You are on page 1of 65

የሕብረ ብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ምንነት፣

ባህሪያት እና የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ

በኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ለ 17 ኛው

የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች


ቀን ለአሠልጣኞች ሥልጠና የተዘጋጀ

መስከረም/2015
አዲስ አበባ

ii | P a g e
ማውጫ ገፅ
I. ማውጫ .................................................................................................................................................................... i

II. መግቢያ......................................................................................................................................................................... 1

II. የሥልጠናው ዓላማ፣.......................................................................................................................................................... 1

III. የሥልጠናው ዝርዝር ዓላማዎች፣.................................................................................................................................... 2

III. ክፍል አንድ፡- የፌዴራሊዝም ፅንሰሀሳብ እና የፌዴራል ፖለቲካ ሥርዓቶች፣.........................................................3

1.1 መግቢያ...............................................................................................................................................3

1.2. የፌዴራሊዝም ፅንሰሀሳብ፣....................................................................................................................3

1.3. የፌዴራል ፖለቲካ ሥርዓቶች (Federal Political Systems)፣.....................................................................7

1.3.1 ኮንፌዴሬሽን (የተገደበ ኮንፌዴራል መንግሥት እና ጠንካራ የኮንፌዴሬሽን አባል መንግሥታት)...............7

1.3.2 ፌዴሬሽን (ጠንካራ የፌዴራል መንግሥት እና ጠንካራ የፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት)፣............................8

1.3.3 ፌደራሲ (Federacy)፣.....................................................................................................................9

1.3.4 አሶሼትድ ስቴትስ/ Associated states/፣..........................................................................................9

1.3.5 የፌዴሬሽን ቅርጽ ያለው የፌዴራል ሥርዓት፣.....................................................................................9

IV. 1.4. ፌዴሬሽኖች የሚያመሳስሏቸው የጋራ ባህሪያት እና የሚያለያዩአቸው ጉዳዮች፣.....................................10

1.5. የፌዴሬሽኖች የጋራ ባህሪያት፣..............................................................................................................11

1.5.1. ከሁለት ያላነሱ መንግሥታት መኖር፣..............................................................................................11

1.5.2. በአንድ ሰነድ ተጠቃሎ የሚገኝ (በተለምዶ የተጻፈ)፣ የበላይ የሆነ እና በቀላሉ የማይሻሻል ሕገ መንግሥት
መኖር፣.................................................................................................................................................12

1.5.3. ሕገመንግሥታዊ የሆነ የሥልጣን ክፍፍል፣........................................................................................12

1.5.4. ሁለት ም/ቤቶች መኖር፣..............................................................................................................15

1.5.5. በፌዴሬሽኑ ውስጥ አለመግባባቶችን የሚፈታ ተቋም መኖር፣............................................................16

1.6. ፌዴሬሽኖችን እርስ በእርስ የሚለያያቸው ጉዳዮች፣................................................................................17

1.7. የፌዴሬሽኖች አፈጣጠር ሂደት፣...........................................................................................................22

V. 1.8 ማጠቃለያ፣.......................................................................................................................................................... 23

ክፍል ሁለት፣ ሕብረብሔራዊ ፌዴሬሽኖች፣...................................................................................................................... 25

VI. -.............................................................................................................................................................................. 25

2.1. መግቢያ፣...........................................................................................................................................25

i|Page
2.2.ሕብረብሔራዊነት እና ሕብረብሔራዊ ፌዴሬሽን፣.................................................................................................... 25

2.3. የሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት መርሆዎች፣..................................................................................................... 27

2.4 የኢትዮጵያዊያን ህብረ ብሄራዊነትና የአንድነት መሰረት ማህበረ ባህላዊ ውቅሮች..................................................28

2.5. ከሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ሶስት ዋና ዋና የሆኑ አከራካሪ ጉዳዮች፣...........................29

2.5.1 የመንግሥት መፍረስ (state disintegration)፣.....................................................................................29

2.5.2 ፖለቲካዊ ዋልታ ረገጥነት (political polarization)፣.............................................................................31

2.5.3 የውስጥ ህዳጣን ቡድኖች (internal-minorties) መብት አለመከበር፣.......................................................32

2.6. ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት መድኃኒት ወይስ እርግማን?.............................................................................. 34

2.7. ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት የሚከተሉ ሃገራት ተሞክሮዎች...........................................................................37

2.7.1. የተመረጡ ህብረብሄራዊ የሆኑ ሀገራት ተሞክሮዎች.............................................................................37

2.7.2. የሲዊዝ ኮንፌደሬሽን (1848 እ.አ.አ)..................................................................................................37

2.7.3. የህንድ ዩኔን (1950..........................................................................................................................40

2.8.ህብረ በሄራዊ በሆኑ ሀገራት ብዝኃነትን የሚገልጹበት አግባቦች፣.................................................................42

2.9. የህብረ ብሄራዊ ፌደራላዊ ስርዓት የተገበሩ ሀገራት ስኬት እና ልምድ..........................................................45

2.10. ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት እና የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ፣...........................................................46

2.10.1. የተገኙ መልካም ነገሮች፣............................................................................................................47

2.10.2. ያጋጠሙ ተግዳሮቶች፣...............................................................................................................48

2.10.3. በቀጣይ ቢሠራባቸው ተብለው የቀረቡ ምክረ ሃሳቦች፣....................................................................53

2.11 ማጠቃለያ፣................................................................................................................................................................. 57

ክፍል ሶስት፣ ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት እና የሰላም ግንባታ፣................................................................................ 58

3.1. መግቢያ፣...........................................................................................................................................58

3.2. ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት የሰላም ግንባታ ያላቸው ግንኙነት፣.........................................................58

3.3. የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገመግገስት እና ዘላቂ ሠላም.............................................................................................61

3.4. ማጠቃለያ፣.......................................................................................................................................63

4. ዋቢ መጻሕፍት................................................................................................................................................................ 64

ii | P a g e
I. መግቢያ
በሀገራችን የፌዴሬሽን ቅርጽ ያለው የፌዴራል ሥርዓት የሚደነግግ ሕገ መንግሥት ከፀደቀ ሃያ ስምንት
ዓመታት ያስቆጠረ ቢሆንም በፌዴራሊዝም፣ በፌዴራል ፖለቲካ ሥርዓት፣ በሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት
ምንነት እና ባህሪያት እንዲሁም በሃገራችን ሕብረ ብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ላይ በማኅበረሰቡ ውስጥ
ተቀራራቢ የሆነ አረዳድ የተያዘበት ነው ብሎ መወሰድ አይቻልም። በመሆኑም ለ 17 ኛ ጊዜ የሚከበረውን
የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ በዕውቀት ላይ
የተመሠረተ ውይይት በማድረግ በማኅበረሰቡ ውስጥ ተቀራራቢ የሆነ አረዳድ መፍጠር የሚያስችሉ ሥራዎች
በመሥራት በሃገራችን ትክክለኛ የሆነ ሕብረብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት እየገነቡ በመሄድ ሕብረብሔራዊ
አንድነትን እና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ወሳኝ በመሆኑ የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦችን ቀንን

አስመልክቶ ለሚሰጡ ሥልጠናዎች የሚውል ይህ የሥልጠና ጽሑፍ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።

የሥልጠና ጽሑፉ ፌዴራሊዝም እና የፌዴራል ሥርዓት ፅንሰ ሀሳብ፣ የፌዴራል ፖለቲካል ሥርዓት ዓይነቶች፣

የፌዴሬሽን ቅርጽ ያላቸው የፌዴራል ፖለቲካል ሥርዓቶች የጋራ ባህሪያት እና የተለያዩ የሚያደርጓቸው

ጉዳዮች፣ ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ጽንሰ ሃሳብ እና ባህሪዎች፣ ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ጋር

ተያይዞ የሚነሱ አከራካሪ ጉዳዮች፣ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት በኢትዮጵያ አና ባለፉት ጊዜያት

በሀገራችን የተተገበረው ፌደራሊዘምን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች እንዲሁም ህረ ብሄራዊ ፌደራሊዝምና

ሰላም ግንባታ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች እንዲካተቱ ተደርጎ ተዘጋጅቷል።

II. የሥልጠናው ዓላማ፣


የዚህ የሥልጠና ዋና ዓላማ በሀገራችን በየደረጃው የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች በፌዴራል ሥርዓት ውስጥ

እንደሚኖር ዜጋ በሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ላይ ተቀራራቢ የሆነ ግንዛቤ እንዲይዙ ማድረግ ነው፡፡

በተጨማሪም ሰልጣኞች በሀገራችን የሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ግንባታ ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ

ማበርከት የሚያስችሉበት ግንዛቤ በመፍጠር ሕብረብሔራዊ አንድነትና ዘላቂ ሰላምን የሚያጠናክሩ

ተግባራትን ለማከናወን መሰረት ለመጣል ነው።

1|Page
III. የሥልጠናው ዝርዝር ዓላማዎች፣
የስልጠናውን ዋና ዓላማ ለማሳካት ሰልጣኞች ከሥልጠናው በኋላ እንዲያሳኩ የሚጠበቁ በርካታ ዝርዝር
ዓላማዎች ተለይተዋል። እነዚህም፡-

 የፌዴራሊዝም ፅንሰሀሳብ፣ ፌዴራላዊ አስተሳሰብና ፍልስፍና፣


 የፌዴራላዊ ፖለቲካ ሥርዓት ዓይነቶች እና ባህሪያት፣
 የፌዴሬሽን ቅርጽ ያላቸው የፌዴራል የፖለቲካ ሥርዓቶች የጋራ ባህሪያትና የሚለያዩባቸውን
ጉዳዮች፣
 የሕብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ጽንሰ ሃሳብ እና ባህሪያት፣
 የሕብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ጋር ተያይዞ የሚነሱ አከራካሪ ጉዳዮች በደጋፊና ነቃፊ
በሆኑ እይታዎች የሚነሱ ሃሳቦች፣ እነዚህ አከራካሪ ጉዳዮች መሠረት በማድረግ የሃገራችን
ነባራዊ ሁኔታዎች (ያጋጠሙ መልካም ነገሮች እና ተግዳሮቶች) ምክንያታዊ በሆነ አግባብ
ሥርዓቱ የጋጠሙትን ተግዳሮቶችና አዎንታዊ ጎኖች በመረዳት አዎንታዊ ጎኖችን ለማዳበርና
አሉታዊ ጎኖችን የፌዴራል ሥርዓቱን በሚያጠናክር መልኩ ለመፍታት የሚቻልበትን የጋራ
ግንዛቤ ይዘው ሕብረ ብሔራዊ አንድነት እና ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት ወደ ተግባራዊ
እንቅስቃሴ የሚገቡበት ምቹ መደላድል መፍጠር ነው።

2|Page
II. ክፍል አንድ፡- የፌዴራሊዝም ፅንሰሀሳብ እና የፌዴራል ፖለቲካ ሥርዓቶች፣

1.1 መግቢያ

ፌዴራሊዝም አንድ የፖለቲካ ሥርዓትን ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በሕዝቦች ፍላጎትና ምርጫ
ለመገንባት የሚያስችል አስተሳሰብ ወይም አማራጭ ሀሳብ ነው። የፌዴራል ፖለቲካ ሥርዓት ደግሞ
የፌዴራሊዝም አስተሳሰብ በተግባር የሚገለፅበት ተጨባጭ የፖለቲካ አደረጃጀት ነው። የፌዴራሊዝምን
ፅንሰሀሳብ ተግባራዊ ለማድረግ የፌዴራል ፖለቲካ ሥርዓት አስፈላጊ ነው። ፌዴራሊዝም እንደ
አስተሳሳብ ሁሌም ሊኖር ይችላል። የፌዴራል ሥርዓት ግን ያለ ፌዴራላዊ አስተሳሰብ እውን ማድረግ
አዳጋች ነው። በዚህ ክፍልም የፌዴራሊዝም ፅንሰ ሀሳብ እና የፌዴራል ፖለቲካል ሥርዓትን
እንመለከታለን።

1.2. የፌዴራሊዝም ፅንሰሀሳብ፣


ፌዴራሊዝም እንደ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ በጋራ ለመቀጠል የወሰኑ ማኅበረሰቦች የራስ እና
የጋራ ጉዳዮችን አጣምሮ ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ ለማስተናገድ የሚያስችል ሥርዓትን መፍጠር ታሳቢ
ያደረገ ፍልስፍና ነው፡፡ ፍልስፍናው ይህን አስተሳሰብ እና አስተሳሰቡ የሚገለፁባቸው እሴቶችን የመያዝ፣
የመደገፍ እና በተግባር የመግለፅ ጉዳዮችን የሚያካትት ነው። በፌዴራሊዝም ዙሪያ ሰፊ ምርምር ያካሄደው
ኤላዘር (1987) እንደገለፀው ፌዴራሊዝም ሕዝቦች በእኩልነት መርህ፣ በመነጋገርና በመወያየት በቃል
ኪዳን ማሳሪያነት የፖለቲካ ማኅበረሰብን የሚገነቡበት አማራጭ መንገድ ነው። ተመራማሪው
እንዳብራራው ሀገራት የፖለቲካ ማኅበረሰብን የሚገነቡበት ሦስት አማራጭ መንገዶች አሉ። እነዚህም
1 ኛ/ አካባቢዎችን በኃይል በመቆጣጠር(Conquest) የፖለቲካ ማኅበረሰብ መገንባት፣ ትልልቅ ግዛቶችን
(ኢምፓየሮችን) በመገንባት የሚገለጽ ሲሆን 2 ኛ/ የፖለቲካ ማኅበረሰቡ በተፈጥሮአዊ ሂደት ራሱን
መገንባት(Organic Development) 3 ኛ/ በቃል ኪዳን፣ በሕዝቦች ፍላጎት፣ ስምምነት፣ የፖለቲካ
ማኅበረሰብ መገንባት(Covenantal) ናቸው።

የፖለቲካ ማኅበረሰብን በወረራ የመገንባት አማራጭ ጉልበት ያላቸው ሀገራት በኃይል ወረራ በማካሄድ፣
ሰፊ ሀገር የሚገነቡበት ወይም በኃይል የመንግሥት ግልበጣ ወይም አብዮታዊ ንቅናቄ በማድረግ የነበረ
መንግሥትን በማስወገድ ጠንካራና የተማከለ የፖለቲካ ማኅበረሰብን ለመገንባት የሚያስችል የቆየ
አስተሳሰብና የሀገር ግንባታ አማራጭ መንገድ ነው። ይህ አስተሳሰብ አምባገነናዊና የተማከለ ሥልጣን
ከላይ ወደ ታች የሚያወርድ እና በአብዛኛው የተማከለ ተዋረዳዊ የመንግሥት ሥርዓት ለመፍጠር
የሚያስችል ነው።

3|Page
የተፈጥሯዊ ሂደት /Organic Development/ አማራጭ የማኅበረሰቡን ተፈጥሯዊ ሂደት ተከትሎ
የሚገነባበት ነው። በዚህ መንገድ ከቤተሰብ፣ ቤተሰብ እየሰፋ ደግሞ ጎሳ፣ መንደርና ሰፋ ወደአለው
ማኅበረሰብ የሚያድግበት፣ በሂደቱም የተለያዩ ማኅበራዊ ተቋማት፣ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቶችና
የፖለቲካ አደረጃጀቶች የሚፈጠሩበት ነው። ይህ አስተሳሰብ የፖለቲካ ማኅበረሰብን ተፈጥሯዊ ሂደትን
ተከትሎ እንዲገነባ የሚያስችል በመሆኑ በዘርፉ ተመራማሪዎች ይሁንታ የሚሰጠው ነው። በዚህ
መንገድ የሚገነባው የፖለቲካ ማኅበረሰብ መሃል እና ዳር የሚፈጥር በመሆኑ ሥልጣን በመሃል
የተማከለ እንዲሆንና ወደ ዳር በተዋረድ የሚወርድበትን የመንግሥት አደረጃጀትን የሚገነባበት ነው።

በቃል ኪዳን/Covenantal/ የፖለቲካ ማኅበረሰብ የመገንባት አማራጭ የሰው ልጆች በእኩልነት መርህ
በመነጋገርና በመወያየት፣ ስምምነት ላይ በመድረስ በቃል ኪዳን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን
የሚመሠርቱበት አማራጭ ሀሳብ ነው። ይህ አስተሳሰብ ሰዎች ወይም የተለያዩ ማኅበረሰቦች
ተፈጥሯዊ መብቶቻቸውን ባከበረና ባስጠበቀ መልኩ የጋራ ፖለቲካ ማኅበረሰብ ለመገንባት ያስችላል።
በዚህ መንገድ የሚገነቡ የፖለቲካ ሥርዓቶች ያልተማከሉና ተዋረዳዊ ያልሆኑ በአንድም ሆነ በሌላ
መንገድ በባህሪያቸው ፌዴራላዊ የሆኑ ናቸው።

ፌዴራሊዝም የሰው ልጆች በእኩልነት መርህ አንድ ላይ በመሰባሰብ ሰፊና ጥልቀት ያለውን ውይይትና
ድርድር በማድረግና ስምምነት ለይ በመድረስ ተፈጥሯዊ መብቶቻቸውን ለራሳቸው በማስቀረት በቃል
ኪዳን ወይም ጥብቅ በሆነ ውል ማሰሪያነት ሰፊና ጠንካራ የጋራ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ማኅበረሰብ
ለመገንባት የሚያስችል ሀሳብ ወይም አማራጭ መንገድ ነው። ውሉ የሕጋዊ ብቻ ሳይሆን የሞራላዊ
ተጠያቂነትን የሚያስከትል በመሆኑ የቃልኪዳን ውሉ ከሌሎች ውሎች የተለየ ከመሆኑም በላይ
ሞራላዊ መሠረት ያለው ትስስሩ ለቃልኪዳኑ መከበር ወሳኝ ተደርጎ ይታያል።

ፌዴራሊዝም የሚለው ጽንሰ ሃሳብ የቃሉ መነሻ የመጣው ፌዴራል ከሚለው ቃል ሲሆን ፌዴራል
የሚለው ቃል ደግሞ የተወሰደው ፌዱስ/foedus/ ከተባለው የላቲን ቃል ነው። ትርጉሙም
ቃልኪዳን/covenant/ ወይም ጥብቅ ውል/compact/ ማለት ነው (ኤላዘር 1987)። አስተሳሰቡም
በመሠረታዊነት በቃልኪዳን ወይም ጥብቅ በሆነ ውል የተመሠረተ ሕብረት ወይም አጋርነትን የሚገልፅ
ነው። የፌዴራል ፖለቲካ ሥርዓት ፍልስፍና ሕብረት የሚያደርጉ አካላት የራሳቸውን ህልውና/Integrity/
በጠበቀ ወይም ባከበረ መልኩ በጋራ ለመኖር የሚያስችል አንድ የፖለቲካ ማኅበረሰብ በቃልኪዳን
ማሰሪያነት የሚገነባበት ነው። በተመሳሳይ መልኩም በርገስ(2006) ፌዱስ የሚለው ቃል “tie”
የሚለውን የጠበቀ፣ የታሰረ ውል መሆኑን በማብራራት ውሉ የሰዎችን የግል እና የጋራ ፍላጎቶችን
አንድ ላይ ለማጣጣም የሚያስችል ፅንሰ ሀሳብ መሆኑንም አመላክቷል።

4|Page
ኮቪናንት የሚለው ቃል በመጀመሪያ ጥቅም ላይ የዋለው ለስነ መለኮታዊ ዓላማ ነው( ኤላዘር 1987)፣
ኮቪናንት በሰው ልጆች እና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን/ያለውን/ ሕብረት የሚያመላክት እንደነበረ
ዳንኤል ኤላዘር (1987) ያብራራል። የጥንተእሥራኤል አሥራሁለቱ ነገዶች እና የዚያን ወቅት
የእሥራኤል መንግሥት የተመሠረተበትም ሥርዓት ለፌዴራሊዝም አስተሳሰብ መነሻ ተደርጎ የሚወሰድ
ነው። የኮቪናነት አስተሳሰብ በሂደት ከስነመለኮታዊ/መንፈሳዊ/ እሳቤ በመላቀቅ ለፖለቲካ ሥርዓት
ግንባታ እንዲውል በመደረጉ ፅንሰሀሳቡ ፖለቲካዊ ቅርጽ ይዞ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሥርዓት ግንባታ
አንዱ መንገድ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።

የፌዴራሊዝምን ፅንሰሀሳብ በተሟላ መልኩ ለመረዳት የዘርፉ ምሁራን ለፅንሰ ሀሳቡ የሰጡትን
ትርጉሞች አጠር ባለ መልኩ መመልከት ተገቢ ነው። የዘርፉ ምሁራን የሰጡት ትርጓሜ በአብዛኛውም
በእንግሊዝኛ በመሆኑ ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ ሲተረጎም ሊፈጠሩ የሚችሉ ልዩነቶችን ለማጥበብ
ሁለቱም እንዲቀርቡ ተደርጓል።

 Federalism is the general term for what may be reflected as self-rule and shared-rule
relationships (Elazar 1987) ፌዴራሊዝም የራስ አስተዳደርና የጋራ አስተዳደር የሚያስተሳስር
ጥቅል ሀሳብ ነው።
 The conventional view with regard to federalism is a form of non-centeralised mode of
organizing government (Elazar 1987 ) ፌዴራሊዝም የተማከለ አስተዳደር የሌለበት
የመንግሥት አደረጃጀትን ለመገንባት የሚያስችል አማራጭ ነው።
 Federalism has been represented as centeralizing and decenteralising ideology as well as
a doctorine of balance( Burgess 2006) ፌዴራሊዝም የተማከለ እና ያልተማከለ የመንግሥት
አደረጃጀት አስተሳሰብና በሁለቱ መካከል ያለውን ሚዛን የሚገልፅ እሳቤ ነው።
 Federalism can be considered as an ideology which holds that the ideal organization of
human affairs is best reflected in the celebration of diversity through unity (Watts 1996)
ፌዴራሊዝም ትክክለኛው የሰው ልጆች ፖለቲካዊ አደረጃጀት የሚገለፀው ልዩነቶችን ባከበረ
ወይም ዕውቅና በሚሰጥ አንድነት ውስጥ ነው የሚል አስተሳሰብ ነው።

ከነዚህ ትርጉሞች መረዳት የሚቻለው ፌዴራሊዝም ሰዎች/የተለያዩ ማኅበረሰቦች በራሳቸው ፈቃድ


ህልውናቸውንና ነፃነታቸውን ባከበረ መልኩ በጋራ/በአንድ ላይ ለመኖር የሚያስችል የጋራ ፖለቲካ
ማኅበረሰብ ለመገንባት የሚያስችል አስተሳሰብ ወይም አማራጭ መንገድ ነው።

የፌዴራሊዝም ፅንሰሀሳብ ሁለት መሠረታዊ መርሆዎችን አንድ ላይ አጣምሮ የያዘ ነው። እነዚህም
ሁለቱ መሠረታዊ መርሆዎች የፌዴራል ሃሳብ /Federal Idea/ ወይም የፌዴራል መርሆ/Federal

5|Page
Priniciple/ በሚል የሚታወቁ ናቸው(ኤላዘር 1987)። ሁለቱ መሠረታዊ መርሆዎች የጋራ
አስተዳደር/Shared rule / እና የራስ አስተዳደር/ Self rule /ናቸው። የጋራ አስተዳደርና የራስ አስተዳደር
መርሆዎች የፌዴራሊዝም ፅንሰ ሀሳብና ፍልስፍናን የሚገልፁ ወይም የሚወክሉ ናቸው። የጋራ እና
የራስ አስተዳደር መርሆዎች የተለያዩ የፖለቲካ ማኅበረሰቦች አንድ ላይ በማሰባሰብ የጋራ ጠቀሜታ
ባላቸው ጉዳዮች የጋራ አስተዳደር እንዲሁም በግል ጉዳዮች ላይ የራስ አስተዳደር እንዲመሠርቱ
የሚያስችል በመሆኑ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሥርዓት ለመገንባት የጎላ ሚና አላቸው።

የፌዴራሊዝም መሠረታዊ መርሆዎች በአሁኑ ጊዜ ባለ ብዙ ብሔሮች ወይም ባለ ብዙ ባህሎች


ባሉባቸው ማኅበረሰቦች ልዩነቶቻቸውን ባከበረ መልኩ አንድነትን ለመገንባት/Unity in Diversity/
ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው የዘርፉ ምሁራን ይገልፃሉ (ኪሚሊካ 1998; ጋግኖን 2001; ዋትስ 2006)

የፌዴራሊዝም አስተሳሰብ ከሰው ልጆች ተፈጥሯዊ ባህሪ ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት መሆኑን
አንዳንድ የዘርፉ ምሁራን ይገልፃሉ (ኤላዘር 1987)። የሰው ልጆች በባህሪያቸው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ
እንስሳ በመሆናቸው በማኅበራዊ አደረጃጀቶች ራሳቸውን እያቀፉ፣ የግል ጉዳዮቻቸውን በማስጠበቅ
በጋራ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ ሁለቱን አንድ ላይ አመዛዝነው የሚሄዱ በመሆኑ የፌዴራሊዝም
አስተሳሰብ ከሰው ልጆች ተፈጥሯዊ ባህሪ ጋር የተያየዘ ነው።

የፌዴራሊዝም አስተሳሰብ ለሰው ልጆች በግል እና በጋራ አንድ ላይ እንዲኖሩ የሚያስችላቸው በርካታ
መሠረታዊ እሴቶችን በውስጡ ያካተተ ነው። እነዚህም እሴቶች ሰብዓዊነት፣ እኩልነት፣ ነፃነት፣ ፍትሕ፣
የሌላን ጉዳይ እንደራስ አድርጎ የማየት፣ መቻቻል፣ ዕውቅና መስጠት፣ መከባበር የሚሉ ናቸው። ይህም
የፌዴራሊዝም አስተሳሰብ የሰው ልጆችን መሠረታዊ መብቶችና ነፃነቶች ባከበረ መልኩ አንድ የጋራ
ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ተመራጭ እንዲሆን አስችሎታል፣

1.3. የፌዴራል ፖለቲካ ሥርዓቶች (Federal Political Systems)፣


ፌዴራሊዝም በሕዝቦች ነፃ ፍላጎት በውይይትና በድርድር የግል ነፃነታቸውንና ህልውናቸውን በጠበቀ
መልኩ የጋራ የፖለቲካ ማኅበረሰብ ለመገንባት የሚያስችል አስተሳሰብ መሆኑን ተመልክተናል።
የፌዴራሊዝም አስተሳሰብ አካል የሚለብሰውና ተግባራዊ የሚደረገው በፌዴራላዊ ፖለቲካዊ ሥርዓቶች
ነው። የፌዴራሊዝም ፅንሰሀሳብና መርሆ ለበርካታ የፌዴራላዊ ሥርዓቶች መፈጠር መነሻ ነው። በዚህ
ክፍል የፌዴራሊዝምን አስተሳሰብ የሚጋሩ የተለያዩ የፌዴራል ሥርዓት ዓይነቶችን በአጭሩ
እንመለከታለን።

6|Page
1.3.1 ኮንፌዴሬሽን (የተገደበ ኮንፌዴራል መንግሥት እና ጠንካራ የኮንፌዴሬሽን አባል መንግሥታት)
የኮንፌዴሬሽን ቅርጽ ያለው ፌዴራል ፖለቲካዊ ሥርዓት ቀደምት ህልውና ያላቸው የተለያዩ
መንግሥታት ወይም የፖለቲካ ማኅበረሰቦች አንድ ላይ በመሰባሰብ ነፃነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ
ለተወሰነ ዓላማ የጋራ መንግሥት ወይም የኮንፌዴራል መንግሥት ለመመሥረት የሚስማሙበትና
የኮንፌዴራል መንግሥት የሚመሠርቱበት ነው። የኮንፌዴራል መንግሥቱ ከአባል መንግሥታት ተቆርሶ
በሚሰጥ ሥልጣን የሚመሠረት ሲሆን፣ የኮንፌዴራሉ አስፈጻሚ አካላት ከአባል መንግሥታቱ
የሚወከሉና የኮንፌዴሬሽን ተግባሩንም ለመፈፀም ከአባላቱ በሚሰጥ ድጎማ ላይ የሚደገፍ ነው።
በኮንፌዴሬሽኑ የጋራ መንግሥቱ በአብዛኛው የሚሰጠው ኃላፊነት የሀገር መከላከያና ደኅንነት፣ የውጪ
ጉዳይ፣ የጋራ ገበያና የመሳሰሉ ተግባራት ጋር የተያያዘ ሆኖ ሥልጣኑም አባል መንግሥታት ቆርሰው
የሚሰጡት ሲሆን አባል መንግሥታት ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤቶች ናቸው። በአጠቃላይ ኮንፌዴሬሽን
የኮንፌዴራል መንግሥቱ የተገደበ ሥልጣን ያላው፣ ደካማ እና ያልተረጋጋ እንዲሁም በኮንፌዴሬሽኑ
መሥራች አባላት ጥገኛ የሆነ እና አባል መንግሥታቱ ጠንካራ የሆኑበት የፌዴራል ፖለቲካ ሥርዓት
ነው።

በኮንፌዴሬሽን የፖለቲካ ሥርዓት የኮንፌዴሬሽን መሥራች አባላት የኮንፌዴሬሽን መንግሥቱን


የሚቆጣጠሩ ከመሆኑም በላይ በጋራ በሚያፀድቁት ሕገ መንግሥት የራሳቸውን ሉዓላዊ ሥልጣን
የሚያስቀሩበት ነው። ከዚህም ባለፈ የኮንፌዴሬሽን አባል መንግሥታት በማንኛውም ጊዜ
ከኮንፌዴሬሽን ለመውጣት ወይም ለመገንጠል በሚያስችላቸው መንገድ በሕገ መንግሥቱ አስቀድመው
የሚወስኑ በመሆኑ የኮንፌዴራሉ መንግሥቱ ይሁንታ ሳያስፈልጋቸው መገንጠል የሚችሉበት እድል
አላቸው። በዚህ ረገድም ኮንፌዴሬሽን የፌዴራል ሥርዓት በመሥራች አባላቱ ቋሚ ሕብረት ለመገንባት
ያላቸው ቁርጠኝነት ዝቅተኛ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። የኮንፌዴራል መንግሥቱ ሥልጣኑን
የሚያገኘው በቀጥታ በሕዝብ በሚደረግ ምርጫ ሳይሆን አባል መንግሥታት ቆርሰው በሚሰጡት
በመሆኑ በቀጥታ ከሕዝብ ጋር የማይገናኝና ለሕዝብም በቀጥታ አገልግሎት የማያቀርብ ስለሆነ ያለው
ቅቡልነትም በቀጥታ በሕዝብ ሥልጣን ከሚያገኙት አባል መንግሥታቱ ያነሰ ነው። በአሁኑ ጊዜ
የኮንፌዴሬሽን ቅርጽ ያለው ፌዴራላዊ ፖለቲካ አደረጃጀት የሚከተሉ ሀገራት የሉም ብሎ
መደምደም ይቻላል። ሆኖም የተወሰኑ ታሪካዊ ምሳሌዎች ሲዊዘርላንድ 1291 እስከ 1847፣ ዩናይትድ
ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ 1776-1789 መጥቀስ ይቻላል(ዋትስ 1996)።

1.3.2 ፌዴሬሽን (ጠንካራ የፌዴራል መንግሥት እና ጠንካራ የፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት)፣


የፌዴሬሽን ቅርጽ ያለው የፌዴራል ፖለቲካል ሥርዓት በሕዝብ የተመረጡ እና ቀጥታ ከሕዝብ ጋር
የሚገናኙ፣ በተለያዩ አግባቦች ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ጠንካራ ፌዴራላዊ መንግሥት እና ጠንካራ
የፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታትን ያካተተ የፖለቲካ ሥርዓት ነው። የፌዴራል ሥርዓቱ የሚመሠረተው

7|Page
የፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት በእኩልነት መርህ በጋራ ተወያይተው እና ተስማምተው በሚያፀድቁት
የቃልኪዳን ሰነድ ወይም ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ነው። በስምምነታቸውም መሠረት የፌዴራል
መንግሥቱ በተሰጠው የሥልጣን ወሰን በራሱ እንዲሁም የአባል መንግሥታት በተሰጣቸው የሥልጣን
ወሰን በራሳቸው የሚወስኑበትና በትብብርና በቅንጅት የሚሠሩበት ሥርዓት ነው። በፌዴሬሽኑ
የፌዴሬሽኑን አንድነት የሚመለከቱ እና የጋራ የሆኑ ጉዳዮች ተለይተው ለፌዴራል መንግሥቱ የሚሰጡ
ሲሆን ለፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታትም ከባቢያዊ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ሥልጣኖች ተለይተው
ይሰጣሉ። የፌዴራል መንግሥቱና የፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት የተሰጣቸውን ሥልጣን ተግባራዊ
ለማድረግ እንዲችሉና የትግበራ ወጫቸውን መሸፈን እንዲችሉ በየበኩላቸው ገቢ የማሰባሰብና ወጪ
የማድረግ ሥልጣን ይሰጣቸዋል። ይህ የሥልጣንና ተግባር እንዲሁም የወጪና የገቢ ክፍፍልም ሕገ
መንግሥታዊ መሠረት ያለው ነው።

በአብዛኛው ፌዴሬሽኑ የሚመሠረትበት ትርክት አብሮነት፣ በጋራ ማደግ፣ በጋራ ችግሮችን መፍታት፣
ወንድማማችነት፣ አንዱ በአንዱ ላይ እምነት ማሳደር፣ ከባባያዊ ፍላጎትና አቅምን ከሀገራዊ ፍላጎትና
አቅም አስተሳስሮ መሄድ፣ ጠንካራ የጋራ ሀገር መፍጠር ወዘተ. በመሆኑ የፌዴሬሽኑ አባል
መንግሥታት ከመለየት ይልቅ ቋሚ የሆነ ፖለቲካል ሕብረት ለመመሥረት ያላቸው ቁርጠኝነት ከፍተኛ
ነው። በመሆኑም ፌዴሬሽኑ የተመሠረተበት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት በቀላሉ የማይሻሻልና ረዘም ያለ
ጊዜ እንዲያገለግል ተደርጎ የሚቀረፅ ነው።

1.3.3 ፌደራሲ (Federacy)፣


ፌደራሲ ሰፊ ያልሆነ ወይም ትንሽ ሀገር ከአንድ ሰፊ የፌዴሬሽን ቅርጽ ካለው የፌዴራል ሥርዓት
ከሚከተል መንግሥት ጋር ከፌዴሬሽን አባል መንግሥታት በተለየ ግንኙነት (Assymetrically) ሲጣመር
የሚመሠረት የፖለቲካ ሥርዓት ነው። በፌደራሲ የሚጣመረው መንግሥት ከሌሎች የፌዴሬሽን አባል
መንግሥታት አንፃር ከፍተኛ የሆነ ራሱን የማስተዳደር ሥልጣን ያለው ነው። ሆኖም በፌደራሲ
የተጣመረው መንግሥት በፌዴራል መንግሥቱ ወይም በጋራ ሥልጣን ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ አነስተኛ
ነው። በፌደራሲ የሚመሠረተው የፌዴራል ሥርዓት ከኮንፌዴሬሽን ይልቅ የፌዴሬሽን ቅርጽ ካለው
ሥርዓት ጋር የሚመሳሰል ሲሆን ግንኙነቱም ሊቋረጥ የሚችለው በጋራ ስምምነት ብቻ ነው።
የፌደራሲ ምሳሌዎችን ለማየት ፖርቶሪኮ ከዩናይትድ ሰቴትስ ኦፍ አሜሪካ እንዲሁም ቡታን ከህንድ
ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማየት ይቻላል (ዋትስ 1996)

1.3.4 አሶሼትድ ስቴትስ/ Associated states/፣


አሶሽትድ ስቴት ልክ እንደ ፌደራሲ ሥርዓት ሰፊ ያልሆነ ሀገር ከሌላ ሰፊ የፌዴሬሽን መንግሥት
ከአባል መንግሥታት ልዩ በሆነ ግንኙነት(Assymetrically) ሲጣመር የሚመሠረት የፌዴራል ፖለቲካዊ

8|Page
ሥርዓት ነው። በዚህ ሥርዓት የሚፈጠረው ግንኙነትም ከሌሎቹ የፌዴራል መንግሥታት ጋር ሲነፃፀር
ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን ለተጣማሪው የሚያስቀር በመሆኑ ነፃነቱ ከፍተኛ ነው።
በፌዴራል መንግሥቱ ወይም በጋራ ሥልጣን ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖም ዝቅተኛ ነው። የሁለቱ
መንግሥታት ግንኙነትም ቀደም ብሎ በተደረገ ስምምነት በአንዳቸው ተናጠላዊ ፍላጎት ሊቋረጥ
ይችላል። አሶሽትድ ሰቴትስ ምሳሌዎችን ለማየት የዩናትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ከማርሻል ያላቸውን
ግንኙነት ማየት ይቻላል( ዋትስ 1996)።

1.3.5 የፌዴሬሽን ቅርጽ ያለው የፌዴራል ሥርዓት፣


የፌዴሬሽን ቅርጽ ያለው የፌዴራል የፖለቲካ ሥርዓት በሕዝብ ለሥልጣን የሚበቁ እና በተሰጣቸውን
ሥልጣን ክልል በቀጥታ ለሕዝቡ አገልግሎት የሚሰጡ ጠንካራ የፌዴራል እና ጠንካራ የፌዴሬሽኑ
አባል መንግሥታትን ያካተተ የፌዴራል ሥርዓት መሆኑን ተመልክተናል። ፌደሬሽኖቹ ፌዴሬሽን
የሚያሠኛቸው በጋራ የሚጋሯቸው ባህሪያት ያሏቸው ሲሆን በዓለም ላይ የሚገኙ ፌዴሬሽኖች
አንድና ያው ባለመሆናቸው የሚለያዩአቸው ከአፈጣጠራቸው እና ከነባራዊ ሁኔታዎቻቸው ጋር
የተያያዙ ጉዳዮች ያሉ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም እነዚህ ጉዳዮች ዘርዘር ባለ መልኩ እንደ አንድ
ክፍል በክፍል ሦስት ቀርበዋል።

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት የፌዴራል ፖለቲካዊ ሥርዓት የሚጋሩ አደረጃጀቶች በተጨማሪም ዩኒየን፣
ሊግ፣ ኮንዶሚኒየም፣ ያልተማከለ አሀዳዊ ሥርዓት ተጠቃሽ የሆኑ የፌዴራል ፖለቲካል ሥርዓት ባህሪ
የሚጋሩ አደረጃጀቶችን መጥቀስ ይቻላል ።

9|Page
III. 1.4. ፌዴሬሽኖች የሚያመሳስሏቸው የጋራ ባህሪያት እና የሚያለያዩአቸው
ጉዳዮች፣
ፌዴሬሽኖች ፌዴሬሽን ተብለው በአንድ ቡድን የተመደቡ የፌዴራል ፖለቲካ ሥርዓቶች እንዲሆኑ
ያስቻላቸው የጋራ ባህሪያት ያሏቸው ሲሆን በሌላ በኩል ፌዴሬሽኖች የተፈጠሩበት ማኅበራዊ፣
ፖለቲካዊና ኢኮኖሚዊ ሁኔታዎች ነጸብራቅ በመሆናቸው አንድና ያው አይደሉም፡፡ በመሆኑም በዚህ
ከፍል የጋራ ባህሪያቸው እና የሚለያዩባቸው ጉዳዮች በዝርዝር ቀርበዋል።

1.5. የፌዴሬሽኖች የጋራ ባህሪያት፣


ለረጅም ጊዜ በፌዴራሊዝም ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች ፌዴራሊዝምና ተያያዥ የሆኑ ጽንሰ ሃሳቦችን
ማለትም የፌዴራል ፖለቲካል ሥርዓት፣ ፌዴሬሽን፣ ኮንፌዴሬሽን፣ የመንግሥታት ግንኙነት የመሳሰሉትን
ለመለየትና እያንዳንዱን ፅንሰ ሀሳብ ለማብራራት እና አንዱን ከአንዱ የሚለዩትን እና አንድ
የሚያደርጉትን ገጽታዎች ወይም ባህሪያት ለመለየት የሚደረጉ ጥረቶች ላይ ያተኮረ ነበር (በርገስ
2006; ዎትስ 1996; ኤላዛር 1987)። በዚህም ሂደት የፌዴሬሽን ቅርጽ ያላቸውን የፌዴራል ፖለቲካል
ሥርዓቶች የጋራ የሆነ መገለጫቸውን ወይም ባህሪያት በአጥኚዎች ተለይተዋል። ፌዴሬሽኖች በሃያ
አንደኛው ክፍለ ዘመን በብዛት ጥቅም ላይ የዋሉና በመዋል ላይ የሚገኙ ፌዴራላዊ የመንግሥት
አደረጃጀቶች ናቸው (ዋትስ 1996; በርገስ 2006; ኤላዛር 1987)። በመሆኑም ፌዴሬሽኖችን ፌዴሬሽን
ተብለው እንዲለዩ የሚያደርጓቸው ገጽታዎች ወይም ባህሪያቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላል።

1.5.1. ከሁለት ያላነሱ መንግሥታት መኖር፣


ፌዴሬሽኖች ሕገ መንግሥታዊ ዕውቅና ያላቸው ቢያንስ ሁለት መንግሥታት ይኖራቸዋል። እነዚህም
የፌዴራል መንግሥትና የፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት ናቸው። አንዳንድ ፌዴሬሽኖች በፌዴራሉ ወይም
ሀገራዊ ሕገ መንግሥታቸው ለሦስት መንግሥታት ዕውቅና ይሰጣሉ። እነዚህም የፌዴራል መንግሥት፣
የክልል መንግሥታት እና ከክልል መንግሥታት በታች ያሉ ከባቢያዊ አስተዳደሮች ናቸው።

በፌዴሬሽኖች ቢያንስ ሁለቱ መንግሥታት ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን ያላቸው በመሆኑ የፌዴራል


መንግሥቱ የአባል መንግሥታቱን ሥልጣን አክብሮ አባል መንግሥታት የፌዴራል መንግሥቱን ሥልጣን
አክብረው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል። የፌዴራል መንግሥት በተሰጠው የሥልጣን ወሰን የበላይ ሲሆን
አባል መንግሥታት ደግሞ በተሰጣቸው የሥልጣን ክልል የበላይ ናቸው። ሆኖም ሁለቱ መንግሥታት
የተሰጣቸውን ሥልጣንና ኃላፊነት ለመወጣት ትስስርና ቅንጅት የማይቀር የሥርዓቱ ገጽታ ተደርጎ
ይወሰዳል።

10 | P a g e
ፌዴሬሽኖች የሁለቱን መንግሥታት መጠሪያ ፌዴሬሽኑ ከተመሠረተበት ሃገር አስተዳዳር ታሪክ ጋር
በተያያዘ፣ ፌዴሬሽኖች ሊያሳኩት የሚፈልጉትን ግብ አመላካች በሆነ እና ተለምዷዊ በሆነ ምክንቶች
የተለያዩ ስያሜዎችን ለፌዴራል መንግሥቱና ለፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታቱ ይሰጣሉ። የፌዴራሉን
መንግሥት በአንዳንድ ሃገራት ጠቅላላ መንግሥት፣ የፌዴራል መንግሥት፣ የሕብረቱ መንግሥት፣ የኮመን
ዌልዝ መንግሥት የሚሉ የተለያዩ ስያሜዎች ያላቸው ሲሆን አባል መንግሥታት ደግሞ ብሔራዊ
ክልላዊ መንግሥት፣ ፕሮቪንስ፣ ሌንደር፣ ካንቶን፣ ሪፐብሊኮች፣ራስ ገዝ ሪጅኖች፣ ስቴትስ፣ የፌዴራል
ቴሪተሪዎች፣ የከተማ መንግሥት እና በመሳሰሉት ስያሜዎች ይታወቃሉ።

1.5.2. በአንድ ሰነድ ተጠቃሎ የሚገኝ (በተለምዶ የተጻፈ)፣ የበላይ የሆነ እና በቀላሉ የማይሻሻል ሕገ
መንግሥት መኖር፣
ፌዴሬሽኖች ቢያንስ በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ፌዴሬሽኑን በመሠረቱት አካላት መካከል ተከታታይ የሆነ
ውይይትና ድርድር ውጤት እንደሆኑ ይወሰዳል። የፌዴራሊዝም አስተሳሰቡ በራሱ ውይይትና ድርድርን
መሠረታዊ መርህ አድርጎ የሚወስድ አስተሳሰብ ነው( ኤላዛር 1987)። ሕገ መንግሥቱ የአባል
መንግሥታት ባደረጉት ውይይትና ድርድር የተስማሙባቸውንና የተቀበሉአቸውን ስምምነቶች በጽሑፍ
የሚሰንዱበት የቃል ኪዳን ሰነዳቸው ነው። ፌዴሬሽኑ የሚመሠረተው ሕገ መንግሥትን መሠረት
አድርጎ ሲሆን ሕገ መንግሥቱም በዋናነት የፌዴሬሽኑን መጠሪያ፣ የሕገ መንግሥቱን ዓላማዎችና
ግቦች፣ ሕገ መንግሥታዊ መርሆዎችን፣ የዜጎችን መብቶችና ነጻነቶች፣ የመንግሥትና ዜጎች ግንኙነቶች፣
የዜጎች ግዴታዎች፣ የመንግሥት አወቃቀር፣ የፌዴራል መንግሥቱ እና የአባል መንግሥታቱን ሥልጣንና
ተግባር፣ የመንግሥት አካላትን ሥልጣንና ተግባር፣ ወዘተ… ባካተተ መልኩ የሚይዝ የስምምነት ሰነድ
ነው።

ፌዴሬሽኖች የሚያዘጋጁትን ሕገ መንግሥት በተቻለ መጠን ሁሉ ረዘም ላለ ጊዜ የሚያገለግል እና


በቀላሉ የማይሻሻል አድርገው ያዘጋጃሉ። በፌዴሬሽኖች የሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች በአንደኛው
መንግሥት በተናጥል የማይፈፀሙ ሲሆን የፌዴራል መንግሥቱና የአባል መንግሥታትን ተሳትፎ በተለያዩ
አግባቦች የሚጠይቅ ነው። ሕገ መንግሥቱ በቀላሉ እና በአንድ አካል የማይሻሻል መሆኑ ፌዴሬሽኖችን
በሁለቱም መንግሥታት ስምምነት የተፈጠሩ የሁለቱንም ስምምነት የሚጠይቅ መሆኑን የሚያመላክት
ከመሆኑም በላይ የፌዴሬሽኖችን ዘላቂነት ለመጠበቅና ቋሚ ሕብረት ለመገንባት ያስችላል ተብሎ
ይገመታል።

1.5.3. ሕገመንግሥታዊ የሆነ የሥልጣን ክፍፍል፣


በፌዴራል መንግሥትና በፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት መካከል ሕገ መንግሥትን መሠረት አድርጎ
የሚኖረው የሥልጣን ክፍፍል ፌዴሬሽኖችን የሚያመሳስል ዋና ባህሪ ነው። ፌዴሬሽኖች በሕገ

11 | P a g e
መንግሥቱ ሕግ የማውጣት፣ የመፈጸም እና የመተርጎም እንዲሁም ገቢ የመሰብሰብ እና ወጪ
የማውጣት ሥልጣኖችን ለፌዴራል መንግሥቱ፣ ለአባል መንግሥታት እንዲሁም ለአካባቢ አስተዳደሮችና
ከተማ አስተዳደሮች(ለከባቢያዊ መንግሥታት በሕገመንግሥቱ ሥልጣን በደነገጉ ፌዴሬሽኖች ) በዝርዝር
ይከፋፈላሉ። ሁለቱም መንግሥታት ሕግ የማውጣት፣ሕግ የማስፈጸም እና የዳኝነት ሥልጣን እና
የራሳቸውን ገቢ የመሰብሰብና ወጪ የማውጣት ሥልጣን ያላቸው መሆን በሥልጣን ወሰናቸው
ራሳቸውን ችለው እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል ሲሆን ተግባራዊ አፈጻጸሙ ግን ከፌዴሬሽን፣ ፌዴሬሽን
እና በየወቅቱ በፌዴሬሽኖች በሚኖሩ የፓርቲ-ፖለቲካል ዳይናሚክስ፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ሁኔታዎች
ጋር ተያይዞ የሚታይ ነው። በጥቅሉ ብዙ ፖሊሲ ጉዳዮች በትብብርና በትስስር የሚተገበሩ
መሆናቸውን የፌዴሬሽኖች አንዱ ባህሪ ተደርጎ የሚታይ በመሆኑ የመንግሥታት ግንኙነት የሚያሳልጥ
ሂደት መኖር እንደ አንድ የጋራ ባህሪያቸው ይታያል። በፌዴሬሽኖች ሕገመንግሥታዊ የሥልጣን
ከፍፍሎችን የሚያካሄዱበት አግባብ ለፌዴራል መንግሥቱ ተለይቶ የተሰጠ ሥልጣን፣ ለፌዴሬሽኑ አባል
መንግሥታት ተለይቶ የተሠጠ ሥልጣን፣ ጣምራ ሥልጣን እና ቀሪ ሥልጣኖች በሚል ማዕቀፍ
የሚታወቁ ናቸው።
1.5.3.1 የፌዴራል መንግሥቱ ሥልጣን፣
ለፌዴራል መንግሥቱ ሀገራዊ የሆኑ እና የጋራ (ሁሉንም አባል መንግሥታት የሚመለከቱ፣ ከአንዱ አባል
መንግሥት በላይ ተሻጋሪ የሆኑ) ወይም በሀገር ደረጃ ተግባራዊ ቢደረጉ የተሻለ ውጤማነትን ያመጣሉ
ተብለው የሚገመቱ ሥልጣኖች ተለይተው የሚሰጡበት ነው። በአብዛኛዎቹ ፌዴሬሽኖች ለፌዴራል
መንግሥት በዋናነት የሀገር ሉዓላዊነትን የማስጠበቅ (የመከላከያና ደኅንነት)፣ የውጭ ግንኙነት፣
የጉምሩክና የውጭ ንግድ ገቢዎች፣ የገንዘብና ፋይናንስ ፖሊሲ ጉዳዮች፣ ከሁለት በላይ አባል
መንግሥታትን የሚመለከቱ ጉዳዮች፣ አንድ የኢኮኖሚና ፖለቲካ ማኅበረሰብ ለመገንባት እና የጋራ
አስተዳደርን ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑ ሕጎችና ፖሊሲዎች፣ የዜግነትና ኢሚግሬሽን፣ ወዘተ…ላይ ሕግ
የማውጣት፣ የመፈፀምና የመተርጎም ሥልጣኖች ተለይተው ይሰጣቸዋል። የፌዴራል መንግሥት
ሥልጣን እንደየፌዴሬሽኖቹ የሚለያይ ሲሆን እንደሚከተሉት የፌዴሬሽን ሞዴል የሚወሰን ነው።
በአጠቃላይ ግን እንደ ሀገር ተግባራዊ ቢደረጉ የተሻለ ፋይዳ አላቸው ተብለው የሚለዩ ሥልጣኖች
ተዘርዝረው ለፌዴራል መንግሥቱ በሕገ መንግሥቱ ይሰጣሉ።

1.5.4.2 የፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት ሥልጣን፣


ለፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት የሚሰጡ ሥልጣኖች በዋናነት የመንግሥታቱን ተጨባጭ ሁኔታ ማዕከል
ያደረጉ፣ ለማኅበረሰቡ በቅርበት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉና ከባቢያዊ ፍላጎቶች እና አቅሞችን
መሠረት አድርጎ ከባቢያቸውን ለማገልገል እና እንደ ሃገር አስተዋፅኦ ሊያደርጉ የሚያስችሉ ጉዳዮችን

12 | P a g e
የሚያካትቱ ይሆናሉ። በተለይ ሕብረብሔራዊ በሆኑ ፌዴሬሽኖች ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውን
እንዲያሳድጉና ቋንቋቸው እንዲያድግ አጋዢ የሚሆኑ ሥልጣኖችን ያካትታል። በአብዛኛው ፌዴሬሽኖች
ለአባል መንግሥታት የሚሰጡ ሥልጣኖች የግብርና ልማት፣ የጤና፣ የትምህርት፣ የባህል፣ የቱሪዝም፣
ከባቢያዊ የሰላምና ፀጥታ፣ በተለዩ ምንጮች ገቢ የማሰባሰብ፣ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን የማቅረብ
ወዘተ…የሚመለከቱ ናቸው። የአባል መንግሥታት በነዚህ ተለይተው በሚሰጡ ሥልጣኖች ሕግ
የማውጣት፣ የመፈጸምና የመተርጎም ሥልጣን ይኖራቸዋል። በፌዴራሊዝም አስተሳሰብ ሥልጣን
ለመከፋፈል የሳብሲዲያሪቲ መርህን መከተል ከባቢያዊ መንግሥታት በሚችሉት መጠን ድረስ
የከባቢያቸውን ችግር እንዲፈቱ፣ ከባቢያዊ ፍላጎት እና አቅም ላይ መሠረት ያደረገ ውጤታማና
ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና የፌዴራል መንግሥቱ ከነርሱ አቅም በላይ በሆኑ ጉዳዮች እንዲያተኩር
ይጠቅማል ተብሎ ይወሰዳል። መርሁ የሥልጣን መከፋፈል መነሻ የታችኛውን አስተዳደር እርከን
በማድረግ በታችኛው አስተዳደር እርከን አቅም በተሻለ መንገድ መፈጸም የማይችሉ ጉዳዮች ቀጥሎ
ላለው እርከን መስጠት ያለባቸው እና እንዲህ እያለ የፌዴራል መንግሥቱ እንደ ሃገር የፌዴሬሽኑ አባል
መንግሥታት በተሻለ ሁኔታ መፈጸም የማይችሏቸውና ከአቅማቸው በላይ የሆኑ ጉዳዮችን መፈጸም
የሚያስችል ሥልጣን ይኖረዋል ማለት ነው። ይህ እሳቤ በአውሮፓ ሕብረት እየተሞከረ ያለ መሆኑ
ይገለፃል ( በርገስ 2006)፣፣

1.5.4.3 የጋራ (ጣምራ ሥልጣን)፣


ጣምራ ሥልጣኖች ለፌዴራል መንግሥቱና ለአባል መንግሥታት በጋራ የተሰጡ ሥልጣኖች ናቸው።
በሥልጣን ክፍፍሉ ወቅት ሁሉንም ሥልጣኖች ልቅም አድርጎ ለፌዴራል መንግሥቱ እንዲሁም ለአባል
መንግሥታት ለይቶ ለመስጠት አስቸጋሪ ይሆናል። እነዚህም ሥልጣኖች የፌዴራል መንግሥቱንም ሆነ
የአባል መንግሥታትን የሚመለከቱ ናቸው። በአብዛኛዎቹ ፌዴሬሽኖች ጣምራ ሥልጣን ተደርገው
የሚወሰዱ ሥልጣኖች በተለይ በጋራ የገቢ ምንጮች ግብርና ታክስ በሁለቱ መንግሥታት በጣምራ
የሚተዳደሩባቸው ናቸው። በጣምራ የተሰጡ ሥልጣኖች ተግባራዊ ለማድረግ የፌዴራል እና አባል
መንግሥታት ተቀራርበው መሥራት ይኖርባቸዋል።

1.5.4.4. ቀሪ ሥልጣኖች፣
በሥልጣን ክፍፍል ወቅት ሁሉንም ሥልጣኖች በዝርዝር በመለየት መከፋፈል አደጋች ይሆናል።
በሥልጣን ክፍፍሉ ለፌዴራል መንግሥቱ በተናጥል ሆነ ለፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት በተናጥል እና
ለሁለቱ መንግሥታት በጣምራ ከተሰጡት ሥልጣኖች ውጭ የሆኑ ሥልጣኖች ቀሪ ሥልጣኖች በመባል
ይታወቃሉ። ቀሪ ሥልጣኖችን በሚመለከት አንዳንዶቹ ለፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት ሌሎች
ለፌዴራሉ መንግሥት ይሰጣሉ።

13 | P a g e
ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት የሥልጣን ክፍፍል በተጨማሪ ለፌዴራል መንግሥት ሀገራዊ የሆኑ ደረጃዎችን
እና ሀገራዊ ፖሊሲዎች እና ስትራቴጅዎችን ከማውጣት ጋር ተያይዞ ከሚኖረው ሥልጣን ጋር በተገናኘ
አባል መንግሥታት እነዚህን ስታንዳርዶች፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች መሠረት ባደረገ መልኩ
የተሰጣቸውን ሥልጣን መፈጸም ስለሚጠበቅባቸው ፌዴራል መንግሥቱ በተወሰኑ ጉዳዮች ማዕቀፍ
ሥልጣን እንዳለው የሚወሰድበት ሁኔታ ያለ መሆኑን ግንዛቤ ሊያዝበት ይገባል። በሌላ በኩል የፌዴራል
መንግሥት ሀገራዊ የሆነ ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች የማውጣት የመፈጸም ሥልጣን ሲኖረው አባል
መንግሥታት የመንግሥታቸውን ፖሊሲና ሰትራቴጂ የማውጣትና የመተግበር ሥልጣን የሚሰጥበት
ሁኔታ ሁለቱ መንግሥታት በአንድ ፖሊሲ ጉዳይ ሀገራዊ እና ከባቢያዊ በሆነ አግባብ ሥልጣንን
የሚጋሩበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። በመሆኑም በፌዴሬሽኖች የሥልጣን ከፍፍል በሕገመንግሥቱ
ከተቀመጠው በዘለለ በአንድ ሀገር ውስጥ ለአንድ ሕዝብ ወደ ተግባራዊ አፈጻጸም ሲመጣ ትስስሩና
ግንኙነትን አይቀሬ ስለሚያደርገው በሥርዓቱ ውስጥ የመንግሥታት ግንኙነት ከፍተኛ አንድምታ
ይኖረዋል።

1.5.4. ሁለት ም/ቤቶች መኖር፣


አንዳንድ አሃዳዊ ሥርዓት የሚከተሉ ሃገራትም ሁለት ም/ቤቶች ያሏቸው ቢሆንም ሁሉም
ፌዴሬሽኖችን ሁለት ምክር ቤቶች ያሏቸውና የላይኛው ምክር ቤት አባላት ከሚወከሉበት አግባብና
ም/ቤቶቹ ከሚኖራቸው ተግባርና ኃላፊነት ጋራ ተያይዞ ፌዴሬሽኖችን የሚያመሳስላቸው ሌላኛው
ባህሪ ነው። የላይኛው ምክር ቤት በአብዛኛው ከተወሰኑ ፌዴሬሽኖች ውጭ (ምሳሌ የአሜሪካ ሴኔት
ከ 1963 በኋላ) በፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት የሚወከሉበት ነው። በምክር ቤቱም የፌዴሬሽኑን አባል
መንግሥታት የሚመለከቱ እና በአባል መንግሥታቱ ላይ ተፅእኖ ሊያሳርፉ የሚችሉ ጉዳዮች
የሚመክሩበትና ውሳኔ የሚሰጡበት ሲሆን በሀገር ደረጃ የጋራ ሥልጣንን ለማስፈጸም በሚወጡ
ፖሊሲዎችና ሕጎች የፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት ሃሳቦች የሚካተቱበት መድረክ ተደርጎ ይወሰዳል።
ሆኖም የላይኛው ምክር ቤት ስያሜ እና ተግባር እንደየፌደሬሽኖቹ ይለያያሉ። የላይኛው ምክር ቤት
ቡንደሥራት፣ ሴኔት፣ ካውንስል ኦፍ ሰቴትስ፣ ፐሮቪንሻል ካውንስል፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ወዘተ…
የሚባሉ ስያሜዎች አሉት። ከምክር ቤቱ ሥልጣን አንፃርም በአንዳንድ ፌዴሬሽኖች ከታችኛው ምክር
ቤት ጋር አቻ የሆነ ሥልጣን ያለው ሲሆን በሌሎች ደግሞ ከፍ ያለ ሥልጣን አላቸው፣ በአንዳንዶች
ደግሞ ሃገራዊ በሆኑ ሕግና ፖሊሲዎች ማውጣት ላይ ከመሳተፍ አኳያ ዝቅ ያለ ሥልጣን አላቸው።

1.5.5. በፌዴሬሽኑ ውስጥ አለመግባባቶችን የሚፈታ ተቋም መኖር፣


በፌዴሬሽኑ ውስጥ ሕገመንግሥቱን ተግባራዊ ከማድረግ ጋር ተያይዞ የሚነሱ አለመግባባቶች የሚፈታ
አካል በሁሉም ፌዴሬሽኖች መኖሩ የፌዴሬሽኖች የጋራ ባህሪ ተደርጎ ይወሰዳል።

14 | P a g e
ይህን ተግባር የሚያከናውኑ ተቋማት ስያሜና አደረጃጀት የሚለያይ ሲሆን ለአብነትም በአሜሪካ፣
የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሌላው መደበኛ የፍርድ ቤት ሥራው በተጨማሪ ይህን ተግባር
ያከናውናል፣ በጀርመን ለዚሁ ተግባር ብቻ የተቋቋመ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ያለ ሲሆን፣
እንዲሁም በሀገራችን የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባኤ ሙያዊ ድጋፍ እያገኘ
ውሳኔ የሚሰጥ ምክር ቤት ነው፣፣

1.5.6. የመንግሥታት ግንኙነትን የሚያሳልጡ ሂደቶች መኖር፣


የመንግሥታት ግንኙነት አንዱና ዋነኛው የፌዴራል ሥርዓት ተግባራዊነት መገለጫ ሲሆን በማንኛውም
ፌዴሬሽን አይቀሬ ነው። አስፈላጊነቱ የሚመነጨውም ሁሉም የጋራና የግል ጉዳዮች ሕገ መንግሥት
በፀደቀበት ወቅት ሊታዩና ዕልባት ሊያገኙ ስለማይችሉ ቀጣይነት ያለው ግንኙነትና ውይይት አስፈላጊ
ስለሚሆን፣ በየጊዜው የሚኖሩ ተለዋዋጭ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎች በጋራ እየተነጋገሩ
ከወቅቱ ጋር ራስን አዛምዶ መሄድ አስፈላጊ በመሆኑ፣ በሥልጣን ክፍፍሉ የጣምራ ሥልጣኖች ስለሚኖሩና
አተገባበራቸውም ግንኙነትና ምክክርን ስለሚጠይቁ፣ በተመሳሳይ ቦታና ሕዝብ ላይ የሚተገበሩ ፖሊሲዎችና
ሕጎች በተወሰነ መልኩም ቢሆን ማጣጣምና አተገባበሩን ማቀናጀት አስፈላጊ ነው፣፣

በመንግሥታት መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን በጋራ መፍታት አስፈላጊ መሆኑ እና በአንጻራዊነት


ተመጣጣኝ በሆነ የታክስ መጠን፣ በአንጻራዊነት ተመጣጣኝ የሆነ አገልግሎት በአንድ ፌዴሬሽን ውስጥ የሚኖሩ
ሁሉም ዜጎች በሚኖሩበት አካባቢ ማግኘት ያለባቸው በመሆኑ ይህን ለመፈጸም በገቢና ወጪ ክፍፍል ዙሪያ
በጋራ መነጋገርና መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ፣ በአንድ ፌዴሬሽን ውስጥ የሚገኙ በተለያዩ የልማት ደረጃ ያሉ
ክልሎችን በአንፃራዊነት ወደ ተቀራራቢ ደረጃ ለማምጣት በጋራ መሥራት አስፈላጊና የፌዴራላዊ ሥርዓት
አንዱ እሴት የሆነው ሶሊዳሪቲ መገለጫ ተግባራዊ የሚደረግበት፣ እንደ ሃገር ልማቶችን ለማሳካት አስፈላጊ
መሆኑ እና አንድ ፌዴራላዊ ማኅበረሰብ የመፍጠር አስፈላጊነት በፌዴሬሽኖች የመንግሥታት ግንኙነትን
የሚያሳልጡ የአሠራር ሥርዓቶች መኖር ፌዴሬሽኖችን የጋራ የሚያደርግ ሌላው ባህሪያቸው ነው።

1.6. ፌዴሬሽኖችን እርስ በእርስ የሚለያያቸው ጉዳዮች፣

በዓለም ላይ የሚገኙ ፌዴሬሽኖች ከላይ በዝርዝር የታዩት የጋራ ባህሪያት ያሏዋቸው ቢሆንም ሁሉም አንድ
ዓይነት አይደሉም። ፌዴሬሽኖች ከአመሠራረታቸውና ከሚከተሉት የአስተዳደር ሥርዓት እንዲሁም
ከሚገኙበት ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚዊና ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተያያዙ የተለዩ የሚያደርጓቸው ጉዳዮች
ያሉ ሲሆን በዝርዝር እንደሚከተለው ቀርበዋል።
1.6.1.1 ሕብረብሔራዊ እና ሕብረብሔራዊ ያልሆኑ ፌዴሬሽኖች
ፌዴሬሽኖች በውስጣቸው የሚታየውን ብዝኃነት ዕውቅና በመስጠት በተያያዘ አካባቢ የሚኖሩና
በአካባቢው አብላጫ ቁጥር ያላቸው ብሔሮች የፌዴሬሽኑ አባል በመሆን ራስን በራስ የማስተዳደር

15 | P a g e
ከመፍቀድና ካለመፍቀድ ጋር ተያይዞ ፌዴሬሽኖች ሕብረብሔራዊ፣ ሕብረብሔራዊ ያልሆኑ (በፌዴሬሽኑ
አባል መንግሥታት አወቃቀር ለማንነት፣ ለቋንቋና፣ ለባህል ዕውቅና የማይሰጡ) በሚል ፌዴሬሽኖች
ይለያያሉ።

1.6.1.2 ሕብረብሔራዊ ፌዴሬሽኖች (Multi-national Federations)፣


ሕብረብሔራዊ ፌዴሬሽን በአንድ የፖለቲካ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የብሔር ማንነቶችን
የራስ አስተዳደር እንዲኖራቸው በማድረግ የጋራ የፖለቲካ ማኅበረሰብ ለመገንባት የሚያስችል ሥርዓት
ነው። የአባል መንግሥታት ወሰናቸው ወይም ድንበራቸው የተለያዩ ብሔር ወይም ሌሎች ማንነቶችን
አሰፋፈር ታሳቢ ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን የብሔር ማንነቶቹ ባሉበት የራሳቸውን አስተዳደር
የመመሥረት እንዲሁም በፌዴሬሽኑ የጋራ አስተዳደር የመሳተፍ ምቹ ሁኔታ ይፈጥርላቸዋል።
በሕብረብሔራዊ ፌዴሬሽኖች የፌዴሬሽን አባል መንግሥታት አወቃቀር ሌሎች መስፈርቶች
እንደተጠበቀ ሆኖ በዋናነት መነሻ የሚያደርገው የተለያዩ ማንነት ያላቸውን ብሔሮች የራስ በራስ
ማስተዳደርን ነው። ሕብረብሔራዊ ፌዴሬሽኖች የተለያዩ የብሔር ማንነቶች ራሳቸውን በራሳቸው
የሚያስተዳድሩበትን እንዲሁም ልዩነቶችን ዕውቅና የሚሰጥ አንድነትን ለመገንባት የሚያስችል በመሆኑ
ባለብዙ ማንነቶች ባሉባቸው የፖለቲካ ማኅበረሰቦች ተመራጭ የሆኑ የፌዴራል ሥርዓቶች ናቸው።

1.6.1.4. ሕብረብሔራዊ ያልሆኑ (ለማንነቶች ራስን በራስ ማስተዳደር ዕውቅና የማይሰጡ) ፌዴሬሽኖች፣
ሕብረብሔራዊ ያልሆኑ ፌዴሬሽኖች ለብሔሮች ወይም ሌሎች ማኅበረሰቦችን ራስን በራስ ማስተዳደር
ዕውቅና የማይሰጡና በፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት አወቃቀር እንደ መነሻ የማይወሰዱ ናቸው።
ሕብረብሔራዊ ያልሆኑ ፌዴሬሽኖች በፌዴሬሽኑ ውስጥ የተለያዩ ማንነቶች፣ ባህሎች እና ቋንቋዎች
በጭራሽ የሌሉባቸው ፌዴሬሽኖች ሳይሆኑ በጊዜ ሂደት በፌዴሬሽኑ ውስጥ የሚኖሩ አብላጫ ያላቸው
ሕዝቦች ማንነት ጎልቶ የወጣባቸውና በአብዛኛው ቅቡልነት ያገኘ አብዛኞቹ ሌሎች የባህል፣ የቋንቋ
ልዩነቶች መልቲከልቸራሊዝምን (ብዝኃ ባህልን) መሠረት ባደረገ ራስ በራስ ማስተዳደርን ሳይጨምር
ለማክበር የሚጥሩ የፌዴሬሽን ዓይነቶች ናቸው። የፖለቲካ ማኅበረሰቡ በሂደት በተለያዩ ሁኔታዎች
አብዛኛው አንድ ዓይነት ቋንቋ፣ ተመሳሳይነት ያለው ባህል፣ አኗኗር ዘይቤ ያለው ከሆነ በወሰን ተለይቶ
የተለየ ዕውቅና የሚሰጠው ማኅበረሰብ አይኖርም።

1.6.1.5 ሥልጣን በግልጽ የተከፋፈለበት (ፕሬዜዳንታዊ) እና ሥልጣን፣ የተዋሐደበት (ፓርላሜንታዊ) የመንግሥት


አወቃቀር የሚከተሉ ፌዴሬሽኖች
በፌዴሬሽኖች የሕግ አውጭና ሕግ አስፈጻሚ ተቋማት የሚኖራቸውን የሥልጣን ክፍፍል ለመተግበር
በሚከተሉት አደረጃጃት በመሠረታዊነት በሁለት መሠረታዊ ምድቦች ሊከፋፈሉ ይችላሉ። እነዚህም
የአስፈጻሚና የሕግ አውጪ አካሉ የተለያዩ የሆኑበት ወይም የፕሬዚዳንሻል ሥርዓት የሚከተሉ ፌዴሬሽኖች

16 | P a g e
እና ለሕግ አውጪ አካል ተጠሪ የሆነ ፓርላሜንታዊ አስፈጻሚ አካል ያላቸው ፓላሜንታዊ ሥርዓት የሚከተሉ
ፌዴሬሽኖችን በሚል የሚታወቁ ናቸው። ሆኖም በአብዛኛው የተለመደ ባይሆንም በተወሰኑ ፌዴሬሽኖች
ተግባራዊ እየሆነ ያለ ቅይጥ የሆነ የፕሬዜዳንሻያልና የፓርላሜንታዊ ሥርዓት አጣምሮ የያዘ ሥርዓት
የሚከተሉ ፌዴሬሽኖች ለምሳሌ ራሽያና ፓኪስታን ያሉ መሆኑን ጠቅሶ ማለፍ ተገቢ ነው። በሁለቱ
የመንግሥት አካላት መካከል በግልጽ የሥልጣን ክፍፍልን ከአስፈጻሚው አፈጣጠር ጋር ተያይዞ የሚከፋፍለው
ሥርዓት የፌዴራል መርህ የሆነውን በተለያዩ እርከን ባሉ መንግሥታት መካከል ያለውን የሥልጣን መከፋፈል
በአስፈጻሚውና ሕግ አውጪው መካከል በሚኖር ሥልጣን መከፋፈል የሚያሰፋ ሲሆን ለዚህም ምሳሌ
የሚሆነው የፕሬዚዳንት-ኮንግረንስ ተቋማት በአሜሪካ ማየት ይችላል። ይህ ሞዴል በሁሉም የላቲን አሜሪካ
ፌዴሬሽኖችና በናይጄሪያ 1999 ሕገ መንግሥት ጥቅም ላይ ውሏል። ከዚህ ትንሽ ለየት ያለ ምሳሌ ኮሊጊያል
የሆነውና የተወሰነ ተርም ያለው የሲዊዘርላንድ አስፈጻሚን መውሰድ ይቻላል።

ከዚህ በተቃራኒም ፓርላሜንታዊ ሥርዓትን በሚከተሉ ፌዴሬሽኖች በፌዴራል እና በፌዴሬሽኑ አባል


መንግሥታት መካከል ሥልጣን የተከፋፈለ ቢሆንም በሁሉም እርከኖች ሕግ አስፈጻሚው አካል በሕግ
አውጪው አካል አብላጫ ድምጽ ባለው ፓርቲ ወይም- የፓርቲዎች ጥምረት የሚያዋቅርና ተጠሪነቱም ለሕግ
አውጪው አካል ስለሚሆን የሥልጣን ክፍፍሉ ግልጥ ብሎ የሚታይ አይደለም። ይህም የሕግ አስፈጻሚው
አካል ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ በሕግ አውጪው ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል ከሚል መርህ የተነሳ ሲሆን
ሕግ አስፈጻሚው በቀጥታ በሕዝብ ራሱን ችሎ እንደ አስፈጻሚ የሚመረጥ አይደለም ።

የሕግ አስፈጻሚው አካል የተለያየ ዓይነት አደረጃጀቶች መኖር በፌዴራል ሥርዓቱ አተገባበር ላይ መሠረታዊ
በሆነ መልኩ ጫና መፍጠሩ አልቀረም (ዋትስ 1996)። በመጀመሪያ ደረጃ የፌዴራል መንግሥቱ ወካይነትና
ውጤታማነት ላይ የራሱ ጫና ይፈጥራል። ለምሳሌ በፓርላሜንታዊ ሥርዓት የሚገኝ የሕግ ፈጻሚ አካልን
በጋራ የማቋቋም (ጋራዊ) ባህሪው ከባቢዎች በአስፈጻሚው ውስጥ ውክልና እንዲኖራቸው ለማድረግና
በካቢኔው ውስጥ የፖለቲካል ፓርቲ ጥምረት ዕድልን በእጅጉ ይፈጥራል። ይህ እድል በሌላ መልኩ ክልሎች
በሀገራዊ ፖሊሲዎችና ሕጎች ላይ ድምጻቸውን ያሰሙበታል ተብሎ የሚወሰደው የሁለተኛው ምክር ቤት
ደካማ የሆነ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት መኖርን ያካክሳል። በዚህ ሥርዓት የላይኛው ወይም ሁለተኛው
ምክር ቤት ደካማ የሆነበት አንዱና ዋናው ምክንያቱ ሁለተኛው ምክር ቤት በአብዛኛው ለአስፈጻሚው አካል
መተማመኛ የሚሰጥ ምክር ቤት ባለመሆኑ ነው(ዋትስ 1996) ብዙዎቹ በፓርላሜንታዊ ሥርዓት የሚገኙ
ሁለተኛ ምክር ቤቶች በሕገ መንግሥቱ ምክንያት ወይም በተግባር የሕግ አውጪውና የሕግ አስፈጻሚ አካሉ
የተለያየባቸው ፌዴሬሽኖች ያላቸውን ያህል ጠንካራ የሆኑ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት የላቸውም።
የአስፈጻሚው አካል በፌዴራልና በክልል መንግሥታት ያላው አወቃቀር በመንግሥታት ግንኙነት ባህሪና ሂደት
ላይ ትርጉም ያለው ተፅዕኖ ይኖረዋል(ዋትስ 1996)። የሕግ አውጪና አስፈጻሚ አካል በተለያየበት አግባብ
የመንግሥታት ግንኙነት አግባቦች ብዙ የተለያዩ ፌዴራል- ክልል ቻናሎች አስፈጻሚውን ከአስፈጻሚው፣ ሕግ

17 | P a g e
አውጪውን ከሕግ አውጪው የሚገናኙበት ብዙ አውድ ያለው ግንኙነት የሚፈጠርበትን አጋጣሚ
ያመቻቻሉ። ግሮድዚን( 1983) ማርብል ኬክ ፌዴሬሽን የሚለውን ዓይነት ነው። በፓርላሜንታዊ ፌዴሬሽን
አስፈጻሚ አካል (ካቢኔው) በሕግ አውጪው አብላጫ ድምፅ እየተደገፈ የበላይነት የሚይዝበት በመሆኑ
የመንግሥታት ግንኙነቱ በዋናነት በሁሉም ደረጃ ያለው አስፈጻሚ አካል የሚገናኝበት ቻናል ስለሚሆንና
ሂደቱንም ይኸው አካል በዋናነት ስለሚቆጣጠረው “የአስፈጻሚው ፌዴራሊዝም” የሚል ስያሜ አግኝቷል።
ይህ ዓይነት ሥርዓት በዋናነት በጀርመን፣ አውስትራሊያና ካናዳ ጎልቶ የሚታይ ቢሆንም የህንድ፣ የማሌዥያ፣
ኦስትሪያ፣ ቤልጂየምና ስፔንም የዚሁ ዓይነት ሂደት የመንግሥታት ግንኙነቱ የሚለይበት ባህሪ ነው።

1.6.1.6 የተመጣጠነ እና ያልተመጣጠነ ሥልጣን ያላቸው የፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታትን ያቀፉ ፌዴሬሽኖች፣
በብዙ ፌዴሬሽኖች መደበኛ የሆነው የሕግ ማውጣትና የሕግ ማስፈፀም ሥልጣን እና ገቢን
የመሰብሰብና ወጪ የማድረግ ሥልጣን ለሁሉም የፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት በተመጣጠነ መልኩ
በሕገመንግሥቱ የሚደነገግ ሲሆን በተወሰኑ ፌዴሬሽኖች በሕገመንግሥቱ ለተወሰኑ የፌዴሬሽኑ አባል
መንግሥታት የተለየ ሥልጣን የሚሰጡ እንዳሉ ይታወቃል። ይህም የፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት
ካላቸው ጂኦግራፊያዊ ስፋት እና የሕዝብ ቁጥር፣ የተለየ ማኅበራዊና ባህላዊ ጥንቅር፣ በቋንቋና
በብሔር የተለዩ መሆን፣ የተለየ የአከባቢያዊ ሁኔታ፣ ፌዴሬሽኑን የተቀላቀሉበት የተለየ ሁኔታን እና
ሌሎችንም ተጨማሪ ምክንያቶች መሠረት በማድረግ በሕግ የተደነገገ በተወሰነ ጉዳይ ላይ የተለየ
ሥልጣን ይሰጣሉ። ይህም ዲ-ጁሪ አሴሜትሪ/ የሕግ መሠረት ያለው አለመመጣጠን/ ያሏቸው አባል
መንግሥታት ያለው ፌዴሬሽን ይፈጥራል እንደ ምሳሌም ቤልጄየም፣ ቦዝኒያኽርዞጎቢና፣ ካናዳ፣
ኮሞሮስ፣ ህንድ፣ ማሌዥያ፣ ራሽያና ስፔንን መውሰድ ይቻላል (ዋትስ 1996)።

ይህ በክልል መንግሥታት መካከል አለመመጣጠን ሲኖር በፌዴሬሽኑ ላይ ተጨማሪ ውስብስብነትን


የሚያመጣ ነው። ይህ ሕግን መሠረት ያደረገ በፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት መካከል የሚታይ ልዩነት
በተወሰኑና ልዩነቱ እንዲፈጠር ምክንያት የሆኑ ጉዳዮች ባሉባቸው ፌዴሬሽኖች የሚታይ ሲሆን
በፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት መካከል በተግባር የሚታይ ልዩነት (ዲ-ፋክቶ አለመጣጣም) ግን በሁሉም
ፌዴሬሽኖች የሚታይ ነባራዊ ጉዳይ ተደርጎ ይወሰዳል። ይህም ዲ-ፋክቶ አሴሜትሪ በሚል ጽንሰ ሃሳብ
ይገለጻል። አባል መንግሥታቱ በቆዳ ሰፋታቸው፣ በሕዝብ ቁጥራቸው፣ በኢኮኖሚያዊ አቅማቸው፣ በገቢ
አቅማቸውና በሚሰበስቡት የገቢ መጠን፣ በሚገኙበት አግሮኢኮሎጅ፣ ወዘተ.. ተመሳሳይ ሊሆኑ
አይችሉም።

የሕግ መሠረት ያለው የሥልጣን አለመመጣጠን መቀበል ከባቢያዊ ልዩነቶችን ለማስተናገድ ሲባል
የሚወሰድ እርምጃ ቢሆንም የተለየ ለመሆን ያለው ግፊትና በሌሎች ደግሞ እኩል የመስተናገድ
ጥያቄዎች በካናዳና በስፔን እንደታየው ብዙ ጉዳዮች የልዩነት እና ያለመረጋጋት ምንጭ ሆነው

18 | P a g e
ይታያሉ። ሆኖም በተወሰኑ ፌዴሬሽኖች እንደታየው ከከባቢያዊ የራስ አስተዳደር ጥያቄ ጋር ተያይዞ
የሚፈጠረውን ጫና እና ግፊት ለመቋቋምና ጥያቄውን በተወሰነ መልኩ ለማስተናገድ የተመጣጠነ እና
ያልተመጣጠነ የሥልጣን ክፍፍል በሕገመንግሥታዊ የሥልጣን ክፍፍል ማካተት እንደ አማራጭ
ይወሰዳል።

1.6.1.7 የተማከሉ እና ያልተማከሉ ፌዴሬሽኖች፣


የፌዴራሊዝም አስተሳሰብ ከመነሻው ከመማከል ጋር ተያይዞ የሚፈጠር የተማከለና ያልተማከለ የሚል
መገለጫዎች መነሻ የማያደርግና የአስተሳሰቡ መነሻ አለመማከል ( non-centralization) ቢሆንም
(ኤላዛር 1987) በአንድ ፌዴሬሽን ውስጥ የሚደረግ የሥልጣን ክፍፍል መሠረት አድርጎ የተማከሉና
ያልተማከሉ ፌዴሬሽኖች በሚል ከፋፍሎ ማየት የተለመደ ነው። ፌዴሬሽኖች ሕገ መንግሥቱን
መሠረት ያደረገውን የሥልጣን ክፍፍሉን መሠረት አድርጎ ለፌዴራል መንግሥቱ እና ለአባል
መንግሥታት የሚሰጡትን የሥልጣን ስፋትና ጥበት መሠረት አድርጎ ሕገመንግሥቱ የተማከለ ወይም
ያልተማከለ ፌዴራል ሥርዓትን እንደሚያሳይ ተደርጎ ይወሰዳል። የተማከሉ ፌዴሬሽኖች ከፍተኛ
ሥልጣን በሕገመንግሥቱ ለፌዴራል መንግሥት የሚሰጡ ሲሆኑ ያልተማከሉ ፌዴሬሽኖች ለአባል
መንግሥታት ከፍተኛ የሆነ የራስ ገዝ አስተዳደርና ነፃነት የሚሰጡ ፌዴሬሽኖች ናቸው።

በተለይ በሥልጣን ክፍፍሉ ወቅት ሁሉንም ሥልጣኖች ሕገመንግሥቱ በተቀረጸበት ወቅት ዘርዝሮ
መጨረስ ስለማይቻልና በየጊዜውም ከሚኖሩ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚዊና ፖለቲካዊ ለውጦች ጋር ተያይዞ
የሚፈጠሩ አዳዲስ መፈጸም ያለባቸውን ተግባራት ለመፈጸም ተግባራቱን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ
ሕጋዊ ሥልጣን ያለው አካል መኖር የግድ ስለሚል እንደነዚህ ያሉ ጉዳዮችን ለማስተናገድ በጥቅሉ ቀሪ
ሥልጣን በሚል ለአንዱ አካል በሕገመንግሥቱ ይሰጣል። ይህን ቀሪ ሥልጣን ለፌዴሬሽኑ አባል
መንግሥታት የሚሰጥ ሕገመንግሥት ያልተማከለ የፌዴራል ሥርዓትን ግብ ያደረገ ተደርጎ ይወሰዳል።
ቀሪ ሥልጣን ለፌዴራል መንግሥቱ የሚሰጥ ሕገ መንግሥት የተማከለ ፌዴራላዊ ሥርዓት የመረጠ
ተደርጎ ይወሰዳል። ሕገመንግሥታዊ የሥልጣን ክፍፍሉን መሠረት አድርጎ የተማከሉ እና ያልተማከሉ
ፌዴሬሽኖች የሚፈጠሩበት ሁኔታ ከላይ በተዘረዘረው መልክ የሚታይ ቢሆንም ዋናው ጉዳይ
የፌዴሬሽኖች ተግባራዊ እንቅስቃሴ እና በፌደሬሽኖቹ ውስጥ ያለውን መስተጋብር መሠረት አድርጎ
ፌዴሬሽኖች በተግባር የተማከሉና ያልተማከሉ የሚሆኑበት ሂደት ሰፊ የሆነ ፖለቲካ፣ማኅበራዊና
ኢኮኖሚዊ አመልካቾችን መሠረት አድርጎ የሚመላከትበት ሂደት ያለ ሲሆን ከአመልካቾችም መካከል
ለምሳሌ የፓርቲ ሥርዓቱ፣ የፌዴራል መንግሥቱና አባል መንግሥታቱ በራሳቸው የሚጥሉትና
የሚሰበስቡት ገቢና የሚያወጡት ወጪ መጠን፣ ክልሎች ከፌዴራል መንግሥቱ በሚያገኙት ድጎማ
የሚሸፈነው ወጪ መጠን ከአጠቃላይ ወጪያቸው፣ ክልሎች በራሳቸው የሚወስኑባቸው ጉዳዮችና
የሚያቀርቡት አገልግሎት ስፋት፣ ከፌዴራል መንግሥቱ የሚያገኙት ድጎማ ዓይነት (ጥቅል ድጎማ፣

19 | P a g e
በዓላማ የተገደበ ድጎማ) በጥቅሉ ፌዴሬሽኖች የተማከሉና ያልተማከሉ መሆን የንፅፅር ጉዳይ ነው እንጂ
ፍጹም የተማከለ እና ፍጹም ያልተማከለ ፌዴሬሽን የሌለ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው።

1.7. የፌዴሬሽኖች አፈጣጠር ሂደት፣


ፌዴሬሽኖች ከአመሠራረት አንፃር ቀደምት ነፃ የነበሩ የፖለቲካ ማኅበረሰቦች በጋራ አንድ ላይ
በማሰባሰብ ሰፊ ውይይት በማድረግ የጋራ ፖለቲካ ማኅበረሰብ ሲመሠርቱ ወደ አንድ የመጡ (coming
together) ፌዴሬሽኖች የሚባሉ ሲሆን በአንድ አሃዳዊና በተማከለ ሀገር የሚተዳደሩ የነበሩ አካላት
በጋራ የነበረውን ሀገረ መንግሥት ለማስቀጠል ሲወስኑና ፌዴሬሽን ሲመሠርቱ በአንድ ላይ የያዘ
(Holding together) ፌዴሬሽን ይባላሉ።

የፌዴሬሽኖች አመሠራረት ሁለቱንም ባህሪያት በያዘ መልኩም የተወሰኑት አባል መንግሥታቱ ወደ


አንድ በመምጣትና ቀደም ሲል አሐዳዊ የነበረ ሥርዓት በመፍረሱ ወደ አንድ ከመጡት ጋር በመቀላቀል
ሁለቱ ሂደት በአንድ ፌዴሬሽን አመሠራረት የሚታይበት አጋጣሚዎችም አሉ፣፣ ለዚህ እንደ ምሳሌ
የካናዳን እና የህንድ ፌዴሬሽን አመሠራረት ሂደት መውሰድ ይቻላል።ከእነዚህ ልዩነቶች በተጨማሪም
ፌዴሬሽኖች በቆዳ ስፋታቸው፣ በሕዝብ ብዛታቸው፣ የፌዴሬሽን አባል መንግሥታት ቁጥር፣ የኢኮኖሚ
አቅማቸው፣ ገቢ ማመንጨትና የማሰባሰብ አቅም፣ የመፈጸም ብቃትና አቅማቸው የተለያዩ ናቸው።
አንዳንድ ፌዴሬሽኖች በጣም ሰፊ የቆዳ ስፋት ያላቸው ናቸው። አንዳንዶቹ ፌዴሬሽኖች ደግሞ
በጣም ትንሽ የሆነ የቆዳ ስፋት ያላቸው ናቸው። ፌዴሬሽኖች ከሕዝብ ብዛት አንጻርም የተለያዩ
ናቸው። አንዳንድ ፌዴሬሽኖች የሕዝብ ብዛታቸው በጣም ብዙ የሆኑ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ በጣም
ትንሽ ቁጥር ያላቸው ናቸው። ለአብነት ያህልም ህንድ ከአንድ ቢሊዮን በላይ ሕዝብ ሲኖራት ሴንት
ኪትስና ኔቪስ ያላት የሕዝብ ብዛት 64000 ብቻ ነው። ከህንድ ግዛቶች አንዷ የሆነችው ኡታ ፕራድሻ
160 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ሲሆን ኔቪስ 12 ሺህ የሕዝብ ብዛት ብቻ አላት። ከፌዴሬሽን መሥራች
አባላትም ቁጥር አንፃር ሁለት አባል መንግሥታት ያላቸው እንዲሁም ከሁለት በላይ ያላቸው በሚል
ይለያያሉ። አንዳንድ ብዙ የአባል መንግሥታት ያላቸው ሰፊ ፌዴሬሽኖች እስከ 89 የሚደርሱ አባል
መንግሥታት አላቸው። ሩሲያ 89 አባል መንግሥታት ሲኖራት አሜሪካ ደግሞ 50 ስቴቶች እንዲሁም
ሴንት ኪትስና ኔቪስ ደግሞ ሁለት አባል መንግሥታት ብቻ አላት (ዋትስ 1996)።

IV. 1.8 ማጠቃለያ፣


በዚህ ክፍል ፌዴራሊዝም አንድ ማኅበረሰብ እንደ አንድ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ማኅበረሰብ በጋራ
መቀጠልን እና አንድ ትልቅና ጠንካራ ሃገር በመመሥረት ትልቅ ሃገር ከመሆን ጋር ተያይዞ የሚገኙ ዕድሎችን
ለመጠቀም እና ትልቅ ሀገር ከመሆን ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ለማስወገድ፣ እንዲሁም

20 | P a g e
ትንሽ ሀገር ከመሆን የሚገኙ ዕድሎችን ለመጠቀም እና ተግዳሮቶችን ለማስወገድ የራስ እና የጋራ አስተዳደር
መርሆዎችን መሠረት ያደረገ አስተሳሰብ ሲሆን ይህን አስተሳሰብ መያዝ፣ ማድነቅ እና አስተሳሰቡ በተጨባጭ
ፖለቲካዊ አደረጃጀት እንዲገለጽ መደገፍን የሚያጠቃልል ፍልስፍና ነው። ፌዴራሊዝም ለሰው ልጆች በጋራ
ለመኖር እና የጋራ ጉዳዮቻቸውን በጋራ የግል ጉዳዮቻቸውን በግል ለመተግበር ጠቃሚ የሆኑ እሴቶች ያሉትና
እነዚህን እሴቶች መላበስ ለአስተሳሰቡ በተግባር መተርጎም ወሳኝ መሆናቸው በዝርዝር ቀርቧል። ፌዴራል
ፖለቲካዊ ሥርዓት የሥልጣን ክፍፍልን መሠረት አድርጎ የሚፈጠር የፖለቲካ ሥርዓት መሆኑን እና ሥርዓቱ
የተለያዩ ሥልጣን ክፍፍሎችን መሠረት ባደረጉ የመንግሥት አወቃቀር ዓይነቶች ተግባራዊ እንደሚሆን
የፌዴራል ፖለቲካዊ ሥርዓትን የሚጋሩ የተለያዩ መንግሥታት አደረጃጀት ዓይነቶችና ባህሪያቶቻቸው
በዝርዝር ቀርበዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በዚህ ክፍል ፌዴሬሽን የሚለውን የፌዴራል ፖለቲካል ሥርዓት አደረጃጀት
ባህሪያት በዝርዝር የተመለከትንበት ነው። ይህ የፌዴሬሽን ቅርጽ ያለው የፌዴራል ሥርዓት
የተፈጠረው ሳይታሰብ 1789 በሰሜን አሜሪካ እንደሆነ ይወሰዳል። በወቅቱ አሜሪካኖች ከእንግሊዝ ቅኝ
ግዛት ነጻ ከወጡ በኋላ ፈጥረውት የነበሩት የኮንፌዴሬሽን ቅርጽ ያለው አደረጃጀት አላሠራቸው ስላለ
ይህን ለማሻሻል በፊላደልፊያ ተሰብሰበው ሲመክሩና ሰፊ ውይይት ሲያደረጉ ቆይተው የኮንፌደራሉ
መንግሥት የጋጠሙትን እጥረቶች የሚፈታ ጠንካራ ሀገራዊ/ የፌዴራል መንግሥትና የኮንፌዴሬሽኑ
አባል የነበሩ መንግሥታት የነበራቸውን ራስን በራስ የማስተዳደር ሥልጣን የማይጋፋ አደረጃጀት
ለመፍጠር በሠሩት ሥራ የተፈጠረ ሁለት ጠንካራ መንግሥታትን የያዘ አንድ ፌደራል ሪፐቢሊክ
መፍጠር የቻሉና ስያሜውም ፌዴሬሽን የሚል ሆኖ የተፈጠረ ነው።

በመሆኑም አሜሪካ ዘመናዊ የሆነው የፌዴሬሽን ቅርጽ ያለው የፌዴራል ሥርዓት የጀመረበት ሀገር
ተደርጋ ትወሰዳለች( በርገስ 2006)፣፣ ፌዴሬሽን የሚለው የፌዴራል ፖለቲካ ሥርዓት ይህን የወል ስም
እንዲያገኝ ያስቻሉትን የጋራ ባህሪያቱን በዝርዝር በዚህ ክፍል የቀረበ ሲሆን ፌዴሬሽኖች የከባቢያዊ
ነባራዊ ሁኔታ ውጤቶች እንደመሆናቸው አንድ እና ያው አይደሉም፣፣ በመሆኑም ፌዴሬሽኖች
የሚለያዩባቸው ጉዳዮች በዝርዘር ታይተዋል። ስለሆነም ይህን ጉዳይ በውል መረዳት በሀገራችን
ከምንከተለው የፌዴራል ሥርዓት ጋር ተያይዞ የተስተካከለ አረዳድ እንዲኖረንና በሥርዓቱ ትግበራ
የሚጋጥሙ ችግሮችን በየወቅቱ ሥርዓቱን በሚያጠናክር መልኩ እየፈቱ ለመሄድ ያግዛል ተብሎ
ይታመናል።

21 | P a g e
ክፍል ሁለት፣ ሕብረብሔራዊ ፌዴሬሽኖች፣

የመወያያ ጥያቄዎች፡- ሕብረብሕራዊነት ማለት ምን ማለት ነው? የሕብረ ብሔራዊ


ፌዴሬሽኖች ዋና መገለጫቸው ምንድን ናቸው? ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ
ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት እንዴት ታዩታላችሁ? ተወያዩበት?

V. -

2.1. መግቢያ፣
ሕብረብሔራዊ ፌዴሬሽን ብሎ ማለት በአንድ ሀገረ መንግስት ወሰን የተለያዩ
ብሔሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች የራስ እና የጋራ ጉዳዩቻቸውን አጣምረውና በየጊዜው
አመዛዝነው ለመኖር የሚመሠረቱ አደረጃጀት ነው። ሕብረብሔራዊ ፌዴሬሽኖች
ብሔሮች አብላጫ ቁጥር ይዘውና ተያያዥነት ባለው መልካዓ -ምድር ሰፍረው
በሚገኙበት ቦታ በአንድ በኩል ራስን በራስ የማስተዳደር ሥልጣን የሚያገኙበትና በሌላ
በኩል ደግሞ እንደ ሃገር በጋራ አስተዳደር ተሳታፊ የሚሆኑበትን እድል አደረጃጀትም
ነው፡፡ የፌደሬሽኖቹ ዋነኛ እሳቤም ልዩነቶችን ባከበረ መልኩ ጠንካራ ሀገር ለመገንባት
ብዝኃነት ባለበት ሀገር ውስጥ ሕብረብሔራዊ ፌዴሬሽን የተሻለ አማራጭ ነው የሚል
ነው።

በዚህ ክፍል ሕብረብሔራዊነት፣ ሕብረብሔራዊ ፌዴሬሽን፣ ከሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት


ጋር ተያይዞ የሚነሱ ሦስት ዋና ዋና የሆኑ አከራካሪ ጉዳዮች፣ ሕብረብሔራዊ ፌዴራሊዝም መድኃኒት ወይስ
እርግማን በሚል የሚነሱ ሀሳቦች፣ ሕብረብሔራዊ የሆኑ ሌሎች ፌዴሬሽኖች ሕብረብሔራዊነትን እና

22 | P a g e
ብዝኃነትን የሚገልጹበት መንገድ፣ ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት እና የሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ

እንመለከታለን።

2.2.ሕብረብሔራዊነት እና ሕብረብሔራዊ ፌዴሬሽን፣


ሕብረብሔራዊነት ሁለት ቃላትን አጣምሮ የያዘ ሀረግ ነው። ሕብር እና ብሔራዊነት።
ሕብር የሚለው ቃል ብዙ፣ መልከ ብዙ፣ ዓይነት ብዙ፣ የተለያዩ ቀለሞችን የሚያመላክት
ሲሆን፣ ብሔር የሚለውን (ጉብናወር 1999) በሚከተለው መልኩ ገልጾታል፣፣ “ብሔር አንድ ማኅበረሰብ ነን
የሚል እሳቤ ያላቸው፣ የሚጋሩት የጋራ ባህል በግልጽ ከሚታወቅ መልክዓምድር ጋራ ራሳቸውን የሚያያይዙ፣
ያለፈ የጋራ ጉዳይ እና የወደፊት የጋራ ፕሮጀክት አለን ብለው የሚያስቡና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ

ያላቸው ሰዎች የተሰባሰቡበት ቡድን ነው»፣፣ ሕብረብሔራዊነት ሲባል ደግሞ ብዙ ወይም

የተለያዩ ብሔሮች በአንድነት በጋራ መኖርን የሚገልፅ ነው።

ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ሕብረብሔራዊ የሆኑ ማኅበረሰቦችን ለማስተዳደር ብሔሮች በሰፈሩበት


ተያያዥ በሆነ መልክዓምድር ላይ ለብሔሮች የራስን ገዝ አስተዳደርን ማደራጀትና በሃገር ደረጃ በአንድ ሀገራዊ
ፌዴራላዊ መንግሥት ማዕቀፍ በጋራ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎን ማረጋገጥን መሠረት ያደረገ ፌዴራላዊ
አደረጃጀት ነው። ሕብረብሔራዊ ዴሞክራሲ በአንድ ሐገረ መንግሥት ውስጥ ራሳቸውን እንደ አንድ ብሔር
አድርገው የሚወስዱ ማኅበረሰቦች ከመኖር ጋር ተያይዞ የእነዚህ ማኅበረሰቦች ፍላጎትና ጥያቄ ዴሞክራሲያዊ
በሆነ መንገድ ለማስተናገድ የሚካሄድበት ዴሞክራሲያዊ ሂደት ነው።

በሌላ መልኩ ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ማለት የቡድን ማንነት መገለጫዎች በሥርዓቱ

መሠረታዊ የፖለቲካ አስተሳሰቦችና የመንግሥት አወቃቀሮች የሚንፀባረቁበት ነው። የቡድን

ማንነት መገለጫዎች የሚባሉት ደግሞ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ታሪካዊ

መሰረት፣ ማኅበራዊ መስተጋብር ወዘተ. ናቸው። ስለሆነም ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት

ብዝኃነትንና ሕብረትን በማጣመር አንድነትን የሚያስቀጥል ሥርዓት ነው።

ብዝኃነት ማለት በአንድ ሃገር ውስጥ በተለያዩ ማንነቶች የሚገለፁ የተለያዩ ቡድኖች ግልፅ
በሆነ አሰፋፈር ወይም ታሪካዊ ምንጭ ተካተው ሲገኙ ነው። ሕብረት ማለት ደግሞ ብዝኃነትን
በማክበርና በጋራ ጥቅምና ፍላጎት ላይ በመመሥረት አብሮ የመቀጠል ውሳኔ ወይም ስምምነት
ማለት ነው።
23 | P a g e
ብዝኃነትንና ሕብረትን ለማስቀጠል ደግሞ ከብዝኃነት የሚመነጩ ነገር ግን በሕብረት
የሚሟሉ ፍላጎቶች መኖራቸው የግድ ይላል። በተጨማሪም ለጋራ ጥቅም ሲባል የተከወነ
የጋራ ታሪካዊ ፍፃሜም መኖርን ይሻል። በተጨማሪም የባህል፣ የቋንቋ፣ የሃይማኖት፣
የአሰፋፈር፣ የገበያና የንግድ፣ እንዲሁም ሰፋ ያለ ማኅበራዊ ትስስርና መወራረስ መኖር
ብዝኃነትንና ሕብረትን ለማስቀጠል እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መስተጋብሮች ናቸው። ስለሆነም
ሕብረብሔራዊ ፌዴራሊዝም በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ሕብረት ወይም አንድነትና
ማንነቶች የሚጎለብቱበት ውህድ ነው።

ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓትን ለመገንባት አስፈላጊ የሆኑ የጋራ ፍላጎቶች መኖር አለበት።
በተለይም ሰፊ ገበያ፣ ጠንካራ የመከላከያ ኃይል፣ በዓለም አቀፍ ግንኙነት ጠንካራ
የዲፕሎማሲና የመደራደር አቅም፣ ጠንካራ የንግድ ልውውጥ አቅምና የመሳሰሉት መኖር
ጠንካራ የሆነ ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓትን ለመገንባት አስፈላጊ ናቸው። በሌላ በኩል
ደግሞ የጋራ ማንነት መገለጫዎች በተለይም የጋራ ዜግነት፣ የጋራ ሰንደቅዓላማ፣ የጋራ ታሪካዊ
ፍፃሜ፣ ከአብሮነት የሚመነጭ የጋራ ሀገራዊ ስሜት፣ ወዘተ…መኖር ለሕብረብሔራዊ
ፌዴራል ሥርዓት ስኬት ወሳኝ ናቸው።

2.3. የሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት መርሆዎች፣


ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓትን በሚተገብሩ ሀገራት ውስጥ ሊጣሱ የማይገባቸው

መርሆዎች አሉ። እነዚህም መርሆዎች የቃል ኪዳን ማሰሪያ የሆነ ሕገመንግሥት መኖርና
መከበር፣ በስምምነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ ሕብረት መኖር፣ ብዝኃነት የሚያንፀባርቅ
የፖለቲካ አወቃቀር በማዕከልና በክልሎች መከተል፣ መከባበር፣ መቻቻል፣ መደጋገፍ ወይንም
በጋራ የመኖር እሴቶችን ማጎልበት፣ ወዘተ ናቸው።

በጥቅሉ ይህ የፌዴራላዊ አደረጃጀት ባለብዙ ብሔር በሆኑ ሀገራት ብዝኃነትን እና ከዚያ ጋር ተያይዞ የሚኖሩ
የፖለቲካ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶችን በአንጻራዊ ሁኔታ በተሻለ መልኩ ለማስተዳደር ብሔሮች
በሰፈሩበት መልክዓምድር ራሳቸውን የማስተዳደር ሉዕላዊ ሥልጣን መስጠት እንደ አንድ የተሻለ አማራጭ
የሚወሰድ ነው። ሆኖም ከአደረጃጀቱ ጋር የተያያዙ አከራካሪ የሆኑ ጉዳዮች ያሉ ሲሆን ከነዚህ አከራካሪ
ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ሰፊ የፖለቲካ እና አካዳሚክ ውይይቱ ሲደረግበት ቆይቷል፤ አሁንም እየተደረገበት
ይገኛል።
24 | P a g e
በሚካሄዱ የፖለቲካም ሆነ አካዳሚክ ውይይቶች አደረጃጀቱ ሕብረብሔራዊ ለሆኑ ሃገሮች የሚያስገኘውን
ጠቀሜታ የበለጠ አጉልተው የሚያሳዩም ሆነ ተግዳሮቶቹን አጉልተው የሚያሳዩ የአስተሳሰቡ ደጋፊዎችም ሆነ
ነቃፊዎች ያሉ ሲሆን ነቃፊዎቹም ሆኑ ደጋፊዎች ጉዳያቸውን ለማሰረዳት የሚያቀርቧቸው ምሳሌዎች
የየራሳቸውን አስተሳሰብ የሚደግፉ የተመረጡ ሀገሮችን ብቻ በመሆኑ የጥናት ዘዴያቸው ላይ ውስንነት
እንዳለባቸው ይጠቆማል( ኮስለር 2018)።

በሥርዓቱ ለብሔሮች ሕገመንግሥታዊ ዕውቅና መስጠትና ተያያዥ በሆነ መልክዓምድር ለሰፈሩ ብሔሮች
የራስን በራስ ማስተዳደር ሥልጣን በፌዴራል ደረጃ የጋራ አስተዳዳር በመመሥረት ብዝኃነትና አንድነትን
አመጋግቦ ለመሄድ በራሱ በቂ ስለማይሆን ሕብረብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት ውጤታማ የሚሆንበት ሆነ
ለችግር የሚጋለጥበት ከሕገመንግሥታዊ ድንጋጌው በዘለለ ብዙ የሀገራቱ ነባራዊ ሁኔታዎች ወሳኝ መሆናቸው

ይገለፃል። ሃገራት በውስጣቸው ላሉ ብሔሮች ራስን በራስ አስተዳደር በሚሰጡት ዕውቅና

እና የፌዴሬሽኑ አባል የሆኑ መንግሥታት አንዱ ወይም ከዚያ በላይ ቋንቋን፣ ባህልን
ወይም ሌላ የብሔር መገለጫዎችን መሠረት አድርጎ የተደራጁ ከሆኑ እንደነዚህ ያሉ
ፌዴሬሽኖች ሕብረብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ይባላሉ (ሃል 2004 )፣፣

2.4 የኢትዮጵያዊያን ህብረ ብሄራዊነትና የአንድነት መሰረት ማህበረ ባህላዊ ውቅሮች


የኢትዮጵያ ህዝቦች ባሳለፉት በርካታ ዘመናት በተከናወኑ ከፍተኛ የህዝቦች እንቅስቃሴ
በመነጨ እጅግ የተጋመደና የተዋሀደ ድርብ ድርብርብ ማንነትን ፈጥረዋል፡፡ ለህብረ
ብሄራዊነት መሰረቶች የሆኑ ማህበረ ባህላዊ እሴቶችና ታሪካዊ ክስተቶችን በተመለከተ
ዶናልድ ሌቪን(1974) እንደሚከተለው ያብራራል፡፡ እነሱም አንደኛ ልዩ ልዩ የኢትዮጵያ
ህዝቦች ባለማቋረጥ የእርስ በእርስ ግንኙነት የማድረጋቸው ሂደት ሁለተኛ በርከት ያሉ
ሀገር አቀፍና ኢትዮጵያን መሰል የሆኑ የወል የባህል ቅርሶች መኖር( ለምሳሌ ባህላዊ
የግጭት አፈታት ስርዓቶች፣ባህላዊ በዓላት፣ቅርሶች) አንዲሁም በየግዜው የውጭ ኃይል
በአገሪቱ ላይ ጣልቃ ለመግባት በሚቃጡበት ጊዜ ለመከላከል አብረው በጋራ መቆማችው
እንደሆነ ያብራራል፡፡ በታሪክ የነበሩት የንግድ እንቅስቃሴ ሲራራ
ንግድ፣እምነቶች፣ቋንቋዎች (አፍሮ እስያዊ፣ኒሎ ሰሃራ)፣ገበያዎች ህዝቦቹን ከአንድ ማንነት
በላይ ሄደው አስተሳስረዋል፡፡ የአኗኗር ዘይቤያችን( እርሻ፣እንሰት፣ከብት እርባታ)ም እንዲሁ

25 | P a g e
የሀገራችንን ህዝቦች ልዩነታቸው እንደተጠበቀ የሚያስተሳስሩ ድርና ማግ መሆናቸውን
ምሁራን ይገልጻሉ፡፡ በተጨማሪም ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶቻችን ለአብነትም
አበልጅ፣አይን አባት፣ጉዲፈቻ፣የክርስትና
አባት፣ጉርብትና፣እድሮች፣እቁቦች፣ጌዝ፣ወንፈል፣መድረሳ፣የቄስ ትምህርት ቤት፣ለመንግስት
ያለን እሳቤዎችም እንዲሁ የሀገራችን ድንቅ ሶፍት ሀይል ናቸው፡፡ እነዚህ እሴቶች
ለህብረ ብሄራዊ ማህበረሰብና ለስርዓቱ ግንባታ መሰረት በመሆን ያገለግላሉ፡፡የሀገራችንን
ህዝቦች ከአንድ እምነት፣ቋንቋ፣ቦታ፣ብሄር..በላይ የሚያስተሳስሩትን እነዚህን ማህበረ
ባህላዊ እሴቶች ጎልተው እንዲወጡ መስራት፣ከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎቻቸው እነዚህ
ሀገር በቀል ተቋማት በታሪክ ያለቸው ሚናን እዲገነዘቡ በውይይት፣በድራማ፣በስነ ጽሁፍ
እንዲያውቁ እንዲገነዘቡ ማድረግ ለዘላቂ ሰላማችንና ለሀገራ መንገስት ግንባታ ተግባራት
እጅግ ወሳኝ ነው፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች፡- ከሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ጋር ተያይዞ የሚነሱ


አከራካሪ ጉዳችን ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ችግሮችና
መፍትሄዎቻቸው ላይ ተወያዩ፣

2.5. ከሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ሶስት ዋና ዋና የሆኑ አከራካሪ


ጉዳዮች፣
የሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ አደረጃጀቶች ጋር ተያይዞ ይህን ፌዴራላዊ አደረጃጀት የሚከተሉ ሀገራት
የመንግሥት መፍረስ (state disintegration)፣ የፖለቲካ ዋልታ ረገጥነት (political polarization)፣ የውስጥ
ህዳጣን ቡድኖች (internal-minorities) መብት አለመከበር ጋር ተያይዞ ችግሮች ይገጥማቸዋል የሚሉ የንድፈ
ሀሳብና አንዳንዴም ከተሞክሮ የሚነሱ ክርክሮች በዘርፉ አጥኝዎች ይካሄዳሉ። በመሆኑም የክርክሩን ጭብጥና
የሚቀርቡ የመፍትሔ ሃሳቦች በዝርዝር ማየት በሀገራችን ለሚገነባው ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት
ችግሮችን ዝርዝር ባህሪያትና መፍትሄ አቅጣጫዎችን በመረዳት ችግሮቹን ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታውን መሠረት

26 | P a g e
አድረጎ ለመፈተሽና መፍትሄ እየሰጡ የሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓቱን ሁሉም የኔ ነው በሚለው መልክ
እያጎለበተ ለመሄድ ጠቃሚ በመሆኑ እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርቧል።

2.5.1 የመንግሥት መፍረስ (state disintegration)፣


ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት አሁንም የማይናቅ ሕዝባዊ ተቀባይነት ያለው ቢሆንም፣ በጊዜ ሂደት ዋነኛ
አከራካሪ የሆኑ ጉዳዮች ተሰንዝረውበታል። በአንድ ቡድን ሊጠቃለሉ የሚችሉ አጥኝዎችና የፖሊሲ
አውጪዎች ጽንሰ ሃሳብን ተግባራዊ ማድረግ፣ ተግባራዊ ለሚያደርጉት መንግሥታት መፍረስ መረማማጃ
የሚሆን ድንጋይ እንደማስቀመጥ ይቆጠራል የሚል ነው። ዋናው የሃሳባቸው ማጠንጠኛ ሕብረብሔራዊ
ፌዴራሊዝም መገንጠልን ያበረታታል፤ ጽንሰ ሃሳቡ ብሔርን መሠረት አድርገው ለተመሠረቱ ክልሎች ጠቃሚ
የሆኑ ማበረታቻዎችን እና የፖለቲካል አቅም /ሀብት / በማቅረብ የመገንጠል ሙከራና ተግባር እንዲፈጽሙ
ያደርጋቸዋል። በተመረጡ የፖሊሲ መስኮች ቀላል የማይባል ሥልጣን ያለው ራስ ገዝ የሆነ የክልል
ፓርላሜንት፣ ፈጻሚ አካልና ፐብሊክ ሰርቪስን በቀላሉ ወደ አንድ ራሱን የቻለ ነፃ መንግሥት ብሔራዊ
ተቋማት መቀየር ይቻላል።

ከዚህም በተጨማሪ በብሔር ላይ የተመሰረቱ የክልል መንግሥታት በነሱ ሥልጣን ሥር የሚገኙ ወሳኝ የሆኑ
የባህል፣ የቋንቋ፣ የትምህርትና የሚዲያ ጉዳዮች አሁን ከሚገኙበት መንግሥት እሳቤ በዘለለ የብሔረ
መንግሥት መመሰረቻ ፕሮጀክት አድርገው ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

ሌላው ጉዳይ በሕብረብሔራዊ ፌዴሬሽን ሁኔታ ብዙ የከባቢያዊና የህዳጣን ፓርቲዎች የሚፈለፈሉበት እድል
ሰፊ በመሆኑና እነዚህ ፓርቲዎች ከቅርብ ጊዜም ሆነ ከረጅም ጊዜ አኳያ ካላቸው ፖለቲካዊ እምነት ወይም
ከፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ የግል ፍላጎት በመነሳት የመገንጠል ጥያቄ ማቅረባቸው እንደማይቀር
ያስረዳሉ(ሲንደር 2000)፣፣

በመሠረቱ መንግሥታት ብዙውን ጊዜ መገንጠልን በጥርጣሬ ስለሚመለከቱትና ማንኛውም መንግሥት ራሱን


ማስቀጠል ከራሱ ተፈጥሮ የሚመነጭ ፍላጎት ያለው በመሆኑ ይህ እይታ መፈጠሩ የሚጠበቅ ነው። ጉዳዩም
ከብሔረ መንግሥት (nation-state) እሳቤዎች ጋር ተያይዞ የሚታይም ነው። በብሔረ መንግሥት እሳቤዎች
በብሔረ መንግሥቱ ውስጥ የሚኖሩ ማኅበረሰቦች የሚያነሱት የብሔር ጥያቄ፣ የብሔር ዕውቅና ለመስጠት ይቃወማሉ
ዕውቅና መስጠቱ ቀስቃሽ፣ በብሔረ መንግሥቱ ላይ ክህደት የመፈጸም አድርገው ይመለከቱታል፣፣ መነሻ እሳቤውም
በሀገረ መንግሥቱ አንድ ብሔር ነው ያለው፣፣ ይህም ሁሉም ዜጎች የሚጋሩት ብሔር ነው የዜግነት
ሕጉም ማን የብሔረ መንግሥቱ አባል እንደሆነ ማን እንዳልሆነ ድንበር ያስቀምጣል፣፣

በመሆኑም ሕገ መንግሥት የሚቀርጹ ሰዎች ከዚህ ጉዳይ የመራቅ ዝንባሌን ያሳያሉ። ምክንያቱም
የሚያረቋቸው አንቀጾች ራሱን የሚቀርጹትን ሕገ መንግሥት የሚያፈርሱ እንዳይሆን በመስጋትና

27 | P a g e
የሜድሶኖዊያን ፖለቲካል አስተሳሰብ "የሕገ መንግሥት ትልቁ ተግባሩ ራሱን ማስቀጠሉ ነው" በመባል
የሚታወቀውን እሳቤ በመመራት ሕገመንግሥቱን ራሱን ሊያፈርሱ ከሚችሉ አንቀጾች መቆጠብ ይመርጣሉ።

ሌላው የሀገር አንድነትን ከማጣት ጋር ተጨማሪ ሆኖ የሚመጣው ጉዳይ የመንግሥታት መፈራረስ ያለ ሰፊና
ከፍተኛ ግጭት የሚከናወንበት አግባብና አጋጣሚ ውስን መሆኑ ነው። በተግባርም የተወሰኑ ፌዴሬሽኖች
የዌስትኢንዲስ ፌዴሬሽን(1962)፣ የሮዴሽያና ኒያሳላንድ ፌዴሬሽን(1963) የቸኮዝሎቫኪያ ፌዴሬሽን( 1993)
በአብዛኛው በሰላማዊ መንገድ መፍረስ ችለዋል(ዋትስ 2007)። መንግሥታት አንዳንዴ ተገቢ ከሆነው ስጋት
የሃገርን አንድነትንና ሰላምን ከማስጠበቅ ባለፈ መልኩ ብዙውን ጊዜ ታሪካዊ ከሆኑ ምክንያቶች ጋር በማያያዝ
ይህን ዓይነት የፌዴራል አደረጃጀትን በበጎ አለማየት ይታይባቸዋል። ለምሳሌ በመሃልና ምሥራቅ አውሮፓ ያሉ
ሃገሮች ኮሚኒስት ባለብዙ ብሔር ፌዴሬሽኖች መፍረስና የሌኒን እሳቤ በጉዳዩ ላይ የፈጠረውን ተጽእኖ
በማየት ራስ ገዝ ለሚለው ጽንሰ ሃሳብ ጤነኛ የማይመስል ጥላቻ የያዙበት ሁኔታ የተፈጠረበት ሁኔታ ይታያል
(ፓሌርሞ 2012)።

በሌላ እይታ ብዙዎቹ የሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ደጋፊዎች መገንጠል አደጋ መኖሩን ባይክዱም
ከመነሻው ብሔሮችን መሠረት አድረገው የተዋቀሩ ዩኒቶች በቂ የራስ ገዝ ሥልጣን ማግኘታቸው መገንጠልን
እንዳያስቡና ሀገራዊ አንድነቱን ለማስቀጠል ፍላጎት እንዲያድርባቸው ያደርጋቸዋል። በዚህ ዕይታ
ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓትን የሚደገፉ ተመራማሪዎች ጽንሰሃሳቡን እንደ ተቃርኖ ያዩታል። በአንድ
በኩል ህዳጣን ለሆኑ ብሔሮች ከመገንጠል የተሻለ የሚሠራ አማራጭ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ መገንጠልን
ተጨባጭ የሆነ አማራጭ የሚሆንበትን ሁኔታ ይፈጥራል(ኪሚሊካ 1998)። በሌላ አገላለጽ ሕብረብሔራዊ
ፌዴራሊዝም ህዳጣን ብሔሮች ለመገንጠል የሚኖራቸውን አቅም የሚጨምር የመገንጠል ፍላጎታቸውን ግን
የሚቀንስ ተደርጎ ይታያል። የፌዴራል ሥርዓትን ለውድቀት የሚያበቁ ምክንያቶችን በቀላሉ በንድፈሃሳብ
ደረጃ ማስቀመጥ ባይቻልም በግልጽ በመንግሥት መፍረስና አለመቀጠል ካልታየ በቀር፣ ሕብረብሔራዊ
ፌዴራል ሥርዓቶች ከሌሎች ፌዴራል ሥርዓቶች ለመውደቅ የበለጠ የተጋለጡ ተደርገው ይወሰዳሉ። ሆኖም
በደንብ ሊተኮርበት የሚገባ ጉዳይ ሕብረብሔራዊ የሆኑ ሀገሮች ለችግሮቹ የሚጋለጡት ፌዴራል ስለሆኑ
ሳይሆን ፌዴራል የሆኑ ችግሮችን በአግባቡ ስለማይፈቱና አሃዳዊ ሥርዓት የማይሆን አማራጭ ስለሆነባቸው
ነው (ዋትሰ 2007)።

2.5.2 ፖለቲካዊ ዋልታ ረገጥነት (political polarization)፣


ሌላው ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ላይ የሚነሳው ትችት ብሔሮችን መሠረት ያደረገ መልክዓምድራዊ
አደረጃጀት በብሔሮች መካከል ያለ ልዩነትን ዘላቂ ሆኖ እንዲቀጥል በማድረግ ዋልታ ረገጥ የሆነ የፖለቲካ
አካሄድ አግባቦች እንዲጎለብቱ ያደርጋል የሚል ነው። ይህ ጉዳይ ቀደም ብሎ ካየነው የመገንጠል ጉዳይም
በተወሰነም መልኩ ተያይዞ ሊታይ የሚችል ሲሆን እይታውም በአንድ መልኩ የተማከለ ሃሳብ በሚያቀነቅኑና

28 | P a g e
በሌላ በኩል ደግሞ የልዩነት ሃሳብን በሚያቀነቅኑ ሁለት ዋልታ ረገጥ ሀሳቦች የቀን ተቀን የፖለቲካውን መድረክ
ይቆጣጠሩትና በዚህ አውድ ውሰጥ በቀን ተቀን የሚካሄድ የተለመደ ነባራዊ ሁኔታንና መግባባትን መሠረት
ያደረገ ፖለቲካን በእጅጉ ሊገድቡት ይችላሉ። ይህን በትንቅንቅ ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ዳይናሚክስ
እንዲኖር የሚያነሳሳው ምክንያት በሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ሕጋዊ በሆነ መልኩ ለሁለት
ለሚወዳደሩ የብሔረ መንግሥት ፕሮጀክቶች ዕውቅና ስለሚሰጥና የጋራ መንግሥቱ ከራስ ገዝ መንግሥቱ ጋር
ስለሚያፋጥጥ ነው (ሮደር 2009)፣፣

«ዋልታ ረገጥነት የመግባባት ባህል እንዳይኖር ያደርጋል» የሚለው ስጋት በኤላዛርም (1994) የተገለጸ ነበር።
የሱ ስጋት በብሔር ላይ የተመሠረተ ፌዴራላዊ ሥርዓት ብሔርተኝነቱ ሁሉንም ጉዳይ ለመግባባት ዝግጁ
ባልሆነ የብሔር መነጽር እይታ ውስጥ እንዲወድቅ በማድረግ ነጻ መንግሥት እንዳይኖርና ለዴሞክራሲ
መሠረት የሆነውን መደራደርና መግባባት እንዳይኖር በማድረግ ፌዴራል ሥርዓቱ ውጤታማ እንዳይሆን
ያደርገዋል። ፌዴራሊዝም በድርድርና በመግባባት ላይ የተመሠረተ መካከለኛ መንገድ ነው። ማንኛውም
ማኅበረሰብ ለመግባባት ዝግጁ እን ዳይሆን አጋዢ የሆነ ገጽታዎች ለፌዴራል ሥርዓት መኖር በጣም
አስቸጋሪ ይሆናሉ- የማይቻል እንኳ ባይሆንም (ኤላዛር 1994)።

ለዚህ ችግር እንደ መፍትሄ የሚወሰደው በሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ዋልታ ረገጥ አስተሳሳቦችን
ጨርሶ ማጥፋት ባይቻልም በአንድ ፌዴራላዊ ሥርዓት ተሳስረው ለመቀጠል የወሰኑ ብሔሮች ተወራራሽና
ተመጋጋቢ የሆነ ማንነትና እየገነቡ የመሄድ እና በአስተሳሰብ ደረጃም የራስንም ሆነ የጋራ አስተዳደር ሚዛናዊ
በሆነ መልኩ የመጠቀም እና ሁሌም ሚዛን ጠብቆ የመሄድ አስተሳሰብ በአብላጫው በፌዴሬሽኑ ውስጥ
በሚኖረው ማኅበረሰብ ውስጥ ተቀባይነትና ደጋፊ ያለው አስተሳሰብ እንዲሆን መሥራትን ይጠይቃል። ይህን
ማድረግ እሰከተቻለና የሚያጋጥሙ ችግሮች የፌዴራል ሥርዓቱን በሚያጠናክር መልኩ እየተፈቱ እሰከሄዱ
ድረስ የዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦች ዳር እና ዳር ላይ መኖር መሀሉ ሚዛናዊ አስተሳሰብ እሰከያዘ ድረስ የፌዴራል
ሥርዓቱ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ተግዳሮቶችን ለመወጣት ይችላል ተብሎ ይታሰባል።

2.5.3 የውስጥ ህዳጣን ቡድኖች (internal-minorties) መብት አለመከበር፣


ሌላው ከመገንጠል እና ከዋልታ ረገጥ ፖለቲካ ጋር አብሮ የሚነሳው ሦስተኛው ትችት ከአፈጣጠሩ ከመነሻው
መልክዓምድርና ብሔርን በጥብቅ ማቆራኘት ጋር ተያይዞ የሚታየው ክፍተት ነው። ጽንሰ ሀሳቡ ለብሔሮች
የሠፈሩበትን መልክዓምድር መሠረት አድረጎ ራስ ገዝ አስተዳደር ሲሰጥ ብሔሮች የሚገኙበት መልክዓምድር
አንድ ወጥ የሆነ አድርጎ በማየት በተግባር በመሬት ላይ የሚታየውን ብዝኃነት ግንዛቤ ውስጥ አላስገባም የሚል
ነው። አንዳንድ አጥኚዎች በንደፈ ሃሳብ ደረጃም ሆነ ከተግባራዊ አፈጻጸም በመነሳት በሕብረብሔራዊ
ፌዴራል ሥርዓት ይህ እጥረት እንደሚታይበት አጉልተው አሳይተዋል( ፓሌርሞ 2015፣ ኮስለር 2015)፣፣

29 | P a g e
ዋናው ነጥብ በይበልጥ የብሔርና መልክዓምድር ትስስር የጠነከረ ከሆነ የጽንሰ ሃሳቡ መነሻ ይኽው ስለሆነ
የበለጠ ብሔሩ የኔ ራስ ገዝ ክልል ነው ብሎ በሚያስተዳድረው ክልል ውስጥ የሚኖሩ የውሰጥ ህዳጣን
ማኅበረሰቦች የሚያገኙት የሕግ ዕውቅና ሆነ ጥበቃ በተሟላ መልኩ ላይሆን ይችላል። የዚህ አመክንዮ
በመልክዓምድሩ የራስ ገዝ ሥልጣን ያለው ብሔር ይህ መልክዓምድር እንደ የራሱ ራስ ገዝ ሥልጣን ተግባራዊ
የሚያደርግበት ክልል አድርጎ በመውሰድ ከህዳጣን ማኅበረሰቦች ጋር ለመጋራት ፍላጎት አያሳድርም። ተቃርኖ
በሚመስል መልኩ ሕብረብሔራዊ ፌዴራሊዝም በሀገር ደረጃ ለብዝኃነት ዕውቅና ቢሰጥም በክልሎች ደረጃ
ለብዝኃነት ዕውቅና ያልሰጠበት ሁኔታ ይታያል።

በአንድ በኩል ጽንሰሃሳቡ አሃዳዊ የሆነውን ብሔረ መንግሥት ለማስወገድ ከፍተኛ ተነሳሽነትን የሚያሳይ
ሲሆን በሌላ በኩል ይህንኑ ሞዴል ብሔረ ክልል በሚል ተክቷል። ስለሆነም በህዳጣን እና አብላጫ ባለው
ማኅበረሰብ መካከል ያለውን የግንኙነት ችግር ሀገራዊ ከሆነ መልኩ ወደ ክልላዊ ወደ ሆነ መልኩ ቀይሮታል።

ይህ ብሔርና መልክዓምድርን በጥብቅ ያቆራኘ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓት ባህሪ የሆነው ችግር ቀደም ብሎ
በካርል ሬነር ( 2005) በሚከተለው መልኩ የተለየ ጉዳይ ነው፣፣ "በኔ መልክዓምድር ውስጥ የምትኖር ከሆነ ለእኔ
ውሳኔዎች ተገዢ መሆን፣ ለኔ ሕግ ተገዢ መሆን፣ የኔን ቋንቋ መናገር፣ ይህ የአገዛዝ መገለጫ እንጂ የእኩልነት
መብት አይደለም"፣፣ ሬነር ችግሩን ከላይ በትምህርተ ጥቅስ በተቀመጠው መልኩ ከማብራራቱም በላይ ለዚህ
ችግር መፍትሄ ብሎ ያቀረበው ሀሳብ በሌላ ብሔር መልክዓምድር ውስጥ ለሚኖሩ ህዳጣን ማኅበረሰቦች
መልክዓምድር አልባ ራስ ገዝነት( non-territorial autonomy) መስጠትን ነው።

መልክዓምድር አልባ ራስ ገዝ አደረጃጀት አሁን ካሉ ተጨባጭ የሆነ መረጃዎች አኳያ ተግባራዊነቱ በጣም
ደካማ ሆኖ ታይቷል። ጽንሰ ሃሳቡ ለፖሊሲ አውጪዎች ማራኪ ከመሆንና ለችግሩ መፍትሄ ሰጥተናል ለማለት
ጥቅም ላይ ከመዋል የዘለለ ትርጉም ያለው አይደለም። በመሆኑም መልክዓምድር አልባ ራስ ገዝነት ትክክለኛ
ራስገዝነት አይደለም (ኮክሌ 2006)። ሆኖም እንደ አንድ አማራጭ መፍትሄ የየክልሉን ነባራዊ ሁኔታና የህዳጣን
ማኅበረሰቦችን አሰፋፈር መሠረት አድርጎ መጠቀም ችግሩን ለመፍታት አንድ ተጨማሪ መፍትሄ አድርጎ
ማየት ይቻላል።

ከመልክዓምድር አልባ ራስ ገዝነት በዘለለ በብሔረ ክልል ውስጥ የሚኖሩ የውስጥ ህዳጣን ማኅበረሰቦችን ችግር
ለመፍታት ሌሎች መፍትሄዎችን ማየት ተገቢ ነው። አንዱ መፍትሄ ሊሆን የሚችለው በብሔረ ክልሉ ላለው
አብላጫነት ላይ መሠረት ላደረገ እንቅስቃሴ ውጫዊ የሆነ ተጨባጭ የሆነ ወሰን ማስቀመጥ ይሆናል ይህ
ሲባል መሠረታዊ የሆኑ የሰው ልጅ መብቶችና ነጻነቶች /bill of rights/ ሰፋ ባለ መልኩ በፌዴራል /ሀገራዊ/
ሕገመንግሥቱ ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ የፌዴራል መንግሥቱ ህዳጣን ማኅበረሰቦችን በተመለከተ ጣልቃ
የሚገባበት ሥልጣን መስጠት፣ በሌላ መልኩ ውስጣዊ በሆነ መልኩ አብላጫ ድምጽን መሠረት አድርጎ ውሳኔ

30 | P a g e
የሚሰጥበትን አካሄድ ላይ ገደብ ማስቀመጥና ሥልጣን በክልል ደረጃ ለህዳጣን ቡድኖች በማጋራት በራሱ
በብሔረ-ክልሉ ሕገ መንግሥት መፍታት ይቻላል።

በአጠቃላይ ራስገዝነት በህዳጣን ብሔሮች ላይ የሚኖር ማግለልና ጭቆና ምላሽ ቢሆንም ራሱ በቀላሉ
ተመልሶ ሌሎችን ህዳጣን ቡድኖች የማግለያና የመጨቆኛ መሣሪያ ስለሚሆን ጉዳዩን በጥንቃቄና የሁሉንም
መብት በሚያከብርና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ መተግበር ይጠይቃል።

2.6. ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት መድኃኒት ወይስ እርግማን?


ስለ ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ጠቀሜታና ችግሮች የሚደረጉ ውይይቶች በከፍተኛ ሁኔታ ጫፍ
የወጡ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ደጋፊዎቹ እንደ መድኃኒት ሲያዩት የሚቃወሙት ደግሞ እንደ ርግማን
ያዩታል። ሆኖም ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት መድኃኒት ነው ወይስ እርግማን? የሚለውን ጥያቄ
በተሟላ መልኩ መመለስ የማይቻልና የሕገመንግሥታዊ ቅርጹን ብቻ ዐይቶ ይህ ነው ማለት አጠቃላይ ስዕሉን
ስለማይሰጥ ጉዳዩን በነባራዊ ሁኔታዎች የሚወሰን ነው ብሎ መውሰድ የተሻለ ነው።

የእያንዳንዱ ሀገር ነባራዊ ሁኔታ የተለያየ በመሆኑ ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት መድኃኒት ወይም
እርግማን የሚሆነው እነዚህ ነባራዊ ሁኔታዎች ሲኖሩ ነው ብሎ አጠቃላይ የሆነ ድምዳሜ ላይ መድረስ
ባይቻልም የፌዴራል ሥርዓቶችን ተሞክሮ እርስ በእርስ በማነጻጸር በተደረጉ ጥናቶች የሚከተሉት ነባራዊ
ሁኔታዎች ለሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ደጋፊና ችግር ሊፈጥሩ የሚችሉ ነባራዊ ሁኔታዎች ተደርገው
ይወሰዳሉ።

1 ኛ. አብላጫ ቁጥር ያለው ቡድን የሚያሳድረው ዴሞግራፊያዊ ተጽዕኖ ልዩነት ሊፈጥር የሚችል አንደ ነባራዊ
ሁኔታ ተደርጎ ይወሰዳል። የዚህ ሃሳብ አካሄድ ይህ ዓይነት ነባራዊ ሁኔታ አብላጫ ቁጥር ያለው ቡድን ህዳጣኑ
ቡድን የጠየቁትን ለመፍቀድ ይቀለዋል፤ ምክንያቱም ምንም ዓይነት በራሱ ላይ የመጣ ጉዳይ ላይመስለው
ስለሚችልና በኢኮኖሚም ሆነ በፖለቲካው ዘርፍ መገንጠልን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመከላከል ጠንካራ
አቅም እንዳለው ስለሚሰማው (ኦሌሪ 2001)። ከዴሞግራፊው ነባራዊ ሁኔታ በተጨማሪ ይህን ጉዳይ
በመልክዓ ምድራዊ አደረጃጀቱ እንዴት ይስተናግዳል የሚለውን ማየት ያስፈልጋል። ባለፉት ሦስት አስርት
ዓመታት የተደረጉ ጥናቶች እንደሚመላክቱት በአደረጃጀቱ ሕብረብሔራዊ የሆኑና ሁለት ብቻ የፌዴሬሽኑ
አባላት የሆኑ መንግሥታትን ያቀፉ ፌዴሬሽኖች (ድያዲክ ፌዴሬሽኖች) የተረጋጉና ቀጣይነት ያላቸው
እንደማይሆኑ አሳይተዋል። እነዚህ ሁለት አባል መንግሥታት አፍራሽ ወደ ሆነ ውድድር በመግባትና የሁለትዮሽ
ዋልታ ረገጥ የሆነ የፖለቲካ አሰላለፍ በመፍጠር ብዛት ያላቸው ክልሎች በአባልነት ያቀፉ ፌዴሬሽኖች ውስጥ
በክልሎች መካከል የተለያዩ ጉዳዮች ላይ መፈጠር የሚቻለውን ያህል የተለያዩ ትስስሮሽ መፍጠር

31 | P a g e
ስለማይችሉና በሁለቱ መካከል ያለ ክፍተትን ብቻ እያጎሉ ስለሚሄዱ ፌዴሬሽኑ የመፍረስ እድሉ አንጻራዊ
በሆነ መልኩ ከሌሎች ፌዴሬሽኖች በበለጠ ሰፊ የሚሆንበት አጋጣሚ እንደሚኖር ጥናቶች ያሳያሉ።

2. ሌላው ከሶሻል-ዴሞግራፊክ ልዩነት ጋር የሚያያይዘው የእነዚህ ልዩነቶች ለምሳሌ የብሔር፣የቋንቋ፣


የሃይማኖት ልዩነቶች አንዱን አንዱ የሚያቋርጥ ነው ወይስ ተሳስረው የሚሄዱ ናቸው የሚለው ጉዳይ ወሳኝ
ተደርጎ ይታያል። እነዚህ ልዩነቶች አንዱን አንዱ አቋርጦ በሚሄድባቸው ሕብረብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ለምሳሌ
የተለያዩ ብሔሮች ቢሆኑም በአብዛኛው ተመሳሳይ ሃይማኖት የሚጋሩ የተለያዩ ሃይማኖት ቢኖራቸውም
ቋንቋ የሚጋሩ፣ የተለያዩ ቋንቋ ቢኖራቸውም ሃይማኖትን የሚጋሩ ማኅበረሰቦች ያሉበት ሕብረብሔራዊ
ፌዴሬሽን የመቀጠል እድሉ ሰፊ ተደርጎ ይወሰዳል።

3. የፌዴራል ሥርዓቱ ሲመሠረት የነበሩ ታሪካዊ ሂደቶችም የራሳቸው ጫና ይኖራቸዋል። በኃይል በአንድ ላይ
እንዲቀመጡ ከተደረጉ ፌዴሬሽኖች ይልቅ ወደ አንድ በመምጣት ወይም ሥልጣን ወደታች በማውረድ
የመሥራች የፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታትን ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ የተመሠረቱ ፌዴሬሽኖች ውጤታማ
የመሆን የተሻለ ዕድል ይኖራቸዋል።

4. ምንም እንኳን ለሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ስኬታማነት አስፈላጊ ቅድመሁኔታ ባይሆንም በኢኮኖሚ
መስክ የሚገኝ ብልጽግና በፌዴራል ሥርዓቱ ቀጣይነት ላይ የራሱ በጎ ተጽእኖ እንደሚኖረው ይታመናል።
ምክንያቱም ወሳኝ ከሆኑ ሃብቶች ውስንነት ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ የሚችሉ ግጭቶች እንዳይኖሩ በማድረግ
ሥርዓቱ የተረጋጋ እንዲሆን የማድረግ እድል ስለሚፈጥር ነው። በሌላ በኩል የኢኮኖሚ ውድቀት በአንጻራዊ
መልኩ የተሻለ ሃብት አለን የሚሉ የክልል መንግሥታት ሌሎች የኛን ሃብት በመካፈል ወደኋላ ያስቀሩናል በሚል
ስጋት የመለየት ሀሳብን ሊይዙ የሚችሉበት አጋጣሚ ሰፊ ነው።

5. ጅኦፖለቲካል ዳይናሚክስና ዓለምአቀፍ ተዋናዮች በተለይም በሀገሪቱ ያሉ ብሔሮችን የሚጋሩ ሌሎች


መንግሥታት መኖር በሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ ጫና ሊፈጥር ይችላል። ጫናው
በአዎንታዊ ሆነ በአሉታዊ መልኩ የሚገለጽ ሊሆን ይችላል። በሌላ በኩል ሌሎች ሀገሮችም ሕብረብሔራዊ
ፌዴራላዊ ሥርዓት በሚመሠርቱ ሀገራት ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡበት አጋጣሚ ይፈጠራል። ይህም አጋጣሚ
የሀገሮችን ነባራዊ ሁኔታና የሕዝቦችን ተሳትፎ ባላረጋገጠ መልኩ ጣልቃ የገቡ ሀገራት ያላቸውን ተሞክሮና
ብሔራዊ ፍላጎት መሠረት ያደረገ የፌዴራል ሥርዓት በሀገሮች ላይ በመጫን ሥርዓቱ የተረጋጋና ቀጣይነት
ያለው እንዳይሆን ተጨማሪ ምክንያት ሊሆን ይችላል።

6. ዴሞክራሲና የሕግ የበላይነት በሰፈነበት የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓት የሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት
ውጤታማ የመሆን እድል በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል። ምክንያቱም እንደዚህ ያለ ሥርዓት ብዙ ዓይነት
የፖለቲካ አስተሳሰቦች እንዲኖሩ ስለሚፈቅድና ብዝኃነት ባህል እየሆነ የመሄድ እድሉ ሰፊ በመሆኑና ችግሮችን

32 | P a g e
በውይይትና በድርድር መፍታት የተለመደ አካሄድ እየሆነ ስለሚመጣ ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓቱም
በዚሁ አግባብ እየዳበረና እየተጠናከረ መሄዱ የሚችልበት እድል ሰፊ ነው።

7. ሌላው መሠረታዊ የሆነ ለማንኛውም የፌዴራል ሥርዓት ወሳኝ የሆነ ጉዳይ የፌዴራል የፖለቲካ ባህል መኖር
ነው። የተወሰኑ የፌዴራል ባህል ጉዳዮች ለምሳሌ ለፌዴራል ሥርዓቱ ተገዢ መሆን፣ የሌላውን ጉዳዩ እንደ ራስ
ማየት፣ በድርድር ለችግሮች መፍትሄ መስጠት፣ የወንድማማችነትና አብሮነትን አስተሳሰብና እሴት ማዳበር፣
በሕገመንግሥት እንዲካተቱ ማድረግ የሚቻል ቢሆኑም መሠረታዊ ጉዳዩ ግን ይህ ባህል በፖለቲካል ሊህቃኑና
በማኅበረሰቡ ውስጥ የፖለቲካ ባህል አካል እየሆነ እና እየዳበረ መሄድ ነው። ይህ ፌዴራል የፖለቲካ ባህል
ለሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓቶች ውጤታማ መሆን እንደ አንድ ቁልፍ ጉዳይ ይወሰዳል።

2.7. ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት የሚከተሉ ሃገራት ተሞክሮዎች

2.7.1. የተመረጡ ህብረብሄራዊ የሆኑ ሀገራት ተሞክሮዎች


በአሁናዊ አለማዊ ሁኔታ ለፖለተካ መረጋጋት፤ ለፖለቲካ ህብረት፤ ለዴሚክራሲያዊ ስርዓት እና ዘላቂ ሠላም
ግንባታ ብዝሃነትን ማስተናገድ የዉጤታማ ፌደራል ስርዓቶች መገለጫ ተደርጎ ይወሰዳል ሆኖም ሁለም
ፌደሬሽኖች የተሳካላቸዉ የማይሆኑበት አጋጣሚ ሰፊ ነዉ፡፡ ከዚህ አኳያ በአንጻራዊ መልኩ የተሻሉ የሚባሉ
ሁለት ህብረብሄራዊ ፌደሬሽኖች ተሞክሮ እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡ በዓለማችን ከሚገኙ ፌደራላዊ ሥርዓት
ከሚከተሉ 28 ሃገራት መካከል ሁለት ፌደሬሽኖች የተመረጡበት ምክንያት የመጀመሪያዉ ሁሉንም
ፌደሬሽኖች ህብረ በሄራዊ ስላልሆኑ ህብረ በሄራዊ የሆኑነትን መለየት ይጠይቃል

ሌላዉ ዋናዉ ጉዳይ ለምን ሁለት ፌደሬሽኖች ተመረጡ የሚለዉ ሲሆን ለዚህ ለስልጠና በተዘጋጅ አጭር
ጽሁፍ ከሁለት በላይ ማስተናገዱ ከጊዜና ከስልጠናዉ ባህሪ አኳያ ይበልጥ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር
ከመሆኑ አንጻር ተገቢ ስለማይሆን ሁለቱ የተመረጡ ፌደሬሽኖች ብዝሃትን ከማሰተናገድ አኳያ የተሻለ ስዕል
ያስይዛሉ በሚል ታሳቢ ነዉ፡፡ የተመረጡት ሁለት ፌደሬሽኖችም ሲዊዘርላንድ እና ህንድ ናቸዉ፡፡

ሲዊዘርላንድ ህብረ ብሄራዊ የሆነች የፌደራል ስርዓትን ረዘም ላሉ ዘመናት የምትከተል ሃገር ስትሆን ስርዓቷም
ተቋማዊ የሆነ እና ጠንካራ የሚባል በመሆኑ ሀገራችንም ህብረ ብሄራዊ የሆነ የፌደራል ሰርዓት ስለምትከተል
ከሲዊዘር ላንድ የዳበረ ልምድ መቃኘት የተሻለ እይታ ይሰጣል በሚል መነሻ የሲዊዘርላንድ ተሞክሮ ቀርቧል፡፡

33 | P a g e
የህንድ ዩኔንም በብዝሀነቱ የተሞላ እና ብዝሃነትን ለማስተናገድ የተለያዩ እርምጃዎችን ዩኔኑ ከተፈጠረ ጀምሮ
የወሰደ እና አንጻራዊ በሆነ መልኩ ዴሞክራሲዊ የሆነ የፌደራል ስርዓት በመተግበር ላይ ያለ በመሆኑ የህንድን
ፌደራል ስርዓት መዳሰስ ለኢትዩጵን ህብረ ብሄራዊ የተሸለ እይታ ይፈጥረል በሚል ታሳቢ የተወሰደ ነዉ፡፡

2.7.2. የሲዊዝ ኮንፌደሬሽን (1848 እ.አ.አ)


ሲዊዘርላንድ በምዕራብ አዉሮፓ የምትገኝ 7 ሚለዩን የሚጠጋ ትንሽ የህዝብ ቁጥር ያላት ሃገር ብትሆንም
ብዝሃነትን ከማስተናገድ አኳያ ትምህርት ሊወሰድባት የሚቻልባት ሃገር ናት፡፡ ከ 1291 እ.አ.አ ጀምሮ
የኮንፌደሬሽን ቅርጽ ያለዉ የፌደራል ፖለቲካ ስርዓት የምትከተል እና በብዙ ዉጣዉረዶችም ቢሆን የፌደራል
ስርዓቱን አስቀጥላ የቆየች ሲሆን በ 1847 እ.አ.አ የራስ አስተዳደር ላይ ትኩረት በመስጠት የቆየዉን
ግንኙነታቸዉን ለማስቀጠል በሚፈልጉ እና በወቅቱ ከነበረዉ የኢኮኖሚ ሁኔታ አንጻር ቀደም ሲል ከነበረዉ
አደረጃጀት የበለጠ የጋራ ጉዳዩቻቸዉን ማስፈጸም የሚችል አደረጃጀት በሚሹ ካንቶኖች መካከል
የሃይማኖት መልክም ይዞ የዞነደር ቡንድ የሚባል ስያሜ የተሰጠዉ የዕርሥ በዕርሥ ግጭት የነበረ ሲሆን
ግጭቱን በመፍታት መጠሪያዉ አሁንም ድረስ የሲዊዝ ኮንፌደሬሽን ቢሆንም የህብረ ብሄራዊ ፌደሬሽን
ቅርጽ ያለዉ የፌደራል ፖለቲካል ስርዓት አሁን ያለዉን ቅርጽ ይዞ 1848 ጀምሮ በመከተል ላይ የምትገኝ
ሃገር ናት፡፡ ሲዊዝ 26 ካንቶኖች ያሏት ሲሆን የቋንቋና ሃይማኖት ብዝሃነት ( ሮመን ካቶሊክ እና
ፕሮቴስታንት) በማስተናድ ጠኝካራ ህብረ ብሄራዊ ፌደራል ስርዓት የገነባች ሃገር ናት፡፡ በሲዊዘርላንድ 3
ኦፊሻል ቋንቋ ( ጀርመን፤ፈረሳይ፤ ጣላያን) ሮማንሽ ብሄራዊ እዉቅና ያለዉ ቋንቋ በፌደራል ደረጃ ጥቅም ላይ
በመዋል የሚገኙ ሲሆን በካንቶኖች ደረጃ የማህበረሰቦችን አሰፋፈር መሰረት ባደረገ መልኩ 17 ካንቶኖች
ጀርመንኛ ቋንቋ ብቻ፤4 ካንቶኖች ፈረንሳይኛ ብቻ፡ 1 ካንቶን ጣሊያንኛ በቻ የሚነገርበት ሲሆን 3 ካንቶኖች 2
ቋንቋ (ጀርመንኛ እና ፈረንሳይኛ) ፤ 1 ካንቶን 3 ቋንቋዎች (ጀርመንኛ፤ ጣሊያንኛ፤ ሮማንሽ) ይነገርበታል
በፌደራል መንግሥቱና በካንቶኖች መካከል ባለዉ የስልጣን ክፍፍል ለፌደራልና ለካንቶን መንግሥታት
በተናጥል የተሰጠና ቀሪ ሥልጣን (Residual power) ለካንቶኖች የተሠጠ ነዉ
ህገመንግሥቱ የፌደራል ህጎችንና ፖሊሲዎች በካንቶኖች እዲፈጸሙ ያዛል ከዚህም ጋር ተያይዞ መደበኛ የሆነ
ጠንካራ የመንግሥታት ግንኙነት በተለይም ጠንካራ የጎንዮሹ የመንግስታ ግንኑነት ፌደሬሽኑ መገለጫ ነዉ፡፡
ህገመንግሥቱን የመተርጎም ሥልጣን Federal Tribunal( Court) የተሰጠ ሲሆን በአወቃቀሩም ለቋንቋ
ከባቢዎች ተመጣጣኝ ዉክልና በሚሰጥ መልኩ የሚዋቀር አካል ነዉ፡፡ ፌደሬሽኑ ሁለት ም/ቤት- ብሄራዊ
ም/ቤት (Nationalrat) የካንቶኖች ም/ቤት-ስቴንደ ራት ( standrate) ያሉተ ሲሆን በሰቴንደ ራቱ ሁለም 20
ካንቶኖች 2 ተወካይ ሲኖራቸዉ 6 ካንቶኖች 1 ተወካይ አላቸዉ፡፡
የስራ አስፈፃሚዉ ( Federal Council) ለተወሰነ ጊዘ በፌደራል ፓርላማዉ የተመረጠ በቡድን የሚሠራ 7
አመራሮች ያቀፈ አካል ሲሆን የፕሬዚዳንቱ ሥልጣን በ 7 አባላት በቅብብሎሽ በየአመቱ የሚያዝ
ነዉ፡፡

34 | P a g e
የሲዊዝ ፌደሬሽን ከሚታወቅባቸዉ ስርዓቶች አንዱ የቀጥታ ዴሞክራሲ ሲሆን ይኽም ህዝቡ በብዙ ጉዳዩች
ላይ በሚሳተፍበት ህዝበዉሳኔ እና ህዝበዉሳኔ እንዲሰጥበት ሀሳብ የማመንጨት ለዉ መብት ጋር ጤይዞ
የሚታይ ነዉ ፤፤ የህ ጉዳይ መኖር ደግሞ ህግአዉጭዉም ሆነ አሰፈጻሚዉ በሚከናወናቸዉ ተግባራት
የማህበረሰቡን ፍላጎት መሰረት የደረግ እንዲሆን አስገዳጅ ሁኔታዎችን ይፈጥራል ምክንያቱም በጉዳዩ ላይ
ማህበረሰቡ ሪፍረንደም እንዲካሄድበት የሚስችል ድምጽ ማሰባሰብ እና ጉዳዩ በፊፍረንደም እንዲወሰን
የማድግ እድሉ ሰፊ ስለሆነ፡፡
ሎላዉ የሲዉዘርላንድ ፌደሬሽን መገለጫ የመነግስታ ግንኙነታቸዉ ነዉ፡፡ የመንግስታት ግንኙነታቸዉ ስያሜ
የትብብር ፌደራሊዝም ሲሆን ህገመንግሥታቸዉ የትብብር ፌደራሊዝምን መርሆዎች የያዘ ነዉ፡፡ በተለይ
በ 2004 እ.አ.አ በተደረገዉ የህገመንግስት ማሻሻያ ጋር ተያይዞ የሲዊዚ ካንቶኖች እርስ በእርስ መተባባር
በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ብቻ ሳይሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ ከሆነ ህገመንግስታዊም ግዴታ ሁኖ ተወስዶል
(በራዉን, 2009). ከዚህም የሀገራችን ፌደራል ስርዓት ለሞክሮ ሊወስድበት የሚችልበት ጉዳይ መሆኑን
ማመላከት ተገቢ ነዉ፡፡ ምክንጡም ህብረብሄራዊ በሆኑነፌደሬሽኖች የክልሎች እርስ በእርስ መተባባር እና
መደጋጋፍ ለስርዓቱ ቀጣይነት እና የጠረጋጋገ መሆነ ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ፡፡

የሲዊዘር ላንድ ፌደራል ስርዓት ዋና ዋና ገጽዎች

 ለካንቶኖች በቂ የራስን ጉዳይ በራስ መወሰነን ስልጣን ለሚሰጥ እና የጋራ እና የተቀናጀ ተግባር
ለመፈጸም ለሚያስችል ረቂቅ የሆነ ሚዛነዊነትን ለሚከተል ጥልቅ የሆነ እና ረጅም ጊዜ ያለዉ
ቁርጠኝነት የሚታይበት የፌደራል ስርዓት

 ዉይይት፤ድርድር፤ስምምነትን መሰረት ያደረገ እና ትብብር ላይ ተመስርቶ መፍትሄ የሚሰጥ ስር


የሠደደ ባህል መኖር

 የተለመደ ጠንካራ የሆን የጎንዩሽ በካንቶኖች መካካል የሚደረግ ትብብር እና የተወሰኑ የተዋረድ
የፌደራ አካለትን የሚያካትቱ የግንኙነት ስርዓቶች መኖር

 ለሲዊዝን ፖለቲካ ስርዓት ልዩ የሆነዉ የቀጥታ ዴሞክራሲ

 ቢሂደት በአንጻራዊ መልኩ እየተማከለ የመጣዉን ሂደት መልሶ በአንጻረዊ መልኩ የልተማከለ
እቅጣጫ እንዲያይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዋች

35 | P a g e
2.7.3. የህንድ ዩኔን (1950)

የፌደራል አሰተሳሰብ፤ተቋማትና የአሠራር ሥርዓቶች በልዩነት የተሞላን እና ብዙ ህዝብ ያለዉ ሃገር እንዴት
ከጋማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ አቻችሎ ማስቀጠል እንደቻለ የሚያሣየን የህንድ
ፌደራላዊ ሥርዓት ነዉ፡፡ በ 1947 ህንድ እንደዚህ በአንፃራዊ መልኩ በተረጋጋ ሁኔታ ትቀጥላለች ብሎ
የሚያስቡ የተወሰኑ በነበረሩበት 1947 ከቅኝግዛት ነፃ ወጣች በጥር 1950 የፌደራል ዩኔን ሕንድ
ተመሰረተች ለፌደሬሽኑ መመስረት የብሪቲሽ ኢንድያን አክት 1935 እንደ አንድ መነሻ ተደርጎ ይወሰዳል ፡፡
ለፌደሬሽኑ መመስረት ዋና ያስተሳሰብ መሠረት

 የህንድ ብዝሃነት፤ የደህንነትና የመበታተን ሥጋት

 ጠንካራ ፌደራል መንግሥት ያለዉ ዩኔን

ብዝሃነትን በማሰተናገድ ለችግሩ መፍትሄ ይሰጣል የሚል እሳቤ የፌደሬሽኑ አመሰራራት መነሻ ሆኖ ይገኛል፡፡

ህንድ ሃያ ዘጠኝ በህንድ states የሚባሉ የክልል መንግስታት ፤አንድ ብሄራዊ ካፒታል ቴሪተሪ- ኒዉደህሊ እና
በዩኔኑ መንግስት አስተዳደር ስር ያሉ ስድስት ቴሪተሪዎችን ያቀፈች ፓርላሜንታሪያዊ የፌደራል ስርዓት
የምትከተል ሃገር ስትሆን ህንድ ሰፊ ብዝሃት መገለጫዎች ያሏት 22 በሄራዊ ቋንቋዎች፤ ከ 200 በላይ
ዳይሌክቶች፤ሰባት ሃይማኖት ፤ብዛት ያላቸዉ ኢትኒክ ቡድኖች በተለያዩ ካሰቶች የተከፋፈሉ ያቀፈች ይህን
ማስተናገድ እና ይህን በፌደራላዊ ዴሞክራሲዊ አግባብ ለማስተናገድ ከፍተኛ ጥረት የምታደርግ እና
እንጻራዊ በሆነ መልኩ የተሻለ አፈጻጸም ያላት ፌደሬሽን ናት (አሮራ 2010).

የህንድ ፌደሬሽን አፈጣጠር ስንመለከት ሁለተንም ማለትም ወደታች ስልጣን በማወረድ ( devolution ) እና
ስልጣን ወደ አንድ በማምጠት ( coming together) አጣምሮ የያዘ ነበር ቀደምሲል የብሪቲሽ ኢንዲያ
ፕሮቪንሶች ለነበሩት ግዛቶች ስልጣንን ወደታች በማወረድ እና ከ 1947 እስከ 1950 ባሉት ጊዚያት ቀደም ሲል
የፕሪንሶች መንግስታት ተብለዉ የሚታወቁትን ወደ አንድ በማምጣት የተፈጠረ ነዉ፡፡

ህንድ ሰፊ የቋንቋ፤ የባህል፤ የሃይማኖት፤ የአሰተሳሰብ ብዝሃነቶችን የምታስተናግድ ፌደሬሽን ከመሆኗም በላይ
የምትከተለዉ ፌደራላዊ ፓርላሜንታዊ ስርዓት ነዉ፡፡ መጀመሪያ ፌደሬሽኑ ሲመሰረት የተማከለ ገጽታ ያለዉ
እና ፌደሬሽኑ የተካተቱ የክልል መንግስታት አከላለል ቋንቋን እና ባህልን ግንዛቤ ዉስጥ ያላስገባ ቢሆንም
በሂደት የክልል መንግሥታትን እነደገና መልሶ በህንድ የሚያደራጅ ኮሚሽን- 1955 የክልል 1956-66 የክልል
መንግሥታት በዋናነት ቋንቋንና ብሄርን መሰረት ማድረግ እንደገና ተደራጅተዋል ሆኖም አሁንም የሚነሱ
የራስን በራስ ማስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ዕየተሰጠ የሚሄድበት አግባብ ያለ መሆነ ይታወቃል

36 | P a g e
በህንድ ዩኔን የስቴቶች ወሰን አከላለል ከመነሻዉ ስንመለከት ለቅኝ ግዛ አስተዳደሩ ምቹ በሚሆን መልኩ የተካለሉ
ቢሆንም ከነጻነት በኋላ ቋንቋን እና ማነወነትን መሰረት አድርጎ እንደገና መልሶ የማደራጀት ስራ ተስርቷል
በዚህም አዳዲስ ስቴቶች ከነባር ስቴቶች ወጥተዉ የተደራጁበት አጋጣሚ ተፈጥሯል አዳዲስ ስቴቶች
ለመፈጠር እንደምክንያት የሚቀርበዉም የማንነት ጥቄዎች እና በነባር ስቴቶች በበቂ አልተካተትነም እና
እኩል ተጠቃሚነት ዕድል አልተፈጠረልነም የሚሉ ሃሳቦች ያሉ መሆኑ ይነሳሉ ሆኖም ህንድ መንነቶችን
ለማስተናገድ የሚያስችል የህዳጣን መብቶችን የሚስጠብቅ ህገመንግስታዊ ስርዓት ያላት እና መንነቶችን
በተለያዩ አግባቦች በማስተደናገድ ትታወቃለች ፤ በህንድ ስቴቶችን መልሶ ባደራጀት ሂደት በዚህ መልክ
ከተፈጠሩት ስቴቶች የቅርብ ጊዜዋ ቴላንጋአና ከአንደራ ፕራዲሽ በ 2014 ተከፍላ የወጣች ናት (ሲንግ እና
ሳከስን 2015).፡፡ ህንድ ለቋንቋና ለማንነቶት እዉቅና እና በፌደራ ስርዓቱ የራስ አስተዳደራቸዉን በመፍቀድ
ተለያዩ መንነቶች የራሳቸዉን ጉዳይ በራሳቸዉ የሚወስኑነበት እና በጋራ ጉዳይ እንደ ሀገር የሚሳተፉበትን
አደረጃጀት በመፍጠር ህብረ ብሄራዊ ከሆኑ ፌደሬሽኖች ልትመደብ የምትችል ሃገር ናት በህንድ ሒንዲ እና
እንግሊዘኛ ኦፊሻል ቋንቋ ሲሆን ፤18 ህገመንግሥታዊ እወቅና ያላችዉ የከባቢያዊ ቋንቋዋች አሉ፡፡

የህገመንግሥቱ መሥራቶች ጠንካራ መዕከላዊ መንግሥት ያለዉ የተማከለ መንግሰት ባህሪ ያለዉ ፌደሬሽ
ለመመስረት ቢሹም፣ የህብረተሰቡ ፌደራል ባህሪና የከባቢያዊነት ሥሜት መንግሥቱ በሂደት የፌደራል ባህሪ
የተለበሰ መንግሥት እየሆነ መሄድ ችሏል

የሕንድ ህግ አዉጭ አካል ሁለት ም.ቤቶች ያሉት ሲሆን የላይኛዉ ም/ቤት አደረጃጀት- በክልል መንግሥታት
ም/ቤት ቀጥተኛ ባልሆነ ምርጫ የሚመረጡ እና 12 ተጨማሪ ተወካዩች በቀጥታ በፕሬዘዳንቱ የሚወከሉ
ያቀፈ ነዉ፡፡ የታችኛዉ ም/ቤት አንድ ሰዉ አንድ ድምጽ በሚል አግባብ በሚካሄድ በምርጫ በሚገኝ ዉክልና
የሚዋቀር ነዉ፡፡ በህነድ ህገመንግስታዊ የስልጣን ክፍፍል

-የፌደራል ሥልጣን ዝርዝር

 -የክልል መንግሥታት ሥልጣን ዝርዘር

የጋራ ሥልጣን ዝርዝር

 -ቀሪ ስልጣን ለዩኔን

በሚል በፌደረል መንግስቱ እና በክልል መነግስታት መካከል የተከፋፋለ ነዉ፡፡

ህንድ ከሳካሪስ ሪፖርት በኋላ መደበኛ የመንግስታት ግንኙነት( Inter-state Council) ተቃማዊ በሆነ
መልኩ የተዋቀረ ሲሆን ከዚ በፊት የአዉራ ፓፐርቲ ስርዓቱ በመደበኛ መነግስታ ግንኙነቱ ላይ ቻና
ሲፈጥር እንደነበር ይገለጻል

37 | P a g e
ህንድ በጃሙ እና ካሽሚር ካለዉ የተለየ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ህገመንግሥታዊ የሆነ ከባቢዊ በሆኑጉዳዩች
የተለየ ሥልጣን ለሁለቱ ከባቢዎች በመስጠት ችግሩን ለመፍታት ጥረቶችን ያደረገች ሲሆን ችግሩ
አሁንም የቀጠለ እና በፌደራ መነግስቱ እና በከባዐ አስተዳደሮቹ መካከል የግጭት ምንጭ ሁኖ ይታያል
ሆኖም የፌደራል ስርዓቱ መሰረት በማድረግ የከባቢዎችን የተለየ ሁኔታ ማስተናገድ ባይቻል ኖሮ እነዚህ
ከባቢዎች ከህንድ ወደ መለየት ሊሄዱ የሚችለበት ሁኔታ ሰፊ ሊሆን እንደሚችል መገመት አዳጋች
አይደለም፡፡ ሕነድ ሌላ ከአብዛናዉ ፌደሬሽኖች የተለየ የሚደርጋት በ 1999 በህገመንግሥቱ 73 እና 74 ኛ
ማሻሻያለከባባያዊ መንግሥታት (ፔንችያትስ እና ማዘጋጃ ቤቶች) ህገመንግሥታዊ እዉቅና መሥጠቷ ነዉ
ይህ በአብዛኛዉ ፌደሬሽኖች ለክልል መንግስታት የሚተዉት ጉዳይ ተደርጎ የሚታይ ነዉ፡፡

2.8.ህብረ በሄራዊ በሆኑ ሀገራት ብዝኃነትን የሚገልጹበት አግባቦች፣


በየትኛውም ሀገር ውስጥ በተለያየ እይታ የሚገለጹ የብዝኃነት መገለጫዎች እንዳሉ
ብዙዎች ይስማማሉ። ስለዚህ የትኛውም ሀገር በውስጡ የሚታዩ የብዝኃነት ገለጫዎች
በተለይም ወሳኝ የሆኑ የማንነነት መገለጫዎች ተብለው የሚገለጹ የቋንቋ፣ የሀይማኖት፣
የባህል፣ የታሪክና የመሳሰሉ የማንነት መገለጫዎች ይኖሩታል። ስለዚህ ሀገራት የእነዚህ
የማንነት መገለጫዎች ስብስቦች ናቸው ተብሎ ይታመናል።

ሕብረብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት የሚከተሉ ሀገራት የተለያዩ ስልቶችን


በሕገመንግሥቶቻቸው በመንደፍ የብዝኃነት መገለጫዎችን ያቅፋሉ። በዚህ ርዕስ ሥር
እነዚህን ብዝኃነትን ለማቀፍ የሚረዱ ስልቶችን ለማየት እንሞክራለን።

ፌዴረሽኖች ከሕገመንግሥት መግቢያ ጀምሮ የቃላት አጠቃቀምን ባካተተ መልኩ


የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ብዝኃነትን ያንጸባርቃሉ። በዚሁ መሠረት
ሕብረብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት የሚከተሉ ሀገራት ብዝኃነትን የሚያቅፉበትን
ወይንም ዕውቅና የሚሰጡበትን ዘዴዎች ለማየት እንሞክራለን።

የሕገመንግሥት መግቢያ፣ ሕብረብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት የሚከተሉ ሀገራት


በሕገመንግሥቶቻቸው መግቢያ ጀምሮ ሕብረብሔራዊነትን ያንጸባርቃሉ። ለምሳሌ
የስዊዝን ሕገመንግሥት ያየን እንደሆነ በሕገመንግሥቱ መግቢያ ካንቶኖች
ለሕብረብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት በተለይም ብዝኃነትን ከመቀበልና ከማቀፍ አንጻር
ቁርጠኝነታቸውን ያሳዩ ሲሆን፣ በዚሁ መሠረት ብዝኃነታቸውን በማክበርና በጋራ

38 | P a g e
ለመኖር ከመወሰናቸውም አልፈው አንዱ ሌለኛውን በማክበርና በእኩልነት ለመኖር
ቃልኪዳን መግባታቸውን ገልጸዋል። ስለዚህ በስዊዝ ሕገመንግሥት መግቢያ ላይ
የተገለጸው ለሕብረብሔራዊነት ወይም ለብዝኃነትና ለእኩልነት የተሰጠውን ቦታ
ያንጸባርቃል። ለዚህም ነው ፍሊነር የተባሉት ምሁር ልክ እንደ አሜሪካ ሕገመንግሥት
“እኛ የአሜሪካ ሕዝብ…” በማለት ካንቶኖች የስዊዝ ፌዴሬሽን የወጥነት መፍትሄን
አልተከተሉም ብለው ይገልጻሉ። ይልቁንስ “የካንቶኖች ሕዝቦች” በማለት ይገልጻሉ።
በተመሳሳይ መልኩ የስፔን ሕገመንግሥት በመግቢያው ብዝኃነትን በብዙ ቁጥር የተቀበለ
ሲሆን፣ በዚሁ መሠረት ሕገመንግሥቱ “ሀገረ-ስፔን ሁሉንም ስፓኒያርዶችንና ሁሉንም
የስፔን ሕዝቦች ሰብዓዊ መብቶችን፣ ባህሎቻቸውን፣ ወጎቻቸውን፣ ቋንቋዎቻቸውን እና
ተቋሞቻቸውን ያስከብራል” በማለት ያትታል።

ከስዊዝም ሆነ ከስፔን ሕገመንግሥቶቹ መግቢያ የምንረዳው እነዚህ ሀገራት ለብዝኃነትን


ወይንም ለማንነት መገለጫዎች ዕውቅና እንደሰጡ ከመግለጻቸውም በላይ ሀገራቱ
የተመሠረቱት በእነዚህ የማንነት መገለጫ ምሰሶዎች ላይ እና እነዚህን ምሰሶዎች
መጠበቅ እንዳለባቸው ያስገነዝበናል።

ምልክቶችን መጠቀም፣ ሌላኛው ሕብረብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት ለብዝኃነቶች


ዕውቅናን የሚሰጡት የተለያዩ ምልክቶችን በመጠቀም ሲሆን፣ ፌዴሬሽኖቹ
የሚጠቀሟቸው እነዚህ ምልክቶች ደግሞ የሀገሪቱን መጠሪያ ጨምሮ፣ ሀገሪቱ
የምታከብራቸውን ሕዝባዊ በዓላት፣ በህንፃዎቻቸው ላይ የሚሰቅሉዋቸው
ሰንደቅዓላማዎች፣ ኦፊሰላዊ ዓርማዎች እና የመሳሰሉትን የሚጨምር ነው። ይህ ማለት
ደግሞ ሕብረብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓትን የሚከተሉ ሀገራት ሕብረብሔራዊነትን
የሚገለጹ ባህሪያትን ያንጸባርቃሉ ማለት ነው።

ስሞችና ቃላት፣ ስሞችና ቃላት ወሳኝ የሆኑ ጠቀሜታዎች አሉዋቸው። ለምሳሌ


የቤልጅየምን ሕገመንግሥት ያየን እንደሆነ የሕገመንግሥቱ የመጀመሪያው አንቀጽ
ፌዴሬሽኑ “ማኅበረሰቦችንና ክልሎችን ያቅፋል” በማለት ይደነግጋል። ይህ
የቤልጅየምን ሕገመንግሥት የቃላት አጠቃቀም ብዝኃነትን ከማቀፍ አንጻር ወሳኝ

39 | P a g e
እርምጃ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። በአጠቃላይ መደበኛ የሆነ የቃላት አጠቃቀም ሀገሪቱ
ብዝኃነትን ከመቀበልና ከማቀፍ አንጻር ወሳኝ ጉዳይ ተብሎ ሊወሰድ ይችላል።

ሰንደቅ ዓላማ፣ ሰንደቅ ዓላማ የአንድ ሀገር መገለጫ ሆኖ፣ በተለይም ሕብረብሔራዊ
የፌዴራል ሥርዓት በሚከተሉ ሀገራት ሰንደቅ ዓላማ ሕብረብሔራዊነትን ከማንጸባረቅ
አንጻር ከፍተኛውን ሚና ይጫወታል። ለምሳሌ የስፔንን ሕገመንግሥት ካየን
ሕገመንግሥቱ የስፔንን ሰንደቅ ዓላማ ከመግለጽ አልፎ ለክልሎች ሰንደቅ ዓላማዎች
ሕገመንግሥታዊ ዕውቅና ሰጥቷል። እነዚህም ሰንደቅ ዓላማዎች ከፌዴራሉ ሰንደቅ
ዓላማ ጋር በክልሎቹ በዓላት ቀን ጨምሮ በህንጻዎች ላይ መሰቀል እንዳለባቸውም
ጭምር ደንግጓል። ስለሆነም ለክልሎቹ ሰንደቅ ዓላማዎች የተሰጠው ዕውቅና ሀገሪቱ
ሕብረብሔራዊነትን ከመቀበልና ከማክበር የመነጨ የፖሊሲ አቅጣጫ ተደርጎ ሊወሰድ
ይችላል።

የቋንቋ ፖሊሲ፣ ቋንቋ የማንነት ቁልፍ መገለጫዎች ውስጥ አንደኛው ሲሆን፣


ሕብረብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት የሚከተሉ ሀገራት የቋንቋን ብዝኃነት ያከብራሉ።
ለምሳሌ ስፔን እ.አ.አ እስከ 1978 ድረስ ካስቲላን ቋንቋ የሀገሪቱ ትልቅ ቋንቋ ነበር።
ይሁንና ከ 1978 በኋላ ሌሎች ቋንቋዎች በስፔን ነጻ ማኅበረሰቦች (autonomus communities)
ተጨማሪ ቋንቋዎች ዕውቅና እንዲያገኙ ተደርጓል። በተጨማሪ ካናዳን ያየን እንደሆነ
በተለይም የክዩቤኮችን የዘመናት የቋንቋ ጥያቄን ለመመለስ በማሰብ ካናዳ ውስጥ
ፈረንሣይኛ የሀገሩቱ ኦፊሰላዊ ቋንቋ እንዲሆን ከመደረጉም በላይ፣ ትምህርት ቤቶች
እንግሊዝኛንና ፈረንሳይኛን እንዲያስተምሩ ተደርጓል። በመሆኑም ማንኛውም ሰው
በፌዴራል መንግሥታቱ ተቋማት ውስጥ ለመቀጠር ግድ እንግሊዝኛንና ፈረንሳይኛን
ማወቅ ይጠበቅበታል። በተመሳሳይ መልኩ ደቡብ አፍሪካም እንግሊዝኛን ጨምሮ
ለአሥራ አንድ ቋንቋዎች በሕገመንግሥቷ ዕውቅና ሰጥታለች።

40 | P a g e
2.9. የህብረ ብሄራዊ ፌደራላዊ ስርዓት የተገበሩ ሀገራት ስኬት እና ልምድ ፡-ለተረጋጋ ሀገር መኖር
የስርዓቱ አስፈላጊነት

የህብረ ብሄራዊ ፌደራላዊ የፌደራል ስርዓትን በመተግበር በርካታ ሀገራት እጅግ


የበለጸገና የተረጋጋ ሀገር መፍጠር ችለዋል፡፡እንደ አንደርሰን (2013) ያሉ ምሁራኑ አገላለጽ
በጣም ስኬታማና ዘላቂ የሆነ የፌደራል ስርዓት የገነቡ ሀገሮች ዋነኛ ሚስጥር እንደሚከተለው ነው፤

(1) በሀገራቱ ያለውን የተለያየ ማንነትና ሀገራዊ አንድነት በአግባቡ ማስታረቅ መቻል ( ለምሳሌ ስዊዘርላንድ
እና ህንድ)

(2) ህዝቦቻቸው ከልዩነት ይልቅ ጠንካራ ሀገራዊ ማንነት እንዳላቸው የሚያምኑ እና በኋላ ታሪካቸው የጋራ

ግንዛቤ መፍጠር የቻሉ ( ለምሳሌ ጀርመን እና ስዊዘርላንድ) በመሆናቸው፤

(3) አካታች የህግ፤ የፖሊሲና የድጋፍ አተገባበር ማዕቀፍ ቀርፀው ተግባራዊ በማድረጋቸውና፤

(4) መንግሥታቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ህዝቦች ከልዩነቶች ይልቅ የጋራ እሴቶች የሚያጎለብቱበት ሁኔታ

በመፍጠራቸው ነው ይላል፡፡

ስዊዘርላድ፤ ህንድ፤ጀርመንና በዚህ ረገድ እንደ ጥሩ ማሳያ ሆነው ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ ሀገራት የፌደራል

ስርዓትን የህዝቦች የተለያዩ ማንነቶች እና ሀገራዊ አንድነትን ለማስጠበቅ እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡ ሥርዓቱ

የየሀገራቱን ህዝቦች አንድነት ከማሰጠበቅ ጎን ፍትሐዊ የሀብትና የሥልጣን ክፍፍል የሚያረጋግጡ ጠንካራ

ህጎችና ማዕቀፎችን ዘርግተው ተግባራዊ ለማድረግ ምቹ ሁኔታን ፈጥሮላቸዋል፡፡

የተለያዩ ግጭቶችና የተዛባ ግንኙነት በህዝቦች መካከል በበዙባቸው ሀገሮች ደግሞ ፌዴራሊዝም ከላይ

ከተጠቀሱት ጥቅሞች በተጨማሪ የአንድነትና የሉዓላዊነት ማስጠበቂያ ሆኖ እንዳገለገለ እንደ አንደርሰን

(2013፡3-4) ያሉ ምሁራን በጥናት አረጋግጠዋል፡፡ ለምሳሌ አሉታዊ የሆኑ ታሪካዊ ቁርሾዎችና ትርክቶች

ባላቸውና በሀገረ-መንግስት ምስረታ ሂደት መስማማት በሌለባቸው ሀገራት ፌዴራሊዝም የሀገራዊ አንድነት

ስሜትን እንደገና ለመፍጠር ረድቷል፡፡ የእርስ በእርስ የግጭት ታሪከ ያላቸውና የገንጣይ-አስገንጣይ ድርጅቶች

በበዙባቸው ሀገራት ደግሞ ፌደራሊዝም የሀገራቱን ህልውናና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ እንደሥርዓት

አገልግሏል (አንደርሰን 2013፡3-4)፡፡ በዚህ ረገድ የፌደራሊዝም ጥቅም ፍትሃዊ የሆነ የስልጣንና የሀብት ክፍፍል

ማረጋገጥን፤ የተለያየ ማንነት፤ ባህል፤ ቋንቋ፤ ሃይማኖትና ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ባለበት ሁኔታ

41 | P a g e
ልዩነትንና የተለያዩ ፍላጎቶች አቻችሎ ለማስተዳደር ዕድል ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ፌዴራሊዝም በአንድ በኩል

ሚዛኑን የጠበቀ አገራዊ አንድነትና የተሳሰረ ማንነትን በሌላ በኩል ደግሞ ያለፉትን ታሪካዊ ትርክቶች ላይ

ለአንድነትና ለሉዓላዊነት ሲባል መስማማትን የሚያበረታታ ሥርዓት ይፈጥራል፡፡ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ

በሀገራቸው የቀድሞ ታሪክና ሀገረ-መንግሥት ምሥረታ ሂደቶች ላይ መግባባት ባልተፈጠረባቸው ሀገሮች

በጉዳዮች ላይ የጋራ ግንዛቤ መፍጠርና መስማማት እጅግ አንገብጋቢ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ይህ የሚሆነው በበሳል

ውይይትና ድርድር ስለሆነ እንደኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት ፌዴራሊዚም ብቸኛው መንገድ እንደሆነ የጥናት

ግኝቶች አሳይተዋል፡፡ ጥናቶች እንደሚገልጹት የፌደራል ስርዓት በሚከተሉ ሀገራት ግጭት የሚነሳውና የአገር ግንባታ
ስራው ችግር ውስጥ የሚወድቀው የፌደራል ሰርዓቱ ሊያስገኛቸው የሚችሉት ጥቅሞች በአግባቡ ማሳካት ሣይቻልና
ህዝቦች በሀገራቸው የጋራ ባለቤትነት ስሜት ሲዳከም አልያም ራስ በማስተዳደር ሂደት ሳይተገበር ሲቀር አልያም የብሄር
ማንነቱ ከሚፈለገው በላይ ወደ ጥግ በመግፋት በህዝቦች ዘንድ ሊኖር የሚገባውን ትስስር በማዳከም ሚዛኑ ሲዛባ ነው (
አሰፋ 2010)፡

2.10. ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት እና የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ፣


ሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ሲዳሰስ ሀገራችን ሕብረብሔራዊ የሆነች ሀገር መሆኗን እንደ ነባራዊ ሀቅ መውሰድ
ተገቢነው ። ይህን ሃቅ ለመረዳት ብሔር የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ በዝርዝር ማየት ጠቃሚ ነው። ብሔር
የሚለውን (ጉብናወር 1999) በሚከተለው መልኩ ገልጾታል ብሔር አንድ ማኅበረሰብ ነን የሚል እሳቤ
ያላቸው፣ የሚጋሩት የጋራ ባህል‹ በግልጽ ከሚታወቅ መልክዓምድር ጋራ ራሳቸውን የሚያያይዙ፣ያለፈ የጋራ
ጉዳይ እና የወደፊት የጋራ ፕሮጀክት አለን ብለው የሚያስቡና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ያላቸው ሰዎች
የተሰባሰቡበት ቡድን ነው።“ በመሆኑም በሀገራችን እንደዚህ ዓይነት እሳቤ ያላቸው ለብዙ አስርት ዓመታትም
በዚህ መልክ ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ያሉዋት ሀገር መሆኗ ይታወቃል። ከአንድ ብሔር በላይ
ለሀገሪቱ ፖለቲካ ወሳኝ በሆነበት ሁኔታና የብሔረ -መንግሥት አስተሳሰብና ተግባር በ 15 ኛው ክፍለዘመን
አጋማሽ ጀምሮ በአውሮፓ ተግባራዊ በሆነበት አግባብ ተጽኖ ፈጣሪ (አውራ) ወደ ሆነው አንድ ብሔር መዋጥ
ተግባራዊ ሊሆን የሚችል አማራጭ ሆኖ የሚቀርብበት እድል በሌለበት ሁኔታ ሕብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ
ሥርዓት የተሻለ አማራጭ ሊሆን ይችላል።

በኮምፓራትቭ ፖለቲክስ አንዱ ቁልፉ ጉዳይ ሕብረብሔራዊ ለሆኑ ሀገራት ፖለቲካዊ መረጋጋት የተሻለ
አስተዋጽኦ ሊያደርግ የሚያስችለውን መንግሥታዊ አደረጃጀትን መለየት ነው። ለዚህ አንዱ የሚመከረው
ዜግነትን ከብሔር መነጠል ነው። ልዩነቱ ረቀቅ ያለ ቢሆንም ጠቃሚ የሆነ ጉዳይ ነው። ዜግነት የአንድ
መንግሥት አባል ከመሆን ጋራ የሚመጣ መብትና ግዴታ ሲሆን የፖለቲካዊና ህጋዊ ሁኔታን የሚያመላክት
ስለሆነ በመርህ ደረጃ የተለያዩ ብሔራዊ ማንነት ያላቸው ሕዝቦች ሊጋሩት የሚችል ጉዳይ ነው። በዚህ
መንገድ ዜግነት የተለያዩ ብሔራዊ ማንነት ያላቸው ሕዝቦች በአንድ ጣራ ስር በጋራ እንዲኖሩ ሊያደርግ

42 | P a g e
ይችላል። በሌላ መልኩ በሕብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ብዝኃነትን ከሀገራዊ አንድነትን ጋር ተመጋጋቢ

አድርጎ ለማስኬድ አንዱ መንገድ ብዝኃ እና ተመጋጋቢ የሆኑ ማንነቶች እያበለጸጉ መሄድ መሆኑን የሌሎች
ሕብረ ብሔራዊ የሆኑ ፌዴሬሽኖች ተሞክሮ ያሳያል።ይህ ጉዳይ በኢትዩጵያ ፌዴሬሽን ያለበትን ሁኔታ
በየጊዜው በጥናት እየዳሰሱ መሄድ እና ከጥናቱ ውጤቶች ተነስቶ ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ
ሥራዎችን መሥራት ወሳኝ ጉዳይ ነው፣ከዚህም በተጨማሪ ከላይ በዝርዝር የቀረቡትን ተግዳሮቶች ከሀገራችን
ነባራዊ ሁኔታ አኳያ በዝርዝር በየጊዜው እየፈተሹ በየደረጀው መፍትሄ እየሰጡ መሄድን የሚጠይቅ ሲሆን
በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ሥርዓቱ የተሸለ አማራጭ በመሆንና ሥርዓቱ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች
እየፈታንባቸው በምንሄድባቸው መንገድ እንደ ሀገር ተቀራራቢ የሆነ አስተሳሰብ ይዘን መንቀሳቀስ
የሚጠበቅብን ወቅት ላይ መሆኑን ማመላከት ተገቢ ይሆናል።
እንደ ኢትዩጵያ ባሉ ሕብረ ብሔራዊ በሆኑ ሀገራት የሕብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ግንባታ በዋናነት
በተረዳነው ልክ በየጊዜው ሰርዓታዊ አካሄድ በያዘ መልኩ የፌዴራል ፎርሙላውን ይበልጥ እያጠራን
በምንሄድበት አግባብ እየተገነባ የሚሄድ ፕሮጀክት ተደርጎ ሊታይ ይችለል። በዚህ ፕሮጀክትም አተገባበተር
የተገኙ መልካ ነገሮች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በሚከተለው መልክ ቀርበዋል፣፣

2.10.1. የተገኙ መልካም ነገሮች፣


የሃገራችን የሕብረብሔራዊ ዴሞክራሲዊ ፌዴራል ሥርዓት ግንባታ እንደ አብዛኛው ጉዳዮቻችን ጀማሪና
በውጣውረዶች የተሞላበት እና በትክክለኛው አቅጣጫ እየተተገበረ ነበር ብሎ ማለት ባይቻልም
ፌዴራላዊ አደረጃጀቱ የሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ዕድል በሕገመንግሥት ደረጃ
ያረጋገጠ እና ተግባራዊ መደረግ የተጀመረ መሆኑ እንደ መልካም ነገር ማየት ቢቻልም ከአተገባበሩ ጋር ተያይዞ
ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ የመሆን ውስንነቱ የተገኘውን መልካም ነገር በተገቢው ሥራ ላይ ለማዋል ችግር
ፈጥሮ ቆይቷል።

ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህላቸውን በተግባር የሚገልጹበት ሕዝባዊ ቦታ መገኘታቸው እና


መግለጻቸው፣ በሌላው ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝብ እንዲታወቅ እና የሃገሪቱ ባህል አንድ አካል መሆኑን
እውቅና እንዲያገኝ መሆኑ በሥርዓቱ የተገኙ መልካ ጅምሮች አድርጎ መውሰድ ተገቢ ነው። ከፌዴራል
ሥርዓቱ ጋር ተያይዞ በፌዴራል፣ በክልል፣ በዞን፣ በወረዳ እና በቀበሌ የመንግሥት አካላት መደራጀት የሕዝቡን
በተለያዩ አስተዳደር እርከኖች ያለውን ተሳትፎ የሚጨምርበትና የከባቢውን አቅም እና ፍላጎት አቀናጅቶ
ለመልማት እድል መፈጠሩ እንደ አንድ መልካም ጀምር የሚታይ ሲሆን ለምሳሌም ያህል በየደረጃው
የተቋቋሙ ምክር ቤቶች (ከቀበሌ እስከ ፌዴራል) በውይይት ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲን ለመገንባት
በሕብረተሰቡ ውስጥ የውይይት ባህል እንዲዳብርና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ውሣኔዎች ላይ ለመድረስ የነበሩ
እንቅስቃሴዎች መልካም ቢሆንም የዴሞክራሲያዊነት እና ያሳታፊነት ችግሮች የነበሩባቸው መሆን።

43 | P a g e
የፌዴራል ሥርዓቱን ተግባራዊ ከማድረግ ጋር ተያይዞ እሰከ ውስንነቶቹ ራስን በራስ ማስተዳደር እና የጋራ
አስተዳደር ጋር ተያይዞ የተገኘው ልምድ በቀጣይ ውስንነቶችን የፌዴራል ሥርዓቱን በሚያጠናክር መልኩ
ፈትቶ እና ያሉ መልካም ነገሮችን አጠናክሮ ለመሄድ የሚያስችል ሁኔታን መፍጠሩ በራሱ መልካም ነገር አድርጎ
መውሰድ ይቻላል።

2.10.2. ያጋጠሙ ተግዳሮቶች፣

2.10.2.1. የብሔር መብትንና ሀገራዊ አንድነት አመጣጥኖ አለማየት፣

የፌዴራል ሥርዓት የሕዝቦችን ራስ በራስ የማስተዳደር ሥልጣን ከማጎናጸፍ ባለፈ የሕዝቦች አንድነት እና
የተሳሰረ ግንኙነት በማጠናከር ለአንድነትና ለአገር ግንባታ ያለው ፋይዳ በደንብ ያልታየበት ነበር። ይህም
የሚባልበት ዋና ምክንያት ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የፌዴራል ሥርዓቱ ዋና ትኩረት የሕዝቦችን
ራሳቸው የማስተዳደር ሥልጣን ላይ በማተኮር ባህላቸውን፣ ማንነታቸውን፣ ታሪካቸውን፣ ወዘተ. በማሳደግ
የባህልና የማንነት ተሃድሶ በአገሪቱ ላይ እንዲሰፍን ትልቅ ሚና የተጫወተ ቢሆንም ከሀገራዊ ማነንነት ጋር
አስተሳስሮ ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክር እና ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት አንዱ ስጋት የሆነውን የሃገር
መፍረስን አደጋ በማያስከትል መልኩ አንድነትን ከብዝኃት ጋር ሚዛኑን ጠብቆ ከመሄድ ጋር የሚገናኙ ችግሮች
አሁንም የፌዴራል ሥርዓቱ ላይ የሚያንዥብቡ አደጋዎች ናቸው።

የሀገሪቷን ሕዝቦች ማኅበራዊ እና ባህላዊ ትሰስር ግምት ውስጥ በማስገባት ፌዴራላዊ ሥርዓቱ በአግባቡ ሥራ
ላይ ከዋለ ሥልጣንና ሀብት በሕገመንግሥቱ መሠረት በፌዴራልና በክልል በመከፋፈልና ተገልለናል የሚሉ
ወገኖችም ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ በማድረግና የራሳቸው ማንነት ከሃገራዊ (ኢትዮጵያዊ) ማንነት ሚዛኑ
በጠበቀ መንገድ በመቅረጽና በመምራት እንዲሁም ሕዝቦች በፌዴራል ደረጃ በሚኖሩት ተቋሞች ተመጣጣኝ
ውክልና እንዲኖራቸው በማድረግ አገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በጋራ በመሳተፍና ተጽእኖ ማሳረፍ እንዲችሉ
በማድረግ በአገራቸው ጉዳይ የባለቤትነት ስሜት በማሳደግ ግጭትን ለመፍታት መሣሪያ ከመሆን ባለፈ የጋራ
ቤትን በጋራ በማሳደግ የጋራ ባለቤትነት ስሜት ከፍ እንዲል በማድረግ ለሀገር ግንባታ ሥራ ወሳኝ ተደርጎ
ይወሰዳል። ለዚህም ነው የፌዴራል ሥርዓት በትክክል ከተተገበረ የተለያዩ ወገኖች በራስ ማስተዳደርና በጋራ
አስተዳደሩም በተመጣጣኝ የውክልና ሥርዓት የመሳተፍ እድል በማረጋገጥና የጋራ ባለቤትነት ስሜትን
በማሳደግ ለአገር ግንባታ ወሳኝ መሣሪያ ተደርጎ ይወሰዳል። ይህም ቢሆን የፌዴራል ሥርዓት ለአንድነትና ለአገር
ግንባታ ማለትም የተለያየ ማንነት፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖትና ፖለተካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ባለበት ሁኔታ
ልዩነትን አቻችሎና እነዚህ የተለያዩ ፍላጎቶች አስተናግዶ፣ የብሔርና ሌሎች ፍላጎቶች ባንድ በኩል አገራዊ
አንድነትና የተሳሰረ ማንነት በሌላ በኩል ሚዛኑን ጠብቆ እንዲሄድ ማድረግ ያለውን ጠቀሜታ ብዙ የተባለለት
ነገር አይደለም። በመሆኑም ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓቱ እንደ በታኝ ሞዴል ተደርጎ የመውሰድ የተሳሳተ
ግንዛቤ ሲያዝ ይታያል።

44 | P a g e
እንደሚታወቀው አገራችን የፌዴራል ሥርዓት ዋና መነሻ ለረዢም ዘመን የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት
የነበረውን የሕዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር፣ በሃገራቸው ጉዳይ ላይ እኩል የመሳተፍና የመወሰን ሥልጣን
እንዲኖራቸውና ማንነታቸውና ቋንቋቸው እንዲከበር በሚል የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ያለመ ነው።

ግጭት የሚነሳውና የአገር ግንባታ ሥራው ችግር ውስጥ የሚወድቀው የጋራ ባለቤትነት ስሜት ሲዳከም፣ ራስን
የማስተዳደሩ ሂደት ሳይተገበር ሲቀር ወይም የብሔር ማንነቱ ከሚፈለገው በላይ ወደ ጥግ ሲገፋና የራስ
አስተዳደርን የብቻ አስተዳደር በሚል የተሳሳተ አረዳድ ሲፈጠር ነው፡፡

የሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት አንዱ ሰጋት የሆነው በየከባቢው ተበታነው የሚኖሩ የህዳጣን ሕዝቦች
ሰባዊና ዴሞክራሲያዊ መብት በመጋፋት ሊኖር የሚገባውን ትስስር በማዳከም ሚዛኑ ሲዛባ ነው። በዚህ
መሠረት ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት የሕዝቦችን ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ ከማሳደግ አንጻር የተሻለ ውጤት
ቢመዘገብም የብሔር ማንነትን በማክበር የሕዝቦች የጋራ ማንነት ከመገንባት አንጻር የታየው ሰፊ ችግር
የፌዴራል ሥርዓቱ ዋነኛ ተግዳሮት ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ ችግር የአገር ግንባታ ሥራው ችግር ውስጥ
እንዲወድቅና የሀገራችን ሕዝቦች በሀገራቸው ጉዳይ የጋራ ባለቤትነት ስሜት እንዲዳከም አድርጓል። በሌላ
በኩል የብሔር ማንነቱ ከሚፈለገው በላይ ተገፍቶ ለብሔር ጽንፈኝነት ዳርጎታል፡፡ ይህም ለሥርዓቱ ስጋቶች
ለሆነው ዋልታ ረገጥ አስተሳሰብ መስፋፋት ምክንያት ሆኗል፡፡ በመሆኑም በሕዝቦች ዘንድ ሊኖር የሚገባውን
ትስስር በማዳከም ሚዛኑ እንዲዛባ አድርጎታል።

2.10.2.2. ማንነትን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች መበራከትና ያልተመጣጠነ እድገት እንዲኖር ማድረጉ፣

በ 1987 ዓ.ም. በፀደቀው የኢትዮጵያ ሕገመንግሥት አንቀጽ 46(2) ላይ እንደተመለከተው ክልሎች

የሚዋቀሩት በሕዝብ አሰፋፋር፣ ቋንቋ፣ ማንነትና ፈቃድ ላይ ተመሥርቶ ነው። የክልሎች አወቃቀር ከማንነት

ጋር የሚያያዙ በርካታ ችግሮች እየታዩበት ነው። በፌዴራልና በክልል ደረጃ የፖለቲካ ሥልጣን ክፍፍል፣

ባለቤትነትና ውክልናም የተዛባ ነው፡፡ ከተፈጥሮ ሃብት ክፍፍል፣ ከክልል፣ ከዞን፣ ከወረዳ ወይም ከቀበሌ የድንበር

ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ የሚታዩት ችግሮችም ሰፍተዋል።

ምንም እንኳን የፌዴራል ሥርዓቱ በርካታ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖሊቲካዊ ፋይዳዎችን ያስገኘ

ቢሆንም በማንነት ላይ የተመሠረቱ የአደረጃጀት ጥያቄዎች በየጊዜው እንዲነሱ መንገድ ክፍቷል። የፌዴራል
ሥርዓት አተገባበር የተዛባ ከሆነ በአንጻራዊ መልኩ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሕዝቦች ላይ ትልቅ የሥነልቦና
ጫናና ያለመረጋጋት ስሜት ከመፍጠሩ ባሻገር በፌዴራል ሥርዓቱና በሕዝቦች መካከል አለመተማመን
እንዲስፋፋ የመፍጠር እድሉ ከፍተኛ ነው። ይህም ከአንድነት ይልቅ የራስን ክልል ማደራጀት መብቶቻችንን

ያስከብርልናል ወደሚል መደምደሚያ እንዲደርሱ አደርጓቸዋል። በዚህ ሂደት በሀገራችን የሚገኙ የተለያዩ

45 | P a g e
ክልሎች ወይም የዞን አደረጃጀቶች በጋራ ለረጅም ዓመታት የኖሩ ጭምር በአብሮነት የመቀጠላቸውን ጉዳይ

ጥያቄ ውስጥ አስገብቷል።

ከዚህ ረገድ በኢትዮጵያ የፌዴራል ሥርዓቱ ሁለት ተቃርኖዎችን እያስተናገደ ይገኛል፣ ሥርዓቱ ምንም እንኳን

ማንነትና ቋንቋን መሠረት ያደረጉ ግጭቶችን ለማስታረቅና ብዝኃነትን ለመገንባት የተሻለ ሥርዓት ቢሆንም

ይህ ለብዝኃነት የሚሰጠው ዕውቅና በአግባቡ ስላልተያዘ በሕዝቦች መካከል ልዩነትን በማስፋት ለአክራሪ

ብሔርተኞች መንገዱን በማመቻቸት የአንድ ሀገረመንግሥትን አንድነት ግንባታን በመፈታተን ላይ ይገኛል

(ዮናታን 2016፣ ወንድወሰን በ 2013 ኤሪክና አንደርስበትን (2010፣1-2)፣፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከፍትሐዊ

የሀብትና የሥልጣን ክፍፍል ማዕቀፎች ካለመኖር ጋር ተዳምሮ ሀገሪቱን ፈተና ውስጥ አስገብቷል።

ምሁራን እንደሚሉት የሕዝቦችን ማንነት ማስከበሪያ መንገዶች አብሮነታቸውን በማይጎዳ መልኩ ካልተከናወነ

ግጭት ሊያስነሱ በማይችሉ ጥቃቅን ጉዳዮች ሳይቀር ለዘመናት አብረው የኖሩ ሕዝቦችን ሊያጋጩ የሚችሉ

ሁኔታዎች በቅጽበት እየተፈጠሩ ይሄዳሉ (ዮናታን 2016፣ ወንድወሰን 2013) ።

በሌላ በኩል የፌዴራል ሥርዓቱ ዲሞክራሲዊና ሚዛናዊ ካልሆነ ዋልታ ረገጥ አተገባበሮችና ሀሳቦች ይፈጠራሉ፡፡

በሀሳብ ከመከራከርና ከመተማመን ይልቅ በብሔር፣ በማንነት፣ በሃይማኖት፣ ወዘተ. የተደራጁ ቡድኖች ወይም

ድርጅቶች ከውይይት ባህል ወጥተው የመፈራረጅና በጠላትነት የመተያየት አጋጣሚ ይፈጥራል፡፡ የጋራ

ጉዳዮችን ለማንሳት ጊዜና ምቹ ሁኔታ ወደማያገኙበት አረንቋ ውስጥም ያስገባቸዋል። ይህ ተጨባጭ እውነት

በሀገራችን በሁሉም ደረጃ የሚታይ ሀቅ ነው።

በሌላ በኩል የሀገራችን ፌዴራላዊ ሥርዓት እስከአሁን ያስመዘገባቸው ስኬቶችና ተግዳሮቶች በአግባቡ

ተለይተው የሕዝቡን ጥቅም በሚያረጋግጥ መልኩ መፈተሽ እንዳለበት፣ ከዚህም ጋር ተያይዞ ክፍተቶችን

ለማረም የሚያስችል የፖሊሲ የድጋፍ ማዕቀፍ እንደሚያስፈልግ በፌዴራሊዝም አተገባበር ላይ ጥናት ያደረጉ

ምሁራን ይስማሙበታል። ይህንን ከአንደርሰን (2013)፣ ከጋኢይ (2014) እና ከዮናታን (2016) ጥናታዊ

ግኝቶች ማየት ይቻላል፣፣

ከላይ ከተገለጸው አንጻር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሥርዓት አተገባበር ሲታይ ሰፊ የሕዝብ ቁጥር ያላቸው

ሕዝቦች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን ሕዝቦች አካታችነት ጥያቄ ውስጥ የከተተ

ነው። ይህም ማለት በሀገራችን ፌዴራል ሥርዓት አንጻራዊ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሕዝቦች ባሉበት

46 | P a g e
አስተዳደራዊ አደረጃጀት ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦችን በአካባቢው ፖለቲካዊም ሆነ ማኅበራዊ እንቅስቃሴ

ውስጥ አካቶ መብታቸውን ከማስከበር አኳያ ክፍተት ይታያበታል።

2.10.2.3. አካባቢያዊ አቅምንና ሀብትን በአንድ ማዕከል የማከማቸት ዝንባሌ መኖር፣

እየተገበርነው ያለው የፌዴራል ሥርዓት ከሚታይበት ችግር አንዱ አካባቢያዊ አቅምና ሀብትን በአንድ ማዕከል

(በፌዴራል ዋና ከተማ፣ በክልል፣ በዞንና በወረዳ) ዋና ከተሞች እንዲከማች በማድረግ በአንድ በኩል

በየአካባባቢው ያልተመጣጠነ እድገት እንዲኖር፣ በሌላ በኩል ደግሞ የሀገራችን ሕዝቦች ከጋራ እድገት ይልቅ

በአደረጃጀት ጉዳይ ግጭት ውስጥ እንዲገቡና "ማደግ የምንችለው የራሳችን አደረጃጀት እና ማዕከል ሲኖረን

ነው" ወደሚለው እሳቤ እንዲሄዱ እያደረገ ነው። በእርግጥ በቅርቡ የተመሠረተው የደቡብ ምዕራብ

ኢትዮጵያ ክልል የክልል ብዝኃ ማዕከልነትን አደረጃጀት መከተሉ የሚበረታታ ቢሆንም ይህ አሠራር ዳብሮ

በፌዴራልና በሌሎች አስተዳደራዊ መዋቅሮች እንዲተገበር በማድረግ የሕዝቦች እኩል የመልማት ጥያቄና

አብሮነትን በአንድነት ማስተናገድ ይቻላል።

2.10.2.4. ለሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ጠቃሚ የሆኑ ተግባራትን ያለማከናወን፣

ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓቱ ብዝኃነትን ባቀፈ መልኩ ሃገራዊ አንድነትን ሊያጠናክሩ የሚችሉ
ተግባራትን ማከናወን እንደሚጠይቅ ከሌሎች ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሃገሮች ተሞክሮ መረዳት ይቻላል፡፡
ከዚህም ውስጥ አንዱ ፌዴራል ሥርዓት የሚገነባው አብሮነትን፣የጋራ ፍላጎትን፣ ለአንዱ አንዱ ዕውቅና
መስጠትን፣ ወንድማማችነት፣ መተማመንን መሠረት አድርጎ በመሆኑ እነዚህ ጉዳዮች በሃሳብ እና በትርክት
ደረጃ በተግባር ጎልተው በመውጣት በብዝኃነት ውስጥ ያለው አንድነት እንዲጠናከር ማድረግ ይጠይቃል፡፡

የጋራ ያልሆኑና የሚለያዩ ነገሮች ካሉም እነዚህን ጉዳዮች በማጥራት በውይይት እና ለዘላቂ ሀገር ግንባታ
በሚጠቅም መልኩ መፍታት እና መሻገር ይጠይቃል። ከዚህም ሌላ በጥናት ላይ ተመሥርቶ በውይይት
ከሰንደቅዓላማ፣ ከቋንቋ አጠቃቀም፣ ከሌሎች ሀገራዊ ምልክቶች/ የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት የሰው ሀብት
ስብጥር ወዘተ. ዙሪያ ለብሔራዊ አንድነት ትስስርና ለፌዴራል ሥርዓቱ መጠናከር በሚያግዝ መልኩ በአግባቡ
ካልተመራ በሀገራችን ሕዝቦች መካከል አለመተማመን በመፍጠር የፌዴራል ሥርዓቱን ሊጎዳው ይችላል።

2.10.2.5. ስለፌዴራላዊ ሥርዓት አጠቃላይ ባህሪያት፣ ሥርዓቱ ስለሚገነባበት እሴቶች እና መርሆዎች፣


እንዲሁም ሥርዓቱ የሚጋጥሙት ተግዳሮቶች እየተፈቱ ስለሚሄዱበት አግባብ ተፈላጊው አመለካከት እና
አስተሳሰብ እንዲዳብር የተሠራው ሥራ አናሳ መሆን፣

47 | P a g e
የፌዴራል ሥርዓት ግንባታ ሂደት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሥርዓቱ በየጊዜው እየዳበረና እየተገነባ እንዲሄድ
መሠረት የሚሆኑ ተፈላጊ የሆኑ አሠራሮች እና መርሆዎች እያዳበሩ መሄድን ይጠይቃል። ከዚህም ሌላ
የፌዴራል ሥርዓት እንደማንኛውም ሥርዓት የራሱ የሆኑ ተግዳሮቶች ይኖሩታል፤ ችግሮችም ይገጥሙታል፡፡
የፌዴራል ሥርዓት ከችግር የጸዳ እና ለሁሉም ችግሮች ደግሞ መፍትሄ ሊሆን አይችልም፤ በመሆኑም
የፌዴራል ሥርዓቱ የሚጋጥሙትን ችግሮች በየጊዜው በጥናት ላይ ተመስርቶ የፌዴራል ሥርዓቱን
በሚያጠናክር መልኩ እየፈቱ መሄድ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ጉዳይ ግን በሀገራችን ተፈላጊ የሆነውን የፌዴራላዊ
ሥርዓት አመለካከትን ተላብሶ ችግሮችን በውይይት እና በድርድር እየፈቱ የሚሄድበትና ተፈላጊ የሆነው
አስተሳሰብ ተፈጥሯል ብሎ ደፍሮ መናገር አይቻልም።

የሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት በባህሪው በተቃርኖ ትብብር ላይ የሚገነባ መሆኑን በአግባቡ በመገንዘብ
በማንኛውም ሁኔታ ሚዛን መጠበቅን የሚጠይቅ ነው፡፡ ሁለት እኩል ተፈላጊ የሆኑና ተቃራኒ የሚመስሉ
ጉዳዮችን ሚዛን ጠብቆ በማስኬድ የሁለቱንም ጠቀሜታዎች በብዝኃት ውስጥ ለአንድነት እና ዘላቂ ሰላም
ግንባታ ማዋል ያቻላል፡፡

ለምሳሌ ያህል፡-

 የግለሰብ መብት - የቡድን መብት


 ከባቢያዊ የመልማት ፍላጎት እና አቅም - ሀገራዊ የመልማት ፍላጎት እና አቅም
 የራስ አስዳደር - የጋራ አሰተዳደር
 ብሔራዊ ማንነት- ሀገራዊ ማንነት
 ብዝኃነት- አንድነት

እነዚህን ጉዳዮች በአንድ የፖለቲካ ሥርዓት ለማስተናገድ ውስብስብ መሆናቸውን እና ሁሌም ሚዛን መጠበቅን
የሚጠይቅ መሆኑን ግንዛቤ ያስገባ ሥራ ተሠርቷል ማለት አያስደፍርም፡፡

2.10.3. በቀጣይ ቢሠራባቸው ተብለው የቀረቡ ምክረ ሃሳቦች፣


2.10.3.1. ለሀገረ መንግሥት ግንባታ የሚያግዙ የጋራ እሴቶችን ለይቶ መገንባት፣

እንደ ሕብረ ብሔራዊ ፌዴራል ሞዴል አንዳንድ አገሮች ሕዝቡን ለማስተሳሰርና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት
ግንባታ እንዲኖር ለማድረግ ሲባል ሚት (myth) ላይ የተመሠረተ ታሪክ እንደሚጽፉ ይታወቃል። በአገራችን
ሁኔታ ግን በበርካታ የታሪክና ሌሎች ቁሳዊ ነገሮች ሊጨበጥ የሚችል እውነተኛ አብሮ የመኖር መስተጋብር
መኖሩን ስለሚያመላክቱ፣ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ የሚያስተሳስሩ እነዚህን የጋራ እሴቶችና ታሪኮች
በአግባቡና ሚዛኑ ተጠብቆ መሰነድና ማስተማር የበለጠ ይጠቅማል።

48 | P a g e
ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በብዙ ነገር የሚገናኝና የተሳሰረ ማኅበረሰብ ወደ ግጭት የመግባት እድሉ የቀነሰ
ነው። ከዚህ አንጻር መታየት ያለበት ነጥብ ባለፉት ቅርብ ዓመታት ሕዝቦች በክልልም ይሁን ከዚያ በታች ባሉት
የአደረጃጀት እርከኖች የራሳቸውን ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋ ሲጠቀሙ ራስን የማስተዳደር አንዱ መገለጫ ቢሆንም
ተጨማሪ ሥራ የሚጠይቅ መሆኑ ነው። በአንድ ፌዴራል ሥርዓት ውስጥ የተሳካ የአገር ግንባታና የተሳሰረ
ማንነት ተገነባ የሚባለው፣ ሕዝቦች ራሳቸውን ማስተዳደራቸው አንድ ነገር ሆኖ፣ የሌሎችን ማንነት ማወቅና
ማክበር፣ የዜግነት መብት ማወቅና ማክበር፣ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ጤነኛ የሆነ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት
መፍጠርና የተሳሰረ/ የተጋመደ አገራዊ አንድነት መፍጠር መቻልን ይጠይቃል። ይህ ደግሞ ግልጽ ፖሊሲና
ስትራተጂ የሚያስፈልገውና (ለምሳሌ የባህል፣ የቋንቋ፣ የሚዲያ፣ የትምህርት፣ የታሪክ፣ የሕግ ሥርዓቱ፣
አርት፣ ሃውልቶች፣ ሳንቲሞችና ብሮች ላይ የሚቀመጡ ምልክቶች፣ ወዘተ.) የዚህ ማራመጃ ዋና ማስፈጸሚያ

ናቸው። እነዚህን በርካታ የግንኙነት ሰንሰለቶች ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ መጠቀም ለሀገር ግንባታ እና ሰላም

ትልቅ ሚና ይጫወታል።

2.10.3.2. ብዝኃነትን ያከበረ የተሳሰረና የተዋሐደ ማንነት መገንባት፣

ሌላው ለሰላም ግንባታና ለግጭት መቀነስ ትልቅ ሚና የሚጫወተው፣ አንድ ሕዝብ ከሌላው ሕዝብ በቋንቋ
ወይም በእምነት ሊለይ ቢችልም ሁሉንም ሕዝቦች የሚያስተሳስር ብዙ ሌሎች ገመዶች (ለምሳሌ በመደብ፣
በጉርብትና፣ በኑሮ ሁኔታ፣ በቋንቋ ቤተሰብነት፣ እድር፣ በሞያ ማኅበር፣ በፖለቲካ ድርጅትና፣ አመለካከት፣
በሃይማኖት፣ አገርን ከውጭ ወራሪ ሃይል በጋራ መመከትንና የጋራ ዜግነትን ወዘተ) መኖራቸው መገንዘብና
እነዚህን በርካታ የግንኙነት ገመዶች ተጠቅሞ የሕዝቦችን ግንኙነት ማጠናከር ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ትልቅ
ሚና የሚጫወት መሆኑ ነው። ለምሳሌ ሰዎች በቋንቋ ቢለያዩም በሃይማኖት፣ በጉርብትና አልያም በሙያ
ይተሳሰራሉ። በአንድ ነገር ቢለያዩም፣ አድዋና አድዋን በመሰሉ በርካታ አገርን ከወራሪ ጠላት የማዳን ጦርነቶች
(ከዚያድባሪ ጋር በኢትዮ ሶማሊ፣ በባድመ ወዘተ) አብረው መስዋእት ከፍለዋል። የታሪክ ባለሞያዎች ደግመው
ደጋግመው እንደሚነግሩን ለበርካታ ረዢም ዘመናት አብሮን የቆየ የንግድ፣ የጋብቻ፣ የአብሮ መኖር መስተጋብር
መኖሩን ነው።

2.10.3.3. በሕዝቦችመካከል መተማመንን የሚፈጥሩ ተግባራትን ማከናወን፣

በአንዳንድ አካባቢዎች ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች፣ መፈናቀሎችና ግድያዎች እየታዩ በመሆኑ

ከቀበሌ ጀምሮ ሕዝቦች ከሚለያያቸው የሚያገናኛቸው በርካታ ገመዶች መኖራቸውን በማሳወቅ የእርቅና

የአንድነት መድረኮችን በመፍጠር መተማመንን የመፍጠር ሥራ መሥራት ያስፈልጋል። ከዚህ በፊት

ያሳለፍናቸው በተለይ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት የተከተልነው ፖሊሲ በሕዝቦቻችን መካከል ካሉት በርካታ የጋራ

እሴቶች ይልቅ ልዮነቶችን አጉልቶ የማሳየት ዝንባሌ ስለነበረው በቀጣይ ሕዝቦቻችንን የሚያስተሳስሩት

49 | P a g e
ድርብርብ ማንነቶች መኖራቸውን በማሳየት፣ የሚከናወኑ ተግባራት ሁሉም ሚዛናቸውን የጠበቁ ማድረግ እና

የሚወጡ ፖሊሲና የሕግ እይታዎችም በብዝኃነት እና በአንድነት ዙሪያ ሚዛን የጠበቁ ማድረግን ይጠይቃል።

የአሳለፍናቸው የፖለቲካ ልምምዶች ከኔ ማንነት ውጭ በሆኑ ቡድኖች እየተጠቃሁ ነኝ፣ እየተገለልኩ ነው (a

sense of exclusion) የሚል ስሜት ያዳበረ በመሆኑና በጊዜ ካልታከመ ከዚህ በላይ ችግር ሊመጣ

እንደሚችልም መገመት ይቻላል።

ካለፉት ልምዶቻችን እንደምንረዳው በተለይ በደቡቡ የሀገራችን ክፍል የክልል ጥያቄዎች መበራከት ጀርባ ካሉ

ገፊ ምክንያቶች መካከል ተገፋሁ የሚሉ ቡድኖች የራስን ማንነት ወደ መፈለግና ምቹ መኖሪያ (safe haven)

ቢኖረኝ ደኅንነቴን ማረጋገጥ እችላለሁ ወደሚል እንደገፋቸው፣ ይህ ምቹ ቦታም የራስ ክልል ነው ወደሚል
ድምዳሜ አድርሶናል ብለውም ያምናሉ።

2.10.3.4. የመንግሥታት ግንኙነቶች ማጠናከር፣

በፌዴራል ሥርዓት የፌዴራል ሥርዓቱን የሚመለከቱ ሁሉም ጉዳዮች የፌዴራል ሥርዓቱን ለመደንገግ

በሚደረጉ ውይይቶች እና የፌዴራል ሥርዓቱን የደነገገው ሕገመንግሥት በጸደቀበት ወቅት ሊጠናቀቁ

አይችሉም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአንድ ሃገር በሚኖሩ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ለውጦች የፌዴራል

ሥርዓቱ ሊያካትታቸው የሚገቡ አዳዲስ ጉዳዮች ይኖራሉ። እነዚህን ሁኔታዎች በየወቅቱ እያካተቱ ፌዴራል

ሥርዓቱን ሚዛን ጠብቆ እንዲሄድ ማድረጉ አስፈላጊ በመሆኑ እና በአንድ ሃገር የሚገኙ ለአንድ ሕዝብ

በተለያየ አግባብ አገልግሎት የሚያቀርቡ መንግሥታት የሚሠሩትን ሥራ ማቀናጀት እና ማናበብ

ለውጤታማነነቱ ከፍተኛ አስተዎጽኦ ስለሚኖረው የመንግሥታት ግንኙነትን ማጠናከር አስፈላጊ ነው፡፡

የመንግሥታት ግንኙነት መጠናከር፣ በሚታወቅ እና መተንበይ በሚቻል አግባብ መከናወኑ፣ መንግሥታት

እርስበርስ የሚደርጉት ግንኙነት በጨመረ ቁጥር ትምምኑና ትብብሩ እየጨመረ መሄዱ በመካከላቸው

የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በቀላሉ ለመቅርፍ ያስችላል፡፡ በጋራ በሚጋሩት ወሰን አካባቢ የሚኖሩ

ማኅበረሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን በጋራ አቅደው የሚተገብሩበት እድል ሰፊ ይሆናል፤ ይህም

ወሰኖች የግጭትና የይገባኛል ማእከሎች መሆናቸው ቀርቶ የጋራ ልማት ማእከሎች የመሆን ዕድላቸው ሰፊ

ነው። የመንግሥታት ግንኙነት የአንድ ፌዴራል ሥርዓት ተግባራዊነት ዋነኛ መገለጫ በመሆኑ እና

መገናኘት፣መመካከር የፌዴራል ሥርዓት የሚመራበት ዋነኛ መንገድ በመሆኑ በ 2013 በጀት ዓመት የጸደቀውን

50 | P a g e
በኢፌዴሪ የመንግሥታት ግንኙነት ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1230/2013 ካለው ጅምር እንቅስቃሴ

ይበልጥ አጠናክሮ ወደ ሥራ ማስገባቱ ይመከራል፡፡

2.10.3.5. ሕገመንግሥታዊነትን ማስፈን፣

የፌዴራል ሥርዓት አንዱ መገለጫው ሕገመንግሥታዊነቱ ነው። የፌዴራል ሥርዓት ያለ ሕገመንግሥት


የማይታሰበውን ያህል ሕገመንግሥት ደግሞ ያለ ሕገመንግሥታዊነት የታሰበለትን ዓላማ ሊያሳካ እና
ዴሞክራቲክ የሆነ፣ የተረጋጋ እና ቀጣይነት ያለው የፌዴራል ሥርዓት እውን ሊያደርግ አይችልም። በፌዴራል
ሥርዓት ሕገመንግሥቱ ካልተከበረ እና በሥርዓቱ ለመተዳደር የወሰኑ መንግሥታት ሊተዳደሩበት የወሰኑትን
ሕግ ካላከበሩ እና ሕገመንግሥቱን በመጣስ የሚንቀሳቀሱ ከሆነ በአንድ ፌዴራላዊ ሥርዓት አብሮ መቀጠልን
አደጋች ከማድረጉም በላይ ‹‹ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን እናስከብራለን›› በሚሉ እና ሥርዓቱን በመጣስ
በሚንቀሳቀሱ አካላት መካከል ግጭት በመፍጠር ሥርዓቱ የመፍረስ አደጋ ያጋጥመዋል።

በፌዴራል ሥርዓት ሕገመንግሥት፣ መንግሥት ከዜጎች ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ከመወሰን በዘለለ በሥርዓቱ
የታቀፉ መንግሥታትን የሥልጣን እና የሃብት ክፍፍል የሚወሰን በመሆኑ የሕገመንግሥታዊነት አለመከበር
የዜጎችን መብት መጣስን ከማስከተሉ ጎን ለጎን የመንግሥታትን በሕገመንግሥቱ የተሰጣቸውን ሥልጣን እና
ኃላፊነት መጣስን ስለሚያስከትል ለፌዴራል ሥርዓቱ አደጋ መሆኑ የማይቀር ነው። በተጨማሪም እንደ
ኢትዮጵያ ባሉ ሕብረብሔራዊ በሆነ ፌዴሬሽኖች ሕገመንግሥታዊነት አለመስፈን የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና
ሕዝቦችን መብትን መጣስ ሊያስከትል እንደሚችል መገንዘብ ተገቢ ነው። ስለሆነም ሕገመንግሥታዊነትን
ማክበር የሚያስችል የአመለካከት እና የአስተሳሰብ ሥራዎችን መሥራት ይህን በተግባር መግለጽ ያስፈልጋል።

ሕገመንግሥታዊነት በሕገመንግሥቱ ውስጥ የተካተቱ እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ቡድን መሻሻል አለባቸው
ብለን የምንወሰዳቸው አንቀጾች እንኳ ቢኖሩ ሕገመንግሥቱ ያስቀመጠውን ሥርዓት ተከትሎ እንዲሻሻሉ
መሥራት ይጠይቃል። በሀገራችን ፌዴራላዊ ሥርዓቱ ለሚያጋጥሙት አብዛኛዎቹ ችግሮች መፍትሄ የሚሆነው
ሕገመንግሥታዊነት ባህል የሚሆንበት ደረጃ የሚደርስ ተግባር ማከናወን ሲቻል ነው። ዙሮ ዙሮ የፈለገውን
ዓይነት ሕገመንግሥት ቢኖርም ያለሕገመንግሥታዊነት ዋጋ አይኖረውም።

2.11 ማጠቃለያ፣
በዚህ ክፍል ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ለሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ካለው ጠቀሜታ አኳያ ሥርዓቱ
ከጽንሰ ሃሳብ ጀምሮ በሰፊው የተብራራ ሲሆን ከሕብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ጋር ተያይዞ የሚነሱ
አከራካሪ ጉዳዮች በዝርዝር ቀርበዋል። ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓትን መድኃኒት ወይስ እርግማን በሚል
በቀረበው ሐሳብ ሥርዓቱ ውጤታማ ሊሆን የሚያስችሉና የማያስችሉ ጉዳዮች ከተደረጉ ጥናቶች በመነሳት

51 | P a g e
በዝርዝር ቀርበዋል። በመጨረሻም ሕብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ አንጸር
ተዳስሷል፡፡ መልካም ጉዳዮችና ውስንነቶች ቀርበዋል፡፡ ብዝኃነትን ያቀፈ አንድ ጠንካራ ሀገረ መንግሥትን
ለመገንባት የሚስችሉ ምክረ ሃሰቦች ተመላክተዋል።

በመጨረሻም የሕብረብሔራዊነትን ነባራዊ ሁኔታ ተቀብለው ፈተናውን ያለፉ ጥቂት ሃገራት ሲሆኑ
ነባራዊ ሁኔታው የሚፈጥረውን ፈተና ከማለፍ ይልቅ ብዙዎቹ ነባራዊ ሁኔታውን እንደሌለ መካድ እና
የተለየ ነባራዊ ሁኔታ ለመፍጠር የሚታትሩ ሆነው ታይተዋል። የተለየ ሁኔታ ለመፍጠር
የሚጠቀሙባቸው ስልቶችም ውህደት (assimilation) ፣ በኃይል ማፈናቀል፣ እጅግ በከፋ ሁኔታ ጫፍ
ሲይዝ ደግሞ የተለየ ማንነትን ለማጥፋት መንቀሳቀስን ይጨምራል።

የሕብረብሔራዊ ዴሞክራሲ ትልቁ ፈተና በብሔረ መንግሥቱ እና ራሳቸውን በብሔር የሚገልጹ


ማኅበረሰቦች መካከል ከሚኖረው የፖለቲካ ተቃርኖ መፍትሄ የሚያመጣ ስትራቴጅና ስልት ማበጀት
ነው። ሀገራችንም ነባራዊ ሁኔታውን በመቀበል ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ዴሞክራሲያዊ በሆነ
አግባብ ለመገንባት በየጊዜው የሚነሱ ጥያቄዎች ሥርዓቱን በሚያጠናክር እና ነባራዊ ሁኔታዎችን
መሠረት ያደረገ መልስ መስጠት የሚስችሉ ሥራዎች እየሠሩ መቀጠል ይጠይቃል። ይህን እውን
ለማድረግ ደግሞ የሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ውስብስብ የሆነ እና ሁሌም ሚዛን መጠበቅን፣
በየጊዜው የሁሉንም ማኅበረሰብ ሕገመንግሥታዊነት እና ፌዴራላዊ አስተሳሰቡን እየገነቡ መሄድን
የሚጠይቅ ፌዴራላዊ ሂደት መሆኑን ግንዛቤ ያስገቡ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጅዎችን በየጊዜው እየነደፉ
መንቀሳቀስ ይጠይቃል፡፡

ክፍል ሶስት፣ ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት እና የሰላም ግንባታ፣

3.1. መግቢያ፣
ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት በራሱ ተፈላጊ፣ ጠቃሚና ብዝኃነትን ባቀፈ አንድነት ውሰጥ መኖር ለሰው
ልጆች በራሱ የመጨረሻ ግብ ተደርጎ ቢወሰድም ሥርዓቱ በትክክልና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ መተግበር ለሰላም
ግንባታ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። ስለሆነም በዚህ ክፍል የሰላም ግንባታ እና ሕብረብሔራዊ ፌዴራል

52 | P a g e
ሥርዓት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች እና የኢ ፌ.ዴ.ሪ ህገመንግስት የህብረበሄራዊ ፌደራል ስርዓት እና የሰላም
ግንባታ ማእቀፍ መሆኑን በሚተነትን መልክ ቀርቧል።

3.2. ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት የሰላም ግንባታ ያላቸው ግንኙነት፣


የሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት እና የሰላም ግንባታ ያላቸውን ግንኙነት ከመተንተኑ በፊት ሕብረብሔራዊ
ፌዴራል ሥርዓት በአለፉት ክፍሎች በስፋት የተብራራ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ የሰላም ግንባታ ስለሚለው
ጽንሰ ሃሳብ መነሻ የሚሆን ማብራሪያዎችን ማቅረብ ጠቃሚ ይሆናል።

በሰላም ጥናት፣ ሰላም የሚለው ጽንሰ ሃሳብ አሉታዊ መልክ ያለው ሰላም (Negative Peace)፣ ግጭት
(ብጥብጥ ማቆም) አለመኖር እና አዎንታዊ መልክ ያለው ሰላም (positive peace) ለግጭት መንስኤ
ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን ከመሠረቱ ለመለወጥ መዋቅራዊ ለውጥ ላይ መሥራት፣ መዋቅራዊ
የሆነ ግጭት አለመኖር፣ ማኅበራዊ ፍትሕ መኖር ወዘተ… በሚያጠቃልል መልኩ ከፋፍሎ ማየት
የተለመደ ነው (ጋልቱንግ 1975)።

የሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ግንባታ ከመነሻው በሕዝቦች መፈቃቀድ ላይ የሚመሠረት እና


ሁሉም ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ በራስ አስተዳደር እና የጋራ አስተዳደር የሚሳተፉበት፣
የከባቢያቸውን አቅም እና ፍላጎት ከሀገራዊ ልማትና ፍላጎት ጋር አስተሳስረው የሚተገብሩበት፣ የእኩል
ተጠቃሚነት ዕድል የሚፈጥሩበትና ማንም የማይገለልበት ስለሚሆን አዎንታዊ ሰላም ለማስፈን
የሚያስፈልጉ መዋቅራዊ ለውጦችን በማምጣት፣ ማኅበራዊ ፍትሕን ማረጋገጥና መዋቅራዊ የሆኑ
ግጭቶችን ማስወገድ የአዎንታዊ ሰላም መሠረት አድርጎ ማየት ይቻላል። ይህ የሚሆነው ግን ሥርዓቱ
ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ከተተገበረ እና በዚህ ጽሑፍ ቀደም ባሉት ክፍሎች በዝርዝር የቀረቡት
ለሥርዓቱ ተግባራዊነት አስፈላጊ የሆኑ እሴቶችና መርሆዎች በማኅበረሰቡ ውስጥ እየዳበሩ ከሄዱ፣
የሚያጋጥሙትን ችግሮች ሚዛናዊ ሆኖ ሥርዓቱን በሚያጠናክር መልኩ እየፈቱ ለመሄድ የሚያስችሉ
ተቋማትንና የአሠራር ሥርዓቶችን እያጠናከሩ መሄድ ሲቻል ነው።

ከሰላም ጽንሰ ሃሳብ ጋር ተያይዞ ጆን ጋልቱንግ (1975) የሰላም ሦስቱ ዘዴዎች ( three approaches to peace)
ማለትም ሰላም መጠበቅ (Peacekeeping)፣ ሰላም መፍጠር (Peacemaking)፣ ሰላም መገንባት
(Peacebuilding) በሚል ጽንሰ ሃሳቡን ይበልጥ ያብራራዋል።ሰላም ግንባታ ግጭትን ከማስተዳደር እና
ከመፍታት አልፎ ትራንስፎርም የማድረግ ጉዳይ ይጨምራል። ትራንስፎርም ለማድረግ ደግሞ ማካተትን፣
ሶሻላይዜሽን፣ ማኅበራዊ ካፒታልን በግጭት ዙረያ ያለን አመለካከት እና አሰተሳሳብ መቀየርን፣ በማኅበረሰቡ
ውስጥ እርስ በእርስ እና በመንግሥት እና ማኅበረሰብ መካከል የሚኖሩ የግንኙነት አግባቦችን
ማስተካከል ይጠይቃል።

53 | P a g e
የሰላም ግንባታ የሚጠይቀውን ከላይ የተዘረዘሩ ተግባራትና ሂደቶች ደግሞ ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት
ዴሞክራሲያዊና ሚዛናዊ በሆነ አግባብ ሲተገበር የሚፈጠሩና የሥርዓቱ ተግባራዊነት መሠረቶች ስለሆኑ
ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓትን በትክክለኛው አቅጣጫ መተግበርና ሰላምን መገንባት መሆኑን
ማስቀመጥ ተገቢ ነው።

በሃገራችን አሉታዊ ሰላም እንኳ ለማምጣት ከሚታዩ ችግሮች እና የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ራስን
በራስ ከማስተዳደር፣ በጋራ ጉዳዮች ላይ እኩል ተሳትፎ ከማድረግ ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ የሚከሰቱ ችግሮች
ምንጩ ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ነው የሚል እይታ በተወሰኑ ክፍሎች እንዳለ ይታወቃል፡፡ ሆኖም
ሥርዓቱ ዴሞክራሲያዊና ትክክለኛ በሆነ መንገድ ሚዛን ጠብቆ ከተተገበረ የግጭት ምንጭ ሳይሆን በሀገራችን
ነባራዊ ሁኔታ የሰላም ግንባታ መሠረት ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም የእኔ ነው የማይለው ሥርዓት ሰላምን
ሊገነባ አይችልምና፡፡ ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ግን የሁሉንም ፍላጎት አንጻራዊ በሆነና በተሻለ
መንገድ ማስተናገድ የሚችል በመሆኑ ሰላምን ይገነባል።

ከዚህም ሌላ የሰላም እሴቶችን ብንመለከት ለምሳሌ፡- መቻቻል፣ ዕውቅና መስጠት፣ መከባባር፣ የሃሳብ
ልዩነትን መቀበል፣ የሰላም መገንቢያ መሣሪያዎች ሲሆኑ እነዚህ እሴቶች የሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት
እሴቶች በመሆናቸው የሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ዴሞክራሲዊ በሆነ አግባብ ማጠናከር የሰላም
ግንባታ ጉዳይ ነው፡፡

ሌላው የግጭት መንስኤዎች እንደ ግጭቱ አውድ ብዙና የተለያዩ ቢሆኑም ዙሮ ዙሮ በሃብት ላይ ከመወሰን ጋር
ስለሚያያዝ ይህን ውሳኔ ለመስጠት ከሚኖር ሥልጣን ጋር መቆራኘታቸው አይቀርም፡፡ በመሆኑም ሰላም
ለመገንባት ከሥልጣን ጋር ያለንን እይታ ማስተካከል፣ የሕዝብን ልዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነትን መቀበልና
ለተፈጻሚነቱ መሥራት፣ ሥልጣን ለመያዝም ሆነ ለመልቀቅ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓትን ተከትሎ መሆን
እዳለበት ማመንና መቀበል በአጠቃላይ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓት መገንባትንና ሕገመንግሥታዊነትን መተግበር
ይጠይቃል።

ሕገ መንግሥት፣ ፌዴራላዊ ሥርዓት እና የሕግ የበላይነት የማይነጣጠሉ መሆናቸውን እና ፌዴራላዊ


ሥርዓት ያለ ሕገ መንግሥት የማይታሰብ ሲሆን ፌዴራላዊ ሥርዓቱም ሆነ ሕገ መንግሥቱ ያለ የሕግ
የበላይነት ፋይዳ ቢስ የሚሆኑበት ሁኔታ ሰፊ ነው፡፡ ስለሆነም እንደ አንድ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ
ማኅበረሰብ በጋራ ለመቀጠል የወሰኑ በሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት የተዋቀሩ ማኅበረሰቦች
ሥርዓታቸውን የመሠረቱበትን ሕገመንግሥት ለማክበር እና ለመተግበር ያላቸው ፍላጎትና ተነሳሽነት ከፍ ያለ
ስለሚሆን ሕገመንግሥታዊነት እያረጋገጡ የመሄድ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡

54 | P a g e
በመሆኑም ሁሉም ጉዳይ በንግግር እና በውይይት፣ ሕግና ሕግን ተከትሎ ስለሚፈጸም ቀጣይነት ያለው ሰላምን
የማረጋገጥ እና ሰላምን እየገነቡ መሄድ ያስችላል። ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ሂደቱ አካታች እና ሁሉም
አካላት በተለይም ዝቅተኛ ቁጥር ያላቸው ማኅበረሰቦች ድምጽ የሚሰማበትና ተሳትፏቸው በተገቢው
የሚረጋገጥበት መሆን ይኖርበታል።ይህ በተለይ በባለ ብዙ ብሔር፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ ወዘተ. በሆኑ
ፌዴሬሽኖች ውስጥ ውሳኝ ጉዳይ ይሆናል። የአመለካከት፣ የአስተሳሰብ ሆነ የባህል፣ የቋንቋ፣ የብሔር
ብዙኃነትን በማካተት ሁሉንም የፌዴራል የስምምነቱ አካል ማድረግ ጠቃሚ ነው። ይህ ጉዳይ
የሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት መሠረታዊ መገለጫ ስለሆነ ሁሉም ማኅበረሰብ የተካተተበት
ሥርዓት፣ የሰላም ግንባታ መሠረት እንደሚሆን አጠያያቂ አይሆንም።
በመጨረሻም የሁሉም ነገር ግጭትም ሆነ ሰላም መነሻው ሃሳብ በመሆኑ ሰላምን ለመገንባት
ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ሃሳብን የመገንቢያ ዘዴዎች፣ ሃሳብን የማዋዋጥ ዘዴ፣ የማስማማት ዘዴ፣ የመተባበር
እና የማቀናጀት ዘዴና እምነትን እየፈጠሩ የመሄድ ዘዴ መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህ ዘዴዎች ሕብረብሔራዊ
ፌዴራላዊ ሥርዓት እየተገነባ የሚሄድባቸው ዘዴዎች ስለሆኑ ሰላም ግንባታ እና ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ
ሥርዓት ግንባታን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች አድርገው ያሳዩናል።

3.3. የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገመግገስት እና ዘላቂ ሠላም


ቀደም ባሉት ክፍሎች የዘላቂ ሰለም ምንነት እና ህብረብሄራዊ ፌደራላዊ ስርዓት መገንባት ዘላቂ ሰላምን
ከመገንባት ጋር ያላቸዉን ግንኙነት ከሁለቱ ጽንሰ ሃሳቦች መሰረታዊ ባህሪ በመነሳት መዳሰሳችን ይታወሳል፡፤
ከዚህም ጋር በማያያዝ ፌደራል ስርዓት ህገመንግስታዊ ስርዓት መሆኑን እና ህገመንግስታዊ ስርዓቱ ተግባራዊ
ከሆነ እና ህገመንግስታዊነት የአስሳሰባችንም ሆነ የእለት ተእለት ተግባራችን መገለጫ ከሆነ ህብረብሄራዊ
ፌደራል ስርዓቱን በትክክለኛዉ አቅጣጫ ለመገንባት ከማስቻሉም በላይ ለዘላቂ ስላም መሰረት እንደሚሆን
አይተናል፡፡ ከዚህ በመነሳት የኢ.ፌ.ዴ ሪ. ህገመንግስት ሕብረብሄራዊ ፌደራላዊ ስርዓቱ እና ዘላቂ ሰላም
የሚገነባበት መሠረታዊ የህግ ማእቀፍ በመሆኑሁሉንም ሕገመንግስቱ የያዛቸዉን አንቀጾች ለዘላቂ ሰላም
ካላቸዉን አንደምታ መተንተን ተገቢ እና የሚቻል ቢሆንም በዚህ ማስልጠኛ ጽሁፍ ቀደም ብለዉ በጽሁፉ
ከቀርቡት መሰረታዊ ጉዳዩች በተጨማሪ ለዘላቂ ሰላም መሰረታዊ መነሻ የሚሆኑትን በህመንግስቱ መግቢያ
ላይ የተቀመጠዉ እና የሕገመንግስቱን ዓለማ የሚሳየዉን ክፍል እና በአንቀጽ 1 ህገመንግስቱ የሚደነግገዉን
የመንግስት አወቃቀር ከዘላቂ ሰላም አኳያ ገለጭ በመሆናቸዉ በነሱ ላይ በመገደብ እንደሚከተዉ ቀርቧል ፡፡

ህገመንግስቱ በመግቢያዉ #እኛ የኢትዬጵያ ብሄር ፤በሄረሰቦች ሕዝቦች በሀገራችን ኢትዩጵያ ዉስጥ ዘላቂ
ሰላም፤ዋስትና ያለዉ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ፤ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገታችን እንዲፋጠን የራሳችን እድል
በራሳችን የመወሰን መብታችን ተጠቅመን በነፃ ፍላጎታችን፤ በህግ የበላይነት እና በራሳችን ፈቃድ ላይ
የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ ለመገንባት ቆርጠን በመነሳት---# በሚል የሚጀምር ሲሆን
በህገመንግስቱ መግቢያ የመጀመሪያዉ ከፍል በግልጽ እንደ ተመላካተዉ የህገመንግስቱ አንዱ መሰረታዊ ግቡ

55 | P a g e
ወይም ሊያሳካዉ ያለመዉ ዓላማ ዘላቂ ሰላም ነዉ፡፡ በመሆኑም በሀገሪቱ የሚተገበሩ ማንኛዉም ጉዳዩች
ይህን የሕገመንግስቱን ዓላማ ታሳቢ ያደረጉ መሆን እንደሚኖርባቸዉ ያስገድዳል፡፡ዘላቂ ሰላም የሕገመንግስቱ
ዋናዉ መሰረት መሀኑንም ያመላክታል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ይህን ህገመነግስታዊ ዓላማ ለማስፈጸም መዋቀር
ያለበት መንግስት ምን ዓይነት መንግስት እንደሆን በሀገመንግስቱ የመጀመሪያዉ አንቀጽ ፌደራላዊና
ዴሞክራሲዊ መንግስታዊ አወቃቀርን አወቃቀርን ደንግጓል ይህን ድንጋጌ መሰረት አድርጎ ፌደራላዊ እና
ዴሞክራሲያዊ መንግስት ማዋቀር በራሱ ለዘላቂ ሰላም ወሳኝ የሆኑ ጉዳችን የያዘ ነዉ፡፡ ፌደራላዊ የሆነ ስርዓት
ህገመንግስታዊ ድርብ የስልጣን ከፍፍል ያለበት፤ ስልጣን ባንድ ቦታ የማይከማችበት፤ ሁሉም የራሱን
በሚመለከቱ ጉዳዩች እና በጋራ ጉዳች በሚኖሩ ዉሳኔዎች የሚሳተፍበት፤ የፖለቲካ ተሳትፎዉን የሚያሰፋበት፤
ለማንነቱ እዉቅና የሚያገኝበት የተሰጠዉን እዉቅና መሰረት አድረጎ ራሱን የሚገልጽበት፤ በጋራ ጉዳዩች
እኩል ተሳትፎ የሚደርግበት እና እኩል እድልም የሚፈጥርበት፤ የሁሉም መብት አንጻራዊ በሆነ መልኩ
በተሻለ ሁኔታ የሚከበርበት፤ ሁሉንም አካታች የሆነ ማንም የማይገለልበት ስርዓት እየዳበረ የሚሄድበት
በመሆኑ የፌደራል ስርዓቱ በጠንካራ ተቋማት፤ አሰራር ስርዓቶች፤ ፌደራላዊ አስተሳሰብ እና አመለካከቶች
ተደግፎ የዘላቂ ሰላም እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ መዋቅራዊ ችግሮችን በመፍታት መዋቅራዊ
ትራንሰፎርሜሽን በማምጣት ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት የሚያስችል የመንግስታዊ አወቃቀሩ አንዱ ገጽታ
ነዉ፡፡ በመሆኑም አሁን በየከባቢዉ የሚታዩ ግጭቶችን እየፈቱ የዘላቂ ሰላም ግንባታዉን ለማስኬድ
የመንግስታዊ ስርዓቱን አንዱን ገጽታ በአግባቡ ተረድቶ በህብረተሰቡም ዉስጥ ተፈላጊዉ ግንዛቤ እንዲያዝ
መስራት ይጠይቃል፡፡

ሁለተኛዉ የመንግስት አወቃቀር ገጽታ ዴሞክራሲያዊ የሆነ መንግስት ማዋቀርን ይጠይቃል፡፡ ዴሞክራሲ
የሕዝቦችን የስልጣን ባለቤትነት የሚገልጽ ከመሆኑም በላይ የህዝቦች ሰብአዊ መብቶች መከበርን፤ ስልጣን
በህዝቦች ፈቃድ የሚገኝ መሆኑን፤ በህግ እና በህግ ከተደነገገዉ ወጭ ስልጣን መያዝም ሆነ ለመያዝ መሞከር
ወንጀል መሆኑን፤ በህብረተሰብ ዉስጥ የተለያዬ ብዝሃነቶች ያሉ እና እነዚህን የሚያስተናግድ ስርዓት መገንባት
አስፈላጊ መሆኑን፤ የህግ የበላይነትን ወዘተ-- መሰረት የሚደርግ የመንግስት አወቃቀር ሰርዓት ነዉ፡፡ በዚህ
ስርዓት የሕዝቦች አኩልነት የሚከበረበት እና ህዝቦች የስልጣን ባለቤት የሚሆኑበት ፤ የሚኖሩ አለመግባባቶች
በንግግር እና በዉይይት፤ በድርድር የሚፈቱበት በመሆኑ ይህ ስርዓት ግጭትን በመፍታት ለዘለቂ ሰላም ግንባታ
መሰረት መሆኑ አጠያያቂ አይሆንም ለዚህም ይመስላል በሰላም ጥናት #ዴሞክራሲያዊ ሰላም# የሚል ንድፈ
ሃሳብ የተፈጠረዉ፡፡ የዚህ ንድፈ ሃሳብ ዋናዉ ማጠንጠኛዉ ዴሞክራሲያዊ የሆኑ ሀጋራት ዕርስ በዕርስ ወደ
ጦርነት አይገቡም በዉስጣቸዉ ሰላም ይኖራቸዎል የሚል ነዉ፡ለዚህም እንደ አመክኒዋ የሚወሰደዉ
በዴሞክራሲያ ስርዓት የስልጣን ባለቤት ሕዝብ በመሆኑ እና ህዝቡ ደግሞ ችግሮች በዉይይት ተፈትተዉ
በጦርነት ምክንያት የኢኮኖሚም ሆነ ማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ መሆን ስለማይፈልግ ዴሞክራሲዊ ስርዓት
የሚከተሉ መንግስታትም ወደ ጦርነት ከመግባታቸዉ በፊት ደጋግመዉ እንዲያስቡና ጉዳዩን የመጨረሻ

56 | P a g e
አማራጭ አድርገዉ እንዲያዩ ያደርጋቸዎል ምክንያቱም መንግስታቱ ለምርጫ ህዝብ ፊት ስለሚቀርቡ እና
ህዝቡም ከሰላም ጋር ተያይዞ በአከናወኑት ተግባር ስለሚቀጣቸዉ ወይም ስለሚደግፋቸዉ ነዉ

በህገመንግስቱ በግልጽ የተቀመጡት ፌደራላዊ እና ዴሞክራሲያዊ የሆነ የመንግስት አወቃቀር ከዚያዉሳለ


ፌደራላዊ ስርዓት ዴሞክራሲያዊ ካልሆነ የተረጋጋ እና ዘላቂ ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ ዴሞክራሲዊ ሊሆን የግድ
ይለዋል ፡፡ ስለሆነም ፌደራላዊ እና ዴሞክራሲዊ የሆነ የመንግስት አወቃቀር ብዝሃነት መገለጫዉ በሆነ ሀገር
ዉስጥ ብዝሃነት ጋር ተያይዘዉ የሚኖሩ መዋቅራዊ ችግሮችን ፌደራላዊ እና ዴሞክራሲዊ በሆነ አግባ
በመፍታት ዘላቂ ሰላንምን በገንባት የሜያስችል መንግስታዊ አወቃቀር በህገመንግስቱ የተደነገገ መሆኑን
መረዳት እና ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ ከሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች የሚጠበቅ ነዉ፡፡

3.4. ማጠቃለያ፣
በዚህ ከፍል 17 ኛው ኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን መሪ ቃል “ሕብረብሔራዊ
አንድነት ለዘላቂ ሰላም“ መሠረት በማድረግ የሰላም ጽንሰ ሃሳብ፣ የሰላም ግንባታ ከአዎንታዊ ሰላም
ጋር የሚያያዝ መሆኑን እና አዎንታዊ ሰላም በማኅበረሰቡ ውስጥ ለመዋቅራዊ ግጭት መሠረት ሊሆኑ
የሚችሉ ጉዳዮችን መለወጥ እና አካታች የሆነ ሥርዓትን መገንባትን የሚጠይቅ መሆኑን፣ የሰላም
ግንባታ መሠረት የሆኑ እሴቶች እና የግንባታ ዘዴዎች ለአውዱ በሚመጥን መልኩ ታይቷል፡፡
የሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ግንባታ በተስተካከለ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ከሄደ
ሥርዓቱ በራሱ ካለው ተፈላጊነት በተጨማሪ የሰላም ግንባታ ዋና መሣሪያ መሆኑን እና የሰላም
ግንባታ እና የሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ግንባታ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸው
በዝርዝር የቀረበበት ነው።

በመሆኑም ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓታችን ያሉበትን ውስንነቶች አስወግደን ጥንካሬዎችን


አጠናክረን ከተገበርን በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የሰላም ግንባታችን እውን የመሆን እድሉ ሰፊ ነው።

57 | P a g e
4. ዋቢ መጻሕፍት
Ann Ward and Lee Ward (2009) eds. The Ashgate Research Companion to Federalism.
Ashgate Publishing Limited. London.
Barnett Hilarie (2013). Constitution and Administrative Law 10th ed. Ruteldge, UK.
Bunce, V., (1999). Subversive Institutions፣ The Design and the Destruction of Socialism

and the State. Cambridge University Press, Cambridge.

Burgess, Michael (2006) Comparative federalism፣ theory and practice. Rutledge. Abingdon

Burgess (2012). In Search of the Federal Spirit፣ Theoretical and Empirical Perspectives
in Comparative Federalism. Oxford University Press, Oxford
Choudhry, S., (2008a). Bridging Comparative Politics and Comparative Constitutional

Law፣ Constitutional Design for Divided Societies. In S. Choudhry (ed.) Constitutional


Design for Divided Societies፣ Integration or Accommodation? Oxford University Press,
Oxford, 3–40.

Dietmar Braun (2009). Constitutional Change in Switzerland. Publius፣


The Journal of Federalism. Volume 39 number2, pp.314-340
Douglas V. Verney(1995) Federalism, Federative Systems, and Federations፣
The United States, Canada and India. Publius፣ The Journal of Federalism 25፣2, 81-97
Elazar Daniel J (1980). The Political Theory of Covenant፣ Biblical Origins
and Modern Developments. Publius፣ The Journal of Federalism, 1-30
Elazar Daniel, (1987). Exploring Federalism.፣ University of Alabama Press, Tuscaloosa.
Elazar, D., (1994). Federalism and the Way to Peace. Institute of Intergovernmental

Affairs, King- ston.

Filippov Mikhail, Ordeschook Peter C. and Shevtsova Olga, (2004). Designing Federalism፣ A
Theory of Self-Sustainable Federal Institutions. Cambridge University Press, New York
Gagnon Alain-G. (2001), The moral foundations of asymmetrical federalism፣

a normative exploration of the case of Quebec and Canada, in Alain-G. Gagnon and
James Tully, (eds.), Multicultural democracies, UK, Cambridge University Press

58 | P a g e
Galtung, Johan.( 1975). “Three approaches to peace፣ Peacekeeping, peacemaking

and Peacebuilding”. Peace, war and defence፣ Essays in peace research. 2፣ 282–304.
Copenhagen፣ Christian Ejlers.

Galtung Johan (1967). Theories of Peace፣ A Synthetic Approach to Peace Thinking.

International Peace Research Institute, Oslo


Gordon M. Freeman (1980). The Process of Covenant. Publius፣
The Journal of Federalism, 71- 81
Grodzins Morton (1983), The American system፣ A new view of government.
Chicago፣ RandMcNall
Hale, H., (2004). Divided we Stand፣ Institutional Sources of Ethnofederal State Survival

and Collapse. World Politics 56(2), 165–193.

Hart, Vivien. (2001). Constitution-making and the transformation of conflict. Peace and

Change 26፣ pp, 153–75.

Henkin Louis (1994). Elements of Constitutionalism. Occasional Paper Series, Center for

the Study of Human Rights, Columbia Uninversity.

Henrard, K. (2005). “Participation,” “Representation” and “Autonomy” in the

Lund Recommendations Conventions. International Journal on Minority and Group


Rights 2/3(12), 133–168. and their Reflections in the Supervision of the FCNM and
Several Human Rights

Hirschman, A., (1970). Exit, Voice, and Loyalty፣ Responses to Decline

in Firms, Organizations,and States. Harvard University Press, Cambridge.

Kincaid John ((1990). Value and Value Tradeoffs in Federalism. Publius፣


The Journal of Federalism, 25፣2, 29-44
Kössler, K., 2015. Conclusions፣ Beyond the Illusion of Ethno-Culturally Homogenous

59 | P a g e
Territory. In T. Malloy & F. Palermo (eds.) Minority Accommodation Through
Territorial and Non-Territorial Autonomy. Oxford University Press, Oxford, 245–272.

Kössler Karl (2018). Governing Divided Societies through Territorial Autonomy?

From (too) Great Expectations to a Contextualist View. Journal of Ethnic Studies 81


pp 21-41

Kymlicka, W., (1998). Is Federalism a Viable Alternative to Secession? In P. B. Lehning


(ed.) Theories of Secession. Routledge, London.

Palermo, F.,( 2012). Central, Eastern and South-Eastern Europe and Territorial Autonomy፣

Are They Really Incompatible? In A. G. Gagnon & M. Keating (eds.) Political


Autonomy and Divided Societies፣ Comparative Territorial Politics. Palgrave Macmillan,
Basingstoke, 81–97.

Palermo, F.,( 2015). Owned or Shared? Territorial Autonomy in the Minority Discourse.

In T. Malloy & F. Palermo (eds.) Minority Accommodation Through Territorial and


Non-Territorial Autonomy. Oxford University Press, Oxford.

Riker, William H.,(1964). Federalism፣ Origin, Operation, Significance. Little Brown, Boston

Roeder, P. G., (1991). Soviet Federalism and Ethnic Mobilization. World Politics 43(2), 196–
232.

Roeder, P. G., (2009)(. Ethnofederalism and the Mismanagement of Conflicting

Nationalisms. Regional & Federal Studies 19(2), 203–219.

Saunders Cheryl ( 1995). Constitutional Arrangements of Federal Systems. Publius፣


The Journal of Federalism 25፣2, pp. 61-79
Simeon Richard (2009). Constitutional Design and Change in Federal Systems፣ Issues
and Questions. Publius፣ The Journal of Federalism volume 39 number 2, pp.241-26.
Snyder, J., (2000). From Voting to Violence፣ Democratization and Nationalist Conflict.

Norton, New York

60 | P a g e
Watts, R., (2007). Multinational Federations in Comparative Perspective. In M. Burgess &

J. Pinder (eds.) Multinational Federations. Routledge, London, New York.

Watts, R., (1996). Comparing Federal Systems in the 1990s. McGill-Queen’s University

Press, Montreal, King- ston.

Watts R. L, (2001). ‘Intergovernmental Relations፣ Conceptual Issues.’ In፣ Levy Norman and
Tapscott (eds.). Intergovernmental Relations in South Africa፣ The Challenge of Co-
operative Government. Cape Town፣ School of Government University of the Western
Cap

Wibbels Erik, (2005). Federalism and the Market፣ Intergovernmental Conflict and Economic
Reform in the Developing World. New York፣ Cambridge University Press.

61 | P a g e

You might also like