You are on page 1of 55

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ንግድ ቢሮ
.
የንግድ አሰራርና ህጋዊነት
የሥራ ማንዋል

ለኢንስፔክሽን ባለሙያዎች የተዘጋጀ ስልጠና


ሰኔ 2013 ዓ/ም

አቅራቢ፡- ሰፋዓለም አቦረዳኝ


የስልጠናው ገዢ ህጎች

ተንቀሳቃሽ ሰዓት አክብሮ


ስልክን በመገኘት
ማጥፋት በአግባቡ
/make it መጠቀም
silent
በንቃት መሳተፍ
ከዚህ ስልጠና ምን እንጠብቃለን ?
የስልጠናው ይዘት

ክፍል አንድ
 መግቢያ
 የማንዋሉ ዓላማ
 የማንዋሉ አስፈላጊነት
 በማንዋሉ ውስጥ የተካተቱ ዋና ዋና
ተግባራት
የቀጠለ …

ክፍል ሁለት
የንግድ ህጋዊነት ቁጥጥር
የተደራጀና የጠራ የነጋዴ መረጃ መያዝ፣
የህብረተሰቡን ጤንነት፣ ደህንነት፣ ባህልና
ፀጥታ የሚያውኩ ህገ-ወጥ የንግድ ተግባር
ስለመከላከል፣
የቀጠለ …

ክፍል ሦስት
ስምሪት፡ ስነ-ምግባር፡ አሰራር የውስጥ እና
የውጪ ኢንስፔክሽን
ክፍል አራት
ሕገ-ወጥ ንግድ ሥራ እና እርምጃ አወሳሰድ
ለክስ የሚያበቁ ጥፋቶች
ክፍል አንድ
1.1. መግቢያ
የንግድ ክትትልና ቁጥጥር ስራውን ለውጤታማ
ለማድረግ ቀደም ሲል ወጥቶ የነበረው የንግድ ምዝገባና
ፍቃድ አዋጅ 686/2002፣ 980/2008 እና
የማስፈጸሚያ ደንብ ቁጥር 392/2009 መነሻ ያደረገ
የአሰራር ማንዋል በማዘጋጀት ህገ-ወጥ የንግድ
እንቅስቃሴዎች ለመግታት ጥረት ተደርጋል፤
የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ማሻሻያ ቁጥር
1150/2011 እና እሱን ለማስፈፀም ደንብ ቁጥር
461/2012 የተተካ በመሆኑ ቀደም ሲል የነበረውን
የአሰራር እና ህጋዊነት የማስከበር ማንዋል አዲስ
… የቀጠለ
በBPR ጥናት ውጤት መሰረት በዳይሬክቶሬቱ
የሚመደቡ ፈፃሚዎች ተልእኮአቸውን መፈጸም
የሚችሉበትን ተጨማሪ ማብራሪያ ማዘጋጀት
በማስፈለጉ፤
ግልጽነት ላይ የተመሠረተ አገልግሎት ለመስጠት፤
ሠራተኛውም ወጥነት ያለው የአሠራር ዘዴ
እንዲከተል ለማድረግ ይቻል ዘንድ የአሠራር ማንዋል
ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኗል፤
በተለይ ህገ-ወጦች ላይ የሚወሰደዉ እርምጃ የበለጠ
ፍትሃዊ እና አስተማሪነቱ ጤናማ መሆኑን ለማረጋገጥ፣
1.2. የማንዋሉ አላማ

የንግድ አሰራሩ ህግን ተከትሎ እንዲከናወን


በማስቻል ፍትሃዊ፤ ፈጣን፤ ውጤታማ፤ ጥራትና
ምቹነት ያለው አሰራር እንዲኖር በማድረግ
ደንበኛውን/ተገልጋዩን/ ማርካት፤
ባለሙያዎች ሥራቸውን ከማዕከል እስከ ወረዳ
ድረስ ወጥነት ባለው አግባብ እንዲያከናወኑ
ማስቻል፤
የንግድ ህገ-ወጥነትን የመከላከል አፈፃፀም
የተሳካና ውጤታማ እንዲሆን አስተዋጽኦ
1.3. የማንዋሉ አስፈላጊነት
 የወጡ አዋጆችን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ የሚታዩ
ክፍተቶችን ለመሙላት፤
 በባለሙያው፣ በነጋዴውና በሸማቹ ዘንድ የሚታዩ
አላስፈላጊ መጉላላትን ለመቅረፍ፤
 ጊዜንና ንብረትን በአግባቡ ለመጠቀም ፤
 በህገ-ወጦች ላይ የሚወሰደዉ እርምጃ ፍትሃዊ እና
አስተማሪ እንዲሆን ለማስቻል፣
 የተጠያቂነት አሰራር እንዲኖር፤
1.4. በማንዋሉ ውስጥ የተካተቱ ዋና ዋና
ተግባራት
ጥናት ማካሄድ፣ ሥልጠና መስጠት፤
ህዝብ ተሳትፎን ማሳደግ፣
የንግድ ሥራ ኢንስፔክሽን /የውስጥ እና የውጪ/
የህጋዊ ስነ-ልክ ካሊብሬሽንና ኢንስፔክሽን
የክትትልና ድጋፍ ተግባራት
ቅሬታ፣ አቤቱታ መቀበል ማጣራትና ምላሽ
መስጠት
ለኢንስፔክሽን የሚያገለግሉ ልዩ-ልዩ ቅጻ-ቅጾች
ማዘጋጀት
ክፍል ሁለት
የንግድ ህጋዊነትን ስለማስከበር
 የንግድና የግብይት ስርዓታችን ቁልፍ ችግሮች
ተብለዉ ከተለዩ እጥረቶች መካከል አንዱና ዋናዉ
የመንግስት ህግ የማስከበር አቅምና አሰራር ደካማ
መሆን ነው፤
 ነፃ ገበያ ስርዓት በሚከተሉ ሀገራት መንግስት
የንግድ ስርዓቱን የሚያዛቡ ህገ-ወጥ አሰራሮችን
በመከላከል የነጋዴዉንና የሸማቹን ሚዛናዊ ጥቅም
የማስጠበቅ ሚና አለዉ፡፡
 የንግድ ህግ ማስከበር አቅም ጉድለቶች
የመረጃ ስርዓት፣
…የቀጠለ
የክህሎት፣ የአመለካከትና የአሰራር እጥረቶች
(ቁጥጥርና እርምት አወሳሰድ ላይ የሚታዩ)
እነዚህን ችግሮች ፈትሾ ለማስተካከል ግልፀኝነት
ያለው ወጥ አሰራር መፍጠር ይገባል፡፡
2.1. የተደራጀና የጠራ የነጋዴ መረጃ መያዝ፣
የተደራጀ፣ ግልፅና ተጠያቂነት ሊያመጣ የሚችል
መረጃ ስርዓት አለመዳበር ስነ-ምግባር ለጎደላቸዉ
ህገ-ወጥነት ምሽግ ነዉ፡፡
በመሆኑም መረጃ ላይ የሚታየዉን ደካማ አሰራር
መቀየርና ማሻሻል የክትትልና ቁጥጥር ቁልፍ
ተግባር ተደርጎ ተወስዷል፡፡
2.1.1. ነጋዴዉን በአድራሻዉ በብሎክ ስርዓት
መከፋፈል (የነጋዴ መረጃ አደረጃጀት)
ነጋዴዎች/የንግድ ድርጅቶች/ መረጃ፣
በአድራሻ፣ በንግድ ዘርፍ፣ በንግድ መስክ፣ (በንግድ
ምዝገባና ንግድ ፈቃዱ፣ በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር)
መዝግቦ ለድጋፍና ክትትል ስራዎቻችን ምቹ በሚሆን
መንገድ እንዲደራጅ ይደረጋል፡፡
 ነጋዴዉ በአካባቢዉ በየልማት ቀጠናዉ በብሎክ
እንዲከፋፈልና በግልጽ እንዲለይ ማድረግ ይጠበቃል፡፡
በዚህ አግባብ የተደራጀ መረጃ ለንግድ ኢንስፔክሽንና
ሬጉላቶሪ ባለሙያዎች በቋሚነት ለድጋፍና ክትትል
ስራዎች ባለቤት ይመደባል፡፡
2.1.1. ነጋዴዉን በአድራሻዉ በብሎክ ስርዓት
መከፋፈል (የነጋዴ መረጃ አደረጃጀት)
ነጋዴዎች/የንግድ ድርጅቶች/ መረጃ፣
በአድራሻ፣ በንግድ ዘርፍ፣ በንግድ መስክ፣ (በንግድ
ምዝገባና ንግድ ፈቃዱ፣ በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር)
መዝግቦ ለድጋፍና ክትትል ስራዎቻችን ምቹ በሚሆን
መንገድ እንዲደራጅ ይደረጋል፡፡
 ነጋዴዉ በአካባቢዉ በየልማት ቀጠናዉ በብሎክ
እንዲከፋፈልና በግልጽ እንዲለይ ማድረግ ይጠበቃል፡፡
በዚህ አግባብ የተደራጀ መረጃ ለንግድ ኢንስፔክሽንና
ሬጉላቶሪ ባለሙያዎች በቋሚነት ለድጋፍና ክትትል
ስራዎች ባለቤት ይመደባል፡፡
ከነጋዴዎቹ መካከል በአፈጻጸማቸው የተሻ”ሉ ነጋዴዎችን
ክፍል ሦስት
የንግድ ህጋዊነት ክትትልና
ቁጥጥር ስራዎች ትኩረት

17
3.1 የህብረተሰቡን ጤንነት፣ ደህንነት፣ ባህልና ፀጥታ
የሚያውኩ ህገ-ወጥ የንግድ ተግባር ስለመከላከል፣
• ነጋዴ የህብረተሰቡን ጤንነትና የአካባቢ ደህንነቱን ጠብቆ
መስራት ይጠበቅበታል፡፡
• ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር ቅንጅታዊ
አሰራር በመፍጠር እነዚህን ህገ-ወጥ ተግባራት መከላከል
ይጠበቅበታል፡፡
3.2 ቢሮዉ የንግድ ፈቃድ የማይሰጥባቸዉ መጤ
ባህሎችን ስለመከላከል፣
• በየደረጃው የሚገኝ አመራር ከሚመለከታቸው ጋር ቅንጅታዊ
አሰራር መፍጠር (የመግባቢያ ሰነድ መፈራረም) ይጠቅበታል፣
• የጥቆማ ስልኮችን በየቦታዉ ለህብረተሰቡ በሚታይ ቦታ
መለጠፍና ማስተዋወቅ
• ህብረተሰቡ ጥቆማ እንዲያቀርብ ማበረታታት፣
• ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ፖሊስ፣
ሠላምና ጸጥታ (ደንብ ማስከበር) ት/ጽ/ቤት፣ ጤና ቢሮ፣
አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን… ወዘተ እነዚህን ህገ-ወጥ
ተግባራት መከላከል ይጠበቅበታል፡፡
3.3. የምርት ጥራትን ስለመከታተል፣

• ሸማቹ ማህበረሰብ ጥራት ያለዉ ምርት የማግኘት መብት


አለዉ፡፡
• በከተማችን ከባዕድ ነገሮች ጋር የተደባለቀ ምርት፣
የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸዉና የተበላሹ የኢንዱስትሪ
ምርቶች ለገበያ ይቀርባሉ፣
• በኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ እና የጥራትና ተስማሚነት
ምዘና ባለስልጣን በኩል የተቀመጡ አስገዳጅ የኢትዮጵያ
ደረጃዎችን
• የመጠቀሚያ ጊዜ፣ የምርቶች መጠን (ክብደትና ስፍረት)
ማእከል በማድረግ መስራት፤
3.4. የደረሰኝ ግብይትና መረጃ አያያዝ

 የአንድ ነጋዴ ህጋዊነት መገለጫዎች መካከል በህጋዊ ደረሰኝ


ላይ የተመሰረተ ግብይት ማካሄዱ ነዉ፡፡
 በግብይት ተዋናዮች መካከል የደረሰኝ ቅብብሎሽ መኖር
እንዳለበት የንግድ አሰራርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ
እንዲሁም የግብር ስርዓቱን ለመደንገግ በወጡ አዋጆችና
ደንቦች ላይ ሰፍሯል፡፡ 
ስለደረሰኝ አሰራር
 የመግዣ ደረሰኞች (Payment Vouchers)
 የመሸጫ ደረሰኞች (Receipts)
3.5. ለንግዱና ለሸማቹ ማህበረሰብ ስልጠና
መስጠትና ግንዛቤ ማስጨበጥ
 የንግዱና ሸማቹ ማህበረሰብ የአመለካከትና የክህሎት
ለማሳደግ ለግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች ጊዜ ሰጥቶ መስራት
ይገባል፡
ለንግዱ ማህበረሰብ
 በነፃ ገበያ ስርዓቱ ዉስጥ ሊከተለዉ ስለሚገባ የንግድ አሰራር

 ፍትሃዊ ያልሆነ የንግድ አሰራርና ተጽእኖ መከላከል
ስለሚቻልበት፣
 የሸማች ደህንነትን ስለማስጠበቅ
 የሸማቹ ማህበረሰብ በነጻ ገበያ ስርዓቱ ውስጥ ደህንነቱንና
3.6. የምርት ወይም አገልግሎት ዋጋ ክትትል
• በቅድመ ሽያጭ የዋጋ ቁጥጥር የሚደረግባቸዉ ሸቀጦችን
የሚመለከት ሲሆን እነዚህ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጥ
መሆናቸዉ በንግድ ሚኒስቴር የህዝብ ማስታወቂያ
የወጣባቸዉና ዋጋ ተመን የተተመነባቸዉ ሸቀጦች ናቸዉ፡፡
• በድህረ ሽያጭ የዋጋ ክትትል በነጻ ገበያ የሚቀርቡ ሸቀጦች
የሚስተዋል ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ተከታትለን
ስርዓት የምናስይዝበት የዋጋ ክትትል ስርኣት ነዉ፡፡
ክፍል አራት

የአሰራር ስምሪት፡ ስነ-ምግባር፡


የውስጥ እና የውጪ
ኢንስፔክሽን
4.1. የንግድ ኢንስፔክሽን ባለሙያ ስምሪት

• የክትትል ሰራተኞች በየቀጠናዉ /በመንደር/ በቋሚነት


ይመደባሉ፤
• የንግድ ክትትልና ቁጥጥር እና የህጋዊ ስነ-ልክ ባለሙያዎች
ተቀናጅተዉ በየቀጠናዉ ስምሪት ይወስዳሉ፤
• ተቆጣጣሪዎች በተመደቡበት ቀጠና የነጋዴዉን የጠራ መረጃ
ይይዛሉ፤
• በየሳምንቱ የመስክ ክትትልና ቁጥጥር ፕሮግራም አዘጋጅተዉ
ከፀደቀ በኋላ የእለት ስምሪት ይወስዳሉ፤
• የስምሪት ፕሮግራሙ በመደበኛ የስራ ሰዓት ብቻ ያከናውናሉ፤
• በበዓላት ቀናት፣ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ከስራ ሰዓት ውጪ
ለሚኖር ስምሪት ከሚመለከተው የስራ ኃላፊ ፍቃድ የተሰጠበት
…የቀጠለ
• ባለሙያዎች ከሁለት ማነስ ወይም ከሶስት መብለጥ የለባቸዉም፤
• የማዕከልም ሆነ የክፍለ ከተማ የቁጥጥርና ክትትል እና የህጋዊ
ስነ-ልክ ባለሙያዎች በወረዳ ያለውን አካል ይደግፋሉ፤
• አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከቢሮ ወይም ከክ/ከተማ ጽ/ቤት በሚሰጠው
ልዩ ተልእኮ መሰረት በቀጥታ በንግድ መደብሮች ተገኝተው
የቁጥጥር ስራ ያከናውናሉ፤
• በህገ-ወጦች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዳሉ፤
• የወሰዱትን እርምጃ ለቅርብ ኃላፊና ለወረዳው ንግድ ጽ/ቤት
ያሳውቃሉ፡፡
• ክስ እንዲመሰረትም መረጃዎችን አደራጅተው ለክ/ከተማው የክስ
ምርመራና ክትትል ኬዝ ቲም ያቀርባሉ፡፡
4.2. የንግድ ኢንስፔክሽን ባለሙያ ስነ-ምግባር
• ህገ-ወጦች ላይ ከአድርባይነት የፀዳ እርምት የመዉሰድ፤
• የክትትል ተግባሩ የንግድ ህግ ማስከበር ስራ ላይ ትኩረት
ያደረገ መሆን አለበት፤
• ነጋዴዉ ተላልፎ የተደረሰበትን የደንብ ጥሰት ሳያዛባ በቃለ
ጉባኤ አስደግፎ ሪፖርት ማቅረብ፤
• አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እዉነታዉን ማእከል ያደረገ የምስክርነት
ቃል በፍ/ቤት ተገኝቶ መስጠት፣
…የቀጠለ
• ህገ-ወጦች ላይ ከአድርባይነት የፀዳ እርምት የመዉሰድ፤
• የክትትል ተግባሩ የንግድ ህግ ማስከበር ስራ ላይ ትኩረት
ያደረገ መሆን አለበት፤
• ነጋዴዉ ተላልፎ የተደረሰበትን የደንብ ጥሰት ሳያዛባ በቃለ
ጉባኤ አስደግፎ ሪፖርት ማቅረብ፤
• አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እዉነታዉን ማእከል ያደረገ የምስክርነት
ቃል በፍ/ቤት ተገኝቶ መስጠት፣
• በሃሰት ነጋዴዉን አለመወንጀል ወይም በሃሰት የምስክርነት
ቃል አለመስጠት፤
…የቀጠለ
• በማንኛዉም ሰዓት ወደ ንግድ መደብር ሲገባ ማንነትን
የሚገልፅ ባጅና ማንነታቸዉን ለነጋዴዉ አስረድተዉ የድጋፍ፣
ክትትልና ቁጥጥር ስራን ማከናወን፣
• በክትትልና ቁጥጥር የተያዙ ቃለ-ጉባኤዎች በየእለቱ ለቡድን
መሪ የቡድን መሪ በሌለበት ለጽ/ቤት በማቅረብ መወሰድ
ያለበት እርምት በጋራ ዉሳኔ በማስተላለፍ እርምጃ ይወስዳል፣
• የሚወሰደዉ እርምጃ ለነጋዴዉ በጽሁፍ ይገለፃል፡፡ ለነጋዴዉ
የሚሰጠዉ መግለጫ ጥፋቱን በመግለፅ የሚያስረዳና
የተላለፈዉን የህግ ድንጋጌ ያካተተ መሆን አለበት፡፡
…የቀጠለ

• ደንብ ተላልፎ የተገኘ ንግድ ድርጅት ላይ የተወሰደ እርምጃ


እሽግ ሲነሳ የቡድን መሪ ወይም ጽ/ቤት ኃላፊ ማወቅ
ይኖርበታል፡፡ የቡድን መሪ ወይም የጽ/ቤት ኃላፊዉ ሳያዉቅ
አስተዳደራዊ እርምጃ መነሳት የለበትም፡፡
• ተመሳሳይ የደንብ ጥሰት ፈፅመዉ የተገኙ ነጋዴዎች ላይ
የሚወሰደዉ አስተዳደራዊም ሆነ ህጋዊ እርምጃ ተመሳሳይ
መሆን አለበት፡፡
4.3. የውጭ ኢንስፔክሽን ስራዎች ትኩረት
• የንግድ ሰራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሚነግዱ፤
• የንግድ ፈቃዳቸውን ሳያድሱ በሚሰሩት ፤
• በጅምላ ፈቃድ የችርቻሮ ስራ መስራት ወይም በተቃራኒው
መስራት፤ ( ከመስክ ወይም ከዘርፍ ውጪ)
• ተመሳሳይነት የሌላቸውን /ተቃራኒ የንግድ ስራዎች በአንድ
ድርጅት ውስጥ መስራትን፤ /የህሊና ግምት/
• ከተሰጠው ንግድ ፈቃድ ውጭ የንግድ ስራ የሚያከናውኑትን፤
(የፍቃድ መስጪያ መደቦች እንደ ሪፈረንስ)
• ከአድራሻ ውጭ የሚነግዱትን፤
• የምዝገባና የፈቃድ ማስረጃዎች በድርጅት ውስጥ
…የቀጠለ
• ከተሰጠው የንግድ ስም ውጭ አለመጠቀሙን፤
• ሳያሳውቁ ቅርንጫፍ ከፍተው የሚሰሩትን፤ (በጣም ትኩረት የሚሹ)
• በተሰረዘ የንግድ ፈቃድ የሚሰሩትን፤
• መሠረታዊ ሸቀጦችን ከተመን በላይ ዋጋ ጨምረው
የሚሸጡትን/የህዝብ ማስታወቂያን በሚተላለፉት ላይ/
• የዋጋ ዝርዝር የማይለጥፉትን፤
• ለሸጡት ሸቀጥ ተገቢውን ደረሰኝ የማይሰጡትን፤
• የንግድ እቃዎችን መደበቅና ያለአግባብ ማከማቸትን፤
• የመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎች የአቅርቦትና የስርጭት አፈጻጸምን፤
• የልኬት መሳሪያዎችን በማዛባት የሚሰሩትን፣
ክፍል አምስት

ሕገ-ወጥ ንግድ ሥራ እና እርምጃ አወሳሰድ


5.1. የእሸጋ እርምጃ ከመውሰድ በፊት
የሚደረጉ ቅድመ ጥንቃቄዎች
• የእሳት አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ማንኛውም ነገር በማስወገድ
የአሌክትሪክ ሶኬቶችን እንዲነቅሉ፣ የሚበላሹ ነገሮችን፣ መገልገያ
ሰነዶችን የመሳሰሉትን እንዲያወጣ በማድረግ የንግድ መደብሩ
ይታሸጋል፡፡
• በአዋጅ ቁጥር 980/2008 መሰረት ቢሮው ወይም ጽ/ቤቱ
የሚወስደው አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተጠበቀ ሆኖ ጉዳዩ ለፖሊስ
ጣቢያ ቀርቦና ምርመራው ተጣርቶ ለአቃቤ ህግ እንዲተላለፍ
በማድረግ በወንጀል ክስ ተመስርቶ በፍ/ቤት ሲረጋገጥ ቅጣቱ
የሚፈፀም ይሆናል፡፡
• በፍርድ ቤት ክስ የተመሰረተበት እና እሸጋ የተፈፀመበት ነጋዴ
ወደህጋዊነት ሲመለስ የንግድ ድርጅቱ ይከፈታል ህገ ወጥ በነበረበት
ከእሸጋ በፊት…
• በድርጅቱ ውስጥ የተገኘውን ንብረት ተቆጣጣሪዎች በቃለ-
ጉባኤ በመመዝገብ የድርጅቱን ባለቤት ወይም ተወካይ
በማስፈረም መያዝና ንብረቱ እንዳይወጣ ወይም እንዳይሸሽ
በፖሊስ አማካኝነት ጥበቃ እንዲደረግለት በደብዳቤ ማሳወቅ
ይኖርበታል፡፡
• የንግድ ምዝገባና ፍቃድ ሳይኖረው ሲነግድ የተደረሰበትና
የንግድ ድርጅቱ የታሸገበት ነጋዴ የንግድ ድርጅቱ በታሸገበት
ዕለት መረጃዎች ተደራጅተው ቢበዛ በሁለት ቀናት ውስጥ ክስ
እንዲመሰረት ለክፍለ ከተማ ክስ ምርመራ መላክ አለበት፡፡
…የቀጠለ
• ክፍለ ከተማ የደረሱትን መረጃዎች በ3 ቀናት ውስጥ ለፖሊስ
ክስ እንዲመሰረት የክስ ማመልከቻ እና ምስክሮቹን በመያዝ
ቃል እንዲሰጡ ያደርጋል፡፡
• ህገ ወጥ ሆነው አስተዳደራዊ እርምጃ የተወሰደባቸው የንግድ
ድርጅቶች ላይ ክስ ሳይመሰርት ያቆየው ባለሙያና አመራር
ተጠያቂነት ይኖርበታል፤
5.2. የጥፋት አይነቶችና
የሚወሰዱ
አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃዎች
5.2 .1. ከጥር 1 እስከ ሰኔ 30 ባልታደሰ የንግድ ስራ
ፍቃድ ሲነግድ የተገኘ ነጋዴ በተመለከተ
• የ24 ሰዓት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲደርሰዉ በማድረግ
የንግድ ድርጅቱን ለእሸጋ ዝግጁ እንዲያደርግ ይደረጋል፡፡
• ነጋዴውም ፈርሞ እንዲቀበል ይደረጋል ፍቃደኛ ካልሆነ በንግድ
መደብሩ በር ላይ ይለጠፋል፡፡
• የ24 ሰዓት የማስጠንቀቂያ ጊዜው እንዳበቃ በ12 ሰዓት ጊዜ
ዉስጥ የንግድ ድርጅቱ ይታሸጋል፣
• የፀና ንግድ ስራ ፈቃድ ሳይኖረው በንግድ ስራ ላይ ተሰማርቶ
በመገኘቱ መረጃው ተደራጅቶ በወንጀል ክስ ተመስርቶበት
በአዋጁ 980/2008 እና በማሻሻያ አዋጅ 1150/2011
መሰረት እንዲቀጣ ይደረጋል፡፡
5.2 .2. ከሰኔ 30 በኋላ ያልታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ
በአዋጁ መሰረት የተሰረዘ ስለሆነ
• ለነጋዴዉ የ24 ሰዓት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲደርሰዉ ይደረጋል፣
• ነጋዴውም ፈርሞ እንዲቀበል ይደረጋል ፍቃደኛ ካልሆነ በንግድ
መደብሩ በር ላይ ይለጠፋል፡፡
• 24 ሰዓት እንደሞላ በ12 ሰዓት ዉስጥ የንግድ ድርጅቱ ይታሸጋል፣
• መረጃ ተደራጅቶ ክስ ይመሰረታል፣
• በፍ/ቤት ዉሳኔ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፣
• ፈቃዱን በወቅቱ ስላለማደሱ ያቀረበው ምክንያት በቢሮው፣ በፅ/ቤቱ
ኃላፊ ተቀባይነት ካገኘ በቅጣት ሊከፍል የሚገባውን ገንዘብ 10 ሺህ
ብር ከፍሎ አዲስ ንግድ ፈቃድ አውጥቶ እንደመጣ የንግድ መደብሩ
ይከፈትለታል፡፡ የተመሰረተው ክስ ግን ቀጣይነት ይኖረዋል፡፡
5.2 .2. ካስመዘገበዉ የንግድ ዘርፍ ዉጪ
ሲነግድ/ሲያመርት/ አገልግሎት ሲሰጥ የተደረሰበት
ነጋዴ፤
• ከተሰጠው ፍቃድ ውጪ መስራቱ ተገልጾለት በ 30 ቀናት ውስጥ ዘርፉን
እንዲያስተካክል የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡፡
• በ 30 ቀናት ውስጥ ማስተካከያዉን አድርጎ ሪፖርት ማድረጉን በመስክ
ክትትል ማረጋገጥ፡፡
• በተሰጠው 30 ቀናት ውስጥ ማስተካያ ያላደረገ ነጋዴ በቀጥታ የንግድ
ድርጅቱ ለ15 ቀናት እንዲታሸግ ይደረጋል፤
• መረጃ ተደራጅቶ ክስ ይመሰረታል፣ በፍ/ቤት ዉሳኔ መሰረት ተፈጻሚ
ይሆናል፣
• ዘርፉን አስተካክሎ ሲቀርብ የ15 ቀናት እሸጋ ሲያበቃ እሽጉ እንዲነሳ
ይደረጋል፣
5.2 .3. ኦሪጅናል የንግድ ፈቃዱን በንግድ መደብሩ
በሚታይ ቦታ ያልሰቀለ ነጋዴ
• የሚበላሽ ምርት ወይም አገልግሎት ካለ የ24 ሰዓት የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ በመስጠት የንግድ ድርጅቱ ለ7 (ሰባት) ቀናት
ታሽጎ ይቆያል፡፡
• ከእሸጋዉ በኋላ ያልታረመ ወይም ተመሳሳይ ጥፋት ላይ
ተሰማርቶ ከተገኘ የንግድ ስራ ፍቃዱ ለ1 ወር ታግዶ የወንጀል
ክስ ይመሰረትበታል፡፡
5.2 .4. የዋጋ ዝርዝር በንግድ መደብሩ በሚታይ ቦታ
ያልሰቀለ/ያልለጠፈ/ነጋዴ፣
• የሚበላሽ ምርት ወይም አገልግሎት የሚኖር ከሆነ የ24 ሰዓት
ማስጠንቀቂያ በመስጠት የንግድ ድርጅቱ ለ5 ቀናት ታሸጎ
ይቆያል፡፡
• የዋጋ ዝርዝር ለመለጠፍ እና ከስህተቱ ለመታረም ዝግጁ
ስለመሆኑ በሚያቀርበው የፅሁፍ ማመልከቻ መሰረት ከ5ኛው
ቀን በኋላ እሸጋው ይነሳል፡፡
• ለሁለተኛ ጊዜ ተመሳሳይ ጥፋት ከፈጸመ የንግድ ድርጅቱ
ለ2ወር እንዲታሸግ በማድረግ የንግድ ፍቃዱ ታግዶ በወንጀል
ክስ ይመሰረትበታል፡፡
5.2 .5. ካስመዘገበዉ የንግድ አድራሻ ዉጪ ወይም
የአድራሻ ለዉጥ ሳያሳዉቅ ሲሰራ የተደረሰበት ነጋዴ
• ከአድራሻ ውጪ የሚነግድ በ1ወር ውስጥ
እንዲያስተካከል ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፣
• በማስጠንቀቂያዉ ያላስተካከለ የሚበላሽ ምርት ወይም
አገልግሎት የሚኖር ከሆነ የ24 ሰዓት ማስጠንቀቂያ
በመስጠት የንግድ ድርጅቱ ለ15 ቀናት እንዲታሸግ
ይደረጋል፣
• የአድራሻ ለዉጥ ማስተካከያ አድርጎ ሪፖርት ካደረገ
የእሸጋ ጊዜው በተጠናቀቀ በ12 ሰዓት ዉስጥ እሸጋዉ
ይነሳል፣
5.2 .5. ደረሰኝ ጋር በተያያዘ

• በደረሰኝ አሰራር የማይጠቀም ነጋዴ የ24 ሰዓት ማስጠንቀቂያ


በመስጠት ለ7 ቀናት የንግድ ድርጅቱ ይታሸጋል፣ በዚህ
ያልታረመ የንግድ ፍቃዱ እንዲታገድ ይደረጋል፡፡
• ለህጋዊ ነጋዴ ደረሰኝ ለመስጠት ፍቃደኛ ያልሆነ ነጋዴ ወይም
የተጭበረበረ ደረሰኝ የሰጠ አምራች፣ አስመጪ ወይም ጅምላ
ነጋዴ በ24 ሰዓት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የንግድ
ድርጅቱ ለ15 ቀናት ይታሸጋል፤ መረጃ ተጣርቶም ክስ
ይመሰረትበታል፡፡ መረጃውን ከአዲስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን
ማድረስ ይገባል፡፡
5.2 .6. ቢሮው ፍቃድ የማይሰጥባቸው መጤ
ባህሎችን ስለመከላከል፤
• ከሚመለከታቸው የፖሊስና ደንብ ማስከበር (ሰላምና ጸጥታ) ጋር ቅንጅት
መፍጠር፣
• ህብ/ቡ ጥቆማ ሊሰጥባቸው የሚገቡ ስልኮችን በድርጅቶች ላይ
መለጠፍና ጥቆማ መቀበል፤
• የአነቃቂ ተክል ወይም ሌላ የንግድ ፍቃድ ይዘዉ ጫት ማስቃምና ሺሻ
የማስጨስ አገልግሎት ሲሰጡ የተደረሰባቸዉ የንግድ ድርጅቶች
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ወዲያውኑ ለ60 ቀናት
ደርጅታቸው ታሽጎ እንዲቆይ ይደረጋል፣
• ከ60 ቀናት እሸጋ በኋላ የንግድ ቤቱ በሚገባው ግዴታ መሰረት በተሰጠው
ፍቃድ እንዲሰራ ድርጅቱ ይከፈትለታል፡፡ ነገር ግን ተመሳሳይ ድርጊት
ላይ ተሰማርቶ የተገኘ ነጋዴ የንግድ ስራ ፈቃዱ ይሰረዛል፡፡ መረጃዎች
ተደራጅተው ክስ ይመሠረታል፡፡
5.2 .7. ከምርት ጥራት መጓደል ጋር ተያይዞ
የሚስተዋሉ ህገ-ወጥነትን የምንከላከልበት
አግባብ
• በየወረዳዉ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን
በሚያመርቱት የምርት አይነት ለይቶ ማወቅ መረጃዉን
ለክትትልና ቁጥጥር ስራ ማዋል፣
• አስገዳጅ የኢ/ት ደረጃ የወጣላቸው ምርቶች
የሚያመርቱ ድርጅቶች የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት
ያላቸው መሆኑንና የጥራት ምልክት መጠቀማቸውን
ማረጋገጥ
5.2 .7. ከምርት ጥራት መጓደል ጋር ተያይዞ
የሚስተዋሉ ህገ-ወጥነትን የምንከላከልበት
አግባብ
• በየወረዳዉ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በሚያመርቱት
የምርት አይነት ለይቶ ማወቅ መረጃዉን ለክትትልና ቁጥጥር
ስራ ማዋል፣
• አስገዳጅ የኢ/ት ደረጃ የወጣላቸው ምርቶች የሚያመርቱ
ድርጅቶች የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑንና
የጥራት ምልክት መጠቀማቸውን ማረጋገጥ
• የጥራት ደረጃቸው ላይ ጥቆማ የቀረበባቸው ድርጅቶች ለተስማሚነት
ምዘና ናሙናው ተልኮ እንዲመረመር ይደረጋል፤ ወጪውንም ነጋዴው
ይሸፍናል፡፡ ምርቱ የጥራት ችግር ካለበት ድርጅቱ ለ2 ወራት ይታሸጋል፣
ፍቃዱም ይታገዳል፤
…የቀጠለ

• የአገልግሎት ጊዜ ያለፈበትን የኢንዱስትሪ ምርት ለሽያጭ


ሲያቀርብ የተገኘ የንግድ ድርጅት ለ30 ቀናት ታሽጎ መረጃ
ተደራጅቶ ክስ እንዲመሰረትበት ይደረጋል፡፡
• አገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸዉ ምርቶች ምርቱ በተገኘባቸዉ
ነጋዴዎች ወጪ ተሰብስቦ ከአከባቢ ጥበቃ፣ ከጤና ጽ/ቤት፣
ከንግድ ጽ/ቤት፣ ከፖሊስ ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ እንዲወገድ
ይደረጋል፡፡
…የቀጠለ
• ባዕድ ነገር ተቀላቅሎ በምርቶች ላይ ሲሸጥ ወይም ምርቱ ችግር አለበት
ተብሎ በሚጠረጠርበት ጊዜ ናሙና በመውሰድ ለሚመለከተው አካል
ማስመርመር ይገባል፡፡
• አካሂዱም ቁጥጥር ኦፊሰር፤ ፖሊስ የተጠርጣሪው ደርጅት ባለቤት
በጋራ ናሙናውን በሁለት መያዣ ይወስዳሉ ለዚሁም ይፈራረሙበታል፡፡
• በተለይ የደርጅቱ ባለቤት የተወሰደው ናሙና የራሱ መሆኑን በፊርማው
ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
• በዚሁ መሰረት አንዱን ጽ/ቤቱ ላይ ማሰቀመጥ ሌለውን በላቦራቶሪ
በመላክ በተቀመጠ ስታንደርድ እንዲመረመር ለሚመለከተው አካል
በግንባር ወስዶ ማስረከብና ውጤቱን ተከታትሎ ግድፈት ያለበት ከሆነ
ለህግ መቅረብ፡፡
• በዚህ ሂደት የንግድ ድርጅቱ ታግዶና ታሽጎ ይቆያል፡፡
5.2.8. የምርት ወይም አገልግሎት ዋጋ ቅድመ
ሽያጭ ዋጋ ቁጥጥር፣
• የንግድ ሚኒስቴር መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጥ መሆናቸዉን ማስታወቂያ
ያወጣባቸውና ዋጋ የተተመነባቸዉ ሸቀጦችን የሚመለከት ነዉ፣
• የዋጋ ተመኑን የንግዱ ማህበረሰብና ሸማቹ ማህበረሰብ በአግባቡ
እንዲያዉቃቸዉ ማድረግ፣
• እያንዳንዱ የንግድ ድርጅት በተመኑ መሰረት የዋጋ ዝርዝርና
የተጠቃሚዎች ትስስር በየመደብራቸዉ ለሸማቹ ማህበረሰብ በሚታይ
መልኩ እንዲለጥፍ/እንዲያኖር ይደረጋል፣
• ሸቀጦቹ በተተመነዉ ዋጋና መጠን መሰረት እየተሸጠ መሆኑን
ህብረተሰቡ በራሱ እንዲከታተልና መመሪያዉን እንዲያስከብር የጥቆማ
ስልኮችን በየንግድ መደብሮቹ መለጠፍ፣ በጥቆማ አቀራረብ ህብረተሰቡ
ግንዛቤ እንዲኖረዉ ማድረግ፣
5.2.9. የምርት ወይም አገልግሎት ዋጋ ድህረ
ሽያጭ የዋጋ ቁጥጥር
• ድህረ ሽያጭ የዋጋ ቁጥጥር ለማካሄድ በዋናነት የሸቀጦችን ዋጋ
በየጊዜዉ በትኩረት መከታተልና ግልጽ መረጃ መያዝ
ያስፈልጋል፡፡ በዚህ አግባብ በየወቅቱ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ
ጭማሪ የሚታይባቸዉ ሸቀጦች ከመነሻቸዉ ጀምሮ የዋጋ
ጭማሪዉ መንስኤ መታወቅ ይኖርበታል፡፤
… የቀጠለ
• ድህረ ሽያጭ የዋጋ ቁጥጥር ለማካሄድ በዋናነት የሸቀጦችን ዋጋ
በየጊዜዉ በትኩረት መከታተልና ግልጽ መረጃ መያዝ ያስፈልጋል፡፡
በዚህ አግባብ በየወቅቱ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ የሚታይባቸዉ
ሸቀጦች ከመነሻቸዉ ጀምሮ የዋጋ ጭማሪዉ መንስኤ መታወቅ
ይኖርበታል፡
• ነጋዴዎች ለገበያ የሚያቀርቧቸዉን ሸቀጦች የዋጋ ዝርዝር በየንግድ
መደብራቸዉ እንዲለጥፉ ማድረግና ምክንያታዊ ያልሆነ ዋጋ ጭማሪ
ሲታይ ለየወረዳዉ ንግድ ጽ/ቤት እንዲያሳዉቁ ማድረግ፣
• ነጋዴዉ የዋጋ ግንባታዉን ሲያቀርብ ምርቱን ከየት እንደገዛ ህጋዊ
ማስረጃ (ደረሰኝ) ማቅረቡን ማረጋገጥ፣
…የቀጠለ
• በዋጋ ግንባታው ምክንያታዊ የሆነ የዋጋ ጭማሪ ሳይኖር የተጋነነ የዋጋ
ጭማሪ አድርጎ የታየ ነጋዴ ከዋጋ ጭማሪው በፊት ይሸጥ ወደ ነበረዉ
ዋጋ መልሶና አስተካክሎ የዋጋ ዝርዝር ለጥፎ በዚሁ አግባብ ሽያጭ
እንዲያካሄድ ይደረጋል፣
• የዋጋ ግንባታዉን በተሰጠዉ ጊዜ ገደብ ዉስጥ ያላቀረበ ነጋዴ የንግድ
ድርጅቱ ታሽጎ እንዲያቀርብ ይደረጋል፣ ማስረጃዉን እንዳቀረበ እሽጉ
ይነሳል፣
• የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ አድርጎ የተገኘው ነጋዴ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ
ካልቻለ ሸቀጡን በህጋዊ መስመር እንዳልገዛዉ ወይም ሆን ብሎ የዋጋ
ንረት እየፈጸመ የሚገኝ ተደርጎ ስለሚወሰድ የንግድ ፈቃዱ እንዲታገድ
ይደረጋል፡፡
…የቀጠለ
• በዋጋ ግንባታው ምክንያታዊ የሆነ የዋጋ ጭማሪ ሳይኖር የተጋነነ የዋጋ
ጭማሪ አድርጎ የታየ ነጋዴ ከዋጋ ጭማሪው በፊት ይሸጥ ወደ ነበረዉ
ዋጋ መልሶና አስተካክሎ የዋጋ ዝርዝር ለጥፎ በዚሁ አግባብ ሽያጭ
እንዲያካሄድ ይደረጋል፣
• የዋጋ ግንባታዉን በተሰጠዉ ጊዜ ገደብ ዉስጥ ያላቀረበ ነጋዴ የንግድ
ድርጅቱ ታሽጎ እንዲያቀርብ ይደረጋል፣ ማስረጃዉን እንዳቀረበ እሽጉ
ይነሳል፣
• የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ አድርጎ የተገኘው ነጋዴ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ
ካልቻለ ሸቀጡን በህጋዊ መስመር እንዳልገዛዉ ወይም ሆን ብሎ የዋጋ
ንረት እየፈጸመ የሚገኝ ተደርጎ ስለሚወሰድ የንግድ ፈቃዱ እንዲታገድ
ይደረጋል፡፡
አመሰግናለሁ

You might also like