You are on page 1of 2

ስለአሻራ የሰዓት መቆጣጠሪያ

ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች

አሻራ እንዴት ነው የምሰጠው


ቢሮ ውስጥ ተሰቅለው በሚገኙት የጣት አሻራ ማሽኖች ጋር በመሄድ በምስሉ ላይ
እንደሚታየው አሻራዎን ያስነብቡ።

ጣትዎን ከታች በምስሉ ላይ እንደሚታየው አሻራ ማንበቢያው መስታወት ላይ መሃል ለመሃል እና ሙሉ ለሙሉ ያስቀምጡት።

ትክክለኛ አሻራ አሰጣጥ


የተሳሳተ አሻራ አሰጣጥ

በቀን ስንት ግዜ አሻራ መስጠት አለብኝ?


አንድ ሰራተኛ በቀን 4 ግዜ አሻራ መስጠት አለበት። ጠዋት እና ከሰዓት ወደ ስራ ሲገቡና ሲወጡ መስጠት አለቦት። ማለትም
1. ጠዋት ወደ ስራ ሲገቡ 2፡30 ላይ
2. ለምሳ ሲወጡ 6፡30 ላይ
3. ከምሳ ሲመለሱ 7፡30 ላይ
4. መጨረሻ ከስራ ሲወጡ 11፡30 ላይ

ጠዋት ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት ቀድሜ አሻራ መስጠት እችላለሁ?


አዎ ይችላሉ ፣ ከ2፡30 በፊት መተው ቢነኩ ሲስተሙ 2፡30 እንደገቡ ነው የሚቆጥረው። ይህ ህግ ለስራ ሰዓት መውጫም ተመሳሳይ ሲሆን
ለምሳሌ ለምሳ ለመውጣት 6፡30 እንደመንካት አሳልፈው 6፡45 ቢነኩት ልክ 6፡30 እንደወጡ ነው የሚቆጠረው። የትርፍ ሰዓት ስራ
(overtime) ለመስራት ከሆነ ቀድመው የገቡት ወይም ዘግይተው የወጡት። የገቡበትን ወይም የወጡበት ሰዓት ይመዘግብሎታል። ነገር ግን
የትርፍ ሰዓት ስራ ከመስራቶት በፊት በቅድሚያ የትርፍ ሰዓት ለመስራት ኃላፊዎ መጽደቅ ይኖርበቸዋል።

ከስራ ሰዓት መግቢያ አርፍጄ አሻራ ብሰጥ ቀሪ እሆናለሁ?


መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በተለያዩ ችግሮች ሊረፍድባቸው እደሚችል በመገንዘብ 15 ደቂቃ ድረስ እረፍዶ አሻራ ቢሰጥ እንደረፈደ
አይቆጠርም።
ለምሳሌ

 አንድ ሰራተኛ እስከ 2፡45 ድረስ መጥቶ ቢነካ አርፋጅ አይባልም።


ከ15 ደቂቃ በላይ ግን ካረፈደ ግማሹን ቀን እንደቀረ ነው የሚቆጥረው
ለምሳሌ

 ጠዋት 2፡46 በኋላ ቢነካ የጠዋት የስራ ክፍለ ግዜውን እንደ ቀረ ነው የሚቆጠረው።
 ከሰዓት 7፡46 በኋላ ቢነካ የከሰዓት የስራ ክፍለ ግዜውን እንደ ቀረ ነው የሚቆጠረው።

በአ/አ/ከ/አ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮና በደልሲያን ኮንሰልቲንግ www.dulcons.com የተዘጋጀ


ከስራ ሰዓት መውጫ በፊት ቀድሜ አሻራ ብሰጥስ?
ከስራ ሰዓት መውጫ በፊት አሻራ ከሰጡ እንደ ቀሪ ነው የሚቆጠሩት።

ለስራ ጉዳይ ከቢሮ ወጥቼ በሰዓቱ አሻራ መስጠት ባልችልና ቀሪ ብሆን ምን ማድረግ እችላለሁ?
ሲስተሙ በተመደበው ሰዓት አሻራ ካልተሰጠ እንደ ቀሪ ነው የሚቆጥረው። ነገር ግን ለስራ ክፍሉ ሃላፊ በመንገር በቀላሉ ሃላፊው
አቴንዳንሱን ማስተካከል/መቀየር/ ይቻላል።
ለምስሌ ሹፌሮች ወይም የመስክ ስራ ያለባቸው ሰራተኞች ለስራ ከቢሮ ውጭ ቢሆኑ ሲስተሙ ቀሪ ያደርጋቸዋል ነገር ግን የስራ ክፍል
ሃላፊዎ ቀሪውን እንደ ገቡ አድርጎ ማስተካከል ይቻላል።

ለምሳ ከቢሮ አልወጣም ፤ 6፡30 እና 7፡30 አሻራ መስጠት አለብኝ?


አዎ ፤ ለምሳ ባይወጡም በተባሉት ሰዓቶች አሻራ መስጠት አለቦት።

የስራ ሰዓት መደቤ ከመደበኛው የስራ ሰዓት ውጭ ነው። መች ነው አሻራ መስጠት ያለብኝ?
እንደ ተመደቡቡት የስራ ሰዓት መግቢያና መውጫ ሰዓት ላይ መንካት ይኖርቦታል።
ለምስሌ የጽዳት ሰራተኞች የስራ ሰዓት መደብ ከጠዋት ከ1፡00 - 10፡00 ከሆነ ፤ በ1፡00 ላይ ሲገቡ ፣ 6፡30 ለምሳ ሲወጡ ፣ 7፡30 ሲመለሱ
እና 10፡00 ላይ ሲወጡ መንካት አለባቸው።

ሲስተሙ ቀሪ ብሆን ደሞዜን ይቆርጥብኛል?


የአንድ ሰራተኛ ደምወዝ ከመቁረጡ በፊት ሰራተኛው ቀሪ የሆነበትን ቀን ማስረጃ ካለው እንዲያቀርብ ይጠየቃል ለምሳሌ እንደ ህክምና
ማስረጃ ያሉትን። ማስረጃ ካለው ቀሪ የሆነውን ቀን ማስተካከል ይቻላል። ነገር ግን ማስረጃ ማቅረብ ያልቻለባቸውን ቀናት ሲስተሙ ደሞዝ
ይቀንሳል።

በተለያዩ ምክንያቶች ባረፍድ ወይም ቀሪ ብሆን ለማስተካከል ምንድን ነው ማድረግ ያለብኝ?


ሲስተሙ የስራ ሰዓትን መቆጣጠር እና ማስተካከልን በተመለከተ ሙሉ ስልጣን የሚሰጠው ለስራ ክፍል ሃላፊው ነው። ስለዚህም
ያረፈዱበትን ወይም ቀሪ የሆኑበትን ቀናት ለማስተካካል የስራ ክፍል ሃላፊዎን ያነጋግሩ።

ፍቃድ/እረፍት ስወጣ እንዴት ነው የሚሆነው?


ፍቃድ በሚወጡበት ግዜ የሰው ሃይል አስተዳደር የስራ ክፍል የፍቃድ ግዜውን ሲስተሙ ላይ እንዲመዘገብ ስለሚያደርግ ሲስተሙ በዚህ
ግዜ ውስጥ ቀሪ አያደርጎትም።

የስራ መደቤ በጊዚያዊነት ወይም በቋሚነት ከቢሮ ውጭ በሚሆንበት ግዜ ምንድን ነው ማድረግ ያለብኝ?
የስራ ክፍል ሃላፊዎ እና የሰው ሃይል አስተዳደር የስራ ክፍል በመነጋገር ሲስተሙ ላይ በግዚያዊነት ወይም በቋሚነት አሻራ ሳይሰጡ
እዲስተናገዱ ይደረጋል።

ማሽኑ አሻራዩን በትክክል ማንበቡን እንዴት አውቃለሁ?


አሻራዎን በትክክል በማሽኑ ሲነበብ የራይት ምልከትና ስምዎን ያሳይዎታል።አሻራዎ በትክክል
ካልተነበብ ግን በቀይ X ምልክት ያሳይዎታል። በዚህ ግዜ ደግመው ራይት ምልክት እና
ስምዎን እስኪያወጣሎት ድረስ ይሞክሩት።

ማሽኑ አሻራዩን አላነብ ቢለኝ ምን ማድረግ አለብኝ አሻራ በትክክል መነበቡን የሚያሳይ ምስል
አሻራዎ አልነበብ ካለ የሚከተሉትን ነግሮች ይሞክሩ
1. ጣትዎት አሻራ ማንበቢያውን ሙሉ ለሙሉ መሸፈኑን እና መሃል ለመሃል መሆኑን ያረጋግጡ
2. ጣትዎት ላይ ውሃ ወይም እርጥበት ካለ አሻራ ከመስጠትዎ በፊት ያድርቁት
3. ጣትዎት ላይ ጉዳት ከደረሰበት ሌላኛውን ያልተጎዳና በሲስተሙ የተመዘገበ ጣትዎን ይጠቀሙ
4. የጣት አሻራዎ ቆዳ በጣም ደረቅ ከሆነ ፤ አሻራ ከመስጠትዎ በፊት ጣትዎት ላይ ይተንፍሱበት
5. ከላይ የተገለጹትን ሞክረው ማሽኑ አሻራዎን አላነብም ከለ የሰው ሃይል አስተዳደር የስራ ክፍልን ያነጋግሩ

መብራት ሲጠፋ አሻራ ማሽኑ ይሰራል?


ማሽኑ በመብራት ሃይል ስለሚሰራ መብራት በማይኖርበት ግዜ አይሰራም። በዚህ ወቀት የገባ ፣ ያረፈደና የቀረን ሰራተኛ አቴንዳንስ የክፍሉ
ሃላፊ መብራት ሲመጣ እዲያስተካክለው ይደረጋል።

ማሽኑን ከስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ውጭ ዝም ብዩ ሄጄ ብነካው ምን ይሆናል?


ማሽኑ ሁልግዜም የመጀመሪያ ግዜ ሲነኩት ወደ ቢሮ ገቡ ብሎ ይቆጥራል። ሁለተኛ ሲነኩት ደግሞ ወጡ ብሎ ይቆጥራል። ስለዚህ ከስራ
መግቢያና መውጫ ሰዓት ውጭ ሄደው ቢነኩት ቀድመው እንደ ወጡ ስለሚቆጥርቦት ከስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ውጭ አይንኩት።

በአ/አ/ከ/አ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮና በደልሲያን ኮንሰልቲንግ www.dulcons.com የተዘጋጀ

You might also like