You are on page 1of 26

የቤንሻንጉል ነጋዴ ሴቶች ማህበር ምስረታ ላይ

ማህበራትን ማቋቋምና መገንባት አስመልክቶ


የተዘጋጀ ጽሁፍ

በንግድ ሚኒስቴር
የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት
2015
ማህበር ምን ማለት ነው?

•ፈቃደኛ የሆኑ አባላት ያሉት


•ትርፋማ ያልሆነ
•የረጅምና የአጭር ጊዜ ዓላማ አንግቦ አላማውን ለማሳካት
የሚንቀሳቀስ ማለት ነው
ማህበር ማቋቋም ለምን ያስፈልጋል?

•የጋራ ዓላማን በህብረት ለማስፈጸም


•በጋራ ድምጽን ለማሰማት
•የሎቢና አድቮከሲ ስራዎችን ለመስራት
•እርስ በርስ ኔትዎርኪንግ ለመፍጠር
የነጋዴ ሴቶች ማህበራት ጥቅም

•በፖሊሲዎች እና ፕሮግራሞች ውስጥ የሴቶች ጉዳይ


እንዲካተት ያግዛል
•የጋራ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚያስገኙ ስራዎችን ያከናውናል
•የነጋዴ ሴቶች የተባበረ ድምጽ እንዲሰማ እና ዋጋ
እንዲኖረው ያደርጋል
•ለአባላቱ የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጣል
•በጋራ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል
•ነጋዴ ሴቶች ከወንዶች የተለየ ፍላጎት ስላላቸው ይህንኑ
ፍላጎታቸውን ያሟላል
ነጋዴ ሴቶችን የሚያጋጥሙ ችግሮች

•ስራ ለመጀመር የግል ሃብት አለመኖር


•ለባንክ ብድር ማስያዣ ማጣት
•አዳዲስ ስራዎችን ለመጀመር በራስ መተማመን ማጣት እና
በተለመዱ ስራዎች መሰማራት
•ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ
•የመረጃ እና የኔትዎርክ እጦት
•የጊዜ እረፍት ማጣት( ቤተሰብ ማስተዳደር ልጆች ማሳደግ)
•ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ መስራት አለመቻል
ማህበራት የሚሰጡት አገልግሎት

•የስልጠና አገልግሎት፣ኤግዚቢሽንና ባዛርን ማዘጋጀት


•ቢዚነስ ካውንስሊንግ ሜንተሪንግ አገልግሎት መስጠት
•አድቮከሲ እና ሎቢንግ
•የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
•የገበያ አገልግሎት( ገበያ ማፈላለግ ፣የገበያ ትስስር መፍጠር)
ማህበር እንዴት ይቋቋማል

•ማህበር የሚቋቋመው በአባላቱ ነጻ ፍላጎት ነው


•ማህበሩ ሲቋቋም መተዳደሪያ ደንብ ያስፈልገዋል
•በመተዳደሪያ ደንቡ የሚካተቱ ጉዳዮች
✓የማህበሩ አላማና የሚያከናውናቸው ተግባራት
✓የአባላቱ መብትና ግዴታ
✓የቦርድ አባላት ምርጫ( የማህበሩ ሊቀመንበር ምርጫ፣ የቆይታ
(የስልጣን)ጊዜ እና ቆይታቸው ሲያልቅ እንዴት መተካት እንደሚቻል
፣መብትና ግዴታቸው፣ውሳኔዎች እና አፈጻጸማቸው፣የፋይናንስና ወይም
ገንዘብ ነክ ጉዳዮች እንዴት መፈጸም እንዳለባቸው ያካትታል)
የቀጠለ…
የአስፈጻሚዎች አወቃቀር

ጠቅላላ ጉባኤ------ኦዲት-------ስራ አስፈጻሚ------------ጸሀፊ----------


የፋይናንስ ሃላፊ-----------ሌሎች ሰራተኞች
ጠቅላላ ጉባኤ
• ጠቅላላ ጉባኤ አባላቱ በሙሉ የሚሰበሰቡበት ነው
•የቦርድ አባላትን እና የኮሚቴ አባላትን ይመርጣሉ
•የማህበሩን በጀትና ስትራቴጂ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ያጸድቃሉ
•በጠቅላላ ጉባኤው አባላት ማህበራቸው የሚጠናከርበትን ሃሳብ ያቀርባሉ
ተቀባይነት ካገኛ ያጸድቃሉ ወይም በድምጽ ብልጫ ይወስናሉ
የቀጠለ …

ስራ አስፈጻሚ

•ስራ አስፈጻሚ በጠቅላላ ጉባኤው የሚመረጥ ሲሆን


የቦርዱን ፖሊሲና ስትራቴጂ ለማስፈጸም የሚመረጥ
ነው
•ሊቀመንበር ፣ገንዘብ ያዥ፣ ጸሃፊና ሌሎች አባላት
ይኖሩታል
•እንደ አስፈላጊነቱ ጊዜያዊና ንዑሳን ኮሚቴዎች
ያቋቁማሉ
•ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ይገናኛሉ
የቀጠለ…
ፕሬዝዳንት/ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር/

•የበላይ አካል ወይም ስራ አስፈጻሚ ውሳኔ ተግባራዊ


ታደርጋለች
•የቀን ከቀን የማህበሩን ስራ ትከታተላለች
•ማህበሩን በመወከል ስብሰባዎችን ትሳተፋለች
የቀጠለ …

ፀሀፊ
•ለስብሰባ የሚሆኑ አጀንዳዎችን ታዘጋጃለች
•ቃለ ጉባኤ ትይዛለች
•የማህበሩን አስተዳደር ትከታተላለች
የፋይናንስ ሀላፊ
•የማህበሩን ገቢና ወጪ ትከታተላለች
በመተዳደሪ ደንቡ መካተት ያለባቸው ጉዳዮች

•የማህበሩ ስም
•ማህበሩ ተልዕኮና ራእይ ሊኖረው ይገባል( በውስጡም አጭርና ገላጭ
በሆነ መንገድ ማህበሩ ለምን እንደተቋቋመ፣ምን ምን ስራዎችን
እንደሚያከናውን፣የሚሰጣቸውን አገልግሎት ማካተት ይኖርበታል)
•የማህበሩ ዓላማ (ጥቅልና ዝርዝር ዓላማ)
•አዲስ አባላት የማህበሩ አባል መሆን ሲፈልጉ ማJላት የሚገባቸው
መስፈርቶችና ቅደመ ሁኔታዎች
•የአባላት መዋጮ
•ጠቅላላ ጉባኤ ለመጥራት (ቅድመ ሁኔታዎች፣የጊዜገደብ)
የቀጠለ…

•የቦርድ አባላት አመራረጥ


•የአባላት እና የተመረጡ የቦርድ አባላት መብትና ግዴታ
•የፋይናንስ እና ኦዲት ህግ
•የባለድርሻ አካላት ሚና
•በማህበሩ የሚከለከሉ (መተግበር የሌለባቸው ነገሮች)
•ደንቡ የሚሻሻልባቸው ሁኔታዎች
አዳዲስ አባላትን ወደ ማህበሩ ለማስገባት የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች

•አዳዲስ አባላትን ለመቀበል ግልጽ የሆነ መመሪያ ማስቀመጥ


•የውይይት መድረክ ፣ኤግዚቢሽን እና ባዛር በማዘጋጀት ፍላጎት ያላቸውን
አባላት መጋበዝ፣ መለየት እና መመዝገብ
•አዳዲስ አባላትን ተመጣጣኝ (ዝቅተኛ) ዋጋ በመተመን እንዲመዘገቡ ማድረግ
•ማህበሩ አመታዊ መጽሄቶችን በማዘጋጀት ተነባቢ ማድረግ
የቀጠለ …

•ማስታወቂያ ፣በራሪ ወረቀቶች ፣ፖስተሮች ፣ዌብ ሳይቶች እና ሚዲያ በመጠቀም


ማህበሩን ማስተዋወቅ
•አባላትን ሊጠቅሙና ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ተግባራትን ማከናወን ፣በኤግዚቢሽን
እንዲሳተፉ ፣ከሌሎች ማህበራት ገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ምርታቸውን
እንዲያስተዋውቁ መርዳት
•ለሁሉም ሴቶች የማህበሩን አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ (ለተማሩ ፣ላልተማሩ
እና ለአካል ጉዳተኞች ወ.ዘ.ተ)
•የማህበሩ አባላት ንግዳቸው የሚያድግበትንና የሚሻሻልበትን መንገድ መፈለግ
ነባር አባላትን ከማህበሩ ጋር ለማቆየት መደረግ
የሚገባቸው ሁኔታዎች

•ስብሰባዎች ሲደረጉ የአባላቱን ፍላጎት ያገናዘበ ጊዜና ሰዓት ማመቻቸት


•አባላቱ በማህበሩ ቆይታቸው የኛ ነው የሚለውን መንፈስ እንዲያዳብሩ
ማህበሩ ስትራቴጂ ፕሮግራሞችን ሲቀርጽ እንዲሳተፉ ማድረግ
•የባንክ ብድር ለሚፈልጉ የማህበሩ አባላት ከባንኮች ጋር በመነጋገር ለሴቶች
የሚሆኑ ፓኬጆች ካሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ
•በዝቅተኛ ንግድ ለተሰማሩ የቁጠባና ብድር ማህበራት እንዲያቋቁሙ ማገዝ
የቀጠለ…

•እርዳታ ስለሚሰጡ ድርጅቶች መረጃ መስጠት


•የቁሳቁስ እና የገንዘብ እርዳታ የሚያገኙበትን ዘዴ ማመቻቸት
•ወቅታዊ መረጃዎችን ማሳወቅ (ግብር ፣አዳዲስ አዋጆች ደንቦች እና መመሪያዎች)
•ከንግዱ ዘርፍ ጋር በተያያዘ ከሚሰሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ
አካላት ጋር የስራ ግንኙነት እንዲፈጥሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
•የተሻለ እንቅስቃሴ ያላቸውን የማህበሩ አባላትን በሚድያ እንዲቀርቡ እና ልምዳቸውን
እንዲያካፍሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
አድቮከሲ ( አጥብቆ መደገፍ ፣ መከራከር)

ፖሊሲዎች ፕሮግራሞች ሲቀረጹ በአንድ አጀንዳ ላይ አቋም ሲያዝ ግራና


ቀኙን አይቶ ከማህበሩ ጥቅም አንጻር እንዲሰራ ሁኔታዎችን ለማስቀየር
የሚደረግ ሂደት ነው
አድቮከሲ ለማድረግ

•የንግግር ችሎታ ያስፈልጋል


•የህብረተሰብ ትኩረት መሳብ አለበት
•ውሳኔዎችን ወደ ተፈለገው አቅጣጫ/ጉዳይ ማምጣት ያስፈልጋል
•ጉዳዮችን መለየት
•መፍትሄዎችን መለየት
•ለአድቮከሲው ተግባር እቅድ ማውጣት
•የአድማጮችን ሁኔታ ማወቅ
•ደጋፊ ወገኖችን ማወቅ
•መልዕክቱ (ቅስቀሳው የሚተላለፈው) በሚዲያ ከሆነ ከስድስት ነጥብ
ያልበለጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ማዘጋጀት እና ቃላቶችን አለማወሳሰብ
ዝግጅት እና እቅድ

•ለማህበሩ የሚያስፈልጉ ነገሮችን መለየትና የተለዩት ጉዳዮች ላይ መስማማት


•ድርድር ስለሚደረግባቸው ሰዎች እና ድርጅቶች ጥናት ማካሄድ እነሱ ምን
እንደሚፈልጉ ማወቅ
•ተደራዳሪዎች እሴቶችን በመከፋፈል መደራጀት
•ገለልተኛ ቦታ መፈለግ
•አጀንዳዎችን በደንብ ማጠናከር
•የጊዜ ገደብ ማውጣት
•ነጥቦችን በጥሞና ማቅረብ
•የሌለውን ወገን ጭብጦች ማዳመጥ
•በጋራ ሊያግባቡ የሚችሉ ነጥቦችን መፈለግ
የተስማሙበትን ነጥብ በግልጽ ማስቀመጥ
ማህበር እንዴት ይጠናከራል?

ማህበርን ለማጠናከር ከአባላቱ ከሚሰበሰበው


መዋጮ ባሻገር የተለያዩ ዘዴዎችን መጠቀም
ያስፈልጋል፡፡ ከውስጥ እና ከውጭ ገቢዎች
የቀጠለ …

የውስጥ የገቢ ምንጮች


•የአባላት መዋጮ
•ዝግጅቶችን በማድረግ የተጠራቀሙ ሂሳቦችን እንዲከፈሉ ማድረግ
•ገንዘብ ያዧ በየቦታው እየዞረች እንድትሰበስብ ማድረግ
•ደብዳቤ መላክ ( በተለይ የተጠራቀመ ሂሳብ ካለ)
•ወርሃዊ ስብሰባዎችን ጊዚያቸውን ጠብቆ በማካሄድ እንዲከፍሉ ማድረግ
የውጭ የገቢ ምንጮች
•ማህበሩ ኢንቨስት ካደረገበት የሚገኝ ( ቦንዶች ፣አክስዮኖች መግዛት)
•ከእርዳታ ድርጅቶች እና ከመንግስት
ገንዘብ ፋይናንስ አስመልክቶ

ገንዘብ ነክ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ግልጽነትና ተጠያቂነት መኖር አለበት ከማህበሩ አመኔታ


ለማትረፍ
•ገቢና ወጭ በግልጽ መታወቅ አለበት
•ገቢና ወጭ በደንብና በትክክል መመዝገብ አለበት
•በማህበሩ ስም በተከፈተው የባንክ ደብተር መጠቀም
•የፋይናንስ ጉዳይን አስመልክቶ ለስራ አስፈጻሚ አካላት ወቅቱን የጠበቀ ሪፖረት መቅረብ
አለበት
•የማህበሩ መገልገያ እቃዎች ቆጠራ በየጊዜው መካሄድ አለበት
•አጠቃላይ የፋይናንስ ሁኔታ በየአመቱ መጨረሻ ተዘጋጅቶ ለጠቅላላ ጉባኤው መቅረብ አለበት
•የማህበሩ ገቢና ወጭ ትክክለኛነት በውጭ ኦዲተር መረጋገጥ አለበት
ግምገማ

•የተሰጠው አገልግሎት ምን ጥቅም እንዳስገኘ


•በማህበሩ የተካሄዱ ስራዎች የነጋዴ ሴቶችን ፍላጎት ያJላ
መሆን አለመሆኑን መፈተሸ
•ለቀጣይ የስራ ጊዜ መካተት መሻሻል ስለሚገባቸው
ተግባራት
•ፈጻሚን እና ተጠቃሚን በተመለከተ
•የስራዎችን አፈጻጸም እና ተግባራዊነትን በተመለከተ
ማጠቃለያ

በአጠቃላይ ማህበር
•በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ
•አባላት ያሉት
•ወርሃዊ መዋጮ ያለው
•የሚመራበት መተዳደሪያ ደንብ ያለው
•ግልጽ ፣ የተጠያቂነት አሰራር የዘረጋ እና ለሁሉም
የማህበሩ አባላት በእኩልነትና በፍታሃዊነት ማገለግል
አለበት፡፡
አመሰግናለሁ!!!

You might also like