
ኢንዱስትሪው ግብዓት አቅራቢ መሆናቸው ታሳቢ ተደርጓል፡፡

እነዚህ ተቋማት ውሱን ሃብትና ሰፊ የሰው ጉልበት ከመጠቀማቸው አንፃርም ከሀገራችን


ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚሄዱ ናቸው፡፡ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በተወሰነ የካፒታል
መነሻ በመንቀሳቀስ በሂደት ወደ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ሊሻጋሩ በሚችሉበት
አኳሃን በመንግስት ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ለእነዚህ ተቋማት በተደረገው ሰፊ
አንቅስቃሴ ከ2003 እስከ 2006 ዘጠኝ ወራት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈፃፀም
ብቻ የተፈጠረው የስራ እድል 5 ሚሊዮን 678 ሺህ 544 ደርሷል።

12
የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ስራ ከጅምሩ በርካታ ፀረ-ልማት ሃይሎችና ግለሰቦች የተለያዩ
ስያሜዎችን በመስጠት ቢያብጠለጥሉትም የእነዚህን አፍራሽ ሃይሎች አሉባልታና
የማጥላላት ዘመቻ በተግባር በማምከን የበርካታ ዜጎችን ህይወት ከማሻሻሉም በላይ በሀገር
ኢኮኖሚ ላይም የማይናቅ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡ አሁን አሁን ከቴክኒክና
ሙያና ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ ወጣቶች በዘርፉ እየተሰማሩ
ይገኛሉ፡፡ ከ2004 እስከ 2006 ባሉት ግዜያት ብቻ 146 ሺህ 545 የዩንቨርሲቲና የኮሌጅ
ምሩቃን ዘርፉን ተቀላቅለዋል፡፡

በዘርፉ ያለው የቴክኖሎጂ ሽግግርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ነው፡፡ የተቋማቱን


የጥራትና የምርታማነት ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ ተስማሚ የማምረቻ መሳሪያዎችን
በመፈተሽና በማማከር ኢንተርፕራይዞቹን ተጠቃሚ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው፡፡
ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋር በማቀናጀት ክፍተታቸውን መሙላት የሚያስችል ስልጠና
በመሰጠቱና በራሳቸው ቀላል ማሽኖች የሚሰሩበት መንገድ በመፈጠሩ አሁን የብሎኬት
ማምረቻ ማሽን፣ ቀላል የእርሻ ማሽን፣ ቡናን ጨምሮ የተለያዩ ጥራጥሬዎች መፈልፈያ
ማሽኖች፣ ዘመናዊ የሽመና ማሽንና መሰል ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማቅረብ
ግብርናውን ከመደገፍ ባሻገር ለሚቋቋሙ አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችም የግብአት አቅርቦት
ችግርን እርስ በእርስ በማቃለል በማያቋርጥ የዕድገት አዙሪት ውስጥ ገብተው ይገኛሉ፡፡
በዘርፉ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ወደ ታዳጊና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የሚያደርጉት
ሽግግርም ተስፋ ሰጪ ነው።

በአነስተኛ ጥቃቅን ተቋማት ልማት አመርቂ ውጤቶች ማስመዝገብ የቻልን ቢሆንም


አሁንም ካለው የስራ አጥነት ቁጥር አንፃር ብዙ ስራ መስራት ይጠይቃል። ተቋማቱ
ያለባቸውን የግብአት አቅርቦት እጥረት፣ የገበያ ትስስር ችግር እንዲሁም የመስሪያና
የመሸጫ ቦታ ችግር ለመፍታት መረባረብ ይኖርብናል። በኢንተርፕራይዞቹ
የሚስተዋለውን የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር እና ጠባቂነት የማስተካከል
ጉዳይም እንዲሁ ትኩረት የሚሻ ነው።

13
2.2 የመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት መጀመራቸው

የደርግ ስርዓት በተገረሰሰበት ማግስት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ተንገራግጮ የቆመበት ሁኔታ ነበር
የተፈጠረው፡፡ የነበሩት ጥቂት የኢንዱስትሪ ተቋማትም ለሰራተኛ ደመወዝ እንኳ መክፈል
አቅቷቸው ከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀው ነበር፡፡ ይህንን ሁኔታ በሚገባ በመገንዘብ ምንም
እንኳን ሀገሪቱ የተጠራቀመ ካፒታልና በዘርፉ የሰለጠነ በቂ ባለሙያ ባይኖራትም ባላት
ውስን አቅም የኢንዱስትሪው ዘርፍ መጫወት የሚገባውን ሚና በአግባቡ እንዲወጣ ግልፅ
አቅጣጫ ተቀምጦ ነበር፡፡ ያለንን ውስን ዓቅም አሟጠን እየተጠቀምን በቀጣይነት ደግሞ
አቅማችንን እየገነባን እንደምንሄድ ታሳቢ ያደረጉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን ተቀርጸው
ተግባራዊ በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡

የዳበረ ኢኮኖሚ ለመገንባት የኢንዱስትሪ ዕድገት አስፈላጊነት ለጥያቄ የሚቀርብ


አይደለምና ለዘርፉ መሰፋፋትና ቀጣይ ዕድገት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እየተረባረብን
እንገኛለን፡፡ በሀገሪቱ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ስርዓት ከመዘርጋት ባሻገር የግል ባለሃብቱ
የኢንዱስትሪ ልማቱ ዋነኛ ሞተር መሆኑን ጭምር በስትራቴጂው በመጠቆም የግል ዘርፉን
የሚያበረታቱ አያሌ ተግባራት በመፈፀም ላይ ናቸው፡፡ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ
ባለሃብቱ በሀገራችን የሚያደርገው እንቅስቃሴም በየጊዜው እድገት እያሳየ ነው፡፡

በሀገራችን ትኩረት አድርገን የምንሰራባቸው የኢንዱስትሪ መስኮች ከፍተኛ ካፒታል


የማይጠይቁ ነገር ግን በከፍተኛ የሰው ጉልበት የሚታገዙ መሆን እንዳለባቸው አቅጣጫ
አስቀምጠናል፡፡ በሌላም በኩል የሀገራችን ኢንዱስትሪ በጅምር ላይ ያለ እንደመሆኑ
መጠን በቀጣይነት ማደግ ያለበት ቢሆንም አሁን ያለን የቴክኖሎጂ ዓቅም ትንሽ ነው፡፡
ስለሆነም አሁን ባለንበት ሁኔታ ዝቅተኛ ቴክኖሎጂ፣ መለስተኛ ካፒታልና ሰፊ የሰው
ጉልበት የሚጠይቁ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ላይ ማተኮሩ ከዕድገት ደረጃችን
አንፃር ተገቢና ትክክለኛ አቅጣጫ ነው፡፡

የሀገራችን የኢንዱስትሪ ዘርፍም ከዚህ መሰረታዊ እምነት በመነሳት ከፍተኛ የስራ እድል
መፍጠሪያ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግሩ ማዕከልና የኢንዱስትሪ መስፋፋት መሰረት በሆኑት
በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አማካኝነት ለግሉ ባለሃብት የተመቻቸ ሁኔታ
ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ያለ ነው። በዚህም ባለፉት 23 ዓመታት ከ2
ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ የግል ባለሃብቶች በተለያዩ ዘርፎች በመሰማራት 30 ቢሊዮን 333

14
ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል በማንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡ የውጭ ሀገር ባለሃብቶችም
መዋእለ ንዋያቸውን በማፍሰስ ሃገራችን ለኢንቨስትመንት የተመቸች ሃገር መሆኗን
ምስክርነታቸውን እየሰጡ ናቸው፡፡ ባለፉት 23 ዓመታትም 7 ሺህ 270 የውጭ ሃገር
ባለሃብቶች ከ89 ቢሊዮን 78 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል በማንቀሳቀስ በሀገር ኢኮኖሚ
ላይ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ናቸው፡፡

የሀገር ውስጥ ባለሃብቱ በፋይናንስ ኢንዱስትሪው ላይ ምንም ተሳትፎ ያልነበረበት ያ የድሮ


ታሪክ ተቀይሮ ዛሬ የግል ባንኮች፣ የግል የመድን ድርጅቶች፣ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት
እና ሌሎች የግል ዘርፎች በሀገራችን እያበቡ ይገኛሉ፡፡ ቀደም ሲል በመንግስት ቁጥጥር
ስር የነበሩና በግል ዘርፉ አቅም ሊካሄዱ የሚችሉ ድርጅቶችን ወደ ግል በማዞርም የግል
ባለሃብቱን ሚና ለማጠናከር እየሰራን ነው፡፡

መንግስት የግል ባለሃብቱ ሊገባባቸው በማይችሉ ነገር ግን ለኢንዱስትሪው መዳበርና


ለአጠቃላይ ኢኮኖሚው አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ በሚችሉ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ላይ
በመሳተፍም ኢንዱስትሪው በቀጣይነት እንዲስፋፋ በትኩረት እየሰራበት ነው፡፡ የብረታ
ብረትና ኢንጅነሪግ ኮርፖሬሽን፣ የስኳር ልማት ስራዎች፣ የኬሚካልና የማዳበሪያ
ፋብርካዎች፣ የመድሐኒትና የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪዎች ወዘተ የዚህ አቅጣጫ
ማሳያዎች ናቸው።

መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪ ልማት የግሉ ዘርፍ ዋና አንቀሳቃሽ በመሆኑ የግል


ባለሀብቱ በኢንዱስትሪው ዘርፍ በስፋት እንዲሳተፍና የኢኮኖሚ ዕድገቱንም ለማፋጠን
በተለይ የማምረቻ ኢንዱስትሪው በኢኮኖሚው ውስጥ የጎላ ድርሻ እንዲጫወት ለማድረግ
በዘርፉ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች በመንግስት የሚሰጡ የተለያዩ ማበረታቻዎችና ድጋፎች
ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ተደርጓል። የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በባህሪው ከፍተኛ ካፒታልና
ቴክኖሎጂ የሚጠይቅ በመሆኑ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ከውጭ ባለሃብቶች ጋር በጣምራ
እንዲሰሩም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

የኢንዱስትሪ ዞኖችን በማደራጀት ልማታዊ ባለሃብቱ በዘርፉ የሚያደርገውን ተሳትፎ


ለማሳደግም እንዲሁ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው። በዚሁ መሠረት በአዲስ አበባ፣
በኮምቦልቻ፣ በድሬዳዋና በሐዋሳ በድምሩ 3 ሺህ 537 ሄክታር መሬት የኢንዱስትሪ

15
ሚኒስቴር ከየከተሞቹ የተረከበ ሲሆን የኢንዱስትሪ ዞኖችን የማልማት ስራም እየተጠናከረ
ነው፡፡ የግል ባለሃብቶችን ተሳትፎ ከማበረታታት አንፃር አስፈላጊ የሆኑ ዕቃዎች ከውጭ
ሲያስገቡ ከቀረጥ ነፃ በማድረግ፣ የግብር ክፍያ የእፎይታ ግዜ በመስጠት እንዲሁም
የመሬት አቅርቦት እየተመቻቸላቸው ይገኛል። በውጤትም ከተለያዩ የዓለማችን
አካባቢዎች የተለያዩ ባለሃብቶች ወደ ሀገራችን በመግባት በጨርቃ ጨርቅ፣ ቆዳና የቆዳ
ውጤቶች፣ አግሮ ኢንዱስትሪና መሰል የኢንዱስትሪ መስኮች ላይ እየተሰማሩ ይገኛሉ፡፡

የመካከለኛና ትላልቅ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት በወጪ ንግድ የሚመራ፣ የውጭ


ምንዛሬ ዕጥረትን የመቅረፍና ለግብርና ልማት ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠር ዓላማዎቹ
አኳያ ባለፉት ሶስት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የትግበራ ዓመታት መነሻ የሚሆኑ
ውጤቶች ማስመዝገብ የጀመርን ቢሆንም አሁንም ዘርፉ በርካታ ተግዳሮቶች ያሉበት
ነው። በተለይ ደግሞ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ ያስገኛሉ ተብለው የሚጠበቁት የጨርቃ-
ጨርቅና አልባሳት እና የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪዎች የተያዘላቸው ግብ በማሳካት
እጥረቶች ይታዩበታል፡፡ ስለሆነም በነዚህ ኢንዱስትሪዎች ያሉትን ማነቆዎች ለመፍታት
እየተደረጉ ያሉ ማሻሻያዎችን ማጠናከርና የግሉን ዘርፍ ኢንቨስትመንት ማደፋፈር
አንገብጋቢ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በሌላ በኩል የገቢ ምርቶችን የሚተኩ አምራች ፋብሪካዎችን
ለማስፋፋት የተደረገው ጥረት በተለይ በስሚንቶ ምርት ረገድ አመርቂ ውጤት የተገኘበት
ነው፡፡

2.3 የኢንዱስትሪው ዘርፍ የኢኮኖሚው መሪ የመሆን አቅጣጫና ፋይዳው

ኤክስፖርት መር የኢንዱስትሪ ስትራቴጂያችንን በተሳካ ሁኔታ በመፈፀም የኢንዱስትሪ


ዕድገታችን ማፋጠን እንደሚገባ በኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂያችን ላይ በግልፅ
ተቀምጧል፡፡ አለም ወደ አንድ የተሳሰረች መንደር እየተለወጠች ባለችበት በአሁን ወቅት
ለመድረኩ የሚመጥን የኢንዱስትሪ አቅጣጫ መከተል የግድ ይላል፡፡ ሀገራት በአለም
ገበያ ተወዳዳሪ የሆኑ ሸቀጦችንና ምርቶችን ማቅረብ ካልቻሉ በዓለም ገበያ ይቅርና በሀገር
ውስጥም ምርቶቻቸውን መሸጥ መለወጥ የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ለዚህም ነው
ምርታማነትን ለማሻሻል ሌት ተቀን የሚጣጣር የኢንዱስትሪ ዘርፍ መፍጠር ካልተቻለ
በስተቀር ፈጣን የኢንዱስትሪ ዕድገት ማሰብ አይቻልም የምንለው፡፡ በዓለም ገበያ

16
ለመወዳደር ኤክስፖርቱ በፍጥነትና በጥራት እየጎመራ መሄድና በውጭ ገበያ ተወዳዳሪ
የሆኑ ምርቶችን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

ኢንዱስትሪ የሀገራትን ማህበራዊ ለውጥ በማምጣትና ዘመናዊ አኗኗርን በማስፈን በኩል


ወደር የለውም፡፡ የኢንዱስትሪ መዳበር የሃገራችን ኢኮኖሚ በተሻለ ሁኔታ በመገንባት
ማህበራዊ ልማታችን ለማፋጠን የሚያስችለን ተጨማሪ የፋይናንስ አቅም ይፈጥርልናል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ኢንዱስትሪዎች ሰፊ የሰው ሃይል የመያዝ አቅማቸው ከፍተኛ በመሆኑ
የዜጎችን ገቢ በቀጣይነት በማሳደግ ረገድ ጉልህ ድርሻ አላቸው፡፡ የኢንዱስትሪ መዳበር
ቀጣይነት ያለው ዕድገት በማረጋገጥ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል
ጭምር ነው፡፡

የኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ይዟቸው ከሚመጡ ፋይዳዎች መካከል የቴክኖሎጂ እውቀትና


ዓቅም ግንባታ ይገኙበታል። ኢንዱስትሪዎች በተስፋፉ ቁጥር ኢንዱስትሪዎቹን
የሚያንቀሳቅሱ በርካታ ሙያተኞች ማስፈለጋቸው አይቀርም። ለዚህ ሲባል ደግሞ በዘርፉ
ተወዳደሪ የሆኑ ሙያተኞችን ማፍራት የግድ ይላል ማለት ነው። ስለሆነም በዘመናዊ
ዕውቀትና ክህሎት የተካኑ ዜጎች በማፍራት የሀገሪቱ ቀጣይ ዕድገት የሚፋጠንበት ሁኔታ
ይፈጠራል። በአጠቃላይ የኢንዱስትሪ ዕድገት የህዝባችን የአኗኗር ዘይቤ በመሰረቱ
ከመቀየሩ በላይ የኢኮኖሚያችን መዋቅራዊ ትራንስፎርሜሽን የማረጋገጥ ተልዕኮም
የተሸከመ ነው።

የኢኮኖሚውን መዋቅር በሚመለከት ባለፉት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የትግበራ


ዓመታት የግብርና ዘርፍ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ መጠነኛ የሆነ ቅነሳ እያሳየ
ሲሆን የኢንዱስትሪና የአገልግሎት ዘርፎች ደግሞ በአንፃሩ መጠነኛ ጭማሪ እያስመዘገቡ
ነው። ይህም የያዝነው መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር ግብ በተያዘለት አቅጣጫ መሰረት
እየሄደ መሆኑን የሚያሳይ ውጤት ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው። ይሁንና የኢንዱስትሪዉ
ዘርፍ በተለይ አምራች ኢንዱስትሪው ከጠቅላላ ኢኮኖሚው ከ5 በመቶ ያነሰ ድርሻ ይዞ
በመቆየቱ የመዋቅር ሽግግሩ በሚፈለገው ፍጥነት እንዳይሄድ አድርጎታል። በመሆኑም
በቀሪው ጊዜ በአጠቃላይ የኢንዱስትሪው ዘርፍ እስካሁን የተገነቡ አቅሞችን ቀልጣፋና
ውጤታማ በሆነ አግባብ አሟጥጦ በመጠቀም ከሌሎች ዘርፎች የላቀ ዕድገት
እንዲያስመዘገብ ማድረግ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል፡፡

17
2.4 ዘመናዊ አከታተምና የህዳሴ ጉዞአችን

ከተሞቻችን በከፋ ድህነት ውስጥ ተዘፍቀው የስራ አጦች መኖሪያ ሆነው ቆይተዋል፡፡
ያልተማከለ አስተዳደር ሳይዘረጋላቸው፣ ራሳቸው የማስተዳደር ስልጣን ሳይኖራቸው ለበላይ
አካል ብቻ እየታዘዙ በመቆየታቸው የመልካም አስተዳደር፣ የህግ የበላይነት፣ የግልፅነትና
የአሳታፊነት ስርዓት ሳይሰፍንባቸው ቆይቷል፡፡ የከተሞቻችን አመሰራረት ከገጠር ጋር
የነበረው ትስስር የተጠናከረ አልነበረም፡፡ ከተሞቻችን ባለፉት ስርዓቶች ያሳለፉትን
ችግርና ብሶት በመሰረቱ መፍታት ይቻል ዘንድ ለከተሞች ዕድገት ልዩ ትኩረት ሰጥተን
እየሰራን እንገኛለን።

የከተሞች ዕድገት ማረጋገጥ ለምንፈልገው የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን መሰረታዊ


መደላድል የሚፈጥር በመሆኑ የከተሞች ችግር መፈታት በይደር የሚታለፍ ጉዳይ
አይደለም። በመሆኑም የከተሞች የመሰረተ ልማት ዝርጋታና የመኖሪያ ቤት ችግር
ማቃለል የወቅቱ የከተሞች አንገብጋቢ ጥያቄ ነው። የከተማውን ነዋሪ ህዝብ የመኖሪያ ቤት
ችግር በማቃለልና ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል በማረጋገጥ በኩል ወደር የሌለው የተቀናጀ
የቤቶች ልማት ፕሮግራም ለከተሞቻችን ለተሰጠው ልዩ ትኩረት አንድ ማሳያ ተደርጎ
ሊወሰድ ይችላል። የመብራት፣ የውሃ፣ የቴሌኮም፣ የመንገድ እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች
ዝርጋታም በከተሞች ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የሀገራችን ኢንዱስትሪዎች በቀጣይነት እየተስፋፉ በሄዱ ቁጥር በኢንዱስትሪዎቹ ተቀጥሮ


የሚሰራና የሚያሰራ የሰው ቁጥር በቀጣይነት እየጨመረ መሄዱ አይቀርም። ከኢንዱስትሪ
መስፋፋት አብሮ የሚከተለው ጉዳይ የከተሞች መስፋፋት እና በአገልግሎት ዘርፍ
የሚሰማራው የሰው ኃይል መጨመር ነው። ከተሞች በጨመሩና በተስፋፉ ቁጥር ደግሞ
አሁን ያለው የተበታተነ የአኗኗር ዘይቤ በመሰረቱ ይቀየርና ወደ ከተሜነት ይስፋፋል
ማለት ነው። ስለሆነም አብዛኛው ህዝባችን የገጠር ነዋሪ ሳይሆን የከተማ ነዋሪ የሚሆንበት
ሁኔታ ይፈጠራል ማለታችን ነው። አብዛኛው ህዝባችን የከተማ ነዋሪ ሆነ ማለት ደግሞ
ቀጣዩ ትውልድ በአዲስ ማሕበራዊ መዋቅር መሰረት የተፈጠረ ይሆንና ለዘመናዊ
ዕውቀትም ሆነ ዘመናዊ ህይወት እጅግ ቅርብ ይሆናል። በመሆኑም በአሁኑ ወቅት
በገጠሮቻችን እያጋጠሙን ያሉ ከኋላቀርነት የሚመነጩ አንዳንድ የአስተሳሰብና የክህሎት

18
ችግሮች እንዲሁም ጎታች ልማዳዊ አሰራሮች በመሰረቱ ይቀየሩና እነዚህ ችግሮች
በቀጣይነት እየተፈቱ ይሄዳሉ።

በአጠቃላይ የከተሞች መስፋፋት አብዛኛው ህዝብ በከተሞች እንዲኖርና አነስተኛ ቁጥር


ያለው ህዝብ ደግሞ በገጠሮች አካባቢ እንዲኖር በማድረግ አብዛኛው ህዝብ ዘመናዊ
ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሚሆንበት ሁኔታን በመፍጠር ከተቀረው ዓለም ጋር የቅርብ ትስስር
እንዲኖረው ያስችላል። ስለሆነም የሀገራችን የኑሮ ሁኔታ በመሰረቱ ተቀይሮ የሀገራችንን
ህዳሴ ለማሳካት የተመቻቸ ሁኔታ ይፈጥርልናል።

የነባር ከተሞች መስፋፋትም ሆነ የአዳዲስ ከተሞች መቆርቆር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ


እና በእነዚህ ከተሞች ያለው የመሰረተ ልማት ዝርጋታና አቅርቦትም በቀጣይነት
እየተሻሻለ ቢሆንም የመሰረተ ልማት አቅርቦት ከማሟላት አንፃር አሁንም ፈታኝ እየሆነ
ነው። በተለይ ደግሞ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ማረጋገጥ፣ ጥራት ያለው የመሰረተ
ልማት አቅርቦት እንዲሁም የመኖሪያ ቤት ችግር የከተሞቻችን ፈተናዎች ናቸው።
እነዚህን ችግሮች በዘላቂነት መፍታት እንዲቻል የከተሞች ልማትና ዕድገት ፕሮግራም
ተዘጋጅቶ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም የከተማ ነዋሪው ህዝባችን ለዘመናት በላዩ
ላይ ተጭኖት የነበረ ጉስቁልና በከተሞች ካለው የከፋ የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል
ኢኮኖሚ ጋር ተዳምሮ ችግሮቹ ትዕግስቱን እየተፈታተኑት በመሆኑ በቀጣይም ልዩ
ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ ይሆናል።

በእስካሁኑ የከተማ ማስፋፋት እንቅስቃሴአችን ማለትም አዳዲስ የገጠር ከተሞች


በመፍጠርም ሆነ ነባር ከተሞቻችን በማስፋፋትና ደረጃቸው በቀጣይነት በማሻሻል ረገድ
አበረታች ውጤቶች ተገኝቷል። ይሁንና የከተሞች ፕላን በአግባቡ ያለማዘጋጀት እና ፕላኑ
ሲዘጋጅም ህዝቡን በስፋት ያለማሳተፍ ችግሮች ስላሉ በቀጣይነት መፍታት ይኖርብናል።
የከተሞችን ፈጣንና ተለዋዋጭ ባህርይ የተከተለ መዋቅራዊ ፕላን ማዘጋጀትና በቀጣይነት
መከለስ የሚገባን ቢሆንም በርካታ ከተሞች ቀድሞ የተዘጋጀ ፕላን ስለሌላቸውና
የተዘጋጀውም ቢሆን በየወቅቱ የማይከለስ በመሆኑ በከተሞቻችን ዕድገት ላይ አሉታዊ ጫና
መፍጠሩ አልቀረም። ከከተሞች የማስፋፊያ አካባቢዎች የመዋቅራዊ ወይም የአካባቢ ፕላን
ውጭ ከየአቅጣጫው የሚታየው ሕገ ወጥ የመሬት ወረራም ሌላኛው የከተሞቻችን
ተግዳሮት በመሆኑ በቀጣይነት ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው። ከተሞቻችን ደረጃቸው የጠበቁ

19
የህዝብ ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የአረንጋዴ ቦታዎችን አካተው በመስራት ረገድም
በርካታ ውስንነቶች ይታይባቸዋል።

3. የሰው ኃብት ልማት

በአንድ ሀገር የሚፈለገውን ዕድገትና ልማት በማምጣት ቀጣይነት ወዳለው የስኬት ጎዳና
ለመገስገስ የሰው ኃብት ልማት ወሳኝ ነው። ሀገራችን የተያያዘችውን የተሃድሶ ጉዞ
በሚፈለገው ደረጃ ለማሳካት በዕውቀት የዳበረ፣ በክህሎት የተካነና በአመለካከቱ የተቃና
ዜጋ ማፍራት የግድ ይላል፡፡ በዚህም በርካታ ስኬቶችን በማስመዝገብ ላይ ነን። በሰው
ሃብት ልማት ዘርፍ የህዳሴ ጉዟችን የሚገኘበት ሁኔታ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

3.1 የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ

ሀገራችን ለትምህርት በሰጠችው ከፍተኛ ትኩረት ሁሉም የሀገራችን ህዝቦች ትምህርትን


በቅርብ ርቀት የሚያገኙበት ፍትሃዊ ስርዓት ሰፍኖ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህፃናትና
ወጣቶችን የዘመናዊ እውቀት ተቋዳሽ ማድረግ ተችሏል። የሀገራችንን ዘላቂ ልማት
ማረጋገጥ የሚቻለው ሀገሪቱ የነደፈቻቸውን ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች በጥልቀት ተገንዝቦ
በብቃት መፈፀምና ማስፈፀም የሚችል ብቃት ያለው የሰለጠነ የሰው ኃይል መፍጠር
ሲቻል በመሆኑ ለሰው ኃብት ልማት የተሰጠው ትኩረት እጅግ ከፍተኛ ነው። በ1982ዓ.ም
በመላ ሀገሪቱ ትምህርት ቤት ገብተው የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር ከ2.9 ሚልዮን በታች
የነበረ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2005ዓ.ም በትምህርት ገበታ ላይ ያሉ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች
ቁጥር በስድስት እጥፍ ገደማ አድጎ 17.3 ሚልዮን ደርሷል፡፡

በተለያየ ምክንያት በመደበኛው ትምህርት ትምህርታቸውን የመከታተል ዕድል ያላገኙ


ዜጎች ከሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት ፍትሐዊ ተጠቃሚ በመሆን የህይወት ክህሎታቸውን
በቀጣይነት እንዲገነቡና የተሻለ አምራች ዜጋ ሆነው በሀገሪቱ የህዳሴ ጉዞ የድርሻቸውን
ማበርከት እንዲችሉ አማራጭ የጎልማሶች ትምህርት መርሐ ግብር አዘጋጅተናል። በዚህም
በአሁኑ ወቅት 4ሚሊዮን 990ሺህ 453 ጎልማሶች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው፡፡
በእስካሁኑ ጥረታችን በድምሩ ከ12 ሚልዮን በላይ ጎልማሶችን የዚህ መርሃ ግብር ተጠቃሚ
ማድረግ ችለናል።

20
በተመሳሳይ ሁኔታ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን ሽፋን ለማሳደግ በተደረገው ሁሉን አቀፍ
ጥረትም በርካታ ውጤቶች ማስመዝገብ ተችሏል። በ1983ዓ.ም ወደ 416ሺህ የሚጠጉ
ተማሪዎች ብቻ በማስተናገድ 6 በመቶ ብቻ የነበረውን የሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ሽፋን
በ2006 ዓ.ም ከ40 በመቶ በላይ ማድረስ የተቻለ ሲሆን ከ2 ሚልዮን በላይ ተማሪዎች
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ።

የትምህርት ጥራትና አግባብነት በማረጋገጥ ረገድ ያሉትን ውስንንቶች በቀጣይነት


ለማስተካከልም በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው። የትምህርት ጥራትና አግባብነት
ተግዳሮቶች በቀጣይነት መፍታት የሚያስችል የተሟላ የትምህርት ጥራት ፓኬጅ
ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር በመገባቱም በየደረጃው መልካም ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው።
የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ስራዎች በ2002 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ
ማጠናቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 2.0 እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡት 62.25% የነበረ
ሲሆን ይህን ምጣኔ በ2005 ዓ.ም ወደ 73.34% ከፍ ማድረግ ተችሏል። በሌሎች
የትምህርት ደረጃዎችም ተመሳሳይ ውጤቶች እየተገኙ ነው። የትምህርት ጥራት የማረጋገጥ
ስራ በቀጣይም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የሚከናወን ይሆናል።

3.2 የከፍተኛ ትምህርት

የከፍተኛ ትምህርት ስርዓታችን ዜጎች ኢኮኖሚያችን የሚፈልገውን ከፍተኛ ሙያ


የሚቀስሙበት ነው። ዘርፉ በዛሬ ላይ ብቻ የታጠረ ሳይሆን የነገይቱን ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ
ፍላጎት ሊያሟላ የሚችል በአመለካከቱ የተቃና፣ በዕውቀቱና በክህሎቱ የዳበረ ዜጋ
የሚፈልቅበት በመሆኑ በዚህ ደረጃ የሚሰጡ የንድፈ ሐሳብና የተግባር ትምህርቶች ሀገራዊ
ሁኔታችንን ታሳቢ ያደረጉና ችግር ፈቺ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ በርካታ ስራዎች
እየተከናወኑ ነው።

ዩኒቨርስቲዎቻችን የሀገሪቱ ኢንዱስትሪ ዕድገት የሚፈልገውን ዓይነት የሰው ኃይል


በብቃትና በብዛት እንዲያዘጋጁ ለማስቻል አዳዲስ ሥርዓተ ትምህርቶች ከመዘጋጀታቸውና
ሞጁለር የትምህርት አቀራረብ ከመጀመሩ በተጨማሪ ከተለያዩ ባለድርሻ መስሪያ ቤቶች
ጋር በመቀናጀት ወደ ተግባር የተገባበት ሁኔታ ፈጥረናል። በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ

21
የሚሰጠውን ትምህርት ጥራትና አግባብነት በቀጣይነት በማሻሻል ዓለም አቀፍ ደረጃውን
ለመጠበቅ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ኢኮኖሚው የሚፈልገውን ከፍተኛ ብቃት ያለው የሰው ሃይል ማፍራት እንዲቻል አጠቃላይ
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ካለፉ ተማሪዎች መካከል 40 በመቶ በምህንድስና፣ 30
በመቶ በሌሎች የተፈጥሮ ሳይንስ መስኮች የቀሩት 30 በመቶዎች ደግሞ በተለያዩ
የማህበራዊ ሳይንስ መስኮች እንዲማሩ አቅጣጫ ተቀምጦ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በማስፋፋትና በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በመገንባት


ተደራሽ እንዲሆኑ የተከናወነው ስራ አመርቂ ውጤት እያስገኘ ነው። እስከ 1983ዓ.ም
ድረስ ሁለት ብቻ የነበሩ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የመቀበል አቅማቸውም በዓመት ከ3
ሺህ የማይበልጥ ነበር። በአሁኑ ጊዜ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን ቁጥር ወደ 32 ከፍ
ማድረግ የተቻለ ሲሆን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ ግማሽ ሚሊዮን
የሚሆኑ ተማሪዎች ተቀብለው እያስተማሩ ይገኛሉ።

የከፍተኛ ትምህርትን በማስፋፋት፣ የቅበላ ዓቅማችንን በቀጣይነት በማሳደግ እንዲሁም


በተቋማቱ የሚሰጠውን ትምህርት ጥራትና አግባብነት በቀጣይነት በማሻሻል ስኬታማ
ተግባራት እየተከናወኑ ቢሆንም ሰላማዊ የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚፈታተኑ ችግሮች
ይስተዋላሉ፡፡ ከነዚህ ችግሮች አንዱ የአክራሪነትና ፅንፈኝነት እንቅስቃሴ ነው፡፡
ፅንፈኛውና አክራሪው ሃይል በእነዚህ ተቋማት አንድ ጊዜ በሃይማኖች ሽፋን ሌላ ጊዜ
ደግሞ የብሔር ታፔላ በመለጠፍ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማደናቀፍ ዓልሞ
የሚሰራበት ጊዜ ቀላል አይደለም። ይህ ደግሞ “ትምህርት በማናቸውም ረገድ ከሃይማኖት፣
ከፖለቲካና ባህላዊ ተፅእኖዎች ነፃ በሆነ መንገድ መካሄድ አለበት” የሚለውን ሕገ
መንግስታዊ ድንጋጌ የሚፃረር በመሆኑ በቀጣይነት መስተካከል የሚገባው ሲሆን ለዚህም
የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አመራሮች፣ መምህራንና ሌሎች ሰራተኞች ግንባር ቀደም
ተዋናይ መሆን ይኖርባቸዋል።

3.3 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ፕሮግራም ኢኮኖሚያችን የሚፈልገውን መካከለኛ


ሙያ ያለው ዜጋ የማብቃት ተልዕኮ ያነገበ ነው። ስራ ፈጣሪ ዜጎች በማፍራት በኩልም

22
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ጉልህ ሚና ይጫዎታሉ። እነዚህ ተቋማት
መደበኛ እና አጫጭር ስልጠናዎች በመስጠት የኢንዱስትሪውን ፍላጎት በማሟላት
የሀገራችን የኢንዱስትሪ ዕድገት በመደገፍ ላይ ይገኛሉ።

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ፕሮግራም በጥራት መከናወኑ የኢኮኖሚ ዕድገት


በማረጋገጥ ድህነትን ለማስወገድ የተያያዝነውን የህዳሴ ጉዞ ለማሳካት ዓይነተኛ መሳሪያ
ነው። በመሆኑም ተቋማቱ የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከል የሚሆኑበትን አሰራር የማጠናከርና
የስልጠና ጥራቱን በሁሉም ደረጃ በማሻሻል ከገበያው ፍላጎት ጋር የማጣጣም ስራ
በቀጣይነት እየተሰራበት ነው። ተቋማቱ ለሀገር ዕድገት ቁልፍ ሚና ባላቸው የስራ መስኮች
ላይ እንዲያተኩሩ እየተደረገም ነው። የእነዚህን ተቋማት ውጤታማነት በቀጣይነት
ለማጠናከርም በውጤት ላይ የተመሰረተና ያልተማከለ የአሰራር ስርዓት የመፍጠር ስራው
ትኩረት ተሰጥቶታል። ባለፉት ዓመታት ዘርፉን ለማሳደግ በተሰጠው ትኩረት በተለያዩ
ሙያዎች የስልጠና ፕሮግራሞች ተቀርፀው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዝቅተኛና መካከለኛ
ሙያተኞችን ለማሰልጠን ተችሏል።

የቴክኒክና ሙያ ስልጥና ፕሮግራም ስርዓተ ትምህርቱ የነበሩበትን ጉድለቶች


ለማስተካከልም የዘርፉ ደረጃዎች ከጀርመን የዳበረ ልምድ ተቀምረውና ከሀገራችን ነባራዊ
ሁኔታ ጋር ተጣጥመው ተግባር ላይ እንዲውሉ ተደርገዋል። ብዛት ያላቸውን መምህራንን
ለማሰልጠን ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን፡፡ በዚህም በ2005ዓ.ም ብቻ 2ሺህ 101
ሴቶች የሚገኙባቸው 12ሺህ 779 መምህራን ሰልጥነዋል።

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋሞች የንድፈ ሐሳብ ማሰልጠኛ ተቋሞች ብቻ ሳይሆኑ


የተግባር ልምምድ ስልጠና የሚሰጥባቸው የምርትና የአገልግሎት ተቋሞች ጭምር ናቸው።
የምናመርታቸውን ሸቀጦችና አገልግሎቶች በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ ሰልጣኞቹ
በተግባር የተደገፈ እውቀትና ክህሎት እንዲጨብጡ በማድረግ ረገድም ስኬታማ ስራዎች
እየተከናወኑ ነው። በዚህም የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋሞች በአሁን ሰዓት አዳዲስ
ቴክኖሎጂዎች የሚመረቱባቸውና የሕብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ ምርምሮች የሚካሄድባቸው
ማዕከላት ወደ መሆን እየተሸጋገሩ ይገኛሉ። ይህም የሀገራችን ህዳሴ ለማሳካት የሚያስችለን
እርሾ በመፍጠር በኩል ተቋማቱ ገንቢ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው።

23
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፕሮግራሙ ስራ ፈጣሪ ዜጋ በማፍራትም ሆነ ለኢንዱስትሪው
የሚያስፈልገውን መካከለኛ ሙያ ያለው የሰለጠነ የሰው ኃይል በማምረት ረገድ ውጤታማ
ስራዎች ያከናወኑ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል ቢያሳይም አሁንም ተቋማቱ በሌላ
መንገድ መማር ያልቻሉ የወደቁ ሰዎች የሚሰበሰቡባቸው አድርጎ የማየት የተሳሳተ
አመለካከት በአመራሩም ሆነ በፈጻሚው ዘንድ ይታያል፡፡ ዘርፉ አማራጭ ያጡ ዜጎች
የሚሰበሰቡበት ሳይሆን ዜጎች ህይወታቸውን ለመምራት የሚያስችላቸውን ሙያ ለማግኘት
አልመው የሚገቡበት እና በአመለካከት፣ በዕውቀት እና በክህሎት የሚዳብሩበት ትልቅ
የዓቅም ግንባታ ዘርፍ እንደሆነ በቀጣይነት የማስገንዘብ ስራው ተጠናክሮ መቀጠል
የሚገባው ሲሆን ዋናው ትኩረት ግን ተቋማቱ በሚያካሂዱት የእለት ተእለት ግንባታ እና
ከተቋማቱ የሚወጡ ዜጎች በሚያሳዩት የተግባር ብቃት ይህን የተዛባ አመለካከት
የሚሰብሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይሆናል።

3.4 የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢኖቬሽን ዕድገት እንደመንደርደሪያ አቅም

ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለአንድ ሀገር መዘመንና ዘላቂ ዕድገት ወሳኝና የማይተካ ሚና አለው።
የኢንዱስትሪ አብዮት ተከትሎ የአውሮፓ ሀገራት ራሳቸውን ለማሳደግና ታላቅ ሀገር
ለመባል በትጋት በመስራታቸው እንደየትጋታቸው ከዘርፉ በመጠቀም አስተማማኝ ለውጥ
ማምጣት አስችሏችዋል። የለውጡ ማጠንጠኛ ደግሞ ጊዜው የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ
አሟልቶ መገኘት ነበር። ይህን እውነታ በመረዳት በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በማደግ
ላይ ያሉ ሀገራት የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ዕድገታቸው እውን ለማድረግ ደፋ
ቀና ሲሉ ይታያሉ።

የሀገራችንን ህዳሴ ለማረጋገጥ አስፈላጊ ከሆኑት ጉዳዮች ሳይንስና ቴክኖሎጂ ይገኝበታል።


ያለ ቴክኖሎጂ የምናመርተው ምርት ተወዳዳሪ መሆን አይችልም፣ ያለ ቴክኖሎጂ
የሚፈለገው የምርት ጥራትና የምርታማነት ፍጥነት ሊረጋገጥ አይቻልም። የግብርናም ሆነ
የኢንዱስትሪ ዕድገት ቀጣይነታቸው እንዲረጋገጥ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሊደገፉ ይገባል።

ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለህዳሴ ጉዟችን ያለው አስፈላጊነት ለክርክር የማይቀርብ ቢሆንም


የዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ ያላት ሀገር የመፍጠር የቅርብ ጊዜ ግባችንን ለማሳካት ዋናው
ትኩረታችን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ማፍለቅ ሳይሆን አሁን በስራ ላይ ያሉትን በአግባቡ
የመጠቀም ዓቅማችን የመገንባት ጉዳይ ነው። ስለሆነም የቀጣይ ትኩረታችን ለህዳሴ

24
ጉዟችን የሚያግዙ በሌሎች ሀገራት የተፈጠሩ ቴክኖሎጂዎችን መኮረጅና በላቀ ፍጥነትና
ብቃት የመጠቀም ዓቅማችን በመገንባት ሌሎች የበለፀጉ ሀገራት የደረሱበት ደረጃ ላይ
መድረስ ነው።

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገት ለሀገራችን ህዳሴ እውን መሆን ከፍተኛ ሚና እንዳለው


በአግባቡ በመረዳት ከፌዴራል እስከ ክልል ባሉ የመንግስት መዋቅሮች ራሱን የቻለ
የሳይንስና ቴክኖሎጂ መስሪያ ቤት በማቋቋም አዳዲስ የሳይንስ እና የፈጠራ ስራዎችንና
ግኝቶችን ማበረታታትና በቅርብ ድጋፍና ክትትል የሚያገኙበትን ሁኔታ መፍጠር
ችለናል። ሀገር አቀፍ የሳይንስ፣ የሒሳብ፣ የምርምርና የፈጠራ ውጤቶች ቀን በማዘጋጀት
በየዘርፉ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ግለሰቦችና ቡድኖች በየዓመቱ የማበረታቻ ሽልማት
መስጠት የጀመርነውም ዘርፉን በቀጣይነት ለማሳደግ ያስቀመጥነው ዓላማ ለማሳካት ነው።
በዚህም በያዝነው ዓመት ብቻ በመላ ሀገሪቱ በእነዚህ ዘርፎች የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ
49 ሴቶች የሚገኙበት 241 የሚሆኑ ተማሪዎች፣ መምህራን እና ተመራማሪዎች ተሸላሚ
ሆነዋል።

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስራችን አሁንም ልዩ ትኩረት የሚሻ እና ዘርፉን የሚፈታተነውን


የአቅም ችግር መፍታት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ የትምህ,ርት ተቋማት
ለሳይንስና ቴክኖሎጂ የሚሰጡት ትኩረት አሁንም ከሚፈለገው ደረጃ ላይ ስላልደረሰ
የአመራሩና የትምህርት ተቋማቱ ማህበረሰብ ልዩ ትኩረት ሰጥተው መንቀሳቀስ
ይኖርባቸዋል፡፡

3.5 ጤናው የተጠበቀ ዜጋን የመገንባት ስራችን

የባለፉት ስርዓተ መንግስታት ይከተሉት በነበረው የተሳሳተ የጤና ፖሊሲ ምክንያት


በመከላከል ብቻ በቀላሉ ሊድኑ በሚችሉ በሽታዎች ሳቢያ ዜጎቻችን ለሞትና ለከፋ የጤና
ችግር ሲጋለጡ ኖረዋል። የሁሉም ስራዎቻችን አልፋና ኦሜጋ የህዝብ ጥቅም ማረጋገጥ
በመሆኑ መከላከልን ማዕከል ያደረገ የጤና ፖሊሲ በማዘጋጀት የዜጎች ጤንነት በቀጣይነት
በማሻሻል ጤንነቱ የተጠበቀ አምራች ዜጋ በመፍጠር ረገድ ስኬታማ ስራዎች በማከናወን
ላይ እንገኛለን።

25
የጤና ፖሊሲያችን ሰፊውን ህዝብ ለማገልገል የተቃኘና በመሰረታዊ የጤና አገልግሎት
ላይ ያተኮረ በመሆኑ ህዝባዊ ተቀባይነት ያለውና የህዝቡን ተጨባጭ የጤና ችግሮች
በመፍታት ረገድ ውጤታማነቱን የተመሰከረለት ነው። ባለፉት 23 አመታት በተከናወኑ
ውጤታማ ስራዎች ሀገር አቀፍ የጤና ሽፋናችን በቀጣይነት እየተሻሻለ ይገኛል። ሀገር
አቀፍ የመሠረታዊ ጤና አገልግሎት ሽፋናችንን በ1983ዓ.ም ከነበረበት 41 በመቶ
በ2005 ወደ 93.4 በመቶ ከፍ ማድረግ ችለናል።

እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ በሀገሪቱ የነበሩ የጤና ተቋማት ብዛት እጅግ አነስተኛ ሲሆን
ፋሽስታዊው የደርግ ስርዓት ከተገረሰሰ ወዲህ ግን የጤና አገልግሎት ተቋማት ብዛትና
ተደራሽነት በቀጣይነት በማደግ ላይ ይገኛል። ለምሳሌ በ1983ዓ.ም 72 የነበረው
የሆስፒታሎች ቁጥር በ2006 ዓ.ም ወደ 310 ያደገ ሲሆን የጤና ጣቢያዎች ቁጥርም ከ154
ወደ 3ሺህ 250 ከፍ ማድረግ ችለናል። በሽግግር ዘመኑ ምንም ያልነበረውን የጤና ኬላ
ግንባታም በያዝነው ዓመት ከ16 ሺህ በላይ ማሳደግ ተችሏል። በየደረጃው የሚገኙ የጤና
ባለሙያዎች ቁጥርም በተመሳሳይ ሁኔታ እያደገ ይገኛል። ለዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት
መሰረት የአገልግሎት ሽፋኑን በቀጣይነት በማሳደግ ሀገራችን የህፃናትን ሞት በመቀነስ፤
ወባንና ሌሎች በሽታዎችን እንዲሁም የኤችአይቪ ኤድስ ስርጭትን በመግታት ለዓለም
አቀፉ ደረጃ አርአያ እንድትሆን አስችሏታል።

በአጠቃላይ በጤናው ዘርፍ የተገኙ ውጤቶች የጤና ፖሊሲያችንን አቅጣጫ ትክክለኛነት


የሚያረጋግጡ አበረታች ስኬቶች በመሆናቸው የስኬቶቹ ባለቤት የሆነውን ህዝባችን ይዘን
አሁንም ሌላ አዲስ ታሪክ መስራት እንደምንችል ልምድ የወሰድንበት ነው። ይሁን እንጂ
አሁንም በጤናው ዘርፍ የምንፈልገውን ያህል ውጤት ለማስመዝገብ በአገልግልት አሰጣጥ
ላይ የሚታዩትን የጥራት መጓደሎች፣ የህክምና ቁሳቁሶች እጥረት፣ አልፎ አልፎ
የሚያጋጥም የባለሙያዎች የስነምግባር መጓደል፣ በመድሃኒት አቅርቦትና ስርጭት ላይ
የሚስተዋሉ ችግሮችን እና የመሳሰሉትን መፍታት ግድ ይለናል።

4. የመሰረተ ልማት

ሀገራችን የጀመረችው የህዳሴ ጉዞ በማሳካት የህዝባችን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ


ይቻል ዘንድ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች ማከናወን

26
ይኖርብናል። የመሰረተ ልማት ተቋማት በስፋትና በጥራት ባልተሟሉበት ሁኔታ
የጀመርነውን ፈጣን ዕድገት ዳር ማድረስ አይቻልም። በመሆኑም ልማታዊ መንግስታችን
ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ሀገር በቀል የፖሊሲ ማዕቀፍ በማዘጋጀትና የህዝቡን
ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ በከፍተኛ ቁርጠኝነት በመንቀሳቀሱ ባለፉት 23 ዓመታት
ውጤታማ ስራዎች በማከናወን የሀገሪቱ የመሰረተ ልማት ተደራሽነት ትርጉም ባለው
መልኩ ማሻሻል ተችሏል። በመሰረተ ልማት ረገድ የህዳሴ ጉዞችን የሚገኝበትን ሁኔታ
እንደሚከተለው እንመልከት፡፡

4.1 የመንገድ ልማት

መንገድ ሀገሪቱ የተያያዘችውን አንድ የኢኮኖሚ ማሕበረሰብ የመገንባት ራዕይ በሚፈለገው


ሁኔታ እውን ለማድረግ እጅግ ወሳኝ ከሆኑት ዘርፎች መካካል ግንባር ቀደሙ ነው።
በአንድ የሀገሪቱ አካባቢ የተመረተ ምርት ወይም አገልግሎት በአጭር ጊዜና በተመጣጣኝ
ዋጋ ወደ ማዕከላዊ ገበያ ብሎም ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለማድረስ ጥራት ያለው መንገድ
ያስፈልጋል። እንዲሁም ከማዕከላዊ ገበያ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች መድረስ
የሚገባቸው ምርቶችና አገልግሎቶች በወቅቱ ወደ ተጠቃሚዎች ለማድረስ የመንገድ ሚና
እጅግ ከፍተኛ ነው። በተለይ ለአርሶ አደሩና ለአርብቶ አደሩ አስፈላጊ የሆኑ የግብርና
ቴክኖሎጂዎችና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ የምርት ግብአቶች በተፈለገው ጊዜ በማዳረስ
የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በማድረግ በኩል ጥራት ያለው መንገድ
መኖር አለበት። ለዚህም ነው መንግስታችን ሀገር አቀፍ የመንገድ ኔትዎርክ መርሐ ግብር
ቀርፆ ለተፈፃምነቱ በከፍተኛ ቁርጠኝነት በመረባረብ ላይ የሚገኘው።

በሌላም በኩል ሀገራችን ከጎረቤት ሀገራት በተለይ ደግሞ ከወደቦች ጋር የሚያገናኙ ዓለም
አቀፍ ደረጃቸው የጠበቁ መንገዶች ያስፈልጓታል። ሀገራችን የምታመርታቸው ምርቶችና
አገልግሎቶች በአጭር ጊዜ ወደ ወደቦች በማድረስ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ መሰረት
ወደየመዳራሻቸው በመላክ ተወዳደሪነታችን በመገንባት በኩልም መንገድ በጣም አስፈላጊ
ቅድመ ሁኔታ ነው።

27
የመንገድ ዘርፍን አስፈላጊነትና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በአግባቡ በመገንዘብ ባለፉት 23
ዓመታት ከፍተኛ ስራዎች ማከናወን ተችሏል። ስለሆነም እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ 18 ሺህ
81 ኪሎ ሜትር ብቻ የነበረው የሀገራችን የመንገድ ርዝመት በ2005ዓ.ም ወደ 86 ሺ ኪሎ
ሜትር ገደማ ከፍ ማድረግ ተችሏል። በመንገድ ዘርፍ የተመዘገበው ዕድገት በመንገዶች
ርዝመት ብቻ ሳይሆን በጥራትም ጭምር ነው፡፡ ለአብነት በ1989 በጥሩ እና በደህና ይዞታ
ላይ የሚገኝ መንገድ 48 በመቶ ብቻ የነበረ ሲሆን ይህ ምጣኔ በ2005 ወደ 90 በመቶ ከፍ
ማድረግ ተችሏል፡፡

በመንገድ ዘርፍ ለተመዘገቡ ስኬቶች የመንግስታችን ቁርጠኝነትና የህዝባችን ሁሉን አቀፍ


ተሳትፎ ደግሞ ፖሊሲዎቻችንና ስትራቴጂዎቻችን መሬት ላይ በማስነካት ተጨባጭ
ውጤት በማስመዝገብ በኩል የተጫወቱት ሚና ተኪ የለውም። በዘርፉ የፈጠርነው የግንባታ
ዓቅምም ከመንገድ ግንባታው የማይታናነስና ሀገሪቱ በቀጣይነት ለሚታካሂዳቸው ሰፋፊ
የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ሰፊ የመፈፀምና የማስፈፀም ዓቅም መገንባት ያስቻለ
ልምድ ያገኘንበት ነው። በዘርፉ በርካታ የሀገር ውስጥ ተቋራጮችና አማካሪዎች
ከመፍጠራችን በተጨማሪ በዘርፉ የፈጠርነው የስራ ዕድልም እጅግ ከፍተኛ ነበር። እናም
በሀገራችን የተገነቡትና በመገንባት ላይ የሚገኙ መንገዶች ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያረጋገጡና
በማረጋገጥም ላይ የሚገኙ ናቸው ማለት ይቻላል።

4.2 የባቡር ልማትና ተወዳዳሪነታችን፣

የሀገሪቱ ምርት በዓይነትም ሆነ በመጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ ሲሆን


በዕድገታችን ልክ ወደ ውጭ የምንልካቸውና ከውጭ የምናስገባቸው ምርቶች በመጨመር
ላይ ናቸው። እነዚህን እያደጉ ያሉ የወጭ እና የገቢ ምርቶቻችን በተለመደው
የትራንስፖርት ዘይቤ ለማጓጓዝ በዋጋ እና በፍጥነት ተወዳዳሪ መሆን አይቻልም።
በመሆኑም በርካታ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በአጭር ጊዜ ማመላለስ የሚያስችለን
የትራንስፖርት ስርዓት መዘርጋትና በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል ይኖርብናል። ለዚህ ደግሞ
ሀገር አቀፍ የባቡር ኔትዎርክ መዘርጋት የተሻለ አማራጭ ነው።

የባቡር ትራንስፖርት ከፍተኛ መጠን ያላቸው የምርት ግብአቶችና ምርቶችን በተመጣጣኝ


ዋጋ እና በተሻለ ፍጥነት በማጓጓዝ በኩል ወደር የሌለው የትራንስፖርት ዓይነት ነው።
የባቡር ኔትዎርክ ግንባታ ስራችን በረዥምና በአጭር ጊዜ ዕቅድ የሚፈፀም ሆኖ 5ሺህ ኪሎ

28
ሜትር የሚሆን አጠቃላይ ርዝመት የሚሸፍን ነው፡፡በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዳችን
ውስጥም 2 ሺህ 395 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ለመዘርጋት አቅደን እየተረባረብን
እንገኛለን፡፡ ፕሮጀክቱ በአንድ በኩል የሀገራችን ወጪና ገቢ ምርቶችን በተሻለ ፍጥነት
በማስወጣትና በማስገባት በጉዞ ይባክን የነበረውን ጊዜ በመቆጠብ አገራችን ከዘርፉ
የምታገኘው ጥቅም የሚያሳድግ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያን ከጎረቤት አገሮች
ጋር በማገናኘት በአገራቱ መካከል የሚኖረውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ
ግንኙነትና ትስስር በእጅጉ የተሳለጠ ያደርገዋል።

ከአገር አቋራጭ የባቡር መስመር ዝርጋታ በተጨማሪ በመዲናችን አዲስ አበባ የሚገነባው
የቀላል ባቡር ፕሮጀክት ስራው ሲጠናቀቅ በሁለት አቅጣጫ በአንድ ሰዓት 80 ሺህ
መንገደኞችን ማጓጓዝ እንዲችል ተደርጎ እየተገነባ ነው፡፡ አጠቃላይ ርዝመቱ 34.35 ኪሎ
ሜትር የሚሸፍነው ይህ ፕሮጀክት በመጭው አመት አጋማሽ ለማጠናቀቅ ርብርብ
እየተደረገ ይገኛል፡፡

እንደ መንገድ ዘርፉ ሁሉ በባቡር መስመር ዝርጋታውም ከፍተኛ ልምድ ከመቅሰማችን


በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ የስራ ዕድል በመፍጠር በዘርፉ ቀጣይነት ያለው የውስጥ ዓቅም
በመገንባት በኩል ተጨማሪ ዓቅም እየፈጠርን እንገኛለን። ይህ ደግሞ ሀገራችን ወደፊት
ለምታካሂዳቸው መሰል ግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታ የውስጥ ዓቅም የሚፈጥር ነው።

4.3 የኃይል አቅርቦትና የኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን፣

ከግብርና መር የኢንዱስትሪ ልማት ወደ ኢንዲስትሪ መር የኢኮኖሚ ልማት ለመሸጋገር


በፈጣን ሁኔታ እየገሰገሰች ላለችው ኢትዮጵያ አስተማማኝ ጥራት ያለው በቂ የኃይል
አቅርቦት መኖር እጅግ ወሳኝ ቅድመ ሁኔታ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። የኃይል አቅርቦት
የሀገሪቱ ኢንዱስትሪ ከማንቀሳቀስ በላይ የዜጎቻችን የእለት የኃይል ፍጆታ በማሟላት
የአካባቢ መራቆትን በመታደግ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት የመጨመር ተልዕኮ
ጉዳይም ነው። በሌላም በኩል ሴቶች ለማገዶ ፍለጋም ሆነ በእንጨት ለማብሰል
የሚያጠፉትን ጊዜና ጉልበት በመቀነስ ተጠቃሚነታቸው የማረጋገጥ ስራም ጭምር ነው።

በኢንዱስትሪ የበለፀገች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ በመገንባት የሀገራችንን ህዳሴ ዕውን


ማድረግ ይቻል ዘንድ የኢኔርጂ ዘርፍ በተለይ ደግሞ ከኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት

29
ዓቅማችን በቀጣይነት በማሳደግ ረገድ የበርካታ ስኬቶች ባለቤት ሆነናል። በባለፉት
ስርዓቶች በከተሞች ብቻ ታጥሮ የነበረውን የሀገራችን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት
በቀየስነው ፍትሐዊ የኃይል አቅርቦትና ተደራሽነት ስትራቴጂ መሰረት በየጊዜው በማደግ
ከፍተኛ ስኬቶችን በማስመዝገብ ላይ እንገኛለን፡፡ እስከ 1983ዓ.ም ድረስ በ361 ሜጋ ዋት
ላይ ብቻ ታጥሮ የነበረው የሀገራችን የኤሌክትሪክ ኃይል በአሁኑ ወቅት ወደ 2 ሺህ 177
ሜጋ ዋት ከፍ ብሏል።

የሀገራችን የኢኔርጂ ምንጮች ከታዳሽ ሃይል የሚገኙና ቀጣዩ የሀገራችን የዕድገት አቅጣጫ
ግምት ውስጥ በማስገባት እየተከናወኑ የሚገኙ መሆናቸው ደግሞ የዘርፉን ዕድገት
አስተማማኝ ያደርገዋል። ለዘርፉ በሰጠነው ከፍተኛ ትኩረት መሰረት ሀገራችን ያላት
የታዳሽ ሃይል (የውሃ፣ የንፋስ፣ የፀሃይ፣ የጂኦቴርማልና የባዮ ፊዩል) ምንጮችን በአግባቡ
በማልማት የራሳችን የልማት ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር ለጎረቤት ሀገራት ጭምር
የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ጎረቤቶቻችንንም ጭምር የምንጠቅምበት ሁኔታ እየፈጠርን
እንገኛለን።

ሀገራችን ከፍተኛ የውሃ፣ የነፋስ፣ የፀሐይና የእንፋሎት ታዳሽ ሃይሎች የኤሌክትሪክ ኃይል
የማመንጨት ዓቅም አላት። በመሆኑም ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመገንባት
በምናደርገው ያለሰለሰ ርብርብ ለእድገታችን በቂ እና ከበቂ በላይ የሆነ መልማት የሚችል
እምቅ ኃይል ይዘን ወደፊት ለመገስገስ የሚያስችለን የተመቻቻ ሁኔታ ያለን ነን። እናም
በዘርፉ ያለንን ያልተነካ ሃብት በአግባቡ እያለማን የራሳችን ፍላጎት ከማሟላት በላይ
ለጎረቤቶቻችን እና ለሌሎች አካባቢዎችም መሸጥ እንችላለን። የወደፊቱ
የኢንዱስትራያላዜሽን ዕድገታችን በየጊዜው ከሚዋዥቀው የዓለም የነዳጅ ገበያ በከፍተኛ
ሁኔታ የተላቀቀ እና በራሳችን አስተማማኝ ዓቅም ላይ የተገነባ ለማድረግ የሚያስችሉን
አቅጣጫዎች ነድፈን በመንቀሳቀሳችን ውጤቱን ከወዲሁ ማጣጣም ጀምረናል።

በጥቂት አመታት ውስጥ ከ8ሺ እስከ 10ሺ ሜጋ ዋት ሃይል ለማመንጨት ባቀድነው


መሰረት ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ቀርፀን ስኬታማ ተግባሮችን እየፈፀምን እንገኛለን፡፡በአሁኑ
ጊዜ ደግሞ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ በርካታ ግዙፍ የኃይል ማመንጫ
ፕሮጀክቶች እየገነባን ሲሆን ፕሮጀክቶቹ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽሽን ዕቅዱ
በተያዘላቸው አቅጣጫ መሰረት እየተከናወኑ ነው።

30
በኢነርጂ ዘርፍ ያገኘው ስኬት ግን አልጋ ባልጋ የተገኘ አልነበረም። ዘርፉ ካሉት
ፈተናዎቹ መካከል በዋናነት የሚጠቀሰው የፋይናንስና የማስፈፀም ዓቅም ማነስ ነው።
በተለይ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶቻችን በተያዘላቸው ጊዜ መሰረት
ለማከናወን ከፍተኛ ካፒታልና ክህሎት የሚጠይቁ በመሆናቸው በተፈለገው ፍጥነት
ከመፈፀም አንፃር በርካታ ፈተናዎች የበዙበት ቢሆንም መንግስትና ህዝብ በሚያደርጉት
ርብርብ ችግሮቹን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

4.4 የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት

በሀገሪቱ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት በማምጣት የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ


በሚደረገው ሀገራዊ ርብርብ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ኢኮቴ) አገልግሎት
ከፍተኛ ሚና ከሚጫወቱ ዘርፎች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው። የቴሌኮም አገልግሎት
ተደራሽነትን በቀጣይነት በማስፋፋት አርሶና አርብቶ አደሩ አገልግሎቱን በመጠቀም
ካለበት ቦታ ሆኖ የገበያ ሁኔታ የሚከታተልበት የተመቻቸ ሁኔታ በመፍጠራችን የህዝባችን
ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት በቀጣይነት እየተጠናከረ ይገኛል።

በቴሌኮም ዘርፍ የአምስት ዓመቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ እውን ለማድረግ


ሰፋፊ እንቅስቃሴዎች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡ እስከ 1983ዓ.ም ድረስ በከተሞች በተለይ
ደግሞ በአዲስ አበባ ላይ ታጥሮ የነበረውን የቴሌኮም አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታ ከመሰረቱ
በመቀየር በአሁኑ ሰዓት የገጠሩን ሕብረተሰብ ጨምሮ አብዛኞቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች
የመደበኛና የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ማድረግ ተችሏል። በዚህም
ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ከፈጣኑ ዕድገታችን ፍትሐዊ ተጠቃሚ በመሆን ላይ ይገኛሉ።
በ1982ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ 56ሺህ 557 ብቻ የነበረው የቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር
በ2006ዓ.ም በተንቀሳቃሽ ስልክ 25 ሚልዮን 660ሺህ ደንበኞችን በመደበኛ ቴሌፎን ደግሞ
734 ሺህ ደንበኞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ማድረግ ተችሏል። በዳታ እና
በኢንተርኔት አገልግሎትም እንዲሁ 5 ሚልዮን 700ሺህ ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ
ናቸው።

ክልሎች ከወረዳዎች እንዲሁም ወረዳን ከወረዳ የሚያገናኘውና በመካከላቸው የተሳለጠ


የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ከፍተኛ ድጋፍ እያደረጉ ያሉት ወረዳ ኔት፤ ስኩል ኔት እንዲሁም
ዜጎች በኢንቴርኔት አማካኝነት የፍትሕ አገልግሎት ተደራሽ የሚሆኑበት ዘመናዊ የፍትህ

31
ስርዓት በመዘርጋቱ የመረጃ ፍሰቱን የተሳለጠ እያደረጉት ይገኛል፡፡ እነዚህ
የቴሌኮሚዩንኬሽን አገልግሎትን መሰረት አድርገው የተጀማመሩ አሰራሮች በቀጣይም
ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል።

የቴሌኮም ተደራሽነት ለማስፋፋት በተደረገው ርብርብ በርካታ መሻሻሎች እየታየ ቢሆንም


የአገልግሎቱን ጥራት ከማረጋገጥ አንፃር ግን ቀጣይ ስራ የሚጠይቅ ነው። ለጥራት ችግሩና
ለኔትዎርክ መቆራረጡ መፍትሔው በአንድ በኩል ባለው ኔትዎርክ አገልግሎቱን ለማሻሻል
ያልተቋረጠ ጥረት ማድረግ ሲሆን ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ደግሞ እያከናወንን
ያለነውን የማስፋፊያ ስራ በተፈለገው ጥራትና ጊዜ ማጠናቀቅ በመሆኑ ከፍተኛ ርብርብ
እያደረግን እንገኛለን። በዚሁ መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ የነበረው ችግር ወሳኝ በሆነ
ሁኔታ የተፈታ ሲሆን በሌሎቹ የአገሪቱ አካባቢዎችም ችግሩ በቅርብ ጊዜ በአስተማማኝ
ሁኔታ ይፈታል፡፡

5. ሕገ መንግስታዊና ስርአታችን የህዳሴያችን መሰረት

የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት ካለፉት ጨቋኝ ስርአቶች ህግጋተ መንግስት ከሚለይባቸው


ቁልፍ ባህርያቶች መካከል የኢትዮጵያን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የሉአላዊ ስልጣን
ባለቤቶች ማድረጉ ነው። ሕገ መንግስታችን በህዝቦች መካከል እኩልነትን በማረጋገጥና
ነባራዊ የሀገራችን ገፅታ ለሆነው ብዝሃነታችን ዋስትና በመስጠት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ
ከፍቷል። በአዲሲቱ ኢትዮጵያ የብሔር፣ የቋንቋ፣ የእምነትና የሃይማኖት፣ የጾታ፣
የአመለካከት እኩልነት የፌዴራል ስርዓቱ ልዩ ባህርያትና የዴሞክራሲያችንም መሰረታዊ
ምሶሶዎች ሆነው ተደንግገዋል።

ህገ መንግስታዊ ስርአታችን ለሀገራችን የህዳሴ ጉዞ መሰረት የጣለ በሀገራችን ለዘመናት


ተንሰራፍቶ የነበረውን ጸረ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ጥሎት ያለፈውን ጠባሳ ያነጻ
ለልማታችን፣ ለዴሞክራሲያችን እና ለሰላማችን ዋስትና ነው፡፡ የህገ መንግስታዊ ስርዓቱን
ዋና ዋና ጉዳዮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

32
5.1 የሕገ መንግስታችን መሰረታዊ መርሆዎች፣

የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት የአዲሲቱን ኢትዮጵያ መፃኢ ዕጣ ፋንታ የሚወስኑ መሰረታዊ


መርሆዎችን በግልፅ በማስቀመጥ ኢትዮጵያ ሁሉም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች
በመቻቻልና በመከባበር በጋራ የሚኖሩባት፤ ኢትዮጵያዊነትን ደግሞ ፈቅደውና አምነው
የሚቀበሉት የጋራ ክብርና ማንነት በማድረግ የሀገሪቱ ፖለቲካዊ ስርዓት በአዲስ መሰረት
ላይ መገንባት ችሏል።

በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት መሰረት የሀገሪቱ ሉአላዊ ስልጣን ባለቤቶች የኢትዮጵያ


ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ናቸው። “ንጉስ አይከሰስም፣ ሰማይ አይታረስም” በሚል
መርህ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሸጋገር የነበረው የፊውዳል ስርዓት እንዲሁም
አምባገነናዊ የደርግ ስርዓት ይከተሉት የነበረ ኢዴሞክራሲያዊና ፀረ ህዝብ ስርዓት
በመሰረቱ ተቀይሮ የመንግስታዊ ስልጣን ብቸኛ ባለቤቶችና እውነተኛ ምንጮች
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔሰረቦችና ህዝቦች መሆናቸውን የኤፌዴሪ ሕገ መንግስት ዋስትና
ሰጥቷቸዋል።

የሕገ መንግስት የበላይነትም በሕገ መንግስቱ ከተቀመጡ መሰረታዊ መርሆዎች መካከል


አንዱ ነው። ሕገ መንግስቱ የሀገሪቱ የበላይ ሕግ ነው ብሎ በግልፅ በመደንገግ ማንኛውም
ሕግ፣ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከሕገ
መንግስቱ ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው በማያሻማ አኳሃን
አስቀምጦታል። ይህም በሀገራችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመንግስት ስልጣን ላይ ግልፅ
በሆነ ሁኔታ ገደብ በመጣል ሁሉም ነገር ከሕግ በታች መሆኑን ያበሰረና የአንድነታችንና
የእኩልነታችን ወርቃማ ምሰሶ ተደርጎ የሚወሰድ ነው።

ሰብአዊ መብቶችና ነፃነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ፤ የማይጣሱና የማይገፈፉ


መሆናቸውን ዕውቅና በመስጠት የዜጎችና የህዝቦች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችና
ነፃነቶች ተገቢ የሆነ ሕጋዊ ከለላ የሰጠ ሕገ መንግስትም ነው። ይህ መርሆ የሀገራችን
ህዝቦች ለበርካታ ዘመናት ሲታገሉለት የነበረውን የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችና
ነፃነቶች መከበርና ሕጋዊ ዋስትና የማግኘት ጉዳይ በተገቢው ሁኔታ በመመለስ ዜጎች
ተሸማቅቀው ሳይሆን በዜግነታቸው ተከብረውና ኮርተው የሚኖሩባት ሀገር ለመመስረት
ያስቻለ የማዕዘን ድንጋይ ነው።

33
የመንግስትና የሃይማኖት መለያየትም ሌላኛው የሕገ መንግስቱ ወሳኝ መርሆ ነው። ሕገ
መንግስታችን ካለፉት የአገራችን መንግስታት ህገ መንግስቶች በተለየ መልኩ ተራማጅና
ዴሞክራሲያዊ ባህርይ ከሚያለብሱት ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው በመንግስትና በሃይማኖት
መካከል ያለውን ግንኙነት በግልጽና በማያሻማ መንገድ ማስቀመጡ ነው። በኢፌዲሪ ህገ
መንግስት መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ መሆናቸውን፣ መንግስታዊ ሃይማኖት
እንደማይኖር እንዲሁም መንግስት በሃይማኖት፣ ሃይማኖት ደግሞ በመንግስት ጉዳይ ላይ
ጣልቃ መግባት እንደማይችሉ ግልፅ የሆነ ሕገ መንግስታዊ ክልከላ ተበጅቶላቸዋል።

5.2 የቡድንና የግለሰብ መብቶች፣

ሕገ መንግስታችንን ዴሞክራሲያዊ ባህርያት ከሚያላብሱት መሰረታዊ መርሆዎች መካከል


የቡድንና የግለሰብ መብቶችን በተመለከተ ያስቀመጠው ዋስትና ይገኝበታል። ሕገ
መንግስታችን የግለሰብና የቡድን መብቶች ሳይሸራረፉና አንዱ በሌላኛው ሳይሸበብና
ሳይደፈቅ በተሟላ ሁኔታ ያለገደብ እንዲከበሩ በግልጽ ደንግጓል። ባለፉት 23 አመታትም
እነዚህ መብቶች በተጨባጭ በመከበራቸው በአገራችን ለተረጋገጠው ፈጣን፣ ቀጣይነት
ያለውና ፍትሃዊ ዕድገትና የተረጋጋ ሰላም የራሳቸውን አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ
ይገኛሉ።

አዲሲቱ ኢትዮጵያ ሁሉም ብሔሮች፣ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች፣ ሃይማኖቶች፣ ፆታዎች ወዘተ


በእኩልነት የሚኖሩባትና ማንኛውም የሀገሪቱ ዜጋም በዘር፣ በብሔር፣ በብሔረሰብ፣ በቀለም፣
በፆታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣በፖለቲካ፣ በማሕበራዊ አመጣጥ፣ በሃብት፣ በትውልድ ወይም
በሌላ አቋም ልዩነት ሳይደረግበት እኩልና ተጨባጭ የሕግ ዋስትና የማግኘት መብቱ ሕገ
መንግስታዊ ከለላ አግኝቷል። በተግባርም የቡድንና የግለሰብ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ
መብቶችና ነፃነቶች ሳይሸራረፉ እንዲከበሩ በተደረገው ሁሉን አቀፍ ርብርብ ወርቃማ
ስኬቶች ማስመዝገብ ችለናል።

የሀገራችን ጨቋኝ ስርአቶች በህዝቦች እልህ አስጨራሽ ትግል ግብአተ መሬታቸው


ቢፈፀምም ህጋዊና ሕገ-ወጥ መንገዶችን እያጣቀሱ የሚንቀሳቀሱ የአገራችን ኪራይ ሰብሳቢ
ሃይሎች የህዝቦችን ማንነትና ህልውና በአደባባይ በመካድና በማለባበስ በብሔሮች፣
በብሔረሰቦች፣ በሃይማኖቶች፣ ባህሎች ወዘተ መካከል መበላለጥን በመስበክ ያለፉት ፀረ-
ህዝብ ስርአቶች ይከተሏቸው የነበሩትን አድሎአዊና ኢ-ፍትሃዊ ፖሊሲዎች ለመመለስ

34
እየተረባረቡ ይገኛሉ። እነዚህ ኃይሎች በአገራችን ብዝሃነት እንዳይኖር ቢኖርም በመልክአ
ምድር ከፋፍሎ ማስተዳደር እንጂ ማንነትና የህዝብ ፈቃድን መሰረት አድርጎ መደራጀትን
አምርረው የሚኮንኑ ጥገኞች ናቸው።

ህገ መንግስቱ የግለሰብ መብቶች ከቡድን መብቶች ጋር የሚመጋገቡና አንዱ ሌላውን


የሚገነባ እንጂ የሚጣረሱ አለመሆናቸውን፣ የግለሰብ መብቶች መጣስ እዛው ሳለ የቡድን
መብቶች መጣስን የሚያስከትልና በተቃራኒውም የቡድን መብቶች መጣስ የግለሰብ
መብቶች ጥሰትን የሚያስከትል እንደሆነ በውል በመገንዘብ ሁለቱ መብቶች በእኩልነት
የሚከበሩበት መርህ አስቀምጧል። የግለሰብን መብት ሰጥቶ የቡድን መብት በተመሳሳይ
ሁኔታ ካልተከበረ ሁለቱ መብቶች የሚጣሱበት ሁኔታ መፈጠሩ አይቀርም። ለምሳሌ አንድ
ሰው የመማር መብቱ ቢከበርለትና ነገር ግን የቡድን መገለጫ የሆነው የቋንቋ እኩልነት
ካልተረጋገጠለት ያ ሰው በማያውቀውና በማይገባው ቋንቋ እንዲማር እየተገደደ በመሆኑ
ሁለቱም መብቶች ሳይከበሩ የሚቀሩበት ሁኔታ ይፈጠራል። በተመሳሳይ ሁኔታ አንድ ዜጋ
የእምነት ነፃነቱ ቢረጋገጥለትና ነገር ግን የሃይማኖት እኩልነት ካልተረጋገጠ እንዲሁም
ሃይማኖታዊ ስርዓታቸውን በሚፈልጉት ቋንቋ መፈፀም ካልቻሉ ሁለቱ መብቶች ሳይከበሩ
የሚቀሩበት አሊያም ተሸራርፈው የሚከበሩበት ሁኔታ መፈጠሩ አይቀሬ ይሆናል። ለዚህም
ነው የቡድንና የግልሰብ መብቶች ሳይነጣጠሉና ሳይበላለጡ በእኩልነት መከበር አለባቸው
የምንለው።

እነዚህ አፍራሽ ሃይሎችና ያለፈው ስርአት ናፋቂዎች ግን በግለሰብና በቡድን መብቶች


ዙሪያ ከዴሞክራሲያዊ ስርዓት መርሆዎች በእጅጉ ያፈነገጡ አመለካከቶችን ከማራመድ
ባለፈ በመብቶቹ መካከል መበላለጥና መቀዳደም እንዳለ አድርገው በማቅረብ ዜጎችን
ለማደናገር ይጥራሉ።

5.2.1 የብሔር ብሔረሰቦች መብት መከበርና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ፣

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩልነትና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ጥያቄ


ከ1960ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ አንስቶ ሲነሳ የነበረ ቢሆንም በየጊዜው የነበሩ ገዥ መደቦች
ለጥያቄው የሰጡት ምላሽ የተገላቢጦሽ በመሆኑ የሀገራችን አንድነት ተደጋጋሚ አደጋዎች
ሲጋረጡበት ኖሯል። ለበርካታ ጊዜያት ከቀጠሉ አንገብጋቢ ጥያቄዎች መካከል ግንባር
ቀደም በመሆን ሁሉንም የሀገራችን ህዝቦች የየራሳቸው አማራጭ እስከመፈለግ

35
ሲያደርሳቸውና ከየወቅቱ ገዥዎች ሲያፋልማቸው የነበረው ይህ የእኩልነት ጥያቄ እስከ
1983ዓ.ም ደረስ ትክክለኛ ምላሽ ሳያገኝ ቆይቷል። የደርግን ስርዓት ለመገርሰስም ከግንባር
ቀደም ምክንያቶቹ አንዱ ነበር የብሔር ጥያቄ።

የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት ከሌሎች ሕገ መንግስቶች ከሚለይበት መሰረታዊ ጉዳዮች


መካከል ለብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የሰጠው መብት ሲሆን ይህም “ማንኛውም
የኢትዮጵያ ብሔር፣ብሔረሰብ፣ ህዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን እስከ መገንጠል
ያለው መብቱ በማናቸውም መልኩ የተጠበቀ ነው” በማለት በግልፅ አስቀምጦታል። ይህ
መብት በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ጨቋኝና ተጨቋኝ እንደማይኖር ከማረጋገጡም በላይ
በዴሞክራሲያዊ ሁኔታ አብሮ ለመኖር የማያስችሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢፈጠሩ እንኳን
በሰላማዊ መንገድ ያለ ደም መፋሰስ መለያየት እንደሚሻል የሚደነግግ ነው። ለዚህም ነው
የብሔሮችና ብሔረሰቦች የእኩልነት ጥያቄ በማያሻማ መልኩ መመለስ የአዲሱ
ዴሞክራሲያዊ ስርዓታችን ቋሚ ምሶሰ ነው የምንለው።

ይሁን እንጂ የድሮ ስርዓት ናፋቂ ኃይሎችና ግለሰቦች “አንድ ሀገር፣ አንድ ቋንቋ፣ አንድ
ሃይማኖት” የሚል ያረጀ ያፈጀ ፀረ ህዝብ አስተሳሰብ በማቀንቀን ይህ መብት ሀገር
ይበታትናል በማለት ህዝቦች በረዥምና መራራ ትግላቸው የተጎናፀፉትን መብት
ሲያብጠለጥሉት ይታያሉ። የባለፉት 23 ዓመታት ተሞክሮአችን የሚያሳየው ግን እነዚህ
ሃይሎች እንዳራገቡት መበታተንን ሳይሆን አብሮነትና በመከባበር ላይ የተመሰረተ
ዴሞከራሲያዊ ስርዓት የተገነባባትና በከፍተኛ ፍጥነት ህዳሴዋን ለማረጋገጥ ወደ ፊት
እየገሰገሰች ያለች ሀገርን ነው። ሁሉም የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እጅ
ለእጅ ተያይዘው በፀረ ድህነት ትግሉ ላይ ባካሄዱት ያላሰለሰ ጥረትም እነሆ ሀገራችን
እጅግ ፈጣን ዕድገት ከሚያስመዘግቡ ጥቂት የዓለማችን ሀገራት አንዷ ሆናለች።
አንድነታችንም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረና የጋራ ራዕያችን ለማሳካት የምናደርጋቸው
እንቅስቃሴዎችም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበቱና ከአንድ ስኬት ወደቀጣዩ ከፍተኛ ስኬት
እየተሸጋገሩ ይገኛሉ።

36
5.2.2 የሃይማኖቶች እኩልነት፣ የእምነት ነፃነትና ሴኩላሪዝም ለህዳሴአችን፣

በሕገ መንግስቱ እውቅና ካገኙ መሰረታዊ መብቶች ውስጥ የሃይማኖት እኩልነትና


የእምነት ነጻነት ይገኝበታል፡፡ የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት መንግስትና ሃይማኖት
መለያየታቸውና መንግስት ከየትኛውም ሃይማኖት ነፃ በሆነና ለማንኛውም ሃይማኖት
ውግንና በሌላው አኳሃን መመስረት እንዳለበት በግልፅ ይደነግጋል። በዚህም ሃይማኖታዊ
ያልሆነ የመንግስት ስርዓት መገንባት እንዳለበት በማያሻማ መልኩ መደንገጉ ሕገ
መንግስቱ ሰፊ ህዝባዊ ተቀባይነት እንዲጎናፀፍ አስችሎታል። መንግስትና ሃይማኖት
ባይለያዩ ኖሮ መንግስት ሁሉንም ሃይማኖቶች በእኩልነት ሊያስተናግድ በፍጹም
አይችልም ነበርና ሃይማኖታዊ ያልሆነ (ሴኩላር) ስርዓተ መንግስት መመስረቱ ተገቢና
ትክክለኛ ውሳኔ ነበር።

የመንግስትና የሃይማኖት መለያየት እንደተጠበቀ ሆኖ የሃይማኖት እኩልነትና የእምነት


ነፃነትም ሕገ መንግስታዊ ዋስትና አግኝተዋል። በአዲሲቱ ኢትዮጵያ ማንኛውም ሰው
የመረጠውን ሃይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል፣ ሃይማኖቱንና እምነቱን
ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣ የመከተል፣
የመተግባር፣ የማስተማር ወይም የመግለፅ ሕገ መንግስታዊ ዋስትና አግኝቷል።
በተግባርም ሀገራችን የሃይማኖት እኩልነትና የእምነት ነፃነት የተረጋገጠባት ሀገር በመሆን
በዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ዘንድ የመቻቻልና የመከባበር ጥሩ ምሳሌ ለመሆን በቅታለች።

ይሁን እንጂ ይህ መብት በአግባቡ ተከብሮ እያለ ምንም ዓይነት ሃይማኖታዊ ይዘት
የሌላቸው ነገር ግን ፖለቲካዊ ግብ ያነገቡ የአክራሪነትና የፅንፈኝነት እንቅስቃሴዎች
ይታያሉ። በሃይማኖት ስም የሚካሄድ አክራሪነት የመጨረሻ ግቡ ሃይማኖታዊ መንግስት
ማቋቋም ነውና ኢ-ህገመንግስታዊ አስተሳሰብና ድርጊት ነው፡፡ አክራሪነት በሃገራችን
ለዘመናት የቆየውን በሃይማኖቶች መካከል ተቻችሎ የመኖር እሴት በመሸርሸር
በሃይማኖቶችና ተከታዮቹ መካከል ግጭትና አለመተማመን የመፍጠር ስልትን የሚከተል
የአንድነታችን ፀርም ጭምር ነው፡፡

እነዚህ ሃይሎች በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት ይህን ፀረ ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴ


ለመመከት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በሃይማኖት ላይ ጣልቃ እንደገባ በማስመሰል
ያለመታከት መንግስትን ሲወነጅሉ ይታያሉ፡፡ መንግስት የህዝብን ሰላምና ፀጥታ

37
የማስከበር ህገ መንግስታዊ ኃላፊነቱ መወጣት ይችል ዘንድ ፀረ-አክራሪነትና ፅንፈኝነት
ትግሉ ማጠናከርና አክራሪነትና ፅንፈኝነትን መመከት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ገባ
የሚያስብል ምንም ዓይነት ምክንያታዊ ጥያቄ የሚያስነሳ ባለመሆኑ በዚህ ረገድ የሚነሳ
ቅሬታም ተቀባይነት የሌለው ተራ ማደናገሪያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው።

5.2.3 የፆታ እኩልነትና የተዛቡ ግንኙነቶችን ማስተካከል አስፈላጊነት፣

የሀገራችን ሶሲዮ-ኢኮኖሚክ ታሪክ በወንዶች የበላይነት የተመሰረተ ሆኖ ለበርካታ ዘመናት


የፆታ እኩልነት የሚባል ነገር የማይታሰብበት ነበር። በመሆኑም ሴቶች ከወንዶች ጋር
እኩል ንብረት የማፍራት፣ የመጠቀም፣ የማስተላለፍ እንዲሁም በማሕበራዊና ፖሊቲካዊ
ጉዳዮች እኩል የመወሰን መብት አልነበራቸውም። እንዲያውም የሀገራችን ሴቶች እንደ
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከሚደርስባቸው ዓፈናና ጭቆና በተጨማሪ ሴት በመሆናቸው
ብቻ ሌላ የመከራ ፅዋ ይጎነጩ ስለነበር ጭቆናው በእነሱ ላይ ድርብ ነበር።

ለዚህም ነበር የዓፈናና የጭቆና ስርዓቱ ለመገርሰስ በተካሄደው መራራ ትግል ሴቶች
ከወንዶች ጋር እኩል የተዋደቁት። በከፈሉት ክቡር መስዋእትነትም የፆታ እኩልነት
ተረጋግጧል። የኢፌዴሪ ሕገ መንግስትም ሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል መሆናቸውንና
በመካከላቸውም ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግባቸው እኩል የሕግ ጥበቃ
እንደሚደረግላቸው በግልፅ በመደንገግ የፆታንም ሆነ ማንኛውንም ዓይነት መበላለጥ ሕገ
ወጥ አድርጎታል። ሕገ መንግስታችን ሴቶች ከወንዶች ጋር እኩል መሆናቸውን ከመደንገጉ
በተጨማሪ ሴቶች በበታችነትና በልዩነት በመታየታቸው የደረሰባቸውን የታሪክ ቅሪት
ከግምት ውስጥ በማስገባት እንዲታረምላቸው ተጨማሪ የድጋፍ መብት ተጠቃሚ መሆን
እንደሚገባቸው ያስቀምጣል።

የፆታ እኩልነት መከበር ከሚያስፈልግበት ምክንያቶች ውስጥ ከሀገራችን ህዝብ ግማሽ


ቁጥሩን የሚይዙት ሴቶች ያገለለና ለተሳትፎአቸው ተገቢውን ዕውቅና ያልሰጠ የልማት፣
የሰላም እና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ስራ በአንድ በኩል ግማሽ የልማት ኃይል
ያመከነ በመሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ የግማሽ ኃይሉ ይሁንታ ያልታከለበት በመሆኑ
የሚፈለገው ውጤት ማምጣት የማይቻል በመሆኑ ነው። ስለሆነም የሴቶችን የእኩልነት
መብት ማክበርና ማስከበር ለሴቶች የሚሰጥ ችሮታ ሳይሆን ተፈጥሯዊና ዴሞክራሲያዊ
መብታቸው ሲሆን በሀገራችን እድገትና ብልፅግና ደግሞ ተኪ የሌለውን ወሳኝ ሃይል

38
የማሳተፍ ጉዳይ ነው፡፡ በተጨባጭ አሁን እየተመዘገበ ያለው ፈጣን፣ ቀጣይነት ያለውና
ፍትሐዊ ዕድገትም የሴቶች ሁሉን አቀፍ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጣችን ያገኘነው
ስኬት ነው። በመሆኑም የሴቶች እኩልነት የማረጋገጥ ጉዳይ የዴሞክራሲ መርህ ስለሆነ
ብቻ ሳይሆን ሀገራችን የተያያዘችው የህዳሴ ጉዞ እውን ለማድረግ አማራጭ የሌለው አጀንዳ
በመሆኑ እየተጠናከረና እየጎለበተ የሚሄድ ነው።

5.2.4 የዴሞክራሲ ባህልና ተቋማት ግንባታ ለህዳሴአችን፣

በሀገራችን ሁኔታ ዴሞክራሲ የተሻለ የአስተዳደር ዘይቤ በመሆኑ መርጠን የምንከተለው


ብቻ ሳይሆን በግድ መተግበር ያለብን የህልውና ጥያቄ የመመለስና ያለመመለስ ጉዳይ
ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ የየራሳቸው የአኗኗር ዘይቤ፣ ታሪክ፣ ሃይማኖትና እምነት፣ ቋንቋ፣
ባህልና ወግ ያላቸው በርካታ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የሚኖሩባት የብዙሃን ሀገር
እንደመሆኗ መጠን ብዙሃነታችንን በአግባቡ በማስተናገድ አንድነታችን ጠብቀን ለመቀጠል
የዴሞክራሲ ስርዓት የግድ አስፋላጊ የሆነ የህልውናችን መሰረት ነው።

ዴሞክራሲ ለሀገራችን የህልውና ጉዳይ እንጂ የአማራጭ ጥያቄ አይደለም የምንለው


ሀገራችን የበርካታ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መኖሪያ በመሆኗ ብቻ ሳይሆን
የእኩልነት ጥያቄ በተለይ ደግሞ የብሔር ብሔረሰቦች፣ የሃይማኖት፣ የፆታ እና መሰል
እኩልነት ጥያቄዎች ለዘመናት ተገቢ የሆነ ምላሽ ባለማግኘታቸው ሀገራችን በመበታተን
አፋፍ ላይ አድርሷት እንደነበር በተጨባጭ ያለፍነው የቅርብ ጊዜ ትውስታችን በመሆኑ
ጭምር ነው። ለዚህም ነው የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ስራ የሞት ሽረት ጉዳይ ነው
የሚል ፅኑ እምነት ይዘን በስርዓተ ትምህርት ከሚሰጠው የዴሞክራሲ ስርፀትና ግንዛቤ
በተጨማሪ የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ የማቋቋምና የማጠናከር ስራውን በጥብቅ
ዲሲፕልን በመተግበር ላይ የምንገኘው።

የኢፌዴሪ መንግስት ይህን ፅኑ እምነት በአግባቡ መተግበር እንዲችልና የዴሞክራሲያዊ


ስርዓት ግንባታውን በተሳካ ሁኔታ ለማስኬድ በየደረጃው ያሉ የህዝብ ምክር ቤቶች፣
የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሙያና የብዙሃን ማሕበራት፣ ሚዲያ፣ ገለልተኛ የሆነ የዳኝነት
ስርዓት፣ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ እንዲሁም የስነ-ምግባርና ፀረ
ሙስና ኮሚሽን በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ስራው ላይ ያላቸው ገንቢ ሚና በውል

39
በመገንዘብ ተቋማቱ የሚጠበቅባቸው አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ሌት ተቀን እየተጋ
ይገኛል።

ዴሞክራሲያዊዊ ስርዓቱን በአስተማማኝ መሰረት ላይ ለመገንባት በየደረጃው ያሉ የህዝብ


ምክር ቤቶችንና የህዝቡን የውክልናና ቀጥተኛ ተሳትፎ በማጠናከር ረገድ አበረታች
ውጤቶች በማስመዝገብ ላይ እንገኛለን። እነዚህ ምክር ቤቶች ህዝቡ በቀጥታም ሆነ
በተዘዋዋሪ መንገድ የሚሳተፍባቸውና የህዝብ ድምፅ የሚደመጥባቸው ተቋማት
በመሆናቸው በሀገር ግንባታ ሂደት ላይ ያላቸው ሚና ተኪ የለውም። ለዚህም ነው ምክር
ቤቶቹ የህዝብ ሉአላዊነት መገለጫ እንደሆኑ በሕገ መንግስቱ በግልፅ የተቀመጠው።

የሀገራችንን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በዘላቂነት ማጠናከር ይቻል ዘንድ የመድብለ ፓርቲ


ስርዓት መኖር ከፍተኛ ሚና አለው። በመሆኑም የኢፌዴሪ መንግስት የሀገራችንን
የፖለቲካ ፓርቲዎች ለማጠናከር የተለያዩ ስራዎች በማከናወን ላይ ይገኛል። የሀገራችን
ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሀገሪቱ ህዳሴ ለማረጋገጥ የሚያስችል የፖሊሲ አማራጭ
ቢኖራቸውም ባይኖራቸውም ከበስተጀርባቸው ያለው የተወሰነ የሕብረተሰብ ክፍል ፍላጎት
ዕውቅና ከመስጠት በተጨማሪ ህዝቡ በመረጃ የተመሰረተ ውሳኔ መስጠት እንዲችል
የፓርቲዎቹ መጠናከር አስፋላጊ ያደርገዋል።

በዚህ ረገድ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ እየተጫወተ ያለው ግንባር ቀደም ሚና ታሪካዊ ነው
ማለት ይቻላል። ኢህአዴግ የሀገሪቱ ሕገ መንግስትንና ሌሎች ሕጎች አክብረው በሰላማዊ
መንገድ የተቃውሞ ፕሮግራሞቻቸውን የሚያራምዱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በህዝብ
ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ቢኖራቸውም ባይኖራቸውም አብሮ ለመስራት በገባው
ቃል መሰረት ከ2003ዓ.ም ጀምሮ ሀገር አቀፍ የጋራ ምክር ቤት አቋቁሞ እየሰራ ሲሆን
በአሁን ወቅትም ከስምንት ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ጋር አብሮ እየሰራ ይገኛል። ይህም
ድርጅቱ ለመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላለው ቁርጠኝነት ግልፅ
ማረጋገጫ ተደርጎ የሚወሰድ ነው።

የሚዲያ ነፃነትን በማረጋገጥ፣ ገለልተኛ የሆነ የዳኝነት ስርዓት በመገንባት እና ሌሎች


የዴሞክራሲ ተቋማት በማጠናከር ረገድም ሀገራችን አመርቂ ስኬቶች በማስመዝገብ ላይ
ትገኛለች። ከሁሉም በላይ ደግሞ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታውን ቀጣይነት ለማረጋገጥ
በስርዓተ ትምህርት ደረጃ ተቀርፆ በሀሉም የትምህርት ደረጃዎች በስነ ዜጋና ስነ ምግባር

40
ትምህርቶች እየተሰጠ ያለው የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ስርፀት በማጠናከር በዴሞክራሲያዊ
ባህል የዳበረ ትውልድ የመገንባት ስራችን ለዴሞክራሲያችን ማበብ ወሳኝ ሚና እየተወጣ
ነው፡፡

6. በህዳሴ ጉዞአችን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

እስካሁን በቀረቡ ርእሰ ጉዳዮች ላይ የሀገራችን ህዳሴ ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስኬታማ


ተግባራት እና በየዘርፍ ያሉ ማነቆዎችና ተግዳሮቶች በአጭር በጭሩ ለማየት ሞክረናል።
የስኬቶቻችን ምንጭም ከሀገራችን ህዝቦች የልማት፣ የሰላም እና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች
የሚመነጩ ሀገር በቀል ፖሊሲዎቻችን እና ህዝብና መንግስት ለፖሊሲዎቻችን ተፈፃሚነት
ያደረጉት ያለሰለሰ ርብርብ እንደሆነ ለማብራራት ተሞክሯል። ሀገራችን ፈጣን፣ ቀጣይነት
ያለውና ፍትሃዊ የህዝቦች ተጠቃሚነት የተረጋገጠበት ዕድገት በማስመዝገብ በዓለም
አቀፍ ደረጃ እጅግ ፈጣን ዕድገት ከሚያስመዘግቡ ጥቂት ሀገራት ተርታ ማሰለፍ
መቻላችንም አይተናል።

በየዘርፉ ያስመዘገብናቸው ስኬቶቻችን በቀጣይነት በማጠናከር የሀገራችን ህዳሴ ለማፋጠን


ትኩረት የሚሹ የህዳሴአችን ተግዳሮቶች ላይ አነጣጥረን መረባረብ ይኖርብናል።
የሀገራችን ዕድገት ቀጣይነት ማረጋገጥና ከአንድ የድል ምዕራፍ ወደ ቀጣዩ ከፍተኛ የድል
ምዕራፍ ማሸጋገር የምንችለውም በየዘርፉና በየምዕራፉ የሚያጋጥሙን ተግዳሮቶች
በቀጣይነት እየለየን መፍታት ስንችል በመሆኑ በዚህ ክፍል በህዳሴ ጉዟችን ትኩረት
የሚሹ ዋና ዋና ጉዳዮች ቀርበዋል።

6.1 የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ መሰረት በመናድ ህዳሴአችን ማስቀጠል

የሀገራችን ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ የህዳሴ ጉዞ በማፋጠን የህዝቦችን ተጠቃሚነት


በዘላቂነት ማረጋገጥ የምንችለው የዕድገታችን ማነቆ የሆነው የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል
ኢኮኖሚ ከመሰረቱ በመናድ በምትኩ ልማታዊ ፖለቲካል ኢኮኖሚ መገንባት ስንችል
ነው። የኪራይ ሰብሳቢነት የበላይነት በሰፈነበት ሁኔታ የሀገራችን ቀጣይነት ያለው ዕድገት
ማረጋገጥ እንደማይቻል ተሰምሮበት ያደረ ጉዳይ ነው። የኪራይ ሰብሳቢነት የህዳሴ
ጉዟችን ዋነኛ እንቅፋት መሆኑ ታምኖበት ባለፉት አመታት በተደረገው ጥረት አበረታች

41
ውጤቶች ታይተዋል፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር
በሚፈለገው ደረጃ በልማታዊ አስተሳሰብ አልተተካም፡፡

ስለሆነም የሀገራችን ቀጣይ ዕድገት በማረጋገጥ ህዳሴእችን እውን ይሆን ዘንድ የኪራይ
ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ መሰረት መናድና ልማታዊነትን በማጠናከር የሀገራችን
ብሩህ ተስፋ የማስቀጠል ጉዳይ በአማራጭነት የሚቀርብ ሳይሆን የህልውና ጥያቄ በመሆኑ
ከፍተኛ የሆነ ትግልና ርብርብ ማድረግ ይኖርብናል። የትግሉን ግለትና አድማስ በማስፋት
ልማታዊ አስተሳሰብና ተግባር ማጠናከር የምንችለው ደግሞ መላውን ህዝብ ባሳተፈ መልኩ
በቁርጠኝነት መታገል ሲቻል ነው። ኪራይ ሰብሳቢነት የህዳሴ ጉዟችን እንቅፋት መሆኑን
የጋራ መግባባት ፈጥሮ የልማታዊ አስተሳሰብና ተግባር የበላይነቱን እንዲይዝ አበክረን
መስራት ይኖርብናል፡፡ በሌላ ጽኁፍ በዝርዝር የቀረበውን የኪራይ ሰብሳቢነት መሸሸጊያ
ዋሻ የሆኑትን ትምክህትና ጠባብነት የመታገል ጉዳይም ከዚሁ ጋር ተያይዞ መታየት
ይኖርበታል፡፡

6.2 መልካም አስተዳደር ማረጋገጥ የህልውና ጉዳይ ነው

መልካም አስተዳደር የማረጋገጥ ጉዳይ በአጠቃላይ ሲታይ ከፖለቲካል ኢኮኖሚ ጋር


ተያይዞ የሚታይ በመሆኑ ቀደም ሲል ካነሳነው የኪራይ ሰብሳቢነት ትግል ተነጥሎ
አይታይም፡፡ ይሁን እንጅ አሁን ካለው ሁኔታ አኳያ ሲታይ ጉዳዩን ለብቻው ትኩረት
ሰጥቶ ማየት ያስፈልጋል፡፡ በሀገራችን እየተመዘገበ ያለው ፈጣን፣ ቀጣይነት ያለውና
ፍትሐዊ ዕድገት በዘላቂነት በማፋጠን የሀገራችን ህዳሴ እውን ይሆን ዘንድ የህዝባችን
እርካታ በቀጣይነት ማረጋገጥ ይኖርብናል። የህዝባችን እርካታ በቀጣይነት ለማረጋገጥ
ደግሞ የሕግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራዎቻችን በቀጣይነት ማጠናከር ፣ ህዝቡ በስፋት
በማሳተፍ በመሰረታዊ አቅጣጫዎቻችን እና ውሳኔዎቻችን ላይ የጋራ መግባባት
የሚፈጥርበት ሁኔታ ማጠናከር፣ የግልፅነትና የተጠያቂነት አሰራሮቻችን በማጠናከር
በየደረጃው ከህዝባችን ጋር ቀጣይነት ያለው መተማመን መፍጠር፣ ህዝቡ ከእያንዳንዷ
የልማት ውጤት ፍትሐዊ ተጠቃሚነቱን እንዲያረጋግጥ በቀጣይነት መስራት እንዲሁም
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ አኋሃን መፈፀም ይኖርብናል ማለት
ነው።

42
አሁን ባለው ሁኔታ ግን በየጊዜው የማስፈፀም አቅማችን እየገነባን እና በርካታ ውጤታማ
ስራዎች እያከናውንን ብንሆንም የህዝባችን እርካታ በማረጋገጥ ረገድ በርካታ ችግሮች
አሉብን። እንዲያው ከህዝቡ በየወቅቱ ከሚነሱ መሰረታዊ ጥያቄዎች መካከል የመልካም
አስተዳደር ችግር እየሆነ መጥቷል። ችግሮቹም ከተሳትፎ፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት ማነስ
እንዲሁም ከቀልጣፋነትና ውጤታማነት ጋር የተያያዙ ናቸው ማለት ይቻላል።

ስለሆነም ህዝባችን በዕቅዶቻችን እና አፈፃፀማቸው ላይ በስፋት እንዲሳተፍ በማድረግ


የዕቅዶቻችን ባለቤት እና ተቆጣጠሪ የማድረግ ስራችን በቀጣይነት አጠናክረን መቀጠል
ይኖርብናል። ህዝብ በስፋት የተሳተፈባቸው ስራዎች ከፍተኛ የሆነ የመፈፀም ዕድል
ያላቸው ከመሆኑም በላይ በየደረጃው የሚገኙ ጥንካሬዎችና ድክመቶች እራሱ ህዝቡ
እየገመገመ እና አስፈላጊ የሚባሉ ማስተካከያዎች እያደረገ የሚሄድ በመሆኑ በጉድለቶቹ
ከማማረር ይልቅ የጉድለቶቹ መንስኤዎችን ነቅሶ በማውጣት የመፍትሔው አካል
የሚሆንበት ሁኔታ ይፈጠራል። በመሆኑም በዚህ ረገድ እየተነሱ ያሉ የህዝብ ቅሬታዎች
ህዝቡን በስፋት በማሳተፍ ለመፍታት በከፍተኛ ቁርጠኝነት መረባረብ ይኖርብናል።

የህዝቡ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ ለማረጋገጥ በምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉም


አሰራሮቻችን ለህዝቡ ግልፅ በማድረግ በአፈፃፀም ሂደት የሚያጋጥሙ ጥንካሬዎችና
ድክመቶች ተከትሎ የሚመጣው ተጠያቂነትም ምን እንደሆነ ከህዝቡ ጋር መግባባት
መፍጠር ይኖርብናል። ህዝቡ በየደረጃው በሚኖሩን ዕቅዶች እና አፈፃፀሞቻችው ላይ ግልፅ
የሆነ መረጃ እንዲኖረው በማድረግ በአንድ በኩል ለተፈፀፃሚነታቸው በባለቤትነት መንፈስ
እንዲረባረብ በሌላ በኩል ደግሞ በየደረጃው ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙን እንኳን ህዝቡ
ሁኔታው እንዴት እንደተፈጠረ በቂ መረጃ አለውና ጠያቂ ሳይሆን ወደ መፍትሔ
አፈላላጊነት ማሸጋገር እንችላለን። በዚህም በየደረጃው ከህዝባችን የሚነሱ ቅሬታዎች
በመፍታት ህዝቡ በልማት ስራው ላይ እንዲያተኩር በማድረግ የሀገራችን ህዳሴ ማቀላጠፍ
የሚያስችለን የተመቻቸ ሁኔታ መፍጠር ያስችለናል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ አሁን ለህዝቡ እየሰጠን ያለነው አገልግሎት በቀጣይነት በማሻሻል
ቀልጣፋና ውጤታማ ማድረግ ይኖርብናል። ህዝቡ እየተማረረብን ካሉ የመልካም
አስተዳደር ጉድለቶች መካከል አብዛኞቹ በፍጥነት ትክክለኛ ምላሽ ካለመስጠት
የሚመነጩ ናቸው ማለት ይቻላል። ለህዝባችን የምንሰጠው አገልግሎት ቀልጣፋና

43
ውጤታማ ማድረግ ቻልን ማለት በአንድ በኩል የህዝባችን እርካታ አረጋገጥን ማለት ሲሆን
በሌላ በኩል ደግሞ ህዝቡ አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያጠፋው ጊዜ ወደ ልማት ስራው
በማዞር በተያያዝነው የህዳሴ ጉዞ ላይ የሚያደርገው ተሳትፎ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ
ያስችለናል ማለት ነው።

መልካም አስተዳደር የማረጋገጥ ስራችን የአማራጭ ጉዳይ ሳይሆን የህልውናችን መሰረታዊ


ጥያቄ ነው። በመሆኑም አማራጫችን መልካም አስተዳደር በማስፈን በኩል ያሉብን
ችግሮች በቀጣይነት እየፈተሹ ከህዝቡ ጋር በመመካከር ችግሮቹ እየፈቱና የእርምት
እርምጃ እየወሰዱ በመሄድ ልማታዊ አስተሳሰብ በመገንባት በልማታችን እና ቀጣይ
የሀገራችን ዕድገት ላይ ብሔራዊ መግባባት አጠናክሮ መቀጠል ብቻ መሆኑን በውል
መገንዘብ ያስፈልጋል። ስለሆነም መልካም አስተዳደር የማስፈን ርብርባችን ጊዜ የማይሰጥ
እጅግ አንገብጋቢ የህልውና ጥያቄ መሆኑ በግልፅ ተገንዝብን አፈፃፀሙም በጥብቅ
ዲሲፕሊን ልንከውነው የሚገባ ወሳኝ አጀንዳ እንደሆነ ከጋራ መግባባት ላይ መድረስ
አለብን።

6.3 አክራሪነትና ሽብርተኝነት

አክራሪነትና ሽብርተኝነትም ሰላማችንንና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደታችንን


በእጅጉ እየተፈታተኑነ ያሉ ሳንካዎች ናቸው። የአክራሪዎችና አሸባሪዎች መሰረታዊ ዓላማ
ሀገራችን የተያየዘችውን ፈጣንና ፍትሐዊ ዕድገት በማደናቀፍ ሕገ መንግሰቱንና ሕገ
መንግስታዊ ስርዓቱን በሕገ ወጥ መንገድ በመናድ የሀገራችን የህዳሴ ጉዞ መቀልበስ ነው።
የሃይማኖት እኩልነትና የእምነት ነፃነት የተሟላ ሕገ መንግስታዊ ዋስትና ባገኙባት
አዲሲቱ ኢትዮጵያ ለሃይማኖት አክራሪነት መነሻ የሚሆን ምንም ዓይነት ተጨባጭ መነሻ
ባይኖርም በሃይማኖት ሽፋን ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳዎቻቸው ለመፈፀምና ለማስፈፀም
የሚፈልጉ ፀረ-ሰላም ሃይሎች ከልማት አጀንዳችን ለማስወጣት የማይፈነቅሉት ድንጋይ
የለም። የተለያዩ ሰበቦችና የማደናገሪያ አጀንዳዎች እየቀረፁ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ
ጣልቃ እየገባ ነው፣ የአንዱ ሃይማኖት መብት አልተከበረም፣ የእምነት ነፃነት አልተከበረም
ወዘተ በማለት የሚንቀሳቀሱ የውጭና የውስጥ ሃይሎች የሀገራችን ሰላም ለማወክ ሲጥሩ
ይታያሉ።

44
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ስጋት የደቀነው ሽብርተኝነትም በተመሳሳይ ሁኔታ የሀራችን
የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጉዞአችን ተጨባጭ አደጋ እየሆነ ይገኛል።
በመሰረቱ ሽብርተኝነት ማለት የአንድን ቡድን የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም የርእዮተ
አለም ዓላማን በሌሎች ላይ በሃይል ለመጫን በመንግስትና በህዝብ ላይ እንዲሁም
በመንግስትና በህዝብ ንብረት ላይ ከፍተኛ የሆነ አደጋ በመፍጠር ወይም የአደጋ ስጋቶችን
በመደቀን በዜጎች ላይ ሽብርና አለመረጋጋት የመፍጠር ዓላማ ያለው ተግባር ነው። እናም
በተለይ ሀገራችን ከምትገኝበት የምስራቅ አፍሪካ በተለይ ደግሞ ከአፍሪካ ቀንድ አካባቢ
የሚነሱ የሽብር አደጋዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሀገራችን ሰላምና መረጋጋት በማወክ
ረገድ ከፍተኛ ሚና አላቸው።

ሽብርተኝነት የሰላም፣ የልማት፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶቻችንን በተረጋጋ


ሁኔታ እንዳናከናውን ከፍተኛ ስጋት በመፍጠር ወይም እንደሚፈጠር በማስመሰል በሽብር
እንዲንዋጥና ፈርተንና ተጨናንቀን እጅና እግራችንን አጣጥፈን እንዲንቀመጥ አልያም
ተገድደን የሽብርተኞች ዓላማና ግብ ማስፈፀሚያ እንዲሆን የሚያስገድድ አፍራሽ ተግባር
ነው። ሽብርተኝነት ሀገራችን የጀመረችው የህዳሴ ጉዞ በማጨናገፍ የድህነትና የኋላቀርነት
ዕድሜ የሚያራዝም በመሆኑ መላው ህዝባችን እስከ አሁን እያደረገ እንዳለው አምርሮ
ሊታገለው የሚገባ እኩይ አስተሳሰብና ተግባር ነው።

ስለሆነም በአክራሪነትና በአሸባሪነት ላይ የጀመርነው ትግልም የህዳሴ ጉዞአችን ለማረጋገጥ


የምናደርገው ርብርብ ሌላኛው ገፅታ ነውና ላፍታም ቢሆን ፋታ የማይሰጥ ትግል ሆኖ
ይቀጥላል። የጸረ ሰላም ሃይሉ ትኩረት አድርጎ ከሚሰራባቸው ተቋማት የትምህርት
ተቋማት በተለይ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ስለሆነ በእነዚህ ተቋማት የሚደረገው
የፀረ አክራሪነት ትግል ቀጣይ ስራ የሚጠይቅ ይሆናል።

6.4 የኒዮሊበራልዝም ዘመቻ የመመከት አስፈላጊነት

በአሁኑ የግሎባላይዜሽን ዘመን ዓለም በአዲሱ የመረጃ ትስስር መረብ አማካኝነኝት


በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማሕበራዊ ዘርፎች ይበልጥ እየተሳሰረች ሲሆን በአንድ
የዓለማችን ጫፍ የተከሰተን ጉዳይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በሌላኛው የዓለም
ጫፍ በሚገኙ ሀገራትና ህዝቦች ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛል። ትስስሩ አወንታዊም
አሉታዊም ገፅታ ያለው ሲሆን በዚህ ንኡስ ርእስ ላይ የምናየው ግን የኒዮሊበራል ርእየተ

45
ዓለም እና የርእዮ ዓለሙ አክራሪዎች በህዳሴ ጉዞአችን ላይ ሊፈጥሩት የሚችሉት አፍራሽ
ሚናን ይሆናል።

እንደሚታወቀው ከገበያ አክራሪው የኒዮ-ሊበራል ኃይል ጋር ባሉን መሰረታዊ የርእዮተ-


ዓለም ልዩነቶች ምክንያት የተለያዩ ሰበቦች እያፈላለገ አሊያም የፈጠራ ወሬዎችን
እየተጠቀመ በተደጋጋሚ ሲወነጅለን ቆይቷል። የተለያዩ አጋጣሚዎች በመጠቀምም
የርእዮቱ ተሸካሚዎች እንድንሆን ያልሞከረው የጫና ዓይነትም ሆነ ያልፈነቀለው ድንጋይ
የለም ማለት ይቻላል። የፖሊሲ ነፃነታችን ጠብቀን ከራሳችን ተጨባጭ ሁኔታ የመነጩና
የራሳችን የዕድገት ጥያቄዎችን በአግባቡ መመለስ የሚያስችሉን ሀገር በቀል የፖሊሲ
አማራጮቻችን ተከትለን ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት ማረጋገጥ ስንችል ደግሞ ዕድገቱ
ተቀብሮ የማይቀር የአደባባይ ምስጢር እየሆነ በመምጣቱ ክርክሩ ከኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች
ይልቅ ዕድገቱ በዴሞክራሲያዊ ሁኔታ የመጣ አይደለም፣ በሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች
አከባበር ላይ ችግሮች አሉባት ወዘተ እያለ ያስመዘገብነው ዕድገት በማጥላላት ላይ
ከተጠመደ ሰንበትበት ብኋል።

በተለይ ደግሞ ምርጫ በመጣ ቁጥር የሚያቀነባብራቸው ውንጀላዎችና የፈጠራ ወሬዎች


በመጠንም ሆነ በዓይነት በመጨመር የሀገራችን ገፅታ ለማጠልሸት የሚያደርገው
የተቀነባበረ ዘመቻ ፈታኝ መሆኑ አይቀርም። በተቀነባበረ መልኩ የሚከናወን የማጥላላት
ዘመቻም እንደ የአመሜሪካ ድምፅ ሬድዮ (VOA) የመሳሰሉት የርእዮቱ ባለቤቶችና ደጋፊ
የሆኑ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋሞች፣ እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች እና አሜንስቲ
ኢንተርናሽናል የመሳሰሉ የሰብአዊ መብት ተማጓች በሚል ስም የተደራጁ የኒዮልበራል
ሃይል አክራሪ ድርጅቶች፣ የሀገር ውስጥ አፍራሽ ኃይሎች እና የግል የሕትመት ሚዲያው
በቅብብሎሽ ነው። ይህ የማጥላላት ዘመቻ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ወደ ሀገራችን
እንዳይገባ ጫና በመፍጠር፣ የሀገራችን ፈጣን ዕድገት በማብጠልጠል በጎ ገፅታችን
በማበላሸት ወዘተ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ሚና መጫወቱ አይቀርም። ስለሆነም የውስጥ
ስራችን በማጠናከር ከድህነትና ከኋላቀርነት የምንላቀቅበት ጊዜ የማሳጠር ርብርባችን
በማጠናከር እዛው ሳለ ደግሞ የሀገራችን ትክክለኛ ገፅታ በቀጣይነት በመግለፅና አመራጭ
አስተሳሰብ ካላቸው ሀገራት ጋር ያለን ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር መመከተ
ይኖርብናል።

46

You might also like