You are on page 1of 20

ጥር/2011 ዓ.


ማውጫ

የጥናቱ ዋና ዋና ጽንሰ ሀሳቦች ትርጉም .......................................................................................... 2


ምዕራፍ አንዴ .............................................................................................................................. 3
መግቢያ ....................................................................................................................................... 3
1. የጥናቱ ዲራ (Background of the Study) ......................................................................... 3
2. የጥናቱ ዓሊማ (Objectives of the Study)......................................................................... 3
3. ጥናቱ የሚመሌሳቸው ጥያቄዎች ......................................................................................... 4
4. የጥናቱ አስፈሊጊነት ............................................................................................................ 4
5. የመረጃ ምንጮች................................................................................................................ 4
6. የመረጃ አሰባሰብ ስሌት ....................................................................................................... 4
7. የጥናቱ ወሰን ..................................................................................................................... 5
ምዕራፍ ሁሇት ............................................................................................................................. 6
የተዛማጅ ጽሁፎች ቅኝት............................................................................................................... 6
2. የኮንሰስዮን ዉሌ ሉቋረጥ የሚችሌባቸው ሁኔታዎች፡- ........................................................... 7
2.1 ኮንሰስዮንን መሌሶ መግዛት (Redemption) (3236/1/) .................................................. 7
2.2 ስሇባሇኮንሴሲዮኑ መብት እጦት መበየን (Withdrawal Order) አ/ጽ 3238) ..................... 7
2.3 በባሇኮንሴሲዮን ዴክመት ምክንያት ማስያዝ እና ዉሌ እንዱቋረጥ ማዴረግ (Sequestration)
7
ምዕራፍ ሶስት .............................................................................................................................. 9
የመረጃ ግኝትና ትንተና ................................................................................................................. 9
ምዕራፍ አራት ........................................................................................................................... 13
በጥናቱ የተሇዩ ችግሮችና የመፍትሔ ሏሳቦች ............................................................................... 13
ምዕራፍ አምስት ......................................................................................................................... 18
ማጠቃሇያ .................................................................................................................................. 18

ii
በወሊይታ ዞን አስተዲዯር የፉንደኒያና የህሇና ቆርኬ ሰው ሠራሽ ዯን አጠቃቀምና
አያያዝ ችግር ሇመፍታት የተዘጋጀ ጥናት ሠነዴ

የጥናቱ ዋና ዋና ጽንሰ ሀሳቦች ትርጉም

1. "ኮንሴሽን" ማሇት አንዴን የመንግሥት ዯን ሀብት በጥቅም ሊይ ሇማዋሌ ሲባሌ


ሇማንኛውም ሰው ሇተወሰነ ጊዜ በውሌ ማኮናተር ነው፡፡
2. "ሰው ሠራሽ ዯን" ማሇት በሰው አማካኝነት ችግኝ በመትከሌ ወይም በላሊ ዘዳ የሇማ
ዯን ነው፡፡
3. "የአገሌግልት ዋጋ /ሮያሉቲ/" ማሇት ዯንና የዯን ውጤት ሽያጭ ሊይ ሲውሌ ዯኑንና
አካባቢውን መሌሶ ሇማሌማት አግባብ ባሇው አካሌ የሚሰበሰብ ክፍያ ነው፡፡
4. "የዯን ማኔጅመንት ፕሊን" ማሇት የተፈጥሮ ወይም የሰው ሠራሽ ዯን በዘሊቂ የዯን
አስተዲዯር መርህ መሠረት በዝርዝር በማጥናት ሇዯን ሀብቱ ሌማት፣ ጥበቃና
አጠቃቀም የሚወጣ ዕቅዴ ነው፡፡
5. "ዘሊቂ የዯን አስተዲዯር" ማሇት የዯንና ብዝሀ-ህይወት ሌማት ጥበቃና አጠቃቀም
በዘሊቂነት ማስቀጠሌ ነው፡፡
6. "የዯን ውጤቶች ማዘዋወሪያ ፈቃዴ" ማሇት የዯን ውጤቶችን ከማምረቻ ቦታ ወዯ
ተሇያዩ ቦታዎች ሇማንቀሳቀስ የሚሰጥ የምርቱን መነሻና መዴረሻ የሚገሌጽና ሇተወሰነ
ጊዜ አገሌግል የሚሰጥ ፈቃዴ ነው፡፡
7. "የአካባቢ ሕዝብ" ማሇት ዯኑ ከሇማበት መሬት በአንፃራዊ ቅርበት ባሇው አስተዲዯራዊ
እርከን ውስጥ የሚኖር ሕዝብ ነው፡፡
8. "የዯን ውጤቶች ማዘዋወሪያ ፈቃዴ" ማሇት የዯን ውጤቶችን ከማምረቻ ቦታ ወዯ
ተሇያዩ ቦታዎች ሇማንቀሳቀስ የሚሰጥ የምርቱን መነሻና መዴረሻ የሚገሌጽና ሇተወሰነ
ጊዜ አገሌግል የሚሰጥ ፈቃዴ ነው፡፡
ምንጭ፦ አዋጅ፣ ዯንብና መመሪያ

2
ምዕራፍ አንዴ

መግቢያ

1. የጥናቱ ዲራ (Background of the Study)

ከሊይ በትርጉም ክፍሌ እንዯተመሇከትነዉ "ኮንሴሽን" ማሇት አንዴን የመንግሥት ዯን ሀብት


በጥቅም ሊይ ሇማዋሌ ሲባሌ ሇማንኛውም ሰው ሇተወሰነ ጊዜ በውሌ ማኮናተር ነው፡፡ የዯን
ሀብት በኮንሰሽን ሇአንዴ ዴርጅት በማከራየት መጠቀም እንዯሚቻሌ የዯቡብ ብሔሮች፣
ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክሌሌ መንግስት ስሇዯን ሌማት፤ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር ፻፵፯
/፪ሺ፬ ዓ.ም አንቀጽ 8 (5) ሊይ ይዯነግጋሌ፡፡ ይሁን እንጂ አንዴ ዯን በኮንሴሽን ከመሰጠቱ
በፊት በአንቀጽ 8(1) መሠረት የዯን ማኔጅሜንት ፕሊን መዉጣት አሇበት፡፡ ይህ የማኔጅሜንት
ፕሊን ሲረቀቅ የአከባቢ ማህበረሰብ የዋጋ ተመን ሲወጣ መሳተፍ እንዲሇበት ይህን ዯግሞ
አንቀጽ 8 (2) ያስገዴዲሌ፡፡ ማህበረሰቡ በዯን ሀብት ሊይ ያሇውን ተጠቃሚነት እንዱያጎሇብትና
የባሇቤትነት ስሜት እንዱያሳዴር ከመንግስት ዯን ሽያጭ ተጠቃሚ እንዱሆን በአንቀጽ 8 (4)
ሊይ ተዯንግጓሌ፡፡ አጠቃቀሙ የወዯፊት የዯን ቀጣይነት በማይጎዲ ሁኔታ መሆን እንዲሇበት እና
የህብረተሰብን ተጠቃሚነት ባረጋጠ መሌክ መሆን እንዲሇበት በአዋጁ መግቢያዉ ሊይ
ይናገራሌ። በነዚህና በላልች ባሌተነሱ ጉዲዮች ሊይ መነሻ በማዴረግ ከአዋሣ ቺፕዉዴ ፋብሪካ
የተዯረገውን ዉሌ ከፍትሏብሔር ህግ፣ ከዯን አዋጅ እና ከንግዴ ህግ አንጻር የህብረተሰብን
ተጠቃሚነት ምን ያህሌ እንዯሚያረጋግጥ በመፈተሽ የዯን አያያዝና አጠቃቀም ችግር በዘሊቂነት
ሇመፍታት ነዉ፡፡

2. የጥናቱ ዓሊማ (Objectives of the Study)

የጥናቱ ዓሊማዎች፡-

1. ዘሊቂ የዯን ሌማት እንዱኖር ሇማዴረግ፣


2. የህብረተሰብን ተጠቃሚነትን ሇማረጋገጥ፣ እና
3. በዯኑ አከባቢ ያሇዉን ህገወጥ ጭፍጨፋና ንግዴ ሇማስቆም እንዱሁም የተጠናከረ ጥበቃ
ኃይሌ በመመዯብ ዝርፊያዉን መግታት።

3
3. ጥናቱ የሚመሌሳቸው ጥያቄዎች

1. በዉለ መሠረት በአሥራኛው ዓመት ይገኛሌ ተብል የተገመተው ዯን በሜ/ኩብ ተገኝቷሌ?


ካሌተገኘ እንዲይገኝ ያዯረገዉ ችግር ምንዴር ነዉ?
2. በ20ኛው ዓመት ይገኛሌ ተብል የሚገመተው ዯን በሜ/ኩብ በእንዱህ ዓይነት ሂዯት
ይገኛሌ?
3. የመጀመሪያውን/ነባር ምርት በውለ መሠረት በጊዜ ቆርጦ ያሇማንሳት የማን ችግር ነው?
ያሌተነሳዉ እንጨት ሊዯረሰዉ ኪሣራ ተጠያቂ ማነዉ? አሁን ያሌተቆረጠ እንጨት
ንብረትነቱ የማን ይሆናሌ?
4. ሁሇተኛው ኮንሴሽን ውሌ በመንግሥት ሊይ ጫና አያበዛም?
5. የአቆራረጥ ሁኔታ ሙያዊ አሠራር የጠበቀ ነው?
6. ገዥ ሇሦስተኛ ወገን መብት ማስተሊሇፉ ከህግ አንፃር እንዯት ይታያሌ?
7. ሇዯን ያሇው ጥበቃና እንክብካቤ ሁኔታ እንዯት ይታያሌ?
8. የዯን አስተዲዯር ዕቅዴ በየዓምስት ዓመት መከሇስ የሚገባው ተከሌሶ ነበር?

4. የጥናቱ አስፈሊጊነት

በፉንደኒያ እና በሂሇና ቆርኬ አከባቢ ያሇዉ የዯን ሌማት፣ አጠቃቀምና አያያዝ፥ ችግር
የሚታይበት ስሇሆነ ሇማስተካከሌ ታሌሞ ነዉ፡፡ ከተፈጠሩ ችግሮች የተወሰኑትን ሇመጥቀስ
ያህሌ፡- በዉሌ ሊይ የሚታይ ችግር፣ የአቆራረጥ ችግር፣ የጥበቃ ቸግር፣ የአከባቢ ህብረተሰብ
ይህ3ባሇቤትነት ስሜት፣ ወዘተረፈ።

5. የመረጃ ምንጮች

የመርጃ ምንጭ ብሇን የመረጥናቸው የኮንሴሽን ውሌ፣ የተሻሻሇው የኮንሴሽን ውሌ፣ የሽያጭ
ውሌ፣ የዯቡብ ክሌሌ የዯን አዋጅ እና መመሪያ፣ የፍትሏብሔር ህግ፣ የተሇያዩ ምሁራን
የጻፉት ማብራሪያ፣ ማህበራዊ ሚዱያ፣ የዯን አስተባባሪዎች፣ የዯን ጥበቃ ኃሊፊዎች፣ የአከባቢ
ማህበረሰብ፣ ወዘተ ናቸው።

6. የመረጃ አሰባሰብ ስሌት

4
የተከተሌነው የመረጃ አሰባሰብ ስሌት Qualitative እና Quantitative Approach ያቀሊቀሇ
ሲሆን

1. Qualitative Approach በተመሇከተ ቃሇ-መጠይቅ ማዴረግና መስክ ምሌከታ


(Observation) ነው።
2. Quantitative approach በተመሇከተ የዯን ቆጠራ እና የዋጋ ተመን ስታትስቲክስ
ማሰባሰብ ነው።

7. የጥናቱ ወሰን

ጥናቱ የሚያካሌሌበት ቦታዎች በወሊይታ ዞን የፉንደኒያና የህላና ቆርኬ ዯን ናቸዉ፡፡

5
ምዕራፍ ሁሇት

የተዛማጅ ጽሁፎች ቅኝት

በፍትሏብሔር ህግ አንቀጽ 3207 (1) መሠረት አንዴ የህዝብ አገሌግልት ሥራ የሚባሇዉ


መንግስት ይኀን ሥራ የግሌ የሆነ ዴርጅት በሚገባ ሇማካሄዴ የማይችሇዉ ነዉ ብል ወስኖ
በጠቅሊሊ ሇህዝቡ አስፈሊጊነት ያሇዉ ነዉ በማሇት ራሱ/መንግስት የሚያካሂዯዉ ነዉ፡፡ በአንጻሩ
ዯግሞ የህዝብ አገሌግልት የመንግስት ሥራ የሚባሇዉ አንዴ ባሇኮንሴሲዮን (grantee )
የህዝባዊ አገሌግልት ሥራን ስሇአገሌግልቱ የሚከፈሇዉን ከሚገሇገለበት ሰዎች በመቀበሌ
ሇማካሄዴ ካንዴ የመንግስት መስሪያ ቤት ጋራ ያዯረገዉ ዉሌ ነዉ፡፡ አንቀጽ 3207 (2)፡፡ አቶ
ወንዯወሰን ወከነ ባሰፈረዉ ጽሁፍ ሊይ እንዲስቀመጠዉ ኮንሰሽን ግሌጽ የሆነ ዉሌ እንዲሌሆነ
ይናገራሌ፡፡ ቢሆንም ከአስተዲዯራዊ ዉሌ ዉስጥ ይፈረጃሌ፡፡ በዚህ ዓይነት ዉሌ አራት ነገሮችን
ሌብ ሌንሌ ይገባሌ፡-

ባሇኮንሴሲዮን (ገዥ) (Grantee)፡- ከተዋዋይ ወገኖች አንደ ሲሆን ይህ ግሇሰብ የህዝብ


አገሌግልት ሇማቅረብ የተስማማ ነዉ፡፡

ኮንሴሲዮንን የሰጠ አካሌ (ሻጭ) (Grantor)፡- የመንግስት ባሇሥሌጣን ሲሆን የባሇኮንሴሲዮንና


ሥራዉን የሚቆጣጠር ነዉ፡፡

የህዝብ አገሌግልት ሥራ ( Public Service )፡- የመንግስት ጠሌቃገብነት የሚጠይቅ ሥራ


ነዉ፡፡ ሇዚህም ነዉ የኮንሴሽን ውሌ የአስተዲዯር ውሌ ነው ብሇን የፈረጅነዉ፡፡

ክፊያ (Renumeration )፡- ክፊያ መኖሩ ዉለን ገንዘብ ነክ ስምምነት (Onerous) ያዯርገዋሌ፡፡
ባሇኮንሴሲዮን (Grantee) አገሌግልቱን በነጻ አይዯሇም የሚሰጠዉ፡፡ ይሁን እንጂ የኮንሴሲዮን
ዉሌ ትርፍ ሊይ የተመሠረተ አይዯሇም፡፡ ማሇትም እንዯማንኛዉም ዓይነት ላሊ ሥራ
ባሇኮንሴሲዮን ሇትርፍ ብል የፈሇገዉን ተመን በህዝብ ሊይ ሉጥሌ አይችሌም፡፡ የህዝብ እኩሌ
ተጠቃሚነት ሉረጋገጥ ይገባሌ፡፡ ሇዚህም ነዉ ከሊይ እንዲነሳነዉ የመንግስት ቁጥጥርና ክትትሌ
አስፈሊጊ ነዉ የተባሇዉ፡፡

ከዯኑ አንፃር ስንመሇከተው መንግስት ሇዴርጅቱ ሙለ በሙለ ሇዴርጅቱ ትተዉታሌ እንጂ


ቁጥጥር እያካሄዯ አይዯሇም።

6
2. የኮንሰስዮን ዉሌ ሉቋረጥ የሚችሌባቸው ሁኔታዎች፡-

የኮንሰስዮን ዉሌ መቋረጥ የንግዴ ህግ ዉጤት ያስከትሊሌ፡፡ (Art 3229/1-2) ሌክ አንዴ


ዴርጅት በኪሣራም ይሁን በላሊ ምክንያት ሲፈርስ ያሇው ዓይነት ሂዯት ይኖረዋሌ። የኮንሰሲዮን
ዉሌ እንዱቋረጥ የሚያዯርጉ ምክንያቶች

2.1 ኮንሰስዮንን መሌሶ መግዛት (Redemption) (3236/1/)


ከቃለ ትርጉም እንኳን ስንነሳ መሌሶ መግዛት ማሇት አንዴን የራስ የሆነ ንብረት ዋጋ ከፍል
ወዯኋሊ መመሇስ የሚሌ ትርጉም ይይዛሌ። ይህ መሌሶ መግዛት የኮንትራት ጊዜ ከመዴረሱ
በፊት ዉሌ የማቋረጥ ሂዯት ነዉ፡፡ መሌሶ ሇመግዛት የግዴ ባሇኮንሴሲዮን ጥፋት መፈጸም
የሇበትም፡፡ የመንግስት አካሌ ዉለ ይብቃኝ ያሇ እንዯሆነ ዉለ እንዱቋረጥ በቂ ምክንያት ነዉ፡፡
መንግስት ከገዢው ወስድ ሇላሊ አካሌ ሇመስጠት አይሁን እንጂ ዉለን በማንኛዉም ጊዜ
አቋርጦ ንብረቱን ማስመሇስ ይችሊሌ፡፡ መሌሶ መግዛት ሻጩ ሇገዢ ካሳ እንዱከፈሌ ያዯርጋሌ

2.2 ስሇባሇኮንሴሲዮኑ መብት እጦት መበየን (Withdrawal Order) አ/ጽ 3238)


ይህም ቢሆን የዉሌ ጊዜ ከመዴረሱ በፊት የኮንሴሲዮን ዉሌ ማቋረጥ ነዉ፡፡ ይሄ ሉሆን
የሚችሇዉ የዉሌ ተቀባይ ከባዴ ጥፋት ሲፈጽም ነዉ፡፡ በግሌጽ ካሌተከሇሇ በስተቀር የአስተዲዯር
መስሪያ ቤት ፍርዴ ቤት ሳይሄዴ ብቻውን ዉለ ሉያቋርጥ ይችሊሌ፡፡ የመብት እጦት መበየን
ዉለን በጭራሽ ያፈርሰዋሌ።

• እንዯምክንያት ሉጠቀሱ የሚችለ ነጥቦች ሇምሳላ፡- ዛፉን ሲቆርጥ አቆራረጡ ቀጣይ ምርትን
ታሳቢ ያሊዯረገ መሆኑ

• ዯኑ አከባቢ ያሇዉን ጸጥታ ሇማስከበር ዝግጁ ያሇመሆኑ

2.3 በባሇኮንሴሲዮን ዴክመት ምክንያት ማስያዝ እና ዉሌ እንዱቋረጥ ማዴረግ


(Sequestration)

ባሇኮንሴሲዮን (ገዥ) ዯኑን ሇማስተዲዯር አቅም የሇዉም ብል መንግስት ካመነ ዕገዲ ሉጥሌ
ይችሊሌ።

• በዯኑ ጉዲይ ስንመሇከት ዴርጅቱ በጊዜ እንጨቱን ቆርጦ ሇሚቀጥሇዉ ዙር አሇማዴረሱ

• በዯኑ አከባቢ ያሇዉን ዝርፊያ ማስቆም አሇመቻለ

7
• ሇራሱ ቆርጦ ባሇመጨረሱ ምክንያት ሇላሊ ዴርጅት አሳሌፎ መስጠቱን እንዯምክንያት
ማንሳት ይቻሊሌ፡፡ ይኄ የመንግሥትን የቅዴሚያ መብት የሚገዴብ ነዉ፡፡ ሇምሳላ፦ ከሌክ ያሇፈ
የምርት ማንሻ ጊዜ መሰጠቱ (በ20ኛው ዓመት ሇሽያጭ የሚዯርስ ዛፍ እስከ ስዴስት ዓመት
ቆይተው መነሳቱ ፍትሏዊነትን ያሳጣሌ፡፡ ዴርጅቱ ሲፈሌግ ሇሦስተኛ ወገን እንዱሸጥ ማዴረግ
ከህዝብ ጥቅም ይሌቅ ሇግሇሰብ ጥቅም ትኩረት የሚያዯርግ መሆኑ፣

8
ምዕራፍ ሶስት

የመረጃ ግኝትና ትንተና

በወሊይታ ዞን ዋና አስተዲዯር እና ሏዋሳ ችፕውዴ ፋብሪካ መካከሌ ከግንቦት 13/2000 ዓ.ም


እስከ ግንቦት 13/2020 ዓ.ም ሇ20 (ሀያ) ዓመት የሚቆይ ኮንሴሽን ዉሌ እንዱሁም በ2004
ዓ.ም በተሻሻሇው ኮንሴሽን ውሌ 4 (አራት) ዓመት ያሌተከፈሇበት ምርት ማንሻ ጊዜ እና
አሁንም ምርቱ ተነስቶ ካሊሇቀ 2 (ሁሇት) ዓመት ምርቱ ማሳው ሊይ ሇቆየበት ጊዜ ካሳ
የተከፈሇበት ዓመት ተጨምሮ ባጠቃሊይ ሇ26 (ሀያ ስዴስት) ዓመት በተገባው ኮንሴሽን ዉሌ
ሊይ እና በአፈፃፀም የሚታዩ ችግሮች እንዯሚከተሇው ቀርቧሌ።

የኮንሴሽንና ሽያጭ ውልች መነሻ ያዯረጉት የዯን አስተዲዯር ዕቅዴ ( Forest


Management Plan ) ቢሆንም ዝርዝር ሓሳቦችን ሇማወቅ ዕቅደን ማግኘት አሌተቻሇም።
በኮንሴሽን ውሌ መሠረት የዯን አስተዲዯር ዕቅዴ በየአምስት ዓመት ሌዩነት መከሇስ የነበረበት
ሆኖ ዕቅደ እንዯተከሇሰ የሚገሌፅ ትክክሇኛ መረጃ ወይም ሰነዴ ማግኘት አሌተቻሇም። ይህ
የዯን አስተዲዯር ዕቅዴ የዯን ዋጋ የተተመነበትና እንዱሁም በቀጣይነት ዯኑን ሇማሌማትና
ሇማስተዲዯር የተረከበው ዴርጅት ዯኑን እንዳት ማሌማትና ማስተዲዯር እንዯሚችሌ አቅጣጫ
የሚያሳይ ነው። መንግስትም ቢሆን የዯን ቁጥጥርና ክትትሌ የሚያዯርገው በዚህ ዕቅዴ ሊይ
በመመርኮዝ ነው።

በኮንሴሽን ውሌ አንቀጽ 8 መሠረት ዯኑ ተቆርጦ መነሳት ያሇበት ሦስት ጊዜ ሲሆን


የመጀመሪያ ነባር የዛፍ እንጨት ምርት አንዴ ሜትር ኩብ እንጨት በ70 ብር ህሳብ ሲቆረጥ፣
ሁሇተኛው ዯግሞ አንዯኛ ዙር ሊይ ያቆጠቆጠ የዛፍ እንጨት ምርት አንዴ ሜ/ኩብ እንጨት
በ81.24 ብር እና በሦስተኛ ዯረጃ ዯግሞ ሁሇተኛ ዙር የሚያቆጠቁጥ የዛፍ እንጨት ምርት
አንዴ ሜ/ኩብ እንጨት በ94.28 ብር እንዯሚሸጥ ይዯነግጋሌ፡፡ በዚህ ውሌ መሠረት
የመጀመሪያው ምርት በመጀመሪያው 10 ዓመት ውስጥ ተቆርጦ ማሇቅ ነበረበት። የመጀመሪያ
10 ዓመት እንዯተጠናቀቀ ሁሇተኛው ምርት ሇሽያጭ መቅረብ ነበረበት። ይህ በውሌ ሊይ
የተዯነገገው ሳይከበር አሁንም የመጀመሪያ ምርት እየተነሳ ይገኛሌ። ገዢው ሇቀጣይ ምርት
ታሳቢ በማዴረግ በቶል በመዲዲ በመቁረጥ እንጨቶችን ማንሳት እንዲሇበት ውለ ያስገዴዲሌ።
ይሁን እንጂ ገዥው ገና ከመጀመሪያው ምርት ቀሪ የሆነውን 47% እንጨት እያነሳ በመሆኑ

9
በመንግሥት ጥቅም ሊይ ጉዲት አዴርሷሌ። ምክንያቱም ይኸ 47% እንጨት በቶል ተቆርጦ
ቅጥያው አዴጎ ሇሽያጭ ቢቀርብ ኖሮ ሇመንግሥት በግምት ከ50(አምሣ) ሚሉዮን ብር በሊይ
ገቢ የሚያስገባ ነበረ። ሽያጭ ውሌ አንቀጽ 7(7.2) የዯን ምርት ከቦታ ማንሳትን በተመሇከተ
ገዢው በራሱ ፕሮግራም የሚያነሳው መሆኑ እንዯተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን በመጀመሪያ አሥር
ዓመት በሚቆረጠው ቅጥያ ሽያጭ ሊይ የመጀመሪያው (ነባሩ) ዯን ባሇመነሳቱ የዞኑ ጥቅም
እንዲይጎዲ ገዢው አስፈሊጊውን ጥንቃቄ ያዯርጋሌ ይሊሌ። ይኸ በውሌ ሊይ የተመሇከተው
ተግባራዊ አሇመሆኑ እና ውለን ባሌፈጸመው አካሌ ሊይ እርምጃ አሇመወሰደ ሇህገ-ወጥነት
በር የከፈተ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሎሌ፡፡ እስከ ግንቦት 14/2010 ዓ.ም በወቅቱ በባሇሙያዎች
ዯኑ ያሇበት ዯረጃ በተጠናው መሠረት በግምት 47% የሚሆን የመጀመሪያ ምርት ሳይቆረጥ
የታሇፈ በመሆኑ ዞኑ ማግኘት የነበረበት ከ50 ሚሉዮን ብር በሊይ የሚገመት ገንዘብ ዞኑ
እንዱያጣ አዴርጓሌ፡፡

የመጀመሪያው 10 ዓመት ካበቃ በኃሊ ሻጭ ከገዢው ጋር ስሇቀጣይ የዯን ምርት የዋጋ ተመን
መነጋገር ሲገባው የመጀመሪያ ምርት ዛፍ ተመን ወጥቶሇት እንዯሚቆረጥ ውሌ ተገብቶ እያሇ
ውሌን በመጣስ ገዢ 50 ሺህ ፖሌ ዉለ ካበቃ በኃሊ ሇሦስተኛ ወገን የሸጠ ሲሆን 63 ሺህ
እንጨት በውለ ጊዜ የተሸጠ ቢሆንም እየተቆረጠ ይገኛሌ።

በተሸሻሇው 2004 ዓ/ም ውሌ መሠረት 3ተኛ ወገን ሆነው ዯኑን የገዙ ግሇሰቦችና ዴርጅቶች
ትምባሆ ዴርጅት፣ ሶድ ዩንቨርሲቲ፣ ባንግታዎ ኃሊፊነቱ የተ/የግሌ ማህበር እና ዋንዛ
እንደስተሪ ናቸው። የዯን አቆራረጥ በሽያጭ ውሌ አንቀጽ 7 (7.1) መሠረት በመዯዲ መሆን
እንዲሇበት የሚዯነግግ ቢሆንም እነዚህ 113700 ፖሌ የገዙ ሦስተኛ ወገን ዴርጅቶች
እየመረጡና የሚፈሌጉትን ብቻ እየቆረጡ ቀጣይ የሚያቆጠቁጥ ምርት ጥቅም እንዲይሰጥ
ወይም ዲግም እንዲያቆጠቁጥ እያዯረጉ መሆናቸውን በቦታው ባዯረግነው ምሌከታ መረዲት
ችሇናሌ፡፡ በፍትሏብሔር ህግ አንቀጽ 3206(2) መሠረት ዋና ተዋዋይ ሦስተኛ ወገን
ሇሚፈጽመው ሇማንኛውም ዓይነት ጥፋት ተጠያቂ እንዯሚሆን በግሌጽ ያስቀምጣሌ። ይህም
ቢሆን እርምጃ አሌተወሰዯበትም። የአቆራረጥ ሁኔታዉ ሲታይ ውለን መሠረት ባዯረገ መሌክ
በመዯዲ ሳይሆን እየመረጡ መሆኑ ቀጣይ በሚያቆጠቁጥ ዛፍ ሊይ ጉዲት የሚያዯርስ መሆኑን
አረጋግጠናሌ፡፡

በሺያጭ ውሌ አንቀጽ 9(2) መሠረት ሮያሉቲ ክፊያ ማንጠባጠብና ሇታሇመሇት አሊማ ከመዋሌ
አንጻር ተግባራዊ አሇመሆን
10
ገዥ አካሌ በኮንሴሽን ውሌ 11 (8) መሠረት የዯኑን ቀጣይነት የሚያረጋግጡ ሥራዎችን
(ዯኑን ማሳሳት፣ ችግኝ የመትከሌና ከከፍታ የተቆረጡ ግንድችን በወቅቱ የማሳጠር) መሥራት
ሲገባዉ በቸሌተኝነት አሌፏሌ፡፡ በኮንሴሽን ውሌ ዯኑ ሲሸጥ ፑንደኒያን የማሳሳት ተግባርና
ሂላና ቆርኬ ዯንን 500,000 ዛፍ ችግኝ በመትከሌ ሇመጠቀም የዯን አስተዲዯር ዕቅዴ ሊይ
የተቀመጠ ቢሆንም ተግባራዊ እንዲሌሆነ በወቅቱ ከነበሩት ከዯን አስተባባሪዎች መረዲት
ተችሎሌ፡፡

ከዚህ በፊት ዯኑ ተሽጦ ሇሶድ ከተማ አስፋሌት ማሠሪያ የዋሇ ቢሆንም በዋናነት በዯኑ ዙሪያ
ያሇው ህብረተሰብ በአካባቢው የተሇያዩ የሌማት ሥራዎች (ግንባታዎች) ተሠርተውሇት
ተጠቃሚና የባሇቤትነት ስሜት የሚያሳዴር ሥራ አሌተሠራም፡፡

በየዯረጃው ያለ የሥራ ኃሊፊዎች በዯኑ ስሇሚከሰተው ችግር ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ የቅርብ
ክትትሌና በአጥፊዎች ሊይ በተሇያዩ የህግ ማዕቀፎች መሠረት እርምጃ እንዱወሰዴ የተዯረገበት
ሁኔታ ያሇመኖር ሇችግሩ መባባስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷሌ፡፡

በፑንደኒያ ዯን ሊይ እየተፈጠረ ያሇውን የጥበቃ ችግር በተመሇከተ እሰከ 2008 ዓ/ም ዴረስ
ዯኑን በህገ-ወጥ መንገዴ ገብቶ የሚጨፈጭፍ ሃይሌ ብዙም ያሌበዛ እንዯነበር የዯን ጥበቃ
ክፍሌ ኃሊፊዎችና የዯን አስተባባሪዎች ይናገራለ፡፡ ከ20008 በኋሊ ግን ህገ-ወጥ የአካባቢው
የዯን ጨፍጫፊዎች በተዯራጀ ሁኔታ ማሇትም ( ነጋዳዎች፣ ጥበቃዎች፣ ዯሊሊዎች እንዱሁም
የአካባቢው ከሌጆች እስከ አዋቂዎች ቀንም ሆነ ማታ እየዘረፉ ይገኛለ፡፡ ዯኑን በህገ ወጥ
መንገዴ ከሚጨፈጭፉ ቀበላያት መካከሌ ሇምሳላ፡- ኦፋ ጋንዲባ፣ አማሊቃ፣ ሁምቦ ሊሬና፣
ጉቱቶ ሊሬና፣ ኮይሻ ጎሊ፣ ኮይሻ ዋንጋሊ፣ አንሶሜ ገንበሊ፣ ዋጭጋ ቡሻ፣ ሾጮራ ኦሴ፣ ሀባ
ገሬራ፣ ቶሜ ገሬራ፣ ማንቴ ገሬራ፣ ኦፋ ሰሬ እና ዋራዛ ገሬራ ናቸው፡፡ በአሁኑ ሰዓት በቀን
ቢያንስ ከሁሇት መቶ በሊይ በአህያ ጋሪ እንዱሁም በጭነት መኪናዎች በመጨፍጨፍ
ሇማገድ በየቀኑ ወዯ ከተማ እና ከዞን ውጪ እየተጓጓዘ ስሇመሆኑና ሇቀጣይ ዯኑ ከጥቅም ወጪ
መሆኑ በአካሌ ምሌከታ ማየት ተችሎሌ፡፡

ከዚህ በፊት ዯኑ ሲጠበቅ የነበረው በሶድ ዙሪያ ወረዲ፣ በሁምቦ ወረዲና ሶድ ከተማ በጋራ
በኃሊፊነት ሲሆን በወቅቱ የተፈጠረ ችግር የጎሊ አሌነበረም፡፡ አሁን ግን የሶድ ከተማ አስተዲዯር
ሙለ በሙለ ከተረከበ ወዱህ ግን ከአቅሙ በሊይ በመሆኑ መቆጣጠር አሌተቻሇም፡፡ አሁን

11
ሊይ በዯኑ የሚዯረግ ጭፍጨፋ ወዯ ዝርፊያ ተቀይሮ ቀጣይ የዯኑ ህሌውና አዯጋ ዉስጥ
እየወዯቀ ነዉ፡፡

የከተማው አጠና ተራ በፑንደኒያ ዯን አቅራቢያ መኖሩ ማታ ማታ ዯኑ እየተጨፈጨፈ


በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ወዯ አጠና ተራ እየተጓጓዘና እየተረከቡት መሆኑ ብቻም ሳይሆን
የአጠናው ተራ አካባቢ የህገ-ወጦች መመሸጊያ መሆኑ ሇማረጋገጥ ተችሎሌ፡፡

ዯኑ በቂ ጥበቃ ስሌጠና በወሰደ ኃይሌ ወይም አቅም ባሊቸው ተመሊሽ ሠራዊት እየተጠበቀ
ባሇመሆኑና የጥበቃ መሣሪያ ካሇመኖሩ የተነሳ ጥበቃዎች በዘራፊዎች ወይም በዯን
ጨፍጫፊዎች ጉዲት እየዯረሰባቸውና ህገወጦችን ሲያዩዋቸው የሚሸሹ መሆናቸውን ሇማወቅ
ተችሎሌ፡፡

በየጊዜው በህገ-ወጥ መሌክ የዯን ምርቱን ሲያዘዋዉሩና ሲጨፈጭፉ የተያዙ ግሇሰቦች ሊይ


አስፈሊጊው የእርምት አርምጃ የማይወሰዴና ሇህግ የማይቀርቡ በመሆኑ በማንአሇብኝነት እንኳን
ማታ ቀንም ሆነ ጥዋት በግሌጽ ሲያጓጓዙ ይታያሌ። እንጨት የሚያጓጓዙት በምሽትና እስከቀኑ
ሁሇት ሰዓት የቤት መሥሪያ እንጨት፣ የማገድ፣ ወዘተ በአህያ ጋሪ፣ በአይሱዙ መኪና ከጉቱቶ
ሊረና እስከ ሶድ ዩኒቨርሲቲዴረስ ባሇው መንገዴ የቃኘ ሰው ማረጋገጥ ይችሊሌ፡፡

12
ምዕራፍ አራት

በጥናቱ የተሇዩ ችግሮችና የመፍትሔ ሏሳቦች

ከሊይ ያገኘዉን መረጃ መሠረት በማዴረግ የጥናት ቡዴን የሚከተለትን ችግሮች በመሇየት
የመፍትሔ ሀሳብ ያቀርባሌ፡፡

1. ሇኮንሴሽን ዉሌ መነሻ የሆነዉ የዯን አስተዲዯር ዕቅዴ ያሇመገኘቱ እና ምንም እንኳ የዯን
አስተዲዯር ዉሌ በየአምስት ዓመቱ እንዱከሇስ ዉለ ቢናገርም እስካሁን የተከሇሰበት ሁኔታ
አይታይም፡፡ የዯን አስተዲዯር ዕቅዴ ዯኑን በቀጣይነት ሇመቆጣጠርና ክትትሌ ሇማዴረግ
ወሳኝ ነዉ፡፡ እንዱሁም የዯን ተመን የሚወጣዉ በዚህ ዕቅዴ ሊይ መነሻ በማዴረግ ነዉ፡፡
ከዚህም ባሻገር የህብረተሰብ ተሳትፎም የሚረጋገጠዉ በዚህ ጥናት መነሻ ተዯርጎ ነዉ፡፡
ይሁን እንጂ ይኀንን ጥናት ስናዯርግ ዋናውም ሆነ የተከሇሰ የዯን አስተዲዯር ዕቅዴ
ማግኘት አሌተቻሇም፡፡

መፍትሔ

 የቀዴሞ የዯን አስተዲዯር ዕቅዴ ካሇበት ተፈሌጎ እንዱገኝ ቢዯረግ፣


 የዯን አስተዲዯር ዕቅዴ በማዉጣት ቀጣይ የዯኑን ሌማት፣ አስተዲዯርና አጠቃቀም
ቢመራ፣
2. በዉለ መሰረት ዛፉ በሀያ ዓመት ዉስጥ ሦስት ጊዜ መቆረጥ አሇበት፡፡ ይሁን እንጂ
እስካሁን ባሇዉ ሁኔታ ዯኑ ሁሇተኛ ዙር መቆረጥ ሲገባዉ 1ኛ ዙርም ተቆርጦ አሊሇቀም፡፡
ከመጀመሪያዉ 53% ብቻ ተቆርጦ ገና 47% ሳይቆረጥ እንዲሇ በግንቦት ወር 2010 ዓ.ም
የተጠናዉ ጥናት ያሳያሌ፡፡ ይህ ዯግሞ ተከታይ ምርት በጊዜ እንዲይዯርስ በማዴረግ የዞኑን
ጥቅም ይጎዲሌ፡፡ በገንዘብ ቢተመን ከ50 ሚሉዮን ብር በሊይ ኪሣራ በመንግስት ሊይ
እንዱዯርስ አዴርጓሌ፡፡

መፍትሔ

 የዞን አስተዲዯር የዯረሰበትን ኪሣራ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ዴርጅቱን ካሣ በመጠየቅ


ቀጣይ አቅጣጫ ሊይ መወሰን

13
3. በዉለ መሠረት እንጨቶቹ መቆረጥ የሚገባቸዉ በመዲዲ ሆኖ ሳሇ ነገር ግን ከገዥዉ
ዴርጅት እንጨት የገዙ ሦስተኛ ወገኖች ሇቀጣይ ምርት ምንም ርህራሄ በላሇበት ሁኔታ
እየዘሇለ የፈሇጉትን መርጠው በመቁረጣቸዉ ምክንያት እንጨቶች በእምቡጥ ሊይ
የሚወዴቁ ሲሆን ቀጣይ ምርት ወጥ በሆነ መንገዴ እንዲይዯርስ እያዯረገ ይገኛሌ፡፡

መፍትሔ

 በዚህ ምክንያት በመንግስት ሊይ ሇዯረሰው ኪሣራ ዴርጅቱን ተጠያቂ ማዴረግ


4. የሮያሉቲ ክፊያ ተንጠባጥቦ የሚከፈሌ ሲሆን ሇታሇመሇት ዓሊማ እየዋሇ አይዯሇም።

መፍትሔ

 ሮያሉቲ ክፊያ ማስከፈሌና ሇተባሇበት ዓሊማ (ችግኝ ሇመትከሌ፣ ዯኑን ሇማሳሳት፣


ከከፍታ የተቆረጡ እንጨቶችን የማስተካከሌ፣ ወዘተ ) እንዴውሌ ማስዯረግ
5. ከዯኑ ሽያጭ በተገኘ ገንዘብ ከዚህ በፊት የሶድ ከተማ አስፋሌት ነበር የተሠራው። የዯኑ
ዙሪያ አከባቢ ሰዎች በዯኑ ሊይ የባሇቤትነት ስሜት ተሰምቷቸው እንዱጠብቁ የተሠራሊቸው
የሌማት ሥራ የሇም። በዯቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክሌሌ መንግሥት የሰው
ሰራሽ ዯን አጠቃቀም ዯንብ ቁጥር 50/1998 ዓ.ም አንቀጽ 9 ሊይ ከሰው ሠራሽ ዯን ሽያጭ
እና ከኮንሴሽን የሚሰበሰበው ገቢ በሚከተሇው ዴርሻ መሠረት ሇሌማት ይውሊሌ፡፡
በዞን ዯረጃ ከተሸጠ፦
ሀ/ ሇዞን አስተዲዯር 10%
ሇ/ ሇወረዲ አስተዲዯር 20%
ሏ/ ሇቀበላ አካባቢ ሌማት 50%
መ/ ዯኑን እንዯገና ሇማሌማት 20%

መፍትሔ

 በርግጥ ከዚህ በፊት የሶድ ከተማ አስፋሌት የተሠራው በህዝብ ስምምነት ቢሆንም
ሇቀጣይ የአከባቢ ህብረተሰብ ተጠቃሚ የሚሆንበት ሁኔታ ቢመቻች
6. በውለ መሠረት በአሥረኛ ዓመት ያቆጠቆጠው ምርት መሸጥ አሇበት። ይሁን እንጂ
ዴርጅቱ ቅጥያውን መግዛት ቀርቶ የመጀመሪያውንም ምርት አንስቶ አሌጨረሰም። ይህ

14
ዯግሞ ዞኑ ከሁሇተኛው ምርት የሚያገኘውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖሇቲካዊ
ጠቀሜታን ይጎዲሌ።

መፍትሔ

 በውለ መሠረት የመጀመሪያውን የዯን ምርት በጊዜ ያሊነሳ ዴርጅት ቅጥያውንም ቢሆን
ተረክቦ በተገቢ ሁኔታ የማንሳቱ ሁኔታ ስሇሚያጠራጥር ዞኑ ህጋዊ አቅጣጫ
ሉያስቀምጥ ይገባሌ። ምክንያቱም ዴርጅቱ ቅጥያውንም ምርት እገዛሇሁ የሚሌ ከሆነ
በሦስተኛው ምርት ሊይ አሁንም ጉዲት በማዴረስ መጀመሪያ ወዯ 50 ሚሉዮን ብር
ገዲማ የከሰርነው እንዲሇ ሆኖ ሇተጨማሪ እጥፍ ኪሣራ ሌዲርገን ይችሊሌ።
7. የተሻሻሇውን የኮንሴሽን ውሌ በተመሇከተ ሇዴርጅቱ ካሳ ከተከፈሇበት 2 ዓመት ጋር
አጠቃሊይ 6 ዓመት ጨምሯሌ። ይህ ዯግሞ ከፍትሏብሔር ህግም ከመመሪያውም ወጣ
ያሇ ነው። ምክንያቱም የአንዴ ኮንሴሽን ዓመት ከ20 ዓመት መብሇጥ እንዯላሇበት የዯቡብ
ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክሌሌ መንግስት የመንግስት ሰዉ ሠራሽ ዯን አጠቃቀም
መመሪያ ቁጥር 1/1998 ዓ.ም አንቀጽ 11 (ሀ) (5) ሊይ ይዯነግጋሌ። የሚጨመር ከሆነ
ተጨማሪ 20 ዓመት ወይም ላሊ የኮንሴሽን ዓመት ይጨምራሌ እንጂ 4 ዓመት በነፃ
በመሌቀቅና ሁሇት ዓመት ከፍል ምርቱን እንዱያነሳ የሚሌ አካሄዴ ከህጉ ወጣ ያሇ ነው።
ህጉ 20 ዓመት ብል ገዯብ ሲሰጥ በ10 ዓመት ውስጥ ላሊ ምርት መዴረስ አሇበት በማሇት
ነው። ይህ ሇዴርጅቱ የተጨመረው ቁጥ ቁጥ ዓመት መመሪያውን ይጥሳሌ።

መፍትሔ

 የዞኑ መንግስት አሁንም ሇዚህ ሀሳብ ትኩረት ሰጥቶ የተጨመረውን ዓመት እንዯገና
ማጠን አሇበት።
8. ከዯን ጥበቃ ጋር ተያይዞ ዯኑ በከፍተኛ ሁኔታ በነጋዳዎች፣ በዯሊሊዎች፣ በአከባቢ
ማህበረሰብ፣ ወዘተ እየተዘረፈ እንዲሇ ከሊይ አይተናሌ።

መፍትሔ

 የተጠናከረ (ትጥቅ ተሰጥቶ) ሠራዊት በመመዯብ ዯኑን ከህገ-ወጦች መጠበቅ፣


 የአከባቢ ማህበረሰብ ዯኑን በባሇቤትነት ስሜት እንዱጠብቅ ማወያየትና ግንዛቤ
መፍጠሪያ ማዘጋጀት፣ እና

15
 የአከባቢ ማህበረሰብ ከዯን ሽያጭ ተጠቃሚ እንዱሆኑ ማዯረግ፣
9. የዯቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክሌሌ መንግስት የመንግስት ሰዉ ሠራሽ ዯን
አጠቃቀም መመሪያ ቁጥር 1/1998 ዓ.ም አንቀጽ 14 (2) (ሇ) (4) ሊይ የባሇሀብት
ግዳታዎችን ሲዘረዝር ባሇሀብት በኮንሴሽን መሌክ የወሰዯዉን ሀብት የመጠበቅ፣
የመከሊከሌና የመንከባከብ ግዳታ አሇበት፡፡ ነገር ግን እነዚህን ሀሊፊነቶችን በአግባቡ
እየተወጣ እንዲሌሆነ ከሊይ ያነሳናቸዉ ማሳያዎች በግሌጽ ያስረዲለ፡፡

መፍትሔ

 ከእንግዱህ በኃሊ ባሇዉ ጊዜ በዯኑ ቀጣይነት ሊይ ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት አሇበት፡፡


10. በየዯረጃው ያለ የሥራ ኃሊፊዎች በዯኑ ሇሚከሰተው ችግር የቅርብ ክትትሌና በአጥፊዎች
ሊይ በተሇያዩ የህግ ማዕቀፎች መሠረት እርምጃ እንዱወሰዴ የተዯረገበት ሁኔታ ያሇመኖር
ሇችግሩ መባባስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷሌ፡፡

መፍትሔ

 በህዝብ ሀብት ሊይ እየዯረሰ ያሇውን ጉዲት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በየዯረጃው ያለ


የሥራ ኃሊፊዎች (የዞን፣ የወረዲና የከተማ አስተዲዯሮች፣ የጸጥታ ኃሊፊዎች፣
የኃይማኖት መሪዎች፣ የአከባቢ ሽማግላዎች እና ላልችም በዯኑ ጉዲይ ሊይ
እንዱመካከሩ ማዴረግ።
11. ከዚህ በፊት ዯኑ ሲጠበቅ የነበረው በሶድ ዙሪያ ወረዲ፣ በሁምቦ ወረዲና ሶድ ከተማ በጋራ
በኃሊፊነት ሲሆን በወቅቱ የተፈጠረ ችግር የጎሊ አሌነበረም፡፡ አሁን ግን የሶድ ከተማ
አስተዲዯር ሙለ በሙለ ከተረከበ ወዱህ መቆጣጠር ከአቅሙ በሊይ ሆኗሌ፡፡

መፍትሔ

 በመመሪያ አንቀጽ 9(2) የዯኑን ጥበቃ ሇሶድ ከተማ አስተዲዯር ብቻ ከመተው ይሌቅ
አጎራባች ወረዲዎችም በቅንጅት እንዱሠሩ ማዴረግ
12. በየጊዜው በህገ-ወጥ መሌክ የዯን ምርቱን ሲያዘዋዉሩና ሲጨፈጭፉ የተያዙ ግሇሰቦች ሊይ
አስፈሊጊ የእርምት እርምጃ የማይወሰዴና ሇህግ የማይቀርቡ መሆናቸዉና ወዯ ህግ ፊት
የቀረቡትንም ቢሆን ዛፍ ብቻ ተረክቦ ሰዎችን ነጻ መሌቀቅ ይታያሌ፡፡

መፍትሔ

16
 የፍትህ አካሊት ከዯኑ ጋር በተያያዘ ሇሚመጡ ክሶች ሌዩ ትኩረት ሰጥተው እንዱሰሩና
ፍርዴ ቤቶች አስተማሪ የሆነ ቅጣት እንዱሰጡ የምክክር መዴረክ መፍጠር

17
ምዕራፍ አምስት

ማጠቃሇያ

የጥናት ቡዴን በፑንደኒያና ህሇና ቆርኬ ሰዉ ሠራሽ ዯን ዙሪያ የሚታየዉን የአያያዝና


አጠቃቀም ችግር እንዱያጠና በተሰጠዉ ተሌዕኮ መሰረት ከሊይ በምዕራፍ አራት በተሇዩ
ችግሮችና መፍትሔዎች መነሻ በማዴረግ ጥናቱን እንዯሚከተሇዉ ይዯመዴማሌ፡፡

1. ዉለ የሚቀጥሌ ከሆነ ከሊይ ሇተነሱ ችግሮች መፍትሔ በሰጠ ሁኔታ መሆን ይገባሌ፡፡
2. በኮንሴሽን ዉሌ አንቀጽ 16(16.1) መሠረት ዉለን ስሇማሻሻሌ ሲናገር “አስፈሊጊ ሆኖ
በተገኘ ጊዜና ሁሇቱ ተዋዋይ ወገኖች በሚያዯርጉት ስምምነት መሠረት የዉለን አካሌ
በማይነካ/በማይጎዲ መሌክ ዉለን ማሻሻሌ ይቻሊሌ“ ይሊሌ፡፡ በዚህ አንቀጽ መሠረት
2004 ዓ.ም ሊይ ገዥ የዉሌ ማሻሻያ ጥያቄ አቅርቦ እንዱሻሻሌ አዴርጓሌ፡፡ በዚያዉ ሌክ
ዞኑም የራሱን ጥቅም የሚጎደ ዴንጋገዎችን ከዉለ ዉስጥ እንዱወጡ መዯራዯር
ይችሊሌ፡፡ ይህንን ማዴረግ እንዱችሌ በፍትሏብሔር ህግ አንቀጽ 3216(1) ሊይ ባንዴ
ወገን ብቻ ስሇሚዯረግ የዉሌ መሇዋወጥ በሚሌ ርዕስ “ ኮንሴሲዮን ሰጪ ( መንግስት)
የሆነዉ መስሪያ ቤት ዉለ በሚጸናበት ጊዜ ስሇሥራዉ መሌካም አካሄዴ ወይም
ስሇተሰጠዉ አገሌግልት ሥራ መሻሻሌ አስፈሊጊ መስል የታየዉን ማንኛዎችንም
ግዳታዎች በባሇኮንሴሲዮኑ (ገዥ) ሊይ ሉጥሌበት ይችሊሌ “ ይሊሌ፡፡ በዚህ አንቀጽ ንዑስ
አንጽ 3 ሊይ “ ማናቸዉም ይህን ተቃራኒ የሆነ ቃሌ ዋጋ የሇዉም “ ይሊሌ፡፡ ይህ
ሇመንግስት ብቻ የተሰጠ ሌዩ መብት (Prerogative Right of Administrative
Authorities) ተብል ይጠራሌ፡፡ ስሇዚህም የዞኑ መንግስት ይህን መብት በመጠቀም
ዉለን ከእንዯገና ማጠን ይችሊሌ፡፡ ሇምሣላ፡- በመጀመሪያ ኮንሴሽን ዉሌ አንቀጽ 10
(10.9) ሊይ “ ገዢ ከሻጭ ጋር የገባዉን የዉሌ ስምምነት ሇላሊ አካሌ ወይም ወገን
አሳሌፎ መስጠት የሇበትም “ ይሊሌ፡፡ ነገር ግን በተሻሻሇዉ ኮንሴሽን ዉሌ አንቀጽ 4 ሊይ
ሇሦስተኛ ወገን ማስተሊሇፍ እንዯሚቻሌ ተዯንግጓሌ፡፡ በዚህ በተሻሻሇዉ ኮንሴሽን ዉሌ
አንቀጽ 4 ሊይ “ ገዢዉ መብቱን ሇ3ኛ ወገን የሚያስተሊሌፍበት ሂዯት በማንኛዉም
ሁኔታ የሻጩን ጥቅም የሚጎዲ፣ የሚቀንስ፣ ተጨማሪ ወጪ የሚያስወጣ ወይም
አፈጻጸሙን የሚያከብዴ ሉሆን አይገባም “ ይሊሌ፡፡ ነገር ግን እነዚህ የገዙ 3ኛ ወገኖች
ሇዯኑ ሕይወት ምንም ዓይነት ዯንታ የላሊቸዉ ናቸዉ፡፡ በፍትሏብሔር ህግ አንቀጽ

18
3206(1) ሊይ “ የአስተዲዯር መስሪያ ቤቱ ዉሌን ሇላሊ ሇመሌቀቅ ወይም ሇሁሇተኛ
ተቋራጭ ሇማዴረግ ሇሚቀርብሇት የፈቃዴ ጥያቄ መሌሱን በአእምሮ ግምት ተገቢ በሆነ
ጊዜ ዉስጥ መሆን አሇበት “ ይሊሌ፡፡ በዚህ አንጽ ንዑስ 3 ሊይ ዯግሞ “ የአስተዲዯር
መስሪያ ቤቱ በላሊ ዉልች ዉስጥ ስሇ ዉልች ሇላሊ ማሳሇፍ ወይም ስሇሁሇተኛ
ተቋራጭ ረገዴ የመከሌከሌ ወይም የመፍቀዴ በተሇይ የሆነ መብት አሇዉ፡፡ “ ይሊሌ፡፡
ይህ አንቀጽ ሇአስተዲዯር መስሪያ ቤት ያሌተገዯበ መብት ይሰጣሌ፡፡ ስሇዚህም ዞኑ
አሁንም ቢሆን ሇዚህ ጉዲይ ትኩረት ሰጥቶ ውለ መሻሻሌ ካሇበት ይህንን ከግምት
ውስጥ አስግብቶ መሆን አሇበት፡፡
3. በተሻሻሇዉ ኮንሴሽን ዉሌ አንቀጽ 3 (9.5) ሊይ “ …ገዥዉ ምርቱን አንስቶ
የማይጨርስ ከሆነና የዉለ ጊዜም ያሌተሇወጠ ከሆነ ገዢዉ ያሌተነሳዉን ምርት
ሇመንከባከብ የወጣዉን ወጪ ሳይጠይቅ በቦታዉ ያሇዉን ምርት ያሇምንም ቅዴመ
ሁኔታ ሇሻጩ ሇቅቆ ይወጣሌ “ ይሊሌ፡፡ ይህን ሲሌ ከ 26 ዓመት በኃሊ ያሌተነሳዉን
እንጨት ሇቅቆ ይወጣሌ ማሇት ነዉ፡፡ ይህንን አንቀጽ በምስሇት (Analogy) እስከ
10ኛዉ ዓመት ያሌተነሳዉን 47% የመጀመሪያ ምርት እንጨት ዞኑ መዉረስ ተገቢ
ነዉ፡፡
4. በስተመጨረሻም የዞኑ መንግስት እነዚህን አማራጮችንም አሌፈሌግም የሚሌ ከሆነ
ከሊይ የተዘረዘሩትን የገዢ ችግሮችን በመጥቀስ ዴርጅቱን ካሣ በመጠየቅ ዉለን ማፍረስ
ይችሊሌ፡፡

19

You might also like