You are on page 1of 1

ቀን 16/2/13 ዓ.

ፋይናንስ ዜና

በፋይናንስ ግልፅነትና ተጠያቂነት ዙሪያ ለወረዳ የፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ዩኒት ለ 120
የወረዳ የፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በሂሳብ ሪፖርት አቀራረብ ስርዓት ወቅቱን የጠበቀ የፋይናንሺያል
ሪፖርት፣ በመንግስት ግዥ አስተዳደር መሰረት ግዥ የመፈፀምና ንብረቶችን ማስተዳደር፣ የውስጥ ኦዲት
ሥርዓቱን ለማጠናከር የአስፈፃሚ አከላትን አቅም ማጎልበት፣ በፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነትና በበጀት
አዘገጃጀት አስተዳደር ዙሪያ በእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች አዳራሽ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው አብዛኞቹ የወረዳው አመራሮች አዲስ እንደመሆናቸው መጠን የአስፈፃሚ አካላት የፋይናንስ
አስተዳደር አቅማቸውን ማጎልበትና ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚሰሩ መሰረታዊ ተግባራትን ክፍተት መሰረት
ያደረገ አቅም ይገነባል፡፡

በቀጣይም በፕሮግራሙ ከታቀፉ ዋና ዋና ተግባራት አንዱ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደሩን የማጠናከር


ስራ በመሆኑ ሙያዊ የድጋፍ አገልግሎቶችና ስልጠናዎችን በየደረጃው ለሚገኙ አካላት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ኮሙኒኬሽን ዘርፍ

You might also like