Professional Documents
Culture Documents
BANK Letter of Guarantees
BANK Letter of Guarantees
com
ገዙ አየሇ መንግስቱ
የዋስትና ሰነድች1 ባንኮች በተሇይም ሇዯንበኞቻቸው ከሚሰጧቸው የብዴር አገሌግልቶች
መካከሌ ዋነኞቹ ናቸው። የዋስትና ሰነድች በባንኮች የሚሰጡት ዯንበኞች የተሇያዩ
ስምምነቶችን ከላልች ሶስተኛ ወገኞች ጋር ፈጽመው ያሇባቸውን ግዳታ በአግባቡ
ሇመወጣታቸው ከባንኮች ዋስትና እንዱሰጥሊቸው በሚያቀርቡት ጥያቄ መሰረት ነው።
የዋስትና ዯብዲቤ የሚሰጠውም አንዴን ሰው የብዴር አገሌግልት ወይም እቃዎቸንና
አገሌግልቶችን ሇላሊ ሶስተኛ ወገን በብቃት እንዱያቀርብ መተማመኛ በመሆን ነው።2 ዋስትና
ሰነዴም አንዴ ሰው አንዴን የተሇየና የተወሰነ ስራ ሇላሊ ሰው ሇመስራት ግዳታ ከገባ ይኸው
ሰው በውለ መሰረት የገባውን ግዳታ መፈጸም የሚችሌ መሆኑን ሇማረጋገጥ ላሊው ሰው
የሚያቀርበው ውሌ ነው።3 የዋስትና ሰነድች የባንክ የብዴር አይነቶች ወይም የብዴር
አገሌግልት መሆናቸውን ከማየታችን በፊት ግን የዋስትና ሰነድች ምን ማሇት እንዯሆኑ ማየቱ
ተገቢነት ይኖረዋሌ።
1
የዋስትና ሰነድች በተሇያዩ ስያሜዎች የሚጠሩ ሲሆን በዚህም መሰረት በእንግሉዝኛ ‘independenundertakings’, ‘performance
bonds/guarantees’, ‘tender bonds/guarantees’, ‘independent (bank) guarantees’, ‘demand guarantees’, ‘first demand
guarantees’, ‘bank guarantees’, and ‘default undertakings’ በሚለ ስሞች ሉጠሩ ይችሊለ። ከዚህ በተጨማሪም እነዚሁ
ሰነድች’standby Letters of Credit’ ተብሇው ሉጠሩ እንዯሚችለ የተሇያዩ ጽሁፎች ያሳያለ። See M Coleman ‘Performance
Guarantees’ (1990) Lloyd’s Maritime and Commercial Law Quarterly 223 at 223. በዚህ መጽሀፍ ውስጥም
የዋስትና ሰነድች የሚሇው ጥቅሌ ስያሜን ሇመጠቀም የተሞከረ ሲሆን አንዲንድቹ ስያሜዎችም የዋስትና አይነቶችን የሚያመሇክቱ
መሆኑን መገንዘብ ያስፈሌጋሌ።
2
MC Kuchhal (2015), Merchantile Law, VIKAS PUBLISHING HOUSE PVT LTD.
3
የፌዯራሌ ጠቅሊይ ፍርዴ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር መዝገብ ቁጥር 47004፤ በአመሌካች የኢትዮጵያ መዴን ዴርጅት እና ተጠሪ
ባላ ገጠር ሌማት ዴርጅት፤ ቅጽ 12 የተሰጠ የሰበር ውሳኔ።
www.abyssinialaw.com
በቀጥታ ግዳታውን እንዯሚወጣ በማረጋገጥ የሚዘጋጅ ነው። የዋስትና ሰነድችን በተመሇከተ
የህግ ሽፋን የሰጠው የተባበሩት መንግስታት ኮንቬንሽን (UN Convention on
Independent Guarantees and Standby Letters of Credit) የዋስትና ዯብዲቤ ምን
ማሇት እንዯሆነ እና የዋስትና ዯብዲቤ አይነቶችንም ሇመዘርዘር ሞክሯሌ።4 በዚሁ አሇም
አቀፍ ህግ መሰረትም የዋስትና ዯብዲቤ በአዘጋጁ (በብዛት ባንኮች ሲሆኑ) ዯብዲቤው
ሇተዘጋጀሇት ተጠቃሚ ዋስትና የተገባሇት ግዳታ በባሇዕዲው የማይከፈሌ ቢሆን የዋስትና
ዯብዲቤውን የጻፉት ባንኮች ባሇዕዲውን ተክተው ክፍያውን (ዕዲውን) ሇመክፈሌ ዋስትና
እንዯሚሆኑ በመግሇጽ የሚሰጥ ዯብዲቤ ነው። ይሁንና ግን ይህ ኮንቬንሽን የሚያገሇግሇው
አሇም አቀፍ የሆኑ ግብይቶችን በተመሇከተ እንዯሆነ ተገሌጿሌ።5 ኮንቬንሽኑንም የፈረሙት
ሀገሮች ጥቂት በመሆናቸው ሁለም ሀገሮች በዚህ ስምምነት መሰረት ይዲኛለ ባይባሌም
አብዛኛው ሀገራት ግን የዋስትና ሰነድችን በተመሇከተ በሚያወጧቸው ህጎች የዚህን ስምምነት
አንቀጾች ከግንዛቤ በመክተት ሉሆን ይችሊሌ። ኮንቬንሽኑ በተሇይም የተሇያዩ አይነት የዋስትና
ዯብዲቤ አይነቶች እንዲለ ዯንግጓሌ።
ዋስትና የገንዘብ፣ የሰው እንዱሁም የንብረት እና የሰነዴ ዋስትና ሉሆን ይችሊሌ። እነዚህ
የዋስትና አይነቶች ግን በየራሳቸው ሌዩነት ያሊቸው ሲሆን ሁለንም በተመሳሳይ መሌኩ
ትርጉም በመስጠት ወይም አንደን በአንደ እያቀያየርን መጠቀም በመሰረታዊነት ያለትን
የተሇያዩ የዋስትና አይነቶች እና ያሊቸውን ጠቀሜታ የሚያጠፋ ይሆናሌ። በዋናነት በንብረት፤
4
UN Convention on Independent Guarantees and Standby Letters of Credit, articles 1 and 2.
5
ዝኒ ከማሁ፤ አንቀጽ( 1)።
www.abyssinialaw.com
በሰው እና በሰነዴ ዋስትና መካከሌ ያሇውን ሌዩነት ሇመገንዘብ የፍትሐብሔር ህጉን
ዴንጋጌዎች መመሌከት ያስፈሌጋሌ።
በሀገራችን በተሇይም እነዚህ የዋስትና አይነቶች በአሇም አቀፍ ዯረጃም በተገባር ሊይ መዋሌ
የጀመሩትና ይህ ሌማዴም ወዯ ሀገራችን ገብቶ በባንኮች መተግበር የጀመረውም የንግዴ ህጉና
የፍትሐብሔር ህጉ ከወጡ በኋሊ በመሆኑ የዋስትና ሰነድን በተመሇከተ የፍትሐብሔር ህጉን
መሰረት በማዴረግ የሚሰጡ የፍርዴ ቤት ውሳኔዎችም ሆነ የህግ ትርጉሞች በመሰረታዊነት
እነዚህ በባንኮች በአገሌግልት ሊይ የሚውለ የዋስትና ሰነዴ አይነቶችን የማይወክለ
የሚሆኑት።6 በአሇም አቀፍ ዯረጃም ቢሆን የዋስትና ሰነድችን በተሇይም (Independent
6
MICHELLE KELLY-LOUW (2008), SELECTIVE LEGAL ASPECTS OF BANK DEMAND GUARANTEES, PhD thesis.
Banks in the United States developed the use of standbyletters of credit as a result of the accepted construction of
the United States’ National Bank Act of 3 June 1864 (as amended) which precluded the United States banks from
giving guarantees as part of their banking business. በተጨማሪም በአብዛኛው የዋስትና ሰነድችን በአሇም አቀፍ ዯረጃ የሚገዙ
ህጎች፣ እንዯ URDG 458 እና URDG 758 በተግባር ሊይ የዋለት ከ1992 እስከ 2010 በሆኑት ጊዜያት እንዯሆነ ሰነድቹ ያሳያለ።
www.abyssinialaw.com
Letter of Guarantees) በተመሇከተ በኮዴ መሌክ የወጣውና በአብዛኛው ሀገሮችና
ተቋማት አገሌግልት ሊይ የሚውሇው URDG 458 የሚባሇው ሰነዴ ሲሆን ሰነደም ከጥቂት
አመታት በኋሊ URDG 758 በሚሌ ተሻሻል ቀርቧሌ።7 ስሇዚህም የዋስትና ሰነድች ታሪካዊ
አመጣጥና በተግባር አገሌግልት ሊይ መዋሌ የጀመሩትም የኢትዮጵያ የፍትሐብሔርና የንግዴ
ሕግ ከወጡ በኋሊ መሆኑን መገንዘብ ይቻሊሌ።
በፌዯራሌ ጠቅሊይ ፍርዴ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዝገብ 47004 በተሰጠ አስገዲጅ
የህግ ውሳኔ መሰረት የመሌካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ውሌ በፍትሐብሔር ሕግ ዴንጋጌዎች
መሰረት የሚገዛ መሆኑን ገሌጿሌ።8 ሰበር ችልቱ በርካታ ትንታኔዎችን በጉዲዩ ሊይ ሇመስጠት
የተጓዘበት ርቀት ጥሩ የሚባሌ ቢሆንም በመሰረታዊነት ግን ውሳኔው ሁለንም የህግ ባሇሙያ
ሉያስማማ የሚችሌ አይመስሌም። ሇዚህም ዋነኛ ምክንያቱ በውሳኔው ሊይ የዋስትና ሰነዴን
የዋስትና ውሌ ሲሌ የገሇጸው ሲሆን ከሊይ በተመሇከትነው መሰረት ግን ሰነደ በባንኮች
ተዘጋጅቶ የዋስትና ተጠቃሚውም ሆነ አበዲሪው በዚህ ሰነዴ ሊይ ምንም አይነት የስምምነት
ፊርማ ሳያስቀምጡ፤ እንዯላልች ውልችም ምስክሮች መኖርም ሆነ መፈረም ሳያስፈሌጋቸው
በባንኮቹ ብቻ ተፈርመው ሇዋስትና ተጠቃሚው የሚሰጡ ሰነድች ናቸው።
7
ዝኒ ከማሁ።
8
የፌዯራሌ ጠቅሊይ ፍርዴ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር መዝገብ ቁጥር 47004፤ አመሌካች የኢትዮጵ ያ መዴን ዴርጅት እና ተጠሪ
ባላ ገጠር ሌማት ዴርጅት፤ ቅጽ 12።
www.abyssinialaw.com
ያሌተመሰረተ መሆኑን የሚያሳይ ነው በሚሌ ያስቀመጠው ነው።9 ይህ ትንታኔም በአንዴ
በኩሌ የሰው ዋስትናን ከሰነዴ ዋስትና ጋር ሇማመሳሰሌ የተዯረገ ይመስሊሌ። ይሁንና ስሇሰው
ዋስትና የተቀመጠው ይህ ትንታኔ በምንም መሌኩ የሰነዴ ዋስትናን የሚወክሌ አይዯሇም።
ምክንያቱ ዯግሞ በባንኮችም ሆነ በኢንሹራንስ ዴርጅቶች የሚሰጡ የሰነዴ ዋስትናዎች
እስካሁን ባሇው ተጨባጭ ሁኔታ በችሮታ የሚሰጡ ሳይሆን በተሇይ ባንኮች የሰነዴ
ዋስትናዎችን ሇመጻፍ ከተጠቃሚው ጋር የንብረት ወይም የገንዘብ መያዣ ውሌ የሚገቡ
ሲሆን የዋስትና ሰነድቹንም ሇተጠቃሚው የሚጽፉት የዋሰትና መጠኑን መሰረት አዴርገው
በሚቀበለት የገንዘብ ኮሚሽን እንጂ በችሮታ አሇመሆኑ ነው።
ችሮታም የሰው ዋስትና መሰረታዊ መሇያ ባህሪ እንጂ ሇሰነድች ዋስትና የሚሰራ ጉዲይ
አይዯሇም። የሰነዴ ዋስትና ሇመጻፍም ባሇእዲው ሳያውቅ መጻፍ የማይቻሌ ሲሆን የሰነዴ
ዋስትናን ሇመጻፍ የግዳታ ባሇእዲው በአካሌ ቀርቦ ሇባንኩ ማመሌቻ ማስገባትና ሇሰነደ
መጻፍ መሰረት የሆነውን የመያዣ ውሌ መዋዋሌ ግዴ የሚሌ ነው። በመሆኑም የሰነዴ ዋስትና
ሇመስጠት የባሇእዲው መቅረብና ስሇዋስትናው ማወቅ የግዴ ነው። በላሊ በኩሌ ከሊይ
ሇመግሇጽ እንዯተሞከረው የዋስትና ሰነዴ የፍትሐብሔር ህጉ ከወጣ በኋሊ የመጣ ጽንሰ ሀሳብ
በመሆኑ ይህንን ግዳታ ወዯፍትሐብሔር ህጉ ወስዯን ትርጉም ሇመስጠት መሞከሩ አግባብ
ያሌሆነ መሆኑ ነው። በመሆኑም የሰበር ችልቱ የሰነዴ ዋስትናን ከሰው ዋስትና ጋር ሇማዛመዴ
የሞከረበት ትንታኔው ከዚህ በሊይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ተቀባይነት ያሇው
አይመስሌም።ይህ የሚያመሇክተንም በመሰረቱ እነዚህ የዋስትና አይነቶች በሌማዴ ባንኮች
በተግባር በሰፊው ይጠቀሙባቸው እንጂ አገሌግልታቸው ተሇይቶ እንዳት እንዯሚዘጋጁ እና
በምን ህግ እንዯሚገዙም የሚገሌጽ ግሌጽ የህግ ዯንጋጌ አሁን ባለት የንግዴ ህግም ሆነ
በፍትሐብሔር ህግ ውስጥ የላሇ መሆኑን ነው።
9
የፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ 921ን ይመሌከቱ።
www.abyssinialaw.com
ሳይጠበቅበት የተባሇው ግዳታ እንዲሌተፈጸመ በአበዲሪው ሲገሇጽሇት በዋስትና ዯብዲቤው
የጊዜ ገዯብ ውስጥ መሆኑን በማረጋገጥ የሚከፈለ የዋስትና ዯብዲቤዎች ናቸው። በሁኔታ ሊይ
የተመሰረቱ የዋስትና ዯብዲቤዎች ዯግሞ ዋሱ ሇአበዲሪው የዋስትና ግዳታውን ሇመወጣት
እንዱያስችሇው ባሇአዲው (ዋስትና የተገባሇት ሰው) ግዳታውን ያሌተወጣው በማን ጥፋት
ነው የሚሇውን ካረጋገጠ በኋሊ እና ጥፋቱ የባሇእዲው መሆኑ ከተረጋገጠ በኋሊ የሚወጣው
ግዳታ ነው።
11
የፌዯራሌ ሰበር ሰሚ ችልት መዝገብ ቁጥር 47004።