You are on page 1of 42

ስለሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች አንዳንድ መሰረታዊ ነጥቦች

ሳባ አበረ ♣

መግቢያ

ዛሬ ዛሬ ያለ ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶች የንግዱን አለም ማሰብ አዳጋች ሆኗል፡፡ ጥሬ ገንዘብን ይዞ


ከቦታ ቦታ መዘዋወር የሚያስከትለውን ከፍተኛ አደጋ ከመቀነስም ሆነ ለሚደረጉ ግብይቶች
እንደ ዋስትና መሰጠት መቻላቸው ብሎም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው
መተላለፍ መቻላቸው፣ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን ተመራጭ የግብይት አንቀሳቃሽ ሞተር
እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ታዲያ ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶች ያላቸውን ከፍተኛ
ጠቀሜታ ከግምት ውስጥ በማኖር ተገቢው የህግ ጥበቃ እንዲኖራቸው ማድረጉ አስፈላጊ ጉዳይ
ነው፡፡ በመሆኑም የንግድ ህግ መነሾ የሆነው የአሜሪካ ዩኒፎርም ኮሜርሺያል ኮድ(UCC)
ለመጀመሪ ጊዜ በ1880ዎቹ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን ለዐለም ያስተዋወቀ ህግ ሲሆን
በቀጣይም በካናዳ እና በእንግሊዝ እውቅና ተሰጥቷቸው የግብይቱን ሂደት እንዲቀላቀሉ
ተደርገዋል፡፡ በ20ኛው ክፍለ-ዘመን አጋማሽ አካባቢ በስራ ላይ የዋለው የኢትዮጵያ የንግድ
ህግም በአራተኛ መጽሐፍ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች እና የባንክ ስራ ህግ በሚል ታላቅ ርዕስ
ስር ሽፋን ተሰጥቶታል፡፡

እንደ ህጉ አገላለጽ የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ ማለት የተወሰነ ገንዘብን ያለ ምንም ቅድመ
ሁኔታ ላምጪው ወይም ስሙ ለተጠቀሰለት ሰው እንዲከፈል ትእዛዝ የሚሰጥበት/ቃል
የሚገባት/ ሰነድ ሲሆን ይህ ሰነድ በአውጪ የተጻፈ እና የተፈረመ መሆን አለበት፡፡

በህጉ እውቅና የተሰጣቸው የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች የሀዋላ ወረቀት፣ ቼክ፣ የተስፋ ሰነድ፣
የመንገደኞች ቼክ፣ እንዲሁም በዕቃ መጋዘን ለተቀመጡ ዕቃዎች የሚሰጡ የምስክር ወረቀቶች
ናቸው፡፡ እያንዳንዳቸው ሰነዶች የየራሳቸው ጠባያት ቢኖሯቸውም ሁሉን አንድ የሚያደርጓቸው
የጋራ መገለጫዎችም አሏቸው፡፡ ከዚህ አንጻር የንግድ ህጉ ድንጋጌዎች እለት ከእለት
በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች አማካኝነት የሚደረጉ ግብይቶች ላይ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

!LLM,LLB,!በአብክመ የፍትህ ባለሙያዎች ማሰልጠኛ እና የህግ ምርምር ኢንስቲትዩት የህግ ተመራማሪ፡፡ ጽሁፉን
በማዘጋጀት ሂደት ሀሳቦችን በማካፈል እንዲሁም ተገቢውን ግብዐት በማሰባሰብ የረዳችሁኝን ሁሉ እያመሰገንኩ
በጽሁፉ ላይ አስተያየት መስጠት ለሚፈልግ በ saba.abere@gmail.com መጠቀም ይቻላል፡፡

!
በሚፈታ መልኩ የተዘጋጁ መሆን አለመሆናቸውን መመርመር፣ ብሎም በህግ ተርጓሚው
በኩል (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎትን ጨምሮ) ስለ ሰነዶቹ አጠቃላይ
ባህሪያት ያለውን መረዳት ለመገንዘብ ያስችል ዘንድ ይህ ጽሁፍ ተዘጋጅቷል፡፡ በተለይም
የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ የመተላለፍ ባህሪን መሰረት አድርገው
የሚነሱ መቃወሚያዎች ምንነት እና ውጤቶቻቸው፣ በሰነዶቹ ላይ የሚነሱ የይርጋ ጥያቄዎች
እና ውጤቶቻቸው፣ ቼክን በሚመለከት ደግሞ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ መቁረጥ የሚያስከትለውን
ተጠያቂነት እንዲሁም ከተጠያቂነት ለመዳን የሚቀርቡ መከላከያዎችን በሚመለከት በፍርድ
ቤቶቻችን ወጥ የሆነ ግንዛቤ የሌለ መሆኑን የጽሁፉ አካል ከተደረጉ የተለያዩ ውሳኔዎች
መመልከት ይቻላል፡፡ በመሆኑም በዚህ ጽሁፍ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን አጠቃላይ ባህሪያት
ከተግባራዊ አፈጻጸማቸው አንጻር በመተንተን ፍርድ ቤቶቻችን ሊከተሉዋቸው የሚገቡ
አቅጣጫዎች ተመላክቷል፡፡

ትርጓሜ እና ጽንሰ ሀሳብ


ተላላፊ የገንዘብ ሰነድ ማለት የተወሰነ መጠን ያለውን ገንዘብ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ
ላምጪው ወይንም ስሙ ተለይቶ ለተጠቀሰው ሰው ወይም ለታዘዘለት ሰው እንዲከፈል
የሚያዝዝ/ ቃል የሚገባ/፣ በአውጪው የተጻፈ እና የተፈረመ ሰነድ ማለት ነው1፡፡ በማዘዝ
መታዘዝ ሂደቱ ቢያንስ ከ ሁለት ያላነሱ ሰዎች ሲኖሩ ክፍያው እንዲፈጸም ያዘዘው ሰው(the
drawer)፣ ገንዘቡን እንዲከፍል የታዘዘው ሰው(the drawee)፣ እንዲሁም ክፍያው
እንዲፈጸምለት የታዘዘለት ሰው(the payee) ተሳታፊ ከመሆናቸውም በላይ ሰነዱ አንዴ
ከወጣም በኋላ በቀላሉ በጀርባ በመፈረም ወይም ሰነዱን በመስጠት ብቻ ለሌላ 3ኛ ወገን
መተላለፍ መቻሉ ተላላፊ የገንዘብ ሰነድ ተመራጭ የግብይት አንቀሳቃሽ ሆኖ በማገልገል ላይ
ይገኛል፡፡2

የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ሌሎች መብትን ከሚያጎናጽፉ ሰነዶች በልዩ ሁኔታ የትኩረት
ማዕከል ለመሆን የበቁት በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፉ መሆናቸው እና በህግ መሰረት
ሰነዱን በጅ ያደረገ ሰው በሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን መብት በራሱ ስም ሊጠቀምበት መቻሉ
ነው፡፡ በብዛት የተለመዱቱ የሚተላላፉ የገንዘብ ሰነዶች:- የሀዋላ ወረቀት፣ ቼክ እና የተስፋ

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
1
Roger LeRoy Miller, Gaylord A. Jentz, fundamentals of business law, Thomson corporation,
USA, 2007, page 356
2
ዝኒ ከማሁ

!
ሰነድ ሲሆኑ በአሁኑ ጊዜ በአብዛኛው የዓለም አገራት ተቀባይነት አግኝተው ጥቀም ላይ እየዋሉ
ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የኩባያዎችን ድርሻ፣እንዲሁም ከመንግስት የሚደረጉ የቦንድ ግዢዎች
እንደተላላፊ የገንዘብ ሰነዶች ሊታዩ ይችላሉ፡፡ በልዩ ሁኔታ በሰነዱ ላይ የተጠቀሰው መብት
በመጋዘን ለተቀመጡ ዕቃዎችን ለመውሰድ ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም በሰነዱ ላይ የእቃው ዋጋ
በገንዘብ ተተምኖ ሊቀመጥ የይገባል3፡፡ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ከሰው ወደ ሰው በአብዛኛው
የሚተላለፉት ለውል ማስፈጸሚያ ዓላማ ሲሆን በተለይም የሽያጭ ውልን፣ የኪራይ ውልን፣
የብድር ውልን፣ እንዲሁም ክፍያን የሚያቀላጥፉ መሳሪያዎች ናቸው፡፡4
ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶችን ከሌሎች በንብረት ላይ መብትን ከሚያጎናጽፉ ሰነዶች ለየት
የሚያደርጓቸው የራሳቸው የሆኑ አላባውያን አሏቸው፡፡ እነዚህ አላባውያን የተላላፊ የገንዘብ
ሰነዶችን ዙሪያ መለስ የሚያዋቅሩ ምሰሶ እና ማገር በመሆናቸው መመልከቱ አስፈላጊ
ይሆናል፡፡

የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች አላባውያን

1.! ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ክፍያ እንዲፈጸም የሚያዘ መሆን፡- ሰነዱ ያለምንም ቅድመ
ሁኔታ ክፍያ እንዲፈጸም የሚያዝ ወይም ቃል የሚገባ መሆን ይኖርበታ ሲባል ለሰነዱ
አከፋፈል ይረዳ ዘንድ ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያስቀምጥ እንደሆነ የሰነዱን ተላላፊነት (
ከሰው ወደ ሰው የመተላለፍ) መሰተረታዊ ባህሪይ የሚጻረር ይሆናል ማለት ነው፡፡
በመሆኑም በሰነዱ ላይ ይህ ሁኔታ ወይም ድርጊት ሲፈጸም ወይም ሳይፈጸም የቀረ
እንደሆነ ክፍያው ይፈጸማል/አይፈጸምም/ የሚል ሀረግ ገብቶ እንደሆነ የሰነዱን
ተላላፊነት ያስቀረዋል፡፡ የሰነዱን ተላላፊነት ከሚያስቀሩ ምክንያቶች መካከል፡- ለሰነዱ
መጻፍ ምክንያት የሆነውን ውል መፈጸም አለመፈጸም እንዲንተራስ ማድረግ ዋነኛው
ነው፡፡ በርግጥ ሰነዱን ያወጣው ሰው እና ተቀባዩ የቀደመ ግንኙነት ቢኖራቸውም ሰነዱ
በተቀባዩ ብቻ የማይወሰን እና ለሌላ ሶስተኛ ወገን በቀላሉ እንዲተላለፍ የሚያስፈልግ
በመሆኑ በመካከላቸው ያለው ግንኙነት ይህንን ተላላፊ ባህሪ ሊያስተጓጉል አይገባም፡፡
ሰነዱን በሰጠው እና ሰነዱን በተቀበለው ሰው መካከል ለሚፈጸም ክፍያ ግን የቀደመ

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
3
Fasil Alemayehu, Merhatbeb Teklemedhin, Law of Banking, Negotiable Instruments and
Insurance Teaching Material, 2009, page, 79
4
Cheeseman, Business law, ethical, international & E-commerce 4th edition e-biz page 450

!
ግንኙነታቸውን መሰረት አድርጎ የሚቀርብን መቃወሚያ የሚከለክል አይሆንም፡፡5 በሌላ
አነጋገር አንድ ሰነድ ተላላፊ የገንዘብ ሰነድ እንዳይሆን ከሚያደርጉት ቅድመ ሁኔታዎች
መካከል በሰነዱ እንዲከፈል ግልጽ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠ እንደሆነ፣ የመብቱ
አከፋፈል በሌላ ሰነድ ላይ እንዲደገፍ የተደረገ እንደሆነ፣ ከሰነዱ የሚገኘው
መብት/ግዴታ በሌላ ሰነድ ላይ የተጻፈ እንደሆነ ይገኙበታል፡፡6
2.! በጽሁፍ የተደረገ እና የተፈረመ መሆን፡- ይህም ሰነዱ በአውጪው የተፈረመ መሆን
እና አውጪው ወይም ህጋዊ ወኪሉ ስም በሰነዱ ፊት ለፊት ላይ መጻፍ ይኖርበታል፡፡7
3.! እንደቀረበ የሚከፈል አልያም ወደፊት ተለይቶ በታወቀ ጊዜ የሚከፈል መሆን፡- ቼክ
እንደቀረበ ከሚከፈል የገንዘብ ማስተላለፊያ ሰነድ ዋነኛው ነው፡፡ በመሆኑም ሰነዱን
የያዘው ሰው በማንኛውም የስራ ሰዓት ቼኩን ለባንክ በማቅረብ ክፍያ እንዲፈጸምለት
መጠየቅ ይችላል(የመጠየቂያ ጊዜው እስካላለቀ ድረስ)፡፡ በሌላ በኩል ሰነዱ ወደፊት
ተለይቶ በታወቀ ጊዜ የሚከፈል መሆን ይችላል፡፡ ከዚህ አንጻር ክፍያው በዚህ ቀን
ወይም አንድ ድርጊት ከተከናወነ በኋላ ይሆናል በሚል ሊጻፍ ይችላል፡፡ ሆኖም ድርጊቱ
የታወቀና በርግጥም ሊመጣ ያለ መሆን ይኖርበታል አልያ እርግጠኛ ባልሆነ ድርጊት
ላይ የተመሰረተ ማድረግ መሰረታዊ ባህሪውን የሚያሳጣው በመሆኑ ተቀባይነት
አይኖረውም፡፡8
4.! የተወሰነ ገንዘብን (መጠኑ ተለይቶ የሚታወቅ ገንዘብን) ለመክፈል የሚደረግ መሆን፡-
በሰነዱ ላይ ሊከፈል የሚገባው የገንዘብ መጠን ተለይቶ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡ ክፍያው
በአንዴ አልያም በየጊዜው ሊደረግ እንዲሁም ወለድንና ሌሎች ክፍያዎችን
የሚያጠቃልል ሊሆን ቢችልም ጠቅላላ መጠኑ ግን በግልጽ በሰነዱ ላይ መጠቀስ
ይኖርበታል፡፡9
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
5
Alfred W. Bays, unconditional promise to pay, American Comercial law series available at
http://chestofbooks.com/business/law/American-Commercial-Law-Series/B-Must-Contain-An-
Unconditional-Promise-Or-Order-To-Pay-A.html retrived on 7/18/17 3:10 AM
6
! Mallor, Barness, Bowers, Langvardt, Bussiness Law, the Ethical, Global and E-commerce
Environment, 4th edition, MacGraw-Hill international edition, New York 2010 page 811-817
7
Roger LeRoy Miller. Gaylord A.Jenetz, Fundamentals of Bussiness Law Excerpted cases,
Arlington Texas 2007 USA, page 355-359
8
ከላይ የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 6
9
ከላይ የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 7!

!
5.! ሰነዱ ለተጠቃሚው መሰጠት ይኖርበታል፡- የገንዘብ ማስተላለፊያ ሰነዱ ለተጠቃሚው
እስካልተሰጠ ድረስ መዘጋጀቱ ወይም መጻፉ ብቻ ዋጋ አያሰጠውም፡፡ በዚህ ረገድ በሰነዱ
ላይ ያለው መብት ከሰነዱ ተለይቶ ሊሰራበት ወይም ሊተላለፍ የማይችል በመሆኑ ሰነዱ
ለተጠቃሚው መተላለፍ የግድ ይለዋል፡፡10

እኒህ አላባውያን በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ አንድ ሰነድ እንደ ተላላፊ የገንዘብ ሰነድ
ተቆጥሮ በህጉ የተነገሩ ጥበቃዎች ይደረጉለታል፡፡

ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶች የህግ እውቅና ተችሯቸው አገልግሎት ላይ መዋል ከጀመሩ አያሌ
ምዕተ-አመታትን አስቆጥረዋል፡፡ ቀድሞ ነገር እኒህ ሰነዶች የተፈጠሩት ጥሬ ገንዘብ
ለማስተላለፍ ዓላማ ሲሆን በዚህ ረገድ ነጋዴዎች ብዛት ያለውን ገንዘብ ይዘው ሲዘዋወሩ
ሊከሰት የሚችለውን የመዘረፍ አደጋ ለመከላከል በማሰብ ነበር፡፡ በጊዜ ብዛት ታድያ የሚተላለፉ
የገንዘብ ሰነዶች የሚመሩበት ህግ በነጋዴዎች አማካኝነት የዳበረ ሲሆን ይኅም በእንግሊዝ
ፍድቤቶች ተቀባይነት በማግኘቱ የኮመን ሎው የህግ ስርዐት ዐካል ለመሆን በቅቷል፡፡ ከዚያም
የአሜሪካ ኮመን ኮሜርሺያል ኮድ (UCC) በ 1882 እኤአ በስራ ላይ ሲውል የሚተላለፉ
የገንዘብ ሰነዶችን የሚመለከቱ ዝርዝር ድንጋዎችን በመያዝ እውቅና ሰጥቷል፡፡ ቀጥሎም የካናዳ
መንግስት የሐዋላ ህግን በ1890ዎቹ ስራ ላይ ዋለ፡፡11 አሁን አሁን ዘመናዊ የንግድ ልውውጥ
ያለ ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶች አስተናባሪነት የማይታሰብ እየሆነ መጥቷል፡፡

በኢትዮጵያ የህግ ስርዐት ለሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች በ1952 ዓ.ም በወጣው የንግድ ህግ
እውቅና የተሰጠ ሲሆን ከ ቁጥር 715 እስከ ቁጥር 895 ባሉት ድጋጌዎች እኒህ ሰነዶች
የሚመሩባቸውን አሰራሮች ዝርዝር ተቀምጧል፡፡

በህጉ እውቅና የተሰጣቸው ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶች የሀዋላ ወረቀት፣ ቼክ፣ የመክፈል የተስፋ
ሰነድ፣ የመንገድ ቼክ፣ በዕቃ መጋዘን ለተቀመጡ ዕቃዎች ምስክር ወረቀቶች ሲሆኑ በዕቃ
መጋዘን ለተቀመጡ እቃዎች የሚሰጡ የምስክር ወረቀቶችን በሚመለከት በፍትሐብሄር ህግ

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
10
!ዝኒ ከማሁ
11
NEGOTIABLE INSTRUMENTS፣ available at
http://cyberadvocate.in/pluginfile.php/465/mod_resource/content/1/NEGOTIABLE%20INSTRUMENTS.
pdf retrived on 7/18/17 3:10 AM!

!
በቁጥር 2813-2824 የተደነገጉ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት የሚኖራው መሆኑ በአንቀጽ 732
ተመልክቷል፡፡

በንግድ ህጉ ከአንቀጽ 715-731 ስለሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ትርጓሜ፣ በሰነዱ ምክንያት


ስለሚመጡ ግዴታዎች፣ በህግ መሰረት ስለሚገኝ ባለቤትነት፣ በሰነዱ ላይ ስለሚነሱ
መቃወሚያዎች፣ እንዲሁም ሰነዱን ስለማስተላለፍ የተደነገጉ ጠቅላላ ድንጋጌዎችን የያዘ ሲሆን
ከአንቀጽ 732-895 የተመለከቱት ደግሞ በህጉ እውቅና ስለተሰጣቸው የሚተላለፉ የገንዘብ
ሰነዶች ማለትም የሀዋላ ወረቀት፣ የተስፋ ሰነድ እንዲሁም ቼክን የሚመለከቱ ዝርዝር ጉዳዮችን
የያዙ ድንጋጌዎች ናቸው፡፡ ከላይ እንደተገለጸው በእቃ ማስቀመጫ መጋዘን ለተቀመጡ እቃዎች
የሚሰጡ የምስር ወረቀቶች እንደሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች የሚቆጠሩ ቢሆንም አመራራቸውን
በሚመለከት ግን የፍትሐብሄር ህጉ ድንጋጌዎች የሚሰሩባቸው መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በአንቀጽ 715/1/ በተሰጠው ትርጓሜ መሰረት የሚተተላለፍ የገንዘብ ሰነድ ማለት መብቱ
ከሰነዱ ተለይቶ ሊሰራበት ወይም ሊተላለፍ የማይችል የአገልግሎት መብት ያለበት ሰነድ ሁሉ
ነው፡፡ ይህ ትርጉም በጥቅሉ የሚያተኩረው ሰነዱ ለተጠቃሚው ተላልፎ እስካልተሰጠ ድረስ
ተጠቃሚው መብት አግኝቷል ለማለት የማያስችል ስለመሆኑ ነው፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት
አንድም ሰነዱን ለሌላ ሰው በመስጠት ብቻ በሰነዱ ላይ የተገለጸውን መብት ማስተላለፍ
የሚቻል መሆኑ፣ አንድም መብት አለኝ የሚል ሰው ሰነዱን በጅ ማድረግ የሚገባው በመሆኑ
ክፍያ ይፈጸምለት ዘንድ ሰነዱን ማቅረብ የሚገባው መሆኑ፣ የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድን ሌሎች
ባለቤትነትን ከሚያረጋግጡ ሰነዶች ልዩ ያደረገው መሆኑን ይገነዘቧል፡፡!

የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች አላባውያን ተብለው የታወቁትን ዝርዝር ባህሪት በንግድ ህጉ


የተለያዩ ድንጋጌዎች ተካተው መገኘታቸው የሰነዶቹን ተግባራዊ አጠቃቀም የሚያቀላጥፍ
መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ክፍያ የሚፈጸምበት ሰነድ
ስመሆኑ፣በጽሁፍ መደረግ እና በአውጪው መፈረም የሚገባው ስለመሆኑ፣ የተወሰነ የገንዘብ
መጠንን የሚገልጽ መሆን የሚገባው ስለመሆኑ በአንቀጽ 735፣823፣ 827 የተገለጸ ሲሆን፣
ሰነዱ እንደቀረበ አልያም ወደ ፊት ተለይቶ በታወቀ ጊዜ መከፈል የሚገባው ስለመሆኑ
በአንቀጽ 769፣ 854 ተደንግጓል፡፡ ሌላው መሰረታዊው ጉዳይ ሰነዱ ለተጠቃሚው መሰጠት
የሚገባው ስለመሆኑ እና ተጠቃሚውም መብቱን ለመጠየቅ ሰነዱን ይዞ መቅረብ ያለበት
ስለመሆኑ አንቀጽ 715፣ 716 ጥምር ንባብ ያስረዳሉ፡፡

!
አንቀጽ 715 በትርጓሜው የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ ማለት መብቱ ከሰነዱ ተለይቶ ሊሰራበት
ወይም ሊተላለፍ የማይችል ያገልግሎት መብት ያለበት ሰነድ ሁሉ መሆኑን ሲገልጽ አንቀጽ
716 በበኩሉ የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ የያዘ ሰው ይኀንኑ ለእዳ ከፋዩ በማቅረብ በሰነዱ ውስጥ
ያለውን መብት ማግኘት እንደሚገባው፣ እዳ ከፋዩም ሰነዱ እስካልተሰጠው ድረስ ለክፍያ
የማይገደድ መሆኑን ብሎም እዳ ከፋዩ ከባድ አታላይነት ወይም ቸልተኝነት ካላደረገ በቀር
ምንም ይህ ሰው እውነተኛው ባለመብት ባይሆንም እንኳ ሰነዱ የባለገንዘብነት ስም ለሰጠው
ሰው ክፍያ የፈጸመ እንደሆነ ከሀላፊነት የሚድን መሆኑን መግለጹ ሰነዱን በጅ ማድረግ
ብቸኛው የመብት ማግኛ መንገድ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

በዘርፉ የመጀመሪያ የሚባለው የአሜሪካ ወጥ የንግድ ህግ (UCC) እንዲሁም የ1982ቱ የካናዳ


የሀዋላ ወረቀት ህግ እውቅና ከሰጣቸው እንደ ቼክ፣ የሀዋላ ወረቀት፣ የተስፋ ሰነድ የመሳሰሉ
የሚተላለፉ የንዘብ ሰነዶች በተጨማሪ የኢትዮጵያ የንግድ ህግ በእቃ ማስቀመጫ ለተቀመጡ
እቃዎች የሚሰጥ የምስክር ወረቀትን እንደሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ ተቆጥሮ የህግ ጥበቃ
ተሰጥቶታል፡፡ ይህ መሆኑ መሰረታዊውን የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ባህሪ ወደ ጎን የተወ
ይመስላል፡፡ ለምን ቢሉ እንደሚታወቀው የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች የሚዘጋጁት የተወሰነ
ገንዘብን ለመክፈል ሲሆን በሰነዱ ላይ የሚያጎናጽፉት መብትም በገንዘብ የሚተመን መሆን
አለበት፡፡

በንግድ ህጉ በአንቀጽ 732/1/ እንደተነገረው የንግድ ወረቀቶች ማለት በገንዘብ መከፈል


የሚሆነው ግዴታ የሚናገሩ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ናቸው፡፡ ከዚህ አንጻር የፍትሐብሄር
ህጉ ድንጋጌዎች በአደራ ለተቀመጡ እቃዎች የሚሰጡ የምስክር ወረቀቶች እና ደረሰኞች
የሚያጎናጽፉትን መብቶች ሲያመለክት የደረሰኝ እና የመያዣውን ማስቀመጫ የምስክር ወረቀት
ሰነዶች ሁለቱንም ባንድነት የያዘ ሰው በሸቀጥ ማከማቻ ቦታ የተቀመጡትን እቃዎች
እንዲሰጡት ለማስገደድ እንደሚችል ደንግጓል፡፡12 በመሆኑም ሰነዶቹን የያዘው ሰው ገንዘብ
እንዲሰጠው ሳይሆን በአደራነት የተቀመጠውን እቃ እንዲሰጠው የማስገደድ መብት ብቻ ነው
ያለው ማለት ነው፡፡ እንዲህ በሆነ ጊዜ ታዲያ በእቃ መጋዘን ለተቀመጠ እቃ የሚሰጥ የምስክር
ወረቀት የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነድ ለመባል የሚበቃው በህግ የተቀመጡ መስፈርቶችን ሲያሟላ
ነው፡፡ ይኀውም ሰነዶችን በጀርባ በመፈረም በሰነዱ ላይ ያለውን መብት ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ
ከተፈለገ የእዳውን ልክ እና ወለዱን እንዲሁም የሚከፈልበትን ቀን ለይቶ ማመልከት የግድ
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
12
!የፍትሐብሄር ህግ ቁጥር 2816/1/

!
የሚል መሆኑን በቁጥር 2818 ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን
መሰረታዊ ባህሪ ሳይጥስ በገንዘብ የሚተመን መብትን በማመልከት የምስክር ወረቀቱን
የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ ማድረግ ይቻላል ማለት ነው፡፡

ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶችን በተለያዩ መደቦች ውስጥ በመመደብ መመልከት ይቻላል፡፡


የመጀመሪያው መደብ ገንዘብ ለመክፈል ትእዛዝ የሚሰጥበት ሰነድ(order to pay) ሲባል
ሌላኛው መደብ ደግሞ ገንዘብ ለመክፈል ቃል የሚገባበት ሰነድ(promise to pay) ሊባል
ይችላል፡፡ ቼክ እና የሀዋላ ወረቀት ገንዘብ እንዲከፈል ትእዛዝ የሚሰጥባቸው ተላላፊ የገንዘብ
ሰነዶች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል የተስፋ ሰነድ ገንዘብ ለመክፈል ቃል የሚገባበት የሚተላለፍ
የገንዘብ ሰነድ ነው፡፡13 የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ እንደቀረበ የሚከፈል(demand instrument)
አልያም ወደ ፊት ተለይቶ በታወቀ ጊዜ የሚከፈል (time instrument) ተብሎም ሊመደብ
ይችላል፡፡ እንደቀረበ የሚከፈል ሰነድ ማለት አምጪው ሰነዱን ለከፋዩ ባቀረበ ጊዜ የሚከፈል
ሰነድ ሲሆን ቼክ ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ ነው፡፡14 ወደ ፊት ተለይቶ በታወቀ ጊዜ የሚከፈል
ሰነድ ግን በሰጪ እና ተቀባዩ ስምምነት መሰረት ሰነዱ ለከፋዩ ከቀረበ በኋላ በተወሰነ ጊዜ
ውስጥ ክፍያው ሊፈጸም ይቻላል፡፡ የሀዋላ ወረቀትም ሆነ የተስፋ ሰነድ በዚህ አይነት ሊዘጋጁ
ይቻላል፡፡15 ቼክ ግን ምንጊዜም እንደቀረበ የሚከፈል ሰነድ ነው፡፡16

የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ ላምጪው የሚከፈል(bearer instrument) አልያም ለታዘዘለት ሰው


በሚከፈል (order instrument) በሚልም ይከፈላል፡፡17 ለታዘዘለት ሰው የሚከፈል ሰነድ ከሆነ
በሰነዱ ላይ ክፍያ የሚፈጸምለት ሰው ስም በግልጽ ይጻፋል ወይም ይህ ሰው ላዘዘለት ሌላ ሰው

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
13
የንግድ ህግ ቁጥር 735፣ 823፣ 827
14
!የንግድ ህግ ቁጥር 854
15
የንግድ ህግ ቁጥር 769፣ 825/ለ/
16
ቼክ እንደቀረበ የሚከፈል መሆኑን በአንቀጽ 827 መገለጹ ለዋስትና መያዣ ሆኖ ማገልገል አይችልም የሚል
ክርክር ቢኖርም በዚህ ረገድ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድበቤት በሰበር ችሎቱ በሰጠው ውሳኔ ቼክ እንደቀረበ
የሚከፈል ሰነድ መሆኑን ነአንቀጽ 827/840 መደንገጉእንዲሁም ቼክ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በአውጪው ላይ
ሀላፊነት የሚጥል መሆኑ ቼክ በዋስትና እንዳይሰጥ እገዳ የሚጥል አይደለም፡፡ ቼክ የሚሰጥበትን ምክንያት
በሰጪው እና በተቀባዩ የሚወሰን እንጂ በህጉ የተዘረዘረ አይደለም በሚል መከራከሪያውን ውድቅ ያደረገው
መሆኑን ከፋይል ቁጥር 24435 በ ቅጽ 12 በአመልካች ሁዳ መሃመድ እና በ ተጠሪ ፍጹም ግርማ መካከል
በተደረገው ክርክር ውሳኔ ሰጥቷል
17
የንግድ ህግ ቁጥር 719

!
ይከፈላል ማለት ነው፡፡ ይህ ስሙ በሰነዱ ላይ የተገለጸው ሰው ለሌላ ሶስተኛ ወገን ሰነዱን
ስሙን በመጻፍ ወይም በመፈረም ብቻ ሊያስተላልፍ ይችላል፡፡ ሰነዱን ያወጣው
ሰውም/ባለእዳው/ ቀድሞ ሰነዱን ለሰጠው ሰው ወይም ይህ ሰው ሰነዱን ላስተላለፈለት ሌላ
ሶስተኛ ሰው ክፍያውን የመፈጸም ግዴታ አለበት፡፡ ላምጪው የተባለ ሰነድ በሌላ በኩል
የሰነዱን ተጠቃሚ ሰው ያልለየ፣ሰነዱን በጅ ያደረገ ማንኛውም ሰው ተጠቃሚ የሚሆንበት
የሰነድ አይነት ነው፡፡ በዚህ ሰነድ አይነት አውጪው ሰነዱን ለያዘ ለማንኛውም ሰው ክፍያ
ለመፈጸም ስምምነት አለው ተብሎ ይወሰዳል፡፡

በህግ እውቅና የተቸራቸው የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን አንድ የሚያድርጓቸው የጋራ ባህሪያት
ያላቸው ቢሆንም እርስ በእርስ የሚለያዩባቸው አያሌ ቁምነገሮችም አሉ፡፡ ለአብነት ያህል
የሀዋላ ወረቀት እና ቼክ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ክፍያ እንዲፈጸም ትእዛዝ (order)
የሚሰጥባቸው ሰነዶች ሲሆኑ የመክፈል የተስፋ ሰነድ ግን የተባለው ክፍያ እንደሚከፈል ቃል
የሚገባበት(promise) ሰነድ ነው፡፡18 ከዚህ የተነሳ በቼክ እና የሀዋላ ወረቀት የእዝ ሰንሰለት
ውስጥ ሰነዱን የሚያወጣው ሰው፣ ክፍያውን የሚፈጽመው ሰው እንዲሁም ክፍያው
የሚፈጸምለት ሰው የግድ ተሳታፊ ሲሆኑ የመክፈል የተስፋ ሰነድን በሚመለከት ግን ሰነዱን
የሰጠው ሰው(ከፋዩ) እና ሰነዱ የተሰጠው ሰው(ተከፋዩ) ብቻ ተሳታፎ ይኖራቸዋ፡፡19 በመሆኑም
ቼክ እና የሀዋላ ወረቀትን በሚመለከት ከፋዩ ሶስተኛ ሰው እንደመሆኑ መጠን ይህ የተባለው
ሶስተኛ ሰው ክፍያውን ስለመፈጸሙ ‘እሺ’ ማለት ይኖርበታል፡፡ በተስፋ ሰነድ ግን ከፋዩ እራሱ
ሰነዱን ያወጣው ሰው በመሆኑ ለመክፈል ‘እሺ’ ማለት አይገባውም፡፡ በተጨማሪም ሀዋላ
ወይም ቼክ ለከፋዩ ወይም ለአውጪው ለራሱ ተከፋይ ሊሆን የሚችል ሰነድ ሲሆን በተስፋ
ሰነድ ግን በምንም ሁኔታ ለአውጪው ለራሱ የሚከፈልበት ሁኔታ የለም (እራሱ ለራሱ
የሚገባው ቃል ስለማይኖር)

በቼክ እና የሀዋላ ወረቀት መካከል ያለው መሰረታዊ ልዩነት በቼክ አማካኝነት ክፍያ
እንዲፈጽም የሚታዘዘው ባንክ እና መሰል የፋይናንስ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ብቻ ሲሆን
የሀዋላ ወረቀት ግን ማንኛውም ሰው( ባንክን ጨምሮ) ሊታዘዝ ይችላል፡፡ እንዲሁም ቼክ
እንደቀረበ የሚከፈል(payable at demand) ሲሆን የሀዋላ ወረቀት ግን እንደቀረበ አልያም ወደ
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
18
የንግድ ህጉን ቁጥር 735፣827 ይመለከቷል
19
!S.S. Kundu, principles of Insurance and banking, available at
http://www.ddegjust.ac.in/studymaterial/mcom/mc-207-f.pdf retrived on 7/18/17 3: 08 Am

!
ፊት ተለይቶ በታወቀ ጊዜ የሚከፈል ሊሆን ይችላል( አንቀጽ 735፣827)፡፡ እንዲሁም ቼክ
ከተቆረጠ በኋላ ‘አትክፈል’ በሚል ትእዛዝ ክፍያ እንዳይፈጸም ማቋረጥ የሚቻል ሲሆን የሀዋላ
ወረቀትን በሚመለከት ግን ይህ ሁኔታ አይፈቀድም፡፡20

እንዲሁም በቼክ እና በሌሎቹ የሀዋላ ወረቀት፣ የተስፋ ሰነድ መካከል ያለው ሌላው መሰረታዊ
ልዩነት ወለድን በሚመለከት ነው፡፡ በቼክ ውስጥ ወለድን የሚጠቅስ ቃል ሁሉ እንዳልተጻፈ
የሚቆጠር ሲሆን ሀዋላ እና የተስፋ ሰነድን በሚመለከት ግን የወለዱ መጠን በግልጽ
እስከተቀመጠ እና በዚያው ሰነድ ላይ እስከተጻፈ ድረስ ተዋዋይ ወገኖች ወለድን በሰነዱ ውስጥ
የማስገባት መብት ያላቸው መሆኑን ከአንጽ 739፤825/2/፣ እና 835 ድምር ንባብ መረዳት
ይቻላል፡፡

ሰነዶችን ስለማስተላለፍ

ሰነዱ በተሰጠ ጊዜ በሰነዱ ላይ ያለው የባለለቤትነት መብትም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ


ከሰጪው ወደ ተቀባዩ መተላለፍ መቻሉ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን ከሌሎች የባለቤትነት
መብት ማረጋገጫ ከሆኑ ሰነዶች(ለምሳሌ የቤት ካርታ) የተለዩ ያደርጋቸዋል፡፡ በተጨማሪ
ሰነዱን በቅን ልቡና ያገኘ ሰው ሰነዱን ከሰጠው ሰው ወይም ከዋናው ባለቤት የተሻለ የመብት
ጥበቃ የሚያገኝ መሆኑ በውል ህግ እንዳለው መብትን ስለማስተላለፍ የተነገሩ ድንጋጌዎች
ተፈጻሚ አይሆኑበትም፡፡ እንደሚታወቀው ውል ግዴታ የሚፈጥረው በተዋዋይ ወገኖች መካከል
ብቻ እንደመሆኑ መጠን በውሉ የተጠቀሱ መብት እና ግዴታዎችን ወደ ሶስተኛ ወገን
ማስተላለፍ በተፈለገ ጊዜ ተዋዋይ ወገኖች ፍቃድ እና እውቅና የግድ ይላል፡፡21
ተላላፊ የገንዘብ ሰነድን በተመለከተ ግን ሰነዱን የያዘው ሰው የማንም ይሁኝታ ሳያስፈልገው
ለፈለገው ሰው ሰነዱን በዋጋ ማስተላለፍ ይችላል፡፡ እንዲሁም በአጋጣሚ ሰነዱ በእጁ የገባም
ሰው ቢሆን በክፉ ልቡና ያገኘው መሆኑ እስካልተረጋገጠ ድረስ ተጠቃሚነቱን የሚከለክለው
የለም፡፡ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፉ፣ በጁ ላደረጋቸው ሰው

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
20
የንግድ ህግ ቁጥር 857
21
Hennery campbel Black, Blacks law dictionary 9th edition, West Publishing Company, 2009
USA, page 1136

!
በሙሉ መብትን የሚያጎናጽፉ በመሆናቸው ባለእዳው ሰነዱን ለያዘው ሰው ሁሉ የመክፈል
ግዴታ አለበት22
ሰነዶችን ማስተላለፍ(የሰነዶች ተላላፊነት) ማለት ሰነዱን በህጋዊ መንገድ ያገኘው ሰው ለሌላ
ሶስተኛ ሰው የሚሰጥበት ብሎም ይህ የተባለው ሶስተኛ ሰው የሰጪውን መብት የሚያገኝበት
እና ክፍያው በራሱ ስም የሚያገኝበት መንገድ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ይህ የማስተላለፍ
አስፈላጊነትም ለተላለፈለት ሶስተኛ ሰው ሰጪው ያለውን ሙሉ መብት ለማጎናጸፍ ነው፡፡
መጀመሪያ ሰነዱን ያገኘው ሰው ለሌላ ሶስተኛ ሰው ካስተላለፈው በኋላ ሰነዱን በጅ ያደረገ ሰው
ህጋዊውን የማስተላለፍ ስርዐት ተከትሎ እስካስተላለፈ ድረስ ክልከላ የለበትም፡፡ ሆኖም ማንም
ሰው በህገ ወጥ መንገድ ያገኘውን ሰነድ ሊያስተላልፍ አይችልም፡፡
የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ ስሙ ለተጻፈለት ሰው፣ አልያም የታዘዘለት ሰው፣ አልያም
ላምጪው በሚል ሊዘጋጅ የሚችል ሲሆን ሰነዱ በእጁ የገባ ሰውም በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ
ሌላ ሰው ሊያስተላልፈው ይችላል፡፡23 በዚህ ረገድ በስም የሆነ ሰነድን በእጅ የያዘ ሰው ተጠቃሚ
ለመሆኑ በሰነዱ ላይ እና በአውጪው መዘገብ መመዝገቡ በሰነዱ ላይ ያውን መብት
እንዲጠቀምበት ስልጣን የሚሰጠው ሲሆን ላምጪው ተብሎ የተዘጋጀ ሰነድ እንደሆነ ግን
ማንኛው ሰነዱን የያዘ ሰው በሰነዱ የመጠቀም መብት አለው ማለት ነው፡፡

የማስተላለፊያ መንገዶች
1.! ሰነዱን በመስጠት ብቻ ማስተላለፍ፡- ለአምጪው ተብለው የተጻፉ የሚተላለፉ የገንዘብ
ሰነዶች ሰነዱን በማስተላለፍ ብቻ ሌላ ተጨማሪ ጽሁፍ ወይም በጀርባው መፈረም
ሳያስፈልገው ሊከናወን ይችላል፡፡ በመሆኑም ለአምጪው ተብሎ የተዘጋጀን ሰነድ በእጁ
የገባ ሰው ይህንኑ በማቅረብ ብቻ ሰነዱ ላይ ያለውን መብት ሊሰራበት ይችላል፡፡ ከፋዩም
ላምጪው ተብለው የተዘጋጁትን ሰነዶች ለያዙ ሰዎች በሙሉ ክፍያ ለመፈጸም ግዴታ
አለበት፡፡24
2.! በጀርባ በመፈረም እና ሰነዱን በመስጠት ማስተላለፍ፡- በትእዛዝ የሚለውን ሰነድ
የማስተላለፍ ተግባር በጀርባው በመፈረም እና ባለጥቅም ለሆነው ሰው ሰነዱን በመስጠት
ይፈጸማል/አንቀጽ 724/፡፡ በፊርማ ማስተላለፍ የአስተላለፊውን ፊርማ፣የሚተላለፍለትን
ሰው ስም እና ማስተላለፉ የተፈጸመበትን ቀን ይይዛል፡፡ ሆኖም ሰነዱን በፊርማ
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
22
ዝኒ ከማሁ
23
የንግድ ህግ ቁጥር 719
24
!የንግድ ህግ ቁጥር 721/1/2

!
የማስተላለፉ ነገር በቅድመ ሁኔታዎች ላይ መመስረት አይኖርበትም፡፡25 እንዲሁም
ሰነዱ ሲተላለፍ እላዩ ላይ ያለወ መብት ሙሉ በሙሉ ሳይከፋፈል ለተቀባዩ
ይተላለፋል፡፡
3.! በስም የሆነውን ሰነድ የማስተላለፍ ተግባር የሚፈጸመው፡- የተላለፈለትን ሰው ስም
በሰነድ ላይ በማግባት እና በአውጪው መዝገብም ውስጥ በመጻፍ ነው፡፡ እንዲሁም
በአዲሱ አምጪ ስም የተጻፈ አዲስ ሰነድ በመስጠት መተላለፉ ሊፈጸም ይቻላል፡፡
ይኀውም አሰጣጥ በመዝገቡ ውስጥ መመልከት አለበት፡፡26 ሆኖምየማስተላለፍ ስርዐት
ከሰነዱ የተላላፊነት ባህሪ አንጻር ለአሰራር አመቺ ባለመሆኑ በብዛት ጥቅም ላይ
የሚውል አይደለም፡፡
ማስተላለፍን በተመለከት ሊነሳ የሚገባው ሌላ አብይ ጉዳይ መደበኛ የማስተላለፍ ውጤት
(Transfer of negotiable instruments through assignment) ነው፡፡

በመሰረቱ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን ለየት ከሚያደርጓቸው ባህሪያቸው አንዱ ሰነዱ


የተላለፈለት ሶስተኛ ወገን ካስተላለፈለት ሰው የተሸለ ጥበቃ የሚያገኝ መሆኑ ነው፡፡ ይኀውም
ሰነዱን በቅን ልቡና የያዘ ሰው ባለእዳው በባለገንዘቡ ላይ የሚያነሳቸው በግል ግንኙነት ላይ
የተመሰረቱ መቃወሚያዎች አይነሱበትም፡፡ የመደበኛ የማስተላለፍ ውጤት ግን ይህንን መብት
አያጎናጽፍም፡፡ በርግጥ የንግድ ህጉ “የመደበኛ የማስተላለፍ ውጤት” ምን ማለት እንደሆነ
ትርጉም የሰጠ ባይሆንም ከሌላው ማስተላለፍ የተለየ እንደሆነ የፍትሐብሄር ህጉን አንቀጽ
1966 እንዲሁም የሌሎች ሀገራት አሰራር ተሞክሮ ዋቢ ማድረግ ይቻላል፡፡

በፍትሐብሄር ህጉ አንቀጽ 1966 እንደተነገረው ባለእዳው የገንዘቡ ማስከፈል መብት ለሌላ ሰው


ተላልፎ መሰጠቱን ባወቀበት ጊዜ በነበረውና ሊያቀርባቸው በሚችለው የመቃወሚያ ነገሮች
መብት አስተላላፊውን ሊቃወም ይችል እንደነበረው ሁሉ መብት ተቀባዩን ሊቃወምባቸው
ይችላል፡፡ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን በሚመለከት ባለእዳው በባለገንቡ ላይ የሚያነሳቸው
መቃወሚያዎች በሁለቱ መካከል ያለን ግንኙነትመሰረት ያደረገ መቃወሚያ፣ እና ጽኑ
መቃወሚያ ሲሆኑ ሰነዱን በቅን ልቡና በያዘ ሰው ላይ ግን በሁለቱ መካከል ያለን ግንኙነት

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
25
የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች መለያ ባህሪያት አንዱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ክፍያ እንዲፈጸም ትእዛዝ
የሚሰጥበት ወይም ቃል የሚገባበት መሆኑን ያስታውሷል
26
!የንግድ ህግ ቁጥር 723!

!
መሰረት ያደረገ መቃወሚያ ሊቀርብ አይችልም፡፡ መተላለፉ የመደበኛ መተላለፍ ከሆነ ግን ይህ
መቃወሚያ ሊነሳ ይችላል ማለት ነው፡፡

ለመሆኑ እንደምን ባለ ሁኔታ ነው “የመደበኛ ማስተላለፍ ውጤት” የሚፈጠረው የሚለውን


ለማየት የንግድ ህጉን ተገቢነት ያላቸውን ድንጋጌዎች መቃኘት ያስፈልጋል፡፡

የመጀመሪያው በአንቀጽ 730 የተመለከተው ሲሆን በትእዛዝ የሆነን ሰነድ በጀርባው በመፈረም
እና እና ሰነዱን በመስጠት የሚተለላፍ በመሆኑ ከዚህ ውጪ የሚደረግ ማስተላለፍ ለምሳሌ
ሰነዱን በመስጠት ብቻ የሚደረግ ማስተላለፍ መደበኛ የማስተላለፍ ውጤት ይኖረዋል፡፡ ከዚህ
የተነሳ ሰነዱ የተላለፈለት ሰው ሰነዱን ባስተላለፈለት ሰው ላይ የሚነሱ መቃወሚያዎች ሁሉ
በርሱም ላይ ይነሱበታል ማለት ነው፡፡

እንደገና ባለሰነዱ በጀርባ በመፈረም በሚያስተላልፍበት ጊዜ ‘በትእዛዝ ያልሆነ’ ወይም ይህንን


የመሰለ ቃል በሰነዱ ላይ አስገብቶ እንደሆነ መተላለፉ የመደበኛ መተላለፍ ውጤት ብቻ
የሚኖረው መሆኑን በአንቀጽ 746/2/ እና 842/2/ ተደንግጓል፡፡ ስለሆነም ይህንን የመሰል ቃል
በሰነዱ እያለ በትእዛዝ ሰነዱን ማስተላለፍ የመደበኛ የመተላለፍ ውጤትን ያስከትላል ማለት
ነው፡፡ እንዲሁም ከእንቢታ ማስታወቂያ፣27 ወይም ይህን ከመሰለ ማረጋገጫ ወይም ቼኩን
ለማቅረብ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የሚደረግ የጀርባ ፊርማ የመደበኛ የማስተላለፍ ውጤ የሚኖረው
መሆኑን በአንቀጽ 755 እና 852 ተገልጧል፡፡ በመሆኑም ሰነድ በዚህ ሁኔታ የተላፈለት ሰው
ባስተላለፈለት ሰው ላይ የሚነሱ መቃወሚያዎች ሁሉ ይነሱበታል፡፡

ሌላው ቼክን ብቻ የሚመለከት ሲሆን ‘የማይተላለፍ’ የሚል ቃል የተጻፈበትን የተሰረዘ28 ቼክ


የተቀበለ ሰው በቼኩ ላይ ቼኩን ከሰጠው ሰው የበለጠ መብት ሊኖረው አይገባም፡፡ ይኀውም
ቼኩን ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ በፈለገ ጊዜ እሱ ራሱ ካለው መብት የበለጠ መብት

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
27
! የእንቢታ ማስታወቂያ ከፋዩ እዳውን መክፈል አለመክፈሉን የሚያረጋጥበት መንገድ ሲሆን በአንቀጽ 781
እንደተገለጸው የእንቢታ ማስታወቂያ የእሺታ ወይም የእንቢታ ማስታወቂያ በባለስልጣን ጽሁፍ ማረጋገጥ የሚገባ
መሆኑን ልብ ይሏል
28
!ሰረዝ ያለበት ቼክ ለባለባንክ ወይም የባንክ ደንበኛ ለሆነ ሰው ብቻ የሚሰጥ ቼክ ሲሆን በቼኩ ፊት ለፊት ሁለት
የሰረዝ ምልክት በትይዩ በማድረግ የሚፈጸም ነው፡፡ በመሆኑም ክፍያ የሚፈጸምለት ሰው የባንክ ደንበኛ የሆነ ሰው
ብቻ በመሆኑ ቼክን በስርቆት አማኝነት ያገኘ ሰው ተከታትሎ ለመያዝ የሚያስችልን አሰራር ይፈጥራል(አንቀጽ
864)

!
ለማስተላለፍ የማይችል በመሆኑ በርሱ ላይ ሊነሱ የሚችሉ መቃወሚያዎች ሁሉ ሰነዱን በጅ
ባደረገው ሰው ላይም ተፈጻሚ ይሆንበታል (አንቀጽ 865)

የቅን ልቡና ያዥ (Holder in due course)


የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች አገኛኘትን(አያያዝ) በሚመለከት በያዡ መብት ላይ ወሳኝ ሚና
የሚኖራው ሁለት የአያያዝ ሁኔታዎች አሉ፡፡ እነዚህም ተራ ያዥ እና የቅን ልቡና ያዥ
ተብለው ይታወቃሉ፡፡

ተራ ያዥ ማንኛውም የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድን በህጋዊ መንገድ ያገኘ ሰው ሲሆን ይህ ሰው


በሰነዱ የተጠቀሰውን ገንዘብ በራሱ ስም ለማግኘት መብት ያለው ሰው ነው፡፡29 ተራ ያዥ ሰነዱ
በመጀመሪያ የተሰጠው ሰው( ተከፋዩ)፣ አልያም በፊርማ የተላፈለት ሰው ሊሆን ይችላል፡፡
ሰነዱ ላምጪው የሚከፈል ሆኖ የተዘጋጀ እንደሆነ ግን ሰነዱን በእጁ የያዘ ማንኛውም ሰው
ተራ ያዥ በመባል ይጠራል፡፡ ተራ ያዥ ስለ ገንዘብ አከፋፈሉ ያለውን መብት በተመለከተ ልክ
እንደ መደበኛ የመተላለፍ ውጤት፣ በመደበኛው የውል ህግ መብትን ስለማስተላለፍ
የሚመለከቱ ህግጋት ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡30 እንደሚታወቀው በውል ህግ አንድ ሰው
በባለቤትነት ወይም በባለይዞታነት የያዘውን መብት ከሚያስተላልፍ በቀር ካለው መብት በላይ
ሊያስተላልፍ አይችልም፡፡ እንዲሁም የማስተላለፉን ተግባር ሲያከናው ለባለእዳው ማሳወቅ
ግዴታ አለበት፡፡ በመሆኑም በውል መሰረት የተገኘን መብት/ግዴታ የተላለፈለት ሰው መብቱን
ባስተላለፈለት ሰው ላይ ሊነሱ የሚችሉ መቃወሚያዎች ሁሉ ይነሱበታል ማለት ነው፡፡
እንዲሁም ባለእዳው መተላለፉን አልቀበልም በሚል ውሉን ለመፈጸም እንቢ ለማለት
ይችላል፡፡ በተመሳሳይ ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶችን በሚመለከት ተራ ያዥ የሆነ ሰው በውል
መሰረት መብት እንደተላለፈለት ሰው ሁሉ ሰነዱን ባስተላለፈለት ሰው ላይ ስለ ገንዘቡ
አከፋፈል ሊነሱ የሚችሉ መቃወሚያዎች ሁሉ ይነሱበታል፡፡

ነገር ግን ሰነዱን የያዘው ሰው የሰነድ አገኛኘቱ በቅን ልቡና የተፈጸመ እንደሆነ የቅን ልቡና
ያዥ ነውና በህግ ልዩ ጥበቃ ይደረግለታል፡፡ በንግድ ህጉ አንቀጽ 718 እንደተመለከተው
መዘዋወሩን በሚመሩት ደንቦች መሰረት በቅን ልቡና አንድ የማይተላለፍ የገንዘብ ሰነድ እጅ

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
29
! Edward T. Fagan, The Concept of Good Faith in Negotiable Instrument Law, Indian Law
Journal, article 2, volume 32 issue I 1956, page 9
30
የፍትሐብሄር ህግ ቁጥር 1966 እና ተከታዮቹን ይመለከቷል

!
ያደረገ ሰው መልስ ተብሎ ሊከሰስ አይችልም በሚል ባለመብቱን የሚጠብቅ ድንጋጌ የተካተተ
ሲሆን ከፍ ብሎ በአንቀጽ 717/3 ዝቅ ብሎ በአንቀጽ 752፣ 850 ላይ ደግሞ አምጪው ሰነዱን
ባገኘበት ጊዜ እዳ ከፋዩን ለመጉዳት ሆነ ብሎ ያደረገው ነገር ካልሆነ በቀር ከዚህ በፊት ሰነዱን
ይዘው ከነበሩት ሰዎች ጋር በግል ግንኙነቶች ላይ የተመሰረቱት መቃወሚያዎች እዳ ከፋዩ
ሰነዱን የያዘውን ሰው ሊቃወሙት አይችሉም በሚል ተደንግጓል፡፡ ይህ ማለት ባጭሩ
በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ላይ ከሚነሱ መቃወሚያዎች አንዱ የሆነው በግል ግንኙነት ላይ
የተመሰረተ መቃወሚያ በቅን ልቡና ያዥ ላይ አይነሳበትም ማለት ነው፡፡
ሆኖም ሰነዱ እንዴት ባለ ሁኔታ ሲያዝ ነው አንድ ሰው የቅን ልቡና ያዥ ነው ሊባል
የሚችለው? የሚለውን የንግድ ህጉ መመዘኛዎችን አላስቀመጠም፡፡ በመሆኑም በአፈጻጸም ረገድ
ሊነሳ የሚችለውን ክርክር ለመቋጨት የፍትሐብሄር ህጉን ስለንብረት ባለቤትነት የሚደነግጉ
ድንጋጌዎች ፣ የሌሎች ሀገራትን ህግጋት፣ እንዲሁም የፍርድቤት ውሳኔዎች መመልከት
ያስፈልጋል፡፡
በፍትሐብሄር ህጉ አንቀጽ 1128 የገንዘብ እና ሌሎችም ግዙፍነት የሌላቸው ነገሮች መብቶች
ላምጪው በተሰጠው ሰነድ ውስጥ ሲገኙ እንደ ተንቀሳቃሽ ንብረት ሆነው የሚቆጠሩ መሆኑን
በመግለጹ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች እንደሚንቀሳቀሱ ንብረቶች የሚቆጠሩ መሆኑን ልብ
ይሏል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በፍትሐብሄር ህጉ አንቀጽ 1161 ቅን ልቡና ሲተረጎም ግዙፍነት
ያለው የተንቀሳቃሽ ነገር ባለሃብት ለመሆን በቅን ልቡና ዋጋ ሰጥቶ ውል የተዋዋለ ሰው
የተባለውን ተንቀሳቃሽ ነገር እጅ ሲያደርግ በቅን ልቡናው ምክንያት የዚህ ንብረት ባለሀብት
ይሆናል ተብሏል፡፡ ከዚህ ትርጓሜ መረዳት የሚቻለው አንድ ሰው የቅን ልቡና ያዥ ነው
ለመባል አንድም ንብረቱን በዋጋ መያዝ የሚገባው መሆኑን፣ እንዲሁም ደግሞ ንብረቱን በጅ
ማድረግ የሚገባው መሆኑን ነው፡፡ ይህንን አጠቃይ ትርጓሜ ለሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች
በመጠቀም ሰነዱን በቅን ልቡና በተደረገ ውል በዋጋ ያገኘ እና በእጁ ያደረገ ሰው የዚሁ ሰነድ
እና በውስጡ የያዘውን ሀብት ባለቤት መሆኑን መረዳት ያሻል፡፡
የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን በሚመለከት የቅን ልቡና ያዥ በሌሎች አገራት ሰፋ ያለ መመዘኛ
የተቀመጠለት ሆኖ እናገኘዋን፡፡ አንድ ሰው ሰነዱን በዋጋ ያገኘ እንደሆነ፣ ሰነዱን በሚያገኝበት
ጊዜ ምንም አይነት መቃወሚያ (ከባለቤትነት አንጻር) ሊነሳበት አይችልም ብሎ በበጎ ህሊና
በማመን የተቀበለ እንደሆነ፣ ሰነዱን የመክፈያ ጊዜው ሳያልፍ የተቀበለ እንደሆነ፣ በሰነዱ ላይ
በግልጽ የሚታይ የማጭበርበር፣ የመለወጥ ስራ የሌለበት እንደሆነ አምጪው በቅን ልቡና
እንዳገኘው ይቆጠራል፡፡ በጥቅሉ ሰነዱን የያዘው ሰው ሰነዱን ባገኘበት ጊዜ ሰነዱን በህግ ፊት

!
ዋጋ የሚያሳጡት ነገሮች ያሉበት መሆኑን እውቅና የሌለው እንደሆነ የቅን ልቡና ያዢ ነው
ለማለት ይቻላል፡፡ አለማወቁም የመነጨው በሰነዱ ላይ የሰነዱን ህጋዊነት የሚያሳጡ ሁነቶች
በማንኛውም ምክንያታዊ ሰው አይን በግልጽ ሊታዩ የማይችሉ የሆኑ እንደሆነ ነው31
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ነጥብ አንድ ሰው ሰነዱን በቅን ልቡና አልያዘም ማለት በክፉ
ልቡና ይዞታል ተብሎ ሊያስገምተው ይችላል ወይ የሚለው ነው፡፡ ይህንን በሚመለከት
በአንቀጽ 717/1/3፣ 752፣ 850 ድጋጌዎች መካከል ተቃርኖ ወይስ ተመጋጋቢነት አለ
የሚለውም የክርክር መንስኤ እንደሆነ አቶ ገዙ አየለ የኢትዮጵያ የባንክ እና የሚተላለፉ
የገንዘብ ሰነዶች በሚል ርዕስ ባዘጋጁት መጽሀፍ ገልጸዋል፡፡32 እንደ አቶ ገዙ ገለጻ በ አንቀጽ
717/1/3 በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች አከፋፈል ላይ ስለሚቀርቡ መቃወሚያዎች በሚደነግገው
ድንጋጌ ላይ ባለ እዳው ሰነዱን በያዘው ሰው ላይ የግል ግንኙነታቸውን መሰረት ያደረገ
መቃወሚያ ሊያነሳ የሚችል መሆኑን የደነገገ ሲሆን በአንቀጽ 752፣ 850 ላይ ደግሞ
አምጪው ሰነዱን ባገኘበት ጊዜ እዳ ከፋዩን ለመጉዳት ብሎ ያደረገው ካልሆነ በቀር በሀዋላ
ወረቀት፣ በቼክ መሰረት እንዲከፍሉ የተጠየቁት ሰዎች አውጪው ጋር ከቀድሞዎቹ
አምጪዎች ጋር ባላቸው በግል ግንኙነታቸው በተመሰረቱት መከላከያዎች አምጪውን
ሊቃወሙት አይችሉም ይላል፡፡ በጠቅላላው የህጉ ክፍል የግል ግንኙነቶች መቃወሚያ ሆነው
መነሳት የሚችሉ መሆናቸው ሲደነገግ በልዩ ክፍሉ ደግሞ የግል ግንኑነት መቃወሚያ ሆኖ
የሚነሳው ሰነዱን የያዘው ሰው እዳ ከፋዩን ለመጉዳት ሆነ ብሎ ያደረገ እንደሆነ ነው በሚል፣
በተለይም ቼክን በሚመለከት ቼክ በባህሪው እንደቀረበ የሚከፈል ሰነድ በመሆኑ የግል
ግንኑነትን መሰረት ያደረገ መቃወሚያ ሊነሳበት አይችልም ከዚህ አንጻር እኒህ ድንጋጌዎ እርስ
በርስ የሚጋጩ በመሆኑ ሊሻሻሉ ይገባል በሚል አስተያየት ተሰጥቷል፡፡ ሆኖም እነዚህ
ድጋጌዎች በርግጥ እርስ በርስ ይመጋገባሉ ከሚባ በቀር ይጋጫሉ ወይ የሚለውን መመልከት
ያሻል፡፡
መጀመሪያ ክፉ ልቡና ማለት ምን ማት ነው የሚለውን ስንመለከት
“Bad faith is an intentional dishones act by not fulfilling legal or
contractual obligations, misleading another, entering in to an

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
31
ከላይ የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 28 ገጽ 18
32
ገዙ አየለ መንግስቱ፣የኢትዮጵያ የባንክ እና የሚተላፉ የገንዘብ ሰነዶች ሕግ፣ 2009፣ ገጽ 146

!
agreement without the intention or means to fulfil, or violating basic
standards of honesty in dealing with others”33
ይህም በግርድፉ ሲተረጎም አንድ ሰው ያለበትን የውል ወይም የህግ ግዴታ ላለመወጣት
በማሰብ ሆነ ብሎ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት የፈጸመ እንደሆነ፣ ሌሎችን ያታለለ እንደሆነ፣
የማይፈጽመውን ግዴታ ስምምነት ያደረገ እንደሆነ፣ እንዲሁም ከሌሎች ሰዎች ጋር በሚኖረው
መስተጋብር ከታወቁት የእውነተኛት መርህ በተቃራኒው የሚሰራ እንደሆነ ክፉ ልቡና አለው
ማለት ነው፡፡ ከዚህ ትርጉም የምንረዳው የክፉ ልቡና መኖር የቅን ልቡና አለመኖርን የሚያሳይ
መሆኑን ነው፡፡
አንድ የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ የያዘ ሰው ሰነዱን በዋጋ ያገኘ እንደሆነና ሰነዱን በሚያገኝበት
ጊዜ በሰነዱ ላይ ማናቸውም አይነት መቃወሚያ አይነሳበትም ብሎ በማመን የያዘ እንደሆነ
የቅን ልቡና ያዥ በመሆኑ በባለእዳው እና ሰነዱን ባስተላለፈለት ሰው መካከል ያለ የግል
ግንኙነትን መሰረት ያደረጉ መቃወሚያዎች አይነሱበትም፡፡ ሆኖም ይህ ሰው ሰነዱን
በሚይዝበት ጊዜ በክፉ ልቡና እዳ ከፋዩን ሊጎዳ የሚችል አድራጎት በመፈጸም ሰነዱን ያገኘ
እንደሆነ፣ ማለትም ሰነዱ የትኛውም አይነት መቃሚያ ሊነሳበት የሚችል መሆኑን እያወቀ፣
ወይም የሰነዱ መክፈያ ጊዜ ማለፉን እያወቀ ሰነዱን የተቀበለ እንደሆነ እዳ ከፋዩን ለመጉዳት
ሆነ ብሎ በክፉ ልቡና ያገኘው ነውና ሰነዱን ባስተላለፈለት ሰው ላይ ሊነሳ የሚችለው
ማናቸውም አይነት መቃወሚያ በርሱም ላይ ደግሞ ይነሳበታል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ሰነዱን
በሚያገኝበት ጊዜ እዳ ከፋዩ ላይ ተገቢ ያልሆነ ጫና ለማሳደር ያደረገው ነገር ከሌለ እና ሰነዱን
በህጋዊ መልኩ በዋጋ ያገኘው እንደሆነ ይህ ሰው የቅን ልቡና ያዥ ነውና በእዳ ከፋዩ እና
ሰነዱን ባስተላፈለት ሰው መካከል ያለን ግኙነት መሰረት ተደርጎ መቃወሚያ አይነሳበትም፡፡
በተጨማሪም አንቀጽ 717/1 በባለገንዘቡ እና በባለ እዳው መካከል ያለን ግንኙነት በነርሱው
መካከል መነሳት የሚችል መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን ንዑስ አንቀጽ 3 ግን ይህ በሁለቱ
መካከል ያለ ግንኙነት ሰነዱ በተላለፈለት ሰው ላይ( እዳ ከፋዩን ለመጉዳት ያደረገው ነገር ከሌለ
በቀር) የማይሰራ መሆኑን የሚገልጽ ነው፡፡ በዚሁ ትክክል አንቀጽ 752፣ 858 እንደሚደነግጉት
ይህ በሁለቱ መካከል ያለ ግንኙነት ሰነዱ በተላለፈለት ሰው ላይ የሚነሳው፣ ሰነዱን በክፉ
ልቡና ባለእዳውን የሚጎዳ አድራጎት በመፈጸም ያገኘው እንደሆነ ነው

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
33
ከላይ የግርጌ ማስታወሻ ቁጥ 21 ገጽ 159

!
በመሆኑም አንቀጽ 752፣850 የአንቀጽ 717/1/3/ ማብራሪያዎች እንጂ ተቃራኒዎች
እንዳልሆኑ፣ ብሎም ማስረዳት እስከተቻለ ድረስ የቅን ልቡና አለመኖር የክፉ ልቡና መኖር
አመላካች መሆኑን መረዳት ተገቢነት ይኖረዋል፡፡34
ሰነዱን የያዘው ሰው በግል ግንኙነት ላይ የተመሰረተ መቃወሚያ ሳይቀርብበት ለክፍያ የተገባ
ነው ለማለት ይህ ሰው የቅን ልቡና ያዥ መሆን ይገባዋል፡፡ ተራ አምጪ የሆነ እንደሆነ ግን
ሰነዱን ባስተላለፈለት ሰው ላይ ሊነሳ የሚችል ማናቸውም አይነት መቃወሚያ በርሱም ላይ
ደግሞ ሊነሳበት ይችላል፡፡ ከዚህም የተነሳ የቅን ልቡና ያዥ ከጠቅላላው ውል ህግ በልዩ ሁኔታ
መዘዋወሩን በሚመሩት ህግጋት መሰረት ሰነዱን ያገኘው እንደሆነ ሰነዱን ካስተላለፈለት ሰው
የተሻለ ጥበቃ ይደረግለታል፡፡35 ሆኖም የሰነዱን ይዘት መሰረት አድርገው ሊነሱ የሚችሉ ጽኑ
መቃወሚያዎች ሊነሱበት የሚችሉ መሆኑ እንደተጠበቀ ነው፡፡

የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች አከፋፈል ላይ የሚነሱ መቃወሚያዎች


አምጪው ሰነዱን የያዘበት አኳኋን ስለገንዘቡ አከፋፈል እንዲሁም በከፋዩ በኩል ሊነሱበት
የሚችሉትን መቃወሚያዎች ይወስናል፡፡ ይኀውም አምጪው በተላላፊ የገንዘብ ሰነዶች
የመጠቀም መብት የቅን ልቡና ያዥ ወይም ተራ ያዥ መሆኑ የሚነሱበት መቃወሚያዎች
ብሎም ገንዘቡን የማግኘት መብቱን ይወስናል፡፡

በመሰረቱ በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን በሚመለከት ባለእዳው/አውጪው/ ሁለት አይነት


መቃወሚያዎችን በማንሳት ገንዘቡ ተከፋይ እንዳይሆን ማድረግ እንዲችል የህግ ጥበቃ አለው፡፡
እኒህ መቃወሚያዎች አንዱ በማንኛውም ሰው ላይ ሊነሱ የሚችሉ መቃወሚያዎችን
የሚጠቀልል ጽኑ መቃወመያ ሲሆን ሌላው መቃወሚያ ግን በተራው ያዥ ላይ ብቻ ወይም
በመደበኛ የመተላለፍ ስርዐት በተላለፈለት ሰው ላይ ሊነሱ የሚችሉ የመቃወሚያ ዝርዝሮችን
የያዘ ሆኖ በአውጪው እና ሰጪው የሁለቱ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ መቃወሚያ ተብሎ
ይጠራል፡፡
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
34
የፌዴራል ጠቅላይ ፍድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአመልካች ሉሀና ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኃ/የ/የግ/ ማህ እና
በተጠሪ ማክሮ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ በፋይል ቁጥር 90434፣ የቼክን አከፋል በተመለከተ ባለ
እዳው ከአምጪው ጋር በሁለቱ የግል ግኙነት የተመሰተረ መቃወሚያ ካለው ማስረጃ አቅርቦ የማሰማት መብት
እንዳለው እና ክሱ ቼክን የተመለከተ በመሆኑ ብቻ በተፋጠነ ስነስርዐት መታየት አለበት የሚባል አለመሆኑን፣
አምጪው ሰነዱን በሚይዝበት ጊዜ በክፉ ልቡና የያዘ እንደሆነም ይኀው መቃወሚያ ሆኖ ሊቀርብበት እንደሚችል
ተወስኗል
35
የንግድ ህግ ቁጥር 718

!
የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ የመተላለፍ ባህሪው በሰነዱ አከፋፈል ላይ
የሚነሱ መቃወሚያዎች አጠቃቀም ላይም የራሱ የሆነ ተጽእኖ አለው፡፡ ይኀውም በግል
ግንኙነት ላይ የተመሰረተው መቃወሚያ በሰጪው እና ተቀባዩ መካከል ብቻ ተወስኖ የሚቀር
ሲሆን ሰነዱ ወደ ሌላ ሰው ከተላለፈ ሰነዱን የተቀበለው ሰው ይህ አይነቱ መቃወሚያ
የሚነሳበት ሰነዱን ካስተላፈለት ሰው ጋር ብቻ ባለው ግንኙነት ነው፡፡ ጽኑ መቃወሚያ የሆነ
እንደሆነ ግን ሰነዱን በሰጠው እና በተቀበለው ሰው መካከል ብቻ ሳይወሰን ሰነዱ ለተላለፈለት
በማንኛውም ሰው ላይ ሊነሳ ይችላል፡፡

በርግጥ በሁለቱ ግንኙነትን መሰረት አድርጎ የሚነሳ መቃወሚያ በከሳሽ እና ተከሳሽ መካከል
ያለን ግንኙነት መሰረት አድርጎ የሚነሳ መቃወሚያ ተብሎ ሊወሰድ ሲችል አንድም ለሰነዱ
መሰጠት ምክንያት የሆነው ግንኙነትን አልያም ሌላ ህጋዊ ግብይት የተካሄደበት ግንኙነትን
መሰረት ያደረገ ሊሆን ይችላል፡፡ ጽኑ መቃወሚያ በሌላ በኩል በሰነዱ በራሱ ላይ ባሉ
ጉድለቶች ላይ ተመስርቶ የሚነሳ መቃወሚያ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

የንግድ ህጉ በአንቀጽ 717/1/ ስለመቃወሚያዎች ሲደነግግ ዕዳ ከፋዩ ሰነዱን በያዘው ሰው


በሁለቱ የግል ግንኙነቶች ላይ በተመሰረቱት፣ በሰነዱ አጻጻፍ ፎርም፣ እና እንዲሁም በሰነዱ
ላይ በተጻፉት ቃሎች ካልሆነ በቀር ሌላ መቃወሚያ ሊቀርብበት አይችልም፡፡ እንዲሁም
ፊርማን በማስመሰል የተሰራ፣ ችሎታ ወይም ሰነዱ ሲወጣ የውክልና ስልጣን ባለመኖሩ ወይም
ክስ ለማቅረብ አስፈላጊ የሆኑት ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው የተነሱትን መቃወሚዎች
ለማቅረብ ይችላል ሆኖም አምጪው ይህን ሰነድ ባገኘበት ጊዜ እዳ ከፋዩን ለመጉዳት እያወቀ
ያደረገው ካልሆነ በቀር ከዚህ በፊት ሰነዱን ይዘው ከነበሩት ሰዎች ጋር በግል ግንኙነት ላይ
በተመሰረቱ ክርክሮች እዳ ከፋዩ ሰነዱን የያዘው ሰው ሊቃወመው አይችልም በሚል
አስቀምጧል፡፡ በሌላ በኩል አምጪው የሀዋላ ወረቀቱን ወይ ቼኩን ባገኘበት ጊዜ አውቆ እዳ
ከፋዩን ለመጉዳት ካላደረገ በቀር በሀዋላ ወረቀቱ መሰረት እንዲከፍሉ የተጠየቁ ሰዎች ወይም
በቼኩ መሰረት የተከሰሱ ሰዎች ከአጪው ጋር ወይ በፊት አምጪ ከሆኑት ጋር በግል
ግኙነታቸው በተመሰረቱ መቃወሚያዎች አምጪው ሊቃወሙት አይችሉም በሚል በአንቀጽ
752፣850 ተደንግጓል፡፡

እኒህ ድንጋጌዎች ሰፊ እና ጥልቅ የሆኑ ዝርዝር መመዘኛ ሊወጣላቸው የሚገቡ ሀሳቦችን


በጥቅል የያዙ ቢሆንም በዚህ ረገድ በህግ የተሰጠ ትርጓሜ የለም፡፡ በትርጉም የዳበረ አሰራርም
በብዛት አይታይም፡፡ በተለይ በሁለቱ የግል ግንኙነቶች ላይ የተመሰረቱ መቃወሚያዎች ምን

!
ምንን የሚያካትቱ ናቸው? ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ መለያ ባህሪው ያለ
ምንም ቅድመ ሁኔታ ክፍያ መፈጸም ሆኖ ሳለ በሁለቱ የግል ግንኙነት የተነሳ ክፍያን
መቃወም ይህንን ባህሪ የሚጻረር አይሆንም ወይ የሚለው ሌላ መልስ የሚያሻው ነጥብ ነው፡፡
በተጨማሪም ይህ በሁለቱ መካከል ያለ ግንኙነት እንደ መቃወሚያነት የሚነሳው ሰነዱ
መጀመሪያ ለተሰጠው ሰው ላይ ብቻ ነው ወይስ ከርሱ በኋላ በህግ መሰረት ለተላለፈላቸው
ሰዎችም ነው የሚለውም አብሮ መታየት ይኖርታል፡፡

የንግድ ህጉ አንቀጽ 717 ሲታይ ሁለቱንም አይነት መቃወሚዎች ማለትም በሁለቱ መካከል
ያለን ግንኙነት መሰረት ያደረገን መቃወሚያን እንዲሁም ጽኑ መቃሚያን በአንድነት አጣምሮ
የያዘ ድንጋጌ ሆኖ እናገኘዋለን

1.1.! በአውጪው እና ሰጪው መካካል ያለን ግንኙነት መሰረት ያደረገ መቃወሚያ፡-

ለህትመት ከበቁት የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድቤት የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች መካከል በቅጽ
12 በፋይል ቁጥር 24435 ላይ በሁለቱ የግል ግንኘነቶች ላይ የተመሰረቱ መቃወሚያዎች ምን
ማለት እንደሆነ ሲያብራራ አንቀጽ 717 ሁለት አይነት ገጽታ ያላቸውን መቃወሚያዎችን የያዘ
ሲሆን በንዑስ አንቀጽ 1፣3 የተመለከተው በከሳሽ ተከሳሽ መካከል የሚኖርን ግንኙነት
በመካከላቸው የሚቀር ግንኙነት እንጂ በሌሎች ሰዎች ላይ ሊነሱ የማይችሉ መቃወሚያዎች
ባለመሆናቸው ሰነዱን ለሌላ ያስተላለፈ ሰው ክፍያውን እንዲፈጽም ክስ ሲቀርብበት ከሌሎች
አምጪዎች ጋር ወይም ከዋናው አውጪ ጋር ያለውን የግል ግንኙነት መሰረት አድርጎ
አምጪውን ሊቃወመው አይችልም፡፡ ይህ ሰው ግን ከአምጪው ከራሱ ጋር ያለውን የግል
ግንኙነት መሰረት አድርጎ ሊቃወመው ይችላል፡፡ ይኀም right in personem ከሚለው
መሰረታዊ መርህ የመነጨ በመሆኑ መቃወሚያው በከሳሽ ተከሳሽ መካከል የሚቀር እንጂ
ሌሎች ሰዎች ላይ ተግባራዊ አይሆንም፡፡ በሌላ በኩል በንዑስ አንቀጽ 2 ላይ የተመለከቱ
መቃወሚያዎች ሰነዱን የሚመለከቱ መቃወሚያዎች ሲሆኑ ሰነዱን በጁ ባደረገ በማኛውም
ሰው ላይ ሊነሱ የሚችሉ እና ሰነዱን ተከትለው የሚሄዱ መቃወሚያዎች በመሆናቸው real
defence በመባል የሚታወቁ እና right in rem የሚለውን መርህ ተከትለው የተሰናዱ
መቃወሚያዎች መሆናቸውን ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡36 በተጨማሪም በሁለቱ መካከል ያለን

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
36
! የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ በአመልካች ሀጂ መሀመድ አደም፣ በመልስ ሰጪ
ፍጹም ግርማ፣ የፋይል ቁጥር 24435፣ ቅጽ 12 ገጽ 521-524

!
ግኙነት ምን ሊሆን ይችላል የሚለውን በሚመለከት ደግሞ የህ ግንኙነት ሊተረጎም የሚገባው
የንግድ ህጉን አላማ የሚያሳካ እና ከተለመደው የንግድ እና ግብይት ግንኙነቶችን እንጂ ከነዚህ
ውጪ የሚኖሩ ግላዊ ግንኙነቶችን የሚመከት ሊሆን አይችልም በሚል ተብራርቷል፡፡37 ይህ
ማብራሪያ በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚገባ ሁኔታ የተሰጠ ማብራሪያ እና ሌሎች ክርክሮች
ሊቋጩ የሚገቡበት ሁኔታዎች የሚያመላክት፣ ከሌሎች ሀገራት የህግ ማዕቀፋትም የሚስማማ
በመሆኑ ፍርድቤቶች ተግባራዊ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡

ለመሆኑ በባለእዳው እና ባለገንዘቡ መካከል ያለ ግንኙነት ምን ምን ሁኔታዎችን ያጠቃልላል?


የንግድ ህጉ አንቀጽ 717/1/3/ በሁለቱ መካከል ያለን ግንኙነት ምን ምን እንደሚያጠቃልል
ዝርዝር ሁኔታዎች የሌሉት በመሆኑ፣ ከላይ በሰበር ችሎቱ የተሰጠው ማብራሪያም በሁለቱ
መካከል የሚኖር ግንኙነት ምንድነው የሚለውን ከመግለጽ ባለፈ ምን ምን ጉዳዮችን ይይዛል
የሚለውን የሚዘረዝር ባለመሆኑ፣ ለመረዳት ያመች ዘንድ ከሌሎች ሀገራት የህግ ማእቀፎች
በተለይም የሚተላፉ የገንዘዘብ ሰነዶች ጅማሬ የሆነው UCC ያሰናዳውን መመልከት ተገቢነት
ይኖረዋል፡፡ ከዚህ አንጻር ሰነዱን በሰጠው እና ሰነዱን በተቀበለው ሰው መካከል ያለን ግብይት
መሰረት ያደረገ ግንኙነት ሲሆን ከዚህ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡፡

ውልን አለመፈጸም፡- ሰነዱ እንዲሰጥ ምክንያት የሆነን ውል በተቀባዩ በኩል ያልተፈጸመ


እንደሆነ ሰነዱን ያወጣው ሰው እንደውሉ አልፈጸመም በሚል ገንዘብ እንዳይከፈል መቃወሚያ
ሊያደርገው ይችላል፡፡38

የቅድመ ሁኔታዎች አለመሟላት፡- እንዲሁም አንድ ውል ሲመሰረት በቅድመ ሁኔታዎች ላይ


እንዲቆም ተደርጎ የተመሰረተ እንደሆነ የቅድመ ሁኔታው መሟላት/አለመሟላት/ በሰነዱ ላይ
የተገለጸውን መብት እንዳይጠቀም መቃወሚያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡39

ያለዋጋ የተሠጠ ሰነድ፡- የሚተላለፈው ሰነድ የተሰጠው ያለ ዋጋ እንደሆነ ሰጪው ኋላ


አልከፍልም ለማለት አልያም ክፍያው እዳይፈጸም መቃወሚያ ሊያቀርብ ይችላል:: በዚህ ረገድ
ቀደም ባሉት ጊዜያት የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ የሚሰጠው ገንዘብ ለማስተላለፍ አላማ በመሆኑ

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
37
ዝኒ ከማሁ
38
ከላይ የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 7 ገጽ 368
39
ከላይ የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 6 ገጽ 837-838!

!
በሰጪው እና ተቀባዩ መካከል ተመዛዛኝ ጥቅም አለ ተብሎ ይገመታል፡፡ በመሆነም ያለዋጋ
የተሰጠ ሰነድ ይህንኑ ምክንያት በማድረግ መቃወሚያ ማድረግ ይቻላል፡፡40

መሳሳት፡- አንድ ውል በሚደረግበት ጊዜ የሚፈጠር መሳሳት ለውሉ መፍረስ ምክንያት


እንደሚሆነው ሁሉ አንድን ውል ተፈጻሚ ለማድረግ የሚሰጥ ተላላፊ የገንዘብ ሰነድ በዋናው
ውል ላይ መሳሳት የተፈጠረ እንደሆነ ይህ ስህተት ሰነዱ ጥቅም ላይ እንዳይውል መቃወሚያ
ሆኖ ሊቀርብ ይችላል፡፡41

መብትን መተው፡- ባለገንዘቡ ለባለ እዳው ገንዘቡን ወይም መብቱን በህግ አግባብ የተወለት
እንደሆነ ሆኖም ሰነዱ ለሌላ ሶስተኛ ወገን ተላልፎ እደሆነ ይህ ሶስተኛ ወገን ተራ ያዥ የሆነ
እንደሆነ ዋናው ባለገንዘብ መብቱን መተው ገንዘቡ እንዳይከፈል መቃወሚያ ሆኖ ያገለግላል፡፡

ያለ ሰነድ ክፍያ መፈጸም፡- በተወሰኑ ሁኔታዎች ሰነዱ ሳይይቀርብ ክፍያ ሊፈጸም ይችላል፡፡
እንዲህ በሆነ ጊዜ ምንም እንኳ ሰነዱ ለሌላ ሶስተኛ ወገን ተላልፎ ቢሆንም ይህ ሶስተኛ ወገን
የቅን ልቡና ያዥ ካልሆነ በቀር ባለእዳው የገንዘቡን ቀድሞ መከፈል እንደ መቃወሚያ ሊነሳው
ይችላል፡፡

የሰነዱ መሰረቅ፡- የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ በእጁ የያዘ ሰው የሰነዱ ባለመብት እንደሆነ
የሚገመት በመሆኑ ሰነዱ የመሰረቅ እና ትክክለኛ ባለመብት ያልሆነው ሰው እጅ የመግባት
እድሉ ከፍ ያለ ነው፡፡ በመሆኑም ሰነዱን በእጁ ያደረገ ሰው ተራ አምጪ የሆነ እንደሆነ የሰነዱ
መሰረቅ መቃወሚያ ሆኖ ይቀርብበታል ሆኖም አምጪው የቅን ልቡና ያዥ የሆነ እንደሆነ ይህ
መቃወሚያ ሊነሳበት አይችልም፡፡ ሆኖም ሰነዱን በሀሰት አመሳስሎ የሰራ እና ባለመብት የሆነ
ሰው(ከተረጋገጠበት) እንደ ተራ አምጪ አይቆጠርም42

በሰነዱ ላይ ያለፈቃድ ተጨማሪ ነገሮችን ማስገባት፡- ሰነዱ አውጪው ባልፈቀደበት እና


በማያውቅበት ሁኔታ አዲስ ነገር የተጨመረበት እንደሆነ ይህ ሁኔታ መቃወሚያ ሆኖ ሊነሳ
ይችላል፡፡ ነገር ግን በሰነዱ ላይ ያለፈቃድ ቁጥር፣ አሀዝ መጨመር በሀሰት አመሳስሎ

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
40
!ዝኒ ከማሁ
41
ከላይ የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 37
42
ዝኒ ከማሁ

!
ከመስራት የሚለይ በመሆኑ በማንኛውም ተራ አምጪ ላይ መቃወሚያ ሆኖ የሚነሳ ሲሆን
በቅ ልቡና ያዥ ላይ ግን መቃወሚያ አይሆንበትም፡፡ በሚወጣበት ጊዜ ጉድለት ያለው ቼክ
ለተደረጉት ስምምነቶች ተቃራኒ በመሆን የተሞላ እንደሆነ በክፉ ልቡና ቼኩን ካላገኘ ወይም
ሲያገኝ ከባድ ጥፋት ካላደረገ የነዚህ ስምምነቶች አለመፈጸም በአምጪው ላይ መቃወሚያ
ሊሆን አይችልም43

ማታለል፡- ከተዋዋይ ወገኖች አንዱ ውሉን ያደረገው በመታለል እንደሆነ ክፍያ እዳይፈጸም
መቃወሚያ ሆኖ ሊነሳ ይቻላል፡፡ ማታለሉም የመተፈጸመው ውሉን በሚመለከቱ መሰረታዊ
ፍሬ ነገሮች እንደሆነ ተታላዩ ባይታለል ኖሮ ውሉን አይዋዋልም ነበር ለማለት የሚያስችል
ሲሆን በተራ ያዥ ላይ መቃወሚያ ሆኖ ሊነሳ ይችላል( የፍትሐብሄር ህጉን ድንጋጌዎች
ይመለከቷል)

በርግጥ እኒህ መዘርዝሮች ፍጹማውያን ናቸው ማለት አይደለም በመሆኑም ፍርድቤቶች


በሁለቱ መካከል በተመሰረቱት ግንኙነቶች ግንኙነቶቹ ህጋዊ ግብይት የተደረገባቸው
መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ክርክር እንዲደረግባቸው ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

አንዳንድ ጸሀፍት የሁለቱ የግል ግንኙነት በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ላይ በተለይም እንደ ቼክ
ባሉ ሰነዶች ላይ ሊነሱ አይገባም በዚህ ረገድ ያለውም የህግ ድንጋጌ ሊሻሻል ይገባል የሚል
መከራከሪያ ያቀርባሉ44፡፡ ምክንያቸውንም ሲያስቀምጡ ቼክ የዋስትና ሰነድ ሆኖ የሚያለግል
ተላላፊ የሰነድ አይነት አይደለም፡፡ ይልቁንም የቼክ ዋነኛ ተግባር እና አገልግሎት ጥሬ ገንዘብን
ተክቶ በቀረበ ጊዜ ለክፍያ መክፈያነት ማገልገል እና ጥሬ ገንዘብ ይዞ የመንቀሳቀስ ችግር
መቅረፍ ነው እንጂ እንደ ዋስትና ሰነድነት ማገልገል አይደለም፡፡ በመሆኑም ይህ አይነት
መቃወሚያ ሊቀርብበት አይገባም በሚል ይከራከራሉ፡፡ በርግጥ ይህን አይነት መከራከሪያ ከሳሽ
ተከሳሾችም ፍርድቤት ሲቀርቡ የሚያቀርቡት መሆኑን ከተለያዩ መዛግብት መረዳት ይቻላል፡፡45

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
43
!የንግድ ህግ ቁጥር 744፣ 841
44
ገዙ አየለ መንግስቱ፣ የኢትዮጵያ የባንክ እና የሚተላለፉ ሰነዶች ህግ፣ 2009፣ ገጽ 146-148
45
የፌዴራል ጠቅላይ ፍድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአመልካች ሉሀና ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኃ/የ/የግ/ ማህ እና
በተጠሪ ማክሮ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ በፋይል ቁጥር 90434፣ የቼክን አከፋል በተመለከተ ባለ
እዳው ከአምጪው ጋር በሁለቱ የግል ግኙነት የተመሰተረ መቃወሚያ ካለው ማስረጃ አቅርቦ የማሰማት መብት
እንዳለው እና ክሱ ቼክን የተመለከተ በመሆኑ ብቻ በተፋጠነ ስነስርዐት መታየት አለበት የሚባል አለመሆኑን፣

!
ሆኖም የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች በመያዣነት የሚሰጡ መሆኑን የፍትሐብሄር ህጉንና
የንግድ ህጉን ድንጋጌዎች የጣምራ ንባብ መረዳት ይቻላል፡፡

የፍትሐብሄር ህጉ አንቀጽ 2866 ንዑስ አንቀጽ 2 ሲነበብ፡- “የንግድ መለዋወጫ መሆናቸው


በጽሁፍ የተገለጸው የገንዘብ መጠየቂያ መብት የሆኑትን ሰነዶች በመያዣ የመሰጠቱ ስርዐት
የሚፈጸመው በንግድ ህጉ ላይ የተመለከቱት ደንቦች መሰረት ነው፡፡”

የእንግሊዘኛውን ቅጅ ስንመለከት “the pledging of claims and rights established by


negotiable instruments shall be carried out in accordance with the provisions of
article 950-958 of the commercial code”

የዚህን ድንጋጌ ይዘት ስንመለከት የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች በመያዣነት ለመስጠት


እንደሚቻል ሆኖም ዝርዝር አፈጻጸሙ በንግድ ህጉ የሚመራ መሆኑን ከአማርኛው ቅጅ ይልቅ
የእንግሊዘኛው ቅጅ በአግባቡ ገልጾታል፡፡ የትኞቹ የሰነድ አይነቶች በመያዣነት ሊሰጡ
እንደሚችሉ እና በምን አግባብስ ሊሰጡ እንደሚችሉ ለማወቅ የፍትሐብሄር ህጉን አቅጣጫ
ሰጪነት በመከተል የንግድ ህጉን ተገቢነት ያላቸውን ድንጋጌዎች መመልከት ተገቢ ነው፡፡
በንግድ ህጉ አንቀጽ 950 እንደተገለጸው ሊተላለፉ የሚችሉ ሰነዶች ሁሉ ምንም አይነት ቢሆኑ
በዚህ ክፍል በተነገሩት ውሳኔዎች መሰረት በመያዣነት ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ከዚህ ድንጋጌ
መረዳት የሚቻለው ቼክም ሆነ የሀዋላ ወረቀት ወይም የተስፋ ሰነድ እንዲሁም ማንኛውም
በህግ የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ ተብሎ የሚቆጠር ሁሉ በመያዣነት የሚሰጥ መሆኑን ነው፡፡
በርግጥ ይህ ድንጋጌ ስለባንክ አሰራር በተደነገጉት ድጋጌዎች ውስጥ መሆኑ ባንክ ስለሚይዘው
መያዣ ብቻ ነው የሚመለከተው በሚል መውሰድ ቢቻልም የፍትሐብሄር ህጉ የሚተላለፉ
የገንዘብ ሰነዶችን በመያዣነት አያያዝ ከሌላው ንብረት በተለየ በንግድ ህጉ እንዲመራ ማድረጉ
በየትኛውም ሁኔታ ሰነዱን በመያዣነት መስጠት ለሚፈልጉ ሰዎችም ጭምር እንዲያገለግል
ለማድረግ ያሰበ ይመስላል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የንግድ ህጉን ድንጋዎች ለባንክ ብቻ እንዲያለግል
የሚደረግ ከሆነ በግለሰቦች መካከል የሚደረግን የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች መያዣን

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
አምጪው ሰነዱን በሚይዝበት ጊዜ በክፉ ልቡና የያዘ እንደሆነም ይኀው መቃወሚያ ሆኖ ሊቀርብበት እንደሚችል
ተወስኗል፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አመልካች ሀጂ መሀመድ አደም፣ መልስ ሰጪ
ፍጹም ግርማ የፋይል ቁጥር 24435፣ ቅጽ 12 ገጽ 521-524

!
በሚመለከት የህግ ሽፋን የለውም ወደ ሚለው ድምዳሜ ይወስዳል፡፡ በመሆኑም የንግድ ህጉ
ድንጋጌዎች(አንቀጽ 950-958) በግለሰቦች መካከል ለሚኖርም ግብይት ያገለግላል፡፡ በመሆኑም
ቼክን ለብድር መያዣ አድርጎ መስጠት ይቻላል ተብሎ መተርጎም ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም
ቼክ ለምን አገልግሎት እንደሚሰጥ በተዋዋይ ወገኖች የሚወሰን እንጂ በህግ የተገደበ ባለመሆኑ
እንደቀረበ የሚከፈል መሆኑን መሰረት በማድረግ ለመያዣነት አይውልም የሚል ማደማደሚያ
ላይ መድረስ አይቻልም፡፡46 ለዚህም ይመስላል በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ ቼክን በዋስትና
የመስጠት የዳበረ ልምድ ይታያል በዚህ ረገድም በፍርድቤት በሚቀርብ ክርክር ቼክ ለዋስትና
አይሰጥም ተብሎ የሚቀርብ መቃወሚያን በፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎትም ተቀባይነት
የማይኖረው፡፡ በመሆኑም ምንም እንኳ ከባህሪው አንጻር ቼክ እንደቀረበ የሚከፈል ቢሆንም
ለብድር መያዣነት አገልግሎት አይውልም የሚል ክልከላ በህግ ያልተደረገበት መሆኑን
መገንዘብ ይገባል፡፡
1.2.! ጽኑ መቃወሚያ/ real/universal defense/
ጽኑ መቃወሚያ በማንኛውም ሰው ላይ ሊነሳ/ሊጸና/ የሚችል መቃወሚያ ሲሆን መነሻ ሀሳቡም
መቃወሚያው የሰነዱን ትክክለኛነት መቃወምን የሚመለከት በመሆኑ ሰነዱን በያዘው
በማንኛውም አይነት ሰው ላይ (የቅን ልቡና ያዥም ሆነ ተራ ያዥ ቢሆን) መቃወሚያው
ይሰራበታል፡፡ በሌላ በኩል ግላዊ ግንኙነትን መሰረት ያደረገ መቃወሚያ መሰረት የሚያደርገው
በተዋዋይ ወገኖች መካከል የሚደረግን ስምምነት እና ስምምነቱን ተከትሎ በሚመነጭ ህጋዊ
መብት ላይ ነው፡፡ የንግድ ህጉ በሁለቱ ግንኙነት መሰረት ከሚደረግው መቃወሚያ ይልቅ ጽኑ
መቃወሚያ መዘርዝሮችን ሰፋ አድርጎ የያዘ መሆኑን ከአንቀጽ 717/1/2/ ድንጋጌዎች መረዳት
ይቻላል፡፡ በዚህ ድንጋጌ በሰነዱ አጻጻፍ ፎርም እና በሰነዱ በተጻፉት ቃሎች፣ ፊርማን
በማስመሰል የተሰራ፣ ችሎታ ወይም ሰነዱ ሲወጣ የውክና ስልጣን ባለመኖሩ ወይ ክስ
ለማቅረን አስፈላጊ የሆኑት ሁኔታዎች ባለመሙዋላታቸው የተነሳ መቃወሚያ ማቅረብ የሚቻል
መሆኑን ተገልጿል፡፡

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
46
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ የፋይል ቁጥር 24435፣ በቅጽ 12፣ በአመልካች ሀጂ
መሀመድ አደም በተጠሪ ፍጹም ግርማ ገጽ 525

!
ጽኑ መቃወሚያ ባጠቃላይ የችሎታ ማጣትን፣ ህገወጥ ውልን፣ የውል መቋረጥን የሚመለከቱ
ጉዳዮችን የሚያካትት ነው፡፡47 ጽኑ መቃወሚያ በሚከተሉት ምክንያቶች ሊነሳ ይችላል፡፡48

ሀሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀት፡- የባለእዳውን ፊርማም ሆነ በሰነዱ ላይ የተገለጹ ነገሮችን በሀሰት


ማዘጋጀት አንድ መቃወሚያ ሲሆን በሀሰት በተዘጋጀ ሰነድ ምክንያት ማንም ሰው ሊገደድ
አይችልም፡፡ በመሆኑም ሰነዱን የያዘው ሰው የቅን ልቡና ያዥም ሆነ ተራ ያዥ ይህ
መቃወሚያ ሊነሳበት ይችላል፡፡ የንግድ ህጉ አንቀጽ 717/2 በማስመሰል የተሰራ ሰነድ ሲል
ይህንኑ ሁኔታ የሚጨምር መሆኑን ልብ ይሏል

የሰነዱን ይዘት በመሰረታዊነት መለወጥ፡- የሰነዱን ይዘት በማናቸውም ሁኔታ ተዋዋይ ወገኖች
ሳይስማሙ መለወጥ ህገወጥነት ነው፡፡ ይህ የመለወጥ ሁኔታ በተለያዩ መንገዶች የሚፈጸም
ሲሆን ያላለቀ ጽሁፍን መጨረስ፣ የፊደል ወይም አሃዝ ጭማሪ ማድረግ፣ እንዲሁም
ማንኛውንም ጭማሪ ወይም ልዋጭ ያለፈቃድ ማድረግ የሰነዱን ይዘት መቀየር ሆኖ
ይቆጠራል፡፡ በአብዛኛው ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶችን በሚመለከት የሚደረግ የይዘት ለውጥ
የተወሰነውን የሰነድ ክፍል ቆርጦ ማውጣት፣ በተጠቀሰው የገንዘብ መጠን፣ በቀኑ፣ በወለድ
መጠኑ ላይ ለውጥ ማድረግ ነው፡፡ እንዲህ ያለው ለውጥ ምንም እንኳ የተቀነሰው/የተጨመረው
ገንዘብ በጣም አነስተኛ ቢሆን፣ የተጨመረው/የተቀነሰው ቀን አንድ ቀን ስንኳ ቢሆን ለውጡ
መሰረታዊ በመሆኑ በማንኛውም ሰው ላይ መቃወሚያ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ነገር ግን
የአውጪውን አድራሻ ወይንም በፊደል የተጻፈውን የገንዘብ መጠን በአሃዝ ከተጻፈው ጋር
ለማመሳሰል የተደረገ ለውጥ መሰረታዊ ለውጥ የማይባል በመሆኑ ለመቃወሚያነት
አያገለግልም፡፡ መሰረታዊ የሆነ የይዘት ለውጥ በተደረገ ጊዜ ሰነዱን በቅን ልቡና የያዘ ሰው
ከአውጪው በመጀመሪያው ሰነድ የተገለጸው የገንዘብ መጠን እንዲክሰው ሊጠይቀው ይችላል፡፡
አምጪው ተራ አምጪ የሆነ እንደሆነ ግን ይህ መብት አይኖረውም፡፡ በሌላ በኩል ቀድሞውኑ
ተጽፎ ያላለቀ ሰነድን ያለፈቃድ በሌላ ሰው ጽሁፉ እንዲያልቅ ተደርጎ እንደሆነ በቅን ልቡና
ሰነዱን በያዘው ሰው ላይ መቃወሚያ ሆኖ ሊነሳበት አይችልም በመሆኑም ሰነዱን ያወጣው
ሰው በቸልተኝነቱ ለፈጠረው ስህተት ዋጋ መክፈል ስለሚኖርበት ክፍያውን ሊፈጽም ግዴታ

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
47
Francis M. Burdick, Real and Personal Defenses in Actions on Negotiable Paper, cornell Law
Review, volume 3 issue 3, article 1, 1918 page 171
48
RogerbLeRoy Miller, Gaylord A. Jentz, Fundamentals of business law, excerpted cases,
Business Law Accounting USA 2007 p.367

!
አለበት፡፡49 አሁንም የንግድ ህጉ አንቀጽ 717/2 በማስመሰል የተሰራ ሰነድ ሲል ይህንኑ ሁኔታ
የሚጨምር መሆኑን ልብ ይሏል

መክሰር፡- እንደማንኛውም እዳን ከመክፈል ነጻ እንደሚያደርግ ምክንያት በፍርድቤት የተረጋገጠ


መክሰር ባለእዳው ከሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች አከፋፈልን በሚመለከት በማንኛውም ሰው ላይ
ጽኑ መቃወሚያ ሆኖ ሊነሳ ይችላል፡፡50

የህግ ችሎታ አለመኖር፡-ህጋዊ ግብይት ለመፈጸም እድሜያቸው የማይፈቅድ ህጻናት፣ የአእምሮ


ድቀት ያለባቸው ሰዎች እንዲሁም ህጋዊ ውክልና የሌላቸው ሰዎች የሚተላለፉ የገንዘብ
ሰነዶችን አውጥተው እንደሆነ ይህ ሁኔታ ጽኑ መቃወሚያ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል፡፡ በንግድ ህጉ
አንቀጽ 717/2 በግልጽ እንደተነገረው ሰነዱን የሰጠው ሰው የህግ ችሎታ አልያም ተገቢው
ውክልና ሳይኖረው እንደሆነ ጽኑ መቃወሚያ በመሆኑ ሰነዱን ለክፍያ ባቀረበው በማንኛውም
ሰው ላይ ሊነሳ ይቻላል ማለት ነው፡፡

ህገወጥነት፡- ለሰነዱ መጻፍ ምክንያት የሆነው ግብይት/ውል/ ህገ ወጥ የሆነ እንደሆነ ይህ


ሁኔታ በማንኛውም ሰው ላይ ጽኑ መቃወሚያ ሆኖ ሊነሳ ይችላል፡፡ እንደሚታወቀው አንድ
ውል በህግ ዘንድ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ለውል ማቋቋሚያ የሚያስፈልጉ ፍሬ ነገሮች
በሙሉ መሟላት አለባቸው፡፡ እኒህ ፍሬነገሮችም የተዋዋዮች ችሎታ፣ ፍቃድ፣ የውሉ ፍሬ
ነገር ህጋዊነት እና የውሉ ፎርም ነህግ በታዘዘው መሰረት መሆን ያለበት ነው፡፡51 ከዚህ አንጻር
የውሉ ህገወጥነት ውሉን ፍርስ(void) የሚያደርገው በመሆኑ እና ፈጽሞ እንዳልተሰራ
የሚያስቆጥረው በመሆኑ ይህንን ውል መሰረት አድርጎ የሚቀርብ ማናቸውም የክፍያ ጥያቄ
እንደሌለ የሚቆጠር በመሆኑ የውሉ ህገወጥነት ጽኑ መቃወሚያ ሆኖ በማንኛውም ያዥ ላይ
የቅን ልቡና ያዥ ቢሆን እንኳ ሊነሳበት ይችላል ማለት ነው፡፡

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
49
!የግርጌ ማስታወሻ ቁጥር 46 ገጽ 179
50
የግርጌ ማታወሻ ቁጥር 47
51
የፍትሐብሄር ህግ ቁጥር 1678

!
በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ላይ የተጠቀሱ መብቶች በይርጋ ቀሪ ስለሚሆኑባቸው
ሁኔታዎች

ማንኛውም መብት ግዴታን አብሮ የሚያስከትል እና በመብቱም ለመጠቀም በህግ የተጣለን


ግዴታ መወጣት ወይም በህግ የተቀመጠን የጊዜ ገደብ ማክበር የተገባ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡
ከዚህ አንጻር በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ላይ የተነገረን መብት ለመጠቀም በሰነዶቹ ላይ
ከሚቀርቡ መቃወሚያዎች ባሻገር ሰነዶቹ ጥቅም ላይ የሚውሉባቸው የጊዜ ሰሌዳዎች
ተቀምጠዋል፡፡ የሐዋላ ወረቀትን በሚመለከት አምጪው በእሺ ባዩ/በከፋዩ/ ላይ የሚደረጉት
ክሶች ሁሉ በሰነዱ ላይ ከተመለከተው የመክፈያ ቀን አንስቶ በ 3 አመት ይርጋ ቀሪ የሚሆን
ሲሆን፣ አምጪው በጀርባ ፈርመው ባስተላለፉ ሰዎች እና በአውጪው ላይ የሚያቀርበው ክስ
በሚገባ ጊዜ የእንቢታ ማስታወቂያ ከተደረገበት ቀን አንስቶ በ 1 አመት ይርጋ ቀሪ የሚሆን
መሆኑን እንዲሁም በጀርባ የሚፈርሙ ሰዎች እርስ በርሳቸው ወይም በአውጪው ላይ
የሚያቀርቡት ክስ በጀርባ የፈረመው ሰው የወረቀቱን ዋጋ ከከፈለበት ቀን ወይም ራሱ
ከተከሰሰበት ቀን አንስቶ በ 6 ወር ይርጋ ቀሪ የሚሆን መሆኑን በአንቀጽ 817 ተደንግጓል፡፡

ቼክን በሚመለከት ደግሞ በጀርባ በሚፈርሙት ሰዎች፣ በአውጪው እና ሌሎች ተገዳጆች ላይ


የሚቀርቡ የአምጪው የክስ አቤቱታዎች ቼኩን ለማቅረብ የተወሰነው ጊዜ ካለፈ ጀምሮ በ 6
ወር ይርጋ ይታገዳል፡፡ እንዲሁም ተገዳጁ የቼኩን ዋጋ ከከፈለበት ቀን ወይም ራሱ ከተከሰሰበት
ቀን አንስቶ ላንድ ቼክ አከፋፈል እያንዳንዱ ተገዳጅ በሌሎች ተገዳጆች ላይ ያለው የክስ ማቅረብ
መብት በ 6 ወር ይርጋ ይታገዳል፡፡ በተጨማሪም አምጪው በከፋዩ ላይ የሚያቀርበው ክስ
ቼኩን ለማቅረብ የተወሰነው ጊዜ ካለቀ ጀምሮ በ 3 አመት ይርጋ የሚታገድ መሆኑን በአንቀጽ
881 ተገልጧል፡፡ ከዚህ አንጻር ሰነዱን የያዘው ሰው ስለገንዘብ አከፋፈሉ ምንም አይነት
ተቃውሞ ባይቀርብበት እንኳ በዚህ በተገለጸው ጊዜ ሰነዱን ካላቀረበ የመብቱ ተጠቃሚ
አይሆንም ማለት ነው፡፡

ከይርጋ ጋር ተያይዞ የሚነሳው አከራካሪ ጉዳይ የተስፋ ሰነድን በሚመለከት ተግባራዊ


የሚሆነው የጊዜ ሰሌዳ የትኛው ነው የሚለው ነው፡፡ በንግደ ህጉ አንቀጽ 825 የሀሐዋላ
ወረቀት በሚመለከት የተጻፈው የይርጋ ደንብ በተስፋ ሰነድም ላይ ተፈጻሚ የሚሆን መሆኑን
የደነገገ በመሆኑ አንቀጽ 817 የተስፋ ሰነድ አከፋፈልን በሚመለከት ጥቅም ላይ የሚውል
ድንጋጌ ነው፡፡ ሆኖም ይህ የይርጋ ድንጋጌ የተስፋ ሰነድን መሰረታዊ ባህሪ ከግምት ውስጥ

!
ያላስገባ መሆኑን ለማየት ይቻላል፡፡ በዚህ ጽሁፍ መጀመሪያ አካባቢ እንደተገለጸው የተስፋ
ሰነድ ከሀዋላ ወረቀት ወይም ቼክ የሚለየው መሰረታዊ ባህሪ በማዘዝ መታዘዝ ሰንሰለቱ ውስጥ
ለመክፈል ተስፋ የሚሰጠው ሰው እና ክፍያው እንዲፈጸምለት ተስፋ የተሰጠው ሰው ብቻ
ሱታፌ የሚኖራቸው መሆኑ ተገልጧል፡፡ ከዚህ ባህሪ አንጻር በአንቀጽ 817 ላይ ተቀመጠውን
የጊዜ ገደብ ስንመለከት “ከሐዋላ ወረቀት የተነሳ በእሺ ባዩ ላይ የሚቀርበው ክስ ሁሉ
ለመክፈያው ቀን አንስቶ በ 3 ዓመት ይርጋ የሚታገድ መሆኑ፣ አምጪው በጀርባ በፈረሙ
ሰዎች እና በአውጪው ላይ የሚያቀርበው ክስ በሚገባ ጊዜ እንቢታ ማስታወቂያ ከተደረገበት
ወይም ያለኪሳራ የሚመለስ የሚል ቃል (ሰረዝ የተጨመረ) ባለበት ጊዜ ከመክፈያ ቀኑ አንስቶ
በ 1 ዓመት ይርጋ ቀሪ ይሆናል” በሚል ተደንግጓል፡፡ በመሰረቱ የተስፋ ሰነድን በሚመለከት
በከፋዩ እና ተከፋዩ መካከል ጣልቃ የሚገባ ሌላ ሶስተኛ ወገን የሌለ በመሆኑ እሺ ማለትም ሆነ
የእንቢታ ማስታወቂያ ማድረግ አይጠበቅም፡፡ በሀዋላ ወረቀት እና የተስፋ ሰነድ መካከል ያለው
መሰረታዊ ልዩነት የተስፋ ሰነድን የሚከፍለው ሰነዱን ያወጣው ሰው እራሱ ሲሆን በሀዋላ
ወረቀት ጊዜ ግን ክፍያውን የሚፈጽመው ከአውጪው ሌላ የሆነ ሶስተኛ ወገን በመሆኑ በህግ
መሰረት እሺ ማለትም ሆነ የእንቢታ ማስታወቂያ መስጠትም መብት አለው፡፡ ታዲያ ይርጋውን
በተመለከተ እሺ ማለትም ሆነ የእንቢታ ማስታወቂያ በማይሰጥበት ሁኔታ የትኛውን ይርጋ
ድንጋጌ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ግልጽ አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ ተከራካሪ ወገኖች
ለየራሳቸው የሚጠቅማቸውን የጊዜ ገደብ ለመከራከሪያነት ሊያቀርቡት እንደሚችሉ አንድ
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቀረበ ጉዳይ ላይ ለመመልከት ይቻላል፡፡

በሰበር የቀረበው አቤቱታ እንደሚያመለክተው 1ኛ ተጠሪ ያለበትን የብር 107,440 እዳ


ለመክፈል እንዲያስችለው በ2ኛ ተጠሪ አማካኝት የቃል ኪዳን ሰነድ ፈርሞ ቢሰጥም በገባው
ቃል መሰረት አልከፈለኝም በማለት አመልካች የመሰረተውን ክስ መነሻ ያደረገውን ክርክር
በሚመለከት ተጠሪዎች ለክሱ በሰጡት መልስ ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል፣ በውክልና ሰነዱ ላይ
ያለው ፊርማ የ2ኛ ተጠሪ አይደለም በሚል ተከራክረዋል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ
የተመለከተው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት 2ኛ ተጠሪ ፊርማውን በመካዱ ፊርማው
እንዲመረመር ቢታዘዝም አመልካቹ ዋናውን ሰነድ ማቅረብ አልቻለም በሚል አመክንዮ ክሱን
ውድቅ አድርጎታል፣ ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድቤትም ውሳኔውን
በማጽናቱ መዝገቡ በሰበር የደረሰው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ

!
ለመሆኑ ይርጋውን በሚመለከት አግባብነት ያለው የህግ ድንጋጌ የትኛው ነው? የሚለውን
ጭብጥ በመያዝ ከዚህ እንደሚከተለው ማብራሪያ እና አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል

“……..በአንቀጽ 817/1 እና 2 መካከል ያለውን ልዩነት ለመረዳት በጥንቃቄ


መታየት ያለበት የጊዜው መርዘም ማጠር ሳይሆን በ ሁለቱ ድጋጌዎች መካከል
ያለው ልዩነት ምንድነው የሚለው ነው፡፡ የመጀመሪያው ክሱ በእሺ ባዩ ላይ
የሚቀርብ እንደሆነ ገልጾ መቅረብ ያለበት ከመክፈያው አንስቶ በ 3 አመት ጊዜ
ውስጥ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ክሱ የሚቀርበው በጀርባ
በፈረሙ ሰዎች እና በአውጪው ላይ መሆኑን በአንድ በኩል ሲገልጽ በሌላ
በኩል ደግሞ የሀዋላ ወረቀቱ በሚገባው ጊዜ “የእንቢታ ማስታወቂያ” የተደረገበት
ወይም ያለኪሳራ የሚመለስ የሚል ቃል ያለበት እንደሆነ ያመለክታል፡፡ ከዚህ
አንጻር ተጠሪዎች የተከሰሱት የሰነዱ አውጪ በመሆናቸው እንደሆነ ግልጽ
ነው፡፡ በዚህ ሰነድ መሰረት ግንኙነት የተፈጠረው በተጠሪዎች እና በአመልካች
መካከል ብቻ እንደሆነ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ በሰነዱ የተመለከተውን ገንዘብ
ለመክፈል ‘እሺ’ ባዮች ተጠሪዎች እንደሆኑም መታወቅ አለበት፡፡ በሰነዱ ላይ
በንግድ ህጉ ቁ.817/2/ የተመለከቱት ሁኔታዎች አሉበት አልተባለም፡፡
በመሆኑም ተጠሪዎች ከእነሱ ውጪ ሌላ ሰው ያለ ይመስል የይርጋ
መቃወሚያው መታየት ያለበት በንዑስ ቁጥር 2 መሰረት ነው በማለት ያቀረቡት
መከራከሪያቸው ተገቢነት የለውም……..”52

ይህ ትንታኔ እና ውሳኔ መሰረታዊውን የተስፋ ሰነድ ባህሪ ወደ ጎን የተወ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡


በመሰረቱ የተስፋ ሰነድ የሁለትዮሽ ግንኙነትን የሚመሰርት የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ በመሆኑ
ከፋይ ሌላ ሶስተኛ ወገን ካለመኖሩ የተነሳ በከፋዩ እና ተከፋዩ መካል እሺ ማለትም ሆነ
የእንቢታ ማስታወቂያ ማውጣት አስፈላጊ አይደለም፡፡ ሌሎችን የሀዋላ ወረቀትንና ቼክ የሆኑ
እንደሆነ ግን ከፋዩ ሰነዱን ካወጣው ሰው ውጪ ሌላ ሶስተኛ ወገን በመሆኑ ክፍያውን
ከመፈጸሙ በፊት ‘እሺ’ የማለት አልያም በህግ መሰረት ‘የእንቢታ ማስታወቂያ’ የመስጠት
ግዴታ/መብት አለው ማለት ነው፡፡ በተስፋ ሰነድ ግን ከፋዩ እራሱ ሰነዱን ያወጣው ሰው ሆኖ
እያለ አልያም ሰነዱን በጀርባ ፈርመው ያስተላለፉ ሰዎች ሆነው እያለ ለመክፈል እሺም
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
52
! የፌ/ጠፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ የፋይል ቁጥር 48242፣ አመልካች የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት
ተጠሪዎች እነ ቦጋለ መስቀሌ 2 ሰዎች ቅጽ 12 ገጽ 496-498

!
እምቢም የሚልበት ምክንያት የሌለው በመሆኑ ይህ ድንጋጌ ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም፡፡
በመሆኑም ህጉ በዚህ ረገድ የሀዋላ ወረቀት ድንጋጌዎችን በውሰት ሲጠቀም የተስፋ ሰነድን ልዩ
ባህሪ ከግምት ውስጥ ማስገባት ነበረበት፡፡ የሰበር ችሎቱም ህግን በመተርጎም ሀላፊነቱ
የሰነዶቹን ልዩ ባህሪያት ከግምት ውስጥ የሚያስገባ ውጤታማ የሆነ የህግ አተረጓጎም መርህን
ሊከተል ይገባ ነበር፡፡

የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድን በጅ ያደረገ ሰው በህግ በተገለጸው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ሰነዱን
ለከፋዩ ያላቀረበ እንደሆነ ሰነዱን መሰረት አድርጎ የሚያቀርበው ክስ በይርጋ ቀሪ የሚሆን
ቢሆንም መብቱን ሙሉ ለሙሉ ያጣል ማለት ግን አይደለም፡፡ በንግድ ህጉ አንቀጽ 799
እንደተነገረው በሐዋላ ወረቀት ላይ የተመሰረቱ ግዴታዎች ጊዜያቸው በማለፉ ወይ በይርጋ
ምክንያት የቀሩ ቢሆን እንኳ አውጪውና እሺ ባዩ ህግ በማይፈቅደው አኳኋን ያለአግባብ
በመበልጸግ ባገኙት ገንዘብ መጠን ለአምጪው ሀላፊዎች ናቸው፡፡ ይህ ድንጋጌ ለቼክም ሆነ
ለተስፋ ሰነድ በውሰት የሚያገለግል መሆኑን በአንቀጽ 886 ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም
አምጪው ስልጣን ባለው ፍርድቤት ያለአግባብ መበልጸግ ክስ በፍትሐብሄር ህጉ ድጋጌዎች
መሰረት ማቅረብ ይችላል ማለት ነው፡፡

ይህንን ድንጋጌ በአግባቡ ካለመረዳት የተነሳ የክርክር መነሾ መሆኑን ከሌላ የፌዴራል ጠቅላይ
ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ መመልከት ይቻላል፡፡ በሰበር ችሎቱ የቀረበው ክርክር
በአመልካች እና ተጠሪ መካከል በተደረገ የሰሊጥ ሽያጭ ውል መነሻ ተጠሪ ከአመልካች የገንዘብ
ክፍያ የሰጠው ቼክ ከፋይ ባንክ ዘንድ በቂ ስቅ የሌለው መሆኑ ተረጋግጦ በቼክ መሰረት
በአመልካች በኩል ቀርቦ የነበረው ክስ በንግድ ህግ ቁጥር 881 መሰረት በይርጋ ጊዜ ቀሪ
በመባሉ በንግድ ህጉ ቁጥር 799 መሰረት ያለአግባብ መበልጸግ ክስ ቢቀርብም ጉዳዩ
በመጀመሪያ ደረጃ የቀረበለት የአብክመ ጠ/ፍርድቤት ጉዳዩ በይርጋ የሚታደግ ከሆነ ያለአግባብ
መበልጸግ ክስ ሊቀርብ አይችልም በሚል መዝገቡን ዘግቶታል፣ በይግባኝ ጉዳዩን የተመለከተው
የፌዴራል ጠቅለይ ፍ/ቤትም ውሳኔውን በማጽናቱ ጉዳዩ ለሰበር ቀርቧል፡፡የሰበር ችሎቱም የግራ
ቀኙን ክርክር እንዲሁም ተገቢነት ያላቸውን የህግ ድንጋጌዎች በመመልከት የንግድ ህጉ
አንቀጽ 799 በይርጋም ሆነ በሌሎች ህጋውያን ምክንያቶች በሰነዱ ላይ የተገለጸውን መብት
መጠቀም ያልተቻለ እንደሆነ ባለመብቱ ያለአግባብ መበልጸግ ክስ በማቅረብ መብቱን ማስከበር
የሚችል መሆኑን በማመልከት ይህ መብት በራሱ በይርጋ የማይታገድ ከሆነ ደግሞ ባለመብቱ

!
መብቱን ሊሰራበት የሚችል መሆኑን በማብራራት የስር ፍርድቤቶችን ውሳኔ ውድቅ
አድርጎታል፡፡53

የሰበር ውሳኔው አግባነት ያለው ሆኖ ይታያል ምክንያቱም ምንም እንኳ በይርጋ የተነሳ መብት
የሚታጣ መሆኑን በመገለጹ የተነሳ በቀጥታ ሰነዶችን መሰረት በማድረግ ክስ የማቅረብ መብት
ቢገደብም ሌሎች መብት የማስከበሪያ መንገዶችን በመጠቀም መብትን ማስከበር የሚቻል
መሆኑን ከአንቀጽ 799/1/ መረዳት ይቻላል፡፡

ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ሌላው ነጥብ በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ላይ የተመለከተን
መብት በይርጋ ቀሪ የሆነ እንደሆነ ያለአግባብ መበልጸግ የሚመለከት ክስን ለማየት ስልጣን
የሚኖረው የትኛው ፍርድቤት ነው የሚለው ነው፡፡

ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶችን በሚመለከት የሚቀርብ ፍትሐብሄራዊ ክርክር የፌዴራል መንግስቱ


ስልጣን መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5/7 ላይ ተመልክቷል፡፡ በዚህ መሰረት
በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን በሚመለከት የሚቀርብ ክስ እንደ ገንዘቡ መጠን በፌዴራል
ፍርድቤቶች በተዋረድ የሚታይ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ሆኖም የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድን
መሰረት ያደረገ ያለአግባብ መበልጸግ ክስ የመዳኘት ስልጣን ያለው ፍርድቤት የትኛው ነው
የሚለው የክርክር ምክንያት እንደሆነ አንድ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
ላይ የቀረበን ክርክር ዋቢ እናደርጋለን፡፡ የሰበር ችሎቱ በፋይል ቁጥር 10451154 በአመልካቾች
እነ ዳኜ ሀይሉ 2 ሰዎች እና በተጠሪዎች እነ አለምሰገድ አጥናፉ 2 ሰዎች መካከል በቀረበ
ክርክር በስር ፍርድቤት በተጠሪዎች አማካኝነት የተጠየቀው ዳኝነት አመልካቾች የእቁብ ዳኛ
እና ሰብሳቢ ሆነው እቁብ የደረሰን በመሆኑ ቼክ ተቆርጦ ተሰጥቶን ገንዘቡን ለማውጣት ወደ
ባንክ ስንሄድ በቂ ስንቅ የሌለ በመሆኑ ገንዘባችን ይከፈለን በሚል በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ
ፍርድቤት የቀረበ ክስ ሲሆን የከፍተኛ ፍርድቤቱ የአመልካቾችን አቤቱታ በመደገፍ ተከሳሾች
የተባለውን ክፍያ እንዲፈጽሙ ውሳኔ በማስተላለፉ ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የክልሉ
ጠቅላይ ፍ/ቤትም ውሳኔውን አጽንቶታል ሆኖም መዝገቡ በሰበር የደረሰው የክልሉ ጠ/ፍቤት
ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ክሱ የቀረበው ቼክን በሚመለከት በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 25/88
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
53
! የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ በፋይል ቁጥር 40173፣ በአመልካች አምባሰል የንድ ስራዎች
ኃ/የተ/የ/ማህበር፣ በተጠሪ አብድልቃድር ጁሀር፣ በቅጽ 12፣ ገጽ 491-495!
54
! የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ በፋይ ቁጥር 104511፣ በአመልካቾች እነ ዳኜ ሀይሉ ሁለት ሰዎች እና
በተጠሪዎች እነ አለምሰገድ አጥናፉ 2 ሰዎች፣ በቅጽ 17 ገጽ 273-275

!
አንቀጽ 5/7 መሰረት የፌዴራል ፍርድቤት በመሆኑ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለኝም በሚል
መዝገቡን ዘግቶታል፡፡55

ለመሆኑ በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ጋር ተያይዞ የሚነሱ ክርክሮች በሙሉ የፌዴራል


ፍርድቤቱ ስልጣን ናቸው ለማለት የሚያስችል የህግ መሰረት አለ ወይ የሚለውን መመልከት
ያስፈልጋል፡፡ በርግጥ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5/7/ ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶችን በሚመለከት
የሚቀርብ ፍትሐብሄራዊ ክስ የፌዴራል ፍርድቤቶች ስልጣን መሆኑን ደንግጓል፡፡ ሆኖም ግን
ይህ ድንጋጌ ጥቅም ላይ መዋል የሚኖርበት የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች የክርክሩ መንስኤ
ወይም የክስ ምክንያት ሆነው ሲቀርቡ መሆን አለበት፡፡ በሌላ በኩል ግን ሰነዶቹ የክርክር
ምክንያት ሳይሆኑ አንድ የቀረበ ክርክርን ለማስረዳት የቀረቡ አስረጂዎች እንደሆኑ
በፍትሐብሄር ስነስርዐት ህጉ መሰረት ጉዳዩን ለማየት የስረ-ነገር እና የግዛት ስልጣን
ያለው(እንደየሁኔታው የክልሉ/የፌዴራሉ) ፍርድቤት ጉዳዩን ይዳኘዋል እንጂ የፌዴራል
ፍርድቤቱ ስልጣን ነው የሚባል ባለመሆኑ አዋጅ ቁጥ 25/88 ጥቅም ላይ የሚውልበት
አንዳችም ምክንያት አይኖርም፡፡ በመሆኑም ፍርድቤቶች በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች በክርክር
ውስጥ የተጠቀሱ እንደሆነ ጉዳን የመዳኘት ስልጣን የየትኛው ፍርድቤት ነው የሚለውን ነጥብ
ለማጣራት ሰነዶቹ የክርክር ምክንያቶች ወይም አስረጂዎች ሆነው መቅረባቸውን መለየት
ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡

በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ መቁረጥ የሚያስከትለው ተጠያቂነት


ማንም ሰው ሊያዝበት የሚችል በቂ ስንቅ ሳይኖረው ቼክ የቆረጠ እንደሆነ የፍትሐብሄር ብሎም
የወንጀል ተጠያቂነት ይኖርበታል፡፡ ከዚህ አንጻር የንግድ ህጉ በቂ ስንቅ ለቼክ መቆረጥ ቅድመ-
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
55
! ጉዳዩ በሰበር የቀረበለት የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በቀረበው የሰበር አቤቱታ መሰረት ጠ/ፍቤቱ መዝገቡን
መርምሮ የግራ ቀኙ መሰረታዊ ክርክር እቁብን ተከትሎ ያዋጡት ገንዘብ መክፈያ ቀኑ ደርሶ አመልካቾች የእቁብ
አመራር በመሆናቸው ተጠቃሹን ገንዘብ የመክፈል ሀላፊነት ስላላቸው ቼክ ቆርጠው በሰቷቸው መሰረት ወደ ባንክ
ቤት በመሄድ ገንዘባቸውን ባለማግኘታቸው የእቁብ ግንኙነታቸውን መሰረት አድርጎ እንዲከፈላቸው የቀረበ ዳኝነት
እንጂ የክርክሩ መሰረት ቼክ አይደለም፡፡ ቼክ የእቁብ ገንዘብ ላለመከፈሉ ማረጋገጫ ሆኖ በተራ ሰነድ ማስረጃነት
የቀረበ እጂ በዋናነት እራሱ በንግድ ህጉ የተመለከቱት አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች አተገባበር ለመመርመር
የሚያስችል ክርክር በሚያስነሳ መልኩ የቀረበ ያለመሆኑን ከክርክሩ ይዘት ለመረዳት የምችለው ጉዳይ የክርሩ
አጠቃይ ይዘት የእቁብ ገንዘብ ይከፈለኝ ጥያቄ መሰረት አድርጎ ቼኩን በተራ የሰነድ ማስረጃነት የቀረበበት ሆኖ ሳለ
የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የግራቀኙን የተጠየቀውን ዳኝነት እና የክርክሩን አቅጣጫ ባላገናዘበ መልኩ ጉዳዩ በአዋጅ
ቁጥር 25/88 ስር የሚታይ ነው ሲል መዝገቡን መዝጋቱ አግባብ አይደለም በሚል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ !

!
ሁኔታ መሆኑን ሲደነግግ፡- አውጪው ለራሱ ተቀማጭ ገንዘብ በከፋዩ ዘንድ ያለውና በግልጽ
ወይም በዝምታ ባንድ ስምምነት መሰረት አውጪው በዚሁ የተነሳ ገንዘቡን በቼክ ሊያዝበት
መብት ያለው ካልሆነ ቼኩ ተጽፎ ሊወጣ አይችልም በሚል በአንቀጽ 830 ላይ ይገልጻል፡፡
በዚህም መሰረት አውጪው ሰነዱ ለክፍያ በቀረበ ጊዜ በቂ ስንቅ ባለመኖሩ የተነሳ ክፍያው
እምቢ የተባለ እንደሆነ አውጪው ሰነዱን ባወጣበት ሰዐት በቂ ስንቅ የነበረ መሆኑን የማስረዳት
ግዴታ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም አውጪው ለአከፋፈሉ ዋስትና በመሆኑ ከዚህ ዋስትና
ሀላፊነት ለመዳን የሚጻፈው ቃል ሁሉ እንዳልተጻፈ ይቆጠራል፡፡56

የሚተላለፉ ገንዘብ ሰነዶች በጀርባ ፊርማን በማኖር ለሌላ ሶስተኛ ወገን መተላለፍ እንደሚችሉ
የታወቀ ነው፡፡ እንዲህ በሆነ ጊዜ ሰነዱን በጀርባ ፈርሞ ያስተላለፈ ሰው ተቃራኒ የውል ቃል
ከሌለ በቀር ስለ ገንዘቡ አከፋፈል ለአምጪው ዋስ የሚሆን ሲሆን ሆኖም በጀርባ የሚፈርመው
ሰው አዲስ በጀርባ መፈረምን መከልከል ይችላል፡፡ በመሆኑም ይህን ክልከላ ተላልፎ አዲስ
መፈረም የተፈጸመ እንደሆነ ከልካዩ ስለ ገንዘቡ አከፋፈል ዋስ እንዲሆን አይገደድም57

እንዲሁም ባንድ ቼክ የሚገደዱ ሰዎች ሁሉ ለአምጪው በአንድነት ሳይከፋፈሉ ሀላፊዎች


ሚሆኑከመሆኑም ባሻገር አምጪው ሊገደዱበት በገቡት ተርታ ሳይገደድ በነዚህ ሰዎች ላይ
በእያንዳንዱ ወይም በሁሉም ላይ አምጪው ክስ ለማቅረብ መብት ያለው መሆኑን በአንቀጽ
872/1/2 ላይ ተደንግጓል፡፡ በመሆኑም አምጪው ቼኩን እንዳቀረበ በቂ ስቅ ባለመኖር አልያም
አትክፈል በሚል ትእዛዝ የተነሳ ክፍያውን የተከለከለ እንደሆነ ስልጣን ላለው የዳኝነት አካል
ከቼኩ ያልተከፈውን ቀሪ ገንዘብ፣ አቤቱታው ከቀረበበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ህጋዊ ወለድ፣
ለእንቢታ ማስታወቂያ ወይም ይህንን ለመሰለ መግለጫ ወይም ለተላኩት ማስታወቂያዎች
የወጡትን እንዲሁም ያደረጋቸውን ሌሎች ወጪዎች፣ ቢበዛ ከመቶ የአንዱን ሲሶ የኮሚሲዮን
አቤቱታ ካቀረበበት ሰው ሊጠይቅ የሚችል መሆኑን በአንቀጽ 873/1/2/ መብት ተሰጥቶታል፡፡
እንዲሁም ባንድ ቼክ የሚገደዱ ሰዎች ሁሉ ለአምጪው ባለባቸው የማከፋፈል ሀላፊነት
የተነሳ የቼኩን ዋጋ የከፈለ ሰው የከፈለውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ፣ የተባለውን ገንዘብ
ከከፈለበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ህጋዊ ወለድ፣ ያደረጋቸውን ወጪዎች፣ ከ ሺህ ሁለት እጅ
የማይበልጥ ኮሚሲዮን፣ ተገዳጅ ከሆኑት ሰዎች መጠየቅ እንደሚችል ቀጥሎ ባለው አንቀጽ
874 ተመልቷል፡፡
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
56
! የንግድ ህግ ቁጥር 840
57
የንግድ ህግ ቁጥር 750፣ 846

!
የወንጀል ተጠያቂነት
ማንም ሰው ቼክ በሚወጣበት ወይም ቼኩ ለባንክ በሚቀርብበት ጊዜ የሚያዝበት በቂ ገንዘብ
አለመኖሩን እያወቀ ቼክ ያወጣ/የሰጠ/ እንደሆነ በቀላል እስራት ወይም እንደነገሩ ከባድነት
ከአስር አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እና በመቀጮ የሚቀጣ መሆኑን፣ አድራጎቱ
የተፈጸመው በቸልተኝነት ከሆነ ደግሞ በመቀጮ ወይም ከአንድ አመት በማይበልጥ ቀላል
እስራት የሚቀጣ መሆኑን በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 693/1/2/ ተደንግጓል፡፡ በዚህ
ድንጋጌ መሰረት ማንኛውም በቂ ስንቅ የሌለው ቼክ አውጪ የሚቀጣ መሆኑን ለመረዳት
ይቻላል፡፡
ሆኖም ይህ ክስ በሚቀርብበት ጊዜ ተከሳሹ የግል ግንኙነትን መሰረት ያደረገ መቃወሚያ
በማቅረብ ከወንጀል ተጠያቂነት ሊድን ይችል ይሆን? የሚለው ጥያቄ በተግባር የሚንጸባረቅ
መሰናክል ነው፡፡ ለማብራራት ያህል ተዋዋይ ወገኖች ባላቸው የውል ግንኙነት የተነሳ ለስራ
ማስኪያጃ ወይም የውል አካል አድርገው ቼክ ከተሰጣጡ በኋላ አንደኛው ወገን እንደ ውሉ
እየፈጸመ አይደለም በሚል በባንክ ያለን ገንዘብ ወጪ በማድረግ ቼኩ ለክፍያ በሚቀርብበት ጊዜ
በቂ ስንቅ ስለማይኖር አምጪው ክፍያውን አያገኝም ማለት ነው፡፡ አምጪውም የወንጀል ክስ
በሚመሰርትበት ወቅት ተከሳሹ በቂ ስንቅ ነበረኝ ነገር ግን ከሳሹ እንደውሉ እየፈጸመ ባለመሆኑ
ገንዘቤን ከባንክ ወጪ አድርጌያለሁ የሚል የንግድ ህጉን አንቀጽ 717/1/ መሰረት ያደረገ
መከራከሪያ ቢያቀርብ የወንጀል ጉዳዩን የሚመለከተው ፍርድቤት ይህንን መከራከሪያ ከግምት
ውስጥ ሊያስገባው ይችላል ወይ የሚለውን ጥያቄ መመለስ ያስፈልጋል፡፡
ስለ ወንጀል ተጠያቂነት ከተነሳ መጀመሪያ ሊታሰብ የሚገባው አብይ ነጥብ የወንጀል ህግ ዓላማ
ምንድርነው የሚለው ነው፡፡ በዚህ ረገድ ባለፉት ክፍለ ዘመናት የዳበረው የወንጀል ህግ ዓላማ
ለአጥፊው ተገቢውን ቅጣት በመስጠት አጥፊውንም ሆነ ሌላውን ማህበረሰብ የወንጀል ድርጊት
ደግሞ እንዳይፈጽም ማስጠንቀቅ እና ማስተማር ነው፡፡ ይህ ሀሳብ በኢፌድሪ የወንጀል ህግ
አንቀጽ 1 በስፋት እንደተመለከተው የወንጀል ህግ ዓላማ ለጠቅላላው ጥቅም ሲባል የአገሪቱን
መንግስት፣ የህዝቦቹን፣ የነዋሪዎቹን፣ ሰላም፣ ደህነት፣ ስርዓት፣ መብት እና ጥቀም የመጠበቅ
እና የማረጋገጥ ሲሆን ከአላማው ዝቅ ብሎ የወንጀል ህጉ ግብ ወንጀል እንዳይፈጸም መከላከል
ነው፡፡ ይኅንን የሚያደርገው ደግሞ ስለወንጀሎች እና ስለቅጣታቸው በቅድሚያ በማስጠንቀቅ፣
ማስጠንቀቂያነቱ በቂ ባልሆነበት ጊዜ ወንጀል አድራዎች ተቀጥተው ሌላ ወንጀል ከመፈጸም

!
እንዲቆጠቡ እና ለሌሎች ማስተማሪያ እንዲሆኑ ወይም እንዲታረሙ በማድረግ ወይም
ተጨማሪ ወንጀሎችን እንዳይፈጽሙ እርምጃዎች እንዲወሰድባቸው በማድረግ ነው፡፡
ሆኖም አጥፊዎችን ተገቢ ቅጣት ሰጥቶ ለማስተማርም ሆነ ለማስወገድ መጀመሪያ
ጥፋተኝነታቸው በህግ ስልጣን በተሰጠው ፍርድቤት መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ የወንጀል ቅጣት
በሰዎች ህይወት እና ነጻነት ላይ የሚገዳደር ከመሆኑ አንጻር ስልጣን የተሰጠው አካልም
ጥፋተኛ ብሎ ቅጣትን ለመወሰን ጥብቅ የሆኑ መስፈርቶች መከተል ይኖርበታል፡፡ ቀድሞ ነገር
አንድ ድርጊት ወንጀል ተብሎ ሊያስቀጣ የሚችለው ሁሉም የድርጊት፣ የህግ፣ እና የሞራል
ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ነው፡፡ የህግ ፍሬ ነገር ስንል፡- ድርጊቱ በወንጀል
ህግም ሆነ ሌሎች ህግጋት የሚያስቀጣ መሆን፣ የድርጊት ፍሬ ነገር ስንል፡- በህግ
የተከለከለው ድርጊት በገቢር መፈጸሙ፣ የሞራል ፍሬ ነገር ስል ደግሞ አደራጊው በህግ
የተከለከለውን ድርጊት የፈጸመው ወንጀል በማድረግ ሀሳብ የሆነ እንደሆነ ጉዳዩ የቀረበለት
ፍርድቤት በወንጀል ህጉ አንቀጽ 23/2/ መሰረት ጥፋተኛ ብሎ ለወንጀሉ የተቀመጠው
ተመጣጣኝ ቅጣት ይቀጣዋል፡፡
የህግ እና የድርጊት ፍሬ ነገሮች መሟላታቸውን ፍርድቤቱ ህጉንና በገቢር የተፈጸምውን
ድርጊት በማመዛዘን በቀላሉ መረዳት ይቻለዋል፡፡ የሞራል ፍሬ ነገርን በተመለከተ ግን
አድራጊው ድርጊቱን የፈጸመው ወንጀል ለመፈጸም በማሰብ መሆኑን ለማወቅ የሰው ልብ እና
ኩላሊት ለመመርመር መለኮታዊ ችሎታን የሚያጠይቅ በመሆኑ በጥንቃቄ ሊታይ የሚገባው
ጉዳይ ነው፡፡ ድርጊቱ የተፈጸመው አድራጊው ምንም ጥፋት ሳያደርግ ወይም ከአቅም በላይ
በሆነ ኃይል ምክንያት፣ ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ ነገር እንደሆነ በወንጀል ሊፈረድ
አይችልም፡፡ አንድ ሰው በህግ የተከለከለውን ድርጊት ሲፈጽም የወንጀሉን ውጤት አስቦ እና
አቅዶ፣ ወይም ማሰብ እና ማቀድ እየቻለ በንዝህላልነት የፈጸመው እንደሆነ ወንጀል የመፈጸም
አሳብ አለው ያስብለዋል፡፡58
ማንም ሰው በህግ የተከለከለውን ግርጊት መፈጸሙ ብቻ ጥፋተኛ አያደርገውም ይልቁንም
ድርጊቱን የፈጸመው ወንጀል የመስራት ሀሳብ ኖሮት መሆን ይገባዋል የሚለው ሀሳብ መነሻ
የተገኘው ከወንጀል ህጉ ከአንቀጽ 57 የተገኘ ነው፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት ማንም ሰው
ጥፋተኛነቱ ካልተረጋገጠ በቀር ሊቀጣ አይችልም፡፡ ጥፋተኛ ለመባልም ለድርጊቱ ሀላፊ የሆነው
ሰው አስቦ ወይም በቸልተኝት አንድ ወንጀልን አድርጎ እንደሆነ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ለድርጊቱ
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
58
! Philip Graven, An Introduction to Ethiopian Penal Law Article 1-84, Haile Silasie I University,
Adiss Ababa, Ethiopia, 1965, page 152-159!

!
ሀላፊ የሆነው ሰው ድርጊቱን የፈጸመው ወንጀል በማድረግ ሀሳብ ወይም ቸልተኝነት የሆነ
እንደሆነ ብቻ የወንጀል ተጠያቂነት ይኖርበታል ማለት ነው፡፡ ምንም እንኳ ማንም በህግ
የተከለከልን ድርጊት የፈጸመ ሰው ለድርጊቱ ሀላፊ ነው ተብሎ የህግ ግምት ቢወሰድበትም
ማንም ሀላፊ የሆነ ሰው ግን በወንጀል ተጠያቂ ነው ተብሎ ድምዳሜ አይሰጥም፡፡ ይልቁንም
ድርጊቱን የፈጸመው ወንጀል በማድረግ ሀሳብ መሆኑን ከሳሽ የሆነው አካል ማስረዳት
ይኖርበታል፡፡
ወደ ተነሳንበት ሀሳብ ስንመለስ አንድ ሰው ቼክ በሚወጣበት ወይም ቼኩ ለባንክ በሚቀርብበት
ጊዜ የሚያዝበት በቂ ገንዘብ አለመኖሩን እያወቀ ቼክ ያወጣ/የሰጠ/ እንደሆነ በወንጀል ተጠያቂ
እንደሚሆን በ ወንጀል ህጉ አንቀጽ 693 ተደንግጓል፡፡ ታድያ ይህ ሰው ቼኩን በሚሰጥበት ጊዜ
በቂ ስንቅ የነበረው እና ቼኩ ለክፍያ በሚቀርብበት ጊዜ በቂ ስንቅ ባለመኖሩ ምክንያ የወንጀል
ክስ ሲቀርብበት የንግድ ህጉን አንቀጽ 717 መሰረት አድርጎ ገንዘቡን ወጪ ያደረኩት
አውጪው የሚጠበቅበትን የውል ግዴታ ባለመፈጸሙ የተነሳ ነው የሚል ፍትሐብሄራዊ
ክርክር ቢያቀርብ ፍርድቤቱ መከራከሪያውን እንደምን ይቀበለዋል የሚለው ነጥብ መታየት
አለበት፡፡
ይህ የወንጀል ድንጋጌ በምዕራፍ ሦሥት በንብረት መብቶች ላይ በሚፈጸሙ የማታለል
ወንጀሎች ስር የሚጠቃለል በመሆኑ የማታለል ወንጀል እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡ ማታለል ደግሞ
በአንቀጽ 992 እንደተተረጎመው ማንም ሰው ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው የማይገባ ብልጽግናን
ለማግኘት በማሰብ አሳሳች የሆኑ ነገሮችን በመናገር፣ የራሱን ማንነት ወይም ሁኔታ በመሰወር፣
ወይም መግለጽ የሚገባውን ነገር ባለመግለጽ፣ የሌላውን ሰው የተሳሳተ ግምት በመጠቀም፣
በማለድረግም ሆነ ባለማድረግ፣ሌላውን ሰው አታልሎ የራሱን ወይም የ3ኛ ወገንን የንብረት
ጥቅም የሚጎዳ አድራጎት እንዲፈጽም ያደረገ እንደሆነ አታላይ ተብሎ ይቀጣል፡፡
በዚህ ጽሁፍ መጀመሪያ አካባቢ እንደተገለጸው ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶች በተለይም ቼክ የጥሬ
ገንዘብ ምትክ ብሎም የእዳ መተማመኛ ወይም መያዣ ሆኖ ስለሚያገለግል የግብይቱን አለም
በጥሩ ሁኔታ የሚያቀላጥፍ መሆነ ተገልጧል፡፡ ከዚህ አንጻር ሽያጭ በቼክ ቢደረግ፣ አልያም
ቼክ ለዋስትና፣ ለመልካም የስራ አፈጻጸም ዋስትና፣ ለስራ ማስኪያጃ ተብሎ በተዋዋይ ወገኖች
ጥቅም ቢውል ቼኩን የተቀበለው ሰው ገንዘብ የተቀበለ ያህል እምነት ይሰማዋል፡፡ ሆኖም
ሰጪው ይህን እምነት ወደ ጎን በመተው በቂ ስንቅ የሌለው ቼክ ቆርጦ ቢሰጥ ይህንን እምነቱን
በልቷልና፣ እምነት መብላት ብቻ ሳይሆን የሌላውን ሰው የንብረት ጥቅም የሚጎዳ አድራጎት
በመፈጸም ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና አግኝቷልና አታላይ በመሆኑ ቅጣት ይገባዋል፡፡ ሆኖም ይህ

!
ሰው ቼኩን በሚቆርጥበት ጊዜ በቂ ስንቅ ኖሮት ነገር ግን ቼክ የተቆረጠለት ሰው
የሚጠበቅበትን ሀላፊነት ባለመወጣቱ ምክንያት እኔም በውላችን መሰረት ልገደድ አይገባም
በሚል ገንዘቡን ከባንክ ወጪ ቢያደርግ በርግጥ የማታለል ሀሳብ ቀድሞውኑ ነበረው ለማለት
የሚያስደፍር አይሆንም፡፡
በዚህ ረገድ በፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠውን ውሳኔ ስንመለከት
በተከሳሽ ላይ የቀረበው ክስ የወንጀል ህጉን አንቀጽ 693/1/ በመተላለፍ በባን የሚያዝበት በቂ
ገንዘብ ያለመኖሩን እያወቀ ቼክ የቆረጠ በመሆኑ እና ቼኩም ለክፍያ በቀረበ ጊዜ ክፍያ
ሳይፈጸምለት በመመለሱ ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ማውጣት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ ተከሳሽ
በበኩሉ ቼኩ በተበዳይ ላይ የተፈጸመ የማታለል ተግባር የለም ቼኩ በሚሰጥበት ጊዜ በቂ ስንቅ
እንደሌለው ተበዳዩ ያውቅ ነበር፡ ገንዘብ ከደንበኞች ተሰብስቦ እስኪሰጠው ድረስ ለመያዣ
የተሰጠ እንጂ ባንክ ቤት ቀርቦ እንዲመነዘር አይደለም የተሰጠው የሚል መቃወሚያ
አቅርቧል፡፡ ጉዳዩ በሰበር የደረሰው ጠቅላይ ፍርድቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ፡-
“……….ተበዳይን መሰረት ያደረገ ማታለል ስለመፈጸሙ ከላይ ከተመለከቱ የህ
ድንጋጌ አኳያ ጥያቄ ውስጥ ሊገባ ይችል ይሆናል(ሰረዝ የተጨመረ)፡፡ ሆኖም
ግን የወ/መ/ህ/ቁ 693/1/ በምንመለከትበት ጊዜ ርዕሱ “የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖር
ቼክ ማውጣት” የሚል ሲሆን በዚሁ አንቀጽ ንዑስ 1 ስር ማም ሰው ቼክ
በሚያወጣበት በቂ ገንዘብ ያለመኖሩን እያወቀ ቼክ ያወጣ እንደሆነ በሚል
ተደንግጓል፡፡ ይኄንን ስለ ቼክ የሚደነግገውን የወንጀል አንቀጽ ስንመለከት
በወ/መ/ህ/ቁ 692/1/ ስር ከላይ የተመለከተውን የወንጀል አፈጻጸም ከግል
ተበዳይ/ተታሏል/ ከሚባለው ግለሰብ አኳያ ያልታየ መሆኑን ነው (ሰረዝ
የተጨመረ)፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ በተለይም የቼክ ሰነድ ለአምጪው ወዲያውኑ
የሚከፈል እና በንግድ ህጉ ከተቀመጡት ውስን መቃወሚያዎች ውጪ
ሊቀርቡበት የማይገባ በመሆኑ በቼክ አውጪው ላይ ሀላፊነት የጣለ ይመስላል፡፡
ይኄም ማለት ከላይ የተመለከተው የወ/መ/ህ/ ንባብ አንድ ቼክ ያወጣ ሰው በቂ
ስንቅ መኖሩን ማረጋገጥ እንዳለበት እና ቼኩ በተሰጠበት ጊዜ ወይም ለክፍያ
በቀረበበት ጊዜ በቂ ስቅ ያለመኖሩ ብቻ የተጠቀሰውን የወንጀል ሀላፊነት
እንደተቋቋመ የሚቀበለው መሆኑን ነው” የሚል ውሳኔ ሰጥቷል59
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
59
!የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ቸሎት ውሳኔ፡- አመልካች አዱኛ አንበሎ፣ ተጠሪ የፌዴራለ ዐቃቤ ህግ
የፋይል ቁጥር 67947 ቅጽ12፣ገጽ 246-250

!
በመሰረቱ የንግድ ህጉ አንቀጽ 717 በሚተላላፉ የገንዘብ ሰነዶች አከፋፈል በሁለቱ የግል
ግንኙነትን መሰረት አድርጎ አውጪው መቃወሚያ ሊያደርግ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡ ይህም
ማለት ሰነዱን ዋጋ በማሳጣት ክፍያ አልፈጽምም በማለቱ ክርክር ቢቀርብ ተከሳሹ
በመካከላቸውን ያለውን ግንኙነት (በዋናነት የውል ግንኙነት) መሰረት አድርጎ መቃወሚያ
ሊያቀርብ ይችላል ፍርድቤትም የመቃወሚያውን ተገቢነት መርምሮ የክፈል/አትክፈል/ ውሳኔ
ይሰጣል ማለት ነው፡፡ እዳ ከፋዩ የሁለቱን ግንኙነት መሰረት አድርጎ የሚያቀርበው መቃወሚያ
ሚዛን የሚደፋ ከሆነ ከፍትሐብሄር ሀላፊነቱ ይድናል ማለት ነው፡፡ ታዲያ እንዲህ በሆነ ጊዜ
ቼክ ከቆረጡ በኋላ ገንዘቡን ከባንክ ሙሉ በሙሉ ቢያወጣውም ወይም የመቃወሚያ ክርክር
አድርጎም ቢረታ በውጤት ደረጃ በባለገንዘቡ ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም ፡፡ በመሆኑም
ገንዘቡን ከባንክ ያወጣው ህጋዊ ምክንያት መሆኑን ለማሳየት ከተቻለ እና የማታለል ሀሳቡን
ማረጋገጥ እስካልተቻለ ድረስ በወንጀል ተጠያቂ ማድረግ ወንጀል ህጉን አንቀጽ 23 መጣረስ
ይሆናል፡፡
ሌላው ቼክን ዋጋ ማሳጣት ከሚቻልባቸው መንገዶች አንዱ የአትክፈል ትእዛዝ በ አንቀጽ 854
መሰረት መስጠት ነው፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት ቼክ የቆረጠው ሰው ቼኩ ለክፍያ ከመቅረቡ
በፊት ለባንኩ ‘የአትክፈል’ ትእዛዝ ምንም አይነት ምክንያት መስጠት ሳያስፈልገው ማዘዝ
ይችላል፡፡ እንዲህ በሆነ ጊዜ አምጪው በመብቱ ሊጠቀም የሚችለው ለሚመለከተው ፍርድቤት
የክፍያ ይፈጸምልኝ ክስ በማቅረብ ነው፡፡ በሁለቱ የግል ግንኙነት ወይም በሌላ መቃወሚያ
ምክንያት ገንዘቡ ተከፋይ እንዳይሆን በባንክ የተቀመጠን ገንዘብ ሙልጭ አድርጎ ማውጣት
በህግ የተቀመጠ መፍትሔ አይደለም፣ ይህ አይነቱ ድርጊት ፍትህን በራስ እጅ እንደማድረግ
ሊቆጠርም የሚችል ከመሆኑም በላይ በወንጅ ህጉ አንቀጽ 693 ደረቅ ቼክ በመቁረጥ ሊያስከሰስ
የሚችል አደገኛ ድርጊት ነው፡፡ ሆኖም ፍርድቤት ደረቅ ቼክ መቁረጥን በሚመለከት ክስ በቀረበ
ጊዜ ወንጀሉ የማታለል ወንጀል እንደመሆኑ መጠን ድርጊቱ የተፈጸመው ለማታለል ታስቦ ነው
ወይ የሚለውን መመርመር ይጠበቅበታል፡፡ እዚሁ ጋር ተያያዥነት ያለውን ሀሳብ ላንሳ
በርግጥ በኢትዮጵያ የህግ ስርዐት እውቅና ባይኖረውም በሌች ሀገራት ኦቨር ድራፍት(over
draft) የሚባል አሰራር አለ ይኀውም አውጪው በባንኩ ካስቀመጠው ገንዘብ የበለጠ ቼክ ቆርጦ
እንደሆነ በባንኩ እና አውጪው የቀደመ ውል መሰረት ባንኩ ክፍያውን ሙሉ ለሙሉ ፈጽሞ
ከአውጪው የሚጠይቅበት ስርዐት አላቸው እንዲህ በሆነ ጊዜ ድርጊቱ ወንጀል አይሆንም
ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ወንጀል በቀረበ ጊዜ በተለይም ተከሳሹ ፍትሐብሄራዊ መከራከሪያ

!
አቅርቦ እንደሆነ ወንጀሉ የማታለል ወንጀል እንደመሆኑ መጠን የማታለሉ ፍሬ ነገር ተሟልቶ
መሆኑን ማረጋገጥ ይጠይቃል፡፡
የማታለል ሀሳብ መኖር፣ እና በቂ ስንቅ አለመኖሩን ማወቅ የወንጀሉ ማቋቋሚያ ፍሬ ነገሮች
መሆናቸውን በአንዳነድ ሀገራት የህግ ስርዐት ተካቷል፡፡ በዚህ ረገድ በቂ ስንቅ አለመኖሩ እና
ባለእዳውም በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ለመክፈል እንቢተኛ የሆነ እንደሆነ የማታለል ሀሳብ
እንዳለው ማስረጃ ይሆናል፡፡60 ነገር ግን በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ክፍያውን የፈጸመ
እንደሆነ የወንጀል ተጠያቂነት አይኖርበትም፡፡ በሌላ በኩል ቼኩ የተሰጠው እንዲሁ ያለ ዋጋ
የሆነ እንደሆነ በተመሳሳይ የወንጀል ተጠያቂነትን አያስከትልም፡፡61 ይኀውም ከላይ እንተገለጸው
ቼክ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ለሚደረግ ግብይት ክፍያ፣ የብድር ዋስትና ወይም መሰል ህጋዊ
ግንብይተን ለማቀላጠፍ ጥቅም ላይ የሚውል ሰነድ እንደመሆኑ መጠን ሰነዱ ያለ ዋጋ ተሰጥቶ
አንደሆነ ሰጪው የማታለል ሀሳብ አለው ተብሎ የማይገመት በመሆኑ የወንጀል ጥፋት
አይሆንም ማለት ነው፡፡
በእርግጥ አንቀጽ 693 በደፈናው በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ መቁረጥ የሚያስቀጣ መሆኑን
ከመደንገግ ውጪ ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች ቢፈጠሩ በምን አግባብ መስተናገድ አለባቸው
የሚለውን መልስ አይሰጥም፡፡ ሆኖም ህግን የመተርጎም ስልጣን ያለው ፍርድቤት ያለውን
ነባራዊ ሁኔታ፣ የህጉን ጠቅላላ አላማ ከግምት ውስጥ በማስገባት ተገቢነት ያለው ውሳኔ ሊሰጥ
ይገባል፡፡ በዚህም መሰረት ከላይ የተጠቀሰው የሰበር ውሳኔ የወንጀል ህግ አንቀጽ 693 አቀራረጽ
እና አላማ የማታለል ተግባርን በመፈጸም የሶስተኛ ወገንን ጥቅም የሚጎዱ ድርጊቶችን
ለመከላከል የተደነገገ ነው በማለት ሀተታውን ካስቀመጠ በኋላ ያለ በቂ ምክንያት ድርጊቱ
በማታለል ሀሳብ ተፈጸመም አልተፈጸመ ተጠያቂነት ያመጣል በሚል ቅኝት የሰጠው ውሳኔ
ተገቢነት የለውም፡፡

የማጠቃለያ ሀሳብ
ሀገር በኢኮኖሚው ዘርፍ እየበለጸገች በሄደች ቁጥር ግብይትን የሚያቀላጥፉ የህግ እና የአሰራር
ስርዐቶችን መዘርጋት የሚያስፈልግ ከመሆኑም በላይ የተዘረጉትን የህግ እና የአሰራር ስርዐቶች
በአግባቡ ተረድቶ ለተፈጻሚነታቸው የየራሱን ድርሻ ማበርከት የሁሉም የመንግስት አካላት

!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
60
! Comercial Law League of America, Summary of States Bad check Law, January, 2007,
available at http://www.alqlist.com/NSFChecks.html reitrived on 7/19/17 9:44 AM
61
ዝኒ ከማሁ!

!
ሀላፊነት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ ላምጪው ወይም ስሙ ተለይቶ
ለተጠቀሰ ሰው እንዲከፈል የሚያዝዝ ወይም ቃል የሚገባ ሰነድ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ከዚህ
ትርጉም የሚመዘዙ በርካታ ልዩ ባህሪያት ያሉት ሲሆን የመጀመሪያው እና ዋነኛው ያለ ምንም
ቅድመ ሁኔታ ክፍያ እንዲፈጸም ትእዛዝ የሚሰጥበት/ቃል የሚገባበት/ ሰነድ መሆኑ የሚተላለፍ
የገንዘብ ሰነድን ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ እንዲተላለፍ እድል ሰጥቶታል፡፡ ሌላው በጽሁፍ መሆን
እና በአውጪው የሚፈረም መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ከአውጪው ወይም ህጋዊ ወኪሉ
ውጪ የሚደረግ የሰነድ አጻጻፍ እና አፈራረም በህግ ተቀባይነት የለውም ማለት ነው፡፡ ሌላው
የሚከፈለውን ገንዘብ በግልጽ የሚያሳይ እና የገንዘብ አከፋፈሉም በጥሬ ገንዘብ መሆን
ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም ሰነዱ ከሰው ወደ ሰው ሲተላለፍ ለክፍያ አዳጋች አይሆንም ማለት
ነው፡፡ በሌላ በኩል በሰነዱ ላይ ያለውን መብት ለመጠቀም ሰነዱን በጅ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
ከዚህ አንጻርም በሰነዱ ላይ መብት አለኝ የሚል አካል ሰነዱን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በንግድ
ህጉ እውቅና የተሰጣቸው የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች የሀዋላ ወረቀት፣ የተስፋ ሰነድ፣ ቼክ
የመንገደኞች ቼክ እና በእቃ ማስቀመጫ ለተቀመጡ እቃዎች የሚሰጡ የምስክር ወረቀቶች
ናቸው፡፡ እያንዳንዳቸው ሰነዶች ከላይ ከተሰጠው ትርጉም አንጻር አያሌ ተመሳስሎቶች
ቢኖሯቸውም ልዩ የሚያደርጓቸውም በርካታ ቁምነገሮች አሉ፡፡ የተወሰኑቱ እንደቀረቡ
የሚከፈሉ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ተለይቶ በታወቀ ጊዜ የሚከፈሉ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል
አንዳንዶቹ ክፍያ እንዲፈጸም ትእዛዝ የሚሰጥባቸው ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ ክፍያ ለመፈጸም
ቃል የሚገባባቸው ናቸው፡፡ እንዲሁም አንዳንዶቹ ሰነዶች በማዘዝ መታዘዝ ሂደቱ ከ ሶስት
ያላነሱ ሰዎች ተሳታፊ የሚሆኑባቸው ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ በሁለት ሰዎች ብቻ የሚከናወኑ
ናቸው፡፡
ተላላፊ የገንዘብ ሰነዶችን በሚመለከት አትኩሮት የሚሻው ጉዳይ የሰነድ አያያዙ በመብት
አጠቃቀሙ ላይ የሚኖረው ሚና ነው፡፡ በዚህ ረገድ ሰነዱን በቅን ልቡና የያዘ ሰው ሰነዱን
ባወጣው እና ሰነዱ ቀድሞ በደረሰው ሰው መካከል ያለ የግል ግንኙነት መቃወሚያ ሆኖ
ሊነሳበት አይችልም፡፡ በሌላ በኩል ያዡ ተራ ያዥ የሆነ እንደሆነ ግን ሰነዱን ባወጣው ሰው እና
ቀድሞ ሰነዱ በደረሰው ሰው መካከል ያለ የግል ግንኙነት ስለ ገንዘብ አከፋፈሉ መቃወሚያ ሆኖ
ሊነሳበት ይችላል፡፡ በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ላይ የሚነሱ መቃወሚያዎች ሁለት ሲሆኑ
ጽኑ መቃወሚያ እና በሁለቱ የግል ግንኙነት መሰረት የሚነሳ መቃወሚያ ነው፡፡ በመሆኑም
ያዡ ተራ ያዥ ወይም በመደበኛ መተላፍ ስነስርዐት የተለላለፈለት ሰው እደሆነ በሁለቱ
መካከል ያለ ግል ግንኙነት መቃወሚያ ሆኖ ይነሳበታል፡፡ ሆኖም ያዡ የቅን ልቡና ያዥ የሆነ

!
እንደሆነ ግን ሊነሳበት የሚችለው መቃወሚያ ጽኑ መቃወሚያ ብቻ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ህጉ
በላይ በአፋዊ ይህንን የመሰለ አረዳድ ቢኖረውም በተጨባጭ ግን ህጉን በመተርጎም ሂደት
የተለያዩ ግድፈቶች ሲፈጸሙ ማየት ተችሏል፡፡ በተለይም በሰነዱ ላይ የሚነሱ መቃወሚያዎች
ምንነት እና በምን ሁኔታዎች ሊነሱ እንደሚገባ፣ በየትኞቹ ሰነዶች ላይ ሊነሱ እንደሚገባ፣
የይርጋ መቃወሚያን በሚመለከት ደግሞ የትኛው የጊዜ ሰሌዳ ለየትኛው ሰነድ
እንደሚያገለግል፣ በቼክ ላይ የሚቀርብ ክርክር በተፋጠነ ስነስርዐት እንዲታይ በከሳሹ የሚቀርን
ጥያቄ በሙሉ በመቀበል በንግድ ህጉ መሰረት የሚነሱ መቃወሚያዎችን ወደ ጎን በመተው
የሚሰጡ ውሳኔዎች የሰነዶቹን ባለዋጋነት የሚሸረሽሩ ናቸው፡፡ የስረነገር ስጣንን በሚመለከትም
ክርክሩ የተነሳው በቼክ ስለሆነ ብቻ የፌዴራል ፍርድቤቶች ስልጣን ነው ተብሎ የሚሰጠው
ውሳኔ የሰነዶቹን ልዩ ባህሪ ከግምት ውስጥ ያላስገባ ሆኖ ይገኛል፡፡በተጨማሪም ስንቅ የሌለው
ቼክ ስለሚያስከትለው የፍትሐብሄር እና የወንጀል ተጠያቂነት አንጻር ሊነሱ ስለሚገቡ
መከላከያዎች ያልተካከለ መረዳት ያለ መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ፍርድቤቶች ከተሰጡ
ውሳኔዎች ለመረዳት ይቻላል፡፡ በመሆኑም ፍርድቤት የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን የሚመለከቱ
ክርክሮች በሚነሱበት ጊዜ የንግድ ህጉን ተገቢነት ያላቸውን ድጋጌዎች ከሌሎች ህግጋት ጋር
በማጣጣም ውሳኔ መስጠት ያስፈልጋል፡፡
የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ግብይትን በማቀላጠፍ ረገድ የማይተካ ሚና የሚጫወቱ መሆኑን
ባለመዘንጋት ህግ አውጪው አካልም ከሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ባህሪያት ጋር የማይስማሙ
ድጋጌዎችን በተለይም የተስፋ ሰነድን በሚመለከት በሀዋላ ወረቀት ላይ የሚሰሩ ድንጋጌዎችን
በሙሉ ለተስፋ ሰነድም እንዲሰሩ በማድረጉ በተጨባጭ ለአፈጻጸም የማያመች በመሆኑ ለሰነዱ
ተገቢውን የህግ ሽፋን መስጠት ይገባዋል፡፡
!

You might also like