You are on page 1of 36

ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር እና ባለአንድ

አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በአዲሱ


የንግድ ሕግ

የአሰልጣኞች ስልጠና
በላይሁን ይርጋ
ከፍተኛ የፖሊሲ እና ሕግ አማካሪ
belayhunyirga2@gmail.com
0912418717
ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር
ምንነትና መሰረታዊ ባሕሪያት (495)
 በንግድ ህጉ አንቀጽ 494 መሰረት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል
ማህበር ማለት ማናቸውም ማህበርተኛ ካስገባው መዋጮ
በላይ አላፊ የማይሆንበት ማህበር ማለት ነው፡፡
 የዚህ አይነቱ ማህበር የአባላት ቁጥር ከሁለት ያላነሰና ከሃምሳ
ያልበለጠ እንደሆነ በንግድ ህጉ በግልጽ ተቀመጧል፡፡ የመነሻ
ካፒታሉም ከአስራ አምስት ሺህ ብር ያነሰ መሆን አይችልም
496/1/
 የሰዎች ማኅበራት እና የካፒታል ማኅበር ቅይጥ ስለመሆኑ
 ከሰዎች ማኅበራት ጋር የሚጋራው ዋና ባህሪ (የአባላት
ስበጥር ለመጠበቅ በአክሲዮን ዝውውር ላይ የሚደረግ
ገደብ፣ የሕጉ ድንጋጌዎች በብዛት ፈቃጅ እና ክፍተት
ለሞምላት ያለሙ መሆን)
 ከካፒታል ማኅበራት ጋር የሚጋራቸው ባህሪያት
(አባላት ለማኅበሩ ዕዳ ያላቸው ተጠያቂነት በመዋጮ
መገደብ(495(1)(3)፣295፣ የአባላት ሞት፣ ኪሳራ ወዘተ
በማኅበሩ ህልውና ላይ ለውጥ የማያመጡ መሆን)
 የሚተላለፉ የግዴታ ምስክር ወረቀቶች ያለማውጣት
495(5)፣ አክሲዮን ባህሪ፣ የግዴታ ምስክር ወረቀቶች
ወዘተ)
 ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጥቅም

 ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚመራው እንደ አክሲዮን


ማህበር ሁሉ በቦርድ ሳይሆን በራሳቸው በባለቤቶቹ መሆኑ፡፡
 ይህም ከሽርክና ማህበር ጋር ተመሳሳይነት አንዲኖረው
ያደርገዋል፡፡ (ከፈለጉ ግን በዳይሬክተሮች ቦርድ እንዲመራ
በመመስረቻ ፅሁፍ ሉወስኑ ይችላሉ)
 እንደ አክሲዮን ማህበር ሁሉ ለመመስረት ብዙ ሂደቶችን
ማለፍ የማይጠይቅ መሆኑ፣
 ኃላፊነተ የተወሰነ መሆኑ፡- እንደ አክሲዮን ማህበራት ሁሉ ኃላፊነቱ
የተወሰነ የግል ማህበር ባለአክሲዮኖች በማህበሩ ላይ ካላቸው ድርሻ በላይ
በእዳ ሊጠየቁ አይችሉም፡፡
 ያልተገደበ የጊዜ ቆይታ ያላቸው መሆኑ፡- ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል
ማህበር በተወሰኑ አባላት የግል ሁኔታ ህልውና በቀላሉ አደጋ ላይ ሊወድቅ
አይችልም፡፡ ስለዚህ በገበያው ውስጥ ረጅም ጊዜ የመቆየት እድል አለው፡፡
 ካፒታሉን ለማሳደግ ቀላል መሆኑ፡- ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
ኃላፊነቱ የተወሰነ በመሆኑና ከፋይናንስ ተቋማት በቀላሉ ብድር ማግኘት
የሚችል በመሆኑ ካፒታሉን ለማሳደግና ለማስፋፋት ምቹ ሁኔታን
ይፈጥርለታል፡፡
 ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጉዳት
 አክሲዮን ከማህበሩ አባላት ውጭ ለሆኑ ሰዎች የማይተላለፍ መሆኑ፡፡
 የሚተላለፍ ከሆነም ሁሉም አባላት መስማማት ያለባቸው መሆኑ (ነገር ግን
በውርስ ሊተላለፍ ይችላል)፣
 እንደ አክሲዮን ማህበር ሁሉ አክሲዮኖችን በገበያ ላይ አውጥቶ መሸጠ እና
አዳዲስ ኢንቨስተሮችን መሳብ የማይችል መሆኑ፣
 ከፍተኛው የአባላት ቁጥር የተገደበ በመሆኑ እና አክሲዮን ለገበያ የማይሸጥ
በመሆኑ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እድገት በእነዚህ አባላት ሀብት ብቻ
የተወሰነ ነው፡፡
አባላት ለማኅበሩ የሚያደርጉት መዋጮን በተመለከተ የተደረጉ
ለውጦች
ባለ አክሲዮኖች ቁጥር ወደ አንድ ዝቅ ማለት

1. ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የባለአክሲዮኖች ቁጥር ወደ አንድ ዝቅ ካለ እና


በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ሌላ ሰው በባለአክሲዮንነት ካልገባ ማህበሩ ይፈርሳል።
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተደነገገው ቢኖርም፤ የባለአክሲዮኖች ቁጥር ወደ
አንድ ዝቅ ካለበት ቀን ጀምሮ በስድስት ወራት ውስጥ የመመስረቻ ጽሁፉን
በማሻሻል ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አድርጎ ማስመዝገብ
 አንቀጽ 499. ለማህበሩ ምስረታ የሚያስፈልጉ ጠቅላላ
ሁኔታዎች

1. ማንኛውም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚመሰረተው ዋና


ገንዘቡ በሙሉ ሲከፈል እና የመመስረቻ ጽሁፉ በንግድ መዝገብ
ውስጥ ሲገባ ነው።
2. በጥሬ ገንዘብ በተሸጡ አክሲዮኖች ላይ የተጻፈው ዋጋ ማህበሩ
ከመመዝገቡ በፊት በመመስረት ላይ ባለው ማህበር ስም በተከፈተ
ዝግ የባንክ ሒሳብ ውስጥ መቀመጥ አለበት፡፡
አንቀጽ 500. የመመስረቻ ጽሁፉ ይዘት

 የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ የሚከተሉትን ማካተት ይኖርበታል፡-

1. የባለአክሲዮኖችን ስም፣ ዜግነትና አድራሻ፤

2. የማህበሩን ስም፣ ዋና መሥሪያ ቤት፣እንዳሉም ቅርንጫፎቹን፤

3. የማህበሩን የንግድ ዓላማ፤


1. የማህበሩን ዋና ገንዘብ መጠን እና ይኸው በሙሉ የተከፈለ መሆኑን
የሚያሳይ መግለጫ፤
2. እያንዳንዱ ባለአክሲዮን የከፈለውን የገንዘብ መጠን፤

3. በዓይነት የተከፈለ መዋጮ ካለ ግምቱን፤

4. እያንዳንዱ ባለአክሲዮን የያዘውን የአክሲዮን ብዛት፤

5. የትርፍ አከፋፈል ሥርዓት፤


1. ዳይሬክተሮች ካሉት ብዛታቸውንና ሥልጣናቸውን፤
2. የሥራ አስኪያጆችን ቁጥርና ሥልጣናቸውን፤
3. ኦዲተሮች ካሉ ብዛታቸውን፤
4. ማህበሩ የሚቆይበትን ጊዜ፤
5. ማህበሩ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የሚያስታውቅበትን መንገድና ጊዜ፤
6. እንዲሁም በማህበሩ ሥራ አመራር፣ በማህበሩና በአባላት ወይም በአባላት መካከል ያለውን
ግንኙነት የሚመለከቱ ጉዳዮችን፤
7. ሌሎች በሕግ ወይም በባለአክሲዮኖች ስምምነት እንዲካተቱ የተወሰኑ ጉዳዮችን፡፡
 አንቀጽ 501. ተቀባይነት ያለው መዋጮ

 ከሞያ አገልግሎት በስተቀር ሌሎች በዚህ ሕግ አንቀጽ 186


የተመለከቱት የገንዘብና ሌሎች የዓይነት መዋጮዎች ኃላፊነቱ
ለተወሰነ የግል ማህበርም ተፈጻሚነት አላቸው፡፡
 የሙያ አገልግሎት ተቀባይነት ያለው መዋጮ እንዳልሆነ በግልጽ ስለመደንገጉ
(501፣ 186 v. 229(1)) ፣ 519} ነባሩ ምንም አይልም ነበር
 በጥሬ ገንዘብ የሚደረግ መዋጮ ማሕበሩ ከመመስረቱ በፊት በምስረታ ላይ
ባለው ማኅበር ስም በተከፈተ ሂሳብ ውስጥ እንዲገባ ስለመደንገጉ vs የማህበሩ
ዋና ገንዘብ በሙሉ መግባቱን የሚያስረዳ መግለጫ (499 v. 517(g)
 በዓይነት የተደረገ መዋጮ እንደነገሩ ሁኔታ በማኅበሩ ስም መመዝገቡን ወይም
አስፈላጊው የንብረት ባለቤትነት ማስረጃ መዘጋጀቱን የማረጋገጥ ኃላፊነት
በግልጽ በማኅበሩ በማህበሩ ስራ አስኪያጅ ወይም የዳየሬክተሮች ቦርድ ላይ
መጣሉ (502/5vs. 519/) vs. የበፊቱ እንዲህ አየነት ግዴታ አይጥልም
 የዓይነት መዋጮ ግምት ላይ በአክሲዮን ማሕበር እና ኃላፊነቱ በተወሰነ የግል
ማኅበር መኃል ልዩነት ስለመኖሩ 502(2፣3፣4) v. 257)
የባለአክሲዮኖች መብቶች ላይ የተደረጉ ለውጦች
 የማኅበሩንፋይናንስ ወይም የማኅበርተኛውን ጥቅም በሚነካ ጉዳይ
ላይ አስፈላጊ የሆኑትን የማኅበሩን ሂሳቦች/ሰነዶች የመመርመር
አንዲሁም ጥያቄ የማቅረብ መብት፤ ለዚሁ ተግባር ባለሞያ ረዳት ይዞ
መቅረብ ስለመቻሉ (504)
 የመረጃ
መብት በሕግ የተከለከሉ ወይም ማኅበሩን ከባድ ጉዳት ላይ
የሚጥሉ ጉዳዮችን አያካትትም (504/2/)
 ማሕበርተኛ የሆነ ሰው አክሲዮን ለውጭ ሰው ከመሸጡ በፊት በዛው
ዋጋ እንዲገዙት ለማሕበርተኞች ዕድል እንዲሰጥ ስለመደንገጉ፣ 508(3)
በአክሲዮን ዝውውር ላይ ስለተደረጉ ለውጦች
የፍርድ አፈፃፀምን በተመለከተ
 የበፊቱ አንቀበልም የማለት መብት ይሰጧቸውና ግን ከዚያስ የሚለውን
አይመልስም፣ የፍርድ አፈፃጸም መሆኑንም አይናገርም 523/5/
 በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት አክሲዮን በሚሸጥበት ጊዜ ማኅበርተኞች የመጣውን
ገዥ ሁሉ አንቀበልም የሚሉበት ዕድል (523/5/) ተቀየረ በ510)
 በሕጉ በፍርድ አፈጻጸም ጊዜ የሚሸጠውን አክሲዮን ወይ ባለአክሲዮኖች መግዛት
አለባቸው ወይም ማኅበሩ መግዛት አለበት
 ማኅበሩ አክሲዮን መግዣ መጠባበቂያ ገንዘብ ከሌለው የማኅበሩ ካፒታል
ይቀነሳል ባለአክሲዮኖችም ካፒታል ከመቀነሱ በፊት ከማኅበሩ ገንዘብ የመጠየቅ
መብት ላገኙ ሰዎች ባንድነት እና በነጠላ ተጠያቂ ይሆናሉ (510/3 እና 4)
ውርስን በተመለከተ
 ተቃራኒ ድንጋጌ በመመስረቻ ጽኁፍ ከሌለ እና ማኅበሩ በቂ
የመጠባበቂያ ገንዘብ ካለው ወራሾች ማህበሩን በመቀላቀል
እና አክሲዮኖቹን ለማኅበሩ በመሸጥ መካከል ሙሉ ምርጫ
አላቸው፣ በነባሩ ህግ ግን ወራሸች እንደሚወርሱ ብቻ
ተናግሮ አባል ሆኖ መቀጠል ወይስ ድርሻ ይዞ መውጣት
ግልፀ አደርገውም 511(2,3/) v. 524)
በማኅበሩ ሥራ አመራር ላይ የተደረጉ ለውጦች
 ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ እንዲኖረው በመመስረቻ
ጽሁፍ መወሰን ስለመቻሉ (513/1)
 የዲረክተሮች ቦርድ በሚኖርበት ጊዜ ስለቦርዱ በአክሲዮን ማኅበር ስር የተደነገጉት
ተፈጻሚ እንደሚሆኑ ተደነገገ (513/3/)
 የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ማኅበሩ ቦርድ ካለው በቦርድ ይሾማል ተጠሪነቱም ለቦርዱ
ይሆናል (5171/)
 በመመስረቻ ጽሁፍ ውስጥ ግልጽ የሆነ ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር በመመስረቻ
ጽኁፍ ላይ የተሾመም ቢሆን ስራ አስኪያጁ በመደበኛ ጉባዔ ከኃላፊነት ይነሳል 517(2)
v. 527(1) እና 536(2)
 ሥራ አስኪያጅ ካለበቂ ምክንያት ቢሻርም ካሳ ከመጠየቅ ያለፈ መብት እንደሌለው
በግልጽ ተደንግጓል (517(2) v. 527(3) &(4))
 ኦዲተርን የተመለከቱ ለውጦች
 አስር እና ከዛ በላይ ባለአክሲዮን ያለው ወይም ጠቅላላ ሃብቱ
5 ሚሊዮን የሚደርስ ማኅበር አንድ ነጻ እና ገለልተኛ ኦዲተር
እንዲኖረው ስለመደንገጉ (518)
 በ1952ቱ ኮድ 20 በላይ አባላት ያሉት ድርጅት ቢያንስ 3
ተቆጣጧሪዎችን እንዲሾም ሕጉ ያስገድዳል (538)
ጉባዔዎችን የተመለከቱ ለውጦች
 በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ጉባኤዎችን መሳተፍ ይችላሉ፣
ድምፃቸውንም በቃል መስጠት ይችላሉ ሆኖም ከአክሲዮን ማኅበር
አንጻር ሲታይ ገደቦች አሉበት 520
 የአባላት ቁጥር ምንም ያህል ቢያንስም ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ
ማድረግ ግዴታ ስለመደረጉ (521 v. 532) vs. ከሀያ በላይ የሆኑ
ማህበርተኞች ባሉባቸው ማህበሮች ውስጥ----
 ቦርዱ/ስራ አስኪያጁ ወይም ኦዲተሩ ከማኅበሩ ዋና ገንዘብ 10
በመቶ የሚወክሉ ሰዋች ጠቅላላ ጉባዔ እንዲደረግ ከጠየቁ ስብሰባ
መጥራት አለባቸው (521/4/ v. 532) v. ስራ አስኪያጅ፣ ተቆጣጣሪ
ወይም ከማህበሩ እኩሌታ በላይ ድርሻ ያላቸው
 በዚህ አንቀጽ ኃላፊነት የተሰጣቸው አካላት ጉባዔውን ለመጥራት
ካልቻሉ ወይም ፈቃደኛ ካልሆኑ ወይም በማንኛውም ባለአክሲዮን
ጠያቂነት በቂ ምክንያት ሲኖር ፍርድ ቤት ጠቅላላ ጉባዔውን
የሚጠራና የመወያያ አጀንዳ የሚያዘጋጅ ሰው ሊሾም
ይችላል(521/5/)
ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር
ትርጓሜ (534 እና 536(1))
 አንድ ሰው በግሉ በሚሰጠው መግለጫ መሠረት የተቋቋመ የንግድ ማኅበር ነው
 አባሉ የሚሰጠው መግለጫ ሰነዶችን ለማረጋገጥ ሥልጣን በተሰጠው አካል ፊት መደረግ
አለበት፤ መግልጫውም በንግድ መዝገብ ውስጥ መግባት አለበት
 ማኅበሩ ከአባሉ የተለየና የተነጠለ የራሱ የሕግ ሰውነት አለው
 አባሉ የራሱን መዋጮ ሙሉ በሙሉ እስከ ከፈለ ድረስ ማኅበሩ ላይ ለሚፈለገው ዕዳ በግሉ
አይጠየቅም
 ስለማኅበሩ የተደነገጉት ልዩ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ማኅበሩ በመሰረታዊ ባኅረው ኃላፊነቱ
የተወሰነ የግል ማኅበር ነው (545)
የማኅበሩ አባል ለማኅበሩ ዕዳ ሙሉ ተጠያቂነት
ሊኖርበት ስለመቻሉ (534)
 ማኅበሩን፣ ወይም የማኅበሩን ገንዘብ ጠያቂዎች ጉዳት ላይ የሚጥል ህገ-ወጥ
ድርጊት ሆን ብሎ ከፈፀመ፤
 የባለ አንድ አባል ማኅበር ንብረትን ከራሱ ንብረት ጋር ከቀላቀለ፤
 የባለ አንድ አባል ማኅበርን እና የራሱን ማንነት ካልነጣጠለ፤
 ስለ ማኅበሩ የፋይናንስ አቋም የማኅበሩን ገንዘብ ጠያቂዎች ሊያሳስት የሚችል
መረጃ ሆን ብሎ ካወጣ፤
የማኅበሩ አባል ለማኅበሩ ዕዳ ሙሉ ተጠያቂነት …
የቀጠለ
 ያለ ተመጣጣኝ ክፍያ የማኅበሩን ሀብት ለራሱ ወይም ለሶስተኛ ወገኞች የግል
ጥቅም ካዋለ፤
 በሕግ ሊከፈል ከሚችለው በላይ የትርፍ ክፍያ ከፈጸመ፤ ወይም
 ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን ከፈጸመ
የማኅበሩ ምስረታ

 ማኅበሩን ለመመስረት በአባሉ በግል የሚሰጠው መግለጫ የመመስረቻ ጽሁፍ ይዘት


ያለው ስለመሆኑ (536)
 አባሉ የሞተ፣ የጠፋ ወይም በፍርድ የተከለከለ እንደሆነ ስለ ወራሾቹ ወይም ስለ አባሉ ሆኖ
ሕጋዊ ተግባራትን እንዲፈጽም የታጨው የንብረት ጠባቂ ሰው ስም በጽሑፉ ውስጥ
መመልከት አለበት
 ዕጩ ንብረት ጠባቂው ዕጩነቱን የተቀበለ መሆኑን ሰነዶችን ለማረጋገጥ ሥልጣን
በተሰጠው አካል ፊት ካላረጋገጠ በስተቀር፤ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር
ሊመሠረት አይችልም (537(1))
 አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ለተለያዩ ባለ አንድ አባል ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ማኅበራት
የንብረት ጠባቂ ሆኖ መመረጥ አይችልም (537(2)
የማኅበሩ ምስረታ እና በዓይነት የተደረገ መዋጮ
(540)
 አባሉ በዓይነት ያደረገው መዋጮ ካለ የመዋጮው ምንነትና ዋጋው (ወይም
ግምቱ) አባሉ በሚሰጠው መግለጫ ውስጥ በግልጽ መጠቀስ አለበት
 በዓይነት የተደረገ መዋጮን ዋጋ በተመለከተ አባሉ የሰጠው ግምት ትክክል
መሆኑን የሚያጣራ የምሥረታ ወቅት ኦዲተር መሾም አለበት
 ኦዲተሩ በዓይነት የተደረገን መዋጮ ለመተመን የሚጠቀምበትን ዘዴ እራሱ
ይወስናል፤ በሚያቀርበው ሪፖርት ውስጥም የተከተለውን ዘዴ መግለጽ
አለበት
 አባሉ ያቀረበው የዓይነት መዋጮ ዋጋ ኦዲተሩ ከተመነው ዋጋ በላይ የሆነ
እንደሆነ ኦዲተሩ የተመነው ዋጋ የጸና ይሆናል
ምስረታ እና በዓይነት የተደረገ መዋጮ . . .
የቀጠለ
 የዓይነት መዋጮ ግምት የተጋነነ ከመሆኑ የተነሳ ሦስተኛ ወገኖች ላይ
ለሚደርሰው ጉዳት አባሉና ኦዲተሩ በአንድነትና በተናጠል ኃላፊ ናቸው
 ሆኖም ከዓይነት መዋጮ ግምት መጋነን ጋር በተያያዘ የሚቀርብ ክስ
መዋጮው ገቢ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ አምስት ዓመት ከሞላ በይርጋ
ይታገዳል
 የሚቀርብ ክስ የዓይነት መዋጮው በተገቢው ሁኔታ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ
በአምስት ዓመት ውስጥ ካልቀረበ ተቀባይነት የለውም፡፡
የተከለከለ ምስረታ (539)

 አንድ ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሌላ ባለአንድ


አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሊያቋቁም አይችልም
 ማንኛውም በጉዳዩ ያገባኛል የሚል ወገን ይህን ክልከላ በመተላለፍ
የተመሠረተ ማኅበር እንዲፈርስ ማኅበሩ በተቋቋመበት ሥፍራ
ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ሊያመለክት ይችላል
 ማኅበሩ እንዲፈርስ ክስ የማቅረብ ዕድል ቢኖርም፤ ክልከላውን
በመተላለፍ ሦስተኛ ወገኖች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት አባሉና ማኅበሩ
ባንድነትና በተናጠል ኃላፊ ናቸው
ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲፈርስ
የሒሳብ አጣሪዎች ሹመት፣ ስልጣን፣ ሃለፊነት፣
የትርፍ እና ኪሳራ አከፋፈል ወዘተ… የተመለከቱ
ድንጋጌዎች እንዲካተቱ መደረጉ
የግለሰብ ነጋዴ ድርጅትን ወደ ባለአንድ አባል
ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ስለመለወጥ (538)
 ግለሰብ ነጋዴ የንግድ ድርጅቱን ወደ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ
የግል ማኅበርነት መለወጥ ይችላል
 ለውጡ ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ምስረታን
የተመለከቱ የምስረታ መግለጫ(የመመስረቻ ጽኁፍ፣ የዓይነት
መዋጮ ግምት ወዘተ … ማሟላት አለበት
 ግለሰብነጋዴው ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር
ከመመሥረቱ በፊት ለገባበት ዕዳ ሁሉ ከማኅበሩ ጋር በአንድነት እና
በተናጠል ኃላፊ ነው
የማኅበሩ የሥራ አመራር፡- ጠቅላላ ጉባዔ
(542)

 የማኅበሩ ከፍተኛ የአስተዳደር አካል ጠቅላላ ጉባዔ ነው


 ብቸኛው ማህበርተኛ የአንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር አባላት
ጠቅላላ ጉባዔ ያለውን ሥልጣን ይኖረዋል
 አባሉበጠቅላላ ጉባዔ ሥልጣኑ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ቃለ-ጉባዔ
ስብሰባው በተደረገ ከሦስት ሳምንታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በጽሑፍ
ተዘጋጅተው የማህበሩ ማህደር ውስጥ መቀመጥ አለባቸው
የማኅበሩ የሥራ አመራር፡- ጠቅላላ ጉባዔ …
የቀጠለ
 በማኅበሩ ምሥረታ ጊዜ በተሰጠ መግለጫ ውስጥ የተካተቱትን
ነገሮች የሚለውጥ ማንኛውም ውሳኔ ውሳኔው በንግድ መዝገብ
ውስጥ መግባት አለበት
 የአባሉ ውሳኔዎች ከላይ የተገለጹትን ያላሟሉ ቢሆኑ እንኳን በሕግ ፊት
የጸኑ ናቸው፤
 ሆኖምጉድለቱ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት አባሉና
ማኅበሩ በአንድነት እና በተናጠል ተጠያቂዎች ናቸው
የማኅበሩ ሥራ አመራር - ዋና ሥራ አስኪያጅ

 ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ዋና ሥራ


አስኪያጅ ሊኖረው ይገባል
 አባሉ ራሱ ወይም ሌላ ሰው የማኅበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ
ሊሆን ይችላል
 ዋና ሥራ አስኪያጁ አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር
ሥራ አስኪያጅ ያለው ሥልጣን እና ተጠያቂነት ይኖረዋል
የማኅበሩ መፍረስ

 ማኅበሩ የሚፈርስባቸው ምክንያቶች አስፈላጊው ለውጥ


ተደርጎባቸው ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የሚፈርስባቸው
ምክንያቶች ናቸው
 ያለበትን ዕዳ በሙሉ የከፈለ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል
ማኅበር ሲፈርስ የማኅበሩ ሀብት ሳይጣራ ባለበት ሁኔታ
በጠቅላላው ለአባሉ ሊተላለፍ ይችላል፤
 በማናቸውም ምክንያት ማኅበሩ ከፈረሰ በኋላ ገንዘብ ጠያቂዎች
የቀረቡ እንደሆነ አባሉ በግሉ ተጠያቂ ይሆናል
የማኅበሩ መፍረስ … የቀጠለ

 ንብረት ሳይጣራ ባለበት ሁኔታ ለአባሉ ከመተላለፉ ጋር በተያያ በአባሉ ላይ


የሚቀርበው ክስ ገንዘብ ጠያቂው የማኅበሩን መፍረስ ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ
በአምስት ዓመት ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል
 የማኅበሩ ሀብት ለአባሉ ከተላለፈ ከአሥር ዓመት በኋላ ምንም ዓይነት ክስ
ሊቀርብ አይችልም
 አባሉ በምርጫው መደበኛው የሃብት ማጣራት ስርዓት የተከተለ እንደሆነ ከላይ
የተመለከትነው የተለየ ተጠያቂነት አይኖርበትም
አመሰግናለሁ!!!

You might also like