You are on page 1of 9

የትምህርት/ሥልጠና ውል

ይህ የትምህርት/የሥልጠና ዉል በኢ.ፌ.ዴ.ሪ.የጤና ሚኒስቴር ከዚህ በኋላ ዉል ሰጪ ተብሎ


በሚጠራዉ እና በአቶ/ወ/ሮ …………………………………………..ከዚህ በኋላ ዉል ተቀባይ
ተብሎ በሚጠራዉ መካከል ዛሬ..……………….ቀን…………………ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ
ተፈረመ፡፡
አንቀጽ 1

የዉሉ ዓላማ

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የጤና ሚኒስቴር ተቀጥረው የሚያገለግሉ ሰራተኞችን አስመልክቶ ሚኒስቴር


መስሪያ ቤቱ ባወጣዉ የትምህርት/ሥልጠና መመሪያ ቁጥር ሚያዚያ 2013 ዓ.ም መሠረት
ውል ተቀባይ የትምህርት/ሥልጠና ተጠቃሚ እንዲሆኑና ትምህርቱን/ሥልጠናዉን ካጠናቀቁ
በኋላ ለሚሰሩበት መ/ቤት የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል ነዉ፡፡
አንቀጽ 2

ስለ ተዋዋይ ወገኖች

1) ዉል ሰጪ………………………………

አድራሻ፣

ክ/ከተማ………………………..

ወረዳ…………………………….

ስልክ ቁጥር……………………..

2) ዉል ተቀባይ……………………………..
I. ጠቅላላ ሁኔታ
አድራሻ፣
ክ/ከተማ…………………………
ወረዳ…………………………….

የቤት ቁጥር……………………..

ስልክ ቁጥር፡- የቢሮ፡ ………………………

የቤት፡ ………………………

ሞባይል፡ ……………………

የጋብቻ ሁኔታ፡ …………………………….

II. የስራ ሁኔታ


የስራ ቦታ፡ ……………………………….. አድራሻ…………………………

የስራ ሁኔታ/ማዕረግ፡ ………………………

ወርሃዊ የገቢ መጠን፡ ……………………..

III. የትምህርት ሁኔታ


የትምህርት ክፍለ ጊዜ፡ ሀ) መደበኛ ለ) ሳንድዊች ሐ) የተልዕኮ/ኦንላይን መ) ከስራ ሰአት
ውጪ (ቅዳሜ እና እሁድ ጨምሮ)
ትምህርቱ የሚሰጥበት ቦታ፡ ሀ) ሀገር ውስጥ ለ) ውጪ ሀገር

IV. ትምህርቱ/ሥልጠናው የሚፈጀው ጊዜ ………………….


V. የሚጠበቅ የአገልግሎት ግዴታ …………………………
VI. ትምህርቱ የተገኘበት ሁኔታ
ሀ) በግል ጥረት የተገኘ ስኮላርሺፕ ለ) በመ/ቤቱ ስፖንሰርነት
አንቀጽ 3
የዉሉ የገንዘብ መጠን
እኔ የዉል ተቀባይ ከዉል ሰጪ ጋር የ…………………………….ብር የዉል ስምምነትን
በዛሬ ቀን…………………..…ፈፅሜያለሁ፡፡
አንቀጽ 4

የዉል ሰጪ ግዴታ

1) ውል ተቀባይ በትምህርት/ሥልጠና ላይ እያሉ አግባብነት ባለው መመሪያ መሠረት


አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
2) ውል ተቀባይ ትምህርቱን/ሥልጠናዉን አጠናቆ ሲመለስ በተማረበት የትምህርት
ዝግጅት መሰረት መ/ቤቱ መድቦ የማሰራት ግዴታ አለበት፡፡
አንቀጽ 5

የዉል ተቀባይ ግዴታ

ዉል ተቀባይ፡-
1) ለመማር በዉል የተስማማዉን የትምህርት/ሥልጠና መስክ ያለ ዉል ሰጪ ፈቃድ
መቀየር አይችልም፡፡
2) ትምህርቱን/ሥልጠናዉን በአግባቡ ይከታተላል፡፡
3) የትምህርት/ሥልጠና ጊዜዉን ያለበቂ ምክንያት ማራዘም አይችልም፡፡
4) አሳማኝ በሆነ ምክንያት የትምህርት/ሥልጠና ጊዜዉ የሚራዘምበት ሁኔታ ሲፈጠር
ጉዳዩን ከአስረጂ ሠነዶች ጋር በማያያዝ ለሰዉ ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ያቀርባል፡፡
5) ትምህርቱን/ሥልጠናውን እንዳጠናቀቀ ለውል ሠጪ ሪፖርት የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
6) ትምህርቱን/ሥልጠናውን እንዳጠናቀቀ ውል ሠጪ በሚመድብበት ቦታ ለ…………
ወራት/ዓመት ያህል ጊዜ ውል ሰጪ መ/ቤትን የማገልገል ግዴታ አለበት፡፡
7) ያለ በቂ ምክንያት ወይም ያለ ውል ሰጪ ቅድሚያ የጽሁፍ ስምምነት
ትምህርቱን/ሥልጠናውን በተገቢው ጊዜ ሳያጠናቅቅ ወይም የሚገባውን የአገልግሎት
ግዴታ ሳይወጣ ቢቀር፣ ውል ሰጪ ዉሉ ላይ የተጠቀሰዉን ገንዘብ እና ሌሎች ተያያዥ
ወጪዎች ከእነ ህጋዊ ወለዱ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
8) የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 7 ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ የአገልግሎት ግዴታዉን
ያልተወጣ እንደሆነ በፍትሐ ብሔር ህግ አንቀጽ 1889 መሠረት የዉሉን የገንዘብ
መጠን 50% ለዉል ሰጪ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
9) በዉል የገባዉን የአገልግሎት ግዴታ ተወጥቶ ያላጠናቀቀ የትምህርት/ሥልጠና ዕድል
ተጠቃሚ በሌላ ውድድር ላይ መሳተፍም ሆነ ሌላ ማንኛውንም ዓይነት ተመሳሳይ
የዉል ግዴታ መግባት አይችልም፡፡
10)ውል ተቀባይ በየስድስት ወሩ በትምህርት ገበታው ላይ ስለመሆኑ የአማካኝ ውጤት
ሪፖር ለውል ሰጭ የመላክ ግዴታ አለበት፡፡
አንቀጽ 6

የዉል ተቀባይ ባለቤት

እኔ አቶ/ወ/ሮ ………………………..የተባልኩ የዉል ተቀባይ ባለቤት፣ ባለቤቴ ይህን


ስምምነት እንድትፈፅም/እንዲፈፅም ተስማምቻለሁ፡፡
ፊርማ………………. ቀን……………….

አንቀጽ 7

ስለ ዋስትና

ውል ተቀባይ ከዚህ በታች ከተመለከቱት የዋስትና ዓይነቶች አንዱን በዋስትና መልክ


አቅርቧል፡፡

1) የንብረት ዋስትና
i. ተንቀሳቃሽ ንብረት
የንብረቱ አይነት …………………..
የንብረቱ ባለቤት ሙሉ ስም፡ ……………………….. አድራሻ፡- ከተማ ………..
ክፍለ ከተማ…………….. ወረዳ …………. የቤት ቁጥር …………. ስልክ ቁጥር
…………… የንብረቱ ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር …………………….
ii. የማይንቀሳቀስ ንብረት
የይዞታ ባቤት ስም …………………..
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- ከተማ ………………………. ክፍለ ከተማ
……………. ወረዳ ……………….. የቤት ቁጥር …………….. የካርታ
ቁጥር……………… ስልክ ቁጥር……………
የይዞታ ባለቤት የትዳር አጋር ስም………………….
አድራሻ፡- ከተማ …………. ክፍለ ከተማ ………… ወረዳ…………. የቤት ቁጥር
…………….. ስልክ ቁጥር …………………
2) የሰዉ ዋስትና
እኔ የዉል ተቀባይ ከላይ በፍቃዴ ተስማምቼ የገባኋቸውን ግዴታዎች ለመወጣት
…………ያህል ዋሶችን አቅርቤአለሁ፡፡ እነሱም፡-

ተ.ቁ የዋሶች ስም አድራሻ የጋብቻ ፊርማ


ክ/ከ ወረዳ የቤ.ቁ ስልክ ቁጥር ሁኔታ

1
2
3

አንቀጽ 8

የዋስትና መጠን

ዋሶች ውል ተቀባይ በውሉ የተጣለበትን ግዴታ ሳይወጣ ቢቀር የውል ተቀባይን ግዴታ
በአንድነት እና በነጠላ ለመወጣት እስከ ብር……………….. የሚደርስ ዋስትና ገብተዋል፡፡

አንቀጽ 9

የዋሶች ግደታ

1) ለውል ተቀባይ ዋስ ለመሆን በዚህ የውል ስምምነት ላይ ፊርማቸውን ያኖሩ ግለሰቦች


በአንድነትና በጋራ አላፊነት በህግ ፊት ተጠያቂ ናቸው፡፡
2) ከውል ተቀባዩ ጋር በአንድነትም ሆነ በተናጠል ለትምህርት/ሥልጠና የወጣውን ገንዘብ
ይከፍላሉ፡፡
3) ከላይ በዋስነት የቀረቡት ሰዎች በህግ ፊት ከውል ተቀባይ በአንድነትና በተናጠል ለውሉ
ተፈፃሚነት ተጠያቂ ናቸው፡፡ ይህም ሲባል ተዋዋዩ በውሉ መሠረት ሳይፈፅም ቢቀር
በማንኛውም ወቅት ውል ሰጪው ውል ተቀባይን ስለእዳው አስቀድሞ ለመጠየቅ
ሳይገደድ ሙሉ እዳውን ከውል ተቀባዩ ወይም ከዋሶች (በጋራ ወይም በተናጠል)
የመጠየቅ ወይም ክስ መስርቶ በአንድነት እና በነጠላ እዳውን የማስከፈል መብት
አለው፡፡
አንቀጽ 10

ስለ ዋስ ባለቤት

1) እኔ አቶ/ወ/ሮ ………………….. የዋስ ባለቤት የሆንኩ ግለሰብ ከዚህ በላይ ባለቤቴ


አቶ/ወ/ሮ …………….. በ……… ……….. ቀን 20…… ዓ.ም በገባው/በገባችው
ግዴታ መሠረት ለመፈፀም በዋስትናው ግዴታ በሙሉ ፍቃደኝነት የተስማማሁ
መሆኔን በፊርማዬ አረጋግጣለሁ፡፡
ፊርማ………………… ቀን ……………………..
2) እኔ አቶ/ወ/ሮ ………………….. የዋስ ባለቤት የሆንኩ ግለሰብ ከዚህ በላይ ባለቤቴ
አቶ/ወ/ሮ …………….. በ……… ……….. ቀን 20…… ዓ.ም በገባው/በገባችው
ግዴታ መሠረት ለመፈፀም በዋስትናው ግዴታ በሙሉ ፍቃደኝነት የተስማማሁ
መሆኔን በፊርማዬ አረጋግጣለሁ፡፡
ፊርማ …………………… ቀን ……………………..
3) እኔ አቶ/ወ/ሮ ………………….. የዋስ ባለቤት የሆንኩ ግለሰብ ከዚህ በላይ ባለቤቴ
አቶ/ወ/ሮ …………….. በ……… ……….. ቀን 20…… ዓ.ም በገባው/በገባችው
ግዴታ መሠረት ለመፈፀም በዋስትናው ግዴታ በሙሉ ፍቃደኝነት የተስማማሁ
መሆኔን በፊርማዬ አረጋግጣለሁ፡፡
ፊርማ …………………. ቀን ……………………..

አንቀጽ 11

ስለ መስማማት
እኛ ከዚህ በላይ በአንቀጽ 10 ላይ ስማችን የተጠቀሰው ዋሶች በአንድነት እና በነጠላ
አላፊነታችንን ለመወጣት ፊርማችንን አኑረናል፡፡ ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ግዴታዎች
የምንወጣ መሆናችንን በፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡
ስም ፊርማ

1ኛ ዋስ፡ ……………………………….. ……………………..

2ኛ ዋስ፡ ……………………………….. ……………………..

3ኛ ዋስ፡ ……………………………….. ……………………..

አንቀጽ 12

የውሉ አካል የተደረጉ ሰነዶች

ከዚህ የውል ስምምነት ጋር መያያዝ ያለባቸው ሰነዶች የሚከተሉት ናቸው፡፡


1) ከሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት የተላከ ደብዳቤ፣
2) የዋስትና ግዴታ እንዲገቡ የተፃፈ ደብዳቤ፣
3) ንብረት ለሚያሲዙ የቤት ካርታ ቅጂ እና የእገዳ ደብዳቤ ዋናውን እና አራት ቅጂ፣
4) የዋስትና ግዴታ ገቢዎች ከመ/ቤቶቻቸው የደመወዝ መጠን እና ሌሎች መረጃዎችን
አጽፈው ያመጡበት ሰነድ፡፡
አንቀጽ 13

የዉሉ ገዥ ሕግ

የዚህ ዉል አተረጓጎም እና አፈፃፀም አግባብነት ባለዉ የኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ይሆናል፡፡

አንቀጽ 14

ዉሉ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

1. ይህ ዉል በተዋዋይ ወገኖች ከተፈረመበት ቀን አንስቶ ውል ተቀባይ የውል ግዴታውን


ሙሉ በሙሉ እስከሚወጣ ድረስ የፀና ይሆናል፡፡
2. ተዋዋይ ወገኖች ፊርማቸውን ያስቀመጡት በተለያየ ቀን ከሆነ መጨረሻ ላይ
የተመለከተውን ቀን ውሉ የተፈረመበት ቀን እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

አንቀጽ 15

የውሉ ቅጂ ብዛት እና አያያዝ

ይህ የውል ሰነድ በአራት ቀጂ ተዘጋጅቶ 1 ቅጂ ለውል ተቀባይ፣ 1 ቅጂ በመ/ቤቱ የሰው ሀብት


አስተዳደር ዳይሬክቶሬት፣ 1 ቅጂ የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት እና 1 ቅጂ በሕግ ጉዳዮች
ዳይሬክቶሬት ይቀመጣል፡፡
አንቀጽ 16

የዉል ተቀባይ እና የዉል ሰጪ ስለመስማማታቸው

የዉል ተቀባይ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ለመወጣት በመስማማት ከዉል ሰጪ ጋር


መስማማታቸውን በፊርማቸው አረጋግጠዋል፡፡

ስለዉል ሰጪ የዉል ተቀባይ

ስም…………………………………. ስም………………………………

ፊርማ ……………………………… ፊርማ ………………………….

ቀን ………………………………… ቀን …………………………….

አንቀጽ 17

ስለ ምስክሮች

እኛ ስማችን ከዚህ በታች የተገለፀው ምስክሮች የዉል ሰጪ፣ የዉል ተቀባይ፣ የዉል ተቀባይ
ባለቤት እንዲሁም ዋሶቻቸው እና ባለቤቶቻቸው ይህን ውል በፍቃደኝነት መፈረማቸውን
መመልከታችንን በፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡
በእለቱ የነበሩ ምስክሮች ስም እና ፊርማ
ስም ፊርማ ክ/ከተማ ወረዳ የቤት ቁጥር

1………………………………፣……………..፤……………….፤…………….፣ …………….

2……………………………...፤……………..፤……………….፤……………..፤ …………….

3……………………………...፤……………..፤……………….፤……………..፤ …………….

You might also like