You are on page 1of 9

የትብብር ስልጠና መመሪያ(ረቂቅ)

መግቢያ

የውጤት ተኮር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና በባህሪው በጣም ትላልቅ እና ውድ ማሽኖችን የሚሹ በመሆኑ
በማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ብቻ ስልጠናውን በመሸፈን ጥራቱን የጠበቀ ስልጠና መስጠት ባለመቻሉ 30%ቱ ሙያ ነክ
ንደፈ ሃሰብ ማስጨበጫ ስልጠና እና የተግባር ስልጠና እጅ ማፍታቻ ልምምድ በማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ
በመስጠት፣70%ቱ ደግሞ የተግባር ስልጠና በልማት ድርጅቶች ውስጥ በትብብር ስልጠና የሚሸፈን ሆኖ የስልጠናውን
ጥራት ለማስጠበቅ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው በመታመኑ፣

በተጨማሪ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስርዓት ዋንኛው ዓላማ ለሁሉም ትኩረት ዘርፎች እና ለልማት ድርጅቶች
በመካካለኛ እና በዝቅተኛ ደረጃ ብቁ የሰው ሃይል ማፍራት ሲሆን የልማት ድርጅቶች ስልጠናው ላይ በመሳተፍ በቂ የሰው
ሃይል በማፍራት ረገድ የራሳቸውን ድርሻ መወጣት አለባቸው፡፡ ከሁሉም በላይ ሰልጣኞች በልማት ድርጅት ውስጥ ሲሰለጥኑ
እውነተኛ የስራ ቦታ በመሆኑ ለስራው የሚያስፈልገው እዉቀት፣ክህሎት እና አመለካከት በቀላሉ ሊቀስሙት የሚችሉበትን
እድል ስለሚፈጥር ተመራጭ ስለሚያድርገው ይህንን ተግባር በተገቢው ለመፈጸም የአሰራር ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ
በመሆኑ ይህንን መመሪያ ማውጣት አስፈልጓል፡፡

ክፍል አንድ
ጠቅላላ
1. አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ 'የፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የትብብር ስልጠና መመሪያ' ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2. ትርጓሜ

1. ‘የትብብር ስልጠና' ማለት ማሰልጠኛ ተቋማትና የልማት ድርጅቶች በትብብር የሚሰጡት የስልጠና ዘዴ ነው፡፡
2. ‘የልማት ድርጅት' ማለት በትብብር ስልጠና ማእቀፍ የሚሳተፍ ምርት ወይም አገልግሎት ለመስጠት በመንግስት፣
መንግስታዊ ባልሆነ አካል ወይም በግል የተቋቋመ ድርጅት ሆኖ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝንም
ይጨምራል፡፡
3. ‘ኤጀንሲ' ማለት የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ ነው፡፡
4. 'ማሰልጠኛ ተቋም' ማለት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና በመስጠት ላይ የተሰማራ በፌዴራል ደረጃ
የሚቋቋም ስልጠና ሰጪ ተቋም ነው፡፡
5. ‘የማሰልጠኛ ውስጥ አሰልጣኝ' ማለት በማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ በማሰልጠን ስራ የተሰማራ ሰው ነው፡፡
6. ‘የልማት ድርጅት ውስጥ አሰልጣኝ' ማለት በልማት ድርጅት ውስጥ የሚሰራ ባለሙያ ተመዝኖ ብቁ በመሆን
የማሰልጠን ስነ ዘዴ ወስዶ በትብብር ስልጠና ሰልጣኞችን የሚያሰለጥን ሰው ነው፡፡

1
7. ‘ሰልጣኝ' ማለት ሙያ ለመቅሰም ወይም ያለውን ችሎታ ለማዳበር ሲል በፌዴራል መንግስት የሚተዳደሩ
ማሰልጠኛ ተቋሞችና በልማት ድርጅቶች ትብብር በሚሰጥ የስልጠና መርሃ ግብር ውስጥ ስልጠና የሚከታተል
ግለሰብ ነው።
8. ‘የሙያ ብቃት ምስክር ወረቀት' ማለት በኤጀንሲው ስም በብቃት ማዕከላት የሚሰጥ ብሄራዊ የምስክር ወረቀት
ሲሆን የሰነዱ ባለቤት በሙያ ብቃት ምዘና ሥርዓት ተመዝኖ ብቃቱ የተረጋገጠ መሆኑን የሚያስረዳ ሰነድ ነው፤
9. ‘የሙያ ደረጃ' ማለት በሥራ ዓለም በሚገኙ ሙያተኞች የሚዘጋጅ የሙያ ደረጃ ሲሆን ሰዎች በሥራ ዓለም
ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ ሊኖራቸው የሚገባውን ብቃት የሚያመለክት ነው፡
10. ‘የሙያ ብቃት ምዘና ማለት በትብብር ስልጠና ወቅት ተገቢውን የሙያ ብቃት ላይ የደረሰ ስለመሆኑ
የማረጋጥ ሂደት ነው፡፡
11. ‘ብቃት አሃድ ማለት የተወሰነ ስራ ለማከናወን ለስራ ቦታ የሚገባውን ክህሎት፣ እውቀት እና አመለካከት
የያዘና መተግበር የሚያስችል ነው ፡፡
12. 'ኢንዱስትሪ' ማለት የሙያ ብቃት ምዘና መስጫ ማዕከል በመሆን ሙያ ብቃት ምዘና ላይ የሚሳተፉ
ምርት ወይም አገልግሎት ለመስጠት በመንግስት ፣መንግስታዊ ባልሆኑ አካል ወይም በግል የተቋቋመ ድርጅት ሆኖ
ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፐራይዞች ይጨምራል፤
13. 'የሥራ አመራር ቦርድ' ማለት በፌዴራል ደረጃ የሚቋቋም ማሰልጠኛ ተቋማት በበላይነት የሚመራ አካል
ነው፤
14. በማንኛውም በወንድ ፆታ የተገለጸው አገላለጽ ሴትንም ይጨምራል፡፡

3. የተፈፃሚነት ወሰን

ይህ መመሪያ በማንኛውም ' የልማት ድርጅት ' እና ' በፌዴራል ደረጃ የተቋቋሙ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና
ማሰልጠኛ ተቋማት' እንዲሁም ሰልጣኞች ላይ ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡

4. ዓላማ
በፌዴራል መንግስት የተቋቋሙ ማስልጠኛ ተቋማት እና በልማት ድርጅቶች ውስጥ የሚካሄደውን ትብብር ስልጠና
በተቀናጀና ጥራቱን በጠበቀ መንገድ እንዲመራ ለማድረግ የአስራር ስርዓት ለመዘርጋት በማስፈለጉ ይህ መመሪያ
ተዘጋጅቷል፡፡
ክፍል ሁለት
የትብብር ስልጠና ስረዓት ሂደት
5. የትብብር ስልጠና ደረጀዎች

2
የትብብር ስልጠና አንዱ የውጤት ተኮር ስልጠና አሰጣጥ ሥነ ዘዴ ሲሆን የሚካሄደው በማስልጠኛ ተቋም እና በልማት
ድርጅት መካከል ነው፤ትብብር ስልጠናን ውጤታማ ለማድረግ የሚከተሉትን ቅድመተከተል ጠብቆ ማስኬድ
ያስፈልጋል፤
1. በማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ የሚሰጡ ሙያና ደረጃ መሠረት ለትብብር ስልጠና የሚሆኑ ልማት ድርጅቶችን
መለየት፣ማጥናት፣መምረጥ፤
2. የትብብር ስልጠና የጋራ እቅድ ማቀድ፤
3. ትብብር ስልጠና ለማከሄድ እና ውጤታማ ለማድረግ በማስልጠኛ ተቋም እና በልማት ድርጅት መካከል መግባቢያ
ስምምነት ሰነድ መፈራረም ፤
4. በተቋም እና በልማት ድርጅት ውስጥ ትብብር ሥልጠና የሚሰጥባቸውን ቦታዎችን ማዘጋጀት፤
5. ስልጠና የሚሰጡ የማሰልጠኛ ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ውስጥ አሰልጣኞችን መመደብ፤
6. በእቅዱ መሠረት ስልጠናውን መስጠት፤
7. የሥልጠናውን ሂደት መከታተል/በትብብር ሥልጠና ቦታዎች ላይ በመገኘት ቁጥጥር ማድረግ፤
8. የሰለጠኑበትን ብቃት አሃድ ወይም ደረጃ ላይ ሙያ ብቃት ምዘና ማከናወን፤
9. የትብብር ስልጠና እና የምዘና ውጤት ሪፖርት ማድረግ፤

6. ለትብብር ስልጠና የሚመረጡ የልማት ድርጅቶች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች


1. ህጋዊ ሰውነት ያለው፤
2. ለማሰልጠኛ ተቋማት ቅርብ የሆነ፤
3. በበቂ ሁኔታ የተደራጀ እና ለስልጠና ምቹ የስራ ቦታ ያለው፤
4. ብቁ የሆኑ የኢነዱስትሪ ውስጥ አሰልጣኞች ያሉት፤
5. ሰልጣኞችን የመቀበል ፍላጎት ያለው፤
6. ስረዓተ ትምህርት ላይ የተዘረዘሩትን መሳሪያዎችን ያሟላ፤
7. ከማሰልጠኛ ተቋማት ጋር የስምምነት ሰነድ መፈራርም የሚችል፤
8. ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ የሆነ፡፡

7. የማስልጠኛ ተቋማት እና የልማት ድረጅቶች የትብብር ስልጠና የጋራ እቅድ


1. የትብብር ሥልጠና ፕሮግራም ከመጀመሩ በፊት የልማት ድረጅቶችና ማስልጠኛ ተቋማት የስልጠናው ሂደት ላይ
የጋራ እቅድ ማቀድ አለባቸው፤
2. የጋራ እቅዱ የሙያ ደረጃና ስርአተ ትምህርት መሰረት ያደረገ መሆን አለበት፤
3. የጋራ እቅዱ ስልጠና የሚሰጥባቸ ሙያዎች፣ደረጃዎች፣ብቃት አሃዶች እና ርሶች እንዲሁም ስልጠናው የሚሰጥበት
ቦታ አሰልጠኝ በግልጽ ለይቶ ማስቀመጥ አለበት፤
4. የመጀመሪያው የጋራ እቅድ ሥራ ስርአተ-ትምህርትን ከኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ጋር የማዘጋጀት ሊሆን ይችላል፤
5. የስልጠና እቅድ በኢንዱሰትሪ ውስጥም ሆነ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ውስጥ ተፈፃሚ ይሆናል፤
3
6. የትብብር ስልጠና እቅድ እንደ አሰፈላጊነቱ በየዓመቱ ሁለት ጊዜ ሊታደስ ይችላል፡፡
8. የትብብር ስልጠና የጋራ ሥምምነት ሰነድ ይዘት
1. የትብብር ስልጠና የጋራ ስምምነት ሰነድ የሚፈረመው በማሰልጠኛ ተቋም እና በልማት ድርጅት መካከል ነው፡፡
2. የስምምነት መግባቢያ ሰነድ መያዝ ያለበት ነጥቦች፡
ሀ. የማሰልጠኛ ተቋሙ እና የልማት ድርጀርቱ ስምና አድራሻ፤
ለ. የትብብር ስልጠናው የሚሰጥበት ሙያዎችና ደረጃዎች፤
ሐ. የሙያው አይነትና የሚፈጀው ጊዜ፤
መ. የስልጠናው ቀንና የሚፈጀው ጊዜ፤
ሠ. የሚሳተፉ ሰልጣኞች ብዛት ፤
ረ. ከስልጠናው የሚጠበቅ ውጤት፤
ሰ. የተፈራራሚዎች ሃላፊነትና ተግባራት፤
ሸ. የበላይ ሃላፊዎች ፊርማ፤
ኀ.የተፈራራሚዎች ቅሬታ አቀራረብ ሂደት
ነ. የክትትልና ግምገማ አግባብነት፡፡
3. የጋራ ስምምነት ሰነድ በየአመቱ የሚታደስ ይሆናል፤

9. በልማት ድርጅት እና በማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ የትብብር ስልጠና ቦታ ማዘጋጀት


1. ለትብብር ስልጠና መደበኛ የሆነ ሁለት ቦታ መዘጋጀት አለበት፣ አንዱ በማሰልጠኛ ተቋማት ሲሆን ሌላኛው በልማት
ድርጅት ውስጥ ይሆናል፣ የትብብር ስልጠናን በአንድ ቦታ ብቻ ማካሄድ አይቻልም፡፡
2. ለትብብር ስልጠና የተመረጡ ቦታዎች የትብብር ስልጠና ስምምነት ሰነድ በተፈራረሙ የበላይ ኃላፊዎች በየጊዜው
መታያት አለበት ፡፡

10. የትብብር ስልጠና አሰልጠኞችን መመደብ


1. ከቴክኒክና ሙያ ትምህረትና ሥልጠና ተቋማት አንድ አሰልጣኝ ለአንድ ለተወሰነ ሙያ በአስተባባሪነት ይመደባል፤
2. ከልማት ድርጅት በሙያው በቂ ልምድ ያለውና ብቁ የሆነ ባለሙያ በኢንዱስትሪው ውስጥ በአሰለልጣኝነት
ይመደባል፤
3. ከኢንዱስትሪ የሚመደበው ባለሙያ ስልጠናው በሚሰጥበት ሙያ ምዘና ወስዶ የብሄራዊ ምስክር ወረቀት ያገኘ
መሆን አለበት፤
4. ከልማት ድረጅትና ከማሰልጠኛ ተቋማት የሚመደቡ አሰልጣኞች በዋናነት የትብብር ስልጠና ሂደትን
ያስተባብራሉ፡፡
11. የማሰልጠኛ ተቋማት እና የልማት ድርጅት ውስጥ የሙያ ብቃት ምዘና ሂደት
1. አሰልጣኞች በሚያወጡት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በትብብር ስልጠና ወቅት የሰልጣኞችን ብቃት ለማረጋገጥ ተቋም
እና የልማት ድርጅት ውስጥ የሙያ ብቃት ምዘና ይካሄዳል፤
4
2. ምዘናው የሚካሄደው በስልጠናው መሃል ከሆነ በንዑሰ ብቃት አሃድ መጨረሻ ወይም ብቃት አሃድ መጨረሻ ላይ
ሊሰጥ ይችላል፣የስልጠና ማጠናቀቂያ ከሆነ ከሁሉም ብቃት አሃዶች የተዘጋጀ ማጠቃለያ ምዘና ሊሆን ይችላል ፡፡

12. የትብብር ስልጠና ሽፋን


1. በማሰልጠኛ ተቋማት የሚሰጡ ሁሉም የስልጠና ፕሮግራሞች፣ደረጃዎች፣ብቃት አሃዶች እና ለትብብር ስልጠና
የተመደበ ሙሉ ሰዓት በትብብር ስልጠና መሸፈን አለበት፤
2. ሁሉም ሰልጣኞች ሙሉ በሙሉ በትብብር ስልጠና መሳተፋቸው ግንዛቤ ውስጥ በማስጋበት የትብብር ስልጠና
ሽፋን ይለካል፤ አለካኩ ኤጀንሲው በሚያወጣ መለኪያ ስታነደርድ መሠረት ይፈጸማል፤

13. የትብብር ስልጠና ጥራት


የትብብር ስልጠና አተገባበር በሶስት ምእራፍ ይከፈላል እነሱም የዝግጅት ምዕራፍ፣ የትግበራ ምዕራፍ እና የማጠቃለያ
ምዕራፍ በመክፈል ይለካል፣አለካኩ ኤጀንሲው በሚያወጣ መለኪያ ስታነደርድ መሠረት ይፈጸማል፤

14. በትብብር ስልጠና ላይ የሚሰተፉ አካላት


1. የማሰልጠኛ ተቋማት
2. የልማት ድርጅቶች
3. ሰልጣኞች
4. የተቋም እና የኢንዱስትሪ ውስጥ አሰልጣኞች

ክፍል ሦሥት
የሚመለከታቸው አካላት ተግባር እና ኃላፊነት

15. የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ተግባር እና ኃላፊነት


1. የትብብር ስልጠናን ጥራት ለማስጠበቅ የሚያስፈልግ መመሪያ፣ስታንዳርድ እና ማኑዋል ያዘጋጃል፤
2. የትብብር ስልጠና ሂደት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ይሰራል፤
3. በፌዴራል ደረጃ ከትኩረት ዘርፍ መስሪያቤቶች እና ከልማት ድርጅቶች ዋና መስሪያቤቶች ጋር የትብብር
ስልጠና የስምምነት ሰነድ ያፈራረማል፤
4. ኢንዱስትሪዎችን የማነቃነቅና የማደራጀት ስራ ይሰራል፤
5. ለትብብር ሥልጠና መሳካት የተለያዩ የዘርፍ መስሪያ ቤቶችን ያስተባብራል፡፡
16. የትኩረት ዘርፍ መስሪያ ቤቶች ተግባር እና ኃላፊነት

5
1. የትብበር ስልጠና ስራን በጋራ ለመስራት ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ጋር
የስምምነት ሰነድ መፈራረም፤
2. የትብበር ስልጠናን ስራ አፈጻጸምን በተመለከተ የጋራ እቅድ ማቀድ፤
3. ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ጋር በመተባባር ለልማት ድርጅቶች ትብብር ስልጠና
ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራት ይኖርበታል፡፡

17. የማሰልጠኛ ተቋማት የሥራ አመራር ቦርድ ተግባር እና ኃላፊነት


1. አከባቢ ባሉ የልማት ደድርጅቶች የትብብር ስልጠና ማእከል እንዲሆኑ የግንዛቤ መስጠት እና የንቅናቄ ስራ
ይሰራሉ፣
18. የማሰልጠኛ ተቋማት ተግባር እና ኃላፊነት
1. ለስልጠናው ሰልጣኞችን መመልመል፤
2. ከልማት ድርጅቶች ጋር በመተባበር የስልጠና ፕሮግራሙን እቅድ ማዘጋጀት ፤
3. በስልጠና ፕሮግራሙ ውሰጥ የሰልጣኞችን አመዳደብ መከታተልና መቆጣጠር፤
4. የትብብር ስልጠናውን ከሰልጣኙ አጠቃላይ የትምህርትና የሥልጠና ፕሮግራም ጋር ማቀናጀት፤
5. የመግባቢያ ሰነድ ከሚመለከተው ኢንዱስትሪ ጋር መፈራረም ይኖርበታል፡፡

19. የማሰልጠኛ ተቋማት አሰልጣኝ ተግባር እና ኃላፊነት


1. በልማት ድርጅቶች ውስጥ የሚካሄዱ ስልጠናዎችን በማደራጀት ሂደት ውስጥ መሳተፍ፤
2. ከልማት ድርጅቶች ውስጥ አሰልጣኞች ጋር በመሆን ስርዓተ ትምህረቱን ማዘጋጀት፤
3. ለሰልጣኞች ስለስልጠናው ማብራርያ መስጠት፤
4. የስልጠና እቅድ ማዘጋጀት እንዲሁም ከስራው ጋር ማቀናጀት፤
5. ሰልጣኞች በልማት ድርጅቶች ውስጥ በስራ ላይ የሚሰማሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤
6. በልማት ድርጅቶች ከሚሰጥ የተግባር ስልጠና በፊት ሰልጣኙ በሙያው የንድፈሃሳብ መሰረታዊ እውቀትና
ብቃት ማጎልበቱን ማረጋገጥ፤
7. የስልጠናው አፈጻጸምና የተገኘውን ውጤት በተመለከተ በልማት ድርጅቶች እና ለቴክኒክና ሙያ ትምህረትና
ስልጠና ተቋም ሪፖርት ማቅረብ፤
20. የልማት ድርጅቶች ተግባርና ኃላፊነት
1. የመግባቢያ ሰነድ ከማሰልጠኛ ተቋም ጋር መፈራረም፤በየአመቱ ማደስ፤
2. የትብብር ስልጠና ከማሰልጠኛ ተቋም ጋር በመሆን በአመት ሁለት ጊዜ የጋራ እቅድ ማዘጋጀት፤
3. የስልጠና እቅዱን መሰረት በማድረግ የስልጠና ቦታዎች እና መገልገያዎችን ማደራጀት ፤
6
4. የትብብር ስልጠና የክትትልና ቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት፤
5. በወጣው እቅድ መሰረት ድርጅቱ ተገቢውን ስልጠና ለሰልጣኞች መሰጠቱን ስልጠናው፤ በተጠናቀቀ በአስር
ቀናት ጊዜ ውስጥ ለማሰልጠኛ ተቋማት በጽሁፍ ማሳወቅ፤እና
6. የኢንዱስትሪ ውስጥ አሰልጣኝ መመደብ ይኖርበታል፡፡

21. የልማት ድርጅቶች ውስጥ አሰልጣኝ ተግባር እና ኃላፊነት


1. በድርጅቶች ውስጥ የሚካሄዱ ስልጠናዎችን በማደራጀት ሂደት ውስጥ መሳተፍ፤
2. ከማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ አሰልጣኞች ጋር በመሆን ስርዓተ ትምህረቱን ማዘጋጀት፤
3. ለሰልጣኞች ስለስልጠናው ማብራርያ መስጠት፤
4. የትብብር ስልጠና እቅድ ማዘጋጀት እና መተግበር፤
5. ሰልጣኞች በልማት ድርጅቶች ውስጥ በስራ ላይ የሚሰማሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤
6. ሰልጣኞችን መከታተል እና የምዘናውን ውጤት መዝግቦ መያዝ፤
7. የስልጠናውን አፈጻጸምና የተገኘውን ውጤት በተመለከተ ለልማት ድርጅቶች እና ማሰልጠኛ ተቋም
ሪፖርት ማቅረብ፤
22. የሰልጣኞች ቤተሰብ ተግባር እና ኃላፊነት
1. በትብበር ስልጠና ወቅት ወላጆች ልጆቻቸውን የመከታተል እና የመምከር ግዴታ አለባቸው፤
23. የሰልጣኝ ተግባር እና ኃላፊነት
1. የስልጠና ፕሮግራሙን ግብ ለማሳካት ተገቢውን የቴክኒክና ሙያ ብቃት ማዳበር፤
2. በስልጠና ፕሮግራሙ ሂደት የሚሰጣቸውን ስራ በጥንቃቄ ማከናወን፤
3. በአሰልጣኝ እና በሌሎች እንዲከታተሏቸው በተመደቡ ሰዎች የሚሰጣቸውን መመሪያ ማክበር፤
4. ስልጠናው በሚካሄድበት ስፍራ (ቅጥር ግቢ) ለተፈቀዱና ለተከለከሉ ጉዳዩች ተገቢውን ግምት በመስጠት
አክብሮ መፈጸም፤
5. መሳሪያዎች፣ማሽኖችንና ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን በጥንቃቄ መጠቀም፤
6. ማንኛውንም የሥራ ሚስጥር መጠበቅ፤
7. በስልጠናው ፕሮግራሙ በወጣው እቅድ መሰረት ስልጠናውንና የብቃት ምዘናውን መውሰድ፤
8. የስልጠናውን ሂደት ከጅምሩ እስከ ፍፃሜ መመዝገብ (maintaning record book)

7
ክፍል አራት
የዲሲፕሊን አፈጻጸምና የቅሬታ አቀራረብ ስነስርአት

24. ዲሲፕሊን
1. ሰልጣኞች በተመለከተ
1.1. ለአንድ አመት ከስልጠና የሚያሳግድ የዲሲፕሊን ግድፈት
ሀ. ማንኛውንም የሥራ ሚስጥር አለመጠበቅ ፣
ለ. በትብብር ስልጠና ቦታ አምባጓሮ መፍጠር፣
ሐ. ሆን ብሎ የመሰልጠኛውን መሳሪያ ለጥፋት የዳረገ ፣የሰረቀና ያሰረቀ

1.2. ከሁለት አመት በላይ ከተመዛኝነት የሚያሳግዱ የዲሲፕሊን ግድፈቶች


በአንቀጽ 24 በንኡስ አንቀጽ 1.1 ላይ የተዘረዘሩትን የዲሲፕሊን ግድፈቶች ተቀጥቶ ጥፋቱን በድጋሚ ከፈጸመ
እንደ ጥፋቱ ክብደት ከሁለት አመት እስከ አምስት አመት ጊዜ ድረስ ለምዘና እንዳይቀርብ ይደረጋል፡፡
2. የልማት ድርጅትን በተመለከተ
የልማት ድረጅቶች ዲሲፐሊን አፈጻጸም ከተቋማት ጋር በተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ መሰረት
የሚፈጸም ይሆናል፡፡
3. አስልጣኞች በተመለከተ
አሰልጣኝ በስልጠና ወቅት በሚፈጽመው የዲሲፕሊን ግድፈት በተመለከተ የመንግስት ሰራተኛ ከሆነ የፌደራል
መንግስት ሰራተኞች የዲሲፕሊን አፈጻጸምና የቅሬታ አቀራረብ ስነስርአት በሚኒስትሮች ምክርቤት ደንብ ቁጥር
77/1994 መሰረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከልማት ድረጅት የመጣ ከሆነ የዲሲፕሊን ግደፈቶች በድርጁቱ
ደንብ፣መመሪያ፣ህብረት ስምምነት እና በውስጥ አሰራር ተጠያቂ ይሆናል፡፡

25. የቅሬታ አቀራረብ

1. በስልጠና ወቅት የሚቀርቡ ማንኛውም ቅሬታ ቅሬታው በተፈጠረ በ 5 ቀናት ውስጥ መቅረብ ያለበት ሆኖ
ቅሬታው የሚስተናገደው የትብብር ስልጣና በሚሰጥበት የልማት ድርጅት ይሆናል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ቅሬታው የቀረበለት የልማት ድርጀት በዚህ
መመሪያ መሰረት በ 5 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ተገቢውን ምላሽ መስጠት አለበት ፡፡
3. ነገርግን የቀረበው ጉዳይ ከአቅሙ በላይ ከሆነና የቀረበው ቅሬታ አግባብነት ያለው ከሆነ ቅሬታውን ወደ
ማሰልጠኛ ተቋም በማቅረብ ጉዳዩን ተከታትሎ የመጨረሻውን ውጤት ለቅሬታ አቅራቢው በ 10 ቀናት ውስጥ
ማሳወቅ አለበት፡፡

8
4. ቅሬታ አቅራቢው በልማት ድረጅቱ የተሰጠው ምላሽ ያላረካው ከሆነ በቀጥታ ለማሰልጠኛ ተቋሙ ማቅረብ
የሚችል ሆኖ ማሰልጠኛ ተቋሙ ቅሬታውን መርምሮ በ 5 ቀን ውስጥ ውሳኔውን ለቅሬታ አቅራቢው ማሳወቅ
ይኖርበታል፡፡
5. በውሳኔው አጥጋቢ መልስ ካላገኘ ቅሬታውን እስከ 10 ቀናት ለስራ አመራር ቦርድ ማቅረብ አለበት፣ ለስራ
አመራር ቦርዱ የቀረበለትን ቅሬታ በ 30 ቀናት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል ፣ ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡

ክፍል አምስት

ልዩልዩ ድንጋጌዎች

26. ስለ መመሪያው ተፈጻሚነት


ይህ መመሪያ በስራ ላይ በሚገኙ የሙያ ብቃት ምዘና ማእከላትም ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡

27. ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች


ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረኑ መመሪያዎች ወይም ልማዳዊ አሰራሮች ተፈጻሚነት አይኖራቸውም፡፡

28. መመሪያ የሚጸናበት ጊዜ


ይህ መመሪያ ከ-----------ዓ.ም ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

You might also like