You are on page 1of 10

ydb#B B/@éC½ B/@rsïCÂ ?

ZïC KLL mNGST


db#B nU¶T Uz@È
DEBUB NEGARIT GAZETA OF THE SOUTHERN NATIONS,
NATIONALITIES AND PEOPLES REGIONAL STATE

bdb#B B/@éC½ B/@rsïCÂ


፲፰ ›mT q$_R ፬ ሀዋሳ ?ZïC KLል Mክር b@T 13 Year No 8
ጥቅምት ፰ቀን ፪፼ዓ.ም -ÆqEnT ywÈ ደንብ Hawassa, August 9/2007

በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት


የጥቃቅንና አነስተኛ ንግድና ኢንዱስትሪን የገበያ ዕድል ለማስፋፋትና ለማበረታታት የወጣ
ደንብ ቁጥር 60/1999 ለማሻሻል የወጣ ደንብ ቁጥር 98/2004

መግቢያ

በኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ እንደተመለከተው አብዛኛው የከተማ ነዋሪ በጥቃቅንና


አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ተሰማርቶ በሚያገኘው ገቢ የሚተዳደር በመሆኑ ዘርፉ የተለየ ድጋፍ
ሊሰጠው ስለሚገባ፣

ዘርፉ በባህርይው የሰው ኃይል በብዛት የሚሰማራበት፣ ካፒታል ቆጣቢና በተለይም አገራዊ
ባለሀብቶችን ወደ ኢንዱስትሪ ልማት መስክ ለማስገባትና ለመካከለኛው እና ከፍተኛው
ኢንዱስትሪ ልማት መሠረት ለመጣል የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ፣

ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በየሙያ ዘርጉ ሰልጥነው የሚመረቁ ወጣቶች


በአነስተኛ ካፒታል በግልና በቡድን ገቢ የሚያስገኝ ሥራ ፈጥረው በኢኮኖሚያዊ የልማት
እንቅስቃሴ ውስጥ በብዛት እንዲሳተፉ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣

ከማምረቻ፣ መስሪያና መሸጫ ቦታ፣ ከብድር አቅርቦት፣ ከገበያ ማስተዋወቅ ልምድ ማነስ፣
ከሥልጠና ከቅድመ ክፍያ እና ከመሳሰሉት ጋር በተያያዘ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ተወዳዳሪ
ምርትና አገልግሎ ማቅረብ እንዲችሉ መደገፍ ተገቢ በመሆኑ፣

ለኢንዱስትሪ ልማት እና ለስራ ዕድል ፈጠራ የተለየ አስተዋፅኦ የሚያበረክተውን ዘርፍ


በመደገፍ ረገድ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተግባርና ኃላፊነታቸውን እንዲገነዘቡ፣ ተገቢውን
ድጋፍ የሚሰጡበትንና ለአፈፃፀም አመቺ የሆነ ሕጋዊ መሠረት እንዲኖራቸው ማድረግ
አስፈላጊ ስለሆነ፣

Page 1436 of 2280


አገራችን በሚቀጥሉት ዓመታት በምትተገብረው በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ
የኢንዱስትሪ መሠረት በመጣል በዕቅድ ዘመኑ ማብቂያ ኢንዱስትሪ መሪነቱ እንዲረከብ ታሳቢ
መደረጉና ለዚህም በከተሞች የኢንዱስትሪ መሠረት ለመጣልና ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር
ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር ለማድረግ በአዲስ መልክ በአገር አቀፍ ደረጃ የጥቃቅንና
አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ የፀደቀ በመሆኑና ከትርጓሜ ጀምሮ ትኩረት
የተሰጠ በመሆኑ በተሻሻለው የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ ሕገ-መንግስት አንቀጽ ፹፯ ንዑስ ፯ አንቀፅ
መሰረት የክልሉ መስተዳድር ም/ቤት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡

ክፍል አንድ

ጠቅላላ

1. አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግስት ለጥቃቅንና አነስተኛ ንግድና ኢንዱስትሪን የገበያ ዕድል
ለማስፋፋትና ለማበረታታት የወጣ ደንብ ቁጥር 60/1999 ለማሻሻል የወጣ ደንብ ቁጥር
98/2004 ዓ.ም ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2. ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፡-
1. "ማህበር" ማለት በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪ ማሕበራት ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት
ያላቸው ሰዎች የተደራጁት እና በህግ መሠረት የተመዘገበ ስብስብ ማለት ነው፡፡
2. "የመንግሥት መሥሪያ ቤት"/ተቋም ማለት ንብረትነቱ ሙሉ በሙሉ ወይም ከአምሳ
በመቶ በላይ የክልሉ፣ የዞን፣ የወረዳ፣ የልዩ ወረዳና የከተማ አስተዳደር ንብረት የሆነ
ነው፡፡
3. "አሠሪ መሥሪያ ቤት" ማለት ከማበራት ጋር ውል የገባ የመንግሥት መ/ቤት ወይም
ተቋም ነው፡፡
4. "ንዑስ የሥራ ውል /ሳብ ኮንትራት/" ማለት ዋናውን ስራ በዋናው ሥራ ተቋራጮች
ማሰራትና የተወሰኑ ስራዎችን ደግሞ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሰጥ
ማድረግ ነው፡፡
5. "ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ" ማለት የኢንተርፕራይዙን ባለቤት፣ የቤተሰብ አባላትና
ተቀጣሪ ሰራተኞችን ጨምሮ እስከ አምስት ሰዎች ቀጥሮ የሚያሰማራና የጠቅላላ

Page 1437 of 2280


ካፒታሉ መጠን ህንፃን ሳይጨምር በአገልግሎ ዘርፍ ከብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ወይም
በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከብር 100.000 (አንድ መቶ ሺህ) ያልበለጠ ኢንተርፕራይዝ ነው፡፡
6. "አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ" ማለት የኢንተርፕራይዙን ባለቤት፣ የቤተሰብ አባላትና
ተቀጣሪ ሰራተኞችን ጨምሮ ከስድስት እስከ ሰላሳ ሰዎች የሚያሰማራና የጠቅላላ
ካፒታሉ መጠን ሕንፃን ሳይጨምር በአገልግሎት ዘርፍ ከብር 50,001 (ሃምሳ ሺህ
አንድ) እስከ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ወይም በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከብር 100,001
(አንድ መቶ ሺህ አንድ) እስከ 1,500,000 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ) ያልበለጠ
ኢንተርፕራይዝ ነው፡፡
7. "አገልግሎት አቅርቦት" ማለት የሥራ ክፍያ ያልሆነና ገቢ የሚያስገኝ ማንኛውም
አገልግሎት የመስጠት ሥራ ነው፡፡
8. "የደንብ ልብስ" ማለት የመንግሥት መ/ቤት ወይም ተቋም ሰራተኞ የሥራ ልብስ፣
የተማሪዎች ዩኒፎርም፣ የስፖርት ትጥቅ፣ ለትያትር ባለሙያዎች አገልግሎት የሚውሉ
የመድረክ ልብሶች፣ ለሕዝብ በዓላት ማድመቂያ የሚሆኑ ልብሶች እና የመሳሰሉት
ናቸው፡፡
9. "የሲቪል ኮንስትራክሽን" ማለት ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ህንፃዎች፣ መንገዶች፣
መስኖ ልማቶች፣ የከተማና የገጠር ንጹህ ውኃ አቅርቦቶች፣ ግንባታዎች፣ ጥገናዎች፣
ማስፋፊያዎችና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
፲፩. "ክልል" ማለት የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ማለት ነው፡፡
፲፪. "ሰው" ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ነው፡፡
፲፫. "ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ" ማለት በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ለሕብረተሰቡ የሚገነቡ
የጋራ መኖሪያ ቤቶችን፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች
መኖሪያ ቤቶችንና ሌሎች ግንባታዎችን ለመስራት የተቋቋመ መንግስታዊ ተቋም ማለት
ነው፡፡
፲፬. "የአካባቢ ልማት ፕሮጀክት" ማለት በክልሉ መስተዳድር፣ በዞኖች፣ በወረዳዎች፣ በልዩ
ወረዳዎችና ከተሞች ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ሕንፃዎች እና ቢሮዎች፣ ለጥቃቅንና
አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አገልግሎት የሚሰጡ የማምረቻ፣ የማሳያና የመሸጫ
ማዕከላት፣ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ማዕከላት፣ የወጣቶች መዝናኛ ማዕከላት
የመሳሰሉት ግንባታዎች ፕሮግራም ነው፡፡
፲፭. "የመሠረተ ልማት ፕሮጀክት" ማለት በክልሉ የሚገነቡ የመንገድና ድልድይ፣ የመጠጥ
ውሃ ሥራዎች፣ የፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መስመሮች፣ የመፀዳጃ ቤቶችና የመሳሰሉት
ግንባታዎቸ ፕሮግራም ነው፡፡

Page 1438 of 2280


ተሰማርቶ በማምረት በመነገድና አገልግሎት በመስጠት ተግባር ላይ የተሰማሩ ናቸው፡፡
፲፯. "አልባሳት" ማለት ለመንግሥት ተቋማት አገልግሎት የሚውሉ መጋረጃዎች፣ የጠረጴዛ
ልብሶችና የመሳሰሉት ሲሆኑ፣ በአንቀሳቃሾች እሴት ተጨምሮባቸው የተዘጋጁ ሌሎች
የጨርቃጨርቅ እና የቆዳ ውጤቶችንም ይጨምራል፡፡
3. የፆታ አገላለጽ
በዚህ ደንብ በወንድ ጾታ የተገለጸው የሴት ጾታን ያካትታል፡፡
4. የደንቡ ተፈፃሚነት ወሰን
ይህ ደንብ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች
እንዲሁም ደንቡን በማስፈጸም ግዴታ ባለባቸው ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ክፍል ሁለት

ስለማህበራት፣ የንግድና የሥራ ፈቃድ፣

5. የጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበር አባልነት በተመለከተ


1. በኮንስትራክሽን ተግባር ለመሠማራት የሚደራጁ የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት
አባላት ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ተመርቀው በወጡ
ተመራቂዎች እና ሙያውን በልምድ ባገኙ ባለሙያዎች ስብጥር ሊደራጁ ይችላል፡፡
የአባላት ስብጥር በንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ በሚያወጣው መመሪያ
ይወሰናል፡፡
6. የንግድና የሥራ ፈቃድ
የንግድና ሥራ ፈቃድን በተመለከተ በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 686/2002 መሠረት
ዝርዝሩ ለእያንዳንዱ የሥራ ዘርፍ በተመለከተው ዓይነት የሚያወጣ ይሆናል፡፡
1. በኮንስትራክሽን ሥራዎች ለሚደራጁ ማህበራት እንደሁኔታው ከደረጃ 10 ጀምሮ
ብቃታቸው እየታየ የግንባታ፣ የንግድና የሥራ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡
2. የኮንስትራክሽን ግብአቶች ማለትም የእንጨትና የብረት ውጤቶች፣ ጠጠር፣ ፕሪካስት
ቢም፣ ብሎኬት፣ አግሮስቶን ቱቦ፣ ጥርብ ድንጋይ፣ አሸዋ እና የመሳሰሉትን ለማምረት
የሚደራጁ ማህበራት አግባብነት ካለው የመንግስት መ/ቤት ወይም ተቋም የብቃት
ማረጋገጫ፣ የንግድና የሥራ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡
3. አልባሳትና የእንጨት ሥራ ውጤቶን በማዘጋጀት ሥራ ዘርፍ ለሚደራጁ ጥቃቅንና
አነስተኛ ማህበራት የሚመለከተው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ወይም ተቋም ንግድና
የሥራ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡

Page 1439 of 2280


4. ምግብና ምግብ ነክ የሆኑ ምርቶችን እሴት እየጨመሩ ለማቅረብ ለሚደራጁ ጥቃቅንና
አነስተኛ ማህበራት የሚከለከተው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ወይም ተቋም ንግድና
የሥራ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡
5. ከግብርና ልማት ሥራ ጋር ተዛማጅነት ላላቸው የሥራ መስኮች የሚያገለግሉ
መሣሪያዎችን ለማምረት ለሚደራጁ ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት የሚመለከተው
የመንግሥት መሥሪያ ቤት ወይም ተቋም ንግድና የሥራ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡
6. በሌላ ማናቸውም ዓይነት ኢኮኖሚያዊ ወይም ማበራዊ ፋይዳ ባለው የከተማ ጽዳት
የመጠበቅ እና መሰል አገልግሎት ለማቅረብ ለሚደራጁ ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት
የሚመለከተው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ወይም ተቋም ንግድና የሥራ ፈቃድ
ይሰጣቸዋል፡፡
ክፍል ሦስት

ለአንቀሳቃሾች ስለሚደረግ ማበረታቻ

7. በመሠረተ ልማት፣ አካባቢ ልማት እና በቤቶች ግንባታ ሥራ ለተሠማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ


ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣል፤
1. ከብር 1,000,000.00 /አንድ ሚልዮን ብር/ የማይበልጥ ዋጋ ያለው የኮንስትራክሽን
ሥራ የመንግሥት መሥሪያ ቤት/ ተቋም/ ሥራውን እንዲሠራ አወዳድሮ ለአሸናፊው
ይሰጣል፡፡ ዋጋው የቀድሞ ሥራዎች እና የግንባታው የመሐንዲስ ግምት ከግንዛቤ ገብቶ
አሠሪው መ/ቤትና የኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ በጋራ ይወስናሉ፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ የጥቃቅንና አነስተኛ
ማኅበር በሶስት ዙር የተገኘው አጠቃላይ ገቢ ብር 3,000,000 /ሦስት ሚልዮን ብር/
እስካልሞላ ድረስ ከተመሳሳይ ማህበራት ጋር የመወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም
ብር 3,000,000/ ሦስት ሚልዮን ብር/ ከሞላ ለሌሉቹ እድል ለመስጠት ሲባል በዚህ
ልዩ መብት ተጠቃሚ አይሆንም፡፡
3. ይህ ደንብ የሚመለከተው አንድ ማኅበር ሊሰራው ውል ከገባበት ሥራ ዋጋ እስከ 20
ከመቶ በቅድሚያ ይከፈላል፡፡
4. ከአንድ በላይ የሆኑ የጥቃቅንና አነስተኛ ማሕበራት በጋራ ተሰባስበው ከሌሎች ደንቡ
የማይመለከታቸው የሥራ ተቋራጮች ጋር በጨረታ ሥርዓት በሚወዳደሩበት ጊዜ
በጨረታው ለዋጋ ከተያዘው ነጥብ 3 ከመቶ ላቀረቡት ዋጋ ባገኙት ነጥብ ላይ
ለማበረታታት ይደመርላቸዋል፡፡

Page 1440 of 2280


5. ይህ ደንብ የማይመለከተው የሥራ ተቋራጭ የሚወዳደርበትን ሥራ ቢያሸንፍ ከሥራው
ጠቅላላ ዋጋ ከ30 ከመቶ የማያንስ ዋጋ ያለውን ሥራ በሰብ ኮንትራት ለጥቃቅንና
አነስተኛ ማኅበራት ሰጥቶ ለማሰማራት ግዴታ የገባ የሥራ ተቋራጭ በጨረታው ለዋጋ
ከተያዘው ነጥብ 3 ከመቶ ላቀረበው ዋጋ ባገኘው ነጥብ ላይ ለማበረታቻነት
ይደመርለታል፡፡
6. ከላይ በዚህ አንቀጽ ንዑስ ፬ አንቀጽ እና ፭ የተገለጹትን በተመለከተ ለተጫራቾች
በጨረታ ሰነድ ላይ መገለጽ ይኖርበታል፡፡

8. በመሠረተ ልማት፣ አካባቢ ልማትና በቤቶች ልማት ግንባታ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን


ለሚያመርቱና ለሚያቀርቡ ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
1. ብር 700,000 /ሰባት መቶ ሺህ ብር/ የማይበልጥ ዋጋ ያላቸውን የግንባታ ግብአቶችን
ለመግዛት የሚፈልግ የመንግስት መሥሪያ ቤት/ ተቋም/ የጥቃቅንና አነስተኛ
ማህበራትን አወዳድሮ ሥራውን ለአሸናፊው ይሰጣል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ የጥቃቅንና አነስተኛ
ማህበር በሶስት ዙር የተገኘው አጠቃላይ ገቢ ብር 2,100,000 / ሁለት ሚሊዮን አንድ
መቶ ሺህ ብር/ እስካልሞላ ድረስ ከተመሳሳይ አንቀሳቃሾች ጋር የመወዳደር መብቱ
የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ብር 2,100,000 /ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ብር/ ከሞላ
ለሌሎቹ እድል ለመስጠት ሲባል በዚህ ልዩ መብት ተጠቃሚ አይሆንም፡፡
3. የመንግሥት ተቋማት የኮንስትራክሽን፣ የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶችን ለመግዛት
ሲፈልጉ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት ምርት ውጤቶች ቅድሚያ በመስጠት
አወዳድረው መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ቢሮው ለጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት ለማመረቻ መሣሪያዎች ወይም ማሽነሪዎች
መግዣ እና ለጥሬ ዕቃ መግዣ የሚውል ብድር የሚያገኙበትን ሁኔታ ከብድር አቅራቢ
ድርጅቶች ጋር በጋራ ያመቻቻል፡፡
5. ምርቱ ወይም አገልግሎቱ እንዲቀርብለት ያዘዘው አካል በመስፈርቱ መሠረት በወቅቱ
እስከቀረበለት ድረስ በሥራ ትዕዛዝና በውሉ መሠረት ክፍያውን ፈጽሞ ምርቱን ወይም
አገልግሎቱን የመቀበል ግዴታ አለበት፡፡
6. የሥራ ትዕዛዝ ያለው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ወይም ተቋም አምራቹ ወይም
አገልግሎት ሰጪው ለሥራው የሚያስፈልጉትን ግብአቶች በቅድሚያ የሚያገኝበትን
ሁኔታ ያመቻቻል፡፡

Page 1441 of 2280


7. ይህ ደንብ የማይመለከተው የሥራ ተቋራጭ የሚወዳደርበትን ሥራ ቢያሸንፍ ከሥራው
ጠቅላላ ዋጋ ከ30 ከመቶ የማያንስ ዋጋ ያለውን ሥራ በሰብ ኮንትራት ለጥቃቅንና
አነስተኛ ማኅበራት ሰጥቶ ለማሠራት ግዴታ የገባ የሥራ ተቋራጭ በጨረታው ለዋጋ
ከተያዘው ነጥብ 3 ከመቶ ላቀረበው ዋጋ ባገኘው ነጥብ ላይ ለማበረታቻነት
ይደመርለታል፡፡

9. የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶችን ለቤቶች ልማት ሆነ ለሌላ መንግስት መሥሪያ ቤት


ወይም ተቋም ለሚያቀርቡ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
1. ከብር 700,000 /ሰባት መቶ ሺህ ብር/ የማይበልጥ ዋጋ ያለው የእንጨትና ብረታ
ብረት ለመግዛት የሚፈልጉ የመንግስት መሥሪያ ቤት/ ተቋም/ ሥራውን እንዲሠራው
ለዘርፉ ለተደራጁ አወዳድሮ ይሰጣል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ የጥቃቅንና አነስተኛ
ማህበር በሶስት ዙር የተገኘው አጠቃላይ ገቢ ብር 2,100,000 / ሁለት ሚሊዮን አንድ
መቶ ሺህ ብር/ እስካልሞላ ድረስ ከተመሳሳይ አንቀሳቃሾች ጋር የመወዳደር መብቱ
የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ብር 2,100,000 /ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ብር/ ከሞላ
ለሌሎቹ እድል ለመስጠት ሲባል በዚህ ልዩ መብት ተጠቃሚ አይሆንም፡፡
3. ቢሮው ለጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት ለማመረቻ መሣሪያዎች ወይም ማሽነሪዎች
መግዣ እና ለጥሬ ዕቃ መግዣ የሚውል ብድር የሚያገኙበትን ሁኔታ ከብድር አቅራቢ
ድርጅቶች ጋር በጋራ ያመቻቻል፡፡
4. የሥራ ትዕዛዝ ያለው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ወይም ተቋም አምራቹ ወይም
አገልግሎት ሰጪው ለሥራው የሚያስፈልጉትን ግብአቶች በቅድሚያ የሚያገኝበትን
ሁኔታ ያመቻቻል፡፡
፲. በአልባሳት ግዢ ወቅት ለጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት ቅድሚያ ይሰጣል፣
1. ከብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ የማይበልጥ ዋጋ ያለው የጨርቃጨርቅና
አልባሳት ሥራ ያለው የመንግስት መሥሪያ ቤት/ ተቋም/ ሥራውን እንዲሠራው
ለዘርፉ ለተደራጁ ማኅበራት አወዳድሮ ለአሸናፊው ይሰጣል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ የጥቃቅንና
አነስተኛ ማህበር በሶስት ዙር የተገኘው አጠቃላይ ገቢ ብር 1,500,000 / አንድ
ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር/ እስካልሞላ ድረስ ከተመሳሳይ አንቀሳቃሾች ጋር
የመወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ብር 1,500,000 /አንድ ሚሊዮን አምስት

Page 1442 of 2280


መቶ ሺህ ብር/ ከሞላ ለሌሎቹ እድል ለመስጠት ሲባል በዚህ ልዩ መብት ተጠቃሚ
አይሆንም፡፡
3. የደንብ ልብስ ጫማ እና አልባሳትን ለመግዛት የሚፈልግ የመንግሥት መሥሪያ ቤት
ወይም ተቋም አልባሳትን በማምረት ወይም እሴት በመጨመር የሚያቀርቡ
ጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት እርስ በርስ አወዳድሮ ይገዛል፡፡
፲፩. ምግብና ምግብ ነክ ምርቶች ግዢ ወቅት ለጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ቅድሚያ
ይሰጣል፣
1. ምግብና ምግብ ነክ ምርቶችን መግዛት የሚፈልግ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ወይም
ተቋም ምግብና ምግብ ነክ ምርቶችን በማዘጋጀት ወይም እሴት በመጨመር
የሚያቀርቡ ጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት እርስ በርስ አወዳድሮ ይገዛል፡፡
2. ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ የማይበልጥ ዋጋ ያለው ምግብ ነክ
ምርቶች መግዛት የሚፈልጉ መሥሪያ ቤቶች/ተቋም/ ሥራውን እንዲሠራ በምግብ ነክ
ዘርፍ ለተደራጁ ማኅበራት አወዳድሮ አለሸናፊው ይሰጣል፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ የጥቃቅንና
አነስተኛ ማህበር በሶስት ዙር የተገኘው አጠቃላይ ገቢ ብር 1,500,000 / አንድ
ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር/ እስካልሞላ ድረስ ከተመሳሳይ አንቀሳቃሾች ጋር
የመወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ብር 1,500,000 /አንድ ሚሊዮን
አምስትመቶ ሺህ ብር/ ከሞላ ለሌሎቹ እድል ለመስጠት ሲባል በዚህ ልዩ መብት
ተጠቃሚ አይሆንም፡፡
4. የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ወይም የሠራተኞች ተቋማት የሠራተኞ ክበባትን
በኮንትራት ለመስጠት ሲፈልጉ ዘርፉ ለተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት
ቅድሚያ ሰጥቶ በማወዳደር ሥራውን ይሰጣል፡፡
፲፪. የማበረታቻ ሥርዓቱን በተመለከተ
1. ይህ ማበረታቻ በደንቡ ላይ የተዘረዘሩ ቅድመ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው
ማንኛውም ሥራ ለኪራይ ሰብሳቢነት በማያጋልጥ መልኩ በውድድር ብቻ የሚሰጥ
ይሆናል፡፡
2. በዚህ ማበረታቻ ሥርዓት መሠረት ሥራውን የተረከቡ ማህበራት ለሌላ አካል
አሳልፎ መስጠት አይችሉም፡፡

Page 1443 of 2280


3. በዚህ ማበረታቻ ሥርዓት መሠረት ለአንድ ሥራ ሁለት ጊዜ የውድድር ማስታወቂያ
ወጥቶ በቂ ተወዳዳሪ ካልተገኘ ከቀረቡት ተወዳዳሪዎች ውስጥ አነስተኛ ዋጋ
ላቀረበው ማህበር መስጠት ይቻላል፡፡

፲፫. ስልጠና ስለመስጠት

1. በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተሰማሩት ማህበራት የሥልጠና ፍላጎታቸው


እየተጠና የማብቃት ስልጠና በመንግሥት ይሰጣቸዋል፡፡
2. የስልጠና ወጪን በተመለከተ ማኅበራቱ አቅማቸው በፈቀደ መልኩ እንዲጋሩት
ይደረጋል፡፡

፲፬ . የብድር አቅርቦት

የብድርና ቁጠባ ተቋማት በብድር አሰጣጥ ተግባራቸው የሥራ ትዕዛዝ ለተቀበሉ


የጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት ቅድሚያ ይሰጣሉ፡፡

፲፭. ቁጥጥርና ተጠያቂነት

1. ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራትን ለማጠናከር ሲባል ድጋፍ የሚሰጣቸው ሆኖ ዝርዝር


መሥፈርትና ጥራትን በተመለከተ መልኩ በውሉ መሠረት የማጠናቀቅ ግዴታ
አለባቸው፡፡
2. የጥራትና የጊዜ መሥፈርት በውለታው መሠረት ስለመጠበቁ ተረካቢው
የመንግሥት መ/ቤት/ተቋም/እና ሌሎች አግባብነት ያላቸው የመንግሥት ተቋማት
ቁጥጥርና ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ በተመለከተው መሠረት ጥራቱን የጠበቀ ምርት
ወይም አገልግሎት ያላቀረበ የጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበር ለሥራ ዘርፍ አግባብነት
ባለው የመንግስት ተቋም ከተረጋገጠ በቀጣይነት የማበረታቻ ዕድል ተጠቃሚ
አይሆንም፡፡

Page 1444 of 2280


ክፍል አራት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

፲፮ . የመተባበር ግዴታ፣

በክልሉ ውስጥ የሚገኝ እያንዳንዱ የመንግሥት መ/ቤትና ተቋም ይህንን ደንብ


የማስፈፀም ግዴታ አለበት፡፡

፲፯. ተፈፃሚነት የሌላቸው ሕጎች

ከዚህ ደንብ ጋር የሚጋጭ ደንብ፣ መመሪያ ወይም ልማዳዊ አሰራር በዚህ ደንብ
የተካተቱ ጉዳዮችን በተመለከተ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡

፲፰. መመሪያ የማውጣት ስልጣን፣

የንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ይህንን ደንብ ለማስፈፀም የሚረዳ መመሪያ


ሊያወጣ ይችላል፡፡

፲፱. ደንብ ስለማሻሻል

ይህ ደንብ በክልሉ መስተዳድር ም/ቤት ሊሻሻል ይችላል፡፡

፳. ደንቡ ስለሚፀናበት ጊዜ

ይህ ደንብ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል መስተዳደር ምክር ቤት ከፀደቀበት ከጥቅምት 8 ቀን


2004 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

ሽፈራው ሽጉጤ

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ

መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር

Page 1445 of 2280

You might also like