You are on page 1of 263

የአማራ ክልል የፍትሕ ባሇሙያዎች ማሰልጠኛና የሕግ

ምርምር ኢንስቲትዩት የሕግ መፅሔት

ቅፅ ፭ ሰኔ ፪ሺ፲
Vol. 5 June 2010

ዋና አዘጋጅ
ጋሻዬ ቢያዴግ (LLB, LLM) (የህግ ጥናትና ምርምር አስተባባሪ)

የኢንድቶሪያል ኮሚቴ አባላት

ጋሻው ዘውደ (LLB, LLM) ዋና ዲይሬክተር

ፀጋዬ ወርቅአየሁ (LLB, LLM) ጠቅላይ ፍርዴ ቤት ዲኛ)

ኢዮስያስ ዯምሴ (LLB, LLM) ክልል አቃቤህግ)


ምህረት አለማየሁ (LLB, LLM) ባህር ዲር ዩኒቨርስቲ ህግ ትምህርት ቤት ም/ዱን)
ማውጫ ገፅ
1. የዋና ዲይሬክተር መልዕክት ........................................................................ .......................... I

2. በኢትዮጵያ የውል ምዝገባ ለቤት ሽያጭ ውል መሰረታዊ እና አስገዲጅ መስፇርት


ነውን? (በሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔወች ዋቢነት የቀረበ) .................................. ............................. 1
ወርቅነህ አለሙ

3. በአዱሱ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዲዯር ሕግ ላይ የሚታዩ በጎ ጎኖች


እና ችግሮች............................................................................................... ............................ 25
በሪሁን አደኛ

4. በኢትዮጽያ የወንጀል ፍትህ አስተዲዯር ውስጥ በጊዜ ቀጠሮ መፇቀዴ ወይም በዋስትና
መከልከል፣ በጥበቃ ስር ማቆየት የጽንሰ ሀሳብ ይዘትና ክርክር አመራር .............................. 57
ሰለሞን ጎራው

5. በወንጀል ይግባኝ ሥርአት የእስራት ቅጣት እንዲይፇጸም ማገዴና አመልካችን በዋስትና


የመልቀቅ ጽንሰ ሀሳብ ......................................................................................................... 106
ሳባ ዯመቀ

6. ዯጋጋሚ ወንጀለኛነት እና የቀዴሞ የወንጀል ሪከርዴ የህግ ማዕቀፍ እና ተግባራዊ


አፇጻጸም በአማራ ክልል ...................................................................... .............................. 139
ይማም ሰይዴ

7. ተከሳሽ በሌለበት የወንጀል ክርክር ስለማዴረግ፡ ህጉና አፇፃፀሙ በአማራ ክልል ፍርዴ
ቤቶች ................................................................................................................................. 164
ታፇሰች ወልዳ

8. በምርመራ ወቅት በፖሊስ ጣቢያ የተሰጠ የምስክሮች ቃል በፍርዴ ቤት እንዱቀርብ


ስለሚዯረግበት የህግ አግባብ፣ በፍርዴ ቤት ያለው ተቀባይነትና ተግባራዊ አፇጻጸሙ በአማራ
ክልል ፍርዴ ቤቶች ............................................................................. ............................. 187
ሰለሞን ተገኝወርቅ

9. በሴቶች ላይ የሚፇጸሙ ፆታዊ ጥቃቶች ፍትሃብሔራዊ መፍትሔዎች በኢትዮጵያ


የህግ ማዕቀፍ .................................................................................................................... 205
ይበልጣል ይመር

10. የመሬት ይዞታ ይገባኛል እና የይርጋ መከራከሪያ በአማራ ብሔራዊ ክልል የመሬት አዋጅ
ከፌዯራል መንግስት የህግ ማዕቀፍ አንጻር ............................................................................ 236
ጋሻዬ ቢያዴግ
የዋና ዳይሬክተር መልዕክት

የአብክመ የፍትህ ባሇሙያዎች ማሠልጠኛና የህግ ምርምር ኢንስቲትዩት በደንብ ቁጥር


74/2003 ዓ.ም መሠረት ሲቋቋም የፍትህ ባሇሙያዎች በእውቀት፣ በክህሎት፣ በስነ-ምግባርና
አመሇካከት ብቁና የህዝብ አገልጋይነት ስሜት የተላበሱ እንዲሆኑ ሇማስቻል ተከታታይነት
ያሇውና አዳጊ ስልጠና መስጠት እና የክልላችን የፍትህ ስርዓት ተደራሽነት፣ ከቅልጥፍና፣
ጥራት፣ ውጤታማነትና ተገማችነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ሳይንሳዊ በሆነ የህግ ጥናትና
ምርምር በመሇየት የመፍትሄ ኃሳቦችን ማመንጨትና ሇፍትህ ስርዓቱ መሻሻል አስተዋፅኦ
ማድረግ ነው፡፡ በዚህ መሠረት በቅድመ ስራና ስራ ላይ ከ8,000 በላይ ባሇሙያዎችን
በማሠልጠን እና በማስመረቅ ሇፍትህ ስርዓቱ ላይ የሰው ኃብት ልማት አቅም ግንባታ ላይ
አትኩሮ በመስራት ሇፍትህ ስርዓቱ ውጤታማነት ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡

ከአጫጭር ጊዜ ስልጠና አኳያ የባሇድርሻ አካላትን ፍላጐት እና ጥያቄ መሠረት ያደረገ


የፍላጐት ዳሰሳ ጥናት ተሰርቶ በዚህም ላይ የተመሠረተ ስርዓተ ትምህርት ተቀርጾ ሇዚህ
የሚመጥን የስልጠና ማንዋል ተቀርጾ በተቀናጀና በተደራጀ አኳኃን በተሇያዩ ጭብጦች ላይ
አትኩሮ ከ16,000 በላይ የሚሆኑ ባሇሙያዎችን በማሰልጠን ውጤታማነቱን አሳድጓል፡፡

ባሇፉት ሁሇት ዓመታት የባሇድርሻ ፍላጐት እና ጥያቄ እንዲሁም በኢንስቲትዩቱ መነሻነት በ50
ርዕሰ ጉዳዩች ላይ የጥናትና የምርምር ስራ በማከናወን የህግ መጽሄት ቁጥር 1 እና 2,3,4
ጥቅም ላይ እንዲውል ጥረት ተደርጓል፡፡ ይህም ሇክልለ የፍትህ ስርዓት መሻሻል ጉልህ
አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ በዚህ በጀት ዓመትም የጥናትና የምርምር ስራዎች የተሰሩ ሲሆን
በኢዲቶሪያል ቦርድ ከሚታወቁና ከሚያግባቡ የጥናትና የምርምር ስራዎች መስፈርትና መሇኪያ
አንፃር ታይተውና ተመርምረው ተቀባይነትና ይሁንታ አግኝተው ሇህትመት ብቁ ናቸው የተባለ
የምርምር ስራዎችን በዚህ መፅሄት በማሳተም የኢንስቲትዩቱ ሇ5ኛ ጊዜ የሆነውን ቁጥር 5
የህግ መፅሄት በአክብሮት ስናቀርብ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ በመሆኑም ይህን ስራ የሰሩትን
የውስጥና የውጭ ተጋባዥ ተመራማሪዎች በአርትኦት የተሳተፉት ሙህራንና የኢዲቶሪያል
ቦርድ አባላት በራሴና በኢንስቲትዩቱ ስም ከፍ ያሇ ምስጋናየን እያቀረብኩ ሇአንባቢያን መልካም
ንባብ እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቴን ሇመግሇፅ እዋዳሇሁ፡፡

አመሰግናለሁ!
በኢትዮጵያ የውል ምዝገባ ለቤት ሽያጭ ውል መሰረታዊ እና አስገዳጅ
መስፈርት ነውን? (በሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔወች ዋቢነት የቀረበ)

በወርቅነህ Aለምነው

1. መግቢያ
የIትዮጵያ የፍታብሄር ህግ Aንቀጽ 1723 የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የተመለከተ
የባለቤትነት፣ የAላባ ጥቅም መብት፣ የመያዣ ወይም የሌላ Aገልግሎት መብት ለማቋቋም
ወይም ለማስተላለፍ የሚደረጉት ውሎች Eንዲሁም የክፍያ ወይም የማዛወር ሁሉ
በጽሁፍና በሚገባ Aኳኋን በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው
ፊት መሆን Aለባቸው በማለት ይደነግጋል፡፡ በሌላ በኩል ስለ ቤት ሽያጭ በሚደነግገው ልዩ
ክፍል የፍታብሄር ህጉ በAንቀጽ 2877 ስር የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከት ሽያጭ ውል
በጽሁፍ ሳይደረግ የቀረ Eንደሆነ ፈራሽ Eንደሚሆን ደንግጓል፡፡ ነገር ግን ይህ Aንቀጽ የሽያጭ
ውሉ ውል ለማዋዋል በህግ ስልጣን በተሰጠው የመንግስት Aካል ፊት መመዝገብ ያለበት
ስለመሆን ወይም Aለመሆኑ የሚለው ነገር የለም፡፡

የIትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር 214481
ላይ በሰጠው የህግ ትርጉም ቤቶችን የሚመለከቱ የሽያጭ ውሎች በህጉ ዘንድ ተቀባይነት
የሚኖራቸው የግድ በጽሁፍ ሲደረጉ Eና ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው Aካል ፊት
ሲመዘገቡ ብቻ ነው የሚል ትርጉም ሰጥቷል፡፡ ሰበር ሰሚ ችሎቱ የሰጠው ይህ የህግ ትርጉም
የውይይት Aጀንዳ የሆነበት ምክንያት ትርጉሙ ቀደም ሲል ለብዙ Aመታት ከነበረው የውል
Aመሰራረት ልማድ የተለየ በመሆኑ ነው፡፡ የቤት ሽያጭ ውሎች ለብዙ Aመታት ያህል
በIትዮጵያ ውስጥ ሲፈጸሙበት የነበረውን ልምድ ስንመለከት ውሎቹ በጽሁፍ ይደረጋሉ፡፡
ነገር ግን ውሎቹ በፍትህ ጽህፈት ቤቶች በሚገኙ የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ቢሮወች


LL.B, በንግድ ህግ LL.M፣ ቀደም ሲል የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ፣ በAሁኑ ጊዜ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህግ
መምህር፣ ማንኛውም Aይነት Aስተያየት በ I-ሜይል Aድራሻ worknehalemnew@gmail.com. መላክ
ይችላሉ፡፡ የዚህ ጽሁፍ Aዘጋጅ ለጽሁፉ መሳካት ገንቢ Aስተያት በመስጠት AስተዋጽO ላበረከቱ የህግ መጽሄቱ
Iዲቶሪያል ኮሚቴ Aባላት በተለይም ለAቶ ጋሻየ ቢያድጌ ከፍተኛ የሆነ ምስጋና ያቀርባል፡፡
1
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ውሳኔወች, ቅጽ 4, የሰበር መዝገብ ቁጥር -21448, 1999 ዓ.ም ገጽ. 40.
ወይም በሌላ ውል ለማዋዋል በህግ ስልጣን በተሰጠው የመንግስት Aካል ፊት ሲመዘገቡ
Aልነበረም፡፡ የባንኮችና ሌሎች ገንዘብ Aበዳሪ የፋይናንስ ተቋማትን Aሰራር ስንመለከትም
Eንዲሁ ለብድር ገንዘብ ቤቶችን ለማስያዝ የሚመሰረቱ ውሎች ውል ለማዋዋል በህግ ስልጣን
በተሰጠው የመንግስት Aካል ፊት Aይመዘገቡም፡፡ ስለሆነም የ I.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት ይህንን
በመገንዘብ ባንኮችና ሌሎች ገንዘብ Aበዳሪ የፋይናንስ ተቋማት ለብድር ቤቶችን ለማስያዝ
ከተበዳሪወች ጋር የሚፈጽሙት ውል በፍታብሄር ህጉ Aንቀጽ 1723 መሰረት ሊተረጎም
Aይገባም በማለት የሚደነግገውን Aዋጅ ቁጥር 639/2001 ደንግጓል፡፡

ስለሆነም የቤት ሽያጭ ውል ምዝገባ በየደረጃው ባሉ ዳኞችና በሌሎች የህግ ባለሙያወች


ዘንድ የሚያከራክር ጉዳይ ነው፡፡ የሚያከራክሩትን ነጥቦችም በዚህ ጽሁፍ በስፋት
Eንመለከታለን፡፡

2. የጽሁፉ ጠቀሜታ Eና Aላማወች

ይህ ጽሁፍ ጠቅለል ባለ መልኩ ሶስት Aላማወችና ጠቀሜታወች ያሉት ሲሆን Eነሱም፡-

ሀ. በIትዮጵያ ህጎች ውስጥ ስላለው የቤት ሽያጭ ውል Aጻጻፍ (ፎርም)ን መሰረታዊ ሀሳቦች
ለህግ Aውጭዎች፣ ለዳኞች፣ ለፍታብሄር Aቃቤ ህጎች፣ ለህግ መምህራን Eና ተማሪወች፣
ለጠበቃወች፣ ለህግ ባለሙያወች Eና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ሌሎች Aካላት ምርምርን መሰረት
ያደረገ ጠቃሚ መረጃ ለማቅረብ፤

ለ. የቤት ሽያጭ ውል Aጻጻፍ (ፎርም)ን Aስመልክቶ ወደፊት ለሚጻፉ ሌሎች ጽሁፎች


Eንደማጣቀሻ ምንጭ Eንዲሆን፤

ሐ. የቤት ሽያጭ ውል Aብዛኛውን የማህበረሰባችንን ክፍል የሚመለከት ጉዳይ በመሆኑ


ማህበረሰባችን በጉዳዩ ላይ ያለውን ግንዛቤ የበለጠ ለማሳደግ Eገዛ ለማድረግ፣ የሚሉት ናቸው፡፡

3. የጽሁፉ Aዘገጃጀት ዘዴ (Methodology)


ይህ ጽሁፍ Aይነታዊ ማስረጃወችን (qualitative data) በመጠቀመም የተዘጋጀ ነው፡፡ ጽሁፉ
በIትዮጵያ የህግ ማEቀፍ ውስጥ የቤት ሽያጭ ውሎች Aጻጻፍ (ፎርም)ን በተመለከተ የወጡ
ፖሊሲወችንና የተደነገጉ ህጎችን ይተነትናል፡፡ የI.ፌ.ዴ.ሪ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት የቤት ሽያጭ ውሎች Aጻጻፍ (ፎርም) ን በተመለከተ የሰጣቸው የህግ ትርጉሞች
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ካሳተማቸው ከ ቅጽ Aንድ ይህ ጽሁፍ Eስከታተመበት ድረስ ከወጡት
ቅጾች ውስጥ Eስከ ቅጽ 20 ድረስ መርጦ በማውጣትና የተለያዩ የህግ ባለሙያወች ያላቸውን
Aቋም በመተንተን Aስተያየት ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የዚህ ጽሁፍ Aዘጋጅ
በፌዴራልና በክልል ፍርድ ቤቶች የሚሰሩ የፍርድ ቤት ዳኞችን ቃለ መጠይቅ በማድረግ የቤት
ሽያጭ ውሎች Aጻጻፍን በተመለከተ ያላቸውን Aቋም ለማካተት ተሞክሯል፡፡ ከዚህ
በተጨማሪም Aዘጋጁ ከዚህ ቀደም በ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበረ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ
ያለውን ልምድ Eና የፍርድ ቤቶችን Aሰራር በምልከታ በመቃኘት በጽሁፉ ውስጥ Eንዲካተት
Aድርጓል፡፡ በIትዮጵያ ውስጥ የቤት ሽያጭ ውሎች Aጻጻፍ ዘመናዊና ውጤታማ Eንዲሆን
Eንዲሁም ወጥ በሆነ መንገድ Eንዲተገበር የሚረዱ በጉዳዩ ላይ Eንደ ሞዴል የሚጠቀሱ
የተመረጡ የበለጸጉ Aገራትን ህጎችና Aሰራሮች በዚህ ጽሁፍ ውስጥ Eንዲካተቱ ተደርገዋል፡፡

4. የቤት ሽያጭ ውሎች Aጻጻፍ ስርAት

በAለማችን ላይ ባሉ የተለያዩ የህግ ስርAቶች ውስጥ ተቀባይነት ያገኙ 3 (ሶስት) Aይነት የቤት
ሽያጭ ውል Aጻጻፍ ስርAቶች Aሉ፡፡ Eነሱም፡- ውልን በጽሁፍ መመስረት (written form)፣
ውልን ማረጋገጥ (authentication) Eና ውልን መመዝገብ (registration) የሚባሉት ናቸው፡፡
ከዚህ በመቀጠል ሁሉንም ተራ በተራ Eንመለከታለን፡፡

4.1. ውልን በጽሁፍ መመስረት (written form)

በAለማችን ላይ በሚገባ የሚታወቀው የውል Aጻጻፍ ስርAት ውልን በጽሁፍ መመስረት


ነው፡፡2 በብዙ Aገሮች የውል ህግ ማEቀፍ ውስጥ Aንድ ውል በጽሁፍ መመስረት ያለበት
ስለመሆኑ የህግ ድንጋጌ ካለ የውሉን ህጋዊነት ለመረዳት Aስፈላጊ ከሆኑ መስፈርቶች መካከል
ውልን በጽሁፍ ማድረግ Aንዱ መስፈርት ነው፡፡3 Eንደሚታወቀው በጽሁፍ የተመሰረቱ
ውሎች በቃል ከተደረጉ ውሎች በተሻለ የውል ግዴታ ስለመመስረቱ የማስረዳት Aቅም
Aላቸው፡፡4 በዚህም ምክንያት ይመስላል Iትዮጵያውያን Aበው “በቃል ያለ ይረሳል በጽሁፍ
ያለ ይወረሳል” በማለት የገለጹት፡፡ በተለይ ደግሞ ትልቅ ግምት የሚሰጣቸውና ብዙ የሆነ

2
H.G Beale (General Editor), Chitty on Contracts, General Principles, 28th Edition, Volume 1, 1999, London,
Sweet and Maxwell, p. 262
3
George. Krzeczunowicz, Formation and Effects of Contract in Ethiopian Law, 1983, Addis Ababa University,
Faculty of law, p. 8.
4
William .P. Anson, Principles of English Law of Contract, 19th ed. 1945, Oxford University Press, p. 67.
የገንዘብ ግምት ያላቸው ውሎች በጽሁፍ Eንዲመሰረቱ ይመከራል፡፡ ውሎችን በጽሁፍ
ስለመመስረት ስናስብ ሶስት ነገሮችን ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል፡፡ የመጀመሪያው ልዩ
የሆነ ሰነድ (special document)፣ ሁለተኛው ፊርማ(signature) ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ
ምስክሮች(witnesses) ናቸው::5 ከዚህ በመቀጠል ሁሉንም ተራ በተራ Eናያለን፡፡

4.1.1. ልዩ የሆነ ሰነድ (special document)

ልዩ የሆነ ሰነድን በተመለከተ የIትዮጵያ የፍታብሄር ህግ በAንቀጽ 1721 (1) ስር ውል


በጽሁፍ Eንዲደረግ ግዴታ ሲኖር ልዩ በሆነ Aሰራር (በተለየ ሰነድ) ተገልጾ በውሉ ግዴታ
ያለባቸው ሰወች ሁሉ ሊፈርሙበት Eንደሚገባ ይደነግጋል፡፡ ይህም ተዋዋይ ወገኖች
የተመሰረተውን ውል ለመፈጸም ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚገልጹበት የውል ሰነድ ነው፡፡6
ዋናውን ውል የመለወጥ ጉዳይ ለውሉ በተደነገገው የAጻጻፍ ስርAት (ፎርም) መሰረት
በተመሳሳይ መልኩ መደረግ Eንዳለበት በፍታብሄር ህጋችን Aንቀጽ 1722 ስር ተደንግጓል፡፡

4.1.2. ፊርማ (signature)

Aንድ ተዋዋይ ወገን በውል ሰነዱ ላይ ስሙ መገለጹ ብቻ በቂ Aይደለም፡፡ በውል ግዴታ


ያለባቸው ሰወች ሁሉ ውሉ ላይ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡7 ፊርማውን በውል
ሰነድ ላይ የፈረመ ተዋዋይ ወገን ስለገባበት የውል ግዴታ በጥሞና Aስቦ Eና Aምኖበት
ፊርማውን Eንዳስቀመጠ ይታመናል፡፡ ስለሆነም ውሉ ሳይፈጸም ቢቀር ሀላፊነቱን ቀድሞ
በፊርማው Eንደወሰደ ይቆጠራል፡፡

ፊርማን በተመለከተ የሚነሳው ሌላው ጉዳይ የፊርማ ስርAትን በወኪል Aማካኝነት ማከናወን
ይቻላል ወይ የሚለው ነው፡፡ በIትዮጵያ የፍታብሄር ህግ Aንቀጽ 1728 (1) መሰረት ፊርማ
በውሉ ተገዳጅ በሆነ ሰው Eጅ መጻፍ ይገባዋል፡፡ ነገር ግን በውክልና ህግ መሰረት ተወካይ
ወካይን በመወከል ውል ሊፈራረም ይችላል፡፡ በፍታብሄር ህጉ Aንቀጽ 2199 Eንደተመለከተው
ውክልና ማለት ተወካይ የተባለ Aንድ ሰው ወካይ ለተባለው ሰው Eንደራሴ ሆኖ Aንድ ወይም
ብዙ ህጋዊ ስራወች በወካዩ ስም ለማከናወን ግዴታ የሚገባበት ውል ማለት ነው፡፡ ህጋዊ

5
የIትዮጵያ የፍታብሄር ህግ፣ ነጋሪት ጋዜጣ፣ Aዋጅ ቁጥር 165/1952፣ Aንቀጽ 1727 (1)
6
George. Krzeczunowicz, Formation and Effects of Contract in Ethiopian Law, 1983, Addis Ababa University,
Faculty of law, p. 75
7
የIትዮጵያ የፍታብሄር ህግ፣ ነጋሪት ጋዜጣ፣ Aዋጅ ቁጥር 165/1952፣ Aንቀጽ 1727 (1)
ስራወች ከሚባሉት ተግባራት መካከል ተወካይ ወካይን በመወከል የሚፈራረማቸው ውሎች
ይጠቀሳሉ፡፡

ታዋቂው የህግ ምሁር ጆርጅ ችችኖቪች የIትዮጵያ የፍታብሄር ህግ Aንቀጽ 1728 ን


በተመለከተ በሰጡት Aስተያየት “ፊርማ በሰው Eጅ መጻፍ ይገባዋል” የሚለው Aባባል ፊርማን
ከ Eጅ ጽሁፍ ውጭ ሜካኒካል በሆነ መንገድ መፈረም Eንደማይቻል ይጠቁማል በማለት
ይገልጻሉ፡፡8 የIትዮጵያ የውል ህግ የተዋዋይ ወገኖች ፊርማ በውል ሰነዱ በየትኛው ክፍል ላይ
መፈረም Eንዳለበት የሚለው ነገር የለም፡፡ ለAብነት ያህል- የስዊዘርላንድ Aገር የውል ህግ
ፊርማ በውል ሰነዱ የታችኛው ክፍል (በግርጌ) በኩል መፈረም ያለበት ስለመሆኑ Eና ከAንድ
በላይ ገጾች ያሉት የውል ሰነድ ከሆነ በEያንዳንዱ ገጽ ላይ ተዋዋይ ወገኖች ፊርማቸውን
ማስቀመጥ Eንዳለባቸው በግልጽ ደንግጓል፡፡9 Eንደ የዚህ ጽሁፍ Aዘጋጅ Eምነት ከሆነ
በIትዮጵያም በተመሳሳይ ተዋዋይ ወገኖች በስዊዘርላንድ የውል ህግ በደነገገው Aግባብ
ፊርማቸውን ቢያስቀምጡ መልካም ነው፡፡

ቤላ በኩል በIትዮጵያ የፍታብሄር ህግ Aንቀጽ 1728 (2) መሰረት “ለመፈረም የማይችል ሰው


በጽህፈት ፊርማው ፋንታ የጣት ምልክት መተካት ይችላል፡፡” ነገር ግን “ማየት የተሳናቸው
ሰወች ወይም ያልተማሩ ሰወች የጣት ምልክት ፊርማ የEነሱ ፊርማ መሆኑን ውል Aዋዋይ
ሹም ወይም Aንድ ፍርድ ጸሀፊ ወይም Aንድ ዳኛ በስራቸው ላይ ሆነው ያረጋገጧቸው ካልሆነ
Aያስገድዳቸውም፡፡”10 ሌላው ነጥብ ደግሞ በተለያዩ የAካል ጉዳቶች ምክንያት Eጅ የሌላቸው
ወይም Eጃቸውን ማንቀሳቀስ የማይችሉ ሰወች በEጅ ጽሁፍ ለመፈረምም ሆነ በጣት ምልክት
ለመፈረም Aይችሉም፡፡ ስለሆነም የEነዚህ ወገኖች የፊርማ Eጣ ፋንታ ምን ሊሆን Eንደሚገባው
በፍታብሄር ህጋችን ውስጥ በግልጽ ተብራርቶ Aልተቀመጠም፡፡ ስለሆነም ህጉ ወደፊት ሲሻሻል
ይህንን ጉዳይ ሊያካትት ይገባል፡፡ Eነዚህ ወገኖች በውሉ ለመገደድ ያላቸውን ፈቃድ በፍርድ
ቤት ፊት ወይም በውል Aዋዋይ ቢሮዎች በኩል Eንዲያረጋግጡ በማድረግ ፊርማ መፈረም
ባለመቻላቸው ምክንያት ከሚደርስባቸው የመጭበርበር ስጋት ነጻ ሊደረጉ ይገባል፡፡

8
George. Krzeczunowicz, የግርጌ ማስታወሻ 6፣ ገጽ 75.
9
William .P. Anson, Principles of English Law of Contract, 19th ed. 1945, Oxford University Press, p.76.
10
የIትዮጵያ የፍታብሄር ህግ፣ ነጋሪት ጋዜጣ፣ Aዋጅ ቁጥር 165/1952፣ Aንቀጽ 1728 (3)
4.1.3. ምስክሮች ( Witnesses)
የIትዮጵያን ህግ ጨምሮ የሌሎች Aገራት ህጎች ተዋዋይ ወገኖች Aንድን ውል ተስማምተው
የፈጸሙ ስለመሆናቸው Eና የውሉ ቃል ምን Eንደሆነ ለማረጋገጥ ምስክሮች የግድ Aስፈላጊ
ስለመሆናቸው ይደነግጋሉ፡፡11 ምስክር ለመሆን በጾታ ወይም በዜግነት ምክንያት ክልከላ ሊኖር
Aይገባም፡፡12 ይሁን Eንጅ ማንኛውም ምስክር ለAካለ መጠን የደረሰ (18 Aመት የሞላው)
Eንዲሁም በህግ ወይም በፍርድ ያልተከለከለ መሆን ይገባዋል፡፡13 ስለሆነም በIትዮጵያ
የፍታብሄር ህግ Aንቀጽ 1727 (2) መሰረት Aንድ ውል በህግ ፊት Eንዲጸና የግድ በትንሹ
በሁለት ምስክሮች ፊት መረጋገጥ Aለበት፡፡ ምስክሮችም Eንደ ተዋዋይ ወገኖች ፊርማቸውን
በውል ሰነዱ ላይ መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ምስክሮች ለAንዱ ተዋዋይ ወገን ዋስ ነን ብለው
በመግለጽ የውል ግዴታ የገቡ ካልሆነ በስተቀር ስለ ውሉ Aፈጻጸም የዋስትና ሀላፊነት
የለባቸውም፡፡14 ይሁን Eንጅ የምስክሮች ሚና ውል የተፈጸመ ስለመሆኑ Eና የውል
ድንጋጌወቹን ለማረጋገጥ ብቻ የተወሰነ Aይደለም፡፡ ውል በጽሁፍ Eንዲሆን ህግ ባዘዘ ጊዜ
የጽሁፍ ውሉ የተቀደደ፤ የተሰረቀ ወይም የጠፋ መሆኑ ከተረጋገጠ ውሉን በምስክሮች
ማስረዳት ይቻላል፡፡15
4.2. ውል ማረጋገጥ ( Authentication)

በጽሁፍ የተዘጋጁ ውሎች በማስረጃነት ከመቆጠራቸው በፊት ትክክለኛ ስለመሆናቸው


ሊረጋገጡ ይገባል በማለት የሚያሳስቡ ብዙ የህግ ምሁራን Aሉ፡፡ ከEነዚህ ምሁራን መካከል
ጆን ዊሊያም የተባሉት የህግ ምሁር የጽሁፍ ውል ትክክለኛ ስለመሆኑ በሌሎች ማስረጃወች
ሊረጋገጥ ይገባል በማለት Aስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡16 ነገር ግን ይህንን Aስተያየት የሚተቹ
ሌሎች ህግ ምሁራን Aሉ፡፡ ለAብነት ያህል፡ ኤል - ሌቪን የተባሉት የህግ ምሁር የጽሁፍ
ውሎች ትክክለኛነት የግድ በሌሎች ማስረጃወች ሊረጋገጥ ይገባል ካልን ቀልጣፋ የሆነ የንግድ
ግንኙነት Eንዳይኖር Eያደረግን ነው በማለት ይከራከራሉ፡፡17 ይሁን Eንጅ ብዙ የህግ ስርAቶች

11
ዝኒ ከማሁ፡ Aንቀጽ 1727 (2)
12
ዝኒ ከማሁ፡ Aንቀጽ 1729 (2)
13
ዝኒ ከማሁ፡ Aንቀጽ 1729 (1)
14
ዝኒ ከማሁ፡ Aንቀጽ 1730 (2)
15
ዝኒ ከማሁ፡ Aንቀጽ 2003
16
John William Strong, Liberalizing the Authentication of Private Writings, Cornell Law Rev. Vol.52, 1966-1967,
p. 284.
17
A. L. Levin, Authentication and Content of Writings, Rutgers Law Review, Vol.10, No.3, 1955-1956, p. 634
የውሎችን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ተAማኒነት ያለው የንግድ ልውውጥ ለማካሄድ Aስፈላጊ
መሆኑን በማመን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

Aቶ ሚሊዮን Aሰፋ የተባሉ የህግ ምሁር ውል ማረጋገጥ ማለት የውል ግዴታ ያለባቸውን
ተዋዋይ ወገኖች ፊርማ ማረጋገጥ ማለት ነው በማለት ትርጉም ሰጥተዋል፡፡18 Eንደ Aቶ
ሚሊዮን Aሰፋ Aገላለጽ ውል ማረጋገጥ ሁለት Aይነት ገጽታወች ያሉት ሲሆን የመጀመሪያው
የውል ግዴታ ያለባቸውን ተዋዋይ ወገኖች ፊርማ በምስክሮች ፊት ማረጋገጥ ነው፡፡ ሁለተኛው
ደግሞ የተዋዋዮቹን ፊርማ በህግ ስልጣን በተሰጣቸው የመንግስት ተቋማት ውስጥ በመሄድ
ማረጋገጥ ነው፡፡19

4.3. የውል ምዝገባ (Registration)


የምዝገባ ጽንሰ ሀሳብ የተጀመረው ከ ሮማ ህግ (Roman law) ስለመሆኑ ይታመናል፡፡20
የውል ምዝገባ ጽንሰ ሀሳብ ደግሞ በ 20 ኛው ክፍለ ዘመን መግቢያ Aካባቢ Eንደተጀመረ
የተለያዩ ጽሁፎች ይጠቁማሉ፡፡21 ውልን በህግ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው የመንግስት
ቢሮ ውስጥ ማስመዝገብ የውሉን ትክክለኛነት ከማረጋገጡም በላይ በውሉ ተዋዋይ ያልነበሩ
ሌሎች ሶስተኛ ወገኖች ስለ ውሉ Eውቅና Eንዲያገኙ ያስችላል፡፡22

የIትዮጵያ የውል ህግን ስንመለከት በፍታብሄር ህግ Aንቀጽ 1723 ስር “የማይንቀሳቀሱ


ንብረቶችን የተመለከተ የባለቤትነት፣ የAላባ ጥቅም መብት፣ የመያዣ ወይም የሌላ Aገልግሎት
መብት ለማቋቋም ወይም ለማስተላለፍ የሚደረጉት ውሎች Eንዲሁም የክፍያ ወይም
የማዛወር ሁሉ በጽሁፍና በሚገባ Aኳኋን በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ውል ለማዋዋል
ስልጣን በተሰጠው ፊት መሆን Aለባቸው” የሚል ድንጋጌ Eናገኛለን፡፡ ነገር ግን የዚህን Aንቀጽ
ትርጉም በተመለከተ ዳኞች፣ የህግ ምሁራን Eና ሌሎች የህግ ባለሙያወች የተለያዩ
Aስተያየቶችን ይሰጣሉ፡፡ Eነዚህን Aስተያየቶች በስፋት የምንመለከታቸው ይሆናል፡፡

18
Million Assefa, Form of Contract Relating to Immovables in Ethiopia, the Law and Interpretation, Wonber,
Alemayehu Haile Memorial Foundation’s Periodical, 6th half year, April/may 2010, p. 21.
19
ዝኒ ከማሁ
20
Yohanes Heroui, Registration of Immovables under the Ethiopian Civil Code; An Overview in Comparative
Perspective, Ethiopian Bar Review, Vol.2, No.2, March 2008, p.51.
21
Martin Dixon, Principles of Land Law, third edition, 1999, Cavendish Publishing Limited, p.10
22
ዮሀንስ ህሩይ፡ የግርጌ ማስታወሻ 20
5. የቤት ሽያጭ ውል Aጻጻፍ ስርAትን በተመለከተ የሌሎች Aገራት Aሰራር

በተለያዩ Aገራት ህጎች ውስጥ የቤት ሽያጭ ውል Aጻጻፍ ስርAትን በተመለከተ የተለያዩ
Aቋሞች ይንጸባረቃሉ፡፡ በEንግሊዝ Aገር የህግ ስርAት መሰረት የቤት ሽያጭ ውሎች የግድ
በጽሁፍ መሰራት Aለባቸው፡፡23 ነገር ግን የውል ምዝገባ Eንደ መሰረታዊ መስፈርት
Aይወሰድም፡፡24 የAሜሪካን Aገር የቤት ሽያጭ ውል ህግ ከEንግሊዝ Aገር የውል ህግ
(Statute of Fraud Law) የተቀዳ ሲሆን የAሜሪካው የውል ህግ የሚለየው የቤት ሽያጭ
ውሎችን የመረጃ መረብ (Iንተርኔት) ን በመጠቀም በኤሌክትሮኒክስ የAጻጻፍ ስርAት መሰረት
መመስረት ይቻላል፡፡25 ታላቁ የህግ ምሁር ፕላኒዮል Eንደገለጹት ከበለጸጉት Aገራት ህጎች
ውስጥ የጀርመን Aገር የቤት ሽያጭ ውል ህግ የተለየ ነው፡፡26 በጀርመን Aገር የፍታብሄር ህግ
Aንቀጽ 873 መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በጽሁፍ ሊደረግ ይገባል፡፡
በተጨማሪም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው የመንግስት ቢሮ ውስጥ ካልተመዘገበ ውሉ
በህግ ፊት ተቀባይነት የለውም፡፡27 ስለሆነም በጀርመን Aገር የፍታብሄር ህግ መሰረት የቤት
ሽያጭ ውል ምዝገባ Aንዱ መሰረታዊ መስፈርት ነው፡፡

በሌላ በኩል በፈረንሳይ Aገር የውል ህግ መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል


በሚመለከተው የመንግስት Aካል ፊት ባይመዘገብም ውሉ ተቀባይነት Aለው፡፡28 ስለሆነም
በፈረንሳይ Aገር Aንድ ውል በህግ ፊት ያለውን ተቀባይነት ለማረጋገጥ Eንደ መስፈርት
Aያገለግልም ማለት ነው፡፡ በፈረንሳይ Aገር የውል ምዝገባ Aላማ ለ 3ኛ ወገኖች ስለ ውሉ
መኖር Eውቅና ለመስጠት Eና በውሉ ላይ ቅድሚያ መብት ያላቸውን ሰወች ለመለየት ብቻ
Eንደሆነ የተለያዩ ጽሁፎች ይጠቁማሉ፡፡29 በAንዳንድ የደቡብ Aሜሪካ Aገራት ህጎች፡- ለAብነት
ያህል፡ በAርጀንቲና የፍታብሄር ህግ መሰረት የቤት ሽያጭ ውል በጽሁፍ መደረግ ያለበት

23
H.G Beale (General Editor), Chitty on Contracts, General Principles, 28th Edition, Volume 1, 1999, London,
Sweet and Maxwell, p. 262.
24
ዝኒ ከማሁ
25
Electronic Notary Statute // http://www.azleg.state.az.us/ars/41/00352.htm.(Last visited September 20, 2015).
26
Planiol, Treatise on the Civil Law, Volume 1, Part 2, Louisiana State Law Institute, p.529 as cited in Yohannes
Herui, Supra note 100, p. 34.
27
K.W. Ryan, An Introduction to the Civil Law, 1962, Sydney Hallstead Press, p.176.
28
ዝኒ ከማሁ
29
K.W. Ryan, የግርጌ ማስታወሻ 27፡
ሲሆን ነገር ግን ውሉ የግድ መመዝገብ Aይጠበቅበትም፡፡30 በAርጀንቲና የምዝገባ ዋና Aላማ
ልክ Eንደ ፈረንሳይ ህግ Aላማ ሁሉ ውሉን ለ 3ኛ ወገኖች ለማሳወቅ Eና Aንድ ቤትን
በተመለከተ የተመሰረቱ ሌሎች የሽያጭ ውሎች ካሉ ውሎቹ የተመዘገቡበትን ቀን በመመልከት
Eና ለውሎቹ የተሰጡትን የምዝገባ ቁጥሮች በማየት ቀድሞ የተመዘገበውን ውል ተቀባይነት
Eንዲኖረው ለማስቻል ነው፡፡ (First to registered, first in right)::31 ነገር ግን ውሉ
ባለመመዝገቡ ምክንያት ውሉ Eንዲፈርስ መጠየቅ Aይቻልም፡፡

6. በIትዮጵያ የውል ምዝገባ ለቤት ሽያጭ ውል መሰረታዊ Eና Aስገዳጅ መስፈርት ነውን?

ከIትዮጵያ የፍታብሄር ህግ Aንቀጾች መካከል 1723 ን Eና 2877 ን በጋራ ስንመለከት የቤት


ሽያጭ ውል በጽሁፍ ሳይደረግ የቀረ Eንደሆነ ፈራሽ ይሆናል፡፡ ስለሆነም የቤት ሽያጭ ውል
በጽሁፍ መደረግ Eንዳለበት ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን በIትዮጵያ የውል ምዝገባ ለማይንቀሳቀስ
ንብረት ሽያጭ ውል መሰረታዊ Eና Aስገዳጅ መስፈርት ነውን? በሚለው ጥያቄ ዙሪያ በዳኞች፣
ህግ ምሁራን Eና በህግ ባለሙያወች መካከል ክርክር ይነሳል፡፡ ለክርክሩ መነሻ የሆነው
የIትዮጵያ የፍታብሄር ህግ Aንቀጽ 1723 ሲሆን ይህ Aንቀጽ “የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን
የተመለከተ የባለቤትነት፣ የAላባ ጥቅም መብት፣ የመያዣ ወይም የሌላ Aገልግሎት መብት
ለማቋቋም ወይም ለማስተላለፍ የሚደረጉት ውሎች Eንዲሁም የክፍያ ወይም የማዛወር ሁሉ
በጽሁፍና በሚገባ Aኳኋን በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው
ፊት መሆን Aለባቸው” በማለት ይደነግጋል፡፡ በቁጥር ቀላል የማይባሉ ዳኞችና የህግ
ባለሙያወች የቤት ሽያጭ ውል በጽሁፍ Eስከተደረገ ድረስ የውሉ Aለመመዝገብ በውሉ
ህልውና ላይ Aሉታዊ ውጤት ሊኖረው Aይገባም በማለት ይከራከራሉ፡፡32 ለዚህም
ምክንያታቸውን ሲገልጹ በፍታብሄር ህግ Aንቀጽ 1723 ስር የተደነገገው ድንጋጌ ጠቅላላ
ድንጋጌ ሲሆን ስለ ቤት ሽያጭ ውል በልዩ ሁኔታ የሚደነግጉት የፍታብሄር ህግ Aንቀጾች
2877 Eና 2878 ሲሆኑ Eነዚህ ድንጋጌወች የቤት ሽያጭ ውል የግድ መመዝገብ Aለበት
የሚሉ ባለመሆናቸው በህግ Aተረጓጎም መርህ መሰረት በልዩ ሁኔታ የተደነገጉት Aንቀጾች

30
Armando J. Tirado, Notarial and Other Registration Systems, Notaries in Latin America, Florida Journal of
International law, vol.11, 1996, pp.183 -184.
31
ዝኒ ከማሁ
32
George. Krzeczunowicz, ግርጌ ማስታወሻ 6 ገጽ 74. እንዲሁም Rene David, Commentary on Contracts in
Ethiopia, translated by Michael Kindred, 1973, Haile Sellassie I university, Faculty of Law, p.32. ይመልከቱ
ተግባራዊ ሊደረጉ ይገባል (Special provision of law prevails over general provision of
law)፡፡

በፍታብሄር ህጋችን Aንቀጽ 2877 ስር “የAንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ንብረቱ


ባለበት Aገር በሚገኘው የማይንቀሳቀስ ሀብት መዝገብ ካልተጻፈ በቀር በ 3ኛ ወገኖች ዘንድ
ውጤት ሊያስገኝ Aይችልም” የሚል ድንጋጌ Eንገኛለን፡፡ ይሁን Eንጅ ውሉ Aለመመዝገቡ
በተዋዋይ ወገኖች መካከል ስለሚኖረው ውጤት Aንቀጹ ያስቀመጠው ነገር የለም፡፡ ስለሆነም
በIትዮጵያ የውል ህግ ላይ Aስተያየታቸውን የጻፉት ታላላቅ የህግ ምሁራን፡- ለAብነት ያህል፡
ፕሮፌሰር ጆርጅ ችችኖቪች33፣ፕሮፌሰር ሬኒ ዴቪድ34፣ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ35፣ Aቶ
ሚሊዮን Aሰፋ36፣ Aቶ ዮሀንስ ህሩይ37፣ Aቶ መክብብ ጸጋው38 በሰጡት Aስተያየት የቤት
ሽያጭ ውል Aለመመዝገብ በተዋዋይ ወገኖች ዘንድ ያለውን ግዴታ ቀሪ ሊያደርገው Aይገባም፡፡
Eንደነሱ Aስተያየት የቤት ሽያጭ ውል ባይመዘገብም በጽሁፍ ከተደረገ በተዋዋይ ወገኖች
መካከል ግዴታን ለመፍጠር በቂ ነው፡፡

በፕሮፌሰር ጆርጅ ችችኖቪች Aስተያየት መሰረት የምዝገባ ዋናው Aላማ ውል ስለመኖሩ ለ 3ኛ


ወገኖች ለማስተዋወቅ ነው፡፡ በፍታብሄር ህጋችን Aንቀጽ 1720 (3) ስር “ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ
በቀር ስለ ውል ጉዳይ የተወሰኑ የማስታወቂያ ድንጋጌወችን Aለመፈጸም ውሉን ፈራሽ
Aያደርገውም” የሚለውን ድንጋጌ ለAስተያየታቸው Eንደማጣቀሻ ጠቁመዋል፡፡39

ፕሮፌሰር ሬኒ ዴቪድ በበኩላቸው የምዝገባ መስፈርትን ከቀረጥና ግብር መስፈርቶች ጋር


ማገናኘት ተገቢ Aለመሆኑን ጠቅሰዋል፡፡40 ስለሆነም የምዝገባ መስፈርት Aለመሟላት ውሉን
ፈራሽ ሊያደርገው Aይገባም በማለት በፍታብሄር ህግ Aንቀጽ 1720 (2) ስር ያለውን ድንጋጌ
በAስረጅነት ጠቁመዋል፡፡ ይህ ንUስ Aንቀጽ “Eንደ ቴምብር መክፈል ወይም Eንደ መመዝገብ

33
George. Krzeczunowicz ዝኒ ከማሁ -
34
Rene David, ግርጌ ማስታወሻ 32 ገጽ 32.
35
ጥላሁን ተሸመ፣የውል ህግ መሰረታዊ ባህሪያት፣ 1988, የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት, ምርምር Eና
ህትመት ክፍል, ገጾች 64-67.
36
Million Assefa, ግርጌ ማስታወሻ 18 ገጽ 21.
37
Yohanes Heroui, ግርጌ ማስታወሻ 20 ገጽ 51.
38
Mekibib Tsegaw ,Contracts Relating to Immovables and the Question of Form; Current Concerns (Amharic)
Ethiopian Bar Review, Vol.2, No.1, (2007), p. 166.
39
የግርጌ ማስታወሻ 6፡ ፕሮፌሰር ጆርጅ ችችኖቪች
40
የግርጌ ማስታወሻ 32፡ ፕሮፌሰር ሬኒ ዴቪድ
ግዴታ ያሉት ስለ ውል ጉዳይ የተወሰኑት የቀረጥና የግብር ድንጋጌወች Aለመፈጸም ውሉን
ፈራሽ Aያደርገውም” በማለት ይደነግጋል፡፡

በመሰረቱ ከዚህ ነጥብ ጋር ተነጥሎ መታየት ያለበት ጉዳይ የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ
መስፈርት ነው፡፡ በፍታብሄር ህጋችን Aንቀጽ 1195 (1) መሰረት የቤት ባለንብረት መሆንን
በማወቅ በAስተዳደር ክፍል ለAንድ ሰው የተሰጠ የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት ማስረጃ
የተሰጠው ሰው የቤቱ ባለሀብት Eንደሆነ ያስቆጥረዋል፡፡ ነገር ግን የቤት ሽያጭ ውል Aጻጻፍ
ስርAት (ፎርም) መስፈርቶች ግን ውሉ በተዋዋይ ወገኖች Eና በ 3ኛ ወገኖች ላይ
የሚያስከትላቸውን ከውሉ ጋር ተያያዥ የሆኑ ግዴታወችን ለመረዳት የሚያስችሉ ናቸው፡፡41

ታዋቂው የህግ ምሁር Aቶ ዮሀንስ ህሩይ የሚያነሱት ሌላው ነጥብ ደግሞ Eንደ Iትዮጵያ
ዘመን Aቆጣጠር በ 1952 ዓ.ም ከወጣው የIትዮጵያ የፍታብሄር ህግ በኋላ ፍርድ ቤቶችና
የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ ጽህፈት ቤቶች በምን Aግባብ Eና ስነ-ስርAት መሰረት ውሎችን
Eንደሚመዘግቡ በግልጽ የሚያብራራ Aዋጅም ሆነ ደምብ ለረጅም ጊዜ Aልነበረም፡፡42 ስለሆነም
በEያንዳንዱ የIትዮጵያ ክፍለ Aገራት የቤት ሽያጭ ውሎችን ለመመዝገብ የተቋቋሙ ተቋማት
በበቂ ሁኔታ ባልተደራጁበት ሁኔታ የቤት ሽያጭ ውል ካልተመዘገበ በቀር ፈራሽ ነው የሚል
Aቋም መውሰድ ተገቢ Aይደለም ሲሉ Aስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡43

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትን ጨምሮ ሌሎች ዳኞችና የህግ ባለሙያወች
ደግሞ የማይንቀሳቀስ ንብረቶችን የሚመለከቱ ውሎች በህጉ ዘንድ ተቀባይነት የሚኖራቸው
በጽሁፍ ሲደረጉ ብቻ ሳይሆን ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው Aካል ፊት ሲመዘገቡ
ጭምር ነው የሚል Aቋም Aላቸው፡፡44 ይህን Aቋም Eንደ Iትዮጵያ ዘመን Aቆጣጠር ከ 1999
ዓ.ም ጀምሮ የIትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት Aቋም ሆኖ
Eናገኘዋለን፡፡ የሰበር ሰሚ ችሎቱ በሰበር መዝገብ ቁጥር 2144845 ላይ በሰጠው የህግ ትርጉም
ይህንኑ Aቋም ያጠናከረ ሲሆን ይህ ትርጉም በብዙ የህግ ባለሙያወች ዘንድ የውይይት Aጀንዳ
ለመሆን ችሏል፡፡46 ሰበር ሰሚ ችሎቱ በጉዳዩ ላይ የሰጠው የህግ ትርጉም የማይንቀሳቀስ

41
ዝኒ ከማሁ
42
የግርጌ ማስታወሻ 20፡ ዮሀንስ ህሩይ
43
ዝኒ ከማሁ
44
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔወች፣ ቅጽ 4፣ መዝገብ ቁጥር- 21448፣ የIፌዲሪ
ጠ/ፍ/ቤት የጥናትና የህግ ድጋፍ መምሪያ፣ 1999 (በIትዮጵያ Aቆጣጠር)፣ ገጽ 40
45
ዝኒ ከማሁ
46
Yohannes Heroui, ግርጌ ማስታወሻ 20 ገጽ.31
ንብረቶችን የሚመለከቱ የሽያጭ ውሎች በህጉ ዘንድ ተቀባይነት የሚኖራቸው የግድ በጽሁፍ
ሲደረጉ Eና ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው Aካል ፊት ሲመዘገቡ ብቻ ነው የሚል ነው፡፡
ሰበር ሰሚ ችሎቱ የሰጠው ይህ የህግ ትርጉም የውይይት Aጀንዳ የሆነበት ምክንያት ትርጉሙ
ቀደም ሲል ለብዙ Aመታት ከነበረው የውል Aመሰራረት ልማድ የተለየ በመሆኑ ነው ሲሉ
Aንዳንድ የህግ ባለሙያወች ይገልጻሉ፡፡47

ምዝገባ መሰረታዊ መስፈርት ነው በማለት የሚከራከሩት ዳኞችና የህግ ባለሙያወች


ከፍታብሄር ህጉ Aንቀጽ 1723 በተጨማሪ የዚሁን ህግ Aንቀጽ 3052 ን ያነሳሉ፡፡ Aንቀጽ
3052 የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ በማናቸውም Aይነት ሰነድ ላይ የተመሰረተ ሲሆን
ከተጻፈበት ቀን Aንስቶ ንብረቱ በሚገኝበት Aገር ባለው ርስት መዝገብ ላይ ካልተጻፈ በቀር
ማንኛውንም ውጤት Aያገኝም በማለት ይደነግጋል፡፡ ስለሆነም ለቤት መያዣ ውል ምዝገባ
Aስገዳጅ መስፈርት ከሆነ ለቤት ሽያጭ ውልም Eንዲሁ ምዝገባ Aስገዳጅ መስፈርት ሊሆን
ይገባል በማለት Aስተያየታቸውን ይሰጣሉ፡፡48 ስለዚህ በፍታብሄር ህጋችን Aንቀጽ 1723 Eና
Aንቀጽ 1720 (1) መሰረት ያልተመዘገበ የቤት ሽያጭ ውል Aንዱን የምዝገባ መሰረታዊ
መስፈርት ያላሟላ ስለሆነ Eንደ ረቂቅ ብቻ ይቆጠራል በማለት ይገልጻሉ፡፡49

የI.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ Aዋጅ ቁጥር 25/1988 ን


ለማሻሻል ባወጣው Aዋጅ ቁጥር 454/97 መሰረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ
ችሎት የሚሰጣቸው የህግ ትርጉሞች በሁሉም ደረጃ በሚገኙ የፌዴራልና የክልል ፍርድ
ቤቶች ላይ Aስገዳጅ የሆነ ውጤት Aላቸው፡፡50 ተዋዋይ ወገኖች በመካከላቸው ህጋዊ ውል
መኖሩን Eስካላመኑ ድረስ የቤት ሽያጭ ውሉ የምዝገባ መስፈርቱን Aላሟላም በሚል
ምክንያት ውሉን ለማፍረስ ይቻላል፡፡ ስለሆነም ሰበር ሰሚ ችሎቱ በ ቅጽ 4፣ በመዝገብ ቁጥር-
21448 የሰጠውን ውሳኔ Eስከ Aሁን ድረስ በግልጽ ያልሻረው በመሆኑና ችሎቱ የሰጠው ይህ
የህግ ትርጉም Aስገዳጅ በመሆኑ በመርህ ደረጃ በIትዮጵያ የውል ምዝገባ ለማይንቀሳቀስ
ንብረት ሽያጭ ውል መሰረታዊ Eና Aስገዳጅ መስፈርት ነው በማለት መደምደም ይቻላል፡፡

47
ዝኒ ከማሁ
48
የግርጌ ማስታወሻ 1፡ ሰበር መዝገብ ቁጥር- 21448
49
ዝኒ ከማሁ
50
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ Aዋጅ ቁጥር 25/1988 ን ለማሻሻል የወጣው Aዋጅ ቁጥር 454/97፣
Aንቀጽ 2 (1)
ይሁን Eንጅ ቀደም ሲል Eንዳየነው በIትዮጵያ የቤት ሽያጭ ውሎች ለብዙ Aመታት ያህል
ሲፈጸሙበት የነበረውን ልምድ ስንመለከት ውሎቹ በጽሁፍ ከመደረጋቸው ውጭ ውል
ለማዋዋል በህግ ስልጣን በተሰጠው የመንግስት Aካል ፊት ሲመዘገቡ Aልነበረም፡፡ የባንኮችና
ሌሎች ገንዘብ Aበዳሪ የፋይናንስ ተቋማትን Aሰራር ስንመለከት ደግሞ ለብድር ገንዘብ ቤቶችን
ለማስያዝ የሚመሰረቱ ውሎች ውል ለማዋዋል በህግ ስልጣን በተሰጠው የመንግስት Aካል
ፊት ሲመዘገቡ Aይስተዋልም፡፡ ስለሆነም የ I.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት ይህንን በመገንዘብ ባንኮችና
ሌሎች ገንዘብ Aበዳሪ የፋይናንስ ተቋማት ለብድር ገንዘብ ቤቶችን ለማስያዝ ከተበዳሪወች ጋር
የሚፈጽሙት ውል በፍታብሄር ህጉ Aንቀጽ 1723 መሰረት ሊተረጎም Aይገባም በማለት
የሚደነግገውን Aዋጅ ቁጥር 639/2001 ደንግጓል፡፡ በሌላ በኩል በ 2001 ዓ.ም የሰበር ሰሚ
ችሎቱ በተወሰነ መልኩ የAቋም መለሳለስ በማድረግ በሰበር መዝገብ ቁጥር 36887፡ በቅጽ 12
ላይ በሰጠው የህግ ትርጉም የቤት ሽያጭ ውል ስለመኖሩ በተዋዋይ ወገኖች የታመነ ከሆነ
ውሉ ባይመዘገብም በጽሁፍ መደረጉ ብቻ ህጋዊ Eውቅና ያሰጠዋል በማለት ወስኗል፡፡
በተጨማሪም የቤት ሽያጭ ውል ባለመመዝገቡ ምክንያት Eንዲፈርስ ተዋዋይ ወገኖች
ካልጠየቁ በስተቀር ፍርድ ቤቶች በፍታብሄር ህጉ Aንቀጽ 1808 (2) መሰረት በራሳቸው
Aነሳሽነት ውሉ Eንዲፈርስ ማድረግ Aይችሉም የሚል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም Eነዚህን
ከላይ የተጠቀሱትን ልዪነቶች Eንደ ልዩ ሁኔታወች (exceptions) መቁጠር ይቻላል፡፡

የዚህ ጽሁፍ Aዘጋጅ Aቋምን ስንመለከት ደግሞ ቀደም ሲል ለብዙ Aመታት የነበረው የቤት
ሽያጭ ውል Aመሰራረት ልማድ Aሁንም በAብዛኛው የህብረተሰባችን ክፍል የቀጠለ በመሆኑ
የቤት ሽያጭ ውል የጽሁፍ ውል ሊያሟላቸው የሚገባቸውን ህጋዊ መስፈርቶች Eስካሟላ
ድረስ በፍርድ ቤትም ይሁን በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤቶች ባይመዘገብም ውሉ
Eውቅና ሊሰጠው ይገባል በማለት ያምናል፡፡ ለዚህም Aቋሙ Eንደ ዋና ማስረጃ የሚጠቅሰው
ምክንያት ስለ ቤት ሽያጭ ውል በልዩ ሁኔታ የሚደነግጉት የፍታብሄር ህግ Aንቀጾች 2877
Eና 2878 ሲሆኑ Eነዚህ ድንጋጌወች የቤት ሽያጭ ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል ውጤት
Eንዲኖረው የግድ መመዝገብ Aለበት የሚሉ ባለመሆናቸው በህግ Aተረጓጎም መርህ መሰረት
በልዩ ሁኔታ የተደነገጉት Aንቀጾች ከ ጠቅላላ ድንጋጌው Aንቀጽ 1723 ይልቅ ለጉዳዩ
Aግባብነት Aላቸው፡፡ ይሁን Eንጅ ምንም Eንኳን ምዝገባ Aስገዳጅ መስፈርት Aይደለም ብለን
ብናምንም የቤት ሽያጭ የሚያከናውኑ ሰወች ውሉን በሚመለከተው የመንግስት Aካል ፊት
Eንዲያስመዘግቡ ሊመከሩ ይገባል፡፡ ምክንያቱም፡ በAንደኛ ደረጃ የውሉ ምዝገባ Aንቀጽ 2878
Eንደሚጠቁመው ለ 3ኛ ወገኖች ስለ ውሉ መኖር Eውቅና ይፈጥራል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ Aንድ
ቤትን በተመለከተ የተመሰረቱ ሌሎች የሽያጭ ውሎች ካሉ ውሎቹ የተመዘገቡበትን ቀን
በመመልከት Eና ለውሎቹ የተሰጡትን የምዝገባ ቁጥሮች በማየት ቀድሞ የተመዘገበውን ውል
ተቀባይነት ለማረጋገጥ ይጠቅማል፡፡ በሶስተኛ ደረጃ በገለልተኛ የመንግስት ቢሮ ውስጥ የቤት
ሽያጭ ውሉ Aንድ ቅጅ መቀመጡ ቅን ልቦና የሌላቸው ተዋዋይ ወገኖች በEጃቸው ያለውን
የውሉን ቅጅ Aንዳንድ ክፍሎች በሀሰት ለመሰረዝና ለመደለዝ Eድል Aይፈጥርላቸውም፡፡

ሰንጠረዥ 1- የIትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የቤት ሽያጭ


ውሎችን ምዝገባ በተመለከተ የሰጣቸው የህግ ትርጉሞች Aጭር መግለጫ
ውሳኔዎቹ
የተሰጡበት
የሰበር መዝገብ የቅጹ Eና ጊዜ፣ Eንደ የሰበር ሰሚ ችሎቱ Aቋሞችና
ተ.ቁ
ቁጥር የገጽ ቁጥር Iትዮጵያ ትርጉሞች
ዘመን
Aቆጣጠር
የቤት ኪራይ ውል በ Iትዮጵያ
ቅጽ 1, ሀምሌ 19, የፍታብሄር ህግ Aንቀጽ 1723
1 15992
ገጽ 68 1997 መሰረት መመዝገብ
Aይጠበቅበትም፡፡
ሚያዚያ 30, ቤቶችን የሚመለከቱ የሽያጭ
ቅጽ 4,
21448 ውሎች በህጉ ዘንድ ተቀባይነት
ገጽ 40 Eና 1999 እና የሚኖራቸው የግድ በጽሁፍ ሲደረጉ
2 Eና
ቅጽ 8, ጥቅምት 27፣ Eና ውል ለማዋዋል በህግ ስልጣን
34803
ገጽ 294 በተሰጠው Aካል ፊት ሲመዘገቡ
2001
ነው፡፡
የቤት ስራ ተቋራጭነት ውል
Aጻጻፍ መደረግ የሚገባው
ቅጽ 7, በፍታብሄር ህግ Aንቀጾች 3019
3 32222 የካቲት 4, 2000 Eና 3020 መሰረት Eንጅ በAንቀጽ
ገጽ 170
1723 መሰረት Aይደለም፡፡ ስለሆነም
የቤት ስራ ተቋራጭነት ውል
መመዝገብ Aይጠበቅበትም፡፡
ቤትን የተመለከተ የስጦታ ውል
ቅጽ 7, መጋቢት 2, መደረግ ያለበት በፍታብሄር ህግ
17742
ገጽ 49 Eና 2000 Eና Aንቀጾች 2443፣ 881 Eና 882
4 እና መሰረት Eንጅ በAንቀጽ 1723
ቅጽ 8, ሀምሌ 2,
39803 መሰረት Aይደለም፡፡ ስለሆነም ቤትን
ገጽ 387 2001 የተመለከተ የስጦታ ውል
መመዝገብ Aይጠበቅበትም፡፡
Aንድ የቤት ሽያጭ ውል
ባለመመዝገቡ ምክንያት Eንዲፈርስ
ፍርድ ቤቶች ሲወስኑ የፍታብሄር
ቅጽ 7, ግንቦት 7፣ ህግ Aንቀጽ 1815 (1)ን መሰረት
5 29233
ገጽ 153 2000 በማድረግ ተዋዋዮቹን በተቻለ
መጠን ውሉ ከመደረጉ በፊት ወደ
ነበሩበት ሁኔታ Eንዲመለሱ
ማድረግ ይገባቸዋል፡፡
ሰዎች በማህበር በመደራጀት
የሕብረት ስራ ማህበር በማቋቋም
የሚገነቡትን ቤት ሽያጭ Aጻጻፍ
መታየት ያለበት ከፍታብሄር ሕግ
ቅጽ 8, ህዳር 9፣
6 36294 ቁጥር 1723 Aንፃር ሣይሆን
ገጽ 319 2001 ከህብረት ሥራ ማህበራት Aዋጅ
ቁጥር 147/91 Aንፃር ነው፡፡
ስለሆነም የማህበር ቤት በ Aንቀጽ
1723 መሰረት መመዝገብ
Aይጠበቅበትም፡፡
Aንድ የቤት ሽያጭ ውል
ባይመዘገብም Eንኳን ውሉን
ለመፈጸም የተሰራውን ስራ
ለማፍረስ የማይቻል ሲሆን ወይም
Aስቸጋሪ ሆኖ ሲገኝ ወይም ከፍ ያለ
ቅጽ 8, ሀምሌ 7፣ መሰናክል የሚያመጣ ከሆነ
7 39336
ገጽ 337 2001 የተሰሩት ስራወች Eንደረጉ
Aንዲቀሩ በፍታብሄር ሕግ ቁጥር
1817 (1) መሰረት ፍርድ ቤቶች
መወሰን ይችላሉ፡፡
ባንኮችና ሌሎች ገንዘብ Aበዳሪ
የፋይናንስ ተቋማት ለብድር ቤቶችን
ለማስያዝ ከተበዳሪወች ጋር
ቅጽ 8, ሀምሌ 9፣ የሚፈጽሙት ውል በፍታብሄር ህጉ
8 38666 Aንቀጽ 1723 መሰረት ሊተረጎም
ገጽ 337 2001
Aይገባም፡፡ (በዚህ ጉዳይ ላይ
ተፈጻሚነት ያለው Aዋጅ ቁጥር
639/2001 ነው፡፡…በጸሀፊው
የተጨመረ)
የቤት ሽያጭ ውል ስለመኖሩ
በተዋዋይ ወገኖች የታመነ ከሆነ
ውሉ ባይመዘገብም በጽሁፍ
ቅጽ 10, መደረጉ ብቻ ህጋዊ Eውቅና
36887 ታህሳስ 6፣
ገጽ 133 ያሰጠዋል፡፡ በተጨማሪም የቤት
Eና 2002 Eና ሽያጭ ውል ባለመመዝገቡ
9 Eና
ህዳር 18፣ ምክንያት Eንዲፈርስ ተዋዋይ
43825 ቅጽ 13, ወገኖች ካልጠየቁ በስተቀር ፍርድ
2001
ገጽ 233 ቤቶች በፍታብሄር ህጉ Aንቀጽ
1808 (2) መሰረት በራሳቸው
Aነሳሽነት ውሉ Eንዲፈርስ ማድረግ
Aይችሉም፡፡
Aንድ የቤት ሽያጭ ውል በጽሁፍ
ከተደረገ በኋላ በፍታብሄር ህጉ
Aንቀጽ 1727 (2) መሰረት ቢያንስ
ቅጽ 12, መጋቢት 22፣ ሁለት ምስክሮች ያልፈረሙበት
10 57356
ገጽ 98 2003 ከሆነ ውሉ ውል ለማዋዋል በህግ
ስልጣን በተሰጠው Aካል ፊት
የተመዘገበ ቢሆንም Eንኳን
ተቀባይነት Aይኖረውም፡፡
ውል ለማዋዋል በህግ ስልጣን
በተሰጠው Aካል ፊት በፍታብሄር
ህጉ Aንቀጽ 1723 መሰረት
ቅጽ 14, ጥቅምት 19፣ ያልተመዘገበ የቤት ሽያጭ ውል
11 78398
ገጽ 73 2005 Eንደ ረቂቅ ስለሚቆጠር በፍታብሄር
ህጉ Aንቀጽ 2005 (1) መሰረት
Eንደ Aሳማኝ ማስረጃ መውሰድ
Aይቻልም፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ
በተመለከተ መንግስት ካለበት
ኃላፊነት የተነሳ በተዋዋይ ወገኖች
መካከል ውል Eንዲዋዋሉ Eና
ቅጽ 16, መዝገብ Eንዲያደራጁ የተወሰነ
`12 98079 ሰኔ 16፣ 2006
ገጽ 227 Aካልን ባላደረገበት ጊዜና ቦታ
በAካባቢው የሚፈፀሙ ልማዳዊ
Aሰራሮችን ህጋዊ መሰረት
የላቸውም ለማለት የማይቻል
ስለመሆኑ፣ ከፍ/ሕ/ቁ. 3364
Aንድ የቤት ሽያጭ ውል በፍርድ
ፈራሽ ነው ተብሎ ተዋዋዮች
ወደነበሩበት Eንዲመለሱ ሲወሰን
ንብረት የመመለስ ግዴታ ያለበት
ሰው ንብረቱን ለውጦ ወይም ከዛ
ቅጽ 18,
13 99634 ሰኔ 1፣ 2007 በላይ ወጭ Aውጥቶ ላወጣው ወጭ
ገጽ 182 ያለውን መብት ያለAግባብ መበልጸግ
በሚለው የፍታብሄር ህጉ
ድንጋጌወች መሰረት መጠየቅ
ይችላል፡፡ የፍታብሄር ህጉ Aንቀጽ
1818 Eና የፍታብሄር ስነ ስርAት
ህግ ቁጥር 392 (1) ይመልከቱ
ተዋዋዮች ቤት በሽያጭ ሲተላለፍ
በህጉ በተደነገገው መሰረት ውል
ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው Aካል
ፊት ቀርቦ የማስመዝገብ ግዴታን
ቅጽ 19, የካቲት 28፣ ስምምነታቸው ላይ ካካተቱትና ነገር
14 99124
ገጽ 211 2008 ግን ይህንን ተፈጻሚ ማድረግ
ካልተቻለ በፍታብሄር ህጉ Aንቀጾች
1723፣ 1810 Eና 1885 (1)
መሰረት የተዘጋጀው ስምምነት
ረቂቅ Eንጅ ውል Aይደለም፡፡

ምንጭ- የጸሀፊው ዝግጅት


7. በIትዮጵያ ሕግ ውል ለማዋዋል በህግ ስልጣን የተሰጣቸው ተቋማት
7.1.1. ፍርድ ቤቶች
በIትዮጵያ ታሪክ በ1937 ዓ.ም በAጼ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ
ውል ለማዋዋል ስልጣን የተሰጠው ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ሬጅስትራር ነበር፡፡51 በመቀጠል
በAውራጃ ፍርድ ቤቶችና በወረዳ ፍርድ ቤቶች ለሚገኙ ሬጅስትራር ጽህፈት ቤቶች ስልጣኑ
ተሰጥቶ ነበር፡፡52 የነበረው Aሰራርም በ 1958 ዓ.ም በወጣው የፍታብሄር ስነ- ስርAት ህግ
ምክንያት ቀሪ ሳይሆን ሬጅስትራር ጽህፈት ቤቶች ውል የማዋዋል ስልጣናቸውን ቀጥለው
ነበር፡፡53 ነገር ግን በ 1962 ዓ.ም የሬጅስትራር ውል የማዋዋል ስልጣን ተነስቶ የውል ክፍል
(Contract Section) የሚባል ጽህፈት ቤት በፍርድ ቤቶች ውስጥ ተቋቋመ፡፡54

በደርግ ዘመነ መንግስት ደግሞ በ 1968 ዓ.ም የውል ክፍል ተብሎ የተመሰረተው ጽህፈት
ቤት ከከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ተነጥሎ በAዋጅ ቁጥር 8/1980 መሰረት በፍትህ ሚኒስቴር ስር
በተቋቋመው የፍታብሄር ጉዳዮች ክፍል ስር Eንደገና Eንዲቋቋም ተደረገ፡፡55 ከዚህ ጊዜ ጀምሮ
ፍርድ ቤቶች የነበራቸው ውል የማዋዋል Aሰራር ተቋረጠ፡፡56

በIትዮጵያ የፍታብሄር ህግ ውስጥ ፍርድ ቤቶች ውል ለማዋዋልና ውልን መዝግቦ


ለማስቀመጥ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል፡- በAንቀጽ 1723 መሰረት የቤት ሽያጭ
ውል በፍርድ ቤት ፊት ሊደረግና ሊመዘገብ ይችላል፡፡ በAንቀጽ 630 መሰረት ደግሞ የጋብቻ
ውል Aንድ ግልባጭ በፍርድ ቤት መዝገብ ውስጥ ሊቀመጥ Eንደሚችል የተደነገገ ቢሆንም
ይህ Aንቀጽ በተሻሻለውና በ1992 ዓ.ም በወጣው የፌዴራል የቤተሰብ ህግ የተሻረ ሲሆን
በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ Aንቀጽ 28 መሰረት ፍርድ ቤቶች የነበራቸው የጋብቻ ውልን
የማስቀመጥ ስልጣን ተሸሮ ውሉ በክብር መዝገብ ሹም መመዝገብ Eንዳለበት ተደንግጓል፡፡

51
Abate Yimer, The Function of the Notary Public of Ethiopia, 1985, unpublished, Justice and Legal System
Research Institute (JLSRI), p. 19
52
ዝኒ ከማሁ
53
Yohannes Heroui, ግርጌ ማስታወሻ 20 ገጽ 60
54
Thomas Gebreab and Girma Wakjira, The Duties and Responsibilities of the Notary in Ethiopia, 1981, Ministry of
Justice, unpublished, p. 18.
55
Yohannes Heroui, የግርጌ ማስታወሻ 20
56
ዝኒ ከማሁ
7.1.2. የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽህፈት ቤት

በI.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት ከ1985 ዓ.ም በAዋጅ ቁጥር 41/1985 መሰረት የውል ክፍል ጽ/ቤቱ
ከፍትህ ሚኒስቴር ወጥቶ በቀድሞ የክልል 14 መስተዳደር የፍትህ ቢሮና የክልል ፍርድ ቤት
ስር ተዋቅሮ ተደራጀ፡፡57 ከ1988 ሚያዝያ ወር ጀምሮ ራሱን ችሎ በ ጽህፈት ቤት ደረጃ
ተዋቅሮ የውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት በመባል ተጠሪነቱ ለAዲስ Aበባ ከተማ መስተዳደር
ሥራ Aስፈፃሚ ኮሚቴ Aድርጎ Aገልግሎቱን ሲሰጥ ቆይቶ በዚሁ ወቅትም የማቋቋሚያ ደንብ
ቁጥር 26/1993 በምክር ቤቱ ወጥቶለታል፡፡58 በ1995 ዓ.ም የAዲስ Aበባ ከተማ Aስተዳደርን
በAዲስ መልክ ለማደራጀት በተደረገው Eንቅስቃሴ ቀደም ሲል በህግ ተቋቁሞ ሲሠራ የነበረው
“የውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት” በAዲስ Aበባ ከተማ Aስተዳደር ሥር በክፍል ደረጃ
ለመስተዳድሩ ጽ/ቤት ተጠሪ ከነበረው የልደትና ጋብቻ ምዝገባ Aገልግሎት ጋር በመቀላቀል
”የውልና የክብር መዝገብ ማስረጃ Aገልግሎት” በሚል ስያሜ Eንዲደራጅ በከተማው
የAስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት Aገልግሎት Aካላት ማቋቋሚያ Aዋጅ ቁጥር 2/1995 መሠረት
ተወስኖ ራሱን የቻለ ህጋዊ ተቋም ሆኖ በምክር ቤቱ በጀት ተመድቦለትና በካቢኔው ኃላፊ
ተሹመለት Eስከ ሰኔ 1998 ዓ.ም በዚሁ መልክ ሲሠራ ቆይቷል፡፡59

የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ ሥራ በመላ Aገሪቱ ተፈፃሚነት የሚኖረው Aንድ ወጥ የፌዴራል


ህግ ቢመራ በዜጐች መካከል የሚከናወኑ የንግድና ሌሎችንም የIኮኖሚ Eና ህጋዊ ግንኙነቶች
በማቀላጠፍ ረገድ ከፍተኛ AስተዋጽO ያለው መሆኑን በመታመኑ ይህንኑ ሥራ የሚያከናውኑ
ተቋማትን ተግባርና ኃላፊነት በህግ በመደንገግ Aዋጅ ቁጥር 334/1995 በህዝብ ተወካዮች
ምክር ቤት በመውጣቱ የAሁኑ ተቋም በAዋጁ መሰረት የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት
ተብሎ Eንዲሰየም ተደረገ፡፡60 ከላይ የተጠቀሰው Aዋጅ በ1995 ዓ.ም Aጋማሽ Aካባቢ ፀድቆ
በነጋሪት ጋዜጣ ቢወጣም ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር ሳይገባ Eስከ 1997 ዓ.ም ከቆዬ በኋላ
በማሻሻያ Aዋጅ ቁጥር 467/1997 መውጣት ምክንያት Aዋጁ ወደ ተግባር መለወጥ Eንቅስቃሴ
በመጀመር ተጠሪነታቸው ለየከተማው መስተዳድር ምክር ቤቶች ተደርገው Eንዲቋቋሙ በAዋጁ

57
ዝኒ ከማሁ
58
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ህጋዊ ድረ-ገጽ http://www.dara.gov.et
59
ዝኒ ከማሁ
60
ዝኒ ከማሁ
ታስበው የነበሩ የAዲስ Aበባና የድሬዳዋ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤቶች ተጠሪነታቸው
ለፌዴራል ፍትህ ሚኒስቴር ሆኖ በAዋጁ የተዘረዘሩትን ተግባራት Eንዲያከናውኑ ተደረገ፡፡61

ከሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ ኤጀንሲ ህጋዊ ድረ-ገጽ (Web-site) መረዳት Eንደሚቻለው


የኤጀንሲው ዋና ተልEኮወች፡- የሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ ሥራ Eምነት የሚጣልበት፣
ለፍትህ ስርዓቱና ለIንቨስትመንት መሳለጥ የሚያግዝ ማስረጃ በማስገኘት በAገር ውስጥና
በዓለም Aቀፍ ደረጃ በሰዎችና በድርጅቶች የሚደረጉ የውልና ሌሎች ግንኙነቶች የሚወስኑ
ሰነዶች Aግባብ ባላቸው ህጎች መሰረት በማጣራት ማረጋገጥ፣ መመዝገብና ሲፈለጉ ሊገኙ
የሚችሉበት Aስተማማኝ ሁኔታ በጥንቃቄና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የመረጃ ስርዓት Aደራጅቶ
መያዝ፣ናቸው፡፡62

ኤጀንሲው በAሁኑ ሰAት የሚያከናውናቸው የሰነድ ማረጋገጥ ተግባራት የሚከተሉትን


ያጠቃልላል፡፡ ሰነዶችን የማረጋገጥና የመመዝገብ፣ የሰነድ ቅጅዎችን ከዋናው ጋር በማመሳከር
ትክክለኛነታቸውን ማረጋገጥና መመዝገብ፣ ቃለ መሃላና በቃለ መሃላ የሚሰጡ ማረጋገጫዎችን
መቀበልና መመዝገብ፣ ባለጉዳዮች ሲጠይቁ EንደAስፈላጊነቱ የፊርማ Eና/ወይም የማህተም
ናሙና መያዝ፣ ለመረጋገጥ በሚወርቡ ሰነዶች ላይ የሚፈርሙ ወይም የፈረሙ ሰዎችን
ችሎታ፣ መብትና ሥልጣን ማረጋገጥ፣ ለመረጋገጥ የሚቀርቡ ሰነዶችን ሕጋዊነት
ማረጋገጥ፣በሕግ የባለቤትነት ማረጋገጫ የሚሰጥባቸው ንብረቶች ለማስተላለፍ በሚደረጉ
ውሎች፣የንብረት Aስተላላፊውን ባለመብትነትና ንብረቱ በመያዣነት ያልተሰጠ ወይም በፍርድ
ቤት ትEዛዝ ያልታገደ መሆኑን ማረጋገጥ፣ ስለተረጋገጡና ስለተመዘገቡ ሰነዶች ሥልጣን
ባለው Aካል ሲጠየቅ ማስረጃ መስጠት፣ Eንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን
ያከናውናል፡፡63

8. የIትዮጵያ ህግ ያስቀመጠውን የAጻጻፍ ስርAት ያልተከተሉ የቤት ሽያጭ


ውሎች Eጣ ፋንታ

ሁሉንም የህግ ባለሙያወች የሚያስማማው ጉዳይ የቤት ሽያጭ ውል Aጻጻፍ ስርAት የጽሁፍ
ስርAት (Written Form) ሲሆን Aንድ የጽሁፍ ውል ምን ምን መስፈርቶችን መሟላት

61
ዝኒ ከማሁ
62
ዝኒ ከማሁ
63
ዝኒ ከማሁ
Eንዳለበት ቀጥለን Eንመለከታለን፡፡ Aንድ ተዋዋይ ወገን በጽሁፍ ውሉ ላይ ስሙ መገለጹ ብቻ
በቂ Aይደለም፡፡ በፍታብሄር ህግ Aንቀጽ 1727 (1) Eና Aንቀጽ 1728 (2) መሰረት በውል
ግዴታ ያለበት ተዋዋይ ወገን ውሉ ላይ ፊርማውን የማስቀመጥ ግዴታ Aለበት፡፡ በተጨማሪም
በAንቀጽ 1727 (2) መሰረት Aንድ ውል በህግ ፊት Eንዲጸና ቢያንስ በሁለት ምስክሮች ፊት
መረጋገጥ Aለበት፡፡ ምስክሮችም በጽሁፍ ውሉ ላይ ሊፈርሙበት ይገባል፡፡ ስለሆነም ከላይ
የተገለጹትን የጽሁፍ ውል መስፈርቶች Aንዱንም ያላሟላ የቤት ሽያጭ ውል ፈራሽ ይሆናል፡፡

በፍታብሄር ህግ Aንቀጽ 1720 (1) መሰረት Aንድ የቤት ሽያጭ ውል ህጉ ያስቀመጠውን


የAጻጻፍ መስፈርት ያላሟላ ከሆነ Eንደ ረቂቅ ብቻ ስለሚቆጠር በህግ ፊት Aውቅና
Aይሰጠውም፡፡ ስለሆነም በAንቀጽ 1808 (2) መሰረት የቤት ሽያጭ ውሉ ለውል Aጻጻፍ በህግ
የተደነገገውን የAጻጻፍ ስርAት (ፎርም) Aልጠበቀም በማለት ከተዋዋዮቹ Aንዱ ወይም
ማንኛውም በጉዳዩ ላይ ጥቅም ያለው ሰው ውሉ Eንዲሰረዝ ለፍርድ ቤት ማመልከት
ይችላል፡፡ ነገር ግን የቤት ሽያጭ ውል ባለመመዝገቡ ምክንያት Eንዲፈርስ ተዋዋይ ወገኖች
ካልጠየቁ በስተቀር ፍርድ ቤቶች በፍታብሄር ህጉ Aንቀጽ 1808 (2) መሰረት በራሳቸው
Aነሳሽነት ውሉ Eንዲፈርስ ማድረግ Aይችሉም በማለት ሰበር ሰሚ ችሎት ወስኗል፡፡64 ፍርድ
ቤቱም ውሉ Eንዲሰረዝ ሲወስን Aንቀጽ 1815 (1)ን መሰረት በማድረግ ተዋዋዮቹን በተቻለ
መጠን ውሉ ከመደረጉ በፊት ወደ ነበሩበት ሁኔታ Eንዲመለሱ ማድረግ ይገባዋል፡፡ በመሆኑም
ውሉን ለመፈጸም የተሰራ ስራ ሁሉ ቀሪ ሆኖ በማናቸውም Aኳኋን ውጤት የሌለው
ይሆናል፡፡65 ነገር ግን የውሉ መሰረዝ ወይም መፍረስ ቅን ልቦና ላለው ሶስተኛ ወገን
የተሰራው ስራ ውጤት ያለው ከሆነ ውሉ የAጻጻፍ መስፈርቶችን ያላሟላ ቢሆንም ቅሉ ፍርድ
ቤት ውሉ Eንደረጋ Eንዲቆይ ማዘዝ ይችላል፡፡66 በተጨማሪም ውሉን ለመፈጸም የተሰራውን
ስራ ለማፍረስ የማይቻል ሲሆን ወይም Aስቸጋሪ ሆኖ ሲገኝ ወይም ከፍ ያለ መሰናክል
የሚያመጣ ከሆነ የተሰሩት ስራወች Eንደረጉ Aንዲቀሩ ፍርድ ቤት መወሰን ይችላል፡፡67 ፍርድ
ቤቱ ይህንን Aቋም ከያዘ ተገቢ መስሎ የታየውን ኪሳራ በማስከፈል ወይም ሌላ ተገቢ ነው

64
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔወች፣ ቅጽ 10፣13፣ መዝገብ ቁጥር- 36887 Eና
43825፣ የIፌዲሪ ጠ/ፍ/ቤት የጥናትና የህግ ድጋፍ መምሪያ፣ 2001 Eና 2002 በቅደም ተከተል
65
የIትዮጵያ የፍታብሄር ህግ Aንቀጽ 1815 (2)
66
ዝኒ ከማሁ Aንቀጽ 1816
67
ዝኒ ከማሁ Aንቀጽ 1817 (1)
ያለውን ውሳኔ በመወሰን ተዋዋዮቹን ውሉ ከመደረጉ በፊት ወደ ነበሩበት ሁኔታ መመለስ
ይችላሉ፡፡68
9. ማጠቃለያ
ይህ ጽሁፍ የቤት ሽያጭ ውል Aጻጻፍ ስርAትን በተመለከተ በIትዮጵያ ህግ ውስጥ ያሉትን
Aከራካሪ ነጥቦች የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በጉዳዩ ላይ የሰጣቸውን
የህግ ትርጉሞች ዋቢ በማድረግ ለመተንተን ሞክሯል፡፡ ከIትዮጵያ የፍታብሄር ህግ Aንቀጾች
መካከል 1723 ን Eና 2877 ን በጋራ ስንመለከት የቤት ሽያጭ ውል በጽሁፍ ሳይደረግ የቀረ
Eንደሆነ ፈራሽ ይሆናል፡፡ ስለሆነም የቤት ሽያጭ ውል በጽሁፍ መደረግ Eንዳለበት ግልጽ
ነው፡፡ ነገር ግን በIትዮጵያ የውል ምዝገባ ለማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል መሰረታዊ Eና
Aስገዳጅ መስፈርት ነውን? በሚለው ጥያቄ ዙሪያ በዳኞች፣ ህግ ምሁራን Eና በህግ
ባለሙያወች መካከል ክርክር ይነሳል፡፡ የቤት ሽያጭ ውል Aጻጻፍ ስርAትን በተመለከተ ሰበር
ሰሚ ችሎቱ በ 1999 ዓ.ም በሰበር መዝገብ ቁጥር 21448 ላይ በሰጠው የህግ ትርጉም
በIትዮጵያ የፍታብሄር ህግ Aንቀጽ 1723 መሰረት ማንኛውም የቤት ሽያጭ ውል በጽሁፍ
መደረግ ብቻ ሳይሆን የምዝገባ መስፈርትን የግድ ማሟላት Aለበት፡፡

ይህ የህግ ትርጉም ከተሰጠ በኋላ ብዙ ክርክሮች የተነሱ ሲሆን ውሳኔው Iትዮጵያ ውስጥ
ከነበረው የቤት ሽያጭ ውል Aጻጻፍ ልማድ የተለየ ከመሆኑ ባሻገር በልዩ የቤት ሽያጭ ውል
የህግ ድንጋጌወች መሰረት ምዝገባ Eንደ መሰረታዊ መስፈርት ሊቆጠር Aይገባም በማለት
ጸሀፊው Aስተያየቱን Aቅርቧል፡፡ የ I.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት ይህንን በመገንዘብ ባንኮችና ሌሎች
ገንዘብ Aበዳሪ የፋይናንስ ተቋማትን ጥቅም ለመከላከል በማሰብ ተቋሞቹ ለብድር ገንዘብ
ቤቶችን ለማስያዝ ከተበዳሪወች ጋር የሚፈጽሙት ውል በፍታብሄር ህጉ Aንቀጽ 1723
መሰረት ሊተረጎም Aይገባም በማለት የሚደነግገውን Aዋጅ ቁጥር 639/2001 ደንግጓል፡፡
የሰበር ሰሚ ችሎቱ ቀስ በቀስ የAቋም መለሳለስ በማድረግ በ 2001 ዓ.ም የሰበር ሰሚ ችሎቱ
በተወሰነ መልኩ የAቋም ለውጥ በማድረግ በሰበር መዝገብ ቁጥር 36887፡ በቅጽ 12 ላይ
በሰጠው የህግ ትርጉም የቤት ሽያጭ ውል ስለመኖሩ በተዋዋይ ወገኖች የታመነ ከሆነ ውሉ
ባይመዘገብም በጽሁፍ መደረጉ ብቻ ህጋዊ Eውቅና ያሰጠዋል በማለት ወስኗል፡፡

68
ዝኒ ከማሁ Aንቀጽ 1817 (2)
Eንደ ጸሀፊው Aቋም ቀደም ሲል ለብዙ Aመታት የነበረው የቤት ሽያጭ ውል Aመሰራረት
ልማድ Aሁንም በAብዛኛው የህብረተሰባችን ክፍል የቀጠለ በመሆኑ የቤት ሽያጭ ውል
የጽሁፍ ውል ሊያሟላቸው የሚገባቸውን ህጋዊ መስፈርቶች Eስካሟላ ድረስ በሰነዶች
ማረጋገጫና ምዝገባ ጽህፈት ቤት ባይመዘገብም ውሉ Eውቅና ሊሰጠው ይገባል፡፡ ለዚህም
Aቋሙ Eንደ ዋና ማስረጃ የሚጠቅሰው ምክንያት ስለ ቤት ሽያጭ ውል በልዩ ሁኔታ
የሚደነግጉት የፍታብሄር ህግ Aንቀጾች 2877 Eና 2878 ሲሆኑ Eነዚህ ድንጋጌወች የቤት
ሽያጭ ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል ውጤት Eንዲኖረው የግድ መመዝገብ Aለበት የሚሉ
ባለመሆናቸው በህግ Aተረጓጎም መርህ መሰረት በልዩ ሁኔታ የተደነገጉት Aንቀጾች ከ ጠቅላላ
ድንጋጌው Aንቀጽ 1723 ይልቅ ለጉዳዩ Aግባብነት Aላቸው፡፡ ይሁን Eንጅ ምንም Eንኳን
ምዝገባ Aስገዳጅ መስፈርት Aይደለም ብለን ብንከራከርም የቤት ሽያጭ የሚያከናውኑ ሰወች
ውሉን በሚመለከተው የመንግስት Aካል ፊት Eንዲያስመዘግቡ ሊመከሩ ይገባል፡፡ ምክንያቱም፡
በAንደኛ ደረጃ የውሉ ምዝገባ Aንቀጽ 2878 Eንደሚጠቁመው ለ 3ኛ ወገኖች ስለ ውሉ
መኖር Eውቅና ይፈጥራል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ Aንድ ቤትን በተመለከተ የተመሰረቱ ሌሎች
የሽያጭ ውሎች ካሉ ውሎቹ የተመዘገቡበትን ቀን በመመልከት Eና ለውሎቹ የተሰጡትን
የምዝገባ ቁጥሮች በማየት ቀድሞ የተመዘገበውን ውል ተቀባይነት ለማረጋገጥ ይጠቅማል፡፡
በሶስተኛ ደረጃ በገለልተኛ የመንግስት ቢሮ ውስጥ የቤት ሽያጭ ውሉ Aንድ ቅጅ መቀመጡ
ቅን ልቦና የሌላቸው ተዋዋይ ወገኖች በEጃቸው ያለውን የውሉን ቅጅ Aንዳንድ ክፍሎች
በሀሰት ለመሰረዝና ለመደለዝ Eድል Aይፈጥርላቸውም፡፡

10. ምክረ- ሀሳቦች


የዚህ ጽሁፍ Aዘጋጅ የቤት ሽያጭ ውሎች ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው የመንግስት
ቢሮ ውስጥ ቢመዘገቡ መልካም መሆኑን ያምናል፡፡ ነገር ግን ውሎቹ የጽሁፍ መስፈርቶችን
Aሟልተው ከተገኙ ባለመመዝገባቸው ምክንያት ፈራሽ ሊደረጉ Aይገባም፡፡ ስለሆነም የቤት
ሽያጭ ውል Aጻጻፍ ስርAትን በተመለከተ ለሚነሱ ውዝግቦች መነሻ የሆነው የፍታብሄር ህግ
ቁጥር 1723 ከልዩ የቤት ሽያጭ ውል ድንጋጌወች ጋር በማይጋጭ መልኩ መሻሻል Eንዳለበት
የዚህ ጽሁፍ Aዘጋጅ ያምናል፡፡ በሚሻሻልበት ጊዜ ምዝገባ ለውሉ ህልውና Aስገዳጅ መስፈርት
Aለመሆኑ ሊገለጽ ይገባል፡፡
በሌላ በኩል የሰበር ሰሚ ችሎት ዳኞች ምንም Eንኳን ከፍተኛ የሆነ የስራ ጫና Eና የተጣበበ
ጊዜ ቢኖራቸውም በተቻለ መጠን የቤት ሽያጭ ውል Aጻጻፍ ስርAትን በተመለከተም ሆነ
በሌሎች ጉዳዮች ላይ የህግ ትርጉም ከመስጠታቸው በፊት የAገሪቱን ማህበራዊ፣ Iኮኖሚያዊ፣
ባህላዊ Eና ሞራላዊ ነባራዊ ሁኔታወችን ግምት ውስጥ በማስገባትና ከህጎች ጋር በማገናዘብ
ጥልቅ የሆነ ጥናት ማካሄድ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የህግ ትርጉሞች በጥናት የተደገፉ ከሆኑ
የAወዛጋቢነት ባህሪ ሳይኖራቸው ለረጅም Aመታት ገዥ የህግ ትርጉሞች የመሆን Eድል
ይኖራቸዋል፡፡ ስለሆነም ሰበር ሰሚ ችሎቶች የቤት ሽያጭ ውል Aጻጻፍ ስርAትን በተመለከተ
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ Aዋጅ ቁጥር 25/1988 ን ለማሻሻል በወጣው Aዋጅ ቁጥር
454/97 Aንቀጽ 2 በሰጣቸው ስልጣን መሰረት Eርስ በEርስ የሚቃረኑ ውሳኔወችን በግልጽ
በመሻር በጉዳዩ ላይ Aንድ ወጥ የሆነ Eና ተገማች የሆነ የህግ ትርጉም Eንዲኖር ማድረግ
ይጠበቅባቸዋል፡፡
በተጨማሪም የሰበር ሰሚ ችሎት ዳኞች የትምህርት ዝግጅታቸውን Aይነት (specialization)
Eና የዳኝነት ስራ ልምዳቸውን መሰረት በማድረግ በሚመለከታቸው ችሎት የሚመለከታቸውን
ጉዳይ Eንዲወስኑ ሊመደቡ ይገባል፡፡ በዚህም መሰረት የቤት ሽያጭ ውል Aጻጻፍ ስርAትን
በተመለከተ የሚቀርቡ ጉዳዮችን በውል ህግ ላይ Eውቀት ያላቸው ዳኞች ቢወስኑ የተሻለ
ጥራት ያለው ውሳኔ መስጠት ይችላሉ፡፡ በሌሎች Aገራት ለAብነት ያህል በAሜሪካ፣
በፈረንሳይ፣ በEንግሊዝ፣ በሆላንድ፣ በጣሊያን፣ በደቡብ Aፍሪካ ያለው ተሞክሮ ይህንን
የሚያጠናክር ነው፡፡69

69
Cour de Cassation, The Role of the Court of Cassation in France, accessed at http://www.courdecassation.fr , last
visited on 12/12/2013, pp.1-14፣ Gianluca Gentili, Italian Constitutional and Cassation Courts, Hein on line, 2011,
accessed at http://www.academia.edu , last visited on December 16, 2013, pp.73-88. ፣ Taylor Mattis, Precedential
Value of Decisions of the Court of Appeals of the State of New Mexico, USA, 1992, Southern Illinois University,
School of Law, p. 541, the home page of the Website of Supreme Court of the Netherlands, accesses at
http://www.rechtspraak.nl , last visited on December 10,2013, p. 1. James Lee, The Doctrine of Precedent and the
Supreme Court, Inner Temple Academic Fellow’s Lecture, 2011, page 21, Accessed at j.s.f.lee@bham.ac.uk , last
visited on December 13, 2013, Ulf Bernitz, Retroactive Legislation in a European Perspective- on the importance of
general Principles of law, 2009, page 58, accessed at www.scandinavianlaw.com last visited on December 12, 2013.
Deborah k. Mc Knight, Retroactivity of Statutes; What Constitutional limits are there on the retroactive application
of laws? , 2005, accessed at www.house.leg.state.com last visited on 12/13/2013, p. 8 ይመልከቱ፡፡
በAዲሱ የAማራ ክልል የገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ሕግ ላይ የተካተቱ ዋና ዋና
ለውጦች Eና የሚታዩ ችግሮች
በሪሁን Aዱኛ ምሕረቱ
1. መግቢያ
መሬት በተፈጥሮ የተገኘ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከመሆኑም በላይ ሌሎች የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ
ንብረቶችን ለማፍራት Aስፈላጊ የሆነ መተኪያ የሌለዉ ሀብት ነው፡፡ መሬት ከንብረት መብት Aኳያ
ለሀገራችን Aርሶ Aደሮች የኑሮ ዋስትና ነው። ማህበራዊና Iኮኖሚያዊ ጠቀሜታን በማረጋገጥ ረገድ
ለመንግስት ቁልፍ የፖለቲካል Iኮኖሚው መገለጫ የሆነ ሀብት ነው። ይህን ትልቅ ዋጋ ያለው
የሕዝብና የመንግስት ሀብት በAግባቡ ለማስተዳደርና Aጠቃቀሙን ለማሳለጥ የሚያገለግሉ በፌደራል
መንግስት Eና በክልሎች የሕግ ማEቀፎች ወጥተው Eየተሰራባቸው ይገኛል።

ከግንቦት 21 ቀን 1998 ዓ/ም ጀምሮ በAማራ ክልል ሥራ ላይ የነበረው የገጠር መሬት Aስተዳደርና
Aጠቃቀም ሕግ Aዋጅ ቁጥር 133/1998 Eና ማስፈጸሚያ ደንቡ ቁጥር 51/1999 መሆኑ ይታወቃል፡፡
ሆኖም Eነዚህ ሕጎች ተግባራዊ ሲደረጉ በርካታ ችግሮች በማጋጠማቸው1 ሕጎቹን ማሻሻል በማስፈለጉ
የተሻሻለው የAማራ ክልል የገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም Aዋጅ ቁጥር 252/2009 ታውጇል፡፡
የዚህ Aዋጅ ማስፈጸሚያ ደንብ ቁጥር 159/2010ም Eንዲሁ ጸድቆ ወጥቷል፡፡


በሪሁን Aዱኛ ምሕረቱ (LL.B, LL.M)፣ ቀደም ሲል የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ Eና በAማራ ክልል የፍትሕ
ባለሙያዎች ማሰልጠኛና የሕግ ምርምር Iኒስቲትዩት Aሰልጣኝ፣ ቀጥሎም የAማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ዳኛ በመሆን የሠራ ሲሆን በAሁኑ ጊዜ ጠበቃ Eና የሕግ Aማካሪ በመሆን Eየሠራ ይገኛል፡፡
1
ፍትሕ ለማግኘት በሚደረግ ጥረት ውስጥ በAማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ከሚቀርቡ ጉዳዮች ውስጥ Eጅግ
የሚበዛው የመሬት ክርክር ነው፡፡ ክርክሮቹ ከወረዳ ፍርድ ቤት ጀምሮ Eስከ ክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ
ችሎት Eንዲሁም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ የሚደርሱ Eና በቅርቡ ደግሞ Eስከ
ፌደሬሽን ምክር ቤት የሚዘልቁና መቋጫ የሌላቸው ሲሆኑ ይታያሉ። መቋጫ የለሽ ለሆነ የመሬት ክርክር ወይም
የተዛባ ፍርድ መንስኤዎች ምንድን ናቸው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በተግባር ከሚታዩ ችግሮች በመነሳት
ፀሐፊው “ለገጠር መሬት ክርክር መበራከት መንስኤዎችና ዋና ዋና መገለጫዎች በAማራ ክልል” በሚል ርEስ
በAማራ ክልል ምክር ቤት በመጋቢት ወር 2009 ዓ/ም በተካሄደው ክልል Aቀፍ የገጠር መሬት Aስተዳደርና
Aጠቃቀም ኮንፈረንስ ላይ ሁለት መሰረታዊ ምክንያቶችን በመተንተን Aቅርቦ ነበር። ከቀረቡት ምክንያቶች
Aንደኛው በመሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ሕጎች ላይ የሚታዩ ችግሮች የሚል ነበር፡፡ ይኸውም፡-
1. የክልሎች ሕግ የማውጣት ስልጣን በዜጎች ላይ ያመጣው የመብት መለያየት፡- በውርስ፣ በኪራይ፣ በስጦታ
መብት Eና ይዞታ መብት የሚታጣባቸው ሁኔታዎች ላይ ከክልል ክልል ሰፊ ልዩነት መኖሩ፤
2. የገጠር መሬት ውርስ ቅደም ተከተል ፍትሐዊ Aለመሆኑ፤
3. የገጠር መሬት ክርክር በይርጋ የሚታገድ መሆን Aለመሆኑ በAግባቡ ሳይደነገግ መታለፉ፤
4. የገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ሕጎች በየወቅቱ ለባለይዞታዎች የተለያየ መብት በመስጠታቸው
ቋሚና የተረጋጋ መብት Aለመኖሩ፤
5. ወጥ የሆነ የመሬት ግብይት ፎርማሊቲ Aለመደንገጉ፤
6. የከራይ ዘመን መርዘም Eና የኪራይ ተመን ገደብ Aለመኖር፤
7. የመሬት ስጦታ ሊሻር የሚችል መሆን Aለመሆኑ Aለመደነገጉ፤ Eና
8. የገጠር መሬት Aጠቃቀም ፖሊሲና ሕግ Aለመኖሩ የሚሉ ነበሩ፡፡
ሁለተኛው ምክንያት በገጠር መሬት ሕጎች Aፈጻጸም ላይ የሚታዩ ችግሮች ሲሆን ይህም በየደረጃው ባሉ የመሬት
Aስተዳደርና Aጠቃቀም መስሪያ ቤቶች፣ በተከራካሪ ወገኖች በራሳቸው Eንዲሁም በፍርድ ቤቶች ላይ የሚታዩ
ችገሮችን የሚመለከት ነው፡፡
1
Aዲሱ Aዋጅ ከቀድሞው Aዋጅ በEጥፍ ቁጥር ድንጋጌዎችን የያዘ፣ በጣም ሰፊ መግቢያ Eና በርካታ
የትርጓሜ ንUስ Aንቀጾችን ያካተተ Eንዲሁም Aዳዲስ ሀሳቦችን ያቀፈ ሆኖ ታውጇል፡፡ ለAዋጁ መሻሻል
ምክንያት የሆኑ Aስር መሰረታዊ ነጥቦችም መግቢያው ላይ ተካተዋል፡፡ ይኸውም፡-

1. Aርሶ Aደሮችም ሆነ ከፊል Aርብቶ Aደሮች በያዙት የገጠር መሬት ላይ ያላቸውን የተጠቃሚነት
መብት ይበልጥ ማስፋት ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤

2. በክልሉ ዉስጥ ተበታትኖ የሚኖረዉን Aርሶ Aደርና ከፊል Aርብቶ Aደር ወደ ተወሰኑ ማEከላት
በማሰባሰብ ሁለንተናዊ ለሆነ Eድገት ተጠቃሚ የሚያደርግ ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤

3. ሀገራችን የAርብቶ Aደሮችን በመሬት የመጠቀም መብት Aስመልክቶ በAህጉራዊና በዓለም


Aቀፋዊ ደረጃ የፈረመቻቸውን ስምምነቶች በክልሉ ዉስጥ ተግባራዊ ማድረግ Aስፈላጊ ሆኖ
በመገኘቱ፤2

4. የግል ባለሀብቱ Eና Aግባብ ያላቸዉ ድርጅቶች መሬትን በAግባቡ በማልማት፣ በመጠቀምና


በመጠበቅ ረገድ የሚኖራቸዉን ተሳትፎ ለማጠናከር Eና ጥረታቸዉ ከክልሉ መንግሥት
የልማት ዓላማዎች ጋር Aንዲቀናጅ ለማድረግ በማስፈለጉ፤

5. በክልሉ ዉስጥ የገጠር መሬት ምዝገባ መረጃን በጥራት ለማደራጀትና ለባለይዞታዎች በAግባቡ
ለማሰራጨት የሚያስችል ምቹ Eና ደረጃዉን የጠበቀ የሕግ ማEቀፍ በመፍጠር ሕጋዊ የመሬት
ባለይዞታዎች የይዞታ ዋስትናቸዉ ተጠናክሮ ማየት በማስፈለጉ፤

6. ሕገ-ወጥ የወል መሬት ወረራን በመከላከልና በግልም ሆነ በወል ይዞታቸዉ ላይም ቢሆን
ያልተፈቀዱ ግንባታዎችን በመቆጣጠር የገጠር መሬትን ዉጤታማና ዘላቂ Aጠቃቀም ማረጋገጥ
Aስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

7. ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ግጭቶችን ለመቀነስ የክልሉ መንግስት Eና ባለይዞታዎች


Aስተማማኝ የመረጃ Aገልግሎት የሚያገኙበትን ዘመናዊ የመሬት መረጃ ስርዓት መዘርጋት Eና
ተግባራዊ ማድረግ በማስፈለጉ፤

8. በተለያዩ የክልሉ የስነ ምህዳር ቀጠናዎች ላይ ተመስርቶ ፈርጀ-ብዙ የገጠር መሬት Aጠቃቀም
Eቅድ በማውጣትና በመተግበር የተፈጥሮ ሀብታችን በዘላቂነት በመጠበቅ Eና በማልማት
ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ Aንዲቻል Aስተዳደሩንና Aጠቃቀሙን በሕግ መደንገግ
Aስፈላጊ በመሆኑ፤

9. ሴቶች፣ ሕጻናት፣ Aካል ጉዳተኞች፣ Aቅመ ደካሞች Eና Aረጋዊያን የገጠር መሬት ባለይዞታ
የመሆን መብታቸው Eንዲጠናከር በዝርዝር መደንገግ በማስፈለጉ፤

2
See UN Interenational Convention to Combat Desertfication in Countries Experiencing Serious Drought and/or
Desertification, Particularily in Africa, enacted in 1994, in which Ethiopia is Signatory.
2
10. በክልሉ ዉስጥ Aንዳንድ የገጠር ቀበሌዎች ወደ Aቅራቢያዉ የከተማ Aስተዳደር ክልል
በሚጠቃለሉበት ወይም የገጠር መሬት ለሕዝብ Aገልግሎት Aንዲዉል በሚፈለግበት ጊዜ
ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ከይዞታቸዉ Eንዲነሱ ሲደረግ ተገቢና ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ
የሚያገኙበትንና በዘላቂነት የሚቋቋሙበትን Aሠራር በሕግ መደንገግ Aስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ
የሚሉ ናቸው፡፡

የዚህ ጽሑፍ Aላማም የተሻሻለውን ገጠር መሬት Aስተዳዳርና Aጠቃቀም Aዋጅ ከማስፈጸሚያ ደንቡ
ጋር በማገናዘብ Aጭር ዳሰሳ ማድረግ Eና ሕጎቹ ላይ የሚታዩ መልካም ጎኖች Eና ችግሮችን ለመጠቆም
ነው፡፡ በመሆኑም ፅሑፉ በሀገራችን ብሎም በክልላችን Eስካሁን ያሳለፍነውን የመሬት ስሪት ታሪካዊ
ዳራ በመዳሰስ ይጀምራል፡፡ Aሁን ባለው ሁኔታ በክልላችን ውስጥ የገጠር መሬትን በማግኘት፣
በመጠቀም፣ በማስተላለፍ Eና መብቱ ቀሪ በሚሆንባው ሁኔታዎች ላይ ከቀድሞው ሕግ Aንጻር
የተጨመሩ ወይም የተሻሻሉ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ፡፡ Eንዲሁም Aዋጁ ያካተታቸውን መልካም ነገሮች Eና
ችግሮችን ይተነትናል፡፡ ለችግሮቹም የመፍትሔ Aቅጣጫ ይጠቁማል፡፡
2. የገጠር መሬት ስሪት በIትዮጵያ፡- ከታሪካዊ ዳራው Eስከ Aሁን Aጭር Eይታ
የመሬት ስሪት (Land Tenure) ማለት Aርሶ Aደሮችና ሌሎች የመሬት ተጠቃሚዎች መሬት
የሚይዙበትን ሁኔታ Eና የAጠቃቀሙን ስርዓት የሚገልጽ ጽንሰ ሀሳብ ነው፡፡3 ይህ ትርጉም የመሬት
ስሪት መሬት ከማግኘት መብት የሰፋና የመብቱን ደረጃም ሆነ መብቱን ተግባራዊ ለማድረግ
የሚያስፈልጉ ተቋማትን የሚያካትት መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡ በAንድ ሀገር ያለው የመሬት ስሪት
ግንኙነት በመሬት ባለይዞታ መሆንንና በመሬት መጠቀምን በተመለከተ Aንድ ሰው ከሌላው ሰው ጋር
Eንዲሁም ግለሰቦች ከመንግስት ጋር ያላቸውን ማህበራዊ፣ Iኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት
የሚገለፅበት ጽንሰ ሀሳብ ነው፡፡

በAንድ ሀገር ያለው የመሬት ስሪት ዓይነት የመሬት ባለይዞታዎችን መብት በማስፋትም ሆነ በማጥበብ
ረገድ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ በተለይ Eንደ Iትዮጵያ ባሉ ለንብረት መብት ዋናው መሰረት መሬት
በሆነባቸው Eና Aብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል በባህላዊ የግብርና ስራ በሚተዳደርባቸው ሀገሮች የመሬት
ስሪቱ የመሬት ባለይዞታዎችን የንብረት መብትም ሆነ የEያንዳንዱን ባለይዞታ ማህበራዊና Iኮኖሚያዊ
ደረጃ በመወሰን ረገድ ከፍተኛ AስተዋፅO ይኖረዋል፡፡ የቅደመ 1967 ዓ/ም Iትዮጵያ የገጠር መሬት
ስሪትም የራሱ የሆነ ባህሪይ የነበረውና በውስጡ በርካታ ስሪቶችን ያካተተ ነበር፡፡4 ከ17ኛው ክፍለ ዘመን
ጀምሮ የሀገራችን የገጠር መሬት ስሪት የጋራ ይዞታ፣ የግል ይዞታና የመንግስት ይዞታ በሚል ሊከፈል
ይችላል፡፡5 በEነዚህ ስሪቶች ስር ሊካተቱ የሚችሉ የመሬት ይዞታ Aይነቶች ደግሞ በርካታ ነበሩ፡፡

3
Kenneth H. Parsons, Land Tenure, the University of Wisconsin press, Wisconsin (1963) p. 44; see also W.D.
Ambaye, Land Rights and Expropriation in Ethiopia, Springer Interenational Publishing Switzerland 2015, p. 36
4
Aberra Jembere, Legal History of Ethiopia 1434 - 1974: Some Aspects of Substantive and Procedural Law, Lieden
Arika-studie centrum (1998) p.123
5
Ibid
3
ለምሳሌ፡- የቤተክርስቲያን ይዞታ፣ የጉልት ይዞታ Eና የርስት ጉልት ይዞታን የሚያካትቱ ናቸው፡፡
በሰሜን Iትዮጵያ የነበረው የመሬት ስሪት ለብቻው ተለይቶ ሲታይ ደግሞ የግል ይዞታ፣
የቤተክርስቲያን ይዞታ Eና የመንግስት ይዞታ ተብሎ ይከፈል ነበር፡፡6

የርስት ይዞታ የሚባለው በሰሜኑና በመካከለኛው Iትዮጵያ በከፊል የነበረ የመሬት ስሪት ሲሆን የዚህ
ስሪት መለያ ባህሪው ዘራቸውን ወደ ላይ ቆጥረው የስሪቱ ቆርቋሪ ሰው የጋራ ተወላጆች መሆናቸውን
የሚያረጋግጡ ሰዎች የጋራ ይዞታ መሆኑ ነው፡፡7 የጉልት ይዞታ የሚባለው ለተፈፀመ ውለታ
ባለመሬቶች ለመንግስት የሚከፍሉትን ግብር ተቀብሎ ለግል ለመጠቀም Eንዲቻል የሚሰጥ መብት
ሲሆን ባለፈው ለተፈፀመና ወደ ፊትም ሊፈፀም የሚችል የAንድን Aካባቢ የማስተዳደርና ፀጥታ
የማስከበር ተግባር ለሚፈጽም ሰው በግል የሚሰጥ የመሬት ይዞታ መብት በመሆኑ ለልጅ የሚተላለፍ
Aይደለም፡፡8 የርስት ጉልት ይዞታ ደግሞ በርስት ስሪት Aካባቢዎች ከርስት ይዞታ በተጨማሪ በግል
ይዞታ Aካባቢ ደግሞ ከግል ባለቤትነት በተጨማሪ ከመሬቱ የሚሰበሰበውን ግብር ሰብስቦ ለግል
ለመጠቀም ከመንግስት የሚሰጥ መብት ሲሆን መብቱ የሚሰጠውም ለመንግስት ለተሰጠ Aገልግሎት
ነው፡፡ በመሬቱ ላይ ካሉ የርስተኝነት ይዞታ ወይም ከግል ባለቤትነት በተደራቢነት የሚሰጥ በመሆኑም
መልሶ ሊወሰድ የማይችልና ለተወላጅ ሁሉ በማንኛውም ሁኔታ ሊተላለፍ የሚችል ይዞታ ነው፡፡9

የግል የመሬት ስሪት በAብዛኛው በደቡብ የIትዮጵያ ክፍል የነበረ ሲሆን ለEያንዳንዱ ባለይዞታ ሙሉ
የመሬት ባለቤትነት መብት የሚሰጥ ስሪት ነበር፡፡ የግል የመሬት ስሪት የግል ባለቤትነት መብት ያለበት
ስሪት በመሆኑም መሬቱ ሊሸጥ ወይም በሌላ ሁኔታ ለማንኛውም ሰው ሊተላለፍ የሚችልበት የይዞታ
ዓይነት ነበር፡፡10 የመንግስት ይዞታ በየትኛውም የIትዮጵያ ክፍል የነበረ ስሪት ሲሆን መሬቱን
መንግስት ለሚፈልገው ተግባር የሚያውልበት፣ ሲፈልግ ለባለሟሎቹ Eንደመተዳደሪያ የሚሰጥበት
ወይም ለመንግስት ለሚገብር ተጠማጅ የሚሰጥበት የይዞታ ዓይነት ነበር፡፡11

በAጠቃላይ በሀገራችን ቀደም ሲል በነበረው የመሬት ስሪት በርስት ስርዓት ከሚመራው Eና


በቤተክርስቲያን ይዞታ ሥር ከነበረው መሬት በስትቀር12 የገጠር መሬት Eንደሌሎች ንብረቶች ያለምንም
ገደብ በሽያጭ፣ በውርስ፣ በስጦታም ሆነ በሌሎች ሁኔታዎች ከAንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው የሚተላለፍ

6
Ambaye, Supra note 3, p. 39
7
የገጠር መሬትን የሚመለከቱ ሕጎችና Aፈጻጸም በፍትሕ Aካላት ባለሙያዎች ስልጠና ማEከልለ ረጅም ጊዜ ስራ
ላይ ስልጠና ፕሮግራም የተዘጋጀ (ያልታተመ)፣ ገጽ 8
8
Aberra Jembere, Supra note 4, p. 141
9
Ibid
10
ማህተመስላሴ ወልደ መስቀል ስለ Iትዮጵያ የመሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ግብር ጠቅላላ Aስተያየት፣ 1970
(ያልታተመ)፣ ገጽ 14
11
Desalegn Rahmatto, Agrarian Reform in Ethiopia, Scandinivian Institute of African Studies, uppsala (1984), p. 20
12
ሞላ መንግስቱ፣ የገጠር መሬት ስሪት በIትዮዽያ፡- በሕግ የተደነገጉ መብቶችና በAማራ ብሔራዊ ክልል ያለው
Aተገባበር፣ የIትዮዽያ የሕግ መጽሔት፣ 22ኛ ቮልዩም፣ ቁጥር 2፣ 2001 ዓ/ም፣ ገጽ 157 Eና 158
4
ነበር፡፡13 ይኸውም በሰሜኑና መካከለኛው Iትዮዽያ በከፊል የነበረው የገጠር መሬት ስሪት የርስት ይዞታ
ስለነበር መሬት ከAንዱ ወደ ሌላው ሰው የሚተላለፈው ዘራቸውን ቆጥረው በሚመጡ የጋራ ተወላጆች
መካከል ብቻ ነበር። Eንደዚህ Aይነት ስሪት ባለበት Aካባቢ የርስት ተወላጆች መሬታቸውን ለመጠየቅ
ምንም ነገር የማያግዳቸው መሆኑን ከፍ/ሕ/ቁ 1168(1) ድንጋጌ ይዘት መረዳት ይቻላል። Eንዲሁም
በEነዚህ Aካባቢዎች ሲሶ መሬት በIትዮዽያ Oርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ይዞታ ሥር ሆኖ
ለቤተክርስቲያን Aገልግሎትና ለካህናት መተዳደሪያ ያገለግል የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ስለሆነም በዘውዳዊ ስርዓት የነበረው የመሬት ስሪት ለAርሶ Aደሩ የመሬት ባለቤትነትም ሆነ የመሬት
ባለይዞታነትና ተጠቃሚነት ምንም ዓይነት ዋስትና የማይሰጥ የሀገሪቱን የEርሻ መሬት በEጣት
ለሚቆጠሩ ሰዎች ባለቤትነትና Aዛዥነት ስር ያደረገና ሰፊውን Aርሶ Aደር ለጭሰኝነት Eና ለባርነት
የዳረገ Eንደነበር ይህም በ1966 ዓ/ም ለተደረገው ህዝባዊ ቁጣና Aብዮት መሰረታዊ ምክንያት የነበረ
መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡

በ1967 ዓ/ም የተደረገው የመሬት ስሪት ለውጥ በ1966 ዓ/ም የተካሄደው ሕዝባዊ Eንቅስቃሴ በሀገሪቱ
ያስከተለው Aጠቃላይ የስርዓት ለውጥ ውጤት Aካል ነበር፡፡ ሕዝባዊ Eንቅስቃሴውን ተከትሎ የደርግ
መንግስት የዘውድ Aገዛዙን ተክቶ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ የሀገሪቱ የፖለቲካ ስርዓት ሶሻሊስታዊ
ርEዮተ ዓለምን Eየተከተለ በመምጣቱ የIኮኖሚ ስርዓቱም Aብሮ በመለወጡ የመሬት ስሪት ለውጥ
ተደርጓል፡፡ የገጠር መሬት ስሪት ለውጡ በAዋጅ ቁጥር 31/1967 ሲታወጅም በመጀመሪያ AጽንOት
የሰጠው Eንደ Iትዮጵያ ባሉ በEርሻ የሚተዳደሩ ሀገሮች Aንድ ሰው በህብረተሰቡ ውስጥ ሊኖረው
የሚችለው የኑሮ ደረጃ፣ መብት፣ Eንዲሁም ክብርና ማEረግ የሚወሰነው ከመሬት ጋር ባለው ግንኙነት
በመሆኑ የዜጎችን Eኩልነት ለማስከበር የመሬት ስሪቱን መለወጥ Aስፈላጊ መሆኑን ነው፡፡14 የፖለቲካ
ስርዓቱ የሶሻሊስት ርEዮተ ዓለም ተከታይ በመሆኑም መሬትን የመሳሰሉ ሀብት ማፍሪያዎች የግል
ባለቤትነት መብት በስርዓቱ ተቀባይነት ስለማይኖረው የመሬት ስሪቱ በሀገሪቱ Aንድ ወጥ ሆኖ በAዋጁ
Aንቀጽ 3(1) “የሕዝብ ይዞታ” ተብሎ ታውጇል፡፡ የመሬት ስሪቱ የህዝብ ይዞታ Eንዲሆን በመታወጁ
መሬት ሊሸጥ ሊለወጥ የማይችል የህዝብ ሀብት Eንዲሆን ተደረገ፡፡ ስለዚህም በርስት፣ በግል ወይም
በመንግስት ይዞታ ስር የነበረው የገጠር መሬት ሁሉ የህዝብ ይዞታ በመደረጉ ማንኛውም በEርሻ
ለመተዳደር የሚፈልግ ሰው መሬት የማግኘት Eኩል መብት Eንዲኖረው ተደርጓል፡፡

ይሁን Eንጅ የመሬት ስሪቱ መሰረታዊ መርህ በዚህ መልኩ ቢታወጅም Aርሶ Aደሮች በመሬት ላይ
ያላቸው የመጠቀም መብት Eጅግ የጠበበ Eንዲሆን ተደርጎ ነበር፡፡ የመጀመሪያው የመብቱ ውሱንነት

13
የIትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የፍትሐ ብሔር ሕግ፣ 1952 ዓ/ም፤ ለምሳሌ በቁጥር 2875 Eና ተከታይ ድንጋጌዎች
መሠረት መሬት በሽያጭ ይተላለፍ ነበር፡፡ በቁጥር 826 Eና ተከታይ ድንጋጌዎች መሠረት በውርስ ለወራሾች
በተቀመጠው ቅደም ተከተል Eና ከቁጥር 2427 Eስከ 2470 በተደነገገው Aግባብ በስጦታ ከAንዱ ወደ ሌላው
መተላለፍ ይችል ነበር። (ከዚህ በኋላ የፍትሐ ብሔር ሕግ ድንጋጌዎች ሲጠቀሱ “የፍ/ሕ/ቁ” Eየተባለ ይገለጻል።)
14
የገጠር መሬትን የህዝብ ሀብት ለማድረግ የወጣ Aዋጅ ቁጥር 31/1967፣ መግቢያ
5
የሚታየው በAዋጁ Aንቀጽ 5 ላይ የይዞታ መሬትን በውርስ፣ በስጦታም ሆነ በሌላ መንገድ ማስተላለፍ
በመከልከሉ ነው፡፡ ባለይዞታው ሲሞት/ስትሞት ብቻ የትዳር ጓደኛው ወይም Aካለ መጠን ያላደረሰ ልጅ
Eነዚህ ከሌሉ ደግሞ Aካለ መጠን ያደረሰ ልጅ ተተክቶ በመሬቱ የመጠቀም መብት Eንደሚኖረው በዚሁ
Aዋጅ Aንቀጽ 5 በልዩ ሁኔታ ተደንግጓል፡፡ በዚህ ክልከላ ምክንያትም የመሬት ባለይዞታው ያለው
መብት ከAንድ የመሬት ተከራይ ያለፈ Aልነበረም፡፡ ሁለተኛው ውስንነት ማከራየትን ጨምሮ በሌላ
ሁኔታ የመሬት ይዞታ መብትን መገልገል መከልከሉ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በEርጅና፣ በህመም፣
Aካለ መጠን ባለማድረስ ወይም ለሴቶች ካልሆነ በቀር በይዞታ መሬት ላይ ሌላ ሰው ቀጥሮ ማሳረስ
የተከለከለ Eንደነበር ከAንቀጽ 4(1) መረዳት ይቻላል። ይህም ሲታይ በሕግ የተሰጠውን መሬት
የማግኘት መብት በተግባር ለመጠቀም የነበረውን የመብት ጠባብነትና Aስቸጋሪነት ያስገነዝበናል፡፡

በ1980 ዓ/ም የወጣው የIሕድሪ ሕገ መንግስትም የገጠር መሬት ስሪትን በተመለከተ ቀደም ብሎ
ከታወጀው ስሪት የተለየ ያመጣው ለውጥ Aልነበረም፡፡ ስለሆነም የደርግ የመሬት ስሪት ለAብዛኛው
የህብረተሰብ ክፍል መብት የሚነፍገውን ነባሩን የመሬት ስሪት በማስወገድ መልካም ገጽታ ያለው
ቢሆንም የመሬት ባለይዞታዎችን መብት በማጥበቡ ከንብረት መብት Aንፃር ለAርሶ Aደሮች የጎላ
የመሬት የተጠቃሚነት ለውጥ ሳያመጣ ቀርቷል፡፡

በ1983 ዓ/ም ደርግን ከስልጣን ያስወገደው IሕAዴግ በትግል ወቅት Eንደመታገያ ያነሳቸው ከነበሩ
ጥያቄዎች Aንዱ ደርግ የገጠር መሬት ጥያቄን በAግባቡ Aልመለሰውም የሚለው ነበር፡፡ ሆኖም ሐምሌ
15 ቀን 1983 ዓ/ም የወጣው የሽግግር መንግስት መተዳደሪያ ቻርተር Aንዳንድ መሰረታዊ የፖለቲካ
Aቅጣጫዎችን ከመጠቆሙ በስተቀር15 ቻርተሩ በሕገ መንግስት Eስኪተካ ድረስ የገጠር መሬት ስሪቱ
በነበረበት በመቀጠሉና የመሬት Aስተዳደሩም የEለት ከEለት ችግሮችን በማቃለል ላይ ተወስኖ በመቆየቱ
ስለመሬት ስሪት ለውጥ ከሚወጣው Aዲስ ሕገ መንግስት ድንጋጌ ሲጠበቅ ቆይቷል፡፡

ይህ ሕገ መንግስትም በደርግ መንግስት ከነበረው በተለየ ሁኔታ የሀገሪቱ የንብረት ባለቤትነት መብት
ሥርዓት በግል ባለቤትነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን በAጠቃላይ ደንግጐ የገጠር መሬት የባለቤትነት
መብት የመንግስትና የህዝብ ብቻ ነው በማለት Aውጇል፡፡16 የIፌዲሪ ሕገ መንግስት Aንቀጽ 40(3)
የገጠር መሬትን በተመለከተ የሚደነግገው ሁለት መሰረታዊ ነጥቦችን ነው፡፡ Aንደኛው የመሬት
ባለቤትነት የመንግስትና የሕዝብ ነው የሚለው ሲሆን ሁለተኛው መሬት ሊሸጥ ሊለወጥ Aይችልም
የሚለው ነው፡፡ ሁለቱም ነጥቦች ለገጠር መሬት ባለይዞታዎችና ተጠቃሚዎች መብት የሚሰጡ ሳይሆኑ
በተጠቃሚዎች መብት ላይ የተጣሉ ገደቦች ናቸው፡፡ ሕገ መግስቱ የመረጠው በመሬት ላይ የተፈቀዱ
መብቶችን በሙሉ ዘርዝሮ በመደንገግ ፈንታ Aንድ የንብረት ባለመብት ሊኖሩት ከሚችሉት መብቶች

15
የሽግግሩ መንግስት ቻርተር ቁጥር 1/1983፣ Aንቀጽ 10
16
የIፌዲሪ ሕገ መንግስት፣ Aዋጅ ቁጥር 1/1987፣ Aንቀጽ 40(1) ማንኛውም Iትዮጵያዊ የግል ንብረት ባለቤት
የመሆን መብት Eንዳለው ሲደነገግ የዚሁ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ 3 ግን ከንUስ Aንቀጽ 1 በተለየ ሁኔታ የገጠርም
ሆነ የከተማ መሬት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የሕዝብ ብቻ መሆኑን ደንግጓል፡፡
6
ውስጥ መሬትን በተመለከተ የተከለከሉትን በዝርዝር ማስቀመጥን ነው፡፡ ስለዚህ በIትዮጵያ የገጠር
መሬት ስሪት መሰረት Aንድ የመሬት ተጠቃሚ ከAንድ የንብረት ባለቤት ከሚኖረው መብት በተለየ
የከለከለው መሸጥና መለወጥን ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ሕገ መንግስቱ የይዞታ ወይም የመጠቀም
መብትን በሌላ ሁኔታ ማስተላለፍን መከልከለ Aለመፈለጉን የሚያሳይ ነው፡፡

በሌላ Aገላለጽ የገጠር መሬት ስሪት የመሬት ባለቤትነቱ የመንግስትና የህዝብ መሆኑን Eና Aርሶ
Aደሮች17 ከሚያገኙት መሬት ያለመነቀል መብት Eንዳላቸው መደንገጉ የሚያስገነዝበው በመሬት ላይ
የሚኖራቸው መብት የይዞታ መብት መሆኑን ነው፡፡ የይዞታ መብት በይዞታ መብቱ ላይ ተመስርቶ
ከሚገኘው የመጠቀም መብት የተለየ ነው፡፡ ይኸውም የባለቤትነት መብት፣ የይዞታ መብትና የመጠቀም
መብት የተለያዩና ከመጀመሪያው ወደ መጨረሻው በቅደም ተከተል Eየጠበቡ የሚመጡ ናቸው፡፡
ምክንያቱም የባለቤትነት መብት መሸጥን ጨምሮ ማንኛውንም በንብረት ላይ ሊኖር የሚችል መብት
ሁሉ የሚያካትት ከመብቶች ሁሉ የሰፋ መብት ሲሆን የይዞታ መብት ደግሞ በIፌዲሪ ሕገ መንግስት
መሰረት የገጠር መሬትን በተመለከተ Aንድ የመሬት ባለቤት ሊኖረው ከሚችለው መብት ላይ በመሸጥ
ወይም በመለዋወጥ መሬትን ለሌላ ሰው ማስተላለፍን ብቻ ለይቶ በመከልከል ሌሎችን መብቶች ግን
የጠበቀ የመብት ዓይነት ነው፡፡ የመጠቀም መብት ደግሞ Aንድ የገጠር መሬት የይዞታ መብት ያለው
ሰው በመሬቱ የመጠቀም መብቱን ለሌላ ሰው ሲያስተላልፍ የተላለፈለት ሰው የሚኖረው መብት ነው፡፡18

የብሔራዊ ፖሊሲ መርሆዎችና ዓላማዎች በተዘረዘሩበት የIፌዲሪ ሕገ መንግስት ምEራፍ Aስር


Aንቀጽ 89(5) ላይ መንግስት መሬትና የተፈጥሮ ሀብትን በሕዝብ ስም በይዞታው ሥር በማድረግ
ለሕዝቡ የጋራ ጥቅምና Eድገት Eንዲውሉ የማድረግ ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ተደንግጓል፡፡ መሬትና
የተፈጥሮ ሀብት Aጠቃቀምና ጥበቃን በተመለከተ ሕግ የማውጣት ስልጣን የፌደራል መንግስት
Eንደሆነ የሕገ መንግስቱ Aንቀጽ 51(5) ይደነግጋል፡፡ በዚሁ ሕገ መንግስት Aንቀጽ 52(2)(መ) ድንጋጌ
መሰረት ደግሞ ክልሎች የፌደራሉ መንግስት የሚያወጣውን ሕግ መሰረት Aድርገው መሬትንና
የተፈጥሮ ሀብትን የማስተዳደር ስልጣን Aላቸው፡፡ በሌላ መልኩ የሕገ መንግስቱን Aንቀጽ 50(9)
የፌደራል መንግስቱ በዚሁ ሕገ መንግስት Aንቀጽ 51 ከተሰጡት ስልጣንና ተግባሮች መካከል Eንደ
Aስፈላጊነቱ ለክልሎች በውክልና ሊሰጥ Eንደሚችል ደንግጓል፡፡

ሕገ መንግስቱ ከጸደቀ በኋላ የፌደራል መንግስት የገጠር መሬትን በተመለከተ ስለ ስሪቱ፣ ስለመብቱ
ወሰንና ስለAስተዳደሩ የሚደነግግ ሕግ ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጣው Aዋጅ ቁጥር 89/1989ን ነው፡፡19
Aዋጁ ለክልሎች ሕግ Aወጣጥ Eንደመመሪያ የሚያገለግሉ መርሆዎችን የያዘ Eንጅ ዝርዝር ድንጋጌዎች
Aልነበረውም፡፡ ክልሎች Eንዲያወጡ ለሚጠበቀው ዝርዝር ሕግ Eንደመመሪያ ሆኖ ለማገልገልም

17
ለዚህ ጽሑፍ Aላማ ሲባል “Aርሶ Aደሮች” የሚለው Aገላለጽ ከፊል Aርብቶ Aደሮችን Eና Aርብቶ Aደሮችንም
ያካትታል፡፡
18
ለምሳሌ በኪራይ ለተወሰነ ጊዜ ቢያስተላልፍ
19
የፌደራል መንግስት የገጠር መሬት Aስተዳደር Aዋጅ ቁጥር 89/1989፣
7
ግልጽነት የጎደለው ነበር፡፡ Aዋጁ የመሬት ባለይዞታዎች መሬታቸውን ለግብርና ስራ የማዋል፣
የማከራየትና ለቤተሰብ Aባላት የማውረስ መብት ያላቸው መሆኑን የሚጠቁሙ Aቅጣጫዎችን በAንቀጽ
2(3)፣ 5 Eና 6 ያካተተ ነበር።

ቀጥሎም Aዋጅ ቁጥር 89/1989ን ማሻሻል በማስፈለጉ የተሻሻለው የገጠር መሬት Aስተዳደርና
Aጠቃቀም Aዋጅ ቁጥር 456/1997 ወጥቷል፡፡20 ይህ Aዋጅ ከAዋጅ ቁጥር 89/1989 በተሻለ መልኩ
ከመሬት Aጠቃቀምና Aስተዳደር ጋር የተያያዙ መብትና ግዴታዎችን የሚመለከቱ ዝርዝር ድንጋጌዎችን
ይዟል፡፡ Aዋጅ ቁጥር 456/1997 ከሞላ ጎደል የIፌዲሪ ሕገ መንግስትን መሰረት በማድረግ የወጡ
የIኮኖሚ ልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎችን ተግባራዊ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ የወጣ ሕግ
ነው፡፡ ከAዋጁ መግቢያ መረዳት የሚቻለውም በርካታ የገጠር ልማት ዓላማዎችን የያዘ መሆኑን ነው፡፡
Eነዚህንም ዘላቂ ልማት (sustainable development) ማረጋገጥ፣ Aርሶ Aደሩ በመሬት ላይ ያለውን
የንብረት መብት ማጠናከር፣ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ሴቶች በመሬት ላይ ያላቸውን መብት
ማረጋገጥ፣ ማህበራዊ ደህንነትን ማረጋገጥ፣ Aጥጋቢ የገጠር መሬት መረጃ ስርዓትን ማረጋገጥ Eና
ቀልጣፋ የገጠር መሬት Aስተዳደር ስርዓት መዘርጋት የሚሉ ናቸው፡፡

በAዋጅ ቁጥር 456/1997 Aንቀጽ 17(1) መሰረት ክልሎች ይህን Aዋጅ ለማስፈጸም የሚስፈልጉ ዝርዝር
ድንጋጌዎችን የያዘ የገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ሕግ Eንዲያወጡ ውክልና ሰጥቷል፡፡21
ይህንን Aዋጅ ተከትሎ የAማራ ክልል የገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ሕጎችን Aውጥቷል፡፡
Eነዚህም ቀደም ሲል Aዋጅ ቁጥር 46/1992፣ በኋላም ይህን Aዋጅ ያሻሻለው Aዋጅ ቁጥር 133/1998
Eና ማስፈፀሚያ ደንቡ ቁጥር 51/1999 ወጥተው ለAመታት ሥራ ላይ ቆይተዋል፡፡22 Aሁን ደግሞ
በቅርቡ Aዋጅ ቁጥር 252/2009 Eና ማስፈጸሚያ ደንብ ቁጥር 159/2010 ተሻሽለው ወጥተዋል፡፡
ሎሎች ክልሎችም የየራሳቸውን ሕጎች Aውጥተዋል፡፡23
3. በAዲሱ የAማራ ክልል የገጠር መሬት Aስተዳዳርና Aጠቃቀም ሕግ የተካተቱ ዋና ዋና
ጠቃሚ ጉዳዮች (መልካም ጎኖች)
የIትዮጵያ Aርሶ Aደሮች ለEረሻም ሆነ ለግጦሽ የሚጠቀሙበት የገጠር መሬት በነጻ የማግኘት፣
የመጠቀም Eና ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብት ያላቸው መሆኑን የIፌዴሪ ሕገ መንግስት Aንቀጽ

20
የIትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት የገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም Aዋጅ ቁጥር
456/1997፣ ከዚህ በኋላ “Aዋጅ ቁጥር 456/1997” Eየተባለ ይጠራል።
21
በሕገ መንግስቱ Aንቀጽ 51 መሰረት ከፌደራል መንግስት ለክልሎች የሚሰጠው ውክልና ሕግ የማውጣት
(በAዋጅ ቁጥር 456/1998 Aንቀጽ 17 Eንደተሰጠው Aይነት)፣ ሕግ የመተርጎም (በህገ መንግስቱ Aንቀጽ 80
መሰረት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ስልጣን ለክልል ፍርድ ቤቶች Eንደተሰጠው Aይነት) ወይም ሕግ የማስፈጸም
(ክልሎች የተጨማሪ Eሴት ታክስ ሰብስበው ለፌደራል መንግስት Eንደሚሰጡት Aይነት) ሊሆን ይችላል፡፡
22
በEርግጥ በክልሉ በመጀመሪያ የወጣው የመሬት ሽግሽግ የተደረገበት Aዋጅ ቁጥር 16/1989 ነው። የAዋጅ ቁጥር
133/1998 ማሻሻያ Aዋጅ ቁጥር 148/1999 ደግሞ ቀደም ሲል የመሬት ክርክር በቀበሌ ማህበራዊ ፍርድ ቤት
ጀምሮ ይካሄድ የነበረውን በማስቀረት ክርክሩ በወረዳ ፍርድ ቤት Eንዲጀምር ለማድረግ Aላማ መታወጁን
ማስታወስ ያስፈልጋል።
23
ጸሐፊው የሌሎች ክልሎችን የመሬት ሕጎች የመዳሰስ ዓላማ ስለሌለው በዝርዝር መግለጽ Aላስፈለገውም፡፡
8
40(4)(5) ይደነግጋል፡፡ በሕገ መንግስቱ Aንቀጽ 40(4) መሰረት የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ሰው
የሚከለከለው መሬቱን መሸጥ Eና በሌላ ንብረት መለወጥ ብቻ Eንደመሆኑ መጠን Aርሶ Aደሮች በነጻ
ያገኙትን መሬት በተለያየ መልኩ የመጠቀም፣ በስጦታ ወይም በውርስ የማስተላለፍ፣ የማከራየት Eና
ተያያዥ መብቶች ይኖራቸዋል፡፡ Aዋጅ ቁጥር 456/1997 Aንድ የመሬት ባለይዞታ ያሉትን መብቶች
በበቂ ሁኔታ ባይዘረዝርም መጠቀም፣ ማከራየት Eና ማውረስ Eንደሚችል በጥቅሉ ይጠቁማል፡፡ Aዲሱ
የክልላችን Aዋጅ ቁጥር 252/2009 የገጠር መሬት የይዞታ መብት የሚገኝባቸው መንገዶች፣ የገጠር
መሬት ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን፣ የባለይዞታዎችን መብትና ግዴታዎች፣ ግዴታን
Aለመወጣት የሚያስከትለውን Eርምጃ፣ የይዞታ መሬት የሚታጣባቸውን ሁኔታዎች፣ የመረጃ Aያያዝ
ስርዓቱን፣ የክርክር Aፈታት ዘዴዎችን Eና ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎችን ይዟል፡፡ ስለሆነም ቀጥለን
Aዲሱ Aዋጅ ከቀድሞው ሕግ Aንጻር ያመጣቸውን Aዳዲስ ሀሳቦች Eና መልካም ጎኖች Eንመለከታልን፡፡

3.1 Aነስተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች የመሬት ይዞታ ሊኖራቸው Eንደሚችል መደንገጉ


በAዋጅ ቁጥር 252/2009 Aንቀጽ 7(1) Eና 10(1) Eንደተደነገገው የገጠር መሬት ባለይዞታ ለመሆን
ወይም መሬትን ከሚያስተዳድረው Aካል መሬትን በነጻ በድልድል ለማገኘት ሶስት መሰረታዊ
መስፈርቶች ያስፈልጋሉ፡፡ Eነዚህም፡- የክልሉ ነዋሪ መሆን፣ በዋነኝነት በግብርና ሥራ መተዳደር ወይም
በዚሁ የሥራ መስክ ለመተዳደር መፈለግ Eና Eድሜ 18 ዓመትና በላይ መሆን የሚሉ ናቸው፡፡ ቀደም
ሲል የነበረው የክልላችን Aዋጅ ዝርዝሩ በደንብ የሚወሰን ሆኖ ከግብርና ውጭ በሆነ ሥራ ላይ
የተሰማራና ገቢ የሚያገኝበት ቋሚ መተዳደሪያ ያለው ሰው በመሬት ይዞታ የመጠቀም መብቱን
Eንደሚያጣ ይደነግግ ነበር፡፡24 ዝርዝር ሁኔታዎችን የሚወስነው ደንብ ደግሞ በዝቅተኛ መነሻ
ደመወዝነት Eንዲከፈል በመንግስት ከተወሰነው Aማካይ የወር ደመወዝ መጠን ያላነሰ ገቢ በሚያስገኝ
ቋሚ ስራ ላይ ተቀጥሮ መገኘት Eና ከግብርና ሥራ ውጭ በሆነና ግብር በሚያስከፍል የሥራ መስክ
ተሰማርቶ መገኘት የገጠር መሬት ይዞታ የሚታጣባቸው ሁኔታዎች መሆናቸውን ይደነግጋል፡፡25

ይሁን Eንጅ Aዲሱ Aዋጅ በልዩ ሁኔታ Aነስተኛ የወር ገቢ በሚያስገኝ Eንደ ዘበኛነት፣ ፅዳት፣ ተላላኪና
ፖስተኛ Aይነት ሥራ የተቀጠሩ ሠራተኞች በቀጥታ በግብርና ሥራ Eየተዳደሩ Aይደለም በሚል የገጠር
መሬት ባለይዞታ ከመሆን የማይከለከሉ መሆኑን ይደነግጋል፡፡26 ይህም ሕግ Aውጭው በዝቅተኛው
የመንግስት የሥራ መደብ Eና ተመሳሳይ ሥራ ላይ ተቀጥረው የሚገኙ ዜጎች የሚያገኙት ደመወዝ
በጣም Aነስተኛ ስለሆነ ለኑሮ Aስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለማሟላት በቂ Aለመሆኑን ግምት ውስጥ
Aስገብቶ ያካተተው Aዲስ ድንጋጌ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡

24
የAዋጅ ቁጥር 133/1998፣ Aንቀጽ 12(1)(ሀ)
25
ደንብ ቁጥር 51/1999፣ Aንቀጽ 14(1)(ሀ)(ለ)
26
Aዋጅ ቁጥር 252/2009፣ Aቀንጽ 7(2)፤ ቀደም ሲል ደንብ ቁጥር 51/1999 Aንቀጽ 14(2) ላይ በብሔራዊ
Aገልግሎት የተመደበ ማንኛውም ሰው የገጠር መሬት ባለይዞታነቱ ቀሪ ሊደረግ Eንደማይችል ይደነግግ ነበር፡፡
9
በሌላ በኩል የገቢ መጠኑ የቱንም ያህል ቢሆን Aስቀድሞ የተሰማራበት ቋሚ መተዳደሪያ የግብርና
መስክ ሆኖ ሳለ በጥረቱ ተጨማሪ ሀብት በመፍጠርና ከዚሁ የተነሳም ወደ Iንቨስትመንት ሥራ
ለመሸጋገር የበቃ ማንኛውም ታታሪ Aርሶ Aደር ለግብርና ሥራ የተሰጠውን የገጠር መሬት ይዞታ በዚህ
Aዋጅ መሰረት Eንዲያጣ የማይደረግ ስለመሆኑ ተደንግጓል፡፡27 የዚህ ድንጋጌ Aላማም Aርሶ Aደሮች
ለዘመናት ከኖሩበት ከEጅ ወደ Aፍ የሆነ ኑሮ ተላቀው የተሻለ ቴክኖሎች በመጠቀም በመሬታቸው ላይ
በቂ ምርት Eያመረቱ በቂ ጥሪት Eያፈሩ ከEርሻ ሥራ ውጭም ወደ ንግድና Iንቨስትመንት ሥራ
Eንዲሰማሩ ለማበረታታት ነው፡፡ በዚህ ሂደት የሚቀየሩ Aርሶ Aደሮች መሬታቸውን Eንዲያጡ ከተደረጉ
ሌሎች Eነዚህን ውጤታማ Aርሶ Aደሮች Eያዩ Eንዳይበረታቱ ያደርጋል ተብሎ ይታሰባል፡፡28

3.2 ሴቶች፣ ህጻናት፣ Aካል ጉዳተኞች፣ Aረጋዊያንና Aቅመ ደካሞች ልዩ ትኩረት ማግኘታቸው፣
በAዋጁ መግቢያ ላይ የቀድሞው Aዋጅ Eንዲሻሻል ካስፈለገባቸው ምክንያቶች ውስጥ Aንዱ ሴቶች፣
ሕጻናት፣ Aክል-ጉዳተኞች፣ Aቅመ-ደካሞች Eና Aረጋዊያን ያላቸዉ በገጠር መሬት የመጠቀም መብት
Eንዲጠናከር ዝርዝር ሁኔታዎችን የሚደነግግ ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ነው ይላል፡፡ የAዋጁ
Aንቀጽ 5(6) መሰረታዊ መርሆዎችን ሲደነግግ የገጠር መሬት ድልድል በሚካሄድበት ጊዜ ወላጆቻቸውን
ላጡ ሕፃናት፣ ለAካል ጉዳተኞች፣ ለAቅመ ደካሞች፣ ለሴቶችና ለAረጋውያን ቅድሚያ Eንዲሰጥ
የሚያደርግ የAሠራር ስርዓት ተቀርጾ በሥራ ላይ Eንደሚውል ይገልጻል፡፡

የመሬት ድልድል በሚደረግበት ወቅትም Eነዚህ ወገኖች በግብርና ሥራ የሚተዳደሩ ወይም ለመተዳደር
የመረጡ ሆነው ሳለ ለዚሁ ዓላማ የሚያስፈልገው የEርሻ መሬት የሌላቸው ወይም ያነሳቸው Eንደሆነ
መሬት በማግኘት ረገድ የቀደምትነት መብት Eንደሚኖራቸው የAዋጁ Aንቀጽ 10(4) ይገልጻል፡፡ ሊሰጥ
የሚችለው የመሬት መጠን ችግሩ ላለባቸው ጠያቂዎች ሁሉ Eኩል ሊዳረስ የማይችል ከሆነ Eንደ
ቅደም ተከተላቸው ወላጆቻቸዉን በሞት ላጡ ሕፃናት፣ ለAካል ጉዳተኞች፣ ለAቅመ ደካሞች፣ ለሴቶችና
ለAረጋውያን ይሰጣል፡፡29 በመስኖ ልማት ፕሮጀክት ምክንያት የሚካሄድን የገጠር መሬት ሽግሽግ
ተከትሎ የመስኖ መሬት ክፍፍል በሚከናወንበት ጊዜ መሬታቸውን ያጡ ወይንም ይዞታቸው
የተቀነሰባቸው ሰዎች ከተስተናገዱ በኋላ ትርፍ መሬት የተገኘ Eንደሆነ Eንዲሁም በቀበሌ ማEከላት
ውስጥ ቤት መስሪያ ቦታ በማግኘት ሂደት Eነዚህ ወገኖች ከሌሎች ወገኖች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡30

በተጨማሪም ሞግዚት ወይም ሕጋዊ ወኪል የሌላቸው ሕፃናት፣ የAካል ጉዳተኞች፣ የAቅመ ደካሞች፣
የሴቶችና የAረጋውያን ይዞታ የሆነ መሬት በሚመዘገብበትና በሚረጋገጥበት ወቅት Eነዚሁ ወገኖች
በስፍራው ካለመገኘታቸው የተነሳ መብታቸው Eንዳይጣስ ብርቱ ጥንቃቄ መደረግ ይኖርበታል፡፡31

27
Aዋጅ ቁጥር 252/2009፣ Aንቀጽ 22(3)
28
ምናልባት የዚህ ድንጋጌ Aስፈላጊነት ጊዜያዊ ሊሆን ይችላል፡፡ በርካታ Aርሶ Aደሮች በዚህ ሂደት Eስከሚለወጡ
ተግባራዊ ሆኖ ሀገር ስትለወጥ ቀሪ ሊሆን የሚችል መብት ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡
29
Aንቀጽ 12(3)
30
የAዋጁ Aንቀጽ 14(4) Eና Aንቀጽ 31(6)
31
Aንቀጽ 39(1)
10
Eንዲሁም በሕጋዊ Aሳዳሪ ወይም በሞግዚት ጥበቃ ስር የሚተዳደሩ ሕፃናት፣ Aረጋዊያንና በፍርድ
የተከለከሉ ሰዎች ወይም የAEምሮ መታወክ ያለባቸው ስለመሆኑ በፍርድ የተረጋገጠላቸው
ባለይዞታዎች የመሬት ይዞታቸውን ሲያከራዩ ውሉ የነርሱን ጥቅም በማይጎዳ ሁኔታ ስለመደረጉ
ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ የቤተ-ዘመድ ጉባኤ የመከረበትና ውል ለመዋዋል ሥልጣን የተሰጠው Aካል
ያጸደቀው ሰነድ ከኪራይ ውሉ ጋር ተያይዞ ለምዝገባ መቅረብ ይኖርበታል፡፡32 የEነዚህ ሁሉ ድንጋጌዎች
ይዘት ሕግ Aውጭው ለEነዚህ ወገኖች ከፍተኛ ጥበቃ ለማድረግ የሞከረ መሆኑን ያሳያል፡፡

3.3 የመሬት ይዞታን ከማከራየት መብት ጋር ተያይዞ የተሻሻሉ ጉዳዮች መኖር


ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ ራሱን ከይዞታው Eስከማፈናቀል በማያደርስ ሁኔታ በይዞታ መሬቱ
ላይ የመጠቀም መብቱን ለሌላ ለማንኛውም ለግብርና ሥራ ለሚያውል ሰው በኪራይ ውል ማስተላለፍ
Eንደሚችል Aንቀጽ 15(1) (2) ይደነግጋል፡፡ የገጠር መሬት ኪራይ ውል ስምምነት Eስከ ሁለት ዓመት
ለሚዘልቅ ጊዜ የተደረገ ከሆነ መሬቱ ለሚገኝበት ቀበሌ መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ጽ/ቤት Eና ከዚያ
ለበለጠ ጊዜ የተደረገ ከሆነ ደግሞ ለወረዳ የገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ጽ/ቤት ቀርቦ
መመዝገብ ይኖርበታል፡፡33 ይህም ቀደም ሲል በነበረው ሕግ ከ3 ዓመት በታች የሚደረግ የመሬት
ኪራይ ውል የመመዝገብ ግዴታን የማይጥለውን ድንጋጌ Aሻሽሎታል፡፡34 ይህ መሆኑ በAንድ በኩል
Aዋጅ ቁጥር 456/1997 Aንቀጽ 8(2) ማንኛውም Aይነት የመሬት ኪራይ ውል Eንዲመዘገብ
የሚጥለውን ግዴታ ያከብራል፡፡ በሌላ በኩል ከ3 ዓመት በታች የሚደረግ ኪራይ Eንዲመዘገብ ግዴታ
Aለመቀመጡ ባለዞታዎች ያለጽሑፍ Eና ያለምዝገባ መሬታቸውን ካከራዩ በኋላ የኪራይ ዘመኑን በቃል
Eያራዘሙ ሲቆዩ ከረጅም ዘመን በኋላ Aልፎ Aልፎ በተግባር ይከሰት የነበረውን ተከራይ በራሱ ስም
Aስመዝግቦ የመገኘት ችግርን ያስወግዳል፡፡ ምክንያቱም ለሁሉም Aይነት የመሬት ኪራይ ውል ምዝገባ
ግዴታ ሲሆን Eና በዚህ መልኩ ሲደረግ ማስረጃ በቀላሉ ስለሚገኝ የዚህ Aይነት ችግርን ያቃልላል፡፡

በAዲሱ Aዋጅ መሰረት ከፍተኛው የገጠር መሬት ኪራይ ውል ዘመን ቋሚ የፍራፍሬ ተክሎችን ወይም
የተመረጡ የዛፍ ዝርያዎችን የተመለከተ Eንደሆነ 30 ዓመት ሲሆን ለዓመታዊ ሰብሎች ደግሞ 10
ዓመት ነው፡፡ ከ30 ዓመት Eና ከ10 ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ ተደርጎ የተገኘ የመሬት ኪራይ ውል
ስምምነት ቢኖር Eንደቅደም ተከተላቸዉ ለ30 ዓመት Eና ለ10 ዓመት Eንደተደረገ ይቆጠራል፡፡35 ይህ
ድንጋጌ ከቀድሞው Aዋጅ በተሻለ ሁኔታ ነባራዊ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ ያስገባ ነው፡፡ ይኸውም ሕግ
Aውጭው ቋሚ የፍራፍሬ ተክሎችን ወይም የተመረጡ የዛፍ ዝርያዎችን የተመለከተ ኪራይን 30
ዓመት Eንዲሆን ማድረጉ Eነዚህን ተክሎች በመትከል Aሳድጎ ፍሬ ለማግኘት የሚፈጀውን ረጅም ጊዜ

32
Aንቀጽ 15(12)
33
Aንቀጽ 15(8)
34
Aዋጅ ቁጥር 133/1998፣ Aንቀጽ 18(2)(5)
35
Aዋጅ ቁጥር 252/2009፣ Aንቀጽ 15(9)
11
ግምት ውስጥ ያስገባ ነው፡፡ ለሰብል የሚውል መሬት ግን በየዓመቱ ፍሬ ስለሚሰጥ በAንጻራዊነት
የኪራዩን ዘመን Aጭር ጊዜ ማድረግ ለባለይዞታዎች የሚኖረውን ጥቅም ያገናዘበ ነው ማለት ይቻላል፡፡

በሌላ በኩል Aዲሱ Aዋጅ የኪራይ ውል Aደራረግ ፎርማሊቲን ከቀድሞው በተለየ ሁኔታ ደንግጓል፡፡
ይኸውም የገጠር መሬት ኪራይ ውል በጽሑፍ መሆን Eና የመሬቱን ስፋት፣ የኪራዩን ዘመን፣
የክፍያውን መጠን Eንዲሁም የAከፋፈሉን ሁኔታ በግልጽ የሚያሳይ መሆን Eንዳለበት ከቀድሞው ሕግ
ጋር ተመሳሳይ ድንጋጌ ይዟል፡፡36 በተጨማሪ ግን የኪራይ ዉል ስምምነቱ ሕጋዊ የዉል ማቋቋሚያ
ሁኔታዎችን Aሟልቶ ካልተገኘ ወይም ተከራዩ በተከራየዉ መሬት ላይ ጉዳት ካደረሰ ወይም
ከስምምነታቸው ዉጭ ፈጽሞ ከተገኘ ዉሉ ፈራሽ Eንደሚሆን ይደነግጋል፡፡37 በፍትሐ ብሔር ሕጋችን
ስለ ውል ሕግ በሚደነግገው መጽሐፍ ክፍል መረዳት Eንደሚቻለው የውል ማቋቋሚያ ሁኔታዎች
የሚባሉት ችሎታ፣ ጉድለት የሌለበት ፈቃድ፣ በቂ የሆነ Eርግጠኛነት ያለው የሚቻልና ህጋዊ የሆነ
ጉዳይ Eና የውል Aጻጻፍ ፎርም ናቸው፡፡38

3.4 የውርስ ቅደም ተከተሉ ለልጆች ቅድሚያ መስጠቱ Eና ተያያዥ መሻሻሎች መኖር
የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ማንኛውም ሰው የይዞታም ሆነ የመጠቀም መብቱን በግብርና ሥራ
ለሚተዳደር ወይም በዚሁ ሙያ መተዳደር ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው በኑዛዜ ሊያስተላለፍ Eንደሚችል
Aንቀጽ 17(1) ይደነግጋል፡፡ የኑዛዜው Aደራረግ በፍትሐ ብሔር ሕግ ውስጥ Eንደተደነገገው ግልጽ
ኑዛዜ የሚደረግበትን መስፈርቶች ማሟላት Eና በወረዳ መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ጽ/ቤት ቀርቦ
መመዝገብ ያለበት መሆኑን Aንቀጽ 17(4) ይደነግጋል፡፡ በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ ተናዛዡ Eየተናገረ
ማንኛውም ሌላ ሰው ወይም ተናዛዡ ራሱ የሚጽፈው ሲሆን ኑዛዜው በተናዛዡና Aራት ምስክሮች ፊት
መነበብ፣ ቀን በግልጽ የተጻፈበት፣ የተናዛዡን ቃል ሊለውጥ የሚችል ፍቀት Eና ስርዝ ድልዝ
የሌለበት፣ ተናዛዡና ምስክሮቹ ወዲያውኑ የፈረሙበት መሆን Aለበት።39 ምስክሮቹም Aካለ መጠን
የደረሱ፣ በፍርድ ወይም በሕግ ያልተከለከሉ መሆን Eና ኑዛዜው የተጻፈበትን ቋንቋ የሚያውቁ
Eንዲሁም የተጻፈውን ለመስማት ወይም ለማንበብ ራሳቸው ችሎታ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።40
በAዲሱ Aዋጅ ይህ የኑዛዜ ፍርማሊቲ መካተቱ ቀደም ሲል በነበረው ሕግ ስለኑዛዜ ምንም Aይነት
ፎርማሊቲ ባለመካተቱ በAሠራር Eያጋጠሙ የነበሩ ውዝግቦችን ያስቀራል ተብሎ ይታሰባል፡፡41

36
Aንቀጽ 15(3)(4)
37
Aንቀጽ 15(11)
38
የፍትሐ ብሔር ሕግ፣ ቁጥር 1678
39
ዝኒ ከማሁ፣ Aንቀጽ 881 Eና 889(1)፣ በEርግጥ በAንቀጽ 882 Eንደተደነገገው ከምስክሮቹ መካከል Aንዱ ዳኛ
ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን የተሰጠው Aካል ሲሆን Eና ኑዛዜው የተደረገው ይህ ሰው ሥራውን
በሚያከናውንበት ቦታ ከሆነ የጸና ኑዛዜ ለማድረግ ሁለት ምስክሮች ይበቃሉ።
40
ዝኒ ከማሁ፣Aንቀጽ 883
41
በቀድሞው ሕግ በAዋጁም ሆነ በደንቡ ስለ ኑዛዜ ፎርማሊቲ በዝምታ ያለፈው ስለነበር Eና በመሬት Aስተዳዳርና
Aጠቃቀም ቢሮ በወጣው መመሪያ ላይ ብቻ ኑዛዜ በፍርድ ቤት መጽደቅ Aለበት የሚል ድንጋጌ በመካተቱ የሕግ
ባለሙያዎች ሁለት Aይነት Aተያየት ነበራቸው፡፡ የመጀመሪያው የመሬት ይዞታን በኑዛዜ ማስተላለፍ ራሱን የቻለ
ወይም ሌላ ንብረትን ከማስተላለፍ የተለየ በመሆኑ በፍርድ ቤት Eንዲፀድቅ መደረጉ ተገቢ ነው። ምክንያቱም
12
በሌላ በኩል ባለይዞታው መሬቱን በኑዛዜ ሳያወርስ የሞተ ወይም የሰጠው ኑዛዜ ፈራሽ ሆኖ የተገኘ
Eንደሆነ መብቱ Eንደ ቅደምተከተላቸው በግብርና ሥራ ለሚተዳደር ወይም በዚሁ ሙያ መተዳደር
ለሚፈልግ የሟች ልጆች፣ ወላጅ/ጆች ወይም ሕግ ለሚፈቅድለት ለማንኛውም ሌላ የቤተሰቡ Aባል
Eንደሚተላለፍ Aንቀጽ 17(5) ይደነግጋል፡፡ የሟች ልጆች ወይም ከልጆቹ Aንዱ ቀድመዉ ሞተዉ
ወይም ሞቶ Eንደሆነ Eና ወደታች የሚቂጠሩ ተወላጆችን ትተዉ/ትቶ Eንደሆነ Eነዚሁ ተወላጆቻቸዉ
ቀድመዉ በሞቱት ልጆች ምትክ ሆነዉ Eንዲወርሱ ይደረጋል፡፡42

ከዚህ Aንጻር Aዲሱ Aዋጅ ቢያንስ ሶስት መሰረታዊ መሻሻሎችን Aድርጓል፡፡ የመጀመሪያው የኑዛዜ
Aደራረግ ፎርም በፍትሐ ብሔር ሕጉ የተደነገጉትን ጥብቅ መስፈርቶች Eንዲከተል ማድረጉ ነው፡፡
ይህም ከኑዛዜ ጋር ተያይዞ የነበሩ የፎርማሊቲ ውዝግቦችን በማጥፋት ረገድ የራሱ ሚና ይኖረዋል፡፡
ሁለተኛው መሻሻል ልጆች ቅድሚያ የመውረስ መብት መስጠቱ ነው፡፡ ይህም ቀደም ሲል የቤተሰብ
Aባል ከልጆችም ቀድሞ የሚወርስበት Aሠራር ስለነበር ፍትሐዊነትን ከማስፈኑም በላይ የውሸት
የቤተሰብ Aባል ነን Eያሉ ሲወርሱ የነበሩ ሰዎች በመኖራቸው በዚህ የተነሳም የሟች ልጆች ላይ ይደርስ
የነበረውን ችግር ያስወግዳል፡፡ ሶስተኛው ማሻሻያ ምትክ ወራሽነትን ማካተቱ ነው፡፡ ይኸውም ከመሬት
ባለይዞታው ልጆች መካከል ከባለይዞታው ቀድሞ የሞተ ልጅ ቢኖርና ልጆች ወልዶ ከሞተ የዚህ ቀድሞ
የሞተ ሰው ልጆች በሟች Aባታቸው ተተክተው የAያታቸውን መሬት የመውረስ መብት ይኖራቸዋል፡፡43

3.5 የይዞታ መሬትን Aስይዞ ገንዘብ መበደር መፈቀዱ


ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ በዚህ Aዋጅ ከተፈቀደው ከ30 ዓመት ላልበለጠ ጊዜ የመጠቀም
መብቱን በሀገሪቱ ብሔራዊ ባንክ Eውቅና ለተሰጠው ሕጋዊ የገንዘብ ተቋም የብድር ዋስትና Aድርጎ
ሊያስይዝ Eንደሚችል Aንቀጽ 19(1) ይደነግጋል፡፡ ተበዳሪው በብድር ውሉ ውስጥ በተጠቀሰው የጊዜ
ገደብ Eዳውን ያልከፈለ Eንደሆነ Aበዳሪው በብድር ውሉ ለተጠቀሰው ጊዜ በመሬቱ የመጠቀም መብት
የሚኖረው ሆኖ የተገኘ Eንደሆነ የዚሁ መብቱ ወሰን በመሬቱ ላይ ከተሰጠው የመጠቀም መብት ያለፈ
ሊሆን Aይችልም፡፡44 Aበዳሪው መሬቱን ራሱ የማያለማው ሆኖ ለሶስተኛ ወገን የሚያከራየው ከሆነ Eና
መሬቱን ከAበዳሪው በውል ለመውሰድ Eስከ ተስማማ ድረስ ተበዳሪው ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡45

ፍርድ ቤቱ ሲያፀድቅ ኑዛዜ የተደረገለት ሰው በሕግ የተፈቀደለት ሰው መሆን Aለመሆኑን Aረጋግጦ ስለሚሆን
የሕጉን ዓላማ ለማሳካት ይጠቅማል የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው Aተያየት ደግሞ Aዋጁና ደንቡ የመሬት ኑዛዜ
ፎርማሊቲዎችን ያላስቀመጡ ስለሆነ የገጠር መሬት ኑዛዜ ፎርማሊቲዎች መታየት ያለባቸው ከፍትሐ ብሔር
ሕጉ የኑዛዜ ድንጋጌዎች Aንጻር መሆን Aለበት። በAዋጅና በደንብ ያልተደነገገን ግዴታ መመሪያ ሊደነግግ
Aይችልም የሚል ነው፡፡ በሪሁን Aዱኛ ምሕረቱ “የገጠር መሬት ይዞታን የሚመለከቱ ውሎች᎓- ፎርም፣ ምዝገባና
ሕጋዊ ውጤቱ በAማራ ክልል” የAማራ ክልል የፍትሕ ባለሙያዎች ማሰልጠኛና የሕግ ምርምር Iንስቲትዩት
የሕግ መጽሔት ቅጽ 2፣ ቁጥር 1፣ (2007 ዓ/ም) ገጽ 190-192 ይመለከቷል፡፡
42
Aንቀጽ 17(6)
43
በፍትሐ ብሔር ሕጉ ቁጥር 842(3) ላይ የተደነገገው መብት ለገጠር መሬት ውርስም ተግባራዊ Eንዲሆን
በAዲሱ Aዋጅ መካተቱን መገንዘብ ይገባል፡፡
44
Aንቀጽ 19(2)
45
Aንቀጽ 19(3)
13
Aርሶ Aደሮች መሬታቸውን በዋስትና Aስይዘው የመበደር መብት በAዲሱ Aዋጅ የተካተተ Aዲስ መብት
ነው፡፡ ይህ ድንጋጌ መቀመጡ መሬት ለAርሶ Aደሩ የበለጠ Iኮኖሚያዊ ጠቀሜታው Eንዲጎላ Eና
መሬታቸውን መያዣ በማድረግ ብድር በመውሰድ ወደ ተሻለ ምርታማነት Eና የኑሮ ደረጃ Eንዲቀየሩ
የሚያግዝ ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ይህ መብት በፌደራል የገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ረቂቅ
Aዋጅ Aንቀጽ 16 ላይም ተደንግጓል፡፡ የዚህ ረቂቅ Aዋጅ ሀተታ ዘምክንያት Eንደሚያሳየው Aበዳሪዎች
ግለሰቦችም ሊሆኑ Eንደሚችሉ የተገለጠ ቢሆንም Aዲሱ የክልላችን Aዋጅ Eና ማስፈጸሚያ ደንብ ቁጥር
159/2010 Aንቀጽ 9 ግን Aበዳሪዎች ብሔራዊ ባንክ Eውቅና የሰጣቸው የፋይናንስ ተቋማት ብቻ
መሆናቸውን ይደነግጋሉ፡፡46

መሬትን Aስይዞ የመበደር መብት በፍትሐ ብሔር ሕጉ ከተቀመጡት የመያዣ ድንጋጌዎች Aንጻር
ልዩነት Aለው፡፡ ይኸውም በፍትሐ ብሔር ሕጉ የተደነገገው የመያዣ ጽንሰ ሀሳብ ተበዳሪው ብድሩን
መክፈል ካልቻለ መያዣውን ለዘለቄታው ለAበዳሪው ለማስረከብ ሊስማማ ይችላል፤ ካልሆነም መያዣው
ተሸጦ Eዳው ይከፈላል፡፡47 የይዞታ መሬቱን መያዣ Aድርጎ የተበደረ ሰው ግን ብድሩን መመለስ ካልቻለ
ተበዳሪው የቀረበት የብድር ገንዘብ Eስከሚያልቅ ብቻ የኪራይ ውጤት ባለው መልኩ መሬቱን
በጊዜያዊነት ለAበዳሪው Aስረክቦ Eንዲቆይ ነው የሚገደደው፡፡

3.6 ይዞታ ለህዝብ Aገልግሎት ሲወሰድ የመልሶ ማቋቋም ሥራ ግዴታ ሆኖ መቀመጡ


ከሕገ መንግስቱ ጀምሮ ቀደም ሲል የነበሩ ሕጎች ባለይዞታዎች ይዞታቸውን ለህዝብ ጥቅም ሲለቁ
በቅድሚያ ተመጣጣኝ ካሳ ሊከፈላቸው Eንደሚገባ ከመደንገግ ባለፈ ተነሽዎችን መልሶ ስለማቋቋም
የሚሉት ነገር Aልነበረም፡፡ ሆኖም በተግባር የቱንም ያክል ካሳ ቢከፈል መልሶ የማቋቋም ሥራ
ካልተሰራ በተነሽዎች ላይ Eያጋጠመ ያለውን ችግር በመገንዘብ Aዋጅ ቁጥር 252/2009 Eንቀጽ 26(1)
በቅድሚያ ካሳ ከመክፈል ግዴታ በተጨማሪ ተነሽዎች በዘላቂነት የሚቋቋሙበትን Aማራጭ ማመቻቸት
ለAስተዳደሩ Eንደ ግዴታ ሆኖ ተደንግጓል፡፡

መልሶ ማቋቋም ማለት በሕግ መሰረት ካሳ ተከፍሏቸዉ የመሬት ይዞታቸዉ ለሕዝብ Aገልግሎት ሲባል
ከመወሰዱ የተነሳ የተፈናቀሉ ባለይዞታዎች ቀደም ሲል የነበራቸዉን ማኅበራዊና Iኮኖሚያዊ
ተጠቃሚነት ለማስቀጠል ወይም ለማሻሻል በክልሉ መንግስት የሚከናወን ተግባር መሆኑን የAዋጁ
Aንቀጽ 2(42) ትርጉም ሰጥቶታል፡፡ በዚህ Aዋጅ መሰረት በልማት ምክንያት ከመሬታቸው የሚፈናቀሉ

46
ይህ ሁኔታ በክልላችን Aዋጅ Eና በፌደራሉ ረቂቅ Aዋጅ መካከል ያለ Aንድ መሰረታዊ ልዩነት ነው፡፡ በረቂቅ
Aዋጁ መያዣው የሚቆይበት ከፍተኛው ጊዜ 15 ዓመት ቢሆንም የክልላችን Aዋጅ ግን የጊዜ ገደቡን 30 ዓመት
ማድረጉ ሌላ ልዩነት ነው፡፡ ሶስተኛው ልዩነት Aበዳሪው መሬቱን በማከራየት ወይም ራሱ በማልማት በውሉ
ውስጥ ከተጠቀሰው ጊዜ በፊት ቀሪውን Eዳ ማግኘት ከቻለ በውሉ ከተጠቀሰው ጊዜ በፊት በመሬቱ የመጠቀም
መብቱ የሚቋረጥ መሆኑ ደንብ ቁጥር 159/2010፣ Aንቀጽ 9(5) መደንገጉ ነው፡፡ ረቂቅ Aዋጁ ግን Aበዳሪው
የፈለገውን ያህል ከቀሪው የብድር ገንዘብ በላይ ቢያመርትበት ጊዜ ገደቡ ከማለቁ በፊት መሬቱ የማይመለስ
መሆኑን ይጠቁማል፡፡
47
የፍ/ሕ/ቁ 3060(2) Eና 3061
14
ባለ ይዞታዎች ፍላጎታቸው Eየታየ በሚነደፉ የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክቶች Eንዲታቀፉ ይደረጋል፡፡48
ዝርዝር የመልሶ ማቋቋም ተግባራት Eንዴት መሰራት Eንዳለባቸው ደግሞ በደንብ ቁጥር 159/2010
Aንቀጽ 15 ላይ ተደንግዋል፡፡49 ይኸውም Aግባብ ያለው የወረዳ Aስተዳደር ጽ/ቤት የገጠርን መሬት
ለህዝብ Aገልግሎት ለማዋል Aስፈላጊ ሆኖ ያገኘው Eንደሆነ ተገቢውን ካሳ በቅድሚያ በመክፈልና
ተፈናቃዩ በዘላቂነት የሚቋቋምባቸውን የተለያዩ Aማራጮች ከወዲሁ በማመቻቸት ማንኛውንም የመሬት
ባለይዞታ ወይም ተጠቃሚ ማስለቀቅ ይችላል፡፡ ሆኖም Eርምጃው ተግባራዊ የሚደረገው ለባለመብቶች
በቅድሚያ ተገቢው የቦታ Aቅርቦት መሟላቱ ከተረጋገጠ በኋላ ይሆናል፡፡50 በየትኛውም ከተማ የፕላንና
Aስተዳደር ወሰን ክልል ውስጥ ለሚኖሩ ባለይዞታዎች ትክ የመኖሪያና የመስሪያ ቦታ ተለይቶ
Eንዲዘጋጅና ለተፈናቃዮች Eንዲቀርብ ይደረጋል፡፡51 ከከተማ Aስተዳደር ውጭ በህዝብ ጥቅም
Aስገዳጂነት ከሕጋዊ ይዞታቸው የሚነሱ የገጠር መሬት ባለይዞታዎች በሕጉ መሰረት Aማራጭ የሰፈራ
ቦታ፣ ትክ የEርሻና የግጦሽ መሬት Eንዲያገኙ ይደረጋል፡፡52

ዝርዝር የመልሶ ማቋቋም ትግባራትን በተመለከተም በልማት ምክንያት ከመሬታቸው የሚፈናቀሉ ህጋዊ
ባለይዞታዎች ይኸው መፈናቀል የሚያስከትልባቸው ጉዳት ከወዲሁ ታይቶ፡-53
 Eንደየፍላጎታቸው በተናጠልም ሆነ በጋራ በመደራጀት በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተፈላጊው
ፕሮጀክት ተቀርጾላቸው ወደስራ Eንዲገቡ ይደረጋል፤
 በራሱ በክልሉ መንግሥትም ሆነ በAልሚ ባለሀብቶች Aማካኝነት የስራ Eድል በቅድሚያ
Eንዲፈጠርላቸውና ለስራ የደረሱ የቤተሰብ Aባሎቻቸውም በAካባቢው በሚካሄደው ልማት
ተጠቃሚዎች Eንዲሆኑ ተገቢው ክትትልና ድጋፍ ይደረግላቸዋል፤
 Eንዳስፈላጊነቱ የብድር Aገልግሎት ወይም ሌላ Aይነት ልዩ ድጋፍ ይመቻችላቸዋል፤
 የሚያቀርቧቸው ምርቶች በገበያ ረገድ ተወዳዳሪዎች Eንዲሆኑ በስልጠናና በግብይት Eሴት
ሰንሰለት ትስስር ፈጠራ ረገድ ተገቢው ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡

3.7 የገጠር መሬት Aጠቃቀም Eቅድ ማዘጋጀት Eንደሚገባ መደንገጉ


Aዲሱ Aዋጅ ካካተታቸው ቁምነገሮች ውስጥ Aንዱ የመሬት Aጠቃቀም Eቅድ Eንዲዘጋጅ የሚያስገድድ
ድንጋጌዎችን መያዙ ነው፡፡54 በዚህ Aንቀጽ መሰረት የክልሉ የገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ቢሮ

48
Aንቀጽ 26(9)
49
በEርግጥ ብዙም ሥራ ላይ ባይውልም በቅርቡ የAብክመ ለህዝብ ጥቅም ሲባል መሬታቸውን የሚለቁ የገጠር
ባለይዞታዎችን መልሶ ለማቋቋም Eና ይዞታቸውን ለማስተዳደር የወጣ መመሪያ ቁጥር 26/2008 የነበረ መሆኑን
መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
50
ደንብ ቁጥር 159/2010 Aንቀጽ 15(1)
51
Aንቀጽ 15(2)፤ በከተማ የፕላን ወሰንም ሆነ በገጠር ቀበሌ ማEከላት ውስጥ በግል ይዞታቸው ላይ የመኖሪያ
ቤት ወይም የንግድ ድርጅት የመገንባት ፍላጎታቸውን የገለጹ Eንደሆነ ተቋቋሚዎች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
Aንቀጽ 15(3)
52
Aንቀጽ 15(4)
53
Aንቀጽ 15(5)
15
Aገር Aቀፉን የመሬት Aጠቃቀም Eቅድ መነሻ በማድረግ ወይም ከራሱ ነባራዊ ሁኔታዎች በመነሳት
በክልሉ ውስጥ የሚተገበር መሪ የመሬት Aጠቃቀም Eቅድ ያዘጋጃል፡፡ የዞን ገጠር መሬት Aስተዳደርና
Aጠቃቀም መምሪያዎች የክልሉን የመሬት Aጠቃቀም Eቅድ መሠረት በማድረግ በዞኑ ነባራዊ ሁኔታ
የሚተገበር የራሳቸውን መሪ የመሬት Aጠቃቀም Eቅድ ያዘጋጃሉ፡፡ የወረዳ መሬት Aስተዳደርና
Aጠቃቀም ጽ/ቤቶችም የዞናቸውን የመሬት Aጠቃቀም Eቅድ መሰረት በማድረግ Eንደ ወረዳቸው ነባራዊ
ሁኔታ የሚተገበር የራሳቸውን መሪ የመሬት Aጠቃቀም Eቅድ ያዘጋጃሉ፡፡ Eንዲሁም Aካባቢያዊ
የመሬት Aጠቃቀም Eቅድ ቀበሌን ወይም ተፋሰስን መሰረት ያደረገና ነዋሪውን ሕብረተሰብ ያሳተፈ ሆኖ
በወረዳ ገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ጽ/ቤት የቴክኒክ ድጋፍ ይዘጋጃል፡፡

የትኛውም የገጠር መሬት ለAንድ ለተወሰነ Aገልግሎት Eንዲውል የመሬት Aጠቃቀም Eቅድ ሲዘጋጅ
የተሻለ የIኮኖሚ ጠቀሜታ የሚሰጥ መሆኑ፣ በAካባቢ ላይ የሚያስከትለው ተጽEኖ Aለመኖሩ ወይም
ተጽEኖው Aነስተኛ ሆኖ መገኘቱ Eና Aገልግሎቱ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሆኑ
Eየተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል።55 በጥናት ላይ ተመስርቶ ካልሆነ በስተቀር በማናቸውም የገጠር
መሬት ይዞታ ላይ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ያለ ወቅታዊ የAጠቃቀም Eቅድ በዘፈቀደ Aይቀየርም፡፡56
በክልል፣ በዞንም ሆነ በወረዳ ደረጃ የሚዘጋጁ መሪ የገጠር መሬት Aጠቃቀም Eቅዶች Eንደተገቢነቱ
Aገር-Aቀፉን Eቅድ ወይም የAስተዳደር Eርከኑን Eቅዶች ታሳቢ በማድረግ ከ10 Eስከ 15 ዓመት
በሚሆን ጊዜ ውስጥ ወቅታዊ መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡57

Aዲሱ Aዋጅ የገጠር መሬት በEቅድ Eንዲመራ ለማድረግ ትኩረት ከሰጠባቸው ሁኔታዎች Aንዱ ለገጠር
ቀበሌ ማEከላት መገንቢያ ቦታ Aመራረጥ Eና Aሰጣጥ ጉዳይ ነው፡፡ በAዋጁ Aንቀጽ 31 Eንደተደነገገው
በክልሉ በሚገኙ በሁሉም የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ የቀበሌ ማEከላት Eንዲኖሩ ይደረጋል፡፡ በገጠር ቀበሌ
ማEከላት ውስጥ የሚተገበረው የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቦታ Aሰጣጥ ስርዓትና ግንባታው የሚያሟላቸው
ስታንዳርዶች በደንብ የሚወሰን ሆኖ Eድሜው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነና በቀበሌው ውስጥ ቢያንስ
ለተከታታይ ሁለት ዓመት ነዋሪ ሆኖ በግብርና፣ በንግድ ወይም በሌሎች በማናቸውም መንግስታዊና

54
Aንቀጽ 29(1-6)፤ በAንቀጽ 2(4) ትርጉም መሰረት "የመሬት Aጠቃቀም Eቅድ" ማለት Aካላዊ፣ Iኮኖሚያዊና
ማኅበራዊ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ የገጠር መሬት ሊሰጥ ከሚችለው የተለያዩ የመሬት Aጠቃቀም
Aማራጮች መካከል የመሬት መጎሳቆልንና የAካባቢን ብክለት ሳያስከትሉ ከፍተኛ Iኮኖሚያዊ ጠቀሜታ
የሚያስገኙት Aማራጮች ተወዳድረው የሚወሰኑበትና ተግባራዊ የሚደረጉበት የAሠራር ዘዴ ነው፡፡
55
Aንቀጽ 29(7)
56
Aንቀጽ 32(1)፤ ሆኖም ይህ ድንጋጌ ተዳፋትነታቸዉ ከ50% በላይ የሆኑ የመሬት ይዞታዎች ወደ ቋሚ ተክሎች
ማልሚያነት ከማሸጋገር የሚከለክል Aይሆንም::
57
Aንቀጽ 30፤ በAካባቢ ደረጃ የሚዘጋጅ Aሳታፊ የገጠር መሬት Aጠቃቀም Eቅድ EንደAስፈላጊነቱ የሚከለስበትና
ወቅታዊ የሚደረግበት ጊዜ ገደብ በደንብ ይወሰናል፡፡
16
መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚሠራ ማንኛውም ሰው በገጠር ቀበሌ ማEከላት ውስጥ የመኖሪያ ቤት
መሥሪያ ቦታ ያገኛል፡፡58

በገጠር ቀበሌ ማEከላት ውስጥ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ቢሮው ለገጠር ቤቶች Aሠራር የሚያወጣውን
የዲዛይንና የግንባታ ጥራት መስፈርቶች Aሟልተው ስለመገኘታቸው በወረዳ ገጠር መሬት Aስተዳደርና
Aጠቃቀም ጽ/ቤት ካልተረጋገጠ በስተቀር ሊሸጡ፣ የEዳ ዋስትና ሆነው ሊያዙም ሆነ በማናቸውም
መንገድ ለሶስተኛ ወገን ሊተላለፉ Aይችሉም፡፡59 Eንዲሁም የገጠር ቀበሌ ማEከላት ተብለው
ከተመረጡት ስፍራዎች ውጭ በEርሻ፣ በግጦሽ፣ በወል Eና በደን መሬቶች ላይ ማናቸውንም Aይነት
Aዲስ ግንባታ ማካሄድ የተከለከለ ነው::60 ሆኖም የመሬት Aጠቃቀም Eቅድ ተዘጋጅቶ ባልተሰጠበት
Aካባቢ Aርሶ Aደሩ በመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተሩ ላይ ባስመዘገበው የይዞታ መሬቱ ውስጥ ለራሱና
ለAካለመጠን ለደረሱ ልጆቹ በሚበቃ መጠን የመኖሪያ ቤት ከመገንባት Aይታገድም፡፡61

3.8 የገጠር መሬት መረጃ Aያያዝ ዘመናዊ Eንዲሁን መታሰቡ


Aዲሱ Aዋጅ ከቀድሞው በጠነከረ ሁኔታ በግል ይዞታነት፣ በወል ወይም በመንግስት የተያዘ፣ ለደን
ልማት ወይም ለሌሎች መሰል ተግባራት የተከለለ የትኛውም የገጠር መሬት በባህላዊ መንገድ ወይም
በዘመናዊ መሳሪያ ተለክቶ የባለይዞታዎችን የይዞታ መጠንና Aዋሳኝ ድንበሮች የሚያሳይ ካርታ
ተዘጋጅቶ ይህንኑ ከሚያረጋግጥ ደብተር ጋር Eንደሚሰጣቸው ይደነግጋል፡፡62 የትኛውም መሬት
በሚለካበት ጊዜ በተቻለ መጠን የመሬቱ Aዋሳኝ ባለይዞታዎች ወይም ተወካዮቻቸው በስፍራው
ተገኝተው ድንበሮቻቸውን Eንዲያሳዩ ጥሪ ይደረግላቸዋል፡፡63 መሬቱ ከተለካ በኋላ መጠኑ በተለያዩ
ምክንያቶች ተለውጦ የተገኘ Eንደሆነ Eንደገና ተለክቶ Aዲስ ካርታ ይዘጋጅለታል፡፡

በዚህ መልኩ Aግባብ ባለው የገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም Aካል ኃላፊነት የተለካ ማናቸውም
የገጠር መሬት ይዞታ ለዚሁ ዓላማ በተቋቋመው የመሬት መዝገብ ውስጥ ይመዘገባል፡፡ ምዝገባውም
የመሬቱን ባለይዞታ ሙሉ ስም፣ ይዞታው የተገኘበትን ሁኔታ፣ የመሬቱን Aዋሳኞች፣ የለምነቱን ደረጃ፣
መሬቱ የሚውልበትን Aገልግሎትና ባለይዞታው ያሉበትን ግዴታዎች የሚገልጽ መረጃ Aካቶ መያዝ
ይኖርበታል፡፡64 የገጠር መሬት ምዝገባ መረጃ ባሕረ-መዝገብ በሁለት ቅጅ ተዘጋጅቶ Aንደኛው ቅጂ

58
Aንቀጽ 31(5)፤ ሆኖም ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ሕፃናት፣ Aካል ጉዳተኞች፣ Aቅመ ደካሞች፣ ሴቶችና
Aረጋውያን Eንደ ቅደም ተከተላቸው በማEከላቱ ውስጥ የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ በቅድሚያ የማግኘት መብት
ይኖራቸዋል፡፡
59
Aንቀጽ 31(5)
60
Aንቀጽ 32(1)
61
Aንቀጽ 32(2)
62
Aንቀጽ 33(1) - (3)
63
Aንቀጽ 33(4)፤ በመሬቱ Aለካክና በድንበሩ Aከላለል ረገድ ቅሬታ የተሰማው ማንኛውም ባለይዞታ ቅር
የተሰኘበትን ምክንያት በዝርዝር በመግለጽ ልኬታው በተጠናቀቀ 30 ቀናት ውስጥ ጉዳዩ Eንደገና ይታይለት ዘንድ
በየደረጃው ለሚገኘው የገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም Aካል የማቅረብ መብት Aለው፡፡
64
Aንቀጽ 34(1)(2)
17
በሚመለከተው ቀበሌ ጽ/ቤትና ሁለተኛው ቅጅ ደግሞ ቀበሌው በሚታቀፍበት ወረዳ ገጠር መሬት
Aስተዳደርና Aጠቃቀም ጽ/ቤት ይቀመጣሉ፡፡65

በሀሰተኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ የተካሄደ ማናቸውም ምዝገባ ሕጋዊ ውጤት Aይኖረውም፡፡ በመዝጋቢው
ስህተት ምክንያት በማንኛውም ሰው ላይ ጉዳት የደረሰ Eንደሆነ ስህተቱን የፈጠረው የመንግሥት Aካል
በፍትሐ ብሔር Eና በወንጀል ኃላፊነት ተጠያቂ ይሆናል፡፡66 Aስመዝጋቢዉም ቢሆን በምዝገባዉ
ለተፈጠረው ስህተት የራሱ AስተዋፅO Eንደነበረው የተረጋገጠ ከሆነ በፍትሐ ብሔርና ተገቢ ሆኖ
ሲገኝም በወንጀል ሕግጋት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

የገጠር መሬት ባለይዞታ ወይም የማሳ ወይም የሁለቱም ለውጥ በሚያጋጥምበት ጊዜ የመሬት ምዝገባ
ሰነዱም ወቅታዊ መደረግ ይኖርበታል፡፡ የምዝገባ መረጃውን ወቅታዊ የማድረጉ ተግባር በቀበሌ Eና
በወረዳ የመሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ኮሚቴዎች Aማካኝነት ይከናወናል፡፡ ለሚመለከተው Aካል
በጊዜው ቀርቦ ወቅታዊ ያልተደረገ ማናቸውም የገጠር መሬት የምዝገባ መረጃ ለውጥ ወይም ማሻሻያ
በሕግ ፊት ውጤት Aይኖረውም፡፡67 Eንዲሁም ከመሬቱ ጋር ተያያዥነት ያለውን መብትና ግዴታ
የሚመለከት ማናቸውም ጉዳይ መሬቱ በሚገኝበት ወረዳ ላለው የገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም
ጽ/ቤት ቀርቦ ካልተመዘገበ በስተቀር በሶስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሆኖ ሊቀርብባቸው Aይችልም፡፡68

የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ማንኛውም ሰው የመሬቱ ዝርዝር የተመዘገበበት Eና በሕግ የተደነገጉ
ዋና ዋና መብቶችና ግዴታዎች የሚያሳይ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በስሙ ተዘጋጅቶ Eና ፎቶግራፍ
ተለጥፎበት ይሰጠዋል፡፡69 የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የባለይዞታው በሕግ የተጠበቀ መብት ማስረጃ
ነው፡፡ ይህንኑ የሚቃረን ጠንካራ የጽሑፍ ማስረጃ Eና ይበልጥ የሚያሳምን ምክንያት ካልቀረበ በስተቀር
የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በስሙ ተዘጋጅቶ የተሰጠው ማንኛውም ሰው የመሬቱ ሕጋዊ ባለይዞታ
Eንደሆነ ይቆጠራል፡፡ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር Eያለ ዳኞች ሌሎችን የሰነድም ሆነ የሰው
ማስረጃዎችን ቅድሚያ ሰጥተው ሊቀበሉና ሊመለከቱ Aይችሉም፡፡70

Aዲሱ Aዋጅ በዚህ መልኩ የመሬት ይዞታ በAግባቡ ተለክቶ ካርታና ደብተር ተዘጋጅቶለት Eንዲያዝ
መደረጉ የባለይዞታዎችን የይዞታ ዋስትና ከማጠናከሩም በላይ ክርክሮች ሲኖሩ በቀላሉ ፍትሐዊ ውሳኔ
ለመስጠት የሚያስችሉ የሰነድ ማስረጃዎችን Eዲቀርቡ ያስችላል ብሎ መደምደም ይቻላል፡፡

65
Aንቀጽ 42(1)፤ በሁለቱ የባሕረ-መዝገብ ቅጂዎች መካከል ልዩነት ተፈጥሮ የተገኘ Eንደሆነ መረጃዉ Eንደገና
Eንዲጣራና Eንዲስተካከል ይደረጋል፡፡
66
Aንቀጽ 34(5)(6)
67
Aንቀጽ 43(1)፣(2) Eና (6)
68
Aንቀጽ 34(3)
69
Aንቀጽ 35(1) Eና (6)፤ የወል መሬት ተጠቃሚዎች የሆኑ ባለይዞታዎች ይህንኑ የሚያመለክት የመሬት ይዞታ
ማረጋገጫ ደብተር በስማቸው ተዘጋጅቶ ይሰጣቸዋል፡፡ የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆኑ ተቋማትም ይዞታ
ማረጋገጫ ደብተር በስማቸው ተዘጋጅቶ ይሰጣቸዋል፡፡
70
Aንቀጽ 35(2) Eና (5)
18
3.9 በበርካታ ጉዳዮች ላይ ትርጉም በመስጠት ቀደም ሲል የነበሩትን የግልጽነት ችግሮች መቅረፉ
Aዲሱ Aዋጅ ከቀድሞው Aዋጅ በተሻለ ሁኔታ በርካታ ጉዳዮች ላይ በትርጉም ክፍሉ ግልጽ ትርጉም
መስጠቱ በAሠራር ያጋጥሙ የነበሩ ችግሮችን ይቀርፋል፡፡ ለምሳሌ በቀድሞው Aዋጅ Aስተዳደራዊ
ዉሳኔ ማለት ምን ማለት Eንደሆነ ትርጉም ባለመሰጠቱ ቀደም ሲል Aስተዳደራዊ ውሳኔ የሚሹ Eና
በፍርድ ቤት ሊወሰኑ የሚገባቸውን ጉዳዮች በመለየት ረገድ ሲያጋጥሙ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት
ያስችላል፡፡ በAዲሱ Aዋጅ Aስተዳደራዊ ዉሳኔ ማለት Aንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ባለጉዳዮች፣
በይዞታ መብትና መጠቀም ጥያቄ ሲያቀርቡ ወይም በተቃራኒው ግዴታወቻቸውን ሳይወጡ ሲቀሩ
Aግባብነት ያላቸዉን የመረጃ ምንጮች በመጠቀምና Aስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በሕዝብ በማስተቸት ጉዳዩ
በሚመለከተው የመሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም Aካል ከተጣራ በኃላ በጽሁፍ የሚሰጥ ማናቸውም
ውሳኔ ሲሆን ከገጠር መሬት ልኬታ፣ ምዝገባ፣ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር Aሰጣጥ፣ ከመሬት
Aጠቃቀም Eቅድ፣ ከይዞታ መታጣት Eና ከሌሎች ተዛማጅ Eርምጃዎች ጋር በተገናኘ የሚተላለፉ
ትዛዞችን ያጠቃልላል በማለት የAዋጁ Aንቀጽ 2(44) ግልጽ ትርጉም ይሰጠዋል፡፡

ሌላ ምሳሌ ብንወስድ በቀድሞው Aዋጅ "የገጠር መሬት" ማለት ስልጣን ያለው Aካል ከተማ ብሎ
ከከለለው ውጭ የሚገኝ መሬት ነው በሚል ትርጉም በመስጠቱ በከተማ ክልል ውስጥ የሚገኙ የገጠር
ቀበሌዎች ላይ የሚነሱ የገጠር መሬት ክርክሮች በተለይ የከተማ ነክ ጉዳዩች ፍርድ ቤት
በተቋቋመባቸው ከተሞች ዙሪያ የመሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም Aካላት ተከራካሪ ሲሆን የሥረ ነገር
ስልጣን ያለው የከተማ ነክ ጉዳዮች ፍርድ ቤት ነው ወይስ መደበኛ ፍርድ ቤት የሚለው ብዙ ፍርድ
ቤቶችን ያወዛግብ ነበር፡፡ Aዲሱ Aዋጅ ግን "የገጠር መሬት" ማለት በገጠር የAስተዳደር ወሰን
የተጠቃለሉ የገጠር መሬት ይዞታዎችን Eና በከተሞች የAስተዳደርና የፕላን ወሰን ክልል ውስጥ ያለ
ማንኛውም የገጠር መሬት ነው በማለት ግልጽ ትርጉም በመስጠቱ የነበረውን ችግር ይቀርፋል፡፡

4. በAዲሱ Aዋጅ ላይ የሚታዩ ዋና ዋና ችግሮች


ከላይ በክፍል 3 ሥር ለማንሳት Eንደተሞከረው Aዲሱ Aዋጅ በርካታ በጎ ጎኖችን Aካቶ የወጣ ቢሆንም
ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶት በቂ የባለሙያ Aስተያየቶችን ባለማካተቱ ወይም ለማካተት ባለመፈለግ Eና
በችኮላ በመታወጁ በርካታ ችግሮችንም ይዞ ወጥቷል፡፡ ከEነዚህም ዋና ዋናዎቹን Eንደሚከተለው
ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡

4.1 የገጠር መሬት ይዞታ በነፃ ከማግኘት የEኩልነት መብት ጋር የተያያዙ ችግሮች
የIትዮጵያ Aርሶ Aደሮች ለግጦሽም ሆነ ለEርሻ Aገልግሎት የሚጠቀሙበት መሬት በነፃ የማግኘት
መብት ያላቸው መሆኑን የIፌዴሪ ሕገ መንግስት Aንቀጽ 40(4) Eና (5) ይደነግጋል፡፡ ይህን ሕገ
መንግስት ተከትሎ በፌደራል መንግስቱ የወጣው Aዋጅ ቁጥር 456/97 Aንቀጽ 5(1)(ሀ) በግብርና ሥራ
ለሚተዳደሩ Aርሶ Aደሮች የገጠር መሬት በነፃ Eንዲያገኙ Eንደሚደረግ ይደነግጋል፡፡

19
ይሁን Eንጅ የAማራ ክልል የገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም Aዋጅ ቁጥር 252/2009 የገጠር
መሬትን በነፃ በማግኘት ረገድ Aላስፈላጊ ማዳላትን የሚፈጥሩ በርካታ ድንጋጌዎችን Aካቷል፡፡
የመጀመሪያው ሴቶችን በተመለከተ ያለAግባብ የገጠር መሬት ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ነው፡፡ የሕገ
መንግስቱ Aንቀጽ 35(7) ሴቶች ንብረት የማፍራት፣ የማስተዳደር፣ የመቆጣጠርና የማስተላለፍ መብት
ያላቸው መሆኑን ሲደነግግ በተለይ መሬትን በመጠቀም፣ በማስተላለፍ፣ በማስተዳደርና በመቆጣጠር
ረገድ ከወንዶች ጋር Eኩል መብት ያላቸው መሆኑን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይደነግጋል፡፡ የAዋጅ ቁጥር
456/97 Aንቀጽ 5(1)(ሐ) ድንጋጌ ከላይ ፊደል “ሀ” ላይ ሁሉም Aርሶ Aደሮች የገጠር መሬት በነጻ
Eንደሚያገኙ ካስቀመጠው ድንጋጌ በተጨማሪ በግብርና ሥራ መሰማራት የሚፈልጉ ሴቶች የገጠር
መሬት የማግኘትና የመጠቀም መብት ያላቸው መሆኑን ይደነግጋል፡፡ የሕገ መንግስቱም ሆነ የዚህ
Aዋጅ ድንጋጌዎች ዓላማ ቀደም ባሉት ዘመናት በሀገራችን ከነበረው ሴቶችን ከወንዶች Aንፃር Eኩል
ያለማየት ችግር ለመቅረፍ ሴቶች ከወንዶች ጋር Eኩል የመሬት ባለይዞታ Eንዲሆኑ ማረጋገጥ ነው፡፡71

ከዚህ Aንጻር የክልላችን Aዋጅ ከሕገ መንግስቱ Eና ከፌዴራል የገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም
Aዋጅ ባፈነገጠ መልኩ ሴቶች ከወንዶች በፊት መሬት Eንዲያገኙ የሚያደርጉ በርካታ Aላስፈላጊ
የማዳላት ድጋጌዎችን Aካቷል፡፡ ይኸውም በመርህ ደረጃ Aዋጅ ቁጥር 252/2009 Aንቀጽ 5(2) በክልሉ
ውስጥ የሚኖር ማንኛውም Aርሶ Aደር በፆታም ሆነ በሌላ ማናቸውም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግበት
የገጠር መሬት ይዞታ በነፃ የማግኘት Eኩል መብት ያለው መሆኑን ቢደነግግም Aንቀጽ 5(6) ላይ ደግሞ
የገጠር መሬት ድልድል በሚካሄድበት ጊዜ ወላጆቻቸውን ላጡ ህፃናት፣ ለAካል ጉዳተኞች፣ ለAቅመ
ደካሞችች ለሴቶችና Aረጋዊያን ቅድሚያ Eንዲሰጥ የሚያደርግ የAሠራር ስርዓት ተቀርፆ በሥራ ላይ
Eንደሚውል ይደነግጋል፡፡ የገጠር መሬት ስለማግኘት የሚደነግገው የAዋጅ Aንቀጽ 10(4)ም Eነዚህ
ወገኖች በግብርና ሥራ የሚተዳደሩ ወይም ለመተዳደር የመረጡ ሆነው ሳለ ለዚሁ የሚያስፈልገው
የEርሻ መሬት የሌላቸው ወይም ያነሳቸው Eንደሆነ ይህንኑ በማግኘት ረገድ የቀደምትነት መብት
ያላቸው መሆኑን ይደነግጋል፡፡ የAዋጅ Aንቀጽ 12(3)ም መሬትን የሚያስታድረው Aካል ያለው መሬት
ለሁሉም መሬት ጠያቂዎች መደረስ የማይችል ከሆነ ለEዚህ ወገኖች ብቻ የሚሰጥ መሆኑን
ይደነግጋል፡፡ Eንዲሁም በAንቀጽ 13(4) መሰረት በመስኖ መሬት ሽግሽግ ወቅት Eዚህ ወገኖች ቅድሚያ
ያገኛሉ፡፡ በገጠር ቀበሌ ማEከላት ውስጥ የመሬት Aሰጣጥና Aጠቃቀም ስለመወሰን የተደነገገው Aንቀጽ
31(6) Eነዚህ ከላይ የተዘረዘረሩ ወገኖች በማEከላቱ ውስጥ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ በቅድሚያ
የማግኘት መብት ያላቸው መሆኑት ይደነግጋል፡፡

Aዋጁን ለማስፈፀም የወጣው ደንብ ቁጥር 159/2010ም Aንቀጽ 4(2)፣ 6(9)፣ 23(2) ተመሳሳይ
ሁኔታዎችን ይደነግጋሉ፡፡ ከEነዚህ ድንጋጌዎች በAጠቃላይ የምንረዳው በሕገ መንግስቱ Eና በAዋጅ
ቁጥር 456/1997 ከተደነገገው የEኩልነት መብት ውጭ በማንኛውም ጊዜ በትርፍነት የተያዘ መሬት

በEርግጥ በሀገራችን ከAዋጅ ቁጥር 31/67 መውጣት ጀምሮ የሴቶችን ከወንዶች Eኩል መሬት የማግኘት መብት
71

ለማረጋገጥ ጥረት መደረጉም ሊዘነጋ Aይገባም፡፡


20
ሲገኝ በቅድሚያ ለEነዚህ ወገኖች ብቻ በመስጠት ሌሎች ዜጎች መሬት Eንዳያገኙ ማድረግ ሕጋዊም
ምክንያታዊም Aይደለም፡፡ ምክንያቱም በAንድ በኩል ሕገ መንግስቱም ሆነ የፌዴራሉ Aዋጅ ሴቶችም
ሆነ ሌሎች ከላይ የተዘረዘሩ ወገኖ መብታቸው ሳይጣስ Eኩል መሬት የማግኘት መብትን Aጎናፀፉ Eንጅ
የማዳላት ወይም ለEነዚህ ወገኖች ቅድሚያ የሚሰጥ ድንጋጌ Aላካተቱም፡፡ ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናት፣
Aካል ጉዳተኞች፣ Aቅመ ደካሞ፣ ሴቶችና Aረጋዊያን ልዩ የመብት ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው መሆኑ
Aከራካሪ Aይደለም፡፡ ልዩ የመብት ጥበቃ ሲባል ግን ለመብት ጥሰት ተጋላጭ ወገኖች (Vurnerable
group) ስለሆኑ በEኩልነት Eንዲስተናገዱ Eንጅ ለEነሱ የበለጠ መብት ለመስጠት Aይደለም፡፡ የህፃናት
መብትን የሚደነግገው የሕገ መንግስቱ Aንቀጽ 36(2) ማንኛውም ተቋም ህጻናትን የሚመለከት Eርምጃ
በሚወስድበት ጊዜ የህፃናት ደህንነት በቀደምትነት መታሰብ Aለበት በማለት የሚደነግገው ህጻናት
ያላግባብ Eዳይበደሉ Eንጅ ለEነሱ በማዳላት ሌላ ሰው ለመበደል Aይደለም፡፡

ውስን ሀብት የሆነው መሬት ከላይ ለተዘረዘሩት ወገኖች ብቻ ቅድሚያ በመስጠት ከEነዚህ ወገኖች
ውጭ ያለው Aምራች ሀይል የራሱን መሬት Eንዳያገኝ ማድረግ Aብዛኛውን ሰው በተለይ የገጠሩን
ወጣት ሥራ Aጥነት በማስፋፋት የራሱን Aሉታዊ ችግር ይፈጥራል፡፡ ከዚህ Aንፃር በሕገ መንግስት ላይ
ሳይደነገግና ለAዋጅ ቁጥር 252/2009 መወጣት የውክልና ስልጣን የሰጠው Aዋጅ ቁጥር 456/1997
ያላካተተውን ከEኩልነት መርህ ያፈነገጠና Aብዛኛውን ማህበረሰብ ተጎጅ የሚያደርጉ ድንጋጌዎችን
ማካተቱ ተገቢነት የለውም፡፡

በሌላ በኩል Aዋጅ ቁጥር 252/2009 ከላይ ከተዘረዘሩት Aካላት ውጭ ባሉ የገጠር መሬት ጠያቂዎች
መካከል ልዩነት መፍጠሩም ሌላ ችግር ነው፡፡ ይኸውም ደንብ ቁጥር 159/2010 Aንቀጽ 4(3) መሰረት
Eነዚህ ወገኖች በሌሉበት ጊዜ ወይም ቅድሚያ Aግኝተው ከተስተናገዱ በኋላ ትርፍ መሬት
መኖሩ የታወቀ Eንደሆነ ይኸው መሬት በህዝብ ተሳትፎ ለሚለዩ ሌሎች Aመልካቾች ከዚህ
በታች በተገለፀው ቅደምተከተል Eንዲሰጣቸው ይደረጋል፡-
ሀ. ጎጆ የወጣና ልጅ ያለው፤
ለ. ጎጆ የወጣና ልጅ የሌለው፤
ሐ. ያላገባ ወይም ጎጆ ያልወጣ ወጣት፤
መ. ያገባ ሆኖ በትዳር ጓደኛው ስም የተመዘገበ የጋራ ይዞታ ቢኖረውም የራሱ ይዞታ የሌለው፤
ሠ. በህግ ከተፈቀደው Aነስተኛ የመሬት ይዞታ በታች መሬት ያላቸው ባለይዞታዎች ይላል፡፡

በዚህ ድንጋጌ ውስጥም የEኩልነት መርህ ተጥሷል፡፡ ለምሳሌ በፊደል “ሀ” Eና “ለ” መካከል ያለው
ልዩነት የተፈጥሮን ሕግ ሳይቀር የሚቃረን ነው፡፡ ልጅ መውለድ የEግዚAብሔር ስጦታ Eንጅ ሰዎች
በራሳቸው ችሎታ ብቻ የሚያገኙት Aይደለም፡፡ ከዚህ Aንፃር ልጅ የወለደን ሰው ልጅ ከሌለው ሰው
ማስቀደም ማለት ልጅ መውለድ ባልቻሉ ሰዎች ላይ ተጨማሪ የሞራል ድቀት የሚያመጣና Aላስፈላጊ
ማዳላትን የሚፈጥር ነው፡፡ Eንዲሁም በፊደል “ሐ” የተቀመጠው ያላገባን ወይም ጎጆ ያልወጣን ወጣት

21
ከፊደል “ሀ” Eና “ለ” ቀጥሎ በ3ኛ ደረጃ መሬት Eንዲያገኝ ማድረግም ተገቢ ያልሆነ ልዩነት መፍጠር
ነው፡፡ ብዙ ወጣቶች ትዳር መስርተው ልጅ ከመውለዳቸው በፊት የEኔ የሚሉት ንብረት ኑሯቸው
ቤተሰብ ለመምራት በማሰብ ትዳር ሳይመሰርቱ ይቆያሉ፡፡ መበረታታትም ያለበት ሰው መተዳደሪያ
ሳይኖረው Aግብቶ Eንዳይወልድ Eና ራሱም ሆነ ቤተሰቡ ለችግር Eንዳይጋለጥ ነው፡፡ ከዚህ Aንፃር
ባገባና ባላገባ ሰው መካከል ልዩነት መፍጠር በAግባቡ ያልተጠና Eና በዘፈቀደ የተደነገገ ሕግ መሆኑን
ያሳያል፡፡ በሌላ Aገላለጽ ከሕገ መንግስቱ ጀምሮ የፌዴራል መንግስት Aዋጅ ቁጥር 456/1997
Eንዲሁም Aዋጅ ቁጥር 252/2009 Eድሜው 18 ዓመትና በላይ የሆነው በEርሻ የሚተዳደር ወይም
ለመተዳደር የፈለገ ሰው የገጠር መሬት በነፃ የሚያገኝ መሆኑን ይደነግጋሉ Eንጅ ያገባና ያላገባ፣ ልጅ
ያለውና የሌለው Eያሉ ልዩነት Aያደርጉም፡፡ ስለሆነም ይህ ሁኔታ ተገቢነት የሌለው ልዩነት ወይም
የEኩልነት መብትን የሚጥስ መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡

4.2 የውርስ ድንጋጌዎች የፍትሐዊነት ችግር መኖር Eና ተያያዥ ችግሮች


ውርስን በተመለከተ የAዋጅ ቁጥር 252/2009 Aንቀጽ 17(1) የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ማንኛውም
ሰው የይዞታም ሆነ የመጠቀም መብቶቹን በግብርና ሥራ ለሚተዳደር ወይም በዚሁ ሙያ መተዳደር
ለሚፈልግ ማንኛውም ሌላ ሰው በኑዛዜ ሊያስተላለፍ ይችላል በማለት ይደነግጋል፡፡ የዚሁ Aዋጅ Aንቀጽ
16(1) ደግሞ ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ የይዞታም ሆነ የመጠቀም መብቱን በክልሉ ዉስጥ
ለሚኖር Eና በግብርና ሥራ ለሚተዳደር ወይም በዚህ ሙያ መተዳደር ለሚፈልግ ልጅ ወይም የልጅ
ልጁ ወይም ለማንኛውም ሌላ የቤተሰብ Aባል ወይም መረጃውን በጽሑፍ Eስካረጋገጠ ድረስ በወቅቱ
Eየጦረው ላለና Aገልግሎኛል ወይም Eያገለገለኝ ነው ብሎ ላመነው ሌላ ማንኛውም ሰው በስጦታ
ማስተላለፍ Eንደሚችል ይደነግጋል፡፡

በኑዛዜ ጊዜ Aካለ መጠን ያላደረሰን የተናዛዡን ልጅ ከህጋዊ ወራሽነት የሚነቅል ከሆነ በሕግ ፊት
የማይፀና ስለመሆኑ Aንቀጽ 17(3) ሲደነግግ በስጦታ ጊዜ ባለይዞታው ያደረገው ስጦታ Aካለ መጠን
ያልደረሱ ልጆቹን ወይም የቤተሰብ Aባላትን መብት ሙሉ በሙሉ በሚጎዳ ወይም ለEነሱ በቂ ድርሻ
በማያስቀር ሁኔታ የተከናወነ ከሆነ በሕግ ፊት ተቀባይነት የማይኖረው ስለመሆኑ Aንቀጽ 16(3)
ይደነግጋል፡፡ በመሰረቱ ኑዛዜ ተናዝዡ ከሞተ በኋላ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ ስጦታ ደግሞ ሰጭው
በህይወት Eያለ ጀምሮ የሚፈፀም መሆኑ ካልሆነ በስተቀር በሁለቱ መካከል ጉልህ ልዩነት የለም፡፡
በAዋጅ ቁጥር 252/2009 ግን በሁለቱ መካከል ሰፊ ልዩነት Aለ፡፡ የመጀመሪያው በስጦታ ጊዜ ሕጉ
የስጦታ ተጠቃሚዎችን በግልጽ ለይቶ ያስቀምጣል፡፡ በኑዛዜ ጊዜ ግን የገጠር መሬት ባለይዞታ የመሆን
መብት ላለው ለማንኛውም ሰው ማስተላለፍ Eንደሚቻል ይገልፃል፡፡ በሁለቱም ድጋጌዎች መካከል
ያለው ይህ ልዩነት ከምን Aንፃር Eንደሆነ ግልጽነት ይጎድለዋል፡፡

በኑዛዜ ጊዜ ከውርስ ሊነቀሉ የማይችሉት Aካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ብቻ ሆኖ Eያለ በስጦታ ጊዜ
ስጦታው Aካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ወይም የቤተሰብ Aባላትን ጥቅም ከጎዳ Eንደሚፈርስ መደንገጉ

22
ሲታይ Aጠቃላይ Aዋጁ ከያዛቸው መርሆዎች Aንፃር በስጦታ ጊዜ የቤተሰብ Aባልን መብት ከጎዳ
ይፈርሳል የሚለው ይዘት ፍፁም ያልታሰበበት ነው፡፡ ምክንያቱም Aዲሱ Aዋጅ ከቀድሞው Aዋጅ በተለየ
ሁኔታ የቤተሰብ Aባላትን በማራቅ ለልጆች ቅድሚያ በመስጠት Eንዲወርሱ ከመደንገጉ Aንፃር በስጦታ
ጊዜ Aካለ መጠን የደረሱ ልጆች መብት ቢጎዳም ስጦታው የማይፈርስ ሆኖ Eያለ የቤተሰብ Aባላትን
መብት ቢጎዳ ስጦታው በሕግ ፊት ተቀባይነት የለውም ተብሎ መደንገጉ ተገቢ ስላልሆነ ነው፡፡ ሕግ
ሲወጣ Aጠቃላይ Aዋጁ ያስቀመጣቸውን መርሆዎች ያልተቃረኑ ወጥነት ያላቸው (Consistent)
ድንጋጌዎችን መያዙ መረጋገጥ Aለበት፡፡ ስለሆነም Aዲሱ Aዋጅ ኑዛዜ ላይ Aካለ መጠን ላልደረሱት
ልጆች ብቻ ጥበቃ Aድርጎ ስጦታ ላይ ግን የቤተሰብ Aባላትን Aካለ መጠን ከደረሱ ልጆች Aስበልጦ
መብታቸው ከተጎዳ ስጦታው ይፈርሳል በማለት መደንገጉ ሲታይ በተለይ Aዋጁ የቤተሰብ Aባላትን
Aርቆ ለልጆች ልዩ ትኩረት በመስጠት መሬት Eንዲወርሱ ካስቀመጠው የውርስ ድንጋጌ Aኳያ
የሚጋጭና ፍጹም ስህተት ያለበት ነው፡፡

በሌላ በኩል የAዋጁ Aንቀጽ 17(5) ባለይዞታው በኑዛዜ ሳያወርስ የሞተ ወይም የሰጠው ኑዛዜ ፈራሽ
ሆኖ የተገኘ Eንደሆነ መብቱ Eንደ ቅደምተከታላቸው በግብርና ሥራ ለሚተዳደር ወይም በዚሁ ሙያ
መተዳደር ለሚፈልግ የሟች ልጆች፣ ወላጅ/ጆች ወይም ሕግ ለሚፈቅድለት ለማንኛውም ሌላ የቤተሰቡ
Aባል ይተላለፋል በማለት ይደነግጋል፡፡ ይህ ድንጋጌ ቀደም ሲል ከነበረው Aዋጅ ቁጥር 133/98 Eና
ደንብ ቁጥር 51/99 Aንፃር Aላስፈላጊ ልዩነቶችን (በተለይም በልጆች መካከል) በማስወገድ በAንፃራዊነት
የተሻለ ቢሆንም Aሁንም ግን ከችግር የፀዳ Aይደለም፡፡ ይኸውም ሁሉንም Aይነት የሟች ልጆች በAንድ
መደዳ Eኩል ወራሽ ማድረጉ የራሱ ችግሮች ይኖሩታል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት የሟች Aካለ መጠን
የደረሱም ሆነ ያልደረሱ Eንዲሁም መሬት ያላቸውም ሆነ የሌላቸው ልጆች Eኩል የመውረስ መብት
Aላቸው ማለት ነው፡፡ ከቀድሞ ሕጎች Aንጻር Aዲሱ Aዋጅ Aካለ መጠን የደረሱና ያልደረሱ ልጆች
መካከል የነበረውን ልዩነት ማስቀረቱ Eና ከቤተሰብ Aባላት በፊት ልጆች Eንዲወርሱ መደንገጉ ተገቢ
ነው፡፡ ሆኖም መሬት ባላቸው Eና መሬት በሌላቸው ልጆች መካከል ልዩነት Aለመፈጠሩ Aሁንም
የፍትሐዊነት ችግር መከሰቱ Aይቀርም፡፡

ይኸውም በጸሐፊው Eምነት Aዲሱ ሕግ Eንደቀድሞው በደረቁ መሬት ባለውና መሬት በሌላው ልጅ
መካከል ልዩነት በመፍጠር ቆራጣ መሬት ያለው ልጅም መሬት Eንዳለው ተቆጥሮ መሬት Eንዳይወርስ
የማድረግ ውጤት ሳይኖረው ፍትሐዊነትን ለመጠበቅ በሁለቱ መካከል Aንጻራዊ ልዩነት መፍጠር
ነበረበት፡፡ ጉዳዩን የበለጠ በምሳሌ ለማሳየት ያክል ሟች ሁለት ልጆች Eና 4 ቃዳ መሬት Aለው
Eንበል፡፡ Aንዱ ልጅ የራሱ 8 ቃዳ መሬት ቢኖረው Eና ሌላው ልጅ ምንም መሬት ባይኖረው
የAባታቸውን መሬት Eኩል ሲካፈሉ መጨረሻ ላይ የራሱ መሬት የነበረው ልጅ 10 ቃዳ መሬት
ሲሆንለት መሬት ያልነበረው ልጅ ግን 2 ቃዳ መሬት ብቻ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ
ፍትሐዊነትን Aያረጋግጥም፡፡ ከዚህ Aንጻር ሟች በርካታ መሬት ቢኖረው Eና Aንዱ ልጅ Aነስተኛ

23
መሬት ቢኖረው መሬት የሌለው ልጅ መሬት ያለውን ልጅ ያክል በቅድሚያ Aንስቶ ቀሪውን መሬት
Eኩል Eንዲካፈሉ የሚያደርግ Aይነት ድንጋጌ ቢካተት ኖሮ ፍትሐዊነት ይረጋገጥ ነበር፡፡ ምክንያቱም
መሬት በተፈጥሮ የሚገኝ ውስን ሀብት ስለሆነ ከAንዱ ሰው ወደ ሌላ ሰው ሲተላለፍ በተቻለ መጠን
ፍትሐዊ የተፈጥሮ ሀብት ክፍፍልን መሰረት Aድርጎ መሆን ይኖርበታል፡፡

ከዚሁ ከውርስ ድንጋጌ ሳንወጣ የAዋጁ Aንቀጽ 17(5) የወራሾችን ቅደም ተከተል ሲደነግግ ከልጆች
ቀጥሎ ወላጆች ወይም የቤተሰብ Aባላት ይወርሳሉ የሚለው Aገላለጽ በ"ወይም" በመያያዙ ወላጆች Eና
የቤተሰብ Aባላት የውርስ ቅደምተከተላቸው Eኩል Aይደለም ወይ? የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ በEርግጥ
ድንጋጌው Aቀማመጡ ችግር Aለበት፡፡ ምክንያቱም በተለምዶ "ወይም" የሚለው Aያያዥ ከሁለት
Aንዱን በAማራጭ በEኩልነት የሚያሳትፍ ነውና፡፡ ሆኖም በAንድ በኩል ድንጋጌው ከላይ ሲጀምር
በቅደምተከተል የሚል Aገላለጽ መጠቀሙ ሲታይ በሌላ በኩል ቀደም ሲል የሟች የቤተሰብ Aባል
ያልሆነ ሰው ሁሉ የቤተሰብ Aባል ነኝ Eያለ ያላግባብ መሬት ለመውሰስ የሚደረገውን ሽሚያ በማየት
ሕግ Aውጭው የቤተሰብ Aባላት መጨረሻ ላይ Eንዲወርሱ የማድረግ ሀሳብ ያለው ስለሆነ ከልጅች
ቀጥሎ ወላጆች ይወርሳሉ ብሎ መተርጎሙ የተሸለ ነው፡፡

4.3 ከክርክር Aፈታት ዘዴዎች ጋር የተያያዙ ችግሮች


በመጀመሪያ ደረጃ Aማራጭ የሙግት መፍቻን በተመለከተ የAዋጅ ቁጥር 456/1997 Aንቀጽ 12
የመሬት ይዞታን Aስመልክቶ ክርክር ሲነሳ በቅድሚያ ተከራካሪ ወገኖች ክርክሩን በውይይትና
በስምምነት Eንዲፈቱ ጥረት ይደረጋል፤ በስምምነት መፍታት ካልተቻለ በተከራካሪ ወገኖች በተመረጡ
ሽማግሌዎች Aማካይነት በሽምግልና ይታያል፤ ወይም በክልሎች በሚወጣው የገጠር መሬት Aስተዳደርና
Aጠቃቀም ሕግ መሰረት ይወሰናል በማለት ይደነግጋል፡፡ የክልላችን Aዋጅ ቁጥር 252/2009 Aንቀጽ 52
የገጠር መሬት ይዞታና የመጠቀም መብትን በሚመለከት የሚፈጠሩ Aለመግባባቶችና የሚነሱ ክርክሮች
የሚፈቱበትን ስነ ሥርዓት የደነግጋል፡፡ ይኸውም በመጀመሪያ ደረጃ በራሳቸው በባለጉዳዮቹ መካከል
በሚካሄድ ውይይት Eና በሚደረግ ስምምነት Eንዲፈቱ ይደረጋል፡፡ ተከራካሪ ወገኖች Aለመግባባታቸውን
በስምምነት ሊፈቱ ካልቻሉ ራሳቸው በሚመርጧቸው ሽማግሌዎች Aስታራቂነት ጉዳያቸው Eልባት
Eንዲያገኝ ይደረጋል፡፡

በተግባር በበርካታ ፍርድ ቤቶች የሚነሳው ጥያቄ የገጠር መሬት ክርክር ሲኖር ባለጉዳች Aማራጭ
የሙግት መፍቻ ዘዴዎችን ሳይጠቀሙ ወይም ሳይሞክሩ በቀጥታ በፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ ይችላሉ
ወይስ Aይችሉም የሚለው ነው፡፡ ይህን ጉዳይ በተመለከተ Aዋጅ ቁጥር 133/1997 Aንቀጽ 29 Eና
ደንብ ቁጥር 51/1999 Aንቀጽ 35 ምርጫውን ለተከራካሪዎች በመተው በAማራጭነት ደንግገው የነበረ
መሆኑ ይታወቃል፡፡ Aዲሱ Aዋጅ በቅድሚያ Aማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴን መጠቀም Eንደግዴታ
ይደነግጋል፡፡ ይህም ምናልባት የፍርድ ቤቶችን መጨናነቅ በመቀነስ ረገድ Eና Aንዳንዴም ለባለጉዳዮች
ለራሳቸውም ጠቃሚ ውጤት ሊያስገኝ የሚችል ቢሆንም ባለጉዳዮች የAማራጭ የሙግት መፍቻ

24
ዘዴዎችን ጥቅም በመረዳት Aለመግባባትታቸውን ከመደበኛ ፍርድ ቤት ውጭ Eንዲፈቱ ጥረት መደረግ
ከሚኖርበት በስተቀር በAስገዳጅነት መደንገግ ተገቢ Aይደለም፡፡ ምክንያቱም Aማራጭ የሙግት መፍቻ
ዘዴ በፈቃድ ላይ የተመሰረተ የክርክር መፍቻ መንገድ Eንደመሆኑ መጠን ተከራካሪዎች በግዴታ
Eንዲገቡበት መደንገግ የለበትም፡፡ በግዴታ Eንዲፈጸም ሲደረግም ውጤታማ የመሆን Eድሉ ዝቅተኛ
ነው፡፡ AለምAቀፋዊ መርሁም የሚያሳየው ይህንኑ ነው፡፡72 በመንግስት በኩል ይህን ዘዴ ተግባራዊ
Eንዲደረግ የሚያግዝ ተቋም ሳይኖር Eንዴትስ በግዴታ ተግባራዊ ሊደረግ Eና ውጤት ሊያስገኝ
ይችላል? የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡

በተጨማሪም የAዋጁ Aንቀጽ 52(2) Aለመግባባቱ ያልተፈታ Eንደሆነ ይኸው ከታወቀበት ቀን ጀምሮ
ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ጉዳዩ ለAቅራቢያው ወረዳ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ይችላል ብሎ መደንገጉ ሲታይ
በ30 ቀናት ውስጥ ለወረዳ ፍርድ ቤት ክሱ ሳይቀርብ ቢቀር ከዚህ ጊዜ በኋላ ክሱ ሊቀርብ Aይችልም
ማለት ነው? ይህ ገደብ የተቀመጠበት Aላማስ ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ያስነሳል፡፡ በጸሐፊው
Eምነት ይህ ድናጋጌ ታስቦበት የተቀመጠ ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡ ምክንያቱም ባለጉዳዮች
በመካከላቸው ያለውን Aለመግባባት በAማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎች ለመፍታት ጥረት Aድርገው
መስማማት ካልቻሉ ክስ የማቅረብ መብታቸው በይርጋ Eስካልታገደ ድረስ በፈለጉት ጊዜ ለመደበኛ
ለፍርድ ቤት ክስ የማቅረብ መብት Aላቸው፡፡ ከዚህ Aንጻር በ30 ቀናት ውስጥ የግዴታ ክሱ መቅረብ
Aለበት ማለት ከዚህ መርህ Aንጻር ተገቢ ካለመሆኑም በላይ የAርሶ Aደሩን የመሬት ይዞታ መብት
የማጥበብ ውጤት ስለሚኖረው ተቀባይነት ሊኖረው Aይገባም፡፡

Aስተዳደራዊ ውሳኔዎችን በተመለከተ የAዋጁ Aንቀጽ 33(5) በመሬት Aለካክና በድንበር Aከላለል ረገድ፣
Aንቀጽ 38(1) የገጠር መሬት ይዞታን በመመዝገብ Eና በማረጋገጡ ሂደት፣ Aንቀጽ 40(1) በምዝገባ
ሂደት ተረጋግጦ የተያዘ መረጃ የመጨረሻ ሆኖ መዝገብ ውስጥ ከመግባቱ በፊት Eና Aንቀጽ 43
የባለይዞታ ወይም የማሳ ወይም የሁለቱም ለውጥ በሚያጋጥምበት ጊዜ መረጃን ወቅታዊ በማድረግ
ሂደት የሚሰጡ Aስተዳደራዊ ውሳኔዎች ላይ ቅሬታ ያለው ባለይዞታ ቅሬታ የሚያቀርብባቸውን ተቋማት
Eና የሚያቀርብበትን ጊዜ የሚደነግጉ ናቸው፡፡ በAጠቃላይ ግን የAዋጁ Aንቀጽ 52(6) Eንደሚደነግገው
የገጠር መሬትን ከመለካት፣ ከማስተዳደርና ከሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ጋር በተየያዘ የወረዳ ገጠር መሬት
Aስተዳደርና Aጠቃቀም ጽ/ቤቶች በሚሰጡት Aስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ወገን
ይኸው በደረሰው በ30 ቀናት ውስጥ ክሱን ለወረዳዉ ፍርድ ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡ የወረዳዉ ፍርድ
ቤት የጽ/ቤቱን ውሳኔ ያጸናው Eንደሆነ ይግባኙን ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ይግባኙ
የቀረበለት ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የሥር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ያጸናው Eንደሆነ ውሳኔው የመጨረሻ
ይሆናል በማለት ይደነግጋል፡፡

72
Stacey Keare, Reducing the cost of Civil Litigation: Altrenative Dispute Resolution, PLRI Public Law Research
Institute; Fekadu Petros, Underlining Distinctions beteween Altrenative Dispute Resolution, Shimglina and
Arbitration, Mizan Law Review, Vol 3, No. 1, p. 116 & 119
25
በAዲሱ Aዋጅ በወረዳ መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ጽ/ቤት ውሳኔ ያልተስማማ ሰው ይግባኝ ለዞን
መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም መምሪያ ሊያቀርብ የሚችልበትን ሁኔታም የሚደነግግ ይዘት ያለው
Aንቀጽ Aካቷል፡፡ ለምሳሌ በAዋጁ Aንቀጽ 43(1)(2)(3) ድንጋጌዎች መረዳት Eንደሚቻለው የባለይዞታ
ወይም የማሳ ወይም የሁለቱም ለውጥ በሚያጋጥምበት ጊዜ የመሬት ምዝገባ ሰነዱ በቀበሌ Eና በወረዳ
የመሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ኮሚቴዎች Aማካኝነት ወቅታዊ መደረግ ይኖርበታል፡፡ ኮሚቴው
በሰጠው Aስተዳደራዊ ውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን Aቤቱታውን በጽሑፍ Aዘጋጅቶ ለወረዳ ገጠር መሬት
Aስተዳደርና Aጠቃቀም ጽ/ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡ በጽ/ቤቱ ውሳኔ ያልተስማማ Eንደሆነ ደግሞ ለዞኑ
መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም መምሪያ ወይም ለወረዳ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል፡፡

ከዚህ መረዳት የሚቻለው Aስተዳደራዊ ውሳኔዎች ከቀበሌ መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ጽ/ቤት
ጀመረው በይግባኝ ለወረዳ መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ጽ/ቤት ከቀረቡ በኋላ ቀጥሎ በቅሬታ
Aቅራቢው ምርጫ ለዞን መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም መምሪያ ይግባኝ ወይም ለወረዳ ፍርድ ቤት ክስ
ሊቀርብ Eንደሚችል ነው፡፡ ይኸውም በየትኛውም ሁኔታ በየደረጃው ባሉት በመሬት Aስተዳደርና
Aጠቃቀም ተቋማት Aስተዳደራዊ ውሳኔ ያልረካ ሰው ለወረዳ ፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ የሚቻል መሆኑን
ያሳያል፡፡ ይህም ከቀድሞው ሕግ በሁለት መልኩ የተለየ መሆኑን Eንገነዘባለን፡፡ የመጀመሪያው
የቀድሞው ሕግ በወረዳ መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ጽ/ቤት Aስተዳደራዊ ውሳኔ ያልተስማማ ሰው
ለዞን መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም መምሪያ ይግባኝ የማቅረብ መብት Aይሰጥም ነበር፡፡ ሁለተኛው
ልዩነት የቀድሞው ሕግ በወረዳ መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ጽ/ቤት Aስተዳደራዊ ውሳኔ ያልተስማማ
ሰው የነበረው መብት ለወረዳ ፍርድ ቤት ይግባኘ ማቅረብ ሲሆን በAዲሱ ሕግ ግን Aዲስ ክስ የማቅረብ
መብት Aለው፡፡ ከዚህ Aንጻር በAዲሱ Aዋጅ ከAስተዳደራዊ ውሳኔዎች ላይ ይግባኝ ጠይቆ ከማሳረም
ይልቅ Aዲስ ክስ Eንዲቀርብ መደንገጉ ተገቢ Aይመስልም፡፡ ምክያቱም የዚህ Aይነት የክርክር Aፈታት
መርህ Aላማ በAስተዳደራዊ ውሳኔ ያረካ ሰው በውሳኔው ላይ ይግባኝ ጠይቆ ማሳየት (review of
administrative decisions) Eና መፍትሔ ማግኘት Eንጅ Aዲስ ክስ የሚቀርብ ከሆነ መጀመሪያም
ቢሆን Aስተዳደራዊ ውሳኔ ለማግኘት መድከም Aያስፈልግም ነበር ማለት ነው፡፡ ከዚህ Aንጻር የቀድመው
ሕግ የተሸለ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

በሌላ በኩል በፍርድ ቤት የሚደረግ የክርክር Aፈታት ዘዴን በተመለከተ Aዋጅ ቁጥር 252/2009 Aንቀጽ
52(2) የገጠር መሬት ይዞታና የመጠቀም መብትን በሚመለከት የሚፈጠር Aለመግባባት በEርቅ
ያልተፈታ Eንደሆነ ይኸው ከታወቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ጉዳዩ ለAቅራቢያው ወረዳ
ፍርድ ቤት ሊቀርብ ይችላል በማለት ይደነግጋል፡፡ በAንቀጽ 52(3) መሰረት ደግሞ የወረዳዉ ፍርድ ቤት
በመጀመሪያ ደረጃ ተመልክቶ ውሳኔ የሰጠበት ማናቸውም ጉዳይ በ30 ቀናት ውስጥ ለከፍተኛ ፍርድ
ቤት ይግባኝ ሊቀርብበት ይችላል፡፡ በዚህ Aንቀጽ በወረዳ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቀር የተሰኘ ወገን ለከፍተኛ
ፍርድ ቤት ይግባኝ መጠየቅ የሚችለው በ30 ቀን ብቻ ሆኖ የተደነገገው ከምን Aንጻር Eንደሆነ ግልጽ

26
Aይደለም፡፡ ምክንያቱም ምንም Eንኳን ሕግ Aውጭው መደበኛው የፍትሐ ብሔር ክርክር ይግባኝ
ከሚጠየቅበት 60 ቀን ያነሰ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ መደንገግ የሚችል ቢሆንም73 የዚህ Aይነት መብት
Aጥባቢ ድንጋጌ ሲቀመጥ በቂ Eና Aሳማኝ ምክንያት ያስፈልጋል፡፡ በገጠር መሬት Aስተዳደርና
Aጠቃቀም ሕግ ተጠቃሚም ሆነ ተጎጅ የሚሆኑት Aርሶ Aደሮች Eንደመሆናቸው መጠን ያልተማረና
መብቱን በAግባቡ የማያውቅ Aርሶ Aደር ባለበት ክልል Eንዲህ Aይነት መብት የሚያጠብ ሕግ
ማውጣት ተገቢነት የለውም፡፡
4.4 በሕጎቹ ላይ Aላስፈላጊ Aገላለጾችና ድግግሞሽ የማካተት ችግር
Aዲሱ Aዋጅ የራሱ የሆኑ በጎ ጎኖች ቢኖሩትም በርካታ የሀሳብ ድግግሞሽ ወይም Aላስፈላጊ ድንጋጌዎች
የያዘ ስለሆነ የሕግ Aወጣጥ መስፈርትን Aሟልቶ በAግባቡ የተረቀቀ ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡
ለማሳያ ያክል የሚከተሉትን ማየት በቂ ነው፡፡

1. ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት፣ Aካል ጉዳተኞች፣ Aቅመ ደካሞችን፣ ሴቶችንና የAረጋዊያንን መብት


የሚመለከቱ ድንጋጌዎች በየAንቀጹ ያላግባብ ተደጋግሟል፡፡ ይህም ከላይ በክፍል 4.1 ሥር
በተቀመጠው Aግባብ በሌሎች ዜጎች ላይ ያላግባብ የሚያዳላ ከመሆኑም በላይ በሕግ Aወጣጥ መርህም
Eነዚህን ወገኖች መጥቀም ከተፈለገ Eንኳን ጠቅለል Aድርጎ በAንድ ድንጋጌ ከገጠር መሬት ይዞታ
Aሰጣጥና ተያያዥ ተግባራት ጋር በተገናኘ የEነዚህ ወገኖች መብት ቅድሚያ Eንዲያገኝ Aድርጎ
መደንገግ ይቻል ነበር፡፡ ለምሳሌ በAዋጁ Aንቀጽ 39(1) ላይ ሞግዚት ወይም ሕጋዊ ወኪል የሌላቸው
ሕፃናት፣ የAካል ጉዳተኞች፣ የAቅመ ደካሞች፣ የሴቶችና የAረጋውያን ይዞታ የሆነ መሬት
በሚመዘገብበትና በሚረጋገጥበት ወቅት Eነዚሁ ወገኖች በስፍራው ካለመገኘታቸው የተነሳ መብታቸው
Eንዳይጣስ ብርቱ ጥንቃቄ መደረግ ይኖርበታል በሚል Eንደተደነገገው Aይነት Aንድ Aንቀጽ
ማስቀመጥ ይቻል ነበር፡፡

2. ስለ ምትክ ወራሽነት የሚደነግገው የAዋጁ Aንቀጽ 17(6) የሟች ልጆች ወይም ከልጆቹ Aንዱ
ቀድመዉ ሞተዉ ወይም ሞቶ Eንደሆነና ወደታች የሚቂጠሩ ተወላጆችን ትተዉ/ትቶ Eንደሆነ
Eነዚሁ ተወላጆቻቸዉ የሟቹ የቤተሰብ Aባል ሆነዉ ተገኝተዉ ካልወረሱ በስተቀር ቀድመዉ
በሞቱት ልጆች ምትክ ሆነዉ Eንዲወርሱ ይደረጋል በማለት ይደነግጋል፡፡ በAዲሱ Aዋጅ የቤተሰብ
Aባል ከልጆች በፊት የሚወርስበት ሁኔታ የቀረ ከመሆኑ Aኳያ ቀድመው የቤተሰብ Aባል ሆነው
ካልወረሱ በስቀር የሚለው Aገላለጽ በከንቱ የገባ ነው፡፡

3. Aንቀጽ 17(7) በጋብቻ የተወለዱና ከጋብቻ ውጭ የተወለዱ ልጆች Eኩል የመውረስ መብት ያላቸው
ስለመሆኑ በቤተሰብ ሕጉ ተደንግጎ Aድሮ Eያለ በመሬት Aዋጁ Eንዲህ Aይነት ድንጋጌ ማካተት
በሕግ ስርዓቱ ውስጥ የድግግሞሽ ውጤት ያለው ነው፡፡

73
ለምሳሌ በAሠሪና ሠራተኛ Aዋጅ ቁጥር 377/1996 Aንቀጽ 138(3) የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ Aንድ ወር ነው፡፡
ይህ የሆነበት የራሱ ምክንያት Aለው፡፡ ለIንዱስትሪው የሥራ ፍጥነት ሲባል ነው፡፡
27
4. Aንቀጽ 17(8) ደግሞ ማንኛውም ሰው ሳይናዘዝ በሞተበት ወቅት በግብርና ሥራ የሚተዳደር ወይም
ለመተዳደር የሚፈልግ ወደታች የሚቆጠር ተወላጅ የሌለው ሆኖ በግብርና ሥራ የሚተዳደሩ ወይም
ለመተዳደር የሚፈልጉ ወላጅ/ጆች ካለው ወይም ካሉትና Aስቀድሞ ያላቸው የገጠር መሬት ይዞታ
መጠን ከከፍተኛው የይዞታ ጣሪያ በታች መሆኑ የታወቀ Eንደሆነ የመሬት ይዞታውን Eነርሱ
የመውረስ መብት ይኖራቸዋል፤ ዝርዝሩ በደንብ ይወሰናል፤ በማለት ይደነግጋል፡፡ ይህ ድንጋጌ
ጭራሽ Aስፈላጊ Aልነበረም፡፡ ምክንያቱም ወላጆች የልጆቻቸውን መሬት የሚወርሱበት ሁኔታ
በAንቀጽ 17(5) ሥር የተካተተ ሆኖ Eያለ በድጋሜ በAንቀጽ 17(8) ሥር ተመሳሳይ ሀሳብ
ማስቀመጡ Aስፈላጊ Aይደለም፡፡ በደንብ ሊወሰን የሚችል የወላጅ Aወራረስ ሁኔታ ሳይኖር ዝርዝሩ
በደንብ ይወሰናል መባሉም በጣም የሚገርም ነው፡፡ ካስፈለገም ዝርዝር በደንብ ይወሰናል ተብሎ
ለደንቡ ስልጣን መስጠት የነበረበት በAንቀጽ 17(5) ሥር ነው፡፡ በዚህ ንUስ Aንቀጽ ሥር ለደንቡ
ስልጣን ተሰጥቶ ቢሆን ኑሮ ምናልባልትም ከላይ የተነሳውን የፍትሐዋነት በችግር ይቀርፍ ነበር፡፡

5. የAዋጁ Aንቀጽ 35(2) Eና (5) ድንጋጌዎች የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የባለይዞታው በሕግ
የተጠበቀ መብት ማስረጃ ነው፡፡ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር Eያለ ዳኞች ሌሎችን የሰነድም ሆነ
የሰው ማስረጃዎችን ቅድሚያ ሰጥተው ሊቀበሉና ሊመለከቱ Aይችሉም፡፡ ይህንኑ የሚቃረን ጠንካራ
የጽሑፍ ማስረጃ Eና ይበልጥ የሚያሳምን ምክንያት ካልቀረበ በስተቀር የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር
በስሙ ተዘጋጅቶ የተሰጠው ማንኛውም ሰው የመሬቱ ሕጋዊ ባለይዞታ Eንደሆነ ይቆጠራል፡፡
በማለት ይደነግጋሉ፡፡ ይህም በፍ/ሕ/ቁ 1195 Eና 2010(2) Aንጻር ለሰነድ ማስረጃ የተሰጠውን
ግምት Eና Eንዴት ማስተባበል Eንደሚቻል የተደነገገ ከመሆኑ Aኳያ በሕግ ስርዓቱ ውስጥ ሌላ
ድግግሞስ ከመሆኑም በላይ ለዳኞችም ሆነ ለሌሎች የሕግ ባለሙያዎች ግራመጋባትን የሚፈጥር
ነው፡፡ Aገላለጹም ሕጉን ግልጽ ከማድረግ ይልቅ የሚያወዛግብ ነው፡፡ Eነዚህ ድንጋጌዎች ባይኖሩም
ስለማስረጃ ሕጋችን የተደነገጉትን Aጠቃላይ መርሆዎች ግምት ውስጥ በማስገባት ሊመለስ የሚችል
ጉዳይን የበለጠ በሚያምታታ ሁኔታ መደንገግ ተገቢ Aልነበረም፡፡

6. Aመግባባቶች ስለሚፈቱበት ሁኔታ የሚደነግገው Aንቀጽ 52(4)-(8) ያሉት ድንጋጌዎች Aላስፈላጊ


ድግግሞሽ ናቸው፡፡ ይኸውም በስተዳደራዊ ውሳኔ ቅር በመሰኘትም ሆነ ጉዳዩ በEርቅ ባለማለቁ
ለወረዳ ፍርድ ቤት ቀርቦ በተወሰነው ጉዳይ ቅረታ ያለው ወገን ይግባኙን ለከፍተኛ ፍርድ ቤት
ያቀርባል፡፡ ይግባኝ የቀረበለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት የወረዳውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ካጸናው ውሳኔው
የመጨረሻ ይሆናል፡፡ ይግባኙ የቀረበለት ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ የሻረው
ወይም ያሸሻለዉ Eንደሆነ ግን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ ይግባኝ ሊቀርብበት ይችላል፡፡
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡ በመጨረሻ ደረጃ በተሰጡ የከፍተኛም
ሆነ የጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ውሳኔዎች ላይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት Aለበት የሚል ወገን
Aቤቱታዉን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሊያቀርብ ይችላል፡፡ Eነዚህ Aገላለጾች

28
የይግባኝ ስርዓቱን በተመለከተ በክልሉ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ Aዋጅ ቁጥር 223/2007 በግልጽ
ከተደነገገው Aገላለጽ Aኳያ Aላስፈላጊ ድግግሞሽ ስለሆኑ ምንም ጥቅም የላቸውም፡፡ በሌላ Aገላለጽ
በስተዳደራዊ ውሳኔ ቅር በመሰኘትም ሆነ ጉዳዩ በEርቅ ባለማለቁ ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ
Eንደሚቀርብ መደንገግ ብቻ በቂ ነበር፡፡ ምክንያቱም ለወረዳ ፍርድ ቤት የቀረበ ክስ ውሳኔ ሲያገኝ
ቀጥሎ ወደየትኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ Eንደሚጠየቅ በፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ ሕግ ተደንግጎ ያደረ
ጉዳይ ነው፡፡
5. ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ላይ የሚታዩ ችግሮች
Aዲሱ Aዋጅ የማጠቃለያ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ላይም በርካታ ጥያቄ የሚፈጥሩና ለAሠራር
የሚያስቸግሩ ድንጋጌዎችን ይዟል፡፡ Eነዚህ ችግሮች በተወሰነ መልኩ ማየት ይገባል፡፡
1. የፍትሐ ብሔር ሕግ Aግባብነት የሚለው የAዋጅ Aንቀጽ 54 በዚህ Aዋጅ Aንቀጽ 15፣ 16 Eና 17
ያልተሸፈኑ የገጠር መሬት ኪራይ፣ ስጦታ፣ ውርስና ሌሎች ፍትሐ ብሔር ነክ ጉዳዮችን
በተመለከተ Eንደነገሩ ሁኔታ Aግባብነት ያላቸዉ 1952 ዓ/ም የፍትሐ ብሔር ሕግ ድንጋጌዎች
ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል በማለት ይደነግጋል፡፡ ይህ Aገላለጽ ምን ማለት ነው? ለምሳሌ በመሬት
Aዋጁ መሰረት ሊወርስ ወይም ስጦታ ሊቀበል የማይችል ሰው የፍትሐ ብሔር ሕጉን መሰረት
ተደረጎ ሊወርስ ወይም ስጦታ ተቀባይ ሊሆን ይችላል ማለት ነውን? Aይደለም፡፡ ይልቁንም የዚህ
ድንጋጌ ይዘት በፍትሐ ብሔር ሕጉ የሚታወቁ ጽንሰ ሀሳቦች ለምሳሌ ከወራሽነት መንቀል፣
ለውርስ ያልተገባ መሆን፣ የመጥፋት ውሳኔ የሚሉና ተመሳሳይ ሀሳቦች ቢያጋጥሙ በቀጥታ
Eነዚህን ሀሳቦች የሚመለከቱ የፍትሐ ብሔር ሕጉ ድንጋጌዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ ማለት ነው፡፡74

2. ስለ ይርጋ የሚደነግገው Aንቀጽ 55 የገጠር መሬትን በወረራ ወይም በሌላ በማናቸውም ሕገ ወጥ


መንገድ ይዞ በመገልገል ላይ የሚገኝ ማንኛውም ሰው መሬቱን Eንዲለቅ በማንኛውም ሌላ ሰው
ወይም ሥልጣን ባለው የመንግሥት Aስተዳደር Aካል ሲጠየቅ ወይም በመደበኛ ፍርድ ቤት ሲከሰስ
የይርጋ ጊዜ ገደብን በሥነ ስርዓት መቃወሚያነት ሊያነሳ Aይችልም በማለት ይደነግጋል፡፡ ይህ
Aገላለጽ ሁሉንም Aይነት የገጠር መሬት ክርክሮች ይርጋ የላቸውም የሚያስብል ሆኖ መወሰድ
Aይኖርበትም፡፡ ለምሳል ጉዳዩ የመሬት ውርስ ክርክር ቢሆን ይርጋ የለውም ብሎ ለመተርጎም ይህ
ድንጋጌ Aያካትተውም፡፡

74
ይህን ሀሳብ የበለጠ ለማጉላት በፌደራል የገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ረቂቅ Aዋጅ ማብራሪያ ላይ
የተወሰደውን ሀሳብ ማየት ይጠቅማል፡፡ … በፍትሐ ብሔር ሕጉ የተቀመጡ ጉዳዮችን Eንደ Aግባብነታቸው
ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡ ለምሳሌ መጥፋትን ብንወስድ በፍትሐ ብሔር ሕጉ ተደንግጎ ያደረ ጉዳይ ነው፡፡
በመሆኑም Aንድ ሰው የመጥፋት ውሳኔ ከተላለፈበት በፍትሐ ብሔር ሕጉ በሚያስቀምጠው ገደብ መሰረት
በጠፋው ሰው ይዞታ ስር የነበረውን መሬት ወራሾች ጠይቀው ሊከፋፈሉት ይችላሉ፡፡ Eነዚህን ዝርዝር ጉዳዮች
በዚህ Aዋጅ ከማየት ይልቅ የፍትሐ ብሔር ሕጉ ድንጋጌዎች Eንደ Aግባብነታቸው ተፈጻሚ Eንደሚሆኑ
Aስቀምጦ ማለፉ የተሻለ ነው ይላል፡፡ ገጽ 33

29
በፌደራል የገጠር መሬት Aስተዳደርና Aጠቃቀም ረቂቅ Aዋጅ ማብራሪያ ላይ የተወሰደው ትንታኔ
ይህን ሀሳብ ያጠናክራል፡፡ ይኸውም የይርጋ ድንጋጌዎች ለምሳሌ ጉዳዩ ከውል ጋር የተያያዘ ከሆነ
የፍትሐ ብሔር ሕጉ Aንቀጽ 1845 Aግባብነት ይኖረዋል፡፡ ሌሎች ከወል መሬት ወረራ ጋር
የተያያዙ ጉዳዮች ከመጀመሪያም ሕገ ወጥ Eና ወንጀል በመሆናቸው መሬቱን ለማስመለስ
የሚደረግ ክርክር በይርጋ የሚታገድ Aይሆንም፡፡ Eንዲህ Eንዲህ Eያለ Eንደ ሁኔታው የፍትሐ
ብሔር ሕጉ የይርጋ ድንጋጌ ሕጉ ይቀበላቸዋል ይላል፡፡

3. የፍርድ ቤት ውሳኔ በገጠር መሬት ይዞታ ላይ ስለሚኖረው ውጤት የሚደነግገው Aንቀጽ 56


ማንኛውም የገጠር መሬት ባለ ይዞታ የፍርድ ቤት ውሳኔን ለማስፈጸም በሚሰጥ ትEዛዝ ከይዞታው
Aይፈናቀልም ወይም ይዞታው ለEዳ መክፈያ በሚል ለሌላ Aካል ሊተላለፍ Aይችልም በማለት
ይደነግጋል፡፡ ይህ ድንጋጌ የገጠር መሬት Aይሸጥም በሌላ ንብረት Aይለወጥም ከሚለው ህገ
መንግስታዊ ክልከላ ጋር ተያይዞ ነው መተርጎም ያለበት፡፡ ይህ ማለት በፍትሐ ብሔር ለተፈጠረ
ግንኙነት የገጠር መሬት ለEዳ መክፈያ ተብሎ Aይያዝም ለማለት ነው፡፡ ይህ Aተረጓጎምም ቢሆን
በጠባቡ መታየት ይኖርበታል፡፡ ለምሳል ከመሬቱ የሚገኘውን ምርት ወይም መሬቱን በማከራየት
Eዳ Eንዲከፈል ከማዘዝ የሚከለክል ተደርጎ ሊወሰድ Aይገባውም፡፡

4. የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎችን የያዘው Aንቀጽ 57 ይህ Aዋጅ ከመጽናቱ በፊት ከገጠር መሬት ይዞታና
Aጠቃቀም ጋር በተያያዙ በሌሎች ሕጐች የተቋቋሙ መብቶችና ግዴታዎች ቀደም ሲል የነበሩ
ሕጐችን መሰረት Aድርገው Eስከተገኙና ይህንን Aዋጅ በግልጽ Eስካልተቃረኑ ድረስ
ተፈፃሚነታቸው ይቀጥላል፡፡ ይህ Aዋጅ ከመውጣቱ በፊት ፍርድ ቤት ቀርበው በመታየት ላይ ያሉ
ማናቸውም መሬት-ነክ ጉዳዮች በተጀመሩበት Aግባብ የመጨረሻ Eልባት Eንዲያገኙ ይደረጋል፡፡
ይላል፡፡ በዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ 1 ላይ ይህንን Aዋጅ በግልጽ Eስካልተ ቃረኑ ድረስ
ተፈፃሚነታቸው ይቀጥላል የሚለው Aገላለጽ ምን ማለት ነው? ለምሳሌ በቀድሞው Aዋጅ መሰረት
የቤተሰብ Aባል በመሆን መሬት ካለው የሟች ልጅ ቀድሞ የወረሰ ሰው ቢኖር Aሁን ካለው
Aወራረስ ቅደም ተከተል ጋር ይቃረናል ተብሎ ተፈጻሚነቱ ሊቀር ነው?

በመጀመሪያ ደረጃ ይህን Aዋጅ Eስካልተቃረኑ ድረስ ተፈጻሚነታቸው ይቀጥላል የሚለው ሀረግ ያላግባብ
የተቀመጠ ነው፡፡ ይህ ማለት ከፍትሐ ብሔር ሕጉ ድንጋጌዎች ጀምሮ በተለያዩ ጊዚያት በሀገራችን
በርካታ የገጠር መሬት ሕጎች ታውጀዋል። Eነዚህ ሕጎች በየዘመናቸው ለመሬት ባለይዞታዎች
የሚሰጡት መብት ወጥነት Aልነበረውም፤ Aሁንም የለውም፡፡75 ለምሳሌ በAዋጅ ቁጥር 133/1998 Eና
ደንብ ቁጥር 51/1999 መሰረት የቤተሰብ Aባል ከልጅ ቀድሞ የሚወርስበት Aጋጣሚ በጣም ብዙ ነበር፡፡
Aሁን በወጣው Aዋጅ ቁጥር 252/2009 ደግሞ ልጅ Eያለ የቤተሰብ Aባል ሊወርስ Aይችልም፡፡

75
ለምሳሌ Aዋጅ ቁጥር 133/1998 ከAዋጅ ቁጥር 46/1992 የተሻለ Eና የሰፋ መብት ለባለይዞታዎች Eና
ለወራሾቻቸው ይሰጣል፡፡ Aሁን ደግሞ Aዋጅ ቁጥር 252/2009 በAንጻራዊነት የተሻለ መብት ይሰጣል፡፡
30
ቀደም ብለው የተሰሩ ሥራዎች ይህን Aዋጅ Eስካልተቃረኑ ድረስ ተፈጻሚነታቸው ይቀጥላል የሚለውን
በደረቁ ብንወስደው ቀደም ብሎ በAዋጅ ቁጥር 133/1998 Eና ደንብ ቁጥር 51/1999 መሰረት ከልጆች
ቀድመው የወረሱ የቤተሰብ Aባላት በሙሉ ድርጊቱ የAሁንን Aዋጅ ስለሚቃረን መፍረስ Aለበት የሚል
ድምዳሜ ላይ ያደርሰናል፡፡ Eንዲሁም ቀደም ሲል የነበረው ሕግ በልጆች መካከልም ቢሆን Aካለ መጠን
የደረሰና ያልደረሰ፣ መሬት ያለውና የሌለው Eያለ ልዩነት ስለሚያደርግ ይህን መሰረት ተደርጎ ለዘመናት
ሲሰራበት ስለኖረ ከAሁኑ ሕግ Aንጻር ይቃረናል ማለት ነው፡፡ ይህ Aተረጓጎም ማህበራዊ Eና Iኮኖሚ
ቀውስ ያስከትላል፡፡ ምክንያቱም የቀድሞቹ የገጠር ሕጎች መሰረት Aድርገው በርካታ የመሬት ውርስ
ተከናውኖ ከነችግሩም ቢሆን የወረሱ ሰዎች የይዞታ መብታቸውን Aደላድለው Eየኖሩ ባለበት ሁኔታ
መብቱን ያገኘህበት ሕግ ከAዲሱ ሕግ ጋር ይቃረናል በሚል ማፍረስ ቢጀመር ክልላችን የማይወጣው
ችግር ውስጥ መውደቁ Aይቀርም፡፡76

76
ይህን Aዋጅ መሰረት Aድርገው በርካታ ሰዎች በዚህ መንገድ ቀደም ሲል የተወረሱ መሬቶች ላይ በርካታ ክሶች
በፍርድ ቤቶች Eያቀረቡ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የሚቀርቡት ጉዳዮች ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት ትርጉም ተሰጥቶ
በቀድሞ ሕጎች የተሰሩ ሥራዎች Eንደረጉ Eንዲቀሩ ካልተደረጉ በስተቀር ውጤቱ Aደገኛ መሆኑ Aይቀርም፡፡
31
ማጠቃለያ
በAማራ ክልል ቀደም ሲል ሥራ ላይ የነበረው Aዋጅ ቁጥር 133/1998 Eና ማስፈጸሚያ ደንቡ ቁጥር
51/1999 ላይ በተግባር በርካታ ችግሮች በማጋጠማቸው Aዋጅ ቁጥር 252/2009 Eና ማስፈጸሚያ
ደንብ ቁጥር 159/2010ም ተሻሽሎ ወጥቷል፡፡ Aዋጁ የተሻሻለበት ዋና ዋና ምክንያቶች የAርሶ Aደሮችን
በመሬት የመጠቀም መብት ይበልጥ ለማስፋት፤ ተበታትኖ የሚኖረዉን Aርሶ Aደር ወደ ተወሰኑ
ማEከላት በማሰባሰብ ሁለንተናዊ ለሆነ Eድገት ተጠቃሚ ለማድረግ፤ የግል ባለሀብቶች መሬትን
በማልማት ረገድ ያላቸውን ሚና ለማጠናከር፤ የገጠር መሬት ምዝገባ መረጃን በጥራት ለማደራጀት፤
ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራን Eና ሕገ ወጥ ግንባታን ለመቆጣጠር፣ የገጠር መሬትን በEቅድ በመጠቀም
ለመጭው ትውልድ ለማስተላለፍ፤ ለመብት ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ ወገኖችን መሬት የማግኘትና
የመጠቀም መብት ይበልጥ ለማስከበር፤ የገጠር መሬት ለሕዝብ ጥቅም ሲወሰድ ለባለይዞዎች
ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ የሚያገኙበትን Eና በዘላቂነት የሚቋቋሙበትን Aሠራር በሕግ መደንገግ
በማስፈለጉ የሚሉ ናቸው፡፡

በዚህ መሰረት Aዲሱ Aዋጅ ከቀድሞው Aዋጅ በEጥፍ ቁጥር ድንጋጌዎችን የያዘ፣ በጣም ሰፊ መግቢያ
Eና በርካታ የትርጓሜ ንUስ Aንቀጾችን ያካተተ Eንዲሁም Aዳዲስ ሀሳቦችን ያቀፈ ሆኖ ታውጇል፡፡
በዚህ ጽሑፍ Aዘጋጅ Eምነት ይህ Aዋጅ ሁለት ገጽታዎችን ይዞ ወጥቷል፡፡ የመጀመሪያው ገጽታ
የAዋጁ መውጣት ያመጣቸው መልካም ነገሮች ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ Aዋጁ ያካተታቸው ችግሮች
ናቸው፡፡ Aዋጁ ያመጣቸው መልካም ጎኖች ውስጥ የሚመደቡት ዋና ዋናዎቹ Aነስተኛ ገቢ ያላቸው
ሰዎች የመሬት ይዞታ ሊኖራቸው Eንደሚችል መደንገጉ፤ ለመብት ጥሰት ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች ልዩ
ትኩረት መስጠቱ፤ የመሬት ይዞታን ከማከራየት መብት ጋር ተያይዞ የኪራይ ዘመኑ ለሰብልና ለቋሚ
ተክሎች በሚል ልዩነት ማምጣቱ፤ የውርስ ቅደም ተከተሉ ለልጆች ቅድሚያ መስጠቱ Eና ተያያዥ
መሻሻሎች መኖራቸው፤ የይዞታ መሬትን Aስይዞ ገንዘብ መበደር መፈቀዱ፤ ይዞታ ለህዝብ Aገልግሎት
ሲወሰድ የመልሶ ማቋቋም ሥራ ለመንግስት ግዴታ ሆኖ መደንገጉ፤ የገጠር መሬት መረጃ Aያያዝ
ዘመናዊ Eንዲሁን መታሰቡ Eና የገጠር መሬት Aጠቃቀም Eቅድ ማዘጋጀት Eንደሚገባ መደንገጉ
የሚሉት ናቸው፡፡

ሁለተኛው ገጽታ በAዲሱ Aዋጅ በርካታ ችግሮች መኖራቸው ሲሆን ዋና ዋናዎቹ የገጠር መሬት ይዞታ
በነፃ ከማግኘት መብት ጋር ተያይዞ የEኩልነት መብትን ያላከበሩ ድንጋጌዎች መኖራቸው፤ የውርስ
ድንጋጌዎች Aሁንም የፍትሐዊነት ችግርን መቅረፍ Aለመቻላቸው፤ ከክርክር Aፈታት ዘዴዎች ጋር
የተያያዙ በርካታ ችግሮች መኖራቸው፤ በAንዳንድ ድንጋጌዎች ላይ Aላስፈላጊ Aገላለጾችና ድግግሞሽ
መኖር Eና ከልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ላይ የሚታዩ ለAሠራር Aስቸጋሪ የሆኑ ችግሮች መኖራቸው የሚሉ
ናቸው፡፡ ከዚህ Aንጻር Eነዚህ ችግሮች በቶሎ ታይተው Eና በAግባቡ ተጠንተው በድንጋጌዎቹ ላይ
ተገቢው ማሻሻያ ቢደረግ መልካም ነው፡፡

32
በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ውስጥ በጊዜ ቀጠሮ መፈቀድ ወይም
በዋስትና መከልከል በጥበቃ ሥር ማቆየት የፅንሰ ሃሳብ ይዘትና የክርክር አመራር
ሰሎሞን ጐራው አዳነ#
አህፅሮተ- ይዘት
የነፃነት መብትን ለ,በመገደብ በጥበቃ ሥር ለሚቆዩ ሰዎችን መብት ከማሕበረሰቡ ጠቅላላ ጥቅም ጋር
በማጣጣም ረገድ የዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን ሰነዶችና በሀገራት የወንጀል ፍትህ አስተዳደራቸው ሕግ ላይ
ገደቦችን ያካትታሉ፡፡ በኢትዮጵያ ሕግ መንግስት ውስጥም ፍርድ ቤት ወዲያው መቅረብና የመያዝን
ሕጋዊነት ማረጋገጥ፣ ፍትህ እንዳይጓደል በቁጥጥር ሥር መቆየት ካልሆነ በስተቀር በዋስ መውጣት፣
የነፃነት መብት እና ሌሎችም መብቶችም ተካተዋል፡፡ የጊዜ ቀጠሮ መብት መርማሪ አካል ተጠርጣሪን
ሰው ምርመራውን እስከሚያጠናቅቅ ድረስ በሕግ ቁጥጥር ስር እንዲቆይ የሚጠየቅበት የሕግ ሥርዓት
ነው፡፡ የዋስትና መብት በህግ ቁጥጥር ስር ያለ ሰው የጊዜ ቀጠሮው ሲጠናቀቅ፣ ሳይፈቀድ ሲቀር
ወይም የጊዜ ቀጠሮ ካልተጠየቀ ከክስ በፊትም ሆነ በኋላ ክርክሩን ከማረፊያ ቤት ውጭ በዋስ ሆኖ
እንድከራከር የሚጠይቅበት ሥርዓት ነው፡፡ ዋስትና የማይፈቀድ ከሆነም ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር
እንድቆይ ይገዳዳል፡፡ በቁጥጥር ሥር ማቆየትን በተመለከተም በዓለም ላይ ከሚታዩ የወንጀል ሥነ
ሥርዓት ሞደሎች ውስጥ የወንጀል ቁጥጥር መር ወይም ሥነ ሥርዓታዊ ፍትህን የሚያሰፍን መሆኑ
ላይ ልነት አለው፡፡1 በወንጀል ተጠርጥረው የሚያዙ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር የሚቆዩበት ሁኔታ
የወንጀል ቁጥጥር መር ፖሊሲን መከተልን የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ በዋስትና መልቀቅ ሥነ ሥርዓታዊ
ፍትህን የመከተል አዝማሚያ የሚያሳይ ነው፡፡ አሁን አሁን ላይ በኢትዮጵያ እየወጡ ያሉ ሕጎች
ምርመራ ሲደረግ ወይም ክስ ሲሰማ በቁጥጥር ሥር መቆየትን የመምረጥ ሁኔታ የሚያሳዩ ናቸው፡፡
ሆኖም ፍርድ ቤቶች በቁጥጥር ሥር ማድረግን በተመለከተ ሲወስኑ የማሕበረሰቡን ጥቅም እና የተከሰሰ
ሰውን መብት በማስጠበቅ ለተወዳዳሪ ግቦች ተገቢ ምላሽ በመስጠት የፍትህ ሥርዓቱ እምነት
የሚጣልበት እንዲሆን ማስቻልን ይጠበቅባቸዋል፡፡2
በዚህ ፅሁፍ ውስጥም በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ውስጥ በወንጀል የተጠረጠረ ሰው
በቁጥጥር ሥር መቆየት እና ዋስትና የመለቀቅ መብትን በሚመለከት ጽነሰ ሃሳቡን፣ በሀገራችን ያለውን
የሕግ ማዕቀፍና በተግባር የፍርድ ቤት አሰራርን ተቀባይት ካላቸው መርሆች ጋር በማነፃፀርና
የተመረጡ መዝገቦችን ጋር በማጣቀስ የሚመርመር ይሆናል፡፡ ይህ ጽሑፍም የጊዜ ቀጠሮና በዋስትና

# LLB, LLM, በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳኝነት ያገለገለ ሲሆን በእብሁኑ ሰዓት በወሎ ዩኒቨርስቲ በመምህርነት እያገለገለ ይገኛል።
1
Packer, Herbert L., “Two Models of Criminal Procedure,’ University of Pennsylvania Law Review”,
Vol. 113, No. 1, 1964፣ ገጽ 1- 68
2
Sue King et al, The Remand Strategy: Assessing Out Comes, Currenet Issues in Criminal
Justice, vol. 19. No. 3, March 2008, ገጽ 329.

1
መከልከል ምክንያት በቁጥጥር ሥር መቆየት (በማረፊያ ቤት መቆየት) የፅነሰ ሃሳብ መቀላቀልና
የክርክር አመራር ወጥነት አለመኖርን የመብት አጠባበቅ ጉድለት እንዲከሰት ማድረጉን የሚያሳይ ነው፡፡
1. መግቢያ
በወንጀል ፍትህ አስተዳደሩ ውስጥ ተጠርጣሪው በቀደምትነት ከፍትህ አካላቱ ጋር በሚኖረው
የመጀመሪያው ንክኪ (መያዝ) ላይ ከሚነሱት ሥነ ሥርዓታዊ ሒዴቶች ውስጥ በጥበቃ ስር
የመቆየት ግዴታና በዋስትና የመለቀቅ መብት ተጠቃሾች ናቸው፡፡3 በጥበቃ ሥር መሆንንም
ብላክስቶን የተባለ ፀሐፊ እንደሚለው ሰው ከተከሰሰበት ጊዜ ጀምሮ ባለው ሂዴት ውስጥ ግልጽ
ያልሆነ ሂዴት በመሆኑ የተያዘውን ሰው የሰብአዊ መብቱን መጠበቅ አጅግ አስፈላጊ ነው፡፡4
በቁጥጥር ሥር ማዋልም የሚመጣው እርሱ በእርሳቸው የሚወዳደሩ ግቦችን ከዋስትና ሕጉ እና
በቁጥጥር ሥር ማድረግን የሚወሰኑ አካልት ከሚሰሩበት ሁኔታ በመነሳት ነው፡፡5
በጥበቃ ሥር የመሆን ግዴታ እና የዋስትና መብት በዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሰነዶች፣ በሕገ
መንግስት እና በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ውስጥ እንደሁኔታው ተካተው ይገኛሉ፡፡ በዓለም
አቀፍ ደረጃ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ማብቃት በኋላ የሰብአዊ መብት አስፈላጊነትን መሰረት
ያደረጉ ሰነዶች ፀድቀዋል፡፡6 በሰነዶችም ከተረጋገጡት መብቶች አንደኛው መብት የነጻነት
መብት ነው፡፡ በሀገራችን ከሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነው ሕገ መንግስቱ አንቀጽ 17(1) ስለነፃነት
መብት ሲገልፅ “በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ ማንኛውም ሰው ወንድም ሆነ ሴት
ነፃነቱን/ቷን አያጣም/አታጣም” በሚል ተደንግጓል፡፡ እንዲሁም በድንጋጌው ንዑስ 2 ላይ

3
የኢትዮጵያ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ፣ 1954፣ አዋጅ ቁጥር 185፣ ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ፣ 32ኛ ዓመት፣ በልዩ
ሁኔታ የታተመ፣ ቁጥር 1 (ከዚህ በኋላ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ እየተባለ የሚጠራ) የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ
የወንጀል ምርመራ፣ ክስ አመሰራረት፣ ክስ መስማትና ውሳኔ አሰጣጥን የሚያካትት ነው፡፡
4
ብላክስቶን ከክስ በፊት በቁጥጥር ስር መሆኑን አስመለክቶ ሲጽፍ እንደሚለው፡- "[I]mprisonment on remand
is only for safe custody, and not for punishment: therefore, in this dubious interval between the
commitment and trial, a prisoner ought to be used with the utmost humanity; and neither
beloaded with needless fetters, or subject to other hardships than such as areabsolutely requisite
for the purpose of confinement only; though what are so requisite, must too often be left to the
discretion of the gaolers... " ------, The period of Remand and The Treatment of of Prisoners of
Awaiting Trial, Editorial, Aus & NZ Journal of Criminology, Sept 1972, vol 12፣ ገጽ 129- 131.
5
ከላይ የግርጌ ማስታወስያ ቁጥር 2
6
ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ፣ 1948 እ.ኤ.አ፣ በኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን
የታተመ፣ የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳኖች፣ አዲስ አበባ፣ 2004 ዓ.ም፣ አንቀፅ 9 [ከዚህ በኋላ ዓለም
አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ እየተባለ የሚጠራ]; የሲቭልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣
እ.ኤ.አ1966፣ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የታተመ፣ የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳኖች፣ አዲስ
አበባ፣ 2004 ዓ.ም፣ አንቀፅ 9(1) [ከዚህ በኋላ የሲቭልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን እየተባለ
የሚጠራ]; የአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር፣ 1979 እ.ኤ.አ፣ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን
የታተመ፣ የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳኖች፣ አድስ አበባ፣ 2004 ዓ.ም፣ አንቀፅ 7(1)፤ የአውሮፓ
የሰብአዊ መብቶች ቃል ኪዳን፣በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የታተመ፣ የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል
ኪዳኖች፣ አድስ አበባ፣ 2004 ዓ.ም፣ አንቀፅ 5(1).

2
ስለመታሰር ሕጋዊነት ሲገልፅ “ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ ሊያዝ፣ ክስ
ሳይመሰረትበት ወይም ሳይፈረድበት ሊታሰር አይችልም” በሚል የተቀመጠ ነው፡፡7 ከሰነዶች
ጥቅል ንባብም የነፃነት መብት መሰረታዊ መብት በመሆኑ መያዝና በጥበቃ ሥር መሆን በልዩ
ሁኔታና በሕግ በሚደነገግ አግባብ ብቻ ሊገደብ ስለመቻሉ ያሳያል፡፡
የኢትዮጵያ ሕገ መንግስትም የሰብአዊ መብቶችንም ሲተረጎሙም እነዚህን ሰነዶች በማገናዘብ
መሆን እንዳለበት በግልፅ እውቅና ሰጥቷል፡፡8 ኢትዮጵያም እነዚህ የዓለም አቀፍ ሰነዶች ፈራሚ
በመሆኗ የሐገሪቱ ሕግ አካል ተደርገዋል፡፡9 የነፃነት መብትን ለማስፈፀም የተደነገገውን በጥበቃ
ሥር ማቆየት እና የዋስትና መብት የሚሉትን ፅንሰ ሀሳቦችን በማካተት መወሰን የሚያስችል
ይሆናል፡፡10 ከዚህ በተጨማሪም አሁን ተፈፃሚነት ያለው የ1958“ቱ” ወንጀል ሥነ ሥርዓት
ሕግ ውስጥ በቁጥጥር ሥር መሆን እና የዋስትና መብት አቀራረፅ ግልፅ መስፈርትን
ስለመከተሉ የሕግ ማዕቀፉንና የፍርድ ቤቶችን አሰራር መቃኘት የሚገባ ነው፡፡11 የሁለቱ ፅንሰ
ሀሳቦች ሕጋዊ ትርጉም አንደኛው የሌለኛው ግልባጭ በመሆኑ የሕግ ማዕቀፍ መደራረብና
በተግባር ያለውን የችሎት አሰራር ሲቃኝ የግልጽነት መጓደል ይስተዋላል፡፡ የግልፅነት መጓደል
የክርክር አመራሩን የሚያወሳስብና የተጠርጣሪዎችን መብት ሕጋዊ ምላሽ ለመስጠት
የሚያጣብብ አልፎ አልፎም የሰብአዊ መብት ጥሰትም የመፍጠር አጋጣሚ እንዳለ ማስተዋል
ይቻላል፡፡12 በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ በቁጥጥር ሥር መቆየት እና በዋስትና

7
በሕገ መንግስቱ ውስጥ የነጻነት መብትም በዓለም አቀፍ ቃል ኪዳች ተቀራራቢ በሆነ አግባብ ተከቷል፡፡
በተለይም የድንጌው እንግሊዘኛው ቅጂ ይበልጥ ተመሳሳይነት አለው፡፡
8
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት፣ 1987፣አዋጅ ቁጥር 1፣ ፌደራል ነጋሪት
ጋዜጣ፣ 1ኛ ዓመት፣ ቁጥር 1 (ከዚህ በኋላ የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት እየተባለ የሚጠራ) አንቀፅ 13(2)ን
ይመልከቱ፡፡ Adem Kassie, “Human Rights under the Ethiopian Constitution: A Descriptive
Overview”, Mizane Law Review, Vol. 5 No.1 (2011)፣ ገፅ 45-71፡፡ ሕገ መንግስታዊ ትርጉም ለፌደሬሽን
ምክር ቤት የተሰጠ ስልጣን ቢሆንም ፍርድ ቤቶችም የዓለም አቀፍ ሰነዶችንም ከሕግ መንግስት በታች ግን
ከአዋጆች በላይ በማድረግ ማስፈጸም የሚኖርባቸው መሆኑን የሕግ ምሁራን ይገልፃሉ፡፡ ይህ አተረጓጎምም ከሕገ
መንግስቱ በተለየ ሁኔታ ዓለም አቀፍ ሰነዶችን በቀጥታ ለመተርጎም ያስችላቸዋል፡፡ ሆኖም ዓለም አቀፍ ሰነዶች
ከሕግ መንግሰት በታች ናቸው መባሉ ከሀገሪቱ አዋጆችና ሌሎች የበታች ህጎች ጋር እያጣመሩ መወሰን
ያስችላቸዋል፡፡ ሆኖም አደም ካሴ በራሱ እንደሚለው አገሪቱ የሲቭል ሎው ሕግ ሥርዓት ያዘነበለበት ስለሆነ
የውጭ ሕግን አጣቅሶ የመወሰን ልምድ የለም፡፡ በተግባርም የሚታየው ይህ እውነታ ነው፡፡
9
የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 9(4)
10
ዝኒ ከማሁ
11
በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 59 ላይ የጊዜ ቀጠሮና ዋስትና አብረው የሚታዩ ይመስላሉ፡፡ ለጊዜ ቀጠሮ
ክርክር አመራር በቂ ሽፋን አለ ለማለት የሚያስችል ግን አይደለም፡፡
12
ተጠርጣሪው ባልተገባ መልኩ በቁጥጥር ሥር የሚውል ከሆነ ለእርሱ የሚሆነውን ማስረጃ መሰብሰቡ
ስለሚደናቀፍ በአግባቡ ባለመከራከሩ ጥፋተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ አደገኛ የሆነ ተጠርጣሪ ቢለቀቅ ደግሞ የክርክር
ሂዴቱን በተለይም የዓቃቤ ሕግ ማስረጃን እስከማጥፋት ሊደርስ ስለሚችል ፍትህ መዛባቱ የማይቀር ነው፡፡

3
የመለቀቅ ሁኔታ አፈፃፀም በታወቀ የሕግ ማዕቀፍና ተቀራራቢ ትርጉም ካልተመራ ቀጣዩን
የወንጀል ክርክር ምዕራፍ ያልተገባ ጫና ውስጥ ሊያስገባው መቻሉ የማይቀር ነው፡፡13
በወንጀል የተጠረጠረና የተያዘ ሰው በጥበቃ ሥር እንዲቆይ ሊሆን የሚችለው በሁለት
ሁኔታዎች ነው፡፡ የመጀመሪው ፖሊስ ለተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የጊዜ ቀጠሮን ሲጠይቅና
ሲፈቀድለት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የተጠረጠረ ሰው በዋስትና እንዲለቀቅ አቤቱታ ሲያቀርብና
ዋስትና ሲከለከል የሚመጣ ውጤት ነው፡፡ በመሆኑም የጊዜ ቀጠሮና የዋስትና አቤቱታ ቀርቦ
በውጤት ደረጃ በጥበቃ ሥር መቆየትን የሚያስከትሉበት ሁኔታ ስለሚኖር በወንጀል ፍትህ
አስተዳደሩ ውስጥ ሁለቱ ክርክሮች እየተቀላቀሉ የሚቀርቡ ሲሆን በፍርድ ቤትም ሕጋዊ
ትርጉማቸው ላይ ግልጽ አቋም አለመኖሩ ይስተዋላል፡፡ የጊዜ ቀጠሮና የዋስትና ክርክርን
በተመለከተ ከመዝገብ አከፋፋት ጀምሮ እስከ ውሳኔ አሰጣጥ የክርክር አመራር ወጥነት መጓደል
ይታያል፡፡ የወጥነት መጓደሉም የፍትህ ሥርዓቱን ተገማችነት የሚሳጣ እና ተጠርጣሪዎችን
ላልተገባ እንግልት መዳረጉ የማይቀር ነው፡፡
የሠለጠኑት ምዕራባዋያን ሀገራትን ጨምሮ ጥፋተኝነታቸው ሳይወሰን በቁጥጥር ሥር የሚሆኑ
ሰዎች ቁጥር ከጠቅላላው ታራሚ ቁጥር ጋር ሲነፃፀር ድርሻው ቀላል የማይባል በመሆኑ
የጉዳዩን አሳሳቢነት ያመለክታል፡፡14 በጥናት የተለየውም የችግሩ ምንጭም የፖሊሲ፣ የሕግ
ማዕቀፍ፣ ውሳኔ ሰጭ አካላት ግንዛቤና የተጠርጣሪዎች ባህሪ መሆናቸውን የሚስገንዘብ ነው፡፡
የዚህ ፅሁፍ ዓላማም የጊዜ ቀጠሮ እና በዋስትና መብቶችን ከሕግ ሳይነሱ ያላቸው ይዘትና
በኢትዮጵያ ሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ያላቸው ይዘት እና በተግባር በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር
ውስጥ ያለው የክርክር አመራር የሚነሱትን ሀሳቦችን በመነሻነት በማቅረብ በዘርፉ ባለሙያዎች
በኩል በውይይትና ሀሳብን በመሞገት ተቀራራቢ ግንዛቤ ለመፍጠር ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ የፅንሰ
ሀሳቦች መለየት መቻልም በባለጉዳዮች አቤቱታቸውን ለይተው እንዲያቀርቡና የፍትህ
አስተዳደሩም ቀልጣፋ ምላሽ መስጠት ያስችለዋል የሚለውን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

13
Rick Sarre et al, “Remand in Custody: critical factors and key issues, Trrends & Issues in
Criminal Justice”, Australian Institute of Criminology, No.310, May 2006፣ ገጽ 1-6፣ ተጠርጣሪው
በአንድም ሆነ በሌላ ሁኔታ በቁጥጥር ሥር ከዋለ ክሱን የመከላከል እድሉ እየጠበበ መሄዱ የማይቀር ነው፡፡
14
ዝኒ ከማሁ

4
2. በኢትዮጵያ በጥበቃ ሥር መቆየት (ጊዜ ቀጠሮ) እና ዋስትና መብት ፅነሰ ሀሳብና
የሕግ ማዕቀፍ

2.1 በኢትዮጵያ በወንጀል ተጠርጥሮ የመያዝ ሕጋዊ ውጤት


የነፃነት መብት በኢፌዲሪ ሕግ መንግስቱ አንቀጽ 19(4) እና (6) መሰረት በቁጥጥር ሥር
መቆየት እና ዋስትና መከልከል ስለመቻሉ የሚያመለክቱ ድንጋጌዎች ተካተዋል፡፡ በሌሎች
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጎች ውስጥም በወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘ ሰውን ቆይታ ሁኔታ
በሚመለከት የሕግ ሽፋን አለው፡፡15
በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 17(1) ላይ “በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ …” የነፃነት መብት
የማይታጣ መሆኑ ተደንግጓል፡፡ ከዚህ የህግ አቀራረጽ ሥንነሳም ሕግ አውጪው በሚያወጣው
ሕግ መሰረት ብቻ በጥበቃ ሥር መቆየት ይገባዋል የሚለውን የሚያስገነዝበን ነው፡፡ ከዚህ ሕግ
መንግስታዊ አዛዥ ድንጋጌ በመነሳት በ1958 ዓ.ም የወጣው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግና
ሌሎች ሥነ ሥርዓታዊ ይዘት ያላቸው ሕጎች16 ተጠርጣሪው በማረፊያ ቤት (በጥበቃ ስር)
እንዲቆይ ወይም በዋስትና እንዲለቀቅ የሚደረግበትን ሁኔታ እንዲንመርምር ያስገድደናል፡፡
የነፃነት መብትን ለመገደብም አንደኛው ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው በተለምዶ
እንደሚጠራው “የጊዜ ቀጠሮ” እንዲፈቀድለት ሲጠይቅ እና ሁለተኛው ደግሞ የተጠረጠረው
ሰው በዋስትና ለመለቀቅ አቤቱታ ሲያቀርብና ሲከለከል ነው፡፡ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቅ ማለት
ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሲጠይቅ ለፖሊስ ጥያቄ በፍርድ ቤት ዳኛ ተመዝኖ
የሚፈቀድለት ከሆነ ተጠርጣሪን በማረፊያ ቤት እንዲቆይ ለማድረግ የሚያስችለው አንደኛው
ሁኔታ ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀ ማለት ሁልጊዜ ውጤቱ በጥበቃ ሥር
መሆንን የማያስከትልና በዋስትና የመለቀቅ ቀጥተኛ ግልባጭ አድርጎም መውሰድ አሳማኝ
አይሆንም፡፡ ስለሆነም ተጠርጣሪን በማረፊያ ቤት (በጥበቃ ስር) እንዲቆይ ማድረግ ወይም
በዋስትና እንዲለቀቅ ማድረግ በወንጀል ተጠርጥሮ የመያዝ ተከታይ የሕግ ውጤት ነው፡፡
ከሁለቱ አንደኛው ውጤት ሊመጣ የሚችለው ደግሞ ፖሊስና ተጠርጣሪ በሕግ በተዘረጋው

15
የተሻሻለው የጸረ ሙስና የሥነ ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ፣ 1997፣ አዋጅ ቁጥር 434፣ ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ፣ 11ኛ
ዓመት፣ ቁጥር 19 (ከዚህ በኋላ የጸረ ሙስና አዋጅ ቁጥር 434/97 እየተባለ የሚጠራ) እና ስለፀረ ሽብርተኝነት የወጣ
አዋጅ፣ 2001፣ አዋጅ ቁጥር 652፣ ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ፣ 15ኛ ዓመት፣ ቁጥር 57 (ከዚህ በኋላ የፀረ ሽብርተኝነት
አዋጅ ቁጥር 652/2001 እየተባለ የሚጠራ)
16
በመቀጠልም የተያዘ ሰው የተያዘበት ሁኔታ ሕጋዊ መሆኑ ከተረጋገጠም በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር
59(1) መሰረት ተጠርጣሪው በማረፊያ ቤት (በጥበቃ ስር) እንዲቆይ ማድረግ ወይም ዋስትና በመፍቀድ ክርክሩ
እልባት እንዲያገኝ የሚደረግበት ሥርዓት ተዘርግቷል፡፡

5
አግባብ አቤቱታ ሲያቀርቡና ግራ ቀኙ ክርክር አቀርበው የዳኛ ውሳኔ ሲያገኝ መሆን
ይኖርበታል፡፡
የፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ አቤቱታ የሚመራው በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ
ቁጥር 59(2) እና (3) መሰረት ነው፡፡ የዋስትና አቤቱታ ልፈታ ክርክር ደግሞ በወንጀል ሥነ
ሥርዓት ሕግ ቁጥር 64 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት የሚመራ ነው፡፡17 ቀጥለን
ተጠርጣሪው በማረፊያ ቤት (በጥበቃ ስር) እንዲቆይ ማድረግ እና በዋስትና የመለቀቅ መብት
የሚመራባቸውን የሕግ ማዕቀፍ ዘርዘር ባለ መልኩ የምንመለከታቸው ይሆናል፡፡

2.2 በጥበቃ ሥር መቆየት ፅንሰ ሀሳብ የሕግ መሰረቱ


በጥበቃ ሥር መቆየት የሚለው ፅነሰ ሀሳብ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶ በቅጣት መልክ
ከመሰጠቱ በፊት የነፃነት መብት የሚገደብበት ሁኔታን የሚያስከትል ሕጋዊ አሰራር ነው፡፡
ንፁህ ሆኖ መገመት የሚለውን ሕገ መንግስታዊ መርህን የሚያጣብብ የህግ ማዕቀፍ ነው፡፡18
ሆኖም የነፃነት መብትን መገደብ የሚያስፈልገውም የማሕበረሰቡን ጥቅም ከተጠርጣሪው መብት
ጋር በማነፃፀር ሚዛን የሚደፋ ሲሆን ነው፡፡ በዚህም የጥቅም ግጭትንም ለማስታረቅ በሕገ
መንግስቱ፣ በዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን ሰነዶችና ሌሎች የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጎች ውስጥ
በቁጥጥር ሥር መሆንን አስመለክቶ የሕግ ማዕቀፍ የሚቀረፅ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡

2.2.1 በጥበቃ ሥር የመቆየት መነሻ ፅነሰ ሃሳብና ወሰኑ


በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሰነዶች ላይ የነፃነት መብትን ለማስከበር ሰው በወንጀል
ተጠርጥሮ ሲያዝ በዋስትና መፈታት በመብት ደረጃ ተቀምጧል፡፡19 ሆኖም መብቶች ሁልጊዜ
ያለገደብ የተቀመጡ ባለመሆናቸው አስቀድሞ በታወቀ ሕግ ገደብ ሊጣልባቸው ስለመቻሉ
አመላካች ድንጋጌዎች አሉ፡፡ በእነዚህ ሰነዶች ይዘትም ላይ በወንጀል ተጠርጥሮ መያዝን
የሚመለከት አንድ ወጥ መመሪያ ባይኖርም ጭራሹን መርህ አልባ ነው ማለት አይቻልም፡፡20
በሌሎች የወንጀል ፍትህ አስተዳደሮችና ሕገ ሳይንስ ውስጥ በወንጀል መፈጸም መጠርጠር
ምክንያት የተያዘ ሰው ክስ ከመቅረቡ በፊትም በተጠረጠረበት ወንጀል ምክንያት በማቆያ ቦታ

17
በሌሎች ልዩ ሕጎችም (ጸረ ሙስና አዋጅ ቁጥር 434/97 እና ጸረ ሽብር ሕግ 652/2001) በማረፊያ ቤት
የሚቀርብበትንና መስፈርቱ የሚጠቀሱ ቢሆንም መሰረተ ሀሳቡ ግን ይህ ድንጋጌ መሆን አለበት፡፡
18
ንፁህ ሆኖ መገመት የሚለው የሕግ ግምት መነሻው በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ያልተባለ ሰው እንደማንኛውም ንፁህ
ሰው ስለሚገመት ያለበቂ ምክነያትና አስፈላጊነት የነፃነት መብቱ ሊገደብ አይገባም የሚለውን የሚመለከት ነው፡፡
19
ከላይ የግርጌ ማስታወስያ ቁጥር 6
20
Human Rights and Pre-trial Detention, A Hand Book of International Standards relating to
Pretrial Detention, Centre For Human Rights Geneva, United Nations, New York and Geneva,
1994፣ ገጽ 1- 50

6
ነፃነቱ ተገድቦ ሊቆይ የሚችልበትን ሁኔታ “በጥበቃ ሥር መቆየት” ወይም “Remand In
Custody”21 በሚል ፅንሰ ሀሳብ ይገልፁታል፡፡ በጥበቃ ሥር መቆየት የሚለውን ትርጉም ከሕገ
ሳይንሱ አንጻር መነሻ መያዝ ያስፈልጋል፡፡ “Remand In Custody” የሚለውን የእንግሊዘኛ
አገላለፅ በአንድ ላይ ትርጉም የተሰጠበትን ባናገኝም የቃላቱን ተናጠላዊ ትርጉም በመገጣጠም
የሀረጉን ጥቅል ይዘት በማየት ግንዛቤ ሊወሰድበት ይችላል፡፡
ብላክስ ሎው የህግ መዝገበ ቃላትም በሰጠው ትርጉም፡- “Custody- The care and control
of a thing or person for inspection, preservation, or security”22 በሚል ይገልፀዋል፡፡
ይህም ወደ አማርኛ ሲመለስ “ጥበቃ- አንድን ነገር ወይም ሰው ለምርመራ፣ ጠብቆ ለማቆየት
ወይም ለፀጥታ ሲባል መንከባከብ ወይም መቆጣጠር” የሚል ነው፡፡ በተጨማሪም በዚሁ
መዝገበ ቃላት ላይ “Remand- To recommit (an accused person) to custody after a
preliminary examination <the magistrate, after denying bail, remanded the
defendant to custody>” የሚል ነው፡፡ የዚህ አማርኛ አቻ ትርጉም “መመለስ- የተከሰሰን
ሰው ከጠየቁ በኋላ ለጥበቃ መመለስ ነው፡፡ ዳኛ ዋስትና ከከለከለ በኋላ ተከሳሽን በጥበቃ ሥር
እንዲሆን የሚመልስበት ሁኔታ ነው” የሚለውን ትርጉም የሚሰጥ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ስለሆነም
የሁለቱ ቃላት ቅንጅታዊ ትርጉም የሚያሳያን በጥቅሉ የተጠረጠረን ሰው በጥበቃ ስር እንዲቆይ
የሚደረግበትን አሰራር የሚያሳዩና ተቀራራቢ ትርጉም የተሰጠበት ነው፡፡23
በቁጥጥር ሥር መቆየት የሚለው ፅንሰ ሃሳብ ክርክር ሲጀመር ብቻ ሳይሆን ክርክሩ
እስከሚጠናቀቅ ድረስ ባለው ደረጃ ሊነሳ የሚችል የዋስትና መብት ግልባጭ ግዴታ ነው፡፡
በቁጥጥር ሥር የማዋልን ትርጉም በተመለከተ ጆን ሀዋርድ የኦንታሪኦ ማህበረሰብ ሕትመት
እንደሚለው፡-
Those on “remand” are individuals who are being held in custody while awaiting a
further court appearance. While a relatively small percentage have been tried and found

21
በሕግ መዝገበ ቃላት “Remand In Custody” የአማርኛ አቻ ትርጉሙ “ለጥበቃ መመለስ” የሚል ይዘት ያለው
መሆኑን ያሳያል፡፡ Remand In Custody, Remand or Custodial Remand የሚሉ አገላለፆችን እናገኛለን፡፡
ይህም በሀገር ውስጥ ሕግ ውስጥ የጊዜ ቀጠሮ ከሚለው ጋር የሚቀረራብ ነው፡፡ ይህም ዋስትና የተከለከለ ሰውም
እስራቱ ጊዜዊ መሆኑና የፍርድ ቤት ቁጥጥር የሚያስፈለገው መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
22
Black Law’s Dictionary, 9th Ed., 2009, s.v. “Remand in Custody”
23
ይህ ጉዳይ በተቀራራቢ ሁኔታም በሌላ መዝገበ ቃላት ትርጉም ተሰጥቶታል፡፡ Oran’s Dictionary of the
Law, 3rd Ed., 2000, s.v. “Remand”፣ መመለስን ሲተረጉም፡- “Remand- Send back. For example, a
higher court may remand (send back) a case to a lower court, directing the lower court to take
some action. Also, a prisoner is remanded to custody when sent back to jail after failing to
meet, or being denied release on, bail.” ከዚህ ትርጓሜም በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 341
መሰረት መዝገብ መመልስ ከሚለው ጋር በሚቀራረብ መልኩ ትርጉም ያለው መሆኑን ያሳያል፡፡

7
guilty and are awaiting sentencing, the majority are awaiting trial. Some may be
awaiting a decision with respect to bail, others have been denied bail and, unless
released through judicial review, will remain in custody until their trial.24
ይህ አገላለፅ ወደ አቻ የአማርኛ ትርጉም ሲመለስ፡-
ለጥበቃ የተመለሱ ሰዎች የሚባሉት በቁጥጥር ሥር ያሉና በቀጣይ ፍርድ ቤት ለመቅረብ
የሚጠባበቁ ሰዎች ማለት ነው፡፡ ጥቂት ቁጥር ያላቸው ሰዎች ጥፋተኛ ተብለው ቅጣት
የሚጠባበቁ ሲሆን አብዛኞቹ ግን ክስ መስማትን የሚጠባበቁ ናቸው፡፡ አንዳንዶችም ዋስትናን
በሚመለከት ውሳኔ የሚጠብቁ እና ሌሎች ደግሞ ዋስትና የተከለከሉ ሲሆን በፍርድ ቤት ክለሳ
ውሳኔ ካልተለቀቁ ክርክሩ እስከሚቋጭ ድረስ በጥበቃ ስር እንዲቆዩ ይደረጋል፡፡25
ከዚህ አገላለፅም በጥበቃ ሥር መቆየት የሚለው ፅንሰ ሀሳብ ተጠርጣሪው ከተያዘበት ጊዜ
ጀምሮ የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ የሚቀጥል መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ የጥፋተኝነት
ውሳኔ ከተሰጠም በኋላ ተጠርጣሪው በቅጣት መልኩ እንዲታሰር ካልተወሰነ በስተቀር ቀጣይነት
ያለው ጉዳይ መሆኑን ያመለክታል፡፡
በቁጥጥር ሥር መሆን የሚለው ፅነሰ ሀሳብ እነ-ሱ ኪንግ እንደሚገልፁት የጊዜ ቀጠሮ እና
የዋስትና ጉዳይ ሊነሳ የሚችለው ተጠርጣሪው ክርክር በሚመራበት ጊዜ በሶስት እርከኖች ላይ
ነው፡፡26 በመጀመሪያ ምርመራውን የሚያጣራው ፖሊስ የሚጣራውን ወንጀል ምን እንደሆነ
መወሰኑና ተጠርጣውን በቁጥጥር ሥር ማዋል ማስፈለጉን መምረጡ ላይ ይመሰረታል፡፡
ተጠርጣሪውን በመጥሪያ የሚጠራ ከሆነ ወይም እንዲመጣ በመንገርና ተመሳሳይ ሁኔታዎች
ምርመራው ከቀጠለ እና ተጠርጣሪው ካልተያዘ በስተቀር በቁጥጥር ስር መሆን እንዲሁም
የዋስትና ጉዳይ ጥያቄ የሚሆንበት አጋጣሚ አይኖርም፡፡ ሁለተኛው ፖሊስ ዋስትና በራሱ
ሊፈቅድ ወይም ሊከለክል የሚችልበት ደረጃ ነው፡፡ ፖሊስ ዋስትና የሚከልክል ከሆነም
በመከልከሉ ላይ ለፍርድ ቤት ይግባኝ የሚቀርብበት ሥርዓት አለ ማለት ነው፡፡ በሶስተኛ
ደረጃም በፍርድ ቤት የተጠረጠረን ሰው በቁጥጥር ስር የመዋል ያለመዋል ጉዳይ በመጨረሻ
የሚወሰንበት ሂዴት ነው፡፡ ፖሊስ አስቀድሞ ዋስትና የፈቀደለት ተጠርጣሪና ወይም በፍርድ
ቤት ክርክር ጊዜ ተቃውሞ ያልቀረበባት ተጠርጣን ፍርድ ቤት ውሳኔ ሲሰጥ አስቀድሞ ምላሽ

24
ከላይ የግርጌ ማስታወስያ ቁጥር 2 እና Remand in Ontario, “A Backgrounder, John Howard Society
of Ontario”, September 2005፣ ገጽ 1-4
25
ትርጉም የራሴ ነው፡፡
26
ከላይ የግርጌ ማስታወስያ ቁጥር 2፣ ገጽ 329. Key decisions about remand or bail are made at
three different points in the processes through which a defenedant’s case is progressed. These
are: The Apprehension Phase, The Police Bail Phase and The Court Bail Phase.

8
ያገኘ ጉዳይ ነው ማለት ይቻላል፡፡27 በተጨማሪም በቁጥጥር ስር መሆን ከሚታሰረው ሰው
ቁጥር ያለው ንፅፅራዊ ብዛትም አሳሳቢ እንደሆነ ፅሑፎች ያመለክታሉ፡፡28 ለምሳሌም በካናዳና
በአውስትራሊያ አንዳንድ ግዛቶች ላይ ጥናት ሲደረግ ከፍርድ በፊት በቁጥጥር ስር የሚሆኑ
ሰዎች ከጠቅላላው እስረኛ መጠን አንፃር እስከ 60% የሚደርስ ብዛት እንዳለ በጥናት
ተረጋግጧል፡፡29
በመሆኑም በሌላው የፍትህ አስተዳደር ውስጥ በቁጥጥር ስር መሆን በኢትዮጵያ ጊዜ ቀጠሮ
ተብሎ የሚታወቀውን የሚያካትት እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ ሆኖም በቁጥጥር ሥር መሆን
ከጊዜ ቀጠሮ ከሚለው ጽንሰ ሀሳብ የሰፋ ማዕቀፍ ያለው መሆኑን የሚያልክት ነው፡፡
እንደሌሎች ሀገራትም በኢትዮጵያም ከፍርድ ቤት ጥፋተኛ ሳይባሉ የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥርና
የአያያዝ ሁኔታ አሳሳቢነቱን በአሁን ወቅት በሀገሪቱ ሚዲያዎች የሚተላለፉ ፕሮግራሞችን
ማየቱ በቂ ነው፡፡

2.2.2 በወንጀል ተጠርጥሮ በጥበቃ ሥር መቆየት (ጊዜ ቀጠሮ) በኢትዮጵያ ሕገ


መንግስት
በሕገ መንግስቱም አንቀፅ 19(4) በቁጥጥር ስር የመሆንን ፅንሰ ሀሳብ ሲያካትት “… ፍትህ
እንዳይጓደል ሁኔታው የሚጠይቅ ከሆነ ፍርድ ቤቱ የተያዘው ሰው በጥበቃ ስር እንዲቆይ
ወይም ምርመራውን ለማከናወን አስፈላጊ በሆነ መጠን ብቻ ሊፈቀድ ይችላል”30 በሚል
የተደነገገውን እናገኛለን፡፡ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር ማድረግን ፍርድ ቤት ሲወስን
የማሕበረሰቡን ደህንነት በመጠበቅ እና የግለሰቡን የነፃነት መብት በማክበር መካከል ያለውን
ተወዳደሪ ግብን ማሳካትን ታሳቢ ማድረግን የሚያመለክት ነው፡፡31 የድንጋጌው ይዘትም ፍርድ
ቤት በቁጥጥር ሥር የማድረግ ውሳኔን የሚያስተላልፍ አካል መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን
ምርመራውን የሚያካናውኑት አካላት ተጨማሪ ጊዜ በመጠየቅና በፍጥነት የምርመራ ሥራውን
በማከናወን ረገድ ሚና ያላቸው መሆኑን ያሳያል፡፡
በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 19(4) ላይ ያሉ ፅንሰ ሀሳቦችን ዘርዘር ባለ መልኩ መመልከት ይገባል፡፡
በቀዳሚነትም የተያዘ ሰው “በጥበቃ ሥር እንዲቆይ… ሊፈቀድ ይችላል” የሚለውን ፅነሰ ሀሳብ

27
ዝኒ ከማሁ
28
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 2፣ ገፅ 2፡፡ አውስተራሊያ፣ እንደሊዝና ሌሎች ሀገራት የቅድመ ክስ ታሳሪዎች
ቁጥር ከፍተኛ እየሆነ በመሄዱ የፖሊሲ ጉዳይ እደረጉት ይገኛል፡፡
29
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 24
30
የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት፣ አንቀፅ 19(3)(ሰርዝ የተጨመረ)
31
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 2፣ ገፅ 329-30

9
የሚመለከት ነው፡፡32 የተያዘ ሰው ፍርድ ቤት ሲቀርብም በራሱ በሕገ መንግስቱ በጥበቃ ሥር
እንዲቆይ ሊደረግ ስለመቻሉ የሚያሳይ ነው፡፡ የተጠረጠረ ሰው በጥበቃ ሥር እንዲሆን
ማድረግም ሕገ መንግስቱ የወንጀል ቁጥጥር መር ሞደልን መምረጡን ያመለክታል፡33
ፖሊስ ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዜጎችን ያለአግባብ በመያዝ የሰብዓዊ መብት ጥሰት
ተግባር እንዳይፈጽም ለመከላከል ሐገራት በህግ ከሚያደርጉት ጥበቃ አንዱ በህገ መንግስት
መሰረት የተያዘ ሰው ፍርድ ቤት በህግ በተቀመጠው አጭር የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲቀርብ
ማድረግና የመያዙን ሕጋዊነት ማረጋገጥ ነው፡፡34 በሀገራችንም የተያዘ ሰው በ48 ሰዓት ውስጥ
ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ማድረግ በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 19(3) ከሰብአዊ መብቶች አንደኛው
ሆኖ እውቅና እንዲሰጠው ሆኗል፡፡35
ተጠርጣሪው ከተያዘ በኋላ ፍርድ ቤት ወዲያውኑ እንዲቀርብ የሚያስፈልገው የእስሩን
ህጋዊነት ለማረጋገጥ ነው፡፡36 ተጠርጣሪው እንደቀረበ ፍርድ ቤቱ ማንነቱን አረጋግጦ ከመዘገበ
በኋላ ተጠርጣሪው በምን ዓይነት ወንጀል ተጠርጥሮ እንደተያዘ ለተጠርጣሪው ሊገለፅለት
ይገባል፡፡ የወንጀሉን ዓይነት ከመግለፅም ያለፈ በተጠረጠረበት ወንጀል ለመታሰር የሚያበቃ
ምክንያት ያለ መሆኑንም ፍርድ ቤቱ የማረጋገጥ ግዴታ ያለበት መሆኑን ያሳያል፡፡ ለመታሰር
የሚያበቃ ምክንያት የለም የሚባል ቢሆን ተጠርጣሪውን በጥበቃ ሥር ለማቆየት የሚያችል
ሁኔታ የለም በሚል ቢያንስ በዋስ መፍታት ተገቢነት ያለው ይመስላል፡፡37 ለዚህም በአንቀጽ
19(4) ላይ የፖሊስ መኮንን ወይም ሕግ አስከባሪው የያዘበትን ምክንያት ቀርቦ ማስረዳት
ያለበት መሆኑን ግዴታ ጥሏል፡፡ በእርግጥ ተጠርጣሪውን በሕግ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ
ሳይቀርብ ከቀረ ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪው ሲያመለክት የተጠርጣሪውን የአካል ነፃነት

32
በንዑስ ድንጋጌው የእንግሊዘኛ ትርጉም ላይ “.. to remain in custody… remand…” የሚሉ ቃላትን
ይጠቀማል፡፡
33
Simeneh Kiros Assefa, “THE PRINCIPLE OF THE PRESUMPTION OF INNOCENCE AND ITS CHALLENGES
IN THE ETHIOPIAN CRIMINAL PROCESS”, Mizane Law Review, Vol 6, No. 2, 2012፣ ገፅ 277-280
የተጠርጣሪውን መብት የሚያጣብብ ቢሆንም ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ሊደረግ የሚችል ነው፡፡
34
አካልን ነጻ የማውጣት መብት (Habeas corpus ) የሚባለው የመንግስት ባለሥልጣናትን በሕገ ወጥ መንገድ
ሰውን በመያዝ ለፍርድ ቤት ሳያቀርቡ ሲቀሩ አቤቱታ የሚቀርብበት ነው፡፡ ይህም በወንጀል ጉዳይ የተያዘም ሰው
አቤቱታው እና ክርክሩ የፍትሐብራዊ መፍትሔ የሚሰጠው ነው፡፡ ይህንንም የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት
ሕጉና አዋጅ ቁጥር 223/2007 አካተውታል፡፡ የተሻሻለው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍርድ ቤቶች
ማቋቋሚያ አዋጅ፣ 2007፣ ዝክረ ሕግ ጋዜጣ፣ አዋጅ ቁጥር 223፣ 20ኛ ዓመት፣ ቁጥር 4 የሆነውን ይመልከቱ፡፡
ይህም ለታሰሩ ሰዎች በልዩ ሁኔታ የሚፈቀድ መብት መሆኑን ያሳያናል፡፡ በዚህ ጽሁፍ ላይ ይህን በተመለከተ
ብዙም ትኩረት ማድረግ አልተቻለም፡፡
35
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 1 ይመልከቱ፡፡ ይህ መብትም በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 29(1)
መሰረት በወንጀል ተጠርጥረው ለተያዙ ሰዎች የተረጋገጠ መብት ነው፡፡
36
የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 19(3)
37
Wondwossen Demissie, “The Right to Bail in Ethiopia: Respective Roles of the Court and the
Legislatures”, Journal of Ethiopian Law, Vol. 23, No.2, 2009፣ ገፅ 21-37

10
እንደከበርለት ለፍትሐብሔር ችሎት የማቅረብ መብት አለው፡፡38 የ48 ሰዓት ፍርድ ቤት
የማቅረቢያ ጊዜ ከታለፈ ተጠርጣሪው የመለቀቅ መብት ሊኖረው ይችላል፡፡ ሆኖም ተጠርጣሪው
ከባድ ወንጀል ሰርቶ ቢሆን ያለቀረበው ሕግ አስከባሪ ላይ የሕገ መንግስት ድንጋጌ በመጣሱ
አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ የሚገባ ሊሆን ይችላል፡፡ በተባለው ጊዜና በኋላ ግን
ተጠርጣሪው የተያዘበትን እንኳ የሚያስረዳ ከሌለ ተጠርጣሪውን መልቀቅ ዳኞች የዜጎችን ሕገ
መንግስታዊ የማክበርና የማስከበር ግዴታ ያላባቸው በመሆኑ ደፍረው ማዘዝ ይኖርበቸዋል፡፡
በሕገ መንግስቱ በጥበቃ ሥር እንዲቆይ ለመወሰን የተያዘው ሰው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ
ሲጠየቅበት ወይስ የዋስትና መብት ተጠይቆ ሲከልከል መሆኑ ላይ የግልፅነት ጉድለት አለ፡፡
ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መጠየቅ (ጊዜ ቀጠሮ) የሚለው በቁጥጥር ሥር ማድረግ ከሚለው
የተለየው “ወይም” በሚል አያያዥ ቃል በመሆኑ በአማራጭነት የተቀመጠ እና ከተጨማረ ጊዜ
መጠየቅ የተለየና ራሱን የቻለ ፅነሰ ሀሳብ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ የዋስትና መብት ደግሞ
በአንቀፅ 19(6) ላይ የተቀመጠ ነው፡፡ ከድንጋጌው ጥቅል ይዘት አንጻር ሲታይ በጥበቃ ሥር
ማቆየት የሚለው ተጠርጣሪውን አስመልክቶ ለጊዜው የሚያስረዳ አካል ባይቀርብም እንኳ
ፍርድ ቤቱ የተያዘውን ሰው ወዲውኑ መልቀቁ ፍትህ ይጓደላል ብሎ ከገመተ ሥልጣን ያለው
የፖሊስ መኮነን ወይም ሕግ አስከባሪ አስተያየት የሚሰጠበትን ሁኔታ ለመጠየቅ ዓላማ ለውስን
ቀናት ወይም ሰዓታት ተጠርጣሪን በጥበቃ ስር ማቆየት የሚቻልበትን ልዩ ሁኔታ የሚገልጽ
ነው በሚል መውሰድ ይቻላል፡፡ ይህ ግን በጠባቡ መተርጎም ያለበት መሆኑን ለተጨማሪ
የምርመራ ጊዜ 14 ቀን ገደብ መኖሩና ክስም በ15 ቀን መቅረብ ያለበት መሆኑ ታሳቢ ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡39 ከዚህ በተጨማሪም በተምዶ እንደሚታወቀው የተያዘ ሰው በጥበቃ ሥር እንቆይ
ማድረግ ዋስትናን በመንፈግ ወይም ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ በፍርድ ቤት ውሳኔ
የነፃነት ገደብ እንደሆነ መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡
ሁለተኛው ፅንሰ ሃሳብ ደግሞ የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 19(4) ላይ ፍርድ ቤት “… ምርመራ
ለማካሄድ ተጨማሪ ጊዜ ሲጠይቅ አስፈላጊ በሆነ መጠን ብቻ ሊፈቅድ ይችላል” በሚል
የተደነገገውን ፅነሰ ሀሳብ ይዘቱን መመልከት ተገቢ ነው፡፡ በዚህ ንዑስ አንቀፅ የተጨማሪ
ምርመራ ጊዜ የሚለው ፅንሰ ሀሳብ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 59(2) እና (3)

38
የፌደራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ፣ 1988፣ አዋጅ ቁጥር 25፣ ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ፣ 2ኛ ዓመት፣
ቁጥር 15 (ከዚህ በኃላ አዋጅ ቁጥር 25/88 እየተባለ የሚጠራ)
39
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀፅ 59(3) እና 109፤ ለምሳሌ ተጠርጣው በራሱ በሰው ግዲያ ተጠርጥሮ
መያዙን ቢገልፅና ግን ለጊዜው ቀርቦ የሚያስረዳ ያሰረው አካል ባይገኝ ተጠርጣውን መልቀቅ ለሕብረተሰቡ ጥቅም
እአስፈላጊ ከመሆኑ በተጨማሪም ተጠርጣሪውንም ሊደርስበት ከሚችል አደጋ መጠበቅ ይሆናል፡፡

11
መሰረት በተለምዶ የጊዜ ቀጠሮ ከሚለው ጋር የሚጣጣምና አሰራሩ ሕገ መንግስታዊ መሰረት
ያለው መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ሆኖም በሌሎች የወንጀል ፍትህ አስተዳደሮች ውስጥ
ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለማከናወን የተያዘ ሰውን በቁጥጥር ሥር ማድረግን የሚያመለክት
ሽፋን ያላቸውን ብዙም አይስተዋሉም፡፡ በሌላ መልኩ የተያዘው ሰው የዋስትና አቤቱታ
ሲያቀርብ በማስረጃ አሰባሰቡ ላይ ጣልቃ የሚገባ ከሆነ ራሱን ችሎ ዋስትና ሊያስከለክለው
የሚያችልና በቁጥጥር ሥር እንዲሆን ሊያደረገው ስለመቻሉ የሚያሳዩ ናቸው፡፡40
ይህ እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በፍርድ ቤት የጊዜው ሁኔታ ቁጥጥር እየተደረገበት
ለመርማሪ መፈቀዱ ለወንጀል መርማሪም ሆነ ለተያዘው ሰው የየራሱ ጥቅም አለው፡፡
በመጀመሪያ የወንጀል ምርመራ የሚያደረግ አካል ለምርመራ እየተባለ የሚሰጠው ጊዜ በሕግ
ክስ ለማቅረብ የሚሰጠው ጊዜ እንዳያጥርበት እና ለምርመራ የሚሰጠውን የጊዜ ገደብ ራሱን
ችሎ ለማስላት የሚያስችልና ክስ ለመመስረት አላስፈላጊ መጣደፍ እንዳይኖር የሚያስችል
ይሆናል፡፡41 ሁለተኛው ጥቅም የተያዘው ሰው የዋስትና አቤቱታ ሲያቀርብ ማስረጃ ያጠፋል
ወይም በምርመራ ሥራው ጣልቃ ይገባል ለውስን ጊዜ ብቻ መታሰሩ በንፅፅር ዋስትና ጠይቆ
ቢከልከል ክስ እስከሚቀርብ ድርስ ለተራዘመ ጊዜ በጥበቃ ሥር እንዳይቆይ የማድረግ ሁኔታን
የሚያስቀር ይሆናል፡፡42
ሌላው የተያዘ ሰውን በጥበቃ ሥር ለማድረግ በሕገ መንግስቱ የተቀመጠው መስፈርት “ፍትህ
እንዳይጓደል ሁኔታው የሚጠይቅ ከሆነ” በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ብቻ በጥበቃ ሥር እንዲቆይ
ሊወስን ስለመቻሉ ተድንግጓል፡፡ በተለይም “ፍትህ እንዳይጓደል” የሚለው አገላለፅ የማህበረሰቡን
የደህንነት መብትና የግለሰቡን የነፃነት መብት በማስታረቅ ረገድ በቁጥጥር ሥር እንዲሆን
የሚወሰነው አካል ግምት ውስጥ ማስገባት ያለበት መሆኑን አስረጅ ነው፡፡ መስፈርቱ “ሆኖም
ፍትህ እንዳይጓደል ሁኔታው የሚጠይቅ ከሆነ…” የሚለው የተጠረጠረው ሰው የግድ በጥበቃ
ሥር ሆኖ ምርመራ ካልተከናወነ ምርመራውን ማድረግ የማይቻል መሆኑን ፍርድ ቤት በልዩ
ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ያለበት መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ የፖሊስ ምርመራ
ሲደረግ ተጠርጣሪው ከሕግ ቁጥጥር ውጭ ቢሆን ለምሳሌ ምስክር ማባበል ወይም ካለው
ኃላፊነትና አጋጣሚ ምክንያት ማስረጃ ሊሆን የሚችልን ነገር ሊሰውር ወይም ሊያበላሽ ይችላል

40
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 2 እና 13
የአሜሪካ እና አውስተራሊያ የወንጀል ፍትህ አስተዳደሮ ይህንን ጉዳይ የሚያሳዩ ናቸው፡፡
41
በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 109 መሰረት የምራመራ ጊዜ ካልተፈቀደ ፐሊስ የምርመራ ውጤን
ውዲያው ለዐቃቤ ሕግ አስተላልፎ በ15 ቀን ጊዜ ውስጥ ክስ እንዲቀርብ ሕግ ያስገድዳል፡፡
42
በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 109

12
የሚያሰኝ ሲሆን ነው፡፡43 ፍትህ እንዳጓደል የሚለው መስፈርት በአንዳንድ የፍትህ አስተዳደሮች
ውስጥ ለተያዘው ሰው ደህንነትም ጭምር ሲባል ሊደረግ ስለመቻሉ ያመለክታሉ፡፡44 ተመሳሳይ
ሀሳብም የደቡብ አፍሪካ ሕገ መንግስት ውስጥ የተካተተ መሆኑን እናገኛለን፡፡45
ተጨማሪ የምርመራ ጊዜም በፖሊስ መኮንን ሲጠየቅ አስፈላጊነቱን መፍቀድ ያለበትና
የቆይታውን ጊዜ መወሰን ያለበት የፍርድ ቤት ሥልጣን መሆኑን ያሳያል፡፡ ሕግ አውጪውም
የጊዜ ቀጠሮ የሚሰጥበትን ጣሪያ ማስቀመጡ የሕግ አስከባሪዎች በፍጥነት እንዲሰሩ የሚያተጋ
ሲሆን በፀረ- ሽብርተኝት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 20(3) ላይ ዝቅተኛ የጊዜ ቀጠሮ ጊዜ
28 ቀን መሆኑ የሕገ መንግስታዊነት ጥያቄ ሊያነሳ ይችላል፡፡ የጊዜ ማስፈላግ ወይም
አለማስፈለጉና የጊዜው መጠን ከፍትህ መጓደል ጋር እየተገናዘበ በፍርድ ቤት የሚወሰን እንጅ
በሕግ አውጭ አስቀድሞ መደንገጉ እንደፀሃፊው ግንዛቤም ተገቢ አይመስልም፡፡ ለዚህ ችግሩም
ፖሊስ ራሱ ምርመራውን ጨርሻለሁ እያለ 28 ቀን መሙላት አለበት በሚል የተያዘውን ሰው
ለዚሁ ቀን ያክል በቁጥጥር ሥር ማቆየቱ ምክንያታዊነት ይጎደልዋል፡፡ ይልቁንም ትርጉም
መሰጠት ያለበት ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የመስጠት ወይም ያለመስጠት ሥልጣን
ያለው ፍርድ ቤት የህግ መንግስት ድንጋጌውን በመጥቀስ ለምርመራ የሚሰጠውን ጊዜ ማሳጠር
ይችላል ወይ የተሰጠውን ጊዜ አዲስ ነገር ሲገኝ በማቋረጥ ወደ ቀጣዩ የክርክር ደረጃ መግባት
ይችላል የሚለውን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡
ከሕገ መንግስቱ የአንቀጽ 19(4) አገላለፅ ተጨማሪ ጊዜ የመጠየቅን ሙሉ ክርክር የሚሳይ
አይደለም፡፡ ሆኖም በድንጋጌው የማይቀረው ነገር ፍርድ ቤት ምክንያቱን ከፖሊስ በበቂ ሁኔታ
ማጣራት አለበት፡፡ የተጠርጣሪውም ሐሳብም መሰማት አለበት፡፡ ግራ ቀኙ የሚያቀርቡትንም
ሃሳብ መሰረት በማድረግ ችሎቱ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ጊዜው ለመወሰን አመላካች
(prima facia) ማስረጃ ሊመለከት ይገባዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ተጨማሪ ጊዜ ከመስጠቱ በፊት
የተጀመረ የፖሊስ ምርመራ ጊዜ ካለ የደረሰበትን ደረጃ ለማወቅ፣ የቀረውን ምርመራ
ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገውን ጊዜ ለመገመት እንዲሁም የጊዜ መሰጠቱን አስፈላጊነት
ለማረጋገጥ ፖሊሱን ማብራሪያ በመጠየቅና የፖሊስ ምርመራ መዝገብን በመመልከት ማጣራት
ይጠበቅበታል፡፡

43
ከዚህ ውጭ ግን ፖሊስን ሊያስፈራራ ይችላል ወይም ለወደፊቱ ሊገኝ አይችልም የሚለውን ሀሳብ የመሳሰሉ
በዚህ መካተት የለባቸውም፡፡
44
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 13፣ ገጽ 333፤ ደቡብ አውስተራሊያ ክፍለ ሀገር የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ
ለተከሳሹ ጥቅም ሲባል ዋስትና ሊሰጥ የሚችልና ከዚህ ባለፈም ሕክምናዊ ይዘትም ያለው ትዕዛዛ ሊሰጥ ስለመቻሉ
መረዳት ይቻላል፡፡
45
Jerome Chaskalson and Ynze De Jong, Crimininal (In)Justice in South Africa, ገጽ 86-95

13
በሕገ መንግስቱ መሰረት በጥበቃ ሥር መቆየት የሚለው አረዳድ የተጠርጣሪውን አያያዝና
ቆይታ በመርማሪው እጅ እንዲሆን ማድረግን ታሳቢ የሚያደረግ ይመስላል፡፡46 ሆኖም
ተጠርጣሪን ለረጅም ጊዜ በመርማሪ ቁጥጥር ሥር እንዲቆይ ማድረግ ያልተገባ ውጤት
ሊያመጣ ይችላል፡፡ ተጠርጣሪው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከሆነ አላግባብ ተገዶ የእምነት ቃል
እንዲሰጥና በሕገ መንግስት ገደብ የተደረገበትን ተከሳሹ ለማስረጃ ምንጭነት መሰረታዊ
የሆነውን ያለመገደድ መብት በሂዴት የሚሸረሽር ይሆናል፡፡47 የሕገ መንግስት ድንጋጌ
አወቃቀርም ተጠርጣሪ በጥበቃ ሥር መቆየቱን ከደነገገ በኋላ በተከታይነት ያለመገደድ
መብቱንና በመገደድ የተገኘ ማስረጃ ውድቅ መሆኑን ማስቀመጡ አርቃቂዎች በጉዳዩ ላይ
አስቀድሞ ስጋት የነበራቸው መሆኑን ጠቋሚ ነው፡፡48 ይህን ይበልጥ ለመገንዘብም በሕገ
መንግስቱ አንቀፅ 17(2) መሰረት የሰው ነፃነት ከሕግ ውጭ አይገደብም ስለሚል የወንጀል ሥነ
ሥርዓት ሕጉ ሲታይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የት መቆየት አለባቸው የሚለውን
ደንግጓል፡፡49 ተጠርጣሪዎች መቆየት ያለባቸው የወህኒ ቤት ደንብ50 አያያዝ በሚፈቅደው
መሰረት በማረፊያ ቤት መሆን እንዳለበት በሕግ መደንገጉ ፖሊስ ተጠርጣሪውን እንደፈለገ
በሚያገኝበት ጣቢያ ከሚቆዩ ይልቅ አስፈላጊ አገልግሎቶች በሚገኙበትና የታራሚ አያያዝን
በሕግ አግባብ በሚያከብር ማረፊያ ቤት ሊሆን ይገባል የሚለውን የሚያመለክት ነው፡፡ ለዚህ
ማጠናከሪያም “ማረፊያ ቤት”51 የሚለው የሥነ ሥርዓት ሕገ እና የሕገ መንግስቱም “ጥበቃ”
የሚለው አገላለፅ ለተጠርጣሪው ጥቅም ሲባል ከተፈረደባቸው ሰዎች ተለይቶ መቆየትን

46
የኢፈዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪፖርት ለኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እቸኳያ ስብሰባ፣ የኢትዮጵያ
ቴሌቪሽን፣ ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡፡ ከዚህ ላይ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር
ዓብይ አህመድ ተጠርጣሪዎችን በጨለማ እስር ቤት እንዲሁም ያለ ክስ ለረጅም ጊዜ በእስር መቆየት ሕገ
መንግስቱን በመጣስ በመንግስት በኩል የተፈጠረ አሸባሪነት ነው እስከማለት ደርሰዋሰል፡፡ በጥበቃ ሥር መቆየት
የሚለው የሕግ መንግስት ድንጋጌና ሕጋዊነቱን የፍትህ አካላት እርስ በራሳቸው ቁጥጥር ስለማይደርጉ ለከፋ
የሰብአዊ መብት ጥሰትና የሕዝብ አመኔታንም በመንግስት ላይ እስከመቀነስ የሚያደርስ መሆኑ በሐገሪቱ አሁን
ላይ የተፈጠረውን ሁኔታ የምንረዳው ነው፡፡
47
የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 19(5)
48
የኢፌዲሪ ሕገ መንግስቱ የፀደቀው ከደርግ በጅምላ የመብት ጥሰት ፈፅሟል ከተባለ በኋላ የወጣ በመሆኑ
እውነታው ሩቅ ያልነበረ መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም፡፡
49
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 61
50
የአማራ ክልል የማረሚያ ቤቶች የታራሚዎችን አያያዝ በሚመለከተው መሰረት የታሰሩ ሰዎችን መያዝ የሚገባ
ነው፡፡ የመብት ጥሰትም ካላ ፍርድ ቤት በማጣራት ተገቢውን ርምጃ መውሰድ የሚገባ ይሆናል፡፡
51
አዲስ በሚረቀቀው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ላይ ለማካተት ተሞክሯል፡፡ ሥጋቱ ግን ተጠርጣሪዎች ፖሊስ
ጣቢያ መርማሪዎች ያሉበት ሰለሚሆን ተጠርጣዎችን ከማቆየት ለጥበቃ ብቻ በተመደበ ማረሚያ ቤት ማቆየት
የሚገባ የሰብአዊ መብት ጥሰትን ለመከላከል የሚያስችል ነው፡፡

14
የሚመለከት እንደሆነ ግምት ውስጥ የሚያስገባ እንጂ በመርማሪ እጅ እንዲሆን መፈለግን
የሚያሳይ ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡52
የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 19(4) ለተጨማሪ ጊዜ መፍቀድና በቁጥጥር ሥር እንዲሆን ለመወሰን
ፍትህ እንዳይጓደል ማድረግ በተጨማሪም የተጠርጣሪውን የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብቱን
በሚያስጠብቅ አግባብ የሕግ አስከባሪ ባለስልጣኖች ምርመራውን ማድረግ ያላባቸውና ፍርድ
ቤት ቀርቦ ውሳኔ የማግኘት መብትን በማያጓትት አግባብ መሆን ይኖርበታል፡፡ በጥበቃ ሥር
መቆየትና ጊዜ ቀጠሮ መስጠት ግን “ወይም” በሚል ቃል መያያዛቸው የዋስትና መብትና
ሌሎች የወንጀል ክርክር ምዕራፎች ዝግ አለመሆናቸውን ያሳያል፡፡ ይህም የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ
የሚቀረብ ከሆነ ለውስን ጊዜ ብቻ ጠብቆና ሲጠናቀቅ፤ ተጠርጣሪው በሕገ መንግስት አንቀፅ 17
የተከበረለትን የነፃነት መብት ለማስፈፀም በዚሁ ሰነድ አንቀፅ 19(6) መሰረት ዋስትና የመጠየቅ
መብት መከበር አለበት፡፡

3.2.1 በጥበቃ ሥር መቆየት በኢትዮጵያ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉና በሌሎች


ሕጎች53
በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉ ላይ በሕገ መንግስቱ እንደተመለከትነው በማረፊያ(ጥበቃ) ሥር
እንዲቆይ ማድረግ የሚለው ፅነሰ ሀሳብ ለውስን ጊዜ ብቻ ፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ እስከሚቀርብ
ድረስ ወይም ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ (ጊዜ ቀጠሮ) ተሰጥቶት ወይም የዋስትና መብት
በህግ አግባብ ሲከለከል ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር የሚቆይበትን የሕግ ውጤት የሚያመለክት
የሕግ ሥርዓት መሆኑን የሚያስገነዝበን ነው፡፡ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ህጉ ላይ “በማረፊያ
ቤት ማቆየት” የሚለው አገላለፅ በሕገ መንግስቱ “በጥበቃ ሥር እንዲቆይ” ከሚለው ጋር
ተመሳሳይ ፅነሰ ሀሳብ ነው፡፡
የጊዜ ቀጠሮ የሚለው ሀሳብም ከዋስትና ክርክር በፊት ተከሳሹ በቁጥጥር ሥር ሆኖ በጥብቅ
የቀጠሮ ፖሊሲ ተከሳሹ ላይ ምርመራ የሚያደርግበት አግባብ ነው፡፡ የሲቭልና ፖለቲካ
መብቶች ቃል ኪዳን ፈራሚዎች የሕግ ስርዓትን ሀገራት ሳይከተሉ ተጠርጣሪን መያዝና
በቁጥጥር ሥር መዋል የድንጋጌውን አንቀፅ 9(1) የሚጥስ ነው በሚል ወስኗል፡፡ ኢትዮጵያም

52
እየተሻሻለ ባለው የወንጀል ሥነ ሥርዓት የትርጉም ክፍል ላይ ማቆያ ቤት፣ ማረፊያ ቤት እና ማረሚያ ቤት
የሚሉ ተርጉሞችን ለማከተት ተሞክሯል፡፡ እስካሁን በጸደቀ ሕግ በሀገራችን ማረፊያ ቤት የሚለው ተለይቶ
የተቀመጠ አይደለም፡፡ ሆኖም ሕጉ እስከሚፀድቅ ድረስ በመፍትሔነት የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ጥበቃ
የሚያደርግበት ሁኔታ ይህን ያገናዘበ እንዲሆን ይጠበቅበታል፡፡ ፍርደኛ የሆኑና ያልሆኑትን በመለየት ማሰር
የሚቻል ይሆናል፡፡
53
የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 እና የፀረ ሙስና አዋጅ ቁጥር 434/1997

15
የቃል ኪዳኑ ሰነድ ፈራሚ እንደመሆኗና የህግ አካል ስላደረገች ይህንን ግዴታ በሚያሟላ
አግባብ መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ የሰብአዊ መብት ድንጋጌን አንቀጽ
9(1)“ን” በሪፖርቱ በሰጠው ትርጓሜ ላይ አንድ ሰው የአገር ውስጥ ሕግ (domestic
legislation) ከሚለው ውጭም ተይዞ የሚቆይ ከሆነ የሕጋዊነት መርህ የሚጣስ መሆኑን
አመለክቷል፡፡54 የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ (Human Rights Committee) ድንጋጌውን በጥበቃ
ሥር መሆን ከሕጋዊነት መርህ አንፃር ሪፖርት ሲያቀርብ፡-
`[A]rbitrariness’ is not to be equated with ‘against the law’, but must be interpreted more
broadly to include elements of inappropriateness, injustice, lack of predictability such
that remand in custody must not only lawful but also reasonable in all cricumstances.55
በሚል ይገልፀዋል፡፡ ይህም ወደ አማርኛ አቻ ትርጉም ሲመለስ፡-

“ዘፈቀዳዊነት” የሚለው “ሕግን መቃረን” ከሚለው ጋር የሚመጣጠን ሳይሆን፤ ይልቁንም ሰፋ


ባለ መልኩ ሲተረጎም ታሳቢ መደረግ ያለባቸው ፍሬ ነገሮች ተገቢ ያለመሆንን፣ ኢፍትዊነት፣
ተገማችበት አለመኖር ናቸው፡፡ ይህ ማለት በሕጋዊ መንገድ መያዝን ተከትሎ በቁጥጥር ስር
መሆን ሕጋዊ ከመሆኑ በተጨማሪ ከሁኔታው አኳያ ምክንያታዊና አስፈላጊ መሆን አለበት፡፡56

ከዚህ ትርጓሜም ማዕከላዊ ሕጋዊ ሁኔታን መያዝን ተከትሎ በቁጥጥር ስር መቆየት ሕጋዊ
ነው መባል ብቻ በቂ አይሆንም፡፡ ይልቁንም ከጠቅላላው የምርምራ ሂዴት አንጻር “ምክንያታዊና
አስፈላጊ” መሆኑን ትኩረት ማስፈለጉን መሰረት ያረገ ነው፡፡ ስለሆነም በወንጀል ሥነ ሥርዓት
ሕግ ቁጥር 59(1) መሰረት የተያዘ ሰው የተያዘበት ሁኔታ ሕጋዊ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ
ተጠርጣሪው በማረፊያ ቤት (በጥበቃ ስር) እንዲቆይ ማድረግ ወይም ዋስትና በመፍቀድ የሚገባ
መሆኑ በመርህ ደረጃ ተደንግጓል፡፡ ስለሆነም በኢትዮጵያ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ውስጥ
የጊዜ ቀጠሮ የሚለውን ፅነሰ ሃሳብ ተካቷል ለማለት ይቻላል፡፡
በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉ አንቀፅ 60 ላይም በወሕኔ ቤት ደንብ እንድቆዩ በግልፅ የተቀመጠ
መሆኑ ዳኞች የተያዘ ሰው ችሎት ሲቀርብ ማረፊያ ቤት ካለ ለዚህ ተቋም ወይም ከሌለ
በማረሚያ ቤት እንዲቆይ ማዘዝ የሚጠበቅባቸው መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ የተያዘ ሰው
በማረፊያ ቤት መቆየቱንም ፍርድ ቤት ማዘዝ መቻሉ ተጠርጣሪው በሕግ አግባብ በሚተዳደር
ተቋም ውስጥ ሰብአዊ መብቱ ተከብሮለት እንዲቆይ ማድረግን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ በሀገራችን
የተጠረጠረ ሰው እንደሲቭል ሎው የሕግ ሥርዓት በምርመራ ተግባሩ ላይ እንዲሳተፉና

54
የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ በፕሮቶኮል ሀገራት ሲቀበሉት የሰብአዊ መብትን በተመለከተ ትርጓሜ (ሪፖርት)
የመስጠት ሥልጣን ያለው አካል ነው፡፡
55
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 37፣ ገጽ 16፣ ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር ገጽ 9፣ Communication
No.305/1988, HRC Report 1990, Annex IX.
56
ትርጉም የራሴ ነው፡፡

16
ምርመራውን እንዲያግዙ አይጠበቅም፡፡ ይልቁንም በአመዛኙ የወንጀል ፍትህ አስተዳደሩ
አወቃቀር ፍልሚያዊ ይዘት ያለው በመሆኑ ተጠርጣሪውን በምርመራ ሥራው ላይ
እንዳያስተጓጉል ማድረግ ብቻ ግዴታ አለበት፡፡57 ስለሆነም የምርመራ ሥራውን ተጠርጣሪው
ሰው ክርክሩን አላገዘም በሚል ብቻ ማዘግየት ተቀባይነት ማግኘት አይኖርበትም፡፡
በጊዜ ቀጠሮ ጉዳይም በማረፊያ ቤት መቆየት በዋስትና መከልከል ምክንየት በማረፊያ ቤት
ከመቆየት ጋር የዓላማ ልዩነት አለው፡፡ የጊዜ ቀጠሮ ጥበቃ ሥር መሆን ዓላማው ፖሊስ
የምርመራ ሥራውን ሲያከናውን ተጠርጣሪው ከሕግ አስከባሪ አካላት ቁጥጥር ውጭ ቢወጣ
የምርመራ ስራውን ሊያደናቅፍ ይችላል የሚለውን ታሳቢ በማድረግ የተጠርጣሪን ሕገ
መንግስታዊ የመንቀሳቀስ መብት በሕግ የሚገድብ በቂ ምክንያት ነው፡፡ ይህም ጉዳዩ በዋስትና
መብት የሚያስፈቅድ ስለመሆን አለመሆኑ ማጣሪያ ማድረግ ሳያስፈልግ የተጠርጣሪው
የመንቀሳቀስ መብትን ሊገደብ የሚችለበት አግባብ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ክስ ከመቅረቡ በፊት
የዋስትና መብትን መከልከል ከጊዜ ቀጠሮ ሂዴት ሲኖር ወይም ሳይጠየቅ ሲቀር የሚመጣ ሆኖ
ዓላማው በጉዳዩ ላይ ክስ መመስረት ወይም ያለመመስረት ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ
ተጠርጣሪው ከቁጥጥር ውጭ መሆን ስለሌለበት የመንቀሳቀስ መብቱ ሊገደብ ይገባል የሚለውን
ታሳቢ የሚያደረግ ነው፡፡ ስለሆነም የጊዜ ቀጠሮ እስራት የአጭር ጊዜ ግብ ያለው ሲሆን
ዋስትናን በመከልከል የሚሰጥ እስራት ግን በንፅፅራዊ አገላለፅ የረጅም ጊዜ ግብ ያለው ነው፡፡
በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀፅ 59 ንዑስ 2 እና 3 መሰረትም ፖሊስ ተጨማሪ
የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ሲጠይቅ ተጠርጣሪውን በማረፊያ ቤት እንዲቆይ ሊታዘዝ ይችላል፡፡
በሌላ መልኩ ደግሞ ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ የማይጠይቅ ወይም ያልተፈቀደለት ከሆነ፣
ተጠርጣሪው በዋስትና ልፈታ የሚል አቤቱታ ሲያቀርብ ከወንጀሉ ይዘትና ከተጠሪጣሪው
ሁኔታ አኳያ ዋስትና ሲነፈግ በማረፊያ ቤት እንዲቆይ የሚደረግበት ነው፡፡ ስለሆነም በማረፊያ
ቤት የተያዘ ሰው እንዲቆይ ለማዘዝ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መፈቀድ ወይም ዋስትና
መከልከል ግድ ይላል ማለት ነው፡፡
ሌላው በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 93 መሰረት የቀዳሚ ምርመራ ያደረገው ፍርድ ቤት
“የተያዘን ሰው [ተከሳሽን] በማረፊያ ቤት እንዲቆይ” ማዘዝ ስለመቻሉ ተደንግጓል፡፡ ከዚህ ላይ
በእርግጥ የወንጀል ምርመራ አካል የሆነው የቀዳሚ ምርምራ ሂዴት የጊዜ ቀጠሮ ከመጠየቅ

57
Fisher, Stanley Z., “Traditional Criminal Procedure in Ethiopia,” The American Journal of
Comparative Law, Vol. 19, 1971፣ ገጽ 709-746 እና ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 1

17
ጎን ለጎን አብሮ ሊቀርብ መቻሉ መገደብ የለበትም፡፡58 የቀዳሚ ምርመራ አድራጊ ፍርድ ቤት
የጊዜ ቀጠሮ ያልተሰጠበትን ክርክር ብቻ የዋስትና ጉዳይ ሊመለከት ይችላል፡፡ ቀዳሚ ምርመራ
አድራጊ ፍርድ ቤት ምስክሮችን የሚሰማ ሲሆን ሌላው የምርመራ ሂዴት ገና ያልተጠናቀቀ
ቢሆን ጊዜ ቀጠሮ ወይም ዋስትና ሊጠይቅ ስለሚችል በቀረበለት አቤቱታ መሰረት ሊያስተናገድ
ይችላል፡፡ ሆኖም ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ አስቀድሞ በሌላ ፍርድ ቤት ከተሰጠ ወይም ራሱ
ከሰጠ ትዕዛዝ እስከሚፈፀም ድረስ መጠበቅ የሚገባ ይሆናል፡፡
በማረፊያ ቤት መቆየት የጥፋተኝነት ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት የነፃነት መገደብን የሚያመጣና
በማረፊያ ቤት ቆይታውም ከፍርድ በፊት እንደጥፋተኛ ያለመቆጥር መብትን መሰረት ባደረገ
መልኩ ነፃ ሊባሉ የሚችሉ የመኖራቸው ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት መወሰን የሚገባ
ነው፡፡ በተለይም ደግሞ በማረፊያ ቤት የቆይታ ጊዜው የሚገደብበትን ሁኔታና የቆይታ ጊዜን
ማሰላሰል ይጠይቃል፡፡
ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ወይም የጊዜ ቀጠሮ በመስጠት በማረፊያ ቤት
ቆይታ ጊዜ ምን ያክል መሆን አለበት የሚለው ብዙም ትኩረት የተሰጠው አይመስልም፡፡
በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉ ላይ ፖሊስ ምርመራውን ያለበቂ ምክንያት ባያጠናቅቅ ፍርድ ቤት
ምን ያህል ጊዜ የጊዜ ቀጠሮ ሊፈቅድ እንደሚችልም በህጉ ላይ በግልጽ ያልተመለከተ ቢሆንም
ያለበቂ ምክንያት ተጨማሪ ጊዜ ሊፈቅድ አይገባም፡፡59 ተጠርጣሪ በማረፊያ ቤት እንዲቆይ
መደረግ ያለበት ፍትህ እንዳይጓደል ሁኔታው የሚጠይቅ ሲሆን ብቻ ስለመሆኑ በሕግ
መንግስቱ አንቀፅ 19(4) ላይ ተደንግጓል፡፡ ስለሆነም የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳይኖር የጊዜ
ቀጠሮ ችሎት በጥንቃቄና በጥብቅ መስፈርት በጥበቃ ሥር የመቆየትን አስፈላጊነቱን እየመዘነ
እያንዳንዱን ጉዳይ እያጣራ ተጨማሪ ጊዜ መፍቀድ ይጠበቅበታል፡፡ ይህም በአግባቡ ከተተገበረ
የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ አያስፈልግም፡፡ ፖሊስ ምርመራውን ያለበቂ ምክንያት ማዘግየት
የሌለበት ስለመሆኑ በሕገ መንግስቱ ጭምር እውቅና ያገኘ ጉዳይ ነው፡፡ የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ
ለሰብዓዊ መብት ጥበቃ ጠቀሜታ ቢኖረውም የራሱ የሆነ ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡60

58
የቀዳሚ ምርምራ አድራጊ ፍርድ ቤት ግን በራሱ ዋስትና ጉዳይን ሊመለከት ስለመቻሉ በህጉ ላይ ተመላክቷል፡፡
59
በፀረ ሽብርተኝት አዋጅ ቁጥር 652/2001 መሰረት ለቅድመ ምርመራ የእስራት ጊዜ ጣሪያው 4 ወር መሆን
አለበት የሚለው መልካም ቢሆንም ዝቅተኛው 28 ቀን ይሆናል ማለቱ ግን ጉድለት ነው፡፡ ከሽብር ወንጀል ባነሰ
ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮች ግን ለመራካታ ጊዜ ሲያሳስር ይታያል፡፡
60
ለምሳሌ ተጠርጣሪው ከህግ ውጪ ከሌሎች የወንጀል ተሳታፊዎች ጋር በመሆን ሴትን ጠልፎ የደበቀ ቢሆን
እና የተጠለፈችው እንዳትለቀቅ የተያዘው ተጠርጣሪ ለመተባበር ባይፈልግ ወይም የተለዩ የተወሳሰቡ ጉይዮች
ቢያጋጥሙ እና ምርመራው በህግ የተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማጠናቀቅ ባይቻል ሊፈጠር የሚችለውን
አስቸጋሪ ሁኔታ አስቀድሞ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡

18
በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 59(2) እያንዳንዱ የምርመራ ጊዜ ከ14 ቀን መብለጥ
የለበትም በሚል መደንገዱ ማሳነስ መቻሉን የሚያሳይ ነው፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ግን የጊዜ
ቀጠሮን ፅንሰ ሃሳብ ይዞ የመጣው የፀረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 ዝቅተኛው 28 ቀን
ሲሆን ከፍተኛው 4 ወር ነው በሚል ተደንግጓል፡፡ ከጊዜ ቀጠሮ አፈቃቀድ ጋር ተያይዞ 14 ቀን
ተጨማሪ ምርመራ የማጣሪያ ጊዜ የዕረፍት እና የበዓል ቀናትን ማካተቱን በተመለከተ ጥያቄ
ይነሣል፡፡ በዚህ ረገድ የታሰረው ሰውን መብት በሚጎዳ ሁኔታ መተርጎም አግባብነት የለውም፡፡
የእስራት ቀን አቆጣጠር መሆን ያለበት ሁሉንም ቀናት መሆኑን ግንዛቤ መውሰድ ይገባል፡፡
የጊዜ ቀጠሮ የሚያስተናግድ ችሎት የስልጣን ወሰን በተግባር ጥያቄ ሲያስነሳ ይታያል፡፡ ችሎቱ
ተጠርጣሪው አላግባብ የተያዘ መሆኑን ቢያረጋግጥ ያለዋስትና ሊለቅ መቻሉ ያከራክራል፡፡
በሕጉ ላይ ተጠርጣሪን በጥበቃ ሥር ከማቆየትና እና በዋስትና ከመልቀቅ ውጪ የተቀመጠ ሌላ
ሶስተኛ አማራጭ ያለ አይመስልም፡፡ ከዚህ አንጻር፣ የክርክር አመራሩ በሂዴት የምንመለከተው
መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ችሎቱ ተጠርጣሪውን በዋስትና ብቻ መልቀቅ አለበት ሊባል
ይችላል፡፡ ነገር ግን ተጠርጣሪው በስህተት መያዙን ፖሊስ ጭምር እያረጋገጠ ዋስትና አቅርብ
ማለት ትርጉም የለውም፡፡ በፍርድ ቤትም ቀርቦ ምርመራ የሚጣራበት በቂ ምክንያት የሌለ
መሆኑ እስከታወቀ ድረስ ፍርድ ቤት የተጠረጠረን ሰው መልቀቁ የፍትህ ሥርዓቱን ቅልጥፍና
እና ፍትሐዊነት የሚያሰፍን ይሆናል፡፡ የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 19(4) ላይ ድንጋጌ ይዘትም
በሕገ ወጥ መንገድ የተያዘ ሰው የሚለቀቅ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ የመልቀቅ ውሳኔ ሲሰጥም
በፖሊስና በፍርድ ቤት መካከል የስልጣን ቁጥጥር ስለሚኖር ያልተገባ አሰራር ይኖራል
የሚለውም ሚዛን የሚደፋ አይመስልም፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች ለመቅረፍ የተዘጋጀው
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ህግ ረቂቅ አሁን ካለው ህግ መሰረታዊ ልዩነት የሌለውና የህጉን
ችግሮች የማይቀረፍ በመሆኑ ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶ ተሻሽሎ ሊያሰራ በሚችል መልኩ
መፅደቅ አለበት፡፡61

2.3 በወንጀል ክርክር የዋስትና መብት ፅነሰ ሃሳብና የሕግ ማዕቀፍ


የዋስትና መብት በወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘ ሰው በቁጥጥር ስር የመሆን ግዴታ ግልባጭ
መብት ነው፡፡ የዋስትና መብትም በዓለም ዓቀፍ ሰነዶችና በሕገ መንግስቱ መሰረት የተረጋገጠ

61
በረቂቁ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ላይ ለጊዜ ቀጠሮ የጊዜ ገደብ 6 ወር ተብሎ የተቀመጠ ሲሆን ይህ ከላይ
በተገለጹት ምክንያቶች ችግር ሊፈጥር ስለሚችል ሊታሰብበት ይገባል፡፡ የጊዜ ገደቡ ባይከበርስ ምን ውጤት
ይኖረዋል የሚለው ምላሽ ያገኘ ባለመሆኑም እንደገና ሊፈተሽ ይገባዋል፡፡ በመሆኑም አሁን ያለው ወንጀል ሥነ
ሥርዓት ህግ እና ረቂቅ ሕጉ ያለባቸው ችግሮች በሚገባ ተጠንቶ የወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ፀድቆ በስራ ላይ
መዋል ይጠበቅበታል፡፡

19
ሰብአዊ መብት ነው፡፡ የዋስትና መብት ፅንሰ ሃሳብ፣ የሕግ ማዕቀፍና የሕጉን አፈፃጸም
የምንመለከት ይሆናል፡፡

2.3.1 የዋስትና መብት ፅነሰ ሀሳብና ወሰኑ


የዋስትና መብትም ከነፃነት መብት ጋር የተያያዘና ከጥንት ዘመን ፈላስፋው ፕላቶ62 ጀምሮ
የሚታወቅ መብት ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን ሰነዶች ውስጥም የነፃነት መብትን
በማስጠበቅ በቀዳሚነት የዋስትና መብት በመርህ ደረጃ የተረጋገጠ መብት ነው፡፡63 ዋስትና
መብት መሆኑን የሚቀበሉት ቃል ኪዳን ሰነዶችም አብዛኞቹ ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸው እና
የሀገሪቱ የሕግ አካል በመሆናቸው ተፈፃሚነት አላቸው፡፡64 የሲቭልና ፖለቲካ መብቶች ቃል
ኪዳን አንቀጽ 9(3) የሚለው፡-
በወንጀል ክስ የተያዘ ወይም የታሰረ ሰው ከዳኛ ዋይም በሕግ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ዘንድ
በአፋጣኝ ሊቀርብ ይገባል፡፡ ተገቢ በሆነ ጊዜ ውስጥም ዳኝነት የማግኘት መብት አለው፡፡ ዳኝነትን
የሚጠባበቁ ሰዎችን በእስር ማቆየት እንደመደበኛ አፈፃፀም ሊታይ አይገባውም፡፡ ይሁን እንጂ
ከእስር መልቀቁ ግለሰቡን ጉዳዩ በሚታይበት ጊዜ እንዲቀርብ ወይም ፍርዱ እንዲፈጸመለት
ለማድረግ እንዲያመች በዋስትና ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይችላል፡፡65
የዚህ ንዑስ ድንጋጌ አወቃቀርም ዋስትና መፍቀድ መብት መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡
የሌሎች ሀገሮች ልምድም ሲታይ የአሜሪካን አገር ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአንድ በስታክ እና
ቦይሌ ጉዳይ ላይ ሲወስን ዋስትናን መከልከል ለዘመናት በተደረገው ትግል የመጣን ንጹህ ሆኖ
የመገመት መብት በሚያጣብብ ነው በሚል ገልፆታል፡፡66 የአሜሪካን የፌደራሉ የዋስትና
ማሻሻያ ሕግ 1984 ተብሎ የሚታወቀው ተጠርጣሪው ለሕዝበ አደገኛ ነው ወይም ፍርድ ቤት
ቀጠሮውን አክብሮ ሊቀርብ አይችልም ካልተበላ በስስተቀር በዋስትና መፈታት መብት መሆኑን
ይደነግጋል፡፡67 የደቡብ አፍሪካ ሕግ መንግስትም ፍትህ የማይጓደል እስከሆነ ድረስ ዋስትና

62
Caleb Foot, Forward: Comment on the New York Bail Study, University of Pennsylvania Law
Review Vol.106፣ ገፅ 685፣ በግድያ ወንጀል ዋስ በመጥራት ከእስራት መውጣት ስለመቻሉ የታወቀ ስለመሆኑ
የሚያስዳ ነው፡፡
63
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 2
64
ሕገ መንግስቱ አንቀፅ 9 እና 13፡፡
65
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 6
66
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 62 ገጽ 685 እና ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 37፣ ገጽ 16
67
The Federal Reform Bail Act of 1984, 18 U.S.A. Article 3141 et seq., in John M. Scheb et al,
Criminal Law and Procedure, USA, 2011, ገጽ 520

20
መፈታት መብት መሆኑን ተደንግጎ የሚገኝና ይህንን ለማስፈጸም የወጡት ሕጎችም ከዚሁ ጋር
የሚጣጣም ነው፡፡68
ጻሐፊዎችም እንደሚሉት የዋስትና መብት ሊገደብ የሚገባው በቁጥጥር ሥር ማቆየትን
አስፈላጊነት የሚወሰነው ፍትህ እንዳይጓደል የሚለውን የፖሊሲ ግብ መሰረት በማድረግ ነው፡፡
የዋስትና ግብ በቁጥጥር ሥር የማድረግ ግብን በማገናዘብ የሚታይ ነው፡፡ የተያዘ ሰውን
ዋስትናውን በመከልከል በቁጥጥር ስር ለማቆየት ሶስት ሰፋፊ ግቦችን ያሳካል በሚል ስትራቴጅ
ሊቀረፅ ስለመቻሉ በዘርፉ የተፃፉ ፅሁፎች ያመለክታሉ፡፡69
አንደኛው የፍትህ አስተዳደሩ ልዕልና መጠበቅና ታማኝቱን ማሳደግ ነው፡፡ በዚህ ግብ ውስጥም
የተጠረጠረው ሰው ባልተገባ ምግባሩ ምክንያት ለምሳሌ ምስክሮችን በማወኩ ወይም ማስረጃ
በማጥፋቱ ተጠቃሚ መሆን የለበትም የሚለውን የሚመለከት ነው፡፡ ተጠርጣው ሲከሰስም
ፍርድ ቤት በአካል ቀርቦ ክርክር ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ በዚህ ውሳኔ አሰጣጥም ላይ የፍርድ
ቤቱን ሂደት በራሱ ጥበቃ እንዲያገኝ ለማስቻል በቁጥጥር ሥር ስለመሆን አለመሆኑ የሚወስኑ
አካላት አስቀድመው ሊገነዘቡት የሚገባ ይሆናል፡፡ ሁለተኛው ግብ ደግሞ ማህበረሰቡን ከጥቃት
መጠበቅ ሲሆን የተያዘው ሰው ወንጀል በመፈጸም ላይ የቀጠለ ከሆነ አካላዊ ጥቃት
እንዳይፈፅም መከላከልን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ የመጨረሻው ግብም ለተጠርጣሪው ለራሱ
ጥቅም ሲባል ዋስትና በመከልከል ስለመቻሉ የሚያመለክት ነው፡፡ ተጠርጣሪው በተጠረጠረበት
ወንጀል በራሱ ላይ አደጋ ሊደርስበት የሚችል ሲሆን70 ወይም ሌላ እንክብካቤ ለምሳሌ የጤና
እንክብካቤ ማድረግ አስፈላጊ ሲሆን በቁጥጥር ስር እንዲቆይ ሊወሰን ስለመቻሉ መገንዘብ
ይቻላል፡፡ የዋስትና መብት በሀገራችንም ሕገ መንግስታዊ መሠረት ያለው በመሆኑ የሕግ
ማዕቀፉን እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡

2.3.2 የዋስትና መብት በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት


በመሰረቱ በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ውስጥ ዋስትና መሰረታዊ መብት ነው፡፡ ይህ መብት
ማክበር ንጹህ ሆኖ መገመት ከሚለው ሕገ መንግስታዊ መርህ ጋር ጭምር አብሮ የሚሄድና
የዋስትና መብት በወንጀል ለተጠርጣሩም ሆነ ለተከሰሱ ሰዎች የተሰጠ መብት ነው፡፡71 በሕገ

68
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር፣ ገጽ 86-95
69
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 2፣ ገጽ 334-337
70
ለምሳሌ በሀገራችን የሰው መግደል ወንጀልን በሚመለከት የደም መመልስ ሊኖር ስለሚችል ተጠርጣሪውን
በቁጥጥር ሥር ማድረግ የሚያስፈል ስለሆነ በወንጀል መቅጫ ሥነ ሥርዓት ዋስትና እንዲከለከል ተድግጓል
ማለት ይቻላል፡፡
71
የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 20(3)

21
መንግስቱ አንቀፅ 19(6) መሰረት በዋስትና መፈታት መብት ሲሆን በልዩ ሁኔታ ዋስትና
የሚከለከልባቸው ሁኔታዎች ስለመኖራቸው ይደነግጋል፡፡ ይህ የሕገ መንግስቱ አቀራረፅም
ከዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን ሰነዶችና ልምዶች ጋር የሚጣጣም ነው፡፡ ይልቁንም የሕገ
መንግስታዊ ትርጉም የሚነሳው ዋስትና በልዩ ሁኔታ በፍርድ ቤት ሊከለከል የሚችል መሆኑ
የተደነገገ ሆኖ እያለ ሕገ መንገስቱ ከወጣ በኋላ የሚወጡ ሕጎች ዋስትና አስቅድሞ የሚከለክሉ
ይስተወላሉ፡፡
ዋስትናን በተመለከተ ተፈጻሚነት ያላቸው ሕጎችም ዋስትና በሁለት ዓይነት ሁኔታዎች
ሊከለከል ስለመቻሉ ያሳያሉ፡፡ አንደኛው ዋስትና የሚከለከልበት ሁኔታ በሕግ አውጪው
ዋስትና የሚያስከልክሉ ድንጋጌዎችን አስቀድሞ የሚዘረዘሩበት ሁኔታ ነው፡፡72 ሁለተኛው
ደግሞ ድንጋጌው ዋስትና ባያስከልክልም ዳኞች የነገሩን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ክርክር
ሲቀርብላቸው ዋስትና ሊነፍጉ የሚችሉበት አግባብ የሚያሳየው ነው፡፡73 ሁለተኛው በዳኞች
እንደነገሩ ሁኔታ እየተመዘነ ዋስትና መከልከሉ በዓለም ላይ ያሉት የሕግ ሥርዓች
የሚቀበሉትና ለሕዝብ ጥቅም በሚል የሚከናወን በመሆኑ፣ በአፈፃፀሙ ላይ መጠነኛ ልዩነት
ከመታየቱ በስተቀር፣ በመርህ ደረጃ ብዙም አያከራክርም፡፡74
አንደኛውን ፅነሰ ሀሳብ በተመለከተ የዋስትና መብትን በተመለከተ በሕገ መንግስቱ አንቀፅ
19(6)75 ዋስትንን የሚፈቅደውና የሚከለክለው በፍርድ ቤቶች አንጅ በህግ አውጪው አስቀድሞ
መሆን ሌለበት ስለመሆኑ ክርክር ይቀርባል፡፡ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ህግ አንቀፅ 63“ን”
ጨምሮ አንዳንድ ወንጀሎች ክስ በመቅረቡ ብቻ ዋስትና የሚስከለክሉ አሉ፡፡ ይህን በተመለከተ
የሕገ መንግስታዊነት ክርክር አስነስቶ የሕገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ በጥላሁን አባይና ሌሎች
ጉዳይ76 በሰጠው በውሳኔ ላይ የሕገ መንግስት ትርጉም ስለማያስነሳ ለፌደሬሽን ምክር ቤት
አይቀርብም በሚል ወስኗል፡፡ ከውሳኔው ከተጠቀሰው ውስጥ፡-

72
የሕገ መንግስት አጣሪ ጉባኤውም በእነጥላሁን አባይ ጉዳይ በሰጠው አስተያየት ሕገ መንግስታዊነቱን
አስቀድሞ በህግ መከልከል ይቻላል የሚለው ተወስኗል፡፡
73
በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 67 ሥር ከተዘረዘሩት ንዑስ ድጋጌዎች አንደኛው ሁኔታ ሲሟላ አስቀድሞ
በዋስትና የማያስከልክል ድንጋጌም ቢሆን ዋስትና ሊከለከል ይቻላል፡፡
74
የሕግ ማዕቀፍና የፖሊሲ ሁኔታ ግን በዳኞች ዋስትና መንፈግ በውጤት ደረጃ ዋስትና በሕግ መከልከል ጋር
ሊቀራረብ ይችላል፡፡
75
አንቀጽ 19(6) የሚለውም፡- “የተያዙ ሰዎች በዋስ የመፈታት መብት አላቸው፡፡ ሆኖም በተደነገጉ ልዩ
ሁኔታዎች ፍርድ ቤት ዋስትና ላለመቀበል ወይም በገድብ ምፍታትን ጨምሮ በቂ ሆነ የዋስትና ማረጋገጫ
እንደቀርብ ለማዘዝ ይችላል፡፡”
76
የፌደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን እና እነጥላሁን አባይ፣ በሙስና ወንጀል ዋስትናን የሚከለክለው ሕ
ሕገ መነግስታዊ አይደለም በማለት የቀረበ አቤቱታን በሚመለከት የተሰጠ የህገ መንግስት ትርጉም አስተያየት፣
የኢትዮጵያ የሕግ መጽሔት፣ 23ና ቮልዩም ቁ.2፣ ገፅ 146-153

22
በህግ አውጭ ተለይቶ የተጠቀሰ ወንጀል ዋስትና መብት አያሰጥም መባሉ ዋስትናው በፍርድ
ቤት የማይታይ(non-justiciable) የሚያደርገው አይሆንም፡፡ ዞሮ ዞሮ ዋስትና አያስከለክልም
የሚባለው ወንጀል ዋስትና ለመከልከል በቂ ፍሬ ነገሮች ቀርበዋል አልቀረቡም የሚለውን ነጥብ
መመርመር ያለበት ፍርድ ቤቱ ነው፡፡ የሙስና ወንጀል ዋስትና አያሰጥም የሚል ሕግ ቢኖርም
በአሳሪው ብቻ የሚወሰን ሳይሆን በፍርድ ቤት ሊታመንበት የሚገባ ነገርም መሆን አለበት፡፡
ሙስነ ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን መመልስም ፍርድ ቤቶ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ
እንዲወጡ መገመት አግባብ ነው፡፡ ሕግ አውጪው በአዋጁ አፈጻጸም የሚገጥሙ ችግችን
ተመልክቶ መፍትሔ ማፈላለግ እንዳበትም ይታመናል፡፡77 የሚለውን እናገኛለን፡፡

የአጣሪ ጉባኤውም በሕግ አውጪ ዋስትና መከልከሉ ሕገ መንግስታዊ ትርጉም አያስነሳም


ከሚለው ድምዳሜ ላይ መደረሱ ትችትን የሚቀርብበት ነው፡፡78 “በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች”
የሚለው አስቀድሞ ዋስትና የሚያስከለክሉ ድንጋዎችን መዘርዘር ሳይሆን በወንጀል ሕግ
ቁጥር 67 ያሉ መስፈርቶችን በመዘርዘር ፍርድ ቤት የሚመዝናቸው ማድረግን የሚመለከት
ነው፡፡79 በተለይም ደግሞ የውጭ አገር ልምዶች ዋስትና አስቀድሞ የሚከለክል ሕግ አለ
የሚለው የአጣሪ ጉባዔው የተሳሳት ድምዳሜ ነው፡፡80 ፍርድ ቤቱ ክስ ሲቀርብለት ወይም
በቅድመ ክስ ዋስትና ክርክር ተጠርጣሪው የሚከሰስበትን ድንጋጌ ሲገለፅ የቀረበው ፍሬ ጉዳይ
በማስረጃ መረጋገጥ በራሱ ሲታይ ዋስትና የሚያስከልከል አይደለም በሚል መወሰን ይቻላሉ
የሚለውን የሚጠቁም ነው፡፡ በተግባርም ክስ ሲቀርብ የድንጋጌውንና የፍሬ ጉዳዩን መጣጣም
መመርመር የሚገባ ይሆናል፡፡81 ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ክስ እንዳለ ፍርድ ቤት በመቀበል
ዋስትና የሚከለክል ከሆነ ዋስትና የመፍቀዱና መከልከሉ ሥልጣን ለዐቃቤ ሕግ ተላልፎ
የተሰጠ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡

77
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 37፣ ገጽ 153
78
ዝኒ ከማሁ፣ ገፅ 25፡፡ የአሜሪካ፣ የካናዳ፣ የእንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ እስራኤል የመሳሰሉት ሕጎች ዋስትናን
አስቀድሞ በሕግ የሚከለክል ሕግና አሰራርም የላቸውም፡፡
79
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 37፣ አጣሪ ጉባኤው ግን ልዩ ሁኔታዎች ዋስትና የሚከለክሉ ድንጋጌዎችን
ይጨምራል የሚለው ተፈፃሚነት የሌለውና ግልጸነት የጎደለውም ነው፡፡ ሕገ መንግስትም ቢሆን በመጠጋገን
ለማቆም መሞከር አሳማኝነትና ምክንያተዊነትን ስለሚያጠፋ ጠቅላላው የሕግና ሥርዓትን ተቀባይነትን የሚቀንስ
ይሆናል እንጂ ሌላ ጥቅም አይኖረውም፡፡
80
ዝኒ ከማሁ፣ ከእኛ ሕግ ጋር የሚጣጣመው የአሜረካች ሳይሆን የአርጀንቲና ሕግ ነው፡፡ ሌሎች የሰለጠኑ
ሐገራት ግን ዋስትናን አስቀድሞ ሲከለክሉ አይታይም፡፡
81
ለምሳሌ በቀድሞው የፀረ-ሙስና ወንጀል አንቀፅ 676(1) መሰረት የማህበራት ገንዘብን ያጎደሉ የሚከሰሱበት
ሁኔታ አልነበረም፡፡ ይልቁንም ተገቢው በዚሁ ድንጋጌ ንዑስ ቁጥር 2 ነው፡፡ ዋስትና በማስከልከል ረገድ ንዑስ
ቁጥር 1 የቅጣቱ መጠን ምክንያት ክሱ እንደቀረበ የሚያስከለክል ሲሆን ንዑስ ቁጥር 2 ግን ዋስትና
አያስከለክልም፡፡ ስለሆነም ዐቃቤ ሕግ የተከሳሹን የስራ ድርሻ በክሱ በግልፅ አስፍሮ(የማሕበራት ገንዘብ ያዥ)
በንዑስ ቁጥር 1 ላይ መካከተት አለበት ቢል የማሕበራት ገንዘብ ያዥ መሆኑ ለወደፊት በማስረጃ እስከሚረጋገጥ
ይቆይ ማለቱ ፍትሀዊ ስለማይመስል ድንገጌው ወደ ንዑስ ቁጥር 2 እንድለወጥ ክሱ እንድሻሻል በማድረግ ወይም
በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሕጉን አግባብነት በመወሰን ዋስትና ሊፈቅድለት ይገባል የሚያሰኝ ነው፡፡

23
ሆኖም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም ይህን የሕገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ
ውሳኔ ያገናዘበ ነው ለማለት የሚቻል አይደለም፡፡ የሰበር ሰሚ ችሎቱም ዳኞች ፍሬ ነገርን
ማስረጃ በማስማት ብይን ከመስጠቱ በፊት ለዋስትና ዓላማ የተጠቀሰውን ድንገጌ መመርመር
የለባቸውም በሚል ወስኗል፡፡82 ከዚህ በባሰ ሁኔታም ከወንጀል ህግ ቁጥር 676(1) ወደ አዲሱ
የጸረ ሙስና ወንጀል ሕግ አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 31 ባሉት ዋስትና ሊያስፈቅድ
ወይም ሊያስከለክል የሚችል ቢሆንም ዋስትና መከልከሉ ይሻላል የሚል ግምት ሁሉ ወስዷል፡፡
83
ስለሆነም ፍርድ ቤቶች ግዴታቸውን ሊወጡ ይችላሉ የሚለው በመጨረሻው ፍርድ ቤት
ተቀለብሷል፡፡ ይልቁንም አጣሪ ጉባኤው በፍርድ ቤቶች ላይ እምነት መጣሉ ያላሳመነው
በሚመስል መልኩ በሀተታው ላይ አስፈሯል፡፡ በአስተያየቱ የመጨረሻ ክፍል ላይም “ሕግ
አውጪው… መፍትሔ ማፈላለግም እንዳለበትም ይታመናል” ማለቱ ድምዳሜው ስህተትም
እንዳበት በራሱ ጠቋሚ ነው፡፡ ሕግ አውጪውም ከፖለቲካ ጫና ነፃ በሆነ ጊዜ ስህተቱን ማረም
ያለበት መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው፡፡84
አሁን ላይም ዋስትና አስቀድሞ በሕግ አውጪው መከልከሉን ለማረም ፍርድ ቤቶች
አማራጮችን መጠቀም አለባቸው፡፡ አንደኛው ክስ እንደቀረበ ዋስትና መከልከሉ ላይ በክሱ
የተጠቀሰው ፍሬ ነገርና ድንጋጌውን መጣጣም መሰረት በማድረግ ተገቢውን ውሳኔ መስጠት
የሚገባ ነው፡፡ ሁለተኛው በክርከሩ ሂዴት ውስጥ አዲስ ነገር ሲኖር የተለወጠውን ሁኔታ
ግምት ውስጥ በማስገባት በዋስትናው ላይ ማሻሻያ ውሳኔ መስጠት የሚገባ ይሆናል፡፡ ክሱ
ሲቀርብ ዋስትና በሚያስከለክል ድንጋጌ ቢሆንም በብይን ጊዜ ተከሳሹ ተከላከል የተባለበት
ድንጋጌ ዋስትና ሊያስፈቅድ በሚችል ድንጋጌ ላይ የሚካተት ከሆነ ዋስትና መፍቀድ
የሚቻልበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡85 ከዚህ ላይ የድንጋጌ መለወጥ ሲኖር የሕብረተሰብን

82
ሰይድ ይመር እና የአማራ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙሽና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ፣ የፈደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት፣ 2001 ዓ.ም፣ የሰበር መዝገብ ቁጥር 34077፣ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ
ችሎት ዉሳኔዎች፤ ቅጽ 7፤ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ አዲስ አበባ፤ መጋቢት 09 ቀን 2000፤ ገጽ 287-
291፡፡
83
ሀሰን አብደላ እና የፌደራል ማዕከል ዓቃቤ ሕግ፣ የፈደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት፣ 2008
ዓ.ም፣ የሰበር መዝገብ ቁጥር 117383፣ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔዎች፤ ቅጽ 19፤
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22 ቀን 2008፤ ገጽ 246-249፡፡
84
እስከአሁን ባለው ሁኔታ የመንግስት አሰራር ባብዛኛው ስህተትን ሕገ ሳይንሱ እና ተቀባነት ባላቸው መርሆች
መሰረት ከማረም ይልቅ ሸፋፍኖ ማለፍ የተለመደ ነው፡፡ አሁን ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩን መለወጥ ብቻ እንኳ
ተከትሎ ከዚህ የአስተሳሰብ ችግር የመውጣት አዝማሚያ ስለሚታ አሁን ላይ ተመሳሳይ አቤቱታ ለአጣው ጉበኤ
ቢቀርብ ቀድሞ የያዘውን አቋም ይቀይራል የሚል እምነት አለኝ፡፡
85
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 83 ላይ የተጠቀሰው የሰበር መዝገብ ቁጥር 117383 ላይ እንደተወሰነው ይህ
አሰራር የሚቻል መሆኑን የሚደግፍ ነው፡፡

24
ጥቅም ማስጠበቅ ከሚለው ግብ አንፃር በዋስትና ጉዳዩ ላይ ዐቃቤ ሕግ በወንጀል ሥነ ሥርኣት
ህግ ቁጥር 67 መሰረት ምክንያት ያለው ሥለመሆን አለመሆኑ ማጣራትን መዘንጋት
አይገባም፡፡ ለዚህ መሰረቱ ደግሞ ቀደም ሲል ዐቃቤ ህግ የድንጋጌውን ዋስትና ማስከልከል ብቻ
መሰረት አድርጎ ሊከራከር ስለሚችል አሁን አዲስ ሁኔታ ስለተፈጠረ የመሰማት መብትን
ማክበር የሚገባ ይሆናል፡፡

2.3.3 የዋስትና ፅንሰ ሃሳብ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግና ሌሎች ሕጎች


በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉ ውስጥም ዋስትና በሁለት ዓይነት ሁኔታ ሊከለከል ይችላል፡፡
የመጀመሪው አንድ ሰው በወንጀል የተጠረጠረበት ወንጀል አስቀድሞ በህግ አውጪው ተከለከለ
መሆኑን የተያዘ ሰው በመጠርጠሩ ወይም በመከሰሱ ብቻ ሊታሰር ይችላል፡፡ ይህ የሚሆነው
የተከሰሰበት ወንጀል በዋስ የማያስለቅቀው መሆኑ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 63
በመሳሰሉ ድንጋጌዎች የተደነገገ ከሆነ ነው፡፡86 ከዚህ ድንጋጌ ጋር በሚመሳሰል መልኩ አደገኛ
ቦዘነኔትን ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 384/95 አንቀጽ 6(3)፣87 የፀረ ሙስና ልዩ ሥነ
ሥርኣት አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀፅ 4(1)፣88 የፀረ ሽብር ሕግ አዋጅ ቁጥር 652/2001
አንቀፅ 20(5) ዋስትና በሕግ አውጪው አስቀድሞ የሚከለከልበት ሥርዓት አለ፡፡ ከላይ
እንደተመለከትነው አሁንም የድንጋጌዎችን ህጋዊነት ለፌደሬሽን ምክር ቤት በማቅረብ መፈተሽ
የሚገባ ይሆናል፡፡ ቢያንስ ግን በእነጥላሁን አባይ ጉዳይ አጣሪ ጉባኤው በሰጠው ውሳኔ መሰረት
ፍሬ ጉዳዩን መወሰንን በተመለከተ ግን ፍርድ ቤቶች ሚናቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡
ሁለተኛው ደግሞ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 6789 መሰረት ዋስትና በቁጥጥር ሥር
የሚሆነው አንድ ተጠርጣሪ የዋስ መብት እንዲነፈግ ሊያደርጉት የሚችሉ ሁኔታዎች

86
የዋስትና ጉዳይ በተለይ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 63 መሰረት የተያዘ ሰው የተከሰሰበት ወንጀል
የሞት ቅጣትን ወይም 15 ዓመት ወይም በላይ የሆነ ጽኑ እሥራት የማያስቀጣው ከሆነና ወንጀል የተፈፀመበት
ሰው በደረሰበት ጉዳት የማይሞት የሆነ እንደሆነ ፍርድ ቤት የዋስትና ወረቀት አስፈርሞ ሊለቀው እንደሚችል
ይደነግጋል፡፡
87
አደገኛ ቦዘነኔትን ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ፣ 1996፣ ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ፣ አዋጅ ቁጥር 384፣ 10ኛ
ዓመት፣ ቁጥር 19
88
የተሻሻለው የፀረ ሙስና ልየ ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ አዋጅን ለማሻሻል አዋጅ፣2007፣ ፌደራል ነጋሪት
ጋዜጣ፣ አዋጅ ቁጥር 882፣ 21ኛ ዓመት፣ ቁጥር 37( ከዚህ በኋላ አዋጅ ቁጥር 882/2007 እየተባለ የሚጣራ)
ቁጥር 882/2007 በአንቀጽ 3 ላይ የአዋጅ ቁጥር 434 አንቀጽ 4(1)“ን” በመሰረዝ የዋስትና አቀራረብን ሲያሻሽል
ከ10 ዓመት በላይ በፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ዋስትና ማስከልከሉ እንደተጠበቀ ሆኖ ከ4 ዓመት በላይ ግን
ከ10 ዓመት በታች የሚያስጡ ወንጀሎች ተደራራቢ ሆነው ከ10 ዓመት ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ከሆነ ዋስትና
የሚያስከለክል መሆኑ ተደንግጓል፡፡
89
የፀረ ሙስና አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀፅ አንቀፅ 4(4) ላይም ተቀራራቢ መስፈርቶች ተደንግገዋል፡፡

25
ተሟልተው የተገኙ ከሆነ ነው፡፡ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 67 መሠረት ዋስትና
የጠየቀን ተጠርጣሪ ማመልከቻ መቀበል የማይቻለው:-
ሀ) በዋስትና ወረቀቱ የተመለከቱትን ግዴታዎች የማይፈፀም ነው ተብሎ ሲገመት፤
ለ) ሌላ ወንጀል ይፈጽም ይሆናል ተብሎ የሚገመት ሲሆን፤
ሐ) ማስረጃ ሊያጠፋ ይችላል ተብሎ ሲታሰብ ነው፡፡
ተጠርጣሪው የተከሰሰበት ወንጀል ዋስትና የማይከለከል ቢሆንም ከላይ የተጠቀሱትን የሚያሟላ
ሁኔታዎች ሲኖሩ የዋስ መብቱን ሊያጣ ይችላል፡፡ እነዚህ ፅነሰ ሀሳቦችም በሌሎች የሕግ
ሥርዓትም ውስጥ ያሉ ናቸው፡፡90 የእነዚህን ዋስትና መከልከያ መስፈርቶችን የሚተረጉመበትና
ውሳኔ ሰጭ አካላት ለውሳኔቸው መሰረት የሚያደረጉትን ምክንያት መመዘኑ ላይ ጥንቃቄ
የሚያስፈልገው ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሱት መስፈረቶች ዝግ ናቸው ወይስ ሌሎች መስፈርችን
ማካተት ይቻላል ወይ የሚለው ግልፅነት የጎደለው ነው፡፡ በድንጋው ንዑስ ፊደል “ሀ” ላይ
የጠጠቀሰው ግዴታ የማይፈጸምበት ምክንያት በሚለው በርካታ ነገሮችን ማጤን የሚያስችል
ይመስላል፡፡ ሆኖም ከጠቅላላው የወንጀል መርህ ተከሳሽን በሚጠቅም መልኩ መትረጎም ይገባል
በሚለው መሰረት አስፋፋቶ ተጠርጣሪን ዋስትና መንፈግ ተገቢ አይሆንም፡፡ ይልቁንም ከሕገ
መንግስቱም በመነሳት በገደብ ዋስትና ሲፈቀድ ተጠርጣሪው የተወሰኑ ሰዎች ጋር እንዳይገናኝ፣
ሱስ አመጪ ቁሶችን እንዳይጠቀም በመከልከል፣ ከሀገር እንዳይወጣ ሰነዶችን በአደራ በመያዝና
የመሳሰሉትን በመጠቀም በዋስ እንዲፈጣ ፈጠራዊ ውሳኔዎች ከጊዜ ለውጡ እና የቴክኖሎጀ
ዕድገት ጋር የተጣጣመ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
በዋስትና ወረቀት የሚገለፀው ዋነኛው ግዴታ በቀጠሮ ቀን ያለመቅረት ነው፡፡ ተከሳሹ ተመልሶ
ወደ ፍርድ ቤት የማይመጣ ነው ተብሎ ከተገመተ አይለቀቅም፡፡ ህብረተሰብን በተጠርጣሪው
ሊፈፀም ይችላል ከሚባል ተጨማሪ ወንጀል ለመጠበቅ ሲባልም ዋስትና ሊከላከል ይችላል፡፡
ሌላው ተጠርጣሪው ከዐቃቤ ሕግ ማስረጃዎች ጋር ካለው ቀረቤታም ይሁን በሌላ ምክንያት
ማስረጃ ያጠፋል፣ ምስክሮች ሊያባብል ይችላል የሚል ግምት ካለም የዋስትና መብቱ ተጠቃሚ
ላይሆን ይችላል ማለት ነው፡፡
በዚህ የሕግ አንቀጽ ሥር ከንዑስ ፊደል “ሀ - ሐ” የተጠቀሱትን ሁኔታዎች ለመቀበል ጥያቄው
የቀረበለት ፍርድ ቤት ግምት ብቻ በቂ መሆኑን ያሳያል፡፡ በእነዚህ ንዑስ ድንጋጌዎች ውስጥ
የተጠቀሱት “ግዴታዎቹን የሚፈጽም የማይመስል”፣ “ይሆናል ተብሎ የሚገመት” እና “ይችላል
90
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 2፡፡ በአውስተራሊያ ውስጥ፣ በአሜሪካን እንዲሁም ካናዳ ሀገራት ውስጥ
በመሳሰሉት የህግ ሰርዓቶች ውስጥ ያለና ዋስትና እና በቁጥጥር ስርን ለማጣጣም የሚያገለግሉ መስፈረቶች
ናቸው፡፡ ልዩነቱ ያለው የመስፈርቶች ዝርዝር ልዩነት የሚታይበት ነው፡፡

26
ተብሎ የሚታሰብ” የሚሉት ሐረጎች ግምትን ያመለክታል፡፡ የዚህ አገላለጽም ፍርድ ቤት
ከተባለው ግምት ላይ ለመድረስ ምንም መነሻ ሳይኖረው በዘፈቀደ የሚወሰነው አይሆንም፡፡
ለምሣሌ አንድ ተጠርጣሪ የዋስ መብቱ እንዲከበርለት ለፍርድ ቤቱ ሲያመለክት ዓቃቤ ሕጉ
ወይም መርማሪው ተጠርጣሪው ተደብቆ ከሀገር ሊወጣ ሲል መያዙን ቢያረጋግጥና በዋስትና
መለቀቁን ቢቃወም ፍርድ ቤቱ ይህ ተጠርጣሪ (ተከሳሽ) ቢለቀቅ አይመለስም ብሎ ለመገመት
በቂ መነሻ ምክንያት አለው ማለት ይቻል ይሆናል፡፡ የፌደራል ሰሚ ችሎትም በወንጀል ህግ
ሥነ ሥርዓት ሕግ 67 መሰረት የሚወሰድ ግምቶች በሰፊው መተርጎም የሌለበትና ዋስተና
ሲፈቀድ ከተገቢው ግዴታ ጋር በማቀናጀት መወሰን የሚገባ ስለመሆኑ ወስኗል፡፡91 በዚሁ
ድንጋጌ መሰረትም ድምዳሜ ላይ ለመድረስም ከተለያዩ አካባቢያዊ ሁኔታዎችና ከጉዳዩ ልዩ
ባህሪ እየታየ በፍርድ ቤት ግንዛቤ ሊወሰድባቸው የሚገባ መሆኑን በአስገዳጅት ወስኗል፡፡92
አንዳንድ ጊዜ ተከሳሹ ዋስትና የተነፈገበት ምክንያት ከተለወጠ በኋላም ያላግባብ የሚታሰርበት
አጋጣሚ አለ፡፡ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 67(ሐ) ሥር ማስረጃ ያጠፋል ወይም
ምስክር ያባብላል ተብሎ የታሰረ ተከሳሽ ማስረጃዎቹ ተሰብስቦ ከተጠናቀቀ በኋላ እሥሩ
ሊቀጥል የሚገባበት ምክንያት መኖር የለበትም፡፡
በአጠቃላይ የዋስትና መብት በተለይም በቅድመ ክስ የወንጀል ምርመራ ደረጃ ላይ
የተጠርጣሪው መታሰር ወይም ያለመታሰር ጉዳይ ከመከለከያ ማስረጃ አሰባሰብ ላይ አስተዋፅኦ
ያለው በመሆኑ ሚዛኑን የጠበቀ ሥርዓት እንዲኖር የፍርድ ቤት ሚና ወሳኝነት መኖሩ
የማይቀር ይሆናል፡፡ ተጠርጣሪውም አስቀድሞ የመንቀሳቀስ መብቱ ተገድቦ የሚቆይት በመሆኑ
ምክንያት ሰፊ ጥንቃቄ የሚደረግበት ነው፡፡ ተጠርጣሪውም በመታሰሩ የዕለት ከዕለት የሥራ
እንቅሳቃሴ ስለሚቋረጥም ከስራ መፈናቀል፣ ቤተሰብን ለችግር ማጋለጥ እንዲሁም
ለሚቀርብበት ክስም ማስረጃ ማሰባበሰብ የመሳሰሉት በተከሳሽ በኩል የሚያጋጥሙ ችግሮች
ናቸው፡፡ በጠቅላላው የህብረትሰብ ክፍል በኩል ደግሞ ተጠርጣሪውን ክሱን ያለመከታተል፣ ሌላ
ወንጀል ሊፈፅም መቻሉ፣ ከፍትህ ሊያመልጥ መቻሉ፣ ማስረጃዎችን ሊያጠፋ እንዲሁም
ምስክሮችን ሊያስፈራራ መቻሉ ግምት ውስጥ ገብቶ የተጠርጣሪውን መብት ሊያገድብ የሚችሉ
ምክንቶች ናቸው፡፡

91
አስናቀ በቀለ እና ዓቃቤ ሕግ፣ የፈደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት፣ 2001 ዓ.ም፣ የሰበር መዝገብ
ቁጥር 31734፣ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔዎች፤ ቅጽ 7፤ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ፍርድ
ቤት፤ አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15 ቀን 2000፤ ገፅ 275-282፡፡
92
እነጽጌብርሐን ተሰራ እና ዓቃቤ ሕግ፣ የፈደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት፣ 2001 ዓ.ም፣ የሰበር
መዝገብ ቁጥር 67874፣ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔዎች፤ ቅጽ 13፤ የኢፌዲሪ
ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15 ቀን 2000፤ ገፅ 275-282፡፡

27
3. የጊዜ ቀጠሮ እና የዋስትና የአቤቱታ አቀራረብና የክርክር አመራር
የጊዜ ቀጠሮ እና የዋስትና አቤቱታ ሲቀርብ በፍርድ ቤት ክርክር ተደርጎ የሚወሰን መሆኑ
ይታወቃል፡፡ ሆኖም ተከራካሪዎችን መለየቱንና የክርክር አመራርን በተወቀ መርህ የመስራት
ሁኔታ በፍርድ ቤቶች አይታይም፡፡ የሕጉን ይዘትና አሰራርም በቀጣይ እናያለን፡፡

3.1 የጊዜ ቀጠሮ እና ዋስትና የመመልክት የፍርድ ቤት የስር ነገር ሥልጣን


በወንጀል ሥነ ሥርዓቱ ያለው ድንጋጌ ቁጥር 64 መሰረት የዋስትና አቤቱታ በማናቸውም
ፍርድ ቤት ሊቀርብ ይችላል የሚል ነው፡፡ ሕጉ ቀደም ሲል የወጣ በመሆኑ አሁን ባለው
የመንግስት አወቃቀር የፌደራልና የክልል ፍርድ ቤቶች ሲዋቀሩ የፍርድ ቤቶች የስልጣን
ክፍፍል ሲደረግ የዋስትና ጉዳይ አብሮ ታሳቢ ስለመደረጉ መመርምር የሚገባ ነው፡፡93 ለዚህ
ማሳያም በሂዴት ሥነ ሥርዓታዊ ይዘት ያላቸው የተሻሻለው የፀረ ሙስና ልዩ ሥነ ሥርዓት
እና የማስረጃ ሕግ94 እና የፀረ ሽብር ሕግ ዋስትናንም በተመለከተ ለተለየ ፍርድ ቤት እንዲታይ
ያደረጉበትን ሁኔታን ማጤን ይቻላል፡፡
የጊዜ ቀጠሮ አቤቱታ የት መቅረብ እንዳለበት በግልፅ በሥነ ሥርዓት ሕጉ ላይ የሚያሳይ
ድንጋጌ የለም፡፡ ሆኖም የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ዓላማ በማረፊያ ቤት እንዲቆይ መጠየቅን
የሚመለከት ስለሚሆን እንዲሁም ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የማይፈቀድ ቢሆን ተጠርጣሪው
የዋስትና አቤቱታ ሊያቀርብበት የሚችልበት በተመሳሳይ ፍርድ ቤት እንዲታይ መደረጉ
ተቀባይነት ያለው ትርጉም ይመስላል፡፡95 ስለሆነም የዋስትና ጉዳይን ተመለካች ፍርድ ቤት
የጊዜ ቀጠሮን ጉዳይ የመወሰን የሥረ ነገር ሥልጣን ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
ለዚህ ማሳያም የፀረ ሙስና አዋጅ ቁጥር 434/1997 አንቀጽ 7(4) የቀነ ቀጠሮ፣ በማረፊያ ቤት
የማቆየት፣ ዋስትና እና ሌሎች ጉዳዮች የወንጀል ክሱን ለማየት ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት
የሚታይ መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡ በእርግጥ በአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ የአንቀፅ 7
ንዑስ አንቀጽ 5 የሆነውን ሲጨምር አግባብ ባለው አካል ውሳኔ እነዚህ ጉዳዮች ክሱን ለማየት
ሥልጣን በሌለው በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዲታይ የሥረ ነገር ለውጥ ማድረግ
ስለመቻሉ ተደንገጓል፡፡ ነገር ግን የድንጋጌው ይዘት ግልጽነት የጎደለው መሆኑን መረዳት
ይቻላል፡፡ የፀረ ሽብር ህግ አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 31(1)(ሀ) ላይ በዚህ አዋጅ መሰረት

93
አዋጅ ቁጥር 25/88፣ የፌደራል ጉዳይን ዋስትና በተመለከተ ውክልና ያልተሰጠው የወረዳ ፍርድ ቤት
ቢያስተናገድ ውጤቱ ምን ይሆናል የሚለው በግልጽ የተቀመጠ አይደለም፡፡
94
አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀፅ 7(4) እና አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 31(1)(ሀ)
95
ጊዜ ቀጠሮና ዋስትና በአንድ መዝገብ መስተናገድ አለበት በሚል ለሚከራከሩት የዋስትና ተመልካች ፍርድ ቤት
ይሆናል የሚለውን የሚያጠናክር ነው፡፡

28
የሚቀረቡ ጉዳዮችን የመዳኘት ሥልጣን የፌደራል ከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሆኑን
ተድንገጓል፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 20 መሰረት የተጨማሪ ምርመራ ጊዜ (ጊዜ ቀጠሮ) እና ዋስትና
በአዋጁ መሰረት የሚስተናገድ በመሆኑ ጊዜ ቀጠሮና ዋስትና ክርክሮች ከላይ ለተጠቀሱት ፍርድ
ቤቶች ብቸኛ የሥረ ነገር ሥልጣን ያላቸው መሆኑን መረዳት የሚገባ ነው፡፡96 በመሆኑም
አንዳንድ የዋስትና እና የጊዜ ቀጠሮ ክርክሮች በልዩ ሁኔታ ሥልጣን ለተሰጠው ፍርድ ቤት
እንዲታይ ህግ ሊያስገድድ ስለሚችል ልዩ ሕጎችን በቅደሚያ መዳሰስ ተገቢ ይሆናል፡፡

3.2 የጊዜ ቀጠሮና ዋስትና አቤቱታ አቀራረብና ተከራካሪዎች


ተጠርጣሪዎች አንድ ጊዜ በምርመራ ሂዴቱ ውስጥ ከገቡ በኋላ በሁለት ዓይነት ሁኔታ
በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ሊሆን ይችላል፡፡97 የመጀመሪያው መርማሪው አካል የምርመራ
ስራውን ሲያከናውን የማስረጃ አሰባሰቡ እንዳይደናቀፍ ተጠረጣሪውን በማረፊያ ቤት እንዲቆይ
አቤቱታ የሚቀርብበትን የጊዜ ቀጠሮን የሚመለከት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ተጠርጣሪው
የዋስትና አቤቱታ አቅርቦ ዋስትና የማይፈቀድለት ከሆነ በማረፊያ ቤት እንዲቆይ ሊደረግ
የሚችለበት ሁኔታ ነው፡፡ ሁለቱም ጉዳዮች የአቤቱታ አቀራረቡና የክርክር አመራሩና
በመካከላቸው ያላቸውን ልዩነት እንመለከታለን፡፡

3.2.1 የጊዜ ቀጠሮ አቤቱታ የአቀራረብና የክርክር አመራር


ተጠርጣሪን በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ሳይባል በወንጀል ሥነ ሥርኣተ ላይ “በማረፊያ ቤት
መቆየት”98 እና በሕገ መንግስቱ ላይ ደግሞ “በጥበቃ ሥር መቆየት” በሚለው የሚገልፀው ፅንሰ
ሃሳብ ነው፡፡ ይህም በተለመዶ “የጊዜ ቀጠሮ” እየተባለ ፋይል ተፍቶ የሚቀርበው ነው፡፡ ለጊዜ
ቀጠሮ ወይም ተጨማሪ ጊዜ መጠየቅን በተመለከተ ስለክርክር አመራሩና ስለተከራካሪዎች
ማንነት ሕገ መንግስቱና የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጎች ያሳያሉ፡፡
በመጀመሪያ ሕገ መንግስቱ አንቀፅ 19(4) ላይ ተጠርጣሪውን የያዘው ፖሊስ መኮነን ወይም
የሕግ አስከባሪ አቤቱታ አቅራቢ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር እንዲሆን
ዳኝነት የመጠየቅ መብት የሕግ አስከባሪ እንጂ የተጠርጣሪው እንዲሆን አይጠበቅም፡፡ የተከሰሰ

96
በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 78(2)፤ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሥልጣን በ2/3ኛ ድምጽ በፌደራሉ ምክር ቤት
እስካልተነሳ ድረስ በሕገ መንግስታዊ ውክልና የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሥልጣን ነው፡፡ በሐምሌ ወር 2010
ዓ.ም የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ለክልሉ ምክር ቤት ሪፖርት ሲያቀርቡ ወደ ፌደራል በህግ ወጥ
መንገድ ተወሰደ የሚለው ትክክል ነው፡፡ ውክልናው ተራ ውክልና ሳይሆን ሕገ መንግስቱን መሰረት ደረገና በልዩ
ሁኔታ በሕዝብ ተወካዮች ውሳኔ ብቻ የሚነሳ ነው፡፡
97
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ ፖሊሲ፣ 2003 ፣ የፍትህ ሚኒስቴር፣ አድስ
አበባ፤ የወንጀል ሕግ ፖሊሲዎች አራት ሲሆኑ አንደኛው የመንግስት ግዴታ በሚያመላክት አግባብ የሰፈረ ነው፡፡
98
ወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 59(1)

29
ሰውም በምርመራ ሥራው ላይ በንቃት የመሳተፍ ግዴታ አይኖርበትም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ
ደግሞ ጊዜ ቀጠሮን የመጠየቅ ክርክር አቀራረብን የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 59(2)
እና (3) ያሳያሉ፡፡ በዚሁ ድንጋጌ ንዑስ ቁጥር 2 ላይም በግልፅ ምርመራው ያልተፈፀመ
እንደሆነ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው የሚጠይቅ ስለመሆኑ በግልፅ
ተደንግጓል፡፡ በንዑስ ቁጥር 3 ላይ የአቤቱታው አቀራረብም በፅሁፍ መሆን ያለበት መሆኑን
በፖሊስ ላይ ግዴታ ይጥላል፡፡99
የጊዜ ቀጠሮን ሁኔታም አስመልክቶ ይግባኝ መቅረቡን በተመለከተ በሕጉ ላይ የሚያመለክት
አይደለም፡፡ ሆኖም የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 75 በሰበር ሰሚ ችሎት
እንደተተረጎመው የይግባኝ መብት መፍቀድ ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ጉዳዩን በኃላፊነት
ስሜት እንዲሰሩ ያደደረጋል፡፡ የሕጉ መነሻ የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ ጊዜዊ ዓላማ ያለው ነው
የሚለውን ታሳቢ ያደረገ ሊሆን ይችላል፡፡ በተግባር ግን በሀገራችንም ሆኖ በሌሎች ሀገሮች
ከውሳኔ በፊት በጊዜ ቀጠሮ ጨምሮ ለወራት ወይም ለዓመታት ጥፋተኝነት ሳይወሰንባቸው
ሊታሰሩ የሚችሉት ሁኔታ ያሉበት ነው፡፡100
በሌላ መልኩ የኢፌዲሪ ሕገ መንግስቱም ሆነ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ድንጋጌዎች ጉድለትም
ተጠርጣሪው በቀረበበት አቤቱታ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ ዕድል ያለው ስለመሆኑ የሚያመለክት
አይደለም፡፡ ፍርድ ቤቶች ግን ወጥነት ባይኖረውም ከልምድና ከእኩልነት መርህ አኳያ
ተጠርጣሪው የነፃነት መብቱን በመገደብ ሊታሰር እያለ ሳይሰማ መወሰን አሳማኝነት
ስለማይኖረው አስተያየቱን መጠየቅ የሚገባ ይሆናል፡፡101 የሕጉ አቀራረፅ ሲታይ በተለይም
የሕግ መንግስቱ አንቀጽ 19(4) መሰረት ጊዜ ቀጠሮ ፍትህ እንዳይጓደል አስፈላጊ ሲሆን ብቻ
የሚፈቀድ መሆኑ እንዲሁም በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጎች ላይ ለጊዜ ቀጠሮ የቀን ገደብ
መኖሩ በቁጥጥር ሥር መቆየትን አስፈላጊነትን መመርመርና መወሰን የፍርድ ቤት ኃላፊነት
መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤት ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመስጠት
ተጠርጣሪን በማረፊያ ቤት ለማቆየት በራሱ አነሳሽነትም ቢሆን አስፈላጊ ሰነዶችን አስቀርቦ
የመመርመር ግዴታ ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፍርድ ቤት ተጠርጣሪውንም ቢሆን

99
የፀረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 20(2) መርማሪው ፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው የመጠየቅ
መብት ያለው መሆኑን የሚያይ ነው፡፡
100
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 20፣ ገጽ 17
101
ዋስትናን በተመለከተ ግን ተጠርጣሪው ዋስትና ሲጠይቅ ዐቃቤ ሕግ ወይም መርማሪ ፖሊስ አስተያየት
እንዲሰጥ የሚደረግበት ሁኔታ በግልፅ ሰፍሯል፡፡

30
መጠየቅና ማጣራትን የሰብአዊ መብቶችን ከማስፈፀም ሕገ መንግስታዊ ግዴታው ጋር
የሚጣጣም ነው፡፡102

3.2.2 የዋስትና አቤቱታ አቀራረብና ክርክር አመራር


የዋስትና አቤቱታ የተያዘ ሰው በተጠረጠረበት ወንጀል በሕግ አካላት ደረጃውን ጠብቆ ውሳኔ
እስከሚሰጥ ድረስ ከማረፊያ ቤት ውጭ ሆኖ ክርክር ለማድረግ የሚቀርብ ሥርዓት ነው፡፡
የዋስትና መብት በፖሊስ103 ወይም በፍርድ ቤት104 ሊፈቀድ የሚችል መብት ነው፡፡ ዋስትናን
በመከልከል የመጨረሻ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን ግን የፍርድ ቤት ነው፡፡
ለፍርድ ቤት የሚቀርብ የዋስትና አቤቱታ ለመለቀቅ የሚቀርብ ማመልከቻ በወንጀል ሥነ
ሥርኣት ሕግ ቁጥር 64 መሰረት በተጠርጣሪው የሚቀርብና በፅሁፍ መሆን አለበት፡፡
በመሆኑም የዋስትና አቤቱታ መቅረብ ያለበት በተጠርጣሪው እንጅ በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ወይም
መርማሪ አካል እንዲሆን አይጠበቅም፡፡ ለዚህም የሕጉን ግልፅ ድንጋጌ በመተው በተግባር
ለተመለደው አሰራር ቦታ መስጠት ተገቢነት የለውም፡፡ በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ላይ ዋስትና
የተከለከለ ሰው የዋስትና አቤቱታ ባለቀረብኩበትና ዳኝነት ባልተጠየቀበት ሁኔታ መብቴ ተገደበ
በሚል አቤቱታ ቢያቀርብ ሕግን ባለመከተሉ ብቻ ውሳኔው መሻርና ተገቢውን ሥነ ሥርዓት
ተከትሎ ይወሰን ሊያሰኝ ይችላል፡፡
የዋስትና አቤቱታ አቀራረብ ሥርኣት የተፈፃሚነቱ ወሰን በክስ መስማት ጊዜ የተገደበ ነው
ለማለት የሚቻል አይደለም፡፡ የዋስትና አቤቱታ ቀርቦ ከተነፈገ ቅድመ ክስ ዋስትና ከሆነ ክሱ
እስከሚቀርብበት ጊዜ ድረስ ወይም ክስ ከቀረበ በኋላ ከሆነ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ
ተጠርጣሪውን በማረፊያ ቤት እዲቆይ ሊደረግ ይችላል፡፡ አንደንድ ጊዜም እስከ ሰበር ክርክር
ድረስ ዋስትና በመንፈግ በማረፊያ ቤት የማቆየት ሁኔታ አለ፡፡ ይልቁንም በሁሉም የክርክር
ደረጃዎች የዋስትና ጥያቄ ሲቀርብ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉ እንደአግባብነቱ ተፈፃሚነት
ኖረዋል የሚለው ሚዛን የሚደፋ ነው፡፡
የዋስትና አቤቱታ የቀረበለት ፍርድ ቤት ቶሎ ውሣኔ መሰጠት እንዳለበት የሚደነግገው ደግሞ
በወንጀል ሥነ ሥርኣት ሕግ ቁጥር 66 ነው፡፡ በዚህ ሕግ መሠረት ፍርድ ቤቱ ማመልከቻው
በደረሰው 48 ሰዓት ውስጥ ውሣኔ መስጠት ያለበት መሆኑን የሚደነግግ ሲሆን ከውሣኔው

102
የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 13(1)
103
ወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 28(1)
104
ወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 59(1)፤ የዋስትና አቀራረብ ሥርዓቱም በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር
63 - 79 ተደንግጓል፡፡

31
በፊት የዓቃቤ ሕጉን ወይም የመርማሪውን ሃሳብና ትችት እንደሚጠይቅ ያስቀምጣል፡፡ ይህ
ድንጋጌም በተግባር ከተጣሱትና ከተዘነጉት ሕጎች ውስጥ አንደኛው ነው፡፡
ለዚህም አስተዋፅኦ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ ወቅቱን የጠበቀ መልስ አለመቅረቡ ነው፡፡
በመሰረቱ ዐቃቤ ሕግም በመርማሪ አካል በኩል ስለሚሆን የዋስትና መፈቀድ መብትን በተግባር
እንዲከለከል ምንአልባት ፍልጎት ሊኖረው ይችላል፡፡ በመሆኑም ዐቃቤ ሕግ በዋስትና
ማመልከቻው ላይ ሃሳብ እንዲሰጥ ሲጠየቅ የምርመራ መዝገቡ በእጄ ስለሌለ የምርመራ
መዝገቡን ከፖሊስ ወስጄና ተመልክቼ አስተያየቴን ለማቅረብ ጊዜ ያስፈልገኛል ይላል፡፡ ይህንን
ፍርድ ቤት መቀበል ሳይሆን መርማሪውን አስተያየትና ከምርመራ መዝገቡ ጋር መርምሮ ሕግ
ባስቀመጠው የ48 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ውሣኔ ለመስጠት ይኖርበታል፡፡ ከሕጉ ከተቀመጠው ጊዜ
በላይ ጉዳዩን የሚያራዝም የተጨማሪ ጊዜ ሊጠይቅና ሊፈቀድለት የሚገባ አይደለም፡፡ ሆኖም
የዋስትና ጉዳዮችን ለብቻው የሚያዩ ችሎቶች ባለመኖራቸው እንዲሁም ዳኞች የጊዜ ገደቡን
አክብረው ውሣኔ ለመስጠት ሲቸገሩ ይታያል፡፡105 ስለሆነም ክስ ለፍርድ ቤት በቀረበበት ጉዳይ
ከሆነ ዐቃቤ ሕግ የምርመራ መዝገቡን አይቶ ክስ የሚያዘጋጅ እንደመሆኑ እና በፍርድ ቤት ክስ
ያልተመሠረተበት ጉዳይ ከሆነም መርማሪው ምርመራ መዝገቡ በእጁ የነበረ እንደመሆኑ
መጠን ወዲያውኑ አስተያየቱን ለመስጠት ይቸገራል ሊባል አይችልም፡፡ ፍርድ ቤቶችም ቢሆኑ
የዋስትና ማመልከቻ ከሌሎች ጉዳዮች በተለየ ሁኔታና በአጭር ጊዜ እንዲወስኑ ሕግ የሚጠይቅ
በመሆኑ ቅድሚያ ሰጥተው ሊወስኑ ይገባል፡፡
ተጠርጣሪ (ተከሳሽ) ያቀረበው በዋስ የመለቀቅ ማመልከቻ ተቀባይነት ካገኘ ተከሳሹ ዋስ
እንዲጠራ ወይም ገንዘብ እንዲያስይዝ ይታዘዛል፡፡106 ነገር ግን የዋስትና ልክን በመወሰን ረገድ
ለተመሳሳይ ጉዳዮች በዳኞች ዘንድ ያለው ልዩነት ከፍተኛ ነው፡፡ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ
ቁጥር 69 ሥር ፍርድ ቤት የዋስትና ገንዘብ መጠንን በመሰለው እንደሚወስን ቢደነገግም
የወንጀሉን ከባድነት፣ ተከሳሹ ከቀጠሮ የማይቀር መሆኑን የተከሳሹንና የዋሱን ሀብት መጠን፣
ሲለቀቅ ያለውን አደጋ (በህዝብ ፀጥታ ላይ) ማገናዘብ እንደሚገባም ሠፍሯል፡፡ የዋስትና ውሉ
ግዴታ መጠንና ዓይነት መጠቀስ አለበት፡፡ የግዴታው መጣስም ዋስትና በተከለከለበት ነጥብ
ላይ መሆን ይኖርበታል፡፡

105
ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ውስብስብ ሁኔታዎች ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ዳኞችና ዓቃቤ ሕጐች ፍትህ እንዳይጓደል
በጥንቃቄ ሊሰሩ ይገባል፡፡
106
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 68፤ በአሜሪካን የሕግ ሥርዓት ውስጥ የዋስትና መብት የንግድ ባሕሪ
እየተላበሰ ነው የሚሉ አሉ፡፡ በአሜሪካን ሀገር ውስጥ አከራካሪው ዋስትና መፍቀድ ሳይሆን ገንዘብ የሌላቸው
ሰዎች በተግባር ከፍተኛ ገንዘብ እየተጠየቁ ዋስትና ተከለከሉ የሚል ነው፡፡

32
ለአንድ ተከሳሽ የዋስትና ወረቀት ፈርሞ ዋስ የሆነ ሰው ተከሳሹ በየቀጠሮው ፍርድ ቤት
እንዲቀርብ የማድረግ ግዴታና ኃላፊነት አለበት፡፡ የዋስትና ግዴታ የሚገባ ሰው ይህ ግዴታው
ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ በፍርድ ቤት ይወሰናል፡፡ ይህ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉ
የሠፈረ ቢሆንም107 ብዙ ጊዜ ፍርድ ቤቶች ሲጠቀሙበት አይታይም፡፡ በወንጀል ሥነ ሥርዓት
ሕግ ቁጥር 71(2) መሠረት የዋስትናው ግዴታ የሚቆይበትን ጊዜ የመወሰን ልምድ ባለመኖሩ
አንዳንዴ ችግር ሊከሰት ይችላል፡፡108 የዋስትና ወረቀት ፈርሞ ግዴታ የገባ ሰው ፍርድ ቤት
ግዴታው የሚቆይበትን ጊዜ ካልወሰነ ጉዳዩ ዕልባት እስኪያገኝ ድረስ ይቆያል፡፡ ነገር ግን
ተጠርጣሪ(ተከሳሽ) በዋስ ከተለቀቀ በኋላ እንደገና ከተያዘ ወይም ዋሱ የዋስትና ግዴታውን
ፍርድ ቤት ቀርቦ ካወረደ ጉዳዩ ከማለቁ በፊትም ግዴታው ቀሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለሆነም
ፍርድ ቤት በተለይ ከክስ በፊት የዋስ መብታቸውን ለሚጠብቅላቸው ተጠርጣሪዎች የዋሶቹን
የግዴታ ጊዜ በመወሰን የዋሶቹ የግዴታ ጊዜ ያላግባብ እንዳይራዘም ስለሚያደርግ የወንጀሉን
ከባድነትና ነባራዊውን ሁኔታ በማገናዘብ ሕጉን መተግበሩ ጠቃሚ ነው፡፡109
የዋስትና ማመልከቻው ተቀባይነት ያላገኘ ተጠርጣሪ ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በሀያ ቀናት
ውስጥ ይግባኝ ማመልከቻውን ማቅረብ እንደሚችል የተደነገገ ነው፡፡110 ይህን አንቀጽ
አስመልክቶ የሚነሳው ጥያቄ ይግባኝ ለማለት የተፈቀደው ለተከሳሽ/ተጠሪጣሪ ብቻ መሆኑ
የሚለው ነው፡፡ በዚህ ረገድ ተከሳሽ ያለውን መብት ለማሳየት ሕጉ በዚህ መልክ የተቀረፀ እንጂ
የዋስ መብት በማይፈቅድ ወንጀል የተከሰሰን ሰው በፍርድ ቤት በዋስ ቢለቀቅ ዓቃቤ ሕግ
ይግባኝ እንዳይጠይቅ የሚከለክለው አለመሆኑን የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎትም አስገዳጅ ውሳኔ
ሰጥቶበታል፡፡111

107
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 71
108
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 67፣ ገጽ 522፤ በቅድመ ክስ መለቀቅ ላይ ዋስትና ዓይነቶች የራስ
ዋስትና(personal recognizance)፣ በሌላ ሰው ቁጥጥር ስር እንዲቆይ ማድረግ (release to the custody of
another)፣ ገንዘብ ወይም ንብረት ማስያዝ(posting an individual bond) እና የሌላ ሰው አርቦን በመክፈል
ዋስትና ማስያዝ (posting a suerty bond/bail bond) የሚባሉት አሉ፡፡ በአሜሪካኖች የተለመደው የመጨረሻ
ሲሆን ተጠርጣሪዎች የዋስትናውን 10% ያክል ለድርጅት ይከፍሉና በዋስ ይወጣሉ፡፡ በዚህም አሳሳቢው ጉዳይ
ዋስተና ገንዘብ ባለመኖር እንዳከለከል ጥንቃቄ ይደረግ የሚለው እስከሕገ መንግስታቸው ይዘልቃል፡፡ ዋስትናንም
የንግድ ሥራ በማድረጋቸው ተወቃሾች ናቸው፡፡
109
ዋስትና በምን ስም መያዝ አለበት የሚለው መለየት ይኖርበታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ተከሳሽ የሆነ ሰው ዋስ
እንዲጠራ ሲደረግ ሌላ ሰው በስሙ ገንዘብ ያስይዝና ይጠፋል፡፡ በዚህ ጊዜ ገንዘቡን ያስያዘው ሰው ቀርቦ ገንዘቡ
ይለቀቅልኝ በማለት ሲጠይቅ ሊለቀቅለት ስለመቻሉ ያከራክራል፡፡ በአንድ ወቅት የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ደቡብ ጎንደር ተዘዋዋሪ ችሎት፣ መዝገብ ቁጥር 14049፣ አስካል ዘርፉ እና ዐቃቤ ሕግ በሚለው መዝገብ ላይ
ይግባኝ ባይ የዋስትና ገንዘብ ለሌላ ሰው አስይዛና ተከሳሹ ሳይቀርብ ቀርቶ መዝገብ በተዘጋበት ገንዘቡ
እንደለቀቅላት ቅሬታ አቅርባ ገንዘቡ አይመልስም የሚለው ውሳኔ ፀንቷል፡፡
110
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 75
111
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 9

33
ፍርድ ቤት በዋስ የለቀቀውን ሰው መልሶ ማሰር ወይም ሌላ ዋስ እንዲጠራ ሊያደርግ ይችላል፡፡
ይህ የሚከሰተው በበርካታ ምክንያቶች ነው፡፡ ዋሱ ቢሞት፣ ከሀገር ቢጠፋ፣ ወይም ግዴታውን
ሊወጣ የማይችል መሆኑ ሲታወቅ ነው፡፡112 ተከሳሽ ዋስ ጠርቶ ከእስር ከተለቀቀ በኋላ
በቀጠሮው ቀን ባይቀርብ እንዲያዝ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ዋሱም የዋስትና ግዴታ የገባበትን የገንዘብ
መጠን ለመንግሥት ገቢ የማያደርግበት ምክንያት ካለው ቀርቦ እንዲያስረዳ ይጠየቃል፡፡ ካላስረዳ
ገንዘቡን ገቢ እንዲያደርግ ይታዘዛል፡፡113 ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው ዋሱ ግዴታ የገባበትን
ገንዘብ ከመክፈል ያለፈ ሌላ ተጠያቂነት እንደሌለበት ነው፡፡ በሕጉ ከተመለከተው ውጭ ዋሱን
ተከሳሽን ይዘህ ቅረብ ማለትም ሆነ ዋሶችም የግዴታቸውን ወሰን ባለመረዳት ፍርድ ቤት
ቀርበው ተከሳሹን ይዘው ለመቅረብ እንዲችሉ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው መጠየቅ ተገቢ
አይሆንም፡፡
ፖሊስ ዋስትና ከመፈቀዱ በፊት ተጨማሪ የምራመራ ጊዜ የሚጠይቅ ከሆነ የዋስትና ጥያቄን
ማስተናድ የሚቻል አይሆንም፡፡ ይልቁንም በቅድመ ክስ ዋስትና አቤቱታ ላይ ዋስትና የሚነፈግ
ቢሆን የሚቆይበት ጊዜ ተለይቶ የሚታወቅ አይደለም፡፡ ይህ ሲሆን ግን ጥፋተኛ ሳይባል የታሰረ
ሰው ላልተወሰነ ጊዜና ክስ እንኳ ሳይቀርብበት ለዓመታት ጭምር እንዲታሰር ዕድል ሊፈጥር
ይችላል፡፡ ዐቃቤ ሕግ ክስ ሳይመሰርት አላግባብ ተጠርጣሪው ታስሮ ካዘገየም ፍርድ ቤቶች ሚና
ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀፅ 109 መሰረት የምርመራ መዝገቡ
የደረሰው ዐቃቤ ሕግ በ15 ቀን ውስጥ ክስ ማቅረብ አለበት በሚል ተደንግጓል፡፡ ይህ ከሆነ
ደግሞ ዋስትና ለቅደመ ክስ ሂዴት ሲፈቀድ ለተወሰነ ቀን ብቻ ዋስትና መከልከል ወይም በ15
ቀን ውስጥ ክስ ካልቀረበበት ለፍርድ ቤት አቤቱታ እንዲያቀርብ እድል በመስጠት ሊወሰን
ይችላል፡፡ ፍርድ ቤት የዘገየበትን ሁኔታ በማጣራት በህጉ ምርመራ በፍጥነት መከናወን አለበት
የሚለውን የሥነ ሥርዓት ሕግ ይዘት ማስፈፀም አለበት፡፡ ይህም አሰራር ዐቃቤ ሕግ ክስ
የማቅረቢያ ጊዜውን ሕጉ ከሰጠው ጊዜ በላይ ቢያራዝም ፍርድ ቤቶች የሚቆጣጠሩበት አግባብ
ሊኖር ይገባል፡፡114

112
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 70-74
113
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 76
114
የኢትዮጵያ ቴሌቪሽን፣ ሐምሌ 27 ቀን 2010 ዓ.ም በተላለፈው ዜና ላይ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በተደረገው
ሠልፍ ላይ ጥቃት ያደረሱ ሰዎች ዋስትና ሲነፈጉ 15 ቀን ለዐቃቤ ሕግ የክስ ማቀረቢያ ጊዜ ተሰጠጣቸው
የሚለው የሚደገፍ አሰራር ነው፡፡ ከአሁን ቀደምም የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የሚሰራበት መሆኑን ጸሀፊው
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ በነበረበት ጊዜ የተረዳው ጉዳይ ነው፡፡

34
3.2.3 የጊዜ ቀጠሮና የዋስትና አቤቱታ አቀራረብ መሰረታዊ ልዩነት
ጊዜ ቀጠሮ እና ዋስትና ተጠርጣሪውን በማረፊያ ቤት እንዲሆን የሚያደርጉበት አጋጣሚ
መኖሩ ላይ ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ተጨማሪ ጊዜ የሚፈቀድበት በቂ ምክንያት ከሌለ እና
የተጠረጠረበት ወንጀል ዋስትና የማያስነፍግ ከሆነ ተጠርጣሪው በዋስትና እንዲለቀቅ ፍርድ
ቤቱ ማዘዝ አለበት የሚለው አገላለጽ ላይም ክርክር ሲያስነሳ ይታያል፡፡ በመጀመሪያው በአንድ
ወገን በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ላይ መከራከር አለባቸው የሚሉት መሰረት የሚያደርጉት የወንጀል
ሥነ ሥርኣት ህግ ቁጥር 59(2) የጊዜ ቀጠሮ ካልተፈቀደ ዋስትና መፈቀድ አለበት በሚል
ተደንግጓል፡፡ የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ከተዘጋ ለተጠርጣሪዎች መብት ለመስጠት ሲባል በዚያው
መዝገብ ዋስትና መፍቀድ ይገባል የሚሉ አሉ፡፡ በርካታ የሕግ ባለሙያዎችን የሚያሳስባቸው
ተጠርጣሪው በጊዜ ቀጠሮው መዝገብ ላይ ዋስትና ካልተየለት ራሱን ችሎ አቤቱታ ሊያቀርብ
አይችልም የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የዋስትና ክርክር ራሱን ችሎ
ተጠርጣሪው በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 64 መሰረት አቤቱታ አቅርቦና አመልካች
የሆነበት መዝገብ ተከፍቶ ተገቢው ክርክር መደረግ አለበት የሚል ሀሳብ አለ፡፡
የጊዜ ቀጠሮ እና ዋስትና የዓላማ መቀራረብና በውጤት ደረጃ ተጠርጣሪውን በማረፊያ ቤት
የማቆየት ውጤት ስላለቻው ብቻ ተመሳሳይ ናቸው የሚባል አይሆንም፡፡ በልዩነት ደግሞ
የዓላማ፣ የቆይታ ጊዜ፣ የሚጠይቀው አካል፣ የሚቋረጥበት ሁኔታ፣የክርክር የሚነሳበት ደረጃ
ላይ የሚነፀባርቅበት አግባብ አለ፡፡ ስለሆነም ልዩነት ያላቸውን ጉዳዮች በአንድ መዝገብ ላይ
ማስተናገድ ተገቢነትን ማጤን የሚገባ ነው፡፡ ሁለቱ ጉዳዮች በአንድ መዝገብ መስተናገዱ
ያልታሰቡ ችግሮችን የሚያስከትል ስለመሆኑ እንደሚከተለው ማሳያዎች አሉ፡፡
በመጀመሪያ የጊዜ ቀጠሮ የማይጠየቅበት ሰው ሁልጊዜ በዋስትና ይፈታል የሚለው ድምዳሜ
የሕገ መንግስቱንም ድንጋጌ ያከበረ አይደለም፡፡ የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ በህግ አውጪው አስቀድሞ
የሚከለከል ወይም የሚፈቀድ ሳይሆን የወንጀል መርማሪ ምርምራውን ለማከናወን እንዲረዳው
ተጠርጣሪውን በጥበቃ ስር በማድረግ ለማጣራት እንዲችል ጊዜ እንዲሰጠው የፍርድ ቤትን
ይሁንታ የሚጠይቅበት ሁኔታ ነው፡፡115 ይልቁንም በሕግ ዋስትና በሚያስከለክል ድንጋጌ ወይም
በፍርድ ቤት ታይቶ ዋስትና የመከልከል ሁኔታ ባለበት ሁኔታ ጊዜ ቀጠሮ ካልተሰጠ የግድ
በዋስትና መለቀቅ ነው መባሉ የሕግ ድጋፍ ያለው ሀሳብ አይመስልም፡፡

115
የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 19(4) እና የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 59(2) እና (3) ጣምራ ንባብ
ይህንን ፅንሰ ሃሳብ የሚያሳይ ነው፡፡

35
ሁለተኛ ደግሞ በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ላይ በዋስትና ጉዳይ ላይ አግባብ ያለው አካል ክርክር
ሳያደርግ የመወሰን ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ የወንጀል መርማሪዎች በወንጀል ሥነ ሥርዓቱም
እንደተመለከተው ተግባራቸው የምርመራ ስራቸውን አጠናቀው ክስ ለሚያቀርበው ሥልጣን
ላለው ዐቃቤ ሕግ ማስተላለፍ ነው፡፡ በተጨማሪም የዋስትና መብትን የመጠየቅ መብት ያለው
ተጠርጣሪው ነው፡፡ ይህ ከሆነ በአመልካችነት መዝገቡ መከፈት ያለበት ተጠርጣሪው አመልካች
ሆኖ ተጠሪ ደግሞ ሲቻል ለጉዳዩ አግባብነት ያለው ዐቃቤ ሕግ116 ወይም ከሌለ መርማሪው
ስለመሆኑ በሕግ የተደነገገ ነው፡፡117 ስለሆነም በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ላይ አከራክሮ መወሰን
ያልተጠየቀ ዳኝነት ከመሆኑም በላይ የተጠረጠረ ሰው በአግባቡ መብቱን እንዳይጠይቅ
የሚደርግና ለጉዳዩ ተገቢው የሆነው ዐቃቤ ሕግ መልስ እንዲያቀርብ እድል የማይሰጥ አሰራርን
የሚፈጥር ይሆናል፡፡
በሶስተኛ ደረጃ በጊዜ ቀጠሮና የዋስትና በመጠኑም ቢሆን የዓላማ ልዩነት አላቸው፡፡ የጊዜ
ቀጠሮ ዓላማ የወንጀል መርማሪ የወንጀል ምርምራ እንከሚያጠናቅቅ ድረስ ያለውን ሂዴት
የሚመለከት ነው፡፡ ፖሊስ ዋስትና ቢቃወም እንኳ ምርምራውን እስከሚያጠናቀቅ ጊዜ ድረስ
ተጠርጣሪው በማስረጃ አሰባሰብ ላይ ጫና ይፈጥራል የሚለውን ብቻ በመጠቅስ በመከራከር
ነው፡፡ አንድ ከባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተጀመረ ጉዳይ የዚህን ክርክር አመራር
መቀላቀል ችግር የሚያሳይ ነው፡፡ በከፍያለው አደባባይ እና ዐቃቤ ሕግ118 በባህር ዳር ከተማ
ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 101410 በሆነው ሲከራከሩ ላይ ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ
አቤቱታ ሲያቀርብ እንደሚከተለው አቅርቧል፡፡ በአቤቱታው ይዘትም፡-
… የምርመራ ቡድኑም እየተንቀሳቀሰ እየሰራ እና ማስረጃ እያሰባሰበን ሲሆን በተከሳሽ ላይ
አመላካች ማስረጃዎች እያገኘን በመሆኑ ተከሳሽ በዋስ ቢወጣ ላይገኝና ማስረጃውን ሊያበላሽብን
ስለሚችል ቀሪ ማስረጃዎችም ሰብስበን ያልጨረስን በመሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 59(3) መሰረት
የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንድሰጠን ስንል እንጠይቃለን፡፡
በሚል የቀረበ ነው፡፡ ከዚህ ማስረጃ መሰብሰብ ዓላማ በመለስ መዝገቡ የተላለፈለት ዓቃቤ ሕግ
ክሱ የሚመሰረትበትን ድንጋጌ ዋስትና ሊያስከለክል የሚችል መሆን አለመሆኑንና በዋስትና
ቢወጣ ለወደፊቱ ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቶም ቢሆን ምስክሮችን እስከሚያሰማ ተጠርጣሪው

116
የፌደራል ወንጀል ጉዳይ ሥልጣን ያለው የፌደራል ዐቃቤ ሕግ ነው፡፡ በሌላ መልኩ የፀረ-ሙስናና የገቢዎችና
ጉሙሩክ ዐቃቤ ሕግን የሚመለከት ጉዳይ በልዩ አቃቤ ሕግ የሚታይ ነው፡፡ ምንአልባትም የምርመራ ስራውን
ለፖሊስ ወክሎ ክሱ ግን በልዩ ዐቃቤ ሕግ በኩል የሚስተናገድ ነው፡፡
117
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 64
118
ከፍያለው አደባባይ እና ዐቃቤ ሕግ፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የሰበር መዝገብ
ቁጥር 67712፣ 2010 ዓ.ም (ያልታተመ)፡፡

36
ሊያስከትል የሚችለውን የፍትህ መዛባት የሚመለከት አይደለም፡፡119 በዚህ ምክንያትም
እንደሁኔታው የተጠርጣሪው መብትን ወይም የተጎጅዎችን መብት (የሕዝብን ጥቅም)
የሚመለከት ክርክሮች በሕግ አግባብ ሙግት ሳይደረግ ውሳኔ የሚሰጥበትን ሁኔታ የሚፈጥር
ይሆናል፡፡ በከፍያለው አደባባይ ጉዳይ ላይ የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ላይ ጉዳዩ ሲስተናገድ የወረዳ
ፍርድ ቤቱ ለ5ኛ ጊዜ የጊዜ ቀጠሮ አልፈቅድም በሚል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ተጠርጣሪውም
በዋስትና ማመልከቻ ሳያቀርብ እና ዳኝነት ሳይጠይቅ እንዲሁም ያቀረበውን ፖሊስን ወይም
ሥልጣን ያለውን ዓቃቤ ሕግ መልስ እንዲሰጠበት ሳያደርግ ወይም በቃል እንኳ ሳይሰማ
በቀጥታ ለ5000 ብር የሚበቃ ዋስ ሲያቀርብ ከእስር እንዲፈታ በሚል ወስኗል፡፡ ይህ ትዕዛዝም
ወንጀሉ ከባድ ቢሆን ተጠርጣሪው ለሕዝብ ፀጥታ አደገኛ ቢሆን መቻኮል ያለበት መሆኑን
የሚያሳይ አሰራር ነው፡፡ ዋስትና መፍቀድ በበቂ ምክንያት ሲደገፍ እንጅ ሁልጊዜ ተገቢ ውሳኔ
ነው ብሎ መደምደም የሚገባ አይሆንም፡፡
በአራተኛ ደረጃ የዋስትና ጉዳይ በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ላይ ተደርቦ ሲስተናገድ አንዳንድ ጊዜ
የትዕዛዝ ግጭት ይፈጠራል፡፡ እንዲህ በሆነ ጊዜ በማረሚያ ቤቶች እና በፍርድ ቤቶች መካከል
የትዕዛዝ አፈፃፀም ችግር ሲከሰት ይስተዋላል፡፡ ከላይ ባየነው የከፍያለው አደባባይ ጉዳይ የጊዜ
ቀጠሮ እና የዋስትና መዝገቦች ላይ በዋስትና መዝገቡ ላይ ዋስትና የተከለከለ ሲሆን
በተቃራኒው ደግሞ በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ላይ ደግሞ ዋስትና ተፈቅዷል፡፡ ሁለቱም ትዕዛዞች
እኩል የሥልጣን እርከን ባላቸው ችሎቶች የተሰጡ በመሆኑ እና ትዕዛዞችም እኩል ተፈፃሚነት
ያላቸው ስለሆኑ አንዱን መርጦ መፈፀም ዘፈቀዳዊ አሰራር ይሆናል፡፡ ሌላው ቀርቶ በጊዜ
ቀጠሮ የዋስትና ጉዳይ ከተስተናገደ እና ራሱን ችሎ የዋስትና መብት ከተስተናገደ ለይግባኝ
መሰረት የሆነው መዝገብና በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ የተሰጠው ትዕዛዝ ጋር ከተጋጩ የይግባኝ
ሥርዓት ትዕዛዝ የአፈፃፀም እና የይግባኝ ክርክር አመራርም ላይ ችግር አለው፡፡
ለዚህ ማሳያውም በከፍያለው አደባባይ ጉዳይ ላይ በዋስትና በዋስትና መዝገቡ ላይ ክርክር
ተደርጎ ተመሳሳይ ፍርድ ቤት የጉዳዩን ክብድት መዝኖ በተሰጠው ትዕዛዝ ላይ እስከ ክልሉ
ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ ክርክር እየተደረገ እያለ፤ በሌላ መልኩ የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ
እየተስተናገደ ስለነበር የወረዳው ፍርድ ቤት በጊዜ ቀጠሮ መዝገቡ ላይ ተጠርጣሪው በዋስትና
እንደለቀቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የሰበር ችሎቱ ጉዳዩን አጣርቶ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት በጊዜ
ቀጠሮ መዝገብ ላይ ዋስትና መፈቀዱን ተረዳው እንጅ የአመልካች ዋስትና መከልከል ተገቢ
የሚለውን ወረዳው ፍርድ ቤት ውሳኔ በቅርቡ ከሰጠው ውሳኔ ጋር ስለሚቃረን ውጤቱ ምን

119
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥሮች 63 እና 67

37
ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል፡፡ ይህ ሁኔታም የሚያስገነዘብን የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ በሌላ
ፍርድ ቤትም ቢሆን ከተጀመረ የዋስትና ጉዳዩ መስተናገድ የሌለበት መሆኑን ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ
የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ መኖሩን ካረጋገጠ የዋስትና መዝገቡን ለጊዜው በመዝጋት መጠበቅ ወይም
በሌላ ፍርድ የማመልከት መብቱን መጠበቅ አለበት፡፡ አለበለዚያ የትዕዛዝ ግጭት ሊፈጠር
ስለሚችል ለአፈፃፀም አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡120
ሲጠቃልም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ በተስተናገደው የከፍያለው አደበባይ ጉዳይ
የሚያሳየን የጊዜ ቀጠሮና ዋስትና ከአለመለየት ክርክሩን የተደበላለቀ እንዲሆን አንዳደረገው
ነው፡፡ የዋስትና ክርክሩም በሕግ አግባብ የተስናገደ ሳይሆን ከጊዜ ቀጠሮ ጋር ያለውን ፅነሰ
ሀሳብ ዐቃቤ ሕግም ሆነ ችሎቱ ባለመለየት መወሰናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ የባሕር ዳር ከተማ
ወረዳ ፍርድ ቤት አመልካች በዋስትና ልፈታ የሚል አቤቱታ አቅርቦ ተጠሪ ዐቃቤ ሕግ ማስረጃ
ተሰብስቦ ያለተጠናቀቀ ስለሆነ የጊዜ ቀጠሮ ክርክር እስኪጠናቀቅ ድረስ አመልካች የጠየቀውን
ዋስትን እቃወማለሁ በማለት መልስ ሰጥቷል፡፡ ችሎቱም በአመልካቸ ላይ የተጀመረው የጊዜ
ቀጠሮ ክርክር ያልተቋጨ መሆኑን ግንዛቤ በመወሰድ ተጠርጣሪው አስቀድሞ ከእስር ቢወጣ
ማስረጃ ያጠፋል በሚል በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 67(ሐ) መሰረት ዋስትና
አልተፈቀደም በማለት ወስኗል፡፡ ሆኖም በትንሽ ቀናት ልዩነት፣ በዋስትና መዝገቡ ላይ የሰጠው
ውሳኔ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የጊዜ ቀጠሮ ክርክሩ ላይ በመዝገብ ቁጥር 101410 በሆነው ለ5
ተከታታይ የጊዜ ቀጠሮ መሰጠቱን በመግልፅ ለ5000 ብር የሚበቃ ዋስትና በመፍቀድ
መዝገቡን ዘግቶታል፡፡
የሰበር ችሎቱም የወረዳው ፍርድ ዋስትና በመከልከሉ ላይ የሰበር ክርክር የሚደረግ ቢሆንም
የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡን አስቀርቦ ተመልክቷል፡፡ አመልካችም የዋስተና መብቱ በባህር ዳር ከተማ
ወረዳ ፍርድ ቤት አቅርቦ የተነፈገ ቢሆንም በዚሁ ጉዳይ በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ዋስተና
የተፈቀደለት መሆኑ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለዋስትና አቤቱታው ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ከታች
በተፈጠረው የተዛባ አሰራርም የሰበር ችሎቱም የዋስትናውን ጉዳይን ራሱን ችሎ አለመመዘኑ
ስህተት ነው፡፡ በሌላ መልኩ ግን የወረዳው ፍርድ ቤት በጊዜ ቀጠሮው መዝገብ ላይ ዋስትና

120
ይህን ችግር በአንድ መዝገብ ላይ የተከሰተ አጋጣሚ ሳይሆን ፀሀፊው በደቡብ ወሎ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና
በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተለይም በሰበር ችሎት ደጋግሞ የሚከሰት ችግር እንደነበር የሚገነዘበው ነው፡፡

38
ፈቅዶለት እያለ በዋስትና መዝገቡ መከልከሉን ቢያፀና የትኛው ውሳኔ መፈፀም አለበት
የሚለውን ሀሳብ ቀሪ አያደርገውም፡፡121
ሲጠቃለለም ለተጠርጣሪው የጊዜ ቀጠሮውን መዝገብ ሲዘጋ የዋስትና አቤቱታ የማቅረብ መብት
ያለው መሆኑን እስከተነገረው ድረስ የዋስትና አቤቱታ ላያቀርብ ይችላል የሚለው የሰውን
በምክንያታዊነት ማሰብ መቻሉን የሚሰጥስ ነው፡፡ ይህ የሚያጠራጥር ልዩ ሁኔታ ካለም በሕገ
መንግስቱ አንቀጽ 20(5) መሰረት ፍትህ እንዳይጓደል በመንግስት ወይም ከጠበቆች የነፃ
አግልግሎት ጠበቃ እንዲቆም ማድረግ ይሻላል እንጅ ሊሆን ይችላል የሚለውን ብቻ መሰረት
በማድረግ ሕግን መጣስ ተገቢ አይሆንም፡፡ በተጨማሪነትም ተጠርጣሪው ጊዜ ወስዶና
በጠበቃም ታግዞ የሚያቀርበው አቤቱታ የበለጠ መብቱን ለማስጠበቅ የሚያስችለው መሆኑ
የማይቀር መሆኑም ግንዛቤ መውሰድ የሚገባ ይሆናል፡፡

3.3 የጊዜ ቀጠሮ እና ዋስትና የሚነሳባቸው የክርክር ደረጃዎች


የጊዜ ቀጠሮ እና የዋስትና ጉዳይ በተለያየ የክርክር ደረጃ ላይ ሊነሳ ይችላል፡፡ የጊዜ ቀጠሮ
ጉዳይ ብዙውን ጊዜ ክስ ከመቅረቡ በፊት የሚቀርብ ነው፡፡ የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይም ማስረጃ
በማሳባሰቡ ሂዴት ላይ ተርጣሪጣሪው ጣልቃ የሚገባ ከሆነ ይህን ለማስቀረት ስለሚሆን
በቅድመ ክስ ሂዴት ላይ የሚቀርብ ጉዳይ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የዋስትና መብት ከቅድመ
ክስ ጀምሮ እስከ የሰበር ክርክር ድረስ የሚነሳበት ሁኔታ አግባብ እንዳለ እንረዳለን፡፡ ስለሆነም
የዋስትና ክርክር የሚነሳበትን ክርክር ደረጃ የሚያጋጥሙ ችግን እንመለከታን፡፡

3.3.1 የቅድመ ክስ ዋስትና መብትና ተግባራዊነቱ


ተጠርጣሪው እጅ ከፍንጅ ወንጀል ሲፈፀም በመያዙ ወይም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመያዙ
ወይም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመያዙ ተጠርጣሪው ለፖሊስ ቃሉን ከሰጠ በኋላ የቆይታው ጉዳይ
ወደ ዋስትና መብት ጥያቄ መግባቱ የማይቀር ነው፡፡ ይህን በተመለከተም በሕገ መንግስቱ
የተያዘ ሰው ወደ ፍርድ ቤት በ48 ሰዓት ይቀርባል የሚለው እንደተጠበቀ ሆኖ122 ፖሊስ
ተጠርጣሪን ሁልጊዜ ፍርድ ቤት የማቅረብ ግዴታ የለበትም፡፡ በአማራጭም በወንጀል ሥነ
ሥርኣት ህጉ አንቀፅ 28(2) የታሰረውን ተጠርጣሪ ፖሊስ የዋስትና ወረቀት አስፈርሞ

121
የሰበር ችሎቱ መርምሮ የሚያፀናው የወረዳውን የዋስትና መዝገብ ስለሚሆን በጊዜ ቀጠሮ የተሰጠውን ውሳኔ
የበላይ ፍርድ ቤት ለውጦታል የሚባል አይደለም፡፡ የሁሉም ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ደረጃውን ጠብቆ እስካልተሻረ
ድረስ መከበር ማስፈለጉ የሚነቀፍ መሆን የለበትም፡፡
122
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 29(1) እና የኢፌዲሪ ሕገ መንግስቱ አንቀጽ 19(3)

39
ተጠርጣውን ሊለቅ ስለመቻሉ ተደንግጓል፡፡ ይህ መብት ያልተጠበቀለት ተጠርጣሪ ብቻ የዋስ
መብቱ እንዲጠበቅለት ለፍርድ ቤት ማመልከት ስለመቻሉ ድንጋጌው ያመለክታል፡፡
ይህም በራሱ በቅድመ ክስ ሂዴት ውስጥ በሁለት የተለያዩ አካላት የዋስትና አቤቱታን
ሊያስተናግዱ የሚችሉበት ሁኔታ ያለ መሆኑን ያሳያል፡፡ የመጀመሪያው ተቋምም ከላይ
እንደተገለፀው ፖሊስ የያዘውን ተጠርጣሪ በዋስ ሊለቀው ይችላል፡፡ ይህን ለማድረግ ወንጀሉ
በጽኑ እሥራት የማያስቀጣ ሊሆን ወይም ደግሞ ተጠርጣሪው ወንጀሉን ለመፈፀሙ አጠራጣሪ
ሆኖ መገኘት ይኖርበታል፡፡123 ከዚህ ላይ “ወንጀል መፈጸሙ አጠራጣሪ ሲሆን” የሚለው
ተጠርጣሪው ወንጀል መፈፀሙን የሚያመለክተው ሁኔታ በጣም አነስተኛ ነው የሚያሰኘው
ሲሆን ነው፡፡ ይህም ፖሊስ የሚጠቀመው የማስረጃ ምዘና ደረጃ የጥርጣሬው ደረጃ ከፍተኛ
መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡124 ከዚህ ላይ ተጠርጣሪው በስህተት የተያዘ ይልቁንም ሌላ ተገቢው
ተጠርጣሪ መያዙ ቢታወቅ ወደ ፖሊስ የቀረበ ሰው ሁሉ ዋስትና መፈረም ይገባዋል ወይ
የሚለውን ማጤን ይገባል፡፡ ይህን አሰራር ፖሊስ ተጠርጣሪን ሲይዝ በቂ ጥርጣሬ ላይ
መመስረትና ከመያዙ በፊት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያለበት መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው፡፡
በተጨማነት ፖሊስ ጠርጥሮ ከያዘው ለፍርድ ቤትም ቢሆን አቅርቦ ያለምክንያት መያዙን
በመጥቀስ ፍርድ ቤት እንዲለቅለት ሊጠይቅ ይችላል የሚለውን ሊያመጣ ይችላል፡፡ ይህ ሁሉ
ግን የሕግ ሽፋን የሌለውና የንፁሀንን መብት ጋር በእጅጉ የተገናኘ ጉዳይ ስለሆነ መፍትሔ
ያስፈልገዋል፡፡ ፖሊስ በዚህ የሀሳብ ፍጭት ውስጥ ከገባ ግን ተገቢውን ተጠርጣሪ ለመያዝ
እንዳይችል እንቅፋት ስለሚሆን ተገቢ ያልሆነ ተጠርጣሪ መሆኑን ፖሊስ ከተገነዘበ ያለዋስ
ሊለቀው ይችላል የሚለውን አማራጭ ማሳቡ ተገቢ ነው፡፡125
በቅደመ ክስ ሂዴት ሌላው ዋስትና ጉዳይን የሚያስናግደው ፍርድ ቤት ነው፡፡126 ፖሊስ
በወንጀል ጠርጥሮ በመያዝ ለፍርድ ቤት ያቀረበውን ተጠርጣሪ ፍርድ ቤቱ በዋስትና ወረቀት
በማስፈረም ሊለቀው ይችላል፡፡127 ፍርድ ቤት ዋስትና የሚፈቅደው ተጠርጣሪው የተጠረጠረበት

123
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 28
124
ፖሊስ የወንጀል መፈፀሙን ሁኔታ አመላካች ማስረጃ ካለው በቂ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ እንደ ፍርድ ቤት በቂ
ጥርጣሬ ተፈጥሯል ወይስ አልተፈጠረውም የሚለውን ጭብጥ ይዞ ሙሉ ክርክሩን ለማድረግ የሚገደድ
አይሆንም፤ ክርክሩ ገና በመጀመሩም ይህ የሚቻልም አይሆንም፡፡
125
አንዳንድ ጊዜ የፖሊስ ባልደረቦች በቂ ማስረጃ እያላቸው የምርመራ መዝገቦችን እንዳልነበር አድርገው ያጠፋሉ
የሚለውን አልፎ አልፎ ሀሜት ይሰማል፡፡ ይህ እንዳይሆንም ፖሊስ የያዘውን ሰው ማንነትና የለቀቀበትን
ምክንያት መጥቀስ እንደመፍትሔነት ሊቀመጥ ይችላል፡፡
126
ለዐቃቤ ሕግ ግን ዋስትና ጉዳይ ላይ እንድወስን ዕድል የተጠበትን ሁኔታ አንመለከትም፡፡ ለዚህ መሰረት
የሚሆነው ደግሞ ዐቃቤ ሕግ የምርመራ መዝግቡ የሚደረሰው ተጠርጣሪው ለፍርድ ቤት ከቀረበና እንድሁም
የምርመራ ሂዴቱን ካፈ በኋላ ስለሆነ ነው የሚለውን መሰረት ያደረገ ሊሆን ይችላል፡፡
127
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 59(1)

40
ወንጀል የዋስትና መብት የማያስከለክለው፣ ምርመራ እየተካሄደበት ከሆነ መለቀቁ በማስረጃ
ማሰባሰቡ ሂደት ላይ እንቅፋት የማይፈጥር፣ ቢለቀቅ ግዴታውን አክብሮ የሚቀርብ መሆኑን፣
መለቀቁ ለሕዝብ ፀጥታና ሠላም አስጊ አለመሆኑና ሌላ ወንጀል የማይፈጽም መሆኑን
በማገናዘብ ሊሆን ይገባል፡፡
በቅድመ ክስ ዋስትናን በተመለከተ ተጠርጣሪው የዋስትና ግዴታውን ባያከብር በምን አግባብ
የዋስትና ግደታው ይፈፀማል የሚለውን መመልከት ይገባል፡፡ ለፖሊስ ሆነ በፍርድ ቤት
የሚሰጥ የዋስትና ግዴታም በሕግ አግባብ ከተገባ ሕጋዊ ውጤት ማስከተል ይኖርበታል፡፡
በቅድመ ክስ ዋስትና በተጠርጣሪው ላይ የሚጥለው ግዴታ በፖሊስ ተገቢው ምርመራ
እስከሚደረግ ድረስ ለምርመራ ስራው መተባበርን የሚጠይቅ ግዴታ ነው፡፡
አንደኛው ሁኔታም ለፖሊስ ተጠርጣሪው የዋስትና ግዴታ ሲገባ የግዴታው ዓይነትና ሁኔታ
በግልፅ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡128 ከዚህ በተጨማሪም ተጠርጣሪው በእርግጥም የገባውን
የዋስትና ግዴታ አላከበረም የሚያሰኝ ሁኔታ ስለመፈጠሩ ከገባው ግዴታ አንፃር መመርመር
የሚገባ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ለፖሊስ የተሰጠ ዋስትና ሳይከበር ከቀረ ተጠርጣሪውን በፍርድ ቤት
ትዕዛዝ መያዙ እንደተጠበቀ ሆኖ ለዋስትና የገባበትን ግዴታ እና ግዴታውን እንዲፈፅም
ተገቢው እውቅና ኖሮት በእርግጥም ዋስትናውን አላከበረም የሚለውን በፍርድ ቤት በፍተሐ
ብሔር የክርክር ዓይነት ማከራከር ይገባል የሚል ሀሳብ አለ፡፡ የግዴታው አግባብ በአንድ ወገን
የተገባ ቢመስልም በፅሁፍ የሚደረግና የሕግ እውቅና የተሰጠው ልዩ ውል ስለሆነ የህግ
ውጤት እንዲኖረው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡129 አለበለዚያ በዋስትና ጉዳዩ ላይ ክርክር ከተነሳ
ፖሊስ በቀጥታ ዋስትናን ገቢ ያድረግ የሚለውን በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠውን የንብረት
መብት ተገቢውን ክርክር በፍርድ ቤት ሳይደረግበት የሚታጠበት ሁኔታን ያመጣል፡፡
ሁለተኛው በቅድመ ክስ ሂዴት ተጠርጣሪው ለፍርድ ቤት ዋስትና ሰጥቶ ዋስትና ባያከብረስ
ውጤቱ ምንድነው የሚለውም ጥያቄ ነው፡፡ ለዚህም ከወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 79
ጋር አብሮ ሊታይ የሚችል ነው፡፡ ተጠርጣሪው የገባው ግዴታ ዓይነትና ማድረግ ያለበት
ወይም የሌለበት ጉዳይ በግልፅና ቢያንስ ውል ሲገባ ለተጠርጣሪው መገለፅ አለበት፡፡

128
የኢትዮጵያ ንጉሰ ነግስት የፍትሐ ብሔር ሕግ፣ 1952፣ አዋጅ ቁጥር 165፣ ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ፣ 19ኛ
ዓመት፣ ቁጥር 15 (ከዚህ በኋላ የፍትሐ ብሔር ሕግ)፣ ከከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1922 እና ተከታዮች ለጉዳዩ
አግባብነት ሊኖረው ይችላል፡፡
129
የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1728 ተዋዋዮች መፈረም ያለባቸውና ሁለት ምስክሮችም መፈረም ያለባቸው
ስለመሆኑ ይጠበቃል:: ተቀራራቢ በሆነ መንገድ በፍርድ ቤት የሚገባ ዋስትና በራሱ በቀጥታ ፍርድ ቤቱ
የሚስፈፅም ይሆናል፡፡ ሆኖም በፖሊስ ለተቀራራቢ ዓላማ በተቀራራቢ መንገድ የሚገባን ዋስትና ፖሊስ በቀጥታ
ገቢ ያድርግ ባይባልም ቢያንስ ተጠርጣሪው ዋስትና መፈረሙን በፍርድ ቤት አረጋግጦ መወሰን የህጋዊነት መርህ
የሚያሰፍን ይሆናል፡፡

41
ተጠርጣሪው የዋስትና ግዴታውን የተዋዋለው ከፍርድ ቤት ጋር በመሆኑ የዋስትና ግዴታ
መኖሩ የፍርድ ቤት ግንዛቤ (judicial notice) የሚወሰድበት ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ግዴታውን
አለመወጣቱን ወይም መጣሱን በተመለከተ ግን ፖሊስ ወይም ዐቃቤ ሕግ አመላካች ማስረጃ
ማምጣት ይኖርበታል፡፡ ተጠርጣሪውም ይህን የሚያፈርስ ሁኔታ አለ በሚል ለማሳየት ማስረጃ
ማቅረብ ቢፈልግስ መከልከል የለበትም የሚለው ተቀባነት ያለው ጉዳይ ነው፡፡
በቅዲመ ክስ የተገባ የዋስትና ግዴታው የክርክር ደረጃ ክስ ቀርቦበት ለፍርድ ቤት ቀርቦ
ከሚሰማት ቀን ግን ማለፍ የለበትም፡፡ የዋስትና ግዴታውንም በፖሊስ የተገባ ከሆነ የጊዜ ገደብ
ለማበጀት ያስቸግር ይሆናል፡፡ ሆኖም የዋስትናው ጊዜ ገደብ የሚወሰነው በክርክሩ ሂዴት
ፍጥነት ላይ ነው፡፡ ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በፍጥነት አጣርቶ ሥልጣን ላለው ዐቃቤ ሕግ
የመላክ ግዴታ ይጥልበታል፡፡ ዐቃቤ ሕግም የምርመራ መዝገቡ እንደደረሰው በመዝገቡ ላይ
ውሳኔ መስጠት ይኖርበታል፡፡ ክስ ካቀረበበም በ15 ቀናት ውስጥ መሆን አለበት፡፡ ስለሆነም
በዚህ ጊዜ ውስጥ የቅድመ ክስ ሂዴት የሚቋጭ መሆን ይኖርበታል፡፡ ክርክሩም ከተቋጨ
ዋስትናው ላስፈረመው አካል ቀርቦ ዋስትናው እንድለቀቅ ማድረግ የሚገባ ነው፡፡ ፖሊስ ከሆነም
በራሱ ዋስትናውን ከማውረድ የሚከለከል አይደለም፡፡ በሌላ መልኩ ግን ዋስትናው በቅድመ ክስ
የተያዘበት ሰው ክርክሩን በመንግስት በኩል ምላሽ ሳይሰጠው ቢቀር የዋስትናው ግዴታ
ለተራዘመ ጊዜ መቆየት አይኖርበትም፡፡ ይህን በተመለከተ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ቢቀርብ የክስ
ምክንያት ያለው ነው በሚል አከራክሮ መወሰን የሚገባ ነው፡፡ በቅዲመ ክስ ዋስትና ግዴታ
የተገባለት ጉዳይ ክስ የማይቀርብ መሆኑ ከተረጋገጠ ቀሪ መሆን አለበት፡፡
ክስ ከቀረበ ደግሞ የቅድመ ክስ ዋስትና ክስ እስከመቅረብ ያለውን ሂዴት ስለሚያሳይ ክስ ቀርቦ
ክርክር ከተጀመረም ዋስትናው እንደአዲስ የሚቀርብ ነው፡፡ ከዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ግን
ተጠርጣሪው ለፖሊስ በገባው ዋስትና ክስ በቀረበብኝ ጊዜ ፍርድ ቤት እቀርባለሁ የሚል ሲሆን
ውጤቱ ምን መሆን አለበት የሚል ነው፡፡ ተጠርጣሪው ክሱ የሚቀርብበትና ክሱ የሚሰማበት
ቀን መቸ እንደሆነ አያውቅም፡፡ ፖሊስ የዚህን ግዴታ መጣስ ለማሳያትም ክስ የተመሰረተ
መሆኑንና ክሱ የሚሰማበትን ቀን የነገረው መሆኑን የሚሳይ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
የቅድመ ክስ ዋስትናው ክርክር መደረግ ያለበት ችሎት ክሱን በሚሰማው ፍርድ ቤት መሆን
ያለበት ይመስላል፡፡130

130
ከላይ እንዳየነው ውል መኖርና የውል ግዴታ ማፍረስን የሚመለከትም በተለይም ፍትሐ ብሔር ክርክርን
የሚስከትል ይሆናል፡፡ የክስ መሰማቱንም የሚያንዛዛ ይሆናል፡፡

42
3.3.2 ክስ በሚሰማበት ጊዜ ስለሚቀርብ ዋስትና
አስቀድሞ በቅድመ ክስ ጊዜ ዋስትና የተፈቀደ ወይም የተከለከለ ቢሆን ክሱ ሲቀርብ እንደገና
የዋስትና ጥያቄ ይስተናገዳል፡፡ ክስ ሲቀርብ የዋስትና ጉዳይን ማስተናገድ እንደገና ለመወሰን
አዲስ ምክንያት ሊኖር ይችላል፡፡ በተለይም ደግሞ ዐቃቤ ሕግ የሚከሰስበትንም ድንጋጌ ለይቶ
ስለሚያቀርብ የዋስትና ጉዳዩን እንደአዲስ ለማስተናገድ በቂ ምክንያት ይሆናል፡፡ ለዚህም
ምርመራው ሲጣራ ድንጋጌው ዋስትና የሚያስከለክል ነው ተብሎ በሂዴት የማያስከለክል
ድንጋጌ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ በግልባጩም ጉዳዩ ዋስትና አያስከልክልም በሚል ምርመራ ተጣርቶ
በመጨረሻ ግን ዋስትና የሚያስከለክል ድንጋጌ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ቀድሞውንም ምንም አይነት
የዋስትና ክርክር ሳይቀርብ ቀጥታ ክስም ሊቀርብ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ከምርመራ በፊት
የዋስትና ጥያቄ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 67“ን” መሰረት ተደርጎ ምርመራ
እንዳይደናቀፍ በሚል ዋስትና ሊነፈግ ይችላል፡፡ በሂደትም ምርመራው ተጠናቆ ክስ ከቀረበ
በኋላ ይህ ስጋት ከተወገደ ዋስትና መከልከል ተገቢ ላይሆን ይችላል፡፡ አስቀድሞ ዋስትና
ተፈቅዶ ክስ በቀረበ ጊዜ ግን የወንጀል ሕግ ቁጥር 67“ን” መሰረት በማድረግ የዋስትና ይከልከል
ጥያቄ ቢቀርብ ፍርድ ቤት የሚያስተናግድ ነው፡፡ በዚህ ደረጃ የዋስትና መብት መከልከል
የሚያስፈልገው ምስክሮች ወይም ማስረጃ እስከሚሰማ ድረስ ጥበቃ ሊሆን ይችላል፡፡131
በዚህ ደረጃ የሚቀርብ የዋስትና ጥያቄ ከቅደመ ክስ ዋስትና ጥያቄ የሚለየው ክሱ ተለይቶ
የቀረበ መሆኑ ነው፡፡ እንዲህ በሆነ ጊዜ የክስ መሻሻል እንዲደረግ ወይም የተጠቀሰው የክሱ
ፍሬ ነገርና ድንጋጌው ግልፅ ተቃርኖ ከሌለው የዋስትና ጉዳዩ ክስ የቀረበበትን ደንጋጌ መሰረት
የሚያደረግ ነው፡፡ ይህም የሕገ መንግስት አጣሪ ጉበኤ የሰጠውን ውሳኔ እንደ መሪ ሀሳብ
መውሰድ ተገቢነት አለው፡፡132
በዚህ የክርክር ደረጃ ላይ የዋስትና ጥያቄ ከጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ተለይቶ ይቅረብ የሚለውን
ክርክር የሚስነሳ አይደለም፡፡ ስለሆነም ቀድም ሲል ያለውን ክርክር በዚህ ደረጃ መድገም
አስፈላጊነት አይኖረውም፡፡ ከቅዲመ ክስ ዋስትና ጋር ያለውን ሂዴት ግን በመጠኑም ቢሆን
ማጤን ሊያስፍልግ ይችላል፡፡ በክስ መስማት ጊዜ የሚስተናገድ የዋስትና ጥያቄ አቀራረቡ ግን
ተገቢውን ትኩረት ተሰጥቶት ሙሉ ክርክር ሲደረግ አይተዋልም፡፡ በዋስትና ጉዳዩ በራሱ ማን
መጀመር አለበት የሚለው በፍርድ ቤቶች ወጥ አሰራርን ሲከተሉ አይታዩም፡፡ አንዳንድ ዳኞች

131
አሰራሩም ዐቃቤ ሕግንም ሆነ ተከሳሽን እንደአግባብነቱ ሊጠቅም ይችላል፡፡
132
በኢፌዲሪ ሕገ መንግስቱ አንቀፅ 19(6) ሲተረጉም የሕገ መንግስት አጣሪ ጉባኤው በሰጠው አስተያየት
መሰረት ዳኞች የክሱን ፍሬ ነገር በመመዘን ሊወስኑ ይችላሉ የሚለውን ማጤን ያስፈልጋል፡፡

43
ዋስትና ዐቃቤ ሕግ ካልተቃወመ በስተቀር ተከሳሹ መጠየቅ የለበትም የሚሉ አሉ፡፡ አንዳንድ
ጊዜም ዐቃቤ ሕግ ክስ ሲሰማ ድንጋጌው ዋስትና በሕግ የሚያስከልክል ሆኖ እያለ ዐቃቤ ሕግ
የዋስትና ተቃውሞ የለኝም ሲል በዋስትና ዳኞች የሚለቁበት ሁኔታ አለ፡፡133 የወንጀል ሥነ
ሥርዓት ሕግ ቁጥር 64 መሰረት የዋስትና ጥያቄ በተከሰሰ ሰው እንደሚቀርብ ስለሚያሳይ
የዋስትናውን ጥያቄ ተከሳሹ ቢጀምር ተገቢ ይመስላል፡፡ በመርህ ደረጃ ክርክርን መጀመር
ያለበት እንዲፈፀምለት የሚጠያቅ አካል መሆን ይኖርበታል፡፡ ቢያንስ ተከሳሹ ስለቆይታው
መጠይቅና ዐቃቤ ሕግም ምላሽ እንደሰጥ ማድረግ በሚዛናዊነት በዋስትና ጉዳይ ላይ ለመወሰን
ያስችላል፡፡134 ፍርድ ቤቱም ለዋስትና ጉዳዩ ማስረጃ ማስቀርብ ካለበት ተመልክቶ ዋስትናው
በአመላካች ማስረጃ መሰረት መወሰን ይገባል፡፡
ጉዳዩ በውሳኔ እልባት ሲያገኝ የተገባው የዋስትና ገዴታ እስከዚሁ ደረጃ ድረስ ስለሆነ በዚህ ጊዜ
የክስ መስማት ዋስትና ጉዳይ በዚህ የሚቋጭ ይሆናል፡፡ ይህ ስለመሆኑም በውሳኔው ላይ
ትዕዛዝ መስጠት ይገባል፡፡ አለበለዚያ ግን ፍርድ ቤቱ አቤቱታ በቀረበለት ጊዜ ዋስትናው ቀሪ
ስለመሆኑ ትዕዛዝ መስጠት ይጠበቅበታል፡፡ አንዳንድ ዳኞችም ውሳኔ ከተሰጠ ትዕዛዝ ባይሰጥም
በቀጥታ መለቀቅ አለበት የሚሉ አሉ፡፡ ነገር ግን ይህ ሁኔታ አሳመኝ አይመስልም፤ በትዕዛዝ
እንዲያዝ የተደረገውን ንብረት በትዕዛዝ ማንሳት የሚገባ ይሆናል፡፡
በዐቃቤ ሕግ ጥፋት ከመጨረሻ እልባት ሳይሰጠው ቀርቶ መዝገቡ ቢዘጋ የዋስትናው ጉዳይ
በእንጥልጥል መቆየቱን ያለውን ተገቢነት መመልከት ይገባል፡፡ ዐቃቤ ሕግ ክሱን ያነሳ ከሆነ፣
ዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ወይም ማስረጃ ማቅረብ ሳይችል ቢቀር135 ወይም ክሱ እንዲሻሻል
ትዕዛዝ ሰጥቶ ባያሻሽል እና በመሳሳሉት ሁኔታዎች መዝገቡ ቢዘጋ የዋስትናው ጉዳይ እልባት
መስጠት የሚገባ ነው፡፡ ክርክሩም የተቋረጠው በዐቃቤ ክስ ጉድለት በመሆኑ ተከሳሹን
ላልተወሰነ ጊዜ136 በንብረቱ ላይ የመጠቀም መብቱን መገድብ የሚገባ አይሆንም፡፡ በሌላ መለክ

133
ፀሐፊው በደቡብ ወሎ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የከፍተና ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኖ ሲሰራ ያስተዋለው፡፡
134
እንደአማራጭም ዋስትናውን ማከራከሩ እንደተጠበቀ ሆኖ ክሱ በሕግ ዋስትና የሚያስከለክል ከሆነ ተከሳሹ
በዋስ ልውጣ የሚልበትን ምክንያት እንደጀምር ማድረግና የዐቃቤ ሕግን መልስ መስማት ተገቢ ይሆናል፡፡ በሌላ
መልኩ ግን ድንጋጌው በመጠቀሱ ምክንያት ብቻ ዋስትና የማያስከለክል ከሆነ ዐቃቤ ሕግ በሌላ ምክንያት ዋስትና
የሚስከልክል ምክንያት ካለው ይህንኑ እንዲያቀርብ እድል መስጠትና ተከሳሽ ምላሽ እንዲሰጠበት ማድረግ
የሚስፈልግ ይሆናል፡፡
135
ተከሳሹን ባለማግኘት መዝገቡ ቢዘጋ ተከሳሽን ባገኘ ጊዜ መዝገቡን ያንቀሳቅስ ተብሎ ሊወሰን የዋስትና ገንዘቡ
ለመንግስት ገቢ ይሁን በሚል ማዘዝ የሚቻል ይሆናል፡፡ ሆኖም በዓቃቤ ሕግ ጥፋት ቀጠሮ ለማስለወጥ የሚስቸል
በቂ ምክንያት ሳይኖር መዝገቡ ከተዘጋ ዋስትና ለምን ያህል ጊዜ መቆየት አለበት የሚለው ግልፅነት የለውም፡፡
136
ይህን ጊዜ ቢበዛ ክሱ በይርጋ የሚቋረጥትን ጊዜ ሊሆን ይገባል የሚል መከራከሪያ የሚያቀርቡ ይኖራሉ፡፡
ሆኖም የይርጋው ጊዜ እስከሚያልቅ መጠበቅ ረጅም ጊዜ ነው፡፡

44
በተከሳሽ ችግር ወይም ክሱ ተቋረጠው ፍርድ ቤቱ የስር ነገር ስልጣን አለመኖርን የሚመለከት
ቢሆን ክሱን ሲቋርጥ ዋስትናውን መልቀቅ ላይ ችግር ይኖረዋል፡፡
በአዲስ ምክንያት የዋስትና መከልከልን የህግ ሽፋን አለው፡፡137 አዲስ ምክንያት የሚለው ደግሞ
ተከሳሽ ዋስትና የተከለከለበት ምክንያት በሂዴት ቢጠፋ በዋስ መውጣት ይኖርበታል፡፡ ለዚህም
መነሻው የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን እንዳይመሰክሩ ያደርጋል የሚለውን ፍርድ ቤቱ አሳምኖት
ዋስትና ቢከለክለው ምስክሮች ከተሰሙ በኋላ ምክንያቱ ቀሪ ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት ተከሳሽን
ዋስትና መከልከልና ማሰር ተገቢ አይሆንም፡፡ አንደኛው አማራጭ ፍርድ ቤቱ በሂዴት
የሚቋረጥ መሆኑን የሚያውቀው ስለሆነ በምስክሮች ከተሰሙ በኋላ በዋስትና ይውጣ በሚል
ለመዘዝ ይችላል፡፡ ምስክሮች ከተሰሙ በኋላና ሌላም ዋስትና ለመፍቀድ የሚያስችል አዲስ
ምክንያት ቢቀርብ ለመከልከል ምክንያቱ ተቋርጧል በሚል አቤቱታ ሲያቀርብ ማስተናገድ
ምክንያታዊ ይሆናል፡፡138
በክስ መስማት ሂዴት ውስጥ አዲስ ነገር መገኘት በበላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ ይታረም ማለት
ተገቢነት አይኖርም፡፡ የመጀመሪያው የይግባኝ ጊዜው ሊያልፍ ይችላል፡፡ ሁለተኛው ነገር አሁን
የቀረበው ጉዳይ አዲስ ስለሆነ ለይግባኝ ክርክር መሰረት ለማድረግም ያስቸግራል፡፡ ይህን አሰራር
መፍቀድ ግን ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል የቀረበለትን ክርክር ሲወስን የፈጠረውን ስህተት ማረምን
የሚጨምር መሆን የለበትም፡፡ ለምሳሌ ዋስትና የሚስከለክልን ጉዳይ ዋስትና በስህተት የፈቀደ
ፍርድ ቤት ሌላ ጊዜ በአዲስ ነገር ተገኘ በሚል ማረም የሚገባ አይሆንም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ
ጉዳይ በይግባኝ የሚታረም ይሆናል፡፡ ዐቃቤ ህግ ይግባኝ መጠየቅ ስለመቻሉ ላይ የግልፅነት
ችግር የነበረ ሲሆን የሰበር ችሎቱ ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ ማለት ስለመቻሉ ተወስኗል፡፡139

3.2.3 በይግባኝ እና በሰበር ክርክር ደረጃ የሚቀርብ ዋስትና


በዋስትና መከልከል ወይም መፈቀድ ጉዳይ ላይ ራሱን ችሎ ይግባኝ ማለት ስለመቻሉ ከላይ
ተመልክተናል፡፡ በዚህ ክፍል የምንመለከተው ዋስትና በይግባኝና በሰበር ክርክር ላይ ራሱን ችሎ
በመብት ደረጃ የሚቀርብ ስለመሆኑ ነው፡፡

137
ማስረጃው ከተሰበሰበ እና ከተለየ በኋላ በማስረጃ መሰብሰብ ችግር ምክንያት ዋስትና ያስከለክላል የተባለ ሰው
የመከልከያ ምክንያቱ ቀሪ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
138
ከዐቃቤ ሕግ ጋር ዕኩል ሚዛን ላይ ማድረግ ይገባል፡፡ ይግባኝ ማለት መቻልን ለዐቃቤ ከተሰጠ አዲስ ነገር
ለተከሳሽም የሚሆን መብት መሆን ይኖርበታል፡፡ ከዚህ ላይ እንደምሳሌ አንድ ምስክሮችን ያስፈራራል የተባለ ሰው
ዋስትና ተከልክሎ ማረሚያ ቤት ከገባ በኋላ በበሽታ እግሩና እጁ መንቀሳቀሱ የማይችል ቢሆን ዋስትና አንድ ጊዜ
ተከልክለሀል በሚል መወሰን ተገቢነት ያለው አይመስልም፡፡
139
ከላይ የግርጌ ማስታወሽያ ቁጥር 83

45
ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለተው የስር ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ወይም በነፃ የመሰናበት
ውሳኔ ቢሰጥና በተከሳሹ ወይም በዐቃቤ ሕግ በኩል የይግባኝ አቤቱታ ቢቀርቡ ውጤቱ ምን
ይሆናል የሚለውን የሚመለከት ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሚደረግ ክርክር ላይ
ክርክሩ ሲጠናቀቅ የዋስትና ክርክሩ ይጠናቀቃል፡፡ ዋስትናው ሳይለቀቅ ቢቀር እንኳ በበላይ
ፍርድ ቤት ለሚደረግ ክርክር እንደዋስትና ሊሆን አይችልም፡፡ ሆኖም ግን በፀረ ሙስና ጉዳይ
ላይ ዋስትና የተከለከለ ሰው ይግባኝ የሚባል ቢሆን ፍርዱን በሰጠው ፍርድ ቤት ክልከላውን
ማዘግየት ይገባል በሚል ልዩ ሁኔታ ተደንግጓል፡፡140
በነጻ በተለቀቀ ተከሳሽ ላይ ዓቃቤ ህግ ይግባኝ ባለ ጊዜ የዋስትና ጥያቄ የሚስተናገድበት ሁኔታ
ክርክር ሲያስነሳ ይስተዋላል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ በተከሰተ ጊዜ በተለያዩ ዳኞች ሶስት
ዓይነት ትርጉሞች እየተሰጡ ሲተገበሩ ይታያል፡፡ አንደኛው ሀሳብ የጉዳዩ አይነት ምንም ይሁን
ምን የዋስትና ጉዳይ በጭብጥነት አይነሳም፡፡141 ለዚህ መሰረት የሚያደርጉት ደግሞ የሥር
ፍርድ ቤት ጉዳዩን መርምሮ በፍርድ ነፃ ያለውን ሰው ዋስትና መከልከል የህግ ድጋፋ የለውም
የሚለውን መሰረት ሀሳብ የያዘ ነው፡፡142 ከዚህ ላይ ግን በትዕዛዝ ለምሳሌ የሥር ፍርድ ቤት
ክርክሩን ሳያጠናቅቅ በስረ ነገር ስልጣን አለመኖር ምክንያት መዝገቡን ቢዘጋ መዝገቡ ሥልጣን
ላለው ፍርድ ቤት የሚተላለፍ ቢሆን የዚህ ክርክር ተጠቃሚ የሚሆን አይመስልም፡፡
ሁለተኛው ሀሳብ ደግሞ ቀድሞውንም በሕግ ዋስትና ለሚያስከለክሉ ወንጀሎች የዋስትና ጉዳይ
በይግባኝ ደረጃ በጭብጥነት መያዝ አለበት የሚለው ነው፡፡ ዓቃቤ ህግ ይግባኝ ያለበት ወይንም
የሰበር አቤቱታ የቀረበበት ጉዳይ ተከሳሹን ያስቀርባል ተብሎ ክርክር የሚደረግበት በሆነ ጊዜ
እና ጉዳዩም ከመነሻው ዋስትና የሚያስከለክል በሆነበት ጊዜ ተከሳሹ ተይዞ ጉዳዩን በማረፊያ
ቤት ሆኖ እንዲከታተል ሊደረግ ይገባል፡፡143
ሶስተኛው ሀሳብ የጉዳዩ አይነት ምንም ይሁን ምን የዋስትና ጉዳይ በጭብጥነት ሊያዝ ይገባል
የሚሉ ናቸው፡፡ ዋስትና በማይከለክሉ ጉዳዮች ላይ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 67
አንፃር እየታየ የዋስትናው ጉዳይ እልባት መደረግን ሕጉ የሚስቀር አይደለም፡፡ ለምሳሌነትም
በይግባኝ ክርክሩ ላይ ተከሳሽ ሊቀርብ አይችልም ቢባል ወይም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት
በሚሰማው ማስረጃ ላይ ተከሳሽ ጫና ፈጥሯል ቢባል ማለፍ የሚገባ አይሆንም፡፡

140
የፀረ ሙስና አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀፅ 5
141
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 193
142
በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 20(3)
143
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 63 እና በአዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 4 መሰረት ከ10 ዓመት ፅኑ
እስራት በላይ ሊያስቀጡ በሚችሉ የሙስና ወንጀሎች

46
በሌላ መልኩ ይግባኝ ያቀረበ ሰው በዋስትና ልለቀቅ በሚል አቤቱታ ሲያቀርብ ፍርድ
እንዳይፈጸም ስለሚታገድበት ሁኔታ በወንጀል ሥነ ሥርኣት ሕግ ቁጥር 188 ላይ ተደንግጓል፡፡
ይህን በተመለከተ ሁለት ዓይነት ሀሳቦች ይንጸባረቃሉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ዋስትና
ከሚስከለክለው በሕጉ ከተመለከተው ዝቅተኛው ጣሪያ በታች ከሆነ ዋስትና መፍቀድ ይገባል
የሚል ነው ክርክር ይቀርባል፡፡ ይህም በፀረ ሙስና ወንጀል ከ10 ዓመት በላይ የሚስጣ ወንጀል
ክርክር ሲነሳ ዋስተና ያስከለከለ ቢሆንም ቅጣት ሲወሰን ከ10 ዓት በታች ከሆነ ተከሳሹ ይግባኝ
ካቀረበ ዋስትና መከልከል አይገባም የሚል ነው፡፡
በሌላ መልኩ ሊያስቀጣ እንደሚችል በሚል በስር ፍርድ ቤት ሳይቀጣ እንኳ ዋስትና
የተከለከለን ሰው አሁን ቅጣቱ ያነሰ ቢሆንም ጥፋተኛ ተብሎ የተቀጣን ሰው መልቀቅ ተገቢነት
የለውም የሚል ክርክር ይቀርባል፡፡144 ክስ የቀረበበት ድንጋጌ ዋስትና ወደማያስከልክል ድንጋጌ
ከተለወጠ እና በዚህ ላይም ያስቀርባል ከተባለ ዋስትና መፍቀዱ ተገቢነት ያለው ይመስላል፡፡
እንደፀሐፊው ሃሳብ ክሱን በሰማው ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶ በይግባኝ ክርክር
ለይ ዋስትና ጥያቄ ማቅረብ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክስ ሲቀርብ እንደሚቀርብ ዋስትና
በዕኩል ሚዛን ላይ የሚቀመጥ መሆን የለበትም፡፡ የበላይ ፍርድ ቤት ቅጣቱን መገደብ ያለበት
ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ቢታሰር የማይተካ ጉዳት ይደርስበታል የሚለውን ድምዳሜ ላይ
መድረስ ይኖርበታል፡፡ በተግባር የሚያጋጥመው ነገር በተለይም በሰበር አጣሪ ችሎቱ ያስቀርባል
ሲባል ይፈቱና ጥፋተኝነቱ ሲፀና መልሶ ማስገባት ፈተና የሚሆንበት አግባብ አለ፡፡ ይህን ችግር
ለመቀነስ ቀጠሮውን በተቻለ መጠን አጭር በማድረግ እልባት መስጠት እንዲህ አይነት ሞራላዊ
ሁኔታን ይቀንሳል፡፡145
በመጨረሻም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትም በስር ፍርድ ቤት የሚደረግ ክርክር በተለያየ ምክንያት
እንደገና እንድደረግ ሲያዝ የጥፋተንነት ውሳኔን ይሽራል፡፡ እንዲህ በሆነ ጊዜ የዋስትና ጉዳዩ
ራሱ መወሰን አለበት ወይስ ቀድሞ በተወሰነው አግባብ መቀጠል አለበት የሚለውም ምላሽ
ያለው አይደለም፡፡ ውሳኔው ሲሻር የስር ፍርድ ቤቱ ዋስትናን እንደአዲስ አከራክሮ መወሰን
የሚገባው ሊኖርበት ይችላል፡፡ ሆኖም የበላይ ፍርድ ቤቱ የዋስትናን ጉዳይ ላይ አስቀድሞ
መወሰን የሚስችለው ሁኔታ ለምሳሌ ድንጋጌው ያስከለክላል የሚለውን ግምት ውስጥ

144
ፀሀፊው በስራ ላይ እንደታዘበው አንዳንድ ዳኞች በጸረ ሙስና በዋስ ለቀው በሰው መግደል ጉዳይ ላይ ዋስተና
ይከለክላሉ፡፡ በሌላ መልኩ ዋስትናን መከልከል ከህገ መንግስቱ አንቀፅ 19(6) መሰረት ከጅም አከራካሪ ስለሚሆን
ዋስትናን ወደ መፍቀድ ማመዘኑ ተገቢ ይመስላል፡፡
145
አንድ ጊዜ ማረሚያ ቤትን የያ ሰው ወደ ማረሚያ ቤት ሲመልስ መክበዱን በችሎት ተረድቸዋሉ፡፡ ፖሊሶችም
የታሰሩ ሰዎች ከተፈቱ በኋላ ወደ ማረሚያ ቤት መመልሰ ከባድና ሰዎችን ለመያዝ እየተቸገሩ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡

47
በማስገባት ዋስትና በመከልከል ቢመልሰው ችግር ላይኖረው ይችላል፡፡ በነጻ ወይም በዋስ
የተለቀቁ ተከሳሾች ሆነው ውሳኔው ሲሻር ተከሳሾችን ወደሥር ፍርድ ቤት ሲመለሱ በምን
አግባብ የሽግግር ዋስትና ይኑር የሚለው ወጥ መፍተሔ የሚስፈልገው ነው፡፡
4. ማጠቃለያ
በወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘ ሰው በወንጀል ፍትህ አስተዳደሩ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ቆይታውን
መወሰን እንደሀገሩ ወንጀል ሥነ ሥርዓት ህግ ሞዴል ሊወሰን ይችላል፡፡ የወንጀል ፖሊሲውም
የወንጀል ቁጥጥር መር ወይም ሥነ ሥርዓታዊ ፍትህን የሚያሰፍን ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ
ወንጀል ፍትህ አስተዳደርም ምጣኔው ሊለያይ ይችላል እንጅ ሁለቱን የወንጀል ሥነ ሥርዓት
ሞደሎች በማጣመር መያዙ የማይቀር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕግ መንግስትም ወደ ሥነ
ሥርዓታዊ ፍትህን የሚያዘነብል ነው ቢባልም ፍትህ እንዳይጓደል ሲባል በቁጥጥር ሥር
ማቆየት እንደሚቻል ተደንግጓል፡፡ አሁን ላይ የሚወጡት ልዩ ወንጀሎችም ለምሳሌ የፀረ-ሙስና
እና ጸረ ሽብረጸኝነትን ለመቆጣጠር የወጡ አዋጆችም በቁጥጥር ሥር ማቆየትን የሚመርጡ
ናቸው፡፡
በወንጀል የተጠረጠረ ሰውን ቆይታ በሚመለከት በአንድ በኩል የማሕበረሰቡን ጥቅም
ለማስጠበቅ በቁጥጥር ሥር ማቆየት የሚያስፈልግ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የተከሰሰ ሰውን
መብት በማስጠበቅ ለተወዳዳሪ ግቦች ተገቢ ምላሽ በመስጠት የፍትህ ሥርዓቱ እምነት
የሚጣልበት እንዲሆን ማስቻልን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ፍርድ ቤቶችን የዋስትና ክርክርን ሲወስን
በጥንቃቄ መሆን እንዳበት የሚያሳይ ነው፡፡
በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ውስጥም በወንጀል ተጥርጥሮ የተያዘን ሰው በቁጥጥር
ሥር ለማድረግ በሁለት ምክንያቶች በፍርድ ቤት ውሳኔ ሊታዘዝ ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው
ፖሊስ ምርመራውን ባለመጠናቀቁ ምክንያት ተጠርጣሪውን የግድ በቁጥጥር ሥር ማድረግ
ያስፈልጋል የሚለው ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ተጠርጣሪው የዋስትና አቤቱታ ሲያቀርብ ዋስትና
ሳይፈቀድለት ሲቀር ነው፡፡
በሀገራችን የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ውስጥም የጊዜ ቀጠሮ ፅንሰ ሃሰብም ለምርመራ ሲባል
በቁጥጥር ስር መሆንን የሚመለከት ሲሆን በዋስትና ምክንያት በቁጥጥር ሥር መሆንን
የሚያካትት አይደለም፡፡ ይህም ከሌሎች ፍትህ አስተዳደሮች ለየት ያለ አሰራርና ፅነሰ ሀሳባዊ
ይዘት ያለው ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በጊዜ ቀጠሮ ምክንያት በቁጥጥር ስር መሆን በዋስትና
መከልከል በቁጥጥር ስር ከመሆን በተሻለ ሁኔታ የፍርድ ቤት ክትትል ይደረግበታል፡፡ ሆኖም
ሕገ ሳይነሱም የሚያሳየው ጥፋተኛ ሳይባል በቁጥጥር ስር መሆን ከጊዜ ቀጠሮ ጋር ተመሳሳይ

48
ፅንሰ ሀሳብ ያላውና የነፃነት መብቱን የሚገድብ ነው፡፡ በዚህ ምክንያትም ለተራዘመ ጊዜ
መታሰር የማይተካ ጉዳት ስለሚያስከትል ፍርድ ቤቶች በፍጥነት ክስ መቅረብን እና በክስ
መስማት ሂዴት አጭር ቀጠሮ መስጠት የተፋጠነ ፍትህ የማግኘትን ሕገ መንግስታዊ መብት
የሚያረጋግጥ አሰራር ሊከተሉ ይገባል፡፡
የዋስትና መብትን በመከልከል በቁጥጥር ሥር የሚደረግበት አግባብን በተመለከተ በሕግ
መንግስቱ ከዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን ሰነዶች ጋር የሚጣጣም ይዘት ያለው ቢሆንም በሕግ
አውጪው አስቀድሞ ዋስትና የሚከለከልበት የሥነ ሥርዓት ሕግ መኖሩ ሕገ መንግስቱን
አንቀፅ 19(6) የሆነውን የሚጥስ ነው፡፡ ይህን የሕገ መንግስት ትርጉም መዛባትም ስህተቱ
በፍርድ ቤቶችም እንዲቀጥል የሚያደርግና የሕግ የበላይነትን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡
በቁጥጥር ሥር መሆን በጊዜ ቀጠሮ ቅድመ ክስ ላይ የሚነሳ ሲሆን በዋስትና መከልከል
ምክንያት በሁሉም የክርክር ደረጃ ሊነሳ ይችላል፡፡ የዋስትና መብትም በፖሊስና በፍርድ ቤት
ሊሰጥ ይችላል፡፡ በፖሊስ የሚሰጥ ዋስትና አፈጻጸምን በተመለከተ የዳበረ አሰራር የለም፡፡
በፍርድ ቤትም ቢሆን የሚሰጥ ዋስትና በሕግ አተረጓጎምም ሆነ የአሰራር ወጥነት የሚታይበት
አይደለም፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የጊዜ ቀጠሮ እና የዋስትና ጉዳይ ክርክር አመራርና በየትኛው የክርክር
ደረጃ ይነሳሉ የሚለው ወጥነት ያለው አይደለም፡፡ የጊዜ ቀጠሮና የዋስትና አቤቱታና ክርክር
አመራር ውስጥ፡- በተካራካሪዎች ማንነት ልዩነት፣ ክርክር አቀራረብ መለያየት፣ የይግባኝ
አቀራረብ መቀላቀል፣ የትዕዛዝ ግጭትን መፈጠር እና የክርክሩ ግብ መለያየት ስለሚኖር ሁለቱ
ክርክሮች በአንድ መዝገብ ይልቅ በተለያየ መዝገብ ማስተናገድ የተሻለ ይሆናል፡፡ የሁለቱ ፅነሰ
ሀሳቦች መቀላቀል ፍርድ ቤቶች በራሳቸው የክርክር አመራር ጉደለት ባለጉዳዮችን እንድጉላሉ
በማድረግ የፍትህ መዘግየትን በመፍጠር የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈጸምን የሚያሟላ
ይሆናል፡፡ ሲጠቃለልም በወንጀል የተጠረጠረ ሰው በቁጥጥር ሥር ለማድረግ በጊዜ ቀጠሮ
መፍቀድም ሆነ በዋስትና መከልከል ወጥ አሰራር የሌለ በመሆኑ በሕገ መንግስቱ የተረጋገጡ
መብቶች በሕግ አውጪው ተገቢው ጥበቃ፣ በፍርድ ቤት ተገቢው የሕግ አተረጓጎምና
የአስፈጻሚው አካል የሕግ አፈፃፀም መፈተሽና ማሳደግ የሚገባ ይሆናል፡፡

49
በወንጀል ይግባኝ ሥርአት የእስራት ቅጣት እንዳይፈጸም

ማገድና፤ አመልካችን በዋስትና የመልቀቅ ጽንሰ ሀሳብ


ሳባ ደመቀ*
አጽዕሮተ ይዘት
በአብዛኛዎቹ የአለማችን የወንጀል ፍትህ አስተዳደሮች በይግባኝ ሂደት የስር ፍርድ ቤት ፍርድ
እንዳይፈጸም በማገድ አመልካችን በዋስትና መልቀቅ ተቀባይነት ያለው ሥርዓት ነው፡፡ ይኸውም
ይግባኙ ታይቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ በስር ፍርድ ቤቱ የተላለፈው የእስራት ቅጣት አፈጻጸም ቀጣይነት
በአመልካች ላይ የሚያስከትለውን የማይተካ ጉዳት የመከላከል ቁልፍ አላማ አለው፡፡ በኢትዮጵያ
የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኙ እስኪቋጭ ቅጣትን በማገድ
አመልካች በዋስትና እንዲወጣ ለማዘዝ ስለመቻሉ በአንቀጽ 188 ደንግጓል፡፡ ይሁን እንጂ ድንጋጌው
የቅጣት ፍርድ በመርህ ደረጃ መፈጸም እየተገባው በልዩ ሁኔታ ሊታገድ የሚችልባቸውን ምክንያቶች
በዝርዝር አላመለከተም፡፡ በዚህም የተነሳ ድንጋጌው ዋስትና በሚከለክሉ ወንጀሎች ጥፋተኛ ተብሎ
ለተቀጣ ሰው ተፈጻሚ አይሆንም የሚሉ ሀሳቦች ይንጸባረቃሉ፡፡ ሆኖም ይህ ጽሁፍ ድንጋጌው
የሚናገረው ፍርድን ስለማገድ በመሆኑ ጉዳዩን ለመወሰን መሰረት ሊደረግ የሚገባው እራሱ የስር ፍርድ
ቤቱ “ፍርድ” እንጂ የወንጀሉ ዋስትና ፈቃጅነት /ነፋጊነት ሊሆን አይገባም የሚል ሀሳብን ያነሳል፡፡
በመሆኑም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ማመልከቻው ሲቀርብለት የድንጋጌውን አላማ በአግባቡ ለማሳካት
በሚያስችል መልኩ ይግባኝ የተባለበት “ፍርድ” ውስጥ ሊታረም የሚገባው መሰረታዊ ነጥብ መኖሩን
የማረጋገጥ ቅድመ ሁኔታን (The Merit- requirement) መመርመር ቀዳሚ ተግባሩ ሊያደርገው
ይገባል፡፡ ይህም ሥርዓት ይግባኝ ላቀረቡ ሁሉ እንደ መብት የሚጠየቅ ባለመሆኑ አመልካቹ ፍርድ
ቤቱን ማሳመኑ (The burden of proof requirement) በተጨማሪነት የሚመዘን ነጥብ ይሆናል፡፡
ከአመልካች ጎን ለጎን የህብረተሰቡንና የፍትህን ፍላጎት ማጣጣም ወሳኝ በመሆኑ አመልካች ቅጣቱ
ታግዶለት በዋስትና ቢወጣ ለህብረሰተሰቡ አደጋ የማይሆንና ከፍትህ/ቅጣት የማይሸሽ (The character
/circumstance requirement) መሆኑን መፈተሸ ሌላኛው የፍርድ ቤቱ የእገዳ ትእዛዝ መሰረት ሊሆን
ይገባዋል፡፡የጥናቱ አላማ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ በይግባኝ ፍርድን ማገድና አመልካችን በዋስትና የመልቀቅ
ሥርዓት እሳቤዎችን (concept) መፈተሽ በመሆኑ የተጠቀመው የጥናት ዘዴ ጽንሰ ሀሳባዊ (Doctrinal)
ነው፡፡

ቁልፍ ቃላት---የወንጀል ይግባኝ ሥርዓት፣ ፍርድ፣ ፍርድ ማገድ፣ ዋስትና፣ መሰረታዊ


ነጥብ፣ የማስረዳት ሸክም

*
LLB,LLM, በአብክመ የፍትህ ባለሙያዎች ማሰልጠኛ እና የህግ ምርምር ኢንስቲትዩት የህግ ተመራማሪ
መግቢያ
1. የወንጀል ይግባኝ ሥርዓት በጠቅላላው
የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ ያለው የፍርድ ሂደት ሶስት ዋና ዋና
ክፍሎች ላይ ያጠነጥናል ፡፡ የመጀመሪያው ከችሎት መቅረብ በፊት ያለውን ሂደት የሚሸፍን
ቅድመ ችሎት (pre-trial) የሚባለው ሲሆን በተጠርጣሪው ላይ መደበኛ ክስ ተመስርቶበት
በሚኖረው አጠቃላይ የክርከር ሂደት ውስጥ የጥፋተኛነት ወይም ነጻ የመሰኘት ፍርድ
የሚተላለፍበት ችሎት (trial) ደግሞ በሁለተኛው ሂደት ወስጥ ይሸፈናል፡፡ ሶስተኛው እና
የመጨረሻው ሂደት በተለይም የቅጣት ፍርድ የሚተላለፍበትና ይህንንም ተከትሎ የሚኖር
የይግባኝ ሥርዓትን ሁሉ የሚያጠቃልለው ድሕረ-ችሎት (post trial) የሚሰኘው ነው፡፡1
በተለይም የፍርድ ክለሳ መንገዶች ከፍ ያሉ ፍርድ ቤቶች በበታች ፍርድ ቤቶች የሚፈጸሙ
ስህተቶችን አጥርተው በማረም መሰረታዊ እና የሥነ ሥርዓታዊ የሕግ ማእቀፎችን በተግባር
ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲዳብሩ በማድረግ ረገድ ወሳኝነታቸው የጎላ ነው፡፡2ፍርድ
ከሚከለስባቸው ሥርዓቶች ውስጥ የተካተተው ይግባኝ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ ከፍ ባለ
ፍርድ ቤት ቀርቦ እንደገና እንዲታይ የማድረግ ሂደት እንደሆነ ይታወቃል፡፡3 ትርጉም ባለው
መልኩ በሲቪል ሎው እና ኮመን ሎው ሥርዓቶች ውስጥ ጉልህ ቦታ ያለው ዘመናዊው
የወንጀል ይግባኝ ሥርዓት ደግሞ በርካታ አላማዎችና ተግባራት ያሉት ነው፡፡ በመጀመሪያ
ደረጃ ይግባኝ በስር ፍርድ ቤቶች የተፈጸሙ ስህተቶችን የማረም አላማን የያዘ በመሆኑ
ስህተትን ተከትሎ የሚመጣውን የፍትህ መጓደል ለመቆጣጠር የሚያስችል ሁለተኛ እድል
መስጠት ላይ ያተኩራል፡፡4 በመሰረቱ የፍትህ መጓደል በአንድ በኩል ኩነቶችን በማረጋገጥ

1
John M.Scheb and John M.Scheb ǁ, Criminal law and Procedure, fifth edition, Thomas and
Wadsworth, 2005.
2
ዝኒ ከማሁ፣.በመሰረቱ ፍርድ ክለሳ በግርድፉ ይግባኝ ቀደም ሲል የተሰጠ ውሳኔ ወይም ብይን እንዲሻር፣
እንዲሻሻል በአጠቃላይ እንዲከለስ የሚቀርብ አቤቱታን የሚመለከት ቢሆንም የኮመን ሎው የሕግ ሥርዓትን
ማዕከል በሚያደርጉ የፍርድ ሂደቶች ውስጥ ፍርድ ክለሳ በእንግሊዝኛው ( trial de novo , appeal of rights
,discretionary review and post conviction relief የሚባሉ አይነቶችን ሁሉ የሚያቅፍ ሰፊ ሂደት እንደሆነ
ጹሁፎች ያስረዳሉ፡፡
3
Bryan A. Garner, Black’s Law dictionary, 9th ed., 2009, West Thomson Reuters business
.p.112-113
“Appeal Is a proceeding undertaken to have a decision reconsidered by bringing it to a higher
authority; the submission of a lower court’s or agency’s decision to a higher court for review and
reversal.“
4
Nathan A.Smyth,The Limitation of the right to appeal in criminal cases,Harvard Law
Review,vol.17,s(mar.,1904 .pp.317-330) https://www.jstor.org/stable/pdf/1322987.pdf
ሂደት ፍርድ ቤቱ የቀረቡለትን ማስረጃዎች በአግባቡ ባለመፈተሹ፤በተሳሳቱ ፣በሀሰተኛ ወይም
አግባብነት በሌላቸው ማስረጃዎች በመመስረቱና በመሳሰሉት ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ተከሳሽ በስር ፍርድ ቤት ራሱን ለመከላከል በሚያስችለው የችሎት ሂደት
ውስጥ ባለማለፉ ምክንያት ኢ-ፍትሃዊ ውሳኔ ይተላለፋል፡፡5 የይግባኝ ሥርዓት ደግሞ በእነዚህ
ሁኔታዎች ሳቢያ የመጣ የመብት ጥሰትን በሚገባ ለማረም የሚያስችል አውድ ተደርጎ
ይወሰዳል፡፡ ሁለተኛው ተግባር በስር ፍርድ ቤቶች/ችሎቶች የህግ ወጥነት በማምጣት ላይ
ያተኩራል ፡፡ በዋናነት በእርማቱ ሂደት ሕግጋት የበለጠ ግልጽ የሚደረጉና መርሆዎችም
የሚቀመጡ በመሆኑ የሕግ አተረጓጎምና አፈጻጸም ወጥነት በስር ፍርድ ቤቶች/ችሎቶች እየዳበረ
ይመጣል፡፡6 ሌላው ተግባር ከተቋማዊ ውጤታማነት ጋር የሚገናኝ ሲሆን በተለይም ህብረተሰቡ
በይግባኝ ስርዓት የሚታረሙ የፍትህ መጓደሎችን በመመልከት በጠቅላላው የወንጀል ፍትህ
አስተዳደሩም ሆነ በተቋማቱ ላይ ያለው እምነት እንዲጨምር ማስቻል ነው፡፡7 ከዚህ ሁሉ በላይ
ክስ አቅራቢዎችም ሆኑ በየደረጃው ያሉ ፍርድ ቤቶችም ሁለተኛ ማጣራት የሚደረግበት
ይግባኝ መኖሩን ታሳቢ በማድረግ ስህተት ላለመፈጸም የተሻለ ጥንቃቄን እንዲያደርጉ የሚያግዝ
ሲሆን ተጠያቂነትም እንዲረጋገጥ መንገድ ይከፍታል፡፡8
ይህ መብት በበርካታ የሰብአዊ መብት ሰነዶች እና ስምምነቶች እውቅና የተሰጠው ሲሆን አለም
አቀፉ የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ቃልኪዳን9 በአንቀጽ 14 ማንኛውም በወንጀል ጉዳይ
ጥፋተኛ የተባለ ሰው የተላለፈበት የጥፋተኛነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔ በሕግ መሰረት ከፍ ባለው
ፍርድ ቤት እንዲታረምለት ይግባኝ የማለት መብት እንዳለው በግልጽ አስቀምጧል፡፡ የኢፌዲሪ
ሕገ መንግስትም እውቅናና ጥበቃ ከሰጣቸው መሰረታዊ የሰዎች መብቶች መካከል ይግባኝ
አንዱ ተደርጎ የተካተተ ሲሆን የተከሰሱ ሰዎች ክርክሩ በሚታይበት ፍርድ ቤት በተሰጠባቸው
ትዕዛዝ ወይም ፍርድ ላይ ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ይግባኝ የማለት መብት እንዳላቸው

5
Peter D Marshall, A comparative Analysis of the right to appeal ,Duck journal of comparative
& internarional law ,vol 22,2011. www.scholarship.Law.duke.edu(cgi).
6
ዝኒ ከማሁ
7
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 4
8
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 5
9
Article 14 (5), The United Nations, International covenant on Civil and Political Rights, is
amultilateral treaty adopted by the United Nations general Assembly with resolution 2200A (XXl)
on 16 December 1966 . It has been inforce since 23march, 1976. (ከዚህ በኋላ እንደነገሩ ሁኔታ
በአጭሩ ICCPR) ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
ይህ ቃልኪዳን “Everyone convicted of a crime shall have the right to his conviction and sentence
being reviewed by a higher tribunal according to law.” በማለት የይግባኝን መብትነት አመልክቷል፡፡
https://treaties.n.org/doc/publication/unts/volume%20999/volume-999-i-14668-english.pdf
ይደነግጋል፡፡10 የመብቱን ቁልፍነት ማዕከል ባደረገ መልኩ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ የወንጀል ፍትህ አስተዳዳር ፖሊሲም11 የይግባኝ ሂደትን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ
ለማጠናከር የሚያስችሉ የአሰራር ሥርዓቶች ተግባራዊ እንደሚደረጉ በማስቀመጥ በተለይም
በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 20 እንደተመለከተው ማንኛውም ሰው በወንጀል በተከሰሰበት ጉዳይ ላይ
ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝ ወይም ፍርድ የሕግ ወይም የፍሬ ነገር ስህተት አለው ብሎ ካመነ
ቅሬታውን በሕግ ተለይቶ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ይግባኝ ለማየት ሥልጣን ላለው
የበላይ ፍርድ ቤት በጽሁፍ የማቅረብ መብት ያለው መሆኑን ያመለክታል፡፡ በሌላም በኩል
ዐቃቤ ሕግም ተመሳሳይ መብት እንዳለው በመግለጽ ይህንን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ግን
በፍርድ ቤቱ የተሰጠው ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ የሕግ ወይም የፍሬ ነገር ስህተት ያለው መሆኑን
ከማረጋገጥ በተጨማሪ በጉዳዩ ላይ ይግባኝ ባይቀርብበት የሕዝብ ጥቅም የሚጎዳ መሆኑን
ማመን እንደሚጠበቅበት ያስቀምጣል፡፡12 የህብረሰተቡን ጥቅም የሚወክለው ዐቃቤ ሕግ በስር
ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ፍትሃዊነት እንደጎደለው ወይም የፍርድ ጥበብ በእጅጉ እንዳነሰው
ካመነ ላቀረበው ክርክር በዚህ መልኩ ድጋፍ ያልሰጠውን ውሳኔ ለማሳረም የሚችልበት
ሥርዓት ሊኖር ይገባል ፡፡13 በዚህ ረገድ የደቡብ አፍሪካ የሕግ ኮሚሽን በመንግስት ወይም
በዐቃቤ ሕግ በኩል ሊቀርብ የሚችልን የይግባኝ ቅሬታ ተገቢነት ከህብረተሰብ ፍላጎት ጋር
አስተሳስሮ የሰጠውን ማብራሪያ መመልከት ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም ፦ " የህዝብ ጥቅም ወይም
ፍላጎት በቀላሉ አንድን ሕግ ደንገጎ አውጥቶ ማስቀመጥ ላይ የሚወሰን አይደለም፡፡ ይልቁንም
’የህብረተሰብ ፍላጎት ’ እጅግ ሰፋ ባለ መልኩ ፍትሀዊ በሆነ ችሎት ቀርበው የነበሩ ወንጀለኞች
ጉዳዩን አከራክሮ ፍርድ በሰጠው ፍርድ ቤት/ ችሎት ግልጽ የችሎታ ማነስ ወይም ስህተት ነጻ
እንዳይወጡ ማድረግን የሚያካትት ጽንሰ ሀሳብ ነው፡፡" በማለት ያስቀመጠ ሲሆን ይኸውም
በስር ፍርድ ቤት ያላግባብ የሚሰጥን በነጻ የማሰናበት ውሳኔ ለማስተካከል ይግባኝ ይህንን
የህብረተሰብ ፍላጎት ማሳኪያ አንዱ መንገድ መሆኑን ያሳያል፡፡14 የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ

10
አንቀጽ 20 (6)፣የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት፣1987፣ የፌደራል ነጋሪት
ጋዜጣ፣አዋጅ ቁጥር 1/1987፣1ኛ አመት ቁጥር 1፣አዲስ አበባ፣(ከዚህ በኋላ የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት ተብሎ
ሊጠራ ይችላል፡፡)
11
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፣የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ፖሊሲ፣ፍትህ ሚኒስቴር፣የካቲት
25 ቀን 2003 ዓ.ም
12
ዝኒ ከማሁ
13
Anne Bowen, Double Jeopardy and Judicial Accountability: when is an Acquittal not an
Acquittal? Arizona State Law Journal.
14
Mervan Bennun, Prosecusion appeals against acquittals: The law commission’s proposals,
SACJ, 2002. “The public interest is not simply to have the law declared .The public interest
ሥርዓት ሕጉም ከቁጥር 181 እስከ 196 ባሉት ድንጋጌዎች በወንጀል ጉዳይ ላይ የስር ፍርድ
ቤት የሚሰጣቸው ትዕዛዞች ወይም ውሳኔዎችን ተከትሎ ይግባኝ ማቅረብ ስለሚቻልባቸው እና
ስለማይቻልባቸው ትዕዛዞች፣የይግባኝ ማመልከቻው ሊይዝና ሊከተል ስለሚገባው ይዘት፣
ይግባኝን ለማየት ስልጣን ስላላቸው ፍርድ ቤቶች እርከን እና ቅሬታው መቅረብ የሚገባበት
የጊዜ ወሰን ጭምር ለይቶ አስቀምጧል፡፡15 ሕጉ በቁጥር 181 የወንጀል ፍርድ ቤት በተከሳሹ
ላይ ጥፋተኛ መሆኑን በመፍረዱ ፣ለጊዜው የመልቀቅ ወይም ነጻ የመልቀቁ ፍርድ በመስጠቱ
የሚቀርቡ የይግባኝ ቅሬታዎች ሁሉ የሚስተናገዱት ለዚሁ በተዘጋጀው አምስተኛ መጽሐፍ ስር
በተመለከቱት ድንጋጌዎች አግባብ እንደሆነ በግልጽ ደንግጎ እናገኘዋለን፡፡16 በመሰረቱ ስራ ላይ
ባለው የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ሥርዓታችን በሚመራው የፍርድ ሂደት ውስጥ በግራ ቀኙ
ያሉትን ማለትም ተከሳሽ ወይም ዐቃቤ ሕጉ የሚኖራቸው ይግባኝ የማቅረብ መብት ፍርድ ቤቱ
የሚሰጠውን ትእዛዝ ወይም ፍርድ መሰረት የሚያደርግ ይሆናል ፡፡17 በዚህ መልኩ የይግባኝ
ቅሬታ የቀረበለት ፍርድ ቤት በዋናነት በስር ፍርድ ቤቱ የተሰጠውን ትዕዛዝ ወይም ፍርድ
በተመለከተ የሚሰጠው ውሳኔ በሥነ ሥርዓቱ ተለይቶ የጠቀመጠ ነው፡፡18 ይኸውም፦ ይግባኝ
ሰሚው ፍርድ ቤት ይግባኙን ለመመልከት በቂ ምክንያት አለ ብሎ ካሰበ ሀ)ተከሳሹን ነጻ
በመልቀቅ ወይም ለጊዜው በመልቀቅ ይግባኝ በተባለ ጊዜ ትእዛዙን ሰርዞ ስልጣን ያለው ሌላ
ፍርድ ቤት ነገሩን እንደገና እንዲያይ ማዘዝ ወይም ጥፋተኛ ነው ብሎ እንደ ሕጉ ሊፈርድበት
ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ይግባኝ የተባለው በጥፋተኛነቱ እና በቅጣቱ ላይ ከሆነ ደግሞ

goes much wider and it includes that guilty persons should not be acquitted because of clear
error or incompetence.” በማለት በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ውስጥ ይህ ፍላጎት ያለውን ሰፊቦታ ያሳያል፡፡
15
አንቀጽ 181-196፣ የኢትዮጵያ ፡ንጉሠ፡ነገሥት፡ መንግሥት፡ የወንጀለኛ፡ መቅጫ፡ሕግ ሥነ፡ሥርዓት፣ቁጥር
1/1954 ዓ.ም፣ ነጋሪት ጋዜጣ ፣አዲስ አበባ፣1954 ዓ.ም፣ (ከዚህ በኋላ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ
ወይም የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ ተብሎ በአጭሩ ሊጠቀስ ይችላል፡፡)
16
ዝኒ ከማሁ ፣የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 181
17
ዝኒ ከማሁ፣የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 142 እና 149 (2) ፣ የወ/መ/ሕ/ሥ/ሠ፣ምክንያቱም
የመጀመሪያው የሥነ ሥርዓት ህጉ በቁጥር 141 የክሱ ባለቤት የሆነው ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ክስ በበቂ ማስረጃ
ያላስረዳ እንደሆነ እና መከላከያ መስረጃ መስማት ሳያስፈልግ ተከሳሹን ጥፋተኛ የሚያድርገው ሳይሆን ከቀረ
ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በነጻ እንዲለቀቅ ትእዛዝ እንደሚሰጥ ይደነግጋል፡፡አንቀጽ 141 ፣ የወ /መ/ሕ/ሥ/ሥ/ በዚህ
ረገድ በአንጻሩ ዐ/ሕጉ ባቀረበው ማስረጃ ተከሳሽ ስለተመሰከረበት እንዲከላከል የተሰጠውን ብይን አንቀጽ 142
፣የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ ተከትሎ በመከላከያ ማስረጃ ማስተባበል ከቻለም በተመሳሳይ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ አይደለም
የሚል ፍርድ በማሳለፍ በማረፊያ ቤት ካለም እንዲለቀቅ የሚል ትእዛዝ በተጨማሪ በተከሳሽ ላይ የተላለፈው
ቅጣትም አንሷል የሚል ቅሬታም ሊቀርብ ይችላል፡፡ በሌላ በኩልም ተከሳሽ ደግሞ በዐቃቤ ሕግ ወይም በግል
ከሳሹ በኩል የቀረበበትን ክስ ማስተባበል ካልቻለ እና ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ሆኖ ካገኘው የጥፋተኛነት ውሳኔ
ያስተላልፋል ቅጣትም ይወስናል ፡፡ አንቀጽ149 (3) እና (5)፣የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ በዚህ መልኩ በተሰጠው ውሳኔ
ቅሬታ የተሰማው ተከሳሽም በእምነቱ የተሰጠ ውሳኔ እስካልሆ ድረስ እንደነገሩ ሁኔታ በጥፋተኛነቱ እንዲሁም
በቅጣቱ ላይ ይግባኝ ማመልከቻውን ለበላይ ፍርድ ቤት ለማቅረብ ይችላል ማለት ነው፡፡ አንቀጽ 185
(1)፣የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ.
18
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 15 ፣የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 195
የጥፋተኛነት እና የቅጣት ውሳኔውን ሰርዞ ተከሳሹን በነጻ ለመልቀቅ ፤ ወይም ፍርዱን ለውጦ
ወይም ሳይለውጥ ቅጣቱን ሊያጸና ፤ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡ ጥፋተኛ ነው
በተባለበት ውሳኔ ላይ ብቻ ይግባኝ በተባለ ጊዜ ፍርዱን እና ቅጣቱ ሰርዞ ተከሳሹን በነጻ
ለመልቀቅ ይችላል፡፡ ሆኖም የቀረበው ይግባኝ ቅጣቱን ብቻ የተመለከተ ከሆነ የስር ፍርድ ቤቱ
የወሰነውን ቅጣት ለማጽናት፤ ወይም ደግሞ አሻሽሎ ለመጨመር ወይም ለመቀነስ እንደሚችል
ቁጥር 195 ያስገነዝባል፡፡ በተለይ ከተከሳሾች መብት አንጻር በዚህ አግባብ የሚከወነው የወንጀል
ይግባኝ ስርአት በስር ፍርድ ቤት ባልተገባ መንገድ ጥፋተኛ ተብለው በእስር በሚገኙ ግለሰቦች
ላይ ህብረተሰቡ በያዘው የጥፋተኛነት እምነት ውስጥ ምክንያታዊ ጥርጣሬ ለመፍጠር
የሚችሉበትን ልዩ እድል ይፈጥራል ፡፡19 ስለሆነም ይግባኝ በስህተት፣ በቸልተኛነት ወይም ሆነ
ተብሎ በተሰጠ ኢ-ፍትሀዊ ፍርድ ምክንያት ግለሰቦች እስከ ወዲያኛው ለእስር እንዳይዳረጉ
በእጅጉ ያግዛል፡፡20 ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በመርህ ደረጃ በየትኛውም የወንጀል ፍትህ
አስተዳዳር ውስጥ በገለልተኛ ፍርድ ቤት ተገቢውን ክርክር አድርጎ ጥፋተኛ ተብሎ በእስራት
እንዲቀጣ የተወሰነበት ሰው ይግባኙ ታይቶ እስኪወሰን ድረስ እስራቱ ታግዶ በዋስትና
እንዲወጣ በልዩ ሁኔታ እስካልተፈቀደለት ድረስ ወድያውኑ ቅጣቱን መፈጸም መጀመር
ይኖርበታል፡፡21 በዚህም ጽሁፍ በይግባኝ ሥርዓት የእስራት ቅጣት ፍርድን በማገድ ይግባኝ
አመልካችን በዋስትና የመልቀቅ ሂደት ይዳሰሳል፡፡

2. በይግባኝ ጊዜ የእስራት ቅጣትን ስለማገድ


2.1 የእስራት ቅጣት አፈጻጸምን የማገድ አላማ
ከፍ ሲል ለማብራራት እንደተሞከረው የይግባኝ ሥርዓት የተደራጀው ጉዳዮችን በመጀመሪያ
ደረጃ አከራክረው የሚወስኑ ፍርድ ቤቶች በሠጧቸው ፍርዶች ስህተት ምክንያት የሚደርስን
የፍትህ መጓደል ወይም ጉዳት ለመቀነስ የሚያስችል ሁለተኛ እድል መስጠት ነው፡፡ ከዚህ
አኳያ የእስራት ቅጣት አፈጻጸም እገዳ ማሳካት የፈለገው አላማም ማዕከል የሚያደርገው
በቅጣቱ መቀጠል ምክንያት በተከሳሽ ላይ የሚደርስን ጉዳት መከላከልን የተመለከተ በመሆኑ
የይግባኝ ሥርዓት አጠቃላይ አላማና ባህሪይ ቅጥያ /አካል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡22 ይህ ሥርዓት

19
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 4
20
ዝኒ ከማሁ
21
Doug Keller, Resolving a “SUBSTANTIAL QUESTION”: Just who if entitled to bail pending
appeal under the bail reform Act of 1984? Florida Law review, vol 60. 2008.
http://www.floridalawreview.com/wpcontent/uploads/2010/01/Keller_BOOK.pdf
22
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 5
በብዙዎቹ የአለማችን የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግጋት እውቅና የተሰጠው ሲሆን "በይግባኝ
ሰሚ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱ ታግዶ በዋስትና ያልተለቀቀና በመጨረሻም የጥፋተኛነቱ ውሳኔ
የተሻረለት የስር ፍርድ ቤት ጥፋተኛ የሚደርስበት ኢ-ፊትሀዊነት ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ
በተመለከተው ፍርድ ቤት ትእዛዝ ታስሮ በመጨረሻም ከቀረበበት ክስ በነጻ ከተሰናበተ ተከሳሽ
ጋር ተመሳሳይ ነው " በሚል ንጽጽራዊ ምልከታ አስፈላጊነቱ ይገለጻል ፡፡23 በህንድ የእስራት
አፈጻጸም እገዳን የተመለከተ ድንጋጌ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉ ውስጥ የመካተቱን አላማ
ያብራራበት ሪፖርትም በተመሳሳይ መልኩ የሚታይ ነው፡፡ ሪፖርቱም የስር ፍርድ ቤቱ ፍርድ
እንደገና እስኪከለስ ምናልባትም ይግባኝ ባይ የተጣለበትን የእስራት ቅጣት እየፈጸመ
እንዲቀጥል ተደርጎ በመጨረሻም በይግባኝ ፍርድ ቤቱ ነጻነቱ ቢረጋገጥ ያሳለፈው በደል
የማይካስ ስለሚሆን ቅጣቱን ለጊዜው ማገድ ከዚህ አደጋ እንደሚታደግ በማብራራት ይህ ሂደት
ከይግባኝ ሥርዓት አጠቃላይ አላማ ጋር የተሳሰረ መሆኑን ያሳያል፡፡24 በተለይ የይግባኙ ሂደት
መጨረሻ የጥፋተኛነቱን ውሳኔ የሚሽር በሚሆንበትና የእስሩ መቀጠል በግለሰቡ ላይ የማይካስ
ጉዳትን በሚያመጣበት ሁኔታ ጥፋተኛውን በእስር ቤት መቆለፍ በየትኛውም መመዘኛ ፍትሀዊ
ሊሆን አይችልም፡፡25 ይህ ሁኔታ ደግሞ በይግባኝ ሂደት ፍርድ እንዳይፈጸም ማገድና ይግባኝ
ባይን በዋስትና የመልቀቅ ወይም በእንግሊዝኛው (stay of execution) እርምጃን እጅግ ወሳኝ
ያደርገዋል፡፡ በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ውስጥም ይግባኝ ፍርድ ቤቱ የእስራት
ቅጣትን እንዳይፈጸም ማገድ የሚችልበት ሁኔታ ማመልከቻው ከነሚቀርብበት ጊዜ ጭምር
"ፍርድ እንዳይፈጸም ስለማገድ" በሚል ርዕስ በአንቀጽ 188 ስር ተደንግጓል፡፡26 ከወንጀል
ይግባኝ ሥርዓት አኳያ በማንኛውም ደረጃ ባለ ፍርድ ቤት የሚሰጥ የተሟላ “ፍርድ” ሁለት
ዋና የፍርድ አስተያየቶችና ውሳኔዎችን የያዘ ነው፡፡ አግባብነት ባለው ሕግ ተጠንቶና ተመዛዝኖ
ተከሳሹ ጥፋተኛ መሆኑን የሚገልጸው የፍትህ አስተያየት የመጀመሪያው ሲሆን በዚህ መልኩ
በተደረሰው ጥፋተኛነት መሰረት ሊሰጠው የሚገባውን የቅጣት መጠን የሚወስነው የፍትህ

23
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 21 ፣"A defendant who is denied bail pending appeal and his conviction
reversed suffers the same injustice as a defendant who is imprisoned before trial and
subsequently acquitted ". በማለት የዚህን ስርአት ወሳኝነት ይገልጻሉ፡፡
24
THE CODE OF CRIMINAL PROCEDURE, 1973, ACTS NO. 2 OF 1974 and Report No.268
Amendments to Criminal Procedure Code, 1973 –Provisions Relating to Bail, 23 may 2017.p74
"This provision was inserted because when an appeal is filed, the conviction needs to be re-
judged and pending such decision, if it so happens that the appellant has undergone some
part of the sentence, and ultimately is adjudged as innocent, his suffering becomes irreversible.”
25
ዝኒ ከማሁ
26
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 15፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 188
27
አስተያየትና ውሳኔ ደግሞ ሌላኛው ነው፡፡ ድንጋጌው በይግባኝ ጊዜ በስር ፍርድ ቤት በኩል
የተሰጠ ፍርድ የሚታገድበትና የእስራት ቅጣት አፈጻጸምም እስከ ሂደቱ መቋጫ ድረስ ሊቆም
እንደሚችል ይደንግግ እንጅ ይህ የሚሆንበትን አላማ ያስቀመጠ አይደለም ፡፡ በርግጥ ወደፊት
ይወጣል ተብሎ የሚታሰበው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ረቂቅ ይህ ሥርዓት የሚመራበትን
አዳዲስ ሁኔታዎች ያስቀመጠ ሲሆን ከፍ ብሎ በተለያዩ ጹሁፎች እንደተገለጸው ሁሉ ተፈጻሚ
የሚሆነው የተሰጠው ፍርድ ፣ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ ቢፈጸም የማይተካ ጉዳት ይደርሳል ተብሎ
ሲታመን እንደሆነ በማስቀመጥ አላማውን ያመላከተበትን አግባብ ማየት ይቻላል፡፡28 ይህ
የእስራት ቅጣት አፈጻጸም እንዲታገድ የሚጠይቀው ማመልከቻ የሚቀርብበትን ጊዜ በተመለከተ
በስራ ላይ ያለው የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ ቁጥር 188 ተከሳሹ ይግባኙ እስኪወሰን የእስራት ቅጣቱ
እንዳይፈጸምበት ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ማመልከቻ ለማቅረብ የሚቻለው ይግባኙ ከመሰማቱ
በፊት በማንኛውም ጊዜ ወይም ደግሞ ይግባኙ በሚሰማበት በማንኛውም ጊዜ ሊሆን
እንደሚችል ነው ፡፡29 በርግጥ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ይህንን ለመከልከልም ሆነ ለመፍቀድ
ስልጣን ያለው ቢሆንም በአንጻሩ መፈጸማቸው ይደርሳል ተብሎ የታሰበውን ጉዳት
የማያስከትሉና የስር ፍርድ ቤቱ ለጥንቃቄ ሲባል የሰጣቸው ትእዛዞች፤ ማለትም ተበዳይን
ለመካስ፣ለፍርድ ሂደቱ የወጣ ወጭንና የመሳሰትን ወጭዎች እንዳይፈጸሙ ለማገድ
እንደማይችል መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡30 ይህ ገደብ መኖሩ ደግሞ በተጨባጭ የእስራት አፈጻጸም
እገዳን ላይ ለመወሰን ለይግባኝ ሰሚው የተሰጠው ስልጣን (discretionary power) ለልዩ አላማ
በጠባቡ ተግባራዊ መደረግ ያለበት ለመሆኑ ጥሩ መገለጫ ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡
2.2 የእሥራት ቅጣትን ለማገድ የሚያበቁ ምክንያቶች
በአብዛኛው በቅጣት መቀጠል የሚመጣ ጉዳትን የመከላከል ቁልፍ አላማ ያለው ይህ የይግባኝ
ስርአት ሂደት በርካታ ክርክሮች የሚስተዋሉበት ሲሆን ለዚህም በዋናነት ሂደቱ ከሚመራባቸው
ሁኔታዎች ጋር አብረው የሚታዩ ሁለት የተለያዩ ፍላጎቶች መኖራቸው በቀዳሚ ምክንያትነት
ይጠቀሳል፡፡31 በአንድ በኩል ጥፋተኛው ይግባኙ ታይቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ በይግባኝ ሰሚ
ፍርድ ቤቱ በኩል በዋስትና እንዳይወጣ ማድረግ በራሱ የስር ፍርድ ቤቱን የጥፋተኛነት ውሳኔ
ህጋዊ ነው የሚል እውቅና የመስጠት ውጤት አለው የሚለውን የግለሰቡን ፍላጎት መነሻ

27
ጊዜያዊ አከራካሪ አስተያየት፡ስለወንጀል ይግባኝ፣የኢትዮጵያ የሕግ መጽሔት፣1ኛ ቮልዩም፣ቁጥር2፣1953ዓም
28
አንቀጽ 360፣ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ርፐብሊክ ፡የወንጀል ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ
ሕግ፣አዋጅ ቁጥር …/2009 ፣የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፣2009 ዓ.ም፣ ረቂቅ (ጸድቆ ያልወጣ)
29
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 15 ፣የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርአት ሕግ አንቀጽ 188 (2) እና (5)
30
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 15 ፣የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርአት ሕግ አንቀጽ 188 (3) እና (4)
31
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 21
ያደርጋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ህብረተሰቡ የእስር ቅጣትን በሚያስከትል የወንጀል ድርጊት
ጥፋተኛ መሆናቸው ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በጸዳ መልኩ የተረጋገጠባቸው ግለሰቦችን በማሰር
ራሱን የመጠበቅ ከፍተኛ የፍትህ ፍላጎት አለው፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው ይግባኙ እስኪጠናቀቅ
ድረስ እስራቱ ታግዶ በዋስትና ሊለቀቅ የሚችለው በምን በምን ሁኔታዎች ነው ? የሚለው
ጉዳይ በጥፋተኛው እና በህብረተሰቡ ፍላጎቶች መካከል ያለ ጥንቃቄ የሚፈልግ ሚዛን ይሆናል
32
ማለት ነው፡፡ በርግጥ የሥነ ሥርዓት ሕጋችን አንቀጽ 188 ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ
በይግባኝ ባይ-ጥፋተኛ በኩል የቀረበን የፍርድ መፈጸም ይታገድልኝ ማመልከቻ ሲቀርብለት
ሂደቱ እስኪቋጭ ድረስ በዋስትና ወረቀት ሊለቀው የሚችልበት ስልጣን ያለው መሆኑን
ከማስቀመጥ ባለፈ ይህንን ለመወሰን የሚያስችሉ መሰረቶችን ወይም መርሆዎችን
(guidelines) አላስቀመጠም፡፡ እንዲህ በሆነ ጊዜ በሕግ ባለሙያዎች ዘንድ የአስተሳሰብ እና
የአሰራር ልዩነቶች መኖራቸው የማይቀር ነው ፡፡ በመሆኑም በይግባኝ ቅጣትን በማገድ ይግባኝ
ባይ- ጥፋተኛን በዋስትና መልቀቅን ለተመሳሳይ አላማ በሕጎቻቸው ውስጥ ያካተቱ ሀገራት
የሕግ ማዕቀፎችን መዳሰስ ለተሻለ አረዳድ ወሳኝነት ይኖረዋል ፡፡ ለአብነት የአሜሪካ ፌደራል
የወንጀል ሥነ ሥርዓትን33 ብንወስድ ይግባኝ ባይ - ጥፋተኛ ያቀረበው ይግባኝ ተመርምሮ
እስኪጠናቀቅ ድረስ ባለው ጊዜ እስራቱ እንዲታገድለት ያቀረበው ማመልከቻን ለመወሰን
በይግባኝ ሰሚው መሰረት ከሚደረጉ ነጥቦች መካከል፤
ሀ) በዋስትና ከእስር ቢወጣ በማህበረሰቡ ወይም በሌሎች ግለሰቦች ላይ የደህንነት ስጋት ሊሆን
የማይችል ወይም ቅጣቱን ላለመፈጸም ከፍትህ የመሸሽ አዝማሚያ የሌለው መሆኑ፤
ለ) ይግባኙን ያቀረበው ሆነ ብሎ የቅጣት መፈጸሙን ለማጓተት የማይመስልና ይግባኙ
Ø በስር ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ መሻርን የሚያስከትል መስሎ በሚታይበት ጊዜ ወይም
Ø ድጋሚ በአዲስ ችሎት እንዲታይ የሚያደርግ ትዕዛዝ ሊያሰጥ የሚችል መስሎ በሚታይበት
ጊዜ ፤
Ø ሊሰጥ የሚገባው ቅጣት የእስራት ቅጣትን የማያስከትል መስሎ በሚታይበት ጊዜ ፤
Ø የሚወሰነው ቅጣት ከፈጸመው የእስራት ጊዜና የይግባኙ ሂደት ይወስዳል ተብሎ ከሚጠበቀው
የሚያንስ የሚመስል፤
መሰረታዊ የሕግ ወይም የፍሬ ነገር ጥያቄዎችን (Substantial question of Law or fact)
የሚያስነሳ መሆኑ ይገኙበታል፡፡
32
ዝኒ ከማሁ
33
18 U.S. Code § 3143 - Release or detention of a defendant pending sentence or appeal,
U.S.code>Title 18>part II>Chapter 207> §3142, https://www.law.cornell.edu/uscode/text/18/3143
በመሆኑም አመልካቹ ቅጣቱ ቢታገድለትና በዋስትና ቢወጣ ከፍትህ የማይሸሽ፤ ለጠቅላላው
ህብረተሰብ የደህንነት ስጋት የማይሆን እና ያቀረበው ይግባኝም መሰረታዊ የህግ ወይም የፍሬ
ነገር ጥያቄ እንደሚያስነሳ በግልጽና ጠንካራ ማስረጃ የዳኝነት አካሉን ማሳመን
ይጠበቅበታል፡፡34 እዚህ ላይ በምርመራው ሂደት በፍርዱ ውስጥ የሚታረም መሰረታዊ ነጥብ
መኖሩን በጥንቃቄ መለየት የስር ፍርድ ቤትን ፍርድ የመቀየር እድልን የሚያሳይ በመሆኑ
ቅጣቱ እንዲቀጥል ማድረግ የማይካስ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል የሚል ግንዛቤን ለመያዝ በእጅጉ
ያግዛል፡፡35 ስለሆነም አመልካች የመጀመሪያ ደረጃ የወንጀል ክርክሩ በሂደቱም ሆነ በውጤቱ
ላይ ግልጽና የተረጋገጡ ችግሮች የነበሩበት ስለመሆኑ ለቅሞ ማውጣት ሊጠበቅበት ይችላል፡፡36
በመሰረቱ የይግባኝ ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ እስራቱን አግዶ አመልካችን በዋስትና ለመለቀቅ
በስር ፍርድ ውስጥ ሊስተካከል የሚገባ መሰረታዊ ነጥብ መኖሩ ብቻውን በቂ ሊሆን
እንደማይችል ግንዛቤ ሊወሰድበት ይገባል፡፡ ምክንያቱም በወንጀል ፍርድ አስተዳደር ስርአቱ
ውስጥ ሁልጊዜ ከአመልካቹ መብት ጎን ለጎን ያለው የህብረተሰቡ ፍላጎነትም ቅጣቱን ለማገድና
በዋስትና በመልቀቅ ወይም ባለመልቀቅ የይግባኝ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሌላኛው ወሳኝ መሰረት
መሆን ይገባዋል፡፡ በመሆኑም አመልካቹ ተፈቅዶለት ቢወጣ ምን አልባት ቅጣቱን ላለመፈጸም
የማምለጥ ወይም ለህብረተሰቡ አደጋ የመሆን ስጋት አለመኖሩን የማረጋገጥ ሃላፊነት በፍርድ
ቤቱ ላይ ማረፉ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡37 ከአሜሪካ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ልንረዳው የሚገባው
ሌላው ቁልፍ ነጥብ ደግሞ ፍትህን በመቃረን ቅጣትን ለማጓተት ታስቦ የቀረበ ይግባኝ
ሊስተናገድ የሚችል አለመሆኑ ነው፡፡ ይኸውም ቀድሞውኑም ይህ ሥርዓት የተቀረጸው
የእስራት ቅጣት መቀጠል የማይተካ ጉዳት ሊያደርስባቸው የሚችል ቅን ልቦና ያላቸው ሰዎችን
ለመጠበቅ ከመሆኑ ጋር አጣምሮ በመመርመርና በመወሰን ረገድ ፍርድ ቤቱ ከፍተኛ ሀላፊነት
ያለበት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ በመሰረቱ በይግባኝ ሥርዓት በስር ፍርድ ቤት የተላለፈ እስራት
እንዳይፈጸም ማገድን ለመወሰን የሚያስችሉ ምክንያቶችን ማስቀመጥም ሆነ መወሰን በተግባር

34
ዝኒ ከማሁ
35
Simeneh Kiros ,criminal Procedure Law ,Principles ,Rules and Practices ,Xlibris corporation,
USA.2009.p 453-455
36
የህንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በState of Maharashtra v. Gajanan, AIR 2004 SC 1188. በዚህ በታወቀ
ጉዳይ ላይ ከሰጠው የውሳኔ ሐተታ ውስጥ የተወሰደ ፡፡ https://indiankanoon.org/doc/51674427/
37
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 21፣
ቀላል አይደለም፡፡38ለዚህም ነው ቅጣትን ማገድ በፍርድ ቤቱ መዝገብ ላይ በሚሰፍሩ ጠንካራ
ምክንያቶች መደገፍ እና በውሳኔው ውስጥ በአግባቡ በጽሁፍ መስፈር አስፈላጊ የሚሆነው፡፡39
2.3 የእስራት ቅጣት አፈጻጸም የሚታገድለት ማነው?
ከዚህ ሥርዓት ጋር በተያያዘ መነሳት ያለበት ሌላው ጉዳይ በስር በፍርድ ቤቱ የተወሰነበት
ፍርድ መፈጸም በይግባኝ የሚታገድለት ተከራካሪ ማንነት እና ሀላፊነት ጋር ይያያዛል፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ ይህ የማይተካ ጉዳትን የመከላከል አላማ ያለው የፍርድ እገዳ ትዕዛዝ
አድማስ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህጉ የተወሰነ መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ
ሂደት የሚመራበት አንቀጽ 188 ርዕሱ “ፍርድ እንዳይፈጸም ስለ ማገድ” ይበል እንጂ ንዑስ
አንቀጽ 2 በርግጥም የሚታገደው ፍርድ እስራትን ያስከተለው ፍርድ ብቻ እንደሆነ በግልጽ
አስቀምጦታል፡፡ በዚህም መሰረት የቅጣት ፍርድ ይታገድልኝ ጥያቄ ሊቀርብ የሚችለው
ጥፋተኛ በተባለውና የእስሩ አፈፃጸም ታግዶለት ከእስር ውጭ ለጊዜው መሆኑ የሚጠቅመው
በአንጻሩም ቢከለከል የሚጎዳው የስር ፍርድ ቤት ጥፋተኛን/ይግባኝ ባይን ይሆናል፡፡40 በሌላ
በኩል የድንጋጌው ተፈጻሚነት በጠንካራ ምክንያቶች ላይ የሚመሰረት በመሆኑ በስር ፍርድ
ቤት ውሳኔ ላይ ይግባኝ ያቀረቡ አመልካቾችን ወይም የስር ጥፋተኛዎችን በሙሉ ለማስተናገድ
የተቀረጸና በመብትነት የሚጠየቅ አለመሆኑንም ጭምር ማስታወስ ተገቢነት አለው፡፡41 ከዚሁ
ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለእስራት እገዳ በሚቀርብ የይግባኝ ባይ ማመልከቻ ላይ በወንጀል ክርክር
ሂደቱ ውስጥ በተከራካሪነት ያሉት ወገኖች (ማለትም፤ የህብረተሰቡን ፍላጎት የሚወክለው
ዐቃቤ ሕግ፣ የግል ከሳሽ ወይም የግል ተበዳዩች) ሚና ምን ሊሆን ይችላል የሚለውን ማየት
ያስፈልጋል፡፡ የሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 188 ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ የእገዳ ማመልከቻው

38
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 24
39
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 24 " … suspension of the sentence must be accompanied by reasons
recorded by the court, this requirement for justifying the suspension of sentence indicate that
there must be a careful consideration of the relevant factors and the order directing the
suspension of sentence must not be cursory in nature. "
40
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 15፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 188 አርዕስት የአማርኛው ቅጅ
“ፍርድ እንዳይፈጸም ስለ ማገድ” እና የእንግሊዝኛው ቅጅም “stay of execution” በሚል ካስቀመጠ በኋላ
በንዑስ ቁጥር (2) የጥፋተኛነት ፍርድን ተከትሎ የሚሰጠው የፍርድ እገዳ የእስራት ቅጣት ፍርድ እንደሆነና
ይህም እስራት የተወሰነበትን የስር ጥፋተኛ እንደሚመለከት ግልጽ አድርጎታል፡፡ በሌላ በኩል ግን በስር ፍርድ ቤቱ
የተሰጠ በነጻ የመልቀቅ ፍርድን በመቃወም ይግባኝ ያቀረበ ዐ/ሕግ ወይም የግል ከሳሽ ይህ ፍርድ እንዲታገድና
በነጻ የተሰናበተው ተከሳሽ እንዲታሰር ፍርድ ቤቱን ለመጠየቅ የሚችልበት ዝርዝር ሁኔታና ይህም ጥያቄ
የሚስተናገድበት ሥነ ሥርዓታዊ አግባብ ምን ሊሆን ይገባል? የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ራሱን የቻለ ዝርዝር
ጥናት የሚያስፈልገው መሆኑ ግንዛቤ ሊወሰድበት ያስፈልጋል፡፡
41
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 24
ሲቀርብለት የማገድ ትእዛዝ ለመስጠት እንደሚችል ሲያስቀምጥ ጉዳዩ የሚመለከታቸው
የክርክሩ አካላት በማመልከቻው ላይ አስተያየት መስጠት ስለመቻላቸው በግልጽ የሚናገረው
ነገር የለም፡፡ ከዚህ የተነሳም በተግባር በአንዳንድ ጉዳዩች በዚህ መልኩ የሚቀርብ የእገዳ
ማመልከቻ ላይ እንደነገሩ ሁኔታ የዐቃቤ ሕግ ወይም የግል ከሳሽ/ሾች አስተያየት ሳይሰማ
የተሰጡ ውሳኔዎችን እንመለከታለን፡፡42 በመሰረቱ በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ውስጥ ከተከሳሽ
ጎን ያለው ሌላኛው ተከራካሪ ወገን የወንጀል ድርጊት ፈጽመዋል በሚል ክስ ያቀረበባቸው
ግለሰቦች በሕግ አግባብ ጥፋተኛ እንዲሰኙ ብቻ ሳይሆን የተላለፈባቸው ቅጣት እስራትም ከሆነ
በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲፈጽሙ ይፈልጋል፡፡43 ከዚህ አንጻር ይህንን ሚዛናዊ ፍላጎት
ባማከለ መንገድ (የስር ተከሳሾች) ይግባኝ ባዮች የእስራት ቅጣቱ ታግዶላቸው ቢወጡ የደህንነት
ስጋት የሚሆኑ ወይም የተላላፈባቸውን ቅጣት ላለመፈጸም ከፍትህ የሚሸሹ ስለመሆናቸው
በተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉባቸው ሁኔታዎች ካሉ መቀበል ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ
ያግዛል በሚል ጸሀፊዋም ታምናለች፡፡ለዚህም ነው በአንዳንድ ሀገራት የሕግ ልምድ እነዚህን
ፍላጎቶች በአግባቡ ለማጣጣም ሲባል በይግባኝ ሂደት የእስራት ይታገድልኝ ጥያቄ ሲቀርብ
ማመልከቻው ለዐቃቤ ሕጉ ፣ለግል ከሳሹ ወይም ለግል ተበዳዩ እንዲደርሰው እና ተቃውሞም
ካለው እንዲያቀርብ የሚፈቀድበትን ሥርዓት የምንመለከተው፡፡44
3. በይግባኝ ቅጣት በሚታገድበት ጊዜ ይግባኝ ባዩን በዋስትና ስለመልቀቅ
በወንጀል ይግባኝ ሂደት ውስጥ በቅን ልቦና የስር ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ግድፈት እንዲታረምለት
የሚጠይቅ የስር ጥፋተኛ /ይግባኝ ባይ በእስራቱ መቀጠል የማይተካ ጉዳት እንዳይደርስበት

42
ለአብነት የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወ/ሰ/መ/ቁ 03-19212 በሰበር አመልካች አቶ ምዑዝ ገ/ህይወት እና
በክልሉ ዐቃቤ ሕግ መካከል በነበረው ክርክር የሰጠውን ውሳኔ መመልከት ይቻላል፡፡ በዚህ ጉዳይ አመልካች በስር
ፍርድ ቤቱ የተላለፈበት የጥፋተኛነት ውሳኔ የማስረጃ ምዘና መርህን የጣሰ ነው በሚል ካቀረበው አቤቱታ ጋር
አያይዞ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የእስራት ቅጣቱ ታግዶ በዋስትና እንዲለቀቅ የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 188(2)ን ጠቅሶ
ለችሎቱ እንዳመለከተ መዝገቡ ያሳያል፡፡ ፍርድ ቤቱም የአመልካችን ማመልከቻ ተቀብሎ የሰበር ችሎቱ ውሳኔ
እስኪሰጥ ድረስ እስራቱ እንዲቀጥል ቢደረግ በአመልካች ላይ የማይተካ በደል ይደርሳል በማለት አመልካች የብር
አምስት ሽህ ብር (5000 ሽህ ብር) ዋስትና ጠርቶ እንዲወጣ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ምንም እንኳን
ዐቃቤ ሕግ ፍርድ ቤቱ እግዱን ከፈቀደ በኋላ በዋናው ጉዳይ ላይ ሀሳብ ሲሰጥ በተጨማሪነት እግዱን በዝርዝር
የተቃወመ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ከመነሻው ዐቃቤ ሕግ እንዲያውቅና በማመልከቻው ላይ ሀሳብ እንዲሰጥ ያደረገበት
ሁኔታ ስለመኖሩ መዝገቡ አያሳየንም፡፡
43
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 21
44
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 24 ፣ለምሳሌ በሕንድ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ መሰረት በስር ፍርድ ቤት
የእሥራት ቅጣት የተላለፈበት ይግባኝ ባይ የፍርድ ይታገድልኝ ማመልከቻ ሲያቀርብ እንደጉዳዩ ሁኔታ ለዐቃቤ
ሕጉ ፣ለግል ከሳሹ ወይም ለተበዳዩ ማመልከቻው እንዲደርሳቸውና ተቃውሞም ካላቸው እንዲሰሙ ይደረጋል፡፡
መጠበቅን ማዕከል ያደረገው የእስራት ማገድ ሥርዓት አመልካችም በበኩሉ ዋስትና
እንዲያቀርብ ቅድመ ሁኔታን ያስቀምጣል ፡፡ ይህንን ሥርዓት በሕግ ማዕቀፎቻቸው ውስጥ
ያካተቱ የተለያዩ ሀገራት ልምድም ከፍ ሲል በተመለከቱት ሁኔታዎች እስራቱ የታገደለት ሰው
ከእስር ለመለቀቅ የሚችለው በዋስትና መሆኑን ያሳያሉ፡፡ በተመሳሳይ የወንጀለኛ መቅጫ
ሥርዓት ሕጋችን አንቀጽ 188ን (2) "ተከሳሹ ይግባኙ እስኪወሰን ድረስ በዋስትና ወረቀት
የተለቀቀ እንደሆነ የእስራቱ ቅጣት የይግባኙ ፍርድ ቤት ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ አይጀመርም፡፡”
በማለት እገዳውን ከዋስትና ጋር አስተሳስሮታል፡፡

3.1 የዋስትና ጽንሰ ሀሳብ


3.1.1 የዋስትና ምንነት
በመሰረታዊነት ጽንሰ ሀሳቡ ከጥንታዊቷ ሮም የተነሳው "ዋስትና" የሚለው ቃል ከወንጀል ሕግ
አንጻር45 በእስር ወይም ጥበቃ ስር ያለን ሰው ወደፊት ፍርድ ቤት ለመቅረቡ ማረጋገጫ
የሚሆን መያዧ እንዲያቀርብ በፍርድ ቤቱ የሚጠየቅ እና በምላሹም ከእስር እንዲወጣ
የሚደረግበት ሥርዓት እንደሆነ በሕግ ጉዳዩች ዙሪያ ትርጉም በመስጠት ተጠቃሽ የሆነው
ብላክስ ሎው መዝገበ ቃላት አስቀምጦታል፡፡46 ከትርጓሜውም እንደምንረዳው ዋስትና በነጻ
የሚሰጥ ስጦታ ባለመሆኑ የተያዘውን ግለሰብ ከእስር ነጻ የመሆን ፍላጎት እና ህብረተሰቡ
ያጠፉ ሰዎች በፍርድ ቤት ቀርበው እንዲዳኙ ያለውን ፍላጎት ሚዛን መጠበቅን ማዕከል
ማድረግ ይኖርበታል፡፡47 የዋስትናን አጠቃላይ ሂደት በአግባቡ ለመምራት የሚወጣ የሕግ
ማዕቀፍ ደግሞ በዋናነት የተከሰሰው ሰው ጥፋተኛነቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ንጹህ ሆኖ የመገመት
መብቱን ማረጋገጥ እና የህብረተሰቡና የፍትህ ፍላጎት ሚዛን የመጠበቅ መርሆዎችን መሰረት
ማድረግና መከተል አለበት፡፡48 ዋስትና ተጠርጣሪው ወይም ተከሳሽ ከእስሩ ውጭ የሚሆንበት
ሂደት በመሆኑ በአንድ በኩል የነጻነት ፍላጎቱን ያረጋግጥለታል፡፡ ሁለተኛውና ከህብረተሰቡ
የሚመነጨው ፍላጎት ደግሞ በሶስት መልኩ ሊታይ ይችላል፡፡ በየትኛውም የህብረተሰብ ክፍል
ውስጥ አንድ ሰው የወንጀል ተግባርን ፈጽሟል በሚል የተጠረጠረ እንደሆነ በሕግ በተዘረጋው

45
Timothy R.Schnacke, Michael R.Johnes and Claire M.B.Brooker, The History of Bail and pre-
trial release, Pre-trial Justice Institute ,2010. የዋስትና ጽንሰ ሀሳብ በሀገረ አሜሪካ ግንዛቤ የተወሰደበት
የ1000 ሽህ (የአንድ ሽህ )አመት እድሜ ካለው የእንግሊዝ ልምድ ተወስዶ እንደሆነ በዚሁ ዙሪያ የተሠራው
ይህ ጥናታዊ ጽሁፍ ያብራራል፡፡ "ዋስትና" ወይም በእንግሊዝኛው" Bail " የሚለው ቃል "Bailer" ከሚለው
የፈረንሳይ ቃል የተወሰደና ጥሬ ትርጉሙም መያዝ መይም መቆጣጠር የሚል ነው፡፡
46
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 3፣ ገጽ 160
47
Kelali kiros, The bail Justice in Ethiopia፡ challengs of its administration ,Addis Abeba
University, school of Law, 2011.
48
ዝኒ ከማሁ
የወንጀል ፍትህ ሂደት እንዲያልፍና ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘም ሊቀጣ ይገባል የሚለው ቀዳሚው
ነው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ግለሰቡ በዋስትና ቢለቀቅ በእርሱ ላይ የሚመሰክሩበትን ምስክሮች
ሊያስፈራራ ፤ሀሳባቸውን ሊያስቀይር ወይም ሌሎች ማስረጃዎችን ሊያጠፋ ይችላል ከሚል
49
ስጋት የሚመነጨው ደግሞ ሁለተኛው ነው፡፡ ሶሰተኛው ደግሞ ግለሰቡ ቢለቀቅ ሌላ የወንጀል
ተግባር ውስጥ የማይገባ መሆኑን ከማረጋገጥ የደህንነት ትኩረት ጋር ይያያዛል፡፡50 ከዚህም
በመነሳት ህብረተሰቡ የግለሰቡ ከእስር መለቀቅ እነዚህ ፍላጎቶቹን አደጋ ላይ የማይጥል
ስለመሆኑ እንዲረጋገጥለት ይፈልጋል፡፡51 ሌላው የዋስትና ሕግ መሰረት መሆን ያለበት ጉዳይ
ደግሞ ዋስትና ቅጣት ሳይሆን የተከሳሹን ፍርድ ቤት መቅረብ ማረጋገጫ ዘዴ መሆኑ ነው፡፡
ስለሆነም የሚወሰነው የዋስትና ማስከበሪያው መጠን የሚወረሰው የዋስትና ገንዘብ ተከሳሹን
ወደ ችሎት ለመመለስ በበቂ ሁኔታ ያገለግላል ወይስ አያገለግልም በሚል ሚዛን መለካት
ይኖርበታል፡፡52 በዋስትና ሕግ መሰረትነት የሚጠቀሰው ተጨማሪው መርህ ደግሞ የዋስትና
ክልከላ ቅጣት ሊሆን አይገባም የሚለው ነው ፡፡ ትርጉም ባለው መልኩ ዋስትና ለመፍቀድም
ሆነ ለመንፈግ ተከሳሹ ወደፊት ፍርድ ቤት በተፈለገ ጊዜ የሚቀርብ ከመሆኑ ፣በፍርድ ሂደቱ
ውስጥ ጣልቃ የማይገባ ከመሆኑ እንዲሁም ለጠቅላላው ህብረተሰብ የደህንነት ስጋት መሆን
አለመሆኑን በመዳሰስ ሊሆን ይገባል፡፡53 ከዚህ ጋር በተያያዘ በጥንት ዘመን ሀላፊነት
የሚሰማቸውን ሰዎች ቃለ መሀላ መቀበል የተከሰሰን ሰው ፍርድ ቤት መቅረቡን ለማረጋገጥ
የሚያበቃ ቅድመ ሁኔታ እንደነበረ ሁሉ በዘመናዊው አሰራር የራስ ዋስትና ወይም የተወሰነ
ገንዘብ በመያዧነት መያዝ ለዚሁ አገልግሎት እንዲውል ተደርጓል፡፡54 በዘመናዊው የዋስትና
ታሪክ ውስጥ የዋስትና መያዧን በቅድመ ችሎት እስራት ማስወገጃ ስልትነት መጠቀም
የዳበረው ሰዎችን ያለአግባብ በእስራት ማቆየት ወይም መልቀቅን ከተመለከቱ በርካታ
ውሳኔዎች በመነሳት እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ ፡፡55
3.1.2 ዋስትናን የተመለከቱ አለም አቀፍ መለኪያዎች

49
Between a Rock and Hard Place; Bail decisions in three South frican Countries, the Open
Society Foundation for South Africa, Colinton House, The Oval, Newlands, Cape Town, 7700,
South Africa,2008
50
ዝኒ ከማሁ
51
Wondwossen Demissie, The Right to Bail in Ethiopia: Respective Roles of the Court and the
Legislature
52
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 49
53
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 49
54
Joseph L.Lester, presumed innocent, feared dangerous፡The eighth amendment’s right to
bail,Northern Kentucky law review, 32 N. Ky. L. Rev. 2 2005.
55
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 47
የዋስትና መብት መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች እና ነጻነቶችን በተመለከቱ አለም አቀፍ ሰነዶች
እና ስምምነቶች እውቅና ተሰጥቶታል፡፡ በዚህ ረገድ ለብዙ አህጉራዊም ሆነ አገር አቀፍ
ሕግጋት መሰረት የሆነው አለም አቀፉ የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ቃልኪዳን በአንቀጽ
9(3)56 በወንጀል የተከሰሱ ሰዎች ዋስትና ተነፍጓቸው ጉዳያቸውን በእስር ሆነው
የሚከታተሉበት ሁኔታ ጠቅላላ መርህ ሊሆን እንደማይገባ ይደነግጋል፡፡ በመሰረቱ የተባበሩት
መንግስታት ድርጅት (The UN Working Group on Arbitrary Detention (UNWGAD)
ከዋስትና ጋር ተያይዞ ባጠናውም ጥናት ዋስትና ተነፍገው በእስር ሆነው ጉዳያቸውን
የሚከታተሉ ሰዎች የዋስትና መብት ተከብሮላቸው ከእስር ውጭ ሆነው ከሚከራከሩ ሰዎች
57
ጋር ሲነጻጸሩ በፍርድ ነጻ የመባል እድላቸው እጅግ አናሳ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ይኸውም
ነባራዊ ሁኔታ የዋስትና መብት አለመከበር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሌሎች መብቶች
እንዲጣሱ መንገድ የሚከፍት መሆኑን በሚገባ የሚያሳይ ነው፡፡ የዋስትና መብት ከበርካታ
መሰረታዊ የሰዎች መብቶች ጋር የሚገናኝ ሲሆን በተለይም በወንጀል የተጠረጠሩ እና የተከሰሱ
ሰዎችን በቀጥታ የተመለከቱ አለም አቀፍ መርሆዎች አካል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ከእነዚህም
መካከል በፍርድ ሂደት ወንጀለኛነት እስካልተረጋገጠ ድረስ ንጹህ ሆኖ የመገመት መብት ፣
የነጻነትና ካልተገባ አያያዝ የመጠበቅ መብት እንዲሁም የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት
በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ሲሆኑ ያላቸውን ጥብቅ ቁርኝት በመጠኑ መዳሰስ ያስፈልጋል፡፡
ሀ) ዋስትና ፤ ንጹህ ሆኖ የመገመት መርህ
ቀዳሚው የዋስትና ህግ መሰረታዊ መርህ ዋስትና ቅጣት ባለመሆኑ በወንጀል የተጠረጠረ
ወይም አልፎ ክስ የቀረበበት ሰው የፍትህ ፍላጎት እስከፈቀደ ድረስ በዋስትና ከእስር ሊለቀቅ
ይገባል የሚል ሲሆን ይኸውም በወንጀል ፍትህ አስተዳዳር ውስጥ ቁልፍ ከሆነው ንጹህ ሆኖ
የመገመት መርህ ጋር በቀጥታ ይገናኛል፡፡58 ለዚህም የሚቀርበው መነሻ ወንጀል ፈጽሟል
በሚል ተጠርጥሮ አልያም ተከሶ የቀረበ ሰው እንደ ማንኛውም ንጹህ የማህበረሰቡ አባል ከከሳሹ

56
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 9 ፣ICCPR Article 9(3),"Anyone arrested or detained on a criminal charge
shall be brought promptly before a judge or other officer authorized by law to exercise judicial
power and shall be entitled to trial within a reasonable time or to release. It shall not be the
general rule that persons awaiting trial shall be detained in custody…"
57
United Nations Commission on Human Rights, Report of the Working Group on Arbitrary
Detention,Dec.12,2005(E/CN.4/2006/7),availableat:http://ap.ohchr.org/documents/alldocs.aspx?doc_id
=11600
58
P J Schwikkard, The Presumption of Innocence: What is it? -- 11 S. Afr. J. Crim. Just.
391,1998.
ያነሰ ነጻነትም ሆነ ክብር ሊሰጠው አይገባም የሚል ነው፡፡59 በወንጀል ጉዳይ ንጹህ ሆኖ
የመገመት መብት በበርካታ አለማቀፋዊ ልቀት ባላቸው የሰብአዊ መብት ሰነዶች ውስጥ
የተካተተ ሲሆን ሁሉን አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ60 “Article 11 (1) Everyone
charged with a penal offence has the right to be presumed innocent until
Proved guilty according to law in a public trial at which he has had all the
guarantees necessary for his defence." በማለት በወንጀል የተከሰሰ ማንኛውም ሰው
በህግ መሰረት ጥፋተኛነቱ እስካልተረጋገጠ ድረስ ንጹህ ሆኖ የመገመት መብት ያለው መሆኑን
ብቻም ሳይሆን ከቀረበበት ክስ ራሱን ነጻ ለማውጣት የሚያስችለውን መከላከያ ማቅረብ
በሚችልበት ችሎት የመቅረብ መብትና ጥበቃ እንዳለው በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ በተመሳሳይ
ይህ መርህ በአለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ቃልኪዳን (ICCPR) አንቀጽ14 (2)
፣ በተባበሩት መንግስታት የታሰሩ ሰዎች አያያዝ ዝቅተኛ መርሆዎች61( The UN standard
minimum Rules for the treatment of prisioners ( mandella Rules 111 ) እና
በሌሎች መሰል ስምምነቶች ውስጥ በአግባቡ ተካቷል፡፡ ሀገሪቱ ላጸደቀቻቸው አለም አቀፍ
የሰብአዊ መብት ሰነዶች እና ስምምነቶች የህግ አካልነት በአንቀጽ 9(4) እና 13 (2) እውቅና
የሰጠው የኢፌዲሪ ሕገ መንግስትም የተከሰሱ ሰዎችን መብት በሚዘረዝረው አንቀጽ 20(3) ስር
የተከሰሱ ሰዎች በፍርድ ሂደት ባሉበት ጊዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደጥፋተኛ ያለመቆጠር
መብት እንዳላቸውምና ጥፋተኛ የሚያሰኛቸውን መንገድም ለመዝጋት … በራሳቸው ላይ
በምስክርነትም ጭምር እንዲቀርቡ ያለመገደድ መብት እንዳላቸው በግልጽ ደንግጓል፡፡62 በዚህ
አግባብ ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በጸዳ መልኩ የተከሳሹን ጥፋተኛነት የማረጋገጥ ሸክምን በከሳሽ
አካል ላይ የሚጥለው ንጹህ ሆኖ የመገመት መርህ63 ዋስትናን ጠቅላላ መርህ ፤እስራትን

59
Margaret S. Gain, The Bail Reform Act of 1984 and United States v. Salerno: Too Easy to
Believe, 39 Cases. W. Res. L. Rev. 1371, 1989
Available at: http://scholarlycommons.law.case.edu/caselrev/vol39/iss4/7
60
Article 11, The Universal Declaration of Human Rights (UDHR) is a declaration adopted by
the United Nations General Assembly resolution 217 A (III) of 10th December, 1948 in Paris.(
ከዚህ በኋላ በአጭሩ UDHR ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡
61
Rule 111(2), The UN standard minimum Rules for the treatment of prisioners (the Nelson
Mandella Rules)
https://www.unodc.org/documents/justice-and-prison-reform/GA-RESOLUTION/E_ebook.pdf
62
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 10፣ የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 20
63
Simeneh Kiros The principles of presumption of innocence and its challenges in the Ethiopian
criminal process Mizan law Review, Vol. 6 No.2, 2012.
ደግሞ ልዩ ሁኔታ በማድረግ ወጥነቱና ምክንያታዊነቱ ይገጻል፡፡64 ለዚህም ነው የአሜሪካ
ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአንድ ወቅት በሰጠው ማብራሪያ "የአንድ የወንጀል ተጠርጣሪ ወይም
ተከሳሽ ንጹህ ሆኖ የመገመቱ ጉዳይ ማሳያው ችሎቱ እስኪያልቅ ድረስ በዋስትና መለቀቁን
ማረጋገጥ በመሆኑ ይህንን መብት ማስከበር ካልተቻለ ከብዙ ምዕተ አመታት ትግል በኋላ
የተረጋገጠው ንጹህ ሆኖ የመገመት መርህ ትርጉሙን ያጣል፡፡" በማለት ያስቀመጠው ፡፡65
ለ) ዋስትና፤የነጻነትና ከህግ ውጭ ከሆነ አያያዝ/ እስራት የመጠበቅ መብት
ነጻነትን መንፈግ በማንኛውም ሰው አጠቃላይ ህይወት ውስጥ በእጀጉ ጣልቃ መግባት በመሆኑ
በወንጀል ክስ ሂደት ውስጥ ተከሳሾች ከእስር ውጭ የሚሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት በአለም
ላይ ያሉ በርካታ የወንጀል ፍትህ አስተዳደሮች መሰረታዊ አካል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡66 በዚህ
አግባብ የወንጀል ፍትህ አስተዳደሮች ቢያንስ በሕግ ደረጃ የወንጀል ተከሳሾች ነጻነታቸው
ሳይነፈግ ጉዳያቸውን በችሎት እየቀረቡ መከታተላቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የተለያዩ
መንገዶችን ያዳበሩ ሲሆን ዋስትና አንዱ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡67 ከሰዎች ተፈጥሮ የሚመነጨው
የነጻነት መብት በብዙዎቹ የሰብአዊ መብት እና ነጻነት ስምምነቶች ውስጥ የተካተተ ሲሆን
ሁሉን አቀፍ ሰብአዊ መብት መግለጫ (UDHR) በአንቀጽ 9 ሰዎች ያላቸውን ሁለንተናዊ
ነጻነት በማወጅ ካልተገባ ወይም ከህግ ውጭ ከሆነ አያያዝም ጭምር የመጠበቅ መብት
እንዳላቸው ያስገነዝባል፡፡68 በተመሳሳይ አለም አቀፉ የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ቃልኪዳን
(ICCPR) በወንጀል ምክንያት የታገተ ወይም የታሰረ ሰው በዋስትና መውጣት እንዳለበት
በግልጽ ያስቀምጣል፡፡69 በዋናነት የአንድን አያያዝ ተገቢነትና ሕጋዊነት በመወሰን ሂደት ግለሰቡ
ፍትህን ለመሸሽ የሚያስብ ከመሆኑ፣ ማስረጃዎች ውስጥ ጣልቃ ከመግባት እና ጠቅላላውን

64
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 24
65
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 54 “A person is presumed innocent of a criminal charge until he is
proved guilty. This well known principle suggests that no one should ever be kept in detention
awaiting trial.” በማለት አመክኖን ያስቀምጣል፡፡
66
Kristen Peterson, A comprehensive study of bail legislation in Malawi, Mozambique and Brundi,
civil society Prison initative, A Comparative Study of Bail Legislation in Malawi, Mozambique and
Burundi ፣Dullah Omar Institute 2016.
67
ዝኒ ከማሁ
68
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 60 ፣UDHR Article 9
69
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 9 ፣ ICCPR Article 9 (1), “everyone has the right to liberty and security
of person. No one shall be subjected to arbitrary arrest or detention. No one shall be deprived
of his liberty except on such grounds and in accordance with such procedure as are established
by law. 3) Anyone arrested or detained on a criminal charge shall be brought promptly before a
judge or other officer authorized by law to exercise judicial power and shall be entitled to trial
within a reasonable time or to release. It shall not be the general rule that persons awaiting trial
shall be detained in custody…”
የህብረተሰብ ክፍል ከተጨማሪ ወንጀል ከመጠበቅ ጋር ያሉት ሁኔታዎች ጋር በጥንቃቄ
መመዘን እንዳለባቸው የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚቴ በአንድ ጉዳይ ላይ
ከሰጠው ማብራሪያ ለመረዳት ይቻላል፡፡70 ከዚህ ውጭ በሆነ መልኩ ላልተወሰነ ጊዜ በእስር
ማቆየት፣ ዋስትናን ወደፊት ሊኖር ከሚችል ጥፋተኛነትና ቅጣት ክብደት አንጻር ብቻ
መመዘን፣ የተጋነነ የዋስትና ገንዘብ መጠየቅ እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች የዋስትና አላማ
የሆነውን የነጻነት መብትን የሚጥሱና አያያዙንም ሕገ ወጥ የሚያደርጉ እንደሆኑ ይጠቀሳል፡፡71
ለበርካታ አህጉራዊና ሀገራዊ የሕግ ማዕቀፎች መሰረት የሆኑት እነዚህ ስምምነቶች ለመብቱ
ከሰጡት ትኩረት የግለሰቦች ነጻነት ከሕግ ውጭ በሆነ መንገድ እንዳይጣስ የማክበርና
የማስከበር ሀላፊነትንም ጭምር በአባላት ላይ ይጥላሉ፡፡72 በዚህ ረገድ የአፍሪካ ሰብአዊ እና
ህዝቦች መብት ቻርተርም በተመሳሳይ የነጻነት መብት ለህዝበ አፍርካ ትልቅ ትርጉም እንዳለው
በማስታወስ ማንኛውም ሰው ከሕግ ሥርዓት ውጭ በሆነ መልኩ ነጻነቱ ሊገፈፍ እንደማይገባ
ዋስትና ይሰጣል፡፡73
ሐ) ዋስትና፤ የተፋጠነ ፍትሕ የማግኘትና በፍትሐዊ ችሎት የመዳኘት መብት
የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት ከፍ ብሎ የተመለከትናቸው ንጽህ ሆኖ የመገመት እና
የነጻነት መብቶች ቅጥያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡74 ምክንያቱም ንፁህ ሆኖ የሚገመተው ሰው
በተቻለ ፍጥነት ገለልተኛ በሆነ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት ያለው ሲሆን ይኸውም ፍርድ
ቤቱ የግለሰቡን አያያዝም ሆነ የእስሩን ህጋዊነት በመመርመር በዋስትና ለመውጣት የሚገባው
መሆን አለመሆኑን ለመወሰን ስለሚያስችው ነው ፡፡75 በዚህ ረገድ ICCPR እና የአውሮፓ
የሰብአዊ መብት ቻርተርን (ECHR) የመሰሉ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች ተከሳሽን ምክንያታዊ
በሆነ ዋስትና ከእስር መልቀቅ ከሳሽ ወገን ክስ ማቅረብ /አለማቅረብን ለመወሰን ለሚወስደው

70
UnitedNationsCommunicationNO458/1991,UNDoc.ICCPR/C/51/Don10Augest,1994.
http://opil.ouplaw.com/view/10.1093/law:ihrl/2262unhrc94.case.1/law-ihrl-2262unhrc94
71
ዝኒ ከማሁ
72
ለአብነት UDHR,ICCPR መግቢያዎች እና ድንጋጌዎቹን መመልከት ይቻላል፡፡ከእነዚህ ሰነዶች ጋር በተጣጣመ
መንገድም የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት ስለ ሰብአዊ መብቶችና ነጻነቶችን የተመለከቱ ድንጋጌዎችን በያዘው ምዕራፍ
ሶስት አንቀጽ 13 ሁሉም የፌደራል ሆኑ የክልል የመንግስት አካላት (ሕግ አውጭው ፣ሕግ አስፈጻሚና የዳኝነት
አካላት) የሰብአዊ መብቶችና ነጻነቶችን የማክበርና የማስከበር ሀላፊነት ያለባቸው መሆኑን ይደነግጋል፡፡
73
African Charter on Human and peoples’s Right, Adopted on 27, June 1981, OAU Doc.
CAB/LEG/67/3 rev. 5, 21 I.L.M. 58 (1982), entered into force 21 October 1986.
74
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 24
75
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 24
የጊዜ መጓተት መፍትሔ አድርገው የወሰዱት ይመስላሉ፡፡76በዚህረገድ
በማንኛውም ሁኔታ ታስረው ወይም ታግተው የሚገኙ ሰዎችን መብት ለመጠበቅ በተባበሩት
መንግስታት ድርጅት የወጣው መመሪያ መርህ /Principle/ 39 ‟Anyone arrested or
detained on a criminal charge shall be brought promptly before a judge or other
officer authorized by law to exercise judicial power and shall be entitled to trial
with in a reasonable time or to release. It shall not be the general rule that
persons awaiting trial shall be detained in custody…" በማለት ግለሰቡ በተፋጠነ
ሁኔታ ቀርቦ የዋስትና መብቱ ሊከበርለት እንደሚገባ ይደነግጋል፡፡77 በዚሁ አግባብ የኢፌዲሪ
ሕገ መንግስትም ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ውጭ ነፃነቱን እንደማያጣ እና ፤ሊያዝ
ሆነ ክስ ሳይቀርብበት ወይም ሳይፈረድበት እንደማይታሰር በመርህ ደረጃ የደነገገ ሲሆን የነጻነት
መብት መገለጫ የሆነው ዋስትናን አስመልክቶም በተለይም የተያዙ ሰዎች በዋስ የመፈታት
መብት እንዳላቸው ይደነግጋል፡፡78 በመሆኑም የእነዚህ አለም አቀፋዊ ፣አህጉራዊ እና ሀገራዊ
አድማስ ያላቸው የሕግ ማዕቀፎች ይዘት በዋስትና ከእስር የመለቀቅ መብት ከሰዎች መሰረታዊ
የነጻነት መብት ጋር ብቻም ሳይሆን የተጠረጠሩ ወይም የተከሰሱ ሰዎች ላላቸው ንጹህ ሆኖ
የመገመት መብት መገለጫ እንደሆነ ያስገነዝባል፡፡ በርግጥ ይህ ከእስር የመለቀቁ ጉዳይ ከዚህ
ግለሳባዊ ፍላጎትም ጎን ለጎን ያለን የጠቅላላውን ማህበረሰብ ጥቅምና ፍላጎትም ማጣጣም
ስላለበት እንደነገሩ ሁኔታ በበቂ ዋስትና ቅድመ ሁኔታ ሊፈጸም ወይም በልዩ ሁኔታ ሊነፈግም
እንደሚችል በተጨማሪነት መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በአብዛኛው ዋስትና ተጠርጣሪውን በያዘው
የፖሊስ ተቋም እና በፍርድ ቤቶች ሊሰጥ ይችላል፡፡79 በፍርድ ቤት ከሚሰጡ የዋስትና አይነቶች
መካከል ደግሞ በመጀመሪያ ደረጃ ክርክር ጊዜ የሚቀርበው ዋስትና (Bail pending Trial) እና
በይግባኝ ጊዜ የሚኖረውን ዋስትና (Bail Pending appeal) በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ ፡፡80

76
Monica Mocovei, The right to liberity and security of the person of Art.5of the European
Convention on Human Rights, Human rights hand book No.5, Council of Europe, 2002.
77
United Nations Body of principles for the protection of all persons under any form of detention
and imprisonment, Adopeted by General Assembly Resolution No 43/173, 1988.
www…un.org/ruleoflaw/files/bodyfprinciples
78
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 10፣ የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 9(4) ፣ 17 እና 19
79
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 15፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 28፣ 64- 79፤ በተመሳሳይ
ወደፊት ይወጣል ተብሎ የሚጠበቀው የወንጀል ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አንቀጽ 153 ( 3) ስር
ዋስትና እንደነገሩ ሁኔታ በመርማሪ አካል ወይም በፍርድ ቤት ሊሰጥ እንደሚችል አመልክቷል፡፡
80
Nwasu Mercy, A comparative Analysis: The Practice of bail pending Trial in Nigeria and the
The United States of America ,2016 ,www.papers.ssrn.com/5013/papers.fm
3.2 ዋስትና፤ በመጀመሪያ ደረጃ ክርክር ጊዜ
በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ውስጥ የዋስትና ሥርዓት በአንድ በኩል የተጠረጠሩ ወይም
የተከሰሱ ሰዎች ከእስር ነጻ የመሆን ፍላጎት እና በሌላ በኩል እነዚህ ግለሰቦች የፍርድ
ሂደታቸውን ለመከታታል ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ይገባል የሚለውን የህብረተሰቡ ፍላጎት
ለማጣጣም የሚሞክር በመሆኑ ግጭት የሚያጣው አይደለም፡፡81 በተመሳሳይ በኢትዮጵያ
የወንጀል ፍትህ አስተዳደርም የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓትን ጨምሮ ዋስትናን የተመለከቱ
ድንጋጌዎችን በየጊዜው ይዘው የሚወጡ ዝርዝር የሕግ ማዕቀፎች ይዘት ከሕገ መንግስቱ
መርሆዎች እና አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች ጋር ያላቸው መጣጣም ሲያከራክር
ይስተዋላል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ሕገ መንግስቱ በአንቀጽ 19 በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ
ሰዋች በዋስትና ከእስር የመለቀቅ መብት ያላቸው መሆኑን ማወጁ እንደተጠበቀ ሆኖ እዛው ላይ
የህብረተሰቡን ፍላጎት ሚዛን በጠበቀ መልኩ ይህ መብት ሊገደብም እንደሚችል "…ሆኖም
በሕግ በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች ፍርድ ቤቱ ዋስትና ላለመቀበል ወይም…ለማዘዝ እንደሚችል
አስቀምጧል፡፡82 ይህውም የሕገ መንግስቱ አቀማመጥ ዋስትና ሊገድብ የሚችለው ውስን እና
በግልጽ ሕግ በተመለከቱ ልዩ ሁኔታዎች ብቻ እንደሆነ ፤ ከዚህም ውጭ የሆነ የክልከላ
ምክንያት ጠቅላላውን የዋስትና ጽንሰ ሀሳብ ፤አላማና መንፈስም ሆነ ሕገ-መንግስታዊ መርህ
እንደሚጥስ ለመገንዘብ ያስፈልጋል ፡፡ በመሆኑም እነዚህን ልዩ ሁኔታዎች በመወሰን ረገድ
መለኪያ መሆን ያለበት እራሱ የዋስትና አላማ በመሆኑ የሚቀርቡት ምክንያቶች ከዚሁ አኳያ
የተቃኙ ሊሆን ይገባል የሚሉ ሀሳቦች በተለያዩ የሕግ ባለሙያዎች ዘንድ ይነሳሉ፡፡83 ከዚህ
አንጻር የዝርዝር ህጎቻችንን አቀማመጥና ይዘት ከሕገ መንግስቱ ድንጋጌ ጋር መመልከት
ያስፈልጋል ፡፡ በቅድሚያ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉን ብንወስድ በአንቀጽ 67
በዋስትና ወረቀት የመልቀቅ ማመልከቻን መቀበል የማይቻለው፤84
ሀ) በዋስትና ወረቀት የተመለከቱትን ግዴታዎች አመልካቹ የሚፈጽም የማይመስል እንደሆነ፤
ለ) አመልካቹ ቢለቀቅ ሌላ ወንጀል ይፈጽም ይሆናል ተብሎ የሚገመት ከሆነ ፤
ሐ) ምስክሮቹን በመግዛት ( በማባበል ወይም አስረጅ) የሆኑበትን ያጠፋ ይሆናል ተብሎ
የሚገመት ሲሆን ፤ እንደሆነ ያስቀምጣል ፡፡

81
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 24
82
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 10፣ ኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 19 (5)
83
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 51
84
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 15፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 67
ዋስትናን የማያሰጡ ወንጀሎችን ከመዘርዘር ይልቅ ልዩ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ፍርድ ቤቱ
እንደነገሩ ሁኔታ እየመዘነ የሚወስንበትን አግባብ በዚህ መልኩ መደንገግ የዋስትናን አጠቃላይ
አላማን ማዕከል የሚያደርግና ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚጣጣም አቀራረጽ እንደሆነ
ይጠቀሳል፡፡85 ዋስትናን የመፍቀድ ወይም የመከልከሉን ጉዳይ እንደነገሩ ሁኔታ ከፍርድ ሂደቱ
ውጤታማነት ፣ከጠቅላላው ማህበረሰብ ሰላምና ደህንነት ጋር አስተሳስሮ ማስቀመጥ በሌሎች
ሀገሮች የሕግ ማዕቀፎችም ጭምር ባብዛኛው የሚታይ ልምድ ነው፡፡ ለአብነት በእንግሊዝ
ዋስትና ከማያሰጡ ልዩ ሁኔታዎች መካከል ቀጠሮውን አክብሮ አይቀርብም ፤ወይም
በማስረጃዎች እና በአጠቃላይ የፍርድ ሂደቱ ውስጥ ጣልቃ ይገባል እና ሌላ የወንጀል ድርጊት
ይፈጽማል የሚለው ጠንካራ እምነት በፍርድ ቤቱ መያዝ ይጠቀሳሉ፡፡86 ደቡብ አፍሪካን
ብንመለከት ከ1994 በፊት በነበረው ሁኔታ በአንዳንድ ከባድ የፖለቲካ እና ሌሎች ከባድ
ወንጀሎች የተጠረጠሩ ወይም የተከሰሱ ሰዎች ስልጣን በነበረው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ዋስትናን
ይከለከሉ ነበር፡፡87 ነገር ግን በሂደት በሀገሪቱ ውስጥ የዋስትና መብትን ጨምሮ ሌሎች የዜጎች
መብቶችን ለማረጋገጥ የተደረገውን ትግል ተከትሎ እነዚህ መብቶች በሕገ መንግስትም ጭምር
መሰረታዊ መብቶች ሆነው እንዲካተቱ ተደረገ ፡፡88 በሀገሪቷ የወንጀል ሥነ ሥርዓት እጅግ
ከባድ በተባሉ እንደ ሰው መግደልን በመሰሉ ወንጀሎች ሳይቀር ተከሳሹ በእስር መቆየቱ የፍትህ
ፍላጎት አለመሆኑን የሚያረጋግጥ በቂ ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ አቅርቦ የማስረዳት ሸክሙን

85
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 51
86
Bail Act of UK 1976 (c.63) ,persons entitled to Bail : suplimentary provisions
https://www.legislation.gov.uk/ukpga/1976/63, Exceptions to right to bail
The defendant need not be granted bail if the court is satisfied that there are substantial
grounds for / believing that the defendant, if released on bail (whether subject to conditions or
not) would—
a) fail to surrender to custody, or
B) Commit an offence while on bail, or
C) interfere with witnesses or otherwise obstruct the course of justice,Whether in relation to
himself or any other person.
87
Wium de Villiers, Problematice aspects with regard to bail under the South African Law: The
Reverse onus provisions and the admission of the evidence of the applicant for bail at the later
criminal trial revisited. www.repository.up.ac.za/bitstream/handel/2263
88
ዝኒ ከማሁ
መወጣት ከቻለ በዋስትና ሊወጣ ይችላል፡፡89 በአሜሪካ The Bail Reform Act 1984 ተብሎ
የሚጠራው ዋስትናን የተመለከተ ሕግ በተለይም ዋስትናን ከግለሰቡ ነጻነት ብቻ ሳይሆን
ከህብረተሰቡ ሰላምና ደህንንት ጋር ለማጣጣም ሲባል ሁለት የሚስተባበሉ የመከልከል
ግምቶችን ወይም በእንግሊዝኛው Rebuttable presumpttions against release
አስቀምጧል፡፡90 የመጀመሪያው የግለሰቡን የቀደመ የወንጀል ታሪክን የሚመለከት ግምት ወይም
( previous -violater presumption) ሲሆን ከዚህ በፊት ግለሰቡ በወንጀል ተከሶ በዋስ
በነበረበት ወቅት በሌላ ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ የተቀጣ ከነበረ በድጋሚ ዋስትና ቢፈቀድለት
የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ላይ ስጋት ይሆናል የሚለው ነው፡፡ ሌላኛው ግምት ደግሞ
በቀጥታ ግለሰቡ የተጠረጠረበት ወይም የተከሰሰበትን የወንጀል ድርጊት ባሕሪይን ይመለከታል፡፡
በዚህም መሰረት ክሱ ከአደገኛ እጽ፣ በአደገኛ የጦር መሳሪያ የተፈጸመ መሆኑን የሚያሳይ
(drug-and- firearm-offender presumption) ወይም ቆይተው የተካተቱትን የሽብር ወይም
አቅመ ሄዋን ወይም አዳም ባላደረሱ ተጎጂዎች ላይ የተፈጸመ (sex offences) ከሆነ
በተመሳሳይ ግለሰቡ በዋስትና መለቀቁ የህብረተሰቡን ደህንነት አደጋ ላይ ይጥላል የሚለው
91
ግምት ይወሰድበታል፡፡ ስለሆነም በእነዚህ ሁኔታዎች ተከሳሹ በዋስትና ቢለቀቅ ለህብረተሰቡ
ደህንነት ስጋት እንደማይሆን ፍርድ ቤቱን የሚያሳምን ማስረጃ በማቅረብ ግምቶቹን
ማስተባባበል ይጠበቅበታል፡፡92 በመሰረቱ የወንጀል ባህሪን/ጠባይን (criminal behavior)
መግታት የወንጀል ፍትህ አስተዳዳር አንዱ አላማ በመሆኑ ይህንን ለማሳካት ግለሰቡን
በዋስትና የመለቀቅ ጉዳይን በመወሰን ሂደት ውስጥ ወጥቶ ሌላ የወንጀል ተግባር ውስጥ
የማይገባ መሆኑን በተለያየ መንገድ በጥንቃቄ መፈተሽ አግባብነት እንዳለው ይጠቀሳል፡፡93
ሁለተኛው አይነት የዋስትና ክልከላ መሰረት ደግሞ በቀጥታ የተጠረጠረበትን የወንጀል አይነት
እና ከባድነትን ማዕከል የሚያደርግ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ
ሥነ ሥርዓት ሕግ በአንቀጽ 63 ዋስትና የሚከለከልበትን ተጨማሪ መንገድ ሲያስቀምጥ፤94

89
ዝኒ ከማሁ፣ "The Reverse onus provisions” በወንጀል የተከሰሰ ሰው በዋስ ለመውጣት ይቻለው ዘንድ በዋስ
መውጣቱ የፍትህ ፍላጎት እንደሆነ ፍርድ ቤቱን ሊያሳምን የሚችል በቂ ማስረጃ የማቅረብ ሸክም ያለበት
ስለመሆኑ የሚያስቀምጡ ድንጋጌዎችን ለማመልከት የሚውል ሀረግ ነው፡፡
90
David N. Adair Jr, The Bail Reform Act 1984, Third Edition, Federal Judicial Center, 2006
91
ዝኒ ከማሁ
92
ዝኒ ከማሁ
93
Una Ni Raifeartaigh, Reconciling Bail with the Presumption of Innocence, Oxford journal of
legal studies vol 17, 1997.
94
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር15፣የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 63፡፡ በመሰረቱ የሥነ ሥርዓት ሕጉ
በቁጥር 67 በተመለከቱት ሁኔታዎች በዋስትና ወረቀት መልቀቅ የማይቻልባቸው ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው
(1) ማንኛውም የተያዘ ሰው የተከሰሰበት ወንጀል የሞት ቅጣትን ወይም አስራ አምስት አመት
ወይም ከዛ በላይ በሆነ ጽኑ እስራት የማያስቀጣው ከሆነ እና ወንጀል የተፈጸመበት ሰው
በደረሰበት ጉዳት የማይሞት የሆነ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ የዋስትና ወረቀት አስፈርሞ ለመልቀቅ
ይችላል፡፡ በማለት ይደነግጋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አዲሱ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ረቂቅ ሕግ
በግልጽ ዋስትና የሚያስከለክሉ ወንጀሎች የሚል ርእስ የያዘ ድንጋጌዎችንን በማካተት ዋስትና
በወንጀል አይነት እንደሚከለከል ተደርጎ እንደተቀረጸ መመልከት ይቻላል፡፡95 በመሰረቱ በስራ
ላይ ካለው የሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 63 ንዑስ አንቀጽ 1 በተጨማሪ በልዩ ሁኔታ የወጡ
አንዳንድ ዝርዝር የወንጀል ሕግ ማዕቀፎች በወንጀል አይነት ዋስትናን ይከለክላሉ፡፡ ለአብነት
አደገኛ ቦዘኔነትን ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ብንወስድ በአንቀጽ 6(3) “… በአደገኛ ቦዘኔነት
ወንጀል በሚገባ ተጠርጥሮ የተያዘ ሰው በዋስትና አይለቀቅም፡፡” በማለት በግልጽ ደንግጓል፡፡96
የሙስና97 እና የሽብር98 ወንጀሎችን የተመለከቱ ልዩ የወንጀል ሕግ ማዕቀፎችም ቢሆኑ
በተመሳሳይ የዋስትና መብት መጣበብ የሚስተዋልባቸው ማዕቀፎች ናቸው፡፡ በዚህ መልኩ
ዋስትናን ለመፍቀድም ሆነ ለመከልከል ግለሰቡ የተጠረጠረበትን ወይም የተከሰሰበትን ወንጀል
መሰረት የሚያደርጉት የሕግ ማዕቀፎች ዋስትና መከልከልን መርህ ያደረጉ በመሆናቸው ከሕገ
መንግስቱ አንቀጽ 19(5) ድንጋጌና ሀገሪቱ ተቀብላ የሕግ አካል ካደረገቻቸው አለም አቀፍ
የሰብአዊ መብት ሰነዶችና ስምምነቶች ጋር ይጣረሳሉ ፡፡ የሚሉ ክርክሮች በዳኞችም ሆነ ሌሎች
የሕግ ባለሙያዎች ዘንድ በየጊዜው ይቀርባሉ ፡፡99 በርግጥ የሌሎች ሀገራትን የሕግ ማዕቀፎች
ስንመለከት በሕንድ የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ የህብረተሰቡን እና የሀገርን
ደህንነት ማዕከል አድርገው የወጡ እንደ የናርኮቲክ እጽ እና ሌሎች አደገኛ ንጥረ ነገሮችን

ነገር ግን ፍርድ ቤቱ በዋስትና ወረቀት እንዲለቅ ከሆነ በርግጥም የህብረተሰቡ ፍላጎት የሆነውን የፍርድ ሂደቱን
በተፈለገ ጊዜ እየቀረበ ለመከታታል የሚያስችለው በቂ ዋስትና ለማቅረብ የሚችል መሆኑን ሲያረጋግጥ መሆኑን
የዚሁ ሥነ ሥርዓታዊ ድንጋጌ ንዑስ አንቀጽ 2 እና 3 ጣምራ ንባብ ያስረዱናል፡፡
(1) የዋስትና ወረቀት ወይም ያለዋስ በማስፈረም የሚለቀው ሰው በሚፈለግበት እንዲቀርብ የሚያደርገው ብቁ ዋስትና
መሆኑን ፍርድ ቤቱ ካልተረዳው በቀር የተያዘው ሰው የዋስትና ወረቀት በማስፈረም መልቀቅ አይችልም፡፡
(2) የዚህ ቁጥር ድንጋጌ ቢኖርም በቁጥር 67 የተነገረው እንደተጠበቀ ነው ፡፡ በሚል ይደነግጋል፡፡
95
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 28 ፣የኢፌዲሪ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ረቁቅ አንቀጽ154
96
የአደገኛ ቦዘኔነት መቆጣጠሪያ አዋጅ ቁጥር 384/1996 ፣አስረኛ አመት፣ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 19 አዲስ አበባ
ጥር 18 ቀን 1996 ዓ.ም
97
የተሻሻለው የጸረ-ሙስና ልዩ ሥነ- ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 882/2007፣ሀያ አንደኛ
አመት፣ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 37፣መጋቢት 25 ቀን 2007ዓ.ም
98
የጸረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001፣አስራ አምስተኛ አመት ፣ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 57፣ነሀሴ 22 ቀን 2001
ዓ.ም
99
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 51
መቆጣጠርን የተመለከተው ሕግ100፣የሽብርተኛነት እና ሥርዓት የማወክ ድርጊቶችን ለመከላከል
የወጣ ህግ101፣ ሽብርተኛነትን ለመከላከል የወጣ ሕግ102 እና ሌሎችን ልዩ የሕግ ማዕቀፎችን
እናገኛለን፡፡ በእነዚህ ልዩ የወንጀል ህግጋት የዋስትና ክልከላ ጠቅላላ መርህ ዋስትና መፍቀድ
ደግሞ ልዩ ሁኔታ ነው፡፡ በመሆኑም እንደ ወንጀሉ ስፋትና አደገኛነት እየታየ ዋስትና የሚወሰን
ሲሆን ከፍተኛ የዋስትና ገንዘብ የሚያስጠይቅ ከመሆኑም አልፎ ከነጭራሹ ዋስትና ሊያስከለክሉ
የሚችሉባቸው ሁኔታዎችም አሉ፡፡103 በባንግላዲሽ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ህግም በግልጽ
ዋስትና የሚያሰጡ እና ዋስትና የማያሰጡ ወንጀሎች የሚል ክፍፍል ያለ ሲሆን ዋስትና
በሚያሰጡ ወንጀሎች ጊዜ ተጠርጣሪው ወይም ተከሳሹ ተመጣጣኝ የዋስትና ገንዘብ በማስያዝ
የመውጣት የማይስተባበል መብት ይኖረዋል፡፡104
በመሰረቱ ዋስትናን በፍርድ ቤት በሚመዘኑ ሁኔታዎች ከመወሰን ይልቅ ክልከላ የሚያደርጉ
ድንጋጌዎች በሕግ አውጭው መቀመጣቸው ዋስትናን ጠቅላላ መርህ ያደረገውን የሕገ
መንግስቱ አንቀጽ 19 (6)ን የሚቃረኑ በመሆኑ ኢ- ሕገ መንግስታዊ እንዲሰኙ ለሕገ መንግስት
አጣሪ ጉባኤ ቀርበው ነበር ፡፡105 ሆኖም ጉባዔው የሌሎች ሀገራት ልምድንም በማሳየት ዋስትና
የሚከለክሉት ሕግጋት ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 19(6) ጋር የሚቃረኑ ባለመሆናቸው ጉዳዩ
በፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገ-መንግስታዊ ትርጉም እንዲሰጠው መላክ የሚችል አለመሆኑን
በመግለጽ ወስኗል፡፡ በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት106 መሠረት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገ
መንግሥትን የመተርጎም ሥልጣን ያለው አካል ሲሆን የዚህን አካል ሥልጣን እና ተግባር

100
Narcotics Drug and Phychotropic Substances Act, section 32 (1) I and ii The Narcotic drugs
and Psychotopic substances Act 1985, www.narcoticsindia.nic.in/uphold/download
101
The Terriorist and Disruptive Activities prevention Act, 1985 No.31 of 1985.
www.theindianlawyer.in/statutesbareacts/acts.
102
The Prevention of Terriorism Act, 2002.
www.canlovefm.com/india-the-prevention-of-terriorism Act.
103
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 24 ፣ከዚህም በተጨማሪ በመደበኛው የህንድ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ህግ ግለሰቡ
የተከሰሰበት ድንጋጌ ጥፋተኛ ተብሎ የሚያስቀጣው በሞት ወይም በእድሜ ልክ እስራት በሚያስቀጣ ወንጀል
ከሆነ ዋስትና እንደ መብት ተከሳሹ ሊጠይቅ አይችልም፡፡ section 437,(1) I and ii, Indian code of
criminal procedure,Act No .2 of 1974 በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ዋስትና ሊፈቅድ የሚችለው በተመረጡ ልዩ
ሁኔታዎች ሲሆን የተከሳሹ ከአስራ ስድስት አመት እድሜ በታች መሆን ፤ ሴት ከሆነች ፤ህመምተኛ መሆን
ይገኙባቸዋል፡፡
104
Shahidul Islam and Golam Moula, The Right of Getting Bail of an Arrested Person in
Bangladesh—A Legal Study of Theories and Practice, Beijing Law Review, Vol 5, 2014, p34-48.
http://www.scirp.org/journal/blr.
105
የግረጌ ማስታወሻ ቁጥር 51
106
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር10፣ የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 62(1)
ለመዘርዘር በወጣውም አዋጅ107 ሥርም ሕገ መንግሥቱን የመተርጎም ሥራ የዚሁ ምክር ቤት
መሆኑና ዝርዝር ስልጣንና ተግባሩም በግልጽ ሰፍሯል፡፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 56(1) ሥር
ደግሞ ምክር ቤቱ በቀረበለት ጉዳይ የሚሰጠው ውሣኔ የመጨረሻ ስለመሆኑ የተደነገገና ንዑስ-
አንቀጽ 2 ትም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች ውሣኔውን የማክበር እና የመፈፀም ግዴታ
ያለባቸው ስለመሆኑ አስገዳጅነት ባለው መልኩ አስቀምጣል፡፡108 በመሆኑም በዚሁ አግባብ
የሕግ ማእቀፎቹ ሕገ መንግስታዊ ትርጓሜ እንደማያስፈልጋቸው የተወሰነ በመሆኑ ወደፊት
በሰፊው ተፈትሸው እልባት እስኪሰጣቸው ድረስ በዚህ አግባብ እየተፈጸሙ ይገኛሉ፡፡
3.3 ዋስትና፤ በይግባኝ ቅጣትን በማገድ ጊዜ
ከፍ ብሎ በክፍል አንድ ላይ ለማብራራት እንደተሞከረው ይግባኝ ፍርድ ቤቱ የቅጣት
ይታገድልኝ ማመልከቻውን መርምሮ ካመነበት የእስራት ቅጣቱ መፈጸም እንዲታገድ ትዕዛዝ
ለመስጠት እንደሚችል ለማየት ተሞክሯል፡፡ በዚህ ረገድ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉ
በአንቀጽ 188(2) ላይ ፍርድ ቤቱ አመልካችን የሚለቀው እንዲሁ ሳይሆን በዋስትና እንደሆነ
ያሳያል፡፡109 ይህ አይነት የሕግ አቀራረጽም በሌሎች ሀገሮች የወንጀል ፍትህ አስተዳደሮችና
የህግ ማዕቀፎች ተቀባይነት ያለው መሆኑን አይተናል፡፡ ሆኖም ድንጋጌው የይግባኝ አመልካች
የሆነው የስር ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ዋስትና እንዲያቀርብ ያስቀምጥ እንጅ የሚያቀርበው ዋስትና
ምንን ግምት ውስጥ ማስገባት እንዳለበት በግልጽ አልደነገገም፡፡ ከዚህ አንጻር በይግባኝ ደረጃ
በአመልካች - ጥፋተኛ በኩል እንዲቀርብ የሚፈለገው ዋስትና ምንን መሰረት ሊያደርግ ይገባል?
የሚለውን ጥያቄ ይነሳል፡፡ በመሰረቱ የይግባኝ ቅሬታው ተመርምሮ እስኪወሰን ድረስ ባለው ጊዜ
የእስራት ቅጣት ታግዶ እንዲቆይ የሚፈቀድለት አመልካች የሚያቀርበው ዋስትና መሰረት
የሚያደርገው ጉዳይ በተግባርም የተለያዩ ሀሳቦች የሚነሱበት ነው፡፡ በተለይም ከፍ ብለን
እንደተመለከትነው በስራ ላይ ያሉት የሕግ ማዕእቀፎች ዋስትናን በሁኔታ እና በወንጀል
አይነት ጭምር የሚፈቅዱ እና የሚከለክሉ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ በይግባኝ የእስራት ቅጣት
የሚታገድላቸው አመልካቾች ተገቢነት ቀድሞውኑ በመጀመሪያ ደረጃ ከቀረበባቸው የወንጀል
ሕግ ድንጋጌ ዋስትና ፈቃጅነት እና ከልካይነት ጋር የግድ መያያዝ አለበት የሚሉ ክርክሮች
በውሳኔዎች ላይ ይታያሉ፡፡110 በተመሳሳይ ዋስትናን የተመለከቱ ጉዳዩች በሁሉም የወንጀል

107
አንቀጽ 3 ፣የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ለማጠናከርና ስልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር የወጣ አዋጅ፣ ነጋሪት ጋዜጣ
፣ቁጥር 251/1993፣ ሰባተኛ አመት ፣ቁጥር 41፣ሰኔ 21፣ ቀን 1993፣አዲስ አበባ፡፡
108
ዝኒ ከማሁ፣ አንቀጽ 56
109
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 15 ፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 188
110
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 42 ፣የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደሴ ምድብ ችሎት በወ/ሰ/መ/ቁ 03-19212
በአመልካች አቶ ምዑዝ ገ/ህይወት እና መልስ ሰጭ ዐ/ሕግ መካከል ለነበረው ክርክር የሰጠው ውሳኔ በተግባር
ክርክር ደረጃዎች የሚመዘኑበት አግባብ ክስ በቀረበባቸው መሰረታዊ ድንጋጌዎች እና የወንጀለኛ
መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 63 እና 67 ላይ ሊመሰረት ስለሚገባ ቅጣት ማገድና
በዋስትና የመውጣት ሥርዓት ዋስትና ለሚያስከለክሉ ወንጀሎች ተፈጻሚ ሊሆን አይችልም
የሚሉ ሀሳቦችም ይነሳሉ፡፡111 ከዚህም ባሻገር የእስራት ቅጣት ይታገድልኝና በዋስትና ልለቀቅ

ለሚንጸባረቁት የተለያዩ አረዳዶች ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ ለጉዳዩ መነሻ የሆነው አመልካች በሰሜን ወሎ ዞን
ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢፊዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543(3) እና 559(2)ን ተላልፎ ሲያሽከረክረው በነበረው
መኪና ባደረሰው አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት እንዲያልፍ እና በሌሎች አምስት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት
እንዲደርስ አድርጓል በሚል ክስ ቀርቦበት ነበር ፡፡ በዚህም መሰረት ክርክር ሲካሄድ ከቆየ በኋላ ፍርድ ቤቱ
በተከሰሰባቸው ሁለቱም ድንጋጌዎች ጥፋተኛ በማለት በሰባት አመት እስራት እና በብር 6000 (ስድስት ሽህ ብር)
መቀጮ እንዲቀጣ ይወስናል፡፡ አመልካችም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ያቀረበውን ይግባኝ የተመለከተው የአብክመ
ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደሴ ምድብ ችሎት ጥፋተኛነቱንና ቅጣቱን በማሻሻል በሶስት አመት እስራት እንዲቀጣ
ይወሰንበታል፡፡ አመልካችም በሂደት የስር ፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የማስረጃ ሕግ ስህተት የተፈጸመበት
ነው በሚል ዝርዝር አቤቱታ ለሰበር ችሎቱ አቅርቧል፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎቱም የስር ፍርድ ቤቱ ለውሳኔው
መሰረት የሆኑትን ማስረጃዎች በመመዘን ሂደት ውስጥ የጣሰው የማስረጃ ምዘና መርህ መኖሩን ለማረጋገጥ
አቤቱታውን አስቀርቦታል፡፡ በዚህ ሂደት የሰበር አመልካች ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ባለው ጊዜ የእስራት ቅጣቱ
ታግዶ እንዲቆይ እንዲታዘዝለት የወ/መ/ሕሥ/ሥ/ቁ 188 (2) ጠቅሶ አመልክቷል፡፡ ችሎቱም አመልካች
ከተወሰነበት የእስራት ጊዜ ውስጥ አንድ አመት ያህሉን የፈጸመ በመሆኑና አመክሮው ሲታሰብ የተወሰነበትን
የሶስት አመት ከሶስት ወር እስራት እያጠናቀቀ በመሆኑ ዋናው ጉዳይ እስኪቋጭ ድረስ እስራቱን እንዲቀጥል
ቢደረግ የማይተካ በደል ሊደርስበት እንደሚችል በማስቀመጥ አመልካች የብር አምስት ሽህ ብር (5000 ሽህ ብር)
ዋስትና ጠርቶ በውጭ ሆኖ እንዲከራከር ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ በዚህ አግባብ አመልካች ቅጣቱ ታግዶ በዋስትና
ከተለቀቀ ከአንድ ወር (1ወር ከ 6 ቀን) በኋላ ዐ/ሕግ በዋናው የይግባኝ ቅሬታ ላይ መልስ ይዞ እንዲያቀርብ
ተደርጓል፡፡ ዐ/ህግም በዋናው ጉዳይ ላይ ከሰጠው መልስ በተጨማሪ የአመልካችን የቅጣት እገዳና በዋስትና
መውጣትን በተመለከተ የተለያዩ የህግ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ አስተያየት ያቀረበ ሲሆን የአመልካች
ጠበቃም ምላሽ ሰጥተውበታል፡፡ በሁለቱም በኩል የቀረቡት አስተያየቶች የዚህ ጽሁፍ ማዕከል የሆነው ጥያቄ
ትኩረት በመሆናቸው ዝርዝር ይዘታቸውን መመልከቱ ወሳኝነት አለው፡፡ የመዝገቡ ግልባጭ እንደሚያስረዳው
የዐ/ሕግ አስተያየት ሁለት ነጥቦች ላይ ያጠነጥናል፡፡ የመጀመሪያው በይግባኝም ሆነ በሰበር ደረጃ ዋስትናን
ለመፍቀድም ሆነ ለመንፈግ ክስ የቀረበበት ድንጋጌ መሰረት ሊደረግ ይገባል የሚል አቋም የሚንጸባረቅበት ነበር፡፡
ከዚህም በመነሳት አመልካች በስር ፍርድ ቤቱ ተከሶና ጥፋተኛ ተብሎ የተቀጣበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543 (3)
ከወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 63 ጋር ተጣምሮ ዋስትናን የሚያስከለክል በመሆኑ አመልካች
ቅጣቱ ታግዶለት በዋስትና ሊወጣ እንደማይገባ የሚገልጽ ሲሆን ፤ በሁለተኛው ደረጃ የቀረበው አስተያየት ደግሞ
የስር ፍርድ ቤት የጥፋተኛነት ውሳኔ በበላይ ፍርድ ቤቶች ለመመርመር ያስቀርባል መባሉ ብቻውን ውሳኔው
በርግጠኛነት የሚሻር ወይም አመልካች ነጻ ነው ወደሚል መደምደሚያ ሊወስድ አይችልም የሚል ነው፡፡ በአንጻሩ
አመልካች በጠበቃው አማካኝነት ያቀረበው ምላሽ ደግሞ በዐ/ሕግ በኩል የቀረቡትን አስተያየች በሌላ አተያይ
የሚመለከት ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ይኸውም የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 63 ተጠቅሶ የዋስትና
ተቃውሞ ሊቀርብ የሚችለው በመጀመሪያ ደረጃ ክርክር ወቅት ብቻ ሲሆን በሰበር ደረጃ ያለ የዋስትና ጥያቄ
የሚስተናገደው ቅጣትን ስለማገድ በተመለከተው የሥነ ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 188 አግባብ ነው፡፡ አመልካችም
የዋስትና ጥያቄውን ያቀረበው በሰበር ደረጃ በመሆኑ የሥነ ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 63 ተጠቅሶ ዋስትና
የሚከለከልበት አግባብ አይኖርም የሚል ነበር፡፡ በመጨረሻም ችሎቱ በግራ ቀኙ አስተያየቶች ላይ ብይን ሳይሰጥ
ቅሬታውን መርምሮ በይግባኝ የተመለከተውን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በአብላጫ እንዳጸናው በውሳኔው
ሀተታ ላይ ተመልክቷል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል በአጣሪ ችሎቱ የተሰጠው ቀሪ እንዲሆንና
አመልካችም ታግዶለት የነበረውን የእስራት ቅጣት እንዲፈጽም ለማረሚያ ቤቱ ተጨማሪ ትዕዛዝ የሰጠበትን
አግባብ ያሳየናል፡፡
111
አብነት ከአቶ በሪሁን አዱኛ ታምራት፣በአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደሴ ምድብ ችሎት አስተባባሪና ዳኛ ጋር
መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በተደረገ ቃለ መጠይቅ አስተያየቱ ቀርቧል ፡፡ ይህ ሀሳብም በተመሳሳይ ከአቶ
ወልደኪሮስ አድማሱ፣ በአብክመ ፍትሕ ቢሮ የደሴ ቋሚ ምድብ አስተባባሪ እና ዐ/ህግ ጋር መጋቢት 25ቀን
2010ዓ.ም በተደረገው ቃለ መጠይቅ ተንጸባርቋል፡፡ አስተያየት ሰጭዎቹ አክለውም በወንጀል ጉዳይ ዋስትና
ማመልከቻዎች በግልጽ ቀርበው ፍርድ ቤቱ ምላሽ ሳይሰጥባቸው የሚታለፉበት አጋጣሚም
ይስተዋላል፡፡112 በመሰረቱ ይግባኙ እስኪቋጭ ከእስራት ቅጣት እገዳው ጋር ተያይዞ በአመልካች
በኩል የሚቀርበው ዋስትና በመጀመሪያ ደረጃ ክርክር ከሚጠየቀው ዋስትና ጋር ተመሳሳይ
መሆን፣ አለመሆኑንም ሆነ የሚመዘንበትን አግባብ ከፍ ብለው ከተነሱት ሀሳቦች ጋር አጣምሮ
መመርመር ያስፈልጋል፡፡ እንደሚታወቀው በመጀመሪያ ደረጃ ክርክር ሂደት (Pending Trial)
ተከሳሹ ጉዳዩ ታይቶ ጥፋተኛነቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ንጹህ ሆኖ የመገመት መብት አብሮት
የሚቀጥል የመሆኑን ያህል ህብረተሰቡም ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ሰዎች ቅጣታቸውን
እንዲፈጽሙ ያለው ፍላጎትም እኩል ተቀባይነት ያለው መርህ ነው፡፡ ክርክሩ ተጠናቆ እውነቱ
እስኪረጋገጥ ባለው ጊዜ እነዚህን እርስ በርስ የሚጋጩ ፍላጎቶች ማስታረቅ የሚያስፈልግ

የሚመራበት አግባብ ወጥ በመሆኑ ዋስትና በመጀመሪያ ደረጃ ክርክር ፣በይግባኝ ወይም በሰበር ደረጃ በሚል
ተከፋፍሎ ሊታይ አይገባም የማለት ያብራራሉ፡፡ ከዚህ አኳያ በማንኛውም እርከን ላይ የሚገኝ ፍርድ ቤት
ከዋስትና ጋር የተገናኙ ጉዳዮች ሲቀርቡለት ለመፍቀድም ሆነ ለመከልከል እንደነገሩ ሁኔታ ዋስትናን የተመለከቱ
የሥነ ሥርዓት ሕጉ ድንጋጌዎች 67 እና 63ን እና ልዩ የወንጀል ሕግጋትን በተመሳሳይነት መሰረት ማድረግ
የግድ ይኖርበታል፡፡ በሚል ሀሳባቸውን ያጠናክራሉ፡፡
112
ለአብነት በአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወ/ይ/መ/ቁ 02-18832 በይግባኝ ባይ አለምነሽ ሽሜ እና መልስ ሰጭ
የክልሉ ዐቃቤ ሕግ መካከል በነበረው ክርክር ላይ የሰጠውን ውሳኔ መመልከት ይቻላል፡፡ ጉዳዩ የተነሳው ቀደም
ሲል አመልካች በባህር ዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሌላ ተከሳሽ ጋር በመሆን በ2007 ዓ.ም የወጣውን
አዋጅ ቁጥር 909/2007 አንቀጽ 6ትን በመተላለፍ በሕገ ወጥ መንገድ የሰዎች ዝውውርን ማድረግ ወንጀል
ፈጽማለች በሚል ክስ በመቅረቡ ነው፡፡ ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ጉዳዩን መርምሮ ድንጋጌውን ወደ አንቀጽ 3
በመቀየር ጥፋተኛ ካላት በኋላ በ13 አመት (በአስራ ሶስት አመት ጽኑ እስራት) እና በ3000 ሽህ (ሶስት ሽህ ብር)
የገንዘብ መቀጮ እንድትቀጣ ወስኗል፡፡ ይህንንም ውሳኔ በመቃወም አመልካች ይግባኝ ቅሬታዋን ለአማራ ጠቅላይ
ፍርድ ቤት አቅርባለች፡፡ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱም የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ለማረም የሚያስችል መሰረታዊ
ነጥብ እንዳለ በማየት ጉዳዩን ከመረመረና ቅሬታው ከደረሰው ከወራት በኋላ የስር ፍርድ ቤቱን የጥፋተኛነትም ሆነ
የቅጣት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ በመሻር ይግባኝ ባይን በነጻ እንድትሰናበት ወስኗል፡፡ እዚህ ላይ ለመመልከት
የተፈለገው ነጥብ አመልካች የስር ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እርምት የሚያስፈልገው መሰረታዊ ስህተት ያለበት መሆኑን
በቅሬታዋ ከማስቀመጥ ባለፈ ይግባኙ ታይቶ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ እስራቱን መፈጸም መቀጠሏ የማይተካ ጉዳት
እንደሚያደርስባት በመግለጽ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 188 መሰረት ቅጣቱ ታግዶ በዋስትና ለመለቀቅ እንዲፈቀድላት
አመልክታ እንደነበር ነው፡፡ ሆኖም ፍርድ ቤቱ ለዚህ ማመልከቻ ምላሽ ሳይሰጥ እንዳለፈው መዝገቡ ያሳያል፡፡ ይኸ
አይነት ህጋዊ መሰረት ያለው ጥያቄ ህጋዊ ውሳኔ ማግኘት ሲኖርበት መታለፉ ሥነ ሥርዓታዊ አለመሆኑ
እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይም ሕጉ ማሳካት የፈለገውን የማይተካ ጉዳትን የመቀነስ የፍትህ ፍላጎት በተግባር
እንዲሸራረፍ ማድረጉ አይቀርም፡፡
ሲሆን በዚህ ሂደት የሚኖረው ዋስትና ተግባርም ይኸው ይሆናል፡፡113 በዚህ መልኩ ተከሳሹ
ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ባከራከረው ፍርድ ቤት የጥፋተኛነት ፍርድ ከተላለፈበት በኋላ ግን
በፍርድ ሂደቱ አብሮት የነበረው ንጹህ ሆኖ የመገመት መብት ጥበቃ ያቆምና ከባድ በሆነ
የጥፋተኛነት ግምት (Presumption of Legal Guilt) ይተካል፡፡114 ይኸውም ይግባኝ ሰሚው
የቀረበው ይግባኝ (Pending Appeal) እስኪቋጭ ድረስ እስራቱ ታግዶ አመልካች በዋስትና
እንዲለቀቅ የሚሰጠው ትዕዛዝ በመጀመሪያ ደረጃ የችሎቱ ሂደት (pending trial) የጠበቀውን
ንጹህ ሆኖ የመገመት መብትን ተንተርሶ እንደማይሆን ያስገነዝባል፡፡ በመሆኑም በይግባኝ ሂደት
በዋስትና የመውጣቱ ጥያቄ በመርህ ደረጃ ልክ እንደ መጀመሪያ የክርክር ሂደት በመብትነት
የሚጠየቅ አይሆንም ማለት ነው፡፡115 ይህ ሁኔታ ደግሞ በይግባኝ ሥርዓት የእስራት ቅጣት
እንዳይፈጸም የሚሰጠው እገዳና ዋስትና በመጀመሪያ ደረጃ የክርክር ሂደት ወቅት ዋስትና
በሚመዘንበት አይነት እንዲመራና እንዲለካ አያደርገውም፡፡ ይልቁንም ይህ ጉዳይ ድንጋጌው
ሊያሳካው ካሰበው ልዩ አላማ፣ በአመልካች በኩል ከሚቀርቡት ምክንያቶች እንዲሁም
ከጠቅላላው የህብረተሰቡና የፍትህ ፍላጎት አንጻር በጥንቃቄ ተመዝኖ የሚወሰን መሆን
ይኖርበታል፡፡ በቀዳሚነት የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት አንቀጽ 188 “ፍርድ እንዳይፈጸም
ማገድ” የሚል ርዕስ ከመያዙም በተጨማሪ በስሩ ያሉት አንቀጾች ይዘትም ይህ ሥርዓት በስር
ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ሆኖ የእስራት ቅጣት የተፈረደበት ይግባኝ ባይን እንደሚመለከት
ይገልጻል፡፡116 ይኸውም አገላለጽ የዚህን ስርአት አላማ ተፈጻሚነት አመልካች ክስ ከቀረበባት
ወይም ጥፋተኛ ከተባለበት ድንጋጌ ዋስትና ፈቃጅነት ወይም ነፋጊነት ይልቅ በስር ፍርድ ቤቱ
የተሰጠው “ፍርድ” ማዕከል ሊሆን እንደሚገባ ያመላክታል፡፡ ከአላማውም አኳያ ድንጋጌው
የተካተተው ይግባኝ የተባለበት ፍርድን የተከተለ የእስራት ቅጣት አፈጻጸም ቀጣይነት
በአመልካች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለማስወገድ ነው፡፡ ይህ ደግሞ አላማውን በፍርድ
ከሚደርሰውን ጉዳት እንጅ በአመልካች ላይ ከተጠቀሰው የወንጀል ሕግ ድንጋጌ ዋስትና
ፈቃጅነትና ከልካይነት ጋር በቀዳሚነት እንዲተሳሰር አያደርገውም፡፡ ትርጉም ባለው መልክም
በስር ፍርድ ቤት የተሠጠ የእስራት ቅጣት በመርህ ደረጃ መፈጸም ሲገባው በልዩ ሁኔታ
በይግባኝ የቅጣት ማገድና በዋስትና የማቆየት ሥርዓት መኖሩ በራሱ በልዩ መልኩ ሊታይ

113
Fabian A. Kwiatek and Richard J.snider, Bail, pending Appeal, Mandatory or Discretionary?
1cath. U.L. Rev.93 (1951).
Available at:http://Scholarship.Law.edu/Lawreview/vol1I/iss2/8
114
ዝኒ ከማሁ
115
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 80
116
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 15 ፣ወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 188
የሚገባ የመሆኑ ማሳያ ነው፡፡ በርግጥ ይህ ሥርዓት ፍርድ የተላለፈባቸውና ይግባኝ ያቀረቡ
አመልካቾችን በጠቅላላ የሚያስተናግድ እንዳልሆነም አጽዕኖት ሊሰጠው ይገባል፡፡ በዚህ መልኩ
አላማውን መገንዘብ እንደተጠበቀ ሆኖ በይግባኝ የእስራት ቅጣት እንዳይፈጸም በማገድ
አመልካችን በዋስትና መልቀቅን ለመወሰን ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን በጥንቃቄ መመርመር
አላማውን በአግባቡ ሊያሳካ ይችላል ብላ ጸሀፊዋ ታምናለች፡፡ የመጀመሪያው ነጥብ በይግባኝ
ቅሬታ የቀረበበት ፍርድ ይዘትን የሚመለከት ሲሆን የስር ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ውስጥ የሚታረም
መሰረታዊ ነገር መኖሩን የማረጋገጥ ቅድመ ሁኔታ ወይም በእንግሊዥኛው (Merit-
requirement) የተባለው መመዘኛ ነው፡፡117 ይኸውም ስህተቱ መሰረታዊ መሆኑ በመጨረሻ
የሚኖረው የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጣ መሆኑን
ለመፈተሽ ወሳኝነት ያለው ከመሆኑ ባለፈ አላማው በልዩ ሁኔታ በጠባቡ የሚፈጸም ለመሆኑ
ጥሩ ማሳያ ይሆናል ፡፡ ምክንያቱም የስር ፍርድ ቤቱ ውሳኔን የማያስለውጥ ምክንያትን
መቀበል የቅጣት ማገዱን አስፈላጊነት ትርጉም አልባ ስለሚያደርግ ነው፡፡ ስለሆነም በስር ፍርድ
ቤቱ ውሳኔ ውስጥ ሊታረም የሚገባው ነጥብ መኖሩን መፈተሽ ለዚህ ሥርዓት ተፈጻሚነት
ቁልፍና ተቀዳሚ መመዘኛ በመሆኑ ዳኞች በከፍተኛ ጥንቃቄ መመዘን ይጠበቅባቸዋል፡፡
መሰረታዊ ግድፈትን በመመርመር ውስጥ ደግሞ እንደ ጉዳዩ ሁኔታ ከፍርዱ የሚነሱ ለምሳሌ፦
ይግባኙ የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ መሻርን ሊያስከትል የሚችል መሆን አለመሆኑን ፤ሊሰጥ
የሚገባው ቅጣት የእስራት ቅጣትን የማያስከትል መሆን አለመሆኑን ፤የሚወሰነው ቅጣት
አመልካች ከፈጸመው የእስራት ጊዜ እና የይግባኙ ሂደት ይወስዳል ተብሎ ከሚጠበቀው ጊዜ
ሊያንስ የሚችል ስለመሆኑና የመሳሰሉ ነጥቦችን ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል፡፡
ሁለተኛው ቅድመ ሁኔታ የማስረዳት ሸክምን የሚመለከተው (burden of proof
requirement) ሲሆን አመልካች ቅጣቱ ታግዶ በዋስትና ሊወጣ የሚያስችለውን ምክንያት/ቶች
በግልጽ አቅርቦ ከማሳመን ጋር የሚያያዝ መለኪያ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ለማብራራት
እንደተሞከረው ይግባኝ ባይ ጥፋተኛ ስለተባለ ልክ እንደ ስር ፍርድ ቤት ሂደት ንጹህ ሆኖ
የመገመት እና በዋስትና የመውጣት ጥያቄን በመብትነት ሊያነሳ አይችልም፡፡ በመሆኑም
የእስራት ቅጣት አፈጻጸም ታግዶለት በዋስትና እንዲወጣ ባቀረበው ማመልከቻ ውስጥ በዚህ
ሥርዓት ተጠቃሚ የሚያደርጉትን ጥብቅ ምክንያቶች የማቅረብና ፍርድ ቤቱን የማሳመን ሸክም
(Reverse onus) ያለበት በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ይህንን ሀላፊነት በአግባቡ መወጣቱን ማረጋገጥ

117
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 21
ይኖርበታል፡፡118 በዚህ መልኩ በምክንያቶች ተደግፎ የሚቀርበው በዋስትና የመለቀቅ ማመልከቻ
በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ፍቅድ ስልጣን ተመዝኖ የሚወሰን መሆኑ ድህረ-ቅጣት ዋስትና
(post conviction Bail) የሚታይበትን አግባብ በመጀመሪያ ደረጃ ክርክር ጊዜ ከሚኖር ዋስትና
(trial bail) የተለየ ያደርገዋል፡፡119 ቀደም ሲል ለማብራራትም እንደተሞከረው በወንጀል
የፍትሕ ሥርዓታችን ዋስትና በወንጀል አይነት ብቻ ሳይሆን ፣በሥነ ሥርዓት ሕጉ በተቀመጡ
ሁኔታዎችና መሰረታዊ የወንጀል ህግጋትን ከወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 63
(1) ጋር አጣምሮ በማየት ለመከልከል ይቻላል፡፡120 ሆኖም ይህ ሁኔታ በሥነ ሥርዓት ሕጉ
አንቀጽ 188 ስር የተመለከተውንና በእስራት ቅጣት ማገድ ጊዜ የሚኖረውን በዋስትና የመልቀቅ
ስርአት አድማስ ዋስትና በማያሰጡ ወንጀሎች ተፈጻሚነት እንዳይኖረው አድርጎ ትርጉም
ለመስጠት አያስችልም፡፡ ይልቁንም በዚህ ሥርዓት አመልካች የሚለቀቀው በዋስትና እንደሆነ
የመደንገጉ ሀሳብ የህብረተሰቡና የፍትህ ፍላጎትን ለማጣጣም እንደሆነ መውሰድ ምክንያታዊ
ይሆናል፡፡ ለዚህም ነው አመልካቹ ቅጣቱ እንዲታገድለት የሚያስችሉትን ጠንካራ ምክንያቶች
ማቅረቡም ሆነ ይግባኝ ሰሚው በፍርዱ ውስጥ የሚታረም መሰረታዊ ግድፈት መኖሩን
በዝርዝር ማረጋገጡ ብቻውን ቅጣት ለማገድ በቂ የማይሆነው፡፡121 ይህም ፍርድ ቤቱ በርግጥም
አመልካች የዋስትና ግዴታውን ለመወጣት የሚበቃ ባህሪይ ያለው መሆኑን በተጨማሪነት
መመርመር እንደሚኖርበት ያስገነዝባል፡፡ በዚህም ሂደት የሚኖረው ዋስትና ዋና ትኩረት
አመልካች በዋስትና ከተለቀቀ በኋላ ይግባኝ ሰሚው የስር ፍርዱን ቢያጸና ወይም የተለየ ውሳኔ
ቢሰጥ ለመፈጸም ሊቀርብ ስለመቻሉ በመሆኑ በባህሪይና ሁኔታ መለኪያዎች የሚመዘን
ይሆናል ማለት ነው ፡፡

118
Criminal Law book. www.Criminal law book.calindex
119
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 24
120
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 35695 በአመልካች የአማራ ክልል ዐ/ሕግ እና
ተጠሪ አቶ ተመስገን አዲስ መካከል በነበረው ክርክር ኀዳር 11 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ ቅጽ 9 ፣
የኢትዮጵያ ፌዴራሊዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጥናትና የሕግ ድጋፍ መምሪያ ህዳር 2003
ዓ.ም አዲስ አበባ፡፡ በዚህ ውሳኔ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎቱ በአመልካች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ የተሻሻሉና
የተለወጡ ሁኔታዎች በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ጋር ያላቸውን ተፈፃሚነትና ፍርድ
ቤቶች ሊከተሉት የሚገባ የሕግ አተረጓጎም ምን መሆን አለበት? የሚል ጭብጥ ተይዞ ነበር፡፡ በዚህም መሰረት
በአዱሱ የወንጀል ሕግ ቅጣታቸው ከፍ ብሎ የተደነገጉ ወንጀሎች የዋስትና ጥያቄና ተከሳሽ በሌለበት እንዲታይ
የሚቀርቡ የሥነ-ሥርዓት ጥያቄዎች 1949 ዓ.ም በወጣው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የነበረውን ሁኔታ ግምት
ውስጥ ማስገባትና ትርጓሜ መስጠት ሣያስፈልግ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ከአዱሱ የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች ጋር
በቀጥታ አጣምሮ በማየት መወሰን እንደሚኖርባቸው አትቷል፡፡ በዚህም መሰረት አንቀጽ 543 ንዑስ አንቀጽ 3
እስከ አስራ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ
ቁጥር 63 ንኡስ አንቀጽ 1 የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟላና የዋስ መብት የሚያሰጥ አለመሆኑን አስገዳጅ
የህግ ትርጉም ቀደም ሲል ሰጥቶበታል፡፡
121
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 35፣ ገጽ 233-240
4. ማጠቃለያ እና ምክረ ሀሳቦች
4.1 ማጠቃለያ

በወንጀል ተከሶ በነጻና ገለልተኛ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ የተባለ ማንኛውም ሰው በመርህ ደረጃ
የተወሰነበት ቅጣት እንዲፈጽም ማድረግ የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ጠቅላላ ፍላጎት ነው፡፡
በዚሁ ልክ ደግሞ የስር ፍርድ ቤቶች በፍርዶቻቸው በፈጸሟቸው ግድፈቶች ምክንያት ንጹህ
ሰዎች ያለአግባብ እንዳይቀጡ የሚታደግ ሁለተኛ እድል ማዘጋጀትም ተመሳሳይ የፍትህ ፍላጎት
በመሆኑ ለእርማት የሚሆን የይግባኝ ሥርዓት ተበጅቷል፡፡ በዚህ ንጹሀንን የመጠበቅ ሥርዓት
ውስጥ ደግሞ የአመልካች ይግባኝ ተመርምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የእስራት ቅጣቱን ማስቀጠል
አመልካች ላይ የማይካስ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ ከታመነ ቅጣቱን በማገድ አመልካች
በዋስትና የሚወጣበት ቀዳዳ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 188 ስር አካቷል፡፡
ይሁን እንጂ የሥነ ሥርዓት ሕጉ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ የእስራት ቅጣት ፍርድን በማገድ
አመልካችን በዋስትና ለመልቀቅ ስልጣን እንዳለው እንጂ ይህንን በመወሰን ረገድ መሰረት
ሊደረጋቸው የሚገቡ ነጥቦችን በዝርዝር አላስቀመጠም፡፡ ከዚህም የተነሳ በተግባርም የእስራት
ቅጣት ማገጃ ሁኔታዎችን ለመወሰን የሚያስችሉ ነጥቦች ምን ሊሆኑ ይገባል በሚለው ነጥብ
ላይ የተለያዩ ሀሳቦች እና ክርክሮች ይንጸባረቃሉ፡፡ በዋናነትም ይግባኝ ፍርድ ቤቱ ይህን
ለመወሰን ከመነሻው ይግባኝ ባይ በስር ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ የተባለበት ድንጋጌ ዋስትና
የሚፈቅድ ወይም የሚከለክል መሆኑን ማየት ቀዳሚ መስፈርት ሊደርገው ይገባል የሚለው
ይነሳል፡፡ ለዚህም የሚቀርበው መከራከሪያ ዋስትና በየትኛውም የክርክር ደረጃ ተመሳሳይ
ምዘናና አፈጻጸም የሚከተል በመሆኑ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 188 የፍርድ እገዳና በዋስትና
የመልቀቁ ጉዳይም ዋስትና በሚያስከለክሉ ወንጀሎች ለተቀጣ አመልካች ተፈጻሚ ሊሆን
አይችልም የሚል ነው፡፡ በርግጥም በሕግ ሥርዓታችን ዋስትናን የሚያስከለክሉ ወንጀሎች
እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ይህ ሁኔታ በይግባኝ ሂደት የእስራት ቅጣት የሚታገድበትና
አመልካችም (የስር ፍርድ ቤት ጥፋተኛ) በዋስትና የሚለቀቅበትን ሥርዓት በተቀጣበት ድንጋጌ
ዋስትና ፈቃጁነት ወይም ነፋጊነት መመዘኛ እንዲያልፍ አያደርገውም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ
ከአላማው ስንነሳ ድንጋጌው የተካተተው በማንኛውም የህግ ድንጋጌ ጥፋተኛ ተብሎ በእስራት
የተቀጣ አመልካች ይግባኙ እልባት እስኪያገኝ ድረስ ባለው ጊዜ የእስራቱ ቀጣይነት
ሊያመጣበት የሚችለውን ጉዳት ለማስወገድ ታስቦ ነው፡፡ ይህ አላማውም የድንጋጌውን
የተፈጻሚነት አድማስ ከስር ፍርድ ቤቱ “ፍርድ” እንጅ አመልካች በስር ከተከሰሰበት ወይም
ከተቀጣበት ድንጋጌ ዋስትና ፈቃጅ ወይም ከልካይ መሆን ጋር አያስተሳስረውም፡፡ ይህ
እንደተጠበቀ ሆኖ ቅጣትን ማገድ ለሁሉም ይግባኝ ባዩች ተግባራዊ ማድረግ ዋናውን የቅጣት
መፈጸም መርህን የሚቃረን በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ማመልከቻው ሲቀርብለት እስራትን
ባስከተለው ፍርድ ውስጥ ሊታረም የሚገባው መሰረታዊ ስህተት መኖሩን በጥንቃቄ መመርመር
ይኖርበታል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ከእስር መለቀቅ እንደመብት የሚጠየቅ ባለመሆኑም
አመልካች በርግጥም ፍርዱ ስህተት ያለበትና በዚህ ፍርድ የመጣው እስራት መቀጠልም
የማይተካ ጉዳት ሊያደርስበት የሚችል መሆኑን በዝርዝር ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡ እዚህ ላይ
ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ሌላው ነጥብ በስር ፍርድ ውስጥ የሚታረም መሰረታዊ ግድፈት
መኖሩን ማረጋገጥ ብቻውን ፍርዱን ለማገድ በቂ ተደርጎ ሊወሰድ አለመቻሉ ነው፡፡ ይልቁንም
በወንጀል ፍትህ ሂደት ውስጥ ከግለሰቦች ፍላጎት በተጨማሪ የህብረተሰቡንና የፍትህ ጥብቅ
ፍላጎት በዚህም ሥርዓት መጠበቅ ይኖርበታል፡፡ ከዚህ አንጻር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን
ሲያግድ አመልካችን የሚለቀው በዋስትና በመሆኑ ቁልፍ የሆኑትን የዋስትና መሰረቶችን
ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም አመልካች ቅጣቱ ታግዶለት በዋስትና
ቢለቀቅ ከፍትህ የማይሸሽና ለማህበረሰቡም አደጋ አለመሆኑን መፈተሽ የፍርድ ቤቱ ተጨማሪ
ቁልፍ የዋስትና መመዘኛና ተግባር ይሆናል ፡፡
በአጠቃላይ ድንጋጌው በሥነ ሥርዓት ህጉ የመካተቱ አላማ ግድፈት ባለበት ፍርድ ምክንያት
የሚመጣ የማይካስ ጉዳትን መከላከል በመሆኑ የወንጀሉ ዋስትና ፈቃጅነትን /ነፋጊነትን
የተፈጻሚነት መመዘኛ ከማድረግ ይልቅ የድንጋጌውን አላማ፣ በፍርዱ ውስጥ የሚታረም
መሰረታዊ ነጥብ መኖር እንዲሁም የህብረተሰቡና የፍትሕ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ መወሰን
ይገባል፡
4.2 ምክረ ሐሳቦች
በወንጀል ይግባኝ ሥርዓት ቅጣትን በማገድ ይግባኝ አመልካች በዋስትና እንዲወጣ የማድረግ
ሂደት አላማ ይግባኙ እስኪጠናቀቅ ድረስ በእስራቱ መቀጠል ምክንያት በይግባኝ ባይ ላይ
የማይካስ ጉዳት እንዳይደርስ መጠበቅን ማዕከል ያደርጋል ፡፡ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱም
በመሰረታዊነት የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ መርምሮ እስኪቋጭ አመልካቹ በዋስ እንዲወጣ
ያቀረበው ማመልከቻ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት የአመልካቹን ብቻ ሳይሆን የጠቅላላውን ማህበረሰብ
ፍላጎት ማዕከል ያደረጉ መመዘኛዎችን በጥንቃቄ መመርመር ይኖርበታል፡፡
በቀዳሚነት ይህ ሥርዓት በልዩ ሁኔታ ተግባራዊ መሆን ያለበት በመሆኑ ማመልከቻው
ስለቀረበ ብቻ ተፈጻሚ ሊሆን እንደማይችል ይታወቃል፡፡ ከዚህ አኳያ በስር ፍርድ ቤቱ ውሳኔ
ውስጥ ምንአልባትም የውሳኔውን ይዘት የመቀየር ውጤት ሊያስከትል የሚችል ነጥብ መኖሩን
በጥንቃቄ መመርመር ከይግባኝ ሰሚው በቀዳሚነት ይጠበቃል፡፡ በተለይም ይህንን በማሳየት
ረገድ አመልካች ፍርድ ቤቱን ለማሳመን በቂ ምክንያቶችንም ማቅረብ የቻለ ስለመሆኑ
ማረጋገጥም ወሳኝ ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ድንጋጌው ጥፋተኛ የተባሉ ሰዎች በአግባቡ
ቅጣታቸውን እንዲፈጽሙ በማድረግ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ በጥበቅ ከሚፈልገው
የጠቅላላው ህብረተሰብ ፍላጎት ጋርም መመዘን ይጠበቅበታል፡፡ በዚህም በፍርድ እገዳ ሥርዓት
ላይ የተመለከተውን ዋስትና ይህንኑ ፍላጎት በሚያጣጥም መንገድ ከአመልካች ባህርይ ጋር
አያይዞ ማየት ሌላኛው ከፍርድ ቤቱ የሚጠበቅ መመዘኛ ሊሆን ይገባዋል ፡፡ በዚህ አግባብ
አመልካች ቅጣቱ ሊታገድለት ከቻለ የሚቆየው በዋስ በመሆኑ ቢወጣ በሌላ የወንጀል አድራጎት
ውስጥ የማይገባ፤ ቅጣቱን ለመፈጸምም ሆነ በሚፈለግበት በማንኛውም ጊዜ ከፍትህ የማይሸሽ
መሆኑን በአግባቡ በመመዘን የድንጋጌውን መንፈስና አላማ የሚያሳካ ትዕዛዝ መስጠት
ያስፈልጋል፡፡
ሌላው በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ውስጥ ከተከሳሽ ጎን ለጎን ዐቃቤ ህግ ፣የግል ከሳሽ ወይም
ተጎጅዎች እንደ ነገሩ ሁኔታ የክርክሩ ሂደትም ሆነ ውጤቱ ይመለከታቸዋል፡፡ ከዚህ አኳያ
የእስራት ቅጣት የሚታገድና በዋስትና መለቀቅን በሚያስከትለው ስርአት በዋናነት በአመልካች
በኩል የሚቀርቡትን ምክንያቶች ሆነ የአመልካቹ ባህሪና ሁኔታ መመዘኛዎች ላይ
የሚኖራቸውን አስተያየት እንደነገሩ ከግምት ውስጥ ማስገባት ምክንያታዊ ይሆናል፡፡ በአንድ
በኩል የዋስትና አላማ በራሱ በግለሰቦችን ብቻ ሳይሆን የህብረተሰቡን ፍላጎት ማመዛዘን ያለበት
መሆኑ በራሱ የእነዚህን አካላት አስተያያት መቀበልን አስፈላጊ ያደርገዋል፡፡ በሌላ በኩል በእስሩ
መቀጠል ምክንያት የማይተካ ጉዳት ሊደርስባቸው ከሚችሉ ይግባኝ ባዩች ውጭ የሕግ
አውጭውን ፍላጎትና የድንጋጌውን አላማ በክፉ ልቦና መጠቀም የሚፈልጉ አመልካቾችን
ለማጥራት የእነዚህን አካላት ሀሳብ መቀበል የበለጠ ያግዛል፡፡
በይግባኝ የስር ፍርድ ቤቱን የእስራት ቅጣት ፍርድ አፈጻጸም በማገድ አመልካች በዋስ
እንዲወጣ ትዕዛዝ የመስጠት ጉዳይ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ፍቅድ ስልጣን ስር ቢሆንም
ሕግ አውጭው በዚህ ድንጋጌ ሊያሳካው ያሰበውን አላማ በአግባቡ ለማሳካት በአመልካች በኩል
የሚቀርቡት ምክንያቶች በጠንካራ ማስረጃዎች መደገፋቸውን ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን በጥንቃቄ
የመመዝገብና ውሳኔ የመስጠት ልምድ ማዳበር ወሳኝ ነው፡፡
ደጋጋሚ ወንጀለኛነት እና የቀድሞ የወንጀል ሪከርድ የህግ ማዕቀፍ እና ተግባራዊ አፈጻጸም
በአማራ ክልል

ይማም ሰይድ ሐሰን*

አጽህሮተ ይዘት

የአጥፊዎች የቀድሞ የወንጀለኝነት ማስረጃ (Criminal recored) እና ደጋጋሚ ወንጀለኝነት (Recidivism)


የወንጀል ቅጣት የሚከብድባቸዉ ምክንያቶች ናቸዉ፡፡ የቀድሞ የወንጀል ማስረጃ ያለባቸዉ እና ደጋጋሚ ወንጀለኛ
ሆነዉ የተገኙ አጥፊዎች እንደ አደገኝነት መጠናቸዉ ሊያርም አና ሊያስተምር የሚችል ቅጣት ይጣልባቸዋል፡፡
ይህም በብዙ ሀገሮች የተለመደ እና አፈጻጸሙም በህግ የሚመራ ነዉ፡፡ በዚህ ጥናት ዉስጥ የቀድሞ የወንጀለኝነት
ማስረጃ (Criminal recored) እና ደጋጋሚ ወንጀለኝነት (Recidivism) ትርጉም፣ ዓላማ፣ የህግ ማዕቀፍ እና
አፈጻጸም በተመለከተ የተለያዩ ሀገራት ተሞክሮ ተዳሷል፡፡ ኢትዮጵያም በ1997 ዓ.ም በወጣዉ የኢፌድሪ የወንጀል
ህግ እና በተሸሻለዉ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ዓ.ም መሰረት የቀድሞ የወንጀለኝነት
ማስረጃ እና ደጋጋሚ ወንጀለኝነት በቀረበ ጊዜ ፍርድ ቤቶቻችን ቅጣት አክብደዉ ይወስናሉ፡፡
የዚህ ጥናት ዓላማ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስር በሚገኙ የፍትህ ተቋማት ዉስጥ የቀድሞ የወንጀል
ማስረጃ ያለባቸዉ እና ደጋጋሚ ወንጀለኛ ሆነዉ የተገኙ አጥፊዎች የቅጣት ማክበጃ አፈጻጸም በ1997 ዓ.ም
ከወጣዉ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ እና ተሻሽሎ ከወጣዉ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ዓ.ም
አንጻር ምን እንደሚመስል መመርመር ነዉ፡፡
የጥናቱ ዘዴ አይነታዊ ሲሆን ለጥናቱም የደቡብ ወሎ ዞን፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ደቡብ ጐንደር ዞን እንዲሁም
የምዕራብ ጐጃም ዞን ፍትህ መምሪያ፣ ከፍተኛ ፍ/ቤቶችን፣ የፖሊስ ተቋማትን ለማካተት የተሞከረ ሲሆን
በተጨማሪም በእነዚሁ ዞኖች የሚገኙ የተመረጡ የወረዳ ፍ/ቤት፣ ፍትህ ጽ/ቤቶች እና ፖሊስ ጽ/ቤቶችን ተግባራዊ
አሠራር ተዳሷል፡፡ ቃለ መጠይቅ፣ የፅሁፍ መጠይቅ እና የትኩረት የቡድን ውይይት ለመረጃ መሠብሠቢያነት
ተጠቅሟል፡፡
በጥናቱም ዉስጥ የቀድሞ የወንጀል ማስረጃ ያለባቸዉ እና ደጋጋሚ ወንጀለኛ ሆነዉ በተገኙ አጥፊዎች መካከል
የቅጣት ማክበድ አፈጻጸሙ መደበላለቅ የሚታይበት ከመሆኑም ባሻገር በሁለቱ የቅጣት ማክበጃዎች መካካል
ያለዉን የጽንስ ሀሳብ ልዩነት ብዙዎቹ የህግ ባለሙያዎች በአግባቡ አለመገንዘባቸዉን በጥናቱ ለማረጋገጥ
ተችሏል፡፡
ስለሆነም በህጉ እና በአፈጻጸሙ መካካል ያሉትን ልዩነቶች ነቅሶ በማዉጣት ተገቢነት ያላቸዉ የመፍትሄ ሀሳቦች
ተጠቁመዋል፡፡

ቁልፍ ቃላት የቀድሞ የወንጀለኝነት ማስረጃ (Criminal recored) ፣ደጋጋሚ ወንጀለኝነት (Recidivism)፣ ልማደኛ
ደጋጋሚ (Persistent offender) ፣ የወንጀለኛነት ባህሪ (Criminal behaviour) እና የማስረጃ ምንጭ (Data
source)

*LLM, LLB በአብክመ የፍትህ ባለሙያዎች ማሰልጠኛ እና የህግ ምርምር ኢንስቲቲዩት አሰልጣኝ እና
ተመራማሪ፡፡ ጊዜያችሁን እና እዉቀታችሁን ላጋራችሁኝ ሁሉ ምስጋናየ የላቀ ነዉ፡፡
1. መግቢያ

ደጋጋሚ ወንጀለኝነት ማለት አጥፊዉ "የተወሰነበትን የእስራት ቅጣት በሙሉ ወይም በከፊል
ከፈጸመበት ወይም ይህ ቅጣት በይቅርታ ከቀረበት ቀን ጀምሮ በአምስት አመት ጊዜ ዉስጥ
መነሻ ቅጣቱ ስድስት ወር የሆነ ቀላል እስራት ማስቀጣት የሚችል አዲስ ወንጀል አስቦ ያደረገ
እንደሆነ1 ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የቀድሞ ወንጀለኛነት ማስረጃ ማለት አጥፊዉ የደጋጋሚ
ወንጀለኝነትን መለኪያዎች ሳያሟላ ነገር ግን ካሁን በፊት በተመሳሳይ ወይም በሌላ ወንጀል
ተሳትፎ የሚያዉቅ እና በዚሁም ወንጀል ቢያንስ ጥፋተኛ የተባለ ነዉ፡፡2 አንድ አጥፊ
የደጋጋሚነት ወይም የቀድሞ ወንጀለኛነት ማስረጃ ከቀረበበት የወንጀል ቅጣቱን ለማክበድ በቂ
ምክንያቶች ናቸዉሆኖም ግን የወንጀል ደጋጋሚነት እና የቀድሞ የጥፋተኝነት (የቅጣት
ሪከርድ)መዳረሻቸዉ ቅጣትን ማክበድ ቢሆንም የቅጣቱን መጠን ለማክበድ የሚሰጣቸዉ ደረጃ
ግን ፍጹም የተለያየ ነዉ፡፡

ይህም ስርዓት እንደ ሌሎች ሀገሮች ሁሉ በኢትዮጵያየወንጀል ፍትህ አስተዳዳር ዉስጥ የህግ
ማዕቀፍ ኖሮት ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝ ነዉ፡፡ ሆኖም ግን በአፈጻጸምም ሆነ በህግ ይዘቱ
ረገድ ከችግር የጸዳ አይደለም፡፡ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በየደረጃዉ በሚገኙ ፍትህ
ተቋማት ዉስጥ ደጋጋሚነትን እና በቀድሞ ወንጀለኛነትን በቅጣት ማክበጃነት አያያዝ እና
አሰላል ዙሪያ ከሚታዩችግሮች መካካል ደጋጋሚነትን እንደ ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ መዉሰድ፣
የደጋጋሚነትመለኪያ መስፈርቶችን በአግባቡ ተንትኖ አለመረዳት፣ የደንብ መተላለፍ
ደጋጋሚነትን ከመደበኛ ወንጀል ደጋጋሚነት ጋር መቀላቀል፣ ደጋጋሚነትን እና በቀድሞ
ወንጀለኛነትን ለማስረዳት ተገቢነት ያለዉን የማስረጃ ምንጭ አለመለየት እና ሌሎችም ሊጠቀሱ
ይችላሉ፡፡

እነዚህን ችግሮች ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማጥናት እና ዘላቂ የሆነ መፍትሄ በማፈላለግ ጉዳዩ
ለሚመለከታቸዉ አስፈጻሚ እና ህግ ተርጓሚ አካላት ለመጠቆም በማሰብ ይህ ጥናት
ተከናዉኗል፡፡

1
የኢፌዴሪየወንጀልሕግ፣አዋጅቁጥር 414/1997፣ነጋሪትጋዜጣ፣1997፣አንቀፅ 67
(ከዚህበኋላየኢፌዴሪየወንጀልህግ)
2
ዝኒ ከማሁ አንቀጽ 84(ሐ)
የጥናቱ መሰረታዊ ጥያቄዎች፡-

1. የወንጀል ደጋጋሚነት እና የቀድሞ ወንጀለኝነት (የቅጣት ሪከርድ)ልዩነት አላቸዉን?


2. የወንጀል ደጋጋሚነት እና የቀድሞ ወንጀለኝነት (የቅጣት ሪከርድ)መለኪያዎች ምንምን
ናቸዉ?
3. የወንጀል ደጋጋሚነት እና የቀድሞ ወንጀለኝነት (የቅጣት ሪከርድ)መለኪያዎች
ለአፈጻጸም ምቹ ናቸዉን?
4. የወንጀል ደጋጋሚነትንም ሆነ የቀድሞ ወንጀለኝነትን ለማስረዳት የሚቀርቡ ማስረጃዎች
መቅረብ ያለባቸዉ ከየት ነዉ? የሚሉት ናቸዉ፡፡

ስለሆነም በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስር በሚገኙ የፍትህ ተቋማት የሚስተዋሉ


የወንጀል ቅጣት ማክበጃ አሰላል ችግሮችን በሳይንሳዊ ዘዴ በማጥናት የመፍትሄሀሳቦችን
በጥናቱ ለማመላከት ተሞክሯል፡፡

1.1. የደጋጋሚነትምንነት እና ጽንስ ሀሳብ

Recidivist (ደጋጋሚ ወንጀለኛ) የሚለዉ ቃል የመጣዉ recidere ከሚለዉ የላቲን ቃል ሲሆን


ትርጉሙም to fall back (ወደ ቀድሞ ማንነት መመለስ) ማለት ነዉ፡፡3

ንድፈ ሀሳባዊትርጉሙ(Conceptual definition) ካሁን በፊት በወንጀል ተቀጥቶ ቅጣቱን


በሙሉ ወይም በከፊል ፈጽሞ ከወጣ በኋላ ወደ ቀድሞ የወንጀል ባህሪዉ መመለስ
(Elderbroon & King, 2014)ማለት እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ ነገር ግን በተግባር ላለዉ
አፈጻጸም ምላሽ የሚሰጥ(operational definition)ትርጉምን በቀላሉ የምንገልጸዉካለመሆኑም
ባሻገር መለኪያዎችምያስፈልጉታል፡፡4 ስለሆነም ደጋጋሚነትን ተከትለዉ በሚመጡ የተለያዩ
መለኪያ መስፈርቶች ምክንያት ፀሀፍቶች ለደጋጋሚነት ወጥ የሆነ በተግባር ላለዉ አፈጻጸም
ምላሽ የሚሰጥ (Operational Definition)ትርጉም ማስቀመጥ አልቻሉም፡፡ በዚህም ምክንያት
በጉዳዩ ዙሪያ ንፅፅራዊ ጥናት ለሚያከናዉኑ ሙህራን ጭምር ወጥ የሆነ መረጃ ማግኘት ትልቅ
ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡

3
MICHAEL D. maltz, Recidivism (Originally published by Academic Press, Inc., Orlando, Florida), 2001,
Internet edition available at http://www.uic.edu/depts/lib/forr/pdf/crimjust/recidivism.pdfp. 54.
4
ዝኒ ከማሁ
ጥፋተኛዉ የፈጸማቸዉ የቀድሞዉ እና አዲሱ ወንጀል ክብደት እና ዓይነት፣ የቀድሞዉን
ወንጀል በከፊል ወይም በሙሉ ፈጽሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ አዲሱን ወንጀል
እስከሚፈጽምበት ያለዉ የጊዜ እርዝመት፣ የቀድሞ እና አዲሱ ወንጀል የቅጣት ዓይነቶች፣
በደጋጋሚነት ማዕቀፍ ዉስጥ የሚካተቱና የማይካተቱ አካላት እና ወንጀሎች እንድሁምመሰል
መለኪያዎች የየሀገራቱን የወንጀል ፖሊሲ መሰረት አድረገዉ የሚቀረጹ በመሆናቸዉ
ደጋጋሚነት ወጥ የሆነ ትርጉም እንዳይኖረዉ ምክንያት ሆኗል፡፡5

አንድን አጥፊ ደጋጋሚ ነዉ ወይስ አይደለም የሚለዉን ለመለየት መለኪያዎችን ከመጠቀማችን


በፊት ሁለት ጉዳዮችን በትኩረት ማየት ይገባናል፡፡ እነዚህም ጉዳዮች የመጀመሪያዉ ተገቢነት
ያለዉ ወይም ትክክለኛ መለኪያ የትኛዉ ነዉ የሚለዉን መወሰን ነዉ፡፡ ይህም ማለት ወጥ
የሆነ የደጋጋሚነት መለኪያ ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ የምንጠቀመዉንመለኪያ መምረጥ ተቀዳሚ
ተግባራችን መሆን አለበት ማለት ነዉ፡፡6

ሁለተኛዉ ደግሞትክክለኛ የመረጃ ምንጭ መምረጥሲሆን የመረጃ ምንጮቻችን


ለመለኪያዎቻችን ዉጤታማነት መሰረቶች ናቸዉ፡፡ ስለሆነም የምንጠቀማቸዉ የመረጃ
ምንጮች አጥፊዉ ላይ የሚያስከትሉትን አሉታዊ ዉጤት ታሳቢ በማድረግ እና የወንጀል
ፍትህ አስተዳደሩን ዓላማ ለማሳካት ያስችል ዘንድ የመረጃ ምንጭ መረጣ ላይ ተገቢዉን
ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነዉ፡፡ ስለሆነም የመረጃ ምንጮቻችን ምን ያህል ትክክለኛ እና
ያለቀላቸዉ መረጃዎች ናቸዉ የሚለዉን ጉዳይ ሁልጊዜ ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡በግደለሽነት
የተሰበሰቡ እና እርግጠኛ ያልሆኑ መረጃዎች ለፍትህ ስርዓቱ የሚጠቅሙ ካለመሆናቸዉም
ባሻገር ጥፋተኛዉን ግለሰብ ዋጋ የሚያሰከፍሉ አንዳንድ ጊዜም ደግሞአላግባብ ተጠቃሚ
የሚያደርጉም እንዳይሆኑ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡7

አንድን አጥፊ ደጋጋሚ ወንጀለኛ ነዉ ወይስ አይደለም የሚለዉን ለመወሰን መለኪያዎች


እንደሚያስፈልጉን ከላይ በዝርዝር ታይቷል፡፡ይሁን እንጅ ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል እና
ወጥ የሆነ መለኪያ ወይም መስፈርት የለም፡፡ ነገር ግን ብዙ ሀገራት በተቀራራቢነት

5
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 4
6
Tayler Ruggero , Jamie Dougherty and John Klofas, Ph.D. Measuring Recidivism: Definitions, Errors, and Data
Sources, Working Paper , February 2015 , p. 3.
7
ዝኒ ከማሁ
የሚጠቀሙባቸዉንመለኪያዎች ማየቱ ተገቢም አስፈላጊም ነዉ፡፡8ስለሆነም በዝርዝር መታየት
ያለባቸዉ መለኪያዎችም እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡

1.1.1. የተወሰነበትን የእስራት ቅጣት በሙሉ ወይም በከፊል የፈጸመ ወይም እስራቱ
በይቅርታ የቀረ

አጥፊዉ ከአሁን በፊት ነጻነትን በሚያሳጣ የእስራት ቅጣት የተቀጣ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከዚህ
ዉጭ የደንብ መተላላፍ ወንጀሎችን ሳይጨምር ያሉ የገንዘብ ቅጣቶች እና የግዴታ ስራዎች
ለደጋጋሚ ወንጀለኛነት መለኪያ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

አንዳንድ ሀገራት የደንብ መተላላፍ ወንጀሎችን ማካተታቸዉ እንደተጠበቀ ሆኖ አጥፊዉ አዲስ


ወንጀል ሳይፈጽም የይቅርታ ወይም የፈተና ጊዜ መርሆዎችን በመጣሱ ብቻ እንደ ደጋጋሚ
ቆጥረዉ ቅጣት የሚያከብዱ አሉ፡፡9 ሌላዉ እዚህ ላይ መታየት ያለበት አጥፊዉ የቀድሞ
ቅጣቱን በከፊል የፈጸመ መሆን አለበት ሲባል ፍርድ ቤቱ ካስተላለፈበት የእስራት ቅጣት
ቢያንስ ግማሹን እስራት የታሰረ እና በእስራት ላይ እያለ በድጋሜ ወንጀል ቢፈጽም ማለት
ነዉን? ወይስ አጥፊዉ ቢያንስ ግማሹን እስራት ከፈጸመ እና ህጋዊ ስርዓቱን ተከትሎ
ከመደበኛ የእስራት መፈቻዉ በፊት ተፈቶ ከወጣ በኋላ ወንጀል በመፈጸሙ የሚመጣ
ደጋጋሚነት ነዉ የሚለዉ በግልጽ አልተቀመጠም፡፡

1.1.2. ቅጣቱንበከፊልወይምበሙሉከፈጸመ ወይም


በይቅርታከወጣጀምሮአዲስወንጀልእስከፈጸመበትያለዉጊዜ

ብዙዎቹ ሀገራት ይህንን የክትትል ጊዜ ከማስረዘም ይልቅ ማሳጠርን በመምረጥ


ሁለትወይምሶስትዓመትእንዲሆን በህጋቸዉ ዉስጥ ያካተቱ ሲሆን አንዳንድ ሀገራትደግሞ
ወደታች ዝቅ ብለዉስድስት ወር የክትትል ጊዜ ያስቀምጣሉ ጥቂቶቹ ደግሞ ወደ አምስት
ዓመት ከፍ አድርገዉ በመደንገግ የክትትል ጊዜዉን አስረዝመዉእናገኛቸዋለን(Lyman and
Lobuglio 2007)፡፡ የክትትሉ ጊዜ ረጅም በሆነ ቁጥር በደጋጋሚነት የሚቀጡ አጥፊዎች
በዚያኑ ያህል እንደሚጨምር ግልጽ ነዉ፡፡ ስለሆነም ቅጣት አጥፊዉን ከማስተማር እና
ሌሎችን ከማስጠንቀቅ አንጻር ያለዉ ጠቀሜታ እንደተጠበቀ ሆኖ ሀገራት የኢኮኖሚ

8
. ዝኒ ከማሁ
9
. የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 8
አቅማቸዉን እና የህዝባቸዉን ጥቅም መሰረት በማድረግ የክትትል ጊዜዉን ርዝመት
ይወስናሉ፡፡

1.1.3. ቅጣቱን በከፊል ወይም በሙሉ ከፈጸመ ወይም ቅጣቱ በይቅርታ ከቀረ በኋላ አስቦ
አዲስ ወንጀል የፈጸመ

አጥፊዉደጋጋሚ ወንጀለኛ ለመባል ካሁን በፊት በፈጸመዉ ወንጀል መቀጣቱ እንደተጠበቀ ሆኖ


በድጋሜ ሌላ አዲስ ወንጀል መፈጸም እና በዚህም ወንጀል ጥፋተኛ መባል አለበት፡፡10
ምክንያቱም የቀድሞዉ ወንጀል ሪከርድ ለአዲሱ ወንጀል ቅጣት ማክበጃነት ከማገልገል ባለፈ
ፋይዳ የሌለዉ በመሆኑ እና እንደ ጥፋተኛ ያለመቆጠር መብትን ጥበቃለማድረግ ሲባል
የቀድሞዉ ሪከርድ ከጥፋተኝነት በኋላ የሚቀርብ በመሆኑ ነዉ፡፡ ይህ አዲስ ወንጀል ታስቦ
(intentionaly) የተፈጸመ መሆን ይኖርበታል፡፡

1.1.4.በደጋጋሚነት የማይካተቱ ጉዳዮች እና አካላት፡-

ብዙ ሀገራት ወጣት አጥፊዎች የቀድሞ ጥፋተኝነት ተመዝግቦ እንዳይቆይ የሚከለክል ህግ


አላቸዉ፡፡ ይህ ማለት አንድ የተጠረጠረ ሰዉ ወጣት በነበረ ጊዜ ጥፋተኛ የተባለበት እና
የተቀጣበት ጉዳይ አዋቂ ከሆነ በኋላ ለሚያጠፋዉ ጥፋት በሪከርድነት አይቀርብበትም ማለት
ነዉ፡፡ ስለሆነም አዋቂ ከሆነ በኋላ ያጠፋዉ ጥፋት እንደ መጀመሪያ ጥፋት ይያዝለታል
ደጋጋሚም አይባልም፡፡ ስለሆነም ኢትዮጵያን ሳይጨምር ብዙ ሀገራት የወጣት ጥፋተኞች
ሪከርድ የሚመዘገበዉ ለጥናት አድራጊዎች በመረጃነት እንዲያገለግል ብቻ እንጅ የቀድሞ
ወንጀለኝነቱን ለማረጋጋጥ እና የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ለማድረግ አይደለም፡፡11

ከላይ የተዘረዘሩት መለኪያዎች እንደተጠበቁ ሆነዉ ኢትዮጵያን ጨምሮ ተጨማሪ


መለኪያዎችን የሚጠቀሙ ሀገራትም እንዳሉ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ ለምሳሌ አዲስ የተፈጸመዉ
ወንጀል ቅጣት ቢያንስስድስት ወር ቀላል እስራት የሚያስቀጣ መሆን እንዳለበት በኢትዮጵያ
እንደ ተጨማሪ መመዘኛ ይወሰዳል፡፡12

1.2. የወንጀለኝነት ማስረጃ (Criminal Record)

10
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 9
11
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 3፣ ገጽ 58.
12
ዝኒ ከማሁ
የወንጀለኝነት ማስረጃ በተጠርጣሪዉ ላይ የሚተላለፍ የጥፋተኝነት ወይም የቅጣት ዉሳኔ
ማስረጃን የሚመለከት ነዉ፡፡ አንድ ተጠርጣሪ ፍርድቤት ተከሶ ቀርቦ ራሱ ባመነዉ ወይም
ፍርድ ቤቱ በማስረጃ ባረጋገጠዉ መሰረት ጥፋተኛ ካለ በኋላ ቅጣት ያስተላልፋል፡፡ ጉዳዩን
ያየዉ ፍርድ ቤትም ሆነ ጉዳዩን ሲከታተለዉ የነበረዉ ዐቃቤ ህግ መዝግቦ ያስቀመጠዉን
የጥፋተኝነት ወይም የቅጣት ማስረጃ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለተቋማት ወይም ለግለሰቦች ይፋ
ያደርጋል፡፡ ነገር ግን አጥፊዎቹ ህጻናት ወይም ወጣቶች ከሆኑ መረጃዉ በጥብቅ ስነ-ስርዓት
ለጥናታዊ ጽሁፍ ካልሆነ በቀር ይፋ እንዳይሆን ይደረጋል፡፡13

1.3. የአጥፊዉ የቀድሞ የወንጀለኝነት ባህሪ (Criminal history)

የአጥፊዉ የቀድሞ ባህሪ የወንጀለኝነት ማስረጃን (Criminal Record) የሚያካትት ሲሆን


በተጨማሪም ተጠርጣሪዉ ጥፋተኛ መባል እና አለመባሉ ግምት ዉስጥ ሳይገባበየደረጃዉ ባሉ
የፍትህ ተቋማት የተከናወኑ ዝርዝር ሂደቶችን የሚያጠቃልል ነዉ፡፡ ከነዚህም መካከል ከአሁን
በፊት በፍርድ ቤት ቀጠሮ መሰረት ያልቀረበ ከነበረ፣ ጥፋተኛ የሚያስብል ማስረጃ ባለመኖሩ
ከክሱ በነጻ ከተሰናበተ፣ ፍርድ ቤቱ ያልቋጨዉ በእንጥልጥል ላይ ያለ ጉዳይ ካለ፣ የተጠየቀ
የዋስትና ጉዳይ ከነበረ ስለዚሁ ጉዳይ ዝርዝር ሁኔታ እና የመሳሰሉትን ሁሉ የሚያካትት
የማስረጃ አያያዝ ስርዓት ነዉ፡፡14

ከዚህ በተጨማሪም ፖሊስ ጣቢያ በወንጀል ተጠርጥሮ የቀረበ እና የተያዘ ሰዉን በሚመለከት
የሚሰጠዉ እና ተመዝግቦ የሚቀመጥ ማስረጃ ሲሆን ተጠርጣሪን ቃል መቀበል፣ እስራት ፣
የሚሰጡ ማስጠንቀቂያዎች፣ ክሶች፣ የተጠርጣሪዎች ፎቶ ፣ የጣት አሻራ እና በመረጃ ባለሙያ
የሚሰበሰቡ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ተመዝግበዉየሚቀመጡበት ስርዓት ነዉ፡፡ እነዚህ
መረጃዎች ሁልጊዜ ትክክለኛ ላይሆኑ ይችላሉ ነገር ግን ለፖሊስ ስራ እስካስፈለጉ ድረስ
ተጠብቀዉ ይቆያሉ፡፡ እነዚህ መረጃዎች ሊወገዱ ወይም ሊሰረዙ የሚችሉት ክሱ ከተሰረዘ
ወይም ከተተወ፣ ተጠርጣሪዉ በነጻ ከተለቀቀ ወይም በይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት
ዉሳኔዉ ከተሻረ፣ መረጃዉ ለረጅም አመት የቆየ እና በጥቃቅን ወንጀሎች የተላለፈ የጥፋተኝነት
ዉሳኔ ከሆነ ነዉ፡፡

እዚሁ ላይ የሚነሳዉ ሌላዉ ጉዳይ ቅጣትን በሚያስፈጽሙ ተቋማት ስለ ታራሚዎች


የሚይዙት መረጃ ነዉ፡፡ ቅጣት ተላልፎባቸዉ ማረሚያ ቤት ከገቡበት እለት ጀምሮ ቅጣታቸዉን

13
Freehills Sydney, Convictions and Criminal Records, October 2004, pp 1-10.
14
ዝኒ ከማሁ
አጠናቀዉ እስከሚወጡ ድረስ ያለዉን የባህሪ መሻሻል፣ የተሰጣቸዉን ይቅርታ እና የፈተና ጊዜ
በአግባቡ ስለመወጣታቸዉ እና መሰልስራዎችንበበቂ ሁኔታ መረጃ መያዝን ሁሉ የሚያጠቃልል
ነዉ፡፡
1.4. የደጋጋሚነትእና የቀድሞ ወንጀለኝነት የመረጃ ምንጮች /Data source/

ደጋጋሚነትን ለመለካት የምንጠቀምባቸዉን የቀድሞ የጥፋተኛዉን መረጃዎች ከፖሊስ፣


ከፍርድ ቤት ወይም ከማረሚያ ቤቶች ልናገኝ እንችላለን፡፡ ሶስቱም ተቋማት በተለያየ ደረጃ
ያለን የአንድ ግለሰብ የቀድሞ የተበጣጠሰ መረጃ ያሳዩን ይሆናል እንጅ ራሳቸዉን ችለዉ ሙሉ
መረጃ ሊሰጡን አይችሉም፡፡ የወንጀል ፍትህ አስተዳደሩ ስራ በቅብብሎሽ የሚከናወን በመሆኑ
መረጃዉ የሚኖራቸዉ በሚያከናዉኑት ስራ ልክ ነዉ፡፡ስለሆነም የቀድሞ የጥፋተኛዉን
መረጃዎች የምናገኝበት ሀገር አቀፍ ማዕከል ቢኖር የዘርፉ ስራ ይሳለጣል፡፡15

የአሜሪካዉ የስለላ ድርጅት (Federal Bureau of Investigation /FBI/) የሀምሳ ክፍለ ሀገራት
(States) የታሰሩ፣ የተከሰሱ፣ጥፋተኛ የተባሉ፣ በምርመራ እና ፍርድ ሂደት ዉስጥ ያሉ
በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳያቸዉ የተቋረጡ ወይም ቅጣታቸዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የጨረሱ
ግለሰቦችን ሙሉ የወንጀል ታሪክ በጣት አሻራ መለያ ቁጥር መሰረት መዝግቦ ይይዛል፡፡16 የዚህ
ዓይነት አሰራር ከስልሳ ዓመት በፊት የተጀመረ ሲሆን በጊዜ ሂደትም እየሰፋ እና እያደገ
መጥቷል፡፡ሌሎች ሀገራትም የመረጃ ትንተና እና ምዘና ማዕከላትን በየአስተዳደራዊ ክልሎች
ያቋቋሙሲሆን እነዚህ ማዕከላት ያለቀለት ማስረጃ ወደ አንድ የሀገሪቱ የመረጃ ማዕከል
ይልካሉ፡፡እንዲህ ዓይነት የመረጃ ማዕከላት መቋቋሙ ይበል የሚያሰኝ ተቋማዊ አደረጃጀት
ቢሆንም ጠንካራ የመረጃ ልዉዉጥ ስርዓት ከሌለ በመሀል ሳንደርስባቸዉ የሚያመልጡ
የወንጀለኛ መረጃዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ልብ ሊባል ይገባል፡፡

የሰዉ ልጅ እንቅስቃሴ በፍጥነት እየጨመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የወንጀለኞች የቀድሞ ባህሪ


መረጃ ልዉዉጥ በሀገር ዉሰጥ ብቻ ሳይወሰን የሌሎች ሀገራትን እገዛ እና ትብብርም
የሚጠይቅ ነዉ፡፡ ነገር ግን ሀገራት የተለያየ የደጋጋሚነት መለኪያ ከመጠቀማቸዉ አንጻር
ማስረጃዉን ለማጠናቀር የተጠቀሙበት መለኪያ፣ ማስረጃዉን ለማግኘት ያለዉ አስቸጋሪነት፣
አብሮ ለመስራት የሚኖረዉ ቅንነት፣ ሌላ አካል የሰበሰባቸዉ ማስረጃዎች ተዓማኒነት እና
የመሳሰሉት ምክንያቶች ተደማምረዉ ሀገራዊ መረጃዎችን ብቻ እንድንጠቀም እንገደዳለን፡፡17

15
. Measuring Recidivism at the Local Level: A Quick Guide, Available at
https://www.urban.org/sites/default/files/recidivism-measures_final-for-website.pdfp. 1.
16
. የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 6፣ ገጽ 4.
17
.የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 3፣ ገጽ 61.
በየደረጃዉ ያሉ የፍትህ ወይም የህግ ተቋማት ከየትኛዉም የመንግስት ተቋማት በበለጠ የመረጃ
አያያዝ ስርዓታቸዉ የተደራጀ እና ዘመናዊ ሊሆን ይገባል፡፡ ስራዉ አንድ ቦታ ተጀምሮ እዛዉ
የማያልቅ እና የቅብብሎሽ ስራ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መረጃዉ ሶስተኛ ወገን በሚፈልገዉ
መልኩ የተደራጀ መሆን አለበት፡፡

1.5. የደጋጋሚነት እና የቀድሞ ወንጀለኝነት ሪከርድ ተጨማሪ ህጋዊ ዉጤቶች

በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ስርዓት ማዕቀፍ ዉስጥ ፍርድቤቶች ጥፋተኛዉ ላይ ቅጣት


ከመጣላቸዉ በፊት የተጠርጣሪዉን የቀድሞ የወንጀለኝነት ባህሪን ግምት ዉስጥ በማስገባት
ቅጣቱን እንደ ቅጣት ማክበጀዉ አይነት አክብደዉ ይወስናሉ፡፡18

ፍርድቤቶች የሚያስተላልፉት ነጻነትን የሚያሳጣ ቅጣት እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ ግለሰብ


የቀድሞ ግለሰባዊ ታሪኩ መልካም ካልነበረ በተለይም በወንጀል ተግባር የተሳተፈ እና ጥፋተኛ
የተባለ እንድሁም ቅጣት ተላልፎበት የነበረ ከሆነ በስራ ቅጥር፣ በንግድ ስራዉ እና መሰል
እንቅስቃሴዎቹ ላይ በሚመለከተዉ አካል እገዳ ይጣልበታል፡፡

ስለሆነም የግልም ሆኑ የመንግስት ተቋማት በወንጀል ተሳትፈዉ ጥፋተኛ የተባሉ አዳዲስ


ሰራተኞችን የማይቀበሉ ሲሆን በስራ ላይ ያሉ ሰራተኞችንም ቢሆን ከደረጃ እድገት
ያግዳሉ፤ከስራም ያባርራሉ፡፡ካሁን በፊት በማጭበርበር፣ እምነት በማጉደል፣ በማታለል እና
በመሳሰሉት ወንጀሎች ተከሶ ጥፋተኛ የተባለ ግለሰብ በሌሎች የተለየ መታመንን በሚጠይቁ
የንግድ እና የሙያ ስራዎች ላይ ፈቃድ ማዉጣትም ሆነ በስራዎቹ ላይ ተሰማርቶ
መስራትአይችልም፡፡19ቅጣቱን እየፈጸመ ያለ ታራሚየዲሞክራሲያዊ መብት መገለጫ ከሆኑት
መካከል የመምረጥ እና የመመረጥ መብቶቹ ሊታገድ ይችላል፡፡

ይህ ማለት ግንአንድ ጊዜ ጥፋት የፈጸመ ሰዉ እድሜ ልኩን የቀድሞ ጥፋቱ እየተመዘዘ ከላይ
የተዘረዘሩ መብቶቹን እንዳይጎናጸፍ እንቅፋት ይሆንበታል ማለት አይደለም፡፡ የቀድሞ
የጥፋተኝነት ሪከርድ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ከወንጀለኝነት መዝገብ ይሰረዛል፡፡ ነገር ግን
የማይሰረዙ እና የወንጀለኝነት ባህሪ (Criminal history)አካል ሆነዉ የሚቆዩ የወንጀል
ማስረጃዎችምአሉ፡፡ተመዝግቦ የቆየ የቀድሞ የጥፋተኝነት ሪከርድ ጉዳዩ በሚመለከታቸዉ

18
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 3፣ ገጽ 54.
19
ዝኒ ከማሁ
የመንግስት ተቋማት ካልሆነ በስተቀር የትኛዉም ግለሰብ መረጃዉን ሊያገኘዉ እና ሊጠቀምበት
አይችልም፡፡
2. የወንጀል ደጋጋሚነት እና የአጥፊዉ የቀድሞ የወንጀለኝነት ማስረጃ በኢትዮጵያ
የወንጀል ህግጋት
2.1. የወንጀልደጋጋሚነት

በኢፌድሪ የወንጀል ህግ ከልዩ የቅጣት ማክበጃዎች መካከል አንዱ ደጋጋሚ ወንጀለኝነትነዉ፡፡


በህጉ በተመለከተዉ መሰረት አንድ ወንጀል አድራጊ በተደጋጋሚ ወንጀል አድርጓል ተብሎ
ቅጣት የሚከብድበት በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 67 መሰረት የማይነጣጠሉ የደጋጋሚነት
መለኪያዎች ሲሟሉ አነደሆነ ከዚሁ ድንጋጌ መረዳት ይቻላል፡፡ ስለሆነም በኢትዮጵያ የወንጀል
ፍትህ ስርዓት ደጋጋሚነት ማለት "የተወሰነበትን የእስራት ቅጣት በሙሉ ወይም በከፊል
ከፈጸመበት ወይም ይህ ቅጣት በይቅርታ ከቀረበት ቀን ጀምሮ በአምስት አመት ጊዜ ዉስጥ
መነሻ ቅጣቱ ስድስት ወር የሆነ ቀላልእስራት ማስቀጣት የሚችል አዲስ ወንጀል አስቦ ያደረገ
እንደሆነ ነዉ"20፡፡ይህን ድንጋጌ ስንመለከት ከተራ ትርጉምነት ባለፈ ዝርዝር የደጋጋሚነትን
መለኪያዎች በግልጽ ያካተተ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ስለሆነም አንድን ድርጊት የተደጋገመ የወንጀል
ድርጊት ስለመሆኑ ወይም የወንጀል ድርጊት ፈጻሚዉን ግለሰብ ደጋጋሚ ወንጀለኛ ነዉ ለማለት
የሚከተሉት መለኪያዎች ሳይነጣጠሉ መሟላት እንዳለባቸዉ በግልጽ ያመለክታል፡፡

2.1.1. የቀድሞዉቅጣት ነጻነትን የሚያሳጣ የእስራት ቅጣት መሆን አለበት፡-

ካሁን በፊት ነጻነትን ከሚያሳጡ ቅጣቶች ዉጪ በገንዘብ መቀጮ፣ በግደታስራ፣ በተግሳጽ፣


በማስጠንቀቂያ እና በወቀሳ የተቀጣ አጥፊ ቅጣቱን በከፊል ወይም በሙሉ ካጠናቀቀ ጀምሮ
በአምስት አመትጊዜ ዉስጥ መነሻዉ ስድስት ወር ቀላል እስራት የሚያስቀጣ አዲስ ወንጀል
አስቦ ቢፈጽምም እንኳን በደጋጋሚነት ሊቀጣ አይችልም፡፡ ይህም በቀጥታ ከስዊዝ የወንጀል ህግ
የተወሰደ ነዉ፡፡21

እዚህ ላይ በትኩረት መታየት ያለበት ህጋዊ ሰዉነት ያላቸዉድርጅቶች የወንጀል ተካፋይ በሆኑ
ጊዜ የወንጀል አድራጊዉ ተፈጥሯዊ ባህሪ ማረሚያ ቤት አስገብተን ነጻነትን የሚያሳጣ የእስራት
ቅጣት ልንቀጣቸዉ የምንችል ባለመሆኑ በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 90(3) እና (4)
መሰረት የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣል ይታወቃል፡፡ ስለሆነም የህግ ሰዉነት የተሰጠዉ ድርጅት
በወንጀል ደጋጋሚነት የማይጠየቅ አጥፊ የሚያደርገዉ ሲሆን በሌላ በኩል በኢፌድሪ የወንጀል
ህግ ቁ.34(2) መሰረት አጥፊዉ ከስህተቱ የማይማር ከሆነ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ድርጅቱ

20
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 1
21
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የተሻሻለዉ የወንጀል ህግ ሀተታ ዘምክንያት፣ 1997፣ አንቀጽ 67.
እንዲታገድ ፣እንዲዘጋ እንዲሁም እንዲፈርስ ፍርድ ቤቶች ተጨማሪ ቅጣት መቅጣት
ስለሚችሉ ደጋጋሚነት ላይ የታየዉ ክፍተት በዚኽኛዉ በወንጀል ህግ አንቀጽ 34(2) መሰረት
ይሞላል የሚል መከራከሪያ የሚያቀርቡ አሉ፡፡ ነገር ግን በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 34(2)
መሰረት የሚጣለዉ ቅጣት ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጸመዉን ወንጀል መሰረት በማድረግ
የወንጀሉን አፈጻጸም፣ የወንጀሉን ክብደት፣የፈጻሚዉን አደገኝነት መሰረት ተደርጎ ስለሚተላለፍ
ተጨማሪ ቅጣት እንጅ የቀድሞ የወንጀል ጥፋትን ታሳቢ የሚያደርግ አለመሆኑ ልብ ሊባል
ይገባል፡፡

ሌላዉ የቀድሞ ጥፋታቸዉ ከደንብ መተላለፍ ዉጪ የሆነና በገንዘብ ብቻ የሚያስቀጣ የወንጀል


ድርጊት ቢሆንና ይህንኑ ቅጣት በከፊል ወይም በሙሉ ከፈጸሙ በኋላ በአምስት አመት ጊዜ
ዉስጥ ሌላ ከስድስት ወር በማያንስ ቀላል እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ፈጽመዉ ጥፋተኛ
የተባሉ የተፈጥሮ ሰዎች ደጋጋሚ ሊባሉ አይችሉም፡፡

ስለሆነም አጥፊዉ ከአሁን በፊት የተቀጣዉ ለደጋጋሚነት አንድ መስፈርት ሆኖ የሚቀርበዉ


ቅጣት ነጻነትን የሚያሳጣ የእስራት ቅጣት መሆኑ የግድ ነዉ፡፡

2.1.2. የቀድሞ የእስራት ቅጣቱን በሙሉ ወይም በከፊል የፈፀመ ወይም በይቅርታ የወጣ
፡-

አጥፊዉ በፍርድ ቤት የተጣለበትን የእስራት ቅጣት ያጠናቀቀ ወይም በይቅርታ የወጣ ከሆነ
ብዙ የሚያከራክር ጉዳይ ላይኖር ይችላል፡፡ነገር ግን ህጉ እስራቱን በከፊል የፈጸመ ሲል ምን
ለማለት ፈልጎ ነዉ? የሚለዉንመፈተሸ ተገቢነት ያለዉ ይመስላል፡፡

እስራቱን በከፊል የፈጸመ ሲል በፍጥነት ወደ አዕምሯችን የሚመጣዉ በአመክሮ ከማረሚያ


ቤት የወጣን ጥፋተኛ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ፍርድ ቤት ከጣለበት ቅጣት ከፊሉንእስራት
የፈጸመ ነገር ግን ከማረሚያ ቤት ያልወጣ ታሳሪ አስቦ መነሻዉ ስድስት ወር ቀላል እስራት
የሚያስቀጣሌላ አዲስ ወንጀል ቢፈጽም ደጋጋሚ ወንጀለኛ ይባላልን?22

22
ተከሳሽ ሀብታሙ አረጋ ካሁን በፊት በሌላ ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ ቅጣቱን በደሴ ማረሚያ ቤት እየፈጸመ እያለ
የማይገባዉን ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ የኢፌድሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ692(1)ን በመተላለፍ ጥር 9 ቀን 2009
ዓ.ም ከቀኑ በግምት 8፡30 ሲሆን በዚሁ ማረሚያ ቤት የግል ተበዳይ አበባዉ መሀመድን የሽመና ስራ ዉጤት
ለሚስቴ ልኬ ላሽጥልህ በማለት 28 ጋቢ የአንዱ ዋጋ 450 ብር በአጠቃላይ 12600 (አስራ ሁለት ሺህ ስድስት
መቶ)ብር የሚያወጣ ጋቢ ወስዶ ገንዘቡን ያልመለሰ በመሆኑ በማታለል ወንጀል ተከሷል፡፡ ምንም እንኳን
የኢፌድሪ ወንጀል ህግ ቁ.692(1) በቀላል እስራት ወይም ነገሩ ከባድ በሆነ ጊዜ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ
የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 67 ደጋጋሚነትን በሚመለከት ስላለዉ ጥፋተኝነት ሲደነግግ
"የተወሰነበትን የእስራት ቅጣት በሙሉ ወይም በከፊል ከፈጸመበት ወይም ይህ ቅጣት
በይቅርታ ከቀረበት ቀን ጀምሮ በአምስት አመት ጊዜ ዉስጥ መነሻ ቅጣቱ…"
በማለትለማስቀመጥ የሞከረ ሲሆን የእንግሊዝኛ ቅጁም ቢሆን

The courtshall aggravate the penality on the ground of recidivism


when a fresh intentional crime the minimum penality of which is six
month of simple imprisonment has been committed with in five
years of serving a sentence of imprisonment in whole or in part or
having been remitted by pardonበሚልተጽፎእናገኘዋለን፡፡

አንድ አጥፊ በፈጸመዉ ወንጀል ምክንያት የተጣለበትን ቅጣት በከፊል ወይም በሙሉ አጠናቆ
ሲወጣ ጥፋቱን ያስተላለፈዉ ፍርድቤትም ሆነ ቅጣቱን ተከታትሎ ያስፈጽም የነበረዉ ማረሚያ
ቤት አጥፊዉ ታርሟል ወይም ተስተካክሏል የሚል ግምት ይወስዳሉ፡፡ ይህ በፍርድ ቤት እና
በማረሚያ ቤት በኩል የሚወሰድግምትሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ አጥፊዉ ቅጣት ከተላለፈበት
ዕለት ጀምሮ በጥፋቱ ተጸጽቶ በተመሳሳይ የወንጀል ተግባር ዉስጥ ይሳተፋል ተብሎ
አይገመትም፡፡ ከዚህም ባሻገር በማረሚያ ቤት ጥብቅ ክትትል ስር ሆኖ ድርጊቱን መፈጸሙ
ሲታይ ለመታረም ያልተዘጋጀ እና ለማህበረሰቡ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ስለሆነም
እንዲህ ዓይነት አጥፊዎች ከቀድሞ ቅጣታቸዉ መማር ያልቻሉ ሆነዉ ሳሉ ከደጋጋሚ
ወንጀለኛነት ማዕቀፍ ዉጪ መሆናቸዉ አሳማኝ አይመስልም፡፡

ሌላዉ ጉዳይ ተከሳሽ አስራ ሁለት ዓመት እና በላይ የሚያስቀጣ ወንጀል በመፈጸሙ የተነሳ
በሌለበት ቅጣት ተላልፎ እያለ ይሄዉ ተከሳሽ ታስቦ የተፈጸመ መነሻ ቅጣቱ ስድስት ወር ቀላል
እስራት የሚያስቀጣ አዲስ ወንጀል ፈጽሞ ቢገኝ በቀደመዉ ወንጀል ቅጣት የተላለፈ
በመሆኑተደራራቢ ወንጀል አይደለም፡፡በሌላ በኩል በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 67 መሰረት
የደጋጋሚነት መስፈርትንም አያሟላም፡፡ ስለሆነም ቅጣቱ በይርጋ እስካልታገደ ድረስ እንደ
ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ በመዉሰድ አንድ እርከን ብቻ ቅጣቱን ማክበድ ለህግ የበላይነት ተገዥ
ባለመሆን ራሱን ደብቆ ለቆየ ወንጀለኛ ተገቢ የቅጣት አሰላል አይሆንም፡፡

ቀላል እስራት የሚያስቀጣ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አዲስ የተፈጸመዉ ወንጀል ከስድስት ወር በማያንስ ቀላል
እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ቢሆን ደጋጋሚ ወንጀለኛ ይባላል ወይ?
2.1.3. የቀድሞ የእስራት ቅጣቱን በሙሉ ወይም በከፊል ከፈፀመ ወይም በይቅርታ ከወጣ
በኋላ በአምስት ዓመት ጊዜ ዉስጥ ሌላ አዲስ ወንጀል የፈጸመ መሆን

ይህ የአምስት ዓመት ጊዜ መቆጠር የሚጀምረዉ የእስራት ቅጣቱን በሙሉ ወይም በከፊል


ከፈፀመ ወይም በይቅርታ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ አዲስ ወንጀል እስከፈጸመባት ዕለት ያለዉን ጊዜ
እንደሆነ የወንጀል ህጋችን በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ ይህም ማለት ማረሚያ ቤቱ ካሁን በፊት
አጥፊዉ በፈጸመዉ ወንጀል ታርሟል እንድሁም መልካም ዜጋ ሆኗል ብሎ አስቦ ከማረሚያ
ቤት ከለቀቀዉ ዕለት ጀምሮ የሚታሰብ መሆኑን በግልጽ የሚያመላክት ነዉ፡፡

ነገር ግን የቀድሞዉን ጉዳይየተመለከተዉ ፍርድ ቤት ቅጣት ካስተላለፈበት ዕለት ጀምሮ አዲስ


ወንጀል እስከፈጸመበት ጊዜ ድረስ የሚሰላዉ የአምስት ዓመት ጊዜ ለደጋጋሚ ወንጀለኝነት
ፍጹምስህተት ነዉ፡፡ ለደጋጋሚ ወንጀለኝነት የአምስት ዓመት የክትትል ጊዜን ስሌት ለማወቅ
ማረሚያ ቤት የሚሰጠን ማስረጃ በህጉ መሰረት አግባብነት ያለዉ ማስረጃ ነዉ፡፡ በደጋጋሚ
ወንጀለኝነት መለኪያ ዉስጥ ይህ የአምስት አመት ጊዜ ከፍተኛዉ እና ረጅሙ ነዉ፡፡ የጊዜዉ
መርዘም አጥፊዎችለረጅም ጊዜ ራሳቸዉን ከወንጀል ድርጊት እንዲታቀቡ የሚያግዝ ቢሆንም
በተለያየ ምክንያት ተገፍተዉ ወደ ወንጀል የሚገቡ ሰዎች በዚህ መለኪያ ዉስጥ ለመግባት ሰፊ
እድል ስለሚኖር የደጋጋሚ ወንጀለኞች ቁጥር መጨመሩ አይቀሬ ነዉ፡፡

2.1.4. አዲስ የተፈጸመዉ ወንጀል ከስድስት ወር በማያንስ ቀላል እስራት የሚያስቀጣ


መሆኑ፡-

ስለሆነም አዲስ የተፈጸመዉ ወንጀል ነጻነትን የሚያሳጣ ቅጣት የሚያስቀጣ ድርጊት መሆን
ያለበት ሲሆን በተጨማሪም ቅጣቱ ከስድስት ወር ያላነሰ ቀላል እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል
መሆኑን ከህጉ እንረዳለን፡፡ ይህ ሲባል የስድስት ወሩ ቅጣት የሚሰላዉ ፍርድ ቤቱ በወንጀሉ
ላይ የሚይዘዉንመነሻ ቅጣት ነዉ ወይስ በህጉ ልዩ ክፍል ለወንጀሉ የተደነገገዉን መነሻ ቅጣት
የሚለዉን በአግባቡ ማየት ተገቢ ሲሆን በዚህ ረገድ ሁለቱንም ሀሳቦች የሚደግፉ ባለሙያዎች
እና ጽሁፎች አሉ፡፡

የመጀመሪያዉ መከራከሪያ ይህ ስድስት ወር መሰላት ያለበት በህጉ ልዩ ክፍል የተቀመጠዉን


የስድስት ወር መነሻ ቅጣት ሳይሆን ጉዳዩን የያዘዉ ፍርድ ቤት የሚይዘዉን መነሻ ቅጣት
ታሳቢ ያደረገ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ብዙ ወንጀሎች እስከ አምስት አመት የሚደርስ ቀላል እስራት
ቢያስቀጡም መነሻ ቅጣታቸዉ አስር ቀን ወይም ሶስት ወር ከሆነ እነዚህን ወንጀሎች የፈጸሙ
ሰዎች በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 67 መሰረት ደጋጋሚ ወይም ልማደኛ ደጋጋሚ
ተብለዉ ሳይቀጡ ሊቀሩ ስለሚችሉ የህግ አዉጪዉን ሀሳብ ለማግኘት በቅጣት አወሳሰን ላይ
ሊያመጣ የሚችለዉ ልዩነት መታየት እንዳለበት ጠቋሚ ናቸዉ፡፡23

በሌላ በኩል ደግሞ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግም ሆነ በተሻሻለዉ የወንጀል ቅጣት
አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ዓ.ም መሰረት ዐቃቤ ህግ የቅጣት ማክበጃ የሚያቀርበዉ
ፍርድ ቤቱ መነሻ ቅጣት ከወሰነ በኋላ ቢሆንም መነሻ ቅጣቱ ግን ለተከራካሪ ወገኖች ግልጽ
እንዲሆን የሚፈቅድ ስነ-ስርዓት የለም፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ለወንጀሉ የሚያስቀምጠዉ መነሻ
ቅጣት መሰረት መደረግ አለበት ካልን ጥፋተኛዉ ደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ እና
በዚሁ መሰረት ቅጣቱ ከብዶ እንዲወሰን ለማሳሰብ ፍርድ ቤቱ የያዘዉን መነሻ ቅጣት መጠየቅ
እና ማወቅ ግደታ ሊሆን ነዉማለት ነዉ፡፡

በ1996 ዓ.ም የወጣዉ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 67 መሰረት አዲስ ለተፈጸመዉ ወንጀል
የተቀመጠዉ የስድስት ወር ቀላል እስራት መነሻ ቅጣት ግልጽነት የሚጎለዉ ቢሆንም ከመነሻዉ
ህጉ ሲቀረጽ የጠቅላላ የወንጀል ህጋችንን መነሻ ቅጣቶች ታሳቢ ሳያደርግ የተቀመጠ መስፈርት
በመሆኑ የተነሳ የመጣ ችግር ነዉ፡፡ በህጉ ልዩ ክፍል ከተደነገገዉ መነሻ ቅጣት ይልቅ ፍርድ
ቤቱ በወንጀለኛዉላይ የሚፈርደዉን መነሻ ቅጣት ታሳቢ ያደረገ መስፈርት ነዉ ብሎ
መተርጎሙ ደጋጋሚ ወንጀለኛነት ተገማች መለኪያ እንዳይኖረዉ የሚያደርግም ጭምር ነዉ፡፡
የሌሎች ሀገራት ልምድም የሚያሳየዉ አዲስ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እንደ ኢትዮጵያ የቅጣት
መጠን መለኪያ ያላቸዉ አለመሆናቸዉን ነዉ፡፡

2.1.5. አዲስ የተፈጸመዉ ወንጀል ታስቦ የተፈጸመ መሆን ፡-

ስለሆነም በቸልተኝነት የተፈጸመዉ ወንጀል ከሆነ ለቀድሞ ወንጀል ሪከርድ ካልሆነ በቀር
ለደጋጋሚነት መስፈርት ሊሆን አይችልም ማለት ነዉ፡፡

2.2. ልማደኛ ደጋጋሚ (Persistent Recidivist)

ደጋጋሚ ወንጀለኛ ማለት በ1997 ዓ.ም ተሻሽሎ በወጣዉ የወንጀል ህግ አንቀጽ 67 ስር


የተገለጸዉ እንደሆነ ከላይ በዝርዝር ያየነዉ ሲሆን አንድን ደጋጋሚ ወንጀለኛ ልማደኛ
የሚያስብለዉ ምንድን ነዉ? አንድ አጥፊ ልማደኛ ደጋጋሚ ነዉ ለመባል የደጋጋሚ
ወንጀለኛነትን መስፈርት ማሟላቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪ በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት
23
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 21
የተሳተፈ መሆን ይጠበቃል፡፡ ይህም ማለት አጥፊዉ ከአሁን በፊት በማታለል ወንጀል ጥፋተኛ
ተብሎ ተቀጥቶ ከነበረ በተመሳሳይ የማታለል ወንጀል ጥፋተኛ መባልን የሚጠይቅ ነዉ፡፡
ስለሆነም አጥፊዉ አንድ አይነት ወንጀልን ደጋግሞ የመፈጸም ልምድ ያለዉ መሆን እንዳለበት
የሚያሳየን ነዉ፡፡ ነገር ግን አንድን አይነት ተመሳሳይ ወንጀል ለምን ያህል ጊዜ ደጋግሞ
የፈጸመ ነዉ ልማደኛ ደጋጋሚ የሚባለዉ የሚለዉ መልስ የለዉም፡፡ሆኖም ግን ልማደኛ
ደጋጋሚ ከደጋጋሚ ወንጀለኛ ተጨማሪ መለኪያ እና ክብደት ሊኖረዉ እንደሚገባ ህጉ
ካስቀመጠዉ የቅጣት መጠን መረዳት ይቻላል፡፡ስለሆነም ልማደኛ ደጋጋሚ ለመባል ተመሳሳይ
የሆኑ ወንጀሎችን ከሁለት ጊዜ በላይ ደጋግሞ መፈጸም አለበት፡፡የቅጣት አጣጣሉንም
በተመለከተ በ1997 ዓ.ም ተሻሽሎ በወጣዉ የወንጀል ህግ አንቀጽ 88(2) ስር በግልጽ
ተገንግጓል፡፡

2.3. ደጋጋሚነት በደንብ መተላለፍ ወንጀሎች

ከመደበኛ ወንጀሎች በመለስ በተደጋጋሚ የደንብ መተላላፍ ወንጀሎችን የሚፈጽሙ አጥፊዎች


ደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆናቸዉን ለማረጋጋጥ እንደ መለኪያ መወሰድ ያለበት በ1997 ዓም
ተሻሽሎ በወጣዉ የወንጀል ህግ አንቀጽ 67 ሳይሆን የዚሁ ህግ አንቀጽ 769 (1) ነዉ፡፡ የደንብ
መተላለፍወንጀሎችን ተላልፎ ደጋጋሚ ወንጀለኛ ለማለት "የደንብ መተላለፍ ወንጀል
በመፈጸሙ የተፈረደበትን ቅጣት በሙሉ ወይም በከፊል ከፈጸመበት ወይም በይቅርታወይም
በይርጋ ቀሪ ከሆነበት ጊዜ አንስቶ በአንድ አመት ጊዜ ዉስጥ አዲስ የደንብ መተላለፍ ጥፋት
የፈጸመ" እንደሆነ ነዉ፡፡እዚህ ላይ መታየት ያለበት አዲሱም ሆነ የቀድሞዉ ወንጀል የደንብ
መተላለፍ ወንጀል መሆን አለባቸዉ፡፡ አጥፊዉ ቀድሞ የፈጸመዉ ወንጀል መደበኛ የወንጀል
ድንጋጌን ተላልፎ ቢሆን እና አሁን የተፈጸመዉ አዲስ ወንጀል የደንብ መተላለፍ ቢሆንስ?
እንድህ በሆነ ጊዜ ቅጣቱ በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 84 (1)(ሐ) መሰረት በጠቅላላ
የቅጣት ማክበጃነት የሚቀርብ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡

2.4. የቀድሞ የወንጀለኝነት ማስረጃ/የወንጀለኛ ሪከርድ

የቀድሞ የጥፋተኝነት ሪከርድ ማለት አጥፊዉ ከአሁን በፊት በፈጸማቸዉ የወንጀል


ድርጊቶችመሰረትጥፋተኛ የተባለ ወይም ጥፋተኛ ተብሎ ቅጣት የተጣለበት ስለመሆኑ
በሚመለከተዉ አካል ተመዝግቦ የተቀመጠ ማስረጃ ሲሆን የኢፌድሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 67ን
የማያሟላ መደበኛ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ነዉ፡፡
የቀድሞ የጥፋተኝነት ሪከርድ ከመደበኛ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡
የኢፌድሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 84(1)(ሐ) መሰረት ይህ የቅጣት ማክበጃ ለፍርድ ቤቱ
የሚቀርበዉ ማንኛዉም የቅጣት ማክበጃ በሚቀርብበት የህግ ስርዓት መሰረት ተከሳሹ በአዲሱ
ወንጀል ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ ነዉ፡፡

እንደ ደጋጋሚነት ካሁን በፊት የፈጸመዉ እና ጥፋተኛ የተባለበት ወንጀል ለምን ያህል ጊዜ
እንደ ጥፋተኝነት ሪከርድ ተመዝግቦ እንደሚቆይ በኢፊድሪ ወንጀል ህግ የተገለጸ ነገር የለም፡፡
የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 116-122 ያሉት ድንጋጌዎችም ቢሆኑ የክስ ማቅረቢያን ይርጋ
የሚመለከቱ እንጅ የቀድሞ የወንጀል ሪከርድ ሊቀርብ የሚችልበትን የጊዜ እርዝማኔ ሊወስኑ
የሚችሉ አይደሉም፡፡ የቀድሞ የወንጀል ሪከርድ ያለበት ግለሰብ በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ
233 መሰረት ፍርድቤት ቀርቦ እስካልተሰየመ ድረስ ወይም በቀድሞ ወንጀሉ ምህረት
እስካልተደረገለትድረስ ሪከርዱ እንደተመዘገበ ይቆያል፡፡ ስለሆነም በእኛ የወንጀል ፍትህ ስርዓት
አስተዳደር አንድ ግለሰብ በወጣትነቱ ጥፋተኛ ተብሎ የተቀጣዉ የወንጀል ሪከረድ ስሙ
እንዲታደስለት ካልጠየቀ በቀር በእርጅና ዘመኑም ለሚፈጽመዉ ወንጀል የቅጣት ማክበጃ ሆኖ
ይቀጥላል ማለት ነዉ፡፡

ሌላዉ መታየት ያለበት ጉዳይ የቀድሞ ወንጀለኛነት ማስረጃን እንደ ቅጣት ማክበጃ ምክንያት
ወስደን የምናከብድባቸዉ ልዩ የህግ ድንጋጌዎች አሉን እነዚህም የኢፌድሪ የወንጀል ህግ ቁጥር
525(2)(ሠ)፣539(2) እና መሰል ድንጋጌዎች ሲሆኑ የዚህ ጽሁፍ የትኩረት ነጥቦች
ባለመሆናቸዉ በዝርዝር አልተዳሰሱም፡፡

2.5. የደጋጋሚነት እና የቀድሞ ወንጀለኝነት ህጋዊ ዉጤቶች

በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 67 መሰረት ደጋጋሚ ነህ የተባለ አጥፊ በኢፌድሪ የወንጀል


ህግ አንቀጽ188 (1) መሰረት ለአዲሱ ወንጀል በህጉ ልዩ ክፍል ከተደነገገዉ ጣራ ቅጣት
በማለፍ መወሰን እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ፍርድቤቱ በህጉ ልዩ ክፍል ለአዲሱ ወንጀል ወይም
ድርጊቶቹ ተደራራቢ ሆነዉ በተገኙ ጊዜ ከአዳዲሶቹ ወንጀሎች ከባድ ለሆነዉ ወንጀል
የተደነገገዉን ጣራ ቅጣት እጥፍ እስኪሆን ቅጣቱን ሊያከብድ ይችላል፡፡ ይህም ማለት አንድ
ተከሳሽ ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ በኢፌድሪ የወንጀል አንቀጽ 67 መሰረት ደጋጋሚ ወንጀለኛ
መሆኑ እንደ ልዩ የቅጣት ማክበጃ የቀረበበት ከሆነ ፍርድ ቤቱ በቅጣት አወሳሰን መመሪያዉ
ሳይወሰን ቅጣቱን ማክበድ ይችላል ማለት ነዉ፡፡
አንድ ተከሳሽ ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ ደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆኑ ከተረጋገጠ ደጋጋሚ በመሆኑ
ብቻ የሚያጣቸዉ መብቶች ያሉ ሲሆን ከነዚህም መካከልደጋጋሚ ወንጀለኛ የሆነ ጥፋተኛ
ግለሰብ በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 191 እና 192 መሰረት ፍርድ ቤቱ የሚጥለዉ ቅጣት
በገደብ እንደማይታለፍ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 194(1)(ሀ) ያስቀምጣል፡፡ በተጨማሪም
ጥፋተኛ የተባለዉ ግለሰብ ልማደኛ ደጋጋሚ መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ ከሆነ ምንም እንኳን
ታራሚዉ መልካም ባህሪ ያለዉ እና ፍርድ ቤቱ ካስተላለፈዉ የእስራት ቅጣት ሁለት
ሶስተኛዉን ያጠናቀቀ ቢሆንም በአመክሮ አይፈታም፡፡

አጥፊዉ ልማደኛ ደጋጋሚ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ለአዲሱ ወንጀል በልዩ ህጉ ከተደነገገዉ ጣራ


ቅጣት እጥፍ በማለፍ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን ማሳደግ የሚችል ሲሆን የሚወሰነዉ ቅጣት ግን
ምንጊዜም ቢሆን ለቅጣቱ አይነት በህጉ ጠቅላላ ክፍል ከተደነገገዉ ጣራ ቅጣት መብለጥ
እንደሌለበት መረዳት ይቻላል፡፡

በኢፌድሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 84 መሰረት ጠቅላላ ቅጣት ማክበጃ የቀረበባቸዉ ጥፋተኞች


በኢፌድሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 183 እና የተሻሻለዉ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር
2/2006 አንቀጽ 21(1) መሰረት እንደ አንድ የቅጣት ማክበጃ ተወስዶ ቅጣቱ አንድ እርከን
እንድያድግ ይደረጋል፡፡

3. የወንጀል ደጋጋሚነት እና የቀድሞ የጥፋተኝነት/የቅጣት ሪከርድ ተግባራዊ አፈጻጸም


በአማራ ክልል

በአብክመ የፍትህ ተቋማት ዉስጥ ያሉ ባለሙያዎች በነዚህ ሁለት የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች
ዙሪያ ያላቸዉ ግንዛቤ ወጥ ካለመሆኑም ባሻገር በቂ ግንዛቤ የሌላቸዉ ባለሙያዎችም ቁጥር
ቀላል አለመሆኑን አመላካች ጉዳዮች አሉ፡፡ በመርማሪ ፖሊሶቻችን ካሁን በፊት ተመዝግቦ
የተቀመጠ እና የተደራጀ የወንጀለኞች ታሪክ ምዝገባ ስርዓት ባለመኖሩ በተመሳሳይ ወረዳ ካሁን
በፊት አጥፊዎች የተቀጡትን ቅጣት ማቅረብ እየተቻለ አይደለም፡፡ በዚህም ምክንያት መርማሪ
ፖሊስ ተከሳሽን ቃል ሲቀበል ካሁን በፊት ተከሳሹ ወንጀል ፈጽሞ ስለማወቅ እና አለማወቁ
በመጠየቅ የሚሰጠዉ ምላሽ የተከሳሹን የቀድሞ ታሪክ ማወቂያ ብቸኛዉ መንገድ እየሆነ
መጥቷል፡፡24ፖሊስ እያቀረበ ያለዉ ማስረጃ አካባቢዉ ያለዉን እና ጊዜዉ የፈቀደለትን ብቻ
ነዉ፡፡ ፖሊሱ በራሱ ጥረት የሚያዉቀዉ የጥፋተኞች የቀድሞ የወንጀል ሪከርድ ቢኖር እንኳን

24
ዋና ሳጅን ነፈጋ አድስ ፣ የፋርጣ ወረዳ የወንጀል ምርመራ ክፍል አስተባባሪ፣ጥር 16 2010 ዓ.ም የተደረገ ቃለ
መጠይቅ
የማስረጃ አያያዝ ስርዓታችን ደካማ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የማስረጃዉ ተአማኒነት እና
አግባብነት ሰፊ ክፍተት ያለበት ነዉ፡፡

ዐቃቤ ህግ ይዞ በሚከራከርባቸዉ የወንጀል መዛግብት ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞች ላይ የቅጣት


አስተያት እንዲሰጥ ሲጠየቅ የፖሊስ ምርመራ መዝገብ ላይ የተጠቀሰየቀድሞ የወንጀል ሪከርድ
ካለ ይህንኑ እንደወረደ የሚያቀርብ ሲሆን በምርመራ መዝገቡ ላይ ምንም የተመዘገበ የወንጀል
ሪከርድ ከሌለ የጥፋተኛዉን የቀድሞ የወንጀል ታሪክ ለማወቅ ጥረት ሲያደርግ አይታይም፡፡
አልፎ አልፎም የማስረጃ ዉስንነት እንደተጠበቀ ሆኖ መርማሪ ፖሊሱ በምርመራ መዝገቡ ላይ
መዝግቦ ያስቀመጠዉን የጥፋተኛዉን የቀድሞ የወንጀል ሪከርድ በቅጣት ማክበጀነት ፍርድ ቤት
የማያስመዘግቡ ዐቃቤያነ ህጎችም አሉ፡፡25 ሌላዉ እዚሁ ላይ የሚነሳዉ ትልቅ ጉዳይ
በጥፋተኛዉ ስም ተመዝግበዉ የቆዩ የቀድሞ የወንጀል ታሪኮችን በኢፌድሪ የወንጀል ህግ
አንቀጽ 67 እና 769 መሰረት ሳይፈተሹ እና የደጋጋሚነትን መስፈርት የሚያሟሉ ጉዳዮች
ሁሉ በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 84 (1)(ሐ) መሰረት እንደ ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ
እየተወሰዱ ቅጣቱ የሚከብድ መሆኑ ነዉ፡፡

ጉዳይ-1

ሰይድ መሀመድ የተባለ ተከሳሽ በዐቃቤ ህግ መዝገብ ቁጥር 761/2010 በደሴ ከተማ ወረዳ
ፍርድ ቤት የኢፌድሪ ወንጀል ህግአንቀጽ 669(3)(ለ)ን በመተላለፍ ጥር 23 ቀን 2003 ዓ.ም
ከቀኑ 5፡00 ሲሆን ከግል ተበዳይ ሰይድ አራጋዉ ቤት የበር ቁልፍ ሰብሮ በመግባት ግምቱ
34800(ሰላሳ አራት ሺህ ስምንት መቶ) ብር የሚያወጣ ንብረት ሰርቆ ሲሄድ በመያዙ ክስ
ተመስርቶበት ጥፋተኛ የተባለ ሲሆን ካሁን በፊት ይሄዉ ግለሰብ ኑሬ መሀመድ በሚል ስም
በዚሁ ፍርድ ቤት በፍ/ቤት መዝገብ ቁጥር 0212579 ሀምሌ 28 ቀን 2009 ዓ.ም በስርቆት
ወንጀል በስድስት ወር ቀላል እስራት ተቀጥቷል ዐቃቤ ህግም የቀድሞ ቅጣቱን እንደ ጠቅላላ
የቅጣት ሪከርድ በመዉሰድ እና ይሄንኑ ለፍርድ ቤቱ በማሳሰብ ቅጣቱ አንድ እርከን ከፍ ብሎ
ተወስኗል፡፡

ጉዳይ-2

ተከሳሽ ሀያቱ ምትኩ በዓቃቤ ህግ መዝገብ ቁ. 313/2010 የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ


494(1)ን በመተላለፍ ህዳር 3 ቀን 2010 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡00 ሲሆን የግል ተበዳይ ኑሪያ

25
. የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 24
ምትኩን መኖሪያ ቤት በማቃጠሉ፤ በዚሁ ጊዜ እና ቦታ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 560ን
ተላልፎ የግል ተበዳይ ጡሀ ምትኩን አንገት በማነቁ በፈጸመዉ የእጅ እልፊት
ወንጀልእንዲሁም በዚሁ ጊዜ እና ቦታ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 580ን ተላልፎ የግል
ተበዳይ ጡሀ ምትኩን እገልሀለሁ በማለት የዛተበት እና ያስፈራራዉ በመሆኑ በሶስት
ተደራራቢ ክሶች ጥፋተኛ ተብሏል፡፡ ይኽዉ ተከሳሽ ካሁን በፊት የስርቆት ወንጀል ፈጽሞ
በመዝገብ ቁጥር 02106009 በዚሁ ፍርድ ቤት በ8 ወር ቀላል እስራት ተቀጥቷል፡፡ ዐቃቤ
ህግም ሶስት ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ አቅርቦ የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽ በአንድ
አመት ከስምንት ወር ቀላል እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

ጉዳይ-3

ተከሳሽ ተስፋሁን አዳነ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 669(3)ን ተላልፎ ነሀሴ 14 ቀን 2009
ዓ.ም ከምሽቱ 3፡00 ሲሆን የግል ተበዳይ በላይነሽ ካሳንብር 4,600.00(አራት ሺህ ስድስት
መቶ) የሚያወጣ ንብረት በመዉሰዱ በዐቃቤ ህግ መዝገብ ቁ.126/2009 ክስ ተመስርቶበት
የጎንደር ወረዳ ፍርድቤትም ጥፋተኛ ብሎታል፡፡ ተከሳሽ ካሁን በፊት በዚሁ ፍርድቤት በስርቆት
ወንጀል ተከሶ ሰኔ 18 /2006 ዓም በዋለዉ ችሎት በ8 ወር ቀላል እስራት እና በሌላ ተመሳሳይ
ወንጀል ደግሞ ነሀሴ 06 /2006 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በሁለት ዓመት ከስምንት ወር ቀላል
እስራት ተቀጥቷል፡፡ ስለሆነም በከሳሽ ዐቃቤ ህግ በኩል ሁለት ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃዎች እና
በተከሳሽ በኩል አንድ የቅጣት ማቅለያ ቀርቦ በስድስት ዓመት እስራት እንዲቀጣ ተወሰኗል፡፡

ከላይ ያነሳናቸዉ ጉዳዮች በአብክመ የፍትህ ተቋማት ዉስጥ ያሉትን የአፈጻጸም ክፍተቶች
በትንሹም ቢሆን የምንመለከትበት ሲሆን ከክፍተቶቹም መካከል፡-

• በየደረጃዉ ያሉ የፍትህ ተቋማት ባለሙያዎች በወንጀል ደጋጋሚነት እና በቀድሞ


ወንጀለኝነት ማስረጃ መካከል ያለዉን ልዩነት በዉል አለመረዳት፣
• ደጋጋሚነትን እንደ ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት መዉሰድ፣
• ደጋጋሚነትን ለማስረዳት የምናቀርበዉን ማስረጃ ከየት መምጣት እንዳለበት
አለመለየት፣
• የማስረጃ አያያዝ ስርዓታችን ደካማ መሆን እና
• የቅጣት ዓላማን በሚያሳካ መልኩ ቅጣትን አለመጣል ጥቂቶቹ ናቸዉ፡፡
ደጋጋሚነትን አሟልተዋል ተብለዉ ለፍርድ ቤት እንደ ልዩ የቅጣት ማክበጃ የሚቀርቡ
ጉዳዮችም ቢሆኑ ካሁን በፊት ጥፋተኛዉ ስለመቀጣቱ የፍርድ ቤትን የመዝገብ ቁጥር
ከመግለጽ ዉጪ በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 67 መሰረት ቅጣቱን በሙሉ ወይም በከፊል
ከጨረሰ ወይም በይቅርታ ከወጣ በኋላ በአምስት ዓመት ጊዜ ዉስጥ አዲስ ወንጀል
ስለመፈጸሙ የሚያስረዱ አይደሉም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ታስቦ የተፈጸመዉ አዲስ ወንጀል
ቢያንስ ስድስት ወር የሚያስቀጣ መሆን እንዳለበት ከ1949ኙ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ በተለየ
ሁኔታ የ1996ቱ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ ላይ ተቀምጧል ፡፡

ታስቦ የተፈጸመዉ አዲስ ወንጀል የደንብ መተላለፍ ቢሆን እና አጥፊዉ ካሁን በፊት የደንብ
መተላለፍ ወንጀል ሪከርድ መኖሩ ቢረጋገጥ ወደ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 769 በመሄድ
በደንብ መተላለፍ ደጋጋሚ ወንጀለኝነት ቅጣቱ እንድከብድ ማሳሰብ ሲገባን በኢፌድሪ የወንጀል
ህግ አንቀጽ 67 መሰረት ለመለካት መሞከር ህጉ ከተቀረጸበት አላማ ዉጪ ስራ ላይ እንዲዉል
ማድረግይሆናል፡፡

ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ በሚያቀርቡት የቅጣት አስተያየት መሰረት የመጨረሻ ዉሳኔ በጉዳዩ ላይ


የሚያስተላልፍ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዐቃቤ ህግበጥፋተኛዉ ላይ ካሁን በፊት ፈጽሞት የነበረዉን
የወንጀል ሪከርድ በማቅረብ ቅጣቱ ከብዶ እንዲወሰንለት የሚያሳስባቸዉ መዝገቦች ትንሽ
የሚባሉ አይደሉም፡፡ከነዚህም ጉዳዮች ዉስጥ ጥፋተኛዉ የቀድሞዉን ቅጣት በሙሉ ወይም
በከፊል የጨረሰ መሆኑን፣በአምስት ዓመት ጊዜ ዉስጥ ሌላ አዲስ ወንጀል ስለመፈጸሙ፣ አዲሱ
ወንጀል ታስቦ ስለመፈጸሙ፣ አዲሱ ወንጀል ቢያንስ ስድስት ወር ቀላል አስራት የሚያስቀጣ
ስለመሆኑ ፍርድ ቤቱ እያወቀ ዐቃቤ ህግ በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 188 መሰረት ከብዶ
ይወሰንልኝ ባለማለቱ አንድ ደረጃ ብቻ በማሳደግ የሚወሰኑ የቅጣት ዉሳኔዎች ቀላል
አይደሉም፡፡

ሌላዉ ምክንያቶቹ የተለያዩ ቢሆኑም አሁን ያለዉ ማህበረሰብ በአንድ ቦታ ተወስኖ የሚኖር
አይደለም፡፡የህብረተሰቡ እንቅስቃሴ ከመቸዉም ጊዜ በላይ ፈጣንና የማያቋርጥ ሆኗል፡፡ ስለሆነም
ወንጀለኞች የማህበረሰቡ አካል እንደመሆናቸው መጠን የወንጀል መረጃ አያያዝ ስርዓታችን
ከህዝቡ እንቅስቃሴ ጋር እኩል የሚራመድ እና የዘመነ ሊሆን ግድ ነዉ፡፡ በወንጀል ፍትህ
አስተዳደር ስርዓቱ ዉስጥ በጣም ብዙ እና ዉስብስብ ችግሮች ያሉ ቢሆንም የመረጃ አያያዝ
ስርዓታችን ደካማ መሆን እና ሀገር አቀፍ የወንጀል መረጃ ማዕከል አለመኖሩ እያስከፈለን
ያለዉ ዋጋ ቀላል አይደለም፡፡
ደጋጋሚ እና ልማደኛ ደጋጋሚ ተብለዉ ለጥፋታቸዉ ከፍ ያለ ተመጣጣኝ ቅጣት ሊጣልባቸዉ
የሚገቡ አጥፊወች በመረጃ አያያዝ ስርዓታችን ድክመት ምክንያት ካሁን በፊት ያለባቸዉን
የወንጀል ሪከርድ ሳንደርስበት በመቅረታችን የተነሳ እንደመጀመሪያ አጥፊዎች የሚቀጡ
ደጋጋሚ ወንጀለኞች በቁጥር ትንሽ አይደሉም፡፡ አሁን አሁን በተለይም ስርቆት፣ ዘረፋ፣
ማታለል እና መሰል ወንጀሎች ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ ለሚፈጽሙ ግለሰቦች ከባድ ቅጣት
እንዳይቀጡ የመረጃ አያያዝ ስርዓታችን ትልቅ መደበቂያ ዋሻ ሆኗቸዋል፡፡
ማጠቃለያ

በዚህ ጥናት የደጋጋሚነትእና የቀድሞየጥፋተኝነት ሪከርድማስረጃ ጽንስ ሀሳብ፣አስፈላጊነት እና


ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ከመዳሰሳቸዉምበላይ በአማራ ክልላዊ መንግስት ስር በሚገኙ የፍትህ
ተቋማት ያለዉን ተግባራዊ አፈጻጸም ከኢፌድሪ የወንጀል ህግ እናተሻሽሎ ከወጣዉ የቅጣት
አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ዓ.ም አንጻር ተቃኝቷል፡፡

በዚህም መሰረት በህጉእና በአፈጻጸም ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮች ተለይተዋል፡፡ ስለሆነም


ለችግሮቹ መፍትሄ ናቸዉ የተባሉ ነጥቦች በጥናቱ ዉስጥ ለማካተት ተሞክሯል፡፡ የጥናቱ
አንኳር ነጥቦችም እንደሚከተለዉ በአጭሩ ቀርበዋል፡፡

§ ህግን የሚፈራ ሳይሆን ህግን የሚያከብር ማህበረሰብ መፍጠር ለፍትህ አስተዳደር


ስርዓቱ ያለዉ ፋይዳ ቀላል አይደለም፡፡ ስለሆነም የደጋጋሚነት የክትትል ጊዜን
እርዝማኔ ከሌሎች ሀገሮች ልምድ አንጻር ጣራዉን መጠቀማችን ማህበረሰቡ ላይ
የሚፈጠረዉን የወንጀል ስጋት መቀነሱእንደተጠበቀ ሆኖ ወደ ማረሚያ ቤት የሚገባዉን
ታራሚ ቁጥር ላይ ያለዉ ተጽኖ ቀላል ባለመሆኑ አስጨናቂ እና የማያፈናፍኑ ህጎች
ዘላቂ መፍትሄ ሊሆኑ አይገባም፡፡
§ በ1996 ዓ.ም የወጣዉ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 67 መሰረት አዲስ ለተፈጸመዉ
ወንጀል የተቀመጠዉ የስድስት ወር ቀላል እስራት መነሻ ቅጣት ግልጽነት የሚጎለዉ
ቢሆንም ከመነሻዉ ህጉ ሲቀረጽ የጠቅላላ የወንጀል ህጋችንን መነሻ ቅጣቶች ታሳቢ
ሳያደርግ የተቀመጠ መስፈርት በመሆኑ የተነሳ የመጣ ችግር ነዉ፡፡ በህጉ ልዩ ክፍል
ከተደነገገዉ መነሻ ቅጣት ይልቅ ፍርድ ቤቱ በወንጀሉ ላይ የሚይዘዉን መነሻ ቅጣት
ታሳቢ ያደረገ መስፈርት ነዉ ብሎ መተርጎሙ ደጋጋሚ ወንጀለኛነት ተገማች መለኪያ
እንዳይኖረዉ የሚያደርግ ነዉ፡፡ ስለሆነም የደጋጋሚነት ጽንስ ሀሳብን እና የጉዳዩን
ክብደት ታሳቢ ያደረገ አተረጓጎም አይደለም፡፡
§ ህጻናት እና ወጣት አጥፊዎች ወንጀል የሚፈጽሙት ሁኔታዎችን እንደ አዋቂ አጥፊ
አገናዝበዉ እና በነጻ ምርጫ ዉስጥ ሆነዉ ነዉ ተብሎ አይገመትም፡፡ ስለሆነም ለህጻናት
እና ወጣት አጥፊዎች የተለየ ትኩረት መደረጉን ከኢፌድሪ የወንጀል ህግ የተለያዩ
ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል፡፡ እንዲህ አይነት ልዩ ጥበቃ ከማድረጉ አንጻር የኢፌድሪ
የወንጀል ህግ እንደ ሌሎች ሀገራት ህጎች በተለይ ህጻናት አጥፊዎችን ከደጋጋሚ
ወንጀለኝነት የህግ ማዕቀፍ ዉጪ ሊያደርግ ይገባነበር፡፡
§ የመረጃ አያያዝ ስርዓታችን በጣም ደካማ ከመሆኑ የተነሳ አንድ ፍርድ ቤት ዉስጥ
በተደጋጋሚ ጥፋት እየፈጸመ ቅጣት የሚተላለፍበት አጥፊ በድጋሜ ይሄዉ ግለሰብ ሌላ
አዲስወንጀል ፈጽሞ ሲመጣ እና ጥፋተኛ ሲባል የቀድሞ ጥፋቶቹ እና ቅጣቶቹ አንድም
በደጋጋሚነት ካልሆነም በወንጀል ሪከርድነት ተከታትሎ የሚያቀርባቸዉ ባለመኖሩ
ደጋጋሚ አጥፊዎች እንደመጀመሪያ አጥፊ ሲቀጡ ይታያል፡፡ ይህ ደግሞ አጥፊዎች
በጥፋታቸዉ ተምረዉ ወደ መልካም ባህሪ እንዲመለሱ ከማድረግይልቅ ከህግ ጋር
ድብብቆሽ እየተጫወቱ በጥፋታቸዉ እንዲገፉበት ምክንያት ሆኗል፡፡
§ በአብክመ የፍትህተቋማት ያለዉ የወንጀል መረጃ አያያዝ ስርዓት ደካማ መሆኑ
እንደተጠበቀ ሆኖ የፍትህ ስራየቅብብሎሽ ስራበመሆኑ ለእነዚህ የፍትህ ተቋማት
የሚመጥን እና ጠንካራ የመረጃ ልዉዉጥ ስርዓት ያለበት የወንጀል የመረጃ ማዕከል
ሊኖር ይገባል፡፡
§ በኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 64 መሰረት አንድ አጥፊ የተጣለበትን ቅጣት
በማረሚያ ቤት ዉስጥ ሆኖ እየፈጸመ ባለ ጊዜ ሌላ መነሻ ቅጣቱ ስድስት ወር
የሚያስቀጣ አዲስ ወንጀል አስቦ ቢፈጽም በማረሚያ ቤት ጥብቅ ክትትል ዉስጥ
እያለድርጊቱን መፈጸሙ አጥፊዉ ለመታረም ዝግጁ አለመሆኑን እና አደገኝነቱን
የሚያሳይ በመሆኑ በደጋጋሚ ወንጀለኝነት ማዕቀፍ ዉስጥአለመካተቱ ተገቢ አይደለም፡፡
§ በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 67 ወይም 769 መሰረት ደጋጋሚ ወንጀለኝነትን
የሚያሟሉ ጉዳዮች የቅጣት አሰላል ሂደቱ አንድም በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 188
ካልሆነም ደግሞ 769(2) መሰረት በልዩ ሁኔታ ቅጣቱ መክበድ ሲገባዉ እንደ ተራ
የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ተወስዶ ቅጣቱን በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 84(1)(ሐ)
መሰረት ማክበድ በተደጋጋሚ የሚታይ የአፈጻጸም ስህተት ነዉ፡፡ ይህ ደግሞ በየደረጃዉ
ያለዉ የህግ ባለሙያ በደጋጋሚ ወንጀለኝነት እና በቀድሞ ወንጀለኝነት (የወንጀል
ሪከርድ) መካካል ያለዉን ልዩነት በአግባቡ ካለመረዳት የመጣ ነዉ፡፡
ተከሳሽ በሌለበት የወንጀል ክርክር ስለማድረግ፡ ህጉና አፈፃፀሙ በአማራ ክልል
ፍርድ ቤቶች

ታፈሰች ወልዴ*

አህፅሮተ ይዘት

በመሰረቱ ተከሳሽ በተከሰሰበት ጉዳይ ቀርቦ መከራከር ዋነኛው የወንጀል ስነ ስርአት ፅንሰ ሃሳብ
መሰረት ነው፡፡ ከዚህ ጽንሰ ሃሳብ መሰረት በሚለይ ሁኔታ ልዩ የወንጀል ስነ ስርአት ህጎች
ተግባራዊ የሚደረጉበት ሁኔታ በብዙ ሃገራት ህግ ውስጥ ተካቶ ይገኛል፡፡ በክርክር ወቅት
የተከሳሽ የመገኘት መብት ከፍታሃዊ የሙግት ስርአት ጋር በእጅጉ ተቆራኝቶ የሚታይ ሲሆን
ነገር ግን ይህ መብት ምሉእ(ABSOLUTE) አይደለም፡፡ ምክንያቱም ይህ መብት የማህበረሰቡን
ደህንነት ባሳካ መልኩ ተግባራዊ መሆን ስላለበት ጭምር ነው፡፡ እነዚህን ሁለት ፅንፎች
ሊያማክል በሚችል ልዩ ሁኔታ ተከሳሽ በሌለበት የወንጀል ክርክሮች ማካሄድም በሃገራችን
የወንጀል ስነ-ስርአት ህግ ውስጥ የተካተተ ነው፡፡ የፅሁፉ አላማም ተከሳሽ በሌለበት የሚደረጉ
የክርክር ሂደቶች ላይ እየታዩ ያሉትን ችግሮች ይዳስሳል፡፡ የጥናቱም ዘዴ አይነታዊ ሆኖ ውሳኔ
ያረፈባቸውን የፍርድ ቤት መዝገቦች ሆን ብሎ በመለየት የተመረመሩ ሲሆን ተግባራዊ
አፈጻፀም ላይ የሚገጥሙ ችግሮችን ለመለየት ከባለሙያዎች ጋር ቃለ-መጠይቆች ተደርገዋል፡፡
በመሆኑም ይህን የጥናት ዘዴ በመመርኮዝ በተሰበሰቡ ዳታዎች መሰረት ተከሳሽ በሌለበት
የሚደረጉ ክርክሮች ላይ የሚሰጡ ውሳኔዎች ልዩነቶች ያለባቸው ሲሆኑ በተለይም በወንጀለኛ
መቅጫ ስነ-ስርአት ህግ አንቀጽ ቁጥር 161 ዙሪያ የሚነሱ የትርጉም ልዩነቶች በፍርድ ቤቶች
የሚሰጡ ውሳኔዎች ወጥና ተገማች እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል፡፡

*
LLM,LLB,በአብክመ የፍትህ ባለሙያዎች ማሰልጠኛ እና የህግ ምርምር ኢንስቲትዩት ተመራማሪ
1.ተከሳሽ በሌለበት የወንጀል ክስ ስለመስማት አስፈላጊነት
በወንጀል የሙግት ስርአት ውስጥ ተከሳሽ በተገኘበት ክርክር ማካሄድ መሰረታዊው ጽንሰ ሃሳብ
ነው፡፡ ሆኖም ተከሳሽ መጥሪያ ደርሶት በክርክር ሂደት ውስጥ ተሳታፊ ያለመሆኑ የተበደሉ
ሰዎች ፍትህ እንዳያገኙ ብሎም ፍትህን በእጃቸው እንዲያስገቡ የሚገፋፋ ምክንያት ከመሆኑም
ባሻገር መንግስት የማህበረሰቡን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ፍትህ መረጋገጥ እንዳይችል
ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ተከሳሽ በሌለበት የሚታዩ ጉዳዮች የተፋጠነ ውሳኔ በመስጠት የህግ
ስርአቱን ከማቀላጠፍ ባሻገር ተከሳሽ ባለመቅረቡ ምክንያት የሚጠፉ፣ የሚበላሹ ማስረጃዎች
፣በምስክርነት የሚቀርቡ ሰዎች የሚሰጡትን የምስክርነት ቃል ከመዘንጋት የሚታደግ ሲሆን
ተከሻሹ ጭራሹኑ እንዳይቀጣና የወንጀል ህግ አላማ የሆነውን የማረምና የማነጽ አላማን ሳይሳካ
እንዳይቀር ያደርጋል፡፡1 በሌላ ጎኑ የግለሰብ ነጻነትን ስንመለከት በክርክር ሂደት ውስጥ ተሳታፊ
እንዲሆን ተፈቅዶለት ከህግ በመሸሽ በክርክሩ ተሳታፊ ሳይሆን ሲቀር በልዩ ሁኔታዎች ተከሳሽ
በሌለበት ክርክሩ ይካሄዳል፡፡ በአለም አቀፍ የሲቪል እና ፖለቲካል መብቶች የቃልኪዳን ሰነድ
በአንቀፅ 14 ንኡስ ቁጥር 3 ላይ እንደተመለከተውም ‹‹ማንኛውም ሰው በተከሰሰበት የፍርድ
ሂደት ላይ በአካል የመገኘት መብት አለው ፣ራሱም በመገኘት የቀረበበትን ክስ የመከላከል
መብት ወይም በጠበቃው እርዳታ እየታገዘ የመከላከል መብት አለው፡፡›› የሚለውን የዚህን
ድንጋጌውን ትርጉም የተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ መብት ኮሚቴ በጄነራል ኮሜንት ቁጥር
13 (General Comment No.13) ሲያብራራ2
“When exceptionally for justified reasons trials in absentia are held, strict
observance of the rights of the defense is all the more necessary.”
ይህም በግርድፉ ሲተረጎም ‹‹በተወሰኑና ምክንያታዊ በሆኑ ሁኔታዎች ተከሳሽ በሌለበት የክስ
ጉዳዮች ሲታዩ የተከሳሽ መብቶች ጥብቅ በሆኑ ሁኔታዎችም ሊታዩ ይገባቸዋል›› በማለት
አስቀምጧል፡፡ በመሆኑም በልዩ ሁኔታዎች ተከሳሽ በሌለበት ክርክሮች የሚታይበት ሁኔታ
እንዳለ ሲገልጽልን ነገር ግን ተከሳሽ በሌለበት ክርክር ሊካሄድ የሚችሉባቸው ምክንያታዊ
ሁኔታዎች ምንድን ናቸው የሚለውን ይኋው ኮሚቴ አላስቀመጠም፡፡3

1
Lucas Tasar, ‘Trial in Absentia: Rescuing the "Public Necessity" Requirement to Proceed With
a Trial in the Defendant's Absence’ (2009) Barry Law Review Vol. 12, p. 153, 165
2
General Comment No. 13: Equality before the courts and the right to a fair and public hearing
by an independent court established by law (Art. 14) 04/13/1984.
file:///C:/Users/pc/AppData/Local/Temp/UN_Equality_before_courts_General_Comment_13_1984-
1.pdf
3
ዝኒ ከማሁ
2. በወንጀል የተከሰሱ ሰዎች ጉዳያቸውን ለመከታል ስላላቸው መብት

2.1. በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት ስር

የተከሰሱ ሰዎች መብቶችን በተመለከተ በህገ መንግስት አንቀጽ 204 ላይ በዝርዝር የተመለከተ
ሲሆን አጭር በሆነ ግዜ ውስጥ ጉዳያቸው እንዲታይ ከመደንገግ አንስቶ የቀረበባቸውን ማስረጃ
የመመልከት፣የቀረቡባቸውን ምስክሮች የመጠየቅ፣ለመከላከል የሚያስችላቸውን ማስረጃ ማቅረብ
ወይም የማስቀረብ ፣ምስክሮቻቸው ቀርበው እንዲሰሙ ማድረግ፣በመረጡት ጠበቃ የመወከል
ወይም ጠበቃ ለማቆም አቅም በማጣታቸው ፍትህ የሚጓደልበት ሁኔታ ሲያጋጥም ከመንግስት
ጠበቃ ስለሚያገኙበት ሁኔታ በህገ-መንግስቱ ተቀምጧል፡፡ ሆኖም ክስ የቀረበባቸውን ሰዎች
መብት የኢ.ፌ.ድ.ሪ. ህገ መንግስቱ በዝርዝር ሲያስቀመጥ በክስ ሂደት ውስጥ የተከሳሽን በአካል
የመገኘት መብትን በግልጽ ደንግጎ አላስቀመጠውም፡፡ ነገር ግን በህገ መንግስቱ አንቀፅ
9(4)5መሰረት ሃገራችን የተቀበለቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የህግ አካል ተደርገው
የሚወሰዱ መሆናቸው በዚሁ ህገመንግስት ላይ የተቀመጠ ሲሆን ኢትዮጵያ ካጸደቀቻቸውና
አባል ከሆነችባቸው ሰነዶች አንዱ የሆነው የሲቪልና የፖለቲካ የቃልኪዳን ሰነድ ተከሳሽ በአካል
የመገኘት መብትን አካቶ በውስጡ ይዟል፡፡ የዚሁ ህገ መንግስት አንቀጽ 13(2)6 በህገ መንግስቱ
የተቀመጡት የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች ኢትዮጵያ ካጸደቀቻቸው አለም አቀፍ
ህግጋቶች፣ከአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ስምነቶች እንዲሁም አለም አቀፍ ሰነዶች ጋር
ተጣጥመው መተርጎም እንዳለባቸው ያስቀምጣል፡፡ ስለሆነም በአካል የመገኘት መብትን በህገ
መንግስቱ ስር አልተካተተም ለማለት አይቻልም፡፡

2.2. ፍትሃዊ የክስ ስርአት (Fair trial)


በአንድ ሃገር የወንጀል ሙግት ስርአት ውስጥ መኖር እና መረጋገጥ ከሚገባቸው መርሆች
አንዱ ፍትሃዊ የክስ ስርአት ነው፡፡ ፍትሃዊ የክስ ስርአት( Fair trial) ትርጉምን የብላክስ ሎው
መዝገበ ቃላት በሚመለከተው መልኩ ያስቀምጠዋል፡፡ Fair trial ‹‹a trial by impartial and
disinterested tribunal inaccordance with regular procedure››7ይህም በግርድፉ
ሲተረጎም ፍትሃዊ ክርክር ማለት ገለልተኛ እና የማይመለከተው ትሪቢውናል መደበኛ ህግና

4
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክሪያሳዊ ሪፐብሊክ ህገመንግስት የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ አዋጅ ቁጥር 1/1987፣1ኛ
አመት ቁጥር 1፣አዲስ አበበባ
5
ዚኒ ከማሁ
6
ዝኒ ከማሁ
7
Bryan.A.Garner, Blacks law dictionary, 2004,8th edition,west a Thomson business, p.634
ስርአትን ተመርኩዞ ክርክር ማካሄድ እንደ ማለት ነው፡፡ በፍትሃዊ የክስ ስርአት ውስጥ
የተከሳሽ በክርክር ወቅት መገኘት ዋነኛው መሰረት ጽንሰ ሃሳብ ከመሆኑ አንጻር ተከሳሽ
በሌለበት ክርክር በማካሄድ የተሰጠ ውሳኔስ እንዴት ፍትሃዊ ሊባል ይችላል የሚል ጥያቄ
ይነሳል፡፡
የፍትሃዊ ክርክር ስርአት መብት በውስጡ የተለያዩ ዘርፎች ያጠቃለለ ቢሆንም እንደ አጠቃላይ
መርህ ተከሳሽ ሁልግዜም ቢሆን የተከሰሰበትን ፍርድ የመመለስ፣የቀረበበትን ማስረጃ
ማስተባበል እንዲሁም የቀረቡበትን ምስክሮች የመጠየቅ መብቶችን በተመቻቹ ሁኔታዎች
ሊተገበርለት የሚገባበትን ሁኔታዎችን የሚያካትት መርህ ነው፡፡8 ፍትሃዊ የክስ ክርክር ስርአት
በአንድ የወንጀል ስርአት ውስጥ አለ ለማለት ተከሳሹ እንደ ንጹህ የመገመት መብት መኖር
፣ያለምንም መጓተቶች መዳኘት መቻል፣በአካል ተገኝቶ መከራከር ወይም በጠበቃው በኩል
መከራከር፣የቀረቡበትን ምስክሮችን መመርመር እና ለመከላከያ የሚሆኑትን ምስክሮች መጥራት
የሚያስችል መብቶችን በውስጡ አካቶ ሲይዝ ነው፡፡
አለም አቀፍ የሲቪል እና ፖለቲካል መብቶች የቃልኪዳን ሰነድ አንቀፅ 14 ንኡስ ቁጥር(3)9ስር
አንድ ተከሳሽ ክስ ሲቀርብበት ዝቅተኛ የሆኑ የመብት ጥበቃዎች (minimum safeguard)
ሊደረጉለት ይገባል በማለት ሰነዱ ያስቀምጣል፡፡ እነዚህም ዝቅተኛ ጥበቃዎች ተፈፀሚነታቸው
እኩል በሆነ መልኩ
• ተከሳሽ በአካል በተገኘበት ክሱን ማካሄድ
• ተከሳሹ ራሱን እንዲከላከል ወይም በጠበቃ አማካኝነት ክሱን እንዲከላከል ማድረግ
እንዲሁም ጠበቃ ማቆም የማይችል ከሆነና ፍትህ መጓደልን ያመጣል ተብሎ የሚታሰብ
ከሆነ በነጻ ጠበቃ ሊቆምለት እንደሚገባ ይኸው የቃል ኪዳን ሰነድ ያስቀምጣል፡፡ በሰነዱ
ላይ የተቀመጡትንም ዝቅተኛ ዋስትናዎች እንደሚከተለው በዝርዝር እንመለከታቸዋለን፡፡
2.2.1.ተከሳሽ በአካል በተገኘበት ክሱን ማካሄድ (the right to be present)
በክስ ክርክር ወቅት የተከሳሽ በአካል የመገኘት መብት ከከሳሹ አካል ተከሳሽን ክሱ የሚሰማበትን
ቦታ፣መቼ እና የት እንደሚሰማ አስቀድሞ ከማሳወቅ ግዴታ ጋር የሚቆራኝ ነው፡፡ ይህም
ተከሳሽም በተባለው ግዜ እንዲቀርብ ማድረግ የሚያስችል እና ተከሳሽን ያለበቂ ምክንያት
ከክርክሩ ውጭ እንዳይሆን የሚረዳ መብት ነው፡፡ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት

8
Sarah J. Summers, Fair Trials (Hart Publishing 2007) ገጽ 113 እንዲሁም
9
The International Covenant on Civil and Political Rights (adopted on 16 December 1966,
entered into force on 23 March 1976 art. 14(3)
ኮሚቴ በጄኔራል ኮሜንት ቁጥር 3210ስር ተከሳሽ በሌለበት ክርክር ለማካሄድ መወሰድ
ስላለባቸው ጥንቃቄዎች ሲያስቀምጥ ተከሳሽ በሌለበት ክርክር ከመደረጉ በፊት ዐቃቤ ህጉ
አስፈላጊውን ጥረት በማድረግ ተከሳሽ የተከሰሰበትን ጉዳይ ለማሳወቅ ጥሪ እንዲደርሰው
ማድረጉን ለፍርድ ቤቱ ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሲቪልና የፖለቲካል
የቃል ኪዳን ሰነድ አንቀፅ14(3)መ11 ላይ እንደተቀመጠውም ከሳሽ ለተከሳሽ የተከሰሰበትን ክስ
አስቀድሞ በማሳወቅ ክሱ መቼና የት እንደሚካሄድ መግለፅ መቻል ያለበት መሆኑን በግዴታነት
ያስቀምጣል፡፡ ይህ ሳይሆን ተከሳሽ በሌለበት ክርክር ማካሄድ ተከሳሽ በክርክር ወቅት በአካል
የመገኘት መብቱን የሚጣረስ ነው በማለት በጄኔራል ኮሜንቱ ላይ አስፍሯል፡፡
2.2.2. ተከሳሹ ራሱን እንዲከላከል ወይም በጠበቃ አማካኝነት የመወከል መብት(the right to
defend onself or to be represented by legal council)
ይህ መብት ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ እና ማስረጃ አውቆ ራሱን እንዲከላከል የሚያስችል መብት
ሲሆን በህገ-መንግስቱም በአንቀፅ 20(5)12 ላይ ተደንግጎ እናገኛዋለን፡፡ ይህ መብት ተከሳሽ
ከአድሎ በጸዳ መልኩ የቀረቡበትን ምስክሮች የመመርመር እድል ማግኘትና ለመከላኪያ
የሚሆኑትንም ምስክሮች አቅርቦ የማሰማት መብትንም በውስጡ ያካትታል፡፡ ሌላው ከዚህ ጋር
ተያይዞ ሊነሳ የሚገባው ተከሳሽ በአብዛኛው የህግ እውቀት የሌለው በመሆኑ ጉዳዩን አይቶ
የሚከራከራከርለት ጠበቃ ማቆም የተከሳሽ ሙሉ መብት ነው ፡፡ በዚህ መብት ስር በፈለገው
ጠበቃ የመወከል፣ችሎታ ባለው ጠበቃ የመወከል መብት በተለይም ይህን ማድረግ አቅም
ከሌለው ፍትህ እንዳይጓደል በሚል በመንግስት ጠበቃ ሊቆምለት የሚያስችል ድንጋጌ በውስጥ
ያካትታል፡፡ ሆኖም በሃገራችን ተከሳሽ በሌለበት በሚደረጉ ክርክሮች ላይ የክርክሩን ሚዛናዊነት
ለማስጠበቅ በጠበቃ የመወከል ስነስርአት የለም፡፡
አሁን አሁን እየዳበሩ የመጡ እይታዎች ተከሳሽ በክርክር ላይ ሳይገኝ ቢቀር እንኳን ሳይወከል
እንዳይቀርና ተከሳሹ ራሱ ባለመገኘቱ ምክንያት የቀረቡበትን ማስረጃዎች መከላከል ባይችልም
የተከሳሹን መብት እንዲሁም የክርክሩን ሚዛን ለማስጠበቅ ሲባል ጠበቃ ሊቆምለት ይገባል
የሚሉ እይታዎች ብቅ ብለዋል፡፡13 በተለይም ይህ አሰራር በፈረንሳይ በቀላል ወንጀሎች

10
UNHRC General Comment No. 32 Right to equality before courts and tribunals and to a fair
trial
11
ከላይ የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 9
12
ከላይ የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 4
13
N.W. Taylor, ‘Trial: defendant voluntarily absenting himself from trial – representatives
withdrawing from trial’ (October 2006) Criminal Law Review 952.
የተከሰሱ ሰዎች መብታቸውን በመተዋቸው ምክንያት በሌሉበት ጉዳያቸው ሲታይ በጠበቃ
እንዲወከሉ የሚደረግበት አሰራር አለ፡፡14 ከዚህ በተጨማሪም በአለምአቀፍ ትሪቡናልስ15ይህ
አሰራር በመጠኑ እየተተገበረ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ተከሳሽ በክርክር ሂደቱ ላይ ባይገኝም ጠበቃ
ተገኝቶ እንዲከራከር መፍቀድ የፍታሃዊነትን ሚዛን ከፍ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ
በሃገራችንም ተከሳሽ በሌለበት የሚታዩ ጉዳዮች በጠበቃ መወከል የሚያስችል የስነስርአት ህግ
ቢዳብር መልካም ነው፡፡
3.የተከሰሱ ሰዎች ጉዳያቸው በሌሉበት ስለሚታይበት ሁኔታ

3.1.ተከሳሽ በሌለበት የወንጀል ክርክር ማድረግ ትርጉም

ተከሳሽ በሌለበት ክርክር ማድረግ የሚለው ፅንሰ ሃሳብ መነሻ ነው ተብሎ የሚወሰደው
በተለይም ለወንጀል ጉዳዮች አጠቃቀም በዋነኝነት ተለይቶ በመዋል ሰፊ እውቅና ያገኘው
አብሰንሺያ ‹‹absentia›› የሚለው የላቲን ቃል ነው፡፡16 ይህ ቃል በግርድፉ ወደ አማረኛ
ሲተረጎም ባልተገኘበት (በሌለበት) ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በሃገራችን የወንጀለኛ መቅጫ
ስነስርአት ህግ አንቀጽ 16017 ላይ ተከሳሽ በሌለበት የሚታዩ ጉዳዮችን የገለጸበት አግባብ ከዚህ
ቃል የሚለይ ቃል መርጧል፡፡ በሌለበት(default) የሚለው ቃል ትርጓሜ ብላክስ ሎው መዝገበ
ቃላት ሲያስቀምጠው፡- ‹‹default ፡- to fail to appear or to answer›› በሚል ነው፡፡ ይህም
ወደ አማረኛ ሲተረጎም ሊቀርብ ያለመቻል ወይም መልስ ለመስጠት ያለመቻል የሚል ትርጓሜ
አለው፡፡18 ተከሳሽ በሌለበት ክርክር የማድረግ ፅንሰ ሃሳብም ተከሳሹ በፍርድ ቤት በአካል ሳይገኝ
በሌለበት ጉዳዩን ተመልክቶ ውሳኔ መስጠት ነው፡፡ ሆኖም የወንጀል ስነስርአት ህጋችን
የተጠቀመበት በሌለበት(default) የሚለው ፅንሰ ሃሳብ ከ‹‹absentia›› ከሚለው ፅንሰ ሃሳብ ጋር
መሰረታዊ ልዩነት አለው ወይ የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ በወንጀለኛ መቅጫ ስነስርአት ህጋችን
ከጅምሩም ይሁን በክርክር ሂደት ላይ ለማይቀርቡ ተከሳሾችን በተመለከተ ልንከተል ስለሚገባን
ስነ ስርአታዊ አካሄድ እንደ ፍትሃብሄር ስነስርአት በውስጡ አላካተተም፡፡ ይህንንም ለመመለስ

14
የፈረንሳይ የወንጀል ስነስርአት ህግ አንቀጽ 411(1), Aaccused charged with an offense punishable by
a fine or less than two years' imprisonment may waive appearance upon proper application to
the court, and still be represented by counsel.
15
Evert F. Stamhuis,Absentia trials and the right to defend ,University of Western Ontario,
London Ontario, Canada ,2001 p.727
16
IBA Report on the ‘Experts’ Roundtable on trials in absentia in international criminal justice,
International Criminal Court and International Criminal Law Programme, September 2016
17
የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መንግስት የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርአት ህግ ቁጥር 1/1954 ዓ.ም ነጋሪት ጋዜጣ
፣አዲስ አበባ አንቀጽ ቁጥር160 (ከዚህ በሃላ የወ/መ/ስ/ስ/ህግ) በሚል ሊጠቀስ ይችላል፡፡
18
የግርጌ ማስታወሻ 7፣449
የሌሎች ሃገሮችን ልምድም ስንመለከት አብሰንሺያ ‹‹absentia›› የሚለውን ቃላት በተለይ
ሁኔታ ለወንጀል ጉዳዮች የሚጠቀሙ ሲሆን ለፍታብሄራዊ ጉዳዮች ደግሞ በሌለበት(default)
የሚለውን ቃላት ይጠቀማሉ፡፡ በሃገራችን ተከሳሽ በሌለበት የሚደረግ ክርክር በሌለበት(default)
ተብሎ የመቀመጡን ምክንያት በግልፅ የሚመልስልን ፅሁፍ ባይገኝም እንደ ፍትሃብሄር
ህጋችን የተከሳሽን ያለመቅረብ ውጤት አለማንሳቱ አንደ አንድ የህግ ክፍተት ከመውሰድ ባሻገር
ከፍታብሄር ህጉ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም (ውጤት) አለው ለማለት ግን አያስደፍረንም፡፡
3.2. አንድ ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩ እዲታይ የሚወሰነው መቼ ነው?
የወንጀል ህግ መርህ ተከሳሽ ባለበት ክርክር ተደርጎ ውሳኔ መስጠት ቢሆንም ይህ መርህ
በልዩ ሁኔታ ሊታለፍ ይችላል፡፡ በተግባርም ከክርክሩ ጅምር ካልቀረቡ ተከሳሾች አንስቶ
በክርክር መሃል የሚቀሩ ተከሳሾች ላይ በሌሉበት ክርክር በማድረግ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
በስነስርአት ህጋችን ስር በክርክር መሃል የሚቀሩ ተከሳሾችን በተመለከተ የመዝገቡ ውጤት
ምን ይሆናል በሚል በግልጽ ባለመመላከቱ ምክንያት የተለያየ የአሰራር ልዩነት ፈጥሯል፡፡
ሆኖም ይህንን እና ተያያዥ ጥያቄዎችን በሚፈታ መልኩ ሰበር ተከታዩን ውሳኔ ወስኗል፡፡
19
የዚህ ክርክር አመጣጥ ባጭሩ ተከሳሽ የወንጀል ህግ አንቀጽ 555(1)ለ በመተላለፍ በሰው
አካል ላይ ከባድ ጉዳት የማድረስ ወንጀል ፈጽሟል በማለት ክስ ቀርቦበት ድርጊቱን
አለመፈፀሙን ክዶ ተከራክሯል፡፡ ዐቃቢ ህግም ምስክሮቹን አቅርቦ ካሰማ በኋላ ተከሳሽ
እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ ተከሳሽ መከላኪያ ምስክሮቹን እንዲያሰማ በተደጋጋሚ ቀጠሮ
ቢሰጥም ተከሳሽ ሊቀርብ ባለመቻሉ ምክንያት ዐቃቢ ህግ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/161 መሰረት ጉዳዩ
በሌለበት እዲታይለት ለፍርድ ቤቱ አሳስቧል፡፡ ሆኖም ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ የተከሰሰበት ድንጋጌ
በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/161 የሚታይ አይደለም በማለት ፖሊስ ተከሳሽን ካለበት ቦታ አፈላልጎ
ሲያቀርበው የዐቃቤ ህግ መዝገቡን የማንቀሳቀስ መብቱን ጠብቆ ዘግቶታል፡፡ በዚህም ውሳኔ
አቃቤ ህግ ቅር በመሰኘቱ ለክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣እንዲሁም ሰበር
ሰሚ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም አቤቱታውን ባለመቀበል ሰርዘውታል፡፡
ጉዳዩ ለፌደራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት20 ሲቀርብ ተከታዩን ጭብጥ በማንሳት ያስቀርባል ብሏል፡፡
‹‹ተከሳሽ መከሰሱን አውቆ ምስክር ከተሰማበትና መከላክያ ምስክር ይዞ ባለመቅረቡ የመከላከል
መብቱ ታልፎ ውሳኔ እንዲሰጥ የቀረበው አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ያለመቀበሉ ተገቢ ነው ወይስ

19
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.የወንጀል ህግ ፣አዋጅ ቁጥር 414/1996 ፣አንቀጽ 596
20
የፍደራል ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር የመ/ቁጥር 127813 አቃቤ ህግ እና አንዱአለም ገናናው
መስከረም 22/2010 የተሰጠ ውሳኔ(ያልታተመ)
አይደለም›› በማለት በዚህ ጭብጥ መሰረት ጉዳዩን ሲመረምር ‹‹ ተጠሪ ክሱ በሚሰማበት ቀን
ቀርቦ የዐቃቢ ህግ ምስክሮች ከተሰሙና መከላኪያ ምስክር አቅርቦ እንዲያሰማ በተቀጠረበት ቀን
ሳይገኝ የቀረ በመሆኑ በህገመንግስቱ አንቀፅ20(4) ተከሳሽ የተሰጠውን ምስክሮችን የመመርመር
እና የመጠየቅ መብቱ ሙሉ በሙሉ በተከበረበት ሁኔታ ተጠሪ በራሱ ፍቃድ የተጠበቀለትን
የመከላከል መብት የተወው ሲሆን ይህም መሆኑ ዳኞች የቀረበውን ማስረጃ መርምሮ ውሳኔ
ከመስጠት የሚያግዳቸው አይደለም›› በማለት መዝገቡን የስር ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ በተገኘ ግዜ
ይንቀሳቀስ ማለቱ አግባብነት የለውም የሚል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ይኸው ፍርድ ቤትም በፍርድ
ሃተታው ላይ በስር ፍርድ ቤቶች ሲነሳ የነበረውን ጉዳዩ በሌለበት መታየት አለበት የለበትም
የሚለውን ክርክር በማንሳት ‹‹ፍርድ ቤቱ አንድን ጉዳይ ተከሳሽ በሌለበት ማየት እንዲችል
ተከሳሹ በቀጠሮው ቀን ቀርቦ ያለ በቂ ምክንያት መቅረቱ ሲረጋገጥ ብቻ መሆኑን
በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/161(1)እና (2)ሀ ንባብ የሚያሳየን ነው፡፡ አንድ ጉዳይ በሌለበት ታየ የሚባለው
መቼ ነው? ተከሳሽ በሌለበት የወንጀል ክስ የሚታይበት ሁኔታ የሚደነግጉት ከወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/
161እስከ 16421 የተደነገጉት ድንጋጌዎች ይዘት ትርጉምና ተፈፃሚነት ውጤት እንዲሁም
በወንጀል የተከሰሰ ሰው በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት በሌለበት ታይቶ ከሚሰጥ ፍርድ እንዴት
አይነት ጉዳይ ነው የሚለውን የህገመንግስቱ አንቀፅ 20(4) እና ከወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/149(1)እና(4)
ድንጋጌ ይዘት መንፈስ ጋር መታየት አለበት፡፡›› በማለት አስቀምጧል፡፡ ይህ ውሳኔ የሃተታ
ግልጽነት የጎደለው ቢሆንም ካጠቃላይ የሃተታው መንፈስ የምንረዳው ጉዳዩ በሌለበት
የሚታየው ተከሳሽ ክስ ለመስማት በተቀጠረበት ቀን ሲቀር (ከጅምሩ) ሲሆን በክርክር መሃል
የሚቀሩ ተከሳሾችን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ በህገ መንግስቱ የተሰጠውን በአካል
የመገኘት መብት መጠቀም እንዳልፈለገ ተቆጥሮ ውሳኔ መስጠት ያለበት መሆኑን ነው፡፡
በመሆኑም ከዚህ ውሳኔ ከሀታታዎቹ መንደርደሪያ እና ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች ይዘት
የምንረዳው ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዮች መታየት ያለባቸው ከጅምሩ በክርክር ላይ ያልተገኙ
ተከራካሪዎችን የሚመለከት መሆኑን እንዲሁም በክርክር መሃል የሚቀሩን ተከሳሾች
በተመለከተ በህገመንገስቱ የተሰጠውን የመደመጥ መብት ያልተጠቀመበት ተከሳሽ መብቱን
እንደተወ ተቆጥሮ በጉዳዩ ላይ ፍርድ ቤቱ የመሰለውን ከመወሰን የሚያግደው አለመሆኑን
የሚያሳይ የትርጉም ይዘት አለው፡፡

21
ከላይ በግርጌ ማስታወሻ 17፣አንቀጽ 161 እስከ 164
በአሜሪካ ፍርድ ቤት22 እ.አ.አ.1912 የተሰጠ የመጀመሪያ ውሳኔ ተከሳሽ ፍርድ ቤት መቅረብ
ካልፈለገ መብቱን በፍቃዱ እንደ ተወ ተቆጥሮ ውሳኔ ሊሰጠው እንደሚገባ ተወስኗል፡፡ ይህም
ውሳኔ የአሜሪካ የፌደራል ህግ የወንጀል ስነስርአት አዋጅ ላይ ተካቶ መብትን መተው የሚል
ጽንሰ ሃሳብን እንዲዳብር አድረጓል፡፡ ሆኖም ተከሳሽ ይህን መብቱን ስለመተው በጽሁፍ ወይም
በችሎት ቀርቦ የሚገልጽ ሲሆን በክርክር ወቅት የመቅረብ መብትን መተወ በሚለውም ጽንሰ
ሃሳብ በአሜሪካ ህግ ስርአት ውስጥ በኬዝ ሎውም ሆነ በህግ የዳበረ ስርአት ነው፡፡23 ነገር ግን
በሃገራችን መብትን መተው የሚል ጽንሰ ሃሳብ ተካቶ የማይገኝና ከተከሳሽ ድርጊት በመነሳት
ግምት ለመውሰድ የሚያስችለን የህግ ማዕቀፍ የሌለ ሲሆን ከላይ የተጠቀሰውም የሰበር
ውሳኔም ዓላማ ውሳኔዎችን ከመቋጨት እና የተከሳሽን መብት ከህዝብ ጥቅም ጋር በመመዘን
የተሰጠ ውሳኔ ነው ማለት ይቻላል፡፡
4.በተግባር እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች

4.1.የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርአት ህግ ቁጥር161 አተረጓጎም በፍርድ ቤቶች

Ø የመጀመሪያው አተረጓጎም

የዚህ ድንጋጌ ትርጉም ዋነኛ መከራከሪያ ተከሳሽ በሌለበት የሚታዩ ጉዳዮች በልዩ ሁኔታ
የተቀመጡ በመሆናቸው መተርጎም ያለባቸው በጠባቡ ነው፡፡ ሌላኛው መከራከሪያ ሃሳባቸው
በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ161 ላይ እንደተቀመጠው ተከሳሽ በሌለበት ክርክር ሊደረግ የሚገባው የቅጣት
መነሻቸው 12 አመትና ከዚያ በላይ ጽኑ እስራት የሚያስቀጡ ድንጋጌዎችን በሚመለከት ብቻ
ነው፡፡ ለዚህ ትርጉም እንደ ምክንያቱን የሚያስቀምጡት ይህ ልዩ ስነስርአት የተቀመጠበት
አላማ ከወንጀሉ ከባድነት አንፃር ሲሆን ተከሳሾች ባለመገኘታቸው ብቻ ጉዳያቸው ሳይታይ
እንዳይቀር ነው፡፡ የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርአትም የቅጣት መነሻቸው 12 አመት እና ከዚያ

22
Diaz v. United States, 223 U.S. 442 (1912).
23
Eugene L. Shapiro, ‘Examining an Underdeveloped Constitutional Standard: Trial in Absentia
and the Relinquishment of a Criminal Defendant's Right to be Present’ (2012) Marquette Law
Review Vol. 96, ገጽ.593, 616 እንዲሁም የአሜሪካው
FEDREAL RULE CRIMINAL Procedure 43, advisory committee notes n.1–3 (1944). Rule 43
was rephrased, effective December 1, 2011, retaining the consequence that the right to be
present is waived by a defendant who is voluntarily absent from trial. According to Rule 43 (c);
the defendant should be present at the beginning of the process then s/he can waive this right,
or because of her or his disruptive behavior, the court can order the removal the defendant from
the courtroom.
በላይ የሆኑ ወንጀሎችን የሚመለከት ብቻ መሆን አለበት የሚል ነው፡፡ በአጠቃላይ በዚህ
አተረጓጎም መሰረት በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ161 ላይ የተቀመጠው የቅጣት መስፈርት መነሻ እንጂ
መድረሻ ተደርጎ ሊወሰድ አይገባውም ብለው ክርክራቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ ይህንም አቋማቸውን
በሚከተሉት መዝገቦች ላይ ለአብነት ማየት እንችላለን፡፡
ተከሳሽ የወንጀል ህግ አንቀጽ 27(1) እና 540 በመተላለፍ24 የመግደል ሙከራ አድርጓል በሚል
ክስ የቀረበበት ሲሆን ተከሳሽ የተከሰሰ መሆኑን አውቆ እንዲቀርብ መጥሪያ እንዲላክለት
ቢደረግም ባለመቅረቡ እንዲሁም የጥሪ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዲወጣ ቢደረግም
አሁንም ተከሳሹ ሊቀርብ ባለመቻሉ ምክንያት ዐቃቤ ህግ ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ
ባቀረበው ማሳሰቢያን መሰረት ፍርድ ቤቱ የቅጣት መነሻቸው 12 አመት በታች ሆነው
ጣሪያቸው ግን ከ12 አመት በላይ የሚያስቀጡ ወንጀሎችን ሊያካትት ይገባል ወይስ አይገባም
የሚለውን ጭብጥ በመያዝ በአብላጫ ድምጽ የሚከተለውን ብይን ሰጥቷል፡፡ የውሳኔው
ዝርዝርም፡-
‹‹ የአንድ ወንጀል ከባድነት ቀላልነት የሚወሰነውም በሚያስቀጣው ቅጣት በመሆኑ ህጉም 12
አመትን እንደ መለያ አድርጎ ያስቀመጣቸው መነሻቸው ከ12 ዓመት እና ከዚያ በላይ
ለሚያሳስሩ ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ነው፡፡ በመሆኑም የቅጣት መነሻው ከ12 አመት በታች
ቢሆንም ጣሪያቸው 12 አመት በላይ በሚሆንበት ግዜ ጉዳዩ በሌለበት ይታይ የሚያስብል
አይደልም፡፡ ለምሳሌ የወንጀል ህግ 67025 የወንብድና ወንጀል ከ1 አመት እስከ15 አመት
ሊደርስ በሚችል እስራት የሚያስቀጣ ሲሆን ጣሪያው 15 አመት ስላለ ብቻ ተከሳሽ በሌለበት
እንዲካሄድ ማድረጉ ተከሳሽ አንድ አመት ሊቀጣ የሚችል እድል ያለው ከመሆኑ አንፃር
በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.161(2)(ሀ)ስር የተቀመጠውን ከ12 አመት በታች በማያንስ ፅኑ እስራት
የሚያሳስር የሚለውን ሀረግ የሚያሟላ አይሆንም፡፡ በሌላ በኩል የወንጀል ህግ ድንጋጌዎች
በሚተረጉሙበት ግዜ ድንጋጌዎቹ ሊሳኩ ከሚፈልጉት አላማ በተጨማሪ የተከሳሹን መብት
በማያጣብብ መልኩና ተከሳሹን በሚጠቅም ሁኔታ መተርጎም አለባቸው፡፡ ስለዚህ ተከሳሹ ላይ
የቀረበው የወንጀል ድንጋጌ መነሻ 12 አመት በታች በመሆኑ በሌለበት ሊታይ አይገባም››
በሚል በአብላጫ ድምጽ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

24
ዐቃቤ ህግ እና አንዱአለም እሸቴ በአ.ብ.ክ.መ.የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል መዝገብ ቁጥር
02-10929 በቀን 26/04/2008 የተሰጠ ውሳኔ እንዲሁም የግርጌ ማስታወሻ 20፣አንቀጽ 27 እና 540
25
የግርጌ ማስታወሻ 20፣አንቀጽ 670
በሌላ ጉዳይም በቁጥር 3 ተከሳሾች በተከሰሱበት የወንጀል ድርጊት ዐቃቤ ህግ አንቀፅ 32(1)ሀ
እና 620(2)ሀ በመጥቀስ በተከሳሾች ላይ ክስ አቅርቦባቸው26 1ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ሊቀርቡ
ባለመቻላቸው ጉዳዩ በሌሉበት እንዲታይ ዐቃቤ ህግ ባሳሰበው መሰረት ፍርድ ቤቱ የሚከተለው
ብይን ተሰጥቷል፡፡
‹‹1ኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበው ክስ በአማራጭ ሲሆን የተጠቀሱበት ድንጋጌም በአንደኛው ክስ ከ5
አመት እስከ 20 ዓመት በሌላው ክስ ደግሞ 3 አመት እስከ 15 የሚያስቀጣ ሲሆን በ3ተኛ
ተከሳሽ ላይ የተጠቀሰውም የህግ ድንጋጌ ከ 5አመት እስከ 20 አመት ሊደርስ የሚችል ጽኑ
እስራት የሚያስቀጣ መሆኑ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ስለሆነም ተከሳሶች ጥፋተኛ ተብለው ቢቀጡ
ቅጣቱ ከአምስት አመት ጀምሮ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ስለሆነም በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 161(2)ሀ
ደግሞ ተከሳሽ በሌለበት ክሱን ለመስማት እና ክሱ ሊቀጥል የሚችለው ቅጣቱ 12 አመት
በታች በማያንስ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ መሆኑን በግልጽ አስቀምጧል፡፡ ስለዚህ ከዚህ ድንጋጌ
አንጻር እና ተከሳሾች ክስ የቀረበባቸው ድንጋጌ ጋር በመመርመር ክርክሩ ተከሳሾች በሌሉበት
ሊቀጥል አይገባም›› በማለት ብይን ተሰጥቷል፡፡
Ø ሁለተኛው ትርጓሜ
ይህ መከራከሪያ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ161 ስር የተቀመጠው የቅጣት መስፈርት ሊታይ የሚገባው
የቅጣት መነሻው ሳይሆን የቅጣት መድረሻው መሆን አለበት፡፡ ለዚህም ምክንያት ብለው
የሚያስቀምጡትም የወንጀል ቅጣት አቀማመጥ ከ-እስከ በሚል የተቀመጠ በመሆኑ አብዛኛውን
ድንጋጌዎች ጥቅም አልባ ያደርጋል፡፡ ስለዚህም መነሻው ምንም ይሁን ምን መድረሻው 12
አመት ጽኑ እስራትን የሚያስቀጣ ከሆነ ጉዳዩ በሌለበት ታይቶ ውሳኔ ሊሰጥ ይገባዋል በሚል
የሚቀመጥ ክርክር ነው፡፡ ይህን ትርጓሜ የሰፋ ተግባራዊነት ያለው ሲሆን ለአብነትም
ተከሳሽ የወንጀል ህግ አንቀጽ 27(1) እና 54027 በመተላለፍ ተራ የሰው መግደል ሙከራ
ወንጀል ፈጽሟል በሚል ክስ ቀርቦበት የስር ፍርድ ቤት ጉዳዩ በሌለበት የሚታይ አይደለም
በሚል መዝጋቱን አስመልክቶ ዐቃቤ ህግ ባቀረበው ይግባኝ28 መሰረት ጉዳዩ በሌለበት መታየት
የለበትም የተባለው በአግባቡ ነው ወይ የሚለውን ጭብጥ ፍርድ ቤቱ በመያዝ እንደሚከተለው

26
አቃቤ ህግ እና እነ ዝናቤ ሞላ በቁጥር 3 ሰዎች፣በአ.ብ.ክ.መ. የራያ ቆብ ወረዳ ፍርድ ቤት የወንጀል መዝገብ
ቁጥር 0202509 20/03/2008 ዓ.ም.የተሰጠ ውሳኔ
27
የግርጌ ማስታወሻ 20፣አንቀጽ 540
28
ዐቃቤ ህግ እና ይመር ሰይድ በአ.ብ.ክ.መ. ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደቡብ ወሎ ዞን እና አካባቢዋ የይግባኝ ወንጀል
መዝገብ ቁጥር 02-03683 13/11/2008 ዓ.ም የተሰጠ ውሳኔ
መርምሮታል፡፡ የፍርድ ውሳኔውም ከላይ በአብይነት የተጠቀሰው መዝገብ ውሳኔን የሻረ
በመሆኑ የውሳኔውን ዝርዝር እንደሚከተለው እናያለን ፡፡
‹‹በመርህ ደረጃ የወንጀል ጉዳይ ተከሳሽ ባለበት ሊካሄድ እንደሚገባው ግልጽ ነው በልዩ ሁኔታ
ግን በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/ 193፣160እና ተከታዮቹ ባሉት ድንጋጌዎች ተከሳሽ በሌለበት የወንጀል
ሙግት እንደሚካሄድ ተቀምጧል፡፡ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/161(2) ስር ተከሳሽ በሌለበት ሊታዩ
የሚችሉ ጉዳዮች ሲያስቀምጥ ከአስራ ሁለት አመት በታች በማያንስ የሚያሳስር በሚል
የተቀረጸ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ድንጋጌ ከወንጀል ህጉ ላይ ያሉትን ድንጋጌዎች እና ስነ-
ስርአቶች ሊያሳካ ከፈለገው ዓላማ እና ግብ ጋር አስተሳስሮ ማየት ይጠይቃል፡፡ በዚህም
የወንጀል ህጉ ላይ ከተጠቀሱት የወንጀል ድንጋጌዎች መነሻ ቅጣት 12 አመት የሆነ የለም፡፡
በመሆኑም ይህ ድንጋጌ ሊተረጎም የሚገባው ህግ አውጭው ያስቀመጠውን የቅጣት ጣሪያ
እንጂ ወለሉን በማየት አይደለም፡፡›› በማለት ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡
እንዲሁም በሌላ ጉዳይ ተከሳሽ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 27(1) እና 597(1) ስር
የተመለከተውን በመተላለፍ በሴት ልጆች መነገድ ሙከራ ወንጀል29 ክስ ቀርቦበት በአካባቢው
ተፈልጎ ሊቀርብ ባለመቻሉ የጋዜጣ ጥሪ የተደረገለትና ያልቀረበ በመሆኑ ጉዳዩ በሌለበት
በመታየት የጥፋተኝነትና እና የቅጣት ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡ በተመሳሳይም ተከሳሽ የኢ.ፈ.ዲ.ሪ
የወንጀል ህግ አንቀፅ 27(1) እና 696(ሐ)በመተላለፍ ከባድ ማታለል ሙከራ30 ወንጀል ፈጽሟል
በሚል ክስ ቀርቦበት በጋዜጣ ጥሪ የተደረገለት ቢሆንም ሊቀርብ ባለመቻሉ ምክንያት በሌለበት
እንዲታይ ትዕዛዝ ቢሰጥም ተከሳሽ ሊገኝ ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ በተከሳሽ ላይ
የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
በመሆኑም የቅጣት መነሻ ወለላቸው ዝቅ ብሎ የቅጣት መድረሻ ጣሪያቸው ከፍ ብሎ የተደነገጉ
ድንጋጌዎችን በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ161 መሰረት ተከሳሽ በሌለበት የሚታይበት አሰራር አለ፡፡
4.2. ተከሳሽ በሌለበት የሚካሄዱ ክርክሮች በይግባኝ ስርአት ስር

በይግባኝ ክርክር ወቅት በፍርድ ቤት መገኘት(appearance) ከመጀመሪያ ደረጃ ክርክር በተለየ


ሁኔታ የመልስ ሰጭ መቅረብ አስገዳጅ አይደልም፡፡ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 193(2)31 ስር ተደንግጎ

29
በአ.ብ.ክ.መ. ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደቡብ ወሎ እና አካባቢዋ ምድብ ችሎት የወንጀል መዝገብ ቁጥር 0202991
ጌትዬ ተድላ እና ዐቃቤ ህግ ፣መጋቢት 8/2008 የተሰጠ ውሳኔ፡፡
30
በአ.ብ.ክ.መ. ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደቡብ ወሎ እና አካባቢዋ ምድብ ችሎት የወንጀል መዝገብ ቁጥር 02-03979
ዐቃቤ ህግ እና እንድሪስ ዓሊ፣ታህሳስ 20/2009 የተሰጠ ውሳኔ፡፡
31
ከላይ በግርጌ ማስታወሻ ቁጥር17፣አንቀጽ 193(2)፣
እንደሚገኘው ‹‹መልስ ሰጭው ወይም ጠበቃው ያልቀረቡ እንደሆነ ነገሩ በሌሉበት ይቀጥላል››32
በሚል የተቀረጸ ነው፡፡ በይግባኝ ወቅት ጉዳዩ በሌለበት ሊታይ የሚችለውም መልስ ሰጭ
ካልቀረበ ወይም በጠበቃ መወከል ሳይችል ሲቀር ብቻ ይሆናል፡፡ ዐቃቤ ህግ ይግባኝ
በሚልባቸው ጉዳዮች ላይ መልስ ሰጭ(የስር ተከሳሽ) መቅረብ ሳይጠበቅበት ጉዳዩን በጠበቃው
አማካኝነት እንዲከታተል ህጉ መፍቀዱ በባለሙያዎች ዘንድ የአቋም ልዩነቶች ፈጥሯል፡፡
አንዳንዶች ህጉ ግልጽ በሚሆንበት ግዜ ምንም አይነት ትርጓሜ አያስፈልገውም፡፡ በመሆኑም
መልሰ ሰጭ ባይቀርብም ጠበቃው እስከቀረበ ድረስ መስተናገድ አለበት እንጂ እንደ መጀመሪያ
ክርክር ተገዶ ሊቀርብ አይገባውም የሚል አቋም የሚያንጸባረቁ ሲሆን በሌላ በኩል በወንጀል
ጉዳዮችን ላይ ተከሳሹ መገኘት አለበት ምክንያቱም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ጉዳዩን
ያስቀርባል ማለቱ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ የሚያርምበት አግባብ ስለሚኖር መልስ ሰጭው
እራሱ በአካል መገኘት አለበት እንጂ የጠበቃው መገኘት ብቻ በቂ አይደለም የሚል መከራከሪያ
ያቀርባሉ፡፡33 ይህንንም ክርክር በዚህ መዝገብ ስር ማየት እንችላለን፡፡
ይግባኝ ባይ በስር ፍርድ ቤት የወንጀል ህግ አንቀጽ 539(1)ሀ34 በመተላለፍ ከባድ የግድያ
ወንጀል ፈጽሟል በሚል ክስ ቀርቦበት የስር ፍርድ ቤት ክሱን ተከላክሏል በማለት ተከሳሽን
በነጻ ማሰናበቱ አግባብ አይደለም በማለት ዐቃቤ ህግ የይግባኝ አቀረበ፡፡ የመልስ ሰጭም ጠበቃ
(መልስ ሰጭው ሳይቀርብ) በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.193 መሰረት ያቀረብነው የፅሁፍ መልስ
ይያያዝልን በማለታቸው ዐቃቤ ህግ ጉዳዩ የግድያ ወንጀል በመሆኑ መልስ ሰጭ ተገዶ ሊቀርብ
ይገባል ጠበቃውም ብቻውን ቀርቦ መልስ ይያያዝልኝ ማለቱ ተገቢነት የለውም በማለት
ተቃውሟል፡፡ ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ የሚከተለውን ብይን ሰጥቷል፡፡
‹‹የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/193 መልስ ሰጭው ወይም በጠበቃው አማካኝነት ቀርቦ መልስ እንዲያቀርብ
በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ ህጉም ግልጽ በመሆኑ መተርጎም አያስፈልገውም››፡፡35 በማለት የአቃቤ
ህግን ተቃውሞ ውድቅ በማድረግ የመልስ ሰጭን ጠበቃ መልስ ከመዝገቡ ጋር በማያያዝ
በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡
4.3. ክርክር መሃል ስለሚቀርቡ/ስለሚቀሩ ተከሳሾች

32
ዝኒ ከማሁ
33
አቶ ወልደኪሮስ አድማሱ የደቡብ ወሎ እና አካባቢዋ የፍትህ ቢሮ ቋሚ ምድብ ችሎት የስራ ሂደት አስተባበሪ
በቀን 3/8/2010 ዓ.ም የተደረገ ቃለ መጠይቅ
34
ከላይ በግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 20፣አንቀጽ 539(1)ሀ
35
ዐቃቤ ህግ እና አቶ ገብሬ መስፍን በጠቅላይ ፍርድ ቤት የጎንደር ቋሚ ምድብ ችሎት የወንጀል ይግባኝ ቁጥር
02- 01303 በቀን11/04/2010 ዓ.ም የተሰጠ ውሳኔ
በተግባር የሚታዩ ችግሮች ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱ ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩ መታየት
ከጀመረ በኋላ ተከሳሽ በፖሊስ ተይዞ ወይም በራሱ አነሳሽነት ቢቀርብ ጉዳዩ እንዴት ሊወሰን
ይገባል የሚለው ነጥብ ነው፡፡ ተከሳሽ ከመጀመሪያውኑ ሳይገኝ በመቅረቱ ወይም በክርክሩ
መሃል ባለ በአንዱ ሂደት ሲቀር የመዝገቡ ውጤት ምን ይሆናል የሚለው ነጥብ
በባለሙያዎች ዘንድ የተለያዩ አቋሞች ፈጥሯል፡፡36 ሌላው ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚነሳው
አሳማኝ በሆነ ምክንያት መቅረቱን የሚያሳይ ማስረጃ በማቅረቡ ምክንያት ክርክሩን ወደ ኋላ
ሊመለስበት የሚያስችል የስነስርአት አካሄድ በህጋችን ማእቀፍ ስር አለ ወይ ይህስ በተግባር
በሚገጥምበት ግዜ እንዴት ተደርጎ ክርክሩ ወደኃላ ሊመለስ ይገባዋል የሚለው ጥያቄ ነው፡፡
ጉዳያቸው በሌሉበት እየታየ ባለበት የክርክር ሂደት መሀል ላይ ተከሳሽ በመቅረቡ ምክንያት
የተሰጠ ውሳኔን ለማሳየነት እንመልከት፡፡
37
ተከሳሾች የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1)ሀ እና 671(1)ሀእናለ በመተላለፍ ግምታቸው 30,000
የሚያወጡ ከብቶችን በመሳሪያ በማስፈራራት ከግብረአበሮቻቸው ጋር የወሰዱ በመሆናቸው
ከባድ ውንብድና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው አንደኛው ተከሳሽ በአድራሻው ሊገኝ
ባለመቻሉ የጋዜጣ ጥሪ ከተደረገለት በኋላ ፍርድ ቤቱ በሌለበት ጉዳዩ እየታየና ተከሳሽ
እንዲከላከል ብይን በተሰጠበት የክርክር ሂደት ላይ ፖሊስ ተከሳሽን አድኖ በመያዙ ምክንያት
ፍርድ ቤት ተከሳሹን በክርክሩ ውስጥ በማስገባት እና ክርክሩ ከደረሰበት እንዲቀጥል በማድረግ
በብይኑ መሰረት ተከሳሹ የመከላከያ ምስክሮች አቅርቦ እንዲያሰማ አድርጓል፡፡ ተከሳሽም ላይ
የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ተከሳሽም በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ38
ቅሬታውን በማቅረብ የአቃቤ ህግ ምስክሮች በሌለሁበት የተሰሙ በመሆኑ የተሰጠው ውሳኔ
አግባብነት የሌለውም በመሆኑ እንዲሻርልኝ በማለት ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤትም ጉዳዩን ተመልክቶ
የሚከተለውን ወስኗል፡፡
‹‹ በሌለበት ታይቶ ውሳኔ እንዲወሰን ብይን የተሰጠበት ተከሳሽ ጉዳዩ ፍጻሜ (ፍርድ)ከማግኘቱ
በፊት ቢገኝ በፖሊስ ተገዶ ወደ ፍርድ ሊገባ ይገባል ወይ የሚለውን የሚገዛ ግልጽ ድንጋጌ

36
አቶ ቸርነት ተገኘ የሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት 15/05/2010ዓ.ም የተደረገ ቃለ መጠይቅ ፡፡
ተከሳሽ በሌለበት የሚታዩ ጉዳዮችን በተመለከተ የአሰራር ክፍተቶች በዞኑ በመኖራቸው ከጠቅላይ ፍርድ ቤት
የሰበር ዳኞች ባለሙያዎችን በማስመጣት ፍርድ ቤቱ ስልጠና የሰጠ መሆኑና ይህም ስልጠና በአሰራር ላይ
የሚታዩ የትርጉም ልዩነቶችን በማንሳት ለባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን ጠቅሰዋል፡፡
37
ዐቃቤ ህግ እና በላይ መንጌ የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል መዝገብ ቁጥር 02-10881
20/10/2009 ዓ.ም የተሠጠ ውሳኔ እንሁም የግርጌ ማስታወሻ 21
38
በላይ መንጌ እና ዐቃቤ ህግ(ይግባኝ) በወንጀል ይግባኝ መዝገብ ቁጥር 02-04202 በቀን ህዳር 19/2009ዓ.ም
የተሰጠ ውሳኔ
የለም እንዲህ ከሆነ ደግሞ ፍርድ ቤቱ የተከሳሽን መብት በማያጣብብ መልኩ ህጉ ፍፃሜ
የሚያገኝበትን (የተሻለ ውጤት) አተረጓጎም ሊከተል ይገባው ነበር፡፡ ይግባኝ ባዩ በችሎት ተገኝቶ
በሌለሁበት የተደረገው ክርክር ተሰርዞ ባለሁበት የአቃቤ ህግ ምስክሮች ይሰሙ በማለት
ያቀረበው ክርክር አግባብነት ያላቸውን ስነ ስርአት ህግ ድንጋጌዎች ባማከለ ሁኔታ አይቶ
ማስተናገድ ሲገባው ክርክሩ ወደ ኋላ አይመለስም ነገርግን የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ቃል
ተገልብጦ ለይግባኝ ባዩ ደርሶት እና መከላኪያ ማስረጃ ያሰማ በማለት ብይን መስጠቱ ክርክሩ
በዘፈቀደ በሆነ የፍርድ ሂደት እንዲመራ አድርጎታል፡፡ በአጠቃላይ ክርክሩ ከፊሉ ተከሳሽ
በሌለበት ከፊሉ ተከሳሽ ባለበት መሆኑን መዝገቡ የሚያሳይ በመሆኑ ይህ ደግሞ በወንጀል ስነ
ስርአት ህጉም ሆነ በወንጀል ሙግት ስርአት ውስጥ እውቅና ያልተሰጠው ኢ-ስነ ስርአታዊ
የሆነ የፍርድ ሂደት ሆኖ አግኝተነዋል›› በማለት የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር
የአሁን ይግባኝ ባይ ባለበት የአቃቤ ህግ ምስክሮች እንዲሰሙ እና ቀጣይ ሂደቱም ስነስርአታዊ
ህጉን ተከትሎ በይግባኝ ባይ ላይ ተገቢ ነው ያለውን ውሳኔ እንዲሰጥ በነጥብ መልሷል፡፡
4.4.ጉዳያቸው በሌሉበት የታየ ተከሳሾች ያላቸው መፍትሄዎች ዙሪያ የሚታዩ ችግሮች
Ø ጉዳያቸውን ሊታይ የሚገባው በየትኛው ፍርድ ቤት ነው
ተከሳሽ በሌለበት የተደረጉ ውሳኔዎች እንዲነሱ የሚቀርቡ አቤቱታዎች በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.198
መሰረት ጉዳዩን ላየው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡ የቀረበውን ምክንያት አሳማኝ መሆኑን ይኸው
ፍርድ ቤት ከተቀበለው በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.202 መሰረት ጉዳዩን ስልጣን ላለው ሌላ ፍርድ ቤት
እንዲወስንበት እንደሚያስተላልፍ በስነስርአቱ ተደንግጓል፡፡ ሆኖም በአሰራር ደረጃ ጉዳዩን ያየው
ፍርድ ቤት ተከሳሽ አሳማኝ የሆነ ምክንያት አቅርቦ ሲገኝ እንደገና ጉዳዩን በዚያው ፍርድ ቤት
የማየት አሰራር አለ፡፡39
ጉዳዩን እንደገና ማየት
በሌለበት ጉዳዩ ታይቶ ውሳኔ የተሰጠው ማንኛውም ሰው ውሳኔውን ለሰጠው ፍርድ ቤት
አቤቱታ ማቅረብ (opposition) ይችላል፡፡ ይሁንና ነገሩ እንደገና ታይቶ ከዚህ በፊት የተሰጠበት
ውሳኔ እንዲነሳለት ለማድረግ በቂ ምክንያት (just cause) ማቅረብ መቻል አለበት፡፡ በመሆኑም
ወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ199 መሰረትም በሌለበት የተሰጠው ውሳኔ እንዲነሳ አመልካች ማሳየት ያለበት
ምክንያቶች (just cause) ተብለው ከተጠቀሱት ውስጥ ፡-
Ø እንዲቀርብ መጥሪያ ያልደረሰው እንደ ሆነ ማሳየት

39
ወንዳቸው ሰራው የማዕከላዊ ጎንደር አስተዳደር የወንጀል የስራ ሂደት የወንጀል ዐቃቤ ህግ ጋር
በቀን12/05/2010 የተደረገ ቃለ መጠይቅ
አንድ ተከሳሽ የተከሰሰበትን ወንጀል በግልፅ በሚያሳይ ሁኔታ እንዲሁም በተባለው ግዜና ቦታ
ባይገኝ የሚያስከትልበትን የወንጀል ተጠያቂነት በማሳወቅ ከሳሽ ግዴታውን መወጣቱን ለፍርድ
ቤቱ ማሳየት አለበት፡፡ ይህም ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው እና ካጸደቀቻቸው ስምምነቶች አንዱ
የሆነው የሲቪልና የፖለቲካል የቃል ኪዳን ሰነድ አንቀፅ 14(3)መ40 ላይ ከተጠቀሱት መብቶች
ውስጥ የሚካተት ነው፡፡ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚቴ በጄኔራል ኮሜንት
ቁጥር 32 ላይ በሰጠው ትንታኔ41 ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዮች ከመታየታቸው በፊት ከሳሹ አካል
ተከሳሽ በፍርድ ቤት እንዲቀርብ ጥረት ማድረጉን ለፍርድ ቤቱ ማሳየት ሊወሰዱ ከሚገባቸው
የጥንቃቄ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ መሆኑን በኮሜንቱ አስቀምጧል፡፡
በሃገራችን ብሎም በክልላችን ያለው የመጥሪያ አደራረስ መንገድ ኃላ ቀር ሊባል የሚችልና
የመጥሪያ አደራረስ ስርአት ለማስፈጸም የሚያስችል የራሱ የሆነ ተቋም የሌለው እና
በአብዛኛውም በፖሊስና በቀበሌ አስተዳደር ድጋፍ ላይ ያተመረኮዘ ነው፡፡ ምንም እንኳን
ሃገራችን ተቋሞችን ለማጎልበት የሚያስችል ሰፊ ነዋለ መዋይ ባይኖራትም የመጥሪያ አደራረስ
ስርአቱን በማሻሻል አሁን አሁን ሃገራችን ተጠቃሚ እየሆነች ያለችባቸውን የመገናኛ መንገዶች
ከመጠቀም አንጻር ሰፊ እጥረቶች ይታያሉ፡፡ ለአብነትም አመልካች42 በሌለበት የተሰጠው ውሳኔ
እንዲነሳለት አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ለዚህም አመልካች እንደ ምክንያት ያነሳው ከአድራሻው
ያልጠፋ እና መጥሪያ በአግባቡ ያልደረሰው መሆኑን በተጨማሪም የጋዜጣ ጥሪ ሳይደረግለት
የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ በኢ.ፌ.ድ.ሪ. ህገ-መንግስት አንቀጽ 20(4) በመጥቀስ በክሱ ወቅት
ሳይገኝ የቀረቡበትን ምስክሮች ሳይመረምር፣ የመከላኪያ ምስክርም ሳያሰማ የተሰጠው ውሳኔ
እንዲነሳለት ጠይቋል፡፡43 ይህንኑ አቤቱታ መሰረት በማድረግም ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ህግ መልስ
እንዲሰጥበት ያደረገ ሲሆን ዐቃቤ ህግም44 ተከሳሽ በአስመዘገበው አድራሻ የክፍሉ ፖሊስ
አፈላልጎ ሊያገኘው ያልቻለ በመሆኑ የጋዜጣ ጥሪ እንዲቀርብ በተደረገው መሰረትም ሊቀርብ
ባለማቻሉ የተሰጠው ውሳኔ የሚነቅፍ አይደለም በማለት ለፍርድ ቤቱ መልስ ሰጥቷል፡፡ ፍርድ
ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ አመልካች መጥሪያ በአግባቡ እንዳልደረሰው በበቂ
ሁኔታ ያላስተባበለ በመሆኑ ውሳኔውን አጽንቶታል፡፡

40
ከላይ የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 9
41
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚቴ በጄኔራል ኮሜንት ቁጥር 32
42
የወንጀል መዝገብ ቁጥር 02-03136 ፣በሌለበት የተሰጠ ውሳኔ እንዲነሳለት አመልካች ሄኖክ አለማየሁ በለጠ
ለአ.ብ.ክ.መ. ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደሴ ምድብ ችሎት በቀን 17/11/2009ዓ.ም. ማመልከቻ ያቀረበው
43
በአ.ብ.ክ.መ. ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደሴ ምድብ ችሎት የወንጀል መዝገብ ቁጥር 0203136 በቀን የተሰጠ ውሳኔ
44
በአብክመ ፍትህ ቢሮ የደሴ የወንጀል የስራ ሂደት በቁጥር ወ/የ/ሂ 241/2010 በቀን 20/02/2010ዓ.ም ለፍርድ
ቤቱ የጻፈው መልስ
በሌላ በኩል አቃቤ ህግ45 ተከሳሽ በስር ፍርድ ቤት የቀረበበትን ከባድ ውንብድና ወንጀል ፍርድ
ቤቱ ተከላክሏል በሚል በነጻ ማሰናበቱ በአግባቡ አይደለም በሚል ባቀረበው ይግባኝ ላይ መልስ
ሰጭን ፖሊስ በአድራሻው ፈልጎ ባለመቅረቡ እንዲሁም በአድራሻው አለመገኘቱንም ፖሊስ
በድብዳቤም ሆነ በአካል ቀርቦ እንዲያስረዳ በተደጋጋሚ ቀጠሮ ቢሰጥም ቀርቦ ሊያስረዳ
ባለመቻሉ ምክንያት ተከሳሽ በተገኘ ግዜ አቃቤ ህግ መዝገቡን የማንቀሳቀስ መብቱን ጠብቆ
መዝገቡ እንዲዘጋ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ይህም ውሳኔ መጥሪያ ለተከሳሽ በአግባቡ መድረሱን
ካልተረጋገጠ በስተቀር ጉዳዩ ማየት እንደማይቻልና ለተከሳሽ መጥሪያ የማደረስ ሃላፊነት
ያለበት አካል በአግባቡ ግዴታው እንዲወጣ የሚያደርግ ነው፡፡ መጥሪያ በአግባቡ አልደረሰኝም
በሚል የሚቀርቡ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚደረገው ምዘና ከጉዳይ ጉዳይ የሚለይ እና ለአንዱ
ፍርድ ቤት ተቀባይነት ያለው ጉዳይ በሌላ ፍርድ ቤት ተቀባይነት የሚያጣበት አግባብ አለ፡፡
በተለይም የጋዜጣ ጥሪን በተመለከተ ተከሳሽ አርሶ አደር በመሆኑ ማንበብም ሆነ መጽፍ
የማይችል፣ በሚኖርበት አካባቢ ጋዜጣ የማይደርስ እና ጋዜጣ የማንበብ ልምድ የለም በሚሉ
ምክንያቶች ጉዳዩች እንደገና እንዲታይ የሚደረጉበት አሰራሮች አሉ፡፡46
Ø ራሱ ወይም ጠበቃው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መቅረብ ያልቻሉ እንደሆነ
ከዐቅም በላይ የሆነ ችግር ተብለው የተጠቀሱት ምክንያቶች አሁንም ለፍርድ ቤቶች የተሰጠ
ፍቁደ ስልጣን ነው፡፡ በመሆኑም ከጉዳይ ጉዳይ የሚቀርቡላቸውን ከአቅም በላይ የሆነ ችግር
ተብለው ሊወሰዱ የሚገቡ ምክንያቶች መዝነው ውሳኔ እንደሚሰጡባቸው የድንጋጌው መንፈስ
ያሳየናል፡፡47 በተለይም ለፍርድ ቤቱ በአመልካቹ ከሚቀርቡ ከአቅም በላይ ተብለው ሊጠቀሱ
የሚችሉ ምክንቶች ውስጥ ህክምና ሲከታተሉ መቆየት፣ጸበል መክረም እንዲሁም ከሃዘን ጋር
የተያያዙ ጉዳዮች በአብዛኛው በምክንያትነት እንደሚቀርቡና የሚቀርቡትንም ምክንያቶች
በጥንቃቄ መመዘን ያስፈልጋል ብለዋል፡፡48

5.ችግሮቹ እንዴት ይፈቱ

5.1.የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.161 አተረጓጎም በፍርድ ቤቶች

45
አ.ብ.ክ.መ. ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባህር ዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፣ዐቃቤ ህግ እና መከተ አድማሱ
የመዝገብ ቁጥር 02-05173 በቀን 28/05/2010 የተሰጠ ውሳኔ ባህር ዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
46
አቶ በሪሁን አዱኛ በጠቅላይ ፍርድ ቤት በደቡብ ወሎ ዞን የወንጀል የስራ ሂደት አስተባባሪና ዳኛ ጋር ሚያዝያ
4/2010ዓ.ም የተደረገ ቃለ መጠይቅ
47
የግርጌ ማስታወሻ ፣199
48
የግርጌ ማስታወሻ 46
በዚህ ድንጋጌ ዙሪያ የሚቀርቡ አከራካሪ ትርጉሞችን የተመለከትን ሲሆን የህጎች የቃላት
አጠቃቀም አሻሚ በሚሆን ግዜ ድንጋጌውን ትርጉም በሚሰጥ መልኩ መተርጎም አንዱ
መፍትሄ ነው፡፡ ህግን ለመተርጎም ከሚረዱን ዘዴዎች አንዱ የህግ አውጭው አሳብ ምንድን
ነው የሚለውን መረዳት ቢሆንም ይህ ስነ-ስርአት ሲቀረፅ የነበሩ ውይይቶች ወይም ሃሳቦች
ምንድናቸው የሚለውን የሚመልሱልን ተደራጅተው የተቀመጡ ጽሁፎች አናገኝም፡፡49ሆኖም
የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.160 ይዘት ከልዩ ስነ ስርአቱ ጠቅላላ አላማ አንጸር በማየት ትርጉም ሊሰጠው
ይገባል፡፡ እንዲህም ሲሆን በወንጀል ህጉ የድንጋጌዎች አቀራረጽ ከ-እስከ በሚል የተቀመጡ
ከባድ ተብለው የሚጠቀሱትም ወንጀሎች ለምሳሌ እንደ ውንብድና፣ ተራ ሰው መግደል
መነሻቸው ዝቅ ብለው ተደንግገው የሚገኙ በመሆናቸው የቅጣት መነሻ ወለሉን በመተው
የቅጣት መድረሻውን ጣሪያውን በመመልከት በልዩ ስነስርአት ህጉ የሚታዩ ጉዳዮች እንዲሰፉ
ያደርጋል፡፡ ሌላው ከዚህ ጋር ተያይዞ አብሮ መነሳት ያለበት ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ
የሚፈለግበት አመክንዮ ሲሆን ይህም ውሳኔዎችን ከመቋጨት ጀምሮ የተፋጠነ የፍትህ አሰጣጥ
ስርአት በማስፈን ተከሻሹ ጭራሹኑ ሳይቀጣ እንዳይቀር በማድረግ የማህበረሰቡን ደህንነት
የማስጠበቅ አላማ እንዲሳካ የሚያደርግ ከመሆኑ አንፃር ድንጋጌውን በጠባቡ መተርጎም እና
ለጥቂት አናቅጽት ብቻ ስራ ላይ እንዲውል ማድረግ የዚህን ልዩ ስነስርአቱን ዓላማ የሚያጠብ
ይሆናል፡፡ ተከሳሽ በሌለበት የሚካሄድ የወንጀል ስነ-ስርአት ያላት ሃገር ተብላ የምትጠቀሰው
ፈረንሳይ ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩን ለማየት መለኪያ መስፈርት አድርጋ የምትገለገለው
የተፈፀመው ወንጀል ከባድ ወንጀል (FELONY) መሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ በፍርድ ቤቱ
ማጅስትሬት (magistrate) አማካኝነት ከባድ ወንጀል ይዘት አላቸው ተብለው በወንጀል ህጉ
የተደነገጉትን ብቻ ሳይሆን የወንጀሉን አፈጻፀም በመለካት አሲዝ (Assize) ለተባለው የፈረንሳይ
ከፍተኛው የመጀመሪያ ፍርድ ቤት( highest court of first instance) አጣርቶ በመላክ
ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ ይደረጋል፡፡50 በሌላ በኩል በእንግሊዝ ተከሳሽ በሌለበት
ክርክሮች የማድረግ ስርአት በኬዝ ሎውም ሆነ በህግ ዳብሮ ባናገኘውም መብታቸውን
በፍቃደኝነት ለሚተው( waiving of rights consensually) ሰዎች በሌሉበት ጉዳያቸውን

49
Ethiopian Criminal Procedure Teaching Material ,History of Ethiopian Criminal
Procedure,Aderajew Teklu and Kedir Mohammed, Justice and Legal System Research Institute
https://chilot.me/wp-content/uploads/2011/06/criminal-procedure.pdf Accessed at 20/7/2018
4:30a.m.
50
ከላይ በግረጌ ማስታወሻ ቁጥር 14፣እንዱሁም Ade'har Esmein, A history of continental criminal
procedureP.62-63(1913).
የሚታይበት ስርአት የተዘረጋ ሲሆን ይህም ስነስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ የሚፈቀደው ቀላል
ለሆኑ ወንጀሎች ብቻ ነው፡፡51 ከላይ የጠቀስኳቸው የሃገራቱ ልምድ የሚያሳየን ተከሳሽ
በሌለበት ጉዳዮችን ለማየት መስፈርት ተደርጎ የሚወሰደው ከሚያስቀጣው የቅጣት መጠን
ይልቅ የወንጀሉ ከባድነት ወይም ቀላልነት ላይ የተመረኮዘ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም
በሃገራችን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ስነስርአት ላይ የተጠቀሰው የቅጣት መጠን የወንጀሉን
ከባድነት ወይም ቀላልነት ከመለካት አኳያ ተደርጎ ቢወሰድ በተሻለ መልኩ ድንጋጌዎችን በስራ
ላይ የሚያውል አሰራር ይፈጥራል፡፡ አሁን በረቂቅ ላይ ያለው የወንጀል ስነስርአትም ይህን
መመዘኛ የተጠቀመ መሆኑን ማየት እንችላለን፡፡52
ከዚህ በተጨማሪም ከዚህ በፊት ሲያገለግል የነበረው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ከተቀየረ እና
በአዲስ የወንጀል ህግ ከተተካ በኋላ እሱን ተከትሎ መቀየር የነበረበት የወንጀለኛ መቅጫ
ስነስርአት ህግ ሳይሻሻል በመቅረቱ ምክንያት በስነስርአቱ ላይ የተቀመጡትን ድንጋጌዎችን ወደ
ድሮው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ድንጋጌዎች ጋር ወስዶ በማያያዝ ሲተረጎሙ ይታያል፡፡ ይህም
በመሆኑ የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት በአዲሱ የወንጀል ህግ የተሻሻሉና የተለወጡ ሁኔታዎች
በተመለከተ ከወንጀለኛ መቅጫ ስነስርአት ህግ ድንጋጌዎች ጋር ያላቸውን ተፈጻሚነትና ፍርድ
ቤቶች ሊከተሉት የሚገባ የህግ አተረገጓም ምን መሆን አለበት የሚለውን እንደሚከተለው
አስቀምጧል፡፡53
‹‹ …ሆኖም ህግ አውጭው በአዲሱ የወንጀል ህግ ያወጣቸውና ያሻሻላቸውን ጉዳዮች ባሉበት
ሁኔታ በቀጥታ ከነበረው የስነስርአት ህግ ድንጋጌዎች ጋር ተጣጥመው ተፈፃሚ እንዲሆኑና
እንዲተረጎሙ ፍላጎትና ሃሳብ አለው ተብሎ መወሰድ ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም በአዲሱ የወንጀል
ህግ ቅጣታቸው ከፍ ብሎ የተደነገጉ ወንጀሎች የዋስትና ጥያቄና ተከሳሽ በሌለበት እንዲታይ
የሚቀርቡ ስነስርአት ጥያቄዎች 1949 ዓ.ም በወጣው የወንጀለኛ መቅጫ ስነስርአት ህግ

51
Criminal Justice Act 1988, s.134.፣እንዲሁም Kenneth A. Goldman ,Criminal Waiver: The
Requirements of Personal Participation, Competence and Legitimate State Interest, California Law
Review vol.54 p.1275
52
የኢፌድሪ የወንጀል ስነስርአት ህግ ረቂቅ አዋጅ
በዚህም ረቂቅ የወንጀል ስነስርአት ህግ ላይ ለአምስት ተከታታይ ቀጠሮ ተከሳሽ መቅረብ ያልቻለ እንደሆነ ፍርድ
ቤቱ ጉዳዩ በሌለበት እንዲታይ እንደሚወስንና በሌለበት ሊታዩ የሚገባቸውም ወንጀሎች ከቀላል ወንጀሎች ውጭ
መሆን አለባቸው በሚል ያስቀምጣል፡፡
53
የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ እና አቶ ተመስገን አዲስ የሰበር መዝገብ ቁጥር 35695 ፣ቅፅ 9፣ህዳር 11/2001
ዓ.ም ውሳኔ ያገኘ፡፡
የነበረውን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ትርጓሜ መስጠት ሳያስፈልግ የስነስርአት ህጉን
ከአዲሱ የወንጀል ድንጋጌዎች ጋር በቀጥታ አጣምሮ ማየት ይኖርባቸዋል፡፡››
የዚህም የሰበር ውሳኔ ይዘት የአዲሱን የወንጀል ህግ እና የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አጣጥሞ
መተርጎም ማስቻል እና ተከሳሽ በሌለበት የሚታዩ ጉዳዮችን በተመለከተ ወደ ድሮ የወንጀለኛ
መቅጫ ህግ ጋር ሄዶ ማጣቀስ ሳያስፈልግ በአዲሱ የወንጀል ህግ የተቀመጡ የቅጣት
ድንጋጌዎችን ከስነስርአት ህጉ ድንጋጌዎችን ጋር ተጣጥመው በመተርጎም እንዲሰሩ ነው፡፡
በአጠቃላይ ‹‹12 አመት በታች በማያንስ የሚያሳስር ወንጀል የሰራ›› የሚለው የድንጋጌው
የቋንቋ አጠቃቀም ችግር ያለበት ቢሆንም ከድንጋጌው ጠቅላላ መንፈስ የምንረዳው የተፈጸመው
ወንጀል ከባድነት ለማሳየት የቅጣቱ መጠን መቀመጡን ነው፡፡ ሌላው በወንጀል ህጉም ሆነ
በሌሎች አዋጆች የተቀመጡት ድንጋጌዎች አቀራረጽ ከጥቂት ወንጀሎች በስተቀር መነሻ
ቅጣታቸው ዝቅ ያለ በመሆኑም 12 አመት ቅጣትን መነሻ አድርጎ መውሰድ የልዩ ስነስርአት
ህጉን አላማ እንዲሳካ አያደርገውም፡፡
5.2. በይግባኝ ስርአት ስር ተከሳሽ በሌለበት የሚካሄዱ ክርክሮች
በይግባኝ ስነ ስርአት ጉዳዩ በሌለበት መታየት የሚችለው መልስ ሰጭ ራሱ ወይም ጠበቃው
መቅረብ ካልቻሉ ነው፡፡ ይህም ከመደበኛ ክርክሮች በተለየ በጠበቃ መወከል ከቻለ በግዴታ
መቅረብን ከማስቀረቱም ባሻገር በሌለበት የሚደረግ ክርክር (default) ተግባራዊ አይደረግም፡፡
በይግባኝ ግዜ ጉዳዩ ልክ እንደ መጀመሪያ ክርክር በሌለበት ታይቶ ሊወሰን የሚችለው መልስ
ሰጭው ወይም ጠበቃው መቅረብ ሳይችሉ ሲቀሩ ብቻ ነው፡፡ ከላይ እንደተመለከትንው በዚህ
ዙሪያ የሚነሱ ክርክሮች ውስጥ የወንጀል ጉዳይ ግላዊ በመሆኑ ራሱ ተከሳሹ በአካል መገኘት
አለበት የሚል እና የክርክሩን የመጨረሻ ውጤት አይቶ ሊጠፋ የሚችልበት አግባብ ስለሚኖር
በይግባኝ ወቅት መልስ ሰጭ መቅረብ አለበት፡፡ ምንም እንኳን የተጠቀሰው ምክንያት በተግባር
የሚታይ ችግር ቢሆንም ተገዶ እንዲቀርብ ለማድረግ ግን አያበቃም፡፡ ምክንያቱም በስነስርአት
ህጉ በአማረኛውም ሆነ በእንግሊዘኛው ትርጉም በማያሻማ መልኩ በአማራጭ በጠበቃው በኩል
የይግባኝ ክርክሩን መከታተል መልስ ሰጭ እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም ተከሳሾችን
በአድራሻ በማፈላለግ የተላለፈባቸውን ውሳኔ ተግባራዊነት የሚያስፈጽም የፖሊስ አካል በበጀት
እና በሰው ሃይል በማደራጀት ከህግ የመሸሸግ ችግር መቅረፍ የሚቻል ሲሆን
የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/193(2) ግን መተርጎም የማያስፈልገው ግልጽ ድንጋጌ በመሆኑ እንዲሁ
ተግባራዊ ማድረጉ የተሻለ አሰራር ይፈጥራል፡፡
5.3.በክርክር መሃል ተከሳሾች ስለመቅረብና ስለመቅረት

ተከሳሾች በክርክር መሃል ቢቀርቡ ወይም በክርክር መሃል ቢቀሩ ጉዳያቸው እንዴት
መስተናገድ ይችላል የሚለውን የሚገዛ ድንጋጌ በስነ ስርአት ህጋችን ስር የለም፡፡ በተለይ
ጉዳያቸው በሌሉበት እየታየ ከፍርድ በፊት ቢቀርቡና ላለመቅረባቸውም በቂ ምክንያት ያላቸው
ከሆነ ተጀምሮ በነበረው ክርክር ላይ ውሳኔ ማሳረፍ ሳያስፈልግ ተከሳሽ ባለበት እንደገና ክርክር
ማድረግ የተሸለ አሰራር ይፈጥራል፡፡ ይህም ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን ሳያስገባ ውሳኔ በጉዳዩ ላይ
ቢሰጥበትም ተከሳሽ በቂ ምክንያት እስካቀረበ ድረስ ጉዳዩ እንደገና የሚታይበት የህግ ማዕቀፍ
በመኖሩ ነው፡፡ በመሆኑም ክርክሩ አንዴ ከተጀመረ በሚል ማስቀጠሉ የተፋጠነ ፍትህ
ከመስጠት እንዲሁም ውሳኔዎችን ሳይንዛዙ መቋጨት ያስችላል፡፡

5.3.በክርክር መሃል ተከሳሾች ስለመቅረብና ስለመቅረት

በመሰረቱ ተከሳሽ በክርክር መሃል ቢቀርብ ወይም በክርክር መሃል ቢቀሩ ጉዳያቸው እንዴት
መስተናገድ ይችላል የሚለውን የሚገዛ የስነስርአት ድንጋጌ የለም፡፡ በተለይ ጉዳያቸው በሌሉበት
እየታየ ከፍርድ በፊትም ቢቀርቡና ላለመቅረባቸው በቂ ምክንያት ያላቸው ከሆነ ተጀምሮ
በነበረው ክርክር ላይ ውሳኔ ማሳረፍ ሳያስፈልግ ተከሳሽ ባለበት እንደገና ክርክር ማድረግ
ይቻላል፡፡ ይህም ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን ሳያስገባ ውሳኔ በጉዳዩ ላይ ቢሰጥበትም ተከሳሽ በቂ
ምክንያት እስካቀረበ ድረስ ጉዳዩ እንደገና የሚታይበት የህግ ማዕቀፍ በመኖሩ ነው፡፡
በመሆኑም ክርክሩ አንዴ ከተጀመረ በሚል ማስቀጠሉ የስነ ስርአት ህጉን አላማ እንዲሳካ
አያደርገውም፡፡

በሌላ በኩል በቂ ምክንያት ሳይኖራቸው ጉዳያቸው በሌሉበት በመታየት ላይ እያለ ተከሳሾች


ቢቀርቡ ሊደረግ የሚገባው ምንድን ነው የሚለው በተግባር የሚገጥም ችግር ነው፡፡ ተከሳሹ
በፖሊስ ተይዞም ይሁን በራሱ ተነሳሽነት በክርክር መሃል ከቀረበ ከደረሰበት የክርክር ሂደት
ጀምሮ ተሳታፊ ማድረግ ሊወሰድ የሚገባ አማራጭ ነው፡፡ ይህም የተከሳሽን የመከላከል እና
በክርክር ወቅት የመገኘት መብቱን አስፍቶ በማየት በህጉ ያልተሸፈነውን ይህን የስነስርአት
ክፍተት መሙላት ይቻላል፡፡ በክስ ሂደት ላይ የመገኘት መብት እና የመከላከል መብት ህገ
መንግስታዊ መብት ሲሆኑ እነዚህን መብቶች ያለበቂ ምክንያት ያልተጠቀመበት በመሆኑ
እስከመጨረሻው የክርክሩ አካል ልትሆን አይገባም ሊባል ግን አይችልም፡፡ አንድ ተከሳሽ
በሌለበት የተሰጠበት ውሳኔ እንደገና ሊታይለት የሚቻልባቸው ምክንያቶች በስነስርአት ህጉ
የተቀመጡ ሲሆን ይህን አሟልቶ ካልተገኘ በቅጣቱ ላይ ካልሆነ በቀር ምንም አይነት አማራጭ
አይኖረውም፡፡ በመሆኑም በደረሰበት የክርክር ሂደት ገብቶ መከራከሩ እራሱን እንዲከላከል
የሚያግዘው ሲሆን ሌላው የቅጣት ማቅለያዎችንም እንዲያቀርብ ይረዳዋል፡፡ እነዚህ መብቶች
ደግሞ ለተከሳሹ የተሰጡ መብቶች በመሆናቸው በስነስረአታዊ ህጎች አመራር ሊሸረሸሩ
አይገባም፡፡ ምክንያቱም የስነስርአት ህጎች ጠቀሜታም ክርክሮችን ከማሳለጥ ባሻገር መብቶችም
ተፈጻሚ እንዲሆን ማስቻል በመሆኑ ነው፡፡
ስለዚህ ተከሳሽ በመብቱ ያልተጠቀመበትን የክርክር ሂደት እንዲያልፈው በማድረግ ከደረሰበት
እንዲቀጥል ማስቻል ለተከሳሽ የተሻለ መብት የሚሰጥ በመሆኑ ተግባራዊ ቢደረግ የሚታየውን
ክፍተት የሚሞላ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጉዳዩ በሌለበት በመታየት ላይ እያለ የተያዘ ተከሳሽ
በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ተመልክቶ ባለበት እንዲታይ ሊወስን እንደሚችል ረቂቅ
የስነስርአት ህጉ ሲያስቀምጥ ይህም ለፍርድ ቤቱ ፍቁደ ስልጣን ላይ የተመረኮዘ መሆንኑን
የድንጋጌው መንፈስ ያሳየናል፡፡54 ይህም አሁን በተግባር እየታየ ያለውን ተግባራዊ ችግር ረቂቅ
አዋጁ ወደስራ ሲገባ እንደሚቀርፈው ይገመታል፡፡
በሌላ በኩል ጉዳያቸው ባሉበት ሲታይ ቆይቶ የክርክሩን አዝማሚያ በማየት የሚቀሩ ተከሳሾችን
በተመለከተ መብታቸውን እንደተው ተቆጥሮ ፍርድ ቤቶች በጉዳዩ ላይ ውሳኔ መስጠት
የሚችሉ መሆኑን የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 12781355 ውሳኔ
ሰጥቶበታል፡፡
5.4.በሌሉበት የተሰጡ ውሳኔዎች ከተነሱ በሃላ ማየት ያለበት አካል
የዚህ ድንጋጌ አላማ ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩን ያያው ፍርድ ቤት ነገሩን እንደገና ተከሳሽ ባለበት
ቢያየው ከአድሎ ነጻ አይሆንም በሚል እሳቤ የተቀረፀ መሆኑን ከድንጋጌው ይዘት መረዳት
ይቻላል፡፡ አሁን በተግባር ያለው አሰራርም በዚያው ፍርድ ቤት ጉዳዩ እየታየ ያለበት አግባብ
በመኖሩ በህግ አውጭው ሃሳብ እና በተግባራዊ አፈጻጸም ላይ ክፍተት ያለ በመሆኑን ይህን
ሊያርም የሚችል አሰራር በፍርድ ቤቶች አስተዳደር ተግባራዊ ሊደረግ ይገባዋል፡፡
5.5.የመጥሪያ አደራረስ ስርአትን ማሻሻል
የመጥሪያ አደራረስ ስርአት በአግባቡ ለተከሳሽ ለማድረስ በሚያስችል መልኩ ያልተቀረፀና
የጋዜጣ ጥሪንም አስመልክቶ ከሚቀርቡ አቤቱታዎች መሃከልም በስርጭትም ይሁን ጋዜጣ
በማንበብ ልምድ እጥረት ሊያስተላልፈው የሚገባው መልክት ለተፈላጊው ሰው ሳይደርስ
ይቀራል፡፡ በተለይም ፖሊስን፣ቀበሌ አስተዳደርን በመጠቀም መጥሪያ የማስተላለፍ ስርአትም

54
ከላይ በግርጌ ማስታወሻ 44፣ አንቀጽ 291.
55
ከላይ በግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 22
ከሰው ሃይል ማነስ፣ከበጀት ችግር አንጻር ተደራሽነቱ አናሳ በመሆኑ በአግባቡ የመጥሪያ
አደራረስ ስርአት እየተከናወነ ነው ለማለት አይስደፍርም፡፡ ይህንንም ችግር አሁን ካለበት ኋላ
ቀር አሰራር ለመቀየር በማሰብ በረቂቅ አዋጁ ላይ የመጥሪያ አደራረስ ስርአት ተከሳሽ
ከሚኖርበት ቀበሌ አማካኝነት መጥሪያ እንዲደርሰው ማድረግ፣ በአጭር የጽሁፍ መልእክት፣
በስልክ፣ በፋክስ ፣በድህረ ገጽ ወይም በፖሰታ በእነዚህ መንገዶች ማድረስ ካልተቻለ መገናኛ
ብዙሃን በመጠቀም ለተከሳሹ መጥሪያ እንዲደርሰው ማስቻል ሲሆን በሌላ በኩል ላቅመ አዳም
ለደረሰ የቤተሰቡ አባል መጥሪያ የማድረስ ስርአትን በውስጡ አካቶ ይዟል፡፡56 በመሆኑም ይህ
አሰራር አሁን ካለው የመጥሪያ አደራረስ ሰፋ ያለ አማራጮችን ይዞ በመቅረቡ በዚህ ዙሪያ
እየተፈጠሩ የሚገኙ ችግሮችን በእጅጉ ይቀንሳል ተብሎ ይታሰባል፡፡ በዚህ ረቂቅ አዋጅ ስለ
መጥሪያ አደራረስ ስርአት መርህ በአንቀፅ 276(3) ሲያስቀምጥ ‹‹ፍርድ ቤቱ በዚህ ሕግ
መሰረት መጥሪያ ባልደረሰውና ባልቀረበው ተከሳሽ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ ወይም ሂደት
በሌለበት እንዳልተሰጠ ይቆጠራል››57በማለት የሚደነግግ ሲሆን ይህም መጥሪያ እንዲሰጥ
ሃላፊነት የተጣለበት አካል ሃላፊነቱን በአግባቡ (due diligence) እንዲወጣ ከፍተኛ ግዴታ
የሚጥል ነው፡፡ በአጠቃላይ መጥሪያ አደራረስ ስርአት ላይ የሚታዩትን ከፍተኛ የተግባር
ክፍተቶች የመጥሪያ አደራረስ ዘዴዎችንም ዘመኑ ወደደረሰባቸው ግኝቶች መቀየር መፍታት
ይገባል፡፡
6.ማጠቃለያ
ተከሳሽ በሌለበት የሚካሄዱ ክርክሮች በአንድ በኩል የተከሳሹን መብት በሌላ በኩል
የህብረተሰቡን መብት ባማከለ ልዩ ሁኔታ የሚፈቀድ የክርክር ስርአት ነው፡፡ በዚህ ልዩ
የስነስርአት ህግ ስር የተቀመጠው ድንጋጌ ይዘት ግልጽነት ችግር ያለበት ሲሆን የተዘበራረቁ
አሰራሮችንም ፈጥሯል፡፡ እነዚህን የትርጉምና ብሎም የአሰራር ልዩነቶች ለማጥበብ የሚያስችል
የስነስርአት ህግ ማሻሻልም ሆነ ገዢ የሆነ ወጥ ትርጉሞች እስካሁን አልተሰጠም፡፡ በክልሉም
በሚገኙ ፍርድ ቤቶች ስር ተከሳሽ በሌለበት የሚደረጉ ክርክሮች ላይ የሚንጸባረቁ የስነስርአት
ድንጋጌዎች አተረጓጎም እና አተገባበር መለያየት ተገማች እና ወጥነት ያላቸውን ውሳኔዎች
ለመስጠት ተግዳሮት ፈጥሯል፡፡

56
የግርጌ ማስታወሻ 44
57
ዝኒ ከማሁ
በምርመራ ወቅት በፖሊስ ጣቢያ የተሰጠ የምስክሮች ቃል በፍርድ ቤት እንዲቀርብ
ስለሚደረግበት የህግ አግባብ፣ በፍርድ ቤት ያለው ተቀባይነትና ተግባራዊ አፈጻጸሙ በአማራ
ክልል ፍርድ ቤቶች፡፡

በሰለሞን ተገኘወርቅ1

አጽርኦተ ይዘት

ይህ አጭር ጽሁፍ ትኩረት የሚያደርገው በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ ቁጥር (ወ.መ.ስ.ስ.ህ.ቁ.)


145 ስር ተደንግጎ የሚገኘው ለፖሊስ የተሰጠ የምስክርነት ቃል ክሱን በሚሰማው /በሚያከራክረው/
ፍርድ ቤት ፊት ተቀባይነት የሚኖረውና ፍርድ ቤቱ ማስረጃውን እንደ ማስረጃ የሚቀበለው በምን
ሁኔታና ለምን ዓላማ ነው የሚለውን ነጥብ የሚመለከት ነው፡፡ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ
በግልጽ እንደተመለከተው ለፖሊስ የተሰጠ የምስክርነት ቃል በፍርድ ቤት ሊታይና እንደ ማስረጃ
ሊወሰድ የሚችል መሆኑ አከራካሪ ጉዳይ አይደለም፡፡ አከራካሪው ጉዳይ ፍርድ ቤት ይህን ማስረጃ እንደ
ማስረጃ የሚቀበለው ምን ሁኔታ ሲያጋጥምና በምን መልኩ ነው? የሚለው ነው:: የዚህን ድንጋጌ
አፈጻጸም በሚመለከት በባለሙያዎች ዘንድ የተለያዩ ግንዛቤዎች እንዳሉ ይስተዋላል፤ በተግባርም
በፍርድ ቤቶች ዘንድ የተለያዬ ትርጉም እየተሰጠ ሲሰራ እንመለከታለን፡፡ በብዙ ባለሙያዎች ዘንድ
ያለው ግንዛቤና በተግባርም በስፋት የሚሰራበት ለፖሊስ የተሰጠ የምስክርነት ቃል ፍርድ ቤት
ሊመለከተው የሚችለውና እንደ ማስረጃ የሚቀበለው ቀደም ሲል ስለወንጀሉ ፈጻሚና አፈጻጸም ማስረጃ
በመሆን ለፖሊስ ምስክርነታቸውን የሰጡ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ጉዳዩን ለማየት /ለማከራከር/ ስልጣን
ባለው ፍርድ ቤት በበቂ ምክንያት ቀርበው መመስከር ሳይችሉ ሲቀሩ ለፖሊስ የተሰጠው ምስክርነት
ፍርድ ቤቱ እንደሚመለከተውና ከማስረጃ ሚዛን ውስጥ በማስገባት ማስረጃውን መዝኖ እንዲሰራበት
ተብሎ የተደነገገ እንደሆነ የሚከራከሩ አሉ፤ በዚሁ ግንዛቤ መሰረትም ይሰራሉ:: በሌላ በኩል ይህንን
ሀሳብ የሚቃወሙ ባለሙያዎች እንደሚሉት ለፖሊስ የተሰጠ የምስክርነት ቃል ፍርድ ቤት ሊቀበለውና
ድንጋጌውም ተፈጻሚ የሚሆነው የዐቃቤ ህግ ምስክሮች የሰጡት የምስክርነት ቃል ጉዳዩን በሚያየው
ፍርድ ቤት ፊት ቀርበው የሰጡት የምስክርነት ቃል ለመርማሪ ፖሊስ ከሰጡት ቃል ጋር ተቃራኒ
/አስጠቂ/ በሆነ ጊዜ ነው በማለት ሀሳባቸውን ያስቀምጣሉ፡፡

በባለሙያዎች ዘንድ ከላይ የተመለከቱት ሁለት ዓይነት ግንዛቤዎችና አሰራሮች ቢኖሩም የህግ አውጭው
ሀሳብና የድንጋጌው አላማ በፖሊስ የተሰጠ የምስክርነት ቃልን ፍርድ ቤት ሊመለከተው የሚችለው
ሰነዱ ኮፒ ተደርጎ እንደ ጽሁፍ ማስረጃ ዓይነት ሳይሆን የዓቃቤ ህግ ምስክሮች በፍርድ ቤት ቀርበው
የሰጡት ቃል ቀደም ሲል ለመርማሪ ፖሊስ ከሰጡት ቃል ጋር የሚቃረን /አስጠቂ/ ሲሆን ይህንኑ

1
ሰለሞን ተገኘወርቅ (LLB, LLM) ቀደም ሲል በአብክመ ፍትህ ባለሙያዎች ማሰልጠኛና ህግ ምርምር ኢንስቲትት የሰሩ ሲሆን
በአሁን ወቅት በአብክመ ፍትህ ቢሮ የክልል ዐቃቤ ህግ ሆነው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡
በፍርድ ቤት የተሰጠውን ምስክርነት ውሸት መሆኑን ለማስተባበል ሲባል ፍርድ ቤቱን አስፈቅዶ ዐቃቤ
ህግ ወይም ተከሳሽ በመሪ ጥያቄ ወይም በመስቀለኛ ጥያቄ አማካኝነት የተሰጠውን የምስክርነት ቃል
ማስተባበል እንዲችሉ በማሰብ የተቀረጸ ድንጋጌ እንደሆነ ግንዛቤ መያዝ ይገባል፡፡

1. ስለምስክርነት አንዳንድ ነጥቦች

ማስረጃ የአንድን አከራካሪ ጭብጥ መኖር ወይም አለመኖር በማረጋገጥ የዳኛን አእምሮ
በማሳመን ወደ አንድ ድምዳሜ ላይ የሚያደርስ ፍሬ ነገር ነው2፡፡ በወንጀል ምርመራ ሂደት
ውስጥ ጠንካራ የሆነ የወንጀል ምርመራ ስርዓት አለ ሊባል የሚችለው ስለወንጀሉ አፈጻጸም
በሚመለከት በዝርዝር ሊያስረዱ የሚችሉ ማስረጃዎችን ሰብስቦ አጥፊውን ፍርድ ቤት አቅርቦ
ጥፋተኛ ለማስባል የሚያስችል አሳማኝና በቂ ማስረጃ በህግና በስርዓት መሰብሰብ ሲቻል ነው፡፡
በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ውስጥ የአንድን የወንጀል ድርጊት መፈጸምና አለመፈጸም፣
የወንጀል ፈጻሚውን ማንነት ለመለየት የሚያስችል አግባብነትና ተቀባይነት ካላቸው ከተለያዩ
የማስረጃ ዓይነቶች ውስጥ ምስክርነት (የሰው ማስረጃ) ዋነኛው ነው፡፡ ስለሆነም ምስክርነት
ከአንድ የወንጀል ድርጊት ጋር በተያያዘ የወንጀል አድራጊውን ሁኔታ በአግባቡ ለዳኛው
በማስረዳትና አጥፊን ከንጹህ በመለየት ሂደት ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያለው ነው፡፡ ምክንያቱም
ምስክርነት በወንጀል ጉዳይ ክርክር በሚደረግበት ጊዜ ወንጀሉ መቼ ተፈጸመ፣ የት ተፈጸመ፣
እንዴት ተፈጸመ፣ በምን ተፈጸመ፣ በማን(እነማን) ተፈጸመ፣ በምን ምክንያት ተፈጸመ
የሚሉትን የወንጀል ድርጊቱን ዋና ዋና ማቋቋሚያ ፍሬ ነገሮችና ጭብጦች ለመለየትና በግልጽ
ለማሳየት የሚያስችል በመሆኑ ነው3፡፡

ምስክርነት ከሌሎች ማስረጃዎች አንጻር ሲታይ ምናልባትም ረጅም እድሜ ያስቆጠረና በፍርድ
ቤትም የወንጀሉን አፈጻጸም በአግባቡ በማረጋገጥ በኩል አግባብነት ያለው ማስረጃ ነው4፡፡
በተለይም ምስክርነት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሀገራት በወንጀል ፍትህ ስርዓቱ ውስጥ
ክርክሮችን ለማስረዳት ያለው ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡ ምክንያቱም በሀገራችን ሳይንሳዊ የወንጀል
የምርመራ ዘዴን ተጠቅሞ የቴክኒክ ማስረጃዎችን ለመሰብሰብ ከፍተኛ የሆነ የእውቀት፣
የዘመናዊ መሳሪያ እና የሰለጠነ የሰው ሀይል እጥረት የሚታይ በመሆኑ ነው፡፡ ታዲያ
ምስክርነት አጥፊን ከንጹህ ለመለየት እንዲያስችል በፍርድ ቤት የሚቀርቡ ምስክሮች የስነ-

2
ታጠቅ ታደሰ፣ የማስረጃ ህግ መሰረተ ሀሳቦች፣ አዲስ አበባ ዩ ኒቨርስቲ መጻህፍት ማእከል፣ 1997 ዓ.ም፣ገጽ 1
3
ዝኒ ከማሁገጽ 161-163
4
ዝኒ ከማሁ ገጽ 161-165
ስርዓት ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ምስክሮቹ እውነት ለመናገራቸው ቃለ-መሀላ ፈጽመው
ምስክርነታቸውን መስጠት ይኖርባቸዋል፤ ምስክርነታቸውም ስነ-ስርዓት ህጉ በሚፈቅደው
መሰረት የተለያዩ ጥያቄዎችን በማለፍ የተፈተነና ተዓማኒ መሆን ይገባዋል፡፡

2. የምስክሮች ቃል የሚፈተን ስለመሆኑ

ምንም እንኳን ምስክርነት ለወንጀል ክርክር ትልቅ የማስረጃ ምንጭ ሆኖ የሚያገለግል ቢሆንም
በተለይም በአሁኑ ወቅት የምስክር ቃል በባህሪው ብዙ ህጸጾች ያሉበትና ተዓማኒነቱን ሊቀንሱ
የሚችሉ ምክንያቶች እየተስተዋሉ ነው፡፡ ምስክርነት በተፈጥሮው በሰዎች የስሜት ህዋሳት ላይ
ተመስርቶ የሚሰጥና በሰው የማስታወስ ችሎታ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ የራሱ ጉድለት ያለበት
ነው፡፡ ስለሆነም የሰው ምስክርነት እንደ ማስረጃ ከመወሰዱ በፊት የተለያዩ ስርዓቶችን ማለፍ
ይኖርበታል፡፡ አንድ ምስክር በፖሊስ ጣቢያ ወይም በፍርድ ቤት ቀርቦ ምስክርነቱን ከመስጠቱ
በፊት ምስክሩ በአካልና በአእምሮ ብቁ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህም ማለት ምስክሩ
የተፈጸመውን ድርጊት ለመረዳት የሚችል መሆኑ፣ ድርጊቱን ተገንዝቦ በማስታወስ
ለሚመለከተው አካል (ለፍርድ ቤት ወይም ለመርማሪ ፖሊስ) እንደገና ለመግለጽ የሚችል
መሆኑ፣ ምስክሩ ቃለ-መሀላ የሚፈጽም (ፍርድ ቤት) እና እውነት በመመስከርና ሀሰት
በመመስከር መካከል ያለውን ልዩነት የሚረዳ መሆን ይገባዋል፣ የምስክሩ የአካልና የአእምሮ
ብቃት የሚቀርብለትን ጥያቄ ለመረዳትና ለመመለስ የሚያስልች መሆኑ መታየት እንዳለበት
ጠቅላላ የማስረጃ ህግ መርህ ያስገነዝባል5፡፡

ምስክርነት የተለያዩ እንከኖች እንዲኖሩበት የሚያደርጉ የተለያዩ ምክንያቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡


ከእነዚህ ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ምስክሩ ሰው በመሆኑ ምክንያት ድርጊቱ በተፈጸመ ጊዜ
የተመለከተውን ወይም የሰማውን ወይም በሌሎች የስሜት ህዋሳቶቹ አማካኝነት የተረዳውን
ነገር ለመርማሪ ፖሊስ ወይም ክርክሩን ለሚያየው ፍርድ ቤት ቀርቦ ሲመሰክር ቀድሞ
የሚያውቀውን እውነታ አስታውሶ ላይመሰክር ይችላል፡፡ በሌላ በኩል የሰው ምስከርነት ጉድለት
የሚመጣው በምሰክሩ ከውስጡ በመነጨ ወይም በተካራካሪ ወገኖች ተጽእኖ በመነሳት ቀደም
ሲል ለፖሊስ የሰጠውን ቃል በመቀየር ሀሰት ሊመሰክር የሚችልበት ሁኔታ ያጋጥማል፡፡
በተጨማሪ ምስክሮች በቂም በቀልና በጥላቻ በመነሳሳት ወንጀል ያልፈጸመ(ሙ) ግለሰብን(ቦችን)

5
Gary L. wells and Elizabeth A.፣ Eye witness testimony፣ https// public.psych iastate edu/glweslannual review፣ 2003 ገጽ 53
የተወሰደው ሰኔ 15/2010 ዓ.ም
በሀሰት በመደራጀት አላግባብ በሀሰት በመክሰስ /በመመስከር/ እንዲቀጡ ሊያደርጉ ይችላሉ፣
በተመሳሳይ ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦች ለድርጊታቸው ተገቢውን ቅጣት እንዳያገኙ በማሰብ
በሀሰት በመከላከያ ምስክር በመደራጀት ወንጀል የፈጸሙ ሰዎች ነጻ እንዲወጡ ሊያደርጉ
ይችላሉ6፡፡ እንዲሁም ምስክሮች ጉዳዩን በሚመለከተው ፍርድ ቤት ቀርበው ከመመስከራቸው
በፊት በሞት ሊለዩ ይችላሉ፣ በጽኑ ህመም ምክንያት ፍርድ ቤት ቀርበው መመስከር
የማይችሉበት ሁኔታ ያጋጥማል፣ ከሀገር ሊወጡ ይችላሉ፣ ቀደም ሲል ካስመዘገቡት አድራሻ
ሊጠፉ ወይም ሊሰወሩ ይችላሉ፡፡ እነዚህና ሌሎች መሰል ምክንያቶች በሰው ምስክር ላይ
የሚታዩ ጉድለቶች ናቸው፡፡

ታዲያ ምስክርነት እንደዚህ ዓይነት ህጸጾች የሚታዩበት ስለሆነ ችግሩን ለመቀነስ የወንጀል ስነ-
ስርዓት ህጉ የምስክሮች ቃል የሚጣራበትንና የሚፈተንበትን ስርዓት ዘርግቶ እናገኘዋለን፡፡
የምስክሮች ቃል ተዓማኒ እንዲሆን ምስክር በሚሰማበት ወቅት በአግባቡ መፈተን ይኖርበታል፡፡
ማስረጃው የሚፈተነው በዋና ጥያቄ፣ በመስቀለኛ ጥያቄ፣ በመሪ ጥያቄ ወይም በማጣሪያ ጥያቄ
ሊሆን እንደሚችል በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ ላይ ተመልክቷል፡፡ በመስቀለኛ ጥያቄ
ወይም በመሪ ጥያቄ የምስክር ቃል ሲፈተን የጥያቄው ዋና ዓላማ የተሰጠውን ምስክርነት
ማስተባበልና በፍርድ ቤቱ ዘንድ ተዓማኒ ተደርጎ እንዳይታይ ለማድረግ ነው፡፡ የምስክርነትን
ቃል በመስቀለኛ ጥያቄ ወይም በመሪ ጥያቄ የሚፈተንበትና የሚስተባበልበት ዘዴ
በእንግሊዘኛው “impeachment” ተብሎ የሚታወቅ ነው7፡፡ የምስክሩ ቃልም የሚፈተነው የስነ-
ስርዓት ህጉ ምስክር በሚሰማበት ወቅት በተከራካሪ ወገኖች በኩል የቀረቡ ምሰክሮች
የሚጠየቁበትንና የምስክርነት ቃሉ የሚፈተንበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ በተቀመጠው ስርዓት
መሰረት ነው፡፡

3. በምርመራ ወቅት ለፖሊስ የተሰጠን የምስክርነት ቃል ፍርድ ቤት


ስለሚመለከትበት ሁኔታ እና የወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ ድንጋጌ

አንድ ወንጀል የተፈጸመ መሆኑን መርማሪ ፖሊስ መረጃ በደረሰው ጊዜ ምንም ዓይነት ጊዜ
ሳያጠፋ ወንጀሉን ያስረዳሉ የተባሉ ማስረጃዎችን ሁሉ እንደየአግባብነታቸው መሰብሰብና
መተንተን እንደሚገባው የወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ ያስገነዝባል፡፡ ከሚሰበሰቡት
ማስረጃዎች ውስጥ የምስክር ቃል አንዱና ዋነኛው ሲሆን በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ

6
ሀብታሙ በቃሉ፣ በአብክመ ፍትህ ቢሮ የደብረ ብርሀን ቋሚ ምድብ ዐቃቤ ህግ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ፣ ሰኔ 9/2010 ዓ.ም
7
ከላይ በግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 4
አንቀጽ 30 ስር መርማሪ ፖሊስ የምስክር ቃል እንዴት መቀበልና መመዝገብ እንዳለበት
ዝርዝር ስርዓቱን የሚያመለክት ድንጋጌ እናገኛለን፡፡ ማስረጃዎችም ተሰብስበው ካለቁ በኋላ
የምርመራ መዝገቡ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ትይዩ የሆነ ስልጣን ላለው
የዐቃቤ ህግ መስሪያ ቤት እንደሚላክና እንደሁኔታው የምርመራ መዝገቡን የሚመለከተው
ዐቃቤ ህግ ክስ የመመስረት፣ ለተጨማሪ ምርመራ የመላክ ወይም የክስ አላቀርበም ውሳኔ
ሊሰጥ እንደሚቸል የስነ-ስርዓት ህጉ ያስገነዝባል8፡፡ የምርመራ መዝገቡም ክስ የሚያስመሰረት
ሆኖ በተገኘ ጊዜና ዐቃቤ ህግ ክስ ከመሰረተ በኋላ ክርከር እንደሚጀምር በክርክር ሂደትም ዐቃቤ
ህግና ተከሳሽም የየራሳቸውን ምስክሮች እንደሚያሰሙ ስነ-ስርዓት ህጉ ያስቀምጣል፡፡ ምስክሮች
በሚሰሙበት ጊዜ ተከራካሪዎቹ ወገኖች ስነ-ስርዓት ህጉ እንዳስቀመጠው እንደ አግባብነቱ የዋና
ጥያቄ፣ የመስቀለኛ ጥያቄና የመሪ ጥያቄ የሚጠይቁበት ስርዓት ተዘርግቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም
ማጣሪያ ጥያቄ የሚጠይቅበት ሁኔታ ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም ፍርድ ቤቶች ለትክክለኛ
ፍትህ አሰጣጥ አስፈላጊ ነው ብለው ሲያምኑ በዐቃቤ ህግ ወይም በተከሳሽ የማስረጃ ዝርዝር
ውስጥ ያልተጠቀሱ ምስክሮችን ማስቀረብና መስማት እንደሚችሉ ህግ አውጭው ስልጣን
ሰጥቷቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተከሳሹ ወይም ዐቃቤ ህጉ ሲያመለክቱ የዐቃቤ ህግ
ምስክሮች ለፖሊስ የሰጡትን ቃል ፍርድ ቤቱ ሊመለከተው የሚችልበት እድል እንዳለ
በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ በቁጥር 145 ስር እንደሚከተለው ተደንግጎ ይገኛል፡፡

(1) ዐቃቤ-ህጉ ወይም ተከሳሹ ሲያመለክት በፖሊስ ምርመራ ጊዜ የተሰጠውን የምስክርነት ቃል


ፍርድ ቤቱ ሊመለከተው ይችላል፡፡

(2) ከዚህ በኃላ ለትክክለኛ ፍርድ አሰጣጥ የሚጠቅም መስሎ ከታየው የዚህ ቃል ግልባጭ
ለተከሳሹ እንዲደርሰው አድርጎ በዚህ መሰረት ምስክሩ የሰጠውን ቃል ለማስተባበል ይቻላል፡፡

ከላይ በተመለከተው አንቀጽ በንኡስ ቁጥር 1 ስር የተገለጸው ዓረፍተ ነገር እንደሚያመለክተው


ዐቃቤ ህጉ ወይም ተከሳሹ ሲያመለክቱ በፖሊስ ምርመራ ወቅት የተሰጠ የምስክሮችን ቃል
ክሱን የሚያየው /የሚያከራክረው/ ፍርድ ቤት የምርመራ መዝገቡን አስቀርቦ ሊመለከተው
እንደሚችል በግልጽ የተቀመጠና ጥያቄ የማያስነሳ ጉዳይ ነው፡፡ አከራካሪው ነጥብ ዐቃቤ ህጉ
ወይም ተከሳሹ በምርመራ ወቅት በፖሊስ ጣቢያ የተሰጠው የምስክርነት ቃል እንዲቀርብላቸው
የሚያመለክቱትና ፍርድ ቤቱም እንዲመለከተው የሚደረገው በክርክር ሂደት ምን ሁኔታ

8
የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት፣ የወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ፣ 1954 ዓ.ም፣ አንቀጽ 37፣አንቀጽ 38(ሐ)፣ አንቀጽ 42(1-ሀ) ስር
የተመለከተውን ዝርዝር ድንጋጌዎች ይመልከቱ፡፡
ሲያጋጥም ነው የሚለው ነጥብ ነው፡፡ እንዲሁም በዚሁ ድንጋጌ በንኡስ ቁጥር 2 ስር
በተመለከተው ዓረፍተ ነገር ላይ ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ የሚጠቅም በሆነ ጊዜ የምስክሩ(ሮቹ)
ቃል ግልባጭ ለተከሳሹ እንዲደርሰው በማድረግ ዐቃቤ ህግ የምስክሩን ቃል “ለማስተባበል”
ይችላል ተብሎ የተደነገገው ነው፡፡ ከላይ በተገለጸው ድንጋጌ ስር የሚታየው የክርክር መነሻና
በባለሙያዎች ዘንድ የሚታየው የግንዛቤ ልዩነት የሚመነጨው ዐቃቤ ህግ ወይም ተከሳሽ
የዐቃቤ ህግ ምስክር ቀደም ሲል ለፖሊስ የሰጠውን የምስክርነት ቃል ፍርድ ቤቱ
እንዲመለከትላቸው አቤቱታ የሚያቀርቡትና ፍርድ ቤቱም እንደ ማስረጃ የሚወስደው መቼና
በምን ዓይነት መንገድ ነው የሚለው ነው፡፡ ይህን ነጥብ በሚመለከት በክልላችን በሚገኙ ፍርድ
ቤቶች በሚሰሩ ዳኞች፣ ዐቃብያነ ህግና ጠበቆች ዘንድ በዋናነት በሁለት ሊከፈል የሚችል
አረዳድና አተረጓጎም እንዳለ ይስተዋላል፡፡ አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚገልጹትና በተግባርም
ሲሰሩ የሚታየው በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ ቁጥር 145 (1፣2) ስር የተቀመጠው
ድንጋጌ ተፈጻሚ የሚሆነውና ለፖሊስ የተሰጠ የምስክርነትን ቃል ፍርድ ቤት ሊመለከተው
የሚችለው ቀደም ሲል ስለወንጀሉ አፈጻጸምና የወንጀሉን ፈጻሚ ማንነት በሚመለከት
በቀጥታም ይሁን ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ምስከሩ አውቃለሁ በማለት ለመርማሪ ፖሊስ
ምስክርነቱን የሰጠ ምስክር ክሱን ለማየት ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ፊት ቀርቦ መመስከር
ሳይችል በቀረ ጊዜ ተፈጻሚ የሚደረግ ነው የሚል ነው፡፡ ይህ ማለት ምስክሩ ክርክሩ
በሚሰማበት ጊዜ የዐቃቤ ህግ ምስከር በህይወት ከሌለ፣ ከሀገር ከወጣ፣ ቀደም ሲል
ባስመዘገበው አድራሻ ካልተገኘ ወይም በጽኑ ህመም ምክንያት ፍርድ ቤት ቀርቦ መመስከር
ካልቻለ የዓቃቤ ህግ ምስከር/ሮች/ ባለሰማታቸው /ባለመቅረባቸው/ ክርክሩ መቋረጥ
ስለማይገባው ወይም የዐቃቤ ህግ ምስክሮችን በማፈላለግ ምክንያት ፍትህ እንዳይጓተት ሲባል
ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ የተሰጠውን የምስክርነት ቃል ሊመለከተውና በማስረጃነት ተቀብሎ
ከማስረጃ ምዘና ውስጥ በማስገባት ውሳኔ ሊሰጥ የሚችልበትን እድል የሚፈጥር ስነ-ስርዓት
ነው በማለት ያስቀምጣሉ፤ በዚሁም አረዳድ በተግባር ሲሰሩ ይታያል9፡፡ እነዚህ ባለሙያዎች
ለክርክራቸው ማጠናከሪያና ማነጻጸሪያ የሚያደርጉት በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ ቁጥር
144 ስር የተደነገገውን የቀዳሚ ምርመራ ዓላማ ነው፡፡ እንደሚታወቀው በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-
ስርዓት ህጉ ላይ በግልጽ እንደተመለከተው ቀዳሚ ምርመራ የሚደረግበት ዋናው ዓላማ ማስረጃ
ጠብቆ ለማቆየት (preservation of evidence) ነው፡፡ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ

9
በሰሜን ሽዋ ዞን ፍትህ መምሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሚሰሩ ከተወሰኑ የወንጀል ዐቃብያነ ህጎችና ዳኞች ጋር የተደረገ ውይይት
ሰኔ 13፣ 2010 ዓ.ም
ቀዳሚ ምርመራ በአስገዳጅነት እንዲደረግ የተቀመጠው ለከባድ ሰው መግደል ወንጀልና ለከባድ
ውንብድና ወንጀሎች ነው፡፡ በሌሎች ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ ቀዳሚ ምርመራ እንዲደረግ ካላዘዘ
በስተቀር ቀዳሚ ምርመራ የሚደረግበት አግባብ እንደማይኖር መገንዘብ ይቻላል፡፡ ታዲያ ከከባድ
ሰው መግደልና ከከባድ ውንብድና ወንጀሎች ውጭ በሆኑ ወንጀሎች ቀዳሚ ምርመራ
ስለማይደረግ የምስክር ቃል የማይጠበቅበት (preservation of evidence) ስለማይኖር የክርክር
ሂደቱ እንዳይቋረጥ ወይም እንዳይጓትት በማሰብ በስነ-ስርዓት ህጉ የተቀየሰ ስልት እስከሌለ
ድረስ በክርክር ሂደቱ ላይ እንቅፋት እንደሚያጋጥም የሚታወቅ ነው፡፡ እንደነዚህ ባለሙያዎች
አረዳድ ለዚህ ችግር መፍትሄ የሚሆን የወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ በአንቀጽ 145 ስር
የተመለከተውን ድንጋጌ ህግ አውጭው ያስቀመጠበት ምክንያት፡፡ ይሄውም ቀዳሚ ምርመራ
እንዲደረግ ህጉ በማያስገድድበት ጊዜና ዓቃቤ ህግም ቀዳሚ ምርመራ እንዲደረግ ባላዘዘበት
ወቅት ምስክሮች ባለመቅረባቸው ምክንያት ክርክሩ እልባት ሳያገኝ መቅረት የለበትም በሚል
እምነት ለፖሊስ የተሰጠ ምስክርነት በቀዳሚ ምርመራ ወቅት እንደተሰጠ ምስክርነት ዓይነት
ተቆጥሮ በፍርድ ቤት እንደ ማስረጃ እንዲወሰድ በማሰብ የተቀረጸ ድንጋጌ ነው10፡፡ እንደነዚህ
ባለሙያዎች አረዳድ ከሆነ ቀዳሚ ምርመራ ባልተደረገባቸው ወንጀሎች ስለወንጀሉ ያስረዳሉ
ተብለው ምስክርነታቸውን ለፖሊስ የሰጡ ምስክሮች ጉዳዩ በሚታይበት ወቅት በሞት
በመለየት፣ በጽኑ ህመም ምክንያት ለመመስከር ብቁ አለመሆን፣ ከሀገር በመውጣት ፍርድ ቤት
አለመቅረብ ወይም ምስክሩ በአድራሻው ባለመገኘት ፍርድ ቤት መቅረብ ካልቻሉና ምስክሮቹ
ቀርበው ባለመመስከራቸው ክርክሩ መቋረጥ ስለማይገባው ህግ አውጭው ይህንን ክፍተት
ለመሙላት በሚል ለመርማሪ ፖሊስ የተሰጠው የምስክርነት ቃል እንደ ማስረጃ ተወስዶ
ማስረጃው እንዲመዘን በማሰብ የተቀመጠ ነው በማለት ሀሳባቸውን ይገልጻሉ11፡፡

በሌላ በኩል ከላይ የተገለጸውን አተረጓጎም የማይቀበሉ ባለሙያዎች አንደሚሉት


በወ.መ.ስ.ስ.ህ.ቁ 145(1፣2) ስር የተቀመጠው ድንጋጌ ተፈጻሚ የሚሆነው የዐቃቤ ህግ
ምስክር/ሮች/ ፍርድ ቤት ቀርበው መመስከር ባልቻሉ ጊዜ ሳይሆን የቀረቡት የዐቃቤ ህግ
ምስክሮች ቀደም ሲል ፖሊስ ለይ ከሰጡት ምስክርነት ጋር የሚቃረን ወይም አስጠቂ የሆነ
ምስክርነት በሰጡ ጊዜ ዐቃቤ ህግ ወይም ተከሳሹ በፍርድ ቤት የተሰጠውን ምስክርነት
ለማስተባበል የሚችሉበትን እድል ለመፍጠር ሲባል የተቀረጸ ድንጋጌ ነው በማለት
መከራከሪያቸውን ያቀርባሉ፡፡ እነዚህ ባለሙያዎች እንደሚሉት የድንጋጌውን ዓላማና የህግ

10
11
´’> ŸTG<
ዝኒ ከማሁ
አውጭውን ሀሳብ ለመረዳት ድንጋጌውን በአግባቡ መረዳት እንደሚገባ ያስቀምጣሉ፡፡ ይሄውም
በአንቀጽ 145 (2) ስር በአማርኛው ቅጂ ላይ እንደተመለከተው “….. ለትክክለኛ ፍርድ አሰጣጥ
የሚጠቅም ሆኖ ከታየው …. ምስክሩ የሰጠውን ቃል ለማስተባበል ይቻላል” በሚል የተቀመጠ
ሲሆን ይሄው ድንጋጌ በእንግሊዘኛው ቅጂ ላይ “… such statement may be used to
impeach the creadit of the witness…” በሚል ተቀምጧል፡፡ ከላይ ከተገለጸው ዓረፍተ
ነገር መረዳት እንደሚቻለው ፖሊስ ላይ የተሰጠውን ምስክርነት ፍርድ ቤቱ የሚመለከተው
ምስክሩ የሰጠውን ቃል ለማስተባበል እንዲቻል እንደሆነ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ምስክሩ
ጉዳዩን በሚያው ፍርድ ቤት ቀርቦ እንደመሰከረ ያስገነዝባል፡፡ የሚስተባበለውም ቃል ቀደም
ሲል የዐቃቤ ህግ ምስከር በመሆን ፖሊስ ላይ ምስክርነቱን የሰጠ ምስክር ክሱን በሚሰማው
ፍርድ ቤት ቀርቦ እንዲመሰክር ሲጠየቅ ቀድሞ ለመርማሪ ፖሊስ ከሰጠው ቃል የሚቃረን
/አንዳንድ ጊዜም አስጠቂ/ ምስክርነት የሰጠ እንደሆነ አሁን በፍርድ ቤት የተሰጠው ምስክርነት
ተዓማኒነት የሌለው መሆኑን ዐቃቤ ህግ ወይም ተከሳሽ ለማስተባበል እንዲችል በማሰብ
የተቀመጠ እንደሆነ የሚያስገነዘብ ነው በማለት ይከራከራሉ፡፡ ስለሆነም ፖሊስ ላይ የተሰጠ
የምስክርነት ቃል በፍርድ ቤት ተቀባይነት የሚኖረው ፍርድ ቤቱ ምስክሩ ቃሉን ቀይሮ
ምስክርነት የሰጠ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ምስክርነቱ አስጠቂ የሆነበት ወገን ምሰክርነቱን
ለማስተባበል እንዲችል እድል ለመስጠት በሚል ህግ አውጭው ያስቀመጠው ነው ሲሉ
ክርክራቸውን ያጠናክራሉ፡፡ ይህን መከራከሪያ የሚያቀርቡ ባለሙያዎች እንደሚሉት በወንጀለኛ
መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ ቁጥር 145 ስር በፍርድ ቤት የተሰጠውን ምስክርነት ማስተባበል
የሚችለው ዐቃቤ ህግ ብቻ ሳይሆን ተከሳሽም ሊያስተባብል የሚችልበት ጊዜ እንዳለ
ያስቀምጣሉ፡፡ ይሄውም የዐቃቤ ህግ ምስከር ፖሊስ ላይ የሰጠው ቃል ፍርድ ቤት ቀርቦ
ከሰጠው ቃል ጋር የሚቃረን ከሆነና ፍርድ ቤት ቀርቦ የሰጠው ቃል ተከሳሽን የሚጎዳ ወይም
ለመርማሪ ፖሊስ ከሰጠው የተለየ ከሆነ ተከሳሹ የዐቃቤ ህግ ምስክር ቀደም ሲል ለመርማሪ
ፖሊስ የሰጠው አሁን ፍርድ ቤት በመሰከረው ዓይነት አይደለም በማለት ለፍርድ ቤቱ
በማመልከት የምርመራ መዝገቡ እንዲቀርብለት እንደሚያመለክትና ፍርድ ቤቱም ልዩነት
መኖሩን ከተረዳ ተከሳሹ ምስክሩ የሰጠውን ቃል ማስተባበል እንዲችል መፍቀድ ያለበት
መሆኑን ያመለክታል በማለት ይከራካራሉ12፡፡ ይህንንም ሀሳብ የሚያጠናክሩት በአንቀጽ 145
በአርእስቱ ላይ “በፖሊስ የተሰጠ ቃል በማስረጃነት ሊቀርብ ስለመቻሉ” በሚል የተገለጸው

12
በላቸው ኪዳኑ፣በአብክመ ፍትህ ቢሮ የደብረ ብርሀን ቋሚ ምድብ ዐቃቤ ህግ ሰኔ 10፣2010 ዓ.ም፡፡ ሀብታሙ ትርፌ፣ ሰሜን ሽዋ ዞን ፍትህ
መምሪያ ዐቃቤ ህግ፣ ሰኔ 12፣2010 ዓ.ም
ጥቅል አገላለጽ ዐቃቤ ሀግም ሆነ ተከሳሽ ባመለከቱ ጊዜ ተፈጻሚ መሆኑን ያሳያል፡፡
በተጨማሪም የዚሁ ድንጋጌ 145(1) ስር “ዐቃቤ ህጉ ወይም ተከሳሹ ሲያመለክት በፖሊስ
ምርመራ ጊዜ…..” በማለት የተቀመጠው ሀሳብ ዐቃቤ ህግም ሆነ ተከሳሹ እንደአግባብነቱ
የምርመራ መዝገቡ እንዲቀርብላቸው ሲያመለክቱ ለሁለቱም እድሉ የተሰጠ መሆኑን
የሚያመለክት ነው በሚል ነው፡፡

የወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ ቁጥር 145 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በሚመለከት


በባለሙያዎች ዘንድ ከላይ የተቀመጡት ሁለት ዋና ዋና ክርክሮች የተቀመጡ ሲሆን የዚህን
ድንጋጌ ዓላማና የህግ አውጭውን ሀሳብ በሚመለከት እንደዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ እምነት ከሆነ
ድንጋጌው ተፈጻሚ የሚሆነው የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ክሱን በሚሰማው ፍርድ ቤት ቀርበው
መመስከር ሳይችሉ ሲቀሩ ሳይሆን ፍርድ ቤት ቀርበው የሰጡት ቃል ፖሊስ ላይ ቀርበው
ከመሰከሩት ጋር ሲቃረን ወይም አስጠቂ ምስክር በሆኑ ጊዜ የሚል ነው፡፡ ምክንያቱም
በወ.መ.ስ.ስ.ህ.ቁ. 145 ስር የተቀመጠውን ድንጋጌ ይዘት ስንመለከት በንኡስ ቁጥር 1 ስር
የተቀመጠው ዓረፍተ ነገር እንደሚያሳየው ለፖሊስ የተሰጠውን ቃል ፍርድ ቤቱ ሊመለከተው
ይችላል ካለ በኋላ በንኡስ ቁጥር 2 ስር ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ “…..የሰጠውን ቃል
ማስተባበል…” ይችላል በሚል ከተቀመጠው ሀሳብ መገንዘብ የሚቻለው ፍርድ ቤቱ የምስክሩን
ቃል የሚመለከተው በቀጥታ በማስረጃ በመቀበል ሳይሆን ምስክሩ ለመርማሪ የሰጠው ቃልና
በፍርድ ቤት ቀርቦ በዋና ጥያቄ ወቅት የሰጠው ቃል ልዩነት ካለው ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ
እንዲረዳ ቃሉን በመስቀለኛ ጥያቄ ለማስተባበል እንዲችል የተፈቀደ መሆኑን ነው፡፡ ይህ ማለት
በአንቀጹ 145(1) ስር እንደተመለከተው ፍርድ ቤቱ የምርመራ መዝገቡን ተመልክቶ ፖሊስ
ላይ በተሰጠው ምስክርነትና ፍርድ ቤት በተሰጠው ምስክርነት መካከል ልዩነት ከሌለ መዝገቡን
ተመልከቶ በአንቀጹ 145(2) ስር ወደ ተመለከተው ላይሄድ እንደሚችልና ዐቃቤ ህጉ ወይም
ተከሳሹ በመስቀለኛ ጥያቄ ማስተባበል እንዳይችሉ ለማድረግ እንደሚችል ስልጣን የተሰጠው
መሆኑን ያመለክታል፡፡ በሌላ በኩል ከላይ እንደተመለከትነው አንዳንድ ባለሙያዎች
እንደሚሉት የአንቀጽ 145(1፣2) ዓላማ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች በበቂ ምክንያት ፍርድ ቤት
ቀርበው መመስከር ባልቻሉ ጊዜ ፖሊስ ላይ የተሰጠውን ምስክርነት በቀዳሚ ምርመራ
እንደተሰጠ ማስረጃ አድርገው ይውሰዱት ቢባል የሚቀርበው መከራከሪያ የተሳሳተና የተከሳሹን
ህገ መንግስታዊ መብት የሚጋፋ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ
መንግስት አንቀጽ 20(4) ላይ እንዲሁም በሲቭልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም ዓቃፍ ቃል ኪዳን
አንቀጽ 14(1-ሠ) ስር በግልጽ እንደተመለከተው ማንኛዉም በወንጀል የተከሰሱ ሰዎች
“የቀረቡባቸውን ማናቸውንም ማስረጃ የመመልከት፣ የቀረቡባቸውን ምስክሮች የማወቅና
የመጠየቅ…”መብት ያለቸው ስለመሆኑ ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ለፖሊስ የተሰጠው
የምስከርነት ቃል እንዳለ እንደ ማስረጃ ሆኖ ይወሰድ ከተባለ የተከሳሽን መስቀለኛ ጥያቄ
የመጠየቅ ህገ መንግስታዊ መብቱን ይጋፋል፤ የተሰጠውም ምስክርነት በመስቀለኛ ጥያቄ እና
በማጣሪያ ጥያቄ ተፈትኖ ያለፈ ባለመሆኑ ተዓማኒነት ሊኖረው አይችልም፡፡ በሌላ በኩል
በወ.መ.ስ.ስ.ህ.ቁ 144 ስር የተቀመጠው በቀዳሚ ምርመራ አድራጊ ፍርድ ቤት የተሰጠው ቃል
ስንመለከት ምስክሩ ቃለ መሀላ ፈጽሞ የሰጠው እንዲሁም መስቀለኛ ጥያቄና ማጣሪያ ጥያቄ
የተጠየቀበት ያለቀለት ማስረጃ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ እንዳለ ቢቀበለው የተከሳሽን መብት የማይጎዳ
ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አንድ በምስክርነት የተጠራ ሰው የሚሰጠው ቃል እንደ ማስረጃ
ለመቆጠር ከሚያስፈልጉት ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ምስክሩ እውነት
ለመናገር በቃለ-መሀላ ማረጋገጥ ይኖርበታል13፡፡ በወ.መ.ስ.ስ.ህ.ቁ 145 ስር ወደተደነገገው
ስንመጣ በፖሊስ ምርመራ ወቅት ምስክሮች ቃላቸውን ከመስጠታቸው በፊት የሚሰጡት ቃል
እውነት ስለመሆኑ ቃለ-መሀላ የሚፈጽሙበት ሁኔታ የሌለ በመሆኑ ፍርድ ቤቶች ያለ ቃለ-
መሀላ የተሰጠን የምስክርነት ቃል ሊቀበሉ የማይገባ ስለሆነ የወ.መ.ስ.ስ.ህ.ቁ. 145 ስር ያለው
ድንጋጌ ዓላማ ለፖሊስ የተሰጠ ምስክርነት እንዳለ ይወሰድ ከተባለ ይህን መሰረታዊ የወንጀል
ስነ-ስርዓት ሂደት ከግምት ያላስገባ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም በፖሊስ ጣቢያ ለመርማሪ ፖሊስ
የሚሰጥ ምስክርነት ገለልተኛ በሆነ ተቋምና በግልጽ የተሰጠ እንዲሁም እውነት ለመናገር ቃለ
መሀላ ተፈጽሞ የተሰጠ ምስክርነት ዓይደለም፡፡ በአንጻሩ በቀዳሚ ምርመራ አድራጊ ፍርድ ቤት
የተሰጠ ምስክርነት ዋና ጥያቄ፣ መስቀለኛ ጥያቄና ማጣሪያ ጥያቄ ተጠይቆ የምስክሩ ቃል
ተፈትኖ ያለፈ በመሆኑና ተከሳሽም በህገ መንግስትና በሌሎች ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች
የተሰጠውን ምስክሮቹን የመጠየቅ መብቱን ተጠቅሞ መስቀለኛ ጥያቄ የጠየቀ በመሆኑ
ማስረጃውን እንዳለ ፍርድ ቤቱ ቢወስደው ተዓማኒ የሆነና ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ነው፡፡
በቀዳሚ ምርመራ ጊዜ ምስክሮቹ ዋና ጥያቄ መስቀለኛ ጥቄና ማጣሪያ ጥያቄ በመጠየቅ
የምስክርነት ቃል አሰጣጥ ስርዓቱ መደበኛ ችሎት በሚሰማበት ዓይነት የተሰጠ ምስክርነት
ስለመሆኑ በወ.መ.ስ.ስ.ህ.ቁ. ከአንቀጽ 84-86 ካሉት ድንጋጌዎች መረዳት እንችላለን፡፡ በዚሁ
ህግ አንቀጽ 88 ላይ በቀዳሚ ምርመራ የተሰጠ ምስክርነት እንዲመዘገብ የተፈለገበት ዋናው
ምክንያት የተሰጠው ምስከርነት በአንቀጽ 147(3) መሰረት መስቀለኛ ጥያቄ እንደሚቀርብበት

13
ከላይ በግርጌ ማስታወሻ ቁጥር5፣ አንቀጽ 136(3)
ለማረጋገጥ ነው14፡፡ በዚህም ዓይነት ሂደት ውስጥ ያለፈ ማስረጃ በሌላ ፍርድ ቤት ማስረጃ ሆኖ
ሊቀርብ ቢችል ህጋዊና ስነ-ስርዓት ህጉን የጠበቀ ነው፡፡ በሌላ በኩል ግን ለመርማሪ ፖሊስ
የተሰጠ ቃል ልክ እንደ ቀዳሚ ምርመራ ጥብቅ ስርዓቶችን አልፎ ባልመጣበት ሁኔታ የዐቃቤ
ህግ ምስክሮች ፍርድ ቤት ቀርበው መመስከር ባልቻሉ ጊዜ ለፖሊስ የሰጡትን ምስክርነት
በቀጥታ እንደ ማስረጃ መውሰድ ህግ አውጭው በወ.መ.ስ.ስ.ህ.ጉ 145 ስር ያስቀመጠውን
ዓላማ በአግባቡ ያገናዘበ ዓይደለም፤ምስክሩ ፍርድ ቤት ባልቀረበበት ሁኔታ ለመርማሪ ፖሊስ
የተሰጠው ቃል እውነትነት አጠራጣሪ ከመሆኑም በላይ የተከሳሹን ሰብዓዊና ህገ መንግስታዊ
መብት የሚነፍግ ነው15፡፡ ይህንን ከላይ የተጠቀሰውን ሀሳብ በሚያጠናክር መልኩ የተሻሻለው
የጸረ ሙስና ልዩ የስነ-ስርዓትና የማስረጃ ህግ አዋጅ በአንቀጽ 44 ስር በሚከተለው መልኩ
ተደንግጎ ይገኛል16፡፡

1. በዐቃቤ ህግ ወይም በመከላከያ ምስክርነት የቀረበ ማንኛውም ሰው በምስክርነት


በተጠረጠረበት ጉዳይ እውነቱን ለመናገር ባለመፈለግ ቀድሞ ከሰጠው የምስክርነት ቃል
ጋር የሚቃረን ቃል የሰጠ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ምስክሩን ያቀረበውን ወገን መሪ ጥያቄ
እንዲጠየቅ ሊፈቅድለት ይችላል፡፡

2. ፍርድ ቤቱ መሪ ጥያቄ እንዲጠይቅ ከመፍቀዱ በፊት ተቃራኒ የምስክርነት ቃል የሰጠ


መሆኑን ምስክሩን ይጠይቀዋል፡፡ ምስክሩ ተቃራኒ የምስክርነት ቃል መስጠቱን ካመነ
መሪ ጥያቄውን ይፈቅዳል፡፡

3. ምስክሩ ተቃራኒ የምስክርነት ቃል መስጠቱን የካደ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ምስክሩ


ተቃራኒ ቃል መስት አለመስጠቱን ይወስናል፡፡

ከላይ በተገለጸው አዋጅ በአንቀጽ 44(1) ስር ከተመለከተው መረዳት እንደሚቻለው በዐቃቤ ህግ


ወይም በተከሳሹ በኩል የቀረበ ምስክር ላቀረበው ወገን አስጠቂ ምስክር በሆነ ጊዜ ምስክርነቱን
ለማስተባበል እንዲችል ፍርድ ቤቱ መሪ ጥያቄ እንዲጠይቅ ሊፈቅድ የሚችልበትን ስርዓት የያዘ
ነው፡፡ የዚሁ ድንጋጌ ንኡስ ቁጥር 2 እንደሚያመለክተው ፍርድ ቤቱ መሪ ጥያቄ እንዲጠይቅ
ከመፍቀዱ በፊት ምስክሩ ሀሰት የመሰከረ መሆን አለመሆኑን ይጠይቀዋል፤ ምስክሩ ካመነ መሪ
ጥያቄ እንዲጠይቅ ይፈቅዳል፡፡ ምስክሩ መዋሸቱን ካላመነ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ ማጣራት
እንደሚያደርግ በንኡስ ቁጥር 3 ተመልክቷል፡፡ እዚህ ላይ በአጽንኦት ማየት የሚገባን ጉዳይ
14
ከላይ በግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 1፣ ገጽ 183
15
ዝኒ ከማሁ
16
የተሻሻለውየጸረ-ሙስናልዩየስነ-ስርዓትናየማስረጃህግአዋጅቁጥር 434/1997
ቢኖር ጉዳዩ የሙስና ወንጀል በሆነ ጊዜ ዓቃቤ ህግ በምርመራ ወቅት ለፖሊስ የተሰጠውን
የምስክርነት ቃል ማቅረብ ሳያስፈልገው መሪ ጥያቄ እንዲጠይቅ እንዲፈቀድለት ሊያመለክት
የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ መገንዘብ ይገባል፡፡ ከላይ ከተገለጸው የጸረ ሙስና ልዩ የስነ-ስርዓትና
የማስረጃ ህግ በተጨማሪ ረቂቅ የወንጀል ስነ-ስርዓት ህጉ በአንቀጽ 287 ስር ተመሳሳይ ይዘት
ባለው መልኩ እንደሚከተለው ተደንግጓ እናገኘዋለን፡፡

1. የዐቃቤ ህግ ምስክር በፍርድ ቤት ቀርቦ የሚሰጠው የምስክርነት ቃል በፖሊስ ምርመራ ጊዜ


ከተሰጠ የምስክርነት ቃል ጋር የሚጣረስ እንደሆነ የምስክሩን ቃል ለማስተባበል ዐቃቤ ህግ
ወይም ተከሳሹ ሲያመለክት ፍርድ ቤቱ የፖሊስን የምርመራ መዝገብ ሊመለከተው ይችላል፡፡
2. ፍርድ ቤቱም የዚህ ግልባጭ ለተከሳሹ እንዲደርሰው ያደርጋል በማለት ያስቀምጣል

ከላይ ከተገለጹት ሁለት አዋጆች መነሻ በማድረግ የወ.መ.ስ.ስ.ህ.ቁ. 145 ስር የተገለጸውን


ፍርድ ቤቶች ተግባራዊ ሲያደርጉና ሲተረጉሙ በምርመራ ወቅት በፖሊስ የተሰጠን
የምስክርነት ቃል እንደ ማስረጃ ቀጥታ በመቀበል ሳይሆን የዐቃቤህግ ምስክር ቀድሞ ከሰተው
ቃል ጋር የሚጋጭ ምስክርነት በሰጠ ጊዜ ይህንኑ ለማስተባበል መሪ ጥያቄ እንዲጠይቅ እድል
ለመስጠት መሆን ይገባዋል፡፡ ከዚህ ውጭ ግን አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚሉትና በተግባርም
እንደሚሰራው የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ፍርድ ቤት መቅረብ ባልቻሉ ጊዜ ዓቃቤ ህግ የምርመራ
መዝገቡን በማቅረብ ቀደም ሲል ለፖሊስ የተሰጠው ምስክርነት ፍርድ ቤቱ እንዲይዝልን
በማለት የሚያቀርበው አቤቱታና አንዳንድ ዳኖችም ይህንኑ ተቀብለው የሚሰሩበት አግባብ ከስነ-
ስርዓት ህጉ ፍላጎት ጋር የማይጣጣም ስለሆነና ለፍትህ አስተዳደርም ስለማይረዳ ሊታረም
የሚገባው ነው፡፡ በተጨማሪ በወ.መ.ስ.ስ.ህ.ቁ 145(1፣2) ስር ያለው ተፈጻሚ መሆን ያለበት
የዐቃቤ ህግ ምስክሮች አስጠቂ ሲሆኑ ብቻ ሳይሆን ተከሳሽም የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ፖሊስ ላይ
ከሰጡት ቃል ጋር የሚቃረን ቃል ሰጥተዋል ብሎ ሲያምን የምርመራ መዝገቡ እንዲቀርብለት
ሊያመለክት ይችላል፤ ፍርድ ቤቱም መፍቀድ እንደሚገባው ከላይ በተጠቀሱት የጸረ ሙስና ልዩ
የስነ-ስርዓት ህግ፣ ከረቂቅ ስነ-ስርዓት ህጉና ከወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ ድንጋጌዎች
መገንዘብ ይገባል፡፡
3. በአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ያለው ተግባራዊ አሰራር

በአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ከወረዳ እስከ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባሉ የቀጥታም ሆነ የይግባኝ
ክርክሮች ላይ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ ቁጥር 145 ስር የተደነገገውን ድንጋጌ
ተፈጻሚ በማድረግ በኩል ወጥ የሆነ አሰራር አይታይም17፡፡ በዚህም የተነሳ ለመርማሪ ፖሊስ
የተሰጠን ምስክርነት እንደማስረጃ የሚወሰደው በምን ሀኔታ ነው የሚለውን ጉዳይ በሚመለከት
የተለያዬ አሰራር እንዳለ ባለሙያዎችም ይገልጻሉ፤ መዛግብትም ይጠቁማሉ፡፡ በክልሉ በብዙ
ፍርድ ቤቶች ወይም ችሎቶች በወ.መ.ስ.ስ.ህ.ቁ. 145 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በሚመለከት
ፍርድ ቤቶች ለፖሊስ የተሰጠን የምስክር ቃል የሚመለከቱትና እንደ ማስረጃ የሚወስዱት
የዐቃቤ ህግ ምስክር/ሮች/ በቂ ተብሎ በሚገመት ምክንያት ማለትም ምስክሩ በህይወት ከሌለ፣
በከፍተኛ የጤና ችግር ምክንያት ምስክርነቱን መስጠት ካልቻለ፣ ምስክሩ ከሀገር ከወጣ ወይም
ምስክሩ በአድራሻው ሊገኝ ካልቻለ ዐቃቤ ህግ ምስክሩ ቀደም ሲል ለፖሊስ የሰጠው ቃል እንደ
ማስረጃ ይያዝልን በማለት ያመለክታል፤ ፍርድ ቤትም ይህንኑ በመቀበል ፖሊስ ላይ ምስክሩ
የሰጠውን የምስክርነት ቃል ኮፒ ተደርጎ ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝ ካደረገ በኋላ ማስረጃ ሚዛን
ውስጥ በማስገባት ውሳኔ ሲሰጥ በስፋት ይታያል18፡፡ ይህንን ሀሳብ በሚደግፍ መልኩ የተወሰኑ
ውሳኔዎችም እንዳሉ መዛግብት ያሳሉ፡፡ ለምሳሌ በከሳሽ የሰሜን ሽዋ ዞን ዓቃቤ ህግ በተከሳሽ
ንጉስ ተክለዮሀንስ መካከል በነበረው ከባድ ሰው መግደል ወንጀል የዓይን ምስክር የነበረው
ግለሰብ በሞት በመለየቱ ምክንያት ዐቃቤ ህግ ምስክሩ ፖሊስ ላይ የሰጠው ቃል እንዲያዝለት
ባመለከተው መሰረት ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ላይ የተሰጠውን ቃል ኮፒ ተደርጎ ከመዝገቡ ጋር
እንዲያያዝ አድርጎ ተከሳሽን ጥፋተኛ ለማለት ፖሊስ ላይ የተሰጠው ምስክርነት የማስረጃ ሚዛን
ውስጥ በማስገባት ፍርድ ቤቱ እንደተጠቀመበት የፍርድ ቤቱ መዝገብ ያለመክታል19፡፡ እዚህ
ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ነጥብ ምስክሩ ፖሊስ ላይ ቀርቦ የሰጠውን ቃል ከሌሎች የሰው
ምስክሮች ቃል ጋር በማጣመር ፍርድ ቤቱ ሲመዝን የማስረጃውን ክብደትና የማስረዳት አቅም
በተመለከተ ፍርድ ቤቱ እንደየሁኔታው የሚመዝነው መሆኑ ግምት ውስጥ ሊገባ የሚገባው
ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በከሳሽ የሰሜን ሽዋ ዞን ዐቃቤ ህግ በተከሳሽ እነ አይደፈር

17
ፍቃዱ አንዳርጌ፣ የሰሜን ሽዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ፣ሰኔ 12/2010 ዓ.ም የተደረገ ቃለ መጠይቅ
18
ሀብታሙ በቃሉና በላቸው ኪዳኑ፣ በአብክመ ፍትህ ቢሮ የክልል ዐቃቤ ህግ ጋር በተደረገ ውይይት በክልሉ ውስጥ በተለያዩ

ዞኖችና ወረዳዎች በሰሩበት አጋጣሚ በጽሁፉ ላይ በተቀመጠው ዓይነት እንደሚሰራ ይጠቁማሉ ቃለ መጠይቁ የተደረገው ሰኔ

10/2010 ዓ.ም
19
የሰሜን ሸዋ ዞን ከ/ፍ/ቤት የወ/መ/ዝ/ቁ. 02-40140 ይመልከቱ፡፡
መታፈሪያ20 መካከል በነበረው ክርክር እንደተመለከተው ዐቃቤ ህግ ምስክሮቹን አሰምቶ ከጨረሰ
በኋላ ለፍርድ ቤቱ አስተያየት አቅርቧል፡፡ ይሄውም ሁለተኛና ሶስተኛ የአቃቤ ህግ ምስክሮች
ፖሊስ ላይ የሰጡትን ምስክርነት ቀይረው የሰጡ ስለሆነ ምርመራውን ላጣራው ፖሊስ የሰጡት
ቃል ይያዝልኝ በማለት አሳስቧል፡፡ በዐቃቤ ህግ አስተያየት ላይ መልስ እንዲሰጥ የተጠየቀው
የተከሳሽ ጠበቃ እንደገለጸው ምስክሮች ለፖሊስ የሰጡት ቃል ለፍርድ ቤት ሊቀርብ የሚችለው
ምስክሩ ከሞተ፣ ከአገር ከወጣ ወይም በማንቻውም ሁኔታ ችሎት ቀርቦ መመስከር ካልቻለ
እንጂ ምስክሩ ቀርቦ በመሰከረበት ሁኔታ ፖለስ ላይ የሰጠው ቃል ይቅረብልኝ በማለት የቀረበው
አስተያየት የስነ-ስርዓት ህጉን ዓላማ ያልተከተለ ስለሆነ ውድቅ ሊደረግ ይገባል በሚል
ተከራክሯል፡፡ ፍርድ ቤቱም በቀረበው የግራ ቀኙ ክርክር ላይ ብይን ሳይሰጥ በዝምታ
እንዳለፈው የፍርድ ቤቱ መዝገብ ያመለክታል፡፡

በሌላ በኩል አንዳንድ ፍርድ ቤቶች ወይም ችሎቶች የዓቃቤ ህግ ምስክር መቅረብ ስላልቻለ
ምስክሩ ፖሊስ ላይ የሰጠውን ቃል ይያዝልን በሚል ዐቃቤ ህግ የሚያቀርበውን ክርክር ሲቀበሉ
አይታይም፡፡ ለምሳሌ በከሳሽ የመርሀቤቴ ወረዳ ዐቃቤ ህግ በተከሳሽ ባዩ ጌታቸው መካከል
በነበረው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክርክር የግል ተበዳይ የነበረችው የዓይን ምስክር
በአድራሽዋ ልትገኝ ባለመቻሏና ፍርድ ቤት ቀርባ ባለመመስከሯ ዐቃቤ ህግ ለችሎቱ ለፖሊስ
የሰጠችው ቃል እንዲያዝለት ቢያመለክትም በመጀመሪያ ደረጃ ጉዳዩን ሲመለከት የነበረው
የወረዳው ፍርድ ቤትም ሆነ ክርክሩን በይግባኝ የተመለከተው የሰሜን ሽዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ
ቤትና የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ክርክሩን ሳይቀበሉት ቀርተው
ተከሳሽ በነጻ እንደተሰናበተ መዝገቦቹ ያመለክታሉ21፡፡

ከላይ ከተመለከተው በተጨማሪ በአማራ ክልል ባሉ አንዳንድ ፍርድ ቤቶች በወ.መ.ስ.ስ.ህ.ቁ


145 ስር የተቀመጠውን ድንጋጌ ተፈጻሚ የሚያደርጉት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ለመርማሪ
ፖሊስ የሰጡትን ቃል ጉዳዩን በሚያየው ፍርድ ቤት ፊት ቀርበው ከመሰከሩት ቃል ጋር
የሚቃረን ሲሆን ዐቃቤ ህግ ለመርማሪ ፖሊስ የሰጡት ቃል የምርመራ መዝገቡ ይያዝልኝ
በማለት ያመለክታል፤ ፍርድ ቤቱም ይህንን ተቀብሎ የምርመራ መዝገቡ እንዲቀርብ በማድረግ
ማስረጃወን በመቀበል ከማስረጃ ሚዛን ውስጥ በማስገባት ውሳኔ እንደሚሰጥ ባለሙያዎች

20
የሰ/ሽ/ዞን ከ/ፍ/ቤት የወ/መ/ዝ/ቁ. 02-41118 ይመልከቱ
21
የሰሜን ሽዋ ዞን ፍትህ/መ/የወ/ይ/መዝ.ቁ. 20/2010፣ የሰ/ሽ/ዞ/ከ/ፍ/ቤት የወ/መዝ.ቁ 02-16151
ይጠቁማሉ22፡፡ ይህ የባለሙያዎቹ አስተያየትም በክርክሮች (በመዛግብት) ላይ ተፈጻሚ ሲሆን
ይታያል፡፡ ለምሳሌ በከሳሽ ዐቃቤ ህግ በተከሳሽ ወርቅዬ ዘገዬ መካከል በነበረው የውንብድና
ወንጀል የዓቃቤ ህግ ምስክር በሀሰት በመመስከሩ ቀደም ሲል ምስክሩ ለፖሊስ የሰጠው ቃል
እንዲያያዝ ተደርጎ ውሳኔ የተሰጠ መሆኑን የፍርድ ቤቱ መዝገብ ያመለክታል23፡፡ እዚህ ላይ
ትኩረት ሊደረግበት የሚገባው ነጥብ ዐቃቤ ህግ ምስክሬ አስጠቂ ስለሆነብኝ ለመርማሪ ፖሊስ
የሰጠው ቃል ይያዝልኝ በማለት ሲያመለክት ፍርድ ቤቱም የምርመራ መዝገቡን ካስቀረበ በኋላ
አስጠቂ ምስክር ተመስክሮብኛል ያለው ዐቃቤ ህግ መስቀለኛ ጥያቄ ወይም መሪ ጥያቄ
እንዲጠይቅ በማድረግ አስጠቂ የሆነበትን ምስክርነት እንዲያስተባብል ማድረግ ሲገባው ፍርድ
ቤቱ ከምርመራ መዝገቡ ላይ የምስክሩ ቃል ኮፒ ተደርጎ ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝ በማድረግ
ውሳኔ ሲሰጥ ይታያል፡፡ ይህም ከድንጋጌው ዓላማና ሀሳብ ውጭ ነው፡፡ የድንጋጌው ዓላማ
አስጠቂ ምስክር ሲሰጥ ወይም ተከሳሽ የዐቃቤ ህግ ምስክር ፖሊስ ላይ ከሰጠው ቃል ጋር
በሚቃረን መልኩ በፍርድ ቤት መሰከረብኝ በማለት ሲያመለክት በፍርድ ቤት የተሰጠውን ቃል
ለማስተባበል ዐቃቤ ህግ ወይም ተከሳሽ መስቀለኛ ወይም መሪ ጥያቄ እንዲጠይቅ በማሰብ
የተደነገገ ድንጋጌ ነው፡፡ በሌላ በኩል የዐቃቤ ህግ ምስክሮች በፍርድ ቤት ቀርበው ሲመሰክሩ
ሀሰት ስለመሰከሩ ቀደም ሲል ለፖሊስ የሰጡት ቃል ይታይልን በማለት ዐቃቤ ህግ
የሚያቀርበውን መከራካሪያ የማይቀበሉ ችሎቶችም እንዳሉ ይስተዋላል፡፡ ለምሳሌ በከሳሽ
የሰሜን ሽዋ ዞን ፍትህ መምሪያ በተከሳሽ መኮንን በላቸው መካከል በነበረው የሰው መግደል
ወንጀል የወንጀሉን ፈጻሚ በቀጥታ አይቻለሁ በማለት የዓይን ምስክር ሆና የቀረበችው ግለሰብ
ጉዳዩን በሚመለከተው ፍርድ ቤት ቀርባ ስትመሰክር አላየሁም በማለት ቃሏን ቀይራ
የመሰከረች በመሆኑ ዐቃቤ ህግ ለፖሊስ የሰጠችው ምስክርነት ይታይልኝ በማለት አቤቱታ
አቅርቦ ገዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ሰልጣኑ ሲመለከት የቆየው የሰሜን ሽዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ
ቤት ሳይቀበለው ቀርቷል24፡፡ በዚሁ ብይን ቅር በመሰኘትና ተከሳሽም ነጻ በመሰናበቱ አግባብ
አይደለም በማለት ይግባኙን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደብረ ብርሀን ቋሚ ችሎት አቅርቦ
የክልሉ ዐቃቤ ህግም የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዐቃቤ ህግ ምስክር የነበረችው ለፖሊስ
የሰጠችውን ቃል በመቀየሯ ምክንያት ዐቃቤ ህግ ምስክሯ ለፖሊስ የሰጠችው ቃል ፍርድ ቤቱ

22
ፍቃዱ አንዳርጌ፣ የሰሜን ሽዋዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ጋር ሀምሌ 2፣ 2010 ዓ.ም የተደረገ ቃለ መጠይቅ እንዲሁም
ከሀብታሙ አዲስ፣ የምእራብ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ የባህር ዳር ክላስተር ምድብ የወንጀል የስራ ሂደት አስተባባሪ፣ ሰኔ 15
2010 ዓ.ም የተደረገ ቃለ መጠይቅ
23
የሰ/ሽ/ዞ/ከ/ፍ/ቤት የወ/መዘ/ቁ. 02-39159 ከሳሽ ዐቃቤ ህግ ተከሳሽ ወርቅ ዘገዬ
24
የሰሜን ሽዋ ዞን ከ/ፍ/ቤት የወ/መዝ.ቁ 0236732
ይመልከትልኝ በማለት የተከራከረ ቢሆንም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የቀረበውን
ይግባኝ አልተቀበለውም25፡፡ በሌላ በኩል አንዳንድ ጊዜ ተከሳሽ የዐቃቤ ህግ ምስክር የመሰከረው
አላግባብ ነው ፖሊስ ላይ የሰጠው ምስክርነት አሁን ፍርድ ቤት በሰጠው ዓይነት አይደለም
በማለት ሲያመለክት የምርመራ መዝገቡን ፍርድ ቤት አስቀርቦ የሚመለከትበት ጊዜም እንዳለ
ይታያል26፡፡

የወ.መ.ስ.ስ.ህ.ቁ. 145 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በሚመለከት የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎተ27


በአመልካች የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዓቃቤ ህግ በተጠሪ
ሀብታሙ ካርሎ መካከል በነበረው ክርክር ተጠሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 556(2-ሐ) ስር
የተመለከተውን በመተላለፍ በፈጸመው የድብደባ ወንጀል ዐቃቤ ህግ ክስ አቅርቦ ሲከራከር
ቀደም ሲል ወንጀሉ ሲፈጸም አይተናል በማለት የመሰከሩ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ሀሰት
በመመስከራቸው የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ለፖሊስ የሰጡት ቃል ይያዝልኝ በማለት ዐቃቤ ህግ
ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ለተመለከተው ፍርድ ቤትም ሆነ በየደረጃው ላሉ ለክልሉ የይግባኝና
የሰበር ሰሚ ችሎቶች አቅርቦ አቤቱታው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ ዐቃቤ ህግም የሰበር
አቤቱታውን ለፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበ ሲሆን የአቤቱታው መነሻም የዐቃቤ ህግ
ምስክሮች ፖሊስ ላይ የሰጡትን ቃል ፍርድ ቤት ላይ በመቀየራቸው በወ.መ.ስ.ስ.ህ.ቁ 145
መሰረት ለፖሊስ የሰጡት ቃል ይያዝልኝ በማለት ባስስብም ፍርድ ቤቶቹ አልተቀበሉኝም
ይህም መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው የሚል ነው፡፡ ሰበር ሰሚ ችሎቱም አቤቱታው ያስቀርባል
ካራከረ በኋላ በወንጀል ክርክር ወቅት በተከራካሪ ወገኖችም ሆነ በፍርድ ቤት ምስክሮች
የሚጠየቁት ጥያቄዎች አይነታቸው የትኞቹ እንደሆኑ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ
ቁጥር 137፣ 138 እና 140 ስር የተመለከተ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ በተጨማሪም ግልጽ ያልሆኑ
ነጥቦችን ለማጣራት በዚሁ ህግ በአንቀጽ 136(4) እና 143(1) ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች
አስታውሷል፡፡ በተመሳሳይ በወ.መ.ስ.ስ.ህ.ቁ. 145 መሰረት ዓቃቤ ህጉ ወይም ተከሳሹ
ሲያመለክቱ ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ የተሰጠውን ቃል ሊመለከተው እንደሚችል ህጉ ቢያመለክትም
የዚህ ድንጋጌ መሰረታዊ ዓላማ በምርመራ ጊዜ የተሰጠውን ቃል በፍርድ ቤት ምስክሩ ቀርቦ
ቢለውጠው ይሄው ምስክርነት እንዲቃናና ፍርድ ቤት ለያዘው ክስ ሁልጊዜ ክብደት እንዲሰጠው
ለማድረግ ነው ተብሎ አይታሰብም በሚል የውሳኔ ሀተታውን ደምድሞ የቀረበው አቤቱታ

25
የአብከመ ፍትህ ቢሮ የወ.መዝ.ቁ. 21/2008፣የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት የወ/ይ/መዝ.ቁ 02-16806፣
26
በላቸው ኪዳኑ፣ በአብክመ ፍትህ ቢሮ የደብረ ብርሀን ቋሚ ምድብ ዐቃቤ ህግ ሰኔ 11፣2010 ዓ.ም
27
የፌደራል ሰበር ሰሚችሎት የወ/መ/ ቁ. 111498 ቅጽ 9 ይመልከቱ
ተገቢ እንዳልሆነና የስር ፍርድ ቤቶች መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት እንዳልፈጸሙ በመወሰን
የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ አጽንቷል፡፡ እዚህ ላይ ሰበር ሰሚ ችሎቱ በዝምታ
ያለፈውና በአግባቡ ሊመለከተው ይገባ የነበረው ጉዳይ ይህ ድንጋጌ አከራካሪ እንደመሆኑ መጠን
ሰበር ሰሚ ችሎቱ ለትርጉም ክፍትና እስካሁን ድረስ ገዢ የሆነ ትርጉም ያላገኘ በመሆኑ ሰበር
ሰሚ ችሎቱ ከተቋቋመለት ወጥ የሆነ የህግ አተረጓጎም እንዲኖር የማድረግ ዓላማ መሰረት
በወ.መ.ስ.ስ.ህ.ቁ 145 ስር የተቀመጠው ለፖሊስ የተሰጠ ምስክርነትን ፍርድ ቤት
የሚመለከተው ለምን ዓላማና እንዴት ነው የሚለውን ትርጉም ሰጥቶበት ማለፍ ይገባው ነበር፡፡
አሁንም ቢሆን የዚህን ድንጋጌ አተረጓጎም በሚመለከት በባለሙያው ዘንድ ወጥ የሆነ አቋም
የማይታይና ብዥታ ያለበት በመሆኑ ሰበር ሰሚ ችሎቱ በህግ የተጣለበትን ሀላፊነት በመወጣት
ወደፊት በድንጋጌው ላይ ተገቢ የሆነ ትርጉም በመስጠት ገዢ የሆነ ውሳኔ ቢሰጥ በበታች
ፍርድ ቤቶች የሚታየውን የተለያዬ አረዳድና አተረጓጎም ለማስቀረት ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡

4. ማጠቃለያ

በወ.መ.ስ.ስ.ህ.ቁ.145 (1፣2) ስር የተቀመጠውን ድንጋጌ በሚመለከት በባለሙያዎች ዘንድ


ሁለት ዓይነት ግንዛቤ እንዳለና በተግባርም ወጥ የሆነ አሰራር እንደሌለ ለመረዳት ይቻላል፡፡
አንዳንድ ባለሙያዎች ድንጋጌውን የሚረዱትና ተግባራዊ የሚያደርጉት የዓቃቤ ህግ ምስክሮች
በቂ በሚባል ምክንያት ፍርድ ቤት ቀርበው መመስከር ባልቻሉ ጊዜ ቀደም ሲል ለመርማሪ
ፖሊስ የሰጡት ቃል ሊያዝ ይገባል በሚል ዓቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ ያሳስባልም ፍርድ ቤቶችም
ይህንኑ ተቀብለው ማስረጃው ኮፒ ተደርጎ ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝ በማድረግ በማስረጃ ምዘና
ውስጥ በማስገባት ውሳኔ ሲሰጡ ይስተዋላል፡፡ በሌላ በኩል በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ
ቁጥር 145 ስር የተመለከተውን ለፖሊስ የተሰጠ ምስክርነት በፍርድ ቤት ተቀባይነት
የሚኖረው የቃቤ ህግ ምስክሮች ፍርድ ቤት ቀርበው ሲመሰክሩ ቀድመው ከሰጡት ቃል ጋር
የሚቃረን ሲሆን ይህንኑ ለማስተባበል ሲባል ዐቃቤ ህጉ ወይም ተከሳሹ ሲያመለክቱ ለመርማሪ
ፖሊስ የተሰጠውን ምስክርነት ፍርድ ቤቱ ሊመለከተው እንደሚችል ዓላማውም፣ ፍርድ ቤት
ላይ የተሰጠውን ምስክርነት ተዓማኒነት የሌለው ለማድረግ ነው፡፡ ማለትም ፖሊስ በምርመራ
ወቅት የተሰጠ የምስክርነት ቃል በፍርድ ቤት ተቀባይነት ሊኖረው የሚገባው የዐቃቤ ህግ
ምስክር በመሆን የቀረበው ምስክር ለዐቃቤ ህግ አስጠቂ ሲሆንበት ፍርድ ቤቱን በማስፈቀድ
መስቀለኛ ወይም መሪ ጥያቄ በመጠየቅ በፍርድ ቤት ቀርቦ የሰጠው ቃል ተዓማኒ እንዳልሆነ
በማሳየት ምስክርነቱን ለማስተባበል እንዲችል ነው፡፡ ከዚህ ውጭ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ፍርድ
ቤት ቀርበው ባልመሰከሩበት ሁኔታ ለፖሊስ የሰጡት ቃል ይያዝልን በማለት ዐቃቤ ህግ
የሚሰጠው አስተያየትና አንዳንድ ፍርድ ቤቶች ወይም ችሎቶችም በዚሁ መንገድ ፖሊስ ላይ
የተሰጠው ቃል ኮፒ እንዲደረግና ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝ ተደርጎ የሚሰራበት አግባብ ተገቢ
ያልሆነነና የድንጋጌውን ዓላማ ያልተከተለ ስለሆነ ሊታረም የሚገባው ነው፡፡ የድንጋጌውን ዓላማ
በአግባቡ ለመረዳት የጸረ ሙስና ልዩ የስነ-ስርዓትና የማስረጃ ህግ እንዲሁም ረቂቅ የስነ-ስርዓት
ህጉ ላይ የተቀመጡትን ተመሳሳይ ድንጋጌዎች ከወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ ድንጋጌ ጋር
አጣምሮ መመልከትና መረዳትም ይገባል፡፡ ይህም ማለት ምስክሩ ፍርድ ቤት ቀርቦ
ባልመሰከረበት ሁኔታ ለመርማሪ ፖሊስ የሰጠውን ቃል በቀዳሚ ምርመራ አድራጊ ፍርድ ቤት
እንደተሰጠ ምስክርነት በማስረጃነት ለመቀበል የሚቀርቡ ሁኔታዎች ተከሳሹ በሌለበት፣
በምስክርነት የቀረበበትን ምስክር የመጠየቅ ህገ መንግስታዊ መብቱ ባልተከበረበት እና
ምስክሮቹ ቃለ-መሀላ ባልፈጸሙበት ሁኔታ በፖሊስ ምርመራ ወቅት የተሰጠ የምስክርነት ቃል
እንደ ማስረጃ በመውሰድ ከማስረጃ ምዘና ውስጥ አስገብቶ ውሳኔ መስጠት ስህተት ነው፡፡
ስለሆነም በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ ቁጥር 145 ስር የተመለከተው ድንጋጌ ተፈጻሚ
መሆን ያለበትና ሊተረጎም የሚገባው የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ፍርድ ቤት ቀርበው ከመሰከሩ
በኋላ አስጠቂ ከሆኑ ዐቃቤ ህጉ ወይም ተከሳሹ የተሰጠውን ምስከርነት ለማስተባበል በመስቀለኛ
ጥያቄ ወይም በመሪ ጥያቄ አማካኝነት የሚያስተባብሉበት ስርዓት ለመፍጠር በማሰብ የተቀረጸ
ድንጋጌ እንደሆነ ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ጠቃሚ ነው፡፡
በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶች ፍትሃብሔራዊ መፍትሔዎች
በኢትዮጵያ የህግ ማዕቀፍ

ይበልጣል ይመር

አፅሮተ-ይዘት

በአሁኑ ወቅት ፆታዊ ጥቃት የሚለዉ ሐረግ ለጆሮ አዲስ አይደለም፡፡ ይሁንና ፆታዊ ጥቃት
ማለት ምን ማለት እንደሆነ ትርጉም የሚያስቀምጥ የህግ ድንጋጌ በኢትዮጵያ የለም፡፡ ፆታዊ
ጥቃት፤ ፆታዊ ትንኮሳና አስገድዶ መድፈር የሚሉት ሃረጎች በተግባር ሲደበላለቁ ይስተዋላል፡፡
እነዚህ ሃረጎች በተወሰነ መልኩ የሚገናኙ ግን የሚለያዩም ናቸዉ፡፡ የፆታዊ ጥቃት ትርጉም
ከፅንሰ ሃሳቡ ጋር ሲጣመር ፆታን መሰረት ያደረጉ በሴቶች ወይም በወንዶች ላይ የሚፈፀሙ
ጥቃቶችን ሁሉ ያካትታል፡፡ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ ፆታዊ ጥቃትን የሚተረጉም ድንጋጌ
ባይኖረዉም በተበታተነ ሁኔታ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶችን አካቷል፡፡
በሴቶች ላይ የሚፈፀሙት ፆታዊ ጥቃቶች በከፍተኛ ደረጃ የስነ ልቦና ወይም የአእምሮ ጉዳት
በማድረስ ጥቃቱ ከተፈፀመበት ቅፅፈት ጀምሮ እስክ ህይወት ፍፃሜ ድረስ የሚዘልቅ ጠባሳ
ይጥላሉ፡፡ ጉዳቱ ከድብርት እስከ ራስን መጥላትና ራስን ማጥፋት እንደሚደርስ ጥናቶች
ያሳያሉ፡፡ በጤና ላይ ስነ ህይወታዊና አካላዊ መቃወስ ያስከትላሉ፡፡ እነዚህ የስነ ልቦናና የጤና
ጉዳቶች ያለን ንብረት የማጥፋት፤ ስራን መልቀቅ፤ የስራ ችሎታና ፍላጎትን ወዘተ በማሳጣት
የገንዘብ ጉዳት ያደርሳሉ፡፡ የገንዘብ፤ የጤናና የህሊና ጉዳት የደረሰበት ሰዉ ለጉዳቱ ከተቻለ
በተመዛዘነ መልኩ ካልተቻለ በርትዕ ካሳ ማገኘት የሰዎች ተፈጥሮዊ መብት ሲሆን
የመንግስታት ደግሞ ጉዳት ለደረሰበት ሰዉ ፍትህና ካሳ ማስከፈል ወይም መክፈል ግደታ
ነዉ፡፡ ይሁንና ለእነዚህ ጉዳቶች በተሟላ መልኩ የሚያስከፍል የህግ ድንጋጌ የለም፡፡ ይህ
ጥናት የፆታዊ ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶች ያሏቸዉን ፍትሃ ብሔራዊ የህግ ማዕቀፎች ብቻ
የሚዳስስ በመሆኑ የጥናቱ ዘዴ ፅንሰ ሃሳባዊ (Doctrinal) ነዉ፡፡

LLB,LLM በአብክመ የፍ/ባ/ማ/ህ/ም/ኢ/ተመራማሪ email yibeeyimer@yahoo.com

1
1. መግቢያ

በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች (Violence against Women) እስከ 1980ዎቹ ድረስ በዓለም
አቀፍ ደረጃ ትኩረት ያልተሰጠዉ ጉዳይ ወይም ችግር ነበር፡፡1 ይሁንና በ1980ዎቹ መጀመሪያ
ጀምሮ በየአገራቱ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደራጁ የሴቶች ማህበራት በሴቶች ላይ
የሚፈጸሙ ፆታዊ፤ አካላዊ፤ ስነ ልቦናዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቃቶች ዓለም አቀፍ
ትኩረት እንዲሰጣቸዉ ጥረት አድርገዋል2፡፡ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት ምንድን እንደሆነ
እስከ አሁን ድረስ ሁሉን የሚያግባባና ወጥ የሆነ ትርጉም የለዉም በተለያዩ የሙያ ዘርፎች
እንዲሁም አካባቢዎች የተለያዩ ቃላቶች ይሰጡታል፡፡ ለምሳሌ Family Violence, Gender Based
Violence, Domestic Violence, Spose Abuse, Sexualized Violence, Intimate/ non-intimate partner
Violence…በሚል ይገለፃል፡፡ በዚህ ፅሁፍ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ሁሉንም ዓይነት ጥቃቶች
ሳይሆን ከሴትነት ጋር የተያያዙትን ጥቃቶች ማለትም Sexual Violence3 ብቻ እንመለከታለን፡፡

1.1. ፆታዊ ጥቃት ምንድን ነው?

ፆታዊ ጥቃት በ መዝገበ ቃላቶች ውስጥ ትክክለኛ ትርጉሙ ምን እንደሆነ ማወቅ አዳጋች
ነው4፡፡ የህግ ትርጉሙን በተመለከተ በኢትዩጵያ ህግጋት ውስጥ ፆታዊ ጥቃት ማለት ምን

1
Ellsberg Mary and Heise Lori, Researching Violence against Women; A Practical Guide for Researcher and
Activists, USA, World Health Organization, 2005, page, 5 available at
https://patth.azureedge.net/media/documents/GBV_rvaw_front.pdf
2
ዝኒ ከማሁ ገፅ 5
3
ለምሳሌ አንድ ወንድ አንዲት ሴትን ቢደበድባት የአካል ጉዳት ወንጀል ነዉ፡፡ ይህም ተራ ወይም ደረቅ ወንጀል ሲሆን አንድ
ወንድ አንዲትን ሴት ቢደፍራት ይህ አድራጎቱ በሴትነቷ ምክንያት የተፈፀመባት ድርጊት በመሆኑ በሴትነት ላይ የተፈጸመ
ወንጀል ወይም ጥቃት (Sexual Violence) በሚል ለመግለፅ ተሞክሯል፡፡
4
ለምሣሌ ዘርጋው ከፍተኛ የአማረኛ መዝገበ ቃላት፡- ጥቃት ማለት 1.ግፍ፣ ጭቆና፣ በደል፣ ወረታ፣ የሃይል እርምጃ ሢለው፡፡

Sexual Violence ምንድን ነው ስንል ደግሞ የተለያዩ መዝገበ ቃላቶች እንደሚከተለው ይተረጉሙታል፡፡ ለምሣሌ፡- Black’s

law Dictionary Sexual Violence The use of physical force, usually accompanied by fury Vehemence or
4
outrage, especially physical force, unlawfully exercised with the intent to harm.

ይህም ወደ አማረኛ ሢመለስ ብስጭት ና በደል የተቀላቀለበት አካላዊ ጐልበትን በመጠቀም ሌሎችን ለመጉዳት በማሠብ

በጉልበት ከህግ ውጭ የፈፀመ ጥቃት ነው ማለት ይቻላል፡፡ Oxford Dickonary በበኩሉ Violence Behavior involving

physical force intended to hurt damage or kill some one or something. በማለት ተርጉሞታል፡፡

2
ማለት እንደሆነ በግልፅ ትርጉም አልተቀመጠለትም፡፡ የኢ.ፊ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግን ብንመለከት
በመፅሃፍ አምስት ስር በሌሎች ሠዎችና በቤተዘመድ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ከአንቀፅ
538 - 661 ደንጓል፡፡ በውስጡ አራት ርዕሶች፣ በእያንዳንዱ ርዕሰ ስር ምዕራፎች፣ በየምዕራፎቹ
ስር ክፍሎች ተዋቅረዋል፡፡ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃት እየተባሉ በልምድ የሚታወቁ
ወንጀሎች በየርዕሶች፣ ምዕራፎችና ክፍሎች ተበታትነው ይገኛሉ፡፡ ለማሣያ ያህል የቤት ውስጥ
ጥቃት /አንቀፅ 564, የሴትን ልጅ ብልት መስፉት አንቀፅ 566 በርዕስ 1 በምዕራፍ 3 ስር
ሢገኙ አስገድዶ መደፈር (አንቀፅ 620) በርዕሰ 4 ምዕራፍ 1 ክፍል 1 ይገኛል፡፡5 በመሆኑም
ፆታዊ ጥቃት ማለት ምን እንደሆነ ትርጉም ካለማስቀመጡም ባሻገር በተበታተነ ሁኔታ
መደንገጉ ድርጊቱን ለመረዳት አደጋች ያደርገዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የፆታዊ ጥቃት ትርጉምን ስንመለከት የዓለም ጤና ድርጅት (WHO)
Sexual Violence is ‘Any sexual act, attempt to obtain a sexual act, unwanted sexual comments or
advances, or acts to traffic or otherwise directed against a person’s sexuality using coercion, by
any person regardless of their relationship to the victim, in any setting, including but not limited
to home and work’6 በማለት ትርጉም ሰጥቶታል፡፡ ይህም በግርድፉ ወደ አማርኛ ሢመለስ
“ፆታዊ ጥቃት ማለት ማንኛውም ፆታዊ ድርጊት፡- ፆታዊ ድርጊት ለማግኘት መሞከር፣
ያልተፈለገ ፆታዊ አስተያየት ወይም ሙገሣ ወይም ለማዘዋወር የሚደረግ ድርጊት፡- ወይም
የሰዎችን ፆታዊ ጥቅም በሃይል ለማግኘት የሚደረጉ አድራጐቶች ሆነው፤ ከተጐጅው ጋር
ያለው ግንኙነት ከግምት ውስጥ ሳይገባ በማናቸውም ሁኔታና በስራና በመኖሪያ ቤት ሣይገደብ
የሚፈፀም ድርጊት ነው፡፡” የሚል ትርጉም ይሰጣል፡፡

በሌላ በኩል የጥናትና ምርምር ድርጅቶች7 Sexual violence is defined as: being physically
forced to have sexual intercourse when you did not want to, having sexual intercourse because
you were afraid of what your partner might do, and/or being forced to do something sexual that
you found humiliating or degrading በማለት የስራ ትርጉም ሰጥተዉታል፡፡ ሌላዉ በሴቶች ላይ
የሚደርሱ ፆታዊ ጥቃት ምን እንደሆነ ትርጉም የሠጠው ህግ በ1993 (እ.ኤ.አ) በተባበሩት
መንግስታት ዉሳኔ የፀደቀዉ (Declaration on the Elimination of Violence against Women)

5
የአ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አዋጅ ቁጥር 414/1996፤
6
The World Health Organization (WHO), report, Understanding and addressing violence against women, 2013,
page 2
7
Global and regional estimates of violence against women, page 13

3
/DEVAW/ በሚባል የሚጠራው መግለጫ ነው፡፡ በዚህ ህግ አንቀፅ 1 ላይ “Violence against
women” means any act of gender-based violence that results in, or is likely to result in, physical,
sexual or psychological harm or suffering to women, including threats of such acts, coercion or
arbitrary deprivation of liberty, whether occurring in public or in private life.8
በሴቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃት ማለት ፆታን መሰረት ያደረገ ማንኛውም ድርጊት ሆኖ አካላዊ፣
ፆታዊ ወይም ስነ-ልቦናዊ ጉዳትን ወይም ስቃይን በሴቶች ላይ ያስከተለ ወይም ሊያስከትል
የሚችሉ ድርጊቶች፣ ማስገደድ ወይም የጋራ ና የግል ህይወት ነፃነትን ያለህግ መቀማት ነው፡፡
በሚል ሊተረጐም ይችላል፡፡ በተጨማሪም በዚሁ ህግ በአንቀፅ ሁለት ላይ Violence against
women shall be understood to encompass, but not limited to, the following (a) Physical, sexual
and psychological violence occurring in the family, including battering, sexual abuse of female
children in the household, dowry- related violence. Marital rape, Female genital mutilation and
other traditional practices harmful to women, non-spousal violence and violence related to
exploitation.

(b) Physical, sexual or psychological violence with in the general community, including rape,
sexual abuse, sexual harassment and intimidation at work in educational institutions and
elsewhere, trafficking in women and forced prostitution.9 በማለት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ
ጥቃቶችን ስንረዳ ማካተት ያለባቸውን ብቸኛ ያልሆኑ ድርጊቶችን ዘርዝሯል፡፡ በመሆኑም
በቤተሠብ ውስጥ የሚታዩ አካላዊ፣ ፆታዊና ስነ ልቦናዊ ጥቃት ስንል መጐንተልን ጨምሮ
እንደ በቤት ውስጥ ያሉ ህፅናት ሴቶች ላይ የሚደረጉ ፆታዊ በደሎች፣ በከጥሎሽ ጋር የተያያዙ
ጥቃቶች፣ የጋብቻ ላይ አስገድዶ መደፈር፣ የሴት ልጅን ብልት መተልተል፣ እና ሌሎች ሴቶች
ላይ የሚያደርሱ ጐጅ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲሁም ከጋብቻ ዉጭ ያሉ ጥቃት ነክ
ብዝበዛዎችን ያካትታል፡፡ በማህበረሠቡ ውስጥ ያሉ አካላዊ፣ ፆታዊ ና ስነ-ልቦናዊ ጥቃቶች
ስንል በስራ ቦታ ና በትምህርት ተቋማቶች የሚታዩ የአስገድዶ መደፈር፣ ፆታዊ ጉዳትና ፆታዊ
ትንኮሣና ማስፈራሪያዎችን ያካትታል፡፡ እንዲሁም የሴቶች ህገወጥ ዝውውርና የግዳጅ ሴተኛ
አዳሪነትንም ይጨምራል፡፡

8
.Declaration on the Elimination of Violence against Women Proclaimed by General Assembly resolution

48/104 of 20 December 1993


9
ዝኒ ከማሁ አንቀፅ 5 2(1)እና(2)

4
ሌላዉ መገለፅ ያለበት ነጥብ አንዳንድ የፆታዊ ጥቃት ዓይነቶች በዋነኝነት አስገድዶ መድፈር
በሰዉ ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች (Crime against Humanity) አካል ሊሆን የሚችልበት
እድል አለ፡፡ ይህም በዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት ህግ (International Criminal Court Statute
10
ዉስጥ ተካቷል፡፡ በእርግጥ የአስገድዶ መድፈር ድርጊቱ የተፈጸመዉ በስፋት ወይም በተጠና
መልኩ ሲሆን በሰዉ ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ክፍል ሊሆን እንደሚችል የዚህ ህግ
አንቀፅ 7(1) በግልፅ ያሳያል፡፡ በመሆኑም በሰዉ ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች አካል
የሚያደርገዉ ገፅታ በዚህ ፅሁፍ የሚሸፈን አይሆንም፡፡

1.2. በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች

ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በተለያዩ መልኩ ይገለፃሉ፡፡ ከእነዚህም ዉስጥ ዋና ዋናዎቹ
sexual violence, Sexual harassment, Sexual assault, Sexual abuse ,rape ናቸዉ፡፡ እነዚህ
አገላለፆች በመለዋወጥ ስንጠቀምበት ይስተዋላል፡፡11 በተለይም Sexual Violence, Sexual
Harassment, Sexual Assault የሚሉትን ቃላቶች ልዩነቶች መረዳት ጠቀሜታዉ ከፍ ያለ
በመሆኑ በዚህ ፅሁፍ እንደሚከተለዉ ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡

ፆታዊ ጥቃት ምን እንደሚመስል ከፍ ሢል በትርጉሙ ክፍል ተመልክቷል፡፡ ፆታዊ ትንኮሣ


(Sexual Harassment) ፆታዊ ጥቃት ጋር ያለውን ልዩነት መረዳት ያስፈልጋል፡፡ብላክስ ሎዉ
መዝገበ ቃላት Sexual harassment “A type of employment discrimination consisting in verbal or
physical abuse of sexual nature ይለዋል፡፡ ይህም ፆታዊ ትንኮሳ ፆታ ነክ ልዩነት ሆኖ ያልተፈለገ
ወሲባዊ ሙገሳ፤ጥያቄና መድልኦ እንዲሁም ሌሎች ወሲባዊ ተፈጥሮ ያላቸዉ ቃላዊ እና
አካላዊ ድርጊቶች ያካትታል፡፡ በተጨማሪም Sexual harassment is a form of sex discrimination
that involves unwelcome sexual advances, requests for sexual favors, and other verbal and
physical conduct of a sexual nature12. በሌላ መልኩ ፆታዊ ትንኮሳ Sexual Harassment can be a
conduct which is unwelcome to its recipient allows a distinction to be drawn between inoffensive

10
For the purpose of this Statute, "crime against humanity" means any of the following acts when committed as
part of a widespread or systematic attack directed against any civilian population, with knowledge of the attack:…
(g) Rape, sexual slavery, enforced prostitution, forced pregnancy, enforced sterilization, or any other form of
sexual violence of comparable gravity;
11
Sexual violence: prevalence, dynamics and consequences, page,6
www.who.int/violence_injury_prevention/resources/.../en/guidelines_chap2.pdf,
12
Deirdre McCann, Sexual harassment at work: National and international responses,International Labour
Organization 2005,page 3

5
and unacceptable behaviour according to the context in which it takes place13 በሚል ይገለፃል
ይህም ሲተረጎም “ማንኛዉም ዓይነት ያልተፈለገ ባህርይ ሆኖ በተለይም ትንኮሳ የተደረገበትን
ሰዉ በሚያስከፋና ባልተቀበለዉ ሁኔታ ሲከናወን ነዉ”፡፡ የሚል መልዕክት ያስተላልፋል፡፡

ፆታዊ ትንኮሳ በአለም አቀፍ ደረጃ እዉቅና እየተሰጠዉ የመጣዉ ከ1970ዎቹ በኃላ ነዉ፡፡ እስከ
1970ዎቹ ድረስ ስም እንኳን አልነበረዉም፡፡ በ1970ዎቹ መጀመሪያ ገደማ የአሜሪካ ሴቶች
በሚያደርጉት የሴቶች መብት እንቅስቃሴ (feminist movement) ዉስጥ ፆታዊ ትንኮሳን
በፌዴራሉ የፀረ- ልዩነት ህግ ስር እንዲካተት ጥያቄያቸዉን ማቅረብ ጀመሩ፡፡ በዚሁ መሰረት
በ1970ዎቹ አጋማሽ በወጣዉ የአሜሪካ የፌደራል ሰብዓዊ መብቶች ህግ (federal civil rights
act) ፆታዊ ትንኮሳ ፆታን መሰረት ያደረገ ጉዳት እንደሆነ እዉቅና በመስጠት የህጉ አካል
ተደረገ፡፡ ይሁንና ፆታዊ ትንኮሳ በአለም አቀፍ ደረጃ ብዙም እዉቅና ያልተሰጠዉና ገና በጅምር
ላይ ነበር፡፡ ለዚህም ይመስላል በተባበሩት መንግስታት በ1979 የፀደቀዉ በሴቶች ላይ
የሚደረግ ማንኛዉንም አድሏዊ ልዩነት ማስወገድ ስምምነት ( Conventions on the Elimination
of all forms of Discrimination Aganst Women) /CEDAW/ ላይ ፆታዊ ትንኮሳን አስመልክቶ
ግልፅ ክልከላ ያላስቀመጠዉ፡፡ የኃላ ኃላ በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛዉንም አድሏዊ ልዩነት
ማስወገድ ስምምነት ኮሚቴዎች ፆታዊ ትንኮሳን እየተገነዘቡትና በሪፖርታቸዉ እያካተቱት
መጡ፡፡ በመጨራሻም በ1989 ፆታዊ ትንኮሳ በሴቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃትና የእኩልነት
መብታቸዉን በእጅጉ እየጎዳ ያለ መሆኑን ባቀረቡት ሪፖረት አሳሰቡ፡፡ በዚሁ መሰረት
በተባበሩት መንግስታት ዉሳኔ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ማስወገድ ድንጋጌ
(Declaration on the Elimination of Violence Against Women) /DEVAW/ ፀደቀ፡፡ በዚህ ድንጋጌ
አንቀፅ 2 (ለ) … sexual harassment and intimidation at work in educational institutions and
elsewhere,… በሚል ተካተተ፡፡ ይህም ፆታዊ ትንኮሳና ማስፈራሪያ በትምህርትም ተቋማት፣
በስራ ቦታና በየትኛዉም አካባቢ መፈፀም በሴቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃትና አካል ሆኖ ተቆጠረ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የዓለም አቀፍ የሰራተኞች ድርጅት (ILO) በ1999 ባንግ ኮክ ላይ በካሄደዉ
4ኛዉ የሴቶች ስብሰባ ላይ ፆታዊ ትንኮሳን እዉቅና ሰጠ፡፡ ከዚህ ባሻገር የተባበሩት መንግስታት
ጠቅላላ ጉባኤ በቤጅንግ ቃልኪዳንና የድርጊት ምቹ ሁኔታ The Beijing Declaration and Platform
for Action በ1995 የፀደቀዉ ፆታዊ ትንኮሳ የሴቶችን የእኩልነት መብት የሚጋፋ ድርጊት ነዉ፡፡
ስለሆነም ይህን ድርጊት ለመዋጋት መንግስታት ልዩ ትኩረት በመስጠት እንዲሠሩ
13
ዝኒ ከማሁ ገፅ 2

6
ተስማምተዋል፡፡ ፆታዊ ትንኮሳ በብዙ መልኩ ይገለፃል14፡፡ እነዚህም በአካል ከመንካት እስከ
መጉዳት፣ ምልክት ከማሳየት እስከ ፆታ ነክ ግብዣ፣ በቃላት ወሲባዊ ቀልድ ከመቀለድ እስከ
ወስብ ነክ ስድቦች፣ እንዲሁም በማሞገስ፣ በማድነቅና ልዩ ስጦታ መስጠትን ያካትታል፡፡ ከዚህ
የምንገነዘበው ፆታዊ ትንኮሣ በአካል ወይም በምልክት የሚገለፀው ፆታዊ ፍላጐቶች
(ድርጊቶችን) በሌላኛው ሠው ላይ ማሣደር ነው፡፡ በመሆኑም ፆታዊ ትንኮሣ ድርጊቶች ወንጀል
ናቸው ተብለው በኢትዩጵያ የህግ ሥርዓት አልተካተቱም፡፡

አሁን በቅርቡ የወጣዉ የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር1068/2010 ፆታዊ ትንኮሳን
እንደሚከተለዉ ተርጉሞታል፡፡ “ፆታዊ ትኮሳ ማለት በስራ ቦታ የሚፈፀም ሆኖ ከሌላዉ ወገን
ፈቃድ ወጭ የሚቀርብ የወሲብ ሃሳብ ወይም ጥያቄ ወይም ሌላ ወሲባዊ ተፈጥሮ ያለዉ የቃል
ወይም የአካል ንክኪ ተግባር ሲሆን የሚከተሉትን ያካትታል፡፡

ሀ/ ከሌላዉ ወገን ፈቃድ ዉጭ የመሳም፤ የሰዉነት አካልን የመዳሰስ፤ የመጎንተል፤ወይም


የመሳሰለዉን የሰዉነት ንክኪ የመፈፀም ድርጊት

ለ/ ወሲብ አዘል በሆነ ሁኔታ ተጠቂዉን መከታተል ወይም እንቅስቃሴዉን መገደብ

ሐ/ ለቅጥር፤ ለደረጃ ዕድገት፤ ለዝዉዉር፤ለድልድል፤ለስልጠና፤ ለትምህርት፤ለጥቅማ ጥቅም


ወይም ማንኛዉንም የሰዉ ሃብት አመራር ተግባር ለመፈፀም ወይም ለመፍቀድ ወሲብን
እንደቅደመ ሁኔታ ማስቀመጥ”15 ወሲባዊ ትንኮሳን ሊያካትቱ የሚችሉ ተግባራቶች ናቸዉ፡፡

Sexual Assault ከ Sexual Violence ጋር በተመሣሣይነት ስንጠቀምበት ይስተዋላል፡፡ ብላክስ ሎዉ


መዝገበ ቃላት Assault ትርጉም ሢሠጠው ‘The threat or use of forceon another that causes that
person to have a reasonable apprehension of imminent harmful or offensive conduct: the act of
putting on another person in reasonable fear or apprehension of an immediate battery by means
of an act amounting to an attempt or threat to commit battery.’ በመሆኑም Assault ከትንኮሣ ጎላ
ያለ አካላዊ ና ስነልቦናዊ ጫና በግለሠቡ ላይ ያስከትላል፡፡ በህግ ረገድ በአትዮጵያ ወንጀል ህጉ

14
Physical conduct • Physical violence • Physical contact, e.g. touching, pinching • The use of job-related threats or
rewards to solicit sexual favours Verbal conduct • Comments on a worker’s appearance, age, private life, etc. •
Sexual comments, stories and jokes • Sexual advances • Repeated social invitations • Insults based on the sex of
the worker • Condescending or paternalistic remarks Non-verbal conduct • Display of sexually explicit or
suggestive material • Sexually-suggestive gestures • Whistling
15
የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር1068/2010 አንቀፅ 2/13 በተመሳሳይ አድሱ የአ.ብ.ክ.መ መንግስት ሰራተኞች
አዋጅ ቁጥር 253/2010 አንቀፅ 2/13

7
አንቀፅ 560 የእጅ እልፊት፤ እንዲሁም በአንቀፅ 840 የእጅ እልፊትና ቀላል ሃይል ድርጊት
በሚል ያካተታቸዉን ወንጀሎች የእንግሊዝኛወ ቅጅ አንቀፅ 560 assault; ሲለዉ በአንቀፅ 840
assault and minor acts of violence በሚል ተክቶታል ወይም ተጠቅሟል፡፡ በአንቀፅ 560 ላይ
የተመለከተዉ የእጅ እልፊትን ወይም assault ይዘት ስንመለከት “ማንም ሰዉ የአካል ጉዳት
ወይም የጤንነት ጉድለትን ሳያደርስ በሌላዉ ሰዉ ላይ የእጅ እልፊት ወይም የመግፋት ድርጊት
መፈፀመ” እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ ይሁንና ቀላል የሆኑ ሰንበሮች የደም መቋጠር ምልክቶች
ወይም በቶሎ የሚያልፍ ህመም ወይም ስቃይ እንደ አካል ጉዳት ወይም እንደ ጤና ጉድለት
እንደማይቆጠር ድንጋጌዉ ይናገራል፡፡ በደንብ መተላለፍ ረገድ የተመለከተዉ አንቀፅ 840
እንዲሁ ማንም ሰዉ ሌላዉን ሰዉ ሳይመታ ወይም ሳያቆስል የእጅ እልፊት ወይም ቀላል
የሃይል ድርጊት መፈፀም እንደሆነ ያስረዳል፡፡

በተጨማሪም በኢትዩጵያ የፍትሃብሔር ህግ አንቀፅ 2038 በእንግሊዝኛው ቅፅ physical assault


በሚል ርዕስ (1) A person commits an offence where he intentionally makes contact with the
person of another against the latter;s will. ተደንግጓል፡፡ የዚህም የአማርኛ ቅጅ ሰውነትን
ስለመጉዳት በሚል ርዕስ (1) አንድ ሰው ሆነ ብሎ ሌላው ሰው ሣይፈቅድ በሚያደርገው
መንካት በዚህ በመንካቱ ጥፉተኛ ነው በሚል ተደንግጓል፡፡

የዚህ ድንጋጌ ይዘት እንደሚነግረን ሰውን ያለፈቃዱ መንካት ጥፉት እንደሆነ ነው ይህ


ማለትም መንካቱ ጉዳት ቢያደርስም ባያደርስም ጥፉት ነው፡፡ ይህም የሰወችን የግል ነፃነት
/ለመጠበቅ ያሰበ ይመስላል፡፡ በመሆኑም assault ከ violence ያነሠ ክብደት እንዳለው ያሳያል፡፡
በመሆኑም በዚህ ፅሁፍ በሴቶች ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች የሚለውን ሃሣብ በእንግሊዝኛው
violence ማለታችን ነው፡፡

1.3 በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ህግ የተካተቱ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጾታዊ


ጥቃቶች

የወንጀል ህግ የአንድን ሀገር ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ ለማስጠበቅ


የሚያስችል፣ የግለሰቦችን ሁለንተናዊ መብት እና ነጻነት የሚያስከብር መሆን ይጠበቅበታል፡፡
ቀደም ሲል ስራ ላይ የነበረውና የተሻረው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ በጊዜና በተለያዩ ምክንያቶች
ህጉ ከወጣ በኃላ የመጣውን ዓለማቀፋዊ እድገት፣ አስተሳሰብ እና ሌሎች ሁለንተናዊ ለውጦችን
ያገናዘበ አልነበረም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሴቶችን መብት ጨምሮ ሌሎች አሁን ስራ ላይ

8
የዋለው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት ካካተታቸው እና ሀገሪቱ ካጸደቀቻቸው አለምአቀፍ የሰብአዊ
መብት ስምምነቶች እና ሰነዶች ጋርም የተጣጣመ አልነበረም፡፡ በመሆኑም ይህ ህግ እንዲሻሻል
ከሆነ በኋላ በ1996 በወጣው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ህግ እንዲተካ ተደርጓል፡፡ በዚህ አግባብ
የተሻሻለው የወንጀል ህግ በተለይም ለሴቶችና ህጻናት መብትና ደህንነት ጥበቃ የሰጡ
ድንጋጌዎችን ይዟል፡፡ በዋናነት እንደ በግብረ-ሥጋ ነፃነትና ንጸህና ላይ የሚፈጸሙ ወጀሎችን
(አንቀጽ 620-628)፣ ለተፈጥሮ ተቃራኒ ባህሪይ የሆኑ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ድረጊቶችን
(አንቀጽ 629-632)፣ የተለያዩ ጎጅ ልማዳዊ ድረጊቶችን (አንቀጽ 561-562)፤ ጠለፋ (አንቀጽ
587-590)፣ ያለእድሜ ጋብቻ (አንቀጽ 647-648)፣ አካል ላይ ጉዳት ማድረስ (አንቀጽ 555-560)
፣ በትዳር ጓደኛ ወይም ከጋብቻ ዉጭ በሆነ ግንኙነት ባላቸዉ ሰዎች መካከል የሚፈጸም ጥቃት
(አንቀጽ 564)፣ የዝሙት ተግባር (አንቀጽ 635-638)፣ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ህፃናትን
መጉዳት (አንቀጽ 576) እና የመሳሰሉትን በዝርዝር አስቀምጧል፡፡

Ø በግብረ ስጋ ንጽህና ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች

በግብረ ስጋ ንጽህና ላይ ከሚፈጸሙ ወንጀሎች መካከል የአስገድዶ መድፈር ወንጀልን ስንመለከት


ከእለት ወደ እለት እየተበራከተ በመምጣቱና ቅጣቱ የማስፈራራት ሀይል እንዲኖረውና
ፈጻሚውም በቀላል ቅጣት እንዳይታለፍ በሚል ህግ አውጭው ቀድሞ ለድንገጌው ከተቀመጠው
የቅጣት መነሻ ወደ አምስት አመት ክፍ አድርጎታል፡፡ በመሆኑም ማንም ሰው የሀይል ድርጊት
በመጠቀም ወይም በብርቱ ዛቻ ወይም ህሊናዋን እንድትስት ወይም በማናቸውም ሌላ መንገድ
መከላከል እንድትችል በማድረግ ከጋብቻ ውጭ አስገድዶ ከአንዲት ሴት ጋር የግብረ ስጋ
ግንኙነት የፈጸመ እንደሆነ ከአምስት ዓመት እስከ አስራ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት
እንደሚቀጣ አንቀጽ 620(1) ስር ተመልክቷል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአዲሱ የቤተሰብ ህግ
ዝቅተኛው የጋብቻ እድሜ አስራ አምስት አመት መሆኑ ቀርቶ አስራ ስምንት አመት ሆኗል፡፡
ስለሆነም ወንጀሉ የተፈፀመዉ እድሜያቸው አስራ ሶስት አመት በሆና አስራ ስምንት አመት
ባልሞላት ሴት ልጅ ላይ ሲሆን ወይም ወንጀሉ የተፈመጸው በጥፋተኛው መሪነት ቁጥጥር
ወይም ስልጣን ስር በሆነ የመጦሪያ ቤት የመማጠኛ፣ የህክምና፣ የትምህርት ፣የጠባይ
ማረሚያ፣ የመታሰሪያ ወይም የተያዙ ሰዎች መቆያ ተቋማት ውስጥ በምትገኝ ወይም በተከሳሹ
ጥበቃ ወይም ቁጥጥር ስር በምትገኝ ወይም የእሱ ጥገኛ በሆነች ሴት ላይ ሲሆን ወይም
በእድሜ መግፋት በአካል ወይም በአዕምሮ ህመም፣በመንፈስ ድክመት ወይም በማናቸውም ሌላ
ምክንያት የድርጊቱን ምንነት /ባህሪይ/ ወይም ቁጥጥር ስር በምትገኝ ወይም የእሱ ጥገኛ በሆነች

9
ሴት ላይ ሲሆን ወይም በዕድሜ መግፋት በአካል ወይም በመንፈስ ድክመት ወይም በሌላ
ምክንያት የድርጊቱን ምንነትም ሆነ ውጤትም ለማወቅም ሆነ ለመከላከል በማትችል ሴት ላይ
ከሆነ ወይም ይህ ድፍረት የተፈጸመው በጭካኔ በማሰቃየት ወይም ቁጥራቸው ከአንድ በላይ
በሆኑ ወንዶች ከሆነ ቅጣቱ ከብዶ ከአምስት አመት እስከ ሀያ አመት ሊደርስ በሚችል ጽኑ
እስራት ያስቀጣል16፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በአንቀጽ 620 (4) ስር አስገድዶ ከደፈራት በኃላ ከህግ
ውጭ ተበዳዩዋን ይዞ ካቆየ ወይም ጠለፋ ካለ ወይም በድፍረቱ ምክንያት በሽታ የተላለፈባት
ከሆነ እነዚህን የሚመለከቱ የዚሁ ህግ ድንጋጌዎች በተደራቢነት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

ሌላው በአንዲት ሴት ላይ የደረሰውን ከፍ ያለ ቁሳዊ ችግር ወይም የህሊና ሃዘን ምክንያት


በማድረግ ወይም በጠባቂነት፣ በአሰሪነት፣ አስተማሪነት ፣በአሳዳሪት ይህንን በመሰለ ግንኙነት
ምክንያት ያገኘውን ስልጣን እና ሀላፊነት በመጠቀም ከተባለችው ሴት ጋር የግብረ ስጋ ግንኙት
የፈጸመ ወይም የግብረ ስጋ ግንኙነት የመሰለ ድርጊት ወይም ለንጽህና ተቃራኒ የሆነ ድርጊት
ከፈጸመባት እና ሴትዮዋም ድርጊቱን በመቃወም አቤቱታ ካቀረበች በቀላል እስራት እንደሚቀጣ17
ይደነግጋል፡፡

እንደሚታወቀው ሀገሪቱ ከፈረመቻቸውች የህጻናት መብቶች ኮንቬንሽን እና ከህገ መንግስቱ


አንጻር ማናቸውም አካለ መጠን ያላደረሱ ማለትም አስራ ስምንት አመት ያልሞላቸው ህጻናት
ሁለንተናዊ የህግ ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በመሆኑም ይህንንን ልዩ ትኩረት ከግምት ውስጥ
ያስገቡ የወንጀል ህግ ድንጋጌዎች እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡ የመጀመሪያው እድሜያቸው አስራ
ሶስት አመት አመት በላይ ሆኖ አስራ ስምንት አመት ካልሞላት ሴትም ሆነ ወንድ ልጅ ጋር
ፈቅደው ይሁን በማታለል ወይም በማናቸውም ሌላ መንገድ የሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት
ከወንጀሉ አደገኛነትና ከልጆች ጥበቃ አንጻር ከፍተኛ ቅጣት ተመልክቷል፡፡ በቅጣት ረገድ
በተለይም ድርጊቱ የተፈጸመው በሴት ህጻን ላይ ከሆነ ግን ከሶስት አመት እስከ አስራ አምስት
አመት ለመድረስ በሚችል ጽኑ እስራት የሚቀጣ ይሆናል18፡፡

በመሰረቱ የወንጀል ህጉ በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ህጻናት ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት
መፈጸምን ብቻ በመቅጣት አልተወሰነም፡፡ ይልቁንም የግብረ ስጋ ግንኙነትም ባይሆን ይህን

16
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 5፣ አንቀፅ 620(1)ና (2)
17
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 5 አንቀፅ 625
18
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 5 አንቀፅ 626(1)ና (2)

10
የመሰለ ድርጊት ወይም ለንጽህና ክብር ተቃራኒ የሆነ ማናቸውም አይነት ድርጊት የፈጸመ
ወይም በፊታቸው እንዲህ አይነት ተግባርን ያደረገ ወይም ይህ አይነት ድርጊት እንዲፈዕም
/እንድትፈጽም የገፋፋ ማንም ሰው ከሶስት ወር በማያንስ ቀላል እስራት ወይም እስከ አምስት
አመት ሊደርስ በሚችል ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ ጨምሮ በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 ስር
አስቀምጦ እናገኛለን፡፡ በተለይም የግብረ ስጋ ድፍረቱ የተፈጸመበት ህጻን የአጥፊው ተማሪ
፣የቤት ሰራተኛ፣ በሞግዚትነት ወይም በአደራ ወይም በማናቸውም ሌላ መንገድ በእርሱ ቁጥጥር
ስር በሚገኝ ልጅ ላይ ከሆነ አጥፊው ከሶስት አመት እስከ አስር አመት ሊደርስ በሚችል ጽኑ
እስራት የሚቀጣ ሲሆን በሌላ በኩል ተበዳዩዋ ሴት ከሆነች ደግሞ ቅጣቱ ይበልጥ ከብዶ
ከአምስት አመት እስከ ሀያ አመት ሊደርስ በሚችል ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ መሆኑን ከንዑስ
አንቀጽ 4 ለመረዳት ይቻላል፡፡ እንዲሁም የተፈጸመው ድርጊት በንዑስ አንቀጽ 3 የተገለጸው
ከሆነ አጥፊው ከሰባት አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡ ይህ ሁሉ ድርጊት ከዚህ
አልፎ በተበዳይ ላይ አካላዊ፣ ስነ ልቦናዊ ጉዳትን ወይም ሞትን ያስከተለ እንደሆነ እነዚህን
ድርጊቶች የተመለከቱ ድንጋጌዎች በተደራቢነት ተፈጻሚ እንደሚሆኑም መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡19
በእርግጥ እድሜቸው አስራ ሶስት አመት ያልሞላቸው ሴት ልጆች የአካላቸውም ሆነ የአዕምሮ
ብቃታቸው እድሜያቸው በአስራ ሶስት እና በአስራ ስምንት አመት መካከል ከሚገኙ ሴት ልጆች
ጋር የማይመጣጠን እና የሚፈጸምባቸውም ድርጊት የበለጠ ጉዳት የሚያስከትል ነው፡፡ በዚህም
ምክንያት ይህ ድፍረት የተፈጸመው እድሜዋ አስራ ሶስት አመት ባልሞላት ህጻን ላይ ከሆነ
አድራጊው ከአስራ አምስት አመት እስከ ሀያ አምስት አመት ለመድረስ በሚችል ጽኑ እስራት
ከብዶ የሚቀጣ ሲሆን ፈጻሚዋ ሴት ከሆነች ደግሞ ከአስር አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት
እንዲሆን ተደርጓል፡፡20 ይህ አድራጎት በተለይም ሞትን አስከትሎ ከሆነ ደግሞ ሞትን
የሚመለከተው የዚሁ የወንጀል ህግ ድንጋጌ በተደራቢነት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ
የአስገድዶ መድፈሩ ወይም በግብረ ስጋ ድፍረቱ ድርጊት እርግዝና ከመጣ ፤ፈጻሚው በአባላዘር
በሽታ መያዙን እያወቀ ተበዳዩዋን /ተበዳዩን ካስያዘ ወይም ደግሞ በደረሰው በደል ጭንቀት
ምክንያት ተበዳይዋ/ተበዳዩ ራሷን/ራሱን ካጠፋ ደግሞ ህጉ ለድፍረት ወንጀሉ ከፍ ያለ ቅጣት
ካላስቀመጠ በቀር ከአምስት አመት እስከ ሀያ አምስት አመት ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ21
ተቀምጧል፡፡ አስገድዶ መድፈር ወይም ሌሎች የግብረስጋ ግንኙነት በደል ወንጀል የፈጸመ ሰው

19
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 5 አንቀፅ 626(4)ና (5)
20
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 5አንቀፅ 627(1)ና (2)
21
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 5 አንቀፅ 628

11
ብዙውን ጊዜ ከድርጊቱ በኋላ ከተበዳይዋ ጋር ጋብቻ ለመፈጸም የሚያደርገው መስማማት ከክስና
ከቅጣት ለመዳን በመሆኑ በነባሩ ህግ በዚህ አግባብ በሚደረገው ጋብቻ መሰረት የነበረው የክስና
የቅጣት ስረዛ ድንጋጌ ተሽሯል፡፡

Ø ከሴቶች እና ህጻናት ስነ ምግባር

በሴቶች እና ህጻናት ላይ ከሚፈጸሙ የወንጀሎች ውስጥ ህጉ በተለይም ከስነ ምግባር ብልሹነት


ጋር የተያያዙ ድርጊቶችን በክፍል ለይቶ በወንጀልነት የፈረጀ ሲሆን የተወሰኑትን ለማየት
እንሞክራለን፡፡ በህጉ አንቀጽ 635 እና ተከታይ ድንጋጌዎች እንደተመለከተው ማንም ሰው
ለጥቅም ሲል ወይም የሌላውን ሰው ፍትወተ ስጋ ለማርካት ሴቶችን ወይም አካለ መጠን
ያላደረሱ ልጆችን በፈቃዳቸውም ቢሆን ወደ ዝሙት አዳሪነት እንዲሰማሩ በማነሳሳት ፣በማባበል
ወይም በሌላ በማናቸውም መንገድ በመገፋፋት በማቃጠር የነገደ ከቦታ ቦታ ያዘዋወር ወይም
ለዝሙት ለማቅረብ በዝሙት አዳሪ ቤት ካስቀመጠ ከአምስት አመት ባልበለጠ ጽኑ እስራት እና
ከአስር ሽህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ያስቀጣል፡፡ በዚህ በኩል ህጉ በተለይም ለሴቶች
እና ህጻናት ከሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የተነሳ ይህ አድራጎት የሚያስከትለው ቅጣት
የሚከብድበትን ሁኔታ አስቀምጧል፡፡ የተበዳዩ አካለ መጠን ያደረሰች መሆን፣ በወንጀል ፈጻሚው
እና በተበዳይ መከከል ያለው የጋብቻ፤ የደምም ሆነ በህግ ያሉ እንደ ጉዲፈቻ፤ ሞግዚትነት እና
የመሳሰሉት ግንኙነቶች መኖር እንዲሁም ይህንን ተግባር እንደሙያ አድርጎ መያዝና የማታለል
እና የሀይል ድርጊቶች መኖር ቅጣቱን ከሶስት አመት እስከ አስር አመት ሊደርስ የሚችል ጽኑ
እስራት እና ከሀያ ሽህ ብር የማይበልጥ መቀጮ ከሚያስቀጡ ሁኔዎች ውስጥ ይገኙበታል22፡፡

Ø ከጋብቻ ስርዓት ጋር የተያያዙ ወንጀሎች

የወንጀል ህጉ በምእራፍ ስድስት ስር ከጋብቻ ጋር የተያያዙ የወንጀል ድርጊቶችን አስመልክቶ


ዝርዝር ድንጋጌዎችን በጋብቻ ስርአት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች በሚል ክፍል አስቀምጦ
ይገኛል፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ በተለይም ከፍ ሲል የተመለከትናቸውንና ህገ መንግስቱ ሆነ
የቤተሰብ ህግ ማዕቀፎች ለጋብቻና ሴቶች ከሰጧቸው ጥበቃ ጋር የሚጣጣሙ ድንጋጌዎችን
ማየት ይቻላል፡፡ በመሰረቱ የተከለከለ ጋብቻን በመፈጸም እና በማስፈጸም ረገድ ህጉ ሚና
ያላቸውን ማለትም ከህግ ውጭ የተጋቡ፣ ለጋብቻው ፈቃዳቸውን የሰጡ፣ በምስክርነት የቀረቡ
እና ጋብቻውን ያስፈጸሙ አካላትን መቅጣት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንም ሰው ጋብቻውን

22
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 5 አንቀፅ 636

12
አስቀድሞ ጋብቻውን ለማፍረስ ወይም እንዳይጸና ለማድረግ የሚያስችሉ ህጋዊ ምክንያቶች
መኖራቸውን አስቦ ከሌላው ተጋቢ ከደበቀ ወይም ማንነቱን ለሌላው ተጋቢ በመደበቅ፣
በማሳሳት፣ በማታለል ወይም በማጭበርበር ጋብቻ ከፈጸመ በእስራት ወይም በገንዘብ መቀጮ
እንደሚቀጣ ህጉ አስቀምጧል23፡፡ በህግ የተከለከለ ጋብቻን አስቦ ያስፈጸመ ማንም ሰው ፤አስቦ
ጋብቻውን የፈጸመ ተጋቢ ወይም ለዚህ አይነቱ ጋብቻ ምስክር የሆነ ሰው ከሶስት አመት
በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም ከአምስት ሽህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል፡፡ ሆኖም ይህ
የሆነው በቸልተኛነት መሆኑ ከተረጋገጠ ቅጣቱ ከሶስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም
በመቀጮ ሊሆን ይችላል24፡፡ ይሁን እንጅ ህገ ወጥ ጋብቻን መፈጸምም ሆነ ማስፈጸም በዚህ
አግባብ በወንጀል ሊያስጠይቅ የሚችለው ጋብቻው ከፈረሰ ብቻ መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል፡፡
ያለእድሜ ጋብቻን አስመልቶ አንቀጽ 648 ማንም ሰው አስቦ አግባብነት ያለው የቤተሰብ ህግ
ካስቀመጠው ዝቅተኛ የጋብቻ እድሜ በታች አካለመጠን ያላደረሰችውን ልጅ ያገባ ሰው
የተበዳዩዋን እድሜ መሰረት ያደረገ ቅጣትን በሁለት መልኩ አስቀምጧል፡፡ የመጀመሪያው
ተበዳይዋ እድሜዋ አስራ ሶስት አመት ወይም ከዛ በላይ ከሆነ ከሶስት አመት በማይበልጥ ጽኑ
እስራት የሚያቀጣ ሲሆን ሁለተኛው እድሜዋ ከአስራ ሶስት አመት በታች ሲሆን ግን ቅጣቱ
ከሰባት አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ከፍ ተደርጎ የተቀረጸ ነው፡፡

Ø በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች አማካኝነት በሴቶች እና ህጻናት ሕይወት ፣አካል እና


ጤና ላይ ጉዳት በማድረስ የሚፈጸሙ ወንጀሎች

የወንጀል ህጉ በቀድሞው ህግ ትኩረት ያልተደረገባቸውንና በሴቶች እና ህጻናት ህይወት ፣አካል


እና ጤና ላይ ጉዳት በማድረስ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለይቶ በማወቅ ትኩረት እንዲያገኙ
ለማድረግ አሰባስቦ በምዕራፍ ሶስት ስር እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ የመጀመሪያው ድርጊት እርጉዝ
ሴትን በማሸት ወይም በመውለድ ላይ ያለች ሴትን አካል በማርገፍገፍ ወይም አዲስ የተወለደን
ህጻን ግግ ማስወለቅ፣ክትባት እንዳይከተብ በማድረግ ወይም ይህንን የመሳሰሉ ጎጂነቱ በህክምና
ሞያ የታወቀ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመፈጸም እርጉዧ ሴት ወይም ህጻን ህይወት እንዲያልፍ
ማድረግ የአካል ወይም የአዕምሮ ጉዳት ያደረሰ ሰው እንደሚቀጣ የህጉ አንቀጽ 561፣562 እና
563 ጣምራ ንባብ መረዳት ይቻላል፡፡ በዚሁ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ወስጥ እንዲካተት የተደረገው

23
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 5 አንቀፅ 646 (1)ና (2)
24
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 5 አንቀፅ 647(1-3)

13
ደግሞ ሴትን መግረዝ ነው፡፡ ይህ ድርጊት ከህጻናት ሴቶች በተጨማሪ በትላልቅ ሴቶች ላይም
ሊፈጸም የሚችል በመሆኑ የድንጋጌው ይዘት ጥበቃውን ሰፋ አድርጎ በየትኛውም የእድሜ ክልል
ያለችን ሴት ሁሉ የሚመለከት ሲሆን ቅጣቱም ከሶስት ወር በማያንስ ወይም ከአምስት መቶ ብር
በማያንስ መቀጮ ተደርጎ ተደንግጓል፡፡ የሴትን ብልት መስፋትም ሴቶችን ለከፍተኛ ስቃይና
ጉዳት የሚዳርግ ጎጂ ልማድ በመሆኑ በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ የሚጣለው ቅጣት ጠንከር ቢል
ውጤት ያስገኛል በሚል ግምት ከአምስት እስከ አስር አመት ሊደርስ በሚችል ጽኑ እስራት ከፍ
ብሏል፡፡ በዚህ ድርጊት ሳቢያም አካላዊ ሆነ የጤና ጉዳት ከደረሰም በወንጀል ሕጉ ከፍተኛ ቅጣት
የሚጥል ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ቅጣቱ ከአምስት ዓመት እስከ አስር አመት የሚደርስ ጽኑ
እስራት ይሆናል25፡፡ ህጉ ከእነዚህ ልማዳዊ ድርጊቶች ውጭ ያለ፤ ኢ-ሰብአዊና ጎጂነቱ በህክምና
በተረጋገጠ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ምክንያት የአካል፣ የአዕምሮ ጉዳት ወይም ሞት እንዲደርስ
ያደረገ ሰውም በጉዳቱ ቅለትና ክብደት መሰረት እንደሚቀጣ በተጨማሪነት መገንዘብ ይገባል26፡፡

Ø በሴቶች የግል ነጻነቶች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች

የወንጀል ህጉ በሰው የግል ነጻነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የተመለከቱ በርካታ ዝርዝር


ድንጋጌዎችን አስቀምጧል፡፡ በዚህ ረገድ ሰውን መጥለፍ በጠቅላላው እንደሚያስቀጣ ከማስቀመጡ
በተጨማሪ ሴትን መጥለፍ ደግሞ ግልጽ ስያሜ ተሰጥቶት ራሱን የቻለ ድንጋጌ እንዲይዝ
ተደርጓል፡፡ ማንም ሰው አንዲትን ሴት አገባታለሁ በሚል ሀሳብ በሀይል የጠለፈ ወይም
ድርጉቱን የፈጸመው በማስፈራራት ፣በዛቻ ፣በተንኮል ወይም በማስፈራራት ፈቃደኛ እንድትሆን
በማድረግ ከሆነ ከሶስት አመት እስከ አስር አመት ሊደርስ በሚችል ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡ ነገር
ግን አድራጊው ከጠለፋውም በኋላ ሴትዮዋን አስገድዶ የደፈራት መሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ
ይህንን የድፍረት ወንጀል በሚመለከተው ህግ አግባብ ተጨማሪ ቅጣት እንደሚወሰንበት
ተመልክቷል፡፡ ከዚህ ባለፈ አዲሱ ህግ በነባሩ ህግ ያልነበረ እና ተበዳይዋ በጠላፊው ድርጊት
ለደረሰባት የህሊናና የማቴሪያል ጉዳት አግባብነት ባላቸው የፍትሃብሔር ህግ ድንጋጌዎች
መሰረት ካሳ የመጠየቅ መብቷን የሚጠብቅ ድንጋጌ ተካቷል፡፡ ጠላፊው የተጠላፊዋ ሴት
የአዕምሮ ህመምተኛ ወይም ራሷን መከላከል የማትችል ወይም እንዳትችል የተደረገች መሆኑን
እያወቀ ከሆነ ቅጣቱ ከቀድሞው ህግ ከብዶ ከአምስት አመት እስከ አስራ አምስት አመት

25
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 5 አንቀፅ 566
26
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 5 አንቀፅ 567

14
የሚደርስ ጽኑ እስራት ተደርጓል፡፡ እነዚህ ድንጋጌዎች ሴትን መጥለፍ የተመለከቱ ድንጋጌዎች
በየትኛው የእድሜ ክልል የሚገኙትን ሴቶችን እንደሚመለከት ያስቀመጠ አይደለም፡፡ ከዚህም
በመነሳት ተጠላፊው ሴትም ሆነ ወንድ ድርጊቱ የተፈጸመው በእድሜያቸው የተነሳ ልዩ ጥበቃ
የሚያስፈልጋቸው አካለ መጠን ያላደረሱ ህጻናት (ማለትም ከአስራ ስምንት አመት በታች
የሆኑትን) ላይ በሆነ ጊዜ ተፈጻሚ የሚሆን ድንጋጌ በአንቀጽ 589 ተለይቶ ተቀምጧል፡፡
ድንጋጌው ከአምስት እስከ አስራ አምስት አመት ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ ሲሆን እንደወንጀሉ
የአፈጻጸም ሁኔታ፤ ክብደት እና ቅለት መሰረት ያደረጉ ቅጣቶችም በዝርዝር ተደንግገዋል፡፡

2. በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች የሚያስከትሉት ጉዳት


2.1 የስነ ልቦና ጉዳት

የዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት (WHO) የ2013 ሪፖርት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች
በየትኛውም የአለም ክፍል እየጨመሩ መሆኑን ያሳያል፡፡ እንደ ሪፖርቱ ግኝት ከሆነ በዓለም
ላይ ካሉ ሴቶች ውስጥ 35% ያህል በቅርብ ጓደኞቻቸው ወይም ጓደኞቻቸው ባልሆኑ ሠዎች
ጥቃት ይፈፀምባቸዋል27፡፡ እንደዚህ ሪፖርት ገልፃ በዓለም አቀፍ ደረጃ 38% የሚሆኑት ሴቶች
ግድያ የተፈፀመው በቅርብ ጓደኞቻቸው ነው28፡፡ በሴቶች ላይ ፆታዊ ጥቃት ከተፈፀመባቸው ጊዜ
ጀምሮ ተጎጅዎች የአካል፤ የስሜት፤ የአእምሮና የፀባይ መለዋወጥ እንዲሁም ያልተለመደ
ምልክት ይታይባቸዋል፡፡ በስሜታቸዉ ላይ የሚታዩ መለዋወጦች ከትንሹ ፍርሃት ጀምሮ ራስን
እስከ ማጥፉት29 ይደርሣል፡፡

የፆታዊ ጥቃት ሠለባ የሆኑ ሤቶች ቀድሞ ባልነበረባቸው ሁኔታ ፍርሃት (fear)
ያደርግባቸዋል፡፡ በተለይም ድጋሜ ጥቃት ይደርስብኛል በሚል መፍራት፣ ድርጊቱ
የተፈፀመበትን ሁኔታ መፍራት፤ ምሣሌ ጥቃቱ የተፈፀመው በማታ ቢሆን ማታን መፍራት፣
ማህበራዊ ግንኙነቶችን መፍራት ጥቃቱ የተፈፀመው ገበያ እሄደች ባለች ሴት ላይ ቢሆን ገበያ
መሄድን መፍራት በጥቃቱ የተነሣ የጤና ችግር ያደርስብኛል ብሎ መፍራት ሊሆኑ ይችላል30፡፡

27
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 7 ገፅ 9
28
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 7 ገፅ 9
29
Gender based violence, Health and the role of health sector, 2009, page3 available at
siteresources.worldbank.org/INTPHAAG/Resources/AAGGBVHealth.pdf
30
Evelyne Josse, “They came with two guns” The Consequences of Sexual Violence for the Mental Health of
Women in Armed Conflicts, 2010, The International Review of the Red Cross, Volume 92, Number 877, page 184

15
ሌላው ከፍርሃት ከፍ ያለው ደረጃ ስጋት (Anxity) የሚባለው ነው፡፡ ስጋት ከፍርሃት የሚለየው
ምንም ዓይነት የጥቃቱን አስታዋሽ ነገሮች በሌሉበት ደህንነት አለመሠማት ነው፡፡ ፆታዊ ጥቃት
የደረሰባቸው ሴቶች ሌላ ጥቃት በቤተሠቦቸ (በልጆቼ፣በእህቶቼ፣ በጓደኞቸቼ ወዘተ) ይደርሣል
ብሎ መስጋትም ሌላኛው አስከፊ ገፅታ ነው፡፡ ስጋቱ እየዋለ ሢያድር ትኩረት ማጣትና
እንቅልፍ ማጣትን ያስከትላል31፡፡

ከፍ ሢል ከተመለከትናቸው ከፍርሃትና ከስጋት ከፍ ያለው ደረጃ ጭንቀት (Anguish)


የሚባለው ነው፡፡ የፆታዊ ጥቃት ሠለባ የሆነች ሴት የተፈፀመባትን ጥቃት በማሰብ በጭንቀት
ውስጥ ትኖራለች፡፡ የጭንቀት ደረጃውም የሠውነቷን ስነ-ህይወታዊ ተግባራት ያቋውሣል32፡፡
በጭንቀት ጫና ወይም ደረጃ ውስጥ ያለች ሴት የልብ ምቷ መደበኛ አይሆንም፡፡ የአተነፉፈስ
ሥርዓቷ የተዛባ ይሆናል፡፡

በሌላ መልኩ መገለፅ ያለበት ስነ-ልቦናዊ ጫና ድብርት (depression)33 ነው፡፡ ድብርት ውስጥ
ያለች የፆታዊ ጥቃት ሠለባ ሤት ተስፉ መቁረጥና ሀዘን ይታይባታል፡፡ በህይወት ለመኖር
ፍላጐት አይኖራትም ማልቀስ፣ ራስን ስለማጥፋት ማሠብ፣ ወዘተ የመሣሠሉ ምልክቶች
ይታዩባታል፡፡

የፆታዊ ጥቃት የደረሠባቸው ሴቶች በአብዛኛው ማፈር፣ራስን መውቀስ ለራስ ያለን ዋጋ ዝቅ


አድርጐ ማየት (ለምሣሌ እኔ ሚስት መሆን አልችልም፣ እናት መሆን አይገባኝም ወዘተ
ማለት) ሌላኛው ገፅታ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ራስን እንደጥፉተኛ መቁጠር፣ በራስ ባህርይ
መበሣጨት፣ ራስን ያልታደልኩና የተረገምኩ ነኝ ብሎ ማሠብ ይታያል፡፡ ከዚህ ባሻገር መናደድ
ይስተዋላል፡፡ የፆታዊ ጥቃት ሠለባ የሆኑ ሴቶች በጉዳት አድራሹ ላይ እጅግ ይናደዳሉ፡፡
ከዚህም አልፎ በቤተሠብ ላይ፣ ወይም በጠቅላላ በወንዶች ላይ መናደድ ይታያል34፡፡

በመጨረሻ ሊታይ የሚገባው ሄድ-መጣ የሚባለው የደስታ ስሜት (Euphoria) በጾታዊ ጥቃት
ተጐጅዎች ላይ ይስተዋላል፡፡ እንዲሁም ለሌላው ዓለም አለመጨነቅ በተለይም ለስራ፣
ለትምህርት፤ ለጓደኛ ግዴለሽ መሆን ያጋጥማል፡፡

31
ዝኒ ከማሁ ገፅ 185
32
ዝኒ ከማሁ ገፅ 186
33
ዝኒ ከማሁ ገፅ 184
34
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 1 ገፅ 23

16
ከዚህ በላይ የተመለከትናቸው የስነ-ልቦና ጉዳቶች የአካላዊ ምቾት ማጣት ምልክቶች
(Physiological Symptoms) ያመጣሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ ዋነኞቹ የውስጣዊ የአካል ክፍሎች
አሠራር ማዛባት፤ ማለትም የአተነፉፈስ፣ የደም ዝውውር፣ የምግብ መፈጨትና መወገድ
ሥርዓት ላይ ተፅእኖ ይፈጥራሉ፡፡ በፍርሃት፣ ስጋት፣ ጭንቀትና ድብርት ውስጥ ያሉ ሴቶች፣
ማስተወክ፣ ማላብ፣ ማስቀመጥ የመሣሠሉ ህመሞች ይታዩባቸዋል፡፡ ሌላኛው ጉዳት ወሢብ
የመፈፀም እክል (Sexual dysfunctions)35 ናቸው፡፡ የፆታዊ ጥቃት የደረሠባት ሴት የወሲብ
ፍላጐት የላትም ከዚህም አልፎ ወሲብን መጥላት፣ በወሲብ አለመርካት ይታይባታል፡፡ በሌላ
መልኩ ከወር አበባ አለመኖር፣ የወር አበባ መብዛት፣ እንዲሁም የተዛባ የወር አበባ (Menstrual
disorders) ያጋጥማታል፡፡

2.2. የጤና ችግር

በእርግጥ የስነ-ልቦና ችግር የጤና ችግር ነው፡፡ የጤና ችግር ከዚህ በተጨማሪም በአካል ላይ
የሚታዩ የጤና መጓደሎችን ለማለት ነው፡፡ ፆታዊ ጥቃት የደረሠባቸው ሴቶች ውስብስብ ለሆኑ
የአካል ነክ ጤና ችግሮች ያደርጋሉ፡፡ በተለይም የአስገድዶ መደፈር ጥቃት የደረሠባቸው ሴቶች

§ ያልተፈለገ እርግዝና
§ ላልተፈለገና ያለጥንቃቄ ለሚፈፀም ውርጃ
§ ኤች አይ ቪ ኤዲስን ጨምሮ ለሌሎች በግብረ ስጋ ግንኙነት ለሚተላለፉ በሽታዎች
§ ግብረ ስጋ ግንኙነትን የመፈፀም እክል (Sexual dysfunctions)
§ መካንነት
§ ለሽንት ባንባ ቁስለት
§ የወገብ ህመምና /የወገብ አጥንት የሚያስቆጣ በሽታ36 (pelvic pain and pelvic
inflammatory disease) በሴቶች ላይ የሚፈፀም የአስገድዶ መደፈር ጥቃት በሴቶች
የመራቢያ አካላት (ብልት) ላይአካላዊ የሆነ የጤና ችግር ያስከትላል፡፡

በተለይም እንደ

v የብልት መቀደድ
v የብልት መላላጥ
35
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 30 ገፅ 3
36
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 11 ገፅ 12

17
v የብልት መቅላት
v የብልት ማበጥ (ደም መቋጠ)
v ሰንበር ማውጣት
v ራስ ምታት
v ድካም37፣ ወዘተ ህመም ያስከትላል::

የክብደት መቀነስ (በተጠቂዎችም ሆነ እርግዝና ከተፈጠረ በህፃናት ላይ) ከዚህ በተጨማሪ


የፆታዊ ጥቃት ተጐጅ የሆኑ ሴቶች ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሣዩት38 በርካታ ሤቶች
የአደንዛዥ ዕፅና የአልኮል መጠጥ ሡስ ውስጥ ይገባሉ፡፡ አንድ ጥናት “violence against women
is the most pervasive yet underrecognized human rights violation in the world. It is also a
profound health problem that saps women’s energy, compromises their physical and mental
health, and erodes their self-esteem. In addition to causing injury, violence increases women’s
long-term risk of a number of other health problems, including chronic pain, physical disability,
drug and alcohol abuse, and depression”39 በማለት ያስቀምጣል፡፡ ወደ አማርኛ ሲመለስ በሴቶች
ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶች እጅግ ስር የሰደዱ ግን ገና በቅጡ ዕዉቅና ያልተሰታቸዉ
የሰብዓዊ መብት ጥሰትቶች ናቸዉ፡፡ የሚያሰከትሉት የጤና ጉዳት የሴቶችን የአካልና አእምሮን
ጤንነት በማወክ ሙሉ አቅማቸዉን የሚሰልብና በራሳቸዉ እንዳይቆሙ የሚያደርግ ነዉ፡፡
በተጨማሪም የሚደርሰዉ ጉዳትና ጥቃት በጨመረ ቁጥር የረጅም ጊዜ ጤና ነክ ቀዉሶችን
እንደ ፅኑ ህመም፤ የአካል ጉዳተኝነት፤ የአደንዛዥ እፅና መጠጦች ሱሰኝነታና ድብርትን
ያስከትላል የሚል ይሆናል፡፡
አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ፆታዊ ጥቃት የደረሠባቸው ሴቶች ራሣቸውን ማጥፉት መሞከራቸዉ
ሌላው ገፅታ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ክብራችን ተነካ የሚሉ ቤተሰቦች ፆታዊ ጥቃት
የደረሠባቸው ሴቶች ይገሏቸዋል፡፡ በአንዳንድ ሃገራት ፆታዊ ጥቃት የተፈፀመባቸዉ ሴቶች
የቤተሰባቸዉን ክብር ነክተዋል በሚል ግድያ (Honour Killing) ይፈፀምባቸዋል40፡፡

37
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 11 ገፅ 12
38
Non fatal and Fatal Outcomes of sexual violence ( Direct & Indirect Physical and Mental Health proplems)
Injury, Post traumatic stress, Femicide , Functional impairment, Depression, Suicide, Physical symptoms,
Anxiety, Maternal mortality, Poor subjective health, Phobias/panic disorders, AIDS-related , Permanent
disability
39
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 1 ገፅ 9
40
Wafaa Abdelhadi Honour Crimes and Violence against Women Preventing and Punishing Honour Crimes 2016,
Tilburg University available at arno.uvt.nt/show.cgi?fid=139874, page 10

18
3. በኢትዮጵያ ህግጋት የተካተተ የፆታዊ ጥቃት መፍትሔዎች
3.1. በወንጀል የፍትህ አስተዳደር የተደነገጉ መፍትሔዎች

በወንጀል ህጉ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ በበርካታ መፅሃፎች፣ ምዕራፎችና ክፍሎች የተካፈፋለ ነው፡፡ የዚህ


ህግ መፅሃፍ አምስት በሌሎች ሠዎችና በቤተዘመድ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ከአንቀፅ 538-
661 ደንግጐ ይዟል፡፡ በተለይም በመፅሃፍ አምስት ምዕራፍ ሁለት በሠው አካልና ጤና ላይ
የሚፈፀሙ ወንጀሎች ከአንቀፅ 553-560 ተመላክተዋል፡፡ አንቀፅ 553 መርህ ነው፡፡ ይህ መርህ
ማንም ሠው አስቦ ወይም በቸልተኛነት በማናቸውም ነገር ወይም ዘዴ የሌላውን ሠው አካል
ያጐደለ ወይም ጤንነቱን የጐዳ እንደሆነ በዚህ ምዕራፍ በተመለቱት ድንጋጌዎች መሠረት
ይቀጣል ይላል፡፡ ድንጋጌዎቹ ማናቸውንም በሰውነት ላይ የሚፈፅሙትን የእጅ እልፊቶችን፣
መምታትን፣ ማቁሠልን፣ የአካል ማጉደልን፣ ጉዳቶችን ወይም ጥፉቶችን እንዲሁም በሰው
አካል ወይም የአእምሮ ጤንነት ላይ የሚፈፀሙትን ጉዳቶች ሁሉ ያጠቃልላሉ፡፡ ድንጋጌዎቹ
የሚያመለክቱት ማንም ሠው በሌላ ሠው አካል ወይም ጤንነት ላይ አስቦም ይሁን
በቸልተኝነት በምንም መልኩ ጉዳት ያደረሠ እንደሆነ እንዳደረሰው ጉዳት ልክ እንደሚቀጣ
ነው፡፡ የሚፈፅማቸው ወንጀሎችም ታስቦ የሚፈፀም ከባድ የአካል ጉዳት፣ ቀላል የአካል ጉዳት፣
በቸልተኛነት የሚፈፀም የአካል ጉዳት እና የእጅ እልፊት እንደሆኑ ከአንቀፅ 555-560 ያሉት
ድንጋጌዎች ያስረዳሉ፡፡ በእርግጥ የእነዚህ አንቀጾች ርዕስ የአካል ጉዳት በሚል የተቀመጠ
ቢሆንም በይዞታቸው የአካል ጉዳቶች ብቻ ሳይሆኑ የአእምሮ ጤንነትን ጉዳት ተካቷል፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ ፆተዊ ጥቃቱ ሞትን ካስከተለ የወንጀል ህጉ አንቀፅ 538-541 ተፈፃሚ ሊሆን
ይችላል41፡፡ ሲጠቃለል እነዚህ ድንጋጌዎች በሴቶች ላይ ፆታዊ ጥቃት የፈፀሙ ሰዎችን
በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ያስችላሉ፡፡ የወንጀል ህጉ አንቀፅ 553 (2) “ፍርድ ቤቱ ለተበዳዩ
የሚከፈለውን የጉዳት ካሣ የሚወሰነው የጉዳቱን ከባድነትና የተከራካሪ ወገኞችን ሁኔታ ከግምት
ውስጥ በማስገባት በዚህ ህግ ስለ ጉዳት ካሣ በተደነገገው ጠቅላላ ድንጋጌ መሠረት ይሆናል”
በሚል አስቀምጧል፡፡ እነዚህን ሁለት ንዑስ አንቀጾች ስናያቸው በሰው የአካል፣ የአእምሮ
ጤንነት ላይ ጉዳት ያደረሠ ሠው ጉዳቱም ከከባድ የአካል ጉዳት እስከ ቀላሉ የእጅ እልፊት

41
የወንጀል ህግ አንቀፅ 620(3)፤ 626(5)፤ 627(5) የአስገድዶ መድፈር ድርጊት ሞትን ያስከተለ እንደሆነ ቅጣቱ የእድሜ ልክ
እንደሚሆን ያሳያል፡፡

19
ቢሆንም እንዲሁም በአካል ከሚታዩ ጉድለቶች እስከ የአእምሮ ጠንቅ እስከሚሆኑት ጉዳቶች
ሁሉ ተበድያለሁ የሚል ሠው የጉዳት ካሣ የሚያገኝበት ሥርዓት ተዘርግቷል ማለት ነው፡፡

3.2 በወንጀል ህጉ የተካተቱ ፍትሃብሔራዊ መፍትሔዋች

የጉዳት ካሣ እንዴት እንደሚከፈል የሚነግረን የወንጀል ህጉ አንቀፅ 101 እና 102 ነው፡፡


አንቀፅ 101 ንብረትን መተካት ወይም የጉዳት ካሣና ኪሣራን መክፈል የሚል ርዕስ ኖሮት፤
“ወንጀሉ በተበዳዩ ወይም በተበዳዩ ባለመብቶች ላይ ከፍ ያለ ጉዳት ባደረሠባቸው ጊዜ ተበዳዩ
ወይም ስለተበዳዩ መብት ያላቸው ሠዎች በዳዩ ያደረሠባቸውን ጉዳት እንዲከሣቸው፣
ያጠፉውን ወይም ያፈረሠውን እንደነበረ እንዲመልስ እንዲሁም ለደረሠባቸው ጉዳት
ተመዛዛኝነት ያለው ካሣ በኪሣራ ስም እንዲከፍላቸው እንዲፈረድበት ሊጠይቁ ይችላሉ” በማለት
ተደንግጓል፡፡ እንዲሁም ይህንን ለማድረግ የፍትሃብሔር ክስ ከወንጀል ክሱ ጋር አጣምረው
ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ ይህም በወንጀል ስነ-ስርዓት ህጉ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት
ይመራል ይላል፡፡ እዚህ ላይ ከፍ ያለ ጉዳት በደረሠባቸው ጊዜ ማለቱ ምን ማለት ነው? ከፍ
ያለ ጉዳት የሚባለው የትኛው ጉዳት ነው? የሚሉት ጥያቄዎች ሊነሱ ይችላሉ፡፡ እነዚህን
ጥያቄዎች ለመመለስ የዚህን አንቀፅ እንግሊዝኛ ቅጅ እንመልከት፡፡ Article 101- Restitution of
property, compensation for damages and costs “where a crime has caused considerable
damage to the injured person or to those having rights from him, the injured person or the
persons having rights from him shall be entitled to claim that the criminal be ordered to make
good the damage or to make restitution or to pay damages by way of compensation. To this
end they may join their civil claim with the criminal suit. Such claim shall be governed by the
provisions laid down in the criminal procedure code.” ይላል፡፡ ከዚህ የምንረዳው ከፍ ያለ
ጉዳት በእንግሊዝኛው Considerable damage ማለት ነዉ፡፡ በመሆኑም ከፍ ያለ ጉዳት ማለቱ
ዝቅተኛ ጉዳት ከሆነ የጉዳት ካሣ አያስጠይቅም ማለት ሣይሆን ከግምት ውስጥ የሚገባ
(Considerable) ጉዳት ከደረሠ በሚል መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በሌላ አገላለፅ ከፍ ያለ ጉዳት
(Considerable damage) የጉዳቱን መጠን እንጂ የሚከፈለዉን የጉዳት ካሳ ልክ ለማሳየት
አይደለም፡፡ ካሳዉ በፍትሃብሔር ህጉ በተመለከተዉ መሰረት ተመዛዛኝ ወይም ርዕትን ከግምት
ዉስጥ ያስገባ መሆን ይኖርበታል፡፡ ሃተታ ዘምክንያት ላይ ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡ ከግምት
ውስጥ የሚገባ ጉዳት በሚል ካልተረዳነው ከላይ በአንቀፅ 553 ላይ የተመለከቱት የእጅ

20
እልፊት፣ ማቁሠል ወዘተ እንደቀላል ጉዳት ተቆጥረው ካሣ አያስጠይቁም ወደሚል
ማደማደሚያ ያደርሠናል፡፡ ይህም ትክክል አይመስልም፡፡

በተጨማሪም የፍትሃብሔር ክስ ከወንጀል ክሱ ጋር ተጣምሮ ይቀርባል፤ የሚመራው በወንጀል


ስነ-ስርዓት ህጉ ነው ማለቱ ምን ማለት ነው? እንደሚታወቀው በብዛት የወንጀል ክሱን
የሚያቀርበው ዓቃቤ ህግ ነው፡፡ በዚህ ድንጋጌ ላይ ግን ተበዳዩ ከወንጀሉ ክስ ጋር የፍትሐብሄር
ክሱን አጣምሮ ሊያቀርብ ይችላል ሲል ምን ማለቱ ነው፡፡ የወንጀሉን ክስ እኮ ተበዳዩ
የሚያቀርብበት ሁኔታ ውሱን ነው፡፡ አገላለጹ ጉዳይን ማጣመር ከሆነ ከሳሹ አንድ መሆን
አለበት፡፡ ከሳሾቹ የተለያዩ በሆኑበት ሁኔታ ጉዳይን እንዴት አድርገን ነው የምናጣምረው?
የሚለዉም ግልፅ አይደለም፡፡ በእርግጥ ድንጋጌዉ ፈቃጅ ነዉ፡፡ ተበዳዩ ከፈለገ ራሱን በቻለ
የፍትሃብሔር መዝገብ የጉዳት ካሳ ጥያቄ ማቅረብ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከወንጀል መዝገቡ ጋር
የጉዳት ካሳ ጥያቄ ማቅረብ የሚችልበትም እድል ሊኖር እንደሚችል የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ
ሥርዓት ህጉ ከአንቀፅ 154-159 አስቀምጧል፡፡ አንቀፅ 154(1) በወንጀሉ የተበደለዉ ሰዉ
ወይም እንደራሲዉ የነገሩ መሰማት ሲጀምር ነገሩን የሚሰማዉ ፍርድ ቤት (to the court trying
the case ይላል የእንግኒዝኛዉ ቅጂ) ለደረሰበት ጉዳት ካሳ እንዲያዝለት መጠየቅ ይችላል፡፡
የሚፈለገዉ ካሳ አይነትና ልክ በፅሁፍ ወስኖ ያመለክታል፡፡ ማመልከቻዉን ሲያቀርብ በህግ
የተወሰነዉን የዳኝነት እንደ ፍትሃብሔ ነገር መክፈል የለበትም ይላል፡፡ በመሆኑም የወንጀል
ክሱ በወንጀል ዐ/ህግ በቀረበበት መዝገብ ጭምር ተበዳዩ ወይም እንደራሲዉ ወይም ስለተበዳዩ
መብት ያላቸው ሠዎች የጉዳት ካሳ ጥያቄ አጣምረዉ ሊያቀርቡ እንደሚችሉ በግልፅ ያሳያል፡፡
ነገር ግን ይህ የክስ መጣመር በፍትሃብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀፅ 11(1) ላይ ካለዉ
የተለየ ነዉ፡፡ ምክንያቱም በፍትሃብሔር ሥነ ሥርዓቱ አንቀፅ 11(1) አነጋገር መሰረት ክሱ
የሚጣመረዉ ተከራካሪዎቹ በአንድ ዘንግ የተመደቡ (…the same parties in the same court…
ይላል የእንግሊዝኛዉ ቅጂ) ሲሆኑ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ስለዚህ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት
ህጉ አቀራረብ ከፍትሃብሔር ሥነ ሥርዓቱ አንቀፅ 11(1) ሃሳብ በተለየ መልኩ ነዉ፡፡ በሌላ
መልኩ ዐ/ህግ በራሳቸዉ መከራከራ የማይችሉ ሴቶችን ወክሎ ፍትሃብሔራዊ ክርክር
የሚያደርግበት አሰራርና የህግ መዕቀፍ ተዘርግቷል፡፡ ስለዚህ የፆታዊ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ሴቶች
የጉዳት ካሳ ጥያቄ ዐ/ህግ ከወንጀል መዝገቡ ጋር አብሮ ቢያቀርብ የወንጀል ሃላፊነቱን
በተረጋገጠዉ መዝገብ ላይ የፍትሃብሔር ሃላፊነትና ካሳ ለማስወሰንና የካሳ ጥያቄዉ ሳይጓተት
መፍትሔ ለመስጠት የተሻለ ይሆናል፡፡

21
ሌላው በዚህ ድንጋጌ መታየት ያለበት የካሣዎቹ ዓይነት ምንድን ናቸው የሚለው ነው፡፡
በድንጋጌው በግልፅ እንደሚታየው፡-

Ø ንብረትን መተካት (Restitution of property)


Ø የጠፉውን ወይም የፈረሠውን እንደነበር መመለስ (Making good the damage)
Ø ኪሣራ መክፈል (to pay cost)
Ø ለጠፉ ለፈረሠ ነገር የጉዳት ካሣ መክፈል (to pay damage by way of
compensntion

የጉዳት ካሣ ደግሞ በፍትሃብሔር ህጉ 2090ና 2092 ግልፅ የሆኑ ጉዳቶች (ዕለታዊና ለወደፊት
ሊደርስ የሊችሉ ጉዳቶች እንዲሁም 2105 የህሊና ጉዳት) ሁሉ ሊያካትት ይችላል፡፡

አንቀፅ 102 ደግሞ ለተበዳዩ የሚሠጠው ካሣ አፈፃፀም ያሣያል፡፡ ይህውም፡-

“(1) ወንጀለኛው ወይም ስለ እርሱ ተጠያቂ የሆኑት እንደነገሩ ሁኔታና ወይም በኑሮአቸው
ምክንያት በተበዳዩ ላይ ለደረሠው ጉዳት ሊክሱ የማይችሉ መሆናቸው በታወቀ ጊዜ
ከወንጀለኛው ላይ ከተያዘው ገንዘብ ውስጥ ወይም ከመቀጮው ውስጥ ወይም በጉልበት ሥራ
ተለውጦ ከሚያገኘው ገቢ ሂሣብ ውስጥ ወይም ከተወረሠው ንብረት ሂሣብ ውስጥ ለተበዳዩ
እንዲከፈል ፍርድ ቤቱ ለማዘዝ ይችላል፡፡

(2) መንግስት ለተበዳዩ በከፈለው የካሣ ገንዝብ ልክ ለተበዳዩ መብት ተተክቶ ጉዳቱን ባደረሠው
ወንጀለኛ ላይ በቀጥታ ሊጠይቅና ሊቀበል ይችላል” በሚል ተደንግጓል፡፡

ከዚህ ድንጋጌ የምንገነዘበው በዳዩ መካስ የሚችል ከሆነ በጉዳቱ ልክ እንዲከስ ማድረግ መርህ
ሆኖ በዳዩ መካስ የማይችል መሆኑ ከታወቀ ግን ከተያዘው ዕቃ፣ ከዋስትና መያዝ፣ ከመቀጮ፣
በጉልበት ስራ ከተገኘው ንብረትና ከተወረሠው ንብረት ላይ ለተበዳዩ ካሣ ሊካፈል እንደሚገባ
ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ነገሮች ባይኖሩስ እንዴት ይሆናል? የሚል ጥያቄ ማንሳት
ይገባል፡፡ በተጨማሪም ንፁስ ቁጥር ሁለት መንግስት በተበዳዩ በከፈለው የካሣ ገንዘብ ልክ
በተበዳዩ መብት ተተክቶ በወንጀለኛው ላይ ጥያቄ እንደት ያቀርባል? ማለትም መንግስት ስለ
ወንጀለኛው ሆኖ ለተበዳዩ ካሣ የሚከፍልበት አጋጣሚ አለን? ወይስ ከላይ ከተዘረዘሩት
ማለትም ከዋስትና ገንዘቡ ከመቀጮው ከተወረሠው ወዘተ ንብረት ላይ ለተበዳዩ ስለተከፈለ
ይህንን ገንዘቡን ነው መንግስት ተተክቶ የሚጠይቀው የሚሉት ነጥቦች ምላሹ ያስፈልጋቸዋል፡፡

22
በሃተታ ዘምክንያቱ ላይ “በቁጥር 105 (2) በዳዩ ወይም ስለእርሱ መብት ያላቸው ለበዳዩ
ሊክሱ በማይችሉ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ሊያዝባቸው ከሚችሉት አማራጮች ውስጥ በዋስትና መያዝ
ስም ካስያዘው ገንዝብ ውስጥ በሚለው ሀረግ በተጨማሪ “ከመቀጮው ውስጥ” የሚል ሃረግ
ተጨምሯል፡፡ ይህም ተበዳዩ ሊካስበት የሚችለው አማራጭ መንገድ ከፍ እንዲያደርግለት
ያስችላል በማለት ነው የሚል ምክንያት ተቀምጧል፡፡” ከዚህ ውጭ መንግስት ለተበዳዩ በአንቀፁ
ከተመለከቱት ውጭ ስለመክፈሉ ወይም ስላለመክፈሉ የተገለፀ ነገር የለም፡፡

በፀሃፊዉ እምነት የአንቀፀ 102 (2) መንግስት ለተበዳዩ በከፈለው የካሣ ገንዝብ ልክ ለተበዳዩ
መብት ተተክቶ ጉዳቱን ባደረሠው ወንጀለኛ ላይ በቀጥታ ሊጠይቅና ሊቀበል ይችላል የሚለዉ
አገላለፅ ከተያዘው ዕቃ፣ ከዋስትና መያዝ፣ ከመቀጮ፣ በጉልበት ስራ ከተገኘው ንብረትና
ከተወረሠው ንብረት ላይ ለተበዳዩ ካሳ በተከፈለዉ ጊዜ መንግስት ከእነዚህ ጉዳዮች ላይ
የሚያገኘዉ ገቢ ስለቀረበት (ማለትም ለተበዳዩ በካሳ መልክ ስለተከፈለ) ይህንን የቀረበትን ገቢ
ከጉዳት አድራሹ ላይ እንዲያገኝ ያለመ ነዉ፡፡ በመሆኑም አንቀፀ 102 (2) መንግስት ስለ
ወንጀለኛው ሆኖ ለተበዳዩ ካሣ የሚከፍልበትን ስልት የፈጠረ አይደለም፡፡ በሌላ አነጋገር የተያዘ
ዕቃ ወይም የዋስትና የመቀጮ ገንዘብ ወይም በጉልበት ስራ የተገኘና ከተወረሠው ንብረት በሌለ
ጊዜ መንግስት ለተበዳዩ ካሳ የሚከፍልበት ህግ አይደለም፡፡

3.3 የወንጀል ፍትህ ፖሊሲና ሌሎች የሰብዓዊ መብቶች ህግጋት

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትህ ሚኒስቴር በ2003 ዓ.ም የወንጀል ፍትህ ፖሊሲ አዘጋጅቷል፡፡ ምንም እንኳ
ፖሊሲዉን መሰረት ያደረገ በዚህ ርዕስ ዙሪያ ስራ ላይ የዋለ የወንጀል ህግ ባይወጣም
የወንጀል ጉዳት የደረሰባቸዉ ሰዎች ካሳ እንዲያገኙ የሚያስችሉ የህገ ማዕቀፍ ሊኖሩ እንደሚገባ
ተመልክቷል፡፡ በፍትህ ፖሊሲዉ ክፍል ስድስት ስር በወንጀል ጉዳት የደረሰባቸዉን ሰዎች
መብት ስለማክበር በሚል ንዑስ ርዕስ ስር በወንጀል ጉዳት የደረሰባቸዉን ሰዎች መብት
በአግባቡ ማስከበር እንዲቻል የተፈፀመዉ የወንጀል ዓይነት ወይም የተጎጂዉን ግላዊ ሁኔታ
መሰረት ያደረገ እና ለልዩ ለልዩ ፍላጎቶቻቸዉም ተገቢዉን ምላሽ በመስጠት ላይ ያተኮረ
አሰራር በወንጀል ፍትህ ሥርዓቱ ዉስጥ እንዲዘረጋ ይደረጋል፡፡ ሕፃናትን ጨምሮ በሌሎች
ሁኔታዎች በወንጀል ድርጊት ለሚደርስ ጉዳት ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ተገቢዉን ጥበቃ
እና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችሉ ልዩ የድጋፍ እርምጃዎች ይወሰዳሉ፡፡ በወንጀል ድርጊት
ጉዳት የደረሰባቸዉ ሰዎች ለደረሰዉ ጉዳት በፍርድ ቤት ወይም በሌሎች አማራጭ ዘዴዎች

23
የካሳ ጥያቄ በማቅረብ ተገቢዉን ካሳ በአፋጣኝ እንዲያገኙ ማድረግ የሚያስችል አመች የሆነ
የአሰራር ሥርዓት ሊዘረጋ ይገባል፡፡ የወንጀል ተጎጂዎች በተፈፀመባቸዉ የወንጀል ድርጊት
ሳቢያ ከደረሰባቸዉ ሥነ ልቦናዊ ቀዉስ እና ካጋጠማቸዉ ሌሎችም ተያያዥ ችግሮች በአግባቡ
እንዲላቀቁ ተገቢ የሆነ ድጋፍ እና የምክር አገልግሎት የሚያገኙበት ሥርዓት መዘርጋት
ይኖርበታል በሚል ተመልክቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች የድርጊት መርሃ ግብር የፆታዊ
ጥቃት ተጎጂ ሴቶችን የሚደግፍና የሚንከባከብ ጊዜያዊ መጠለያ በሁሉም ክልሎችና የከተማ
አስተዳደሮች ቢያንስ አንደ መጠለያ ማዕከል ሊዘጋጅ እንደሚገባ ተቀምጧል፡፡
እዚህ ላይ የሌሎች ሃገራትን ተሞክሮ እንመልከት

እንግሊዝና ዊልስ

እንግሊዝና ዊልስ የወንጀል ጥቃት ሠለባ የሆኑ ዜጐች በመንግስት የሚካሱበት ሥርዓት አለ፡፡
ይህ ሥርዓት የሚተገበረውም የወንጀል ጉዳት ካሣ ባለስልጣን (Criminal Injuries Compensation
Authority (CICA)42 በሚባለው የመንግስት አደረጃጀት ነው:: ይህ መስሪያ ቤት የአካል
ጉዳቶችን እና የሚካሱበትን ታሪፍ በመዘርዘር ለተጐጅዎች ካሣ ይከፍላል፡፡ የአእምሮ ጉዳት
መነሻው የአካል ጉዳት ወይም የፆታዊ ጥቃት ከሆነ ካሣ ይወሠንለታል፡፡ በዚህ ህግ የአካል
ወይም የአእምሮ ጉዳት የደረሰባቸው ሠዎች እንደ ንፁሃን ተጐጅዎች ተቆጥረው ወንጀለኛዉ
ቢቀጣም፣ ባይጠየቅም ወይም ቢከሰስም ባይከሠስም እንዲሁም ቢታወቅም ባይታወቅም ካሣ
የማግኘት መብት አላቸው43፡፡ የተጐጅዎች ግዴታ ጥቃቱ በተፈፀመባቸው ጊዜ ለፖሊስ
ማሣወቅና ለምርመራ መተባበር ነው፡፡ የአእምሮ ጉዳት ደርሷል የሚባለውም በህክምና
የተረጋገጠ የሣይካትሪክ ወይም የሳይኮሎጅካል ህመም ሢኖር ነው44፡፡ እነዚህም ከጥቃት በኃላ
የሚከሰት የአእምሮ መታወክ (Post Traumatic Stress Disorder)፣ ድባቴና የመሣሠሉትን45

42
The Criminal Injuries Compensation Schame, 2012, Ministry of Justice available at
http://www.nationalarchives.gov.uk/doc/open-government-licence
43
Vinson and Elkins, Compensation for the Mental Suffering of Rape Victims and Rape and Prostitution Laws
Relating to Minors: A Comparative Study, 2013, Beijing Zhongze Women’s Legal Counseling and Service Center,
page 20
44
ዝኒ ከማሁ ገፅ, 18
45
እንደ Anxiety, tension, insomnia, irritability, loss of confidence, agoraphobia and
preoccupation with thoughts of guilt or self-harm

24
ያካትታል፡፡ ድባቴው የሚቆይበት ጊዜን በግምት ውስጥ ያስገባ ካሣ እንደሚከፈል ታሪክ
ያሳያል46፡፡

የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ወይም ሙከራ የደረሠባቸው ሴቶች ጥቃቱ ወይም ሙከራዉ
ሊያስከትልባቸው የሚችልው የስነ-ልቦና ከፍተኛ ነው በሚል ምክንያት በቂ ካሣ መንግስት
ይክሣቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአስገድዶ መድፈር ጉዳት የደረሠባቸው ሴቶች በበዳዩ ላይ
የፍትሃብሔር ክስ የማቅረብ መብት አላቸው፡፡ እንድሁም የወንጀሉን ጉዳይ ለሚያየው ፍርድ
ቤቱ ለደረሠባቸው ጉዳት ካሣ እንዲከፈላቸው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ይሁንና የወንጀሉን ጉዳይ
በሚያየው ፍርድ ቤት አማካኝነት ወንጀለኛው ወደ ማረሚያ ቤት ከተላከ በዚሁ ችሎት ካሣ
መጠየቅ አይችሉም47፡፡

ካናዳ

ካናዳ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ የፌደራል ስርዓት የምትከተል ሃገር ነች፡፡ በመሆኑም በሁሉም
የሃገሪቱ ክልሎች ተፈፃሚነት ያለው የወንጀል ህግ አላቸው48፡፡ ይሁንና ክልሎች የራሣቸው
የሆነ የወንጀል ድርጊት ሠለባዎች ካሣ ህግ አላቸው፡፡ በተለይም የአልበርታና የኦንታርዮ
የተባሉትን ግዛቶች የወንጀል ፍትህ ሥርዓት በጥቂቱ እንመለከታለን፡፡ በአልበርታ ግዛት
የተጐጅዎች ወንጀል ህግ (Victims of Crime Act) ወይም የAlberta Compersation Act የሚባል
ህግ አለ፡፡ በዚህ ህግ የስነ-ልቦና ጉዳቶች ውስጥ በአስገድዶ መደፈር ጥቃት ስነ ልቦናቸዉን
የተጐዱ ሴቶች የሚካሡበት ደንብ ሲኖር ይህም የተጀመረው የወንጀል ተጠቂዎችን በገንዘብ
የመደገፍ ዕቅድ (The Victims of Crime Financial Benefits Program) አካል ነው49፡፡ ይህም
በግዛቷ የፍትህ ቢሮ የህዝብ ደህንነት ክፍል ሆኖ ተደራጅቷል፡፡ በመሆኑም ጥቃት የደረሠበት
ሠው ወንጀሉን በተገቢው ጊዜ ለፖሊስ ማመልከት ይኖርበታል፤ እንዲሁም አስፈላጊ የሚባሉ
መረጃዎችን፣ ሠነዶችን፣ የምርመራ ውጤቶችን ወዘተ ለፖሊስ ለመስጠት ተባባሪ መሆን
አለበት50፡፡ ካሣ ለማግኘት የሚቀርብ ማመልከቻ ከሁለት ዓመት በኋላ እንደማይቀርብ
ተደንግጓል፡፡ የጥቃቱ አደገኛነትና ጐጅነት ከግምት ውስጥ እየገባ እንደየ ጉዳዬች የሚከፈል

46
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 43 ገፅ 18
47
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 43 ገፅ 19
48
The Criminal Code of Canada, 1985
49
The Alberta Compensation Act established the Victims of Crime Fund and introduced the Victims of
Crime Financial Benefits Program.
50
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 43 ገፅ 12

25
የካሣ ገንዘብ አለ፡፡ የአስገድዶ መደፈር ወንጀልን አስመልክቶ በመንግስት ከሚከፈለው የጉዳት
ካሣ በተጨማሪ ተጐጅዎች በፍርድ ቤት ተጨማሪ ካሣ የሚጠይቁበት ሥርዓት አለ፡፡
በመሆኑም የግዛቱ ዐ/ህግ በወንጀለኛው ላይ ማንኛውንም ጉዳትና ኪሣራ አስመልክቶ ካሣ
ለተጐጅዎች እንዲከፈል መጠየቅ ይችላል፡፡ ጉዳቱም የስነ-ልቦና ችግሮች ጨምሮ ሌሎች
ጉዳቶች ሁሉ እንዲካሡ የሚደረግ ነው51፡፡

ሌላኛው የካናዳ ክልል (ግዛት) ኦንታርዮ ነች፡፡ በአንታርዬ የካሣ ህግ መሠረት የተቋቋመው
የወንጀል ተጠቂዎች የካሣ ቦርድ አለ፡፡ ይህ ቦርድ የወንጀል ጥቃት ያደረሡ ድርጊቶችን
በመዘርዘር እንዴት እንደሚካሱ ይሠራል፡፡ በዚህ ህግ መሠረት ፆታዊ ጥቃት በቀጥታም ይሁን
በተዘዋዋሪ መልኩ በሴቶች ላይ ጉዳትና ህመም እንዲሁም ሞት ያስከተለ እንደሆነ ካሣ
እንደሚከፈላቸው ይወሰናል52፡፡

3.4 በፍትሃብሔር ህጉ የተደነገጉ መፍትሔዎች

ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸዉ ሴቶች በዋናነት ፍትሃብሔራዊ መፍትሔ ያሰቀመጠዉ በከዉል


ዉጭ አላፊነት ህግ ነዉ፡፡ የዚህ ህግ ዋና ዓለማ ጉዳት ለደረሰበት ሰዉ ካሳ ማስከፈል ነዉ፡፡
ይህም በሰዎች መካከል ምንም ዓይነት የዉል ግንኙነት ሳይኖር በሌላ ሰዉ ለሚደርስ ጉዳት
ሃላፊነት በህግ የተጣለበት ሰዉ ጉዳት ለደረሰበት ሰዉ የሚከፍላቸዉን ፍትሃብሔራዊ ካሳዎችን
ያካትታል፡፡ በኢትዮጵያ የከዉል ወጭ አላፊነት ህግ53 መሰረት ካሳ ለማገኘት ጉዳት መድረሱን
ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ ጉዳት በሰዉ ጥቅም ላይ የሚደርስ ኪሳራ ሲሆን እሱም የገንዘብ ወይም
የህሊና ጥቅምን የሚነካ ወይም የሚጎዳ ሊሆን ይችላል፡፡54 የገንዘብ ጉዳት አሁኑኑ የደረሰ
ወይም ገና ወደፊት የሚደርስ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲሁም የህሊና ጉዳት በሚል
ተመልክቷል55፡፡ የገንዘብ ጉዳት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተጎጂዉን ጥቅም ወይም ገቢ
ያራቁታል፡፡ ሃብቱን ያሳጣዋል፡፡ ገቢዉ እንዳይጨምር ያደርጋል፡፡ ሃብቱ እንዳያድግ
ያደናቅፋል፡፡ ስራዉን እንዲያጣ ያደርጋል፡፡ የካሳ ዓይነቶች በሁለት መልኩ ይፈፀማሉ፡፡
እነዚህም በገንዘብ መካስ (pecuniary compensation) እና በሌላ አኳኃን መካስ (other modes of

51
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 43 ገፅ 12
52
የግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 43 ገፅ 13
53
የኢትዮጵያ ፍትሃብሔር ህግ (1952)፣ 4ኛ መፅሃፍ ስለግደታዎች በሚለዉ 13ኛ አንቀፅ ከቁጥር 2027-2161 ተደንግጓል፡፡
54
ንጋቱ ተስፋዬ ከዉል ዉጭ አላፊነት እና አላግባብ መበልፀግ ህግ፤ 1999 ዓ.ም ሁለተኛ እትም፤ ገፅ 129
55
ግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 53፤ (ኢትዮጵያ ፍትሃብሔር ህግ) አንቀፅ 2090፤ 2092፤ የህሊና ጉዳት አንቀፅ 2105

26
compensation)56ናቸዉ፡፡ በእነዚህ ዘዴዎች የሚካሱት የገንዘብ ወይም የህሊና ጉዳት
የደረሰባቸዉ ተጎጅዎች እንደሆኑ የኢትዮጵያ ፍትሃብሔር ህግ ከአንቀፅ 2090-2123
ያስገነዝባል፡፡ የካሳ አከፋፈል ስርዓቱም ለደረሰዉ የገነዘብ ጉዳት የተመዛዘነ ወይም የተመጣጠን
ካሳ መክፈል57፤ በርትዕ ካሳ መክፈል58፤ ዕቃን በመመለስ፤ በዓይነት በመተካት፤ የማደሻና
የማገጃ ትዕዛዝ በመስጠት59 መካስ እንደሚቻል ተመልክቷል፡፡

በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃትን አስመልክቶ በኢትዮጵያ የፍትሃብሔር ህግ


የተደነገጉትን ሁኔታዎች ስንመለከት በአንቀፅ 2038 ሰውነትን ስለመጉዳት (physical assault)
በሚል ርዕስ

(1) አንድ ሰው ሆነ ብሎ ሌላው ሰው ሣይፈቅድ በሚያደርገው መንካት በዚህ በመንካቱ


ጥፉተኛ ነው፡፡
(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ ሰዉየዉን በቀጥታም ሆነ ወይም በሌላ ህይወት ባለዉ ወይም
በሌለዉ ነገር አማካይነት ቢነካዉም ጥፋተኛ ነዉ፡፡
(3) በሌላ ሰዉ ላይ ጉዳት ለማድረግ የተደረገ የመዛት ሁኔታ ብቻ በጠቅላላዉ ጥፋት
አይባልም በሚል ተደንግጓል፡፡

ከዚህ እንደምንገነዘበዉ አንድ ሰዉ ሌላዉን ለመጉዳት ወይም ለማስቀየም አስቦ ያለፈቃዱ


ከነካዉ በመንካቱ ብቻ ጥፋተኛ እንደሚሆን ነዉ፡፡ ይህ ድርጊት ድብደባ ወይም የእጅ እልፊት
ሊባል ይችላል፤እንዲህ አይነቱ አድራጎት በሰዉነት ላይ ጉዳት ባያስከትልም ሶስቱ ሁኔታዎች
ማለትም ንክኪ፤ የተፈፀመዉ ንክኪ ያለፈቃድ መሆንና ታስቦ የተፈፀመ ንክኪ መሆን
እስከተሟሉ ድረስ ጥፋት ይሆናል60፡፡ በድንጋጌዉ ንዑስ ቁጥር 2 ላይ የተመለከተዉ ሃሳብ
ደግሞ የሚነግረን ንክኪዉ በቀጥታ ወይም በሌላ ሕይወት ባለዉ ወይም በሌለዉ ነገር
አማካኝነት ሊፈፀም እንደሚችል ነዉ፡፡

56
ግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 53፤ (ኢትዮጵያ ፍትሃብሔር ህግ)፣ በገንዘብ መካስ ከአንቀፅ 2090-2117 እንዲሁም በሌላ አኳኃን
መካስ ከአንቀፅ 2118-2123 ተመልክተናል፡፡
57
ግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 53፤ (ኢትዮጵያ ፍትሃብሔር ህግ)፣ አንቀፅ 2090፤ 2091
58
ግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 53፤ (ኢትዮጵያ ፍትሃብሔር ህግ)፣ ከአንቀፅ 2099- 2104
59
ግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 53፤ (ኢትዮጵያ ፍትሃብሔር ህግ)፣ ከአንቀፅ 2118-2123
60
ግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 54፤ (ንጋቱ ተስፋዬ)፤ ገፅ 54

27
ይሁንና የዚህን አንቀፅ ልዩ ሁኔታዎች ህጉ በዝርዝር በአንቀፅ 2039 ላይ ሰውነትን መጉዳት
በሚል ተከሳሽ የሆነ ሰዉ ጥፋተኛ የማያስብሉት በቂ ምክንያቶች ናቸዉ የተባሉትን ከዚህ
በታች በተመለከተዉ መልኩ በዝርዝር አስቀምጧቸዋል፡፡

ሀ/ ከሳሹ ሥራዉን የሚቃወም መሆኑን ተከሳሹ በአዕምሮዉ ግምት ሊያስገባዉ የማይችል


መሆኑ የታወቀ እንደሆነ
ለ/ ስራዉ የተፈፀመዉ በሚገባ አኳኃን ለራሱ ወይም ለሌላ ሰዉ ለመከላከል ወይም በደንብ
በእጁ ያለዉን ወይም የያዘዉን ንብረት ለመጠበቅ ሲል እንደሆነ
ሐ/ ስራዉ የተፈፀመዉ ተከሳሹ ልጁን የአደራ ልጁን ተማሪዉን ወይም አሽከሩን በሚገባ
ለመቅጣት ሲል በሰዉነቱ ላይ ተገቢ የሆነዉን አቀጣጥ ፈፅሞበት እንደሆነ
መ/ ከሳሹ አደገኛ እብድ በመሆኑ ጉዳት እንዳያደርስ በሌላ አኳኃን ለመከላከል
ስላልተቻለዉና ተከሳሹ ስራዉን የፈፀመዉ በሚገባ አኳኃን እንደሆነ
ሠ/ የተከሳሹ ስራ አዕምሮ ባለዉ ሰዉ ግምት የሚገባ ነዉ የሚያሰኝ ሌላ ማናቸዉም
ምክንያት በተገኘ ጊዜ ሁሉ ነዉ፡፡

ሌላዉ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃት የተመለከተዉ በአንቀፅ 2114 ላይ ያለዉ የንፅህና
ክብር ስለመድፈር (sexual outrage) ነዉ፡፡

ይህም ፡- (1) ማንኛዉም ሰዉ በመድፈር ስራ ወይም ለክብር ንፅህና ተቃራኒ በሆነ ተግባር
በወንጀል የተቀጣ እንደሆነ ዳኞቹ ለተደፈረችዉ ሴት ለደረሰባት የህሊና ጉዳት ማካካሻ
የሚሆን ተገቢ ካሳ ለመቁረጥ ይችላሉ፡፡
(2) አንዲት ሴት ወይም ልጃ ገረድ በሃይል የተደፈረች እንደሆነ ለሴቲቱ ባል ወይም
ለተገሰሰችዉ ልጃ ገረድ ቤተዘመዶች ተገቢ የህሊና ጉዳት ካሳ ሊቆረጥ ይቻላል፡፡

በመሰረቱ የንፅህና ክብር መድፈር (sexual outrage) ድርጊት ፍትሃብሔራዊ ሃላፊነት


የሚያስከትለዉ የህሊና ጉዳት ያስከትላል በሚል እሳቤ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ይህ ድንጋጌ የሰፈረዉ
የህሊና ጉዳት ካሳ በሚያስፈልጋቸዉ ከአንቀፅ 2105-2117 ክፍል ነዉ፡፡ የህሊና ጉዳት ካሳ
መጠንም እጅግ ቢበዛ እስከ አንድ ሺህ ብር61 ብቻ የሚደርስ ነዉ፡፡ ከላይ በዝርዝር ለማመላከት
እንደተሞከረዉ የአስገድዶ መደፈር ወንጀል የተፈፀመባት ሴት የደረሰባትና በዕድሜዋ ሙሉ

61
ግርጌ ማስታዎሻ ቁጥር 53፤ (ኢትዮጵያ ፍትሃብሔር ህግ)፣ አንቀፅ 2116(3)

28
ሊደርስባት የሚችለዉን የስነ ልቦና ጠባሳ (እንደ ፍርሃት፤ ጭንቀትና ድብርት የመሳሰሉትን)
ሙሉ በሙሉ ፍትሃብሔራዊ መፍትሔ አግኝቷል ለማለት አይቻልም፡፡

የአስገድዶ መደፈር ወንጀል ከዚህ በላይ ለማመላከት እንደተሞከረዉ በተጠቂዎች ላይ የአካል፤


የስነ ልቦናና የጤና ጉዳቶች ሊያስከትል ይችላል፡፡ እነዚህ ጉዳቶች በተጠቂዎች ላይ ስለመድረሱ
የሚያሳይ የጤና ምርመራ ልምድ እንኳን በብዛት አይታይም፡፡ ይህ ፅሁፍ ህጉን ብቻ እንጂ
የህጉን አተገባበር የሚፈተሺ ባይሆንም ለግንዛቤ ይረደኝ ዘንድ አጋዥ የሚሆኑ መዝገቦችን
ለመመልከት በባህር ጋር ከተማ አስተዳደር ፍትህ ፅ/ቤት በ2010 ዓ.ም ዉሳኔ ያገኙ መዝገቦችን
አይቼ ነበር፡፡ በሁሉም የአስገድዶ መደፈር ወንጀል መዝገቦች ላይ የፍትሃብሐር ጉዳት ካሳ
ጥያቄ አልቀረበም62፡፡ በመሰረቱ ይህ የህክምና ማስረጃ ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያቱ የተጠቂዋን
ጉዳት ለማወቅ ሳይሆን ተከሳሹ ወንጀሉን ስለመፈፀሙ ማስረጃ ለማገኘት ነዉ፡፡ በሌላ አነጋገር
ዐቃቢ ህግ ስለ ተጎጅዋ የአካል፤ የጤናና የስነ ልቦና ጉዳት አላሳሰበዉም፡፡ የየኤች አይ ቪ፤
የጉበት ቫይረስ፤ የአባለዘርና የእርግዝና ምርመራ የተገረገዉም በወንጀለኛዉን ላይ የሚቀርበዉን
ክስ ለማክበድ ነዉ፡፡ የወንጀል ህጉም እንደዚህ ዓይነት ድንጋጌ ስለያዘ፡፡ ዐቃቢ ህግ ወይም
ፖሊስ ለወንጀል ክሱ የህክምና ማስረጃ ባያስፈልገዉ ኖሮ የህክምና ምርመራ ላይደረግ ይችላል፡፡
እጅ ከፍንጅ በቀረበ ክስ63 የህክምና ምርመራ አልተደረገም፤ተከሳሹም በአምስት አመት ፅኑ
እስራት ተቀጥቷል፡፡ በመሆኑም ከሳሽ (ፖሊስ ወይም ዐቃቢ ህግ) ያለኝ ማስረጃ ተከሳሽን
በወንጀል ለማስቀጣት በቂ ነዉ ብሎ ካሰበ የህክምና ምርመራ አያስደርግም፡፡ ከእነዚህ ጉዳዮች
በመነሳት የከሳሽ ዋነኛ ትኩረትና ግብ ወንጀል ፈፃሚን ማስቀጣት እንጂ የጥቃት ሰነባ
የሆነችዉን ሴት ፍትህ እንዲታገኝ ማድረግ አይደለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

1. ማጠቃለያ

62
የባህር ዳር ከተማ ፍትህ ፅ/ቤት ዐ/ ህግ ከአቶ ዮሃንስ…. (መዝገብ ቁጥር 428/10 በቀን 3/02/10 ዓ.ም የቀረበ ክስ)
በአንድ የህክምና ምርመራ ዉጤት የተገለፁት ፍሬ ነገሮች የሚያሳየዉ “…በተደረገዉ የማህፀን አካላዊ ምርመራ
በታችኛዉ ብልቷ ጫፍ 2 ሴንቲ ሜትር የሚሆን የድንግልና ንጣፍ መሰንጠቅ ታይቷል፡፡ ይህም የክብረ- ንፅህና
መገርሰስን ያረጋግጣል፡፡ ብልቷም በደም ተነካክቷል፡፡ የኤች አይ ቪ፤ የጉበት ቫይረስ፤ የአባለዘርና የእርግዝና
ምርመራ ዉጤቱ ለጊዜዉ ነፃ እንደሆነች ያሳያል” ይላል፡፡ በዚሁ ክስ ዝርዝር ላይ ….ተከሳሹ የሃይል ድርጊት በመጠቀም
አስገድዶ በመድፈር ክብረ ንፅህናዋን የገሰሰና ግራ ጡቷንና ግራ ጆሮዋን ነክሶ ጉዳት ያደረሰባት መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ይሁንና
የተከሰሰዉ በአስገድዶ መድፈሩ ብቻ ነዉ፡፡ የህክምና ምርመራዉና ዉጤቶም እነዚህን ሁሉ ጉዳቶች አላከተተም፡፡
63
የባህር ዳር ከተማ ፍትህ ፅ/ቤት ዐ/ ህግ ከአቶ ደርባቸዉ…..(መዝገብ ቁጥር 98/10 በቀን 6/11/09 የቀረበ ክስ) “ተከሳሹ የሃይል ድርጊት
በመጠቀም ወይም በብርቱ ዛቻ ግል ተበዳይን በግምት 5፡30 ፀጉሯን ይዞ በመጎተት ባጃጅ ዉስጥ አስገብቶ ወደ
ሆቴል ወስዶ አልጋ ይዞ አስገድዶ ደፍሯታል…”63 ይላል፡፡

29
ፍትህ ላንዱ ጉዳት ያደረሰበት ሰዉ በፈፀመዉ ጉዳት በወንጀል ተቀጥቶ ማየት ሲሆን ለሌላ
ፍትህ አገኘሁ የሚለዉ በወንጀል ድርጊቱ የተነሳ ያጣዉን ገንዘብና ጥቅም ወይም የተጎዳዉን
አካሉንና አእምሮዉን የሚጠግን ማካካሻ በካሳ መልክ ሲያገኝ ነዉ፡፡ ለሌላዉ ጉዳት አድራሹ
በፈፀመዉ ድርጊት ተፀፅቶና ደንግጦ ተጎጅዉን ይቅርታ ሲጠይቀዉ ፍትህ አገኘሁ ሊሆን
ይችላል፡፡ እንዲሁም አንዳዱ እዉነታዉን ለማህበረሰቡ ወይም ጉዳት አድራሹ በቀጥታ መናገር
ነዉ64፡፡ የኢትዮጵያ የወንጀል ህግ ዓላማ ለጠቅላላዉ ጥቅም ሲባል የህዝቦቹንና የነዋሪዎቹን
ሰላምና ደህንነት መጠበቅና ማረጋገጥ በመሆኑ ወንጀል ሲፈፀም ወንጀለኛዉ የሚቀጣዉ
ለጠቅላላዉ ጥቅም ሲባል (ማለትም ተጨማሪ ወንጀል እንዳይፈፅም ወይም ለሌላዉ
ማስተማሪያ እንዲሆን) በመሆኑ ተጎጅዎችን ያረካ የወንጀል ፍትህ ስርዓት ስለመረጋገጡ
ብዙዎች ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ ምንም እንኳ ይህ ፅሁፍ ተግባሩን ሳይሆን ህጉን ብቻ የዳሰሰ ቢሆንም
ህጉን ለመዳሰስ ያነሳሳን ነገር ግን የአስገድዶ መደፈር ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶች ከጉዳቱ በኃላ
ለንፅህና መጠበቂያ፤ ለመጠለያ ና ለህክምና ምርመራ የሚሆነ ገንዘብ ባለመኖሩ ባሰቃቂ ሁኔታ
በጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ማገኘታችን ነበር፡፡ ዐ/ህግ ተጎጂዎቹ ምን መፍትሔ ያግኙ
የሚለዉ ብዙም አያሳስበዉም፡፡ ይልቁንም ትኩረቱ ወንጀል ፈፃሚዉን ማስቀጣት ነዉ፡፡
የተጎጅዎችም አስፈላጊነት ለምስክርነት እንጂ እነሱ ፍትህ ስለማገኘታቸዉ የሚጨነቅ አካል
የለም ቢባል ስህተት አይሆንም፡፡ በመሆኑም የፆታዊ ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶች ለሚደርስባቸዉ
የስነ ልቦና ጉዳት በሥነ ልቦናና ሥነ አእምሮ ባለሙያዎች እየተረጋገጠ እንደጉዳቱ ልክ የገንዘብ
ካሳ የሚከፈልበት ስልት ያስፈልጋል፡፡ የፆታዊ ጥቃት የተፈፀመባቸዉ ሴቶች በተለይም
የአስገዲዶ መድፈር ድርጊት ተጠቂ ሴቶች ድርጊቱ ሊያስከትልባቸዉ የሚችለዉ የጤና
ችግሮችን በህክምና በመለየት ወይም ሙያዊ ግምት በማስቀመጥ የገንዘብ ካሳ የሚያገኙበት
ስርዓት ሊዘረጋ ግድ ይላል፡፡ የፍትሃብሔር ህጉ በአንቀፅ 2114 ላይ ያለዉ የንፅህና ክብር
ስለመድፈር የሰፈረዉ ድንጋጌ የሚያስክሰዉ የህሊና ጉዳት ብቻ ነዉ፡፡ ይሁንና የአስገዲዶ
መድፈር ድርጊት በርካታና የተወሳሰብ የጤና ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፡፡ በመሆኑም እነዚህ

64
Amy Kasparian የተባለች ፀሃፊ በ2014 Justice beyond bars በሚለዉ ፅሁፏ “For some [‘victims/survivors’],
justice is simply the perpetrator’s conviction and incarceration. For others, justice is receiving
compensation from the offender or the state to help with civil matters like securing safe housing,
affording counseling, or repairing property damage. To others, it is having a meaningful opportunity to
tell one’s story to the community, or perhaps directly to the offender. And yet still, to other victims,
justice is having the offender publicly acknowledge and apologize for the harm caused. In short, justice
to rape victims can manifest itself in many diverse forms that often do not necessarily rely on the
traditional criminal justice idea of punishment” በማለት ትገልፃለች

30
ጉዳቶች የሚካሱበት ህግ ተሻሽሎ ሊወጣ ይገባል፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጅል ህግ ከወንጀል ፍትህ
ስርዓቱ ጋር የጉዳት ካሳ ጥያቄዎች ተጣምረዉ እንዲቀርቡ የሚፈቅዱ በመሆኑ በሴቶች ላይ
በሚፈፀሙ የፆታዊ ጥቃት ክርክሮች ጊዜ የጉዳት ካሳ ጥያቄዎችን አካቶ በማቅረብ ተጠቂዎች
ካሳ እንዲያገኙ የሚያስችል ስራ ዐቃቢ ህግ ሊሰራበት ይገባል፡፡ የአብክመ
ፍ/ባ/ማ/ህ/ም/ኢንስቲትዩት ይህንን ፅሁፍ በማዳበር ለዳኞች፤ ዐቃቢያን ህጎችና መርማሪ
ፖሊሶች ጉዳዩ ትኩረት እንዲያገኝ የሚያስችል ስልጠና ማመቻቸት ይኖርበታል፡፡

31
የመሬት ይዞታ ይገባኛል እና የይርጋ መከራከሪያ በአማራ ብሔራዊ ክልል የመሬት አዋጅ
ከፌደራል መንግስት የህግ ማዕቀፍ አንጻር፡

ጋሻዬ ቢያድግ§

አህጽሮተ ይዘት
በንብረት ህግ ማዕፍ ዉስጥ ተቀባይነት ያላቸዉ ንብረት የሚገኝባቸዉ መንገዶች ዉስጥ አንዱ
ባለ እጅ (ይዞታ) (adverse possession) አንዱ ነዉ፡፡ ይህ መንገድ ረጅም ታሪክ ያለዉ ሲሆን
በሮማዊያን ህዝቦች ዘንድ መነሻ ሲኖረዉ በእንግሊዝ የመሬት ህግ እንደስረዓት እንደተዘረጋ
መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህ አሰራር የራሱ የሆነ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አመክኒኦ
(justifications) አሉት፡፡ ይህ አሰራር ከይርጋ ህግ ጋር ቀጥተኛ ትስስር ስለአለዉ የይርጋ ህግ
የተመሰረተባቸዉ አጠቃላይ ምክንያቶች ለዚህ አሰራር በአመክኒኦነት ይወሰዳሉ፡፡ ከመሬት
ይዞታ ጋር በተያያ ህገ ወጥ ይዞታን የሚበረታታ ነዉ በሚል የሚቀርብበት ትችት ቀላል
አይደለም፡፡ ለመሆኑ በኢትዮጵያ የህግ ማዕቀፍ ዉስጥ የዚህ አሰራር ትርጉምና ተቀባይነት ምን
ይመስላላ? በተለይም፣ የመሬት ይዞታን አስመልክቶ ጥበቃ ለማድረግ የፌደራል የህግ ማዕቀፍ
እና የአማራ ብሔራዊ ክልል የመሬት አዋጅ ቁጠር 252/2009 ያላቸዉ አkም አብሮ የሚሄድ
ነዉ፣ የሚሉትን ጥያቄዎች በዚህ ጽሁፍ የተዳሰሱ ሲሆን የሌሎች ሀገራት ህግና ተሞክሮን
መሰረት በማድረግ የፌደራል እና የክልሉን የህግ ማዕቀፎች ላይ ዓይነታዊ በሆነ የጥናት ዘዴ
ትንታኔ በማድረግ፤ የባለእጅ(ይዞታ) አሰራር በፌደራል ደረጃ በህግም ይሁን በፍርድ ቤት ዉሳኔ
የተዘረጋ ሲሆን የአማራ ብሄራዊ ክልል በበኩሉ ይህን አሰራር ቀሪ እንዲሆን በግልጽ
አስቀምጧል፡፡ ክልሉ መነሻ ያደረገዉ የዜጎች የመሬት ይዞታን የተሻለ ጥበቃ ለማድረግ አስፈላጊ
ነዉ ብሎ በማሰብ ይመስላል፡፡ ነገር ግን የፌደራሉም ይሁን የክልል ህግ ማዕቀፍ ሲታዩ ህገ
ወጥ የሆነ የመሬት ወረራን ለመከላከልና የዜጎችን የይዞታ መብት የሚጠብቁ የወንጀልም
ይሁን የፍታብሄር ጥበቃዎች በቂ ናቸዉ፡፡ እነዚህን አማራጮች ተጠቅሞ ይዞታዉን በወቅቱ
ያላስከበረ ባለይዞታ ደግሞ አጠቃላይ ከህዝብ ጥቅም አንጻር፣ ከኢኮኖሚያዊ እና መህበራዊ
ምክንያቶች አንጻር በመመዘን ይህ ስርዓት ሊዘረጋ ይገባል፡፡ ስርዓቱ ሲዘረጋ ግን የተለያዩ
የጥንቃቆ ቅድመ ሁኔታዎች ማስቀመጥና የጊዜ ደገቡን ረዘም በማድረግ ያሉትን ችግሮች
መቅረፍ ይገባል፡፡

ቁልፍ ቃላት፡- ባለእጅ (ይዞታ)፣ ህገ-ወጥ ይዞታ፣ ይርጋ፣ ሰባዊ ብት፣ የህዝብ ጥቅም ፣ አመክኒኦ
1. ባለ እጅ (ይዞታ) የማድረግ የማድረግ አሰራር ጽንሰ ሀሳብ
ባለእጅ (ይዞታ) (dverse Possession) ማድረግ ማለት ለተከታታይ ጊዜ በንብረቱ በመጠቀም
የሚገኝ የይዞታ መብት ነዉ፡፡ይህ አሰራር የቀድሞ የንብረት ባለቤትን ግልጽ ወይም በተዘዋዋሪ
መንገድ ባለቤትነቱን የሚቃረን ወይም የሚያሳጣ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ባለሀብት
የሚሆንበት አንዱ መንገድ ነዉ፡፡1የህግ መዝገበ ቃላት የሆነዉ ብላክስሎዉ ባለ እጅ ማድረግ
አሰራርን ሲተረጉም የማይንቀሳቀስ ንብረት የባለቤትነት ማግኛ መንገድ ሲሆን ይህም በጊዜ እና
ቅድመሁኔታዎችን ማሟላትን ይጠይቃል፡፡ እነዚህ ቅድመሁኔታዎችም ማንም ሳይፈቅድለት
በንብረቱ ሲጠቀምበት የቆየ መሆኑን ማስረዳት፣ ይህን ንብረት የተጠቀመበት ሁኔታ ደግሞ
በግልጽና በባለቤትነት ስሜት መጠቀምና በህግ የተቀመጠዉን የጊዜ ገደብ ማሟላቱን ማሳየት
አለበት ይላል፡፡2ከዚህ መዝገበ ቃላት ትርጉም ጋር የሚመሳሰል አገላለጽ በአንድ ታዋቂ
የእንግሊዝ የፍርድ ቤት ዉሳኔ የሚከተለዉ ተመልክቶ ስራ ላይ ዉሏል፡፡
Adverse possession means possession of the land which is
inconsistent with the title of the true owner: this inconsistency
necessarily involves an intention to exclude the true owner, and all
other persons, from enjoyment of the estate or interest which is
being acquired የሚል ነዉ፡፡3
ወደ አማረኛ ሲመለስ ባለእጅ (ይዞታ) ማለት መሬትን በይዞታ ስር በማድረግ የቀድሞ
ባለቤትን በሚቃረን ወይም በሚጋፋ መልኩ ይህ ባለእጅ (ባለ ይዞታ) ያደረገ ሰዉ ይንን
መሬት በባለቤትነት ስሜት እና የቀድሞ ባለቤትና ሌሎችን የሚያገል አጠቃቀም ስርዓት
ነዉ የሚል ይሆናል፡፡ ከመሬት ይዞታ ጋር በተያያ ባለእጅ የማድረግ አሰራር (Adverse
Possession) አንድ ጸሀፊ ሲገልጽ ‹የሌላ ሰዉ መሬት መያዝ ሲሆን በተለይም በእርግጥም
መሬቱን በእርሱ ቁጥጥር ስር በማድረግ በግልጽ እና በባለቤትነት ስሜት ማለትም ሌሎችን
በማግለል ለተከታታይነት ሲጠቀምበት የቆየ መሆኑን እና በህግ የተቀመጠዉን የጊዜ ገደብ

§LLB, LLM, በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ህግ ምርምር ኢንስቲትዩት የህግ
ጥናትና ምርምር አስተባባሪ ፡፡ ማንኛዉም አስተያየት በgashayebiadge@yahoo.com ላይ ማድረስ ትችላላችሁ፡፡
1
The Doctrine of Adverse Possession Law Essays LawTeacher, UK (November 2013)
የተገኘዉ<http://www.lawteacher.net/free-law-essays/land-law/the-doctrine-of-adverse-possession-law-
essays.php?cref=1> (መጋቢት 16 2010 ዓ.ም) የተገኘ፡፡
2
ዝኒ ከማሁ፡፡
3
Murphy v Murphy [1980] IR 183 የሚለዉን የፍርድ ቤት ጉዳይ ይመልከቱ፡፡
ካሟላ ባለመሬት ይሆናል›4 በማለት ያስቀምጣል፡፡ ከላይ የተመለከቱት ተቀባይነት ያላቸዉ
የባለእጅ የማድረግ አሰራር ትርጉም የጋራ ነጥቦች አሉ፡፡ እነርሱም መሬቱን በእርግጥም
መቁጥጥር ስር ማድረግ፣መሬቱን በህግ የተቀመጠዉን የጊዜ ገደብ ማሟላት እና መሬቱን
በግልጽና ሌሎችን በሚያገል መንገድ በመሬቱ መጠቀምን ያጠቃልላል፡፡5በዚህ መሰረት ባለእጅ
መሆን አሰራርን ተግባራዊ ከማድረግ በፊት እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች በጥንቃቄ መመርመርን
እና መሟላታቸዉን ማረጋገጥ ይጠይቃል፡፡
2. ባለእጅ (ይዞታ) አሰራር ታሪካዊ ዳራ
ባለእጅ የማድረግ አሰራር የረጅም ጊዜ ታሪክ ባለቤት ሲሆን ከክርስቶስ ልደት በፊት በ2250
ዓመተ ዓለም በሀሙራቢ ህግ ነዉ፡፡6 በጥንታዊ የግሪክና ሮማዊያን ህዝቦች ዘንድ የሰዎች
መንፈስ በሚቀመጡበት ወይም በሚይዙት መሬት ላይ ይወሰናል የሚል ነበር፡፡7 በዚህ
አመክኒኦ ይህ ሰዉ በህግ የዚህ መሬት ባለቤት ይሆናል ማለት ነዉ፡፡ ይህ የዳበረ አሰራር የህግ
ድጋፍ በማግኘቱ ሰዎች በተወሰነ የጊዜ ገደብ የተጠቀሙበትን መሬት ባለቤት እንዲሆኑ
አስችሏል፡፡ይህ ህግ የሮማዊያን የንብረት ህግ መነሻ ያደረገ ሲሆን በሲቪል የህግ ስርዓትም
የዳበረ ነዉ፡፡8 በሮማዊያን ህግ ዩስካፒዮ (Usucapio የሚል የላቲን ቃላል ሲሆን በሌሎች
የኮመን ሎዉ ተከታይ ሀገራት ደግሞ አድቨርስ ፖሰሽን (adverse possession) በሚባል
ይታወቃል፡፡ ይህን ለማየት የሚከተለዉን ጥቀስ ይመለከቷል፡፡
<The Usucapioof Roman law, as adoptedincivil law systems, represents what is often
called acquisitive prescriptionin the sense that adverse possession conferred a positive
title>9..ስለሆነም አንዳንድ ጸሀፊዎች ባለእጅ ማድረግ (adverse possession
ከእንግሊዝ ህግ እንደመነጨ ይነገራሉ፡፡10በእንግሊዝ የይርጋ ህግ በ1632 እንደ

4
Larissa Katz, “Exclusion and Exclusivity in Property Law” (2008) 58 U.T.L.J. 275
5
Madson, T.S. 1989. Rhode Island Real Property LawGainesville: LSS Publishing Company
6
Barry Nicholas, an IntroductiontoRoman law (Oxford University Press, 1962) 107–15. በተጨማሪ The Twelve

Tables ህግን ይመለከቷል፡፡


7
ዝኒ ከማሁ
8
የግርጌ ማስታወሳ ቁጥር
9
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 6፡፡
10
Boudewijn Bouckaert etal ADVERSE POSSESSION TITLE SYSTEMS, Center for Advanced
Studies in Law and Economics Researcher, University of Ghent, Faculty of Law. በዚህ ጽሁፍ
አውሮፓዊያን አቆጣጠር የባለእጅ ወይም adverse possession እንደተጀመረ
ጸሀፍት ይናገራሉ፡፡
ነገር ግን የቃላት ለዉጥ ካልሆነ በስጠቀር በሮማዊያን ህግ 2250 ዓመተ ዓለም ዩስካፕዮ
በመባል ከሚታወቀዉ የላቲን ቃል የመጣ መሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ ይህም በሮማዊያን
ዘንድ ዩስካፕዮ የነበረዉ ወደ እንግሊዝ የመሬት ህግ ሲደርስ አድቭርስ ፖሰሽን (adverse
Possession የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ ስለዚህ በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ ተመሳሳይ
መሆናቸዉን ማየት ይገባል፡፡
የኢትዮጵያ የፍትሀብሄር ህግ የተቀበለዉ የሲቪል ሀገራት አገላላጽ ሲሆን በቁጥር 1168
ላይ እንደተመላከተዉ ባለእጅ (ይዞታ (usucaption) የሚል ነዉ፡፡ በተለይም የእንግኛዉ ቅጅ
በትክክል እንደሚያሳየዉ የኢትዮጵያ የፍታብሄር ህግ በዚህ ረገድ ከሮማዊያን ህግ የተወሰደ
መሆኑን ያመለክታል፡፡ ይሁን እንጅ ከላይ እንደገለጽሁት በኮመን ሎዉና በሲቪል ሎዉ
መካካል የቃላት ልዩነት ካልሆነ በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ አንድ አይነት ናቸዉ፡፡ ስለሆነም በዚህ
ጽሁፍ ቃላቶቹ በዓማራጭ የተጠቀምሁባቸዉ መሆኑን መግለጽ እፈልጋልሁ፡፡
ለብዙሀኑ ህዝብ ጥቅም (utilitarianism) ሲባል የንብረት ህግ መሰረት ሲሆን ንብረት ጥበቃ
ሊደረግለት የሚገባ እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡ ጽንሰ ሀሳቡም ንብረት ለህብረተሰብ ጥቅም ሲባል
በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት ያስረዳል፡፡ ጥቅም ላይ ያልዋለ ንብረት ወይም ጦም
ያደረ መሬት በመጨረሻ የሚጎዳዉ ህብረተሰቡን ስለሆነ ይህን የሚከላከል አሰራር ንብረቱን
ባለእጅ ያደረገዉን ሰዉ መብት እዉቅና በመስጠት ነዉ፡፡11ይህ የሮማዊያን ህግ እንዳስቀመጠዉ
የንብረት ባለቤት የሆነ ሰዉ በአንድ በኩል ያልተገደበ መብት ያለዉ ሲሆን ነገር ግን ይህ
መብት ፍጹም ገደብ የማይጣልት አይደለም፡፡ በመርህ ደረጃ በህግ የንብረት ባለመብቱ
ያለማንም ጣልቃ ገብነት ያልተገደበ መብት አለዉ፡፡ ነገር ግን የመሬት ባለቤት የሆነ ባለሀብት
መሬቱን አላግባብ እንዳያባክነዉ እና ለኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ማዋል እንዳለበት በልዩ ሁኔታ

የሚከተለዉን ዓረፍተ ነገር እንገኛለን፡፡ <Adverse possession was formalized in English common law in
1632 in the Statute of Limitations>.ከዚህ አገላለጽሁለት መልዕክት መገንዘብ ይቻልል፡፡ አንደኛዉ ባለእጅ
ማድረግ እና የይርጋ ህግ ያላቸዉን ግንኙነት ሲሆን ሌላኛዉ ደግሞ የኮመን ሎዉ ህግ በእንግሊዝ ሀገር
እንደተጀመረዉ adverse possession የሚል ቃላት መጠቀማቸዉን ይገልጻል፡፡ በዚህም የእንግሊዝ የመሬት ህግ
ለኮምን ሎዉ ባለእጅ የማድረግ አሰራር መነሻ በመሆን ያገለግላል፡፡
11
Itzchak Tzachi Raz, Use It or Lose It: Adverse Possession and Economic Development
Working Paper August 2017
ግዴታ ይጥላል፡፡ የመሬት ባለቤት የሆነ ሰዉ መሬቱን በአግባቡ ሳይጠቀም የቀረ እንደሆን
የባለቤትነት መብቱን የሚያጣበት ስርዓት ነዉ፡፡ ይህ አሰራር በዘመናዊ የንብረት ህግ በሁሉም
ሀገራት ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ አሰራር ነዉ፡፡12
የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንዳጠኑት ባለ እጅ (adverse possession በጊዜ ገደብ መሆንና
ከይዞታ ያለመፈናቀል ወይም የይዞታ ዋስትና መስጠት ያላቸዉን ግንኙነት በተመለከተ
የሚያሳየዉ ጠንካራ የይዞታ ዋስትና ካለ ምርታማነት ይቀንሳል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ
ባለይዞታዎች በጥብቅ የጊዜ ገደብ የተቀመጠላቸዉ ከሆነ እና መሬታቸዉን በአግባቡ
የማይጠቀሙበት በሆነ ጊዜ መብታቸዉ ወደ ሌላ ሰዉ እንደሚተላለፍ ባወቁ ቁጥር ምርትና
ምርታማነት ይጨምራል፡፡ ለዚህ ዋና ምክንያት ደግሞ መሬቱን በአግባቡ የመጠቀምና ስራ ላይ
የማዋል ሁኔታ ስለሚጨምር ነዉ፡፡13 ስለሆነም ይህ አሰራር መዘርጋቱ የመሬት ባለቤት የሆኑ
ሰዎች መሬታቸዉን በአግባቡ እንዲከባከቡ፣ እንዲያለሙ፣ እና ምርትና ምርታማነትን
ለመጨመር አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡
በንብረት ጽንሰ ሀሳብ ዙሪያ ሰፊ እና ዝርዝር ምርምር ያደረገዉ ጸሀፊ ጆን ሎክ ስለ ንብረት
መብት እና ስለሚኖሩት ገደቦች ሲያስቀምጥ ንብረትን ጥቅም ላይ ማዋል የሚቻለዉ ንብረቱን
በአግባቡ እና ከብክነት በጸዳ መልኩ የተጠቀምንበት እንደሆነ ነዉ፡፡14ጆን ስቱዋርት ሚል
በበኩሉ በመሬት ላይ ብቸኛ ባለመብት ለመሆን መሬቱን በተግባር መጠቀምና በመሬቱ ላይ
ምርት ማምረት ይጠበቅበታል፡፡15እነዚህ የሞራል ፈላስፋዎች ስለ ባለእጅ የማድረግ አሰራር
(adverse possession) በሚገባ እንዳስቀመጡት የመሬት ባለመብት መሬቱን በአግባቡ
ሳይጠቀሙበት ከቀረ ይዞታዉን ሊያጣ እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡
3. ከይርጋ ህግ ጋር ያለዉ ግንኙነት
የባለእጅ (ይዞታ) የማድረግ አሰራር አንደኛዉ ገጽታ ይርጋ ነዉ፡፡ የባለእጅ ማድረግ አሰራር
ከቅድመ ሁኔታዎች ዉስጥ በህግ የተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ መሟላት አለበት የሚለዉ ነዉ ፡፡

12
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 11
13
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 11
14
John Lock, The Second Treatise of Government (2002) በ Tzachi Raz በግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 11
ላይ እንደተጠቀሰዉ፡፡
15
John Stuart Mil, Principles of Political Economy (1848), በ Tzachi Raz በግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 11
ላይ እንደተጠቀሰዉ፡፡
ይህ ደግሞ ቀጥተኛ የይርጋ ጽንሰ ሀሳብ የሚያመለክት ነው፡፡16 የይርጋ ዓላማ ሰዎችን ለረጅም
ጊዜ ከቆዩ ክሶች ለመከላከል ነዉ፡፡ የአማረኛ መዝገበ ቃላት ላይ ስለ ይርጋ የተቀመጠዉ ቃላት
‹ረጋ› ሲሆን ‹የሰዉ ሀሳቡ ከመዉጣቱ ከመዉረድ በሀሳብ ከመዞር ከመባከን ከመናወጥ ጸጥ›
አለ በሚል ይገለጻል ፡፡17 ከሳሽ ለረጅም ጊዜ ክሰ ባለማቅረቡ ምክንያት ማስረጃዎች ሊጠፉ
ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ተከሳሽን ለረጅም ጊዜ ከቆየ ክስ ለመከላከል ዓላማ አለዉ፡፡ በንብረት ህግ
ጽንሰ ሀሳብ የንብረትን የባለቤትነት መብት የሚያረጋግጡ ሰነዶችን በጊዜ ገደብ ቀሪ የሚሆኑ
ከሆነ ይህንን መብት መጠየቅ አይቻልም፡፡ይህም የተረጋጋ መብት እንዲኖረን፣በህግ የበላይነት
ላይ እምነት እንዲኖር እና ክርክሮች መቋጫ እንዲኖራቸዉ ለማድረግ ነዉ፡፡18
ይርጋ ክስ እንዳይቀርብ ወይም ይዞታን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስን የሚከለክል ነዉ፡፡ በመብቱ
ላይ የሚተኛ ከሳሽ መብቱ በጊዜ ገደብ መታገድ ይገባዋል በሚል አመክኒኦ ይህ ህግ በሁሉም
የህግ ስርዓት ተቀባይነት አለዉ፡፡19 በህግ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ክስን አለማቅረብ መብት
የመሬት ባለቤትነትን ሊያሳጣ ይችላል፡፡ ስለሆነም የመሬት ይዞታን ባለእጅ ያደረገ ሰዉ እና
በቀድሞ የመሬት ባለቤት መካከል በህግ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ላይ ክርክር በማድረግ ዉሳኔ
መሰጠት አለበት፡፡ በህግ የተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ካለፈ መሬቱን ባለእጅ ያደረገዉ ሰዉ የመሬቱ
ባለመብት ሲያደርግ በሌላ በኩል ደግሞ ባለመሬት መሬቱን የሚያጣበት አሰራር ነዉ፡፡ ይርጋ
የቀድሞ ባለመሬት መብት እንዲቋረጥ ያደርጋል፡፡ መሬቱን ባለእጅ ያደረገ ሰዉ ደግሞ መብት
ያጎናጽፋል፡፡ ነገር ግን የቀድሞ ባለመሬት መብቱ የተቋረጠዉ ባለእጅ ካደረገዉ ሰዉ አንጻር ብቻ
እንጅ በአንጻራዊነት ከሌሎች ሰዎች የተሻለ መብት ሊኖረዉ ይችላል፡፡ ይህ ማለት በአጋጣሚ
ይህ የመሬት ይዞታ አሁን ባለእጅ ካደረገዉ ሰዉ ቁጥጥር ዉጭ ቢወጣ እና በሌላ ሰዉ እጅ
ቢገባ የቀድሞ ባለመሬት መብቱን የሚጠይቅበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል፡፡ መብቱ የተቋረጠዉ

16
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 10ን ይመልከቱ
17
ተሰማ ሀብተ ሚካኤል ከሰቴ ብርሀን ተሰማ የአማረኛ መዝገበ ቃላት ኩራዝ አሳታሚ ፣ 1972 ዓ.ም ገጽ 280
18
The aim of the period of limitation is to prevent citizens from being oppressed by stale claims,
to protect settled interests from being disturbed, to bring certainty and finality to disputes and so
on. ይህ ዓላማ በሁሉም የይርጋ ህግ የሚደነግግ አዋጅ ዉስጥ ተካቶ ይገኛል፡፡በአብዛኛዉ ሀገራት የይርጋን
ሥርዓት የሚደነግግ እራሱን የቻለ አዋጅ አላቸዉ፡፡በዚህም ስለይርጋ ዓላማ ከላይ በተቀመጠዉ አግባብ
ያስቀምጣሉ፡፡ Limitation Act 1980 (UK) c 58, s 15. በተመሳሳይ ስለ ባለእጅ (ይዞታ እና ስለ ይርጋ
የተቀመጠዉ ግንኙነት ምን ይዘት እንዳለዉ ያሳያል፡፡
19
ለምሳሌ፡- የእንግሊዝ የይርጋ ህግ (sections 3) ፣ የደች ህግ ፣ የፈረንሳይ፣የስፔን፣ ወዘተ የመሳሰሉትን
ይመልከቱ፡፡
ፍጹማዊ በሆነ መልኩ ሳይሆን መሬቱን ባለእጅ ካደረገዉ ሰው አንጻር ብቻ ነዉ፡፡ይህም
ባለእጅና የይርጋ ጊዜ ገደብ የሚመሳሰሉበት ነጥብ ነዉ፡፡ ስለሆነም ባለእጅ አሰራርን በተግባር
ለማዋል የይርጋን ክርክር ማለፍ ይጠይቃል፡፡
ባለ እጅ (ይዞታ) የማይንቀሳቀስ ንብረት ለረጅም ጊዜ በመጠቀም የሚገኝ መብት ሲሆን ይህም
በንብረት ህግ ዉስጥ ንብረት ማግኛ አንደኛዉ መንገድ ነዉ፡፡ በሌሎች ሀገራት ባለ እጅ ማደረግ
(adverse possession) አሰራር መሬት የማግኛ መንገድ ጭምር ነዉ፡፡20 የሚከተለዉን
ዓረፍተ ነገር በዉል ይህን ያሳያል፡፡
<The Usucapioof Roman law, as adopted in civil law systems, represents what is often
called acquisitive prescription in the sense that adverse possession conferred a positive
title to land>21
በኢትዮጵያ የህግ ማዕቀፍ ዉስጥ በባለእጅ (ባለይዞታ) መሆንን የተመከተዉ የፍታብሔር ህግ
ቁጥር 1168-69 ያሉት ድንጋጌዎችን ስንመለከት የባለእጅ (ባለይዞታ) አሰራር እና የይርጋ ህግ
ትስስር እንዳላቸዉ በግልጽ ተመላክቷል፡፡ በፍታብሄር ህግ ቁጥር 1169 ላይ የባለእጅ (ይዞታ)
መካከል ያለዉን ቀጥተኛ ትስስር እንደሚከተለዉ ተደንግጓል፡፡
…ስለ ይርጋ መቋረጥ የተነሩት፣ዉሳኔዎች፡ ስለ ይዞታም ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡ እንዲሁም
በይርጋ ህግ ስለ መከራከርና በስራ ላይ ስለ ማዋል፣ በይርጋ መከራከር ስለመተዉ የተነገሩት
የዚሁ አንቀጽ ዉሳኔዎች የተጠበቁ ናቸዉ፡፡
ይህ የህግ ክፍል በሌሎች ሀገራት የባለእጅ (ይዞታ) እና የይርጋ ህግ በአንድ አዋጅ
የሚደነገገዉን ዓይነት በዚህ የፍታብሄር ቁጥር ላይ ተመልክቷል፡፡ ስለሆነም ከመሬት ይዞታ
ጋር የሚነሳ ክርክር በይርጋ ጽንሰ ሀሳብ የሚያልፍ መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡ በኢትዮጵያ
የፍታብሄር ህግ መሰረት አንድ ልዩ ሁኔታ አለ፡፡ ይህዉም የመሬቱ አመጣጥ ከዘርና ርዕስት
የወረደ ከነበረ ይህ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡ ይሁን እንጅ ርዕስት የሚለዉ አሰራር በአዋጅ ቀሪ
ስለሆነ ይህ ልዩ ሁኔታ ተግባራዊ አይሆንም፡፡ በተጨማሪም ይህ አሰራር አሁን በስራ ላይ
ካለዉ የመሬት ስሪት አንጻር መታየትና መፈተሽ ይገባል፡፡ በኢትዮጵያ የፍታብሄር ቁጥር 1168
መሰረት ባለእጅ (ይዞታ) አሰራር የንብረት ባለቤትነት ጨምሮ የሚገኝበትና የሚተላለፍበት

20
Kaser M Roman Private Law (trans by Dannenbring R, 3rd ed 1980) 130; Krause LE “The
History and Nature of Acquisitive Prescription and of Limitation of Actions in Roman-Dutch Law”
(1923) 40 South African Law Journal 26-41 3
21
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 6 ላይ ይመለከቱ፡፡ ሰረዝ ለትኩረት የተጨመረ፡፡
መንገድ ነዉ፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለዉ የመሬት ስሪት ደግሞ የመሬት ባሌቤትነት የመንግስትና
የህዝብ22 በመሆኑ በፍታብሄር ህግ በተቀመጠዉ ስርዓት መሰረት የመሬት ባሌቤትነት ወደ
ግለሰብ ሊተላለፍ አይችልም፡፡ ይልቁንም በአሁኑ ሰዓት ግለሰቦች በመሬት ላይ ያላቸዉ መብት
የይዞታና የመጠቀም መብት ብቻ ነዉ፡፡ ስለሆነም የፍታብሄር ህግ ቁጥር 1168-69 ስር
የተመለከተዉ ይዞታ የሚተላለፈዉ ከላይ የተመላከተዉ ግለሰቦች ያላቸዉ መብት ብቻ ነዉ፡፡
ስለዚህ የሚተላለፈዉ የይዞታና የመጠቀም መብት ብቻ ነዉ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የፌደራል
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከመሬት ይዞታ በተያያዘ በመዝገብ ቁጥር ላይ የመሬት
ይዞታ ክርክር በ10 ዓመት ሊታገድ ይገባል የሚል ዉሳኔ አስተላልፏል፡፡23ይህ ዉሳኔ ከተነሳዉ
ክርክርና ጭብጥ አንጻር ትክክል ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን በዉሳኔዉ ሀተታ ላይ የተመላከተዉ
ምክንያት ግለጽነት የጎደለዉ ይመስላል፡፡ ሁሉንም የመሬት ይርጋ ክርክር በፍታብሄር ህግ
ቁጥር 1845 ላይ የተመለከተዉ ይሆናል የሚል ድምዳሜ በዚህ ጽሁፍ ጸሀፊ እምነት ትክክል
አይደለም፡፡ የዚህ ጽሁፍ አላማ ይህን ዉሳኔ ለመተቸት ስላልሆነ ከዚህ በላይ በዝርዝር
አልሄድበትም፡፡ ይሁንና በዚህ ዉሳኔ መሰረት ባለእጅ (ይዞታ) ክርክርን በ10 ዓመት ይታገዳል
ይላል፡፡
ባለእጅ (adverse possession) ለመሆን መሟላት የሚገባቸዉ ቅድ መሁኔታዎች የሚከተሉት
ናቸዉ፡፡
3.1 አዉነተኛ ይዞታ፡ ንብረቱ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሲሆን የመሬት ይዞታ መሆን መቻል
አለበት፡፡ ባለ እጅ (adverse possession) ያደረገዉ ሰዉ ይዞታዉን በእርግጥም
በእርሱ ቁጥጥር ስር በማድረግ የሚጠቀምበት መሆኑን ማሳየት ይኖርበታል፡፡

22
የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት፣ አዋጅ ቁጥር 1/1987፣ አንቀጽ 40(3) የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት ባለቤትነት
መብት የመንግስትና የሕዝብ ብቻ መሆኑን ደንግጓል፡፡
23
ብዙ ጊዜ ከመሬት ጋር በተያያዘ የይርጋ ክርክርን ለማንሳት ያለዉ ችግር በባለሙያዎች ዘንድ የሚነሳዉ ብዥታ
<መሬት ይርጋ> የለዉም የሚል ጠቅላላ አገላለጽ ነዉ፡፡ ይህ ብዥታ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ዉሳኔም
ጭምር የተንጸባረቀ ይመስላል፡፡ይህም የመሬት ይዞታ ክርክር በመሬት ህጎች ስላልተቀመጠ በጠቅላላ የዉል ህግ
1845 ላይ የተመለከተዉ ይርጋ ሊሆን ይገባል በማለት ሀተታዉን አስቀምጧል፡፡ ይህን አገላለጽ በዉል
ከተመረመረ አጠቃላይ ከመሬት ጋር የሚነሳ የይርጋ ክርክር በ10 ዓመት የሚመለስ ነዉ የሚመስለዉ፡፡ ነገር ግን
ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚነሱ የክርክር ዘዉጎች የተለያ ናቸዉ፡፡ ከመሬት ጋር በተያያ የዉርስ፣የሰብል ይገባኛል፣
የካሳ ጥያቄ፣ እና ሁከት ይወገድልኝ፣ ይዞታ ይመለስልኝ …ወዘተ. የመሳሰሉት የዳኝነት ጥያቄዎች የይርጋ ክርክር
ለማንሳት በጥያቄዎች አግባብ የተለዩ የይርጋ ገደቦችና ስላለ በዚህ አግባብ ጥያቄዉን በዉል በመረዳትና የይርጋ
ጊዜዉን መለየት የስፈልጋል፡፡
ለሶስተኛ ወገን ግልጽ በሆነ መልኩ የሚጠቀምበትና ከእዚህ ቀደም የዚህ መሬት
ባለይዞታ የነበዉን ሰዉ መብት በሚጋፋና በሚቃረን ሁኔታ ለተከታታይ ጊዜ መጠቀም
መቻል አለበት፡፡ ህጉ በሚያስቀምጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ባለማቋረጥ የተጠቀመበትና
እዉነተኛ ባለይዞታ የነበረዉን ሰዉ መብት በግልጽ የሚቃረን ድርጊት መፈጸም
አለበት፡፡ እዚህ ላይ የቀድሞ ባለይዞታ የነበረ ሰዉ ይዞታዉን በፍጹም ማጣት
ይኖርበታል፡፡ የቀድሞ ባለይዞታ በፈቃዱ ይዞታዉን ቢያስተላልፍ ይህ ድርጊት ይዞታን
አያሳጣዉም ፡፡ ነገር ግን ይህ በፍቃድ ይዞታ ያገኘ ሰዉ በሌላ ጊዜ ሀሳቡን በመቀየር
እናም እዉነተኛ ባለይዞታ የነበረዉን ሰዉ መብት በሚጋፋ መልኩ ይዞታዉን
የሚጠቀምበት፣ በግልጽ ለሶስተኛ ወገንም በሚታይና በሚታወቅ መልኩ ባለይዞታ
መሆኑን ከገለጸ እናም በህጉ የተቀመጠዉ ጊዜ ካለፈ ይህ ሰዉ ባእጅ ወይም ባለይዞታ
የመሆን ጥያቄ ወይም መብት ሊኖረዉ ይችላል፡፡
3.2 ግልጽ እና ተከታታይ የሆነ ይዞታ፡ይህ ቅድመ ሁኔታ ባለእጅ አድራጊ ሰዉ መሬቱን
በምን ሁኔታ ሲጠቀምበት እንደቆየ የሚያጠይቅ ነዉ፡፡ ይህም ባለእጅ አድራጊዉ
መሬቱን የቀድሞ ባለቤትን በሚቃረንና ግልጽ በሆነ መልኩ ለተከታታ ጊዜ መጠቀምን
ያመለክታል፡፡በተለይም ከዚህ በላይ እነድተመለከተዉ ይህ ባለእጅ የማድረግ አሰራር
ከይርጋ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ተከታታይነት የሚታየዉ በይርጋ ህግ ዉስጥ የይርጋ
ማቋረጫ ምክንያችን የሚመለከት ነዉ፡፡
3.3 የባለቤትነት ስሜት ፡ ይህም ባለእጅ መብት ጠያቂዉ መሬቱን ሲይዝ የሀሳብ
ሁኔታዉ ምን መሆን እንደአለበት ያሳያል፡፡ ስለሆነም የባለእጅ መብት ጠያቂዉ የሀሳብ
ክፍል መሬቱን በባለቤትነት (animus possidendi) የሀሳብ ሁኔታ መሆን አለበት
የሚለዉን ያሳያል ፡፡24 የቀድሞ ባለቤትን የሚቃረን፡ ከላይ እንደተገለጸዉ ባለእጅ
አድራጊዉየ ቀድሞ ባለቤትን የሚቃረን ተግባር መፈጸምን የሚመለከት ነዉ፡፡ እነዚህ
ከዚህ በላይ የተመላከቱት ቅድመ ሁኔታዎችን በአጠቃላይ በአንድ ላይ ተሟልተዉ
መገኘት ይገባቸዋል፡፡ ስለሆነም ቅድመ ሁኔታዎችን ስመረምር ሁሉንም በአጠቃላይ
(Cumulatively) እንጅ በተናጠል አይደለም፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱን ቅድመ ሁኔታ እርስ
በዕርስ የተያያዙ ስለሆኑ በአጠቃላይ መመርመር አለበቻዉ፡፡
3.4 ባለእጅ የማድረግ አሰራር የማይሰራባቸዉ ሁኔታዎች

24
Jourdan S Adverse Possession (2003) ከዓረፍተ ነገር 8-01–8-25 ጀምሮ ያለዉን ይመልከቱ ፡፡
መሬቱ የመንግስት ከሆነ ብዙ ጊዜ ሀገራት የመንግስት የመሬት ይዞታ በተመለከተ በጊዜ ገደብ
የማይቋረጥ ነዉ በማለት ይበይናሉ፡፡ ለዚህ ብይን መነሻ በመሆን የሚጠቀሱ ሁለት ምክንያቶች
አሉ፡፡ እነዚህም 1/ በመንግስት ይዞታ ስር ያለ መሬት መንግስ ህብረተሰቡን በመወከል የያዘዉ
እና የቀጣዩ ትዉልድ ሀብት በመሆኑ በይርጋ ህግ ይህ ይዞታ በመቋረጥ ወደ ግለሰቦች
ሊተላለፍ አይገባም የሚል ነዉ፡፡2/ በመንግስት ይዞታ የሚያዙ መሬቶች ሰፋፊና ለቀጥጥር
የማይመች እና አሰተዳደራዊ ወጭ ከፍተኛ በመሆኑ የመንግስት ይዞታዎችን ላይ የይርጋ ህግ
ወይም ባለ እጅ የማድረግ አሰራር ተግባራዊ አይደረግም፡፡25
3.5 የዉል ግንኙነት ካለ
ባለእጅ የማድረግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ መሟላት ካለባቸዉ ቅድመ ሁኔታዎች ዉስጥ
አንዱ መሬቱን በቁጥጥትር ስር በማድረግ እየተጠቀመበት የሚገኘዉ ሰዉ በባለቤትነት ሀሳብ
መያዝ አለበት የሚለዉ ነዉ፡፡ ይህ ማለት የሌላ ሰዉ መሬትን በዉል ወይም በኪራ በመያዝና
በህግ የተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ በማለፉ ብቻ የባለእጅ መብት ማቅረብ እንደማይችል
ያስገነዝባል፡፡ ይህም ባለእጅ መብት ጠያቂዉ መሬቱን ሲይዝ የሀሳብ ሁኔታዉ ምን መሆን
እንደአለበት ያሳያል፡፡ ስለሆነም የባለእጅ መብት ጠያቂዉ የሀሳብ ክፍል መሬቱን በባለቤትነት
(animus possidendi) የሀሳብ ሁኔታ መሆን አለበት፡፡26 ከዚህ ዉጭ በኪራይ ወይም በሌላ
አግባብ የሌላ ሰዉ መሬት በመያዝ ለረጅም ጊዜ በመቆየት ብቻ የባለእጅ መብት የመጠየቅ
መብትን አያጎናጽም፡፡
የብዙ ሀገር የይርጋ ህግ ሲዳሰስ ባለእጅ መብት የማይጠየቅባቸዉ ልዩ ሁኔታዎች (execptions
ተዘርዝረዋል፡፡ ለምሳሌ፤ ባለመሬቱ በሀገር መከላከያ ጥሪ በተሰማራ ወቅት ከሆነ፣ከዕድሜ ልክ
በታች በመታሰር በማረሚያ ቤት ከሆነ፣ በፍርድ በዕድሜ ከ18 ዓመት በታች ከሆነ የሚሉትን
ልዩ ሁኔታዎች በባለእጅ መብት የማይጠየቅባቸዉ ወይም የይርጋ ህግ የማይሰራባቸዉ ናቸዉ፡፡
እነዚህ ሁኔታዎች የመሬት ባለመብት ያላቸዉን የጥበቃ መጠን የሚያሳዩ ሲሆን በሌላ በኩል
ደግሞ ባለእጅ አሰራር ተግባራዊ የሚሆንባቸዉ ሰዎች በህግ የተሠጣቸዉን መብት መጠቀም
እየቻሉ ነገር ግን ሳይጠቀሙ በቀሩት ላይ እነደሆነ ልብ ይሏል፡፡
4. ህገ- ወጥ የመሬት ወረራ (squatter) እና ባለእጅ (ይዞታ) የማድረግ አሰራር (adverse
possession) ያለቸዉ ግንኙነት

25
Krause LE “The History and Nature of Acquisitive Prescription and of Limitation of Actions in
Roman-Dutch Law” (1923) 40 South African Law Journal 26-41 31
26
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 24 ላይ ይመልከቱ ፡፡
መሬት ወረራ ማለት ሳይፈቀድለት የሌላ ግለሰብ መሬት መያዝ ነዉ፡፡ መብት ሳይኖርህ በሌላ
ሰዉ መሬት ላይ ህግ ከሚፈቅድልህ ዉጭ በመያዝ ለመጠቀም መሞከርን ይመለከታል
፡፡ይህምበብዙ ሰዎች ዘንድ ትልቅ ማህበራዊ ችግር ሲሆን የመሬት ዝርፊያ በማለት
ይገልጹታል፡፡ ብላክስ ሎዉ ስለመሬት ህገ ወጥ ወራራ (squatter) ትርጉም ሲያስቀምጥ
እንደሚከተለዉ ነዉ፡፡
‹[o]ne who settles on another's land, without legal title or authority. A person
entering upon lands, not claiming in good faith the right to do so by virtue of
any title of his own or by virtue of some agreement with another whom he
believes to hold the title. Under former laws, one who settled on public land in
order to acquire title to the land በተመሳሳይ አንድ ዳኛ ስለመሬት ወረራ እንዲህ ሲል
አስቀምጧል፡፡„…a squatter…is one who, without colour of right, enters on an
unoccupied house or land, intending to stay there as long as he can>
ስለሆነም ህጋዊ ህገወጥ የመሬት ወረራ ትርጉም ሳይፈቀድለት ወይም ህጋዊ ምክንያት
ሳይኖረዉ የሌላ ሰዉ መሬት በመያዝ መጠቀምን ይመለከታል፡፡ ይህ ትርጉም የመንግስት
መሬትም ይሁን የግለሰብ ይዞታን ሳይፈቀድለት መጠቀምን ይመለከታል፡፡ ይህን ድርጊት
ሀገራት በወንጀል ህግም ይሁን በፍታብሄር ህግ ጥበቃ ያደርጋሉ፡፡ ስለሆነም የዜጎች የይዞታም
ይሁንን የባለቤትነት መብት ከፍተኛ ጥበቃ ስለሚያስፈልግ በተሟላ መልኩ አስፈላጊዉን ሁሉ
ማድረግ መሰረታዊ የሰባዊ መብት ተገርጎ ይወሰዳል፡፡ ለምሳሌ፡ የአዉሮፓ ህብረት
የሚከተለዉን ደንግጎ ይገኛል፡፡
‹Protocol 1 Art.1 of the European Convention on Human Rights provides (1)
every natural or legal person is entitled to the peaceful enjoyment of his
possessions. No one shall be deprived of his possessions except in the public
interest and subject to the conditions provided for by law and by the general
principles of international law›
ይህ ድንጋጌ እንዳስቀመጠዉ የሰዎች በንብረት ላይ ያላቸዉ ይዞታ በሰባዊ መብት ደረጃ
በመፈረጅ ጥበቃ ያደረግለታል፡፡ የዚህ ስምምነት ፈራሚ ሀገራት ደግሞ ይህን የማክበር ግዴታ
አለበቸዉ፡፡27 ስለሆነም ሀገራት በህጎቻቸዉ ለይዞታ ጥበቃ ለማድረግ በወንጀልና በፍታብሄር
ህግ ጥበቃያ ደርጋሉ፡፡28

27
European Convention for the Protection of Human Rights and Fundamental Freedoms 1950
28
ለምሳሌ፣Criminal Law Act 197 of England and walse ::
በዚህ ረገድ የኢትዮጵያን የህግ ማዕቀፍ ስንመለከት የኢፊድሪ የወንጀል የወንጀል ህግ አንቀጽ
685-88 ላይ እንደተመለከተዉ የወንጀል ህግ የሰዎችን ይዞታ ሁከት እንዳይፈጠርባቸዉ ጥበቃ
የሚያደርግ ነዉ፡፡ ስለሆነም የሰዎችን የመሬት ይዞታ በህገ ወጥ መንገድ በመያዝም ይሁን
በሌላ በማናቸዉም መንገድ ሁከት የተፈጠረበት ከሆነ ይህ የወንጀል ህግ አጥፊዎች ላይ ቅጣት
እንዲተላለፍ በማድረግ ጥበቃ ያደርጋል፡፡ በተመሳሳይ በ1952 የወጣዉ የፍታብሄር ህግ ከቁጥር
1146-48 ላይ እንደተመለከተዉ ይዞታ ላይ ስለሚፈጠር ሁከት መፍትሄ አስቀምጧል፡፡29
ስለዚህ የግለሰቦች ይዞታ በህገ ወጥ መልኩ እንዳይያዝ የተሟላ ጥበቃ የሚያደርግ የህግ
ማዕቀፍ አለ ማለት ይቻላል፡፡ በህገ ወጥ መልኩ የግለሰቦች ይዞታ እንዳይያዝ ጥበቃ
የሚደረግለት ከሆነ በተግባር የሚታየዉን ለማንሳት ያህል ብዙ ጊዜ የፍታብሄራዊ ክርክሮች
በተለይም ሁከት ይወገድልኝ የሚል ክርክር የተለመደ ሲሆን በወንጀል ህግ ግን ጥበቃዉ
በተግባር እየተሰራበት አይደለም፡፡30
የንብረት መብት እዉቅና ከተሰጠዉ ጀምሮ ይህ መብት ከሰባዊ መብት ጋር አበሮ መታየት
አለበት ወይስ የለበትም የሚለዉ ሀሳብ አከራካሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ለዚህ በምክንያትነት
የሚጠቀሰዉ ንብረት የጥቂት ባለጸጎች ነዉ ስለሆነም አብዛኛዉን ድሀ ማህበረሰብ ለማግለል
የሚያገለግል መሳሪያ ነዉ በሚል ነዉ፡፡31 ሁሉን ዓቀፍ ዓለም አቀፍ የሰባዊ መብት ብያኔ
በ1948 ሲታወጅ የንብረት መብትን ልክ እንደ አንድ የሰባዊ መብት በማካተት ነበር ፡፡32በዚህ
መሰረትም ማንኛዉም ሰዉ ከህግ ዉጭ በሆነ አሰራር ወይም በዘፈቀደ የንብረት መብቱን
አያጣም በሚል ያስቀምጣል፡፡ ነገር ግን የሰባዊ መብትን በአስገዳጅ ሁኔታ የደነገገዉ የሲቭልና
የታለቲካ መብቶች እና የኢኮኖሚ፣ማህበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ሰነድ ስለንብረት መብት
ምንም ያስቀመጠዉ ነገር የለም፡፡33

29
የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የፍትሐ ብሔር ሕግ፣ 1952 ከቁጥር 1168-69 ላይ ይመልቱ፡፡
30
ይሁን እንጂ በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 685-88 ላይ በተግባር እየተሰራበት አይደለም፡፡
31
Cheneval, “Property Rights as Human Rights”, in H. de Soto and F. Cheneval, Realizing
Property Rights, Rueffer & Rub, Swiss Human Rights Book, Vol. I, 2006, at 11
32
Universal Declaration of Human Rights (UDHR), which in 1948 proclaimed in its Article 17 that
“[e]veryone has the right to own property alone as well as in association with others” and that
“*no one shall be arbitrarily deprived of his property.”
33
International Covenant on Civil and Political Rights, International Covenant on Economic, Social
and Cultural Right በዚህ የሰባዊ መብት ሰነድ ላይ የንብረት መብት በተለየ ሁኔታ ግልጽ የሆነ ድንጋጌ
አልተሠጠዉም፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ ህገ መንግስት አንቀጽ -40 (4) ስለንብረት መብት
የሚከተለዉን ያስቀምጣል፡፡ የኢትዮጵያ አርሶአደሮች መሬት በነጻ የማግኘትና ከመሬታቸዉ
ያለመነቀል መብታቸዉ የተከበረ ነዉ፡፡ አፈጻጸሙን በተመለከተ ዝርዝሩ በህግ ይወጣል፡፡
ስለሆነም ከህገ መንንግስቱ ጀምሮ ትልቅ ትኩረት የተሰጠዉ ከመሆኑ ባሻገር ይህ ክፍል የሰባዊ
መብት ተደርጎ የተቀመጠ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ፡፡ ይህም የመሬት የይዞታ መብት
ከሰባዊ መብት ጋር የተመደበና ትኩረት የተሰጠዉ መሆኑን ያስረዳናል፡፡
ከዚህ በላይ የተመለከቱት የህግ ማዕቀፎች የግለሰቦችን የይዞታ መብት ከህገ ወጥ ይዞታ
የሚከላከሉ ከሆነ ባለእጅ (ይዞታ) የማድረግ አሰራር እንዴት ተግባራዊ ሊሆን ይችላል? የሚል
ጥያቄ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል፡፡ በህግ ወጥ መልኩ የሰዎች ይዞታ የተያዘ እንደሆነ ጥበቃ
የሚያድርግ ሲሆን ወደ ባለእጅ (ይዞታ) የሚሸጋገረዉ በህግ የተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያለፈ
ከሆነ ብቻ ነዉ፡፡ ስለዚህ ግለሰቦች ይዞታቸዉን ከህገ ወጥ ይዞታ የማይከላከሉ እና መብታቸዉን
በአግባቡ ሳይጠቀሙ የቀሩ እንደሆነ ባለእጅ (ይዞታ) የሚለዉ አሰራር የተግባራዊ ይደረጋል፡፡
ይህም የሚያሳየን በመርህ ደረጃ የሰዎች የይዞታ መብት ጥበቃ የሚደረግለትና ግለሰቦችም
በይዞታቸዉ ሰላማዊ በሆነ መልኩ የመጠቀም እንደ አንድ የሰባዊ መብት ተደረጎ ይወሰዳል፡፡34
ነገር ግን ይህ መብት ፍጹማዊ (absolute) ነዉ ወይ? የዚህ ጥያቄ መልስ በአሉታዊ መልኩ
የሚታይ መሆኑን የሚያሳዩ የተለያዩ ሁኔታዎችን ወስደን ልንመለከት እንችላለን፡፡
የመጀመሪያዉ ለህዝብ ጥቅም ሲባል ግለሰቦች በመሬትም ይሁን ሌላ ንብረት ላይ ያላቸዉን
የይዞታ መብት የሚያጡበት ስርዓት አለ፡፡ በዚህም መንግስት ካሳ በመክፈል የግለሰቦችን ይዞታ
የሚወስድበት ስርዓት ነዉ፡፡ ይህ የሚያሳየን የግለሰቦች ይዞታ በልዩ ሁኔታ ሊታጣ
የሚችልበትን ነዉ ፡፡ በተመሳሳይ የባለእጅ (ይዞታ) አሰራር የተዘረጋ ከሆነ በአንድ በኩል
አንደኛዉ ይዞታ የሚገኝበት መንገድ ነዉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የግለሰቦችን የይዞታ መብት
የሚያሳጣ ነዉ፡፡ ስለሆነም የባለእጅ አሰራር የሚዘረጉ ሀገራት ይህንን ልክ እንደ ህዝብ ጥቅም
በመቁጠር ግለሰቦች በህግ ይዞታቸዉ ህገ ወጥ በሆነ አያያዝ እንዳይወሰድባቸዉ ካደረጉ በ|ላ
ይህን በመጠቀም መብታቸዉን ሳያስከብሩ ከቀሩና ጊዜ ያለፈባቸዉ ከሆነ ይዞታቸዉን ሊያጡ
ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የባለእጅ(ይዘታ) ማብራሪያ (Justification) በመዉሰድ ሰዎች በልዩ ሁኔታ

34
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 27 ላይ ይመልከቱ፡፡
ይዞታቸዉን የሚያጡበት ስርዓት ይዘረጋል፡፡ ይህ ስርዓት ለረጅም ጊዜ ተቀባይነት ያገኝ አሰራር
እና በሁሉም ሀገራት በሚባል ሁኔታ የሚሰራበት መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡35
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ አሰራር የዜጎችን የይዞታ መብት የሚጋፋ ነዉ በሚል ክርክር
ሲቀርብበት ይስተዋላል፡፡36 በተለይም ይህ አሰራር ህገ ወጥነትን የሚያበረታታ ነዉ ስለሆነም
ተቀባይነት ሊኖረዉ አይገባም የሚል ሰፊ ተቃራኒ ክርክር ሲቀርብበት ይስተዋል፡፡37 ከዚህ ጋር
በተያያዘ በኢትዮጵያ የፌደሬሽን ምክር ቤት በተወሰነ ደረጃ አከራካሪ ዉሳኔ ወስኗል፡፡38 ይህን
ዉሳኔ ተከትሎ የአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት የመሬት ይዞታን በተመለከተ በህገ ወጥ
መልኩ የተያዘ ይዞታ የይርጋ መከራከሪያን በማንሳት መከራከር አይቻልም የሚል በአዋጅ
ቀጥር 252/2010 ላይ አካትቶ ይገኛል፡፡39 ይህ ደግሞ ባለእጅ ማድረግ አሰራርን ሙሉ በሙሉ
የሚያስቀር ነዉ፡፡ የዚህ ጽሁፍ ዓላማም የዚህን አዋጅ ተገቢነት በምክንያት መገምገም ነዉ፡፡
ይህ አዋጅ ባለእጅ(ይዞታ)ን ለማስቀረት የደረሰበት ድምዳሜ ተገቢነት በዉል መመርመር እና
ከሌሎች ሀገራት ልምድ አንጻር መተቸት ነዉ፡፡ ለዚህ ንጽጽር የሚያግዘን የሚከተለዉን
የእንግሊዝ የፍርድ ቤት ጉዳይ ማየት እንሞክር፡፡ የኢትየጵያና የእንግሊዝ የመሬት ስሪት
አንጻር የተለየ መሆኑን ብገነዘብም ጉዳዩ ከይዞታ ጋር የተያያዘ ስለሆነ አንደምታዉ ተመሳሳይ
ነዉ፡፡
በእንግሊዝ ህግ ይህ አሰራር የመሬት ክርክሮችን በመፍታት ቁልፍ መርህ ሆኖ ቆይተል፡፡
ይሁን እንጂ ይህ አሰራር በእንግሊዝ ህዝብ ዘንድ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የለዉም፡፡
40
በመሬት ወረራ ምክንያት ባለይዞታዎች ይነቀላሉ፣ የመንግስት ይዞታም ወደ ግለሰቦች
እንዲተላላፍ መንገድ የሚከፍት አሰራር ነዉ፡፡ በዚህ ምክንያትም ይህ አሰራር የመሬት ይዞታ

35
በሲቭል ሎዉ እና በኮመን ሎዉ ተከታ ሀገራት ተቀባይ ነት ያለዉ አሰራር መሆኑን ከግርጌ ማስታወሻ ቁጥር
6 ላይ ይመልከቱ፡፡በተጨማሪም Dixon MJ “Adverse Possession in Three Jurisdictions” 2006
Conveyancer 179-187
36
JA Pye (Oxford) Ltd and Another v Graham and Another [2000] Ch 676 ፣ JA Pye (Oxford)
Ltd v Graham [2001] Ch 804 ፣ JA Pye (Oxford) Ltd v Graham [2003] 1 AC 419 እነዚህን
የእንግሊዝ የፍርድ ቤት ጉዳይ ይመልከቱ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ክርክር የተደረበት ሁኔታ ያሳያሉ፡፡
37
Stake JE “The Uneasy Case for Adverse Possession” (2001) 89 Georgetown Law Journal
2419-2474
38
የኢፌዴሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት 4ኛ የፓርላማ ዘመን ፣5ኛ ዓመት፣ 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ሰኔ 18 ቀን 2007
ዓ.ም፡፡
39
የተሻሻለው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መወሰኛ አዋጅ ቁጥር
252 /2009 ዓ.ም
40
Dixon M “Adverse Possession and Human Rights” 2005 Conveyancer 345-351
ስርቆትን የሚፈቅድ ነዉ በሚል ይተቻል፡፡ ይህ መሰረታዊ ክርክር በመስተዋሉ ምክንያት
የሰዎችን ሰባዊ መብት የሚጥስ ስለሆነ የመሬት ምዝገባ ሥርዓት ባለበት ሁኔታ ጠቀሜታዉ
እየቀነሰ መጥቷል የሚሉ ትችቶች አሉበት፡፡ በሌላ በኩል ትችቶች ይኑሩ እንጅ ህጋዊ እዉቅና
ተሰጥቶት እየተሰራበት ይገኛል፡፡ የአሰራሩ መነሻ አንድ ይዞታ በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ በሆኑ
ባለይዞታዎች ቁጥጥር ስር ሊሆን አይችልም የሚል ነዉ፡፡

ባለእጅ (ይዞታ) የሚጠይቅ ሰዉ በህግ ዕዉቅና የተሰጠዉ ሁከት ፈጣሪ ነዉ፡፡ ይህ ሰዉ


በይዞታዉ የመጠቀምና ሌሎችን የመከልከል (እዉነተኛ) ባለይዞታዉን ጭምር መብት
ያጎናጽፈዋል፡፡ ስለዚህ በህግ እዉነተኛ ባለይዞታዎች መብት የሚያጡበት በአንጻሩ ደግሞ ሁከት
ፈጣሪዉ የይዞታ መብት የሚያገኝበት አሰራር ነዉ፡፡ ይህም ግለሰቦች በንብረት ላይ ያላቸዉን
የመብት አድማስ የሚያጠብ ነዉ፡፡በዚህ አሰራር ላይ ጠንከር ያለ ትችት የሚቀርብበት በተለይ
አጠቃላይ ከህግ ፍልስፍና አንጻር ሲታይ ነዉ፡፡ አንድ ጸሀፊ እንዳስቀመጠዉ ህግ የሚወጣዉ
ፍትህን ለማስተዳደር ነዉ ይላል፡፡ ስለሆነም ባለእጅ ( ይዞታ)ን አሰራር የሚፈቅድ ህግ ፍትህን
ከማስተዳደር አኳያ ሲታይ ፍታዊነቱ ጥያቄ ዉስጥ ይገባል ይላል ፡፡41 ይህም ህጉ ራሱ ሌቦችን
ጥበቃ በመስጠት ባለይዞታ የሚያደርግ አሰራር ነዉ፡፡ እዉነተኛ ባለይዞታዎች መብት
የሚቀጡበት በአንጻሩ ደግሞ የሰዉችን መሬት በወረራ የያዙ ሰዎች መብት የሚያገኙበት
አሰራር ፍታዊነቱን የሚቃወሙ ሰዎች አሉ፡፡42
የእንግሊዝ ፍርድ ቤት ዉሳኔ እና የአዉሮፓ የሰባዊ መብት ፍርድ ቤት እይታ
ሁለት የግል ኩባንያዎች ጀ.ኤ ፔይ(ኦክስፎርድ) ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ እና ጀ.ኤ
ፔይ (ኦክስፎርድ) መሬት ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ በስማቸዉ የተመዘገበ 23 ሔክታር
መሬት ባለቤት ነበሩ፡፡ በአዋሳኝም አቶ ግርሀም የተባለ ግለሰብ በግጦሽ ስምምነት
መሬቱን ይዞት ይቆያል፡፡ እንደ አዉሮፓዊያን አቆጣጠር ሕዳር 31ቀን 1983 የግጦሽ
ዉል ስምምነቱ የሚያበቃበት እና አቶ ግርሀምም መሬቱን የሚለቅበት ጊዜ ነበር፡፡
ይሁን እንጅ መሬቱ በአቶ ግርሀም እጅ ሆኖ ቀጠለ፡፡ ጥር 1984 እንደገና ዉል
ይታደስልኝ የሚል ጥያቄ ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ይሁንና አቶ ግርሀም
መሬቱን እንደያዘዉ እስከ 1999 ከባለቤቶች ፍቃድ ዉጭ በእርሻ ስራ ሲጠቀምበት ቆየ፡፡

41
Dockray M “Why do we Need Adverse Possession?” 1985 Conveyancer 272-284
42
Pascoe, Susan, 2011. Europe, human rights and land law in the 21st century: an English
example. Available from Middlesex University’s Research Repository
በ1997 አቶ ግርሀም ለመሬት ምዝገባ ባለስልጣን መሬቱ በስሙ እንዲመዘገብለት እና
መሬቱን ባለእጅ ያደረገዉ መሆኑን አመለከተ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የቀድሞ የመሬት
ባለቤቶች መሬቱን እንደሚያጡ አስታወቀ፡፡ይህን በመቃወም የመሬቱ ባለቤቶች የመሬት
ምዝገባዉ እንዲሰረዝላቸዉ አመለከቱ፡፡ አቶ ግርሀምም በይርጋ መቃወሚያነት በ1980
በተደነገገዉ የእንግሊዝ አዋጅ መሰረት ክርክር አቀረበ፡፡ ይህም አዋጅ አንድ ሰዉ
መሬቱን በ12 ዓመት ዉስጥ በእጁ ካላደረገ የይመለስልኝ ጥያቄ ማቅረብ አይችልም፡፡
የከፍተኛ ፍርድ ቤቱም በየካቲት 4/2000 በሰጠዉ ዉሳኔ አቶ ግርሀም መሬቱን
በይዞታዉ ስር በማድረግ ሲጠቀምበት በመቆየቱ ይህም በስሙ የማስመዝገብና ባለቤት
የመሆን መብት ስለሚያጎናጽፈዉ ጥያቄዉን ሳይቀበለዉ ቀረ፡፡ የኩባንያዉ ባለቤቶችም
ይግባኝ በመጠየቅ ይህን ዉሳኔ ማሻር ቻሉ፡፡ነገር ግን አቶ ግርሀም ይግባኝ ለ ሀዉስ ኦፍ
ሎርድስ በማቅረብ እንደገና የከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ዉሳኔ እንዲጸና ተደርጓል፡፡
ይህንን ዉሳኔ በመቃወም ለአዉሮፓ የሰባዊ መብት ፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ፡፡
የቅሬታዉ ምክንያትም የእንግሊዝ የባለእጅ (adverse possession) ህግ የአዉሮፓን
የሰባዊ መብት ኮንቬንሽን ፕሮቶኮል 1 አንቀጽ 1 የሚቃረን ነዉ በሚል ነዉ፡፡ ፍርድ
ቤቱም በእንግሊዝ ፍርድ ቤት በጊዜዉ ማቅረብ መብታቸዉን ባለመጠቀምና ለጠቅላላ
ህዝብ ጥቅም የተቀመጠዉን የይርጋ ህግ ከአዉሮፓ የሰባዊ መብት ኮንቬንሽ ፕሮቶኮል
1 አንቀጽ 1ላይ የተመለከተዉን በንብረት በሰላም የመጠቀም መብትን (Right to
peaceful enjoyment of property) ላይ የተለየ ተጽኖ የለዉም የሚል ዉሳኔ
አስተላልፋል፡፡ ፍርድ ቤቱ በአብላጫ ድምጽ በሰጠዉ ዉሳኔ ሀገራት ለጠቅላላዉ ለህዝብ
ጥቅም ሲባል የሚያወጡዋቸዉ ህጎች ንብረትን በሰላም የመጠቀም መብትን
የሚያጣብቡ ቢሆንም ሚዛን ዉስጥ ለማስገባትና ገደብ ለመጣል መብት አላቸዉ፡፡
ስለሆነም በእንግሊዝ የይርጋ ህግ 1908 ላይ የተቀመጠዉ ባለእጅ (adverse
possession) የአዉሮፓዊያን የሰባዊ መብት ኮንቬንሽ ፕሮቶኮል 1 አንቀጽ 1 ጋር
የሚጣረስ አይደለም በማለት ምክንያት አስቀምጧል፡፡
ከዚህ ዉሳኔ የምንገነዘበዉ ባለእጅ (ይዞታ) አሰራር በራሱ የሰዎችን የንብረት መብት የሚጋፋ
አይደለም የሚለዉን ድምዳሜ ነዉ፡፡ ምንም እንኳ ይህ ስርዓት መዘርጋቱ ጥያቄ የሚያነሱ
ሰዎች ቢኖሩም ሀገራት ከህዝብ ጥቅም አንጻር በመመዘን ይህን ስርዓት አስፈላጊነት ላይ ባለዉ
ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ43 ጠቀሜታዉ ቢተገብርት የሰዎችን መብት የሚጋፋ አይደለም፡፡
ይህ አሰራር በክርክር የተፈተሸ ስርዓት ካለዉ ጠቀሜታ አንጻር በልዩ ሁኔታ ተግባራዊ ሊሆን
የሚገባዉ ስርዓት ነዉ፡፡ በእንግሊ የመሬት ህግ እንደ አዉሮፓዊያን አቆጣጠር በ2002 ላይ
ሲሻሻል ስርዓቱን ያስቀጠለ ሲሆን አንድ ጥብቅ ማሻሻያ ግን ተጨምሮበታል፡፡ይህም ስነ-
ስርታዊ ሲሆን ባለእጅ (ይዞታ) ተጠቃሚዉ ሰዉ ይህ መብቱን ያገኘዉ በይዞታ ስረዓት መሆኑን
ለመሬት መዝጋቢ ባለስልጣን ማሳወቅ ይጠበቅበታል፡፡44
በአዲሱ ህግ (2002) መሰረትም አንድ ሰዉ ባለእጅ የማድረግን አሰራር በመጠቀም የመሬት
ባለቤት ለመሆን ስለመሬቱ የቀድሞ ባለቤት ማስታወቂያ መስጠት ይኖርበታል የሚል ግዴታ
ያስቀምጣል፡፡ ይህ ባለእጅ አድራጊ መሬቱን በስሙ ከማስመዝገቡ በፊት ለቀድሞ ባለቤት
ማስታወቂያ በመሬት መዝጋቢዉ ባለስልጣን በኩል ይነገረዋል፡፡ ማስታወቂያ ተነግሮት
የማይቃወም ከሆነ መሬቱን በፈቃዱ እንደለቀቀዉ ተቆጥሮ ለአዲሱ ባለመሬት ይመዘገብለታል፡፡
ይህ አሰራርም የሰዎችን መሰረታዊ መብት የሚጠብቅ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ መሰረታዊ
ዓላማዉም የመሬት ባቤቶችን በተለያየ ምክንያት ከእጃቸዉ የወጣዉን የመሬት መብት ጥበቃ
በማድረግ ነዉ፡፡
በኢትዮጵያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ህገ መንግስታዊ ዉሳኔ ባለእጅ (ይዞታ)ን አስመልክቶ
የኢፊድሪ ህገ መንገስት ህገ መንገስታዊ ትርጉም የሚያስፈልጋቸዉን ጉዳዮች በህገ-መንግስት
አጣሪ ጉባዔ ከተጣራና ህገ-መንግስታዊ ትርጉም የሚያስፈልገዉ ከሆነ የመጨረሻ ዉሳኔ
እንደሚሰጥ ያስቀምጣል፡፡ በዚህ መሰረት መጋበት 2 ቀን 2007 ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር 682/04
ላይ የህገ መንግስት አጣሪ ጉባዔ የህገ መንግስት ትርጉም የሚያስፈልገዉ መሆኑን ስለተረዳ
ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የዉሳኔ ሀሳብ በማቅረብ ልኮታል፡፡
የጉዳዩ አመጣጥ ስንመለከት በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግት ሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር
ዉስጥ ሙሌ ወረዳ ፍርድ ቤት የተጀመሬ የመሬት ይዞታ ይገባኛል ክርክር ነዉ፡፡ ክርክሩ
በወ/ሮ ማሚቱ ሰብለ እና ወ/ሮ ሙሉ ጉርሙ መካከል ሲሆን ወ/ሮ ማሚቱ ሰብለ በ1971 ዓ.ም

43
Land Registration for the Twenty-First Century: A Conveyancing Revolution – Number 271
(July 200) section 4.3.2 በዚህ የእንግሊዝ የመሬት ምዝገባ አዋጅ ላይ የባለእጅ (ይዞታ) አሰራር ዓላማ
ጠቀምጧል፡፡እነዚህም (adverse possession encourages owners not to sleep on their rights፣to
ensure that a possessor can feel confident that his right cannot be called into question after a
certain period of time has elapsed) የሚሉት ሲታዩ በአዲሲ የመሬት ምዝገባ አዋጅም ከቀድሞ አሰራር ጋር
ተመሳሳይ ዓላማ ይዞ የተቀረጸ ነዉ፡፡
44
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 42 ላይ ይመልከቱ፡፡
ከባለቤታቸዉ ጋር በጋራ የተመሩት የእርሻ መሬት እያረሰ ከሚሰጣቸዉ ልጃቸዉ በኪራይ
ሰጥተዉት ይኖሩ ነበር፡፡ ይሁን እጅ ይህ ግለሰብ በሞት ከተለየ በ|ላ የሟች ሚስት የአሁን
ተጠሪ ሰብሉን ስለከለከለችንና መሬተሁንም አለቅም በማለቷ ወደ ፍርድቤት ከርክር ይገባሉ፡፡
የሟች ሚስት ወ/ሮ ሙሉ ገርሙ በበኩላቸዉ መሬቱን በስማቸዉ የተመዘገበና ለ12 ዓመት
በስማቸዉ ተመዝግቡ ሲጠቀሙበት የቆዩ መሆኑን ከወረዳዉ የመሬት አስተዳደር ጭምር
ማስረጃ በማቅረብ ተከራክረዋል፡፡ በየደረጃዉ የሚገኙ የኦሮሚያ ፍርድ ቤትም የወ/ሮ ማሚቱ
የይዞታ ጥያቆ በ10 ዓመት ይርጋ የተገደበ በመሆኑ ወ/ሮ ሙሉ ጉርሙን ልትጠየቅ አስችልም
በማለት ዉሳኔ አሰተላልፈዋል፡፡45 ይህን ዉሳኔ በመቃወም ወ/ሮ ማሚቱ ሰብለ ለህገመንግስት
አጣሪ ጉባዔ አቅረበዋል፡፡ አጣሪ ጉበዔዉም የኦሮሚ ፍርድ በቶች የሰጡት ዉሳኔ በህገ-መንግሰቱ
አንቀጽ 40(4) ላይ የተመለከቱን አርሶ አደሮች መሬት በነጻ የማግኘትና ከይዞታቸዉም
ያለመነቀል መብትን የመቃረን ነዉ በማለት ለፌደሬሽን ምክርቤት ህገ መንግስታዊ ትርጉም
እንዲሰጥበት የዉሳኔ ሀሳብ አቀረበ፡፡ የፌደሬሽን ምክር ቤትም ዉሳኔዉን ከመረመረ በ|ላ
በተከራካሪዎች መካከል የኪራይ ዉል ስለአለ የይዞታ ክርክር የሚያስነሳ አይደለም የሚል
ድምዳሜ እና የህገ መንግስቱን አንቀጽ 40 (4) ን የሚቃረን እንዲሁም የሴቶች ከወንዶች
የእኩልነት መብት የሚቃረን ዉሳኔ ስለሆነ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 9 መሰረት ዉድቅ
አደርጎታል፡፡
1. ይህ የፌዴሬሽን ምክርቤት ወሳኔ ከባለእጅ (ይዞታ) ወይም የይርጋ ክርክር ጋር የሚገናኝ
ነዉ ወይስ አይደለም የሚለዉ ክርክር በባለሙያዎች ዘንድ ልዩነት አለ፡፡ ስለሆነም
ይህንን ወሳኔ ከይዞታ ክርክር ጽንሰ ሀሰብ ጋር መመርመር አስፈላጊ ነዉ፡፡ የባለእጅ
(ይዞታ) ይመለስልኝ ጥያቄ ሲቀርብ መሬቱን በእጁ ያደረገዉ ሰዉ ደግሞ የሚያነሳዉ
መከራከሪያ መሬቱን በባለቤትነት ስሜት በእዉነተኛ ቀጥርር በማድረግና የቀድሞ
የመሬቱ ባለቤትም ይሁን ሌሎችን በሚያገል ሁኔታ ስጠቀምበት የቀየሁና በህግ
የተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያለፈ ስለሆነ ይህ የመሬት ይዞታ ወደእኔ የተላለፈና የቀድሞ
ባለይዞታም መብቱን በወቅቱ ባለመጠየቁ ከዚህ በ|ላ መብት የሎለዉ ስለሆነ ሊጠይቀኝ
አይችለም የሚል ይዘት አለዉ ፡፡ ይህ መከራከሪ የህግና የፍሬ ነገር ክርክር የያዘ
ጭብጥ ነዉ፡፡ ስለሆነም የምናረጋግጣቸዉ ፍሬ ነገሮችን ማጣራት እና በህግ መልስ

45
በየደረጃዉ የሚገኙ የኦሮሚያ ፍርድ ቤቶችም ለዉሳኔያቸዉ መነሻ ያደረጉት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 69302 ቅጽ-13 ላይ የሰጠው የመሬት ይዞታ ጥያቄ በ10 ዓመት የተገደበ ነው
የሚለዉ አሰደዳጅ ዉሳኔ ነዉ፡፡
የሚያገኙትን ደግሞ መልስ መስጠትን ይመለከታል፡፡ ይህን ስናደርግ የተሟላ የይዞታ
ይገባኛል ክርክር ይሆናል፡፡ በሌላኛዉ ወገን የተነሳዉ ወይም በአሁኑ ጉዳይ ወ/ሮ ሙሉ
ጉርሙ የሚያነሱት መከራከርያ ደግሞ መሬቱን በባለእጅ (ይዘታ) ((adverse
possession)) ያገኘሁት ነዉ የሚለዉ ክርክር ቀጥታ የይርጋ ጉዳይ እንደሆነ ቀደም
ሲል አይተናል፡፡46 ስለዚህ በአሁኑ ጉዳይ ወ/ሮ ሙሉ የሚያነሱት መከራከርያ 12
ዓመት በስሜ ተመዝግቦ ባለእጅ(ይዞታ) አድርጌ የተጠቀምሁበት ነዉ የሚለዉ
መከራከርያ ሲታይ ለዉሳኔ መሰረት የሚሆነዉ ጭብጥ በትክክልም የባለእጅ(ይዞታ)
ክርክር ስለሆነ የይርጋ ክርክር እንዳለዉ መዉሰድ ተገቢ ነዉ ብሎ ጸሀፊዉ ያምናል፡፡
ከፌደሬሽ ምክርቤት ዉሳኔ ጋር የማልስማዉ ፍሬ ነገሩን የተገነዘበበት ሁኔታ ነዉ፡፡
ማለትም በመካከላቸዉ የኪራይ ዉል ስለ አለ የይዞታ ክርክር አይደለም በማለት
የደረሱበት ድምዳሜ የፍሬ ነገር አረዳድ ላይ ይሆናል፡፡ በእርግጥ በትክክል
በተከራካሪዎች መካከል የኪራይ ዉል ካለ የይዞታም ይሁን የይርጋ ክርክር አያስነሳም
የሚለዉ ነጥብ ላይ ልዩነት የለኝም ወይም የፌደሬሽ ምክርቤት ዉሳኔ ትክክል ነዉ፡፡
ነገር ግን በየደረጃዉ ከሚገኙ የኦሮሚያ ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ መረዳት የሚቻለዉ
መጀመሩያ ወ/ሮ ማሚቱ በኪራይ የሰጠችዉ የእርሻ መሬት መሬትን በሚያስተዳድረዉ
የወረዳዉ መሬት አስተዳድር አማካኝነት ወደ ወ/ሮ ሙሉ የተላለፈ እና 12 ዓመት
የሞላዉ መሆኑን ነዉ፡፡ ይህን ፍሬ ነገር የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተረዳበት ሁኔታ
አጠቃላይ የዉሳኔዉን ጭብጥ ቀይሮታል፡፡ ስለሆነም ወ/ሮ ሙሉ ጉርሙ ባለእጅ
(ይዞታ) መብት ለማንሳት ቅድመ ሁኔታወችን አለሟላችም የሚል ድምዳሜ ያስይዛል፡፡
ስለሆነም ይህ የፌደሬሽን ህገ መንግስታዊ ዉሳኔ ሲታይ ባለእጅ (ይዞታ) አሰራር የህገ
መንግስቱን አንቀጽ 40(4) ላይ የተመለከተዉን የአርሶ አደሮችን ያለመነቀል መብት
የሚቃረን ነዉ የሚል ድምዳሜ ላይ በግልጽ አልደረሰም፡፡ የዚህ ዉሳኔ ፋይዳ ሲታይ
ልክ በአዉሮፓ ህብረት የሰባዊ ፍርድ ቤት አንደ ተሰጠዉ ዉሳኔ በማያሻማ ሁኔታ
ባለእጅ አሰራር ወይም በፍታብሄር ቁጥር 1168-69 ላይ የተመለከተዉ አሰራር ከህገ
መንግስቱ ጋር የሚቃረን መሆን ወይም አለመሆን በአግባቡ በጥኛትና በመረጃ ላይ
የተመሰረተ ህገ መንግስታዊ መልስ የሚያስፈልገዉ ሆኖ ሳለ በአግባቡ የቀረበዉን እንኳ
የፍሬ ነገር ሁኔታ ሳይረዳ የተሰጠዉ ዉሳኔ ለብዙ ክርክር ዳርጓል፡፡
46
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 6 እንዲሁም የፍታብሄር ህግ ከቁጥር 1168-69 ላይ ይመልከቱ፡፡ በተለይም የሌሎች
ሀገራት የመሬት ይዞታ ይገባኛል ወይም ባለእጅ(ይዞታ) እና የይርጋ አዋጅን ይመልከቱ፡፡
2. ይህን የፌደሬሽን ወሳኔ ተከትሎ የአማራ ብሄራዉ ክልል በአዋጅ ቁጥር 252/2009
የመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀምን ለመሻሻል በወጣዉ አዋጅ ላይ በህገ ወጥ መልኩ
የተያዘ መሬት ይዞታ የይርጋ መከራከሪያ ሊቀርብበት አይችልም የሚል መርህ
አስቀምጧል፡፡ የአንቀጽ 55 <ስለ ይርጋ> የሚለዉ ክፍል ሙሉ ይዘት የሚከተለዉ
ነዉ፣
‹የገጠር መሬትን በወረራ ወይም በሌላ በማናቸውም ሕገ-ወጥ መንገድ ይዞ
በመገልገል ላይ የሚገኝ ማንኛውም ሰው መሬቱን እንዲለቅ በማንኛውም ሌላ
ሰው ወይም ሥልጣን ባለው የመንግሥት አስተዳደር አካል ሲጠየቅ ወይም
በመደበኛ ፍርድ ቤት ሲከሰስ የይርጋ ጊዜ ገደብን በሥነ-ስርዓት መቃወሚያነት
ሊያነሣ አይችልም›፡፡

የዚህን ድንጋጌ ትርጉም እና ፋይዳ በመረዳት ስራ ላይ ለማዋል በአግባቡ መመርመር አስፈላጊ


ከሆኑት ምክንያች አንዱ ይህ ድንጋጌ በፍታብሄር ህግ ቁጥር 1168-69 ላይ የተመከተዉን
የመሬት ይዞታ ባለእጅ (ይዞታ) የማድረግ አሰራርን ነዉ፡፡ ድንጋገዉ ግልጽነት የሚጎድለዉ
በመጀመሪያ <የገጠር መሬት> የሚለዉ ቃል የገጠር መሬት በአሁኑ የመሬት ስሪት መሰረት
በመንገስት፣በግል እና የጋራ ይዞታ የሚያዝ በመሆኑ ይህ ክልከላ ለየትኛዉ የይዞታ ዓይነት
ነዉ የሚለዉ ይሆናል፡፡ የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መልኩ በመያዝ የባለእጅ ክርክር
ሊነሳበት ወይም የይርጋ ክርክር ሊቀርብበት እንደመይገባ የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ
ያሳያል፡፡47በኢትዮጵያ የህግ ማዕቀፍ ይህንን ጉዳይ የሚመልስ ግልጽ ህግ ባለመኖሩ በፌደራል
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር የተሰጠ ዉሳኔ አለ፡፡48 የዚህ አዋጅ
አላማም ይህ ለማጠናከር ከሆነ በጥሩ ጎኑ የሚይ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የህግ አዉጭዉ ሀሳብ
በተለያዩ አዋጁ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ላይ የተገለጸዉ የህግ አዉጭዉ ሀሳብ
በአጠቃላይ የግለሰቦችም ይሁን የመንግስት የመሬት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ በመያዝ
የይርጋ ክርክር ሊቀርብበት አይችልም የሚል ነዉ፡፡49 ስለሆነም የዚህ ድንጋጌ ይዘት በግለሰቦች
መካከል የሚነሳዉን የባለእጅ (ይዞታ) ወይም የይርጋ ክርክር የሚያስቀር መሆኑ አይቀርም፡፡

47
የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 25
48
93013 ጥር 30, 2006 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የመዝገብ ቁጥር
49
በዉይይት የተሳተፉ የአብክመ ፍትህ ባለሙያዎች ማሰልጠኛና ህግ ምርምር ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች
እንደገለጹት ይህ ድንጋጌ የግለሰቦችን የመሬት ይዞታ ከህገ ወጥ ሰዎች ለመከላከል ታስቦ የተቀረጸ ድንጋጌ ነዉ፡፡
ይህም በፍታብሄር ህግ ከቁጥር 1168-69 ላይ የተመለከተዉን አሰራር የሚቃረን ይሆናል፡፡
ቀደም ሲል ይህ አሰራር ከዜጎች የንብረት መብት አኳያ በተለይም ፍታዊ ያልሆነ ንብረት
የማጣት ሁኔታ የተከለከለ ስለሆነ ይህ ዜጎች በንብረታቸዉ ላይ ያላቸዉን በሰላም የመጠቀምና
ያለ መነጠቅ (arbitrary deprivation) ነዉ የሚል ከርክር በእንግሊዝ የፍርድ ቤት ዉሳኔ ላይ
አዉሮፓ ህብረት የሰባዊ መብት ፍርድ ቤት መርምሮ ይህ የይርጋ ጉዳይ የራሱ የሆነ አሳማኝ
ማህባራዊና ኢኮኖሚያዊ ምክንያት (justification)50 ስለ አለዉ የዜጎች ንብረት መብትን
አይቃረንም የሚል ዉሳኔ ሰጥቷል፡፡ ከፍ ሲል እንዳየነዉ የፌደሬሽን ምክር ቤትም በዚህ ጉዳይ
ላይ ግልጽ አkም በመያዝ ህገ መንግስታዊ ትርጓሜ አልሰጠበትም፡፡ ሌላዉ በ1952 ዓ.ም
የወጣዉ ኢትዮጵያ የፍታብሄር ህግ አልተሻሻለም፡፡ ምን አልባት ከመሬት ጋር በተያያዘ
በፌደራል ህገ መንግስት አንቀጽ-40 መሰረት የመሬት ባለቤትነት የህዝብና የመንግስት ስለሆነ
የፍታብሄር ህጉ ከቁጥር 1168-9 ላይ ተመለከተዉ የመሬትን ባለቤትነት ሊያስገኝ አይችልም፡፡
ከባለቤትነት በመለስ ያለዉን <የይዞታ መብት> በተመለከተ በይርጋ አማካኝነት በግለሰቦች
መካከል ያለዉን ክርክር ሊፈታ የሚችልበት አጋጣሚ ግን አለ፡፡ እዚህ ላይ የፌደራል ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የወሰነዉ አስገዳጅ ዉሳኔ እድተጠበቀ ሆኖ በዚህ ጸሀፊ እምነት
የመሬት ይዞታ ይገባኛል ጥያቆ ይርጋን በተመለከተ 10 ዓመት ሳይሆን በ1168-9 ላይ
የተመከተዉ የ15 ዓመት የይርጋ ጊዜ ነዉ ብሎ ያምናል፡፡ቀደም ሲል እንደገለጽሁት በአጠቃላይ
አገላለጽ የመሬት ይርጋ 10 ዓመት ይሆናል የሚለዉ የፌደራል ጠቅላይ ፍረድ ቤት ሰበር ሰሚ
ችሎት ዉሳኔ ተገቢ ነዉ ብዬ አላምንም፡፡ በተጨማሪ የመሬት ይዞታ ይገባኛል ጥያቀን
በተመለከተ የሌሎች ሀገራት የዳበረ ልምድ የሚያሳየን ረዘም ያለ የጊዜ ገደብ ሊቀመጥለት
ይገባል፡፡ የአብዛኞች ሀገራት የየርጋ ህግ ከ30-60 ዓመት የሚደርስ ነዉ፡፡ ይህ ጊዜ ሲቀመጥ
የራሱ አመክኒኦ አለዉ፡፡ የግለሰቦች ይዞታ በህገ ወጥ መልኩ እንዳይያዝ ይዞታቸዉ እና ላይ
ሁከት እንዳይፈጠር ረዘም ያለ ጊዜ መቀመጡ ትክክል ይሆናል፡፡
በሌላ በኩል ግን የለባእጅ (ይዞታ) አሰራርን ጭራሹን ክልከላ ማድረግ የይዞታ ዋስትና
የሚያሳጣ ስርዓት፣ ሰዎች ረጅም ጊዜ በቆየና አላስፈላጊ ክርክር እንዲያደርጉ መፍቀድ፣ ሰዎች
በይዞታቸዉ እርገጠኛ በመሆን መሬቱን በአግባቡ እንዳያለሙ (ከዛሬ ነገ ይዞታዬን ሊወሰድብኝ
ይችላል በሚል) ፣ ምርትና ምርታማነት እንዳይጨምር የሚያደርግ ስርዓት ይሆናል፡፡ ስለዚህ
በግልጽ ከላይ እንዳየነዉ የባለእጅ(ይዞታ) አሰራር በሁለት ተቃራኒ ጥቅሞች መካካል የሚዘረጋ
50
Goodman MJ “Adverse Possession of Land – Morality and Motive” (1970) 33 Modern Law
Review 281-288 281.
ስርዓት ስለሆነ በአንድ በኩል የግለሰቦችን የይዞታ መብት ጥበቃ በአግባቡ ማድረግ እነዚህ
የጥበቃ ዘዴዎች ላይ ችግር ካለ ይህንኑ መመርመርና ማስተካከል ይገባል፡፡ እነዚህ ጥበቃዎች
ዘተርግተዉ ነገር ግን ይህ መብቱን ሳይጠቀም የቀረና ሰነፍ የይዞታ ባለመብት ዘላለማዊ ጥበቃ
ማድረግ የአብዛኛዉን ህዝብ ጥቅም የሚጎዳ ስርዓት ይሆናል፡፡ ይህም ከጥንት ጀምሮ በንብረት
ህግ ስርዓት ተቀባይነት የነበረዉና በምክንያት የተደገፈ ስርዓትን የሚቃረን ነዉ፡፡
የአማራ ብሄራዊ መንግስ በመሬት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 252/2009 ላይ ከህገ ወጥ ይዞታ
ጋር በተያያዘ የይርጋ መከራከሪያ ሊሆን አይችልም የሚለዉ ክፍል ከፌደራል የህግ ማዕቀፍ
ጋር የመይጠጣም ሲሆን ለትርጉም ክፍት የሆነ ነዉ፡፡ በኢትዮጵያ ፌገራሊዝም መሰረት
የፌደራልና የክልል ህግ ቅራኔ ካለዘቸዉ እንዴት መተርጎም አለበት የሚል ጥያቄ ሚያስነሳ
ነዉ፡፡ በዚህ ክርክር ዙሪያ ግልጽ የሆነ ሥርዓት የተዘረጋ ስርዓት ባይኖርም ከፌደራል ህገ
መንግስት እና አዋጅ ቁጥር 25/88 ትርጉም ተነስተን የፌደራልና የክልል ህግ መካከል ቅራኔ
ካለ የፌደራል ህግ ተፈጻሚ መሆኑ አይቀርም፡፡ ስለሆነም አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 55
ላይ የተመለከተዉ ሀሳብ ህጋዊነት ጥያቄ የሚስነሳ ይሆናል፡፡

ማጠቃለያ
ከሮማዊያን ህዝቦች አንድ እንደተመሰረተ እና በእንግሊዝ ሀገር በስረዓት ደረጃ የተዘረጋዉ
ባለእጅ (ይዞታ) (adverse possession) በሁሉም ሀገራት ተቀባይነት ያለዉ ነገር ግን በስያሜ
ደረጃ በሮማዊያን ዘንድ ዩዝካፕሽ የሚባል ሲሆን በእንግሊዝና በኮመን ሎዉ ሀገራት ዘንድ
አድቨርስ ፖሰሽ በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ሥርዓት የራሱ የሆነ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ
አመክኖዎች አሉት፡፡ በሌላ በኩል ግን የንብረት ይዞታ በአንድ በኩል የሚያሳጣ በሌላ በኩል
ደግሞ የሚያጎናጽፍ ገጽታ አለዉ፡፡ ይህን ስርዓት ተግባራዊ ከማድረጋችን በፊት በጥንቃቄ
የሚመረመሩ ቅድመ ሁኔታዎችን መሟላታቸዉን መረጋገጥ ይጠይቃል፡፡ ይህም ይዞታዉን
በእዉን በቁጥጥር ስር በማድረግ የቀድሞ የንብረቱ ባለቤትንም ይሁን ሌሎችን በሚያገል
ሁኔታ፣ በግልጽ ለተከታታይ ጊዜ በህግ የተቀመጠዉን የጊዜ ገደብ ማለፍ ይኖርበታል፡፡

ይህ አሰራር ከይርጋ ህግ ጋር ከጥተኛ የሆነ ቁርኝት ስላለዉ የመሬት ይዞታ ይገባኛል እና


ሌሎች የይርጋ መከራከሪያዎች በይርጋ አዋጅ (አክት) ተመላክቶ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የይዞታ
ይገባኛል ክርክር ካለ እና የጊዜ ገደብ ጥያቄን መልስ መስጠት አስፈላጊ ነዉ፡፡ ህገ ወጥ ይዞታ
እና የይዞታ ይገባኛል ክርክር የሚገኛኙበት ነጥብ የለም፡፡ ይህም በህገ ወጥ መልኩ የሌላ
ግለሰብ ይዞታ የሚይዝ ከሆነ በወንጀል እና በፍታብሄር ጥበቃ ስለሚደረግለት በእነኝህ
መንገዶች በመጠቀም መብቱን ማስከበር ይገባወል፡፡ ይዞታ መብት ከንብረት ጋር የተያያዘ
በመሆኑ አንዳንድ ዓለማቀፍና ክልል ዓቀፍ እንዲሁም የሀገራት ህጎች እንደ ሰባዊ መብት
በመቁጥር ጥበቃ ያደርጉለታል፡፡
በተመሳሳይ በኢትዮጵጣ የህግ ማዕቀፍም ከህገ መንግስቱ ጀምሮ የወንጀል ህግ፣የፍታብሄር ህግ
ለመሬትም ይሁን ሌሎች ይዞታዎች ጥበቃ ያደርጋሉ፡፡ ስለሆነም እነዚህን አማራጮች
ተጠቅመዉ ግለሰቦች ያላቸዉን የይዞታ መብት ሊያስከብሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ይህን
መብታቸዉን ባግባቡ ካልተጠቀሙ ለአጠቃላይ የህዝብ ጥቅም ሲባል የባለእጅ አሰራር
በመዘርጋት ህብረተሰቡን ካለአስፈላጊ ክርክሮች መካላከል፣ የሀገሪቱም ይሁን የክልሉ ዉስን
ሀብት የሆነዉን መሬት ኢኮኖሚያዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ የሚያዉል ስርዓት ሊዘረጋ
ይገባል፡፡
የባለ እጅ(ይዞታ) አሰራር የረጅም ጊዜ ታሪክ ባለቤት ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ክርክር
እያስነሳ መጥቷል፡፡ ይህም ከግለሰቦች የይዞታ መብት ጋር የሚቃረን ነዉ የሚል ሲሆን
ለመጀመሪያ ጊዜ ክርክር የተደረገበት በእንግሊ ሀገር የፍርድ ቤት ዉሳኔ በአዉሮፓ ህብረት
የሀባዊ መብት ፍርድ በት ነዉ፡፡ ይህ ፍርድ ቤት ክርክር ካደረገ በ|ላ አሰራሩ ለህብ ጥቅም
ሲባል የተደረገ ከሆነ ከሰዎች መብት ጋር የሚቃረን አይደለም የሚል ብይን ሰጥቷል፡፡ ከዚህ
ዉሳኔ ጭብ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ጉዳይ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ቀርቦ ጉዳዩን በአግባቡ
ሳይመረምር ስለቀረ የይዞታ ክርክር አይደለም የሚል ዉሳኔ በመስጠቱ ዕድሉን ሳይጠቀምበት
ቀርቷል፡፡ ስለሆነም የፍታብሄር ህግ ከቁር 1168-9 ላይ የተዘረጋዉ የባለእጅ(ይዞታ) የማድረግ
አሰራር ተግባራዊነት ይቀጥላል ወይም አልተሻሻለም የሚልዉን መገንዘብ አስፈላጊ ነዉ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመሬት አሰተዳደር አዋጅን ለማሻሻል 252/2009 ሲያወጣ
የህገ ወጥ ይዞታን በተመለከተ የይርጋ መከራከሪያ ሊሆን እንደማይችል ክልከላ አስቀምጧል፡፡
ይህ ክልከላ ከፍታብሔር ህግ 1168-9 ላይ ከተመለከተዉ ስርዓት ጋር የሚቃረን ምክንያታዊ
ያልሆነ እና ተፈጻሚነቱ ጥያቄ ዉስጥ ያለ ነዉ፡፡

You might also like