You are on page 1of 21

ስለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች

የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

(ረቂቅ)

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ


መስከረም 2012
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር Council of Ministers Regulation No. …/2019


…./2011

ስለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የወጣ Council of Ministers Regulation on Civil


የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ Society

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሲቪል ማኅበረሰብ This regulation is issued by the FDRE Council
ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀፅ of Ministers pursuant to Article 89 (1) of the
89(1) መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷል። Civil Society Organizations Proclamation No.
1113/2019.

ክፍል አንድ PART ONE

ጠቅላላ GENERAL PROVISIONS

1. አጭር ርዕስ 1. Short Title


This Regulation may be cited as “Civil Society
ይህ ደንብ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች
Organizations, Council of Ministers Regulation
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ
No…../2019.”
ቁጥር________/2012 ተብሎ ሊጠቀስ
ይችላል።

2. ትርጓሜ 2. Definitions
Unless the context otherwise requires, in this
በዚህ ደንብ ውስጥ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም
Regulation:
የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር፦
1. “Proclamation” means the Civil Society
1. “አዋጅ” ማለት የሲቪል ማኅበረሰብ Organizations Proclamation No.
ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 1113/2011.
ነው።
2. The definitions provided under Article 2 of
2. በአዋጁ አንቀፅ 2 ስር የተሰጡ
the Proclamation shall be applicable to this
ትርጓሜዎች ለዚህም ደንብ ተፈፃሚ
ይሆናሉ። Regulation.

2
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

ክፍል ሁለት PART TWO

የድርጅቶች አመሰራረትና ምዝገባ ESTABLISHMENT AND


REGISTRATION OF ORGANIZATIONS

ንዑስ ክፍል አንድ Sub Section One


የድርጅቶች መቋቋም Establishment of Organizations

3. በምዝገባ ሂደት ላይ ላሉ ድርጅቶች 3. Assistance for Registering Organizations


ስለሚደረግ ድጋፍ

1. ከኤጀንሲው ድጋፍ የሚፈልግ ማንኛውም 1. Any founding member of an Organization


በመመዝብ ሂደት ላይ ያለ ድርጅት under process of registration may request
መስራች ከምዝገባው ጋር የተያያዙ for a letter of support from the Agency to
አስፈላጊ ተግባራትን ለማከናዎን carry out activities relevant to its
ከኤጀንሲው የፅሁፍ ድጋፍ እንዲሰጠው establishment.
መጠየቅ ይችላል።

2. በዚህ አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ 1 መሰረት 2. A letter of support issued in accordance


በኤጀንሲው የሚፃፍ የድጋፍ ደብዳቤ ስለ with sub-Article (1) of this Article shall
ድርጅቱ ምዝገባ፣ የምዝገባ ሁኔታ only state facts relating to the
ወይም ሌሎች ከምዝገባው ጋር የተያያዙ organization’s registration, the status of its
መረጃዎችን እና በምዝገባው የተካተቱ registration or other factual matter relating
ጉዳዮችን ብቻ የሚያካተት መሆን to its registration and the information
አለበት፡፡ contained therein.

3. ኤጀንሲው አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በዚህ 3. Where the Agency finds necessary, it may
አንቀፅ መሰረት የሚፅፈው ደብዳቤ specify the validity period of the letter of
ተቀባይነት የሚያገኝበትን ጊዜ ገድቦ support issued as per this Article.
ሊያስቀምጥ ይችላል።

3
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

4. የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት መቋቋም 4. Establishment of Charitable Endowments

1. ኤጀንሲው በአዋጁ አንቀፅ 21 ንዑስ 1. The Agency, in accordance with Article 21


አንቀፅ 2 መሰረት ለበጎ አድራጎት አላማ sub-Article (2) of the Proclamation, may
በስጦታ ወይም በኑዛዜ የሚሰጥ የንብረት decide, by a Directive, on capital
ወይም የገንዘብ መጠን የበጎ አድራጎት requirement indicating the initial finance or
አላማውን በመነሻነት ሊያሳካ የሚችል value of property required as a donation or
ነው የሚባለውን የገንዘብ መጠን bequest to further a charitable aim.
በመመሪያ ሊወስን ይችላል።

2. የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት መመስረት 2. A person who intends to establish a


ያሰበ ሰው ወይም ህጋዊ ወኪሉ ለበጎ charitable endowment or a legal
አድራጎት አላማ ሊያውል የፈለገውን representative shall deposit the money
የገንዘብ መጠን ገንዘቡን ሊያቋቁም allocated for this purpose in a blocked
በታሰበው ድርጅት ስም ወይም በኤጀንሲው account of the endowment or the Agency.
ዝግ አካውንት ማስገባት ይኖርበታል፡፡ When a request is made to open a blocked
ሊቋቋም በታሰበው የዘለቄታ በጎ አድራጎት account in the name of the intended
ድርጅት ስም ዝግ አካውንት እንዲከፈት charitable endowment, the Agency shall
በተጠየቀ ጊዜ ኤጀንሲው ለባንክ ደብዳቤ
write the bank a letter to that effect.
ይፅፋል።

3. ለበጎ አድራጎት ሥራ የተሰጠው 3. Where the property donated for the


የማይንቀሳቀስ ንብረት በሚሆንበት ጊዜ charitable work is immovable,
ስልጣን ባለው ውል አዋዋይ እና ሰነድ authenticated donation agreement or will
አረጋጋጭ አካል የፀደቀ የስጦታ ውል፤ made orally or in writing or, depending on
በቃል ወይም በፅሁፍ የተሰጠ ኑዛዜ፤ the circumstances, a decision of a court of
እንደነገሩ ሁኔታ የፍርድቤት ውሳኔ law, or any other documents or evidences
ወይም ሌላ ማናቸውም ይህንን that may show the same may be presented.
ሊያረጋግጡ የሚችሉ በህግ ተቀባይነት
ያላቸው ሰነዶች ወይም ማስረጃዎች
ሊቀርቡ ይችላል።

4. የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅቱ 4. Once an Endowment is registered by the


በኤጀንሲው ከተመዘገበ በኋላ ገንዘቡ Agency, the money or the property
ወይም ንብረቱ ወደተመዘገበው ድርጅት indicated under Sub Article 2 of this
ይተላለፋል። Article shall be transferred to its bank
account.

4
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

5. የአደራ እና የዘለቄታ በጎ አድራጎት 5. Utilization of Assets of Charitable Trust


ድርጅት ንብረትን ለበጎ አድራጎት አላማ and Charitable Endowments
ስለማዋል

1. ኤጀንሲው የአደራ ወይም የዘለቄታ በጎ 1. If the Agency ascertains that a property or


አድራጎት ድርጅትን ለማቋቋም የተሰጠ asset donated for the purpose of
ንብረት ወይም ሃብት ለታቀደለት የበጎ establishing a charitable trust or charitable
አድራጎት ዓላማ ከመዋል ይልቅ endowment has been used for the personal
መስራቾቹን፣ ባለአደራዎቹን ወይም benefit of the founders, trustees or
አስተዳዳሪዎቹን በግል ለመጥቀም ተብሎ administrators instead of the intended
እንደዋለ ከደረሰበት ወይም የተሰጠው purpose, or has been transferred back to the
ንብረት ወይም ሃብት ድርጅቱ ከተቋቋመ donor or his heirs after the establishment of
በኋላ ለለጋሹ ወይም ለለጋሹ ወራሾች
the Organization; it may, representing the
እንዲመልስ መደረጉን ከተረዳ የበጎ
beneficiaries of the charitable aim, bring
አድራጎት አላማውን ተጠቃሚዎችን
action in court of law for the restitution of
በመወከል ንብረቱ ወይም ሃብቱ
ለታቀደለት አላማ እንዲውል በፍርድ ቤት the property or asset to the intended
ክስ ሊያቀርብ ይችላል። purpose.

2. ኤጀንሲው የዘለቄታና የአደራ የበጎ 2. If Agency, in the course of facilitating the


አድራጎት ድርጅቶች የሥራ አመራር ቦርድ appointment of members of the
ወይም ባላደራዎች የሚሾሙበትን መንገድ management board or trustees of a
በሚያመቻችበት ሂደት የሥራ አመራር charitable trust or charitable endowment,
ቦርድ ወይም ባላደራዎች አሿሿምን identifies, civil litigation risks relating to
ማንነታቸውን ወይም ተያያዥ ጉዳዮችን the identity or appointment of members of
የሚመለከቱ የፍትሐ ብሔር ክርክሮች the management board or trustees, or other
ውጤት በንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከቱት similar matters; risks provided in Article 21
ስጋቶች ወይም የተጠቃሚዎችን መብትና
sub-article (1); or risks to the rights and
ጥቅም የሚጎዱ ሁኔታዎች እንደሚከሰቱ
interests of beneficiaries, it may refer the
ካመነ ጉዳዩን ለሚመለከተው ፍርድ ቤት
matter to a court of law or submit an
ክስ ሊያቀርብ ወይም ሌላ ጉዳዩን ለያዘው
አካል የጣልቃ ገብ ማመልከቻ ወይም amicus brief to the authority handling the
ማስረጃ ሊያቀርብ ይችላል። matter.

5
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

3. ኤጀንሲው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀፅ 2 3. If the Agency, in the course of implementing
ስር የተመለከተውን በሚያስፈጽምበት ጊዜ the provisions of this Article, identifies a
የወንጀል ድንጋጌዎች ጥሰት መኖሩን ካመነ violation of penal laws, it shall file a
በይዞታው የሚገኘውን መረጃ በማሰባሰብ complaint or claim based on the evidence in
አግባብነት ባለው ህግ መሰረት አቤቱታ its possession and the applicable law; and
ወይም ክስ ያቀርባል፣ አግባብነት ባለው cooperate and provide the necessary support
የወንጀል ህግ አስፈጻሚ አካል ሲጠየቅ in criminal proceedings upon the request of
የወንጀል ስነ ሥርዓት ሂደት ውስጥ the appropriate law enforcement body.
አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ ያደርጋል።

6. ህብረት 6. Consortium

1. ተመሳሳይ አላማ ያላቸው ድርጅቶች 1. Organisations with similar objectives shall


የተመሰረቱበትን የጋራ አላማ በሚገባ be encouraged to form a consortium to
መወጣት እንዲችሉና አባላቱ የተሰማሩበት fulfil their objectives effectively and
ዘርፍ ላይ ቅንጅታዊ አሰራርን promote coordinated
ለማበረታታት ሲባል ህብረት እንዲመሰርቱ
ይበረታታሉ።

2. ህብረቶች አዲስ የሚቀላቀሉዋቸውን አባላት 2. Consortiums shall notify the Agency of the
ጨምሮ በስራቸው ያሉ አባላትን ዝርዝር names of their members including those of
በአመታዊ ሪፖርታቸው ላይ በማካተት new members by appending the list in their
ለኤጀንሲው ማሳወቅ ይኖርባቸዋል። yearly report.

7. የሙያ ማህበራት 7. Professional Associations

1. ለዚህ ደንብ ዓላማ “ሙያ” ማለት ከአንድ 1. For the purposes of this Regulation,
በመንግስት እውቅና ካገኘ የትምህርት “profession” means educational certificate
ተቋም በአንድ ሙያ ዙሪያ ስላለ እውቀት፤ issued by officially recognised educational
ልምድ ወይም ክህሎት የሚሰጥ institution confirming knowledge,
የትምህርት ማስረጃ ወይም ሌላ ሙያን experience or skill relating to a profession
ማረጋገጥ በሚችል የመንግስት አካል or a profession certified by relevant
ወይም ስልጣን ባለው አካል የተረጋገጠ Government or authorized body.
ሙያ ማለት ነው፡፡

2. የሙያ ማህበራትን ውጤታማነት ለማሳደግ 2. In order to enhance the effectiveness of


ማህበራቱ የሚሰማሩበትን የሙያ ዘርፍን professional associations, Governmental
የሚመሩ የመንግስት አካላት ከማህበራቱ bodies shall closely work with and support
ጋር በቅርበት መስራትና ድጋፍ ማድረግ

6
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

ይኖርባቸዋል። those professional associations operating in


the sector they govern.

ንዑስ ክፍል 2 Sub Section Two


የድርጅቶች አመዘጋገብ Registration of Organizations

8. ለምዝገባ የሚያመለክቱ ድርጅቶች አድራሻ 8. Address of Organizations Applying for


Registration

1. ድርጅቶች ለምዝገባ በሚያመለክቱበት 1. If Organizations do not have a permanent


ወቅት የሚመሰረተው ድርጅት ቋሚ address at the time of request for their
አድራሻ የሌለው ከሆነ ለምዝገባ ዓላማ registration, the address of any founding
ሲባል ድርጅቱን የሚወከሉ መስራቾችን፣ member, trustee, and liquidator of
ባላደራዎቸን፣ የውርስ አጣሪዎችን ወይም succession or other appropriate
ሌላ አግባብነት ያላቸውን ተወካዮችን representatives may be used for the
ማግኘት የሚችልበትን አድራሻ መጠቀም purposes of registration.
ይችላሉ።

2. ድርጅቱ ከተመዘገበ በኋላ በሶስት ወር ጊዜ 2. An Organization has the obligation to notify


ውስጥ እንዲሁም በዚህ አንቀፅ ንዑስ the Agency of its permanent address within
አንቀፅ 1 ከተመለከተው የተለየ አድራሻ three months of its registration and
ሲኖረው ወዲያውኑ የድርጅቱን ቋሚ acquisition of an address other than that
አድራሻ ለኤጀንሲው የማሳወቅ ግዴታ referred to in sub-article (1) of this Article.
አለበት።

9. መተዳደሪያ ደንብ 9. Rules

1. በአዋጁ አንቀፅ 60 መሰረት ከምዝገባ 1. The Rules of a local Organization that is to


ማመልከቻ ጋር ተያይዞ ለኤጀንሲው be submitted with the application for
የሚቀርብ የአገር በቀል ድርጅቶች registration in accordance with Article 60
መተዳደሪያ ደንብ በመስራች አባላት of the Proclamation shall include evidence
የተስማሙበት መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ of the consent of the founding members.
ሊያካትት ይገባል።

7
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

2. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 2. The Agency shall implement the provisions
የተመለከተው ኤጀንሲው ለድርጅቶች of sub-article (1), in a manner that will not
የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት hamper the efficiency of its services to
የሚያስችሉትን አሰራሮችን በማይገድብ Organizations.
መልኩ ይተገበራል።

10. ስያሜ እና አርማ ላይ ስለሚቀርብ 10. Opposition On Name and Symbol


ተቃውሞ

1. ድርጅቶች አዲስ ለመመዝገብ ወይም 1. Upon the submission of an application for


የቀየሩትን ስያሜ ወይም አርማ registration or change of name or symbol,
ለማስመዝገብ ማመልከቻ ሲያቀርቡ the proposed name or symbol of an
ምዝገባው ከመፅደቁ በፊት የቀረበው ስያሜ organization shall be published together
ወይም አርማ ከተቃውሞ ጥሪ ማስታወቂያ with a notice of invitation for opposition in a
ጋር በስፋት በሚሰራጭ ወይም ተደራሽ newspaper of general circulation before the
በሆነ ጋዜጣ እንዲታተም ይደርጋል፡፡ registration is approved.

2. ድርጅቶች ስያሜውን ወይም አርማውን 2. The organizations shall have the option to
በራሳቸው በኩል ከላይ በተደነገገው አግባብ publish on its own in line with the above
በጋዜጣ ማሳተም ወይም የማሳተም provision or may use the Agency’s pre-set
ሂደቱን ለማቀላጠፍ በኤጀንሲው አስቀድሞ publication process where such a process
የተደራጀ የማሳተሚያ አሰራር ካለ በዚሁ has been pre-set by the Agency to simplify
አሰራር መጠቀም ይችላሉ፡፡ በሁለቱም the application process. The expenses for
መንገዶች የማሳተሚያው ወጪ publication shall, in either case, be borne by
በአመልካች ድርጅቶች የሚሸፈን ይሆናል፡፡ the applicant.
3. ስያሜ ወይም ዓርማ በጋዜጣ ከታተመበት 3. After the 10th consecutive publishing day,
ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የህትመት the organization must submit proof of
ቀናት በአየር ላይ ከዋለ በኋላ ድርጅቱ publication which shows the date of
የታተመበትን ቀን የሚያሳይ የህትመቱን publication. Where an Organization chooses
ማስረጃ ለኤጀንሲው ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ a publication process pre-set by the Agency,
ድርጅቱ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 2 the Agency shall make available to the
መሰረት በኤጀንሲው አስቀድሞ public the name and symbol of the
የተደራጀውን የስያሜና አርማ ህትመት organizations for a period of 10 consecutive
አሰራር የሚመርጥ ከሆነ ኤጀንሲው
days from its day of announcement.
በአሰራሩ መሰረት ለአስር ተከታታይ ቀናት
ስያሜውንና አርማውን ለሕዝብ እይታ
ክፍት ያደርጋል፡፡

8
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

4. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 3 በተደነገገው 4. Any affected person may, after paying a
መሰረት በታተመው ስያሜ ወይም አርማ prescribed fee, file a notice of opposition
ላይ ተቃውሞ ያለው ማናቸውም ሰው claiming that it may suffer harm from the
ለዚሁ የተመለከተውን ክፍያ በመክፈል name or symbol of an organisation within 10
ጉዳት የሚደርስበት መሆኑን በመጥቀስ day of the publication. The Agency shall
የተቃውሞ አቤቱታውን ከህትመቱ ቀን decide on the merits of the opposition.
ጀምሮ በአስር ተከታታይ የህትመት ቀናት
ውስጥ ለኤጀንሲው ማቅረብ ይችላል፡፡
ኤጀንሲው የቀረበውን ተቃውሞ መርምሮ
ውሳኔ ይሰጣል፡፡

5. የስያሜ ወይም አርማ ተቃውሞው 5. Where an opposition is submitted after the


ከህትመት ቀኑ ጀምሮ ያሉት አስር ቀናት 10th day of publication but before the 30th
በኋላ ሆኖም ከሰላሳ ቀናት በፊት day, the Agency shall continue the
ለኤጀንሲው የቀረበ ከሆነ ኤጀንሲው registration process as if the opposition did
ተቃውሞ እንዳልቀረበ በመቁጠር አስፈላጊ not take place while mediating between the
የምዝገባ ሂደቱን እያከናዎነ ድርጅቱና opposing parties to find an amicable
ተቃውሞ ያቀረበው አካል እንዲግባቡ solution. The Agency shall not take
የሚያደርጉ ስራዎችን ያከናውናል፡፡ measures that delay the registration process
ከአስረኛው ቀን በኋላ የሚቀርቡ
or the work of organisations in relation to
ተቃውሞች በአዋጁ አንቀፅ 58 ላይ
oppositions that are made after the 10th day,
የተመለከቱትን ጉዳዮች የሚያሳዩ ወይም
unless the findings show matters concerning
ለአስተዳደራዊ እርምጃዎች የሚዳርጉ
ካልሆነ በስተቀር ኤጀንሲው በዚህ Article 59 of the Proclamation or entailing
ምክንያት የምዝገባ ሂደቱ የሚያዘገዩ administrative sanctions.
እርምጃዎችን አይወስድም፡፡

ንዑስ ክፍል 3 Sub Section Three

የውጭ ድርጅቶች ምዝገባ Registration of Foreign Organizations

11. የድጋፍ ደብዳቤ 11. Letter of Recommendation

1. በአዋጁ አንቀፅ 58 ንዑስ አንቀፅ 2(ሐ) 1. The letter of recommendation for foreign
የተጠቀሰው ለውጭ ድርጅቶች የሚሰጥ organisations referred in Article 58 sub-
የድጋፍ ደብዳቤ ድርጅቱ በተቋቋመበት
article 2 (c) of the Proclamation, is a letter of
አገር ከሚገኝ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ወይም
recommendation from the Ethiopian
ሚሲዮን የሚፃፍ የድጋፍ ደብዳቤ ማለት
Embassy or Mission located in the country
ነው።

9
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

where such organisation was incorporated.

2. የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከሌለባቸው አገራት 2. The documents of foreign organisations, that


የሚመጡ ድርጅቶች የሚያቀረቡዋቸውን are located in countries where there is no
ሰነዶች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
Ethiopian Embassy or Mission, shall be
ማረጋገጥና የድጋፍ ደብዳቤውንም
authenticated by the Ministry of Foreign
ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማግኘት
Affairs, and the letter of recommendation
ይኖርባቸዋል።
shall also be obtained from the Ministry.

3. በአዋጁ አንቀፅ 58 (2)(ሐ) መሰረት 3. A foreign organization applying for a letter


የድጋፍ ደብዳቤ የሚጠይቅ የውጭ of support in Accordance with Article 58(2)
ድርጅት በአዋጁ አንቀፅ 58 ለምዝገባ
(c) of the Proclamation shall submit
የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ማቅረብ
documents required for registration under
ይኖርበታል፡፡
Article 58 of the Proclamation.

4. በአዋጁ አንቀፅ 58 (2)(ሐ) መሰረት 4. A letter of support submitted by a foreign


ለኤጀንሲው በውጭ ድርጅት የሚቀርብ organization in accordance with sub-Article
የድጋፍ ደብዳቤ በድርጅቱ የቀረቡ ሰነዶች
2 (c) of the Proclamation shall contain an
ድርጅቱ በተቋቋመበት አገር አግባብነት
affirmation that the documents presented by
ባለቸው ህጎች መሰረት በትክክል የተዘጋጁ
the foreign organization are, on the face of
መሆናቸውን ማረጋገጫ የሚሰጥ መሆን
ይኖርበታል፡፡ it, validly prepared in accordance with the
relevant laws of the country in which the
organization is registered.

5. የውጭ ድርጅቶች ለምዝገባ 5. The documents to be submitted by foreign


የሚያቀርቧቸው ሰነዶች በህጋዊ መንገድ organisations for registration shall be
የተረጋገጡና አንድ ላይ የተጠረዙ መሆን
legally authenticated and sealed. Where the
አለባቸው። ሰነዶቹ በህጋዊ መንገድ አንድ
documents are not legally sealed, they are
ላይ ያልተጠረዙ በሚሆኑበት ጊዜ የሰነዶቹ
required to be authenticated on each page.
ሁሉም ገፆች የተረጋገጡ መሆን
ይኖርባቸዋል።

10
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

6. የውጭ ድርጅቶች በኤጀንሲው 6. The Agency may, together with the relevant
ተመዝግበው አህጉራዊ ወይም ንዑስ governmental institutions, determine by
አህጉራዊ ቢሮዎችን በኢትዮጵያ ውስጥ
issuing guideline the special privileges and
በሚያቋቁሙበት ወቅት ስለሚያገኙዋቸው
benefits that foreign organisations
ልዩ መብቶችና ጥቅሞች ኤጀንሲው
registered by the Agency gain from
ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር
በመሆን ዝርዝሩን በመመሪያ ሊወስን establishing regional or sub-regional
ይችላል። offices in Ethiopia.

12. በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚጋበዙ 12. Foreign Organizations Invited by the
የውጭ ድርጅቶች Ministry of Foreign Affairs

1. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ድርጅት


ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ እንዲንቀሳቀስ 1. Where the Ministry of Foreign Affairs has
በሚጋብዝበት ወይም በሚስማማበት ጊዜ solicited or otherwise agreed with a foreign
ድርጅቱ ኤጀንሲው ዘንድ ለምዝገባ ሲቀርብ organization to operate in Ethiopia, the
በዚህ ደንብ አንቀፅ 11 መሰረት ማቅረብ Ministry of Foreing Affaris may provide a
ያለበትን የድጋፍ ደብዳቤ የውጭ ጉዳይ support letter provided under Article 10 of
ሚኒስቴር ሊሰጥ ይችላል፡፡ this Regulation.

2. ኤጀንሲው በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1


መሰረት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ 2. The Agency may expedite the registration
መሰረት የሚመጡ የውጭ ድርጅቶችን process of organizations that the Ministry
ምዝገባ ሂደት እንዲፋጠን ሊያደርግ of Foreign Affairs has invited in
ይችላል፡፡ accordance with this Article.

Part Three
ክፍል ሶስት

ንዑስ ክፍል 1 Sub Section One


ህገወጥ የገንዘብ እንቅስቃሴ Illicit financial flows

13. በወንጀል የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረትን 13. Money laundering and financing
ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን terrorism
በገንዘብ መርዳት

1. ኤጀንሲው ከሚመለከተው የመንግስት 1. . The Agency, in collaboration with the


አካል ጋር በመተባበር በዘርፉ በወንጀል competent government organ, shall
የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረትን ህጋዊ undertake activities of risk assessment and
አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን

11
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን ለመከላከል parallel inspections necessary for Anti-


ስጋቶችን የመለየትና የጎን ለጎን money laundering and countering financing
ምርመራዎችን የማከናወን ስራ ይሰራል። terrorism.

2. ኤጀንሲው ከሚመለከታቸው የመንግስት 2. The Agency shall, in cooperation with the


አካላት ጋር በመተባበር በሲቪል ማኅበረሰብ relevant governmental bodies, issue and
ዘርፍ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ enforce directives and necessary guidelines
ወይም ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ to counter money laundering and financing
የማቅረብ እንዲሁም ሽብርተኝነትን በገንዘብ of terrorism risks in the civil society sector.
የመደገፍ ስጋቶችን ለመከላከል
መመሪያዎችና አስፈላጊ ጋይድላይኖች
በማዘጋጀት ተፈፃሚ ያደርጋል።

3. ኤጀንሲው በወንጀል የተገኘ ገንዘብ ወይም 3. The Agency shall facilitate the inclusion of
ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና procedures necessary to counter threats of
ሽብርተኝነትና በገንዘብ መርዳት ስጋቶች money laundering and financing terrorism
ለመከላከል የሚያስችሉ አሰራሮች in the self-regulatory mechanisms of
የድርጅቶች የራስ በራስ ቁጥጥር ስርዓት organizations.
ውስጥ የሚካተትበትን ሁኔታ ያመቻቻል።

ንዑስ ክፍል ሁለት Sub Section Two

ሀብት ማሰባሰብ፣ ማስተዳደር፣ ማስተላለፍና Acquisition, Administration, Transfer and


ማስወገድ Disposal of Assets

14. ንብረት በሽያጭ ወይም በስጦታ 14. Transferring Assets Through Sale and
ስለማስተላለፍ donation

1. ድርጅቶች ንብረት በሽያጭ ለማስተላለፍ 1. Organisations shall ascertain that their


የሚወስኑበት ሁኔታ ድርጅቱ decision to sale their property will not
የተቋቋመበትን አላማ በሚገባ ሊፈፅም undermine the aims for which they were
እንዳይችል ሚያደርግ ወይም የድርጅቱን established or put their existence in danger.
ህልውና አደጋ ውስጥ ሊጥል የሚችል
አለመሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው።

12
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

2. ድርጅቶች ንብረት ለማስተላለፍ 2. Organisations shall notify the Agency


የሚያስችላቸውን የሽያጭ ወይም የስጦታ transfer of property within fifteen days from
ውል በተዋዋሉ በአስራ አምስት ቀን ጊዜ entering into a saleor donation agreement.
ውስጥ ይህንኑ ለኤጀንሲው ማሳወቅ
ይኖርባቸዋል።

3. ድርጅቶች የማይንቀሳቀስን ንብረት ወይም 3. If Organizations have acquired or transferred


ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ተሽከርካሪዎችና the ownership of immovable properties or
ማሽኖችን በሽያጭ ያገኙ ወይም ያስተላለፉ vehicles or machines of high value, by sale,
ሲሆን ይህንን ግብይት የሚያሳይ ዝርዝር details of such transaction shall be included
በዓመታዊ ሪፖርታቸው ማካተት in their annual report.
አለባቸው።

4. ከሽያጭ ከተላለፈ ንብረት የሚገኙ ገቢዎች 4. Proceeds from the sale of assets shall be
ወደ በጎ አድራጎት ድርጅት የሂሳብ deposited in the bank account of the
አካውንት ገብተው በአዋጁ መሰረት Organization and utilised in accordance with
ለአስተዳደራዊ ወይም ለፕሮግራም the provisions of the Proclamation on
ወጪዎች በተደነገገው መሰረት ጥቅም ላይ administrative program expenses.
መዋል ይኖርባቸዋል።

5. ድርጅቶች ንብረት በሚያስተላልፉብት 5. Organisations shall, when transferring


ወቅት ሽያጭና ንብረትን ለሶስትኛ ወገን property, observe the laws of Ethiopia on
ማስተላለፍን በተመለከተ የወጡትን property sale and transfer of ownership to
የአገሪቱን ህግና ስርዓት ተከትለው መሆን third parties.
ይኖርበታል።

6. ድርጅቶች ንብረትን በስጦታ ማስተላለፍ 6. Organisations shall only transfer properties


የሚችሉት ለሌላ ሲቪል ማኅበረሰብ by donation to other Civil Society
ድርጅት ወይም ለመንግስት ተቋም ብቻ Organization or Government institution.
ይሆናል፡፡
7. ድርጅቶች የንብረት ማስተላለፍ ሂደቱን 7. The Agency shall issue a directive to assist
ህግና ስርዓት ተከትለው እንዲያከናውኑ organisations with transferring ownership of
ለመደገፍና ለመከታተል ኤጀንሲው ዝርዝር their property in accordance with the law.
መመሪያ ያወጣል።

15. የገቢ ማስገኛ ስራዎች 15. Income Generating Activities

1. ለሶስተኛ ወገን ጥቅም የሚቋቋሙ 1. While engaging in income generating


ድርጅቶች በገቢ ማስገኛ ሥራ ላይ activities, Organisations established for the
ለመሰማራት የሚያውሉትን መነሻ ካፒታል benefit of third parties shall make sure the
ሲወስኑ የተጠቃሚዎችን መብትና ጥቅም amount of the start-up capital do not harm
በማይጎዳ መልኩ መሆን ይኖርበታል። the rights and benefits of their

13
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

beneficiaries.

2. ማንኛውም ድርጅት በገቢ ማስገኛ ሥራ 2. The start-up capital used by any organisation
ላይ ለመሰማራት የሚያውለው መነሻ for income generating activities shall be
ካፒታል እንደ ፕሮግራም ወጪ የሚቆጠር considered as a program expense.
ይሆናል፡፡

3. ከገቢ ማስገኛ ስራ የሚገኝ ገቢ እንደ አንድ 3. Proceeds from income generating activities
የድርጅት የገንዘብ ምንጭ ተቆጥሮ ወደ shall be considered as one source of
ድርጅቱ ሂሳብ ገቢ መደረግና በአዋጁ income for the Organization and deposited
አንቀፅ 63(2) መሰረት መዋል in the Organizations’ account and utilised
ይኖርበታል። in accordance with Article 63 (2) of the
Proclamation.

4. ድርጅቶች የገቢ ማስገኛ ሥራ ላይ 4. Organisations shall notify the Agency


ለመሰማራት የንግድ ፈቃድ ባገኙ በአስር within ten consecutive working days since
ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ they have received their business license.
ለኤጀንሲው ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።

5. ለሶስተኛ ወገን ጥቅም የተቋቋሙ 5. The Agency shall monitor the income
ድርጅቶች የተሰማሩበት የገቢ ማስገኛ generating activity of an organization
ሥራው ለታለመለት የበጎ አድራጎት አላማ working for the benefit of third party to
እየዋለና በተገቢው መንገድ እየተመራ ensure that it is managed appropriately and
መሆኑን ኤጀንሲው ይከታተላል። serve its intended purpose.

16. የበጎ አድራጎት ኮሚቴ 16. Charitable Committee

1. በአዋጁ አንቀፅ 51 ስር የተጠቀሰው የበጎ 1. The approval to establish a charitable


አድራጎት ኮሚቴን የሚያቋቁም ውሳኔ፤ committee granted as per Article 51 of the
የኮሚቴ አባላት ማንነትና በኮሚቴው Proclamation, should include evidence of
ውስጥ የሚኖራቸው የሥራ ሃላፊነት፤ the identity of members of the committee
ገንዘብ ሊሰበሰብ የታቀደበትን የበጎ and their responsibilities in the committee;
አድራጎት አላማ ዝርዝር መረጃ፡ ገንዘብ the cause for which fundraising is intended;
ሊሰበሰብ የታሰበበትን መንገድ፤ኮሚቴው the intended method of fundraising; the
የሚቋቋምበትን የጊዜ ገደብ፤የተሰበሰበው specific period of time it is established for;
ገንዘብ ለታቀደለት አላማ የማይበቃ ወይም
and the procedures to be followed where
ከታቀደለት አላማ የበለጠ በሚሆንበት ጊዜ
the funds raised is insufficient for or more
መከተል ስለሚገባ አካሄድ መረጃ የያዘ
than necessary for the intended purpose.
መሆን ይኖርበታል።

14
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

17. ህዝባዊ መዋጮ 17. Public Collections

1. ለዚህ ክፍል ዓላማ “ህዝባዊ መዋጮ” 1. For the purposes of this section “public
ማለት በህዝባዊ ወይም በስራ ወይም collection” means the process of collecting
በመኖሪያ ቦታዎች በመሄድ ወይም ሌላ cash or other types of assets by going to
መንገድ በመጠቀም የሚገኘውን ገቢ ለምን public, work or residential places, or using
እንደሚያውለው ገልፆ ገንዘብ ወይም ሌላ other means, with or without pay, and after
ንብረት በዋጋ ወይም በነፃ ለማሰባሰብ having informed the donor the purpose of
የሚደረግ ጥሪ ማለት ነው። the fundraising.

2. በአዋጁ አንቀፅ 64 (6) መሰረት ሕዝባዊ 2. Notification presented by an Organization in


መዋጮ የሚያካድ ድርጅት ለኤጀንሲው accordance with Article 64 (6) of the
ሲያሳውቅ የህዝባዊ መዋጮውን አላማ፤ Proclamation shall include the purpose,
የሚቆይበትን ጊዜ፤ የመዋጮው duration, ways, and other similar
መንገዶች፣ መዋጮው ሊሰበሰብ information of the Public Collection. If the
የታቀደበትን ቦታና ሌሎች ተመሳሳይ Organization has requested for a letter to
መረጃዎችን አካቶ ማቅረብ አለበት። give recognition of its public collection,
ድርጅቱ ኤጀንሲው የእውቅና ደብዳቤ the Agency shall write the letter upon
እንዲፅፍለት ከጠየቀ ኤጀንሲው ተገቢውን
payment of necessary fee.
ክፍያ በማስከፈል ደብዳቤ ይፅፋል፡፡

3. ማናቸውም ህዝባዊ መዋጮ ያካሄደ 3. Any Organization that has conducted public
ድርጅት የህዝባዊ መዋጮውን አላማ፣ collection shall incorporate in its annual reports
የቆየበትን ጊዜ፣ መዋጮው የተሰባሰበበትን and accounts, the purpose of the public
ቦታዎችና መዋጮውን የሚመለከቱ የሂሳብ collection, its duration, places of collection and
አያያዝ መዛግብትን የሚመለከት ዘገባ the relevant statement of accounts.
በዓመታዊ የሥራና የገንዘብ እንቅስቃሴ
ሪፖርት ውስጥ ማካተት ይኖርበታል።

4. ኤጀንሲው ግለሰቦች ወይም የንግድ 4. The Agency, after assessing procedures for
ተቋማት ከእቃ ወይም ከአገልግሎት communicating and implementing
ወይም ከሌሎች መሰል ሽያጮች commercial advertisements in which
የሚያገኙትን ገቢ በከፊል ለበጎ አድራጎት individuals or commercial entities pledge to
አላማ እንደሚያውል ቃል በመግባት donate part of the proceeds from sale to
የንግድ ማስታወቂያዎችን charitable purposes, shall identify ways to
የሚያሰራጩበትን እናም የሚተገብሩበትን promote this and such other methods of
አሰራር በማጥናት እነዚህ እና ተመሳሳይ charitable giving
አሰራሮች ለበጎ አድራጎት ስራ መስፋፋትና
መጠናከር የሚችሉበትን አግባብ በተለያየ
መንገድ ያመላክታል፣ ይደግፋል።

15
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

18. ወጪ መጋራት 18. Cost Sharing

1. ለዚህ ደንብ አላማ “ወጪ መጋራት” 1. For the purposes of this Regulation “cost
ማለት ለሶስተኛ ወገን ጥቅም የሚሰሩ sharing” means an arrangement whereby, in
ድርጅቶች የተሰማሩበትን የበጎ አድራጎት order to achieve their objectives,
አላማ ለማከናወን ከተጠቃሚው ህብረተሰብ Organizations operating for the benefit of
ጋር በጉልበት፤ በአይነት ወይም በገንዘብ third parties, share costs in cash or in-kind
የአገልግሎቱን ወጪ የሚጋሩበት የአሰራር with the beneficiaries of their services; and
ስርዓት ማለት ሲሆን አቅም ለሌላቸው includes an arrangement whereby, an
የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎቱን በነፃ Organization provides chargeable services
ለመስጠትና አገልግሎቱን ለማስፋፋት
for individuals who are not beneficiaries of
ሲባል የበጎ አድራጎት አላማው ተጠቃሚ
its charitable aim in order to maintain and
ያልሆኑ ሰዎችን አገልግሎቱን በክፍያ
expand its free services.
እንዲያገኙ ማድረግን ያጠቃልላል።

2. ማንኛውም ለሶስተኛ ወገን ጥቅም የሚሰራ 2. Any Organization operating for the benefit
ድርጅት ለተጠቃሚዎች የሚሰጠውን of third parties can provide its services to
አገልግሎት ያለምንም ክፍያ ወይም its beneficiaries for free or a nominal fee in
በመጠነኛ ዋጋ የወጪ መጋራትን መርህ accordance with the principles of cost
ተከትሎ ሊሰጥ ይችላል። sharing.

3. በፈቃደኝነት ለድርጅቶች የሚሰጥ 3. A voluntary service and a process of cost


አገልግሎት እና አግባብነት ባላቸው የግብር sharing which do not generate money or
ህጎች መሰረት እንደ ገቢ የሚቆጠር ገንዘብ asset that is considered taxable as per the
ወይም ሃብት ለድርጅቶች የማያስገባ relevant tax laws shall not be considered as
የወጪ መጋራት አሰራር ለአዋጁ አንቀጽ an income for the purpose of Article 63 (2)
63 (2) አላማ እንደ ገቢ አይቆጠርም። of the Proclamation. The Agency may issue
ወጪ መጋራትን በተመለከተ ኤጀንሲው cost sharing directive.
ዝርዝር መመሪያ ሊያወጣ ይችላል፡፡

ክፍል አራት Part Four


ቦርድ እና የራስ አስተዳደር Board and Self-Regulation

19. ስለኤጀንሲው ቦርድ 19. The Agency Board

1. ኤጀንሲው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች 1. The Civil Society Organizations Agency


ኤጀንሲ ቦርድ ሴክሬታሪያት ሆኖ shall serve as the secretariat of the Board.

16
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

ያገለግላል።

2. ኤጀንሲው የሚያዘጋጀው ዓመታዊ የሥራ 2. In preparing its annual work-plan and


ዕቅድና በጀት የቦርዱን ሥልጣንና budget, the Agency shall take into account
ተግባራት ባገናዘበ መልኩ ይዘጋጃል። the mandate and activities of the Board.

3. በቦርዱ ውስጥ የሚወከሉ የአካል 3. Members of the Board representing the


ጉዳተኞች፤ሴቶች እና ወጣቶች ተወካዮችን disabled, women and youth organizations
ለመምረጥ በየዘርፋቸው ከሚንቀሳቀሱ shall be elected by and from among
ድርጅቶች መካከል በኤጀንሲው አመቻችነት organisations working in their respective
የሚፈፀም ይሆናል። sectors by the facilitation of the Agency.

20. ስለ ድርጅቶች ምክር ቤት እና የራስ 20. Council of Civil Society Organizations


አስተዳደር and Self-Regulation

1. በአዋጁ አንቀፅ 85 በተደነገገው መሰረት 1. Pursuant to Article 85 of the Proclamation,


ኤጀንሲው የምክር ቤቱን መስራች ጉባዔ the Agency shall make necessary
ለማካሄድ ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ preparations and send appropriate
አመቺ በሆኑ መንገዶች ለሁሉም notifications and calls to all Organizations,
ድርጅቶች ተገቢውን መልክትና ጥሪ using convenient methods, of inaugural
ያስተላልፋል። meeting of the Council.

2. የምክር ቤቱ አባልነት በድርጅቶች ሙሉ 2. Membership of the Council is on voluntary


ፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው። ሆኖም basis. However, the code of conduct or its
ምክር ቤቱ የሚያወጣቸው የስነ ምግባር enforcement mechanisms shall be
ደንብና የማስፈፀሚያ ስልት በሁሉም applicable mandatorily on all registered
ድርጅቶች ላይ በአስገዳጅነት ተፈፃሚ organizations.
ይሆናሉ።

ክፍል 5 Part Five


ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች Special Provisions
21. የፕሮጀክት ስምምነት 21. Project Agreement

17
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

1. ማንኛውም ድርጅት በተሰማራበት የስራ 1. Any Organisation may sign a project


መስክ ስልጣን ካለው የፌዴራልና የክልል agreement and cooperate with a Federal or
የመንግስት አካል በትብብር ለመስራት Regional government body entrusted with
የፕሮጀክት ስምምምነት መፈራረም the power of operating in the same sector.
ይችላል።

2. ኤጀንሲው በአዋጁ በተሰጠው ስልጣንና 2. The Agency may sign a project agreement
ተግባራት ዙሪያ ከሚሰማሩ ድርጅቶች ጋር with organisations working on issues
የፕሮጀክት ስምምነት ሊፈራረም ይችላል። related to its powers and functions
provided in the Proclamation.

22. የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና በጎ አድራጊነት 22. Volunteerism and Charity works

1. በንግድ እና ኢንቨስትመንት ሥራ ላይ 1. Commercial and investment companies


የተሰማሩ የቢዝነስ ተቋማት የኮርፖሬት are expected to fulfil their corporate social
ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት responsibility by engaging in charitable
የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ በመሰማራት work or supporting other charitable works
ወይም ሌሎች የበጎ አድራጎት ሥራዎችን in cash or in-kind or by any other method.
በገንዘብ፤ በአይነት፤ ወይም በሌላ መንገድ
መደገፍ ይጠበቅባቸዋል::
2. ድርጅቶች በአገሪቱ የበጎ ፈቃደኝነትን ባህል 2. Organisations shall include, in their self
ለማጎልበት በተለይም ወጣቶችን regulatory mechanisms, issues that foster a
በድርጅቶቻቸው ስራ በበጎ ፍቃደኝነት culture of volunteerism in the country,
እንዲሳተፉ የሚያደርጉ ጉዳዮች በራስ especially by creating volunteer
አስተዳደር ስርዓት ውስጥ እንዲካተት opportunities for the youth in their
ያደርጋሉ። activities.

23. የሲቪል ማኅበረሰብ ፈንድ 23. Civil Society Fund


Local and international governmental and
አገራዊና ዓለም አቀፋዊ መንግስታዊና
nongovernmental organizations may
መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ለሲቪል
provide donation and support to the Civil
ማኅበረሰብ ፈንድ እርዳታና ድጋፍ ሊያደርጉ
Society Fund.
ይቻላል፡፡

24. የተቀላጠፈ አገልግሎት ሰለመስጠት 24. Providing Efficient Services

18
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

1. ኤጀንሲው ለድርጅቶች የተቀላጠፈ 1. The Agency, in order to provide efficient


አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉትን services to Organizations, shall assess and
መንገዶች በማጥናት ኤሌክትሮኒካዊና make available electronic and website-
የድረገጽ መዋቅሮችን፣ ቅፆችና ሞዴል based services, forms and model rules, and
መተዳደሪያ ደንቦችን፣ እና አሰራሮችን perform other similar functions that can
ያዘጋጃል እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ expedite or simplify registration, reporting
ተግባራትን ያከናውናል። አሰራሩን and other services. If feasible, the agency
መዘርጋት ሲቻል ኤጀንሲው በድረ-ገፅ ላይ shall allow organizations to register online
ወይም በፖስት ምዝገባና ሌሎች
or by mail.
አገልግሎቶችን የሚሰጥ ይሆናል፡፡

2. ኤጀንሲው የሲቪል ማኅበረሰብ 2. The Agency shall conduct the study of best
ድርጅቶችን መፍረስ በሚመለከት ምርጥ practices regarding the dissolution of civil
ልምዶችን ያጠናል፤ ከሲቪል ማኅበረሰብ society organizations and initiate the
ዘርፍ ጋር በመመካከር ተገቢ የህግ እና requisite legislative and regulatory reform
የቁጥጥር ስርአት ለውጥ እንዲጀመር in consultation with the civil society sector.
ያደርጋል፡፡

25. የአገልግሎት ክፍያዎች 25. Service Fees

ኤጀንሲው ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች Service fees to be collected by the Agency


የሚጠይቀው የአገልግሎት ክፍያ ከዚህ ደንብ shall be based on the Schedule appended to
ጋር በተያያዘው ሰንጠረዥ በተመለከተው this Regulation.
መሰረት ይሆናል።

26. ሪከርድና ማህደር 26. Record and File

1. በአዋጁ ወይም በዚህ ደንብ መሰረት 1. Any order given by the Agency in
በኤጀንሲው የሚሰጥ ማንኛውም ትእዛዝ accordance with the Proclamation or this
ወይም የድርጅቶችን አሰራር በሚመለከት Regulation, or an enquiry relating to the
የሚቀርብ ጥያቄ በጽሁፍ ተቀምጦ rules of operation for Organizations shall
በሚመለከተው ድርጅት መዝገብ be put in writing and kept in the file of the
ይያያዛል። relevant Organization.

19
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

2. በመረጃ የማግኘት መብት ህግጋት ላይ 2. Without prejudice to the provisions of the


የተቀመጡ መብቶችና ገደቦች እንደተጠበቁ right to information, any Organization has
ሆነው ማንኛውም ድርጅት the right to obtain a copy of its records.
የሚመለከተውን ፋይል ቅጂ የማግኘት
መብት ይኖረዋል።

27. ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ህጎች 27. Repealed Laws

1. የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ለመመዝገብና 1. The Charities and Societies Council of


ለማስተዳደር የወጣው ደንብ ቁጥር Ministers Regulation No.168/2009 is
168/2009 በዚህ ደንብ ተሽሯል፡፡ hereby repealed.

2. ይህንን ደንብ የሚቃረን ማንኛውም ደንብ፤ 2. Any law, regulation, directive and customary
መመሪያ ወይም ልማዳዊ አሰራር በዚህ practice contrary to this Proclamation shall
ደንብ በተመለከቱት ጉዳዮች ላይ have no effect with respect to matters
ተፈፃሚነት አይኖረውም። provided by this Regulation.

28. መመሪያ የማውጣት ስልጣን 28. Power to Issue Directives

ኤጀንሲው ለዚህ ደንብ አፈፃፀም የሚያስፈልጉ The Agency may issue directives necessary to
መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል። give effect to this Regulation.

29. ደንቡ የሚፀናበት ግዜ 29. Effective Date

ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ This Regulation shall come into force as of the
ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል። date of its publication in the Federal Negarit
Gazeta.

አብይ አህመድ (ዶ/ር) Abiy Ahmed (Ph.D)


የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ Prime Minister of the Federal Democratic
ሪፐብሊክ
Republic of Ethiopia

20
ለውይይት የቀረበ ረቂቂ ደንብ Draft Regulation
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ Agency for Civil Society Organizations

ሰንጠረዥ 1፡ የአገልግሎት ክፍያዎች

ተ.ቁ የአገልግሎት አይነት የክፍያ መጠን


በብር በዩ.ኤስ.ዲ
1. የአገር በቀል ድርጅቶች ምዝገባ 500.00
2. የውጭ ድርጅቶች ምዝገባደ -------- 500.00
3. የድጋፍ ወይም ተመሳሳይ ደብዳቤዎች በገፅ 10.00
4. የአርማና ምልክት ምዝገባ 200.00
5. የስያሜና መተዳደሪያ ደንብ ለውጥና መሻሻል 200.00
ምዝገባ
6. የደንበኞች መመሪያ 100.00
7. የበጎ አድራጎት ኮሚቴ ማፀደቅ 300.00
8. የሰነድ ትክክለኛ ቅጂ ወይም ኮፒ በገፅ 10.00

Schedule 1: Service Fees

No. Types of Service Amount of Fee


Birr US Dollar
1. Registration of Local Organisations 500.00
2. Registration of Foreign ---------------------- 500.00
Organisations
3. Support or similar letters per Page 10.00
4. Registration of Emblem and 200.00
Symbol
5. Registration and Amendment of 200.00
Name and Rules
6. Clients Guideline 100.00
7. Approval of a Charity Committee 300.00
8. A Copy or Authenticated Copy of a 10.00
Document per Page

21

You might also like