You are on page 1of 4

Waliya capital goods finance business share company

Clients’ Pre purchase contract


ቀን______________

የቅድመ ግዥ ውል

ውል ሰጭ /አመልካች/ድርጅት/ ሽርክና ማህበር ሙሉ ስም__________________________ አድራሻ፡


ከተማ_______________ ክ/ከተማ___________ ወረዳ____________ ቀበሌ ___________ የስራ
መስክ______________________ የእድገት ደረጃ _________________
ውል ተቀባይ፤ በዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር በ____________ ቅ/ጽ/ቤት አድራሻ፡ ከተማ
_____________ ክ/ከተማ _________ ወረዳ ________ ቀበሌ _______

የካ/ዕቃው ዋና ዋና የአሸና

መግለጫወች ፊ
ተ የካፒታል ዕቃው ዛ
አይነት /ስም/ ት ያንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ ድርጅቱ
የስሪት ስም
ብራንድ ሞዴል
ሃገር

2
3
4
5
6
7
8
9
ድምር
1. የውሉ ይዘት

ውል ሰጭ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የካፒታል ዕቃ ዓይነቶች እና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ መሰረት ውል ተቀባይ
ከአሸናፊ የካፒታል ዕቃ አቅራቢዎች ጋር በተለያዩ የግዥ አይነቶች ተጠቅሞ የካፒታል ዕቃዎችን በመግዛት በፋይናንሻል
ሊዝ ወይም በዱቤ ግዥ

የኪራይ ዓይነት ለውል ሰጭ ማስረከብ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- የካፒታል ዕቃውን ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ሰፊ ወይም ብዙ በሚሆንበት ወቅት እንደ አስፈላጊነቱ
ዝርዝር መግለጫ /Specification/ በማካተት ከዚህ የውል ሰነድ ጋር አባሪ መደረግ ይኖርበታል፡፡

2. የውል ሰጭ ግዴታ

1
Waliya capital goods finance business share company
Clients’ Pre purchase contract
2.1 ውል ሰጭ በአንቀጽ አንድ እንዲገዛለት የተስማማባቸውን የካፒታል ዕቃዎች ዋጋ ቅድሚያ ክፍያ 15% እስከ 40%

በጸደይ ባንክ______________ቅርንጫፍ/ጽ/ቤት በውል ሰጭ ቁጠባ ሒሣብ ቁጥር _____________


/______________________________________/ በዝግ/በብሎክ/ የማስቀመጥ ግዴታ አለበት ፡፡
2.2 ውል ሰጭ ግዥ እንዲፈጸም የጠየቀው የካፒታል ዕቃ ከአሸነናፊ አቅራቢዎች ጋር ውል ተቀባይ የውል ስምምነት

መያዙ እንደተረጋገጠ በአስቸኳይ በውል ሰጭ ሂሳብ ቁጥር በዝግ /በብሎክ/ የተቀመጠው የቅድመ ቁጠባ ገንዘብ

ወደ ውል ተቀባይ የሂሳብ ቁጥር( አካውንት) የማዛወር ግዴታ አለበት ፡፡

2.3 ውል ሰጭ ከአቅራቢ ተቋማት እንዲገዛለት ማመልከቻ ከአቀረበበት ጊዜ ጀምሮ የካፒታል ዕቃውን ለመረከብ
ፈቃደኛ ሳይሆን ቢቀር አ/ማህበሩ ግዥ ለመፈፀም ያወጣቸውን ወጪዎች ማካካሻ የሚሆን የካፒታል ዕቃውን
5% /አምስት በመቶ/ የጉዳት ካሣ ለውል ተቀባይ ለመክፈል በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1791 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት
ግዴታ ገብቷል፡፡
2.4 ውል ሰጭ በአንቀጽ 1 ላይ እንዲገዙለት የተጠቀሱትን የካፒታል ዕቃዎች ወደ ስራ ለማስገባት የሚያሥፈልጉ
የመሰረተ ልማትና የመስሪያ ቦታ የሟሟላት ግዴታ አለበት፡፡
2.5 ውል ሰጭ በአንቀጽ 2.4 የተመለከተውን ግዴታ ሳይወጣ ቢቀር ከርክክብና ከኮሚሽንግ ጋር ለሚፈጠሩ ችግሮች
ሃላፊነት የመውሰድ ግዴታ አለበት፡፡
2.6 በአክሲዮን ማህበሩ ግዥ ተፈጽሞ በዱቤ ግዥ ኪራይ ለሚተላለፍልኝ የካፒታል ዕቃ/ዕቃዎች/ መንግስት የቫት ተመላሽ
ማበረታቻ የፈቀደ ሲሆን ግዥ የተፈጸመበት አቅራቢ ወይም አብዥ ድርጅት በማንኛውም ምክንያት ያቀረባቸው ሰነዶች
በገቢዎች ጽ/ቤት በኩል ተቀባይነት ሳያገኝ ውድቅ ከሆነ ውል ተቀባይን ተመላሽ የሚሆን ገንዘብ የማይጠይቅ መሆኑን
ተስማምቷል፡፤
2.7 ከአቅራቢው ስቶር የሚገዙትን የካፒታል እቃዎች ተከራይ/ውል ሰጪ በራሱ ወጪ በማጓጓዝ ወደ መስሪያ ቦታ

የማድረስ ግዴታ አለበት፤


3. የውል ሰጭ መብት
3.1 የካፒታል ዕቃው ከአቅራቢዎች ግዥ በሚፈጸምበት ጊዜ ከመ/ቤቱ የግዥ ኮሚቴዎች ጋር በጋራ በመሄድ በግዥ
ሂደቱ በመሳተፍ ግዢውን መፈጸም፤
3.2 ከአቅራቢው ስቶር የተገዙለትን መሳሪያዎች አስፈላጊ ከሆነ በራሱ ማጓጓዣ አፈላልጎ በመጫን ወደ ስራ ቦታው
የማድረስ መብት አለው፡፡
3.3 ውል ሰጭ በአንቀጽ 1 ላይ ግዥ እንዲፈጸምለት የተስማማባቸውን የካፒታል ዕቃዎች ከአሸናፊ አቅራቢዎች ጋር
ውል ከተያዘበት ቀን አንስቶ ከ 6 ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የመረከብ መብት አለው፡፡

4. የውል ተቀባይ ግዴታ

4.1 የውል ተቀባይ ውል ሰጭ ያስያዘውን ቅድመ ቁጠባ ገንዘብ ማለትም በዝግ አካውንት(ብሎክ) ከተደረገው
የካፒታል ዕቃ ዋጋ 15% እስከ 40 % በተጨማሪ ቀሪውን ከ 85% እስከ 60 % የካፒታል ዕቃ ዋጋ አጠቃሎ
ለአቅራቢው በመክፈል ግዥ መፈጸም፤

2
Waliya capital goods finance business share company
Clients’ Pre purchase contract
4.2 ውል ተቀባይ በአንቀጽ 1 ላይ የተጠቀሱትን የካፒታል ዕቃዎች ከአሸናፊ አቅራቢዎች ጋር ውል ከያዘበት ጊዜ
ጀምሮ ከ 6 ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
4.3 ውል ተቀባይ ለውል ሰጭ በአንቀጽ 4.2 መሰረት የካፒታል ዕቃዎችን ገዝቶ ማቅረብ በማይችልበት ጊዜ የውል
ሰጭ ባስያዘው የቅድመ ቁጠባ ገንዘብ ላይ በባንክ ቁጠባ ምጣኔ ሙሉ ወራት ለቆየበት ወለድ በማሰብ ለውል ሰጭ
የመክፈል ግዴታ አለበት፤
4.4 ከውጭ ሃገር ተመርተው ወይም አቅራቢው ገዝቶ የሚያቀርባቸውን የካፒታል ዕቃ ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነጻ

መብት የገቡ መሆናቸውን በማረጋገጥ በባለሙያዎች ምርመራ በማድረግ የኢንስፔክሽን ተግባራትን አከናውኖ

ለውል ሰጭ ለማስረከብ ጥረት የማድረግ ሃላፊነት አለበት፡፡

5. የውል ተቀባይ መብት


5.1 ውል ሰጭ በቅድመ ቁጠባ ያስቀመጠውን የካፒታል ዕቃ ዋጋ ከ 15% እስከ 40 % ብሎክ የማስደረግና ከአሸናፊ
አቅራቢዎች ጋር የውል ስምምነት እንደተፈጸመ በዝግ ሂሳብ የተቀመጠውን ገንዘብ በውል ተቀባይ ሂሳብ ቁጥር
ገቢ የማድረግ መብት አለው፤
5.2 ውል ሰጭ የካፒታል ዕቃ ግዥ እንዲፈጸም ከተስማማ በኋላ የካፒታል ዕቃውን ለመረከብ ፈቃደኛ ሳይሆን ቢቀር
ውል ተቀባይ ግዥ ለመፈፀም ያወጣቸውን ወጪዎች ማካካሻ የሚሆን የካፒታል ዕቃውን ዋጋ 5% /አምስት
በመቶ/ የጉዳት ካሣ ውል ሰጭ ካስያዘው የቅድመ ክፍያ ላይ ቀንሶ የማስቀረት መብት አለው፡፡
6. የውሉ ተፈጻሚነት
ይህ ውል ከተፈረመበት ከ______________ ቀን______________ ዓ/ም ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡
ስለ ውል ሰጭ ውል ተቀባይ
ስም_______________________ ስም______________________
ፊርማ_______________________ ፊርማ____________________
ቀን___________________ ቀን_____________________
የትዳር አጋር ሚስት ወይም ባል
ስም_________________________
ፊርማ________________________
ቀን__________________________
እማኞች
1. ስም___________________ፊርማ _____________ ቀን______________
2. ስም __________________ ፊርማ ____________ ቀን______________
3. ስም___________________ ፊርማ____________ ቀን_______________

3
Waliya capital goods finance business share company
Clients’ Pre purchase contract

You might also like