You are on page 1of 88

 

 በጅማደሴ ከተማ የኢትዮ ቴሌኮም 3B+G+Mez+5 ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ


ለመስራት

በኢትዮ ቴሌኮም

እና

በኤፍ.ኢዛምራ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ኩባኒያማህበር

የተደረገ የግንባታ ውል

ሰኔ 2010

አዲስ አበባ

የግዥ ቁጥር፡-----------

1 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ግንቦት 2010

አዲስ አበባ

የግዥ ቁጥር፡-----------

ይህ ውል ዛሬ (---------------------------------ቀን 2010 ዓ.ም.) በኢትዮ ቴሌኮም አድራሻ አዲስ አበበ፣ አበባ፣ ልደታ
ክ/ከተማ ወረዳ፤ 10 ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1047 (ከዚህ በኋላ “አሰሪ” እየተባለ የሚጠራ) በአንድ በኩል እና

በኤፍ ኢ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ .. አድራሻ አ.አ ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11… የቤት ቁጥር …..ስልክ ቁጥር
+251-116290318/25 ፋክስ ቁጥር+251 116290346 ፖ.ሳ.ቁ. 100671, አ.አ (ከዚህ በኋላ “ሥራ ተቋራጭ” እየተባለ
የሚጠራ) በሌላ በኩል በመሆን፣

(ሀ) አሰሪው በጅማ ከተማ የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለማሰራት (ከዚህ በኋላ “የግንባታ ሥራዎች” እየተባሉ
የሚጠሩ) በመፈለጉ እና ሥራ ተቋራጩም የግንባታ ሥራዎቹን ለማከናወን ፍቃደኛ በመሆኑ
(ለ) ሥራ ተቋራጩ ተፈላጊውን የሙያ ችሎታ፣ ሠራተኞችና የቴክኒክ ዕውቀት በመጠቀም የተጠየቁት የግንባታ
ሥራዎች በዚህ የውል ሁኔታዎች መሠረት ለመፈፀም በመስማማቱ ሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች እንደሚከተለው
ተዋውለዋል፡፡

1. ስምምነት

1.1 በዚህ ውል ውስጥ ቃላቶችና አገላለፆች በተጠቀሰው የውል ሁኔታዎች ውስጥ የተሰጣቸውን ተመሳሳይ
ትርጉሞች ይኖራቸዋል።
1.2 የሚከተሉት ሰነዶች የዚህ ውል አካል ሆነው የሚቆጠሩ ይሆናል፡-
1. አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች

2. ልዩ የውል ሁኔታዎች ከነአባሪዎቹ

2 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
3. ከድርድር በኋላ የተከለሰ የቴክኒክ እና የዋጋ መወዳደሪያ ሀሳብ ከግንባታ ስራዎች ዝርዝር (Bill
of Quantities) ጋር
4. የንድፍ ሰነዶች (Drawings)

5. (ሀ)ለነጠላ ዋጋ ውሎች: የግንባታ ስራዎች ዝርዝርና የዋጋ መግለጫ (የስሌት ስህተቶች


ከታረሙ በኋላ)
(ለ)ለጥቅል ዋጋ ውሎች: የጥቅል ዋጋው ዝርዝር (የስሌት ስህተቶች ከታረሙ በኋላ)
6. በውሉ መሰረት የሚሰጡ የመሃንዲስ ትዕዛዞች

7. የስራ ፕሮግራም

8. የፕሮጀክት ስራው ዝርዝር


1.3 አሰሪው ለሥራ ተቋራጩ የሚፈጽመውን ክፍያ ግምት ውስጥ በማስገባት በዚህ ውል ውስጥ
እንደተመለከተው ሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራዎቹን ለማከናወንና በውሉ ድንጋጌዎች መሠረት
ግድፈቶችን ለማረም ከአሰሪው ጋር ግዴታ ገብቷል፡፡
አሰሪው ሥራ ተቋራጩ ለሚተገብራቸው የግንባታ ሥራዎች፣ እንዲሁም ግድፈቶች ለማረም ለገባው ግዴታ የውሉን
ዋጋ ተ.እ.ታን ጨምሮ ብር 247,947,372.79 (ሁለት መቶ አርባ ሰባት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ሰባት ሺ ሶስት
መቶ ሰባ ሁለት ብር ከ ሰባ ዘጠኝ ሳንቲም) ወይም በውሉ ድንጋጌዎች መሠረት ተከፋይ የሚሆነውን መጠን በተባለው
ጊዜና ሁኔታ ለመክፈል ግዴታ ገብቷል፡፡በክፍያ ወቅት አሰሪ 2% ተቀናሽ የገቢ ግብርን ቀንሶ ማሰቀረት ማስቀረት
አለበት፡፡ }ªªÃ ¨Ñ•‹ ÃI”” ¨<M ueT†¨< ›p×Ý uSð[U u›=ƒÄåÁ IÓ Sc[ƒ ¨<M Se`}ªM::

ስለ አሰሪው ስለ ስራ ተቋራጭ

ስም ፡- ---------------------- ስም -------------------------------

ኃላፊነት፡--------------------- ኃላፊነት፡- -----------------------

ቀን፡- ----------------------- ቀን፡- -----------------------------

ፊርማ፡- ----------------------- ፊርማ ፡- ………………….

ምስክሮች በአሰሪዉ በኩል ምስክሮች በስራ ተቋራጭ በኩል


1. ------------------------ 1. ---------------------------
3 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ
ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
2. ------------------------ 2. ------------------------------

3. ------------------------- 3. ------------------------------

በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ግዢ አጠቃላይ የውል ሁኔታ

1. ትርጉም
1.1 በዚህ አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች የተጠቀሱት ርዕሶች የውሉን ትርጉም አይወስኑም፣ አይለውጡም ወይም
አይቀይሩም፡፡
1.2 ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ቃላቶች እና ሐረጎች በዚህ ውል ውስጥ የሚከተለው ትርጉም ይኖራቸዋል፡፡
ሀ. የሥራ መጠን በነጠላ ዋጋ ውል ውስጥ የሚተገበሩ የግንባታ ሥራዎችን ዝርዝር በመያዝ የእያንዳንዱን ብዛት (መጠን) እና
ዝርዝር ነጠላ ዋጋ የሚያሳይ ሰነድ ማለት ነው፡፡

ለ. መጠናቀቅ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 87 መሠረት የውሉ ግዴታዎች በሥራ ተቋራጩ መሟላት ማለት
ነው፡፡

ሐ. የውል ሰነድ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ውስጥ የተዘረዘሩ ሰነዶች፣ ሁሉንም ተያያዦችና ዕዝሎች ጨምሮ የተጠቀሱ
ሁሉንም ሰነዶች የሚያካትት እና የተደረጉ ማሻሻያዎች ካለም የሚጨምር ሰነድ ማለት ነው፡፡

መ. የውል ስራ ከውሉ ጋር በተያያዙ ማናቸውም ተግባር የሥራ ተቋራጩ ሕጋዊ ወኪል እንደሆነ ለአሰሪው በሥራ
መሪ ተቋራጩ በጽሁፍ የተገለጸ ግለሰብ ማለት ሲሆን እንዲሁም በዚህ መንገድ ውክልና የተሰጠውን ሌላ
ተወካይም ይጨምራል፡፡

ሠ. የውል ዋጋ በዚህ ዉል ላይ የተገለጸው ዋጋ ሆኖ በውሉ መሰረት ለተሰራ ስራ የሚፈከል መጠን እንዲሁም አሰሪዉ
ለሥራ ተቋራጩ በውሉ መሠረት መክፈል ይገባዋል ተብሎ በመጨረሻው የሂሳብ ሰነድ የተረጋገጠው ዋጋ
ነው፡፡

ረ. ውል በአሰሪው እና በሥራ ተቋራጩ መካከል የተፈጸመ ገዢነት ያለው የውል ስምምነት ሲሆን የተጠቀሱ የውል
ሰነዶችን ሁሉንም ተያያዦችንም አባሪዎችንና በማጣቀሻ ውስጥ የተካተቱ ሰነዶችንም ይጨምራል፡፡

ሰ.የሥራ ተቋራጭ የግንባታ ሥራዎችን ለአሰሪው የሚያቀርብ የተፈጥሮ ወይም የሕግ ሰው ማለት ነው፡፡

ሸ. ቀን የቀን መቁጠሪያ ቀን ማለት ነው፡፡

ቀ. ጉድለት በውሉ መሠረት ያልተጠናቀቀ/ግድፈት ያለበት ማንኛውም የግንባታ ሥራ ማለት ነው፡፡

4 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
በ.የጉድለቶች የጊዜያዊ ርክክብ ቀንን ተከትሎ ያለ በልዩ የውል ሁኔታዎች ውስጥ የተጠቀሰ ጊዜ ማለት ሲሆን በዚህ ጊዜ
ተጠያቂነት ውስጥ በመሐንዲሱ ትዕዛዝ መሠረት የሥራ ተቋራጩ ሥራዎችን ማጠናቀቅና ጉድለቶችና ስህተቶችን
ጊዜ ማረም ይኖርበታል፡፡

ተ. ንድፍ በውሉ ውስጥ የተካተቱ እና በአሰሪው (ወይም እሱን በሚወክል) በውሉ መሠረት የተጨመሩ እና የተሻሻሉ
የግንባታ ሥራዎች ንድፎች ማለት ሲሆን በመሐንዲሱ የፀደቁ የግንባታ ሥራዎችን ለመፈጸም
የሚያገለግሉ ስሌቶችና መረጃዎችንም ይጨምራል፡፡

ቸ. ብቁ ሀገሮች በጨረታ ሰነዶች በጨረታው ለመተሳፍ ብቁ ናቸው ተብሎ የተዘረዘሩ ሀገሮች ወይም ግዛቶች ማለት ነው፡፡

ኀ. መሐንዲስ በልዩ የውል ሁኔታዎች ውስጥ የተሰየመ ወይም በአሰሪው የግንባታ ሥራዎችን እንዲቆጣጠር፤ እንዲከታተል
እና በሥራ ላይ የዋሉ ቁሶችን የትግበራ ጥራት እንዲፈትሽና እንዲመረምር በጽሑፍ የተመደበ ግለሰብ
ወይም የግለሰቡ ወኪል ማለት ነው፡፡

ነ.የግንባታ የግንባታ ሥራዎችን ለማከናወን ወደ ግንባታ ቦታው የመጡ የሥራ ተቋራጩ ማሽኖች፤ ተሽከርካሪዎች፤
መሣሪያ የተለያዩ መሣሪያዎች፤ መለዋወጫዎችና ሌሎች ማናቸውም ነገሮች ማለት ነው፡፡

ኘ.የመጨረሻ በጉድለት ተጠያቂነት ጊዜው መጨረሻ የሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራዎች የመገንባት የማጠናቀቅ እና
ርክክብ የመጠገን ግዴታዎችን እንደተወጣ የሚገልጽ በመሐንዲሱ/በአሰሪዉ የሚሰጥ/ጡ ሰርተፍኬት/ቶች ናቸው፡፡
ሰርተፊኬት

አ.አጠቃላይ የውል በልዩ የውል ሁኔታ ወይም የውል ስምምነት እስካልተሻሻለ ድረሰ የውሉን ትግበራ የሚገዛ የአስተዳደር፣
ሁኔታዎች የፋይናንስ፣ ህጋዊና የቴክኒካል አንቀጾች የሚገዙበትን አጠቃላይ የውል ድንጋጌዎች የሚያስቀምጥ ሰነድ
“አውሁ” ማለት ነው፡፡

ከ.መልካም ማለት በውሉ ውስጥ በተካተቱት ሁኔታዎች፣ እንዲሁም አግባብነት ባላቸው በንግድ ማህበራት በታተሙ የንግድ ህጎች
የኢንዱስትሪ መሰረት በአገልግሎቶች አቅርቦት ጊዜ ከአቅራቢው የሚጠበቅ የክህሎት ደረጃ፣ ጥንቃቄና አርቆ አስተዋይነት ማለትነው፡፡
ተግባር

ወ. መንግሥት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግሥት ማለት ነው፡፡

5 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ዐ. በጽሑፍ በእጅ ወይም በታይፕ የተመዘገበ ወይም በኢሜል የተፃፈ ሰነድን የሚያካትት ተብሎ ሊተረጐም ይችላል፡፡

ዘ.የታሰበ (የታቀደ) የሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራውን የሚያጠናቅቅበት ቀን ማለት ነው፡፡ የግንባታ ሥራ የሚጠናቀቅበት ቀን
የማጠናቀቂያ ቀን በልዩ የውል ሁኔታዎች ላይ ይመለከታል፡፡ የታቀደ የማጠናቀቂያ ቀን የማራዘሚያ ጊዜ ወይም የማጣደፊያ
(ቶሎ የመጨረስ) ትዕዛዝ በመስጠት በመሐንዲሱ ብቻ ሊቀየር (ሊሻሻል) ይችላል፡፡

የ.የመዘግየት በውሉ ውስጥ የሥራ ተቋራጩ በውሉ በተጠቀሰው የማጠናቀቂያ ጊዜ መሠረት ውሉን ሳይፈጽም ሲቀር
ቅጣት ለአሰሪው መክፈል የሚገባው የቅጣት ገንዘብ ነው፡፡
ደ. ቁሳቁሶች ሥራ ተቋራጩ በግንባታ ሥራው የሚጠቀምባቸው አቅርቦቶች (አላቂ ዕቃዎችን ጨምሮ) ማለት ነው፡፡

ጀ. አባል የሽርክና ወይም የጊዚያዊ ህብረት ወይም የማህበር አባል ማለት ሲሆን አባለቶች ማለት እነኚህ በሙሉ
ማለት ነው፡፡
ገ. ወር የ ቀን መቁጠሪያ ወር ማለት ነው፡፡

ጠ. ወገን አሰሪው ወይም የሥራ ተቋራጭ ማለት ሲሆን የተፈቀደላቸውን ወራሾችንም ይጨምራል፣ እንዲሁም
“ወገኖች” ማለት ሁለቱንም ማለት ነው፡፡

ጨ. መሳሪያ የግንባታ ማከናወኛ መሣሪያዎችና ቁሶች በህግ ወይም በኢትዮጵያ ህግ በግንባታ የሚታቀፍ ከሆነ ሥራው
(Plant) ቋሚ አካል የሚሆነውን ሳይጨምር በግንባታ ቦታው ላይ ጊዜያዊ መዋቅር ማለት ነው፡፡

ጸ. የዋጋ ዝርዝር በሥራ ተቋራጩ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተሞልቶ የሚቀርብ ወይም በግምገማ ወቅት የተለወጠውን ሁኔታ
መግለጫ የያዘ የዋጋ ዝርዝር ሠንጠረዥ ሲሆን የአጠቃላይ ዋጋውን ትንታኔ የሚጨምር ነው፡፡

ፀ. ጊዜያዊ ድምር በውሉ ውስጥ ለግንባታ ሥራዎች ወይም ለዕቃዎች፣ ግንባታ ቁስ፣ መሣሪያዎች ወይም አገልግሎቶች
ወይም መጠባበቂያ የተካተተ ድምር ሲሆን እንደ መሐንዲሱ ትዕዛዝ በሙሉ ወይም በከፊል ጥቅም ላይ
የሚውል ወይም በጭራሽ በጥቅም ላይ የማይውል ማለት ነው፡፡

ፈ.አሰሪ ኢትዮ ቴሌኮም ነው፡፡

ፐ. የግንባታ ቦታ በአሰሪው የግንባታ ሥራ እንዲካሄድበት የተሰጠ ቦታ እና በውሉ የግንባታ ቦታው አካል ተደርገው የተጠቀሱ
ሌሎች ቦታዎች ማለት ነው፡፡

6 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ሀሀ. ልዩ የውል ከውል ስምምነቱ ጋር ተያይዞ ውሉን የሚገዛ እና በነዚህ አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ላይ የበላይነት ያለው
ሁኔታዎች ሰነድ ነው፡፡
ልውሁ

ለለ. በውል ውስጥ የተዘረዘሩ ፍላጎቶቹን እና/ወይም ከግንባታ ሥራዎች አቅርቦት አንፃር የዘረዘሩ የግንባታ
እስፔሲፊኬሽን ዘዴዎች እና ግብዓቶች እና/ወይም ሌላ ጥቅም የሚሰጡ ወይም ሊሳኩ የሚገባቸውን ውጤቶችን
የሚያካትት የግንባታ ሥራዎች ዝርዝር ማለት ነው፡፡

ሐሐ.ስራ በልዩ የውል ሁኔታዎች ላይ የሚገለፅ ቀን ሲሆን የሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራዎችን መተግበር (መፈጸም)
መጀመሪያ ቀን የሚጀምርበት ቀን ነው፡፡

መመ.ንዑስ ሥራ በውሉ ውስጥ የተካተቱ የግንባታ ሥራዎችን በከፊል በግንባታ ቦታው የሚሠራውን ጭምር ለማከናወን
ተቋራጭ ከሥራ ተቋራጩ ጋር ውል ያለው የተፈጥሮ ሰው፣ የግል ወይም መንግሥታዊ አካል ወይም የነዚህ ውህደት
እና የህግ ወራሾቻቸው ወይም የተፈቀደላቸው ወኪሎች ማለት ነው፡፡

ሠሠ. ሶስተኛ ከአሰሪው ፤ሥራ ተቋራጩ እና ንዑስ ሥራ ተቋራጩ ሌላ የሆነ ግለሰብ ወይም አካል ማለት ነው፡፡
ወገን

ረረ.የግንባታ ከሕንፃ፣ መንገድ ወይም ወደ ግንባታ መዋቅሮች ጋር የተያያዙ ግንባታዎች፣ መልሶ


ሥራዎች ግንባታዎች፣ ማሻሻያዎች፣ ማፍረስ፣ መጠገን፣ ማደስ ማለት ሲሆን ከግንባታ ሥራዎቹ ዋጋ
እስካልበለጡ ድረሰ ከግንባታ ሥራው ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን ያካትታል፡፡

2. ኃላፊነት ስለመስጠት

2.1. አሰሪው ለ ሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራ እንዲሰራ ኃላፊነት ሲሰጠው፤


(ሀ) ስራ ተቋራጩ በውሉ አፈጻጸም በማንኛውም ወቅት ሙያዊና ትህትና በተሞላበት ሁኔታ የአሰሪውን
መልካም ገፅታ በማያጎድፍ መልኩ መሆን አለበት፡፡
(ለ) ሥራ ተቋራጩ የውሉ ሁኔታዎችና የፍላጎት መግለጫዎችን በጥንቃቄና በትክክል ይፈጽማል፡፡
(ሐ) ሥራ ተቋራጩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የወጡትን ህጎችና ደንቦች
እንዲሁም መልካም የኢንዱስትሪ ተግባር የሚፈቅደውን ሁሉ ይከተላል፡፡
(መ) ሥራ ተቋራጩ በየጊዜው በሚመለከተው ባለስልጣን እየተሻሻሉ የሚወጡትን ፖሊሲዎች፣ ህጎችና
ስነስርአቶች ያከብራል፡፡

7 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
(ሠ) ሥራ ተቋራጩ በአለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በኢትዮጵያ የጥራትና ደረጃዎች ባለስልጣን የሚወጡትን የጥራት
ደረጃዎች ያከብራል፡፡
(ረ) ሥራ ተቋራጩ በውሉ ዋጋና በዚሁ አንቀጽ የተጠቀሱትን የሀላፊነት አሰጣጥ ቃሎችና ሁኔታዎች ያከብራል፡፡

3. የተዋዋይ ወገኖች ግንኙነት

እዚህ ውስጥ የተካተቱት ማናቸውም ነገሮች (ነጥቦች) በአሰሪው እና በሥራ ተቋራጩ መካከል ያሉ ግንኙነቶች በጌታና ሎሌ ወይም
በአለቃ እና ምንዝር እንደተደረጉ መቆጠር የለባቸውም፡፡ በዚህ ውል መሠረት የሥራ ተቋራጩ የሠራተኞቹንና የንዑስ ሥራ
ተቋራጮችን ሙሉ በሙሉ የመቆጣጠር ሥልጣን አለው፡፡ የግንባታ ሥራውን ማከናወን እና በእነሱና እነሱን በመወከል ለተሰሩ
የግንባታ ሥራዎች ሙሉ ኃላፊነት አለበት፡፡ የሥራ ተቋራጩ በአሰሪው ስም ምንም ዓይነት ኃላፊነት መውሰድ ወይም ምንም ዓይነት
ውል ወይም ግዴታ መግባት የለበትም፡፡

4. ተገቢ ጥንቃቄ

4.1. ሥራ ተቋራጩ የሚከተሉትን ጉዳዮች መገንዘብ እና ማረጋገጥ ይገባዋል


(ሀ) በአሰሪው ወይም ተወካይ የሚሰጠውን መረጃ ትክክለኛነት በተመለከተ ራሱን ለማርካት ተገቢ
የሆነ ማጣራት ማከናወን ይገባዋል፡፡
(ለ) ውሉ ተግባራዊ ከሚሆንበት ቀን በፊት ሁሉንም ተገቢነት ያላቸው ጥያቄዎች ለ አሰሪው አካል ማቅረቡን
ማረጋገጥ አለበት፡፡
ሐ) ውሉ ውስጥ የገባው ራሱ ባደረጋቸው ተገቢ የሆኑ ጥንቃቄዎች በመተማመን ብቻ መሆን አለበት፡፡
4.2. ሥራ ተቋራጩ የሥራውን አከባቢ በመመርመር ለአሰሪው አገልግሎቱን ለመስጠት አመቺ አለመሆኑን በማረጋገጥ
መግለጽ አለበት፡፡ ከዚያም የሥራውን አከባቢ ለማሻሻል መፍትሔ በማቅረብ፤ የጊዜ ሰሌዳ በማዘጋጀትና ተያያዥ
ወጪውን በማውጣት በውሉ መሠረት ሥራው ከመካሄዱ በፊት ቅድመ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለበት፡፡
4.3. ሥራ ተቋራጩ የሥራውን ቦታ ለመመርመር ካልቻለ ወይም አስፈላጊውን የመፍትሔ እርምጃ በማዘጋጀት በአንቀጽ
4.2 መሠረት ለአሰሪው አስቀድሞ ካላሳወቀ ከአሰሪው ማንኛውንም ተጨማሪ ወጪ ወይም ክፍያ የመጠየቅ መብት
የለውም፡፡ እንዲሁም ኃላፊነቱ የሚወድቀው በሥራ ተቋራጩ ላይ ይሆናል፡፡ ያለ አሰሪው የቅድሚያ የጽሑፍ
ፈቃድ ሥራ ተቋራጩ ተጨማሪ ወጪ ወይም ክፍያ ማውጣት የለበትም፡፡
4.4. ከተገቢ ጥንቃቄ ጋር በተያያዘ የሚነሱ አለመግባባቶች በኢትዮጵያ ህግ መሰረት የሚፈቱ ይሆናል፡፡

8 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
5. ማጭበርበርና ሙስና

1.1. ሥራ ተቋራጩ በውል አፈጻጻም ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ተገቢ ስነ-ምግባር እንዲከተል እንዲሁም የሙስና ድርጊት
እንዳይፈፅም ያስፈልጋል ፡፡
1.2. ስራ ተቋራጩ እና/ወይም ሠራተኞቹ፣ ንዑስ የሥራ ተቋራጮቹ፣ ንዑስ አማካሪዎቹ፣ አገልግሎት ሰጪዎቹ እና አቅራቢዎቹ
በጨረታ ውድድር ጊዜ ወይም/እና ይህንን ውል ለማስፈፀም በሚደረግ ጥረት ውስጥ በሙስና፣ በማታለል ተግባር፤
በማሴር፣ በማስገደድ ወይም በመመሳጠር ተግባሮች ላይ ተሰማርተዋል ብሎ ካመነ አሰሪው ለስራ ተቋራጩ የ 14 ቀን
ማስታወቂያ በመስጠት በውሉ መሠረት ውል ያቋርጣል፡፡ የአጠቃላይ የውሉ ሁኔታዎች አንቀጽ 21 (በተለይም በአንቀፅ
21.2. (ቀ)መሰረት) ተግባራዊ ይሆናል፡፡
1.3. የሚከተሉት ቃላት ቀጥሎ የተመለከተውን ፍቺ ይሰጣል፡፡
(ሀ) “የሙስና ድርጊት” ማለት የአሰሪውን ወይም የአሰሪውን ሰራተኛ በግዥ ሂደት ወይም በውል አፈፃፀም ወቅት
በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ለማባበል (ለማማለል) በማሰብ ማንኛውም ዋጋ ያለው ነገር መስጠት
፣ወይንም ለመስጠት ማግባባት ማለት ነው፡፡
(ለ) የማጭበርበር ድርጊት” ማለት ያልተገባን የገንዘብ ወይም ሌላ ጥቅም ለማግኘት ፣ወይም ግዴታን ላለመወጣት
በማሰብ የግዥ ሂደቱንና የውል አፈፃፀሙን በሚጐዳ መልኩ ሀቁን በመለወጥና አዛብቶ በማቅረብ ሆን ተብሎ
የሚፈፀም ድርጊት ነው፡፡
(ሐ) “የመመሳጠር ድርጊት” ማለት ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ተጫራቾች አሰሪው እያወቀም ሆነ ሳያውቀው
በመመሳጠር ውድድር አልባና ተገቢ ያልሆነ ዋጋን መፍጠር ማለትነው፡፡
(መ) “የማስገደድ ድርጊት” ማለት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ህጋዊ ያልሆነ ጥቅም ላመግኘት አሰሪውን ወይም
የአሰሪውን ሰራተኛ በማስፈራራት ወይም በአካላቸውወይም ንብረታቸው ላይ ጉዳት በማድረስ ወይም ጉዳት
ለማድረስ በማሰብ የግዥ ሂደቱን ወይም የውሉን አፈጻጸም ማዛባት ማለት ነዉ፡፡
(ሠ) “የመግታት (የማደናቀፍ) ድርጊት” ማለት፣
(i) በፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሚፈለጉ
መረጃዎችን ሆን ብሎ ማጥፋት ወይም ጉዳዩ የሚያውቁ አባላት ይፋ እንዳያደርጉ በማስፈራራትና ጉዳት
በማድረስ መረጃዎችን እንዳይታወቁ በማድረግ፤ የምርመራ ሂደቶችን መግታት ወይም ማደናቀፍ ማለት
ነው፡፡

(ii) የቁጥጥርና የኦዲት ሥራዎችን ማደናቀፍ ከመግታት ድርጊት ጋር አብሮ የሚታይ ይሆናል፡፡
(iii) ሥራ ተቋራጩ በማንኛውም የጨረታ ሂደት ጊዜ ወይም በውል አፈፃፀም ወቅት በሙስና
፣በማጭበርበር ፣ በመመሳጠር፣ በማስገደድና በማደናቀፍ ተግባር ተካፋይ መሆናቸው ከተረጋገጠ
ለተወሰነ/ላልተወሰነ የጊዜ ገደብ በአሰሪው ስራ ተካፋይ እንዳይሆኑ ይታገዳሉ፡፡

9 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
1.4. በብሔራዊም ሆነ በአለምአቀፍ ደረጃ በማጭበርበርና በሙስና ድርጊት ላይ የተሰማሩ ሥራ ተቋራጩ በአሰሪው
የሚከናወኑ ውሎችን ለመፈጸም ብቁ አለመሆናቸውን የማሳወቅ መብት የአሰሪው ነው፡፡
1.5. ማንኛውም ከማጭበርበርና ከሙስና ጋር በተያያዘ በሥራ ተቋራጩና በአሰሪው ወይም ከ ሥራ ተቋራጩ ጋር
የሚደረገው ግንኙነት በጽሁፍ መሆን አለበት፡፡

6. ትርጓሜ

6.1. በዚህ አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች በአንድ ጾታ የተገለጹት ቃላት ሁሉንም ጾታዎች ይጨምራሉ፡፡ ነጠላን
የሚያሳዩ ቃላት ብዙውንም ይጨምራሉ፡፡ እንደዚሁም ብዙነትን የሚያሳዩ ቃላት ነጠላንም ያካትታሉ፡፡ ርዕሶች
ምንም ተጽዕኖ የላቸውም፡፡ በተለየ ሁኔታ ትርጉም እስካልተሰጣቸው ድረስ ቃላት በውል አባባል ወይንም ቋንቋ
የተለመደው ትርጉም አላቸው፡፡ በዚህ አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች መሐንዲሱ ማብራሪያ
ይሰጣል፡፡
6.2. በልዩ የውል ሁኔታዎች ስለከፊል ማጠናቀቅ ከተገለፀ፣ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች፣ በማጠናቀቂያ ቀን እና
በታሰበው ማጠናቀቂያ ቀን ማጣቀሻዎች ላይና በሁሉም የግንባታ ሥራዎች ላይ ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡
(ከአጠቃላይ የግንባታ ሥራዎች ማጠናቀቂያ ቀንና የማጠናቀቂያ ቀን ብሎ ከታሰበው ማጣቀሻዎች በስተቀር) ።
6.3. ሙሉ ስምምነት
ይህ ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል የተደረጉ ስምምነቶች፣ ሁኔታዎች እና አስፈላጊ ነገሮች ይዟል፡፡ ማንኛውም
ተቆጣጣሪ ወይም የተዋዋይ ወገኖች ወኪል በዚህ ውስጥ ያልተጠቀሱ መግለጫዎች፣ ውክልናዎች፣ ቃል ኪዳን ወይም
ስምምነት የማድረግ ሥልጣን የሌለው ሲሆን ተዋዋይ ወገኖችም በነዚህ ተገዢ ወይ ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

6.4. ማሻሻያ
ምንም ዓይነት የውል ማስተካከያ፣ ማሻሻያ ወይም ሌላ ለውጥ የውል ማስተካከያው ቀኑ ተጠቅሶ በጽሑፍ በግልጽ
ውሉን በመጥቀስ በተዋዋይ ወገኖች እስካልተፈረመ ድረሰ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
6.5. የተተወ ሆኖ ያለመቆጠር
(ሀ) በማንኛውም ወገን የሚደረግ የውል አፈጻጸም መዘግየት ወይም የውሉን ቃሎችና ሁኔታዎች አለማክበር ወይም
የሌላውን ተዋዋይ መብት መጣስ፣ የተጣሰውን የውል ግዴታ ሌላው ቸል በማለቱ ብቻ ቀጣይ ውል ማፍረስን
እንደተቀበለ አያስቆጥርም፡፡
(ለ) በውሉ ውስጥ የተጠቀሱት የተዋዋይ መብቶች፣ ሥልጣኖች ወይም መፍትሔዎች መቅረት የሚረጋገጠው ቀን
በተፃፈበትና በሕጉ አግባብ ስልጣን በተሰጠው ተወካይ በተፈረመ ፅሑፍ ሆኖ፣ እንዲቀር የተደረገውን መብት
በግልጽ መጥቀስና እንዲቀር የተደረገበትን ደረጃ መግለጽ ያስፈልጋል፡፡
6.6. ተከፋፋይነት
ማንኛውንም የውሉ ድንጋጌ ወይም ሁኔታ መከልከል ወይም ዋጋ ማጣት ወይም ያለመከበር የሌላውን ባለዋጋነት
ወይም መከበር ወይም መፈፀምን አያስቀርም፡፡

10 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ለ. ውል

7. የውል ሰነዶች

7.1. በውሉ ውስጥ በተካተቱት ሰነዶች መካከል ግጭት ቢኖር ከዚህ በታች በተመለከተው ቅደም ተከተል መሠረት
ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፡፡
(ሀ) የግንባታ ውል አባሪዎቹም ጭምር
(ለ) በአሰሪው ለስራ ተቋራጩ የተፃፈ የአሸናፊነት ደብዳቤ
(ሐ) ልዩ የውል ሁኔታዎች እና በልዩ የውሉ ሁኔታዎች ውስጥ የተጠቀሰ ማንኛውም ሰነድ
(መ) አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች
(ረ) የቴክኒክ እና የዋጋ መወዳደሪያ ሀሳብና የግንባታ ስራ ዝርዝር
(Bill of Quantities)
(ሰ) የንድፍ ሰነዶች (Drawings)
(ሸ) ለነጠላ ዋጋ ውል: የግንባታ ስራ ዝርዝር (Bill of Quantities) እና የዋጋ መግለጫ (የስሌት ስህተቶች
ከታረሙ በኋላ)
(ቀ) ለጥቅል ዋጋ ውሎች: የጥቅል ዋጋው ዝርዝር ((የስሌት ስህተቶች ከታረሙ በኋላ)
7.2. ውሉን የሚመሠርቱ ሰነዶች የተያያዙ፣ የሚደጋገፉና ገለጭ እንዲሆኑ ሆነው የታቀዱ ናቸው፡፡
7.3. ማንኛውም በውሉ መሠረት በአሰሪው ወይም በስራ ተቋራጩ እንዲሟላ የሚጠይቅ ወይም የተፈቀደ የውል አፈፃፀም
ተግባር እንዲሁም ማንኛውም ተፈፃሚ እንዲሆን የሚጠይቅ ወይም የሚፈቅድ ሰነድ ተፈፃሚ ሊሆን የሚችለው በልዩ
የውል ሁኔታዎች ውስጥ ሥልጣን በተሰጠው ሰው ትዕዛዝ የተሰጠበት ሲሆን ብቻ ነው፡፡
7.4. ይህ ውል በአሰሪውና በስራ ተቋራጩ መካከል የተደረገውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ የሚይዝ ነው፡፡ ስለሆነም ውሉ
ከመፈረሙ በፊት በተዋዋዮቹ መካከል ከተደረጉት ማናቸውም ግንኙነቶች፣ ድርድሮችና ስምምነቶች (በቃል ወይም
በፅሑፍ ተደርጐ ቢሆንም) የበላይነት ይኖረዋል፡፡ የየትኛውም ተዋዋይ ወገን ወኪል በዚህ ውል ከተመለከተው ውጪ
መግለጫ የመስጠት፣ ማረጋገጫ የመስጠት ወይም ቃልኪዳን የመግባት ወይም በዚህ ውል ያልተጠቀሱትን ስምምነቶች
የማድረግ ሥልጣን የለውም፡፡ የዚህ ዓይነቱ ተግባር ተፈፅሞ ቢገኝ ተዋዋዮቹ አይገደዱበትም ወይም ባለዕዳ
አይሆኑም፡፡

8. ውሉ የሚመራበት/የሚገዛበትሕግ

በልዩ የውል ሁኔታዎች በሌላ ሁኔታ ካልተገለጸ በስተቀር ውሉ፤ ፍቺዎችና ትርጉሞች፤ እንዲሁም የተዋዋዮች ግንኙነት
በኢትዮጵያ ሕጐች መሠረት የሚገዛና የሚተረጐም ይሆናል፡፡

11 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
9. የውል ቋንቋ

በሥራ ተቋራጩና በአሰሪው የተመሰረተው ውልም ሆነ በተዋዋዮቹ መካከል የተደረጉት ሁሉም ተያያዥ መፃፃፎችና
ሰነዶች በአማርኛ ይጻፋሉ፡፡

10. ማስታወቂያዎችና የፅሑፍ ግንኙነቶች

10.1. በማንኛውም በውሉ መሠረት በአንዱ ተዋዋይ ለሌላው ወገን የሚሰጠው ማስታወቂያ በውሉ በተጠቀሰው መሠረት
በፅሑፍ መሆን አለበት፡፡ በፅሑፍ የተደረገ ግንኙነት ማለት ፅሑፉ ለተቀባዩ መድረሱ ሲረጋገጥ ነው፡፡
10.2. አንድ ማስታወቂያ ውጤት ሊኖረው የሚችለው ማስታወቂያው በአካል ለተዋዋዩ ሕጋዊ ተወካይ ሲደርስ ወይም
በልዩ የውል ሁኔታዎች ውስጥ በተመለከተው አድራሻ የተላከ ከሆነ ነው፡፡

10.3. ተዋዋይ ወገን በልዩ የውል ሁኔታዎች ውስጥ በተመለከተው አድራሻ የፅሑፍ ማስታወቂያ በመላክ አድራሻውን
ሊቀይር ይችላል፡፡

11. በኃላፊነት ላይ ያለው አካል ስልጣን

የሥራ ተቋራጩ የሽርክና፤ ጊዜያዊ ህብረት (ጥምረት) ወይም ማህበር ከሆነ ወይም ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ
አካላት ያቀፈ ከሆነ፤ ሁሉም አካላት በጋራና በተናጠል በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት የውሉን ቃላት የማሟላት ግዴታ
አለባቸው፡፡ አባላቱ በልዩ የውል ሁኔታዎች ውስጥ የተጠቀሰውን አባል እንደ መሪ ሆኖ የሚሰራ ይወክላሉ፡፡ በጋራ
ማህበሩ ወይም በጊዜያዊ ማህበሩ የተወከለው/ኃላፊነት የተሰጠው ሰው ኮንትራት ይፈርማል፡፡ ጨረታ ከቀረበ ወይም
ውል ከተፈረመ በኋላ ያለአሰሪው ዕውቅና የጋራ ማህበሩ ወይም ጊዜያዊ ማህበሩ ጥምረት መቀየር አይቻልም፡፡

12. መሀንዲስና የመሀንዲሱ ተወካይ

12.1. በልዩ የውል ሁኔታዎች በተለየ ሁኔታ ካልተገለጸና ምንም ዓይነት ገደብ ከሌለበት በስተቀር በዚህ ውል በስራ
ተቋራጩ እንዲወሰድ የሚፈለግ ወይም የተፈቀደ እርምጃ እና እንዲሁም እንዲተገበር የሚፈለግ ወይም የተፈቀደ
ማንኛውም ሰነድ በልዩ የውል ሁኔታዎች በተሰየመው መሐንዲስ ይፈጸማል (ይተገበራል)፡፡ በልዩ የውል ሁኔታዎች
ካልተጠቀሰ በስተቀር መሐንዲሱ የሥራ ተቋራጩን ከማናቸውም በውሉ ያለበትን ግዴታ ነፃ ሊያደርገው አይችልም፡፡
12.2. በመሐንዲሱ የሚሰጥ ማንኛውም ማስታወቂያ፣ መረጃና የሥራ ግንኙነት ለወከለው አሰሪ ወይም ስራ ተቋራጭ
እንደተሰጠ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
12.3. መሐንዲሱ ማናቸውንም ሥራዎቹንና ሀላፊነቶቹን ለሥራ ተቋራጩ ካሳወቀ በኋላ ለወኪሉ ሊሰጥ ይችላል፣
እንደዚሁም ውክልናውን የሥራ ተቋራጩን ካሳወቀ በኋላ ሊሰርዝ ይችላል፡፡
12 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ
ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
12.4. የመሐንዲሱ ወኪል ሚና የግንባታ ሥራዎችን መቆጣጠርና መፈተሽ እና በሥራ ላይ የዋሉ የግንባታ ቁሶችን
መመርመርና መፈተን፤ እንዲሁም የሥራ ጥራትን መቆጣጠር ነው፡፡ የመሐንዲሱ ወኪል በልዩ የውል ሁኔታዎች
ተፈቅዶ ትዕዛዝ እስካልተሰጠ ድረስ የሥራ ተቋራጩን በውሉ ካሉበት ግዴታዎች ነፃ የማድረግ፣ የትግበራ ጊዜውን
የሚያራዝም ወይም በአሰሪው ላይ ተጨማሪ ወጪ የሚያስወጣ ትዕዛዝ መስጠት አይችልም። ከዚህ በተጨማሪ
ስምምነት በተደረሰባቸው የግንባታ ሥራዎች መጠን ላይ ለውጥ ማድረግ አይችልም፡፡
12.5. በውክልና ቃላት መሠረት በመሐንዲሱ ወኪል ለሥራ ተቋራጩ የተሰጠ ትዕዛዝ (የተላለፈ መልዕክት)
እንደሚከተለው ከሆነ በመሐንዲሱ ቢሰጥ ኖሮ ያለው ዓይነት ውጤት ይኖረዋል፡፡
(ሀ) በመሐንዲሱ ተወካይ በኩል የግንባታ ሥራን፣ ቁስን ወይም መሣሪያን ባለማፅደቅ በኩል የታየን
ድክመት መሐንዲሱ ተወካዩ ያላፀደቃቸውን ነገሮች የማፅደቅ ሥልጣኑን የማይነፍግ ከሆነና፤
(ለ) መሐንዲሱ እንደነዚህ ዓይነት ትዕዛዞችን ሙሉ በሙሉ እንዲቀየሩ እና ይዞታቸው እንዲለወጥ
የማድረግ ነፃነቱ የተጠበቀ ከሆነ ነው፡፡
12.6. በመሐንዲሱ የሚሰጡ መመሪያዎች ለውጥ/ወይም ትዕዛዞች በአስተዳደራዊ ትዕዛዞች መልክ ሊሆኑ ይገባል፡፡
እንደነዚህ ዓይነት ትዕዛዞች ቀንና ቁጥር ሊኖራቸው ሲገባ በመሐንዲሱ ተመዝግበው ግልባጮቹ እንደየአስፈላጊነቱ
ለሥራ ተቋራጩ ወኪል በእጁ መሰጠት ይኖርበታል፡፡

13. ኃላፊነትን ለሌላ ማስተላለፍ

13.1. ኃላፊነት ለሌላ ማስተላለፍ ማለት ስራ ተቋራጩ ውሉን በሙሉ ወይም በከፊል በፅሑፍ ስምምነት ለሦስተኛ
ወገን ማስተላለፍ ማለት ነው፡፡
13.2. በሚከተሉት ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር ስራ ተቋራጩ አሰሪውን በቅድሚያ የፅሑፍ ፍቃድ ሳያገኝ ውሉን
በሙሉም ሆነ በከፊል ወይም ከውሉ ጋር የተያያዘ ጥቅሞችና ፍላጐቶች ለሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ የለበትም፡፡
(ሀ) ለስራ ተቋራጩ ደንበኛ ባንክ በዚሁ ውል መነሻነት የመክፈል ግዴታ ሲኖርበት፣
(ለ) ለስራ ተቋራጩ የመድን ዋስትና የሰጠው አካል ከስራ ተቋራጩ መብት ጋር በተያያዘ ከዕዳና ከኪሣራ
ለመውጣት ሲባል ለሌላ ሰው የወጣውን ወጪ ለመተካት፡፡
13.3. በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ንዑስ አንቀጽ 13.2 ዓላማ መሠረት አሰሪው ኃላፊነትን ለሌላ ወገን ለማስተላለፍ
ጥያቄ በመቀበሉ ምክንያት ስራ ተቋራጩ በውል አፈፃፀም ከሚኖረው ግዴታ (በተላለፈውም ሆነ ባልተላለፈው)
ነፃ አያደርገውም፡፡
13.4. ስራ ተቋራጩ ከአሰሪው ፈቃድ ሳያገኝ ኃላፊነቱን ለሌላ ካስተላለፈ ያለምንም የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ በአጠቃላይ
የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 19 እና 21 ውስጥ በተመለከተው መሠረት የውል መቋረጥ መብቶች ተግባራዊ
ያደርጋል፡፡
13.5. ኃላፊነት የሚተላለፍለት ወገን በጨረታ አሸናፊ ምርጫ ጊዜ አገልግሎት ላይ የዋሉትን የብቁነት መስፈርቶች
(eligibility criteria) ማሟላት ይኖርበታል፡፡

13 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
13.6. ማናቸውም ኃላፊነትን ለሌላ የማስተላለፍ ተግባር በዚህ ውል መሰረት የሚከናወን ሲሆን በዚህ ዉስጥ ያሉትን
ቃሎችና ሁኔታዎች ማካተት ይኖርበታል፡፡

14. ንዑስ ተቋራጭ

14.1. ንዑስ ተቋራጭነት ተቀባይነት የሚኖረው በስራ ተቋራጩና በንዑስ ተቋራጩ መካከል ከፊል ውሉን ለማከናወን
የፅሑፍ ስምምነት ሲኖር ብቻ ነው፡፡
14.2. ስራ ተቋራጩ በውሉ ውስጥ ላልተካተቱ ንዑስ ተቋራጮች የግንባታ ስራዎችን ለመስጠት ሲፈልግ በቅድሚያ
ከአሰሪው የፅሑፍ ፈቃድና ይሁንታ ማግኘት አለበት፡፡ የንዑስ ተቋራጩ ማንነትንና ሊሰጡት የታሰቡትን
የግንባታ ስራዎች ለአሰሪው ማሳወቅ አለበት ፡፡ አሰሪው በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 1 ዐ መሠረት
ማስታወቂያው በደረሰው በ 15 ቀናት ውስጥ ከበቂ ምክንያቶች ጋር ውሳኔውን ያሳውቃል፡፡
14.3. ንዑስ ተቋራጭነት ይህንን ውል መሰረት በማድረግ የሚሰጥ ሲሆን የንዑስ ተቋራጭነት ቃሎች በዚህ ውል
ከተመለከቱት ሁኔታዎች ጋር የሚጣጣሙ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
14.4. ንዑስ ተቋራጮች በጨረታ አሸናፊ ምርጫ ጊዜ አገልግሎት ላይ የዋሉትን የብቁነት መስፈርቶች ማሟላት
ይኖርባቸዋል፡፡
14.5. ስራ ተቋራጩ በንዑስ ተቋራጩ፣ በወኪሎቹ ወይም በሠራተኞቹ ለሚፈጠሩ ድርጊቶች፣ ስህተቶችና
ግድየለሽነቶች የራሱ ስህተቶችና ግድ የለሽነቶች እንደሆኑ በመቁጠር ኃላፊነት መውሰድ አለበት፡፡ አሰሪው
የውል ግዴታው በንዑስ ተቋራጭ እንዲከናወን መፍቀዱ ወይም ንኡስ ተቋራጩ ውሉን እንዲያከናውን
በመፍቀዱ ምክንያት ስራ ተቋራጩን ከኃላፊነት ነፃ አያደርገውም፡፡
14.6. ንዑስ የሥራ ተቋራጩ ጉድለቶች ተጠያቂነት ጊዜ በላይ ለዋናው የሥራ ተቋራጭ የግንባታ ሥራዎች፣
ቁሶችና አገልግሎቶች እያቀረበ ከሆነ የሥራ ተቋራጩ በጉድለት ኃላፊነት ጊዜ ካለፈ በኋላ በማንኛውም ጊዜ
ጊዜው ላልተላለፈበት ጊዜ ባለው ግዴታ የሚመጣውን ጥቅም ለአሰሪው ማስተላለፍ አለበት፡፡
14.7. ስራ ተቋራጩ ያለአሰሪው ፈቃድ ከፊል/ ሙሉውን ውሉን ለንዑስ ተቋራጭ ከሰጠ አሰሪው ያለምንም የፅሑፍ
ማስታወቂያ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 19 እና 21 በተመለከተው መሠረት የውል ማቋረጥ
መብቶችን ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
14.8. ንዑስ ተቋራጩ ግዴታዎቹን በመወጣት ረገድ ደካማ ሆኖ ከተገኘ አሰሪው ወይም መሀንዲሱ እሱን ሊተካ
የሚችል በአሰሪው ተቀባይነት ፡ ብቃትና ልምድ ያለው ሌላ ንዑስ ተቋራጭ እንዲያቀርብ ወይም ሥራውን ራሱ
ስራ ተቋራጩ እንደገና እንዲያከናውን ሊጠይቁት ይችላሉ፡፡

14 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
15. የግንባታ ለውጥ ወይም ማሻሻያ

15.1. መሐንዲሱ የግንባታ ሥራዎች በተገቢው መንገድ እንዲጠናቀቁ ወይም እና በጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ
በየትኛውም የግንባታ የሥራ ክፍል ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ትዕዛዝ የመስጠት ሥልጣን አለው፡፡ ማሻሻያዎቹ
የግንባታ ሥራዎች መጨመርን፣ መተውን፣ መተካትን፣ የጥራት፤ ብዛት፣ ቅርጽ፣ ባሕሪ፣ ዓይነት፣ ቦታ፣ ልኬት፣
ከፍታ ወይም የመስመር ለውጦችን እና በተጠቀሰ የቅደም ተከተል ፣ ዘዴ ወይም ስራዎችን የመፈጸሚያ ጊዜ
ለውጦችን ያካትታሉ፡፡ ምንም ዓይነት የማሻሻያ ትዕዛዝ ውሉን ውድቅ ሊያደርግ አይችልም፡፡ ነገር ግን ሁሉም
ማሻሻያዎች በውል ዋጋ ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ ካለም በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 15.5 እና 15.7
መገመት ይኖርበታል፡፡
15.2. ሁሉም የለውጥ ትዕዛዞች በጽሑፍ መሰጠት ይኖርባቸዋል፣ እንዲሁም የሚከተሉትን ሁኔታዎችን በመገንዘብ
ይሆናል፡፡
(ሀ) በማንኛውም ምክንያት መሐንዲሱ የቃል ትዕዛዝ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው፣ በተቻለ ፍጥነት
ትዕዛዙን በለውጥ ትዕዛዝ ማረጋገጥ ይኖርበታል፣
(ለ) ሥራ ተቋራጩ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች 15.2 “ሀ” የተሰጠውን የቃል ትዕዛዝ በጽሑፍ ካረጋገጠና
ወዲያውኑ መሃንዲሱ ማረጋገጫውን በጽሑፍ እስካልተቃረነው ድረስ ለማሻሻያው የለውጥ ትዕዛዝ
እንደተሰጠ ሆኖ ይቆጠራል፡፡
ሐ) በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 63 መሠረት የግንባታ ዋጋ ስራው ሲተመን በግንባታ ሥራ መጠን
ሠንጠረዥ ወይም በዋጋ ሠንጠረዥ የተጠቀሰው የግንባታ የሥራ መጠን መጨመር ወይም መቀነስ
ቢያሳይ የማሻሻያ የለውጥ ትዕዛዝ እንዲሰጥ አያስፈልግም፡፡
15.3. በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 15.2 ከተጠቀሰው በስተቀር መሐንዲሱ ከማንኛውም የማሻሻያ የለውጥ
ትዕዛዝ በፊት የማሻሻያውን ባሕሪና ቅርጽ ለሥራ ተቋራጩ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ ይህን ማስታወቂያ እንዳገኘ
የሥራ ተቋራጩ በተቻለ ፍጥነት ለመሐንዲሱ የሚከተሉትን የያዘ ሃሳብ (proposal) ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
(ሀ) መፈጸም ያለባቸው ተግባራት ካሉ የተግባራቱ መግለጫ፣ ወይም መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች
እና የሚከናወኑበት ፕሮግራም፣ እና
(ለ) ለተግባራቶቹ አፈጻጸም ወይም በውል ውስጥ የሥራ ተቋራጩን ግዴታዎች ላይ አስፈላጊ የሆነ
ማንኛውም አስፈላጊ የሆኑ የፕሮግራም ማሻሻያ፣ እና
(ሐ) በዚህ አንቀጽ በተመለከቱ ደንቦች የሚደረግ ማንኛውም የውል ዋጋ ማስተካከያዎች
15.4. በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 15.3 የተመለከተውን ሥራ ተቋራጩ ያቀረበውን ሰነድ እንደደረሰው፣
መሃንዲሱ አሰሪውን እና እንደአስፈላጊነቱ የሥራ ተቋራጩንም በማማከር በተቻለ ፍጥነት ማሻሻያውን መፈጸም
እንዳለበት ወይም እንደሌለበት መወሰን ይኖርበታል፡፡ መሐንዲሱ ማሻሻያው መካሄድ አለበት ብሎ ከወሰነ
ማሻሻያው በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 15.3 የሥራ ተቋራጩ ባቀረበው ዋጋና ሁኔታዎች ወይም

15 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
መሐንዲሱ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 15.5 ባሻሻለው መሠረት በመግለጽ የለውጥ ትዕዛዝ መስጠት
ይኖርበታል፡፡
15.5. በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 15.2 እና 15.4 መሠረት በመሐንዲሱ የታዘዙ የማሻሻያ ሥራዎች ዋጋ
በሚከተሉት መርሆዎች መሠረት በመሐንዲሱ መረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡

(ሀ) የግንባታ ሥራው በግንባታ ሥራ መጠን ዝርዝር ወይም የዋጋ ሠንጠረዥ ከተጠቀሰው ሥራ ተመሳሳይ ባህሪና በተመሳሳይ
ሁኔታዎች የተፈጸመ ከሆነ በነዚህ ሰነዶች ላይ በተመለከተው መሰረት ተመን እና ዋጋዎች ይሰጣል (ይገመታል)፡፡

(ለ) የግንባታ ሥራው ተመሳሳይ ባህሪይ የሌለው ወይም በተመሳሳይ ሁኔታዎች ያልተከናወነ ከሆነ በመሐንዲሱና
በሥራ ተቋራጩ መካከል በሚደረግ ድርድር ስምምነት ላይ የሚደረስበት ዋጋ ካለው የገበያ ዋጋ ጋር
መጣጣም ይኖርበታል፡፡
(ሐ) ከውሉ በአጠቃላይ ወይም በከፊል ባህሪና መጠን ጋር ማንኛውም የማሻሻያ ባህሪ ወይም መጠን
ሲወዳደር በመሐንዲሱ አመለካከት በውሉ ውስጥ በማንኛውም የግንባታ ሥራ ተመን ወይም ዋጋ
ምክንያታዊ ሆኖ ካላገኘው መሐንዲሱ ተገቢ እና ምክንያታዊ ነው የሚለውን ተመን ወይም ዋጋ መስጠት
ይችላል፡፡
(መ) ማሻሻው አስፈላጊ የሆነው የሥራ ተቋራጩ ውሉን በመጣሱ (ባለማክበሩ) ምክንያት ከሆነ ከዚህ ማሻሻያ ጋር
የተያያዙ ተጨማሪ ወጪዎችን በሥራ ተቋራጩ ይሸፈናሉ፡፡

15.6. የሥራ ተቋራጩ ማሻሻያ የሚጠይቅ የለውጥ ትዕዛዝ እንደደረሰው ማሻሻያዎቹ በዚህ አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች
ውስጥ እንዳሉ በመቁጠር ማሻሻያውን መፈጸም ይኖርበታል፡፡ የግንባታ ሥራዎች የጊዜ ማራዘሚያ መጽደቅን
ወይም የውል ዋጋ መስተካከልን በመጠበቅ መዘግየት አይኖርባቸውም፡፡ የማሻሻያ ትዕዛዙ ከውል ዋጋ
ማስተካከያው ከቀደመ፣ የሥራ ተቋራጩ ለማሻሻያ ሥራው ያወጣውን ወጪ እና የወሰደውን ጊዜ መዝግቦ
ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡ እነዚህ ሰነዶች በማንኛውም ተገቢ ጊዜ በመሐንዲሱ ለሚደረግ ምርመራ ክፍት መሆን
ይኖርባቸዋል፡፡
በጊዜያዊ ርክክብ ወቅት ከሥራ ተቋራጩ ጥፋት ውጪ በለውጥ ትዕዛዝ ወይም በሌሎች ምክንያቶች በግንባታ ሥራዎች
ዋጋ ላይ የሚመጣ መጨመር ወይም መቀነስ ከመጀመሪያው የውል ዋጋ ወይም በማሻሻያው እንደተሻሻለው ከ 25%
ከበለጠ፣ መሐንዲሱ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 15.5 መተግበር ምክንያት በውል ዋጋው ላይ የሚመጣውን
መቀነስ ወይም መጨመር ከአሰሪው እና ከሥራ ተቋራጩ ጋር ከተመካከረ በኋላ መወሰን ይኖርበታል፡፡ የሚወሰነው
ድምር የግንባታ ሥራዎች ዋጋ ከ 25% በጨመረው ወይም በቀነሰው መጠን መሠረት ይኖርበታል፡፡ ይህ ድምር
ለአሰሪውና ለሥራ ተቋራጩ መገለጽ ይኖርበታል፡፡ እንደዚሁም በዚሁ መሠረት የውል ዋጋው መስተካከል አለበት፡፡
15.7. በውል ቃሉ ላይ የሚደረግ ማንኛውም ለውጥ በጽሑፍ መመዝገብ እና በሥራ ተቋራጩ እና በአሰሪው ሕጋዊ
ስምምነት (ፊርማ) መተግበር አለበት፡፡ የተጠቀሰውን የለውጥ ሰነድ በለውጡ ምክንያት በውሉ ላይ መደረግ
የሚገባቸውን ሁሉንም ማስተካከያዎች ማካተት ይኖርበታል፡፡
15.8. ለውጦች ተግባራዊ የሚሆኑት በተፈረመው ሰነድ ውስጥ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ሲሆን በዚህ ሰነድ ውስጥ ተለይቶ
እስካልተጠቀሰ ድረስ ወደ ኋላ ሄዶ ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም፡፡

16 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
15.9. ለእያንዳንዱ ሰነድ ቀንና ተከታታይ ቁጥር መሰጠት አለበት፡፡ አሰሪው እና የሥራ ተቋራጩ የለውጥ ሰነዱን ዋናውን ቅጂ
የማግኘት መብት አላቸው፡፡
15.10. በዚህ የለውጥ ሰነድ ውስጥ ከተቀመጠው በስተቀር ውሉ ፀንቶ የሚቆይ እና ተፈፃሚነቱ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

16. በሕጐችና በደንቦች ላይ የሚደረግ ለውጥ

በልዩ የውል ሁኔታዎች ውስጥ በሌላ አኳኋን ካልተጠቀሰ በስተቀር የግንባታ ስራው የማስረከቢያ ቀን ወይም የውሉን ዋጋ ላይ ተፅእኖ
የሚያደርግ እና በግንባታ ቦታው ላይ ተፈፃሚነት ያለው ማንኛውም ሕግ፣ ደንብ፣ ትዕዛዝ ወይም የሕግ አቅም ያለው ውስጠ ደንብ
ታትሞ ቢወጣ፣ ቢሻር፣ በደረሰው ቀውስ ምክንያት የማስረከቢያው ቀን አይስተካከልም ወይም የውሉን ዋጋ መጨመር ወይም መቀነስ
አይገባውም ፡፡

17. ግብሮችና ታክሶች

በልዩ የውል ሁኔታዎች ውስጥ በተለየ ሁኔታ እስካልተጠቀሰ ድረስ የሥራ ተቋራጩ ከግንባታ ሥራው ጋር የተያያዙ
ግብሮችን እና ሌሎች ተከፋዮችን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ውስጥም ሆነ ውጭ ላሉ የከተማ
መስተዳድሮች፣ የክልል ወይም ብሔራዊ መንግሥታት ባለሥልጣኖች የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል፡፡

18. አስገዳጅ የውል ሁኔታ

18.1. ለዚህ ውል ዓላማ ሲባል አስገዳጅ ሁኔታዎች ማለት ከሥራ ተቋራጩ አቅም በላይ የሆኑ ያልተጠበቁ፣
ማስወገድ የማይችላቸውና በተፈለገው ሁኔታ ግዴታውን ለመፈፀም የማያስችሉ የሚከተሉት ክስተቶች ሲፈጠሩ
ማለት ነው፡፡
(ሀ) ውሉን እንዳይፈፅም የተደረገ የመንግስት ክልከላ፣
(ለ) የተፈጥሮ አደጋዎች ማለትም የመሬት መንቀጥቀጥ፣ እሳት፣ ፍንዳታዎች፣ አውሎ ንፋስ፣ጐርፍ ወይም ሌሎች
አደገኛ የአየር ሁኔታዎች፣
(ሐ) ዓለም አቀፍ ወይም የእርስ በርስ ጦርነቶች
(መ) ሌሎች በኢትዮጵያ ፍተሐብሔር ህግ ላይ የተመለከቱ አስገዳጅ ሁኔታዎች፣
18.2. የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲከሰቱ እንደ አስገዳጅ ሁኔታዎች አይቆጠሩም፡፡
(ሀ)ያልተጠበቀ ክስተት ተደርጎ እንዲወሰድለት ያነሳሰው ተዋዋይ ወገን ቁጥጥር ውስጥ ያለ በተዋዋይ
ወገኑ የንግድ ተቋሙ ቅርንጫፎች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር የሥራ ማቆም አድማ ወይም ጠቅላላ
መዘጋት፣
(ለ)ውሉን ከማስፈፀም አንፃር የጥሬ ዕቃዎች ዋጋ መወደድ ወይም መርከስ፣

17 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
(ሐ)አዲስ ሕግ በመውጣቱ ምክንያት የተዋዋይ ወገኑ ግዴታ አፈፃፀም ወጪ ማክበድ ፣
(መ) በሥራ ተቋራጩ ወይም በንዑስ ተቋራጩ ወይም በወኪሉ ወይም በሠራተኞቹ ሆነ ተብሎ ወይም
በግድየለሽነት የሚፈጠሩ ችግሮች፣
(ረ) የሥራ ተቋራጩ በሚከተሉት ላይ በቅድሚያ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ የነበረበት ሲሆን፤
I. ውሉ ስራ ላይ የሚውልበት ጊዜ መገመት የሚገባው እና፣
II. ግዴታን በመወጣት ሂደት ሊያስወግዳቸው ወይም ሊቋቋማቸው የሚችሉትን ሁኔታዎች
(ሠ) የገንዘብ እጥረት ወይም ክፍያዎችን አለመክፈል፣
18.3 ከአስገዳጅ ሁኔታዎች በመነጨ ምክንያት የሥራ ተቋራጩ የውል ግዴታዎችን ባለመፈፀሙ ምክንያት የውሉን
ቃሎችና ሁኔታዎች በሚፈቅደው መሠረት አስፈላጊውን ጥንቃቄና አማራጭ መፍትሔዎች ለመፈለግ ጥረት እስካደረገ ድረስ
ውሉን እንደጣሰ አይቆጠርበትም፡፡

18.4 በአስገዳጅ ሁኔታዎች ምክንያት ተፅእኖ የደረሰበት ተዋዋይ ወገን የሚከተሉትን ተገቢ እርምጃዎች መውሰድ
አለበት፡፡
(ሀ) በአጭር ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ለመፈፀም ያላስቻሉትን ሁኔታዎች ማስወገድ፣ እና
(ለ) በአስገዳጅ ሁኔታዎች ምክንያት የሚመጡ ውጤቶችን (ጉዳቶችን) ለመቀነስ ጥረት ማድረግ፣
18.5 አስገዳጅ ሁኔታዎች ሲከሰቱ የሥራ ተቋራጩ ለአሰሪው በአስቸኳይ እንዲሁም በማንኛውም መንገድ የተከሰተው
ችግርና ምክንያቱን ማስረጃ በማቅረብ ቢበዛ በ 14 ቀናት ውስጥ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ችግሮቹ
ተወግደው መደበኛ ሥራዎች በሚጀመሩበት ጊዜ በአቸስኳይ ማሳወቅ አለበት፡፡
18.6 በዚህ ውል መሰረት ስራውን ለማጠናቀቅ የሚፈጀው ጊዜ ስራ ተቋራጩ በአስገዳጅ ሁኔታ ምክንያት ስራውን
መስራት ላልቻለበት ጋር እኩል ለሚሆን ጊዜ መራዘም አለበት፡፡
18.7 በአስገዳጅ ሁኔታዎቹ ክስተት ምክንያት የግንባታ ሥራዎችን ማከናወን በማይችልበት ጊዜ በ አሰሪው መመሪያ
መሠረት የሥራ ተቋራጩ ከግንባታ ቦታው መልቀቅ ይኖርበታል፤
18.8 የሥራ ተቋራጩ ባልተጠበቀ አጋጣሚ ምክንያት የግንባታ ሥራዎችን ማከናወን ካልቻለበት ቀን ጀምሮ ሰላሳ
(3 ዐ) ቀናት ሳያልፍ ተዋዋይ ወገኖች በቀና ልቦና እርስ በእርሳቸው በመመካከር ያልተጠበቀ ሁኔታው የሚያደርሰውን
ጉዳት ለመቀነስ የሚያስችል ተገቢ ቃላት ላይ ለመስማማት ሁሉንም ምክንያታዊ ጥረቶች በማድረግ የውሉ ትግበራ
የሚቀጥልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባቸዋል፡፡
18.9 በተዋዋይ ወገኖች መካከል አስገዳጅ ሁኔታዎች ስለመከሰቱ ወይም መጠኑ ላይ አለመስማማት ከተፈጠረ ጉዳዩ
በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 26 መሠረት መፈታት ይኖርበታል፡፡

19. የውል ግዴታ ማፍረስ

19.1. አንደኛው ተዋዋይ ወገን በውሉ ውስጥ ከተጠቀሱት ግዴታዎቹ ማናቸውንም ያልተወጣ ከሆነ የውል ግዴታን
እንደጣሰ ይቆጠራል፣

18 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
19.2. የውል ግዴታ መጣስ በሚኖርበት ጊዜ የውል ግዴታ በመፍረሱ ምክንያት የተጐዳው ወገን የሚከተሉትን
እርምጃዎች ይወስዳል፡፡
(ሀ) በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች መሠረት የጉዳት ካሣ መጠየቅ፣ እና /ወይም
(ለ) ውሉን ማቋረጥ
19.3. የጉዳት ካሳው ለአሰሪው የሚከፈል በሚሆንበት ወቅት አሰሪው ካሣውን ለሥራ ተቋራጩ ከሚከፍለው
ክፍያ ቀንሶ ያስቀራል ወይም አግባብነት ያለውን ዋስትና እንዲከፈለው ይጠይቃል፡፡

20. ስለማገድ

20.1. መሐንዲሱ የግንባታ ስራው እንዲቆም ባዘዘ ጊዜ የስራ ተቋራጩ መሃንዲሱ አስፈላጊ ነው ብሎ ባመነበት መንገድ
እና ጊዜ ወይም ጊዜያቶች የግንባታ ስራውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ማቆም አለበት ፡፡
20.2. የግንባታ ሥራው በተቋረጠበት ወቅት የሥራ ተቋራጩ እንደአስፈላጊነቱ የግንባታ ሥራዎቹን፣ ተቋማቱን፣
ተከላዎች፣ መሣሪያዎቹንና ቦታውን ከማንኛውም ብልሽት (deterioration) ጥፋት ወይም ጉዳት መከላከል
ይኖርበታል፡፡ እገዳው የመጣው በሚከተሉት ምክንያቶች ካልሆነ በስተቀር እንዲህ ዓይነቱን ከመከላከል ጋር
በተያያዘ የሚወጡ ተጨማሪ ወጪዎች ከውል ዋጋው ጋር የሚደመሩ ይሆናል፤
(ሀ) በውሉ ውስጥ ከተጠቀሰ ወይም
(ለ) እገዳው በሥራ ተቋራጩ ጥፋት ምክንያት አስፈላጊ ከሆነ ወይም
(ሐ) በግንባታ ቦታው በተፈጠረ የዘወትር የተለመደ የአየር ሁኔታ ምክንያት ወይም
(መ) ለደህነትና የግንባታ ሥራዎች በከፊልም ሆነ በሙሉ በትክክል መፈጸም አስፈላጊ ከሆነና እንደዚህ
ዓይነቱ አስፈላጊነት የተፈጠረው በመሐንዲሱ ወይም በአሰሪው በተፈፀመ ወይም ሳይፈፀም በቀረ
ተግባር እስካልሆነ ወይም በአንቀጽ 44 በተጠቀሱት ስጋቶች እስካሆነ ድረስ፡፡
20.3. የሥራ ተቋራጩ የሥራ እገዳ ትዕዛዝ በደረሰው በሰላሳ (3 ዐ) ቀናት ውስጥ ለመሐንዲሱ በውል ዋጋ ላይ
ተጨማሪ የመጠየቅ ሃሣብ እንዳለው እስካላሰወቀ ድረስ በውል ዋጋው ላይ ተጨማሪ ክፍያ የማግኘት መብት
አይኖረውም ፡፡
20.4. መሐንዲሱ ከአሰሪውና ከሥራ ተቋራጩ ጋር ከተመካከረ በኋላ ከሥራ ተቋራጩ ጥያቄ አንጻር በመሐንዲሱ
አስተያየት ሚዛናዊና ምክንያታዊ የሚለውን ተጨማሪ ክፍያ እና/ወይም የግንባታ ጊዜ ማራዘሚያን ይወስናል፡፡
20.5. የእገዳው ጊዜ ከ 12 ዐ ቀናት ከበለጠና እገዳው በሥራ ተቋራጩ ጥፋት ካልሆነ የሥራ ተቋራጩ ለመሐንዲሱ
በሚያቀርበው ማስታወቂያ በ 3 ዐ ቀናት ውስጥ ሥራውን እንዲጀምር ፍቃድ እንዲሰጠው ጥያቄ ማቅረብ
ወይም ውሉ እንዲሰረዝ ፈቃድ ሊጠይቅ ይችላል፡፡
20.6. የጨረታውን አሸናፊ የመምረጥ ሂደት ወይም በውል ትግበራ ወቅት የጎላ ስህተት ወይም ተቀባይነት የሌላቸው
አሠራሮች ወይም በጥርጣሬ ወይም የተረጋገጠ ማጭበርበር የነበረበት ከሆነ ክፍያው ወይም/እና የውሉ ትግበራ
ይታገዳል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ስህተት፣ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ወይም ማጭበርበር በሥራ ተቋራጩ ምክንያት

19 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ከሆነ አሰሪው ክፍያ አልፈጽምም ማለት ወይም/እና እንደ ስህተቱ ወይም ተቀባይነት የሌለው አሠራሩ ወይም
ማጭበርበሩ አደገኝነት መጠን የተከፈለን ገንዘብ ማስመለስ ይችላል፡፡ የሥራ ተቋራጩ በሌላ ከአሰሪው ጋር
በተፈጸመ ውል ላይ ወይም በዚህ ውል ላይ ሌላ ተፅዕኖ ሊያሳድር የሚችል የስህተት፣ ተቀባይነት የሌለው
አሠራር ወይም ማጭበርበር ጥርጣሬ ወይም የተረጋገጠ መረጃ ሲኖር ክፍያ ሊቋረጥ ይችላል፡፡

21. ውል መቋረጥ

በ አሰሪው የሚደረግ የውል ማቋረጥ፤


21.1. ውል የሚቋረጠው በ አሰሪውና በሥራ ተቋራጩ በተገባው ውል ውስጥ የተካተቱትን ሌሎች መብቶች ወይም
ስልጣኖች በማይነካ መልኩ መሆን አለበት፡፡
21.2. አሰሪው በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች የተመለከቱትን ምክንያቶች ሲያጋጥሙ ለሥራ ተቋራጩ ለውሉ መቋረጥ
ምክንያቱን እና የውሉ ወቋረጥ ተፈፃሚ የሚሆንበት ቀን በመግለፅ ከ 3 ዐ ቀናት ያላነሰ የፅሑፍ ማስታወቂያ
በመስጠትና (በፊደል “ኘ” ከዚህ በታች የተጠቀሰው ሁኔታ ሲያጋጥም ከ 6 ዐ ቀን ያላነሰ የፅሑፍ ማስታወቂያ
በመስጠት ፣ በፊደል  ቀ የተጠቀሰው ሁኔታ ሲያጋጥም የ 14 ቀን ያላነሰ የፅሑፍ ማስታወቂያ በመስጠት
እንዲሁም በፊደል  ረ የተጠቀሰው ሁኔታ ሲያጋጥም ያለምንም ማስጠንቀቂያ) በዚህ ንዑስ አንቀጽ 21.2
ከ(ሀ) እስከ (አ) ከተዘረዘሩት አንዱ ሲከሰት ውሉን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡

(ሀ) ሥራ ተቋራጩ የግንባታ ስራዎቹን በውሉ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ሳይፈፅም ሲቀር ወይም በአጠቃላይ
የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 723 መሠረት በተራዘመለት ጊዜ ሳያከናውን ሲቀር፣
(ለ) ሥራ ተቋራጩ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 20 መሠረት የእገዳ ግዴታውን እንዲወጣ የተሰጠውን
የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ/ማስታወቂያ በ 3 ዐ ቀናት ወይም አሰሪው በፅሁፍ የሰጠው/ያፀደቀው ተጨማሪ
ቀናት ውስጥ ጉድለቶችን ለማስተካከል ካልቻለ፤
(ሐ) ሥራ ተቋራጩ ዕዳውን መክፈል ሲያቋርጥ ወይም ሲከስር ለ ውህደት ወይም ለመልሶ መቋቋም
(reconstruction) ሲቀር በ አበዳሪው ምህረት ሲደረግለት፣
(መ) ሥራ ተቋራጩ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ንዑስ አንቀጽ 26.2 መሰረት በተደረገ ውይይት በተደረሰበት
የመጨረሻ ውሳኔ መሠረት ሳይፈፅም ሲቀር፣
(ሠ) ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ሥራ ተቋራጩ ከ 6 ዐ ቀናት ላላነሰ ጊዜ የግንባታ ስራውን መፈፀም
የሚያቅተው ሲሆን፣
(ረ) ሥራ ተቋራጩ ያለአሰሪው ስምምነት ውሉን ወይም ሥራውን ለንዑስ ተቋራጭ ቢያስተላልፍ፣
(ሰ) ሥራ ተቋራጩ ከስራ ስነምግባር ጥሰት ጋር በተያያዘ ጥፋተኝነቱን አሰሪው በማንኛውም መንገድ
ሲያረጋግጥ፡

20 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
(ሸ) ሥራ ተቋራጩ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 21.2 (ቀ) ላይ በተገለጸው ምክንያት ከአሰሪው ጋር በገባው ሌላ
ውል የማፍረስ ተግባር መፈፀሙ ሲታወቅ፣
(ቀ) ሥራ ተቋራጩ በጨረታ ውድድር ወቅት ወይም ውሉን በሚያስፈፅምበት ጊዜ በማጭበርበርና በሙስና
ድርጊት መሳተፉ ሲታወቅ፣
(በ) በውሉ ማሻሻያ ሰነድ ካልተመዘገበ በስተቀር የሥራ ተቋራጩ ድርጅት መሠረታዊ የሆነ የሕግ ሰውነት፣ ባህሪ
ወይም የመቆጣጠር ስልጣን ለውጥ ሲያደረግ፣
(ተ) ማናቸውም ውሉን ለማስፈፀም የማያስችሉ ሕጋዊ ሁኔታዎች ሲከሰቱ፣፡
(ቸ) ሥራ ተቋራጩ ተፈላጊውን ዋስትና ሳያቀርብ ሲቀር ወይም ዋስትና የሰጠው አካል በገባው ቃል መሠረት
ቃሉን ሳይጠብቅ ሲቀር፣
(ኀ) የአሰሪው የግዥ ፍላጐት አሳማኝ በሆነ ምክንያት ሲለወጥ፣
(ነ) በውል ዋጋውና ገበያ ላይ ባለው የገበያ ዋጋ ሰፊ ልዩነት በመኖሩ ምክንያት የ አሰሪው ጥቅሞች የሚጐዳ ሆኖ
ሲገኝ፣
(ኘ) አሰሪው በራሱ ፍላጐትና አመቺነት ውሉን ምንጊዜም ሊያቋርጠው ይችላል፣
(አ) ንዑስ አንቀጽ 27.1(ለ) ላይ የተቀመጠው የጉዳት ካሳ መጠን ጣሪያ /ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያደረሰ የውል
ግዴታ መዘግየት ካለ፡፡
በስራ ተቋራጩ የሚደረግ የውል ማቋረጥ፤
21.3. ሥራ ተቋራጩ በዚህ ንዑስ አንቀጽ ከ(ሀ) እስከ (መ) ከተጠቀሱት ሁኔታዎች አንደኛው ሲያጋጥም ከ 3 ዐ ቀናት
ያላነሰ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ማቋረጥ ይችላል፡፡
(ሀ) አሰሪው በውሉ መሰረት ለሥራ ተቋራጩ መክፈል የሚገባውን ክፍያ (በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ
26 መሠረት አለመግባባት ከተነሳበት በስተቀር) ከስራ ተቋራጩ ጥያቄ በቀረበለት በ 45 ቀናት ውስጥ
ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ፣
(ለ) አሰሪው በውሉ ግዴታ የገባበትን መሠረታዊ የሆነ ጉዳይ ሳይፈፅም በመቅረቱ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ
በደረሰው በ 45 ቀናት ጊዜ ውስጥ (በሥራ ተቋራጩ በጽሑፍ በተሰጠው ተጨማሪ ጊዜ ውስጥ) በውሉ
መሠረት ሳይፈፅም የቀረ እንደሆነ፣
(ሐ) አሰሪው ውሉ ውስጥ ባልተጠቀሰ ወይም የሥራ ተቋራጩ ጥፋት ባልሆነ ምክንያት የግንባታ
ሥራው ለ 18 ዐ ቀናት እንዲታገድ ካደረገ፣
(መ) ሥራ ተቋራጩ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከግንባታ ስራው ዋነኛውን ክፍል ከ 6 ዐ ቀናት ባላነሰ ጊዜ
መፈፀም ሳይቻል የቀረ እንደሆነ፣
(ረ) አሰሪው በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 26 መሠረት አግባብነት ያለው ፍ/ቤት በተሰጠው
የመጨረሻ ውሳኔ (የይግባኝ አቤቱታ ሊቀርብበት የማይችል ውሳኔ) መሠረት ሳይፈፅም የቀረ እንደሆነ፣
በውል ማቋረጥ ምክንያት የሚነሱ አለመግባባቶች፤

21 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
21.4. በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ንዑስ አንቀጽ 21.2 ከ(ሀ) እስከ (ነ) ወይም በንዑስ አንቀጽ 21.3 የተዘረዘሩት
ሁኔታዎች ስለመከሰታቸው በሁለቱም ወገኖች ያለመግባባት ሲፈጠር፤ አንደኛው ወገን የውል ማቋረጥ
ማስጠንቀቂያ በደረሰው በ 45 ቀናት ውስጥ ያለመግባባቱ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 26
በተመለከተው መሠረት እንዲፈታ ያቀርባል፡፡ይህ በሆነበት ጊዜ በውሉ በተመለከተው የግጭት አፈታት ውሳኔ
መሰረት ካልሆነ በስተቀር ውሉ መቋረጥ አይኖርበትም፡፡
21.5. በአጠቃላይ የውሉ ሁኔታዎች ንዑስ አንቀጽ 21.2 ከ(ሀ) እስከ (ነ) በተመለከተው ምክንያት አሰሪው ውሉን
ሲያቋርጥ በሥራ ተቋራጩ ወጪ በሙሉ ወይም በከፊል ያልተጠናቀቁትን ስራዎች በራሱ (በአሰሪው) ወይም
በሌላ ስስተኛ ወገን እንዲሰሩ ያደርጋል፡፡ ይሁን እንጂ ሥራ ተቋራጩ ውል ያልተቋረጠባቸው ግዴታዎች
መፈፀሙን ይቀጥላል፡፡
21.6. አሰሪው ውሉን ያቋረጠው በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ንዑስ አንቀጽ 21.2 (ኘ) ምክንያት ከሆነ ውሉ
የተቋረጠው ለአሰሪው አመቺነት ሲባል መሆኑን በመግለጽ የውል መቋረጡ ወሰንን እና ከመቼ ጀምሮ
ተግባራዊ እንደሚሆን ይገለፃል፡፡

22. ውል ሲቋረጥ የሚፈፀም ክፍያ

22.1. ውል የተቋረጠው በሥራ ተቋራጩ መሰረታዊ የውል መጣስ ከሆነ መሐንዲሱ በውሉ መሰረት የተከናወነው
የግንባታ ሥራ እና የቀረቡ የግንባታ ቁሶች ዋጋን በማሰብ ከነዚህ ዋጋዎች ላይ የቅድሚያ ክፍያዎችን እና በልዩ
የውል ሁኔታዎች መሠረት ላልተጠናቀቀው ሥራ የሚቀነስ መቶኛ በመቀነስ የክፍያ ሰነድ ይሰጣል፡፡ የአሰሪው
ሊያገኝ የሚገባው ድምር መጠን የሥራ ተቋራጩ ከቀሪው ክፍያ የሚበልጥ ከሆነ ቀሪው ለ አሰሪው መከፈል
የሚገባ ዕዳ ይሆናል፡፡
22.2. ውሉ የተቋረጠው በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ንዑስ አንቀጽ 21.2 (ኘ) መሰረት ከሆነ ወይም በአሰሪው
መሰረታዊ የውል መጣስ ከሆነ፣ መሐንዲሱ ለተጠናቀቁ የግንባታ ሥራዎች፣ ለታዘዙ የግንባታ ቁሶች፣ የግንባታ
መሣሪያዎች፣ ለታዘዙ ቁሶች፣ የግንባታ መሣሪያዎችን ለማንሳት የሚያስፈልግ ወጪ፣ ለግንባታ ሥራው ተብሎ
የተቀጠሩ የሥራ ተቋራጩ ሠራተኞችን የመመለሺያ ወጪ እና የሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራዎችን
ለመከላከልና ለመጠበቅ የሚያስፈልገውን ወጪ የክፍያ ሰነድ እስከተዘጋጀበት ቀን ድረስ የተሰጠን የቅድሚያ
ክፍያ በመቀነስ የክፍያ ሰነድ ይሰጣል፡፡
22.3. አሰሪው ውሉን ያቋረጠው በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ንዑስ አንቀጽ 21.2 (ሐ) ምክንያት ከሆነ ለሥራ
ተቋራጩ የሚከፈለው ካሳ አይኖርም።ይህ አይንቱ የውል የማቋረጥ ድርጊት አሰሪው ያለውን የመክሰስ መብት
ወይም ሌላ መፍትሔ የሚጎዳ ወይም የሚገድብ መሆን የለበትም፡፡

22 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
23. ከውል መቋረጥ በኋላ ያሉ ሁኔታዎች

23.1. በውሉ መሰረት ውሉ ከተቋረጠ ወይም ከተጠናቀቀ በኋላ እንዲተገበሩ የሚፈለጉትን የውሉ ግዴታዎች፣
ድንጋጌዎችና ሁኔታዎች ውሉ ከተቋረጠ ወይም ከተጠናቀቀ በኋላም ቢሆን ሁለቱም ወገኖች ለማክበር
ተስማምተዋል፡፡
23.2. ውሉ የተቋረጠው በሥራ ተቋራጩ ጥፋት ከሆነ በግንባታ ቦታ ላይ ያሉ ሁሉም የግንባታ ቁሶች፣ ተቋም፣
መሣሪያ ጊዜያዊ የግንባታ ሥራዎች እና የግንባታ ሥራዎች የአሰሪው ንብረት ሆነው ይቆጠራሉ፡፡
23.3. ውሉ ከተጠናቀቀ /ከተቋረጠ በኋላ በሙሉም ሆነ በከፊል ከግንባታ ስራዎቹ ጋር በተየያዘ የተያዙ
መረጃዎች፣ ሰነዶችና መዝገቦች (በኤሌክትሮኒክስ ወይም በሌላ መንገድ የተያዙትንም ይጨምራል) ሥራ
ተቋራጩ ለአሰሪው ማስረከብ አለበት፡፡ሆኖም ግን በሰነዶቹ፣መረጃዎች ወይም ጽሑፎች ከግንባታ ስራው ጋር
ብቻ የሚያያዝ እስካልሆነ ድረስ ወይም ቅጂዎቻቸውን በህግ እንዲይዝ የሚጠበቅበት ከሆነ ወይም እነዚህን
ሰነዶች ፣መረጃዎች ወይም ጽሑፎች ውሉ ከመፈረሙ በፊት ያገኛቸው እስከሆነ ድረስ ሥራ ተቋራጩ የነዚህን
ቅጂዎች ማስቀመጥ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሥራ ተቋራጩ በርክክብ ወቅት ለ አሰሪው ሙሉ ትብብር
ማድረግ አለበት፡፡ የሚያደርገው ትብብርም ውጤታማ በሆነ ሁኔታ አሰሪው የግንባታ ስራውን ሰነዶችን፣
ሪፖርቶችን፣ ማጠቃለያዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ያለምንም እንቅፋት ለማስተላለፍ እንዲችል የሚያስፈልጉ
ሰነዶችን፣ ሪፖርቶችን፣ ማጠቃለያዎችንና ሌሎች መረጃዎችን በተሟላ ሁኔታ አሰሪው እንዲያገኘው ማድረግንም
የሚያካትት ይሆናል፡፡

24. የመብቶችና ግዴታዎች መቋረጥ

24.1. ውሉ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 21 መሠረት ሲቋረጥ ወይም በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ
88 መሰረት የመጨረሻ ርክክብ ሰርተፍኬት ሲሰጥ ፤ከዚህ በታች ከተጠቀሱት በስተቀር ከውሉ ጋር የተያያዙት
መብቶችና ግዴታዎች ይቋረጣሉ፡፡
(ሀ) እነዚህ መብቶችና ግዴታዎች በውሉ መቋረጥ ወይም መጠናቀቅ ቀን የነበሩ ከሆነ፣
(ለ) በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 28 የተመለከተው ምስጢራዊነት ግዴታ ፣
(ሐ) በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 56 መሠረት አቅራቢው የሂሳብ ሰነዶችና ሌሎች ጽሑፎችን ኦዲትና
ምርመራ እንዲደረግባቸው የመፍቀድ ግዴታ ፣
(መ) ለተዋዋይ ወገኖች በሕግ የተሰጠ መብት ሲሆን፣

23 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
25. የግንባታ ስራ ማቆም

25.1. በአጠቃላይ የውል ሁኔታ አንቀጽ 21 መሰረት በአንዱ ተዋዋይ ወገን በማስታወቂያ ውል እንደተቋረጠ የሥራ
ተቋራጩ ማስታወቂያው እንዳወጣ/እንደተቀበለ የግንባታ ሥራዎችን ሥርዓት ባለው መንገድ ለሟቋረጥ
አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን በሙሉ መውሰድ፣ የግንባታ ቦታውን ደህንነቱን አስተማማኝ እና የተጠበቀ
ማድረግ፣ የግንባታ ቦታውን በተቻለ ፍጥነት መልቀቅ እና ለእነዚህ ጉዳዮች የሚወጣውን ወጪ ለመቀነስ እና
ዝቅተኛ ለማድረግ የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
25.2. መሐንዲሱ ውል ከተቋረጠ በኋላ በተቻለ ፍጥነት በልዩ የውል ሁኔታዎች ላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የስራውን
ዋጋ እና ለሥራ ተቋራጩ መከፈል የሚገባውን ክፍያ ተመን ማዘጋጀትና ማጽደቅ ወይም ማፀደቅ ይኖርበታል፡፡
25.3. ውል በሚቋረጥበት ጊዜ መሐንዲሱ በተቻለ ፍጥነት የግንባታ ሥራዎችን ከመረመረ በኋላ በሥራ ተቋራጩ
የተከናወኑ የግንባታ ሥራዎች ሪፖርት ማዘጋጀት እና የጊዜያዊ መዋቅሮች፣ የግንባታ ቁሶች፣ ተቋም እና
መሣሪያዎች ቆጠራ ማካሄድ ይኖርበታል፡፡ ቁጥጥር እና ቆጠራ በሚካሄድበት ጊዜ የሥራ ተቋራጩ እንዲገኝ
መጠራት ይኖርበታል፡፡ መሐንዲሱ የሥራ ተቋራጩ ለግንባታ ሥራው የተቀጠሩ ሠራተኞች ያልተከፈለ ዕዳ እና
ለአሰሪው መክፈል ያለበት ዕዳ ካለ ይህን የሚያሳይ የሂሳብ ሰነድ ማዘጋጀት ይገባዋል፡፡

26. የአለመግባባቶች አፈታት

26.1. የአሰሪው በጽሑፍ ካላሳወቀው በስተቀር ሥራ ተቋራጩ አለመግባባቶች የወሉን መጽናት (validity of
contract) ጨምሮ በሚፈጠሩበት ጊዜም ቢሆን የውሉ ሁኔታዎች ማስፈፀሙን ለመቀጠል ሁለቱም ወገኖች
ተስማምተዋል፡፡
26.2. ከውሉ የሚመነጩ ማንኛውንም አለመግባባቶች ወይም ውዝግቦች አሰሪውና ሥራ ተቋራጩ በሰላማዊ ድርድር
ለመፍታት ማንኛውንም ጥረት ያደርጋሉ፡፡
26.3. ተዋዋዮቹ የተነሱትን አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ መፍታት ካልቻሉ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ንዑስ
አንቀጽ 26.4 በተመለከተው የአለመግባባቶች አፈታት ሥርዓት መሠረት የሚከናወን ይሆናል፡፡
26.4. ከላይ በንዑስ አንቀጽ 26.3 መሠረት ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች አንድ ሲኒየር የሆነ ሰው በተገኘበት
አለመግባባቶቻቸውን ለመፍታት ውይይት ያካሄዳሉ፡፡ ውይይቱ የሚካሄደው በአሰሪው ሰብሳቢነት ሲሆን
የስብሰባው ውጤቶችም በቃለ-ጉባኤ ይመዘገባሉ፡፡እንደዚህ ዓይነት ስብሰባዎች የሚካሄዱት ስምምነት
በተደረሰባቸው ቦታዎች (በስልክ የሚካሄድ ስብሰባም ይጨምራል) በሰብሳቢው ፍላጐት መሠረት ሲሆን
ዓላማቸውም አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ነው፡፡
26.5. ተዋዋዮች አለመግባባትን ወይም ውዝግብን ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ ባለው በ 28 ቀናት ውስጥ በሰላማዊ
መንገድ ለመፍታት ካልቻሉ አንደኛው ወገን የኢትዮጵያ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት
ሊያቀርበው ይችላል፡፡
27. የመዘግየት ቅጣት
24 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ
ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
27.1. በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 18 በተመለከተው ካልሆነ በስተቀር ሥራ ተቋራጩ የግንባታ
ስራዎቹን በሙሉ ወይም በከፊል በውሉ ጊዜ ውስጥ መፈፀም ሲያቅተው ሌሎች የመፍትሔ እርምጃዎች
እንደተጠበቁ ሆነው አሰሪው የውል ዋጋን መሠረት አድርጎ የጉዳት ማካካሻውን በሚከተሉት ስልቶች ሊቀንስ
ይችላል፡፡
(ሀ) ያልተሰሩ ግንባታ ስራዎች ዋጋ ላይ በየቀኑ ዐ.1% ወይም 1/1 ዐዐዐ (ከአንድ ሺህ አንድ) ቅጣት ግንባታ
ስራዎቹ እስከሚተገበሩት ቀን ድረስ የሚቀጥል፡፡
(ለ) ከፍተኛው የመዘግየት ቅጣት መጠን/ ጣሪያ ከውል ዋጋው 1 ዐ% በላይ መብለጥ አይችልም፡፡
27.2. ሥራ ተቋራጩ ውል በመፈጸም ረገድ በመዘግየቱ በአሰሪው ስራ ላይ ጉዳት የሚደርስ ሲሆን አሰሪው
በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 21 መሰረት ከፍተኛው የመዘግየት ቅጣት መጠን (10%) እስኪደርስ
ድረስ መጠበቅ ሳያስፈልገው የቅድሚያ ማስታወቂያ በመስጠት ውሉን ሊያቋርጥ ይችላል።

27.3. የማጠናቀቂያ ቀኑ የጉዳቶች ማካካሻ ከተከፈለ በኋላ ከተራዘመ መሐንዲሱ የሥራ ተቋራጩ ከሚገባው በላይ
የጉዳት ካሳ እንዳይከፍል ቀጣይ የክፍያ ሰነዶችን በማስተካከል ማረም ይኖርበታል፡፡

28. ሚስጢራዊነት

28.1. ተዋዋይ ወገኖች ሰነዶችንና መረጃዎችን ለሦስተኛ ወገን ሳያስተላልፉ በሚስጢር መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ያለአንደኛው ወገን ስምምነት የተፃፈ ስምምነት ወይም በሌላኛው ወገን የተሰጠውን ማንኛውም ሰነድ (ማስረጃ)
ወይም ሌላ መረጃ ከውል በፊት፣ በውል ጊዜ ወይም በኋላ የተሰጠ ቢሆንም እንኳ ለሌላኛው ተዋዋይም ሆነ
ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት ከሕግ ጋር የሚቃረን፣ ተቀባይነት የሌለውና ውድድርን የሚገታ ተግባር ነው፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ቢኖሩም ሥራ ተቋራጩ ለንዑስ ተቋራጭ ለውሉ አፈፃፀም የሚረዱትንና ከአሰሪው
የተረከባቸውን ሰነዶች፣ ማስረጃዎችና ሌሎች መረጃዎች ምስጢርነታቸው እንዲጠበቅ ቃል በማስገባት ሊሰጠው
ይችላል፡፡
28.2. አሰሪው ከሥራ ተቋራጩ የተቀበላቸውን ሰነዶች፣ ማስረጃዎችና ሌሎች መረጃዎች ከውሉ ጋር ለማይዛመዱ
ምክንያቶች ሊገለገልበት አይችልም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታም ሥራ ተቋራጩ ከአሰሪው የተቀበላቸውን ሰነዶች፣
መረጃና ሌላ ማስረጃ ከተፈለገው ግዥ ወይም ተያያዥ አገልግሎት ውጭ ለሌላ ዓላማ አይገለገልበትም፡፡

28.3. በዚህ አንቀጽ የተጣሉት የምስጢራዊነት ግዴታዎች ቢኖሩም ቀጥለው የተዘረዘሩት ሁኔታዎች በተዋዋይ ወገኖች
ላይ ተግባራዊ አይሆኑም፡፡
(ሀ) አሰሪው ወይምሥራ ተቋራጩ የውሉን አፈፃፀም ፋይናንስ ከሚያደርጉ ሌሎች ተቋማት ጋር የሚጋራው መረጃ፣
(ለ) በተዋዋዮች ጥፋት ባልሆነ ሁኔታ ውሉ በሚመሰረትበት ወቅት ወይም ወደፊት በሕዝብ ይዞታ ሥር
የሚገባ መረጃ፣
(ሐ) መረጃውን ለማውጣት ሕጋዊ ሥልጣን ባለው አካል አማካኝነት ሦስተኛ አካል ዘንድ የደረሰ መሆኑ ሲረጋገጥ፣

25 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
(መ) መረጃው ይፋ በወጣበት ጊዜ ለተዋዋይ ወገን ከመድረሱ አስቀድሞ በሶስተኛ ሰው የተያዘ ለመሆኑ ሊረጋገጥ
የሚችል ሲሆን፣
(ሠ) አንደኛው ተዋዋይ ወገን መረጃው ይፋ እንዲሆን በጽሑፍ የፈቀደ መሆኑ ሲረጋገጥ፣
28.4. ተዋዋይ ወገኖች ውሉ ከመመስረቱ በፊት የነበራቸውን ጠቅላላ እውቀት፣ ልምድና ክህሎት ለመጠቀም
አይከለከሉም፡፡
28.5. አሰሪው ከኦዲቲንግና ከወቅታዊ የገበያ ዋጋዎች ጥናት ጋር የተያያዙ ምስጢራዊ መረጃዎች ሥራ ተቋራጩን
በየጊዜው በጽሑፍ እያሳወቀ ለሶስተኛ ወገን መስጠት ይችላል፡፡ መረጃውን የሚቀበሉት የሶስተኛ ወገን አካላትም
መረጃውን ለተፈለገበት ዓላማ በመጠቀም ረገድ በምስጢር እንዲጠብቁና እንዲጠቀሙ አሰሪው ጥረት
ያደርጋል፡፡ አሰሪው በተጨባጭ መረጃ ትክክለኛውን የገበያ ዋጋ ሳያረጋግጥ የዝቅተኛ ዋጋ ጥያቄ አያቀርብም፡፡
28.6. ሥራ ተቋራጩ ከዚህ በታች በተመለከቱት ሁኔታዎች ተስማምቷል፡፡
(ሀ) በንዑስ አንቀጽ 28.6 (ለ) መሠረት መረጃን ይፋ ማድረግ ወይም አለማድረግ ውሳኔ የአሰሪው ውሳኔ ብቻ
መሆኑን፣
(ለ) በንዑስ አንቀጽ 28.6 (ሀ) መሠረት አቅራቢው በመረጃዎች ይፋ ማድረግና አለማድረግ ሂደት ከአሰሪው ጋር
መተባበር አለበት፡፡በዚሁ ረገድ አቅራቢው የግዥ ፈፃሚው አካል የሚያቀርብለትን የትብብርና የድጋፍ ጥያቄ
በ 5 የሥራ ቀናት ውስጥ መልስ ለመስጠት ተስማምቷል፡፡
28.7. ሥራ ተቋራጩና ንዑስ ተቋራጩ በቁጥጥራቸው ስር የሚገኘውን መረጃ አሰሪው ሲጠይቅ በ 5 የሥራ ቀናት (ወይም
አሰሪው በሚወሰነው ሌላ የጊዜ ገደብ) መስጠት አለባቸው፡፡
28.8. አሰሪው የሥራ ተቋራጩን ምስጢራዊ መረጃ ይፋ በማድረግ ሂደት መመሪያዎች በሚፈቅዱት መሠረት ስራ
ተቋራጩን ማማከር ይኖርበታል፡፡
28.9. በዚህ አንቀጽ የተዘረዘሩት የምስጢራዊነት የውል ሁኔታዎች ውሉ ከመመስረቱ በፊት በተዋዋይ ወገኖች ዘንድ
የነበሩ የሚስጢራዊነትን ሁኔታዎች በማንኛውም ሁኔታ ሊያሻሽሉ አይችሉም፡፡
28.10. ይህ አንቀጽ ያካተታቸው የምስጢራዊነት ሁኔታዎች (የግል መረጃን ይጨምራል) ላልተወሰነ ጊዜ ፀንተው ይቆያሉ፡፡
በዚህ ውል በሌላ አኳኋን ካልተገለፀ በስተቀር የዚህ አንቀጽ ሁኔታዎች ውሉ ከተቋረጠ ወይም ከተጠናቀቀ በኋላ
ለ 3 ዓመታት ፀንተው ይቆያሉ፡፡
28.11. ሥራ ተቋራጩ በዚህ አንቀጽ የተመለከቱትን ሁኔታዎች ሳይፈፅም ሲቀር አሰሪው ወዲያውኑ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ
በመስጠት ውሉን የማቋረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

29. ልዩ-ልዩ

29.1. ማናቸውንም ውሳኔ ፣ተግባር ወይም አሰሪው ሊተገብራቸው የሚገቡ ነገሮችን አሰሪው በአጠቃላይም ሆነ በዝርዝር
ስልጣን በተሰጠው በማንኛውም ሰው ሊፈጸም ይችላል፡፡ ሥራ ተቋራጩ በጽሑፍ የዚህን ሰው ማንነት ሲጠይቅ
አሰሪው ያሳውቃል፡፡

26 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
29.2. ሥራ ተቋራጩ በየጊዜው ከአሰሪው በሚቀርብለት ጥያቄ መሰረት የውሉን ሁኔታዎች በተግባር ላይ ለማዋል
የሚያስፈልጉትን ማንኛውንም አግባብነት ያላቸው ተግባራት እና/ወይም ተጨማሪ ሰነዶችን የማስፈጸም ተግባር
ይኖረዋል።
29.3. ማንኛውም የውሉ ድንጋጌ በየትኛውም ቦታ በሚገኝ ስልጣን ባለው አካል ውድቅ ከተደረገ ወይም ህጋዊ
ተፈጻሚነት እንዳይኖረው ከተደረገ ውድቅ መደረጉ ለቀሪው የውሉ ድንጋጌዎች ላይ ተጽዕኖ
አይኖረውም፡፡ በተጨማሪም በአንድ ቦታ በሚገኝ ስልጣን ባለው አካል የውል ድንጋጌ ውድቅ መደረግ
ወይም ህጋዊ ተፈጻሚነት እንዳይኖረው መደረግ ለሌላ ማንኛውም ቦታ ህጋዊ ተፈጻሚነቱን
የሚያሳጣ ወይም ውድቅ የሚያደርገው አይሆንም፡፡
29.4. አንደኛው ተዋዋይ ወገን ሌላኛውን ተዋዋይ ወገን የውል ግዴታውን እንዲፈፅም ባለመጠየቁ ወይም የውል ጥሰትን
ተከትሎ መብቱን አለመጠየቁ ወይም መውሰድ የሚገባውን እርምጃ አለመውሰዱ ይህንን ወይም ተከታይ የውል
ጥሰቱ እንዳልተፈፀመ አይቆጠርም፡፡
29.5. እያንደንዱ ተዋዋይ ወገን ውሉን ለማዘጋጀት ወይም ለማስፈጸም የሚወጡትን የህግና ሌሎች ማንኛውም
ወጪዎችን የየራሱን የመሸፈን ሀላፊነት አለበት፡፡
29.6. ሥራ ተቋራጩ በማንኛውም ፍ/ቤት ወይም በማንኛውም የአስተዳደር አካላት የፋይናንስ ሁኔታ ወይም የንግድ
ስራውን ወይም እንቅስቃሴውን ሊነካ ወይም ሊያስጠይቅ የሚችል ያልተዘጋ የክስ ሂደት ወይም የሚያሰጋ ሁኔታ
የሌለው መሆኑን ዋስትና ይሰጣል፡፡ ከዚሁ በተጨማሪ ሥራ ተቋራጩ ውሉን ለመዋዋል የሚያግደው ምንም
አይነት የውል ሁኔታ እንደሌለ፤ እንዲሁም ሥራ ተቋራጩ በውሉ ውስጥ ሊኖሩ የሚችሉ አደጋዎችና
አጋጣሚዎችን በመገንዘብ ወይም በውሉ ውስጥ ያሉትን ማንኛውም ግዴታዎችና መረጃዎች በመረዳት በዚሁ
መሰረት ሊፈጽም የተስማማ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
29.7. በዚህ ውል ውስጥ የተካተቱት መብቶችና መፍትሔዎች በሌላ ውል ወይም ሰነድ ውስጥ ከተሰጡ መብቶች ወይም
መፍትሔዎች ጋር አብሮ ሊራመዱ የሚችሉ ናቸው፡፡ በዘህ አንቀጽ ውስጥ “መብት’’ ሲባል ማንኛውም ስልጣን፣
ጥቅም ፣ መፍትሔ ወይም ገንዘብ ነክ ባለቤትነት ወይም የዋስትና ባለመብትነትን ያካትታል፡፡

ሐ. የአሰሪው ግዴታዎች

30. ድጋፍ ማድረግና ሰነዶች ስለመስጠት

30.1. የሥራ ተቋራጩ ግዴታዎቹን መወጣት ሂደት ላይ ተፅዕኖ ሊያመጡ የሚችሉ ሕጎች፣ ደንቦችና የኢትዮጵያ
መንግስት የአገር ውስጥ ቀረጥ ትዕዛዞች ወይም መተዳደሪያ ደንቦች ላይ ያሉ መረጃዎችን ግልባጭ (ኮፒ) ለማግኘት
አሰሪውን ድጋፍ መጠየቅ ይችላል፡፡ አሰሪው የተጠየቀውን ድጋፍ በሥራ ተቋራጩ ወጪ መስጠት ይችላል፡፡
30.2. በልዩ የውል ሁኔታዎች እስካልተጠቀሰ ድረስ፣ ሥራ ተቋራጩ የሚከተሉትን ግዥዎች እንዲያካሂድ አሰሪው
አስፈላጊ የሆኑትን ጥረቶች ሁሉ ማድረግና ማመቻቸት ይኖርበታል፡፡

27 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
(ሀ) የሥራ ተቋራጩ፣ ንዑስ የሥራ ተቋራጭ ወይም ሠራተኞች የግንባታ ሥራዎችን ለማከናወን
የሚያስፈልጋቸውን ቪዛዎች፣ ፈቃዶች፣ የሥራና የመኖሪያ ፍቃዶችን ጨምሮ እና ሌሎች
አስፈላጊ ሰነዶች፣
(ለ) በልዩ የውል ሁኔታዎች የተጠቀሱ ሌላ ማንኛውም ድጋፍ

30.3. በልዩ የውል ሁኔታዎች ውስጥ በሌላ መንገድ እስካልተጠቀሰ ድረስ መሐንዲሱ ሥራዎችን ለማከናወን የተዘጋጀ
ንድፍ አንድ ኮፒ እና የሥራ ዝርዝሩን እና ሌሎች የውል ሰነዶችን ሁለት ኮፒ ውሉ በተፈረመ በ 3 ዐ ቀናት ውስጥ
ለሥራ ተቋራጩ ከክፍያ ነፃ መስጠት አለበት፡፡ የሥራ ተቋራጩ ተጨማሪ ንድፎችን፣ የሥራ ዝርዝሮችን እና
ሌሎች ሰነዶችን ኮፒዎቹ እስካሉ ድረስ መግዛት ይችላል፡፡ የሥራ ተቋራጩ የመጨረሻ የሥራ ርክክብ ሲደረግ
ሁሉንም ንድፎች፣ የሥራ ዝርዝሮችና ሌሎች የውል ሰነዶች መመለስ ይኖርበታል፡፡
30.4. ለውሉ ዓላማ አስፈላጊ እስካልሆነ ድረስ ከመሐንዲሱ ፈቃድ ውጭ በአሰሪው የተሰጡ ንድፎች፣ የሥራ ዝርዝሮች
እና ሌሎች ሰነዶች በሥራ ተቋራጩ ለሶስተኛ ወገን መተላለፍ ወይም ጥቅም ላይ መዋል የለበትም፡፡
30.5. መሐንዲሱ የግንባታ ሥራዎች በተገቢውና በቂ በሆነ መንገድ እንዲከናወኑና ችግሮች እንዲፈቱ ለማድረግ
የሚያስችሉ አስተዳደራዊ ትዕዛዞች ከተጨማሪ ሰነዶችና መረጃዎች ጋር ለሥራ ተቋራጩ የመስጠት ሥልጣን
ይኖረዋል፡፡

31. ወደ ግንባታ ቦታ የመግቢያ ፈቃድ ስለመስጠት

31.1. አሰሪው እንደ ግንባታ ሥራዎቹ አፈጻጸም ደረጃ እና በተገቢው ጊዜ እና የሥራዎች ትግበራ ፕሮግራም መሠረት
ለሥራ ተቋራጩ የግንባታ ቦታውን ማስረከብ አለበት፡፡ በፀደቀው የግንባታ ሥራ ፕሮግራም መሠረት አሰሪው
ማስረከብ የሚገባውን የግንባታ ቦታዎችን ካላስረከበ ከዚህ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን እንዳዘገየ ይቆጠራል፡፡ ይህም
የጊዜ መካሻ ሁኔታ ሊባል ይችላል፡፡
31.2. የሥራ ተቋራጩ መሐንዲሱን ወይም በመሐንዲሱ የተፈቀደለትን ወይም ሥልጣን የተሰጠውን ሰው ወደግንባታ
ስራው ቦታ እና ከውሉ ጋር በተገናኘ የሚሰሩ ስራዎች የሚካሄዱበት ወይም ሊተገበር የታሰበ ሌላ ቦታ እንዲገባ
መፍቀድ ይኖርበታል፡፡
31.3. በአሰሪው ለሥራ ተቋራጩ የተሰጠ ቦታ ከውሉ ጋር ለተያያዘ ሥራ ትግበራ ካልሆነ በቀር ለሌላ ዓላማ መጠቀም
አይኖርበትም፡፡
31.4. የሥራ ተቋራጩ ቦታው ላይ እስካለ ድረስ ማንኛውም በሱ ሥር ያለ ቅጥር ግቢ በጥሩ ሁኔታ መያዝ ይኖርበታል፡፡
እንደዚሁም በአሰሪው ወይም በመሐንዲስ ከተጠየቀ ውሉ ሲጠናቀቅ ቦታውን በጊዜ የሚመጣውን ማርጀትና
ለውጥ ታሳቢ በማድረግ መጀመሪያ ወደነበረበት ሁኔታ መመለስ ይኖርበታል፡፡
31.5. የሥራ ተቋራጩ በራሱ ፍላጎት በቦታው ላይ ላደረገው ማሻሻል ክፍያ ማግኘት አይችልም፡፡

28 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
32. ክፍያ

በሥራ ተቋራጩ በዚህ ውል ስር የተከናወኑ የግንባታ ሥራዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት አሰሪው በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች
ምዕራፍ (ሠ) መሠረት ለሥራ ተቋራጩ መክፈል ይኖርበታል፡፡

33. ለሥራ ተቋራጩ ሠራተኞች የሚከፈል ክፍያ መዘግየት

የሥራ ተቋራጩ ሠራተኞች በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕግ መሠረት ማግኘት የሚገባቸው ክፍያዎች ማለትም
የቀን ክፍያ ወይም ደመወዙ እና አበሎች ክፍያ ከዘገየ አሰሪው ለሥራ ተቋራጩ የቀን ክፍያዎች፣ ደመወዝ፣ አበል እና መዋጮዎችን
እንዲከፍል የ 15 ቀናት ማስታወቂያ ሊሰጥ ይችላል፡፡

መ. የስራ ተቋራጩ ግዴታዎች

34. አጠቃላይ ግዴታዎች

34.1. የሥራ ተቋራጩ በጥንቃቄና በብቃት፤ በውሉ በተቀመጡ ነጥቦች መሠረት በውሉ እስከተጠቀሰው ደረጃ ድረስ
የግንባታ ሥራዎችን ዲዛይን ማድረግ እና ማከናወን፣ ማጠናቀቅና የግንባታ ሥራዎች ማናቸውንም ጉድለቶች
ማስተካከል ይኖርበታል፡፡ የሥራ ተቋራጩ በውሉ የተጠቀሱ ወይም ከውሉ ተነስቶ ምክንያታዊ በሆነ መንገድ
ሊተረጎሙ የሚችሉ ጊዜያዊ ወይም ቋሚ ተፈጥሮ ያላቸውን የግንባታ ሥራዎች ዲዛይን ለማድረግ፣ ለማከናወን፣
ለማጠናቀቅና ማንኛውንም ጉድለት ለማስተካከል የሚያስፈልጉ የግንባታ ሥራዎች ሠራተኞችን፣የግንባታ ቁሶችን፣
መዋቅሮችን፣ መሣሪያዎችን ከላይ ሆኖ መቆጣጠር እና መከታተል ይኖርበታል፡፡
34.2. የሥራ ተቋራጩ በውሉ ውስጥ የሚከናወኑ ትግበራዎች እና የግንባታ ዘዴዎች ብቁነት በአስተማማኝነት መቆም እና
ደህንነት ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ ይኖርበታል፡፡
34.3. የሥራ ተቋራጩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ውስጥ በሥራ ላይ ያሉ (ተፈጻሚ ለሆኑ) ሁሉም
ሕጎችና ደንቦች ማክበርና ተገዢ መሆን፤ እንደዚሁም የእርሱ ሠራተኞችና ጥገኞቻቸው በተጨማሪም የአገር ውስጥ
ሠራተኞች ሕጎችና ደንቦችን ማክበር እና ለነሱም ተገዢ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡ የሥራ ተቋራጩ በራሱ፣
በንዑስ የሥራ ተቋራጩ ወይም በሠራተኞቹ ሕጎችና ደንቦች መጣስ ምክንያት ለሚመጣ ማንኛውም የጉዳት ጥያቄ
ለአሰሪው ካሣ መክፈል ይኖርበታል፡፡
34.4. የሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራዎቹ በሥራ ላይ ያሉ የአካባቢ ደህንነት (environmental) እና የጥራት
ደረጃዎችን የሚያሟሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ እንደዚሁም ምንም አይነት ኬሚካል ወይም ሌላ
ምርት/መሣሪያ በጥቅሉ በአካባቢ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ በሚያመጣ መልኩ እና በተለይም በሥራ ቦታ የጤና ችግር
በሚያስከትል መንገድ የሥራ ተቋራጩ በጥቅም ላይ ማዋል የለበትም፡፡ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ የቅርብ ጊዜ
ቴክኖሎጂ፣ ደህንነቱ አስተማማኝ የሆነ መሣሪያ፣ የተለያዩ የግንባታ ሥራ ማሽኖች፤ ቁሶች እና ዘዴዎች የሥራ
ተቋራጩ መጠቀም ይኖርበታል፡፡
29 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ
ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
34.5. የሥራ ተቋራጩ የሚከተሉትን ማናቸውንም እርምጃዎች ከመውሰዱ በፊት አሰሪው በቅድሚያ ማጽደቅ
ይኖበታል፡፡
(ሀ) የሥራ ተቋራጩ በንዑስ የሥራ ተቋራጩ ለሚሠሩ ነገሮች ሁሉ ተጠያቂ እንደሚሆን
በመረዳት የግንባታ ሥራዎችን ክፍል ለማሠራት የሥራ ተቋራጩ ከንዑስ ስራ ተቋራጭ ጋር
ውል በሚገባበት ጊዜ ፡፡
(ለ) በልዩ የውል ሁኔታዎች የተጠቀሰ ማንኛውም ሌላ እርምጃ

34.6. የሥራ ተቋራጩ በመሐንዲሱ የሚሰጡ ማናቸውንም አስተዳደራዊ ትእዛዝ ማክበር (መፈጸም) አለበት፡፡ የሥራ
ተቋራጩ አስተዳደራዊ ትዕዛዙ ከተጠቀሰው መሐንዲስ ሥልጣን ወይም ከውሉ ወሰን በላይ ነው ብሎ ካመነና
የጊዜ ጫና የሚያመጣበት ከሆነ ትዕዛዙ በደረሰው በ 3 ዐ ቀናት ውስጥ ለሚመለከተው የውል አስተዳዳሪ ሃሳቡን
ማብራራትና ማሳወቅ አለበት፡፡ ይህን ማስታወቂያ መስጠት ግን የአስተዳደራዊ ትዕዛዙን ትግበራ ማቋረጥ
የለበትም፡፡
34.7. የሥራ ተቋራጩ ከውሉ ጋር በተያያዘ የተገኙ ሁሉም ሰነዶችና መረጃዎች እንደ ግልና ሚስጥራዊ አድርጎ
መመልከት (መያዝ) አለበት፡፡ ለውሉ አፈፃፀም ጥቅም አስፈላጊ ከሆነ እና ከአሰሪው ወይም ከአሰሪው ጋር
በመመካከር በውል አስተዳዳሪው ከተሰጠ የፅኁፍ ስምምነት ውጭ ማተም ወይም የውሉን ማናቸውንም የተለያዩ
ነጥቦች ይፋ ማድረግ ወይም ውጭ ማውጣት የለበትም፡፡ ሰነዶችን እና መረጃዎችን በማተም ወይም ይፋ
በማድረግ በኩል አለመስማማት ከተፈጠረ የአሰሪው ውሰኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡

35. ብቁነት (ውል ለመፈፀም)

35.1. የሥራ ተቋራጩና ንዑስ ሥራ ተቋራጩ በጨረታ ሰነዱ ከተጠቀሱት ተቀባይነት ያላቸው አገሮች ዜጋ መሆን
አለባቸው፡፡ የሥራ ተቋራጭ ወይም ንዑሰ የሥራ ተቋራጭ ከነዚህ ሀገሮች ዜግነት ካለው ወይም በነዚህ ሀገሮች
የተቋቋመ፣ የታቀፈ፣ ወይም የተመዘገበ እና በአገሩ ሕግ መሠረት የሚሠራ ከሆነ የዚያ አገር ዜጋ እንደሆነ ተደርጎ
ይወሰዳል፡፡
35.2. የሥራ ተቋራጩና ንዑስ የሥራ ተቋራጮች ተቀባይነት ያላቸው አገር ዜጎችን ለሥራው ማሰማራት እና መነሻቸው
ከብቁ አገሮች የሆኑ ዕቃዎችን መጠቀም አለባቸው፡፡

36. የስነ-ምግባር ደንቦች

36.1. የሥራ ተቋራጩ በዚህ ውል የተመለከቱትን ግዴታዎች በታመነ እና ገለልተኛ በሆነ መልኩ ማከናወን አለበት ፡፡
እንዲሁም በሙያዊ ስነምግባር ደንቡ መሰረት ለአሰሪው ታማኝ አማካሪ ሆኖ ስራውን ማከናወን ያለበት ሲሆን
የአሰሪውን የፅኁፍ ፈቃድ ሳያገኝ በማንኛውም ጊዜ ከውሉ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ መግለጫ የመስጠት ወይም
ከውሉ አፈፃፀም ጋር ተቃራኒ የሆኑ ድርጊቶች መፈፀም የለበትም፡፡

30 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
36.2. የሥራ ተቋራጩ፣ ንዑስ ተቋራጩ ወይም የሥራ ተቋራጩ ሠራተኛ ወይም ወኪል ከዚህ ውል ጋር ወይም
ከአሰሪው ጋር በተደረገ ሌላ ውል ጋር በተያያዘ ለማንኛውም ሰው ማባበያ ለመስጠት የጠየቀ፣ ወይም የሰጠ ከሆነ፣
ስጦታዎችና ጉቦ ያቀረበ ከሆነና ተመሳሳይ ድርጊቶችን መፈፀሙ ከተረጋገጠ አሰሪው ውሉን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡
36.3. የሥራ ተቋራጩ ከዚህ ውል ሊያገኝ የሚገባው ሙሉ ክፍያ በውል ዋጋው የተመለከተውን ብቻ ነው፡፡ የስራ
ተቋራጩ ወይም ሰራተኞቹ በዚህ ውል መሠረት ከሚያከናውናቸው ተግባራት ወይም ሊፈጽማቸው ከሚገባ
ግዴታዎች ጋር በተያያዘ የንግድ ኮሚሽን፣ ቅናሾች ወይም ቀጥተኛ ያልሆኑ ክፍያዎች መጠየቅና መቀበል
የለበትም፡፡
36.4. የሥራ ተቋራጩ ያለአሰሪው የፅሁፍ ፈቃድ ከዚሁ ውል ጋር በተያያዘ ወይም በዚህ ውል ላይ ጥቅም ላይ በዋለ
የፈጠራ ውጤት ፅኁፍ ወይም የስራ ሂደት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ምንም ዓይነት ኮሚሽን ፣ የተለየ
ጥቅም ወይም የባለቤትነት ክፍያ መቀበል አይችልም፡፡
36.5. የሥራ ተቋራጩና ሠራተኞቹ ከዚህ ውል ጋር በተያያዘ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ የሚያገኙትን መረጃ
(መረጃው ከውሉ በፊት፣ በውሉ ጊዜ ወይም ከውሉ በኋላ የተገኘ ቢሆንም) በምስጢር መጠበቅ አለባቸው፡፡
አሰሪው በጽሑፍ ካልተፈቀደላቸው በስተቀር መረጃውን ለሦስተኛ ወገን አሳልፈው መስጠት የለባቸውም፡፡
ከዚሁም በተጨማሪ ለዚሁ ውል አፈፃፀም ሲባል ከአሰሪው በጥናትና ምርምር፣ እንዲሁም በሙከራ የተገኙ
ውጤቶችን እና መረጃዎች አሰሪውን በሚጎዳ መልኩ መጠቀም አይገባቸውም ፡፡
36.6. የዚህ ውል ሁኔታዎች ያልተለመዱ የንግድ ወጪዎችን አያስተናግዱም፡፡ ያልተለመዱ የንግድ ወጪዎች የሚባሉት
ውሉ ውስጥ ያልተጠቀሱ ኮሚሽኖች ፣ ሕጋዊ ላልሆኑ ወይም ላልተሰሩ አገልግሎቶች የሚከፈሉ ኮሚሽኖች፣
በግልፅ ላልታወቀ ተከፋይ የተከፈሉ ኮሚሽንኖች ወይም ግብርን ለመሸሽ የተከፈሉ ኮሚሽኖችና የመሳሰሉትን
ያካትታል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ያልተለመዱ የንግድ ወጪ ጥያቄዎች ሲነሱ ውሉ እንዲቋረጥ ይደረጋል፡፡.
36.7. የሥራ ተቋራጩ ከውሉ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ በአሰሪው ውሉ ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ ማረጋገጫ እንዲያቀርብ
ሲጠየቅ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ አሰሪው አጠራጣሪ የሆኑ ያልተለመዱ የንግድ ሁኔታዎች መኖራቸውን
ከገመተ እውነታውን ለማወቅ አስፈላጊ ናቸው የሚላቸውን የሰነድ ማስረጃዎች ሊጠይቅ ወይም በአካል ተገኝቶ
ሊያጣራ ይችላል፡፡

37. የግንባታ ሥራዎች ቁጥጥርና ክትትል

37.1. የሥራ ተቋራጩ ሙሉ የግንባታ ሥራዎችን መቆጣጠርና መከታተል አለበት ወይም ይህን የሚያከናውን የውል
አስተዳደር መመደብ ይኖርበታል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ምደባ በቅድሚያ በመሐንዲስ እንዲፀድቅ መቅረብ አለበት፡፡
37.2. የውል አስተዳዳሪው ከፍላጎት መግለጫ ጋር የሚጣጣም የሙያ ብቃት ሊኖረው ይገባል፡፡ በተጨማሪም የሥራ
ልምዱ በመሐንዲሱ እንዲፀድቅ መቅረብ አለበት፡፡
37.3. የሥራ ተቋራጩ አስቀድሞ የመደበውን የውል አስተዳዳሪ ማንነት ለማፀደቅ በጽሑፍ ለመሐንዲሱ ማሳወቅ
አለበት፡፡ በማንኛውም ጊዜ መሐንዲሱ ማጽደቁን ሊያነሳ ይችላል፡፡ መሐንዲሱ ምደባውን አላፀድቅም የሚል ከሆነ
ወይም ያፀደቀውን ምደባ የሚያነሳ ከሆነ የውሳኔውን መሠረት መግለጽ ይኖርበታል፡፡ የሥራ ተቋራጩም ሳይዘገይ

31 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
አማራጭ የውል አስተዳዳሪ ምደባውን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የሥራ ተቋራጩ ወኪል አድራሻ የሥራ ተቋራጩ
ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች አድራሻ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
37.4. መሐንዲሱ የሥራ ተቋራጩን የውል አስተዳዳሪ የመቀጠል ውሳኔውን (ማፅደቁን) ካነሳ የሥራ ተቋራጩ
ማስታወቂያው እንደደረሰው በተቻለ ፍጥነት የውል አስተዳደሪውን ማንሳትና በመሐንዲሱ ተቀባይነት
ባለው(ባፀደቀው) ሌላ የውል አስተዳደሪ መተካት ይኖርበታል፡፡
37.5. የሥራ ተቋራጩ የውል አስተዳዳሪ እንደተገቢነቱ ለግንባታ ሥራው መከናወን የሚያስፈልጉ ማናቸውንም
ውሳኔዎች የመስጠት ሥልጣን፣ አስተዳደራዊ ትዕዛዞችን የመቀበልና የመፈጸም እና በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች
አንቀጽ 78 የተጠቀሰውን የሥራ መዝገብ ወይም አባሪዎችን የመፈረም ሙሉ ሥልጣን ይኖረዋል፡፡ በማንኛውም
ሁኔታ የሥራ ተቋራጩ የሥራ ዝርዝሮችና አስተዳደራዊ ትዕዛዞች በራሱ ሠራተኞችና በንዑስ የሥራ ተቋራጮቹና
ሠራተኞቻቸው መከበሩን የማረጋገጥ ኃላፊነት ጨምሮ የግንባታ ሥራዎች አጥጋቢ በሆነ ሁኔታ መከናወናቸውን
ማረጋገጥ አለበት፡፡
37.6. ለውል አስተዳዳሪው የተሰጠ ወይም በውል አስተዳዳሪው የተደረገ ማስታወቂያ፣ መረጃ፣ መመሪያ ወይም ሌላ
ልውውጥ ከሥራ ተቋራጩ ጋር እንደተካሄደ ይቆጠራል (ይወሰዳል)፡፡
37.7. የሥራ ተቋራጩ በማንኛውም ጊዜ የውል አስተዳዳሪው ምክትል ሆኖ እንዲሠራ የመደበውን ሰው ማንነት ምክትል
ሆኖ ወይም ተክቶ የሚሠራበት ጊዜ ከመጀመሩ በፊት ለመሐንዲሱ ማሳወቅ አለበት፡፡
37.8. የሥራ ተቋራጩ ለግንባታ ሥራዎች በቦታው የተሰማሩ ሠራተኞች በተገቢ ሁኔታ በሁሉም ጊዜያቶች ሥራቸውን
እንደሚያከናውኑ ለማረጋገጥ ከውል አስተዳዳሪው በተጨማሪ በቂ ተጨማሪ የቁጥጥር ሠራተኞችን ማቅረብ
አለበት፡፡
37.9. በፍላጎት መግለጫ መሠረት ለአስተዳደራዊና ለቁጥጥር ቦታዎች የሚመደቡ ሁሉም ሰዎች በመሐንዲሱ ተቀባይነት
ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡ መሐንዲሱ ብቁ አይደለም ብሎ ያመነበትን ዕጩ ውድቅ የማድረግ ድምጽን በድምጽ
የመሻር መብት (veto) አለው፡፡

38. ሰራተኞች

38.1. በሥራ ተቋራጩ የሚቀጠሩ ሰዎች በቂ ቁጥር ያላቸውና የሰው ኃይልን በተመጣጣነ መንገድ ለመጠቀም
የሚያስችል መሆን አለባቸው፡፡ እነኚህ ሠራተኞች የግንባታ ሥራዎችን ሂደት ለማሳለጥና በብቃት ለማከናወን
የሚያስችል ክህሎትና ልምድሊኖራቸው ይገባል፡፡
38.2. የሥራ ተቋራጩ ሁሉንም ሠራተኞችና የሰው ጉልበት ለማሳተፍ የራሱ አደረጃጀት ማዘጋጀት አለበት፡፡ በኢትዮጵያ
ሕግ የተቀመጠው የክፍያ ዋጋ እና አጠቃላይ የሥራ ሁኔታ በግንባታ ቦታ ላሉ ሠራተኞች እንደ ዝቅተኛ መነሻ ሆኖ
መወሰድ ይኖርበታል፡፡
38.3. የሥራ ተቋራጩ በፍላጎት መግለጫ የተገለጹትን ተግባራት ለመፈጸም በልዩ የውል ሁኔታዎች እንደተመለከተው
በቁልፍ ሠራተኞች ሠንጠረዥ የተሰየሙትን ሠራተኞች ወይም ሌሎች በመሐንዲሱ ተቀባይነት ያገኙ ሠራተኞችን

32 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
መቅጠር ይኖርበታል፡፡መሃንዲሱ ቁልፍ ሰራተኞችን ቅየራ ሊያፀድቅ የሚገባው የሚቀየሩት ሰራተኞች በፍላጎት
መግለጫው ላይ ከተጠቀሱት ሰራተኞች ብቃት እና ችሎታ ጋር የተመጣጠነ ወይም የተሻለ ሲሆን ብቻነው፡፡
38.4. የሥራ ተቋራጩ ቁልፍ ሠራተኞች የግንባታ ሥራዎችን በተገቢው መንገድ ለማከናወን አስፈላጊ እንደሆኑ
ተቀብሏል፡፡ የሥራ ተቋራጩ በማንኛውም ጊዜ የቁልፍ ሠራተኛ ቦታ ከ 1 ዐ የሥራ ቀናት በላይ ክፍት ሆኖ
እንዳይቆይ ማድረግ አለበት፡፡ የሚተካው ሰውም ከበፊቱ የተሻለ ወይም እኩል ብቃትና ልምድ ያለውና የሚተካው
ቁልፍ ሠራተኛ ሊያከናውናቸው የነበራቸውን ተግባራት ለመፈጸም ሙሉ ለሙሉ ብቁ መሆን አለበት፡፡
38.5. መሐንዲሱ የግንባታ ሥራውን በአጥጋቢ ሁኔታ እንዳይከናወን ያሰጋሉ ብሎ ያመነባቸውን ሰራተኞች ምክንያቶችን
በመግለጽ እንዲለወጡ በደብዳቤ ሲያሳውቅ የሥራ ተቋራጩ እነዚህን ሠራተኞች በሙሉ ወዲያውኑ መተካት
አለበት፡፡
38.6. የሥራ ተቋራጩ ሠራተኛ ወይም የሥራ ኃይል አባል የሆነ ሰውን እንዲያነሳ መሐንዲሱ የሥራ ተቋራጩን
ምክንያቱን በመግለጽ ከጠየቀ የሥራ ተቋራጩ ግለሰቡ ከግንባታ ቦታው በሰባት ቀናት ውስጥ መልቀቁን እና
ከውሉ የግንባታ ሥራ ጋር ምንም ዓይነት ቀጣይ ግንኙነት እንደማይኖረው ማረጋገጥ አለበት፡፡

38.7. የስራ ተቋራጩን ሰራተኛ ከመተካት ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ወጪዎች አሰሪው ተጠያቂ አይሆንም። አሰሪው ላይ
በሰራተኞች ለሚነሱ የቅጥር ተጠያቂነት የካሳ ጥያቄዎች የስራ ተቋራጩ ይከፍላል።

39. የካሣ ክፍያና ተጠያቂነት

39.1. የሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራውን ሲያከናውን በወሰዳቸው እርምጃዎች ወይም ሳይወሰድ በቀራቸው ሥራዎች
እንዲሁም ሕግን ወይም የ 3 ኛ ወገንን መብት በመጣሱ (የፈጠራ ባለቤትነት ፣የንግድ ምልክት እና ሌሎች
የአእምሯዊ ንብረት መጣስን ጨምሮ) ምክንያት በአሰሪው፤ ወኪሎቹና ሠራተኞቹ ላይ ለሚመጡ ጉዳቶችን እና
ለሚነሱ ክሶች በራሱ ወጪ የመካስ ፣ የመጠበቅና የመከላከል (የመከራከር) ሃላፊነት አለበት፡፡
39.2. የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲሟሉ የሥራ ተቋራጩ የራሱን ግዴታዎች ባለመወጣቱ ምክንያት ከሚመጡ ማናቸውም
ተግባራት ጥያቄዎች፣ ጥፋቶች ወይም ካሳዎች አሰሪውን፣ ወኪሎቹንና ሠራተኞቹን መካስ፣ መጠበቅና መከላከል
(መከራከር) ይኖርበታል፡፡
(ሀ) እንደዚህ ዓይነቶቹን ተግባራት፣ ጥያቄዎች፣ ጥፋቶች እና ካሳ አሰሪው በአወቀ ከ 3 ዐ ቀናት
የማይበልጥ ጊዜ ውስጥ ለሥራ ተቋራጩ ከተገለጸለት፣
(ለ) የሥራ ተቋራጩ ሃላፊነት የውል ግዴታዎቹን ባለመወጣቱ ምክንያት በቀጥታ ለተደረጉ
እርምጃዎች፣ የካሣ ጥያቄዎች፣ ጥፋቶች እና ጉዳቶች ላይ ብቻ የተወሰነ ነው፡፡ ሆኖም ግን
ባልተጠበቁ ድንገተኛ ሁኔታዎች ወይም ግዴታውን ባለመፈፀሙ ምክንያት በተዘዋዋሪ
በሚመጡ ጉዳቶችን እንዲክስ የሥራ ተቋራጩ ኃላፊ አይሆንም ፡፡

33 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
39.3. የሥራ ተቋራጩ በሚከተሉት ምክንያቶች ለተፈጠሩ እርምጃዎች የካሳ ጥያቄዎች፣ ጥፋቶች፣ ወይም ወጪዎች
ተጠያቂ አይሆንም፡፡
(ሀ) አሰሪው በስራ ተቋራጩ የተሰጡ አስተያየቶችን ከተወ ወይም የሥራ ተቋራጩን እርምጃ፣ ውሳኔ
ወይም አስተያየት ከሻረ ወይም የሥራ ተቋራጩ ያልተስማማበትን ወይም በጥብቅ
የተቃወመውን ውሳኔ ወይም አስተያየት እንዲተገብር ካደረገ ወይም፣
(ለ) የሥራ ተቋራጩ ትዕዘዝ በአሰሪው ወኪሎች፤ ሠራተኞች ወይም ጥገኛ ያልሆኑ የሥራ
ተቋራጮች ተገቢ ባልሆነ መንገድ ከተከናወነ፡፡

39.4. ውሉን በሚገዛው ሕግ ሊወሰን እስከሚችለው ጊዜ ድረስ የሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራው ከተከናወነ በኋላም
በውሉ ውስጥ ለተከሰተ የውል ግዴታን አለመወጣት ተጠያቂ ወይም ኃላፊ ሆኖ ይቆያል፡፡

40. የስራ ተቋራጩ ሊኖረው የሚገባ የመድን ሽፋን

40.1. ሥራ ተቋራጩ የአሰሪውን እና የሥራ ተቋራጩን ስም በጋራ የያዘ በውሉ ውስጥ ተጠያቂ ለሆነባቸው ጥፋቶችና
ጉዳቶች ሊሸፍን የሚችል የመድህን ዋስትና በልዩ የውል ሁኔታዎች በተጠቀሰው መጠን መሠረት ማቅረብ
አለበት፡፡ በልዩ የውል ሁኔታዎቹ እስካልተጠቀሰ ድረስ እንዲህ ዓይነቱ መድህን በሚከተሉት መንገድ መሸፈን
አለበት፡፡
(ሀ) የግንባታ ሥራዎችን፣ በዚሁ የሚካተቱ ቁሳቁሶች እና መሳሪያዎች/ተቋሞች በአስገዳጅ
ሁኔታዎች ወይም በአሰሪው ይሸፈናሉ በተባሉ ስጋቶች (risks) ምክንያት ካልሆነ በቀር
የሁሉንም ጥፋቶችን ወይም ጉዳቶችን ሙሉ ለሙሉ መተኪያ ወጪ፣
(ለ) ጥፋቶችንና ጉዳቶችን ለማረም/ለማስተካከል የሚያስፈልጉ ዋጋዎችንና የሙያተኛ ክፍያን እና
የማፍረሻ እና ማንኛውንም የግንባታ ሥራ ክፍል የማስወገጃ እና ማንኛውም ዓይነት ተፈጥሮ
ያለውን ፍርስራሽ ለማስወገድ ለሚያስፈልጉ ወጪዎች ከላይ ከተገለፀው የመተኪያ ዋጋ ላይ
በተጨማሪ 15%፣
(ሐ) የሥራ ተቋራጩን የግንባታ መሣሪያዎችና በሥራ ተቋራጩ ወደ ግንባታ ቦታው የመጡ ሌሎች
ነገሮች በግንባታ ቦታው ላይ እነሱን ለመተካት የሚያስችል ድምር፣

40.2. የሥራ ተቋራጩ ከግንባታ ሥራው ትግበራ ጋር የተያያዘ የኢንዱስትሪ አደጋዎችንና የፍትሐብሄር ዕዳን ሊሸፍን
የሚችል የመድን ዋስትና የግንባታ ሥራዎችን ለሚያከናውኑ ሠራተኞቹ፣ ለአሰሪው ና ስልጣን ላላቸው ሠራተኞቹ
መግዛት (ማውጣት) ይገባዋል፡፡ የግለሰብ መጎዳትን አሰመልክቶ እንዲህ ዓይነቱ ሃላፊነት ገደብ የሌለው መሆን
ይገባዋል፡፡
40.3. የሥራ ተቋራጩ ለራሱ፣ለህጋዊ ወራሹ ወይም ለወኪሉ የተመደበውን ተግባር በተመለከተ በወሰደው ወይም
ሳይወሰድ በቀረው እርምጃ ምክንያት የሚከሰት የአደጋ ተጋላጭነት እና የፍትሐብሄር ተጠያቂነትን የሚሸፍን

34 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
የመድህን ዋስትና ማውጣት (መግዛት) ይኖርበታል፡፡ የእንዲህ ዓይነቱ የመድህን ዋስትና መጠን ቢያንስ በልዩ
የውል ሁኔታዎች የተጠቀሰውን መሆን ይገባዋል፡፡ በተጨማሪም ሁሉም ንዑስ የሥራ ተቋራጮቹ ተመሳሳይ
የመድን ዋስትና እንዲገዙ ማድረግ አለበት፡፡
40.4. ከላይ የተጠቀሱ የመድን ሽፋን በመጠየቁ ምክንያት አሰሪው በዚህ ውል መሠረት የሥራ ተቋራጩ
የሚመለከተውን የአደጋ ተጋላጭነት በሙሉ ገምግሞ እንደተረዳው መቆጠር የለበትም፡፡ የሥራ ተቋራጩ የአደጋ
ተጋላጭነቱን በጥንቃቄ ገምግሞ በቂ እና/ወይም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ሲወዳዳር ሰፋ ያለ የመድን ዋስትና
መግባት ይኖርበታል፡፡ የሥራ ተቋራጩ የመድን ዋስትናን በበቂ መጠን፣ ጊዜ እና ዓይነት ባለመያዙ ወይም ይዞ
ለመቆየት ባለመቻሉ ከማንኛውም በውሉ ውስጥ ከተጠቀሱ ተጠያቂነት ወይም ሌሎች ግዴታዎች ነፃ ሊሆን
አይችልም፡፡
40.5. የመድህን ዋስትና መገዛት ያለበት በሥራ ተቋራጩ ወጪ ነው፡፡
40.6. በዚህ አንቀጽ ውስጥ የተጠቀሱ ሁሉም የመድን ዋስትናዎች ውሉ ለአሸናፊው ከተገለጸ በ 3 ዐ ቀናት ውስጥ
መግባት ወይም መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በአሰሪውም መጽደቅ አለባቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነት የመድን ሽፋን
ከግንባታ ሥራዎች መጀመሪያ ቀን ጀምሮ እስከመጨረሻው የግንባታ ሥራዎች ርክክብ ድረስ የፀና እና ተግባራዊ
የሚሆን ነው፡፡
40.7. የሥራ ተቋራጩ ወይም የመድን ሰጪው ድርጅት በመድን ሽፋኑ ላይ የታሰበ ማንኛውንም ዓይነት ይዘት ለውጥ
ወይም መሠረዝ ከመደረጉ ከ 3 ዐ ቀናት በፊት ለአሰሪው ሊገልጽለት ይገባል፡፡
40.8. በዚህ ውል ውስጥ ያሉ የግንባታ ሥራዎች ከመጀመሩ በፊት የሥራ ተቋራጩ ወይም የመድን ድርጅቱ ሁሉንም
ተፈላጊ የመድን ሽፋኖች መሟላቱን የሚያስረዳ የመድን ሠርቲፊኬት (Certificate of Insurance (COI))
ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡ የመድን ሠርቲፊኬቱን ለመገምገምና ለማጽደቅ ለአሰሪው መቅረብ አለበት፡፡ ውሉ
በሚፀናበት ጊዜ የሥራ ተቋራጩ ወይም የመድን ድርጅቱ በ አሰሪው ወይም መሐንዲሱ በተጠየቀበት ጊዜ ውሉ
የዕድሳት ማስረጃ ያለው ወይም ሌሎች የመድን ፖሊሲና ሽፋን ለውጦች እና ክፍያ(ፕሪምየም) የሚያሳይ ወቅታዊ
የመድን ሰርቲፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
40.9. የሥራ ተቋራጩ በዚህ አንቀጽ መሠረት ያሉበት ግዴታዎች መወጣት ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የሥራ
ተቋራጩ የግንባታ ሥራው ሲከናወን ከግንባታ ሥራው ጋር የተያያዘ በራሱ፣በንዑስ ስራ ተቋራጩ ወይም
ሰራተኞቹ በንብረት ላይ ለደረሰ ጉዳት እና በሰው ላይ ለደረሰ አደጋ ተጠያቂ የሚሆን ሲሆን የጉዳት ካሳውንም
የመክፈል ሃላፊነት አለበት፡፡

41. የስራዎች ትግበራ ፕሮግራም

41.1. የሥራ ተቋራጩ በልዩ የውል ሁኔታዎች ውስጥ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለመሐንዲሱ የሥራዎች ትግበራ
ፕሮግራም በተግባራትና በወር ከፋፍሎ የሚከተሉትን መረጃዎች በመጨመር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
(ሀ) የሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራዎቹን ሊያከናውን ያሰበበትን ቅደም ተከተል፣
(ለ) ንድፎችን ለማቅረብ እና ለማጽደቅ የሚያስፈልገውን የጊዜ ገደብ፣

35 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
(ሐ) በግንባታ ቦታው ኃላፊነት ያላቸው ሠራተኞች ስም፣ ሙያ፣ ትምህርት እና የልምድ ዝርዝር
(Curriculum Viate) የያዘ የድርጅቱ አወቃቀር የሚያሳይ ንድፍ (Chart)
(መ) የሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራውን ለማከናወን ያሰበበትን የግንባታ ዘዴ ቅደም ተከተልን
ጨምሮ በወር እና በሥራ ባህሪ የሚያሳይ አጠቃላይ መግለጫ
(ሠ) የግንባታ ቦታውን አቀያየስና አደረጃጀት የሚያሳይ ዕቅድና
(ረ) መሐንዲሱ ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ሊፈልጋቸው የሚችል ሌሎች ዝርዝሮችና መረጃዎች

41.2. መሐንዲሱ ከላይ የተገለፁትን ሰነዶች በቀረቡለት በ 10 ቀናት ውስጥ ውይይት እንደሚፈልግ ለስራ ተቋራጩ
እስካላሳወቀ ድረስ በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ሰነዶቹን በማጽደቅ ወይም ማናቸውም አስፈላጊ የሆኑ
አስተያየቶችን በማካተት ለሥራ ተቋራጩ መመለስ ይገባዋል፡፡
41.3. ወቅታዊ ፕሮግራም ማለት በእያንዳንዱ ተግባር የታየውን ተጨባጭ (እውነተኛ) የአፈፃፀም ደረጃ እና አፈፃፀሙ
በቀሪ የግንባታ ሥራዎች የትግበራ ጊዜ ላይ ያመጣው ተፅዕኖ (በሥራዎች ቅደም ተከተል ላይ ያሳየውን ለውጥ
ጨምሮ) የሚያሳይ ፕሮግራም ማለት ነው፡፡
41.4. የሥራ ተቋራጩ በልዩ የውል ሁኔታዎች ውስጥ ከተጠቀሰው የጊዜ ክፍልፋይ ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ወቅታዊ
የሆነውን ፕሮግራም ለመሐንዲሱ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የሥራ ተቋራጩ በዚህ ጊዜ ውስጥ ወቅታዊ ፕሮግራም
ካላቀረበ መሐንዲሱ በልዩ የውል ሁኔታዎች የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ከሚቀጥለው የክፍያ ሰርቲፊኬት
ሊያስቀር (ሊይዝ) ይችላል፡፡ እንደሁም ይህንኑ መጠን (ክፍያ) ወቅታዊ ፕሮግራሙ ከቀረበ በኋላ ለሚመጣው
ተከታይ የክፍያ ጊዜ ድረስ ይዞ ማቆየት ይችላል፡፡
41.5. የፕሮግራሙ በመሐንዲሱ መጽደቁ የሥራ ተቋራጩን ከማናቸውም በውሉ ውስጥ ካሉ ግዴታዎቹ ነፃ
አያደርገውም፡፡ የሥራ ተቋራጩ በማንኛውም ጊዜ ፕሮግራሙን ሊከልስ እና ለመሐንዲሱ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
የተከለሰው ፕሮግራም የለውጥ እና የጊዜ መካሻ ሁኔታዎችን ማሳየት ይኖርበታል፡፡
41.6. ካለመሐንዲሱ ፈቃድ ምንም ዓይነት መሰረታዊ ለውጥ በፕሮግራሙ ላይ ማድረግ አይቻልም፡፡ የግንባታ ሥራዎቹ
የአፈፃፀም ደረጃ ከፕሮግራሙ ጋር ካልተጣጣመ ግን መሐንዲሱ የሥራ ተቋራጩን ፕሮግራሙን እንዲከልስና እና
ለማፅደቅ እንዲያቀርብለት ሊያዘው (መመሪያ ሊሰጠው) ይችላል፡፡

42. የስራ ተቋራጩ ንድፎች (Drawings)

42.1. የሥራ ተቋራጩ የሚከተሉትን ሰነዶች ለማፀደቅ ለመሐንዲሱ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡


(ሀ) በውሉ ወይም በስራ ተግባራት ፕሮግራም ውስጥ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ንድፎችን፣
ሰነዶች፣ ናሙናዎች እና/ወይም ሞዴሎችን ፣
(ለ) መሐንዲሱ ለተግባራት መፈጸሚያ በምክንያታዊነት ሊፈልጋቸው የሚችሉ ንድፎች፣

36 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
(ሐ) ድልድዮችና ሌሎች ብረት ያላቸው አርማታዎች (reinforced conceret) መዋቅሮችን
በተመለከተ፣ የሥራ ተቋራጩ የተጠየቀውን የአፈር ምርመራ የመሠረት ሥራውን ከመጀመሩ
በፊት ማከናወን ይኖርበታል፡፡ የሥራ ተቋራጩ የተጠቀሰው የግንባታ ሥራ ከመጀመሩ አንድ ወር
በፊት የእነዚህን ምርመራዎች ውጤት እና ለመሠረት ስራው የተካሄዱ ስሌቶችን የሚያሳይ
ሶስት ቅጂ ለመሐንዲሱ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
(መ) የሥራ ተቋራጩ ውሉን በተገቢ ሁኔታ ለማከናወን የሚያስፈልገው ሁሉንም ዲዛይኖች፤
የግንባታ ንድፎች፤ ሌሎች ሰነዶችና ቁሶች በተለይም በአርማታ እና ብረት ለሚሠሩ መዋቅሮች
የሚሆኑ የአርማታ ብረት ንድፎችና የዲዛይን ስሌቶች በራሱ ወጪ ማዘጋጀት አለበት፡፡ የሥራ
ተቋራጩ የተባለውን ሥራ ከመጀመሩ ቢያንስ ከአንድ ወር በፊት የግንባታ፣ ዲዛይን እና
የአርማታ ብረት ንድፍ፣ የዲዛይን ስሌት እና ማናቸውም ሌሎች ሰነዶችና ቁሶች እንዲፀድቁ
ለመሐንዲሱ በሶስት ቅጂ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
መሐንዲሱ ንድፎችን፣ የዲዛይን ስሌቶችን፤ ቁሶችንና ሌሎች በ (ሐ) እና (መ) ሥር አስፈላጊ
የሆኑ ሰነዶች በደረሱት በ 15 ቀናት ውስጥ ለሥራ ተቋራጩ ሰነዶቹ ላይ በመፈረም መቀበሉን
መግለፅ ወይም አስተያየት በማከል መመለስ ይኖርበታል፡፡

42.2. መሐንዲሱ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 41.1 የተጠቀሰውን ንድፎችን፣ ሰነዶችን ፣ ናሙናዎችን ወይም
ሞዴሎችን የማጽደቅ ውሳኔ በውሉ ወይም በፀደቀው የስራ ትግበራ ፕሮግራም ላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ
ውስጥ ማሳወቅ ካልቻለ በተወሰነው የጊዜ ገደብ የመጨረሻ ቀን ወይም የጊዜ ገደብ ካልተጠቀሰ ደግሞ እነዚሁኑ
በደረሰው በ 45 ቀናት ውስጥ እንዳፀደቀው ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
42.3. የፀደቁ ንድፎች፣ ሰነዶች፣ ናሙናዎች እና ሞዴሎች በመሃንዲሱ መፈረም ወይም በሌላ መልኩ በመሃንዲሱ እውቅና
ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ በመሐንዲሱ የታዘዙ ካልሆነ በስተቀር ሰነዶቹ ሊተው አይገባቸውም ፡፡ መሐንዲሱ
ሊያፀድቃቸው ያልቻለ ማናቸውም የሥራ ተቋራጩ ንድፎች፤ ሰነዶች፤ ናሙናዎች ወይም ሞዴሎች አስፈላጊ
ነገሮችን እንዲያሟሉ ተሻሽለው ወዲያውኑ በሥራ ተቋራጩ ለመሐንዲሱ እንደገና መቅረብ አለባቸው፡፡ የሥራ
ተቋራጩ የመሐንዲሱን አስተያየት ማስታወቂያ ባገኘ በ 15 ቀናት ውስጥ በሰነዶቹ፣ ንድፎቹ፣ የዲዛይን ስሌቶቹ፣
ወዘተ… የተሰጡትን ተፈላጊ እርማቶች፣ ማስተካከያዎች እና ወዘተ ማድረግ አለበት፡፡ የተስተካከሉት ሰነዶች፣
ንድፎች፣ የዲዛይን ስሌቶች፣ ወዘተ… መሐንዲሱ እንዲያጸድቀው በተመሳሳይ መንገድ እንደገና መቅረብ አለበት፡፡
42.4. የሥራ ተቋራጩ በውሉ ወይም በተከታይ አስተዳደራዊ ትዕዛዞች በተጠቀሰው ቁጥርና አኳኋን የፀደቁ ንድፎች
ተጨማሪ ቅጂዎችን ማቅረብ አለበት፡፡
42.5. የንድፎች፣ ሰነዶች፣ ናሙናዎች ወይም ሞዴሎች በመሐንዲሱ መጽደቅ የሥራ ተቋራጩን በውሉ መሠረት ካሉበት
ግዴታዎች ነፃ አያደርገውም፡፡
42.6. መሐንዲሱ በማናቸውም ተገቢ በሆነ ጊዜ ሁሉንም የውል ንድፎች፣ ሰነዶች፣ ናሙናዎች ወይም ሞዴሎች በሥራ
ተቋራጩ ግቢ ውስጥ የመመርመር መብት አለው፡፡

37 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
42.7. የግንባታ ሥራዎች ጊዜያዊ ርክክብ ከመደረጉ በፊት፣ የሥራ ተቋራጩ አሰሪው የግንባታ ሥራዎች ለመጠቀም፣
ለመጠገንና ለማስተካከል እንዲችል የአጠቃቀም እና የጥገና መመሪያ ከንድፎች ጋር መስጠት አለበት፡፡ በልዩ
የውል ሁኔታዎች በሌላ አኳሃን እስካልተጠቀሰ ድረስ መመሪያዎቹና ንድፎች በውሉ ቋንቋ መሆን አለባቸው፡፡
እንዲሁም የአጠቃቀም እና የጥገና መመሪያ እና ንድፎቹ ለአሰሪው እስካልደረሰው ድረስ ለጊዜያዊ ርክክብ
የሚያስፈልገው ስራ በሙሉ ተሰርቷል ማለት አይቻልም፡፡

43. የጨረታ ዋጋዎች ሙሉዕነት

43.1. የሥራ ተቋራጩ የጨረታ ሰነዱን ከማስገባቱ በፊት የግንባታ ቦታውንና አካባቢውን ፣የመሬቱንና ከሥር ያለውን
አፈር ባህሪ ፈትሾ እና መርምሮ ያመነበት እንደሆነ እና ፣ የግንባታ ቦታውን ይዘት እና ባህሪ፣፣ የግንባታ ሥራውን
ለማጠናቀቅ የሚያስፈልጉ ስራዎችና ቁሶች መጠንና ተፈጥሮ (ባህርይ)፣ ወደ ግንባታ ቦታው የመድረሻ እና
የግንኙነት ዘዴዎች፣ ሊያስፈልገው የሚችለውን የመኖሪያ ቦታ እና በአጠቃላይ ስለአደጋ ተጋላጭነት፣ ለድንገተኛ
ወጪ ተጨማሪ መጠባበቂያዎች እና ሌሎች ያስገባው ጨረታ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ሁኔታዎች ላይ በቂ
መረጃ አግኝቶ ጨረታውን እንዳስገባ ይቆጠራል፡፡
43.2. የሥራ ተቋራጩ ፣ ጨረታውን ከማስገባቱ በፊት የጨረታ ዋጋ እና በስራ ዝርዝር ላይ ወይም የዋጋ ሠንጠረዦች
ላይ የተጠቀሱት ነጠላ ዋጋዎች እና ተመኖች (rates) ትክክለኛነት እና ሙሉእነት አምኖበት ጨረታ እንዳስገባ
ይቆጠራል፡፡ እንዲሁም በውሉ ውስጥ እስካልተጠቀሰ ድረስ እነዚህ ዋጋዎች የሥራ ተቋራጩ ሁሉንም የውል
ግዴታውን ለመወጣት የሚያስችሉ መሆናቸውን እንዳመነ ይቆጠራል፡፡
43.3. የሥራ ተቋራጩ ዋጋዎቹን በራሱ ስሌቶች ሥራዎችና ግምቶች መሠረት እንደወሰናቸው ስለሚታመን ባስገባው
የጨረታ ሰነድ ውስጥ ነጠላ ዋጋ ወይም ጥቅል ድምር ያልተሰጠውን ማንኛውም የግንባታ ስራው አካል የሆኑ
ስራዎችን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ያከናወናል፡፡

44. ያልተጠበቁ የአደጋ ተጋላጭነቶች

44.1. የግንባታ ሥራዎች በሚከናወኑበት ጊዜ የሥራ ተቋራጩ ልምድ ባለው የሥራ ተቋራጭ አስቀድሞ ሊገመት
የማይችል ሰው ሰራሽ መሰናክሎች ወይም ተፈጥሮአዊ ሁኔታዎች ካጋጠመውና የሥራ ተቋራጩ ተጨማሪ ወጪ
ያስከትላል ብሎ ከገመተ እና/ወይም የግንባታ ተግባራትን ማከናወኛ ጊዜ ማራዘም ያስፈልጋል ብሎ ካመነ
በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 68 እና/ወይም 72 መሠረት ለመሐንዲሱ ማስታወቂያ መስጠት አለበት፡፡
በዚህ ዓይነት ማስታወቂያ ውስጥ የሥራ ተቋራጩ ሰው ሠራሹን መሰናክሎች እና/ወይም ተፈጥሮአዊ ሁኔታዎችን፣
የሚጠበቁ ተፅዕኖዎችን ዝርዝር፣ በግንባታ ሥራው ማከናወን ላይ የሚጠበቀውን መዘግየት ተፅዕኖ መጠን እና
እየወሰደ ያለውን ወይም ለመውሰድ ያሰበውን እርምጃ መግለጽ ይኖርበታል፡፡
44.2. መሐንዲሱ ማስታወቂያ እንደደረሰው ከሚከተሉት አንዱን ሊያደርግ ይችላል፡፡

38 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
(ሀ) የሥራ ተቋራጩ እየወሰደ ያለው ወይም ሊወሰድ ያሰባቸው እርምጃዎች ወጪ ግምት
መጠየቅ፣
(ለ) በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ንዑስ አንቀጽ 44.2 (ሀ) መሠረት የቀረቡትን እርምጃዎች
ከማስተካከያ ጋር ወይም እንዳለ ማፅደቅ፣
(ሐ) ሰው ሠራሽ መሰናክሎች ወይም ተፈጥሮአዊ ሁኔታዎች እንዴት መወጣት እንደሚቻል
የጽሑፍ ትዕዛዝ መስጠት፣
(መ) ውሉ እንዲሻሻል፣ ለጊዜው እንዲቋረጥ፣ ወይም ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጥ ማዘዝ፣
መሐንዲሱ የተባሉትን ሰው ሠራሽ መሰናክሎች ወይም ተፈጥሮአዊ ሁኔታዎች (በሙሉ ወይም በከፊል)
ሊከሰቱ እንደሚችሉ ልምድ ባለው የሥራ ተቋራጭ ሊገመት እንደማይችል ከወሰነ፣
(ሀ) የሥራ ተቋራጩ በመሰናክሎቹ ወይም በሁኔታዎቹ ያጋጠመው የመዝግየት ችግር
በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 72 መሠረት ለሥራ ተቋራጩ የሚገባውን የሥራዎቹን
የመተግበሪያ ጊዜ ማራዘም መወሰን ላይ ከግምት ውስጥ ማስገባት፣
(ለ) ከአየር ሁኔታዎች ውጭ የሆኑ ሰው ሠራሽ መሰናክሎች ወይም ተፈጥሮአዊ
ሁኔታዎች በሆኑበት ጊዜ፣ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 68 መሠረት ለሥራ ተቋራጩ
ተጨማሪ ክፍያዎችን መወሰን፣

44.3. በአየር ሁኔታዎች ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮች ሥራ ተቋራጩን በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 68
መሠረት የሚነሳ የክፍያ ጥያቄ ባለመብት አያደርገውም፡፡

44.4. መሐንዲሱ ሰው ሠራሽ መሰናክሎቹ ወይም የተፈጥሮ ሁኔታዎቹ በሙሉም ሆነ በከፊል ልምድ ባለው የሥራ
ተቋራጭ ሊገመቱ ይችላሉ ብሎ ከወሰነ ውሳኔውን ለሥራ ተቋራጩ በተቻለ ፍጥነት ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
45. በስራ ቦታ ላይ የሚኖር የጤናና ደህንነት ሁኔታ
1.6. የሥራ ተቋራጩ በመሐንዲሱ ወይም በአሰሪው አሰሪው ከተፈቀደላቸው ሰዎች በስተቀር በውሉ አፈፃጸም ላይ
ያልተሳተፈን ማንኛውንም ሰው ወደ ግንባታ ቦታው እንዳይገባ የመከልከል መብት አለው፡፡
1.7. የሥራ ተቋራጩ በግንባታ ቦታዎች ደህንነተን የግንባታ ሥራዎች በሚከናወኑበት ጊዜ በሙሉ ማረጋገጥ አለበት፡፡
እንደዚሁም ለሠራተኞቹ፡ ለአሰሪው ወኪሎች እና ሶስተኛ ወገኖች ጥቅም ሲባል የግንባታ ሥራዎች በሚከናወኑበት
ጊዜ ሊደርስ የሚችል ጥፋትና ድንገተኛ አደጋን ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈላጊ እርምጃዎችን ለመውሰድ ኃላፊነት
አለበት፡፡
1.8. የሥራ ተቋራጩ ያሉ መዋቅሮችና የተዘረጉ መስመሮች መጠበቃቸው፣ ባሉበት ሁኔታ መቆየታቸውና መጠገናቸው
እንዲረጋገጥ በራሱ ኃላፊነትና ወጪ ሁሉንም አስፈላጊ እርምጃዎች መውሰድ አለበት፡፡ የሥራ ተቋራጩ
በመሐንዲሱ የሚፈለጉ ወይም ሥራዎችን በተገቢው መንገድ ለመተግበር አስፈላጊነታቸው የተረጋገጠ መብራት፣
መከላከያ፣ አጥር እና የፀጥታ (የደህንነት) መሣሪያዎችን ለማቅረብ ኃላፊነት አለበት፡፡

39 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
1.9. ሥራዎች በሚከናወኑበት ጊዜ የድንገተኛ አደጋ ወይም ጉዳት መድረሱን ወይም ድንገተኛ አደጋና ጉዳት ተከትሎ
ፀጥታ (የደህንነት) ለማስከበር አስቸኳይ እርምጃዎች መውሰድ ካስፈለገ፤ መሐንዲሱ ለሥራ ተቋራጩ አስፈላጊውን
እንዲፈጽም መደበኛ ማስታወቂያ ይሰጠዋል፡፡ የሥራ ተቋራጩ አስፈላጊ እርምጃዎችን ለመውሰድ ፈቃደኛ ካልሆነ
ወይም ካልቻለ፣ መሐንዲሱ ሥራውን የሥራ ተቋራጩ ተጠያቂ ሊሆንበት እስከሚችል መጠን (ወጪ) ድረስ
ስራውን ሊያከናውነው ይችላል፡፡
1.10. የግንባታ ሥራዎች በሚከናወኑበት ጊዜ፣ የሥራ ተቋራጩ እና ሠራተኞቹ ከሥራው ጋር የሚሄዱ የጤናና የደህንነት
እና ሌሎች ደንቦችን ማክበር ይኖርባቸዋል፡፡
1.11. የሥራ ተቋራጩ ከመሐንዲሱ ጋር በጤናና በደህንነት ጉዳዮች ላይ ግንኙነት የሚያደርግ የጤናና የደህንነት ወኪል
መምረጥ ይኖርበታል፡፡
1.12. የሥራ ተቋራጩ ሠራተኞች የራሱ የሥራ ተቋራጩን የአደጋ መመዝገቢያ ሥነ- ሥርዓት መከተል ይኖርበቸዋል፡፡
1.13. ሁሉም ለማስታወቅ የሚቻሉ ድንገተኛ አደጋዎች መሐንዲሱ ወዲያውኑ እንዲያውቃቸው መደረግ አለበት፡፡
1.14. የሥራ ተቋራጩ እሳትን ወይም ሌሎች ጥፋቶችን ለመከላከል ለተዘጋጁ እርምጃዎች የሠራተኞቹን ሙሉ ትብብር
ማረጋገጥ እና ለአሰሪው በሥራ ተቋራጩ አሠራር ወይም በሌሎች ሁኔታዎች ላይ የአደጋ ተጋለጭነትን የሚጨምሩ
ወይም አዲስ ጥፋቶች የሚያመጡ ማናቸውንም ለውጦችን ማሳወቅ አለበት፡፡

1. አዋሳኝ ንብረቶችን ከአደጋ መጠበቅ

1.1. የሥራ ተቋራጩ በራሱ ኃላፊነትና ወጪ የመልካም የግንባታ ልምድ እና በሚታዩ የተሻሉ ሁኔታዎች መሰረት አዋሳኝ
ንብረቶችን ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ ጥንቃቄዎችን እና ጤናማ ያልሆነ(አላስፈላጊ) እንቅስቃሴ (disturbance)
እንዳይፈፀም ማድረግ ይኖርበታል፡፡
1.2. የሥራ ተቋራጩ በጎረቤት የመሬት ባለይዞታዎች ወይም ነዋሪዎች የቀረበ ማናቸውም የገንዘብ ወጪ የሚያስከትሉ
የካሣ ጥያቄዎች የሥራ ተቋራጩ ተጠያቂ እስከሚሆንበት መጠን ድረስ ለአሰሪው መክፈል ይኖርበታል፡፡ ይህ
መሆን ያለበት በጐረቤት ንብረቶች ላይ የደረሰው ጉዳት የተፈጠረው በአሰሪው ወይም በመሐንዲሱ ለሥራ
ተቋራጩ እንዲሰራበት በተሰጠው ዲዛይን ወይም የግንባታ ዘዴ ምክንያት እስካልሆነ ድረስ ነው፡፡

2. በትራፊክ ፍሰት ላይ ጣልቃ ገብነት

2.1. የሥራ ተቋራጩ በልዩ የውል ሁኔታዎች ከተጠቀሰው ውጭ የግንባታ ሥራዎች እና የተተከሉ ወይም የተዘረጉ
የግንባታው አካሎች እንደ መንገድ፣ የባቡር መስመር፣ የውሃ ማጓጓዣ መስመሮች እና የአውሮፕላን ማረፊያዎች
ጉዳት እንደማያመጡ ማረጋገጥ አለበት፡፡ በተለይም መጓጓዣ መስመሮችና መኪናዎችን ሲመርጥ የክብደት
ገደቦችን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
2.2. የሥራ ተቋራጩ አስፈላጊ ነው ብሎ ያመነባቸው ወይም በልዩ የውል ሁኔታዎች የተጠቀሱ ወይም በአሰሪው
የሚፈለጉ መንገዶችን፣ ሐዲዶችን ወይም ድልድዮችን ለመጠበቅ ወይም ለማጠናከር የሚያስፈልጉ የተለዩ

40 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
እርምጃዎችን በሥራ ተቋራጩ ቢከናወኑም ባይከናወኑም በሥራ ተቋራጩ ወጪ መሸፈን ይገባቸዋል፡፡ የሥራ
ተቋራጩ ማንኛውም ሊያከናውን ያሰበውን የተለየ እርምጃ ከመፈጸሙ በፊት ለመሐንዲሱ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
በመንገዶች፣ ሐዲዶች ወይም ድልድዮች ላይ የግንባታ ቁሶችን በማጓጓዝ ምክንያት የደረሰ ጉዳት ጥገና በሥራ
ተቋራጩ ወጪ ይሸፈናል፡፡

3. ገመዶችና ቱቦዎች (Cables and Conduits)

3.1. የሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራውን በሚያከናውንበት ቦታ ከመሬት ሥር የሚያልፉ መስመሮች፣ ቱቦዎች እና
የተተከሉ መዋቅሮች የሚያሳዩ ምልክቶች ሲያጋጥመው እንደነዚህ ዓይነቶቹን ምልክቶች እንዳሉ መጠበቅ ወይም
የግንባታ ሥራዎቹ ትግበራ ለጊዜው እንዲነሱ ግድ የሚል ከሆነ መተካት ይኖርበታል፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ተያያዥ
ሥራዎች የመሐንዲሱ ፈቃድ ያስፈልጋቸዋል፡፡
3.2. የሥራ ተቋራጩ ሁኔታው እንደሚጠይቀው በውሉ ውስጥ በአሰሪው አሰሪውየተጠቀሱ ገመዶችን፣ ቱቦዎችን፣
የተተከሉ መዋቅሮችን (Installation) የመጠበቅ፣ የማንሳት እና የመተካት ኃላፊነት ያለበት ሲሆን ወጪውን
መሸፈን ይኖርበታል፡፡
3.3. የገመዶች፣ ቱቦዎች እና የተተከሉ መዋቅሮች (Installation) መኖር በውሉ ውስጥ ካልተጠቀሰ ነገር ግን በመነሻ
ነጥቦች (Benchmark) ወይም አመልካቾች ከተገኘ የሥራ ተቋራጩ ጥበቃን፣ ማንሳትንና መተካትን አስመልክቶ
ከላይ እንደተጠቀሰው በአጠቃላይ ጥንቃቄ የማድረግ ኃላፊነት እና ተመሳሳይ ግዴታዎች አሉበት፡፡ በእንደዚህ
ዓይነቱ ሁኔታ አሰሪው ሥራው ውሉን ለመፈፀም አስፈላጊ እስከሆነበት ድረስ የሥራ ተቋራጩ ያወጣውን ወጪ
መካስ አለበት፡፡
3.4. ነገር ግን ገመዶችን፣ ቱቦዎችን እና የተተከሉ መዋቅሮችን (Installations) የማንሳት እና የመተካት ግዴታዎች እና
ወጪዎች አሰሪው ሀላፊነቱን ለመቀበል ከወሰነ የሥራ ተቋራጩ ኃላፊነት እና ወጪ አይሆንም፡፡ እንደዚሁም ይህ
ግዴታና በዚህም ምክንያት የሚደረገው ወጪ በሌላ የተለየ አስተዳደር ወይም ወኪል የሚፈጸም እስከሆነ ድረስ
የሥራ ተቋራጩ ኃላፊነት አይሆንም፡፡

3.5. ማንኛውም በግንባታ ቦታው የሚሠራ ሥራ በመንግሥታዊ አገልግሎት ላይ ችግር ወይም ጉዳት ሊያመጣ የሚችል
ከሆነ የሥራ ተቋራጩ ወዲያውኑ በጽሑፍ ለመሐንዲሱ ማሳወቅ አለበት፡፡ በሚያሳውቅበት ጊዜ ግን የግንባታ
ሥራ በተለመደው ሁኔታ ማስኬድ የሚያስችል እርምጃዎች ለመውሰድ ምክንያታዊ የሆነ ጊዜ በመስጠት መሆን
ይገባዋል፡፡

4. የግንባታ ሥራዎች ስለመቀየስ

4.1. የሥራ ተቋራጩ

41 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
(ሀ) በመሐንዲሱ የተሰጠውን የግንባታ ሥራዎች መነሻ መሠረት በማድረግ የመጀመሪያው (Original)
መነሻ ምልክቶችን፣ መስመሮችንና ከፍታዎችን በትክክል የመቀየስ፣
(ለ) የሁሉም የግንባታ ሥራዎች ክፍሎችን ቦታ፣ ስለከፍታ፤ስለልኬቱ እና አቀማመጡ ትክክለኝነት እና
(ሐ) ከላይ ከተጠቀሱት ኃላፊነቶች ጋር ግንኙነት ያላቸው ሁሉንም አስፈላጊ መሣሪያዎች፣
መጠቀሚያዎችና የሰው ኃይል የማቅረብኃላፊነት አለበት፡፡

4.2. የግንባታ ሥራዎች በሚካሄዱበት በማንኛውም ጊዜ በማናቸውም የግንባታ ሥራዎች ክፍል ላይ የቦታ ከፍታዎች፣
ልኬቶች ወይም አቀማመጦች ስህተት ከታዩ እና መሐንዲሱ ከጠየቀ የመሐንዲሱ ፍላጎት እስኪሟላ ድረስ የሥራ
ተቋራጩ በራሱ ወጪ ስህተቱን ማስተካከል ይኖርበታል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ስህተት የተፈጠረው መሐንዲሱ
በሰጠው የተሳሳተ መረጃ ከሆነ ግን የማስተካከያ ዋጋውን መሸፈን የአሰሪው ኃላፊነት ይሆናል፡፡
4.3. የማናቸውም የቅየሳዎች፤ የመስመሮች ወይም የከፍታዎች በመሐንዲሱ መመርመር (checking) የሥራ ተቋራጩን
የእነዚህኑ ትክክለኛነት አስመልክቶ ካለበት ኃላፊነት ነፃ አያደርገውም፡፡ እንደዚሁም የሥራ ተቋራጩ ሁሉንም
በመነሻነት ምልክቶችን፤ የሚታዩ የእንጨት መስመሮች(አጥሮችን)፣ ችካሎች እና ሌሎች ለግንባታ ሥራዎች ቅየሳ
ጥቅም ላይ የዋሉ ነገሮችን በጥንቃቄ መጠበቅና እንዳይበላሹ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

5. የፈረሱ ቁሶች

5.1. ውሉ የማፍረስ ሥራዎችን የሚያካትት ከሆነና የውል ልዩ ሁኔታዎች እና/ወይም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ
ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕግ በተለየ አኳሃን ካላስቀመጠ በስተቀር በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 51
መሰረት በማፍረስ የተገኙ የፈረሱ ቁሶችና ዕቃዎች የአሰሪዉ ንብረት ይሆናሉ፡፡
5.2. በ ልዩ የውል ሁኔታዎች ላይ ከማፍረስ ሥራው የተገኙ ቁሶችና ዕቃዎች በሙሉም ሆነ በከፊል የባለቤትነት መብት
የአሰሪው ከሆነ የሥራ ተቋራጩ ቁሶቹን እና ዕቃዎቹን ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆነውን ጥንቃቄ ሁሉ መውሰድ
አለበት፡፡ በቁሶቹና ዕቃዎቹ ላይ በሥራ ተቋራጩ ወይም በወኪሎቹ ለሚደርሰው ጉዳት የሥራ ተቋራጩ ተጠያቂ
ነው፡፡
5.3. አሰሪው የባለቤትነት መብት ባለው ፍርስራሽ ቁሶች እና ዕቃዎች እነዚህን ለምንም ዓይነት ጥቅም ሊያውላቸው
ቢያስብም መሐንዲሱ ወደሚያሳየው ቦታ ለማጓጓዝ፤ በቦታው ለማከማቸት እና ለማከማቺያ ቦታ የሚያስፈልጉት
ክፍያዎች በሙሉ የሚጓጓዙበት ቦታ ከ 1 ዐዐ ሜትር እስካልራቀ ድረስ በሥራ ተቋራጩ መሸፈን ይገባዋል፡፡
5.4. በልዩ የውል ሁኔታዎች በተለየ ሁኔታ እስካልተካተተ ድረስ የሥራ ተቋራጩ ስብርባሪዎችን፤ ሌሎች የፈረሱ
(ፍርስራሽ) ቁሶችን፣ ቆሻሻዎችን እና የተከመሩ ፍራሾችን በቀጣይነት ከግንባታ ቦታው በራሱ ወጪ ማስወገድ
ይኖርበታል፡፡

42 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
6. ግኝቶች

6.1. በቁፋሮ ወይም በማፍረስ ሥራዎች ጊዜ የተገኙ ማናቸውም ዓይነት ግኝቶች ወዲያውኑ መሐንዲሱ
እንዲያውቃቸው መደረግ አለበት፡፡ መሐንዲሱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕግን ከግምት
ውስጥ በማስገባት እንዴት መታየት እንዳለባቸው ይወስናል፡፡
6.2. የሥራ ተቋራጩ ላደረገው የተለየ ጥረት በመካስ የአሰሪው ይዞታው በሆነ መሬት ላይ በቁፋሮና በማፍረስ ወቅት
የተገኙ ቁሶች አሰሪው የባለቤትነት መብት አለው፡፡
6.3. በቁፋሮ ወይም በማፍረስ ጊዜ የተገኙ ቅርጻ ቅርጾች ፤ረዥም ዕድሜ ያስቆጠሩ ቁሶች እና ተፈጥሮአዊ ነገሮች፣ ቅሪተ
አካል (Numismatic) ወይም ሌሎች ለሳይንሳዊ ጥናት ተፈላጊነት ያላቸው ነገሮች፣ እንደዚሁም የማይገኙ ነገሮች
ወይም ከውድ ድንጋዮች ወይም ብረቶች የተሰሩ ነገሮች የአሰሪው ንብረት ይሆናሉ፡፡
6.4. አለመግባባት (ያለመስማማት) ከተከሰተ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 51.1 እና 51.3 የተገለፀው
አጠቃቀም ላይ አሰሪው ብቸኛ የመወሰን ሥልጣን አለው፡፡

7. ጊዜያዊ የግንባታ ሥራዎች

7.1. የሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ጊዜያዊ ሥራዎችን በራሱ ወጪ ያካሄዳል፡፡ የሥራ
ተቋራጩ ሊያከናውናቸው ያሰባቸውን ጊዜያዊ ሥራዎች የሚያሳይ የሥራ ዝርዝር እና ንድፎች ፣ ለመሐንዲሱ
ከሥራ ዝርዝርና ንድፎች ጋር የሚጣጣሙ ከሆነ እንዲያጸድቀው ያቀርባል፡፡ የሥራ ተቋራጩ ለንድፎቹ ኃላፊነት
በሚወስድበት ጊዜ በመሐንዲሱ የተሰጡ ማንኛውንም አስተያየቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡
7.2. የሥራ ተቋራጩ ለጊዜያዊ ሥራዎች ዲዛይን ኃላፊነት አለበት፡፡
7.3. የመሐንዲሱ ዲዛይኑን ማጽደቅ የሥራ ተቋራጩ ለጊዜያዊ ሥራዎች ዲዛይን ያለበትን ኃላፊነት አይቀይረውም፡፡
7.4. አስፈላጊ ከሆነ የሥራ ተቋራጩ ለጊዜያዊ ሥራዎች ያዘጋጀውን ዲዛይን በሶስተኛ ወገን ማፀደቅ ይኖርበታል፡፡
7.5. በልዩ የውል ሁኔታዎች መሰረት ጊዜያዊ ሥራዎችን ዲዛይን ማድረግ የአሰሪው ኃላፊነት ተደርጎ ከተጠቀሰ
መሐንዲሱ ጊዜያዊ ሥራውን ለማከናወን የሚያስፈልጉ ሁሉንም ንድፎች ለሥራ ተቋራጩ በፕሮግራሙ መሠረት
ሥራዎቹን ለማከናወን በሚያስችለው ተስማሚ ጊዜ ውስጥ ማቅረብ አለበት፡፡ በእንደዚህ ዓይነቱ ሁኔታ አሰሪው
ኃላፊነት ያለበት ለዲዛይኑ ደህንነት እና ምሉዕነት ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን የሥራ ተቋራጩ በተገቢው መንገድ
ለመገንባቱ ተጠያቂ ይሆናል፡፡

8. የአፈር ጥናቶች

በልዩ የውል ሁኔታዎች እና የቴክኒክ የሥራ ዝርዝሮች መሠረት የሥራ ተቋራጩ መሐንዲሱ ያመነበትን የአፈር ምርመራ ለማካሄድ
የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል እና መሣሪያ ለመሐንዲሱ ማቅረብ አለበት፡፡ የሥራ ተቋራጩ ለዚህ ሥራ ጥቅም ላይ ለዋለው ወይም
ለቀረበው የሰው ኃይል እና መሣሪያ ያወጣውን ወጪ በውሉ ውስጥ እስካልተካተተ ድረስ ይከፈለዋል፡፡

43 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
9. ተደራራቢ ውሎች

9.1. የሥራ ተቋራጩ በመሐንዲሱ ፍላጎቶች መሠረት በግንባታ ቦታው ወይም አጠገብ ሥራቸውን ለሚያካሄዱ
በአሰሪውወይም በማናቸውም መንግሥታዊ ባለሥልጣን ለተቀጠሩ ማናቸውም ሌላ ስራ ተቋራጮች በውሉ
ያልተካተቱ ወይም ከአሰሪው ግንባታ ሥራ ጋር ግንኙነት ያላቸው ወይም ተጨማሪ ሥራዎችን በሚሠሩበት ጊዜ
ሥራውን እንዲሰሩ የሚያስችላቸውን ማንኛውንም ተገቢ የሆኑ ምቹ ሁኔታዎች መፍጠር አለበት፡፡
9.2. ነገር ግን የሥራ ተቋራጩ በመሐንዲሱ የጽሁፍ ጥያቄ ፤ለማንኛውም ሌላ የሥራ ተቋራጭ ወይም መንግሥታዊ
አካል ወይም ለአሰሪው ፤ማንኛውንም የሥራ ተቋራጩ እንዲጠግን ኃላፊ የሆነበት መንገድ ወይም መተላለፊያ
ክፍት ካደረገ ወይም ለሌላ ማንኛውም ሰው በግንባታ ቦታው የሥራ ተቋራጩን ጊዜያዊ ሥራዎች፣ ድጋፎች
(scaffold) ወይም ሌላ መሣሪያ እንዲጠቀሙ ከፈቀደ ወይም በውሉ ውስጥ የሌለ ማንኛውንም አይነት
አገልግሎት ካቀረበ አሰሪው የሥራ ተቋራጩ ለሰጠው ጥቅም ወይም አገልግሎት በመሐንዲሱ ሃሳብ ተገቢ ነው
ብሎ ያመነውን የጊዜ ማራዘሚያ እና/ ወይም ክፍያ መፈጸም አለበት፡፡
9.3. የሥራ ተቋራጩ በዚህ አንቀጽ ምክንያት ከማንኛውም ግዴታዎቹ ነፃ ሊሆን አይችልም። እንደዚሁም በአጠቃላይ
የውል ሁኔታዎች አንቀፅ 54.2 ከተጠቀሰው ውጪ ምንም ዓይነት ካሳ ማግኘት አይችልም፡፡
9.4. አንድ ውልን በተመለከተ የተነሳ ቸግር በምንም ዓይነት ሁኔታ የሥራ ተቋራጩ የሌሎችን ውሎችን ትግበራ
እንዲቀይር ወይም እንዲዘገይ መብት አይሰጠውም፡፡ በተመሳሳይ አሰሪው እንደነዚህ ዓይነት ችግሮችን በሌላ ውል
መከፈል ያለባቸውን ክፍያዎች ለማዘግየት እንደ ምክንያት ሊጠቀምባቸው አይገባም፡፡

10. የፈጠራ ባለቤትነትና ፈቃዶች

በልዩ የውል ሁኔታዎች በተለየ ሁኔታ እስካልተመለከተ ድረስ የሥራ ተቋራጩ በውሉ እንደተጠቀሰው የፈጠራ ባለቤትነት መብቶችን፤
ፈቃዶችን፣ ንድፎችን፣ ዲዛይኖችን፣ ሞዴሎችን፣ ወይም መለያ ወይም ንግድ ምልክቶችን በመጠቀሙ ምክንያት የሚመጣን የካሳ ጥያቄ
እንደዚህ አይነቱ መብት መጣስ የአሰሪው እና/ወይም መሐንዲሱ የሰጡትን ዲዛይን ወይም የሥራ ዝርዝር ከመከተል የመጣ እስካልሆነ
ድረስ ለአሰሪው እና ለመሐንዲሱ ካሳ መክፈል ይገባዋል፡፡

11. የሂሳብ አያያዝ፣ ኢንስፔክሽንና ኦዲት

ስራ ተቋራጩ በዚህ ውል መሠረት ለሚያከናውናቸው የግንባታ ስራዎች አለም አቀፍ የሂሳብ አያያዝ መርሆችን የተከተለ ትክክለኛ
የሆኑ የሂሳብ መዝገቦች መያዝ እንዲሁም ንዑስ-ስራ ተቋራጮችም እንዲይዙ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ የሂሳብ መዝገቦቹ ዝርዝር ዋጋዎችና
የስራ ጊዚያቶችን በግልጽ የሚያሳዩ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

44 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
12. የመረጃ አጠባበቅ

12.1. ስራ ተቋራጩ የመረጃ ጥበቃ ህጐች መሠረት ውሉን መፈፀም አለበት፡፡ ስራ ተቋራጩ በተለይ በሚከተሉት
ሁኔታዎች ላይ ተስማምቷል፡፡
(ሀ) አስፈላጊ የሆኑ ቴክኒካዊና ድርጅታዊ የጥበቃ ሥርዓቶችን ለመከተል
(ለ) የውሉን ሁኔታዎች ሲያስፈጽም በአሰሪው ስም የግል መረጃዎችን መጠቀም የሚችለው ከአሰሪው ትዕዛዝ
(ፈቃድ) ሲያገኝ ብቻ መሆኑን፣
(ሐ) በዚህ አንቀጽ በተመለከቱት ግዴታዎች መሠረት ስራ ተቋራጩ የተጠየቁትን ፍላጎቶች የሚያሟላ
መሆኑን ለማረጋገጥ አሰሪው ሲጠይቅ ኦዲት እንዲያደርግ ለመፍቀድና አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለማቅረብ
ተስማምቷል፡፡

12.2.በስራ ተቋራጩ፤ በሠራተኞቹ ወይም በወኪሎቹ አማካኝነት ለሚከሰት የመረጃ መውደም መጥፋት ወይም
መጎዳት፤ እንዲሁም ተዋዋይ ወገኖች ከተስማሙበት ውጭ ፈቃድ ሳያገኙ ወይም በህገ ወጥ መንገድ የግለሰብ ወይም
ሕጋዊ ሰውነት ያለው ሰው የግል መረጃ በመጠቀማቸው ምክንያት በአሰሪው ላይ ለሚደርስበት ጉዳቶች፣ ወጪዎችና
ዕዳዎች ካሣ ለመክፈል ስራ ተቋራጩ ተስማምቷል፡፡

13. የውል አፈፃፀም ዋስትና

13.1.ስራ ተቋራጩ ውሉ ከተፈረመ በኋላ ባሉት አሥራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ ለውሉ መልካም አፈፃፀም
ዋስትና በልዩ የውል ሁኔታዎች የተጠቀሰውን መጠን ዋስትና ያቀርባል፡፡
13.2.ከላይ ያለው ንዑስ አንቀጽ ቢኖርም እንኳ በሁኔታ ላይ የተመሠረተ (conditional) የመድህን ዋስትና እንደ የውል
አፈጻጸም ዋስትና ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
13.3. የውል አፈጻጸም ዋስትናው ገንዘብ ስራ ተቋራጩ የውል ግዴታዎችን መወጣት ሲያቅተው ለ አሰሪው ይከፈላል፡፡
13.4. የውል ማስከበሪያ ዋስትናው በጥሬ ገንዘብ፣ ከታወቀ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ፣ ወይም በ ልዩ የውል ሁኔታ ላይ
የተመለከተው ይዘት ያለው የባንክ ዋስትና መቅረብ አለበት፡፡
13.5. የውል አፈጻጸም ዋስትና ከማቅረቡ በፊት ለሥራ ተቋራጩ ምንም ክፍያ መፈጸም የለበትም፡፡ የውል አፈጻጸም
ዋስትው ውሉ ሙሉ በሙሉ በተገቢው ሁኔታ እስኪጠናቀቅ ድረስ ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
13.6. በውሉ አፈጻጸም ወቅት የውል አፈጻጸም ዋስትና የሰጠው የተፈጥሮ ወይም ህጋዊ ሰው የገባቸውን ቃሎች
መጠበቅ ካልቻለ የውል አፈጻጸም ዋስትናው የፀና አይሆንም (Cease to be valid)፡፡ አሰሪው በበፊቱ
ቃላቶች መሠረት አዲስ የውል አፈጻጸም ዋስትና እንዲያቀርብ ለሥራ ተቋራጩ የፅኁፍ ማስታወቂያ
(Formal notice) ይሰጠዋል፡፡ የሥራ ተቋራጩ አዲስ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ካልቻለ
አሰሪው ውሉን ማቋረጥ ይችላል፡፡

45 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
13.7. አሰሪው በሥራ ተቋራጩ ውል አለመፈፀም ምክንያት የውል አፈፃፀም ዋስትናው ሁኔታ እና መጠን ድረስ
ዋስትና ሰጪው ተጠያቂ የሆነበትን ሙሉ መጠን ከውል ማስከበሪያ ዋስትናው እንዲከፈለው ይጠይቃል፡፡
ዋስትና ሰጪው የተጠየቀውን ማጠን ያለምንም መዘግየት እና ተቃውሞ መክፈል ይኖርበታል፡፡ አሰሪው
በውል ማስከበሪያ ዋስትናው መሠረት የካሳ ጥያቄ ከማንሳቱ በፊት ለሥራ ተቋራጩ ካሳ ሊጠይቅ
ያሰበበትን የውል ጥፋት ሁኔታ ጠቅሶ ማሳወቅ አለበት፡፡
13.8. በልዩ የውል ሁኔታዎች በሌላ ሁኔታ ካልተገለፀ በስተቀር በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀፅ 65 መሰረት
የመጨረሻ የክፍያ ሰነድ ከፈረመ ከ 28 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አሰሪው የውል አፈፃፀም ዋስትናውን
መጠን ሙሉ በ ሙሉ (አለመስማማት ያለበትን መጠን ብቻ በማስቀረት) ለስራ ተቋራጩ ይመልስለታል፡፡

ሠ. ለስራ ተቋራጩ ክፍያ ስለመፈፃፀም

14. አጠቃላይ መርሆዎች

14.1. ልዩ የውል ሁኔታዎች የቅድሚያ ክፍያዎች ፣ በመሃል የሚከፈሉ ክፍያዎች (Interim) እና/ወይም የመጨረሻ
ክፍያዎች የሚመሩበትን አስተዳደራዊ እና ቴክኒካዊ ሁኔታዎች በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች መሠረት
ያስቀምጣል፡፡
14.2. በመሐንዲሱ ለተሰጡ የመሃል ክፍያ ሰርተፍኬቶች እና የመጨረሻ የሂሳብ ሰነዶች አሰሪው ከደረሰው በ 90
ቀናት ጊዜ ውስጥ የሥራ ተቋራጩ ማግኘት የሚገባውን ክፍያ መክፈል አለበት፡፡ የክፍያ ሰርተፍኬት
ከአንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ አስፈላጊ ሁኔታዎች ሳይሟላ የተሰጠ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
14.3. የመሃል የሚከፈል የክፍያ ሰርተፍኬቶች ወይም የመጨረሻ የሂሳብ ሰነዶች የሚከፈለውን መጠን የሚጠቅስ
የክፍያ ሰነድና ሌሎች ደጋፊ ሰነዶች ቅጂ ጋር መቅረብ አለበት፡፡
14.4. የሥራ ተቋራጩ የሚያቀርበው የክፍያ ሰነድ የሚከተሉት ሁኔታዎች ካሟላ በትክክል እንደቀረበ ይቆጠራል፤
(ሀ) በውሉ ላይ የክፍያ ጥያቄን እንዲያስተናግድ ስልጣን ለሰጠው የአሰሪው ሰራተኛ አድራሻ የውሉንና የግዥ
ትዕዛዙን ቁጥር የጠቀሰ የክፍያ ጥያቄው በቀጥታ ሲያቀርብ
(ለ) የክፍያ ሰነዱ የተፃፈበት ቀንና መለያ ቁጥር መያዝ አለበት፣
(ሐ) እንዲከፈል የተጠየቀው የገንዘብ መጠን የክፍያ ጊዜው የደረሰ መሆን አለበት፣
(መ) እንዲከፈል የተጠየቀው የገንዘብ መጠን በውሉ መሠረት በትክክል የተሰላ መሆን አለበት፣

(ሠ) የክፍያ መጠየቂያ ሰነዱ ክፍያ ለማዘጋጀት የሚያስችል የስራ ተቋራጩን ስምና አድራሻ ማካተት አለበት፣
(ረ) በየክፍያ መጠየቂያ ሰነዱ ውስጥ ችግሮች ሲኖሩ ለማሳወቅ እንዲቻል የሚመለከተው ስም ፣ኃላፊነትና የስልክ
ቁጥር ማካተት አለበት፡፡

46 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
(ሰ) የክፍያ መጠየቂያ ሰነዱ ስራ ተቋራጩን የባንክ ቁጥር መረጃ ማካተት አለበት፡፡
(ሸ) እንደአስፈላጊነቱ የክፍያ መጠየቂያ ሰነዱ ከሽያጭ ታክስ ነፃ (የነፃ መብት ካለ) መሆኑ የተረጋገጠ መሆን
አለበት፡፡
ከላይ የተዘረዘሩት ሁኔታዎች ተሟልተው ካልቀረቡ አሰሪው ተሟልተው እስኪቀርቡለት ድረስ ክፍያውን ሊያዘገየው
ይችላል፡፡
14.5. እንዲከፈል የተጠቀሰው ክፍያ የመክፈያ ጊዜው ካልደረሰ ተገቢው ማረጋገጫ ሰነዶች ካልቀረቡ ወይም
የወጣው ወጪ ተቀባይነት የሌለው ከሆነ ለሥራ ተቋራጩ የክፍያ ሰርተፍኬቱ ወይም የመጨረሻ የሂሳብ
ሰነዱ ሊሟላ እንደማይችል በማሳወቅ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 59.2 የተጠቀሰው የጊዜ
ገደብ ተፈጻሚ ላይሆን ይችላል፡፡ የወጣው ወጪ ተቀባይነት የሌለው ከሆነ ጉዳዩን በበለጠ ለማጣራት
በቦታው ምርመራ ሊካሄድ ይችላል፡፡ የሥራ ተቋራጩ ማብራሪያዎች፣ ማሻሻያዎች ወይም ተጨማሪ
መረጃዎች በተጠየቀ በ 30 ቀናት ውስጥ መስጠት ይኖርበታል፡፡ መሐንዲሱ ማብራሪያውን ባገኘ በ 30
ቀናት ውስጥ እንደየአሰፈላጊነቱ የተከለሰ ክፍያ ወይም የመጨረሻ የሂሳብ ሰነድ ወስኖ ይሰጣል፡፡ የክፍያ
ጊዜውም ከዚህ ቀን ጀምሮ ይቆጠራል፡፡
14.6. የሥራ ተቋራጩ ከመጨረሻ የክፍያ መጠን አስበልጦ የተከፈለው ከሆነ የልዩነት መጠኑን የባለእዳነት
ማስታወሻ (debit note) በደረሰው በ 45 ቀናት ውስጥ ለአሰሪው መክፈል ይኖርበታል፡፡
14.7.የሥራ ተቋራጩ አሰሪው ባስቀመጠው ቀነ ገደብ መልሶ ካልከፈለ አሰሪው መከፈል የሚገባውን ቀነ ገደቡ
ያለፈበት ወር የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የቅንስናሽ የወለድ መጠን
እንደተጠበቀ ሆነ ሶስት ከግማሽ በመቶ (3.5%) በዋናው ክፍያ ላይ በመጨመር ማስከፈል ይችላል፡፡
በጊዜው ባለመክፈሉ የሚታሰበው ወለድ የሚሰላው አሰሪው በወሰነው ቀነ ገደብ እለትና ክፍያው
በእርግጥ በተፈጸመበት መካከል ነው፡፡ ማንኛውም ከፊል ክፍያ መጀመሪያ የተወሰነውን ወለድ መሸፈን
አለበት፡፡
14.8. ለአሰሪው ተመላሽ የሚሆን ክፍያ ለሥራ ተቋራጩ መከፈል ካለበት ክፍያ ጋር ሊካካስ (set-off) ይችላል፡፡ ይህ
ሁኔታ ተዋዋይ ወገኖችን በየጊዜው የመክፈል ዘዴን (Installment) የመስማማት መብታቸውን
አያግደውም፡፡ ለአሰሪው መከፈል ያለበትን ተመላሽ ክፍያ ለመክፈል የሚያስፈልገው የባንክ አገልግሎት
ክፍያ በሥራ ተቋራጩ መሸፈን ይኖርበታል፡፡

15. የቅድሚያ ክፍያ

15.1. በልዩ የውል ሁኔታዎች ከተካተተ፣ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ሁኔታዎች ሲሟሉ፣ ሥራ ተቋራጩ ሲጠይቅ እና
የግንባታ ሥራዎችን ከመፈጸም ጋር ለተያያዙ ሥራዎች የቅድሚያ ክፍያ ይከፈላል፡፡

47 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
(ሀ) የውሉ አፈፃፀሙን ከመጀመር ጋር የተያያዙ ወጪዎችን ለመሸፈን ጥቅል ድምር (Lump-sum)
የቅድሚያ ክፍያ

(ለ) የሥራ ተቋራጩ ውሉን ለመፈፀም የሚያስፈልጉ የግንባታ ቁሶችን፣ ተከላዎች (plant) ፣
መሣሪያዎች፣ ማሽኖችና፣ መገልገያ መሣሪያዎችን ለመግዛት ውል መፈራረሙን ማስረጃ
ካቀረበ እና አስቀድሞ ያወጣው ለሌላ ወጪ አንደ ለፈጠራ ባለቤትነት መብት ወይም ለጥናት
ከግምት ውስጥ እንዲገባለት ማስረጃ ካቀረበ

15.2. ልዩ የውል ሁኔታዎች ከአጠቃላይ የውል ዋጋው 30% የማይበልጥ የቅድሚያ ክፍያ መጠን መጥቀስ አለበት፡፡
15.3. የሚከተሉት እስኪሟሉ ድረስ ምንም ዓይነት የቅድሚያ ከፍያ መከፈል የለበትም፡፡
(ሀ) ውል መፈረም
(ለ) በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 58 መሠረት ለአሰሪው የውል ማስከበሪያ ዋስትና
ማቅረብ እና

(ሐ) የሥራ ተቋራጩ ከሚከፈለው ቅድመ ክፍያ ጋር እኩል መጠን ያለው የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና
እንደምርጫው ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና
ለአሰሪው ማቅረብ፡፡

15.4. የቅድሚያ ክፍያ ዋስትናው የተከፈለው የቅድሚያ ክፍያው ከጊዜያዊ ክፍያዎች እየተቀነሰ ሙሉ ለሙሉ
እስኪመለስ ድረስ የሚያገለግል ሆኖ መቆየት(valid) አለበት፡፡
15.5. የሥራ ተቋራጩ የቅድሚያ ክፍያውን ውሉን ለመተግበር የሚያስፈልጉ የግንባታ መሣሪያዎች፣ ተከላዎችን ፣
ቁሶችን እና ግንባታ ለመጀመር ለሚያስችሉ መጓጓዞች ክፍያ ለመፈጸም ብቻ ማዋል አለበት፡፡ የሥራ
ተቋራጩ የቅድሚያ ክፍያው በዚህ መንገድ መወጣቱን የክፍያ ሰነድ ወይም ሌሎች ሰነዶችን ቅጂ
ለመሐንዲሱ በማቅረብ ማሳየት አለበት፡፡ የሥራ ተቋራጩ የቅድሚያ ክፍያውን ምንም ያህሉን መጠን
አላግባብ ቢጠቀም ወዲያውኑ እንደ ዕዳ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ እንደዚሁም በቀጣይ ምንም ዓይነት
ቅድሚያ ክፍያ አይሰጠውም፡፡
15.6. የቅድሚያ ክፍያው ዋስትና ፀንቶ የሚቆያበት ጊዜ ቢያበቃና የሥራ ተቋራጩ ሳያሳድሰው ቢቀር፣ አሰሪው
የቅድሚያ ክፍያውን የሚያክል ከወደፊት የሥራ ተቋራጩ ክፍያ ይቀንሳል ወይም የአጠቃላይ የውል
ሁኔታዎች አንቀጽ 58.6 ተፈፃሚ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
15.7. በምንም ዓይነት ምክንያት ውሉ ቢቋረጥ የቅድሚያ ክፍያውን የሚያስጠብቀው ዋስትና የሥራ ተቋራጩ
መመለስ ያለበትን ቀሪውን የቅድመ ክፍያ ለማግኘት እንዲከፈል አሰሪው ሊጠይቅ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ
ዋስትና ሰጪው በምንም ዓይነት ምክንያት ክፍያውን ሊያዘገይ ወይም ተቃውም ሊያነሳ አይችልም፡፡

48 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
15.8. በዚህ አጠቃላይ የውል ሁኔታ የተሰጠ የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና የቅድሚያ ክፍያው ተመልሶ ተከፍሎ ሲያልቅ
ይለቀቃል፡፡
15.9. የቅድሚያ ክፍያን መስጠት እና መልሶ መክፈልን የሚመለከቱ ተጨማሪ ሁኔታዎችና ሥነ-ሥርዓቶች በልዩ
የውል ሁኔታዎች ውስጥ እንደተገለፀው ይሆናሉ፡፡

16. ቀሪ /የተያዘ ገንዘብ (Retention Money)

16.1. በጉድለት ተጠያቂነት ጊዜ (Defect liability period) ሥራ ተቋራጩ ያሉበትን ግዴታዎች መፈፀም
እንዲያስችል እንደዋስትና ከመሃል ከሚደረጉ ክፍያዎች ላይ ተይዞ የሚቆየው ገንዘብ መጠን እና ሌሎች
ይህንን ዋስትና/መያዣ/ የሚገዙ ዝርዝር ደንቦች በልዩ የውል ሁኔታዎች ውስጥ መጠቀስ ይገባቸዋል፡፡ ቀሪ
ተደርጎ የሚያዘው ገንዘብ በምንም መልኩ ከውል ዋጋው 10% መብለጥ የለበትም፡፡
61.2 የሥራ ተቋራጩ ከፈለገ እና በአሰሪው ከተፈቀደ ለግንባታ ሥራዎች መጀመሪያ የተወሰነው ቀን ሳያልፍ የቀሪ
ገንዘብ ድምሩን በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 58 መሠረት በሚሰጥ የመያዣ ዋሰትና መተካት ይችላል፡፡
16.2. የተያዘው ድምር ወይም የመያዣ ዋስትናው በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 65 የተመለከተው
የተፈረመ የመጨረሻ የሂሳብ ሰነድ በተሰጠ በ 45 ቀናት ውስጥ መለቀቅ አለበት፡፡

17. የዋጋ ማስተካከያ

17.1. የውሉ አፈፃፀም ከአሥራ ስምንት (18) ወራት በላይ እንደሚፈጅ ከተረጋገጠ የውል ዋጋዎች ውሉ ተፈጻሚ
ከሆነበት ቀን ከአሥራ ሁለት (12) ወራት በኋላ የዋጋ ማስተካከያ ማድረግ ይፈቀዳል፡፡
17.2. በዚህ ውል የተወሰነ የግንባታ ሥራን አስመልክቶ የውሉ አፈፃፀም ከአሥራ ስምንት (18) ወራት በላይ የሚፈጅ
እስከሆነ ድረስ የዋጋ ማስተካከያ ጥያቄ ውሉ ተፈጻሚ ከሆነበት ቀን አሥራ ሁለት (12) ወራት በኋላ
ሊቀርብ ይችላል፡፡ የሚስተካከለው ዋጋ ሁለቱ ወገኖች በሌላ ቀን እንዲሆን በፅሑፍ ስምምነት ካላደረጉ
በስተቀር አሰሪው የዚህን ዋጋ ማስተካከያ ማስታወቂያ ከሥራ ተቋራጩ ከተቀበለት ቀን ጀምሮ ከሰላሳ
(30) ቀናት በኋላ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
17.3. ስራ ተቋራጩ የዋጋ ማስተካከያ ጥያቄ ካላቀረበ በስተቀር ሁሉም ዋጋዎች አይቀየሩም፡፡ በ አንቀጽ 62.2 ላይ
እንደተጠበቀ ሆኖ ስራ ተቋራጩ ለመሀንዲሱ የፅሁፍ ማስታወቂያ በመስጠት ይህን ድንጋጌ በማንኛውም
ሰዓት መጠቀም ይችላል፡፡
17.4. በዚህ አንቀፅ ላይ በተገለፀው መሰረት አሰሪው በውሉ ዋጋ ላይ ጭማሪ ወይም ቅናሽ ሊያደርግ ይችላል፡፡
የዋጋ ማስተካከያው ሙሉ ለሙሉ ተከፋይ ሆኖ የሚፈጸመው መጀመሪያ በተያዘው የውል
ማጠናቀቂያ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡

49 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
17.5. የውል ማጠናቀቂያ ጊዜው መጀመሪያ ከተያዘው ጊዜ ካለፈ፤
(ሀ) የመጀመሪያ የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ የዘገየው በሥራ ተቋራጩ ምክንያት/ ጥፋት ከሆነ፣ ዋጋ
ማስተካከያ መጠኑ የመጀመሪያው ማጠናቀቂያ ቀኑ ላይ እንዲቆም ሆኖ በዚህ የዋጋ ማስተካከያ
መጠን የሚደረገው የዋጋ ማስተካከያ ስራው እስከሚጠናቀቅበት ቀን ድረስ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ነገር
ግን ከመጀመሪያው ማጠናቀቂያ ቀን በኋላ የዋጋ ማስተካከያ በሚሰላበት ጊዜ የዋጋ ማስተካከያ
መጠኑ ከቀነሰ የቀነሰው ዋጋ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

(ለ) የሥራ ተቋራጩ ጥፋት ሳይኖር የጊዜ ማራዘሚያው ከተፈቀደ እና አሰሪው አጽድቆ ከሆነ የዋጋ
ማስተካከያው ለተራዘመው ጊዜ በሙሉ ተከፋይ ይሆናል፡፡

17.6. በዚህ ውል ላይ በግልፅ ካልተቀመጠ በስተቀር የዋጋ ማስተካካያ የሚደረገው በልዩ የውል ሁኔታዎች ላይ በግልፅ
ተጠቅሰው ለተቀመጡት ግብዓቶች ብቻ ነው፡፡
17.7. በውሉ ዋጋ ላይ የሚደረጉ ማስተካከያዎች በኢትዮጵያ ማዕከላዊ የስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ወይም የመንግስት
ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የሚሰጡ የዋጋ ኢንዴክሶች ወይም የዋጋ አመላካቾችን ከግምት ውስጥ
ባስገባ መልኩ የተሰላ መጠን መሆን አለበት፡፡
17.8. ከላይ የተገለፀውን የአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ንዑስ አንቀጽ ቢኖርም እንኳ ከታወቀ የአካባቢ አምራች
ወይም ተገቢ የውጭ ሀገር ተቋም ዋጋን አስመልክቶ የሚገኝ መረጃ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ የስታቲስቲክስ
ኤጀንሲ ወይም የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወቅታዊ የዋጋ ኢንዴክሶች የማይሰጡ ከሆነ
ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡
17.9. አሰሪው እንዲከልሰው እና እንዲያፀድቀው የዋጋ ማስተካከያን እንዲወስን የሚያስችሉ ሁሉንም ስሌቶችና
ደጋፊ መረጃዎች ስራ ተቋራጩ ለአሰሪው ማቅረብ አለበት፡፡
17.10. በመነሻነት በሚወሰደው የዋጋ ኢንዴክስ እና በወርሀዊ የዋጋ ኢንዴክስ መካከል በሚፈጠሩ ልዩነቶች ላይ
ተመስርቶ የክፍያ ማስተካከያዎች ላይ ጭማሪ ወይም ቅናሽ ሊደረግ ይችላል፡፡
17.11. በእያንዳንዱ ግብዓት ላይ የሚደረግ ማስተካከያን ለመወሰን የሚከተለውን ቀመር ከላይ ከተገለፁት
መስፈርቶች ጋር በማጣመር ይሰላል፡፡
ፒኤ= [ኤንቪ+ኤ (ኤም ኤል አይ-ቢኤል አይ) +ቢ (ኤም ኤም አይ-ቢኤም አይ) +ሲ (ኤም ኢአይ - ቢኢአይ) +ዲ
(ኤም ኤፍ አይ-ቢኤፍአይ)] (ቢሲ)ኪው

ቢኤልአይ ቢኤምአይ ቢኢአይ ቢኤፍአይ

ፒኤ = ለስራ ተቋራጩ የሚከፈል ወይም ከስራ ተቋራጩ የሚሰበሰብ የዋጋ ማስተካከያ መጠን በኢት ብር

50 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ኤንቪ = ከውሉ የዋጋ ማስተካከያ ድንጋጌ ውጭ የሆነ የውሉ ዋጋ የማይለዋወጥን የእቃ ክፍል ወይም
ክፍልፋይን ይወክላል

ኤ = በ አማካይ የጉልበት ገቢ ማሳያ (Average Labor Category Earnings Index) ለውጦች መሰረት
ማስተካከያ የሚደረግበት የውሉ ዋጋ ክፍልፋይ

ኤምኤልአይ = ተዋዋዩ ባለስልጣን የታቀደውን የዋጋ ጭማሪ በተመለከተ ከስራ ተቋራጩ ማስታወቂያ
በሚቀበልበት ቀን ያለ የተጠቃሚ ዋጋ ኢንዴክስ

ቢኤልአይ = በምርት ወይም አገልግሎት ላይ ተግባራዊ የሚደረግ መነሻ የተጠቃሚ የዋጋ ኢንዴክስ፤ ይህም

(ሀ) በጨረታ መዝጊያ ቀን፣ ወይም

(ለ) በውሉ ዋጋ ላይ ቀደም ሲል ማስተካከያ ከተደረገ አሰሪው የመጨረሻ የዋጋ ማስተካከያን


አስመልክቶ ከስራ ተቋራጩ ማስታወቂያ ከሚቀበልበት ቀን ጀምሮ የአሁኑ የውሉ ዋጋ ተፈፃሚ
እስከሚሆንበት ቀን፡፡

ቢ = በአምራች የዕቃ የዋጋ ኢንዴክስ መሰረት ማስተካከያ የሚደረግበት የውሉ ዋጋ ክፍልፋይ

ኤምኤምአይ = አሰሪው የታቀደውን የዋጋ ጭማሪ አስመልክቶ ከስራ ተቋራጩ ማስታወቂያ በሚቀበልበት
ቀን ያለው የአምራች የዋጋ ኢንዴክስ

ቢኤምአይ = በምርት ወይም አገልግሎት ላይ ተግባራዊ የሚደረግ መነሻ የአምራች የዋጋ ኢንዴክስ፤ ይህም

(ሀ) በጨረታ መዝጊያ ቀን፣ ወይም

(ለ) በውሉ ዋጋ ላይ ቀደም ሲል ማስተካከያ ከተደረገ ተዋዋዩ ባለስልጣን የመጨረሻ የዋጋ ማስተካከያን
አስመልክቶ ከስራ ተቋራጩ ማስታወቂያ ከሚቀበልበት ቀን ጀምሮ የአሁኑ የውሉ ዋጋ ተፈፃሚ
እስከሚሆንበት ቀን፡፡

ሲ = በመሳሪያ አምራች ኢንዴክስ ላይ በሚኖሩ ለውጦች መሰረት ማስተካከያ የሚደረግበት የውሉ ዋጋ


ክፍልፋይ

ኤምኢአይ = ተዋዋዩ ባለስልጣን የታቀደውን የዋጋ ጭማሪ አስመልክቶ ከስራ ተቋራጩ ማስታወቂያ
በሚቀበልበት ቀን ያለው የአገልግሎት አምራች ኢንዴክስ

51 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ቢኢአይ = በአገልግሎት ላይ ተግባራዊ የሚደረግ መነሻ የአገልግሎት አምራች ኢንዴክስ፤ ይህም

(ሀ) በጨረታ መዝጊያ ቀን፣ ወይም

(ለ) በውሉ ዋጋ ላይ ቀደም ሲል ማስተካከያ ከተደረገ አሰሪው የመጨረሻ የዋጋ ማስተካከያን


አስመልክቶ ከስራ ተቋራጩ ማስታወቂያ ከሚቀበልበት ቀን ጀምሮ የአሁኑ የውሉ ዋጋ ተፈፃሚ
እስከሚሆንበት ቀን፡፡

ዲ = በአማካይ የገቢ ኢንዴክስ ለውጦች መሰረት ማስተካከያ የሚደረግበት የውሉ ዋጋ ክፍልፋይ

ኤምኤፍአይ = አሰሪው የታቀደውን የዋጋ ጭማሪ አስመልክቶ ከስራ ተቋራጩ ማስታወቂያ በሚቀበልበት
ቀን ያለው አማካይ የነዳጅ ኢንዴክስ

ቢኤፍአይ = በስራው ላይ ተግባራዊ የሚደረግ መነሻ አማካይ የገቢ ኢንዴክስ፤ ይህም

(ሀ) በጨረታ መዝጊያ ቀን፣ ወይም

(ለ) በውሉ ዋጋ ላይ ቀደም ሲል ማስተካከያ ከተደረገ አሰሪው የመጨረሻ የዋጋ ማስተካከያን


አስመልክቶ ከስራ ተቋራጩ ማስታወቂያ ከሚቀበልበት ቀን ጀምሮ የአሁኑ የውሉ ዋጋ ተፈፃሚ
እስከሚሆንበት ቀን፡፡

ቢሲ = ስራው ላይ ተግባራዊ የሚደረግ ወቅታዊ የውል ዋጋ

ኪው = የስራው መጠን

እንዲሁም

(ሀ) ኤንቪ + ኤ + ቢ + ሲ + ዲ ከ 1.00 ጋር እኩል ሲሆን ነው፡፡

17.12. የእያንዳንዱ የተመዘገበ ክፍል ክፍልፋይ እና በዋጋ ማስተካከያ ቀመር ላይ ተግባራዊ የሚደረጉ ትክክለኛ
ጥምር ክፍሎች በልዩ የውል ሁኔታዎች ይወሰናሉ፡፡
17.13. በውሉ ዋጋ ላይ ለሚደረግ ጭማሪ የሚቀርበው ማመልከቻ የክፍያው ቀን ከሚጀምርበት ቀን ከ 14 ቀን
በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የዋጋ ጭማሪ ከሚቀርብበት ቀን ቀጥሎ ባለው የክፍያ
ቀን ጭማሪ ከተደረገለት ምድብ ጋር በተያያዘ እንደ አዲስ የውሉ ዋጋ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

52 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
17.14. በውሉ ላይ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ ሁለቱ ወገኖች ሌላ ቀን እንዲሆን በጽሁፍ ስምምነት ካላደረጉ
በስተቀር ጭማሪ ከተደረገለት የ ግብዐት ምድብ ጋር በተያያዘ አሰሪው የዋጋ ጭማሪውን አስመልክቶ
ማስታወቂያ ከሚቀበልበት ቀን ጀምሮ ከሰላሳ (30) ቀን በኋላ እንደ አዲስ የውል ዋጋ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
17.15. ስራ ተቋራጩ በውሉ የግንባታ ግብዓቶች (ምርትና አገልግሎት) ዋጋ ላይ ለውጥ የሚያደርግ ከሆነ የታቀዱ
የዋጋ ለውጦችን የያዘ የተከለሰ የዋጋ ዝርዝር ኮፒ ማቅረብ እና የታቀደው የዋጋ ልዩነት በንዑስ አንቀጽ
62.14 እና 62.15 መሰረት ተፈፃሚ የሚሆንበትን ቀን መግለፅ አለበት፡፡
17.16. ስራ ተቋራጩበንኡስ አንቀጽ 62.12 መሰረት የዋጋ ማስተካከያ ማስታወቂያ ወይም ጥያቄ ለአሰሪው
ሲሰጥ ስራ ተቋራጩይህን ሰነድ ወይም የተጠቀሰውን የዋጋ ማስተካከያ ለማገናዘብ የሚያስፈልግ ተገቢ
መረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
17.17. አሰሪው በንዑስ አንቀፅ 62.12 መሰረት ማስታወቂያ የተሰጠበት ወይም ጥያቄ የቀረበበት የዋጋ ጭማሪን
አስመልክቶ ጥያቄ ሲያቀርብ እና ስራ ተቋራጩ አሳማኝ መልስ ሳይሰጥ ቢቀርስራ ተቋራጩለአሰሪው
ባቀረበው መረጃ መነሻነት፣ እና ባቀረበው የዋጋ ማስተካከያ ማስታወቂያ ወይም ጥያቄ መነሻነት የውሉ
ዋጋ ስራ ተቋራጩሊያገናዝበው በሚችለው መጠን ብቻ ጭማሪ የሚደረግበት ሲሆን፡
(ሀ) ተስተካክሎ ጭማሪ የተደረገበት ከ ስራው ጋር የውሉ ዋጋ ሁለቱ ወገኖች በሌላ እንዲሆን በፅሁፍ ስምምነት
ካላደረጉ በስተቀር እንደ ሁኔታው በንኡስ አንቀጽ 62.14 ወይም 62.15 ላይ በተገለፀው ቀን እንደ አዲስ
የውል ዋጋ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
(ለ) ስራ ተቋራጩእስከ አሁን ድረስ ይህን ካላደረገ በንዑስ አንቀጽ 62.16 መሰረት የተከለሰ የዋጋ ዝርዝር
ማቅረብ አለበት፡፡
17.18. በዚህ ስምምነት መሰረት ስራ ተቋራጩየሚደረግ ማንኛውም የዋጋ ቅናሽ አሰሪው በጽሁፍ ስምምነቱን
ካላሳወቀ በስተቀር ውሉ ፀንቶ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ተቀናሽ አይደረግም፡፡

18. የግንባታ ሥራዎች ዋጋ መተመን

የግንባታ ሥራዎችን ዋጋ ለመተመን የሚከተሉት ዘዴዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ፤


(ሀ) ለነጠላ ዋጋ ውሎች፣ (admeasurement)
i. በውሉ መከፈል ያለበት መጠን በውሉ መሠረት ተሰርቶ ያለቀውን ሥራ ብዛት በተቀመጠው
ነጠላ ዋጋ በማባዛት ይሰላል፤
ii. በሥራ መጠን ዝርዝር ውስጥ የተቀመጡት ብዛቶች የግምት ብዛቶች ናቸው እንጂ የሥራ
ተቋራጩ በውሉ መሠረት ግዴታዎችን እንዲያሟላ መተግበር የሚገባውን የግንባታ ሥራዎች
እርግጠኛ እና ትክክለኛ መጠን ተደርጎ መወሰድ የለበትም፤

53 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
iii. መሐንዲሱ የሥራ ተቋራጩ ያከናወነውን የግንባታ ሥራ ትክክለኛ ብዛት በመመልከት ይወስናል፡፡
ለነዚህም ሥራዎች በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 64 መሠረት ይከፈላሉ፡፡ በልዩ የውል
ሁኔታዎች ውስጥ በሌላ ሁኔታ እስካልተጠቀሰ ድረስ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 15
መሠረት በሚደረጉ ማስተካከያዎች ወይም በሌላ የሥራ ተቋራጩ ተጨማሪ ክፍያ እንዲያገኝ
የሚያደርግ የውል ሁኔታ ከሌለ በስቀር በሥራ መጠን ዝርዝር ውስጥ ተጨማሪ ነገር ማስገባት
አይቻልም፡፡
iv. መሐንዲሱ የግንባታ ሥራዎች ማንኛውም ክፍል መለካት በሚፈልግበት ጊዜ ለሥራ ተቋራጩ
በቂ ጊዜ በመስጠት እንዲገኝ ወይም ብቃት ያለውን ወኪሉን እንዲልክ ማስታወቂያ መስጠት
አለበት፡፡ የሥራ ተቋራጩ ወይም ወኪሉ መሐንዲሱን እነዚህን በሚለካበት ጊዜ ማገዝ እና
መሐንዲሱ የሚፈልጋቸውን ሁሉንም ዝርዝሮች ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የሥራ ተቋራጩ ባይገኝ
ወይም ወኪሉን ሳይልክ ቢቀር በመሐንዲሱ የተወሰደው ወይም የፀደቀው ልኬት ሥራ ተቋራጩ
ላይ ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡
(ለ) ለጥቅል ድምር ውሎች በውሉ መሠረት መከፈል የሚገባውን መጠን በአጠቃላይ የኮንትራት ዋጋው
መከፋፈል (breakdown of the overall contract price) መሠረት ወይም በተጠናቀቁ የግንባታ
ሥራ ደረጃዎች ውስጥ የተከፋፈለ (breakdown) የውል ዋጋ መቶኛ መሠረት ይወሰናል፡፡ ነጠላ
ሥራዎች (Items) ከብዛት ጋር አብረው በሚቀርቡበት ጊዜ እነዚህ የሥራ ተቋራጩ ጥቅል ዋጋ
የሰጠባቸው የማይለወጡ (የማይነኩ) ብዛቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም የተከናወነው የግንባታ ሥራ
ብዛት ምንም ቢሆን ይከፈላል፡፡

19. በመሃል የሚደረግ /ጊዚያዊ ክፍያ (Interim Payment)

19.1. በልዩ የውል ሁኔታዎች በሌላ መንገድ እስካልቀረበ ድረስ፣ የሥራ ተቋራጩ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች
አንቀጽ 64.7 እንደተመለከተው በመሀንዲሱ በፀደቀ ፎርም በእያንዳንዱ የወሩ መጨረሻ የጊዜያዊ ክፍያ
ሰነድ ለመሐንዲሱ ማቅረብ አለበት፡፡ ወርሃዊ ሰነዱ እንደተፈፃሚነቱ የሚከተሉት ነጥቦች ይኖሩታል፡፡
(ሀ) እስከሚመለከተው መጨረሻ ጊዜ ድረስ የተከናወኑ ቋሚ የግንባታ ሥራዎች የውል ዋጋ ግምት፤

(ለ) በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 62 መሠረት ማንኛውንም የዋጋ መስተካከል የሚያሳይ
መጠን፤

(ሐ) በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 61 መሠረት እንደ መያዣ ቀሪ መሆን ያለበት መጠን፤

54 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
(መ) በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 64.2 ሥር እንደተቀመጠው በተጠቀሰው ጊዜ ተከፋይ
ወይም/እና በዕዳ መልክ በግንባታ ቦታው ለቋሚ የግንባታ ሥራዎች ታስበው መጥተው ነገር ግን
የቋሚ ግንባታው አካል ያልሆኑ ማንኛውም መዋቅር ያለበት እና የግንባታ ቁስ፤

(ሠ) በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 60 መሠረት የቅድሚያ ክፍያን ለመመለስ መቀነስ ያለበት
መጠን፤ እና

(ረ) ማንኛውም በውሉ መሠረት የሥራ ተቋራጩ ሊከፈለው የሚገባ ድምር።

19.2. የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲሟሉ እና መሐንዲሱ ተገቢ ነው ብሎ ከወሰደው ለቋሚ የግንባታ ሥራ ታስበው
ለመጡ (ነገር ግን ያልተካተቱ) (ተከላዎች) እና ቁሶች ድምር የሥራ ተቋራጩ ክፍያ የማግኘት መብት
አለው፡፡
(ሀ) መሣሪያዎቹና ቁሶቹ ለቋሚ የግንባታ ሥራዎች ከወጣው የሥራ ዝርዝር ጋር የሚጣጣሙ እና
መሐንዲሱ ሊለየው በሚችል መልኩ ተደራጅተው የተቀመጡ ከሆኑ፤

(ለ) እነዚህ ተከላዎችና የግንባታ ቁሶች ከግንባታ ቦታው የደረሱ፤ ለመሐንዲሱ ተቀባይነት ባለው
በተገቢው መንገድ የተከማቹ እና ከማንኛውም ጥፋት ወይም ጉዳት ብልሽት (ጥራት መቀነስ)
የተጠበቁ ከሆኑ፤

(ሐ) የሥራ ተቋራጩ አስፈላጊ ነገሮች ፣ ትዕዛዞች፣ ደረሰኞችና በውሉ መሠረት የተከላዎቹና የግንባታ
ቁሶች አጠቃቀም መሐንዲሱ ባፀደቀው ዕቅድ መስፈራቸው የሚያሳይ መዝገብ እና መዝገቡ
በመሐንዲሱ ለሚደረግ ምርመራ ዝግጁ መሆን አለበት፤

(መ)የሥራ ተቋራጩ ከሰነዱ ጋር በመሐንዲሱ ለመገመት ሊያስፈልጉ የሚችሉ በግንባታ ቦታ ያሉ


ተከላዎችና የግንባታ ቁሶች ግምት እንዲሁም የባለቤትና የክፍያ ማስረጃዎች ጋር ማቅረብ አለበት፤

(ሠ) በልዩ የውል ሁኔታዎች ላይ ካለ፣ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 823 የተመለከቱት
ተከላዎችና የግንባታ ቁሶች ባለቤትነት የአሰሪው እንደሆነ ይቆጠራል፡፡

19.3. በዚህ አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ ተመስርቶ መሐንዲሱ ለተከላዎቹ እና የግንባታ ቁሶች ማናቸውንም
የመሃል /ጊዜያዊ የክፍያ ሰርተፍኬት ማፅደቁ በውሉ ሁኔታዎች መሠረት ያልቀረቡትን ተከላዎችን ወይም
የግንባታ ቁሶችን ያለመቀበል መብቱን አያግደውም፡፡
19.4. የሥራ ተቋራጩ በግንባታ ቦታው በተከላዎቹ እና የግንባታ ቁሶች ላይ ለሚደርስ ማንኛውም መጥፋት ወይም
ጉዳት እና ለማከማቻ እና ለአያያዝ ለሚወጣው ወጪ ኃላፊ ነው። እንደአስፈላጊነቱም በማናቸውም

55 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ምክንያት ሊደርስ ከሚችል ከማንኛውም ጥፋትና ጉዳት ተጋላጭነት ለመሸፈን ተጨማሪ ዋስትና መግባት
ይኖርበታል፡፡
19.5.የመሃል/ጊዜያዊ ክፍያ ሰነድ ለመሀንዲሱ በደረሰ በ 30 ቀናት ውስጥ ይፀድቃል ወይም በመሐንዲሱ አመለካከት
መሠረት ማመልከቻው ለሥራ ተቋራጩ መከፈል የሚገባው መጠን በውሉ መሠረት ይስተካከላል፡፡ በአንድ
ሥራ ዋጋ ላይ ልዩነት ቢኖር የመሐንዲሱ አቋም የበላይነት (ተፈጻሚነት) ይኖረዋል፡፡ ለሥራ ተቋራጩ
መከፈል የሚገባውን በተመለከተ መሐንዲሱ በ 30 ቀናት ውስጥ የመሃከል /ጊዜያዊ የክፍያ ሰርተፍኬት
በማውጣት አሰሪው እንዲከፍል ለሥራ ተቋራጩ ደግሞ እንዲያውቀው ማስተላለፍ አለበት፡፡ ለሥራ
ተቋራጩ ሊከፈለው የሚገባውን መጠንና ክፍያው ለየትኞቹ የግንባታ ሥራዎች እንደሆነም ማሳወቅ
አለበት፡፡
19.6. መሐንዲሱ በጊዜያዊ የክፍያ ሰርተፊኬት ከዚህ በፊት በሰጠው ሰርተፊኬት ላይ ማንኛውንም እርማት ወይም
ማሻሻያ ማድረግ ይችላል፡፡ እንደዚሁም መሐንዲሱ የግንባታ ሥራዎች ወይም ማንኛውም የግንባታ ሥራ
ክፍል በሚፈልገውና በተሟላ መልኩ እየተሰራ አይደለም ብሎ የክፍያ መጠኑን የማሻሻል ወይም
ማንኛውንም ጊዜያዊ የክፍያ ሰርተፍኬት መስጠትን የማቆየት ሥልጣን አለው፡፡
19.7. በልዩ የውል ሁኔታዎች በተለየ ሁኔታ ካልተገለጸ በስተቀር በአንድ ወር አንድ የጊዚያዊ ክፍያ ይፈፀማል፡፡

20. የመጨረሻ የሂሳብ ሰነድ (Final Statement of Accounts)

20.1. በልዩ የውል ሁኔታዎች ውስጥ ሌላ ስምምነት እስከሌለ ድረስ የሥራ ተቋራጩ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች
አንቀጽ 889 እንደተገለጸው የመጨረሻ የርክክብ ሰርተፍኬት ከተሰጠ 90 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በውሉ
መሠረት የተሰራውን የግንባታ ሥራ ዋጋ ዝርዝር እና የሥራ ተቋራጩ ይገባኛል የሚለውን ድምር በደጋፊ
ሰነዶች የሚያሳይ ረቂቅ (Draft) የመጨረሻ የሂሳብ ሰነድ መሐንዲሱ የመጨረሻ የሂሳብ ሰነድ ለማዘጋጀት
ይችል ዘንድ ለመሐንዲሱ ያቀርባል፡፡
20.2. ረቂቅ የመጨረሻ የሂሳብ ሰነዱን እና ሰነዱን ለማረጋገጥ የሚያስፈልጉ ተፈላጊ መረጃዎችን ባገኘ በ 60 ቀናት
ውስጥ መሐንዲሱ የሚከተሉትን ነገሮች የሚወስን የመጨረሻ የሂሳብ ሰነድ ያዘጋጃል፡፡
(ሀ) በመሀንዲሱ አስተያየት በውሉ መሠረት መከፈል የሚገባውን የመጨረሻ ድምር (መጠን)፤

(ለ) ቀደም ብሎ በአሰሪው በተከፈሉት ድምሮች እና አሰሪው በሚገባው ድምር ልዩነት ካለ፤
እንደየሁኔታው አሰሪው ለሥራ ተቋራጩ ወይም የሥራ ተቋራጩ ለአሰሪው መክፈል የሚገባቸው፤

20.3. መሐንዲሱ ለአሰሪው ወይም ሕጋዊ ወኪሉ እና ለሥራ ተቋራጩ በውሉ መሠረት ለሥራ ተቋራጩ መከፈል
የሚገባውን የመጨረሻ መጠን የሚያሳይ የመጨረሻ የሂሳብ ሰነድ ይሰጣል፡፡ አሰሪው ወይም ሕጋዊ ወኪሉ
እና የሥራ ተቋራጩ የመጨረሻ የሂሳብ ሰነዱን በውሉ መሠረት የተከናወነው የግንባታ ሥራ ሙሉ እና

56 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
የመጨረሻ ዋጋ መሆኑን በመቀበል ፈርመው የተፈረመውን ቅጂ ለመሐንዲሱ ይሰጣሉ፡፡ ነገር ግን
የመጨረሻ የሂሳብ ሰነዱ አለመግባባት ያለባቸውና በድርድር ወይም በመስማማት ለመፍታት የሚታሰቡ
ድምሮችን አያካትትም፡፡
20.4. በሥራ ተቋራጩ የተፈረመ የመጨረሻ የሂሳብ ሰነድ በስምምነት ከሚፈቱ ቀሪ ድምሮች በስተቀር በመጨረሻ
የሂሳብ ሰነድ ላይ የተጠቀሰው ድምር በውሉ መሠረት ለሥራ ተቋራጩ መከፈል የሚገባውን ሙሉና
የመጨረሻ መሆኑን የሚያረጋግጥ አሰሪውን ነፃ የሚያወጣ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህም አሰሪው ነፃ የሚሆነው
በመጨረሻ የሂሳብ ሰነድ መሠረት መከፈል የሚገባው ማንኛውም ክፍያ ለሥራ ተቋራጩ ሲፈፀምና
በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 58 መሠረት የውል ማስከበሪያ ዋስትናው ሲመለስለት ነው፡፡
20.5. የሥራ ተቋራጩ በረቂቅ የመጨረሻ የሂሳብ ሰነዱ ይገቡኛል የሚላቸውን ጥያቄዎች እስካላካተተ ድረስ ከውሉ
ጋር በተያያዘ ወይም በውሉ መሠረት ወይም ከግንባታ ሥራዎቹ ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ምንም ዓይነት
ነገሮች/ ጉዳዮች አሰሪው ተጠያቂ አይሆንም፡፡

21. ለንዑስ-ተቋራጭ በቀጥታ ክፍያ ስለመፈፀም

21.1. መሐንዲሱ በአጠቃላይ የውል ሁኔታ አንቀጽ 14 መሠረት ከፀደቀ ንዑስ የሥራ ተቋራጩ የስራ ተቋራጭ
ያለበትን የክፍያ (Financial) ግዴታ አለመወጣቱን የሚገልጽ ጥያቄ/አቤቱታ ሲደርሰው፣ መሐንዲሱ
ለሥራ ተቋራጩ ለንዑስ የሥራ ተቋራጩ እንዲከፍል ወይም ያልተከፈለበትን ምክንያት እንዲገልጽ
ማስታወቂያ ይሰጠዋል፡፡ የሥራ ተቋራጩ በተሰጠው ማስታወቂያ የጊዜ ገደብ ክፍያው ካልተከፈለ ወይም
ምክንያት ካልተሰጠ መሐንዲሱ የግንባታ ሥራው መከናወኑን በራሱ ካረጋገጠ በኋላ ክፍያውን በማፅደቅ ፤
አሰሪውም የሥራ ተቋራጩ ካለው ቀሪ ድምር ወስዶ ንዑስ የሥራ ተቋራጩ የይገባኛል ጥያቄ ያነሳበት
መጠን ይከፍላል፡፡የሥራ ተቋራጩ በዚህ መልክ ቀጥታ ክፍያ ለተፈፀመለት የግንባታ ሥራ ሙሉ ኃላፊነት
አለበት፡፡
21.2. የሥራ ተቋራጩ በንዑስ የሥራ ተቋራጩ ይገባኛል ያለውን ዕዳ በሙሉ ወይም በከፊል አልከፍልም ያለበትን
በቂ ምክንያት ከሰጠ፣ አሰሪው ለንዑስ ሥራ ተቋራጩ አለመግባባት የሌለበትን ዕዳ ብቻ ይከፍላል፡፡ የሥራ
ተቋራጩ ላለመክፈል በቂ ምክንያት ለሰጠበት ድምር አሰሪው ለንዑስ የሥራ ተቋራጩ ክፍያ
የሚፈጽመው ተዋዋይ ወገኖቹ በመግባባት ስምምነት ላይ ከደረሱ ወይም የፍርድ ቤት ውሳኔ ማስታወቂያ
ለመሐንዲሱ በአግባቡ ከደረሰው ብቻ ነው፡፡
21.3. ለንዑስ የሥራ ተቋራጮች በቀጥታ የሚከፈል ክፍያ መጠን ለሰጡት አገልግሎት በውል ዋጋዎች ከተገመተው
ዋጋ መብለጥ የለበትም፡፡ የውል ዋጋ የሚሰላው ወይም የሚገመገመው በሥራ ዝርዝር፣ በዋጋ ሠንጠረዥ፣
በጥቅል ድምር ዋጋ ትንተና(breakdown) መሠረት ነው፡፡

57 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
21.4. ለንዑስ የሥራ ተቋራጭ በቀጥታ የሚደረግ ክፍያ ሙሉ ለሙሉ በልዩ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 59.1
በተጠቀሰው የገንዘብ ዓይነት ነው፡፡
21.5. የዚህ አጠቃላይ የውል ሁኔታ አንቀጽ ነጥቦች በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 67 አግባብ መሠረት
ተግባራዊ በሚሆነው ህግ የብድር ምደባ ወይም የመያዣ ዋስትና ተጠቃሚ የሆኑ አበዳሪዎች መብት
በተመለከተ የሚፈለግ ቅድመ ሁኔታዎች መሠረት ነው፡፡

22. ለሶስተኛ ወገን ክፍያ ስለመፈፀም

22.1. ለሶስተኛ ወገን የሚታዘዙ ማናቸውም የክፍያ ትዕዛዞች የሚፈፀሙት በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 13
ኃላፊነቱ ለሌላ ማስተላለፍ (assignment) ከተሰጠ በኋላ ብቻ ነው፡፡ ማስተላለፉን በሚመለከት አሰሪው
ሊያውቀው ይገባል፡፡
22.2. ለሌላ የተላለፈ ኃላፊነት ተጠቃሚዎችን የማሳወቅ ኃላፊነት የሥራ ተቋራጩ ብቻ ነው፡፡
22.3. የሥራ ተቋራጩ የሆነ ንብረት ከህግ ጋር በተያያዘ ምክንያት በውሉ መሠረት የሚገባውን ክፍያዎች ላይ ተፅዕኖ
ሲያሳድር፣ አሰሪው የሥራ ተቋራጩ ለክፍያ መሰናክል የሆነው ስለመነሳቱ ማስታወቂያ ከደረሰው ጊዜ
አንስቶ ለሥራ ተቋራጩ ክፍያ መስጠት ለመጀመር 30 ቀናት ይኖሩታል፡፡

23. የተጨማሪ ክፍያ ጥያቄ (Claim)

23.1. የሥራ ተቋራጩ በውሉ መሠረት ተጨማሪ ክፍያ ሊያሰጡኝ የሚችሉ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል ብሎ ካመነ
የሥራ ተቋራጩ የሚከተሉትን ማድረግ አለበት፡፡
(ሀ) ተጨማሪ የክፍያ ጥያቄ ማቅረብ ካሰበ የሥራ ተቋራጩ ሁኔታው መከሰቱን ባወቀ በ 15 ቀናት ጊዜ
ውስጥ የክፍያ ጥያቄ የማቅረብ ሃሳብ እንዳለው የተጨማሪ ክፍያ ጥያቄውን ምክንያት በመግለጽ
ለመሐንዲሱ ማሳወቅ አለበት፡፡

(ለ) የተጨማሪ ክፍያ ጥያቄውን ሙሉ እና ዝርዝር ነጥቦች በተቻለ ፍጥነት ለመሐንዲሱ ማቅረብ
አለበት፡፡ መሐንዲሱ ካልተስማማ በስተቀር ማስታወቂያ ከሰጠበት በ 60 ቀናት ውስጥ ዝርዝር
ጥያቄውን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ መሐንዲሱ ከተጠቀሰው 60 ቀናት ቀነ ገደብ ሌላ ከተስማማ፤
ስምምነት የተደረገበት ቀነ ገደብ በማንኛውም ሁኔታ ዝርዝሩ ረቂቅ የመጨረሻ የሂሳብ ሰነዱ
የሚቀርብበት ቀን ከማለፉ በፊት መሰጠት ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በኋላ የሥራ ተቋራጩ መሐንዲሱ
የጥያቄውን ተቀባይነት በሚመረምርበት ጊዜ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ወዲያውኑ ማቅረብ አለበት፡፡

58 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
23.2. መሐንዲሱ የፈለገውን የሥራ ተቋራጩን የይገባኛል ጥያቄ ሙሉና ዝርዝር ሁኔታ ካገኘ የአጠቃላይ የውል
ሁኔታዎች አንቀጽ 44.34 እንደተጠበቀ ሆኖ ከአሰሪው እና እንደአግባቡ ከሥራ ተቋራጩ ጋር ከተነጋገረ
በኋላ የሥራ ተቋራጩ ተጨማሪ ክፍያ ይገባው እንደሆነና እንዳልሆነ ወስኖ ውሳኔውን ለተዋዋይ ወገኖች
ማሳወቅ ይገባዋል፡፡
23.3. መሐንዲሱ የአጠቃላይ የውል ሁነታዎች አንቀጽ አስፈላጊ ነጥቦችን የማያሟሉ የተጨማሪ ክፍያ ጥያቄዎችን
ውድቅ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ረ. ውል አፈፃፀም

24. የስራው ተፈፃሚነት ወሰን

24.1. በልዩ የውል ሁኔታዎች መሠረት፣ መከናወን የሚገባቸው የግንባታ ሥራዎች በተፈላጊ ነጥቦች መግለጫ አባሪ
ውስጥ በተገለፀው መሰረት ይሆናል፡፡
24.2. የሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራዎችን በልዩ የውል ሁኔታዎች በተጠቀሱ የግንባታ ቦታዎች እና ስፍራዎች
በሥራ ዝርዝሮችና ንድፎች ወይም ተዋዋይ ወገኖች በጽሑፍ በተስማሙት መሠረት መገንባትና መተከል
ይኖርባቸዋል፡፡

25. የግንባታ ስራዎችን መጀመር

25.1. አሰሪው የግንባታ ሥራዎች ትግበራ የሚጀምርበትን ቀን በልዩ የውል ሁኔታዎች ወይም በመሐንዲሱ በሚሰጡ
አስተዳደራዊ ትዕዛዞች መወሰን አለበት፡፡
25.2. የግንባታ ሥራዎች ትግበራ የሚጀምርበት ቀን ከውሉ አሸናፊነት ማስታወቂያ በኋላ በተዋዋይ ወገኖች መካከል
ሌላ ስምምነት ከሌለ በቀር ከ 120 ቀናት ማለፍ የለበትም፡፡

26. የግንባታ ስራዎች የሚተገበሩበት ጊዜ

26.1. የግንባታ ሥራዎች የሚተገበሩበት ጊዜ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 70.1 በተወሰነው የስራ
መጀመሪያ ቀን መሠረት ይጀምራል፡፡ጊዜውም በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 72 ሊሰጥ
የሚችለውን የጊዜ ማራዘሚያ በማይነካ መልኩ (እንደተጠበቀ ሆኖ) በልዩ የውል ሁኔታዎች ውስጥ
መቀመጥ ይኖርበታል፡፡

59 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
26.2. የሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራዎችን በመሐንዲሱ እንደተሻሻለው እና በፀደቀው የትግበራ ኘሮግራም
መሠረት ማከናወን እና ይጠናቀቃል ተብሎ በታሰበበት ቀን ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡
26.3. አንድ የሥራ ተቋራጭ ከአንድ በላይ ሎት (lot) አሸንፎ ከሆነ፣ለተለያዩ ሎቶች (lots) የብቻ የትግበራ ጊዜ
የውል አካሎች የተሰጠበት ሁኔታ ካለ፣ የተለያዩ የውል ክፍሎች (lot) የትግበራ ጊዜ ተደማሪ አይሆኑም፡፡

27. የታቀደን የማጠናቀቂያ ጊዜ ስለማራዘም

27.1. የሥራ ተቋራጩ በሚከተሉት ምክንያቶች የታሰበው የማጠናቀቂያ ጊዜ ቢዘገይ ወይም የሚዘገይ ከሆነ የጊዜ
ማራዘሚያ ሊጠይቅ ይችላል፡፡
(ሀ) በኢትዮጵያ ፊዴራላዊ ዲሞክራሲያው ሪፑብሊክ ውስጥ የተለየ የአየር ሁኔታ (ጠባይ) ሲከሰት፤

(ለ) ልምድ ባለው የሥራ ተቋራጭ ምክኒያታዊ ሁኔታ ሊገመት የማይችል ሰው ሰራሽ መሰናክል ወይም
ተፈጥሮአዊ ሁኔታ ሲከሰት፣

(ሐ) በታሰበው የማጠናቀቂያ ቀን ለማጠናቀቅ፣ የማያስችል የጊዜ መካሻ ሁኔታ (compensation event)
መከሰት ወይም ለማሻሻል የለውጥ ትዕዛዝ መስጠት፣

(መ)በሥራ ተቋራጩ ጥፋት ሊሰጡ ከሚችሉት ሌላ የማጠናቀቂያ ቀኑን ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ
አስተዳደራዊ ትዕዛዞች፣

(ሠ)የአሰሪው በውሉ መሠረት ያለበትን ግዴታዎች ለመወጣት አለመቻል፣

(ረ) የሥራ ተቋራጩ ጥፋት ባልሆነ ምክንያት የሚፈጠር ማንኛውም የግንባታ ሥራዎች ለጊዜው
መቋረጥ፣

(ሰ) አስገዳጅ ሁኔታዎች፣

(ሸ) በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ውስጥ የተመለከቱ ማንኛውም ሌላ የሥራ ተቋራጩ ጥፋት ያልሆኑ
ምክንያቶች፣

27.2. የሥራ ተቋራጩ መዘገየት ሊፈጠር እንደሚችል ከተረዳ በኋላ የታሰበውን የማጠናቀቂያ ቀን በሚገምተው
የማረዘሚያ ቀናት እንዲራዘምለት ጥያቄ የማቅረብ ፍላጎት እንዳለው በ 15 ቀናት ውስጥ ለመሐንዲሱ
ማሳወቅ አለበት፡፡ በመሐንዲሱና በሥራ ተቋራጩ መካከል በተለየ ሁኔታ ስምምነት እስከሌለ ድረስ
ማስታወቂያው ለመሐንዲሱ በደረሰ በ 21 ቀናት ውስጥ የሥራ ተቋራጩ ጥያቄዎቹ በጊዜው ሊመረመሩ
እንዲችሉ ሙሉና ዝርዝር ነጥቦችን ለመሐንዲሱ መስጠት አለበት፡፡

60 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
27.3. የሥራ ተቋራጩ ዝርዝር ጥያቄዎች በደረሱት በ 21 ቀናት ውስጥ መሐንዲሱ ከአሰሪው ጋር አግባብ ከሆነም
ከሥራ ተቋራጩ ጋር ከተመካከረ በኋላ በጽሑፍ ማስታወቂያ የታሰበውን የማጠናቀቂያ ጊዜ ማራዘሚያ
ተቀባይነት ካለው፤ ወደፊት ወይም ወደኋላ ተፈጻሚ የሚሆን ሊሰጥ ይችላል፣ ወይም ለሥራ ተቋራጩ
የጊዜ ማራዘሚያ እንደማይገባው ይገልጽለታል፡፡
27.4. የሥራ ተቋራጩ የመዘግየትን ማስታወቂያ ቀደም ብሎ ሳይዘገይ መስጠት ካልቻለ ወይም የመዘግየትን ጉዳይ
ለማየት በሚደረገው ጥረት ተባባሪ ካልሆነ መዘግየቱ አዲስ የታሰበውን የማጠናቀቂያ ቀን ለመገምገም ጊዜ
ሊወሰድ አይችልም፡፡

28. የጊዜ ማራዘሚያ ለመፍቀድ የሚያስችሉ የማካካሻ ሁኔታዎች (compensation events)

28.1. የሚከተሉት የጊዜ ማራዘሚያን ለመፍቀድ የሚያስችሉ የመካሻ ክስተቶች ናቸው፡፡


(ሀ) በአሰሪው በፀደቀው የግንባታ ፕሮግራም ላይ በተቀመጠው የግንባታ ቦታ መረከቢያ ቀን የግንባታ
ቦታውን አካል ለማስረከብ ካልቻለ፣

(ለ) አሰሪው የሌሎች የሥራ ተቋራጮችን ፕሮግራም የሥራ ተቋራጩ በውሉ ውስጥ የሚከናወነውን
የግንባታ ሥራ ላይ ተፅዕኖ በሚያሳድር መልኩ ሲቀየር፣

(ሐ)መሐንዲሱ የማዘግየት ትዕዛዝ ሲሰጥ ወይም የግንባታ ሥራውን በጊዜው ለማከናወን የሚያስፈልጉ
ንድፎችን፣ የሥራ ዝርዝሮችን፣ ወይም መመሪያዎች ሳይሰጥ ሲቀር፣

(መ)መሐንዲሱ የሥራ ተቋራጩን የተሰራ እና ተሞልቶ የተሸፈነ ሥራ እንደገና ተከፍቶ እንዲታይ ወይም
ተጨማሪ ፍተሻ በሥራዎች ላይ እንዲደረጉ ሲደረግና ምንም አይነት ጉድለት ሳያገኝ ሲቀር፣

(ሠ)መሐንዲሱ ያለምክንያት ንዑስ የስራ ተቋራጭ ውሉን ሳያፀድቅ ሲቀር፣

(ረ) መሐንዲሱ በአሰሪው ምክንያት ለመጡ ቀድመው ያልታዩ ሁኔታዎችን ለመፍታት ወይም ለደህንነት
እና ለሌሎች ምክንያቶች ተጨማሪ ሥራዎች ሲያስፈልግ ትዕዛዙ ሲሰጥ ፣

(ሰ) ሌሎች የሥራ ተቋራጮች ፤አገልግሎት ሰጪዎች ወይም የመንግሥት አካላት ወይም አሰሪው ውሉ
ውስጥ በተቀመጡበት ቀናትና ገደቦች መሠረት አለመሥራታቸውና ይህም መዘግየት ሲያስከትል፣

(ሸ) የቅድሚያ ክፍያ መዘግየት፣

(ቀ) የ መሐንዲሱ የጊዜያዊ የክፍያ ሰርተፊኬትን ያለ ምክንያት ማዘግየት፣

61 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
(ተ) ሌሎች በልዩ የውሉ ሁኔታዎች የተብራሩ ወይም በአሰሪው የተወሰኑ የመካሻ ክስተቶች እና አስገዳጅ
ሁኔታዎች፣

28.2. የጊዜ ካሳ ሁኔታው የግንባታ ሥራው ከታሰበው የማጠናቀቂያ ቀን እንዳይጠናቀቅ የሚከለክል ከሆነ የታሰበው
የማጠናቀቂያ ቀን ይራዘማል፡፡ መሐንዲሱ የታሰበው የማጠናቀቂያ ጊዜ መራዘም ይገባው ወይም አይገባው
እንደሆነና በምን ያህል ጊዜ መራዘም እንዳለበት መወሰን አለበት፡፡
28.3. የሥራ ተቋራጩ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ባለመስጠቱ ምክንያት የአሰሪውን ጥቅም በመጥፎ ሁኔታ የሚነካ
ከሆነ የሥራ ተቋራጩ የጊዜ ካሳ አይገባውም፡፡

29. ማፍጠን (ማጣደፍ) Accelaration

29.1. አሰሪው የሥራ ተቋራጩ ከታሰበው የማጠናቀቂያ ቀን በፊት ማጠናቀቅ ከፈለገ፣ መሐንዲሱ ሥራውን
ማጣደፍ የሚያስችል የዋጋ ሀሳብ (proposal) ከሥራ ተቋራጩ ሊቀርብለት ይገባል፡፡ የአሰሪው ይህን የዋጋ
ሀሳብ ከተቀበለው የታሰበው የማጠናቀቂያ ቀን በዚሁ መሠረት በማስተካከል በአሰሪው እና በሥራ
ተቋራጩ ይጸድቃል፡፡
29.2. የሥራ ተቋራጩ ያቀረበው የማፍጠኛ ዋጋ ሀሳብ በአሰሪው ተቀባይነት ካገኘ ከውሉ ዋጋው ውስጥ ይካተታል።
እንደማሻሻያም ይቆጠራል፡፡

30. የማኔጅሜንት ስብሰባዎች

30.1. መሐንዲሱ ወይም የሥራ ተቋራጩ ከሁለቱ አንዳቸው በውሉ ውስጥ የተከናወኑ የግንባታ ሥራዎችን
አስመልክቶ የአሰሪውን የእርካታ ደረጃ ለመወያየት፣ የቀሪ ሥራዎች ዕቅዶችን ለመገምገም፣ እና ቅሬታ
ያለባቸውን ነጥቦች ለመፍታት የሚያስችሉ እርምጃዎች ላይ ለመስማማት መደበኛ የማኔጅመንት ስብሰባ
ላይ እንዲገኝ ሊፈልግ ይችላል፡፡
የሥራ ተቋራጩ እንደነዚህ አይነት አስፈላጊ እርምጃዎችን ሊያደናቅፍ ወይም ስምምነቱን ሊያዘገይ
ወይም ሊነፍግ አይችልም፡፡ እንደነዚህ አይነት ስብሰባዎች በሁለቱም ማለትም በአሰሪውና በሥራ ተቋራጩ
በኩል ሕጋዊ ሥልጣን ያላቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሠራተኞች እና ሌሎች አስፈላጊ ተሳታፊዎች
መገኘት አለባቸው፡፡ለእንደዚህ አይነት ግምገማዎች ተዋዋይ ወገኖች በቋሚ አጀንዳ መስማማት
አለባቸው፡፡
30.2. መሐንዲሱ የማኔጅመንት ስብሰባ ነጥቦች መመዝገብና የመዘገበውን ግልባጭ ለተሳታፊዎች እና ለአሰሪው
መሰጠት ይኖርበታል፡፡ በሚወሰዱ እርምጃዎች ላይ የተዋዋይ ወገኖች ያለባቸውን ኃላፊነት መሐንዲሱ

62 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
በማኔጅመንት ስብሰባው ጊዜ ወይም ከስብሰባው በኋላ መወሰን ይገባዋል፡፡ ውሳኔውንም ለስብሰባው
ተሳታፊዎች በሙሉ በጽሑፍ ይገለጻል፡፡

31. የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ

31.1. የሥራ ተቋራጩ ወደፊት የግንባታ ሥራዎች ጥራትን ሊቀንሱ የሚችሉ፣ የውል ዋጋን የሚጨምሩ ወይም
የግንባታ ሥራዎችን ክንዋኔ ሊያዘገዩ የሚችሉ አጋጣሚዎችን መሐንዲሱ በቅድሚያ ማስጠንቀቅ
ይኖርበታል፡፡ መሐንዲሱ የሥራ ተቋራጩ ወደፊት ከሚፈጠረው ሁኔታ የሚጠበቅ ግምት ዋጋ ወይም
በውል ዋጋ ላይ የሚገጥሙ ሁኔታዎች እና የማጠናቀቂያ ጊዜ ግምትን ሊፈልግ ይችላል፡፡ የስራ ተቋረጩም
ግምቱን በተቻለ ተገቢ ጊዜ ውስጥ ማቅረብ አለበት፡፡
31.2. የሥራ ተቋራጩ ከመሐንዲሱ ጋር እንዴት እንደዚህ አይነት ክስተቶች ወይም ሁኔታዎች እንዳይከሰቱ ማድረግ
ወይም እንዲቀንሱ ማድረግ እንደሚቻል ሃሳብ ማዘጋጀት እና የመሐንዲሱን መመሪያ መተግበር ላይ
መተባበር ይኖርበታል፡፡

32. በትግበራ ወቅት የሚፈጠሩ መዘግየቶች

32.1. የሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራዎችን በውሉ ላይ በተጠቀሰው ጊዜ ማጠናቀቅ ካልቻለ አሰሪው ያለ መደበኛ
ማስታወቂያ እንዲሀም ሌሎች በውሉ ሥር ያሉ መብቶችን ሳይነካ ስራ ተቋራጩ ለዘገየበት የማጣሪያ
ኪሳራ (liquidated damage) ሥራው በእርግጥ በተጠናቀቀበት ቀንና መጀመሪያ በውሉ ይጠናቀቃል
ተብሎ በተባለበት ቀን ወይም (በአጠቃላይ የውሉ ሁኔታዎች አንቀጽ 72) በተራዘመው የማጠናቀቂያ ቀን
መካከል ለእያንዳንዱ ቀን በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 27 የተጠቀሰው መጠን ከፍተኛ መጠን
እስኪደርስ ድረስ ክፍያ የማግኘት መብት አለው፡፡ የግንባታ ሥራዎቹ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ
85 መሠረት በከፊል ርክክብ የተደረገባቸው ከሆነ፣ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 27 መሠረት
የማጣሪያ ኪሳራው ርክክብ የተደረገበት የግንባታ ሥራ ከአጠቃላይ ሥራው ጋር ባለው ክፍልፋይ መጠን
ሊቀነስ ይችላል፡፡
32.2. አሰሪው በአጠቃላይ የውሉ ሁኔታዎች አንቀጽ 27.1(ለ) መሠረት ከፍተኛ የማጣሪያ ኪሳራ ጣሪያ ከመድረሱ
በፊትም ሆነ በኋላ ለሥራ ተቋራጩ ማስታወቂያ በመስጠት የሚከተሉትን ሊያደርግ ይችላል፡፡
(ሀ) የሥራ ማስከበሪያ ዋስትና መውረስ እና/ወይም
(ለ) ውሉን ማቋረጥ
(ሐ) የጉዳት ካሳ መጠየቅ እና
(መ) ከሶስተኛ ወገን ጋር ቀሪውን የግንባታ ሥራ በሥራ ተቋራጩ ወጪ ለማጠናቀቅ ውል መግባት፡፡

63 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
33. የግንባታ ሥራዎች መዝገብ

33.1. የግንባታ ሥራ መዝገብ፣ በልዩ የውል ሁኔታዎች በተለየ ሁኔታ እስካልቀረበ ድረስ፣ በመሐንዲሱ መያዝ
ሲኖርበት ቢያንስ የሚከተሉት መረጃዎች በመሐንዲሱ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
(ሀ) የአየር ሁኔታዎች፣ በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት የተከሰተ የሥራ መቋረጥ፣ የሥራ ሰዓቶች
በግንባታ ቦታው የተቀጠሩ ሙያተኞች ቁጥርና አይነት፤ የቀረቡ የግንባታ ቁሶች፣ በጥቅም ላይ ያለ
መሣሪያና በሚገባ የማይሠሩ መሣሪያዎች፤ የተደረጉ ሙከራዎች፤ የተላኩ ናሙናዎች፣ ያልተጠበቁ
ሁኔታዎች እና እንደዚሁም ለሥራ ተቋራጩ የተሰጡ ትዕዛዞች፣

(ለ) የተቆጠረ (Quantitative) ወይም የማይቆጠር ወይም ጥራት ላይ የተመሠረተ (Qualitative) የተሰሩ
የግንባታ ሥራ ክፍሎች እና የቀረቡ እና ጥቅም ላይ የዋሉ፣ በግንባታ ቦታው ሊረጋገጡ የሚችሉት እና
ለሥራ ተቋራጩ የሚሰጠውን ክፍያ ለማስላት የሚጠቅሙ ዝርዝሮች መግለጫዎች

33.2. መግለጫዎቹ የግንባታ ሥራ መዝገቡ አካል ናቸው። ሆኖም አስፈላጊ ሲሆን በተለየ ሰነድ መመዝገብ
አለባቸው፡፡ መግለጫዎቹ የሚዘጋጁበት ቴክኒካል ደንብ ልዩ የውል ሁኔታዎች ላይ እንደተጠቀሰው መሆን
ይኖርበታል፡፡
33.3. የሥራ ተቋራጩ ወደፊት ሊለኩና ሊረጋገጡ የማይችሉ የግንባታ ሥራዎች፣ አገልግሎቶችና አቅርቦቶች
መግለጫዎች በልዩ የውል ሁኔታዎች መሠረት በተገቢው ጊዜ መስፈራቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ይህን
ማድረግ ካልተቻለ፤በራሱ ወጪ ተቃራኒ ማስረጃ እስካላቀረበ ድረስ የመሐንዲሱን ውሳኔዎች መቀበል
ይኖርበታል፡፡
33.4. በግንባታ ሥራ መዝገቡ ውስጥ እንደየግንባታው ሥራ የአፈጻጸም ደረጃ (progress) የሚገቡ ነጥቦች
በመሐንዲሱ መፈረምና በሥራ ተቋራጩ ወይም ወኪሉ ፊርማ መረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ የሥራ ተቋራጩ
የሚቃወም ከሆነ፣ ሃሳቡን ለመሐንዲሱ መግለጫው መመዝገብ ካለበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ 15 ቀናት
ውስጥ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ የሥራ ተቋራጩ በተባለው ጊዜ ካልፈረመ ወይም የመቃወሚያ ሃሳቡን
ማቅረብ ካልቻለ የሥራ ተቋራጩ በመዝገቡ ላይ በተቀመጡ ነጥቦች እንደተስማማ ይቆጠራል፡፡ የሥራ
ተቋራጩ በማንኛውም ጊዜ የግንባታ ሥራ መዝገቡን መፈተሸ ከሰነዱ ላይ ሳይገነጠል ለራሱ እንደ መረጃ
ያስፈልጉኛል የሚላቸውን ነጥቦች ቅጂዎች ማድረግ ወይም የመውሰድ ይችላል፡፡
33.5. የሥራ ተቋራጩ በተጠየቀ ጊዜ ለመሐንዲሱ የግንባታ ሥራ መዝገቡን በጥሩ ሥርዓት ለመያዝ
የሚያስፈልገውን መረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

64 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
34. የግንባታ ስራው እና ዕቃዎች ጥራትና የመነሻ ሀገር

34.1. በውሉ መሠረት የተገዙ ሁሉም እቃዎች መነሻ አገር የጨረታ ሰነዱ ውስጥ ከተቀመጡት ብቁ ከሆኑ አገሮች
መሆን አለበት፡፡
34.2. የግንባታ ሥራዎች፣ የተለያዩ የሥራዎቹ ክፍሎች እና ቁሶች የሥራ ዝርዝሮች፣ ንድፎች፣ ቅየሳዎች፣
ሞዴሎች፣ ናሙናዎችንና አቀማመጦች እና ሌሎች በልዩ የውል ሁኔታ ውስጥ አስፈላጊ ከሆኑ መስፈርቶች
ጋር የሚሄዱ መሆን ይገባቸዋል፡፡ በሥራ አፈፃፀም ጊዜ በሙሉ ለመለየት እንዲቻል እነዚህ ዝርዝር ነገሮች
በአሰሪው አካሉ ወይም በመሐንዲሱ እጅ መቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
34.3. ማንኛውም በልዩ የውል ሁኔታዎች ላይ የተጠቀሰ የቅድሚያ ቴክኒካል ርክክብ ከሥራ ተቋራጩ ለመሐንዲሱ
በሚላክ ጥያቄ መሠረት ይሆናል፡፡ ጥያቄው እንደ አስፈላጊነቱ ውሉን ፣ የውሉ መለያ (lot) ቁጥር እና
ርክክቡ የሚካሄድበት ቦታ የት እንደሆነ መጥቀስ ይኖርበታል፡፡ በጥያቄው ላይ የተጠቀሱ የግንባታ ሥራ
ክፍሎች (Components) እና ቁሶች በግንባታ ሥራው ከመካተታቸው በፊት ለዚህ አይነቱ ርክክብ
ሁኔታዎችን እንደሚያሟሉ በመሐንዲሱ የተረጋገጡ (Certified) መሆን ይገባቸዋል፡፡
34.4. በግንባታ ሥራዎች ወይም ክፍሎችን በማምረት ሥራ ላይ የሚካተቱ ዕቃዎች ወይም ነገሮች (Item) በዚህ
መንገድ ከቴክኒክ አንፃር ተቀባይነት ቢያገኙም፣ ቀጣይ ፍተሻዎች፣ ጉድለቶች ወይም ስህተቶች
ከተገኘባቸው ውድቅ ሊሆኑና ወዲያውኑ በሥራ ተቋራጩ መተካት አለባቸው፡፡ የሥራ ተቋራጩ ውድቅ
የተደረጉ የግንባታ ቁሶችንና ነገሮችን ለመጠገንና ለማስተካከል ዕድል ሊሰጠው ይችላል። ሆኖም ግን እነዚህ
ዕቃዎችና ነገሮች በግንባታ ሥራው ላይ ለማካተት ተቀባይነት የሚኖራቸው የመሐንዲሱን ጥያቄ
በሚያሟላ መልኩ ከተጠገኑና ጥሩ ከሆኑ በኋላ ብቻ ነው፡፡

35. ምርመራና ፍተሻ

35.1. የሥራ ተቋራጩ የግንባታ ክፍሎችና ዕቃዎች መሐንዲሱ በጊዜ አይቶ ለመረከብ እንዲችል ወደ ግንባታ ቦታው
በጊዜ መደረሳቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡ የሥራ ተቋራጩ በማረጋገጡ በኩል ሊፈጠር የሚችለውን ችግር
በሚገባ ተረድቷል(ያውቃል) ተብሎ ይገመታል። በመሆኑም ግዴታዎቹን በመፈጸም ረገድ ምንም አይነት
ለመዘግየት ምክኒያት እንዲያቀርብ አይፈቀድለትም፡፡
35.2. መሐንዲሱ በራሱ ወይም በወኪሉ የግንባታ ዕቃዎች፤ ክፍሎች እና አሰራሮች የተፈለገው ጥራትና ብዛት
እንደሚያሟሉ ለማረጋገጥ ሲል የግንባታ እቃዎችን፣ ክፍሎች እና አሠራሮችን (workmanship)
ለመቆጣጠር፣ ለመፈተሸ፣ ለመለካት፣ ለመሞከር እና በመዘጋጀት ላይ ያለ የመፍበርክ ወይም የማምረት
ሂደት፣ የማንኛውም የተዘጋጀን ነገር የማምረት ሂደት መቆጣጠር በዚህም መብት ይኖረዋል፡፡ ይህም

65 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
በማምረቻ ቦታ፤ በፋብሪካ ፤ በማዘጋጃ ቦታ፡ በግንባታ ቦታ(cite) ወይም በውል በተጠቀሰው ለዚህ የሚሆን
ቦታ ይካሄዳል፡፡
35.3. ለምርመራዎችና ሙከራዎች ዓላማ ሲባል የሥራ ተቋራጩ፤
(ሀ) ለመሐንዲሱ አስፈላጊ እርዳታ፣ የሙከራ ናሙናዎች ክፍሎች ማሽኖች፣ መሳሪያዎች መገልገያ
መሳሪያዎች ወይም ዕቃዎች እና የሰው ጉልበት በጊዜያዊነት ከክፍያ ነፃ ማቅረብ፤

(ለ) ከመሐንዲሱ ጋር በሙከራው ጊዜና ቦታ ላይ መስማማት፤

(ሐ) በማንኛውም ተቀባይነት (ምክኒያታዊነት) ባላቸው ጊዜያቶች ሙከራዎች በሚደረጉበት ቦታ


መሐንዲሱ መግባት እንዲችል መፍቀድ ይኖርበታል።

35.4. መሐንዲሱ ሙከራ እንዲደረግ ስምምነት በተደረገበት ቀን ካልተገኘ የሥራ ተቋራጩ በተለየ ሁኔታ
በመሐንዲሱ ካልታዘዘ በቀር ሙከራውን ማካሄድ ይችላል። ሙከራውም መሐንዲሱ በተገኘበት
እንደተደረገ ይቆጠራል፡፡ የሥራ ተቋራጩ ወዲያውኑ የተፈራረመና የተረጋገጠ የሙከራ ውጤት ቅጂውን
ለመሐንዲሱ ይልካል፣ መሐንዲሱም በሙከራው ላይ ያልተገኘ ከሆነ በውጤቱ ተገዢ ይሆናል፡፡
35.5. የግንባታ ዕቃዎቹና ክፍሎቹ በዚህ አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች የተጠቀሱ ሙከራዎች ካለፉ መሐንዲሱ ለሥራ
ተቋራጩ ማሳወቅ ወይም በተመሳሳይ የአሠራሩን ሰርተፍኬት ማጽደቅ ይኖርበታል፡፡
35.6. መሐንዲሱ እና የሥራ ተቋራጩ በሙከራ ውጤቱ ላይ ካልተስማሙ እያንዳንዳቸው ያልተስማሙበትን
መግለጫ ለሌላኛው በ 15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ መሐንዲሱ ወይም የሥራ ተቋራጩ
ሙከራው በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲደገም ወይም አንደኛው ተዋዋይ ወገን ከጠየቀ ሁለቱም ተስማምተው
በመረጡት ባለሙያ ሊካሄድ ይችላል፡፡ ሁሉም የሙከራ ውጤቶች ለመሐንዲሱ ይሰጣሉ፣ መሐንዲሱም
ምንም ሳይዘገይ ለሥራ ተቋራጩ ያሳውቃል፡፡ የእንደገና ሙከራው ውጤት የመጨረሻ ነው፡፡ የእንደገና
ሙከራው ወጪ አስተያየቱ ወይም አቋሙ ትክክል እንዳልሆነ የተረጋገጠበት ተዋዋይ ወገን ይሸፍናል፡፡
35.7. መሐንዲሱና ሌሎች በሱ ስልጣን የተሰጣቸው ሰዎች በምርመራና በፍተሻ በመሳተፋቸው ምክንያት ያወቁትን
የማምረትና የትግበራ (operation) ዘዴዎች መረጃ ግዴታቸውን በሚፈጽሙበት ጊዜ ማሳወቅ የሚችሉት
ማወቅ ለሚገባቸው ግለሰቦች ብቻ ነው፡፡

36. ውድቅ ማድረግ (Rejection)

36.1. የተጠቀሰውን ጥራት የሌላቸው የግንባታ ክፍሎችና ቁሶች(እቃዎች) ውድቅ ይደረጋሉ፡፡ ውድቅ በሆኑ የግንባታ
ክፍሎችና ቁሶች ላይ የተለየ ምልክት ሊደረግባቸው ይችላል፡፡ ይህ እነሱን ሊቀይራቸው ወይም የንግድ
ዋጋቸውን ሊያሰጣቸው በሚችል ደረጃ መሆን የለበትም፡፡ ውድቅ የተደረጉ የግንባታ ክፍሎች ወይም
ቁሶች(እቃዎች) ከግንባታ ቦታው መሐንዲሱ በሚያስቀምጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ መወገድ አለባቸው ይህ

66 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ባይሆን ግን መሐንዲሱ በሚያዘው መሰረት በሥራ ተቋራጩ ወጪ እና ሀላፊነት ይወገዳሉ፡፡ ውድቅ
የተደረጉ የግንባታ ክፍሎች ወይም ቁሶች(እቃዎች) የተካተቱበት ማንኛውም የግንባታ ሥራ ውድቅ
ይደረጋል፡፡
36.2. መሐንዲሱ የግንባታ ሥራዎች እየተከናወኑ ባለበት ጊዜና የግንባታ ሥራዎቹ ከመረከባቸው በፊት
የሚከተሉትን የማዘዝ ወይም የመወሰን ሥልጣን አለው፡፡
(ሀ) በመሐንዲሱ አመለካከት በውሉ መሠረት ያልሆኑ ማናቸውንም የግንባታ ክፍሎች ወይም
ቁሶች(እቃዎች) ከግንባታ ቦታው በሚሰጠው ትዕዛዝ ሊጠቀስ በሚችል የጊዜ ገደብ ውስጥ ማስወገድ

(ለ) ተገቢ የግንባታ ክፍሎችና ቁሶች(እቃዎች) መተካት

(ሐ) ከዚህ በፊት የተሞከረ ወይም ጊዜያዊ ክፍያ የተከፈለበት ቢሆንም፣ የሥራ ተቋራጩ ኃላፊ
የሆነባቸው የግንባታ ክፍሎች፤ ቁሶች(እቃዎች)ና አሠራሮችን ወይም ዲዛይኖች በመሐንዲሱ
አመለካከት በውሉ መሠረት አይደሉም ብሎ ካመነ ማስፈረስና በተገቢው መንገድ እንደገና
እንዲከናወኑ ወይም በቂ የሆነ ጥገና እንዲደረግላቸው

36.3. መሐንዲሱ ወዲያውኑ በተቻለ ፍጥነት አለ የሚባለውን ጉድለት በመዘርዘር ውሳኔውን ለሥራ ተቋራጩ
በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት፡፡
36.4. የሥራ ተቋራጩ በሙሉ ፍጥነትና በራሱ ወጪ የተጠቀሱትን ግድፈቶች ማስተካከል አለበት፡፡ የሥራ ተቋራጩ
ይህን ትዕዛዝ ካልፈጸመ አሰሪው ይህንኑ ተግባር እንዲያከናወኑ ሌሎች የመቅጠር መብት ይኖረዋልእና
ይህንን ሥራ ለመፈጸም የሚወጣ ወጪ፤ ተያያዥ ወጪም ጭምር በአሰሪው ከሥራ ተቋራጩ በጊዜው
ካለው ወይም ወደፊት ከሚኖረው ክፍያ ይቀነሳል፡፡
36.5. የዚህ አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ መኖር አሰሪው በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 19 እና 77
ያለውን የካሳ ጥያቄ የማንሳት መብት አይነካም፡፡

37. የግንባታ መሣሪያዎች እና ቁሶች(እቃዎች) ባለቤትነት

37.1. በሥራ ተቋራጩ የቀረቡ ሁሉም መሣሪያዎች፤ ጊዜያዊ የግንባታ ሥራዎች፣ ተቋማት(ተከላዎች) እና የግንባታ
ቁሶች የግንባታ ቦታው ሲመጡ ለግንባታ ሥራዎች ብቻ ይውላሉ ተብሎ ይገመታል። በመሆኑም ከአንድ
የግንባታ ቦታ ክፍል ወደ ሌላኛው ከማዘዋወር በስቀር የሥራ ተቋራጩ ያለመሐንዲሱ ስምምነት ወደ ሌላ
ቦታ ሊወስዳቸው(ሊያነሳቸው) አይችልም፡፡ እንደዚህ አይነቱ ስምምነት ማንኛውንም ሠራተኛ የቀን
ሰራተኞችን፣ መሣሪያዎችን፣ ጊዜያዊ የግንባታ ሥራዎችን፣ ተቋሞችን ወይም የግንባታ ቁሶችን ከግንባታ
ቦታው ወይም ወደየግንባታ ቦታው የሚያጓጉዙ መኪኖችን አይመከለትም፡፡

67 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
37.2. ልዩ የውል ሁኔታዎቹ በግንባታ ቦታው ያሉ በሥራ ተቋራጩ ወይም በማንኛውም የሥራ ተቋራጩ
የሚቆጣጠረው ሌላ ድርጅት ባለቤትነት ሥር ያሉ ሁሉም መሣሪያዎች ፤ጊዜያዊ የግንባታ ሥራዎች፣
ተቋሞችና የግንባታ ቁሶች የግንባታ ሥራዎች በሚከናወኑበት ጊዜ የሚከተሉት ሁኔታዎች ሊያካትት
ይቻላል፤
(ሀ) በአሰሪው ቁጥጥር ሥር መሆናቸውን ወይም
(ለ) ከተቋራጩ ዕዳዎች ጋር ማያያዝ መቻሉን
(ሐ) የቅድሚያ ፍላጎትወይም ደህንነት በተመለከተ ከሌላ ማንኛውም ሁኔታ ጋር ማያያዝ

37.3. በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 21 መሠረት ውሉ በሥራ ተቋራጩ ጥፋት በሚቋረጥበት ጊዜ አሰሪው
በግንባታ ቦታው ያሉ መሣሪያዎች፣ ጊዜያዊ ሥራዎች፣ ተቋሞች(ተከላዎች)ና የግንባታ ቁሶችን የግንባታ
ሥራውን ለማጠናቀቅ የመጠቀም መብት ይሰጠዋል፡፡
37.4. የሥራ ተቋራጩ ወደ ግንባታ የመጡትን መሳሪያዎችን፣ ጊዜያዊ የግንባታ ሥራዎችን፣ ተቋሞችን እና የግንባታ
ቁሶችን ለማከራየት የተደረገ ማንኛውም የኪራይ ስምምነት በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 21
መሠረት የውሉ መቋረጥ ተፈጻሚ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ሰባት ቀናት ጊዜ ውስጥ በግዥ ፈጻሚ
አካሉ የጽሑፍ ጥያቄ መሠረት የሥራ ተቋራጩ በተከራየበት ሁኔታ መሣሪያዎችን፤ ጊዜያዊ ግንባታዎችን፣
ተቋሞችን እና የግንባታ ቁሶችን ከባለቤቱ እንዲከራይ በሚያስችል ሁኔታ መካተት አለበት፡፡ የአሰሪው
ሌሎች የሥራ ተቋራጮችን በመቅጠር በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 21.5 መሠረት ሥራዎችን
እንዲጠናቀቁ የማድረግ መብት ሲቀር አሰሪው አስፈላጊ የሆኑ ክፍያዎችን ለመክፈል ስምምነት መግባት
ይኖርበታል፡፡
37.5. የግንባታ ሥራዎች ከመጠናቀቃቸው በፊት ውል ሲቋረጥ የሥራ ተቋራጩ ለአሰሪው ማንኛውንም
ተቋም(ተከላ)፣ ጊዜያዊ የግንባታ ሥራዎች፣ መሣሪያዎች ወይም የግንባታ ቁሶች በአሰሪው ቁጥጥር ስር
የሆኑትን ወይም በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 82.2(ለ) መሠረት ማስረከብ ይኖርበታል፡፡ ይህን
ማድረግ ካልቻለ የአሰሪው እነዚህ ተቋሞች፣ ጊዜያዊ የግንባታ ሥራዎች፣ መሣሪያዎችና ቁሶች በይዞታው
ሥር ለማድረግ አስፈላጊ ነው ብሎ ያመነበትን ሁሉ ያደርጋል ፡፡ ይህንን ለማድረግ ያወጣውን ወጪም
ከሥራ ተቋራጩ እንዲሸፍን ያደረጋል፡፡

68 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ሰ. ርክክብ እና የጉድለቶች ተጠያቂነት

38. አጠቃላይ መርሆዎች

38.1. ለጊዜያዊ ወይም የመጨረሻ ርክክብ የሚደረግ የግንባታ ሥራዎች ምርመራ በመሃንዲሱ የሥራ ተቋራጩ
በተገኘበት መካሄድ ይኖርበታል፡፡ የሥራ ተቋራጩ የምርመራ ሥራው ከሚካሄድበት ከ 30 ቀናት በፊት
እስከተጠራ ድረስ የሥራ ተቋራጩ አለመገኘት ለምርመራ ሥራው እንቅፋት መሆን የለበትም፡፡
38.2. የግንባታ ሥራዎችን ሁኔታ ለማረጋገጥ ወይም ለጊዜያዊ ወይም የመጨረሻ ርክክብ በተወሰነ ጊዜ ለመረካከብ
የማያስችሉ የተለዩ ሁኔታዎች ከተፈጠሩ፣ ይህንን የተለየ የማያስችል ሁኔታ የሚያረጋግጥ መግለጫ
መሐንዲሱ እንደ አስፈላጊነቱ ከሥራ ተቋራጩ ጋር በመመካከር ያዘጋጃል፡፡ ይህ የማያስችል ሁኔታ ከቀረበ
በ 30 ቀናት ውስጥ ግምገማውን ማካሄድና ርክክብ የመፈፀም ወይም ውድቅ የማድረግ መግለጫ
በመሐንዲሱ መዘጋጀት አለበት፡፡ የሥራ ተቋራጩ እነዚህ ሁኔታዎችን ከግዴታው በመሸሽ የግንባታ
ሥራዎችን ለርክክብ በሚያመች ጊዜ ላለመጨረስ ሊጠቀምባቸው አይችልም፡፡

39. የማጠናቀቂያ ሙከራዎች

39.1. አስቀድመው የተቀመጡ ግምገማዎች እና ሙከራዎች በሥራ ተቋራጩ ወጪ ሳይካሄዱ የግንባታ ሥራዎች
ርክክብ ማድረግ አይቻልም፡፡የሥራ ተቋራጩ ግምገማዎቹና ሙከራዎቹ የሚካሄድበትን ቀን ለመሐንዲሱ
ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
39.2. የውል ቃላቶችና ሁኔታዎች የማያሟሉ ወይም እንደዚህ አይነት ቃላትና ሁኔታዎች ከሌሉ ደግሞ የኢትዮጵያ
ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የንግድ አሰራር መሠረት ያልተከናወኑ የግንባታ ሥራዎች አስፈላጊ
ከሆነ መሐንዲሱን በሚያሳምን መንገድ በሥራ ተቋራጩ ሊፈርሱ እና እንደገና ሊገነቡ ወይም ሊጠገኑ
ወይም በመሐንዲሱ ትዕዛዝ ማስታወቂያ ከተሰጠ በኋላ በሥራ ተቋራጩ ወጪ እንዲፈርሱ እና እንደገና
እንዲገነቡ ይደረጋሉ፡፡ መሐንዲሱ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 20 መሠረት ለጊዜው ሥራ
በተቋረጠበት ጊዜ ወይም ተቀባይነት የሌለው ቁስ ጥቅም ላይ የዋለበት ወይም ግንባታ የተከናወነበት ሁኔታ
ካለ በተመሳሳይ የግንባታ ሥራ ሁኔታዎች መሠረት መሐንዲሱ በሥራ ተቋራጩ ማፍረስና እንደገና
መገንባትን ወይም መሐንዲሱ የሚፈልጋቸው ሁኔታዎች እስኪሟሉ መጠገን ሊጠይቅ ይችላል፡፡

40. ከፊል ርክክብ

40.1. አሰሪው የውሉን አካል የሆኑትን የተለያዩ ተቋማትን፣ የተቋማት ክፍሎችን ወይም የግንባታ ሥራዎችን ክፍል
በተጠናቀቁበት ጊዜ ሊጠቀምባቸው ይችላል፡፡ ማንኛውም ተቋም ወይም የተቋም ክፍል ወይም የግንባታ

69 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ሥራዎች ክፍል መውሰድ ከፊል ጊዜያዊ ርክክብ ከተደረገ በኋላ መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን አስቸኳይ
ሁኔታዎች በሚኖሩበት ጊዜ የግንባታ ሥራዎች ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፡፡ ይህ የሚሆነው የቀሪ
ሥራዎች ቆጠራ በመሐንዲሱ ከተዘጋጀና በቅድሚያ መሃንዲሱ እና ሥራ ተቋራጩ ከተስማሙ ነው፡፡
አሰሪውየተቋሙን ከፊሉን ወይም የግንባታ ሥራዎችን በከፊል በይዞታው ካደረገ በኋላ የሥራ ተቋራጩ
ትክክለኛ ባልሆነ ግንባታ ወይም የግንባታ አፈጻጸም ከሚፈጠረው በስተቀር የሚመጡ ጉዳቶችን
ማስተካከል አይጠበቅበትም፡፡
40.2. ተቋሙ፣ የተቋሙ ክፍል ወይም የግንባታ ሥራዎቹ ክፍል የተጠናቀቁና በውሉ ለተጠቀሰው አገልግሎት ምቹ
ከሆነ መሐንዲሱ በሥራ ተቋራጩ ጥያቄ መሠረት እና የግንባታ ሥራው ሁኔታ የሚፈቅድ ከሆነ ከፊል
ጊዜያዊ ርክክብ ማካሄድ ይችላል፡፡
40.3. በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ንዑስ አንቀጽ 85.1 እና 85.2 የተጠቀሰው ከፊል ጊዜያዊ ርክክብ በሚደረግበት
ጊዜ በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 87 የተመለከተው የጉድለቶች ተጠያቂነት ጊዜ በልዩ የውል
ሁኔታዎች በተለየ ሁኔታ እስካልተጠቀሰ ድረስ፣ ከፊል ጊዜያዊ ርክክብ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ይቆጠራል፡፡

41. ጊዜያዊ ርክክብ

41.1. የግንባታ ሥራዎቹ በበቂ ሁኔታ የተጠናቀቁ ጊዜ ፍተሻን ሲያልፉ፣ የጊዜያዊ ርክክብ ሰርተፊኬት ሲሰጥ ወይም
እንደተሰጠ ሲቆጠር በአሰሪው ይወሰዳሉ፡፡
41.2. የሥራ ተቋራጩ ለመሐንዲሱ በማሳወቅ በሥራ ተቋራጩ እምነት የግንባታ ሥራዎች ይጠናቀቃሉ እንዲሁም
ለጊዜያዊ ርክክብ ዝግጁ ይሆናሉ ብሎ ካሰበበት ከ 15 ቀናት በፊት ሳይቀድም ለጊዜያዊ የርክክብ
ሰርተፊኬት ማመልከት ይችላል፡፡ መሐንዲሱ የሥራ ተቁራጩ ማመልከቻ በደረሰው በ 3 ዐ ቀናት ውስጥ፣
(ሀ) ለሥራ ተቋራጩ ጊዜያዊ የርክክብ ሰርተፊኬት ለአሰሪው ኮፒ በማድረግ ይሰጣል፡፡ በራሱ እምነት
እንደ አግባቡ ያሉትን ቅሬታዎች በውሉ መሠረት የግንባታ ሥራዎች የተጠናቀቁበትን ቀንና ለጊዜያዊ
ርክክብ ዝግጁ የሆኑበትን ቀን ያስቀምጣል፡፡
(ለ) ውድቅ ያደረገበትን ምክንያቶች መስጠት እና በሱ አስተሳሰብ ሰርተፊኬቱ እንዲሰጡ ከሥራ
ተቋራጩ የሚጠበቀውን በመግለጽ ማመልከቻውን ውድቅ ያደርገዋል፡፡

41.3. መሐንዲሱ በ 3 ዐ ቀናት ውስጥ የጊዜያዊ ርክክብ ሰርተፊኬት ካልሰጠ ወይም የሥራ ተቋራጩን ማመልከቻ
ውድቅ ማድረግ ካልቻለ በቀነ ገደቡ የመጨረሻ ቀን ሰርተፊኬቱን እንደሰጠ ይቆጠራል፡፡ ጊዜያዊ የርክክብ
ሰርተፊኬት የግንባታ ሥራዎች በተሟላ ተጠናቀዋል ተብሎ የመቀበል ግምት አያስወስድም፡፡ የግንባታ
ሥራዎቹ በውሉ በክፍሎች ከተከፋፈሉ፣ የሥራ ተቋራጩ ለእያንዳንዱ ክፍል ለየብቻ ሰርተፊኬቶች
ለማግኘት የማመልከት መብት አለው፡፡

70 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
41.4. የግንባታ ሥራዎቹ ጊዜያዊ ርክክብ እንደተካሄደ የሥራ ተቋራጩ ለውል አፈጻጸሙ የማያስፈልጉ ጊዜያዊ
መዋቅሮችን እንደዚሁ የግንባታ ቁሶችን ማፍረስና ማስወገድ ይኖርበታል፡፡ እንደዚሁም ማናቸውንም
የወዳደቁ ነገሮች ወይም መሰናክሎች ማስወገድ እና በውሉ መሠረት በግንባታ ቦታ ሁኔታ ላይ የታየውን
ለውጥ ማስተካከል ይኖርበታል፡፡
41.5. ከጊዜያዊ ርክክብ በኋላ ወዲያውኑ አሰሪው ሁሉንም የግንባታ ሥራዎች እንደተጠናቀቁ ጥቅም ላይ ሊያውል
ይችላል፡፡

42. የጉድለቶች ተጠያቂነት

42.1. የሥራ ተቋራጩ በግንባታ ሥራዎች በየትኛውም ክፍል የሚታዩ በጉድለቶች ተጠያቂነት ጊዜ (defect
liability period) የሚታዩ ወይም ለሚከሰቱ ጉድለቶችና ጉዳቶች የማስተካከል ኃላፊነተ አለበት፡፡
ጉድለቶቹ ወይም ጉዳቶቹ በሚከተሉት ምክንያቶች ሊነሱ ይችላሉ፡፡
(ሀ) ግድፈት ያለው ተቋም(ተከላ) ወይም የግንባታ ቁስ በመጠቀም ወይም ስህተቱ በሥራ ተቋራጩ
የአሰራር ዘዴ ወይም ዲዛይን የተፈጠረ ሲሆን እና/ወይም
(ለ) በጉድለት ተጠያቂነት ጊዜ በሥራ ተቋራጩ የተከናወነ ወይም የተተወ ተግባር

42.2. የሥራ ተቋራጩ በተቻለ ፍጥነት ጉድለቶችና ጉዳቶችን በራሱ ወጪ ማስተካከል አለበት፡፡ የሁሉም የታደሱ
ወይም የተተኩ ሥራዎች የጉድለት ተጠያቂነት ጊዜ የመሐንዲሱን ጥያቄ ባሟላ መልኩ ከታደሱበት ወይም
ከተተኩበት ቀን ይጀምራል፡፡ ውሉ ከፊል ርክክብን የሚፈቅድ ከሆነ የጉድለት ተጠያቂነት ጊዜው
የሚራዘመው መተካት ወይም እድሳት በተደረገባቸው የግንባታ ሥራዎች ክፍሎች ብቻ ነው፡፡
42.3. በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 87.1 በተጠቀሰው ጊዜ እንደዚህ ዓይነት ጉድለት ከታየ ወይም ጉዳት
ከደረሰ አሰሪው ወይም መሐንዲሱ ለሥራ ተቋራጩ ማሳወቅ አለባቸው፡፡ የሥራ ተቋራጩ ጉድለቱን
ወይም ጉዳቱን በማስታወቂያው ላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማስተካከል ካልቻለ የአሰሪው
የሚከተሉትን ሊያደርግ ይችላል፡፡
(ሀ) የግንባታ ሥራውን ራሱ ማከናወን ወይም ሥራው እንዲከናወን ሌላ ሰው በሥራ ተቋራጩ ኃላፊነት
እና ወጪ መቅጠር፣ በዚህ ጊዜ የአሰሪው ያወጣው ወጪ ለሥራ ተቋራጩ ከሚከፈል ገንዘብ ወይም
ዋስትና መቀነስ ወይም ከሁለቱም መቀነስ ወይም/እና
(ለ) ውሉን ማቋረጥ

42.4. ጉድለቱ ወይም ጉዳቱ አሰሪው ከግንባታ ሥራዎቹ በሙሉ ወይም በከፊል የሚያገኘውን ጥቅም በከፍተኛ
ሁኔታ እንዳያገኝ የሚያደርገው ከሆነ፣ የአሰሪው ሌሎች ማካካሻዎች ላይ ያለው መብት ሳይነካ፣ ለዚህ

71 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
የግንባታ ሥራ ክፍል የከፈለውን ክፍያ የተባለውን ክፍል ለመለየት እና የግንባታ ቦታውን ማፅጃ ወጪ ጋር
የማስመለስ መብት አለው፡፡
42.5. ድንገተኛ አስቸኳይ ሁኔታ በሚያጋጥም ጊዜ የሥራ ተቋራጩን ወዲያውኑ ማግኘት ሳይቻል ወይም ተገኝቶም
የሚያስፈልጉ እርምጃዎችን መውሰድ ካልቻለ፣ አሰሪው ወይም መሐንዲሱ የግንባታ ሥራውን በሥራ
ተቋራጩ ወጪ እንዲከናወን ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ አሰሪው ወይም መሃንዲሱ በተቻለ ፍጥነት ለሥራ
ተቋራጩ የተወሰደውን እርምጃ ማሳወቅ አለባቸው፡፡
42.6. ልዩ የውል ሁኔታዎች በተለመደ ማለቅና ማርጀት ምክንያት የሚያስፈልጉ ጥገናዎችን በሥራ ተቋራጩ
መከናወን እንዳለባቸው የሚገልጽ ከሆነ እንደዚህ ዓይነቱ ሥራ ከጊዜያዊ ድምር (Provisonal sum)
ይከፈላል፡፡ ጥገና ወይም መተካት የሚፈልግ ስህተት ወይም ጉድለት እስካልተገኘ ድረስ በአጠቃላይ የውል
ሁኔታዎች አንቀጽ 44 ከተመለከቱ ሁኔታዎች ወይም ትክክለኛ ካልሆነ አጠቃቀም የሚመጣ የጥራት
መቀነስ ወይም ማርጀት ከዚህ ግዴታ ውጪ መሆን አለበት፡፡ ፡፡
42.7. የጉድለት ተጠያቂነት ጊዜ በልዩ የውል ሁኔታዎች ውስጥ መጠቀስ አለበት፡፡ የጉድለት ተጠያቂነት ጊዜው
ካልተቀመጠ 365 ቀናት መሆን አለበት፡፡ የጉድለቶች ተጠያቂነት ጊዜ ከጊዜያዊ ርክክብ ቀን መጀመር
ይኖርበታል፡፡
42.8. የጊዜያዊ ርክክብ ከተደረገ በኋላ እንዲሁም በዚህ የአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ ያለው የጉድለቶች
ተጠያቂነት ጊዜ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ የሥራ ተቋራጩ ከራሱ ጋር ባልተያያዙ ምክንያቶች
ለሚመጡ የግንባታ ሥራዎች ላይ ተፅዕኖ ለሚያደርጉ የአደጋ ተጋላጭነቶች ተጠያቂ አይደለም፡፡ ነገር ግን
የሥራ ተቋራጩ ጊዜያዊ ርክክብ ካደረገበት ቀን ጀምሮ ለግንባታው አስተማማኝነት በኢትዮጵያ ሕግ
በተቀመጠው መሠረት ተጠያቂ ነው፡፡

43. የመጨረሻ ርክክብ

43.1. የጉድለት ተጠያቂነት ጊዜው በሚያበቃበት ቀን፣ ወይም ከአንድ በላይ ጊዜ ካለ የመጨረሻው ጊዜ ሲያበቃ እና
ሁሉም ጉድለቶች ወይም ጉዳቶች ሲስተካከሉ፣ መሐንዲሱ የሥራ ተቋራጩ በውሉ ውስጥ ያሉ
ግዴታዎችን ለመሐንዲሱ ተቀባይነት ባለው መንገድ ያጠናቀቀበትን ቀን በመጥቀስ የመጨረሻ የርክክብ
ሰርተፊኬት ለሥራ ተቋራጩ ይሰጣል፣ ለአሰሪውም ኮፒ ያደረጋል፡፡ የመጨረሻ ርክክብ ሰርተፊኬት ከላይ
የተጠቀሰው ጊዜ በተጠናቀቀ በ 3 ዐ ቀናት ውስጥ ወይም በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 87 የታዘዙ
ማናቸውም የግንባታ ሥራዎች መሐንዲሱ በሚፈልገው መንገድ እንደተጠናቀቁ ወዲያውኑ መሰጠት
ይኖርበታል፡፡
43.2. የመጨረሻ የርክክብ ሰርተፊኬቱ በመሐንዲሱ ተፈርሞ ወደ አሰሪው ካልደረሰ እና ቅጂው ለሥራ ተቋራጩ
ካልደረሰ በቀር የግንባታ ሥራዎቹ እንዳለቁ መወሰድ የለበትም፡፡

72 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
43.3. የመጨረሻ የርክክብ ሰርተፊኬቱ እንዳለ ሆኖ፣ የሥራ ተቋራጩ እና አሰሪው ከመጨረሻ የርክክብ ሰርተፊኬቱ
በፊት በውሉ ውስጥ ያለባቸውን ግዴታ የመፈጸም ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ይህ የሚሆነው የመጨረሻ ርክክብ
ሰርተፊኬቱ በሚሰጥበት ጊዜ ሳይፈጸሙ የቀሩ ግዴታዎች ላይ ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ግዴታዎች ባህሪይ እና
መጠን በውሉ ሁኔታዎች መሠረት ይወሰናል፡፡

73 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ልዩ የውል ሁኔታዎች(ልውሁ)
የሚከተሉት ልዩ የውል ሁኔታዎች አጠቃላይ የውል ሁኔታዎችን የሚያሟሉ ናቸው፡፡ በማንኛውም ጊዜ በልዩ የውል
ሁኔታዎችና በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች መካከል ያለመጣጣም በሚኖርበት ጊዜ በዚሁ ልዩ የውል ሁኔታዎች ውስጥ
የተጠቀሱት ድንጋጌዎች በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ውስጥ ከተጠቀሱት የበላይነት ይየኖራቸዋል፡፡

አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች


ልዩ የውል ሁኔታዎች
(አ.ው.ሁ) አንቀጽ መለያ

ሀ. አጠቃላይ ሁኔታዎች

አ.ው.ሁ. (1.2) (ሰ) ሥራ ተቋራጩ፡- ኤፍ ኢ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ

አ.ው.ሁ. (1.2) (ፈ) አሰሪ ፡-ኢትዮ ቴሌኮም

አ.ው.ሁ. (1.2) (ረረ) የግንባታ ስራዎች ፡-በጅማ ከተማ የ 2B+G+8 ቅርንጫፍ


ፅህፈት ቤት ግንባታ

ለ. ውል

አ.ው.ሁ. 7.1 (ሐ) የሚከተሉት ሰነዶች የልዩ ውሉ አካል ናቸው፡፡

ሀ. የተሻሻለ የቴክኒክ እና የዋጋ መወዳደሪያ ሀሳብና የግንባታ


ስራ ዝርዝር (Bill of Quantities)
ለ. የነጠላ ዋጋ እና የ ለጥቅል ዋጋ ውሎች: የጥቅል ዋጋው
ዝርዝር ((የስሌት ስህተቶች ከታረሙ በኋላ)
ሐ. በአሰሪው በየጊዜው የሚወጡ ትእዛዞች
መ. የስራ መርሃ ግብር
ሰ. ቁልፍ ሰራተኞች ዝርዝር
አ.ው.ሁ. 9.1
የውሉ ቋንቋ፡- አማርኛ

አ.ው.ሁ. 10.2 የአሰሪው አድራሻ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

አሰሪው ኢትዮ ቴሌኮም

74 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ጉዳዩ የሚመለከተው ሰው
ስም
በሮ ቁጥር 201

ፖ. ሳ. ቁ. 1047

የመንገድ ስም ቸርችል መንገድ

ከተማ አዲስ አበባ

ፖ. ሳ. ኮድ 1047

አገር ኢትዮጵያ

ስልክ ቁጥር +251 (0) 115-505678

ፋስክ ቁጥር +251 (0) 115-51577

ኤ.ሜይል አድራሻ

የስራ ተቋራጩ አድራሻ እንደሚከተለው ይሆናል

ስራ ተቋራጭ ኤፍ ኢ ኮንስትራክሽን
ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ
ጉዳዩ የሚመለከተው ሰው አቶ ፍጹም ታዬ
ስም
በሮ ቁጥር

ፓ.ሳ.ቁ 100671, አ.አ

ከተማ አዲስ አበባ

አገር አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ስልክ ቁጥር +251-116290318/25

ፋስክ ቁጥር

ኤ.ሜይል አድራሻ feplc1@yahoo.com,


feplc@yahoo.com
አ.ው.ሁ. 11 መሪ አባል /በሀላፊነት ላይ ያለ
አባል
አ.ው.ሁ 12.1 የአሰሪው መሀንዲስ አድራሻ እንደሚከተለው ነው

መሀንዲስ አኪዩት ኢንጂነሪነግ


ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ

75 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ፓ.ሣ. ቁ 5898

የመንገድ ስም ከሩዋንዳ ኤምባሲ ወደ ቦሌ


ሚካኤል አደባባይ፣ ሩዋንዳ
ጎዳና፣ ኤም ኤም ህንፃ
ከተማ አዲስ አበባ

ፓ.ሣ. ኮድ -------

አገር ኢትዮጵያ

የስልክ ቁጥር +251-118-22-93-93/+251-


96620/50/25/26/27/28
የፋስክ ቁጥር --------+251-116-392120

ኢሜይል አድራሻ acutengineering@gmail.com

አ.ው.ሁ 15.6 በጊዜያዊ ርክክብ ወቅት ከሥራ ተቋራጩ ጥፋት ውጪ በለውጥ


ትዕዛዝ ወይም በሌሎች ምክንያቶች በግንባታ ሥራዎች ዋጋ ላይ
የሚመጣ መጨመር ወይም መቀነስ ከመጀመሪያው የውል ዋጋ
ወይም በማሻሻያው እንደተሻሻለው እስከ 5 % የሚሆነውን ስራ
ትእዛዝ መወሰን የመሀንዲሱ ስልጣን ነው ፡፡ መሐንዲሱ በአጠቃላይ
የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 15.5 መተግበር ምክንያት በውል ዋጋው ላይ
የሚመጣውን ከ 5 % የበለጠ መቀነስ ወይም መጨመር ከሆነ
ከአሰሪው እና ከሥራ ተቋራጩ ጋር ከተመካከረ በኋላ በአሰሪው
እንዲወሰን ማድረግ አለበት፡፡
አ.ው.ሁ 15.8 በለውጥ ትዕዛዝ ምክንያት አጠቃላይ የግንባታ ሥራዎች ዋጋ
በመጀመሪያው አጠቃላይ የውል ዋጋ 25% መብለጥ
አይኖርበትም፡፡
አ.ው.ሁ በጨረታ ሰነድ የማስገቢያ የመጨረሻ ቀን በፊት የግንባታ ስራው የማስረከቢያ ቀን ወይም የውሉን ዋጋ ላይ ተፅእኖ
16.1 አ.ዉ.ሁ.25. የሚያደርግ እና በግንባታ ቦታው ላይ ተፈፃሚነት ያለው ማንኛውም ሕግ፣ ደንብ፣ ትዕዛዝ ወይም የሕግ አቅም ያለው ውስጠ
2 ደንብ ታትሞ ቢወጣ፣ ቢሻር፣ በደረሰው ቀውስ ምክንያት የማስረከቢያውን ቀን ተቋራጩ በለውጡ ምክንያት በደረሰበት
ተፅእኖ መጠን ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ይስተካከላል ፡፡ የውሉም ዋጋ በተመሳሳይ ሁኔታ ይጨመራል/ ይቀነሳል ፡
መሐንዲሱ ውል ከተቋረጠ በኋላ በተቻለ ፍጥነት በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ የስራውን ዋጋ እና ለሥራ ተቋራጩ
መከፈል የሚገባውን ክፍያ ተመን ማዘጋጀትና ማጽደቅ ወይም ማፀደቅ ይኖርበታል፡፡

76 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
አ.ው.ሁ 21 የሚከተለውን ያካቱ
የሥራ ተቋራጩ እንደ ውሉ አለመፈጸም
ሥራ ተቋራጩ ከከሰረ ወይም በእሱ ላይ የመቀበል ትእዛዝ ከተሰጠ ወይም የመክሰር አቤቱታ ካቀረበ ወይም ለአበዳሪዎቹ ጥቅም ነገሮችን ካመቻቸ ወይም
መብቱን አሳልፎ ከሰጠ ወይም በአበዳሪዎቹ የመርማሪዎች ኮሚቴ ውሉን ለማከናወን ከተስማማ ወይም ድርጅት በሚሆንበት ጊዜ ለማፍረስ የንብረት
ማጣራት እየተደረገ ካለ (ለማዋሀድ ወይም እንደገና ለመገንባት አላማዎች ያሉትን በፍቃድ ላይ የተመሠረተ የንብረት ማጣራትን ሳያካትት ) ወይም
ከአሠሪው መጀመሪያ የጽሑፍ ፈቃድ ሳያኝ ሥራ ተቋራጩ ውሉን ለሌላ አሳልፎ ከሰጠ ወይም በእቃዎቹ ላይ የተጣሉ ግዴታዎችን መፈጸም ካለበት
ወይም መሃንዲሱ በራሱ አስተያየት ለአሠሪው በጽሑፍ ስለ ሥራ ተቋራጩ የሚከተለውን ካረጋገጠጠ ፡-
ሀ. ሥራ ተቋራጩ ውሉን የተወ መሆኑን ፣ ወይም
ለ. ያለ በቂ ምክንያት ሥራዎቹን መጀመር ካልቻለ ወይም ከመሃንዲሱ ሥራውን እንዲጀምር የጽሑፍ ማስታወቂያ ከተቀበለ በኃላ በ 28 ቀናት ውስጥ
የሥራዎቹን ግስጋሴ/እርምዳት ካቆመ ፣ ወይም
ሐ. ከመሃንዲሱ እቃዎቹ ተቀባይነት የሌላቸው እና የማይሆኑ ለመሆናቸው በእነዚህ ሁኔታዎች መሠረት ከመሃንዲሱ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ከተቀበለ
በኃላ በ 28 ቀናት ውስጥ ከሣይት እንዲህ አይነቶቹን ማቴሪያሎች ማንሳት/ማስወገድ ካልቻለ ወይም ሥራዎቹን አቁሞ ካልተካ፣ ወይም
መ. በውሉ መሠረት ሥራዎቹን እንዳያከናውን ከመሃንዲሱ በጽሑፍ ቀደም ሲል ማስጠንቀቂያዎች የተሰጡት ቢሆንም በውሉ መሠረት ያሉበትን
ግዴታዎቹን በተከታታይ ወይም በከፍተኛ ቸልተኝነት ካከናወነ ፣ ወይም
ሠ. የውሉን ማንኛውም ክፍል ጥሩ ሥራን በሚጐዳ መልኩ ወይም መሃንዲሱ በተቃራኒ የሰጣቸውን መመሪያዎች በሚከላከል መልኩ ከሰራ ፡፡
እንዲህ ሲሆን አሠሪው ለሥራ ተቋራጩ የ 14 ቀናት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኃላ ወደ ሳይቱ እና ወደ ሥራዎቹ ሊገባ ይችላል እና ሥራ
ተቋራጩን ውሉን የማይሰራ ሳያደርግ በውሉ መሠረት ካሉበት ማናቸውም ግዴታዎች ወይም ኃላፊነቶቹ ነጻ ሳያደርግ ወይም በውሉ መሠረት
ለመሃንዲሱ ወይም ለአሠሪው የተሰጡትን መብቶች እና ሥልጣናት ሳይጻረር ወይም ተቋራጩን ከሣይቱ እና ከሥራዎቹ ማስወጣት ይችላል እና
ሥራዎቹን በራሱ ሊያጠናቀቅ ወይም ሥራዎቹን እንዲያጠናቅቅ ሌላ ማንኛውንም ሥራ ተቋራጭ ሊቀጥር ይችላል፡፡ በውሉ ድንጋጌዎች መሠረት
ሥራዎቹን ለማከናወን አላማ ብቻ የተቀመጡ ተደርገው የሚቆጠሩትን የግንባታ ትክሉን /ፕላንቱን፣ ጊዜያዊ ሥራዎችን እና ማቴሪያሎችን ፣ እና ጥቅም
ላይ ያልዋሉ ማቴሪያሎችን አሠሪው ወይም እንዲህ አይነቱ ሌላ ሥራ ተቋራጭ ለእንዲህ አይነቱ ማጠናቀቅ አግባብ ነው ብሎ በሚያምንበት ሁኔታ
ሊጠቀምባቸው የሚችል ሲሆን በውሉ መሠረት ከተቋራጩ ተከፋይ ሊሆን የሚችልን ማንኛውም የገንዘብ መጠን እንዲውል ከሽያጭ የሚገኘውን
ገንዘብ መጠቀም ይችላል፡፡

77 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
አ.ው.ሁ 22.1 የግንባታው ስራ በተቋረጠ ጊዜ አሰሪው ስራውን ለማስጨረስ
የሚያወጣውን ተጨማሪ ወጪ የሚወክል መጠን ከተቋራጩ የክፍያ
ሰነድ የሚቀነሰው ካልተጠናቀቀው ሥራ 20 ፐርሰንት ይሆናል ፡ ፡

አ.ዉ.ሁ.25.2 አ.ው.ሁ. 26.3- መሐንዲሱ ውል ከተቋረጠ በኋላ በተቻለ ፍጥነት በሁለት ወር ጊዜ


26.4 ውስጥ የስራውን ዋጋ እና ለሥራ ተቋራጩ መከፈል የሚገባውን
ክፍያ ተመን ማዘጋጀትና ማጽደቅ ወይም ማፀደቅ ይኖርበታል፡፡
ንኡስ አንቀጾቹ ተፈፃሚ አይደሉም፡፡
አ.ው.ሁ. 26.3-26.4 አ.ው.ሁ. ንኡስ አንቀጾቹ ተፈፃሚ አይደሉም፡፡ተፈፃሚ አይደለም፡፡
30.2
አ.ው.ሁ. 30.2 አ.ው.ሁ 38.3 ተፈፃሚ አይደለም፡፡የቁልፍ ሰራተኞች ዝርዝር
በአባሪ----------- እንደተመለከተዉ ይሆናል፡፡
በጨረታው ሰነድ የተገለፁት ዋና ዋና የሰው ሃይል ከስራ
ገበታቸው አለመገኘት በወር 20,000.00 (ሃያ ሺ) ለእያንዳንዱ
ባለሞያ አሰሪው ከተቋራጩ ከሚፈፀመው ክፍያ ላይ መቀነስ
ይችላል የተቀነሱትን ባለሞያዎች ለመቀየር ከተገደደ ተመሳሳይ
ወይም የተሻለ የትምርት ደረጃና የስራ ልምድ ባላቸው
ባለሞያዎች መሆን አለበት፡፡

78 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ቁጥር የግንባታ መሳሪያው ዓይነት አቅም የሚያስፈልገው ትንሹ ቁጥር
1 ፕላይ ውድ ፎርም ወርክ ባለፉት 1 ዓመት ቢያንስ 2 ወለል የሚሸፍን
የተገዛ
2 ስቲል ስካፎልዲንግ ባለፉት 3 ዓመት የተገዛ ለጠቅላላ የህንፃው ክፍል
3 ዌል ሎደር 2.5 m3 እና ከዚያ 1
አ.ው.ሁ 34.1 ስራ ተቋራጩ ቢያንስ ከታች
በላይ
4 ፊክስድ አፕ እና ዳውን ሊፍት ወይም ክሬን 1 የተዘረዘሩትን መሳሪያዎች
5 እስካቫተር 1.5 m3 እና ከዚ 1
እና የግንባታ መሳሪያዎች
በላይ
6 እስቲል ድራም ሮለር 12 ቶን 1 ማቅረብ አለበት
7 ገልባጭ መኪና 14 m3 4
8 ወተር ትራክ ከ ስፕሬይ ባር 10¸000 ሊትር 1
9 የአርማታ ሚክሰር 750 ሊትር 3
10 ሰርቪስ ባር 4WD 4 ሰው 2
የሚጭን
11 ኮንክሪት ቫይቭሬተር 6
12 ወተር ፓንፕ 350 1/ደቂቃ 2
13 ጄኔሬተር 100 KVA 2

79 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
አ.ው.ሁ 34.5 (ለ) የአሰሪው ቅድመ መስማማት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ፡
ሀ. ከ ውሉ 10 % የሚበልጡ የለውጥ ስራዎች፣ በአስቸኳይ
ሁኔታ ውስጥ መሀንዲሱ ምክንታዊ ናቸው ብሎ የወሰናቸው
ካልሆኑ በስተቀር
ለ. ከውሉ ጊዜ ከ 25 % በላይ ለሚበልጡ የመዘግየት
ማስረጃዎች
ሐ. የስራ ማጠናቀቂያ የምስክር ወረቀት መስጠት እና የጥገና
የምስክር ወረቀት መስጠት
መ. የውል መቋረጥ
ሠ. ውሉ ውስጥ ላልተካተቱ አዳዲስ ስራዎች አዲስ ነጠላ ዋጋ
ማጽደቅ

80 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
አ.ው.ሁ 38.3 በውለታው ውስጥ የተዘረዘሩትን ስራዎች ለማከናወን የሚያስፈገው የሰው ሃይል ስብጥር እንደሚከተለው ይሆናል ፡፡
አ.ው.ሁ 38.6 ጠቅላላ ተዛማጅ
ቁጥር የሥራ መደብ ብዛት የስራ የሥራ መመዘኛ
ልምድ ዘርፍ
ማስተርስ/ ቢ ኤ ስ ሲ ዲግሪ በሲቪል ምህንድስና
ፕሮጀክት
1 1 10 6 ወይም ተመሳሳይ የሙያ መስክ፣ ፡ፕሮፌሽናል
ኮርድኔተር
መሀንዲስ - 6 (PE VI) ወይም ከዚያ በላይ
ኮንስትራክሽን ቢ ኤ ስ ሲ ዲግሪ በሲቪል ምህንድስና ፡ፕሮፌሽናል
2 2 8 5
መሀንዲስ መሀንዲስ - 5 (PE V) ወይም ከዚያ በላይ
ቢ ኤ ስ ሲ ዲግሪ በ ሲቪል ምህንድስና ፡ፕሮፌሽናል
3 የቢሮ መሀንዲስ 1 8 5
መሀንዲስ - 3 (PE III) እና ከዚያ በላይ
አድቫንስ ዲፕሎማ በ በዪልዲንግ ወይም በሲቪል
4 የህንፃ መሀንዲስ 1 8 5
ምህንድስና ኤኢ- 4 (AE IV) ወይም ከዚያ በላይ
ኮንስትራክሽን የቴክኒካል ት/ት ቤት ዲፕሎማ እና ኢኤ - 2 (EA II)
5 4 8 5
ፎርማን ከዚያ በላይ
6 ቺፍ ሰርቬየር 1 8 5 ዲፕሎማ በ ሰርቬይንግ ቴክኖሎጂ
ቢ ኤ ስ ሲ ዲግሪ በአርክቴክቸር - ፒፒኤአር
7 አርኪቴክት 1 8 4
(PPAR)
ስትራክቸራል ቢ ኤ ስ ሲ ዲግሪ በሲቪል ምህንድስና እና ከዚያ
8 1 8 4
መሀንዲስ በላይ
ኤሌክትሪካል ቢ ኤ ስ ሲ ዲግሪ በኤሌክትሪካል ምህንድስና እና
9 1 8 4
መሀንዲስ ከዚያ በላይ
ሳኒተሪ ቢ ኤ ስ ሲ ዲግሪ በሳኒተሪ ምህንድስና እና ከዚያ
10 1 8 4
መሀንዲስ በላይ
መካኒካል ቢ ኤ ስ ሲ ዲግሪ በመካኒካል ምህንድስና እና ከዚያ
11 1 8 4
መሀንዲስ በላይ

የሥራ ተቋራጩ ሠራተኛ ወይም የሥራ ኃይል አባል የሆነ ሰውን እንዲያነሳ መሐንዲሱ የሥራ ተቋራጩን ምክንያቱን
በመግለጽ ከጠየቀ የሥራ ተቋራጩ ግለሰቡ ከግንባታ ቦታው በሁለት ቀናት ውስጥ መልቀቁን እና ከውሉ የግንባታ ሥራ ጋር
ምንም ዓይነት ቀጣይ ግንኙነት እንደማይኖረው ማረጋገጥ አለበት፡፡

81 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
አ.ው.ሁ 38.6 አ.ዉ.ሁ. 40.3 የሥራ ተቋራጩ ሠራተኛ ወይም የሥራ ኃይል አባል የሆነ ሰውን
እንዲያነሳ መሐንዲሱ የሥራ ተቋራጩን ምክንያቱን በመግለጽ ከጠየቀ
የሥራ ተቋራጩ ግለሰቡ ከግንባታ ቦታው በሁለት ቀናት ውስጥ
መልቀቁን እና ከውሉ የግንባታ ሥራ ጋር ምንም ዓይነት ቀጣይ ግንኙነት
እንደማይኖረው ማረጋገጥ አለበት፡፡
አደጋዎችንና የፍትሐብሔር ዕዳን መሸፈን የሚችል የመድን ዋስትና
ያልተወሰነ ይሆናል።
አ.ዉ.ሁ. 40.3 አ.ዉ.ሁ. 41.1 አደጋዎችንና የፍትሐብሔር ዕዳን መሸፈን የሚችል የመድን ዋስትና
ያልተወሰነ ይሆናል።

የሥራ ተቋቌራጩ ከአሰሪው ሥራውን ማሽነፉን የሚገልፅ ደብዳቤ


አ.ዉ.ሁ. 41.1 አ.ዉ.ሁ. 41.4 የሥራ በ 15 ቀናት
በተቀበለተቋራጩ ከአሰሪው ሥራውንለመሐንዲሱ
ግዜ ውስጥ ማሽነፉን የሥራዎች
የሚገልፅ ደብዳቤ
ትግበራ
በተቀበለ በ 15 ቀናት ግዜ ውስጥ ለመሐንዲሱ የሥራዎች ትግበራ
ፕሮግራም በተግባራትና በወር ከፋፍሎ በአጠቃላይ የዉል ሁኔታዎች
የተመለከቱትን መረጃዎች ማቅረብ ይኖርበታል።

አ.ዉ.ሁ. 41.4 አ.ዉ.ሁ. 58.1 የሥራ ተቋራጩ ወቅታዊ የሆነውን ፕሮግራም በየ 30 ቀናት
ለመሐንዲሱ ማቅረብ አለበት።

ዘግይቶ ለሚገባ የታደሰ ወቅታዊ ፕሮግራም የሚያዘው መጠን ከጊዜያዊ


ክፍያው 0.1 በመቶ (0.1%) ወይም ከሁለት መቶ ሺ ብር (200,000
ብር) አነስተኛው መጠን ነው፡፡
አ.ዉ.ሁ. 58.1 አ.ዉ.ሁ. 58.2 ሥራ ተቋራጩ ውል በተፈራረመ በ 10 ቀናት ግዜ ውስጥ የውለታውን
ዋጋ 10 በመቶ ጋር እኩል የሆነ ለውሉ መልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና
ማቅረብ አለበት።ተፈጻሚነት የለዉም፡፡
አ.ዉ.ሁ. 58.2 አ.ዉ.ሁ 58.3 ተፈጻሚነት የለዉም፡፡ስራ ተቋራጩ በውሉ መሰረት የሚጠበቅበትን
ግዴታ ካልተወጣ አሰሪው የተያዘውን የውል አፈጻጸም ዋስትና መውረስ
አ.ዉ.ሁ 58.3 አ.ዉ.ሁ. 58.4 ስራ ተቋራጩ በውሉ መሰረት የሚጠበቅበትን ግዴታ ካልተወጣ አሰሪው
የተያዘውን የውል አፈጻጸም ዋስትና መውረስ ይችላል፡፡የመልካም ስራ
አፈፃፀም (የውል ማስከበሪያ) ዋስትናው በሁኔታ ላይ
ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank
Guarantee) እና ከታወቀ ባንክ የቀረበ መሆን አለበት።
አ.ዉ.ሁ. 58.4 አ.ዉ.ሁ. 59.1 የመልካም ስራ አፈፃፀም (የውል ማስከበሪያ) ዋስትናው በሁኔታ ላይ
ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank

82 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
Guarantee) እና ከታወቀ ባንክ የቀረበ መሆን አለበት።አጠቃላይ
የክፍያ ሁኔታ እንደሚከተለው ሲሆን የክፍያ ሁኔታዉ ዝርዝር ስለክፍያ
በሚመለከት የውሉ አባሪ ላይ እንደተዘረዘረ ይሆናል፡፡

ሀ) ሁለት ጊዜ የቅድሚያ ክፍያ (10% +10%)

ለ) 13 ጊዜ የመሃል ክፍያ፤ እንዲሁም

ሐ) የመጨረሻ ክፍያ ተከፍሎ የሚፈጸም ይሆናል፡፡

ሁሉም በዚህ ውለታ ስር ያሉ ክፍያዎች በኢትዮጵያ ብር ይሆናሉ

አ.ዉ.ሁ. አጠቃላይ የክፍያ ሁኔታ እንደሚከተለው ሲሆን የክፍያ ሁኔታዉ ዝርዝር ስለክፍያ በሚመለከት የውሉ አባሪ ላይ
59.1 አ.ዉ.ሁ. እንደተዘረዘረ ይሆናል፡፡
59.2
ሀ) ሁለት ጊዜ የቅድሚያ ክፍያ (10% +10%)

ለ) 13 ጊዜ የመሃል ክፍያ፤ እንዲሁም

ሐ) የመጨረሻ ክፍያ ተከፍሎ የሚፈጸም ይሆናል፡፡

ሁሉም በዚህ ውለታ ስር ያሉ ክፍያዎች በኢትዮጵያ ብር ይሆናሉ ክፍያ የሚፈጸመው በ 30 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ይሆናል፡፡

አ.ዉ.ሁ. 59.2 አ.ዉ.ሁ. 60.1 ክፍያ የሚፈጸመው በ 30 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ይሆናል፡፡ቅድመ


ክፍያዎች በሥራ ተቋቌራጩ ጥያቄ ላይ ተመስርቶ የሚከፈል ይሆናል፡፡
አ.ዉ.ሁ. 60.1 አ.ዉ.ሁ. 60.2 ቅድመ ክፍያዎች በሥራ ተቋራጩ ጥያቄ ላይ ተመስርቶ የሚከፈል

አ.ዉ.ሁ. 60.2 አ.ዉ.ሁ. 60.3 ይሆናል፡፡የቅድመ ክፍያ መጠን


የቅድመ ክፍያ መጠን 20 በመቶ
20 በመቶ የውለታ
የውለታ ዋጋ ዋጋ ይሆናል፡፡
ይሆናል፡፡ የውዉሉ
አጠቃላይ ሁኔታ 60.3 ላይ የተቀመጠውዉ እንደተጠበቀ ሆኖ
የሚከተለውዉ ተጨምሯል፡፡

መ. በአሰሪዉ የግንባታ ቦታ ርክክብ ሲደረግ፡-

1 ኛ ቅድመ ክፍያ 10 በመቶ የውለታ ዋጋ የሚፈጸመው ሥራ ተቌራጩ


ውለታ ሲፈራረምበዚህ ንዑስ አንቀጽ ከ ሀ-መ የተቀመጡ ሁኔታዎች
ሲሟሉ ሲሆን፤

83 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
2 ኛ ቅድመ ክፍያ 10 በመቶ የውለታ ዋጋ የሥራ ተቋቌራጩ የቁፋሮ
ስራ ሲያጠናቅቅ፣ ለሙሉ የግንባታ ሥራ የሚያስፈልገውን የአርማታ
ብረት አማልቶ ሲያቀርብ፣ ለግንባታ የሚያስፈልገውን ማሽኖች ማቅረቡ
ሲረጋገጥ በተጨማሪም ሥራ ተቋራጩ ያልተወሰነ የባንክ የቅድመ ክፍያ
ዋስትና እንዲሁም የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ማቅረቡ ሲረጋገጥ
የሚከፈል ይሆናል።

84 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
አ.ዉ.ሁ. 60.3 አ.ዉ.ሁ.60.9 የዉሉ አጠቃላይ ሁኔታ 60.3 ላይ የተቀመጠው እንደተጠበቀ ሆኖ
የሚከተለው ተጨምሯል፡፡

መ. በአሰሪዉ የግንባታ ቦታ ርክክብ ሲደረግ፡-

1 ኛ ቅድመ ክፍያ 10 በመቶ የውለታ ዋጋ የሚፈጸመው ሥራ ተቌራጩ


ውለታ ሲፈራረም በዚህ ንዑስ አንቀጽ ከ ሀ -መ የተቀመጡ ሁኔታዎች
ሲሟሉ ሲሆን፤

2 ኛ ቅድመ ክፍያ 10 በመቶ የውለታ ዋጋ የሥራ ተቋራጩ የቁፋሮ


ስራ ሲያጠናቅቅ፣ ከመሬት በታች ላለው የግንባታ ሥራ
የሚያስፈልገውን የአርማታ ብረት አማልቶ ሲያቀርብ፣ ለግንባታ
የሚያስፈልገውን ማሽኖች ማቅረቡ ሲረጋገጥ በተጨማሪም ሥራ
ተቋራጩ ያልተወሰነ የባንክ የቅድመ ክፍያ ዋስትና እንዲሁም
የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ማቅረቡ ሲረጋገጥ የሚከፈል ይሆናል።

የሚከተሉት ሁኔታዎች የቅድመ ክፍያው ዋስትና ላይ


ተፈፃሚ ይሆናል

ሀ. የቅድመ ክፍያ ዋስትና የግድ አሰፈላጊ ይሆናል

ለ. ቅድመ ክፍያ በቀናት ግዜ የሚፈፀም ይሆናል

ሐ. የቅድመ ክፍያ ዋስትናዎች የሚዘጋጁት በኢትዮጵያ


ብር ሆነው ከእያንዳንዱ ክፍያ ጋር እኩል ሆነው ይዘጋጃሉ

መ. የቅድመ ክፍያ መልሶ መክፈል የሚከተለውን ቅርፅ


ይዘው ከእያንዳንዱ መካከለኛ (የመሃል) ክፍያ እየተቀነሱ
ለአሰሪው የሚከፈሉ ይሆናሉ

1. የቅድመ ክፍያ የመልስ ክፍያ /ከፍተኛው 20 በመቶ ሆኖ/


አ.ዉ.ሁ.60.9 አ.ዉ.ሁ. 61.1 የሚከተሉት ሁኔታዎች የቅድመ ክፍያው ዋስትና ላይ
ተፈፃሚ ይሆናል

85 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ሀ. የቅድመ ክፍያ ዋስትና የግድ አሰፈላጊ ይሆናል

ለ. ቅድመ ክፍያ በቀናት ግዜ የሚፈፀም ይሆናል

ሐ. የቅድመ ክፍያ ዋስትናዎች የሚዘጋጁት በኢትዮጵያ ብር


ሆነው ከእያንዳንዱ ክፍያ ጋር እኩል ሆነው ይዘጋጃሉ

መ. የቅድመ ክፍያ መልሶ መክፈል የሚከተለውን ቅርፅ


ይዘው ከእያንዳንዱ መካከለኛ (የመሃል) ክፍያ እየተቀነሱ
ለአሰሪው የሚከፈሉ ይሆናሉ

2. የቅድመ ክፍያ የመልስ ክፍያ /ከፍተኛው 20 በመቶ


ሆኖ/ ከስራ ተቋራጩ እያንዳንዱ ክፍያ ተቀናሽ
እየተደረገ ለአሰሪው የሚከፈል ይሆናል፡፡ ለሥራ
ተቌራጩ የተከፈሉ መካከለኛ ክፍያዎች ድምር 80
በመቶ የውለታ ዋጋውን ሲያክል ሙሉ ቅድመ
ክፍያው ተመላሽ መሆን ይኖርበታል።
የቅድመ ክፍያ መልስ ክፍያ የሚፈፀመው በኢትዮያ
ብር ነው ከእያንዳንዱ መካከለኛ ክፍያ የሚቀነሰው
የቅድመ ክፍያ መጠን በሚከተለው ቀመር መስራት
ይችላል።

መ= ጠቅ X መክ
ውዋ X0.8

ይህም
መ= የቅድመ ክፍያ ተመላሽ ሒሣብ
ጠቅ= ጠቅላላ ቅድመ ክፍያ
ውዋ= የመጀመሪያው የውለታ ዋጋ
መክ= መላከለኛ ክፍያ

ውጤቱ ከነጥብ በኋላ ወደ ሁለት ቁጥሮች ይጠጋጋልቀሪ

86 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
ተደርጎ የሚያዘው የገንዘብ መጠን ከእያንዳዱ የመካከለኛ ክፍያ 5 በመቶ
ይሆናል፡፡
አ.ዉ.ሁ. 61.1 አ.ዉ.ሁ.62. ቀሪ ተደርጎ የሚያዘው የገንዘብ መጠን ከእያንዳዱ የመካከለኛ ክፍያ 5
በመቶ ይሆናል፡፡ተፈፃሚ አይሆንም
አ.ዉ.ሁ.62.አ.ዉ.ሁ.63 ተፈፃሚ አይሆንምበአጠቃላይ የዉል ሁኔታዎች ላይ የተገለጸው
እንደተጠበቀ ሆኖ ዉሉ የዉሉ የነጠላ ዋጋ ውሎች ይሆናል፡፡
አ.ዉ.ሁ.63 አ.ዉ.ሁ.64.1 በአጠቃላይ የዉል ሁኔታዎች ላይ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ
ዉሉ የዉሉ የነጠላ ዋጋ ውሎች ይሆናል፡፡መካከለኛ ወይም
የጊዜያዊ ክፍያ ሰነድ ለመሃንዲሱ የሚቀርበዉ በዚህ ዉል እና ስለ
አ.ዉ.ሁ.64.1 አ.ዉ.ሁ.64.2 / መካከለኛ ወይም የጊዜያዊ ክፍያ ሰነድ ለመሃንዲሱ የሚቀርበዉ
ሠ/ በዚህ ዉል እና ስለ ጊዜያዊ ክፍያ አፈጻጻም በሚዘረዝረው አባሪ
ላይ በተገለጸዉ ለእያንዳንዱ ክፍያ የተቀመጠው የክፍያ ቅድመ
ሁኔታ (payment milestone) ሲሟላ ይሆናል፡፡በአጠቃላይ
የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 83 የተመለከቱት ተከላዎችና የግንባታ
አ.ዉ.ሁ.64.2 / በአጠቃላይ የውልየአሰሪው
ቁሶች ባለቤትነት ሁኔታዎች 83 የተመለከቱት ተከላዎችና
አንቀጽይቆጠራል።
እንደሆነ
ሠ/አ.ዉ.ሁ.64.7 የግንባታ ቁሶች ባለቤትነት የአሰሪው እንደሆነ ይቆጠራል።መካከለኛ
ወይም የጊዜያዊ ክፍያ የሚፈጸመዉ በዚህ ዉል ላይ ስለ ጊዜያዊ
ክፍያ አፈጻጻም በሚዘረዝረዉ አባሪ ላይ የተገለጸዉ ለእያንዳንዱ
ክፍያ የተቀመጠዉ የክፍያ ቅድመ ሁኔታ (payment
milestone) ሲሟላ ይሆናል፡፡

አ.ዉ.ሁ.64.7 አ.ዉ.ሁ.69.1 መካከለኛ ወይም የጊዜያዊ ክፍያ የሚፈጸመዉ በዚህ ዉል ላይ ስለ


ጊዜያዊ ክፍያ አፈጻጻም በሚዘረዝረዉ አባሪ ላይ የተገለጸዉ
ለእያንዳንዱ ክፍያ የተቀመጠዉ የክፍያ ቅድመ ሁኔታ (payment
milestone) ሲሟላ ይሆናል፡፡የግንባታ ስራዉ 2B+G+8
ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ሲሆን መከናወን
አ.ዉ.ሁ.69.1 አ.ዉ.ሁ.69.2 የግንባታ ስራዉ 2B+G+8 ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ
ሲሆን መከናወን የሚገባቸው የግንባታ ሥራዎች ዝርዝር
በተፈላጊ ነጥቦች መግለጫ አባሪ ውስጥ በተገለፀው
መሰረት ይሆናል፡፡የግንባታው ቦታ ጅማደሴ ከተማ በንድፍ ላይ
በተገለፀው መሰረት ነው።
አ.ዉ.ሁ.69.2 አ.ዉ.ሁ.70.1 የግንባታው ቦታ ጅማ ከተማ በንድፍ ላይ በተገለፀው መሰረት
ነው።ይህ ዉል በተፈረመ በ 10 ቀን ዉስጥ የግንባታ ቦታ ርክክብ
(site handover) ይደረጋል፡፡

87 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል
አ.ዉ.ሁ.70.1 አ.ዉ.ሁ.71.1 ይህ ዉል በተፈረመ በ 10 ቀን ዉስጥ የግንባታ ቦታ ርክክብ (site
handover) ይደረጋል፡፡
የግንባታ ስራ ትግበራ ዝግጅት (mobilization) የሚከናወነዉ
የግንባታ ቦታ ርክክብ እንደተደረገ በ 14 ቀናት ዉስጥ ይሆናል፡፡
ሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራዉን የሚጀምረው የግንባታ ትግበራ
ዝግጅቱ እንደተጠናቀቀ በቀጣዩ ቀን መሆን አለበት፡፡ለግንባታ
የተቀመጠው የውለታ ጊዜ 730 / ሰባት መቶ ሰላሳ/ የመቁጥሪያ
ቀናት ነው፡፡
አ.ዉ.ሁ.71.1 አ.ዉ.ሁ.87.7 ለግንባታ የተቀመጠው የውለታ ጊዜ 730 / ሰባት መቶ ሰላሳ/
የመቁጠሪያ ቀናት ነው፡፡ የጉድለቶች ተጠያቂነት ጊዜ (Defect
Liability Period)365 /ሶስት መቶ ስልሳ አምስት
548 /አምስት መቶ አርባ ስምንት/ የመቁጠሪያ ቀናት ነው።

አ.ዉ.ሁ.87.7 የጉድለቶች ተጠያቂነት ጊዜ (Defect Liability Period)


365 /ሶስት መቶ ስልሳ አምስት/ የመቁጠሪያ ቀናት ነው።

88 በጅማ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ ስራ ለመስራት በኢትዮ ቴሌኮም እና በኤፍ ኢ


ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል

You might also like