You are on page 1of 19

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር

የፌዴራል የከተሞች ስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጄንሲ

የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ሞዴል መመሪያ ቁጥር ----/ 2010 ዓ.ም (ተሻሽሎ የቀረበ)

ግንቦት/2010 ዓ.ም

አዲስ አበባ
መግቢያ

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፍ ከግብርና ቀጥሎ ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠር የዜጎችን
ገቢና የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ድህነትን በመቀነስና የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ የማይተካ ሚና ያለው ዘርፍ
በመሆኑ የዘርፉን ልማት ለማስፋፋትና ለማጠናከር የሚያስችሉ የድጋፍ ማዕቀፍ ማስፈፀሚያ
መመሪያዎችን ከወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ፤

ዘርፉን ይበልጥ ምርታማ፣ ተወዳዳሪ ለማድረግና ያሉትን ህጎች አክብሮ የሚንቀሳቀስ ልማታዊ አስተሳሰብ
ለመፍጠር አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ማደራጀት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል:: የአንድ ማዕከል አገልግሎት
መስጫ ጣቢያዎች ኢንተርፕራይዞች ሕጋዊ ሆነው በምርትና አገልግሎት ሥራዎች እንዲሰማሩ
መንግሥታዊ ድጋፎችን በአግባቡ እንዲያገኙና በሌሎች ተቋማትም የሚሰጡትን አገልግሎቶች በተቀናጀ፣
ግልጽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መልክ ከአንድ ሥፍራ ለመስጠት እንዲያስችል በዘርፉ ልማት የመንግስት
መዋቅር የመጨረሻው እርከን ላይ የሚደራጁ በመሆናቸው::

ቀደም ሲል ሲሰራበት የነበረውን የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ የአንድ ማዕከል አገለግሎት
መስጫ ጣቢያዎች አሰራር ከክልል ክልል የተለያየ በመሆኑ ወጥ የሆነ አደረጃጀትና የተቀራረበ አሰራር
እንዲኖር ለማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 374/2008 አንቀጽ 14
መሠረት ይህ ሞዴል መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

ክፍል አንድ
ጠቅላላ

1
1. አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ “የተሻሻለ የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች የአገልግሎት አሰጣጥ ሞዴል መመሪያ
ቁጥር ------ 2010» ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2. ትርጓሜ
1) "የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ" ማለት የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች
ሕጋዊነትን ለማስፈን እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የሚሰጡ
አገልግሎቶች፣ የመንግስታዊ ድጋፎችና አገልግሎቶች በተቀናጀ መልኩ ከአንድ ስፍራ በአንድ
አስተባባሪ አካል ሥር ካሉ አካላት የሚያገኙበት አደረጃጀት ነው፡፡
2) “ከተማ” ማለት ማዘጋጃ ቤት የተቋቋመበት ወይም 2 ሺህ እና ከዚህ በላይ የሕዝብ ቁጥር ያለውና
ከዚህ ውስጥ 50 በመቶ የሚሆነው የሰው ኃይል ከግብርና ውጭ በሆነ ሥራ የተሰማራ ሆኖ
የሚኖርበት አካባቢ ነው፡፡
3) “የከተማ አስተዳደር” ማለት ቻርተር ያላቸው ከተሞችን ሳይጨምር በሌሎች ከተሞች ውስጥ
እንደ ማዘጋጃ ቤት ያለ የከተማ አስተዳደርና አገልግሎት እንዲሰጥ የተቋቋመና ራሱን የቻለ
አስተዳደራዊ አካል ነው፡፡
4) “ጠቅላላ ካፒታል” ማለት ህንጻን ሳይጨምር ከኢንተርፕራይዙ ጠቅላላ የቢዝነስ ሀብት ላይ ዕዳው
ተቀንሶ የሚገኘው ካፒታል ማለት ነው፡፡
5) “ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ” ማለት የኢንተርፕራይዙን ባለቤት፤ የቤተሰብ አባላትና ተቀጣሪ
ሰራተኞችን ጨምሮ እስከ አምስት ሰዎች የሚያሰማራና የተጣራ ካፒታሉ መጠን በአገልግሎት
ዘርፍ ከብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ወይም በማኑፋክቸሪንግ ፣ በከተማ ግብርና ፣ ባሕላዊ ማዕድን
ማምረትና ግንባታ ዘርፍ ከብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ያልበለጠ ኢንተርፕራይዝ ነው:፡
6) “አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ” ማለት የኢንተርፕራይዙን ባለቤት፤ የቤተሰብ አባላትና ተቀጣሪ
ሰራተኞችን ጨምሮ ከስድስት እስከ ሰላሳ ሰዎችን የሚያሰማራና የተጣራ ካፒታሉ መጠን
በአገልግሎት ዘርፍ ከብር 50,001 (ሃምሳ ሺህ አንድ) እስከ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ወይም
በከተማ ግብርና ፣ ባሕላዊ ማዕድን ማምረትና ግንባታ ዘርፍ ከብር 100,001 (አንድ መቶ ሺህ
አንድ) እስከ 1,500,000 (አንድ ሚልዮን አምስት መቶ ሺ) ያልበለጠ ኢንተርፕራይዝ ነው::
7) "የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት" ማለት የኢንተርፕራይዞቹን ችግር የለየና በፍላጎት ላይ
የተመሠረተ የተሟላ መረጃ የማደራጀትና የመስጠት፣ ስልጠናና ድጋፍ፣ የቴክኖሎጂ ልማት፣
ግብይት፣ ምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስተላለፍን የሚያካትት ድጋፍ ነው፡፡
8) “ሞዴል ኢንተርፕራይዝ” ማለት በጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች እና ከማኑፋክቸሪንግ ውጭ የሚገኙ
አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ፕሮግራም ታቅፎ በራስ ጥረትና የተደረገለትን ድጋፍና ግብአት
በመጠቀም ለላቀ ውጤት የበቃና በልማታዊ አመለካከቱ ለሌሎች መሰል ኢንተርፕራይዞች አርአያ
በመሆን በማስፋፋት ስትራቴጂ ላይ ግንባር ቀደም የልማት ሀይል የሆነ ኢንተርፕራይዝ ነው ፡፡
2
9) “ነባር ኢንተርፕራይዝ» ማለት ሕጋዊ ሰውነት ወይም ፈቃድ አግኝተው ወደ ሥራ ከተሰማሩ አንድ
ዓመት እና በላይ የሞላቸው ሲሆኑ ሲቋቋሙ የተሟላ ወይም /በከፊል የድጋፍ አገልግሎት ያገኙ
ወይም ያላገኙ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡
10) «አዲስ ኢንተርፕራይዝ» ማለት በኢንተርፕራይዞች አደረጃጀት መሠረት ሕጋዊ ፈቃድ አግኝተው
ወደ ሥራ ከተሰማራ አንድ ዓመት ያልሞላቸው ሲሆኑ ሲቋቋም የተሟላ ወይም በከፊል የድጋፍ
አገልግሎት ያገኙ ወይም ያላገኙ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡
11) “የምግብ ዋስትና” ማለት መጠን እና ጥራትን ባማከለ መልኩ በዘላቂነት ምግብ በማግኘት
የእያንዳንዱ ግለሰብ የነፍስ ወከፍ የዕለት ፍጆታን እስከ 2,200 ኪሎ ካሎሪ እንዲደርስ እና
የተመጣጠነ የስርዓተ ምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ በማድረግ ጤናማና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ
ማድረግ ነዉ፡፡
12)“ተጠቃሚ” ማለት የመንግስታዊ ድጋፎችንና ህጋዊነት የማስፈን አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደ አንድ
ማእከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች የሚመጡ ስራ ፈላጊ ዜጎች፣
ኢንተርፕራይዞች/አንቀሳቃሾች/ እና የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ተጠቃሚ ዜጎች ናቸው፡፡
13) “ክልል” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 47/1/
የተመለከቱትን ክልሎች ማለት ሲሆን ለዚህ መመሪያ አፈፃፀም ሲባል የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ
ከተማ አስተዳደርንም ይጨምራል፡፡
14) “ቢሮ” ማለት የክልሉ ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ወይም የስራ እድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና
ኤጀንሲ ስራን የሚመሩ ተቋማት ናቸው፡፡
15) “የክልል ኤጀንሲ” ማለት በየክልሉ የተዋቀሩ የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና
ስራዎችን የሚደግፍና የሚያስተባብር አካል ነው::
16) የፌደራል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ” ማለት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና
ሥልጠናን በበላይነት የሚመራ የፌደራል ኤጀንሲ ነው::
17) ”አነስተኛ የፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት” ማለት ለኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ፣ ብድርና ቁጠባ
አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ናቸው::
18) “የአቅም ግንባታ ሥራዎች” ማለት በየደረጃው የሚገኙትን የዘርፉ ልማት ፈፃሚና ባለድርሻ
አካላትን የሰው ኃይል የማስፈፀም አቅም እና በአደረጃጀትና በአሰራር የማጎልበት ስራዎች ናቸው፡፡
19) "የፆታ አጠቃቀም" በዚህ መመሪያ በወንድ ፆታ የተገለፀ ሁሉ ለሴት ፆታም እኩል የሚያገለግል
ይሆናል፡፡

3. የተፈፃሚነት ወሰን

3
ይህ ሞድል መመሪያ በኢትዮጵያ ከተሞች በሚገኙ የከተማ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ላይ
ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

4. ዓላማ

የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማትና እድገት እንዲሁም


የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን ግልጽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ
መንገድ ከአንድ ስፍራ ወይም ማዕከል ለመስጠት ነው፡፡

5. መርሆዎች
1) የስራ ፈላጊዎች ምዝገባ እና መረጃ አያያዝ ለዘርፉ ልማት ዋነኛ ግብዓት እንዲሆኑ ማድረግ፣
2) ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጡ አገልግሎቶች ተደራሽነትን ማረጋገጥ፤
3) ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጡ አገልግሎቶች በተቀናጀና በተደራጀ አግባብ ወጪ ቆጣቢ በሆነ
መልኩ እንዲሰጡ ማድረግ፤
4) የማዕከሉ ሠራተኞች የስነ-ምግባር መርሆዎችን የተላበሱና ለሚሰጡትም አገልግሎት ኃላፊነትና
ተጠያቂነት አለባቸው፣
5) የሚሰጡ አገልግሎቶች የኢንተርፕራይዞችን ፍላጎት እና የእድገት ደረጃ መሠረት ያደረጉ
ይሆናሉ፤
6) የሴቶች፣ የወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች እኩል እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ
ይሆናል፤
7) የሚሰጡ የመንግስት አገልግሎቶች ለማን፣ መቼ፣ እንዴት እንደሚሰጥ ግልፅ ይደረጋል፤

ክፍል ሁለት

በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች የሚሰጡ አግልግሎቶች


የስራ ዕድል ለመፍጠርና ኢንተርፕራይዞችን ለማልማት በማዕከላቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች በዋናነት
በሁለት የሚከፈሉ ሲሆን እነሱም ህጋዊነት ማስፈንና መንግስታዊ ድጋፎችን የማመቻቸት አገልግሎት
ናቸው፡፡

6. የስራ ፈላዎች ልየታ፣ምዝገባ እና አደረጃጀት አገልግሎቶች


በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ለመሰማራት የሚፈልጉ ስራ ፈላጊ
የህብረተሰብ ክፍሎችን በተለያዩ የአደረጃጀት አማራጮች መዝግቦ ወደ ሥራ ለማስገባት በተገልጋዮች
ፍላጎት መነሻነት የንግድ ሕጉንና ማኑዋሉን መሠረት በማድረግ አገልግሎቱ ይሰጣል፡፡ በመሆኑም ዝርዝር
የአሰራር ሂደቱን በከተማ የስራ ዕድል ፈጠራ አፈፃፀም ማኑዋል ላይ ተቀምጧል፡፡
4
7. ህጋዊነትን ለማስፈን የሚሰጡ አገልግሎቶች
ሀ) በጥቃቅንና አነስተኛ የስራ መስኮች ለመሰማራት የሚፈልጉ እና የመስራት አቅም ያላቸው
እንዲሁም ዕድሚያቸው ከ 18-60 ዓመት የሆኑ ስራ ፈላጊ ዜጎችን መመዝገብ፤
ለ) በአካባቢው በስራ ፈላጊነት የተመዘገቡ ወጣቶች፣ ሴቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች መረጃ
መነሻ በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ማመቻቸት፤
ሐ) ስለ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ዓላማና ጠቀሜታ እንዲሁም ስለአደረጃጀት
አስፈላጊነትና የአደረጃጀት አማራጮች ግንዛቤ ማስጨበጫ የሚሆን ሰፊና ተከታታይ ትምህርት
መስጠት፤
መ) በዘርፉ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ዜጎች ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችል አጫጭር የአመለካከትና
የክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ፤
ሠ) የተጠቃሚዎችን የመደራጀት ጥያቄ ተቀብሎ የመመልመልና በ 1952 ዓ.ም የወጣውን
የኢትዮጵያ ንግድ ሕግ እና የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 686/2002 መሠረት በማድረግ
በግል የንግድ ድርጅት፣ በህብረት ሽርክና ማህበር እና በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
የማደራጀት አገልግሎት መስጠት፤
ረ) የንግድ ማሕበራት መተዳደሪያ ደንብ እና መመስረቻ ፅሁፎችን ማፅደቅ፤
ሰ) የንግድ ዋና ምዝገባ እና የንግድ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት፤
ሸ) የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር መስጠት፤
ቀ) የንግድ ማህበር ስም ስያሜ ምዝገባ አገልግሎት መስጠት፤
በ) የንግድ ሥራ ምዝገባና ፈቃድ ለውጥ የመስጠት አገልግሎት፤
ተ) የንግድ ሥራ ፈቃድ የማደስ አገልግሎት፤
ቸ) የጠፋ ወይም የተበላሸ ንግድ ምዝገባና ፈቃድ ምትክ የመስጠት አገልግሎት፤
ኀ) የዋና ምዝገባ ስረዛ አገልግሎት፤
ነ) የአንድ ማዕከል አገልግሎት መረጃዎችን በዳታ ቤዝ መዝግቦ በመያዝ ለከተማው የስራ ዕድል ፈጠራ
እና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት የማስተላላፍ አገልግሎቶች ናቸው፡

8. መንግስታዊ ድጋፎችና አገልግሎቶች


1) የመረጃ እና ምክር አገልግሎት
ሀ) ለኢንተርፕራይዞች የሚያስፈልጉ የጥሬ ዕቃ፣ የገበያ፣ የቴክኖሎጂ፣ የብድርና የሥልጠና
መረጃዎች አጠናቅሮ መያዝ እና ለሚመለከታቸውና ለሚጠይቁ አካላት ማስራጨት፤
ለ) በዘርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ ዜጎች ባሉ የስራ ዕድል መፍጠሪያ አማራጮች፤ ስለህጋዊነት
ማስፈን እና መንግስታዊ ድጋፍ አሰጣጥ ሂደቶች መረጃ እና ምክር መስጠት፤
5
ሐ) በከተማ የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ለማረጋገጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ለህብረተሰቡና
ለተጠቃሚ ዜ ጎች የመረጃና ምክር አገልግሎት ይሰጣል፤
መ) በማዕከሉ የስራ ክልል ውስጥ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞችን መረጃ በየአይነቱ በአግባቡ ማደራጀት
እና ለሚመለከተው አካል ማስተላለፍ፤
2) የማምረቻና የመሸጫ ሼዶችና ማዕከላትን ማመቻቸት
ሀ) ለኢንተርፕራይዞች የሚያስፈልጉ የማምረቻና የመሸጫ ቦታ ፍላጎት በሥራ ዘርፍ በመለየት
እያደራጀ ለዘርፍ ሀላፊው ወይም ለጽ/ቤት ሀላፊው ያቀርባል፤
ለ) የኢንተርፕራይዞችን የማምረቻና መሸጫ ቦታ ፍላጎት መሠረት በማድረግ ቅድሚያ ማግኘት
ያለባቸውን ኢንተርፕራይዞች ለይቶ ለከተማው የዘርፉ ልማት ጽ/ቤት ማቅረብና በከተማው
የዘርፉ ልማት ምክር ቤት መፅደቁን መከታተል፤
ሐ) ለኢንተርፕራይዞች ማምረቻና መሸጫ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን ከከተማው አስተዳደር
በመረከብ ለዚሁ አፈፃፀም በወጣው መመሪያ መሠረት ውል ይዞ መደልደል፤
መ) ኢንተርፕራይዞች በማምረቻና መሸጫ ማዕከላት ቆይታ ጊዜያቸው የሚሰጣቸውን ድጋፎች
በአግባቡ ተጠቅመው እንዲበቁ ተከታታይና የተቀናጀ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
ሠ) በማምረቻና መሸጫ ክላስተር ማዕከላቱ ውስጥ ያሉ ኢንተርፕራይዞች ከማዕከላቱ ጋር በተያያዘ
የሚያጋጥሟቸውን የመሠረተ ልማት፣ የጥገና፣ የጽዳትና የጥበቃ ችግሮች በወቅቱ እንዲፈቱ
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አስፈላጊውን ግንኙነት ማድረግ፤
ረ) በማምረቻና የመሸጫ ማዕከላት ውስጥ ያሉ ኢንተርፕራይዞች በገቡት ውል መሠረት
በማዕከላቱ እየተጠቀሙና ወቅታዊ ግዴታቸውን እየተወጡ ስለመሆናቸው በመከታተል፣
የኪራይ ክፍያዎች በየወሩ ለከተማው ገቢዎች ጽ/ቤት ገቢ መሆኑን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
ሰ) የማምረቻና የመሸጫ ቦታ ተረክበው በአግባቡ በማይጠቀሙ ኢንተርፕራይዞች ላይ
በመመሪያው መሠረት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፤
ሸ) በማምረቻና መሸጫ ቦታ የመቆያ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ኢንተርፕራይዞች በወቅቱ
መልቀቃቸውንና ቦታው በወቅቱ ለሚመለከተው ተጠቃሚ መተላለፉን መከታተል፡፡

3) የአነስተኛ ፋይናንስ አቅርቦት ድጋፍ አገልግሎት

ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አቅርቦት ተጠቃሚ ከመሆናቸው በፊት የቁጠባና ሂሳብ አያያዝ ባህላቸውን
ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን በቅድመ ብድርና ድህረ ብድር የተቀናጁና የሚደጋገፉ ተግባራት በማከናወን
ኢንተርፕራይዞች የሚቀርብላቸውን ፋይናንስ ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም ያስችላቸዋል፡፡ በመሆኑም
በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የሚከተሉት የቅድመ ብድርና የድህረ ብድር ተግባራት እንደ
የኢንተርፕራይዞቹ የዕድገት ደረጃ ይከናወናሉ፡፡
6
ሀ) የቁጠባ አገልግሎት

(1) በአካባቢው ባለው ህብረተሰብ ዘንድ የቁጠባ ጥቅም በዝርዝር በማሳየት የቁጠባ ባህልን ሊያዳብሩ
የሚችሉ ተግባራትን በማመላከት በዕድሮች፣ በገበያ ቦታዎች ፣ በትምህርት ተቋማት፣ በእምነት
ቦታዎች በወጣቶች ማዕከላት፣ በሴቶችና በወጣቶች ማህበራት እና ሰዎች በብዛት
በሚሰበሰብባቸው በበዓላት ቀናት ተከታታይነት ያለው ግንዛቤ ማስጨበጥ፤
(2) የኢንተርፕራይዞችን የቁጠባ ግንዛቤ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ተከታታይነት ያለው ትምህርት
መስጠት፤
(3) ቅድመ ብድር ቁጠባ ለመቆጠብ አቅም የሌላቸው ኢንተርፕራይዞች በጥሪት ማፍሪያ ፕሮጀክቶች
እና በምግብ ዋስትና ፕሮግራም በህብረተሰብ ተሳትፎ ስራዎች ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ
ከሚያገኙት ገቢ እንዲቆጥቡ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ ፡፡

ለ) የብድር አገልግሎት ማመቻቸት


(1) በአነስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋም የብድር መጠየቂያ ቅጽ መሠረት የብድር ጥያቄው
በኢንተርፕራይዙ እንዲቀርብ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
(2) የብድርና ቁጠባ አጠቃቀም ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠትና ምቹ የስራ ቦታና ዝግጁነት ያለው
መሆኑን ማረጋገጥ፤
(3) በተዘጋጀው የመመልመያ መስፈርት መሰረት የተበዳሪዎችን ምልመላ ማከናወን፤
(4) ተበዳሪዎች በሚሰማሩበት የስራ መስክ ላይ አዋጪ የንግድ ስራ ዕቅድ እንዲያዘጋጁ አስፈላጊው
ሙያዊ ድጋፍ መስጠት፤
(5) የተዘጋጀውን የንግድ ስራ ዕቅድ በአግባቡ የተዘጋጀ መሆኑን በአነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ተወካይ
ባለሙያ በአግባቡ እንዲሰራ ያግዛል፤
(6) የንግድ ስራ እቅዱ የትርፍና ኪሳራ፣ የሀብትና ዕዳ መግለጫ፣ የገንዘብ ፍሰት መግለጫ ማስተካከያ
የሚያስፈልገው ሆኖ ሲገኝ ኢንተፕራይዙ ማስተካከያ እንዲያደርግ ድጋፍ ይሰጠዋል፤
(7) የተስተካከለውን የንግድ ሥራ ዕቅድ መሰረት በማድረግ የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም ተወካይ ሠራተኛ
ኢንተርፕራይዙ ሊበደር የሚችለውን የገንዘብ መጠንና የራሱን አስተያየት በማካተት በአቅራቢያው
ላለው የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም ጽ/ቤት የስራ ዕቅዱን ገምግሞ ብድሩን ለማጽደቅ የሚያስችሉ
ሰነዶችን አሟልቶ በአንድ ማዕከል ማህተም አስደግፎ ለአነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ጽ/ቤት በሸኝ
ደብዳቤ እንዲላክ ይደረጋል፤
(8) ብድሩ በየደረጃው ከጸደቀ በኋላ ኢንተርፕራይዙ ወደ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ጽ/ቤት በአካል
በመቅረብና አስፈላጊውን ውል በመፈጸም ብድሩን እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡

7
(9) ተበዳሪዎች የወሰዱትን የገንዘብ መጠን፣ ብድሩን የሚመልሱበት የጊዜ ሠሌዳ፣ ብድሩ ተከፍሎ
የሚጠናቀቅበት ጊዜ የሚያሳይ መረጃ ለተበዳሪው በግልጽ በማሳወቅ በአንድ ማዕከል አገልግሎት
መስጫ ጣቢያ ተጠናቅሮ እንዲያዝ ይደረጋል፡፡
(10) በአንድ አንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ለተደራጁ የብድር ዋስትና ፈንድ ተጠቃሚ
ለሚሆኑ ኢንተርፕራይዞች በአበዳሪ ተቋሙ የተፈቀደላቸውን የብድር መጠን እና የዕድገት
ደረጃቸውን ታሳቢ በማድረግ ከብድር ዋስትና ፈንዱ የብድር ዋስትና ሽፋን እንዲያገኙ ለአበዳሪው
የፋይናንስ ተቋም ያሳውቃሉ::

(ሐ) የድህረ ብድር ተግባራት


ሀ) በፀደቀው ቢዝነስ ፕላን መሰረት ኢንተርፕራይዞች የወሰዱትን ብድር ላቀዱት ዓላማ ማዋል
እንዲችሉ በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ባለሙያ አማካይነት ተከታታይነት ያለው
ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
ለ) ኢንተርፕራይዞች የወሰዱትን ብድር በገቡት ውል መሠረት እየከፈሉ መሆናቸውን ክትትል እና ድጋፍ
ማድረግ፤
ሐ) ኢንተርፕራይዞች የወሰዱትን ብድር ውጤታማ በሆነ መንገድ ተጠቅመው በገበያ ተወዳዳሪ
እንዲሆኑ ከብድሩ አገልግሎት በተቀናጀ ሁኔታ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት እንዲያገኙ
ማድረግ፤
መ) የወሰዱትን ብድር በንግድ ዕቅዱ መሠረት ተግባራዊ ያላደረጉና በዉላቸው መሠረት መመለስ
ያልቻሉ ኢንተርፕራይዞች ካሉ በወቅቱ ለብድር አቅራቢ ተቋም በማሳወቅ አስፈላጊው የእርምት
እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፤
ሠ) ተደጋጋሚ ብድር ወስደው ውጤታማ በሆነ መንገድ ተጠቅመው ብድሩን የመለሱና
ኢንተርፕራይዛቸውን ያሳደጉ ኢንተርፕራይዞችን የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም በአካባቢው
ህብረተሰብ ዘንድ ታዋቂነትና ተቀባይነት እንዲያገኙ ማድረግ፤
ረ) ውዝፍ ዕዳ እንዳይከሰት ከመከላከል ጀምሮ የተወዘፈንና በብድር ዋስትና ፈንድ የተሸፈነ ብድርን
ከሚመለከታቸው ፈጻሚና ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ማስመለስ፤
ሰ) ብድር ወስደው አላግባብ ያባከኑና ያልመለሱ ኢንተርፕራይዞች ህብረተሰቡ እንዲያውቃቸው
በማድረግ ብድር እንዲመልሱ ጫና ከማድረግ በተጨማሪ ይህ ተግባር ሥነ ምግባር የጎደለው
መሆኑን ህብረተሰቡ እንዲገነዘብ ማድረግ፡፡

4) የገበያ ማመቻቸት አገልግሎት


ሀ) በከተሞችና በገጠር አካባቢዎች ያሉ በተለያዩ ዘርፎች የተለዩ የአካባቢ የገበያ ዕድሎችን ጥቃቅን እና አነስተኛ
ኢንተርፕራይዞች መረጃውን እንዲያገኙና እንዲጠቀሙ ማድረግ፤

8
ለ) በአካባቢ ባሉ የገበያ ዕድሎች አጠቃቀምን በተመለከተ ኢንተርፕራይዞች በዋጋ፣ በጥራት እና በአቅርቦት ተወዳዳሪ
ከመሆን አንፃር ያሉባቸውን ችግሮች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት መፍታት፤
ሐ) የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚፈልጓቸውን ምርትና አገልግሎቶች የግዥ ፍላጎቶች እያደራጀ
ለኢንተርፕራይዞች መረጃውን በመስጠት የማገናኘት ሥራ በማከናወን ኢንተርፕራይዞች የተለያዩ የሽያጭ
ዘዴዎችን እንዲጠቀሙ ማበረታታት፤
መ) የአካባቢ ጥሬ ዕቃን መሠረት ያደረጉ፣ ተወዳዳሪነትን የሚያረጋግጡና የእሴት ሰንሰለትን ማዕከል በማድረግ የተለዩ
ምርቶችን በአካባቢው ህብረተሰብ እንዲታወቁ ማድረግ፤
ሠ) ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚያመርቷቸውን ምርቶች በከተሞች በሚደራጁ የገበያ ማዕከላት እንዲሸጡ
ማድረግ፤
ረ) ኢንተርፕራይዞች በስፋት የሚጠቀሟቸውን ጥሬ ዕቃዎች ከኢንተርፕራይዞቹ መረጃውን በማሰባሰብና በማደራጀት
በጋራ ጥሬ ዕቃዎችን መግዛት እንዲችሉ ማመቻቸት፤
ሰ) የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ምርቶችና አገልግሎቶች በማስተዋወቅ የገበያ ዕድል እንዲያገኙ በየደረጃው
በሚዘጋጁ የንግድ ትርኢትና ባዛር እንዲሁም በምርት ማሳያና መሸጫ ሱቆች ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ
ኢንተርፕራይዞችን መረጃ መለየት እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፤

5) የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ስርዓት ዝርጋታ እና የኦዲት/የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት


ሀ) ኢንተርፕራይዞች መሰረታዊ የሂሳብ አያያዝ ሥልጠና በማኑዋሉ መሠረት እንዲያገኙ
ማመቻቸት፤
ለ) ኢንተርፕራይዞች መሰረታዊ የሂሳብ መዛግብት እንዲያማሉ ድጋፍ መስጠት፤
ሐ) ኢንተርፕራይዞች የሂሳብ መዝገብ መያዛቸውን ማረጋገጥና መዝገብ የማይዙትንም የሂሳብ
መዝገብ መያዝ ጥቅምን በማስረዳት እና የተግባር ድጋፍ በማድረግ የሂሳብ አያያዝ ስርዓት
እንዲዘረጉ ማበረታታት፤
መ) በአነስተኛ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት የጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንተርፕራይዞችን ወጪና ገቢያቸውን፣ ዓመታዊ ትርፋቸውን፣ የሀብትና ዕዳ መግለጫቸውን
እንዲያውቁና ከአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፤
ሠ) ሂሳባቸውን ማስመርመር የሚፈልጉ ኢንተርፕራይዞችን በመለየት የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት
እንዲያገኙ ማመቻቸት፤

9
6) የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ እና ማስፋት
ሀ) የሞዴል ኢንተርፕራይዞች በመስፈርቱ መሠረት በመለየት ምርጥ ተሞክሯቸውን መቀመር እና
ማስፋት፣
ለ) በየደረጃው በሚገኙ የዘርፉ ልማት መዋቅርና በሚመለከታቸው ተቋማት ከድረ-ገጽ፣ በዘጋቢ
ፊልምና በጽሑፍ ተዘጋጅተው የሚተላለፉትን ምርጥ ተሞክሮ እና ልምዶችን
ለኢንተርፕራይዞቹ ማስፋት፤
ሐ) የምግብ ዋስትና ተጠቃሚ የሆኑና የተሻለ ምርጥ ተሞክሮ ያላቸውን መቀመርና ማስፋፋት፡፡

7) የእድገት ደረጃና ሽግግር አገልግሎት


ሀ) የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ አፈጻጸም መመሪያ ላይ በየደረጃው ለሚገኙ
አመራሮችና ፈጻሚዎች ግንዛቤ ማስጨበጥ፣
ለ) የኢንተርፕራይዞችን የዕድገት ደረጃ አፈፃፀም መከታተልና በየደረጃው ለሚገኘው መዋቅር ድጋፍ
ማድረግ፣
ሐ) የኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ ለመወሰን አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ማሰባሰብና
ማደራጀት፣
መ) ኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ አፈጻጸም መመሪያ መሠረት ከታዳጊ እስከ መብቃት የዕድገት
ደረጃዎች የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ ሽግግር መወሰን፣
ሠ) ኢንተርፕራይዞች እንደየዕድገት ደረጃቸው የተቀመጡትን የድጋፍ ማዕቀፎች መሰረት
መፈፀማቸውን መከታተልና ድጋፍ ማድረግ፣

9. በከተሞች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች


1) የሰፈር/የመንደር ልማት ኮሚቴ፣ የመንደርና ቀጠና ምግብ ዋስትና ኮሚቴ እና የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማደራጀት፤
2) ስለ ከተሞች የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ግንዛቤ መፍጠር፤
3) በኮሚቴው አማካኝነት ተጠቃሚ ቤተሰቦች እንዲመለመሉና እንዲመዘገቡ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
4) የተጠቃሚ ቤተሰቦች መረጃ በአግባቡ መያዝ፣ ለሚመለከተው አካል ማስተላለፍ፤
5) ለተጠቃሚ ቤተሰቦች ቅሬታ ወቅታዊ ምላሽ መስጠት፣ ከአቅም በላይ የሆኑትን ለሚመለከተው አካል
ማስተላለፍ፤
6) ተዘዋዋሪ ለሆኑ ተጠቃሚ ቤተሰቦች በቋሚነት በፕሮግራሙ የሚታቀፉበትን ሁኔታ ማመቻቻት፤
7) በተጠቃሚ ቤተሰቦች ልየታ አፈጻጸም ዙሪያ የጋራ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
8) ተጠቃሚዎች ለምረቃ መብቃታቸውን በማረጋገጥ የሽግግር ስራ ማከናወን፤

10
9) በአካባቢ ልማት ስራዎች ተጠቃሚ የሆኑ ዜጎች ከሚያገኙት ገቢ ቆጥበው ወደ መደበኛ የስራ ዕድል ለመሻገር
እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ መደገፍ፣

ክፍል ሶስት
የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የቦታ አመራረጥ፣ አደረጃጀትና የሰው ኃይል

10. የቦታ አመራረጥ

የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅራቢያ ሆኖ ሁለገብ
ድጋፎች መስጠት በሚያስችል ሁኔታ መደራጀት ስለሚኖርበት የቦታ መረጣ ትልቅ ግምት ሊሰጠው
ይገባል፡፡ በመሆኑም፡-

1) የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች በአካባቢው ላሉት ለአገልግሎት ፈላጊዎች አማካይ
ቦታ መሆን አለበት፤
2) ተደራሽነት ያለው መሆን አለበት፤
3) ከሌሎች ደጋፊና ፈጻሚ አካላት የተቀራረበ መሆን አለበት፤
4) የመሥሪያና የመሸጫ ክላስተሮችን ለመከታተልና በቅርበት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል
መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት መመረጥ ይኖርበታል፡፡

11. የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ አደረጃጀት

1) የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ እንደ ክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ በከተሞች አስተዳደር
የመጨረሻው የመንግስት አወቃቀር እርከን ላይ ማለትም በቀበሌ ደረጃ ይደራጃል፡፡
2) በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ከ 15 ሺህ በላይ ህዝብ ቁጥር በሚኖርበት ሁኔታ
ከተሞች ከአንድ በላይ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ማቋቋም ይኖርባቸዋል፡፡
3) የመንግስት ግዙፍ ፕሮጀክቶች በሚገኙበት አካባቢ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ
ይደራጃል፡፡
4) ከ 1-3 ተራ ቁጥር የተጠቀሰውን ታሳቢ በማድረግ የክልል መንግስት ተጨማሪ የአንድ ማዕከል
አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ሊያደራጅ ይችላል፡፡
5) የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ለከተማ የስራ ዕድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ስራን
የሚመሩ ተቋማት ተጠሪ ይሆናል፡፡

11
12. የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የሰው ኃይል

በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች የሚሰጡ አገልግሎቶችንና የሰው ኃይሉን በማስተባባር
በብቃት መምራት የሚችል አንድ አስተባባሪ ይመደባል፡፡

1) የሰው ኃይል አመዳደቡ የስራውን ስፋትና የሙያው ዓይነት የሚጠይቀውን የሠው ኃይል መሰረት
ያደረገ መሆን አለበት፡፡ ይህም በየክልሎቹ ከተሰራው የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ጥናት ጋር
በማጣጣም የሚፈጸም ይሆናል፡፡
2) ከአንድ ማዕከል አገልግሎት ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራ የአነስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋም ባለሙያ፣
ከንግድና ግብይት ልማት ጽ/ቤት፣ ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም፣ ከገቢዎች ፅ/ቤት እና
ከፍትህ ተቋም ይመደባል፡፡
3) የሰው ኃይል ስብጥርና ብዛት እንደጣቢያው የሥራ ስፋት፣ የተገልጋዩ ብዛት እና እንደ ከተሞች ደረጃ
በየክልሎች የሚወሰን ሆኖ እንደ መነሻ በተራ ቁጥር 6 ላይ በተጠቀሰው መልኩ የሚወሰድ ይሆናል፤
4) በእያንዳንዱ የሥራ መደብ የሚመደብ ባለሙያ ሥራ ከመጀመሩ በፊት በጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ፣ በከተማ ምግብ ዋስትና ስትራቴጅና የስትራቴጅዎቹ
ማስፈፀሚያ መመሪያዎችና ማኑዋሎች ላይ ሥልጠና መውሰድ ይኖርበታል፡፡
5) በመንግስት የልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችም አጠቃላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች
ሊወስድ ይገባል፡፡
6) በአንድ ማዕከል የሚከናወኑ ተግባራትን ከግምት በማስገባትና የአንድ ማዕከል አገልግሎትን
ተደራሽነት ከማረጋገጥ አንፃር በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የሚሰጡ አገልግሎቶችን
መሰረት ያደረገ አስተባባሪዎችንና የቢሮ ረዳቶችን ጨምሮ 14 ሠራተኞች የሚስፈልጉ ሲሆን
የምግብ ዋስትና በተጀመረባቸው አካባቢዎች ተጨማሪ 2 ባለሙያ ያስፈልጋሉ፡፡ እነዚህም
ሰራተኞች በሚከተሉት የሙያ ዘርፍ የተካተቱ መሆን አለባቸው፡፡

የስራ መደብ የሰው ኃይል ብዛት


ሀ) የአንድ ማዕከል አስተባባሪ-----------------------------------------------------------------------1
ለ) መረጃ ዴስክ /የጽህፈት አገልግሎትና የቢሮ አስተዳደር-------------------------------------1
ሐ) የስራ ፈላጊዎች ምዝገባ ኦፊሰር----------------------------------------------------------------1
መ) የኢንተርፕራይዞች አደራጃጀትና ህጋዊነት የማስፈን ኦፊሰር------------------------------2
ሠ) የስልጠናና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አመቻች ባለሙያ----------------------1
ረ) የቁጠባና ብድር አመቻች ኦፊሰር---------------------------------------------------------------1
ሰ) የማምረቻና መሽጫ ቦታ ኪራይ አመቻች እና የመሠረተ ልማት ክትትል ኦፊሰር-----1

12
ሸ) የገበያ ትስስር ድጋፍ ኦፊሰር ------------------------------------------------------------------1
ቀ) የተሞክሮ ቅመራ፣ ማስፋትና የደረጃ ዕድገት አሰጣጥ ኦፊሰር-----------------------------1
በ) የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ክትትል፣ ድጋፍና ኦዲት ባለሙያ--------------------------------2
ተ) የግንዛቤ ማስጨበጥና ስራ እድል ፈጠራ ኦፊሰር-------------------------------------------1
ቸ) የእቅድ እና ዳታ ቤዝ ኦፊሰር------------------------------------------------------------------1
አ) የምግብ ዋስትና ባለሙያ------------------------------------------------------------------------2

13. የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የመሥሪያ ቦታ

የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች የዘርፉን ሥራዎች በተገቢው ሁኔታ ለማከናወን የመሥሪያ ቦታ
እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ለሥራ አመቺ በሆነ መልኩ ይዘጋጃል፡፡
1) በሁሉም ክልል የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ በተሟላ መልኩ አገልግሎት መስጠት እንዲችል
አስፈላጊ የሆኑ ቢሮና የመገልገያ ቁሳቁስ እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ የሚሟላ ይሆናል፡፡
2) የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ከተቻለ በዲዛይኑ መሰረት የከተሞች የፋይናስ አቅም ችግር ካለ ግን
ጊዜያው የአገልግሎት መስጫ ጣቢያው ቢያንስ በቂ የማዕከሉ ሰራተኞች መቀመጫ ክፍል፣ የማሰልጠኛ
(የደንበኞች ግንዛቤ ማስጨበጫ) ክፍል፣ የደንበኞች ማረፊያ ክፍል፣ መጸዳጃ ቤት እና የህፃናት ማቆያ ሊኖረው
ይገባል፡፡
3) አቅም በፈቀደ መጠን በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ውስጥ የሠራተኞች አቀማመጥ የሥራ
ፍሰቱን የተከተለ እንዲሆን ይደረጋል፡፡
4) እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ የመስመር ስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲኖራቸው ይመቻቻል፡፡
5) በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ውስጥ የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ የመረጃ
ማሰራጫና የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያመላክቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ እንዲዘጋጁ
ይደረጋል፡፡
6) የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያው የሚገኝበትን አድራሻ የሚያሳይ ታፔላ ግልፅ በሆነ ቦታ
ይለጠፋል፡፡

14. የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ፈፃሚዎችና ባለድርሻዎች አሰራር


በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ለስራ ፈላጊ ዜጎች የስራ ዕድል የመፍጠር ስራ በባህሪው በአንድ ተቋም ጥረት
ብቻ ማከናወን የማይቻል ከመሆኑ የተነሳ ገና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ
ሲቀረፅ ከሁሉም አስፈፃሚ አካላት የተውጣጣ አፈፃፀሙን የሚከታተል ምክር ቤት በየደረጀው
እንደሚቋቋም እና በመንግስት መወቅር የመጨረሻው እርክን ላይ ማለትም በአገልግሎት ፈላጊው
ህብረተሰብ አቅራቢያ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች መከፈት እንዳለባቸው
ተጠቅሷል፡፡ ስራ ፈላጊዎች የሚፈልጓቸው አገልግሎቶችም በአዋጅና በደንብ ለተለያዩ የመንግስት
13
አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተሰጠ ቢሆንም ስራ ፈላጊዎቹ አገልግሎት ፍለጋ ከአንዱ ተቋም ወደ
ሌላው ተቋም በመንከራተት የስራ ጊዜያቸውን ሳያባክኑ በአንድ ጥላ ስር አገልግሎቱን ማግኘት
ስላለባቸው በከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ተቋም መዋቅር ስር ከራሱ ከከተሞች የስራ
ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና፣ ከአነስተኛ ብድር አቅራቢ፣ ከቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና፣ ከንግድና
ግብይት፣ ከገቢዎች ባለስልጣን እና ከፍትህ አካላት ተቋሞች በተውጣጡ ባለሙያዎች የአንድ ማዕከል
አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች በቀበሌ ደረጃ በአገልግሎት ፈላጊው ህብረተሰብ አቅራቢያ ይደራጃሉ፡፡

ስለሆነም ሶስቱ አስፈፃሚ አካላት ማለትም የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና፣ የአነስተኛ
ብድር አቅራቢ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ለማዕከሉ በሚቀረፀው መዋቅር
መሰረት በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎችን በቋሚነት
ቀጥረው መመደብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከባለድርሻ አካላት የንግድና ግብይት፣ ገቢዎች ባለስልጣን እና
የፍትህ አካላት ተቋማት በሁለት አማራጮች የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ሲሆን
አንደኛውና የመጀመሪያው አማራጭ ልክ አንደ ሶስቱ ፈፃሚ አካላት በቋሚነት በአንድ ማዕከል
አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ባለሙያ በመመደብ በተቋማቸው የሚሰጠውን አገልግሎት በአንድ
ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ማቅረብ ነው፡፡ ሁለተኛውና የመጨረሻው አማራጭ ደግሞ
በሀገሪቱ ባሉ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ሁሉ በቋሚነት ባለሙያ የመመደብ አቅም
የለንም የሚሉ ከሆነ በተቋማቸው የሚሰጠውን አገልግሎት በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ
ጣቢያዎች ለመስጠት በሚያስችል ደረጃ የሚያስፈልጉ መሠረተ ልማቶችን በማሟላት በክልል ደረጃ
ለክልሉ የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ወይም እሱን ለሚተካው ተቋም
ከነኃላፊነቱና ተጠያቂነት ውክልና መስጠት ይጠበቅበታል፡፡

ክፍል አራት

የፈጻሚ እና ባለድርሻ አካላት ተግባርና ኃላፊነት


15. የከተማው የስራ ዕድል ፈጠራ እና ምግብ ዋስትናን ሥራ የሚመሩ ተቋማት፤
1) የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች በሰው ኃይልና በፋሲሊቲዎች እንዲሟሉ
ያደርጋል፡፡
2) በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎችን አቅም ይገነባል፡፡
3) የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ዕቅድ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙን በወጣው
የአገልግሎት ስታንዳርድ መሠረት መሆኑን ይገመግማል፡፡
4) የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ከሌሎች ፈፃሚ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እንዲሰራ
ያስተባብራል፡፡

14
5) የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ዕቅድ አፈፃፀም፣ መስተካከል ያለባቸው የአሠራር
ስታንዳርዶችንና የሚያስፈልጉ የአቅም ግንባታ ተግባራት ከአስተያየት ጋር ወደ ላይ ቀጥሎ
ለሚገኝ የስራ ዕድል ፈጠራ እና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት/መምሪያ /ኤጀንሲ ያስተላልፋል፡፡
6) በማዕከላት ደረጃ መመደቢያ ጋይድ ላይን መሠረት አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ
ጣቢያዎችን በየበጀት ዓመቱ በደረጃ በመመደብ የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ማዕከላትን
ለዕውቅናና ሽልማት በማዘጋጀት ድጋፍ ለሚሹ ማዕከላት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡

16. የአነስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋም/ብድርና ቁጠባ ተቋም


1) የአነስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋሙ በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ገብቶ የሚሰራ
ባለሙያ ይመድባል፡፡
2) ለከተማው ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚያስፈልግ የፋይናንስ አቅርቦትን
ያመቻቻል፡፡
3) የብድር ፍላጎትን ለማሟላት የሚያስችል የቁጠባ አሰባሰብ ሥርዓት እንዲኖረው የተለያዩ
አሠራሮችን በመዘርጋት ከአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ጋር ተቀናጅቶ ይሰራል፡፡
4) ለኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አቅርቦት ቀልጣፋ በሆነ መልኩና በወጣው የአገልግሎት አሰጣጥ
ስታንዳርድ መሠረት እየተፈፀመ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
5) በከተማው ያሉ የጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች እና ከማኑፋክቸሪንግ ውጭ የሚገኙ አነስተኛ
ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አቅርቦትን ለማረጋገጥ በቅድመ ብድርና ድህረ ብድር የሚከናወኑ
ተግባራትን በመለየትና በዕቅድ ውስጥ በማካተት ከከተማው የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ
ጣቢያ ጋር ተቀናጅቶ ይሰራል፡፡
6) በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ተመድበው የሚሰሩ የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም
ባለሙያዎችን አቅም በየጊዜው ይገነባል፡፡
7) የኢንተርፕራይዞች የብድር አመላለስ ሁኔታ ጤናማ መሆኑን በመከታተል ጤናማ ያልሆነ የብድር
አጠቃቀም ሲያጋጥም የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ከመፍትሄ ሃሳብ ጋር ለሚመለከተው አካል
ያቀርባል፡፡
8) የብድር ተጠቃሚ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች መረጃ ተደራጅቶ በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ
ጣቢያ እንዲያዝ ያደርጋል፡፡
9) የተሻለ የብድርና ቁጠባ አጠቃቀም ልምድ ላላቸው ኢንተርፕራይዞች የዕውቅናና ማበረታቻ
ሥርዓት ይዘረጋል፡፡

15
17. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም
1) በስራ ፈላጊነት ለተመዘገቡ ዜጎች ወደ ስራ ሊያስገባ የሚችል አጫጭር የአመለካከትና
የክህሎት ስልጠና እንዲሁም ስለ ወቅታዊ የኢንዱስትሪው የሰው ኃይል ፍላጎት ግንዛቤ
ይሰጣል፡፡
2) የከተማው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም ከአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ
ጣቢያ ጋር በመቀናጀት የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ማለትም የኢንተርፕሪነርሽፕ
(የስራ ፈጣሪነት አመለካካት) ስልጠና፣ የክህሎት ስልጠና የካይዘን እና የቴክኖሎጂ እድገት ድጋፍ
የሚሰጣቸውን ኢንተርፕራይዞች በመለየት አገልግሎት ይሰጣል፡፡
3) ኢንተርፕራይዞች የሂሳብ አያያዝ ስርዓት ዝርጋታ አገልግሎት እንዲያገኙ ያመቻቻል፡፡
4) ከአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አመቻች
ኦፊሰር ጋር በመቀናጀት ለኢንተርፕራይዞቹ የተሰጡ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት
መረጃዎች ያደራጃል፡፡
5) ለኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎችን በአንድ
ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ይመድባል፡፡
6) የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት በጋራ ዕቅድ መሰረት መፈጸሙን ከአንድ ማዕከል
አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ጋር በመሆን ይገመግማል የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል፡፡
7) ከመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ጋር በመቀናጀት ኢንተርፕራይዞች ከንድፈ ሀሳብ
ስልጠና ባሻገር የተግባር ስልጠና እንዲያገኙ የመደገፍ ስራ ይሰራል፡፡
8) በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የተመደቡ ባለሙያዎችን የማስፈፀም አቅም
ይገነባል፡፡

18. ንግድና ግብይት ልማት ተቋም/ሥራውን የሚመሩ ተቋማት፤

1) በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ገብቶ አገልግሎት የሚሰጥ ባለሙያ ይመድባል ወይም
ውክልና ይሰጣል፡፡
2) ኢንተርፕራይዞች በንግድ ህጉ እና የአሰራር መመሪያዎች ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው
ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ይሰራል፡፡
3) አዲስ ለሚደራጁ ኢንተርፕራይዞች የንግድ ስም ምዝገባ፣ የዋና ምዝገባ እና የንግድ ፍቃድ
ምዝገባ በአንድ ማእከል አገልግሎት ይሰጣል፡፡
4) የኢንተርፕራይዞችን የንግድ ፈቃድ የማደስ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
5) ህጋዊ አሰራር ያልተከተሉ ኢንተርፕራይዞች የንግድ ፍቃዳቸው እንዲሰረዝ ከሚመለከታቸው
አካላት ጋር በጋራ ይሰራል፡፡

16
6) በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የተመደቡ ባሙያዎችን የማስፈፀም አቅም ይገነባል፡፡

19. ገቢዎች ፅ/ቤት/ተቋም


1) በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ውስጥ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር
አሰጣጥ አገልግሎት የሚሰጥ ባለሙያ ይመድባል፡፡
2) በአዲስ ለሚደራጁ ኢንተርፕራይዞች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ይሰጣል፡፡
3) በግብርና ታክስ አዋጆች፣ደንቦች እና መመሪያዎች ዙሪያ ለኢንተርፕራይዞች
ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ይሰራል፡፡
4) የግብር ክሊራንስ ለሚጠይቁ ኢንተርፕራይዞች መረጃውን በአንድ ማዕከል
አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
5) በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የተመደቡ ባሙያዎችን የማስፈፀም
አቅም ይገነባል፡፡

20. የፍትህ ፅ/ቤት/ተቋም


1) አንቀሳቃሾች ስለ ህግ ያላቸውን ግንዛቤ ማሳደግ፣
2) በማህበራት መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ አዘገጃጀት ለአንድ ማዕከል ባለሙያዎችና
አንቀሳቃሾች ግንዛቤ ማስጨበጥ፣
3) የማህበራትን መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ
በመገኘት ከህግና ከሞራል አኳያ መርምሮ ማፀደቅ፣
4) መንግስታዊ ድጋፎች አጠቃቀም ላይ የሚታዩ ህገወጥ ተግባራትን በህግ አግባብ የእርምት
ዕርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
5) በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የፍትህ አገልግሎት የሚሰጥ ባለሙያ ይመድባል፣
6) በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የተመደቡ ባሙያዎችን የማስፈፀም አቅም ይገነባል፡፡

21. የከተማ አስተዳደር/ ማዘጋጃ ቤት ተግባርና ኃላፊነት


1) ለአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች በቂ በጀት እንዲመደብላቸው ያደርጋል፤
2) ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የመስሪያና መሸጫ የሚሆን ቦታ ያመቻቻል፤
3) በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች መስሪያና መሸጫዎች ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ
ልማት እንዲሟላላቸው ያደርጋል፡፡
4) በጥቃቅንንና አነስተኛ የስራ መስክ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች በፋይናንስ በሚወጡ ጨረታዎች
በልዩ ድጋፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

17
ክፍል አምስት
22. የድጋፍ የክትትልና ግምገማ ሥርዓት
1) ከፈጻሚ አካላት ጋር በየወሩ የጋራ መድረክ በማመቻቸት የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የቴክኒክና
ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋምና የአነስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋም የጋራ ዕቅድ አፈፃፀም
በመገምገም የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ፤
2) በጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች እና ከማኑፋክቸሪንግ ውጭ የሚገኙ አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ
ልማት ሥራ ላይ በአንድ ማዕከል አገልግሎት ያሉ ባለሙያዎች በአመለካከት፣ በክህሎት፣
በግብዓት አቅርቦትና ግብይት ስርዓት የሚታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት የሳምንት፣
የ 15 ቀን፣ የወር፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽና የዓመት የስራ ግምገማ ማድረግ፤
3) የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች የ 15 ቀን፣ የወር፣ የሩብ ዓመት፣ የስድስት ወርና
የዓመት የአፈጻጸም ሪፖርት ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረብ፣
4) ሪፖርቶች በጹሁፍ፣ በቃልና በኤሌክትሮኒክስ መረጃ መረብ በመጠቀም በየደረጃው ላሉ አካላት
ማስተላለፍ፤
5) የክትትልና ድጋፍ ስርዓት አፈጻጸም በሪፖርትና በመስክ ጉብኝት የሚፈጸም ይሆናል፣
6) በየደረጃው ያለው የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ምክር ቤት በየሶስት ወሩ
የዘርፉን ልማት ዕቅድ አፈፃፀምና የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰጪ ፈፃሚና ባለድርሻ አካላት
የአገልግሎት አሰጣጥ አፈፃፀምን በመገምገም አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡
ክፍል ስድስት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

23. መመሪያ ስለማሻሻል

ይህ ሞዴል መመሪያ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንዲሁም ከአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት ጋር


ለማጣጣም መሰረታዊ ይዘቱን ሳይለቅ እንደ አስፈላጊነቱ በክልሉ/ከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ወይም
በፌዴራል ከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር አማካኝነት ሊሻሻል ይችላል፡፡

24. መመሪያው ስለሚጸናበት ሁኔታ

ይህ ሞዴል መመሪያ ከፀደቀበት ከ------------------ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

ጃንጥራር ዓባይ

የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር


18

You might also like