You are on page 1of 10

ገበያ እና ሽያጭ አመራር

ገበያ እና ሽያጭ አመራር


 

በተደረገው ጥናት መሰረት በኢትዮጵያ የንግድ ድርጅቶች በጣም ተስማሚና አስተማማኝ የገበያ ስትራቴጂዎች ከዚህ በታች
ይገለፃሉ፣ አስተያየትም ይሰጥባቸዋል፡፡ ምንም እንኳን የሥልጠናና የገንዘብ ጉዳይ በራሱ በገበያው ዘርፍ ወሳኝ አለመሆኑ
ቢታወቅ ጥናቱን የተወጣለት ለማድረግ ሲባል በስትራቴጂዎቹ ውስጥ የተካተቱ መሆናቸውን ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል፡፡

ሀ/ የምርት ስትራቴጂዎች

 አንዳንድ የንግድ ድርጅቶች በስፋት የማምረትና ስትራቴጂ ማጎልበት ይችላሉ፡፡ ይህ ስትራቴጂ አስተዳደራዊ
ወጭዎችን የመሳሰሉትን በመቀነስ በአነስተኛ ወጭ ብዙ ምርት እንዲመረት የሚያስችል

በመሆኑ ሸማቾች/ተጠቃሚዎች በተራቸው ምርትን ውድ ባልሆነ ዋጋ እንዲያገኙ ያስችላል፡፡ እንዲሁም ሰፊና የተሟሉ
ምርቶችን በተለያየ ዲዛይንና በሙሉ አቅም ማምረት ሸማቾች ከአንድ ቦታ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች በሙሉ ለማግኘት
ያስችላል፡፡ ይህ ስትራቴጂ ባልበሰሉ የምግብ ዓይነቶች፣ የእደ ጥበብ ውጤቶች፣ የማዕድ ቤት ዕቃዎችና ወዘተ ላይ ተፈፃሚ
ሊሆን ይችላል፡፡

 አዲስ ምርት ለመጀመር በሚታቀድበት ጊዜ ምን ዓይነት እቃና በየትኛው ዲዛይን እንደሚመረት መወሰን ያለበት
በተደረገው ምርምርና ጥናት መሰረት መሆን አለበት እንጂ የተወሰኑ ዕቃዎች በጥቂት ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ ተፈላጊ
ስለሆኑ ብቻ መሆን የለበትም፡፡

 በገበያ ላይ ያለው ምርት ተፈላጊነት እየቀነሰ ከመጣ ሽያጩን ባለበት ለማቆየት ዲዛይኑን፣ መጠኑን፣ ባህርዩን፣
ቀለሙን ወዘተ. የመለወጥ አማራጭ አስፈላጊ ነው፡፡ በተጨማሪም እንደዚህ ዓይነቱ ስትራቴጂ ሃሳብ ለማፍለቅና
የቴክኒክ ክህሎት ማሳደግ የሚያስችል ሙያተኝነትን ይፈልጋል፡፡

 የስሪት ስም መስጠት የላቀ ተቀባይነትንና ከፍተኛ ዋጋ ሊያስገኝ ይችላል፡፡ ይህ ስትራቴጂ ጥቂት ወጭና የገበያ
ዘመቻን የሚጠይቅ እንደመሆኑ ለአነስተኛ ድርጅቶች ሊሰራ ቢችልም ለጥቃቅን ድርጅቶች ግን አያዋጣቸውም፡፡
የሆነ ሆኖ የስሪት ሥም አስጣጥ እንድ ሙጫ፣ ወተትና በመሳሰሉት ምርቶች ላይ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል፡፡

 በቁጥር ትንሽ ግን በጥራት ረገድ ምርጥ የሆኑ ምርቶችን ማምረት ሌላው አማራጭ ነው፡፡ ይህ ስትራቴጂ ለቤትና
ለቢሮ ዕቃዎች፣ ለፎቶግራፍ፣ ለፀጉር ሥራ፣ ለሽመና፣ ለጨርቃ ጨርቅና ወዘተ.. የንግድ ስራዎች የበለጠ ተስማሚ
ሊሆን ይችላል፡፡

 
 በጥሬ ዕቃ አምራቾችና ምርቶችን አሻሽለው በመጨረሻ መልኩ በሚያዘጋጁ ድርጅቶች መካከል ግንኙነት መፍጠር
ዋጋ ያለው መልካም አቀራረብ ነው፡፡ ለምሳሌ ሸማ ሰሪዎች ከአቅላሚዎች ጋር ሽርክና መፍጠር ይችላሉ፡፡

 የንግድ ድርጅቶች ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ምርቶቻቸውን እንዲያቀርቡ በአምራቾችና አቅራቢዎች መካከል ግንኙነት
መፍጠር ጥሩ መንገድ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ አነስተኛ ወንበር/ ዱካ ወዘተ. አምራቾች ከጣውላ
አቅራቢዎች ጋር ግንኙነት መፍጠር ይችላሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ መጥበሻና ኩባያ አምራቾች ከብረት ዘንግ
አቅራቢዎች ጋር ግንኙነት መፍጠር ይችላሉ፡፡

 ምርትን መቀነስና በፍጥነት የሚሸጡ ዕቃዎችን ማምረት ላይ ማተኮርና በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ማስተዋወቅ
በየጊዜው የንብረት ዝርዝር ቁጥጥር ማድረግን ለመቀነስ ጥሩ ዘዴ ነው፡፡

ለ/ የዋጋ ትመና ስትራቴደዎች   

 በግብይት ሂደት ዋጋ የተለመደና የስትራቴጂ ዋና አካል እንደመሆኑ አንዳንድ ነጥቦች ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡

 በአንድ አዲስ ምርት ላይ የዋጋ ቅናሽ ማድረግ ምርቱን ለማስተዋወቅና ሸማቾችን ለመሳብ ሁነኛ መሳሪያ ነው፡፡ ይህ
ግን ለተወሰነ አጭር ጊዜ ብቻ መሆን አለበት፡፡

                   የዋጋ ቅናሽ ማድረግ ያልተፈለገ ነገርን የመጣል

ያህል ዝቅተኛ ዋጋ መሆን የለበትም፡፡

 ምርታቸውን ለድርጅቶች ወይም ለኩባንያዎች የሚሸጡ የንግድ ድርጅቶች የዋጋ ቅናሽ ማስታወቂያ ለደንበኞቻቸው
በማራኪ ፖስታ ሊልኩ ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም አነስተኛ ወጪ የሚይዝ ዘዴ ነውና፡፡
 ጥራት ያለው ጥሩ ምርት ማምረትና ተመጣጣኝ ዋጋ የማስከፈል ስትራቴጂ ተግባራዊ የዋጋ መተመን ዘዴ ነው፡፡

 የንግድ ድርጅቶች የበለጠ ተፈፃሚነት ያለው አቀራረብ ዝቅተኛ ጥርት ያላቸውን ምርቶች በማምረት ተመጣጣኝ
ዝቅተኛ ዋጋ ማስከፈል ነው፡፡ የሆነ ሆኖ የዚህ ዓይነቱ አቀራረብ ለማይመለከታቸው ደንበኞች በስህተት ደርሶ ገበያ
እንዲያሳጣ ለዚህ አቀራረብ የሚመጥኑ ደንበኞችና ገበያው በቅድሚያ መለየት አለባቸው፡፡

 ከሁሉም የበለጠ እና በጣም ተመራጭ የሚሆነው የዋጋ አተማመን ስልት የምርት ወጪን መቀነስ እና በማያያዝም
የትርፈን መጠን በመቀነስ አምራቹና ገዢው በጋራ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ስልት መቀየስ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ
ትርፉ አሥር ከመቶ የሆነ ዝቅተኛ ወይም አነስተኛ የንግድ ድርጅት የዛኑ ያህል ወጪውን ቢቀንስ ወደያውኑ ትርፋን
ጥፍ ያደርገዋል፡፡ በዚህ ዓይነት ሽያጭን በማሳደግ ትርፍን ለመጨመር 100% የሽያጭ ማሳደግን ይጠይቃለ፡፡

 ለሚታመን ደንበኛ ልዩ የመጋዘን ወይም የችርቻሮ ሱቅ መደብር ቅናሽ ማድረግ አንድ ሰው ሊያስበው ከሚችለው
በላይ የሚሰራ ስትራቴጂ ነው፡፡

ሐ/ የማስተዋወቅ ስትራቴጂዎች

   በኢትዮጵያ ውስጥ የምርት ማስታወቂያ ማሰራት በጣም ውድ ነው፡፡ ስለዚህ ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች የበለጠ
ውጤታማና ሊሰራላቸው የሚችል የማስተዋወቅ ዘዴ መፈለግ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም ያለ እቅድ ለማስተዋወቅ ከመሞከር
መታቀብ አለባቸው፡፡   

ቀደም ብለን እንደገለጽነው ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች የገንዘብ ጥረት ስላለባቸው እያንዳንዱን ብር በዕቅድ
መጠቀም አለባቸው፡፡

ጥብቅ በሆነ በጀት ምክንያት በደካማ ሁኔታ የተሰራ

ማስታወቂያ በገበያ ውስጥ የማዘቅዘቅ ውጤት አለው፡፡

በአማራጭነት ለኢትዮጵያ ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች ሊያገለግሉ የሚችሉ የማስተዋወቅ መርሐግብሮች
እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

 የፖስተር የማስተዋወቅ ስራ በጣም ጠቃሚና አነስተኛ ወጪ የሚጠይቅ ነው፡፡ ነገር ግን ለእያንዳንዱ ጥቃቅንና
አነስተኛ የንግድ ድርጅት በተናጠል ለማዘጋጀት ይህ ዘዴ ውድ ሊሆን ስለሚችል ድርጅቶቹ ራሳቸውን በየመስኩ
በተለያዩ ቡድኖች በማደራጀት ለምሳሌ በሸክላ ሥራ፣ በሽመና ሥራ፣ በዓሣ አስጋሪነት ሥራ፣ በቆዳ ሥራ፣ ወዘተ..
የተሰማሩት እንደየሙያቸው ዝርዝር መግለጫ የያዘ ፅሑፍ በማሳተም መጠቀም ይችላሉ፡፡ በእንዲህ አይነት
ማስታወቂያዎች በአዳዲስ ምርቶችን ዲዛይኖች ላይ ደንበኞች ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ይቻላል፡፡

   

 የንግድ ትርኢት ገዢዎችን ለማነሳሳትና ለማስተዋወቅም ትልቅ ኃይል አለው፡፡ በመሆኑም የጥቃቅንና አነስተኛ
የንግድ ድርጅቶችን ምርቶች ለገዢዎች ማስተዋወቂያ መንገድ ነው፡፡ የንግድ ትርኢቶችን ማዘጋጀት ውድ በመሆኑ
የንግድ ድርጅቶች ከንግድ ሥራ ማጎልበቻ ድርጅቶች እገዛ ሊያገኙ ይገባል፡፡ በንግድ ትርኢት የምርት ናሙናዎች
ማሳየት ከመቻሉም በላይ አምራቾችና አገልግሎት ሰጭዎች እሳቢ ደንበኞችን በገፅ እንዲገናኙም ያስችላል፡፡
ምክንያቱም “ማየት ማመን ነው” እንደሚባለው ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች አብዛኛውን ጊዜ ሩቅ ቦታና
ጎልተው የማይታዩ በመሆናቸው ፈላጊዎች ያላዩዋቸው የሥራ ውጤቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ ነው፡፡ የንግድ ትርኢት
በራሪ ወረቀቶችን፣ ብሮሹሮችን፣ እና ሌሎች ፅሑፎችን ለማሰራጨት ጥሩ አመቺ ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል፡፡ ይሁን
እንጂ በራሪ ወረቀቶችን ብሮሹሮች የጎብኝዎችን ቀልብ እንዲስቡ ሆነው የተነደፉ መሆን አለባቸው፡፡ የተለያዩ
የምርት ዓይነቶች ፎቶግራፎችም በብሮሹሮቹ ውስጥ መካተት አለባቸው፡፡
 

 በእያንዳንድ ዝግጅቶች ላይ መሳተፍ ውጤታማና በአንፃራዊነት ሲታይ አነስተኛ ወጭ የሚጠይቅ ዘዴ ነው፡፡


ድርጅቶ በጀት ከሌለው የድርጅቱን ሰራተኛ በመላክና ዝግጅቱን እንዲረዳ በማድረግ መሳተፍ በቂ ሊሆን ይችላል፡፡

በዝግጅቶች ላይ መሳተፍ ግብ-ተኮር መሆን አለበት፡፡ መሳተፉ ከድርጅቱ አላማ ጋር የማይገናኝ ከሆነ በጋራ መሥራት
አያስፈልግም፡፡

  

  

 የማስተዋወቁን ዝግጅት አቅም ያላቸውን ገዢዎች በሱቁ ውስጥ በመጋበዝ እንዲጎበኙ በማድረግ ሊከናወን ይቻላል፡፡
በዝግጅቱ ወቅት የተለየ ስጦታ ሊሰጥ ይቻላል፡፡
 በጋዜጦች ወይም በማህበር መፅሄቶች ላይ ማስተዋወቅም ውጤታማ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ታሳቢ ገዢዎች በቅድሚያ
መለየት አለባቸው፡፡
 በራሪ ወረቀቶችን ማዘጋጀትና ማሰራጨት ስትራቴጂካዊ የማስተዋወቅ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የበራሪ
ወረቀቱ ይዘት አንባቢዎች ሊረዱት የሚችሉት መሆን አለበት፡፡ የበራሪ ወረቀቱ ማሳተሙ ውድ ከሆነ የተለያየ ምርት
ያላቸው ድርጅቶች የጋራ በራሪ ወረቀት ማዘጋጀትና ምርቶቻቸውን በመለየት ማመላከት ይችላሉ፡፡ የእያንዳንዳቸው
አድራሻ ለየብቻና በግልፅ መፃፍ አለበት፡፡
 በራሪ ወረቀት መዕልክት ማስተላለፊያ መንገድ ነው፡፡ ስለዚህ በቀላሉ የሚረድትና የማያሰለች መሆን አለበት፡፡
(ቀጥሎ የተመለከተው በራሪ ወረቀት ለሴቶች       ማጎልበቻ ማዕከል ቀደም ሲል በአማካሪው የተዘጋጀ)

  

   

  

መ/ የአስተሻሸግ ስትራቴጂዎች 

አስተሻሸግ በረጅም ጊዜ ግብይት ውስጥ የመወዳደሪያና አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ ስትራቴካዊ አስተሻሸግ ጥራትን፣ አመቺነትንና
አስተማማኝነትን ሊገልፅ ይችላል፡፡

 
አማራጭ የአስተሻሸግ ዘዴዎች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡

 በማጓጓዝ ጊዜ ውድመትን፣ ስርቆትንና ከአያያዝ ጉድለት ሊከሰት የሚችልን ጉዳት ለመቀነስ ተገቢ አስተሻሸግን
መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ ወተት፣ ቅቤ እና ዘይት ለውድመት እና ለስርቆት በበለጠ የተጋለጡ ናቸው፡፡

 የሚታሰበው ገበያ በድጋሚ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል መያዣ የሚፈልግ ከሆነ ተስማሚ፣ ለአየያዝ ምቹ እና
በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውል ማሸጊያ መጠቀም ተገቢ ይሆናል፡፡

 ተፎካካሪ ካለና በአስተሻሸጉ ጠንካራ ከሆነ አዲስ መያዣ ከመሰራቱ በፊት የተፎካካሪውን የአስተሻሸግ ሁኔታ
ማጥናት ያስፈልጋል፡፡

ሠ/ የሽያጭ ስትራቴጂዎች

ደንበኛን ለመለየትና እንዴት ማርካት በበለጠ መንገድ መያዝ እንደሚቻል ለማወቅ ገበያውን በየክፍሉ ማጥናት ይቻላል፡፡
አንዳንድ ስትራቴጂካዊ ነጥቦች ቀጥሎ ቀርበዋል፡፡

 የችርቻሮ ንግድ ሱቆችን መመስረት አስፈላጊ ነው፣ ነገር ግን ቀላል ጉዳይ አይደለም፡፡ የንግድ ምክር ቤቶች እና
የንግድ ማህበራት አባል መሆን ይህንን ለማከናወን የተሻለ ነው፡፡ አንድ የንግድ ድርጅት የቻርቻሮ መሻጫ ቦታን
ለማግኘት በግሉ ከሚንቀሳቀስ ይልቅ በንግድ ምክር ቤቶች እና በማህበራት በኩል ቢሆን የበለጠ እንደሚቀል ጥናቱ
ያስረዳል፡፡

 የንግድ ድርጅቶች ከሁሉ የበለጠ ሀብቱ ገዢው ነው፡፡ ደንበኞችን ማርካት በሽያጭ ውስጥ ከሁሉ የላቀ ስልት
እንደመሆኑ ደንበኛ እንዲረካ ለማድረግ የንግድ ድርጅቶች በርትተው መሥራትና መጓጓት ይገባቸዋል፡፡ ማርኪያ
ዘዴዎች ደንበኞች በምርቱ እና በአያያዙ ደስተኛ ሆነው እንዲቀጥሉ ማስቻል ላይ ማተኮር አለባቸው፡፡

          የንግድ ድርጅቶች ደንበኝነትን መመስረት ደንበኞች ታማኝ ሆነው እንዲቆዩ  

          ለማድረግ ከሁሉ የላቀ መንገድ ነው፡፡

 
 ለቤተሰብ እና ማህበራዊ ግንኙነት ላላቸው ሰዎች ሱቅን ጥሎ መውጣትን ማስወገድ አብይ ጉዳይ ነው፡፡ አለበለዚያ
ከጊዜ በኋላ በእያንዳንዱ ጎብኚ የማይናቅ መጠን ያላቸውና ቢሸጡ ትርፍ ያስገኙ የነበሩ ምርቶች ሊጠቀምባቸው
ይችላል፡፡
 አዋቂና ዝነኛ ከሆኑ የገበያ ማዕከሎች ወይም አከፋፋዮች ጀርባ ሆኖ መሸጥ አንዱ አማራጭ ነው፡፡ በዚህን ጊዜ
ገዢዎች ጥራት ይኑረው አይኑረው አይጠይቁም፡፡ ምርቱ ጥሩ ጥራት እንዳለው ይገምታሉና፡፡ ስለዚህ ይህ ዘዴ
ድርጅቱን በመጠኑም ቢሆን ከፍ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ለምሳሌ “የመስከረምን” የገበያ ማዕከል ወይም የ”ፋንቱ ገበያ”
ተዋቂ የገበያ ማዕከል ናቸው ብለን ብንወድስ እንደ የወጥ ቤት ዕቃዎች፣ የሸክላ ስራዎች፣ የእጅ ስራዎች፣ አነስተኛ
ቁሳቁሶች፣ ጫማ፣ የሽመና ውጤቶች ወዘተ. የሚሸጡ ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች ምርታቸውን በሱቁ
ውስጥ ሊያስቀምጡ እና በተዘዋዋሪ መንገድ ምርቶቻቸውን ሊያስተዋውቁ ይችላሉ፡፡ ምርቶቹ ከገበያ ማዕከሉ
ምርቶች ጋር የግድ የሚወዳደሩ መሆን የለባቸውም፡፡ የገበያው ማዕከሉ በተወሰነ ክልል የሚያከፋፍል ከሆነ በክልሉ
ጥሩ ገበያ ላላቸው የችርቻሮ ሱቆች ሊያከፋፍል ይችላል፡፡

 ጥሩ የግንኙነት ችሎታ ያለው የሽያጭ ሰው መመደብ ጥሩ የሽያጭ ዘዴ ነው፡፡ ማህበራዊ ግንኙነት የሚፈጥሩ
በየጓደኞቻቸው ይሸጣሉ፡፡ ምንም እንኳን ጓደኝነት የሽያጭ ክፋይ አካል ቢሆንም ምርቱ በሚሰጠው አገልግሎት እና
በዋጋው ትክክለኛ መሆን አለበት፡፡

የንግድ ድርጅቶች ደንበኞችን በመያዝ የበላይ እንደሆኑ መቆየት ጠቃሚና መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ ብዙ ወጪም የለውም፡፡

 በጅምላ መሸጥ ፈጣንና በቀላሉ ለማጣራት ያስችላል፡፡ ይሁን እንጂ የሚገኘው ትርፈ መጠን ይህን ያህል ሊሆን
እንደማይችል ሊጤን ይገባል፡፡ በዚህን ጊዜ በአነስተኛ ሰራተኛና ወጪ እንዴት መሸጥ እንደሚቻል ያካተተ ስልት
መንደፍ ይገባል፡፡ በዚህ ዘዴ ውስጥ፡-
 በአነስተኛ ወጭ እንዴት ማሰባሰብና መቆጣጠር እንደሚቻል፣
 የድቤ ሽያጭን እንዴት ጥብቅ ማድረግ እንደሚቻል፣
 እንዴት የሽያጭን መጠንን ማሳደግና የስራ ማስኬጃ ወጪ መቀነስ እንደሚቻል፣ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

ሠ/ የውድድር ስትራቴጂዎች

       ከውደድር ጋር የተያያዙ ዋና ዋና ዘዴዎች ከዚህ በታች ተገልፀዋል፡-

 የንግድ ምክር ቤቶችን እና የንግድ ማህበራት አባል መሆን ከተወዳዳሪዎች ጋር መቀላቀያና ስኬታማ የሆኑ ድርጅቶች
የንግድ ሥራቸውን እንዴት እንደሚያካሂዱ ለመማር አንዱ መንገድ ነው፡፡

 ድርጅቱ በተቀናቃኝ ተፎካካሪዎች ሽኩቻ ከተቸገረ ሽያጭ ተደራድሮ መሸጥን እንደ አንዱ የተወዳዳሪነት ጥቅም
ስልት መጠቀም ይችላል፡፡
 

           በጥቂት የመወዳደሪያ መስኮች ጥሩ ሆኖ ለመገኘት

             መሞከር ብልህነት ያለው ስትራቴጂ ነው፡ በሁሉም

             የንግድ መስኮች ጥሩ ተፎካካሪ መሆን ስለሚያዳግት

             የንግድ ድርጅቶች በውድድሩ

             አጉልቶ የሚያሳያቸው የንግድ መስክ መምረጥ

             አለባቸው፡፡

 ተፎካካሪዎች ከቤት ቤት በመሄድ የሚሸጡ ከሆነ በንግድ ቋሚ ቦታ ላይ ገዢ ያጣ ተፎካካሪ ምርቱን ገዢው መኖሪያ
ድረስ በማቅረብ ጠቀሜታን ሊያዳብር ይችላል፡፡ በዚህም ታዲያ ገዢ የበለጠ ለመግዛት ያለውን ፍላጎት ይህ ሊስት
ሊያመላክት ይገባል፡፡

           ከሁሉም የላቀ ስትራቴጂ ሊሆን የሚችለው

             ድርጅቶችን በውድድሩ አለማካተት ነው፡፡

 በቂ መረጃ የማግኘት ጉዳይ ለውድድር ብቻ ሣይሆን ለሌሎች ግብይት ነክ ሥራዎች ተፈላጊ ነው፡፡ ከዚያም በላይ
ምን የሆነ እንደሆነና ተፎካካሪዎች ምን የሰሩ እንደሆነ ማወቂያ ምንጩ መረጃ ነው፡፡

 የመረጃ ጥረትን ለማስወገድ የንግድ ልማት አገልግሎት የመረጃ ማዕከልን በማቋቋም እና የንግድ ድርጅቶች
በአካባቢያቸው

ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲጠቀሙ ሚና መጫወት ይችላል፡፡ ይህ ያለ ጥርጥር ብዙ በጀት የሚፈልግ ቢሆንም በገንዘብ
ከሚረዱት ጋር በመተባበር ተግባራዊ ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል፡፡

ለማንኛውም የንግድ ድርጅት መረጃ መጠቀም የሚባለው የተሻለ የንግድ ሥራ ማስኬድ ሲያስችል ነው፡፡

ረ/ የጥራት ጋር የተያያዙ ስትራቴጂዎች

 ጥራትን በተመለከተ የንግድ ድርጅቶች በትንሹ ማድረግ የሚገባቸው አሁን ያለውን ጥራት እንደተጠበቀ እንዲቆይ
የሚያስችል ፖሊሲ ማውጣትን እንደ አጠቃላይ ስትራቴጂ መከተል አለባቸው፡፡
 ጠላ ጠጪዎች ስለጠላው ጣዕም በጣም ተጨናቂ ናቸው፡፡ ስለዚህ እንደፍላጎታቸውና እንደምርጫቸው ጠላውን
ማዘጋጀት አንዱ ስልት መሆን አለበት፡፡ ለምሣሌ ምርጫቸው ጉሽ ጠላ ከሆነ በተቃራኒው ድርጅቱ የጠራ ጠላ
የሚያቀርብ ከሆነ የፈለጉትን ያህል ጠላ ካለመጠጣታቸውም በላይ ከነአካቴው ተመልሰው ላይመጡ ይችላሉ፡፡
 የንግድ ድርጅቶች በዕቅድ በመመራትና ወጪያቸውን በመቀነስ የምርታቸውን ጥራት መጨመር ይችላሉ፡፡

ሸ/ የስርጭት (ክፍፍል) ስትራቴጂዎች

     አማራጭ ሃሳቦች ቀጥሎ ይቀርባሉ፡፡

 ለሌሎች መሸጫዎች በደርዘን ማከፋፈል አንዱ ስልስ ነው፡፡ ለምሣሌ ዳቦ ሻጮች በቁርስ ቤቶች፣ የሙጫ (ማስቲሽ)
ፋብሪካዎች ጫማ ለሚሰሩ ድርጅቶች በጅምላ ማከፋፈል ይችላሉ፡፡ የዚህ አይነት አቀራረብ
 በጥሬ ገንዘብ ለመሸጥ፣
 በብዛት ለመሸጥ፣
 ጊዜ ለመቆጠብ፣
 ሕፃናት ጅምላ ሻጭ ቤተሰቦቻቸው ጋር ከመሥራት ይልቅ ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ በማስቻሉ ጥቅም አለው፡፡
 የግዢ ትዕዛዝ በደረሰ ጊዜ ደንበኛው ትዕዛዙን እንደሰጡ ዝግጅቱ መጀመር አለበት፡፡ አንድ ደንበኛ ያዘዘውን ነገር
የጠበቀ የሽያጭ ሰራተኛው ሌላ ነገር የሚሠራ ከሆነ የደንበኛውን ግንኙነት ሊያሻክር ይችላል፡፡
 ዳቦና ወተት የሚሸጡ ድርጅቶች ቤታቸው ውስጥ ሆነው ከሚሸጡ ይልቅ በየገዢዎቹ ቤት ለቤት የዞሩ ሊሸጡ
ይችላሉ፡፡ ቤታቸው ድረስ የሚመጣን አገልግሎት የሚመርጡ ደንበኞች አሉና፡፡
 ድርጅቱ ጥቃቅን ከሚባሉት የሚመደብ እንኳን ቢሆን ምን እንደተሸጠና ምን አንደተከፋፈለ ለይቶ ማውቅና
መዝግቦ መያዝ አለበት፡፡
 ቀደም ሲል የተገለፀው የመሠረተ ልማት ችግር የንግድ ድርጅቶች ላይሻሻል ይችላል፡፡ የሚመለከታቸው
መንግሥታዊ ቢሮዎች ይህንን ጉዳይ ውጤታማ በሆነ መልኩ ሊይዙት ይችላሉ፡፡ ይህ ርዕስ አስፈላጊ እንደመሆኑ
የንግድ ሥራ ልማት አገልግሎት በዚህ ረገድ የበኩሉን ሚና መጫወት አለበት፡፡

    የየዕለቱን የንግድ ሥራ ግንኙነት በስልክ ማድረጉ በጣም ይቀላል፡፡

ቀ/ ከሥልጠና ጋር የተያያዙ ስትራቴጂዎች

     ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች

 የንግድ ሥራ ሃሣብን በማጎልበት ረገድ፣


 ቀላል ምርምሮችን በማድረግ ረገድ፣
 የበለጠ ክብርና ዝና በማግኘት ረገድ፣
 ደንበኞችን በመሳብና በማርካት ረገድ፣
 የገበያው ታወቂ በመሆን ረገድ፣
 በፉክክር በማሸነፍ ረገድ፣
 ብድርና ሌሎች የገንዘብ ምንጮችን በመጠቀም ረገድ፣
 ገንዘባቸውን በቀጥታ ለሽያጭ በሚቀርቡና ያለቀላቸውን ምርቶች ለማምረት ወይም ለመግዘት በማዋል ረገድ
በቋሚት ሊሰለጥኑ ይገባል፡፡
 በጀት የሚፈቅድ ከሆነ በሥልጠናው ወቅት ሊደረግ የሚችለውን ሽያጭ ከ 60-80% የሚሸፍን ማበረታቻ
ለተሳታፊዎች ቢሰጥ ጥሩ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ይህንን

ዘዴ መጠቀም ያለብን ለተወሰነ ጊዜና ተመልሰው ወደ ስልጠናው እንዲመጡና ከስልጠናው እንዲጠቀሙ የማበረታታት
ዓላማን ይዞ መሆን አለበት፡፡
 ገንዘባቸውን እንዴት በአነስተኛ ወጭ መጠቀም እንደሚቻልና ከሽያጭ የሚያገኙትን ገቢ በትክክል መዝግበው
እንዲይዙና እንዲያወራርዱ የሚያስችል ከፍተኛና ተከታታይ ሥልጠና መሰጠት ይቻላል፡፡

 አንዳንድ የንግድ ድርጅቶች ባለቤቶች ሥልጠናውን ሊከታተሉና ሊረዱ የማይችሉ በሚሆንበት ጊዜ ትልልቅ
ልጆቻቸውን ማሰልጠን አንዱ አማራጭ ሊሆን ይችላል፡፡ የልጆችን አመለካከት መቀየር ይቀላልና፡፡

ለጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች ሥልጠና

መስጠት ያለበት ለድርጅቶቹ እድገት ጠቃሚና

በሂደቱም ወደመደበኛ ትላልቅ ድርጅቶች

የሚያድጉበትን ሁኔታ በሚያመላክቱ አካባቢዎች

መሆን አለበት፡፡

በ/ ከፋይናንስ ጋር የተያያዙ እስትራቴጂዎች

ምንም እንኳ ይህ ጉዳይ ከግብይት ጋር በቀጥታ የተያያዘ ባይሆንም የጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶችን ስትራቴጂ
የምናዘጋጅበት ጊዜ ተለይቶ መተው ስለሌበት እንዲካተት ተደርጓል፡፡ አንዳንድ ሃሳቦች ቀጥለው ይቀርባሉ፡፡

 የንግድ ድርጅቶች የገንዘብ ጥረት ያለባቸው እንደመሆኑ መጠን የገንዘብ ዝውውራቸው ቀላልና በማያሳስት ሁኔታ
መሆን አለበት፡፡ በተለይ ለትናንሽ ድርጅቶች፣
 የንግድ ድርጅቶች ገንዘብ ሲያወጡ እጅግ ጥንቁቆች መሆን አለባቸው፣
 የንግድ ድርጅቶች ወጪያቸውንና ሽያጫቸውን መመዝገብ መልመድ አለባቸው፡፡ ጥሬ ገንዘባቸውን የመቆጣጠር
ዲሲፕሊን ሊኖራቸው ይገባል፡፡

   

 ጥሩ የሥራ አፈፃፀም ላላቸው የንግድ ድርጅቶች የብድር አገልግሎት መስጠትን እንደፖሊሲ መጠቀም የገንዘብ
አያያዛቸውን በተመለከተ እንዲያስቡበት ሊያበረታታ ይችላል፡፡ ይህ ዓይነት አቀራረብ እንደ ፕሬጃይኒስት እና
ወርልድ ቪዥን የመሳሰሉ ድርጅቶች እየተሰራበት ይገኛል፡፡

ከላይ የተገለፁት ፋይናንስ ነክ ጉዳዮች በአግባቡ

ካልተያዙ የንግድ ድርጅቶች በቀላሉ


ችግር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡

You might also like