You are on page 1of 6

ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.

ለደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት

ደሴ

ከሳሽ ...ሰይድ አራጋው ክብረት

አድራሻ :- ደሴ ዙሪያ ወረዳ 027 ቀበሌ

ተከሳሽ ...ወርቅየ አሰን እሸቴ

አድራሻ :- ደሴ ዙሪያ ወረዳ 027 ቀበሌ

በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 14፣222 መሰረት የቀረበ ክስ ነው።

የውርስ መሬት እና ሀብት ታስረክበኝ ክስ ነው።

የንብረቱ ግምት 74,000 (ሰባ አራት ሽ ብር)::

- ክሱ የቀረበው በድሀ ደንብ ነው።

- ከሳሽ በህግ ችሎታ የለህም አልተባልኩም።

- የክስ መጥሪያውን ተከሳሽ ስለማትቀበለኝ በደሴ ዙርያ ወረዳ 027 ቀበሌ አስ/ጽ/ቤት በኩል ይሰጥልኝ።

የክሱ ዝርዝር

የከሳሽ ወላጅ አባት ሟች አቶ አራጋው ክብረት ይመር እና ተከሳሽ ወርቅየ አሰን እሸቴ በደሴ ዙሪያ ወረዳ 027 ቀበሌ
ውስጥ ሲኖሩ መሬት ተተምነው ሀብት ንብረት አፍርተው ሳለ ወላጅ አባቴ በድንገተኛ ህመም በእብድ ውሻ ንክሻ
ምክንያት ከዚህ አለም ሲለይብኝ አሁን ከሳሽ በዚህ ክቡር ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 013722 በሆነ በቀን 12/05/2013 ዓ.ም
የወላጅ አባቴ ህጋዊ ወራሽነቴን አሳውጀ ውሳኔ በእኛ ላይ ይገኛል።

1 ኛ. ይህ የወላጅ አባቴ እና የተከሳሽ ይዞታ መሬት እና አዋሳኞች፣

1/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ ሰይድ መርሻ አራጋው ፣ በምዕራብ የሹማ አህመድ ሙሄ ፣ በደቡብ ይመር አሊ ይመር ፣
በሰሜን ይመር አሊ ይመር መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ እዋ።

2/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ አራጌ አህመድ ሞትማ ፣ በምዕራብ አረጋ መርሻ አራጋው ፣ በደቡብ እቴነሽ እሸቱ ሽበሽ ፣
በሰሜን ይመር አሊ ይመር መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ ድንቹ።

3/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ ደምስ አመዴ አበጋዝ ፣ በምዕራብ መንገድ ፣ በደቡብ አሰን አደም በላቸው ፣ በሰሜን
ይመር አሊ መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ ይማም እያሱ።

4/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ መንገድ ፣ በምዕራብ ታደሰ አሊ ሽበሽ ፣ በደቡብ መንገድ ፣ በሰሜን ይማም አደም በላቸው
መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ ዋልኬ።

5/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ ሸለቆ ፣ በምዕራብ ሁሴን እሸቱ ሽበሽ ፣ በደቡብ አሰን ይመር ሽበሽ ፣በሰሜን ታደሰ አሊ
ሽበሽ መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ አይገብር።
6/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ ሸለቆ ፣ በምዕራብ ይመር አሊ ይመር ፣ በደቡብ ይመር አሊ ይመር ፣ በሰሜን መሀመድ
ይመር ልመናው መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ ፈንደዶ።

7/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ ሸለቆ ፣ በምዕራብ ይመር አሊ ይመር ፣ በደቡብ መሀመድ ይመር የሱፍ ፣ በሰሜን ሰይድ
መርሻ አራጋው መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ ፈንደዶ።
8/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ ይመር አሊ ይመር ፣ በምዕራብ በላይ መርሻ አራጋው ፣ በደቡብ ጌታነህ መርሻ አራጋው፣
በሰሜን ይማም ሁሴን መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስም በኒው።

9/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ ይመር አሊ ይመር ፣ በምዕራብ ዘሙ መብራቱ የሻው ፣ በደቡብ አባተ እሸቱ ሽበሽ፣በሰሜን
ይመር አሰን መሀመድ መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ በኒው።

10/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ ይመር አሊ ይመር ፣ በምዕራብ አረጋ መርሻ አራጋው ፣ በደቡብ የሹማ አህመድ ሙሄ ፣
በሰሜን ተዋበች ይመር መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ የማታ ጣይ።

11/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ ይመር አሰን መሀመድ ፣ በምዕራብ አደም ለማ ይመር ፣ በደቡብ ሸለቆ ፣ በሰሜን ታደሰ አሊ
ሽበሽ መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ የማታ ጣይ።

12/ ባህርዛፍ በምስራቅ አራጋው መኮነን ይመር ፣ በምዕራብ መንገድ ፣ በደቡብ መንገድ ፣ በሰሜን ሸለቆ መሬቱ
የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ እርጥብ ሸለቆ።

13/ ግጦሽ በምስራቅ መንገድ ፣ በምዕራብ ሸህ ሰይድ ይማም አሊ ፣ በደቡብ ሸለቆ፣ በሰሜን አራጌ አህመድ ሞትማ
መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ አባ ዘቦቴ።

14/ አመታዊ ሰብልና ባህርዛፍ በምስራቅ ይመር መኮነን ይመር፣ በምዕራብ በላይ መርሻ አራጋው ፣ በደቡብ አሰን መኮነን
ይመር ፣በሰሜን ሸለቆ መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ አረንዛው።

15/ አመታዊ ሰብልና ግጦሽ በምስራቅ ታደሰ አሊ ሽበሽ ፣ በምዕራብ ታደሰ አሊ ሽበሽ ፣ በደቡብ አሰን ይመር ሽበሽ ፣
በሰሜን አሰን ይመር ሽበሽ መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ እቦታው ።

16/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ ጌታነህ መርሻ አራጋው ፣ በምዕራብ መንገድ ፣ በደቡብ ተሾመ አበበ አሊ፣ በሰሜን መንገድ
መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ መስኖ።

17/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ ይመር አሊ ይመር፣ በምዕራብ አሰን ይመር ሽበሽ ፣ በደቡብ መንገድ ፣ በሰሜን ደምሴ
ይመር ሽበሽ መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስም እጥዱ።

18/ ግጦሽ በምስራቅ ገደል ፣ በምዕራብ ወንዝ ፣ በደቡብ አራጌ እሸቴ ይመር ፣ በሰሜን አረጉ አርጋው አመዴ መሬቱ
የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ ብረት መንገድ።

19/ አመታዊ ሰብልና ባህርዛፍ በምስራቅ መንገድ ፣ በምዕራብ ይመር አባተ አሊ ፣ በደቡብ ወንዝ ፣ በሰሜን አረጉ አርጋው
አመዴ መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ የቤት ዙሪያ።

20/ ግጦሽ በምስራቅ ታደሰ አበበ ፣ በምዕራብ ሰይድ እብራሂም ፣ በደቡብ ሰይድ እብራሂም፣ በሰሜን አሰን እብራሂም
መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ ዳገቱ።

21/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ ሰይድ እብራሂም ፣በምዕራብ አወል አሚኑ ፣ በደቡብ ሰይድ እብራሂም፣ በሰሜን አሰን
እብራሂም መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስም ዋሻው።
22/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ ሰይድ እብራሂም ፣በምዕራብ አወል አሚኑ ፣ በደቡብ አወል አሚኑ፣ በሰሜን አወል አሚኑ
መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስም ዋሻው።

23/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ ጉዝጉዝ አሰን ፣ በምዕራብ አሊ መሀመድ ፣ በደቡብ አወል አሚኑ፣ በሰሜን ሰይድ
እብራሂም መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ ብርገጉ።

24/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ አወል አሚኑ ፣ በምዕራብ ሰይድ እብራሂም፣ በደቡብ ካሳው ሰይድ ፣ በሰሜን ታደሰ አበበ
መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ የቤት ዙሪያ።

25/ አመታዊ ሰብል በምስራቅ መንገድ ፣በምዕራብ አህመድ አደም ፣ በደቡብ ሸህ ሙሄ አብተው፣ በሰሜን አወል አሚኑ
መሬቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ ወንዚቱ።

ከተራ ቁጥር 1-19 ያሉት መሬቶች በ 027 ቀበሌ የሚገኙ ሲሆን ከተራ ቁጥር 20-25 ያሉት መሬቶች ደግሞ በ 026
ቀበሌ የሚገኙ ናቸው።

2 ኛ. የሟች ወላጅ አባቴ እና የተከሳሽ ተንቀሳቃሽ ንብረት ፦

1/ በ 027 ቀበሌ 80 ቅጣን ቆርቆሮ የፈጀ መኖሪያ ቤት ግምቱ 60,000( ስልሳ ሽ ብር) ሲሆን ተከሳሽ ድርሻዋን አንስታ
የሟች ልጆች ሶስት ስንሆን የወላጅ አባታችን ድርሻ 30,000( ሰላሳ ሽ ብር) ሲካፈል ለሶስት የከሳሽ ድርሻ በውርስ
10,000( አስር ሽ ብር)::

2/ በ 027 ቀበሌ 65 ቅጣን ቆርቆሮ የፈጀ መኖሪያ ቤት ግምቱ 48,000( አርባ ስምንት ሽ ብር) ሲሆን ተከሳሽ ድርሻዋን
አንስታ የሟች ልጆች ሶስት ስንሆን የወላጅ አባታችን ድርሻ 24,000( ሀያ አራት ሽ ብር) ሲካፈል ለሶስት የከሳሽ ድርሻ
በውርስ 8,000( ስምንት ሽ ብር)::

3/ በ 027 ቀበሌ 40 ቅጣን ቆርቆሮ የፈጀ መኖሪያ ቤት ግምቱ 36,000( ሰላሳ ስድስት ሽ ብር) ሲሆን ተከሳሽ ድርሻዋን
አንስታ የሟች ልጆች ሶስት ስንሆን የወላጅ አባታችን ድርሻ 18,000( አስራ ስምንት ሽ ብር) ሲካፈል ለሶስት የከሳሽ
ድርሻ በውርስ 6,000( ስድስት ሽ ብር)::

4/ በ 026 ቀበሌ 60 ቅጣን ቆርቆሮ የፈጀ መኖሪያ ቤት ግምቱ 42,000( አርባ ሁለት ሽ ብር) ሲሆን ተከሳሽ ድርሻዋን
አንስታ የሟች ልጆች ሶስት ስንሆን የወላጅ አባታችን ድርሻ 21,000( ሀያ አንድ ሽ ብር) ሲካፈል ለሶስት የከሳሽ ድርሻ
በውርስ 7,000( ሰባት ሽ ብር)::

5/ ሁለት በሬዎች ግምታቸው 84,000( ሰማንያ አራት ሽ ብር) ተከሳሽ ድርሻዋን አንስታ የእኛ የሟች ልጆች ድርሻ
42,000(አርባ ሁለት ሽ ብር) ሲካፈል ለሶስት የከሳሽ ድርሻ 14,000( አስራ አራት ሽ ብር)::

6/ አንድ ላም ግምቷ 18,000( አስራ ሰምንት ሽ ብር) ተከሳሽ ድርሻዋን አንስታ የእኛ የሟች ልጆች ድርሻ 9,000(ዘጠኝ
ሽ ብር) ሲካፈል ለሶስት የከሳሽ ድርሻ 3,000( ሶስት ሽ ብር)::

7/ ሁለት ጥጆች አንድ ወንድ አንድ ሴት ግምታቸው 9,000( ዘጠኝ ሽ ብር) ተከሳሽ ድርሻዋን አንስታ የእኛ የሟች ልጆች
ድርሻ 4,500(አራት ሽ አምስት መቶ ብር) ሲካፈል ለሶስት የከሳሽ ድርሻ 1,500( አንድ ሽ አምስት መቶ ብር)::

8/ ሀያ ሁለት በጎች ግምታቸው 66,000( ስልሳ ስድሰት ሽ ብር) ተከሳሽ ድርሻዋን አንስታ የእኛ የሟች ልጆች ድርሻ
33,000(ሰላሳ ሶስት ሽ ብር) ሲካፈል ለሶስት የከሳሽ ድርሻ 11,000( አስራ አንድ ሽ ብር)::

9/ ሁለት ሴት አህዮች ግምታቸው 6,000( ስድስት ሽ ብር) ተከሳሽ ድርሻዋን አንስታ የእኛ የሟች ልጆች ድርሻ
3,000(ሶስት ሽ ብር) ሲካፈል ለሶስት የከሳሽ ድርሻ 1,000( አስራ አራት ሽ ብር)::
10/ በ 2014 ዓ.ም የተሰበሰበ አንድ ክምር የድርቆ ሳር ግምቱ 15,000(አስራ አምስት ሽ ብር) ተከሳሽ ድርሻዋን አንስታ
የእኛ የሟች ልጆች ድርሻ 7,500(ሰባት ሽ አምስት መቶ ብር) ሲካፈል ለሶስት የከሳሽ ድርሻ 2,500( ሁለት ሽ አምስት
መቶ ብር)::

11/ የባህር ዛፍ አትክልት ሰባት ቦታ ግምቱ 60,000( ስልሳ ሽ ብር) ተከሳሽ ድርሻዋን አንስታ የእኛ የሟች ልጆች ድርሻ
30,000(ሰላሳ ሽ ብር) ሲካፈል ለሶስት የከሳሽ ድርሻ 10,000( አስር ሽ ብር)::

የከሳሽ ድርሻ ጠቅላላ ድምር 74,000 (ሰባ አራት ሽ ብር)::

የምጠይቀው ዳኝነት

የክስ ፋይል ተከፍቶልኝ ተከሳሽ በመጥሪያ ተጠርታ ቀርባ ተጠይቃ ብታምን በእምነቷ ብትክድ በማስረጃ አስረጅቼ ፦

1/ ከሳሽ በአቤቱታየ ላይ ዘርዝሬ ያቀረብኳቸውን የውርስ ሀብትና ንብረት የወላጅ አባቴን ድርሻ በአይነትና በመጠን
ተጣርተው እንዲታካፍለኝ እንዲወሰንልኝ።

2/ ከሳሽ ለዚህ አቤቱታ ለዳኝነት፣ ለምስክር አበል፣ ልዩ ልዩ ወጭ ያወጣሁትን ተከሳሽ እንዲትከፍለኝ ሳመለክት ይህ ክሴ
በእውነት የቀረበ ነው።

ከሳሽ ...ሰይድ አራጋው ክብረት

ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ም

ለደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት

ደሴ

ከሳሽ ...ሰይድ አራጋው ክብረት

አድራሻ :- ደሴ ዙሪያ ወረዳ 027 ቀበሌ

ተከሳሽ ...ወርቅየ አሰን እሸቴ

አድራሻ :- ደሴ ዙሪያ ወረዳ 027 ቀበሌ

በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 223 መሰረት የቀረበ የማስረጃ ዝርዝር

ሀ/ የሰነድ ማስረጃ

1. ወራሽነቴን ያረጋገጥኩበት 2 ገጽ ፎቶ ኮፒ።

2. ነፃ ድሀ መሆኔን የ 027 ቀበሌ ማ/ፍ/ቤት የሰጠኝ ማስረጃ 2 ገጽ ፎቶ ኮፒ።

3. ተከሳሽ የይዞታ መሬት ደብተራቸውን ሰለያዘችው ፍ/ቤቱ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 145 መሰረት አቅርቦ ይመልከትልኝ።

ለ/ የሰው ምስክሮች

1. ብዙ የሱፍ ይመር
2. ሸህ መሀመድ አሰን አመዴ

3. መሀመድ በላይ አሊ

የሁሉም አድራሻ ደሴ ዙሪያ ወረዳ 027 ቀበሌ የተባሉት ስለሆኑ ቀርበው እንዲመሰክሩልኝ ስል አመለክታለሁ።

ይህ የማስረጃ ዝርዝር እውነት ነው።

ከሳሽ... ሰይድ አራጋው ክብረት

ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ም

ለደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት

ደሴ

ቃለ መሀላ አቅራቢ ...ሰይድ አራጋው ክብረት

አድራሻ :- ደሴ ዙሪያ ወረዳ 027 ቀበሌ

ተከሳሽ ...ወርቅየ አሰን እሸቴ

አድራሻ :- ደሴ ዙሪያ ወረዳ 027 ቀበሌ

በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 205 መሰረት የቀረበ ቃለ መሀላ

የሚከተለውን ቃለ መሀላ አመለክታለሁ።

ፍሬ ነገሩ

በከሳሽ በእኔ ቃለ መሀላ አቅራቢውና በተከሳሽ መካከል ስላለው የውርስ ሀብትና ንብረት ክስ ክርክር ከሳሽ በአቤቱታየ
ላይ የዘረዘርኩትን የውርስ ንብረት ተከሳሽ ልትሸጥ ልትለውጥ ስለምትችል በደሴ ዙሪያ ወረዳ በ 027 ቀበሌ ውስጥ 80
ቅጣን ቆርቆሮ የፈጀ መኖሪያ ቤት፣ በ 027 ቀበሌ 65 ቅጣን ቆርቆሮ የፈጀ መኖሪያ ቤት፣ በ 027 ቀበሌ 40 ቅጣን ቆርቆሮ
የፈጀ መኖሪያ ቤት፣ በ 026 ቀበሌ 60 ቅጣን ቆርቆሮ የፈጀ መኖሪያ ቤት ፣ ሁለት በሬዎች፣ አንድ ላም፣ ሁለት ጥጆች
አንድ ወንድ አንድ ሴት ፣ ሀያ ሁለት በጎች፣ ሁለት ሴት አህዮች፣ አንድ ክምር የድርቆ ሳር ፣ የባህር ዛፍ አትክልት ሰባት ቦታ
ያለ እነዚህ እንዳይሸጡ እንዳይለወጡ የክርክሩ ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ ቁጥር 154 መሰረት የእግድ
ትዕዛዝ የደሴ ዙሪያ ወረዳ 027 ቀበሌ አስ/ጽ/ቤት እና 026 ቀበሌ አስ/ጽ/ቤት እንዲሰጥልኝ አመለክታለሁ።

ይህ ቃለ መሀላ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ ቁጥር 92 መሠረት እውነት ነው።

ቃለ መሀላ አቅራቢ ሰይድ አራጋው ክብረት

You might also like