You are on page 1of 5

የውል አይነት፡-

አንቀጽ 1

ተዋዋይ ወገኖች

ይህ ውል በዚህ ውል ውስጥ የውል ሰጪ እየተባለ በሚጠራው አቶ ከበደ

አድራሻ አ/አ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ….. የቤት ቁጥር_____ ስልክ ቁጥር

በዚህ ውል የውል ተቀባይ እየተባለ በሚጠራው ኢንጅነር ብሩክ ስራው አድራሻ አ/አ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ
09 የቤት ቁጥር 483 ስ/ቁጥር 0913841832 መካከል 15/06/2010 ዓ.ም ተፈርሟል፡፡

አንቀጽ 2

1.1 የስራ ዝርዝርና ነጠላ ዋጋው ከዚህ የውል ስምምነት ጋር ተያይዞ በቀረበው ዶክመንት መሰረት
የብር መጠን 35927 (ሰላሳ አምስት ሺ ዘጠኝ መቶ ሃያ ሰባት ብር ) ነው፡፡

አንቀጽ 3

የውል ይዘት እና የስራዉ አይነት

ይህ ውል የተፈፀመው በውል ሰጪ የውሃ እና የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ሲሆን በውል ተቀባይ በኩል ደግሞ
ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ ግንባታ ሰርቶ ማስረከብ ነው፡፡

አንቀጽ 4

የግንባታ ሥራዎች ሁኔታ

 ጥራቱን የጠበቀ ግንባታ ሰርቶ ማስረከብ


 ጥራቱንና ደረጃውን በመጠበቅ በባለሙያ ማሰራት ይሆናል፡፡

አንቀጽ 5

የተዋዋይ ወገኖች ግዴታዎች


5.1 የውል ሰጪ ግዴታዎች

5.1.1 በአንቀጽ 8 የተቀመጠውን የክፍያ አፈፃፀም መሰረት በማድረግ ክፍያ መፈፀም፣

5.1.2 ግንባታው ሲጠናቀቀ መረከብ፣

5.1.3 ለሚፈጠሩ ችግሮች በባለቤትነት ችግሩን መፍታት

5.1.4 ግንባታው ሲገነባ የአማካሪው ክትትልና ቁጥጥር ባለሙያ ከስር ከስር ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፡፡

5.2 የውል ተቀባይ ግዴታዎች

5.2.1 በአንቀጽ 4 የተገለፁትን ተግባራት ሲያከናውን ጥራትና ደረጃውን የጠበቁ ግብአቶችን መጠቀም
ይኖርበታል፣

5.2.2 በዚህ ውል በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሥራውን አጠናቆ ለውል ሰጪ ማስረከብ፣

5.2.3 ውሉን በራሱ ምክንያት ካፈረሰ በፍታሃብሄር ህግ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

5.2.4 በውል ሰጪ የሚቀርበው የግንባታ ማቴሪያል ጥራቱና ደረጃውን የጠበቀ መሆን ይኖርበታል፡፡

5.2.5 በውል ላይ የተጠቀሰው ልኬት አንሶ ቢገኝ የዋጋ ልዩነቶችን ማቻቻል፡፡

5.2.6 ዉል ተቀባይ ለሚሰራዉ ማንኛዉም የግንባታ ስራ በአማካሪው ባለሙያ እዉቅና ስር ማለፍ ይኖርበታል፡፡

አንቀጽ 6

የተዋዋይ ወገኖች መብቶች

6.1 የውል ሰጪ መብቶች

6.1.1 በግንባታው ላይ የጥራት ችግር ሲኖር እነዚህን በመለየት ውል ተቀባይ በአማካሪው ቁጥጥር ባለሙያዎች
በሚቀርበው መመሪያ እንዲያስተካክል ማሳወቅ፡፡

6.1.2 በዚህ ውል በተቀመጠው መረካከብያ ጊዜ የውሃ አና ፍሳሽ መሰመር ዝርጋታ ሥራውን ሙሉ በሙሉ
ተጠናቆ መረከብ፣

6.1.4 ውል ሰጪ ሥራውን የመቆጣጠርና ስለ ስራው ውሳኔዎችን የማስተላለፍ መብት አለው፡፡


6.2 የውል ተቀባይ መብቶች

6.2.1 በአንቀጽ 8 በተቀመጠው የክፍያ አፈፃፀም መሰረት ክፍያ ማግኘት መብት ይኖራል፡፡

አንቀጽ 7

የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ (የትቦ ቀበራ) ስራ የማጠናቀቂያ ጊዜ

7.01 የ ውሀ እና ፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ስራ ማጠናቀቂያ ጊዜ ይህ ውል ከተፈረመበት ቀን አንስቶ_______


ቀናት የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

7.1 የክፍያ ሁኔታ

የፍሳሽ መስመር ዝርጋታየክፍያ ሁኔታ

7.1.1 የግንባታው ስራ በመሰራት ላይ እያለ 20% የመሬት ላይ የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ (Upvc) ሲያጠናቅቅ
የሰራውን ስራ ተለክቶ የግንባታ ክፍያ 7185.40 ሰባት ሺ አንድ መቶ ሰማንያ አምስትብር ከ አርባ ሳንቲም
ይከፈለዋል፡፡

ሁለተኛ ክፍያ 10%የ 1 ኛ እና የ 2 ኛ ወለል የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ (Upvc) ስራዎችን ሲጨርስ ስራው
ተለከክቶ ሁለተኘው ክፍያ 3592.70 ሶስት ሺ አምስት መቶ ዘጠና ሁለትብር ከ ሰባ ሳንቲም ይከፈለዋል ፡፡

ሶስተኛ ክፍያ 30% የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ (Upvc) ማለቁ ሲረጋገጥ በአማካሪውታይቶ የሶስተኛ ክፍያ
10778.10 አስር ሺ ሰባት መቶ ሰባ ስምንትብር ከ አስር ሳንቲም ይከፈለዋል፡፡

የውሃ መስመር ዝርጋታ የክፍያ ሁኔታ

የግንባታው ስራ በመሰራት ላይ እያለ 15% የመሬት ላይ የውሃመስመር ዝርጋታ (ppr) ሲያጠናቅቅ የሰራውን
ስራ ተለክቶ የግንባታ ክፍያ 5389.05 አምስት ሺ ሶስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ብር ከ አምስት ሳንቲም
ይከፈለዋል፡፡

ሁለተኛ ክፍያ 10%የ 1 ኛ እና የ 2 ኛ ወለል የውሃመስመር ዝርጋታ (ppr)ስራዎችን ሲጨርስ ስራው ተለከክቶ
ሁለተኘው ክፍያ 3592.70 ሶስት ሺ አምስት መቶ ዘጠና ሁለትብር ከ ሰባ ሳንቲም ይከፈለዋል ፡፡
ሶስተኛ ክፍያ 35% የውሃመስመር ዝርጋታ (ppr)ስራዎችን ማለቁ ሲረጋገጥ በአማካሪውታይቶ የሶስተኛ ክፍያ
12574.45 አስራ ሁለትሺ አምስት መቶ ሰባ አራት ብር ከአርባ ሳንቲም ይከፈለዋል፡፡

7.2 የክፍያ አፈፃጸም

7.2.1 በአንቀጽ 7 ንኡስ አንቀጽ 7.1 የተገለጸው አጠቃላይ ገንዘብ 35927 (ሰላሳ አምስት ሺ ዘጠኝ መቶ ሃያ
ሰባት ብር ) በሶስተኛ ዙር የሚከፈል ይሆናል፡፡

አንቀጽ 8

8.1 ውል ተቀባይ የተሰራውን ስራ መጠን የልኬት ሰነድ ስያቀርብ የቀረበዉ የልኬት ሰነድ በዉል ሰጪዉ
ሲረጋገጥ በተሰራዉ ስራ ልክ ክፍያ ይፈጸማል፡፡

8.2 ዉል ሰጪዉ የተሰራዉን ስራ መጠን ደረጃዉን ጠብቆ የተሰራ መሆኑን ልኬት በተገቢዉ ሁኔታ የተከናወነ
መሆኑን በሚመለከታቸዉ አማካሪ ባለሙያዎች ተረጋግጦ ርክክብ ከተፈፀመ በኋላ የመጨረሻ ክፍያ
ይፈጸማል፡፡

አንቀጽ 9

ውል የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች

9.1 ሁለቱም ወገኖች ውል እንዲቋረጥ ሲስማሙ፣

9.2 በፍትሃብሔር ህግ ቁጥር 1792 እና 1793 መሠረት በህግ ተቀባይነት ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት
በሁለቱም ወገኖች በኩል ሲያጋጥም፣

9.3 በፋይናንስ እጥረት፣ በክህሎት እና በግንባታው ላይ የጥራት ችግር ካለ፣

9.4 ግንባታውን በውል ጊዜ ወይም በወቅቱ ካላጠናቀቀና ስራዉ ደረጃዉን ያልጠበቀ ከሆነ ዉል ሰጪ
እንዲያስተካክል የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት አሻሽሎ ካልተገኘ ዉሉ ሊሰረዝ ይችላል ዉል ተቀባይ
ላወጣዉ ወጪ ዉል ሰጪ ተጠያቂ አይሆንም፡፡

አንቀጽ 1 ዐ
የቅጣት ጊዜ

በኮንስትራክሽን አንቀጽ 47 መሠረት በእያንዳንዱ የዘገየበት ቀን 1/1000 የቅጣት ውሣኔ ተሰጥቷል፡፡

አንቀጽ 11

የውል ህጋዊነት

ይህ ውል በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች በፊርማ ሲረጋገጥ ብቻ ህጋዊነትና ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡

አንቀጽ 12

ውል ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

ይህ የውል ሰነድ ሁለታችንም ተዋዋይ ወገኖች አንብበን የውሉ ቃል የሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች ፈቃድ እና
ፍላጎትን ያሟላ መሆኑን ተቀብለን እንደ ውሉ ለመፈፀም ዛሬቀን---------------------ዓም በፊርማችን
ካፀደቅንበት ጊዜ አንስቶ በአንቀጽ 7 የተገለፀው የመረካከብያ ጊዜ ድረስ ውል ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡

የውል ሰጪ የውል ተቀባይ

ስም ……………………………….. ስም ……………………………

ፊርማ …………………………… ፊርማ …………………………….

ቀን ………………………………. ቀን………………………………

You might also like