You are on page 1of 33

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር

የፌዴራል የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ

የከተማ ቁጠባና ብድር አገልግሎት አሰጣጥ ሞዴል መመሪያ

ቁጥር ------/ 2010 ዓ.ም/ ተሻሽሎ የቀረበ/

ግንቦት/ 2010

አዲስ አበባ
መግቢያ

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፍ ከግብርናው ቀጥሎ ሠፊ የስራ ዕድል የሚፈጠርባቸው
በመሆናቸው ድህነትን ከመቅረፍ እና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ
0
አላቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር በማመቻቸት፣ ለመካከለኛና ከፍተኛ
ኢንዱስትሪዎች ዕድገት ሰፊ መደላደል በመፍጠር ረገድ ለቀጣይ የኢኮኖሚ ዕድገት አይነተኛ መሳሪያ
መሆናቸው ጋር ተያይዞ በመንግስት ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ
በመሆናቸው፣ በጥቃቅን አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ መሰረት የከተማ ቁጠባና ብድር አገልግሎት
አሰጣጥ የኢንተርፕራይዞችን የደረጃ ዕድገት እና የተሻሻለውን የኤጀንሲውን ተልዕኮ ታሳቢ ያደረገ ወጥነት ያለው
ሞዴል መመሪያ ማዘጋጀት በማስፈለጉ እንዲሁም በዘርፉ የሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞችን ልማት ለማስፋፋትና
ለማጠናከር የዕድገት ደረጃቸውን መሰረት ያደረገና ቁጠባ መር የብድር አገልግሎት የሚያገኙበትን ሥርዓት ማሻሻል
በማስፈለጉ እና የፌደራል ኤጀንሲውን መነሻ በማድረግ ሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች እንደ ክልሎች
ተጨባጭ ሁኔታ ከኪራይ ሰብሳቢነት የጸዳ፣ አሳታፊ፣ ፍትሃዊና ውጤታማ በሆነ መልኩ ድጋፉን ለማቅረብ ቁጠባ መር
የብድር አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ለማሻሻል በማስፈለጉ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 374/2008 አንቀጽ
14 መሠረት ይህ ሞዴል መመሪያ ተሻሽሎ ተዘጋጅቷል፡፡

ክፍል አንድ

ጠቅላላ
1. አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ “የተሻሻለ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን የዕድገት ደረጃ መሰረት ያደረገ የከተማ
ቁጠባና ብድር አገልግሎት አሰጣጥ ሞዴል መመሪያ ቁጥር ---------2010 ›› ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2. ትርጓሜ

የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጓሜ የሚሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ መሰረት

1
"ቡድን”” ማለት የፋይናንስ አቅርቦት ለኢንተርፕራይዞች ለማመቻቸት በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ባላቸው
1) "ቡድን
የስራ ዘርፎች የተሰማሩ የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እና ቁጥራቸው ከ 3 እስከ 7 የሚደርሱ
የቡድን ብድር አባላትን ይገልፃል፡፡

2) "የቡድን ዋስትና"
ዋስትና" ማለት የቡድን ተበዳሪዎች ከመካከላቸው አንደኛው ፈቃድ ከተሰጠው አበዳሪ ተቋም
የተበደረውን ብድር ያልከፈለ እንደሆነ ብድሩን መልሶ ለመክፈል በአንድነት ባልተነጣጠለ ኃላፊነት
የሚወስዱበት የዋስትና አሰራር ነው፡፡

3) "የብድር ዋስትና"
ዋስትና" ማለት ለሚወሰድ ብድር በዋስትና የሚቀርብ የቡድን፣ የከተማ አስተዳደር፣ የደመወዝ ወይም
የንብረት መያዣ ነው፡፡

4) "የግዴታ ቁጠባ"
ቁጠባ" ማለት በተቋሙ የብድር ደንበኞች የሚያስቀምጡትና ያለባቸውን የብድር ዕዳ ከፍለው
እስከሚያጠናቅቁ ድረስ ሊወጣ የማይችል የግዴታ ቁጠባ ሲሆን የቅድመ ብድር ቁጠባና መደበኛ ቁጠባ ተብሎ
በሁለት ይከፈላል፡፡

5) "የውዴታ ቁጠባ"
ቁጠባ" ማለት በተቋሙ የብድር ደንበኞችና ሌሎች፣ የህብረተሰብ ክፍሎች ወይም በተቋሞች ፍላጎት
ላይ ተመስርቶ የሚቀመጥ የቁጠባ ዓይነት ሲሆን አስቀማጮቹ በፈለጉ ጊዜ ወጪ ሊያደርጉት የሚችሉት
የውዴታ ቁጠባ ነው፡፡

6) "ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ"
" ማለት የኢንተርፕራይዙን ባለቤት፤ የቤተሰብ አባላትና ተቀጣሪ ሠራተኞች ጨምሮ
እስከ አምስት ሰዎች ቀጥሮ የሚያሰማራና የጠቅላላ ካፒታሉ መጠን ህንፃን ሳይጨምር በአገልግሎት ዘርፍ
ከብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ወይም በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) ያልበለጠ
ኢንተርፕራይዝ ነው:፡

7) "አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ"
" ማለት የኢንተርፕራይዙን ባለቤት፤ የቤተሰብ አባላትና ተቀጣሪ ሰራተኞችን
ጨምሮ ከስድስት እስከ ሰላሳ ሰዎች የሚያሰማራና የጠቅላላ ካፒታሉ መጠን ህንፃን ሳይጨምር በአገልግሎት
ዘርፍ ከብር 50,001.00 (ሃምሳ ሺህ አንድ) እስከ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ወይም በከተማ ግብርና ፣
ባሕላዊ ማዕድን ማምረት እና ግንባታ ዘርፍ ከብር 100,001.00 (አንድ መቶ ሺህ አንድ) እስከ 1,500,000.00
(አንድ ሚልዮን አምስት መቶ ሺ) ያልበለጠ ኢንተርፕራይዝ ነው::

8) "ምስረታ ወይም ጀማሪ (Start up) ደረጃ"


ደረጃ" ማለት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለመመስረት ፍላጎት
ያላቸው ሰዎች እና ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት በየደረጃቸው የሚጠበቅባቸውን ትምህርት በማጠናቀቅና
በቡድን፣ በማህበር እና በግለሰብ ደረጃ በህግ አግባብ ተደራጅተው የራሳቸውን ቁጠባና ከተለያዩ የፋይናንስ
ተቋማት ብድር በመውሰድ ወደ ስራ የገቡትን የሚያካትት ነው፡፡ የምስረታ/
የምስረታ/ጀማሪ ደረጃ ኢንተርፕራይዙ ህጋዊ
አቋም ይዞ የማምረት /አገልግሎት/
አገልግሎት/ የመስጠት ተግባር የሚጀምርበት ነው፡፡

9) "ታዳጊ ወይም መስፋፋት (Growth)


(Growth) ደረጃ"
ደረጃ" ማለት አንድ ኢንተርፕራይዝ የሚሰጠውን ድጋፍ ተጠቅሞ
የገበያ ላይ ዋጋ፣ በጥራትና በአቅርቦት ተወዳዳሪ ሲሆንና ትርፋማነቱ በቀጣይነት ሲረጋገጥ እና በምስረታ ደረጃ
ከነበረው የሰው ኃይል ቁጥርና የጠቅላላ ሃብት መጠን እድገት ያለው እንዲሁም የሂሳብ አያያዝ ሥርዓት

2
የሚጠቀም ማለት ነው፡፡ በዚህ ደረጃ ላይ ኢንተርፕራይዝ በምስረታ ደረጃ ከነበረው ቀጥሮ የሚያሰራው የሰው
ሀይል ቁጥርና ጠቅላላ ሀብት መጠን ዕድገት ይኖረዋል፡፡

10) "በመብቃት (Maturity)


(Maturity) ደረጃ"
ደረጃ" ማለት አንድ ኢንተርፕራይዝ የሚሰጠውን ድጋፍ ተጠቅሞ በገበያ ውስጥ
ተወዳዳሪና ትርፋማ ሆኖ የገበያ ድርሻውን ለማሳደግ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት በስራ ላይ ከዋለና ለዘርፉ
የተቀመጠውን ትርጓሜ መስፈርት ሲያሟላና ወደ ታዳጊ መካከለኛ ደረጃ ሲሸጋገር ወይም ባለበት ደረጃ
(በጥቃቅን ወይም በአነስተኛ ኢንተርፕራይዝነት)
ኢንተርፕራይዝነት) በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪና ትርፋማ ሆኖ የሚቀጥል ሲሆን
ነው፡፡

11) "የመሳሪያ ሊዝ"


ሊዝ" ማለት አንድ የመሣሪያ ባለንብረት ወይም አከራይ እና ንብረቱን መጠቀም በፈለገው ተከራይ
መካከል የሚደረግ የውል ስምምነት ነው፡፡

3. የተፈፃሚነት ወሰን

ይህ ሞዴል መመሪያ በኢትዮጵያ ከተሞች በሚገኙ የከተማ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ላይ ተፈጻሚ
ይሆናል፡፡

4. ዓላማ

የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ለማስፋፋት እና ለማጠናከር የእድገት ደረጃቸውን መሰረት


ያደረገና ቁጠባ መር የብድር አገልግሎት የሚያገኙበትን ሥርዓት ለማሻሻል ነው፡፡

5. መርሆዎች

1) የብድር አገልግሎቱ ቁጠባ መር እና የቤተሰብ ተሳትፎን ያረጋገጠ ይሆናል፡፡


2) የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋማት የብድር አገልግሎት በእድገት ተኮር ዘርፎች ያተኮረ ይሆናል፡፡
3) የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋማት የብደር ገንዘብ ምንጫቸው በአብዛኛው ከቁጠባ የሚገኝ ይሆናል፡፡
4) የብድር አገልግሎቱ የኢንተርፕራይዞችን የደረጃ ዕድገት ታሳቢ ያደረገ ይሆናል፡፡
5) የብድር አመላለስ ምጣኔውም መቶ በመቶ እንዲሆን ይደረጋል፡፡
6) ለሴቶች፣ ለወጣቶች እና ለአካል ጉዳተኞች ቅድሚያ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ክፍል ሁለት
ዋና ዋና አገልግሎቶች
6. በአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች

1) የቁጠባ አገልግሎት
2) የብድር አገልግሎት
3) የመሳሪያ ሊዝ
3
4) የማይክሮ ኢንሹራንስ
5) የሃዋላ አገልግሎት
6) የሶስተኛ ወገን ገንዘብ ማስተዳደር
7) ሌሎች ፋይናንስ አገልግሎቶች ናቸው::

7. የቁጠባ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት

አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት በየዓመቱ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለማበደር በዕቅድ ከሚያዘው ጠቅላላ
የገንዘብ መጠን ውስጥ 80 በመቶ ከቁጠባ መሸፈን አለባቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በከተማው አስተዳደር ውስጥ ለተወሰነ
ጊዜ ያለስራ የሚቀመጥ ገንዘብ ከየተቋማቱ ተለይቶ በአነስተኛ የፋይናስ አቅራቢ ተቋማት እንዲቀመጥና አውት ሶርስ
ሊደረጉ የሚችሉ ፋይናንሻል ስራዎች በአበዳሪ ተቋማቱ እንዲሰሩ በማድረግ የማበደር አቅማቸው እንዲጎለብት
ይደረጋል፡፡

በመሆኑም ሁሉም ፈፃሚ እና ባለድርሻ አካላት የታቀደውን የቁጠባን ባህል ለማሳደግና ለዘርፉ የሚያስፈልገውን ያህል
የገንዘብ መጠን ለማሰባሰብ ትኩረት ሰጥተው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡

8. የቁጠባ አይነቶች

1) የግዴታ ቁጠባና ቅድመ ብድር ቁጠባ


ሀ) በስትራቴጂው ቅድሚያ ትኩረት የተሰጣቸው የሥራ ዘርፎች ላይ የሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ለብድር
አገልግሎቱ ብቁ ለመሆን ከሚበደሩት የብድር መጠን 20 በመቶ አስቀድመው የቆጠቡ መሆን
ይኖርባቸዋል፡፡
ለ) የኤክስፖርት ወይም ተኪ ምርት የሚያመርቱ ኢንተርፕራይዞች ለብድር አገልግሎቱ ብቁ ለመሆን
ከሚበደሩት የብድር መጠን 15 በመቶ አስቀድመው የቆጠቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ሐ) የኤክስፖርት ወይም ተኪ ምርት ከሚያመርቱና በዕድገት ተኮር የስራ ዘርፍ ከተሰማሩ ውጭ ያሉ
የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለብድር አገልግሎት ብቁ ለመሆን እንደ እድገት ደረጃቸው
ከሚበደሩት የብድር መጠን ቅድመ ብድር አስቀድመው መቆጠብ ይኖርባቸዋል፡፡
መ) የቅድመ ብድር ቁጠባ መቆጠብ ለማይችሉ ስራ ፈላጊዎች በየአካባቢው በሚለየው የጥሪት ማፍሪያ
ፕሮጀክቶች ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ ሰርተው ከሚያገኙት 30 በመቶ የግዴታ ቁጠባ በማስቆጠብ
ለብድር የጠየቁትን 20 ከመቶ እንዲቆጥቡ በማድረግ ለብድር ዝግጁ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
ሠ) የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንደ ዕድገት ደረጃቸው መቆጠብ የሚገባቸው ቅድመ ብድር
ቁጠባ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡

2) ጀማሪ ኢንተርፕራይዞች
ሀ) ጀማሪ ኢንተርፕራይዞች ለብድር አገልግሎት ብቁ ለመሆን ከሚበደሩት የብድር መጠን 20 በመቶ
አስቀድመው መቆጠብ ይኖርባቸዋል፡፡
4
ለ) ሆኖም በመንግስት ፕሮጀክት በቀጥታ ወደ ስራ ለሚገቡ ኢንተርፕራይዞች ለግብአትና መሳሪያ ግዢ
የሚሆን ብድር በሶስትዮሽ ውል ተሰጥቷቸው ወደ ስራ ከገቡ በኋላ 20 በመቶ ቁጠባውን እንዲቆጥቡ
ይደረጋል፡፡

3) ታዳጊ ኢንተርፕራይዞች
ሀ) የኤክስፖርት ወይም ተኪ ምርት የሚያመርቱና በእድገት ተኮር ዘርፍ የሚሰማሩ ታዳጊ ኢንተርፕራይዞች
ለብድር አገልግሎት ብቁ ለመሆን ለመበደር ያቀዱትን 15 በመቶ አስቀድመው መቆጠብ ይኖርባቸዋል፡፡
ለ) በስትራቴጂው ቅድሚያ ትኩረት የተሰጣቸው የሥራ ዘርፎች ላይ የሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ለብድር
አገልግሎት ብቁ ለመሆን ከሚበደሩት የብድር መጠን 20 በመቶ አስቀድመው መቆጠብ ይኖርባቸዋል፡፡
ሐ) የኤክስፖርት ወይም ተኪ ምርት ከሚያመርቱና ከዕድገት ተኮር የስራ ዘርፍ ከተሰማሩ ውጭ ያሉ ታዳጊ
ኢንተርፕራይዞች ለብድር አገልግሎት ብቁ ለመሆን ለመበደር ያቀዱትን 25 በመቶ አስቀድመው
መቆጠብ ይኖርባቸዋል፡፡

4) የበቃ ኢንተርፕራይዞች

ሀ) የኤክስፖርት ወይም ተኪ ምርት የሚያመርቱና በእድገት ተኮር ዘርፍ የሚሰማሩ የበቁ ኢንተርፕራይዞች
ለብድር አገልግሎት ብቁ ለመሆን ለመበደር ያቀዱትን 15 በመቶ አስቀድመው መቆጠብ ይኖርባቸዋል፡፡

ለ) በስትራቴጂው ቅድሚያ ትኩረት የተሰጣቸው የሥራ ዘርፎች ላይ የሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ለብድር


አገልግሎት ብቁ ለመሆን ከሚበደሩት የብድር መጠን 20 በመቶ አስቀድመው መቆጠብ ይኖርባቸዋል፡፡

ሐ) የኤክስፖርት ወይም ተኪ ምርት ከሚያመርቱና በዕድገት ተኮር የስራ ዘርፍ ከተሰማሩ ውጭ ያሉ የበቁ
ኢንተርፕራይዞች ለብድር አገልግሎት ብቁ ለመሆን ለመበደር ያቀዱትን 30 በመቶ አስቀድመው መቆጠብ
ይኖርባቸዋል፡፡

5) በብድር ቆይታ ጊዜ ውስጥ የሚሰበሰብ የግዴታ ቁጠባን በተመለከተ

ሀ) ከአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ብድር ተበዳሪ የሆኑ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች

የተበደሩትን ብድር ከፍለው እስከሚያጠናቅቁ ጊዜ ድረስ የግዴታ መደበኛ ቁጠባ እንዲቆጥቡ ይደረጋሉ፡፡

ለ) በዚህም መሰረት እያንዳንዱ ተበዳሪ ኢንተርፕራይዝ ብድሩን ከፍሎ እስከሚያጠናቅቅ ጊዜ ድረስ የብድሩን
መጠን 2 በመቶ በየወሩ እንዲቆጥቡ ይደረጋል፡፡ በብድር ቆይታ ጊዜ ውስጥ የሚሰበሰብ የግዴታ ቁጠባ ብድሩ
በተሰጠ በወሩ መሰብሰብ ይጀምራል፡፡

5
9. የውዴታ ቁጠባ አይነቶች
የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ተማሪዎች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያገኙትን ገቢ በማብቃቃት
እንዲሁም ወጪን በመቀነስ ለስራ የሚያስፈልጋቸውን ካፒታል ለማሳደግና ለተለያዩ ወጪዎች የሚያስፈልጋቸውን
ገንዘብ በብድር አስቀድሞ ለማግኘት ዝግጁ ለመሆን፤ እንዲሁም ጥሪት ለመያዝ ቁጠባን እንደ ባህል በመርህ ደረጃ
መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ለህብረተሰቡ የቀረበ አደረጃጀት ያላቸው ቢሆኑም ተደራሽነታቸውን ይበልጥ
በማስፋትና በማሳደግ ከዚህ በታች በተጠቀሱትና ሌሎችንም ተጨማሪ የውዴታ የቁጠባ አይነቶችን ለህብረተሰቡ
በማስተዋወቅ የገንዘብ አቅርቦትንና የብድር ፍላጎትን ክፍተት መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እነሱም፡-

1) የተቀማጭ/የደብተር ቁጠባ /Pass book Saving /

የደብተር ቁጠባ /Pass book saving/ ማለት ደንበኞች በብር 10 መነሻ የቁጠባ አካውንት በመክፈት ቁጠባ
ሊያጠራቅሙት የሚችሉበት የቁጠባ አገልግሎት ነው፡፡

2) በጊዜ ገደብ የሚቀመጥ ቁጠባ /Fixed time Deposit/

በዚህ የቁጠባ ዓይነት የተቀመጠ ገንዘብ በአነስተኛ የፋይናንስ ተ ቋማት ውስጥ የሚቆይበትን የጊዜ ገደብ አስቀማጩ
ደንበኛ ከተቋሙ ጋር በሚደረገው የውል ስምምነት መሰረት የሚወሰን ሲሆን የወለድ ምጣኔውም/interest rate/
በተቋሙ ውስጥ በሚቆይበት የውል ስምምነት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተሰልቶ የሚከፈል ይሆናል፡፡ ቁጠባው ከውል
ስምምነቱ በፊት ወጪ የሚደረግ ከሆነ አስቀማጩ ወለዱን እንዲያጣ ተደርጎ ዋናውን ገንዘብ ወጪ እንዲያደርግ
ይደረጋል፡፡

3) ወለድ የማይታሰብለት ቁጠባ /Non- interest Bearing Deposit/

ይህ የቁጠባ ዓይነት ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች ገንዘባቸውን በአደራ የሚያስቀምጡበት አሰራር ሲሆን ተቋሙ
ለሚሰጠው አገልግሎት ደንበኞች የኮሚሽን ክፍያ እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡

4) የሙዳይ ባንክ /Piggy Bank/ ወይም የካዝና ቁጠባ

በጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ስራዎች ላይ የተሰማራ/ች ማህበራት እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ
ድርጅት ሰራተኞች የተቋሙ የብድር ደንበኞች የሆኑና ማንኛውም ግለሰብ መጠቀም የሚችልበት ከአበዳው
በሽያጭ፤በስፖንሰር ወይም አበዳው ለዚሁ ተግባር በሚያቀርበው የቁጠባ ሳጥን የሚቆጠብ የቁጠባ ዓይነት ነው፡፡

6
5) የቤት ለቤት/ተንቀሳቃሽ ቁጠባ /Mobile saving Service/

ይህ የቁጠባ አይነት በተቋሙ ቁጠባ ለመቆጠብ ፍላጎት ያላቸው ነገር ግን በሥራ ባህሪያቸው ምክንያት ወደ ተቋሙ
ጽ/ቤት በአካል ቀርበው መቆጠብ ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በስራ ገበታቸው፣በገበያና በመኖሪያ ቦታቸው ድረስ
በመዘዋወር ቁጠባ ለማሰባሰብ የሚያስችል ስርዓት ነው፡፡

10. በቁጠባ ሂሳብ ላይ ስለሚከፈል ወለድና የአወጣጥ ስርዓት


1) የወለድ ሥሌት
በአነስተኛ የፋይናንስ ተቋሙ ወሩን ሙሉ ለተቀመጠ ተቀማጭ ቁጠባ የሚከፈለው የወለድ ምጣኔ የሚወሰነው
በየጊዜው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚያወጣቸውን መመሪያዎች መሰረት በማድረግ እያንዳንዱ አነስተኛ
የፋይናንስ ተቋም በሚያወጣው ማስፈጸሚያ መመሪያ መሰረት ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

2) የቁጠባ አወጣጥ ሥርዓት (Withdrawal Procedures)


የቅድመ ብድር ቁጠባዎች እንደ ጋርዮሽ ገንዘብ /matching fund/ የሚያገለግሉ በመሆናቸው ወጪ መሆን የሚችሉት
ተበዳሪው ለብድር ብቁ ሆኖ ሲገኝ ሲሆን ተበዳሪው በቆጠበው ቁጠባ መጠንና በጸደቀለት የብድር መጠን መካከል
ያለው ልዩነት በብድር ይሰጠዋል፡፡ ይሁን እንጂ በብድር ቆይታ ጊዜ ውስጥ የሚቆጠበው የግዴታ ቁጠባ ወጪ መሆን
የሚችለው ብድሩ ተጠቃሎ ከተከፈለ ሲሆን ሌሎች የውዴታ የቁጠባ አይነቶች ወጪ የሚደረጉት የፋይናንስ ተቋሙና
አስቀማጩ ደንበኛ አስቀድመው በሚያደርጉት ስምምነት መሰረት ይፈጸማል፡፡

3) የቁጠባ ምንጮች
የአነስተኛ ብድር አቅራቢ ተቋማት በየደረጃው ከሚገኙ የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ፣
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት፣ የከተማ አስተዳደር፣ የወረዳ አስተዳደር፣ የዞን መስተዳደርና የክልል መስተዳደር አካላት ጋር
በጋራ በመስራት ያሉትን የቁጠባ ምንጮች አሟጠው መጠቀም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከቁጠባ ምንጮች መካከል ዋና
ዋናዎቹ ከዚህ በታች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡

ሀ) በየአካባቢው የሚገኙ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት

ለ) ከተማ መስተዳድሮች በሊዝ ከሚያስተላልፏቸው የመሬት ይዞታዎች ቅድሚያ ክፍያ የሚሰበስቡትንና


በዝግ የባንክ አካውንት እንዲቀመጥ ከሚያደርጉት ክፍያ፣

ሐ) የከተማ አስተዳደሮች ወይም ተቋሞች ለሚያስገነቧቸው ግንባታዎች ከኮንትራክተሮች በቅድሚያ


የሚያስከፍሉት ሪቴንሽን /Retention/፣

መ) በየአካባቢው ለተለያዩ የልማት ስራዎች የተሰባሰቡ ገንዘቦች፣

ሠ) በየአካባቢው ካሉ ዕድሮች እና የዕቁብ ማህበራት፣

ረ) በየአካባቢው ከሚገኙ የተለያዩ የህዝብ አደረጃጀት ተቋማት፣

ሰ) የውስጥ ገቢ ካላቸው የትምህርት፣ የጤና፣ የግብርና እና የውሃ ተቋማት


7
ሸ) በየአካባቢው ካሉ የቴክኒክና የሙያ ተቋማት

ቀ) የግል ባለሀብቶች

በ) የክላስተር ማዕከላትና

ተ) ተበዳሪ ካልሆኑና የመንግስት ፕሮጀክት ስራዎች ከተሰጡ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችና


ከሌሎች ምንጮች አስፈላጊውን የማስተዋወቅ ስራ በመስራት በየበጀት ዓመቱ የሚያስፈልገውን
የብድር ፍላጎት 80% ከሚሰበሰበው ቁጠባ ለመሸፈን ትኩረት ሰጥተው ይንቀሳቀሳሉ፡፡

11. የብድር አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት

1) የብድር አገልግሎት ተጠቃሚዎች (Target groups)


የግል ኢንተርፕራይዝ፣ በህብረት ሽርክና ማሕበር ወይም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች
የብድር አገልግሎቱ ተጠቃሚ ሲሆኑ እነዚህ ኢንተርፕራይዞች እንደ እድገት ደረጃቸው ጀማሪ (Start up) ፣ ታዳጊ
(Growth) እና የበቁ (Matured) ተብለው ይከፋፈላሉ፡፡ ቀደም ሲል በህብረት ሥራ ማህበር እና በአክስዮን ማህበር
ተደራጅተው በሥራ ላይ የቆዩ ነባር ኢንተርፕራይዞች/ማህበራት የአገልግሎቱ ተጠቃሚነታቸው እንደተጠበቀ
ይሆናል፡፡

2) በብድር ሥርዓቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው የስራ ዘርፎች

ካለው ውስን የብድር አቅርቦት አኳያ፤ ሰፊ የስራ ዕድል ከመፍጠር፣ እሴት (value) የሚጨምሩ ኢንተርፕራይዞችን
ከማስፋፋት፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ቴክኖሎጂዎችን ወደ መካከለኛና ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ለማሸጋገርና የተያዘውን ዕቅድ
እውን ለማድረግ በሌላም በኩል ሴክተሩ የኢንዱስትሪውን ቴክኖሎጂ ሊሸከም የሚችል የሰው ኃይል ማፍራት ይችል
ዘንድ የብድር ስርዓቱ በሚከተሉት የሥራ ዘርፎች ለሚሰማሩት በቅድሚያ ትኩረት ይሰጣል::

ሀ) ሰፊ የስራ ዕድል መፍጠር የሚችሉ የስራ ዘርፎች ላይ ለሚሰማሩ፤

ለ) ከውጭ አገር የሚገቡትን ምርቶች በሚተኩ ሥራ ላይ ለተሰማሩ፤

ሐ) የሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃን የሚጠቀሙ የስራ ዘርፎች ላይ ለሚሰማሩ፤

መ) የአገሪቱን የምርት ስታንዳርድ ለሚያሟሉ ኢንተርፕራይዞች፤

ሠ) በክላስተር ማዕከላት በመሰባሰብ በሞዴልነት ተመርጠው ለሚያመርቱና አገልግሎቶችን ለሚያቀርቡ፤

ረ) ለኤክስፖርት ገበያ የሚያመርቱ ኢንተርፕራይዞች፣

ሰ) የራሳቸው ቁጠባና የመልካም ተበዳሪነት ታሪክ ያላቸው ኢንተርፕራይዞች፤

ሸ) ለብድር ብቁ የሚያደርጋቸውን መስፈርት አሟልተው ሲገኙ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል::

8
ከላይ የተጠቀሱትን ትኩረት የሚሰጣቸው ዘርፎች ግምት ውስጥ በማስገባትበየዘርፎቹ ሊካተቱ የሚችሉ ንዑስ
ዘርፎች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል::

3) የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ (Manufacturing)

ሀ) ጨርቃ ጨርቅና ስፌት (Textile and Garment)

ለ) ቆዳና የቆዳ ውጤቶች (Leather and Leather Products)

ሐ) የምግብና መጠጥ ዝግጅት (Food processing and beverage)

መ) የብረታ ብረትና የኢንጂነሪንግ ምርቶች

ሠ) የእንጨት ሥራዎች (wood work including furniture)

ረ) ባህላዊ የዕደ ጥበብና የጌጣጌጥ ሥራዎች

ሰ) አግሮ ፕሮሰሲንግ (Agro Processing)

ሸ) የግንባታ ግብዓት ምርቶች

12. የኮንስትራክሽን ዘርፍ

1) ሥራ ተቋራጭነት

2) ንዑስ ሥራ ተቋራጭነት

3) ባህላዊ የማዕድን ሥራዎች

4) የከበሩ ድንጋዮች ልማት

5) ኮብል ስቶን ስራዎች(Coble stone)

6) የመሠረተ ልማት ግንባታ ንዑስ ተቋራጭነት

13. የንግድ ዘርፍ

1) የሀገር ውስጥ ጅምላ ሽያጭ፣

2) የሀገር ውስጥ ምርቶች ችርቻሮ ንግድ

3) የጥሬ ዕቃ አቅርቦት

14. የአገልግሎት ዘርፍ

1) የገጠርና አነስተኛ ትራንፖርት አገልግሎት

9
2) ካፌና ሬስቶራንቶች

3) የማከማቻ አገልግሎት

4) የማሸጊያ አገልግሎት

5) የሥራ አመራር አገልግሎት

6) የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት

7) የፕሮጀክት ኢንጂነሪንግ አገልግሎት

8) የምርት ዲዛይንና ልማት አገልግሎት

9) የግቢ የውበትና የጥበቃ እና ፅዳት አገልግሎት

10) የጥገና አገልግሎት

11) የውበት ሳሎን ሥራዎች

12) የኤሌክትሮኒክስና ሶፍት ዌር ልማት

13) የዲኮር ስራ

14) ኢንተርኔት ካፌ

15. የከተማ ግብርና ዘርፍ

1) ዘመናዊ የእንስሳት እርባታ

2) የንብ ማንባት

3) የዶሮ እርባታ

4) ዘመናዊ የደን ልማት

5) ዘመናዊ ችግኝ ማፍላት

6) አትክልትና ፍራፍሬ

7) ዘመናዊ የመስኖ ስራ

8) የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ

9) እንጉዳይ ማምረት

16. የኢንተርፕራይዞች ምልመላ መስፈርቶች

10
የማደራጀት ስራ እንዲሁም ኢንተርፕራይዞች የሚያስፈልጋቸውን ስልጠና በመለየት ወደ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና
ሥልጠና ተቋማት የመላክ ሥራ የዘርፍ ፈጻሚዎችና ባለድርሻ አካላት በአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚያከናውኑት ሆኖ
የብድር አገልግሎት ተጠቃሚዎች ከዚህ በታች የተቀመጡትን የመመልመያ መስፈርቶች ማሟላት የሚጠበቅባቸው
ሲሆን የሚመለምለውና የሚያደራጀው አካል መስፈርቶቹ መሟላታቸውን ያረጋግጣል፡፡ እንዲሁም የተበዳሪዎችን
ሙሉ ዝርዝር መረጃ ለአበዳሪ ተቋሙ አስቀድሞ እንዲላክ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

1) ለቡድን ተበዳሪዎች

በተመረጡ የሥራ ዘርፎች በቡድን ተደራጅተው ለመበደርና ለመሥራት ፍላጎት ያላቸው፣

ሀ) የመሥራት አቅምና ችሎታ ያላቸው አቅማቸውን ተጠቅመውና ሰርተው ለመለወጥ ዝግጁ የሆኑ፤

ለ) በቀበሌው ቋሚ ነዋሪ መሆናቸውን እና በአካባቢያቸው ካለው የፋይናንስ ተቋም እዳ እንደሌለባቸው


የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

ሐ) በጥቃቅንና አነስተኛ የስራ ዘርፎች የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች በተደራጁበት ቀበሌ ቋሚ ነዋሪ ካልሆኑ
በቋሚነት ይኖሩበት ከነበረው ቀበሌ ቋሚ ነዋሪነታቸውን እና ከአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ብድር
እንደሌለባቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

መ) ኢንተርፕራይዞች ከብድር በፊት አነስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋም ባወጣው መስፈርት መሠረት ቅድሚያ
ቁጠባ ማሟላት አለባቸው፡፡

ሠ) ሁሉም የቡድኑ አባላት ወይም የተወሰኑት አባላት በሚሰማሩበት የስራ ዘርፍ ከዩንቨርስቲ፣ ቴክኒክና ሙያ
ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የተመረቁ ወይም ስልጠና የወሰዱ ወይም በልምድ ያገኙት ዕውቀት
ስለመኖራቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣

ረ) በአካባቢያቸው በማንኛውም መጥፎ ሥነ-ምግባር የማይታወቁ ወይም ከደባል ሱሶች ነጻ የሆኑ፣

ሰ) በተመረጡ የሥራ ዘርፎች አዋጭ የሆነ ቢዝነስ ፕላን ማቅረብ የሚችሉ፣

ሸ) ዕድሜያቸው ከ 18 ዓመት በላይ የሆኑ፣ የመስራት አቅምና ችሎታ ያላቸው፣

ቀ) የታደሰ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ ወይም ቁጥሩ ያልተሰጣቸው ቢሆኑም
ለግብር ከፋይነት የተመዘገቡ ለመሆናቸው ከሚኖሩበት ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ
የሚችሉ፣

በ) ነባር ከሆኑ ሂሳባቸውን በአግባቡ እየሰሩ መሆናቸውን ከፈጻሚ አካላት ማረጋገጥ ከቻሉ፣

ተ) የጋብቻ ምስክር ወረቀት ወይም ትዳር አለመኖሩን የሚያስረዳ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ህጋዊ ማስረጃ
ማቅረብ የሚችል፣

ቸ) መስፈርቱን ለሚያሟሉ ሴቶች ምሩቃን ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ ይሰጣል፡፡

11
2) የንግድ ማህበራት ወይም የግል ተበዳሪዎች

ሀ) በኢትዮጵያ የንግድ ህግ መሰረት ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ኢንተርፕራይዞች በቀበሌው ቋሚ ነዋሪ


መሆናቸውን እና በአካባቢያቸው ካለው የፋይናንስ ተቋም እዳ እንደሌለባቸው የሚያረጋግጥ ማሰረጃ
ማቅረብ የሚችሉ፣

ለ) በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች በተደራጁበት ቀበሌ ቋሚ ነዋሪ ካልሆኑ


በቋሚነት ይኖሩበት ከነበረው ቀበሌ ነዋሪነታቸውን እና ከአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ብድር
እንደሌለባቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ሐ) ሁሉም የማህበሩ አባላት ወይም የተወሰኑት አባላት በሚሰማሩበት የስራ ዘርፍ ከዩንቨርስቲ፤ ኢንስቲቲዩት
እና ሙያና ቴክኒክ ማሰልጠኛ ተቋማት የተመረቁ ወይም ስልጠና የወሰዱ፣ወይም በልምድ ያገኙት
ዕውቀት ስለመኖራቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፤

መ) የመስራት አቅምና ችሎታ ያላቸው ሆነው ዕድሜያቸው ከ 18 ዓመት በላይ የሆናቸው፤

ሠ) ነባር ከሆኑ ሂሳባቸውን በአግባቡ እየሰሩ መሆናቸውን የፈጻሚ አካላት ማረጋገጥ ከቻሉ፣

ረ) ለነባር ኢንተርፕራይዞች ሂሳባቸውን በየዓመቱ ኦዲት ያስደረጉና ከቢዝነስ ፕላኑ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፣

ሰ) በንግድ ማህበራት ተደራጅተው ብድር ለመበደር የሚፈልጉ ተበዳሪዎች በማህበራት ማደራጃ በህጋዊ መንገድ
የተደራጁ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣የመተዳደሪያና የመመስረቻ ጽሁፍ ማቅረብ
ይጠበቅባቸዋል፣

ሸ) አካባቢያቸው በማንኛውም መጥፎ ሥነ-ምግባር የማይታወቁ ወይም ከደባል ሱሶች ነጻ የሆኑ፣

ቀ) የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ ወይም ቁጥሩ ያልተሰጣቸው
ቢሆኑም ለግብር ከፋይነት የተመዘገቡ ለመሆናቸው ከሚኖሩበት ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ህጋዊ ማስረጃ
ማቅረብ የሚችሉ፣

በ) በተመረጡ የሥራ ዘርፎች አዋጭ የሆነ ቢዝነስ ፕላን ማቅረብ የሚችሉ፣

ተ) የተሰማሩበት የስራ መስክ ህጋዊና በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው እና የጋብቻ ምስክር ወረቀት ወይም
ትዳር አለመኖሩን የሚያስረዳ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣

ቸ) መስፈርቱን ለሚያሟሉ ሴቶች፣ምሩቃን ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ ይሰጣል፡፡

17. የቅድመ ብድር ተግባራት፡-

1) የማስተዋወቅ ሥራ
አበዳሪ ተቋማት ከላይ የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች በአግባቡ በመስጠት ወጤታማና ትርፋማ የሆኑ
ኢንተርፕራይዞችን ለመሳብ የሚከተሉትን የማስታወቂያና የመቀስቀሻ ዘዴዎች ይከናወናሉ፡፡
ሀ) የሰው በሰው ቅስቀሳ

12
ለ) በየአካባቢው በሚደረጉ ህዝባዊ መድረኮች
ሐ) ውይይቶችና ኮንፈረንሶች በማዘጋጀት
መ) በኤግዚቢሽኖችና ባዛሮች
ሠ) በአካባቢ ባሉት የኤሌክትሮኒክስና የህትመት ሚዲያዎች
ረ) በአካባቢ ባሉት ሌሎች የህዝብ መገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም ይሆናል፡፡

2) የብድርና ቁጠባ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና መስጠት


ሀ) በምርትና አገልግሎት ስራ ላይ ለሚሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ገበያን መሰረት ያደረገ
የሙያና ክህሎት ስልጠናዎችን ይሰጣል፣

ለ) ኢንተርፕራይዞቹ ስራ ከጀመሩ በኃላ ክፍተቶች እየተለዩ ቀጣይ ስልጠናዎችን ይሰጣቸዋል፣

ሐ) ስለቁጠባ ምንነት፣ ስለቁጠባ ዓላማና አስፈላጊነት፣ ስለ ቁጠባ ዓይነቶችና ስለሚያስገኙት ጠቀሜታ ግንዛቤ
ማስጨበጫ ሥልጠና መስጠት

መ) ኢንተርፕራይዞች የሥራ ፈጣሪነትን፣ ታታሪነትን፣ ተወዳዳሪነትንና የቆጣቢነት አመለካከት ለማስፈን


የሚያስችሉ ሥልጠናዎች መስጠት፣

ሠ) ተበዳሪዎች መሰማራት የሚችሉባቸውን የሥራ ዘርፎች፣ ሊደራጁባቸው የሚችሉ የአደረጃጀት አማራጮች


እና በብድር አሰጣጥ ሂደት ሊያሟሉ የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ግንዛቤ መፍጠር፤

ረ) በሚሰማሩበት የሥራ መስክ ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችንና ሊወሰዱ የሚገቡ የመፍትሔ


አቅጣጫዎችን ማመላከት፣

ሰ) ስለሂሳብ መዝገብ አያያዝ እና የሥራ ዕቅድ ጠቀሜታ እንዲሁም አዘገጃጀት ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ፤

ሸ) ለቡድን ተበዳሪዎች መተዳደሪያ ደንብ እንዴት ማዘጋጀት እንዳለባቸው ማሰልጠን፣

ቀ) የብድር አሰጣጥና የብድር አመላለስ ሂደቱ ምን እንደሚመስል ስልጠና መስጠት ፣

በ) ደንበኛው ስለሚፈልገው የብድር መጠን በአግባቡ ማስገንዘብ፣

3) አደረጃጀት
በአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ፋይናንስ ስራ አዋጅ ቁጥር 626/2001 አንቀጽ 16 በተመለከተ መሰረት ፈቃድ የተሰጠው
ተቋም ለቡድኖችም ሆነ ለግለሰቦች ብድር መስጠት ይችላል፡፡ ተቋሙ እንደ አግባብነቱ በራሱ ውሳኔ ያለመያዣ፣
በመያዣ፣ በንብረት ወይም በቡድን ወይም በግለሰብ ዋስትና ብደር መስጠት እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ በዚህም መሰረት
ቀጥሎ በተቀመጡት አደረጃጀት አይነቶች ብድር ማግኝት እንዲችሉ ይደረጋል፡፡

ሀ) የቡድን አደረጃጀት

13
ቁጥራቸው ከ 3 እስከ 7 ህጋዊ ዕውቅና ያላቸው የግል ወይም የማህበር ኢንተርፕራይዞች በአነስተኛ የፋይናንስ ተቋሙ
የቡድን አደረጃጀት መመሪያ መሰረት የሚፈጸም ሆኖ አባላቱም በአግባቡ የሚተዋወቁና የሚግባቡ፣በራሳቸው ፍላጎት
ያለማንም ጣልቃ ገብነት የሥጋ ዝምድና እና የጾታ ልዩነት ሳይደረግባቸው በቡድን ተደራጅተው በቡድን ዋስትና
የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለ) የንግድ ማህበራት አደረጃጀት

በንግድ ማህበራት አደረጃጀት መሠረት (በህብረት ሽርክና ማህበር እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግልማህበር) በህጋዊ መንገድ

የተደራጁ መሆናቸውን የሚያስረዳ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ኢንተርፕራይዞችን እንደየተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ባህሪ

በብድር ዋስትና ፈንድ ዋስትና፣ በከተማ አስተዳደር/ወረዳ ዋስትና እና ሌሎች የዋስትና አማራጮችን በማቅረብ

የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ሐ) የግል ተበዳሪዎች

የግል ተበዳሪዎች የምንላቸው የንብረት፣ የደመወዝ ወይም የፈጠራ የፕሮጀክት ሀሳብ የያዘ የንግድ ስራ ዕቅድ ዋስትና
በማቅረብ ብድር ለመበደር ፍላ¯ት ያላቸው ኢንተርፕራይዞች ማለት ነው፡፡

18. የንግድ ሥራ ዕቅድ ስለማቅረብ


የንግድ ሥራ ዕቅድ በግል ፣ በቡድን ፣ በንግድ ማህበር ተደራጅተው የብድር አገልግሎት ጥያቄያቸውን የሚያቀርቡበት
መነሻ ሰነድ ሲሆን በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጪያ ጣቢያ ባለሙያዎች ቴክኒካል ድጋፍ በብድር ጠያቂው
ኢንተርፕራይዝ ባለቤትነት ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡

የንግድ ዕቅድ 5 ዋና ዋና ክፍሎች ሲኖሩት የመጀመሪያው ክፍል አጠቃላይ መረጃ፣ሁለተኛው ክፍል የገበያ ዕቅድ፣
ሶስተኛው የምርት ዕቅድ፣ አራተኛው የአደረጃጀትና የሰው ኃይል ዕቅድ እና አምስተኛው የፋይናንስ ዕቅድ መያዝ
ይኖርበታል፡፡

የሚዘጋጀው የንግድ ዕቅድ ከአነስተኛ ፋይናንስ ተቋማት ጋር የተናበበና የተጣጣመ ሆኖ በ 3 ኮፒ ተዘጋጅቶ 1 ኛው


ለኢንተርፕራይዙ፣ 2 ኛው ለአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጪያ ጣቢያ እና 3 ኛው ለአበዳሪ ተቋሙ ከድጋፍ ደብዳቤ
ጋር እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡

19. ከደንበኞች የሚጠበቁ ማስረጃዎች

1) የሚሰማራበት የስራ መስክና የብድር መጠየቂያ ማመልከቻ፣


2) የብድር ዋስትና ፈንድ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ማስረጃ፣

14
3) በቅድመ ብድር የቁጠባ ሥርዓት መሰረት ቁጠባ መቆጠቡን የሚያስረዳ ማስረጃ፣

4) የግል ተበዳሪ ወይም የበቃ ኢንተርፕራይዝ ከሆነ በዋስትና የሚቀርበው ንብረት (የስራ መሳሪያ፣ የቤት ካርታ፣
የተሸከርካሪ ሊብሬ) ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ፣

5) በዋስትና የሚቀርበው ንብረት ከዕዳና እገዳ ነፃ መሆኑን የሚያስረዳ መረጃ፣

6) በዋስትናነት የሚቀርበው የደመወዝ ዋስትና ከሆነ ዋስትናውን የሚወስደው መስሪያ ቤት የሚፅፈው


የዋስትና ማረጋገጫ ደብዳቤ፣

7) በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የዋና ምዝገባ፣

8) የጋብቻ የምስክር ወረቀት ወይም ትዳር አለመኖሩን የሚያስረዳ ስልጣን ከተሰጠው አካል ማስረጃ፣

9) የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣

20. የዋስትና አይነቶች

በተበዳሪ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርቡ ዋስትናዎች አነስተኛ የፋይናንስ አቅራቢ ድርጅቶች የሚሰጡት ብድር በወቅቱ
እንዲመለስ ከማድረጉ በተጨማሪ ተቋሞቹ የሚሰጡትን አገልግሎት ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ፣ በብድር
የሚቀርበው ገንዘብ ከተለያዩ የቁጠባ ምንጭ የተሰባሰቡ በመሆናቸውና የብድር መመለስና አለመመለስ ከፋይናንስ
ተቋሙ ሕልውና ጋር በቀጥታ ተያያዥነት ያለው መሆኑ እና ኢንተርፕራይዞች ባጠቃላይም የማህበረሰቡን በብድር
የመጠቀም፣ ብድር ወስዶ በጊዜው የመመለስ ባህልን ለማዳበር ያግዛል፡፡ በመሆኑም የተሰጡ ብድሮች በአግባቡ
እንዲመለሱ ከማድረግ አኳያ ማንኛውም ተበዳሪ ለሚወስደው ብድር ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና እንደ እድገት ደረጃው
ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

ስለሆነም የብድር ዋስትና ዓይነቶች፡

1) የብድር ዋስትና ፈንድ (Credit guarantee fund)


ሀ) የክልል መንግስታት በክልላቸው በየዓመቱ ሊሰጥ የታቀደውን የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን
የብድር ፍላጎት ግምት ውስጥ በማስገባት በየዓመቱ የሚታደስ የብድር ዋስትና ፈንድ እንዲቋቋም
ያደርጋሉ፡፡

ለ) የሚቋቋመው የዋስትና ፈንድ በአነስተኛ የፋይናንስ አቅራቢ ተቋም ዋና መ/ቤት በዝግ ሂሳብ ውስጥ
በሚከፈት የተቀማጭ ቁጠባ ሂሳብ ገቢ የሚደረግ ሲሆን በተቀማጩ ገንዘብ ላይ የፋይናንስ አቅራቢ
ተቋሙ 5 በመቶ ወለድ ይከፍልበታል::

ሐ) የዋስትና ፈንዱ በየዓመቱ አዲስ የበጀት ዓመት እንደገባ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተወስኖ ወደ ፋይናንስ
አቅራቢ ተቋሙ ሂሳብ ገቢ ይደረጋል::

መ) የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ጽ/ቤቶች ኢንተርፕራይዞች በአበዳሪ ተቋሙ
የተፈቀደላቸውን የብድር መጠን እና የዕድገት ደረጃቸውን ታሳቢ በማድረግ ከብድር ዋስትና ፈንዱ
15
የብድር ዋስትና ሽፋን እንዲያገኙ ለአበዳሪው የፋይናንስ ተቋም በአድራሻ በሚጻፍ ደብዳቤ
ያሳውቃሉ::

ሠ) አነስተኛ የፋይናንስ አቅራቢ ተቋሞች የብድሩን 10 በመቶ ዋስትና እንዲሸፍኑ ይደረጋሉ::

ረ) በዋስትና ፈንዱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ኢንተርፕራይዞች የብድሩን 1.5 በመቶ ለዋስትና ፈንዱ ማጠናከሪያ
ይከፍላሉ፡፡

የዋስትና ፈንድ አተገባበር

ሀ) ጀማሪ በቡድን ፣ በግል እና በንግድ ማህበር የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች

(1) ጀማሪ በንግድ ማህበር የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ቅድመ ቁጠባ 20 በመቶ ሲያሟሉ 70 በመቶ
ከብድር ዋሰትና ፈንድ የዋስትና ሽፋን በማግኘት ብድር እንዲበደሩ ይደረጋል::

(2) አበዳሪው የፋይናንስ ተቋም የብድሩን 10 በመቶ ይሸፍናል::

ለ) ታዳጊ በግል ፣ በቡድን እና በንግድ ማህበር የተደራጁ ተበዳሪዎች

(1) በኤክስፖርት ወይም ተኪ ምርት በማምረት የሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ቅድመ ብድር ቁጠባ 15
በመቶ ሲያሟሉ 75 በመቶ፣ ትኩረት በሚሰጣቸው የስራ ዘርፍ የሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ቅድመ
ብድር ቁጠባ 20 በመቶ ሲያሟሉ 70 በመቶ የብድር ዋስትና ሽፋን ያገኛሉ፡፡

(2) አበዳሪው የፋይናንስ ተቋም የብድሩን 10 በመቶ ይሸፍናል::

ሐ) የበቁ በግል ፣ በቡድን እና በንግድ ማህበር የተደራጁ ተበዳሪዎች

(1) በኤክስፖርት ወይም ተኪ ምርት በማምረት የሚሰማሩ ኢንተርራይዞች ቅድመ ብድር ቁጠባ 15
በመቶ ሲያሟሉ 75 በመቶ፣ ትኩረት በሚሰጣቸው የሥራ ዘርፍ የሚሰማሩ ኢንተርፐራይዞች ቅድመ
ብድር ቁጠባ 20 በመቶ ሲያሟሉ 70 በመቶ የብድር ዋስትና ሽፋን ያገኛሉ፡፡

(2) አበዳሪው የፋይናንስ ተቋም የብድሩን 10 በመቶ ይሸፍናል::

መ) በኤክስፖርት ወይም ተኪ ምርት በማምረት እና ትኩረት በሚሰጣቸው የሥራ ዘርፍ ከሚሰማሩት ውጭ


ያሉ ኢንተርፕራይዞች የብድር ዋስትና ሽፋን ተጠቃሚ አይሆኑም፡፡ የአነስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ
ተቋማት በሚጠቀሙባቸው የዋስትና አማራጮች ተጠቅመው እንዲበደሩ ይደረጋል፡፡

ሠ) በብድር ዋስትና ሽፋን የተመለሰ ብድር ለአነስተኛ ፋይናንስ ተቋማት ገቢ ቢደረግም ከተበዳሪ
ኢንተርፕራይዞቹ ቀጣይ ክትትል ተደርጎ ተመላሽ ሊሆን ይገባል፡፡ ለዚህም በየደረጃው ያለ አቃቤ ህግ
እንዲከታተለውና እንዲያስፈጽም ይደረጋል፡፡

2) ሶስትዮሽ ውል ስምምነት
በምርት ገዢ፣አቅራቢና አበዳሪ ድርጅት መካከል በሚደረግ የሦስትዮሽ ውል በመጠቀም በማንኛውም ደረጃ
ላይ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ከአነስተኛ የፋይናስ ተቋም ብድር ሊበደሩ ይችላሉ:: በዚህም መሰረት፡-

16
ሀ) የተመረተውን የኢንተርፕራይዞች ምርት ወይንም አገልግሎት ግዢ የሚፈፅመው ሁለተኛ ወገን
ምርቱን/አገልግሎቱን ለመግዛት መስማማቱን፣ የግዢውን ዋጋ የሚገልፅ እና ለአቅራቢ ኢንተርፕራይዞች
ክፍያውን ከመፈጸሙ በፊት ለአበዳሪ የፋይናንስ ተቋሙ ብድሩን ቀንሶ ለመክፈል መስማማቱን የሚያረጋግጥ
ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል::

ለ) በማንኛውም ደረጃ ላይ የሚገኙ የግል ፣ የቡድን እና የንግድ ማህበር ተበዳሪ ኢንተርፕራይዝ በቅድመ ብድር
መቆጠብ ያለባቸው ቁጠባ እንዳለ ሆኖ ሌላ የግል ዋስትና ማቅረብ ሳያስፈልግ ከብድር ዋስትና ፈንድ
የብድሩን 50 በመቶ የዋስትና ሽፋን ብቻ በማቅረብ ብድር እንዲሰጣቸው ይደረጋል::

3) የንብረት/የደመወዝ ዋስትና
ከብድር ዋስትና ፈንድ (Credit guarantee fund) የዋስትና ሽፋን ማግኘት ለማይገባቸው በማንኛውም ደረጃ ላይ የሚገኙ በንግድ
ማህበር የተደራጁ እና የግል ተበዳሪዎች በቅድመ ብድር መቆጠብ ያለባቸው ቁጠባ እንዳለ ሆኖ ልዩነቱን የዋስትና ሽፋን በግል
በሚያቀርቡት የንብረት/የደሞወዝ ዋስትና ብድር እንዲሰጣቸው ይደረጋል::

ከብድር ዋስትና ፈንድ የዋስትና ሽፋን ማግኘት የማይገባቸውን ኢንተርፕራይዞች የማጣራቱ ስራ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጪያ
ጣቢያ ተግባር ይሆናል፡፡

4) የጠለፋ ዋስትና/የቡድን ዋስትና


ከብድር ዋስትና ፈንድ የዋስትና ሽፋን ማግኘት ለማይገባቸው በማንኛውም ደረጃ ላይ የሚገኙ በንግድ ማህበር የተደራጁ ተበዳሪዎች
በቅድመ ብድር መቆጠብ ያለባቸው ቁጠባ እንዳለ ሆኖ ልዩነቱን የዋስትና ሽፋን ከማህበሩ አባላት አንዱ አባል ለሁሉም ሁሉም አባላት
ለአንዱ በጋራና በተናጠል ዋስ የሚሆኑበትና ለብድሩ መመለስ የአንድነትና የጋራ ኃላፊነት የሚወሰድበት የዋስትና ስርዓት ነው፡፡

5) የመጋዘን አገልግሎት ዋስትና


በህጋዊ መንገድ የመጋዘን አገልግሎት እንዲሰጥ ከተቋቋመ ድርጅት የምርት ጥራቱ የተረጋገጠና በመጋዘን የተከማቸን
ምርት የአገልግሎት ደረሰኝ አበዳሪ ተቋሙ ፣ ተበዳሪውና ምርቱን አስቀማጩ የሚያደርጉትን ስምምነት እንደዋስትና
በመያዝ ብድር ይሰጣል::

አነስተኛ የፋይናንስ አቅራቢ ተቋማቱ ከላይ ከተቀመጡት የብድር ዋስትና አይነቶች በተጨማሪ ሌሎችንም የዋስትና
አማራጮች መጠቀም ይችላሉ፡፡

2) የንግድ ሥራ ዕቅድ የአዋጭነት ግምገማ (Business plan appraisal)

አበዳሪው ተቋም በአካባቢው ያሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን በአግባቡ በመዳሰስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን
የመገምገሚያ ነጥቦችን መሰረት በማድረግ የቀረበውን የንግድ ሥራ ዕቅድ የአዋጭነት ትንተና ያካሄዳል፡፡

ሀ) በተሰማሩበት የምርት፣ የንግድ ወይም የአገልግሎት ሥራ አስመልክቶ የክህሎትና ሥልጠና የወሰዱ መሆናቸውን
ማረጋገጥ ፣

ለ) ደንበኛው የተሰማራበት የሥራ መስክ ያለው የገበያ አዋጭነት፣ የግብአት አቅርቦት፣ በሥራው ላይ ያለው ልምድ ፣
ያደረገው ቅድመ ዝግጅት፣ በአካባቢው ያሉ ተፎካካሪዎችና የገንዘብ እንቅስቃሴውን ይገመግማል፣

17
ሐ) ለምርቱ/ለአገልግሎቱ አስፈላጊ የሆኑ የጥሬ ዕቃ አቅርቦት መገኘቱን፤ ዘላቂነት ያለው መሆኑን ምርቱ/ አገልግሎቱ
በቂ ገበያ መኖሩን፤ እንዲሁም ከትርፋማነት አንፃር እና ከንግዱ የሚገኘው ትርፍ ብድሩን የመመለስ አቅሙን
መገምገም፣

መ) ንግዱ የሚካሄድበት የማምረቻና የመሸጫ ቦታ ለስራው ምቹና ተስማሚ እንዲሁም ህጋዊ መሆኑን ያረጋግጣል ፣

ሠ) ከሥራው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የኢንተርፕራይዙን ጠንካራ እና ደካማ ጎን እንዲሁም ስጋቶችና መልካም


አጋጣሚዎች ይተነትናል፡፡ በዚህም ደንበኛው በተሰማራበት የስራ መስክ ይኖራል ተብሎ የታሰበው የስጋት
መጠንና የብድር የመመለስ አቅም ደረጃ ያወጣለታል፣

ረ) የቀረቡትን አጠቃላይ የብድር ሂደት ሰነዶች ከተቋሙ የብድር አሰራር አንጻር ይተነትናል፣

ሰ) የንግዱን ህጋዊነትና በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ያረጋግጣል፤

ሸ) የንግዱ ባለቤቶች ንግዱን ለማካሄድ ያላቸውን የአመራር ብቃት ያረጋግጣል፣

ቀ) ንግዱ ሊፈጥር የሚችለውን የሥራ ዕድልና ለህብረተሰቡ የሚሰጠው ማህበራዊ ጠቀሜታ ይገመግማል፣

በ) ሕጋዊነትን ከማረጋገጥ አንፃር የንግድ ፈቃድና ምዝገባ ማድረጋቸውን ማረጋገጥ፣

ተ) ኢንተርፕራይዞች ለሚወስዱት ብድር በቂና አስተማማኝ ዋስትና ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣

ቸ) ምርታቸውን ለመሸጥ የሚያስችል አስተማማኝ የገበያ ትስስር ያላቸው ስለመሆኑ ማረጋገጥ፣

ኀ) ፈቃደኛ፣ታታሪና መልካም ሥነ-ምግባር ያላቸው አባላት የተደራጁና ቋሚ አድራሻቸው የታወቀ መሆናኑን


ማረጋገጥ፣

ነ) ያለፈ ብድር አመላላስ ታሪካቸው ጥሩ የሆነና ቁጠባ ለማስቀመጥ ያደረጉትን ጥረት ማረጋገጥና ግብር
ስለመክፈላቸው ማስረጃ ያቀረቡ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣

ኘ)ነባር ኢንተርፕራይዞች ከሆኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ዓመታዊ የሂሳብ መግለጫና የተመረመረ የሒሳብ ሰነድ
ያቀረቡ መሆነቸውን ማረጋገጥ::

3) የብድር መጠን

በመንግስት የትኩረት አቅጣጫ እንደ ሌሎች መንግስታዊ ድጋፎች ሁሉ ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጠው የብድር መጠን
እንደተሰማሩበት የስራ አይነት፣ ቢዝነሱ ብድሩን ለመክፈል ያለው አቅም እና የወሰዱትን ብድር በአግባቡ ለመጠቀም
የሚያስችል የገንዘብ አጠቃቀም አስተዳደር ብቃት በየእድገት ደረጃቸውና በንግድ ስራ እቅዱ መሰረት ይወሰናል፡፡

በዚህ መሰረት በየስራ ዘርፎቹ እንደየዕድገት ደረጃቸው ሊቀርብ የሚገባው የፋይናንስ /ብድር/ አቅርቦት መጠን
የወቅቱን የገንዘብ ግሽበት፣የተለያዩ የአነስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ከሚሰጡት ብድር በመነሳትና የወቅቱን
የስራ እንቅስቃሴ ግምት ውስጥ በማስገባት በአባሪው ላይ በግልጽ ቀርቧል፡፡ የብድር አሰጣጥ አገልግሎት
የኢንተርፕራይዞችን የዕድገት ደረጃ ያገናዘበ፣በየደረጃው ሊጠቀሙ ይችላሉ ተብሎ የተገመተውን የመስሪያ መሳሪያ
ከግምት ውስጥ ያስገባና የኢንተርፕራይዞችን የደረጃ ትርጉም ማለትም የሚያንቀሳቅሱትን ካፒታል እና የሰው ኃይል
18
ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ይህ የእድገት ደረጃን መሰረት ያደረገ የብድር አገልግሎት ኢንተርፕራይዞቹ ከሚያዘጋጁት የተጠና
የንግድ ስራ እቅድ ጋር የተጣጣመ መሆን ይኖርበታል፡፡ በተለይም ጀማሪ ኢንተርፕራይዞች ስራ ሲጀምሩ በአነስተኛ
ካፒታል የሚጀመሩ ስራዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉና ደረጃ በደረጃ የገበያውን የውድድር ሜዳ እየተለማመዱ
ውጤት እንዲያሳዩ በዘርፍ አስፈፃሚ ባለሞያዎች ምክር ማግኘትና መታገዝ ይኖርባቸዋል፡፡

21. ብድር የማጽደቅ ሥልጣን

1). የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጪያ ጣቢያ በውክልና የተሰጠውን የብድር መጠን በመገምገም ያጸድቃል፡፡

2). ከአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጪያ ጣቢያ ውክልና በላይ የሆነ የብድር መጠን አስተያየቱን በመስጠት
በሚቀጥለው ደረጃ ባለው የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አቅርቦ ያጸድቃል፡፡

3). የሥራ ዕቅዱ የቀረበለት አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ጽ/ቤት የስራ ዕቅዱን አዋጭነት ግምገማ በአግባቡ
በማካሄድ ከ 5 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ብድሩ በየደረጃው እንዲጸድቅ ያደርጋል፡፡

4). በዚህ መሰረት የአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት በተዋረድ ብድር የማጽደቅ ሥልጣንና የብድር ውል መፈጸም
እንደ አበዳሪ ተቋም አደረጃጀትና አሰራር ይወሰናል፡

22. በዋስትና የተያዘን ንብረትና ብድርን የኢንሹራንስ ሽፋን እንዲያገኝ ማድረግ የማይክሮ ኢንሹራንስ አገልግሎት

በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በግል፣በቡድን፣ በንግድ ማህበር የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች


የተፈቀደላቸው ብድር ከመለቀቁ በፊት በሚከተለው ሁኔታ የህይወትና ንብረት መድህን ግዴታ ሊወጡ ይገባል፡፡

1) የግል/ማህበር ኢንተርፕራይዝ ተበዳሪዎች የንብረት መድህን ዋስትና

ሀ) የግል ተበዳሪ ኢንተርፕራይዞች ለተፈቀደላቸው ብድር የቀረበው ማስያዣ የንብረት ዋስትና ከሆነ ብድሩ
ተከፍሎ እስኪጠናቀቅ ከአበዳሪ ተቋሙ ወይም ከሁለተኛ ወገን የመድህን አገልግሎት ድርጅት (insurance
company) በየዓመቱ የሚታደስ የመድህን ዋስትና እንዲገቡ ይደረጋል:፡ ይህ የመድህን ዋስትና ሽፋን
የሚያገለግለው በዋሰትና ለቀረበው ንብረት ብቻ ይሆናል፡፡

ለ) የበቁ ኢንተርፐራይዞች ለሚበደሩት ብድር የብድር ዋስትና ፈንድ ሽፋን የማያገኙ በመሆናቸው ለሚበደሩት
ብድር የንብረት ዋስትና የሚያቀርቡ ከሆኑ በዋስትና የሚያዘው ንብረት በተጠቀሰው መሰረት የመድን ዋስትና
ሽፋን ሊደረግለት ይገባል፡፡ አፈጻጸሙም ለግል ኢንተርፕራይዝ ተበዳሪዎች በተጠቀሰው መስረት ይሆናል፡፡

ሐ) የብድሩ መመለሻ ጊዜ ከአንድ ዓመት በላይ ከሆነ ተበዳሪው ግለሰብ የመድህን ሽፋኑን ማሳደስ ይኖርበታል፡፡
በግንባር ቀርቦ የማያሳድስ ከሆነ አበዳሪው የፋይናንስ ተቋም ከራሱ ወጪ በማድረግ የሚያሳድስ ሲሆን
በማሳደስ ሂደቱ ወጪ የተደረጉትን ሂሳቦች በሙሉ በቀሪው ብድር ላይ በመጨመር ያስከፍላል፡፡

19
መ) የመድን ሽፋን አገልግሎቱ በአበዳሪ ተቋሙ የሚሰጥ ከሆነና የብድሩ መመለሻ ጊዜ ከአንድ ዓመት በላይ ከሆነ
በየዓመቱ ከቀሪው የብድር ባላንስ ላይ አረቦን የሚታሰብ ሲሆን ተበዳሪው የመጀመሪያ ዓመት ላይ ሆኖ
ለሚቀጥለው ዓመት የአረቦን ክፍያ የሚውል የአረቦን ቁጠባ (Insurance saving) እንዲቆጥቡ ይደረጋል፡፡
በዓመቱ መጨረሻ የቁጠባው ባላንስ ወደ መድሕን አረቦን ክፍያ ይተላለፋል፡፡

2) የቡድን ተበዳሪ ኢንተርፕራይዞች የህይወት መድን ዋስትና

ሀ) በቡድን የጠለፋ የብድር ዋስትና ሥርዓት የተደራጁ ተበዳሪ ኢንተርፕራይዞች እያንዳንዳቸው በግል የህይወት
መድህን ዋስትና (Micro life insurance) ከአበዳሪው የፋይናንስ ተቋም መግዛት ግዴታ ይሆናል::

ለ) ለዚህ አገልግሎት በእያንዳንዳቸው የብድር ድርሻ በአነስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት በሚወሰነው
መሠረት አረቦን የሚከፈሉ ሲሆን ተበዳሪ ኢንተርፕራይዞች የራስን ሕይወት በራስ እጅ ከማጥፋት ውጭ
በሌላ በማናቸውም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩ በሟች ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ቀሪ የብድር
ባላንስ ይሰረዛል፤ በጠለፋ ዋስትና ያስያዙት ንብረትም ሆነ ሌላ ዋስትና ከእዳው ነፃ ይደረጋል::

ሐ) ሟች በሕይወት እያሉ ከብድሩ የከፈሉት የብድር ተመላሽ ካለ ለወራሽ ተመላሽ አይደረግም::

መ) የብድሩ መመለሻ ጊዜ ከአንድ ዓመት በላይ ከሆነ በየዓመቱ ከቀሪው የብድር ባላንስ ላይ አረቦን ሚታሰብ
ሲሆን ተበዳሪው የመጀመሪያ ዓመት ላይ ሆኖ ለሚቀጥለው ዓመት የአረቦን ክፍያ የሚውል የአረቦን ቁጠባ
(Insurance saving) እንዲቆጥቡ ይደረጋል፡፡ በዓመቱ መጨረሻ የቁጠባው ባላንስ ወደ መድሕን አረቦን ክፍያ
ይተላለፋል፡፡

23. የብድር ውል ስለመፈጸም

የብድር ውል ስምምነት መፈጸም እንደ አበዳሪ ተቋም አደረጃጀትና አሰራር የሚወሰን ይሆናል፡፡

24. ብድር ማሰራጨት

ቅድመ ብድር መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች ከተሟሉ በኋላ ለብድር የጸደቀው ገንዘብ ወደ ተበዳሪዎች የቁጠባ
ሂሳብ ገቢ ይደረጋል፡፡ ወይም በጥሬ ገንዘብ ይሰጣቸዋል፡፡ እንደሚሰማሩበት የስራ ዘርፍና የግዢ ዕቅድ በተለያየ ጊዜ
ይለቀቅላቸዋል፡፡

25. የአገልግሎት ክፍያ

1) ለአበዳሪ ተቋማት የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ

አበዳሪ ተቋማት ለሚሰጡት አጠቃላይ የብድር አገልግሎት እያንዳንዱ ተበዳሪ ኢንተርፕራይዝ ከፀደቀለት ብድር ላይ
የሚከፍለው ክፍያ እንደ አበዳሪ ተቋሙ አደረጃጀትና አሰራር የሚወሰን ይሆናል፡፡

20
2) ለዋስትና ፈንድ ማሳደጊያ የሚውል የአገልግሎት ክፍያ

ኢንተርፕራይዞችን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ በክልል መንግስታት በሚመቻችና በልማት አጋሮች ድጋፍ
ለሚቋቋመው የዋስትና ፈንድ ብድሩ የተፈቀደላቸው ኢንተርፕራይዞች በጸደቀላቸው ብድር ላይ 1.5 በመቶ
የአገልግሎት ክፍያ እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡

26. የብድር ወለድ ምጣኔ

ተበዳሪ ኢንተርፕራይዞች ለሚበደሩት ብድር የብድር ወለድ ምጣኔን በተመለከተ አበዳሪ ተቋማቱ እንደየአካባቢው
ተጨባጭ ሁኔታ የሚወስኑት ይሆናል፡፡ ሆኖም የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋማቱ የማህበራዊ አላማቸውንና
ቀጣይነታቸውን በሚያረጋግጥ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ወለድ ምጣኔ ይወስናሉ፡፡

27. የእፎይታ ጊዜ

ተበዳሪ ኢንተርፕራይዞች ብድር ወስደው ወደ ተግባር ከመግባታቸው በፊት ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ
ሁኔታዎችን ለማዘጋጀት በቀጥታ ወደ ምርት አቅርቦት የማይገቡበት ሁኔታ ስለሚኖር፣

1) እንደስራው ባህሪ እየታየ እስከ 4 ወር ድረስ የእፎይታ ጊዜ የሚሰጥበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ ይሁን እንጂ ተበዳሪዎቹ
ብድሩን ከተበደሩበት ቀን ጀምሮ አበዳሪ ተቋሙ በተፈቀደው ብድር ላይ ወለድ ያሰላል ፡፡

2) ተበዳሪ ኢንተርፕራይዞች የሚያስፈልጓቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉላቸው የእፎይታ ጊዜ በመስጠት


ብድር እንዲወስዱ ማድረግ አላስፈላጊ የሆነ የወለድና ሌሎች ወጪዎች እንዳያስከትልባቸው ብድር
ከመሰጠቱ በፊት ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፣

3) በአመት አንድ ጊዜ፣ በአመት ሁለት ጊዜ ወይም በአመት አራት ጊዜ ተጠቃለው ለሚመለሱ ብድሮች የእፎይታ
ጊዜ አይሰጣቸውም፡፡

ክፍል ሶስት

ድህረ ብድር ተግባራት


በድህረ ብድር የሚደረግ ድጋፍና ክትትል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ
መሰረት በኢኮኖሚው ውስጥ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸውን፣ የሚፈለገውን የቴክኖሎጂ ሽግግርና ሥራን
ከመፍጠር አንፃር በትክክለኛው መሥመር ላይ መሆናቸውን ከማረጋገጥ ባሻገር የተበደሩት ብድር በጤናማ ሁኔታ ላይ
መሆኑን ለማረጋገጥ ያስችላል::

28. በኢንተርፕራይዝ ደረጃ የሚደረግ ድጋፍና ክትትል

አበዳሪው የፋይናንስ አቅራቢ ተቋም እና የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ መደበኛ የጊዜ
ሰሌዳ በማውጣት ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል ያደርጋሉ:: በዚህም
21
1) ብድሩ በየትኛውም የተቋሙ መዋቅር ቢፀድቅም ለደንበኛው ድጋፍና ክትትል በማድረግ ውጤታማ እንዲሆን
ማስቻል እና ሌሎች ሥራዎች በሙሉ የሚከናወኑት ብድሩ በተጠየቀበት ጽ/ቤት ባሉ ሠራተኞች ይሆናል፡፡

2) ሁሉም ደንበኞች ብድሩን በወሰዱ ከ 15 እስከ 30 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ብድሩን በተባለው ተግባር ላይ
ማዋላቸውን በአካል ያረጋግጣሉ፣

3) ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅርበውት በነበረው የሥራ ዕቅድ መሠረት እየተጓዙ መሆኑን
ማረጋገጥ፣

4) ኢንተርፕራይዞች ከካፒታላቸው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የስቶክ ወይንም የማሽነሪ ንብረት መኖሩን ማረጋገጥ፣

5) በሚያቀርቡት ምርት/አገልግሎት ዙሪያ ያለውን የገበያ ሁኔታ መገምገምና እንዲጠናከሩም አስፈላጊውን


ምክርና ድጋፍ ማድረግ፣

6) የኢንተርፕራይዞቹ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ በአግባቡ እየተከናወነ መሆኑን ማረጋገጥና ድጋፍና ምክር
መስጠት፣

7) በኢንተርፕራይዞች ዘንድ ያሉትን ጉድለቶችና ክፍተቶች በመለየት በአካባቢው የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ


ትምህርትና ስልጠና ተቋም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲሰጥ ማድረግ፣

8) ኢንተርፕራይዞች በተሰማሩበት ሥራ መስክ ያሉትን ምቹ ሁኔታዎች (opportunities) እና ስጋቶች


(threats) በመለየት እንደየሁኔታው ችግሮችን መፍታትና ምቹ ሁኔታዎቸን በበለጠ በመጠቀም
ኢንተርፕራይዞች እድገታቸው እዲፋጠን መደገፍ፣

9) የጥሬ ዕቃ አቅርቦትን ሁኔታ በመገምገም ድጋፍና ምክር መስጠት፣

10) ኢንተርፕራይዞች መደበኛና የውዴታ ቁጠባቸውን በአግባቡ እየፈፀሙ መሆኑን ማረጋገጥና በውዴታ ቁጠባም
የበለጠ እንዲጠናከሩ ማበረታታት፣

11) ሁሉም የማህበሩ አባላት በሚፈለገው ደረጃ በሥራው ላይ ሙሉ ጊዜያቸውን እያዋሉ መሆናቸውን፣
በአካልም መኖራቸውን እንዲሁም በማህበሩ ውስጥ የጥቂት ግለሰቦች ተፅዕኖ ያልተስፋፋ መሆኑን ማረጋገጥ፣

12) የወጪ መዝገባቸውን በመገምገም የተጋነኑና ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚገባቸውን የወጪ አይነቶች
በመለየት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ ምክር መስጠት፣

13) የሥራ መስካቸውን የቀየሩ ካሉም ምክንያቱን ማጥናትና የስራ መስኩም የማያዋጣ መሆኑ ከተረጋገጠ
ብድሩን እንዲመልሱ ማድረግ፡፡ ይህንንም ተግባራዊ ማድረግ እንዲቻል በብድር ውል ስምምነቱ እንዲካተት
ይደረጋል፡፡

14) ብድሩን በተጠየቀበት የሥራ መስክ ያላዋሉትን መለየትና በመፍትሔው ዙሪያ ደንበኛውን ማማከርና
አቅጣጫ መስጠት፣

15) የሌሎች አካላትን ድጋፍ የሚሹ ጉዳዮችን መለየትና ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፣

22
16) ደንበኞች በተበደሩት የስራ መስክ ውጤታማ የሚሆኑበትንና ብድሩን መመለስ የሚያስችላቸው የገበያ ሁኔታ
መኖሩን ማረጋገጥና እንደ አስፈላጊነቱ የገበያ ትስስር የሚፈጠርበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣

17) ብድሩን የሚመልሱበትን ቀንና የሚመልሱትን የገንዘብ መጠን በትክክል ማሳወቅ፣

18) በዋስትና የተያዘው ንብረት ያለበትን ደረጃ በየጊዜው መከታተል፣

19) ደንበኞች ያሉባቸውን የክህሎት ክፍተቶች መለየት፣

20) ደንበኞች በተሰማሩበት የሥራ መስክ ውጤታማ ላይሆኑ እንደሚችሉ ከተገመተና በብድር አመላለሱም ላይ
ችግር ያስከትላሉ ተብሎ ከታሰበ ከመፍትሄ ሃሳብ ጋር ሪፖርት ማድረግ፣

21) አካላዊ ጉብኝት የተደረገበትን ዝርዝር ሁኔታ የያዘ የድጋፍ አሰጣጥ መዝገብ ማዘጋጀት፣ በድጋፍ መዝገቡ ላይ
ጉብኝት የተደረገላቸው ደንበኞች እንዲፈርሙ ይደረጋል፡፡ ቢዝነሱ ላይ ለየት ያለነገር ሲያጋጥም ለሌሎች
ኢንተርፕራይዞች በተሞክሮነት እንዲያገለግል በተንቀሳቃሽ ምስልና ፎቶግራፍ እንዲነሳ ይደረጋል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና ተግባራትንና ሌሎችንም ዘላቂና ቋሚ በሆነ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በመገምገም የከተሞች
የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲና የፋይናንስ አቅራቢው ተቋም ድጋፍ መስጠት ዋነኛ መደበኛ
ተግባራቸው ይሆናል::

ከዚህ በተጨማሪ ጀማሪ ኢንተርፕራይዞች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ፤

ሀ) በምርት ጥራት

ለ) በገበያ ውስጥ ዘልቆ የመግባት

ሐ) በቴክኒክና ማኔጅመንት

መ) በንብረትና ሂሳብ አያያዝ

ሠ) አባላት በቅንጅትና በህብረት የመስራት እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ በማተኮር ድጋፍና ክትትል


መስጠት ይኖርባቸዋል::

29. የብድር መመለሻ ጊዜ

ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሰማሩበትን የስራ መስክ ግምት ውስጥ ያስገባ ከፍተኛው የብድር የቆይታ
ጊዜ 36 ወር ወይም 3 ዓመት ብቻ ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት እንደተሰማሩበት የስራ ዘርፍ የሚወሰን

1) በየወሩ የሚመለስ

2) በየሶስት ወሩ የሚመለስ

3) በዓመት ሁለት ጊዜ ወይም አራት ጊዜ ተጠቃሎ የሚመለስና

4) በዓመት አንድ ጊዜ ተጠቃሎ የሚመለስ ብድር ይሰጣል፡፡

23
5) በየወሩ ብድር የሚመልሱ ኢንተርፕራይዞች የምንላቸው ኢንተርፕራይዞቹ ብድር ከወሰዱበት ጊዜ ጀምሮ ወይም
የእፎይታ ጊዜያቸው ከተጠናቀቀ በኋላ በየጊዜው ገቢ ያገኛሉ ተብለው የሚገመቱ የሥራ መስኮች ላይ
የሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞች በዚህ የብድር አመላለስ ሥርዓት ውስጥ እንዲካተቱ ይደረጋል፡፡

6) ምርታቸው ወይም አገልግሎታቸው በየጊዜው እየተሸጠ ገቢ የማያስገኝላቸው እንደ ከተማ ግብርና የመሳሰሉት
የሥራ መሥኮች ላይ የሚሰማሩ የብድር ተጠቃሚዎች በዓመት በአንድ ጊዜ ተጠቃሎ በሚመለስ ፤በዓመት
በሁለት ጊዜ ወይም አራት ጊዜ ተጠቃሎ በሚመለስ የብድር አመላለስ ሥርዓት ውስጥ እንዲካተቱ ይደረጋል፡፡

30. ብድር ማስመለስ

ተበዳሪዎች ብድሩን ለመመለስ በገቡት የውል ስምምነት መሰረትና በአበዳሪው ተቋም የብድር አመላለስ ሥርዓት
መሠረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡

1) ማበረታቻ (incentives)
የፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት በቁጠባ፣በብድር አመላለስና አጠቃቀም እና በመሳሰሉት የደምበኞችን አፈፃፀም
እየገመገመ የወለድ ማሻሻያና የልዩ ልዩ ማበረታቻ ያደርጋል:: አፈጻጸሙም በአበዳሪ ተቋም የውስጥ አሰራር
መሠረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡

2) ብድር የማስመለስ ምጣኔና የአበዳሪ ተቋማት ቀጣይነት


ሀ) ኢንተርፕራይዞች ቀጣይነት ያለው የብድር አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉና ለብድር የሚሆን በቂ የገንዘብ
አቅርቦት እንዲኖር አስቀድሞ የተሰጡ ብድሮች በመመለሽያ ጊዜያቸው መሰረት ሙሉ በሙሉ /100%/
መመለስ ይኖርባቸዋል::

ለ) ያለውን የፋይናንስ አቅርቦት ውስንነት ችግር ለመቅረፍና ተደራሽነትን ይበልጥ ለማሳደግ ሁሉም ፈፃሚ እና
ባለ ድርሻ አካላት ለብድር ማስመለስ ሥራ ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጡ ይገባል::

ሐ) በአነስተኛ የብድር አቅራቢው ቅ/ጽ/ቤት ወይም ንዑስ ቅ/ጽ/ቤት አማካይነት በየሦስት ወሩ የጥቃቅንና
አነስተኛ ተቋማት የብድር የማስመለስ ምጣኔ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ከተገመገመ በኋላ የሶስት ወሩ
በአደጋ ላይ ያለ የብድር ምጣኔ (Portifolio At Risk) 3% በታች ሆኖ ከተገኘ የአበዳሪው ተቋም የገንዘብ
አስተዳደር(liquidity) ጤናማ ለማድረግና ከበላይ ተቆጣጣሪው የብሔራዊ ባንከ የብድር አመላለስ መመሪያ
ጋር ተጣጥሞ እንዲጓዝ ለማስቻል የጥቃቅንና አነስተኛ የብድር አገልግሎቱ በአካባቢው /በከተማው ለጊዜው
እንዲቆም ተደርጎ ሁሉም ፈፃሚና ባለድርሻ አካላት በወቅቱ ሳይከፈል በቀረው ብድር ላይ በመረባረብ
ያስመልሳሉ::

መ) የአካባቢው የብድር አመላለስ ምጣኔ ከ 97% በላይ ሆኖ ሲገኝ የብድር አሰጣጥ ሥራው እንዲቀጥል
ይደረጋል::

24
ሠ)ብድሩ ጤናማ በሆነ መልኩ ተመላሽ ሆነ የሚባለው ተበዳሪው ከስራ እንቅስቃሴው ካገኘው ሽያጭ/ገቢ ላይ
ሲመልስ እንጂ ከዋስትና መያዣ ወይንም ከብድር ዋስትና ፈንድ ተመላሽ የተደረገ ብድር አለመሆኑ
ሊታወቅ ይገባል::

ረ) ደንበኞች ብድሩን በመመለሻ ቀናቸው ካልመለሱ የአበዳሪ ተቋሙ ጽ/ቤት በቀበሌ ደረጃ ካለው ኮሚቴ ጋር
በመሆን የተፈጠረውን ውዝፍ እንዲመለስ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ ውዝፉ በዚህ ኮሚቴ የጋራ ጥረት
በ 7 ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ የእያንዳንዱ ደንበኛ ዝርዝር፣ የውዝፍን መጠንና ምክንያት ያካተተ ሪፖርት
በ 5 ቀናት ውስጥ ለከንቲባ ጽ/ቤት ወይም ለወረዳ አስተዳደር ያሳውቃሉ፡፡

ሰ) የከተማ አስተዳደር ወይም የወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት በሪፖርቱ መሰረት ደንበኞች ውዝፍ ከፈጠሩበት ጊዜ
ጀምሮ ደንበኛውን በማወያየት በ 30 ቀናት ውስጥ እንዲመልሱ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ
ውዝፉ እንዲመለስ ያደርጋል፡፡

ሸ) ከላይ በተቀመጠው አግባብ ብድሩን በወቅቱ ያልከፈሉትን በፎርክሎዠር ህግ (626/2001) መሰረት ለዋስትና
ያስያዙትን ንብረት በመሸጥ እንዲመለስ ማድረግ ወይም ለክስ የሚያበቁ መረጃዎችን በማደራጀት ክስ
እንዲመሰረትባቸው ይደረግባቸዋል፡፡

ቀ) በክስ ብድራቸውን የሚመልሱ ደንበኞች በጥቁር መዝገብ ተለይተው ይያዛሉ፡፡ መረጃውም በየደረጃው
እንዲያዝ ይደረጋል፡፡

በ) በጥቁር መዝገብ የተመዘገበ ደንበኛ በተቋሙ በየትኛውም ጽ/ቤት ብድር እንዳያገኝ ይደረጋል፡፡

ተ) ከላይ በተዘረዘሩት መንገዶች ብድሩ በ 180 ቀናት ውስጥ ተጠቃሎ የማይመለስ ከሆነ ውዝፉን ከነወለዱ
ከዋስትና ፈንዱ ገንዘብ እንዲተካ ይደረጋል፡፡

ቸ) በፎርክሎዠርም ሆነ በክስ ውዝፉ ሳይመለስ ቀርቶ ከብድር ዋስትና ፈንዱ ውዝፉ ለአበዳሪ ተቋማት ከተተካ
በኋላ ከተበዳሪዎች የሚመለሰው ብድር ወደ ዋስትና ፈንዱ የተቀማጭ ሂሳብ ገቢ ይደረጋል፡፡

ኀ) ከዋስትና መያዣ ወይንም ከብድር ዋስትና ፈንድ የሚተካ ብድር የመጨረሻው አማራጭ ሆኖ በተለይ ከብድር
ዋስትና ፈንድ እንዲተካ የሚደረገው ብድር በየስድስት ወሩ (Semi annually) የሚከናወን በመሆኑ ፈፃሚ
አካላት ከዋስትና መያዣ እና ከብድር ዋስትና ፈንድ ሊመለስ የሚችለውን ብድር የአመላለስ ምጣኔ ግምገማ
ላይ ከግምት ውስጥ አይገባም::

3) ውዝፍ ብድር ማስመለስ

ተበዳሪዎች የወሰዱትን ብድር በአግባቡ በሥራ ላይ ካዋሉ በኋላ በወቅቱ የመመለስ ግዴታና ኃላፊነት አለባቸው::
ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች ውዝፍ ከተከሰተ ይህን ውዝፍ የማስመለስ ሥራ የአነስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ
ተቋማት፣ የከተማ የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲዎች እና በየደረጃው ያሉ አመራሮች ተግባር
ይሆናል::

25
በክልል መንግስታት ከተቋቋመውና በተቋሙ ከተቀመጠው የዋስትና ፈንድ ላይ ያለተጨማሪ የህግ ድጋፍ 6 ወራት
ያሳላፉ ውዝፍ ብድሮች ለተቋሙ ገቢ ይደረጋሉ:: ሆኖም ውዝፍ ብድሩ እንዲመለሰ ለሚመለከተው አቃቤ ህግ
የተሟላ መረጃ በመስጠት ብድሩ እንዲመለስ ከፈጻሚ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ይሰራል፡፡

31. ቅጣት

በማንኛውም የዕድገት ደረጃ ላይ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች፣ የግልና የቡድን ተበዳሪዎች፣ አስቀድሞ በተስማሙበትና
በተሰጣቸው የብድር መክፈያ ሰሌዳ (Repayment schedule) መሠረት ብድራቸውን የመከፈል ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡

ብድርን በወቅቱ መክፈልና ያለመክፈል በሚቀጥሉት ዙር ብድሮች ላይ አዎንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖ ከማስከተሉም
በላይ በአበዳሪው ተቋም የገንዘብ ማኔጅመንት (liquidity management) እና የገንዘብ አቅርቦት ላይ ችግር
የሚያስከትል ይሆናል፡፡ በመሆኑም አበዳሪው ተቋም ገንዘቡን በወቅቱ ቢሰበስብ እና መልሶ ቢያበድረው ሊያገኘው
የሚችለውን ገቢ ታሳቢ በማድረግ በእያንዳንዳቸው ባለፉት ቀናት ሳይከፈል በቆየው የብድር ገንዝብ ላይ በአበዳሪው
ተቋም መመሪያ መሰረት እንዲቀጣ ይደረጋል፡፡

32. የውጤት ትንተና ማከናወን

1) ለውጤት ትንተና የሚረዳ መረጃ ማጠናቀር

ሀ) ደንበኞች ምን ያህል ውጤታማ እንደሆኑ ወይም እንዳልሆኑ ለማጥናት እንዲቻል ብድር ከመለሱ በኋላ
ያላቸውን ሀብት መጠን በዝርዝር የሚያሳይ ጥሬ መረጃ ይሰበስባል

ለ) ደንበኛው የሰጣቸው መረጃዎች ትክክለኛ ስለመሆናቸው ከሌሎች የመረጃ ምንጮች

ሐ) እንዲረጋገጥ ይደረጋል

መ) ከዚህ በመቀጠል የተሰበሰበው መረጃ ለትንተና ክፍሉ ይላካል፡፡

2) የውጤት ትንተና ማካሄድ

ሀ) ደንበኞች ብድር ከመውሰዳቸው በፊት ከተሰበሰበው መረጃ ጋር በማነጻጸር የተገኘውን

ለ) ውጤት ይለካል፣

ሐ) የተገኘው ውጤት የሚቀጥለውን ብድር ለማጽደቅና የተለያየ ድጋፍ ሊደረግላቸው

መ) የሚገቡትን ለመለየት እንደተጨማሪ መለኪያ ሆኖ ያገለግላል፣

ሠ) የውጤት ትንተናው በአንድ ማዕከል አገልገሎት መስጪያ ጣቢያ በፈጻሚ አካላት ይከናወናል፡፡

26
ክፍል አራት
የባለድርሻ አካላት ተግባርና ኃላፊነት

33. የፈጻሚ እና ባለድርሻ አካላት ተግባርና ኃላፊነት

1) የክልሉ መንግስት ፣የከተማ አስተዳዳሮች እና የወረዳ አስተዳደሮች ተግባርና ኃላፊነት

ሀ) የፋይናንስ ድጋፍ የሚሰጡ ቋማትን በሰው ሀይል እና በቁሳቁስ ማደራጀትና ማጠናከር፤

ለ) የቁጠባን ባህል የሚያሳድጉ ስራዎችን ከሌሎች የልማት እቅዶች ጋር በማቀናጀት እንዲከናወኑ በበላይነት
በማስተባበር አፈጻጻሙን መከታተልና መደገፍ፤

ሐ) የብድር ዋስትና ፈንድ መመደብና አፈጻጻሙን መከታታልና መደገፍ፤

መ) በትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶችና የትምህርት ተቋማት የአነስተኛ የቁጠባ እና ብድር ተቋማት ቅርንጫፍ
ጽ/ቤት ከፍተው አገልግሎት እንዲሰጡ ምቹ ሁኔታ መፍጠር፤

ሠ) ኢንተርፕራይዞች የተበደሩትን ብድር በወቅቱ እንዲመልሱ የተለያዩ መድረኮችን ተጠቅመው


መልዕክቶችን ያስተላልፋሉ፤

ረ) ከአበዳሪና አደራጅ ተቋማት በሚደርሳቸው ዝርዝር መረጃ መሰረት ውዝፍ ውስጥ የገቡ
ኢንተርፕራይዞችን በማሰባሰብና በማነጋገር ውዝፍ ብድር እንዲመለስ አመራር ይሰጣሉ፤

ሰ) የሚመለከታቸው ድጋፍ ሰጪ አካላት ከአደራጅና አበዳሪ ተቋማት ጋር ተቀናጅተው እንዲሰሩና ውዝፉ


እንዲመለስ እንደየአካባቢው ሁኔታ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ፤

ሸ) የቁጠባ አሰባሰብ፣ የብድር ስርጭት፣ የብድር አመላለስና የውዝፍ ብድር አመላለስን ለመምራት በየደራጀው
መቋቋም የሚገባቸውን ኮሚቴዎች በማቋቋም በኃላፊነትና በተጠያቂነት መንፈስ እንዲሰሩ ያደርጋሉ፡፡

2) አነስተኛ የፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት

ሀ) ለደንበኞች ተደራሽነታቸውን ይበልጥ በማስፋት፤ የደንበኞችን የገንዘብ ደህንነት አስተማማኝ በማድረግ፤


ቀልጣፋና ምቹ አሰራርን በመዘርጋት፣ የተለያዩ ጠቀሜታ ያላቸውን የቁጠባ አይነቶችን በመቅረፅ እና
አደረጃጀታቸውን የበለጠ ምቹ በማድረግ በቁጠባ ላይ በስፋት መስራት አለባቸው::

ለ) የቁጠባ ዕቅዱን አፈፃፀም ከሚመለከታቸው ፈፃሚ አካላት ጋር በመሆን በየጊዜው በመገምገም አስፈላጊውን
የማስተካከያ እርምጃ በማድረግ የገንዘብ አቅርቦትን ቅድሚያ ለትኩረት በሚሰጣቸው ዘርፎች በመስጠት
ካለው የብድር ፍላጎት ጋር የማጣጣም ኃላፊነት አለባቸው::

27
ሐ) የአንቀሳቃሽ ቤተሰቦች ለልጆቻቸው የስራ ባህል እንዲያስተምሩና የቅድመ ብድር ቁጠባ እገዛ በማድረግ፤
ዋስትና በመግባት፤የተበደሩትን ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ እንዲያውሉ በመከታታል፤በብድር አመላለስና
ቁጠባ እንዲሁም በአጠቃላይ በኢንተርፕራይዞቹ ሁለንተናዊ ድጋፍ ላይ የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ
ተከታታይ ግንዛቤ ማስጨበጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡

መ) በግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችና በትምህርት ተቋማት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን በመክፈት ሰራተኞች በቀጣይ
የራሳቸውን ኢንተርፕራይዝ ለማቋቋም የሚያስችላቸውን መነሻ ገንዘብ እንዲቆጥቡ ማድረግ፤

ሠ) በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ገብቶ የፋይናንስ ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጥ ባለሙያ መመደብ፤

ረ) ለተመለመሉ ደንበኞች ስለ ብድርና ቁጠባ ጠቀሜታ እንዲሁም ስለ ብድር አሰጣጡና ብድር አመላለስ ሂደቱ
ማሰልጠን፤

ሰ) ደንበኞች ማሟላት ስለሚገባቸው ቅድመ ሁኔታ እና ስለሚኖራቸው መብትና ግዴታ ማስገንዘብ፤

ቀ) ደንበኞች ስለሚያዘጋጁት የንግድ ስራ ዕቅድ እና ስለሚያስፈልጋቸው የብድር መጠን በአግባቡ ማስገንዘብ፤

በ) በአንድ ማዕከላት ባለሙያዎች ቴክኒካል ድጋፍ ኢንተርፕራይዙ አዘጋጅቶ የሚያቀርበውን የንግድ ስራ ዕቅድ
ገምግሞ ማጽደቅ፤

ተ) የብድር መጠን ማጽደቅና ውል በመዋዋል ብድር ማቅረብ፤

ቸ) ውዝፍ እንዳይከሰት አስቀድሞ መከላከል እንዲቻል የተበዳሪዎችን የብድር አመላላስ ሁኔታ በሚገባ
መከታተልና ተበዳሪው ብድሩን በወቅቱ እንዲመልስ ግንዛቤ እንዲይዝ ያደረጋሉ፣

ኀ) ውዝፍ ብድር አደገኛ መሆኑን ሠራተኛው ተረድቶ እንዲንቀሳቀስ የአቅም ግንባታ ሥራ በቅድሚያ
ያከናውናሉ፣

ነ) የውዝፍ መረጃን በወቅቱ አጣርተው ይይዛሉ፣

ኘ) የውዝፍ መንስኤዎችን በመለየትና ተከታታይነት ያለው ትንተና በመስራት ውዝፍ ከመበራከቱ በፊት
በየደረጃው ያለው አመራር በቂ መረጃ አግኝቶ የተከሰተውን ውዝፍ ለማስመለስ እንደየአካበቢው ተጨባጭ
ሁኔታ ወቅታዊ እርምጃ እንዲወስድ በወቅቱ በማሳወቅ ተቀናጅተው ይሰራሉ፡፡

3) የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ/ቢሮ ጽ/ቤቶች፣

ሀ) አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ቁጠባን ለማሰባሰብ የሚያደርጉትን ጥረት በዋነኛነት መደገፍና ማስተባባር

ለ) ኢንተርፕራይዞችን ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስፈልገውን የብድር አቅርቦት እና ዝግጅት በማጠናከር ድጋፍ


ያደርጋሉ ::

ሐ) የአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማትን የማበደር አቅም ለማጠናከር በሚደረገው የሥራ እንቅስቃሴ ውስጥ
ኃላፊነት በመውሰድ በአካባቢያቸው የሚገኙትን የሚመለከታቸው የመስተዳድር አካላትን ማስተባበርና፤

28
መ) የሕዝብ ንቅናቄ በመፍጠርና ግንዛቤን በማስጨበጥ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት የሚያደርጉትን የቁጠባ
እንቅስቃሴ በግንባር ቀደምነት መደገፍ አለባቸው ::

ሠ) ተበዳሪዎች መሰማራት የሚችሉባቸውን የሥራ ዘርፎች፣ ሊደራጁባቸው የሚችሉ የአደረጃጀት አማራጮች


እና በብድር አሰጣጥ ሂደት ሊያሟሉ የሚገባቸው ቅደመ ሁኔታዎች ግንዛቤ መፍጠር

ረ) በሚሰማሩባቸው የስራ መስኮች ላይ ሊያጋጥማቸው የሚችሉ ችግሮችንና ሊወሰዱ የሚችሉ የመፍትሄ


አቅጣጫዎችን ማስገንዘብ

ሰ) ስለሂሳብ መዝገብ አያያዝ እና የሥራ ዕቅድ ጠቀሜታ እንዲሁም አዘገጃጀት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ
መስራትና ቴክኒካል ድጋፍ ማድረግ

ሸ) የተሰጠ ብድር በወቅቱ መመለስ ሳይችል ሲቀር ከአበዳሪ ተቋም ጋር በመነጋገር የጋራ መፍትሄ በእንጭጩ
ይፈልጋሉ፣

ቀ) ውዝፍ የሆነውን የብድር መጠን መረጃ በየጊዜው መያዝና መንስኤዎቹን በመለየት መተንተንና
ለሚመለከተው አካል እንዲተላላፍ በማደረግ ቀጣይ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ተቀናጅተው ይሰራሉ፣

በ) በየደረጃው ያሉ የአመራር አካላት የውዝፍን መረጃ እንዲያገኙ በማድረግ ከፈፃሚ አካላትና ባለድርሻ አካላት
ጋር ተቀናጅተው ውዝፍ በማስመልሱ ተግባር እንዲሳተፉ ያደርጋሉ፣

4) የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ፣

ኢንተርፕራይዞች የስራ ፈጣሪነት ፣ ታታሪነት ፣ ስለ ቁጠባ ምንነት ስለቁጠባ አላማ እና አስፈላጊነት፣ ስለ ቁጠባ
አይነቶችና ስለሚያስገኙት ጠቀሜታ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት

ሀ) በምርትና አገልግሎት ስራ ላይ ለሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ገበያን መሰረት ያደረገ የሙያና ክህሎት


ስልጠናዎችን በመስጠት በስልጠናው ላለፉት የምስክር ወረቀት መስጠት

ለ) ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የሚወጡ ኢንተርፕራይዞች ወደ መረጡት የሥራ ዘርፍ


ለመሰማራት ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ የራሳቸውን ድርሻ በቁጠባ መልክ አስቀድመው ሊያስቀምጡ
እንደሚገባ ግንዛቤ ማስጨበጥ

ሐ) በየደረጃውና በተለያዩ እርከኖች የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ከውስጥ ገቢ


የሚያገኙትንና በተለያዩ ቦታዎች የሚያስቀምጡትን ጥሬ ገንዘብ በአካባቢያቸው በሚገኙ የአነሰተኛ
የፋይናንስ ተቋማት በማስቀመጥና የተቋሙ ሠራተኞች እንዲቆጥቡ በማድረግ የበኩላቸውን ኃላፊነት
እንዲወጡና የአርአያነት ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ አለባቸው::

ኢንተርፕራይዞች ስራ ከጀመሩ በኃላ ክፍተቶችን ሊሞላ የሚችል ተከታታይነት እና የተሟላ የኢንዱስትሪ


ኤክስቴሽን አገልግሎት ድጋፍ ማድረግ፣

29
34. የአንድ ማዕከል አገልግሎት ጣቢያ ኃላፊነትና ተግባር

1) ስለቁጠባና ብድር ጠቀሜታና የአሰራር ሂደት ለማህበረሰቡ ፣ ለአንቀሳቃሾችና ለስራ ፈላጊዎች ግንዛቤ
ማስጨበጥ፣

2) በተዘጋጀው የመመልመያ መስፈርት መሰረት የተበዳሪዎችን ምልመላ ማከናወን፣

3) ተበዳሪዎች በሚሰማሩበት የስራ መስክ ላይ የንግድ ስራ ዕቅድ እንዲያዘጋጁ ቴክኒካል ድጋፍ መስጠት፣

4) የተዘጋጀውን የስራ ዕቅድ በአግባቡ የተዘጋጀ መሆኑን የአነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ተወካይ ሰራተኛ
ይገመግማል፣

5) የንግድ ስራ ዕቅዱ ማስተካከያ የሚያስፈልገው ሆኖ ሲገኝ ከአዘጋጁ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ጋር


በመሆን የማስተካከያ ስራ ይሰራል፣

6) የተስተካከለውን የንግድ ስራ ዕቅድ መሰረት በማድረግ የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም ተወካይ ሰራተኛ
ኢንተርፕራይዙ ሊበደር የሚችለውን የገንዘብ መጠንና የራሱን አስተያየት በማካተት ለማጽደቅ የሚያስችሉ
ሰነዶችን አሟልቶ በአንድ ማዕከል አገልግሎት ጣቢያ ብድሩን እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡

7) ከአንድ ማዕከል አገልግሎት ጣቢያ ውክልና በላይ የሆኑ የብድር መጠን በሚቀጥለው አካል እንዲጸድቅ
የሚያስችሉ ሰነዶችን አሟልቶ በመላክ ያስፈጽማል፡፡

8) ተበዳሪዎች የወሰዱትን የገንዘብ መጠን፣ ብድሩን የሚመልሱበት የጊዜ ሠሌዳ፣ ብድሩ ተከፍሎ
የሚጠናቀቅበት ጊዜና ሌሎችን መረጃዎች በአንድ ማዕከል ጣቢያ ተጠናቅሮ እንዲያዝ ከማድረግ በተጨማሪ
ድህረ ብድር ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ብድሩ ተጠቃሎ እስከሚመለስ ድረስ ትኩረት ሰጥተው ይንቀሳቀሳሉ፣

9) ውዝፍ እንዳይከሰት ከመከላከል ጀምሮ የተወዘፈንና በብድር ዋስትና ፈንድ የተሸፈነ ብድርን
ከሚመለከታቸው ፈጻሚና ባድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ማስመለስ ዋና ዋና ተግባሮቻቸው ናቸው፡፡

ከላይ የተዘረዘሩ ፈፃሚ እና ባለድርሻ አካላት ከቁጠባ አሰባሰብ ፣ ከብድር አቅርቦት እና ከብድር ማስመለስ ጋር የተያያዙ
እና ሌሎች ተዛማጅ ስራዎችን በኃላፊነት መንፈስ መወጣት ኃላፊነት እና ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ኃላፊነትን በአግባቡ
ባለመወጣት ምክንያት በሚያጋጥሙ የአፈፃፀም ጉድለቶች በግልና የጋራ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡

ክፍል አምስት

የድጋፍና ክትትል እና የግምገማ ስርዓት

35. የክትትል፣ የቁጥጥር እና የግምገማ ሥርዓት መዘርጋት

በከተሞች ውስጥ የሚገኙ የጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ከማኑፋክቸሪግ ውጭ ያሉ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በተሟላ


መንገድ በመደገፍ ሥራ አጥነትን ለመቀነስ እንዲቻል የተቀናጀና የጋራ አሰራር ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ
የሚከተለው የአፈጻጸም ግምገማ ሥርዓት ተዘርግቷል፡፡ በዚህም መሰረት አፈጻጻሙ በትክክል ተግባራዊ ስለመሆኑ
30
በየወቅቱ በየደረጃው መገምገምና ለሚፈጠሩ ችግሮች የጋራ መፍትሔ እያስቀመጡ መሄድ ሌላኛው ቁልፍ ተግባር
ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ሞዴል መመሪያ የተቀመጡት መሰረታዊ መርሆዎች ተግባራዊ መሆናቸውን ለማረጋገጥ

1) የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒሰቴር

የጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች እና ከማኑፋክቸሪግ ውጭ ያሉ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት በየሩብ ዓመትና


ዓመታዊ የስራ ዕቅድ አፈጻጸም ሁሉም የዘርፉ ፈጻሚ አካላት ከፌደራልና ከክልሎች በተገኙበት በዝርዝር
ይገመግማል፣ ቀጣይ አቅጣጫ ይሰጣል፡፡

2) በክልል ደረጃ ያለው አስፈጻሚ አካል

ሀ) የጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች እና ከማኑፋክቸሪግ ውጭ ያሉ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት በየሩብ


ዓመትና ዓመታዊ የስራ ዕቅድ አፈጻጸም ሁሉም የዘርፉ ፈጻሚ አካላት ከክልል ፤ ከዞኖችና ከተሞች
በተገኙበት በዝርዝር ይገመግማል ቀጣይ አቅጣጫ ይሰጣል፡፡

ለ) በክልል ደረጃ የሚዋቀር የጋራ ኮሚቴ የጋራ ዕቅድ ያዘጋጃል፡፡ አጠቃላይ አፈጻጸሙን በየ 3 ወሩ የመስክ
ጉብኝት በማድረግ ይገመግማል፣ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ በጋራ መክሮ የጋራ አቅጣጫ
ያስቅምጣል፣

3) በዞን ደረጃ ያለው አስፈጻሚ አካል

የጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች እና ከማኑፋክቸሪግ ውጭ ያሉ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት በየሩብ ዓመትና


ዓመታዊ የስራ ዕቅድ አፈጻጸም ሁሉም የዘርፉ ፈጻሚ አካላት ከዞን፤ ከወረዳና ከተሞች በተገኙበት በዝርዝር
ይገመግማል ቀጣይ አቅጣጫ ይሰጣል፡፡

4) የከተማ/የወረዳ አስፈፃሚ አካል

የዘርፉ ፈጻሚዎች በየሳምንቱ አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋሉ፣ የብድር ቁጠባ እንቅስቃሴው ሪፖርት ያዳምጣሉ፣
ሁኔታዎችን ይገመግማሉ፣ ለተከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ይሰጣሉ፡፡

5) የመረጃ አያያዝ አደረጃጃትና ልውውጥ

ሀ) መረጃ በአንድ ማዕከል ጽ/ቤትና በአበዳሪ ተቋሙ በአግባቡ መያዝ ይኖርበታል፡፡

ለ) በሁለቱም አካላት የተያዙ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ አንድ ወጥ የሆነ ሪፖርት በየወሩ ከቀበሌ እስከ ክልል ላሉ
ፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ወጥነት ባለው የሪፖርት ፎርማት መሰረት መላክ ይኖርበታል፡፡

ሐ) የመረጃ ልውውጡና አያያዙም ጊዜንና ወጪን ለመቆጠብ እንዲቻል ከማኑዋል አሰራር ወጥቶ በሲስተምና
ዘመናዊ በሆነ አሰራር ተደግፎ እንዲሰራ እና እንዲያዝ መደረግ አለበት፡፡
31
ክፍል ስድስት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

36. መመሪያውን ስለማሻሻል

ይህ ሞዴል መመሪያ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንዲሁም ከአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት ጋር ለማጣጣም
መሰረታዊ ይዘቱን ሳይለቅ እንደ አስፈላጊነቱ በክልሉ/ከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ወይም በፌዴራል ከተማ ልማትና ቤቶች
ሚኒስቴር አማካኝነት ሊሻሻል ይችላል፡፡

37. መመሪያው ስለሚጸናበት ሁኔታ

ይህ ሞዴል መመሪያ ከፀደቀበት ከ------------------ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

አቶ ጃንጥራር ዓባይ
የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር

32

You might also like