You are on page 1of 64

የንግድ ሕግ ማሻሻያ

የፖሊሲ ሰነድ

የንግድ ሕጉን ለማሻሻል የቀረቡ የፖሊሲ


ነጥቦች አጭር ማጠቃለያ
(Executive Summary)

በንግድ ሕግ ማሻሻያ የፖሊሲ ሰነድ አዘጋጅ የቴክኒክ


ኮሚቴ አባላት የተዘጋጀ

መጋቢት 2006 ዓ.ም


ቢሾፍቱ

I
የቴክኒክ ቡድኑ አባላት

1. አቶ ሊቁ ወርቁ
2. አቶ ሃይለ አብርሃ
3. አቶ ምትኩ ማዳ
4. አቶ ተስፋዬ ንዋይ
5. አቶ ኃይለሚካኤል መላኩ
6. አቶ ገበያው ስማቸው
7. አቶ ዮሃንስ ላታሞ
8. አቶ ፍሬው ማሞ
9. አቶ ክፍለጽዮን ማሞ
10. አቶ አስቻለው ቱጂ
11. ወ/ት ራሕዋ መብራሕቱ
12. አቶ ፍጹም ገ/ሥላሴ
13. አቶ ዳንኤል ጥበቡ
14. ወ/ሮ የትናየት በየነ
15. ዶ/ር ሙሉጌታ መንግሥት
16. አቶ ሲሳይ ሉጬ
17. አቶ ገመቹ መረራ
ማውጫ
መግቢያ
መጽሐፍ አንድ
የንግድ ሕጉ አቀራረጽ መነሻና ስለ ነጋዴ የታዩ ዋና ዋና የፖሊሲ ነጥቦች ................................................................................. 1
1. ስለንግድ ሕጉ አደረጃጀት.............................................................................................................1
2. ስለንግድ ጉዳዮች ፍርድ ቤት ........................................................................................................2
3. ስለንግድ ሕግ አደረጃጀት መርህ (Aproaches)..................................................................................4
4. ስለነጋዴ ትርጉም እና ነጋዴ መሆን ስለማይገባቸው አካላት ....................................................................4
5. ስለንግድ ሥራዎች ዝርዝር ...........................................................................................................5
6. ስለንግድ ምዝገባ፣ ስለንግድ ፈቃድና ስለንግድ መዝገብ አስተዳደር ...........................................................6
7. ስለንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ................................................................................................8
ሁለተኛ መጽሐፍ
ስለንግድ ማኅበራት ................................................................................................................................................................ 10
1. በንግድ ማኅበራት ዓይነቶች ላይ ለውጥ ማድረግ፣ .............................................................................. 10
1.1 ተራ የሽርክና ማኅበር ከንግድ ሕጉ እንዲወጣ ማድረግ፣ ................................................................. 10
1.2 የባለሙያዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማኅበር በንግድ ሕጉ ውስጥ እንዲካተት ማድረግ፣ ..................... 10
2. የንግድ ማኅበራት ምስረታን ቀልጣፋ ማድረግ፣ ................................................................................ 11
2.1 ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ለማቋቋም የሚጠየቀውን የአባላት ቁጥር ከሁለት ወደ አንድ ዝቅ እንዲል
መፍቀድ፤ ....................................................................................................................... 11
2.2 የአክሲዮን ኩባንያ በአንድ ሰው እንዲደራጅ መፍቀድ፤ .................................................................. 11
2.3 ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ለማስመዝገብ ገንዘብ በዝግ ሒሳብ እንዲቀመጥ የሚያስገድደውን አሠራር
ማስቀረት፤ ...................................................................................................................... 12
2.4 የንግድ ኩባንያ ለማቋቋም የመተዳደሪያ ደንብ እንዲቀርብ የሚያደርገውን አሠራር ማስቀረት፤ ................... 12
2.5 የአክሲዮን ኩባንያ መመስረቻ ስምምነት ወይም ማሻሻያዎች በኩባንያ አስተዳዳሪዎች ለመዝጋቢው አካል
ቀርበው እንዲረጋገጡ ማድረግ፤............................................................................................. 13
2.6 የንግድ ኩባንያ ለማቋቋም ተቀባይነት ያላቸውን የዓይነት መዋጮዎች በግልጽ ማስቀመጥ፤ ....................... 13
2.7 በዓይነት ለተከፈለ መዋጮ የሚሰጡ አክሲዮኖችን የማስተላላፊያ ጊዜ ማሳጠር፤ ................................... 14
2.8 የአክሲዮን ማኅበራት የምስረታ ሂደት በኦዲተር እንዲመረመር የሚያደርግ አሠራር ተግባራዊ ማድረግ፤ ...... 14
2.9 የአክሲዮን ኩባንያ ለመመስረት የሚያስፈልገው መዋጮ ከተሰበሰበ በኋላ ኩባንያው ሳይመሠረት የሚቆይበትን
የጊዜ ገደብ ማሳጠር፤.......................................................................................................... 15
2.10 ለህዝብ ክፍት የሆነ የአክሲዮን ኩባንያ አደራጅ ለመሆን መስፈርቶች እንዲኖሩ ማድረግ፤ ........................ 15
2.11 በአክሲዮን ማኅበራት ምስረታ ሂደት ተሳታፊ የሚሆኑ ሰዎች መብትና ግዴታ በግልጽ እንዲቀመጥ ማድረግ፤ 15
2.12 ከአክሲዮን ኩባንያ ምስረታ ጋር በተያያዘ በኃላፊነት የሚያስጠይቅ ሁኔታ ሲኖር ከአደራጆች ውጭ ያሉ ሰዎች
ከተጠያቂነት ነጻ እዲሆኑ ማድረግ፤ ......................................................................................... 16
3. የአክሲዮን ማኅበራት ለአምጭው የሚል አክሲዮን ወይም የግዴታ ወረቀት እንዳያወጡ መከልከል፤ ................. 16
4. የቦርድ አደረጃጃትን ማሻሻል ...................................................................................................... 16
4.1 የአክሲዮን ኩባንያዎች ዳይሬክተሮች ቦርድ ባለሁለት ደረጃ መዋቅር አንዲኖረው ለማድረግ የሚያስችል
አማራጭ መፍቀድ፤ ........................................................................................................... 16
4.2 ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ኩባንያዎች በቦርድ እንዲመሩ ማድረግ፤ ................................................ 17
4.3 የአክሲዮን ኩባንያ ጸሐፊ እንዲኖር የሚያደርገውን አሠራር አስገዳጅ ማድረግ፤ ..................................... 17
4.4 ከአክሲዮን አባላት ውጭ ያሉ ሰዎች የቦርድ አባል ሊሆኑ እንዲችሉ መፍቀድ፤...................................... 17
4.5 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ዝቅተኛ የዕድሜ ገደብ መወሰን፤ ...................................................... 18
4.6 ለቦርድ አባልነት ብቁ የማያደርጉ መስፈርቶችን ማስቀመጥ፤............................................................ 18
4.7 የኩባንያ አመራሮች ከሥራ ኃላፊነታቸው ጋር በተያያዘ የፍትሐብሔር ክስ ሲቀርብባቸው ወጭው በኩባንያው
እንዲሸፈን ማድረግ፤ .......................................................................................................... 18
4.8 ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ኩባንያዎች የፋይናንስ ሁኔታ በውጭ ኦዲተር እንዲመረመር ማድረግ፣ ............ 19
5. የኩባንያዎች ጠቅላላ ጉባኤ አሠራርን ማሻሻል፣ ................................................................................. 19
5.1 የአክሲዮን ኩባንያ ካፒታልን በአባላት መዋጮ ለማሳደግ በድምጽ ብልጫ ሊወሰን የሚችልበትን ሁኔታ
መፍቀድ፤ ....................................................................................................................... 19
5.2 በድንገተኛ ጉባኤ ላይ የሚታዩ ጉዳዮች እንደ ሁኔታው በአመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ሊታዩ የሚችሉበትን ሁኔታ
መፍቀድ፤ ....................................................................................................................... 19
6. የአነስተኛ ባለአክሲዮኖችንና አበዳሪዎችን መብት ጥበቃ ማጠናከር ......................................................... 20
6.1 ማንኛውም ባለአክሲዮን በኩባንያው ስም ዳይሬክተሮችን ወይም ሦስተኛ ወገኖችን በሕግ ለመጠየቅ የሚችልበትን
አሠራር ተግባራዊ ማድረግ፤ .................................................................................................. 20
6.2 ጠቅላላ ጉባኤ ለመጥራት የሚያስችለውን የአክሲዮን ብዛት ከ10% ወደ 5% ዝቅ ማድረግ፤ ...................... 20
6.3 በኩባንያው ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው አባላት፣ አመራሮችና ቤተሰቦቻቸው ከኩባንያው ወይም ከኩባንያው ጋር
ግንኙነት ካላቸው ሌሎች ኩባንያዎች ጋር የሚያደርጉት የንግድ ግንኙነት በቅድሚያ በቦርድ እንዲጸድቅ
የሚያደርግ አሠራር መዘርጋት፤ ............................................................................................. 21
6.4 የግዴታ ወረቀት የገዙ አበዳሪዎች ስብሰባ ለመጥራት የሚያስፈልጋቸውን የድምጽ ብዛት ከ20% ወደ 10% ዝቅ
ማድረግ፤ ........................................................................................................................ 21
7. ኩባንያዎች ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ስለማድረግ፤ .............................................................. 21
8. ኩባንያዎች በቡድን ተደራጅተው የሚሰሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት .......................................................... 22
8.1 በቡድን ኩባንያዎች መካከል ግንኙነት የሚመሠርትበትን መስፈርት መወሰን፤........................................ 22
8.2 ኩባንያዎች በቡድን የሚደራጁበትን መንገድ በፍላጎታቸው እንዲወስኑ መፍቀድ፤ ................................... 22
8.3 ወላጅ ኩባንያዎች ለተነጣይ ወይም ዋናው ቡድን ለቡድኑ አባል ኩባንያዎች ዕዳ ተጠያቂ የሚሆኑበትን አሠራር
መዘርጋት፤ ...................................................................................................................... 23
9. የኩባንያዎች መዋሃድ እና መከፋፈል የሚመራበትን ሥርዓት ማጠናከር፤ .................................................. 23
9.1 የኩባንያዎች ውህደት ስምምነት በባለሙያ ግምትና በኦዲት ሪፖርት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ማድረግ፤....... 23
9.2 ኩባንያዎች መከፋፈል የሚችሉበትን ሁኔታ በንግድ ሕጉ ማካተት፤ .................................................... 23
10. የኩባንያዎችን ተጠያቂነት ማጠናከር፤ ........................................................................................... 24
11. የኢንፎርሜሽን ግንኙነት ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሻሻል፤ .................................................................. 24
መጽሐፍ ሦስት
ስለማጓጓዝ (ማመላለስ) ሥራ ............................................................................................................................................... 25
የማጓጓዝ ሕግ የማጠቃለያ ሀሳቦች ........................................................................................................................................ 25
በመድን ሕግ ላይ የቀረቡ ዋና ዋና የማጠቃለያ ሀሳቦች......................................................................................................... 30
የፖሊሲ ሀሳብ አንድ ..................................................................................................................... 30
የፖሊሲ ሀሳብ ሁለት .................................................................................................................... 31
የፖሊሲ ሀሳብ ሦስት .................................................................................................................... 32
የፖሊሲ ሀሳብ አራት .................................................................................................................... 32
የፖሊሲ ሀሳብ አምስት .................................................................................................................. 33
የፖሊሲ ሀሳብ ስድስት .................................................................................................................. 33
የፖሊሲ ሀሳብ ሰባት ..................................................................................................................... 34
የፖሊሲ ሀሳብ ስምንት .................................................................................................................. 36
የፖሊሲ ሀሳብ ዘጠኝ .................................................................................................................... 36
መጽሐፍ አራት
ስለባንክ ሥራዎች
የፖሊሲ ውሳኔ የሚያሻቸው ጉዳዮች ..................................................................................................................................... 37
1. ስለባንኮች አቋቋም .................................................................................................................. 37
2. ስለገጠር ባንኮች ..................................................................................................................... 37
3. የባንኮች በሥራ የሙያ ዘርፍ ስለ መከፋፈል .................................................................................... 37
4. ገንዘብን በአደራ ስለማስቀመጥ .................................................................................................... 38
ትረስት አካውንት ..................................................................................................................... 38
የታዳጊ ወጣቶች ቁጠባ .............................................................................................................. 38
5. ስለሒሳብ መዘጋት .................................................................................................................. 39
6. የባንክ የሒሳብ መግለጫን ስለመስጠት .......................................................................................... 39
7. ገንዘብን ስለማስተላለፍ ............................................................................................................. 39
8. ሰነዶችን በአደራ ስለማስቀመጥ.................................................................................................... 40
9. ስለካዝና ኪራይ ...................................................................................................................... 40
10. በሰነድ ስለሚሰጡ ብድሮች ....................................................................................................... 40
11. የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ጥበቃ .................................................................................... 41
12. የኤሌክትሮኒክ ባንክ አሠራር ...................................................................................................... 41
ስለተላላፊ የገንዘብ ሰነዶች ..................................................................................................................................................... 41
1. ስለሸቀጦች ማረጋገጫ............................................................................................................... 41
2. ስለቅን ልቦና የሕግ ግምት.......................................................................................................... 42
3. ስለተበላሹ፣ ስለወደሙ፣ ስለጠፋ ወይም ስለተሰረቁ ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶች .............................................. 42
4. ስለተላላፊ የገንዘብ ሰነዶችና ሌሎች ውሎች .................................................................................... 43
5. በጀርባ መፈረም ስለሚሰጠው ዋስትና ........................................................................................... 43
6. እሽታ (Acceptance) .............................................................................................................. 44
7. እንቢታ ስለቀረበበት ሰነድ ......................................................................................................... 44
8. ስለ ቼክ ............................................................................................................................... 44
9. ስለማይተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ................................................................................................... 45
አምስተኛ መጽሐፍ
የኪሳራና የመጠበቂያ ስምምነት ሕግን ለማሻሻል የቀረቡ የፓሊሲ ሃሳቦች ........................................................................... 46
1. ስለኪሳራ ሕግ ዓላማዎች ........................................................................................................... 46
2. ስለኪሳራ ሕግ የአፈጻጸም ወሰን ................................................................................................... 48
3. ስለንብረት ጠባቂው፤ መርማሪው ዳኛ፤ ፍርድ ቤቶች፤ ዓቃቤ ሕግና ሌሎች የመንግሥት ተቋማት ሚና .............. 49
4. ሙሉ ለሙሉ ስላልተፈጸሙ ውሎች ............................................................................................. 49
5. ስለመልሶ ማደራጀት ................................................................................................................ 51
6. ውሎችና ስለማፍረስና ዕዳን ስለማቻቻል ........................................................................................ 53
7. ስለባለገንዘቦች ሚና ................................................................................................................. 54
8. ወጪዎች እና የባለገንዘቦች የመብት ደረጃ....................................................................................... 54
9. ነጻ መውጣት......................................................................................................................... 55
መግቢያ
ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በፍጥነት እያደገ ያለው ኢኮኖሚዋንና በሃገሪቷ ውስጥ የሚያስፈልገውን ፈጣን
የንግድ ሥርዓት ለመግዛት እና ለመደገፍ ወቅታዊ የሆነውን የንግድ እንቅስቃሴ ያገናዘበ ዘመናዊ የንግድ
ሕግ መኖር አስፈላጊነት ማስረጃ የሚያሻው አይደለም። አሁን በሥራ ላይ የሚገኘው የንግድ ሕግ ከግማሽ
ክፍለ ዘመን የዘለለ ዕድሜ ያለውና በተጨባጭ መሬት ላይ ያለውን የንግድ ልውውጥ ሙሉ በሆነ መልኩ
ሊገዛ የሚችል ሆኖ ባለመገኘቱ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ አዋጆችና ደንቦች ወጥተው ሥራ ላይ ውለዋል።
እነዚህ የተበታተኑ ብሎም በከፊል ያልተሻሻሉ የንግድ ሥራን ለመግዛት የወጡ ሕግጋት ወጥ ሆነውና
አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ እንዲሁም ሀገራችን ወደፊት ልታሳካቸው የምትፈልጋቸውን የዓለም የንግድ
ድርጅት በአባልነት መቀላቀልን የመሳሰሉ ግቦችን ታሳቢ ያደረገ የንግድ ሕግ ሊኖር እንደሚገባ
በመንግሥት ታምኖበታል።

የንግድ ሕጉን ወደማሻሻሉ ተግባር ከመገባቱ አስቀድሞም የሕጉ ረቂቅ ሃገሪቱ ከምትከተላቸው የፖለቲካዊ
ኢኮኖሚ መርሆዎች እና ከሌሎች ሀገራዊ ፖሊሲዎች ጋር የተጣጣመ ይሆን ዘንድ የተለያዩ የፖሊሲ ውሳኔ
የሚሹ አበይት ጉዳዮች ለይቶ ለውሳኔ እንዲያቀርብ አሥራ ሰባት አባላት ያሉት የቴክኒክ ኮሚቴ
ተዋቅሯል። የቴክኒክ ኮሚቴውም ከታሕሳስ 2 እስከ መጋቢት 26 ቀን 2006 ዓ/ም ድረስ በቢሾፍቱ ከተማ
ተገኝቶ የፖሊሲ ሰነዱን አዘጋጅቷል። የቴክኒክ ኮሚቴው አወቃቀር የተመሠረተው በነባሩ የንግድ ሕግ
መጽሐፍት መሠረት ሲሆን በአምስት ንዑሳን ቡድኖች የተከፋፈለ ነው። በሥራው ሂደትም እያንዳንዱ
ንዑስ ቡድን በየተመደበለት መጽሐፍ ላይ ያገኛቸውን የፖሊሲ ውሳኔ የሚያሻቸውን ጉዳዮችን በመለየትና
አርቃቂው ሊመራባቸው የሚገቡ እና አንደማጣቀሻ ሊጠቀማቸው የሚችሉ ዝርዝር ምክንያቶችን ከሌሎች
ሀገራት ልምድ ጋር በማነፃፀር በማስቀመጥ የፖሊሲ ሰነዱን የመጀመሪያ ደረጃ አጠናቋል።

እያንዳንዱ ንዑስ ቡድን የንግድ ሕጉን መሠረታዊ ችግር ለመለየትና የተሻለ መፍትሔ ለማመላከት ከሌሎች
ሀገራት ልምድ የወሰደ ሲሆን፣ በየመጽሐፉ የተወሰዱት ልምዶች በዋናነት የልማታዊ መንግሥት ኢኮኖሚ
የሚከተሉት ሀገራት ልምድ እንዲሆን ጥረት ተደርጓል። የነኚህ ሀገራት ልምድ የተቀዳው በርዕሰ ጉዳዩ ላይ
የዳበረ ልምድ ካላቸው ምዕራባውያን ሃገራት ሆኖ በተገኘ ጊዜ እና የነኚህ ምዕራባውያን ሀገራትን ልምድ
መውሰዱ የተሻለ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ሁሉ ይኸው ተከናውኗል። በዚህ ሂደት ግን የነዚህ ሀገራት ልምድ
ከሃገራችን የፖሊቲካ ኢኮኖሚ፣ ብሔራዊ ፖሊሲዎችና ነባራዊ ሁኔታ ጋር መጣጣሙ የማረጋገጥ ሥራ
ተሠርቷል።
በየንዑሳን ቡድኑ የተዘጋጁትን አምስት የፖሊሲ ሰነዶች ከሌሎች ሕግጋት እና እርስ በርሳቸው የማጣጣም
ሥራ በመቀጠል ተሠርቷል። በዚህ ሂደትም ሁሉም ንዑሳን ቡድኖች አንድ ላይ በመሰብሰብ የእያንዳንዱን
ንዑስ ቡድን ሥራ የተቸ፣ ያረመ እና ያሟላ ግብዓት ሰጥተዋል። በተሰጡ ግብዓቶች መሠረት ሰነዱን ዳግም
የማስተካከልና የማረም ሥራ ተከናውኗል፡፡ በዚህ ሂደት ሰነዶቹን ከአምስት ሰነድነት ወደ አንድ
ለማምጣት በማሰብ ይህ ሰነድ የተዘጋጀ ሲሆን ዝርዝር የፖሊሲ ሃሳቦቹን በአጭርና ግልጽ በሆነ መልኩ
የሚያስቀምጥ ሰነድ ነው። በዚህ ሰነድ ውስጥ የተካተተና ዝርዝር ማብራሪያ የሚያስፈልገው የፖሊሲ ሃሳብ
ቢኖር ዝርዝር ሐተታውና ምክንያቱን ከዚህ ሰነድ ጋር በአባሪነት ከተያያዘው ዋና የፖሊሲ ሰነድ ማግኘት
ይቻላል።
መጽሐፍ አንድ
የንግድ ሕጉ አቀራረጽ መነሻና ስለ ነጋዴ የታዩ ዋና ዋና የፖሊሲ ነጥቦች

1. ስለንግድ ሕጉ አደረጃጀት

አሁን ባለው ሁኔታ የንግድ እና ንግድ ነክ ሕጎች በንግድ ሕጉ፣ ከንግድ ሕጉ በኋላ በወጡ የተለያዩ አዋጆች
እና ደንቦች እንዲሁም በፍትሐብሔር ሕግ ውስጥ በተበታተነ መልኩ ተደንግገው ይገኛሉ፡፡ ንግድና
ከንግድ ጋር የተገናኙ ግንኙነቶችን የሚገዛ ሕግ በተለያየ መልኩ ተበታትኖ በሚገኝበት ጊዜ በኅብረተሰቡ
ዘንድ ከሚፈጥረው የመገንዘብና የመረዳት ችግር በተጨማሪ ለአስፈጻሚ አካላትም ለመረዳትና
ለማስፈጸም ችግር ይገጥማል፡፡ በተለይም የንግድ ሕግ የተለዩ ባሕርይያት (ፍጥነት የሚፈልግ መሆኑ፣
የባለገንዘቡን መብት የመጠበቅና የመከላከል፣ የንግድ ሕግ ዘርፍ በባሕሪውም ሆነ በተግባራዊነቱ ዓለም
አቀፋዊ መሆኑ፣ የንግድ ሕግ በባሕሪው ተራማጅና ተቀያሪ መሆኑ፤ የንግድ ሕግ ፍትሐዊ የመሆን ባሕሪይ
ያለው መሆኑ፣) ያሉት ከመሆኑ የተነሳ ከሌሎች የግለሰብ ሕጎች (Private Laws) ተለይቶ በአንድ ወጥ
በሆነ መድብል (Code) መደራጀቱ የበለጠ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

የንግድ ሕጉ ተሰባስቦ በአንድ ወጥ መድበል መደራጀቱ በተለይ በንግድ ለመሰማራት ለሚፈልጉ የአገር
ውስጥም ሆነ የውጭ አገር ነጋዴዎች የንግድ ሕጉን በቀላሉ ለመረዳት ከማስቻሉም በላይ አገራችን
ለምታራምደው ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ ጠቃሚነቱ የጎላ ይሆናል ብቻም ሳይሆን ኢንቨስተሮችን ለመሳብ
የራሱ የሆነ ድርሻም ያበረክታል፡፡ በቀጣይ ለዓለም አቀፍ የንግድ ድርጅት አባልነት ለምናደርገው
ዝግጅትም የንግድ ሕጋችንን በተሟላ መልኩ መረዳት ስለሚያስችል በጎ አስተዋፅኦ ይኖረዋል:: በዚህ ዙሪያ
የተለያዩ አገራት ልምድ ለመቃኘት ተሞክሯል፡፡ አንድ የሕግ መድብል (Code) ሲቀረፅ በተቻለ መጠን
ምሉዕ ሆኖ መውጣት ስለሚኖርበት እንደ ኮሪያና ስፔይን የንግድ ሕጎች ለአገር ውስጥ ነጋዴውም ሆነ
ለውጭ አገር ነጋዴ ይበልጥ ቀላል እና ተደራሽ መሆን እንዲችል የሚቀረፀው የአገራችን የንግድ ሕግ
በአዋጅ የወጡ የተበታተኑ ሕጎችን፣ እንዲሁም የንግድ ባሕርይ ያላቸውን ከፍትሐብሔር ሕጉ ውስጥ
የሽያጭ ሕግ፣ የእንደራሴነት ሕግ፣ የኮሚሲዮን ሕግ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት ማስያዣ (Mortgage) ሕግ፣
በአንድ ላይ ያካተተ ቢሆን ይመረጣል የሚለው አንድ ሐሳብ ሆኖ ቀርቧል፡፡

ሌላውና ሁለተኛው አማራጭ ሐሳብ ከንግድ ሕጉ በኋላ በወጡ አዋጆች ውስጥ ያሉትን በማጠቃለል
የፍትሐብሔር ሕጉ ላይ ያሉትን ሳይጨምር በአንድ ላይ ይደራጅ የሚል ነው፣

ስለዚህም በአገራችን የንግድ ሕግ ከግለሰብ ሕግ መድብል በተናጠል ራሱን በቻለ መድብል ምሉዕ ሆኖ
መደራጀት አለበት ለሚለው ዋነኛ ምክንያቶች፡- የአገራችን የወደፊት አቅጣጫ ከሲቪል ጉዳዮች ይልቅ
1
የንግድ ጉዳዮች የሚበዙበት ይሆናል ተብሎ ይታመናል ምክንያቱም አሁን እርሻ ላይ የተመሠረተው
ኢኮኖሚያችን ቀጣይ ወደ ኢንዱስትሪና ንግድ እየተሸጋገረ የሚሄድ ከመሆኑ የተነሳ የንግድ እንቅስቃሴው
እየሰፋና እየተጠናከረ የሚሄድ ይሆናል፡፡ ይህም ሁኔታ ከንግድ ሥራ ጋር ሙሉ አቅሙንና ጊዜውን
የሚሠራ ተቋምና የሕግም ሆነ ሌሎች ተያያዥ ባለሙያን ይጠይቃል፡፡ የንግድ ሕጉ ቢያንስ ለቀጣይ 50
ዓመታት ያገለግላል ተብሎ ቢገመት እንኳን በቀጣይ 50 ዓመታት አገራችንን ምን እንደሚጠብቅ በደንብ
በማየት የንግድ ሕጉ እነዚህን ሁኔታዎች በሚያስችል መልኩ ወጥ ሆኖ በተናጠል መድብል ሊደራጅ
ይገባዋል፡፡ በተጨማሪም የንግድ እንቅስቃሴ የራሱ የሆኑ ልዩ ባሕሪያት ያሉት በመሆኑ፣ የንግድ ሥራን
የሚደነግገው ሕግ ቀላል፣ ቀልጣፋና ጥራቱን የጠበቀና ዘመናዊነትን የተላበሰ እንዲሆን ለማስቻል፣
መንግሥት በኢኮኖሚው በተመረጠ ሁኔታ ለሚኖረው ጣልቃ ገብነት አመቺ እንዲሆን የሚሉት ተደማሪ
ምክንያቶች ናቸው፡፡

የንግድ ሕግ በተናጠል መደራጀት (Autonomy of Commercial Law) ማለት ግን ከሌሎች በግለሰቦች


ሕግ ውስጥ ከሚደነገጉት ጋር በምንም አይገናኝም ማለት ሳይሆን የንግድ ሕጉ ወደ ፍትሐብሔር ሕጉ
የሚያመላክታቸው አጠቃላይና የወል የሆኑ (ለምሣሌ ስለሰዎች ችሎታ፣ ስለውል በአጠቃላይና
የመሳሰሉት) ሕጎች ይኖራሉ፡፡

2. ስለንግድ ጉዳዮች ፍርድ ቤት

ይህ ከላይ በተ.ቁ. 1 ሥር ከታየው ጉዳይ ጋር የተያያዘ ሲሆን የንግድ ሕግ ራሱን በቻለ ምሉዕ መድብል
በሚደራጅበት ሁኔታ ቀጥሎ የሚመጣው ጥያቄ የንግድ ጉዳዮች ከሌሎች የፍትሐብሔር ጉዳዮች ጋር
በተመሳሳይ ፍርድ ቤት መታየት አለባቸው ወይ የሚለው ነው፡፡ ይህን በተመለከተም የሚከተሉት ሁለት
አማራጮች ተቀምጠዋል፡-

ሀ) ከንግድ ሥራ ጋር የተገናኙ አለመግባባቶችን መርምሮ የመፍታትና ውሳኔ የመስጠት ጉዳይ እስከሆነ


ድረስ የተለያየ የአስተዳደር ዳኝነት ተቋም ከማደራጀት ይልቅ አንድ ወጥ አደራጅቶ የኃብትና የሰው
ኃይል በቁጠባ የመጠቀም ጠቀሜታን ማትረፍ የተሻለ ይሆናል፡፡ ስለዚህም ማንኛውንም የንግድ ጉዳይ
የማየት ሙሉ ሥልጣን ያለው የተለያየ ደረጃ ያለው አንድ አስተዳደራዊ የዳኝነት አካል ይደራጅና
በሕግ ጉዳይ ላይ ብቻ ሰበር ይግባኝ የሚቀርብበት ሁኔታ ይፈጠር፡፡ የዚህ አማራጭ አዎንታዊ ጎኑ፡-
አንደኛ የንግድ ጉዳዮችን በሚመለከት መንግሥት ኢኮኖሚውን የመምራት ግዴታውን በአግባቡ
እንዲወጣ በመደበኛ ፍርድ ቤት ከሚወሰንበት የተሻለ ዕድል ይሰጣል፤ ሁለተኛ በንግድ ጉዳዮች
አለመግባባት ሲፈጠር ኅብረተሰቡን ያሳተፈ (የንግድ ማህበረሰቡን ተወካዮች) የፍትሕ አሰጣጥ

2
ሥርዓት እንዲኖር ያደርጋል፤ ሦስተኛ የተለያዩና ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ተግባር የሚፈጽሙ አካላት
መካከል ያለውን የብዥታና የሥልጣን መደራረብ ከማስወገዱም በላይ የኃብትና የሰው ኃይል ብክነትን
ያስወግዳል፣ አራተኛ የአስተዳደር ፍርድ ቤቶች ፈጣን ሥነ-ሥርዓት የሚከተሉና ወጪ ቆጣቢ
መሆናቸው፣ ነጋዴዎች ከፍርድ ቤት ጋር ሲነጻጸር የበለጠ የሚመርጧቸው መሆኑ፣ አንድ ላይ ሲደራጁ
የበለጠ የባለሙያ ልምድና ቸሎታን መጠቀም ይቻላል፡፡ የዚህ አማራጭ አሉታዊ ጎኑ ደግሞ የንግድ
ጉዳዮችን በሚመለከት በሕገ-መንግሥቱ ገለልተኝነቱና ነጻነቱ ከተረጋገጠ አካል ውጭ በከፊል
አስተዳደራዊ የዳኝነት አካል እንዲወሰን ያደርጋል፤ ሁለተኛ በእያንዳንዱ ዘርፍ ያለውን የልዩ ሞያ
ልምድና ችሎታ የመጠቀም ሁኔታን ያጠባል፤ ሦስተኛ የንግድ ጉዳዮች ዙሪያ የሚነሱ አለመግባባቶች
በከፊል በመደበኛ ፍርድ ቤት በከፊል ደግሞ አስተዳደራዊ የዳኝነት ሥልጣን በተሰጣቸው አካላት
የሚታዩበትን ሁኔታ ያስወግዳል፣ አራተኛ የፍሬ ነገር ስህተት ማረሚያ ዕድል ከማሳጣትም በላይ
የይግባኝ መብት ያጠባል፡፡
ለ) የንግድ ጉዳዮችን በሚመለከት የተለየ ክህሎትና ችሎታ የሚጠይቅ ከመሆኑ የተነሳ በተለይም ደግሞ
በንግድ እንቅስቃሴ ዙሪያ ግንዛቤን የሚጠይቅ እንደመሆኑ መጠን እነዚህን ጉዳዮች ለማየትና መርምሮ
ውሳኔ ለመስጠት አስተዳደራዊ የዳኝነት አካላት እንዳሉ ሆነው በመደበኛ ፍርድ ቤት ውስጥ ራሱን
የቻለ የተለየ ችሎት በማደራጀት መሥራት ይቻላል፡፡ የዚህ አማራጭ ጠቀሜታው በንግድ ጉዳዮች
የሚነሳ አለመግባባት ገለልተኛና ነጻነቱ በሕገ-መንግሥቱ በተረጋገጠ መደበኛ ፍርድ ቤት እንዲፈታ
ማድረግ ሲሆን አሉታዊ ጎኑ ግን አንደኛ በንግድ ጉዳዮች የሚከሰት አለመግባባትን ከመፍታት አንጻር
ኅብረተሰቡን የማሳተፍ (በተለይ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮችን) ሁኔታ አይኖርም፤ ሁለተኛ የንግድ
ጉዳዮችን በሚመለከት የባለሙያን ልዩ ልምድና ችሎታ ለመጠቀም ያለው አጋጣሚ ጠባብ ይሆናል፤
ሦስተኛ መንግሥት የአገሪቱን ኢኮኖሚ የመምራት ግዴታ ያለበት እንደመሆኑ መጠን በአስተዳደራዊ
የዳኝነት አካል አለመግባባቶቹ ቢፈቱ የሚኖረውን ያህል ነጻነት እንዳይኖረው ያደርጋል፡፡

ከነዚህ ሁለት አማራጮች መካከል የመጀመሪያው የሚወሰድ በሚሆንበት ጊዜ ተያይዞ ሊነሳ


የሚችለው ነጥብ የሥነ-ሥርዓት ሕግን የሚመለከት ነው፡፡ ከንግድ እንቅስቃሴ የተለየ ባሕሪ እንዲሁም
ከላይ ከተገለጸው የንግድ ሕግ በተለየ እንዲደራጅ ከሚያስገድዱ ተጨባጭና በአገራችን ወደፊት ሊሆን
ይችላል ተብሎ ከሚገመተው አንጻር የክርክርና አለመግባባትን የመፍቻ ሥነ-ሥርዓቱ ቀላል፣ ፈጣንና
ቀልጣፋ ሊሆን ይገባል፡፡ በመሆኑም የአስተዳደራዊ የዳኝነት አካሉ ሊከተለው የሚገባ የተለየ ሥነ-
ሥርዓት ሊቀረጽ የግድ ይላል፡፡

3
3. ስለንግድ ሕግ አደረጃጀት መርህ (Aproaches)

የንግድ ሕግን ለማደራጀት ተጨባጭ ያልሆነ (Subjective) ተጨባጭ የሆነ (Objective) ወይስ የሁለቱ
ቅልቅል (Mixed) መስፈርት ልንከተል ይገባል? የአገራችን የንግድ ሕግ ማዕከል ያደረገው የንግድ ሥራ
የሚያከናውነውን ነጋዴውን ነው ወይስ በነጋዴው የሚከነወነውን የንግድ ሥራ ወይስ ሁለቱን የሚለው
በብዙዎቹ የሕግ ባለሙያዎችና ምሁራን ዘንድ አከራካሪና የሚያወያይ ሆኖ የቆየ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ
የንግድ ሕጉ ምንጭ ከውጭ አገር ማለትም ከፈረንሳይ ከመሆኑም በላይ የሕጉ መነሻ ሰነድ በአግባቡ
ካለመደራጀቱ የተነሳ ይህን በሚመለከት ግልጽነት ይጎድላል፡፡ ስለዚህም አሁን የሚቀረጸው የንግድ ሕግ
ምንን ማዕከል በማድረግ ሊቀረጽ ይገባል ለሚለው ምላሽ ሊቀመጥለት ይገባል፡፡ ይህን በተመለከተ
በዓለም ላይ ያሉ ሦስት መስፈርቶች እና ከነዚህ መስፈርቶች አንጻር የአገራት ተሞክሮ ታይቷል፡፡

ከዚህም የተነሳ ለአገራችን መከተል የሚገባንን በሚመለከት የሚከተሉ አማራጮች ቀርበዋል፡-

ሀ) ተጨባጭ ካልሆነው መስፈርት እና ተጨባጭ ከሆነው መስፈርት ከሁለቱም በመውሰድ የሁለቱን


ቅልቅል መስፈርት ልክ እንደ ፈረንሳይ የንግድ ሕግ መከተል፡- ይህን መንገድ መከተል
ጠቀሜታው በዋናነት የንግድ ሕጉን የበለጠ ግልጽ ማድረግ እንዲቻል የንግድ ሥራን የሚሰራውን
ሰው ማንነት ብቻ በመግለጽ ሳይሆን ምን ዓይነት ሥራዎች ሲሠራ የንግድ ሕጉ ድንጋጌ ተፈጻሚ
እንደሚሆን የሚያሳይ ስለሆነ ነው፡፡ የንግድ ሕጉ የንግድ ሥራው ላይ ወይም ሥራውን
በሚሰራው ሰው ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን በሁለቱም ላይ አትኩሮ ማን ምን ዓይነት ተግባር
ሲፈጽም በንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች እንደሚገዛ ያሳያል፡፡
ለ) እስካሁን ያለውን የአገራችን የንግድ ሕግ የተከተለውን የተጨባጭ ያልሆነውን መስፈርት
በመከተል መቀጠል፣

4. ስለነጋዴ ትርጉም እና ነጋዴ መሆን ስለማይገባቸው አካላት

አሁን በአገራችን ተግባራዊ እየተደረጉ ባሉ የንግድ ጉዳይን በሚደነግጉ ሕጎች ነጋዴ የሚለውን ቃል
ትርጉም ሲሰጥ በተለያዩ ሁኔታዎች ነው፡፡ በንግድ ሕጉ የተደነገገው የነጋዴ ትርጉም ቀጥሎ በወጡ አዋጆች
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀየረና እየተሸሻለ የመጣ መሆኑን እናያለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ምንም እንኳን
የንግድ ሕጉ በሚወጣበት ጊዜ ከነበረው ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት አንዳንድ ተግባራትን የሚፈጽሙ
ሰዎች ነጋዴ እንደማይባሉ የተደነገገ ቢሆንም አሁን ካለንበትና ወደፊት ከምንገምተው ተጨባጭ ሁኔታ

4
አንጻር ባሉበት መቀጠል አለባቸው ወይ የሚለው አዲስ በሚዘጋጀው የንግድ ሕግ ላይ በአጽንኦት
ሊተኮርበት የሚገባ ይሆናል፡፡

በመሆኑም የነጋዴ ትርጉምን በሚመለከት በንግድ ሕጉና ቀጥለው በወጡ የተለያዩ አዋጆች ውስጥ
የተካተቱ ትርጉሞችን አንድነትና ልዩነት እንዲሁም የተለያዩ አገራት ሕግ ተሞክሮ ተዳስሷል፡፡ ከዚህም
በመነሳት የቀጣይ አቅጣጫ መሆን ያለበት፡-

 ነጋዴ የሚለው ትርጉም አሁን ከደረስንበት ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እንዲሁም የወደፊቱን አርቆ
በመውሰድ ከዚያ ጋርም ተጣጥሞ እንዲሄድ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ድርጅቶችን፣
የኅብረት ሥራ ማሕበራትን፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባትና
በማካተት አጠቃላይና የወደፊቱን አርቆ በሚያይ ሁኔታ ሊተረጎም ይገባል፡፡

ነጋዴ የማይሆነውን በሕግ የመለየት አስፈላጊነት በዋናነት አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ስንነሳ ማን ነጋዴ
ሆኖ የነጋዴ ግዴታዎችን የሚወጣና መብቶቹን የሚገለገል እንደሆነ ወይም ነጋዴ መሆን የማይገባው ማን
እንደሆነ በግልጽ ባልተለየበት ሁኔታ በተለያዩ ምክንያቶች መብት የማይገባው ሰው መብት የሚያገኝበት
እንዲሁም ግዴታ ሊጣልበት የማይገባው ሰው ግዴታ ውስጥ የሚገባበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ከዚህም
በላይ በግልጽ ባልተወሰነበት ሁኔታ በየደረጃው ላለ ኃላፊ ወይም ፈጻሚ ውሳኔ የሚተው ይሆናል፡፡ ግልጽ
የሕግ ድንጋጌ ሲጠፋ ብዥታና የግልጸኝነት መጓደል ስለሚኖር ይህ ደግሞ ምንም እንኳን አብዛኛው
በቅንነት የሚሠራ መሆኑ የሚገመት ቢሆንም አልፎ አልፎ ለችግር ማጋለጡ አይቀርም፡፡ ይህን አስመልክቶ
የአገራችን የአሁኑና የወደፊት ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባትና የሌሎች አገሮች ልምድ በሰፊው በማየት
ቀጣይ የሚቀረጸው የንግድ ሕግ ነጋዴ መሆን የማይገባቸውን በሕግ ችሎታ፣ የመንግሥት ኃላፊነትና
ተቀጣሪነት፣ ልዩ ሞያ፣ የሚበረታቱ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ለትርፍ ዓላማ ያልተቋቋሙ፣ ዜግነት፣
እንዲሁም የንግድ ሥራው ልክና መጠን እንደ መሥፈርት በመጠቀም መለየት ይኖርባቸዋል የሚል ሀሳብ
ቀርቧል፡፡ በሌላ በኩል እንደ መሥፈርት ከተቀመጡት ዝርዝሮች የመንግሥት ኃላፊነትና ተቀጣሪነት፣
ለትርፍ ዓላማ ያልተቋቋሙ እና የሚበረታቱ የኅብረተሰብ ክፍሎች በንግድ ሕጉ በመስፈርትነት ሊካተቱ
አይገባም የሚል የተለየ ሀሳብ ቀርቧል፡፡

5. ስለንግድ ሥራዎች ዝርዝር

የንግድ ሥራዎች ዝርዝር በተመለከተ የተጠቃለለ ወይስ አመላካች ተገልጾ ቀሪው በሌሎች ሕጎች
እንዲሸፈን ማስቀመጥ? የንግድ ሥራዎችን በሚመለከት በሥራ ላይ ባለው የንግድ ሕግ አንቀጽ 5 ሥር

5
የተዘረዘሩ 21 የሚሆኑ ተግባራት አሉ፡፡ ከነዚህ ዝርዝሮች አንጻር በተለያየ ጊዜ የሚነሳው ጥያቄና አወዛጋቢ
ነገር አንድ ሰው ከነዚህ ዝርዝሮች ውጪ የሆነ ተግባርን የሞያ ሥራው በማድረግ ለትርፍ የሚሠራ ሲሆን
ነጋዴ ተብሎ ይወሰዳል ወይ የሚለው ነው፡፡ በሌላ አነጋገር በንግድ ሕጉ ቁጥር 5 ሥር የተዘረዘሩት ብቻ
ናቸው ወይ የንግድ ሥራ ተደርገው መወሰድ የሚገባቸው ወይንስ ከነዚያ ጋር ተቀራራቢ የሆኑ ሌሎችም
ይጨመራሉ የሚል ነው፡፡ ከዚህ አወዛጋቢ ጥያቄ ጋር ተያይዞ ከንግድ ፈቃድና ምዝገባ ጋር በተያያዘ
በአንዳንድ ሁኔታዎች የመልካም አስተዳደር ችግር መነሻ ሲሆን ይታያል፡፡ በአካዳሚ ውይይቶችና
ክርክሮች ላይ የሚነሳው ተመሳሳይ ነጥብ በንግድ ሕጉ ቁጥር 5 ሥር የተቀመጠው ዝርዝር ያለቀለት
(exhaustive) ነው ወይንስ አመላካች ብቻ (indicative) ነው የሚለው ነው፡፡ ይህ ሲነሳ በዋናነት
መወሰድ ያለበት ከዝርዝሩ ውጪ የሆነ ተግባርን ወይም አገልግሎትን የሞያ ሥራው በማድረግ ለትርፍ
የሚሠራ ሰው ነጋዴ ይሆናል ወይም አይሆንም የሚለውን የሚወስን ከመሆኑ አንጻር ነው፡፡ አንድ ሰው
ነጋዴ ነው ከተባለ የነጋዴ መብቶችን የሚያገኝ ሲሆን ጎን ለጎን ደግሞ የነጋዴ ግዴታዎችም ያርፉበታልና፡፡

ከዚህ አንጻር የተለያዩ አገራት ሕግ ድንጋጌዎች እና የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታን ለማየት ተሞክሯል፡፡
ከዚያም በመነሳት በአገራችን ወደፊት የሚወጣው የንግድ ሕግ ላይ መሆን የሚገባውን በሚመለከት
የሚከተሉት ሁለት አማራጮች ተቀምጠዋል፡-

ሀ) በንግድ ሕጉ አንቀጽ 5 የተመለከቱትን ዋና ዋና የንግድ ሥራዎችን እንዲሁም ንግድ ሕጉ


ከዘረዘራቸው ውጪ በሥራ ላይ በሚገኙ ሌሎች ሕጎች የተለዩ ዋና ዋና የንግድ ሥራዎችን
አካትቶ የንግድ ሥራዎች ዝርዝር በሙሉነት ቢካተት ተመራጭ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ
በየጊዜው ሊከሰቱ የሚችሉ ለውጦችን ማስተናገድ እንዲቻል በሌላ ሕግ ተጨማሪ የንግድ
ሥራዎች ዝርዝር ሊወጣ እንደሚችል ቢመላከት ችግሩን በዘላቂነት ይፈታዋል፡፡

ለ) የደቡብ ኮሪያን ልምድ በመውሰድ ሁሉንም አንድ ነጋዴ የሚፈጽማቸውን ተግባራት ለንግድ
ድርጅቱ የሚፈጽመው ነው የሚል ግምት ተወስዶ ግምቱ ትክክል አለመሆኑን እስካላስረዳ
ድረስ ሁሉንም የነጋዴ ተግባራት የንግድ ሥራ አድርጎ መውሰድ፡፡

6. ስለንግድ ምዝገባ፣ ስለንግድ ፈቃድና ስለንግድ መዝገብ አስተዳደር

በአገራችን እየተሠራባቸው የሚገኙ የንግድ ምዝገባ፣ ፈቃድ እና አስተዳደር ሕጎች በተለያዩ ሕጎች ውስጥ
ተካትተው የሚገኙ ናቸው፡፡ በንግድ ሕጉ የንግድ ምዝገባና የንግድ መዝገብ አጠቃላይ ድንጋጌ ተካትቶ
የሚገኝ ሲሆን የንግድ ፈቃድን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች በተለያየ ጊዜ በወጡ አዋጆችና ደንቦች ውስጥ

6
ተካትተው ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በንግድ ሕጉ ስለምዝገባና መዝገብ አስተዳደር የተደነገጉት
ድንጋጌዎች የንግድ ፈቃድን በሚመለከት በወጡ አዋጆች ተቀይረዋል፡፡ በመሆኑም የንግድ ምዝገባ፣
ፈቃድና አስተዳደርን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች በሚረቀቀው የንግድ ሕግ እንዴት መታየት አለባቸው
የሚለውን ነጥብ በመያዝ በንግድ ሕጉና ቀጥለው በወጡ የተለያዩ አዋጆች ውስጥ የተካተቱ ድንጋጌዎችን
አንድነትና ልዩነት እንዲሁም የተለያዩ አገራት ሕግ ተሞክሮ ተዳስሷል፡፡ ከዚህም በመነሳት የቀጣይ
አቅጣጫ መሆን ያለበት፡-

ሀ) የአገራችን የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፈቃድና በንግድ መዝገብ የመግባት ዋና ዓላማ (በአጠቃላይ
የቁጥጥር ዋና ዓላማ) የግለሰብ ነጋዴዎችን ፍላጎት በሚመልስ እና የሕዝብ ጥቅምን በሚያስከብር
መልኩ ሁለቱን ዓላማ ያደረገ መሆን አለበት፡፡ በአንድ በኩል የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ቁጥጥር
ዓላማ የግለሰብ ነጋዴ ፍላጎት በማሟላት ነጋዴ በመመዝገቡ ምክንያት የሚያገኛቸው መብትና
ግዴታዎች በግልጽ ማመላከት በተለይ በንግድ ሕጉ የምዝገባ የማስረጃ ግምት (the value of
registration)፣ ያለመመዝገብ የሚስከትለው ውጤት (the consequence of failure to
register)፣ የሚስተባበልና የማይሰተባበል የምዝገባ ማስረጃ (rebuttable or irrebutable
presumptions as to commercial status) እና መመዝገብ ስላለባቸው ማንኛውም ፍሬ ነገርን
አካትቶ መደንገግ አለበት፡፡ በሌላ በኩል የመመዝገብና ፈቃድ የመስጠት ቁጥጥር ዓላማ የሕዝብ
ጥቅም ግልጋሎቶችን መሠረት በማድረግ ፈቃድ በመስጠትና በመመዝገብ ዘርፈ ብዙ አስተዳደራዊ
አገልግሎቶችን (ስታትስቲክስ፣ የሸማቾች ጥበቃ፣ ግብር፣ እና የመሳሰሉት) ከግምት በማስገባት
መሆን ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም በሚሻሻለው የንግድ ሕግ ውስጥ ስለምዝገባ፣ መመዝገብ
ስለሚገባቸው ነገሮች፣ ስለምዝገባ ውጤት፣ ስለንግድ መዝገብና አስተዳደር እንዲሁም ከምዝገባ ጋር
ተያይዘው ያሉ ጉዳይች በአግባቡ እንዲካተቱ ቢደረግ በአገራችን ስንሠራበት የነበረውን የሕግ
ድንጋጌዎች አሻሽሎ ከማስቀጠሉም በላይ የዓለም አቀፍ ምርጥ ተመክሮንም በአግባቡ ለማካተት
ይረዳል፡፡ የንግድ ፈቃድን በሚመለከት በሀገራችን በተለያየ ጊዜ የወጡ ሕጎች በየጊዜውና በየወቅቱ
መንግሥት የአገልግሎቱን አስጣጥ ቅልጥፍናን ማዕከል በማድረግ ሊለዋውጣቸው ስለሚችል
ከንግድ ሕጉ ድንጋጌ ውስጥ እንዳይካተቱ ቢደረግ እና በሌሎች ተዋረድ ሕጎች እንዲካተቱ ማድረግ
የበለጠ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ ይህ በተለይ ወርልድ ባንክ የሚያወጣውን “Doing Business”
ማዕከል በማድረግ በሀገራችን መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ የሚመጡ ባላኃብቶችን ለመሳብ ምቹ
የንግድ ፈቃድ ሥነ ሥርዐቶችን ከግምት በማስገባት በየጊዜው ለውጥ የሚደረግባቸውን ሕጎች
ማሻሻል ያስፈልጋል፡፡

7
ለ) በንግድ ሕጉ ቀድሞ የነበረውና ንግድ ሕጉን ተከትለው የወጡ አዋጆች ያሻሻሏቸው የንግድ መዝገብ
መረጃዎች ኅትመት የግለሰብና የሕዝብ ፍላጎትን ከግምት በማስገባት የንግድ መዝገብ ውስጥ
የሚገቡ አዳዲስ ነጋዴዎችን፣ በንግድ መዝገብ የሚቀየሩ መረጃዎችን (እንደ ስረዛ ወይም መሻሻል
ወይም ለውጥ) በኅትመት በጋዜጣ እንዲወጡ ቢደረግ፡፡ ይህም በሚሻሻለው የንግድ ሕግ ውስጥ
ተካትቶ ቢረቀቅ፡፡ ይህንን ማድረግ ከንግድ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ክርክሮችን በአግባቡና
በአስተማማኝ መልኩ ለመምራት እንዲያስችል በቂ የማስረጃ ምንጭ በመሆን ስለሚያገልገል ነው፡፡

ሐ) የንግድ መዝገብ አስተዳደርና ቁጥጥር በዋናነትና በማዕከላዊነት በንግድ ሚኒስቴር ሥር እንዲደራጅ


ቢደረግ በአገራችን ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ በአግባቡ ለመምራት ከማስቻሉም በላይ በሕገ
መንግሥቱ የተገለጸውን አንድ የፖሊቲካና የኢኮኖሚይ ማኅበረሰብ ለመፍጠርና ለማስተዳደር
ዓይነተኛ መሣሪያ ሆኖ ለማገልገል ይረዳል፡፡ ይህ በሚሻሻለው ንግድ ሕግ ውስጥ በግልጽ ማሳየት፡፡
ነገር ግን የአሠራር ማሻሻያ እንደ ቴክኖሎጂውና እንደአሠራሩ የንግድ ሚኒስቴር በውክልና ወይም
ሌላ ባመቸ በማንኛውም መንገድ ለሌሎች አካላት ሊሰጥ እንደሚችል በግልጽ ቢመላከት፡፡

7. ስለንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ

የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ ድንጋጌዎች የንግድ ሕጉ አካል ተደርገው መወሰድ አለባቸው ወይስ
የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አሁን እየተሠራበት ባለው መልኩ በሌላ ሕጎች ለብቻው ይደራጅ
የሚለውን ነጥብ በስፋት ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡ በንግድ ሕጉ ስለተገቢ ያልሆነ ውድድርና የማይገባ
የውድድር ሥራ ስለሚያስከትለው ውጤት ተካትቶ የሚገኝ ቢሆንም ስለሸማቾች የሚመለከቱ
ድንጋጌዎችን አካትቶ አልያዘም፡፡ በሥራ ላይ ያሉ ሌሎች ሕጎች በንግድ ሕጉ የተመለከተውን የንግድ
ውድድር ድንጋጌዎች በመሻርና የንግድ ውድድርን እና የሸማቾችን ጥበቃ አንድ ላይ አድርጎ በመያዝ
እየተሠራባቸው ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት በሚሻሻለው የንግድ ሕግ ውስጥ የንግድ ውድድርና የሸማቾች
ጥበቃን የሚመለከቱት ድንጋጌዎችን አካትቶ ይረቀቅ ወይንስ ለብቻው በሌላ አዋጅ ይደረጅ ለሚለው
ነጥብ ላይ ልዩ ልዩ ጽንሰ ሐሳቦችን እና የሀገራትን ልምድ በማየት ሁለት አማራጮች ቀርበዋል፡፡

አማራጭ አንድ፡ የንግድ ሕጉ የንግድ ውድድርን እና የሸማቾች ጥበቃ ድንጋጌዎችን በሙሉ እንዲይዝ
ቢደረግ የተሻለ ነው፡፡ የንግድ ሕግ በነጋዴዎች መካከል ብቻ ሳይሆን ነጋዴዎች ከሸማቾች ጋር
ስለሚኖራቸው ግንኙነትም ጭምር ነው፡፡ በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የንግድ ውድድር ሕግ የመጨረሻው
ግብ የሸማቾችን ደህንነት ማረጋገጥ ነው፡፡ በመሆኑም የሸማቾች ጥበቃን እና የንግድ ውድድርን ነጣጥሎ
ለማየት አስቸጋሪ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ጉዳይ የንግድ ሕግ አካል

8
ተደርጎ ቢወሰድ የበለጠ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ይህ አማራጭ በተለይ ንግድ ነክ የሆኑ ነገሮችን በሙሉዕነት
የያዘ የንግድ ሕግ ማውጣት ከሚለው መርህ ጋርም የሚጣጣም አማራጭ ነው፡፡ በተለይ የሸማቾችን
ጥበቃን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን በንግድ ሕጉ ውስጥ አካትቶ ማውጣት የሸማቾች ጥበቃን በሚመለከት
ሕግ የማውጣት ሥልጣን የማን ነው የሚለውን አከራካሪ ሕገ መንግሥታዊ ነጥብ የሚመልስ ይሆናል፡፡
ሸማቾች ከንግድ እንቅስቃሴ በበቂ ሁኔታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና የንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች
በየትኛውም አካባቢ የሚገኘውን ሸማች እኩል በሆኑ ሁኔታ ደረጃቸውን ያማሉ ምርቶች እና
አገልግሎቶችን እንዲያቀርቡ ማድረግ አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመገንባት እየተሠራ ያለውን ሥራ
የሚደግፍ በመሆኑ የፌደራል መንግሥት የሸማቾችን ጥበቃ በተመለከተ ሕግ ማውጣቱ ሕገ መንግስታዊ
ነው የሚለው መከራከሪያ ሀሳብ የሚደግፍ ነው፡፡

አማራጭ ሁለት፡ የንግድ ውድድርን የሚመለከቱ ጉዳዮችን የንግድ ሕጉ አካል በማድረግ የሸማቾች ጥበቃን
የሚመለከቱ ጉዳዮችን በሌላ አዋጅ ውስጥ እንዲሸፈኑ ቢደረግ የሚል ሌላ አማራጭ ሐሳብ ቀርቧል፡፡
በሥራ ያለው የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 813/2006 የሸማቾችን ጥቅም ለማስጠበቅ በሚል
የሚቋቋሙ ማኅበራት የሸማቾችን መብት እና ጥቅም በተመለከተ ሲለሚኖራቸው እንቅስቃሴ ያለው ነገር
የለም፡፡ በሸማቾች ጥበቃ ዓለም አቀፍ ድንጋጌ ውስጥ ሸማቾች ጥቅምና መብታቸውን ሊያስጠብቁ
የሚያስችሉ የተለያዩ ማኅበራትን እና አደረጃጀቶችን መመስረት እንደሚችሉ እና እነዚህ አካላትም
የሸማቾችን ጥቅም በተመለከተ ድምጻቸውን የማሰማት መብት እንዳላቸው በግልጽ የተቀመጠ ቢሆንም፤
ይህ መብት እና ጥበቃ ግን በንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ውስጥ በግልጽ አልተካተተም፡፡
በመሆኑም የንግድ ውድድር የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን ወደንግድ ሕግ ውስጥ በማስገባት የሸማቾች
ጥበቃን በሌላ አዋጅ በሙልዕነት ማውጣት ይጠቅማል፡፡ ይህ በተለይ በአገራችን ያልዳበረ ሕግ
እንደመሆኑ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊቀያየር ወይም ሊለወጥ ወይም ሊሻሻል ስለሚችል በንግድ ሕጉ
ውስጥ አካትቶ ማውጣት ተመራጭ ሃሳብ አይሆንም የሚል ሀሳብ ቀርቧል፡፡

9
ሁለተኛ መጽሐፍ
ስለንግድ ማኅበራት

ከንግድ ማኅበራት ሕግ ጋር በተያያዘ የተለዩት የፖሊሲ ጉዳዮችና የማሻሻያ ሃሳቦች ቀጥሎ የተዘረዘሩት
ናቸው፡፡
1. በንግድ ማኅበራት ዓይነቶች ላይ ለውጥ ማድረግ፣

1.1 ተራ የሽርክና ማኅበር ከንግድ ሕጉ እንዲወጣ ማድረግ፣

ተራ የሽርክና ማኅበር የሚቋቋምበት ዋና ዓላማ የንግድ ሥራ ለመሥራት አይደለም፡፡ ይልቁንም የንግድ


ሥራ ለመሥራት ወይም አይነቱ ሳይገለጽ የሚቋቋም ከሆነ እንደ ህብረት ሽርክና ይቆጠራል፡፡ ከዚህ አኳያ
የንግድ ማኅበር ያልሆነ አደረጃጀት ንግድ ሕጉ ውስጥ ማካተቱ ተገቢ ስለማይሆን ከሕጉ እንዲወጣ ሃሳብ
ቀርቧል፡፡

1.2 የባለሙያዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማኅበር በንግድ ሕጉ ውስጥ እንዲካተት ማድረግ፣

በአገራችን የተለያዩ ሙያ ያላቸው ሰዎች የሽርክና ማኅበር ሲቋቋሙ አይታይም፡፡ ለዚህም በምክንያትነት
የሚቀርበው የሽርክና ማኅበራት ኃላፊነታቸው ያልተወሰነ በመሆኑ አንዱ ለፈጸመው የሙያ ጥፋት የሽርክና
ማኅበሩ ንብረት በቂ ባልሆነ ጊዜ ጥፋት ያልፈጸመው አባል ተጠያቂ ስለሚሆን ነው፡፡ ይህ ሁኔታ
ባለሙያዎች ተስማሚ አደረጃጀት ተጠቅመው ከሙያቸው ተጠቃሚ እንዳይሆኑና ሙያቸውን
በሚጠበቀው ደረጃ እንዳያሳድጉ፣ እንዲሁም ጀማሪ ባለሙያዎች በእነዚህ ማኅበራት ተቀጥረው ልምድ
እንዳያዳብሩ ያደርጋል፡፡ ከዚህም የተነሳ የእነሱም ሆነ የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እንዳይጎለብት መንስኤ
ሲሆን ይታያል፡፡ እየታየ ያለውን የአደረጃጀት ችግር ለመቅረፍ ጠበቆች፣ የሒሳብ ባለሙያዎች፣ ኦዲተሮች፣
አርክቴክቶች፣ የሥራ አመራር አማካሪዎች እና የመሳሰሉት ባለሙያዎች ኃላፊነቱ በተወሰነ የሽርክና ማኅበር
ሊደራጁ የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት አስፈላጊ ነው፡፡ በአጠቃላይ ውይይት ወቅት የጠበቆች
አደረጃጀት በንግድ ሕጉ ይካተት ቢባል እንደ ነጋዴ የሚያስቆጥራቸው ስለሚሆን አደረጃጀታቸው መወሰን
ያለበት በንግድ ሕጉ ሳይሆን በሚተዳደሩበት ደንብ ሊሆን ይገባል የሚል የልዩነት ሃሳብ ቀርቧል፡፡

10
2. የንግድ ማኅበራት ምስረታን ቀልጣፋ ማድረግ፣

ባለኃብቶችም ሆኑ ሥራ ፈጣሪ ዜጎች የንግድ ማኅበራት መስርተው በንግድ ሥራ ለመሠማራት እንዲችሉ


የምሥረታ ቅድመ ሁኔታዎችን ቀላልና ወጭ ቆጣቢ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉት
የማሻሻያ ሃሳቦች ቀርበዋል፡፡

2.1 ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ለማቋቋም የሚጠየቀውን የአባላት ቁጥር ከሁለት ወደ አንድ ዝቅ እንዲል
መፍቀድ፤

ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስፈልገው ዝቅተኛ የአባላት ቁጥር ሁለት ነው፡፡ ይህ
አካሔድ የንግድ ሃሳብና በቂ ካፒታል ያላቸው ግለሰብ ባለኃብቶች ከፍላጎታቸው ውጭ ምንም ዓይነት
አስተዋጽኦ ከሌላቸው ሰዎች ጋር እዲጣመሩ ያደርጋል፡፡ በሌላም በኩል አባላቱ በተለያየ ምክንያት
ከማኅበሩ ቢለቁና አንድ ሰው ብቻ ቢቀር ማኅበሩ ውጤታማ ቢሆንም የሚፈርስ ስለሚሆን በቀሪው አባል
ላይ ጉዳት ያስከትላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ግለሰብ ባለኃብቶች ከማይፈልጉት ሰው ጋር ላለመጣመር
ሲሉ ወደ ግል ንግድ እንዲያተኩሩ ስለሚገፋፋ ኩባንያ በማቋቋም ሊገኙ የሚችሉትን፡- ለንግድ ሥራ
የሚመድቡትን ካፒታል ከግል ኃብት ነጥሎ የማስተዳደር፤ ኃላፊነትን የተወሰነ የማድረግ፤ ውጤታማ
የኩባንያ አሰስተዳደርና የቁጥጥር ሥርዓት የመዘርጋት እና የመሳሰሉትን ጥቅሞች ያሳጣል፡፡ ስለዚህ
ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታና ከሌሎች አገራት ተሞክሮ በመነሣት አንድ የንግድ ሃሳብ የያዘና የካፒታል
አቅም ያለው ሰው ለብቻው ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ እንዲያቋቋም እንዲፈቀድ ሃሳብ ቀርቧል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ሕጉ ላይ ለውጥ ማድረግ አያስፈልግም የሚል የልዩነት ሐሳብ ቀርቧል፡

2.2 የአክሲዮን ኩባንያ በአንድ ሰው እንዲደራጅ መፍቀድ፤

የአክሲዮን ማኅበራትአደራጆች የንግድ ሃሳብ ከማመንጨት ጀምሮ ኩባያንያው እስኪመሠረት ድረስ ሙሉ


ኃላፊነት ወስደው ለምስረታው የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ተግባራት ያከናውናሉ፡፡ የአክሲዮን ኩባንያ
ለማቋቋም የሚያስፈልገውን ፈቃድ ለማግኘት የአደራጆች ቁጥር አምስት መሆን ይኖርበታል፡፡ ይሁን እንጂ
የንግድ ሃሳቡን የሚያመነጨው አንድ ሰው ቢሆንም፣ በአንድ በኩል ሕጉ የሚጠይቀውን ቁጥር ለማሟላት
ሲባል ብቻ የንግድ ሃሳቡም ሆነ የማደራጀት አቅሙ የሌላቸው ሰዎች የአደራጅ አባል እንዲሆኑ የሚያደርግ
ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የንግድ ሀሳብና የማደራጀት ችሎታ ያላቸው ዜጎች የአክሲዮን ኩባንያ መስርተው
ወደ ንግድ ሥራ እንዳይገቡ በማድረግ የሥራ ፈጠራን የሚገድብና በንግድ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ
የሚያደርግ ነው፡፡ ስለሆነም አንድ ሰው የአክሲዮን ኩባንያ ለማደራጀት የሚችልበት ሁኔታ ቢኖር

11
ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ ሆኖም ኩባንያው የሕግ ሰውነት ለማግኘት የአባላቱ ቁጥር ቢያንስ አምስት መሆኑ
እንደተጠበቀ ነው፡፡

2.3 ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ለማስመዝገብ ገንዘብ በዝግ ሒሳብ እንዲቀመጥ የሚያስገድደውን አሠራር
ማስቀረት፤

ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ለመመስረት ቢያንስ አሥራ አምሰት ሺህ ብር በዝግ ሒሳብ መቀመጥ
ይኖርበታል፡፡ ይህ አሠራር ዜጎች ካፒታል ባይኖራቸውም እውቀትና ሙያቸውን ተጠቅመው ወደ ንግድ
ሥራ እንዳይገቡ ስለሚያርግ የሥራ ፈጠራን ይገድባል፡፡ በሌላም በኩል በተግባር እንደሚታየውም በዝግ
ሒሳብ የተቀመጠው ገንዘብ ኩባንያው እደተመዘገበ ወድያውኑ የሚለቀቅ በመሆኑ ሕጉ ያሰበውን ዓላማ
የሚያሳካ አይደለም፡፡ በመሆኑም የኩባንያ ምስረታ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ ከመሆኑ አንጻር ገንዘቡ
በባንክ ከሚቀመጥ ይልቅ ለምስረታው ሥራ እዲውል ቢደረግ በቂ ገንዘብ የሌላቸው ነገር ግን የፈጠራ
ችሎታና እውቀት ያላቸው ከከፍተኛ የትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የተመረቁ ወጣቶችና ሌሎች
ግለሰቦች ኃላፊነቱ በተወሰነ የግል ኩባንያ ተደራጅተው የንግድ ሥራ እንዲያከናውኑ በማድረግ ፈጠራን
ለማበረታታት፣ ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ እንዲሁም ለሃገር ኢኮኖሚ እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ
እንዲያበረክቱ ለማድረግ ከፍተኛ ዕገዛ ያደርጋል፡፡ ይህን ጉዳይ በሚመለከት ያለው አሠራር መቀጠል
አለበት የሚል የተለየ ሐሳብ ቀርቧል፡፡

2.4 የንግድ ኩባንያ ለማቋቋም የመተዳደሪያ ደንብ እንዲቀርብ የሚያደርገውን አሠራር ማስቀረት፤

የንግድ ኩባንያ ለመመስረት የመመስረቻ ጽሁፍ እና የመተዳደሪያ ደንብ ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡ ሆኖም
የሁለቱ ሰነዶች ይዘት የሚመሳሰልበት ሁኔታ አለ፡፡ ሁለቱ ሰነዶች ሊይዙት የሚገባን መሠረታዊ ጉዳይ
በአንድ ላይ አጠቃሎ ማዘጋጀት እየተቻለ ሁለት ሰነዶች እንዲቀርቡ መደረጉ ለማዘጋጀት ጊዜና ወጭን
ከማስከተሉም ሌላ ለምዝገባ የሚቀርቡ ሰነዶችን ቁጥር ያበዛል፡፡ ይህ ደግሞ የመዝጋቢውን አካል የሥራ
ጊዜ የሚያባክን ከመሆኑም በላይ የአላስፈላጊ ሰነዶችን ክምችት በማበራከት የሰነድ ማስቀመጫ እጥረት
ሊፈጥር ይችላል፡፡ ስለዚህ የንግድ ኩባንያዎች ሲመዘገቡ የመመስረቻ ጽሑፍና የመተዳደሪያ ደንብን
መሰረታዊ ሃሳቦች ያካተተ የመመስረቻ ስምምነት ብቻ እንዲያቀርብ በማድረግ እንዲመዘገቡ ቢደረግ
ጊዜና ወጭ ለመቀነስ ያግዛል፡፡

12
2.5 የአክሲዮን ኩባንያ መመስረቻ ስምምነት ወይም ማሻሻያዎች በኩባንያ አስተዳዳሪዎች ለመዝጋቢው አካል
ቀርበው እንዲረጋገጡ ማድረግ፤

የንግድ ማኅበራትን የመመስረቻ ጽሑፍና የመተዳደሪያ ደንብ እና የመሳሰሉትን ሰነዶች ለማረጋገጥ ሁሉም
አባላት ወደ አረጋጋጩ ተቋም በአካል መቅረብ አለባቸው፡፡ በህዝብ የሚመሰረቱ ኩባንያዎች በርካታ
አባላት ያሏቸው ከመሆኑ አንጻር ሁሉም አባላት እንዲቀርቡ መደረጉ ወጭና ውጣ ውረድ በማስከተል ላይ
ይገኛል፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ ሁለት አማራጮች ቀርበዋል፡፡ አንደኛው ሰነዶቹ በኩባንያው
አመራሮች አማካይት ለንግድ ሚኒስቴር እየቀረቡ እንዲረጋገጡ ወይም በአክሲዮን ኩባንያዎች ምስረታ
ጉባኤ ላይ የንግድ ሚ/ር ተወካይ ተግኝቶ እንዲያረጋግጥ ማድረግ ሲሆን ሁለተኛው በአማራጭ አንድ ላይ
የተገለጸውን ተግባር በሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ ጽ/ቤት እዲከናወን ማድረግ የሚሉ ናቸው፡፡ የሁለቱ
አማራጮች ጥቅምና ጉዳት ሲነጻጸር ሰነዶቹ በኩባንያዎች አመራሮች አማካይት ለንግድ ሚ/ር ቀርበው
እንዲረጋገጡ ቢደረግ የተሻለ ይሆናል፡፡ ይህን ሃሳብ በሚመለከት የሕግ ማሻሻያ አያስፈልግም በሚል
የሃሳብ ልዩነት ቀርቧል፡፡

2.6 የንግድ ኩባንያ ለማቋቋም ተቀባይነት ያላቸውን የዓይነት መዋጮዎች በግልጽ ማስቀመጥ፤

የንግድ ኩባንያ ለመመስረት የሚዋጣ መዋጮ የገንዘብና የዓይነት መዋጮ በሚል ይታወቃል፡፡ ሆኖም
የንግድ ሕጉ የዓይነት መዋጮ ምን ዓይነት የመዋጮ አይነቶችን እንደሚያካትትም ሆነ የትኛው ዓይነት
መዋጮ ለየትኛው የንግድ ኩባንያ ዓይነት ተቀባይነት እንዳለው በግልጽ አያሳይም፡፡ በዚህም ምክንያት
አንዳንድ ሰዎች የሙያ አገልግሎት፣ የሊዝ መብት፣ የፓተንት፣ የመልካም ስም፣ የቅጂ መብት እና
የመሳሰሉት በመዋጮነት ሊያዙልን ይገባል በሚል የሚያቀርቡት ጥያቄ ተቀባይነት የማያገኝበት ሁኔታ
ስላለ ኃብታቸውን ተጠቅመው በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተው ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ዕንቅፋት በመሆን
ላይ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል የቀረበው የዓይነት መዋጮ ከንግድ ማህበራቱ ባሕርይይ አኳያ ያለው
አግባብነት ሳይጤን ተቀባይነት ይኑረው ቢባል በኩባንያው አባላትም ሆነ ከኩባንያው ጋር የንግድ ግንኙነት
ባላቸው ሶስተኛ ወገኖች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡ የሙያ አገልግሎትን በተመለከተ ዋጋውን
ለመተመን አስቸጋሪ ስለሆነ፣ አገልግሎት ለመሰጠት ግዴታ የገባው ሰው ግዴታውን ለመወጣት ፈቃደኛ
ሆኖ ባይገኝ አስገድዶ ለማሰራት የሚቻልበት ሁኔታ ስለሌለ፣ ኩባንያዎች ኃላፊነታቸው ባላቸው ኃብት
መጠን የተወሰነ በመሆኑ ኩባንያው ቢከስር አገልግሎት ለመስጠት ግዴታ የገባን ሰው ሦስተኛ ወገኖች
በኩባንያው ላይ ለሚያቀርቡት የዕዳ ጥያቄ ኃላፊ ማድረግ ስለማይቻል እንዲሁም የዓይነት መዋጮ
ኩባንያው ሕጋዊ ሰውነት ከማግኘቱ በፊት ሙሉ በሙሉ ገቢ መሆን ስላለበት ለኩባንያ ምስረታ

13
በመዋጮነት ሊቀርብ አይችልም፡፡ ስለዚህ የንግድ ኩባንያ ለመመስረት የሙያ አገልግሎት ሳይጨምር
ማንኛውም በገንዘብ ሊተመን የሚችል የዓይነት መዋጮ ተቀባይነት እንዳለው በንግድ ሕግ ውስጥ በግልጽ
በማስቀመጥ አሁን እየተከሰተ ያለውን ችግር ማስወገድ ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል የሙያ አገልግሎት
በመዋጮነት እንዳይቀርብ ሊከለከል አይገባም የሚል የተለየ ሃሳብ ተንጸባርቋል፡፡

2.7 በዓይነት ለተከፈለ መዋጮ የሚሰጡ አክሲዮኖችን የማስተላላፊያ ጊዜ ማሳጠር፤

ኩባንያ ለመመስረት የሚቀርብ የዓይነት መዋጮ ኩባንያው ከሚመዘገብበት ቀን በፊት በሙሉ መከፈል
ይኖርበታል፡፡ ሆኖም የዓይነት መዋጮ ለከፈሉ ሰዎች አክሲዮኖች የሚሰጡትም ሆነ ባለኃብቱ በሽያጭም
ሆነ በሌለ መንገድ ሊያስተላልፋቸው የሚችለው የአክሲዮን ኩባንያው ከተመዘገበ ከሁለት ዓመት በኋላ
ነው፡፡ ይህ ድንጋጌ የዓይነት መዋጮውን ፈጽመው ወደ አክሲዮን ኩባንያው የባለቤትነት መብት ያዛወሩ
አባላት ድርሻቸውን በመሸጥ፣ በዋስትና በማስያዝና በመሳሰሉት ተጠቃሚ እንዳይሆኑ መብታቸውን
የሚያጠብ ነው፡፡ በመሆኑም የጊዜ ገደቡ ወደ አንድ ዓመት ዝቅ እንዲል ሃሳብ ቀርቧል፡፡

2.8 የአክሲዮን ማኅበራት የምስረታ ሂደት በኦዲተር እንዲመረመር የሚያደርግ አሠራር ተግባራዊ ማድረግ፤

በአክሲዮን ኩባንያ ምስረታ ወቅት ለኩባንያው ምስረታ የሚውሉ የተለያዩ ሰነዶች የማዘጋጀት፣ ኃብት
የማሰባሰብ፣ ክፍያ የመፈጸም እንዲሁም የአክሲዮን ኩባንያው ከተቋቋመ በኋላ ደግሞ በምስረታ ወቅት
በአደራጆች የወጡ ወጭዎች የመተካትና የመሳሰሉት ተግባራት ይከናወናሉ፡፡ ከአክሲዮን ማኅበራት
ምስረታ ጋር በተያያዘ በርካታ ውዝግቦች ይከሰታሉ፡፡ ከእነዚህም ውዝግቦች ውስጥ በአክሲዮን ኩባንያው
አባላትና በአደራጆች መካከል የሚነሱ ይገኙበታል፡፡ የአክሲዮን ማኅበራት ሲመሰረቱ የምስረታ ሂደታቸው
በሕግ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች በትክክል ስለማሟላታቸውና የአክሲዮን አባላትን መብት የጠበቁ
ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ አካል የለም፡፡ በዚህም ምክንያት የምስረታ ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያሟሉ
የተመሰረቱና አክሲዮን የአባላትን ጥቅም በከፍተኛ ሁኔታ እየጎዱ ያሉ ኩባንያዎች እንዳሉ ይገለጻል፡፡

የአክሲዮን ኩባንያ ሲመሠረት አመሰራረቱ ተገቢውን ሕጋዊ አሠራር የተከተለ ስለመሆኑ ከምዝገባ በፊት
በኦዲተር እንዲመረመር ቢደረግ ወደ ንግድ ሥራ በሚገቡም ሆነ ከኩባንያው ጋር የንግድ ግንኙነት
በሚመሰርቱ ሦስተኛ ወገኖች ላይ መተማመን እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

14
2.9 የአክሲዮን ኩባንያ ለመመስረት የሚያስፈልገው መዋጮ ከተሰበሰበ በኋላ ኩባንያው ሳይመሠረት
የሚቆይበትን የጊዜ ገደብ ማሳጠር፤

ከአክሲዮን ኩባንያ ምስረታ ጋር በተያያዘ ከሚነሱ ችግሮች መካከል ካፒታሉን አሟልቶ ያሰባሰበ ኩባንያ
እስከ አንድ ዓመት ድረስ ሳይመሠረት ሊቆይ የሚችልበት ሁኔታ መፈቀዱ እንዲሁም የአንድ ዓመት የጊዜ
ገደቡ መቆጠር የሚጀምርበት ጊዜ በግልጽ አለመቀመጡ ናቸው፡፡ ይህም የተዋጣው ገንዘብ እንዲባክን
እንዲሁም የአሠራር ግልጽነት እንዳይኖር ምክንያት በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ችግሩን ለመፍታት
ለምስረታ በቂ ካፒታል ያሰባሰበ የአክሲዮን ኩባንያ የአክሲዮን ሽያጭ ከተዘጋበት ቀን አንስቶ በስድስት
ወራት ጊዜ ውስጥ እንዲመዘገብና ካልተመዘገበ በአባልነት መቀጠል ያልፈለገ አባል ያዋጣውን ገንዘብ
መልሶ የመውሰድ መብት እንዲኖው እንዲደረግ ሃሳብ ቀርቧል፡፡

2.10 ለህዝብ ክፍት የሆነ የአክሲዮን ኩባንያ አደራጅ ለመሆን መስፈርቶች እንዲኖሩ ማድረግ፤

ከአክሲዮን ኩባንያ አደራጆች ጋር በተያያዘ የተለያዩ ችግሮች ይስተዋላሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንደኛው
ለአክሲዮን ኩባንያ ምስረታ የተዋጣ ገንዘብ በአደራጆች የሚመዘበርበት ሁኔታ መኖሩ ነው፡፡ ይህም
ኅብረተሰቡ በኩባንያዎች ላይ እምነት እንዲያጣ ስለሚያደርግ እንዳይስፋፉ መንስኤ ሊሆን ይችላል፡፡
ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ለመፍታት የኩባንያ አደራጅ የሚሆኑ ሰዎች ሊያሟሏቸው
የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በሕጉ ውስጥ ማካተት ያስፈልጋል፡፡ እነዚህም ቅድመ ሁኔታዎች ከዚህ
በፊት ከኩባንያ አደራጅነትና አመራር ጋር በተያያዘ የወንጀል ጥፋት ያለመፈጸም፤ አደራጆች ለአክሲዮን
ኩባንያው ከተፈቀደው ጠቅላላ ካፒታል የተወሰነውን እንዲገዙ ማድረግና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ከዚህ ጋር
በተያያዘ በቸልተኝት ወንጀል የፈጸሙ ሰዎች የኩባንያ አደራጅ ከመሆን ሊከለከሉ አይገባም የሚል የልዩነት
ሃሳብ ቀርቧል፡፡

2.11 በአክሲዮን ማኅበራት ምስረታ ሂደት ተሳታፊ የሚሆኑ ሰዎች መብትና ግዴታ በግልጽ እንዲቀመጥ
ማድረግ፤

በንግድ ሕጉ ውስጥ በአደራጆችና መሥራቾች መካከል ያለው ልዩነት በግልጽ ባለመቀመጡ የሁለቱን
መብትና ግዴታ በግልጽ ለመረዳት የሚቻልበት ሁኔታ የለም፡፡ ይህም ለውዝግብ ምክንያት በመሆን ላይ
ይገኛል፡፡ ክፍተቱን ለማስተካከል ሁለት አመራጮች ቀርበዋል፡፡ አንደኛው አደራጅ የሚለው በሕጉ
ትርጉም ይሰጠው መሥራች የሚባሉትን ግን ኩባንያዎች እንደ ፍላጎታቸው ይወስኑት የሚል ሲሆን
ሁለተኛው አማራጭ አደራጅና መሥራች የሚባሉት በሕጉ ተለይተው ይቀመጡ የሚል ነው፡፡ ከሁለቱ

15
ባብዛኛው የተመረጠው የመጀመሪያው አማራጭ ነው፡፡ ሆኖም በአንድ በኩል ከሁለቱ አማራጮች
የተሻለው ሁለተኛው ነው፡፡ በሌላ በኩል ሕጉ የግልጽነት ችግር ስለሌለበት ባለበት ሁኔታ ሊቀጥል ይገባል
የሚሉ የልዩነት ሃሳቦች ቀርበዋል፡፡

2.12 ከአክሲዮን ኩባንያ ምስረታ ጋር በተያያዘ በኃላፊነት የሚያስጠይቅ ሁኔታ ሲኖር ከአደራጆች ውጭ ያሉ
ሰዎች ከተጠያቂነት ነጻ እዲሆኑ ማድረግ፤

ከአክሲዮን ኩባንያ ምስረታ ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ኃላፊነት ከአደራጆች በተጨማሪ ሌሎችን የአክሲዮን
ማህበሩ አባላትና ሠራተኞች ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ ይህም አክሲዮን የገዙ አባላትንና የኩባንያውን ሠራተኞች
ጥፋት ሳይፈጽሙ ተጠያቂ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ከአክሲዮን ማኅበራት ምስረታ ጋር በተያያዘ ለሚመጡ
ኃላፊነቶች ተጠያቂ መሆን ያለባቸው አደራጆች፣ የምስረታ ኦዲተሮች፣ ዳይሬክተሮችና ሌሎች የሥራ
መሪዎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡

3. የአክሲዮን ማኅበራት ለአምጭው የሚል አክሲዮን ወይም የግዴታ ወረቀት እንዳያወጡ መከልከል፤

የአክሲዮን ኩባንያዎች የሚያወጧቸው የአክሲዮን እና የግዴታ ወረቀቶች በሰነዱ ላይ የባለቤቱ ስም


የተጻፈበት (Registered) ወይም የባለቤቱ ወይም የያዥው ስም ያልተጻፈበት (Bearer) በመባል
ይታወቀሉ፡፡ ይሁን እንጂ ላምጭው የሚሉ አክሲዮኖችና የግዴታ ወረቀቶች የማን እንደሆኑ ስለማይታወቁ
በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ለማዘዋወር፣ ሽብርተኛነትን ለመርዳት፣ የመንግሰት
ግብርን ለመደበቅና ለመሳሰሉት ችግሮች መንስዔ ሊሆኑ ይችላል፡፡ ስለሆነም እነዚህ ሰነዶች እንዳይወጡ
ሊከለከል ይገባል፡፡ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ሰነዶቹ ሊከለከሉ አይገባም የሚል የልዩነት ሐሳብ
ቀርቧል፡፡

4. የቦርድ አደረጃጃትን ማሻሻል

4.1 የአክሲዮን ኩባንያዎች ዳይሬክተሮች ቦርድ ባለሁለት ደረጃ መዋቅር አንዲኖረው ለማድረግ የሚያስችል
አማራጭ መፍቀድ፤

በአገራችን የአክሲዮን ኩባንያዎች ማደራጀት የሚችሉት ባለ አንድ ደረጃ (One Teir) ቦርድ ብቻ ነው፡፡
ይህ አካሔድ ኩባንያዎቹ እንደ ሥራቸው ባሕርይና የሥራ ስፋት አመቺ ነው ብለው የሚያምኑበትን
የቦርድ አደረጃጀት ዕዳይጠቀሙ አድርጓል፡፡ ባለሁለት ደረጃ ቦርድ ለማቋቋም የሚቻልበት ሁኔታ ቢኖር
በተለይ ትላልቅ የአክሲዮን ኩባንያዎች የሥራ አስፈጻሚ ቦርዱን ተግባራት ለመቆጣጠር የሚያግዝ

16
ተቆጣጣሪ ቦርድ ለማደራጀት ስለሚችሉ በኩባንያው መልካም አስተዳደር ለማስፈን ከፍተኛ አስተዋጽኦ
ያደርጋል፡፡ ስለሆነም አክሲዮን ኩባንያዎች ከባለ አንድ ደረጃ ቦርድ በተጨማሪ ባለ ሁለት ደረጃ ቦርድ
ለማቋቋም የሚችሉበት አማራጭ እንዲፈቀድ ሃሳብ ቀርቧል፡፡

4.2 ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ኩባንያዎች በቦርድ እንዲመሩ ማድረግ፤

አሁን ባለው አሠራር ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ኩባንያዎች ቦርድ ለማቋቋም የሚችሉበት ሁኔታ
የለም፡፡ ከዚህም የተነሳ በርካታ ባለኃብቶች ኩባንያቸውን በአግባቡ ለመምራት እንደተቸገሩ ቅሬታ
በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም የቦርድ አሠራር ተግባራዊ ቢሆን በኩባንያዎች ላይ ቁጥጥር ለማድረግ
አመቺ ይሆናል፡፡ ስለሆነም በትናንሽ ኩባንያዎች ላይ ሊያደርስ የሚችለውን የወጭ ጫና ለመከላከል
ትላልቅ ኩባንያዎች ብቻ በቦርድ ለመመራት የሚችሉበት ሁኔታ ሥራ ላይ ቢውል ጠቃሚ ነው፡፡

4.3 የአክሲዮን ኩባንያ ጸሐፊ እንዲኖር የሚያደርገውን አሠራር አስገዳጅ ማድረግ፤

የአክሲዮን ኩባንያዎች ውጤታማ ለመሆን የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡ እነዚህ ተግባራት


የሚከናወኑት በተለያዩ የኩባያው ኃላፊዎችና ሠራተኞች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የኩባንያ ጻኃፊዎች
በኩባንያውና በዳይሬክተሮች ቦርድ፣ በአክሲዮን ኩባንያው አባላት እንዲሁም በኩባንያውና በመንግሥት
መካከል እንደ ድልድይ ሆነው የሚያገለግሉ በመሆናቸው ለኩባንያዎች ውጤታማነት ከፍተኛ ሚና
አላቸው፡፡

አሁን ባለው አሠራር ኩባንያዎች ጸኃፊ የሚመድቡት አስፈላጊ ሆኖ ካገኙት ብቻ ነው፡፡ የማይመደብበት
ሁኔታ ካለ ደግሞ በኩባንያ አስተዳደር ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል፡፡ ስለሆነም የኩባንያ ጸኃፊ መኖር
አስገዳጅ ቢሆን የጎላ ጠቀሜታ አለው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በሕጉ የተቀመጠው አሠራር ቢቀጥል ችግር
አያመጣም ሚል የልዩነት ሃሳብ ቀርቧል፡፡

4.4 ከአክሲዮን አባላት ውጭ ያሉ ሰዎች የቦርድ አባል ሊሆኑ እንዲችሉ መፍቀድ፤

የአክሲዮን ማኅበራት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሊሆኑ የሚችሉት የአክሲዮን አባላት ብቻ ናቸው፡፡ ይህ
አሠራር ኩባንያዎች አባል ባልሆኑ በኩባንያ አመራር እውቀትና ክህሎት ባላቸው ሰዎች ለመመራት
ያላቸውን እድል የሚያሳጣ ነው፡፡ ስለሆነም ኩባንያዎች አባል ያልሆኑ ባለሙያዎችን በቦርድ አባልነት

17
ሊመድቡ የሚችሉበት አማራጭ መፈቀድ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲሆን የአክሲዮኑ አባላት ያልሆኑ
ዳይሬክተሮች ብዛት ከአንድ ሦስተኛ መብለጥ የለበትም፡፡ እንዲሁም ሰብሳቢው አባል ሊሆን ይገባል፡፡

4.5 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ዝቅተኛ የዕድሜ ገደብ መወሰን፤

የኩባንያ ቦርድ አባላት ዕድሜ በአመራር ብቃት ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ አለው፡፡ በዕድሜ ያልበሰለ ሰው
የቦርድ አባል ቢሆን ኩባንያውን በአግባቡ ይመራዋል ተብሎ አይታመንም፡፡ በአገራችን አንድ ሰው አቅመ
አዳም ደርሷል የሚባለው ዕድሜው 18 ዓመት ሲሞላው ነው፡፡ በሌላ በኩል አንድ ሰው የህዝብ ተመራጭ
ለመሆን ዕድሜው ቢያንስ 21 መሆን ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም የባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ዝቅተኛ
ዕድሜ ገደብ 30 ዓመት ነው፡፡ ስለዚህ ከአገራችንም ሆነ ከውጭ ልምድ አንጻር ተመራጭ የሚሆነው
ዕድሜ 21 ዓመት ነው፡፡ በሌላ በኩል መነሻ ዕድሜው አሥራ ስምንት ዓመት መሆን ይኖርበታል የሚል
የልዩነት ሃሳብ ተሰንዝሯል፡፡

4.6 ለቦርድ አባልነት ብቁ የማያደርጉ መስፈርቶችን ማስቀመጥ፤

የንግድ ሕጉ የቦርድ አባል ለመሆን መሟላት ያለባቸው መስፈርቶችን አላካተተም፡፡ ይህም በመሆኑ ብቃት
የሌላቸውም ሆኑ ከዚህ ቀደም በኩባንያ አደረጃጀትና አመራር ላይ በነበሩበት ጊዜ ወንጀል የፈጸሙ
ግለሰቦች የቦርድ አባል በመሆን የኩባንያዎችን ጥቅም የሚጎዱበት ሁኔታ አለ፡፡ ስለዚህ በተለይ ቀደም ሲል
በኩባንያዎች በቦርድ አባልነት፣ ኦዲተርነት እና በመሳሰሉት ኃላፊነቶች ላይ ተመድበው ሲሰሩ ከሥራቸው
ጋር በተያያዘ በፈጸሙት ጥፋት በዚህ ዓይነት ሥራ ላይ እንዳይሰማሩ የተከለከሉ ወይም በወንጀል የተቀጡ
ሰዎች በቦርድ አባላትን እንዳይሳተፉ የሚገድብ አሠራር ተግባራዊ ቢደረግ ኩባንያዎችን ውጤታማ
ለማድረግ ይረዳል፡፡ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከፍ ብለው የተጠቁሱት ወንጀሎች የተፈጸሙት
በቸልተኝነት ከሆነ ለክልከላ ምክንያት ሊሆን አይገባም የሚል የተለየ ሀሳብ ቀርቧል፡፡

4.7 የኩባንያ አመራሮች ከሥራ ኃላፊነታቸው ጋር በተያያዘ የፍትሐብሔር ክስ ሲቀርብባቸው ወጭው


በኩባንያው እንዲሸፈን ማድረግ፤

የኩባንያ ዳይሬክተሮች፣ ኦዲተሮች እና ሌሎች ሥራ አስፈጻሚዎች ከአመራር ኃላፊነታቸው ጋር በተያያዘ


የሚከሰሱባቸው በርካታ አጋጣሚዎች አሉ፡፡ ይህ ደግሞ ልንከሰስ እንችላለን የሚል ሥጋት
እንዲያድርባቸው ስለሚያደርግ ኃላፊነት ወስደው ለመሥራት ፈቃደኛ የሚሆኑ አመራሮችንና
ባለሙያዎችን ማግኘት አስቸጋሪ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ የኩባንያ አመራሮች ከሥራ
ኃላፊነታቸው ጋር በተያያዘ በሚመሩት ኩባንያ ከቀረበባቸው የፍትሐብሔር ክስ ነጻ ከሆኑ፤ ክሱ የቀረበው
18
በሦስተኛ ወገኖች ከሆነ ደግሞ ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙም የክሱ ወጭ በኩባንያው እንዲሸፈን ከኩባንያው
ጋር ሊስማሙ የሚችሉበት ሁኔታ በሕጉ ውስጥ ቢካተት ጠቀሜታ አለው፡፡

4.8 ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ኩባንያዎች የፋይናንስ ሁኔታ በውጭ ኦዲተር እንዲመረመር ማድረግ፣

በሥራ ላይ ባለው ሕግ ኦዲተር እንዲኖራቸው የሚገደዱት ከሃያ በላይ አባላት ያላቸው ኃላፊነታቸው
የተወሰነ የግል ኩባንያዎች ናቸው፡፡ ሆኖም ከተጠቀሰው ቁጥር ያነሰ አባላት ያላቸው ትላልቅ ኩባንያዎች
ያሉ በመሆኑ ሂሳባቸው በኦዲተር የማይመረመር ከሆነ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡
በሌላ በኩል ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ አባል ባላቸው አነስተኛ ኩባንያዎች ላይ የኦዲት ግዴታ ተጥሎ
ትላልቆቹን ጥቂት አባላት ስላላቸው ብቻ ከኦዲት ነጻ ማድርጉ የፍትሐዊነት ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ስለዚህ
የኦዲት ግዴታ ከአባላት ቁጥር ይልቅ በኩባንያዎች የፋይናንስ አቅም ላይ የተመሠረት እንዲሆን ሃሳብ
ቀርቧል፡፡

5. የኩባንያዎች ጠቅላላ ጉባኤ አሠራርን ማሻሻል፣

5.1 የአክሲዮን ኩባንያ ካፒታልን በአባላት መዋጮ ለማሳደግ በድምጽ ብልጫ ሊወሰን የሚችልበትን ሁኔታ
መፍቀድ፤

ኩባንያዎች ካፒታላቸውን ከሚያሳድጉበት መንገድ አንደኛው የአክሲዮን ሽያጭ ነው፡፡ በንግድ ሕጉ


የኩባንያውን ካፒታል ለማሳደግ የሁሉንም የአክሲዮን አባላት ስምምነት ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም ሁሉም
የአክሲዮን አባላት ሳይስማሙ ቢቀሩ የኩባንያዎችን እድገት ይጎዳል፡፡ ስለዚህ የኩባንያውን ካፒታል
ለአባላት ተጨማሪ አክሲዮን በመሸጥ ማሳደግ በተፈለገ ጊዜ ቢያንስ በሦስት አራተኛ ድምጽ ከተደገፈ
የኩባንያው ካፒታል እንዲጨምር ለማድረግ የሚያስችል አሥራር ተግባራዊ ቢደረግ እየታየ ያለውን ችግር
ሊቀርፍ ይችላል፡፡

5.2 በድንገተኛ ጉባኤ ላይ የሚታዩ ጉዳዮች እንደ ሁኔታው በአመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ሊታዩ የሚችሉበትን
ሁኔታ መፍቀድ፤

አሁን ባለው አሠራር የመመስረቻ ጽሑፍና የመተዳዳሪያ ደንብ የሚሻሻሉት በድንገተኛ ጉባኤ ነው፡፡
ሆኖም በድንገተኛ ጉባኤ የሚወሰኑ ጉዳዮች መደበኛው አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በሚጠራበት ወቅት
ሊያጋጥሙ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ለመወሰን ከመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሌላ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ይጠራ
ቢባል ተጨማሪ ወጭና ጊዜ የሚጠይቅ ከመሆኑም በላይ የአክሲዮን አባላት በተቀራራቢ ቀን ስብሰባ

19
ቢጠሩ ላይገኙ የሚችሉበት እድል ሰፊ ነው፡፡ ስለዚህ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ
ሊወሰኑ የሚገባቸው ጉዳዮች በመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ሊታዩ የሚችሉበት ሁኔታ ቢኖር የኩባንያዎችን
አሠራር የሚያቀላጥፍና ወጭ ለመቀነስ የሚረዳ ይሆናል፡፡

6. የአነስተኛ ባለአክሲዮኖችንና አበዳሪዎችን መብት ጥበቃ ማጠናከር

6.1 ማንኛውም ባለአክሲዮን በኩባንያው ስም ዳይሬክተሮችን ወይም ሦስተኛ ወገኖችን በሕግ ለመጠየቅ
የሚችልበትን አሠራር ተግባራዊ ማድረግ፤

በሃገራችን የአክሲዮን አባላት በኩባንያው ላይ ጉዳት ያደረሱ የቦርድ አባላትን ወይም ሶስተኛ ወገኖችን
ኩባንያውን ወክለው ክስ የሚመሰርቱበት ሁኔታ ብዙም አይስተዋልም፡፡ ለዚህ ደግሞ በምክንያትነት
የሚጠቀሰው የአክሲዮን አባላትን 20% ድጋፍ የሚፈልግ በመሆኑን ይህን ድጋፍ ለማግኘት አስቸጋሪ
ስለሚሆን ነው፡፡ ስለዚህ በኩባንያዎች ስም የኩባንያውን ኃላፊዎች ወይም ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች
ለመክሰስ በሕጉ የተቀመጠውን ዝቅተኛ የድምጽ መጠን ከ20% ወደ 5% ዝቅ ማድረግ ይህንን ድምጽ
ማሰባሰብ ካልተቻለ ደግሞ ማንኛውም የኩባንያው አባል ያለበቂ መረጃ ክስ ቢመሰርት ሊደርስ
የሚችለውን ጉዳት ለመሸፈን የሚበቃ ገንዘብ አስቀድሞ በማስያዝ መክሰስ የሚችልበት ሁኔታ ቢፈቀድ
የኩባንያ መልካም አስተዳደር ለማስፈን ይረዳል፡፡ ይህን ጉዳይ በተመለከተ በሕጉ የተቀመጠውን አሠራር
ማሻሻል አስፈልጊ አይደለም የሚል የተለየ ሃሳብ ቀርቧል፡፡

6.2 ጠቅላላ ጉባኤ ለመጥራት የሚያስችለውን የአክሲዮን ብዛት ከ10% ወደ 5% ዝቅ ማድረግ፤

በንግድ ሕጉ የተቀመጠውን ጠቅላላ ጉባኤ የመጥራት ግዴታ ተግባራዊ የማያደርጉ በርካታ አክሲዮን
ማኅበራት እንዳሉና ከእነዚህ መካከል የተወሰኑት ስብሰባ ጠርተው እንደማያውቁ ለዚህ ደግሞ ዋናው
ምክንያት ዳይሬክተሮች ጉባኤ መጥራት ባልቻሉ ጊዜ በአባላት ጉባኤ ለመጥራት የሚያስችለውን 10%
ድምጽ ማሰባሰብ አስቸጋሪ ስለሚሆን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በስብሰባ ወቅት ተጨማሪ አጀንዳ
ለማስያዝ የማይፈቀድ በመሆኑ ቦርዱ አጀንዳውን ራሱ ብቻ በመቅረጽ ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ የሚደግፉ
አባላትን ሃሳብ ብቻ ተቀብሎ ውሳኔዎች የሚተላለፉባቸው አጋጣሚዎች አሉ፡፡ በመሆኑም ጠቅላላ ጉባኤ
እንዲጠራ ለመጠየቅ የሚስችለው 10% የአባላት ቁጥር ወደ 5% ዝቅ ቢደረግ እንዲሁም የተጠቀሰውን
ቁጥር የሚያሟሉ አባላት በጉባዔ ወቅት አጀንዳ ለማስያዝ የሚችሉበት አሠራር ቢፈቀድ የአነስተኛ
አባላትን መብት ለማስጠበቅ ያግዛል፡፡

20
6.3 በኩባንያው ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው አባላት፣ አመራሮችና ቤተሰቦቻቸው ከኩባንያው ወይም ከኩባንያው ጋር
ግንኙነት ካላቸው ሌሎች ኩባንያዎች ጋር የሚያደርጉት የንግድ ግንኙነት በቅድሚያ በቦርድ እንዲጸድቅ
የሚያደርግ አሠራር መዘርጋት፤

ከኩባንያ መልካም አስተዳደር ጋር ተያይዘው ከሚነሱ ችግሮች መካከል የኩባንያ አመራሮችና ከፍተኛ
ድርሻ ያላቸው የአክሲዮን አባላት አነስተኛ ድርሻ ያላቸውን የአክሲዮን አባላት ጥቅም በሚጎዳ መልኩ
የሚያደርጉት የንግድ ግንኙነት አንዱ ነው፡፡ ሆኖም በንግድ ሕጉ እንደዚህ ዓይነት ችግሮች እንዳይከሰቱ
ለመከላል የሚያስችል ድንጋጌ አልተቀመጠም፡፡ ስለዚህ ክፍተቱን ለመሙላት ለኩባንያው ቅርበት ያላቸው
ሰዎች ከኩባንያው ወይም ከኩባንያው ጋር የንግድ ግንኙነት ካለው ሌላ ኩባንያ ጋር የንግድ ግንኙነት
ከማድረጋቸው በፊት በዳይሬክተሮች ቦርድ እንዲጸድቅ የሚያደርግ አሠራር ቢዘረጋ ተመራጭ ነው፡፡

6.4 የግዴታ ወረቀት የገዙ አበዳሪዎች ስብሰባ ለመጥራት የሚያስፈልጋቸውን የድምጽ ብዛት ከ20% ወደ 10% ዝቅ
ማድረግ፤

ኩባንያዎች ለሥራ የሚያስፈልጋቸውን ካፒታል ለማሰባሰብ የግዴታ ወረቀት የሚሸጡበት ሁኔታ የተለመደ
ነው፡፡ የግዴታ ወረቀት የገዙ ሰዎች ያበደሩትን ገንዘብ መልሰው ስለሚያገኙበት ሁኔታ ለመመካከር
ኩባንያዎች የአበዳሪዎች ስብሰባ እንዲጠሩ ለመጠየቅ የሚችሉት ከአጠቃላይ የግዴታ ወረቀት ገዥዎች
20% ድጋፍ ማግኘት ሲችሉ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ይህ የድምጽ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ አነስተኛ ይዞታ
ያላቸው የግዴታ ወረቀት ገዥዎች ለኩባንያው ያበደሩትን ገንዘብ በቀላሉ ለማስመለስ ሊቸገሩ ይችላሉ፡፡
ስለዚህ የግዴታ ወረቀት የያዙ አበዳሪዎች የሚያስፈልጋቸው አነስተኛ ድምጽ ከ20% ወደ 10% ዝቅ
እንዲል ሃሳብ ቀርቧል፡፡

7. ኩባንያዎች ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ስለማድረግ፤

ኩባንያዎች ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት በአካባቢው ማህበረሰብና በአካባቢ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ


የሚችሉበት አጋጣሚዎች ሰፊ ነው፡፡ ሆኖም የንግድ ሕጉ ኩባንያዎች ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት
ለሚያደረሱት ጉዳት ማኅበራዊ ኃላፊነት እንዲወስዱ አያስገድድም፡፡ ስለሆነም ኩባንያዎች
እንደየአቅማቸው ሃገሪቱ በምታደርገው የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ የሚሳተፉበትን ሁኔታ የሚያመቻች
ድንጋጌ በሕጉ ውስጥ ቢካተት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ይህን ጉዳይ በሚመለከት ኩባንያዎች ማኅበራዊ
ኃላፊነት እዲወጡ በሕግ ሊገደዱ አይገባም የሚል የተለየ ሃሳብ ተነስቷል፡፡

21
8. ኩባንያዎች በቡድን ተደራጅተው የሚሰሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት

8.1 በቡድን ኩባንያዎች መካከል ግንኙነት የሚመሠርትበትን መስፈርት መወሰን፤

ኩባንያዎች ተቧድነው ቢሰሩ ትርፍን ለመሳደግና ኪሳራን ለመቀነስ፤ በቡድኑ ኩባንያዎች መካከል የብድር፣
የዋስትና እና የፕሮጀክት ፋናንስ አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ፤ ኃብታቸውን በቀላሉ ለመሸጥ እና
ለመለወጥ፣ የቡድኑ አባል ኩባንያዎች በተለያዩ አገራት ተቋቁመው የሚሰሩ ከሆነ እያንዳንዱ ቡድን
የሚገኝባቸው አገራት የሚጠይቁትን የሕግ መስፈርት ለማሟላትና የመሳሰሉትን ጥቅሞች ለማግኘት
ያስችላቸዋል፡፡ በሌላ በኩል የሚቧደኑበት ሁኔታ በሕግ ካልተደነገገና በመንግሥት ተገቢው ቁጥጥር
ካልተደረገ የንግድ ውድድር ሚዛንን በማዛባት በበላይነት ገበያ የመቆጣጠር፣ ለወላጅ ኩባንያው ጥቅም
ሲባል አነስተኛ ድርሻ ያላቸውን የተነጣይ ኩባንያ የአክሲዮን አባላት ጥቅም የመጉዳት፤ ግብር የመደበቅ
እና የመሳሰሉትን ችግሮች ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም የተቧደኑ ኩባንያዎችን መብትና ግዴታ
ለመለየትና ተገቢውን ቁጥጥር ለማድረግ የሚቧደኑበትን መስፈርት መወሰን ያስፈልጋል፡፡ ይህን
በሚመከለት ሁለት ዓይነት መስፈርቶች አሉ፡፡ አንደኛው መስፈርት የወላጅና ተነጣይ (Holding-
Subsidiary) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ተቆጣጣሪና በቁጥጥር ሥር ያሉ ኩባንያዎች (Controlling and
Controlled Companies) ግንኙነት በመባል ይታወቃሉ፡፡ እነዚህ መስፈርቶች በተናጠል ወይም
በጥምረት በሥራ ላይ ሊውሉ የሚችልበት ሁኔታ አለ፡፡

ስለዚህ የኩባንያዎችን መቧደን ለመወሰን ከወላጅና ተነጣይ ግንኙነት በተጨማሪ የአክሲዮን አባልነት
ግንኙነት ሳይኖር በውል በሚገኝ መብት መሠረት የኩባንያውን አመራርና የአሠራር አቅጣጫ የመወሰን
(የቁጥጥር) ሥልጣን መኖርን በመስፈርትነት መጠቀም ተመራጭ ነው፡፡

8.2 ኩባንያዎች በቡድን የሚደራጁበትን መንገድ በፍላጎታቸው እንዲወስኑ መፍቀድ፤

ኩባንያዎች በቡድን የሚደራጁበት መንገድ ባለመደንገጉ ያሉት የአደረጃጀት አማራጮች የሚያስገኙላቸው


ጥቅሞችና የሚያስከትሏቸው ግዴታዎች ምን እደሆኑ አስቀድመው የሚያውቁበትና የተሻለ ነው ብለው
የሚያምኑበትን አማራጭ ለመከተል የሚችሉበት ሁኔታ ስለሌለ ተቧድኖ በመሥራት በሚገኘው እድል
ተጠቃሚ እንዳይሆኑ አድርጓል፡፡ በብዙ አገራት ኩባንያዎች የሚቧደኑት የተነጣጠለ (Separate Entitiy
approach) ወይም አንድ ወጥ (Single Enterprise Apprach) በሚል በሚታወቁት ሁለት ዓይነት
መንገዶች ነው፡፡ እነዚህ አደረጃጀቶች የየእራሳቸው የሆኑ ጠቀሜታዎች ያሏቸው ናቸው፡፡ ከዚህ አንጻር

22
ኩባንያዎች እንደ ተጨባጭ ሁኔታቸው እያዩ ከሁለቱ አደረጃጀቶች ተስማሚ ነው ብለው የሚያምኑበት
ተግባራዊ ቢያደርጉ ጠቃሚ ይሆናል፡፡

8.3 ወላጅ ኩባንያዎች ለተነጣይ ወይም ዋናው ቡድን ለቡድኑ አባል ኩባንያዎች ዕዳ ተጠያቂ የሚሆኑበትን
አሠራር መዘርጋት፤

በሃገራችን ወላጅ ኩባንያዎች ወይም ዋና ቡድኖች በሥራቸው ላሉ ኩባንያዎች ዕዳ ተጠያቂ የሚሆኑበት


ሥርዓት አልተዘረጋም፡፡ በመሆኑም የኩባንያዎቹን ኃብትና ንብረት በተለያየ መንገድ በቀላሉ ወደ ራሳቸው
ሊያስተላልፉ የሚችሉበት እድል አለ፡፡ ይህም በተነጣይ ወይም በቡድን አባላቱ ኩባንያዎች አነስተኛ
አክሲዮን አባላትና ከእነዚህ ኩባንያዎች ጋር የንግድ ግንኙነት ባላቸው ሦስተኛ ወገኖች ላይ ጉዳት ሊያደርስ
ይችላል፡፡ ስለዚህ ጉዳቱን ለመከላከል ኩባንያዎች በአንድ ወጥ አደረጃጀት ስልት የተደራጁ ከሆነ፤ ወይም
በቡድኑ ስር ያሉ ኩባንያዎች በዋናው ቡድን ስም የሚጠቀሙ ከሆነ ወይም ወላጅ ወይም ተቆጣጣሪው
ኩባንያዎች በሥራቸው ያሉ ኩባንያዎችን በሚመለከት ያለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ሳይወጡ ከቀሩ
ለተነጣይ ወይም በቁጥጥራቸው ሥር ላሉ ኩባንያዎች ዕዳ ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉበትን አሠራር መዘርጋት
አስፈላጊ ነው፡፡

9. የኩባንያዎች መዋሃድ እና መከፋፈል የሚመራበትን ሥርዓት ማጠናከር፤

9.1 የኩባንያዎች ውህደት ስምምነት በባለሙያ ግምትና በኦዲት ሪፖርት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ማድረግ፤

ኩባንያዎች በሚዋኃዱበት ወቅት ሂደቱ በኦዲተር የሚመረመርበትም ሆነ ንብረታቸው በባለሙያ


እንዲገመት የሚደረግበት አሠራር የለም፡፡ ንብረቱ በባለሙያ ካልተገመተና በኦዲተር ካልተመረመረ
የኩባንያው መብትና ኃላፊነት በአግባቡ ሳይታወቅና ሳይጣራ አብሮ ስለሚተላለፍ የጠቅላዩ ኩባንያ ዕዳ
እንዲጨምር ሊያደርግ ወይም የአክሲዮን አባላቱን ጥቅም ሊጎዳ ይችላል፡፡ በመሆኑም ትላልቅ ኩባንያዎች
ሲዋሃዱ ንብረታቸው በባለሙያ እንዲገመትና በኦዲት ምርመራ እንዲረጋገጥ ቢደረግ ከዚሁ ጋር በተያዘ
ሊደርስ የሚችለውን ችግር ለመከላከል ያስችላል፡፡

9.2 ኩባንያዎች መከፋፈል የሚችሉበትን ሁኔታ በንግድ ሕጉ ማካተት፤

የንግድ ኩባንያዎች እንደገና ከሚደራጁበት (Reconstruction) መንገድ አንዱ ክፍፍል (Division) ነው፡፡
ሆኖም በንግድ ሕጉ ውስጥ ይህን የሚመለከት ድንጋጌ አልተካተተም፡፡ ይህም በመሆኑ እንደዚህ ዓይነት
ሁኔታዎች ቢፈጠሩ ተግባራዊ ለማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ የለም፡፡ ስለዚህ የሚረቀቀው የንግድ ሕግ

23
ኩባንያዎች የሚከፋፈሉበትን ሥርዓትና ሲከፋፈሉ የኩባንያው ባለአክሲዮኖች መብትና ግዴታ ወደ ሌሎች
ኩባንያዎች እንዴት እና በምን ዓይነት መንገድ አከፋፍሎ ማስተላለፍ እንደሚቻል በግልጽ መደንገግ
ይኖርበታል፡፡

10. የኩባንያዎችን ተጠያቂነት ማጠናከር፤

በንግድ ሕጉ የንግድ ማኅበራትን ተጠያቂነት የሚመለከቱ ድንጋጌዎች በበቂ ሁኔታ ካለመቀመጣቸውም


በላይ ያሉትም ቢሆኑ በአጥጋቢ ሁኔታ በተግባር ውለዋል ለማለት አያስደፍርም፡፡ በመሆኑም የኩባንያ
አመራሮች ካላቸው ኃላፊነት ጋር በተያያዘ ለሚፈጸሙ ጥፋቶች ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉባቸው ሁኔታዎች
በግልጽ ቢደነገጉ እየታየ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ያግዛል፡፡

11. የኢንፎርሜሽን ግንኙነት ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሻሻል፤

የኢንፎርሜሽን ግንኙነት ቴክኖሎጅ በኩባንያዎችና በአክሲዮን አባላት እና በባለድርሻ አካላት እንዲሁም


በኩባንያዎች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያቀላጥፍ ከመሆኑም ሌላ ወጭን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል፡፡
ሆኖም የንግድ ሕጉ በወጣበት ወቅት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ግንኙነት ጥቅም ስላልታወቀ የሰነድ ወይም
የወረቀት ግኑኝነቶችን ብቻ ታሳቢ ያደረጉ ድንጋጌዎችን እንዲያካትት ተደርጓል፡፡ በመሆኑም የሚሻሻለው
ሕግ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ግንኙነትን ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ይኖርበታል፡፡

24
መጽሐፍ ሦስት
ስለማጓጓዝ (ማመላለስ) ሥራ
የማጓጓዝ ሕግ የማጠቃለያ ሀሳቦች

1. አደረጃጀትና አወቃቀሩ በግልጽ የሚታይ ችግር ስለሌለው መሰረታዊ ለውጥ ማድረግ


አያስፈልገውም፡፡ ሆኖም አደረጃጀቱን የበለጠ ግልጽ ማድረግ ስለሚያስፈልግ ከሚከተሉት
አማራጮች አንዱ ተመርጦ አደረጃጀቱ ሊስተካከል ይገባዋል፡፡

አማራጭ አንድ፡ የየብስ፣ የአየር፣ የባህር፣ የባቡር፣ የመልቲ ሞዳል በማለት እያንዳንዱን በመለየት
በየራሱ ቲኬትን፣ መብትና ግዴታን እያስቀመጠ መሄድ፤ ወይም
አማራጭ ሁለት፡ ሁሉንም የማጓጓዣ አይነቶች በአንድ ላይ በማጠቃለል የጉዞ ሕግ በማድረግ
የትኬቱ ዓይነትና ይዘት ሁሉንም ሊያቅፍ በሚችል መልኩ የአጓጓዥ፣ የላኪና ተቀባይ
መብትና ግዴታዎችን ወጥ በሆነና ሁሉንም በሚያቅፍ መልኩ ተዘጋጅቶ ልዩ ሁኔታ
የሚያስፈልገውን ብቻ ለይቶ በማስቀመጥ ሕጉን መቅረጽ ይቻላል፡፡ ስለሆነም አዲሱ
የንግድ ሕግ የትኛውን አደረጃጀትና ቅርጽ መያዝ እንዳለበት ለውሳኔ የቀረበ ሲሆን በጥናት
ቡድኑ እምነት ሁለተኛው አማራጭ ቢሆን የሚል እምነት አድሮበታል፡፡
2. የማጓጓዥ ሕጉ በሦስተኛው መጽሐፍ ውስጥ ግንኙነት ከሌለው የመድን ሕግ ጋር ተዳብሎና
በአንቀጽ ተከፍሎ መገኘቱ ትክክል ስላልሆነ ከመድን ሕግ ተነጥሎ እራሱን በቻለ መጽሐፍ
መደራጀት ይኖርበታል፡፡ በማለት የጥናት ቡድኑ ያምናል፡፡
3. የየብስ ትራንስፓርት ሕግ እና የመልቲ ሞዳል ትራንስፓርት ሕግ አዋጆች በቅርቡ በ1999 ዓ.ም.
የወጡ በመሆኑ በንግድ ሕጉ ላይ ከሚገኘው ድንጋጌ በብዙ መልክ ተሻሽለዋል፣ በነዚህ የማጓጓዣ
ሥራዎች ጋር በተገናኘ ያሉ አንገብጋቢ ጉዳዮችንም ተመልክተዋል፡፡ እነዚህ የየብስ ትራንስፓርት
ሕግ እና የመልቲ ሞዳል ትራንስፓርት ሕግ ከአንዳንድ ልዩነቶች በስተቀር አብዛኛው
ድንጋጌዎቻቸው ከሲ ኤም አር (CMR) ኮንቬንሽን እና ከመልቲ ሞዳል ትራንስፓርት ኮንቬንሽን
የተወሰዱ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት የያዙት ጠቅላላ የሕግ መስፈርት ዓለም አቀፍ ደረጃ የጠበቀና
በዝርዝር የሚተነትን የሕግ ማዕቀፍ የያዙ በመሆኑ እነዚህን እንዳሉ በመጠቀም አዲሱ የንግድ ሕግ
ሊዘጋጅ ይገባዋል፡፡
4. የየብስ የዕቃ ማጓጓዝ ሕጉ ለሚደርስ ጉዳት የካሳ ክፍያው ሲ ኤም አር ያወጣውን መስፈርት ኤስ ዲ
አር (Special Drawing Right) የምንዛሬ መስፈርትን በመክፈያነት ሲያስቀምጥ የአየር ዕቃ
ማጓጓዝን የሚመለከተው የንግድ ሕጉ ለሚደርስ ጉዳት የካሳ ክፍያ በኢትዮጵያ ብር እንደሆነ

25
ሳይሻሻል እስካሆን ተቀምጧል፡፡ ይሄንን ልዩነት የተጣጣመ ለማድረግና በየጊዜው የሚለዋወጠውን
የገንዘብ ምንዛሪ ልዩነት ወጥ ወደሆነ የገንዘብ ምንዛሬ ለማቀራረብ ያስችል ዘንድ የካሳ መጠኑ በብር
ከሚሆን በኤስ ዲአር (SDR) የገንዘብ ምንዛሬ ደረጃ በወጥነት ሊስተካከል ይገባል፡፡
5. ሲ ኤም አር ኮንቬንሽን በሳጥን ውስጥ ያለ አስክሬንን የማጓጓዝ ሥራ ላይ ተፈጻሚ እንደማይሆን
በአንቀጽ 1 ላይ ሲደነግግ አዋጅ ቁጥር 547/1999 በግልጽ አልከለከለም፡፡ ህጋችንን ከዓለም አቀፍ
ሕግ እና አሠራር ጋር ማጣጣም አስፈላጊ ከመሆኑም በላይ የሰው ልጅ ከህልፈተ ህይዎት በኋላ
ለአስከሬን የሚሰጠውን ክብር ዝቅ ከማድረግ አልፎ በውልና አፈጻጸም ረገድ ችግር የሚፈጥር
ስለሆነ በሳጥን ውስጥ ያለ አስከሬን በማጓጓዝ ሥራ ሕግ ውስጥ ተፈፃሚ እንደማይሆን ሊደነገግ
ይገባዋል፡፡
6. የሞንትሪያል ኮንቬንሽን የፓስታ የማጓጓዝ ሥራን ከወሰኑ ውጪ እንደሆነ ሲደነግግ የንግድ ሕጉ ግን
በወሰኑ ላይ ገደብ አላስቀመጠም ስለሆነም አዲስ የሚረቀቀው የንግድ ሕግ የፖስታ የማጓጓዝ ሕግ
ራሱን የቻለ የሕግ ማዕቀፍ ስላለው ከወሰኑ ውጭ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡
7. በየብስ የማጓጓዝ ሥራ፣ በሀገር ውስጥ ውሃ ማጓጓዝ ሥራ እና የባቡር ማጓጓዝ ሥራ ከንግድ ሕጉ
ጋር በአንድ ላይ በተመሳሳይ ድንጋጌዎች ይተዳደራሉ፡፡ ይሁንና የየብስ የማጓጓዝ ሕግ አብዛኛው
ድንጋጌ ሲ ኤም አር(CMR)ን መሠረት አድርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡ ይህ ኮንቬንሽን የየብስ ጉዞ ሲል
በክፍያ በመሬት ላይ የሚካሄዱ ጉዞዎችን ብቻ ሲያካትት በሀገር ውስጥ ውሃ እና የባቡር ማጓጓዝን
አያካትትም፡፡ በሌላ በኩል በሀገር ውስጥ ውሃ እና የባቡር ማጓጓዝ ሥራን በአንድ ላይ ጠቅልሎ
ማስቀመጥ የነዚህ የማጓጓዣ ሥራዎች ልዩ ባሕርይያት በሕግ እንዳይሸፈኑ አድርጎታል፡፡ እስካሁን
ድረስ በኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ውሃ እና የባቡር የማጓጓዝ ሥራ በጣም አነስተኛ ከመሆኑ አንጻር
በአንድ ላይ በመሬት ከሚካሄዱ ጉዞዎች ጋር መታየቱ የጎላ ችግር ባያስከትልም፤ በአሁኑ ሰዓት
ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ውሀን እና የባቡር ትራንስፓርት ዘርፉን የማስፋፋት ሥራ በሰፊው
እየተካሄደ መሆኑን ከግምት በማስገባት እነዚህ የትራንስፓርት ዘርፎች እራሳቸውን ችለው የሕግ
ቅርጽ ቢይዙ የጎላ አስተዋጽዖ ይኖረዋል፡፡
8. የየብስ ዕቃ ጉዞ ሕግ ከሲ ኤም አር ሀሳብን በመውሰድ የተቀባይ መብት እና ግዴታን በዝርዝር
ሲያስቀምጥ የአየር ሕግ ግን አጭርና ብዙ ሀሳቦችን ያልያዘ ስለሆነ አዲስ የሚረቀቀው ሕግ
በተመሳሳይ ሁኔታ እነዚህን ፅንሰ ሀሳቦች በመያዝ የአየር ጉዞ ሕግ የተቀባይ መብት እና ግዴታን
በሰፊው በመዘርዘር በሕግ ማእቀፎቹ ሊካተት ይገባዋል፡፡
9. በንግድ ሕጉ የአየር እና የየብስ አጓጓዥ በመንገደኛ ላይ ለሚደርስ ጉዳት የሚከፍለው የካሳ መጠን
ከአርባ ሺህ የኢት/ብር ሊበልጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡ የአየር መንገደኛ የጉዳት ካሳን

26
በተመለከተ የሞንትሪያ ኮንቬንሽን በሰው ህይወት መጥፋት ወይም አካል ላይ ለሚደርስ ጉዳት
የኃላፊነት ወሰን አልገደበም፡፡ ይህ በዓለም አቀፍ ኮንቬንሽኑና በአየር ማጓጓዝ ሕግ መካከል ያለ
ልዩነት ነው፡፡ በተጨማሪም የካሳው መጠን በደረሰው ጉዳት ልክ ወይስ ወደፊት በርግጠኝነት
ሊደርስ ይችላል ተብሎ የሚገመት ጉዳትን ጨምሮ ስለመሆኑና ጠቅላላ የካሳ መጠኑ አወሳሰን
(Damage Assessments) በንግድ ሕጉ ስላልተካተተ ለፍርድ አወሳሰን አስቸጋሪ ስለሚያደርገው
የሚዘጋጀው ንግድ ሕግ ይህን ሀሳብ በማካተት፡-

አማራጭ አንድ፡ በአሁኑ ሰአት ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ውሃ እና የባቡር የማጓጓዝ ሥራ በጣም
አነስተኛ ከመሆኑ አንጻር በአንድ ላይ በየብስ ከሚካሄዱ ጉዞዎች ጋር መታየቱ ተገቢ
ነው ብሎ መከራከር ይቻላል፡፡ ስለዚህ ሕጉ አሁን ባለበት ይቀጥል፡፡
አማራጭ ሁለት፡ ኢትዮጵያ ወደፊት የሀገር ውስጥ ውሀን በመገደብ የሀይል ምንጭ እንዲሆን
ከመሥራት ባለፈ ለትራንስፓርት አገልግሎት እንዲውል ሰፊ ሥራ እየተሰራ
ከመሆኑም በላይ ለቱሪዝም መስፋፋት እና ለመዝናኛነትም እንዲያገለግል
የሚደረገውን ጥረት ውጤት ላይ ለማድረስ የሀገር ውስጥ የውሀ ጉዞ ሕግ እራሱን
ችሎ እንዲቀመጥ ማድረግ፡፡ በተጨማሪም ሀገሪቱ የያዘችውን የባቡር ማጓጓዣ ሥራ
መስፋፋት ከግምት በማስገባት እና ይህ የትራንስፓርት ዘርፍ እንደ ሌሎች ሀገራት
እራሱን ችሎ የሕግ ቅርጽ ቢይዝ የጎላ አስተዋጽዖ ስለሚኖረው የባቡር ጎዞና
ትራንስፖርት ሕግ እንደየብስና አየር ጉዞ ሕግ ራሱን ችሎ ሊቀረጽ ይገባዋል፡፡ በጥናት
ቡድኑ እምነት ሁለተኛው አማራጭ ቢሆን የሚል እምነት አድሮበታል፡፡
10. የየብስ እና የአየር ሕግ የተመዘገበ እና ያልተመዘገበ ጓዝ ላይ ልዩነት በመፍጠር ለተመዘገበ ጓዝ
አጓጓዥ ላይ ኃላፊነት ሲጥል፣ ላልተመዘገበ ጓዝ ግን በአጓጓዡ ላይ የጣለው ግዴታ የለም፡፡ የአየር
ጓዝን በተመለከተ የሞንትሪያል ኮንቬንሽን ከንግድ ሕግ በተለየ መልኩ አጓጓዥ ለተመዘገበም ሆነ
ላልተመዘገበ ጓዝ ሀላፊ ያደርጋል፡፡ የአየር አጓጓዥ በሚጭነው ጓዝ ላይ ከየብስ አጓጓዥ የተሻለ
ቁጥጥር አለው፡፡ ስለዚህ በሞንትሪያል ኮንቬንሽን መሠረት ላልተመዘገበ ጓዝ አጓጓዥ በፈጸመው
ጥፋት ምክንያት ለሚደርስ ጉዳት ሃላፊ ሊደረግ ይገባዋል፡፡
11. የየብስ ሕግ ላኪ ለሚያስጭነው ዕቃ በአግባቡ ባለመታሸግ ለሚደርስ ጉዳት ኃላፊነትን ሲጥልበት
በአየር ጉዞ ግን በላኪ ላይ ስለአስተሻሸግ በግልጽ ያስቀመጠው ገደብ ወይም ግዴታ የለም፡፡ ስለዚህ
ላኪ ዕቃ ሆነ ጓዝ በአግባቡ ባለማሸጉ ለሚደርስ ጉዳት ሀላፊ ለማድረግ ለአተረጓጎም የተጋለጠና

27
ግልጽ ባለመሆኑ እንደየብሱ ጉዞ በግልጽ ሀላፊነቱን የማን እንደሆነ ሊያሳይ በሚችል መልኩ ሊቀረጽ
ይገባል፡፡
12. ላኪ የላከው ዕቃ በአግባቡ መታሸጉን እና የታሸገው ዕቃ በመላኪያ ሰነድ ላይ የተገለጸው መሆኑን
የማረጋገጥ ግዴታ አለበት፡፡ ነገር ግን ላኪው የላከው ዕቃ በአግባቡ ታሽጎ በውስጡ ያለው
ከማጓጓዣ ሰነድ ላይ ያልተገለፀ ሕገወጥ ዕቃ ሆኖ ቢገኝ የላኪው ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ፤
ሳይታሸግ ለአጓጓዡ የቀረበለትን ዕቃ አጓጓዥ ሲረከብ ሕገወጥ ዕቃ አለመሆኑን የማጣራት፣
በቀረበው የመላኪያ ሠነድ መሠረትም ዕቃውን አጓጓዡ መረከብ እንዳለበትና ከተረከበው በኋላ
ዕቃው ከመላኪያው ሰነድ የተለየ ሆኖ ከተገኘ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን የሚገልጽ በላኪና በአጓጓዥ
ላይ ኃላፊነት የሚጥል ድንጋጌ በሚቀረጸው ሕግ ሊካተት ይገባል፡፡
13. አደገኛ ዕቃዎችንና ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎችን በተመለከተ በየብስ ሕጉ ላይ
እንዳለውና የአደገኛ ዕቃዎች ማጓጓዣ ረቂቅ ደንብ ላይ በተገለጸው መሠረት የአየር ጉዞ ሕጉም ላይ
ላኪው በሚያስረክብበት ጊዜ ለአጓጓዡ ዕቃውን በተመለከተ ማሳወቅ እና ምን ዓይነት ጥንቃቄ
ማድረግ እንዳለበት በግልጽ ሊደነገግ ይገባል፡፡
14. ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ማስረከብ ካልቻለ ወይም በጓዙ ውስጣዊ ጉድለት ወይም በላኪና
ተቀባይ ጥፋት ምክንያት ከሆነ አጓዥ ከኃላፊነት የሚድን መሆኑ በጉዞ ላይ የሚደርስ የዕቃው
የክብደት ወይም ውስጣዊ ጉድለት ምክንያት አጓጓዥ በኃላፊነት የማይጠየቅ መሆኑ የየብስ ጉዞ ሕግ
ሲደነግግ የአየር ጉዞ ሕግ ግን አጓጓዡ ወይም ወኪሉ ጉዳት እንዳይደርስ አስፈላጊውን ጥንቃቄ
ማድረግ ወይም ለማድረግ የማይቻል መሆኑን ካስረዳ ከኃላፊነት እንደሚድን ይደነግጋል፡፡ይህም
የላኪውን ግዴታ በግልጽ በማሳየት እረገድ ልዩነት ያስከትላል፡፡ ስለዚህ ሕጉ ልዩነቱን በሚያጠብ
መልኩ ሊዘጋጅ ይገባል፡፡
15. የአየር ዕቃ ጉዞ ተቀባባይ አጓጓዦች ላደረሱት ኃላፊነት እንደ አንድ መቆጠራቸው ዕቃዎችን
በተመለከተ ላኪው በኃላፊነት መጠየቅ የሚገባው የመጀመሪያውን አጓጓዥ ሲሆን የመጀመሪያው
አጓጓዥም ሌሎቹን በቅደም ተከተል በመጠየቅ መብት ያላቸው መሆኑና ሁሉም አጓጓዦች ለላኪውና
ለተቀባይ የማይከፋፈል የአንድነት ኃላፊነት አለባቸው፡ በሌላ በኩል የየብስ ጉዞ ሕግ ተቀባባይ
አጓጓዦች ላደረሱት ኃላፊነት ላኪው የመጀሪያውን አጓጓዥ፣ የመጨረሻውን አጓጓዥ ወይም ጉዳት
ያደረሰውን አጓጓዥ በኃላፊነት መጠየቅ ይችላል ይህም ሀሳብ ከሲ ኤም አር ኮንቬንሽን የተወሰደ
ሲሆን የአየር ጉዞ ሕግ ግን ከሞንትሪያል ኮንቬንሽን በተለየ መልኩ ተቀምጧል፡፡ ስለዚህም የዓለም
አቀፍ ሕጎችን በመጠቀም እንደየብስ ዕቃ ማጓጓዝ ሕጉ ሁሉ የአየር ዕቃ ማጓጓዝ ሕጉም ሊስተካከል
ይገባል፡፡

28
16. የአየር ጉዞ ወቅት ለሚከሰት ጉዳት አጓጓዥ በ1999 በተደረሰው የሞንትሪያል ኮንቬንሽን መሠረት
ሃላፊ ቢሆንም ከላይ እንደተገለጸው በንግድ ሕጉ ያልተካተቱ በርከት ያሉ ክስተቶች ምክንያት
ከኃላፊነት ነጻ ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የየብስ ጉዞ በተመለከተ ሲ ኤም አር (CMR)በአንቀጽ
17(4) የተዘረዘሩት ሁኔታዎች አጓጓዥን ለሚደርስ ጉዳት ከኃላፊነት ነጻ ይሆናል፡፡

አማራጭ አንድ፡ የሚዘጋጀው የንግድ ሕግ በሞንትሪያል ኮንቬንሽን እና የየብስ አጓጓዥ በዓለም አቀፍ
ሲ ኤም አር (CMR) ኮንቬንሽን በአንቀጽ 17(4) የተዘረዘሩት ሁኔታዎች በማካተት
ሕጉን መቅረጽ፡፡ በጥናት ቡድኑ እምነት ይህን አማራጭ ቢሆን የሚል እምነት
አድሮበታል፡፡

አማራጭ ሁለት፡ የማጓጓዣ ህጋችን በዓለም አቀፍ ስምምነቶች ተቀባይነት ያገኘውን የአጓጓዦች
የኃላፊነት ወሰን ግልጽ ባልሆነ ምክንያት አልተቀበለውም ወይም ዕቃ ላይ አደጋ
የመድረሱ እድል በጣም አነስተኛ እየሆነ ስለመጣ ህጋችን ለአጓጓዦች በኮንቬንሽኖች
የተቀመጠውን ጥበቃ ሳያደርግላቸው ቀርቷል ብሎ በመገመት ሕጉ ምንም ለውጥ
ሳይደረግበት አሁን ባለበት ይቀጥል፡፡

17. ዕቃ ላኪው በሰጠው ተጨማሪ ትዕዛዝ ምክንያት በአጓጓዥ ላይ ያስከተለውን ወጪዎችን የየብስ ዕቃ
አጓጓዥ ላኪ እንዲተካለት የመጠየቅ መብት አለው፡፡ ይህ መብት ለአየር አጓጓዥም ስላልተሰጠው
ተስተካክሎ ወጥ በሆነ ሁኔታ ለሁሉም የአጓጓዥ ዘርፎች ሊሆን ይገባዋል፡፡
18. የየብስ አጓጓዥ ማስረከብ የማያስችል ሁኔታ ሲያጋጥመው ላኪው ወይም የማዘዝ መብት ያለውን
ሰው ጠይቆ በ30 ቀን ውስጥ መልስ ሳይሰጥ የቀረ እንደሆነ ወይም ዕቃው የሚበላሽ ወይም
የማስቀመጫው ዋጋ ከዕቃው ዋጋ በላይ ከሆነ አጓጓዥ ዕቃውን መሸጥ ይችላል፡፡ የአየር አጓጓዥ
ይህን በተመለከተ ምንም ያለው ነገር ስለሌለ የተመሳሰለ የሕግ አንቀጽ ሊኖረው ይገባል፡፡
19. በአጓጓዥ የሚዘጋጀውን የዕቃ ደረሰኝ በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ ተካትቶ አልተገኘም፡፡ ይሁንና
ኢትዮጵያ አባል የሆነችበት እ.አ.አ. በ1975 ዓ.ም. በጸደቀው የሞንትሪያል ፕሮቶኮል ቁጥር 4 ላይ
አጓጓዥ በኤልክትሮኒክ የሚዘጋጅ የዕቃ ደረሰኝ እንዲያዘጋጅ ፈቅዷል፡፡ በዚህ መሠረትም በአጓጓዥ
የሚዘጋጀው የኤሌክሮኒክ ደረሰኝ በሕግ ውስጥ ያልተካተተ ቢሆንም በፕሮቶኮሉ መሠረት በአየር
አጓጓዦች ተግባራዊ እየተደረገ ነው፡፡ ስለዚህ በሁሉም የማጓጓዣ አይነቶች ይህ የኤልክትሮኒክ
ቲኬት እንደፕሮቶኮሉ በኮድ ውስጥ ሊካተት ይገባዋል፡፡

29
20. የማጓጓዝ ሕግ በውስጡ ብዙ ቴክኒካል ቃላትና ዓረፍተ ነገሮችና ያካተተ በመሆኑ የሚቀረጸው
የንግድ ሕግ የትርጉም ክፍል ሊኖረው ይገባል፡፡ በማለት በአብይ ኮሚቴው ታይተው ውሳኔ
እንዲሰጣቸው፤ እና ነጥቦቹ በዝርዝር ሕግ ረቂቅ ውስጥ እንዲካተቱ እንዲታዘዝ ለውሳኔ ቀርቧል፡፡

በመድን ሕግ ላይ የቀረቡ ዋና ዋና
የማጠቃለያ ሀሳቦች
በአውሮፖ ቀደምት አገሮች የሕግ ፍልስፍና ሥርዓት የተደራጀው የመድን ሕግ የአገራችንን የመድን
አገልግሎት ፍልጎት ለመሸከምና ለማርካት አቅም አንሶት አያውቅም በእርግጥ ኢንዱስትሪው በህብረተሰቡ
ዘንድ በበቂ ሁኔታ ግንዛቤ ያልተወሰደበት በመሆኑ በሀገራችን በአጠቃላይ የምርት እድገት ያበረከተው
አስተዋፆ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡

በሕግ ምሁራንና በቅርብ ጊዜ የመድን ህጋቸውን ባዘመኑ ሀገሮች (ቱርክ፤ ቻይና) እንደተረጋገጠው የመድን
ሕግ መሰረታዊ መርሆች አደረጃጀትና አሠራር አብይ ለውጥ የሚያስፈልገው አይደለም፡፡ የመድን ሥራ
ወጥነትና አለማቀፋዊነት ይዘቱን ጠብቆ እንዲራመድ ለማድረግ በየወቅቱ የሚቀሰሙትን አዳዲስ ሀሳቦችና
አሰራሮች በሕጉ ማዕቀፍ ማካተትና ማደራጅት አስፈላጊ ይሆናል፡፡

ስለሆነም በጥናቱ ላይ በተጠቀሱት የፖሊሲ ሀሳቦች መሠረት የለውጥ ማሻሻያዎችን እንዲካተቱ በማድረግ
የመድን ሕጉ ምሉእነት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ለውሳኔና ለእይታ የቀረቡ የፖሊሲ ሀሳቦች ቀጥሎ
ተዘርዝሯል፡፡ በማጠቃለያ ሀሳቦች የቀረቡ የፖሊሲ ሀሳቦች በጥናቱ ውስጥ የተካተቱ በሙሉ ሳይሆን ዋና
ዋናዎቹ ብቻ ለውሳኔ ቀርበዋል፡፡

የፖሊሲ ሀሳብ አንድ

በፍትሐብሔር ሕግ ስለአስገዳጅ የውል አመሰራረት ድንጋጌዎች የጠመለከተው ቢኖር እማኞችን


በሚመለከት የተቀመጠው የሕግ ሁኔታ በመድህን ውል አመሰራረት ላይ ተፈፃሚነት እንዳይኖረው
ማድረግ፣ የእማኞች አስፈላጊነት አስገዳጅ እንዳይሆን ማድረግ ከሚከተሉት መሰረተሀሳቦች የመነጨ ነው፡-
1. ለመድህን ገቢው የሚሰጠው ፖሊሲ እማኞች በተገኙበት የሚዘጋጅ ሳይሆን በማይለወጥ ቅርጽና
አፃፃፍ በመድህን ሰጪዎች የሚቀርብ ሰነድ መሆን፤
2. የመድህን አሠራር እንዲሁም በኢንዱስትሪው በተለምዶ ተቀባይነት ያገኘው እማኞችን ከየቦታው
እየተጠሩ ለፊርማ ማቅረብ የማይቻል መሆኑ፤
3. በንግድ ሥራዎች ሕግ ሁልጊዜ ተቀባይነት ያገኘን አሠራር ተከትሎ መጓዝ ያለበት መሆኑ፤

30
4. በቀጥታ መድህን ውል አመሰራረት (primary Insurance) የእማኞች መገኘትና መፈረም በሕግ
የማይታለፍ እንኳን ቢሆን ይህ ሁኔታ በጠለፋ መድህን ዋስትና (Reinsurance) የማያስፈልግ
መሆን፤
5. በአንዳንድ ሀገሮች በተለይም በእንግሊዝ የመድህን ሥራ ውል በጽሁፍ ሳይሆን በቃል የሚፈጸም
መሆኑ፤
6. የመድህን አሠራርን የተቀላጠፈ ወጭና ጊዜ ቆጣቢ ከማድረግ አኳያ በውል አሰጣጥና እድሳት ላይ
እማኞችን በአካል እንዲቀርቡ ማድረግ ምክንያታዊነት የሌለው መሆኑ ናቸው፡፡

የፖሊሲ ሀሳብ ሁለት

የመድህን ገቢውን የመደራደር አቅም ለማገልበትና ጥቅሙንም ለመጠበቅ (policy holder protection)
በውል ምስረታ ጊዜና ውል ፀንቶ በሚቆይበት ወቅት የመድህን ሰጪውን ኃላፊነትና ግዴታዎች ይበልጥ
እንዲጨመር ማድረግ፡፡ የፍታሐብሔር ሕግ የውል ቃሎችና አፃፃፎች ተነባቢና ግልጽ መሆን እንዳለበት
የሚደነግግ ሲሆን በመድህን ሥራ ላይ የዋሉ ፖሊሲዎች አገላለጽ ግን ለመረዳት አስቸጋሪና ውስብስብነት
የሚታይባቸው እንደዚሁም በመድህን ሰጪው ብቻ የተቀረጹና ተክኒካዊ ቃሎች ከመሆናቸው የተነሳ
በመድህን ሰጪዎች ላይ ጠንከር ያሉ ግዴታዎች መጣል ተገቢ ይሆናል፡፡ በመድህን ሕጉ ከተገለጹት
ግዴታዎች በተጨማሪ የሚከተሉት ግዴታዎች እንዲጨመሩ ማድረግ፡-
1. በውል አመሰራረት ወቅትና በውሉ ዘመን ጊዜ መድህን ሰጪው ልዩ ጥንቃቄና ትኩረት ሊሰጥባቸው
የሚገቡ የውል ቅድመ ሁኔታ (Conditions/Warrants)፤ ሽፋን የሚሰጣቸው አደጋዎች ፤ የተገለሉ
አደጋዎች ወዘተ በማያሻማና በግልጽ መድህን ገቢውን የማስረዳት ግዴታን መደንገግ
2. ስለመድህን ሥራዎች የሽፋን አይነቶች ውል አመሰራረትና ካሳ ክፍያን በተመለከተ ከፍ ባለ ቅን
ልቦና (Utmost goodfaith) የማስረዳትና የማስገንዘብ በመድህን ሰጪው ላይ ግዴታን መደንገግ
3. በቃል አረዳድና ትርጉም እንዲዚሁም በውል አፈፃፀም አለመግበባቶች ቢከሰቱ የማስረዳት ሸክም
መድህን ሰጪው እንዲሸከም መደንገግ
4. መሰረታዊ እውቀት ከማስፈለጋቸው ጉዳዮች በቀር በመድህን እውቀት ላይ ተመስርተው የሚፈጠሩ
የውል ሁኔታዎችና አገላለፆች ሁሉ ኢትዮጵያ በዋናነት በምትጠቀምባቸው ዋና ዋና ቋንቋዎች
የተዘጋጁ የጽሁፍ መግለጫዎች (Brochures) መድህን ሰጪዎች ለመድህን ገቢዎች የመስጠት
ግዴታ እንዲጣልባቸው መደንገግ ናቸው፡፡

31
የፖሊሲ ሀሳብ ሦስት

ለአካል ጉዳትና ለህመም የሚሰጠው ሽፋን በመድህን ሕጉ በአንድ አንቀጽ ብቻ መደንገጉ


ከኢንዱስትሪውና ከሌሎች ሀገሮች አሠራርና ሕግ ጋር በመጣጣም ተገቢ ይሆናል፡፡ ለአካል ጉዳት
የሚሰጠው የመድህን ሽፋኖች አንዳንዶቹ የካሳ ባሕርይ ይዘት አላቸው አንዳንዶቹ ደግሞ ይህ ባሕርይ
የላቸውም የአካል ጉዳት ካሳ ሽፋን (Workmen compensation policy) በሥራ ቦታ በመደበኛ ሥራና
ከሥራው ጋር በተያያዘ ሁኔታ ለአካል ጉዳት አደጋዎች እንደዚሁም ለሞት የሚሰጥ መድህን ነው፡፡ በሌላ
በኩል በተለምዶ የአካል ጉዳት ፖሊሲ (personal Accident policy /group Accident policy) ተብሎ
የሚታወቀው የመድህን ሽፋን በሥራ ቦታም ሆነ ከሥራ ውጪ፤ ከሥራ ጋር ለተያያዘ እና ለአልተያያዘ
አደጋ የሚሰጥ የ24 ሰዓት ሽፋን ነው፡፡ ሽፋኖቹም በተጠናከረ መልክ በስታንዳርድ ፖሊሲ የተቀረጹና
በስፋት የሚሰራባቸው ናቸው፡፡ የሌሎች ሀገሮች ሕግና አሠራር እንዲሚያሳየው በተለይም በአደጋው
ምክንያት ለሚደርስ ሞት ለህይወት መድህን የተቀረጹት ድንጋጌዎች እንደ አስፈላጊነቱ (Mutatis-
Mutandis) ለዚህኛው እንዲያገለግሉ ተደርገው ሊቀረጹ ይገባል፡፡

የፖሊሲ ሀሳብ አራት

የኢትዮጵያ የመድህን ሕግ ቀጥታ መድንን (Primary Insurance) እንጅ ቀጥታ ያልሆነ የጠለፋ መድህን
ዋስትናን (Reinsurance Arrangemenet) በሚመለከት የሕግ ማዕቀፍ አያካትትም ወይም ሕግ
አውጪው በወቅቱ በዝምታ አልፎታል፡፡ የጠለፋ መድህን ዋስትና በሚመለከት በሚረቀቀው ሕግ ላይ
ማካተት ተገቢና ሊዘለል የማይገባ መሆኑን የሚከተሉት መሠረት ሀሳቦች ለግንዛቤ ሊወሰዱ ይቻላል

1. በብዙ ቢሊዮን ብር ወይም በሌሎች የገንዘብ ቀመሮች የሚተመኑ አብይት ስጋቶች (Mega
Risks) በአንድ ሀገር ውስጥ በሚገኙ የመድህን ድርጅቶች ካፒታል ብቻ ሊሽፍኑ አለመቻል
2. በዓለም አቀፍ የመድህን ሥራ የውስጥና የውጭ ኩባንያዎች አብይት ስጋቶችን በጋራ የመጋራት
ሕግ ልምድና አሠራር የዳበረ መሆኑ
3. በሀገር ውስጥ የመድህን ሰጪ ኩባንያዎች የካፒታል አቅማቸውን ቀስ በቀስ በሂደት እያጎለበቱ
እንዲሄዱና አብዛኛውን ስጋት በራሳቸው አቅም መያዝ እንዲችሉ የጠለፋ መድህን ዋስትና
ሰጪዎች የሽግግር ድልድይ ሆነው ማገልገል መቻላቸው፤
4. የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች የካፒታል አቅማቸው (Capital Adequacy) በእጅጉ ሲዳብር ከውጭ
ወደ ውስጥ የጠለፋ መድህን ሽፋን የመስጠት አቅም የሚፈጥሩ መሆኑ፤

32
5. በኢትዮጵያ ውስጥ የጠለፋ መድህን ሥራ የሚሰሩ መድህን ሰጪዎች በሕግ ማቋቋም ተገቢ
መሆኑ ናቸው፡፡

የፖሊሲ ሀሳብ አምስት

ለሞት የሚደረግ የህይወት ፖሊሲ (Life policy) በሟቹ ፍጹም ፍላጎትና ፈቃድ ላይ የተመሠረት ነው
ሟቹ በህይወት በነበረበት ወቅት ከሞተ በኋላ የፖሊሲው ተጠቃሚዎች እነማን ሊሆኑ እንደሚገባ አሳምሮ
ያውቃል ወይም አያውቅም ተብሎ አይገመትም በሌላ በኩል ደግሞ የህይወት ፖሊሲ ሊታዘዘለት (policy
to order) በሚል ሊሰራ ስለሚችል እንደሌሎች የገንዘብ ሰነዶች ተላላፊ ነው ከዚህ የተነሳ የፖሊሲው
የዝውውር ሂደት ካለአንዳች ገደብ ወይም ከልካይ ሁኔታ ጋር የተያያዘ አይደለም፡፡ ሟቹ የፖሊሲውን
ተጠቃሚዎች በግልጽ ቢሰየምም ቃሉን በመቃረን ፍርድ ቤቶች በግልጽ ያልተሰየሙ 3ኛ ወገኖች የጥቅም
ተካፋይ እንዲሆኑ ውሳኔ ይሰጣሉ ይህ ችግር በይበልጥ ጎልቶ የሚታይ ሲሆን በተቃራኒው ፍርድ ቤቶች
እንደሟቹ ቃል ውሳኔ ይሰጣሉ እነዚህ ሁለት አመለካከቶች በሕግ ምሁራንና ጠበቆችም ላይ
ይንጸባረቃሉ፡፡ ይህንን ክፍተት ለመታደግ ሕጉ ግልጽ እንዲሆን መደንገግ ተገቢ ይሆናል፡፡

ስለሆነም፡-

1. የሟቹን ቃል ለመጠበቅና የሕግ ውጤት እንዲኖረው ለማድረግ ፖሊሲው በተሰጠበት ወቅት በስም
የተጠቀሱ ተጠቃሚዎች የቅድሚያ መብት እንዲኖራቸው ተደርጎ መደንገግ ፤
2. በግልጽ የተሰየሙ ተጠቃሚዎች ባልተገለጸበት ሁኔታ ከሟቹ በሕግ የታወቀ መብትና ፋይናንሲያዊ
ጥቅም ያላቸው 3ኛ ወገኖች ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ መደንገግ፤
3. በሕግ የታወቀ መብትና ጥቅም አላቸው የሚባሉ በሕግ ከታወቀ መብት ወይም ከኢኮኖሚያዊ
ግንኙነት (Insurable interest) የተያያዘ መሆኑን መደንገግ

የፖሊሲ ሀሳብ ስድስት

በመደህን ሕግ አንቀጽ 687/1 ስለክስ አመራር የተደነገገው በራሱ ሕግ ውስጥ እንዲኖረው ማድረግ ተገቢ
ነው፡፡ ሕግ አውጪው ለመድህን ሰጪው የመዳረግ የሰጠውን መብት ያለተጨማሪ የፍትሐብሔር ሕግ
ስነ-ሥርዓት በቀጥታ በክሱ እንዲገባና እንዲከራከር የደነገገው የመድህን ሕግ ሲወጣ ለመድህን ዘርፍ
በሰጠው ልዩ ትኩረት መነሻ ያደረገ ነው ፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ የመድህን ክርክርን በሚመለከት
ተጨማሪ ሕግ መደንገግ አያስፈልገውም ነበር፡፡ ስለሆነም በመድህን ሕጉ የተደነገገው ሃሳብ ይበልጥ
ለማጠናከርና ውጤት እንዲኖረው ለማድረግ በሶስተኛ ወገኖች በሚቀርበው ክስ ውስጥ የመዳረግ መብት

33
መኖሩ በፍርድ ቤቶች እስከተረጋገጠ ድረስ መድህን ሰጪው እስከ ኃላፊነቱ ልክ በቀጥታ ክሱን መምራት
እንደሚችል መደንገግ ይገባል፡፡

የፖሊሲ ሀሳብ ሰባት

በመደህን አሠራር ካሳን ለመክፈል የሚቻለው መሰረታዊ የመድህን መርሆዎች ሲሟሉ ነው፡፡ የመድህን
ተጠቃሚ ለመሆን በቅድሚያ በሕግ የታወቀ ፋይናንሲያዊ ትቅም (Insurable interest) እንዲኖር ይገባል
ቀጥሎም በውል አመሰራረት ጊዜ የከፋ ያለ ቅን ልቦና (Utmost goodfaith) መኖሩን መረጋገጥ
ይኖርበታል፡፡ ቀጥሎ የሚመጣው መርህ የምክንያትና የውጤት ትስስር (Cause and Effect
relationship) እና የቅርበታዊ ምክንያት (proximate cause) ነው፡፡ የዚህኛው መርህ መረጋገጥ ካሳን
ለመክፈል ወይም ላለመክፈል ወሳኝነት ይኖረዋል በመደህን ህጋችን ይህን መርህ በሚመለከት የተደነገገ
ድንጋ የለም ወይም ሕግ አውጪው በዝምታ አልፎታል፡፡ ከዚህ የተነሳ ይህንን መርህ በተመለከተ የታየው
ክፍተት በሚረቀው ሕግ ሊካተት ይገባል፡፡ ጉዳት ያደረሰው ክስተት ጣሪያው (peri) አንድ ብቻ ከሆነና
ሽፋን ከተሰጠው መድህን ሰጪው ከኃላፊነት ጣሪያው ሳያልፍ በደረሰው ጉዳት ልክ ካሳ እንዲከፈል
ይገደዳል፡፡ ክስተቱ ሽፋን ያልተሰጠው ከሆነ መድህን ሰጪው ኃላፊነት የለበትም፡፡

ችግሩ የሚከሰተው ሽፋን የተሰጠውና ሽፋን ያልተሰጠው ክስተት በአንድ ላይ በጋራ (Concurrent
events) ወይም በተከታታይ (Subsquent events) ጉዳት ሲያደርሱ ነው፡፡ ለጉዳቱ መንስኤው የሆነው
የትኛው ክስተት ነው ተብሎ ሲጠየቅ እንደሁኔታው ካሳ እንዲከፈል ወይም እንዳይከፈል ሊደረግ
ይችላል፡፡ ከዚህኛው መርህ ጋር በተያያዘ ሀገሮች ምክንያትና የውጤት ትስስር እንዲሁም የቅርበታዊ
ምክንያ መርህ በህጋቸው ላይ አስፍረዋል፡፡ በፈረንሳይ ይህ መርህ በህጋቸው ያልተደነገገ ሲሆን የእንግሊዙ
ግን በተብራራ መልኩ የሚከተሉት ድንጋጌዎችን አስቀምጧል፡፡

1. በመድህን ውል በሌላ አኳኋን ካልተገለጸ በቀር መድህን ሰጪው ለደረሰው ጉዳት ካሳ ለመክፈል
የሚገደደው የደረሰውን ጉዳት በማይቀር ሁኔታ ለማስከተል የሚችል ጠንካራና ያልተቋረጠ
የምክንያትና የውጤት ትስስር ሲኖር ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም የውጤቱን መድረስ የማይቀር
ያደረገው ዋናው ምክንያት ለደረሰው ውጤት እንደቅርበታዊ ምክንያት ተቆጥሮ ይህ ምክንያት
የመድህን ሽፋን የተሰጠው ከሆነ መድህን ሰጪው ካሳ መክፈል ግዴታ አለበት፡፡
2. እላይ የተገለጸው ትስስር በሚከተሉት ምክንያቶች አይቋረጥም

34
ሀ/ ከደረሰው ጉዳት መንስኤ ጋር በተያያዘ መድህን ገቢው ወይም የመድህን ገቢው ሠራተኞች
የቸልተኝነት ተግባር፤
ለ/ የመድህን ሽፋን በተገባለት አደጋ (Insured peril) ምክንያትነት በመድረስ ላይ ያለን አደጋ
ውጤት ለመቀነስ ወይም ለማስቀረት የሚደረግ ከቅን ልቦና የመነጨ መድህን ገቢው
ሠራተኞች ወይም የአደጋ ሠራተኞች ተግባር፡፡
ሐ/ ለጣልቃ ገቡ የጉዳት መንስኤ ዋንኛና የማይቀር ምክንያት የሆነው የመድህን ሽፋን የተሰጠው
የቀደመው ምክንያት ሲሆን
3. ጣልቃ ገብ የሆነው ክስተት የመድህን ሽፋን የተሰጠው ከሆነና በተናጠልና ከቀድሞው ምክንያት
ጋር ባለተያያዘ ሁኔታ የደረሰውን ጉዳት ለማስከተል የሚችል ሲሆን ለአደጋው መድረስ
እንደቅርበታዊ ምክንያት ተቆጥሮ መደህን ሰጪው ካሳ እንዲከፍል ይገደዳል፡፡
4. ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ እራሳቸውን ችለው ውጤቱን ማድረስ የሚችሉና ለአደጋው
ቅርበታዊ ምክንያት የሆኑ መድህን ሽፋን የተሰጣቸውና የተገለሉ ምክንያቶች በተደራራቢነት
ጉዳት ያደረሱ ከሆነ እና የትኛው መንስኤ ለጉዳቱ ምን ያህል ድርሻ እንዳለው በግልጽ መለየት
የማይቻል ከሆነ ለደረሰው ውጤት ዋንኛ ምክንያት ተደርጎሊወሰድ የሚገባው ሽፋን ያልተሰጠው
ምክንያት ነው፡፡
5. ከላይ በተራ ቁጥር የተገለፀው ቢሆኖርም አንደኛው ምክንያት የመድህን ሽፋን የተሰጠው
ሌላኛው በፖሊሲው ያልተጠቀሰ (uninsured peril) ሲሆን ለደረሰው ውጤት እንደዋንኛ
ምክንያት የሚወሰደው ሽፋን የተሰጠው ምክንያት ነው፡፡
6. ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተጠቀሱት ምክንያቶች በተናጠል ውጤቱን ማድረስ የማይችሉ ሲሆኑና
ተመጋግበው ለጉዳት ምክንያት ከሆነ እንዲሁም በተናጠል ያደረሱትን ጉዳት ለመለየት ካልተቻለ
ሁሉም ምክንያቶች ለጉዳቱ እኩል አስተዋፆ እንዳደረጉ ተቆጥሮ ኃላፊነታቸው በዚሁ መሠረት
ይወሰናል፡፡
7. ከላይ በተራ ቁጥር አንድ የተገለጸው ቢኖርም ለጉዳቱ መንስኤ የሆነው ቅርበታዊ ምክንያት
ሊደርስ የቻለው ሆን ተብሎ በመድህን ገቢው ፤ በመድህን ገቢው የትዳር አጋር፤ ወንድም ወይም
እህት እንዲሁም ወደላይና ወደታች በሚቆጥር የስጋ ዘመዶች እና በመድህን ገቢው ሠራተኖች
ከሆነ መድህን ሰጪው ካሳ መክፈል ግዴታ አይኖርበትም፡፡
8. ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ድንጋዎች ውጪ በተለየ መልኩ ተዋዋይ ወገኖች የመስማማት
መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕግ ከላይ በዝርዝር የተጠቀሰውን የእንግሊዝን ሕግ
በመከተል ስለመርሁ ዝርዝር ድንጋጌ ቢያስቀምጥ ጠቀሜታው የጎላ ይሆናል፡፡

35
የፖሊሲ ሀሳብ ስምንት

በመደህን ሕግ የአደጋ ማስታወቂያ አለመስጠት የሕግ ውጤቱ ምን እንደሚሆን የተደነገገ ነገር የለም ሕጉ
አደጋ ሲደርስ መድህን ገቢው ከአቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር ወዲያውኑ ወይም በአምስት ቀናት የጊዜ
ገደብ ውስጥ ለመድህን ገቢው የማስታወቅ ግዴታ እንዳለበት ችግሩ የሚከሰተው መድህን ገቢው
መረጃውን ጭራሹኑ ያልተሰጠ ወይም ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ በላይ የዘገየ እንደሆነ መደህን ሰጪው ካሳ
የመክፈል ግዴታ አለበት ወይስ የለበትም የሚለው ነው፡፡

የግሪክ ሕግ የአምስት ቀናት፤ የቱርክ ሕግ ደግሞ አስር ቀናት ጊዜ ይሰጣሉ የጊዜ ገደቡ ሲያበቃ የግሪኩ
ሕግ መድህን ሰጪውን ከኃላፊነት ነፃ ያደርጋል፡፡ የቱርክ ሕግ ግን በቸልተኝነት የተፈፀመ መዘግየት
ምክንያት ከሚከፈለው ካሳ ላይ እንደሁኔታው ሲባል የቸልተኝነቱ ከባድነትና ቀላልነት ግምት ውስጥ
ይገባል ማለት ነው፡፡ በቱርክ ሕግ መዘግየት የተባለው በምን ያህል ጊዜ እንደሚገለጽ አልተደነገገም፡፡
ለኢትዮጵያ የሁለቱንም ሀሳቦች በመቀየጥ ክፍቱን መሙላት ይቻላል የሚል ግምት ሊወሰድ ይችላል፡፡

ስለሆነም፡-

1. በመድህን ህጋችን የተቀመጠውን የጊዜ ገደብ ወደ አስር ቀናት ከፍ ማድረግ፤


2. የመዘግየት ጊዜ ከአምስት ቀናት እንዳይበልጥ በማድረግ የወጪ መጋራት ስልትን ተግባራዊ
ማድረግ፤
3. መድህን ገቢውና መድህን ሰጪው የአደጋ ማስታወቂያ የጊዜ ገደብን በሚመለከት በስምምነት
ሊወስኑ ይችላሉ፤
4. በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱት ጊዜያት ሲያበቁ መድህን ሰጪውን ከማንኛውም ኃላፊነት ነጻ
ማድረግና ውሉን መቋረጥ እንደሚችል መደንገግ፤

የፖሊሲ ሀሳብ ዘጠኝ

በሌሎች ሀገሮች (ፈረንረሳይ፣ ጀርመን፣ ቱርክ፣ ቻይና) እንደታየው የመድን ሕግ እራሱን በቻለ መጸሐፍ
መደራጀት ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም ሕጉ ከማጓጓዝ ሕግ መለየት እንዳለበት የጥናቱ ቡድኑ ያምናል፡፡

36
መጽሐፍ አራት
ስለባንክ ሥራዎች
የፖሊሲ ውሳኔ የሚያሻቸው ጉዳዮች

1. ስለባንኮች አቋቋም

በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ ሃገራት እንደሚታየው ባንኮች በተለያዩ የድርጅት አይነቶች እየተቋቋሙ ይገኛሉ፤
ለወደፊቱም የሃገራችን ባንኮች በዚህ መንገድ መራመድ ቢያስፈልጋቸው ለመቀየር እንዲችሉ በአክሲዮን
ማኅበር ብቻ ይቋቋሙ ተብሎ በሕግ መዘጋቱ ቀርቶ ባንኮች በማንኛውም ዓይነት የድርጅት ቅርጽ ብሎም
በግል ኃብት ሊደራጁ የሚችሉበት መርሕ ቢቀመጥ፤ ነገር ግን ተቆጣጣሪው አካል እንደወቅቱ አግባብነትና
እንደዘርፉ ዝግጁነት ባንኮች በምን አግባብ መደራጀት እንደሚኖርባቸው የሚፈቅድበት መንገድ ክፍት
ቢደረግ፡፡

2. ስለገጠር ባንኮች

ባንኮች ተደራሽ ባልሆኑባቸው አካባቢዎች እንዲሁም ዝቅተኛ የሕብረተሰብ ክፍሎች የባንክ አቅርቦት
ተደራሽ እንዲሆን ከብድርና ቁጠባ ህብረት ሥራ ማሕበራት ባለፈ ከመደበኛው የባንክ አወቃቀር ለየት ያሉ
እንደ ህብረት ሥራ ባንኮች ያሉ የባንክ አይነቶች የሚቋቋሙበትና የሚተዳደሩበት የሕግ ማዕቀፍ አስፈላጊ
በመሆኑ የንግድ ሕጉ የባንክ ክፍል ለነዚህ የባንክ አይነቶች የሕግ መሠረት ሊጥል ይገባል፡፡

3. የባንኮች በሥራ የሙያ ዘርፍ ስለ መከፋፈል

ባንኮች በኢንቨስትመንት፣ በልማት፣ በንግድ ወዘተ የባንክ አገልግሎት የሙያ ዘርፎች ላይ መሰማራተቸው
በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል ከመፍጠርና ባልተከፋፈለ ሃሳብ በዘርፉ ጥራት ያለው አገልግሎትን
እንዲሰጡ ያግዛል፤ ስለሆነም ባንኮች በሙያ ዘርፍ ተከፋፍለው እንዲቋቋሙ ቢወሰን ጠቃሚ ነው፤ ባንኮች
በአንድ የሙያ ዘርፍ ሲሰማሩ ብቁ የሰው ኃይልና ዝግጁነት እንዲኖራቸው ብሎም ባንኮች ከተሰማሩበት
የሙያ ዘርፍ ውጪ እንዳይሰማሩ ውሳኔው እንዳያግድ ለማድረግ ተቆጣጣሪው አካል በየሙያ ዘርፉ
የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች እንዲደነግግ ቢወሰንና አንድ ባንክ ከተቋቋመበት የሙያ ዘርፍ ውጪ
ለመሰማራት ቢፈልግ የሚያስፈልጉት መስፈርቶች ተቆጣጣሪው አካል እንዲደነግግ ቢወሰን፡፡

37
4. ገንዘብን በአደራ ስለማስቀመጥ

 ማየት የማይችሉ፣ አካል ጉዳተኞች (የእጅ ጉዳት ያለባቸው ሰዎች) እንዲሁም ማንበብና መጻፍ
የማይችሉ ሰዎች የተቀማጭ ውል ሲዋዋሉ በሰነዶች ማረጋገጫ ወይም ፍርድ ቤት ቀርበው
ማድረግ የማይጠበቅባቸው ይጠበቅባቸዋል የሚለው ድንጋጌ የባንክ ሥራ ቅልጥፍናን የሚጠይቅ
በመሆኑ ተገልጋዩ በፍጥነት አገልግሎቱን እንዲያገኝ ከማስቻል አንጻር አሉታዊ ተጽዕኖን
የሚያስከትል በመሆኑ በውል አዋዋይ ፊት መፈረም ሳያስፈልግ ያባንክ አገልግሎቱ በሚሰጥበት
ወቅት በአንድ ምስክር ፊት እንዲደረግ ቢወሰን፤
 የኦቨር ድራፍት አገልግሎት በዘመናዊ የባንክ አሠራርም ሆነ አሁን በሃገራችን በሚሰጠው የባንክ
አገልግሎት እየተሰራበት የሚገኝ ነው፤ ይህ አገልግሎት ባንኮች አዋጭነቱን ፈትሸው መስጠት
አለመስጠታቸውን እንዲወስኑ ሊፈቀድ የሚገባው በመሆኑ የኦቨር ድራፍት አገልግሎት እንዳይሰጥ
በንግድ ሕጉ የተሰተው ክልከላ እንዲነሳ ቢወሰን፤

ትረስት አካውንት

አንድ ሒሳብ ለሌላ ሰው ጥቅም ተብሎ ሲከፈት ንብረትን ማሸሽን፣ ግልጽ ያልሆኑ የመብት ጥያቄዎችን
ለማስቀረት ሲባል ትረስት አካውንት ለተከፈተለት ሰው ጥቅም ይውል ዘንድ ወይም ሂሳቡ የተጠቃሚው
ነው ለማለት ያስችለን ዘንድ ሂሳቡን የከፈተው ሰው ግልጽ ስምምነት ያስፈልጋል በሚል ቢወሰን፤ ነገር ግን
ሂሳቡን የከፈተው ሰው ሲሞት የተከፈተለት ሰው ባለቤት እንደሚሆን ቢወሰን፤

የታዳጊ ወጣቶች ቁጠባ

በአሁኑ ወቅት ባንኮች ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት እስከ 18 ዓመት ለሆኑ ታዳጊ ወጣቶች የቁጠባ ሒሳብ
አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፤ በዚህም ተጠቃሚዎች ማፍራቱ ይታወቃል፤ ነገር ግን የባንክ አገልግሎት
በውል ላይ የተመሰለተ እንደመሆኑ ለባንክ ውሎች ዓላማ ሲባል የመዋዋል ዕድሜ ከ14 ዓመት
እንደሚጀምር ቢወሰን፤ በተጨማሪም ታዳጊ ወጣቶች ከባንክ ውጪ ላሉ ውሎች በአጠቃላይ የውል ሕግ
መገዛታቸው እንዳለ የሚቆይ ስለሚሆን ኤሌክትሮኒክ ክፍያ እንዲፈጽሙ ወይም ኤሌክትሮኒክ የባንክ
አገልግሎትን በመጠቀም ውል እንዳይፈጽሙ ቢወሰን፤

38
5. ስለሒሳብ መዘጋት

በአሁኑ ሰዓት ሒሳብ መቼ ይዘጋል ውጤቱስ ምን ይሆናል የሚለው አጨቃጫቂና የሕግ መሠረት የሌለው
በመሆኑ ይህን የሚመለከት ድንጋጌ በንግድ ሕጉ ውስጥ ሊካተት የሚገባ ሲሆን አንድ ሰው በመሞቱ
ወይም ችሎታ በማጣቱ ብቻ ሒሳብ ሊዘጋ እንደማይገባ ቢወሰን፤

6. የባንክ የሒሳብ መግለጫን ስለመስጠት

የባንክ የሒሳብ መግለጫን ለደንበኞች ሁሉ በዓመት ቢያንስ አንዴ እንዲሰጥ በሕግ መደንገጉ ከአሠራርም
ከጥቅምም አንጻር ውጤታማ ስለማይሆን ደንበኞች በጠየቁ ጊዜ የሒሳብ መግለጫው እንዲሰጣቸው
ቢደነገግ፤ በተጨማሪም የሚሰጠው የሒሳብ መግለጫ ላይ ቅሬታ ያለበት ሰው ቅሬታውን ማሰማት
የሚችልበት ዝቅተኛው የጊዜ ገደብ በሕጉ ቢደነገግና በተባለው ጊዜ ውስጥ ባያመለክት መብቱን
እንደሚያጣ እንዲገለጽ ቢወሰን፤

7. ገንዘብን ስለማስተላለፍ

 የንግድ ሕጋችን በዋናነት አለማቀፍ የገንዘብ ዝውውርን ሙሉ ለሙሉ የተወው በመሆኑ ሕጉን
ወደፊት ተራማጅ ለማድረግና ይህን አገልግሎት የሕግ መሠረት እንዲኖረው ለማድረግ ዝርዝር
ድንጋጌዎችን እንዲይዝ ቢወሰን፤
 ገንዘብ የተላከለት ሰው ገንዘቡን ቀርቦ እንዲወስድ በሚጠበቅበት የጊዜ ገደብ ያልወሰደ እንደሆነ
የገንዘቡ ዕጣ ፋንታ ምን ይሆናል የሚለውን ሕጉ በዝምታ ያለፈው በመሆኑ ይሕ ገንዘብ ከተወሰነ
የጊዜ ገደብ ቡሃላ ለመንግሥት ገቢ እንዲሆን ቢወሰን፤
 ከሒሳብ ወደ ሒሳብ ገንዘብ በሚተላለፍበት ጊዜ ተቀባዩ ባለገንዘብ የሚሆነው ከላኪው ሒሳብ
ወጪ ሲሆን ነው የሚለው ድንጋጌ ከሒሳብ ሥራ ሥርዓት ጋር አብሮ ስለማይሄድ በማንኛውም
ሁኔታ ይህ ገንዘብ የተላከለት ሰው ሒሳብ ውስጥ ሲገባ ባለገንዘብ እንደሚሆን ቢወሰን፤ ከዛ በፊት
ባለው ጊዜ ላኪው ትዕዛዙን ሊሰርዝ እንደሚችል ቢወሰን፤
 የተላከው ገንዘብ በእጅ የሚሰጥ እንደሆነ የተላከለት ሰው ባለገንዘብ የሚሆነው በተላከ በተወሰነ
ጊዜ ውስጥ እንደሆነ ቢደነገግ፤ በዚህም ጊዜ ላኪው ትዕዛዙን ሊሰርዝ እንደሚችል ቢወሰን፤

39
8. ሰነዶችን በአደራ ስለማስቀመጥ

ሰነዶችን በአደራ ማስቀመጥ እንደ አንድ የባንክ ሥራ ሆኖ መቀመጡ ለባንኮች እንደ ሥራ መስክ ክፍት
ተደርጎ ሊቀመጥ የሚገባ ከመሆኑ ባሻገር ሰነዶች/securities የሚባሉት እነማንን እንደሚያካትት
ተተርጉሞና በአደራ የተቀበሏቸው ሰነዶች ላይ የሚኖራቸው መብት እስከምን ድረስ እንደሆነ ተገልጾ
መዳበር ይኖርበታል የሚል ውሳኔ ቢሰጥ ሚመረጥ ነው፤ ነገር ግን ሰነዶች በገበያ ውስጥ ገብተው
ሊንቀሳቀሱ ስለሚገባ በባንክ መቀመጣቸው አጠቃላይ ኢኮኖሚውን የማያግዝ በመሆኑ ብሎም ባንኮች
ሰነዶችን በአደራ ከማስቀመጥ ይልቅ በሰነዶች የመገበያየት/dealing in securities ሥራ ውስጥ ቢሰማሩ
የሚመረጥ ስለሚሆን በንግድ ሕጉ ያለው ሰነዶችን በአደራ የማስቀመጥ አገልግሎት የሕግ ሽፋን ሊሰጠው
አይገባም የሚል ሃሳብ በቡድኑ ተነስቶ ያወያየ ስለሆነ ውሳኔ ሰጪው ከግምት ቢያስገባው፡፡

9. ስለካዝና ኪራይ

 በኪራይ የተያዘ ካዝና ተከፍቶ ከካዝናው የሚወጣው ዕቃ ለኪራይ ዋጋ አፈጻጸም እንዲውል ፍርድ
ቤት ቀርቦ ማመልከት በፍርድ ቤቱም ሆነ በባንኩ ላይ ወጪን የሚያስከትል ስለሆነ ባንኩ ሌሎች
የመያዣ ንብረቶችን በሚያሸጥበት ሂደት እራሱ እንዲሸጥ ቢወሰን፤ በአንጻሩ ግን ባንኮች ለደንበኛው
ጥቅም የተሸለ ዋጋን ላያስገኝለት ስለሚችል በፍርድ ቤት እንዲያሸጥ የሚለው አሠራር ይቀጥል
የሚለው ሃሳብ ስላወያየ ውሳኔ ሰጪው ይህንን ከግምት ቢያስገባው፤
 በካዝናው ውስጥ የተገኙ የካዝናው ተከራይ ዕቃዎች በዋጋ ሊተመን፣ ሊሸጥ ወይም ሊለወጥ
የማይችል እንደሆነ መጨረሻው ምን ይሁን የሚለውም እንዲሁ ውሳኔ ወደመንግሥት ለሚመለከተው
አካል ጥቅም ላይ እንዲውሉ ወይም በመንግሥት እንዲወገዱ ገቢ የሚደረግበት አሠራር ቢፈቀድ፣
 ባንኩ አግባብ ባለው አካል ሲታዘዝ ወይም ለባንኩ ደህንነት የሚያሰጋ ዕቃ ተቀምጧል ብሎ ሲያምን
ከካዝናው ተከራይ ፈቃድ ውጪ በራሱ ካዝናውን ሊከፍት የሚችልበት ልዩ ሁኔታ በሕጉ ውስጥ
እንዲካተት ቢወሰን፡፡

10. በሰነድ ስለሚሰጡ ብድሮች

ዶክመንተሪ ክሬዲት በተመለከተ የንግድ ሕጉ ወደኋላ የቀረ በመሆኑ አሁን ካለው የዓለም አቀፍ ሰነድ ጋር
በሚስማማ መልኩ መስተካከል አለበት፡፡ ይሁንና ይህ ሕግ በየጊዜው ቢያንስ በአስር ዓመት አንዴ
ማስተካከያ ይደረግበታል፡፡ ስለሆነም ይህን ሕግ በብሔራዊ ባንክ መመሪያ ውስጥ አካቶ ማውጣት አንድ
አማራጭ ነው፤ ዶክመንተሪ ክሬዲትን በተመለከተ ዩኒፎርም ከስተመሪ ፕራክቲስ እና በየጊዜው

40
የሚደረገው ማሻሻያ እንዲሁ የኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አካል ሆነው ይቀጥሉ የሚለው ሌላ አማራጭ ነው፣
የንግድ ሕግን በየጊዜው ከማሻሻል ይህ ከስተመሪ ፕራክቲስ በብሔራዊ ባንክ መመርያ ገብቶ እንዲካተት
ንግድ ሕጉ እንዲያመላክት ቢወሰን፡፡

11. የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ጥበቃ

የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ጥበቃ በሕጉ አንቀጾች ውስጥ ጎልቶ ሊንጸባረቅ የሚገባ ሲሆን በሕጉ
ውስጥ የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ጥበቃ ጉዳይን የማየትና መብታቸውንም በማስፈጸም ረገድ
አንድ አካል ሊኖር ይገባል፤ ስለሆነም አዲስ አካል ማቋቋም ሳያስፈልግ የባንኮች ተቆጣጣሪ አካል /በአሁኑ
ሰዓት ብሔራዊ ባንክ/ ይህንን ኃላፊነት እንዲወስድና ተገቢውን መዋቅር እንዲያዋቅር ቢወሰን፤

12. የኤሌክትሮኒክ ባንክ አሠራር

የባንክ አሠራርን ዘመናዊነት ለማላበስ እንዲያስችል የሚሻሻለው የንግድ ሕግ የኤሌክትሮኒክ የባንክ


አሠራርን በማያግድ መልኩ ሊቀመጥ ይገባል፤ በተጨማሪም ኤሌክትሮኒክ የባንክ አገልግሎት ደንበኞች
ለየት ባለ መልኩ ጥበቃ ሊደረግላቸው የሚገባ ሲሆን በባንኩም በደንበኛውም ጥፋት ሳይሆን ደንበኛው
ገንዘቡ ቢጠፋ ወይም ቢሰረቅ ባንኩ ሃላፊነቱን እንዲሸከም ቢደረግ ለዘርፉ እደገትና ተጠቃሚው በዘርፉ
ያለውን መተማመን እንዲያዳብር ስለሚረዳ በዚህ መልኩ ቢወሰን፡፡

ስለተላላፊ የገንዘብ ሰነዶች

1. ስለሸቀጦች ማረጋገጫ

የሸቀጦች ማረጋገጫ ሰነድ ሁለት ገጽታዎች አሉት አንደኛው በባለመጋዘኑና በባለ ሸቀጦቹ መካከል ያለው
ውል (ፍትሐብሔር) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከባለመጋዘኑ የሚወጣው የማረጋገጫ ሰነድ ያየዘው ሰው
ሰነዱ ባዘለው የገንዘብ ዋጋ መጠን ከሦስተኛው ወገኖች ጋር የሚያደርጋቸው ውሎች በተመለከተ ያለው
ገጽታ ነው በመሆኑ የንግድ ሕጉ የሸቀጦች ማረገጋገጫ ሰነዶችን በተመለከተ ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶች
መሆናቸውን ካስቀመጠ በኋላ በሸቀጥ አስቀማጩና በባለሸቀጡ መካከል የሚኖረው የአደራ ውል
በተመለከተ የፍትሐብሔር ሕጉ አግባብ ያላቸው ደንጋጌዎች ተፈፃሚነት የሚኖራቸው እንደሚሆን
በተላላፊነቱ ግን በንግድ ሕጉ ተካትቶ እንደሌሎች ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶች በዝርዝር እንዲደነግግ
ቢወሰን፡፡

41
2. ስለቅን ልቦና የሕግ ግምት

 ተላላፊ የገንዘብ ሰነድ ገንዘብ ተክቶ የሚሰራ እከሆነ ድረስ ሰነዱን በእጁ ያደረገ ማንኛውም ሰው
ተቃራኒ ማስረጃ እስካልቀረበበት በቅን ልቦና ሰነዱን እንዳገኘው የሚቆጠር በመሆኑ የንግድ ሕጉ
ግን ከዚህ መሰረታዊ መርህ በሚቃረን መንገድ በአንቀጽ 716(1) ሥር ሰነድ ያያዘ ሰው ሕጋዊ
ይዞታ (ባለቤትነት) ያለው መሆኑ ያረጋገጠ እንደሆነ ነው የሚለው ድንጋጌ እንዲቀር ቢወሰን፤
 አንድ ተላላፊ ሰነድ ተቀባይ ከማይሆንባቸው ምክንያቶች አንዱ በአምጭውና በተቀባዩ መካከል
ያሉት የግል ግንኙነቶች መፍረስ እንደሆነ መደንገጉ በሕጉ አንቀጽ 752 የተዋዋዩቹ የግል
ግንኙነቶች እንደ መከላከያ (መቃወሚያ) ሊነሱ እንደማይችሉ ከሚደነግገው ሕግ ጋር
ስለሚቃረን የገንዘብ ሰነድን የሚረካከቡ ነጋዴዎች በመካከላቸው ገንዘብ ነክ የሆነ የውል
ግዴታዎች መኖራቸውን ሕጉ ቢገምትም የሰነዱ ተቀባይነት ግን ካለምንም ቅድመ ሁኔታና
ካለአንዳች ሐተታ እንደቀረቡ ክፍያ የሚፈፀምት መሆኑን ሕጋችን በግልጽ እንዲቀመጥ
ቢወሰን፡፡
 በስም የሆነ ሰነድን በእጁ የያዘ ሰው ተጠቃሚ ለመሆኑ በሰነዱ ላይና በአውጭው መዝገብ መፃፍ
በሰነዱም ላይ የተናገረው ግዴታና መብት ያለው ለመሆኑ ማረጋገጫ ይሆናል ይላል፡፡ ተከፋዩ
በሰነዱ ላይ ስሙ እስከሰፈረና ማንነቱን የሚያረጋግጥ መታወቂያ እስከያዘ ድረስ በአውጪው
መዝገብ ውስጥ መፃፍ የገንዘብ ሰነዶች መተላለፍን አያፋጥንም፤ ይህም አውጪው የተከፋዩን
(የተጠቃሚውን) ስም መዝገቡ ውስጥ ላይሰፍር ስለሚችል እና ቢያሰፍርም ስሙ በተላላፊ ሰነዱ
ላይ መገኘቱ በራሱ በቂ ማረጋገጫ ስለሚሆን ነው፡፡ አውጭው በሚያስተላልፈው የገንዘብ ሰነድ
ላይ የሚያሰፍራቸውን የክፍያ ትእዛዝ መግለጫዎች ሁሉ በመዝገቡ ውስጥ ማስፈር
እንደሚጠበቅበት ሕጉ ይደነገጋል፡፡ ከፍ ሲል በጠቀስነው ምክንያት ግን ይህ አሠራር ለተላላፊ
ሰነዶች ፈጣን ዝውውር ከምቹነት ይልቅ እንቅፋትን የሚፈጥር በመሆኑ ከሕጉ ማስወጣት
ያስፈልጋል፡፡

3. ስለተበላሹ፣ ስለወደሙ፣ ስለጠፋ ወይም ስለተሰረቁ ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶች

ሕጉ በአንቀጽ 731 ሥር የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች በተበላሹ፣ በወደሙ፣ በጠፉ ወይም በተሰረቁ ጊዜ
ሊከተሏቸው የሚያስፈልጉ ሥርዓቶች በሕግ ይወሰናሉ ሲል ቢደነግግም እስካሁን በሕግ ሳይሰፈኑ
ቀርተዋል፤

ለአብነቱ ያህል በUCC አንቀጽ 3-309 እንደሚከተለው እንዲደነገግ ቢወሰን፤

42
ሰነዱን በአግባብ ለሌላ ሰው በማስተላለፍ ካልሆ በቀር በመጥፋት፣ በመውደም በብልሽት፣ ከእጁ
የጠፋበት ሰው በሰነዱ ላይ ያለውን መብት በሕግ ወይም በፍ/ቤት ትእዛዝ ለማስፈፀም የሚችለው
የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲሟሉ ነው፡፡

1. ሰነዱ በእጅ የነበረውና በወቅቱ (ሰነድ በጠፋበት፣ በተሰረቀበት፣ በተበላሸበት፣ ወይም የወደመበት
ወቅት በሰነዱ ተጠቃሚ (ተከፋፋይ የመሆን መብት ጥርጥር ያልነበረው ሲሆን፤
2. ሰነዱ ከእጅ የተወጣው በሕጋዊ ማስተላለፍ ምክንያት ካልሆነ፤
3. ተላላፊ ሰነዱ በመውደሙ፣ የትና በማን እንደተወሰደ ባለመታወቁ፤ በማይታወቅ ሰው እጅ
በመግባቱ ወይም ሊገኝ በማይችል ሰው እጅ በመግባቱ ምክንት አስፈላጊና በቂ ጥረት ቢደረግም
እንኳን ሊገኝ የማይችል መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ፤

እነዚህ አማራጮች እንደመነሻ ያህል ሊያገለግሉን የሚችሉ ሲሆን ሌሎችንም ሕጎች በማስመልከት
ሕጉን ማሟላት ይቻላል፡፡

4. ስለተላላፊ የገንዘብ ሰነዶችና ሌሎች ውሎች

በሕጉ አንቀጽ 717 እና 752 መካከል ቅራኔ ያለ ይመስላል “በዕዳ ከፋዩና ሰነዱን በያዘው ሰው መካከል
የሚኖሩ የውል (የግል) ግንኙነቶች እንደ አንድ መቃወሚያ ሊቀርቡ ይችላሉ” (አንቀጽ 717) በሌላ በኩል
ደግሞ በኋላው ወረቀት መሠረት እንዲከፍሉ የተጠየቁት ሰዎች ከአውጪው ወይም ከበፊተኞቹ
አውጪዎች ጋር ባላቸው የግል (የውል) ግንኙነቶች ምክንያት በአምጭው ላይ መቃወሚያ ሊነሳ
አይቻልም፡፡ (አንቀጽ 752 ሕጉ አንድ አቋም ሊወሰድ ይገባል፤ ይኸውም ተላላፊ ሰነድ በተዘጋጀበት ጊዜ
ወይም ከመዘጋጀቱ ቀደም ብሎ በባለዕዳውና በባለመብቱ መካከል የሚደረጉ ውሎች ከገንዘብ ሰነዱ ጋር
ግንኙነት እንደማይኖራቸው በመግለጽ ሊቀመጥ ይገባል፤ ሆኖም ሰነዱ (በሰነዱ ላይ የተገለጸው በግዴታ
በሌላ ውል ላይ የሚመሠረት ወይም የውል ስምምነቱን ያመነጨው ግብይት አካል መሆኑ ተዋዋዮቹ
ተስማምተው የነበረ ከሆነ በዚያ ውል ምክንት ሰነዱ ሊሻሻል፣ በሌላ ሊተካ ወይም ሊሰረዝ ይችላል፡፡
በዚህ ዓይነት መንገድ ሕጉ የተሟላ እንዲሆን ቢወሰን፤

5. በጀርባ መፈረም ስለሚሰጠው ዋስትና

የጀርባ ፊርማ (Endorsement) በሐዋላ ወረቀት ወይም በሌሎች ተላላፊ ሰነዶች የሚገኙትን መብቶች
ሁሉ ያስተላልፋል፡፡ ሰነድን የሚቀበለው ሰው ወረቀቱን ለባንክ ወይም ለሌላ ሦስተኛ ሰው በማቅረብ
ክፍያውን እንደሚያገኝ በጀርባ የሚፈረመው ሰው ዋስ ነው፤ ሆኖም ዝቅ ብሎ በአንቀጽ 750 (1) “ሥር

43
ተቃራኒ ውል” ካለ ይህ ዋስትና ዋጋ ሊያጣ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ ድንጋጌው የተላላፊ ሰነዶችን
አስተማማኝ ዝውውር የሚጎዳ ነው፡፡ በጀርባ የሚጽፈው ሰው አላፊነት በሌላ ሁኔታ ላይ የማይመሰርት
(Unconditional) እና በሌላ ውል የማይጣስ ስለሆነ ሕጉ ይህን አቋም ማንጸባረቅ ይገባዋል፡፡ የጀርባ
ፊርማ ውጤትን በተመለከተ የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ ንግድ ኮሚሽን (UNCITRAL) ያወጣው
የሕግ ረቂቅ ማገናዘብ ይጠቅማል፡፡

6. እሽታ (Acceptance)

በሕጋችን ውስጥ ከፊል እሽታ በግልጽ የተከለከለ ቢሆንም ከፋዩ በከፊል ሊከፍል እንደሚችል ደግሞ
በመደንገግ አደናጋሪ የሆነ አንቀጽን ይዟል፤ በተጨማሪም የአንሲትራል ኮንቬንሽን በዚህ ረገድ ከፊል
እሽታን የሚፈቅድ ድንጋጌ አለው፤ ይህ መብት ሊከለከል የሚገባበት ዓላማም ግልጽ ስላልሆነ መርሁ
እንዲፈቀድ ቢወሰን፤

7. እንቢታ ስለቀረበበት ሰነድ

ሕጉ አንድ ሰነድ እንቢታ የተሰጠበት (dishonored) ነው የሚባለው ምን ሲሆን ነው በሚለው ነጥብ


ዙሪያ በአንቀጽ 780 ሥር በአጭሩ ያስቀምጥና ከአንቀጽ 781-810 ባሉት አንቀጾች ሥር ግን በአብዛኛው
እንቢታውን ተከትሎ አምጭው ማድረግ ስለሚኖርበት የአፈፃፀም ሂደት በስፋት ይደነግጋል፡፡ እነዚህ
ድንጋጌዎች የአምጭውን መብት ከማስጠበቅ አንጻር ጉዳዩን የሚያወሳስቡና ነጋዴዎች በተላላፊ ሰነዶች
እንዳይጠቀሙ እንቅፋት ሊፈጥሩ የሚችሉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የእኛ ሕግ በእንቢታ ጊዜ ጉዳዩ በመንገስታዊ
(መዝጋቢው) አካል ፊት መፈረምና መመዝገብ ስለሚኖርባቸው ጉዳዮች ይዘረዝራል እንደነዚህ ሰነድ ቀላል
የመገበያያ መሳሪያ መሆን እንደሚገባው ከሚገልጸው መርህ ጋር አይጣጣምም፡፡ ስለዚህ ይህ መርሕ
በUCC እና UNCITRAL ድንጋጌዎች መሠረት እንዲቀረጽ ቢወሰን፡፡

8. ስለ ቼክ

 ቼክ በባክ ብቻ መከፈሉ ቀርቶ ቼክን የሚከፍሉ የፋይናንስ ተቋማት ቼክ እንዲከፍሉ ቢወሰን፤


 ፖስት ዳትድ ቼክ በሃገራችን ይፈቀድ ወይስ ይከልከል የሚለው አነጋጋሪ ነጥብ ነው፤ በአንዳንድ
ሃገራት ይህ ዓይነት ቼክ የተፈቀደ ሲሆን ከክፍያ መሳሪያነት አልፎ የመተማመኛ ሰነድም ሆኖ
ማገልገሉ በጎ ጎን ነው ሊቀጥል ይገባል የሚሉ አስተያየቶች ተገልጸዋል፤ በተቃራኒው ደግሞ ይህ
አሠራር የቼክን ባሕርይ የሚቀይርና የቼክን የክፍያ መሳሪያነት የሚቀንስ በመሆኑ ሊቀር ይገባል

44
የሚለው ሃሳብ ተነስቷል፤ ስለዚህ ቼክ ካለው ባሕሪና በንግዱ ውስጥ ሊኖረው ከሚገባው ሚና
አንጻር ታይቶ ውሳኔ ሊሰጥ ይገባል፤
 የቼክ መክፈያ ጊዜ የለዘመ በመሆኑ የቼክን ባሕሪ አደጋ ላይ የሚጥል ስለሆነ ቼክን ለክፍያ
የማቅረብ ጊዜ አንድ ወር እንደሆነ ቢወሰን፤
 የውጪ ሃገር ቼኮች በንግድ ሕጉ ውስጥ እውቅና እንዲሰጣቸው ቢወሰን፤
 ቼክን በተፈለገው ገዜ ማቆም ቼክን ባሕሪ የሚያዛባ ስለሆነ አንድ ሰው ቼክ እንዳይከፍል ለማቆም
በቂ ምክንያት እንዲያቀርብ ቢወሰን፤ በተጨማሪም ወንጀልን ለመከላከል ሲባል አንድ ሰው የክፍያ
ማቆም ተቀባይነት የሚኖረው በሂሳቡ ውስጥ በቂ ስንቅ ሲኖረው እንደሆነ ቢወሰን፤

9. ስለማይተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች

እንደ ሲፒኦ እና ባንክ ድራፍት የመሰሉት የማይላለፉ የገንዘብ ሰነዶች በተግባር በከፍተኛ ደረጃ ጥቅም ላይ
የሚውሉ ሲሆን በሕግ ግን እውቅና የተሰጣቸው አይደሉም፤ በአንድ ወገን የማይተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች
ዓላማ በሕጉ እውቅና ከተሰጠው ገንዘብ ያለው መሆኑ ከተመሰከረለት ቼክ የሚለይ ስላይደለና በተግባር
ጥቅም ላይ መዋሉም የሕግ ሥርዓት ያለውን ቼክ ከገበያ ስለሚያስወጣ የሕግ ሽፋን አለማግኘቱ አግባብ
ነው የሚል ሃሳብ ቀርቧል፤ ነገር ግን በቡድኑ ጎልቶ የወጣው ሃሳብ የማይተላለፉ ገንዘብ ሰነዶች አማራጭ
ሆነው እንዲቀጥሉ በተለይም ማንኛውም ዓይነት ቼክ ቅድሚያ የቼክ የባንክ ሒሳብ መኖርን ስለሚጠይቅ
ዝርዝሩ በሕግ ተደንግጎ አሠራር ሊበጅለት ይገባል የሚለው ሃሳብ ውሳኔ ቢሰጥበት፡፡

45
አምስተኛ መጽሐፍ
የኪሳራና የመጠበቂያ ስምምነት ሕግን ለማሻሻል የቀረቡ የፓሊሲ ሃሳቦች

1. ስለኪሳራ ሕግ ዓላማዎች

የኪሳራ እና የመጠበቂያ ስምምነት ተብሎ የሚጠራው የንግድ ሕግ መፅሃፍ አምስት የጋርዮች የገንዘብ
ማስከበሪያ መንገድ ነው። በኢትዮጵያ ሕግም የተቀመጠው ብቸኛ የጋርዮሽ ገንዘብ ማስከበሪያ ይኸው
ነጋዴዎችን የሚመለከተው የንግድ ሕግ ክፍል ነው። ከዚህ ውጪ ያለው መንገድ የተናጠል መንገድ ሲሆን
በተለያዩ የሕግ ክፍሎች በተቀመጡ ድንጋጌዎች ይገዛል። የጋርዮሽ መብት ማስከበሪያ መንገድነት የኪሳራ
ሕግ መገለጫ ሲሆን፤ ዋነኛው ዓላማም በተናጠል መብት የማስከበር ሩጫ የሚያመጣውን የንብረት
መባከን ማስቀረት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ተሻሽሎ የሚወጣው የኪሳራ ሕግ የሚከተሉትን
ዓላማዎችንም ማሳካት አለበት፡፡

አንደኛ፡ የኪሳራ ሕግ ተስፋ ላላቸው ድርጅቶችና ነጋዴዎች እንደገና ተደራጅተው የሚወጡበትን እድል
ማስቀመጥ አለበት፡፡ መንግሥት የሚከተላቸው የተለያዩ ፖሊሲዎችና ስትራተጂዎች የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ
የመገንባት ዓላማ ያነገቡ ናቸው። የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ የደም ስር የሆነው ውድድር ሀገርና ሕዝብን
ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ ውድድር ብርቅ (scarce) የሃገር ኃብት ለተሻለና ለበለጠ ጥቅም እንዲውል
ያደርጋል። ውድድር የቴክኒክ እድገትን በማምጣት የሕዝብ ጥቅምን ያስከብራል። አዳዲስ ተክኖሎጂዎች
የነበረን ችግር ይፈታሉ፣ ሸቀጥና አገልግሎት በተሻለ ዋጋና ጥራት ለተጠቃሚው ክፍል እንዲቀርብ
ያደርጋሉ። በአጭሩ እየገነባነው ያለው የኢኮኖሚ ሥርዓት ውድድርን ማዕከል ያደረገ የነፃ ገበያ ሥርዓት
ነው። በዚህ ውድድር ሁሉም አሸናፊዎች ናቸው የሚል ብዥታ ግን የለንም። በውድድር ውስጥ አሸናፊና
ተሸናፊ፥ ዘራሪና ተዘራሪ አለ። አሸናፊ መኖሩ የሚያሳየው የሕዝብ ኃብት የላቀ ጥቅም በሚሰጥ መልኩ
እንደዋለ እና በውድድር መንፈስ በተፈጠረ የቴክኒክ መሻሻል አሸናፊው ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ አዲስ
ሸቀጥና አገልግሎት ወይም ተመሳሳይ ሸቀጥና አገልግሎት በተሻለ ጥራትና ዋጋ አቅርቧል ማለት ነው፡፡
ይህም መልካም ዜና ነው። በአንፃሩ ደግሞ ተሸናፊ መኖሩ የሚያሳየው የሕዝብን ብርቅ ኃብት የሚያባክን
ነጋዴና ድርጅት (ምርትና የምርት ሥርዓት) መቆሙን በመሆኑ ይኽም በአብዛኛው ተፈላጊና መልካም ዜና
ነው። የኢንዱስትሪ ልማት ስትራተጂያችን ወገንተኝነታችን ለማን እንደሆነ በማያሻማ መልኩ
አስቀምጦታል። በርግጥ መደገፍ ካለበት የሚደገፈው በውድድር የተሸነፈው ሳይሆን፤ አሸናፊው እንደሆነ
የምንስማማበት እና የምንከተለው የፖሊሲ አቅጣጫ ቢሆንም የሚከተሉትን ነገሮች ግን ግምት ውስጥ
ማስገባት አለብን።
46
አንድ ግለሠብ ወይም ድርጅት በውድድር ተዘረረ የሚባለው ወጪው ከገቢው ሲበልጥና ዕዳውን መክፈል
ሲያቅተው ነው። ነገር ግን መክፈል ያቃተው ነጋዴ/ድርጅት እውነት በውድድር ተበልጦ፣ ማለትም የተሻለ
አገልግሎት በተሻለ ዋጋና ጥራት ማቅረብ አቅቶት ነው ወይስ ጊዜያዊ የሆነ የገንዘብ ችግር አጋጥሞት ነው
የሚለው ነው? እርግጥ ነው በውድድር ኋላ በመቅረቱ የተነሳ፣ የኃብት አጠቃቀሙን ማላቅ (ማሳለጥ)
አቅቶት፣ ጥራትና ዋጋን ማሻሻል አቅቶት፣ ኋላ ቀር የምርት ሂደትና የአስተዳደር ሥርዓት በመከተሉ የተነሳ፤
የተዘረረ ድርጅት መዘረሩ ተገቢ በመሆኑ ሊደገፍ አይገባውም። በአንፃሩ ደግሞ ችግሩ ጊዜያዊ የገንዘብ
ችግር ከሆነ ድርጅቱ ለጊዜው ቢዘረርም በገበያው ኢኮኖሚ ተሳታፊነቱ ቢቀጥል ሕዝብን ስለሚጠቅም
ይህን መሳይ ድርጅቶች ተስፋ ከሌላቸው ጋር ተዳምረው መውደቅ የለባቸውም። የኪሣራ ሕግ ተስፋ
ያላቸውን ድርጅቶች እንዲቀጥሉ ፋታና እድል በመስጠት፤ ተስፋ የሌላቸውን ደግሞ ችግራቸው ወደ
ጤነኞቹ ሳይዛመት ባግባቡ በማስወገድ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ግቡን እንዲመታ ይረዳል። መልሶ ማደራጀት
(reorganization) በብዙ ሀገራት ተቀባይነት ያገኘ የኪሳራ ሕግ ሚና ሲሆን የኪሳራ ሕግ ባይኖር ኖሮ
ሁሉም መክፈል የማይችሉ ድርጅቶች (ተስፋ ያላቸውም የሌላቸውም) ዕጣ ፈንታቸው መፍረስና መበተን
ነው። እያንዳንዱ ባለገንዘብ መብቱን ለማስከበር በሚያደርገው የተናጠል ጉዞ ባለዕዳው ተስፋ አለው
(ያለበት ጊዜያዊ የገንዘብ ችግር ነው) ወይስ ተስፋ ቢስ ነው (በውድድር ተሸንፏል) ለሚለው የመለያ
ጥያቄ ጊዜ አይኖርም።

ሁለተኛ፤ የኪሳራ ሕግ እንደ ጋርዮሽ መብት ማስከበሪያ መንገድ፤ ንብረት የተናጠል ዘመቻ/መቀራመት
የሚደርስበትን የዋጋ ማጣት በማስቀረት የወለድ መጠንን (cost of credit) የመቀነስ ሚና ይኖረዋል፡፡
ልዩ መያዣ የሌላቸው ባለገንዘቦችን የጋራ ጥቅም የማስከበሪያ ሥርዓት በማስቀመጥ የወለድ መጠን
እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኪሳራ ውሳኔ የተሰጠበትን ድርጅት ወይም ግለሰብ ለይቶ
በማውጣትና ይህን መረጃ ለአበዳሪዎች በማካፈል፤ ከኪሳራ ሕግ ጋር ተያያዞ የሚፈጠር የመረጃ
መለዋወጫ ሥርዓት ብድርን በተሻለ ወለድና ቅድመ ሁኔታዎች በገበያ እንዲቀርብ የማድረግ ሚና
ይኖረዋል፡፡ በአጭሩ የመረጃ በእኩል ደረጃ በገበያ ተዋንያን አለመኖር (information assymtery)
ችግርን በመፍታት የኪሳራ ሕግ የገንዘብ ግብይችን ያበረታታል/ይደግፋል፡፡

ሶስተኛ ዓላማ የአዲስ ጅማሪ ተስፋ መስጠት ነው፡፡ ይህ በተለይ የግለሰብ ነጋዴዎችንና ሸማቾችን
ይመለከታል፡፡ በአንዳንድ ሀገሮች የኪሳራ ሕግ መሠረት ባለዕዳው ያለውን ገንዘብና ንብረት አሳልፎ
በመስጠት ከዕዳው ነጻ መውጣት ይችላል፡፡ ማለትም የከሳሪነትን ውሳኔ በማሰጠትና መክፈል
የማይችሉትን ዕዳ በማሰረዝ ወደፊት የሚያገኙትን ገቢ ከድሮው ዕዳ ነጻ ማውጣት ይችላሉ፡፡ ይህ የአዲስ

47
ጅማሬ ተስፋ ነው፡፡ የድጋሚ እድል፡፡ ይህ መሆኑ ሰዎች የመሥራት ፍላጎታቸው እንዳይበረዝ፤ እንዲሁም
የህዝብ ኃብት ንብረት በመደበቅና በጥቁር ገበያ በመነገድ እንዳይባክን ያደርጋል፡፡

2. ስለኪሳራ ሕግ የአፈጻጸም ወሰን

አሁን ባለበት ሁኔታ የኢትዮጲያ የኪሳራ ሕግ የሚመለከተው ግለሰብ ነጋዴዎችንና የንግድ ሥራ የሚሰሩ
ድርጅቶችን ነው፡፡ የባንኮችና መድኖች ኪሳራ በተለየ መልኩ በብሄራዊ ባንክ ይታያል፡፡ የመንግሥት
የልማት ድርጅቶች የኪሳራ ሕግ በንግድ ሕጉ በተቀመጠው መሠረት ይከናወናል፡፡ ነጋዴ ያልሆኑ
ግለሰቦችን ሆነ ድርጅቶችን አሁን ያለው የኪሳራ ሕግ አይመለከትም፡፡ ሕጉን ከኪሳራ ሕግ ዓላማዎች፤
ከሌሎች ሀገር ሕጎች እና ኢትዮጲያ ከምትከተላቸው ፓሊሲዎች አንጻር ተገምግሞ የሚከተለው የፓሊሲ
ሃሳብ ቀርቧል፡፡

ነጋዴ ያልሆኑ ግለሰቦችን የሚመለከት የኪሳራ ሕግ ስለሌለ፤ ለተናጠል ሩጫና ንብረት መባከን በር
ይከፍታል፡፡ ነገር ግን ነጋዴ ያልሆኑ ግለሰቦች ብዙ ባለገንዘብ ስለማይኖራቸው ይህ ችግር ጎልቶ ላይወጣ
ይችላል፡፡ ነገር ግን ከላይ ከተጠቀሱት የኪሳራ ሕግ ዓላማዎች አንጻር፤ ነጋዴ ላልሆኑ ግለሰቦች የአዲስ
ጅማሬ ተስፋ ያዘለና ነጋዴ ላልሆኑ ግለሰቦች ብድር ያለመያዣ የሚያገኙበትን መንገድ የሚያመቻች
የኪሳራ ሕግ ያስፈልጋል።

አሁን ያለው የባንኮችንና የኢንሹራንስ ድርጅቶችን የኪሳራ ሁኔታ በተለየ (ከንግድ ሕጉ) መልኩ ማየት
ሊቀጥል ይገባል፡፡ እነዚህ የገንዘብ ተቋማት እንደማንኛውም የንግድ ተቋማት በተመሳሳይ የኪሳራ ሕግ
ማእቀፍ ስር ይውደቁ የሚል ድምዳሜ ላይ መድረስ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ አንድምታ አለው፡፡የገንዘብ
ተቋማትን በተመለከት ትኩረታችን መሆን ያለበት የመክሰር አደጋን ማስወገድና ጤንነታቸውን መቆጣጠር
ነው፡፡ ይህ ደግሞ አሁን እንደሚደረገው ለተቆጣጣሪው አካል (በዋናነት ብሔራዊ ባንክ) ቢተው
ይመረጣል፡፡

ምንም እንኳ የመንግሥት የልማት ተቋማት እንደማንኛውም የንግድ ተቋማት በፍርድ ቤት መክሰራቸው
ታውጆ መፍረስ እንደሚችሉ ሕጉ ቢደነግግም፤ በተግባር እንዳይፈርስ የተፈለገን የልማት ተቋም
መንግሥት ካፒታሉን በመጨመር መታደግ ይችላል፡፡ መፍረስ ያለበት ከሆነ ግን በፍርድ ቤት የኪሳራ
ሕግን ድንጋጌዎች በተከተለ መልኩ ይስተናገዳል፡፡ ዞሮ ዞሮ ውሳኔው የመንግሥት ነው፡፡ ይህን አስመልክቶ
ግን የተቀመጠ የሕግ ማእቀፍ የለም፡፡ ምንም እንኳ ይህ ከንግድ ሕጉ ጋር ቀጥታ ባይያያዝም፤ ለዚህ ጉዳይ
የሚሆን የሕግ ማእቀፍ ቢደራጅ የሚል የውሳኔ ሃሳብ ቀርቧል፡፡

48
3. ስለንብረት ጠባቂው፤ መርማሪው ዳኛ፤ ፍርድ ቤቶች፤ ዓቃቤ ሕግና ሌሎች የመንግሥት ተቋማት ሚና

አሁን ያለው የኪሳራ ሕግ የከሳሪውን ንብረትና ንግድ የማስተዳደር ኃላፊነትን በንብረት ጠባቂውና
በመርማሪው ዳኛ መካከል ያከፋፍላል፡፡ ፍርድ ቤቱም የተቆጣጣሪነትና ሙግትን የመፍታት ኃላፊነት
አለበት፡፡ ብዙ ወገኖች በንብረት ማስተዳደሩ ላይ መካፈላቸው አንዱ ሌላውን ለመቆጣጠር ቢረዳም፤
ወጪን የማብዛትና ሂደቱን የማራዘም ውጤት ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም የመርማሪ ዳኛውን እና የንብረት
ጠባቂውን ሥራ አዳብሎ ንብረት ጠባቂው እንዲሰራ፤ መርማሪ ዳኛው የሚሰራቸውን የቁጥጥር ሥራዎች
ደግሞ ፍርድ ቤት ሊያከናውናቸው ይገባል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚነሳው የአቃቤ ሕግና የሌሎች የመንግሥት ተቋማት ሚናን ይመለከታል፡፡ አሁን
ባለው ሕግ አቃቤ ሕግ የኪሳራ የፍርድ ሂደትን ሊያስጀምር እንደሚችል ይናገራል፡፡ ከዚህ አልፎ ግን
በምን ዓይነት ጉዳዮች ነው ለሚለው መልስ አይሰጥም፡፡ በመሆኑም ሕጉ በሚሻሻልበት ወቅት አቃቤ ሕግ፤
ብዙ ዜጎቻችን እንደ ባለገንዘብ የሆኑበትን ድርጅቶች አስመልክቶ የኪሳራ ፍርድ ሂደት ሊያስጀምር
እንደሚገባ ማስቀመጥ አለበት፡፡ እንዲሁም እንደንግድ ሚኒስቴር ያሉት ተቋማት የሚኖራቸውን ሚና
(ለምሳሌ ለንብረት ጠባቂዎች ፍቃድ በመስጠትና በመቆጣጠር፤ አንዳንዴም የንብረት ጠባቂነትን ሚና
በመጫወት) ሊተነተን ይገባል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ከላይ በመጽሐፍ አንድ ስር ከተነሱት ራሳቸውን የቻሉ የንግድ ፍርድ ቤቶች ወይም
ችሎቶች ጋር ተያይዞ ሊመለስ የሚገባው ጥያቄ የኪሣራ ጉዳይን የሚያዩ ችሎቶች ሊኖሩ የሚገባ መሆኑ
ነው። የኪሳራ የፍርድ ሂደትም ሆነ ሌሎች የንግድ ጉዳዮች በአነስተኛ ወጪ፣ በአጭር ጊዜ፤ ቀልጣፋና
በጉዳዩ ዙሪያ የተለየና የዳበረ እውቀት ባላቸው ባለሙያዎች እንዲሰሩ ማድረግ የፍትሕ ስርዓቱ ግብ ነው።
ይህን ተፈፃሚ ለማድረግ ደግሞ የኪሣራ ጉዳይን የሚያዩ ችሎቶች ይህንን የፖሊሲ ውሳኔ ተከትሎ
በሚቋቋሙ የንግድ ፍርድ ቤቶች ወይም በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ውስጥ ሊኖሩ ይገባል።

4. ሙሉ ለሙሉ ስላልተፈጸሙ ውሎች

ከሳሪው ነጋዴ ከፍርድ ሂደቱ በፊት የገባቸው ነገር ግን እሱም ሆነ ሌሎቹ ተዋዋይ ወገኖች
ግዴታዎቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ያልተወጧቸውን ውሎች አስመልክቶ የኪሳራ ሕግ መልስ እንዲሰጥ
ይጠበቃል፡፡ የኢትዮጲያ ሕግ የኪራይ ውልን ብቻ አስመልክቶ ለንብረት ጠባቂው (በመርማሪ ዳኛው
ፍቃድና በባለገንዘቦች ኮሚቴ አሳብ) ለመሰረዝ ወይም ለመቀጠል እንዲወስን ስልጣን ይሰጠዋል፡፡ ይህን
አስመልክቶም ዝርዝር ድንጋጌዎች አስቀምጧል፡፡ የኢትዮጲያ ሕግ ከሌሎች ሀገሮች ሕጎችና ከኪሳራ ሕግ

49
ዓላማዎችና ሀገራችን ከምትከተላቸው ፓሊሲዎች አንጻር ከተመገመ በኋላ የሚቀጥለው የፓሊሲ ሃሳብ
ቀርቧል፡፡

ሕጉ የኪራይ ውል ብቻ ላይ ማተኮር የለበትም፡፡ በአጠቃላይ ሁለቱም ወገኖች ሙሉ ለሙሉ


ያልፈጸሟቸው ውሎችን በተመለከተ፤ የመሰረዝ ወይም የማስቀጠል መብትን ለንብረት ጠባቂው ሊሰጥ
ይገባል፡፡ እነዚህ ውሎች መቀጠልና አለመቀጠል የኪሳራ ሂደቱ ውጤታማነትና የኪሳራ ሕግ ዓላማዎች
መሳካት ወሳኝ ከመሆኑ አንጻር ንብረት ጠባቂው ውሳኔውን ሲሰጥ የሚጠቀመው መመዘኛ፤ ውሉ
ለውጤታማ መልሶ ማደራጀትና ለባለገንዘቦች ጥቅም ያለውን ሚና ነው፡፡ ፍርድ ቤቱም ከዚህ ውሳኔ ጋር
ተያይዞ አቤቱታ ከቀረበለት ተመሳሳይ መመዘኛ መጠቀም ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም እነዚህን ውሎች
ንብረት ጠባቂው ለሶስተኛ ወገን ለማስተላለፍ እንዲችል መፍቀድ ይገባል፡፡

እንዲሁም ምንም እንኳ አንደኛው ወገን ሲከስር ውሉ ይቋረጥል የሚል የውል ቃል ቢኖርም የውሉን እጣ
ፈንታ የመወሰን እድሉ የንብረት ጠባቂው መሆን አለበት፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የውሉ መቀጠል፤ መሰረዝ ወይም ወደ ሶስተኛ ወገን መተላለፍ የሚኖረው የሕግ
ውጤት በአዲሱ የኪሳራ ሕግ ሊተነተን ይገባል፡፡ የንብረት ጠባቂው በምን ያህል ጊዜ ውሳኔውን ያሳውቅ
እንደሚገባው ለመወሰን የኪሳራ ፍርድ ሂደት ያልተንዛዛና ወጪ ቆጣቢ መሆን እንዳለበት ግምት ውስጥ
ባስገባ መልኩ ነው፡፡ አጭር ጊዜ ተቀምጦ፤ አስፈላጊ ከሆነ ምክኒያት በማቅረብ በፍርድ ቤት የሚራዘምበት
ሥርዓት ያስፈልጋል፡፡

ውሉ እንዲቀጥል የሚደረግ ከሆነ የሌሎች ወገኖችን ጥቅም ለማስከበር ሲባል በቂ ዋስትና ሊያገኙ
ይገባል፡፡ እንዲሁም ንብረት ጠባቂው ውሳኔ እስኪሰጥ ድርስ ወይም እንዲቀጥል ከተደረገ በኋላ የበሰሉ
ግዴታዎችን በተመለከተ ያኛው ተዋዋይ ወገን የቅድሚያ መብት ማግኘት አለበት፡፡

ምንም እንኳ አጠቃላይ ሙሉ ለሙሉ ያልተፈጸሙ ውሎችን አስመልክቶ፤ ምርጫውን ለንብረት ጠባቂው
መስጠት ቢገባም አንዳንድ ውሎችን ግን ማስቀጠልም ሆነ ማስተላለፍ እንደማይቻል ማስቀመጥ ይገባል፡፡
ምን ዓይነት ውሎች ናቸው መቀጠልም ሆነ መተላለፍ የማይቸሉት የሚለውን ለመወሰን የውል ሕግ
ድንጋጌዎችን መጠቀም ይቻላል፡፡ ማለትም በውል ሕግ መሠረት ወደ ሌላ ሰው ሊተላለፍ የማይችል ውል
በኪሳራ ሕግ መሠረት እንዲቀጥል ወይም እንዲተላለፍ መደረግ የለበትም፡፡ በዚህ መሠረት የገንዘብ
ውሎች፤ ግላዊ አገልግሎት ለማቅረብ የሚደረግ ውል፤ የብድርና ኢንሹራንስ ውሎች እንዲቀጥሉ ወይም
እንዲተላለፉ መደረግ የለበትም፡፡

50
ውል እንዲቋረጥ ከተወሰነ ወይም ከተገመተ፤ ከሳሪው ግዴታውን እንዳልተወጣ ተቆጥሮ፤ ያኛው ተዋዋይ
ወገን ከሌሎች ባለገንዘቦች ጋር ሊቆጠር ይገባል፡፡

የንብረት ጠባቂውና የመርማሪ ዳኛው ሥራዎቸና ሃላፊነቶች በአንድ እንዲማከሉ ከቀረበው የፓሊሲ ሃሳብ
ጋር በተያያዘ፤ እነዚህ ውሎች ይቀጥሉ ወይ ይቋረጡ የሚለውን ውሳኔ ንብረት ጠባቂው የባለገንዘቦች
ኮሚቴን አሳብ ግምት ውስጥ በማስገባት እንዲወስን ይገባል፡፡ ነገር ግን ለሁሉም ውሳኔዎች የፍርድ ቤትን
እሽታ እንዲያገኝ መጠየቅ ጉዳዮን ሊያንዛዛው ስለሚችል፤ አቤቱታ ሲቀርብ ብቻ ፍርድ ቤት ሊያየው
ይችላል፡፡

5. ስለመልሶ ማደራጀት

መልሶ ማደራጀት/ማዋቀር የዘመናዊ የኪሳራ ሕግ ተጨማሪ ዓላማና አማራጭ የፍርድ ሂደት ነው፡፡
የኢትዮጲያ ሕግ ዘመናዊ ሆኖ እንዲቀጥልና ከዓለም አቀፍ አሠራር ጋር እንዲጣጣም ከተፈለገ የመልሶ
ማደራጀት ሥርዓት አስፈላጊው መሻሻል ተደርጎበት እንዲቀጥል ሊደረግ ይገባል፡፡

የመልሶ ማደራጀት ኢትዮጲያ ከምትከተለው የልማታዊ መንግሥት አስተሳሰብ ጋር የሚጣጣም ነው፡፡


በገበያ ሥርዓት ውስጥ ተወዳድሮ የከሰረ ነጋዴ ከገበያ መውጣት አለበት፡፡ ለዚህ ዓይነት ነጋዴ ምንም
ዓይነት ጥበቃና እገዛ አያስፈልግም፡፡ ይህ የሚሆነው ግን በገበያ ውስጥ ፍጹም የሆነ ውድድር ካለ ነው፡፡
ገበያው እንከን ያለው ከሆነ ግን መክሰር ማለት በውድድር መሸነፍ ማለት አይደለም፡፡ መንግስታችን
የሚከተለው ልማታዊ አስተሳሰብ መነሻም ገበያ ብዙ እንከኖች እንዳሉትና በተለይ እነዚህ እንከኖች እንደኛ
ባሉ ሀገሮች በዛ ብለው መታየታቸው ነው፡፡ ለዚህም ነው መንግስታችን ሚናውን ከሌሊት ዘበኛ ያለፈና
ገበያው በደከመበት እየገባ ማስተካከያ የሚያደርግ በሚል የሚገልጸው፡፡

እንከን በሌለው (ፍጹም በሆነ) የገበያ ሥርዓት ውስጥ፤ በጊዜያዊ ገንዘብ ችግር የተነሳ አንድ ነጋዴ
አይከስርም፡፡ ምክኒያቱን ንግዱ አዋጭ ከሆነና ችግሩ የጊዜያዊ የገንዘብ አቅርቦት ችግር ከሆነ፤ በዚሁ ገበያ
በተለያየ መልኩ (በብድር ወይም በባለቤትነት ድርሻ) ገንዘብ ስለሚያገኝ ከስሮ ከገበያ አይወጣም፡፡
በፍጹም የገበያ ሥርዓት ውስጥ አንድ ነጋዴ መክፈል አቃተው፤ የገንዘብ ችግር አጋጠመው፤ ገንዘቡን
ከገበያ በብድር ወይም ድርሻ በመሸጥ ማግኘት አቃተው ማለት፤ ንግዱ አዋጭ አይደለም፤ በውድድር
ተሸንፏል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ነጋዴ ገበያውን መልቀቁ ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን ያለን የገበያ ሥርዓት
ፍጹም አይደለም፡፡ ምንም እንኳ አዋጭ ንግድ ቢኖረውም፤ ነገዴው እንደፈለገው ገንዘብ ከገበያው
ማግኘት አይችልም፡፡ የገንዘብ ገበያው እንኳን በኛ ሀገር በሌሎቹም ብዙ እንከኖች ያሉበት ነው፡፡

51
በመሆኑም የገንዘብ ችግር ማለት የውድድር አቅም ማጣት ማለት አይደለም፡፡ በእንደዚህ ያለ ጊዜ ልማታዊ
መንግሥት እጁን አጣምሮ ቁጭ አይልም፡፡ ቢያንስ የኪሳራ ሕግ መልሶ ማደራጀትን እንደ አንድ አማራጭ
የፍርድ ሂደት ያስቀምጣል፡፡ መሆን ያለበትም ይኽው ነው፡፡

ስለመልሶ ማደራጀት/ማዋቀር የሚመለከተው የኪሳራ ሕግ ክፍል አስገዳጅ ሳይሆን፤ በባለዕዳውና


በባለገንዘቦች መካከል በተቻለ መጠን ስምምነት ላይ ተደርሶ መዳን የሚችለው ንግድና ነጋዴ እንዲድን
ማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም በባለዕዳውና በባለገንዘቦቹ የሚደረጉ ስምምነቶች ይዘትን ከመደንገግ መቆጠብ
አለበት፡፡ በመሆኑም የኪሳራ ድንጋጌዎች፡ ስምምነቶች ባለዕዳውን ሙሉ ለሙሉ ወደ ነበረበት የሚመልሱ
እንዲሆኑ መጠበቅና የዕዳዎችን መሰረዝ መከልከል የለባቸውም፤ ቢያንስ መከፈል ያለበት የዕዳ መጠን
ብሎ የሚያስቀምጠው ነገር መኖር የለበትም፤ ዕዳን በባለቤትነት ድርሻ ለመቀየር የሚደረግን ስምምነት
መከልከል የለበትም፡፡ ከዚህ አንጻር የኢትዮጲያን ሕግ ማሻሻል ተገቢ ነው፡፡ አሁን ባለው የኪሳራ ሕግ
የተቀመጡት ሁለት አማራጮች፤ ባለዕዳው ከመቶ ይህን ያህሉን በዚህ ያህል ጊዜ እከፍላለሁ በሚል
የሚያቀርበው የስምምነት አሳብ እንደሆነ ያስቀምጣሉ፡፡ እንዳንዴም በዚህ ፋንታ የተወሰነን ንብረት
ለመልቀቅ ሊስማማ እንደሚችል ያስቀምጣሉ፡፡ ከዚህ በተረፈ ግን ለሌላ ዓይነት ስምምነት ሕጋችን ክፍት
አይደለም፡፡

አስገዳጅና አስጨናቂ መንገድ ባይከተልም እንኳ የኪሳራ ሕግ የመልሶ ማደራጀት መርሆችን ማስቀመጥ
አለበት፡፡ ለምሳሌ፤ ገንዘብ ጠያቂዎች በንብረት ማጣራት ሊያገኙ የሚችሉትን የገንዘብ መጠን በመልሶ
ማደራጀትም ማግኘት አለባቸው፡፡

አሁን ያሉት ሁለቱ አማራጭ ስርአቶች ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው መወናበድን ለማስቀረት ሲባል
አሰያየማቸው ቢቀየር፤ አሁን ባለበት ሁኔታ የመጠበቂያ ስምምነት የኪሳራ ሕግ አካል አይመስልም፡፡
በመሆኑም አጠቃላይ የመጽሃፉ ርእስ “የኪሳራ ሕግና መጠበቂያ ስምምነት” የሚለው “የኪሳራ ሕግ”
በሚል ቢተካና የመጠበቂያ ስምምነት እና በኪሳሪ የፍርድ ሂደት ውስጥ የሚቀርበውን የስምምነት አሳብ
በአንድ ላይ የመልሶ ማደራጅት/ማዋቀር ስምምነት በሚል መተካት አለበት፡፡

ከስያሜው መለስ ሲባል ደግሞ፤ ሁለቱን አማራጮች አስመልክተው የተቀመጡት አስገዳጅ ድንጋጌዎችን
ማጣጣም ተገቢ ነው፡፡ በሁለቱም አካሔድ የሚቀርበው ስምምነት በገንዘብ ጠያቂዎች ተቀባይነት ማግኘት
ሲኖርበት የተደነገገው የድምጽ ብልጫ መጠን አስመልክቶ ልዩነት ይታያል፡፡ ይህ መጣጣም አለበት፡፡

52
6. ውሎችና ስለማፍረስና ዕዳን ስለማቻቻል

የኪሳራ ፍርድ ሂደት የሚጀምረው ባለዕዳው ለመጀመሪያ ጊዜ ችግር ውስጥ እንደገባ እና መክሰሩ
እንደማይቀር ካወቀ በኋላ በመሆኑ በመካከሉ የተወሰነ ጊዜ ማለፉ አይቀርም፡፡ ማመልከቻው የቀረበው
በሌሎች ቢሆንም እንኳ እነዚህ ወገኖች ስለሁኔታው እስኪያውቁ ድረስ የተወሰነ ጊዜ ማለፉ የማይቀር
ነው፡፡ በዚህ መካከል ባለዕዳው ንብረቱን የሚደብቅበት፤የውሸት (የይስሙላ) ውሎችን የሚዋዋልበት፤
ስጦታ ለዘመዶችና ጓደኞች የሚሰጥበት፤ እና አንዳንድ ባለገንዘቦችን መርጦ የሚከፍልበት እድል ያገኛል፡፡
እንዲሁም አንዳንድ ባለገንዘቦች እራሳቸውን የተሻለ ቦታ ለማስቀመጥ (ለምሳሌ መያዣ የሌላቸው
ባለገንዘቦች የቅድሚያ መብት ለማግኘት ሲሉ አዲስ የመያዣ ስምምነት በማቋቋም) ጥረት ሊያደርጉ
ይችላሉ፡፡ የዚህ ሁሉ እንቅስቃሴ ገፈት ቀማሽ የሚሆኑት ዋስትና መያዣ የሌላችው ባለገንዘቦች ናቸው፡፡
የኪሳራ ሕግ ለዚህ የመከላከያ ድንጋጌዎች ማስቀመጥ አለበት፡፡

የኢትዮጲያ ሕግ ሊፈርሱ የሚችሉ ብሎ ያስቀመጣቸው አራት ዓይነት ግብይቶች በብዙ ሀገሮች የኪሳራ
ሕጎችም ሊፈርሱ የሚችሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህን አራት ዓይነት ግብይቶች አስመልክቶ ያኛው ወገን
በቅን ልቦና ያደረገው ከሆነ ውሉ ወይም ክፍያው መፍረሱ አግባብ አይደለም፡፡ ቅን ልቦና ግላዊ ቅድመ
ሁኔታ ነው እና ሙግትን ያበረታታል ተብሎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ እንደውም አንዳንድ የሕግ ተንታኞቸ
እንደ ኢትዮጲያ ያሉ የተማረ የሰው ሀይል ችግር ያለባቸው ያላደጉ ሀገሮች ሕጎቻቸውን ሲነድፉ ከግላዊ
ይልቅ ተጨባጭ ድንጋጌዎችን መምረጥ አለባቸው፤ ምክኒያቱም ግላዊን ድንጋጌ በሕግ ትርጉም በጊዜ
ሂደት ለማበልጸግ በቂ የሕግ ባለሙያዎች ስለሚያስፈልግ ይላሉ፡፡ ግላዊ ድንጋጌዎች ከተጨባጭ
አቻዎቻቸው ጋር ሲነጻጸሩ ብዙ ሙግቶችን ያስከትላሉ፡፡ ይህ እሳቤ በተወሰነ መልኩ የንግድና የፍትሃ
ብሄር ሕጎቻችንን ያረቀቀቁትን ሰዎች ያሳመነ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በእርግጥ በዛ ወቅት ተገቢ ስጋትና
ምክር ነው ሊባል ይቻላል፡፡ ነገር ግን ሀገራችን የንግድ ሕጋችን ከወጣበት ዘመን ጋር ሲነጻጸር ከሕግ
ባለሙያዎች ቁጥር አንጻር ብዙ ተራምዳለች፡፡ በመሆኑም ይህ ስጋት የሕጉን ቅርጽና ይዘት ሊወስን
አይገባም፡፡

የዕዳ ማቻቻልን የኢትዮጲያ የኪሳራ ሕግ አይመለከትም፡፡ ነገር ግን ዕዳን ማቻቻል እንደሚፈቀድ


አጠቃላይ የውል ሕግ ይናገራል፡፡ ቅድመ ሁኔታዎችንም ያስቀምጣል፡፡ ነገር ግን ዕዳን በማቻቻል
የባለገንዘቦችን የጋር ጥቅም መጉዳት እንደሚቻል ከሌሎች ሀገሮች መማር ይቻላል፡፡ ከዚህ በፊት ባለው
ፓራግራፍ የተጠቀሰውን የጥበቃ ድንጋጌዎች ዕዳን በማቻቻል ማምለጥ አይገባም፡፡ በመሆኑም ዕዳን

53
ማቻቻል በኪሳራ ሂደት በመሰረቱ ፈቅዶ ነገር ግን የባለገንዘቦችን ጥቅም ከቅን ልቦና ተጻራሪ በሆነ መልኩ
የሚጎዳ ከሆነ ግን መከልከል ይገባል፡፡

7. ስለባለገንዘቦች ሚና

ባለገንዘቦች በኪሳራ ሂደት እና ውሳኔ ውስጥ ከባለዕዳው ባልተናነሰ መልኩ ዋናዎቹ ባለድርሻ አካላት
ናቸው። የኪሳራ የፍርድ ሂደቱ መልሶ ማደራጀትን ከተከተለና በስኬት ከተጠናቀቀ ገንዘባቸውን መልሰው
የሚያገኙበት፤ የኪሳራ ሂደቱ ንብረት ማጣራት ውስጥ ከገባና ከሽያጩ የሚገኝ በቂ ንብረት የማይኖር ከሆነ
ደግሞ ገንዘባቸውን ሊያጡ የሚችሉበት ሁኔታ አለ። በዚህም ምክንያት ነው ባለገንዘቦች በኪሳራ የፍርድ
ሂደቱ ውስጥ ጠንከር ያለ ተጽዕኖ ሊኖራቸው ይገባል የሚባለው። ባለገንዘቦች መብቶቻቸውን ለማስከበር
በተናጠልም ሆነ በጋራ በሚቋቋመው የገንዘብ ጠያቂዎች ኮሚቴ አማካኝነት ሊንቀሳቀሱ እንደሚችሉ አሁን
ባለው የንግድ ሕግም ሆነ በሌሎች ሀገራት ሕግጋት ተገልጿል።

የንግድ ሕጉ የልማታዊ መንግሥት ኢኮኖሚን እና የዓለም የንግድ ድርጅትን በአባልነት መቀላቀልን ታሳቢ
አድርጎ የሚቀረጽ ከመሆኑ አንጻር በኪሳራ ሂደት ውስጥ የሠራተኞችን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል የከሰረው
ሰው ተቀጣሪ ሠራተኞች እንደባለገንዘብ ሊቆጠሩና በገንዘብ ጠያቂዎች ኮሚቴ ውስጥ የኮሚቴው አባል
ሆነው ሊካተቱ ይገባል። የአንድ ነጋዴ መክሰር በርሱ ላይ ብቻ ሳይሆን በርሱ ስር ያሉትን ሠራተኞች እና
ቤተሰቦቻቸውን የሚነካ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር በመሆኑ ሠራተኞች ከከሰረው አሰሪያቸው
የሚጠይቋቸውን ክፍያዎች አስመልክቶ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የሚስተናገዱበት ሁኔታ ሊፈጠር ይገባል።
ይህም መንግሥት የሚደግፈውን የሥራ አጥነት ቅነሳ የሚደግፍ አካሔድና የሠራተኛውን እና የቤተሰቡን
ህይወት አንፃራዊ ዋስትና እንዲኖረው የሚያደርግ በመሆኑ በንግድ ሕጉ ውስጥ በዚሁ መልኩ ሊካተት
ይገባል።

8. ወጪዎች እና የባለገንዘቦች የመብት ደረጃ

የኪሳራ የፍርድ ሂደት የተለያዩ ወጪዎች ያሉበት እና የኪሳራው ሂደት ሁሉም ወጪዎች ለማለት
በሚያስችል መልኩ «የኪሳራው ንብረት» ተብሎ በተለየ ንብረት የሚሸፈንበት ነው። የኪሳራው ንብረት
የከሰረው ሰው ንብረቶች ሲሆኑ ለኪሳራው ሂደት ወጪዎች መሸፈኛ እና በኪሳራው ሂደት በስተመጨረሻ
ለገንዘብ ጠያቂዎች እንደየመብት ደረጃቸው ለማከፋፈልና ዕዳውን ለመክፈል የሚውል ንብረት ነው።
በሀገራችን የኪሣራ ሕግ ድንጋጌዎች ውስጥ የኪሳራው ንብረቶች ተብለው በግልጽ የተለዩ ንብረቶች
ባለመኖራቸው አዲሱ ረቂቅ ይህንን ሊፈታ ይገባል። ከዚህ በተጨማሪ የኪሳራው ንብረት በቅድሚያ

54
የትኞቹን ወጪዎች መሸፈን ይኖርበታል ለሚለው ጥያቄ የኪሳራው ሂደት ወጪዎች መጀመሪያ ሊሸፈኑ
ይገባል በማለት የንግድ ህጋችን በተዘዋዋሪ ሲያመላክት የሌሎች ሀገራት ልምዶችም ተመሳሳይ ሁኔታዎችን
ይደነግጋሉ።

ይሁን እንጂ ኪሳራ የሚታወጅበት ዋነኛው ምክንያት የባለገንዘቦችን ገንዘብ ለማስመለስ እና/ወይም
የባለዕዳው ንግድ እንዲያገግም ለማድረግ ቢሆንም የኪሳራው ንብረት የኪሳራውን ሂደት ወጪዎች ብቻ
በመሸፈን ሊያልቅ ይችላል። ይህ ከሆነ ደግሞ የፍርድ ሂደቱ የተነሳበትን ዓላማ ይስታል። በሌላ አገላለፅ
ባለዕዳው እጅ ላይ የነበረው ንብረት ለባለዕዳውም ሆነ ለገንዘብ ጠያቂዎች ሳይደርስ ወጪዎችን በመሸፈን
ብቻ ባክኖ ይቀራል። ይህ ደግሞ አንድ ጥሩ የሚባል የኪሳራ ሕግ ባሕርይ አይደለም።በመሆኑም
በባለዕዳው እጅ የሚገኘው ንብረት የኪሳራ ሂደቱን ወጪዎች በመሸፈን ብቻ የሚያልቅ መሆኑ የሚታወቅ
በሆነ ጊዜ የቅድሚያ እና ልዩ የመያዣ መብት ላላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች የተናጠል የገንዘብ ጥያቄ
ማስተናገጃ እንዲሆን ሊወሰን ይገባል።

በሀገራችን ከተያዙ የረዥም እና የአጭር ጊዜ እቅዶች ውስጥ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል እና የሥራ
አጥነትን መቀነስ ነው። የኪሣራ የፍርድ ሂደትን ተከትሎ ከሚመጡት ነገሮች አንዱ ንግዱ በሚፈርስበት
ጊዜ የሚከሰቱ የሥራ ማጣት ችግር ነው። በዚህ ጊዜ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጫና መቀነስ የሚቻለው
በኪሣራው ንብረት ክፍፍል ውስጥ ቅድሚያ ተሠጥቷቸው ተካፋይ የሚሆኑበት መንገድ ሲኖር ነው።
የአንድ ሠራተኛ ያልተከፈለ ደመወዝ እና የስንብት ክፍያ ማግኘት እርሱን ብቻ ሳይሆን በስሩ
የሚያስተዳድራቸውን ቤተሰቦቹን ጭምር የሚጠቅም ነገር በመሆኑ ቅድሚያ ተሠጥቷቸው የሚያገኙበት
ሁኔታ ሊፈጠር ይገባል። ከዚሀ በመቀጠል የግብር ዕዳዎች ከከሠረው ሰው ንብረት ውስጥ ለሠራተኞች
ከሚከፈሉ ክፍያዎች በመቀጠል እና ከሌሎች ዕዳዎች በመቅደም ተከፋይ ቢሆን ተጠቃሚው ሃገርና
ሕዝብ በመሆናቸው በግልጽ ሊቀመጥ ይገባል።

9. ነጻ መውጣት

ከኪሳራ ሕግ ዓላማዎች አንዱ የአዲስ ጅማሬ ተስፋ መስጠት ነው። አንድ ባለዕዳ መክፈል ያልቻለውን
ዕዳን በኪሳራ ሕግ ምክንያት ነፃ የሚባል ከሆነ ብዙዎች አንዲያጭበረብሩ እና የሌሎች ሰዎችን ገንዘብ
እንዲያስቀሩ ስለሚያበረታታ ነፃ ሊባል አይገባም የሚሉ መከራከሪያዎች አሉ። በአንፃሩ የሃገራትን ልምድ
እና የዘመናዊ የኪሳራ ሕግ አካሔድ ስንመለከት ባለዕዳውን ነፃ አለማድረግ በዋናነት ባለዕዳው በየጊዜው
የሚያገኘውን ገንዘብ ለዕዳ መክፈያ የሚወሰድበት ከሆነ የመሥራት ፍላጎቱ እንዲቀንስ ከማድረጉ ባሻገር
በተለያየ መንገድ የሚያገኘውን ገንዘብ በአግባቡ ግብር ከፍሎበት ከመጠቀም እና ሀገሪቱን ከመጥቀም

55
ይልቅ በተለያዩ ሰዎች ስምና በጥቁር ገበያ አንዲጠቀም ያደርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ በየትኛውም ዓለም
የኃብት ፈጠራ መነሻ ብድር በመሆኑ ዜጎች ተበድረው ቢከስሩ ያላቸው ንብረት በሙሉ የሚወሰድባቸውና
በተቀረው ዕድሜያቸውም ዕዳ እየከፈሉ የሚኖሩ ከሆነ ማንም ደፍሮ ተበድሮ ኃብት በመፍጠር ራሱንና
ሃገሩን ለመርዳት ያለውን ተነሳሽነት ያኮላሸዋል። በመሆኑም የኪሣራ ሕጋችን ባለዕዳውን ከዕዳ ነፃ
የሚያደርግ ድንጋጌ ሊኖረው ይገባል።

ከዚህ በተጨማሪ በአንድ የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ነጋዴ ተብለው በተለዩ ሁለት አካላት መካከል አድልዖ
ሊኖር አይገባም። በንግድ ሕግ ውስጥ ነጋዴው የንግድ ማኅበር ከሆነ ያለበትን ዕዳ ሙሉ በሙሉ
ባይከፍልም ያለውን ንብረት ለዕዳ መክፈያ በማዋሉ ምክንያት የሚፈርስ በመሆኑ ነፃ ይሆናል። በአንፃሩ
ነጋዴው ግለሰብ በመሆኑ ያለውን ንብረት ለዕዳ መክፈያ ካዋለ በኋላም የሚያገኘው ገቢ ለዕዳ መክፈያ
መዋሉ ፍትሃዊ ስለማይሆን በሕጋችን ውስጥ ነፃ መውጣትን የሚመለከት ድንጋጌ ሊኖር ይገባል።

ይህንን የነፃ መውጣት ድንጋጌ ያለአግባብ የሚጠቀሙ ሰዎችን ለመለየት የወንጀል ሕጉ ላይ ያለው ድንጋጌ
እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ነጋዴው ነፃ የማይወጣባቸው የዕዳ አይነቶች ሊኖሩ ይገባል። የነኚህ የዕዳ አይነቶች
መኖር፣ ከዕዳ ነፃ በመውጣት እና ነፃ ባለመውጣት ካሉት ጽንፎች የኪሳራ ሕጋችንን የሚያወጣ ይሆናል።
እነዚህ ዕዳዎችም የሠራተኞች ያልተከፈለ ደመወዝ እና የስንብት ክፍያ፣ የግብር ዕዳ፣ እንዲሁም
ያልተከፈሉ የኪሣራ ሂደቱ ወጪዎች ሊሆኑ ይገባል።

56

You might also like