Professional Documents
Culture Documents
Enterpreneurship Amharic-Part 1
Enterpreneurship Amharic-Part 1
/የሥራ ፈጠራ/
August 26, 2022 1
1. ኢንተርኘርነርሽኘ ማለት ምንድን ነው?
• ኢንተርፐርነርሽፕ የሚለው ቃል የተወሰደው ኢንተርፐረንደር ከሚል
ከፈረንሳይ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ‹‹መፈፀም›› ማለት ነው፡፡
• ኢንተርኘሪነርሽኘ ሂደት / Process / ሲሆን አንድ ኢንተርኘርነር ከምንም
ነገር ተነስቶ ዋጋ ያለው ነገር የሚፈጥርበትና የሚገነባበት ሂደት ነው፡፡
• ዋጋ ያለውና ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን ለግለሰቦች፣ ለቡድን፣ ለድርጅት እና
ለህብረተሰብ የመፍጠርና የማሰራጨት ሂደት ነው፡፡
• ኢንተርኘርነርሽኘ አዳዲስ የፈጠራ ግኝቶች/የፈጠራ ስራዎች/ የሚገኙበት
ሂደት ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉ ሃብቶችን እንደገና
በመጠቀም አዲስ ነገሮችን የመፍጠር ወይም
• ያለውን ውስን ሃብት ባልተለመደ ወይም ከወትሮው በተለየ መልኩ
በማቀናጀት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን በመጋፈጥና በመቋቋም ለአዲስ
ፈጠራ የሚነሳሱ ኢንተርኘርነሮች አዲስ የሥራ እንቅስቃሴን የሚፈጥሩበት
ሂደት ነው፡፡
August 26, 2022 2
ኢንተርኘሪነርሽኘ ...
• የፈጠራ ስራ ማለት ደግሞ በስራ ፈጣሪ ሰው የተከናወኑ ተግባራት ማለት
ነው፡፡ ይኸውም በማያቋርጥ የስራ ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን
በፅናት ተቋቁሞ ካፒታልን በተገቢ ጊዜና ሁኔታ ስራ ላይ በማዋል ምርት
በማምረት ወይም አገልግሎት በመስጠት ተጨማሪ ሃብት መፍጠር ነው፡፡
• የፈጠራ ስራ የሚባለዉ በእጅ ያለዉ ሀብት ምቹ ሁኔታዎች በሚፈጥሩት
የሥራ ሂደት ዉስጥ አልፎ ወደ ላቀ ዕድገት ሲሸጋገር ነዉ፡፡
• ሥራ ፈጣሪ ሰዉ ልዩ መሣሪያዉ ሥራ ለመፍጠር ምቹ ሁኔታዎችን
በመጠቀም በነበረዉ ሀብት ላይ እድገት የማምጣት ችሎታ ነዉ፡፡
• ለተጨማሪ ሃብት መገኘት የተፈጠረው ስራ ያስገኘው ዉጤት በአካባቢው
ያልተለመደ አዲስ ምርት ሊሆንም ላይሆንም ይችላል፡፡ ምርቱ አዲስ
ቢሆንም ባይሆንም ደረጃውን የጠበቀ ጥራት ያለው ምርት ሲመረት
የፈጠራ ስራ ውጤት ይሆናል፡፡
ስራ ፈጣሪ ማለት አዲስ ድርጅት የሚመሰርት ወይም የተመሰረተውን ድርጅት ወደ ከፍተኛ
ደረጃ ለማሣደግና ምርታማ ለማድረግ ተነሣሽነት ያለው ለውጥ አምጪ ስራ አስኪያጅ
ነው፡፡
ጠንካራ ጐን ደካማ ጐን
– ከጥናት አድራጊዎች
– ከኢግዚቢሽኖችና ባዛሮች ወ.ዘ.ተ