You are on page 1of 81

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ንግድ ቢሮ

የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት


የንግድ ምዝገባና ፈቃድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ
ቁጥር 392/2009 እና ማሻሻያ ደንብ ቁጥር 461/2012

የካቲት 2013 ዓ.ም


አዲስ አበባ
የንግድ ምዝገባና ፈቃድ የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር
392/2009 እና ማሻሻያ ደንብ ቁጥር 461/2012
 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ መሠረታዊ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ፅንሰ

ሀሳቦች ድንጋጌዎችን የያዘ በመሆኑ የማስፈፀሚያ ደንብ በማዘጋጀት

በየደረጃው ህጉን ለሚያስተገብሩ አካላት እና ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ግልፅ የሆነ

የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ማድረግ በማስፈለጉ፣


 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ፍትሀዊ ዘመናዊ
የተቀላጠፈና ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ የንግዱን ማህበረሰብ እርካታ
ለማሳደግ እንዲቻል እና ለአገልግሎት ሰጪ አካላትም ምቹ ማድረግ
በማስፈለጉ፣
የቀጠለ…
የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ስርዓቱ የተሟላ የህግ ማዕቀፍ
እንዲኖረው በማስቻል አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ
ክፍተቶችን በመሙላት ግልፀኝነት እና ተጠያቂነት ያለው አሰራር
በማስፈን መልካም አስተዳደርን ማረጋገጥ በማስፈለጉ፣
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ-መንግስት
አንቀፅ 55 (1) እና በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር
980/2008 መሠረት ይህ ደንብ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡
ክፍል አንድ
1. አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር
392/2009 እና ማሻሻያ ደንብ ቁጥር 461/2012 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2.ትርጓሜ

የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፣


“አዋጅ” ማለት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 እና
ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1150/2011 ነዉ፡፡
በአዋጁ አንቀፅ 2 የተሰጡት ትርጓሜዎች ለዚህ ደንብ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
ክፍል ሁለት
የንግድ ድርጅት ስም እና የንግድ ስም በንግድ መዝገብ
 ስለመመዝገብ፣
 ስለማሻሻል፣
 ስለምትክ እና፣
 ስለስረዛ መስፈርቶች፣
3.የግለሰብ ነጋዴ የንግድ ድርጅት ስም ምዝገባ
የግለሰብ ነጋዴ የድርጅት ስም ለማውጣት የሚጠይቅ አመልካች ከማመልከቻ ቅፁ ጋር
የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1. የግለሰብ ነጋዴ የህግ ስም የግለሰቡን ስም የአባቱን እና የአያቱን
ስም ያካትታል፣
2. ስሙ ቀደም ብሎ የተመዘገበ ከሆነ የቅድመ አያትን ስም
መጨመር፣
3. የቅድመ አያት ስም ድረስ የተያዘ ከሆነ የእናት ስም ተጨምሮ
ይመዘገባል፣
4. የእናት ስም ከተያዘ ሌላ መለያ በመጨመር የዋና የንግድ ምዝገባ
የምስክር ወረቀት ያወጣል፡፡
4.የንግድ ማህበራት የንግድ የድርጅት ስም ስለማስመዝገብ
የንግድ ማህበራት የድርጅት ስም ለማስመዝገብ የሚጠይቅ አመልካች
ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1. የንግድ ድርጅት ስሙን እንዲያፀድቅ የተመረጠው የአንድ አባል
የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት
ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
2. ያልፀደቀ የመመስረቻ ፅሑፍ እና የመተዳደሪያ ደንብ፣
3. ለድርጅታቸው መጠሪያ የመረጡት ሶስት አማራጭ ስሞች፣
4. ያቀረባቸው ሶስቱ አማራጭ ስሞች የተያዙ ከሆነ ሌላ አማራጭ
ስሞችን አመልካቹ ያቀርባል፣
5.የንግድ ስም ምዝገባ የምስክር ወረቀት ስለማውጣት
የንግድ ስም ምዝገባ የምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚጠይቅ አመልካች
ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፣
1. የአመልካቹ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት
ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
2. የአመልካቹን ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የተነሳው
ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
3. በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅ እና ፎቶ ኮፒ፣የወኪሉ እና
የወካዩ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም
የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን
ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4. የንግድ ስሙ አገር አቀፍ ስርጭት ባለው ጋዜጣ የወጣበት ማስረጃ፤
5. የንግድ ስሙን ለረጅም ጊዜ ሲጠቀምበት የቆየ ከሆነ ከአካባቢው
አስተዳደር/መስተዳደር ሲገለገልበት የነበረ ስለመሆኑ የሚያስረዳ ማረጋገጫ
ደብዳቤ፣
6.ስለምትክ የንግድ ስም የምስክር ወረቀት
ምትክ የንግድ ስም የምስክር ወረቀት የሚጠይቅ አመልካች ከማመልከቻ ቅፁ
ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1. የአመልካቹ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት
ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
2. የአመልካቹን ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ
የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶ ግራፎች፣
3. ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅ እና ፎቶ
ኮፒ፣የወኪሉ እና የወካዩ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4. የተበላሸውን የንግድ ስም የምስክር ወረቀት፣
5. የንግድ ስም የምስክር ወረቀት የጠፋበት ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ
ከሚመለከተው የፖሊስ አካል የተሰጠ ማስረጃ፣
7.የንግድ ስም ምስክር ወረቀት ስለማሻሻል
የንግድ ስም የምስክር ወረቀት ማሻሻያ የሚጠይቅ አመልካች ከማመልከቻ
ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
8. የአመልካቹን ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ
የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
9. ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ ዋና ቅጅ እና
ፎቶ ኮፒ፣የወካዩ እና የወኪሉ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም
የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች
የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
10. የፀና የንግድ ስራ ፈቃድ፣
11. የንግድ ማህበር የንግድ ስም እንዲሻሻል ከተጠየቀ በዚህ አንቀፅ
ከተዘረዘሩት በተጨማሪ በሰነድ አረጋጋጭ የተረጋገጠ ቃለ ጉባኤ እና
ስለመሻሻሉ የሚገልፅ ሀገር አቀፍ ስርጭት ባላቸው ጋዜጦች የታወጀበት፣
8.የንግድ ስም የምስክር ወረቀት ስለመሰረዝ
የንግድ ስም የምስክር ወረቀት ለመሰረዝ የሚጠይቅ አመልካች
ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1. የአመልካቹ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት
ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
2. ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅ እና ፎቶ
ኮፒ፣የወኪሉ እና የወካዩ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
3. የንግድ ስም ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
4. የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት፣
9.የግለሰብ ነጋዴ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት
የግለሰብ ነጋዴ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚጠይቅ አመልካች ከማመልከቻ ቅፁ
ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1. የአመልካቹን ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ
የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
2. የአመልካቹ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት
ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
3. አመልካቹ የዋና የስራ አድራሻ እና የቅርንጫፍ የስራ አድራሻ ያለው ከሆነም ይህንን
የሚያረጋግጥ የአድራሻ ማረጋገጫ፣ለንግድ የሚጠቀምበት ቤት የአመልካቹ የራሱ ከሆነ
የባለቤትነት ማረጋገጫ፣ወይም የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ ያላለፈበት የፀደቀ የኪራይ
ዉል፣ወይም የመንግስት ቤቶች ከሆነ በሚመለከተው የመንግስት አካል የሚሰጥ የኪራይ
ዉል፤ ወይም እነዚህን ማስረጃዎች ማቅረብ ካልቻለ ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ
የመስተዳደር አካል የተሰጠ የፁሁፍ ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ በአመልካቹ
የሚሞላ እና በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ አድራሻ”፣
የቀጠለ…
4. ለንግድ ስራዉ የመደበዉ ካፒታል ማሳወቅ፣
5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣
6. አመልካቹ የውጭ ሀገር ዜጋ ከሆነ በዚህ አንቀጽ ከተጠቀሱት በተጨማሪ
የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንዲሁም ቅርንጫፍ የሚከፍት ከሆነ ለቅርንጫፉ
የአድራሻ ማረጋገጫ፣
 የግለሰብ ነጋዴ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀትን በውክልና አስመዝግቦ
ማግኘት የተከለከለ ነው፡፡

 ግለሰብ ነጋዴ በውክልና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀትን ለማውጣት


ሲፈልግ ወኪሉ በሕግ ሥልጣን በተሰጠው አካል የተሰጠ የውክልና ማስረጃ
ማቅረብ አለበት፡፡
10.የሽርክና ማህበራት እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የንግድ
ምዝገባ የምስክር ወረቀት
የሽርክና ማህበራት እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የንግድ ምዝገባ የምስክር
ወረቀት ለማውጣት ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ
አለበት፡-
1. የስራ አስኪያጅ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት
ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
2. የንግድ ማህበሩ ስራ አስኪያጅ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት
ጊዜ ውስጥ የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
3. በመመስረት ላይ ያለ ከሆነ በሁሉም አባላት ተፈርሞ የተሰጠ የውክልና
ማረጋገጫ ዋና ቅጂ ወይም ከዋናው ጋር የተመሳከረ ቅጂ፣
4. ሰነድን ለማረጋገጥ በህግ ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የማህበሩ
የመመስረቻ ፁሑፍና የመተዳደሪያ ደንብ ዋና ቅጂዎች፣
የቀጠለ…
5.በሽርክና ማህበራትና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ውስጥ የውጭ ሀገር
ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በሚኖርበት ጊዜ ከሚመለከተው የመንግስት አካል
የተሰጠ የኢንቨስትመንት ይሁንታ ማረጋገጫ እና የግለሰቦቹ የፀና ፓስፖርት
ዋናው እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
6.በሽርክና ማህበራት እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ውስጥ አባል የሆነ
የውጭ ሀገር የህግ ሰውነት ያለው አካል ከሆነ፡-
ሀ.ከተቋቋመበት ሀገር ህጋዊ ሰውነት ያገኘበትን ማረጋገጫ ሰነድ፣
ለ.አዲስ በሚቋቋመው ማህበር ውስጥ ለመግባት መወሰኑን የሚያሳይ
በሀገሩ ህግ እና በኢትዮጵያ የሰነዶች አረጋጋጭ የተረጋገጠ ቃለ-ጉባዔ
ወይም ደብዳቤ ወይም ተመሳሳይ ሰነድ፣
ሐ.የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣
መ.በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 5 እና 6 መሠረት የሚቋቋም የንግድ
ማህበር ቅርንጫፍ የሚከፍት ከሆነ የቅርንጫፍ አድራሻ ማረጋገጫ
በማመልከቻ ቅፅ ማሳወቅ፣
የቀጠለ…
7.አመልካቹ የዋና የስራ አድራሻ እና የቅርንጫፍ የስራ አድራሻ ያለው ከሆነም
ይህንን የሚያረጋግጥ የአድራሻ ማረጋገጫ፣ለንግድ የሚጠቀምበት ቤት የአመልካቹ
የራሱ ከሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ፣ወይም የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ ያላለፈበት
የፀደቀ የኪራይ ዉል፣ወይም የመንግስት ቤቶች ከሆነ በሚመለከተው የመንግስት
አካል የሚሰጥ የኪራይ ዉል፣ወይም እነዚህን ማስረጃዎች ማቅረብ ካልቻለ
ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ የመስተዳደር አካል የተሰጠ የፁሑፍ
ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ በአመልካቹ
የሚሞላ እና በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ አድራሻ”፣
8.የአዕምሯዊ ፈጠራ ንብረት መዋጮ በሚኖርበት ጊዜ በሰነዶች አረጋጋጭ
የተረጋገጠ ቃለ-ጉባኤ ወይም ተመሳሳይ ሰነድ፣
9.የዓይነት መዋጮ በሚኖርበት ጊዜ የመዋጮው ባለቤትነት የንግድ ምዝገባው
ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ በአንድ የበጀት ዓመት ጊዜ ውስጥ ወደ የሽርክና
ማህበሩ ወይም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበሩ እንደሚተላለፍ የሚያረጋግጥ
በአመልካቹ የተፈረመ ማረጋገጫ፣
10.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣
11.የአክሲዮን ማህበር የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት
የአክሲዮን ማህበራት መሥራቾች የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ለማውጣት
ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለባቸው፡-
1. የስራ አስኪያጅ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
2. የአክሲዮን ማህበሩ ስራ አስኪያጅ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት
ወራት ጊዜ ውስጥ የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው
ፎቶግራፎች፣
3. ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅ እና ፎቶ
ኮፒ፣የተወካዩ እና የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ
ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ
ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ
ኮፒ፣
የቀጠለ…

4.በመመስረት ላይ ያለ ከሆነ በሁሉም አባላት ተፈርሞ የተሰጠ የውክልና


ማረጋገጫ ዋና ቅጂ ወይም ከዋናው ጋር የተመሳከረ ቅጂ፣
5.ሰነድን ለማረጋገጥ በህግ ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የማህበሩ
የመመስረቻ ፁሁፍና የመተዳደሪያ ደንብ ዋና ቅጅዎች፣
6.በአክሲዮን ማህበር ውስጥ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በሚኖርበት
ጊዜ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት የተሰጠ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ማረጋገጫ
እና የፀና ፓስፖርት ዋናው እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶኮፒ፣
7.በአክሲዮን ማህበር ውስጥ አባል የሆነ የውጭ ሀገር የህግ ሰውነት ያለው አካል
ከሆነ፣
ሀ.ከተቋቋመበት ሀገር ህጋዊ ሰውነት ያገኘበትን ማረጋገጫ ሰነድ፣
ለ.አዲስ በሚቋቋመው ማህበር ውስጥ ለመግባት መወሰኑን የሚያሳይ
በሀገሩ ህግ እና በኢትዮጵያ የሰነዶች አረጋጋጭ የተረጋገጠ ቃለ-ጉባዔ
ወይም ደብዳቤ ወይም ተመሳሳይ ሰነድ፣
የቀጠለ…
ሐ.የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣
መ.በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 6 እና 7 መሠረት የሚቋቋም የንግድ ማህበር ቅርንጫፍ
የሚከፍት ከሆነ የቅርንጫፍ አድራሻ ማረጋገጫ በማመልከቻ ቅፅ ማሳወቅ፣
8.አመልካቹ የዋና የስራ አድራሻ እና የቅርንጫፍ የስራ አድራሻ ያለው ከሆነም ይህንን
የሚያረጋግጥ የአድራሻ ማረጋገጫ፣ለንግድ የሚጠቀምበት ቤት የአመልካቹ የራሱ ከሆነ
የባለቤትነት ማረጋገጫ፣ወይም የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ ያላለፈበት የፀደቀ የኪራይ
ዉል፣ወይም የመንግስት ቤቶች ከሆነ በሚመለከተው የመንግስት አካል የሚሰጥ የኪራይ
ዉል፣ወይም እነዚህን ማስረጃዎች ማቅረብ ካልቻለ ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ
የመስተዳደር አካል የተሰጠ የፁሑፍ ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ በአመልካቹ
የሚሞላ እና በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ አድራሻ”፣
9.ከተፈረመ የአክሲዮን ሽያጭ ቢያንስ አንድ አራተኛ ገንዘብ ተከፍሎ በዝግ ሂሳብ ለመቀመጡ ማስረጃ
ያቀርባል፣
10.ዕምሯዊ ፈጠራ ንብረት መዋጮ በሚኖርበት ጊዜ በሰነዶች አረጋጋጭ የተረጋገጠ ቃለ-ጉባኤ ወይም
ተመሳሳይ ሰነድ፣
11.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣
12.የመንግስት የልማት ድርጅቶች ምዝገባ የምስክር ወረቀት
የፌደራል እና የክልል መንግስታት የልማት ድርጅቶች ምዝገባ የምስክር
ወረቀት ለማውጣት ከማመልከቻው ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች
ማቅረብ አለበት፡-
1. የተቋቋመበት ህግ፣
2. የስራ አስኪያጁ የምደባ ደብዳቤ፤
3. የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም
የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና
አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፤
4. ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅ እና ፎቶ ኮፒ፣የወኪሉ እና
የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም
የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና
አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
5. የስራ አስኪያጁ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ
የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
የቀጠለ…
6.አመልካቹ የዋና የስራ አድራሻ እና የቅርንጫፍ የስራ አድራሻ ያለው ከሆነም
ይህንን የሚያረጋግጥ የአድራሻ ማረጋገጫ፣ለንግድ የሚጠቀምበት ቤት
የአመልካቹ የራሱ ከሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ፣ወይም የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ
ያላለፈበት የፀደቀ የኪራይ ዉል፤ወይም የመንግስት ቤቶች ከሆነ
በሚመለከተው የመንግስት አካል የሚሰጥ የኪራይ ዉል፣ወይም እነዚህን
ማስረጃዎች ማቅረብ ካልቻለ ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ
የመስተዳደር አካል የተሰጠ የፁሑፍ ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ በአመልካቹ
የሚሞላ እና በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ አድራሻ”፣

7.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣


13.የንግድ እንደራሴ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ለማውጣት
የሚጠየቁ መስፈርቶች
1. የንግድ እንደራሴው የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
2. የንግድ እንደራሴው ማንነት በግልፅ የሚያሳዩ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ
የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
3. ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅ እና ፎቶ
ኮፒ፣የእንደራሴው የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም
የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና
አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4. ወካዩ ነጋዴ በተቋቋመበት ሀገር ወይም በሚሰራበት አገር የተመዘገበ ህጋዊ ሰውነት ያለው
መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣
5. ለበጀት ዓመቱ ለደመወዝ እና ለስራ ማስኬጃ የሚሆን ቢያንስ ፩፻ሺ /አንድ መቶ ሺ/
የአሜሪካን ዶላር አገር ውስጥ በእንደራሴው ስም ለማስገባቱ ከባንክ የተሰጠ ማረጋገጫ፣
የቀጠለ…
6.የንግድ እንደራሴው በወካዩ ነጋዴ በእንደራሴነት የተሾመበት የተረጋገጠ
ማስረጃ ዋና ቅጅ፣
7.አመልካቹ የዋና የስራ አድራሻ የቅርንጫፍ የስራ አድራሻ ያለው ከሆነም ይህንን
የሚያረጋግጥ የአድራሻ ማረጋገጫ፣ለንግድ የሚጠቀምበት ቤት የአመልካቹ የራሱ ከሆነ
የባለቤትነት ማረጋገጫ፣ወይም የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ ያላለፈበት የፀደቀ የኪራይ
ዉል፤ወይም የመንግስት ቤቶች ከሆነ በሚመለከተው የመንግስት አካል የሚሰጥ የኪራይ
ዉል፣ወይም እነዚህን ማስረጃዎች ማቅረብ ካልቻለ ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ
የመስተዳደር አካል የተሰጠ የፁሑፍ ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ
በአመልካቹ የሚሞላ እና በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ
ሥራ አድራሻ”፣
8.ወካዩ የንግድ ማህበር ከሆነ በዚህ አንቀፅ ከላይ ከተገለፁት በተጨማሪ የተረጋገጡ የመመስረቻ
ፅሁፍና የመተዳደሪያ ደንብ ወይም ድርጅቱ የተቋቋመበት ተመሳሳይ ሰነድ በኢትዮጵያ
ውስጥ ባሉት ሰነድን ለማረጋገጥ በህግ ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ ማስረጃ፣
9.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣
14.በዓለም አቀፍ ጨረታ አሸናፊ ሆነው የሚገቡ የውጭ አገር ድርጅቶች
የምዝገባ ምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚጠየቁ መስፈርቶች
በዓለም አቀፍ ጨረታ አሸናፊ ሆነው የሚገቡ የውጭ አገር ድርጅቶች የምዝገባ ምስክር
ወረቀት ለማውጣት ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ
አለበት፡-
1.የስራ አስኪያጁ የፀና ፓስፖርት ዋናው እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
2.የስራ አስኪያጁ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ የተነሳው ሁለት ፓስፖርት
መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
3.ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅ እና ፎቶ ኮፒ፣የስራ
አስኪያጁን የፀና ፓስፖርት ዋናው እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4.የማህበሩ ህጋዊ ሰውነትን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣
5.ማህበሩ በኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫፍ ለመክፈት መወሰኑን እና ስራ አስኪያጅ መመደቡን
የተረጋገጠ ቃለ-ጉባኤ ወይም ተመሳሳይ ሰነድ፣
6.ጨረታውን ከሰጠው አካል የጨረታ ስምምነት ሰነድና የይመዝገብልኝ የድጋፍ ደብዳቤ፣
7.የስራ ቦታ አድራሻ ማሳወቅ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ በአመልካቹ የሚሞላ እና
በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ አድራሻ”፣
8.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣
15.በሌሎች ህጎች እንዲነግዱ የተፈቀደላቸው ማህበራት የምዝገባ ምስክር
ወረቀት ለማውጣት የሚጠየቁ መስፈርቶች
በሌሎች ህጎች እንዲነግዱ የተፈቀደላቸው ማህበራት የምዝገባ ምስክር
ወረቀት ለማውጣት ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች
ማቅረብ አለበት፡-
1.በሌሎች ህጎች እንዲነግዱ የተፈቀደላቸው ማህበራት አግባብ ካለው
የሴክተር መስሪያ ቤት የተሰጠ የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣
2.ስለሚነግድቡት የስራ ዓይነት፣የካፒታል ምንጭ እና መጠን፣ስለትርፍ
አጠቃቀም፣የማህበሩ አስተዳደር እና መሰል ጉዳዮችን ያካተተ አግባብ ካለው
የሴክተር መስሪያ ቤት የተሰጠ ደብዳቤ፣
3.የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት
ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4.የስራ አስኪያጁን ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የተነሳው ሁለት
የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
የቀጠለ…

5.ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅ እና ፎቶ


ኮፒ፣የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
6.አመልካቹ የዋና የስራ አድራሻ እና የቅርንጫፍ የስራ አድራሻ ያለው ከሆነም
ይህንን የሚያረጋግጥ የአድራሻ ማረጋገጫ፣ለንግድ የሚጠቀምበት ቤት
የአመልካቹ የራሱ ከሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ፣ወይም የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ
ያላለፈበት የፀደቀ የኪራይ ዉል፣ወይም የመንግስት ቤቶች ከሆነ
በሚመለከተው የመንግስት አካል የሚሰጥ የኪራይ ዉል፤ወይም እነዚህን
ማስረጃዎች ማቅረብ ካልቻለ ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ
የመስተዳደር አካል የተሰጠ የፁሑፍ ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ በአመልካቹ
የሚሞላ እና በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ አድራሻ”፣
7.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣
16.የዘርፍ ማህበራት የምዝገባ ምስክር ወረቀት
የዘርፍ ማህበራት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ለማውጣት ከማመልከቻ
ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1. የስራ አስኪያጁ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ
የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
2. የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት
ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
3. ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅና ፎቶ
ኮፒ፣የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4. የተረጋገገጠ የመተዳደሪያ ደንብ ዋና ቅጅ፣
የቀጠለ…

5.አመልካቹ የዋና የስራ አድራሻ እና የቅርንጫፍ የስራ አድራሻ ያለው ከሆነም


ይህንን የሚያረጋግጥ የአድራሻ ማረጋገጫ፣ ለጽ/ቤት የሚጠቀምበት ቤት
የአመልካቹ የራሱ ከሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ፣ወይም የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ
ያላለፈበት የፀደቀ የኪራይ ዉል፣ወይም የመንግስት ቤቶች ከሆነ
በሚመለከተው የመንግስት አካል የሚሰጥ የኪራይ ዉል፤ወይም እነዚህን
ማስረጃዎች ማቅረብ ካልቻለ ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ
የመስተዳደር አካል የተሰጠ የፁሑፍ ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ
በአመልካቹ የሚሞላ እና በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ
አድራሻ”፣
6.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣
17.በውጭ አገር የተቋቋሙ የንግድ ምክር ቤቶች የቅርንጫፍ ምዝገባ
ምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚጠየቁ መስፈርቶች
በውጭ አገር የተቋቋሙ የንግድ ምክር ቤቶች የቅርንጫፍ ምዝገባ
ምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚጠይቅ አመልካች ከማመልከቻ ቅፁ
ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፣
1.እንዲመዘገቡ ከሀገራቸው ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ወይም
ኤምባሲዎቻቸው ወይም ከንግድ ምክር ቤቶቻቸው ወይም ከአገራቸው
አግባብ ካለው አካል የተፈቀደ ስለመሆኑ የፅሁፍ ማረጋገጫ፣
2.በተቋቋሙበት ሀገር የተሰጠ የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር
ወረቀት ወይም ተመሳሳይ ሰነድ፣
የቀጠለ…
3.ቅርንጫፍ ለመክፈት ያመለከተው ንግድ ምክር ቤት ለሚቋቋመው
ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የመደበውን ስራ አስኪያጅ ህጋዊ ደብዳቤ፣
4.የንግድ ምክር ቤቱ ስራ አስኪያጅ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት
ጊዜ የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
5.የአመልካቹ የስራ አድራሻ ማረጋገጫ የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ ያላለፈበት የፀደቀ
የኪራይ ዉል፣ወይም የመንግስት ቤቶች ከሆነ በሚመለከተው የመንግስት
አካል የሚሰጥ የኪራይ ዉል ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ በአመልካቹ የሚሞላ እና
በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ አድራሻ”፣

6.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣


18.የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ስለማሻሻል
የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ለማሻሻል የሚጠይቅ አመልካቹ
ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-

1.የስራ አስኪያጁ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ


የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
2.የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት
ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
3.ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅ እና ፎቶ
ኮፒ፣የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
የቀጠለ…
4.ማሻሻያው የሚደረገው በማህበሩ መተዳደሪያ እና መመስረቻ ፅሁፍ ላይ ከሆነ
የማህበሩ አባላት ማሻሻያ ያደረጉበት የተረጋገጠ ቃለ-ጉባዔ ዋና ቅጅ፣ማሻሻያው
ከካፒታል ጋር የሚያያዝ ከሆነ ከቃለ ጉባኤ በተጨማሪ ይህንኑ የሚያሳይ
ማረጋገጫ፣ወይም የአድራሻ ለውጥ ከሆነ ማሻሻያው የተወሰነበት የተረጋገጠ ቃለ-
ጉባዔ ዋና ቅጅ እና የአድራሻ ማረጋገጫ፣
5.አዲስ ግለሰብ የውጭ ሀገር ዜጋ በነባር የንግድ ማህበር ውስጥ እንዲገባ የሚያደርግ
ከሆነ የኢንቨስትመንት ይሁንታ፣
6.በነባር የንግድ ማህበር ውስጥ የሚገባ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ፁሑፍና
የመተዳደሪያ ደንብ ዋና ቅጅ፣የህጋዊ ሰውነት የምስክር ወረቀት ወይም ተመሳሳይ
ሰነድ እና አዲስ በሚቋቋመው ማህበር ውስጥ እንዲገባ ሥልጣን ባለው የማህበሩ
አካል መወሰኑን የሚያሳይ አግባብነት ባለው የኢትዮጵያ ሰነድ አረጋጋጭ የተረጋገጠ
ቃለ-ጉባዔ ወይም ደብዳቤ እና እንዲሁም ማህበሩ የውጭ አገር ድርጅት ከሆነ
የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣
7.ለግለሰብ ነጋዴ ማሻሻያው የስራ አድራሻ ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ በአመልካቹ የሚሞላ እና
በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ አድራሻ”፣
19.ስለምትክ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት
ምትክ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ለማግኘት የሚጠይቅ አመልካች
ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1.የስራ አስኪያጁ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የተነሳው ሁለት
የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
2.የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት
ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
3.ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅ እና ፎቶ
ኮፒ፣የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4.የተበላሸውን የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
5.የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የጠፋበት ከሆነ ከሚመለከተው የፖሊስ
አካል ማስረጃ፣
20.ምትክ የንግድ እንደራሴ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ለማግኘት
የሚጠየቁ መስፈርቶች
ምትክ የንግድ እንደራሴው የምዝገባ ምስክር ወረቀት ለማግኘት የሚጠይቅ አመልካች
ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1.የንግድ እንደራሴው ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ
የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
2.የንግድ እንደራሴው የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
3.ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅ እና ፎቶ
ኮፒ፣የእንደራሴው የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4.የተበላሸውን የንግድ እንደራሴው የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
5.የንግድ እንደራሴው የምዝገባ ምስክር ወረቀት የጠፋበት ከሆነ ከሚመለከተው
የፖሊስ አካል ማስረጃ፣
21.የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ስለመሰረዝ
የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ለመሰረዝ የሚጠይቅ
አመልካች ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ
አለበት፡-
1. የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች
የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ
ኮፒ፣
2. ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅ
እና ፎቶ ኮፒ የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ
ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም
ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና
አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
3. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ፣
የቀጠለ…

4. የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩን ስረዛ ቃለ-ጉባዔ ዋና ቅጅና


የኦዲት ሪፖርት፣
5. በአመልካቹ ወጪ በአንድ ወር ልዩነት ሁለት ጊዜ የአገር አቀፍ
ስርጭት ባላቸው ጋዜጦች የወጣ ማስታወቂያ ማስረጃ፣
የንግድ ማህበር ምዝገባ ስረዛ የሚፀናው አግባብ ያለው ባለስልጣን ስረዛውን
ተደራሽ በሆነ የኢንፎርሜሽን መገናኛ ቴክኖሎጂ አውታርን ተጠቅሞ
ካሳወቀበት ከአንድ ወር በኋላ፣
6. የንግድ ምዝገባ ስረዛ ከመከናወኑ በፊት ቀደም ብለው
የተሰጡ የንግድ ስራ ፈቃዶች እና የንግድ ስም
የምስክር ወረቀት፣
22.የንግድ እንደራሴ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ለመሰረዝ የሚጠየቁ
መስፈርቶች
የንግድ እንደራሴው ምዝገባ የምስክር ወረቀት ለመሰረዝ አመልካቹ ከማመልከቻ
ቅፁ ጋር የሚከተሉት ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1. የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም
የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና
አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
2. ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅ እና ፎቶ
ኮፒ፣
3. የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4.የንግድ እንደራሴው ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
5.የንግድ እንደራሴው ምዝገባ ስረዛ ከመከናወኑ በፊት ቀደም ሲል የተሰጠው
የንግድ እንደራሴው ልዩ የምስክር ወረቀት ተመላሽ መሆኑ መረጋገጥ አለበት፣
ክፍል ሦስት
የንግድ ስራ ፈቃድ
- ስለመስጠት፣
- ስለማደስ፣
- ስለማሻሻል፣
- ስለምትክ እና፣
- ስለስረዛ መስፈርቶች፣
23.የግለሰብ ነጋዴ የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት
የግለሰብ ነጋዴ የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚጠይቅ አመልካች
ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1. የአመልካቹ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት
ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
2. የግለሰቡን ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የተነሳው
ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
3. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
4. አመልካቹ የውጭ አገር ዜጋ ከሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣
የቀጠለ…
5.አመልካቹ የዋና የስራ አድራሻ እና የቅርንጫፍ የስራ አድራሻ ያለው ከሆነም ይህንን
የሚያረጋግጥ የአድራሻ ማረጋገጫ፣ለጽ/ቤት የሚጠቀምበት ቤት የአመልካቹ የራሱ ከሆነ
የባለቤትነት ማረጋገጫ፣ወይም የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ ያላለፈበት የፀደቀ የኪራይ
ዉል፣ወይም የመንግስት ቤቶች ከሆነ በሚመለከተው የመንግስት አካል የሚሰጥ የኪራይ
ዉል፤ወይም እነዚህን ማስረጃዎች ማቅረብ ካልቻለ ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ
የመስተዳደር አካል የተሰጠ የጽሁፍ ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ በአመልካቹ የሚሞላ እና
በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ አድራሻ”፣
6.የንግድ ስራ ፈቃድ የተጠየቀበት የስራ መደብ የብቃት ማረጋገጫ የሚያስፈልገው
ከሆነ ከሚመለከተው የሴክተር መስሪያ ቤት የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር
ወረቀት፣

 የግለሰብ ነጋዴ የንግድ ሥራ ፈቃድ ምስክር ወረቀትን በውክልና አስመዝግቦ ማግኘት


የተከለከለ ነው፣

 ግለሰብ ነጋዴ በውክልና የንግድ ሥራ ፈቃድ ምስክር ወረቀትን ለማውጣት ሲፈልግ


ወኪሉ በሕግ ሥልጣን በተሰጠው አካል የተሰጠ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
24.የሽርክና ማህበራት እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የንግድ ስራ ፈቃድ
የምስክር ወረቀት
የሽርክና ማህበራት እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት
ለማውጣት ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1.የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
2.የስራ አስኪያጅ እና የወኪሉ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን
ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
3.የንግድ ማህበሩ ስራ አስኪያጅ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ
የተነሳዉ ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
4.ሰነድን ለማረጋገጥ በህግ ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የማህበሩ
የመመስረቻ ፁሑፍና የመተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ፣
5.በሽርክና ማህበራትና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ውስጥ የውጭ ሀገር
ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በሚኖርበት ጊዜ ከሚመለከተው የመንግስት አካል
የተሰጠ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ማረጋገጫ እና የፀና ፓስፖርት ዋናው እና
አስፈላጊ ገፆች ፎቶኮፒ፣
6.በሽርክና ማህበራትና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ውስጥ አባል የሆነ የውጭ ሀገር የህግ
ሰውነት ያለው አካል ከሆነ፣
ሀ.ከተቋቋመበት አገር ህጋዊ ሰውነት ያገኘበትን ማረጋገጫ ሰነድ፣
ለ.በንግድ ማህበሩ ውስጥ ለመግባት መወሰኑን የሚያሳይ በአገሩ ህግ እና በኢትዮጵያ
የሰነዶች አረጋጋጭ የተረጋገጠ ቃለ-ጉባዔ ወይም ደብዳቤ ወይም ተመሳሳይ ሰነድ፣
ሐ.የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣
መ.በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 5 እና 6 መሰረት የሚቋቋም የንግድ ማህበር ቅርንጫፍ
የሚከፍት ከሆነ የቅርንጫፍ አድራሻ ማረጋገጫ በማመልከቻ ቅፅ ማሳወቅ፣
7.አመልካቹ የዋና የስራ አድራሻ እና የቅርንጫፍ የስራ አድራሻ ያለው ከሆነም ይህንን የሚያረጋግጥ
የአድራሻ ማረጋገጫ፣ለጽ/ቤት የሚጠቀምበት ቤት የአመልካቹ የራሱ ከሆነ የባለቤትነት
ማረጋገጫ፣ወይም የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ ያላለፈበት የፀደቀ የኪራይ ዉል፣ወይም የመንግስት ቤቶች
ከሆነ በሚመለከተው የመንግስት አካል የሚሰጥ የኪራይ ዉል፣ወይም እነዚህን ማስረጃዎች ማቅረብ
ካልቻለ ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ የመስተዳደር አካል የተሰጠ የጽሁፍ ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ በአመልካቹ
የሚሞላ እና በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ አድራሻ”፣
8.የንግድ ስራ ፈቃድ የተጠየቀበት የስራ መደብ የብቃት ማረጋገጫ የሚያስፈልገው ከሆነ
ከሚመለከተው የሴክተር መስሪያ ቤት የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣
25.የአክሲዮን ማህበር የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት
የአክሲዮን ማኀበር መሥራቾች የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ለማውጣት ከማመልከቻ ቅፁ ጋር
የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
2. የስራ አስኪያጅ እና የወኪሉ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም
የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች
የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
3. የአክሲዮን ማህበሩ ስራ አስኪያጅ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በ6 ወራት ጊዜ
ውስጥ የተነሳዉ ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
4. ማመልከቻው የተፈረመው በወኪል ከሆነ በሁሉም መስራች አባላት
የተሰጠ የውክልና ማረጋገጫ ሰነድ ዋናው እና የተረጋገጠ ቅጅ፣
5. የተረጋገጠ የማህበሩ የመመስረቻ ጽሁፍና የመተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ፣
የቀጠለ…
6.በአክሲዮን ማህበር ውስጥ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች
በሚኖርበት ጊዜ ከሚመለከተው የመንግስት አካል የተሰጠ የኢንቨስትመንት
ይሁንታ ማረጋገጫ እና የፀና ፓስፖርት ዋናው እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶኮፒ፣
7.በአክሲዮን ማህበር ውስጥ አባል የሆነ የውጭ ሀገር የህግ ሰውነት ያለው
አካል ከሆነ፣
ሀ.ከተቋቋመበት አገር ህጋዊ ሰውነት ያገኘበትን ማረጋገጫ ሰነድ፣
ለ.በንግድ ማህበሩ ውስጥ ለመግባት የተወሰነበት ሰነድን ለማረጋገጥ በህግ
ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ ቃለ- ጉባዔ ወይም ደብዳቤ ወይም
ተመሳሳይ ሰነድ፣
ሐ.የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣
መ.በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ 6 እና 7 መሠረት የሚቋቋም የንግድ ማህበር
ቅርንጫፍ የሚከፍት ከሆነ የቅርንጫፍ አድራሻ ማረጋገጫ በማመልከቻ
ቅፅ ማሳወቅ፣
የቀጠለ…
8.አመልካቹ የዋና የስራ አድራሻ እና የቅርንጫፍ የስራ አድራሻ ያለው ከሆነም
ይህንን የሚያረጋግጥ የአድራሻ ማረጋገጫ፣ ለጽ/ቤት የሚጠቀምበት ቤት
የአመልካቹ የራሱ ከሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ፣ወይም የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ
ያላለፈበት የፀደቀ የኪራይ ዉል፣ወይም የመንግስት ቤቶች ከሆነ
በሚመለከተው የመንግስት አካል የሚሰጥ የኪራይ ዉል፣ወይም እነዚህን
ማስረጃዎች ማቅረብ ካልቻለ ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ
የመስተዳደር አካል የተሰጠ የፁሑፍ ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ በአመልካቹ
የሚሞላ እና በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ አድራሻ”፣
9.ንግድ ስራ ፈቃድ የተጠየቀበት የስራ መደብ የብቃት ማረጋገጫ
የሚያስፈልገው ከሆነ ከሚመለከተው የሴክተር መስሪያ ቤት የተሰጠ
የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣
10.የአክሲዮን ድርሻ ሰርተፍኬት ናሙና እና የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ለመዝጋቢው
አካል መቅረብ አለበት፣
26.የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር
ወረቀት
የፌደራል እና የክልል መንግሥታት የልማት ድርጅቶች የንግድ ስራ ፈቃድ
የምስክር ወረቀት ለማውጣት ከማመልከቻ ቅጹ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች
ማቅረብ አለበት፡-
1. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
2. የተቋቋመበት ህግ፣
3. የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ የምደባ ደብዳቤ፣
4. የስራ አስኪያጁን ማንነት በግልፅ የሚያሳይ ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ
የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
5. የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
የቀጠለ…
6.ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ በድርጅቱ የበላይ ኃላፊ የተወከለበት
ደብዳቤ እና የወኪሉ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
7.አመልካቹ የዋና የስራ አድራሻ እና የቅርንጫፍ የስራ አድራሻ ያለው ከሆነም ይህንን
የሚያረጋግጥ የአድራሻ ማረጋገጫ፣ለጽ/ቤት የሚጠቀምበት ቤት የአመልካቹ የራሱ ከሆነ
የባለቤትነት ማረጋገጫ፣ወይም የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ ያላለፈበት የፀደቀ የኪራይ
ዉል፣ወይም የመንግስት ቤቶች ከሆነ በሚመለከተው የመንግስት አካል የሚሰጥ የኪራይ
ዉል፣ወይም እነዚህን ማስረጃዎች ማቅረብ ካልቻለ ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ
የመስተዳደር አካል የተሰጠ የጽሁፍ ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ በአመልካቹ የሚሞላ እና
በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ አድራሻ”፣
8.የንግድ ስራ ፈቃድ የተጠየቀበት የስራ መደብ የብቃት ማረጋገጫ
የሚያስፈልገው ከሆነ ከሚመለከተው የሴክተር መስሪያ ቤት የተሰጠ
የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣
27.የንግድ እንደራሴ ልዩ የምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚጠየቁ መስፈርቶች
የንግድ እንደራሴ ልዩ የምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚጠይቅ አመልካች ከማመልከቻ ቅፁ
ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1.የእንደራሴው የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
2.የእንደራሴውን ማንነት በግልፅ የሚያሳይ ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የተነሳው
ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
3.የእንደራሴው የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ
ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ
ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4.ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅ እና ፎቶ ኮፒ፣የእንደራሴው
የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ
ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች
ፎቶ ኮፒ፣
5.ለበጀት ዓመቱ ለደመወዝ እና ለስራ ማስኬጃ የሚሆን ቢያንስ ፩፻ሺ /አንድ መቶ ሺ/
የአሜሪካን ዶላር አገር ውስጥ በእንደራሴው ስም ለማስገባቱ ከባንክ የተሰጠ ማረጋገጫ፣
የቀጠለ…
6.አመልካቹ የዋና የስራ አድራሻ እና የቅርንጫፍ የስራ አድራሻ ያለው ከሆነም ይህንን
የሚያረጋግጥ የአድራሻ ማረጋገጫ፣ለጽ/ቤት የሚጠቀምበት ቤት የአመልካቹ የራሱ ከሆነ
የባለቤትነት ማረጋገጫ፣ወይም የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ ያላለፈበት የፀደቀ የኪራይ
ዉል፣ወይም የመንግስት ቤቶች ከሆነ በሚመለከተው የመንግስት አካል የሚሰጥ የኪራይ
ዉል፤ወይም እነዚህን ማስረጃዎች ማቅረብ ካልቻለ ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ
የመስተዳደር አካል የተሰጠ የጽሁፍ ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ
በአመልካቹ የሚሞላ እና በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ
ሥራ አድራሻ”፣
7.የንግድ እንደራሴው የሚያከናውናቸው ተግባራት መግለጫ፣
8.አመልካቹ የውጭ አገር ዜጋ ከሆነ የንግድ እንደራሴነት ልዩ የምስክር
ወረቀት እንደተሰጠው አግባብ ካለው የመንግስት አካል የመኖሪያ እና
የስራ ፈቃድ አውጥቶ የማቅረብ ግዴታ የገባበት ፅሁፍ አብሮ መቅረብ
ይኖርበታል፣
28.በዓለም አቀፍ ጨረታ አሸናፊ ሆነው የሚገቡ የውጭ አገር ድርጅቶች
የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚጠየቁ መስፈርቶች
በዓለም አቀፍ ጨረታ አሸናፊ ሆነው የሚገቡ የውጭ አገር ድርጅቶች የንግድ ስራ ፈቃድ
የምስክር ወረቀት ለማውጣት ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ
አለበት፡-
1.የስራ አስኪያጁ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ
የተነሳው ሁለት ፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
2.የስራ አስኪያጁ የፀና ፓስፖርት ዋናው እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
3.የስራ ቦታ አድራሻ ማሳወቅ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ በአመልካቹ
የሚሞላ እና በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ አድራሻ”፣
4.በዓለም አቀፍ ጨረታ አሸናፊ ሆኖ የገባ ከሆነ ጨረታውን ከሰጠው አካል
የጨረታ ስምምነት ሰነድና የይመዝገብልኝ የድጋፍ ደብዳቤ፣
5.የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
29.በሌሎች ህጎች እንዲነግዱ የተፈቀደላቸው ማህበራት የንግድ
ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት
በሌሎች ህጎች እንዲነግዱ የተፈቀደላቸው ማህበራት ለንግድ ስራ ፈቃድ
የምስክር ወረቀት ለማውጣት ከማመልከቻው ቅፁ ጋር የሚከተሉትን
ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1.የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
2.የስራ አስኪያጁ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ
የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች፣
3.የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም
የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና
አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4.ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅ እና ፎቶ
ኮፒ፣የወኪሉ እና የተወካዩ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
የቀጠለ…
5.አመልካቹ የዋና የስራ አድራሻ እና የቅርንጫፍ የስራ አድራሻ ያለው ከሆነም
ይህንን የሚያረጋግጥ የአድራሻ ማረጋገጫ፣ ለጽ/ቤት የሚጠቀምበት ቤት
የአመልካቹ የራሱ ከሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ፣ወይም የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ
ያላለፈበት የፀደቀ የኪራይ ዉል፣ወይም የመንግስት ቤቶች ከሆነ
በሚመለከተው የመንግስት አካል የሚሰጥ የኪራይ ዉል፣ወይም እነዚህን
ማስረጃዎች ማቅረብ ካልቻለ ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ
የመስተዳደር አካል የተሰጠ የፁሑፍ ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ
በአመልካቹ የሚሞላ እና በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ
አድራሻ”፣
6.የንግድ ስራ ፈቃድ የተጠየቀበት የስራ መደብ የብቃት ማረጋገጫ
የሚያስፈልገው ከሆነ ከሚመለከተው የሴክተር መስሪያ ቤት የተሰጠ
የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣
30.የንግድ ሥራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ስለማደስ
የንግድ ሥራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ለማደስ የሚጠይቅ
አመልካች ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች
ማቅረብ አለበት፡-
1.ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የግብር ክሊራንስ፣
2.ማህበር ከሆነ የኦዲት ሪፖርት፣
3.የስራ አስኪያጁን ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ
የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶ ግራፎች፣
የቀጠለ…
4.ማመልከቻው በወኪል የሚቀርብ ከሆነ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ እና የወኪሉ የታደሰ
የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም

ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣


5.አመልካቹ የዋና የስራ አድራሻ እና የቅርንጫፍ የስራ አድራሻ ያለው ከሆነም ይህንን
የሚያረጋግጥ የአድራሻ ማረጋገጫ፣ለጽ/ቤት የሚጠቀምበት ቤት የአመልካቹ የራሱ ከሆነ
የባለቤትነት ማረጋገጫ፣ወይም የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ ያላለፈበት የፀደቀ የኪራይ
ዉል፤ወይም የመንግስት ቤቶች ከሆነ በሚመለከተው የመንግስት አካል የሚሰጥ የኪራይ
ዉል፤ ወይም እነዚህን ማስረጃዎች ማቅረብ ካልቻለ ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ
የመስተዳደር አካል የተሰጠ የጽሁፍ ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ
በአመልካቹ የሚሞላ እና በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ
ሥራ አድራሻ”፣
31.ንግድ እንደራሴ ልዩ የምስክር ወረቀት ለማደስ የሚጠየቁ መስፈርቶች፣
የንግድ እንደራሴ ልዩ የምስክር ወረቀት ለማደስ የሚጠይቅ አመልካች
ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1.ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የግብር ክሊራንስ፣
2.የእንደራሴው ማንነት በግልፅ የሚያሳይ ባለፉት በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ
የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶ ግራፎች፣
3.ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ እና
የእንደራሴው እና የተወካዩ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4.ማህበር ከሆነ በሁሉም አባላት ተፈርሞ የተሰጠ የውክልና ማረጋገጫ ፎቶ
ኮፒ፣
የቀጠለ…
5.አመልካቹ የዋና የስራ አድራሻ እና የቅርንጫፍ የስራ አድራሻ ያለው ከሆነም
ይህንን የሚያረጋግጥ የአድራሻ ማረጋገጫ፣ ለጽ/ቤት የሚጠቀምበት ቤት
የአመልካቹ የራሱ ከሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ፣ወይም የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ
ያላለፈበት የፀደቀ የኪራይ ዉል፣ወይም የመንግስት ቤቶች ከሆነ
በሚመለከተው የመንግስት አካል የሚሰጥ የኪራይ ዉል፣ወይም እነዚህን
ማስረጃዎች ማቅረብ ካልቻለ ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ
የመስተዳደር አካል የተሰጠ የፁሑፍ ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ
በአመልካቹ የሚሞላ እና በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ
አድራሻ”፣
6.በሚታደስበት በጀት ዓመት 100ሺ (አንድ መቶ ሺ) የአሜሪካ ዶላር
በእንደራሴው ስም ወደ አገር ውስጥ ለማስገባቱ ከባንክ የተሰጠ ማረጋገጫ፣
7.የንግድ እንደራሴው የውጭ አገር ዜጋ ከሆነ ለዘመኑ የታደሰ የስራ እና
የመኖሪያ ፈቃድ፣
32.የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ስለማሻሻል
የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ለማሻሻል የሚጠይቅ አመልካች ከማመልከቻ
ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
2. የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት፣
3. ማሻሻያው የሚደረገው በማህበሩ መተዳደሪያ እና መመስረቻ ፅሑፍ ላይ ከሆነ
የማህበሩ አባላት ማሻሻያው ያደረጉበት የተረጋገጠ ቃለ-ጉባዔ ዋና ቅጅ፣ማሻሻያው
ከካፒታል ጋር የሚያያዝ ከሆነ በተጨማሪ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማረጋገጫ፣ወይም
የአድራሻ ለውጥ ከሆነ ማሻሻያው የተወሰነበት የተረጋገጠ ቃለ-ጉባዔ ዋና ቅጅ እና
የአድራሻ ማረጋገጫ በማመልከቻ ቅፅ ማሳወቅ፣
4. አዲስ ግለሰብ የውጭ ሀገር ዜጋ በነባር የንግድ ማህበር ውስጥ እንዲገባ የሚያደርግ
ከሆነ የኢንቨስትመንት ይሁንታ፣
5. አዲሱ አባል የሕግ ሰውነት ያለው አካል ከሆነ የዚሁ አዲስ አባል የመመስረቻ ፁሑፍና
የመተዳደሪያ ደንብ ዋና ቅጅ፣የመቋቋሚያ የምስክር ወረቀት ወይም ተመሳሳይ ሰነድ
እና አዲስ በሚቋቋመው ማህበር ውስጥ ለመግባት ሥልጣን ባለው የማህበሩ አካል
መወሰኑን የሚያሳይ አግባብነት ባለው የኢትዮጵያ ሰነድ አረጋጋጭ የተረጋገጠ ቃለ-
ጉባዔ ወይም ደብዳቤና ማህበሩ የውጭ ሀገር ከሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣
የቀጠለ…
6.የንግድ ስራ ፈቃድ ማሻሻያ የተጠየቀበት የስራ መደብ ቀደም ብለው
በነበሩት ውስጥ ያልተካተተ እና የብቃት ማረጋገጫ የሚያስፈልገው
ከሆነ ከሚመለከተው የሴክተር መስሪያ ቤት የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ
የምስክር ወረቀት፣
7.ማመልከቻው በወኪል የሚቀርብ ከሆነ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ ዋና
ቅጅ እና ፎቶ ኮፒ የወኪሉ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም
የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች
የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
8.የስራ አስኪያጁን ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ የተነሳው
ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶ ግራፎች፣
33.ስለምትክ የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት
ምትክ የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚጠይቅ አመልካች
ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1.የተበላሸውን የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት፣
2.የመደበኛ እድሳት ጊዜው ያለፈበት ወቅት ምትክ በሚጠየቅበት ጊዜ ከሆነ
ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የግብር ክሊራንስ፣
3.የጠፋበት ከሆነ ከሚመለከተው የፖሊስ አካል ማስረጃ፣
4.የስራ አስኪያጁን ማንነት በግልፅ የሚያሳይ ባለፉት በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ የተነሳው
ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶ ግራፎች፣
5.ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ እና የስራ
አስኪያጁን እና የተወካዩ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
34.ምትክ የእንደራሴ ልዩ የምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚጠየቁ
መስፈርቶች
ምትክ የንግድ እንደራሴ ልዩ የምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚጠይቅ አመልካች
ከማመልከቻው ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1.የተበላሸውን የንግድ የእንደራሴ ልዩ የምስክር ወረቀት፣
2.የንግድ እንደራሴ ልዩ የምስክር ወረቀት የጠፋበት ከሆነ ከሚመለከተው የፖሊስ አካል
ማስረጃ፣
3.የንግድ እንደራሴውን ማንነት በግልፅ የሚያሳይ ባለፉት በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ
የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶ ግራፎች፣
4.ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ እና የእንደራሴው እና
የተወካዩ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ
ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ
ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
5.የመደበኛ እድሳት ጊዜው ያለፈበት ወቅት ምትክ በሚጠየቅበት ጊዜ ከሆነ
ከሚመለከተው አካል የግብር ክሊራንስ፣
35. የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ስለመሰረዝ
የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ለመሰረዝ የሚጠይቅ አመልካች
ከማመልካቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1. ቀደም ሲል የተሰጠ እና የሚሰረዝ የንግድ ስራ ፈቃድ፣
2. የንግድ ስራ ፈቃድ ማሰረዢያ የግብር ክሊራንስ፣
3. የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት
ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
i. የስረዛው ጥያቄ የቀረበው በወኪል ከሆነ በሰነድ አረጋጋጭ
የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ፣

ii.ለንግድ ስራ ፍቃዱ የወሰደው የንግድ ስም ምዝገባ ሰርተፍኬት፣


36.ንግድ እንደራሴ ልዩ ምስክር ወረቀት ለመሰረዝ የሚጠየቁ
መስፈርቶቸ
የንግድ እንደራሴ ልዩ የምስክር ወረቀት ለመሰረዝ የሚጠይቅ አመልካች
ከማመልካቻው ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1.የንግድ እንደራሴው ልዩ የምስክር ወረቀት፣
2.የንግድ ስራ ፈቃድ መሰረዢያ የገቢ ግብር ክሊራንስ፣
3.የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4.የስረዛው ጥያቄ የቀረበው በወኪል ከሆነ በሰነድ አረጋጋጭ የተረጋገጠ
የውክልና ማስረጃ፣
ክፍል አራት
ስለ ልዩ የምሰክር ወረቀት ምዝገባ፤እድሳት፤ምትክ፤ማሻሻያ እና ስረዛ
37. የሆልዲንግ ኩባንያ ምዝገባ ልዩ የምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚጠየቁ
መስፈርቶች፤
የሆልዲንግ ኩባንያው ምዝገባ ልዩ የምስክር ወረቀት ለማውጣት ከማመልከቻው ቅፁ ጋር
የሚከተሉት ማስረጃዎች መቅረብ አለበት፡-
1.የሆልዲንግ ኩባንያ ስለመመስረቱ ሰነድን ለማረጋገጥ በህግ ስልጣን በተሰጠው አካል የተሰጠ
ማረጋገጫ፣
2.የሆልዲንግ ማህበሩ የቡድን አባላት የፀና የንግድ ስራ ፈቃድ ዋናው እና ፎቶ ኮፒ፣
3.የሆልዲንግ አስተባባሪ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ/ኃላፊ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት
ጊዜ ውስጥ የተነሣው ሁለት የፓስፖርት መጠን የላቸው ፎቶ ግራፎች፤

4.የሆልዲንግ አስተባባሪ የንግድ ማህበር ስራ አስኪያጅ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ


ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
38.የሆልዲንግ ኩባንያ ልዩ የምስክር ወረቀት እድሳት የሚጠየቁ መስፈርቶች
የሆልዲንግ ኩባንያው ልዩ የምስክር ወረቀትን ለማደስ የሚጠይቅ አመልካቹ ከማመልከቻ ቅጽ
ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1.የሆልዲንግ ኩባንያው የቡድን አባላት የፀና የንግድ ስራ ፈቃድ፣
2.የሆልዲንግ አስተባባሪ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ/ኃላፊ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት
ጊዜ ውስጥ የተነሣው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶ ግራፎች፣
3.የሆልዲንግ አስተባባሪ የንግድ ማህበር ስራ አስኪያጅ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ
ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4.ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ ዋና ቅጅ እና ፎቶ ኮፒ፣የወካዩ
እና የወኪሉ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ
ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ
ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
39.የሆልዲንግ ኩባንያ ልዩ የምስክር ወረቀት ምትክ ለማውጣት የሚጠየቁ
መስፈርቶች
ምትክ ልዩ የምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚጠይቅ አመልካች ከማመልከቻ
ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለባቸው፡-
1.የተበላሸውን ልዩ የምስክር ወረቀት፣
2.የሆልዲንጉ ኩባንያ ልዩ የምስክር ወረቀት የጠፋበት ከሆነ ከሚመለከተው
የፖሊስ አካል የተሰጠ ማስረጃ፣
3.የሆልዲንግ አስተባባሪ የንግድ ማህበር ስራ አስኪያጅ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ
መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም
ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ
ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4.የሆልዲንግ አስተባባሪ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ/ኃላፊ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ
በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የተነሣው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው
ፎቶ ግራፎች፣
40.የሆልዲንግ ኩባንያ ልዩ የምስክር ወረቀት ማሻሻያ ለማውጣት የሚጠየቁ
መስፈርቶች
የሆልዲንግ ኩባንያ ልዩ የምስክር ወረቀት ለማሻሻል የሚጠይቅ አመልካች
ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለባቸው፡-
1.ከአባላቱ መካከል በማናቸውም ምክንያት ከቡድኑ ቢወጡ ወይም ሌላ አዲስ
የቡድን አባል ወደ ቡድኑ ሲገባ በሠነድ አረጋጋጭ የተረጋገጠ ቃለ ጉባኤ፣
2.የሆልዲንግ ኩባንያ ልዩ የምስክር ወረቀት፣
3.የሆልዲንግ አስተባባሪ የንግድ ማህበር ስራ አስኪያጅ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ
መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም
ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ
ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4.የሆልዲንግ አስተባባሪ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ/ኃላፊ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ
በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የተነሣው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው
ፎቶ ግራፎች፤
41.የሆልዲንግ ኩባንያ ልዩ የምስክር ወረቀት ለመስረዝ የሚጠየቁ መስፈርቶች
የሆልዲንግ ኩባንያ ልዩ የምስክር ወረቀት ለመሰረዝ የሚጠይቅ አመልካች
ከማመልከቻው ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1.የሆልዲንግ ኩባንያው ልዩ የምስክር ወረቀት፣
2.የሆልዲንግ ስምምነት ስለመፍረሱ ሰነድን ለማረጋገጥ በህግ ስልጣን
በተሰጠው አካል የተረጋገጠ ቃለ ጉባኤ፣
3.የሆልዲንጉ ስምምነት ስለመፍረሱ አገር አቀፍ ስርጭት ባላቸው ጋዜጦች
አንድ ጊዜ የታወጀበት፣
የንግድ ማህበር ምዝገባ ስረዛ የሚፀናው አግባብ ያለው ባለስልጣን ስረዛውን ተደራሽ
በሆነ የኢንፎርሜሽን መገናኛ ቴክኖሎጂ አውታርን ተጠቅሞ ካሳወቀበት ከአንድ ወር
በኋላ፣
4.የሆልዲንግ አስተባባሪ የንግድ ማህበር ስራ አስኪያጅ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ
መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም
ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ
ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
42.የጠረፍ ንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚጠየቁ
መስፈርቶች
የጠረፍ ንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚጠይቅ አመልካች ከማመልከቻ ቅፁ ጋር
የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1.የአመልካቹን ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን
ያላቸው ፎቶግራፎች፣
2.የአመልካቹ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ
ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
3.አመልካቹ የዋና የስራ አድራሻ እና የቅርንጫፍ የስራ አድራሻ ያለው ከሆነም ይህንን የሚያረጋግጥ
የአድራሻ ማረጋገጫ፣ለንግድ የሚጠቀምበት ቤት የአመልካቹ የራሱ ከሆነ የባለቤትነት
ማረጋገጫ፣ወይም የኪራይ ከሆነ ጊዜዉ ያላለፈበት የፀደቀ የኪራይ ዉል፣ወይም የመንግስት ቤቶች
ከሆነ በሚመለከተው የመንግስት አካል የሚሰጥ የኪራይ ዉል፣ወይም እነዚህን ማስረጃዎች ማቅረብ
ካልቻለ ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ የመስተዳደር አካል የተሰጠ የጽሁፍ ማረጋገጫ፤
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ በአመልካቹ የሚሞላ
እና በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ አድራሻ”፣
4.ለንግድ ስራዉ የመደበዉ ካፒታል ማሳወቅ፣
5.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣
43.የጠረፍ ንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ለመሰረዝ የሚጠየቁ መስፈርቶች
የጠረፍ ንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ለመሰረዝ የሚጠይቅ አመልካች
ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1.የአመልካቹ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት
ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
2.ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የውክልና ማስረጃ ዋና ቅጅ እና ፎቶ
ኮፒ፣የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
3.የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ፣
4.የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩን ስረዛ ቃለ-ጉባዔ ዋና ቅጅ እና የኦዲት
ሪፖርት፣
44.የጠረፍ ንግድ ልዩ የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ለማውጣት
የሚጠየቁ መስፈርቶች
የጠረፍ ንግድ ልዩ የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚጠይቅ
አመልካች ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1.የጠረፍ ንግዱ ከሚካሄድበት የአካባቢ መስተዳድር ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው እና
ነዋሪ ስለመሆኑ የሚገልፅ ማረጋገጫ፣
2.የጠረፍ ንግድ ስራ ፈቃድ ለማውጣት በሚመለከተው አካል የጠረፍ ንግድ እንዲነግድ
የተፈቀደለት ስለመሆኑ የተሰጠ የፅሑፍ ማረጋገጫ፣
3.የግለሰቡን ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የተነሣው ሁለት
የፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶ ግራፎች፣
4.የግለሰቡ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ
ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ
ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
5.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣
6.ግለሰቡ ስለሚሰራበት አድራሻ ከአካባቢዉ የመስተዳደር አካል የተሰጠ የፁሑፍ
ማረጋገጫ፣
የሚለው ተሰርዞ “አግባብ ያለው አካል በሚያዘጋጀው የምዝገባ ቅፅ ላይ በአመልካቹ የሚሞላ እና
በፊርማው የሚረጋገጥ የአመልካች የንግድ ሥራ አድራሻ”፣
45.የጠረፍ ንግድ ልዩ የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ለማደስ የሚጠየቁ
መስፈርቶች
የጠረፍ ንግድ ልዩ የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ለማደስ የሚጠይቅ
አመልካች ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ
አለበት፡-
1.ከሚመለከተው አካል የግብር ክሊራንስ፣
2.ከሚመለከተው የአካባቢ መስተዳድር የንግድ ስራው እንዲቀጥል የተሰጠ
የድጋፍ ደብዳቤ፣
3.የግለሰቡን ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የተነሳው
ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶ ግራፎች፣
4.የአመልካቹ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት
ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
46.የጠረፍ ንግድ ልዩ የንግድ ስራ ፈቃድ ምትክ የምስክር ወረቀት ለማግኘት
የሚጠየቁ መስፈርቶች
ምትክ የጠረፍ ንግድ ልዩ የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ለማግኘት
የሚጠይቅ አመልካች ከማመልከቻው ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች
ማቅረብ አለበት፡-
1.የተበላሸውን የጠረፍ ንግድ ልዩ የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት፣
2.የጠፋበት ከሆነ ከሚመለከተው የፖሊስ አካል የተሰጠ ማስረጃ፣
3.የመደበኛ እድሳት ጊዜው ያለፈበት የጠረፍ ንግድ ልዩ የንግድ ስራ ፈቃድ
ምትክ በሚጠየቅበት ጊዜ ከሆነ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የግብር
ክሊራንስ፣
47.የጠረፍ ንግድ ልዩ የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ስረዛ የሚጠየቁ
መስፈርቶች
የጠረፍ ንግድ ልዩ የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ለመሰረዝ
የሚጠይቅ አመልካች ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች
ማቅረብ አለበት፡-
1.የጠረፍ ንግድ ልዩ የንግድ ስራ ፈቃድ፣
2.ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የስረዛ ግብር ክሊራንስ፣
3.የአመልካቹ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት
ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
4.የጠረፍ ነጋዴው በጠረፍ ንግድ መመሪያ የተፈቀዱ የምርት ዓይነቶችን
ለአካባቢው ህብረተሰብ ያላቀረበ ከሆነ፣
48.የፍሬንቻይዚንግ ልዩ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ለማግኘት የሚጠየቁ
መስፈርቶች
የፍሬንቻይዚንግ ልዩ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ለማግኘት የሚጠይቅ አመልካች ከማመልከቻ
ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1.የፍሬንቻይዝ ምዝገባ አመልካች በሠነድ አረጋጋጭ የፀደቀ የፍሬንቻይዚንግ ውል ዋናውና
የተረጋገጠ ፎቶ ኮፒ፣
2.የፍሬንቻይዘሩ (ውል ሰጪ) የተመዘገበበትን ምስክር ወረቀት ሰነድን ለማረጋገጥ በህግ
ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ፣
3.የፍሬንቻይዚ (ውል ተቀባይ) የፀና ንግድ ስራ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ፣
4.የፍሬንቻይዚው ስራ አስኪያጅ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የተነሳው
ሁለት የፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶ ግራፎች፣
5.የፍሬንቻይዚው ስራ አስኪያጅ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት
ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን
እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
6.ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ ዋና ቅጅ እና ፎቶ ኮፒ፣የወካዩ
እና የወኪሉ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ
ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ
ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
49.የፍሬንቻይዚንግ ልዩ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ለማደስ የሚጠየቁ
መስፈርቶች፤
የፍሬንቻይዚንግ ልዩ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ለማደስ የሚጠይቅ
አመልካች ከማመልከቻ ቅጽ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ
አለበት፡-
1.የፍሬንቻይዝ ልዩ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
2.የፍሬንቻይዚው ስራ አስኪያጅ የፀና ንግድ ስራ ፈቃድ ዋና ቅጅ እና ፎቶ ኮፒ፣
3.የፍሬንቻይዚው ስራ አስኪያጅ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት ጊዜ
ውስጥ የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን፣ያላቸው ፎቶ ግራፎች፣
4.የፍሬንቻይዚው ስራ አስኪያጅ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና
ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ
መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
5.ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ፣ የወካዩ እና የወኪሉ
የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ
ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና
አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
50.የፍሬንቻይዚንግ ልዩ የንግድ ስራ የምስክር ወረቀት ምትክ ለማግኘት
የሚጠየቁ መስፈርቶች
ምትክ የፍሬንቻይዚንግ ልዩ የምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚጠይቅ አመልካች
ከማመልከቻው ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፡-
1.የተበላሸውን የፍሬንቻይዚንግ ልዩ የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት፣
2.የጠፋበት ከሆነ ከሚመለከተው የፖሊስ አካል የተሰጠ ማስረጃ፣
3.የፍሬንቻይዚው ስራ አስኪያጅ ማንነት በግልፅ የሚያሳይ በስድስት ወራት
ጊዜ ውስጥ የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን፣ያላቸው ፎቶ ግራፎች፣
4.ማመልከቻው በወኪል የቀረበ ከሆነ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ ዋና ቅጅ እና
ፎቶ ኮፒ፣የወካዩ እና የወኪሉ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም
የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች
የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
51.የፍሬንቻይዚንግ ልዩ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ስረዛ የሚጠየቁ
መስፈርቶች
የፍሬንቻይዚንግ ልዩ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ለመሰረዝ የሚጠይቅ
አመልካች ከማመልከቻ ቅፁ ጋር የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ
አለበት፡-
1.የፍሬንቻይዘሩ እና የፍሬንቻይዚ ውል የፀደቀ የማፍረሻ ሰምምነት ሰነድ፣
2.የፍሬንቻይዚንግ ልዩ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
3.ማመልከቻው በወኪል የሚቀርብ ከሆነ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ ዋና ቅጅ
እና ፎቶ ኮፒ፣የወካዩ እና የወኪሉ የታደሰ የቀበሌ/ወረዳ መታወቂያ ወይም
የፀና ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ወይም ከመሥሪያ ቤቶች
የሚሰጡ መታወቂያዎችን ዋናውን እና አስፈላጊ ገፆች ፎቶ ኮፒ፣
52. አምራቾች በችርቻሮ መሸጥ የሚችሏቸው የምርት ዓይነቶች፣
አምራቾች ያመረቱትን ምርቶች በችርቻሮ መሸጥ የሚችሏቸው የምርት ዓይነቶች
የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. በሞተር ኃይል የሚሰሩ የማምረቻ ማሽኖች፣
2. በሞተር ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች፣
3. ዳቦ እና ጣፋጭ ምግቦች፣
4. የቢሮ እና የቤት መገልገያ ዕቃዎች፣
5. የሙዚቃ መሳሪያዎች፣
6. ሶፍትዌር፣
7. ብስክሌቶች፣
8. አሳንሰር እና የተንቀሳቃሽ ደረጃዎች፣
9. የህክምና መሳሪያዎች፣
10. ለምርምር የሚውሉ ኬሚካሎች፣
11. ሬንጅ፣
12. የሲሚንቶ እና የሴራሚክ ውጤቶች፣
13. ሌሎች በባህሪያቸው በችርቻሮ ለመሸጥ የሚያስገድዱ ምርቶች መሆናቸው በሚኒስቴሩ
የታመነበት ሲሆን፣
አምራቾች ከምርት ባህሪያቸው የተነሳ ለችርቻሮ ሽያጭ አስገዳጅነት ያላቸው ምርቶች
በችርቻሮ ሊሸጡ ይችላሉ፣
53.አስመጪዎች በችርቻሮ መሸጥ የሚችሏቸው የምርት ዓይነቶች፣
አስመጪዎች ያስመጡትን ምርቶች በችርቻሮ መሸጥ የሚችሏቸው የምርት
ዓይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. በሞተር ኃይል የሚሰሩ የማምረቻ ማሽኖች፣
2. በሞተር ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች፣
3. የቢሮ እና የቤት መገልገያ ዕቃዎች፣
4. የሙዚቃ መሳሪያዎች፣
5. ሶፍትዌር፣
6. ብስክሌቶች፣
7. አሳንሰር እና የተንቀሳቃሽ ደረጃዎች፣
8. የህክምና መሳሪያዎች፣
9. ለምርምር የሚውሉ ኬሚካሎች፣
10.ሬንጅ፣
11.ሌሎች በባህሪያቸው በችርቻሮ ለመሸጥ የሚያስገድዱ ምርቶች መሆናቸው በሚኒስቴሩ
የታመነበት ሲሆን፣

አስመጪዎች ከምርት ባህሪያቸው የተነሳ ለችርቻሮ ሽያጭ አስገዳጅነት


ያላቸው ምርቶች በችርቻሮ ሊሸጡ ይችላሉ፣
ክፍል አምስት
54. መመሪያ ስለማውጣት፣
1.ለዚህ ደንብ አፈፃፀም ሚኒስቴሩ መመሪያዎችን ማውጣት ይችላል፡፡
55. ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ደንቦችና አሰራሮች፣

2.ከዚህ ደንብ ጋር የሚቃረን ማንኛውም ደንብ ወይም የተለምዶ አሰራር በዚህ


ደንብ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡

ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ

ይህ ደንብ ከመስከረም 4 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡


ግና ለሁ
አመ ሰ

You might also like