You are on page 1of 1

ዜና ፋይናንስ

2/3/13 ዓ.ም

ስልጠናው በሂሳብ አያያዝ፣ በክፍያና ጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ዙሪያ የሚታዩ


የአፈፃፀም ክፍተቶችን ይሞላል ተባለ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር


ዳይሬክቶሬት በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ዘጠኝ (9) ሴክተር መስሪያ ቤቶች 35
ለሚሆኑ የፋይናንስ ዳሬክቶሬቶችና የሂሳብ ባለሙዎች ከጥቅምት 30/13 ዓ.ም እስከ
ህዳር 4/13 ዓ.ም ድረስ በሂሳብ አያያዝ፣ በክፍያና ጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ዙሪያ በቢሮው
12 ኛ ፎቅ አዳራሽ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አቶ ኢያሱ መረሳ እንደገለፁት


ሥልጠናው በ 2012 በጀት ዓመት የሂሳብ አያያዝ፣ የክፍያና ጥሬ ገንዘብ አስተዳደር
የጥሬ ገንዘብ አቀራረብ ላይ የነበሩ ችግሮችና ክፍተቶችን በመለየትና ችግሮቹ ላይ
ትኩረት በማድረግ የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

ስልጠናው የአፈፃፀም ክፍተቶቹን በማረም በ 2013 በጀት ዓመት ተቋማት


በፀደቀላቸው በጀት መሰረት በሂሳብ አያያዝ፣ በክፍያና ጥሬ ገንዘብ አስተዳደር
ከትሬዠሪ ምንጭ፣ ከብድርና ከእርዳታ የወሰዱትን ገንዘብ በፋይናንስ አስተዳደሩ
መመሪያ መሰረት ሂሳባቸውን በወቅቱና በጥራት ዘግተው ሪፖርት ለማቅረብ
ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡

ኮሙኒኬሽን ዘርፍ

You might also like