You are on page 1of 19

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር

የፌዴራል የከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ

የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ ሽግግር አፈፃፀም ሞዴል መመሪያ ቁጥር …… ../2010
.
ዓ ም

/የተሻሻለ/

ግንቦት/ 2010 ዓ.ም


አዲስ አበባ
መግቢያ
የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የኢንዱስትሪ ልማት ሥትራቴጂና የከተማ ልማት ፖሊሲ L ይ
ተመስርቶ የራሱ ፕሮግራምና ዝርዝር የድጋፍ ፓኬጅ ተዘጋጅቶለት ላለፉት ዓመታት በኢንተርፕራይዞች ልማት
አበረታች ውጤት አስገኝቷል:: የድጋፍ ፓኬጁም በተመረጡ ዕድገት ተኮር ዘርፎች ላይ uT}¢` ለኢንተርፕራይዞች
ድጋፍ መስጠት አስችሏል::

u²=IU መሠረት በተለያዩ የምርትና የአገልግሎት ሙያዎች K}WT\ u`ካታ ኢንተርፕራይዞች አስፈላጊው
የማደራጀት፣ የማሰልጠን፣ የፋይናንስና እንዲሁም የማምረቻና የመሸጫ x ታ ›p`x„‹ እ“ የገበያ ƒee` ድጋፎች
እንዲያገኙ በማድረግ ሰፊ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርና ለድህነት p’d ፕሮግራሙ የራሱን አስተዋጽኦ ያበረከተ
በመሆኑ፣ የተሰጡት ድጋፎች ኢንተርፕራይዞቹ በየዕድገት ደረጃቸው ለሚያጋጥሟቸው ችግሮች መፍትሄ በመስጠት
ረገድ ዉስንነት ታይቶባቸዋል:: እንዲሁም ለኢንዱስትሪ MTƒ SW[~ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች MTƒ“
መስፋፋት እንደሆነ በኢንዱስትሪ MTƒ ሥትራቴጂ ሠነድ ላይ በግልጽ የተቀመጠ ቢሆንም እስከ አሁን ተግባራዊ
በማድረግ ሂደት እንደታየው ለኢንተርፕራይዞቹ ሲደረግ የነበረው ድጋፍ ከአንድ የዕድገት ደረጃ ¨ደ ሌላ የዕድገት ደረጃ
ለመሸጋገር የሚያደርጉትን ጥ[ት በ T በረታ ƒ ረገድ የተሟላ አፈጻጸም ያልነበረው በመሆኑ ምክንያት በ 2003 ዓ.ም
የወጣው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ሥትራቴጂ የድጋፍ ማዕቀፍና የአፈፃፀም ሥ M„‹ ሠድን
SW[ƒ በማድረግ ኢንተርፕራይዞችን እንደየዕድገት ደረጃቸው በመክፈል የተቀመጡ c=J”& እ’`c<U Ue[ታ ወይም
ጀማሪ/Start-Up/ ደረጃ፣ ታዳጊ> ወይም መስፋፋት/Growth/ ደረጃ እ“ Swnƒ /Maturity/ ደረጃ “†¨<::

በመሆኑም ይህንን የኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ ክፍፍል SW[ƒ በማድረግ ኢንተርፕራይዞቹ በየዕድገት
ደረጃቸው የሚያስፈልጓቸው ድጋፎች ለመስጠት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ መመሪያዎችና ማኑዋሎች ተዘጋጅተው ሥራ
ላይ ከዋሉ የቆዩ ቢሆንም ኤጄንሲው ከተሰጠው ተልዕኮ እና ካለው ወቅታዊ አደረጃጀት አንፃር የነበሩ ችግሮችን
በመፈተሽ ከኪራይ ሰብሳቢነት የጸዳ፣ አሳታፊ፣ ፍትሃዊና ውጤታማ በሆነ መልኩ ድጋፉን ለማቅረብ
እንዲሁም ይበልጥ ለአሰራር በሚያመች መልኩ ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ
ቁጥር 374/2008 አንቀጽ 14 መሠረት ይህ የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ ሽግግር
ሞዴል መመሪያ ተሸሽሎ ተዘጋጅቷል::

1
ክፍል አንድ

ጠቅላላ
1. አጭር ርዕስ
ይህ ሞዴል መመሪያ “የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ ሽግግር አፈፃፀም ሞዴል
መመሪያ ቁጥር ……. /2010” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል::

2. ትርጓሜ
በዚህ ሞዴል መመሪያ ውስጥ የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር፤
1) ”ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ” ማለት የኢንተርፕራይዙን ባለቤት፤ የቤተሰብ አባላትና ተቀጣሪ ሰራተኞችን
ጨምሮ እስከ አምስት ሰዎች ቀጥሮ የሚያሰማራና የጠቅላላ ካፒታሉ መጠን ህንፃን ሳይጨምር
በአገልግሎት ዘርፍ ከብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ወይም በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ)
ያልበለጠ ኢንተርፕራይዝ ነው:፡
2) ”አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ” ማለት የኢንተርፕራይዙን ባለቤት፤ የቤተሰብ አባላትና ተቀጣሪ ሰራተኞችን
ጨምሮ ከስድስት እስከ ሰላሳ ሰዎች የሚያሰማራና የጠቅላላ ካፒታሉ መጠን ህንፃን ሳይጨምር በአገልግሎት
ዘርፍ ከብር 50,001 (ሃምሳ ሺህ አንድ) እስከ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ወይም በከተማ ግብርና፣
በባህላዊ ማዕድን ማምረት ሥራና በግንባታ ዘርፍ ከብር 100,001 (አንድ መቶ ሺህ አንድ) እስከ 1,500,000
(አንድ ሚልዮን አምስት መቶ ሺ) ያልበለጠ ኢንተርፕራይዝ ነው::
3) “የኢንተርፕራይዝ ደረጃ ሽግግር” ማለት አንድ ኢንተርፕራይዝ ባለበት የዕድገት ደረጃ የሚሰጠውን ድጋፍ
ተጠቅሞ በገበያ ላይ በዋጋ፣ በጥራትና በአቅርቦት ተወዳዳሪ ሆኖ የቀጣይ የዕድገት ደረጃ የሽግግር
መስፈርቶቹን በማሟላት መሸጋገር ሲችል ነው::
4) “የምሥረታ/ጀማሪ ደረጃ” ማለት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለመመሥረት ፍላጎት ያላቸው
ሰዎች እና ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት በየደረጃው የሚጠበቅባቸውን ትምህርት በማጠናቀቅና በማህበር
እና በግለሰብ በሕግ አግባብ ተደራጅተው የራሳቸውን ቁጠባና ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ብድር በመውሰድ
ወደ ሥራ የገቡትን የሚያካትት ነው:: የምሥረታ /ጀማሪ ደረጃ ኢንተርፕራይዝ ሕጋዊ አቋም ይዞ
የማምረትና አገልግሎት የመስጠት ተግባር የሚጀምርበት ነው::
5) “የታዳጊ/መስፋፋት ደረጃ” ማለት አንድ ኢንተርፕራይዝ የሚሰጠውን ድጋፍ ተጠቅሞ በገበያ ላይ በዋጋ፣
በጥራትና በአቅርቦት ተወዳዳሪ ሲሆንና ትርፋማነቱ በቀጣይነት ሲረጋገጥ ነው:: በዚህ ደረጃ ያለ
ኢንተርፕራይዝ በምሥረታ ደረጃ ከነበረው ቀጥሮ የሚያሠራው የሰው ኃይል ቁጥርና የጠቅላላ ሀብት መጠን
ዕድገት ይኖረዋል:: በተጨማሪም ኢንተርፕራይዙ የሂሳብ አያያዝ ሥርዓት የሚጠቀም ይሆናል::
6) “የመብቃት ደረጃ” ማለት አንድ ኢንተርፕራይዝ የሚሰጠውን ድጋፍ ተጠቅሞ በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪና
ትርፋማ ሆኖ የገበያ ድርሻውን ለማሳደግ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት በሥራ ላይ ካዋለና ለዘርፉ
የተቀመጠውን ትርጓሜ መሥፈርት በማሟላት ወደ ታዳጊ መካከለኛ ሲሸጋገር ወይንም በአለበት ደረጃ
በመሆን በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪና ትርፋማ ሆኖ የሚቀጥል ሲሆን ነው::

2
7) “ታዳጊ መካከለኛ ደረጃ” ማለት ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተቀመጠውን የሰው ሃይልና ጠቅላላ ሃብት
መጠን የመብቃት የዕድገት ደረጃ በማለፍ ወደ ኩባንያ ደረጃ የተሸጋገረ የኢንተርፕራይዝ የዕድገት ደረጃ
ነው::
8) “ቋሚ የሥራ ዕድል” ማለት የራሳቸውን ኢንተርፕራይዝ ፈጥረው የሚሰሩ ወይም በሌሎች ድርጅቶች
ውስጥ ከአንድ ዓመት ላላነሰ ጊዜ በቋሚነት ተቀጥረው በፔይሮል ክፍያ በማግኘት የሥራ ዕድል
የተፈጠረላቸው ማለት ነው::
9) “ጊዜያዊ የሥራ ዕድል” ማለት በጥሪት ማፍሪያ ፕሮጀክቶች የራሳቸውን ኢንተርፕራይዝ በጊዜያዊነት
በማቋቋም ወይም በፔይሮል ክፍያ በማግኘት ከአንድ ዓመት ላነሰ ጊዜ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ማለት
ነው::
10) "የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት" ማለት የኢንተርፕራይዞቹን ችግር የለየና በፍላጎት ላይ
የተመሠረተ የተሟላ መረጃ ማደራጀትና የመስጠት፣ ሥልጠና ድጋፍ፣ የቴክኖሎጂ ልማት፣ ግብይት፣ ምርጥ
ተሞክሮ ቅመራና ማስተላለፍን የሚያካትት ድጋፍ ነው፡፡
11) "የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና" ማለት በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፎች ለተሠማሩና
ለሚሠማሩ የኀብረተሰብ ክፍሎች፣ ባለሙያዎች አንድን ምርት ወይም አገልግሎት በብቃት ለማቅረብ፣
ጥራትና ምርታማነትን በቀጣይነት ለማሻሻል፣ የፈጠራ ሥራዎችን ለማበረታታት አመለካከት፣ ዕውቀትና
ክህሎት በማሳደግ በተሰማሩበት ወይም በሚሰማሩበት መስክ ላይ ዕሴትን በመጨመር ልማትን ለማፋጠን
እንዲያስችል የሚሰጥ ሙያዊ ሥልጠና ነው፣
12) "የንግድ ሥራ አመራር ሥልጠና" ማለት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አዋጪ የንግድ መስክን
በመምረጥ፣ በማቋቋምና በመምራት ሂደት ውስጥ በማቀድ፣ በማደራጀት፣ በመምራት፣ በማስተባበርና
በመቆጣጠር ውጤታማ እንዲሆኑ የሚሰጥ ሥልጠና ነው፣
13) “የገበያ ትስስር” ማለት ለአንድ ኢንተርፕራይዝ የገበያ ዕድል ለመፍጠር ከመንግስት ተቋማት ፕሮግራሞችና
ፕሮጀክቶች በአገር ውስጥ ከሚገኙ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ጋር በግብዓት፣ በምርትና
አገልግሎት አቅርቦት በጎንዮሽና በተዋረድ ግንኙነት የሚፈጠር የግብይት ወይም የሥራ ትስስር ነው::
14) “ጠቅላላ ሃብት” ማለት የአንድ ኢንተርፕራይዝ የተከፈለ እና በብድር የተገኘ ሀብት ነው::
15) ”ጠቅላላ ካፒታል” ማለት ህንፃን ሳይጨምር ከኢንተርፕራይዙ ጠቅላላ የቢዝነሱ ሀብት ላይ ዕዳው ተቀንሶ
የሚገኝው ካፒታል ማለት ነው፡፡
16) “የምርት ወይም የአገልግሎት ማስተዋወቂያ ዘዴዎች” ማለት ምርትን ወይም አገልግሎትን ለማስተዋወቅ
የመገናኛ ብዙሃን፣ ንግድ ትርዒትና ባዛር፣ ድረ-ገፅ፣ በራሪ ወረቀት፣ ቢዝነስ ካርድ፣ ቋሚ የማስታወቂያ ሰሌዳ፣
ማሸጊያ እና የመሳሰሉትን ያካትታል::
17) “ኢንዱስትሪ ዘርፍ” ማለት ማኑፋክቸሪንግ (በጥቃቅን ብቻ)፣ ከተማ ግብርና፣ ባህላዊ ማዕድን እና ግንባታ
ዘርፎችን ያካትታል፡፡
18) “አገልግሎት ዘርፍ” ማለት ከኢንዱስትሪ ዘርፍ ውጪ ሆኖ አገልግሎት በመስጠትና በ ሀገር ውስጥ ምርቶች
ንግድና ጥሬ ዕቃ አቅርቦት ሥራ ላይ የሚሰራ የሥራ ዘርፍ ነው::

3
19) "የሙያ ብቃት ምዘና" ማለት አንድ ባለሙያ በተዘጋጀው የሙያ ደረጃ መስፈርት መሰረት የሚጠበቅበትን
ብቃት መያዙ የሚረጋገጥበት ሥርዓት ነው።
20) "ቴክኖሎጂ” ማለት ዕውቀትን፣ ክህሎትን፣ መሣሪያዎችን እና እነዚህኑ ለመጠቀም የሚያስችሉ
ማኑዋሎችን፣ የአሰራር መመሪያዎችና አደረጃጀትን ያጠቃልላል፡፡
21) በዚህ መመሪያ ውስጥ በወንድ ፆታ የተገለፀው የሴትንም ፆታ ያካትታል፡፡

3. የተፈጻሚነት ወሰን
ይህ ሞዴል መመሪያ በኢትዮጵያ ከተሞች በሚገኙ የከተማ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ላይ
ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

4. ዓላማ
በዘርፍ ልማት ለተሰማሩ የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ ለመወሰን፣ ለማሸጋገርና
የኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃን ታሳቢ ያደረጉ ድጋፎች ለመስጠት ነው፡፡

5. መርሆዎች

1) ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጥ ድጋፍ የዘርፉን ልማት አቅጣጫ የተከተለ ይሆናል፣


2) ኢንተርፕራይዞች በእድገት ደረጃቸው ለሚሰጡ መንግስታዊ ድጋፎችና ማበረታቻዎች ዙሪያ ግንዛቤ
እንዲኖራቸው ይደረጋል፣
3) የእያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ የዕድገት ደረጃ መመዘኛዎች በግልፅ እንዲያዉቁት በማድረግ በዕድገት ደረጃ
እንዲመዘኑ ይደረጋል፣
4) የእድገት ደረጃ ሽግግር ሥራ ለደረጃው በተቀመጠው የድጋፍ ማዕቀፎችን በመፈፀም ተግባራዊ እንዲሆን
ይደረጋል፣
5) የእድገት ደረጃ ሽግግር ሥራ አስቀድሞ በተለየና በፍላጎት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ይደረጋል፣
6) የእድገት ደረጃ ሽግግር ስራ በተጨባጭ መረጃ ላይ የተመረተ እንዲሆን ይደረጋል፣
7) የእድገት ደረጃ ሽግግር ሥራ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ያረጋገጠ ሊሆን ይገባል፣

ክፍል ሁለት

የኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ ሽግግር መስፈርቶች

6. ከጀማሪ/ ምስረታ ወደ ታዳጊ የሚሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች ሊያሟሉዋቸው የሚገቡ ዝርዝር


መስፈርቶች
1) በሥራ ዕድል ፈጠራ
ሀ) በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች፤

4
(1) የጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ 3
እስከ 5 ሰዎች እንዲሁም በዓመት ውስጥ በጊዜያዊ እስከ 3 ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆን
አለበት፣
(2) የአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ ከ 6-
10 ሰዎች እንዲሁም በዓመት ውስጥ በጊዜያዊ የሥራ ዕድል ከ 4 እስከ 6 ሰዎች የሥራ ዕድል
የፈጠረ መሆን አለበት::

ለ) በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች፤


(1) የጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ እስ ከ
5 ሰዎች እንዲሁም በዓመት ውስጥ በጊዜያዊ እስከ 2 ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆን አለበት፣
(2) የአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ ከ 6-
8 ሰዎች እንዲሁም በዓመት ውስጥ በጊዜያዊ የሥራ ዕድል ከ 2 እስከ 4 ሰዎች የሥራ ዕድል
የፈጠረ መሆን አለበት::

2) በካፒታል መጠን
ሀ) በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ፤
(1) የካፒታል መጠኑ ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ከብር 50,001 እስከ 75,000 መሆን አለበት፣
(2) የካፒታል መጠኑ ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከብር 120,001 እስከ 500,000 መሆን አለበት::
(3) ጥቃቅን ሆነ አነስተኛ ኢንተርፕራይዙ በብድር ካገኘው ገንዘብ 40% እና በላይ ወይም ከጠቅላላ
የሃብት ውስጥ 20% እና በላይ ለቋሚ ንብረት ያዋለው መሆን አለበት::

ለ) በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ፤


(1) የካፒታል መጠኑ ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ 20,001 እስከ ብር 40,000 መሆን አለበት፣
(2) የካፒታል መጠኑ ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከብር 70,001 እሰከ ብር 200,000 መሆን አለበት፣
(3) ጥቃቅን ሆነ አነስተኛ በብድር ካገኘው ገንዘብ 20% እና በላይ ወይም ከጠቅላላ የሃብት ውስጥ
10% እና በላይ ለቋሚ ንብረት ያዋለ መሆን አለበት::

3) በገበያ መጠን
ሀ) በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ፤
(1) ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ዓመታዊ የሽያጭ መጠን ከብር 120,001 እስከ 200,000 መሆን
አለበት፣
(2) ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ዓመታዊ የሽያጭ መጠን ከብር 200,001 እስከ 300,000 መሆን
አለበት፣
(3) ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ከዓመታዊ የሽያጭ መጠን ውስጥ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ
ኢንተርፕራይዞች ቢያንስ ከ 30% በላይ፣ በብረታ ብረትና እንጨት ንዑስ ዘርፍ የተሰማሩ
ኢንተርፕራይዞች ቢያንስ ከ 50% በላይ እና በተቀሩት ዕድገት ተኮር ንዑሳን ዘርፎች የተሰማሩ
5
ኢንተርፕራይዞች ከ 70% በላይ የተገኘው ሽያጭ ከመንግስት የገበያ ትስስር ውጪ መሆን
አለበት፣
(4) ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከዓመታዊ የሽያጭ መጠን ውስጥ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ
ኢንተርፕራይዞች ቢያንስ ከ 30% በላይ እና በተቀሩት የዕድገት ተኮር ንዑሳን ዘርፎች የተሰማሩ
ኢንተርፕራይዞች ከ 70% በላይ የተገኘው ሽያጭ ከመንግስት የገበያ ትስስር ውጪ መሆን
አለበት፣
(5) ጥቃቅንም ሆነ አነስተኛ ኢንተርፕራይዙ ለሌሎች ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በንዑስ
ኮንትራት ቢያንስ 1 ጊዜ የገበያ ትስስር የፈጠረ መሆን አለበት፣
(6) ጥቃቅንም ሆነ አነስተኛ ኢንተርፕራይዙ ምርት ለማስተዋወቅ ቢያንስ ሦስት ዓይነት ውጤታማ
የማስተዋወቂያ ዘዴዎችን መጠቀም አለበት፣
(7) ጥቃቅንም ሆነ አነስተኛ ኢንተርፕራይዙ በየደረጃው በተዘጋጀ ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ ቢያንስ
አንድ ጊዜ የተሳተፈ መሆን አለበት::
ለ) በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ፤
(1) ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ዓመታዊ የሽያጭ መጠን ከብር 80,001 እስከ ብር 120,000 መሆን
አለበት፣
(2) ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ዓመታዊ የሽያጭ መጠን ከብር 120,001 እስከ 200,000 መሆን
አለበት፣
(3) የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከዓመታዊ የሽያጭ መጠን ውስጥ ከ 70% በላይ የተገኘው
ሽያጭ ከመንግሥት የገበያ ትስስር ውጪ መሆን አለበት፣
(4) ጥቃቅንም ሆነ አነስተኛ ኢንተርፕራይዙ ለሌሎች ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በንዑስ
ኮንትራት ቢያንስ 1 ጊዜ የገበያ ትስስር የፈጠረ መሆን አለበት፣
(5) ጥቃቅንም ሆነ አነስተኛ ኢንተርፕራይዙ ምርትና አገልግሎቱን ለማስተዋወቅ ቢያንስ ሦስት
ዓይነት ውጤታማ የማስተዋወቂያ ዘዴዎችን መጠቀም አለበት::

4) በትርፋማነት
ሀ) በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፤
(1) በዓመቱ ካደረገው ሽያጭ ቢያንስ 10 በመቶ የትርፍ መጠን መሆን አለበት፣
(2) ሥራውን ለማስፋፋት ያዋለው ተጨማሪ ኢንቨስትመንት እና/ ወይም የቁጠባ መጠን ከተጣራው
ካፒታል ከ 15% በላይ መሆን አለበት፡፡
ለ) በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፤
(1) በዓመቱ ካደረገው ሽያጭ ቢያንስ 10 በመቶ የትርፍ መጠን መሆን አለበት፣
(2) ሥራውን ለማስፋፋት ያዋለው ተጨማሪ ኢንቨስትመንት እና/ ወይም የቁጠባ መጠን ከተጣራ
ካፒታል ከ 15% በላይ መሆን አለበት::

5) የኢንተርፕራይዙ ምርታማነት

6
(ሀ) በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ምርታማነት ካለው ሙሉ
የማምረት አቅም 70% እና በላይ መጠቀም አለበት፣
(ለ) ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዙ አባላት ወይም ቋሚ ሰራተኞች መካከል ቢያንስ 50% የሙያ
ብቃት ምዘና ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆና አለባቸው::

6) በተቋማዊ አመራርና አደረጃጀት


ለጥቃቅንም ሆነ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፡-
ሀ) ዘመናዊ የሥራ አመራር ዘይቤ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረ መሆን አለበት፣
ለ) ለተሰማራበት ሥራ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ሥራ ላይ ማዋል እና ዓመታዊ ኦዲት ማስደረግ
አለበት፣
ሐ) የማምረቻ ማዕከል አደረጃጃት የምርት ሂደትን የተከተለና ንጽህናው የተጠበቀ መሆን አለበት፣
መ) የአባላትን እና ሰራተኞችን የሥራ ደህንነት ለመጠበቅ የሥራ ልብስ እንዲሁም እንደ ንዑስ ዘርፉ
ዓይነት የሥራ ላይ የደህንነት መሣሪያዎች እና የመሳሰሉት የተሟሉ መሆን አለባቸው፣
ሠ) ሥራውን ለማስፋፋት የሚያስችል በፅሁፍ የተዘጋጀ የንግድ ዕቅድ ማዘጋጀት አለበት፣
ረ) ከሌሎች ኢንተርፕራይዞች ጋር ስለ ቢዝነስ ሥራ ሃሳብ ለመለዋወጥም ይሁን የጋራ
እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን የሚያስችል የቢዝነስ ግንኙነት መፍጠር አለበት፣
ሰ) በልማት ሰራዊት አደረጃጀት የታቀፈና የነቃ ተሳትፎ ማድረግ አለበት፡፡

7) በመንግሥታዊ ድጋፎች አጠቃቀም


ለጥቃቅንም ሆነ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፡-
ሀ) የሚሰጠውን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ተግባር ላይ ያዋለ መሆን አለበት፣
ለ) የብድር ተጠቃሚ ከሆነ ውዝፍ ብድር የሌለበት መሆን አለበት፣
ሐ) የማምረቻ ማዕከል ተጠቃሚ ከሆነ የኪራይ ውዝፍ ዕዳ የሌለበት መሆን አለበት፣
መ) የተፈጠረለትን የገበያ ትስስር ወይም ዕድሉን በልማታዊ መንገድ የተጠቀመ መሆን አለበት፡፡

8) በቴክኖሎጂ አጠቃቀም
ለጥቃቅንም ሆነ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፡-
ሀ) ኢንተርፕራይዙ ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ለማሻሻል በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና
ተቋማት፣ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶችና ሌሎች የቴክኖሎጂ ተቋማት የሚሰራጩ ተፈላጊና
አዋጭ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቃሚ ለመሆን ቅድመ ዝግጅት ያደረገ መሆን አለበት::
ለ) ኢንተርፕራይዙ ከሚጠቀምባቸው የማምረቻ ወይም አገልግሎት መስጫ መሣሪያዎች ውስጥ ቢያንስ
50% በኢነርጂ ብቻ የሚንቀሳቀስ መሆን አለበት::

9) ግዴታን ስለመወጣት
ለጥቃቅንም ሆነ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፡-

7
ሀ) ኢንተርፕራይዙ የሚጠበቅበትን ዓመታዊ ግብር መክፈል አለበት፣
ለ) ኢንተርፕራይዙ ዓመታዊ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ዕድሳት ማካሄድ አለበት::

7. ከታዳጊ ወደ መብቃት ደረጃ የሚሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፡-


1) በሥራ ዕድል ፈጠራ
ሀ) በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች
(1) የጥቃቅን ኢንተርፕራይዙ የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ ለ 5
ሰዎች እንዲሁም በዓመት ውስጥ በጊዜያዊ የሥራ ዕድል ለ 4 ሰዎችና በላይ የሥራ ዕድል የፈጠረ
መሆን አለበት፣
(2) የአነስተኛ ኢንተርፕራይዙ የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ 11-
30 ሰዎች እንዲሁም በዓመት ውስጥ በጊዜያዊ የሥራ ዕድል ከ 6 ሰዎች በላይ የሥራ ዕድል የፈጠረ
መሆን አለበት፣

ለ) በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች


(1) የጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ ለ 5
ሰዎች እንዲሁም በዓመት ውስጥ በጊዜያዊ የሥራ ዕድል ለ 3 ሰዎችና በላይ የሥራ ዕድል የፈጠረ
መሆን አለበት፣
(2) የአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ 9-
30 ሰዎች እንዲሁም በዓመት ውስጥ በጊዜያዊ የሥራ ዕድል ከ 5 ሰዎች በላይ የሥራ ዕድል የፈጠረ
መሆን አለበት፣

2) በካፒታል መጠን
ሀ) በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ፤
(1) የካፒታል መጠኑ ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ከብር 75,001 እስከ 100,000 መሆን አለበት፣
(2) የካፒታል መጠኑ በከተማ ግብርና፣ በባህላዊ ማዕድን ማምረት ሥራ ወይም በግንባታ ዘርፍ
የተሰማራ አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከብር 500,001 እስከ 1,500,000 መሆን አለበት፣
(3) ጥቃቅን ሆነ አነስተኛ ኢንተርፕራይዙ በብድር ካገኘው ገንዘብ 50% እና በላይ ወይም ከጠቅላላ
የሃብት ውስጥ 25% እና በላይ ለቋሚ ንብረት ያዋለ መሆን አለበት፣
ለ) በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ፣
(1) የካፒታል መጠኑ ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ከብር 40,001 እስከ ብር 50,000 መሆን አለበት፣
(2) የካፒታል መጠኑ ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከብር 200,001 እሰከ ብር 500,000 መሆን አለበት፣
(3) ጥቃቅን ሆነ አነስተኛ ኢንተርፕራይዙ በብድር ካገኘው ገንዘብ 30% እና በላይ ወይም ከጠቅላላ
የሃብት ውስጥ 15% እና በላይ ለቋሚ ንብረት ያዋለው መሆን አለበት::

3) በገበያ መጠን
ሀ) በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ፤
8
(1) ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ዓመታዊ የሽያጭ መጠን ከብር 200,001 እስከ 300,000 መሆን አለበት፣
(2) ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ዓመታዊ የሽያጭ መጠን ከብር 1,000,001 እስከ 2,000,000 መሆን
አለበት፣
(3) ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ከዓመታዊ የሽያጭ መጠን ውስጥ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ
ኢንተርፕራይዞች ቢያንስ ከ 35% በላይ፣ በብረታ ብረትና እንጨት ንዑስ ዘርፍ የተሰማሩ
ኢንተርፕራይዞች ቢያንስ ከ 60% በላይ እና በተቀሩት ዕድገት ተኮር ንዑሳን ዘርፎች የተሰማሩ
ኢንተርፕራይዞች ከ 70% በላይ የተገኘው ሽያጭ ከመንግስት የገበያ ትስስር ውጪ የተገኘ መሆን
አለበት፣
(4) ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከዓመታዊ የሽያጭ መጠን ውስጥ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ
ኢንተርፕራይዞች ቢያንስ ከ 35% በላይ በተቀሩት የዕድገት ተኮር ንዑሳን ዘርፎች የተሰማሩ
ኢንተርፕራይዞች ከ 70% በላይ የተገኘው ሽያጭ ከመንግስት የገበያ ትስስር ውጪ የተገኘ መሆን
አለበት፣
(5) ኢንተርፕራይዙ ለሌሎች ኢንተርፕራይዞች በንዑስ ኮንትራት በዓመት ቢያንስ 2 ጊዜ የገበያ ትስስር
የፈጠረ መሆን አለበት፣
(6) ኢንተርፕራይዙ ምርት ለማስተዋወቅ ቢያንስ አምስት ዓይነት ውጤታማ የማስተዋወቂያ ዘዴዎችን
መጠቀም አለበት፣
(7) ኢንተርፕራይዙ ለደረጃው በተዘጋጀ ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ ሁለት ጊዜ የተሳተፈ መሆን አለበት፡፡
ለ) በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ፤
(1) ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ዓመታዊ የሽያጭ መጠን ከብር 120,001 እስከ ብር 200,000 መሆን
አለበት፣
(2) ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ዓመታዊ የሽያጭ መጠን ከብር 600,001 እስከ ብር 1,200,000 መሆን
አለበት፣
(3) ከኢንተርፕራይዙ ዓመታዊ የሽያጭ መጠን ውስጥ ኢንተርፕራይዞች ከ 70% በላይ የተገኘው ሽያጭ
ከመንግሥት የገበያ ትስስር ውጪ መሆን አለበት፣
(4) ኢንተርፕራይዙ ለሌሎች ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በንዑስ ኮንትራት ቢያንስ 1 ጊዜ
የገበያ ትስስር የፈጠረ መሆን አለበት፣
(5) ኢንተርፕራይዙ ምርትና አገልግሎቱን ለማስተዋወቅ ቢያንስ ሦስት ዓይነት ውጤታማ
የማስተዋወቂያ ዘዴዎችን መጠቀም አለበት፡፡

4) በትርፋማነት
ሀ) በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች
(1) በዓመቱ ካከናወነው ሽያጭ ቢያንስ 15 በመቶ የትርፍ መጠን መሆን አለበት፣
(2) ሥራውን ለማስፋፋት ያዋለው ተጨማሪ ኢንቨስትመንት እና/ ወይም የቁጠባ መጠን ከተጣራ
ካፒታል ከ 20% በላይ መሆን አለበት፣
ለ) በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች
9
(1) በዓመቱ ካከናወነው ሽያጭ ቢያንስ 15 በመቶ የትርፍ መጠን መሆን አለበት፣
(2) ሥራውን ለማስፋፋት ያዋለው ተጨማሪ ኢንቨስትመንት እና/ ወይም የቁጠባ መጠን ከተጣራ
ካፒታል ከ 20% በላይ መሆን አለበት::

5) የኢንተርፕራይዙ ምርታማነት
ጥቃቅንም ሆነ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፡-
(1) በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ ምርትና ምርታማነቱን ለማሳደግ ካለው ሙሉ
የማምረት አቅም ቢያንስ 80% መጠቀም አለበት፣
(2) ለሚያመርታቸው ምርቶችና ለሚያቀርባቸው አገልግሎቶች ዘመናዊ የሥራ አመራርን የተከተለ
የጥራት ቁጥጥር ሥርዓት የዘረጋ መሆን አለበት፣
(3) ለገቢ ወይም ለወጪ ምርቶች የሚውሉ ግብዓቶችን ወይም ገቢ ምርቶችን የሚተካ ምርት
ማምረት አለበት፣
(4) ከአባላት ወይም ቋሚ ሠራተኞች መካከል ቢያንስ 60% የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ የምስክር
ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው::

6) በተቋማዊ አመራርና አደረጃጀት


ጥቃቅንም ሆነ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፡-
(1) ዘመናዊ የሥራ አመራር ዘይቤ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረ መሆን አለበት፣
(2) ለተሰማራበት ሥራ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ሥራ ላይ ማዋል እና ዓመታዊ ኦዲት ማስደረግ አለበት፣
(3) የማምረቻ ማዕከል አደረጃጃት የምርት ሂደትን የተከተለና ንጽህናው የተጠበቀ መሆን አለበት፣
(4) የአባላትን እና ሰራተኞችን የሥራ ደህንነት ለመጠበቅ የሥራ ልብስ እንዲሁም እንደ ንዑስ ዘርፉ
ዓይነት የሥራ ላይ የደህንነት መሣሪያዎች እና የመሳሰሉት የተሟሉ መሆን አለባቸው፣
(5) ሥራውን ለማስፋፋት የሚያስችል በፅሁፍ የተዘጋጀ የንግድ ዕቅድ ማዘጋጀት አለበት፣
(6) ከሌሎች ኢንተርፕራይዞች ጋር ስለ ቢዝነስ ሥራ ሃሳብ ለመለዋወጥም ይሁን የጋራ እንቅስቃሴዎችን
ለማከናወን የሚያስችል የቢዝነስ ግንኙነት መፍጠር አለበት፣
(7) በልማት ሠራዊት አደረጃጀት የታቀፈና የነቃ ተሳትፎ እያደረገ ያለ መሆን አለበት፣

7) በመንግሥታዊ ድጋፎች አጠቃቀም


ለጥቃቅንም ሆነ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፡-
(1) የሚሰጠውን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ሙሉ ማዕቀፎች ተግባር ላይ አውሎ ተጨባጭ
ለውጥ ያመጣና የአሠራር ተሞክሮውን ለሌሎች የሚያካፍል መሆን አለበት፣
(2) ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም ጋር በትብብርና በኩባንያ ውስጥ ሥልጠና መሣተፍ
አለበት፣
(3) ውዝፍ ብድር የሌለበት መሆን አለበት፣

10
(4) የማምረቻ ማዕከል ተጠቃሚ ከሆነ የኪራይ ውዝፍ ዕዳ የሌለበትና ከማዕከሉ ከመውጣቱ በፊት
አስፈላጊውን የፋይናንስና የማምረቻ ቦታ ቅድመ ዝግጅት ያደረገ መሆን አለበት፣
(5) የተፈጠረለትን የገበያ ትስስር ዕድል በልማታዊ መንገድ የሚጠቀም መሆን አለበት፣

8) በቴክኖሎጂ አጠቃቀም
(ሀ) ኢንተርፕራይዙ ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ለማሻሻል በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና
ተቋማት፣ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶችና ሌሎች የቴክኖሎጂ ተቋማት የሚሰራጩ ተፈላጊና አዋጭ
ቴክኖሎጂዎችን ተጠቃሚ መሆን አለበት፣
(ለ) የምርትና አገልግሎት ጥራትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ወቅታዊና የተሻሻለ አሠራር ተጠቃሚ መሆን
አለበት፣
(ሐ) ኢንተርፕራይዙ ከሚጠቀምባቸው የማምረቻ ወይም አገልግሎት መስጫ መሣሪያዎች ውስጥ ቢያንስ
75% በኢነርጂ ብቻ የሚንቀሳቀስ መሆን አለበት::

9) ግዴታን ስለመወጣት
ሀ) ኢንተርፕራይዙ የሚጠበቅበትን ዓመታዊ የገቢ ግብር መክፈል አለበት፣
ለ) ኢንተርፕራይዙ ዓመታዊ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ዕድሳት ማካሄድ አለበት፣
ሐ) የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ የሚጠበቅባቸው ኢንተርፕራይዞች የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
8. ከመብቃት ወደ ታዳጊ መካከለኛ ደረጃ የሚሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች ሊያሟሉዋቸው የሚገቡ
ዝርዝር መስፈርቶች
1) በሥራ ዕድል ፈጠራ
ሀ) በከተማ ግብርና፣ በባህላዊ ማዕድን ማምረት ሥራ እና በግንባታ ዘርፎች የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ
የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ ከ 30 በላይ ሰዎች መሆን አለበት፣
ለ) በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን
ጨምሮ ከ 30 በላይ ሰዎች መሆን አለበት፣
ሐ) በዓመት ውስጥ በጊዜያዊነት የፈጠረው የሥራ ዕድል በከተማ ግብርና፣ በባህላዊ ማዕድን ማምረት ሥራ
ወይም በግንባታ ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ ከ 8 ሰዎች በላይ፣ በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማራ
ኢንተርፕራይዝ ደግሞ ከ 5 ሰዎች በላይ መሆን አለበት::

2) በካፒታል መጠን
ሀ) በከተማ ግብርና፣ በባህላዊ ማዕድን ማምረት ሥራ፣ በግንባታ ዘርፍ የተሰማራ
ኢንተርፕራይዝ፤
(1) የካፒታል መጠኑ ከብር 1.5 ሚሊየን በላይ መሆን ይኖርበታል::
(2) ኢንተርፕራይዙ በብድር ካገኘው ገንዘብ ለቋሚ ንብረት ያዋለው 70% እና በላይ ወይም ከጠቅላላ
የሃብት መጠን ውስጥ 50% እና በላይ መሆን ይኖርበታል::
ለ) በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ፤

11
(1) የካፒታል መጠኑ ከብር 500,000 በላይ መሆን ይኖርበታል::
(2) ኢንተርፕራይዙ በብድር ካገኘው ገንዘብ ለቋሚ ንብረት ያዋለው ከ 40% በላይ ወይም ከጠቅላላ
የሃብት መጠን ውስጥ 30% እና በላይ መሆን ይኖርበታል::

3) በመንግሥታዊ ድጋፎች አጠቃቀም


ሀ) ወደ ኢንቨስትመንት ለመግባት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቀ መሆን አለበት፣
ለ) የቁጠባ መጠኑን ማሳደግ፣ የተጠና ፕሮጀክት ቀርጾ ማቅረብ እንዲሁም ከንግድና ልማት ባንኮች
ለመበደር የሚያስችል የብድር ዋስትና ያዘጋጀ መሆን አለበት፡፡

4) ግዴታን ስለመወጣት
ሀ) ኢንተርፕራይዙ የሚጠበቅበትን ዓመታዊ የገቢ ግብር መክፈል አለበት፣
ለ) ኢንተርፕራይዙ ዓመታዊ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ዕድሳት ማካሄድ አለበት፣
ሐ) አስፈላጊውን የደረጃና የምርት ጥራት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ያገኘ መሆን አለበት፡፡

9. የኢንተርፕራይዞችን የዕደገት ደረጃ መሠረት ያደረገ የድጋፍ ማዕቀፍ


የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንደ የዕድገት ደረጃቸው ከላይ የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት
ከአንድ የዕድገት ደረጃ ወደ ሌላው የዕድገት ደረጃ መሸጋገር እንደሚችሉ ተገልፆል፡፡ ለሽግግር የሚያበቃቸውም
ዋናው ጉዳይ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ሥትራቴጂ የተመለከቱትን የድጋፍ ማዕቀፎች
ለመተግበር በወጡት የማስፈፀሚያ መመሪያዎች እና ማኑዋሎች መሰረት ድጋፍ ሲደረግላቸው ነው፡፡ በመሆኑም
ኢንተርኘራይዞች የዕድገት ደረጃቸውን መሰረት ያደረገና በሥትራቴጅው ላይ የተቀመጡ የሚከተሉት የድጋፍ
ሁኔታዎች ሊመቻችላቸው ይገባል፡፡

1) በምሥረታ/ጀማሪ ደረጃ የሚሰጥ ድጋፍ


ሀ) መነሻ ካፒታል ማመቻቸት፡-
በቅድሚያ የራሳቸው ቁጠባ እንዲኖራቸው ማበረታታትና የሚፈለገውን ቁጠባ ለቆጠቡ ቅድሚያ
በመስጠት ብድር አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከተለያዩ
የተ/ሙ/ኮሌጆች የተመረቁ ወጣቶች ቤተሰቦቻቸው የቁጠባ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው የማበረታታት ሥራ
ይሰራል፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርኘራይዞች ተደራጅተው ለመስራት ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች
በመንግስት ፕሮጀክቶችና ጥረት ማፍሪያ መስኮች ልማታዊ በሆነ መልኩ እንዲሳተፉና መነሻ ካፒታል
እንዲፈጥሩ መደረግ አለበት፡፡

ለ) ሕጋዊ አቋም እንዲኖራቸው ማድረግ፡ ህጋዊ አደረጃጀት፣ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
እንዲኖራቸው መደገፍ አለባቸው፣
ሐ) የቢዝነስ ሥራ አመራር (የኢንተርፕርነርሽፕና ሂሳብ አያያዝ) ብቃት እንዲኖራቸው ሥልጠና መስጠት፣
የተለያዩ የሂሳብ ማኑዋሎችና ሠነዶች እንዲኖሩዋቸው መደረግ አለበት፣
መ) ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንዲችሉ የክህሎትና የቴክኒክ ሥልጠናዎችን መሠጠት አለበት፣

12
ሠ) የአካባቢ ገበያን በሰፊው እንዲጠቀሙ መደገፍ አለባቸው፡፡

2) በታዳጊ/ መስፋፈት ደረጃ የሚሰጥ ድጋፍ


ሀ) የፋይናንስ ድጋፍ በሚመለከት በገበያ ተወዳዳሪ መሆን እንዲችሉ ተከታታይና ከሥራ ባህሪያቸው ጋር
የሚጣጣም ብድር እንዲቀርብላቸው የማድረግና የወሰዱትን ብድር በአግባቡ ሥራ ላይ እንዲያውሉ
መደረግ አለበት፡፡ ለተበዳሪነት የሚበቃቸው የቢዝነስ ፕላን ዝግጅት እንዲያደርጉ መደገፍ አለባቸው፣
ለ) የክህሎት ማበልፀጊያና የቴክኖሎጅ ድጋፍ በመስጠትና የኢንተርፕራይዞቹን ብቃት በማሳደግ የብቃት
ማረጋገጫ እንዲያገኙ ማድረግ፣ የቢዝነስና ሥራ አመራር ሥልጠና እና የምርትና አገልግሎት ጥራትና
ምርታማነት ሥራ አመራር ክህሎት ድጋፍ እንዲያገኙ መደረግ አለበት፣
ሐ) የክልልና ሀገር አቀፍ ገበያ በሰፊው እንዲጠቀሙ በማድረግ የገበያ ትስስርና የገበያ አቅምን ማሳደጊያ
ድጋፍ መሰጠት አለበት፣
መ) የመሥሪያ እና የመሸጫ ቦታ ማዕከላት በተመጣጣኝ የአገልግሎት ክፍያ እንዲያገኙ የማድረግ፣ በተናጠል
ሊያሟሏቸው የማይችሉ የጋራ መገልገያ አቅርቦቶችን እንዲያገኙ መደገፍ አለባቸው፡፡

3) በመብቃት ደረጃ ለሚገኙ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጡ ድጋፎች


ሀ) ቀጣይነት ያለው የጥራትና ምርታማነት ብቃት ማሳደጊያ ድጋፍ መደረግ አለበት፣
ለ) ገበያን ለማስፋት የሚስችል ድጋፍ፣ በየተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ስታንዳርድ
ተጠቃሚ መደረግ አለባቸው፣
ሐ) የመሳሪያ ሊዝ ተጠቃሚ መደረግ አለባቸው፣
መ) የእውቅና የምስክር ወረቀት እንዲያገኙ መደረግ አለበት፣
ከላይ የተጠቀሱት ዋና ዋና የድጋፍ ዓይነቶች በተሟላ ሁኔታ ተፈጻሚ ለማድረግ በተዘጋጁ የዘርፉ
መመሪያዎችና ማኑዋሎች መሠረት እንደየዕድገት ደረጃቸው በዝርዝር ተግባራዊ ሊሆኑ ይገባል፡፡

ክፍል ሦስት

የፈፃሚ አካላት ተግባር፣ ኃላፊነት እና የክትትልና ግምገማ ሥርዓት


የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ ሽግግር አፈፃፀም መመሪያ ተግባራዊነት ሚና ያላቸው
ዋና ዋና አካላት ከተግባርና ኃላፊነታቸው ጋር እንደሚከተለው ቀርቧል::

10. የፈፃሚ አካላት ተግባርና ኃላፊነት


1) የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር
ሀ) ሀገር አቀፍ ደረጃ የዕድገት ደረጃ መስፈርት የያዘ መመሪያ ያወጣል፤ በየጊዜውም
ያሻሽላል፣
ለ) የኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ መሠረት ያደረጉ ድጋፎችን ውጤታማነት ይገመግማል፣
ሐ) የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል፡፡

2) የፌደራል የከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ

13
ሀ) ኢንተርፕራይዞችን እንደየዕድገት ደረጃቸው የድጋፍ ማዕቀፎች አፈፃፀም መከታተልና በሂደትም
እንዲሻሻል ማድረግ፣
ለ) የድጋፍ ማዕቀፎችን ለማስፈፀም የሚረዱ መመሪያዎች እና ማኑዋሎች አተገባበር ላይ ክትትል
ማድረግና አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት አለበት፣
ሐ) የኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ የተመለከቱ መረጃዎችን የማሰባሰብ፣ የማጠናቀርና የማሰራጨት
ሥራ ያከናውናል፣
መ) በዚህ መመሪያ መሰረት ከየክልሉ የተመረጡ የላቀ አፈጻጸም ያላቸውን ወደ ታዳጊ መካከለኛ የተሸጋገሩ
ኢንተርፕራይዞች ዕውቅና እና የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣
ሠ) ወደ ታዳጊ መካከለኛ የተሸጋገሩ የላቁ ኢንተርፕራይዞች በፌደራል ደረጃ እውቅና እና የምስክር ወረቀት
ይሰጣል፣
ረ) ወደ አነስተኛ ማኑፋክቸሪግ የተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞችን ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንዳስትሪዎች
አጀንሲ ወይም በየደረጃው ላሉ መዋቅሮች ፕሮፋይላቸውን በማስተላለፍ የተሻለ ድጋፍ እንዲያገኙ
ያደርጋል፡፡

3) የክልል ከተማ ልማት እና ቤቶች ቢሮ


ሀ) ይህን መመሪያ መነሻ በማድረግ ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ ማውጣት ተግባራዊነታቸውን
ይከታተላል፣
ለ) በዘርፉ ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች እንደየዕድገት ደረጃቸው የማምረቻና የመሸጫ ቦታ በማዘጋጀት
የክላስተር ልማት ያከናውናል፣ ያስተላልፋል አጠቃቀሙን በመከታተል ያረጋግጣል፡፡

4) የክልል የከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲዎች


ሀ) የኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ አፈጻጸም መመሪያ ላይ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮችና ፈጻሚዎች
ግንዛቤ የስጨብጣሉ፣
ለ) የኢንተርፕራይዞችን የዕድገት ደረጃ አፈፃፀም መከታተልና በየደረጃው ለሚገኘው መዋቅር ድጋፍ
ያደርጋሉ፣
ሐ) የኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ ለመወሰን አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማሰባሰብ ያደራጃሉ፣
መ) በአፈጻጸም መመሪያ መሠረት የኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ ሽግግር ይወስናሉ፣
ሠ) ኢንተርፕራይዞች እንደየዕድገት ደረጃቸው በተቀመጡት የድጋፍ ማዕቀፎች መሠረት መፈፀማቸውን
ይከታተላሉ፤ ይደግፋሉ፣
ረ) ኢንተርፕራይዞች ወደ ታዳጊ መካከለኛ ሲሸጋገሩ እውቅና እና የምስክር ወረቀት ይሰጣሉ፡፡

5) የዞን/ከተማ የከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤቶች


ሀ) የኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ አፈጻጸም መመሪያ ላይ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮችና ፈጻሚዎች
ግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ይሠራሉ፣

14
ለ) የኢንተርፕራይዞችን የዕድገት ደረጃ አፈፃፀም መከታተልና በወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ለሚገኘው
መዋቅር ድጋፍ ያደርጋሉ፣
ሐ) የኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ ለመወሰን አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ያሰባስባሉ፣ ያደራጃሉ፣
መ) ከታዳጊ ወደ መብቃት ለሚሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ የምስክር ወረቀት ይሰጣሉ፡፡
6) የከተማ/ወረዳ/1 ማዕከል የከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤቶች
ሀ) ለኢንተርፕራይዞች እንደየዕድገት ደረጃቸው አስፈላጊ ድጋፎችን ይሰጣሉ፣ ወይም እንዲያገኙ
ያመቻቻሉ፣
ለ) የኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ ለመወሰን አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ያሰባበስባሉ፣ ያደራጃሉ፣
ሐ) ለጀማሪ እና ከጀማሪ ወደ ታዳጊ የእድገት ደረጃ ለሚሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ የምስክር
ወረቀት ይሰጣሉ፡፡

7) የክልል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ/ቢሮ

ሀ) ለኢንተርፕራይዞች እንደየዕድገት ደረጃቸው በመለየት ከኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ጋር


የተያያዙ መረጃዎችን ያሰባስባል፣ ያደራጃል፣ ይህን ለሚያስፈፀመው አካል መረጃውን ይሰጣል፣
ለ) ለኢንተርፕራይዞች እንደየዕድገት ደረጃቸው የተሟላና ለውጤታማነት የሚያበቃ የኢንዱስትሪ
ኤክስቴንሽን አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፣
ሐ) ኢንተርፕራይዞች እንደየዕድገት ደረጃቸው በመለየት እና በማፅደቅ ሂደት ይሳተፋል፣
መ) በኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ መሠረት ተፈላጊ፣ ጥልቀትና ስፋት ያለው ለተወዳዳሪነት የሚያበቃ
ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት ይሰጣል፡፡

8) አነስተኛ የፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት


ሀ) ለኢንተርፕራይዞች እንደየዕድገት ደረጃቸው የፋይናንስ አቅርቦት ድጋፍ ያደርጋል፣
ለ) ኢንተርፕራይዞች እንደየዕድገት ደረጃቸው በመለየት እና በመረጣ ሂደት ከብድር አፈፃፀም እና ከቁጠባ
አኳያ የኢንተርፕራይዞችን መረጃ ያሰባስባል፣ ያደራጃል ይህንንም ለሚያስፈፀመው አካል ይሰጣል፡፡

11. ክትትልና ግምገማ እና ግብረ መልስ


ሀ) በየደረጃው ያሉ ፈፃሚ አካላት የአንድ ዓመት ዝርዝር ዕቅድ የሚያዘጋጁ ሆኖ በዕቅዱ ውስጥ ለዕድገት
ደረጃ ሽግግር የተቀመጡ መስፈርቶች እና የድጋፍ አሰጣጥ ማዕቀፍ መሰረት በማድረግ የተዘጋጁ
የተለያዩ መመሪያዎችና ማኑዋሎች እየተፈፀሙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት
በማካተት እና በየደረጃው በማስፀደቅ ለፌደራል የከተሞች ሥራ ዕድል ጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ
ይልካሉ፣
ለ) በተዘጋጀ ዕቅድ መሰረት የየሩብ ዓመቱ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለፌደራል ኤጀንሲ እንዲደርስ የሚደረግ
ሆኖ የፌደራል ኤጀንሲው አስቀድሞ በሚዘጋጅና በፈፃሚ አካላት እንዲታወቅ በሚደረግ ቼክሊስት
መሰረት ወቅታዊ የመስክ ግምገማዎችን በተጨማሪ በማካሄድ ለተጠናከረ ክትትልና ድጋፍ ግብዓት
የሚሆን መረጃ ይሰበስባል፣
15
ሐ) የየሩብ ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርት በየደረጃው ተዘጋጅቶ በፌደራል ኤጀንሲው በኩል ተጠቃሎ በከተማ
ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር መሪነት እንዲገመገም ይደረጋል:: የግምገማውም ውጤት ግብረመልስ እስከ
ፈፃሚ አካላት የመጨረሻው ታችኛው ዕርከን ድረስ ይሰጣል፣
መ) በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ አማካይኝነት የኢንተርፕራይዞችን የዕድገት ደረጃ
የሚያመላክቱ ዝርዝር መረጃዎች እንዲሰባሰቡና እንዲጠናቀሩ በማድረግ በኢንተርፕራይዞቹ
የመጣውን ለውጥ በመገምገም ምርጥ ተሞክሮዎችን እንዲሰፉ ይደረጋል፡፡

የአፈፃፀም አመልካቾች
በዕድገት ደረጃ ሽግግር በተገኘ ውጤት የሚኖሩ የአፈፃፀም አመልካቾች፦

1) ከጀማሪ/ምስረታ ወደ ታዳጊ/መስፋፋት የዕድገት ደረጃ የተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች ብዛትና የዘርፎች


ዓይነት፣
2) ከታዳጊ/መስፋፋት ወደ መብቃት የዕድገት ደረጃ የተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች ብዛትና የዘርፎች ዓይነት፣
3) ከመብቃት ወደ ታዳጊ መካከለኛ የተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች ብዛትና የዘርፎች ዓይነት፣

ክፍል አራት

መብትና ግዴታ

12. የኢንተርፕራይዙ መብትና ግዴታ


1) መብት
ሀ) በዕድገት ደረጃ አሰጣጥና ሽግግር መመሪያ መሠረት ለደረሰበት የዕድገት ደረጃ መስፈርቱን አሟልቶ
ሲገኝ ሰርቲፊኬት የማግኘት መብት አላቸው፣
ለ) በተሰጠው የዕድገት ደረጃ እውቅና ሰርቲፊኬት መሰረት ኢንተርፕራይዙ ማግኘት የሚገባውን ድጋፍ
በደረጃው የማግኘት መብት አላቸው፣
ሐ) በዕድገት ደረጃ አሰጣጥ ላይ ቅሬታ ካለ የማቅረብ እና ምላሽ የማግኘት መብት አላቸው፡፡

2) ግዴታ
ሀ) ኢንተርፕራይዙ ለዕድገት ደረጃ አሰጣጥ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች በሚመለከተው አካል ሲጠየቅ
ሳይደብቅ በግልጽ የመስጠት ግዴታ አለባቸው፣
ለ) መንግስታዊ ድጋፎችን ለማግኘት ሲወዳደር ወይም ሲጫረት የተሰጠውን የዕድገት ደረጃ ሰርቲፊኬት
ይዞ የመቅረብ ግዴታ አለባቸው፣
ሐ) የእድገት ደረጃ ሽግግር ሲያደርግ በፊት የተሰጠውን የእድገት ደረጃ ሰርቲፊኬት እንዲመልስ ይደረጋል፡፡
13. የፈፃሚ አካላት መብትና ግዴታ
1) የፈጻሚ አካላት መብት
ሀ) የዕድገት ደረጃ ለመስጠት የሚያስችሉ መረጃዎችን ከኢንተርፕራይዙና ከሌሎች አጋዥ ሴክተሮች
መጠየቅና መውሰድ ይችላል፣
ለ) ሰብዓዊና ሙያዊ ክብሩ የመከበር፡፡
16
2) የዘርፉ ፈጻሚ ግዴታ
ሀ) በደረጃ እድገት መስፈርቶች እና በአሰራሩ ዙሪያ ለኢንተርፕራይዞች መረጃ መስጠትና ግንዛቤ
የመፍጠር፣
ለ) ለሚሰጠው የእድገት ደረጃ የሚሰበሰቡ መረጃዎችን የማጥራት፣
ሐ) ኢንተርፕራይዞች በመስፈርቶችና ባቀረቡት መረጃ መሠረት የደረሱበትን የዕድገት ደረጃ ሰርቲፊኬት
የመስጠት፡፡

ክፍል አምስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

14. የእድገት ደረጃ ስለማይሰራላቸው ዘርፎች


መነሻ ካፒታል/ ጥሪት የሚያፈራባቸው የሥራ ዘርፎች ህጋዊ ሆነው ወደ መደበኛ እስካልተሸጋገሩ ድረስ እድገት
ደረጃ አይሰራላቸውም፡፡

15. ስለጀማሪ ኢንተርፕራይዝ


ወደ ዘርፉ የሚቀላቀሉ አዲስ ኢንተርፕራይዞች የያዙትን የሰው ሃይልና የካፒታል መጠን መሰረት በማድረግ
በጥቃቅንና አነስተኛ የኢንተርፕራይዝ ዓይነት ተለይተው ጀማሪ የዕድገት ደረጃ ይሰጣቸዋል፡፡

16. ስለ የእድገት ደረጃ አፈፃጸም


የተቀመጠውን የእድገት ደረጃ መስፈርት በልማታዊ በሆነ መንገድ አሟልተው እስከተገኙ ድረስ የእድገት
ደረጃ ሳይጠብቁ ከአንዱ የእድገት ደረጃ ወደ ሌላው ይሸጋገራሉ፡፡

አንድ ኢንተርፕራይዝ ወደ ታዳጊ መካከለኛ ተሸጋግሮ ከመመረቁ በፊት በየደረጃው ድጋፍ ተደርጎለት በሌሎች
የዕድገት ደረጃዎች ያለፈ መሆን አለበት፡፡

17. ሞዴል መመሪያውን ስለማሻሻል

ይህ ሞዴል መመሪያ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንዲሁም ከአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት


ጋር ለማጣጣም መሰረታዊ ይዘቱን ሳይለቅ እንደ አስፈላጊነቱ በክልሉ/ከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ወይም
በፌዴራል ከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር አማካኝነት ሊሻሻል ይችላል፡፡

18. ሞዴል መመሪያው ስለሚጸናበት ሁኔታ


ይህ ሞዴል መመሪያ ከፀደቀበት ከ------------------ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

ጃንጥራር ዓባይ
የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር

17
18

You might also like